added NT books

This commit is contained in:
Larry Versaw 2020-12-27 16:44:39 -07:00
parent f2d352de3b
commit d7aac43019
29 changed files with 15676 additions and 4 deletions

2023
41-MAT.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,2023 @@
\id MAT
\ide UTF-8
\h የማቴዎስ
\toc1 የማቴዎስ
\toc2 የማቴዎስ
\toc3 mat
\mt የማቴዎስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ መጽሐፍ፡፡
\v 2 አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅም ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብም ይሁዳንና የይሁዳን ወንድሞች ወለደ፤
\v 3 ይሁዳም ከትዕማር ፋሬስንና ዛራን ወለደ፤ ፋሬስም ኤስሮምን ወለደ፤ ኤስሮምም አራምን ወለደ፤
\s5
\v 4 አራምም አሚናዳብን ወለደ፤ አሚናዳብም ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶንም ሰልሞንን ወለደ፤
\v 5 ሰልሞንም ከረዐብ ቦዔዝን ወለደ፤ ቦዔዝም ከሩት ኢዮቤድን ወለደ፤ ኢዮቤድም እሴይን ወለደ፤ እሴይም ንጉሥ ዳዊትን ወለደ፡፡
\v 6 ንጉሥ ዳዊትም ከኦርዮ ሚስት ሰሎሞንን ወለደ፤
\s5
\v 7 ሰሎሞንም ሮበዓምን ወለደ፤ ሮብዓምም አብያን ወለደ፤ አብያም አሳፍን ወለደ፤
\v 8 አሳፍም ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥም ኢዮራምን ወለደ፤ ኢዮራምም ዖዝያንን ወለደ፤
\s5
\v 9 ዖዝያንም ኢዮአታምን ወለደ፤ ኢዮአታምም አካዝን ወለደ፤ አካዝም ሕዝቅያስን ወለደ፤
\v 10 ሕዝቅያስም ምናሴን ወለደ፤ ምናሴም አሞጽን ወለደ፤ አሞጽም ኢዮስያስን ወለደ፤
\v 11 ኢዮስያስም በባቢሎን ምርኮ ጊዜ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ፡፡
\s5
\v 12 ከባቢሎን ምርኮ በኋላም፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤
\v 13 ዘሩባቤልም አብዩድን ወለደ፤ አብዩድም ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄምም አዛርን ወለደ፤
\v 14 አዛርም ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅም አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤
\s5
\v 15 ኤልዩድም አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛርም ማታንን ወለደ፤ ማታንም ያዕቆብን ወለደ፤
\v 16 ያዕቆብም ክርስቶስ ተብሎ የሚጠራውን ኢየሱስን የወለደችውን፣ የማርያምን ባል ዮሴፍን ወለደ፡፡
\v 17 ከአብርሃም እስከ ዳዊት፣ የነበሩት ትውልዶች ሁሉ ዐሥራ አራት፤ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ድረስም እንደዚሁ ዐሥራ አራት፤ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ድረስ የነበሩትም ዐሥራ አራት ትውልዶች ናቸው፡፡
\s5
\v 18 የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በሚከተለው መንገድ ተፈጸመ፡- እናቱ ማርያም ዮሴፍን ልታገባው ታጭታ ነበር፤ ነገር ግን ሳይጋቡ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች፡፡
\v 19 ዮሴፍ ጻድቅ ነበረ፤ በመሆኑም እርሷን በሕዝብ ፊት ሊያዋርዳት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ ከእርሷ ጋር የነበረውን የዕጮኛነቱን ግንኙነት በምስጢር ለማቋረጥ ወሰነ፡፡
\s5
\v 20 ዮሴፍ ስለ እነዚህ ነገሮች እያሰበ ሳለ፣ የጌታ መልአክ፣ "የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፣ ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ፤ ምክንያቱም እርሷ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነው።
\v 21 እርሷ ወንድ ልጅ ትወልዳለች፣ ሕዝቡንም ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ" በማለት ተገለጠለት።
\s5
\v 22-23 ይህ ሁሉ የሆነው፣ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ብለው ይጠሩታል፤ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው" ብሎ ጌታ በነቢይ የተናገረው እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 24 ዮሴፍ ከእንቅልፉ ነቃ፣ የጌታ መልአክ አዝዞት እንደ ነበረውም አደረገ፡- ማርያምን እን ደሚስቱ ወሰዳት፡፡
\v 25 (ይሁን እንጂ፣ ልጅ እስከምትወልድ ድረስ ከእርሷ ጋር ግንኙነት አላደረገም፡፡) የሕፃኑንም ስም ኢየሱስ አለው፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ኢየሱስ በቤተ ልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ፣ ጠቢባን ሰዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ እንደዚህም በማለት ጠየቁ፤
\v 2 ‹‹የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ የት ነው? የእርሱን ኮከብ በምሥራቅ አየን፣ ልንሰግድለትም መጥተናል፡፡››
\v 3 ንጉሡ ሄሮድስ ይህን ሲሰማ ተረበሸ፤ መላው ኢየሩሳሌምም ከእርሱ ጋር ታወከ፡፡
\s5
\v 4 ሄሮድስ የካህናቱን አለቆችና የሕዝቡን የሕግ መምህራን ሰብስቦ፣ ‹‹ክርስቶስ የሚወለደው የት ነው? በማለት ጠየቀ፡፡
\v 5 ‹‹በቤተ ልሔም ይሁዳ›› አሉት፤ በነቢዩ የተጻፈው ይህ ነውና፡
\v 6 በይሁዳ ምድር የምትገኚ አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፣ ሕዝቡን እስራኤልን የሚጠብቅ ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልና፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም በኋላ ሄሮድስ ኮከቡ በትክክል በምን ሰዓት ታይቶ እንደ ነበር ሊጠይቃቸው ጠቢባኑን በምስጢር ጠራቸው፡፡
\v 8 ወደ ቤተ ልሔምም ላካቸው፤ ‹‹ሂዱና ሕፃኑን በጥንቃቄ ፈልጉ፡፡ ስታገኙት እኔም ደግሞ እንድመጣና እንድሰግድለት ንገሩኝ›› አላቸው፡፡
\s5
\v 9 ንጉሡ የተናገረውን ከሰሙ በኋላ ሄዱ፤ በምሥራቅ አይተውት የነበረውም ኮከብ ሕፃኑ በነበረበት ላይ እስኪደርስና እስኪቆም ድረስ በፊታቸው ይሄድ ነበር፡፡
\v 10 ጠቢባኑ ኮከቡን ባዩት ጊዜ፣ እጅግ በጣም ተደሰቱ፡፡
\s5
\v 11 ወደ ቤት ገብተው ሕፃኑንም ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት፡፡ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፣ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት፡፡
\v 12 እግዚአብሔር ጠቢባኑን ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ በሕልም አስጠነቀቃቸው፤ ስለዚህም በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ፡፡
\s5
\v 13 ጠበባኑ ከሄዱ በኋላ፣ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣ "ተነሥ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ እኔ እስክነግርም ድረስ እዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልጋልና" አለው፡፡
\v 14 በዚያ ሌሊት ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ፡፡
\v 15 ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ እዚያው ቈየ፡፡ በዚህም ጌታ፣ ‹‹ልጄን ከግብፅ ጠራሁት›› ብሎ በነቢዩ የተናገረው ቃል ተፈጸመ፡፡
\s5
\v 16 ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑ እንደ ተሣለቁበት ሲገነዘብ በጣም ተናደደ፡፡ በቤተ ልሔምና በዚያ አውራጃ የነበሩ ወንድ ሕፃናትን፣ እንደዚሁም ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን ሁሉ ከጠቢባኑ በትክክል በተረዳው ጊዜ መሠረት ልኮ አስፈጀ፡፡
\s5
\v 17 በዚያም በነቢዩ ኤርምያስ ተነግሮ የነበረው፡-
\v 18 ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፣ ልቅሶና መሪር ዋይታ፣ ራሔል ስለ ልጆቿ በማልቀስ፣ ለመጽናናትም እምቢ አለች፣ በሕይወት የተረፈ የለምና›› የሚለው ተፈጸመ፡፡
\s5
\v 19 ሄሮድስ ሲሞት፣ እነሆ፣ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ተገለጠለትና፣
\v 20 ‹‹ሕፃኑን ሊገድሉት የፈለጉት ስለ ሞቱ፣ ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ›› አለው፡፡
\v 21 ዮሴፍ ተነሣ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል አገር ሄደ፡፡
\s5
\v 22 አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ስፍራ ተተክቶ ይሁዳን ይገዛ እንደ ነበረ ሲሰማ ግን ወደዚያ ለመሄድ ፈራ፡፡ እግዚአብሔር በሕልም ካስጠነቀቀው በኋላ፣ ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ፤
\v 23 ናዝሬት በምትባል ከተማ ውስጥም ኖረ፡፡ ይህ በነቢዩ ተነግሮ የነበረውን፣ ናዝራዊ ተብሎ ይጠራል የሚለውን እንዲፈጸም አደረገ፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 በእነዚያ ቀኖች መጥምቁ ዮሐንስ በይሁዳ ምድረ በዳ ፤
\v 2 "መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ" እያለ እየሰበከ መጣ።
\v 3 በነቢዩ ኢሳይያስ፦ "ምድረ በዳ ውስጥ የሚጮኽ ሰው ድምፅ፣ የጌታን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናዎቹንም አስተካክሉ" ተብሎ የተነገረለት ይህ ነውና።
\s5
\v 4 ዮሐንስ ይለብስ የነበረው የግመል ጠጕር፣ በወገቡ የሚታጠቀውም የቆዳ ጠፍር ነው፤ ምግቡም አንበጣና የዱር ማር ነበረ።
\v 5 በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌም፣ መላው ይሁዳና በዮርዳኖስ ወንዝ ዙሪያ ያለ አገር ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
\v 6 ሕዝቡ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ እጅ ተጠመቁ።
\s5
\v 7 ነገር ግን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ብዙዎች ለመጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጡ ባየ ጊዜ፣ "እናንተ የመርዛማ እባቦች ልጆች ከሚመጣው ቊጣ ለማምለጥ ማን አስጠነቀቃችሁ?
\v 8 ለንስሐ የሚጠቅም ፍሬ ይኑራችሁ።
\v 9 ለራሳችሁም አብርሃም አባታችን አለን" ብላችሁ አታስቡ። እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳ ለአብርሃም ልጆችን ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና።
\s5
\v 10 አሁን መጥረቢያው በዛፎቹ ሥር ተቀምጦአል። ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል በእሳት ውስጥም ይጣላል።
\v 11 እኔ ለንስሐ የማጠምቃችሁ በውሃ ነው፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቃል፤ ጫማውን መሸከምም እንኳ አይገባኝም። እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።
\v 12 ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውን በጎተራ ውስጥ ለመክተት መንሹ በእጁ ነው። ገለባውን ግን ፈጽሞ በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።
\s5
\v 13 ከዚያም ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መጣ።
\v 14 ነገር ግን "እኔ አንተ እንድታጠምቀኝ ሲገባ፣ አንተ እንዴት ወደ እኔ ትመጣለህ?" በማለት ሊያስቆመው ሞከረ።
\v 15 ኢየሱስም መልሶ፣ "አሁን ይህን ፍቀድ፤ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ለእኛ ተገቢ ነውና" አለው። ከዚያም በኋላ ዮሐንስ ፈቀደለት።
\s5
\v 16 ኢየሱስ ከተጠመቀ በኋላ፣ ወዲያውኑ ከውሃ ውስጥ ወጣ፤ እነሆም ሰማያት ተከፈቱ። የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ መልክ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲቀመጥ አየ።
\v 17 እነሆ፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው። "በእርሱ እጅግ ደስ ይለኛል" የሚል ድምፅ ከሰማያት መጣ።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ከዚያም በኋላ በዲያብሎስ ሊፈተን መንፈስ ኢየሱስን ወደ ምድረ በዳ መራው፡፡
\v 2 ኢየሱስ ዐርባ ቀንና ዐርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ፡፡
\v 3 ፈታኙ ወደ እርሱ መጣና፣ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ እንጀራ እንዲሆኑ እነዚህን ድንጋዮች እዘዛቸው›› አለው፡፡
\v 4 ኢየሱስ ግን መለሰና፣ ‹‹ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል" አለው፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ ወሰደው፤ በቤተ መቅደስ ሕንጻ ዐናት ላይም አቁሞ፣
\v 6 የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፣ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ ‹እንዲጠብቁህ መላእክቱን ይልካል፣› እና ‹‹እግርህ ድንጋይ እንዳይመታው፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል›› ተብሎ ተጽፎአል አለው፡፡
\s5
\v 7 ኢየሱስም፣ ‹‹‹ጌታ አምላክህን አትፈታተን› ተብሎም ተጽፎአል›› አለው፡፡
\v 8 እንደ ገናም ዲያብሎስ ወደ አንድ ተራራ ወሰደውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ ከሙሉ ክብራቸው ጋር አሳየው፡፡
\v 9 ‹‹ብትወድቅና ብትሰግድልኝ፣ እነዚህን ሁሉ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡
\s5
\v 10 ከዚያም ኢየሱስ፣ አንተ ሰይጣን ከዚህ ሂድ! ‹ለጌታ ለአምላክህ ስገድ፣ እርሱንም ብቻ አምልክ››› ተብሎ ተጽፎአልና አለው፡፡
\v 11 ከዚያ በኋላ ዲያብሎስ ተወው፤ እነሆም፣ መላእክት መጡና ኢየሱስን አገለገሉት፡፡
\s5
\v 12 ኢየሱስ የዮሐንስን መያዝ ሲሰማ፣ ወደ ገሊላ ሄደ፡፡
\v 13 ናዝሬትን ትቶ በመሄድ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በገሊላ ባሕር አጠገብ ባለው በቅፍርናሆም ኖረ፡፡
\s5
\v 14 ይህ የሆነው፣ በነቢዩ ኢሳይያስ ተነግሮ የነበረው እንዲፈጸም ነው፤ ይኸውም፡-
\v 15 ‹‹የዛብሎን ምድርና የንፍታሌም ምድር፣ በባሕሩ አቅጣጫ፣ ከዮርዳኖስ ማዶ፣ የአሕዛብ ገሊላ!
\v 16 በጨለማ ውስጥ የኖረ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፣ በሞት ጥላና ምድር ውስጥ ለሚኖሩትም፣ ብርሃን ወጣላቸው›› የሚለው ነው፡፡
\s5
\v 17 ኢየሱስ ከዚያ ጊዜ አንሥቶ፣ ‹‹መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡
\s5
\v 18 ኢየሱስ በገሊላ ባሕር አጠገብ እየሄደ ሳለ፣ ሁለት ወንድማማቾችን አየ፤ ጴጥሮስ ተብሎ የሚጠራው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ ዓሣ አጥማጆች ስለ ነበሩ፣ ወደ ባሕሩ መረብ እየጣሉ ነበር፡፡
\v 19 ኢየሱስ፣ ‹‹ኑ፣ ተከተሉኝ፤ ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ›› አላቸው፡፡
\v 20 እነርሱም ወዲያውኑ መረባቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
\s5
\v 21 ኢየሱስ ከዚያ ዐለፍ እንዳለም ሁለት ሌሎች ወንድማማቾችን፣ የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን አየ፤ ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በጀልባ ውስጥ መረቦቻቸውን ያበጃጁ ነበር፡፡ ኢየሱስም ጠራቸው፡፡
\v 22 ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
\s5
\v 23 ኢየሱስ በምኵራቦቻቸው ውስጥ እያስተማረ፣ የመንግሥትን ወንጌልም እየሰበከና በሕዝቡ መካከል ያሉ በሁሉም የደዌና የበሽታ ዐይነት የሚሠቃዩትን እየፈወሰ በመላው ገሊላ ተዘዋወረ፡፡
\v 24 ስለ እርሱ በሶርያ ምድር ሁሉ ተወራ፤ ሕዝቡም የታመሙትን ሁሉ፣ በልዩ ልዩ ደዌና ሕመም የሚሠቃዩትን፣ በአጋንንት የተያዙትንና የሚጥል በሽታ ያለባቸውን፣ ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡
\v 25 ከገሊላ፣ ከዐሥሩ ከተሞች፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከይሁዳና ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፡፡
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ኢየሱስ ሕዝቡን ሲያይ፣ ወደ ተራራ ወጣ፤ እዚያም ሲቀመጥ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጡ።
\v 2 እንደዚህ እያለም አስተማራቸው፤
\v 3 በመንፈስ የደኸዩ የተባረኩ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።
\v 4 የሚያዝኑ የተባረኩ ናቸው፤ ይጽናናሉና።
\s5
\v 5 የዋሆች የተባረኩ ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና።
\v 6 ለጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ የተባረኩ ናቸው፤ ይጠግባሉና።
\v 7 የሚምሩ የተባረኩ ናቸው፤ ይማራሉና።
\v 8 ልበ ንጹሖች የተባረኩ ናቸው እግዚአብሔርን ያዩታልና።
\s5
\v 9 የሚያስታርቁ የተባረኩ ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።
\v 10 ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ የተባረኩ ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።
\s5
\v 11 ሰዎች ሲሰድቧችሁና ሲያሳድዷችሁ፣ ወይም በእኔ የተነሣ ክፉውን ሁሉ በእናንተ ላይ በሐሰት ሲናገሩ ብፁዓን ናችሁ።
\v 12 በሰማይ ዋጋችሁ ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፣ ሐሤትም አድርጉ። ሰዎች ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያት በዚህ መንገድ አሳድደዋቸዋልና።
\s5
\v 13 እናንተ የምድር ጨው ናችሁ፤ ጨው ጣዕሙን ካጣ፣ እንደ ገና ጨው እንዴት መሆን ይችላል? ወደ ውጭ ተጥሎ በእግር ከመረገጥ በቀር ፈጽሞ ለምንም አይጠቅምም።
\v 14 እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ የተመሠረተች ከተማ ልትሰወር አትችልም።
\s5
\v 15 ሰዎች መብራት አብርተው ቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ በቅርጫት ሥር አያስቀምጡትም።
\v 16 መልካሙን ሥራችሁን እንዲያዩና በሰማይ ያለ አባታችሁን እንዲያከብሩት መብራታችሁ እንዲሁ በሰዎች ፊት ይብራ።
\s5
\v 17 ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ የመጣሁት ልሽራቸው ሳይሆን ልፈጽማቸው ነው።
\v 18 ምክንያቱም፣ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ፣ ሁሉ እስኪፈጸምም ድረስ፣ ከሕግ እንዷ ፊደል ወይም ቅንጣት ከቶ አታልፍም ብዬ በእውነት እነግራችኋለሁ።
\s5
\v 19 እንግዲህ ከእነዚህ ትእዛዞች ትንሿን የሚሽርና ለሌሎችም እንዲሁ እንዲያደርጉ የሚያስተምር፣ በመንግሥተ ሰማይ ታናሽ ይባላል። የሚጠብቃቸውና የሚያስተምራቸው ግን በመንግሥተ ሰማይ ታላቅ ይባላል።
\v 20 ምክንያቱም፣ ጽድቃችሁ ከሕግ መምህራንና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ልቆ ካልተገኘ መንግሥተ ሰማይ ከቶ አትገቡም እላችኋለሁ።
\s5
\v 21 ለቀደሙት፣ 'አትግደል፣ የገደለ ይፈረድበታል' እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
\v 22 እኔ ግን፣ 'ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ይፈረድበታል፣ ወንድሙን፣ 'አንተ የማትረባ!' የሚለው የሸንጎ ፍርድ፣ 'ቂል' የሚለውም የገሃነመ እሳት ፍርድ ይፈረድበታል።
\s5
\v 23 እንግዲህ መባህን በመሠዊያው ላይ ልታቀርብ ከሆነና ወንድምህ አንዳች ነገር በአንተ ላይ እንዳለው ካስታወስህ፣
\v 24 መባህን በመሠዊያው ፊት ትተህ ሂድ፣ በቅድሚያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ፣ ከዚያም ተመልሰህ መጥተህ መባህን አቅርብ።
\s5
\v 25 ባላጋራህ ለዳኛው፣ ዳኛውም ለአሳሪው አሳልፎ እንዳይሰጥህና በወህኒ ውስጥ እንዳትጣል፣ ወደ ፍርድ ቤት ዐብረኸው እየሄድህ ሳለ ከሚከስስህ ባላጋራህ ጋር በፍጥነት ተስማማ።
\v 26 እውነት እነግርሃለሁ፣ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ ፈጽሞ አትወጣም።
\s5
\v 27 "አታመንዝር" እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤
\v 28 እኔ ግን፣ ሴትን ተመኝቷት የሚመለከት ሁሉ በልቡ አመንዝሯል እላችኋለሁ።
\s5
\v 29 የቀኝ ዐይንህ ቢያሰናክህል አውጥተህ ጣለው፤ መላ ሰውነትህ በገሃነም ከሚቃጠል፣ ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱ ቢጠፋ ይሻልሃልና።
\v 30 የቀኝ እጅህም ቢያሰናክልህ ቆርጠህ ጣለው፤ መላ ሰውነትህ ገሃነም ውስጥ ከሚገባ ከሰውነትህ ክፍሎች አንዱ ቢጠፋ ይሻልሃል።
\s5
\v 31 'ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ የፍቺ ማረጋገጫ ይስጣት' ተብሎአል።
\v 32 እኔ ግን፣ 'በዝሙት ምክንያት ካልሆነ በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ እንድታመንዝር ያደርጋታል፤ ከተፈታች በኋላ የሚያገባትም ምንዝርና ይፈጽማል።
\s5
\v 33 ደግሞም ለቀደሙት፣ በሐሰት አትማል፣ መሐላዎችህንም ለጌታ ስጥ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
\v 34 እኔ ግን ከቶ አትማሉ፤ በሰማይም፣ የእግዚአብሔር ዙፋን ነውና፤
\v 35 በምድርም፣ እግሩ የሚያርፍባት ናትና፤ በኢየሩሳሌምም፣ የታላቁ ንጉሥ ከተማ ናትና።
\s5
\v 36 በራሳችሁም አትማሉ፤ አንዷን ጠጕር ነጭ ወይም ጥቍር ማድረግ አትችሉምና።
\v 37 ነገር ግን ንግግራችሁ 'አዎ፣ አዎ'፣ ወይም 'አይደለም፣ አይደለም' ይሁን። ከዚህ የወጣ ሁሉ ከክፉው ነው።
\s5
\v 38 ዐይን ስለ ዐይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፣
\v 39 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ 'ክፉውን ሰው አትቃወሙት፣ ይልቁን የቀኝ ጕንጭህን ለሚመታህ ሌላውንም አዙርለት።
\s5
\v 40 ማንም ሰው ሊከስስህና ኮትህን ሊወስድ ቢመኝ፣ ካባህንም ይውሰድ።
\v 41 አንድ ምዕራፍ እንድትሄድ ማንም ሰው ቢያስገድድህ፣ ዐብረኸው ሁለት ምዕራፍ ሂድ።
\v 42 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ ከአንተ መበደር ከሚፈልገውም ፊትህን አታዙር።
\s5
\v 43 ባልንጀራህን ውደድ፣ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።
\v 44 እኔ ግን ጠላቶችህን ውደድ ለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ ብዬ እነግራችኋለሁ።
\v 45 ይኸውም በሰማያት ያለ አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው። እርሱ ፀሐይን በክፉዎችና በደጎች ላይ ያወጣል፤ ዝናብም በጻድቃንና በኅጥኣን ላይ ያዘንባል።
\s5
\v 46 የሚወድዷችሁን ብትወዱ፣ ምን ዋጋ ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ እንደዚህ ያደርጉ የለምን?
\v 47 ለወንድሞቻችሁ ብቻ ሰላምታ ብታቀርቡ፣ ከሌሎች የበለጠ የምታደርጉት ምንድን ነው? አሕዛብስ እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?
\v 48 እንግዲህ የሰማይ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተም ፍጹማን ሁኑ።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ሰዎች እንዲያዩአችሁ የጽድቅ ተግባሮቻችሁን በፊታቸው ከማከናወን ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ ከሰማይ አባታችሁ ዋጋ አታገኙም፡፡
\v 2 ስለዚህ አንተ ምጽዋት ስትሰጥ ግብዞች የሰዎችን ከበሬታ ለማግኘት በምኵራቦችና በጐዳና ላይ እንደሚያደርጉት፣ በፊትህ ጥሩንባ አታስነፋ፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
\s5
\v 3 አንተ ግን ምጽዋት ስትሰጥ፣ የቀኝ እጅህ የሚያደርገውን የግራ እጅህ እንዲያውቅ አታድርግ፤
\v 4 ይኸውም ምጽዋትህ በስውር የሚሰጥ እንዲሆንና ከዚያም በስውር የሚያይ አባትህ ዋጋህን እንዲከፍልህ ነው፡፡
\s5
\v 5 ስትጸልዩም እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ ግብዞች ሕዝብ እንዲያያቸው በምኵራቦችና በጐዳና ማእዘኖች ላይ ቆመው መጸለይ ይወዳሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
\v 6 አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ጓዳህ ገብተህ በር ዝጋና በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡
\v 7 ስትጸልይም አሕዛብ እንደሚያደርጉት ረብ የለሽ ድግግሞሽ አታድርግ፤ አሕዛብ በንግግራቸው ብዛት ምክንያት የሚሰሙ ይመስላቸዋልና፡፡
\s5
\v 8 ስለዚህ እንደ እነርሱ አትሁኑ፤ እናንተ ከመለመናችሁ በፊት ምን እንደሚያስፈልጋችሁ አባታችሁ ያውቃልና፡፡
\v 9 እንግዲህ እንደዚህ ጸልዩ፡- ‹በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ፡
\v 10 መንግሥትህ ትምጣ፡፡ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን፡፡
\s5
\v 11 የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፡፡
\v 12 በደላችንን ይቅር በለን፣ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል፡፡
\v 13 ወደ ፈተና አታግባን፣ ከክፉው አድነን እንጂ፡፡› [መንግሥት፣ ኀይል፣ ክብርም የአንተ ነውና፣ ለዘላለም፣ አሜን፡፡]
\s5
\v 14 የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ብትሉ፣ የሰማይ አባታችሁ እናንተንም ይቅር ይላችኋል፡፡
\v 15 የሰዎችን ኀጢአት ይቅር ካላላችሁ ግን፣ የሰማይ አባታችሁ የእናንተን ኀጢአት ይቅር አይልም፡፡
\s5
\v 16 ስትጾሙም ግብዞች እንደሚያደርጉት ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ እንደ ጾመኛ ለመታየት ግብዞች ፊታቸውን ያጠወልጋሉና፡፡ በእውነት እነግራችኋለሁ፣ዋጋቸውን ተቀብለዋል፡፡
\v 17 አንተ ግን ስትጾም ራስህን ተቀባ፣ ፊትሀንም ታጠብ፣
\v 18 ይኸውም፣ በስውር ላለው የሰማይ አባትህ ብቻ እንጂ ለሰዎች ጾመኛ መስለህ እንዳትታይ ነው፡፡ በስውር የሚያይ የሰማይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል፡፡
\s5
\v 19 ብልና ዝገት በሚበላውና ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት በምድር ላይ ሀብትን ለራሳችሁ አታከማቹ፡፡
\v 20 ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡
\v 21 ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛልና፡፡
\s5
\v 22 ዐይን የሰውነት መብራት ነው፡፡ ስለሆነም ዐይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን ይሞላል፡፡
\v 23 ዐይንህ ጤናማ ካልሆነ ግን፣ መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል፡፡ እንግዲህ በውስጥህ ያለው መብራት በእውነት ጨለማ ከሆነ፣ ጨለማው እንዴት ከባድ ይሆን
\v 24 ! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡
\s5
\v 25 ስለዚህ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ምን እንደምትጠጡ፡- ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን?
\v 26 አየር ላይ የሚበርሩ ወፎችን ተመልከቱ! እነርሱ እህል አይዘሩም ወይም አያጭዱም፣ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ፣ የሰማይ አባታችሁ ይመግባቸዋል፡፡ ከወፎች ይልቅ እናንተ እጅግ የሚበልጥ ዋጋ ያላችሁ አይደላችሁምን?
\s5
\v 27 ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ይገኛልን?
\v 28 ስለ ልብስስ የምትጨነቁት ለምንድን ነው?
\v 29 ነገር ግን እነግራችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ክብሩ ሁሉ ከእነዚህ አበቦች እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡
\s5
\v 30 እግዚአብሔር ዛሬ የሚታየውንና ነገ እሳት ውስጥ የሚጣለውን የሜዳ ሣር እንደዚህ ካለበሰ፣ እናንት እምነት የጐደላችሁ! እናንተንማ እንዴት እጅግ የበለጠ አያለብሳችሁም?
\v 31 እንግዲህ ‹ምን እንበላለን? ወይም ‹ምን እንጠጣለን? ወይም ‹ምን እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፡፡
\s5
\v 32 አሕዛብ እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉና፤ የሰማይ አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል፡፡
\v 33 ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡
\v 34 ስለዚህ ለነገ አትጨነቁ፤ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና፡፡ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 አትፍረዱ፥ እናንተም አይፈረድባችሁም።
\v 2 በምትፈርዱበት ፍርድ፥ ይፈረድባችኋል፤በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ፥ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል።
\s5
\v 3 በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳታስተውል፥ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ የምታየው ለምንድን ነው?
\v 4 በአንተ ዐይንህ ውስጥ ግንድ እያለ፣ በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ ማለት እንዴት ትችላለህ?
\v 5 አንተ ግብዝ! በወንድምህ ዐይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ በደንብ አይተህ ለማውጣት፣ በመጀመሪያ በራስህ ዐይን ውስጥ ያለውን ግንድ አስወግድ።
\s5
\v 6 በእግራቸው እንዳይረግጡትና እናንተንም እንዳይቦጫጭቁዋችሁ፤ ቅዱስ የሆነውን ለውሾች አትስጡ፥ እንቁዎቻችሁንም ለዐሳማዎች አትጣሉ።
\s5
\v 7 ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፥ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።
\v 8 የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና፣ የሚፈልግ ሰውም ያገኛል፥ ለሚያንኳኳም ሰው ይከፈትለታል።
\v 9 ከእናንተ መካከል ልጁ እንጀራ ሲለምነው፣ ድንጋይ የሚሰጠው፣
\v 10 ዐሣ ሲለምነው፣ እባብ የሚሰጠው? ምን ዐይነት ሰው ነው?
\s5
\v 11 እንግዲህ፥ እናንተ ክፉዎች የሆናችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ የሚኖር አባታችሁ ለሚለምኑት አብዝቶ መልካም ስጦታን እንዴት አይስጣቸውም?
\v 12 ስለዚህ፣ ማንኛውንም ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ፣ እናንተም ልታደርጉላቸው ይገባል፤ ምክንያቱም ሕጉም ነቢያቱም የሚያስተምሩት ይህንኑ ነው፡፡
\s5
\v 13 በጠባቡ በር ግቡ፣ ምክንያቱም ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ሰፊ፣ የሚሄዱበትም ብዙዎች ናቸው፡፡
\v 14 በሩ ጠባብ፣ ወደ ሕይወት የሚወስደውም መንገድ ቀጭን ስለ ሆነ፣ የሚያገኙት ጥቂቶች ናቸው፡፡
\s5
\v 15 የበግ ቆዳ ለብሰው ከሚመጡባችሁ፣ በትክክል ግን ነጣቂ ተኩላዎች ከሆኑ፣ ከሃሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ።
\v 16 በሚያፈሩት ፍሬ ታውቋቸዋላችሁ፡፡ሰው ከእሾኽ የወይን ፍሬ፣ ወይም ከኩርንችት በለስ ሊሰበስብ ይችላልን?
\v 17 እንደዚያው፥ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፣ መጥፎ ዛፍ መጥፎ ፍሬ ያፈራል።
\s5
\v 18 መልካም ዛፍ ሆኖ መጥፎ ፍሬ የሚያፈራ፣ ወይም መጥፎ ዛፍ ሆኖ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ የለም።
\v 19 ማንኛውም መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፣ ወደ እሳትም ይጣላል።
\v 20 እንግዲህ በሚያፈሩት ፍሬ ታውቋቸዋላችሁ።
\s5
\v 21 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ እንጂ፣" ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣" እያለ የሚጠራኝ ሁሉ፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚገባ አይደለም፡፡
\v 22 በዚያ ቀን ብዙዎች፣ "ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ፣ በስምህ ትንቢት ተናግረን አልነበረም እንዴ፣ በስምህ አጋንንት አስወጥተን አልነበረም እንዴ፣ በስምህስ ብዙ ታላላቅ ነገሮችን አድርገን አልነበረም እንዴ?" ይሉኛል፡፡
\v 23 እኔም፣ “እናንት ክፉ አድራጊዎች፣ የት ዐውቃችሁና ነው? ከእኔ ራቁ ብዬ በግልጽ እነግራቸዋለሁ”
\s5
\v 24 ስለዚህ፣ ቃሎቼን የሚሰማና የሚታዘዛቸው ልክ ቤቱን በድንጋይ ላይ የመሠረተ አስተዋይ ሰውን ይመስላል፡፡
\v 25 ዝናብ ዘነበ፣ ጎርፍም ጎረፈ፣ ነፋስም ነፈሰ ያንን ቤት መታው፤ ይሁን እንጂ ቤቱ በዐለት ላይ ስለ ተመሠረተ፣ አልወደቀም፡፡
\s5
\v 26 ሆኖም ቃሌን ሰምቶ የማይታዘዝ፣ ቤቱን በአሸዋ ላይ የመሠረተ ሞኝ ሰውን ይመስላል፡፡
\v 27 ዝናብ ዘነበ፣ ጎርፍ ጎረፈ፣ ነፋስም ነፈሰ፣ ያንንም ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም ከባድ ሆነ ።
\s5
\v 28 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናግሮ ሲጨርስ፣ ሕዝቡ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
\v 29 ያስተማረውም እንደ ባለስሥልጣን እንጂ ፣እንደ ጽሐፍት አልነበረም።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ኢየሱስ ከተራራው በወረደ ጊዜ፣ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።
\v 2 እነሆ፣ አንድ ለምጻም ወደ እርሱ መጣ፣ “ጌታ ሆይ፣ ፈቃደኛ ከሆንህ፣ ልታነጻኝ ትችላለህ” በማለት በፊቱ ሰገደለት።
\v 3 ኢየሱስም፣ “ፈቃደኛ ነኝ ንጻ” በማለት እፉን ዘርግቶ ዳሰሰው። ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።
\s5
\v 4 ኢየሱስ፣ “ተጠንቀቅ! ለማንም አትናገር። ዝም ብለህ ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ፣ምስክር እንዲሆናቸውም ሙሴ ያዘዘውን ስጦታ አቅርብ”አለው።
\s5
\v 5 ኢየሱስ ወደቅፍርናሆም በገባ ጊዜ፣ አንድ የመቶ አለቃ ወደ እርሱ መጥቶ፣
\v 6 ጌታ ሆይ፣ "አገልጋዬ በከባድ ሕመም ሽባ ሆኖ ቤቴ ተኝቷል" በማለት ለመነው።
\v 7 ኢየሱስ፣ "መጥቼ እፈውሰዋለሁ” አለው።
\s5
\v 8 የመቶ አለቃውም መልሶ፣“ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝም፣ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር አገልጋዬም ይፈወሳል” አለው፡፡
\v 9 እኔ ደግሞ ከሌላው ሥልጣን ሥር ያለሁና በእኔም ሥልጣን ሥር ወታደሮች ያሉኝ ሰው ነኝ። አንዱን “ሂድ” ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም “ና” ብለው ይመጣል፣ አገልጋዬንም 'ይህን አድርግ' ብለው ያደርጋል"፡፡
\v 10 ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ በጣም ተደነቀ፣ ይከተሉት ለነበሩት ሰዎችም “እውነት ነው የምነግራችሁ፣ በእስራኤል እንኳ እንደዚህ ያለ ትልቅ እምነት አላገኘሁም” አላቸው፡፡
\s5
\v 11 እነግራችኋለሁ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ፣ በእግዚአብሔር መንግሥትም ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር በማዕድ ይቀመጣሉ።
\v 12 የመንግሥት ልጆች ግን ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ ውጪው ጨለማ ይጣላሉ፡፡
\v 13 ኢየሱስም የመቶ አለቃውን፣ “ሂድ! እንደ እምነትህ ይሁንልህ" አለው። አገልጋዩም በዚያው ሰዓት ተፈወሰ ፡፡
\s5
\v 14 ኢየሱስ ወደ ጴጥሮስ ቤት በገባ ጊዜ የጴጥሮስን አማት በትኩሳት ታማ ተኝታ አገኛት።
\v 15 ኢየሱስ እጅዋን ነካት፣ ትኩሳቱም ለቀቃት፣ ተነሥታም ታገለግለው ጀመር።
\s5
\v 16 በመሸ ጊዜ፣ ሕዝቡ አጋንንት የያዙአቸውን ብዙዎችን ወደ ኢየሱስ አመጡ፣ እርሱም በቃሉ፣ መናፍስቱን አስወጣቸው፤ ታመው የነበሩትንም ሁሉ ፈወሳቸው።
\v 17 በዚህ ዐይነት፣ በነቢዩ ኢሳይያስ፣ “እርሱ ሕመማችንን ተቀበለ ደዌዎቻችንን ተሸከመ” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ።
\s5
\v 18 ኢየሱስም በዙሪያው ያሉትን ሕዝብ ባየ ጊዜ፣ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።
\v 19 ከዚያም አንድ ጸሐፊ ወደ እርሱ ቀርቦ፣ “መምህር ሆይ፣ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።
\v 20 ኢየሱስም "ቀበሮዎች ጉድጓድ የሰማይ ወፎችም ጎጆዎች አሏቸው። የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያሳርፍበት ምንም ስፍራ የለውም"አለው።
\s5
\v 21 ከደቀመዛሙርቱም ሌላው፣ "ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ እንድሄድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ አለው።"
\v 22 ኢየሱስ ግን፣ “ተከተለኝ፣ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው” አለው።
\s5
\v 23 ኢየሱስ ወደ ጀልባ በገባ ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱም ተከትለውት ገቡ።
\v 24 እነሆም፣ በባሕሩ ላይ ታላቅ ማዕበል ተነሥቶ ጀልባዋ በማዕበል ተሸፈነች። ኢየሱስ ግን ተኝቶ ነበር።
\v 25 ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ መጥተው፣ "ጌታ ሆ፣ እድነን ልንጠፋ ነው" በማለት ቀሰቀሱት።
\s5
\v 26 ኢየሱስ፣ "እናንተ እምነት የጐደላችሁ ስለምን ፈራችሁ?”አላቸው። ከዚያም ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠፀ፣ ከዚያ በኋላ ታላቅ ጸጥታ ሆነ።
\v 27 ሰዎቹም ተገርመው፣ "ይህ ምን ዓይነት ሰው ነው? ነፋሳትና ባሕሩም እንኳ ይታዘዙለታል" አሉ።
\s5
\v 28 ኢየሱስም ወደ ማዶ ወደ ጌርጌሴኖን አገር በመጣ ጊዜ፣ አጋንንት የተቆጣጠራቸው ሁለት ሰዎች ተገናኙት። የመጡትም ከመቃብር ነበርና በዚያ ማንም ማለፍ እስከማይችል ድረስ በጣም ኅይለኞች ነበሩ።
\v 29 እነሆም፣ እየጮኹ፣ "አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ሆይ፣ እኛ ከአንተ ምን ጉዳይ አለን? ጊዜው ሳይደርስ ልታሠቃየን ወደዚህ መጣህን?" አሉ።
\s5
\v 30 ከዚያ አካባቢ ብዙ ሳይርቅ በግጦሽ ላይ ያሉ ብዙ ዐሳማዎች ነበሩ።
\v 31 አጋንንቱም ኢየሱስን፣ "የምታወጣን ከሆነ ወደዚያ የዐሳማዎች መንጋ ስደደን" ብለው መለመናቸውን ቀጠሉ።
\v 32 ኢየሱስም፣ "ሂዱ!"አላቸው። አጋንንቱም ወጥተው ዐሳማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፣ የዐሳማዎቹ መንጋ ሁሉ ወደ ታች ቁልቁለቱን እየተጣደፉ ወደ ባሕሩ ወርደው ውሃው ውስጥ ገብተው ጠፉ፡፡
\s5
\v 33 እነዚያም ዐሳማዎቹን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች ሸሽተው ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ሁሉ ፣ በአጋንንት ተይዘው ስለ ነበሩት ሰለ ሁሉቱ ሰዎችም አወሩ።
\v 34 የከተማውም ሕዝብ ሁሉ ኢየሱስን ለማየት መጡ። ባዩትም ጊዜ አካባቢያቸውን ለቆ አንዲሄድ ለመኑት።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ኢየሱስ ወደ ጀልባ ገባ፤ ባሕሩንም አቋርጦ ወደ ገዛ ከተማው መጣ።
\v 2 እነሆ፣ በምንጣፍ የተኛ አንድ ሽባ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፣ አይዞህ፤ ኅጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው፡፡
\s5
\v 3 አንዳንድ ጸሐፍት ግን እርስ በርሳቸው፣ "ይህ ሰው እኮ እየተሳደበ ነው" ተባባሉ ።
\v 4 ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ፣ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?”
\v 5 ለመሆኑ የሚቀለው፣'ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል' ነው፣ ወይስ 'ተነሣና ሂድ ማለት ነው?'
\v 6 ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ዕወቁ" አለ፡፡ ሽባውንም፣ "ተነሣና፣ምንጣፍህን ይዘህ ወደ ቤት ሂድ" አለው፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም ሰውየው ተነሥቶ ወደ ቤቱ ሄደ።
\v 8 ሕዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ ተገርመው፣ ለሰው እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
\v 9 ኢየሱስም ከዚያ አለፍ እንዳለ፣ ማቴዎስ የሚባለውን ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያ ቦታ ላይ ተቀምጦ አየውና "ተከተለኝ" አለው።እርሱም ተነሥቶ ተከተለው፡፡
\s5
\v 10 ኢየሱስም በቤቱ ውስጥ ለመመገብ በተቀመጠ ጊዜ፣ ቀረጥ የሚሰበስቡ ብዙ ሰዎችና ኃጢአተኞች መጥተው፣ ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርት ጋር አብረው ተመገቡ።
\v 11 ፈሪሳውያንም ይህን ሲያዩ፣ደቀ መዛሙርቱን "ለምንድን ነው መምህራችሁ፣ ከግብር ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላው?" አሏቸው፡፡
\s5
\v 12 ኢየሱስም ይህንን ሲሰማ ፣"ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፡፡
\v 13 'ሂዱና' ምሕረት እንጂ መሥዋዕትን አልፈልግም' የሚለውን ተማሩ፣ እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኅጥአንን ወደ ንስሓ ለመጥራት" ነው አለ።
\s5
\v 14 ከዚያም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣" እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ እንጾማለን ፣የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?" አሉት።
\v 15 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ሰርገኞች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሆኖም ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፣በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ።
\s5
\v 16 ማንም ሰው በአሮጌ ልብስ ላይ ዐዲስ ቊራጭ ጨርቅ አይለጥፍም፤ ምክንያቱም አሮጌውን ልብስ ይቦጭቀዋል፣ ልብሱም የባሰ ይጐዳል።
\s5
\v 17 ሰዎች ዐዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ውስጥ አያስቀምጡም፤ እንደዚያ ካደረጉ አቁማዳው ይፈነዳል፣ የወይን ጠጁ ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይቀደዳል። ይልቁንም ዐዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ውስጥ ያስቀምጡታል፣ ሁለቱም ይጠበቃሉ፡፡"
\s5
\v 18 ኢየሱስ ይህን እየተናገራቸው እያለ፣ አንድ ሹም እየሰገደ ወደ እርሱ መጣ። “ልጄ አሁን ገና ሞተች፣ ነገር ግን ና ና እጅህን ጫንባት በሕይወትም ትኖራለች አለው”።
\v 19 ኢየሱስም ተነሥቶ ተከትሎት ሄደ፤ ደቀ ዛሙርቱም ደግሞ አብረውት ሄዱ።
\s5
\v 20 አንዲት ለዐሥራ ሁለት ዓመት ከባድ የደም መፍሰስ የነበረባት ሴት፣ ከኢየሱስ ኋላ መጥታ የልብሱን ጠርዝ ነካች፤
\v 21 "የልብሱን ጫፍ ብቻ ብነካ ደኅና እሆናለሁ" ብላ ነበርና።
\v 22 ኢየሱስም ዞር ብሎ አያትና፣ “ልጄ ሆይ፣ አይዞሽ እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴቲቱም ወዲያውኑ ደኅና ሆነች።
\s5
\v 23 ኢየሱስም ወደ ሹሙ ቤት በገባ ጊዜ፣ዋሽንት የሚነፉትንና የሚንጫጩትን አይቶ፣
\v 24 "ወደዚያ ዞር በሉ፣ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም"አላቸው። እነርሱ ግን በማፌዝ ሳቁበት።
\s5
\v 25 ሕዝቡን ወደ ውጭ ባስወጡ ጊዜ፥ ኢየሱስ ወደ ክፍሉ ገብቶ እጅዋን ያዘ፤ልጅቱም ተነሣች።
\v 26 ወሬውም በዚያ አካባቢ ሁሉ ተዳረሰ።
\s5
\v 27 ኢየሱስም በዚያ ሲያልፍ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች ተከተሉት፣ ያለ ማቋረጥም፣ "የዳዊት ልጅ ማረን!" እያሉ ይጮኹ ነበር።
\v 28 ኢየሱስም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ፣ ዐይነ ስውሮቹ ወደ እርሱ መጡ። ኢየሱስም፣ "ይህን ለማድረግ እንደምችል ታምናላችሁ?" አላቸው። እነርሱም "አዎን፣ ጌታ ሆይ" አሉት፡፡
\s5
\v 29 ከዚያም ኢየሱስ ዐይኖቻቸውን ዳስሶ፣ "እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ" አላቸው።
\v 30 ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ። ከዚያም ኢየሱስ፣"ይህንን ማንም እንዳያውቅ" ብሎ በጥብቅ አዘዛቸው።
\v 31 ሁለቱ ሰዎች ግን ሄደው ወሬውን በየቦታው አዳረሱት።
\s5
\v 32 ሁለቱ ሰዎች እየሄዱ እያሉ እነሆ፣ በጋኔን የተያዘ ዲዳ ወደ ኢየሱስ አመጡ።
\v 33 ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ። ሕዝቡም ተገርመው፣ "እንዲህ ያለ ከዚህ በፊት በእስራኤል አልታየም" አሉ።
\v 34 ፈሪሳውያን ግን "አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው" ይሉ ነበር።
\s5
\v 35 ኢየሱስ ወደ ከተሞችና መንደሮች ሁሉ ሄደ፣ በየምኩኲራቦቻቸውም ማስተማሩን፣ የመንግሥትን ወንጌል መስበኩንና፣ ማንኛውንም ዐይነት በሽታና ደዌ መፈወሱን ቀጠለ።
\v 36 ሕዝቡንም ሲያይ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ነበርና ራራላቸው።
\s5
\v 37 ለደቀ መዛሙርቱም፣ "መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂት ናቸው።
\v 38 ስለዚህ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ፣ ወደ መከሩ ጌታ አጥብቃችሁ ጸልዩ" አላቸው።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ሁለቱን ደቀ መዛሙርት በአንድ ላይ ጠርቶ፣ ርኩሳን መናፍስትን እንዲያወጡ፣ ሁሉንም ዐይነት በሽታና ደዌ እንዲፈውሱ ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 2 የዐስራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ የመጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖንና ወንድሙ እንድርያስ፣ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብና ወንድሙ ዮሐንስ፣
\v 3 ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፣ ቶማስና ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ፣
\v 4 ቀነናዊው ስምዖን፣አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ።
\s5
\v 5 ኢየሱስ እነዚህን ዐሥራ ሁለቱን "አሕዛብ ወደሚኖሩበት የትኛውም ቦታ አትሂዱ፤ ወደ የትኛውም የሳምራውያን ከተማ አትግቡ።
\v 6 ከዚያ ይልቅ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት በጐች ሂዱ።
\v 7 መንግሥተ ሰማይ ቀርባለች፣ ብላችሁ ስበኩ" ብሎ አስተምሮ ላካቸው።
\s5
\v 8 ሕሙማንን ፈውሱ፣ ሙታንን አስነሡ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትንም አስወጡ፣ በነጻ ተቀብላችኋል በነጻ ስጡ።
\v 9 በቦርሳችሁ ወርቅ ብር ወይም ናስ አትያዙ፤
\v 10 ለሠራተኛ ቀለቡ የሚገባው ስለ ሆነ፣ ለመንገዳችሁ ሻንጣ ወይም ትርፍ ልብስ፣ ወይም ጫማ፣ ወይም በትር አትያዙ።
\s5
\v 11 ወደ የትኛውም ከተማ ወይም መንደር ስትገቡ፣ በዚያ ተገቢ የሆነው ሰው ማን እንደሆን እወቁ፤ ለቃችሁ እስከምትሄዱ ድረስ በዚያው ቆዩ።
\v 12 ወደ ቤት ስትገቡ፣ ሰላምታ ስጡ።
\v 13 ቤቱ የሚገባው ከሆነ ሰላማችሁ ይደርሰዋል፤ የማይገባው ከሆነ ግን ሰላማችሁ ይመለስላችኋል።
\s5
\v 14 እናንተን የማይቀበላችሁን፣ ወይም ቃላችሁን የማይሰማውን በተመለከተ ግን፣ ከዚያ ቤት ወይም ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን አቧራ አራግፉ።
\v 15 እውነት እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ይቀልላቸዋል።
\s5
\v 16 ተመልከቱ፣ እንደ በጎች በተኲላዎች መካከል እልካችኋለሁ። ስለዚህ፣ እንደ እባብ ብልኆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።
\v 17 ከሰዎች ተጠበቁ፣ ወደ ፍርድ ሸንጎ ያቅርቧችኋል፣ በምኲራባቸውም ይገርፏችኋል።
\v 18 ለእነርሱና ለአሕዛብ ምስክር እንዲሆን፣ በእኔም ምክንያት ወደ ገዥዎችና ነገሥታት ፊት ትቀርባላችሁ።
\s5
\v 19 ለፍርድም ሲያቀርቧችሁ፣ በዚያች ሰዓት የምትናገሩት ስለሚሰጣችሁ፣ ምን ወይም እንዴት እንደምትናገሩ አትጨነቁ።
\v 20 በእናንተ ውስጥ የሚናገረው የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ የምትናገሩት እናንተ አይደላችሁም።
\s5
\v 21 ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን፣ ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ተነሥተው ያስገድሏቸዋል።
\v 22 ከስሜ የተነሣ በሰው ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ ነገር ግን ማንም እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል።
\v 23 በዚህች ከተማ በሚያሳድዷችሁ ጊዜ ወደሚቀጥለው ከተማ ሽሹ። እውነት እላችኋለሁ፣ የሰው ልጅ ከመምጣቱ በፊት፣ የእስራኤልን ከተሞች አታዳርሱም።
\s5
\v 24 ደቀ መዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ወይም አገልጋይ ከጌታው በላይ አይደለም።
\v 25 ለደቀ መዝሙር ልክ እንደ መምህሩ፣ ለአገልጋይም ልክ እንደ ጌታው መሆን ይበቃዋል።
\s5
\v 26 እንግዲህ አትፍሯቸው፤ የማይገለጥ የተሰወረ፣ የማይታወቅ የተደበቀ ምንም የለም።
\v 27 በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን፣ በሹክሹክታ የምትሰሙትንም በአደባባይ ተናገሩት፡፡
\s5
\v 28 ሥጋን እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ከዚያ ይልቅ ነፍስንም፣ ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ፍሩ፡፡
\v 29 ሁለት ድንቢጦች በትንሽ ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ሆኖም አንዷም ብትሆን አባታችሁ ሳያውቅ በመሬት ላይ አትወድቅም፡፡
\v 30 የእናንተ ግን የራሳችሁ ጠጉር እንኳን ሳይቀር የተቈጠረ ነው፡፡
\v 31 አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ፡፡
\s5
\v 32 ስለዚህ በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ፣ እኔም በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፡፡
\v 33 በሰው ፊት የሚክደኝን ግን፣ እኔም ደግሞ በሰማይ ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ፡፡
\s5
\v 34 በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ፣ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም፡፡
\v 35 ሰውን በአባቱ ላይ፣ ሴት ልጅን በእናቷ ላይ፣ ምራትን በአማቷ ላይ ለማነሣሣት መጥቻለሁ፡፡
\v 36 የሰውም ጠላቶቹ የገዛ ቤተ ሰቦቹ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 37 አባትን ወይም እናትን ከእኔ የበለጠ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም፤ እንዲሁም ወንድ ልጅን፣ ወይም ሴት ልጅን ከእኔ የበለጠ የሚወድ ለእኔ የተገባ አይደለም።
\v 38 መስቀሉን ተሸክሞ፣ ከኋላዬ የማይከተለኝ የእኔ ሊሆን አይገባውም፡፡
\v 39 ሕይወቱን የሚያገኛት ያጣታል፤ ስለ እኔ ብሎ ሕይወቱን የሚያጣት ግን ያገኛታል፡፡
\s5
\v 40 እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፡፡
\v 41 ነቢይ ስለ ሆነ ነቢይን የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል፤ ጻድቅ ስለ ሆነ ጻድቅን የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል፡፡
\s5
\v 42 እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ታናናሾች ለአንዱ፣ ደቀ መዝሙሬ ስለ ሆነ፣ አንድ ብርጭቆ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳ የሚሰጥ ማንም፣ በምንም ዐይነት ዋጋውን አያጣም፡፡
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፣ ኢየሱስ አሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት አዝዞ ከጨረሰ በኋላ፣ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ከዚያ ሄደ፡፡
\v 2 ዮሐንስ በወህኒ ቤት ሆኖ የክርስቶስን ሥራዎች በሰማ ጊዜ፣ በደቀ መዛሙርቱ መልእክት ላከበት፡፡
\v 3 እንዲህም አለው፣ "የሚመጣው አንተ ነህ፣ ወይስ መጠበቅ ያለብን ሌላ ሰው አለ?"
\s5
\v 4 ኢየሱስም መለሰ እንዲህም አላቸው፤ “ሂዱና፣ ለዮሐንስ የምታዩትንና የምትሰሙትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፤
\v 5 ዕውሮች ብርሃናቸውን እያገኙ፣ አንካሶች እየተራመዱ፣ ለምጻሞች እየነጹ፣ መስማት የተሳናቸው እየሰሙ፣ ሙታን እየተነሡ፣ ድኾችም የምሥራች እየሰሙ ነው፡፡
\v 6 በማንኛውም ሁኔታ በእኔ የማይሰናከል ሁሉ የተባረከ ነው" ።
\s5
\v 7 እነዚህ ሰዎች እንደ ሄዱ፣ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ መናገር ጀመረ፣ እንዲህም አለ፣ "ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? ነፋስ የሚያወዛውዘውን ሸምበቆን?
\v 8 ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ? የሚያምር ልብስ የለበሰውን? በርግጥ፣ ጥሩ ልብስ የሚለብሱ የሚኖሩት በቤተ መንግሥት ነው፡፡
\s5
\v 9 ግን ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን ነውን? አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ከነቢይም የሚበልጠውን ነው፡፡
\v 10 እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ስለ እርሱ ነው፦ 'መንገድህን የሚያዘጋጅ መልእከተኛዬን በፊትህ እልካለሁ፡፡'
\s5
\v 11 እውነት እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም። በመንግሥተ ሰማይ ግን፣ ታናሹ ሰው ከእርሱ ይበልጣል፡፡
\v 12 ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት በዐመፅ ትቸገራለች፣ ዐመጸፀኞች ግን በኅይል ይወስዷታል፡፡
\s5
\v 13 እስከ ዮሐንስ ዘመን ድረስ ሕጉም፣ ነቢያቱም ሁሉ ትንቢት ሲናገሩ ነበርና፡፡
\v 14 እንግዲህ ልትቀበሉት ፈቃደኞች ከሆናችሁ፣ የሚመጣው ኤልያስ እርሱ ነው፡፡
\v 15 የሚሰማ ጆሮ ያለው፣ ይስማ።
\s5
\v 16 ይህን ትውልድ ከምን ጋር ላነጻጽረው? በገበያ ተቀምጠው፣ እየተቀባበሉ እንደሚዘፍኑ ልጆች ነው፡፡
\v 17 'ዋሽንት ነፋንላችሁ፣ አልጨፈራችሁም፤ ሙሾ አወጣንላችሁ እናንተም አላለቀሳችሁም' ይላሉ።
\s5
\v 18 ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላና የወይን ጠጅ ሳይጠጣ በመምጣቱ፣'ጋኔን አለበት' አሉት።
\v 19 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ በመምጣቱ፣ 'ተመልከቱ ይህ ሰው በላተኛና ጠጪ፣ የቀረጥ ሰብሳቢዎችና፣ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነው!' አሉት ነገር ግን ጥበብ በሥራዋ ትክክል ሆነች፡፡
\s5
\v 20 ኢየሱስም ብዙ ታላላቅ ሥራዎች ያደረገባቸውን ከተማዎች፣ ንስሓ ባለመግባታቸው ይገሥጻቸው ጀመር፡፡
\v 21 ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተሳይዳ! በእናንተ የተደረጉት ታላላቅ ሥራዎች በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ ማቅ ለብሰውና፥ ዐመድ ነስንሰው ድሮ ንስሓ በገቡ ነበር፡፡
\v 22 ነገር ግን በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ፣ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል፡፡
\s5
\v 23 አንቺ ቅፍርናሆም፣ እስከ ሰማይ የወጣሽ ይመስልሻልን? በፍጹም፤ ወደ ሲኦል ትወርጂያለሽ፡፡ ለአንቺ እንደተደረጉት ትልልቅ ነገሮች በሰዶም ተደርገው ቢሆን ፣ እስከ አሁን በኖረች ነበር፡፡
\v 24 ነገር ግን እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን፣ ከእናንተ ይልቅ ለሰዶም ይቀልላታል፡፡
\s5
\v 25 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፣ ይህን ከዐዋቂዎችና ከአስተዋዮች ሰውረህ እንደ ሕፃናት ላልተማሩት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።”
\v 26 አዎ፣ አባት ሆይ፣ በፊትህ እጅግ ደስ የሚያሰኝህ ይህ ሆኖአልና፡፡
\v 27 ከአባቴ ሁሉ ተሰጥቶኛል፣ ከአባት በቀር ማንም ልጅን የሚያውቀው የለም፤ ከልጅም በቀር፣ ልጁም ሊገልጥለት ከሚፈልገው በቀር፣ አባትን የሚያውቅ ማንም የለም፡፡
\s5
\v 28 እናንተ ደካሞች፣ ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋላሁ፡፡
\v 29 ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህና በልቤ ትሁት ነኝ፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡፡
\v 30 ቀንበሬ ቀላል፣ ሸክሜም የማይከብድ ነው፡፡
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በሰንበት በእርሻ መካከል ሄደ። ደቀ መዛሙርቱም ተርበው ስለ ነበር፣ እሸቱን እየቀጠፉ ይበሉ ጀመር፡፡
\v 2 ፈሪሳውያንም ያንን ባዩ ጊዜ፣ “ኢየሱስን፣ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት የሚያደርጉትን የማይገባ ነገር ተመልከት” አሉት፡፡
\s5
\v 3 ኢየሱስ ግን፣ "ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በተራቡ ጊዜ ያደረገውን ከቶ አላነበባችሁምን?
\v 4 ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፣ ለካህናት ብቻ እንጂ ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ያልተፈቀደውን የተቀደሰ እንጀራ እንዴት እንደበላ?" አላቸው።
\s5
\v 5 በሰንበት ካህናት በቤተ በመቀደስ ሥራ እንድሚሠሩና፣ ሰንበትን እንደሚያረክሱ፣ በደልም እንደማይሆንባቸው ከሕጉ አላነበባችሁምን?
\v 6 እኔ ግን እላችኋለሁ፣ ከቤተ መቅደስ የሚበልጠው እዚህ አለ፡፡
\s5
\v 7 “መሥዋዕትን ሳይሆን ምሕረትን እፈልጋለሁ” የሚለውን ብታውቁ ኖሮ፣ በደል የሌለባቸውን አትፈርዱባቸውም ነበር፡፡
\v 8 የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነውና።"
\s5
\v 9 ከዚያም ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ፣ ወደ ምኲራባቸው ገባ።
\v 10 እነሆ፣ እጁ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ነበረ፡፡ ፈሪሳውያንም ኢየሱስን በኅጢአት ለመክሰስ፣ "ሕጉ በሰንበት መፈወስን ይፈቅዳልን?" ብለው ጠየቁት፡፡
\s5
\v 11 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ከእናንተ መካከል አንድ በግ ብቻ ብትኖረውና፣ ያቺም በግ ጉድጓድ ውስጥ ብትገባበት፣ በሰንበት የማያወጣት ማን ነው?
\v 12 ታዲያ ሰውማ ፣ ከበግ ይልቅ ምን ያህል ዋጋ ይኖረዋል! ስለዚህ በሰንበት መልካም መሥራት ተፈቅዷል ፡፡"
\s5
\v 13 ከዚያም ኢየሱስ፣ ሰውየውን፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው፡፡ እጁንም ዘረጋ፣ እንደ ሌላውም እጅ ጤነኛ ሆነ፡፡
\v 14 ነገር ግን ፈሪሳውያን ሄደው አሤሩበት፣ እርሱን የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ኢየሱስ ይህን እንዳወቀ፣ ከዚያ ፈቀቅ አለ። ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸው፡፡
\v 16 ሰዎቹን ስለ እርሱ ለሌሎች እንዳይገልጹ አዘዛቸው፣
\v 17 ይህም የሆነው በነቢዩ በኢሳይያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው እንዲፈጸም ነው፤
\s5
\v 18 እነሆ፣ እኔ የመረጥኩት አገልጋዬ፤ የምወደው ነፍሴም ደስ የተሰኘችበት። መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ፍትሕን ለአሕዛብ ያውጃል።
\s5
\v 19 አይጨቃጨቅም ወይም አይጮህም፤ ወይም ማንም ድምፁን በጐዳናዎች ላይ አይሰማም።
\v 20 ፍርድን ለድል እስኪያበቃ ድረስ፤ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤሰውንም የጧፍ ክር አያጠፋም፣
\v 21 አሕዛብም በስሙ ይታመናሉ።"
\s5
\v 22 ከዚያም በአጋንንት የተያዘን ዐይነ ስውርና ዲዳ ሰው ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም ፈወሰው፤ ዲዳውም ተናገረ፣ አየም።
\v 23 ሕዝቡም በመገረም፣ "ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆን እንዴ?" አሉ፡፡
\s5
\v 24 ነገር ግን ፈሪሳውያን ይህን ተአምር በሰሙ ጊዜ “ይህ ሰው በአጋንንት አለቃ በብዔልዜቡል ካልሆነ በቀር አጋንንቱን አያወጣም ነበር" አሉ፡፡
\v 25 ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ ፣“እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ይወድቃል፤ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማ ወይም ቤት ሁሉ አይጸናም፡፡
\s5
\v 26 ሰይጣን ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፣ እርስ በርሱ ተከፋፍሏል፣ መንግሥቱስ እንዴት ይቆማል?
\v 27 እኔ አጋንንትን የማወጣው በብዔልዜቡል ከሆነ፣ ተከታዮቻችሁ በማን ሊያወጡ ነው? ከዚህ የተነሣ እነርሱው ይፈርዱባችኋል፡፡
\s5
\v 28 ነገር ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆነ፣ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥታለች፡፡
\v 29 ማንም ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ቤቱ ገብቶ ንብረቱን እንዴት መዝረፍ ይችላል?፡፡ ካሰረው በኋላ ግን፣ ንብረቱን ይዘርፋል።
\v 30 ከእኔ ጋር ያልሆነ ተቃዋሚዬ ነው፣ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል፡፡
\s5
\v 31 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ማንኛውም ኅጢአትና ስድብ ለሰዎች ይቅር ይባልላቸዋል ፤መንፈስ ቅዱስን የሚሳደብ ግን ይቅር አይባልም፡፡
\v 32 በሰው ልጅ ላይ ማንኛውንም ቃል የሚናገር ይቅር ይባልለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚናገር ግን፣ በዚህ ዓለምም ሆነ በሚመጣው ይቅር አይባልም።
\s5
\v 33 እንግዲህ ዛፍ የሚታወቀው በፍሬው ስለ ሆነ ዛፉን መልካም አድርጉ፤ ፍሬውም መልካም ይሆናል፣ ወይም ዛፉን መጥፎ አድርጉ ፍሬውም መጥፎ ይሆናል፡፡
\v 34 እናንተ የእባብ ልጆች ክፉዎች ስለ ሆናችሁ፣ እንዴት መልካም ልትናገሩ ትችላላችሁ? ምክንያቱም በልብ ውስጥ የሞላውን አፍ ይናገረዋል፡፡
\v 35 . መልካም ሰው በልቡ ውስጥ ካለው መልካም መዝገብ፣ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ልቡ ውስጥ ካለው ክፉ መዝገብ ክፉውን ይወጣል።
\s5
\v 36 ለእናንተም እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ሰዎች ስለ ተናገሯቸው ከንቱ ንግግሮች መልስ ይሰጣሉ፡፡
\v 37 ምትናገሩት ትጸድቃላችሁ፣ በምትናገሩትም ይፈረድባችኋልና፡፡
\s5
\v 38 አንዳንድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን መልሰው ኢየሱስን፣ “መምህር ሆይ፣ ምልክት እንድታሳየን እንፈልጋለን" አሉት።
\v 39 ኢየሱስ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፣ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይፈልጋል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ምንም አይሰጠውም፡፡
\v 40 ዮናስ በትልቅ ዐሣ ሆድ ውስጥ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፣ የሰው ልጅም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በምድር ልብ ውስጥ ይሆናል፡፡
\s5
\v 41 የነነዌ ሰዎች በዮናስ ስብከት ንስሓ በመግባታቸው፣ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፡፡ ደግሞም ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ፡፡
\s5
\v 42 የደቡብ ንግሥት፣ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻዎች መጥታለችና፣ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፡፡ደግሞም ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ፡፡
\s5
\v 43 ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ፣ ዕረፍት ፍለጋ ውሃ በሌለባቸው ቦታዎች ያልፋል፣ ነገር ግን አያገኝም።
\v 44 ከዚያም፣ 'ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ' ይላል። ሲመለስም ቤቱ ጸድቶ ተዘጋጅቶ ያገኘዋል፡፡
\v 45 ከዚያም ይሄድና ከእርሱ ይልቅ የከፉትን ሰባት ሌሎች መናፍስትን ይዞ ይመጣል፣ ሁሉም በዚያ ለመኖር ይመጣሉ፡፡ የዚያም ሰው የመጨረሻው ሁኔታ ከመጀመሪያው የከፋ ይሆናል፡፡ በዚህ ክፉ ትውልድ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ ነው፡፡
\s5
\v 46 ኢየሱስም ለሕዝቡ እየተናገረ እያለ፣ እናቱና ወንድሞቹ ሊያናግሩት ፈልገው፣ በውጭ ቆመው ነበር።
\v 47 አንድ ሰውም፣ "እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ሊያነጋግሩህ በውጭ ቆመዋል" አለው።
\s5
\v 48 ኢየሱስም መልሶ ለነገረው ሰው፣ "እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?" አለው።
\v 49 ከዚያም እጁን ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዘርግቶ፣ "እናቴና ወንድሞቼ እነዚህ ናቸው!
\v 50 በሰማይ ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፣ ወንድሜ፣ እኅቴ እናቴም ነውና" አለ።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በዚያ ቀን ኢየሱስ ከቤት ወጥቶ በባሕር ዳርቻ ተቀመጠ።
\v 2 በጣም ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰበሰቡ፣ ስለዚህ ጀልባ ውስጥ ገብቶ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ቆመው ነበር።
\s5
\v 3 ከዚያም ኢየሱስ በምሳሌ ብዙ ነገር ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ "ዘሪ ለመዘራት ወጣ።
\v 4 ሲዘራም፣ አንዳንዱ ዘር በመንገድ አጠገብ ወድቆ፣ ወፎች መጥተው በሉት።
\v 5 ሌላውም ዘር በቂ አፈር በሌለበት በዐለታማ መሬት ላይ ወደቀ። አፈሩም ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ።
\v 6 ፀሐይ ሲወጣ ግን፣ሥር ስላልነበረው ጠውልጎ ደረቀ።
\s5
\v 7 ሌላው ዘር ደግሞ በእሾኽማ ቊጥቋጦ መካከል ወደቀ፣ እሾኹም አድጎ አነቀው።
\v 8 ሌላው ዘር በመልካም መሬት ላይ ወድቆ ፍሬ አፈራ፤ አንዳንዱ መቶ፣ አንዳንዱ ሥልሳ፣ አንዳንዱም ሠላሳ ፍሬ አፈራ።
\v 9 ጆሮ ያለው ይሰማ።"
\s5
\v 10 ደቀ መዛሙርቱም መጡና ኢየሱስን፣ “ለምንድን ነው ለሕዝቡ በምሳሌ የምትናገረው?" አሉት።
\v 11 ኢየሱስም መልሶ፣ "ለእናንተ የመንግሥተ ሰማይን ምስጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል፣ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም" አላቸው።
\v 12 ምክንያቱም ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል፤ ይበዛለትማል። የሌለው ግን ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
\s5
\v 13 ስለዚህ ለእነርሱ በምሳሌ እነግራቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ቢያዩ እንኳ እያዩ አይደለም፣ ቢሰሙም እየሰሙ አይደለም፣ ወይም አያስተውሉም።
\v 14 በእነርሱ ላይ እንዲህ የሚለው የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጸመ ፦ መስማትን ትሰማላችሁ፣ ነገር ግን በምንም መንገድ አታስተውሉም፣ ማየትን ታያላችሁ፣ ግን ምንም አትገነዘቡትም።
\s5
\v 15 በዐይናቸውም እንዳይመለከቱ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ጆሯቸው ለመስማት ተደፍኗል፣ ዐይናቸውም ተጨፍኗል። እንዳይመለሱና እኔም እንዳልፈውሳቸው የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኗል።
\s5
\v 16 የእናንተ ዐይኖች ግን ስለሚያዩ፣ ጆሮቻችሁም ስለሚሰሙ የተባረኩ ናቸው።
\v 17 እውነት እላችኋለሁ፣ ብዙ ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ለማየት ተመኝተው አላዩም፤ የምትሰሙትን ለመስማት ተመኝተው አልሰሙም።
\s5
\v 18 እንግዲህ የዘሪውን ምሳሌ ስሙ።
\v 19 ማንም የመንግሥትን ቃል ሰምቶ ባያስተውል፣ ክፉው ይመጣል በልቡም የተዘራውን ይነጥቃል። ይህም በመንገድ ዳር የተዘራውን ይመስላል።
\s5
\v 20 በዐለት ላይ የተዘራው ፣ቃሉን የሚሰማና ወዲያውኑ በደሰታ የሚቀበለው ነው፤
\v 21 ሆኖም በራሱ ሥር ስለሌለው፣ የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ነው። በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሚነሣበት ጊዜ፣ ወዲያውኑ ይሰናከላል።
\s5
\v 22 በእሾኽ ተክሎች መካከል የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማ ሆኖ የዓለም ዐሳብ፣ የብልጥግናም አሳሳችነት ቃሉን ያንቁታል፣ ፍሬ ቢስም ይሆናል።
\v 23 በመልካም መሬት ላይ የተዘራው፣ ቃሉን የሚሰማና የሚረዳ ነው፤ በርግጥ የሚያድገውና ፍሬ የሚሰጠውም ይህኛው ነው፤ አንዱ መቶ፣ አንዱም ሥልሳ፣ አንዱም ሠላሣ እጥፍ ያፈራል።
\s5
\v 24 ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ እንዲህ አለ፤ “መንግሥተ ሰማይ በዕርሻው ላይ መልካም ዘር የዘራ ሰው ትመስላለች።
\v 25 ሰዎቹ በተኙ ጊዜ ግን፣ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው መካከል እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ።
\v 26 ቅጠሉም በለመለመና ፍሬ ማፍራት በጀመረ ጊዜ፣ እንክርዳዱ ደግሞ አለ።
\s5
\v 27 የዕርሻው ባለቤት አገልጋዮች መጥተው፣ "ጌታ ሆይ፣ በዕርሻው ላይ መልካም ዘር ዘርተህ አልነበረምን? ታዲያ እንክርዳድ የበቀለው እንዴት ነው?"አሉት።
\v 28 እርሱም፣ “ጠላት ይህን አደረገ" አላቸው። አገልጋዮቹም መልሰው፣"ስለዚህ ሄደን እንድንነቅለው ትፈልጋለህን?" አሉት።
\s5
\v 29 የዕርሻውም ባለቤት፣ 'አይሆንም፣ እንክርዳዱን በምትነቅሉበት ጊዜ ስንዴውንም አብራችሁ ልትነቅሉት ትችላላችሁ 'አላቸው።
\v 30 እስከ መከር ድረስ አብረው ይደጉ። በመከሩ ጊዜ ለኣጫጆቹ፣ "መጀመሪያ እንክርዳዱን ነቅላችሁ እንዲቃጠል አንድ ላይ ሰብስቡ። ስንዴውን ግን ሰብስባችሁ ወደ ጎተራዬ አስገቡት እላቸዋለሁ" አላቸው።
\s5
\v 31 ኢየሱስም ሌላ ምሳሌ ነገራቸው። እንዲህም አለ፤ “መንግሥተ ሰማይ ሰው ወስዶ በዕርሻው ላይ የዘራትን የሰናፍጭ ዘር ትመስላለች።
\v 32 በርግጥ ይህች ዘር ከሌሎች ዘሮች ሁሉ ታንሳለች። በምታድግበት ጊዜ ግን የሰማይ ወፎች በቅርንጫፎቿ እስኪሰፍሩባት ድረስ፣ ከሌሎች ዛፎች ትበልጣለች፡፡
\s5
\v 33 ከዚያም ኢየሱስ ሌላ ምሳሌ ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ ሴት ወስዳ ኩፍ እስኪል ድረስ ከሦስት እጅ ዱቄት ጋር የደባለቀችውን እርሾ ትመስላለች።”
\s5
\v 34 ኢየሱስም ለሕዝቡ እነዚህን ነገሮች ሁሉ በምሳሌ ተናገረ፣ ያለ ምሳሌም ምንም አልነገራቸውም።
\v 35 ይህም ፦ "አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፣ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ የተሰወረውን እገልጣለሁ" ተብሎ በነቢዩ የተነገረው እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 36 ኢየሱስ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ መጥተው "በዕርሻው የነበረውን የእንክርዳዱን ምሳሌ አስረዳን" አሉት።
\v 37 ኢየሱስ መለሰ እንዲህም አለ፤ “መልካሙን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው።
\v 38 ዕርሻው ይህ ዓለም ነው፣ መልካሙ ዘር የመንግሥቱ ልጆች ናቸው። እንክርዳዱ የክፉው ልጆች ናቸው፤
\v 39 ዘሩን የዘራው ጠላት ዲያብሎስ ነው። መከሩ የዓለም መጨረሻ ሲሆን፣ አጫጆቹም መላእክት ናቸው።
\s5
\v 40 ስለዚህ እንክርዳዱ ተሰብስቦ በእሳት እንደሚቃጠል፣ በዓለም መጨረሻም እንዲሁ ይሆናል።
\v 41 የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፣ ከመንግሥቱ ለኅጢአት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን ሁሉና፣ ክፉ አድራጊዎችን ይሰበስቧቸዋል፣
\v 42 ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደ እቶን እሳትም ይጥሏቸዋል።
\v 43 ከዚያም ፃድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ። ጆሮ ያለው ይስማ።
\s5
\v 44 መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፣ አንድ ሰውም አግኝቶ ደበቃት፤ ከደስታውም የተነሳ ያለውን ንብረት ሁሉ ሸጦ ያንን ዕርሻ ገዛው።
\v 45 ደግሞም፣ መንግሥተ ሰማይ የከበሩ ዕንቈች የሚፈልግ ነጋዴን ትመስላለች።
\v 46 በጣም ትልቅ ዋጋ ያለው ዕንቊ ባገኘ ጊዜ፣ ሄዶ ያለውን ንበረት ሁሉ ሸጠና ገዛው።
\s5
\v 47 እንዲሁም፣መንግሥተ ሰማይ ወደ ባሕር የተጣለችና ሁሉም ዓይነት ፍጥረታት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች።
\v 48 መረቡዋ ስትሞላ፣ ዓሣ አጥማጆቹ ወደ ዳር አወጡት። ተቀምጠውም መልካም መልካሙን ሰብስበው በዕቃ አደረጉ፣ የማይጠቅመውን ግን አውጥተው ጣሉት።
\s5
\v 49 በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል፣ መላእክት መጥተው ከጻድቃን መካከል ክፉዎችን ይለያሉ።
\v 50 ከዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት፣ ወደሚነደው እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።
\s5
\v 51 ይህን ሁሉ ተረድታችኋል?" አላቸው። ደቀ መዛሙርቱም፣ “አዎን” አሉት።
\v 52 ከዚያም ኢየሱስ፣ “ ስለዚህ የመንግሥተ ሰማይ ደቀ መዝሙር የሆነ ጸሐፊ ሁሉ፣ ከሀብቱ መካከል አሮጌውንና ዐዲሱን ያወጣ የቤት ጌታን ይመስላል አላቸው"።
\v 53 ከዚያም ኢየሱስ እነዚህን ምሳሌዎች በጨረሰ ጊዜ፣ ከዚያ ስፍራ ሄደ።
\s5
\v 54 ኢየሱስ ወደ ራሱ አገር መጥቶ፣ በምኲራቦቻቸው ሕዝቡን አስተማረ፣ ከዚህም የተነሣ ተገርመው፣ "ይህ ሰው ይህን ጥበቡንና እነዚህን ተአምራት ከየት አገኘ?
\v 55 ይህ ሰው የአናጢው ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማርያም አይደለችም ወይ? ያዕቆብ፣ ዮሴፍ፣ ስምዖንና ይሁዳስ ወንድሞቹ አይደሉም ወይ?
\v 56 እኅቶቹስ ከእኛው ጋር አይደሉም ወይ? ታዲያ ይህ ሰው እነዚህን ነገሮች ሁሉ ከየት አገኛቸው?" አሉ።
\s5
\v 57 በእርሱም ተሰናከሉበት። ኢየሱስ ግን፣ "ነቢይ ከገዛ አገሩና ከገዛ ቤተ ሰቡ በቀር መከበሩ አይቀርም" አላቸው።
\v 58 በአለማናቸውም ምክንያት ፣በዚያ ብዙ ተአምራት አላደረገም።
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ፣ የአራተኛው ክፍል ገዢ የነበረው ሄሮድስ ስለ ኢየሱስ ሰማ።
\v 2 አገልጋዮቹንም፣ "ይህ መጥምቁ ዮሐንስ ነው። ስለዚህ ይህ ሁሉ ኅይል በእርሱ የሚሠራው ከሞት ስለ ተነሣ ነው" አላቸው።
\s5
\v 3 ሄሮድስ፣ በወንድሙ በፊልጶስ ሚስት በሄሮድያዳ ምክንያት፣ ይዞ አሳስሮት ነበርና፡፡
\v 4 ምክንያቱም ዮሐንስ፣ "እርሷን ማግባትህ ተገቢ አይደለም" ይለው ነበር።
\v 5 ሄሮድስ ሊያስገድለው ፈልጎ፣ ሕዝቡን ፈራ፣ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ያዩት ነበር።
\s5
\v 6 ነገር ግን በሄሮድስ የልደት ቀን፣ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከል ስትጨፍር፣ ሄሮድስን ደስ አሰኘችው።
\v 7 በዚህም ምክንያት፣ የምትጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰጣት በመሓላ ቃል ገባላት።
\s5
\v 8 በእናቷም ተመክራ፣ “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ እዚሁ፣ በሳሕን አድርገህ ስጠኝ” አለችው።
\v 9 ንጉሡ በጥያቄዋ በጣም ዐዘነ፣ ነገር ግን በመሓላውና ከእርሱ ጋር እራት ላይ በነበሩት ምክንያት፣ የተናገረው እንዲፈጸም አዘዘ።
\s5
\v 10 ሰው ልኮ፣ በወህኒ ቤት የዮሐንስን ራስ አስቈረጠ።
\v 11 ከዚያም ራሱ በሳሕን ተደርጎ ለልጅቱ ተሰጣት፣ እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠች።
\v 12 ከዚያም የእርሱ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣ በድኑን ወስደው ቀበሩት። ከዚህ በኋላ ሄደው ለኢየሱስ ነገሩት።
\s5
\v 13 ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ፣ በጀልባ ገለል ወዳለ ቦታ ሄደ። ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ ፣ ከየከተሞቹ በእግር ተከተሉት።
\v 14 ከዚያም ኢየሱስ ቀድሞአቸው መጥቶ ብዙ ሕዝብ አየና ራራላቸው፣ ሕመምተኞቻቸውንም ፈወሰ።
\s5
\v 15 በመሸም ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ መጡና፣ “ቀኑ መሽቷል ይህም ስፍራ ምድረ በዳ ነው ። ሕዝቡን ወደ መንደሮች እንዲሄዱና፣ ለራሳቸው ምግብ እንዲገዙ አሰናብት" አሉት።
\s5
\v 16 ኢየሱስ ግን፣ "መሄድ አያስፈልጋቸውም፤ እናንተው የሚበሉትን ስጧቸው" አላቸው።
\v 17 እነርሱም፣ “ እኛ ያለን አምስት እንጀራና ሁለት ዐሣ ብቻ ነው" አሉት።
\v 18 ኢየሱስም፣ "እነርሱኑ ወደ እኔ አምጡአቸው" አለ።
\s5
\v 19 ከዚያም ኢየሱስ ሣሩ ላይ እንዲቀምጡ ሕዝቡን አዘዘ። ዐምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዐሣ ወሰደ፣ ወደ ሰማይ አሻቅቦ እያየ፣ አመሰገነ፤ እንጀራውንም ቈርሶ፣ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጡ።
\v 20 ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡ ከዚያም የተረፈውን ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ ቊርስራሽ ሰበሰቡ።
\v 21 የበሉትም፣ ከሴቶችና ከልጆች ሌላ፣ ዐምስት ሺ ያህል ወንዶች ነበሩ።
\s5
\v 22 እርሱም ሕዝቡን እያሰናበተ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱን ወዲያው ወደ ጀልባ ገብተው፣ ከእርሱ በፊት ወደ ማዶ እንዲሄዱ አዘዛቸው።
\v 23 ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ፣ ብቻውን ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ። በመሸ ጊዜ፣ በዚያ እርሱ ብቻውን ነበር።
\v 24 ጀልባዋ በባሕሩ መካከል እያለች፤ ከተቃራኒ አቅጣጫ ይነፍስ ስለ ነበር፣ በማዕበሉ ክፉኛ ትንገላታ ነበር።
\s5
\v 25 ከምሽቱ በአራተኛው ክፍል፣ ኢየሱስ በባሕሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ እየመጣ ነበር።
\v 26 ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ እየተራመደ ሲያዩት፣ እጅግ ደንግጠው፣ “መንፈስ ነው”ብለው በፍርሀት ጮኹ።
\v 27 ኢየሱስ ግን ወዲያውኑ፣ “አይዟችሁ! እኔ ነኝ! አትፍሩ” ብሎ ተናገራቸው።
\s5
\v 28 ጴጥሮስም መልሶ፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተስ ከሆንህ፣ በውሃው ላይ ወደ አንተ እንድመጣ እዘዘኝ" አለው።
\v 29 ኢየሱስም፣ “ና" አለው። ስለዚህ ጴጥሮስ ከጀልባው ወጥቶ ወደ ኢየሱስ ለመሄድ፣ በውሃው ላይ ተራመደ።
\v 30 ነገር ግን ጴጥሮስ ነፋሱን አይቶ በመፍራት፣ መስጠም በጀመረ ጊዜ ፣ “ጌታ ሆይ፣ አድነኝ” ብሎ ጮኸ።
\s5
\v 31 ኢየሱስም ያኔውኑ እጁን ዘርግቶ ጴጥሮስን ያዘውና፣ “አንተ እምነት የጎደለህ፣ ለምን ትጠራጠራለህ?” አለው።
\v 32 ከዚያም ኢየሱስና ጴጥሮስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ፣ ነፋሱ መንፈሱን አቆመ።
\v 33 በጀልባው ውስጥ የነበሩት ደቀ መዛሙርትም ኢየሱስን፣ “አንተ በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብለው ሰገዱለት።
\s5
\v 34 ከተሻገሩም በኋላ፣ ጌንሳሬጥ ወደ ተባለ አገር መጡ።
\v 35 በዚያም ስፍራ የነበሩ ሰዎች ኢየሱስ መሆኑን ባወቁ ጊዜ፣ በአካባቢው ወዳለ ስፍራ ሁሉ መልእክት ላኩና፣ የታመመውን ሁሉ ወደ እርሱ አመጡ።
\v 36 የልብሱን ጫፍ ብቻ ለመንካት ለመኑት፣ የነኩትም ሁሉ ተፈወሱ።
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 ከዚያም አንዳንድ ፈሪሳውያንና የአይሁድ የሕግ መምህራን ከኢየሩሳሌም ኢየሱስን ለማነጋገር መጥተው እንዲህ አሉ፤
\v 2 "ደቀ መዛሙርትህ የሽማግሌዎችን ወግ የሚጥሱት ለምንድነው? ምግብ ከመብላታቸው በፊት እንደ ወጉ እጃቸውን አይታጠቡምና።"
\v 3 ኢየሱስም መለሰና፣ "እናንተስ ስለ ወጋችሁ ስትሉ ለምን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትተላለፋላችሁ?" አላቸው፡፡
\s5
\v 4 እግዚአብሔር፣ ‹አባትህንና እናትህን አክብር፣› ‹ስለ አባቱ ወይም ስለ እናቱ ክፉ የሚናገር በርግጥ ይሞታል› ብሏልና፡፡
\v 5 እናንተ ግን፣ "አባቱን ወይም እናቱን፣ 'ከእኔ የተቀበላችሁት ማንኛውም እርዳታ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ስጦታ ነው ትላላችሁ፡፡'
\v 6 ያ ሰው አባቱን ማክበር አያስፈልገውም። ስለ ወጋችሁ ስትሉ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፡፡
\s5
\v 7 እናንተ ግብዞች፣ ኢሳይያስ ስለ እናንተ፣
\v 8 'ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤
\v 9 የሰዎችን ትእዛዝ እንደ ሕግ በመቊጠር የራሳቸውን ትምህርት ስለሚያስተምሩ፣ እኔን በከንቱ ያመልኩኛል›› ብሎ ትንቢት በመናገሩ መልካም አድርጓል።
\s5
\v 10 ከዚያ ሕዝቡን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "አድምጡ አስተውሉም፡-
\v 11 ወደ አፍ የሚገባ ሰውን ምንም አያረክስም፡፡ ይልቁንም ከአፍ የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው" አላቸው፡፡
\s5
\v 12 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ኢየሱስን፣ ‹‹ፈሪሳውያን ይህን ቃል ሲሰሙ እንደ ተሰናከሉ ዐወቀሃል? አሉት፡፡
\v 13 ኢየሱስም መለሰና፣ ‹‹አባቴ ያልተከለው ተክል ሁሉ ይነቀላል፤
\v 14 እነርሱን ተዉአቸው፤ ዐይነ ስውር መሪዎች ናቸው፡፡ አንድ ዐይነ ስውር ሌላውን ዐይነ ስውር ቢመራው ሁለቱም ተያይዘው ጕድጓድ ውስጥ ይወድቃሉ፡፡››
\s5
\v 15 ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስን፣ ‹‹ይህን ምሳሌ አብራራልን›› አለው፡፡
\v 16 ኢየሱስ፣ ‹‹እናንተ ደግሞ አሁንም አታስተውሉምን?
\v 17 ወደ አፍ የሚገባው ሁሉ ወደ ሆድ እንደሚሄድና ከዚያም ዐይነ ምድር ሆኖ ወደ ውጭ እንደሚጣል አታስተውሉምን?
\s5
\v 18 ዳሩ ግን ከአፍ የሚወጣ ከልብ ይወጣል፡፡ እነዚህ ነገሮች ሰውን ያረክሳሉ፡፡
\v 19 ከልብ ክፉ ዐሳብ፣ ነፍስ መግደል፣ ምንዝርና፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ የሐሰት ምስክርነትና ስድብ ይወጣሉ፤
\v 20 ሰውን የሚያረክሱት እነዚህ ናቸው፡፡ ነገር ግን ባልታጠበ እጅ መብላት ሰውን አያረክስም፡፡"
\s5
\v 21 ቀጥሎም ኢየሱስ ከዚያ ወደ ጢሮስና ወደ ሲዶና ከተሞች አካባቢ ሄደ፡፡
\v 22 እነሆም፣ አንዲት ከነዓናዊት ሴት ከዚያ አካባቢ ወጣችና ጮኽ ብላ እንዲህ አለች፣ ‹‹የዳዊት ልጅ፣ ጌታ ሆይ፣ ማረኝ፡፡ ልጄ በጋኔን ተይዛ በጣም እየተሠቃየች ነው፡፡››
\v 23 ኢየሱስ ግን አንድም ቃል አልመለሰላትም፡፡ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው፣ ‹‹ይህች ሴት ትጮኽብናለችና ሸኛት›› ብለው ለመኑት፡፡
\s5
\v 24 ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ፣ ‹‹እንደ በግ ወደ ጠፉት የእስራኤል ቤት ሰዎች ካልሆነ በቀር ወደ ማንም አልተላክሁም›› አለ፡፡
\v 25 ነገር ግን ሴቲቱ "ጌታ ሆይ፣ እርዳኝ" በማለት መጥታ በፊቱ ሰገደች፡፡
\v 26 ኢየሱስ መልሶ፣ "የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለቡችሎች መጣል ትክክል አይደለም" አለ፡፡
\s5
\v 27 ሴቲቱ፣ "አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ ከሚወድቀው የተወሰነውን ትርፍራፊ ይበላሉ" አለች፡፡
\v 28 ከዚያም ኢየሱስ መልሶ፣ "አንቺ ሴት እምነትሽ ታላቅ ነው፤ ልክ እንደ ተመኘሽው ይሁንልሽ" አላት፡፡ ልጇም በዚያች ሰዓት ተፈወሰች፡፡
\s5
\v 29 ኢየሱስ ከዚያ ቦታ ወደ ገሊላ ባሕር አቅራቢያ ሄደ፡፡ ከዚያም ወደ አንድ ኮረብታ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ፡፡
\v 30 ብዙ ሕዝብም ወደ እርሱ መጡ፤ አንካሶችን፣ ዐይነ ስውሮችን፣ ዲዳዎችንና ጕንድሾችን፣ እንዲሁም ሌሎች ታመው የነበሩ ብዙዎችን ይዘው መጡ፡፡ በኢየሱስ እግር አጠገብም አስቀመጧቸው፤ እርሱም ፈወሳቸው፡፡
\v 31 ስለዚህ ሕዝቡ ዲዳዎች ሲናገሩ፣ ጕንድሾች ሲፈወሱ፣ አንካሶች ሲራመዱ፣ ዐይነ ስውሮችም ሲያዩ አይተው ተደነቁ፡፡ የእስራኤልንም አምላክ አመሰገኑ፡፡
\s5
\v 32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ "ለሕዝቡ አዝንላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ከእኔ ጋር ሦስት ቀን ቈይተዋል፣ የሚበሉትም የላቸውም፡፡ በመንገድ ላይ ዝለው እንዳይወድቁ ሳይበሉ ዝም ብዬ አላሰናብታቸውም" አለ፡፡
\v 33 ደቀ መዛሙርቱ፣ "በዚህ በረሓ ይህን የሚያህል ብዙ ሕዝብ የሚያጠግብ እንጀራ ከየት እናገኛለን?" አሉት፡፡
\v 34 ኢየሱስ፣ "ስንት እንጀራ አላችሁ?" አላቸው፡፡ "ሰባት እንጀራና ጥቂት ትናንሽ ዐሣ አለ" አሉት፡፡
\v 35 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን መሬት ላይ እንዲቀመጡ አዘዛቸው፡፡
\s5
\v 36 ኢየሱስ ሰባቱን እንጀራና ዐሣዎቹን ይዞ ካመሰገነ በኋላ እንጀራውን ቈርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ ሰጧቸው፡፡
\v 37 ሕዝቡ ሁሉ በሉና ጠገቡ፡፡ ትርፍራፊውንም ሰበሰቡ፤ ትርፍራፊውም ሰባት ቅርጫት ሙሉ ነበር፡፡
\v 38 የበሉትም ከሴቶችና ከልጆች በቀር አራት ሺህ ወንዶች ነበሩ፡፡
\v 39 ከዚያም ኢየሱስ ሕዝቡን አሰናበተና በጀልባም ገብቶ መጌዶን ወደ ተባለ ክፍለ አገር ሄደ፡፡
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም መጥተው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው በመጠየቅ ኢየሱስን ፈተኑት፡፡
\v 2 ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "በመሸ ጊዜ ሰማዩ ቀልቷልና ዝናብ አይኖርም ትላላችሁ
\s5
\v 3 በነጋ ጊዜም፣ ‹ዛሬ ሰማዩ ስለ ጠቈረ ይዘንባል› ትላላችሁ፤ የዘመኑን ምልክት ግን መለየት አትችሉም፡፡
\v 4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፤ ነገር ግን ከነቢዩ ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም፡፡" ከዚያም ኢየሱስ ትቶአቸው ሄደ፡፡
\s5
\v 5 ደቀ መዛሙርቱ ወደ ማዶ ተሻገሩ፤ እንጀራ መያዝን ግን ረሱ፡፡
\v 6 ኢየሱስ፣ "ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም" አላቸው፡፡
\v 7 ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንጀራ ስላልያዝን ነው" ብለው እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡
\v 8 ኢየሱስ ይህን ዐውቆ፣ "እናንተ እምነተ ጎደሎዎች፣ እንጀራ ስላልያዝን ነው ብላችሁ ስለ ምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ?"
\s5
\v 9 ዐምስት እንጀራ ለዐምስቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንደ ሰበሰባችሁ አሁንም አታስተውሉም ወይም አታስታውሱም?
\v 10 ወይም ደግሞ ሰባቱ እንጀራ ለአራቱ ሺህ እንደ በቃና ስንት ቅርጫት እንዳነሣችሁስ አታስታውሱምን?
\s5
\v 11 እኔ የነገርኋችሁ ስለ እንጀራ እንዳልነበረ እንዴት ነው የማታስተውሉት? ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያ እርሾ ተጠንቀቁ፣ ተጠበቁም፡፡"
\v 12 ከዚያም እርሱ ሲነግራቸው የነበረው ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንዲጠበቁ እንጂ፣ ስለ እንጀራ እርሾ እንዳልነበረ ተረዱ፡፡
\s5
\v 13 ኢየሱስም ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ክልል በመጣ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፣ "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ነው ይላሉ?" በማለት ጠየቃቸው፡፡
\v 14 እነርሱ፣ እንዲህ አሉ፤ "አንዳንዶች መጥምቁ ዮሐንስ፣ ሌሎች ኤልያስ፣ የቀሩትም ኤርምያስ፣ ወይም ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ፡፡"
\v 15 "እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?" አላቸው፡፡
\v 16 ስምዖን ጴጥሮስ፣ "አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" በማለት መልስ ሰጠ፡፡
\s5
\v 17 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለው፣ "የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ አንተ የተባረክህ ነህ፤ ይህን የገለጠልህ የሰማዩ አባቴ ነው እንጂ፣ ሥጋና ደም አይደለም፡፡
\v 18 ደግሞም አንተ ጴጥሮስ ነህም እላለሁ፤ በዚህም አለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም፡፡
\s5
\v 19 እኔ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፡፡ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈታውም ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡››
\v 20 ከዚያም ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ለማንም እንዳይናገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዛቸው፡፡
\s5
\v 21 ከዚያን ጊዜ አንሥቶ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ፣ በሽማግሌዎችና በካህናት አለቆች፣ በፈሪሳውያንና በሕግ መምህራንም እጅ ብዙ መከራ መቀበልና መገደል፣ በሦስተኛውም ቀን መነሣት እንዳለበት ለደቀ መዛሙርቱ ይነግራቸው ጀመር፡፡
\v 22 ከዚያም ጴጥሮስ ኢየሱስን ለብቻው ገለል አድርጎ፣ "ጌታ ሆይ፣ ይህ ከአንተ ይራቅ፤ ይህም ከቶ አይሁንብህ" በማለት ገሠጸው፡፡
\v 23 ኢየሱስ ግን ዞር ብሎ ጴጥሮስን፣ "ከፊቴ ዞር በል፣ ሰይጣን! ስለ ሰው እንጂ ስለ እግዚአብሔር ነገር ደንታ የለህምና አንተ ለእኔ እንቅፋት ነህ" አለው፡፡
\s5
\v 24 ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ሊከተለኝ የሚፈልግ ማንም ቢኖር፣ ራሱን መካድ፣ የራሱን መስቀል መሸከምና እኔን መከተል አለበት፡፡
\v 25 ሕይወቱን ለማዳን የሚፈልግ ሁሉ ያጣዋል፤ ስለ እኔ ሕይወቱን የሚያጣ ግን ያገኘዋል፡፡
\v 26 ሰው ሙሉውን ዓለም የራሱ ቢያደርግ ሕይወቱን ግን ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ሰው በሕይወቱ ፈንታ ምን መስጠት ይችላል?
\s5
\v 27 የሰው ልጅ በአባቱ ክብር ከመላእክቱ ጋር ይመጣልና፡፡ ከዚያም ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋል፡፡
\v 28 እውነት እላችኋለሁ፤ እዚህ ከቆማችሁት መካከል የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች አሉ፡፡"
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ከስድስት ቀን በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙን ይዞ ብቻቸውን ወደ ረጅም ተራራ አወጣቸው፡፡
\v 2 በፊታቸውም መልኩ ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን አንጸባረቀ፡፡
\s5
\v 3 እነሆ፣ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው፡፡
\v 4 ጴጥሮስ መልሶ ኢየሱስን፣ "ጌታ ሆይ፣ እዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፡፡ ብትፈልግ እኔ እዚህ ሦስት ዳሶችን፡- አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እሠራለሁ" አለው፡፡
\s5
\v 5 እርሱ ገና እየተናገረ እያለ፣ እነሆ፣ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፡፡ ከደመናውም፣ "በእርሱ እጅግ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ ነበረ፡፡
\v 6 ደቀ መዛሙርቱ ድምፁን በሰሙ ጊዜ ፈሩ፣ በግንባራቸውም ወደቁ፡፡
\v 7 ከዚያም ኢየሱስ መጥቶ ዳሰሳቸውና፣ ‹‹ተነሡ አትፍሩ›› አላቸው፡፡
\v 8 ከዚያም እነርሱ ቀና ብለው ተመለከቱ፣ ነገር ግን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም፡፡
\s5
\v 9 ከተራራ ሲወርዱም ኢየሱስ፣ "የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሣ ድረስ ይህን ያያችሁትን ለማንም አትንገሩ" ብሎ አዘዛቸው፡፡
\v 10 ደቀ መዛሙርቱ፣ "እንግዲያው የአይሁድ ሕግ መምህራን መጀመሪያ ኤልያስ መምጣት አለበት ለምን ይላሉ?" በማለት ጠየቁት፡፡
\s5
\v 11 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፤ "ኤልያስ በርግጥ ይመጣል፣ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል፡፡
\v 12 ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ኤልያስ አስቀድሞ መጥቷል፤ ነገር ግን አላወቁትም፡፡ በዚህ ፈንታ የፈለጉትን ነገር ሁሉ አደረጉበት፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የሰው ልጅ በእነርሱ እጅ መከራ ይቀበላል፡፡››
\v 13 በዚያን ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ የተናገራቸው ስለ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነበረ ተረዱ፡፡
\s5
\v 14 ወደ ሕዝቡ በመጡ ጊዜ አንድ ሰው መጥቶ በፊቱ ተንበረከከ፤ እንዲህም አለው፤
\v 15 "ጌታ ሆይ፣ ልጄን ማረው፣ የሚጥል በሽታ ይዞት በኀይል ይሠቃያል፤ ብዙ ጊዜ በእሳት ወይም በውሃ ውስጥ ይጥለዋልና፡፡
\v 16 ወደ ደቀ መዛሙርትህ አመጣሁት፤ ነገር ግን እነርሱ ሊፈውሱት አልቻሉም፡፡›
\s5
\v 17 ኢየሱስ መልሶ፣ "የማታምኑና ምግባረ ብልሹ ትውልድ፣ እስከ መቼ ድረስ ከእናንተ ጋር እቆያለሁ? እስከ መቼስ እናንተን መታገሥ አለብኝ? እስቲ ወደ እኔ አምጡት" አለ፡፡
\v 18 ኢየሱስ ገሠጸው፤ ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፤ ልጁም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ፡፡
\s5
\v 19 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "እኛ ልናወጣው ያልቻልነው ለምንድን ነው?" አሉ፡፡
\v 20 ኢየሱስ፣ ‹‹በእምነታችሁ ማነስ ምክንያት፤ እውነት እላችኋለሁና፣ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት እንኳ ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ማዶ ሂድ ብትሉት ይሄዳል፡፡ ማድረግ የሚሳናችሁ ምንም ነገር አይኖርም፡፡
\v 21 \f + \ft አንዳንድ የጥንት ቅጂዎች ቊጥር 21ን ያስቀሩታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ዓይነቱ ጋኔን በጾምና በጸሎት ካልሆነ በቀር አይወጣም፡፡ \f*
\s5
\v 22 በገሊላ እያሉ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ "የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፤
\v 23 እነርሱም ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል" አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በጣም ዐዘኑ፡፡
\s5
\v 24 ወደ ቅፍርናሆም በመጡ ጊዜ ግማሽ ሰቅል ቀረጥ የሰበሰቡ ሰዎች ወደ ጴጥሮስ መጥተው፣ "መምህራችሁ ግማሽ ሰቅሉን ቀረጥ አይከፍልምን?" አሉ፡፡
\v 25 እርሱ፣ "አዎ" አለ፡፡ ጴጥሮስ ወደ ቤት በገባ ጊዜ ግን ኢየሱስ መጀመሪያ እርሱን ተናገረው፤ "ስምዖን ሆይ፣ ምን ይመስልሃል? የምድር ነገሥታት ቀረጥ ወይም ግብር የሚሰበስቡት ከማን ነው? ከዜጎቻቸው ወይስ ከውጭ አገር ሰዎች?" አለው፡፡
\s5
\v 26 ጴጥሮስ፣ "ከውጭ አገር ሰዎች" ባለ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "እንግዲያስ ዜጎቹ ከክፍያ ነጻ ናቸው፡፡
\v 27 ነገር ግን ቀረጥ ሰብሳቢዎቹን ኃጢአት እንዲሠሩ እንዳናደርጋቸው ወደ ባሕር ሄደህ መንጠቆ ጣል፤ በመጀመሪያ የምታጠምደውን ዐሣ አፍ ስትከፍት አንድ ሰቅል ታገኛለህ፤ ያንን ወስደህ ስለ እኔና ስለ አንተ ክፈል፡፡››
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 18
\p
\v 1 በዚያው ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ነው?" አሉ
\v 2 ኢየሱስ አንድ ትንሽ ልጅ ጠርቶ በመካከላቸው አቆመው፤
\v 3 እንዲህም አለ፡- "እውነት እላችኋለሁ፤ ንስሐ ካልገባችሁና እንደ ልጆች ካልሆናችሁ በምንም መንገድ ወደ መንግሥተ ሰማያት አትገቡም፡፡
\s5
\v 4 ስለዚህ እንደዚህ ልጅ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ሰው ሁሉ፣ እንዲሁ በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ ይበልጣል፡፡
\v 5 እንደዚህ ያለውን ልጅ በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፡፡
\v 6 ነገር ግን በእኔ ከሚያምነው ከእነዚህ ልጆች አንዱን ኀጢአት እንዲሠራ የሚያደርግ ማንም፣ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቁ ባሕር ቢሰጥም ይሻለዋል፡፡
\s5
\v 7 የመሰናክል ምክንያት በመሆኗ ለዓለም ወዮላት! መሰናክል መምጣቱ ግድ ነው፤ ነገር ግን መሰናክሉን ለሚያመጣ ሰው ወዮለት!
