am_tn/1sa/06/03.md

28 lines
1.7 KiB
Markdown

# የእስራኤል አምላክ
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) የእስራኤልን አምላክ መደበኛ ስም እየጠሩ ነበር ወይም 2) "የእስራኤል አምላክ'፣ እስራኤል ከብዙ አማልክት መካከል አንዱን ያመልኩ እንደነበር ያምኑ ነበር፡፡ 1ሳሙኤል 5፡7 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
# የበደል መሥዋዕት መልሱለት እንጂ ባዶውን አትስደዱት
ባዶውን አትስደዱት የሚሉት ቃላት አንድን ነገር አጠንክሮ መናገሪያ መንገድ ናቸው፡፡ አት፡- "የበደል መሥዋዕት መስደድ አለባችሁ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት)
# ትፈወሳላችሁ
"ከእንግዲህ ወዲህ አትታመሙ'
# እናንተ
እናንተ የሚለው ተውላጠ ስም የብዙ ቁጥር እንደመሆኑ ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያመለክታል፡፡ (አንተ/እናንተ ተመልከት)
# እጁ ከእናንተ አለመራቁ ስለምን ነው
በዚህ ስፍራ "እጅ' የሚለው ቃል እግዚአብሔር መከራን ለማምጣትና ለመቅጣት ያለውን ኃይል ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "መከራችሁን ለምን አላቀለላችሁም' (ምትክ ቃል ተመልከት)
# እጢ
ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡
# አይጦች
ከአንድ በላይ አይጥ