am_tn/2sa/15/27.md

24 lines
1.7 KiB
Markdown
Raw Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# አኪማስ
ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)
# አብያታር
ይህን የወንድ ስም በ2 ሳሙኤል 8፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡
# አንተ ነቢይ አይደለህምን?
ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ሳዶቅን ለመገሰጽ ሲውል በዐረፍተ ነገር ሊተረጎምም ይችላል፡፡ "ሊሆን ያለውን ማወቅ ትችላለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)
# እይ/እነሆ
ይህ ቃል አድማጩ ቀጥሎ ለሚነገረው ትኩረት እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው፡፡ "ስማ/አድምጥ" በሚለው ወስጥ እንደሚገኘው፡፡
# ከአንተ ቃል እስኪመጣ ድረስ
ይህ ለንጉሡ መልዕክተኛ መላክን የሚያመለክት ነው፡፡ "ለእኔ መረጃ ለመስጠት ወደ እኔ መልዕክተኛ እስክትልክ ድረስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)
# መረጃ እንድትሰጠኝ
እዚህ ስፍራ ንጉሡ በኢየሩሳሌም እየሆነ ስላለው መረጃ እንደሚደርሰው ይጠቁማል፡፡ "በኢየሩሳሌም እየሆነ ያለውን እንድትነግረኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)