am_tn/isa/22/15.md

20 lines
1014 B
Markdown
Raw Permalink Normal View History

2021-03-06 16:01:31 +00:00
# ሳምናስ
ይህ በኢየሩሳሌም ያለው የንጉሡ ቤተ መንግሥት መልእክተኛ ነው፡፡
# የቤቱን ኀላፊ
እዚህ ላይ፣ ‹‹ቤቱ›› በንጉሡ ቤተ መንግሥት ያሉትን ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹በንጉሡ ቤተ መንግሥት ለሚሠሩት ሁሉ ኀላፊ የሆነው››
# እዚህ ምን ታደርጋለህ የፈቀደልህስ ማን ነው… ዐለት ውስጥ?
ያህዌ ይህን የሚጠይቀው ሳምናስ ላይ ለማፌዝ ነው፡፡ አማራጭ ትርጒም፣ ‹‹ዐለቱ ውስጥ… ምንም መብት የለህም!
# መቀበሪያ እንድትወቅር… መቃብር እንድትጠርብ… ማረፊያ ቦታ እንድትጠርብ
ሦስቱም ሐረጐች የሚያመለክቱት መቃብር መሥራትን ነው፡፡
# ከፍታዎች ላይ
እስራኤል ውስጥ ታላላቅ ሰዎች ከፍታ ቦታ ላይ መቃብር ይሠሩ ነበር፡፡