36 lines
1.9 KiB
Markdown
36 lines
1.9 KiB
Markdown
|
# አጠቃላይ መረጃ
|
|||
|
|
|||
|
አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ
|
|||
|
|
|||
|
# የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት
|
|||
|
|
|||
|
የአሁኑ ንጉሥ ኢዮራም ምን ያህል ዘመን በእስራኤል እንደ ነገሠ በመግለጽ አካዝያስ በይሁዳ መንገሥ የጀመረበትን ዘመን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአክዓብ ልጅ ኢዮራም የእስራኤል ንጉሥ በሆነ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት››
|
|||
|
|
|||
|
# ዐሥራ ሁለተኛ ዓመት
|
|||
|
|
|||
|
‹‹12ኛ ዓመት››
|
|||
|
|
|||
|
# ሃያ ሁለት ዓመት
|
|||
|
|
|||
|
‹‹22 ዓመት››
|
|||
|
|
|||
|
# ጐቶልያ… ዖምሪ
|
|||
|
|
|||
|
ጐቶልያ የአንድ ሴት ስም ነው፡፡ ዖምሪ የአንድ ሰው ስም ነው፡፡
|
|||
|
|
|||
|
# አካዝያስ በ… መንገድ ሄደ
|
|||
|
|
|||
|
እዚህ ላይ፣ ‹‹ሄደ›› የሰውን ጸባይ ወይም አኗኗር ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹አካዝያስ እንደ ሌሎቹ ኖረ››
|
|||
|
|
|||
|
# የአክዓብ ቤት
|
|||
|
|
|||
|
እዚህ ላይ፣ የአክዓብ፣ ‹‹ቤት›› ቤተ ሰቡን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአክዓብ ቤተ ሰብ››
|
|||
|
|
|||
|
# በያህዌ ፊት ክፉ የሆነውን
|
|||
|
|
|||
|
የያህዌ ፊት የያህዌን ፍርድና መለኪያ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በያህዌ ፍርድ ክፉ የሆነውን›› ወይም፣ ‹‹ያህዌ እንደ ክፉ የሚያስበውን››
|
|||
|
|
|||
|
# የአክዓብን ልጅ አገባ
|
|||
|
|
|||
|
ይህ የሚያመለክተው አካዝያስ ከአክዓብ ጋር ያለውን ቀረቤታ ነው፡፡ የአካዝያስ አባት የአክዓብን ልጅ አግብቶ ነበር፡፡ ይህን የበለጠ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹የአክዓብን ልጅ ያገባ ሰው ልጅ›› ወይም፣ ‹‹የንጉሥ አክዓብ የአማች ልጅ››
|