am_tn/luk/06/31.md

12 lines
1.5 KiB
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# ሰዎች ለእናንተ እንዲያደርጉ እንደምትፈልጉት፣ እናንተም ለእነርሱ እንደዛው አድርጉላቸው
በአንዳንድ ቋንቋዎች ቅደም ተከተሉን መለወጥ የተለመደ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሰዎች ማድረግ ያለባችሁ እናንተ እነርሱ እንዲያደርጉባችሁ እንደምትፈልጉት ነው” ወይም “ለሰዎች ማሰብ ያለባችሁ እነርሱ ለእናንተ እንዲያስቡ በምትፈልጉት መንገድ ነው”
# ምን የተለየ ዋጋ ታገኛላችሁ?
“ምን ዋጋ ታገኛላችሁ?” ወይም “ያንን በማድረጋችሁ ምን አይነት ምስጋናን ታተርፋላችሁ” ይህ በአረፍተ ሃሳብ ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡. አማራጭ ትርጉም፡- “ያንን በማድረጋችሁ ምንም ሽልማትን አታገኙም” ወይም “ያንን በማድረጋችሁ እግዚአብሔር ምንም ሽልማትን አይሰጣችሁም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)
# ተመሳሳይ መጠን ያለውን መልሳችሁ ብትቀበሉ
የሙሴ ሕግ አይሁዳውያን እርስ በርስ በተበዳደሩት ገንዘብ ላይ ወለድን እንዳይቀበሉ ያዝዛል፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)