# ሰዎች ለእናንተ እንዲያደርጉ እንደምትፈልጉት፣ እናንተም ለእነርሱ እንደዛው አድርጉላቸው በአንዳንድ ቋንቋዎች ቅደም ተከተሉን መለወጥ የተለመደ ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለሰዎች ማድረግ ያለባችሁ እናንተ እነርሱ እንዲያደርጉባችሁ እንደምትፈልጉት ነው” ወይም “ለሰዎች ማሰብ ያለባችሁ እነርሱ ለእናንተ እንዲያስቡ በምትፈልጉት መንገድ ነው” # ምን የተለየ ዋጋ ታገኛላችሁ? “ምን ዋጋ ታገኛላችሁ?” ወይም “ያንን በማድረጋችሁ ምን አይነት ምስጋናን ታተርፋላችሁ” ይህ በአረፍተ ሃሳብ ቅርጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡. አማራጭ ትርጉም፡- “ያንን በማድረጋችሁ ምንም ሽልማትን አታገኙም” ወይም “ያንን በማድረጋችሁ እግዚአብሔር ምንም ሽልማትን አይሰጣችሁም” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ) # ተመሳሳይ መጠን ያለውን መልሳችሁ ብትቀበሉ የሙሴ ሕግ አይሁዳውያን እርስ በርስ በተበዳደሩት ገንዘብ ላይ ወለድን እንዳይቀበሉ ያዝዛል፡፡ (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለፀ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)