\v 8 እጅህ ወይም እግርህ ቢያሰናክልህ፣ ቈርጠህ ከአንተ ጣለው፡፡ ሁለት እጆች ወይም እግሮች ኖረውህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል የአካል ጉዳተኛ ወይም አንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃል፡፡
\s5
\v 9 ዐይንህ እንድትሰናከል ቢያደርግህ፣ አውጥተህ ከአንተ ጣለው፡፡ ሁለት ዐይኖች ኖረውህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻላል፡፡
\s5
\v 10 ከእነዚህ ከታናናሾች ማንኛውንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፡፡ በሰማይ ያሉ መላእክታቸው በሰማይ ያለውን የአባቴን ፊት ሁልጊዜ ያያሉና፡፡ 11 (2) ብዙ ምንጮች፣ አንዳንድ የጥንት የሆኑ ቊ. 11ን ያስገባሉ፡፡
\v 11 \f + \ft አንዳንዶቹ ጥንታዊ የሆኑ፣ ብዙ ቅጂዎች ቊ11ን የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቷልና፡፡ \f*
\s5
\v 12 ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት፣ ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ፣ ዘጠና ዘጠኙን በኮረብታው ጥግ ትቶ የጠፋውን ሊፈልግ አይሄድምን?
\v 13 በሚያገኘውም ጊዜ፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል፡፡
\v 14 በተመሳሳይ መንገድ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱ እንዲጠፋ የሰማዩ አባታችሁ ፈቃድ አይደለም፡፡
\s5
\v 15 ወንድምህ ቢበድልህ፣ ሂድና አንተና እርሱ ብቻ ሆናችሁም ጥፋቱን አሳየው፡፡ ቢሰማህ፣ ወንድምህን የራስህ ታደርገዋለህ፡፡
\v 16 ባይሰማህ ግን፣ ቃል ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ይጸናልና፣ ከአንተ ጋር አንድ ወይም ሁለት ተጨማሪ ወንድሞችን ይዘህ ሂድ፡፡
\s5
\v 17 እነርሱንም አልሰማም ቢል፣ ጉዳዩን ለቤተ ክርስቲያን ንገር፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ደግሞ አልሰማም ቢል፣ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ቊጠረው፡፡
\s5
\v 18 እውነት እላችኋለሁ፣ በምድር የምታስሩት ነገር ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የምትፈቱትም ነገር ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል፡፡
\v 19 በተጨማሪም እላችኋለሁ፣ ከእናንተ ሁለቱ በምድር ስለሚለምኑት ስለ ማንኛውም ነገር ቢስማሙ፣ በሰማይ ያለው አባቴ ያደርግላቸዋል፡፡
\v 20 ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት ቦታ እዚያ በመካከላቸው እገኛለሁና፡፡
\s5
\v 21 ከዚያም ጴጥሮስ መጥቶ ኢየሱስን፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ወንድሜ ቢበድለኝ ስንት ጊዜ ይቅር ልበለው? እስከ ሰባት ጊዜ ነውን? አለው፡፡
\v 22 ኢየሱስም፣ ‹‹ሰባ ጊዜ ሰባት እንጂ፣ ሰባት ጊዜ አልልህም›› አለው፡፡
\s5
\v 23 ስለዚህ መንግሥተ ሰማያት ከአገልጋዮቹ ጋር ሒሳብ ሊተሳሰብ የፈለገ ንጉሥን ትመስላለች፡፡
\v 24 መተሳሰቡን እንደ ጀመረ፣ የዐሥር ሺህ መክሊት ዕዳ ያለበትን አገልጋይ ወደ እርሱ አመጡ፡፡
\v 25 ነገር ግን የሚከፍልበት መንገድ ስላልነበረው፣ ጌታው ከሚስቱና ከልጆቹ ጋር ያለውም ሁሉ ተሸጦ ክፍያው እንዲፈጸም አዘዘው፡፡
\s5
\v 26 ስለዚህ አገልጋዩ ወድቆ በፊቱ ተንበረከከ እንዲህም አለ፤ ‹ጌታዬ ሆይ፣ ታገሠኝ፣ ሁሉንም እከፍልሃለሁ፡፡›
\v 27 ስለዚህ የዚያ አገልጋይ ጌታ ስለ ራራለት፣ ተወው፤ ዕዳውንም ሠረዘለት፡፡
\s5
\v 28 ነገር ግን ያ አገልጋይ ወጥቶ አብረውት ከሚሠሩት አገልጋዮች መቶ ዲናር ያበደረውን አንዱን አገልጋይ አግኝቶ ያዘው፤ ጕሮሮውን አነቀውና፣ ‹‹ያለብህን ዕዳ ክፈለኝ›› አለው፡፡
\v 29 ነገር ግን የሥራ ባልደረባው፣ ‹‹ታገሠኝ፣ እከፍልሃለሁ›› በማለት ወድቆ ለመነው፡፡
\s5
\v 30 የመጀመሪያው አገልጋይ ግን አሻፈረኝ አለ፤ በዚህ ፈንታ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ በእስር ቤት ጣለው፡፡
\v 31 የሥራ ጓደኞቹ የሆኑት አገልጋዮች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ፣ በጣም ተበሳጩ፤ መጥተውም ለጌታቸው የሆነውን ሁሉ ነገሩት፡፡
\s5
\v 32 ከዚያም የዚያ አገልጋይ ጌታ ጠራው፣ እንዲህም አለው፤ 'አንተ ክፉ አገልጋይ፣ ስለ ለመንኸኝ ያን ሁሉ ዕዳ ተውሁልህ፡፡
\v 33 እኔ አንተን እንደማርሁህ፣ የሥራ ባልደረባህ የሆነውን አገልጋይ ልትምረው አይገባህም ነበርን?'
\s5
\v 34 ጌታው ተቈጥቶ ዕዳውን ሁሉ እስኪከፍል ድረስ ለሚያሠቃዩት አሳልፎ ሰጠው፡፡
\v 35 ስለዚህም ከእናንተ እያንዳንዱ ወንድሙን ከልብ ይቅር ባይል የሰማዩ አባቴ እንዲሁ ያደርግበታል፡፡"
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፤ ኢየሱስ ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ገሊላን ትቶ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወዳለው ወደ ይሁዳ ጠረፍ መጣ፡፡
\v 2 ብዙ ሕዝብ ተከተሉት፤ እዚያም ፈወሳቸው፡፡
\s5
\v 3 ፈሪሳውያን እንዲህ በማለት ሊፈትኑት ወደ እርሱ መጡ፤ "በማንኛውም ምክንያት ሰው ሚስቱን ቢፈታ ሕጋዊ ነውን?"
\v 4 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፣ "ከመጀመሪያው የፈጠራቸው እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ እንደ ፈጠራቸውና
\s5
\v 5 ደግሞም፣ 'በዚህ ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ አንድ ሥጋም ይሆናሉ' የተባለውን አላነበባችሁምን?
\v 6 ስለዚህ እነርሱ ከእንግዲህ አንድ ሥጋ እንጂ ሁለት አይደሉም፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር አንድ ላይ ያጣመረውን፣ ማንም አይለየው፡፡››
\s5
\v 7 እነርሱ፣ "ታዲያ የፍቺ የምስክር ወረቀት ሰጥተን ከዚያ በኋላ እንድናባርራት ሙሴ ለምን አዘዘን?" አሉት፡፡
\v 8 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "ከልባችሁ ድንዳኔ የተነሣ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ሙሴ ፈቀደላችሁ፤ ነገር ግን ከመጀመሪያው እንደዚያ አልነበረም፡፡
\v 9 እኔ እላችኋለሁ፣ ከዝሙት በቀር ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ፣ ሌላይቱንም የሚያገባ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል፡፡"
\s5
\v 10 ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ "የባልና የሚስት ጉዳይ እንዲህ ከሆነ ማግባት ጥሩ አይደለም" አሉት፡፡
\v 11 ኢየሱስ ግን እንዲህ አላቸው፤ "እንዲቀበሉት የተፈቀደላቸው እንጂ፣ ሁሉም ሰው ይህን ትምህርት አይቀበለውም፡፡
\v 12 በተፈጥሮ ከእናታቸው ማኅፀን ስልብ ሆነው የተወለዱ አሉና፡፡ ሰዎች የሰለቧቸውም ይገኛሉ፡፡ ስለ መንግሥተ ሰማያት ሲሉም ራሳቸውን ስልብ ያደረጉ አሉ፡፡ ይህን ትምህርት መቀበል የሚችል፣ ይቀበለው፡፡››
\s5
\v 13 በዚያን ጊዜ እጁን ጭኖ እንዲጸልይላቸው ሰዎች ልጆችን ወደ እርሱ አመጡ፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ገሠጿቸው፡፡
\v 14 ኢየሱስ ግን፣ "ልጆቹን ተዉአቸው፤ ወደ እኔም እንዲመጡ አትከልክሏቸው፤ መንግሥተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉት ናትና" አለ፡፡
\v 15 15 እጁንም በልጆቹ ላይ ጫነባቸው፤ ከዚያም ያን ቦታ ትቶ ሄደ፡፡
\s5
\v 16 እነሆ፣ አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ ‹‹መምህር ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት እንዳገኝ ምን መልካም ነገር ማድረግ አለብኝ? አለ፡፡
\v 17 ኢየሱስ፣ ‹‹ስለ መልካም ነገር ለምን ትጠይቀኛለህ? መልካም አንድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ወደ ሕይወት ለመግባት ብትፈልግ ትእዛዛትን ጠብቅ›› አለው፡፡
\s5
\v 18 ሰውዬው፣ ‹‹የትኞቹን ትእዛዛት? አለ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "አትግደል፤" "አታመንዝር" "አትስረቅ፤" "በሐሰት አትመስክር፤"
\v 19 "አባትህንና እናትህን አክብር፤" እንዲሁም፣ "ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡"
\s5
\v 20 ወጣቱ፣ "እነዚህን ነገሮች ሁሉ ፈጽሜአለሁ፣ ሌላስ ምን ያስፈልገኛል?" አለው፡፡
\v 21 ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ "ፍጹም ለመሆን ብትፈልግ፣ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድኾችም ስጠው፤ በሰማይም ሀብት ይኖርሃል፡፡ ከዚያም መጥተህ ተከተለኝ፡፡››
\v 22 ነገር ግን ወጣቱ ኢየሱስ የተናገረውን በሰማ ጊዜ፣ ብዙ ንብረት ነበረውና ዐዝኖ ሄደ፡፡
\s5
\v 23 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት መግባት ከባድ ነው፡፡
\v 24 ደግሜ እላችኋለሁ፤ ለባለ ጠጋ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከመግባት፣ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል፡፡"
\s5
\v 25 ደቀ መዛሙርቱ ይህን በሰሙ ጊዜ በጣም ተደነቁና፣ "ታዲያ ማን ሊድን ይችላል?" አሉ፡፡
\v 26 ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተመልክቶ፣ "ይህ ለሰዎች የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል" አለ፡፡
\v 27 ከዚያም ጴጥሮስ መልሶ፣ "ተመልከት፣ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤ ታዲያ ምን እናገኛለን?" አለ፡፡
\s5
\v 28 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ እኔን የተከተላችሁኝ፣ በዐዲሱ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም በዐሥራ ሁለት ዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶችም ላይ ትፈርዳላችሁ፡፡
\s5
\v 29 ስለ ስሜ ቤቶችን፣ ወንድሞችን፣ እኅቶችን፣ አባትን፣ እናትን፣ ልጆችን፣ ወይም ርስትን የተወ ሁሉ፣ መቶ እጥፍ ይቀበላል፣ የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል፡፡
\v 30 ነገር ግን አሁን ፊተኞች የሆኑ ብዙዎች ኋለኞች ይሆናሉ፤ ኋለኞች የሆኑ ብዙዎችም ፊተኞች ይሆናሉ፡፡
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 መንግሥተ ሰማይ ለወይኑ አትክልት ሠራተኞችን ሊቀጥር ማልዶ የወጣ ባለቤትን ትመስላለች።
\v 2 በቀን አንዳንድ ዲናር ሊከፍላቸው ከሠራተኞቹ ጋር ከተስማማ በኋላ፣ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ላካቸው።
\s5
\v 3 ደግሞም በሦስት ሰዓት ገደማ ወጥቶ በገበያ ቦታ ሥራ ፈትተው የቆሙ ሌሎች ሠራተኞችን አየና፣
\v 4 'እናንተ ደግሞ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሂዱ፤ የሚገባችሁንም እከፍላችኋለሁ' አላቸው። ስለዚህ እነርሱም ሊሠሩ ሄዱ።
\s5
\v 5 ደግሞ በስድስት ሰዓትና በዘጠኝ ሰዓት ገደማ ወጥቶ እንደዚሁ አደረገ።
\v 6 አሁንም በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ገደማ ወጥቶ ሥራ ፈትተው የቆሙ ሌሎችን አገኘ። እነርሱንም፣ 'ቀኑን ሙሉ ሥራ ፈትታችሁ እዚህ ለምን ቆማችኋል?' አላቸው።
\v 7 'ማንም ስላልቀጠረን ነው' አሉት። 'እናንተም ደግሞ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሂዱ' አላቸው።
\s5
\v 8 ቀኑ በመሸ ጊዜ፣ የወይኑ አትክልት ባለቤት ሥራ አስኪያጁን፣ 'ሠራተኞቹን ጥራ ከኋለኞቹ አንሥተህ እስከ ፊተኞቹ የሠሩበትን ገንዘብ ክፈላቸው' አለው።
\v 9 በዐሥራ አንደኛው ሰዓት የተቀጠሩት ሠራተኞች በመጡ ጊዜ፣ እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ።
\v 10 ፊተኞቹ ሠራተኞች በመጡ ጊዜ፣ የበለጠ የሚቀበሉ መሰላቸው፤ ነገር ግን እነርሱም ደግም እያንዳንዳቸው አንዳንድ ዲናር ተቀበሉ።
\s5
\v 11 ገንዘባቸውን በተቀበሉ ጊዜ፣ በወይኑ አትክልት ባለቤት ላይ አጕረመረሙ።
\v 12 እንዲህም አሉ፤ 'እነዚህ በመጨረሻ የመጡ ሠራተኞች በሥራ ላይ አንድ ሰዓት ብቻ አሳልፈዋል፤ ነገር ግን አንተ የዕለቱን ሸክምና የሚለበልበውን ሙቀት ከተሸከምነው ከእኛ ጋር እኩል አድርገሃቸዋል።'
\s5
\v 13 ባለቤቱ ግን መልሶ ከእነርሱ አንዱን እንዲህ አለው፤ "ወዳጄ ሆይ፣ አልበደልኩህም። ከእኔ ጋር በአንድ ዲናር አልተስማማህምን?
\v 14 የሚገባህን ተቀብለህ መንገድህን ሂድ፤ ለእነዚህ በመጨረሻ ለተቀጠሩት ሠራተኞች ልክ እንደ አንተው ልሰጣቸው ደስ ይለኛል።
\s5
\v 15 በገዛ ንብረቴ የፈለግሁትን ማድረግ አይገባኝምን? ወይስ እኔ ደግ ስለ ሆንሁ ትመቀኛለህን?
\v 16 ስለዚህ ኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።"
\s5
\v 17 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ስለ ነበር፣ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ለብቻቸው ወሰደ፤ በመንገድ ላይም እንዲህ አላቸው፦
\v 18 እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለሕግ መምህራን ተላልፎ ይሰጣል። ሞትም ይፈርዱበታል፤
\v 19 እንዲዘብቱበት፣ እንዲገርፉት፣ እንዲሰቅሉትም ለአሕዛብ ይሰጡታል። ነገር ግን በሦስተኛው ቀን ይነሣል።"
\s5
\v 20 በዚያን ጊዜ የዘብዴዎስ ልጆች እናት ከልጆቿ ጋር ወደ ኢየሱስ መጣች፤ በፊቱ ተንበርክካም ከእርሱ አንድ ነገር ለመነች።
\v 21 ኢየሱስ፣ "ምን ትፈልጊያለሽ?" አላት። እርሷም፣ "በመንግሥትህ እነዚህ ሁለት ልጆቼ አንዱ በቀኝህ፣ አንዱም በግራህ እንዲቀመጡ እዘዝ" አለችው።
\s5
\v 22 ኢየሱስ ግን መልሶ፣ "የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ የምጠጣውን ጽዋ መጠጣት ትችላላችሁን?" አለ። እነርሱ፣ "እንችላለን" አሉት።
\v 23 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "በርግጥ ጽዋዬን ትጠጣላችሁ። በቀኜና በግራዬ መቀመጥን የምሰጥ ግን እኔ አይደለሁም፤ ነገር ግን በአባቴ ለተዘጋጀላቸው ለእነርሱ ነው።"
\v 24 ሌሎቹ ዐሥሩ ደቀ መዛሙርት ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በሁለቱ ወንድማማች ላይ ተቈጡ።
\s5
\v 25 ነገር ግን ኢየሱስ ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ "የአሕዛብ አለቆች ሕዝባቸውን ጨቊነው ይገዛሉ፤ የበላዮቻቸውም ይሠለጥኑባቸዋል።
\v 26 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መደረግ የለበትም። ይልቁንም፣ ከእናንተ መካከል ታላቅ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን፤
\v 27 ከእናንተም ፊተኛ ሊሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ይሁን።
\v 28 የሰው ልጅ ሊያገለግል፣ ሕይወቱንም ለብዙዎች ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ እንጂ፣ እንዲያገለግሉት አልመጣም።"
\s5
\v 29 ከኢያሪኮ እንደ ወጡ፣ ብዙ ሕዝብ ኢየሱስን ተከተሉት።
\v 30 እነሆ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች በመንገድ ዳር ተቀምጠው ነበር፤ ኢየሱስ ሲያልፍ በሰሙ ጊዜ ጮኽ ብለው፣ "ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ፣ ማረን" አሉ።
\v 31 ሕዝቡ ግን ዝም እንዲሉ በመንገር ገሠጿቸው። ይሁን እንጂ፣ እነርሱ አብዝተው በመጮኽ፣ "ጌታ ሆይ፣ የዳዊት ልጅ ማረን" አሉ።
\s5
\v 32 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ቆም ብሎ ጠራቸውና፣ "ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?" አለ።
\v 33 እነርሱም፣ "ጌታ ሆይ፣ ዐይኖቻችን እንዲከፈቱ ነው" አሉት።
\v 34 ከዚያም ኢየሱስ ራርቶ፣ ዐይኖቻቸውን ዳሰሰ። እነርሱም ወዲያውኑ አይተው ተከተሉት።
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም እንደቀረቡ፣ በደብረ ዘይት ወዳለው ወደ ቤተ ፋጌ መጡ፤
\v 2 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ሁለት ደቀ መዛሙርት ላከ፤ “ወደሚቀጥለው መንደር ሂዱ፤ አህያም ከነውርንጫዋ ታስራ ታገኛላችሁ። ፈትታችሁ ወደ እኔ አምጧቸው፤
\v 3 ማንም ስለዚያ አንዳች ቢናገራችሁ፣ እርሱም ከእናንተ ጋር ፈጥኖ ይሰዳቸዋል።”
\s5
\v 4-5 ይህ የሆነው፣ “እነሆ፣ ንጉሥሽ ትሑት ሆኖ በአህያና በውርንጫዋ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል ብላችሁ ለጽዮን ልጅ ንገሯት” ተብሎ በነቢዩ የተተነበየው ይፈጸም ዘንድ ነው።
\s5
\v 6 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሄደው ልክ ኢየሱስ እንዳዘዛቸው አደረጉ።
\v 7 አህያይቱንና ውርንጫዋን አመጡ፤ ልብሳቸውንም አደረጉባቸውና ኢየሱስ ተቀመጠባቸው።
\v 8 ከሕዝቡ አብዛኞቹ ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፣ ሌሎችም የዘንባባ ዝንጣፊ እየቈረጡ በመንገድ ላይ አደረጉ።
\s5
\v 9 ከኢየሱስ ፊት ይሄዱ የነበሩትና የተከተሉትም ሕዝብ፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ እርሱ የተባረከ ነው። ሆሣዕና በአርያም ይሁን!” በማለት ጮኹ።
\v 10 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ ከተማይቱ በሞላ ታወከችና፣ “ይህ ማን ነው?” አለች።
\v 11 ሕዝቡ፣ “ይህ ከገሊላ ናዝሬት የሆነው ነቢዩ ኢየሱስ ነው” ብለው መለሱ።
\s5
\v 12 ከዚያም ኢየሱስ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደ። በቤተ መቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን አስወጣ። የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛዎችና ወንበሮች ገለበጠ።
\v 13 እንዲህም አላቸው፤ ‘ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል’ ተብሎ ተጽፏል። እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት።"
\v 14 ከዚያም ዐይነ ስውሮችና ሽባዎች ወደ እርሱ ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።
\s5
\v 15 ነገር ግን የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን እርሱ ያደረጋቸውን ድንቅ ነገሮች ባዩና በቤተ መቅደስ ልጆች፣ “ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ” በማለት ሲጮኹ በሰሙ ጊዜ፣ ተቈጡ።
\v 16 “ሕዝቡ የሚሉትን ትሰማለህን?” አሉት። ኢየሱስ፣ “አዎ! ነገር ግን ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ’ የሚለውን ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።
\v 17 ከዚያም ኢየሱስ ትቷቸው ከከተማው ወጣና ወደ ቢታንያ ሄዶ በዚያ ዐደረ።
\s5
\v 18 ኢየሱስ ጠዋት ወደ ከተማው እንደተመለሰ፣ ተራበ።
\v 19 በመንገድ ዳር አንዲት የበለስስ ተክል አየና ወደ እርሷ ሄደ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም። “ሁለተኛ ከቶ ፍሬ አይገኝብሽ” አላት። የበለስ ተክሊቱም ወዲያውኑ ደረቀች።
\s5
\v 20 ደቀ መዛሙርቱ ባዩአት ጊዜ ተደንቀው፣ “የበለስ ተክሊቱ እንዴት ወዲያውኑ ደረቀች?” አሉ።
\v 21 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ "እውነት እላችኋለሁ፣ እምነት ቢኖራችሁና ባትጠራጠሩ፣ በዚች የበለስ ተክል የሆነባትን ብቻ ሳይሆን፣ ይህን ኮረብታ ከዚህ ተነሥተህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት እንኳ ይሆናል።
\v 22 አምናችሁ በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ።”
\s5
\v 23 ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ሲያስተምር የካህናት አለቆችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ወደ እርሱ መጥተው፣ “በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ?” አሉ።
\v 24 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ደግሞ አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ። ያንን ከነገራችሁኝ እኔ ደግሞ በማን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ እነግራችኋለሁ።
\s5
\v 25 የዮሐንስ ጥምቀት ከየት መጣ ከሰማይ ነውን ወይስ ከሰዎች?” እርስ በርሳቸው እንዲህ በማለት ተነጋገሩ፤ “ከሰማይ ነው ብንለው፣ ‘ለምን አታምኑትም? ይለናል።
\v 26 ነገር ግን ‘ከሰው ነው ብንል፣ ዮሐንስን እንደ ነቢይ ስለሚያዩት ሕዝቡን እንፈራለን።”
\v 27 ከዚያም መልሰው ኢየሱስን፣ “አናውቅም” አሉት። እርሱ ደግሞ፣ “እኔም በምን ሥልጣን እነዚህን ነገሮች እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው።
\s5
\v 28 ነገር ግን ምን ይመስላችኋል? አንድ ሰው ሁለት ልጆች ነበሩት፣ ወደ መጀመሪያው ሄዶ፣ ልጄ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ወይኑ አትክልት ስፍራ ሄደህ ሥራ’ አለው።
\v 29 ልጁ መልሶ፣ ‘አልሄድም’ አለ፤ በኋላ ግን ዐሳቡን ለውጦ ሄደ።
\v 30 ሰውዬውም ወደ ሁለተኛው ልጅ ሄዶ ይህንኑ ነገረው። ይህኛው ልጅ መልሶ፣ ‘እሄዳለሁ፣ አባዬ’ አለ። ነገር ግን አልሄደም።
\s5
\v 31 ከሁለቱ ልጆች የአባቱን ትእዛዝ የፈጸመው የትኛው ነው? እነርሱ፣ "የመጀመሪያው” አሉ። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ቀድመዋችሁ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይገባሉ።
\v 32 ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ ወደ እናንተ መጥቶ ነበርና፤ እናንተ ግን አላመናችሁትም፤ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ግን አመኑት። እናንተም ይህ ሲሆን አይታችሁ ታምኑት ዘንድ በኋላ እንኳ ንሰሐ አልገባችሁም።
\s5
\v 33 ሌላም ምሳሌ ስሙ። ሰፊ መሬት ያለው አንድ ሰው ነበር። የወይን አትክልት ተከለ፤ ዐጥር አጠረለት፤ የወይን መጥመቂያ ማሰለት፤ መጠበቂያ ማማ ሠራለት፤ ለወይን ገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
\v 34 የወይን ፍሬ የሚሰበሰብበት ጊዜ እንደ ደረሰ፣ ፍሬውን እንዲቀበሉ ጥቂት አገልጋዮችን ላከ።
\s5
\v 35 የወይኑ ገበሬዎች ግን አገልጋዮቹን ያዙ፤ አንዱን ደበደቡት፣ ሌላውን ገደሉት፤ ሌላውንም በድንጋይ ወገሩት።
\v 36 ባለቤቱ እንደ ገና ከፊተኞቹ የበዙ ሌሎች አገልጋዮችን ላከ፤ ነገር ግን የወይን ገበሬዎቹ ያንኑ አደረጉባቸው።
\v 37 ከዚያ በኋላ ባለቤቱ፣ ‘ልጄንስ ያከብሩታል’ በማለት የገዛ ልጁን ላከ።
\s5
\v 38 የወይን ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ፣ እርስ በርሳቸው፣ 'ይህ ወራሹ ነው፤ ኑ፣ እንግደለውና ርስቱን እንውረስ’ ተባባሉ።
\v 39 ስለዚህ ያዙትና ከወይኑ አትክልት ስፍራ ወደ ውጭ ጣሉት፤ ገደሉትም።
\s5
\v 40 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ባለቤት በሚመጣበት ጊዜ እነዚያን የወይን ገበሬዎች ምን ያደርጋቸዋል?”
\v 41 ሕዝቡ እንዲህ አሉት፤ “እነዚያን ክፉ ሰዎች እጅግ በጣም አሰቃቂ በሆነ መንገድ ያጠፋቸዋል፤ ከዚያም የወይኑን አትክልት ስፍራ ወይኑ በሚያፈራበት ጊዜ ገንዘቡን ለሚከፍሉ ለሌሎች የወይን ገበሬዎች ያከራየዋል።”
\s5
\v 42 ኢየሱስ እነርሱን፣ “ 'ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ። ይህ ከጌታ ዘንድ ሆነ፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው ተብሎ የተጻፈውን ፈጽሞ አላነበባችሁም?
\s5
\v 43 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ትወሰድና ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች።
\v 44 በዚህ ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ሁሉ ይሰባበራል። ድንጋዩ የሚወድቅበትን ሁሉ ግን ይፈጨዋል።”
\s5
\v 45 የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ምሳሌዎቹን በሰሙ ጊዜ፣ የተናገረው ስለ እነርሱ እንደ ሆነ ተረዱ።
\v 46 ነገር ግን ሊይዙት በፈለጉ ጊዜ ሁሉ፣ ሰዎቹ እንደ ነቢይ ይቈጥሩት ስለ ነበር ሕዝቡን ፈሩ።
\s5
\c 22
\cl ምዕራፍ 22
\p
\v 1 ኢየሱስም ደግሞ እንዲህ በማለት በምሳሌ መለሰላቸው፤
\v 2 "መንግሥተ ሰማይ ለልጁ የሰርግ ድግስ የደገሰ ንጉሥን ትመስላለች፡፡
\v 3 ወደ ሰርጉ እንዲመጡ ወደ ጋበዛቸው ሰዎች አገልጋዮቹን ላከ፤ እነርሱ ግን መምጣት አልፈለጉም፡፡
\s5
\v 4 እንደ ገና ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንዲህ በማለት ላከ፤ "እነሆ፣ እራት አዘጋጅቻለሁ፤ በሬዎቼንና የሰቡ ወይፈኖቼን አርጃለሁ፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአልና ወደ ሰርግ ግብዣው ኑ በሏቸው፡፡' "
\s5
\v 5 ሰዎቹ ግን ግብዣውን ከልብ አልተቀበሉትም፡፡ አንዳንዶቹ ወደ እርሻዎቻቸው፣ ሌሎች ደግሞ ወደ ሥራ ቦታቸው ሄዱ፡፡
\v 6 አንዳንዶቹ የንጉሡን አገልጋዮች ደበደቡአቸው፤ አዋረዱአቸው፤ ገደሉአቸው፡፡
\v 7 ንጉሡ ግን ተቈጣ፤ ወታደሮቹን ላከ፤ እነዚያን ነፍሰ ገዳዮች ገደለ፤ ከተማቸውንም አቃጠለ፡፡
\s5
\v 8 ከዚያም ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፤ 'ሰርጉ ተዘጋጅቶአል፤ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች ግን የሚገባቸው ሆነው አልተገኙም፡፡
\v 9 ስለዚህ ወደ ዐውራ መንገድ ማቋረጫ ሄዳችሁ የምታገኙአቸውን ያህል ሰዎች ወደ ሰርጉ ግብዣ ጥሩ፡፡
\v 10 ሰዎቹም ወደ ዐውራው መንገድ ሄደው መልካምም ሆኑ መጥፎዎች ያገኙአቸውን ሁሉ አንድ ላይ ሰበሰቡ፡፡ ስለዚህ የግብዣው አዳራሽ በተጋባዦች ተሞላ፡፡
\s5
\v 11 ንጉሡ ተጋባዦቹን ለማየት ሲመጣ ግን፣ የሰርግ ልብስ ያልለበሰ ሰው አየ፡፡
\v 12 ንጉሡ እንዲህ አለው፤ ‹ወዳጄ፣' የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ? ሰውየውም ዝም አለ፡፡
\s5
\v 13 ከዚያም ንጉሡ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አላቸው፤ እጅና እግሩን አስራችሁ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት፡፡'
\v 14 የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡"
\s5
\v 15 ከዚያም ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስን እንዴት በንግግሩ ማጥመድ እንደሚችሉ ዕቅድ አወጡ፡፡
\v 16 ከዚያም ከሄሮድስ ሰዎች ጋር ደቀ መዛሙርታቸውን ወደ እርሱ ላኩ፡፡ ኢየሱስንም እንዲህ አሉት፤ "መምህር ሆይ፣ አንተ በእውነት የእግዚአብሔርን መንገድ የምታስተምር እውነተኛ ሰው መሆንህን እናውቃለን፤ ሰውን በመፍራት ዐሳብህን አትለውጥም፤ በሰዎች መካከል አድልዎ አታደርግም፡፡
\v 17 እስቲ ንገረን ምን ይመስልሃል? ለቄሳር ግብር መስጠት ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?"
\s5
\v 18 ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፤ "እናንት ግብዞች የምትፈትኑኝ ለምንድን ነው?
\v 19 እስቲ የግብሩን ገንዘብ አሳዩኝ" አላቸው፡፡ እነርሱም ዲናሩን አመጡለት፡፡
\s5
\v 20 ኢየሱስም፣ "ይህ የማን መልክና ስም ነው? አላቸው፡፡
\v 21 እነርሱም፣ "የቄሣር፣" አሉት፡፡ ከዚያም ኢየሱስ፣ "እንግዲያስ የቄሣር የሆነውን ለቄሣር ስጡ፤ የእግዚአብሔር የሆነውን ለእግዚአብሔር ስጡ" አላቸው፡፡
\v 22 ያንን ሲሰሙ ተገረሙ፡፡ ትተውትም ሄዱ፡፡
\s5
\v 23 በዚያው ቀን ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ጥቂት ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጡ፡፡
\v 24 "መምህር ሆይ፣ ‹አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ከሞተ ሚስቱን ወንድሙ እንዲያገባና ለወንድሙ ልጅ እንዲወልድለት ሙሴ ተናግሮአል›
\s5
\v 25 ሰባት ወንድማማች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ሞተ፡፡ ሚስቱ የወንድምየው ሆነች፡፡
\v 26 ሁለተኛውና ሦስተኛውም እስከ ሰባተኛው ድረስ ያንኑ አደረጉ፡፡
\v 27 ከሁሉም በኋላ ደግሞ ሴትየዋ ሞተች፡፡
\v 28 እንግዲህ ሰባቱም ወንድማማች አግብተዋት ነበርና በትንሣኤ ቀን የማንኛው ሚስት ልትሆን ነው?" በማለት ጠየቁት፡፡
\s5
\v 29 ኢየሱስ ግን እንዲህ በማለት መለሰላቸው፤ "መጻሕፍትንም ሆነ የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታወቁ ተሳስታችኋል፡፡
\v 30 ምክንያቱም በትንሣኤ ቀን እንደ ሰማይ መላእክት ይሆናሉ እንጂ፣ አያገቡም፣ ደግሞም አይጋቡም፡፡
\s5
\v 31 ትንሣኤ ሙታንን በተመለከተ፣ እግዚአብሔር
\v 32 "እኔ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ" በማለት ለእናንተ የተናገረውን አላነበባችሁምን? እግዚአብሔር የሕያዋን አምላክ እንጂ፣ የሙታን አምላክ አይደለም፡፡"
\v 33 ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
\s5
\v 34 ኢየሱስ ሰዱቃውያንን ዝም እንዳሰኛቸው ፈሪሳውያን ሲሰሙ፣ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡
\v 35 ከእነርሱ መካከል ሕግ ዐዋቂ የሆነ አንዱ እርሱን ለመፈተን፣
\v 36 "መምህር ሆይ፣ ከሕጉ ሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ የትኛው ነው" ብሎ ጠየቀው፡፡
\s5
\v 37 ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ "እግዚአብሔር አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህና በሙሉ ዐሳብህ ውደድ፡፡"
\v 38 ከሁሉም የሚበልጠው የመጀመሪያው ትእዛዝ ይህ ነው፡፡
\s5
\v 39 ሁለተኛውም ትእዛዝ ያንኑ ይመስላል፤ 'ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፡፡'
\v 40 ሕግና ነቢያት ሁሉ የትመሠረቱት በእነዚህ ሁለት ትእዛዛት ላይ ነው፡፡
\s5
\v 41 ፈሪሳውያን በአንድነት ተሰብስበው እያለ ኢየሱስ አንድ ጥያቄ አቀረበላቸው፡፡
\v 42 "ስለ ክርስቶስ ምን ታስባላችሁ? ለመሆኑ የማን ልጅ ነው?" አላቸው፡፡ "የዳዊት ልጅ ነው" አሉት፡፡
\s5
\v 43 ኢየሱስም፣ "ታዲያ፣ ዳዊት፣ በመንፈስ፣
\v 44 ጌታ ጌታዬን ‹ጠላቶችህን በእግርህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ' በማለት እንዴት ጌታ ብሎ ይጠራዋል?
\s5
\v 45 ዳዊት ክርስቶስን 'ጌታ' በማለት ከጠራው እንዴት የዳዊት ልጅ ሊሆን ይችላል?"
\v 46 ማንም አንዲት ቃል ሊመልስለት አልቻለም፤ ከዚያ ቀን ጀምሮ ጥያቄ ሊያቀርብለት የደፈረ አልነበረም፡፡
\s5
\c 23
\cl ምዕራፍ 23
\p
\v 1 ከዚያም ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል ተናገረ፤
\v 2 "የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል፡፡
\v 3 ስለዚህ የሚያዝዙአችሁን ሁሉ አድርጉ፤ አክብሩትም፡፡ እነርሱ የሚያደርጉትን ግን አታደርጉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው የሚናገሩትን አያደርጉትም፡፡
\s5
\v 4 ለመሸከም የሚያስቸግር ከባድ ሸክም አንሥተው በሰዎች ትከሻ ላይ ይጭናሉ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ግን መሸከም ቀርቶ በጣታቸው ሊያነሡት እንኳ አይፈልጉም፡፡
\v 5 ሥራቸውን ሁሉ የሚያደርጉት በሰዎች ለመታየት ነው፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የልብሳቸውንም ዘርፍ ያስረዝማሉ፡፡
\s5
\v 6 ግብዣ ላይ የከበሬታ ቦታዎችንና በምኵራብ ውስጥ የተለየ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ይፈልጋሉ፤
\v 7 በገበያ ቦታ ሰዎች የተለየ ክብር እንዲሰጧቸውና፣ 'መምህር ሆይ› በማለት እንዲጠሩአቸው ይፈልጋሉ፡፡
\s5
\v 8 እናንተ ግን ያላችሁ አንድ መምህር ብቻ ስለሆነና ሁላችሁም ወንድማማች ስለሆናችሁ ‹መምህር› ተብላችሁ አትጠሩ፡፡
\v 9 በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ፤ ምክንያቱም በሰማይ የሚኖር አንድ አባት ብቻ አላችሁ፡፡
\v 10 ‹ሊቅም› ተብላችሁ አትጠሩ፤ ምክንያቱም ያላችሁ አንድ ሊቅ ብቻ ነው፤ እርሱም ክርስቶስ ነው፡፡
\s5
\v 11 ከእናንተ መካከል ታላቅ የሆነው አገልጋያችሁ ይሁን፡፡
\v 12 ራሱን ከፍ የሚያደርግ ዝቅ ይላል፤ ራሱን ዝቅ የሚያደርግ ከፍ ይላል፡፡
\s5
\v 13 እናንተ፣ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ግን ወዮላችሁ! በሰዎች ፊት መንግሥተ ሰማይን ትዘጋላችሁ፡፡ እናንተ ራሳችሁ አትገቡበትም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ፡፡
\v 14 \f + \ft በጣም የታወቁ የጥንት ቅጂዎች ቊጥር 14 የላቸውም፡፡ (አንዳንድ ቅጂዎች ይህን እዚህና ከቊጥር 12 በኋላ አስገብተውታል)፡፡ \f*
እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ለታይታ ረጅም ጸሎታችሁን በማድረግ የመበለቶችን ቤት ስለምትበሉ ወዮላችሁ! ስለዚህ የበለጠውን ፍርድ ትቀበላላችሁ፡፡ እናንተ ግብዞች የአይሁድ ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ!
\v 15 አንድን ሰው ተከታያችሁ ለማድረግ በባሕርና በምድር ትሄዳላችሁ፤ ተከታያችሁ ካደረጋችሁት በኋላ፣ ከእናንተ እጥፍ የሚከፋ የገሃነም ልጅ ታደርጉታላችሁ፡፡
\s5
\v 16 እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች ወዮላችሁ፤ አንድ ሰው 'በቤተ መቅደሱ ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ባለው ወርቅ ቢምል ግን፣ በመሐላው ይጠመዳል' ትላላችሁ፡፡
\v 17 እናንተ የታወራችሁ ሞኞች፣ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ወርቁ ወይስ ወርቁን የሚቀድሰው ቤተ መቅደሱ?
\s5
\v 18 አንድ ሰው በመሠዊያው ቢምል ምንም ማለት አይደለም፤ መሠዊያው ላይ ባለው ስጦታ ቢምል ግን በመሐላው ይጠመዳል ትላላችሁ፡፡
\v 19 እናንተ ዕውሮች፤ ለመሆኑ የትኛው ይበልጣል ስጦታው ወይስ ስጦታውን የሚቀድሰው መሠዊያ?
\s5
\v 20 ስለዚህ በመሠዊያው የሚምል በመሠዊያውና እርሱ ላይ ባሉ ነገሮች ሁሉ ይምላል፡፡
\v 21 በቤተ መቅደሱ የሚምል በቤተ መቅደስና እርሱ ውስጥ በሚኖረው ይምላል፡፡
\v 22 በሰማይ የሚምል በእግዚአብሔር ዙፋንና በእርሱ ላይ በተቀመጠው ይምላል፡፡
\s5
\v 23 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፣ ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራት ብታወጡም፣ የሕጉን ዋና ዋና ነገሮች ማለትም ፍትሕን፣ ምሕረትንና እምነትን ሥራ ላይ አታውሉም፡፡ ሌላውን ችላ ሳትሉ እነዚህን መፈጸም ነበረባችሁ፡፡
\v 24 እናንተ ዐይነ ስውራን መሪዎች፣ ትንኝን አውጥታችሁ ትጥላላችሁ፤ ግመልን ግን ትውጣላችሁ!
\s5
\v 25 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የጽዋውንና የሳሕኑን ውጫዊ ክፍል ታጠራላችህ፤ ውስጡ ግን ቅሚያና ስስት ሞልቶበታል፡፡
\v 26 አንተ ዕውር ፈሪሳዊ፣ ውጫዊ አካሉም ንጹሕ እንዲሆን በመጀመሪያ የጽዋውንና የሳሕኑን ውስጥ አጽዳ፡፡
\s5
\v 27 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ከውጭ ሲያዩት እንደሚያምር፣ ውስጡ ግን የሞቱ ሰዎች አጥንትና ርኵሰት እንደ ሞላበት መቃብር ናችሁ፡፡
\v 28 በተመሳሳይ መንገድ እናንተም ከውጭ ለሰዎች ጻድቃን ትመስላላችሁ፤ ውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ርኲሰት ሞልቶበታል፡፡
\s5
\v 29 እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! የነቢያትን መቃብር ስለምትሠሩ፣ የጻድቃንን መቃብር ስለምታስጌጡ፣
\v 30 በአባቶቻችን ዘመን ኖረን ቢሆን ኖሮ፣ የነቢያትን ደም በማፍሰስ አንተባበራቸውም ነበር ትላላችሁ፡፡
\v 31 ስለሆነም የነቢያት ገዳይ ልጆች መሆናችሁን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡
\s5
\v 32 እናንተ ራሳችሁም አባቶቻችሁ የጀመሩትን ኃጢአት ትፈጽማላችሁ፡፡
\v 33 እናንተ እባቦች፣ እናንተ የእፉኝት ልጆች፣ ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ?
\s5
\v 34 ስለዚህ ነቢያትን፣ አስተዋይ ሰዎችንና የአይሁድ ሕግ መምህራንን ወደ እናንተ እልካለሁ፡፡ አንዳንዶቹን ትገድላላችሁ፣ ትሰቅላላችሁ፤ ሌሎቹን በምኵራቦቻችሁ ትገርፋላችሁ፣ ከከተማ ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፡፡
\v 35 ከጻድቁ ከአቤል አንሥቶ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካካል እስከ ገደላችሁት የበራክዩ ልጅ ዘካርያስ ደም ድረስ፣ በምድር ላይ በፈሰሰው ጻድቃን ደም ሁሉ ትጠየቃላችሁ፡፡
\v 36 እውነት እላችኋለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 37 ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትን በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን መሰብሰበ ብዙ ጊዜ ፈልጌ ነበር፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም!
\v 38 ስለሆነም ቤታችሁ ወና ሆኖ ይቀራል፡፡
\v 39 'በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስክትሉ ድረስ ከአሁን ጀምሮ አታዩኝም እላችኋለሁ፡፡
\s5
\c 24
\cl ምዕራፍ 24
\p
\v 1 ኢየሱስ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ እየሄደ ሳለ፤ ደቀ መዛሙርቱ የቤተ መቅደሱን ሕንጻ ሊያሳዩት ወደ እርሱ መጡ፡፡
\v 2 እርሱ ግን፣ "እነዚህን ሁሉ ነገሮች ታያላችሁ? እውነት እላችኋለሁ፣ ይፈርሳል እንጂ፣ አንድ ድንጋይ እንኳ በሌላ ድንጋይ ላይ እንደ ተነባበረ አይቀርም" በማለት መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 3 በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ መጥተው፣ "እስቲ ንገረን፤ ይህ ሁሉ የሚሆነው መቼ ነው? የአንተ መምጣትና የዓለም መጨረሻስ ምልክቱ ምንድን ነው?" አሉት፡፡
\v 4 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፣ "ማንም እንዳያሳስታችሁ ተጠንቀቁ፡፡
\v 5 ምክንያቱም ብዙዎች በስሜ ይመጣሉ፤ 'እኔ ክርስቶስ ነኝ' እያሉ ብዙዎችን ያሳስታሉ
\s5
\v 6 ጦርነትንና የጦርነትን ዜና ትሰማላችሁ፤ በፍጹም እንዳትታወኩ፤ ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች እንዲሆኑ ግድ ነው፤ ቢሆንም፣ መጨረሻው ገና ነው፡፡
\v 7 ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፡፡ በተለያየ ቦታ ራብና የምድር መናወጥ ይሆናል፡፡
\v 8 እነዚሀ ሁሉ ግን የምጥ ጣር መጀመሪያ ብቻ ናቸው፡፡
\s5
\v 9 ከዚያም ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል ይገድሏችኋልም፡፡ ስለ ስሜ ሕዝቦች ሁሉ ይጠሏችኋል፡፡
\v 10 ብዙዎች ይሰናከላሉ፤ እርስ በርስ ይካካዳሉ፤ እርስ በርስ ይጠላላሉ፡፡
\v 11 ብዙ ሐሰተኛ ነቢያት ተነሥተው፣ ብዙዎችን ያሳስታሉ፡፡
\s5
\v 12 ዐመፅ ስለሚበዛ የብዙዎች ፍቅር ይቀዘቅዛል፡፡
\v 13 እስከ መጨረሻ የሚታገሥ ግን ይድናል፡፡
\v 14 ለሕዝቦች ሁሉ ምስክር እንዲሆን የመንግሥቱ ወንጌል ለመላው ዓለም ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል፡፡
\s5
\v 15 ስለዚህ በነቢዩ ዳንኤል የተነገረለት የጥፋት ርኲሰት በተቀደሰው ቦታ ቆሞ ስታዩ፣ (ያኔ አንባቢው ያስተውል)
\v 16 በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣
\v 17 ጣራ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ያለውን ምንም ነገር ከቤቱ ለመውሰድ አይመለስ፣
\v 18 በእርሻ ያለ ልብሱን ለመውሰድ አይመለስ፡፡
\s5
\v 19 ልጆች ላሉአቸውና ለሚያጠቡ እናቶች ግን ወዮላቸው!
\v 20 ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፡፡
\v 21 ምክንያቱም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስና ከዚያም በኋላ ፈጽሞ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል፡፡
\v 22 እነዚያ ቀኖች ባያጥሩ ኖሮ፣ ማንም ሥጋ ለባሽ አይድንም ነበር፤ ለተመረጡት ሲባል ግን እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ፡፡
\s5
\v 23 ስለዚህ ማንም "እነሆ ክርስቶስ፣ እዚህ ነው" ወይም፣ 'ክርስቶስ እዚያ ነው' ቢላችሁ አትመኑ፡፡
\v 24 ምክንያቱም ብዙዎችን ለማሳሳት ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት መጥተው ታላላቅ ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋሉ፤ ከተቻለም የተመረጡትን እንኳ ያሳስታሉ፡፡
\v 25 ይህ ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነግሬአችኋለሁ፡፡
\s5
\v 26 ስለዚህ፣ ‹ክርስቶስ በምድረ በዳ ነው› ቢሏችሁ ወደ ምድረ በዳ አትሂዱ ወይም ቤት ውስጥ ነው ቢሏችሁ አትመኑ፡፡
\v 27 መብረቅ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአንዴ እንደሚታይ የሰው ልጅ ሲመጣ እንደዚያው ይሆናል፡፡
\v 28 የሞተ እንስሳ ባለበት ሁሉ፣ በዚያ አሞሮች ይሰበሰባሉ፡፡
\s5
\v 29 ከእነዚህ የመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብት ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉ፡፡
\s5
\v 30 ከዚያም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፤ የምድር ነገዶች ሁሉ አምርረው ያለቅሳሉ፡፡ የሰው ልጅንም በኀይልና በታላቅ ክብር ሲመጣ ያዩታል፡፡
\v 31 መላእክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል፤ እነርሱም፣ ከአንድ የሰማይ ጫፍ እስከ ሌላው ጫፍ ድረስ ከአራቱም ነፋሳት ምርጦቹን ይሰበስቧቸዋል፡፡
\s5
\v 32 ከበለስ ዛፍ ተማሩ፡፡ ቅርንጫፎቿ ሲለመልሙና ቅጠሎች ብቅ ብቅ ሲሉ በጋ መቅረቡን ታውቃላችሁ፡፡
\v 33 እናንተም እነዚህን ሁሉ ስታዩ እርሱ መቅረቡን፣ እንዲያውም በደጅ መሆኑን ዕወቁ፡፡
\s5
\v 34 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም፡፡
\v 35 ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም፡፡
\s5
\v 36 ስለዚያች ቀንና ሰዓት ግን ማንም አያውቅም፤ የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ አያወቁም፤ አብ ብቻ እንጂ ወልድ እንኳ ቢሆን አያውቅም፡፡
\s5
\v 37 በኖኅ ዘመን እንደ ነበረው፣ የሰው ልጅ መምጣትም እንዲሁ ይሆናል፡፡
\v 38 ከጥፋት ውሃ በፊት እንደ ነበረው ዘመን፣ ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባ ድረስ ይበሉና ይጠጡ፣ ያገቡና ይጋቡ ነበር።
\v 39 ጐርፉ መጥቶ እስኪያጠፋቸው ድረስ ምንም አላወቁም፣ የሰው ልጅ ሲመጣም እንዲሁ ይሆናል፡፡
\s5
\v 40 በዚያን ጊዜ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል ሌላው ይቀራል፡፡
\v 41 ሁለት ሴቶች በወፍጮ ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች፡፡
\v 42 ስለዚህ ጌታችሁ በምን ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተጠንቀቁ፡፡
\s5
\v 43 ይህን ግን ዕወቁ፤ ሌባው በየትኛው ሰዓት እንደሚመጣ የቤቱ ባለቤት ቢያውቅ ኖሮ ይጠነቀቅ ነበር፤ ቤቱ አይዘረፍም ነበር፡፡
\v 44 የሰው ልጅ ባልጠበቃችሁት ሰዓት ስለሚመጣ እናንተም ብትሆኑ ተዘጋጅታችሁ መጠበቅ አለባችሁ፡፡
\s5
\v 45 በተገቢው ጊዜ ለቤተ ሰቦቹ ምግባቸውን ለመስጠት ጌታው በቤቱ ላይ ኀላፊነት የሰጠው ታማኝና አስተዋይ አገልጋይ ማን ነው?
\v 46 ጌታው ሲመጣ ያንን እያደረገ የሚያገኘው አገልጋይ የተባረከ ነው፡፡
\v 47 እውነት እላችኋለሁ የምላችሁ፣ ጌታው ባለው ነገር ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ይሾመዋል፡፡
\s5
\v 48 ይሁን እንጂ፣ አንድ ክፉ አገልጋይ በልቡ፣ ‹‹ጌታዬ ከመምጣት ዘግይቶአል ብሎ ቢያስብ፣
\v 49 አገልጋይ ጓደኞቹን መደብደብና ከሰካራሞች ጋር መብላት መጠጣት ቢጀምር
\v 50 የዚያ አገልጋይ ጌታ አገልጋዩ ባልጠበቀው ቀንና በማያውቀው ሰዓት ይመጣበታል፡፡
\v 51 ጌታው ለሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕጣ ፈንታውን ከግብዞች ጋር ያደርግበታል፣ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡
\s5
\c 25
\cl ምዕራፍ 25
\p
\v 1 መንግሥተ ሰማይ መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ለመቀበል የወጡ ዐሥር ድንግሎችን ትመስላለች።
\v 2 ዐምስቱ ሞኞች፣ ዐምስቱ ልባሞች ነበሩ።
\v 3 ሞኞቹ ድንግሎች መብራታቸውን ይዘው ሲሄዱ ምንም ዘይት አልያዙም ነበር።
\v 4 ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር ዘይትም ይዘው ነበር።
\s5
\v 5 ሙሽራው በዘገየ ጊዜ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ሁሉም ተኙ።
\v 6 ዕኩለ ሌሊት ላይ ግን፣ “ሙሽራው መጥቶአልና ወጥታችሁ ተቀበሉት!” የሚል ሁካታ ሆነ።
\s5
\v 7 ያኔ እነዚያ ድንግሎች ሁሉ ተነሥተው መብራታቸውን አዘጋጁ።
\v 8 ሞኞቹም ልባሞቹን፣ “መብራታችን እየጠፋ ስለ ሆነ፣ ከዘይታችሁ ጥቂት ስጡን” አሏቸው።
\v 9 ልባሞቹ ግን፣ “ለእኛና ለእናንተ የሚበቃ ስለሌለን፣ ወደ ሻጮች ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ” በማለት መለሱአቸው።
\s5
\v 10 ለመግዛት ሲሄዱ፣ ሙሽራው መጣ፤ ተዘጋጅተው የነበሩት ግብዣው ላይ ለመገኘት ከእርሱ ጋር ሄዱ፤ በሩም ተዘጋ።
\v 11 በኋላ ሌሎቹ ድንግሎች መጥተው፣ “ጌታው፣ በሩን ክፈትልን” አሉ።
\v 12 እርሱ ግን መልሶ፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ አላውቃችሁም” አላቸው።
\v 13 ስለዚህ ቀኑን ወይም ሰዓቱን አታውቁምና ነቅታችሁ ጠብቁ።
\s5
\v 14 ነገሩ ወደ ሌላ አገር ለመሄድ ያሰበ ሰውን ይመስላልና፤ አገልጋዮቹን ጠርቶ በሀብት በንብረቱ ሁሉ ላይ ኀላፊነት ሰጣቸው።
\v 15 እንደ ዐቅማቸው መጠን ለአንዱ ዐምስት መክሊት፣ ለሌላው ሁለት፣ ለሌላው ደግሞ አንድ መክሊት ሰጣቸውና ሄደ።
\v 16 ዐምስት መክሊት የተቀበለው ወዲያውኑ ሄዶ ነገደበት፤ ሌላ ዐምስት አተረፈ።
\s5
\v 17 ሁለት መክሊት የተቀበለውም እንደዚያው ሌላ ሁለት መክሊት አተረፈ።
\v 18 አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ግን ሄዶ ጉድጓድ ቈፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።
\s5
\v 19 ከብዙ ጊዜ በኋላ የእነዚያ አገልጋዮች ጌታ ተመልሶ መጣና ተሳሰባቸው።
\v 20 ዐምስት መክሊት የተቀበለው አገልጋይ ሌላ ዐምስት መክሊት ጨምሮ አመጣና፣ “ጌታ ሆይ፣ ዐምስት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እኔ ግን ሌላ ዐምስት መክሊት አተረፍሁ” አለ።
\v 21 ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ።' አለው።
\s5
\v 22 ሁለት መክሊት ተቀብሎ የነበረው አገልጋይም መጥቶ፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር። ሌላ ሁለት መክሊት አትርፌአለሁ’ አለ።
\v 23 ጌታውም፣ 'አንተ መልካምና ታማኝ አገልጋይ ደግ አደረግህ! በጥቂት ነገሮች ታምነሃል፤ በብዙ ነገሮች ላይ እሾምሃለሁ። ወደ ጌታህ ደስታ ግባ’ አለው።
\s5
\v 24 ከዚያም አንድ መክሊት የተቀበለው አገልጋይ መጥቶ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበት የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ።
\v 25 ስለዚህ ፈራሁ፤ መክሊትህን መሬት ውስጥ ቀበርሁት። መክሊትህ ይኸውልህ' አለው።
\s5
\v 26 ጌታው ግን መልሶ፣ 'አንተ ዐመፀኛና ሰነፍ አገልጋይ፤ ካልዘራሁበት የማጭድ፣ ካልበተንሁበት የምሰበስብ መሆኔን ታውቃለህ።
\v 27 ስለዚህ ገንዘቤን በባንክ ማስቀመጥ ይገባህ ነበር፤ እኔ ስመጣ ከነወለዱ እወስደው ነበር' አለው።
\s5
\v 28 ስለዚህ መክሊቱን ከእርሱ ወስዳችሁ ዐሥር መክሊት ላለው ስጡት።
\v 29 ላለው የበለጠ እንዲያውም የተትረፈረፈ ይሰጠዋል። ምንም ከሌለው ግን፣ ያው ያለው ነገር እንኳ ይወሰድበታል።
\v 30 ይህን የማይረባ አገልጋይ አውጡና ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት በውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት” አለ።
\s5
\v 31 የሰው ልጅ በክብሩ ከመላእክቱ ሁሉ ጋር ሲመጣ፣ በክብር ዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።
\v 32 አሕዛብ ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛ በጎችን ከፍየሎች እንደሚለይ ሕዝቡን ይለያቸዋል።
\v 33 በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን በግራው ያደርጋቸዋል።
\s5
\v 34 ከዚያም ንጉሡ በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፤ 'እናንተ አባቴ የባረካችሁ ኑ፤ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
\v 35 ተርቤ ነበር ምግብ ሰጣችሁኝ፤ ተጠምቼ ነበር የምጠጣው ሰጣችሁኝ፤ እንግዳ ሆኜ ነበር አስተናገዳችሁኝ፤
\v 36 ተራቊቼ ነበር አለበሳችሁኝ፤ ታምሜ ነበር ተንከባከባችሁኝ፤ ታስሬ ነበር ጠየቃችሁኝ' ይላቸዋል።
\s5
\v 37 ከዚያም ጻድቃን እንዲህ ብለው ይመልሱለታል፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ያገኘንህና ያበላንህ ወይስ ተጠምተህ ያጠጣንህ መቼ ነው?
\v 38 38 እንግዳ ሆነህ ያየንህና ያስተናገድንህ መቼ ነው? ወይም ተራቊተህ ያለበስንህ መቼ ነው?
\v 39 ታምመህ የተንከባከብንህ ወይስ ታስረህ የጠየቅንህ መቼ ነው?
\v 40 ንጉሡም መልሶ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ለእነዚህ ታናናሽ ወንድሞቼ ያደረጋችሁትን ለእኔ አድርጋችሁታል።’
\s5
\v 41 ከዚያም በግራው ያሉትን፣ ‘እናንተ ርጉማን ከእኔ ራቁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ገሃነም እሳት ሂዱ።
\v 42 ምክንያቱም ‘ተርቤ ነበር አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ ነበር አላጠጣችሁኝም፤
\v 43 እንግዳ ሆኜ ነበር አልተቀበላችሁኝም፤ ተራቊቼ ነበር አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜ፣ ታስሬ ነበር፣ እናንተ ግን አልተንከባከባችሁኝም’ ይላቸዋል።
\s5
\v 44 እነርሱም መልሰው እንዲህ ይሉታል፤ ‘ጌታ ሆይ፣ ተርበህ ወይም ተጠምተህ ወይም እንግዳ ሆነህ ወይም ተራቊተህ ወይም ታምመህ ወይም ታስረህ ያላገለገልንህ መቼ ነው?
\v 45 እርሱም መልሶ፣ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ አለማድረጋችሁ ለእኔ አለማድረጋችሁ ነው’ ይላቸዋል።
\v 46 እነዚህ ወደ ዘላለም ቅጣት፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።"
\s5
\c 26
\cl ምዕራፍ 26
\p
\v 1 ኢየሱስ እነዚህን ቃሎች ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤
\v 2 "ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካ እንደሚሆን ታውቃላችሁ፣ የሰው ልጅም ተሰቅሎ እንዲገደል ተላልፎ ይሰጣል፡፡"
\s5
\v 3 ከዚያ የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ቀያፋ በሚሉት ሊቀ ካህናት ግቢ ውስጥ ተሰበሰቡ፤
\v 4 ኢየሱስን በረቀቀ ዘዴ ለማሰርና ለመግደል ተማከሩ፡፡
\v 5 ምክንያቱም፣ በሕዝቡ መሓል ረብሻ እንዳይነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም እያሉ ነበር፡፡
\s5
\v 6 ኢየሱስ በቢታንያ በለምጻሙ ስምዖን ቤት
\v 7 ማዕድ ላይ ተቀምጦ እያለ፣ አንዲት ሴት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ ያለበት የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣችና ራሱ ላይ አፈሰሰች፡፡
\v 8 ደቀ መዛሙርቱ ይህን ሲያዩ በጣም ተቈጥተው፣ "ይህ ብክነት ምንድን ነው?
\v 9 ይህ እኮ ከፍ ባለ ዋጋ ተሸጦ ገንዘቡን ለድኾች መስጠት ይቻል ነበር" አሉ፡፡
\s5
\v 10 ኢየሱስም ይህን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፣ "ይህችን ሴት ለምን ታስቸግሯታላችሁ? ለእኔ መልካም ነገር አድርጋለች፡፡
\v 11 ድኾች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልሆንም፡፡
\s5
\v 12 ይህን ሽቱ እኔ ላይ ባፈሰሰች ጊዜ ለቀብሬ አድርጋዋለች፡፡
\v 13 እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ወንጌል በመላው ዓለም ሲሰበክ ለእርሷ መታሰቢያ እንዲሆን ይህች ሴት ያደረገችውም ይነገርላታል።"
\s5
\v 14 ከዚያም የአስቆሮቱ ይሁዳ የሚባለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ወደ ካህናት አለቆቹ ሄዶ፣
\v 15 "እርሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ለእኔ ምን ትሰጡኛላችሁ?" አላቸው፡፡ እነርሱም ሠላሣ ጥሬ ብር ተመኑለት፡፡
\v 16 ከዚያ ጊዜ ወዲህ እርሱን አሳልፎ የሚሰጥበትን ምቹ ጊዜ ይጠባበቅ ጀመር፡፡
\s5
\v 17 በቂጣ በዓል በመጀመሪያው ግን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ "የፋሲካን እራት እንድትበላ የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?" አሉት፡፡
\v 18 እርሱም፣ "ከተማው ውስጥ ወዳለ አንድ ሰው ሂዱና፣ 'መምህሩ "ጊዜዬ ደርሷል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን በአንተ ቤት ማክበር እፈልጋለሁ' ይልሃል በሉት'" አላቸው፡፡
\v 19 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስ እንደ ነገራቸው አደረጉ፤ የፋሲካንም እራት አዘጋጁለት፡
\s5
\v 20 ምሽት ላይ ከዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት ጋር ለመብላት ተቀመጠ፡፡
\v 21 በመብላት ላይ እያሉ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል" አላቸው፡፡
\v 22 እነርሱ በጣም ዐዘኑ፤ እያንዳንዱም፣ "እኔ እሆንን?" በማለት ይጠያየቁ ጀመር፡፡
\s5
\v 23 እርሱም፣ "አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር እጁን ወደ ሳሕኑ የሚሰደው ነው፡፡
\v 24 የሰው ልጅ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈው ይሄዳል፤ የሰውን ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ግን ወዮለት! ያ ሰው ባይወለድ ይሻለው ነበር" በማለት መለሰላቸው፡፡
\v 25 አሳልፎ የሚሰጠው ይሁዳ፣ "መምህር ሆይ፣ እኔ ነኝ እንዴ?" አለው፤ እርሱም፣ "አንተው ራስህ ብለኸዋል" አለው፡፡
\s5
\v 26 በመብላት ላይ እያሉ፣ ኢየሱስ እንጀራ አንሥቶ ባርኮ ቈረሰ፡፡ "እንካችሁ ውሰዱ፣ ብሉት፤ ይህ ሥጋዬ ነው" ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 27 ጽዋውንም አንሥቶ አመሰገነና ሰጣቸው፤ እንዲህም አላቸው፤ "ሁላችሁም ጠጡት
\v 28 ይህ ለብዙዎች ኀጢአት ይቅርታ የሚፈስ የኪዳኑ ደሜ ነው፡፡
\v 29 እንደ ገና በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋር እስክጠጣው ድረስ ከእንግዲህ ከዚህ ወይን ፍሬ እንደማልጠጣ ግን እነግራችኋለሁ፡፡"
\s5
\v 30 መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ወጡ፡፡
\v 31 ያኔ ኢየሱስ፣ "በዚህ ሌሊት ሁላችሁም በእኔ ምክንያት ትሰናከላላችሁ፤ ምክንያቱም፣ 'እረኛውን እመታለሁ በጎቹም ይበተናሉ' ተብሎ ተጽፎአል፡፡
\v 32 ከተነሣሁ በኋላ ግን ቀድሜአችሁ ወደ ገሊላ እሄዳለሁ" አላቸው፡፡
\s5
\v 33 ጴጥሮስ ግን፣ "ሁሉም በአንተ ቢሰናከሉ እንኳ እኔ አልሰናከልም" አለው፡፡
\v 34 ኢየሱስም፣ "እውነት እልሃለሁ ፣ በዚህች ሌሊት ዶሮ ከመጮኹ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ" አለው፡፡
\v 35 ጴጥሮስም፣ "ከአንተ ጋር መሞት ቢኖርብኝ እንኳ አልክድህም" አለ፡፡ ሌሎችም ደቀ መዛሙርት ሁሉ እንደዚያው አሉ፡፡
\s5
\v 36 ከዚያም ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ጌቴሴማኒ ወደሚሉት ቦታ ሄደ፤ ደቀ መዛሙርቱንም፣ "ወደዚያ ሄጄ እስክጸልይ ድረስ እዚህ ሁኑ" አላቸው፡፡
\v 37 ጴጥሮስንና ሁለቱን የዘብዴዎስ ልጆች ይዞ ሄደ፤ ያዝንና ይጨነቅም ጀመር፡፡ ከዚያም፣
\v 38 "ነፍሴ፣ እስከ ሞት ድረስ በጣም ዐዝናለች፡፡ እዚህ ሆናችሁ ከእኔ ጋር ትጉ" አላቸው፡፡
\s5
\v 39 ጥቂት ራቅ ብሎ በመሄድ በግንባሩ ወድቆ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ የሚቻል ከሆነ ይህ ጽዋ ከእኔ ይለፍ፤ ይሁን እንጂ፣ የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን" አለ፡፡
\v 40 ወደ ደቀ መዛሙርቱ ሲመጣ ተኝተው አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም፣ "ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት ያህል እንኳ መትጋት አልቻላችሁምን?
\v 41 ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፡፡ መንፈስ በእርግጥ ፈቃደኛ ነው፤ ሥጋ ግን ደካማ ነው" አለው፡፡
\s5
\v 42 ለሁለተኛ ጊዜ ጥቂት ፈቀቅ ብሎ ጸለየ፤ "አባት ሆይ፣ እኔ ካልጠጣሁት በቀር ይህ የማያልፍ ከሆነ፣ ፈቃድህ ይሁን" አለ፡፡
\v 43 እንደ ገና ሲመጣ ዐይኖቻቸው ከብደው ነበርና ተኝተው አገኛቸው፡፡
\v 44 እንደ ገና ትቶአቸው ሄዶ ለሦስተኛ ጊዜ ያንኑ ቃል ጸለየ፡፡
\s5
\v 45 ከዚያም ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፣ "አሁንም ዐርፋችሁ ተኝታችኋል? ጊዜው ደርሷል፤ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል፡፡
\v 46 እንግዲህ ተነሡ እንሂድ አሳልፎ የሚሰጠኝ ቀርቧል" አላቸው፡፡
\s5
\v 47 ገና እየተናገረ እያለ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ መጣ፣ ከእርሱም ጋር ከካህናት አለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች የመጡ ሰይፍና ዱላ የያዙ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡
\v 48 በዚህ ጊዜ አሳልፎ የሚሰጠው፣ "እኔ የምስመው እርሱ ነው፤ ያዙት" የሚል ምልክት ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 49 ወዲያውኑ ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ "መምህር ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!" ብሎ ሳመው፡፡
\v 50 ኢየሱስም፣ "ወዳጄ፣ የመጣህበትን ጉዳይ ፈጽም" አለው፡፡ ከዚያም መጡ ኢየሱስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፣ ያዙትም።
\s5
\v 51 ከኢየሱስ ጋር ከነበሩት አንዱ እጁን ዘርግቶ ሰይፍ አወጣ፤ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮ መትቶ ቈረጠ፡፡
\v 52 ያኔ ኢየሱስ፣ "ሰይፍህን ወደ ቦታው መልስ፤ ሰይፍ የሚያነሡ በሰይፍ ይጠፋሉ፡፡
\v 53 አባቴን ብጠይቅ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ መላእክት የማይልክልኝ ይመስልሃል?
\v 54 እንደዚያ ከሆነ ይህ እንደሚሆን የሚናገረው መጽሐፉ ቃል እንዴት ይፈጸማል?" አለው፡፡
\s5
\v 55 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡ፣ "ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ዱላ ይዛችሁ መጣችሁ? በየቀኑ በቤተ መቅደስ ተቀምጬ እያስተማርሁ ነበርሁ፡፡ እናንተም አልያዛችሁኝም ነበር፡፡
\v 56 የነቢያት መጽሐፍ እንዲፈጸም ይህ ሆኗል" አላቸው፡፡ ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ትተውት ሸሹ፡፡
\s5
\v 57 ኢየሱስን የያዙ ሰዎች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ሽማግሌዎቹ ተሰብስበው ወደ ነበሩበት ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ቤት ወሰዱት፡፡
\v 58 ጴጥሮስ ግን ከሩቅ ሆኖ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ተከተለው፤ ወደ ውስጥ ገብቶም የሚሆነውን ለማየት ከጠባቂዎቹ ጋር ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 59 እርሱን ለማስገደል የካህናት አለቆቹና ሸንጎው ሁሉ በኢየሱስ ላይ በሐሰት የሚመሰክሩበትን ሰዎች እየፈለጉ ነበር፡፡
\v 60 ምንም እንኳ ብዙ የሐሰት ምስክሮች ቢመጡም፤ በቂ ማስረጃ አላገኙም፡፡ በኋላ ግን ሁለት ሰዎች ወደ ፊት መጥተው፣
\v 61 "ይህ ሰው፣ 'የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ አፍርሼ በሦስት ቀን ውስጥ እንደ ገና ልሠራው እችላለሁ' ብሏል" አሉ፡፡
\s5
\v 62 ሊቀ ካህናቱ ተነሥቶ፣ "መልስ የለህም? በአንተ ላይ እየመሰከሩብህ ያለው ምንድን ነው?" አለው፡፡
\v 63 ኢየሱስ ግን ዝም አለ፡፡ ሊቀ ካህናቱም፣ "በሕያው እግዚአብሔር አዝሃለሁ፤ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን አለመሆንህን ንገረን" አለው፡፡
\v 64 ኢየሱስም፣ "አንተው ራስህ አልህ፤ ግን ልንገርህ፣ ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታያለህ" በማለት መለሰለት፡፡
\s5
\v 65 ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀደደና፣ "እግዚአብሔርን ተሳድቧል፤ ታዲያ፣ ምስክር የምንፈልገው ለምንድን ነው? አሁን ስድቡን ሰምታችኋል
\v 66 ለመሆኑ፣ ምን ታስባላችሁ?" አለ፡፡ እነርሱም መልሰው፣ "ሞት ይገባዋል" አሉ፡፡
\s5
\v 67 ከዚያም ፊቱ ላይ ተፉበት፣ በጡጫና በጥፊ መቱት፤
\v 68 "አንተ ክርስቶስ እስቲ ትንቢት ተናገር፡፡ ለመሆኑ፣ በጥፊ የመታህ ማን ነው?" አሉት፡፡
\s5
\v 69 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ እደጅ ግቢው ውስጥ ተቀምጦ ነበር፤ አንዲት አገልጋይ ልጅ ወደ እርሱ መጥታ፣ "አንተም ደግሞ ከገሊላው ኢየሱስ ጋር ነበርህ" አለችው፡፡
\v 70 እርሱ ግን፣ "ምን እየተናገርሽ እንደ ሆነ አላውቅም" በማለት በሁሉም ፊት ካደ፡፡
\s5
\v 71 ከግቢው ወደሚያስወጣው በር እየሄደ እያለ፣ ሌላ አገልጋይ ልጅ አየችውና እዚያ ለነበሩት፣ "ይህኛውም ሰውየ ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበረ" አለች፡፡
\v 72 እርሱም፣ "ሰውየውን አላውቀወም" በማለት በመሐላ ጭምር በድጋሚ ካደ፡፡
\s5
\v 73 ጥቂት ቆየት ብሎ እዚያ ቆመው የነበሩት መጥተው ጴጥሮስን፣ "በርግጥ አንተም ብትሆን ከእነርሱ አንዱ ነህ፤ አነጋገርህ ራሱ ያጋልጥሃል" አሉት፡፡
\v 74 ከዚያም፣ "ሰውየውን ጨርሶ አላውቀውም" በማለት ይራገምና ይምል ጀመር፤ ወዲያውኑ ዶሮ ጮኸ፡፡
\v 75 ጴጥሮስ "ዶሮ ሳይጮኽ ሦስቴ ትክደኛለህ" በማለት ኢየሱስ የተናገረውን አስታወሰ፡፡ ከዚያ ወደ ውጭ ወጥቶ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡
\s5
\c 27
\cl ምዕራፍ 27
\p
\v 1 ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆቹና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስን ለመግደል ተማከሩ።
\v 2 አስረው ወሰዱትና ለአገሩ ገዢው ለጲላጦስ አስረከቡት።
\s5
\v 3 አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ ኢየሱስ እንደ ተፈረደበት ባየ ጊዜ ተጸጸተ፣ ሠላሣውን ጥሬ ብር ለካህናት አለቆቹና ለሽማግሌዎቹ መልሶ፣
\v 4 "ንጹሕ ሰው አሳልፌ በመስጠት በድያለሁ" አለ። እነርሱ ግን፣ “ታዲያ፣ እኛን ምን አገባን? የራስህ ጉዳይ ነው” አሉት።
\v 5 ከዚያም ጥሬ ብሩን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወረወረና ወጥቶ ራሱን ሰቀለ።
\s5
\v 6 የካህናት አለቆቹ ጥሬ ብሩን ወስደው፣ “ይህ የደም ዋጋ ስለ ሆነ፣ ከቤተ መቅደሱ ገንዘብ ጋር መቀላቀል ተገቢ አይደለም” አሉ።
\v 7 እርስ በርሳቸው ተነጋግረው የእንግዶች መቀበሪያ እንዲሆን የሸክላ ሠሪውን መሬት ገዙበት።
\v 8 ከዚህ የተነሣ ያ መሬት እስከዚህ ጊዜ ድረስ፣ “የደም መሬት” ተባለ።
\s5
\v 9 በነቢዩ ኤርምያስ፣ “የእርሱ ዋጋ እንዲሆን የእስራኤል ልጆች የተመኑለትን ሠላሣ ጥሬ ብር ወሰዱ፣
\v 10 እግዚአብሔር እንደ አዘዘኝ ለሸክላ ሠሪው መሬት ከፈሉት” ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ።
\s5
\v 11 ኢየሱስ በአገረ ገዢው ፊት ቆመ፤ አገረ ገዢውም፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህ እንዴ?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ እንዳልኸው ነው” በማለት መለሰለት።
\v 12 የካህናት አለቆችና፣ ሽማግሌዎቹ፣ ሲከሱት ምንም አልመለሰም።
\v 13 በዚህ ጊዜ ጲላጦስ፣ “በአንተ ላይ የሚያቀርቡትን ክስ ሁሉ አትሰማምን?” አለው።
\v 14 እርሱ ግን አንድ ቃል እንኳ ስላልመለሰለት አገረ ገዡ በጣም ተደነቀ።
\s5
\v 15 በዓል ሲመጣ አገረ ገዢው ሕዝቡ የሚፈልጉትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።
\v 16 በዚያን ጊዜ በርባን የሚሉት ከባድ ወንጀለኛ በእስር ቤት ውስጥ ነበር።
\s5
\v 17 ተሰብስበው እያለ ጲላጦስ፣ “ማንን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ፣ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን?” አላቸው።
\v 18 ምክንያቱም አሳልፈው የሰጡት በቅናት መሆኑን ያውቅ ነበር።
\v 19 በፍርድ ወንበር ላይ ተቀምጦ እያለ ሚስቱ፣ “በዚያ ንጹሕ ሰው ላይ ምንም እንዳታደርግ፤ እርሱን በተመለከተ በዚህ ሌሊት በሕልሜ ብዙ መከራ ተቀብያለሁ” የሚል ቃል ላከችበት።
\s5
\v 20 የካህናት አለቆቹና ሽማግሌዎቹ በርባን እንዲፈታና ኢየሱስ እንዲገደል እንዲጠይቁ ሕዝቡን ቀሰቀሱ።
\v 21 አገረ ገዢው፣ “ከሁለቱ የትኛውን እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁ?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱም፣”በርባንን” አሉ።
\v 22 ጲላጦስም፣ “ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስንስ ምን ላድርገው?” አላቸው። ሁሉም፣ “ስቀለው” በማለት መለሱ።
\s5
\v 23 እርሱም፣ “ለምን፣ የሠራው ወንጀል ምንድንነው?” አላቸው። እነርሱ ግን፣ “ስቀለው” እያሉ የበለጠ ጮኹ።
\v 24 ስለዚህ ምንም ማድረግ እንዳልቻለና እንዲያውም ዐመፅ እየተነሣ መሆኑን ጲላጦስ ባየ ጊዜ፣ በሕዝቡ ፊት እጁን በውሃ ታጥቦ፣ “እኔ ከዚህ ንጹሕ ሰው ደም ነጻ ነኝ፤ ከእንግዲህ ኀላፊነቱ የእናንተው ነው” አለ።
\s5
\v 25 ሕዝቡ ሁሉ፣ “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” አሉ።
\v 26 ከዚያም በርባንን ፈታላቸው፤ ኢየሱስን ግን ገርፎ እንዲሰቅሉት ሰጣቸው።
\s5
\v 27 የአገረ ገዢው ወታደሮች ኢየሱስን ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱትና ወታደሮቹን ሁሉ ሰበሰቡ።
\v 28 ልብሱን ገፍፈው ቀይ ልብስ አለበሱት።
\v 29 ከዚያም የእሾኽ አክሊል ሠርተው በራሱ ላይ ደፉ፣ በቀኝ እጁ በትር አስያዙት፤ በፊቱ ተንበርክከውም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፣ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ አሾፉበት።
\s5
\v 30 ፊቱ ላይም ተፉበት፤ በትሩን ወስደው ራሱን መቱት።
\v 31 ካፌዙበትም በኋላ ልብሱን አውልቀው የራሱን ልብስ አለበሱትና እንዲሰቀል ወሰዱት።
\s5
\v 32 እንደወጡ ስምዖን የሚሉት የቀሬና ሰው አገኙ፤ መስቀሉን እንዲሸከም አስገደዱት።
\v 33 ጎልጎታ ወደሚባል ቦታ መጡ፤ ትርጕሙም “የራስ ቅል” ማለት ነው።
\v 34 ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሰጡት፤ እርሱ ግን ቀምሶ ሊጠጣው አልፈለገም።
\s5
\v 35 በሰቀሉት ጊዜ ዕጣ በመጣጣል ልብሶቹን ተከፋፈሉ፤
\v 36 ተቀምጠው ይጠብቁትም ጀመር።
\v 37 ከራሱ በላይ፣ “ይህ የአይሁድ ንጉሥ ኢየሱስ ነው” የሚል የክስ ጽሕፈት አኖሩ።
\s5
\v 38 ሁለት ወንበዴዎች አንዱ በቀኙ ሌላው በግራው በኩል ከእርሱ ጋር ተሰቅለው ነበር።
\v 39 የሚያልፉ ሰዎችም ሰደቡት፤ ራሳቸውን እየነቀነቁም
\v 40 “ቤተ መቅደሱን የምታፈርስና በሦስት ቀን የምትሠራ ራስህን አድን። የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ” ይሉት ነበር።
\s5
\v 41 በተመሳሳይ መንገድ የካህናት አለቆች፣ ከአይሁድ የሕግ መምህራንና ከሽማግሌዎቹ ጋር አብረው፣
\v 42 “ሌሎችን አዳነ፤ ራሱን ግን ማዳን አልቻለም። እርሱ የእስራኤል ንጉሥ ነው፣ ከመስቀል ይውረድ፣ ከዚያም እኛ እናምንበታለን።
\s5
\v 43 በእግዚአብሔር ተማምኖአል፤ እርሱ ከወደደ ያድነው፤ ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ብሏል" እያሉ ያፌዙበት ነበር።
\v 44 ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም እንዲሁ ይሰድቡት ነበር።
\s5
\v 45 ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ምድሩን ሁሉ የሚሸፍን ጨለማ ሆነ።
\v 46 በዘጠኝ ሰዓት ኢየሱስ፣ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰባቅታኒ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ ትርጒሙም፣ “አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ” ማለት ነው።
\v 47 እዚያ ቆመው ከነበሩት አንዳንዶቹ ይህን ሲሰሙ፣ “ኤልያስን እየተጣራ ነው” አሉ።
\s5
\v 48 ወዲያውኑ ከእነርሱ አንዱ ሮጦ ሄደና ስፖንጁን የኮመጠጠ ወይን ጠጅ ውስጥ ነክሮ በሸንበቆ በትር አድርጎ እንዲጠጣ ሰጠው።
\v 49 የተቀሩትም፣ "እስቲ ተዉት፤ ኤልያስ መጥቶ ሲያድነው እናያለን” አሉ።
\v 50 ከዚያም ኢየሱስ በድጋሚ በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ።
\s5
\v 51 የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለሁለት ተከፈለ፤ ምድር ተናወጠ፤ ዐለቶችም ተሰነጠቁ፤
\v 52 መቃብሮች ተከፈቱ፤ አንቀላፍተው የነበሩ ብዙ ቅዱሳን ተነሡ።
\v 53 ከትንሣኤው በኋላ ከመቃብር ወጡ፤ ወደ ቅድስት ከተማ ገብተው ለብዙዎች ታዩ።
\s5
\v 54 የመቶ አለቃውና ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩ ሰዎች የምድር መናወጡንና የሆኑትን ነገሮች ሲያዩ በጣም ፈርተው፣ "በእውነት ይህ የእግዚአብሔር ልጅ ነው" አሉ።
\v 55 እርሱን ለመርዳት ከገሊላ ጀምሮ ኢየሱስን ተከትለው የነበሩ ብዙ ሴቶች በሩቅ ሆነው ይመለከቱ ነበር።
\v 56 ማርያም መግደላዊት፣ የያዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያም፣ እንዲሁም የዘብዲዎስ ልጆች እናት ከእነርሱ ጋር ነበሩ።
\s5
\v 57 ምሽት ላይ ዮሴፍ የሚሉት አንድ ሀብታም ሰው ከአርማትያስ መጣ፤ እርሱ ራሱ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር ነበር።
\v 58 ወደ ጲላጦስ መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀ። ጲላጦስም እንዲሰጠው አዘዘ።
\s5
\v 59 ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ፤ በንጹሕ ናይለን ጨርቅ ጠቀለለውና
\v 60 ለራሱ ከዐለት በሠራው መቃብር ውስጥ አኖረው። ከዚያም ትልቅ ድንጋይ አንከባልሎ መቃብሩ ደጃፍ ላይ አድርጎ ሄደ።
\v 61 ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም መቃብሩ ፊት ለፊት ተቀምጠው በዚያ ነበሩ።
\s5
\v 62 በሚቀጥለው ቀን ከዝግጅት በኋላ የካህናት አለቆቹና ፈሪሳውያን በአንድነት ከጲላጦስ ጋር ተሰበሰቡ።
\v 63 እንዲህም አሉ፣ "ጌታ ሆይ፣ ያ አሳሳች በሕይወት በነበረ ጊዜ፣ 'ከሦስት ቀን በኋላ እነሣለሁ' ብሎ እንደ ነበር ትዝ አለን።
\v 64 ስለሆነም፣ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ መቃብሩ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ እዘዝ፤ አለበለዚያ ግን፣ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው ሥጋውን ይሰርቁና ለሕዝቡ፣ ‘ከሞት ተነሣ’ ይላሉ፤ የኋላው ስሕተት ከመጀመሪያው የከፋ ይሆናል” አሉት።
\s5
\v 65 ጲላጦስም፣ “ጠባቂ ወስዳችሁ፣ የሚቻላችሁን ያህል በጥንቃቄ እንዲጠበቅ አድርጉ” አላቸው።
\v 66 ስለዚህ ሄደው መቃብሩ በጥንቃቄ እንዲጠበቅ አደረጉ፤ ድንጋዩን አተሙ፤ ጠባቂ አኖሩ።
\s5
\c 28
\cl ምዕራፍ 28
\p
\v 1 ሰንበት እንዳለፈ፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ማለዳ፣ ማርያም መግደላዊትና ሌላዋ ማርያም ወደ መቃብሩ መጡ።
\v 2 የጌታ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ነበርና ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ መጥቶም ድንጋዩን አንከባልሎ በላዩ ተቀመጠ።
\s5
\v 3 መልኩ እንደ መብረቅ፣ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበር።
\v 4 ጠባቂዎቹ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ እንደ ሞተ ሰውም ሆኑ።
\s5
\v 5 መልአኩም እንዲህ በማለት ተናገረ፤ "አትፍሩ፤ ተሰቅሎ የነበረውን ክርስቶስን እንደምትፈልጉ አውቃለሁ።
\v 6 እንደ ተናገረ ተነሥቷል እንጂ፣ እዚህ የለም፤ ኑና የነበረበትን ቦታ እዩ።
\v 7 በፍጥነት ሄዳችሁ፣ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ በማለት ንገሩ፤ 'እርሱ ከሞት ተነሥቷል፤ ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል። እዚያ ታዩታላችሁ።' እንግዲህ ነግሬአችኋለሁ።”
\s5
\v 8 ሴቶቹ ፈጥነው በፍርሃትና በታላቅ ደስታ ለደቀ መዛሙርቱ ለመንገር ከመቃብሩ እየሮጡ ሄዱ።
\v 9 እነሆ ኢየሱስ አገኛቸውና፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” አላቸው። ሴቶቹም እግሮቹን ይዘው ሰገዱለት።
\v 10 ከዚያም ኢየሱስ፣ "አትፍሩ፤ ሄዳችሁ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ለወንድሞቼ ንገሩ፤ እዚያ ያዩኛል" አላቸው።
\s5
\v 11 ሴቶቹ እየሄዱ እያሉ፣ ከጠባቂዎች ጥቂቱ ወደ ከተማ ሄደው የሆነውን ሁሉ ለካህናት አለቆቹ ነገሩ።
\v 12 ካህናቱ ከሽማግሌዎቹ ጋር ተገናኝተው የሆነውን ሁሉ ሲናገሩ፣ ለወታደሮቹ ብዙ ገንዘብ በመስጠት፣
\v 13 “እኛ ተኝተን እያለ ፣ ሌሊት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት መጥተው አስክሬኑን ሰረቁ” ብለው እንዲናገሩ ነገሩዋቸው።
\s5
\v 14 ይህ ወሬ ወደ አገረ ገዢው ከደረሰ፤ እኛ እናሳምነዋለን፣ እናንተም ከሥጋት ነጻ ትሆናላችሁ" አሏቸው።
\v 15 ወታደሮቹ ገንዘቡን ተቀብለው ፣ እንደ ተነገራቸው አደረጉ። ይህ ወሬ እስከ ዛሬ ድረስ በአይሁድ መሐል በሰፊው ተሰራጭቷል።
\s5
\v 16 ዐሥራ አንዱ ደቀ መዛሙርት ግን ወደ ገሊላ ኢየሱስ ወደ ነገራቸው ተራራ ሄዱ።
\v 17 ባዩት ጊዜ ሰገዱለት፤ አንዳንዶቹ ግን ተጠራጥረው ነበር።
\s5
\v 18 ኢየሱስ ወደ እነርሱ መጥቶ፣ “በሰማይና በምድር ሁሉ ላይ ሥልጣን ተሰጠኝ።
\v 19 ስለዚህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ፣ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስም ስም እያጠመቃችኋቸው፤
\s5
\v 20 እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲያደርጉ እያስተማራችኋቸው፤ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

1270
42-MRK.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1270 @@
\id MRK
\ide UTF-8
\h ማርቆስ
\toc1 ማርቆስ
\toc2 ማርቆስ
\toc3 mrk
\mt ማርቆስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ፡፡
\v 2 በነብዩ በኢሳይያስ እንደተጻፈው እነሆ! መንገድን የሚያዘጋጅላችሁን መልዕክተኛዬን በፊታችሁ እልካለሁ፤
\v 3 መንገድን አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ ብሎ በምድረበዳ የሚጮህ ሰው ድምፅ፡፡
\s5
\v 4 በምድረበዳ እያጠመቀና ለኃጢአት ይቅርታ የንሰሐን ጥምቀት እየሰበከ መጣ፡፡
\v 5 ሁሉና በኢየሩሳሌም ያሉ ሁሉ ወደ እርሱ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እየመጡ ኃጢአታቸውን በመናዘዝ ይጠመቁ ነበር፡፡
\v 6 የግመል ጠጉር ይለብስና ወገቡን በቆዳ መታጠቂያ ይታጠቅ፣ አንበጣና የበረሃ ማርም ይበላ ነበር፡፡
\s5
\v 7 የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት የማልበቃ ከእኔ ይልቅ ታላቅ የሆነ እርሱ ከበስተኋላዬ ይመጣል፡፡
\v 8 በውሃ አጥምቄአችኋለሁ፤ እርሱ ግን በመንፈስ ቅዱስ ያጠምቃችኋል እያለ ይሰብክ ነበር፡፡
\s5
\v 9 ቀናት ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት በመምጣት በዮርዳኖስ ውስጥ በዮሐንስ ተጠመቀ፡፡
\v 10 እንደወጣም ሰማይ ሲከፈት፣ መንፈስ ቅዱስም እንደ እርግብ በእርሱ ላይ ሲወርድ አየ፤
\v 11 ልጄ አንተ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምጽም ከሰማያት መጣ፡፡
\s5
\v 12 መንፈስ ቅዱስ ወደ ምድረበዳ መራው፡፡
\v 13 በሰይጣን እየተፈተነም በምድረበዳ ለአርባ ቀን ቆየ፡፡ ከዱር አራዊትም ጋር ነበረ፤ መላዕክትም አገለገሉት፡፡
\s5
\v 14 ታልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል እየሰበከ ወደ ገሊላ መጣ፡፡
\v 15 ተፈጸመ፤የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለችና ንሰሐ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ ይል ነበር፡፡
\s5
\v 16 ባህር ዳር ሲያልፍ ሳለ ስምዖን ጴጥሮስንና ወንድሙን እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባህር ሲጥሉ አያቸው፤ አሳ አጥማጆች ነበሩና፡፡
\v 17 በኋላዬ ኑና ሰዎችን የምታጠምዱ አደርጋችኋለሁ አላቸው፡፡
\v 18 መረቦቻቸውን ትተው ተከተሉት፡፡
\s5
\v 19 እልፍ እንዳለም የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን እነርሱም በጀልባቸው ውስጥ መረቦቻቸውን ሲጠግኑ አያቸው፡፡
\v 20 ጠራቸው፤ እነርሱም ዘብዴዎስ አባታቸውን ከተቀጣሪ ሰራተኞቻቸው ጋር በጀልባው ውስጥ ትተው ተከተሉት፡፡
\s5
\v 21 ቅፍርናሆም ሔዱ፡፡ ወዲያው በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማራቸው፡፡
\v 22 ጸሐፍት ሳይሆን ትምህርቱ እንደ ባለሥልጣን ስለነበረ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
\s5
\v 23 ርኩስ መንፈስ ያለበት አንድ ሰው በምኩራባቸው ነበረ፡፡
\v 24 የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ! ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ብሎ ጮኸ፡፡
\v 25 ዝም በል! ከእርሱም ውጣ ብሎ ገሰጸው፡፡
\v 26 መንፈስ መሬት ላይ ጥሎ ካንፈራገጠው በኋላ በታላቅ ድምጽ ጮኾ ወጣ፡፡
\s5
\v 27 ሁሉ በጣም ተገረሙና ይህ አዲስ ትምህርት ምንድነው? ርኩሳን መናፍስትን እንኳን በሥልጣን ያዛቸዋልና እነርሱም ይታዘዙለታል በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ፡፡
\v 28 እርሱም በገሊላ አውራጃና በዙሪያው ባሉ ሀገራት ሁሉ ዝናው ወጣ፡፡
\s5
\v 29 እንደወጡ ወዲያው ከዮሐንስና ከያዕቆብ ጋር ወደ ስምዖንና እንድርያስ ቤት መጡ፡፡
\v 30 ጊዜ የስምዖን አማት አተኵሷት ተኝታ ነበርና ወዲያው ስለ እርስዋ ነገሩት፡፡
\v 31 እጇን ይዞ አስነሳት፤ ወዲያውኑ ትኵሳቱ ለቀቃትና አገለገለቻቸው፡፡
\s5
\v 32 ጠልቃ በመሸ ጊዜም ብዙ በሽተኞችንና በአጋንንት የተያዙትን ወደ እርሱ አመጧቸው፡፡
\v 33 ሰው ሁሉ በአንድነት በቤቱ ደጃፍ ተከማችቶ ነበር፡፡
\v 34 በተለያየ በሽታ የታመሙትን ፈወሳቸው፤ ብዙ አጋንንንትንም አወጣ፡፡ አጋንንቱ ማን መሆኑን አውቀውት ነበርና እንዳይገልጡት አዘዛቸው፡፡
\s5
\v 35 እጅግ በማለዳ ተነስቶ ለብቻው ወደ ምድረበዳ ሔደና ጸለየ፡፡
\v 36 ከእርሱ ጋር የነበሩትም ተከተሉት፡፡
\v 37 ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ ይፈልጉሃል አሉት፡፡
\s5
\v 38 የምሥራቹን ቃል እንድሰብክ ወደ ሌሎቹ ከተሞች ደግሞ እንሂድ፣ ስለዚህ ጉዳይ መጥቻለሁና አላቸው፡፡
\v 39 ወዳሉ ምኩራቦቻቸው ሁሉ እየገባ ሰበከላቸው፣ አጋንንትንም አወጣ፡፡
\s5
\v 40 ለምጻም ወደ እርሱ መጥቶ ሰገደለትና ብትፈቅድስ ልታነጻኝ ትችላለህ ብሎ ለመነው፡፡
\v 41 አዘነለት፤ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና እፈቅዳለሁ፣ ንጻ! አለው፡፡
\v 42 ለምጹ ለቀቀውና ንጹህ ሆነ፡፡
\s5
\v 43 ለማንም እንዳይናገር አጥብቆ አዘዘውና ወዲያው ሲያሰናብተው ሳለ
\v 44 ግን ራስህን ለካህን አሳይ፤ ስለመንጻትህ ምሥክር እንዲሆንባቸው ሙሴ ያዘዘውን መስዋዕት አቅርብ አለው፡፡
\s5
\v 45 ግን ሄደና ኢየሱስ በግልጽ ወደ ከተማ ለመግባት እስኪሳነው ድረስ ስለዚህ ነገር አብዝቶ ሊያወራና ሊያሰራጭ ጀመረ፡፡ በመሆኑም በምድረበዳ አካባቢዎች እንዲቆይ ሆነ፤ ሰዎችም ከየአቅጣጫው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ቀናት በኋላ ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ በቤት እንዳለ ወሬው ተሰማ፡፡
\v 2 ሰዎችም ተሰበሰቡ፤ከዚህ የተነሣ በበሩ መግቢያም እንኳ በቂ ቦታ አልነበራቸውም፡፡ ኢየሱስም የእግዚአብሔርን ቃል ነገራቸው፡፡
\s5
\v 3 ሰዎችም አንድ ሽባ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡
\v 4 ብዛት ምክንያት ወደ እርሱ መቅረብ ስላልቻሉ፣ኢየሱስ ባለበት አቅጣጫ ጣሪያውን ነደሉት፡፡ በቀዳዳውም ሽባው ያለበትን ዐልጋ ወደ ታች አወረዱት፡፡
\s5
\v 5 እምነታቸውን አይቶ ሽባውን ሰው፣ "አንተ ልጅ ኀጢአትህ ተሰርዮልሃል" አለው፡፡
\v 6 ግን አንዳንድ ጸሓፍት በዚያ ተቀምጠው ነበር፡፡ ይህ ሰው እንዲህ ብሎ የሚናገረው ለምንድን ነው? እርሱ እግዚአብሔርን ይሳደባል፤
\v 7 ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ይቅር ማለት የሚችል ማን ነው? እያሉ በልባቸው ያጉረመርሙ ነበር፡፡
\s5
\v 8 ኢየሱስ በውስጣቸው እያጉረመረሙ እንደሆነ በመንፈሱ ዐውቆ፣ "በልባችሁ የምታጉረመርሙት ለምንድን ነው? አላቸው፡፡
\v 9 ለሽባው ሰው የትኛውን ማለት ይቀላል? ኀጢኣትህ ተሰርዮልሃል ወይስ ተነሣ ዐልጋህን ተሸክመህ ሂድ ማለት?
\s5
\v 10 እንጂ የሰው ልጅ በምድር ላይ ኀጢኣትን የማስተሰረይ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፣
\v 11 እልሃለሁ፤ ተነሣ! ዐልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ" አለው፡፡
\v 12 እርሱም ተነሣ፤ ወዲያውኑም ዐልጋውን ተሸክሞ በሁሉም ፊት ወጥቶ ሄደ፡፡በዚያ የነበሩትም ሁሉም ተገርመው ስለ ነበር እንዲህ ያለ ነገር ፈጽሞ አይተን አናውቅም በማለት እግዚአብሔርን አከበሩ፡፡
\s5
\v 13 ወደ ባሕሩ ዳርቻ ሄደ፡፡ሕዝቡም በሙሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ አስተማራቸውም፡፡
\v 14 ሲያልፍም የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን ቀረጥ በመሰብሰቢያ ቦታው ተቀምጦ አየውና "ተከተለኝ" አለው፡፡ ተነሥቶም ተከተለው፡፡
\s5
\v 15 በእርሱ(በሌዊ) ቤት ተቀምጦ እየበላ ነበር፡፡ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞችም ከኢየሱስና ከደቀመዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙዎቹም ተከትለውት ነበርና፡፡
\v 16 ጸሓፍትም ከኀጢአተኞችና ከቀራጮች ጋር ሲበላ ሲያዩት ደቀመዛሙርቱን፣ "እርሱ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር የሚበላውና የሚጠጣው እንዴት ነው" አሏቸው፡፡
\s5
\v 17 ይህን ሲሰማ፣ "ሕሙማን እንጅ ጤናሞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም" ፤ እኔ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም አላቸው፡፡
\s5
\v 18 ደቀመዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጾሙ ነበር፡፡ ወደ እርሱም መጥተው የዮሐንስ ደቀመዛሙርትና የፈሪሳውያን ደቀመዛሙርት የሚጾሙት ነገር ግን የአንተ ደቀመዛሙርት የማይጾሙት ለምንድን ነው? አሉት፡፡
\v 19 እንዲህ አላቸው፡፡ሙሽራው አብሮአቸው ሳለ ሚዜዎቹ ይጾማሉ? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እስካለ ሊጾሙ አይችሉም፡፡
\s5
\v 20 ግን ሙሽራው የሚወሰድበት ቀን ይመጣል፡፡ በዚያን ጊዜ በዚያ ቀን ይጾማሉ፡፡
\v 21 አዲስ እራፊ ጨርቅ በዐሮጌ ልብስ ላይ አየይጥፍም፤ ያለበለዚያ የተጣፈው እራፊ ይቀደዳል፡፡ ቀዳዳውም የባሰ ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 የወይን ጠጅ በዐሮጌ ዐቁማዳ ውስጥ የሚያስቀምጥ ማንም ለም፡፡ አለበለዚያ የወይን ጠጁ ዐቁማዳውን ያፈነዳዋል፤የወይን ጠጁና ዐቁማዳውም ይበላሻሉ፡፡ ነገር ግን አዲስ የወይን ጠጅ በአዲስ ዐቁማዳ ውስጥ ያስቀምጣሉ፡፡
\s5
\v 23 በሰንበት ቀን በእህል ማሳ መካከል ያልፍ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርቱም ሲያልፉ እሸት መቅጠፍ ጀመሩ፡፡
\v 24 ፈሪሳውያንም እነሆ በሕግ ያልተፈቀደውን በሰንበት የሚያደርጉት ለምንድን ነው? አሉት፡፡
\s5
\v 25 እንዲህ አላቸው፡፡ ዳዊት በተራበና በተቸገረ ጊዜ ለራሱና አብረውት ለነበሩት ምን እንዳደረገ፣ አብያታር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደገባ፤
\v 26 ብቻ የተፈቀደውን ገጸ ኅብስት እንደ በላ፣ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደሰጣቸው ፈጽሞ አላነበባችሁምን? እንዲህም አላቸው፡፡
\s5
\v 27 የተፈጠረው ለሰው ነው እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፡፡
\v 28 የሰው ልጅ የሰንበትም እንኳ ጌታ ነው፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ምኩራብም ደግሞ ገባ፤ በዚያም እጁ የሰለለችበት ሰው ነበረ፡፡
\v 2 ሰውየውን በሰንበት ቀን ይፈውሰው እንደሆነ ተመለከቱት፡፡
\s5
\v 3 የሰለለችበትን ሰውየም ተነሥ አለው፡፡
\v 4 ሕዝቡንም በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነው ወይስ ክፉ ማድረግ? ሕይወትን ማዳን ወይስ ማጥፋት? አላቸው፡፡ ነገር ግን ሕዝቡ ዝም አሉ፡፡
\s5
\v 5 በቁጣ ሲመለከት፣ በልባቸው ድንዳኔ ዐዝኖ፣ ሰውየውን እጅህን ዘርጋ አለው፤ ዘረጋውም፤ ዳነም፡፡
\v 6 ወጡ፤ ወዲውም እንዴት ሊያጠፉት እንደሚችሉ ከሄሮድስ ወገኖች ጋር በእርሱ ላይ ተማከሩ፡፡
\s5
\v 7 ከደቀ ዛሙርቱ ጋር ወደ ባሕሩ ሄደ፤ ከገሊላም እጅግ ብዙ ሕዝብ ተከትለው፤ ከይሁዳና
\v 8 ከኤዶምያስና ከዮርዳኖስ ማዶ፣ ከጢሮስና ከሲዶና ምን ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገ በመስማት እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ መጣ፡፡
\s5
\v 9 የተነሣ እንዳያጨናንቁት ትንሽ ጀልባ እንዲያቆዩለት ለደቀ መዛሙርቱ ተናገረ፤
\v 10 ፈውሶ ነበርና፡፡ በብዙ ደዌ የሚሠቃዩ ሁሉ ሊዳስሱት ይጋፉት ነበር፡፡
\s5
\v 11 መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ወደቁ፤ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉም ጮኹ፡፡
\v 12 ግን ማንነቱን እንዳይገልጡት አጥብቆ አዘዛቸው፡፡
\s5
\v 13 ወደ ተራራውም ወጣ፤ የሚፈልጋቸውንም ወደ እርሱ ጠራ፤ እነርሱም ወደ እርሱ ሄዱ፡፡
\v 14 ጋር እንዲሆኑ፣ ለመስበክ እንዲልካቸውና
\v 15 ለማስወጣት ሥልጣን እንዲኖራቸው
\v 16 ሁለት ሾመ፤ ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው ስምዖን፣
\s5
\v 17 ልጅ ያዕቆብና የያዕቆብ ወንድም ዮሐንስ፤ እነርሱንም ቦአኔርጌስ ብሎ ጠራቸው፤ የነጎድጓድ ልጆች ማለት ነው፤
\v 18 እንድርያስና ፊልጶስ፣ በርተሎሜዎስና ማቴያስ፣ ቶማስና የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ታዴዎስ፣ ቀናተኛው ስምኦንና
\v 19 የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ፡፡
\s5
\v 20 ኢየሱስ ወደ አንድ ቤት ውስጥ ገባ፡፡ መብላት እንኳ እስከማይችሉ ድረስ እንደ ገና ብዙ ሕዝብ መጥቶ ተሰበሰበ፡፡
\v 21 ዘመዶቹም በሰሙ ጊዜ ይዘውት ሊሄዱ ወደ እርሱ መጡ፤ ዐብዶአል ብለው ነበርና፡፡
\v 22 የወረዱ ጻፎችም ብዔልዜቡል አለበት፤ አጋንንንትን የሚያስወጣውም በአጋንንት አለቃ ነው አሉ፡፡
\s5
\v 23 እርሱ ጠርቶአቸውም በምሳሌ ነገራቸው፤ ሰይጣን እንዴት ሰይጣንንን ማስወጣት ይችላል?
