20 lines
2.2 KiB
Markdown
20 lines
2.2 KiB
Markdown
|
# የፍልስጥኤማውያንን እና የዓረባውያንን መንፈስ በኢዮራም ላይ እንዲነሳ አደረገ
|
||
|
|
||
|
መንፈስን ማነሳሳት ማለት አንድ ሰው እርምጃ ለመውሰድ እንዲፈልግ ማድረግን የሚገልጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው። እዚህ “መንፈስ” ነጠላ ሲሆን ፍልስጤማውያንን እንደ አንድ ቡድን እና ዓረባውያንን እንደ አንድ ቡድን ይመለከታል ፡፡ ኣት: “ፍልስጥኤማውያንና ዓረባውያን በኢዮራም ላይ ተቆጥተው ነበር” (ዘይቤያዊን ፡ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# በኢዮራም ላይ
|
||
|
|
||
|
እዚህ ላይ ኢዮራም የሚያመለክተው ኢዮራምን እና ይገዛው የነበረውን የይሁዳን ህዝብ ነው ፡፡ አት: - “በኢዮራም እና በይሁዳ ሰዎች ላይ” ( ሁሉን በአንዱ ወይም አንዱን በሁሉ መወከልን ፡ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# በኩሾች አቅራቢያ የነበሩትን የፍልስጥኤማውያን እና የዐረባውያን መንፈስ
|
||
|
|
||
|
ፍልስጥኤማውያንና አረቦች ሁለት የተለያዩ አገራት ነበሩ ፡፡ አረባውያን በይሁዳ ደቡብምስራቅ በኩል በኩሽ አቅራቢያ ይኖሩ ነበር ፣ ፍልስጤማውያንም ከይሁዳ በስተ ምዕራብ ይኖሩ ነበር ፡፡ እነዚህ አገራት በተናጥል ተነሳሱ ፡፡ ይህ ግልጽ ሊደረግ ይችላል። ኣት: - “የፍልስጤማውያን መንፈስ እና በኩሾች አቅራቢያ የነበሩት የአረባውያን መንፈስ” (የሚጠበቅ እውቀትን እና ያልተገለጸ መረጃን ፡ይመልከቱ)
|
||
|
|
||
|
# ከታናሹም ልጅ ከአካዝያስ በቀር ልጅ አልቀረለትም
|
||
|
|
||
|
“ታናሹን ልጅ ኢዮአስ በቀር ወንዶች ልጆቹን ሁሉ ወሰዱ” ወይም “ለእርሱ ያስቀሩለት ብቸኛው ወንድ ልጅ የሁሉም ታናሽ የነበረውን ኢዮአስ ነው”
|
||
|
|
||
|
# ታናሽ ልጁ ኢዮአስ
|
||
|
|
||
|
ይህ ልጅ በ 2 ኛ ዜና 22፡ 26 ላይ “አካዝያስ” ተብሎ ተጠርቷል ፡፡
|