Wed Jul 19 2017 12:29:46 GMT+0300 (Jordan Daylight Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2017-07-19 12:29:46 +03:00
parent 0b89cee146
commit 7a2fb903d3
7 changed files with 9 additions and 0 deletions

2
02/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\c 2 1ከዚያም ያህዌ እናደርገው ዘንድ እንደነገረን ወደኋላ ዞረን በበረሃው አቋርጠን ወደ ቀይ ባህር አቅጣጫ ሄድን፣ ለብዙ አመታትም በኤዶም ተንከራተትን፡፡
2ከዚያም ያህዌ እንዲህ አለኝ፣ 3በዚህ ተራራማ ሀገር ለረጅም ጊዜ ስትንከራተቱ ነበር፡፡ አሁን ዙሩና ወደ ሰሜን ተጓዙ፡፡

1
02/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
4ለህዝቡም የይስሃቅ ትውልዶችም በሆኑት በዔሳው ትውልዶች ምድር አቅራቢያ እየተጓዙ እንደሆነ ንገራቸው፡፡ እነርሱ በኤዶም ኮረብታማ ሀገር ይኖራሉ፡፡ እነርሱ ይፈሯችኋል፣ 5ነገር ግን ከእነርሱ ጋር መዋጋት አትጀምሩ፣ ምክንያቱም ከምድራቸው ቁራጭ ስፍራ እንኳን አልሰጣችሁም፡፡ እኔ ያንን ምድር ለዔሳው ትውልዶች ሰጥቻቸዋለሁ፡፡

2
02/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
6በምድራቸው አጠገብ ስትጓዙ፣ ከእነርሱ ምግብና ውሃ ግዟቸው፡፡
7ያህዌ አምላካችን ባደረጋችሁት ማንኛውም ነገር እንደባረካችሁ አትርሱ፡፡ በዚህ ታላቅ ምድረበዳ ስትንከራተቱ የደረሰባችሁ ምን እንደሆነ እርሱ ያውቃል፡፡ ነገር ግን በእነዚህ አርባ አመታት እርሱ ከእናተ ጋር ነበር፣ እርሱ ከእናንተ ጋር በመሆኑ የሚያስፈልጋችሁን ማንኛውንም ነገር አላጣችሁም፡፡

1
02/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
ስለዚህ ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ የዔሳው ትውልዶች በሚኖሩበት ኮረብታማ ሀገር በኩል አላለፍንም፡፡ በዮርዳኖስ ሸለቆ ሜዳ በኩል ያለውን መንገድ ትተን፣ ከጽዮን ጋብር እና ኤላት መጣን፣ ደግሞም በሞአብ በረሃማ መንገድ ተጓዝን፡፡

1
02/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
9ያህዌ እንዲህ አለኝ፣ ‹የሞአብ ሰዎችን አታስቸግሩ፣ ደግሞም ከእነርሱ ጋር መዋጋት አትጀምሩ፣ ምክንያቱም ከእነርሱ ምድር አንዳችም አልሰጣችሁም፡፡ የአብርሃም የወንድም ልጅ የሎጥ ትውልዶች መሆናቸውን አትርሱ፣ እናም እኔ የኤርን ከተማ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡›

1
02/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
10አስቀድሞ ኤሜም የሚባሉ የግዙፋን ትልቅ ወገን በዚያ ይኖሩ ነበር፡፡ እነርሱም የኤናቅ ዝርያዎች እንደነበሩት ግዙፋን ረጃጅሞች ነበሩ፡፡ 11እነርሱና የኤናቅ ዝርያዎች የራፋ ግዙፋን ተብለውም ይጠሩ ነበር፣ የሞአብ ህዝቦች ግን ኤሜም ይሏቸዋል፡፡

1
02/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
12የሆር ህዝብ ወገኖችም አስቀድሞ በኤዶም አካባቢ ኖረዋል፣ ነገር ግን የዔሳው ትውልዶች አስወጥተዋቸው ነበር፡፡ እነርሱ አሸንፈው ገደሏቸው በምድራቸውም ሰፈሩ፣ ቆይቶ የእስራኤል ሰዎች ያህዌ ከሰጣቸው ምድር ጠላቶቻቸውን እንዳባረሩ እንደዚያው አደረጉባቸው፡፡