\v 24 መንግሥትም እርስ በርሱ ቢከፋፈል፣ ያ መንግሥት መቆም አይችልም፤
\v 25 ቤትም እርስ በርሱ ቢለያይ፣ ያ ቤት ጸንቶ ሊቆም አይችልም፡፡
\s5
\v 26 ሰይጣንም እርስ በርሱ ቢቀዋወምና ቢለያይ፣ ፍጻሜው ይሆናል እንጂ መቆም አይችልም፡፡ በመጀመሪያ ኀይለኛውን ሰው ካላሰረና ከዚያም ንብረቱን ካልዘረፈ በቀር፣
\v 27 ወደ ኀይለኛው ቤት መግባትና ንብረቱን መዝረፍ የሚችል የለም፡፡
\s5
\v 28 እላችኋለሁ፤ ለሰው ልጆች ኀጢአታቸው ሁሉ፣ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይቅር ይባላል፤
\v 29 ቅዱስን የሚሳደብ ግን ፈጽሞ ይቅርታ አያገኝም፤ ይልቁንም የየዘለዓለም ኀጢአት ዕዳ አለበት፤
\v 30 ርኩስ መንፈስ አለበት ብለዋል፡፡
\s5
\v 31 ወንድሞቹም መጡ፤ ውጭ ቆመውም እንዲጠሩት ወደ እርሱ ላኩ፡፡
\v 32 ብዙ ሰው ተቀምጦ ነበር፤ ሰዎችም እነሆ፣ እናትህና ወንድሞችህ ውጭ ይፈልጉሃል አሉት፡፡
\s5
\v 33 መለሰላቸው፤ አላቸውም፣ እናቴና ወንድሞቼ ማን ናቸው?
\v 34 ዙሪያ የተቀመጡትን ተመልክቶም፣ እነሆ እናቴና ወንድሞቼ! ምክንያቱም
\v 35 ፈቃድ የሚፈጽም ሁሉ ወንድሜ፣ እኅቴና እናቴ ነው፡፡
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 በባህር አጠገብ ማስተማር ጀመረ፡፡ ከህዝቡ መብዛት የተነሳ በባህር ላይ ባለ ጀልባ ገብቶ ተቀመጠ፡፡ ህዝቡም ሁሉ በባህሩ ዳርቻ ላይ ተሰብስበው ነበር፡፡
\v 2 ነገርም በምሳሌ አስተማራቸው፡፡ በትምህርቱም እንዲህ አላቸው፡፡
\s5
\v 3 ስሙ ዘሪ ሊዘራ ወጣ፡፤
\v 4 በሚዘራበትም ጊዜ አንዳንዱ በመንገድ ዳር ወደቀ ወፎችም መጥተው ለቀሙት፡፡
\v 5 ደግሞ ብዙ አፈር በሌለው በድንጋያማ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ መሬቱ ጥልቀት ስላልነበረው ወዲያው በቀለ፤
\s5
\v 6 በወጣ ጊዜም ጠወለገ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ፡፡
\v 7 ደግሞም አንዳንዱ በእሾህ መካከል ወደቀ እሾሁም አድጎ አነቀው ፍሬም አላፈራም፡፡
\s5
\v 8 አንዳንዱ በመልካም መሬት ላይ ወደቀ አደገ እየበዛ ሄደ ፍሬም አፈራ ሶስት እጥፍ ስልሳ እጥፍ እና መቶ እጥፍ ፍሬ ሰጠ፡፡
\v 9 እንዲህም አለ ጆሮ ያለው ይስማ፡፡
\s5
\v 10 በሆነ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አብረው የነበሩት ስለ ምሳሌዎቹ ጠየቁት፡፡
\v 11 አላቸው ለእናንተ የእግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር ተሰጥቷችኋል፡፡ በውጭ ላሉት ግን እንዲህ አይደለም
\v 12 እንዳያዩ ሰምተውም እንዳያስተውሉ እንደገና ተመልሰው ይቅር እንዳይባሉ ሁሉም ነገር በምሳሌ ይሆንባቸዋል፡፡
\s5
\v 13 አላቸው እናንተ ይህ ምሳሌ አልገባችሁምን? ሌሎቹን ምሳሌዎች ሁሉ እንዴት ትረዳላችሁ?
\v 14 ዘሪው ቃሉን ዘራ፡፡
\v 15 በመንገድ ዳር የወደቁት እነዚህ ናቸው ቃሉ በሚዘራበት ጊዜና ቃሉን እንደሰሙ ወዲያውኑ ሰይጣን መጥቶ በውስጣቸው የተዘራውን ቃል ይወስዳል፡፡
\s5
\v 16 በድንጋያማ መሬት ላይ የወደቁት አነዚህ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ወዲያውኑ በደስታ ይቀበሉታል
\v 17 ሥር የላቸውምና ለጊዜው ይቀበሉታል ከዚያም በቃሉ ምክንያት መከራ ወይም ስደት በሚነሳበት ጊዜ ወዲያወኑ በቃሉ ይሰናከሉበታል፡፤
\s5
\v 18 ቦታ የወደቁት እነዚህ ቃሉን የሰሙ ናቸው
\v 19 አለም ሀሳብና የባለጠግነት ማታለል የሌሎች ነገሮች ምኞት ይገቡና ዘሩን ያንቁታል ፍሬ የማያፈራም ይሆናል፡፡
\v 20 መሬት የወደቁት እነዚህ ቃሉን ሰምተው የሚቀበሉት ናቸው ሰላሳ እጥፍ ስልሳ እጥፍ እና መቶ እጥፍ የሚያፈሩ ናቸው፡፡
\s5
\v 21 አላቸው፡- መብራትን ከፍ ባለ ማስመጫ ላይ እንጂ ከእንቅብ በታች ወይም አልጋ ሥር ያስቀምጡታልን?
\v 22 ሳይገለጥ የሚቀር ነገር የለም በሚስጢር የተደረገ ወደ ብርሃንም የማይወጣ የለም፡፡
\v 23 ያለው ይስማ እንዲህም አላቸው
\s5
\v 24-25 አስተውሉ መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል ለእናንተም የበለጠ ይሰጣችኋል፡፡ ላለው የበለጠ ይጨመርለታል ከሌለው ግን ያ ያለው እንኳ ይወሰድበታል፡፡
\s5
\v 26 አለ የእግዚአብሔር መንግሥት በመሬት ላይ ዘርን የዘራን ሰው ትመስላለች፡፡
\v 27 ሲመሽ ይተኛል ሲነጋም ይነቃል፡፡ እንዴት እንደሆነ ባላወቀው መልኩ ዘሩ አቆትቁጦ በቀለ፡፤
\v 28 ምድር የራሷን ሰብል ፍሬ አፈራች መጀመሪያ ቅጠሉ ቀጥሎም ዛላው በመጨረሻም በዛላው ውስጥ ሙሉ ፍሬ አፈራች፡፡
\v 29 ግን ፍሬው በደረሰ ጊዜ መከር ነውና ወዲያውኑ ማጭድ አዘጋጀ፡፡
\s5
\v 30 እንዲህ አለ የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን እንመስላታለን? ወይም በምን ምሳሌ እንገልጻታለን?
\v 31 ቅንጣት ትመስላለች፡፡ በምድር ላይ በተዘራ ጊዜ ሲዘራ ምንም እንኳ በምድር ካሉ ዘሮች ሁሉ ያነሰ ቢሆንም
\v 32 ጊዜ ያድጋል ቅርንጫፍም ያወጣል የሰማይ ወፎች ከጥላው ሥር እስኪጠለልቡበት ድረስ ከተክሎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ይሆናል፡፡
\s5
\v 33 ሊሰሙ በሚችሉት መጠን ቃሉን በብዙ ምሳሌዎች ተናገራቸው
\v 34 ምሳሌ ምንም አልተናገራቸውም፡፡ ለደቀመዛሙርቱ ግን ለብቻቸው ሁሉንም ነገር ገለጸላቸው፡፡
\s5
\v 35 ቀን በመሸ ጊዜ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው፡፡
\v 36 ህዝቡንም ትተው በጀልባ ወሰዱት፡፡ ሌሎችም ጀልባዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡
\v 37 የነፋስ ማዕበልም ተነሳ ጀልባው እስኪጥለቀለቅ ድረስ ማዕበል ጀልባውን መታው፡፡
\s5
\v 38 ከጀልባው በስተኋለኛው ክፍል ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፡፡ ቀስቅሰውም መምህር ሆይ ስንጠፋ አይገድህምን አሉት፡፡
\v 39 እርሱም ተነሳ ነፋሱንም ገሰጸው ባህሩንም ዝም በል ጸጥ በል አለው፡፡ ነፋሱም ተወ ታላቅ ጸጥታም ሆነ፡፡
\s5
\v 40 ስለምን ፈራችሁ? እምነት የላችሁምን እምነታችሁስ ወዴት አለ አላቸው፡፡
\v 41 ፈርተው እርስ በእርሳቸው ነፋሱና ባህሩ እንኳ የሚታዘዙለት እንግዲህ ይህ ማነው? ተባባሉ፡፡
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ባሕሩ ሌላ ዳርቻ፣ ወደ ጌርጌሴኖን አገር መጡ፡፡
\v 2 ከጀልባዋ ውስጥ ሲወጣም ወዲያውኑ ርኩስ መንፈስ ያለበት አንድ ሰው ከመቃብር ሥፍራ ወጥቶ ተገናኘው፤
\s5
\v 3 በመቃብር ስፍራ አድርጎ ነበር፤ እርሱን በሰንሰለት ሊያስረው የሚችል ሰው አልነበረም፤
\v 4 ጊዜ በእግር ብረትና በሰንሰለት ይታሰር ስለ ነበር፣ ሰንሰለቶቹን ይበጣጥሳቸው፣ እግር ብረቶቹንም ይሰባብራቸው ነበር፤ እርሱን ለመያዝ የሚያስችል ጥንካሬ ያለው ሰውም አልነበረም፡፡
\s5
\v 5 ቀንና ሌሊት በመቃብሮቹና በተራራዎቹ ዘንድ ሰውነቱን በድንጋይ እየቈረጠ ይጮኽ ነበር፡፡
\v 6 ከሩቅ ሲያየው፣ ሮጠና ሰገደለት፤
\s5
\v 7 በመጮኽም፣ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? በእግዚአብሔር አምልሃለሁ፣ አታሠቃየኝ አለ፡፡
\v 8 ርኩስ መንፈስ ከሰውየው ውጣ ብሎት ነበርና፡፡
\s5
\v 9 ማን ነው ብሎም ጠየቀው፤ ብዙ ነንና ስሜ ሌጌዎን ነው አለው፡፡
\v 10 እንዳያባርራቸውም አጥብቆ ለመነው፡፡
\s5
\v 11 በተራራው ጥግ ትልቅ የእሪያ መንጋ ይሰማራ ነበር፡፡
\v 12 በእነርሱ ውስጥ እንድንገባ ወደ እሪያዎቹ ስደደን በማለትም ለመኑት፡፡
\v 13 እዲሄዱ ፈቀደላቸው፡፡ ርኩሳን መናፍስቱም ወጡ፣ በእሪያዎቹም ውስጥ ገቡ፤ ሁለት ሺ ያህል እሪያ ያለበት መንጋም በቁልቁለቱ ላይ ወደ ባሕሩ እየተንጋጋ ሄደ፤ በባሕሩም ውስጥ ሰመጠ፡፡
\s5
\v 14 የሚጠብቁትም ሸሹ፤ በከተማውና በአገሩ ውስጥም አወሩት፡፡ የሆነውንም እንዴት እንደ ነበረ ለማየትም ሰዎች መጡ፡፡
\v 15 ኢየሱስም መጥተው አጋንንት ያደሩበትን፣ ሌጌዎንም እንኳ የነበረበትን ሰው ተቀምጦ፣ ልብስ ለብሶና ልቡም ተመልሶለት አይተው ፈሩ፡፡
\s5
\v 16 ሰዎችም አጋንንት ባደሩበት ሰውየ ላይ የታየው እንዴት እንደ ሆነና በእሪያዎቹ የሆነውም እንዴት እንደ ነበረ ነገሯቸው፡፡
\v 17 ኢየሱስንም ከአገራቸው እንዲወጣ ይለምኑት ጀመር፡፡
\s5
\v 18 ጀልባዋ ውስጥ እየገባ ሳለ፣ በአጋንንት ተይዞ የነበረው ሰው ከአንተ ጋር ልኑር ብሎ ለመነው፡፡
\v 19 አልፈቀደለትም፤ ይልቁንም ወደ ቤትህ፣ ወደ ዘመዶችህ ሂድ፣ ጌታ ለአንተ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገልህ፣ እንዴትም ምሕረቱን ባንተ ላይ እንዳሳየ ንገራቸው አለው፡፡
\v 20 ሄደና ኢየሱስ እንዴት ታላላቅ ነገሮችን እንዳደረገለት ዐሥር ከተማ በሚባለው ውስጥ ማሠራጨት ጀመረ፤ ሰዎችም ሁሉ ተደነቁ፡፡
\s5
\v 21 በጀልባዋ ወደ ሌላ አቅጣጫ ይሄድ በነበረ ጊዜም ደግሞ፣ እጅግ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፤ እርሱም በባሕሩ አቅራቢያ ነበረ፡፡
\v 22 ከምኵራብ ኀላፊዎች አንዱ፣ ኢያኢሮስ የሚባል መጣ፣ እርሱንም አይቶ በእግሩ ሥር ወደቀ፤
\v 23 ልጄ ልትሞት ነው፤ እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ትጭንባት ዘንድ እለምንሃለሁ በማለትም አጥብቆ ለመነው፡፡
\v 24 ዐብሮት ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችም ተከተሉት፤ ይጋፉትም ነበር፡፡
\s5
\v 25 ሁለት ዓመት ደም ይፈስባት የነበረ፣
\v 26 ብዙ ችግር የደረሰባት ብትሆንና ያላትን ሁሉ ብትከፍልም፣ ምንም ያልተሻላት፣ ይልቁንም የባሰባት
\v 27 ሴት ስለ ኢየሱስ ሰምታ ከሕዝቡ በስተኋላ መጣች፣ የኢየሱስንም ልብስ ነካች፡፡
\s5
\v 28 ላት፣ ይልቁንም የባሰባት 27አንድ ሴት ስለ ኢየሱስ ሰምታ ከሕዝቡ በስተኋላ መጣች፣ የኢየሱስንም ልብስ ነካች፡፡ 28ልብሱን ብቻ ከነካሁ እድናለሁ ብላለችና፡፡
\v 29 የሚፈስሰው ደሟ ቆመ፤ ከሕማሟ እንደ ተፈወሰችም በሰውነቷ ታወቃት፡፡
\s5
\v 30 ኢየሱስ ኀይል ከእርሱ መውጣቱን በራሱ በመረዳት፣ ዙሪያውን ወደ ሕዝቡ ተመለከተ፤ ልብሴን የነካው ማን ነው? ብሎም ተናገረ፡፡
\v 31 መዛሙርቱም ሕዝቡ ሲጋፉህ ታያለህ፣ የነካኝ ማን ነውም? ትላለህ፡፡
\v 32 ይህን ያደረገችውንም ለማየት ዙሪያውን ተመለከተ፡፡
\s5
\v 33 ሴትዮዋ ግን በመፍራትና በመንቀጥቀጥ፣ ለእርሷ የተደረገውንም በማወቅ መጣችና በፊቱ ወደቀች፤ እውነቱንም ሁሉ ነገረችው፡፡
\v 34 እርሱም፡- ልጄ ሆይ! እምነትሽ አድኖሻል፤ በሰላም ሂጂ፣ ከሕማምሽም ተፈወሺ አላት፡፡
\s5
\v 35 ኢየሱስ ገና እየተናገረ ሳለ ከምኵራቡ ኀላፊ ቤት ሰዎች መጡ፤ ልጅህ ሞታለች፤ መምህሩን ለምን ታስቸግረዋለህ ብለውም ተናገሩ፡፡
\s5
\v 36 ኢየሱስ የተናገሩትን ሰምቶ የምኵራቡን ኀላፊ “አትፍራ፤ እመን ብቻ” አለው፡፡
\v 37 ኢየሱስ ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብና ከያዕቆብ ወንድም ከዮሐንስ በቀር ማንም እንዲከተለው አልፈቀደም፡፡
\v 38 ወደ ምኵራቡ ኀላፊ ቤት መጡ፤ ኢየሱስ ያዘኑ፣ የሚያለቅሱና የዋይታ ጩኸት የሚያሰሙ ሰዎችን ተመለከተ፡፡
\s5
\v 39 ወደ ውስጥ ገባና “ለምን ታዝናላችሁ? ለምንስ ታለቅሳላችሁ? ልጅቱ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አላቸው፡፡
\v 40 ሰዎቹ በኢየሱስ ሣቁበት፤ እርሱ ግን ሁሉንም ወደ ውጭ አስወጣቸው፡፡ የልጅቱን አባትና እናት፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን ይዞ ልጅቱ ወደ ነበረችበት ክፍል ገባ፡፡
\s5
\v 41 ከዚያም ልጅቱን በእጁ ይዞ “ታሊታ ኩም!” ትርጉሙ “ትንሿ ልጅ ተነሺ እልሻለሁ” ማለት ነው፡፡
\v 42 ወዲያው ልጅቱ ተነሣች፤ መራመድም ጀመረች፡፡ (ዐሥራ ሁለት ዓመቷ ነበርና) በዚህ ሰዎቹ በጣም ተገረሙ፡፡
\v 43 ከዚያም ኢየሱስ ስለዚህ ጕዳይ ማንም ማወቅ እንደሌለበት ለሰዎቹ ጥብቅ ትእዛዛትን ሰጣቸው፤ የምትበላውንም ስጧት አለ፡፡
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ከዚያ ወጥቶ ወደ ገዛ ምድሩ መጣ፤ ደቀመዛሙርቱም ተከተሉት፡፡
\v 2 ሰንበት በሆነ ጊዜም በምኩራብ ውስጥ ሊያስተምር ጀመረ፡፡ የሰሙትም ሁሉ ይህ ሰው እነኚህን ነገሮች ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ ሰው የተሰጠችውስ ጥበብ እንደምን ያለች ናት፤ በእጆቹ የሚደረጉት እነዚህ ታላላቅ ነገሮችስ ምን ትርጉም ይኖራቸው ይሆን?
\v 3 ይህ አናጺው የማርያም ልጅ፤ የያዕቆብና የዮሳ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እህቶቹስ ቢሆኑ እዚህ ከእኛ ጋር አይደሉምን? በማለት ተደነቁ፤ ተሰናከሉበትም፡፡
\s5
\v 4 ኢየሱስም ነብይ በሀገሩ፣ በወገኑና በገዛ ቤተሰቡ ካልሆነ በስተቀር ሳይከበር አይቀርም አላቸው፡፡
\v 5 ላይ እጆቹን ጭኖ ከመፈወስ በስተቀር በዚያ ታላቅ ተአምራት አላደረገም፡፡
\v 6 ምክንያት ተደነቀ፡፡ በየመንደሮቹም እያስተማረ ዞረ፡፡
\s5
\v 7 አሥራ ሁለቱን ወደ ራሱ ጠራና ሁለት ሁለት አድርጎ ይልካቸው ጀመር፤ በእርኩሳን መናፍስት ላይም ሥልጣንን ሰጣቸው፡፡
\v 8 ለጉዞአቸውም ከበትራቸው በቀር ምግብ፣ የመንገድ ሻንጣም ሆነ በገንዘብ ቦርሳቸው ውስጥ ገንዘብ እንዳይዙ አዘዛቸው፡፡
\v 9 በስተቀር ቅያሪ ልብስ አትያዙ አላቸው፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ እስክትወጡ ድረስ በምትገቡበት ቤት በዚያ ቆዩ አላቸው፡፡
\v 11 ቦታ ሁሉ ከማይቀበሏችሁና ከማይሰሟችሁ ሰዎች ምሥክር ይሆንባቸው ዘንድ በጫማችሁ ሥር ያለውን አቧራ አራግፉ፡፡
\s5
\v 12 ደቀ መዛሙርቱም ወጥተው ሰዎች ንሰሐ እንዲገቡ ሰበኩላቸው፡፡
\v 13 ብዙ አጋንንትን አስወጡ፤ ታመው የነበሩ ብዙዎችንም ዘይት ቀብተው ፈወሱአቸው፡፡
\s5
\v 14 ዝናው ወጥቶ ነበርና ንጉሡ ሔሮድስ በሰማ ጊዜ አጥማቂው ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል፤ ስለዚህ እነዚህ ታላላቅ ነገሮች የሚደረጉትም በእርሱ ነው አለ፡፡
\v 15 ግን ሌሎች ኤልያስ ነው አሉ፡፡ ሌሎቹም ነብይ ወይም ከነብያት አንዱ ነው አሉ፡፡
\s5
\v 16 ነገር ግን ሔሮድስ ይህንን ሁሉ በሰማ ጊዜ እኔ አንገቱን ያስቆረጥኩት ዮሐንስ ተነሥቶአል አለ፡፡
\v 17 ባገባት በወንድሙ በፊሊጶስ ሚስት በሄሮድያስ ምክንያት ራሱ ልኮ ዮሐንስን በመያዝ በወህኒ አኑሮት ነበርና፡፡
\s5
\v 18 ዮሐንስም ሔሮድስን የወንድምህ ሚስት ለአንተ ልትሆን አይገባም ይለው ነበር፡፡
\v 19 ሔሮድያዳ ዮሐንስን ትቃወምና ልትገድለው ትፈልግ ነበር፣አልቻለችምም፡፡
\v 20 ሔሮድስ ዮሐንስን ይፈራው ነበር፡፡ ቅዱስና ጻድቅ እንደሆነ በማወቁም ይጠነቀቅለት ነበር፡፡ በሚሰማው ጊዜ ግራ እየተጋባም ቢሆን በደስታ ይሰማው ነበር፡፡
\s5
\v 21 ምቹ ቀን በመጣ ጊዜም ልደቱን አስመልክቶ ሔሮድስ ለመኳንንቱ፣ ለሹማምንቱና ለገሊላ ታላላቅ ሰዎች የእራት ግብዣ አዘጋጀላቸው፡፡
\v 22 የሄሮድያዳ ልጅ ራሷ ገብታ በዘፈነች ጊዜም ሔሮድስንና ከእርሱ ጋር በማዕድ የተቀመጡትን አስደሰተቻቸው፡፡ ንጉሱም ልጃገረዲቱን የምትፈልጊውን ሁሉ ጠይቂኝ እሰጥሻለሁ አላት፡፡
\s5
\v 23 ማናቸውንም የምትፈልጊውን ጠይቂኝ፣ የመንግሥቴን ግማሽም ቢሆን እሰጥሻለሁ ብሎ ማለላት፡፡
\v 24 እርስዋም ወጥታ ወደ እናቷ በመሄድ ምን ልጠይቀው? ብትላት የአጥማቂው የዮሐንስን ራስ አለቻት፡፡
\v 25 እርስዋም ወደ ንጉሱ ፈጥና በመምጣት የአጥማቂውን የዮሐንስን ራስ በሳህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ አለችው፡፡
\s5
\v 26 ንጉሡም እጅግ አዘነ፡፡ ነገር ግን በመሐላዎቹና በማዕድ በተቀመጡት ምክንያት አልተቃወማትም፡፡
\v 27 ንጉሡም ወዲያውኑ ከጠባቂዎቹ አንደኛውን ወታደር ልኮ ራሱን እንዲያመጣ አዘዘው፡፡ እርሱም ሔደና በወህኒ የዮሐንስን ራስ ቆረጠው፤
\v 28 በሳህን አምጥቶም ለልጃገረዲቱ ሰጣት፣ ልጃገረዲቱም ለእናቷ ሰጠቻት፡፡
\v 29 ደቀመዛሙርቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ መጡና አስከሬኑን ወስደው በመቃብር አኖሩት፡፡
\s5
\v 30 ሐዋርያቱም ወደ ኢየሱስ ተመልሰው ያደረጉትንና ያስተማሩትን ነገር ሁሉ ነገሩት፡፡
\v 31 እርሱም እናንተ ራሳችሁ ወደ ምድረበዳ ኑና ጥቂት ጊዜ ዕረፉ አላቸው፡፡ ወደ እነርሱ የሚመጡና የሚሔዱ ብዙዎች ነበሩና ለመብላት እንኳን ጊዜ አጥተው ነበር፡፡
\v 32 በጀልባ ገብተው ወደ ምድረበዳው ፈቀቅ ብለው ሔዱ፡፡
\s5
\v 33 ሲሔዱም ሕዝቡ አዩአቸውና ብዙዎቹ አወቁአቸው፤ እነርሱም ከየከተሞቹ ሁሉ በአንድነት በሩጫ ቀደሟቸው፡፡
\v 34 ወደዚያ በመጣም ጊዜ ብዙ ሕዝብ አይቶ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ይመስሉ ነበርና አዘነላቸው፡፡ ብዙ ነገሮችንም ያስተምራቸው ጀመር፡፡
\s5
\v 35 ቀኑ በመሸ ጊዜም ደቀመዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀርበው ሥፍራው ምድረበዳ ነው፣ ቀኑም መሽቶአል፤
\v 36 በአቅራቢያው ወደሚገኙ ከተሞችና መንደሮች ሔደው ለራሳቸው አንዳች የሚበሉትን እንዲገዙ ሕዝቡን አሰናብታቸው አሉት፡፡
\s5
\v 37 እርሱ ግን መልሶ እናንተ የሚበሉትን ስጧቸው አላቸው፡፡ እነርሱም እንሂድና ይበሉ ዘንድ የአንድን ሰው የስድስት ወር ገቢ በሚያህል ገንዘብ እንጀራ ገዝተን እንስጣቸውን? አሉት፡፡
\v 38 እርሱም ምን ያህል እንጀራ እንዳላችሁ ሂዱና እዩ አላቸው፡፡ ባወቁ ጊዜም ያለው አምስት እንጀራና ሁለት ዓሳ ነው አሉት፡፡
\s5
\v 39 እርሱም ሁሉን በአረንጓዴው ሣር ላይ በቡድን በቡድን እንዲያስቀምጡ አዘዛቸው፡፡
\v 40 እነርሱም በመቶዎችና በሃምሳዎች እየሆኑ በረድፍ ተቀመጡ፡፡
\v 41 እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዓሳ ተቀብሎ ወደ ሰማይ በመመልከት ባረከውና ቆርሶ ለሕዝቡ እንዲያቀርቡት ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ ሁለቱን ዓሳም ለሁሉም አካፈላቸው፡፡
\s5
\v 42 ሁሉም በልተው ጠገቡ፡፡
\v 43 አሥራ ሁለት ትላልቅ መሶብ ሙሉ ቁርስራሽ፣ እንዲሁም ከዓሳው ሰበሰቡ፡፡
\v 44 እንጀራውን የበሉት እነዚያ 5000 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 45 ወዲያውኑ እርሱ ራሱ ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀመዛሙርቱ በጀልባ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተሳይዳ ቀድመውት እንዲሻገሩ ግድ አላቸው፡፡
\v 46 ከተለያቸው በኋላም ሊጸልይ ወደ ተራራ ፈቀቅ አለ፡፡
\v 47 በመሸም ጊዜ ጀልባዋ በባህር ላይ ነበረች፤ እርሱም ብቻውን በምድር ላይ ነበር፡፡
\s5
\v 48 ነፋሱ ከፊት ለፊታቸው እየተቃወማቸው ሳለ ለመቅዘፍ ሲጨነቁ አያቸውና ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባህሩ ላይ እየተራመደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይፈልግ ነበር፡፡
\v 49 ነገር ግን በባህሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ምትሃት ነው ብለው ስላሰቡ ጮኹ፡፡
\v 50 ሁሉም አይተውት ስለነበረ ታወኩ፡፡ እርሱ ግን ወዲያው ተናገራቸውና አይዞአችሁ! እኔ ነኝ አትፍሩ! አላቸው፡፡
\s5
\v 51 ወደ እነርሱ ወጥቶም ወደ ጀልባይቱ ገባ፤ ነፋሱም ተወ፡፡
\v 52 እነርሱም በራሳቸው ያለመጠን ተገረሙ፤ ልባቸው ደንዝዞ ነበርና ስለ እንጀራው አላስተዋሉም፡፡
\s5
\v 53 በተሻገሩ ጊዜም ወደ ጌንሳሬጥ አገር ወደ ባህሩ ዳርቻ መጡ፡፡
\v 54 ከጀልባዋ በወጡ ጊዜም ሕዝቡ ወዲያው አወቁትና
\v 55 በዙሪያው ወዳሉ መንደሮች በሞላ በመሮጥ ህሙማንን በአልጋ ተሸክመው እርሱ እንዳለ ወደሰሙበት ወደዚያ አመጧቸው፡፡
\s5
\v 56 በየትኛውም እርሱ በገባባቸው መንደሮች ወይም ከተማዎች ወይም ሀገሮች ህሙማንን በገበያ ሥፍራዎች ያስቀምጧቸው፣ ቢቻላቸው ሊዳስሱት ካልሆነም የልብሱን ጫፍ ለመንካት ይለምኑት ነበር፤ የዳሰሱትም ሁሉ ይድኑ ነበር፡፡
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ፈሪሳውያንና ከኢየሩሳሌም የመጡ አንዳንድ ጸሓፍት በአንድ ላይ ተሰብስበው ወደ ኢየሱስ መጡ፡፡
\s5
\v 2 ከደቀመዛሙርቱ አንዳንዶቹ በረከሰ እጅ ማለትም ባልታጠበ እጅ እንጀራ ሲበሉ አዩ፡፡
\v 3 (ፈሪሳውያንና ሁሉም አይሁድ የአባቶችን ወግ ስለሚጠብቁ እጆቻቸውን ካልታጠቡ በቀር አይበሉም ነበር)
\v 4 ከገበያ ስፍራ ሲመጡ እጃቸውን ካልታጠቡ በቀር አይበሉም ነበር ፤እንዲሁም ዋንጫዎችን፣ ማሰሮዎችንና የናስ እቃዎችን ማጠብን የመሳሰሉ ሌሎች በርካታ ወጎችን ይጠብቁ ነበር፡፡
\s5
\v 5 ፈሪሳውያንና ጸሓፍት "ደቀመዛሙርትህ በአባቶች ወግ መሰረት የማይጓዙት፣ ነገር ግን ባልታጠበ እጅ የሚበሉት ለምንድን ነው?" ብለው ጠየቁት ፡፡
\s5
\v 6 እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፡፡ ኢሳይያስ ስለ እናንተ ስለ ግብዞች በተናገረው ትንቢት፣ ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ብቻ ያከብረኛል፤ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤
\v 7 ሰው ሠራሽ ሥርዐት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል˝ ተብሎ የተጻፈው ትክክል ነው፡፡
\s5
\v 8 እናንተ የእግዚአብሔርን ሕግ ትታችሁ የሰዎችን ወግ ታጠብቃላችሁ፡፡
\v 9 እንዲህም አላቸው፡፡ ወጋችሁን ለመጠበቅ ስትሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ትሽራላችሁ፡፡
\v 10 ሙሴ፣ «አባትህንና እናትህን አክብር፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ሞትን ይሙት» ብሏልና፡፡
\s5
\v 11 እናንተ ግን አንድ ሰው እናቱን ወይም አባቱን፣ «ከእኔ ልታገኙ የሚገባችሁን እርዳታ ቁርባን አድርጌዋለሁ፤ ማለትም ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ» ቢላቸው፣
\v 12 ከዚህ በኋላ ለአባቱና ለእናቱ ምንም ነገር እንዲያደርግ አትፈቅዱለትም፡፡ ለሌሎች በምታስተላልፉት ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፡፡
\v 13 ይህን የመሳሰሉ ብዙ ነገሮችንም ታደርጋላችሁ፡፡
\s5
\v 14 ደግሞም ሕዝቡን ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ ሁላችሁም ስሙኝ ፤ አስተውሉም፡፡
\v 15 ከውጭ ወደ ውስጡ ገብቶ ሰውን የሚያረክስ ምንም ነገር የለም፡፡
\v 16 ነገር ግን ከውስጡ የሚወጡ ነገሮች እነርሱ ሰውን ያረክሱታል፡፡
\s5
\v 17 ከሕዝቡ ተለይቶ ወደ ቤት እንደ ገባም ደቀመዛሙርቱ ስለ ምሳሌው ጠየቁት፡፡
\v 18 እርሱም፣ «እናንተም አልተረዳችሁምን? ከውጭ ወደ ውስጡ ገብቶ ሰውን የሚያረክሰው ምንም ነገር እንደሌለ አታስተውሉምን?» አላቸው፡፡
\v 19 ምክንያቱም ፣ወደ ውስጡ (ዐፉ) የሚገባው ነገር ወደ ሆዱ እንጂ ወደ ልቡ የሚገባ ስላልሆነ ከሰውነቱ የሚወጣ አይደለምን? ይህን በማለቱ ምግብ ሁሉ ንጹሕ መሆኑን ተናገረ፡፡
\s5
\v 20 20እንዲህም አለ፤ ከሰው የሚወጣ ያ ሰውን ያረክሰዋል፡፡
\v 21 ከውስጥ ከሰው ልብ ክፉ ሐሳብ፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣
\v 22 ምንዝር፣ ስግብግብነት፣ ክፋት፣ ማታለል፣ መዳራት፣ ምቀኝነት፣ ስም ማጥፋት፣ ትእቢት፣ ስንፍና ይወጣሉ፡፡
\v 23 እነዚህ ክፉ ነገሮች ሁሉ ከውስጥ ይወጣሉ፡ ሰውንም ያረክሱታል፡፡
\s5
\v 24 ከዚያም ተነሥቶ ወደ ጢሮስና ሲዶና አካባቢ ሄደ፡፡ ያለበትን ማንም እንዳያውቅም ወደ አንድ ቤት ገባ ፤ሆኖም ሊደበቅ አልቻለም፡፡
\v 25 ወዲያውኑም ስለ እርሱ የሰማችና ትንሽ ልጅዋ በእርኩስ መንፈስ የተያዘችባት አንዲት ሴት ወደ እርሱ መጥታ በእግሩ ሥር ተደፋች፡፡
\v 26 ሴቲቱ ዝርያዋ ከሲሮፊኒቃዊት ወገን የሆነ ግሪካዊት ነበረች፡፡ እርስዋም ኢየሱስ በልጅዋ ውስጥ ያለውን ጋኔን እንዲያወጣላት ለመነቸው፡፡
\s5
\v 27 እርሱም «በመጀመሪያ ልጆች ይጥገቡ፤ የልጆችን እንጀራ ወስዶ ለውሾች መስጠት ተገቢ አይደለምና» አላት፡፡
\v 28 እርስዋ ግን «አዎን ጌታ ሆይ፤ ውሾችም እኮ ከገበታ ሥር የሚወዳድቀውን የልጆችን ፍርፋሪ ይበላሉ፡፡» ብላ መለሰችለት፡፡
\s5
\v 29 ኢየሱስም ፣ እንዲህ በማለትሽ ወደ ቤትሽ ሂጂ ጋኔኑ ከልጅሽ ወጥቷል አላት፡፡
\v 30 ወደ ቤትዋም ሄደች፤ልጅዋም አጋንንቱ ለቅቋት ዐልጋው ላይ ተኝታ አገኘቻት፡፡
\s5
\v 31 ደግሞም ከጢሮስ አካባቢ ተነሥቶ በሲዶና በኩል አድርጎ በዐሥሩ ከተሞች ዐልፎ ወደ ገሊላ ባሕር መጣ፡፡
\v 32 እጁን እንዲጭንበትና እንዲፈውሰው አንድ መስማት የተሳነውና ኮልታፋ ሰው ወደ እርሱ አመጡ፡፡
\s5
\v 33 እርሱም ከሕዝቡ ለይቶ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ወሰደው፤ጣቶቹን በጆሮዎቹ ውስጥ አስገብቶ እንትፍ አለበት፤ምላሱንም ነካው፡፡
\v 34 ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ተመለከተና በረጅሙ ተንፍሶ «ኤፍታህ» አለው፡፡ ይህም ተከፈት ማለት ነው፡፡
\v 35 ጆሮዎቹ ተከፈቱ፤ የታሰረውም ምላሱ ተፈታ፡፡ ጥርት አድርጎም ተናገረ፡፡
\s5
\v 36 ኢየሱስም ይህን ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤ ሆኖም አጥብቆ ባዘዛቸው መጠን አብልጠው አሰራጩት ፡፡
\v 37 እነርሱም ከልክ በላይ ተደንቀው ፣ ሁሉንም ነገር ደኅና አድርጓል፤እርሱ መስማት የተሣነው እንዲሰማ ኮልታፋውም እንኳ እንዲናገር ያደርጋል አሉ፡፡
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 በእነዚያ ቀናት እንደገና ብዙ ህዝብ በተሰበሰበና የሚበሉት ባጡ ጊዜ
\v 2 ኢየሱስም ደቀመዛሙርቱን ወደእርሱ ጠርቶ ህዝቡ ከኔ ጋር ሶስት ቀናት ቆይተዋል የሚበሉትም የላቸውምና እራራላቸዋለሁ
\v 3 ሳይበሉ ብሰዳቸውም በመንገድ ላይ ይደክማሉ አንዳንዶቹም ከሩቅ ሥፍራ ነው የመጡት አላቸው፡፡
\v 4 ደቀመዛሙርቱም በዚህ ምድረበዳ እነዚህን ሁሉ የሚያጠግብ እንጀራ እንዴት ይገኛል ብለው መለሱለት፡፡
\s5
\v 5 ስንት እንጀራ አላችሁ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ሰባት አሉት ፤
\v 6 ህዘቡን በምድር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ ሰባቱንም እንጀራ ተቀብሎ እግዚአብሔርን ካመሰገነ በኋላ ቆርሶ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው እነርሱም ለህዝቡ አቀረቡላቸው፡፤
\s5
\v 7 ጥቂትም ትናንሽ አሦች ነበሯቸው ባርኮም ያንንም አንዲያቀርቡላቸው አዘዘ፡፡
\v 8 ሕዝቡም በልተውም ጠገቡ፡ ደቀመዛሙርቱም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰባት ታላላቅ መሶብ አነሱ፡፡
\v 9 የህዝቡም ቁጥር ቁጥራቸውም አራት ሺ ያህል ነበር፡፡ ከዚያም ኢየሱስ ህዝቡን አሰናበታቸው ፡፡
\v 10 ወዲያውም ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ጀልባ ገብተው ወደ ዳልማኑታ አውራጃ አካባቢ ሄዱ፡፡
\s5
\v 11 ፈሪሳውያንም ወደ ኢየሱስ እርሱ መጥተው ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ምልክትን እንዲያሳያቸው በመፈለግ ሊፈትኑት ይጠይቁት ጀምር፡፡
\v 12 ኢየሱስም እርሱም በመንፈሱ እጅግ ተበሳጭቶ በዚህ ዘመን ያለ ህዝብ ለምን ምልክት ይፈልጋል እዉነት እላችኋለሁ እናንተ ሰዎች አይሰጣችሁም አላቸው፡፡
\v 13 ትቶአቸው እንደገና ወደ ጀልባ ገብቶ ወደ ባህሩ ማዶ ተሻገረ፡፡
\s5
\v 14 ደቀመዛሙርቱም እንጀራ መያዝን ረሱ፡፡
\v 15 በጀልባ ውስጥም ከአንድ እንጀራ በቀር ምንም አልያዙም ነበር።
\s5
\v 16 ኢየሱስ ከፈሪሳዊያንና ከንጉሥ ሄሮድስ እርሾ ተጠንቀቁ ብሎ አሳሰባቸው፡፡ እንጀራ ስላልያዝን ነው ብለው እርስ በእርሳቸው ተነጋገሩ ፡፡
\v 17 ኢየሱስም ይህን አውቆ እንጀራ ስለሌላችሁ ለምን ትነጋገራላችሁ፡፡ እስከአሁን አልገባችሁምን ወይም እስከአሁን አታስተውሉምን ልባችሁ ደንዝዞአልን
\s5
\v 18 አይን እያላችሁ አታዩምን ጆሮ እያላችሁ አትሰሙምን አታስታውሱምን
\v 19 አምስቱን እንጀራ ለአምስት ሺ ባካፈልኩ ጊዜ ስንት መሶብ ቁርስራሽ ሰበሰባችሁ ብሎ ጠየቃቸው እነርሱም አሥራ ሁለት ብለው መለሱለት፡፡
\s5
\v 20 ሰባቱን ለአራት ሺ ባካፈልኩ ጊዜስ ስንት ቅርጫት ቁርስራሽ አነሳችሁ አላቸው ሰባት አሉት ፡፡
\v 21 ገና አታስተውሉምን አላቸው፡፡
\s5
\v 22 ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ፡፡ የአካባቢው ሰዎችም አይነ ስውር የሆነን ሰው ወደ እርሱ አምጥተው እንዲዳስሰው ለመኑት፡፡
\v 23 የአይነስውሩንም ሰው እጅ ይዞ ከመንደሩ ውጭ ወሰደው፡፡ በአይኖቹም ላይ እንትፍ ብሎና እጁን ጭኖ አሁን ይታይሀልን ብሎ ጠየቀው፡፡
\s5
\v 24 ቀና ብሎ ተመለከተና ሰዎች ሲራመዱ እንደዛፍ ሆነው ይታየኛል አለው፡፡
\v 25 እንደገናም እጁን በአይኑ ላይ በጫነበት ጊዜ በሚገባ ተመለከተ የአይኑም ብርሀን ተመለሰለት ሁሉንም ነገር አጥርቶ አየ፡፡
\v 26 ኢየሱስም ወደ መንደሩ እንኳ እንዳትገባ ብሎ ወደ ቤቱ አሰናበተው፡፡
\s5
\v 27 ኢየሱስም ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ፊሊጶስፕ ቂሳሪያ ዙሪያ ወዳሉ መንደርሮች ሄዱ፡ በመንገድም ላይ ሳሉ ሰዎች እኔን ማነው ይላሉ ብሎ ጠየቃቸው
\v 28 እነርሱም መጥምቁ ዮሐንስ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ አንዳንች ግን ከነቢያት አንዱ ብለው መለሱለት፡፡
\s5
\v 29 እንደገናም እናንተስ እኔ ማን እንደሆንኩ ትላለችሁ ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ጴጥሮስም አንተ መሲሁ ነህ በማለት መለሰለት፡፡
\v 30 ስለእርሱ ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው፡፡
\s5
\v 31 የሰው ልጅ ብዙ መከራ እንደሚቀበል በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በጻፎች እንደሚነቀፍና እንደሚገደል በሦስተኛውም ቀን እንደገና እንደሚነሳ እንዳለው ያስተምራቸው ጀመር፡፡
\v 32 ይህንንም በግልጽ ተናገረ፡፡ ጴጥሮስም ወስዶ ሊገስጸው ጀመረ፡፡
\s5
\v 33 ኢየሱስም ዞር ብሎ ደቀመዛሙርቱን አየና ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና ብሎ ጴጥሮስን ገሰጸው፡፡
\v 34 ህዘቡንና ደቀመዛሙርቱንም ወደ እርሱ ጠርቶ ሊከተለኝ የሚወድ ማንም ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ፡፡
\s5
\v 35 ህይወቱን ሊያድን የሚወድ ሁሉ ያጠጣፋታልና ነፍሱን ግን ስለኔ ወይም ስለወንጌል የሚያጣ ያገኛታልና፡፡
\v 36 ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል፡፡
\v 37 ወይስ ሰው ስለነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል፡፡
\s5
\v 38 በዚህ አመንዝራ ኃጢአተኛ ህዝብ ፊት በእኔና በቃሌ የሚያፍርብኝ ማንም ቢኖር የሰው ልጅም ከቅዱሳን መላዕክቱ ጋር በአባቱ ክብር በሚመጣበት ጊዜ ያፍርበታል፡፡
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ኢየሱስም እውነት እላችኋለሁ፣ በዚህ ከቆሙት አንዳንዶቹ የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል መምጣቷን ሳያዩ የማይሞቱ አሉ አላቸው፡፡
\v 2 ከስድስት ቀን በኋላም ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ለብቻቸው ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ላይ አመጣቸው፡፡
\v 3 በፊታቸውም ተለወጠባቸው፤ ልብሱም አጣቢ በምድር ላይ ሊያነጻው እስከማይችል ድረስ ተብለጭልጮ ነጭ ሆነ፡፡
\s5
\v 4 ሙሴና ኤልያስ ታዩአቸው፤ ከኢየሱስ ጋርም ይነጋገሩ ነበር፡፡
\v 5 ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ረቡኒ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴና አንድ ለኤልያስ ሦስት ዳሶችን እንሥራ አለው፡፡
\v 6 እጅግ ፈርተው ስለነበረ የሚመልሰውን አያውቅም ነበር፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ ከደመናውም ውስጥ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ፡፡
\v 8 ድንገት ዙሪያቸውን ሲመለከቱ ከኢየሱስ በቀር ከእነርሱ ጋር ሌላ ማንንም አላዩም፡፡
\s5
\v 9 ከተራራው ሲወርዱ ሳሉም ይህንን ያዩትን ነገር ሁሉ የሰው ልጅ ከሙታን እስኪነሳ ድረስ ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፡፡
\v 10 እነርሱም ቃሉን ይዘው ከሙታን መነሳት ማለት ምን ማለት ነው ተባባሉ፡፡
\s5
\v 11 እነርሱም ጸሐፍት አስቀድሞ ኤልያስ መምጣት አለበት የሚሉት ለምንድነው ብለው ጠየቁት፡፡
\v 12 ኢየሱስም ኤልያስማ በርግጥ አስቀድሞ ይመጣል፤ ሁሉንም ነገር ያስተካክላል፡፡ ስለ ሰው ልጅ ብዙ መከራ እንዲቀበልና እንዲጣል የተጻፈው ታዲያ እንዴት ይሆናል?
\v 13 እኔ ግን እላችኋለሁ! ኤልያስ መጥቷል፤ ስለ እርሱም አንደተጻፈው የወደዱትን አደረጉበት፡፡
\s5
\v 14 ወደ ደቀመዛሙርቱ በመጡ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ከበዋቸው ጸሓፍትም ሲጠይቋቸው ተመለከቱ፡፡
\v 15 ወዲያው ሕዝቡ ሁሉ ኢየሱስን ባዩት ጊዜ እጅግ ተገርመው ወደ እርሱ በመሮጥ ሰላምታ ሰጡት፡፡
\v 16 እርሱም ስለምንድነው የምትጠይቋቸው? ብሎ ጠየቃቸው፡፡
\s5
\v 17 ከሕዝቡም መሐል አንዱ መምህር ሆይ! ዲዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወዳንተ አመጣሁት፡፡
\v 18 በሚወስደው ቦታ ሁሉ ይጥለውና አረፋ ያስደፍቀዋል፣ ጥርሱን ያንቀጫቅጭና ያደርቀዋል፡፡ እንዲያወጡት ደቀመዛሙርትህን ጠየቅኳቸው፣ እነርሱም አልቻሉም፡፡
\v 19 ኢየሱስም መልሶ እናንተ የማታምኑ ትውልዶች እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሳችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት አላቸው፡፡
\s5
\v 20 ወደ እርሱም አመጡለት፤ ባየውም ጊዜ ወዲያው መንፈሱ በምድር ላይ በኃይል ጥሎ እያንፈራገጠ አረፋ አስደፈቀው፡፡
\v 21 ኢየሱስም የልጁን አባት ይህ ከያዘው ምን ያህል ጊዜ ሆነው? ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም ከሕጻንነቱ ጀምሮ ነው፡፡
\v 22 ብዙ ጊዜ ሊያጠፋው በውሃና በእሳት ላይ ይጥለዋል፤ የሚቻልህ ከሆነ እዘንልንና እርዳን አለው፡፡
\s5
\v 23 ኢየሱስም የሚቻልህ ከሆነ አልክን ለሚያምን ሁሉም ነገር ይቻላል አለው፡፡
\v 24 ወዲያው የልጁ አባት ጮኸና አምናለሁ፣ እንዳምንም እርዳኝ አለው፡፡
\v 25 ኢየሱስ ሕዝቡ እየሮጠ ሲመጣ ተመልክቶ እርኩሱን መንፈስ አንተ ዲዳ ደንቆሮም መንፈስ ከእርሱ እንድትወጣ ተመልሰህም እንዳትገባበት አዝሃለሁ ብሎ ገሰጸው፡፡
\s5
\v 26 መንፈሱም ካንፈራገጠው በኋላ ጮኾ ወጣ፡፡ ብዙዎች ሞተ እስኪሉ ድረስም እንደ ሞተ ሰው ሆነ፡፡
\v 27 ኢየሱስ ግን እጁን ይዞ አስነሳው፤ እርሱም ተነሣ፡፡
\s5
\v 28 ወደ ቤት በገቡ ጊዜም ደቀመዛሙርቱ እኛ ልናስወጣው ያልቻልነው ለምንድነው? ብለው ለብቻው ጠየቁት፡፡
\v 29 ኢየሱስም እንዲህ ዓይነቱ ወገን በጸሎት ካልሆነ በስተቀር አይወጣም አላቸው፡፡
\s5
\v 30 ከዚያም ወጥተው በገሊላ በኩል አለፉ፤ በዚያ መሆኑን ማንም እንዲያውቅ አይፈልግም ነበር፡፡
\v 31 ደቀመዛሙርቱንም እንዲህ ሲል አስተማራቸው፤ የሰው ልጅ በሰዎች እጅ ታልፎ ይሰጣል፣ ይገድሉታልም፣ ከተገደለ ከሶስት ቀን በኋላም ይነሣል አላቸው፡፡
\v 32 ነገር ግን የተናገራቸውን አላስተዋሉም፤ እንዳይጠይቁትም ፈርተው ነበር፡፡
\s5
\v 33 ወደ ቅፍርናሆም መጡ፤ በቤት ሳሉም መንገድ ላይ ስለምን ጉዳይ ነበር የምትነጋገሩት ብሎ ደቀመዛሙርቱን ጠየቃቸው፡፡
\v 34 ከእነርሱ ማን ይበልጥ እንደሆነ ተከራክረው ነበርና ዝም አሉ፡፡
\v 35 ተቀምጦም አሥራ ሁለቱን ጠራቸው፣ እንዲህም አላቸው፣ ከእናንተ የመጀመሪያ ሊሆን የሚወድ የሁሉ መጨረሻና አገልጋይ ይሁን፤
\s5
\v 36 ትንሽ ልጅ በመካከላቸው አቁሞና አቅፎት እንዲህ አላቸው፤
\v 37 ማንም እንደዚህ ካሉት ታናናሽ ልጆች አንዱን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፣ እኔንም የሚቀበል የሚቀበለው የላከኝን ነው እንጂ እኔን አይደለም፡፡
\s5
\v 38 ዮሐንስም መምህር ሆይ! አንድ ሰው በስምህ አጋንንትን ሲያስወጣ አየነው፤ ስለማይከተለንም ከለከልነው አለው፡፡
\v 39 ኢየሱስ ግን በስሜ ተአምራትን አድርጎ ፈጥኖ በእኔ ላይ ክፉ ሊናገር የሚችል የለምና አትከልክሉት፤
\s5
\v 40 የማይቃወመን ሁሉ ከእኛ ጋር ነው አለው፡፡
\v 41 እውነት እላችኋለሁ የክርስቶስ በመሆናችሁ ምክንያት አንድ ብርጭቆ ውሃ እንድትጠጡ የሚሰጣችሁ ዋጋውን አያጣም፡፡
\s5
\v 42 በእኔ ከሚያምኑ ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከእምነቱ የሚያስት ሰው ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ላይ ታሥሮ በጥልቅ ባህር ላይ ቢጣል ይሻለው ነበር፡፡
\v 43 እጅህ ለመሰናከልህ ምክንያት የምትሆን ከሆነ ቆርጠህ ጣላት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ እሳቱ ወደማይጠፋበት ወደ ሲዖል ከምትሔድ አካልህ ጎሎ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃልና፡፡
\v 44
\s5
\v 45 እግርህ ለመሰናከልህ ምክንያት የሚሆን ከሆነ ቆርጠህ ጣለው፤ ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ሲዖል ወደ እሳቱ ከምትጣል አንድ እግር ኖሮህ ወደ ሕይወት ብትገባ ይሻልሃል፡፡
\v 46
\s5
\v 47 ዐይንህ ለመሰናከልህ ምክንያት የምትሆን ከሆነ አውጥተህ ጣላት፤
\v 48 ሁለት ዐይን ኖሮህ ትሉ ወደማይሞትበት፣ እሳቱ ወደማይጠፋበት ከምትገባ አንድ ዐይና ሆነህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ብትገባ ይሻልሃል፡፡
\s5
\v 49 እያንዳንዱ ሰው በእሳት ይቀመማል፡፡
\v 50 ጨው መልካም ነው፤ የጨውነት ጣዕሙን ቢያጣ ግን ምን ታደርጉታላችሁ? በእያንዳንዳችሁ ሕይወት የጨውነት ጣዕም ይኑርባችሁ! እርስ በርሳችሁም በሰላም ኑሩ፡፡
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ኢየሱስም ከዚያ ተነስቶ ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ወደ ይሁዳ አውራጃዎች መጣ፡፡ ብዙ ህዝብም በአንድ ላይ ሆነው እንደገና ወደ እርሱ መጡ፡፡ እንደልማዱም ያስተምራቸው ጀመር፡፡
\v 2 ፊሪሳውያንም ወደ ኢየሱስ መጥተው ሊፈትኑት አንድ ሰው ሚስቱን መፍታት ተፈቅዶለታል ሲሉ ጠየቁት፡፡
\v 3 እርሱም መልሶ ሙሴ ምን ብሎ አዘዛችሁ አላቸው፡፡
\v 4 እነርሱም የፍቺውን ጽፈት ሰጥቶ ይፍታት ብሎ ደንግጓል አሉት፡፡
\s5
\v 5 ኢየሱስ ግን ሙሴ ስለልባችሁ ድንዛዜ ይህን ትዕዛዝ ሰጣችሁ እንጂ
\v 6 ከፍጥረት መጀመሪያ ግን እግዚአብሔር ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፡፡
\s5
\v 7 በዚህም ምክንያት ሰው እናቱንና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል
\v 8 ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ ስለዚህም አንድ ሥጋ እንጂ ከእንግዲህ ሁለት አይደሉም
\v 9 እንግዲህ እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየው አላቸው፡፡
\s5
\v 10 በቤትም ሳሉ ደቀመዛሙርቱ ስለጉዳዩ እንደገና ጠየቁት፡፡
\v 11 ኢየሱስም ማንም ሚስቱን ፈቶ ሌላይቱን ቢያገባ በሚስቱ ላይ ያመነዝራል፡፡
\v 12 እንዲሁም እርሷም ራሷ ባሉዋን ትታ ሌላ ሰው ካገባች ታመነዝራለች አላቸው ፡፡
\s5
\v 13 ህዝቡም እንዲዳስሳቸው ህጻናትን ወደ ኢየሱስ ያመጡ ነበር፡፡ ደቀመዛሙርትም ገሰጹዋቸው፡፡
\v 14 ኢየሱስ ግን ባየ ጊዜ በቁጣ ተሞልቶ ህጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተው አትከልክሏቸው፡፡ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና አላቸው፡፡
\s5
\v 15 እውነት እላችኋለሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ህጻን ሆኖ የማይቀበላት ሊገባባት አይችልም፡፡
\v 16 ህጻናቱንም አቅፎ እጁን ጭኖ ባረካቸው፡፡
\s5
\v 17 በመንገድም ሳሉ አንድ ሰው ወደእርሱ ሮጠና በፊቱ ተንበርክኮ ቸር መመህር ሆይ የዘላለምን ህይወት እንድወርስ ምን ማድረግ ይገባኛል? ብሎ ጠየቀው ፡፡
\v 18 ኢየሱስም ለምን ቸር ትለኛለህ ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ቸር የለም አለው፡፡
\v 19 ትዕዘዛትን ታወቃለህ አትግደል አትስረቅ አታመንዘር በሀሰት አትመስክር አታታልል አባትህንና እናትህን አክብር አለው፡፡
\s5
\v 20 እርሱም መምህር ሆይ እነኚህን ሁሉ ከልጅነቴ ጀምሮ ጠብቄአለሁ አለው፡፡
\v 21 ኢየሱስም አይቶ ወደደውና አንዲት ነገር ቀርታሀለች ሂድ ያለህን ሁሉ ሽጥና ለድሆች ስጥ መዝገብም በሰማይ ይቆይሀል መጥተህም ተከተለኝ አለው፡፡
\v 22 እርሱም ብዙ ሀብት ነበረውና በሰማው ነገር ፊቱ ተቁሮ እያዘነ ሄደ፡፡
\s5
\v 23 ኢየሱስም ዙሪያውን ተመለከተና ደቀመዛሙርቱን ለሀብታሞች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ነው አላቸው፡፡
\v 24 ደቀመዛሙርቱም በንግግሩ እጅግ ተገረሙ፡፡ ኢየሱስ እርሱ ግን መልሶ ልጆች ሆይ በሀብታቸው ለሚታመኑ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት እንዴት ከባድ ነው አላቸው፡፡
\v 25 ሀብታም ሰው ወደ መንግስተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢሾልክ ይቀላል አላቸው፡፡
\s5
\v 26 ደቀመዛሙርቱም እጅግ ተገርመው እንግዲያውስ ማን ሊድን ይችላል አሉት፡፡
\v 27 ኢየሱስም ወደ እነርሱ ተመከተና ለሰዎች ይህ አይቻልም ነገር ግን ለእግዚአብሔር ይቻላል ለእግዚአብሔር ሁሉ ይቻላልና አላቸው፡፡
\v 28 ጴጥሮስም ጌታ ሆይ እኛ ሀሉን ትተን ተከልንህ ይለው ጀመር፡፡
\s5
\v 29 ኢየሱስም እውነት እላችኋለሁ ስለኔና ስለ ወንጌል ቤቱን ወንዱሞቹን ወይም እህቶቹንወይም እናቱን ወይም አባቱን ወይም ልጆቹን ወይም መሬቱን የሚተው
\v 30 በዚህ ዓለም መቶ እጥፍ ቤቶችን ወንድሞችን እህቶችን እናቶችን ልጆችንና መሬት ከስደት ጋር በሚመጣውም አለም የዘላለምን ህይወት የማይቀበል የለም
\v 31 ነገር ግን ብዙዎች ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ አላቸው፡፡
\s5
\v 32 ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ሳለ ኢየሱስ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር፡፡ እጅግም ተገርመው ነበር የሚከተሉትም በጣም ፈርተው ነበር፡፡ አስራሁለቱን እንደገና ወስዶ ሊደርስበት ያለውን ነገር ይነግራቸው ጀመር፡፡
\v 33 እነሆ ወደ ኢየሩሳሌም እንሄዳለን የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል እነርሱም ሞትን ይፈርዱበታል ለአህዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፡፡
\v 34 አህዛብም/ፈሪሳዊያን ይቀልዱበታል ይተፉበታል ይገርፉታል ይገድሉታልም ከሶስት ቀን በኋላም ይነሳል እያለ ይነግራቸው ጀመር፡፡
\s5
\v 35 የዘብድዮስ ልጆች ያዕቆብና ዮሀንስ ወደ ኢየሱስ ቀርበው መምህር ሆይ የምንጠይቅህን ሁሉ እንድታደርግልን እንለምንሀለን አሉት፡፡
\v 36 እርሱም ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋለችሁ አላቸው፡፡
\v 37 እነርሱም በክብርህ በምትሆንበት ጊዜ አንዳችን በቀኝህ አንዳችን በግራህ እንድንቀመጥ ፍቀድ አሉት፡፡
\s5
\v 38 ኢየሱስ ግን የምትለምኑትን አታውቁም እኔ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ እኔ የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን አላቸው፡፤
\v 39 እነርሱም እንችላለን አሉት፡፡ ኢየሱስም እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ እኔ የምጠመቀውን ጥምቀት ትጠመቃላችሁ
\v 40 ነገር ግን በግራዬና በቀኜ መሆን ለተዘጋጀላቸው ነው እንጂ እኔ የምሰጠው አይደለም አላቸው፡፡
\s5
\v 41 አሥሩ ደቀማዘሙርትም ይህን በሰሙ ጊዜ በያዕቆብና በዮሀንስ ላይ ተቆጡ፡፡
\v 42 ኢየሱስም ወደ እርሱ ጠርቶ የአህዛብ አለቆች በሚመሩዋቸው ላይ እንደሚሠለጥኑባቸው ታላላቆቻቸውም እንደሚገዙዋቸው ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\v 43 በእናንተ ዘንድ ግን እንዲህ አይደለም ነገር ግን ከእናንተ ማንም የበላይ(ታላቅ) ለመሆን የሚፈልግ የሁሉ አገልጋይ ይሁን
\v 44 ፊተኛ ለመሆን የሚፈልግም የሁሉ ባሪያ ይሁን
\v 45 የሰው ልጅም ሊያገለግል ነፍሱንም ለብዙዎች ቤዛ ሊያደርግ እንጂ እንዲያገልግሉት አልመጣም አላቸው፡፡
\s5
\v 46 ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱም ወደ ኢያሪኮ መጡ፡፡ ከደቀመዛሙርቱና ከብዙ ህዝብ ጋር ከኢያሪኮ በመውጣት ላይ ሳለ የጤሚዮስ ልጅ ዓይነ ስወሩ ለማኝ በርጠሚዮስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር፡፡
\v 47 የናዝሬቱ ኢየሱስ እያለፈ መሆኑን ሲሰማ የዳዊተ ልጅ ኢየሱስ ሆይ እራራልኝ እያለ ጮኸ፡፡
\v 48 ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሰፁት፡፡ እርሱ ግን አብዝቶ የዳዊት ልጅ ሆይ እራራልኝ ብሎ ጮኸ፡፡
\s5
\v 49 ኢየሱስም ቆመና ጥሩት አለ፡፡ እነርሱም አይዞህ መምህሩ ይጠራሀልና ተነሳ አሉት፡፡
\v 50 በርጠሚዮስም ልብሱን ጥሎ እየዘለለ ወደ ኢየሱስ መጣ፡፡
\s5
\v 51 ኢየሱስም ምን እንዳደርገልህ ትወዳለህ አለው፡፡ ዓይነ ስውሩም ሰው መምህር ሆይ ማየት እንድችል አለው፡፡
\v 52 ኢየሱስም መንገድህን ሂድ እምነትህ አድኖሀል አለው፡፡ ወዲያውም አየ ኢየሱስንም ተከትሎ ሄደ፡፡
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም፣ ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ሁለቱን ላካቸው፡፡
\v 2 እንዲህም አላቸው፣ ፊት ለፊታችን ወዳለው መንደር ሂዱ፤ወዲያው እንደ ገባችሁም ማንም ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ ውርንጫ መንገድ ዳር ታስሮ ታገኛላችሁ፡፡ ፍቱትና አምጡልኝ፤
\v 3 ማንም ለምን ይህን ታደርጋላችሁ ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልገዋል በሉት፤ እርሱም ይለቅቀዋል አላቸው፡፡
\s5
\v 4 እነርሱም ሄዱ፤ አንድ ውርንጫ ከቤት ውጭ በመንገድ ዳር ታስሮ አገኙ፤ ፈቱትም፡፡
\v 5 በአካባቢው ከቆሙት አንዳንዶቹ ሰዎች ለምን ፈታችሁት? አሏቸው፡፡
\v 6 እነርሱም ልክ ኢየሱስ እንዳላቸው ነገሯቸው፤ ለቀቋቸውም፡፡
\s5
\v 7 ደቀመዛሙርቱም ውርንጫውን ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሳቸውንም አለበሱት፤ ኢየሱስም ተቀመጠበት፡፡
\v 8 ብዙ ሰዎችም ልብሳቸውን ፣ሌሎችም ከየቦታው ቅርንጫፎችን ቆርጠው በሚሄድበት መንገድ ላይ አነጠፉ፡፡
\v 9 ከፊት የቀደሙት ከኋላውም የተከተሉት ሆሳእና! በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው፤
\v 10 የሚመጣው የአባታችን የንጉሥ ዳዊት መንግስት የተባረከ ነው፤ ሆሳእና በአርያም እያሉ ጮኹ፡፡
\s5
\v 11 ኢየሩሳሌም እንደ ደረሰ ወደ ቤተመቅደስ ገባ፡፡ በአካባቢው ያለውን ሁሉ ተመለከተ፤መሽቶም ነበርና ከዐሥራ ሁለቱ ጋር ወደ ቢታንያ ሄደ፡፡
\v 12 በማግስቱም ከቢታንያ እንደ ወጡ ተራበ፤
\s5
\v 13 አንዲት ቅጠሏ ያቆጠቆጠ በለስ ከርቀት አየ፡፡ ምናልባት አንዳች አገኝባት ይሆናል በማለት ወደ እርሷ መጣ፡፡ ሲደርስ ግን በለስ የሚያፈራበት ጊዜ ስላልነበረ ከቅጠል በቀር ምንም አላገኘባትም፡፡
\v 14 ስለዚህም ማንም ሰው ለዘላለም ምንም ፍሬ አያግኝብሽ ብሎ ረገማት፡፡ ደቀመዛሙርቱም ሰሙት፡፡
\s5
\v 15 ወደ ኢየሩሳሌምም እንደ መጡ ወደ ቤተመቅደስ ገባ፤ በዚያም የሚሸጡትንና የሚገዙትን አባረረ፤የገንዘብ ለዋጮችን ጠረጴዛ የርግብ ሻጮችንም መቀመጫቸውን ገለበጠባቸው፡፡
\v 16 ማንም ሰው በቤተ መቅደስ ውስጥ ዕቃ ይዞ እንዳይመላለስ ከለከለ፡፡
\s5
\v 17 አስተማራቸውም፤ ቤቴ የአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ይባላል ተብሎ አልተጻፈምን? እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው፡፡
\v 18 ሊቀ ካህናቱና ጸሓፍትም፣ይህን ሲናገር ሲሰሙ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ተደንቀው ስለ ተከተሉት ፈርተው ነበርና እንዴት እንደሚገድሉት ማሰብ ጀመሩ፡፡
\v 19 ኢየሱስም በየምሽቱ ከከተማ ይወጣ ነበር፡፡
\s5
\v 20 በማለዳ ሲያልፉም በለሲቱ ከሥሯ ደርቃ አገኟት፡፡
\v 21 ጴጥሮስም አስታውሶ መምህር ሆይ! እነሆ፤የረገምሃት በለስ ደርቃለች አለው፡፡
\s5
\v 22 ኢየሱስም እንዲህ አለው፡፡ በእግዚአብሔር እመን፤
\v 23 እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም በልቡ ሳይጠራጠር ይህን ተራራ ከዚህ ተነቅለህ ወደ ባሕር ውስጥ ተወርወር ቢልና የተናገረው እንደሚፈጸም በልቡ ቢያምን ይሆንለታል፡፡
\s5
\v 24 ስለዚህ እላችኋለሁ፤የጸለያችሁትንና የለመናችሁትን ነገር ሁሉ እንደምትቀበሉ ብታምኑ ይሆንላችሁማል፡፡
\v 25 ለጸሎት ስትቆሙ፣ በማንም ላይ ቅርታ ቢኖራችሁ፣ የሰማዩ አባታችሁ ኀጢአታችሁን ይቅር እንዲላችሁ ይቅር በሉ፡፡
\v 26 እናንተ ግን ይቅር ባትሉ በሰማያት ያለው አባታችሁ ደግሞ የቅር አይላችሁም፡፡
\s5
\v 27 በድጋሚም ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ኢየሱስ ወደ ቤተመቅደስ ሲገባም ሊቀ ካህናት፣ጸሓፍትና ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሱስ መጥተው፣
\v 28 እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይም እነዚህን ነገሮች እንድታደርግ ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው? አሉት፡፡
\s5
\v 29 ኢየሱስም አንድ ጥያቄ ጠይቃችኋለሁ እናንተም መልሱልኝ፤ እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ እነግራችኋለሁ አላቸው፡፡
\v 30 መልሱልኝ፤ የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነው? ወይስ ከሰው? አላቸው ፡፡
\s5
\v 31 እነርሱም እርስ በርሳቸው ተመካከሩ፤ ከሰማይ ነው ብንል ታዲያ ለምን አላመናችሁበትም? ይለናል፤
\v 32 ነገር ግን ከሰው ነው ብንል ደግሞ ሰዉ ሁሉ ዮሐንስ ነቢይ ነው ብሎ አምኖበታል ብለው ሕዝቡን ፈሩ፡፡
\v 33 ለኢየሱስም አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ ኢየሱስም እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው፡፡
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 ኢየሱስም በምሳሌ ይነግራቸው ጀመር፡፡ አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤በዙሪያው ዐጥር ሠራ፤ለወይን መጭመቂያ የሚሆን ጕድጓድ ቈፈረ፤ማማም ሠራ፡፡ ለገበሬዎችም አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ፡፡
\v 2 በወቅቱ የወይኑን ፍሬ እንዲቀበል አንድ አገልጋይ ወደ ገበሬዎቹ ላከ፡፡
\v 3 እነርሱም አገልጋዩን ያዙት፤ ደብድበውም ባዶ እጁን ሰደዱት፡፡
\s5
\v 4 በድጋሚም ሌላ አገልጋይ ላከ፤እነርሱም ፈነከቱት፤ አሳፈሩትም፡፡
\v 5 ሌላም አገልጋይ ወደ እነርሱ ላከ፤ እርሱንም ገደሉት፡፡ ብዙዎች ሌሎችንም ላከ፤ አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ ሌሎቹንም ገደሉ፡፡
\s5
\v 6 የወይኑ ተክል ባለቤት አንድ ተወዳጅ ልጅ ነበረው፤ልጄን ያከብሩታል በማለት በመጨረሻ እርሱን ላከው፡፡
\v 7 ገበሬዎቹ ግን እርስበርሳቸው እንዲህ አሉ፡፡ ይህ ወራሹ ነው ኑ እንግደለው ሀብቱ ሁሉ የእኛ ይሆናል ተባባሉ፡፡
\s5
\v 8 ልጁንም ያዙት፤ ገደሉት፤ከወይኑ ቦታ ውጭም ጣሉት፡፡
\v 9 የወይኑ ተክል ባለቤት በዚህ ጊዜ ምን ያደርጋል? ይመጣና ገበሬዎቹን ያጠፋቸዋል፤የወይን ቦታውንም ለሌሎች ይሰጣቸዋል፡፡
\s5
\v 10 ይህን የመጽሓፍ ቃል አላነበባችሁምን? እነሆ ግንበኞች የናቁት ድንጋይ እርሱ የማእዘን ድንጋይ ሆነ፤
\v 11 ይህ ከጌታ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው፡፡
\v 12 ኢየሱስ ምሳሌውን የተናገረው ስለ እነርሱ እንደ ሆነ ስለ ተገነዘቡ እጃቸውን ሊጭኑበት ፈለጉ፤ነገር ግን ሕዝቡን ስለ ፈሩ፤ትተውት ሄዱ፡፡
\s5
\v 13 እነርሱም በንግግር እንዲያጠምዱት አንዳንድ ፈሪሳውያንና ከሄሮድስ ወገን የሆኑ ሰዎችን ላኩ፡፡
\v 14 ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ እንዲህ አሉት፤መምህር ሆይ፣ አንተ እውነተኛ እንደ ሆንህ ለማንም በይሉኝታ እንደማታደርግ፣ለሰው ፊትም እንደማታዳላ ነገር ግን የእግዚአብሔርን መንገድ በእውነት እንደምታስተምር እናውቃለን፡፡ ለቄሳር ግብር መክፈል ተገቢ ነው? ወይስ አይደለም?
\v 15 እንክፈል ወይስ አንክፈል? አሉት፡፡ ኢየሱስ ግን ግብዝነታቸውን ዐውቆ ለምን ትፈትኑኛላችሁ? አላቸው፡፡ እንዳየው አንደ ዲናር አምጡልኝ አላቸው፡፡
\s5
\v 16 እነርሱም አመጡለት፡፡ ኢየሱስም ይህ ምስል ቅርጹም የማን ነው? አላቸው፡፡ እነርሱም የቄሳር ነው አሉት፡፡
\v 17 ኢየሱስም እንግዲህ የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር ስጡ አላቸው፡፡ እጅግም ተገረሙበት፡
\s5
\v 18 ትንሣኤ ሙታን የለም የሚሉ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ ብለው ጠየቁት፡፡
\v 19 መምህር ሆይ፣ ሙሴ፣ አንድ ሰው ልጅ ሳይወልድ ሚስቱን ትቶ ቢሞት፣ ወንድሙ እርስዋን አግብቶ ለወንድሙ ዘር ይተካለት ብሎ ጽፎልናል፡፡
\s5
\v 20 ሰባት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ የመጀመሪያው ሚስት አገባ፤ ዘር ሳይተካም ሞተ፡፡
\v 21 ሁለተኛውም አገባት፤ እርሱም ዘር ሳይተካለት ሞተ፡፡ ሦስተኛውም እንዲሁ፡፡
\v 22 ሰባቱም ለወንድማቸው ዘር አልተኩም፡፡ ከሁሉም በኋላ ሴቲቱም ደግሞ ሞተች፡፡
\v 23 ታዲያ ይህች ሴት በትንሣኤ የየትኛው ሚስት ትሆናለች? አሉት፡፡ ሰባቱም አግብተዋት ነበርና፡፡
\s5
\v 24 ኢየሱስም የምትስቱት መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኀይል ስለማታውቁ አይደለምን?
\v 25 በትንሳኤ ጊዜ ሰዎች አያገቡም፤ አይጋቡም፤ ነገር ግን በሰማይ እንደ መላእክት ይሆናሉ እንጂ፡፡
\s5
\v 26 ነገር ግን ሙታን እንደሚነሡ በሚነድደው ቁጥቋጦ ውስጥ እኔ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያእቆብ አምላክ ነኝ ሲል እግዚአብሔር ለሙሴ የተናገረውን አላነበባችሁምን? እጅግ ትስታላችሁ፡፡
\v 27 እርሱ የሕያዋን አምላክ እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፡፡
\s5
\v 28 ከጸሓፍት አንዱ መጣና በአንድነት ሆነው ሲጠይቁት እንዴት በጥሩ ሁኔታ እንደ መላሰላቸው አይቶ፣ ከሕግ ፊተኛው የትኛው ነው? ብሎ ኢየሱስን ጠየቀው፡፡
\v 29 ኢየሱስም ፊተኛው፣ እስራኤል ሆይ ስማ! አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፤
\v 30 አንተም አምላክህን እግዚአብሔርን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህ፣በፍጹም አሳብህ፣ በፍጹምም ኀይልህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡
\v 31 ሁለተኛዋም ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትለዋ ናት፡፡ ከእነዚህ የሚበልጥ ምንም ሌላ ትእዛዝ የለም አለው፡፡
\s5
\v 32 ሰውዬውም መምህር ሆይ፣በእውነት መልካም ብለሃል፤ እርሱ አንድ ነው፤ከእርሱም በቀር ሌላ የለም፤ እርሱን በፍጹም ልብ፣ በፍጹም ማስተዋል፣
\v 33 በፍጹም ኀይል መውደድና ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ ሁሉንም ዓይነት መስዋእትና የሚቃጠል መሥዋእት ከማቅረብ ይበልጣል አለ፡፡
\v 34 ኢየሱስም ሰውዬው በማስተዋል እንደ መለሰለት ባየ ጊዜ አንተ ከእግዚአብሔር መንግስት የራቅህ አይደለህም አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ማንም ሰው ምንም ጥያቄ ሊጠይቀው አልደፈረም፡፡
\s5
\v 35 ኢየሱስም መለሰላቸው፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ሲያስተምር፣ ጸሓፍት ክርስቶስ የዳዊት ልጅ ነው የሚሉት እንዴት ነው? አለ፡፡
\v 36 ዳዊት ራሱ በመንፈስ ቅዱስ ጌታ ጌታዬን ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው፡፡
\v 37 ዳዊት ራሱ ጌታዬ ብሎ ይጠራዋል፤ ታዲያ እንዴት ልጁ ይሆናል? ሕዝቡም በደስታ ይሰማው ነበር፡፡
\s5
\v 38 ኢየሱስም እንዲህ አለ፡፡ ከጸሓፍት ተጠንቀቁ፤ የተንዘረፈፈ ልብስ ለብሰው መሄድን ይወድዳሉ፤ እነርሱ በገበያ ቦታ ሰላምታን፣
\v 39 በምኩራብም የክብር ወንበር፣ በግብዣም የክብር ቦታ ላይ መቀመጥ ይወድዳሉ፡፡
\v 40 ለይምሰል ጸሎት በማስረዘም የመበለቶችን ቤት ይበዘብዛሉ፡፡ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ፡፡
\s5
\v 41 ኢየሱስም በመባ መቀበያው ፊት ለፊት ተቀመጠ፡፡ ብዙ ሰዎች በመባ መቀበያው ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ ተመለከተ፡፡ ብዙ ሃብታሞች ብዙ ገንዘብ ይጨምሩ ነበር፡፡
\v 42 ከዚያም አንዲት ድኻ መበለት መጥታ ሁለት ናስ ጨመረች፤ይህም የብር ሩብ ነው፡፡
\s5
\v 43 እርሱም ደቀመዛሙርቱን ወደ ራሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ይህች መበለት በመባ መቀበያው ውስጥ ገንዘባቸውን ከጨመሩት ሁሉ አብልጣ ሰጠች፡፡
\v 44 እነርሱ ከትርፋቸው ሰጥተዋልና፡፡ እርስዋ ግን ከጉድለቷ ሰጠች፤ ያላትን ሁሉ ሰጠች፤ ኑሮዋን እንኳ ሳይቀር ሁሉንም ሰጠች፡፡
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 ኢየሱስ ከቤተመቅደስ ሲወጣ ሳለ ከደቀመዛሙርቱ አንዱ መምህር ሆይ፤ እንዴት ያሉ ድንጋዮችና እንዴት ያሉ ሕንጻዎቹ እንደሆኑ ተመልከት! አለው፡፡
\v 2 እርሱም እነዚህን ታላላቅ ሕንጻዎች ታያለህን? ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ እንደዚህ አይቀርም አለው፡፡
\s5
\v 3 ኢየሱስ በደብረዘይት ተራራ ላይ በቤተመቅደሱ ትይዩ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስና እንድርያስ
\v 4 ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚፈጸሙበት ምልክቱስ ምንድነው? ብለው ለብቻው ጠየቁት፤
\s5
\v 5 ኢየሱስም ማንም እንዳያስታችሁ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ አላቸው፡፡
\v 6 ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ! እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ፡፡
\s5
\v 7 ጦርነትንና የጦርነትን ወሬ በምትሰሙበት ጊዜ አትታወኩ፤ እነዚህ ነገሮች የግድ መፈጸም አለባቸው፤ ነገር ግን መጨረሻው ገና ነው፡፡
\v 8 ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፡፡ በተለያዩ ቦታዎች የምድር መንቀጥቀጥ፣ ረሃብም ይሆናል፡፡ እነዚህ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው፡፡
\s5
\v 9 እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፡፡ ወደ ሸንጎዎቻቸው ያቀርቧችኋል፣ በምኩራቦች ውስጥ ትደበደባላችሁ፡፡ ለእነርሱ ምስክር እንዲሆን በእኔ ምክንያት በገዢዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ፡፡
\v 10 አስቀድሞ ወንጌል ለሕዝቦች ሁሉ ይሰበካል፡፡
\s5
\v 11 ወደ ፍርድ በሚያቀርቧችሁና አሳልፈው በሚሰጧችሁ ጊዜ አስቀድማችሁ ምን እንደምትናገሩ አትጨነቁ፤ ነገር ግን በዚያች ሰዓት የምትናገሩት ይሰጣችኋልና፤ የሚናገረውም መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም፡፡
\v 12 ወንድም ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፣ አባትም ልጁን፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን በመቃወም ተነስተው ይገድሏቸዋል፡፡
\v 13 ስለስሜም በሰዎች ሁሉ ትጠላላችሁ፡፡ ነገር ግን እስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል፡፡
\s5
\v 14 የጥፋትን እርኩሰት በማይገባው ቦታ ቆሙ ስታዩት (አንባቢው ያስተውል) በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤
\v 15 በቤቱ ጣሪያ ላይ ያለም አንዳች ይወስድ ዘንድ አይውረድ፣ ወደ ቤትም አይግባ፤
\v 16 በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመልከት፡፡
\s5
\v 17 ነገር ግን በእነዚያ ወራት ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!
\v 18 በክረምት እንዳይሆን ጸልዩ፡፡
\v 19 እግዚአብሔር ከፈጠረው ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያልሆነ ወደፊትም የማይሆን ታላቅ መከራ በእነዚያ ቀናት ይሆናልና፡፡
\v 20 ጌታ ቀኖቹን ባያሳጥር ኖሮ ሥጋን የለበሰ ሁሉ አይድንም ነበር፡፡ ነገር ግን ስለመረጣቸው ስለ ምርጦቹ ሲል ቀኖቹን አሳጠረ፡፡
\s5
\v 21 አንድ ሰው እነሆ ክርስቶስ በዚህ ነው ወይም እነሆ በዚያ ነው ቢላችሁ አትመኑት፡፡
\v 22 ሐሰተኛ ክርስቶሶችና ሐሰተኛ ነብያት ይነሣሉና፤ ቢቻላቸው የተመረጡትን ለማሳት ድንቆችንና ምልክቶችን ያሳያሉ፡፡
\v 23 ነገር ግን አስተውሉ፤ እነሆ አስቀድሜ ሁሉንም ነገር ነግሬአችኋለሁ፡፡
\s5
\v 24 ከመከራው በኋላ በእነዚያ ቀናት ፀሐይ ትጨልማለች፣ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፣
\v 25 ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፣ በሰማያት ውስጥ ያሉ ኃይላትም ይናወጣሉ፡፡
\v 26 እነርሱም የሰው ልጅ በደመና ውስጥ በታላቅ ኃይልና ክብር ሲመጣ ያዩታል፡፡
\v 27 ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ ለእርሱ የተመረጡትን ከአራቱም ነፋሳት በአንድ ላይ እንዲሰበስቡለት መላዕክትን ይልካቸዋል፡፡
\s5
\v 28 ምሳሌውን ከበለስ ዛፍ ተማሩ፤ ቅርንጫፏ ሲለሰልስ፣ ቅጠሏም ሲያቆጠቁጥ ያን ጊዜ በጋ መቃረቡን ታውቃላችሁ፡፡
\v 29 እናንተም ደግሞ እነዚህ ነገሮች ሲፈጸሙ በምታዩበት ጊዜ የሰው ልጅ በበር ላይ መሆኑን ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\v 30 እውነት እላችኋለሁ፣ እነዚህ ነገሮች እስኪፈጸሙ ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም፡፡
\v 31 ሰማይና ምድር ያልፋል፣ ቃሌ ግን አያልፍም፡፡
\v 32 ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት በስተቀር የሰማይ መላዕክትም ቢሆኑ፣ ልጅም ቢሆን ማንም አያውቅም፡፡
\s5
\v 33 ጊዜው መቼ እንደሆነ አታውቁምና አስተውሉ፣ ንቁና ጸልዩ፡፡
\v 34 ነገሩ ለአገልጋዮቹ ሥልጣን፣ ለእያንዳንዳቸውም የሥራ ድርሻ በመስጠት ዘበኛውም ደግሞ እንዲጠብቅ አዝዞት ቤቱን ትቶ ወደ ሩቅ ሀገር የሚሔድን ሰው ይመስላል፡፡
\s5
\v 35 35የቤቱ ጌታ በምሽት፣ ወይም በእኩለ ሌሊት፣ ወይም ዶሮ ሲጮህ፣ ወይም ጠዋት ላይ ምን ጊዜ እንደሚመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ!
\v 36 በድንገት ሲመጣ እንቅልፍ ላይ ሆናችሁ እንዳያገኛችሁ፡፡
\v 37 ለእናንተ የምነግራችሁን ለሁሉም እናገራለሁ፣ንቁ!
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 ከሁለት ቀን በኋላ የፋሲካና የቂጣ በዓል ነበር፡፡ የካህናት አለቆችና ጸሓፍት እንዴት አድርገው በተንኮል ይዘው ሊገድሉት እንደሚችሉ ያስቡ ነበር፡፡
\v 2 ነገር ግን የህዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል ቀን አይሁን ተባብለው ነበር፡፡
\s5
\v 3 እርሱም በቢታኒያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት በማዕድ ተቀምጦ ሳለ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የከበረ ሽቱ የያዘ የአልባስጥሮስ ጠርሙስ ይዛ መጣች፡፡ ጠርሙሱንም ሰብራ ሽቱውን በኢየሱስ በራሱ ላይ አፈሰሰች ፡፡
\v 4 ነገር ግን ከመካከላቸው አንዳንዶቹ እንዲህ ያለው የሽቱ ማባከን ያስፈለገው ለምንድነው በማለት የተበሳጩ አንዳንድ ሰዎች ነበሩ
\v 5 ይህ ቅባት ከሦስተ መቶ ሽልንግ በላይ ተሸጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበር እያሉ በእርሷ ላይ አጉረመረሙ፡፡
\s5
\v 6 ኢየሱስ ግን ተዋት ለምን ታስቸግሯታላችሁ እርሷ መልካምን ነገር አድርጋልኛለች፡፡
\v 7 ድሆች ሁሉጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው በፈለጋችሁም ጊዜ መልካም ልታድጉላቸው ትችላላችሁ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም፡፡
\v 8 እርሷ ከመቃብር በፊት ሰውነቴን ሽቱ በመቀባት የምትችለውን አድርጋለች፡፡
\v 9 ደግሞም እውነት እላችኋለሁ ይህ ወንጌል በዓለም ዙሪያ በሚሰበክበት ጊዜ ሁሉ ይህች ሴት ያደረገችው ነገር ለመታሰቢያዋ ይነገራል አላቸው፡፡
\s5
\v 10 ከአስራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ እንዴት አሳልፎ ይሰጠው ዘንድ ወደ ካህናት አለቆች ሄደ
\v 11 እነርሱም በሰሙ ጊዜ ደስ አላቸው ገንዘብም ሊሰጡት ቃል ገቡለት፡፡እርሱም አሳልፎ ሊሰጠው አመቺ ጊዜ ይጠብቅ ነበር፡፡
\s5
\v 12 የፋሲካን መስዋዕት በሚያቀርቡበት በቂጣ በዓል የመጀመሪው ቀን ደቀመዛሙርቱ ፋሲካን ትበላ ዘንድ የት እናዛገጅልህ ብለው ጠየቁት፡፡
\v 13 እርሱም ከደቀመዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ ወደ ከተማ ሂዱ ወዲያውም አንድ ሰው ውሃ ተሸክሞ ታገኛላችሁ ተከትላችሁትም ሂዱና
\v 14 ወደሚገባበት ቤት ገብታችሁ የቤቱን ባለቤት መምህሩ ከደቀመዛሙርቴ ጋር ፋሲካን እበላ ዘንድ የእንግዳ ክፍሌ የትኛው ነው ብሎሀል ብላችሁ ጠይቁት
\s5
\v 15 እርሱ ራሱ በሰገነት ላይ ያለ በቤት ዕቃ የተደራጀና የተዘጋጀ ሰፊ አዳራሽ ያሳያችኋል በዚያም አዘጋጁልን ፡፡
\v 16 ደቀመዛሙርቱም ወጥተው ወደ ከተማ መጡ ልክ እንዳላቸውም አገኙ ፋሲካንም አዘጋጁ፡፡
\s5
\v 17 በመሸም ጊዜ ከአስራ ሁለቱ ጋር መጣ፡፡
\v 18 ተቀምጠውም በመመገብ ላይ ኢየሱስ አውነት እላችኋለሁ በማዕድ ከኔ ጋር ያለ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል አላቸው፡፡
\v 19 እነርሱም እጅግ አዝነው በየተራ እኔ እሆንን ይሉት ጀምር፡፡
\s5
\v 20 ኢየሱስም ከእኔ ጋር ወደ ወጥ ሳህኑ የሚነክረውና ከአስራሁለቱ አንዱ ነው አላቸው፡፡
\v 21 የሰው ልጅስ ስለ እርሱ እንደተጻፈው ይሄዳል የሰው ልጅ አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ግን ወዮለት ባይወለድ ይሻለው ነበር አላቸው፡፡
\s5
\v 22 እየተመገቡም ሳለ እንጀራን አንስቶ ከባረከ በኋላ ቆርሶ ሰጣቸውና ውሰዱና ብሉ ይህ ስጋዬ ነው አላቸው፡፡
\v 23 እንዲሁም ጽዋውን አንስቶ አመስግኖ ለደቀመዛሙርቱ ሰጣቸው ሁሉም ጠጡ፡፡
\v 24 እርሱም ይህ ለብዙዎች የሚፈስ የቃል ኪዳን ደሜ ነው ፡፡
\v 25 እውነት እላችኋለሁ በእግዚአብሔር መንግስት እንደገና እንደ አዲስ እስከምጠጣበት ቀን ድረስ ከዚህ ወይን ከዚህ በኋላ አልጠጣም፡፡
\s5
\v 26 መዝሙርም ከዘመሩም በኋላ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዱ፡፡
\v 27 ኢየሱስም እረኛውን እመታለው በጎቹም ይበታተናሉ ተብሎ እንደተጻፈ ሁላችሁ ትሰናከላላችሁ
\s5
\v 28 ከተነሳሁ በኋላ ግን ወደ ገሊላ እቀድማችኋለሁ አላቸው፡፡
\v 29 ጴጥሮስም ሁሉ ቢሰናከሉ እኔ ግን አልሰናከልም አለው፡፡
\s5
\v 30 ኢየሱስም አውነት እልሃለሁ ዛሬ ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ አለው፡፡
\v 31 እርሱ ግን እጅግ እየጮኸ እስከሞት እንኳ ቢሆን አልክድህም አለው፡፡ ሌሎቹም እንደዚያው አሉ፡፡
\s5
\v 32 ጌቴ ሴማኒ ወደሚባል ሥፍራም መጡ፡፡ ደቀመዛሙርቱንም እስክ ጸልይ ድረስ በዚህ ተቀመጡ አላቸው፡፡
\v 33 ኢየሱስም ጴጥሮስን ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ሄደ እጅግ ሊያዝንና ሊተክዝ ጀመረ፡፡
\v 34 ነፍሴ እስከሞት ድረስ እጅግ አዝናለች በዚህ ሆናችሁ ትጉ ንቁም አላቸው፡፡
\s5
\v 35 ጥቂትም ፈቀቅ ብሎ ሄደ፤ በግንባሩም ተደፍቶ የሚቻል ከሆነ ይህች ሰዓት ሰዓቲቱ እንድታልፍ መጸለይ ጀመረ፡፡
\v 36 አባት ሆይ ለአንተ ሁሉ ይቻላል ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ነገር ግን የእኔ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን አለ፡፡
\s5
\v 37 ወደ እነርሱም መጣ ተኝተውም አገኛቸው ጴጥሮስንም ስምዖን ተኝተሀልን ለአንድ ሰዓት እንኳ ልትተጋ አልቻልክምን፡፡
\v 38 ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ፡፡ መንፈስ ዝግጁ ነው ሥጋ ግን ደካማ ነው አለው፡፡
\v 39 ተመልሶም ሄደና ያንኑ ቃል ደግሞ ጸለየ፡፡
\s5
\v 40 እንደገና ወደ ደቀመዛሙርቱ በመጣ ጊዜ አሁንም ተኝው አገኛቸው አይናቸው በእንቀልፍ ከብዶ ስለነበር የሚመልሱለትንም አያውቁም ነበር፡፡
\v 41 ለሦስተኛም ጊዜ ወደ እነርሱ መጣና እንግዲህስ ይበቃል ተኙ እረፉም የሰው ልጅ ለኃጢአተኞች አልፎ ይሰጥ ዘንድ ሰዓቲቱ ደርሳለች ፡፡
\v 42 ተነሱ እንሂድ እነሆ አሳልፎ የሚሰጠኝ በደጅ ነው አላቸው፡፡
\s5
\v 43 ወዲያውም ገና በመናገር ላይ ሳለ ከአስራ ሁለቱ አንዱ የነበረው የአስቆሮቱ ይሁዳ መጣ ፡፡ ከእርሱም ጋር ከካህናት አለቆች፣ ከጸሓፍትና ከሽማግሌዎች ዘንድ የተላኩ ብዙ ህዝብ ሠይፍና ቆመጥ ይዘው መጡ፡፡
\v 44 አሳልፎ የሚሰጠውም የምስመው እርሱ ነውና ያዙት በጥንቃቄ ውሰዱት ብሎ ምልክት ሰጥቷቸው ነበር፡፡
\v 45 በመጣም ጊዜ በቀጥታ ወደ ኢየሱስ ቀርቦ መምህር ሆይ ብሎ ሳመው፡፡
\v 46 እነርሱም ይዘው ወሰዱት፡፡
\s5
\v 47 ነገር ግን በዚያ ከቆሙት መካከል አንዱ ሰይፉን መዘዘ፤ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ጆሮም ቆረጠው፡፡
\v 48 ኢየሱስም መልሶ ወንበዴ እንደምትይዙ ሰይፍና ቆመጥ ይዛችሁ ልትይዙኝ መጣችሁን
\v 49 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ እያስተማርከ ከእናንተ ጋር በነበርኩ ጊዘ አልያዛችሁኝም፡፡ ነገር ግን የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆኗል አላቸው፡፡
\v 50 ሁሉም ትተውት ሸሹ፡፡
\s5
\v 51 እርቃኑን ከበፍታ በተሰራ ጨርቅ የሸፈነ አንድ ወጣት ይከተለው ነበር ሊይዙትም ባሉ ጊዜ
\v 52 የበፍታ ጨርቁን ነጠላውን ትቶ ራቁቱን አመለጠ፡፡
\s5
\v 53 ኢየሱስንም ወደ ሊቀ ካህናቱ ይዘውት መጡ፡፡ የካህናት አለቆች፣ ሽማግሌዎችና ጸሓፍትም አብረውት መጡ፡፡
\v 54 ጴጥሮስም እስከ ሊቀካህናቱ ግቢ ድረስ በሩቅ ሆኖ ይከተለው ነበር፡፡ ከዚያም ከጠበቃዊዎች ጋር እሳት እየሞቀ ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 55 ሊቀ ካህናቱና ጉባኤው ሁሉ በኢየሱስ ላይ ሞት የሚያስፈርድበት ምክንያት ይፈልጉ ነበር ነገር ግን ሊያገኙ አልቻሉም፡፡
\v 56 ብዙዎች በሀሰት ቢመሰክሩበትም ምስክርነታቸው እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነበር፡፡
\s5
\v 57 ሦስት ሰዎችም ተነስተው በሀሰት መሰከሩበት እንዲህም አሉ
\v 58 ይህንን በእጅ የተሰራ ቤተመቅደስ በሶስት ቀን አፍርሼ እንደገና በሶስት ቀን ውስጥ በእጅ ያልተሰራ ሌላ ቤተመቅደስ እሰራለሁ ሲል ሰምተነዋል ፡፡
\v 59 የእነርሱም ምስክርነት ቢሆን እርስ በእርሱ የሚጣረስ ነበረ፡፡
\s5
\v 60 ሊቀ ካህናቱም ተነስቶ በመካከል ቆመና ለሚመሰክሩብህ መልስ አትሰጥምን ብሎ ጠየቀው፡፡
\v 61 ኢየሱስ ግን ዝም አለ መልስም አልሰጠም፡፡ ሊቀ ካህናቱም በድጋሚ የቡሩኩ ልጅ መሲሁ አንተ ነህን ብሎ ጠየቀው
\v 62 ኢየሱሰም አዎ ነኝ የሰው ልጅ በኃይሉ ቀኝ ተቀምጦ በሰማይ ደመና ሲመጣ ታዩታላችሁ አለው፡፡
\s5
\v 63 ሊቀካህናቱም ልብሱን ቀደደና ከእንግዲህ ምን ሌላ ምስክር ያስፈልጋል
\v 64 እግዚአብሔርን ሲሳደብ ሰምታችኋል ታዲያ ምን ታስባለችሁ ፡፡ ሁሉም ሞት ይገባዋል አሉ፡፡
\v 65 አንዳነዶቹም ይተፉበት ፊቱንም ሸፍነው ትንቢት ተናገር እያሉ ያሾፉበት ጀመር፡፡ መኮንኖችም በእጃቸው እየጎሰሙ ወሰዱት፡፡
\s5
\v 66 ጴጥሮስም በሊቀ ካህናቱ ግቢ እሳት በመሞቅ ላይ ሳለ
\v 67 አንዲት የሊቀ ክህናቱ የቤት ውስጥ ሠራተኛ አየችውና አንተ በትክክል ከናዝሬቱ ኢየሱስ ጋር ነበርክ አለችው፡፡
\v 68 እርሱ ግን የምትይውን አላውቀውም ምን እንደምታወሪም አልገባኝም ብሎ ካደ፡፡ ወደ ዋናው በር መግቢያ በሄደ ጊዜ ዶሮ ጮኸ
\s5
\v 69 ሠራተኛይቱም አይታው በዚያ ላሉት ወታደሮች ይህ ከእነርሱ አንዱ ነው አለቻቸው፡፡
\v 70 እርሱ ግን እንደገና ካደ፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በዚያ ከቆሙት መካከል አንዳንዶቹ ጴጥሮስን አንተ የገሊላ ሰው ስለሆንክ በትክክል ከእነርሱ አንዱ ነህ አሉት፡፡
\s5
\v 71 እርሱም የምትሉትን ሰው አላውቀውም ብሎ መማልና መራገም ጀመረ፡፡
\v 72 ወዲያውም ለሁለተኛ ጊዜ ዶሮ ጮኸ ጴጥሮስም ኢየሱስ ዛሬ ሌሊት ዶሮ ሁለት ጊዜ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትክደኛለህ ያለውን ቃል አስታወሰ ነገሩንም ባሰበ ጊዜ አለቀሰ፡፡
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 ወዲያውኑም በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፣ ከጸሓፍት፣ ከሸንጎም አባሎችም ሁሉ ጋር ተማከሩ፤ ኢየሱስን አስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።
\v 2 ጲላጦስም፣አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም ሲመልስ አንተ እንዳልከው ነኝ አለው።
\v 3 የካህናት አለቆችም ብዙ ክስ አቀረቡበት።
\s5
\v 4 ጲላጦስም ስንት ክስ እንዳቀረቡብህ ተመልከት! ምንም አትመልስምን? ብሎ እንደገና ጠየቀው።
\v 5 ኢየሱስ ግን ጲላጦስ እስኪደነቅ ድረስ ምንም መልስ አልሰጠም።
\s5
\v 6 በየበዓሉ ሕዝቡ ጲላጦስ እንዲፈታላቸው የጠየቁትን አንድ እስረኛ የመፍታት ልማድ ነበረው።
\v 7 በዚያም ኹከት ቀስቅሰው ግድያ ከፈጸሙ ሰዎች ጋር የታሰረ አንድ በርባን የሚባል ሰው ነበር።
\v 8 ሕዝቡም ወደ ጲላጦስ ቀርበው የተለመደውን እንዲያደርግላቸው ጠየቁት።
\s5
\v 9 ጲላጦስም "የአይሁድን ንጉሥ" እንድፈታላችሁ ትፈልጋላቸሁን? አላቸው።
\v 10 እንዲህ ያለው የካህናት አለቆች ኢየሱስን አሳልፈው የሰጡት በቅናት መሆኑን ያውቅ ስለ ነበር ነው።
\v 11 የካህናት አለቆች ግን በእርሱ ፈንታ በርባን እንዲፈታላቸው ጲላጦስን እንዲጠይቁ ሕዝቡን ቀሰቀሱ።
\s5
\v 12 ጲላጦስም መልሶ ታዲያ በዚህ የአይሁድ ንጉሥ ብላችሁ በምትጠሩት ሰው ላይ ምን ላድርግበት? አላቸው።
\v 13 እነርሱም "ስቀለው!" እያሉ እንደገና ጮኹ።
\s5
\v 14 ጲላጦስም "ለምን? ምን በደል ፈጽሟል?" አላቸው። እነርሱም "ስቀለው!" እያሉ አብዝተው ጮኹ።
\v 15 ጲላጦስም ሰዎቹን ደስ ለማሰኘት ብሎ በርባንን ፈቶ ለቀቀላቸው፤ኢየሱስን ግን አስገርፎ እንዲሰቀል አሳልፎ ሰጠው።
\s5
\v 16 ወታደሮቹም ኢየሱስን ፕራይቶሪዮን ወደሚባለው ግቢ ወሰዱት፤ወታደሮቹንም ሁሉ ጠሩ፤
\v 17 ሐምራዊ ልብስ አለበሱት፤ የእሾኽ አክሊልም በራሱ ላይ ደፉበት፡፡
\v 18 "የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን!" እያሉ ሰላምታ ይሰጡት ነበር።
\s5
\v 19 በመቃ ዐናቱን እየመቱ፤ ምራቃቸውን ተፉበት፤ በፊቱም ተንበርክከው ሰገዱለት።
\v 20 አላግጠውበትም ሐምራዊውን ልብስ አወለቁበት፤ የራሱንም ልብስ አልብሰው፤ሊሰቅሉ ወሰዱት።
\v 21 በመንገድ ሳሉም የቀሬና ሰው የሆነውን የእስክንድርንና የሩፎስን አባት ስምዖንን ከገጠር ሲመጣ አግኝተው፤ የኢየሱስን መስቀል ተሸክሞ ከእነርሱ ጋር እንዲሄድ አስገደዱት።
\s5
\v 22 ከዚያም በኋላ ኢየሱስን ጎልጎታ ተብሎ ወደሚጠራው ቦታ ወሰዱት፤ ትርጉሙም፡- "የራስ ቅል ስፍራ" ማለት ነው።
\v 23 ከከርቤ ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅም ሰጡት፤ እርሱ ግን አልጠጣውም።
\v 24 ከዚያም ሰቀሉት፤ ልብሶቹንም ማን ምን እንደሚወስድ ዕጣ ተጣጥለው ተከፋፈሉ።
\s5
\v 25 ከጧቱ ሦስት ሰዓት ሲሆን ሰቀሉት፡፡
\v 26 "የአይሁድ ንጉሥ" የሚል የክስ ጽሑፍ በመስቀሉ ዐናት ተጽፎ ነበር።
\v 27 ከኢየሱስም ጋር ሁለት ወንበዴዎችን አንዱን በቀኙ፣አንዱንም በግራው ሰቀሉ።
\v 28 መጽሓፍ "ከዐመፀኞች ጋር ተቈጠረ፤" የሚለው ቃል ተፈጸመ።
\s5
\v 29 በአጠገቡ ያልፉ የነበሩትም ሰዎች ራሳቸውን በንቀት እየነቀነቁ እንዲህ በማለት ይሰድቡት ነበር፣ "አንተ ቤተ መቅደስን አፍርሰህ በሦስት ቀን የምትሠራ ሆይ!
