20 lines
1.9 KiB
Markdown
20 lines
1.9 KiB
Markdown
|
# ከማህተም በታች እንዳለ ጭቃ/ሸክላ የምድር መልኳ ይለወጣል
|
||
|
|
||
|
በምሽት፣ ሰዎች በግልጽ መመልከቱ አይችሉም፣ ማለዳ ግን ማህተም በሸክላ ላይ ግልጽ ምስልን እንደሚፈጥር ብርሃን የሁሉንም ነገር ቅርጽ በግልጽ መለየት ያስችላል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# እንደ ቁራጭ ጨርቅ እጥፋት በእርሷ ላይ የሚገኙ ነገሮች ሁሉ በግልጽ ይታያል
|
||
|
|
||
|
እዚህ ስፍራ "እርሷ" የሚለው የሚያመለክተው ምድርን ነው፡፡ ይህ ሀረግ በዚህ ስንኝ ከሚገኘው የመጀመሪያው ሀረግ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ከክፉ ሰዎች "ብርሃናቸው" ይወሰዳል
|
||
|
|
||
|
ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማለዳ የክፉ ሰዎችን ‘ብርሃን' ይወሰዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# የእነርሱን ‘ብርሃን'
|
||
|
|
||
|
ክፉዎች ጨለማን ብርሃናቸው አድርገው ይቆጥራሉ፣ ምክንያቱም ክፉ ስራቸውን ሚሰሩት በጨለማ ሲሆን ደግሞም ከጨለማ ጋር ቅርርብ አላቸው፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# የተነሳው ክንዳቸው ይሰበራል
|
||
|
|
||
|
የተነሳው የክፉዎች እጅ የሚለው የሚወክለው ሀይላቸውን እና ክፉ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት ነው፡፡ ነገር ግን የማለዳው ብርሃን ስወጣ ክፉዎች እነዚያን ክፉ ነገሮች ማድረጋቸውን ያቆማሉ፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)
|