am_tn/isa/28/13.md

20 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# ስለዚህ … የእግዚአብሔር ቃል
ስለዚህ … የእግዚአብሔር መልእክት
# ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ
አነዚህ ኢሳይያስ እንዴት እያስተማራቸው እንዳለ ለመተቸት ሰካራሞቹ ነቢያትና ካህናት የሚጠቀሙባቸው ቃላት ናቸው፡፡ ይህንነ በኢሳይያስ 28፡10 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡
# ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲሰበሩም፣ እንዲጠመዱ፣ እንዲማረኩም
ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የአሦር ሠራዊት ይመጣና ያሽንፋቸው፣ ምርኮኞችም አድርጎ ይወስዳቸው ዘንድ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት)
# ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲሰበሩም
ሕዝቡ በጦርነት በጠላት ሠራዊት መሸነፉ ሕዝቡ እንደሚወደቅና እንደሚሰበር ተደርጎ ተነገሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)
# እንዲጠመዱ
የእስራኤልን ሕዝብ የሚማርኩ የጠላት ወታደሮች እንሰሳን በወጥመድ እንደሚያጠምዱ አዳኞች ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)