\v 30 እስቲ አሁን ራስህን አድን፤ከመስቀልም ውረድ!"
\s5
\v 31 እንደዚሁም የካህናት አለቆች ከጸሓፍት ጋር ሆነው እርስበርሳቸው እንዲህ እያሉ ያፌዙበት ነበር፤ "ሌሎችን አድኖአል፤ ራሱን ማዳን ግን አይችልም" አሉ፡፡
\v 32 "አይተን እንድናምንበት መሲሑ የእስራኤል ንጉሥ እስቲ አሁን ከመስቀል ይውረድ" ከእርሱ ጋር የተሰቀሉት ወንበዴዎችም ይሰድቡት ነበር።
\s5
\v 33 ከቀኑም ስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።
\v 34 ዘጠኝ ሰዓት ሲሆን ኢየሱስ፣ "ኤሎሄ፣ ኤሎሄ፣ ላማሰበቅታኒ፤" ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ትርጓሜውም "አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?" ማለት ነው።
\v 35 በዚያም ቆመው ከነበሩት ሰዎች አንዳንዶቹ ሰምተው "እነሆ! ኤልያስን ይጣራል፤" አሉ።
\s5
\v 36 ከእነርሱም አንዱ ሮጠና ሆምጣጤ በሰፍነግ ሞላ፤ "ኤልያስ መጥቶ ያወርደው እንደ ሆነ እንይ" አለ።እንዲጠጣውም በመቃ ላይ አድርጎ ለኢየሱስ ሰጠው፡፡
\v 37 ከዚያም ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፤ መንፈሱንም ሰጠ።
\v 38 የቤተ መቅደሱም መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዶ ከሁለት ተከፈለ።
\s5
\v 39 በመስቀሉ ፊት ለፊት ቆሞ የነበረ የመቶ አለቃ ኢየሱስ እንዴት መንፈሱን እንደ ሰጠ ባየ ጊዜ፣ "ይህ ሰው በእርግጥ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፤" አለ።
\v 40 በሩቅ ሆነው የሚመለከቱ ሴቶችም በዚያ ነበሩ። ከእነርሱም መካከል መግደላዊት ማርያም፣ የታናሹ ያዕቆብና የዮሳ እናት ማርያም፣ሰሎሜም ነበሩ።
\v 41 እነርሱ ኢየሱስ በገሊላ በነበረበት ጊዜ ይከተሉትና ያገለግሉት ነበር። እንዲሁም ከኢየሱስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሌሎች ብዙ ሴቶችም ነበሩ።
\s5
\v 42 መሽቶ ስለ ነበርና የሰንበት ዋዜማና ለሰንበት የመዘጋጃ ጊዜ ስለ ነበር፡፡
\v 43 የተከበረ የሸንጎ አባል የነበረ ዮሴፍ የሚባል የአርማትያስ ሰው መጣ። እርሱም የእግዚአብሔርን መንግሥት የሚጠባበቅ ሰው ነበር። በድፍረትም ወደ ጲላጦስ ፊት ቀርቦ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ለመነው።
\v 44 ጲላጦስም "እንዴት እንዲህ በቶሎ ሞተ?" ብሎ ተደነቀ። የመቶ አለቃውንም ጠርቶ፣ "ከሞተ ቈይቶአልን?" ሲል ጠየቀው።
\s5
\v 45 የኢየሱስን መሞት ከመቶ አለቃው ከሰማ በኋላ አስከሬኑን እንዲወስድ ለዮሴፍ ፈቀደለት።
\v 46 ዮሴፍም የከፈን ልብስ ገዛ፤ የኢየሱስን አስከሬን ከመስቀል አውርዶ ገነዘው፤ ከዐለት ተወቅሮ በተዘጋጀ መቃብር ውስጥ አስቀመጠው። ትልቅ ድንጋይም አንከባሎ የመቃብሩን መግቢያ ዘጋ።
\v 47 መግደላዊት ማርያምና የዮሳ እናት ማርያምምሰ ኢየሱስን የት እንዳኖሩት አዩ።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 ሰንበት ካለፈ በኋላም መጥተው ይቀቡት ዘንድ መግደላዊት ማርያም፣ የያዕቆብ እናት ማርያምና ሰሎሜ ሽቶ ገዙ፡፡
\v 2 ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ጎህ በቀደደ ጊዜ ወደ መቃብሩ መጡ፡፡
\s5
\v 3 እርስ በርሳቸውም ድንጋዩን ከመቃብሩ መግቢያ ማን ያንከባልልናል ይባባሉ ነበር፡፡
\v 4 አሻግረው ሲመለከቱም ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ተንከባሎ አዩት፡፡
\s5
\v 5 ወደ መቃብሩም ገብተው የሚያንጸባርቅ ነጭ ልብስ የለበሰ አንድ ወጣት በስተቀኝ ተቀምጦ አዩና ተገረሙ፡፡
\v 6 እርሱም አትገረሙ፣ የምትፈልጉት ተሰቅሎ የነበረውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ነው፡፡ ያኖሩበትን ቦታ ተመልከቱ፤ እርሱ በዚህ የለም፣ ተነሥቷል፡፡
\v 7 ነገር ግን ሂዱ፣ ለጴጥሮስና ለደቀመዛሙርቱም እንደነገራችሁ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፣ በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሯቸው አላቸው፡፡
\s5
\v 8 እነርሱም መገረምና ፍርሃት ወድቆባቸው ነበርና ከዚያ ወጥተው ከመቃብሩ ሸሹ፡፡ ፈርተውም ነበርና ለማንም አንዳች አልተናገሩም፡፡
\s5
\v 9 ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን በማለዳ በተነሳ ጊዜ ሰባት አጋንንት አውጥቶላት ለነበረችው ለመግደላዊት ማርያም አስቀድሞ ታያት፡፡
\v 10 እርሷም ከኢየሱስ ጋር የነበሩት እያዘኑና እያለቀሱ ሳሉ ሄዳ ነገረቻቸው፡፡
\v 11 እነርሱም ሕያው እንደሆነና ለእርሷም እንደታያት በሰሙ ጊዜ አላመኑም፡፡
\s5
\v 12 ከእነዚህ ነገሮች በኋላም ከእነርሱ ሁለቱ ወደ ገጠር በመሄድ ላይ ሳሉ ኢየሱስ በሌላ ሰው መልክ ተገለጠላቸው፡፡
\v 13 እነርሱም ሄደው ለተቀሩት ነገሯቸው፤ እነርሱንም አላመኗቸውም፡፡
\s5
\v 14 ከዚያም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ለራሳቸው ኢየሱስ ተገለጠላቸውና ስለ ልባቸው ጥንካሬና ከትንሳኤው በኋላ ያዩትን ስላላመኗቸው ወቀሳቸው፡፡
\v 15 እንዲህም አላቸው፣ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት በሙሉ ስበኩ አላቸው፡፡
\v 16 ያመነና የተጠመቀም ይድናል፣ ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡
\s5
\v 17 ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፣ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፣
\v 18 እባቦችን ይይዛሉ፣ የሚገድል ነገር እንኳን ቢጠጡ አይጎዳቸውም፣ እጆቻቸውን በህሙማን ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይፈወሳሉ፡፡
\s5
\v 19 ጌታ ኢየሱስ ይህንን ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ወጥቶም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡
\v 20 እነርሱም ወጥተው በየቦታው ሰበኩ፡፡ ጌታም ቃሉን ተከትለው በሚመጡ ምልክቶች እያጸና ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፡፡ አሜን፡፡

2212
43-LUK.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,2212 @@
\id LUK
\ide UTF-8
\h ሉቃስ
\toc1 ሉቃስ
\toc2 ሉቃስ
\toc3 luk
\mt ሉቃስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ብዙዎች በእኛ ዘንድ ስለተፈጸሙት ጉዳዮች ታሪኩን በቅደም ተከተል ለማስቀመጥ ሞክረዋል፣
\v 2 ይህም የዓይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት በመጀመሪያ ለእኛ ባስተላለፉልን መሠረት ነበር፡፡
\v 3 ስለሆነም፣ እጅግ የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፣ እኔም የእነዚህን ነገሮች ሂደት ከመጀመሪያው በትክክል ከመረመርኩ በኋላ፣ በቅደም ተከተላቸው መጻፍ መልካም መስሎ ታየኝ፡፡
\v 4 ይህንንም ያደረግሁት ስለ ተማርኸው ነገር እውነቱን ታውቅ ዘንድ ነው፡፡
\s5
\v 5 በይሁዳ ገዢ፣ በሄሮድስ ዘመን ከአብያ ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፡፡ ሚስቱም ከአሮን ልጆች የነበረችና ስሟም ኤልሳቤጥ የሚባል ነበር፡፡
\v 6 ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፣ የእግዚአብሔርን ሕግጋትና ትእዛዛት ሁሉ ያለ ነቀፋ እየጠበቁ ይኖሩ ነበር፡፡
\v 7 ነገር ግን ኤልሳቤጥ መካን ስለነበረች ልጅ አልነበራቸውም፣ በዚህ ጊዜ ደግሞ ሁለቱም አርጅተው ነበር፡፡
\s5
\v 8 በዚህን ጊዜ፣ ዘካርያስ በክፍሉ ተራ የክህነት አገልግሎቱን እየፈጸመ በእግዚአብሔር ፊት የሚሆንበት ጊዜ ደረሰ፡፡
\v 9 የትኛው ካህን እንደሚያገለግል ለመምረጥ በሚፈጸመው ልምድ መሠረት፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን ዕጣ ደረሰው፡፡
\v 10 እርሱ ዕጣን በሚያጥንበት ወቅት፣ ሕዝቡ ሁሉ በውጭ ይጸልይ ነበር፡፡
\s5
\v 11 በዚህን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና በዕጣኑ መሠዊያ በስተቀኝ ቆመ፡፡
\v 12 ዘካርያስ በተመለከተው ጊዜ ደነገጠ፣ ፍርሃትም በእርሱ ላይ ወደቀ፡፡
\v 13 ነገር ግን መልአኩ፣ “ጸሎትህ ተሰምቶአልና ዘካርያስ ሆይ፣ አትፍራ፡፡ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ፡፡
\s5
\v 14 ሐሴትና ደስታ ይሆንልሃል፣ ብዙዎችም በእርሱ መወለድ ሐሴት ያደርጋሉ፡፡
\v 15 በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና፣ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮም በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ይሆናል፡፡
\s5
\v 16 ከእስራኤል ሕዝብም ብዙዎቹ ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመለሳሉ፡፡
\v 17 በእግዚአብሔርም ፊት በኤልያስ መንፈስና ኃይል ይመላለሳል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው የማይታዘዙት በጻድቃን ጥበብ ይሄዱ ዘንድ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች ለመመለስና የተዘጋጁትን ሕዝብ ለእግዚአብሔር ያዘጋጅ ዘንድ ነው” አለው፡፡
\s5
\v 18 ዘካርያስም፣ “እኔ ያረጀሁ በመሆኔና ሚስቴም ዕድሜዋ የገፋ በመሆኑ፣ ይህንን እንዴት ማወቅ እችላለሁ?” አለ፤
\v 19 መልአኩም፣ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህንን የምሥራች እነግርህ ዘንድ ተልኬያለሁ፡፡
\v 20 እነሆ፣ እነዚህ ነገሮች እስኪፈጸሙ ድረስ ጸጥ ትላለህ፣ መናገርም አትችልም፡፡ ይህም የሚሆነው በትክክለኛው ጊዜ የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንክ ነው፡፡”
\s5
\v 21 በዚህን ጊዜ ሕዝቡ ዘካርያስን እየተጠባበቁ ነበር፣ ለረጅም ጊዜ በቤተ መቅደስ በመቆየቱም ተደነቁ፡፡
\v 22 በወጣ ጊዜ ግን ሊያነጋግራቸው አልቻለም፤ እነርሱም በቤተ መቅደስ በነበረበት ጊዜ ራእይ እንደ ተገለጠለት ተገነዘቡ፡፡ ለእነርሱ ምልክት ብቻ እየሰጣቸው ጸጥ ብሎ ቆየ፡፡
\v 23 የአገልግሎቱም ወቅት እንዳበቃ ወደ ቤቱ ለመመለስ ተነሣ፡፡
\s5
\v 24 ከዚህም ወቅት በኋላ ሚስቱ ኤልሳቤጥ ፀነሰች፤ ለአምስት ወራትም ራሷን ሰወረች፣ እንደዚህም አለች፣
\v 25 “በሕዝብ ዘንድ የነበረብኝን ነቀፌታ ለማስወገድ ብሎ በሞገስ ተመልክቶኝ እግዚአብሔር ለእኔ ያደረገልኝ ይህንን ነው፡፡”
\s5
\v 26 ስድስት ወሯ በነበረ ጊዜ መልአኩ ገብርኤል ናዝሬት ወደተባለች የገሊላ ከተማ ተላከ፡፡
\v 27 የተላከውም ዮሴፍ ለተባለ ከዳዊት ነገድ ለሆነ ሰው ወደ ታጨች አንዲት ድንግል ነበር፡፡ የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር፡፡
\v 28 ወደ እርሷም መጣና እንደዚህ አላት፣ “እጅግ የተከበርሽ ሆይ፣ ሰላም ለአንቺ ይሁን! እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነው፡፡”
\v 29 እርሷ ግን በንግግሩ በጣም ግራ ተጋባች፣ ምን ዓይነት ሰላምታ ሊሆን እንደሚችልም በማሰብ ተደነቀች፡፡
\s5
\v 30 መልአኩም፣ “ማርያም ሆይ፤ አትፍሪ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አግኝተሻል፤
\v 31 እነሆ፣ ፅንስ በማሕፀንሽ ውስጥ ይፀነሳል፣ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፡፡ ስሙንም ‘ኢየሱስ’ ትይዋለሽ፡፡
\v 32 እርሱም ታላቅ ይሆናል፣ የልዑልም ልጅ ይባላል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፡፡
\v 33 በያዕቆብም ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሣል፣ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም፡፡"
\s5
\v 34 ማርያምም ለመልአኩ፣ “ከማንም ወንድ ጋር ተኝቼ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል?” አለችው፡፡
\v 35 መልአኩም እንደዚህ በማለት መለሰላት፣ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑል ኃይልም በአንቺ ላይ ያርፋል፤ ከዚህ የተነሣም የሚወለደው ቅዱሱ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል፡፡
\s5
\v 36 እነሆ፣ ዘመድሽም ኤልሳቤጥ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን ትባል ለነበረችው ለእርሷ ይህ ስድስተኛ ወሯ ነው፡፡
\v 37 ለእግዚአብሔር የሚሳነው ምንም ነገር የለምና፡፡”
\v 38 ማርያምም፣ “እነሆ፣ የእግዚአብሔር ባሪያው ነኝ፤ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ፡፡” ከዚያ በኋላም መልአኩ ትቷት ሄደ፡፡
\s5
\v 39 ከዚያ በኋላ፣ ማርያም ተነሥታ በእነዚያ ቀናት በኮረብታማው አገር በይሁዳ ወዳለች ወደ አንዲት ከተማ በፍጥነት ሄደች፡፡
\v 40 ወደ ዘካርያስም ቤት ሄደችና ለኤልሳቤጥ ሰላምታ አቀረበችላት፡፡
\v 41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ እንደዚህ ሆነ፣ በማሕፀኗ ያለው ፅንስ ዘለለ፣ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፡፡
\s5
\v 42 ድምፅዋን ከፍ በማድረግ ጮክ ብላ፣ “ከሴቶች መካከል አንቺ የተባረክሽ ነሽ፣ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡
\v 43 የጌታዬ እናት ወደ እኔ እንድትመጣ ይህ ለምን ሆነ?
\v 44 እነሆ፣ የሰላምታሽ ድምፅ ወደ ጆሮዬ በመጣ ጊዜ በማሕፀኔ ውስጥ ያለው ሕፃን በደስታ ዘለለ፡፡
\v 45 ከጌታ የተነገሩላት ነገሮች እንደሚፈጸሙ የምታምን እነሆ እርሷ የተባረከች ናት፡፡”
\s5
\v 46 ከጌታ የተነገሩላት ነገሮች እንደሚፈጸሙ የምታምን እነሆ እርሷ የተባረከች ናት፡፡” 46. ማርያምም፣ “ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፣
\v 47 መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ሐሴት ታደርጋለች፡፡
\s5
\v 48 የሴት ባሪያውን ውርደት ተመልክቶአልና፡፡ እነሆ፣ ከዚህ በኋላ ትውልድ ሁሉ የተባረከች ይሉኛል፡፡
\v 49 ብርቱ የሆነ እርሱ ለእኔ ታላቅ ነገር አድርጎልኛልና፣ ስሙም ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 50 ለሚያከብሩት ምሕረቱ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው፡፡
\v 51 በክንዱ ብርታትን ገልጾአል፣ ስለ ልባቸው ሐሳብ የሚታበዩትን በትኖአቸዋል፡፡
\s5
\v 52 ገዢዎችን ከዙፋናቸው አውርዷቸዋል፣ ዝቅ ያሉትንም ከፍ አድርጓቸዋል፡፡
\v 53 የተራቡትን በመልካም ነገር አጥግቧቸዋል፣ ባለጠጎችን ግን ባዶአቸውን ሰድዷቸዋል፡፡
\s5
\v 54 ምሕረት ማድረጉን ያስታውስ ዘንድ ለባሪያው ለእስራኤል ረድኤቱን ልኮለታል፣
\v 55 ይህንንም ያደረገው (ለአባቶቻችን እንደተናገረው) ለአብርሃምና ለዘሩ ለዘላለም፡፡”
\s5
\v 56 ማርያም ከኤልሳቤጥ ጋር ሦስት ወራት ያህል ተቀመጠች፣ ከዚያ በኋላም ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡
\v 57 በዚያን ጊዜ ኤልሳቤጥ የምትወልድበት ወቅት ደረሰ፣ ወንድ ልጅም ወለደች፡፡
\v 58 ጎረቤቶቿና ዘመዶቿ እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዳበዛላት ሰሙ፣ ከእርሷም ጋር ደስ አላቸው፡፡
\s5
\v 59 ልጁን የሚገርዙበት ስምንተኛው ቀን በመጣ ጊዜ፣ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ሊሰይሙት ፈልገው ነበር፡፡
\v 60 እናትዬዋ ግን መልስ ሰጠቻቸው፣ “አይሆንም፣ ስሙ ዮሐንስ ይሆናል” አለች፡፡
\v 61 እነርሱም ለእርሷ፣ “ከዘመዶችሽ መካከል በዚህ ስም የተጠራ የለም” አሏት፡፡
\s5
\v 62 በምን ስም እንዲጠራ እንደሚፈልግ አባቱን በምልክት ጠየቁት፡፡
\v 63 አባቱም ሰሌዳ እንዲያቀርቡለት ጠየቀና፣ “ስሙ ዮሐንስ ነው” ብሎ ጻፈ፡፡ በዚህም ሁሉም ተደነቁ፡
\s5
\v 64 ወዲያውኑም አንደበቱ ተከፈተ፣ ምላሱም ተፈትቶ ተናገረ፣ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡
\v 65 በዙሪያቸውም በሚኖሩት ሰዎች ዘንድ ፍርሃት መጣባቸው፣ የእነዚህም ነገሮች ዜና በኮረብታማው በይሁዳ አገር ሁሉ ተሠራጨ፡፡
\v 66 ዜናውን የሰሙትም ሁሉ፣ የእግዚአብሔር እጅ ከእርሱ ጋር ነበርና “እንግዲህ ይህ ልጅ ምን ሊሆን ይሆን?” እያሉ ነገሩን በልባቸው ጠበቁት፡፡
\s5
\v 67 አባቱም ዘካርያስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣
\v 68 “የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ የመቤዠት ሥራ በመሥራት ሕዝቡን ረድቶታልና፡፡
\s5
\v 69 ከባሪያው ከዳዊት ዝርያዎች መካከል ለባሪያው ለዳዊት ቤት የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፡፡
\v 70 ይህም በጥንት ዘመን በነበሩት በቅዱሳን ነቢያቱ እንደ ተናገረው ነው፡፡
\v 71 ከጠላቶቻችንና ከሚጠሉን ሁሉ ያድነናል፡፡
\s5
\v 72 ይህንን የሚያደርገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየትና ቅዱስ ኪዳኑን፣
\v 73 ማለትም ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ለማስታወስ ነው፡፡
\v 74 መሐላውን የማለውም እኛ ከጠላቶቻችን ድነን በዘመኖቻችን ሁሉ በእርሱ ፊት በመሆን ያለ ፍርሃት፣
\v 75 በቅድስናና በጽድቅ እርሱን እንድናገለግለው ነው፡፡
\s5
\v 76 አዎን፣ አንተም ሕፃን የእርሱን መንገድን ለማዘጋጀት በጌታ ፊት ስለምትሄድና ሕዝብንም ለመምጣቱ ስለምታሰናዳ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡
\v 77 ለኃጢአቶቻቸው ይቅርታ የሚያገኙትን የድነት ዕውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፡፡
\s5
\v 78 ይህም ከእግዚአብሔር አምላካችን መልካም ምሕረት የተነሣ ከእርሱ የተነሣ የፀሐይ ብርሃን በእኛ ላይ እንዲያርፍብንና
\v 79 በጨለማና በሞት ጥላ ላሉት እናበራላቸው ዘንድ ነው፡፡ ይህንንም እግሮቻችንን በሰላም መንገድ ይመራው ዘንድ ያደርገዋል፡፡”
\s5
\v 80 ልጁም አደገ፣ በመንፈሱም ጠነከረ፣ ለእስራኤልም እስኪገለጥ ድረስ በምድረ በዳ ኖረ፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ አውግስጦስ ቄሣር በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይቆጠሩ ዘንድ ዐዋጅ አወጣ፡፡
\v 2 ይህም ቄሬኔዎስ የሶርያ ገዥ በነበረበት ጊዜ የተደረገ የመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ነበር፡፡
\v 3 ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለሕዝብ ቆጠራው ወደየራሱ ከተማ ሄደ፡፡
\s5
\v 4 ዮሴፍም የዳዊት ቤተሰብ ዝርያ ስለነበረ በገሊላ ከነበረችው ከናዝሬት ተነሥቶ የዳዊት ከተማ ወደምትባለው የይሁዳ ከተማ ወደ ነበረችው ወደ ቤተ ልሔም ተጓዘ፡፡
\v 5 ይመዘገብ ዘንድ ለእርሱ ታጭታ ከነበረችውና የመውለጃዋን ቀን እየተጠባበቀች ከነበረችው ከማርያም ጋር ወደዚያ ስፍራ ሄደ፡፡
\s5
\v 6 እዚያም በነበሩበት ጊዜ የምትወልድበት ወቅት ደረሰ፡፡
\v 7 የበኩር ልጅዋ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፣ በመታቀፊያ ጨርቅም በሚገባ ጠቀለለችው፡፡ በእንግዳ መቀበያውም ስፍራ ስላልነበረ በእንስሳት መመገቢያ ግርግም ውስጥ አስተኛቸው፡፡
\s5
\v 8 በዚያው አካባቢ በሌሊት የበግ መንጎቻቸውን እየጠበቁ በመስክ የነበሩ እረኞች ነበሩ፡፡
\v 9 በድንገትም የእግዚአብሔር መልአክ ለእነርሱ ተገለጠላቸው፣ የእግዚአብሔርም ክብር በእነርሱ ዙሪያ አበራላቸው፤ እነርሱም በጣም ፈሩ፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ በኋላ መልአኩ፣ “ለሕዝብ ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚሆን የምሥራች ይዤላችሁ መጥቻለሁና አትፍሩ፡፡
\v 11 ዛሬ በዳዊት ከተማ፣ አዳኝ ተወልዶላችኋል፤ እርሱም ክርስቶስ ጌታ ነው፡፡
\v 12 ለእናንተም ይህ ምልክት ይሰጣችኋል፣ ሕፃን በመታቀፊያ ጨርቅ ተጠቅልሎ፣ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ፡፡”
\s5
\v 13 በድንገትም ከመልአኩ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ፣
\v 14 “ከፍ ባለ ስፍራ ለሚኖረው ለእግዚአብሔር ክብር፣ በምድርም እርሱ ደስ በሚሰኝባቸው ሕዝቦች መካከል ሰላም ይሁን፡፡” ይሉ ነበር፡፡
\s5
\v 15 መላእክቱም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በሄዱ ጊዜ፣ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ወደ ቤተልሔም እንሂድና፣ እግዚአብሔር ለእኛ የገለጠልንን ይህንን የሆነውን ነገር እንመልከት፡፡” ተባባሉ፡፡
\v 16 በችኮላ ወደዚያ ሄደው ማርያምንና ዮሴፍን አገኝዋቸው፣ ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ ተመለከቱት፡፡
\s5
\v 17 ይህንን ከተመለከቱ በኋላ ስለዚህ ልጅ የተባለውን ለሕዝቡ አስታወቁ፡፡
\v 18 ያዳመጡአቸውም ከእረኞቹ በተነገራቸው ነገር ተደነቁ፡፡
\v 19 ስለሰማችው ነገር ሁሉ ማርያም እያሰላሰለች በልብዋ ትጠብቀው ነበር፡፡
\v 20 ልክ እንደ ተነገራቸው ስለ ሰሙትና ስላዩት ስለ ማንኛውም ነገር እረኞቹ እግዚአብሔርን እያከበሩና እያመሰገኑ ተመለሱ፡፡
\s5
\v 21 ሕፃኑ የሚገረዝበት ስምንተኛው ቀን በደረሰ ጊዜ በማሕፀን ከመፀነሱ በፊት በመልአኩ በተሰጠው ስም ኢየሱስ ብለው ጠሩት፡፡
\s5
\v 22 በሙሴ ሕግ መሠረት የመንጻታቸው ወራት በተፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ያቀርቡት ዘንድ በኢየሩሳሌም ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ
\v 23 ይህም፣ “ማሕፀንን የሚከፍት ማንኛውም ወንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል” ተብሎ በሕጉ እንደ ተጻፈው ነው፡፡
\v 24 በእግዚአብሔር ሕግም በተነገረው መሠረት መሥዋዕት ማለትም ‘ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች’ ያቀርቡ ዘንድ መጡ፡፡
\s5
\v 25 በኢየሩሳሌምም የሚኖር ስሙ ስምዖን የተባለ ሰው ነበር፡፡ ይህ ሰው ጻድቅና የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚያከብር ነበር፤ ለእስራኤል መጽናኛም የሚሆነውን ይጠባበቅ ነበር፣ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበር፡፡
\v 26 እግዚአብሔር የቀባውን ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፡፡
\s5
\v 27 የሕጉ ሥርዓት የሚጠይቀውን ሊያደርጉለት ወላጆቹ ሕፃኑ ኢየሱስን ይዘው በመጡበት ቀን በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ መጣ፡፡
\v 28 ከዚያም ስምዖን በእጆቹ አቅፎት፣ እግዚአብሔርን እያመሰገነ፣
\v 29 “ጌታ ሆይ፣ እንግዲህ፣ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው፣
\s5
\v 30 ዓይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና
\v 31 ይህም ድነት አንተ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸው ነው፡፡
\v 32 እርሱም ለአሕዛብ መገለጥ ብርሃን፣ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው፡፡”
\s5
\v 33 የልጁም አባትና እናት ስለ እርሱ እየተነገረ ባለው ነገር ተደነቁ፡፡
\v 34 ከዚያ በኋላ ስምዖን ባረካቸውና እናቱን ማርያምን፣ “በጥንቃቄ አድምጪ! ይህ ልጅ በእስራኤል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ምክንያት፣ ክፉም ለተናገሩበት ምልክት የሚሆን ነው፡፡
\v 35 የብዙዎች የልባቸው ሐሳብ ይገለጥ ዘንድ የአንቺም የራስሽ ልብ በሰይፍ የሚወጋ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 36 ሐና የተባለች ነቢይትም በዚያ ነበረች፤ እርሷም ከአሴር ነገድ የሆነ የፋኑኤል ልጅ ነበረች፡፡ ዕድሜዋ እጅግ የገፋ ሲሆን ከጋብቻዋ በኋላ ከባልዋ ጋር ለሰባት ዓመታት ቆይታለች፡፡
\v 37 ከዚያ በኋላ ለሰማንያ አራት ዓመታት መበለት ሆና ኖራለች፡፡ ከቤተ መቅደስ በፍጹም ሳትለይ ቀንና ሌሊት በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን ታመልክ ነበር፡፡
\v 38 ልክ በዚያን ሰዓት ወደ እነርሱ መጥታ እግዚአብሔርን ማመስገን ጀመረች፡፡ የኢየሩሳሌምን መቤዠት ለሚጠባበቁ ለማንኛዎቹም ሰዎች ስለ ልጁ ትናገር ነበር፡፡
\s5
\v 39 እንደ እግዚአብሔር ሕግ እንዲያደርጉ የሚፈለግባቸውን ማንኛውንም ነገር ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ገሊላ ወደ ራሳቸው ከተማ ወደ ናዝሬት ተመለሱ፡፡
\v 40 ልጁ አደገ፣ ጠነከረ፣ በጥበብም ጨመረ፤ የእግዚአብሔር ጸጋም በ እርሱ ላይ ነበረ፡፡
\s5
\v 41 ወላጆቹም ለፋሲካ በዓል በየዓመቱ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር፡፡
\v 42 አሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ በተለመደው ጊዜ እንደገና በዓሉን ለማክበር ሄዱ፡፡
\v 43 ለበዓሉ መቆየት ያለባቸውን ሁሉንም ቀናት ከቆዩ በኋላ ወደ ቤታቸው መመለስ ጀመሩ፡፡ ልጁ ኢየሱስ ግን በኢየሩሳሌም ቀረ፣ ወላጆቹም ይህንን አላወቁም ነበር፡፡
\v 44 ከእነርሱ ጋር ይጓዙ ከነበሩት መንገደኞች ጋር የነበረ መስሏቸው ስለነበረ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፡፡ ከዚያ በኋላም በዘመዶቻቸውና በወዳጆቻቸው ዘንድ ፈለጉት፡፡
\s5
\v 45 ባላገኙትም ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው በዚያ ሊፈልጉት ጀመሩ፡፡
\v 46 ከሦስት ቀን በኋላ እያዳመጣቸውና ጥያቄዎችን እየጠየቃቸው በመምህራን መካከል ተቀምጦ በቤተ መቅደስ ውስጥ አገኙት፡፡
\v 47 ያዳመጡት ሁሉ በማስተዋሉና በሚሰጣቸው መልሶች ተገረሙ፡፡
\s5
\v 48 ባዩትም ጊዜ ተደነቁ፡፡ እናቱም እርሱን፣ “ልጄ ሆይ፣ ለምን እንደዚህ አደረግኸን? አድምጠኝ፣ እኔና አባትህ ተጨንቀን አንተን ስንፈልግህ ነበርን” አለችው።
\v 49 እርሱም፣ “ለምን ነበር የፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንደሚገባኝ አታውቁምን?”
\v 50 ነገር ግን እንደዚያ ሲል ምን ማለቱ እንደነበረ አልገባቸውም፡፡
\s5
\v 51 ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር ወደ ናዝሬት ተመለሰ፣ ይታዘዝላቸውም ነበር፡፡ እናቱም ይህንን ሁሉ ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር፡፡
\v 52 ኢየሱስ ግን በጥበብና በሰውነት ቁመና ማደጉን ቀጠለ፣ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ፊት ያለው ሞገስ እየጨመረ ሄደ፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ጢባርዮስ ቄሣር በነገሠ በአሥራ አምስተኛው ዓመት፣ ጴንጤናዊው ጲላጦስ የይሁዳ ገዥ፣ ሄሮድስ የገሊላ አራተኛው ክፍል ገዥ፣ ወንድሙ ፊልጶስ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ የአራተኛው ክፍል ገዥ፣ ሊሳኒዮስም የሳቢላኒስ አራተኛው ክፈል ገዥ
\v 2 እንደዚሁም ሐናና ቀያፋ ሊቃነ ካህናት በነበሩበት ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ለዘካርያስ ልጅ ለዮሐንስ በምድረ-በዳ መጣ፡፡
\s5
\v 3 ለኃጢአት ይቅርታ የንስሓን ጥምቀት እየሰበከ በዮርዳኖስ ወንዝ አውራጃ ሁሉ ተመላለሰ፡፡
\s5
\v 4 ይህም በነቢዩ በኢሳይያስ መጽሐፍ፣ “በምድረ-በዳ የሚጣራ ሰው ድምፅ፣ ‘የእግዚአብሔርን መንገድ አዘጋጁ፣ ጎዳናውንም አቅኑ፡፡
\s5
\v 5 ሸለቆ ሁሉ ይሞላል፣ ተራራውና ኮረብታው ደልዳላ ይሆናል፣ ጠማማው መንገድ ቀና ይሆናል፣ ሸካራውም መንገድ የተመቸ ይሆናል፡፡
\v 6 ሰዎችም ሁሉ የእግዚአብሔርን ማዳን ያያሉ፡፡’”
\s5
\v 7 ስለዚህ በእርሱ ለመጠመቅ ይመጣ ለነበረው ከፍተኛ ቁጥር ላለው ሕዝብ ዮሐንስ እንደዚህ አላቸው፣ “እናንተ የመርዘኛ እባብ ልጆች፣ ሊመጣ ካለው ቁጣ እንድትሸሹ ማን አስጠነቀቃችሁ?
\s5
\v 8 ለንስሓ የሚሆን ፍሬ አፍሩ፣ እርስ በርሳችሁም፣ ‘አባታችን አብርሃም አለን’ አትበሉ፣ ምክንያቱም ከእነዚህ ድንጋዮች እንኳን እግዚአብሔር ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል፡፡
\s5
\v 9 መጥረቢያ በዛፎች ግንድ ሥር ተቀምጦአል፤ ስለዚህ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተቆርጦ ወደ እሳት ውስጥ ያጣላል፡፡”
\s5
\v 10 ከዚያ በኋላ ተሰብስበው የነበሩት ሰዎች እንደዚህ ብለው ጠየቁት፣ “እንግዲህ ምን እናድርግ?”
\v 11 እርሱም እንደዚህ ብሎ መለሰላቸው፣ “አንድ ሰው ሁለት ልብስ ካለው ምንም ለሌለው ለሌላ ሰው ይስጠው፤ ትርፍ ምግብ ያለውም እንደዚሁ ያድርግ፡፡”
\s5
\v 12 ከዚያ በኋላም አንዳንድ ቀረጥ ሰብሳቢዎች ለመጠመቅ መጡና እንደዚህ አሉት፣ “መምህር ሆይ፣ እኛስ ምን ማድረግ ይገባናል?”
\v 13 እርሱም እንደዚህ አላቸው፣ “መሰብሰብ ከሚገባችሁ ገንዘብ በላይ አትሰብስቡ፡፡”
\s5
\v 14 አንዳንድ ወታደሮችም እንደዚህ ብለው ጠየቁት፣ “እኛስ፣ ምን ማድረግ ይገባናል?” እርሱም እንደዚህ አላቸው፣ “ከማንም ላይ አስገድዳችሁ ገንዘብ አትውሰዱ፣ ማንንም በሐሰት አትክሰሱ፡፡ የምታገኙትም ደመወዝ ይብቃችሁ፡፡”
\s5
\v 15 ሕዝቡ የክርስቶስን መምጣት እየተጠባበቁ ሳሉ፣ ሰዎች ሁሉ በልባቸው እርሱ ክርስቶስ ይሆን እያሉ ስለ ዮሐንስ ይደነቁ ነበር፡፡
\v 16 እንደዚህ በማለት ዮሐንስ ለሁሉም መልስ ሰጣቸው፣ “እኔ በበኩሌ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፣ የጫማውን ማሠሪያ መፍታት እንኳን የማይገባኝ ከእኔ ይልቅ ብርቱ የሆነ ይመጣል፡፡ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡
\s5
\v 17 አውድማውን ፈጽሞ ያጠራውና ስንዴውን ወደ ጎተራ ያስገባ ዘንድ የሚያበራይበት መንሽ በእጁ ነው፡፡ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል፡፡”
\s5
\v 18 ሌሎች ብዙ ምክሮችንም በመምከር፣ የምሥራቹን ቃል ለሕዝቡ ሰበከላቸው፡፡
\v 19 የወንድሙን ሚስት ሄሮዳይዳን ስላገባና ስላደረጋቸውም ሌሎች ክፉ ሥራዎች የአራተኛው ክፍል ገዥ የነበረውን ሄሮድስንም ገሰጸው፡፡
\v 20 ሄሮድስ ግን ከዚህም የባሰ ክፉ ሥራ ሠራ፣ ዮሐንስን ወህኒ ቤት አስገብቶ ቆለፈበት፡፡
\s5
\v 21 ሰዎች ሁሉ በዮሐንስ እየተጠመቁ ሳሉ፣ ኢየሱስም ደግሞ ተጠመቀ፡፡ እየጸለየም ሳለ ሰማያት ተከፈቱ፡፡
\v 22 መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል በአካል በእርሱ ላይ አረፈ፣ በዚህም ጊዜ ከሰማይ፣ “አንተ፣ ውድ ልጄ ነህ፤ በአንተ እጅግ ደስ ይለኛል፡፡” የሚል ድምፅ መጣ፡፡
\s5
\v 23 በዚህን ጊዜ ኢየሱስ ራሱ ማስተማር ሲጀምር ዕድሜው ሰላሳ ዓመት ገደማ ነበር፡፡ (ይገመት እንደነበረው) እርሱ የኤሊ ልጅ የነበረው የዮሴፍ ልጅ
\v 24 ኤሊም የማቲ ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣ የሚልኪ ልጅ፣ የዮና ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣
\s5
\v 25 የማታትዩ ልጅ፣ የአሞጽ ልጅ፣ የናሆም ልጅ፣ የኤሲሊም ልጅ፣ የናጌ ልጅ፣
\v 26 የማኦት ልጅ፣ የማታትዩ ልጅ፣ የሰሜይ ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዮዳ ልጅ፣
\s5
\v 27 የዮናን ልጅ፣ የሬስ ልጅ፣ የዘሩባቤል ልጅ፣ የሰላትያል ልጅ፣ የኔር ልጅ፣
\v 28 የሚልኪ ልጅ፣ የሐዲ ልጅ፣ የዮሳስ ልጅ፣ የቆሳም ልጅ፣ የኤልሞዳም ልጅ፣ የኤር ልጅ፣
\v 29 የዮሴዕ ልጅ፣ የአልዓዛር ልጅ፣ የዮራም ልጅ፣ የማጣት ልጅ፣ የሌዊ ልጅ፣
\s5
\v 30 የስምዖን ልጅ፣ የይሁዳ ልጅ፣ የዮሴፍ ልጅ፣ የዮናም ልጅ፣ የኤልያቄም ልጅ፣
\v 31 የሜልያ ልጅ፣ የማይናን ልጅ፣ የማጣት ልጅ፣ የናታን ልጅ፣ የዳዊት ልጅ፣
\v 32 የእሴይ ልጅ፣ የኢዮቤድ ልጅ፣ የቦዔዝ ልጅ፣ የሰልሞን ልጅ፣ የነአሶን ልጅ፣
\s5
\v 33 የአሚናዳብ ልጅ፣ የአራም ልጅ፣ የአሮኒ ልጅ፣ የኤስሮም ልጅ፣ የፋሬስ ልጅ፣ የይሁዳ ልጅ፣
\v 34 የያዕቆብ ልጅ፣ የይስሐቅ ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ፣ የታራ ልጅ፣ የናኮር ልጅ፣
\v 35 የሴሮህ ልጅ፣ የራጋው ልጅ፣ የፋሌቅ ልጅ፣ የአቤር ልጅ፣ የሳላ ልጅ፣
\s5
\v 36 የቃይንም ልጅ፣ የአርፋክስድ ልጅ፣ የሴም ልጅ፣ የኖኅ ልጅ፣ የላሜህ ልጅ፣
\v 37 የማቱሳላ ልጅ፣ የሄኖክ ልጅ፣ የያሬድ ልጅ፣ የመላልኤል ልጅ፣ የቃይናን ልጅ፣
\v 38 የሄኖስ ልጅ፣ የሴት ልጅ፣ የአዳም ልጅ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፡፡
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ከዚያ በኋላ፣ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ወንዝ ተመለሰ፤ መንፈስም ወደ ምድረ-በዳ መራው፡፡
\v 2 በዚያም ለአርባ ቀናት በዲያብሎስ ተፈተነ፡፡ በእነዚያም ቀናት ምንም አልበላም፣ ያም ወቅት በተጠናቀቀ ጊዜ ተራበ፡፡
\s5
\v 3 ዲያብሎስም፣ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ይህ ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዝ” አለው፡፡
\v 4 ኢየሱስም፣ “’ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 5 ከዚያ በኋላም ዲያብሎስ ከፍ ወዳለ ስፍራ ወሰደውና፣ በቅጽበት የዓለም መንግሥታትን ሁሉ አሳየው፡፡
\v 6 ዲያብሎስም ለእርሱ፣ “እነዚህን ሁሉ መንግሥታት ከክብራቸው ሁሉ ጋር እንድትገዛ እኔ ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ ይህንን ማድረግ የምችለው እገዛቸው ዘንድ ለእኔ ስለተሰጡኝ ነው፣ እኔም ለምፈልገው ለማንኛውም ሰው ልሰጣቸው እችላለሁ፡፡
\v 7 ስለዚህ በፊቴ ብትሰግድልኝና ብታመልከኝ፣ ይሄ ሁሉ የአንተ ይሆናል አለው።
\s5
\v 8 ኢየሱስ ግን እንደዚህ ብሎ መለሰለት፣ “’እግዚአብሔር አምላክህን አምልክ፣ እርሱንም ብቻ አገልግል’ ተብሎ ተጽፎአል፡፡”
\s5
\v 9 ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቤተ መቅደሱ ሕንፃ እጅግ ከፍተኛ ስፍራ አቆመውና፣
\v 10 “’ይጠብቁህና ይንከባከቡህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛቸዋል’
\v 11 ደግሞም፣ ‘እግርህም ከድንጋይ ጋር እንዳይጋጭ በእጆቻቸው ወደ ላይ ይይዙሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና፣ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ ራስህን ከዚህ ላይ ወርውር፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 12 ኢየሱስም፣ “’እግዚአብሔር አምላክህን መፈታተን የለብህም’ ተብሎአል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 13 ዲያብሎስም ኢየሱስን መፈተኑን ባበቃ ጊዜ፣ እስከ ሌላ ጊዜ ድረስ ትቶት ሄደ፡፡
\s5
\v 14 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልቶ ወደ ገሊላ ተመለሰ፤ በዚያ አካባቢ በነበሩት ስፍራዎች ሁሉ የእርሱ ዝና ተሰራጨ፡፡
\v 15 በምኩራቦቻቸው አስተማረ፣ ሰዎችም ሁሉ ያመሰግኑት ነበር፡፡
\s5
\v 16 አንድ ቀንም ወዳደገበት ከተማ ወደ ናዝሬት መጣ፡፡ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገባ፣ የእግዚአብሔርንም ቃል ያነብ ዘንድ ቆመ፡፡
\v 17 የነቢዩ የኢሳይያስ የመጽሐፍ ጥቅልል ተሰጥቶት ስለነበረ፣ ጥቅልሉን ሲከፍተው፣
\s5
\v 18 “ለድሆች የምሥራቹን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለምርኮኞች ነፃነትን፣ ለዕውሮች ብርሃናቸው እንደሚመለስላቸው ፣ የተጨቆኑትም መፈታትን እንደሚያገኙ
\v 19 የእግዚአብሔርን የሞገስ ዓመት ዐውጅ ዘንድ ልኮኛል፡፡” የሚለውን ስፍራ አገኘ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያ በኋላ የመጽሐፉን ጥቅልል ዘጋና ለምኩራቡ አገልጋይ ሰጥቶ ተቀመጠ፡፡
\v 21 “እናንተ እየሰማችሁ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ተፈጸመ፡፡” እያለ ሊነግራቸው ጀመረ፡፡
\v 22 በዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ የተናገረውን አስተዋሉ፣ ከአንደበቱም በሚወጣው የጸጋ ቃል ሁሉም ተገረሙ፡፡ እነርሱም፣ “ይህ የዮሴፍ ልጅ ነው፣ አይደለም እንዴ?” ይሉ ነበር፡
\s5
\v 23 ኢየሱስም፣ “በእርግጥ ‘ሐኪም ሆይ፣ ራስህን አድን፤ በቅፍርናሆም እንደምታደርግ የሰማነውን በዚህም በትውልድ ከተማህ አድርግ’ የሚለውን ይህንን ምሳሌ ትመስሉብኛላችሁ፡፡”
\v 24 ደግሞም እንደዚህ አላቸው፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ማንኛውም ነቢይ በገዛ አገሩ ተቀባይነት የለውም፡፡
\s5
\v 25 ነገር ግን እኔ እውነት እላችኋለሁ፣ ለሦስት ዓመታት ተኩል ሰማይ ተዘግቶ ዝናብ ባልነበረበትና በምድሪቱም ሁሉ ረሃብ በነበረበት በኤልያስ ዘመን በእስራኤል ብዙ መበለቶች ነበሩ፡፡
\v 26 ነገር ግን ኤልያስ በሲዶና አጠገብ በሰራፕታ ትኖር ወደነበረችው መበለት ብቻ እንጂ ከእነርሱ ወደ አንዲቱም አልተላከም፡፡
\v 27 በነቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም በእስራኤል ብዙ ለምጻሞች ነበሩ፣ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነርሱ አንዳቸውም አልተፈወሱም፡፡”
\s5
\v 28 በምኩራብ የነበሩት ሰዎች ሁሉ እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ በቁጣ ተሞሉ፡፡
\v 29 ተነሥተው ከከተማይቱ እንዲወጣ አስገደዱት፣ ከገደል ጫፍም ገፍትረው ይጥሉት ዘንድ ከተማይቱ ወደ ተመሠረተችበት ወደ ኮረብታው ጫፍ ገፍተው ወሰዱት።
\v 30 ነገር ግን በመካከላቸው አልፎ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
\s5
\v 31 ከዚያ በኋላም በገሊላ ወደምትገኝ ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ሄደ፡፡
\v 32 በሥልጣን ይናገር ስለነበረ፣ በትምህርቱ ተገረሙ፡፡
\s5
\v 33 በዚያን ቀን በምኩራብ ውስጥ ርኩስ መንፈስ የነበረበት ሰው ነበረ፤ እርሱም በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡
\v 34 “የናዝሬቱ ኢየሱስ ሆይ፣ ከአንተ ጋር ምን አለን? ልታጠፋን መጣህን? ማን እንደሆንክ አውቄሃለሁ፣ አንተ የእግዚአብሔር ቅዱስ ነህ፡፡”
\s5
\v 35 ኢየሱስም ጋኔኑን፣ “ፀጥ ብለህ ከእርሱ ውጣ!” ብሎ ገሠጸው፡፡ ጋኔኑ በሰዎቹ መካከል በጣለው ጊዜ፣ ምንም ጉዳት ሳያደርስበት ከእርሱ ወጣ፡፡
\v 36 ሰዎች ሁሉ በጣም ተደነቁ፣ እርስ በርሳቸውም ስለሆነው ነገር መነጋገር ቀጠሉ፡፡ እነርሱም፣ “እነዚህ እንዴት ያሉ ቃላት ናቸው? ርኩሳን መናፍስትን በሥልጣንና በኃይል ያዛቸዋል፣ እነርሱም ይወጣሉ፡፡”
\v 37 የእርሱም ዝና በአካባቢው ባሉት አውራጃዎች በማንኛውም ስፍራ ወጣ፡፡
\s5
\v 38 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ ከምኩራብ ወጥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ፡፡ በዚያን ጊዜ የስምዖን አማት በከፍተኛ ትኩሳት ታማ ነበር፣ እነርሱም ስለ እርሷ ተማፀኑት፡፡
\v 39 ስለዚህ በአጠገብዋ ቆሞ ትኩሳቱን ገሠጸው፣ ትኩሳቱም ቆመ፡፡ ወዲያውኑም ተነሥታ ልታገለግላቸው ጀመረች፡፡
\s5
\v 40 ፀሐይም በጠለቀች ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ደዌዎች የተያዙትን በሽተኞች ወደ እርሱ አመጡ፡፡ እርሱም እጆቹን በእያንዳንዳቸው ላይ ጭኖ ፈወሳቸው፡፡
\v 41 አጋንንትም፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” እያሉ በመጮኽ ከብዙዎች ወጡ፡፡ ኢየሱስ አጋንንትን ገሠጻቸው፣ እንዲናገሩም አልፈቀደላቸውም፣ ምክንያቱም እርሱ ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና፡፡
\s5
\v 42 ንጋትም በሆነ ጊዜ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ሄደ፡፡ ብዙ የሕዝብ አጀብ እየፈለጉት ነበርና፣ እርሱ ወደነበረበት ስፍራ መጡ፡፡ እነርሱንም ትቷቸው እንዳይሄድ ሊያስቀሩት ሞከሩ፡፡
\v 43 እርሱ ግን እንደዚህ አላቸው፣ “የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ለብዙ ከተሞች መስበክ ይገባኛል፣ ምክንያቱም ወደዚህ የተላክሁት ለዚህ ነው፡፡”
\v 44 ከዚያ በኋላ በመላው ይሁዳ ባሉት ምኩራቦች መስበኩን ቀጠለ፡፡
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ሕዝቡ ከበውት የእግዚአብሔርን ቃል እያዳመጡ ሳሉ፣ ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ሐይቅ ዳር ቆሞ ነበር፡፡
\v 2 ሁለት ጀልባዎች በሐይቁ ጥግ በኩል ሲጎተቱ ተመለከተ፡፡ ዓሣ አጥማጆቹ ከጀልባዎቹ ወርደው መረቦቻቸውን እያጠቡ ነበር፡፡
\v 3 ኢየሱስ የስምዖን ወደ ነበረችው ከጀልባዎቹ ወደ አንዲቱ ገባና ከምድር ጥቂት ፈቀቅ አድርጎ ወደ ውሃ ውስጥ እንዲያስገባት ጠየቀው፡፡ ከዚያ በኋላም በጀልባዋ ውስጥ ተቀምጦ ሕዝቡን ማስተማር ጀመረ፡፡
\s5
\v 4 ንግግሩንም በጨረሰ ጊዜ ለስምዖን፣ “ጀልባይቱን ወደ ጥልቁ ውሃ ፈቀቅ አድርጋትና ዓሣ ለማጥመድ መረቦቻችሁን ጣሉ፡፡” አለው፡፡
\v 5 ስምዖንም፣ “ጌታ ሆይ፣ ሌሊቱን ሁሉ ስንሠራ አደርን ምንም አላጠመድንም፣ ነገር ግን በቃልህ መረቡን እጥላለሁ፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 6 ይህንን ባደረጉ ጊዜ እጅግ ብዙ ዓሣ ያዙ፣ መረቦቻቸውም ሊቀደዱ ደረሱ፡፡
\v 7 ስለዚህ እንዲመጡና እንዲረዷቸው በሌላ ጀልባ የነበሩትን ጓደኞቻቸውን በጥቅሻ ጠሩ፡፡ እነርሱም መጥተው ሁለቱንም ጀልባዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው፡፡
\s5
\v 8 ስምዖን ጴጥሮስ ግን ይህንን በተመለከተ ጊዜ በኢየሱስ ጉልበት ሥር ዝቅ ብሎ በመንበርከክ፣ “ጌታ ሆይ፣ እኔ ኃጢአተኛ ሰው ነኝና ከእኔ ተለይ” አለው፡፡
\v 9 እንደዚህም ያለው ስላጠመዷቸው ዓሣዎች እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተደንቀው ስለነበረ ነው፡፡
\v 10 በዚያም ከነበሩት መካከል የዘብዴዎስ ልጆች ዮሐንስና ያዕቆብ አብረውት ነበሩ፡፡ ኢየሱስም ለስምዖን፣ “ከእንግዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህና፣ አትፍራ፡፡” አለው፡፡
\v 11 ጀልባቸውን ወደ ምድር ባመጧት ጊዜ ሁሉንም ትተው ተከተሉት፡፡
\s5
\v 12 ከከተማዎቹ በአንዲቱ በነበረ ጊዜ፣ መላ ሰውነቱ በለምጽ የተመታ ሰው በዚያ ነበረ፡፡ ኢየሱስንም ባየ ጊዜ በፊቱ ወድቆ፣ “ብትፈቅድስ፣ ልታነጻኝ ትችላለህ፡፡” ብሎ ለመነው፡፡
\v 13 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና፣ “እፈቅዳለሁ፣ ንጻ” አለው፡፡ ወዲያውኑም ለምጹ ከእርሱ ተወገደ፡፡
\s5
\v 14 ለማንም እንዳይነግር አስጠነቀቀው፣ ነገር ግን፣ “ሂድና ራስህን ለካህን አሳይ፣ ሙሴ ባዘዘውም መሠረት ለእነርሱ ምስክር ይሆን ዘንድ ለመንጻትህ መሥዋዕት አቅርብ፡፡” አለው፡
\s5
\v 15 ነገር ግን ስለ እርሱ ያለው ዝና ከዚያም ርቆ ወጣ፤ ብዙም የሕዝብ አጀብ ሲያስተምር ለመስማትና ከሕመሞቻቸው ለመፈወስ በአንድነት ወደ እርሱ መጡ፡፡
\v 16 እርሱ ግን ወደ ገለልተኛ ስፍራዎች ሄዶ በዚያ ይጸልይ ነበር፡፡
\s5
\v 17 ያስተምር ከነበረባቸውም ከእነዚያ በአንዱ ቀን ከገሊላና ከይሁዳ መንደሮችና አውራጃዎች እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ከተማ መጥተው በዚያ የተቀመጡ ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን ነበሩ፡፡ ይፈውስም ዘንድ የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ ላይ ነበረ፡፡
\s5
\v 18 በዚያን ጊዜ ጥቂት ሰዎች ሰውነቱ የደነዘዘ ሰው በቃሬዛ ይዘው መጡ፤ በኢየሱስ ፊትም ያደርጉት ዘንድ ወደ ውስጥ የሚያስገቡበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡
\v 19 ከሕዝቡም ብዛት የተነሣ ሊያስገቡ የሚችሉበትን መንገድ አላገኙም፤ ስለዚህ ወደ ቤቱ ጣሪያ ላይ ወጥተው፣ ሰውዬውን በቃሬዛው ላይ እንዳለ በጣሪያው አሳልፈው በሰዎቹ መካከል ከኢየሱስ ፊት አወረዱት፡፡
\s5
\v 20 ኢየሱስ እምነታቸውን ተመልክቶ፣ “አንተ ሰው፣ ኃጢአትህ ተሰርዮልሃል” አለው፡፡
\v 21 ፈሪሳውያንና ጸሐፍት፣ “የስድብ ቃል የሚናገር ይህ ማን ነው? እግዚአብሔር ብቻ ካልሆነ በስተቀር፣ ኃጢአትን ይቅር ማለት የሚችል ማን ነው?” በማለት መጠየቅ ጀመሩ፡፡
\s5
\v 22 ነገር ግን ኢየሱስ ምን እንዳሰቡ አውቆ፣ “በልባችሁ ይህንን ለምን ትጠይቃላችሁ?
\v 23 የትኛውን ማለት ይቀላል፡- ‘ኃጢአትህ ተሰረየችልህ’ ማለት ወይስ ‘ተነሣና ሂድ’ ማለት?
\v 24 ነገር ግን ለሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፣ ለአንተ፣ ‘ተነሣና ቃሬዛህን ተሸክመህ ወደ ቤትህ ሂድ’ ብዬ እናገራለሁ፡፡"
\s5
\v 25 ከዚያ በኋላ በእነርሱ ፊት ተነሣ፣ ተኝቶበት የነበረውንም ቃሬዛ ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያከበረ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡
\v 26 ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፣ እግዚአብሔርንም አከበሩ፡፡ “በዛሬው ዕለት ያልተለመደ ነገር አየን” እያሉ በፍርሃት ተሞሉ፡፡
\s5
\v 27 እነዚህ ነገሮች ከሆኑ በኋላ፣ ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ በቀረጥ መሰብሰቢያው ስፍራ ተቀምጦ የነበረውን ሌዊ የተባለውን ቀረጥ ሰብሳቢ ተመለከተ፡፡ እርሱንም፣ “ተከተለኝ” አለው፡፡
\v 28 ስለዚህ ሌዊ ሁሉንም ትቶ ተነሥቶ ተከተለው፡፡
\s5
\v 29 ከዚያ በኋላ፣ ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፣ በዚያም ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና በማዕድ ቀርበው ከእነርሱ ጋር የሚመገቡ ሌሎች ሰዎችም ነበሩ፡፡
\v 30 ነገር ግን ፈሪሳውያንና ጻሐፍት በደቀመዛሙርቱ ላይ፣ “ከቀረጥ ሰብሳቢዎችና ከሌሎች ኃጢአተኛ ሰዎች ጋር ለምን ትበላላችሁ ትጠጣላችሁም?” እያሉ ያጉረመርሙባቸው ነበር፡፡
\v 31 ኢየሱስም እንደዚህ በማለት መለሰላቸው፣ “በመልካም ጤንነት ላይ ያሉ ሐኪም አያስፈልጋቸውም፣ ሐኪም የሚያስፈልጋቸው የታመሙ ብቻ ናቸው፡፡
\v 32 እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ለንስሐ ለመጥራት ሳይሆን ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ ለመጥራት ነው፡፡”
\s5
\v 33 እነርሱም ፣ “የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ይጾማሉ ይጸልያሉም፣ የፈሪሳውያን ደቀመዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፡፡ የአንተ ደቀመዛሙርት ግን ይበላሉ፣ ይጠጣሉም፡፡” አሉት፡፡
\v 34 ኢየሱስም ፣ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎቹን እንዲጾሙ ሊያደርጋቸው የሚችል አለን?
\v 35 ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ወቅት ይመጣል በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ፡፡”
\s5
\v 36 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በምሳሌ ተናገራቸው፣ “ማንም ሰው ከአዲስ ልብስ ላይ እራፊ ቀዶ አሮጌ ልብስ አይጥፍም፡፡ እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ፣ ከአዲሱ ልብስ ላይ እራፊ ይቀዳል፣ ነገር ግን ከአዲሱ ልብስ ላይ የተቀደደው እራፊ ከአሮጌው ልብስ ጋር አብሮ አይሄድም፡፡
\s5
\v 37 እንደዚሁም፣ ማንም ሰው በአሮጌው አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ አያስቀምጥም፡፡ እንደዚህ ቢያደርግ፣ አዲሱ ወይን ጠጅ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፣ ወይን ጠጁም ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይበላሻል፡፡
\v 38 ነገር ግን አዲስ ወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ይቀመጣል፡፡
\v 39 ማንም ሰው አሮጌውን ወይን ጠጅ ከጠጣ በኋላ አዲሱን የወይን ጠጅ አይፈልግም፣ ‘አሮጌው ይሻላል’ ይላልና፡፡”
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 በሰንበት ቀን በእህል እርሻ መካከል በሚያልፍበት ጊዜ ደቀመዛሙርቱ እሸት እየቀጠፉና በእጆቻቸው እያሹ እህሉን ይቅሙ ነበር፡፡
\v 2 ገር ግን ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣ “በሰንበት ቀን ማድረግ ያልተፈቀደውን የምታደርጉት ለምንድን ነው?” አሏቸው፡፡
\s5
\v 3 ኢየሱስም ለእነርሱ፣ “ዳዊት በተራበ ጊዜ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ያደረጉትን እንኳ አላነበባችሁምን?
\v 4 ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከተቀደሰው ኅብስት ጥቂት ወሰደ፤ ካህናትም ብቻ ይበሉ ዘንድ የተፈቀደላቸውን ለራሱ በላ። አብረውት ከነበሩትም ለአንዳንዶቸ ይበሉ ዘንድ ሰጣቸው” አላቸው፡፡
\v 5 ከዚያ በኋላም፣ “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው” አላቸው፡፡
\s5
\v 6 በሌላም ሰንበት ቀን ወደ ምኩራብ ገብቶ በዚያ የነበሩትን ሰዎች አስተማራቸው፡፡ በዚያም የቀኝ እጁ የሰለለች አንድ ሰው ነበረ፡፡
\v 7 አንድ የተሳሳተ ነገር ሲያደርግ ተመልክተው ለመክሰስ ምክንያት ያገኙ ዘንድ በሰንበት ቀን አንድን ሰው ይፈውስ እንደሆነ ፈሪሳውያንና ጸሐፍት በትኩረት ይመለከቱት ነበር፡፡
\v 8 እርሱ ግን ምን እንደሚያስቡ አውቆ፣ እጁ የሰለለችበትን ሰውዬ፣ “ተነሣና በሰዎች ሁሉ መካከል ቁም” አለው፡፡ ስለዚህም ሰውዬው ተነሣና በዚያ ስፍራ ቆመ፡፡
\s5
\v 9 ኢየሱስም፣ “ እኔም እናንተን እጠይቃችኋለሁ፡- በሰንበት ሕጋዊ የሚሆነው መልካም ማድረግ ነው ክፉ፣ ሕይወት ማድን ነው ወይስ ማጥፋት?”
\v 10 ከዚያም ዞር ብሎ ሁሉንም ተመለከታቸውና ለሰውዬው፣ “እጅህን ዘርጋ” አለው፤ ዘረጋውም፣ እጁም ዳነለት፡፡
\v 11 ከዚያ በኋላም በቁጣ ተሞልተው፣ በኢየሱስ ላይ ምን እንደሚያደርጉበት እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፡፡
\s5
\v 12 በዚያም ወቅት ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፣ ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር መጸለዩን ቀጠለ፡፡
\v 13 በነጋም ጊዜ ደቀመዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠራ፣ ከእነርሱም ‘ሐዋርያት’ ብሎ የሰየማቸውን አሥራ ሁለቱን መረጠ፡፡
\s5
\v 14 የሐዋርያቱም ስም፣ ስምዖን (ጴጥሮስ ብሎ የሰየመው) ወንድሙ እንድርያስ፣ ያዕቆብ፣ ዮሐንስ፣ ፊልጶስ፣ በርተሎሚዎስ፣
\v 15 ማቴዎስ፣ ቶማስ፣ ያዕቆብ የእልፍዮስ ልጅ፣ ቀናተኛ የተባለው ስምዖን፣
\v 16 የያዕቆብ ልጅ ይሁዳና ከዳተኛ የሆነው ይሁዳ አስቆሮቱ ናቸው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያ በኋላም ኢየሱስ ከተራራው ወረደና በደልዳላ ቦታ ላይ ቆመ፡፡ ከደቀመዛሙርቱ በርከት ያሉት፣ ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርቻ ብዙ ሰዎች በዚያ ነበሩ፡፡
\v 18 ወደዚያ የመጡት እርሱን ሊያዳምጡትና ከበሽታዎቻቸው ሊፈወሱ ነበር፡፡ በርኩሳን መናፍስት ሲጨነቁ የነበሩም ሰዎች ተፈወሱ፡፡
\v 19 የሚፈውስ ኃይል ከእርሱ ይወጣ ስለነበረ፣ በሕዝቡ መካከል ያለ እያንዳንዱ ሰው እርሱን ለመንካት ጥረት ያደርግ ነበር፤ እርሱም ሁሉንም ፈወሳቸ.
\s5
\v 20 ከዚያ በኋላም ወደ ደቀመዛሙርቱ ተመለከተና፣ እንደዚህ አላቸው፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ለእናንተ ናትና፣ እናንተ ድሆች የተባረካችሁ ናችሁ፡፡
\v 21 አሁን የምትራቡ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ትጠግባላችሁና፡፡ አሁን የምታለቅሱ የተባረካችሁ ናችሁ፣ ትስቃላችሁና፡፡
\s5
\v 22 ሰዎች በሚጠሏችሁና በሚያገሏችሁ ጊዜ እንደዚሁም በሰው ልጅ ምክንያት ስማችሁን በክፉ ሲያነሱ የተባረካችሁ ናችሁ፡፡
\v 23 አባቶቻቸው ነቢያትን እንደዚሁ አድርገውባቸው ነበርና ፣ በዚያን ቀን ሐሴት አድርጉ፣ በደስታም ዝለሉ፣ ምክንያቱም በሰማይ በእርግጥ ታላቅ ብድራት ይኖራችኋል፡፡
\s5
\v 24 እናንተ አሁኑኑ መጽናናትን ተቀብላችኋልና፣ ነገር ግን እናንተ ባለጠጎች ወዮላችሁ!
\v 25 በኋላ ትራባላችሁና፣ እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ! በኋላ ስለምታለቅሱና ዋይ፣ ዋይ ስለምትሉ፣ እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ!
\s5
\v 26 ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካም በሚናገሩላችሁ ጊዜ ወዮላችሁ! ምክንያቱም አባቶቻቸው ለሐሰተኛ ነቢያት እንደዚያ ያደርጉላቸው ነበርና፡፡
\s5
\v 27 ለእናንተ ለምታደምጡ ግን እላችኋለሁ፣ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ ለሚጠሏችሁም መልካም አድርጉላቸው፡፡
\v 28 የሚረግሟችሁን መርቁ፣ ለሚያንገላቷችሁም ጸልዩላቸው።
\s5
\v 29 አንድ ጉንጭህን ለሚመታህ ሌላውንም ጉንጭህን አዙርለት፡፡ አንድ ሰው ነጠላህን የሚወስድብህ ከሆነ፣ እጀ ጠባብህን አትከልክለው፡፡
\v 30 ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፣ አንድ ሰው የአንተ የሆነውን የሚወስድብህ ከሆነ፣ እንዲመልስልህ አትጠይቀው፡፡
\s5
\v 31 ሰዎች እንዲያደርጉልህ የምትፈልገውን ሁሉ አንተም ለእነርሱ ልታደርግላቸው ይገባሃል፡፡
\v 32 ኃጢአተኞችም እንኳን የሚወዷቸውን ይወዳሉና የሚወዷችሁን የምትወዱ ከሆነ፣ ምን ምስጋና ትቀበላላችሁ?
\v 33 ኃጢአተኞችም እንደዚያው ያደርጋሉና መልካም ለሚያደርጉላችሁ ብቻ መልካም የምታደርጉ ከሆናችሁ፣ ምን ምስጋና ትቀበላላችሁ?
\v 34 እንደሚመልሱላችሁ ለምትጠብቋቸው ብቻ የምታበድሩ ከሆናችሁ፣ ምን ምስጋና አላችሁ? የሰጡትን ያንኑ ያህል ለመቀበል ተስፋ አድርገው፣ ኃጢአተኞችም እንኳን ለኃጢአተኞች ያበድራሉ፡፡
\s5
\v 35 ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፣ መልካምም አድርጉላቸው፤ ምንም ነገር ስለመቀበል ሳትጨነቁ አበድሯቸው፣ ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፡፡ እርሱ ራሱ ለማያመሰግኑና ለክፉ ሰዎች ቸር ነውና፣ እናንተም የልዑል ልጆች ትባላላችሁ፡፡
\v 36 አባታችሁ መሐሪ እንደሆነ ሁሉ እናንተም መሐሪዎች ሁኑ፡፡
\s5
\v 37 አትፍረዱ አይፈርድባችሁም፤ አትኮንኑ አትኮነኑምም፤ ሌሎችን ይቅር በሉ፣ እናንተም ይቅር ትባላላችሁ፡፡
\s5
\v 38 ለሌሎች ስጡ፣ ለእናንተም የተጠቀጠቀ፣ የተነቀነቀ፣ በእቅፎቻችሁም ተርፎ የሚፈስ መልካም መስፈሪያ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል፡፡ ለሌሎች ለመስፈር በምትጠቀሙበት በዚያው መስፈሪያ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል፡፡"
\s5
\v 39 ከዚያም ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ በኋላም፣ “አንድ ዕውር ሌላውን ዕውር ሊመራው ይችላልን? እንደዚያ ቢያደርግ፣ ሁለቱም ጉድጓድ ውስጥ ይገቡ የለምን?
\v 40 ደቀመዝሙር ከመምህሩ አይበልጥም፤ ነገር ግን አንድ ሰው ፈጽሞ ከተማረ እንደ መምህሩ ይሆናል፡፡
\s5
\v 41 በወንድምህ ዓይን ያለውን ትንሽ ጉድፍ ለምን ትመለከታለህ? ለምንስ በራስህ ዓይን ያለውን ግንድ አትመለከትም? በራስህ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳትመለከት፣
\v 42 ለወንድምህ፣ ‘ወንድሜ ሆይ፣ ዓይንህ ውስጥ ያለውን ጉድፍ ላውጣልህ’ እንዴት ትለዋለህ? አንተ ግብዝ! በመጀመሪያ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ፣ ከዘያም በወንድምህ ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት አጥርተህ ታያለህ፡፡
\s5
\v 43 የተበላሸ ፍሬ የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለምና፣ መልካም ፍሬም የሚያፈራ የተበላሸ ዛፍ የለም፡፡
\v 44 እያንዳንዱ ዛፍ የሚታወቀው በሚያፈራው ፍሬ ነውና፤ ከእሾህ የበለስ ፍሬ አይለቀምም፣ ከቀጋ ቁጥቋጦም የወይን ፍሬ አይቆረጥም፡፡
\s5
\v 45 መልካሙ ሰው በልቡ ካከማቸው መልካም ሀብት መልካም የሆነውን ነገር ያወጣል፤ ክፉም ሰው በልቡ ካከማቸው ክፉ ክምችት ክፉ የሆነውን ያወጣል፡፡ በልቡ ሞልቶ ከተረፈው በአፉ ይናገራልና፡፡
\s5
\v 46 ለምንስ ‘ጌታ ሆይ፣ ጌታ ሆይ’ ትሉኛላችሁ? ለምናገራቸውስ ነገሮች ለምን አትታዘዙም?
\v 47 ወደ እኔ የሚመጣና ለቃሌ የሚታዘዝ ምን እንደሚመስል እነግራችኋለሁ እነግራችኋለሁ፣
\v 48 መሬቱን በጥልቁ ከቆፈረ በኋላ መሠረቱን በዓለት ላይ በማድረግ ቤቱን እንደሚገነባ ሰው ነው፡፡ ጎርፍ በመጣ ጊዜ የውሃው ሙላት ያን ቤት ገፋው፣ ሆኖም በሚገባ ተገንብቶ ነበርና አልነቀነቀውም፡፡
\s5
\v 49 ነገር ግን ቃሌን ሰምቶ የማይታዘዘው ሰው ቤቱን ያለ መሠረት በመሬቱ አፈር ላይ እንደ ሠራው ሰው ነው፤ ጎርፉ በመጣ ጊዜ ቤቱን መታው፣ ወዲያውኑም ፈረሰ፣ ውድም ብሎም ጠፋ፡፡”
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ኢየሱስ ለሕዝቡ የሚናገረውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ፣ ወደ ቅፍርናሆም ገባ።
\s5
\v 2 እጅግ የሚወደውና ሞት አፋፍ ላይ የደረሰ አገልጋይ የነበረው አንድ የመቶ አለቃ ነበረ።
\v 3 ስለ ኢየሱስ በሰማ ጊዜ መጥቶ አገልጋዩን ከመሞት እንዲያድንለት እንዲለምኑት የአይሁድ ሽማግሌዎችን ወደ እርሱ ላካቸው።
\v 4 እነርሱ ወደ ኢየሱስ በቀረቡ ጊዜ፣ "ለእርሱ ይህን ልታደርግለት የተገባ ነው፣
\v 5 ምክንያቱም ሕዝባችንን ይወዳል፣ ምኩራብ የሠራልንም እርሱ ነው" በማለት አጥብቀው ለመኑት።
\s5
\v 6 ስለዚህ ኢየሱስ ዐብሮአቸው መንገዱን ቀጠለ። ነገር ግን ወደ ቤቱ ለመድረስ ጥቂት በቀረው ጊዜ፣ የመቶ አለቃው፣ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት ወዳጆቹን ወደ ኢየሱስ ላካቸው፤ “ጌታ ሆይ፣ አትድከም፣ ምክንያቱም አንተ ወደ ቤቴ ልትገባ የተገባሁ አይደለሁም፤
\v 7 ከዚህ የተነሣ እኔም ራሴ ወደ አንተ ለመምጣት የምገባ አድርጌ እንኳ ራሴን አልቈጥረውም። ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር አገልጋዬ ይፈወሳል፤
\v 8 እኔም ደግሞ ባለ ሥልጣን ነኝና፤ በእኔ ሥር ወታደሮች አሉኝ፤ አንዱን 'ሂድ' ስለው ይሄዳል፤ ሌላውን 'ና' ስለው ይመጣል።
\s5
\v 9 ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ በመቶ አለቃው ተደንቀ፣ ይከተሉት ወደነበሩት ሰዎችም ዞር ብሎ፣ “በእስራኤልም እንኳ እንዲህ ያለ እምነት ያለው ሰው አላገኘሁም” አላቸው።
\v 10 ከዚያም የተላኩት ሰዎች ወደ መቶ አለቃው ቤት ተመልሰው፣ አገልጋዩን ጤናማ ሆኖ አገኙት።
\s5
\v 11 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ኢየሱስ ናይን ወደ ምትባል ከተማ እየተጓዘ ነበር። ከእርሱም ጋር ደቀ መዛሙርቱና ብዙ ሕዝብ ዐብረውት ይሄዱ ነበር።
\v 12 ወደ ከተማይቱም በቀረበ ጊዜ፣ እነሆ፣ ለእናቱ ብቸኛ ልጅ የነበረ ሰው ሞቶ አስከሬኑን ሰዎች ተሸክመው እየሄዱ ነበር። የልጁ እናት መበለት ነበረች፤ በርከት ያሉ ለቀስተኞችም ተከትለዋት ነበር።
\v 13 ጌታም ተመልክቷት እጅግ ዐዘነላትና፣ “አታልቅሺ” አላት።
\v 14 ከዚያም ወደ ቃሬዛው ተጠግቶ ነካው ቃሬዛውን የተሸከሙትም ቆሙ። ኢየሱስ፣ “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ” አለ።
\v 15 ወጣቱም ተነሥቶ መናገር ጀመረ፤ ከዚያም ኢየሱስ ልጁን ለእናትዮዋ ሰጣት።
\s5
\v 16 ከዚያም ሁሉንም ፍርሀት ያዛቸው። “ታላቅ ነቢይ በመካከላችን ተነሥቶአል" "ደግሞ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጎበኝቶአል” በማለት እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
\v 17 ይህ የኢየሱስ ዝና በመላው ይሁዳና በዙሪያው ባለው አገር ሁሉ ተሰማ።
\s5
\v 18 የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አወሩለት።
\v 19 ከዚያም ዮሐንስ፣ “የምትመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ብለው እንዲጠይቁት ከእነርሱ ሁለቱን ወደ ኢየሱስ ላካቸው።
\v 20 ሰዎቹም ወደ ኢየሱስ ቀርበው፣ "'የምትመጣው አንተ ነህን ወይስ ሌ እንጠብቅ?' ብለን እንድንጠይቅህ መጥምቁ ዮሐንስ ልኮናል" አሉ።
\s5
\v 21 በዚያኑ ሰዓት ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን ከተለያየ ደዌና በሽታ ፈወሰ። በአጋንንት የተያዙትን ነጻ አወጣ፣ ዐይነ ስውራንም ማየት እንዲችሉ አደረገ።
\v 22 ኢየሱስ መልእክተኞቹን፣ “ወደ ዮሐንስ ተመልሳችሁ ሂዱና ያያችሁትንና የሰማችሁትን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ ዐይነ ስውራን ያያሉ፣ ሽባዎች ይራመዳሉ፣ ለምጻሞች ይነጻሉ፣ መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፣ ሙታን ይነሣሉ፣ ለድኾችም ወንጌል እየተሰበከ ነው።
\v 23 በማደርጋቸው ነገሮች በእኔ ሳይሰናከል በእምነቱ የሚጸና ሰው የተመሰገነ ነው” አላቸው።
\s5
\v 24 የዮሐንስ መልእክተኞች ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ ስለ ዮሐንስ ለሕዝቡ እንዲህ ይላቸው ጀመር፣ “ምን ልታዩ ወደ በረሐ ወጣችሁ በነፋስ የሚወዛወዘውን ሸንበቆ ለማየት ነውን?
\v 25 ወይስ የወጣችሁት የሚያማምሩ ልብሶች የለበሱትን ለማየት ነውን? እነሆ፣ የሚያማምሩ ልብሶችን ለብሰው በድሎት የሚኖሩ ሰዎች የሚገኙት በአብያተ መንግሥታት ነው።
\v 26 ልታዩ የወጣችሁት ግን ነቢይን ከሆነ፣ እንግዲያውስ ያያችሁት ነቢይን ብቻ ሳይሆን ከነቢያትም የበለጠውን ነው።
\s5
\v 27 ስለ እርሱ፣ ‘እነሆ፣ በፊታችሁ መንገድን የሚጠርግ መልእክተኛዬን እልካለሁ’ ተብሎ ተጽፏል።
\v 28 እላችኋለሁ፣ ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከዮሐንስ የሚበልጥ ማንም የለም፤ ቢሆንም በእግዚአብሔር መንግሥት ከሁሉም የሚያንሰው ይበልጠዋል።
\s5
\v 29 ይህን በሰሙ ጊዜ ቀራጮች እንኳ ሳይቀሩ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔር ጻድቅ እንደ ሆነ ተናገሩ፤ ምክንያቱም እነርሱን ያጠመቃቸው ዮሐንስ ነበር።
\v 30 በዮሐንስ ያልተጠመቁት ፈሪሳውያንና የአይሁድ የሕግ ዐዋቂዎች ግን በራሳቸው ፈቃድ የእግዚአብሔርን ጥበብ ተቃወሙ።
\s5
\v 31 እንግዲያውስ የዚህን ትውልድ ሰዎች ከምን ጋር አመሳስላቸዋለሁ? ምንስ ይመስላሉ?
\v 32 እርስ በርሳቸው በገበያ እየተጠራሩ፥ ‘እንቢልታ ነፋንላችሁ እናንተም አልዘፈናችሁም፣ ሙሾ አወጣንላችሁ እናንተም አላለቀሳችሁም’ እንደሚባባሉ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 33 መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላና ወይን ጠጅ ሳይጠጣ ቢመጣ፣ ‘ጋኔን አለበት’ አላችሁት፣
\v 34 የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ ቢመጣ፦ ‘በላተኛና ጠጪ፣ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ! አላችሁት።
\v 35 ጥበብ ግን በልጆቿ ሁሉ ትክክል እንደ ሆነች ታወቀች።
\s5
\v 36 አንድ ፈሪሳዊም በቤቱ ዐብሮት እንዲመገብ ኢየሱስን ጋበዘው ኢየሱስ ግብዣውን ተቀብሎ ወደ ማዕዱ ቀረበ።
\v 37 እነሆ፣ በዚያ ከተማ በመጥፎ ምግባሯ የታወቀች እንዲት ሴት ኢየሱስ በፈሪሳዊው ቤት ተጋብዞ በማዕድ እንደ ተቀመጠ ተረድታ የአልባስጥሮስ ሽቱ ብልቃጥ ይዛ ወደ ቤቱ ገባችና
\v 38 ከኢየሱስ በስተኋላ ከእግሩ አጠገብ ቆማ ማልቀስ ጀመረች። ከዚያም በእንባዋ እግሩን ማራስና በፀጉሯም ማበስ ቀጠለች፣ እግሩንም ትስመው በሽቱም ትቀባው ነበር።
\s5
\v 39 ኢየሱስን የጋበዘው ፈሪሳዊ ይህንን ባየ ጊዜ፣ "ይህ ሰው በእርግጥ ነቢይ ቢሆን ኖሮ እየነካችው ያለችው ሴት ምን ዓይነት ሴት እንደ ሆነች ባወቀም ነበር" ብሎ በልቡ ዐሰበ።
\v 40 ኢየሱስም መልሶ ፈሪሳዊውን፣ “አንድ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ፈሪሳዊውም፣ “መምህር ሆይ፣ ተናገር” አለው።
\s5
\v 41 ኢየሱስ፣ “ከአንድ አበዳሪ ገንዘብ የተበደሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፣ አንደኛው የአምስት መቶ ዲናር ሌላኛው ደግሞ የሃምሳ ዲናር ዕዳ ነበረባቸው፤
\v 42 የሚከፍሉት ስላልነበራቸው ሁለቱንም ዕዳቸውን ማራቸው። ስለዚህ ዕዳቸው ከተማረላቸው ከእነዚህ ከሁለቱ ማንኛቸው አብዳሪውን የበለጠ የሚወደው ይመስልሃል? አለው።
\v 43 ስምዖንም መልሶ፣ “ብዙ የተተወለቱ ይመስለኛል” አለው። ኢየሱስ፣ “በትክክል መልሰሃል” አለው።
\s5
\v 44 ኢየሱስም ወደ ሴትዮይቱ ዞር ብሎ ስምዖንን እንዲህ አለው፣ “ይህችን ሴት ትመለከታታለህ? እኔ ወደ ቤትህ ገብቼ ለእግሬ ውሃ እንኳን አላቀረብህልኝም፣ እርሷ ግን በእንባዋ እግሬን አራሰች፣ በፀጉሯም አበሰችው፤
\v 45 አንተ አልሳምኸኝም፣ እርሷ ግን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እግሬን ከመሳም አላቋረጠችም።
\s5
\v 46 አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፣ እርሷ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች፣
\v 47 ስለዚህ ለበዛው ኃጢአቷ ብዙ ምሕረትን አግኝታለችና አብዝታ ወዳለች። ጥቂት ኃጢአቱ ይቅር የተባለለት ግን ጥቂት ይወዳል” አለው።
\s5
\v 48 ከዚያም ወደ ሴቱቱ ዞር ብሎ፣ “ኃጢአትሽ ተሰርዮልሻል” አላት።
\v 49 በዚያም ተቀምጠው የነበሩት እርስ በርሳቸው፣ “ኃጢአትን ይቅር የሚል ይህ ማን ነው?” አሉ።
\v 50 ከዚያም ኢየሱስ ሴቲቱን፣ “እምነትሽ አድኖሻል። በስላም ሂጂ” አላት።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ወንጌል እየሰበከና እያወጀ ወደ ልዩ ልዩ ከተሞችና መደሮች መጓዝ ጀመረ። በጒዞውም ወቅት ዐሥራ ሁለቱ፣
\v 2 እንዲሁም ከርኩሳን መናፍስትና ከሕመማቸው የተፈወሱ አንዳንድ ሴቶች ዐብረውት ሄዱ፤ እነርሱም ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት ማርያም፣
\v 3 እንደ የሄሮድስ ቤተ መንግሥት አዛዥ የነበረው የኩዛ ሚስት የነበረችው ዮሐና፣ ሶስና ሌሎችም ብዙ ሴቶች ነበሩ፤ እነዚህ ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን በገንዘባቸው ያገለግሉ ነበር።
\s5
\v 4 ከብዙ የተለያዩ ከተሞች የመጡትን ጨምሮ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ በምሳሌ ተጠቅሞ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፤
\v 5 “አንድ ዘሪ ዘሩን ሊዘራ ወጣ።እንደ ዘራም አንዳንዱ ዘር በመንገድ ዳር ወደቀና ተረገጠ፣ የሰማይ ወፎችም መጥተው በሉት።
\v 6 ሌላው ዘርም በጭንጫ መሬት ላይ ወደቀ፤ በበቀለም ጊዜ እርጥብ አፈር ስላልነበረው ወዲያው ደረቀ።
\s5
\v 7 ሌላውም ዘር በእሾህ መካከል ወደቀ እሾሁም ከዘሩ ጋር ዐብሮት አደገና አነቀው።
\v 8 ከዘሩ አንዳንዱ ግን በመልካም ዐፈር ላይ ወደቀ መቶ እጥፍ ፍሬም አፈራ።" ኢየሱስ ይህንን ከተናገረ በኋላ ጮኽ ብሎ፣ "ጆሮ ያለው ይስማ” አለ።
\s5
\v 9 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ይህ ምሳሌ ምን ማለት እንደ ሆነ ጠየቁት፤
\v 10 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር የማወቅ ዕድል ተሰጥቷችኋል፣ ለተቀሩት ሕዝብ ግን 'እያዩ ስለማያዩ፣ እየሰሙም ስለማያስተውሉ' የሚማሩት በምሳሌ ነው።
\s5
\v 11 ትርጕም እንደዚህ ነው፣ ዘሩ የእግዚአብሔር ቃል ነው።
\v 12 በመንገድ ዳር የወደቁት ሰምተው እንዳይድኑ ዲያብሎስ መጥቶ የሰሙትን ቃል ከልባቸው የሚወሰድባቸው ናቸው።
\v 13 በድንጋይ መካከል የወደቁትም ቃሉን በሰሙ ጊዜ በደስታ የሚቀበሉትና መስማት እንጂ፣ በቃሉ ሥር ስላልሰደዱ ለጊዜው አምነው ፈተና በመጣባቸው ጊዜ፣ እምነታቸውን የሚክዱ ናቸው።
\s5
\v 14 በእሾኽ መካከል የወደቀው ዘር ቃሉን የሰሙ ሰዎች ሲሆኑ፣ በኑሮ ሂደታቸው ወቅት በምድራዊ ሕይወት ዐሳብና በባለጠግነት ምቾት የሚታነቁ በመሆናቸው ፍሬ ወደ ማፍራት የማይመጡ ናቸው።
\v 15 ነገር ግን በመልካሙ ዐፈር ላይ የወደቁት በመልካምና በቅን ልብ ካደመጡ በኋላ ቃሉን አጥብቀው የሚይዙ በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።
\s5
\v 16 እንግዲህ፣ አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ ጎድጓዳ ነገር ውስጥ ወይም ከአልጋ ሥር አያደርገውም። ከዚያ ይልቅ ሁሉም ሰው ብርሃኑን ማየት ይችል ዘንድ ከፍ ባለ ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል።
\v 17 ምክንያቱም የሚታወቅ እንጂ የሚደበቅ፣ ታውቆ ወደ ብርሃን የሚወጣ እንጂ ምሥጢር የሚሆን ነገር የለም።
\v 18 ስለዚህ እንዴት እንደምትሰሙ ተጠንቀቁ፣ ምክንያቱም ላለው ሁሉ የበለጠ ይሰጠዋል፣ ከሌለው ደግሞ እንዳለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።"
\s5
\v 19 ከዚያም የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ ወደ እርሱ መጡ፣ ነገር ግን ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ወደ እርሱ መቅረብ አልቻሉም።
\v 20 ስለሆነም፣ ‘እናትህና ወንድሞችህ ሊያነጋግሩህ ፈልገው እየጠበቁህ ናቸው’ የሚል መልእክት አመጡለት።
\v 21 ነገር ግን ኢየሱስ መልሶ፣ “እናቴና ወንድሞቼ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚያደርጉት ናቸው” አላቸው።
\s5
\v 22 ከዕለታት አንድ ቀን ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ሲሳፈሩ ኢየሱስ፣ "ሐይቁ ማዶ እንሻገር" አላቸው። ከዚያም እነርሱ መቅዘፍ ጀመሩ።
\v 23 ነገር ግን እየቀዘፉ ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደውና በታላቅ ነፋስ የታጀበ ማዕበል በሐይቁ ላይ ስለተነሣ ጀልባቸው ውስጥ ውሃ መግባት ጀመረ'፤ታላቅ አደጋም በፊታቸው ተደቀነ።
\s5
\v 24 ከዚያም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ መጥተው፣ "መምህር ሆይ፣ መምህር ሆይ፣ መሞታችን ነው" በማለት ቀሰቀሱት። እርሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ ነፋሱንና የሚናወጠውን ማዕበል ገሰጸ ጸጥ አደረጋቸው።
\v 25 ከዚያም ኢየሱስ፣ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። ፍርሃት ይዟቸውና በጣም ተደንቀው እርስ በርሳቸው፣ “ነፋሳትንና ባሕርን የሚያዝ እነርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?" ተባባሉ።
\s5
\v 26 ከገሊላ ባሕር በስተ ማዶ በሌላው አንጻር ወደ ነበረው ወደ ጌርጌሴኖን ክልል ደረሱ።
\v 27 ኢየሱስ ከጀልባው ወርዶ ወደ ምድር በተሻገረ ጊዜ፣ አጋንንት የነበሩበት አንድ ሰው አገኘው። ይህ ሰው ለረጅም ጊዜ ልብስ ለብሶ አያውቅም፤ በመቃብር ስፍራ እንጂ፣ በቤትም ውስጥ አልኖረም።
\s5
\v 28 ኢየሱስን ባየው ጊዜ ጮኾ በፊቱ ተደፋ፤ በታላቅም ድምፅ፣ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ! እኔ ከአንተ ምን ጉዳይ አለኝ? እንዳታሠቃየኝ እለምንሃለሁ” አለው።
\v 29 እንደዚህም ያለበት ምክንያት ብዙ ጊዜ ይይዘውና ያሠቃየው የነበረውን ርኩስ መንፈስ ከእርሱ እንዲወጣ ኢየሱስ አዞት ስለነበር ነው። ምንም እንኳ በብረት ሰንሰለት የታሰረና በቁጥጥር ስር እንዲውል የተደረገ ቢሆንም፣ እስራቱን ይበጥስ፣ በአጋንንቱም ግፊት ወደ በረሐ እየሄደ ይንከራተት ነበር።
\s5
\v 30 ከዚያም ጊዜም ኢየሱስ፣ “ስምህ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው፤ እርሱም ብዙ አጋንንት ገብተውበት ነበርና ስሜ፣ "ጭፍራ" ነው ብሎ መለሰ።
\v 31 በውስጡ የነበሩት አጋንንት ወደ ጥልቁ እንዲሄዱ እንዳያዛቸው መለመናቸውን ቀጠሉ።
\s5
\v 32 በዚያም ብዙ ዐሳማዎች በኮረብታው ላይ ለግጦሽ ተሰማርተው ነበር፤ አጋንንቱም ወደ ዐሳማዎቹ ይገቡ ዘንድ እንዲፈቅድላቸው ለመኑት። ኢየሱስ የለመኑትን እንዲያደርጉ ፈቀደላቸው።
\v 33 ስለዚህ አጋንንቱ ከሰውዬው ወጥተው ዐሳማዎቹ ውስጥ ገቡ። ዐሣማዎቹን ከኮረብታው ተጣድፈው ቁልቁል ወረዱ፣ ወደ ሐይቁም ውስጥ ገብተው ሰጠሙ።
\s5
\v 34 ዐሳማዎቹን ሲያሰማሩ የነበሩት ሰዎች ይህን በተመለከቱ ጊዜ ወደ ከተማውና ወደ ገጠሮች ሁሉ ሸሽተው በመሄድ ዜናውን አሠራጩ።
\v 35 ስለዚህ ይህንን የሰሙት ሰዎች የሆነውን ለማየት ወጡ፤ ወደ ኢየሱስም በመጡ ጊዜ አጋንንት የወጡለትን ሰው አገኙት። ሰውዬውም ልብስ ለብሶ ወደ አእምሮውም ተመልሶ በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጦ ሲያዩት፣ ፍርሃት ያዛቸው።
\s5
\v 36 ከዚያም የሆነውን ነገር ያዩ ሰዎች በአጋንንት ቁጥጥር ሥር የነበረው ሰው እንዴት እንደ ዳነ ለሌሎች ተናገሩ።
\v 37 የጌርጌሴኖን ክልልና የዚያ አካባቢ ሰዎች ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ይዟቸው ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ከእነርሱ እንዲሄድ ለመኑት፤ እርሱም ከዚያ ስፍራ ወደ መጣበት ለመመለስ ወደ ጀልባይቱ ገባ።
\s5
\v 38 አጋንንት የወጡለት ሰው ዐብሮት ለመሄድ ኢየሱስን ለመነው።
\v 39 ኢየሱስ ግን፣ “ወደ ቤተ ሰብህ ተመልሰህ እግዚአብሔር ያደረገልህን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ ተርክላቸው” ብሎ አሰናበተው። ሰውየውም ኢየሱስ ያደረገለትን ታላላቅ ነገሮች በከተማው ሁሉ እየመሰከረ ጒዞውን ቀጠለ።
\s5
\v 40 ሁሉም ይጠብቁት ነበርና ኢየሱስ ሲመለስ ሕዝቡ ተቀበሉት።
\v 41 እነሆም ከምኲራብ መሪዎች አንዱ ኢያኢሮስ የተባለ ሰው መጣ፤ እርሱም በኢየሱስ እግር ላይ ወድቆ ወደ ቤቱ ይመጣ ዘንድ ለመነው።
\v 42 ወደ ቤቱ እንዲመጣ የፈለገው ዐሥራ ሁለት ዓመት የሆናት እንድያ ልጁ በሞት አፋፍ ላይ ስለነበርች ነው። ነገር ግን ወደዚያ እየሄደ በነበረበት ጊዜ፣ ብዙ ሕዝብ በመጨናነቅ ይጋፉት ነበር።
\s5
\v 43 በዚያም ለዐሥራ ሁለት ዓመት ደም ሲፈሳት የነበረች፣ ገንዘቧን ሁሉ ለሐኪሞች ብትከፍልም አንዳቸውም ያልፈወሷት አንዲት ሴት ነበረች።
\v 44 እርሷ ከኢየሱስ በስተኋላ መጥታ የልብሱን ጫፍ ነካች፤ የፈሳት የነበረው ደምም ወዲያው ቆመ።
\s5
\v 45 ኢየሱስ፣ “የነካኝ ማን ነው?” አለ። ሁሉም አልነካንህም ብለው በተናገሩ ጊዜ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ሕዝቡ እኮ እየገፋፉህና እያጨናነቁህ ነው” አለው።
\v 46 ኢየሱስ ግን፣ “ከእኔ ኅይል እንደ ወጣ ዐውቄአለሁና አንድ ሰው ነክቶኛል” አለ።
\s5
\v 47 ሴቲቱ ያደረገችውን መደበቅ እንዳልቻለች ባስተዋለች ጊዜ፣ ሴቲቱ እየተንቀጠቀጠች መጣችና በኢየሱስ እግር ሥር ወድቃ በሰዎች ሁሉ ፊት እርሱን ለምን እንደነካችውና እንዴት ወዲያው እንደ ተፈወሰች ተናገረች። ከዚያም ኢየሱስ ሴቲቱን፥
\v 48 “ልጄ ሆይ እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ” አላት።
\s5
\v 49 እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ከምኲራብ አለቃው ቤት አንድ ሰው መጥቶ፣ “ልጅህ ሞታለች። መምህሩን አታድክመው” አለ።
\v 50 ኢየሱስ ግን ይህን በሰማ ጊዜ፣ “እመን ብቻ እንጂ አትፍራ፣ እርሷም ትድናለች” አለው።
\s5
\v 51 ከዚያም እርሱ ወደዚያ ቤት በመጣ ጊዜ፣ ከጴጥሮስ፣ ከዮሐንስ፣ ከያዕቆብ እንዲሁም ከልጅቱ አባትና ከእናትዋ በስተቀር ማንም ዐብሮት እንዲገባ አልፈቀደም።
\v 52 በዚያ ስፍራ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ያለቅሱ ዋይ ዋይም ይሉ ነበር። እርሱ ግን፣ “አታልቅሱ ልጅትዋ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም” አለ።
\v 53 እነርሱ ግን መሞቷን ዐውቀው ስለ ነበር፣ በንቀት ሳቁበት።
\s5
\v 54 እርሱ ግን የልጅቱን እጅ ይዞ፣ “አንቺ ልጅ ተነሽ” አላት።
\v 55 ነፍስዋም ተመለሰች፣ ወዲያውኑም ብድግ አለች። እርሱም የምትበላው እንዲሰጧት አዘዘ።
\v 56 ወላጆቿም ተደነቁ፤ እርሱ ግን ስለሆነው ነገር ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ኢየሱስም ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ጠርቶ በአጋንንት ሁሉ ላይና በሽታዎችን የመፈወስ ሥልጣን ሰጣቸው።
\v 2 የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዲሰብኩና በሽተኞችን እንዲፈውሱ ላካቸው።
\s5
\v 3 እንዲህም አላቸው፤ “ለጒዞአችሁ በትርም ቢሆን፣ የገንዘብም ቦርሳ ቢሆን፣ ስንቅም ቢሆን፣ ገንዘብ ወይም ቅያሬ ልብስ፣ ምንም ነገር አትያዙ።
\v 4 ከዚያ ስፍራ እስከምትወጡ በገባችሁበት ቤት በዚያ ቆዩ።
\s5
\v 5 “የማይቀበሏችሁ ቢኖሩ ከዚያ ከተማ ስትወጡ ምስክር እንዲሆንባቸው ከእግሮቻችሁ ጫማ ላይ አቧራውን አራግፉ።”
\v 6 ከዚያም እነርሱ ከዚያ ተነሥተው የምሥራቹን ወንጌል እየሰበኩ፣ በሄዱባቸውም ስፍራዎች ሁሉ በሽተኞችን እየፈወሱ ያልፉ ነበር።
\s5
\v 7 የአራተኛው ክፍል ገዢ ሄሮድስ እየተደረገ የነበረውን ሁሉ በሰማ ጊዜ፣ በጣም ተሸበረ፣ ምክንያቱም ‘አንዳንዶቹ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቷል፤
\v 8 በሌሎች ዘንድ ደግሞ ኤልያስ ተገልጧል፤ እንደ ገና ሌሎች ከጥንት ነቢያት አንዱ ሕያው ሆኖ ተነሥቷል’ ይሉ ነበር።
\v 9 ሄሮድስም “የዮሐንስን ራስ እኔ አስቈርጬዋለሁ፣ እንዲህ ያለ ነገር የምሰማበት ይህ ማን ነው?” አለ። ሄሮድስም ኢየሱስን ለማየት ጥረት ያደርግ ነበር።
\s5
\v 10 የተላኩት በተመለሱ ጊዜ፣ ያደረጉትን ሁሉ ነገሩት። ኢየሱስ ራሱ ሐዋርያቱን አስከትሎ ቤተ ሳይዳ ወደምትባል ከተማ ሄደ።
\v 11 ነገር ግን፣ ሕዝቡ ስለዚህ ጉዳይ ሰሙና ተከተሉት፣ እርሱም ተቀብሏቸው ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ነገራቸው፣ መፈወሰ የሚያስፈልጋቸውንም ፈወሳቸው።
\s5
\v 12 ቀኑ ወደ መገባደድ ተቃረበ፣ ዐሥራ ሁለቱም ወደ እርሱ መጡና “ያለንበት ቦታ ምንም የሌለበት ምድረ በዳ በመሆኑ ሕዝቡ በአካባቢው ወዳሉት መንደሮችና ገጠሮች ሄደው ማረፊያ ቦታና ምግብ እንዲያገኙ አሰናብታቸው” አሉት።
\v 13 እርሱ ግን፣ “የሚበሉትን እናንተ ስጧቸው” አላቸው። እነርሱም፣ “ወጣ ብለን ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምግብ ካልገዛን በስተቀር አሁን ያለን ከአምስት እንጀራና ከሁለት ዐሣ የበለጠ አይደለም” አሉት።
\v 14 በዚያ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ። እርሱም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ሃምሳ ሃምሳ ሆነው በቡድን እንዲቀመጡ አድርጓቸው” አላቸው።
\s5
\v 15 ስለዚህ እርሱ እንዳላቸው አደረጉ፣ ሕዝቡም ሁሉ ተቀመጡ።
\v 16 እርሱም አምስቱን እንጀራና ሁለቱን ዐሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ ከተመለከተ በኋላ ባርኮ፣ ቈርሶም ለሕዝቡ እንዲያቀርቡላቸው ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው።
\v 17 ሁሉም በልተው ጠገቡ፣ የተራረፈውም የምግብ ፍርፋሪ ተሰበሰበና ዐሥራ ሁለት ቅርጫት ሙሉ ሆነ።
\s5
\v 18 ኢየሱስ ብቻውን ይጸልይ በነበረበት አንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱ ከእርሱ ጋር ነበሩና፣ “ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ነው የሚናገሩት?” ብሎ ጠየቃቸው።
\v 19 እነርሱም፣ “አጥማቂው ዮሐንስ ፣ ሌሎች ደግሞ ኤልያስ፣ እንደ ገና ሌሎች ጥንት ከነበሩት ነቢያት አንዱ ከሙታን ተነሥቶ ነው ይላሉ” አሉት።
\s5
\v 20 “እናንተ ግን እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስ፣ “አንተ ከእግዚአብሔር የመጣህ ክርስቶስ ነህ” ብሎ መለሰ።
\v 21 ነገር ግን ኢየሱስ ይህን ለማንም እንዳይነግሩ በማስጠንቀቅ አዘዛቸው።
\v 22 በተጨማሪም የሰው ልጅ ብዙ መከራ መቀበል እንደሚገባው በሽማግሌዎች፣ በካህናት አለቆችና በሕግ መምሕራን ተቀባይነት እንደማያገኝ፣ እንደሚሞትና በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደሚነሣ በቅድሚያ አስታወቃቸው።
\s5
\v 23 ለሁሉም እንዲህ አላቸው፤ "እኔን መከተል የሚፈልግ ራሱን ይካድ ዕለት ዕለትም መስቀሉን ተሸክሞ ይከተለኝ።
\v 24 ሕይወቱን ሊያድን ጥረት የሚያደርግ ሰው ካለ ያጠፋታል፣ ስለ እኔ ብሎ ሕይወቱን የሚጥል ደግሞ ያድናታል።
\v 25 አንድ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ የራሱን ሕይወት ግን ቢያጣ ምን ይጠቅመዋል?
\s5
\v 26 በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ የሰው ልጅ በራሱ፣ በአባቱ፣ እንዲሁም በቅዱሳን መላእክቱ ክብር በሚመጣበት ጊዜ ያፍርበታል።
\v 27 እኔ ግን በእውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆማችሁት መካከል አንዳንዶቻችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት እስከምታዩ ድረስ ሞትን አትቀምሱም።
\s5
\v 28 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን ገደማ በኋላ ጴጥሮስን፣ ዮሐንስን፣ እንዲሁም ያዕቆብን ይዞ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ።
\v 29 እየጸለየም ሳለ የፊቱ መልክ ተለወጠ ልብሱም በጣም ከመንጣቱ የተነሣ አንፀባረቀ።
\s5
\v 30 እነሆ፣ ሁለት ሰዎች ከእርሱ ጋር ይነጋገሩ ነበር!
