am_tn/2jn/01/01.md

1.9 KiB

2ኛ ዮሐንስ 1፡ 1-3

ሽማግሌው ይህ የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር የነበረውን ሐዋርያው ዮሐንስ የሚያመለክት ነው፡፡ ራሱን “ሽምግሌው” በማለት ይጠራል፡፤ ምክንያቱ አንድም በእድሜው ስላረጀ ወይም የቤተ ክርስቲያን መሪ በመሆኑ ሊሆን ይችላል፡፡ የተመረጠችው ሴት ሽማግሌ እና ልጆቿ በግሪክ ደብዳቤዎች የሚጀምሩት በዚህ ዓይነት መልኩ ነው፡፡ የደብዳቤው ጸሐፊ ማንነት በግልጽ መቀመጥ ይኖረበታል፡፡ አማራጭ ትርጉም: "እኔ ሽማግሌው ዮሐንስ በማለት ደብዳቤውን የጻፈው ለተመረጠችው እና ለልጆቿ ነው፡፡ የተመረጠችው ሴት እና ልጆቿ ይህ በዚያ ያሉትን ማህረ ምእመናን እና አማኞችን ያመለክታል፡፡ በእውነት የሚወዳቸው አማራጭ ትርጉም፡ "በእውነት የሚወዳቸው" በእኛ ስለሚኖርና ከእኛ ጋር ለዘላለም ስለሚሆን እውነት፥ አማራጭ ትርጉም፡ "በእውነት ስለሚናምን እና እስከ ዘላለምን በእምነት ስለምናምን" እውነት ይህ የኢየሱስ ትምህርት የሚያመለክት ነው፡፡ አባት . . . ልጅ ይህ በእግዚአብሔር እና በኢየሱስ መካከል ያለው ግንኙነት ምን እንደሚመስል የሚያመለክት ጠቃሚ የማዕረግ ስም ነው፡፡ (ተመልከት፡ [[rc:///ta/man/translate/guidelines-sonofgodprinciples]]) በእውነት እና በፍቅር አማራጭ ትርጉም: "እውነት ስለሆኑ እና እኛንም ስለሚወዱን" ወይም "በእውነት እኛ ስለሚወዱን" (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-hendiadys]])