# ስለዚህ … የእግዚአብሔር ቃል ስለዚህ … የእግዚአብሔር መልእክት # ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ አነዚህ ኢሳይያስ እንዴት እያስተማራቸው እንዳለ ለመተቸት ሰካራሞቹ ነቢያትና ካህናት የሚጠቀሙባቸው ቃላት ናቸው፡፡ ይህንነ በኢሳይያስ 28፡10 እንዴት እንደተረጎምህ ተመልከት፡፡ # ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲሰበሩም፣ እንዲጠመዱ፣ እንዲማረኩም ይህ በአድራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አት፡- "የአሦር ሠራዊት ይመጣና ያሽንፋቸው፣ ምርኮኞችም አድርጎ ይወስዳቸው ዘንድ' (አድራጊና ተደራጊ ማሰሪያ አንቀጽ ተመልከት) # ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ፣ እንዲሰበሩም ሕዝቡ በጦርነት በጠላት ሠራዊት መሸነፉ ሕዝቡ እንደሚወደቅና እንደሚሰበር ተደርጎ ተነገሮአል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት) # እንዲጠመዱ የእስራኤልን ሕዝብ የሚማርኩ የጠላት ወታደሮች እንሰሳን በወጥመድ እንደሚያጠምዱ አዳኞች ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ (ስዕላዊ ንግግር ተመልከት)