\v 31 እነርሱም በክብር የተገለጡት ሙሴና ኤልያስ ነበሩ። በኢየሩሳሌም ሊፈጽም ስላለው ከዚህ ሕይወት ስለ መለየቱ ይነጋገሩ ነበር።
\s5
\v 32 ጴጥሮስና ዐብረውት የነበሩት እንቅልፍ ከብዶባቸው ነበር። ሙሉ በሙሉ በነቁ ጊዜ ግን የኢየሱስን ክብርና ዐብረውት የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች አዩ።
\v 33 እነርሱ ከኢየሱስ ተለይተው ሲሄዱ፣ ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ለእኛ በዚህ መሆን መልካም ነው፣ አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ደግሞ ለኤልያስ ሦስት ዳሶችን ልንሠራ ይገባናል” አለው። ስለ ምን እየተናገረ እንደ ነበረ አላስተዋለም።
\s5
\v 34 ከዚያም እርሱ ይህን እየተናገረ ሳለ ደመና መጥቶ ጋረዳቸው፤ በዙሪያቸው ከነበረው ደመና የተነሣ ፈሩ።
\v 35 ከደመናው ውስጥ፣ “የመረጥሁት ልጄ ይህ ነው፣ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።
\v 36 የድምፁ መሰማት ባበቃ ጊዜ፣ ኢየሱስ ብቻውን ነበረ። እነርሱም ዝም አሉ፤ በነዚያ ቀናት ስላዩአቸው ስለ እነዚያ ነገሮች ምንም ነገር ለማንም አልተናገሩም።
\s5
\v 37 ከተራራው በወረዱ ማግስት ብዙ ሕዝብ ተሰብስበው ወደ እርሱ መጡ።
\v 38 እነሆም፣ ከሕዝቡ መካከል አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፣ ብቸኛ የሆነውን አንድ ልጄን ትመለከትልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ።
\v 39 ክፉ መንፈስ በላዩ ሲመጣበት በድንገት ይጮኻል፣ እየጣለ ያንፈራግጠዋል፤ አረፋም በአፉ ይደፍቃል። በጭንቅ ለቅቆት ይሄዳል፣ በሚሄድበት ጊዜ ክፉኛ ያቈስለዋል።
\v 40 ክፉውን መንፈስ እንዲያወጡለት ደቀ መዛሙርትህን ለመንኋቸው፣ እነርሱ ግን አልቻሉም” በማለት ጮኸ።
\s5
\v 41 ኢየሱስ እንደዚህ በማለት መልስ ሰጠ፣ “ክፉና ጠማማ ትውልድ፣ ከእናንተ ጋር የምኖረውና የምታገሣችሁ እስክ መቼ ነው? ልጅህን ወደዚህ አምጣው።”
\v 42 ልጁ እየመጣ ሳለ ጋኔኑ ጣለው፣ እጅግም አንፈራገጠው። ኢየሱስ ግን ርኩሱን መንፈስ ገሠጸውና ልጁን ፈወሰው፣ ለአባቱም መልሶ ሰጠው።
\s5
\v 43 ሁሉም በእግዚአብሔር ታላቅነት ተደነቁ። ነገር ግን ሁሉም እርሱ ባደረጋቸው ነገሮች ሁሉ እየተደነቁ ሳሉ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣
\v 44 "የነገርኋችሁን እነዚህን ነገሮች በጥልቀት አስተውሉ፤ ምክንያቱም የሰውን ልጅ በሰዎች እጅ አሳልፈው ይሰጡታል" አላቸው።
\v 45 ነገር ግን ተሰውሮባቸው ስለ ነበረ፣ ይህ አባባሉ ምን እንደ ሆነ ስላልተረዱት ሊገባቸው አልቻለም። ስለዚያ አባባል እርሱን መጠየቅ ፈሩ።
\s5
\v 46 ከዚያም ከእነርሱ መካከል ከሁሉም እጅግ ታላቅ የሆነው ማን ነው የሚለውን ጥያቄ በሚመለከት ክርክር ተነሣ።
\v 47 ኢየሱስ ግን በልባቸው ምን እያሰላሰሉ እንደ ነበሩ ባወቀ ጊዜ፣ አንድ ትንሽ ልጅ ይዞ በአጠገቡ አቆመው፣ እንዲህም አላቸው፤
\v 48 "እንደዚህ ያለውን ሕፃን በስሜ የሚቀበል፣ እኔን ይቀበላል። እኔን የሚቀበል ከሆነ ደግሞ የላከኝን ይቀበላል። ስለሆነም፣ በመካከላችሁ ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና።”
\s5
\v 49 ዮሐንስ መልሶ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፣ አንድ ሰው በስምህ አጋንንት ሲያወጣ አየነው፣ ከእኛ ጋር ስላልሆነ ከለከልነው።"
\v 50 ኢየሱስ ግን፣ “አትከልክሉት፣ ምክንያቱም የማይቃወማችሁ ከእናንተ ጋር ነው” አላቸው።
\s5
\v 51 ወደ ሰማይ የሚሄድበት ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ።
\v 52 ከእርሱ ቀደም ብለው እንዲሄዱ መልእክተኞች ላከ፤ እነርሱም ሊያዘጋጁለት ዘንድ ወደ ሳምራውያን መንደር ገቡ።
\v 53 ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ፊቱን አንቅቶ ስለ ነበር፣ በዚያ የነበሩት ሕዝብ አልተቀበሉትም።
\s5
\v 54 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ያዕቆብና ዮሐንስ ይህን ባዩ ጊዜ፣ “ጌታ ሆይ፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንድናዝ ትወዳለህን?” አሉት።
\v 55 እርሱ ግን ዘወር ብሎ ገሰጻቸው።
\v 56 ከዚያም ወደ ሌላ መንደር ሄዱ።
\s5
\v 57 እየሄዱ ሳሉም አንድ ሰው፣ “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው።
\v 58 ኢየሱስ፣ “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፣ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት መጠለያ የለውም” አለው።
\s5
\v 59 ከዚያም ለሌላውን ሰው፣ “ተከተለኝ” አለው። ሰውዬው ግን፣ “ጌታ ሆይ፣ በቅድሚያ እንድሄድና አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው።
\v 60 እርሱ ግን፣ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፣ አንተ ግን በየስፍራው ሁሉ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት አውጅ” አለው።
\s5
\v 61 ሌላ ሰው ደግሞ፣ “ጌታ ሆይ፣ እከተልሃለሁ ነገር ግን በቅድሚያ የቤተ ሰቤን አባላት እንድሰናበት ፍቀድልኝ” አለው።
\v 62 ኢየሱስ ግን፣ “ዕርፍ በእጁ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም” አለው።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ጌታ፣ ሌሎች ሰባ ሰዎችን ሾመ፤ እርሱ ራሱ ሊሄድባቸው ወዳሰባቸው ከተማዎችና ስፍራዎች ሁሉ ቀድመውት እንዲሄዱ ሁለት ሁለት አድርጎ ላካቸው፤
\v 2 እንዲህም አላቸው፣ "መከሩ ብዙ ነው፣ ሠራተኞች ግን ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስለዚህ ወደ መከሩ ሠራተኞችን እንዲክ የመከሩን ጌታ በአስቸኳይ ለምኑት።
\s5
\v 3 እንግዲህ ሂዱ፣ እነሆ፣ በተኲላዎች መካከል እንደ በጎች እልካችኋለሁ፡፡
\v 4 ለመንገዳችሁ ምንም አትያዙ፤ የገንዘብ ቦርሳም ቢሆን የመንገደኛ ሻንጣም ቢሆን፣ ጫማም ቢሆን አትያዙ፣ በመንገድም ላይ ለማንም ሰላምታ አትስጡ፡፡
\s5
\v 5 ወደ ማንኛውም ሰው ቤት ስትገቡ፣ በቅድሚያ 'ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን' በሉ፡፡
\v 6 በዚያ ቤት ያለው ሰው የሰላም ሰው ከሆነ ሰላማችሁ ያርፍበታል፣ የሰላም ሰው ካልሆነ ደግሞ ሰላማችሁ ይመለስላችኋል፡፡
\v 7 ያቀረቡላችሁን እየበላችሁና እየጠጣችሁ በገባችሁበት በዚያው ቤት ቆዩ፣ ምክንያቱም ሠራተኛ ደመወዙን ማግኘት ይገባዋል፡፡ ከቤት ወደ ቤት ግን አትዘዋወሩ፡፡
\s5
\v 8 ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡና እነርሱም ሲቀበሏችሁ፣ ያቀረቡላችሁን ብሉ፡፡
\v 9 በዚያም ያሉትን ሕመምተኞች ፈውሱ፣ 'የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ቀርባለች' ብላችሁም ንገሩአቸው፡፡
\s5
\v 10 ነገር ግን ወደ ማንኛውም ከተማ ስትገቡ እነርሱ ባይቀበሏችሁ፣ ወደ ጐዳናዎቻቸው ውጡና፣
\v 11 'በጫማችን ላይ የተጣበቀውን የከተማችሁን አቧራ እንኳ በእናንተ ላይ ምስክር ይሆንባችሁ ዘንድ እናራግፈዋለን! የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ ቀረበ ግን ይህንን እወቁ' በሏቸው፡፡
\v 12 እላችኋለሁ፣ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ ይቀልላቸዋል፡፡
\s5
\v 13 ወዮልሽ ኮራዚን! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ ዘንድ የተደረጉት ታላላቅ ታምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርገው ቢሆን ኖሮ፣ የሐዘን ልብስ ለብሰውና ራሳቸውን አዋርደው ከረጅም ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር፡፡
\v 14 ነገር ግን በፍርድ ወቅት ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል።
\v 15 አንቺስ ቅፍርናሆም፣ እስከ ሰማይ ከፍ እንዳልሽ ታስቢ ይሆን? እንደዚያ አታስቢ፣ እስከ ሲዖል ድረስ ትወርጃለሽ።
\s5
\v 16 እናንተን የሚሰማችሁ እኔን ይሰማኛል፣ እናንተንም የማይቀበል እኔን አይቀበለኝም፣ እኔን የማይቀበል ደግሞ የላከኝን አይቀበልም፡፡
\s5
\v 17 ሰባዎቹም ደስ እያላቸው ተመለሱና፣ ጌታ ሆይ፣ አጋንንት እንኳ በስምህ ታዘዙልን" አሉት፡፡
\v 18 ኢየሱስ፣ "ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ
\v 19 እነሆ፣ እባቦችንና ጊንጦችን እንድትረግጡ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፣ በምንም ዓይነት መንገድ ምንም አይጐዳችሁም፡፡
\v 20 የሆነ ሆኖ መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ብቻ ደስ አይበላችሁ፤ ነገር ግን ስማችሁ በሰማይ ስለ ተጻፈ የላቀ ደስታ ይሰማችሁ።"
\s5
\v 21 በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እጅግ ሐሤት አደረገና፣ "የሰማይና የምድር ጌታ፣ አባት ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ከጥበበኞችና ከሚያስተወሉ ሰውረህ እንደ ሕፃናት ለሆኑት ላልተማሩት ለእነዚህ ስለ ገለጽህላቸው አመሰግንሃለሁ፡፡ አዎ፣ አባት ሆይ፣ ይህ በፊትህ ዘንድ መልካም ሆኖአልና።
\s5
\v 22 ሁሉም ነገር ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፣ ከአባትም በቀር ልጁ ማን እንደ ሆነ የሚያውቅ የለም፣ አባትም ማን እንደ ሆነ ከልጁ ወይም ልጁ ሊገልጥለት ከፈለገው ሰው በቀር ማንም የሚያውቅ የለም።"
\s5
\v 23 ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መለስ ብሎ፣ ለእነርሱ ብቻ፣ "እናንተ የምታዩትን የሚያዩ የተባረኩ ናቸው፡፡
\v 24 ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ ያያችሁትን ለማየት ፈልገው ሳያዩ፣ እናንተም የሰማችሁትን ሊሰሙ ፈልገው ሳይሰሙ ቀርተዋል" አለ።
\s5
\v 25 እነሆ፣ አንድ የአይሁድ የሕግ መምህር ሊፈትነው ፈልጎ ብድግ አለና፣ "መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት ለመውረስ ምን ማድረግ ይገባኛል?" በማለት ጠየቀው፡፡
\v 26 ኢየሱስ፣ "በሕጉ የተጻፈው ምንድን ነው? የተረዳኸው እንዴት ነው?" አለው።
\v 27 እርሱም፣ "ጌታ አምላክህን በሙሉ ልብህ፣ በሙሉ ነፍስህ፣ በሙሉ ኃይልህ፣ በሙሉ ዐሳብህም ውደድ፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ" ብሎ መለሰ፡፡
\v 28 ኢየሱስም፣ "በትክክል መልሰሃል፡፡ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ" አለው።
\s5
\v 29 መምህሩ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወዶ፣ ኢየሱስን፣ "ባልንጀራዬ ማን ነው?" ብሎ ጠየቀው፡፡
\v 30 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፤ "አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ እየሄደ ሳለ ወንበዴዎች አግኝተውት ንብረቱን ዘረፉት፣ ደበደቡት፣ በሞት አፋፍ ላይ እያለም ጥለውት ሄዱ።
\s5
\v 31 እንደ አጋጣሚ አንድ ካህን በዚያ መንገድ ሲሄድ ሰውዬውን ተመለከተውና በሌላ በኩል አድርጎ አልፎት ሄደ።
\v 32 በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ ሌዋዊም ወደዚያ ስፍራ መጥቶ በሌላ በኩል አድርጎ አልፎ ሄደ።
\s5
\v 33 አንድ ሳምራዊ ግን እየተጓዘ ሳለ ሰውዬው ወደነበረበት መጣ። ባየውም ጊዜ በርኅራኄ ልቡ ተነካ።
\v 34 ወደ እርሱም ጠጋ ብሎ መድኃኒት ካደረገለት በኋላ ቊስሉን በጨርቅ አሰረለት። እርሱ ይጓጓዝበት በነበረበትም አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ አንድ የእንግዶች ማረፊያ አመጣው፣ እንክብካቤም አደረገለት።
\v 35 በማግስቱ ሁለት ዲናር ከኪሱ አውጥቶ ለእንግዳ ማረፊያው ኅላፊ ሰጠውና፣ "ተንከባከበው፣ ከዚህ በላይ ወጪ የሚያስወጣህ ከሆነ በምመለስበት ጊዜ ያወጣኸውን ትርፍ ወጪ እመልስልሃለሁ" አለው።
\s5
\v 36 "ከእነዚህ ከሦስቱ በወንበዴዎች እጅ ለወደቀው ባልንጀራ የሆነለት የትኛው ይመስልሃል?" አለው።
\v 37 መምህሩም፣ "የራራለቱ ነው" አለ። ኢየሱስም፣ "አንተም ሂድና ይህንኑ አድርግ" አለው።
\s5
\v 38 እየተጓዙ ሳሉም ወደ አንድ መንደር ገባ፤ ማርታ የምትባልም አንዲት ሴት በቤትዋ ተቀበለችው"
\v 39 እርሷም ማርያም የተባለች በኢየሱስ እግር ሥር ተቀምጣ ቃሉን የምትሰማ እኅት ነበረቻት"
\s5
\v 40 ማርታ ግን ምግብ ለማዘጋጀት ባደረገችው ጥረት በጣም ውጥረት በዛባት። ወደ ኢየሱስም ዘንድ መጥታ፣ "ጌታ ሆይ፣ እኔ ብቻዬን ሥራ ስሠራ፣ እኅቴ እኔን ሳትረዳኝና ስትተወኝ አንተ ዝም ትላለህን? እንግዲያውስ እንድታግዘኝ ንገራት" አለችው።
\v 41 ጌታ ግን፣ "ማርታ፣ ማርታ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፣
\v 42 የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ነው፡፡ ማርያም በጣም ትክክል የሆነውን ምርጫ መርጣለች፣ ይህም ደግሞ ከእርሷ አይወሰድባትም›› ብሎ መለሰላት፡፡
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 ኢየሱስ በአንድ ስፍራ መጸለዩን በፈጸመ ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እኛን መጸለይ አስተምረን” አለ።
\s5
\v 2 ኢየሱስም፣ “በምትጸልዩበት ጊዜ፣ 'በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ
\s5
\v 3 የዕለት እንጀራችን በየዕለቱ ስጠን።
\v 4 እኛን የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን። ወደ ፈተናም አታግባን በሉ'" አላቸው።
\s5
\v 5 ኢየሱስም፣ “ከእናንተ ወዳጅ ያለው በእኩለ ሌሊት ውድ ወዳጁ ዘንድ በመሄድ
\v 6 ‘አንድ ወዳጄ ከሌላ ስፍራ ወደ እኔ መጥቶ የማስተናግድበት ምንም ስለሌለኝ፣ ሦስት እንጀራ አበድረኝ የማይለው ማነው’?
\v 7 በቤት ውስጥ ያለው ወዳጁ ‘አታስቸግረኝ፤ በሩ ተዘግቶአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ ተኝተዋል። ለመነሣትና ለአንተ እንጀራ ለመስጠት አልችልም’ ይለዋልን?
\v 8 ምንም እንኳን ወዳጁ ስለሆናችሁ ተነሥቶ እንጀራ ባይሰጣችሁም ያለ ዕረፍት ስለነዘነዛችሁት ብቻ ተነስቶ የምትፈልጉትን ያህል እንጀራ ይሰጣችኋል፤
\s5
\v 9 ለምኑ ይሰጣችኋል፣ ፈልጉ ታገኛላችሁ፣ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤
\v 10 የሚለምን ሰው ሁሉ ይቀበላልና የሚፈልግም ሰው ያገኛል፣ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።
\s5
\v 11 አባት ከሆናችሁት ከእናንተ ዓሣ ሲለምነው በዓሣ ፈንታ እባብ ወይም
\v 12 ዕንቁላል ሲለምነው በዕንቁላሉ ፈንታ ጊንጥ የሚሰጠው ማን ነው?
\v 13 ስለዚህ፣ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠትን የምታውቁ ከሆነ፣ በሰማይ የሚኖረው አባታችሁማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸውም?”
\s5
\v 14 በኋላ ኢየሱስ ጋኔን እያወጣ ነበር፤ እርሱም ድዳ ነበር። ጋኔኑም በወጣ ጊዜ ድዳው ሰውዬ ተናገረ፤ ሕዝቡም ተደነቁ።
\v 15 ነገር ግን ከሕዝቡ አንዳንዶቹ፣ “አጋንንትን የሚያወጣው የአጋንንት አለቃ በሆነው በብዔል ዜቡል ነው” አሉ።
\s5
\v 16 ሌሎች ሊፈትኑት ፈልገው ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት።
\v 17 ኢየሱስ ግን ዐሳባቸውን አውቆ፣ “እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ይፈርሳል፤ እርስ በርሱ የሚለያይ ቤተ ሰብም ይወድቃል።
\s5
\v 18 ሰይጣን ራሱን በራሱ የሚቃረን ከሆነ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? እናንተ ግን እኔን አጋንንትን የሚያወጣው በብዔል ዜቡል ነው ትሉኛላችሁ።
\v 19 እኔ በቡዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ የእናንተ ተከታዮች የሚያወጧቸው በማን ነው? ከዚህም የተነሣ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።
\v 20 እኔ ግን በእግዚአብሔር ኃይል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፣ እንግዲያውስ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ መጥቷል።
\s5
\v 21 21 በሚገባ የታጠቀ ብርቱ ሰው ቤቱን በሚጠብቅበት ጊዜ የቤቱ ንብረት ያለ ስጋት ይሆናል፤
\v 22 ከእርሱ የበረታ ሰው ሲያሸንፈው ግን ያ ከእርሱ የበረታው ሰው መሣሪያውን ይቀማዋል፣ የቤቱንም ሀብት ይበዘብዛል።
\v 23 ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፣ ከእኔ ጋርም የማይሰበስብ ይበትናል።
\s5
\v 24 ርኩስ መንፈስ ከሰው በሚወጣበት ጊዜ ውሃ በሌለባቸው ስፍራዎች እየተዘዋወረ ማረፊያ ይፈልጋል። ምንም ማረፊያ ሲያጣ ‘ወደ ወጣሁበት ቤት እመለሳለሁ’ ይላል።
\v 25 በሚመለስበት ጊዜ ያንን ቤት ተጠርጎና ጸድቶ ያገኘዋል።
\v 26 ከዚያም ከእርሱ ይልቅ የከፉ ሰባት ሌሎችን ከእርሱ ጋር ይዞ ይሄድና ሁሉም በዚያ ሰው ውስጥ ገብተው ይኖራሉ። ከዚያም ያ ሰው በመጨረሻ የሚገጥመው ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ይሆናል።
\s5
\v 27 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በሚናገርበት ጊዜ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዲት ሴት ድምጿን ከፍ አድርጋ፣ “አንተን የተሸከመችህ ማኅፀንና የጠባሃቸው ጡቶች የተባረኩ ናቸው” አለችው።
\v 28 እርሱ ግን፣ “የተባረኩትስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው” አለ።
\s5
\v 29 የሕዝቡም ቊጥር እየጨመረ ሲሄድ፣ እንዲህ ማለት ጀመረ፣ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው። ምልክት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከዮናስ ምልክት በቀር ሌላ ምልክት አይሰጠውም።
\v 30 ልክ ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆነላቸው፣ የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናልና።
\s5
\v 31 የደቡብ ንግሥት በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ጋር ትነሣና ትፈርድበታለች፣ ምክንያቱም የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆም ከሰሎሞን የሚበልጥ በዚህ አለ።
\s5
\v 32 32 የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ይነሡና ይፈርዱበታል፣ ምክንያቱም በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋል፤ እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።
\s5
\v 33 አንድ ሰው መብራት ካበራ በኋላ ብርሃኑ በማይታይበት ሰዋራ ስፍራ አያስቀምጠውም ወይም እንቅብ በላዩ ላይ አይደፋበትም። ነገር ግን ወደዚያ ቤት የሚገቡ እንዲታያቸው ከፍ ባለ ስፍራ ላይ ያስቀምጠዋል።
\v 34 ዓይን የሰውነት መብራት ነው። ዓይንህ ጤናማ ከሆነ፣ መላ ሰውነትህ በብርሃን የተሞላ ይሆናል። ዓይንህ ሕመምተኛ ከሆነ ግን መላ ሰውነትህ ጨለማ ይሆናል።
\v 35 ስለዚህ በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ እንዳይሆን ተጠንቀቅ።
\v 36 እንግዲህ መላ ሰውነትህ ምንም ጨለማ የሌለበትና በብርሃን የተሞላ ከሆነ፣ በዚያን ጊዜ በሙሉ ብርሃኑ መብራት በአንተ ላይ እንደሚያበራ ያህል ይሆናል።
\s5
\v 37 ንግግሩንም ሲያበቃ አንድ ፈሪሳዊ በቤቱ ምግብ ይመገብ ዘንድ ጋበዘው፤ ኢየሱስም ከፈሪሳዊው ቤት ሄዶ ለማዕድ ቀረበ።
\v 38 ኢየሱስ ወደ ማዕድ ከመቅረቡ በፊት እጁን ባለመታጠቡ ፈሪሳዊው ተደነቀ።
\s5
\v 39 ጌታ ግን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ፣ እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጸዳላችሁ፣ ውስጣችሁ ግን በስስትና በክፋት የተሞላ ነው።
\v 40 እናንተ ማስተዋል የሌላችሁ ሰዎች፣ ውጪውን የፈጠረ የውስጡንስ አልፈጠረምን?
\v 41 በውስጥ ያለውን ለድኾች ስጡ፣ ከዚያም ሁሉም ነገር ንጹሕ ይሆንላችኋል።
\s5
\v 42 ነገር ግን እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ምክንያቱም ካመረታችሁት አዝሙድና ጤና አዳም ዐሥራት እያወጣችሁ ፍትሕንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ንቃችሁ ትተዋላችሁ። ሌላውን ነገር ማድረግ ሳትተዉ ፍትሕ ማድረግንና የእግዚአብሔርን ፍቅር መጠበቅ ያስፈልጋችኋል።
\s5
\v 43 እናንተ ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! በምኲራቦች የክብር መቀመጫዎችንና በገበያ ስፍራም የከበሬታ ሰላምታን ትወዳላችሁና።
\v 44 ሰዎች የማን እንደሆኑ ሳያውቁ የሚረማመዱባቸው መቃብሮችን ትመስላላችሁና ወዮላችሁ!"
\s5
\v 45 የአይሁድ የሕግ መምህር የነበረ አንድ ሰው፣ “መምህር ሆይ፣ በምትናገረው ነገር እኛንም እየሰደብኸን ነው” ብሎ መለሰለት።
\v 46 ኢየሱስም እንዲህ አለ፣ “እናንተም የሕግ መምህራን፣ ለመሸከም የሚከብድ ሸክም በሰዎች ላይ ትጭናላችሁና፣ እናንተ ግን እነዚያን ሸክሞች በአንድ ጣታችሁ እንኳ አትነኳቸውምና ወዮላችሁ!
\s5
\v 47 የገደሏቸው የእናንተ አባቶች ሆነው ሳለ እናንተ ግን የቀደሙ ነቢያትን መቃብር የምታንጹ ናችሁና ወዮላችሁ!።
\v 48 ከዚህም የተነሣ አባቶቻችሁ በሠሩት ሥራ ምስክሮችና ከእነርሱም ጋር የምትስማሙ ናችሁና፣ ምክንያቱም እናንተ የመታሰቢያ መቃብራቸውን የምታንጹላቸው ነቢያት በእርግጥም በአባቶቻችሁ የተገደሉ ነበር።
\s5
\v 49 በዚህ ምክንያት በእግዚአብሔር ጥበብ እንዲህ ተብሏል፣ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነርሱ እልካለሁ፣ እነርሱም አንዳንዶችን ያሳድዳሉ ይገድሉማል።
\v 50 ስለሆነም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ሁሉ ደም ይህ ትውልድ ተጠያቂ ነው’።
\v 51 ተጠያቂ የሚሆነውም ከአቤል ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ተገደለው እስከ ዘካርያስ ድረስ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ነው። አዎን፣ ይህ ትውልድ ተጠያቂ ነው እላችኋለሁ።
\s5
\v 52 52 እናንተ የአይሁድ የሕግ መምህራንም የዕውቀትን ቊልፍ ጨብጣችሁ ሳላችሁ እናንተ ራሳችሁ የማትገቡ፣ ሊገቡ ያሉትን እንዳይገቡ የምትከለክሉ ናችሁና ወዮላችሁ!
\s5
\v 53 ኢየሱስ ከዚያ ለመሄድ እንደተነሣ፣ የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ተቃወሙት፣ ብዙ ጉዳዮችን አስመልክተው ከእርሱ ጋር ተከራረኩ።
\v 54 ይህንም ያደረጉት ራሱ በተናገረው ቃል ሊያጠምዱት ፈልገው ስለነበረ ነው።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 ይህ እየሆነ ሳለ እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ በብዙ ሺህ የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ባሉበት ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ይላቸው ጀመር። "ግብዝነት ከሆነው የፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ።"
\s5
\v 2 ነገር ግን የሚገለጥ እንጂ ምንም የተሰወረ፣ የሚታወቅ እንጂ ምንም የተደበቀ ነገር የለም፡፡
\v 3 በጨለማ የተናገራችሁት ማንኛውም ነገር በብርሃን የሚሰማ፣ በጓዳ በጆሮ የተናገራችሁትም በከፍተኛ መድረኮች ላይ የሚታወጅ ይሆናል፡፡
\s5
\v 4 ለእናንተ ለወዳጆቼ፣ እንዲህ እላችኋለሁ፤ ሥጋን የሚገድሉትን ከዚያ በኋላ ግን ምንም ማድረግ የማይችሉትን አትፍሩ።
\v 5 ማንን መፍራት እንደሚገባችሁ እኔ እነግራችኋለሁ። ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም እሳት የመጣል ሥልጣን ያለውን እርሱን ፍሩት። አዎን፣ እርሱን ፍሩት ብዬ እላችኋለሁ።
\s5
\v 6 ሁለት ድንቢጦች ዝቅተኛ ዋጋ ባላቸው ሳንቲሞች ይሸጡ የለምን? ሆኖም ከእነርሱ አንዷም እንኳ በእግዚአብሔር ፊት የተዘነጋች አይደለችም።
\v 7 ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ፀጉሮች እንኳ የተቈጠሩ ናቸው። አትፍሩ፣ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።
\s5
\v 8 በሰዎች ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ይመሰክርለታል፤
\v 9 በሰዎች ፊት የሚክደኝ ግን በእግዚአብሔር መላእክት ፊት የሚካድ ይሆናል ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡
\v 10 በሰው ልጅ ላይ የተቃውሞ ንግግር የተናገረ ማንኛውም ሰው ይቅርታ ያገኛል፣ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የስድብ ቃል የሚናገር ግን ይቅርታ አያገኝም፡፡
\s5
\v 11 በምኲራቦች፣ በገዢዎችና በባለ ሥልጣኖች ፊት በሚያቀርቧችሁ ጊዜ ለቀረበባችሁ ክስ እንዴት መልስ መስጠት እንደሚገባችሁ ወይም ምን ማለት እንዳለባችሁ አትጨነቁ፤
\v 12 መንፈስ ቅዱስ በዚያ ወቅት ምን መናገር እንደሚገባችሁ ይነግራችኋልና"
\s5
\v 13 ከሕዝቡም መካከል አንድ ሰው፣ "መምህር ሆይ፣ ወንድሜ ርስት እንዲያካፍለኝ ንገረው" አለ።
\v 14 ኢየሱስም፣ "አንተ ሰው፣ በእናንተ ላይ ዳኛ ወይም አደራዳሪ አድርጎ የሾመኝ ማን ነው?" አለው።
\v 15 ለእነርሱም እንዲህ አላቸው፣ "ስግብግብነት ከሞላባቸው ምኞቶች ራሳችሁን ጠብቁ፣ ምክንያቱም የአንድ ሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት ላይ የተመሠረተ አይደለም"
\s5
\v 16 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ በማለት ምሳሌ ነገራቸው፤ "የአንድ ሰው ዕርሻ ከፍተኛ ምርት አስገኘለት፤
\v 17 እርሱም፣ 'የተመረተውን እህል የማከማችበት የለኝምና ምን ማድረግ ይገባኛል?' ብሎ በልቡ ዐሰበ።
\v 18 እንዲህም አለ፤ 'እንግዲያውስ እንደዚህ አደርጋለሁ፣ ጐተራዎቼን አፍርሼ በምትኩ ትልልቅ ጐተራዎችን እሠራለሁ፣ የተመረተውን እህልና ሌሎች ንብረቶቼንም ሁሉ አከማችባቸዋለሁ።
\v 19 ነፍሴንም፣ "ነፍሴ ሆይ፣ ለብዙ ዘመን የሚበቃ ብዙ ሀብት ተከማችቶልሻልና አትጨነቂ ብዪ፣ ጠጪ ደስም ይበልሽ እላታለሁ'" አለ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለው፤ "አንተ ሞኝ ሰው፣ ዛሬ ማታ ከአንተ ልትወሰድ ነፍስህ ትፈለጋለች፣ ያዘጋጀሃቸው ነገሮች ታዲያ ለማን ይሆናሉ?"
\v 21 በእግዚአብሔር ፊት ባለ ጠጋ ያልሆነ ለራሱ ግን ሀብትን የሚያከማች ሰው ይህን ይመስላል።
\s5
\v 22 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ምን እንበላለን ብላችሁ ስለ ሕይወታችሁ ወይም ምን እንለብሳለን ብላችሁ ስለ ሰውነታችሁ አትጨነቁ፡፡
\v 23 ምክንያቱም ሕይወት ከምግብ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና፡፡
\s5
\v 24 የማይዘሩትን ወይም የማያጭዱትን ቁራዎችን ተመልከቱ። መጋዘን ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። ከወፎች ይልቅ እናንተ ምን ያህል የላቀ ግምት ያላችሁ ናችሁ?
\v 25 ከእናንተስ ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንዲት ቀን መጨመር የሚችል ማን ነው?
\v 26 ታዲያ፣ ታናሽ የሆነውን ነገር እንኳ ማድረግ የማትችሉ ከሆነ ስለ ሌላው ጉዳይ ለምን ትጨነቃላችሁ?
\s5
\v 27 እንዴት እንደሚያድጉ አበቦችን ተመልከቱ፡፡ አይሠሩም ወይም አይፈትሉም። ሆኖም፣ ሰሎሞን እንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ ከእነዚህ እንደ አንዱ እንዳልለበሰ እኔ እነግራችኋለሁ።
\v 28 ዛሬ ታይቶ ነገ ወደ ቆሻሻ ማከማቻ እንደሚጣለው ሣር በሜዳ ላይ ያለውን እግዚአብሔር እንደዚህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እምነታችሁ ትንሽ የሆነውን እናንተንማ ምን ያህል የበለጠ አያለብሳችሁም?
\s5
\v 29 የምትበሉትንና የምትጠጡትን በመፈለግ አትጨነቁ።
\v 30 በዓለም ውስጥ ባሉት አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ እነዚህን ይፈልጋሉና፣ እናንተም እነዚህን እንደምትፈልጉ አባታችሁ ያውቃል።
\s5
\v 31 ነገር ግን የእርሱን መንግሥት ፈልጉ፣ እነዚህም ነገሮች ይጨመሩላችኋል።
\v 32 አንተ ታናሽ መንጋ፣ መንግሥትን ሊሰጥህ አባትህ እጅግ ደስ ይለዋልና አትፍራ።
\s5
\v 33 ንብረቶቻችሁን ሽጡና ለድኾች ስጡ። በማያረጅ ከረጢት ሌቦች ሊቀርቡትና ብል ሊያጠፋው የማይቻለውን የማያልቀውን ሀብት በሰማይ አከማቹ።
\v 34 ንብረታችሁ ባለበት ልባችሁም በዚያ ይሆናልና።
\s5
\v 35 የሥራ ልብሳችሁን በአጭር ታጥቃችሁ በተጠንቀቅ ቁሙ፣ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
\v 36 በሚመጣበትና በሩን በሚያንኳኳበት ጊዜ ፈጥነው በሩን እንደሚከፍቱለት ጌታቸው ከሠርግ ሲመለስ እንደሚጠባበቁ ሰዎች ሁኑ።
\s5
\v 37 በሚመጣበት ጊዜ ነቅተው ሲጠብቁ ጌታቸው የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች የተመሰገኑ ናቸው። በእርግጥ እላችኋለሁ፣ እርሱም የሥራ ልብሱን ለብሶ ምግብ ለመመገብ እንዲቀመጡ ያደርጋቸውና ወደ እነርሱ መጥቶ ያገለግላቸዋል።
\v 38 ከሌሊቱ በስድስት ሰዓት ወይም በዘጠኝ ሰዓትም እንኳ ቢሆን ሲመጣ ተዘጋጅተው የሚያገኛቸው እነዚያ አገልጋዮች የተመሰገኑ ናቸው።
\s5
\v 39 በተጨማሪ ይህን እወቁ፤ የአንድ ቤት ጌታ ሌባ የሚመጣበትን ሰዓት የሚያውቅ ቢሆን ኖሮ የቤቱ በር እንዲሰበር ባልፈቀደም ነበር፡፡
\v 40 እናንተም እንደዚሁ ዝግጁ ሁኑ፣ ምክንያቱም የሰው ልጅ የሚመጣበትን ሰዓት አታውቁም።"
\s5
\v 41 ጴጥሮስ፣ "ጌታ ሆይ፣ ይህንን ምሳሌ የተናገርኸው ለእኛ ብቻ ነው ወይስ ለሌሎችም ሰዎች ሁሉ ነው?" አለ።
\v 42 ጌታም እንዲህ አለ፣ "ታዲያ ለሌሎቹ አገልጋዮቹ የተመደበላቸውን ምግብ በትክክለኛው ጊዜ ይሰጣቸው ዘንድ ጌታው የሾመው ታማኝና ብልህ አስተዳዳሪ ማን ነው?
\v 43 ጌታው በሚመጣበት ጊዜ ይህን ሲያደርግ የሚያገኘው ያ አገልጋይ የተመሰገነ ነው"
\v 44 እውነት እላችኋለሁ፣ ባለው ንብረት ሁሉ ላይ ይሾመዋል።
\s5
\v 45 ያ አገልጋይ ግን በልቡ፣ 'የጌታዬ የመመለሻ ወቅት ይዘገያል' ቢልና ወንድና ሴት አገልጋዮችን መደብደብ፣ መብላትና መጠጣት እንዲሁም መስከር ቢጀምር፣
\v 46 የዚያ አገልጋይ ጌታ ባልጠበቀው ቀንና ባላወቀው ሰዓት ይመጣል፣ ይቆራርጠዋል፣ ካልታመኑት ጋርም ይደባልቀዋል።
\s5
\v 47 የጌታውን ፈቃድ ያወቀውና እንደ ፈቃዱ ሆኖ ለመገኘት ያልተዘጋጀውና ፈቃዱን ያልፈጸመው ያ አገልጋይ ከፍተኛ ቅጣት ይቀጣል።
\v 48 ነገር ግን ያላወቀና ቅጣት የሚያስከትልበትን ተግባር የፈጸመ ጥቂት ይቀጣል። ብዙ ከተሰጠው ከማንኛውም ሰው ብዙ ይጠበቅበታል፣ ከፍ ያለ አደራ ከተሰጠውም፣ ከእርሱ ብዙ ይፈለግበታል።
\s5
\v 49 የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ለመለኰስ ነው፣ ሆኖም አሁኑኑ ተቀጣጥሎ ባገኘው ደስ ባለኝ ነበር።
\v 50 ነገር ግን የምጠመቀው ጥምቀት አለኝ፣ ያንንም ጥምቀት እስከምፈጽመው ምን ያህል በጭንቀት እጠባበቀዋለሁ!
\s5
\v 51 በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት እንደ መጣሁ ታስባላችሁን? እንደዚያ አታስቡ፣ እነግራችኋለሁ፣ የመጣሁት ይልቁኑ መለያየትን ላመጣ ነው፡፡
\v 52 ከእንግዲህ ወዲህ በአንድ ቤት ውስጥ አምስት ሰዎች ቢኖሩ ሦስቱ በሁለቱ ላይ፣ ሁለቱም በሦስቱ ላይ የሚነሡና የሚለያዩ ይሆናሉ፡፡
\v 53 አባት በልጅ ላይ ልጅም በአባት ላይ፤ አማት በምራት ላይ፣ ምራትም በአማት ላይ ይነሡና ይለያያሉ፡፡
\s5
\v 54 ደግሞም ኢየሱስ ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፤ "በምዕራብ በኩል ደመና ሲያንጃብብ በምትመለከቱበት ጊዜ ወዲያውኑ፣ 'ሊያካፋ ነው' ትላላችሁ፣ እንዳላችሁትም ይሆናል።
\v 55 የደቡብ ነፋስም ሲነፍስ፣ 'የሚያቃጥል ሙቀት ሊመጣ ነው' ትላላችሁ፣ እንዳላችሁትም ይሆናል።
\v 56 እናንተ ግብዞች፣ የምድርንና የሰማይን መልክ እንዴት እንደምትተረጒሙ ታውቃላችሁ፣ ታዲያ የአሁኑን ወቅት እንዴት እንደምትተረጒሙ እንዴት አታውቁም?
\s5
\v 57 እናንተ ራሳችሁ ትክክል የሆነውን ለምን አትፈርዱም?
\v 58 ከባላጋራህ ጋር ወደ ከተማው አስተዳዳሪ በምትሄድበት ጊዜ፣ በመንገድ ላይ ቅራኔህን ለመፍታት ጥረት ማድረግ አለብህና፣ ይህን ባታደርግ ዳኛው ለዕለቱ ተረኛ መኰንን አሳልፎ ይሰጥሃል፣ ተረኛው መኰንንም ወደ ወንጀለኛ ማረፊያ ክፍል ያስገባሃል።
\v 59 ዕዳህን ሙሉ በሙሉ እስካልከፈልህ ድረስ ከዚያ በፍጹም እንደማትወጣ እኔ እነግርሃለሁ።"
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጥተው፣ የገሊላ ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ጲላጦስ ስለ ገደላቸውና ደማቸውንም ከመሥዋዕታቸው ጋር ስላደባለቀባቸው ሰዎች ነገሩት፡፡
\v 2 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "እነዚያ የገሊላ ሰዎች ይህ ሁሉ የደረሰባቸው በዙሪያቸው ካሉት ከሌሎች የገሊላ ሰዎች ይልቅ ኅጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን?
\v 3 አይደለም፤ እናንተም ንስሓ ካልገባችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ ።
\s5
\v 4 ወይም በሰሊሆም ግንብ ተደርምሶባቸው የሞቱ ዐሥራ ስምንት ሰዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉ ሰዎች ይልቅ ኃጢአተኞች ስለ ነበሩ ነውን?
\v 5 አይደለም፤ ሁላችሁም ንስሓ ባትገቡ ትጠፋላችሁ።"
\s5
\v 6 ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ተናገረ፤ "አንድ ሰው በወይን አትክልት ቦታው የበለስ ዛፍ ተከለ፤ ፍሬዋንም ፈልጎ ወደ በለሲቱ መጣ፤ ነገር ግን ምንም ፍሬ አላገኘባትም።
\v 7 እርሱም ለአትክልተኛው እንዲህ አለው፤ "ተመልከት! ሦስት ዓመት ሙሉ ፍሬ ፈልጌ ወደ በለሲቱ መጣሁ፤ ግን ምንም ፍሬ አላገኘሁባትም፡፡ ቊረጣት ስለምን መሬትን ታበላሻለች።"
\s5
\v 8 አትክልተኛውም መልሰና እንዲህ አለ፣ "ለዚህ ዓመት ተዋት ዙሪያዋን ኮትኩቼ ማዳበሪያ አደርግላትና
\v 9 በሚቀጥለው ዓመት ታፈራ ይሆናል፤ ባታፈራ ግን ቊረጣት።"
\s5
\v 10 ኢየሱስም በሰንበት ቀን በአንዱ ምኲራብ እያስተማረ ነበር።
\v 11 ለዐሥራ ስምንት ዓመት ርኩስ መንፈስ ያጐበጣት አንዲት ሴት በዚያ ነበረች፡፡ እርስዋም ከመጒበጧ የተነሣ ቀና ብላ መቆም አትችልም ነበር፡፡
\s5
\v 12 ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና፣ "ተነሺና ከበሽታሽ ተፈወሺ" አላት።
\v 13 በእጁ ዳሰሳት፣ ወዲያውኑም ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም
\v 14 አመሰገነች፡፡ የምኲራቡ አለቃ ግን በሰንበት በመፈወሷ ተቈጣና ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ "ከሳምንቱ ቀኖች ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ ሄዳችሁ በእነዚያ ቀኖች ተፈወሱ እንጂ በሰንበት ቀን አይሆንም አላቸው።"
\s5
\v 15 ጌታ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ "እናንት ግብዞች! በሰንበት ቀን ከእናንተ መካከል በሬውን ወይም አህያውን ከታሰረበት በረት አወጥቶ ውኅ የማያጠጣው ማን ነው?
\v 16 ይህች የአብርሃም ዘር የሆነች ለዐሥራ ስምንት ዓመት በሰይጣን ታስራ የኖረች ሴት በሰንበት ቀን ከበሽታዋ መፈታት አይገባትምን?"
\s5
\v 17 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገረ ጊዜ፣ ይቃወሙት የነበሩ ሁሉ አፈሩ፣ ሕዝቡ ግን በተደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላቸው።
\s5
\v 18 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ "የእግዚአብሔር መንግሥት በምን ትመሰላለች? ከምንስ ጋር አነጸጽራታለሁ?
\v 19 አንድ ሰው የሰናፍጭ ዘር በአትክልት ቦታው እንደተከላት ዛፍዋም አድጋ፣ ወፎች በቅርንጫፎችዋ ላይ ጎጆአቸውን ሠርተው ማረፊያ ያደረጉባት ዛፍ ትመሰላለች።"
\s5
\v 20 እንደ ገናም እንዲህ አለ፤ "የእግዚአብሔርን መንግሥት በምን ላነጻጽራት እችላለሁ?
\v 21 የእግዚአብሔር መንግሥት አንዲት ሴት ሊጡን ሁሉ እስኪያቦካ ድረስ በሶሦስት መስፈሪያ ዱቄት ውስጥ የሰወረችውን እርሾ ትመስላለች።"
\s5
\v 22 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄድ ሳለ በየከተማውና በየገጠሩ እያስተማረ ያልፍ ነበር፡፡
\v 23 አንድ ሰው፣ "ጌታ ሆይ፤ የሚድኑት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸውን?" ብሎ ጠየቀው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤
\v 24 "በጠባብዋ በር ለመግባት ታገሉ፣ ብዙዎች በዚህች በር ሊገቡ ይሞክራሉ ነገር ግን ሊገቡባት አይችሉም።
\s5
\v 25 የቤቱ ጌታ በሩን ይዘጋል፤ እናንተም በደጅ ቆማችሁ፤ አንኳኩታችሁ፣ 'ጌታ ሆይ፤ ጌታ ሆይ፤ እንድንገባ ክፈትልን' ትላላችሁ፡፡ እርሱ መልሶ 'ከየት ነው የመጣችሁት? እኔ አላውቃችሁም' ይላችኋል፡፡
\v 26 ከዚያም እናንተ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ከአንተ ጋር አብረን በልተናል፤ አብረንም ጠጥተናል፤ በአደባባዮቻችንም አስተምረሃል' ትላላችሁ፡፡
\v 27 እርሱ ግን እንዲህ ይመልሳል፤ 'ከየት እንደ መጣችሁ አላውቅም ፤ እናንተ ዐመፀኞች ከእኔ ራቁ እላችኋለሁ፡፡'
\s5
\v 28 በእግዚአብሔር መንግሥት አብርሃምን፤ይስሐቅን፤ ያዕቆብን፤ ነቢያትንም በምታዩበት ጊዜ፤ እናንተ ግን በውጪ ትጣላላችሁ ከዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል፡፡
\v 29 ብዙ ሰዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ፤ ከሰሜንና ከደቡብ መጥተው በእግዚአብሔር መንግሥት በማዕድ ተቀምጠው ይደሰታሉ፡፡
\v 30 ይህንም እወቁ ኋለኞች ፊተኞች፤ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፡፡"
\s5
\v 31 ከዚያ በኋላ፣ አንዳንድ ፈሪሳውያን ወደ እርሱ ቀርበው፣ "ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ወጥተህ ወደ ሌላ ስፍራ ሂድ" አሉት፡፡
\v 32 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "ሂዱና ለዚያ ቀበሮ፣ 'ዛሬና ነገ አጋንንትን አወጣለሁ፤ በሽታኞችን እፈውሳለሁ፤ በሦስተኛም ቀን ሥራዬን እፈጽማለሁ' ይላል በሉት"
\v 33 ይሁን እንጂ ዛሬና ነገ ከዚያም በኋላ ነቢይ ከኢየሩሳሌም በቀር በሌላ ስፍራ መሞት ስለሌበት ወደ ኢየሩሳሌም መንገዴን መቀጠል አለብኝ" አለ።
\s5
\v 34 አንቺ ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድዪ፤ መልእክተኞችሽንም የምትወግሪ ነሽ፡፡ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፡፡ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም፡፡
\v 35 እነሆ፣ ቤታችሁ ባዶ ሆኖ ቀርቶአል፡፡ እላችኋለሁ፣ እናንተ 'በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ ነው' እስከምትሉ ድረስ አታዩኝም፡፡"
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 በሰንበት ቀን ኢየሱስ ከፈሪሳዊያን አለቆች ወደ እንዱ ቤት እንጀራ ሊበላ በገባ ጊዜ፣ የሚያደርገውን ለማየት በቅርበት ይጠባበቁት ነበር፡፡
\v 2 በዚያም በእጅና በእግር ዕብጠት የሚሠቃይ አንድ ሰው በኢየሱስ ፊት ነበር።
\v 3 ኢየሱስ የአይሁድ ሕግ ዐዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን፣ "በሰንበት ቀን መፈወስ በሕግ ይፈቀዳል ወይስ አይፈቀድም? "ብሎ ጠየቃቸው፡፡
\s5
\v 4 እነርሱ ግን ዝም አሉ፡፡ ኢየሱስ የታመመውን ሰው ይዞ ፈወሰውና አሰናበተው፡፡
\v 5 ቀጥሎም ኢየሱስ፣ "ከእናንተ ልጅ ወይም በሬ በሰንበት ቀን በጒድጓድ ውስጥ ቢወድቁ ወዲያውኑ የማያወጣቸው ማን ነው?" አላቸው።
\v 6 እነርሱ ለእነዚህ ነገሮች መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡
\s5
\v 7 ኢየሱስ በግብዣ ቦታ የከበሬታ ወንበር ለመያዝ ሲሽቀዳደሙ በተመለከት ጊዜ እንዲህ በማለት አንድ ምሳሌ
\v 8 ነገራቸው፤ "አንድ ሰው ወደ ሰርግ ግብዣ ቢጠራህ በመጀመሪያ በከበሬታ ቦታ አትቀመጥ፣ ምናልባት በዚያ ቦታ የሚቀመጥ ከአንተ ይልቅ ክብር የሚሰጠው ሰው ተጋብዞ ይሆናል፡፡
\v 9 ሁለታችሁንም የጋበዛችሁ ሰው መጥቶ፣ 'ይህን ቦታ ለሌላ ሰው ልቀቅለት' ይልሃል፣ ከዚያም አንተ በሃፍረት ወደ ዝቅተኛ ቦታ ትሄዳለህ፡፡
\s5
\v 10 ነገር ግን ወደ ግብዣ ስትጠራ በዝቅተኛ ቦታ ተቀመጥ፤ አንተን የጋበዘህ ሰው መጥቶ፤ ወዳጄ ሆይ፣ 'ወደ ከፍተኛ ስፍራ መጥተህ ተቀመጥ' ይልሃል፡፡ ከዚያም በተጋባዦቹ ፊት ሁሉ የተከበርህ ትሆናለህ፡፡
\v 11 ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ዝቅ ዝቅ ይላል፡፡ ራሱንም ዝቅ ዝቅ የሚያደርግ ደግሞ ከፍ ከፍ ይላል፡፡
\s5
\v 12 ኢየሱስ ደግሞ ጋባዡን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፤ "የምሳ ወይም የራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ መልሰው ይጋብዙኛል በማለት ብድራትን በመፈለግ ወዳጆችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ሀብታም ጎረቤቶችህን አትጋብዝ፡፡
\s5
\v 13 ነገር ግን ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ድሆችን፣ የአካል ጒዳተኞችን፣ ሽባዎችንና ዐይነ ስውራንን ጥራ፡፡
\v 14 ይህን በማድረግህ እነርሱ መልሰው ሊከፍሉህ ስለማይችሉ፣ የተባረክህ ትሆናለህ፡፡ በጻድቃን ትንሣኤ ቀንም እግዚአብሔር ብድራትህን ይከፍልሃል፡፡
\s5
\v 15 በማዕድ ተቀምጠው ከነበሩት አንዱ ኢየሱስ የተናገራውን ሰምቶ፣ "በእግዚአብሔር መንግሥት ማዕድ ተቀምጦ እንጀራ የሚበላ ሰው የተባረከ ነው" አለው፡፡
\v 16 ኢየሱስ ግን እንዲህ አለው፤ "አንድ ሰው ትልቅ የእራት ግብዣ አዘጋጅቶ ብዙ ሰዎችን ጋበዘ፡፡
\v 17 የግበዣውም ዝግጅት በተጠናቀቀ ጊዜ ወደ እራት ግብዣው ወደ ተጋበዙት ሰዎች፣ 'ሁሉ ተዘጋጅቶአልና ወደ ግብዣው ኑ' ብሎ መልእክተኞችን ላከ፡፡
\s5
\v 18 ነገር ግን እያንዳንዱ ተጋባዥ ከግብዣው ለመቅረት ምክንያት መደርደር ጀመረ፡፡ የመጀመሪያው፤ "መሬት ስለ ገዛሁ ሄጄ ማየት አለብኝባ ይቅርታ አድርግልኝ አለው፡፡
\v 19 ሌላው፣ 'አምስት ጥማድ በሬዎችን ገዝቻለሁ፣ እነርሱን ልፈትናቸው ስለምሄድ፤ ይቅርታ አድርግልኝ' አለው፡፡
\v 20 ሌላኛውም ሰው፣ 'ሚስት አግብቼ ሙሽራ ስልሆንሁ፣ ልመጣ አልችልም' አለ፡፡"
\s5
\v 21 አገልጋዩ ለጌታው እነዚህን ነገሮች ነገረው። ከዚያም የቤቱ ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን 'ቶሎ ሄደህ በከተማው አውራ ጐዳናዎች ስላች መንገዶች ሁሉ ያሉ ድኾችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ዐይነ ስውራንን፣ ሽባዎችን ሁሉ ወደዚህ እንዲገቡ ጥራቸው' አለው።
\v 22 አገልጋዩም አለው፤ 'ጌታ ሆይ፤ ያዘዝኸኝን ሁሉ አድርጌአለሁ፤ አሁንም ትርፍ ቦታ አለ።'
\s5
\v 23 ጌታውም አገልጋዩን፣ 'ወደ ጎዳናዎችና ወደ ገጠር መንገዶች ውጣ፤ ቤቴም እንዲሞላ ያገኘሃቸውን ሁሉ እንዲገቡ ግድ በላቸው።
\v 24 "እላችኋለሁ፣ በመጀመሪያ ከተጋበዙት ከእነዚያ ሰዎች መካከል አንድ ሰው እንኳ ከእራቴ አይቀምስም' አለው።
\s5
\v 25 ሕዝብም ከኢየሱስ ጋር አብረው እየሄዱ ሳለ፣ እርሱ ዞር ብሎ እንዲህ አላቸው፤
\v 26 "ማንም ወደ እኔ ሊመጣ የሚወድ አባቱንና እናቱን፣ ሚስቱንና ልጆቹን፣ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፣ እንዲያውም የራሱንም ሕይወት ስንኳ ስለ እኔ ብሎ ካልተወ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡
\v 27 የራሱንም መስቀል ተሸክሞ የማይከተለኝ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡"
\s5
\v 28 ከእናንተ አንድ ሰው ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በመጀመሪያ ተቀምጦ የማይተምን ማን ነው?
\v 29 መሠረቱን ሠርቶ መደመደም ቢያቅተው በዚያ የሚያልፉት ሁሉ ፣
\v 30 'ይህ ሰው መገንባት ጀምሮ መደምደም አቃተው እያሉ ይዘብቱበታል' ፡፡
\s5
\v 31 ወይም አንድ ንጉሥ ከሌላ ንጉሥ ጋር ሊዋጋ በሚነሣበት ጊዜ ሃያ ሺህ ሰራዊት አስከትቶ የሚመጣበትን በአሥር ሺህ ሰራዊት ለመመከት ተቀምጦ የማይመክር ማን አለ?
\v 32 መመከት የማይችል ከሆነ የሌላው ሰራዊት ገና ከሩቅ ሳለ መልእክተኛ ልኮ ዕርቅ ይጠይቃል፡፡
\v 33 እንዲሁም ከእናንተ ማንም ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም፡፡
\s5
\v 34 ጨው መልካም ነው፤ ነገር ግን ጨው ጣዕም ካጣ እንዴት ተመልሶ እንደ ገና የጨውነት ጣዕም ሊኖረው ይችላል?
\v 35 ለመሬትም ሆነ ለማዳበሪያነት የማይጠቅም በመሆኑ ወደ ውጪ ይጣላል፡፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!"
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 አንድ ቀንም ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ኅጢአተኞች ሁሉ ኢየሱስን ለመስማት መጡ።
\v 2 ፈሪሳውያንና የሕግ መምህራን፣ "ይህ ሰው ኅጢአተኞችን ይቀበላል፤ ከእነርሱም ጋር ይበላል" በማለት እርስ በርሳቸው አጒረመረሙ።
\s5
\v 3 ኢየሱስ እንዲህ በማለት ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤
\v 4 "ከእናንተ መካከል መቶ በጎች ያሉት ከዚያም ከእነርሱ አንዱ ቢጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን በዱር ትቶ የጠፋበትን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልግ የማይሄድ ማንነው?
\v 5 ባገኘውም ጊዜ ከመደሰቱ የተነሣ በጫንቃው ይሸከመዋል።
\s5
\v 6 ወደ ቤቱም ሲመለስ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ፣ 'የጠፋብኝን በጌን አግኝቻለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል።
\v 7 እንዲሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኅጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።
\s5
\v 8 ወይስ ዐሥር የብር ሳንቲሞች ያላት ሴት ከዐሥሩ አንዱ ቢጠፋበት፣ እስከምታገኛው ድረስ መብራት አብርታ፣ ቤቷንም ሁሉ ጠርጋ በትጋት የማትፈልግ ሴት ማን ናት?
\v 9 ባገኘችም ጊዜ ወዳጆቿንና ጎረቤቶቿን ሁሉ በአንድነት ጠርታ፣ 'የጠፋብኝን የብር ሳንቲሜን አግኝቻለሁና ኑ ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ትላቸዋለች።
\v 10 "እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኅጢአተኛ በእግዚአብሔር መላአክት ፊት ታላቅ ደስታ እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።"
\s5
\v 11 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ "አንድ ሰው ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤
\v 12 ታናሹ ልጅም አባቱን፣ 'አባቴ ሆይ፣ በኋላ ከሀብትህ ከሚደርሰኝ ድርሻዬን ስጠኝ' አለው። አባቱም ሀብቱን ለሁለቱም ልጆቹ አካፈላቸው።
\s5
\v 13 ከጥቂት ቀናትም በኋላ ታናሹ ልጅ ድርሻውን ይዞ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። እዚያም ገንዘቡን ሁሉ አላግባብ እየጨፈረ አባከነ።
\v 14 እርሱም ያለውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ በዚያ አገር ጽኑ ራብ ሆነ። ከዚህም የተነሳ ችግር ላይ ወደቀ።
\s5
\v 15 በዚያም አገር ዐሳማ ያረባ ወደ ነበረ ወደ አንዱ ሰው ዘንድ ሄዶ ተቀጠረ። ሰውዬው ዐሳማዎችን እንዲጠብቅለት አሰማራው።
\v 16 እርሱም የሚበላውን ምግብ የሚሰጠው ስላልነበረ፣ ዐሳማዎቹ ከሚመገቡት መኖ ለመብላት ይፈልግ ነበር።
\s5
\v 17 እርሱም አንድ ቀን ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ አለ፤ 'ምግብ የሚተርፋቸው የአባቴ ቤት ሠራተኞች ስንት ናቸው?
\v 18 እኔ ግን እዚህ የምበላውን አጥቼ በራብ እሞታለሁ! ተነሥቼ ወደ አባቴ ቤት ልሂድና እንዲህ ልበለው፤ "አባቴ ሆይ፣ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት ኅጢአት አድርጌአለሁ።
\v 19 ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ መጠራት አይገባኝም፤ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዱ ቊጠረኝ።"
\s5
\v 20 ስለዚህ ታናሹ ልጅ ተነሥቶ ወደ አባቱ መጣ። ልጁ ገና ከሩቅ እየመጣ ሳለ፤ አባቱ አይቶ በርኅራኄ ሮጦ ተቀበለውና ዐቅፎ ሳመው።
\v 21 ልጁ፣ 'አባቴ ሆይ፣ በእግዚአብሔርና በአንተ ፊት ኅጢአት አድርጌአለሁ። ከእንግዲህ ልጅህ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም' አለ።
\s5
\v 22 አባቱም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ "ፈጥናችሁ ምርጡን ልብስ አምጡና አልብሱት፣ በጣቱ ቀለበት፣ በእግሩም ጫማ አድርጉለት።
\v 23 ከዚያም የሰባውን ወይፈን አምጡና ዕረዱት። እንብላ፤ እንደሰት።
\v 24 ይህ ልጄ ሞቶ ነበረ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶም ነበረ ተገኝቶአል።" ይደሰቱም ጀመር።
\s5
\v 25 ታላቁ ልጅ በዕርሻ ቦታ ነበረ። ወደ ቤትም በተቃረበ ጊዜ፣ ሙዚቃና ጭፈራ ሰማ።
\v 26 ከአገልጋዮቹ አንዱን ጠርቶ፤ ምን እየሆነ እንዳለ ጠየቀው። አገልጋዩም፣ 'ወንድምህ መጥቶአል።
\v 27 በደኅና ስለተመለሰም አባትህ የሰባውን ወይፈን አርዶለታል' አለው።
\s5
\v 28 ታላቁ ልጅ ይህን ሰምቶ ተቈጣ፤ ወደ ቤትም ሊገባ አልፈለገም። አባቱም ወጥቶ እንዲገባ ለመነው።
\v 29 እርሱ ግን አባቱን እንዲህ አለው፤ 'እነሆ፣ ይህን ሁሉ ዘመን እንደ ባሪያ አገለገልሁህ፤ ከትእዛዝህ አንዱንም ሳላጎድል ከአንተ ጋር ኖርሁ፤ ከባልንጀሮቼ ጋር እንድደሰት አንዲት የፍየል ግልገል እንኳ አልሰጠኸኝም፤
\v 30 ነገር ግን ይህ ልጅህ ገንዘብህን ሁሉ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር አባክኖ ሲመጣ፣ የሰባውን ወይፈን አረድህለት።'
\s5
\v 31 አባቱ እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፣ አንተ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር ነህ፤ ያለኝ ሁሉ የአንተ ነው።
\v 32 ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበር፤ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአል። ስለዚህ ልንበላና ልንደሰት ይገባናል።'
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 ደግሞም ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፤ "አንድ ሀብታም ሰው ነበረ፤ እርሱም በንብረቱ ሁሉ ላይ የሾመው አስተዳዳሪ ነበረው። ይህ አስተዳዳሪ ሀብተ ያባክናል ተብሎ ለሀብታሙ ተነገረው።
\v 2 ስለዚህ ሀብታሙ ሰው አስተዳዳሪውን ጠርቶ፣ 'ይህ ስለ አንተ የምሰማው ነገር ምንድን ነው? ከዚህ በኋላ ለእኔ አስተዳዳሪ ልትሆን ስለማትችል ንብረቴን አስረክበኝ' አለው።
\s5
\v 3 አስተዳዳሪው እንዲህ ብሎ አሰበ፤ 'እንግዲህ ጌታዬ ከአስተዳደር ሥራዬ ስለሚያሰናብተኝ፣ ምን ባደርግ ይሻለኛል? ዓቅም ስለሌለኝ፣ ከእንግዲህ መሬት በመቈፈር ለመተዳደር አልችልም፤ መለመንም ያሳፍረኛል።
\v 4 ከአስተዳዳሪነት ሥራዬ ስሰናበት፣ ሰዎች በቤታቸው እንዲቀበሉኝ ካሁኑ ምን እንደማደርግ ዐውቃለሁ።'
\s5
\v 5 ከዚያም አስተዳዳሪው የጌታውን ተበዳሪዎች አንድ በአንድ ጠርቶ፣ የመጀመሪያውን ሰው 'ያለብህ ዕዳ ምን ያህል ነው?' ብሎ ጠየቀው።
\v 6 እርሱም፣ 'አንድ መቶ ማድጋ ዘይት አለብኝ' አለ። አስተዳዳሪውም፣ 'በፈረምኸው ውል ላይ ዐምሳ ማድጋ ብለህ ጻፍ' አለው።
\v 7 ሌላውንም፣ 'አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ?' ብሎ ጠየቀው። እርሱም፣ 'መቶ ኩንታል ስንዴ አለብኝ' አለ፤ በፈረምኸው ውል ላይ ሰማንያ ኩንታል ብለህ ጻፍ' አለው።
\s5
\v 8 ጌታውም እምነት ያጎደው አስተዳዳሪ ያደረገውን ሰምቶ፤ በብልኅነቱ በመደነቅ እንዲህ አለ፤ 'በዚህ ዓለም እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች እግዚአብሔርን ከሚያውቁ ሰዎች ይልቅ በዓለማዊ ሥራቸው ብልኆች ናቸው።
\v 9 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ በዓለም ባላችሁ ሀብት ለራሳችሁ ወዳጆችን አፍሩበት፤ ምክንያቱም ሀብታችሁ ባለቀ ጊዜ በዘላለም ቤቶች ይቀበሉአችኋል።
\s5
\v 10 በጥቂቱ የታመነ ሰው በብዙ ላይ የታመነ ይሆናል፤ በጥቂቱ የሚያምፅ በብዙም ዐመፀኛ ይሆናል።
\v 11 ስለዚህ በዚህ ዓለም ሀብት ካልታመናችሁ እውነተኛውን ሀብትማ ማን አምኖ ይሰጣችኋል?
\v 12 እንደዚሁም በሌላ ሰው ሀብት ካልታመናችሁ የራሳችሁን ማን ይሰጣችኋል?
\s5
\v 13 ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይተዋል፤ ሌላውን ይወዳል፤ አለበለዚያም ለአንዱ ራሱን የሰጠ ይሆናል፤ሌላውን ደግሞ ይንቃል። ስለሆነም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
\s5
\v 14 ገንዘብን የሚወዱ ፈሪሳውያን ይህን ሁሉ ሰምተው፣ በኢየሱስ ላይ አፌዙበት።
\v 15 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ "እናንተ በሰው ፊት ራሳችሁን እንደ ጻድቃን ትቈጥራላችሁ፣ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል። በሰዎች ፊት የከበረ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።"
\s5
\v 16 ሕግና ነቢያት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ሲሠራባቸው ኖረዋል። ከዚያ በኋላ ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወንጌል ተሰብኳል። ሰው ሁሉ ወደዚህ ለመግባት ይጋፋል።
\v 17 ነገር ግን ከሕግ አንድ ነጥብ ዋጋ ከሚያጣ ሰማይና ምድር ቢያልፍ ይቀላል።
\s5
\v 18 ማንም ሚስቱን ፈትቶ ሌላይቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ ከባሏ የተፋታችውንም የሚያገባ ያመነዝራል።
\s5
\v 19 ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ "ሐምራዊና ቀጭን የሐር ልብስ የለበሰ በየቀኑም በምቾትና በደስታ የሚኖር ሀብታም ሰው ነበረ።
\v 20 ሰውነቱ በቊስል የተወረረ አልዓዛር የሚባል ለማኝም በሀብታሙ ሰው ደጅ ይተኛ ነበር።
\v 21 አልዓዛርም ከሀብታሙ ማዕድ የተረፈውን ፍርፋሪ ሊመገብ ይመኝ ነበር። ውሾች እንኳ እየመጡ ቊስሉን ይልሱ ነበር።
\s5
\v 22 ከጊዜ በኋላ ለማኙ ሞተ፤መላእክትም መጥተው ወደ አብርሃም አጠገብ ወሰዱት። ሀብታሙም ሞተ፤ ተቀበረም።
\v 23 ሀብታሙ በሲኦል እየተሠቃየ ሳለ፣ ቀና ብሎ አብርሃም አልዓዛርን በዕቅፉ ይዞት አየ።
\s5
\v 24 እርሱም፣ 'አብርሃም አባት ሆይ፣ ራራልኝ በዚህ ነበልባል እየተሠቃየሁ ስለ ሆነ፣ አልዓዛር የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ እባክህ አልዓዛርን' ላክልኝ ብሎ ጮኸ።
\s5
\v 25 አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ "ልጄ ሆይ፣ አንተ በምድር የሕይወት ዘመንህ መልካም ነገሮችን እንደተቀበልህና በደስታ እንደ ኖርህ፤ አልዓዛርም ክፉ ነገሮችን ሲቀበል እንደ ኖረ አስታውስ። አሁን ግን አልዓዛር እዚህ በምቾት ሲኖር፣ አንተ በሥቃይ ላይ ትገኛለህ።
\v 26 ከሁሉ በላይ ከዚህ ወደ እናንተ ለማለፍ የሚፈልጉ እንዳይሻገሩ እዚያ ያሉትም ወደ እኛ እንዳይመጡ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል አለ።'
\s5
\v 27 ሀብታሙ ሰው እንዲህ አለ፤ 'አባት ሆይ፣ እንግዲያውስ አልዓዛርን ወደ አባቴ ቤተ ሰብ እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤
\v 28 ምክንያቱም አምስት ወንድሞች አሉኝና እነርሱ ወደዚህ ሥቃይ ቦታ እንዳይመጡ ያስጠንቅቃቸው።'
\s5
\v 29 አብርሃም ግን፣ 'ወንድሞችህ ሙሴና ነቢያት አሏቸው፤ እነርሱንም ይስሙአቸው' ብሎ መለሰለት። ነገር ግን
\v 30 ሀብታሙ ሰው፣ 'አብርሃም አባት ሆይ፣ እንደዚህ አይደለም፤ አንድ ሰው ከሙታን ተነሥቶ ሄዶ ቢነግራቸው ንስሓ ይገባሉ' አለ።
\v 31 አብርሃም ግን ሙሴንና ነቢያትን የማይሰሙ ከሆነ፣ አንድ ሰው ከሙታን ተነሥቶ ቢነግራቸው እንኳ አያምኑም' አለው።
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤ "ወደ ኅጢአት የሚያመሩ ነገሮች መምጣታቸው የማይቀር ነው። ነገር ግን ለኅጢአት ምክንያት ለሚሆነው ሰው ወዮለት።
\v 2 በእምነት ደካማ ከሆኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከማስናከል ይልቅ ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል።
\s5
\v 3 ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ተመልሶ ከተጸጸተ ይቅር በለው፤ በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ ተመላልሶ፤
\v 4 'ስለ ሠራሁት ኅጢአት ተጸጸትሁ' እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር ልትለው ይገባል።"
\s5
\v 5 ሐዋርያት ጌታን፣ "እምነት ጨምርልን" አሉት።
\v 6 ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ "የሰናፍጭን ዘር ያህል እምነት ቢኖራችሁ፤ ይህን የሾላ ዛፍ፣ 'ከመሬት ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል' ብትሉት ይታዘዝላችኋል።
\s5
\v 7 "በዕርሻ ወይም በበጎች እረኝነት የተሰማራ አገልጋይ ካላችሁ፣ አገልጋዩ ከሥራ ደክሞ ሲመለስ፣ ወዲያውኑ "ና ተቀመጥና እራትህን ብላ የሚለው ከእናንተ ማን ነው?"
\v 8 "እራቴን አዘጋጅልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣም ወገብህን ታጥቀህ ቆመህ አስተናግደኝ፤ ከዚያ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ ትጠጣለህም አይለውምን?"
\s5
\v 9 ታዲያ አገልጋዩ የታዘዘውን ስለ ፈጸመ ጌታው ያመሰግነዋልን?
\v 10 እንዲሁም እናንተም የታዘዛችሁትን ሁሉ ከፈጸማችሁ በኋላ የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ 'የፈጸምነውም የታዘዝንውን ግዳጃችንን ብቻ ነው' ማለት አለባችሁ።"
\s5
\v 11 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ሳለ፣ ሰማርያንና ገሊላን በሚያዋስነው መንገድ ያልፉ ነበር።
\v 12 ኢየሱስም ወደ አንዲት መንደር በገባ ጊዜ ዐሥር ለምጻሞች አገኙት። እነርሱም ከእርሱ ርቀው ቆሙና
\v 13 ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ "ኢየሱስ ሆይ፣ መምህር ሆይ፣ እባክህ ማረን" እያሉ ጮኹ።
\s5
\v 14 ኢየሱስ ባያቸው ጊዜ፣ "ሂዱና ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ" አላቸው። እነርሱም እየሄዱ ሳሉ፣ ከለምጻቸው ነጹ።
\v 15 ከእነርሱ አንዱ ከለምጹ መፈወሱን ባየ ጊዜ፣ ጮክ ብሎ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ።
\v 16 በኢየሱስ እግር ሥር በግንባሩ ተደፍቶ አመሰገነው። እርሱም የሰማርያ ሰው ነበር።
\s5
\v 17 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፣ "ዐሥሩም ለምጻሞች ተፈውሰው አልነበረምን? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ?
\v 18 ከዚህ ከባዕድ ሰው በቀር እግዚአብርሔን ለማመስገን ተመልሶ የመጣ ሌላ የለምን?"
\v 19 ኢየሱስ ሰውየውን፣ "ተነሥና ሂድ እምነትህ አድኖሃል" አለው።
\s5
\v 20 ፈሪሳውያን ኢየሱስን፣ "የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?" ብለው ለጠየቁት ጥያቄ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "የእግዚአብሔር መንግሥት የምትታይ አይደለችም።" ወይም'እነሆ፣ እዚህ ናት'
\v 21 ወይም 'እነሆ፣እዚያ ናት' የምትባል አይደለችም። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናት።"
\s5
\v 22 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤" ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትናፍቁበት ቀን ይመጣል። ነገር ግን አታዩትም።
\v 23 ሰዎች፣ 'እነሆ፣ ክርስቶስ እዚህ ነው! ወይም እዚያ ነው!' ይሉአችኋል። ነገር ግን እነርሱን ሰምታችሁ አትፈልጉ፤ አትከተሉአቸውም።
\v 24 መብረቅ በሰማይ ላይ ሲበርቅ ከዳር እስከ ዳር እንደሚያበራ፣ የሰው ልጅም በሚመጣበት ቀን እንዲሁ ይሆናል።
\s5
\v 25 ነገር ግን ይህ ከመሆኑ በፊት የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል ይገባል። በዚህ ዘመን ሰዎችም ሊናቅና ሊነቀፍ ግድ ነው።
\v 26 በኖኅ ዘመን እንደሆነው፣ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል።
\v 27 ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡና ነበር። ነገር ግን በዚያን ጊዜ የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉንም አጠፋቸው።
\s5
\v 28 እንደዚሁም በሎጥ ዘመን ሰዎች ይበሉ፣ ይጠጡ፣ ይሸጡ ይገዙ፣ አትክልት ይተክሉና ቤትም ይሠሩ እንደ ነበረ ይሆናል።
\v 29 ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን እሳትና ዲን ከሰማይ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋ።
\s5
\v 30 የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀንም እንዲሁ ይሆናል።
\v 31 በዚያ ቀን በቤቱ ጣሪያ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ ለመውሰድ አይውረድ። በዕርሻም ቦታ ያለ ሰው ወደ ቤቱ አይመለስ።
\s5
\v 32 የሎጥን ሚስት አስታውሱአት። ሕይወቱን ሊያድን በራሱ መንገድ ለመሄድ የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል።
\v 33 ነገር ግን ሕይወቱን ለጌታ አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ያድናታል።
\s5
\v 34 ይህን እላችሏለሁ፣ "በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ላይ ይተኛሉ።
\v 35 ከእነርሱም አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። እንዲሁም ሁለት ሴቶች በአንድ ቦታ አብረው ይፈጫሉ፤
\v 36 አንድዋ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች። ሁለት ሰዎች በአንድ ዕርሻ ቦታ ያርሳሉ፤አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።"
\s5
\v 37 ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስን፦ 'ጌታ ሆይ፤ ወዴት?' ብለው ጠየቁት። እርሱም፦ "በድን ባለበት አሞራዎች ይሰበባሉ።" ሲል መለሰላቸው።
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 18
\p
\v 1 ከዚያም ኢየሱስ ሳይታክቱ ዘወትር መጸለይ እንደሚገባቸው እንዲህ ሲል አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤
\v 2 "በአንድ ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ፤ ሰውንም የማያከብር አንድ ዳኛ ነበረ።
\s5
\v 3 አንዲት ባል የሞተባት ሴትም በዚያ ከተማ ነበረች። እርስዋም ዘወትር ወደ ዳኛው እየመጣች፣ 'ከባላጋራዬ ጋር ስላለኝ ክርክር ፍረድልኝ' ትለው ነበር።
\v 4 ዳኛውም ለረጅም ጊዜ ሊረዳት ፈቃደኛ አልነበረም። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ ብሎ አሰበ፤
\v 5 'ምንም እንኳ እግዚአብሔርን ባልፈራ፣ ሰውንም ባላከብር፣ ይህች ባል የሞተባት ሴት አዘውትራ በመምጣት እንዳታታክተኝ እፈርድላታለሁ።' "
\s5
\v 6 ከዚያም ጌታ እንዲህ አለ፤ "ቅንነት የሌለው ዳኛ የሚናገረውን ስሙ።
\v 7 ታዲያ እግዚአብሔር ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹት ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?
\v 8 ደግሞስ አይታገሣቸውምን? እላችኋለሁ በቶሎ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆን?"
\s5
\v 9 ከዚያም ኢየሱስ ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚመኩና ሌሎችንም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ተናገረ፤
\v 10 "ሁለት ሰዎች ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፤ አንዱ ፈሪሳዊ ሲሆን፣ ሌላው ቀራጭ ነበረ።
\s5
\v 11 ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ በማለት ስለ ራሱ ጸለየ፤ 'እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፣ ዐመፀኛ፣ አመንዝራ፣ ወይም እንደዚህ ቀራጭ እንኳ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ።
\v 12 በሳምንት ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፣ ከማገኘውም ሁሉ ዐሥራት አወጣለሁ።'
\s5
\v 13 "ቀራጩ ግን ከርቀት ቆሞ ዐይኑን ወደ ሰማይ ሳያነሣ ደረቱን እየመታ፣ 'አምላኬ ሆይ፣ እኔን ኅጢአተኛውን ማረኝ!' ይል ነበር። እላችኋለሁ፣
\v 14 "ከሌላው ይልቅ ጻድቅ ሆኖ ይህ ሰው ወደ ቤቱ ተመለሰ ፤ ምክንያቱም ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳል፤ ራሱን የሚያዋርድ ከፍ ከፍ ይላል።"
\s5
\v 15 እንዲዳስሳቸው ሰዎች ልጆቻቸውን ወደ እርሱ ያመጡ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ ይህን ባዩ ጊዜ ገሠጹአቸው።
\v 16 ኢየሱስ ግን ሕፃናትን ወደ እርሱ ጠራቸውና፣ "ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተውአቸው አትከልክሏቸውም። የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና።
\v 17 እውነት እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን በየዋህነት ያልተቀበላት ፈጽሞ አይገባባትም" አለው።
\s5
\v 18 ከአለቆች አንዱ ኢየሱስን፣ "ቸር መምህር ሆይ፣ የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይገባኛል?" ብሎ ጠየቀው።
\v 19 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ "ለምን ቸር ብለህ ትጠራኛለህ? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በስቀር ቸር የለም።
\v 20 ትእዛዛትን ሁሉ ታውቃቸዋለህ፤ እነርሱም፣ 'አትግደል፣ አታመንዝር፣ አትስረቅ፣ በሐሰት አትመስክር፣ እናትህንና አባትህን አክብር የሚሉ ናቸው።"
\v 21 አለቃውም ፣ "እነዚህንማ ከሕፃንነቴ ጀምሬ ጠብቄአቸዋለሁ።"
\s5
\v 22 ኢየሱስ ይህን በሰማ ጊዜ፣ ሰውየውን፣ "እንግዲያውስ ገና አንድ ነገር ማድረግ ይቀርሃል፤ ያለህን ሁሉ ሸጠህ ገንዘቡን ለድኾች ስጣቸው፤ በመንግሥተ ሰማያት ሀብት ይኖርሃል። ከዚያም በኋላ መጥተህ ተከተለኝ" አለው።
\v 23 ሀብታሙ ሰውዬ ግን በጣም ባለጠጋ ስለ ነበረ፣ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ አዘነ።
\s5
\v 24 ከዚያም ኢየሱስ ሰውየው እንዳዘነ አይቶ፣ "ሀብታም ለሆኑ ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት አስቸጋሪ ነው!
\v 25 ሀብታም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" አለ።
\s5
\v 26 የሰሙትም ሰዎች፣ "እንግዲያውስ ማን ሊድን ይችላል?" አሉ።
\v 27 ኢየሱስ፣ "በሰው ዘንድ የማይቻል ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል" ብሎ መለሰ።
\s5
\v 28 ጴጥሮስ፣ "እነሆ፣ እኛ ያለንን ሁሉ ትተን ተከትለንሃል" አለው።
\v 29 ከዚያም ኢየሱስ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ብሎ ቤቱን ወይም ሚስቱን፣ ወይም ወንድሞቹን፣ ወይም ወላጆቹን ወይም ልጆቹን የተወ
\v 30 በዚህ ዓለም ብዙ ዕጥፍ በሚመጣውም ዓለም የዘላለምን ሕይወት የማያገኝ ማንም የለም" አላቸው።
\s5
\v 31 ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርት ወደ እርሱ ከሰበሰበ በኋላ እንዲህ አላቸው፤ "አሁን ወደ ኢየሩሳሌም መሄዳችን ነው፤ ስለ ሰው ልጅ በነቢያት አስቀድሞ የተነገሩት ሁሉ ይፈጸማሉ።
\v 32 እርሱ ለአሕዛብ ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም ያላግጡበታል፤ ያዋርዱታል፤ ይተፉበታልም።
\v 33 ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ከሞት ይነሣል።"
\s5
\v 34 ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ ከተናገራቸው ነገሮች አንዱንም አልተረዱም። ይህ ቃልም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለተባሉትም ነገሮች ምንም አልተረዱም።
\s5
\v 35 ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ በቀረበ ጊዜ፣ አንድ ዐይነ ስውር ምጽዋት እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር፤
\v 36 ሕዝብ ሲያልፉ ሰምቶም እየሆነ የነበረውን ነገር ጠየቀ።
\v 37 እነርሱም፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ በኩል እያለፈ መሆኑን ነገሩት።
\s5
\v 38 ስለዚህ ዐይነ ስውሩ፣ "የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ፣ እባክህ ማረኝ" እያለ ጮኸ።
\v 39 እፊት እፊት ይሄዱ የነበሩት፣ "ዝም በል!" ብለው ዐይነ ስውሩን ገሠጹት። እርሱ ግን ድምፁን የበለጠ ከፍ አድርጎ፣ "የዳዊት ልጅ ሆይ፣ እባክህ ማረኝ" ብሎ ጮኸ።
\s5
\v 40 ኢየሱስ ቆሞ ሰውየውን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዛቸው ። ከዚያም ዐይነ ስውሩ ወደ እርሱ በቀረበ ጊዜ፣ ኢየሱስ፣
\v 41 "ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?" ብሎ ጠየቀው። "ጌታ ሆይ፣ ማየት እፈልጋለሁ" አለ።
\s5
\v 42 ኢየሱስም፣ "እይ። እምነትህም አድኖሃል" አለው። ዐይነ ስውሩም ወዲያውኑ ማየት ቻለ።
\v 43 እግዚአብሔርን እያመሰገነ ኢየሱስን ተከተለ። ሕዝቡ ሁሉ ይህን አይተው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 ኢየሱስ ኢያሪኮ ከተማ ገብቶ እያለፈ ሳለ፣
\v 2 ዘኬዎስ የሚባል አንድ የቀራጮች አለቃና ሀብታም ሰው ወዳለበት ስፍራ ደረሰ።
\s5
\v 3 ዘኬዎስ ኢየሱስ የትኛው እንደ ሆነ ለማየት ይሞክር ነበር፣
\v 4 ነገር ግን አጭር ስለ ነበረ፣ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ አሻግሮ ማየት አልቻለም ነበር። ስለዚህ ኢየሱስ በዚያ መንገድ ያልፍ ስለነበር፣ ከሕዝቡ ቀድሞ ሮጠና ሊያየው በእንድ ሾላ ዛፍ ላይ ወጣ።
\s5
\v 5 ኢየሱስ ወደ ስፍራው በደረሰ ጊዜ፣ ቀና ብሎ ተመለከተና፣ “ዘኬዎስ ሆይ፣ ዛሬ ወደ ቤትህ መሄድ እፈልጋለሁና ቶሎ ውረድ” አለው።
\v 6 ስለዚህ ዘኬዎስ በፍጥነት ወርዶ በደስታ በቤቱ ተቀበለው።
\v 7 ይህን የተመለከቱት ሰዎች ሁሉ፣ “በኃጢአተኛ ሰው ቤት ገባ” በማለት አጒረመረሙ።
\s5
\v 8 ዘኬዎስ ተነሥቶ ቆመና ጌታን፣ “ጌታ ሆይ፣ የሀብቴን ግማሽ ለድሆች እሰጣለሁ፣ ያታለልሁት ሰው ካለ፣ የወሰድሁበትን አራት ዕጥፍ እመልስለታለሁ” አለው።
\v 9 ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ "ዛሬ ድነት ለዚህ ቤት መጥቷል። ምክንያቱም፣ እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነው።
\v 10 የሰው ልጅ የመጣው የጠፉትን ሰዎች ሊፈልግና ሊያድን ነውና” አለ።
\s5
\v 11 እነርሱ እነዚህን ነገሮች እንደ ሰሙ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየተቃረበ ስለ ነበር ሕዝቡ የእግዚአብሔር መንግሥት ወዲያው የሚገለጥ መሰላቸው።
\v 12 ስለዚህ ኢየሱስ ንግግሩን በምሳሌ በመቀጠል እንዲህ አለ፣ “አንድ መኰንን የመንግሥት ሹመት ተቀብሎ ሊመጣ ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ነበር።
\s5
\v 13 ከዚያም፣ ከአገልጋዮቹ ዐሥሩን ጠርቶ ዐሥር ምናን ሰጣቸውና፣ “እስክመጣ ድረስ ይህን ነግዱበት” አላቸው።
\v 14 ነገር ግን የአገሩ ሰዎች ይጠሉት ስለ ነበር፣ 'ይህ ሰው ተመልሶ በእኛ ላይ ገዥ እንዲሆን አንፈልግም' በማለት ተወካዮቻቸውን ከኋላው ላኩበት።
\v 15 መኰንኑም ሹመቱን ተቀብሎ ሲመለስ፣ ነግደው ያተረፉትን ትርፍ ለመተሳሰብ ገንዘቡን የሰጣቸው አገልጋዮቹ እንዲጠሩለት አዘዘ።
\s5
\v 16 የመጀመሪያው አገልጋይ ወደፊቱ ቀረበና፣ 'ጌታ ሆይ፣ ምናንህ ተጨማሪ ዐሥር ምናን አትርፎልሃል' አለው።
\v 17 ጌታውም፣ “ደግ አድርገሃል፣ አንተ ታታሪ አገልጋይ። በጥቂቱ ስለ ታመንህ፣ በዐሥር ከተሞች ላይ ገዥ ትሆናለህ' አለው።
\s5
\v 18 ሁለተኛውም ቀርቦ፣ 'ጌታ ሆይ፣ ምናንህ ዐምስት አትርፏል' አለው።
\v 19 ጌታውም፣ 'በዐምስት ከተሞች ላይ ገዥ ሁን' አለው።
\s5
\v 20 ሌላኛውም መጣና፣ 'ጌታ ሆይ፣ በደንብ አድርጌ በጨርቅ ጠቅለዬ ያስቀመጥሁት ምናንህ ይኸውልህ፣
\v 21 ይህን ያደረግሁት አንተ ጨካኝ ሰው መሆንህን ስላወቅሁ ፈርቼ ነው። አንተ ያላስቀመጥኸውን የምትጠይቅ ያልዘራኸውን የምታጭድ ነህ' አለው።
\s5
\v 22 ጌታውም፣ እንዲህ አለው፤ 'አንተ ክፉ አገልጋይ፣ በአፍህ ቃል እፈርድብሃለሁ። ካላስቀመጥሁበት የምፈልግ፣ ካልዘራሁበት የማጭድ ጨካኝ ሰው መሆኔን ያወቅህ ከሆነ፣
\v 23 ታዲያ ስመለስ ገንዘቤን ከነትርፉ እንዳገኝ ለምን በባንክ አላስቀመጥኸውም?”
\s5
\v 24 ከዚያም ጌታው በዚያ ለቆሙት ሰዎች፣ “ምናኑን ውሰዱበት፣ ዐሥር ላለውም ጨምሩለት' አላቸው፤
\v 25 እነርሱም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አስር ምናን አለው እኮ' አሉት።
\s5
\v 26 ጌትየውም፣ 'ላለው ይጨምርለታል፣ ከሌለው ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።
\v 27 በእነርሱ ላይ ገዥ እንዳልሆን የተቃወሙትን እነዚህን ጠላቶቼን ግን አምጡና በፊቴ ግደሏቸው' አለ።
\s5
\v 28 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ፊቱን ወደ ኢየሩሳሌም በማቅናት መንገዱን ቀጠለ።
\s5
\v 29 ደብረ ዘይት በሚባለው ተራራ አጠገብ ወደሚገኝ ቤተ ፋጌና ቢታንያ በተቃረበ ጊዜ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን
\v 30 እንዲህ ብሎ ላካቸው፤ "ወደሚቀጥለው መንደር ሂዱ። ስትገቡ፣ ማንም ያልተቀመጠበትን አንድ የአህያ ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ። ፍቱትና አምጡልኝ።
\v 31 ማንም፣ 'ለምን ትፈቱታላችሁ?' ብሎ ቢጠይቃችሁ፣ 'ለጌታ ያስፈልገዋል' በሉት" አላቸው።
\s5
\v 32 የተላኩትም ወደ ስፍራው በደረሱ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንደ ነገራቸው፣ የአህያውን ውርንጫ ታስሮ አገኙት።
\v 33 ውርንጫውን እየፈቱ እያለ ባለቤቶቹ፣ 'ውርንጫውን ለምን ትፈቱታላችሁ?' አሉ።
\v 34 እነርሱም፣ “ለጌታ ያስፈልገዋል” ብለው መለሱለት።
\v 35 ወደ ኢየሱስ አመጡትና ልብሳቸውን በውርንጫው ጀርባ ላይ አንጥፈው ኢየሱስ እንዲቀመጥበት አደረጉ።
\v 36 ኢየሱስ በሚሄድበት ጊዜ፣ ከፊቱ ባለው መንገድ ላይ ልብሶቻቸውን ያነጥፉለት ነበር።
\s5
\v 37 ከደብረ ዘይት ተራራ ቁልቁል ወደሚወስደው መንገድ በቀረበ ጊዜ፣ ቊጥራቸው ብዙ የሆነ ደቀ መዛሙርት፣ ስላዩአቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ ደስ እያላቸው፣ “በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው! በሰማይ ሰላም፣
\v 38 ክብርም በአርያም ይሁንለት!” እያሉ በከፍተኛ ድምፅ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።
\s5
\v 39 በሕዝቡ መካከል የነበሩ አንዳንድ ፈሪሳውያን፣ “መምህር ሆይ፣ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው” አሉ።
\v 40 ኢየሱስም፣ “ልንገራችሁ፣ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮችም እንኳ ይጮኻሉ” አላቸው።
\s5
\v 41 ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በተቃረበ ጊዜ እንዲህ በማለት አለቀሰላት፤
\v 42 “ለአንቺ ሰላም የሚያመጣልሽን ነገር ምነው ዛሬ ባወቅሽ ኖሮ! አሁን ግን ከዐይንሽ ተሰውሮብሻል።
\s5
\v 43 ጠላቶችሽ ዙሪያሽን ቅጥር ሠርተው የሚከቡሽና ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስጨንቁሽ ጊዜያት ይመጣሉ።
\v 44 አንቺንና ልጆችሽንም በምድር ላይ ይፈጠፍጣሉ። እነርሱም ድንጋይ በድንጋይ ላይ እንደተነባበረ አይተዉም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያድንሽ መፈለጉን አላወቅሽምና።”
\s5
\v 45 ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ገባና በዚያ ይሸጡ የነበሩትን ያባርራቸው ጀመር፣
\v 46 ከዚያም፣ “የአባቴ ቤት 'የጸሎት ቤት ይሆናል' ተብሎ ተጽፏል፣ እናንተ ግን የወንበዴዎች መሸሸጊያ አደረጋችሁት” አለ።
\s5
\v 47 ስለዚህ ኢየሱስ በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ያስተምር ነበር። ታዲያ የካህናት አለቆች፣ የሕግ መምህራንና የሕዝቡ መሪዎች ሊገድሉት ፈለጉ።
\v 48 ነገር ግን ሕዝቡ ከልብ ያደምጡት ስለ ነበር መንገድ አላገኙም።
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 አንድ ቀን እንዲህ ሆነ፣ ኢየሱስ ሕዝቡን በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያስተምርና ወንጌልን ይሰብክ በነበረ ጊዜ፣ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ መጡ።
\v 2 "እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይም ይህን ሥልጣን የሰጠህ እርሱ ማን ነው?" አሉት።
\s5
\v 3 እርሱም እንዲህ በማለት መለሰላቸው፤ "እኔም አንድ ጥያቄ እጠይቃችኋለሁ፣ እስቲ መልሱልኝ።
\v 4 የዮሐንስ ጥምቀት ከሰማይ ነበር ወይስ ከሰዎች?"
\s5
\v 5 እርስ በርሳቸው ተመካከሩና፣ "'ከሰማይ ነው ብንል፣ 'ታዲያ ለምን አላመናችሁትም ይለናል።
\v 6 ነገር ግን 'ከሰው ነው ብንል' ሕዝቡ ዮሐንስን ነቢይ አድርገው ስለሚቆጥሩ ይወግሩናል" አሉ።
\s5
\v 7 ስለዚህ ከየት እንደ ሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት።
\v 8 ኢየሱስ፣ "እኔም እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን እንደማደርግ አልነግራችሁም" አላቸው።
\s5
\v 9 ለሕዝቡ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፣ "አንድ ሰው ያዘጋጀውን የወይን ዕርሻ ለወይን ገበሬዎች አከራይቶ ረጅም ጊዜ ሊቆይ ወደ ሌላ አገር ሄደ።
\v 10 ምርቱ የሚሰበሰብበት ጊዜ ሲደርስ ከወይኑ የሚገባውን ፍሬ ለማግኘት ወደ ገበሬዎቹ አንድ አገልጋይ ላከ። ነገር ግን የወይኑ ገበሬዎች አገልጋዩን ደብድበው ባዶ እጁን መልሰው ላኩት።
\s5
\v 11 እርሱም አሁንም ሌላ አገልጋይ ላከባቸው፣ ይህንም ደብድበውና አዋርደው ባዶ እጁን መልሰው ላኩት።
\v 12 እንደ ገና ሦስተኛ አገልጋይ ቢልክባቸው፣ እርሱንም አቈሳስለው አውጥተው ጣሉት።
\s5
\v 13 ስለዚህ የወይኑ ዕርሻ ባለቤት፣ 'ምን ላድርግ? የምወደውን ልጄን እልከዋለሁ። ምናልባት እርሱን ያከብሩት ይሆናል' አለ።
\v 14 ነገር ግን የወይኑ ገበሬዎች ባዩት ጊዜ፣ 'ወራሹ ይህ ነው። ዕርሻው የእኛ እንዲሆን እንግድለው' ብለው እርስ በርስ ተመካከሩ።
\s5
\v 15 ከዕርሻው ቦታ አወጡትና ገደሉት። እንግዲህ የዕርሻው ባለቤት ምን ያደርግባቸዋል? መጥቶ እነዚህን የወይን ገበሬዎች ይደመስሳቸዋል፣
\v 16 ዕርሻውንም ለሌሎች ይሰጣል" አላቸው። እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን ነገር ያርቀው!" አሉ።
\s5
\v 17 ኢየሱስ ግን ተመለከታቸውና፣ 'ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማዕዘን ራስ ሆነ' "የሚለው ይህ የመጽሐፍ ቃል ምን ማለት ነው?
\v 18 በዚህ ድንጋይ የሚደናቀፍ ሁሉ ይሰባበራል። ነገር ግን ድንጋዩ የሚወድቅበት ሁሉ ይደቃል" አለ።
\s5
\v 19 ስለዚህ፣ የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች በዚያን ሰዓት ሊይዙት ፈለጉ፣ ምክንያቱም ይህን ምሳሌ የተናገረው በእነርሱ ላይ እንደ ሆነ አውቀዋልና።
\v 20 ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩ። በዐይነ ቁራኛ እየተከታተሉት፣ ለፍርድና ለገዢው ሥልጣን የሚዳርገውን ስሕተት ከንግግሩ ሊያገኙበት ራሳቸውን ጻድቃን አስመስለው የሚቀርቡ ሰላዮችን ላኩበት።
\s5
\v 21 እነርሱ እንዲህ በማለት ጠየቁት፤ "መምህር ሆይ፣ አንተ በትክክል እንደምትናገርና እንደምታስተምር፣ ደግሞም በማንም እንደማትመራ፣ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር መንገድ እውነቱን እንደምታስተምር እናውቃለን።
\v 22 ለቄሣር ግብር መክፈል ተፈቅዷል ወይስ አልተፈቀደም?"
\s5
\v 23 ኢየሱስ ግን ተንኰላቸውን ተረዳ፣ እንዲህም አላቸው፣
\v 24 "አንድ ዲናር አሳዩኝ። በላዩ ያለው የማን ጽሑፍና ምስል ነው?" እነርሱም፣ "የቄሣር ነው" አሉት።
\s5
\v 25 "እንግዲያውስ የቄሣር የሆኑትን ነገሮች ለቄሣር፣ የእግዚአብሔርን ነገሮች ለእግዚአብሔር ስጡ" አላቸው።
\v 26 የሕግ መምህራንና የካህናት አለቆች በሕዝቡ ፊት በንግግሩ ሊያጠምዱት አልቻሉም። ምንም እስከማይናገሩ ድረስ በመልሱ ተደነቁ።
\s5
\v 27 የሙታን ትንሣኤ የለም የሚሉ አንዳንድ ሰዱቃውያን ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ፣
\v 28 እንዲህ ብለው ጠየቁት፤ "መምህር ሆይ፣ ሙሴ አንድ ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት ወንድሙ የዚያን ሰው ሚስት አግብቶ ልጅ ለእርሱ እንዲወልድለት ጽፎልናል።
\s5
\v 29 ሰባት ወንድማማች ነበሩ፤ የመጀመሪያው ሚስት አገባና ልጅ ሳይወልድ ሞተ፤
\v 30 ሁለተኛውም እንደዚሁ አግብቷት ልጅ ሳይወልድ ሞተ።
\v 31 ሦስተኛውም አገባት፤ በዚህ ዓይነት ሰባቱም ሴቲቱን አግብተው ልጅ ሳይወልዱ ሞቱ።
\v 32 በመጨረሻ ሴቲቱም ሞተች።
\v 33 ታዲያ በትንሣኤ ቀን ይህች ሴት የማንኛቸው ሚስት ትሆናለች? ምክንያቱም ሰባቱም አግብተዋታልና።"
\s5
\v 34 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ "የዚህ ዓለም ሰዎች ያገባሉ፣ ይጋባሉም።
\v 35 ነገር ግን የሙታን ትንሣኤንና የዘላለም ሕይወትን ለመቀበል የተገባቸው አያገቡም፣ አይጋቡምም።
\v 36 እንደ መላእክት ስለ ሆኑ፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሊሞቱ አይችሉም። የትንሣኤ ልጆች እንደ መሆናቸው መጠን የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።"
\s5
\v 37 ነገር ግን ሙታን ስለ መነሣታቸው ሙሴ እንኳ በቊጥቋጦው ስፍራ፣ጌታን የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክና የያዕቆብ አምላክ ብሎ በመጥራቱ አሳይቷል።
\v 38 አሁን እርሱ የሕያዋን እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፣ ምክንያቱም ለእርሱ ሁሉም ሕያዋን ናቸው።"
\s5
\v 39 ከሕግ መምህራን አንዳንዶች፣ "መምህር ሆይ፣ ጥሩ አድርገህ መልሰሃል" አሉት።
\v 40 ደግሞም ተጨማሪ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ማንም አልደፈሩም።
\s5
\v 41 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ "እንግዲህ ሰዎች ክርስቶስን የዳዊት ልጅ ነው የሚሉት እንዴት ነው?
\v 42 ዳዊት ራሱ በመዝሙር መጽሐፍ፣ "ጌታ ለጌታዬ ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ
\v 43 እስከማደርግልህ ድረስ 'በቀኜ ተቀመጥ' ይላልና።
\v 44 ስለዚህ ዳዊት ክርስቶስን ጌታ ይለዋል፣ታዲያ የዳዊት ልጅ እንዴት ይሆናል?"
