am_tn/2sa/11/16.md

1.1 KiB

ከተማይቱ ስትከበብ

"ከበባ" የሚለው ቃል "ከበበ" እና "አጠቃ" በሚሉ ግሶች ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የአርሱ ሰራዊት ከተማዋን ከብቦ አጠቃ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ጥቂት የዳዊት ወታደሮች ወደቁ

"ወደቁ" የሚለው ቃል የወታደሮቹ መገደል በተሻለ መንገድ የተገለጸበት ነው፡፡ "የዳዊት ወታደሮች ተገደሉ" ወይም "ከዳዊት ወታደሮች ጥቂቶችን ገደሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ) እናም ኬጢያዊው ኦርዮም በዚያ ተገደለ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ኬጢያዊውን ኦርዮን ጨምሮ" ወይም "የከተማይቱ ሰዎች ኬጢያዊውን ኦርዮንም ገደሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)