am_tn/2ki/08/25.md

1.9 KiB
Raw Permalink Blame History

አጠቃላይ መረጃ

አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ

የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት

የአሁኑ ንጉሥ ኢዮራም ምን ያህል ዘመን በእስራኤል እንደ ነገሠ በመግለጽ አካዝያስ በይሁዳ መንገሥ የጀመረበትን ዘመን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአክዓብ ልጅ ኢዮራም የእስራኤል ንጉሥ በሆነ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት››

ዐሥራ ሁለተኛ ዓመት

12ኛ ዓመት››

ሃያ ሁለት ዓመት

22 ዓመት››

ጐቶልያ… ዖምሪ

ጐቶልያ የአንድ ሴት ስም ነው፡፡ ዖምሪ የአንድ ሰው ስም ነው፡፡

አካዝያስ በ… መንገድ ሄደ

እዚህ ላይ፣ ‹‹ሄደ›› የሰውን ጸባይ ወይም አኗኗር ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አካዝያስ እንደ ሌሎቹ ኖረ››

የአክዓብ ቤት

እዚህ ላይ፣ የአክዓብ፣ ‹‹ቤት›› ቤተ ሰቡን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአክዓብ ቤተ ሰብ››

በያህዌ ፊት ክፉ የሆነውን

የያህዌ ፊት የያህዌን ፍርድና መለኪያ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ ፍርድ ክፉ የሆነውን›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ እንደ ክፉ የሚያስበውን››

የአክዓብን ልጅ አገባ

ይህ የሚያመለክተው አካዝያስ ከአክዓብ ጋር ያለውን ቀረቤታ ነው፡፡ የአካዝያስ አባት የአክዓብን ልጅ አግብቶ ነበር፡፡ ይህን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአክዓብን ልጅ ያገባ ሰው ልጅ›› ወይም፣ ‹‹የንጉሥ አክዓብ የአማች ልጅ››