\s5
\v 45 ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፣
\v 46 "ረጅም ቀሚስ ለብሰው መመላለስ ከሚፈልጉ፣ በገበያ ቦታዎችም ልዩ ሰላምታ፣ በምኲራቦች ከፍተኛ ስፍራ፣ በግብዣ ቦታዎችም የከበሬታ መቀመጫ እንዲሰጣቸው ከሚወዱ የሕግ መምህራን ተጠንቀቁ።
\v 47 ደግሞም እነርሱ ረጅም የሆኑ የማስመሰል ጸሎቶችን እየጸለዩ የመበለቶችን ቤት አለአግባብ ይበዘብዛሉ። እነዚህ የባሰ ቅጣት ይቀበላሉ።"
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 ኢየሱስ ቀና ብሎ ሲመለከት ሀብታም ሰዎች በመባ መሰብሰቢያ ሣጥን ውስጥ ገንዘብ ሲጨምሩ አየ።
\v 2 አንዲት ድኻ መበለት ደግሞ ሁለት ሳንቲሞችን ስትጨምር አየ።
\v 3 ስለዚህ እንዲህ አለ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉም የበለጠ ሰጠች።
\v 4 እነዚህ ሁሉ የሰጡት ስጦታ ከተትረፈረፈ ሀብታቸው ነው። ይህች መበለት ግን በድኽነቷ መተዳደሪያዋን ሁሉ ሰጠች።"
\s5
\v 5 አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ በተዋቡ ድንጋዮች እንዴት እንዳማረና እንዳጌጠ ሲናገሩ ሰምቶ እንዲህ አለ፣
\v 6 "እነዚህ የምታዩአቸው ነገሮች፣ እንዲህ እንደተነባበሩ የማይቆዩበትና የሚፈራርሱበት ጊዜ ይመጣል" አለ።
\s5
\v 7 ስለዚህ፣ "መምህር ሆይ፣ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው? እነዚህ ነገሮች እንደሚፈጸሙ ምልክቱስ ምንድን ነው?" በማለት ጠየቁት።
\v 8 ኢየሱስ፣ "እንዳትስቱ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ብዙዎች 'እኔ ኢየሱስ ነኝ፣ ደግሞም 'ጊዜው አሁን ነው' እያሉ በስሜ ይመጣሉ። አትከተሏቸው።
\v 9 ስለ ጦርነቶችና ሁከቶች ስትሰሙ አትሸበሩ፣ እነዚህ ነገሮች አስቀድመው መፈጸም ይኖርባቸዋል፣ ነገር ግን መጨረሻው ወዲያው አይሆንም" ብሎ መለሰ።
\s5
\v 10 ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ "ሕዝብ በሕዝብ ላይ ይነሣል፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣል።
\v 11 ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ይሆናል፣ ደግሞም በተለያዩ ቦታዎች ራብና ቸነፈር ይከሠታል። አስፈሪ ሁነቶችና ታላላቅ ምልክቶች ከሰማይ ይገለጣሉ።
\s5
\v 12 ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች አስቀድሞ እናንተን ይይዟችኋል፣ ያሳድዷችኋል፣ ለምኩራቦችና ለወህኒ ቤቶች አሳልፈው በመስጠት ስለ ስሜ በገዦችና በነገሥታት ፊት ያቆሟችኋል።
\v 13 ይህም ለእናንተ ለመመስከር ዕድልን ይሰጣችኋል።
\s5
\v 14 ስለዚህ፣ አስቀድማችሁ ምን መከላከያ እናቀርባለን በማለት አትናወጡ፣
\v 15 ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ጠላቶቻችሁ ሊቋቋሙትና ሊቃወሙት የማይችሉትን ቃልና ጥበብ እሰጣችኋለሁ።
\s5
\v 16 ነገር ግን በወላጆች፣ በወንደሞች፣ በዘመዶችና በጓደኞች ተላልፋችሁ ትሰጣላችሁ፣ ከእናንተም አንዳንዶቹን ይገድላሉ።
\v 17 በስሜ ምክንያት በሰው ሁሉ ትጠላላችሁ።
\v 18 ነገር ግን ከራሳችሁ ጠጒር አንዲቱ እንኳ አትጠፋም።
\v 19 በትዕግሥታችሁም ነፍሳችሁን ታተርፋላችሁ።
\s5
\v 20 ኢየሩሳሌም በሠራዊት ተከብባ ስታዩ ጥፋቷ መቃረቡን እወቁ።
\v 21 በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፣ በከተማይቱ መካከል ያሉትም ለቀው ይሂዱ፣ በገጠር ያሉት ደግሞ ወደ ከተማይቱ አይግቡ።
\v 22 የተጻፈው እንዲፈጸም እነዚህ ጊዜያት የበቀል ጊዜያት ናቸውና።
\s5
\v 23 በእነዚያ ቀኖች ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው! በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቊጣ ይወርዳል።
\v 24 በሰይፍም ስለት ይወድቃሉ፤ ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ሁሉ ምርኮኞች ተደርገው ይወሰዳሉ፤ የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ፣ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።
\s5
\v 25 በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ምልክቶች ይታያሉ። በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ከባሕርና ከማዕበል ድምፅ የተነሣ ተስፋ በመቊረጥ ይጨነቃሉ።
\v 26 ከፍርሃትና በዓለም ላይ ሊከሰቱ ያሉትን ነገሮች ከመሥጋት የተነሣ የሚዝሉ ሰዎችም ይኖራሉ። ምክንያቱም የሰማያት ኅይላት ይናወጣሉና።
\s5
\v 27 ከዚያም የሰው ልጅ በኅይልና በታላቅ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።
\v 28 ነገር ግን እነዚህ ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ፣ መዳናችሁ ስለ ቀረበ ንቁ፣ ቀና ብላችሁ ተመልከቱ።
\s5
\v 29 ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ነገራቸው፤ “የበለስ ዛፍና ሌሎች ዛፎችን ተመልከቱ።
\v 30 ቀንበጥ ሲያወጡ፣ በጋ እንደተቃረበ ታውቃላችሁ።
\v 31 ልክ እንደዚሁም እነዚህ ነገሮች መፈጸማቸውን ስታዩ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደ ቀረበ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 32 እውነቱን እነግራችኋለሁ፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከመፈጸማቸው በፊት ይህ ትውልድ አያልፍም።
\v 33 ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ቃሌ ግን አያልፍም።
\s5
\v 34 ልቅ በሆነ አኗኗር፣ በስካርና በጭንቀት ልባችሁ እንዳይከብድ ተጠንቀቁ። ምክንያቱም ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይመጣባችኋል።
\v 35 በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይም ይመጣባቸዋል።
\s5
\v 36 ነገር ግን ከሚከሠቱት ከአነዚህ ነገሮች ሁሉ እንድታመልጡና በሰው ልጅም ፊት ለመቆም እንድትበረቱ ሁልጊዜ ነቅታችሁ ጸልዩ።
\s5
\v 37 ስለዚህ ኢየሱስ በየቀኑ በቤተ መቅደስ ያስተምር፣ ሌሊቱን ደግሞ ወደ ደብረ ዘይት ተራራ እየወጣ ያሳልፍ ነበር።
\v 38 በቤተ መቅደስም ሲያስተምር ሰዎች ሁሉ ሊሰሙት በማለዳ ይመጡ ነበር።
\s5
\c 22
\cl ምዕራፍ 22
\p
\v 1 ፋሲካ የተባለው የቂጣ በዓል ተቃርቦ ነበር።
\v 2 የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ሕዝቡን ይፈሩ ስለ ነበር፣ ኢየሱስን እንዴት አድርገው እንደሚገድሉት ተመካከሩ።
\s5
\v 3 ሰይጣን ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ በሆነው በአስቆሮቱ ይሁዳ ገባበት።
\v 4 አርሱም ኢየሱስን እንዴት አድርጎ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ከካህናት አለቆችና ከሕዝብ መሪዎች ጋር ተነጋገረ።
\s5
\v 5 እነርሱም ደስ አላቸው፣ ገንዘብም ሊሰጡት ተስማሙ።
\v 6 እርሱም ኢየሱስን ለእነርሱ አሳልፎ ለመስጠት ሕዝብ የሌሉበትን ምቹ ጊዜ ይፈልግ ነበር።
\s5
\v 7 የፋሲካ በግ መሥዋዕት የሚደረግበት የቂጣ በዓል ደረሰ።
\v 8 ኢየሱስም ጴጥሮስንና ዮሐንስን፣ “ሂዱና የፋሲካ ምግብ እንድንበላ አዘጋጁልን” ብሎ ላካቸው።
\v 9 እነርሱም፣ “የት እንድናዘጋጅልህ ትፈልጋለህ?” ብለው ጠየቁት።
\s5
\v 10 እንዲህም ብሎ መለሰላቸው፣ “አድምጡ፣ ወደ ከተማው በገባችሁ ጊዜ የውሃ እንስራ ተሸክሞ የሚመጣ ሰው ያገኛችኋል። ይህን ሰው ወደሚገባበት ቤት ተከትላችሁ ግቡ።
\v 11 ከዚያም ለቤቱ ባለቤት፣ 'መምህሩ እንዲህ ይልሃል፤" የፋሲካን እራት ከደቀ መዛሙርቴ ጋር የምበላበት የእንግዳ ክፍል የት ነው?' በሉት።”
\s5
\v 12 እርሱም በፎቁ ላይ ሰፊና በሚገባ የተሰናዳ ክፍል ያሳያችኋል። ዝግጅቱንም በዚያ አድርጉ።
\v 13 ስለዚህ ወጥተው ሲሄዱ፣ ሁሉም ነገር እርሱ እንደተናገረው ሆኖ አገኙት። ከዚያም የፋሲካውን ምግብ አዘጋጁ።
\s5
\v 14 ሰዓቱ ሲደርስ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ዐብሮ ተቀመጠ።
\v 15 ከዚያም እንዲህ አላቸው፤ “መከራ ከመቀበሌ በፊት ይህን የፋሲካ እራት ከእናንተ ጋር ለመብላት በእጅጉ እጓጓ ነበር።
\v 16 በእግዚአብሔር መንግሥት እስከሚፈጸም ድረስ ከዚህ ምግብ ዳግመኛ እንደማልበላ እነግራችኋለሁና።"
\s5
\v 17 ከዚያም ኢየሱስ ጽዋውን አንሥቶ አመሰገነና እንዲህ አላቸው፤ “ይህን ውሰዱና ተካፈሉት።
\v 18 እላችኋለሁ፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከዚህ ወይን ፍሬ ዳግመኛ አልጠጣም።”
\s5
\v 19 እንጀራውን ወሰደ፣ ካመሰገነ በኋላ እንዲህ በማለት ቈርሶ ሰጣቸው፣ “ይህ ለእናንተ የተሰጠው ሥጋዬ ነው። እኔን እያሰባችሁ ተመገቡት።”
\v 20 በተመሳሳይ ሁኔታም፣ ከእራት በኋላ ጽዋውን አነሣና እንዲህ አለ፣ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ የፈሰሰ በደሜ የሚሆን ዐዲስ ኪዳን ነው።
\s5
\v 21 ነገር ግን እኔን አሳልፎ የሚሰጠኝ ከእኔ ጋር በማዕድ እየበላ መሆኑን ልብ በሉ።
\v 22 የሰው ልጅስ እንደተወሰነለት ይሆናል። ነገር ግን አሳልፎ ለሚሰጠው ለዚያ ሰው ወዮለት!"
\v 23 በዚህ ጊዜ እርስ በርሳቸው ይህን ነገር የሚያደርግ ማን እንደ ሆነ ተጠያየቁ።
\s5
\v 24 ከዚያም ከሁሉም የሚበልጥ ማን ሊሆን እንደሚገባው በመካከላቸው ጠብ ተነሣ። እርሱ እንዲህ አላቸው፣
\v 25 “የአሕዛብ ነገሥታት በሕዝብ ላይ ይገዛሉ፣ በእነርሱ ላይ ሥልጣን ያላቸውንም የተከበሩ ገዦች ይሏቸዋል።
\s5
\v 26 ነገር ግን በእናንተ ዘንድ እንዲህ አይሁን። ይልቅ ከእናንተ ታላቅ የሆነ እንደ ታናሽ ይሁን። እጅግ ተፈላጊ የሆነ እንደሚያገለግል ሰው ይሁን።
\v 27 በማዕድ ከተቀመጠውና ከሚያገለግለው የትኛው ታላቅ ነው? በማዕድ የተቀመጠ አይደለምን? እኔ ግን በእናንተ መካከል እንደሚያገለግል ሰው ነኝ።
\s5
\v 28 ነገር ግን እናንተ በፈተናዬ ከእኔ ጋር ጸንታችኋል። አብ ለእኔ መንግሥትን እንደ ሰጠኝ፣
\v 29 በመንግሥቴ በእኔ ማዕድ እንድትበሉና እንድትጠጡ መንግሥትን እሰጣችኋለሁ።
\v 30 ደግሞም በዙፋን ተቀምጣችሁ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይ ትፈርዳላችሁ።
\s5
\v 31 ስምዖን ሆይ፣ ስምዖን ሆይ፣ ተጠንቀቅ፤ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥርህ ፈልጎ ጠይቋል።
\v 32 ነገር ግን እኔ እምነትህ እንዳይጠፋ ጸለይሁልህ። ዳግመኛ ከተመለስህ በኋላ ወንድሞችህን አበርታቸው።”
\s5
\v 33 ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ ወደ እስር ቤትም ይሁን ወደ ሞት ከአንተ ጋር ለመሄድ ዝግጁ ነኝ” አለው።
\v 34 ኢየሱስ፣ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ አላውቀውም ብለህ ሦስት ጊዜ እንደምትክደኝ እነግርሃለሁ” ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 35 ከዚያም ኢየሱስ፣ “ያለ ገንዘብ ቦርሣ፣ ወይም ያለ ስንቅ ወይም ያለ ጫማ በላክኋችሁ ጊዜ ያጣችሁት ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱ፣ “ምንም አላጣንም" ብለው መለሱለት።
\v 36 ከዚያም እንዲህ አላቸው፣ “አሁን ግን የገንዘብ ቦርሣ ያለው ቦርሣውን፣ ደግሞም ስንቁን ይያዝ። ጎራዴ የሌለው ልብሱን ሽጦ ጎራዴ ይግዛ።
\s5
\v 37 እላችኋለሁ፣ 'ከወንበዴዎች እንደ አንዱ ተቈጠረ' ተብሎ ስለ እኔ የተጻፈው መፈጸም አለበት። ይህ ስለ እኔ የተነገረው አሁን እየተፈጸመ ነው።"
\v 38 ከዚያም እነርሱ፣ “ጌታ ሆይ፣ ተመልከት፣ እዚህ ሁለት ጎራዴዎች አሉ” አሉት። እርሱም “ይበቃል” አላቸው።
\s5
\v 39 ከእራት በኋላ ኢየሱስ ብዙ ጊዜ እንደሚያደርገው ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄደ፣ ደቀ መዛሙርቱም ተከተሉት።
\v 40 እዚያ በደረሱ ጊዜ፣ “ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጸልዩ” አላቸው።
\s5
\v 41 ከእነርሱ የድንጋይ ውርወራ ያህል ራቅ ብሎ ሄደና ተንበርክኮ፣
\v 42 “አባት ሆይ፣ ብትወድ ይህን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፣ ነገር ግን የአንተ ፈቃድ እንጂ የእኔ ፈቃድ አይሁን” በማለት ጸለየ።
\s5
\v 43 የሚያበረታታው መልአክም ከሰማይ መጣለት።
\v 44 በጣር ውስጥ ሆኖ በጣም እየቃተተ ጸለየ፣ ላቡም እንደ ትልልቅ የደም ጠብታዎች ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር።
\s5
\v 45 ከጸሎቱ ተነሥቶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመጣ ጊዜ ከሐዘን የተነሣ ተኝተው አገኛቸውና፣
\v 46 “ለምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሡና ጸልዩ” አላቸው።
\s5
\v 47 ገና እየተናገረ እያለ ብዙ ሰዎች ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ይሁዳ እየመራቸው መጡ። ይሁዳም ሊስመው ወደ ኢየሱስ ቀረበ፤
\v 48 ነገር ግን ኢየሱስ፣ “ይሁዳ ሆይ፣ የሰውን ልጅ በመሳም አሳልፈህ ትሰጣለህን?” አለው።
\s5
\v 49 በኢየሱስ ዙሪያ የነበሩት እየሆነ ያለውን ነገር ባዩ ጊዜ፣
\v 50 “በጎራዴ እንምታቸውን?” አሉ። ከዚያም ከመካከላቸው አንዱ በጎራዴ የሊቀ ካህኑን አገልጋይ ቀኝ ጆሮ መታና ቈረጠው።
\v 51 ኢየሱስ፣ “ይህ ይብቃ” አለ። የአገልጋዩንም ጆሮ ዳሰሰ፣ ፈወሰውም።
\s5
\v 52 ኢየሱስ ሊያጠቁት ለመጡ የካህናት አለቆችና የቤተ መቅደስ መሪዎች እንዲሁም ሽማግሌዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወንበዴን እንደሚይዝ ሰው ጐራዴና ዱላ ይዛችሁ ትመጡብኛላችሁን?
\v 53 በየዕለቱ በቤተ መቅደስ ከእናንተ ጋር ሳለሁ አልያዛችሁኝም። ነገር ግን ይህ የእናንተና የጨለማው ሥልጣን ጊዜ ነው።”
\s5
\v 54 ያዙትና ወሰዱት፣ ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤትም አመጡት። ጴጥሮስ ግን ከርቀት ተከተለው።
\v 55 በግቢው መሓል እሳት ካቀጣጠሉና ዐብረው ከተቀመጡ ጴጥሮስ መጥቶ በመካከላቸው ተቀመጠ።
\s5
\v 56 በእሳቱ ብርሃን እንደተቀመጠም አንዲት ገረድ አየችውና በቀጥታ ተመልክታው፣ “ይህ ሰው ደግሞ ከእርሱ ጋር ነበር” አለች።
\v 57 ጴጥሮስ ግን፣ “ሴትዮ፣ የምትዪውን ሰው አላውቀውም” ብሎ ካደ።
\v 58 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ደግሞ፣ ሌላ ሰው አየውና፣ “አንተም ከእነርሱ አንዱ ነህ” አለው። ነገር ግን ጴጥሮስ፣ “አንተ ሰው፣ እኔ አይደለሁም” አለ።
\s5
\v 59 ከአንድ ሰዓት ያህል ጊዜ በኋላ፣ ሌላ ሰው፣ “በእውነት ይህ ሰው ደግሞ ገሊላዊ ስለ ሆነ ከእርሱ ጋር ነበረ” በማለት በጥብቅ ተናገረ።
\v 60 ነገር ግን ጴጥሮስ፣ “አንተ ሰው የምትለውን አላውቅም” አለ። ይህን እየተናገረ እያለ ወዲያው ዶሮ ጮኸ።
\s5
\v 61 ጌታም ዞር አለና ጴጥሮስን ተመለከተው። ጴጥሮስም፣ ጌታ “ዛሬ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ያለውን ቃል አስታወሰ።
\v 62 ጴጥሮስ ወደ ውጭ ወጣና መራራ ልቅሶ አለቀሰ።
\s5
\v 63 ከዚያም ኢየሱስን ይጠብቁ የነበሩት ሰዎች እያላገጡበት ደበደቡት። ዐይኖቹን ከሸፈኑ በኋላ፣
\v 64 “እስቲ ትንቢት ተናገር። አሁን የመታህ ሰው ማን ነው?” በማለት ጠየቁት።
\v 65 እየተሳደቡ፣ ሌሎች ብዙ ነገሮችን በኢየሱስ ላይ ተናገሩ።
\s5
\v 66 እንደነጋም የሕዝቡ ሽማግሌዎች፣ ከካህናት አለቆችና ከሕግ መምህራን ጋር ዐብረው ተሰበሰቡ። ከዚያም ኢየሱስን ወደ ሸንጎው ፊት አቀረቡትና፣
\v 67 “ክርስቶስ ከሆንህ ንገረን” አሉት። እርሱ ግን፣ “እኔ ብነግራችሁ አታምኑም፣
\v 68 ደግሞም ብጠይቃችሁ አትመልሱም።
\s5
\v 69 ነገር ግን ከአሁን ጀምሮ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር ኅይል ቀኝ ይቀመጣል” አላቸው።
\v 70 ሁሉም በአንድነት፣ “እንግዲህ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነሃ?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እኔ እንደ ሆንሁ እናንተ ትናገራላችሁ” አላቸው። እነርሱ፣
\v 71 “እንግዲህ ለምን ምስክር እንፈልጋለን? ሲናገር እኛ ራሳችን ከአፉ ሰምተነዋል” አሉ።
\s5
\c 23
\cl ምዕራፍ 23
\p
\v 1 ሕዝቡ በጠቅላላ ተነሥተው ቆሙ፣ ኢየሱስንም በጲላጦስ ፊት አቀረቡት።
\v 2 “ይህ ሰው ራሱን ክርስቶስ፣ ንጉሥ ነኝ ሲልና ለቄሣር ግብር እንዳይከፈል በመከልከል አገር ሲበጠብጥ አግኝተነዋል” በማለት ይከሱት ጀመር።
\s5
\v 3 ጲላጦስ፣ “አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?” በማለት ጠየቀው። ኢየሱስም፣ “አንተ አልህ” ብሎ መለሰለት።
\v 4 ጲላጦስ የካህናት አለቆችንና የተሰበሰቡትን ሕዝብ፣ “በዚህ ሰው ምንም ስሕተት አላገኘሁበትም” አላቸው።
\v 5 እነርሱ ግን፣ “ከገሊላ ጀምሮ በመላው ይሁዳ፣ እስከዚህ ስፍራም እንኳ እያስተማረ ሕዝቡን ያነሣሣል” በማለት አጥብቀው ተናገሩ።
\s5
\v 6 ስለዚህ ጲላጦስ ይህን በሰማ ጊዜ ሰውየው ገሊላዊ እንደ ሆነ አጠያየቀ።
\v 7 ከሄሮድስ ሥልጣን በታች እንደ ሆነ ተረድቶ በዚያው ሰሞን ኢየሱስን በኢየሩሳሌም ወደ ነበረው ሄሮድስ ላከው።
\s5
\v 8 ሄሮድስ ኢየሱስን ባየው ጊዜ በጣም ደስ አለው፣ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ ሊያየው ሲፈልግ ነበር። ስለ እርሱ ሰምቶ የነበረ ሲሆን፣ አንዳንድ ተአምራት ሲያደርግ ለማየትም ተስፋ ነበረው።
\v 9 ሄሮድስ ኢየሱስን በብዙ ቃሎች ቢጠይቅም፣ ኢየሱስ ግን ምንም መልስ አልሰጠውም።
\v 10 በዚህ ጊዜ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ተነሥተው ቆሙና በኅይለ ቃል ከሰሱት።
\s5
\v 11 ሄሮድስ ከወታደሮቹ ጋር በመሆን ኢየሱስን ሰደበው፣ አላገጠበትም፤ ጥሩ ልብስ ካለበሰው በኋላ መልሶ ወደ ሄሮድስ ላከው።
\v 12 ከዚያን ቀን ጀምሮ ሄሮድስና ጲላጦስ ወዳጆች ሆኑ (ከዚያ በፊት አንዱ የአንዱ ጠበኞች ነበሩ)።
\s5
\v 13 ከዚያም ጲላጦስ የካህናት አለቆችን፣ ገዢዎችንና ሕዝቡን አንድ ላይ ጠራ፤
\v 14 እንዲህም አላቸው፤ “ ይህን ሰው ሰዎችን ለክፉ ድርጊት የሚያነሣሣ አድርጋችሁ ወደ እኔ አመጣችሁት፣ እኔም በፊታችሁ ከጠየቅሁት በኋላ ፣ እነሆ፣ እርሱን በምትከሱባቸው ነገሮች ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።
\s5
\v 15 ሄሮድስም ቢሆን ምንም ነገር አላገኘበትም፤ ምክንያቱም መልሶ ወደ እኛ ልኮታልና፤ እነሆ፣ እርሱን ለሞት የሚያደርስ በዚህ ሰው የተፈጸመ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።
\v 16 ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።" ጲላጦስም በበዓሉ ለአይሁድ አንድ እስረኛ የመፍታት ግዴታ ነበረበት።
\v 17
\s5
\v 18 ነገር ግን እነርሱ በአንድነት፣ “ይህን ሰው አስወግደው፣ በርናባስን ለእኛ ፍታልን!" በማለት ጮኹ።
\v 19 በርናባስ በከተማይቱ ውስጥ አንድ ዐይነት ዐመፅና ግድያ በመፈጸም የታሰረ ሰው ነበር።
\s5
\v 20 ጲላጦስ ኢየሱስን ሊፈታ ፈልጎ እንደ ገና ሕዝቡን አነጋገራቸው።
\v 21 ነገር ግን ሕዝቡ፣ “ስቀለው፣ ስቀለው” እያሉ ጮኹ።
\v 22 ለሦስተኛ ጊዜም እንዲህ አላቸው፤ “ለምን? ይህ ሰው የሠራው ክፋት ምንድን ነው? ለሞት ቅጣት የሚያበቃ ነገር አላገኘሁበትም። ስለዚህ ቀጥቼው እለቀዋለሁ።”
\s5
\v 23 እነርሱ ግን ኢየሱስ እንዲሰቀል በመጠየቅ ሳያቋርጡ አብዝተው ጮኹ። ጩኸታቸውም ጲላጦስን አሳመነው።
\v 24 ስለዚህ ጲላጦስ ፍላጎታቸውን ለማሟለት ወሰነ።
\v 25 እንዲፈታላቸው የጠየቁትን፣ በዐመፅና በግድያ ምክንያት የታሰረውን ሰው ለቀቀላቸው። ኢየሱስን ግን ለፈቃዳቸው አሳልፎ ሰጠው።
\s5
\v 26 እየወሰዱት ሳሉ፣ ከገጠር ይመጣ የነበረ ስምዖን የተባለ የቀሬናን ሰው ያዙና ኢየሱስ ይሸከመው የነበረውን መስቀል አሸከሙት።
\s5
\v 27 እጅግ ብዙ ሕዝብና ለእርሱ የሚያዝኑና የሚያለቅሱ ሴቶች ይከተሉት ነበር።
\v 28 ኢየሱስም ወደ እነርሱ ዞር ብሎ፣ “የኢየሩሳሌም ሴቶች ሆይ፣ ለእኔ ሳይሆን ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ” አለ።
\s5
\v 29 እነሆ፣ 'መካን የሆኑና ያልወለዱ ማኅፀኖች እንዲሁም ያላጠቡ ጡቶች የተባረኩ ናቸው' የሚሉባቸው ቀኖች ይመጣሉና።
\v 30 ከዚያም ተራሮችን፣ 'በላያችን ውደቁ፣ ኮረብቶችንም ክደኑን ማለትይጀምራሉ።'
\v 31 ዛፉ እርጥብ እያለ ይህን ነገር ካደረጉ፣ በሚደርቅበት ጊዜ ምን ይሆናል?"
\s5
\v 32 ሌሎች ሁለት ወንጀለኞችም ከእርሱ ጋር ሊገደሉ ተወሰዱ።
\s5
\v 33 የራስ ቅል ወደሚባል ቦታ በደረሱ ጊዜ፣ እርሱን ከሌሎች ሁለት ወንጀለኞች ጋር ሰቀሉት፥ አንደኛው በቀኙ ሌላኛው በግራው ነበሩ።
\v 34 ኢየሱስ፣”አባት ሆይ፣ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” አለ። ዕጣ ተጣጥለውም ልብሱን ተከፋፈሉ።
\s5
\v 35 “ሌሎችን አዳነ፣ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠ ክርስቶስ ከሆነ አስኪ ራሱን ያድን” በማለት ገዢዎቹ እየዘበቱበት ሳለ ሕዝቡ ቆመው ያዩ ነበር።
\s5
\v 36 ወታደሮቹም ወደ እርሱ ቀርበው፣
\v 37 “አንተ ንጉሥ ከሆንህ ራስህን አድን” በማለት እያሾፉበት ኮምጣጤ ሰጡት።
\v 38 “የአይሁድ ንጉሥ” የሚል ምልክትም ከበላዩ ተደርጎ ነበር።
\s5
\v 39 ከተሰቀሉት ወንጀለኞች አንዱ፣ "አንተ ክርስቶስ ነህን? ራስህንም እኛንም አድን” በማለት ሰደበው።
\v 40 ሌላኛው ግን እየገሠጸው፣ “ከፍርድ በታች ሆነህ እግዚአብሔርን አትፈራምን? እኛ በዚህ ያለነው እንደ ሥራችን ስለ ሆነ፣ ትክክል ነው፣
\v 41 ነገር ግን ይህ ሰው ምንም ጥፋት አላደረገም” ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 42 ቀጥሎም፣ “ኢየሱስ ሆይ፣ በመንግሥትህ ስትመጣ አስታውሰኝ” አለ።
\v 43 ኢየሱስ፣ “እውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትሆናለህ” አለው።
\s5
\v 44 ጊዜው ስድስት ሰዓት ገደማ ነበር፣ የፀሐይ ብርሃን በመቋረጡ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ላይ ጨለማ ሆነ።
\v 45 ከዚያም የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከመሐል ተቀደደ።
\s5
\v 46 ኢየሱስ፣ “አባት ሆይ፣ ነፍሴን በእጅህ አኖራለሁ” በማለት በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህን ከተናገረ በኋላ ሞተ።
\v 47 መቶ አለቃው የተደረገውን ነገር ባየ ጊዜ፣ “ይህ ሰው በእውነት ጻድቅ ነበር” በማለት እግዚአብሔርን አከበረ።
\s5
\v 48 ሁኔታውን ለማየት እጅግ ብዙ ሰዎች በመጡ ጊዜ፣ የተደረጉትን ነገሮች አይተው ደረታቸውን እየደቁ ተመለሱ።
\v 49 ነገር ግን ከገሊላ ጀምሮ የተከተሉት አንዳንድ ወንዶችና ሴቶች ከርቀት ቆመው ይህን ድርጊት ይከታተሉ ነበር።
\s5
\v 50 እነሆ፣ የእግዚአብሔርን መንግሥት መምጣት የሚጠባበቅ፣ ከአይሁድ ከተማ፣ ከአርማቲያ የሆነ ዮሴፍ የሚባል
\v 51 (በውሳኔያቸውና በድርጊታቸው ያልተስማማ) አንድ መልካምና ጻድቅ ሰው ነበረ።
\s5
\v 52 ይህ ሰው ወደ ጲላጦስ በመቅረብ የኢየሱስን አስከሬን እንዲሰጠው ጠየቀው።
\v 53 አስክሬኑን አውርዶ በጥሩ የተልባ እግር ጨርቅ ከፈነውና ማንም ባልተቀበረበት ከድንጋይ በተወቀረ መቃብር ውስጥ አኖረው።
\s5
\v 54 ጊዜው የዝግጅት ቀን የነበረ ሲሆን፣ ሰንበትም እየገባ ነበር።
\v 55 ከእርሱ ጋር ከገሊላ የመጡ ሴቶች ተከትለውት በመሄድ መቃብሩንና አስከሬኑ እንዴት እንዳረፈ አዩ።
\v 56 ከዚያም ተመልሰው ቅመማ ቅመምና ቅባቶችን አዘጋጁ። ሰንበት ስለ ነበር በሕጉ መሠረት ዐረፉ።
\s5
\c 24
\cl ምዕራፍ 24
\p
\v 1 በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ሴቶች ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው በጣም ማልደው ወደ መቃብሩ መጡ።
\v 2 ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት።
\v 3 ወደ ውስጥ ገቡ፣ ነገር ግን የጌታ ኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።
\s5
\v 4 ስለዚህ ነገር ግራ ተጋብተው ሳሉ፣ የሚያብረቀርቅ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በድንገት ከአጠገባቸው ቆመው አገኙ።
\v 5 ሴቶቹ በፍርሃት ተሞልተውና ወደ መሬት አቀርቅረው ሳሉ፣ ሰዎቹ ፣“ስለምን ሕያውን ከሙታን መካከል ትፈልጋላችሁ?
\s5
\v 6 እርሱ በዚህ የለም፣ ተነሥቷል! ገና በገሊላ ሳለ፣
\v 7 እንዴት በኃጢአተኞች ሰዎች እጅ ተላልፎ እንደሚሰጥ፣ እንደሚሰቀልና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሣ የነገራችሁን አስታውሱ" አሏቸው።
\s5
\v 8 ሴቶቹ ቃሎቹን አስታወሱ፣
\v 9 ከመቃብሩም ተመለሱና እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለዐሥራ አንዱና ለተቀሩትም ነገሩ።
\v 10 መግደላዊት ማርያም፣ ዮሐናና የያዕቆብ እናት ማርያም እንዲሁም ሌሎች ሴቶች ሁኔታውን ለሐዋርያት ነገሯቸው።
\s5
\v 11 ነገር ግን ይህ ንግግር ለሐዋርያቱ ቀልድ ስለ መሰላቸው፣ ሴቶቹን አላመኗቸውም፣
\v 12 ሆኖም ግን ጴጥሮስ ተነሣና እየሮጠ ወደ መቃብሩ ሄደ፣ ከዚያም አጎንብሶ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ የተልባው እግር ጨርቅ ለብቻው ተቀምጦ አየ። ከዚያ በኋላ ጴጥሮስ ምን ተፈጥሮ ይሆን ብሎ እያሰበ ወደ ቤቱ ተመለሰ።
\s5
\v 13 እነሆ፣ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያው ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ርቆ ወደሚገኝ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር እየተጓዙ ነበር።
\v 14 ስለሆኑት ነገሮች ሁሉ በመንገዳቸው ላይ እርስ በርስ ይነጋገሩ ነበር።
\s5
\v 15 እየተነጋገሩና እየተጠያየቁ በመሄድ ላይ ሳሉ፣ ኢየሱስ ወደ እነርሱ ተጠግቶ ይሄድ ነበር።
\v 16 ነገር ግን እርሱን እንዳያውቁት ዐይኖቻቸው ተይዘው ነበር።
\s5
\v 17 ኢየሱስ፣ “እናንተ ሁለታችሁ እየተጓዛችሁ የምትነጋገሩት ስለምንድን ነው?” አላቸው። ያዘኑ መስለው ቆም አሉ።
\v 18 ስሙ ቀለዮጳ የተባለ ከሁለቱ አንዱ፣ “በኢየሩሳሌም ሰሞኑን የተደረጉትን ነገሮች የማታውቅ አንተ ብቻ ነህን?" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 19 ኢየሱስም፣ “ነገሮቹ ምንድን ናቸው?” አላቸው።
\v 20 እነርሱም እንዲህ ብለው መለሱለት፣ “የካህናት አለቆችና ገዢዎቻችን ኢየሱስ የተባለውን ናዝራዊና ነቢይ እንዴት አድርገው እንደ ፈረዱበትና ለሞትና ለስቅላት አሳልፈው እንደ ሰጡት ነዋ።
\s5
\v 21 እስራኤልን ነጻ ያወጣል ብለን ተስፋ ያደረግነው እርሱን ነበር። አዎን፣ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ይህ ነገር ከሆነ አሁን ሦስተኛ ቀኑ ነው”
\s5
\v 22 ነገር ግን ጠዋት ወደ መቃብሩ የሄዱ ከእኛ ጋር የሆኑ አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን።
\v 23 ሥጋውን ባላገኙ ጊዜ፣ በመቃብሩ ውስጥ ሥጋውን እንዳላገኙና እርሱ ሕያው ሆኗል ብለው የነገሯቸውን የመላእክት ራእይ አይተናል አሉ።
\v 24 ከእኛ ጋር ካሉት ወንዶችም አንዳንዶች ወደ መቃብሩ ሄደው ልክ ሴቶቹ እንዳሉት ሆኖ አገኙት። ነገር ግን እርሱን አላዩትም”።
\s5
\v 25 ኢየሱስም፣ “ነቢያት የተናገሩትን ሁሉ ለማመን የዘገያችሁ እናንተ ሞኞች!
\v 26 ክርስቶስ በእነዚህ ነገሮች መሠቃየቱና ወደ ክብሩ መግባቱ ግድ መሆኑን አታውቁምን?" አላቸው።
\v 27 ከዚያም ከሙሴ ጀምሮ እስከ ነቢያት መጻሕፍት፣ በመጻሕፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተነገረውን ተረጐመላቸው።
\s5
\v 28 ወደሚሄዱበት መንደር በተቃረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ቀደም ቀደም እያለ መሄድ ጀመረ።
\v 29 ነገር ግን እነርሱ፣ “ቀኑ እየመሸ ጊዜውም እያለፈ ስለ ሆነ ከእኛ ጋር እደር” ብለው ጎተጎቱት። ስለዚህ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ሊያድር ሄደ።
\s5
\v 30 ለመብላት ከእነርሱ ጋር በማዕድ በተቀመጠ ጊዜ፣ እንጀራውን ወሰደና ከባረከው በኋላ ቈርሶ ሰጣቸው።
\v 31 በዚህ ጊዜ ዐይኖቻቸው ተከፈቱና አወቁት። እርሱ ግን ከዐይናቸው ተሰወረባቸው።
\v 32 እርስ በርሳቸው፣ “በመንገድ ላይ አብረን ሳለን ሲያናግረንና መጻሕፍትን ሲከፍት ልባችን በውስጣችን ይቃጠልብን አልነበርምን?” ተባባሉ።
\s5
\v 33 በዚያው ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ዐሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ተሰብስበው እንዲህ እያሉ አገኟቸው፤
\v 34 “ጌታ በእርግጥ ተነሥቷል፣ ለስምዖንም ታይቷል።”
\v 35 ከዚያም በመንገድ ላይ የሆነውን ነገርና ኢየሱስ በማዕድ እንጀራን በሚቈርስበት ጊዜ እንዴት እንደ ታያቸው ተናገሩ።
\s5
\v 36 እነዚህን ነገሮች እየተናገሩ እያሉ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው።
\v 37 እነርሱም ስለ ተሸበሩና በፍርሃት ስለ ተዋጡ መንፈስ ያዩ መሰላቸው።
\s5
\v 38 ኢየሱስ፣ “ለምን ትጨነቃላችሁ? ለምንስ በልባችሁ ጥያቄዎች ይነሣሉ?
\v 39 እኔው ራሴ ስለ መሆኔ እጆቼንና እግሮቼን እዩ። ዳሳችሁም እዩኝ። በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውም" አላቸው።
\v 40 ይህን ተናግሮ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው።
\s5
\v 41 ከደስታ የተነሣ ማመን ተስኗቸው ግራ ተጋብተው ሳሉ፣ ኢየሱስ፣ “የሚበላ ጥቂት ነገር ይኖራችኋል?” አላቸው።
\v 42 የተጠበሰ ዐሣ ሰጡት።
\v 43 ኢየሱስም ወስዶ በፊታቸው በላው።
\s5
\v 44 እንዲህም አላቸው፤ “ከእናንተ ጋር በነበርሁ ጊዜ በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙራት የተጻፈው ሁሉ መፈጸም እንደሚገባው ነግሬአችሁ ነበር።”
\s5
\v 45 ከዚያም መጻሕፍትን ይረዱ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው።
\v 46 እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ ክርስቶስ መሠቃየት፣ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን መካከል መነሣት እንደሚገባው በመጻሕፍት ተጽፏል።
\v 47 ደግሞም ንስሐና የኃጢአት ይቅርታ ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለአሕዛብ ሁሉ በስሙ መሰበክ አለበት።
\s5
\v 48 እናንተ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ናችሁ።
\v 49 እነሆ፣ የአባቴን ተስፋ በእናንተ ላይ እልካለሁ። ኅይልን ከላይ እስከምትቀበሉ ድረስ በዚህ ከተማ ሆናችሁ ተጠባበቁ።"
\s5
\v 50 ከዚያም ኢየሱስ ወደ ቢታንያ እስከሚቃረቡ ድረስ ይዟቸው ሄደ። እጆቹንም አነሣና ባረካቸው፤
\v 51 እየባረካቸውም ሳለ ወደ ሰማይ ከፍ ከፍ አለ።
\s5
\v 52 ስለዚህ እነርሱ ሰገዱለት፣ እጅግ ደስ እያላቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
\v 53 በቤተ መቅደስም ያለ ማቋረጥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።

1673
44-JHN.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1673 @@
\id JHN
\ide UTF-8
\h ዮሐንስ
\toc1 ዮሐንስ
\toc2 ዮሐንስ
\toc3 jhn
\mt ዮሐንስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤
\v 2 ይህም ቃል ከመጀመሪያው ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡
\v 3 ሁሉም ነገር የተሠራው በእርሱ አማካይነት ነው፤ ከተሠሩት ነገሮች ሁሉ ያለ እርሱ የተሠራ አንድም ነገር አልነበረም፡፡
\s5
\v 4 በእርሱ ሕይወት ነበረ፤ያም ሕይወት የሰው ሁሉ ብርሃን ነበር፡፡
\v 5 ብርሃኑ በጨለማ ይበራል፤ ጨለማም ሊያጠፋው አልቻለም፡፡
\s5
\v 6 ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡
\v 7 ሁሉም በእርሱ እንዲያምኑ እርሱ ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ።
\v 8 ስለ ብርሃን ሊመሰክር መጣ እንጂ ዮሐንስ ራሱ ብርሃን አልነበረም፡፡
\s5
\v 9 ወደ ዓለም የሚመጣውና ለሰው ሁሉ ብርሃን ሰጭ የሆነው እውነተኛ ብርሃን እየመጣ ነበር፡፡
\s5
\v 10 እርሱ በዓለም ውስጥ ነበር፤ ዓለሙም የተሠራው በእርሱ ነው፤ ዓለም ግን አላወቀውም፤
\v 11 የራሱ ወደ ሆኑት መጣ፤ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም፡፡
\s5
\v 12 ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆንን መብት ሰጣቸው፡፡
\v 13 እነርሱም ከደምና ከሥጋ ወይም ከሰው ፈቃድ አልተወለዱም፤ ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ፡፡
\s5
\v 14 ቃል ሥጋ ሆነ፤ በመካከላችንም ዐደረ፤ እኛም ጸጋና እውነት የተሞላውን ከአብ ዘንድ ያለውን የአንድያ ልጁን ክብር አየን፡፡
\v 15 ዮሐንስ ስለ እርሱ መሰከረ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ፣ «ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ ይበልጣል፤ 'ከእኔ በፊት ነበርና' ያልኋችሁ ይህ ነው» ይል ነበር፡፡
\s5
\v 16 ከእርሱ ሙላት ሁላችንም በጸጋ ላይ ጸጋ ተቀበልን፤
\v 17 ሕግ በሙሴ በኩል ተሰጥቶ ነበር፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ በኩል መጣ፡፡
\v 18 በየትኛውም ጊዜ እግዚአብሔርን ያየው አንድም ሰው የለም፤ ነገር ግን በአባቱ ዕቅፍ ያለውና እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው አንድያ ልጁ እርሱ እግዚአብሔርን እንዲታወቅ አደረገው፡፡
\s5
\v 19 አይሁድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን ልከው፣ «አንተ ማን ነህ?» ብለው በጠየቁት ጊዜ፣ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው፡፡
\v 20 እርሱ በግልጽ ተናገረ አልካደምም፤ ነገር ግን፣ «እኔ ክርስቶስ አይደለሁም» ብሎ መለሰላቸው።
\v 21 ስለዚህ እነርሱም፣ «ታዲያ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን?» ብለው ጠየቁት፤ እርሱ፣ «አይደለሁም» አላቸው። እነርሱ፣ «ነቢዩ ነህን?» አሉት፤ እርሱ፣ «አይደለሁም» አለ፡፡
\s5
\v 22 ከዚያም እነርሱ፣ «ለላኩን መልስ መስጠት እንድንችል፣ አንተ ማን ነህ? ስለ ራስህስ ምን ትላለህ?» አሉት፡፡
\v 23 እርሱ፣ «ልክ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለው፡- 'የጌታን መንገድ አስተካክሉ' እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ» አላቸው፡፡
\s5
\v 24 ከፈሪሳውያን የተላኩ ሰዎችም ነበሩ።
\v 25 እነርሱ፣ «ክርስቶስ፣ ኤልያስ ወይም ነቢዩ ካልሆንህ፣ ታዲያ ለምን ታጠምቃለህ?» ብለው ጠየቁት፡፡
\s5
\v 26 ዮሐንስ፣ «እኔ በውሃ አጠምቃለሁ፤ ይሁን እንጂ እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ ቆሟል፤
\v 27 ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ነው፤ እኔ የጫማውን ማሰሪያ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ ነኝ» በማለት መለሰላቸው፤
\v 28 ይህ ሁሉ የሆንው ዮሐንስ ሲያጠምቅ በነበረበት በዮርዳኖስ ማዶ በምትገኘው በቢታንያ ነበር፡፡
\s5
\v 29 በማግስቱ ዮሐንስ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ ተመልክቶ እንዲህ አለ፤ «እነሆ፣ የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ይኸውና!
\v 30 'ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበረ ከእኔ ይበልጣል' ብዬ ስለ እርሱ የነገርኋችሁ እርሱ ነው፡፡
\v 31 እኔ አላወቅሁትም ነበር፤ ነገር ግን እርሱ ለእስራኤል ይገለጥ ዘንድ እኔ በውሃ እያጠመቅሁ መጣሁ፡፡»
\s5
\v 32 ዮሐንስ እንዲህ ሲል መሰከረ፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሰማይ እንደ ርግብ ሲወርድና በእርሱ ላይ ሲያርፍ አየሁ፡፡
\v 33 እኔ አላወቅሁትም ነበር፤ ነገር ግን በውሃ እንዳጠምቅ የላከኝ እርሱ፣ 'መንፈስ ሲወርድበትና ሲያርፍበት የምታየው፣ በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው እርሱ ነው' አለኝ፡፡
\v 34 እኔ ይህን አይቻለሁ፤ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነም መስክሬአለሁ፡፡»
\s5
\v 35 ደግሞም በማግስቱ፣ ዮሐንስ ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ቆሞ ሳለ፣
\v 36 ኢየሱስን በአጠገባቸው ሲያልፍ አዩት፤ ዮሐንስም፣ «እነሆ፣ የእግዚአብሔር በግ» አለ፡፡
\s5
\v 37 ሁለቱ ደቀ መዛሙርት፣ ዮሐንስ ይህን ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ተከተሉት፤
\v 38 ከዚያም ኢየሱስ መለስ ብሎ ሲከተሉት አየና፣ «ምን ትፈልጋላችሁ?» አላቸው፡፡ እነርሱ፣ «ረቢ የት ነው የምትኖረው?» አሉት። ረቢ ማለት 'መምህር' ማለት ነው።
\v 39 እርሱ፣ «ኑና እዩ» አላቸው፡፡ ከዚያም እነርሱ መጥተው የሚኖርበትን አዩ፤ በዚያም ቀን ዐብረውት ዋሉ፤ ሰዓቱም ዐሥረኛው ሰዓት ያህል ሆኖ ነበርና፡፡
\s5
\v 40 ዮሐንስ ሲናገር ሰምተው ኢየሱስን ከተከተሉት ከሁለቱ አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ ነበረ፡፡
\v 41 እርሱ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ጴጥሮስን አገኘውና፣ «መሲሑን አግኝተነዋል» አለው። መሲሕ 'ክርስቶስ ማለት ነው'፡፡
\v 42 ወደ ኢየሱስም አመጣው፡፡ ኢየሱስ ጴጥሮስን ተመለከተውና፣ «አንተ የዮና ልጅ ስምዖን ነህ፤ ኬፋ ትባላለህ» አለው። ኬፋ 'ጴጥሮስ ማለት ነው'፡፡
\s5
\v 43 በማግስቱ፣ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ በፈለገ ጊዜ፣ ፊልጶስን አግኝቶ፣ «ተከተለኝ» አለው፡፡
\v 44 ፊልጶስም ጴጥሮስና እንድርያስ ከሚኖሩበት ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር፡፡
\v 45 ፊልጶስ ናትናኤልን አገኘውና፣ «ሙሴ በሕግ፣ ነቢያትም በትንቢት የጻፉለትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስ አግኝተነዋል» አለው፡፡
\s5
\v 46 ናትናኤል፣ «ከናዝሬት መልካም ነገር ይወጣልን?» አለው፡፡ ፊልጶስም መጥተህ እይ አለው፡፡
\v 47 ኢየሱስ፣ ናትናኤል ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ፣ «እነሆ፣ ተንኰል የሌለበት እውነተኛ እስራኤላዊ!» አለ።
\v 48 ናትናኤል፣ «እንዴት ታውቀኛለህ?» አለው፡፡ኢየሱስም፣ «ገና ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አየሁህ» ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 49 ናትናኤል፣ «አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ!» ብሎ መለሰለት፡፡
\v 50 ኢየሱስ፣ «ከበለስ ዛፍ ሥር ሳለህ አየሁህ ስላልሁህ አመንህን? ገና ከዚህ የሚበልጡ ነገሮችን ታያለህ» ብሎ መለሰለት፡፡
\v 51 ኢየሱስ፣ «እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ሰማያት ሲከፈቱ መላእክትም በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ» አለ፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በሦስተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረ፤ የኢየሱስም እናት በዚያ ነበረች።
\v 2 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ተጠርተው ነበር፡፡
\s5
\v 3 የወይን ጠጁ ባለቀ ጊዜ፣ የኢየሱስ እናት ኢየሱስን፣ «የወይን ጠጅ እኮ ዐልቆባቸዋል» አለችው፡፡
\v 4 ኢየሱስ መልሶ፣ «አንቺ ሴት፣ ከዚህ ጋር እኔ ምን ጉዳይ አለኝ? ጊዜዬ እኮ ገና አልደረሰም» አላት፡፡
\v 5 እናቱ ለአሳላፊዎቹ፣ እርሱ «የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ» አለቻቸው፡፡
\s5
\v 6 በዚያ፣ ለአይሁድ የመንጻት ሥርዐት የሚያገለግሉ እያንዳንዳቸው ሁለት ወይም ሦስት እንስራ የሚይዙ ስድስት የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፡፡
\v 7 ኢየሱስ፣ «ጋኖቹን ውሃ ሙሉአቸው» አላቸው፡፡ እነርሱም እስከ አፋቸው ሞሉአቸው፡፡
\v 8 ከዚያም ኢየሱስ አሳላፊዎቹን፣ «ጥቂት ቅዱና ለመስተንግዶው ኀላፊ ስጡት» አላቸው፤ እነርሱም እንዳላቸው አደረጉ፡፡
\s5
\v 9 የመስተንግዶው ኀላፊ፣ ወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ ቀመሰው፤ ከየት እንደ መጣ ግን አላወቀም፤ ውሃውን የቀዱት አሳላፊዎች ግን ያውቁ ነበር፡፡ እርሱም ሙሽራውን ጠርቶ
\v 10 «ሰው ሁሉ መልካሙን ወይን ጠጅ በመጀመሪያ ያቀርባል፤ መናኛውን ሰዎች ከሰከሩ በኋላ ነው የሚያቀርበው፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን ድረስ አቈይተሃል» አለው፡፡
\s5
\v 11 ይህ በገሊላ ቃና የተደረገው ተአምር ኢየሱስ ካደረጋቸው ተአምራዊ ምልክቶች የመጀመሪያ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
\s5
\v 12 ከዚህ በኋላ ከእናቱ፣ ከወንድሞቹና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም ጥቂት ቀናት ቈዩ፡፡
\s5
\v 13 የአይሁድ ፋሲካ ቀርቦ ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡
\v 14 በቤተ መቅደስ ውስጥ በሬዎችን፣ በጎችንና ርግቦችን ሲሸጡ የነበሩ ሰዎችን አገኘ፡፡ ገንዘብ ለዋጮችም ደግሞ በዚያ ተቀምጠው ነበር፡፡
\s5
\v 15 እርሱም የገመድ ጅራፍ አበጅቶ በጎችንና ከብቶችን ጭምር ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣቸው፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ጠረጴዛዎቻቸውንም ገለባበጠ።
\v 16 ርግብ ሻጮችንም፣ «እነዚህን ከዚህ አስወጧቸው፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት ማድረጋችሁን አቁሙ!» አላቸው።
\s5
\v 17 ደቀ መዛሙርቱ፣ «ለቤትህ ያለኝ ቅናት ይበላኛል» ተብሎ የተጻፈውን አስታወሱ፡፡
\v 18 ከዚያም የአይሁድ ባለ ሥልጣኖች፣ «እነዚህን ነገሮች ለማድረግ መብት እንዳለህ ምን ምልክት ታሳየናለህ?» በማለት መለሱለት፡፡
\v 19 ኢየሱስ፣ «ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ እኔ በሦስት ቀን አስነሣዋለሁ» ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያም አይሁድ፣ «ይህን ቤተ መቅደስ ለመገንባት ዐርባ ስድስት ዓመት ፈጅቶአል፤ አንተ በሦስት ቀን መልሰህ ታስነሣዋለህ?» አሉት።
\v 21 ይሁን እንጂ፣ እርሱ ቤተ መቅደስ ብሎ የተናገረው፣ ስለ ራሱ ሰውነት ነበር።
\v 22 ከሙታን ከተነሣም በኋላ፣ ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስ ይህን እንደ ተናገረ አስታወሱ፤ መጻሕፍትንና ኢየሱስ የተናገረውንም ቃል አመኑ።
\s5
\v 23 በፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ሳለ፣ ያደረጋቸውን ተአምራት አይተው ብዙዎች በስሙ አመኑ።
\v 24 ሆኖም፣ ኢየሱስ ሰዎችን ሁሉ ያውቅ ስለ ነበር፣ እነርሱን አላመናቸውም፤
\v 25 ደግሞም በሰው ውስጥ ያለውን ያውቅ ስለ ነበር፣ ማንም ስለ ሰው እንዲመሰክርለት አያስፈልገውም ነበር።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ፣ ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ የአይሁድ ሸንጎ አባል ነበር ፤
\v 2 ይህ ሰው በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፣ «መምህር ሆይ፣ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ክሆነ ሰው በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ማንም ማድረግ ስለማይችል፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ መምህር መሆንህን እናውቃለን» አለው።
\s5
\v 3 ኢየሱስ፣ «እውነት እልሃለሁ፣ ሰው ዳግም ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም» ብሎ መለሰለት።
\v 4 ኒቆዲሞስ፣ «ሰው ካረጀ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ወደ እናቱ ማኅፀን ዳግመኛ ገብቶ ሊወለድ ይችላልን?» አለው።
\s5
\v 5 ኢየሱስ መልሶ፣ «እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፣ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።
\v 6 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፤ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው።
\s5
\v 7 'ዳግም መወለድ አለባችሁ' ስላልሁህ አትደነቅ፤
\v 8 ነፋስ ወደ ፈለገው ይነፍሳል፤ ድምፁን ትሰማለህ፣ ነገር ግን ከየት እንደ መጣ፣ ወዴትም እንደሚሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስም የተወለደ ሁሉ እንደዚሁ ነው።»
\s5
\v 9 ኒቆዲሞስ፣ «ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?» በማለት መለሰ።
\v 10 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «አንተ የእስራኤል መምህር ሆነህ ሳለ እነዚህን ነገሮች አታውቅምን?
\v 11 እውነት፣ እውነት፣ እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ እናንተ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉም።
\s5
\v 12 ስለ ምድራዊው ነገር ነግሬአችሁ ያላመናችሁ፣ ስለ ሰማያዊው ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ?
\v 13 ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር፣ ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም።
\s5
\v 14 ሙሴ እባብን በምድረ በዳ እንደ ሰቀለ፣ እንዲሁ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል።
\v 15 ይህም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው።
\s5
\v 16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤
\v 17 እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ላይ ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው።
\v 18 በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል።
\s5
\v 19 የፍርዱ ምክንያት ይህ ነው፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ነበረ፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ፤
\v 20 ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ድርጊቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።
\v 21 እውነትን በተግባር ላይ የሚያውል ሰው ግን ሥራው እግዚአብሔርን በመታዘዝ የተፈጸመ መሆኑ በግልጽ እንዲታይ ወደ ብርሃን ይመጣል።»
\s5
\v 22 ከዚህ በኋላ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ይሁዳ አገር ሄዱ፤ በዚያ ከእነርሱ ጋር ቆየ፤ ያጠምቅም ነበር፤
\v 23 በዚህ ጊዜ ዮሐንስም በሳሌም አቅራቢያ ሄኖን በተባለ ስፍራ ብዙ ውሃ ስለ ነበረ፣ ያጠምቅ ነበር፤ ሰዎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይጠመቁ ነበር።
\v 24 ምክንያቱም ዮሐንስ ገና በወኅኒ አልተጣለም ነበር።
\s5
\v 25 ከዚያም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአንድ አይሁዳዊ መካከል ስለ መንጻት ሥርዐት ክርክር ተነሣ።
\v 26 ደቀ መዛሙርቱ ወደ ዮሐንስም መጥተው፣ «መምህር ሆይ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው ስለ እርሱ የመሰከርክለት ሰው፣ እነሆ እያጠመቀ ነው፤ ሁሉም ወደ እርሱ እየሄዱ ነው አሉት።»
\s5
\v 27 ዮሐንስ መልሶ እንዲህ አለ፤ «ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በቀር ምንም ነገር ሊቀበል አይችልም።
\v 28 'እኔ ክርስቶስ አይደለሁም' ነገር ግን 'ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ' ማለቴን እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ።
\s5
\v 29 ሙሽሪት ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ አጅቦት ቆሞ የሚሰማው ሚዜው በሙሽራው ድምፅ እጅግ ደስ ይለዋል። አሁን ይህ ደስታዬ ፍጹም ሆኖእል።
\v 30 እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ይገባል።
\s5
\v 31 ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።
\v 32 እርሱ ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን ማንም አይቀበልም።
\v 33 ምስክርነቱን የተቀበለ ሰው የእግዚአብሔርን እውነተኝነት አረጋግጧል።
\s5
\v 34 እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።
\v 35 አብ ወልድን ይወዳል ሁሉንም ነገር በእጁ ሰጥቶታል።
\v 36 በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ለልጁ የማይታዘዝ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በላዩ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም።»
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ፈሪሳውያን ኢየሱስ ከዮሐንስ የበለጠ ብዙ ሰዎችን ደቀ መዛሙርት እንደሚያደርግና እንደሚያጠምቅ ሰሙ፤ ኢየሱስም ይህን ዐወቀ፤
\v 2 (ያጠምቁ የነበሩት ደቀ መዛሙርቱ እንጂ እርሱ ባይሆንም)፣ ኢየሱስ መስማታቸውን ባወቀ ጊዜ
\v 3 የይሁዳን ምድር ለቅቆ ወደ ገሊላ ሄደ።
\s5
\v 4 በሰማርያም በኩል ማለፍ ነበረበት።
\v 5 ከዚያም በሰማርያ ከተማ፣ ያዕቆብ ለልጁ ለዮሴፍ በሰጠው ቦታ አጠገብ ወደምትገኝ፣ ሲካር ወደምትባል ቦታ መጣ።
\s5
\v 6 በዚያም የያዕቆብ የውሃ ጒድጓድ ነበረ፤ ኢየሱስ ከጒዞው ብዛት ደክሞት ስለ ነበር፣ በውሃው ጒድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም እኩለ ቀን አካባቢ ነበር።
\v 7 አንዲት ሳምራዊት ሴት ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፣ ኢየሱስ፣ «እባክሽ የምጠጣው ውሃ ስጪኝ» አላት።
\v 8 ደቀ መዛሙርቱ ምግብ ለመግዛት ወደ ከተማ ሄደው ነበር።
\s5
\v 9 ሳምራዊቷም ሴት፣ «አንተ አይሁዳዊ ሆነህ፣ እኔን ሳምራዊቷን ሴት እንዴት ውሃ አጠጪኝ ትለኛለህ?» አለችው። አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና።
\v 10 ኢየሱስ፣ «የእግዚአብሔርን ስጦታና ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን እንደሆነ ዐውቀሽ ቢሆን ኖሮ ፣ አንቺው በጠየቅሽው፣ እርሱም ሕያው ውሃ በሰጠሽ ነበር» ብሎ መለሰላት።
\s5
\v 11 ሴትዮዋም እንዲህ አለችው፤ «ጌታ ሆይ፣ አንተ መቅጃ የለህም፤ ጒድጓዱም ጥልቅ ነው፤ ታዲያ ሕያዉን ውሃ ከየት ታገኛለህ?
\v 12 አንተ፣ ይህን ጒድጓድ ከሰጠን፣ ከአባታችን ከያዕቆብ ትበልጣለህን? እርሱ ራሱ፣ ልጆቹና ከብቶቹም ከዚሁ ጒድጓድ ጠጥተዋል።
\s5
\v 13 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፤ «ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደ ገና ይጠማል፤
\v 14 እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ግን ፈጽሞ ዳግመኛ አይጠማም፤ ይልቁንም፣ እኔ የምሰጠው ውሃ፣ ከውስጡ የሚፈልቅ የዘላለም ሕይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል።»
\s5
\v 15 ሴትዮዋም፣ «ጌታዬ፤ ከእንግዲህ እንዳልጠማና ውሃ ለመቅዳት ወደዚህ እንዳልመጣ፣ ይህን ውሃ ስጠኝ» አለችው።
\v 16 ኢየሱስም፣ «ሂጂ፣ ባልሽን ጥሪና ወደዚህ ተመልሰሽ ነይ» አላት።
\s5
\v 17 ሴትዮዋ፣ «ባል የለኝም» በማለት መለሰች፤ ኢየሱስ፣ 'ባል የለኝም' በማለትሽ ልክ ነሽ፤
\v 18 አምስት ባሎች ነበሩሽና፤ አሁን ከአንቺ ጋር ያለው ሰው ባልሽ አይደለም፤ ስለዚህ እውነቱን ተናግረሻል» ብሎ መለሰ።
\s5
\v 19 ሴትዮዋ፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ነቢይ እንደ ሆንህ ይገባኛል፤
\v 20 አባቶቻችን በዚህ ተራራ ላይ ሰገዱ፤ እናንተ ግን ሰው መስገድ ያለበት በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ» አለችው።
\s5
\v 21 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላት፤ «አንቺ ሴት፣ በዚህ ተራራም ሆነ በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ እየመጣ መሆኑን እመኚኝ።
\v 22 እናንተ ሳምራውያን ለማታውቁት ትሰግዳላችሁ። እኛ ግን፣ ድነት ከአይሁድ ስለ ሆነ፣ ለምናውቀው እንሰግዳለን።
\s5
\v 23 ይሁን እንጂ፣ በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ አብ እንደዚህ በእውነት የሚሰግዱለትን ሰዎች ይፈልጋልና።
\v 24 እግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ የሚሰግዱለትም በመንፈስና በእውነት ሊሰግዱለት ይገባል።»
\s5
\v 25 ሴትዮዋ፣ «ክርስቶስ የሚባል መሲሕ እንደሚመጣ ዐውቃለሁ፤ እርሱ ሲመጣ ሁሉንም ነገር ይነግረናል» አለችው።
\v 26 ኢየሱስ፣ «አሁን እያነጋገርሁሽ ያለሁት እኔ እርሱ ነኝ» አላት።
\s5
\v 27 ልክ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሰው መጡ፤ ኢየሱስ ከሴት ጋር በመነጋገሩ ተገረሙ፤ ይሁን እንጂ፣ ማንም፣ «ምን ትፈልጋለህ? ወይም ከእርስዋ ጋር ለምን ትነጋገራለህ?» ያለው የለም።
\s5
\v 28 ሴትዮዋ እንስራዋን ትታ ወደ ከተማ ተመለሰች፤ ለሕዝቡም፣
\v 29 «ያደረግሁትን ነገር ሁሉ የነገረኝን ሰው ኑና እዩ፤ እርሱ ክርስቶስ ይሆንን?» አለች፤
\v 30 ሕዝቡ ከከተማ ወጥተው እርሱ ወዳለበት መጡ።
\s5
\v 31 በዚህም መሐል ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን፣ «መምህር ሆይ፣ ምግብ ብላ» አሉት።
\v 32 እርሱ ግን፣ «እናንተ የማታውቁት፣ የምበላው ምግብ አለኝ» አላቸው።
\v 33 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ እርስ በርስ፣ «ምግብ ያመጣለት ሰው ይኖር ይሆን?» ተባባሉ።
\s5
\v 34 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውንም መፈጸም ነው።
\v 35 እናንተ 'መከር ገና አራት ወር ቀርቶታል፤ ከዚያም መከሩ ይመጣል' ትሉ የለምን? ቀና በሉና ዕርሻዎቹን ተመልከቱ፣ መከሩ ደርሷልና እያልኋችሁ ነው፤
\v 36 የሚያጭድ ደመወዙን ይቀበላል፤ ለዘላለም ሕይወት የሚሆን ፍሬም ይሰበስባል፤ ስለዚህ የሚዘራውም፣ የሚያጭደውም አብረው ይደሰታሉ።
\s5
\v 37 'አንዱ ይዘራል፣ ሌላውም ያጭዳል' የሚለው አባባል እውነት የሚሆነው በዚህ ምክንያት ነው።
\v 38 እኔ ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ፤ ሌሎች በሥራ ደከሙ፤ እናንተም በእነርሱ ሥራ ገባችሁ።»
\s5
\v 39 ሴትዮዋ፣ «ያደረግሁትን ሁሉ ነገረኝ» ብላ ስለ እርሱ በሰጠችው ምስክርነት የተነሣ፣ በዚያች ከተማ ከሚኖሩ ሳምራውያን ብዙዎቹ በእርሱ አመኑ።
\v 40 ስለዚህ፣ ሳምራውያኑ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ፣ ከእነርሱ ጋር እንዲቈይ ለመኑት፤ እዚያም ሁለት ቀን ቈየ።
\s5
\v 41 ከቃሉም የተነሣ ሌሎች ብዙ ሰዎች አመኑ።
\v 42 ሴትዮዋንም፣ «የምናምነው አንቺ ስለ ነገርሽን ቃል ብቻ አይደለም፤ እኛ ራሳችን ሰምተነዋል፤ ይህ ሰው በእውነት የዓለም አዳኝ እንደ ሆነ እናውቃለን» ይሏት ነበር።
\s5
\v 43 ከእነዚያ ሁለት ቀናት በኋላም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ገሊላ ሄደ።
\v 44 ነቢይ በገዛ አገሩ እንደማይከበር ኢየሱስ ራሱ ተናግሮ ነበርና።
\v 45 ወደ ገሊላ በደረሰ ጊዜ፣ የገሊላ ሰዎች በደስታ ተቀበሉት፤ እነርሱ በፋሲካ በዓል ወደዚያ ሄደው ስለ ነበር፣ በኢየሩሳሌም ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ አይተው ነበር። እነርሱ ደግሞ ወደ በዓሉ ሄደው ነበርና።
\s5
\v 46 ኢየሱስም ውሃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት፣ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ ዳግመኛ መጣ፤ በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት አንድ ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የሆነ ሹም ነበር፤
\v 47 እርሱም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ መምጣቱን በሰማ ጊዜ፣ ወደ እርሱ ሄደና በሞት አፋፍ ላይ የሚገኘውን ልጁን መጥቶ እንዲፈውስለት ለመነው።
\s5
\v 48 ከዚያም ኢየሱስ፣ «እናንተ ሰዎች ምልክቶችንና ድንቆችን ካላያችሁ አታምኑም» አለው።
\v 49 ሹሙ፣ «ጌታ ሆይ፤ ልጄ ከመሞቱ በፊት እባክህ ውረድ» አለው።
\v 50 ኢየሱስ፣ «ሂድ፤ ልጅህ በሕይወት ይኖራል» አለው። ሰውየው ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አምኖ ሄደ።
\s5
\v 51 በመንገድ ላይ ሳለም፣ አገልጋዮቹ አገኙትና ልጁ ተሽሎት በሕይወት እንዳለ ነገሩት።
\v 52 እርሱም ልጁ የተሻለው በስንት ሰዓት ላይ እንደ ነበረ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ «ትኵሳቱ የለቀቀው ትናንት በሰባተኛው ሰዓት ላይ ነበር» አሉት።
\s5
\v 53 አባትየውም፣ ኢየሱስ «ልጅህ በሕይወት ይኖራል» ብሎት የነበረው በዚያ ሰዓት እንደ ነበረ ተገነዘበ፤ ስለዚህ እርሱ ራሱና ቤተ ሰቡ በሙሉ በኢየሱስ አመኑ።
\v 54 ይህም ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ በመጣ ጊዜ ያደረገው ሁለተኛው ምልክት ነው።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የአይሁድ በዓል ነበረ፤ ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
\v 2 በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ፣ አምስት ጣሪያ ያላቸው መመላለሻዎች ነበሩ። በዚያ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ የሚባል አንድ መጠመቂያ ነበረ።
\v 3 በእነዚህ መመላለሻዎች ወለል ላይ በጣም ብዙ ሕሙማን፣ ዐይነ ስውሮች፣ አንካሶች ወይም ሽባዎች ተኝተው ነበር።
\v 4
\f + \ft አንዳንድ የጥንት ጽሑፎች ይህ ጥቅስ አላቸው፣ ሌሎች ግን ዘለውታል። \f*
«ዐልፎ ዐልፎ የጌታ መልአክ መጥቶ ውሃውን በሚያናውጥበት ጊዜ፣ ቀድሞ ወደ መጠመቂያው የገባ ሰው ከሚሠቃይበት ከማንኛውም በሽታ ይፈወስ ነበር» የሚለውን ክፍል እንድትተዉት እንመክራለን።
\s5
\v 5 በዚያም ለሠላሳ ስምንት ዓመት ሽባ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበረ።
\v 6 ኢየሱስ ሰውየውን እዚያ ተኝቶ ባየው ጊዜ፣ ለረጅም ጊዜ በዚያ መቆየቱን ዐውቆ፣ «መዳን ትፈልጋለህን?» አለው።
\s5
\v 7 ሕመምተኛውም ሰው መልሶ፣ «ጌታ ሆይ፣ ውሃው በሚናወጥበት ጊዜ መጠመቂያው ውስጥ የሚያስገባኝ ሰው የለኝም፤ ለመግባትም ስሞክር ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል» አለው።
\v 8 ኢየሱስ፣ «ተነሥ! የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ» አለው።
\s5
\v 9 ሰውየው ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ የተኛበትንም ምንጣፍ ተሸክሞ ሄደ። ያም ቀን ሰንበት ነበረ።
\s5
\v 10 ስለዚህ የአይሁድ መሪዎች የተፈወሰውን ሰው፣ «ሰንበት ነው፤ ምንጣፍህን ልትሸከም አልተፈቀደልህም» አሉት።
\v 11 እርሱ ግን፣ «ያ ያዳነኝ ሰው፣ 'የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ'» አለኝ ብሎ መለሰላቸው።
\s5
\v 12 እነርሱም፣ «የተኛህበትን ምንጣፍ ተሸክመህ ሂድ» ያለህ ሰው ማን ነው?» ብለው ጠየቁት።
\v 13 የተፈወሰው ሰው ግን ኢየሱስ ከአጠገቡ ፈቀቅ ስላለና በስፍራው ብዙ ሕዝብ ስለ ነበር፣ ማን እንደ ፈወሰው አላወቀም።
\s5
\v 14 በኋላ ኢየሱስ ያን ሰው በቤተ መቅደስ አግኝቶት፣ «እነሆ፣ ተፈውሰሃል፤ ከዚህ የባሰ ነገር እንዳይደርስብህ ከእንግዲህ ኀጢአት አትሥራ» አለው።
\v 15 ሰውየው ሄዶ የፈወሰው ኢየሱስ መሆኑን ለአይሁድ መሪዎች ነገራቸው።
\s5
\v 16 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በሰንበት ስላደረገ፣ የአይሁድ መሪዎች ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር።
\v 17 ኢየሱስ፣ «አባቴ እስካሁን እየሠራ ነው፤ እኔም እሠራለሁ» አላቸው።
\v 18 በዚህ ምክንያት አይሁድ ኢየሱስ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን አባቴ ነው በማለት፣ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ስላደረገ፣ ሊገድሉት አጥብቀው ይፈልጉ ነበር።
\s5
\v 19 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ «እውነት እላችኋለሁ፣ አብ ሲያደርግ ያየውን ነው እንጂ ወልድ ከራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ አብ የሚያደርገውን ሁሉ ወልድም ያንኑ ያደርጋልና።
\v 20 አብ ወልድን ይወዳልና፣ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ነገር ያሳየዋል።
\s5
\v 21 አብ ሙታንን እንደሚያስነሣና ሕይወትንም እንደሚሰጣቸው፣ ወልድም ደግሞ ለሚፈልገው ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል።
\v 22 አብ በማንም ላይ አይፈርድም፤ ነገር ግን ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጥቶታል፤
\v 23 ይኸውም፣ ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ ነው፤ ወልድን የማያከብር፣ የላከውን አብንም አያከብርም።
\s5
\v 24 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ አይፈረድበትም።
\s5
\v 25 እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእኔን፣ የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ አሁንም መጥቶአል፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።
\s5
\v 26 አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና፤
\v 27 ወልድ የሰው ልጅ ስለ ሆነ፣ አብ የመፍረድን ሥልጣን ለወልድ ሰጥቶታል።
\s5
\v 28 በዚህ አትደነቁ፤ በመቃብር ውስጥ ያሉ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፤
\v 29 መልካም የሠሩ ለሕይወት ትንሣኤ፣ ክፉ የሠሩም ለፍርድ ትንሣኤ ይወጣሉ።
\s5
\v 30 እኔ ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም፤ የምፈርደው በሰማሁት መሠረት ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ የራሴን ፈቃድ ስለማልሻም፣ ፍርዴ ትክክል ነው።
\v 31 እኔው ስለ ራሴ ብመሰክር፣ ምስክርነቴ እውነት አይደለም።
\v 32 ስለ እኔ የሚመሰክር ሌላ አለ፤ እርሱ ስለ እኔ የሚሰጠውም ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ።
\s5
\v 33 ወደ ዮሐንስ ልካችሁ ነበር፤ እርሱም ስለ እውነት መስክሮአል፤
\v 34 ይሁን እንጂ፣ እኔ የሰው ምስክርነት የምቀበል አይደለሁም፤ ነገር ግን ይህን የምናገረው እናንተ እንድትድኑ ነው።
\v 35 ዮሐንስ እየነደደ ብርሃን የሚሰጥ መብራት ነበረ፤ እናንተም ለጥቂት ጊዜ በብርሃኑ ሐሤት ልታደርጉ ፈለጋችሁ።
\s5
\v 36 እኔ ያለኝ ምስክርነት ግን ከዮሐንስ ምስክርነት ይበልጣል፡፡ አብ እንድፈጽመው የሰጠኝ፣ እኔም እየሠራሁት ያለሁት ሥራ አብ እንደ ላከኝ ይመሰክራል።
\v 37 የላከኝ አብ እርሱ ስለ እኔ መስክሮአል፤ እናንተም ከቶ ድምፁን አልሰማችሁም፤ መልኩንም አላያችሁም፤
\v 38 እርሱ በላከው አላመናችሁምና ቃሉ በእናንተ አይኖርም።
\s5
\v 39 በእነርሱ የዘላለምን ሕይወት የምታገኙ ስለሚመስላችሁ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ ይመሰክራሉ፤
\v 40 እናንተ ወደ እኔ መጥታችሁ ሕይወት ማግኘት አትፈልጉም።
\s5
\v 41 እኔ ከሰው ክብር አልቀበልም፤
\v 42 ነገር ግን የእግዚአብሔር ፍቅር በእናንተ ውስጥ እንደሌለ ዐውቃለሁ።
\s5
\v 43 እኔ በአባቴ ስም መጥቼ አልተቀበላችሁኝም፤ ሌላው በራሱ ስም ቢመጣ ግን ትቀበሉታላችሁ።
\v 44 እናንተ አንዳችሁ ከሌላችሁ ክብር የምትቀበሉ፣ ነገር ግን ከአንዱ አምላክ የሚመጣውን ክብር የማትሹ ከሆነ፣ እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ?
\s5
\v 45 በአብ ፊት የምከሳችሁ እኔ አልምሰላችሁ፤ የሚከሳችሁ ሌላ አለ እርሱም ተስፋ ያደረጋችሁበት ሙሴ ነው።
\v 46 ሙሴን ብታምኑ ኖሮ፣ እኔን ባመናችሁ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱም የጻፈው ስለ እኔ ነው።
\v 47 ታዲያ እርሱ የጻፈውን ካላመናችሁ፣ ቃሌን እንዴት ታምናላችሁ?»
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የጥብርያዶስ ባሕር ወደሚባለው ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፡፡
\v 2 ብዙ ሰዎች ሕመምተኞችን በመፈወስ ያደረጋቸውን ተአምራት ስላዩ ተከተሉት፡፡
\v 3 ኢየሱስ ወደ ተራራ ወጥቶ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዚያ ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 4 የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ተቃርቦ ነበር፡፡
\v 5 ኢየሱስ ብዙ ሕዝብ ወደ እርሱ ሲመጣ ባየ ጊዜ፣ ፊልጶስን፣ ‹‹ይህ ሁሉ ሕዝብ እንዲበላ እንጀራ ከየት እንግዛ? አለው፡፡
\v 6 ኢየሱስ ይህን ያለው ፊልጶስን ሊፈትን ነበር እንጂ፣ እርሱ ራሱ ሊያደርግ ያሰበውን ያውቅ ነበር፡፡
\s5
\v 7 ፊልጶስ፣ ‹‹ይህ ለእያንዳንዱ ሰው ቍራሽ እንዲደርሰው የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ እንኳ ብንገዛ አይበቃም›› አለ፡፡
\v 8 ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፣ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም የሆነው እንድርያስም ኢየሱስን፣
\v 9 ‹‹አምስት የገብስ እንጀራና ሁለት ዓሣ የያዘ አንድ ልጅ እዚህ አለ፤ ነገር ግን ይህ ለዚህ ሁሉ ሕዝብ ምን ይጠቅማል? አለው፡፡
\s5
\v 10 ኢየሱስ፣ ‹‹ሕዝቡ እንዲቀመጡ አድርጉ›› አላቸው፡፡ ስፍራውም በሣር የተሸፈነ ነበር፡፡ ስለዚህ ቍጥራቸው አምስት ሺህ የሚያህል ወንዶች ተቀመጡ፡፡
\v 11 ከዚያም ኢየሱስ እንጀራውንና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ባረከና ለተቀመጡት ዐደለ፡፡ በተመሳሳይ መንገድ ከዓሣውም የሚፈልጉትን ያህል ዐደላቸው፡፡
\v 12 ሕዝቡ በጠገቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፣ ‹‹አንዳችም እንዳይጣል የተረፈውን ፍርፋሪ ሰብስቡ›› አላቸው፡፡
\s5
\v 13 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ሕዝቡ ከበሉ በኋላ የተረፈውን ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ የገብስ እንጀራ ፍርፋሪ ሰበሰቡ፡፡
\v 14 ከዚያም ሕዝቡ ኢየሱስ ያደረገውን ይህን ምልክት ባዩ ጊዜ፣ ‹‹ይህስ በእውነት ወደ ዓለም የሚመጣው ነቢይ ነው›› አሉ፡፡
\v 15 ኢየሱስም ሊመጡና ይዘው በግድ ሊያነግሡት እንደ ፈለጉ በተረዳ ጊዜ፣ እንደ ገና ለብቻው ወደ ተራራ ጫፍ ወጣ፡፡
\s5
\v 16 በመሸም ጊዜ፣ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ወረዱ፤
\v 17 በጀልባ ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም በባሕር ላይ መጓዝ ጀመሩ፡፡ ጊዜው መሽቶ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር፡፡
\v 18 በዚህ ጊዜ ባሕሩ ከኀይለኛ ነፋስ የተነሣ ይታወክ ነበር፡፡
\s5
\v 19 ከዚያም ደቀ መዛሙርቱ ሃያ አምስት ወይም ሠላሳ ምዕራፍ ያህል እንደ ቀዘፉ፣ ኢየሱስ በባሕር ላይ እየሄደ እነርሱ ወዳሉበት ጀልባ ሲቃረብ አይተውት ፈሩ፡፡
\v 20 ይሁን እንጂ እርሱ፣ ‹‹እኔ ነኝ አትፍሩ›› አላቸው፡፡
\v 21 ከዚያም ጀልባዋ ላይ እንዲወጣ ፈቀዱለት፣ ጀልባዋም ወዲያው ወደሚሄዱበት ስፍራ ደረሰች፡፡
\s5
\v 22 በማግስቱም በማዶ ቆመው የነበሩ ሕዝብ አንድም ጀልባ በባሕሩ ላይ እንዳልነበረ አዩ፤ በዚያ የነበረው አንድ ጀልባ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ያልተሳፈረበት ብቻ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱም ብቻቸውን ከዚያ ሄደው ነበር፡፡
\v 23 ይሁን እንጂ ጌታ አመስግኖ ሰዎቹን እንጀራ ካበላበት ስፍራ አጠገብ፣ ከጥብርያዶስ የመጡ አንዳንድ ጀልባዎች እዚያ ነበሩ፡፡
\s5
\v 24 ሕዝቡም፣ ኢየሱስም ሆነ ደቀ መዛሙርቱ እዚያ እንዳልነበሩ በተረዱ ጊዜ፣ ራሳቸው በጀልባዎቹ ተሳፍረው ኢየሱስን ፍለጋ ሄዱ፡፡
\v 25 በባሕሩ ማዶ ኢየሱስን ባገኙት ጊዜ፣ ‹‹መምህር ሆይ፤ ወደዚህ የመጣኸው መቼ ነው? አሉት፡፡
\s5
\v 26 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እኔን የምትፈልጉኝ ምልክቶችን ስላያችሁ ሳይሆን፣ እንጀራውን በልታችሁ ስለ ጠገባችሁ ነው፡፡
\v 27 ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቁን ወልድ ለሚሰጣችሁ ዘላለም ለሚኖር ሕይወት ሥሩ፤ እግዚአብሔር አብ ማኅተሙን በእርሱ ላይ አትሞአልና፡፡››
\s5
\v 28 ከዚያም፣ ‹‹የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት፡፡
\v 29 ኢየሱስ፣ ‹‹የምትሠሩት የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ በላከው ማመን ነው›› ብሎ መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 30 ስለዚህ እነርሱ እንዲህ አሉት፤ ‹‹አይተን እንድናምንህ ምን ተአምር ትሠራለህ? ምንስ ታደርጋለህ?
\v 31 ‹እንዲበሉ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው› ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ አባቶቻችን በምድረ በዳ መና በሉ፡፡››
\s5
\v 32 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መና እንድትበሉ ከሰማይ የሰጣችሁ ሙሴ አልነበረም፤ ነገር ግን ከሰማይ እውነተኛ እንጀራ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው፤
\v 33 ከሰማይ የሚወርድና ለዓለም ሕይወትን የሚሰጥ የእግዚአብሔር እንጀራ ነውና፡፡››
\v 34 ስለዚህ፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ይህን እንጀራ ዘወትር ስጠን›› አሉት፡፡
\s5
\v 35 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ አይራብም፤ በእኔ የሚያምንም ከቶ አይጠማም፡፡
\v 36 ነገር ግን እኔን አይታችሁ አሁንም ገና ስላላመናችሁብኝ ይህን አልኋችሁ፡፡
\v 37 አባቴ የሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ እኔም አባቴ የሰጠኝን ከቶ ወደ ውጭ አላባርርም፡፡
\s5
\v 38 ከሰማይ የወረድሁት የራሴን ፈቃድ ለማድረግ ሳይሆን የላከኝን ፈቃድ ለመፈጸም ነውና፡፡
\v 39 የላከኝም ፈቃድ፣ እርሱ ከሰጠኝ ሁሉ አንድም ሳይጠፋ፣ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣቸው ነው፡፡
\v 40 የአባቴ ፈቃድ፣ ወልድን አይቶ በእርሱ ያመነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው፡፡ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡››
\s5
\v 41 ከዚያም የአይሁድ መሪዎች፣ ‹‹እኔ ከሰማይ የወረድሁ የሕይወት እንጀራ ነኝ›› በማለቱ አጕረመረሙበት፡፡
\v 42 እነርሱ፣ ‹‹ይህ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን? አባቱንና እናቱንስ የምናውቃቸው አይደሉምን? ታዲያ፣ እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል? ተባባሉ፡፡
\s5
\v 43 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ ‹‹እርስ በርስ ማጕረምረማችሁን ተዉት፡፡
\v 44 አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ የሚመጣ የለም፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፡፡
\v 45 በነቢያት፣ ‹ሁሉም ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ› ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ ከአብ የሰማና የተማረ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፡፡
\s5
\v 46 ከእግዚአብሔር ከሆነው በቀር አብን ያየ ማንም የለም፤ እርሱ አብን አይቶታል፡፡
\v 47 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡
\s5
\v 48 እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ፡፡
\v 49 አባቶቻችሁ በበረሐ መና በሉ፣ ሞቱም፡፡
\s5
\v 50 ሰው በልቶት እንዳይሞት፣ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ይህ ነው፡፡
\v 51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡ ለዓለም ሕይወት እንዲሆነው የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው፡፡››
\s5
\v 52 አይሁድ በዚህ አባባሉ ተቈጥተው፣ ‹‹ይህ ሰው እንዴት እንድንበላ ሥጋውን ሊሰጠን ይችላል? በማለት እርስ በርስ ተከራከሩ፡፡
\v 53 ከዚያም ኢየሱስ፣ ‹‹እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፣ ደሙንም ካልጠጣችሁ የራሳችሁ የሆነ ሕይወት አይኖራችሁም›› አላቸው፡፡
\s5
\v 54 ‹‹ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ፤
\v 55 ሥጋዬ እውነተኛ መብል፣ ደሜም እውነተኛ መጠጥ ነውና፡፡
\v 56 ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ፡፡
\s5
\v 57 ሕያው አብ እንደ ላከኝና እኔ ከአብ የተነሣ እንደምኖር፣ የሚበላኝም ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል፡፡
\v 58 አባቶቻችን በልተውት እንደ ሞቱ ዐይነት ሳይሆን፣ ይህ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ነው፡፡ ይህን እንጀራ የበላ ለዘላለም ይኖራል፡፡››
\v 59 ኢየሱስ ይህን የተናገረው በቅፍርናሆም፣ በምኵራብ ሲያስተምር ነበር፡፡
\s5
\v 60 ከዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ይህን ሲሰሙ፣ ‹‹ይህ ጠንካራ ትምህርት ነው፤ ማን ሊቀበለው ይችላል? አሉ፡፡
\v 61 ኢየሱስ በዚህ ማጕረምረማቸውን በገዛ ራሱ ስላወቀ፣ ‹‹ይህ አሰናከላችሁ እንዴ?
\s5
\v 62 ታዲያ፣ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበረበት ስፍራ፣ ተመልሶ ወደ ላይ ሲወጣ ብታዩ ምን ልትሉ ነው?
\v 63 ሕይወት የሚሰጠው መንፈስ ነው፤ ሥጋ ለምንም አይጠቅምም፡፡ እኔ የነገርኋችሁ ቃላት መንፈስ ናቸው፤ ሕይወትም ናቸው፡፡
\s5
\v 64 ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ መካከል የማያምኑ አንዳንዶች አሉ›› አለ፡፡ ከመጀመሪያው በእርሱ የማያምኑ እነማን እንደ ሆኑና የሚከዳው ማን እንደ ሆነ ያውቅ ነበርና፡፡
\v 65 ደግሞም፣ ‹‹ከአብ ከተሰጠው በቀር ማንም ወደ እኔ ሊመጣ አይችልም ያልኋችሁ ለዚህ ነው›› አለ፡፡
\s5
\v 66 ከዚህ በኋላ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎቹ ትተውት ወደ ኋላቸው ተመለሱ፤ አብረውትም አልተጓዙም፡፡
\v 67 ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን፣ ‹‹እናንተም ትታችሁኝ ልትሄዱ ትፈልጋላችሁን? አላቸው፡፡
\v 68 ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ ‹‹ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን? አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ፤
\v 69 እኛም አምነናል፤ አንድያ የእግዚአብሔር ቅዱስ መሆንህንም ዐወቀናል፡፡››
\s5
\v 70 ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ዐሥራ ሁለታችሁንም መርጫችሁ የለም ወይ? ከእናንተም መካከል አንዱ ዲያብሎስ ነው›› አላቸው፡፡
\v 71 ይህን ያለው ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ ስለ ሆነውና ኋላም ኢየሱስን አሳልፎ ስለ ሰጠው፣ ስለ አስቆሮቱ ስምዖን ልጅ፣ ስለ ይሁዳ ነው፡፡
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አይሁድ ሊገድሉት ይፈልጉ ስለ ነበር፣ ወደ ይሁዳ መሄድ አልፈለገም፤ ስለዚህ እዚያው በገሊላ ውስጥ ይመላለስ ነበር፡፡
\v 2 የአይሁድ የዳስ በዓል የሚከበርበትም ጊዜ ተቃርቦ ነበር፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህ ወንድሞቹ እንዲህ አሉት፤ ‹‹ተነሥተህ ከዚህ ስፍራ ወደ ይሁዳ አውራጃ ሂድ፤ ደቀ መዛሙርትህም ደግሞ አንተ የምትሠራውን ሥራ ይዩ፡፡
\v 4 በሕዝብ ፊት መታወቅ የሚፈልግ ሰው የሚሠራውን ሥራ በድብቅ አያደርግም፡፡ እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም አሳይ፡፡››
\s5
\v 5 ምክንያቱም ወንድሞቹ እንኳ ገና አላመኑበትም ነበር፡፡
\v 6 ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ጊዜዬ ገና ነው፡፡ ለእናንተማ ጊዜው ሁሉ የተመቸ ነው፡፡
\v 7 ዓለም እናንተን ሊጠላችሁ አይችልም፡፡ እኔን ግን በክፉ ሥራው ስለምመሰክርበት፣ ይጠላኛል፡፡
\s5
\v 8 እናንተ ወደ በዓሉ ውጡ፤ እኔ ግን ጊዜዬ ገና ስላልደረሰ፣ ወደ በዓሉ አልሄድም፡፡››
\v 9 እርሱ ይህን ካላቸው በኋላ፣ በገሊላ ቈየ፡፡
\s5
\v 10 ነገር ግን ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ በኋላ እርሱም በግልጽ ሳይሆን በስውር ወደዚያው ሄደ፡፡
\v 11 አይሁድ በበዓሉ ላይ ሊፈልጉት ሄደው፣ ‹‹እርሱ ያለው የት ነው? አሉ፡፡
\s5
\v 12 በሕዝቡም መካከል ብዙ ውይይት ተነሥቶ ነበር፡፡ አንዳንዶቹ፣ ‹‹እርሱ ጥሩ ሰው ነው›› አሉ፤ ሌሎቹም፣ ‹‹አይደለም፣ ሕዝቡን እያሳተ ነው›› አሉ፡፡
\v 13 ይሁን እንጂ፣ አይሁድን ስለ ፈሩ፣ ስለ እርሱ በግልጽ የተናገረ ማንም አልነበረም፡፡
\s5
\v 14 በበዓሉ አጋማሽ ላይ፣ ኢየሱስ ወደ ቤተ መቅደስ ወጥቶ ማስተማር ጀመረ፡፡
\v 15 አይሁድም እየተደነቁ፣ ‹‹ይህ ሰው እንዴት ይህን ሁሉ ዐወቀ? ትምህርት እንኳ አልተማረም›› ይሉ ነበር፡፡
\v 16 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹የማስተምረው ከራሴ አይደለም፤ ነገር ግን ትምህርቴ ከላከኝ ነው›፡፡
\s5
\v 17 ማንም የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ቢፈልግ፣ ይህ ትምህርት ከእግዚአብሔር የመጣ መሆኑን ወይም ከራሴ የምናገር መሆኑን ያውቃል፡፡
\v 18 ከራሱ የሚናገር የራሱን ክብር ይፈልጋል፤ የላከውን ክብር የሚፈልግ ግን እውነተኛ ነው፤ ሐሰትም የለበትም፡፡
\s5
\v 19 ሙሴ ሕግ ሰጥቶአችሁ አልነበረምን? ነገር ግን ከእናንተ ሕጉን የሚጠብቅ አንድም ሰው የለም፡፡ ለመሆኑ፣ ልትገድሉኝ የምትፈልጉት ለምንድን ነው?
\v 20 ሕዝቡ፣ ‹‹ጋኔን አለብህ፤ አንተን ማን ሊገድል ይፈልጋል? ብለው መለሱ፡፡
\s5
\v 21 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ ‹‹አንድን ሥራ በመሥራቴ ሁላችሁም በዚህ ትደነቃላችሁ፡፡
\v 22 ሙሴ ግዝረትን ሰጣችሁ፤ ይህም የመጣው ከአባቶች እንጂ ከሙሴ አልነበረም፤ ስለሆነም፣ በሰንበት ቀን ሰውን ትገርዛላችሁ፡፡
\s5
\v 23 ሰውን በሰንበት ቀን ስትገርዙ የሙሴ ሕግ የማይሻር ከሆነ፣ እኔ በሰንበት ቀን የሰውን መላ አካል ስላዳንሁ ለምን በእኔ ላይ ትቈጣላችሁ?
\v 24 መልክ በማየት ሳይሆን በቅንነት ፍረዱ፡፡››
\s5
\v 25 ከኢየሩሳሌም ከመጡት አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፤ ‹‹ሊገድሉት የሚፈልጉት ይህን ሰው አልነበረም?
\v 26 ተመልከቱ፤ እንዲህ በግልጽ እየተናገረ ምንም አይሉትም፡፡ ገዦቹ እርሱ በትክክል ክርስቶስ መሆኑን ዐውቀው ይሆን?
\v 27 እኛ ግን ይህ ሰው ከየት እንደ መጣ እናውቃለን፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ማንም ከየት እንደ መጣ አያውቅም፡፡››
\s5
\v 28 ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ ‹‹እኔን ታውቁኛላችሁ፤ ከየት እንደ መጣሁም ታውቃላችሁ፤ ሆኖም በራሴ አልመጣሁም፤ የላከኝ ግን እውነተኛ ነው፤ እርሱን ደግሞ እናንተ አታውቁትም፡፡
\v 29 እኔ ከእርሱ ዘንድ ስለ መጣሁ፣ ዐውቀዋለሁ፤ የላከኝም እርሱ ነው፡፡››
\s5
\v 30 እነርሱም በዚህ ጊዜ ሊይዙት ሞከሩ፤ ነገር ግን የነካው አንድም ሰው አልነበረም፤ ምክንያቱም የተወሰነለት ሰዓት ገና ነበር፡፡
\v 31 ይሁን እንጂ፣ በሕዝቡ መካከል ብዙዎች በእርሱ አመኑ፡፡ ያመኑትም፣ ‹‹ክርስቶስ ሲመጣ ይህ ሰው ከሠራው ተአምር የሚበልጥ ሊሠራ ይችላልን? አሉ፡፡
\v 32 ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ ኢየሱስ በሹክሹክታ የሚያወሩትን ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊያስይዙት የጥበቃ ሰዎችን ላኩበት፡፡
\s5
\v 33 ኢየሱስ፣ ‹‹ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ከዚያም ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፡፡
\v 34 ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፡፡ እናንተ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም›› አላቸው፡፡
\s5
\v 35 ስለዚህ አይሁድ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፤ ‹‹ይህ ሰው እንዳናገኘው ወዴት ሊሄድ ነው? ተበትነው በግሪክ ወዳሉት ሰዎች ሄዶ እነርሱን ሊያስተምር ይሆን?
\v 36 ‹ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን አታገኙኝም፡፡ እናንተ እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም› ያለውስ ቃል ምን ማለት ነው?
\s5
\v 37 በታላቁ የበዓሉ ቀን፣ በመጨረሻው ቀን፣ ኢየሱስ ቆሞ ድምፁን ከፍ በማድረግ፣ ‹‹የተጠማ ማንም ቢኖር፣ ወደ እኔ መጥቶ ይጠጣ፡፡
\v 38 ቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተናገሩት፣ በእኔ የሚያምን የሕይወት ውሃ ወንዝ ከውስጡ ይፈልቃል›› አለ፡፡
\s5
\v 39 ይህን ያለው ግን በእርሱ የሚያምኑት ወደ ፊት ስለሚቀበሉት፣ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ፣ መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር፡፡
\s5
\v 40 ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ይህን ቃል ሲሰሙ፣ ‹‹ይህ በእርግጥ ነቢዩ ነው›› አሉ፡፡
\v 41 ሌሎቹ ደግሞ፣ ‹‹እርሱ ክርስቶስ ነው›› አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ግን፣ ‹‹ክርስቶስ ከገሊላ እንዴት ይመጣል!
\v 42 ቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ ከዳዊት ዘር፣ የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከቤተ ልሔም እንደሚመጣ ተናግረው የለምን? አሉ፡፡
\s5
\v 43 ስለዚህ እርሱን በተመለከተ በመካከለቸው መለያየት ተከሠተ፡፡
\v 44 ከእነርሱ አንዳንዶቹ ሊይዙት ፈልገው ነበር፤ ነገር ግን ማንም አልነካውም፡፡
\s5
\v 45 ከዚያም የጥበቃ ሰዎቹ ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ፈሪሳውያን ተመልሰው መጡ፤ የላኳቸውም፣ ‹‹ለምንድን ነው ይዛችሁ ያላመጣችሁት? አሏቸው፡፡
\v 46 የጥበቃ ሰዎቹ፣ ‹‹ከዚህ ቀደም እንደዚህ የተናገረ አልነበረም›› አሏቸው፡፡
\s5
\v 47 ፈሪሳውያንም እንዲህ አሏቸው፤ ‹‹እናንተም ሳታችሁን?
\v 48 ከገዦቹ ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለ?
\v 49 ነገር ግን ሕጉን የማያውቅ ይህ ሕዝብ የተረገመ ነው፡፡››
\s5
\v 50 ከፈሪሳውያን አንዱ፣ ከዚህ በፊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ፣
\v 51 ‹‹መጀመሪያ ከሰውየው ሳይሰማና የሚሠራውን ሳያውቅ፣ የእኛ ሕግ በሰው ላይ ይፈርዳልን? አላቸው፡፡
\v 52 እነርሱ፣ ‹‹አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህ ወይ? ነቢይ ከገሊላ እንደማይመጣ መርምረህ ዕወቅ›› አሉት፡፡
\s5
\v 53 ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ (*53 የጥንት ቅጆች በዮሐንስ 7፡53-8፡11 ላይ ያለውን ክፍል አያካትቱም፡፡)
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ኢየሱስ ወደ ደብረ ዘይት ሄደ።
\v 2 ጠዋት በማለዳ ተመልሶ ወደ ቤተ መቅደስ መጣ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱም ተቀምጦ አስተማራቸው።
\v 3 የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያንም ስታመነዝር የተያዘችን ሴት አምጥተው፤ በመካከላቸው አቆሟት።
\s5
\v 4 ከዚያም ኢየሱስን እንዲህ አሉት፤ «መምህር ሆይ፣ ይህች ሴት ስታመነዝር እጅ ከፍንጅ የተያዘች ናት፤
\v 5 ሙሴ በሕጉ እንዲህ ያሉትን በድንጋይ እንድንወግር አዞናል፤ አንተስ ስለ እርሷ ምን ትላለህ?»
\v 6 ይህን ያሉት እርሱን ወጥመድ ውስጥ ለማስገባትና ለመክሰስ ፈልገው ነው፤ ኢየሱስ ግን ጎንበስ ብሎ በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ።
\s5
\v 7 ጥያቄ ማቅረባቸውን በቀጠሉ ጊዜም፣ ተነሥቶ ቆመና፣ “ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት ሰው በመጀመሪያ ይውገራት” አላቸው።
\v 8 ዳግመኛም ጐንበስ ብሎ፣ በጣቱ መሬት ላይ ጻፈ።
\s5
\v 9 ይህንም በሰሙ ጊዜ፣ ከታላቅ ጀምረው አንድ ባንድ ወጥተው ሄዱ። በመጨረሻ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ለብቻው ቀረ።
\v 10 ኢየሱስ ተነሥቶ በመቆም፣ “አንቺ ሴት፤ የከሰሱሽ ሰዎች የት ናቸው? አንድም የፈረደብሽ የለም?” አላት።
\v 11 እርሷም፣ “ጌታ ሆይ፣ አንድም የለም” አለች። ኢየሱስ፣ “እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁን በኋላ ግን ደግመሽ ኀጢአት አትሥሪ” አላት።
\s5
\v 12 ደግሞም ኢየሱስ ሕዝቡን፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ ቢኖር የሕይወት ብርሃን ያገኛል እንጂ፣ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው።
\v 13 ፈሪሳውያንም፣ “አንተው ስለ ራስህ ስለምትመሰክር፤ ምስክርነትህ እውነት አይደለም” አሉት።
\s5
\v 14 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እኔ ስለ ራሴ ብመሰክር እንኳ ምስክርነቴ እውነት ነው። ከየት እንደ መጣሁ፣ ወዴትም እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤ እናንተ ግን እኔ ከየት እንደ መጣሁ ወይም ወዴት እንደምሄድ አታውቁም።
\v 15 እናንተ በሥጋዊ ዐይን ትፈርዳላችሁ፤ እኔ በማንም አልፈርድም።
\v 16 ብፈርድም እንኳ፣ ብቻዬን አይደለሁም፤ ከላከኝ አብ ጋር ስለ ሆንሁ፣ ፍርዴ እውነት ነው።
\s5
\v 17 አዎን፤ በሕጋችሁ የሁለት ሰዎች ምስክርነት እውነት እንደ ሆነ ተጽፎአል።
\v 18 እኔ ስለ ራሴ እመሰክራለሁ፤ የላከኝም አብ ስለ እኔ ይመሰክራል።”
\s5
\v 19 እነርሱም፣ “አባትህ የት ነው ያለው?” አሉት። ኢየሱስም፣ “እናንተ እኔንም ሆነ አባቴን አታውቁንም፤ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር” አላቸው።
\v 20 ይህንም የተናገረው በቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት አጠገብ ሆኖ ሲያስተምር ነበር፤ ሆኖም ሰዓቱ ገና ስላልደረሰ፣ ማንም አልያዘውም።
\s5
\v 21 ደግሞም፣ “እኔ ተለይቻችሁ እሄዳለሁ፤ እናንተም ትፈልጉኛላችሁ፤ ግን በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ። እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም” አላቸው።
\v 22 አይሁድም፣ “ይህ 'እኔ ወደምሄድበት መምጣት አትችሉም' የሚለው ራሱን ሊገድል ዐስቦ ይሆን?” አሉ።
\s5
\v 23 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ከታች ናችሁ፤ እኔ ግን ከላይ ነኝ። እናንተ ከዚህ ዓለም ናችሁ፤ እኔ ግን ከዚህ ዓለም አይደለሁም።
\v 24 በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ ያልኋችሁ ለዚህ ነው። ምክንያቱም እኔ ነኝ ስላችሁ ካላመናችሁ፣ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ።”
\s5
\v 25 እነርሱም፣ “ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነህ?” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤”ከመጀመሪያው እንደ ነገርኋችሁ ነኝ።
\v 26 ብዙ የምናገረውና ስለ እናንተም የምፈርደው አለኝ። ይሁን እንጂ የላከኝ እርሱ እውነተኛ ነው፤ እኔም ከእርሱ የሰማሁትን፣ ያንኑ ለዓለም እናገራለሁ።”
\v 27 እነርሱ ግን ስለ አብ እየነገራቸው እንደ ነበር አልተረዱም።
\s5
\v 28 ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “የሰውን ልጅ ወደ ላይ ከፍ ስታደርጉት፣ በዚያን ጊዜ እኔው እንደ ሆንሁና ከራሴ አንድም ነገር እንደማላደርግ ታውቃላችሁ። አብ እንዳስተማረኝ ይህን እናገራለሁ።
\v 29 የላከኝ እርሱ ከእኔ ጋር ነው፤ ብቻዬንም አልተወኝም፤ እኔ ሁልጊዜ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር አደርጋለሁና።”
\v 30 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በተናገረ ጊዜ ብዙ ሰዎች በእርሱ አመኑ።
\s5
\v 31 ኢየሱስ በእርሱ ያመኑትን አይሁድ፣ “እናንተ በቃሌ ብትኖሩ፣ በርግጥ ደቀ መዛሙርቴ ናችሁ፤
\v 32 እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል” አላቸው።
\v 33 እነርሱም፣ “እኛ የአብርሃም ዘሮች ነን፤ የማንም ባሪያ ሆነን አናውቅም፤ ታዲያ እንዴት ‘ነጻ ትወጣላችሁ’ ትለናለህ?” አሉት።
\s5
\v 34 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ኃጢአት የሚሠራ ሁሉ የኃጢአት ባሪያ ነው።
\v 35 ባሪያ ለዘለቄታ በቤት አይኖርም፤ ልጅ ግን ለዘለቄታ ይኖራል።
\v 36 ስለዚህ ልጁ ነጻ ካወጣችሁ፣ በርግጥ ነጻ ትወጣላችሁ።
\s5
\v 37 የአብርሃም ዘር መሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ቃሌን ስላልተቀበላችሁ፣ ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ።
\v 38 አባቴ ጋ ያየሁትን እናገራለሁ፤ እናንተም ደግሞ ከአባታችሁ የሰማችሁትን ታደርጋላችሁ።”
\s5
\v 39 እነርሱም መልሰው፣ “አባታችንስ አብርሃም ነው” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “የአብርሃም ልጆችስ ብትሆኑ ኖሮ፣ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር።
\v 40 አሁን ግን ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ለመግደል ትፈልጋላችሁ። አብርሃምኮ ይህን አላደረገም።
\v 41 እናንተ ግን የአባታችሁን ሥራ ትሠራላችሁ።” እነርሱም፣ “እኛ በዝሙት የተወለድን አይደለንም፤ አንድ አባት እግዚአብሔር አለን” አሉት።
\s5
\v 42 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ ስለ መጣሁ፣ በወደዳችሁኝ ነበር፤ በራሴም ፈቃድ አልመጣሁም፤ ነገር ግን እርሱ ላከኝ።
\v 43 ቃሌን የማትረዱት ለምንድን ነው? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው።
\v 44 እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ፤ የአባታችሁንም ፍላጎት ለማድረግ ትመኛላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያውም ነፍሰ ገዳይ ነበር፤ እውነት በእርሱ ዘንድ ስለሌለም፣ በእውነት አይጸናም። ሐሰትንም ሲናገር ከራሱ አፍልቆ ይናገራል፤ ምክንያቱም እርሱ ሐሰተኛ፣ የሐሰትም አባት ነው።
\s5
\v 45 እኔ ግን እውነትን ስለምናገር አታምኑኝም።
\v 46 ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ሰው ማን ነው? እውነትን የምናገር ከሆነስ፣ ታዲያ ለምን አታምኑኝም?
