# አኪማስ ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ) # አብያታር ይህን የወንድ ስም በ2 ሳሙኤል 8፡17 ላይ እንዴት እንደተረጎሙት ይመልከቱ፡፡ # አንተ ነቢይ አይደለህምን? ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ሳዶቅን ለመገሰጽ ሲውል በዐረፍተ ነገር ሊተረጎምም ይችላል፡፡ "ሊሆን ያለውን ማወቅ ትችላለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ) # እይ/እነሆ ይህ ቃል አድማጩ ቀጥሎ ለሚነገረው ትኩረት እንዲሰጥ የሚያደርግ ነው፡፡ "ስማ/አድምጥ" በሚለው ወስጥ እንደሚገኘው፡፡ # ከአንተ ቃል እስኪመጣ ድረስ ይህ ለንጉሡ መልዕክተኛ መላክን የሚያመለክት ነው፡፡ "ለእኔ መረጃ ለመስጠት ወደ እኔ መልዕክተኛ እስክትልክ ድረስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) # መረጃ እንድትሰጠኝ እዚህ ስፍራ ንጉሡ በኢየሩሳሌም እየሆነ ስላለው መረጃ እንደሚደርሰው ይጠቁማል፡፡ "በኢየሩሳሌም እየሆነ ያለውን እንድትነግረኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)