# የእስራኤል አምላክ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) የእስራኤልን አምላክ መደበኛ ስም እየጠሩ ነበር ወይም 2) "የእስራኤል አምላክ'፣ እስራኤል ከብዙ አማልክት መካከል አንዱን ያመልኩ እንደነበር ያምኑ ነበር፡፡ 1ሳሙኤል 5፡7 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ # የበደል መሥዋዕት መልሱለት እንጂ ባዶውን አትስደዱት ባዶውን አትስደዱት የሚሉት ቃላት አንድን ነገር አጠንክሮ መናገሪያ መንገድ ናቸው፡፡ አት፡- "የበደል መሥዋዕት መስደድ አለባችሁ' (ፈሊጣዊ ንግግር ተመልከት) # ትፈወሳላችሁ "ከእንግዲህ ወዲህ አትታመሙ' # እናንተ እናንተ የሚለው ተውላጠ ስም የብዙ ቁጥር እንደመሆኑ ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያመለክታል፡፡ (አንተ/እናንተ ተመልከት) # እጁ ከእናንተ አለመራቁ ስለምን ነው በዚህ ስፍራ "እጅ' የሚለው ቃል እግዚአብሔር መከራን ለማምጣትና ለመቅጣት ያለውን ኃይል ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ምትክ ቃል ነው፡፡ አት፡- "መከራችሁን ለምን አላቀለላችሁም' (ምትክ ቃል ተመልከት) # እጢ ሊሆኑ የሚችሉ ትርጎሞች፡- 1) ከቆዳ ስር የሚወጣ የሚያሰቃይ እባጭ ወይም 2) የአህያ ኪንታሮት 1ሳሙኤል 5፡6ን እንዴት እንደተረጎምክ ተመልከት፡፡ # አይጦች ከአንድ በላይ አይጥ