\v 47 ከእግዚአብሔር ስላልሆናችሁ፣ ቃሉን አትሰሙም።”
\s5
\v 48 አይሁድም፣ “እንግዲህ ጋኔን ያደረብህ ሳምራዊ ነህ በማለታችን እውነት አልተናገርንምን?” በማለት መለሱለት።
\v 49 ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “እኔ ጋኔን የለብኝም፤ እኔ አባቴን አከብረዋለሁ እንጂ፣ እናንተ ግን ታዋርዱኛላችሁ።
\s5
\v 50 እኔ የራሴን ክብር አልሻም፤ የሚሻና የሚፈርድ አንድ አለ።
\v 51 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚጠብቅ ማንም ቢኖር፣ እርሱ ሞትን በፍጹም አያይም።”
\s5
\v 52 አይሁድም፣ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን። አብርሃምም ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን 'ማንም ቃሌን ቢጠብቅ ሞትን አይቀምስም' ትላለህ።
\v 53 አንተ ከሞተው ከአባታችን፣ ከአብርሃም ትበልጣለህን? ነቢያትም ሞተዋል። ለመሆኑ፣ አንተ ማን ነኝ ልትል ነው?” አሉት።
\s5
\v 54 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ራሴን ባከብር፣ ክብሬ ከንቱ ነው፤ እኔን የሚያከብረኝ እናንተ አምላካችን ነው የምትሉት አባቴ ነው።
\v 55 እናንተ እርሱን አላወቃችሁትም፤ እኔ ግን ዐውቀዋለሁ። እኔ ‘አላውቀውም’ ብል እንደ እናንተው ሐሰተኛ እሆናለሁ። ነገር ግን እኔ ዐውቀዋለሁ፤ ቃሉንም እጠብቃለሁ።
\v 56 አባታችሁ አብርሃም ቀኔን በማየቱ ደስ አለው፤ አይቶም ሐሤት አደረገ።”
\s5
\v 57 አይሁድም፣ “ገና ዐምሳ ዓመት ያልሞላህ፣ አንተ አብርሃምን አይተሃልን?” አሉት።
\v 58 ኢየሱስም፣ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ከመወለዱ በፊት እኔ አለሁ” አላቸው።
\v 59 እነርሱም፣ ሊወግሩት ድንጋይ አነሡ፤ ኢየሱስ ግን ራሱን ሰውሮ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ሄደ።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ኢየሱስ በመንገድ ሲያልፍ ፣ ከተወለደ ጀምሮ ዐይነ ስውር የነበረ አንድ ሰው አየ።
\v 2 ደቀ መዛሙርቱ፣ “መምህር ሆይ፤ ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ያደረገው የራሱ ኀጢአት ነው ወይስ የወላጆቹ?” አሉት።
\s5
\v 3 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ፣ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኀጢአት አልሠሩም።
\v 4 የላከኝን ሥራ ቀን ሳለ መሥራት ይገባናል። ማንም ሊሠራ የማይችልበት ሌሊት እየመጣ ነው።
\v 5 በዓለም እስካለሁ፣ የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ።”
\s5
\v 6 ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ፣ መሬት ላይ እንትፍ ብሎ፣ በምራቁ ጭቃ ሠራ፤ በጭቃውም የሰውየውን ዐይን ቀባ።
\v 7 ሰውየውንም፣ “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠበ” አለው፣ ‘ሰሊሆም’ የተላከ ማለት ነው። ሰውየውም ወደዚያው ሄዶ ታጠበ፤ ዐይኑም እያየለት ተመልሶ መጣ።
\s5
\v 8 የሰውየው ጐረቤቶችና ቀድሞ ለማኝ ሆኖ ያዩት ሰዎችም፣ “ይህ ሰው ተቀምጦ ሲለምን የነበረው ሰው አይደለምን?” አሉ።
\v 9 አንዳንዶቹ፣ “እርሱ ነው” አሉ፤ ሌሎችም፣ “ይመስለዋል እንጂ እርሱ አይደለም” አሉ። እርሱ ግን፣ “እኔው ነኝ” አለ።
\s5
\v 10 እነርሱም፣ “ታዲያ፣ ዐይኖችህ እንዴት ተከፈቱልህ?” አሉት።
\v 11 እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ “ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ ሠርቶ ዐይኔን ቀባ፤ ከዚያም፣ ‘ወደ ሰሊሆም ሄደህ ታጠብ’ አለኝ። እኔም ሄጄ ታጠብሁ፤ ዐይኖቼም በሩ።”
\v 12 እነርሱም፣ “ታዲያ፣ እርሱ የት ነው?” አሉ። እርሱም፣ “እኔ አላውቅም” ብሎ መለሰላቸው።
\s5
\v 13 እነርሱም ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ወደ ፈሪሳውያን ወሰዱት።
\v 14 ኢየሱስ ጭቃ ሠርቶ የሰውየውን ዐይን የከፈተው በሰንበት ቀን ነበረ።
\v 15 ፈሪሳውያንም ዐይኑ እንዴት እንደ ተከፈተለት እንደ ገና ሰውየውን ጠየቁት። እርሱም፣ “ዐይኖቼን ጭቃ ቀባ፤ ታጠብሁና ማየት ቻልሁ” አላቸው።
\s5
\v 16 ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎቹም፣ “ኀጢአተኛ የሆነ ሰው እንዴት እንደዚህ ያለ ተአምር ይሠራል?” አሉ። ስለዚህ በመካከላቸው መከፋፈል ተፈጠረ።
\v 17 እንደ ገናም ዐይነ ስውሩን ሰው፣ “ዐይንህን ስለ ከፈተው ሰው ምን ትላለህ?” አሉት። ዐይነ ስውሩም፣ “ነቢይ ነው” አለ።
\v 18 ፈሪሳውያንም ዐይነ ስውር የነበረው ሰው ዐይኖች መከፈታቸውን አሁንም ስላላመኑ፣ ዐይኑ የበራለትን ሰው ወላጆች አስጠሩ።
\s5
\v 19 ወላጆቹንም፣ “ይህ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደ ነው የምትሉት ሰው ልጃችሁ ነውን? ከሆነስ፣ አሁን እንዴት ማየት ቻለ?” ብለው ጠየቋቸው።
\v 20 ወላጆቹም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “ይህ ልጃችን መሆኑንና ዐይነ ስውር ሆኖ መወለዱን እናውቃለን።
\v 21 አሁን እንዴት ማየት እንደ ቻለ ግን አናውቅም፤ ዐይኑን የከፈተለት ማን እንደ ሆነም አናውቅም። እርሱን ጠይቁት፤ ጕልማሳ ነው፤ ስለ ራሱ መናገር ይችላል።”
\s5
\v 22 ወላጆቹ እንዲህ ያሉት አይሁድን ስለ ፈሩ ነበር። ምክንያቱም አይሁድ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው የሚል ሰው ካገኙ፣ ከምኵራብ ሊያስወግዱት ቀደም ብለው ተስማምተው ነበር።
\v 23 ወላጆቹ፣ “እርሱ ጕልማሳ ነው፤ ራሱን ጠይቁት” ያሉትም በዚህ ምክንያት ነበር።
\s5
\v 24 ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው እንደ ገና አስጠርተው፣ “ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፤ እኛ ይህ ሰው ኀጢአተኛ እንደ ሆነ እናውቃለን” አሉት።
\v 25 ሰውየውም፣ “እኔ እርሱ ኀጢአተኛ መሆኑን አላውቅም። ነገር ግን አንድ ነገር ዐውቃለሁ፤ ዐይነ ስውር ነበርሁ፤ አሁን ግን እያየሁ ነው” አላቸው።
\s5
\v 26 እነርሱም፣ “ያደረገልህ ምንድን ነው? ዐይኖችህንስ የከፈተው እንዴት ነው?” አሉት።
\v 27 እርሱም፣ “አስቀድሜ ነግሬአችሁ ነበር! እናንተ ግን አትሰሙም። እንደ ገና መስማትስ ለምን ፈለጋችሁ? እናንተም የእርሱ ደቀ መዛሙርት ለመሆን ትፈልጋላችሁን?” ብሎ መለሰ።
\v 28 ሰደቡትና እንዲህ አሉ፤ “አንተ የእርሱ ደቀ መዝሙር ነህ፣ እኛ ግን የሙሴ ደቀ መዛሙርት ነን።
\v 29 እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው እናውቃለን፤ ይህ ሰው ግን ከየት እንደ መጣ አናውቅም።”
\s5
\v 30 ሰውየውም፣ “ይህ ሰው ከየት እንደ መጣ አለማወቃችሁ የሚገርም ነው፤ ይሁን እንጂ፣ ዐይኔን የከፈተው እርሱ ነው።
\v 31 እግዚአብሔር ኀጢአተኞችን እንደማይሰማ እናውቃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን የሚያመልክና ፈቃዱን የሚያደርግ ሰው ሁሉ እግዚአብሔር ይሰማዋል።
\s5
\v 32 ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ፣ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደን ሰው ዐይን የከፈተ ሰው ከቶ አልተሰማም።
\v 33 ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ፣ አንድም ነገር ማድረግ ባልቻለ ነበር።”
\v 34 እነርሱም፣ መልሰው “አንተ ሁለንተናህ በኀጢአት የተወለደ፣ አሁን አንተ እኛን ታስተምረናለህን?” አሉት። ከዚያም ከምኵራብ አስወጡት።
\s5
\v 35 ኢየሱስም ሰውየውን ከምኵራብ እንዳስወጡት ሰማ። ሰውየውንም አግኝቶ፣ “በሰው ልጅ ታምናለህን?” አለው።
\v 36 እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ አምንበት ዘንድ እርሱ ማን ነው?” አለው።
\v 37 ኢየሱስም፣ “አይተኸዋል፤ አሁን እንኳ ከአንተ ጋር እየተነጋገረ ያለው እርሱ ነው” አለው።
\v 38 ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፣ አምናለሁ” አለ። ከዚያም ሰገደለት።
\s5
\v 39 ኢየሱስም፣ “የማያዩ እንዲያዩ፣ የሚያዩም እንዳያዩ፣ ለፍርድ ወደዚህ ዓለም መጣሁ” አለ።
\v 40 ከእነርሱም ጋር ከነበሩት አንዳንድ ፈሪሳውያን ይህን ሰምተው፣ “እኛም ደግሞ ዐይነ ስውራን ነን ወይ?” አሉት።
\v 41 ኢየሱስም ፣ “ዐይነ ስውራን ብትሆኑማ፣ ኀጢአት ባልሆነባችሁ ነበር። ነገር ግን፣ ‘እናያለን’ ስለምትሉ፣ ኀጢአታችሁ እንዳለ ይኖራል።”
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 “እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ ወደ በጎች በረት በበር ሳይሆን፣ በሌላ መንገድ ተንጠላጥሎ የሚገባ እርሱ ሌባና ወንበዴ ነው።
\v 2 በበር የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው።
\s5
\v 3 በር ጠባቂውም ለእርሱ ይከፍትለታል። በጎቹም ድምፁን ይሰማሉ፤ እርሱም የራሱን በጎች በስማቸው ጠርቶ፣ ወደ ውጭ ይመራቸዋል።
\v 4 የራሱን ሁሉ ካወጣቸው በኋላ፣ ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ በጎቹም ድምፁን ስለሚያውቁ ይከተሉታል።
\s5
\v 5 ባዕድ የሆነውን አይከተሉትም፤ ይልቁንም የባዕዱን ድምፅ ስለማያውቁት ይሸሹታል።”
\v 6 ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ስለ ምን እንደ ሆነ አልገባቸውም።
\s5
\v 7 ኢየሱስም እንደ ገና እንዲህ አላቸው፤ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፤ የበጎች በር እኔ ነኝ።
\v 8 ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ በጎቹ ግን አላዳመጡአቸውም።
\s5
\v 9 በሩ እኔ ነኝ። ማንም በእኔ በኩል ቢገባ፣ ይድናል፤ ይገባል፣ ይወጣልም፤ መሰማሪያም ያገኛል።
\v 10 ሌባው የሚመጣው ሊሰርቅ፣ ሊገድልና ሊያጠፋ ብቻ ነው። እኔ ግን ሕይወት እንዲኖራቸውና እንዲትረፈረፍላቸው መጥቻለሁ።
\s5
\v 11 መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ለበጎቹ ሲል ነፍሱን ይሰጣል።
\v 12 እረኛ ያልሆነው ተቀጣሪ በጎቹም የእርሱ ያልሆኑት፣ ቀበሮ መምጣቱን ሲያይ በጎቹን ጥሎ ይሸሻል ። ቀበሮም ነጥቆአቸው ይሄዳል፤ ይበታትናቸውማል።
\v 13 የሚሸሸውም ተቀጣሪ ስለ ሆነና ለበጎቹ ደንታ ስለሌለው ነው።
\s5
\v 14 መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ የእኔ የሆኑትን ዐውቃቸዋለው፤ የእኔ የሆኑትም ያውቁኛል።
\v 15 አብ እንደሚያውቀኝ፤ እኔም አብን ዐውቀዋለው፤ ነፍሴንም ስለ በጎች እሰጣለሁ።
\v 16 ከዚህ በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ። እነዚያን ደግሞ ማምጣት አለብኝ፤ እነርሱ ድምፄን ይሰማሉ። አንድ መንጋ ይሆናሉ፤ እረኛቸውም አንድ ይሆናል።
\s5
\v 17 አባቴ የሚወደኝ ለዚህ ነው፤ መልሼ ልወስደው እንድችል ነፍሴን እሰጣለሁ ።
\v 18 ነፍሴን ማንም ከእኔ አይወሰድም፤ ግን እኔው ራሴ እሰጣለሁ ። ለመስጠት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ ለመውሰድም ሥልጣን አለኝ። ይህን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀብያለሁ።”
\s5
\v 19 ከዚህ አባባል የተነሣም በአይሁድ መካከል እንደ ገና መከፋፈል ተፈጠረ።
\v 20 ብዙዎች፣ “ጋኔን ስላለበት ዐብዶአል፤ ለምን ታዳምጡታላችሁ?” አሉ።
\v 21 ሌሎችም፣ “ንግግሩ ጋኔን ያለበት ሰው ንግግር አይደለም። ጋኔን ያለበት ሰው የዐይነ ስውርን ዐይን መክፈት ይችላልን?” አሉ።
\s5
\v 22 በኢየሩሳሌምም የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል ደርሶ ነበር።
\v 23 ጊዜው ክረምት ነበረ፤ ኢየሱስም በቤተ መቅደስ በሰሎሞን መተላለፊያ ይመላለስ ነበር።
\v 24 ከዚያም አይሁድ ወደ እርሱ ተሰብስበው፣ «እስከ መቼ ድረስ ልባችንን ታንጠለጥላለህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንህ፣ በግልጽ ንገረን» አሉት።
\s5
\v 25 ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “ነገርኋችሁኮ፤ እናንተ ግን አታምኑም፤ በአባቴ ስም የማደርጋቸው ሥራዎች እነዚህ ስለ እኔ ይመሰክራሉ።
\v 26 እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
\s5
\v 27 በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔ ዐውቃቸዋለሁ፤ እነርሱም ይከተሉኛል።
\v 28 የዘላለም ሕይወት እሰጣቸዋለው፤ ፈጽሞም አይጠፉም፤ ነጥቆ ከእጄ የሚያወጣቸው ማንም የለም።
\s5
\v 29 እነርሱን ለእኔ የሰጠ አባቴ ከሌሎች ሁሉ ይበልጣል፤ ስለዚህ ከአብ እጅ ነጥቆ ሊያወጣቸው የሚችል ማንም የለም።
\v 30 እኔና አብ አንድ ነን።”
\v 31 አይሁድ ሊወግሩት እንደ ገና ድንጋይ አነሡ።
\s5
\v 32 ኢየሱስም መልሶ፣ «ከአብ የሆነ ብዙ መልካም ሥራ አሳይቻችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሥራዎች ውስጥ በየትኛው ምክንያት ትወግሩኛላችሁ?” አላቸው።
\v 33 አይሁድም መልሰው፣ «የምንወግርህ በየትኛውም መልካም ሥራ ምክንያት አይደለም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ላይ በምትሰነዝረው የስድብ ቃል ምክንያት ነው፤ አንተ ሰው ሆነህ ሳለህ፣ ራስህን አምላክ እያደረግህ ስለ ሆነ ነው» አሉት።
\s5
\v 34 ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ «በሕጋችሁ፣ ‘አማልክት ናችሁ አልሁ’ ተብሎ አልተጻፈምን?
\v 35 የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ናችሁ ካላቸው፣ የመጻሕፍት ቃል አይሻርምና፣
\v 36 እኔ ‘የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ስላልሁ፣ አብ ቀድሶ ወደ ዓለም የላከውን እንዴት የስድብ ቃል ሰነዘረ ትሉታላችሁ?
\s5
\v 37 እኔ የአባቴን ሥራዎች የማላደርግ ከሆንሁ አትመኑኝ።
\v 38 ነገር ግን የማደርጋቸው ከሆንሁ፣ በእኔ ባታምኑ እንኳ፣ አብ በእኔ እንዳለ፣ እኔም በአብ እንዳለሁ እንድታውቁና እንድትረዱ፣ በሥራዎቹ እመኑ።»
\v 39 እነርሱም ኢያሱስን እንደ ገና ለመያዝ ሞከሩ፣ እርሱ ግን ከእጃቸው አምልጦ ሄደ።
\s5
\v 40 ኢየሱስ ዮርዳኖስን ተሻግሮ፣ ዮሐንስ በመጀመሪያ ሲያጠምቅበት ወደ ነበረው ቦታ እንደ ገና ሄደ፤ በዚያም ቆየ ።
\v 41 ብዙ ሰዎች ወደ ኢየሱስ መጡ። እነርሱም፣ «በርግጥ ዮሐንስ ምንም ተአምር አልሠራም፤ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነው» ይሉ ነበር።
\v 42 በዚያም ብዙ ሰዎች በኢያሱስ አመኑ።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 አልዓዛር የተባለ አንድ ሰውም ታሞ ነበር። እርሱም ማርያምና እኅትዋ ማርታ በሚኖሩበት መንደር በቢታንያ ይኖር ነበር።
\v 2 ወንድምዋ የታመመባትም የጌታ ኢየሱስን እግር ሽቱ የቀባችውና በጠጕርዋ ያበሰችው ናት።
\s5
\v 3 ከዚያም እኅትማማቹ፣ ‹‹እነሆ፣ የምትወደው ታሞአልና በፍጥነት ድረስ›› በማለት ወደ ኢየሱስ ላኩበት።
\v 4 ኢየሱስ መልእክቱን በሰማ ጊዜ፣ ‹‹ይህ የእግዚአብሔር ልጅ እንዲከብርበት ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ነው›› አለ።
\s5
\v 5 ኢየሱስ ማርታንና እኅቷን እንዲሁም አልዓዛርን ይወድ ነበር፡፡
\v 6 ስለሆነም አልዓዛር መታመሙን በሰማ ጊዜ፣ ኢየሱስ በነበረበት ቦታ ሁለት ተጨማሪ ቀናት ቆየ፡፡
\v 7 ከዚህ በኋላም ደቀ መዛሙርቱን፣ “ወደ ይሁዳ ዳግመኛ እንሂድ” አላቸው፡፡
\s5
\v 8 ደቀ መዛሙርቱ፣ “መምህር ሆይ፣ አይሁድ አሁን ሊወግሩህ ነበር፣ እንደ ገና ወደዚያ ተመልሰህ ትሄዳለህን?” አሉት፡፡
\v 9 ኢየሱስም፣ “በአንድ ቀን ውስጥ አሥራ ሁለት የብርሃን ሰዓታት አሉ አይደለምን? አንድ ሰው በቀን የሚራመድ ከሆነ የቀኑን ብርሃን ስለሚመለከት፣ አይደናቀፍም፡፡
\s5
\v 10 በሌሊት የሚራመድ ከሆነ ግን ብርሃኑ በእርሱ ውስጥ ስለሌለ፣ ይደናቀፋል፡፡”
\v 11 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ተናገረ፣ ከእነዚህም ነገሮች በኋላ፣ “ወዳጃችን አልዓዛር አንቀላፍቷል፣ እኔ ግን ከእንቅልፉ ላነቃው እሄዳለሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ፣ “ጌታ ሆይ፣ ተኝቶስ ከሆነ ይድናል” አሉት፡፡
\v 13 ኢየሱስም የተናገረው አልዓዛር ስለ መሞቱ ነበር፣ እነርሱ ግን ዕረፍት ለማድረግ ስለ መተኛቱ የተናገረ መስሎአቸው ነበር፡፡
\v 14 ከዚያም ኢየሱስ በግልጽ፣ “አልዓዛር ሞቷል
\s5
\v 15 እናንተ ታምኑ ዘንድ እኔ እዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ብሎኛል” አላቸው፡፡
\v 16 ዲዲሞስ የተባለው ቶማስ ባልደረቦቹ ደቀ መዛሙርትን፣ “ከኢየሱስ ጋር እንሞት ዘንድ እኛም ከእርሱ ጋር እንሂድ” አላቸው፡፡
\s5
\v 17 ኢየሱስ በመጣ ጊዜ፣ አልዓዛር በመቃብር ውስጥ አራት ቀን መቆየቱን ተረዳ፡፡
\v 18 ቢታንያ አሥራ አምስት ኪሎ ሜትር ብቻ የምትርቅ ለኢየሩሳሌም ቅርብ ስፍራ ነበረች፡፡
\v 19 ስለ ወንድማቸው ሞት ሊያጽናኗቸው ከአይሁድ ብዙዎቹ መጥተው ነበር፡፡
\v 20 ከዚያም ማርታ ኢየሱስ እንደ መጣ በሰማች ጊዜ፣ ልትቀበለው ወጣች፣ ማርያም ግን በቤት ተቀምጣ ነበር፡፡
\s5
\v 21 ከዚያም ማርታ ኢየሱስን፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትኖር ኖሮ ወንድሜ ባልሞተም ነበር፡፡
\v 22 አሁንም ቢሆን የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰጥህ ዐውቃለሁ” አለችው፡፡
\v 23 ኢየሱስ፣ “ወንድምሽ ይነሣል” አላት፡፡
\s5
\v 24 ማርታ፣ “በመጨረሻው ቀን በሚሆነው በትንሣኤ ከሞት እንደሚነሣ ዐውቃለሁ” አለችው፡፡
\v 25 ኢየሱስ፣ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ፣ በእኔ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፡፡
\v 26 በእኔ የሚኖርና የሚያምንብኝ ሁሉ ፈጽሞ አይሞትም፤ ይህን ታምኛለሽን?” አላት፡፡
\s5
\v 27 እርሷም፣ “አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ አንተ ወደ ዓለም ልትመጣ ያለኸው ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆንህ አምናለሁ” አለችው፡፡
\v 28 ማርታ ይህን ከተናገረች በኋላ እኅቷን ማርያምን በግል ለማነጋገር ትጠራት ዘንድ ሄደችና፣ “መምህሩ እዚህ ነው፣ ሊያነጋግርሽ ይፈልጋል” አለቻት፡፡
\v 29 ማርያም ይህን እንደ ሰማች በፍጥነት ተነሥታ ወደ ኢየሱስ ሄደች፡፡
\s5
\v 30 ኢየሱስም ማርታን ባገኘበት ስፍራ ነበር እንጂ ገና ወደ መንደሩ አልገባም ነበር፡፡
\v 31 ከዚያም በቤት ውስጥ ሆነው ማርያምን ሲያጽናኗት የነበሩት አይሁድ ፈጥና ስትወጣ ባዩአት ጊዜ፣ ወደ መቃብር ሄዳ በዚያ ልታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት፡፡
\v 32 ከዚያም ማርያም ኢየሱስ ወደ ነበረበት መጥታ ስታየው በእግሩ ሥር ወድቃ፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ፣ ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው፡፡
\s5
\v 33 ኢየሱስ እርሷና ዐብረዋት የነበሩት አይሁድ ሲያለቅሱ ተመልክቶ በመንፈሱ ቃትቶና ተጨንቆ፣
\v 34 “ወዴት አኖራችሁት?” አላቸው፡፡ እነርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት፡፡
\v 35 ኢየሱስ አለቀሰ፡፡
\s5
\v 36 ከዚያም አይሁድ፣ “አልዓዛርን ምን ያህል ይወደው እንደ ነበረ ተመልከቱ!” አሉ፡፡
\v 37 ከእነርሱ አንዳንዶቹ ግን፣ “ዓይነ ስውር የነበረውን ሰውዬ ዓይን የከፈተ ይህ ሰው የሞተውን ይህን ሰው እንዳይሞት ማድረግ አይችልም ነበር?” አሉ፡፡
\s5
\v 38 ከዚያም ኢየሱስ አሁንም በውስጡ እየቃተተ ወደ መቃብሩ ሄደ፡፡ መቃብሩ ዋሻ ነበረ፣ ድንጋይም ተገጥሞበት ነበር፡፡
\v 39 ኢየሱስ፣ “ድንጋዩን አንሡት” አለ፡፡ የሟቹ የአልዓዛር እኅት ማርታም ኢየሱስን፣ “ከሞተ አራት ቀን ስለሆነው፣ በአሁኑ ጊዜ ገላው ይበሰብሳል” አለችው፡፡
\v 40 ኢየሱስ ማርታን፣ “ብታምኚስ፣ የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታዪ አልነገርሁሽምን” አላት፡፡
\s5
\v 41 ስለዚህ ድንጋዩን አነሡት፡፡ ኢየሱስም ሽቅብ እየተመለከተ፣ “አባት ሆይ፣ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤
\v 42 ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ ዐውቃለሁ፣ ነገር ግን ይህን ያልሁት አንተ እንደላክኸኝ ያምኑ ዘንድ እዚህ በዙሪያዬ ስለቆመው ሕዝብ ነው” አለ፡፡
\s5
\v 43 ይህን ካለ በኋላ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “አልዓዛር ሆይ፣ ውጣ!” አለ፡፡
\v 44 የሞተው ሰው እጁና እግሩ በመገነዣ ጨርቅ እንደ ተጠቀለለ፣ ፊቱም በጨርቅ እንደ ተሸፈነ ወጣ፡፡ ኢየሱስ፣ “ፍቱትና ይሂድ” አላቸው፡፡
\s5
\v 45 ከዚያም ወደ ማርያም ከመጡትና ይህን ከተመለከቱት አይሁድ አብዛኛዎቹ በእርሱ አመኑ፤
\v 46 ነገር ግን ከእነርሱ አንዳንዶቹ ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሯቸው፡፡
\s5
\v 47 ከዚያም ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያን ጉባዔ ጠርተው፣ “ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶችን እያደረገ ነው፡፡
\v 48 እንደዚሁ የምንተወው ከሆነ፣ ሮማውያን መጥተው ስፍራችንና አገራችንንም ይወስዳሉ” አሉ፡፡
\s5
\v 49 ሆኖም በዚያ ዓመት ሊቀ ካህን የነበረ ከእነርሱ መካከል ቀያፋ የተባለው አንዱ፣ “እናንተ ምንም አታውቁም፤
\v 50 አገሪቱ በመላ ከምትጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት የተሻለ እንደሆነ ከግምት ውስጥ አላስገባችሁም” አላቸው፡፡
\s5
\v 51 እርሱ ይህን የተናገረው ከራሱ አልነበረም፣ ይልቁንም በዚያ ዓመት ሊቀ ካህን ስለ ነበረ፣ ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ፣
\v 52 ደግሞም ስለ ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በልዩ ልዩ ስፍራ የተበታተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ይሰበስብ ዘንድ መሞት እንደሚገባው ትንቢት ተናገረ፡፡
\v 53 ስለዚህ ከዚያ ቀን ጀምሮ ኢየሱስን እንዴት መግደል እንዳለባቸው ዕቅድ አወጡ፡፡
\s5
\v 54 ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ በአይሁድ መካከል በግልጽ መውጣትና መግባቱን ትቶ ኤፍሬም ወደ ተባለው በበረሐው አጠገብ ወዳለው ከተማ ሄደ፡፡ እዚያ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ቈየ፡፡
\v 55 የአይሁድ የፋሲካ በዓልም ቀርቦ ነበረና ብዙዎች ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካው በፊት ከየገጠሩ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር፡፡
\s5
\v 56 ኢየሱስን እየፈለጉት፣ በቤተ መቅደስ ቆመው ሳሉ፣ “ምን ይመስላችኋል? ወደ በዓሉ አይመጣ ይሆን?” እያሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር፡፡
\v 57 ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያኑም ኢየሱስን ይይዙት ዘንድ እርሱ የት እንዳለ ያወቀ ማንኛውም ሰው ጥቆማ እንዲያቀርብ ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 የፋሲካ በዓል ሊከበር ስድስት ቀናት ሲቀሩት ኢየሱስ ከሞት ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡
\v 2 ስለዚህ በዚያ እራት አዘጋጁለት፣ አልዓዛር ከኢየሱስ ጋር በማዕድ ከተቀመጡት ጋር ሲሆን ማርታ ደግሞ ታገለግላቸው ነበር፡፡
\v 3 ማርያም ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ በጣም ውድ የሽቱ ብልቃጥ ወስዳ የኢየሱስን እግር ትቀባ፣ በፀጉሩዋም ታብስ ስለነበር፣ ቤቱ በሽቱው መዓዛ ታወደ፡፡
\s5
\v 4 ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ኢየሱስን አሳልፎ የሚሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ፣
\v 5 “ይህ ሽቱ በሦስት መቶ ዲናር ተሸጦ ለድሆች ያልተሰጠው ለምንድን ነው?” አለ፡፡
\v 6 ይህን ያለው ለድሆች ተገዶላቸው ሳይሆን ሌባ ስለነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢቱን የሚይዘው እርሱ ስለነበረ፣ ከዚያ ውስጥ ለራሱ ጥቂት ይወስድ ነበር፡፡
\s5
\v 7 ኢየሱስ፣ “የያዘችውን ለቀብሬ ቀን እንድታቆየው ፍቀዱላት፤
\v 8 ድሆች ምንጊዜም ከእናንተ ጋር ይሆናሉ፣ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም” አላቸው፡፡
\s5
\v 9 ብዙ የአይሁድ ሕዝብም ኢየሱስ በዚያ እንደነበረ ተረድተው ነበርና ወደዚያ መጡ፣ የመጡትም ለኢየሱስ ብቻ ብለው ሳይሆን ኢየሱስ ከሞት ያስነሣውን አልዓዛርንም ለማየት ጭምር ነበር፡፡
\v 10 የካህናት አለቆች አልዓዛርን ደግሞ ለመግደል በአንድነት የተንኮል ስምምነት አደረጉ፣
\v 11 ምክንያቱም ብዙ አይሁድ የሄዱትና በኢየሱስ ያመኑት ከእርሱ የተነሣ ነበር፡፡
\s5
\v 12 በማግስቱ ብዙ ሕዝብ ወደ በዓሉ መጡ። ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መምጣቱን በሰሙ ጊዜ፣
\v 13 የዘንባባ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው፣ “ሆሣዕና! በጌታ ስም የሚመጣ የእስራኤል ንጉሥ የተባረከ ነው” እያሉ ሊቀበሉት ወጡ፡፡
\s5
\v 14 ኢየሱስ የአህያ ውርንጫ አገኘና ተቀመጠባት፣ ይህንን ያደረገው፣
\v 15 “የጽዮን ልጅ ሆይ፣ አትፍሪ፣ እነሆ፣ ንጉሥሽ በአህያ ውርንጫ ላይ ተቀምጦ ይመጣል” ተብሎ በተጻፈው መሠረት ነው፡፡
\s5
\v 16 ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ ይህን አልተረዱም ነበር፣ ኢየሱስ በከበረ ጊዜ ግን እነዚህ ነገሮች ስለ እርሱ ተጽፈው እንደነበረና እነርሱም እነዚህን ነገሮች ለእርሱ እንዳደረጉለት ተገነዘቡ፡፡
\s5
\v 17 ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር በጠራውና ከሞት ባስነሣው ጊዜ በዚያ የነበሩት ሕዝብም ለሌሎች መሰከሩላቸው፡፡
\v 18 ይህን ምልክት እንዳደረገ ሰምተው ነበርና ሊቀበሉት የወጡትም በዚህ ምክንያት ነበር፡፡
\v 19 ስለዚህ ፈሪሳውያን እርስ በርሳቸው፣ “ምንም ማድረግ እንደማትችሉ ተመልከቱ፣ ዓለሙ ተከትሎታል” ተባባሉ፡፡
\s5
\v 20 በበዓሉ ሊያመልኩ ከሄዱት መካከል አንዳንድ የግሪክ ሰዎችም ነበሩ፡፡
\v 21 እነዚህ በገሊላ ካለችው ከቤተሳይዳ ወደ ሆነው ወደ ፊልጶስ ዘንድ ሄደው፣ “ጌታ ሆይ፣ ኢየሱስን ማየት እንፈልጋለን” አሉት፡፡
\v 22 ፊልጶስ ሄዶ ለእንድርያስ ነገረው፣ እንድርያስና ፊልጶስም ዐብረው ሄዱና ለኢየሱስ ነገሩት፡፡
\s5
\v 23 ኢየሱስም፣ “የሰው ልጅ የሚከብርበት ሰዓት ደርሷል፤
\v 24 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ የስንዴ ዘር ወደ ምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች፡፡” ብሎ መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 25 ሕይወቱን የሚወድ ያጠፋታል፤ ነገር ግን በዚህ ዓለም እያለ ሕይወቱን የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት እንድትጠበቅ ያደርጋታል።
\v 26 ማንም ሊያገለግለኝ የሚወድ ይከተለኝ፤ እኔ ባለሁበት አገልጋዬም በዚያ ይሆናል። ማንም ቢያገለግለኝ አብ ያከብረዋል።
\s5
\v 27 አሁን ነፍሴ ታውካለች ምን እላለሁ? 'አባት ሆይ፣ ከዚህ ሰዓት አድነኝ' ነገር ግን ስለዚህ ጉዳይ ወደዚህ ሰዓት መጥቻለሁ።
\v 28 አባት ሆይ፣ ስምህን አክብረው።» ከዚያም ከሰማይ፣ «አክብሬዋለሁ ደግሞም አከብረዋለሁ» የሚል ድምፅ መጣ።።
\v 29 ባጠገቡ ቆመው የነበሩትና ድምፁን የሰሙት ብዙ ሕዝብ ነጐድጓድ መሰላቸው። ሌሎች ደግሞ «መልአክ ተናግሮታል» አሉ።
\s5
\v 30 ኢየሱስ መልሶ፣ «ይህ ድምፅ የመጣው ስለ እኔ ሳይሆን ስለ እናንተ ነው» አለ።
\v 31 በዚህ ዓለም ላይ የሚፈረድበት ጊዜ አሁን ነው፤ አሁን የዚህ ዓለም ገዢ ወደ ውጭ ይጣላል።
\s5
\v 32 እኔ ከምድር ከፍ ከፍ በምልበት ጊዜ፣ ሰውን ሁሉ ወደ ራሴ እስባለሁ።»
\v 33 ይህን የተናገረው በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚሞት ለማመልከት ነበር።
\s5
\v 34 ሕዝቡ፣ «ክርስቶስ ለዘላለም እንደሚኖር ከሕጉ ሰምተናል። ታዲያ 'የሰው ልጅ ከፍ ከፍ ማለት አለበት እንዴት ትላለህ?' ይህስ የሰው ልጅ ማን ነው?» ብለው መለሱለት።
\v 35 ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ «አሁን ለጥቂት ጊዜ ብርሃን በመካከላችሁ አለ፤ ጨለማ እንዳይውጣችሁ በዚህ ብርሃን ተመላለሱ። በጨለማ የሚመላለስም ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።
\v 36 የብርሃን ልጆች እንድትሆኑ ብርሃኑ እያለላችሁ በብርሃኑ እመኑ።» ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ከእነርሱ ተለየ፤ ተሰወረባቸውም።
\s5
\v 37 ምንም እንኳ ኢየሱስ በሕዝቡ ፊት ብዙ ምልክቶችን ቢያደርግም በእርሱ አላመኑም።
\v 38 ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ፣ «ጌታ ሆይ የተናገርነውን ማን አመነ? የጌታስ ክንድ ለማን ተገለጠ?» በማለት የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 39 በዚህም ምክንያት ማመን አልቻሉም፤ ኢሳይያስ እንደ ገና እንዲህ ብሏልና፤
\v 40 «ዐይኖቻቸውን አሳውሯል፤ ልባቸውንም አደንድኗል፤ ይህም የሆነው በዐይናቸው ዐይተው በልባቸው አስተውለውና ተመልሰው እንዳልፈውሳቸው ነው።»
\s5
\v 41 ኢሳይያስ እነዚህን ነገሮች የተናገረው የኢየሱስን ክብር ስላየና ስለ እርሱም ስለ ተናገረ ነው፤
\v 42 የሆነ ሆኖ ከገዢዎች እንኳ ብዙዎች በኢየሱስ አምነዋል፤ ነገር ግን ፈሪሳውያን ከምኵራብ እንዳያግዷቸው በመፍራት ማመናቸውን አልገለጹም።
\v 43 በእግዚአብሔር ከመመስገን ይልቅ በሰዎች ለመመስገን ወደዱ።
\s5
\v 44 ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፤ «በእኔ የሚያምን በእኔ ብቻ የሚያምን ሳይሆን በላከኝም ያምናል፤
\v 45 እንደዚሁም እኔን የሚያይ የላከኝንም ያያል።
\s5
\v 46 በእኔ የሚያምን በጨለማ ውስጥ እንዳይኖር ብርሃን ሆኜ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤
\v 47 ማንም ቃሌን ሰምቶ ባያደርገው የምፈርድበት እኔ አይደለሁም፤ ዓለምን ለማዳን እንጂ በዓለም ላይ ልፈርድ አልመጣሁምና።
\s5
\v 48 እኔን የሚቃወምና ቃሌንም የማይቀበል የሚፈርድበት አለ፤ በመጨረሻው ቀን የሚፈርድበት እኔ የተናገርሁት ቃል ነው።
\v 49 ምክንያቱም ይህ ቃል ከራሴ የተናገርሁት አይደለም፤ ይልቁን ምን እንደምልና እንደምናገር ትእዛዝ የሰጠኝ የላከኝ አብ ነው።
\v 50 ትእዛዙም የዘላለም ሕይወት እንደሚያስገኝ አውቃለሁ፤ ስለዚህ የምናገረው ቃል አብ እንደ ነገረኝ የምናገረው ነው።»
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ከፋሲካ በዓል በፊት ከዚህ ዓለም ተለይቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት እንደ ደረሰ ስላወቀ፣ ቀድሞውኑ የሚወዳቸውን በዓለም ይኖሩ የነበሩትን የራሱን ወገኖች እስከ መጨረሻው ወደዳቸው።
\v 2 ዲያብሎስም ኢየሱስን አሳልፎ እንዲሰጥ በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ ልብ ክፉ ዐሳብ አስገባ።
\s5
\v 3 ኢየሱስ አብ ሁሉን ነገር በእጁ አሳልፎ እንደ ሰጠው፣ ከእግዚአብሔር እንደ መጣ ወደ እግዚአብሔርም ተመልሶ እንደሚሄድ ዐወቀ፤
\v 4 ከእራት ላይ ተነሣ፤ መጎናጸፊያውንም አስቀመጠ፤ ከዚያም ፎጣ ወስዶ ወገቡ ላይ ከታጠቀ በኋላ
\v 5 በሳሕን ውስጥ ውሃ ጨምሮ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠብና በያዘውም ፎጣ ማበስ ጀመረ።
\s5
\v 6 ወደ ስምዖን ጴጥሮስ መጣ፤ ጴጥሮስም «ጌታ ሆይ የእኔን እግር ልታጥብ ነውን?» አለው
\v 7 ኢየሱስም «የማደርገውን አሁን አይገባህም፤ወደፊት ግን ትረዳዋለህ» በማለት መለሰለት
\v 8 ጴጥሮስም «ፈጽሞ የእኔን እግር አታጥብም» አለው ኢየሱስም «እግርህን ካላጠብሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፈንታ አይኖርህም» ሲል መለሰለት
\v 9 ስምዖን ጴጥሮስም «ጌታ ሆይ እንግዲያስ እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንና ራሴንም እጠበኝ» አለው
\s5
\v 10 ኢየሱስም «ገላውን የታጠበ እግሩን ብቻ ከመታጠብ በስተቀር ሌላ ሰውነቱ ንጹህ ነው፤ እናንተ ንጹሓን ናችሁ ነገር ግን ይህን ስል ሁላችሁንም ማለቴ አይደለም»
\v 11 ኢየሱስ «ሁላችሁም ንጹህ አይደላችሁም» ያለው ኣሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ ያውቅ ስለነበረ ነው
\s5
\v 12 ኢየሱስ እግራቸውን አጥቦ ከጨረሰ በኋላ ልብሱን ለብሶ ተቀመጠ፤ እነርሱንም፣ «ያደረግሁላችሁን ልብ ብላችኋል?
\v 13 'መምህር' እና 'ጌታ' ትሉኛላችሁ። እንደዚያም ስለሆንሁ አባባላችሁ ትክክል ነው።
\v 14 እኔ ጌታና መምህር ሆኜ እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ልትተጣጠቡ ይገባል።
\v 15 እኔ እንዳደረግሁላችሁ እንደዚያው ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ትቼላችኋለሁ።
\s5
\v 16 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም ወይም የተላከ ሰው ከላኪው አይበልጥም።
\v 17 እነዚህን ነገሮች ብታውቁና ብታደርጓቸው የተባረካችሁ ናችሁ።
\v 18 የምናገረው ሁላችሁን በሚመለከት አይደለም፤ የመረጥኋቸውን አውቃለሁና፣ ነገር ግን እንደዚህ የምናገረው እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ የሚለው የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 19 ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ የምነግራችሁ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ እንደሆንሁ እንድታምኑ ነው።
\v 20 እውነት እውነት እላችኋለሁ እኔን የሚቀበል የላክሁትን ይቀበላል፤ እኔን የተቀበለ ደግሞ የላክኝን ይቀባላል»
\s5
\v 21 ኢየሱስ ይህን በሚናገርበት ጊዜ በመንፈሱ ታወከ፤ «እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእናንተ መካከል አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል» ብሎ በግልጽ ነገራቸው
\v 22 ደቀ መዛሙርቱም ስለማን እየተናገረ እንደሆነ ስላልገባቸው እርስ በርስ ተያዩ።
\s5
\v 23 ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የሆነው ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ወደ ደረቱ ተጠግቶ ተቀምጦ ነበር።
\v 24 ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስ ወደዚህ ደቀ መዝሙር ጠጋ ብሎ «ንገረን ለመሆኑ ስለ ማን ነው እየተናገረ ያለው?» በማለት ጠየቀው።
\v 25 ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ የተቀመጠው ደቀ መዝሙርም፣ «ጌታ ሆይ፣ ይህ የምትለው ሰው ማን ነው?» ብሎ ጠየቀው።
\s5
\v 26 ከዚያም ኢየሱስ፣ «ይህን ቍራሽ እንጀራ ከወጭቱ አጥቅሼ የምሰጠው ያ ሰው እርሱ ነው» በማለት መለሰለት። ስለዚህ ቍራሹን እንጀራ አጥቅሶ ለአስቆሮቱ ይሁዳ ሰጠው።
\v 27 ቍራሹንም እንጀራ ከተቀበለ በኋላ፣ ሰይጣን ገባበት። ከዚያም ኢየሱስ፣ «ለማድረግ ያሰብኸውን ፈጥነህ አድርግ» አለው።
\s5
\v 28 ኢየሱስ ለይሁዳ እንደዚያ ለምን እንዳለው በማዕድ ላይ ከተቀመጡት ማንም ያወቀ የለም።
\v 29 አንዳንዶቹ ይሁዳ ገንዝብ ያዥ ስለ ነበር፣ ኢየሱስ «ለበዓሉ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ግዛ» ወይም ለድኾች ገንዘብ ስጥ ብሎ ነግሮታል ብለው ዐሰቡ።
\v 30 ይሁዳ ቍራሹን እንጀራ ከተቀበለ በኋላ፣ ፈጥኖ ወጣ ምሽትም ነበረ።
\s5
\v 31 ይሁዳ በሄደ ጊዜ፣ ኢየሱስ እንዲህ በማለት ተናገረ፤ «አሁን የሰው ልጅ ከብሯል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ከብሯል።
\v 32 እግዚአብሔር በራሱ ያከብረዋል፣ ደግሞም ፈጥኖ ያከብረዋል።
\v 33 ልጆች ሆይ፣ ከእንግዲህ ከእናንተ ጋር የምቆየው ለጥቂት ጊዜ ነው። እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ ይሁን እንጂ፣ ለአይሁድ፣ 'እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም' እንዳልኋቸው፣ ለእናንተም የምናገረው እንደዚያ ነው።
\s5
\v 34 እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ዐዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ።
\v 35 እርስ በርሳችሁም ብትዋደዱ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ ሰዎች በዚህ ያውቃሉ።»
\s5
\v 36 ስምዖን ጴጥሮስ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት ልትሄድ ነው?» ሲል ጠየቀው። ኢየሱስ፣ «ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፣ በኋላ ግን ትከተለኛለህ» በማለት መለሰለት።
\v 37 ጴጥሮስ፣ «ጌታ ሆይ፣ አሁን ልከተልህ የማልችለው ለምንድን ነው? ስላንተ ሕይወቴን እንኳ አሳልፌ ለመስጠት ቈርጫለሁ» አለው።
\v 38 ኢየሱስ፣ «ስለ እኔ ሕይወትህን አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት፣ እውነት እልሃለሁ፣ ዶሮ ሳይጮኽ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ» ብሎ መለሰለት።
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 «ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔ ደግሞ እመኑ።
\v 2 በአባቴ ቤት ብዙ የመኖሪያ ስፍራ አለ፤ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ፣ ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁ ብዬ አልነግራችሁም ነበር።
\v 3 ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም እንድትሆኑ ዳግመኛ እመጣለሁ፣ ወደ ራሴም እወስዳችኋለሁ።`
\s5
\v 4 ወዴት እንደምሄድ መንገዱን ታውቃላችሁ።»
\v 5 ቶማስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ወዴት እንደምትሄድ አናውቅም፣ መንገዱን እንዴት ማወቅ እንችላለን?» በማለት ጠየቀው።
\v 6 ኢየሱስ እንዲህ አለው፤ «እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ፤ በእኔ ካልሆነ በቀር ማንም ሰው ወደ አብ ሊመጣ አይችልም።
\v 7 እኔን ብታውቁኝ ኖሮ አባቴንም ባወቃችሁት ነበር። ከአሁን ጀምሮ ታውቁታላችሁ አይታችሁትማል።»
\s5
\v 8 ፊልጶስ ጌታ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየን ያ ለእኛ በቂያችን ነው» አለው።
\v 9 ኢየሱስ፣ «ፊልጶስ ሆይ፣ ይህን ያህል ጊዜ ከእናንተ ጋር ኖሬ ገና ኣላወቅኸኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል፤ 'እንዴትስ አብን አሳየን' ትላለህ?
\s5
\v 10 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እየነገርኋችሁ ያለው ቃል ከራሴ የምናገረው አይደለም፤ ይልቁንስ ይህን ሥራ የሚሠራው በእኔ ውስጥ የሚኖረው አብ ነው።
\v 11 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ሌላው ቢቀር ከምሠራው ሥራ የተነሣ እመኑኝ።
\s5
\v 12 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ሥራ እርሱም ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፣ እኔ ከሠራሁት የሚበልጥ ሥራ ይሠራል።
\v 13 አብ በልጁ ይከብር ዘንድ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።
\v 14 ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ፣ እኔ አደርገዋለሁ።
\s5
\v 15 የምትወዱኝ ከሆነ ትእዛዜን ትጠብቃላችሁ።
\v 16 እኔም ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣችሁ አብን እለምናለሁ።
\v 17 እርሱም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየው ወይም ስለማያውቀው አይቀበለውም። ይሁን እንጂ፣ ከእናንተ ጋር ስለሚኖርና በውስጣችሁም ስለሚሆን፣ እናንተ ታውቁታላችሁ።
\s5
\v 18 ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፣ ዳግመኛ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
\v 19 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ።
\v 20 በዚያን ቀን እኔ በአብ እንዳለሁ፣ እናንተ በእኔ እንዳላችሁ እኔም በእናንተ እንዳለሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 21 ትእዛዜ በውስጡ ያለ የሚያደርገውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።
\v 22 የአስቆሮቱ ያልሆነው ይሁዳም ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሳይሆን ለእኛ ራስህን የምትገልጠው እንዴት ነው?» ብሎ ጠየቀው።
\s5
\v 23 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ «ማንም ሰው ቢወደኝ ቃሌን ይጠብቃል። አባቴም ይወደዋል፣ ወደ እርሱ እንመጣለን፣ መኖሪያችንንም በእርሱ እናደርጋለን።
\v 24 የማይወደኝ ማንኛውም ሰው ቃሌን አይጠብቅም። የምትሰሙት ቃል የእኔ ሳይሆን፣ የላከኝ የአብ ቃል ነው።
\s5
\v 25 በመካከላችሁ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች ልብ እንድትሉ ነግሬአችኋለሁ።
\v 26 የሆነ ሆኖ፣ አብ በስሜ የሚልከው አጽናኙ መንፈስ ቅዱስ ሁሉንም ነገር ያስተምራችኋል፤ እኔ የነገርኋችሁንም ነገር ሁሉ እንድታስታውሱ ያስችላችኋል።
\v 27 ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።
\s5
\v 28 'እሄዳለሁ፣ ዳግመኛም ወደ እናንተ እመጣለሁ' ብዬ የነገርኋችሁን ቃል ሰምታችኋል። ከወደዳችሁኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ሊላችሁ ይገባ ነበር፤ ምክንያቱም አብ ከእኔ ይበልጣል።
\v 29 ይህ ነገር በሚፈጸምበት ጊዜ ታምኑ ዘንድ አሁን ከመሆኑ በፊት አስቀድሜ ነገርኋችሁ።
\s5
\v 30 የዚህ ዓለም ገዥ እየመጣ ስለሆነ ከዚህ በላይ ከእናንተ ጋር መነጋገር አልችልም።እርሱ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን የለውም፡
\v 31 ነገር ግን አብን እንደምወድ ዓለም ሁሉ ያውቅ ዘንድ በሰጠኝ ትዕዛዝ መሠረት አብ ያዘዝኝን አደርጋለሁ። ተነሱ ከዚህ እንሂድ»
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬው ደግሞ አባቴ ነው።
\v 2 እርሱም በእኔ ላይ ያለውን ፍሬ ያማያፈራውን ማንኛውንም ቅርንጫፍ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውን ግን ይበልጥ ያፈራ ዘንድ ያጠራዋል።
\s5
\v 3 ከነገርኋችሁ ቃል የተነሣ እናንተ ንጹሓን ናችሁ።
\v 4 በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ላይ ካልኖረ በቀር በራሱ ፍሬ ማፍራት እንደማይችል ሁሉ፣ እናንተም በእኔ ካልኖራችሁ ፍሬ ማፍራት አትችሉም።
\s5
\v 5 እኔ የወይን ግንድ ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ የምኖርበት ያ ሰው ብዙ ፍሬ ያፈራል። ያለ እኔ ምንም ነገር ልታደርጉ አትችሉም።
\v 6 ማንም ሰው በእኔ ባይኖር፣ እንደ ቅርንጫፍ ይወገዳል፣ ይደርቃልም፤ ሰዎች ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉታል፣ ይቃጠላልም።
\v 7 በእኔ ብትኖሩ፣ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ ይሰጣችኋል።
\s5
\v 8 ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።
\v 9 አብ እንደ ወደደኝ እኔም ወደድኋችሁ፣ በፍቅሬ ኑሩ።
\s5
\v 10 እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደጠበቅሁና በፍቅሩ እንደምኖር ሁሉ እናንተም ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።
\v 11 ደስታዬ በውስጣችሁ እንዲሆንና ደስታችሁም ፍጹም እንዲሆን እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ።
\s5
\v 12 እኔ የምሰጣችሁ ትእዛዝ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው።
\v 13 ስለ ወዳጁ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ እንዲሰጥ ግድ ከሚል የሚበልጥ ፍቅር ማንም ሰው የለውም።
\s5
\v 14 ያዘዝኋችሁን ነገር ብታደርጉ ወዳጆቼ ናችሁ።
\v 15 ከእንግዲህ አገልጋዮች ብዬ አልጠራችሁም፤ ምክንያቱም አገልጋይ ጌታው ምን እያደረገ እንዳለ አያውቅም። ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ እንድታውቁ ስለ ነገርኋችሁ፣ ወዳጆች ብያችኋለሁ።
\s5
\v 16 እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ ነገር ግን እኔ መረጥኋችሁ፤ ሄዳችሁ ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬአችሁም ዘላቂ ሆኖ እንዲቆይ ሾምኋችሁ። ይህም አብን በስሜ የምትለምኑትን ማንኛውንም ነገር እንዲሰጣችሁ ነው።
\v 17 እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ።
\s5
\v 18 ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ ዕወቁ።
\v 19 ከዓለም ብትሆኑ ኖሮ ዓለም የራሱ እንደሆኑት አድርጎ በወደዳችሁ ነበር። ነገር ግን ከዓለም ስላይደላችሁ ከዓለምም ስለ መረጥኋችሁ ዓለም ይጠላችኋል።
\s5
\v 20 'አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም' በማለት የነገርኋችሁን ቃል ልብ በሉ፤ እኔን አሳድደውኝ ከሆነ፣ እናንተንም ያሳድዷችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው ከሆነ፣ የእናንተንም ቃል ይጠብቃሉ።
\v 21 የላከኝን እርሱን ስለማያውቁ፣ በስሜ ምክንያት ይህን ሁሉ ያደርጉባችኋል።
\v 22 እኔ ባልመጣና ባልነግራቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ለኀጢአታቸው የሚሰጡት ምክንያት የለም።
\s5
\v 23 እኔን የሚጠላ አባቴንም ይጠላል።
\v 24 ማንም ያልሠራውን ሥራ በመካከላቸው ሠርቼ ባላሳያቸው ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ሥራዬን አይተዋል፤ እኔንና አባቴንም ጠልተዋል።
\v 25 ይህም የሆነው በሕጋቸው 'በከንቱ ጠሉኝ' ተብሎ የተጻፈው ቃል እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 26 ከአብ የምልክላችሁ አጽናኝ፣ እርሱም ከአብ የሚወጣው የእውነት መንፈስ በሚመጣበት ጊዜ፣ ስለ እኔ ይመሰክራል።
\v 27 ከመጀመሪያ ጀምሮ ከእኔ ጋር ስለ ነበራችሁ፣ እናንተም ትመሰክራላችሁ።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 «እነዚህን ነገሮች የምነግራችሁ እምነታችሁ እንዳይናወጥ ነው፡፡
\v 2 ከምኵራብ ያስወጡአችኋል፤ እናንተን የሚገድል ሁሉ ለእግዚአብሔር መልካም እንዳደረገ የሚያስብበት ጊዜ መምጣቱ አይቀርም፡፡
\s5
\v 3 እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉት አብንም ሆነ እኔን ስለማያውቁ ነው፡፡
\v 4 ይህን የምነግራችሁ እነርሱ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙበት ጊዜ በደረሰ ጊዜ፣ ነገሮቹን እንድታስተውሷቸውና እንዴት እንደነገርኋችሁ እንድታስቡ ነው፡፡ አብሬችሁ ስለ ነበርሁ ስለነዚህ ነገሮች ቀደም ሲል አልነገርኋችሁም፡፡
\s5
\v 5 ነገር ግን አሁን ወደ ላከኝ እመለሳለሁ፤ ያም ሆኖ ከእናንተ ማንም 'የት ነው የምትሄደው? ˋ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።
\v 6 ምክንያቱም እነዚህን ነገሮች ስላልኋችሁ ልባችሁ በሐዘን ተሞልቷል፡፡
\v 7 ነገር ግን እውነቱን ልንገራችሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል፤ እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡
\s5
\v 8 አጽናኙ በመጣ ጊዜ ስለ ኃጢአት፣ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ ዓለምን ይወቅሳል፤
\v 9 ስለ ኀጢአት በእኔ ባለማመናቸው፤
\v 10 ስለ ጽድቅ እኔ ወደ አባቴ ስለምሄድና ከእንግዲህ ስለማታዩኝ፣ እንዲሁም
\v 11 ስለ ፍርድ የዚህ ዓለም ገዢ ስለ ተፈረደበት ነው፡፡
\s5
\v 12 ብዙ የምነግራችሁ ነገር አለኝ፤ ነገር ግን አሁን ልትረዱአቸው አትችሉም፡፡
\v 13 ነገር ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፣ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ ምክንያቱም እርሱ ከራሱ አይናገርም፤ ነገር ግን ከእኔ የሰማውን ሁሉ እነዚያን ይናገራል፤ ደግሞም ሊመጡ ስላሉ ነገሮች ይነግራችኋል፡፡
\v 14 የእኔ የሆኑትን ነገሮች ወስዶ ስለሚነግራችሁም ያከብረኛል፡፡
\s5
\v 15 የአባቴ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ ስለዚህ ነው መንፈስ ቅዱስ የእኔ የሆኑትን ነገሮች ወስዶ ይነግራችኋል ያልኋችሁ፡፡
\v 16 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁ።»
\s5
\v 17 ከደቀ መዛሙርቱ አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው ‹‹ወደ አባቴ ስለምሄድ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁˋ እያለ የሚነግረን ነገር ምንድን ነው? ተባባሉ፡፡
\v 18 ከዚህም የተነሣ ‹‹ከጥቂት ጊዜ በኋላˋ ሲል ምን ማለቱ ነው። ምን እያለ እንደ ሆነ አናውቅም›› አሉ፡፡
\s5
\v 19 ኢየሱስም ሊጠይቁት በጣም እንደ ፈለጉ አይቶ፣ ‹‹ከጥቂት ጊዜ በኋላ ፈጽሞ አታዩኝም ደግሞም እንደ ገና ከጥቂት ጊዜ በኋላ ታዩኛላችሁˋ ስላልሁት ነገር እርስ በርሳችሁ ትጠያየቃላችሁን?
\v 20 እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ እናንተ ታለቅሳለችሁ ታዝናላችሁም፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተ በሐዘን ትሞላላችሁ፣ ነገር ግን ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል፡፡
\v 21 አንዲት ሴት የመውለጃዋ ወራት በደረሰ ጊዜ፣ የምጧን ሥቃይ እያሰበች ታዝናለች፤ ነገር ግን ከወለደች በኋላ ሕፃን ወደዚህ ዓለም በመምጣቱ ከሚሰማት ደስታ የተነሣ ጭንቀቷን ፈጽሞ አታስበውም፡፡
\s5
\v 22 ደግሞም አሁን ዐዝናችኋል፤ ነገር ግን ተመልሼ አያችኋለሁ፤ ልባችሁም ደስ ይለዋል፤ ደስታችሁንም ማንም ከእናንተ ሊወስድ አይችልም፡፡
\v 23 በዚያም ቀን ምንም ጥያቄ አትጠይቁኝም፤ እውነት፣ እውነት እላችኋለሁ፣ ከአብ ዘንድ ማንኛውንም ነገር ብትለምኑ አብ ስለስሜ ይሰጣችኋል፡፡
\v 24 እስከ አሁን በስሜ ምንም አልለመናችሁም፣ ለምኑ፣ ደስታችሁም ሙሉ ይሆን ዘንድ ትቀበላላችሁ፡፡
\s5
\v 25 እስከ አሁን በምሳሌ ስነግራችሁ ነበር፤ ነገር ግን በምሳሌ የማልናገርበትና ለእናንተ ስለ አብ በግልጽ የምናገርበት ጊዜ ይመጣል፡፡
\s5
\v 26 በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለ እናንተ ወደ አብ እለምናለሁ አልላችሁም፤
\v 27 ምክንያቱም አብ ራሱ እኔን ስለወደዳችሁኝና ከአብ ዘንድ እንደ መጣሁ ስላመናችሁ ይወዳችኋልና ነው፡፡
\v 28 ከአብ ወደዚህ ዓለም መጥቻለሁ፤ እንደ ገናም ይህን ዓለም ትቼ ወደ አብ እሄዳለሁ፡፡»
\s5
\v 29 ደቀ መዛሙርቱ፣ ‹‹እነሆ፣ አሁን በግልጽ ተናገርህ፤ ምንም በምሳሌ አልተናገርህም፡፡
\v 30 አሁን ሁሉን እንደምታውቅና ማንም ጥያቄ ሊጠይቅህ እንደማያስፈልግ አውቀናል። በዚህም ምክንያት አንተ ከአብ እንደ መጣህ እናምናለን» አሉት፡፡
\v 31 ኢየሱስ፣ ‹‹አሁንስ አመናችሁ ማለት ነው?
\s5
\v 32 እነሆ፣ እያንዳንዳችሁ እኔን ብቻዬን ትታችሁ ወደየቤታችሁ የምትበታተኑበት ጊዜ እየመጣ ነው፡፡ አዎን፣ በርግጥም መጥቷል፡፡ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስላለ ብቻዬን አይደለሁም፡፡
\v 33 በስሜ ሰላም እንዲሆንላችሁ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ፡፡ በዓለም ውስጥ ስትኖሩ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዟችሁ፣ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፡፡»
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ እያየ፣ ‹‹አባት ሆይ፣ ሰዓቱ ደርሷል፣ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው
\v 2 ይህም ከአንተ ለተቀበላቸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት እንዲሰጣቸው በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በሰጠኸው ሥልጣን ልክ ነው፡፡
\s5
\v 3 ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተን፣ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲያውቁ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡
\v 4 አባት ሆይ፣ እንዳከናውነው የሰጠኸኝን ሥራ በመፈጸም በምድር ላይ አከበርሁህ፡፡
\v 5 አሁን አባት ሆይ፣ ዓለም ሳይፈጠር በፊት በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር ከአንተ ጋር አክብረኝ፡፡
\s5
\v 6 ከዓለም ለሰጠኸኝ ለእነዚህ ሰዎች ስምህን ገለጥሁላቸው። የአንተ ነበሩ፣ ለእኔም ሰጠሃቸው፣ ቃልህንም ጠብቀዋል።
\v 7 አሁን ከአንተ የተቀበልኋቸው ነገሮች ሁሉ በርግጥ ከአንተ እንደ መጡ አምነዋል፣
\v 8 የሰጠኸኝን ቃል ሰጥቻቸዋለሁና። እነርሱም ተቀብለውታል፤ ከአንተ እንደ መጣሁ አውቀዋል አንተ እንደላክኸኝም አምነዋል።
\s5
\v 9 እነርሱ የአንተ ናቸውና አንተ ለሰጠኸኝ ለእነርሱ እንጂ ለዓለም አልጸልይም፡፡
\v 10 የእኔ የሆነው ሁሉ የአንተ ነው፤ የአንተ የሆነውም ነገር ሁሉ የእኔ ነው፤ እኔ በእነርሱ ከብሬአለሁ፡፡
\v 11 እኔ ወደ አንተ እመጣለሁና። ከእንግዲህ በዓለም አልኖርም፤ እነርሱ ግን በዓለም ውስጥ ናቸው፡፡ ቅዱስ አባት ሆይ፣ እኔና አንተ አንድ እንደ ሆንን አንድ እንዲሆኑ በሰጠኸኝ በስምህ ጠብቃቸው፡፡
\s5
\v 12 ከእነርሱ ጋር እያለሁ በሰጠኸኝ በስምህ ጠበቅኋቸው፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት የተባለው እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ አንዱም እንዳይጠፋ ጋረድኋቸው፡፡
\v 13 አሁን ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ይህን በዓለም ሳለሁ የምናገረው፣ ደስታዬ በእነርሱ ሙሉ እንዲሆን ነው፡፡
\v 14 ቃልህን ሰጥቻቸዋለሁ፤ እኔ ከዓለም እንዳልሆንሁ እነርሱም ከዓለም አይደሉምና ዓለም ይጠላቸዋል፡፡
\s5
\v 15 ከክፉው እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልጸልይም፡፡
\v 16 እኔ ከዓለም እንዳይደለሁ እነርሱም ከዓለም አይደሉም፡፡
\v 17 በእውነት ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው፡፡
\s5
\v 18 አንተ ወደ ዓለም ላክኸኝ፣ እኔም ደግሞ እነርሱን ወደ ዓለም ልኬአቸዋለሁ፡፡
\v 19 እነርሱ በእውነት እንዲቀደሱ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ ቀድሼአለሁ፡፡
\s5
\v 20 ከእነርሱ ምስክርነት የተነሣ በእኔ ስለሚያምኑት ሁሉ እንጂ ስለ እነዚህ ብቻ አልጸልይም፡፡
\v 21 ይህም አባት ሆይ፣ አንተ በእኔ እኔም በአንተ እንዳለሁ እነርሱም አንድ እንዲሆኑ ነው፡፡ ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ እንዲያምን እነርሱም በእኛ እንዲሆኑ እጸልያለሁ፡፡
\s5
\v 22 እኛ አንድ እንደ ሆንን እነርሱም አንድ እንዲሆኑ የሰጠኸኝን ክብር ሰጥቻቸዋለሁ፤
\v 23 ይህም እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ ሆነህ እነርሱ በአንድነት ፍጹማን እንዲሆኑና ዓለም አንተ እንደ ላክኸኝ እኔን በወደድህበት ፍቅር እነርሱንም እንደ ወደድሃቸው እንዲያውቅ ነው።
\s5
\v 24 አባት ሆይ፣ የሰጠኸኝ እነዚህ ስለ ወደድኸኝ ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ የሰጠኸኝን ክብር እንዲያዩ እኔ ባለሁበት እነርሱም ከእኔ ጋር እንዲሆኑ እወዳለሁ፡፡
\s5
\v 25 ጻድቅ አባት ሆይ፣ ዓለም አላወቀህም፤ እኔ ግን አውቅሃለሁ፤ እነዚህም አንተ እንደ ላክኸኝ አውቀዋል፡፡
\v 26 አንተን እንዲያውቁ አድርጌአለሁ፤ እኔን የወደድህበት ፍቅር በእነርሱም እንዲሆንና እኔም በእነርሱ እንድሆን ስምህን አስታውቃቸዋለሁ፡፡
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 18
\p
\v 1 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ ከቄድሮን ሸለቆ ማዶ የአትክልት ስፍራ ወደሚገኝበት ቦታ ሄደ፣ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ አትክልት ስፍራው ገባ፡፡
\v 2 ኢየሱስ በተደጋጋሚ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደዚያ ስፍራ ይመጣ ስለ ነበር አሳልፎ ሊሰጠው ያለው ይሁዳ ቦታውን ያውቅ ነበር፡፡
\v 3 ከዚያም ይሁዳ ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ብዙ ወታደሮችንና ጠባቂዎችን ከተቀበለ በኋላ ፋኖስ፣ ችቦና የጦር መሣሪያ ይዞ ወደ አትክልት ስፍራው መጣ፡፡
\s5
\v 4 ከዚያም እየደረሰበት ያለውን የተረዳው ኢየሱስ ወደ ፊት ወጥቶ፣ ‹‹ማንን ፈለጋችሁ? አላቸው፤
\v 5 እነርሱ፣ ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ብለው መለሱለት፡፡ ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ›› አላቸው፡፡ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳም ከወታደሮቹ ጋር ቆሞ ነበር፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ ‹‹እኔ ነኝ›› ባላቸው ጊዜ ወደ ኋላ አፈግፍገው በምድር ላይ ወደቁ፡፡
\v 7 እንደ ገናም፣ ‹‹ማንን ፈለጋችሁ? አላቸው። እነርሱም፣ ‹‹የናዝሬቱ ኢየሱስን›› ብለው በድጋሚ መለሱለት፡፡
\s5
\v 8 ኢየሱስ፣ ‹‹እኔ ነኝ አልኋችሁ፤ ስለዚህ እኔን የምትፈልጉ ከሆነ እነዚህን እንዲሄዱ ተዉአቸው›› አላቸው፡፡
\v 9 ይህም ‹‹ከሰጠኸኝ ከእነዚህ አንዱም አልጠፋብኝም›› ተብሎ የተነገረው ቃል እንዲፈጸም ነው፡፡
\s5
\v 10 ከዚያም ስምዖን ጴጥሮስ የታጠቀውን ሰይፍ መዞ የሊቀ ካህናቱን አገልጋይ ቀኝ ጆሮውን ቈረጠ፡፡ የአገልጋዩም ስም ማልኮስ ነበረ፡፡
\v 11 ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ ‹‹ሰይፍህን ወደ ሰገባው መልስ፡፡ አብ የሰጠኝን ጽዋ መጠጣት የለብኝም እንዴ? አለው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ ወታደሮቹና አዛዣቸው እንዲሁም የአይሁድ ጠባቂዎች ኢየሱስን ይዘው አሰሩት፡፡
\v 13 በዚያን ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረው ቀያፋ ለሐና አማቹ ስለ ነበረ፣ በመጀመሪያ ወደ ሐና ወሰዱት ፡፡
\v 14 ቀያፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት ይሻላል ብሎ አይሁድን የመከረው ሰው ነው፡፡
\s5
\v 15 ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር ኢየሱስን ተከትለው ሄዱ፡፡ ሌላኛው ደቀ መዝሙር ከሊቀ ካህናቱ ጋር ይተዋወቅ ስለ ነበረ፣ ከኢየሱስ ጋር ወደ ሊቀ ካህናቱ አደባባይ ገባ፡፡
\v 16 ጴጥሮስ ግን በውጭ በር ላይ ቆሞ ነበር፡፡ ከሊቀ ካህናቱ ጋር የሚተዋወቀው ያ ደቀ መዝሙር በር የምትጠብቀውን አገልጋይ አናግሮ ጴጥሮስን ወደ ውስጥ አስገባው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም በር ትጠብቅ የነበረችው አገልጋይ ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተ ከዚህ ሰው ደቀ መዛሙርት አንዱ አይደለህም እንዴ? አለችው፡፡ እርሱ፣ ‹‹አይደለሁም›› አለ፡፡
\v 18 ጊዜው ብርድ ስለ ነበረ፣ አገልጋዮችና ጠባቂዎች እሳት አቀጣጥለው ዙሪያውን ከበው እየሞቁ ነበር፡፡ ጴጥሮስም በዚያ ከእነርሱ ጋር ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፡፡
\s5
\v 19 ከዚያም ሊቀ ካህናቱ ኢየሱስን ስለ ደቀ መዛሙርቱና ስለ አስተማረው ትምህርት ጠየቀው፡፡
\v 20 ኢየሱስ፣ ‹‹ለዓለም ሁሉ በግልጽ ስናገር ነበር፤ ሁልጊዜ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በቤተ መቅደስ ሳስተምር ነበር፤ በድብቅ የተናገርሁት ምንም ነገር የለም፣
\v 21 ታዲያ ለምን ትጠይቀኛለህ? የተናገርኋቸውን ነገሮች ስለሚያውቁ ሲሰሙኝ የነበሩትን ሰዎች ስለተናገርኋቸው ነገሮች ጠይቅ›› ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 22 ኢየሱስ ይህን በተናገረ ጊዜ፣ በዚያ ከቆሙት ጠባቂዎች መካከል አንዱ በጥፊ መታውና፣ ‹‹እንደዚህ ነው ለሊቀ ካህናቱ የምትመልሰው? አለው፡፡
\v 23 ኢየሱስ፣ ‹‹አንዳች ክፉ ነገር ተናግሬ ከሆነ መስክርብኝ፤ በትክክል መልሼ ከሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ? አለው፡፡
\v 24 ሐናም ኢየሱስን እንደ ታሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ወደ ቀያፋ ላከው፡፡
\s5
\v 25 ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት እየሞቀ ነበር። ሰዎቹ፣ ‹‹አንተ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ አይደለህም እንዴ? አሉት። ጴጥሮስ፣ ‹‹አይደለሁም›› ብሎ ካደ፡፡
\v 26 ጴጥሮስ ጆሮውን የቈረጠው ሰው ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች አንዱ፣ ጴጥሮስን፣ ‹‹አንተን በአትክልት ስፍራው ከእርሱ ጋር አላየሁህም እንዴ? አለው፡፡
\v 27 ጴጥሮስ እንደ ገና ካደ፣ ወዲያውም ዶሮ ጮኸ፡፡
\s5
\v 28 ከዚያም ኢየሱስን ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት። ጊዜው ማለዳ ነበረ፣ ይዘውት የመጡት አይሁድ እንዳይረክሱና ፋሲካን መብላት እንዲችሉ ወደ ገዢው ግቢ መግባት አልፈለጉም።
\v 29 ስለዚህ ጲላጦስ ወደ ውጭ ወጥቶ፣ «በዚህ ሰው ላይ ያላችሁ ክስ ምንድን ነው?» ብሎ ጠየቃቸው።
\v 30 እነርሱም፣ «ይህ ሰው ክፉ ባያደርግ ኖሮ ወደ አንተ አናመጣውም ነበር» አሉት።
\s5
\v 31 ስለዚህ ጲላጦስ፣ «እናንተ ወስዳችሁ በሕጋችሁ መሠረት ፍረዱበት» አላቸው። አይሁድ፣ «እኛ ማንንም ሰው ለመግደል አልተፈቀደልንም» ብለው መለሱለት።
\v 32 ይህንም ያሉት ኢየሱስ በእንዴት ዓይነት ሞት እንደሚሞት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።
\s5
\v 33 ጲላጦስ ወደ ግቢው ተመልሶ ኢየሱስን ጠራውና፣ «አንተ የአይሁድ ንጉሥ ነህን?» አለው።
\v 34 ኢየሱስ፣ «ይህን የምትጠይቀኝ ከራስህ ነው ወይስ ሌሎች እንድትጠይቀኝ ስለ ነገሩህ ነው?» አለው።
\v 35 ጲላጦስ፣ «እኔ አይሁዳዊ አይደለሁም፤ ነኝ እንዴ? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ የገዛ አገርህ ሰዎችና የካህናት አለቆች ናቸው፣ ምን አድርገህ ነው?» አለው።
\s5
\v 36 ኢየሱስ፣ «የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለም፤ የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም ቢሆን ኖሮ አይሁድ እንዳይዙኝ አገልጋዮቼ ይዋጉልኝ ነበር። በመሠረቱ የእኔ መንግሥት ከምድር አይደለም» ብሎ መለሰለት።
\v 37 ጲላጦስ፣ «ታዲያ አንተ ንጉሥ ነህ?» አለው፤ ኢየሱስ፣ «እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ተናገርህ፤ የተወለድሁት ወደ ዓለምም የመጣሁት ስለ እውነት ለመመስከር ነው፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ድምፄን ይሰማል» ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 38 ጲላጦስ፣ «እውነት ምንድን ነው?» ካለ በኋላ፣ እንደ ገና ወደ አይሁድ ወጣና፣ «በዚህ ሰው ላይ ምንም ጥፋት አላገኘሁበትም።
\v 39 እንደ ተለመደው በየዓመቱ በፋሲካ በዓል አንድ እስረኛ እለቅላችኋለሁ፣ ታዲያ የአይሁድን ንጉሥ ልፍታላችሁን?» አላቸው።
\v 40 ከዚያም፣ እነርሱ፣ እንደ ገና ጮኸው «ይህን ሰው አይደለም፣ በርባንን ፍታልን» አሉ። በርባን ግን ወንበዴ ነበር።
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 ከዚያም ጲላጦስ ኢየሱስን ወስዶ አስገረፈው።
\v 2 ወታደሮቹ የእሾኽ አክሊል ጐንጕነው በኢየሱስ ራስ ላይ አደረጉ። ሐምራዊ ልብስም አለበሱት።
\v 3 ወደ እርሱ መጥተው፣ «የተከበሩ የአይሁድ ንጉሥ ሆይ!» አሉ በጥፊም መቱት።
\s5
\v 4 ከዚያም ጲላጦስ እንደ ገና ወደ ወጥቶ ሕዝቡን፣ «ምንም ጥፋት እንዳላገኘሁበት እንድታውቁ እነሆ፣ ሰውየውን ወደ ውጭ አወጣላችኋለሁ» አላቸው።
\v 5 ስለዚህ ኢየሱስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶና ሐምራዊ ልብስ ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም፣ «እነሆ፣ ሰውየው!» አላቸው።
\v 6 የካህናት አለቆችና ጠባቂዎቹ ኢየሱስን ባዩ ጊዜ፣ «ስቀለው፣ ስቀለው» እያሉ ጮኹ። ጲላጦስ፣ «እናንተ ወስዳችሁ ስቀሉት፤ እኔ ምንም ወንጀል አላገኘሁበትም» አላቸው።
\s5
\v 7 አይሁድ፣ «እኛ ሕግ አለን፣ በሕጋችን መሠረትም ይህ ሰው ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ አድርጓልና ሞት ይገባዋል» ብለው መለሱ።
\v 8 ጲላጦስ ይህን ሲሰማ የበለጠ ደነገጠ፤
\v 9 ወደ ግቢውም ተመልሶ ኢየሱስን፣ «ከየት ነው የመጣኸው?» ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስ ግን ምንም አልመለሰለትም።
\s5
\v 10 ጲላጦስም ኢየሱስን፣ «አናግረኝ እንጂ፤ ልፈታህም ሆነ ልሰቅልህ ሥልጣን እንዳለኝ አታውቅም እንዴ?» አለው።
\v 11 ኢየሱስ፣ «ከላይ ባይሰጥህ ኖሮ በእኔ ላይ ምንም ሥልጣን ባልኖረህ ነበር። ስለዚህም ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ኀጢአቱ የከፋ ነው» አለው።
\s5
\v 12 ከዚህ መልሱ የተነሣ ጲላጦስ ሊፈታው ፈለገ፣ ነገር ግን አይሁድ፣ «ራሱን ንጉሥ ብሎ የሚጠራ ቄሣርን የሚቃወም ስለ ሆነ፣ ይህን ሰው ብትለቀው አንተ የቄሣር ወዳጅ አይደለህም» እያሉ ይጮኹ ነበር።
\v 13 ጲላጦስ እነዚህን ቃላት በሰማ ጊዜ ኢየሱስን ወደ ውጭ አውጥቶ የድንጋይ ንጣፍ፣ በዕብራይስጥ ግን ገበታ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ።
\s5
\v 14 ቀኑ ለፋሲካ በዓል ዝግጅት የሚደረግበትና ሰዓቱም ከቀኑ ስድስት ሰዓት አካባቢ ነበር። ጲላጦስ አይሁድን፣ «እነሆ፣ ንጉሣችሁ» አላቸው።
\v 15 እነርሱም፣ «አስወግደው፣ አስወግደው፣ ስቀለው!» እያሉ ጮኹ። እርሱ፣ «ንጉሣችሁን ልስቀለውን?» አላቸው። የካህናት አለቆችም፣ «እኛ ከቄሣር በቀር ሌላ ንጉሥ አናውቅም» ብለው መለሱለት።
\v 16 ስለዚህ ጲላጦስ ኢየሱስን እንዲሰቅሉት ፈቀደላቸው።
\s5
\v 17 ከዚያም ኢየሱስን፣ የሚሰቀልበትን መስቀል አሸክመው የራስ ቅል፣ በዕብራይስጥ ደግሞ ጎልጎልታ ወደሚባል ቦታ ወሰዱት።
\v 18 በዚያም ስፍራ ሰቀሉት፤ ሁለት ሌሎች ሰዎችንም በኢየሱስ ግራና ቀኝ ሰቀሉ።
\s5
\v 19 ጲላጦስም ጽሑፍ አዘጋጅቶ በኢየሱስ መስቀል ላይ አስቀመጠ። ጽሑፉም፣ «የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ የአይሁድ ንጉሥ» የሚል ነበር።
\v 20 ኢየሱስ የተሰቀለበት ቦታ ለከተማው ቅርብ ስለ ነበር፣ ብዙ አይሁድ ጽሑፉን ያነቡት ነበር። ጽሑፉም የተጻፈው በዕብራይስጥ፣ በላቲንና በግሪክ ቋንቋዎች ነበር።
\s5
\v 21 የአይሁድ የካህናት አለቆችም ጲላጦስን «እርሱ ራሱን 'የአይሁድ ንጉሥ ነኝ' ብሏል ብለህ ነው እንጂ፣ 'የአይሁድ ንጉሥ' ብለህ መጻፍ የለብህም» አሉት።
\v 22 ጲላጦስም፣ «አንዴ የጻፍሁትን ጽፌአለሁ» አላቸው።
\s5
\v 23 ወታደሮቹ ኢየሱስን ከሰቀሉት በኋላ ልብሱን ወስደው ለእያንዳንዳቸው እንዲዳረስ አድርገው አራት ቦታ ቈራረጡት፣ እጀ ጠባቡንም ወሰዱ።
\v 24 እጀ ጠባቡ ግን ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረና እርስ በርሳቸው «ከምንቀደው ዕጣ እንጣጣልና የሚደርሰው ይውሰደው» ተባባሉ። ይህም የሆነው በቅዱስ መጽሐፍ፣ «ልብሴን ተከፋፈሉት በእጀ ጠባቤም ላይ ዕጣ ተጣጣሉበት» የተባለው ቃል እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 25 ወታደሮቹ ይህን በሚያደርጉበት ጊዜ የኢየሱስ እናት ማርያም፣ የእናቱ እኅት፣ የቀለዮጳ ሚስት ማርያምና መግደላዊት ማርያም በዚያ በኢየሱስ መስቀል አጠገብ ቆመው ነበር።
\v 26 ኢየሱስ እናቱንና ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር አብረው ቆመው ባየ ጊዜ፣ እናቱን «አንቺ ሴት እነሆ፣ ከአጠገብሽ ያለው እንደ ልጅሽ ይሁንልሽ» አላት ፤
\v 27 ደቀ መዝሙሩንም፣ «እነኋት፣ በአጠገብህ ያለችው እንደ እናትህ ትሁንልህ» አለው። ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።
\s5
\v 28 ኢየሱስ ሁሉ እንደ ተፈጸመ ዐውቆ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፈው እንዲፈጸም፣ «ተጠማሁ» አለ።
\v 29 በዚያም በሆምጣጤ የተሞላ ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ ወዲያውም በሆምጣጤ የተሞላ ሰፍነግ በሂሶጵ ወደ አፉ አስጠጉለት።
\v 30 ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከጠጣ በኋላ «ተፈጸመ» አለ። ራሱንም አዘንብሎ ሞተ።
\s5
\v 31 ቀኑ የመዘጋጀት ቀን በመሆኑና ሰንበትም በአይሁድ ዘንድ በጣም የሚከበር ስለነበረ በሰንበት ሥጋቸው በመስቀል ላይ መቆየት ስለሌለበት የሞት ፍርድ የተፈጸመባቸው ሰዎች እግሮቻቸው እየተሰበረ ሥጋቸው ከመስቀል እንዲወርድ አይሁድ ጲላጦስን ለመኑት።
\v 32 ከዚያም ወታደሮቹ መጥተው ከኢየሱስ ጋር ከተሰቀሉት ሰዎች በመጀመሪያ የአንዱን፣ ቀጥሎም የሌላኛውን ሰው እግሮች ሰበሩ።
\v 33 ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ሞቶ ስላገኙት እግሮቹን አልሰበሩም።
\s5
\v 34 ይሁን እንጂ፣ ከወታደሮቹ አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው፣ ወዲያውም ከጐኑ ደምና ውሃ ወጣ።
\v 35 ይህን ያየው ሰው ስለዚህ መስክሯል፣ ምስክርነቱም እውነት ነው። እናንተም እንድታምኑ የተናገረው እውነት እንደ ሆነ ያውቃል።
\s5
\v 36 እነዚህ ነገሮች የሆኑት «ከዐጥንቱ አንድም አይሰበርም» የሚለው የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው።
\v 37 ደግሞም በሌላ መጽሐፍ፣ «የወጉትን ያዩታል» ተብሎ ተጽፎአል።
\s5
\v 38 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ አይሁድን ፈርቶ በድብቅ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረውና ከአርማትያስ ከተማ የሆነው ዮሴፍ የኢየሱስን አስከሬን ለመውሰድ ጲላጦስን ለመነ። ጲላጦስም ፈቀደለት። ዮሴፍም መጥቶ የኢየሱስን አስከሬን ወሰደ።
\v 39 በአንድ ወቅት በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስም አንድ መቶ ነጥር ያህል የእሬትና የከርቤ ቅልቅል ይዞ መጣ።
\s5
\v 40 ስለዚህ የኢየሱስን አስከሬን ወስደው በአይሁድ ባህል አስከሬን ከመቀበሩ በፊት እንደሚደረገው ልማድ አስከሬኑን ሽቱ በተቀባ በበፍታ ጨርቅ ገነዙት።
\v 41 ኢየሱስ ከተቀበረበት ቦታ አጠገብ የአትክልት ስፍራ ነበረ፤ በዚያም ማንም ገና ያልተቀበረበት ዐዲስ መቃብር ይገኝ ነበረ።
\v 42 ቀኑ ለአይሁድ የመዘጋጀት ቀን በመሆኑና መቃብሩም ቅርብ ስለ ነበር፣ የኢየሱስን አስከሬን በዐዲሱ መቃብር አኖሩት።
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 በሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ገና ጨለማ እያለ መግደላዊት ማርያም በሌሊት ወደ መቃብሩ መጣች፤ ድንጋዩ ከመቃብሩ ተንከባሎ አየች።
\v 2 ስለዚህ ወዲያው እየሮጠች ተመልሳ ወደ ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው ወደ ነበረው ደቀ መዝሙር መጥታ፣ «ጌታን ከመቃብሩ አውጥተው ወስደውታል፣ የት እንዳደረጉትም አናውቅም» አለቻቸው።
\s5
\v 3 ከዚያም ጴጥሮስና ሌላኛው ደቀ መዝሙር ወደ መቃብሩ ሄዱ።
\v 4 አብረው እየሮጡ ሳለ፣ ሌላኛው ደቀ መዝሙር ጴጥሮስን ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደረሰ።
\v 5 ጐንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ የበፍታ ጨርቁ ተቀምጦ አየ፣ ወደ ውስጥ ግን አልገባም።
\s5
\v 6 ከእርሱም በኋላ ጴጥሮስ ደረሰና ወደ መቃብሩ ውስጥ ገባ። የበፍታ ጨርቁ ተቀምጦ አየ፣
\v 7 በኢየሱስ ራስ ላይ የነበረውንም ጨርቅ ከበፍታ ጨርቁ ጋር ዐብሮ ሳይሆን ለብቻው እንደ ተጠቀለለ በቦታው ተቀምጦ አየ።
\s5
\v 8 ከዚያም ጴጥሮስ ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደርሶ የነበረው ደቀ መዝሙር ወደ ውስጥ ገባና አይቶ አመነ።
\v 9 ምክንያቱም እስከዚያን ሰዓት ድረስ ኢየሱስ ከሞት እንደሚነሣ በመጻሕፍት የተነገረውን ቃል አላስተዋሉም ነበር።
\v 10 ስለዚህ ደቀ መዛሙርቱ ወደየቤታቸው ሄዱ።
\s5
\v 11 ነገር ግን መግደላዊት ማርያም እያለቀስች ከመቃብሩ ውጭ ቆማ ነበር፤ እያለቀሰችም ጐንበስ ብላ ወደ መቃብሩ ውስጥ ተመለከተ።
\v 12 የኢየሱስ አስከሬን ተጋድሞበት በነበረው ቦታ ላይ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት መላእክት፣ አንደኛው በራስጌ፣ ሌላው ደግሞ በእግርጌ ተቀምጠው አየች።
\v 13 እነርሱም፣ «አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ?» አሏት፤ እርሷም፣ «ጌታዬን ስለወሰዱትና ወዴትም እንዳኖሩት ስለማላውቅ ነው።» አለቻቸው።
\s5
\v 14 ይህን ብላ ዞር ስትል፣ ኢየሱስን እዚያው ቆሞ አየችው፤ እርሱ እንደ ሆነ ግን አላወቀችም ነበር።
\v 15 ኢየሱስ፣ «አንቺ ሴት ለምን ታለቅሽያለሽ፣ ማንንስ እየፈለግሽ ነው?» አላት። እርሷም የአትክልት ስፍራው ጠባቂ መስሏት፣ «ጌታዬ የወሰድኸው አንተ ከሆንህ እባክህ የት እንዳስቀመጥኸው ንገረኝና ልውሰደው።» አለችው።
\s5
\v 16 ኢየሱስም፣ «ማርያም» አላት። ዞር ብላ በአረማይክ ቋንቋ፣ «ረቡኒ» አለችው፤ ትርጓሜውም «መምህር» ማለት ነው።
\v 17 ኢየሱስም«ገና ወደ አብ አልሄድሁምና አትንኪኝ፣ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ መሄዴ ነው ብለሽ ንገሪአቸው» አላት።
\v 18 መግደላዊት ማርያምም ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥታ፣ «ጌታን አየሁት» ብላ ኢየሱስ የነገራትን ሁሉ ነገረቻቸው።
\s5
\v 19 በዚያው ቀን ማለትም ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ምሽት ላይ፣ ደቀ መዛሙርቱ አይሁድን ፈርተው በሮቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆሞ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን» አላቸው።
\v 20 ይህንም ብሎ እጁንና ጐኑን አሳያቸው። ደቀ መዛሙርቱም ጌታን ባዩት ጊዜ፣ ደስ አላቸው።
\s5
\v 21 እንደ ገናም ኢየሱስ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን፣ አብ እንደ ላከኝ እኔም እልካችኋለሁ» አላቸው።
\v 22 ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፣ «መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፣
\v 23 ኀጢአቱን ይቅር ያላችሁት ማንም ይቅር ይባልለታል፣ ኀጢአቱን የያዛችሁበት ማንም ይያዝበታል» አላቸው።
\s5
\v 24 ኢየሱስ ወደ ደቀ መዛሙርቱ በመጣ ጊዜ፣ ከዐሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ሌላ ስሙ ዲዲሞስ የሚባለው ቶማስ ዐብሮአቸው አልነበረም።
\v 25 ኋላ ላይ ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት፣ «ጌታን አየነው እኮ» አሉት። እርሱም፣ «የምስማር ምልክቱን በእጆቹ ላይ ካላየሁ፣ ጣቶቼንም በምስማር ምልክቱና እጄን በጐኑ ካላስገባሁ አላምንም» አላቸው።
\s5
\v 26 ከስምንት ቀን በኋላ ደቀ መዛሙርቱ በቤት ውስጥ ነበሩ፤ ቶማስም ዐብሯቸው ነበረ። በሮቹ ተዘግተው ሳለ ኢየሱስ በመካከላቸው ቆሞ፣ «ሰላም ለእናንተ ይሁን» አላቸው።
\v 27 ቶማስንም፣ «ጣቶችህን አምጣና እጆቼን ንካ፣ እጆችህንም ወደ ጐኔ አስገባ፣ እመን እንጂ የማታምን አትሁን» አለው።
\s5
\v 28 ቶማስም፣ «ጌታዬና አምላኬ» ብሎ መለሰለት።
\v 29 ኢየሱስ «አንተ ስላየኸኝ አመንህ፣ ሳያዩ የሚያምኑ የተባረኩ ናቸው» አለው።
\s5
\v 30 ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፉ ብዙ ምልክቶችን በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤
\v 31 ነገር ግን ይህ የተጻፈው፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ እንድታምኑና አምናችሁም በስሙ ሕይወት እንድታገኙ ነው።
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 እነዚህ ነገሮች ከተፈጸሙ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ ገና በጥብርያዶስ ባሕር አጠገብ ተገለጠላቸው፤ ሁኔታውም እንደዚህ ነበር፦
\v 2 ስምዖን ጴጥሮስ ዲዲሞስ ከተባለው ከቶማስ፣ ከገሊላ አውራጃ ከቃና መንደር ከሆነው ከናትናኤል፣ ከዘብዴዎስ ልጆችና ከሌሎች ሁለት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ጋር ዐብረው ነበሩ።
\v 3 ስምዖን ጴጥሮስ፣ «ዓሣ ለማጥመድ መሄዴ ነው» አላቸው። እነርሱም፣ «እኛም ከአንተ ጋር እንሄዳለን» አሉት። በጀልባ ተሳፍረው ሄዱ፤ ነገር ግን በዚያች ሌሊት ምንም ዐሣ አላጠመዱም።
\s5
\v 4 ቀኑ እየነጋ ሳለ ኢየሱስ መጥቶ በባሕሩ ዳር ቆመ፤ እነርሱ ግን ኢየሱስ እንደ ሆነ አላወቁም ነበር።
\v 5 ከዚያም ኢየሱስ «ልጆች ሆይ፣ የሚበላ ዐሣ አላችሁን?» አላቸው። «የለንም» ብለው መለሱለት።
\v 6 ኢየሱስ፣ «መረባችሁን ከጀልባው በቀኝ በኩል ጣሉት ታገኙማላችሁ» አላቸው። እነርሱም እንደተባሉት መረባቸውን ጣሉ፤ ነገር ግን ከዐሣው ብዛት የተነሣ መረቡን ወደ ጀልባው ውስጥ መጐተት አቃታቸው።
\s5
\v 7 ከዚያም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ስምዖን ጴጥሮስን፣ «ጌታ እኮ ነው» አለው። ጴጥሮስ ጌታ እኮ ነው የሚለውን ቃል በሰማ ጊዜ፣ መደረቢያውን ልብስ ታጥቆ ወደ ውሃው ውስጥ ዘሎ ገባ።
\v 8 ሌሎቹ ደቀ መዛሙርት ግን ከምድር የነበራቸው ርቀት ሁለት መቶ ክንድ ያህል ብቻ ስለ ነበር ዐሣ የሞላውን መረብ እየጐተቱ በጀልባ ወደ ዳር መጡ።
\v 9 ወደ መሬትም በደረሱ ጊዜ፣ በላዩ ላይ ዐሣ የተቀመጠበት ፍምና እንጀራ ተዘጋጅቶ አዩ።
\s5
\v 10 ኢየሱስ፣ «እስኪ ካጠመዳችሁት ዐሣ ጥቂት ወደዚህ አምጡ» አላቸው።
\v 11 ስምዖን ጴጥሮስም ሄዶ 153 ዐሣ የሞላውን መረብ ወደ ምድር ጐተተ፤ ምንም እንኳ የዐሣው ብዛት ከፍተኛ ቢሆንም፣ መረቡ ግን አልተቀደደም ነበር።
\s5
\v 12 ኢየሱስ፣ «ኑ ቍርስ ብሉ» አላቸው። ኢየሱስ እንደ ሆነ አውቀው ነበርና ከደቀ መዛሙርቱ ማንም፣ «አንተ ማነህ?» ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም።
\v 13 ኢየሱስ እንጀራውን አንሥቶ ሰጣቸው፤ ዐሣውንም እንደዚያው አደረገ።
\v 14 ከሞት ከተነሣ በኋላ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ለሦስተኛ ጊዜ ነበር።
\s5
\v 15 ቍርስ ከበሉ በኋላ፣ ኢየሱስ ስምዖን ጴጥሮስን፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ከእነዚህ የበለጠ ትወደኛለህን?» አለው። ጴጥሮስ፣ «አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እንደምወድህማ አንተም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱ፣ «ጠቦቶቼን መግብ» አለው።
\v 16 እንደ ገና ለሁለተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ ትወደኛለህን?» አለው። ጴጥሮስ፣ «አዎን፣ ጌታ ሆይ፣ እንደምወድህማ አንተም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስ፣ «በጎቼን ጠብቅ» አለው።
\s5
\v 17 ለሦስተኛ ጊዜ፣ «የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፣ ትወደኛለህ?» አለው። ለሦስተኛ ጊዜ «ትወደኛለህ ወይ?» ብሎ ስለ ጠየቀው ጴጥሮስ በጣም ዐዘነ። ቀጥሎም፣ «ጌታ ሆይ፣ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህም ታውቃለህ» አለው። ኢየሱስም «በጎቼን መግብ።
\v 18 እውነት፣ እውነት እልሃለሁ፣ ወጣት እያለህ ልብስህን ራስህ ለብሰህ ወደምትፈልገው ቦታ ትሄድ ነበር፤ ስታረጅ ግን ሌላ ሰው ልብስህን አልብሶህ ወደማትፈልገው ቦታ ይወስድሃል፣ በዚያን ጊዜ አንተ እጅህን ከመዘርጋት ውጪ ሌላ ማድረግ የምትችለው ነገር አይኖርም» አለው።
\s5
\v 19 ኢየሱስ ይህን የተናገረው ጴጥሮስ በምን ዓይነት አሟሟት እግዚአብሔርን እንደሚያከብር ለማመልከት ነው። ከዚያም ኢየሱስ ጴጥሮስን፣ «ተከተለኝ» አለው።
\s5
\v 20 ጴጥሮስም ዞር ብሎ በፋሲካ እራት ላይ እያሉ ወደ ኢየሱስ ደረት ጠጋ ብሎ፣ «አሳልፎ የሚስጥህ ማን ነው?» ብሎ የጠየቀውንና ኢየሱስ ይወደው የነበረውን ደቀ መዝሙር ሲከተላቸው አየው።
\v 21 ጴጥሮስ ኢየሱስን፣ «ጌታ ሆይ፣ ይህ ሰውስ ምን ይሆናል?» አለው።
\s5
\v 22 ኢየሱስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል? ዝም ብለህ ተከተለኝ» አለው።
\v 23 በዚህ ምክንያት «ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም» የሚል ወሬ በየ ስፍራው ተሠራጨ። ኢየሱስ ግን ለጴጥሮስ፣ «እኔ እስክመጣ እንዲቆይ ብፈልግስ አንተን ምን ይመለከትሃል?» አለው እንጂ ያ ደቀ መዝሙር አይሞትም አላለውም።
\s5
\v 24 ስለ እነዚህ ነገሮች የመሰከረውና የጻፈው ይህ ደቀ መዝሙር ነው፣ ምስክርነቱም እውነት እንደ ሆነ እናውቃለን።
\v 25 ከእነዚህ ሌላ ኢየሱስ ያደረጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ። እያንዳንዱ ነገር ቢጻፍ ኖሮ ለሚጻፉት መጻሕፍት ማስቀመጫ ዓለም እንኳ የሚበቃ አይመስለኝም።

1896
45-ACT.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1896 @@
\id ACT
\ide UTF-8
\h የሐዋርያት ሥራ
\toc1 የሐዋርያት ሥራ
\toc2 የሐዋርያት ሥራ
\toc3 act
\mt የሐዋርያት ሥራ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ቴዎፍሎስ ሆይ፣ ኢየሱስ እስካረገበት ቀን ድረስ ለማድረግና ለማስተማር የጀመረውን ሁሉ የሚናገረውን የመጀመሪያውን መጽሐፍ ጻፍሁ፤
\v 2 ይህም የሆነው ጌታ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እርሱ የመረጣቸውን ሐዋርያትን ካዘዛቸው በኋላ ነበር፤
\v 3 ለምርጦቹ ከመከራው በኋላ ሕያው ሆኖ ተገልጦላቸዋል። አርባ ቀን እየታያቸው፣ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየተናገረ ቆየ።
\s5
\v 4 ከእነርሱም ጋር ዐብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፤ ነገር ግን "ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን ተስፋ ጠብቁ፤
\v 5 በእርግጥ ዮሐንስ በውሃ አጥምቆ ነበር፤ እናንተ ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ" አለ።
\s5
\v 6 ሐዋርያት በአንድነት ተሰብስበው ሳለ፣ “ጌታ ሆይ፣ ይህ የእስራኤልን መንግሥት የምትመልስበት ጊዜ ነውን?” ብለው ጠየቁት።
\v 7 እርሱም እንደዚህ አላቸው፤ “አብ በገዛ ሥልጣኑ የወሰነውን ጊዜ ወይም ወቅት ማወቅ እናንተን አይመለከትም።
\v 8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ ሲመጣ፣ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፣ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ።”
\s5
\v 9 ጌታ ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ሐዋርያቱ እያዩት ወደ ላይ ዐረገ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰወረው።
\v 10 ትኵር አድርገው ወደ ሰማይ እየተመለከቱ ሳለ፣ ድንገት ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ።
\v 11 እነርሱም፣ “እናንተ የገሊላ ሰዎች፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ለምን እዚህ ትቆማላችሁ? ወደ ሰማይ የወጣው ይህ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ ባያችሁበት ሁኔታ ተመልሶ ይመጣል” አሏቸው።
\s5
\v 12 ከዚያም በኋላ፣ የሰንበት ቀን ጕዞ ያህል ከሚያስሄደው፣ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ካለው ከደብረ ዘይት ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው ሄዱ።
\v 13 ሐዋርያት እዚያ ሲደርሱ፣ ወደሚቈዩበት፣ ወደ ላይኛው ሰገነት ወጡ። እነርሱም ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብ፣ እንድርያስ፣ ፊልጶስ፣ ቶማስ፣ በርተሎሜዎስ፣ ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብ፣ ቀናተኛው ስምዖንና የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ ነበሩ።
\v 14 ሁሉም በአንድነት ሆነው፣ ሴቶቹ፣ የኢየሱስ እናት ማርያምና ወንድሞቹም ጭምር በጸሎት ይተጉ ነበር።
\s5
\v 15 በዚያ ጊዜ ጴጥሮስ 120 ያህል በሚሆኑት ወንድሞች መካከል ቆመ፤ እንደዚህም አለ፤
\v 16 “ወንድሞች ሆይ፣ ኢየሱስን የያዙትንና መርቶ ያመጣውን ይሁዳን በሚመለከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ አስፈላጊ ነበር።
\s5
\v 17 ይሁዳ ከእኛ እንደ አንዱ ተቈጥሮና የዚህን አገልግሎት ድርሻም ተቀብሎ ነበርና።
\v 18 “ይሁዳም ለክፉ ሥራው በተከፈለው ዋጋ መሬት ገዛ። ከዚያም በግንባሩ ተደፋ፤ አካሉ ተሰነጠቀ፤ አንጀቱም ተዘረገፈ።
\v 19 በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ መሬቱ በቋንቋቸው አኬልዳማ [የደም መሬት] ተብሎ እንደሚጠራ ታወቀ።
\s5
\v 20 በመዝሙር መጽሐፍ፦ መኖሪያው ወና ይሁን፤ የሚኖርበት አንድ ሰውም እንኳ አይገኝ፤ ሹመቱንም ሌላ ሰው ይውሰደው፤ ተብሎ ተጽፎአልና።
\s5
\v 21 ስለዚህ ጌታ ኢየሱስ በመካከላችን በገባበትና በወጣበት ጊዜ ሁሉ ዐብረውን ከቈዩ ሰዎች፣
\v 22 ይኸውም ዮሐንስ ካጠመቀው ጥምቀት ጀምሮ ኢየሱስ ከእኛ እስካረገበት ቀን ድረስ፣ ከነበሩት ከእነዚህ አንዱ ከእኛ ጋር የትንሣኤው ምስክር ሊሆን ይገባል።”
\v 23 ኢዮስጦስም የሚባለውን፣ በርስያን ተብሎ የሚጠራውን ዮሴፍንና ማትያስን፣ ሁለት ሰዎችን እንዲቀርቡ አደረጉ።
\s5
\v 24 እንደዚህ ብለውም ጸለዩ፤ “ጌታ ሆይ፣ የሰዎችን ሁሉ ልብ አንተ ታውቃለህ፤ ስለዚህ ከእነዚህ ከሁለቱ የትኛውን እንደ መረጥኸው ግለጥ፤
\v 25 ይኸውም ይሁዳ ወደገዛ ስፍራው ትቶት በሄደው በዚህ አገልግሎትና ሐዋርያነት ውስጥ ስፍራ እንዲያገኝ ነው።”
\v 26 ሐዋርያት ዕጣዎችን ለእነርሱ ጣሉ፤ ዕጣውም ለማትያስ ወደቀ፤ እርሱም ከዐሥራ አንዱ ሐዋርያት ጋር አንድ ሆኖ ተቈጠረ።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በበዓለ ኀምሳ ቀን ሁሉም በአንድነት አንድ ስፍራ ላይ ነበሩ።
\v 2 ድንገት እንደ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ያለ ድምፅ ከሰማይ መጣ፤ ተቀምጠውበት የነበረውን ቤትም ሞላው።
\v 3 እንደ እሳት የተከፋፈሉ ልሳናት ታዩአቸው፤ በእያንዳንዳቸው ላይም ተቀመጡባቸው።
\v 4 ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ እንደ ሰጣቸውም በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።
\s5
\v 5 በዚያን ጊዜ ከሰማይ በታች ካለው ሕዝብ ሁሉ የመጡ፣ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሰዎች፣ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ አይሁድ ነበሩ።
\v 6 ይህ ድምፅ ሲሰማ፣ ብዙ ሕዝብ በአንድነት ተሰበሰበ፣ እያንዳንዱ ሰውም በገዛ ራሱ ቋንቋ ሲናገሩ በመስማቱ ግራ ተጋባ።
\v 7 ሕዝቡ ተደነቁ፤ ተገረሙም፤ “እነዚህ የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ በእውነት የገሊላ ሰዎች አይደሉምን? ብለውም ተናገሩ።
\s5
\v 8 እያንዳንዳቸው በተወለድንበት ቋንቋ ሲናገሩ የምንሰማቸው ለምንድን ነው?
\v 9 የጳርቴና፣ የሜድና የኢላሜጥ ሰዎች፣ በመስጴጦምያም፣ በይሁዳም፣ በቀጰዶቅያም፣ በጳንጦስም፣ በእስያም፣
\v 10 በፍርግያም፣ በጵንፍልያም፣ በግብፅም፣ በቀሬና በኩል በሚገኙት የሊቢያ ክፍሎች የምንኖርም፣ ከሮም የመጣን፣
\v 11 አይሁድና ወደ ይሁዲነት የገባን ቀርጤሳውያንና ዐረባውያን የሆንን እኛም፣ እነዚህ ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ታላላቅ ሥራዎች በራሳችን ቋንቋዎች ሲናገሩ እንሰማቸዋለን።"
\s5
\v 12 ሁሉም ተደነቁ፣ ግራ ተጋቡም፤ እርስ በርሳቸውም፣ “ይህ ነገር ምን ይሆን?” ተባባሉ።
\v 13 ሌሎች ግን፣ “ዐዲስ ወይን ጠጅ ጠጥተው ጠግበው ነው” ብለውም በማፌዝ ተናገሩ።
\s5
\v 14 ነገር ግን ጴጥሮስ ከዐሥራ አንዱ ጋር ቆሞ፣ ድምፁን ከፍ በማድረግ እንደዚህ አላቸው፤ “የይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ፣ ይህ ለእናንተ የታወቀ ይሁን፤ የምናገረውንም አድምጡ።
\v 15 እነዚህ ሰዎች እናንተ እንደምታስቡት አልሰከሩም፤ ምክንያቱም ገና ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነው።
\s5
\v 16 ነገር ግን በነቢዩ በኢዩኤል ይህ ተነግሯል፦
\v 17 ‘በመጨረሻዎቹ ቀናት ይህ ይሆናል፣’ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፤ ‘መንፈሴን ሥጋ በለበሱ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፣ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ ትንቢት ይናገራሉ። ወጣቶቻችሁ ራእይ ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ።
\s5
\v 18 በአገልጋዮቼና በሴት አገልጋዮቼ ላይም በእነዚያ ቀናት መንፈሴን አፈስሳለሁ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ።
\v 19 በላይ በሰማይ ድንቆችን፣ ምልክቶችንም በታች በምድር ላይ፣ ደምን፣ እሳትንና የጢስ ደመናን አሳያለሁ።
\s5
\v 20 ታላቁና ገናናው የጌታ ቀን ከመምጣቱ በፊት፣ ፀሓይ ወደ ጨለማነት፣ ጨረቃም ወደ ደምነት ይለወጣሉ።
\v 21 የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።'
\s5
\v 22 የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ እነዚህን ቃሎች ስሙ፦ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ ኢየሱስ፣ በመካከላችሁ እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ባደረጋቸው ታላላቅ ተግባራት፣ በተኣምራትና በምልክቶች፣ ከእግዚአብሔር ለእናንተ መገለጡ የተረጋገጠ ሰው ነው።
\v 23 አስቀድሞ በተወሰነው የእግዚአብሔር ዕቅድና በቀዳሚ ዕውቀቱ መሠረት፣ ዐልፎ ተሰጥቶአል፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ ሰቀላችሁት፤ ገደላችሁትም፤
\v 24 እግዚአብሔርም የሞትን ጣር ከእርሱ አጥፍቶ አስነሣው፤ ምክንያቱም ሞት እርሱን ይይዘው ዘንድ አልቻለም።
\s5
\v 25 ዳዊት ስለ እርሱ እንዲህ ብሎ ይናገራልና፦ ‘ጌታን ሁልጊዜ በፊቴ አየሁት፤ በቀኜ ነውና አልናወጥም።
\v 26 ስለዚህ ልቤ ተደሰተ፤ አንደበቴም ሐሤት አደረገ። ሥጋዬም በተስፋ ያድራል።
\s5
\v 27 ነፍሴን በሲኦል አትተዋትም፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።
\v 28 የሕይወትን መንገድ ገለጥህልኝ፤ በፊትህም ደስታን ታጠግበኛለህ።’
\s5
\v 29 ወንድሞች ሆይ፣ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት በግልጽ ልነግራችሁ እችላለሁ፤ እርሱ ሞቶአል፤ ተቀብሮአልም፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ ድረስ በእኛ ዘንድ ነው።
\v 30 ስለዚህ ዳዊት ነቢይ ነበረና ከዘሩ በዙፋኑ ላይ አንድን ሰው እንደሚያስቀምጥ እግዚአብሔር በመሐላ ለእርሱ ቃል ገብቶለት ነበር።
\v 31 ዳዊት ይህን አስቀድሞ አየ፤ ስለ ክርስቶስ ትንሣኤም ተናገረ፦ ክርስቶስ በሲኦል አልቀረም፤ ሥጋውም መበስበስን አላየም።
\s5
\v 32 ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር አስነሣው፤ ለዚህም እኛ ሁላችን ምስክሮች ነን።
\v 33 ስለዚህ ከሙታን በመነሣትና በእግዚአብሔር ቀኝ በመቀመጥ፣ ከአብ ቃል የተገባውን መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ፣ እናንተ የምታዩትንና የምትሰሙትን ይህን አፈሰሰው።
\s5
\v 34-35 ዳዊት ወደ ሰማይ አልወጣም፤ ነገር ግን እንዲህ ይላል፦ “ጌታ ለጌታዬ፣ ጠላቶችህን ለእግርህ መርገጫ እስከማደርጋቸው ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”
\v 36 ስለዚህ፣ እናንተ የሰቀላችሁትን ይህን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም ክርስቶስም እንዳደረገው የእስራኤል ወገን ሁሉ በእርግጥ ይወቅ።"
\s5
\v 37 ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ ልባቸው ተነካና ለጴጥሮስና ለቀሩት ሐዋርያት፣ “ወንድሞች ሆይ፣ ምን እናድርግ?” አሉ።
\v 38 ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ እያንዳንዳችሁም ለኀጢአታችሁ ይቅርታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ መንፈስ ቅዱስንም በስጦታነት ትቀበላላችሁ።
\v 39 የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ፣ ጌታ አምላካችን ለሚጠራቸው ሩቅ ላሉት ሁሉም ነውና።”
\s5
\v 40 ጴጥሮስ በሌሎች ብዙ ቃላት መሰከረ፤ “ከዚህ ክፉ ትውልድ ራሳችሁን አድኑ” በማለትም አስጠነቀቃቸው።
\v 41 ከዚያም ሕዝቡ ቃሉን ተቀብለው ተጠመቁ፤ በዚያም ቀን ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች ተጨመሩ።
\v 42 እነርሱም ሐዋርያት በሚያስተምሩት ትምህርትና በኅብረት፣ እንጀራውን በመቊረስና በጸሎትም ይተጉ ነበር።
\s5
\v 43 በሰው ሁሉ ላይ ፍርሀት መጣ፤ ብዙ ድንቆችና ምልክቶችም በሐዋርያት እጅ ተደረጉ።
\v 44 ያመኑት ሁሉ በአንድነት ነበሩ፤ ሁሉም ነገር የጋራ ነበር፤
\v 45 መሬታቸውንና ንብረታቸውን እየሸጡም ለሁሉም እንደሚያስፈልገው አካፈሉ።
\s5
\v 46 በየቀኑም በአንድ ዐላማ በመቅደስ እየተጉ፣ በቤት ውስጥ እንጀራ እየቈረሱም ምግብን ልባዊ በሆነ ደስታና ትሕትና ዐብረው ይመገቡ ነበር፤
\v 47 እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ በሕዝቡም ሁሉ ዘንድ ከበሬታ ነበራቸው። ጌታም የሚድኑትን በየቀኑ በእነርሱ ላይ ይጨምር ነበር።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ፣ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ ነበር።
\v 2 ወደ ቤተ መቅደሱ ከሚገቡ ሰዎች ምጽዋት መለመን እንዲችል፣ ውብ ተብሎ በሚጠራው በቤተ መቅደሱ በር ላይ ሰዎች በየቀኑ በሸክም አምጥተው የሚያስቀምጡት፣ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ዐንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።
\v 3 ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ቤተ መቅደሱ ሊገቡ ሲሉ ባያቸው ጊዜ፣ ምጽዋት ለመነ።
\s5
\v 4 ጴጥሮስ ዐይኖቹን ምጽዋት በሚለምነው ሰውዬ ላይ በማድረግ፣ ከዮሐንስ ጋር “ወደ እኛ ተመልከት” አለው።
\v 5 ዐንካሳውም፣ ከእነርሱ አንድ ነገር ለመቀበል በመጠበቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ።
\v 6 ጴጥሮስ ግን፣ “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ። በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተራመድ” አለው።
\s5
\v 7 ጴጥሮስ ቀኝ እጁን ያዘውና ወደ ላይ አነሣው፤ ወዲያውም እግሮቹና የቍርጭምጭሚቱ ዐጥንቶች ጥንካሬ አገኙ።
\v 8 ዐንካሳው ሰውዬ ወደ ላይ ዘልሎ ቆመ፤ መራመድም ጀመረ፤ ከጴጥሮስና ከዮሐንስ ጋርም እየተራመደ፣ እየዘለለና እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ።
\s5
\v 9 ሰዎች ሁሉ ዐንካሳው እየተራመደ ሲሄድና እግዚአብሔርን ሲያመሰግን አዩት።
\v 10 ምጽዋት ለመቀበል ውብ በሚባለው የቤተ መቅደሱ በር ላይ ይቀመጥ የነበረው ሰውዬ እንደ ሆነም ዐወቁ፤ በእርሱ ላይ ከሆነው የተነሣም በመደነቅና በመገረም ተሞሉ።
\s5
\v 11 ሰውየው የጴጥሮስንና የዮሐንስን እጅ ይዞ ሳለ፣ የሰሎሞን መመላለሻ በሚባለው ደጅ ሰዎች ሁሉ በኀይል እየተደነቁ በአንድነት ወደ እነርሱ ሮጡ።
\v 12 ጴጥሮስ ይህን ሲያይ ለሕዝቡ፣ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ለምን ትደነቃላችሁ? ይህን ሰው በገዛ ኀይላችን ወይም በመንፈሳዊነታችን እኛ እንዲራመድ እንዳደረግን ሁሉ፣ ለምን ዐይናችሁን አፍጥጣችሁ ትመለከታላችሁ? በማለት መልስ ሰጠ።
\s5
\v 13 የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ፣ የአባቶቻችን አምላክ አገልጋዩን ኢየሱስን አክብሮታል። እርሱ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትና ጲላጦስ ሊፈታው ወስኖ ሳለ፣ በፊቱ የካዳችሁት ነው።
\v 14 ቅዱሱንና ጻድቁን ካዳችሁት፤ በእርሱም ፈንታ ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር ከሙታን ያስነሣውን፣ የሕይወትን ጌታ ገደላችሁት፤ እኛም የዚህ ምስክሮች ነን።
\v 16 በእርሱ ስም ማመን አሁን የምታዩትንና የምታውቁትን ይህን ሰው ብርቱ አድርጎታል። አዎ፣ በኢየሱስ ያለው እምነቱ በሁላችሁ ፊት ይህን ፍጹም ጤንነት ሰጠው።
\s5
\v 17 አሁን ወንድሞች ሆይ፣ አለቆቻችሁም እንዳደረጉት ባለማወቅ ያደረጋችሁት እንደ ሆነ ዐውቃለሁ።
\v 18 ነገር ግን እግዚአብሔር በነቢያቱ ሁሉ አፍ የእርሱ ክርስቶስ መከራ መቀበል እንዳለበት አስቀድሞ የተናገረውን አሁን ፈጸመው።
\s5
\v 19 እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ፣ ከጌታ ዘንድም የመታደስ ዘመን እንዲመጣ ንስሓ ግቡ፤ ተመለሱም፤
\v 20 ይኸውም ለእናንተ የመረጠውን ክርስቶስ የሆነውን ኢየሱስን እንዲልከው ነው።
\s5
\v 21 እርሱ ሰማያት ሊቀበሉትና ነገሮች ሁሉ እስከሚታደሱበት ዘመን ድረስ ጠብቀው ሊያቈዩት የሚገባ፣ ከጥንት ጀምሮ በነበሩ ቅዱሳን ነቢያቱ አፍ የተነገረለት ነው።
\v 22 ሙሴ በእርግጥ፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣል። የሚነግራችሁንም ሁሉ ስሙ’ አለ።
\v 23 ያን ነቢይ የማይሰማ ሰው ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።
\s5
\v 24 አዎ፣ ከሳሙኤል ጀምሮና ከእርሱም በኋላ የተናገሩ ነቢያት ሁሉ ስለ እነዚህ ቀኖች ተናግረዋል።
\v 25 እናንተ የነቢያትና ‘በዘርህ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ’ ብሎ ለአብርሃም እንደ ተናገረው፣ ከአባቶቻችሁ ጋር እግዚአብሔር ያደረገው ኪዳን ልጆች ናችሁ።
\v 26 እግዚአብሔር አገልጋዩን ካስነሣ በኋላ በመጀመሪያ ወደ እናንተ ላከው፤ ይኸውም እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ መልሶ ሊባርካችሁ ነው።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ እየተናገሩ ሳሉ፣ ካህናቱና የቤተ መቅደሱ ሹም፣ ሰዱቃውያንም ወደ እነርሱ መጡ።
\v 2 እነርሱም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ሕዝቡን ያስተምሩና ከሙታን መነሣቱንም ያውጁ ስለ ነበረ፣ እጅግ ተበሳጩ።
\v 3 ያዟቸውና በዚያ ጊዜ ምሽት ስለ ነበረ እስከሚቀጥለው ጧት ድረስ በወኅኒ አቈዩአቸው።
\v 4 ነገር ግን መልእክቱን ከሰሙት ብዙ ሰዎች አመኑ፤ ያመኑት ሰዎች ቍጥርም ዐምስት ሺሕ ያህል ነበረ።
\s5
\v 5 በሚቀጥለው ቀን እንደዚህ ሆነ፤ አለቆቻቸው፣ ሽማግሌዎቻቸውና የሕግ መምህራናቸው በኢየሩሳሌም ውስጥ በአንድነት ተሰበሰቡ።
\v 6 ሊቀ ካህናቱ ሐና እዚያ ነበረ፤ ቀያፋም፣ ዮሐንስም፣ እስክንድሮስና የሊቀ ካህናቱ ዘመዶች ሁሉ ነበሩ።
\v 7 ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከላቸው አቁመውም፣ "በማን ሥልጣን ወይም በማንስ ስም ይህን አደረጋችሁ?" ብለው ጠየቋቸው።
\s5
\v 8 ከዚያም ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የሕዝቡ አለቆች፣ ሽማግሌዎችም፣
\v 9 ለታመመ ሰው የተደረገ መልካም ነገርን በሚመለከት በዚህ ቀን እየተጠየቅን ከሆንን፣ ይህ ሰው በምን ዳነ?
\v 10 ይህ ለእናንተ ለሁላችሁ፣ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን፤ ይህ ሰው በፊታችሁ እዚህ በጤንነት የቆመው እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔር ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነው።
\s5
\v 11 ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፣ ነገር ግን የማእዘን ራስ የሆነ ድንጋይ ነው።
\v 12 በሌላ በማንም ድነት የለም፤ ልንድንበት የሚገባ በሰዎች መካከል የተሰጠ ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።”
\s5
\v 13 የጴጥሮስንና የዮሐንስን ድፍረት ሲያዩ፣ ያልተማሩና ተራ ሰዎች እንደ ሆኑ ሲያውቁም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ በማወቅ ተደነቁ።
\v 14 የተፈወሰው ሰውዬ ዐብሯቸው ቆሞ ስላዩት፣ የአይሁድ መሪዎች በእነርሱ ላይ ምንም መናገር አልቻሉም።
\s5
\v 15 ሐዋርያቱ ከሸንጎው ወጥተው እንዲሄዱ ካዘዙ በኋላ፣ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ።
\v 16 እንደዚህም አሉ፤ “በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን እናድርግ? በእነርሱ አማካይነት የታወቀ ተአምር የመፈጸሙ እውነታ በኢየሩሳሌም ለሚኖር ሁሉ ታውቆአልና፤ ልንክደው አንችልም።
\v 17 ሆኖም ይህ በሕዝቡ መካከል የበለጠ እንዳይሠራጭ፣ በዚህ ስም ከእንግዲህ ለማንም እንዳይናገሩ እናስጠንቅቃቸው።”
\v 18 ጴጥሮስንና ዮሐንስን ወደ ውስጥ ጠርተው በኢየሱስ ስም ፈጽሞ እንዳይናገሩም፣ እንዳያስተምሩም አዘዟቸው።
\s5
\v 19 ነገር ግን ጴጥሮስና ዮሐንስ መልሰው እንዲህ አሏቸው፤ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ እናንተን መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል እንደ ሆነ እናንተ ፍረዱ።
\v 20 እኛ ስላየናቸውና ስለ ሰማናቸው ነገሮች ለመናገር ዝም ማለት አንችልም።”
\s5
\v 21 እንደ ገናም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ካስጠነቀቋቸው በኋላ፣ ለቀቋቸው። እነርሱን ለመቅጣት ምንም ምክንያት ለማግኘት አልቻሉም፤ ምክንያቱም ሰዎቹ ሁሉ ለተደረገው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር።
\v 22 ይህ በተአምር የተፈወሰው ሰውዬ ከዐርባ ዓመት በላይ ዕድሜ ነበረው።
\s5
\v 23 ከተለቀቁ በኋላ፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ራሳቸው ሰዎች መጡና የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሏቸውን ሁሉ ነገሯቸው።
\v 24 ሰዎቹ የነገሯቸውን ሲሰሙም፣ ድምፃቸውን በአንድነት ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በውስጣቸው የሚገኘውንም ሁሉ የፈጠርህ ነህ፤
\v 25 በመንፈስ ቅዱስም በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለሃል፦ ‘አሕዛብ ለምን አጕረመረሙ፣ ሕዝቡስ ከንቱ ነገርን ለምን ዐሰቡ?
\s5
\v 26 በጌታ፣ በእርሱ መሲሕም ላይ የምድር ነገሥታት ተነሡ፣ አለቆችም በአንድነት ተሰበሰቡ።’
\s5
\v 27 በእውነት ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ፣ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በቀባኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ በዚህ ከተማ ውስጥ በአንድነት ተሰብስበዋል።
\v 28 የተሰበሰቡትም እጅህና ዐሳብህ አስቀድመው የወሰኑት እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 29 ጌታ ሆይ፣ አሁን ወደ ዛቻዎቻቸው ተመልከት፤ ለባሪያዎችህም ቃልህን በሙሉ ድፍረት እንዲናገሩ ስጥ።
\v 30 ለመፈወስ እጅህን ስትዘረጋው፣ ምልክቶችና ድንቆች በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ስም ይደረጋሉ።"
\v 31 ጸሎት ሲጨርሱ፣ ተሰብስበውበት የነበረው ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃልም በድፍረት ተናገሩ።
\s5
\v 32 ካመኑት እጅግ ብዙዎች አንድ ልብና አንድ ነፍስ ነበራቸው፤ ከእነርሱ አንድም ሰው፣ ያለው ማንኛውም ነገር የራሱ እንደ ሆነ አልተናገረም፤ ይልቁን ሁሉም ነገሮች የጋራ ነበሩ።
\v 33 ሐዋርያቱም በታላቅ ኀይል ስለ ጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ ምስክርነታቸውን ያውጁ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።
\s5
\v 34 በመካከላቸው ችግረኛ ሰው አልነበረም፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ ሸጠው የሽያጩን ገንዘብ ያመጡትና፣
\v 35 በሐዋርያት እግር አጠገብ ያስቀምጡት ነበርና። አከፋፈሉም ይደረግ የነበረው እያንዳንዱ አማኝ በሚያስፈልገው መሠረት ነው።
\s5
\v 36 ሌዋዊ የሆነው፣ ቆጵሮሳዊው ዮሴፍ ሐዋርያት በርናባስ የሚባል ስም ያወጡለት ሰው ነበር (ትርጕሙ የመጽናናት ልጅ ማለት ነው)።
\v 37 እርሱ የነበረውን መሬት ሸጠው፤ ገንዘቡንም አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠው።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ሐናንያ የሚባል አንድ ሰውም ከሚስቱ ከሰጲራ ጋራ መሬት ሸጠ፤
\v 2 የሽያጩን ገንዘብ ከፊል መጠን አስቀረው (ሚስቱም ታውቅ ነበር)፤ ሌላውን የገንዘብ መጠን ግን አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አስቀመጠው።
\s5
\v 3 ጴጥሮስ ግን ሐናንያን እንዲህ አለው፤ “ሐናንያ ሆይ፣ ለመንፈስ ቅዱስ እንድትዋሽና የመሬቱን ዋጋ ከፊል መጠን እንድታስቀር ሰይጣን ልብህን ለምን ሞላው?
\v 4 መሬቱ ሳይሸጥ የአንተ እንደ ሆነ አይዘልቅም ነበርን? ከተሸጠ በኋላስ በአንተ ቊጥጥር ሥር አልነበረምን? በልብህ ይህን ነገር እንዴት ዐሰብህ? የዋሸኸው ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰዎች አይደለም።
\v 5 እነዚህን ቃሎች ሰምቶ፣ ሐናንያ ወደቀ፤ ሞተም። በሰሙት ሁሉ ላይም ታላቅ ፍርሀት መጣ።
\v 6 ጐበዛዝቱ ወደ ፊት መጡና ከፈኑት፤ ወደ ውጭ አውጥተውም ቀበሩት።
\s5
\v 7 ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላ፣ ሚስቱ ምን እንደ ሆነ ሳታውቅ ወደ ውስጥ ገባች።
\v 8 ጴጥሮስ፣ “መሬቱን ይህን ለሚያህል ዋጋ ሸጣችሁት ከሆነ ንገሪኝ” አላት። እርሷም፣ "አዎ፣ ይህን ለሚያህል ነው” አለችው።
\s5
\v 9 ከዚያም ጴጥሮስ፣ “የጌታን መንፈስ ለመፈታተን እንዴት ተስማማችሁ? ተመልከቺ፣ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በር ላይ ነው፤ አንቺንም ወደ ውጭ ያወጡሻል።”
\v 10 እርሷም ወዲያው በጴጥሮስ እግር ሥር ወደቀች፤ ሞተችም፤ ጐበዛዝቱም ወደ ውስጥ ሲገቡ ሞታ አገኟት፤ ወደ ውጭ አወጧትና በባሏ አጠገብ ቀበሯት።
\v 11 በቤተ ክርስቲያን ሁሉና እነዚህን ነገሮች በሰሙት ላይ ታላቅ ፍርሀት መጣ።
\s5
\v 12 በሕዝቡ መካከል ብዙ ምልክቶችና ድንቆች በሐዋርያት እጅ ይደረጉ ነበር። ሁሉም በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በአንድነት ነበሩ።
\v 13 ነገር ግን አንድም ሌላ ሰው እንኳ ከእነርሱ ጋር ለመተባበር ድፍረት አልነበረውም፤ ሆኖም ከሕዝቡ ከፍተኛ አክብሮት ነበራቸው።
\s5
\v 14 አሁንም የበለጡ አማኞች፣ እጅግ ብዙ ወንዶችና ሴቶች ለጌታ ይጨመሩ ነበር፤
\v 15 በሽተኞችንም እንኳ ተሸክመው ወደ መንገድ እያመጡ በዐልጋና በቃሬዛ ላይ ያስቀምጧቸው ነበር፤ ይኸውም ጴጥሮስ ሲያልፍ በተወሰኑት ላይ ጥላው እንዲያርፍባቸውነው።
\v 16 በሽተኞችንና በርኩሳን መናፍስት የሚሠቃዩትን በማምጣት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉ ከተሞች አያሌ ሰዎችም በአንድነት ተሰበሰቡ፤ በሽተኞችም ሁሉ ተፈወሱ።
\s5
\v 17 ነገር ግን ሊቀ ካህናቱና ዐብረውት የነበሩትም ሁሉ ተነሡ (የሰዱቃውያን ወገን የሆነው ማለት ነው)፤ እነርሱም በቅናት ተሞልተው ነበር፤
\v 18 እጃቸውንም በሐዋርያት ላይ ጫኑ፤ በሕዝብ ወኅኒ ውስጥም አስገብተው አሰሯቸው።
\s5
\v 19 ይሁን እንጂ፣ የጌታ መልአክ በሌሊት የወኅኒውን በሮች ከፈተ፤ ወደ ውጭ አውጥቶአቸውም እንዲህ አላቸው፤
\v 20 “ሂዱ፤ በቤተ መቅደስ ውስጥ ቁሙና የዚህን ሕይወት ቃሎች ሁሉ ለአሕዝቡ ተናገሩ።”
\v 21 ይህን ሲሰሙም፣ ንጋት ላይ ወደ ቤተ መቅደስ ገቡና አስተማሩ። ነገር ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጡ፤ ሸንጎውንም በአንድነት፣ የእስራኤል ሕዝብ ሽማግሌዎችንም ጠሩ፤ ሐዋርያቱን እንዲያመጧቸውም ወደ ወኅኒው ላኩ።
\s5
\v 22 ነገር ግን የተላኩት መኰንኖች በወኅኒው ውስጥ አላገኟቸውም፤ ተመልሰው በመሄድም እንዲህ ብለው ተናገሩ፣
\v 23 “ወኅኒው በደኅና እንደ ተቈለፈና ጠባቂዎችም በር ላይ እንደ ቆሙ አግኝተናል፤ በከፈትነው ጊዜ ግን በውስጡ ማንንም አላገኘንም።”
\s5
\v 24 የመቅደሱ ጥበቃ ሹምና ሊቃነ ካህናቱ እነዚህን ቃላት ሲሰሙ፣ እስረኞችን በሚመለከት ምን እንደሚሆን እጅግ ግራ ተጋቡ።
\v 25 ከዚያም አንድ ሰው መጣና፣ “ወኅኒ ውስጥ ያስገባችኋቸው ሰዎች ቤተ መቅደስ ውስጥ ቆመው ሕዝቡን እያስተማሩ ናቸው” ብሎ ነገራቸው።
\s5
\v 26 ስለዚህ ሹሙ ከመኰንኖች ጋር ሄደ፤ መልሶም አመጣቸው፤ ያመጧቸው ግን በኀይል አልነበረም፤ ሕዝቡ በድንጋይ ይወግሯቸዋል ብለው ፈርተው ነበርና።
\v 27 አምጥተዋቸው በነበረ ጊዜ፣ በሸንጎው ፊት አቆሟቸው። ሊቀ ካህናቱም ጠየቃቸው፤
\v 28 እንዲህም አላቸው፤ “በዚህ ስም እንዳታስተምሩ በጥብቅ አስጠንቅቀናችሁ ነበር፤ እናንተ ግን ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋታል፤ የዚህን ሰው ደም በእኛ ላይ ለማምጣትም ትፈልጋላችሁ።”
\s5
\v 29 ጴጥሮስና ሐዋርያቱ ግን መልሰው፣ “ለሰው ከመታዘዝ ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።
\v 30 የአባቶቻችን አምላክ በዕንጨት ላይ በመስቀል የገደላችሁትን፣ ኢየሱስን አስነሣው።
\v 31 አዳኝና የሁሉ የበላይ እንዲሆን፣ ለእስራኤል ንስሓንና የኀጢአት ይቅርታን ለመስጠት እግዚአብሔር በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።
\v 32 እኛና እግዚአብሔር ለሚታዘዙት የሰጠው መንፈስ ቅዱስ የእነዚህ ነገሮች ምስክሮች ነን።”
\s5
\v 33 የሸንጎው አባሎች ይህን ሲሰሙ፣ በጣም ተናደዱ፤ ሐዋርያቱንም ለመግደል ፈለጉ።
\v 34 ነገር ግን የሕግ መምህር የነበረና ሕዝቡም ሁሉ የሚያከብረው ገማልያል የሚባል አንድ ፈሪሳዊ ተነሥቶ፣ ሐዋርያት ለተወሰነ ጊዜ ውጭ እንዲቈዩ አዘዘ።
\s5
\v 35 ከዚያም እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ በእነዚህ ሰዎች ልታደርጉ ያሰባችሁትን በጥንቃቄ ተመልከቱት።
\v 36 ከጥቂት ጊዜ በፊት ቴዎዳስ ትልቅ ሰው ነኝ በማለት ተነሥቶ ነበርና፤ አራት መቶ ያህል ወንዶችም ተከተሉት። እርሱ ተገደለ፤ ይታዘዙለት የነበሩትም ሁሉ ተበታትነው እንዳልነበሩ ሆኑ።
\v 37 ከዚህም ሰው በኋላ፣ የገሊላው ይሁዳ በቈጠራው ቀናት ዐምፆ የተወሰኑ ሰዎችን አስከትሎ ሄደ። እርሱም ሞተ፤ እርሱን ይታዘዙት የነበሩትም ተበታተኑ።
\s5
\v 38 አሁንም እነግራችኋለሁ፤ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ፤ እነርሱንም ተዉአቸው፤ ይህ ዐሳብ ወይም ሥራ የሰዎች ከሆነ፣ ይጠፋል።
\v 39 የእግዚአብሔር ከሆነ ግን፣ ልታጠፏቸው አትችሉም፤ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጋጩም እንኳ እንዳትገኙ።” እነርሱም በዐሳቡ ተስማሙ።
\s5
\v 40 ከዚያም በኋላ፣ ሐዋርያቱን ወደ ውስጥ ጠርተው ገረፏቸው፤ በኢየሱስ ስም እንዳይናገሩም አዘዟቸውና ለቀቋቸው።
\v 41 እነርሱም ስለ ስሙ ይዋረዱ ዘንድ የተገባቸው ሆነው ስለ ተቈጠሩ፣ ደስ እያላቸው ከሸንጎው ወጡ።
\v 42 ከዚያ በኋላ በየቀኑ፣ በቤተ መቅደስና ከቤት ወደ ቤት፣ በተከታታይ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ እንደ ሆነ ያስተምሩና ይሰብኩ ነበር።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 በእነዚህ ወራት፣ የደቀ መዛሙርት ቊጥር እየበዛ በሄደ ጊዜ፣ ከግሪክ የመጡት አይሁድ በዕብራውያን ላይ ማጕረምረም ጀመሩ፤ ምክንያቱም መበለቶቻቸው በየዕለቱ የምግብ ዕደላ ላይ ቸል ተብለውባቸው ነበር።
\s5
\v 2 ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ ጠርተው እንዲህ አሏቸው፤ “የምግብ አገልግሎትን ለመስጠት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል መተው ለእኛ ተገቢ አይደለም።
\v 3 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፣ በዚህ ኀላፊነት ላይ ልንሾማቸው የምንችል መልካም አርአያነት ያላቸውን፣ መንፈስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ መካከል ምረጡ።
\v 4 እኛ ግን፣ ሁልጊዜ በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንቀጥላለን።”
\s5
\v 5 ንግግራቸው ሕዝቡን ሁሉ ደስ አሰኘ። ስለዚህ እምነትና መንፈስ ቅዱስ የሞላበትን እስጢፋኖስን፣ ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞናን፣ ጳርሜናንና ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ።
\v 6 አማኞቹ እነዚህን ሰዎች፣ በጸለዩላቸውና ከዚያም እጃቸውን በላያቸው በጫኑት በሐዋርያት ፊት አቀረቧቸው።
\s5
\v 7 ስለዚህም የእግዚአብሔር ቃል አደገ፤ የደቀ መዛሙርት ቊጥርም በኢየሩሳሌም ውስጥ በብዛት ጨመረ፤ ከካህናትም ብዙዎቹ ለእምነት ታዛዦች ሆኑ።
\s5
\v 8 እስጢፋኖስ ጸጋንና ኀይልን ተሞልቶ፣ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ድንቆችንና ምልክቶችን ያደርግ ነበር።
\v 9 ነገር ግን ነጻ የወጡት ሰዎች ምኵራብ ከሚባለው ምኵራብ፣ ከቀሬናና ከእስክንድርያ፣ ከኪልቅያና ከእስያም የሆኑ ጥቂት ሰዎች ተነሡ። እነዚህ ሰዎች ከእስጢፋኖስ ጋር ይከራከሩ ነበር።
\s5
\v 10 ነገር ግን ሰዎቹ እስጢፋኖስ የተናረገረበትን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም።
\v 11 ከዚያም፣ “እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተናል” እንዲሉ አንዳንድ ሰዎችን በምስጢር አሳመኑ።
\s5
\v 12 ሰዎቹን፣ ሽማግሌዎቹን፣ የሕግ መምህራኖቹንም አነሣሡ፤ እስጢፋኖስንም ይዘው ወደ ሸንጎው አቀረቡት።
\v 13 እንዲህ ብለው የሚናገሩ ሐሰተኛ ምስክሮችንም አመጡ፤ “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን ተቃውሞ መናገርን አያቆምም።
\v 14 ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዐትም ይለውጠዋል ሲል ሰምተነዋል።”
\v 15 በሸንጎው ውስጥ የተቀመጡት ሁሉ አተኵረው ተመለከቱት፤ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት ሆኖ አዩት።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ሊቀ ካህናቱም፣ “እነዚህ ነገሮች እውነት ናቸውን?” አለ።
\v 2 እስጢፋኖስ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ አድምጡኝ፤ የክብር አምላክ ለአባታችን ለአብርሃም በካራን ከመኖሩ በፊት በመስጴጦምያ ሳለ ተገለጠለት፤
\v 3 እግዚአብሔርም፣ 'አገርህንና ዘመዶችህን ተውና እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ' አለው።
\s5
\v 4 ከዚያም በኋላ፣ ጊዜ አብርሃም ከከለዳውያን ምድር ወጥቶ በካራን ኖረ፤ ከዚያም፣ አባቱ ከሞተ በኋላ፣ እግዚአብሔር አሁን እናንተ ወደምትኖሩበት፣ ወደዚህ ምድር አመጣው።
\v 5 ከዚህ ምድር ምንም ርስት፣ የእግር ጫማ ለማሳረፍ የሚበቃ እንኳ አልሰጠውም። ነገር ግን አብርሃም ገና ልጅ ያልነበረው ቢሆንም እንኳ፣ እግዚአብሔር ምድሪቱን ርስት አድርጎ ለእርሱና ከእርሱ በኋላ ለዘሮቹ እንደሚሰጥ ቃል ገባ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ለአብርሃም እንደዚህ እየተናገረው ነበር፤ ይኸውም ዘሮቹ ለተወሰነ ጊዜ በባዕድ ምድር እንደሚኖሩ፣ እዚያ ያሉ ኗሪዎችም በባርነት ውስጥ እንደሚያስገቧቸውና ለአራት መቶ ዓመታት እንደሚያስጨንቋቸው ነው።
\v 7 ‘በባርነት የሚኖሩበትን ሕዝብም እፈርድበታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይወጣሉ፤ በዚህም ስፍራ ያመልኩኛል’ አለ እግዚአብሔር።
\v 8 እግዚአብሔር ለአብርሃም የግዝረትን ኪዳን ሰጠው፤ አብርሃምም የይስሐቅ አባት ሆነ ይስሐቅንም በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ ይስሐቅ የያዕቆብ አባት ሆነ፤ ያዕቆብም የዐሥራ ሁለቱ አለቆች አባት።
\s5
\v 9 አለቆች በዮሴፍ ላይ በቅናት ተነሣሥተው ወደ ግብፅ ሸጡት፤ እግዚአብሔር ግን ከእርሱ ጋር ነበረ፤
\v 10 ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስና ጥበብ ሰጠው። ፈርዖንም ዮሴፍን በግብፅና በቤቱ ባለው ሁሉ ላይ ገዥ አደረገው።
\s5
\v 11 በመላው ግብፅና በከነዓን ራብና ትልቅ ጭንቀት መጣ፤ አባቶቻችንም ምንም ምግብ አላገኙም።
\v 12 ነገር ግን ያዕቆብ እህል በግብፅ ውስጥ እንደ ነበረ ሲሰማ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ አባቶቻችንን ላካቸው።
\v 13 በሁለተኛው ጊዜ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን ገለጠ፤ የዮሴፍ ቤተ ሰብም ከፈርዖን ጋር ተዋወቀ።
\s5
\v 14 ከዘመዶቹ ሁሉ ጋር፣ ሰባ ዐምስት ሰዎች ሆኖ ወደ ግብፅ እንዲመጣ፣ ለአባቱ ለያዕቆብ እንዲነግሩ ዮሴፍ ወንድሞቹን መልሶ ላካቸው።
\v 15 ስለዚህ ያዕቆብ ወደ ግብፅ ወረደ፤ ከጊዜ በኋላም፣ እርሱና አባቶቻችን በዚያ ሞቱ።
\v 16 ወደ ሴኬም ተወስደውም አብርሃም በሴኬም ከኤሞር ልጆች በብር ገዝቶት በነበረው መቃብር ተቀበሩ።
\s5
\v 17 እግዚአብሔር ለአብርሃም ገብቶት የነበረው የተስፋ ቃል ጊዜ ሲቃረብ፣ ሕዝቡ በግብፅ ውስጥ በቍጥር እያደጉና እየበዙ ሄዱ፤
\v 18 በግብፅ ሌላ ንጉሥ፣ ስለ ዮሴፍ ያላወቀ ንጉሥ እስከ ተነሣ ድረስ።
\v 19 ይኸው ንጉሥ ሕዝባችንን አታለለ፤ አባቶቻችንንም አስጨነቀ፤ ሕዝቡም ሕፃናታቸውን በሕይወት እንዳይኖሩ ወደ ውጭ መጣል ነበረባቸው።
\s5
\v 20 በዚያ ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት በጣም ያማረ ነበር፤ በአባቱ ቤትም ሦስት ወር አደገ።
\v 21 ሙሴ ወንዝ ውስጥ ሲጣል፣ የፈርዖን ሴት ልጅ ወስዳ እንደ ልጇ አሳደገችው።
\s5
\v 22 ሙሴ በግብፃውያን ትምህርት ሁሉ የሠለጠነ፣ በንግግሩና በሥራውም ታላቅ ሰው ነበር።
\v 23 አርባ ዓመት ሲሆነው ግን ወንድሞቹን፣ የእስራኤልን ልጆች የመጐብኘት ዐሳብ ወደ ልቡ መጣ።
\v 24 አንድ እስራኤላዊ ሲጠቃ አይቶ፣ ሙሴ ተከላከለለት፤ ያጠቃውንም ግብፃዊ ተበቀለው፤
\v 25 ሙሴ በእርሱ እጅ እግዚአብሔር እያዳናቸው መሆኑን ወንድሞቹ ያስተውላሉ ብሎ ዐሰበ፤ እነርሱ ግን አላስተዋሉም።
\s5
\v 26 በሚቀጥለው ቀን ሙሴ እየተጣሉ ወደ ነበሩ እስራኤላውያን መጣ፤ እርስ በርስ ሊያስታርቃቸውም ሞከረ፤ ‘እናንተ ሰዎች ሆይ፣ ወንድማማቾች ናችሁ፤ እርስ በርስ ለምን ትጐዳዳላችሁ? አለ።
\v 27 ባልንጀራውን የጐዳው ግን ሙሴን ገፈተረው፤ እንደዚህም አለው፤ 'በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ ያደረገህ ማን ነው?
\v 28 ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ትፈልጋለህን?'
\s5
\v 29 ሙሴ ይህን ከሰማ በኋላ ሸሽቶ ሄደ፤ የሁለት ልጆች አባት በሆነበት በምድያም ምድር መጻተኛ ሆነ።
\v 30 አርባ ዓመት ሲያልፍ፣ በሲና ተራራ ምድረ በዳ፣ በቊጥቋጦ ውስጥ በእሳት ነበልባል መልአክ ታየው።
\s5
\v 31 ሙሴ እሳቱን ሲያይ፣ በሚታየው ተደነቀ፤ ሊመለከተው ሲቀርብም፣ እንዲህ የሚል የጌታ ድምፅ መጣ፤
\v 32 ‘እኔ የአባቶችህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅም አምላክ፣ የያዕቆብም አምላክ ነኝ።’ ሙሴ ተንቀጠቀጠ፣ መመልከትም አልቻለም።
\s5
\v 33 ጌታም ለሙሴ እንዲህ አለው፤ ‘የቆምህበት ስፍራ ቅዱስ ነውና ጫማህን አውልቅ።
\v 34 በግብፅ ውስጥ ያሉትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፤ የሥቃይ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁና አሁን ና፤ ወደ ግብፅ እልክሃለሁ።’
\s5
\v 35 “በእኛ ላይ ገዥና ዳኛ ያደረገህ ማን ነው?” ባሉት ጊዜ ተቀባይነትን ያሳጡት ይህ ሙሴ፦ እግዚአብሔር ገዥም ታዳጊም አድርጎ የላከው ነው። እግዚአብሔር ሙሴን በቊጥቋጦው ውስጥ በታየው መልአክ እጅ ላከው።
\v 36 በግብፅና በቀይ ባሕር፣ በአርባ ዓመታቱ ወቅትም በምድረ በዳ ተአምራትንና ምልክቶችን ካደረገ በኋላ፣ ሙሴ ሕዝቡን ከግብፅ አወጣቸው።
\v 37 ‘እግዚአብሔር ከወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል’ ብሎ ለእስራኤል ሕዝብ የተናገረው ያው ሙሴ ነው።
\s5
\v 38 ይህ ሰው ሲና ተራራ ላይ ያናግረው ከነበረው መልአክ ጋር በምድረ በዳው በጉባኤ ውስጥ የነበረ ሰው ነው። ሰው ከአባቶችችን ጋር ነበረ፤ ለእኛ ሊሰጥ ሕያው ቃልን የተቀበለ ሰውም ነው።
\v 39 ይህ አባቶቻችን ለመታዘዝ እንቢ ያሉት ሰው ነው፤ እነርሱም ገፉት፤ በልባቸውም ወደ ግብፅ ተመለሱ።
\v 40 በዚያ ጊዜ አሮንን እንዲህ አሉት፤ ‘የሚመሩንን አማልክት ሥራልን። ከግብፅ ምድር መርቶ ያወጣን ይህ ሙሴ፣ ምን እንዳጋጠመው አናውቅም።'
\s5
\v 41 ስለዚህ እስራኤላውያን በእነዚያ ቀኖች ጥጃ ሠርተው ለጣዖቱ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ከእጆቻቸው ሥራ የተነሣም ደስ አላቸው።
\v 42 እግዚአብሔር ግን ዘወር አለ፤ የሰማይ ከዋክብትን እንዲያመልኩም አሳልፎ ሰጣቸው፤ በነቢያት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ አርባ ዓመት በምድረ በዳ፣ የታረዱ እንስሳትንና መሥዋዕቶችን አቀረባችሁልኝን?
\s5
\v 43 የሞሎክን ድንኳን፣ ሬምፉም የሚባለውን አምላክ ኮከብም፣ ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን ምስሎችም ተቀበላችሁ፤ እኔም ከባቢሎን ወዲያ እሰድዳችኋለሁ።’
\s5
\v 44 አባቶቻችን የምስክሩ ድንኳን በምድረ በዳ ነበራቸው፤ ይኸውም ባየው ምሳሌ መሠረት መሥራት እንዳለበት እግዚአብሔር ሙሴን ሲያናግረው እንዳዘዘው ያለ ነው።
\v 45 ይህ አባቶቻችን በተራቸው ከኢያሱ ጋር ወደ ምድሪቱ ያመጡት ድንኳን ነው። እግዚአብሔር በአባቶቻችን ፊት ባስወጣቸው አሕዛብ አገር ውስጥ ሲገቡ፣ ይህ ሆነ። እስከ ዳዊት ዘመን ድረስ እንደዚህ ነበር፤
\v 46 ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አገኘ፤ ለያዕቆብ አምላክም ማደሪያ ስፍራን ለማግኘት ለመነ።
\s5
\v 47 ነገር ግን ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት ሠራለት።
\v 48 ይሁን እንጂ፣ ልዑሉ በእጅ በተሠሩ ቤቶች ውስጥ አይኖርም፤ ይህም ነቢዩ እንዲህ ብሎ እንደሚናገረው ነው፦
\v 49 ሰማይ ዙፋኔ፣ ምድርም የእግሬ መርገጫ ነው። ምን ዐይነት ቤት ልትሠሩልኝ ትችላላችሁ? ይላል ጌታ፤ ወይስ የማርፍበት ስፍራ የት ነው?
\v 50 እጄ እነዚህን ሁሉ አልሠራችምን?
\s5
\v 51 እናንተ ዐንገተ ደንዳኖች፣ ልባችሁንና ጆሮዎቻችሁን ያልተገረዛችሁ፣ ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስን ትቃወማላችሁ፤ አባቶቻችሁ እንዳደረጉትም ታደርጋላችሁ።
\v 52 ከነቢያት የእናንተ አባቶች ያላሳደዱት የትኛው ነው? እነርሱ ከጻድቁ መምጣት ቀድመው የተናገሩ ነቢያትን ገድለዋል፤ እናንተም አሁን ጻድቁን የምትክዱና የምትገድሉ ሆናችኋል፤
\v 53 መላእክት ያጸኑትን ሕግ ብትቀበሉም አልጠበቃችሁትም።”
\s5
\v 54 አሁን የሸንጎው አባላት እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ፣ በልባቸው እጅግ ተቈጡ፣ ጥርሳቸውንም በእስጢፋኖስ ላይ አፋጩ።
\v 55 እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ፣ ወደ ሰማይ አተኵሮ ተመለከተ፣ የእግዚአብሔርንም ክብር አየ፤ ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየው።
\v 56 እስጢፋኖስ፣ “እነሆ፣ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየሁ” አለ።
\s5
\v 57 የሸንጎው አባላት ግን በታላቅ ድምፅ ጮኹ፤ ጆሮአቸውንም በመድፈን በአንድነት እየሮጡ ወደ እስጢፋኖስ ሄዱ፤
\v 58 ከከተማው አውጥተውም በድንጋይ ወገሩት፤ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል አንድ ወጣት እግር አጠገብ አኖሩ።
\s5
\v 59 እስጢፋኖስን ሲወግሩት፣ ወደ እግዚአብሔር ይጣራ፣ “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ነፍሴን ተቀበል” እያለ ይናገርም ነበር።
\v 60 ተንበረከከና በታላቅ ድምፅ፣ “ጌታ ሆይ፣ ይህን ኀጢአት አትቊጠርባቸው” ብሎ ጮኸ። ይህን ተናግሮም፣ አንቀላፋ።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ሳውል በእስጢፋኖስ ሞት ተስማምቶ ነበር። በዚያም ጊዜ በኢየሩሳሌም በነበረችዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ አማኞችም ሁሉ ከሐዋርያት በቀር በይሁዳና በሰማርያ ተበታተኑ።
\v 2 በመንፈሳዊ ነገር የተጉ ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ መሪር ልቅሶም አለቀሱለት።
\v 3 ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን በጣም ጐዳ፤ ከቤት ወደ ቤት በመሄድም ክርስቲያን ወንዶችንና ሴቶችን ጐትቶ አወጣቸው፤ ወኅኒ ቤት ውስጥም አስገባቸው።
\s5
\v 4 የተበታተኑት አማኞች ግን ቃሉን እየሰበኩ በየቦታው ዞሩ።
\v 5 ፊልጶስ ወደ ሰማርያ ከተማ ወረደ፣ ለሕዝቡም ክርስቶስን ሰበከላቸው።
\s5
\v 6 እጅግ ብዙ ሰዎች ፊልጶስን ሲሰሙትና ያደረጋቸውንም ምልክቶች ሲያዩ፣ በአንድነት እርሱ ለተናገረው ትኵረት ሰጡ።
\v 7 ምክንያቱም ከብዙ ሰዎች ርኩሳን መናፍስት እየጮኹ ወጥተው፣ አያሌ ሽባዎችና ዐንካሶችም ተፈውሰው ነበር።
\v 8 ስለዚህ በዚያች ከተማ ውስጥ ብዙ ደስታ ነበር።
\s5
\v 9 ነገር ግን በዚያች ከተማ ውስጥ ቀደም ሲል የጥንቈላ ሥራ ይሠራ የነበረ ሲሞን የሚባል ሰው ነበረ፤ ተፈላጊ ሰው እንደ ሆነ እየተናገረ የሰማርያን ሰዎች ያስደንቅ ነበር።
\v 10 ሳምራውያን በሙሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ፣ “ይህ ሰው ታላቅ የሚባለው የእግዚአብሔር ኀይል ነው” እያሉ በሚገባ ያደምጡት ነበር።
\v 11 በጥንቈላ ሥራው ለረጅም ጊዜ ያስገርማቸው ስለ ነበር አደመጡት።
\s5
\v 12 ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፊልጶስ የሰበከውን ወንጌል ሲያምኑ ግን ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ።
\v 13 ሲሞንም ደግሞ አመነ፤ ከተጠመቀም በኋላ ከፊልጶስ ጋር መሆንን ቀጠለ፤ የተደረጉ ምልክቶችንና ታላላቅ ተኣምራትን ባየ ጊዜም ተደነቀ።
\s5
\v 14 በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያት ሰማርያ የእግዚአብሔርን ቃል የተቀበለች መሆኗን ሲሰሙ፣ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው።
\v 15 እነርሱም እዚያ ወርደው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጸለዩላቸው።
\v 16 መንፈስ ቅዱስ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በማንኛቸውም ላይ አልወረደም ነበርና፣ እነርሱ በጌታ ኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር።
\v 17 ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፣ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ።
\s5
\v 18 በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጥ ሲያይ፣ ሲሞን ገንዘብ አቀረበላቸው።
\v 19 “እኔም እጁን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንዲችል ይህን ሥልጣን ስጡኝ” አላቸው።
\s5
\v 20 ነገር ግን ጴጥሮስ እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።
\v 21 ልብህ ለእግዚአብሔር የቀና አይደለምና በዚህ ጉዳይ ውስጥ ዕድል ወይም ድርሻ የለህም።
\v 22 እንግዲህ ለዚህ ክፋትህ ንስሓ ግባ፤ ምናልባትም ለልብህ ዐሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ጌታን ለምን።
\v 23 በኀጢአት እስራትና በመራርነት መርዝ ውስጥ እንዳለህ አያለሁና።”
\s5
\v 24 ሲሞንም መልሶ፣ “ከተናገራችኋቸው አንዱም በእኔ ላይ እንዳይፈጸም ወደ ጌታ ጸልዩልኝ” አላቸው።
\s5
\v 25 ጴጥሮስና ዮሐንስ ከመሰከሩና የጌታን ቃል ከተናገሩ በኋላ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ በመንገድም ለብዙ የሰማርያ መንደሮች ወንጌልን ሰበኩ።
\s5
\v 26 የጌታ መልአክ ፊልጶስን፣ “ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ተነሥና ሂድ” አለው። (ይህ መንገድ በበረሓ ውስጥ ነው።)
\v 27 እርሱም ተነሣና ሄደ። እነሆ፣ በኢትዮጵያውያን ንግሥት በሕንደኬ ሥር ትልቅ ሥልጣን የነበረው አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ነበረ። ሰውዬው በንግሥቲቱ ንብረት ሁሉ ላይ ኀላፊነት ነበረው። ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር።
\v 28 ከኢየሩሳሌም በመመለስ ላይ ሳለ፣ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ትንቢተ ኢሳይያስን እያነበበ ነበር።
\s5
\v 29 መንፈስ ፊልጶስን፣ “ሂድ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው።
\v 30 ፊልጶስ ወደ ጃንደረባው ሮጠ፣ ትንቢተ ኢሳይያስንም ሲያነብ ሰማው፤ “የምታነበውን ትረዳዋለህ?” አለው።
\v 31 ኢትዮጵያዊውም፣ “የሚመራኝ ከሌለ እንዴት ልረዳው እችላለሁ?” አለው። ወደ ሠረገላው እንዲወጣና ዐብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው።
\s5
\v 32 ኢትዮጵያዊው ያነበው የነበረ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይህ ነው፦ “እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ፤ በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል ጠቦት፣ አፉን አልከፈተም፤
\v 33 በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ትውልዱን ማን ይናገራል? ሕይወቱ ከምድር ተወግዶአልና።”
\s5
\v 34 ጃንደረባው ፊልጶስን፣ “እባክህ ነቢዩ ስለ ማን ነው የሚናገረው? ስለ ራሱ ወይስ ስለ ሌላ ነው?” አለው።
\v 35 ፊልጶስም መናገር ጀመረ፤ ከዚህም ከኢሳይያስ መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ሰበከው።
\s5
\v 36 እየሄዱ ሳሉ ውሃ አለበት ዘንድ ደረሱ፤ ጃንደረባው፣ “ተመልከት፣ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ ምን ይከለክለኛል?” አለ።
\v 37 ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ፣ መጠመቅ ትችላለህ” አለ። ኢትዮጵያዊውም መልሶ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ” አለ።
\v 38 ኢትዮጵያዊው ሠረገላው እንዲቆም አዘዘና፣ ፊልጶስም ጃንደረባውም ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም አጠመቀው።
\s5
\v 39 ከውሃው ውስጥ ሲወጡ፣ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ከዚያ ወዲያ አላየውም፤ ደስ ብሎትም ጕዞውን ቀጠለ።
\v 40 ነገር ግን ፊልጶስ በአዛጦን ታየ። በዚያ አገር ውስጥ በማለፍ ቂሣርያ እስኪደርስ ድረስ፣ ለከተሞች ሁሉ ወንጌልን ሰበከ።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ሳውል ግን በጌታ ደቀ መዛሙርት ላይ ለግድያም እንኳ እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደ፤
\v 2 የጌታን መንገድ ከሚከተሉት ወንዶችም ሆነ ሴቶች ቢያገኝ፣ ወደ ኢየሩሳሌም አስሮ እንዲያመጣቸው፣ ለምኵራቦች ደብዳቤ እንዲሰጠውም ሊቀ ካህናቱን ጠየቀ።
\s5
\v 3 እየሄደ ሳለ ደማስቆ አጠገብ ሲደርስ፣ በድንገት ከሰማይ ብርሃን በዙሪያው በራበት፤
\v 4 በምድር ላይ ወደቀ፤ “ሳውል፣ ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ” የሚል ድምፅ ሰማ።
\s5
\v 5 ሳውልም፣ "ጌታ ሆይ፣ ማን ነህ?" ብሎ መለሰ፤ ጌታም፣ “አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ፤
\v 6 ነገር ግን ተነሥተህ ወደ ከተማው ግባ፤ ማድረግ ያለብህም ይነገርሃል” አለ።
\v 7 ከዚያም ከሳውል ጋር የተጓዙት ሰዎች ድምፁን እየሰሙ፣ ማንንም ግን ሳያዩና ሳይነጋገሩ ቆሙ።
\s5
\v 8 ሳውል ከወደቀበት ተነሣ፤ ዐይኑን ሲከፍትም ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህም በእጅ እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት።
\v 9 ሦስት ቀን ዕውር ሆኖ ቆየ፤ አልበላም አልጠጣምም።
\s5
\v 10 በዚያ ጊዜ ሐናንያ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር በደማስቆ ነበር፤ ጌታም ለእርሱ በራእይ፣ “ሐናንያ” አለው። እርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ እነሆኝ” አለ።
\v 11 ጌታም መልሶ እንዲህ አለው፤ “ተነሥና ቀጥተኛ ወደሚባለው ጎዳና ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚባል የጠርሴስ ሰውን ፈልግ፤ እርሱ እዚያ እየጸለየ ነውና፤
\v 12 እርሱ እንዲያይ ሐናንያ የሚባል ሰው ሲገባና በእርሱ ላይ እጁን ሲጭንበት በራእይ አይቶአል።”
\s5
\v 13 ሐናንያም መልሶ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፣ ስለዚህ ሰው በኢየሩሳሌም ባሉት ሕዝብህ ላይ ምን ያህል ክፋት እንደ ፈጸመባቸው ከብዙዎች ሰምቻለሁ።
\v 14 ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከሊቀ ካህናቱ ሥልጣን ተቀብሎአል።”
\v 15 ጌታ ግን መልሶ እንዲህ አለው፤ “ሂድ፤ እርሱ በአሕዛብ፣ በነገሥታትና በእስራኤል ልጆች ፊት ስሜን ለመሸከም የተመረጠ ዕቃየ ነውና፤
\v 16 ስለ ስሜ ሲል ምን ያህል መከራ መቀበል እንዳለበትም አሳየዋለሁና።
\s5
\v 17 ስለዚህ ሐናንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁን በሳውል ላይ በመጫንም፣ “ወንድሜ ሳውል ሆይ፣ ስትመጣ በመንገድ ላይ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ እንድታይና መንፈስ ቅዱስን እንድትሞላ ወዳንተ ልኮኛል።”
\v 18 ወዲያው እንደ ቅርፊት ያለ ነገር ከሳውል ዐይን ወደቀ፤ ማየትም ጀመረ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፤
\v 19 በላ፣ በረታም። ሳውል በደማስቆ ውስጥ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ብዙ ቀን ቆየ።
\s5
\v 20 ወዲያውም ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በምኵራብ ውስጥ ዐወጀ።
\v 21 የሰሙትም ሁሉ በመደነቅ እንዲህ አሉ፤ “ይህ ሰው በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ያጠፋው አይደለምን? የመጣውም አስሮ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊያቀርባቸው ነው።”
\v 22 ሳውል ግን ለመስበክ በረታ፣ በደማስቆ ይኖሩ የነበሩ አይሁድንም ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን በማረጋገጥ ግራ አጋባቸው።
\s5
\v 23 ከብዙ ቀን በኋላ፣ አይሁድ ሊገድሉት ዐሰቡ።
\v 24 ሳውል ግን ዐሳባቸውን ዐወቀባቸው። ሊገድሉት የከተማይቱን በሮች ቀንም ሌሊትም ይጠብቁ ነበር።
\v 25 ደቀ መዛሙርቱ ግን በግድግዳው በኩል በቅርጫት አወረዱት።
\s5
\v 26 ሳውል ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ በመጣ ጊዜ፣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ለመገናኘት ሞከረ፤ ነገር ግን ደቀ መዝሙር መሆኑን በመጠራጠር ሁሉም ፈሩት።
\v 27 ይሁን እንጂ፣ በርናባስ ወስዶ ወደ ደቀ መዛሙርቱ አቀረበው። ሳውል ጌታን በመንገድ ላይ እንዴት እንዳየው፣ ጌታም እንደ ተናገረው፣ በኢየሱስ ስም ደማስቆ ውስጥ በድፍረት እንዴት እንደ ሰበከም ነገራቸው።
\s5
\v 28 ሳውል ኢየሩሳሌም ውስጥ ሲገባና ከዚያም ሲወጣ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተገናኘ። በጌታ ኢየሱስ ስም በድፍረት ተናገረ፤
\v 29 ከግሪክ አይሁድ ጋርም ተከራከረ፤ ሊገድሉት ሙከራ ማድረጋቸውን ግን አላቋረጡም።
\v 30 ወንድሞች ስለዚህ ባወቁ ጊዜ፣ ወደ ቂሣርያ አውርደው ወደ ጠርሴስ ላኩት።
\s5
\v 31 ከዚያም በኋላ የይሁዳ ሁሉ፣ የገሊላና የሰማርያ ቤተ ክርስቲያን ሰላም ነበራት፣ ታነጸችም፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት ቤተ ክርስቲያን በቍጥር አደገች።
\v 32 ጴጥሮስም በየቦታው ሲዘዋወር፣ በልዳ ከተማ ወደሚኖሩ ቅዱሳንም ወረደ።
\s5
\v 33 እዚያም፣ ሽባ በመሆኑ ስምንት ዓመት የአልጋ ቊራኛ የነበረን ኤንያ የሚባለውን አንድ ሰው አገኘ።
\v 34 ጴጥሮስ፣ “ኤንያ ሆይ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሥና ዐልጋህን አንጥፍ” አለው። ወዲያውም ተነሣ።
\v 35 በልዳና በሰሮና የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሰውየውን አዩትና ወደ ጌታ ተመለሱ።
\s5
\v 36 በኢዮጴም ጣቢታ የምትባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበረች፤ የስሟ ትርጕም “ዶርቃ” ማለት ነው። ይች ሴት በመልካም ምግባርና ለድኾች በምታደርጋቸው የርኅራኄ ሥራዎች የተሞላች ነበረች።
\v 37 በዚያም ወቅት ታመመችና ሞተች፤ ዐጥበውም ሰገነት ላይ አስቀመጧት።
\s5
\v 38 ልዳ በኢዮጴ አጠገብ በመሆኑና ደቀ መዛሙርቱም የጴጥሮስን በዚያ መኖር ስለ ሰሙ፣ “ሳትዘገይ ወደ እኛ ና” ብለው በመለመን ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ።
\v 39 ጴጥሮስም ተነሣና ከተላኩት ጋር ሄደ። እዚያ ሲደርስ፣ ወደ ሰገነቱ አወጡት። መበለታቱም ሁሉ ዶርቃ ከእነርሱ ጋር ሳለች ትለብሳቸው የነበሩትን ቀሚሶችና ልብሶች እያሳዩትና እያለቀሱ በአጠገቡ ቆሙ።
\s5
\v 40 ጴጥሮስ ሁሉንም ከክፍሉ አስወጣቸውና ተንበርክኮ ጸለየ፤ ከዚያም ወደ አስከሬኑ በመዞር፣ “ጣቢታ ሆይ፣ ተነሺ” አለ። ዐይኖቿን ከፈተች፤ ጴጥሮስንም ስታየው ተነሥታ ተቀመጠች።
\v 41 ጴጥሮስም እጇን ይዞ አነሣት፤ አማኞችንና መበለታቱን ጠርቶም በሕይወት እንዳለች ሰጣቸው።
\v 42 ይህ ጉዳይ በመላው ኢዮጴ የታወቀ ሆነ፤ ብዙ ሰዎችም በጌታ አመኑ።
\v 43 ጴጥሮስ በኢዮጴ ቍርበት ፋቂ ከነበረ ስምዖን ከሚባል ሰው ጋር ብዙ ቀን ቆየ።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 በቂሣርያ ከተማ ውስጥ የኢጣሊቄ ክፍለ ሰራዊት በሚባል የመቶ አለቃ የሆነ ቆርኔሌዎስ የሚባል ሰው ነበረ።
\v 2 እርሱም መንፈሳዊ፣ ከቤተ ሰቡ ጋር እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ ለአይሁድ ብዙ ገንዘብ የሚሰጥና ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር የሚጸልይ ሰው ነበረ።
\s5
\v 3 ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲመጣ በራእይ በግልጽ ታየው። መልአኩ፣ “ቆርኔሌዎስ!” አለው።
\v 4 ቆርኔሌዎስ መልአኩን አተኵሮ ተመለከተውና ፈርቶ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፣ ይህ ምንድን ነው?” መልአኩም መልሶ፣ “ጸሎትህና ምጽዋትህ በመታሰቢያነት ወደ እግዚአብሔር ደርሶአል።
\v 5 ጴጥሮስም ተብሎ የሚጠራውን ስምዖን የሚባለውን ሰውየ ለማስመጣት አሁን ወደ ኢዮጴ ከተማ ሁለት ሰዎችን ላክ።
\v 6 ሰውየው ቤቱ በባሕሩ አጠገብ ከሚገኝ ስምዖን ከሚባለው ከቆዳ ፋቂው ጋር አለ” አለው።
\s5
\v 7 ያነጋግረው የነበረው መልአክ እንደ ሄደ፣ ቆርኔሌዎስ ከሚያገለግሉት ወታደሮች መካከል እግዚአብሔርን ያመልክ የነበረ አንድ ወታደርንና ከቤት አሽከሮቹ ሁለቱን ጠራ።
\v 8 ቆርኔሌዎስ የሆነውን ሁሉ ነግሮአቸው ወደ ኢዮጴ ላካቸው።
\s5
\v 9 በሚቀጥለው ቀን ስድስት ሰዓት አካባቢ፣ በጕዞ ላይ ሳሉና ወደ ከተማዋ ሲቃረቡ፣ ጴጥሮስ ሊጸልይ ወደ ሰገነቱ ወጣ።
\v 10 ራበውና አንዳች ነገር ለመብላት ፈለገ፤ ነገር ግን ሰዎች ምግብ በማዘጋጀት ላይ ሳሉ፣ በተመስጦ ውስጥ ገባ፤
\v 11 ሰማይ ተከፍቶ፣ ትልቅ ሸማ የሚመስል አንድ መያዣ በአራቱ ጠርዞቹ ተይዞ ወደ ምድር ሲወርድም አየ።
\v 12 በውስጡም አራት እግር ያላቸው እንስሳት ሁሉና በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራን፣ የሰማይ ወፎችም ነበሩበት።
\s5
\v 13 “ጴጥሮስ ሆይ፣ ተነሥና ዐርደህ ብላ” የሚል ድምፅ ለጴጥሮስ መጣ።
\v 14 ጴጥሮስም፣ “ጌታ ሆይ፣ አይሆንም፤ ምክንያቱም እኔ ርኩስና አስጸያፊ የሆነ ምንም ነገር ፈጽሞ በልቼ አላውቅም” አለ።
\v 15 እንደገናም ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ጴጥሮስ መጣ፤ “እግዚአብሔር ቅዱስ ያደረገውን ርኩስ ብለህ አትጥራው” የሚል ድምፅ።
\v 16 ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፤ ከዚያም መያዣው ወዲያው ወደ ሰማይ ተመልሶ ተወሰደ።
\s5
\v 17 ጴጥሮስ ያየው ራእይ ምን ትርጕም ሊኖረው እንደሚችል በጣም ግራ ገብቶት ሳለ፣ ወደ ቤት የሚያስሄደውን መንገድ ጠይቀው ካገኙ በኋላ እነሆ፣ ቆርኔሌዎስ የላካቸው ሰዎች በበሩ ፊት ለፊት ቆሙ።
\v 18 ድምፃቸውን ከፍ በማድረግም ጴጥሮስ የሚባለው ስምዖን በዚያ መኖሩንና አለመኖሩን ጠየቁ።
\s5
\v 19 ጴጥሮስ ስለ ራእዩ በማሰብ ላይ ሳለ፣ መንፈስ ቅዱስ ጴጥሮስን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፣ ሦስት ሰዎች ይፈልጉሃል።
\v 20 ተነሥና ውረድ፤ ከእነርሱም ጋር ሂድ። ዐብረሃቸው ለመሄድ አትፍራ፤ ምክንያቱም የላክኋቸው እኔ ነኝ።”
\v 21 ስለዚህም ጴጥሮስ ወደ ሰዎቹ ወርዶ፣ “የምትፈልጉት ሰው እኔ ነኝ። የመጣችሁት ለምንድን ነው?” አላቸው።
\s5
\v 22 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "እግዚአብሔርን የሚያመልክ፣ በአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ዘንድም የተመሰገነ ቆርኔሌዎስ የሚባል ጻድቅ ሰው፣ ወደ ቤቱ ሰው ልኮ እንዲያስመጣህ የእግዚአብሔር መልአክ ነገረው፤ እንዲህ ያደረገውም ከአንተ መልእክትን መስማት እንዲችል ነው።”
\v 23 ጴጥሮስም እንዲገቡና ከእርሱና ዐብረውት ከነበሩ ሰዎች ጋር እንዲቈዩ በእንግድነት ተቀበላቸው። በማግስቱ ጧት ጴጥሮስ ተነሣና ከእነርሱ ጋር ሄደ፤ በኢዮጴ ከነበሩት ወንድሞችም አንዳንዶቹ ዐብረውት ሄዱ።
\s5
\v 24 በሚቀጥለው ቀን ቂሣርያ ደረሱ። ቆርኔሌዎስ እየጠበቃቸው ነበር፤ ዘመዶቹንና የቅርብ ወዳጆቹንም ጠርቶ እንዲሰበሰቡ አደረገ።
\s5
\v 25 ጴጥሮስ ሲገባ፣ ቆርኔሌዎስ አግኝቶት እግሩ ላይ ወድቆ ሰገደለት።
\v 26 ነገር ግን ጴጥሮስ አነሣውና፣ “ተነሥ ቁም፤ እኔ ራሴም ሰው ነኝ” አለው።
\s5
\v 27 ጴጥሮስ ከቆርኔሌዎስ ጋር እየተነጋገረ ወደ ውስጥ ሲገባ፣ የተሰበሰቡ ብዙ ሰዎችን አገኘ።
\v 28 እንዲህም አላቸው፤ "አይሁዳዊ የሆነ ሰው ከሌላ ሕዝብ ከሆነ ጋር መገናኘት ወይም እርሱን መጎብኘት በሕግ እንደማይፈቀድለት እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ። ነገር ግን እግዚአብሔር ማንንም ሰው ርኩስ ወይም አስጸያፊ ብዬ መጥራት እንደማይገባኝ ለእኔ አሳይቶኛል።
\v 29 ሲላክብኝ ሳልከራከር የመጣሁት ከዚህ የተነሣ ነው። ስለዚህ ለምን እንደ ላካችሁብኝ እጠይቃችኋለሁ።"
\s5
\v 30 ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለ፤ “ከአራት ቀን በፊት ልክ በዚህ ሰዓት በዘጠኝ ሰዓት በቤቴ ውስጥ እጸልይ ነበር፤ እነሆም ነጭ ልብስ ለብሶ ፊት ለፊቴ ቆመና፣
\v 31 ‘ቆርኔሌዎስ ሆይ፣ ጸሎትህ በእግዚአብሔር ዘንድ ተሰምቶአል፤ ምጽዋትህም መታሰቢያ ሆኖልሃል።
\v 32 ስለዚህ ወደ ኢዮጴ ሰው ላክና ጴጥሮስም የሚባለውን ስምዖንን ወደ አንተ ጠርተህ አስመጣ። እርሱ በቆዳ ፋቂው በስምዖን ቤት በባሕር አጠገብ ተቀምጦአል’ አለኝ።
\v 33 ስለዚህ ወዲያው ላክሁብህ። አሁን መምጣትህ መልካም አደረግህ። አሁን እንግዲህ እኛ ሁላችን እግዚአብሔር እንድትናገር ያዘዘህን ሁሉ ለመስማት በእግዚአብሔር ፊት እንገኛለን።"
\s5
\v 34 ጴጥሮስም እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ በእውነት ተገንዝቤአለሁ።
\v 35 ይልቁን በማንኛውም ሕዝብ ውስጥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የጽድቅ ተግባራትንም የሚፈጽም ሁሉ በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።
\s5
\v 36 እግዚአብሔር በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የሰላምን የምሥራች ባወጀበት ጊዜ፣ ወደ እስራኤል ሕዝብ የላከውን መልእክት ታውቃላችሁ፦
\v 37 ዮሐንስ ካወጀው ጥምቀት በኋላ፣ በገሊላ በመጀመር በይሁዳ ሁሉ የታዩትን የተፈጸሙ ሁነቶችን እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ፤
\v 38 ሁነቶቹም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስና በኀይል እንዴት እንደ ቀባው የናዝሬቱን ኢየሱስን የሚመለከቱ ናቸው። ኢየሱስ መልካም እያደረገና ለዲያብሎስ የተገዙትን እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና።
\s5
\v 39 በዕንጨት ላይ ሰቅለው የገደሉት ይህ ኢየሱስ ከአይሁድ አገርም በኢየሩሳሌምም ለፈጸማቸው ተግባራት ሁሉ እኛ ምስክሮች ነን።
\v 40 ይህን ሰው እግዚአብሔር በሦስተኛው ቀን አስነሣው፤ እንዲገለጥም አደረገው፤
\v 41 ይኸውም እግዚአብሔር አስቀድሞ መርጦአቸው ለነበሩ ምስክሮች እንጂ፣ ለሕዝቡ ሁሉ አይደለም፦ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ዐብረነው የበላንና የጠጣን እኛው ራሳችን ነን።
\s5
\v 42 ለሕዝቡ እንድንሰብክና በሕያዋንና በሙታን ላይ እንዲፈርድ፣ እግዚአብሔር የመረጠው ይህ እንደ ሆነ እንድንመሰክር አዘዘን።
\v 43 በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኀጢአትን ይቅርታ እንዲቀበል ነቢያት ሁሉ የሚመሰክሩት ስለ እርሱ ነው።”
\s5
\v 44 ጴጥሮስ እነዚህን ነገሮች ገና እየተናገረ ሳለ፣ መልእክቱን በሚሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው።
\v 45 ከተገረዙት ወገን የሆኑ አማኞች፦ ከጴጥሮስ ጋር የመጡትም ሁሉ ተደነቁ፤ ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ በአሕዛብም ላይ ወርዶ ነበር።
\s5
\v 46 እነዚህ አሕዛብ በሌሎች ቋንቋዎች ሲናገሩና እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ ሰምተዋቸዋልና። ከዚያም በኋላ ጴጥሮስ መልሶ፣
\v 47 “እንደ እኛ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉ እነዚህ ሰዎች እንዳይጠመቁ ማን ውሃ ሊከለክላቸው ይችላል?” አለ።
\v 48 በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁም አዘዛቸው። ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር ጥቂት ቀን እንዲቈይ ጴጥሮስን ለመኑት።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 ሐዋርያትና በይሁዳ የነበሩት ወንድሞች አሕዛብ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ተቀብለው እንደ ነበር ሰሙ።
\v 2 ጴጥሮስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቶ በነበረ ጊዜ፣ ከመገረዝ ወገን የነበሩት ነቀፉት፤
\v 3 “ካልተገረዙ ወንዶች ጋር ተባብረሃል፣ አብረሃቸውም በልተሃል!” አሉት።
\s5
\v 4 ጴጥሮስ ግን እንዲህ ብሎ ጉዳዩን በዝርዝር ያብራራላቸው ጀመር፤
\v 5 እኔ በኢዮጴ ከተማ እጸልይ ነበር፤ በተመስጦም አራት ማዕዘን ያለው ታላቅ ሸማ የመሰለ ዕቃ መያዣ ከሰማይ ሲወርድ ራእይ ዐየሁ፤ ወደ እኔ ወረደ፣
\v 6 ትኵር ብዬ ተመለክትሁትና ስለ እርሱ ዐሰብሁ። አራት እግር ያላቸው የምድር እንስሳትን፣ አራዊትን፣ የሚሳቡ ፍጥረታትን፣ የሰማይ አዕዋፍንም ዐየሁ።
\s5
\v 7 በዚያን ጊዜ አንድ ድምፅ፣ “ጴጥሮስ ሆይ፣ ተነሣ፣ አርደህም ብላ!” ሲለኝ ሰማሁ።
\v 8 “ጌታ ሆይ፣ አይሆንም፣ ምክንያቱም ጸያፍ ወይም ርኩስ የሆነ ምንም ነገር ከቶ ወደ አፌ ገብቶ አያውቅም” አልሁ።
\v 9 ነገር ግን ድምፁ ዳግመኛ ከሰማይ፣ “እግዚአብሔር ንጹሕ ነው ያለውን አንተ ርኩስ ብለህ አትጥራው” ብሎ መለሰ።
\v 10 ይህም ሦስት ጊዜ ሆነ፤ ከዚያም ሁሉም ነገር እንደ ገና ወደ ሰማይ ተወሰደ።
\s5
\v 11 እነሆ፣ ወዲያውኑ እኛ በነበርንበት ቤት ፊት ለፊት ሦስት ሰዎች ቆመው ነበር፤ እነርሱም ከቂሣርያ ወደ እኔ የተላኩ ናቸው።
\v 12 መንፈስም ከእነርሱ ጋር እንድሄድ፣ ስለ እነርሱም ልዩነት እንዳላደርግ አዘዘኝ። እነዚህ ስድስት ወንድሞች አብረውኝ ሄዱ፤ ወደ ሰውዬውም ቤት ገባን።
\v 13 እርሱም መልአክ በቤቱ ቆሞ እንዳየና እንዲህ እንዳለውም ነገረን፤ “ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ላክና ሌላው ስሙ ጴጥሮስ የሆነውን፣ ስምዖንን አስመጣ።
\v 14 አንተና ቤተ ሰቦችህ ሁሉ የምትድኑበትን መልእክት ይነግርሃል።”
\s5
\v 15 ለእነርሱ መናገር እንደ ጀመረና ልክ በመጀመሪያ በእኛ ላይ እንደ ሆነው፣ መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ ወረደ።
\v 16 “ዮሐንስ በእርግጥ በውሃ አጥምቆ ነበር፤ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ” ብሎ እንደ ተናገረ፣ የጌታን ቃሎች አስታወስሁ።
\s5
\v 17 እኛ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመንን ጊዜ እንደ ሰጠን ያለ ስጦታ እግዚአብሔር ለእነርሱ ከሰጣቸው እንግዲያ፣ እግዚአብሔርን እቃወም ዘንድ እኔ ማን ነበርሁ?”
\v 18 እነርሱ እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ መልስ አልሰጡም፤ ነገር ግን እግዚአብሔርን አመስግነው፣ “እግዚአብሔር ለአሕዛብ ለሕይወት የሚሆን ንስሓን ደግሞ ሰጥቷቸዋል” አሉ።
\s5
\v 19 ስለዚህ በእስጢፋኖስ መሞት የተጀመረው ሥቃይ ከኢየሩሳሌም የበተናቸው እነዚህ አማኞች እስከ ፊንቄ፣ ቆጵሮስና አንጾኪያ ድረስ ሄዱ። ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን መልእክት ለአይሁድ ብቻ እንጂ ለሌላ ለማንም አልተናገሩም።
\v 20 ነገር ግን ከቆጵሮስና ከቀሬና የነበሩ ሰዎች አንዳንዶቹ ወደ አንጾኪያ መጥተው ለግሪኮች ተናገሩ፤ ጌታ ኢየሱስንም ሰበኩላቸው።
\v 21 የጌታም እጅ ከእነርሱ ጋር ነበረ፤ በቍጥ ብዛት ያላቸው ሰዎች አምነው ወደ ጌታ ዘወር አሉ።
\s5
\v 22 ስለ እነርሱ ወሬ በኢየሩሳሌም ባለችው ጉባኤ ተሰማ፤ በርናባስንም እስከ አንጾኪያ ላኩት።
\v 23 እርሱም መጥቶ የእግዚአብሔርን ስጦታ ባየ ጊዜ፣ ደስ አለው። ከሙሉ ልባቸው ከጌታ ጋር እንዲኖሩ ሁላቸውንም አበረታታቸው።
\v 24 ምክንያቱም እርሱ መንፈስ ቅዱስና እምነት የሞላበት በጎ ሰው ነበር፤ ብዙ ሕዝብም ወደ ጌታ ተጨመሩ።
\s5
\v 25 ከዚያም በርናባስ ሳውልን ሊፈልግ ወደ ጠርሴስ ወጣ።
\v 26 ባገኘውም ጊዜ፣ ወደ አንጾኪያ አመጣው። እንዲህም ሆነ፣ አንድ ዓመት ሙሉ በቤተ ክርስቲያን አብረው ተሰበሰቡ፣ ብዙ ሕዝብንም አስተማሩ። ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያ በአንጾኪያ ክርስቲያን ተባሉ።
\s5
\v 27 በእነዚያ ቀናትም አንዳንድ ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ።
\v 28 ከእነርሱ አንዱ አጋቦስ የተባለው፣ ተነሥቶ ቆመና በመላው ዓለም ላይ ታላቅ ራብ እንደሚሆን በመንፈስ አመለከተ። ይህም በቀላውዴዎስ ዘመን ሆነ።
\s5
\v 29 ስለ ሆነም፣ ደቀ መዛሙርቱ እያንዳንዳቸው እንደ ዐቅማቸው በይሁዳ ላሉት ወንድሞች እርዳታ ለመላክ ወሰኑ።
\v 30 ይህንም አደረጉ፤ በበርናባስና በሳውል እጅ ለሽማግሌዎቹ ገንዘብ ላኩ።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ ንጉሡ ሄሮድስ ሊያሠቃያቸው ከቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን ያዛቸው።
\v 2 የዮሐንስን ወንድም ያዕቆብን በሰይፍ ገደለው።
\s5
\v 3 ይህ አይሁድን ደስ እንዳሰኛቸው ካየ በኋላ፣ ጴጥሮስንም ያዘው። ይህ የሆነው በቂጣ በዓል ጊዜ ነበር።
\v 4 ከያዘውም በኋላ ወደ ወኅኒ አገባው፤ እንዲጠብቁትም እያንዳንዳቸው አራት ወታደሮች ያሏቸው ቡድኖችን መደበ፤ ከፋሲካ በኋላ ወደ ሕዝቡ ሊያቀርበው ዐስቦ ነበር።
\s5
\v 5 ጴጥሮስም በወኅኒው ይጠበቅ ነበር፤ ነገር ግን ስለ እርሱ ጉባኤው ወደ እግዚአብሔር አጥብቆ ይጸልይ ነበር።
\v 6 ሄሮድስ ሊያወጣው ባሰበበት በዚያ ሌሊት፣ ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለቶች ታስሮ በሩን በሚጠብቁ ሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር።
\s5
\v 7 እነሆም የጌታ መልአክ በድንገት በአጠገቡ ታየ፣ በክፍሉም ብርሃን በራ። መልአኩ የጴጥሮስን ጎን መትቶ ቀሰቀሰውና፣ “ፈጥነህ ተነሥ” አለው። በዚያን ጊዜ ሰንሰለቶቹ ከእጆቹ ወደቁ።
\v 8 መልአኩ ጴጥሮስን፣ “ልብስህን ልበስ ጫማህንም አድርግ” አለው። ጴጥሮስም እንዲሁ አደረገ። መልአኩ፣ “መደረቢያህን ልበስና ተከተለኝ” አለው።
\s5
\v 9 ጴጥሮስም መልአኩን ተከትሎ ወደ ውጭ ወጣ። መልአኩ ያደረገው ነገር በእውን እንደ ሆነ ጴጥሮስ አላወቀም። ራእይ ያየ መሰለው።
\v 10 የመጀመሪያውንና ሁለተኛውን ዘብ እንዳለፉ፣ ወደ ከተማይቱ ወደሚያወጣው የብረት በር ደረሱ፤ እርሱም ዐውቆ ተከፈተላቸው። እነርሱም ወጥተው በአንድ መንገድ በኩል ወረዱ፤ መልአኩም ወዲያውኑ ተለየው።
\s5
\v 11 ጴጥሮስም ራሱን ሲያውቅ፣ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅ፣ የአይሁድ ሕዝብም ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንዳዳነኝ አሁን ዐወቅሁ” አለ።
\v 12 ጴጥሮስ ይህን ከተገነዘበ በኋላ፣ ማርቆስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ዮሐንስ እናት ቤት መጣ፤ በዚያ ብዙ ምእመናን ተሰብስበው እየጸለዩ ነበር።
\s5
\v 13 የደጁን በር ባንኳኳ ጊዜ፣ ሮዴ የሚሏት የቤት ሠራተኛ ልትከፍትለት መጣች።
\v 14 የጴጥሮስን ድምፅ ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሣ በሩን መክፈት አቃታት፤ ይልቁን ሮጣ ወደ ቤት ገባች፤ ጴጥሮስ ከበሩ ውጭ መቆሙን ተናገረች።
\v 15 ምእመናኑም፣ “ዐብደሻል” አሏት። እርሷ ግን እንዲሁ ነው ብላ በዐሳብዋ ጸናች። እነርሱም፣ “የእርሱ መልአክ ነው” አሉ።
\s5
\v 16 ጴጥሮስ ግን ማንኳኳቱን ቀጠለ፤ በሩን በከፈቱ ጊዜ፣ ዐይተውት ተደነቁ።
\v 17 ጴጥሮስ ዝም እንዲሉ በእጁ ምልክት ሰጣቸው፤ ጌታ ከወኅኒ እንዴት እንዳወጣውም ነገራቸው። “እነዚህን ነገሮች ለያዕቆብና ለወንድሞች ንገሩ” አላቸው። ከዚያም ቤት ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።
\s5
\v 18 በማግስቱም፣ ጴጥሮስን በሚመለከት ስለ ተከሠተው ነገር በወታደሮች መካከል መደናገጥ ሆነ።
\v 19 ሄሮድስ ጴጥሮስን ፈልጎ ሊያገኘው አልቻለም፤ ጠባቂዎችን መርምሮ እንዲገደሉ አዘዘ። ከዚያም ጴጥሮስ ከይሁዳ ወደ ቂሣርያ ወርዶ በዚያ ተቀመጠ።
\s5
\v 20 ሄሮድስም በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ላይ እጅግ ተቈጥሮ ነበር። የጢሮስና የሲዶና ሰዎች ተሰብስበው ወደ እርሱ ሄዱ። እንዲረዳቸው የንጉሡን ረዳት ብላስጦስን እሺ አሰኙት። ከዚያም ዕርቀ ሰላም እንዲወርድ ጠየቁ፤ ምክንያቱም አገራቸው ከንጉሡ አገር ምግብ ያገኝ ነበር።
\v 21 በቀጠሮ ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥት ለብሶ በዙፋን ላይ ተቀመጠና ንግግር አደረገላቸው።
\s5
\v 22 ሕዝቡም፣ “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ፣ የሰው አይደለም!” ብለው ጮኹ።
\v 23 ሄሮድስ ለእግዚአብሔር ክብር ስላልሰጠ፣ ወዲያውኑ የጌታ መልአክ ቀሠፈው፤ በትል ተበልቶም ሞተ።
\s5
\v 24 የእግዚአብሔር ቃል ግን እያደገና እየሰፋ ሄደ።
\v 25 በርናባስና ሳውል ለኢየሩሳሌም የነበራቸውን ተልእኮ ከፈጸሙ በኋላ፣ ተመለሱ፤ ማርቆስ የተባለውንም ዮሐንስን ይዘው ሄዱ።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በአንጾኪያም ባለችው ጉባኤ አንዳንድ ነቢያትና መምህራን ነበሩ። እነርሱም በርናባስ፣ ኔጌር የተባለው ስምዖን፣ የቀሬናው ወንድሙ ምናሔ፣ ሳውልም ነበሩ።
\v 2 ጌታን እያመለኩና እየጾሙ እያሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ “ለጠራኋቸው ሥራ በርናባስንና ሳውልን ለዩልኝ” አለ።
\v 3 ጉባኤው ከጾመ፣ ከጸለየና እጅ ከጫነም በኋላ አሰናበታቸው።
\s5
\v 4 በርናባስና ሳውልም ለመንፈስ ቅዱስ ታዘዙና ወደ ሴሌውቅያ ወረዱ፤ ከዚያም በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ሄዱ።
\v 5 በስልማና ከተማ በነበሩ ጊዜም፣ በአይሁድ ምኵራቦች የእግዚአብሔርን ቃል ሰበኩ። ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ሊረዳቸው አብሯቸው ነበር።
\s5
\v 6 በደሴቲቱም ሁሉ እስከ ጳፉ በሄዱ ጊዜ፣ ስሙ በርያሱስ የተባለ፣ አንድ አይሁዳዊ የሐሰት ነቢይና አስማተኛ አገኙ።
\v 7 ይህ አስማተኛ አስተዋይ ሰው ከነበረው ሰርግዮስ ጳውሎስ ከተባለው አገረ ገዥ ጋር ተባበረ። ይህ ሰው የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ስለ ፈለገ፣ በርናባስናን ሳውልን ጠራ።
\v 8 ነገር ግን፣ “አስማተኛው” ኤልማስ ስሙ ሲተረጎም እንዲሁ ነውና ተቃወማቸው፤ አገረ ገዡን ከእምነቱ ለመመለስ ሞከረ።
\s5
\v 9 ደግሞ ጳውሎስ የተባለው ሳውል ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞላ፤ ትኵር ብሎም ተመለከተውና
\v 10 እንዲህ አለው፤ “አንተ የዲያብሎስ ልጅ፣ ክፋትና ተንኮል ሁሉ የሞላብህ ነህ። የጽድቅ ሁሉ ጠላት ነህ። የቀናችውን የጌታን መንገድ ማጣመምህን አታቆምምን?
\s5
\v 11 አሁንም ተመልከት፤ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ነችና ትታወራለህ። ለጥቂት ጊዜ ፀሐይን አታይም።” ወዲያውኑ በኤልማስ ጨለማና ጭጋግ ወደቀበት፤ እጁንም ይዘው እንዲመሩት ሰዎችን እየጠየቀ ይዘዋወር ጀመር።
\v 12 አገረ ገዡ የሆነውን ካየ በኋላ፣ ስለ ኢየሱስ በቀረበው ትምህርት ስለ ተደነቀ፣ አመነ።
\s5
\v 13 ጳውሎስና ጓደኞቹም በመርከብ ከጳፉ ተነሥተው በጵንፍልያ ወዳለችው ወደ ጴርጌን መጡ። ዮሐንስ ግን ትቶአቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
\v 14 ጳውሎስና ጓደኞቹ ከጴርጌን ተጕዘው የጲስድያ ወደ ሆነችው አንጾኪያ መጡ። በዚያ በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብተው ተቀመጡ።
\v 15 ሕግና ነቢያት ከተነበቡ በኋላ፣ የምኵራብ አለቆች፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እዚህ ላሉት ሕዝብ የሚሆን የሚያበረታታ መልእክት ካላችሁ፣ ተናገሩ” በማለት መልእክት ላኩላቸው።
\s5
\v 16 ጳውሎስም ቆመና በእጁ ምልክት ሰጥቶ እንዲህ አለ፤ “የእስራኤል ሰዎችና እናንተ እግዚአብሔርን የምታከብሩ፣ ስሙ።
\v 17 የዚህ የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መርጦ በግብፅ ይኖሩ በነበሩበት ጊዜ፣ ሕዝቡን አበዛላቸው፤ በተዘረጋችም ክንድ መርቶ ከዚያ አወጣቸው።
\v 18 ለአርባ ዓመታት ገደማ በምድረ በዳ ታገሣቸው።
\s5
\v 19 በከነዓን ምድርም ሰባት ሕዝቦችን ካጠፋ በኋላ፣ ምድራቸውን ለሕዝባችን ርስት አድርጎ ሰጠ።
\v 20 እነዚህ ሁነቶች ሁሉ በአራት መቶ ሃምሳ ዓመታት ውስጥ ተፈጸሙ። ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር እስከ ነቢዩ ሳሙኤል ድረስ መሳፍንትን ሰጣቸው።
\s5
\v 21 ከዚህ በኋላ፣ ሕዝቡ ንጉሥ ይንገሥልን ብለው ጠየቁ፤ ስለሆነም፣ እግዚአብሔር ከብንያም ነገድ የሆነውን የቂስን ልጅ ሳኦልን ለአርባ ዓመታት ሰጣቸው።
\v 22 ከዚያም እግዚአብሔር እርሱን ከንጉሥነት ከሻረው በኋላ፣ ንጉሣቸው እንዲሆን ዳዊትን አስነሣ። እግዚአብሔር፣ ‘እንደ ልቤ የሆነውን የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ፤ እርሱ እኔ የምፈልገውን ሁሉ ያደርጋል’ በማለት ስለ ዳዊት ተናግሮ ነበር።
\s5
\v 23 ከዚህም ሰው ዘር እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠ አዳኝ ኢየሱስን ለእስራኤል አመጣ።
\v 24 ይህ መሆን የጀመረው ኢየሱስ ከመምጣቱ በፊት፣ ዮሐንስ መጀመሪያ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የንስሐን ጥምቀት ባወጀ ጊዜ ነው።
\v 25 ዮሐንስ ሥራውን እንደ ጨረሰ እንዲህ አለ፤ ‘ማን እንደ ሆንሁ ታስባላችሁ? እኔ እርሱ አይደለሁም። ነገር ግን ስሙ፤ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ ከእኔ በኋላ እርሱ ይመጣል።’
\s5
\v 26 ወንድሞች፣ የአብርሃም ዘር ልጆች፣ እግዚአብሔርንም የምታመልኩ ሆይ፣ የዚህ ድነት መልእክት የተላከው ለእኛ ነው።
\v 27 በኢየሩሳሌም የሚኖሩ፣ አለቆቻቸውም በእርግጥ ኢየሱስን አላወቁትም፤ በየሰንበቱ የሚነበበውን የነቢያትን ድምፅም በእውነት አልተረዱም፤ ስለ ሆነም በኢየሱስ ላይ ሞት በመፍረድ የነቢያትን ቃል ፈጸሙ።
\s5
\v 28 ምንም እንኳ በእርሱ ላይ ለሞት የሚያበቃ ምክንያት ባያገኙም፣ እንዲገድለው ጲላጦስን ለመኑት።
\v 29 ስለ እርሱ የተጻፈውን ሁሉ በፈጸሙ ጊዜም፣ ከዕንጨት ላይ አውርደው በመቃብር አኖሩት።
\s5
\v 30 እግዚአብሔር ግን ከሙታን አስነሣው።
\v 31 ከእርሱ ጋር ከገሊላ ወደ ኢየሩሳሌም የወጡት ብዙዎች ለአያሌ ቀናት ዐዩት። እነዚህ ሰዎች አሁን ለሕዝቡ የሚናገሩ የእርሱ ምስክሮች ናቸው።
\s5
\v 32 ስለ ሆነም እኛ ለአባቶቻችን ስለ ተሰጠው ተስፋ የሚናገር የምሥራች እናመጣላችኋለን፤
\v 33 ኢየሱስን ከሙታን በማስነሣት እግዚአብሔር እነዚህን ተስፋዎች ለእኛ ለልጆቻቸው ጠብቆአል። ይህም ደግሞ በሁለተኛው መዝሙር፦ ‘አንተ ልጄ ነህ፣ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’ ተብሎ የተጻፈ ነው።’
\v 34 ደግሞም ሥጋው እንዳይበሰብስ ከሙታን እንዳስነሣው፦ ‘የተቀደሰውንና እውነተኛውን የዳዊት በረከት እሰጥሃለሁ’ ብሎ ተናግሯል።
\s5
\v 35 በሌላ መዝሙርም፣ ‘ቅዱስህ መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም’ የሚለው ስለዚህ ነው።
\v 36 ዳዊትም በዘመኑ የእግዚአብሔርን ዐሳብ አገልግሎ አንቀላፋ፤ ከአባቶቹ ጋር ተቀበረ፤ መበስበስንም ዐየ።
\v 37 እግዚአብሔር ያስነሣው ኢየሱስ ግን መበስበስን አላየም።
\s5
\v 38 ስለ ሆነም ወንድሞች ሆይ፣ በዚህ ሰው በኩል የኃጢአት ይቅርታ እንደ ተሰበከላችሁ ይህ ለእናንተ የታወቀ ይሁን።
\v 39 በሙሴም ሕግ እንድትጸድቁበት ከማይቻላችሁ ሁሉ፣ በእርሱ የሚያምን ሁሉ ጸድቆአል።
\s5
\v 40 እንግዲያው ነቢያት እንዲህ ሲሉ የተናገሩለት ነገር እንዳይደርስባችሁ ተጠንቀቁ፦
\v 41 ‘እናንተ የምትንቁ፣ ተመልከቱ፤ ተደነቁ፣ ጥፉም፤ አንድ ስንኳ ቢነግራችሁ ከቶ የማታምኑትን ሥራ፣ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’”
\s5
\v 42 ጳውሎስና በርናባስ እንደ ወጡ፣ በሚቀጥለው ሰንበት ይህንኑ ቃል ደግመው እንዲናገሩ ሕዝቡ ለመኑአቸው።
\v 43 የምኵራቡ ስብሰባ እንዳበቃም፣ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ከገቡ ከሚያመልኩ ብዙዎቹ፣ በእግዚአብሔር ጸጋ እንዲጸኑ የመከሩአቸውን ጳውሎስና በርናባስን ተከተሉአቸው።
\s5
\v 44 በሚቀጥለውም ሰንበት፣ ጥቂቶች ሲቀሩ፣ መላው ከተማ የጌታን ቃል ለመስማት አንድ ላይ ተሰበሰበ።
\v 45 አይሁድ ሕዝቡን ባዩ ጊዜ፣ ቅንዓት ሞላባቸውና ጳውሎስ የተናገረውን ተቃወሙ፣ ሰደቡትም።
\s5
\v 46 ጳውሎስና በርናባስ በድፍረት ተናገሩ፤ እንዲህም አሉ፤ “የእግዚአብሔር ቃል መጀመሪያ ለእናንተ መነገሩ አስፈላጊ ነበር። ቃሉን ከራሳችሁ ስትገፉትና ለዘላለም ሕይወት የተገባችሁ እንዳልሆናችሁ ራሳችሁን ስትቈጥሩ ዐይተናችሁ፣ ወደ አሕዛብ ዘወር የምንል መሆናችንን ተመልከቱ።
\v 47 ጌታ፣ ‘እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለድነት ትሆን ዘንድ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌሃለሁ’” በማለት አዞናልና።
\s5
\v 48 አሕዛብ ይህን እንደ ሰሙ ደስ አላቸው። የጌታንም ቃል አከበሩ። ለዘላለም ሕይወት የተመረጡትም አመኑ።
\v 49 የጌታም ቃል በአገሩ ሁሉ ተስፋፋ።
\s5
\v 50 አይሁድ ግን የሚያመልኩትን ታዋቂ ሴቶችን፣ የከተማይቱን ታላላቅ ወንዶችንም ቀሰቀሱ። በጳውሎስና በበርናባስ ላይም ስደት አስነሥተው ከከተማቸው ዳርቻ ወዲያ አውጥተው ጣሏቸው።
\v 51 ጳውሎስና በርናባስ ግን የእግራቸውን ትቢያ አራገፉባቸው። ከዚያም ወደ ኢቆንዮን ከተማ ሄዱ።
\v 52 ደቀ መዛሙርቱም ደስታና መንፈስ ቅዱስ ተሞልተው ነበር።
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 በኢቆንዮንም እንዲህ ሆነ ፤ ጳውሎስና በርናባስ ወደ አይሁድ ምኵራብ አብረው ገብተው፣ ከአይሁድና ከግሪክ ብዙ ሰዎች እስኪያምኑ ድረስ ተናገሩ።
\v 2 ነገር ግን ማመን ያልፈለጉ አይሁድ የአሕዛብን ልብ በመቀስቀስ በወንድሞች ላይ በክፋት አነሣሡአቸው።
\s5
\v 3 ጳውሎስና በርናባስም በጌታ ኀይል በድፍረት እየተናገሩ ረዘም ላለ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ፤ ጌታም ስለ ጸጋው የሚነገረውን መልእክት በማስረጃ ለመደገፍ ጳውሎስና በርናባስ ምልክትና ድንቅ በእጃቸው እንዲደረግ ሰጠ።
\v 4 የከተማዋ አብዛኛው ሕዝብ ግን፣ አንዳንዱ አይሁድን በመደገፍ፣ ሌላው ደግሞ ከሐዋርያት ጋር በመቆም ተከፋፈሉ።
\s5
\v 5 አሕዛብና አይሁድ ጳውሎስንና በርናባስን እንዲያንገላቷቸውና በድንጋይም እንዲወግሯቸው አለቆቻቸውን በማሳመን ጥረት ማድረጋቸውን
\v 6 በተረዱ ጊዜ፣ ወደ ሊቃኦንያ ከተሞች፣ ወደ ልስጥራና ወደ ደርቤ፣ እንዲሁም በአካባቢው ወዳለው ስፍራ ሸሹ፤
\v 7 በዚያም ወንጌልን ይሰብኩ ነበር።
\s5
\v 8 በእግሩ መቆም የማይችልና ሽባ ከእናቱም ማሕፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ተቀምጦ ነበር።
\v 9 ይህ ሰው ጳውሎስ ሲናገር ሰማ። ጳውሎስም ዐይኑን ተከትሎ ይህን ሰው ሲመለከት ለመዳን የሚያስችል እምነት እንዳለው አየ።
\v 10 ስለዚህ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም” አለው፤ ሰውየውም ብድግ ብሎ ተነሣና ወዲያ ወዲህ ይመላለስ ጀመር።
\s5
\v 11 ሕዝቡም ጳውሎስ ያደረገውን ባዩ ጊዜ፣ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ በሊቃኦንኛ ቋንቋ፣ «አማልክት በሰዎች መልክ ወደ እኛ ወርደዋል» አሉ።
\v 12 ስለዚህም በርናባስን «ድያ» አሉት፤ ጳውሎስም ዋነኛ ተናጋሪ ስለ ነበር፣ «ሄርሜን» አሉት።
\v 13 ቤተ ጣዖቱ ከከተማው ውጭ የነበረው የድያ ካህን በሬዎችንና የአበባ ጕንጕን ይዞ ወደ ከተማይቱ በር መጣ፤ እርሱና ሕዝቡም ለእነ ጳውሎስ መሥዋዕት ሊያቀርቡላቸው ፈለጉ።
\s5
\v 14 ነገር ግን ሐዋርያቱ፣ ባርናባስና ጳውሎስ ይህን በሰሙ ጊዜ፣ ልብሳቸውን ቀደው በመጮኽ፣ ፈጥነው ወደ ሕዝቡ መካከል ገቡ፤
\v 15 እንዲህም አሉ፤ «እናንተ ሰዎች፣ ለምን እነዚህን ነገሮች ታደርጋላችሁ? እኛኮ እንደ እናንተው ዐይነት ስሜት ያለን ሰዎች ነን፤ ወደ እናንተም የመጣነው ከእነዚህ ከንቱ ነገሮች፦ ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ፈጠረ፣ ወደ ሕያው እግዚአብሔር እንድትመለሱ የምሥራች ቃል ይዘን ነው።
\v 16 እግዚአብሔር ባለፉት ዘመናት አሕዛብን ሁሉ በገዛ መንገዳቸው እንዲሄዱ ተዋቸው።
\s5
\v 17 ይሁን እንጂ፣ ራሱን ያለ ምስክር አልተወም፤ ምክንያቱም መልካም ሥራ በመሥራት የሰማይን ዝናብና ፍሬያማ ወቅቶችን ሰጥቶአችኋል፤ ልባችሁንም በምግብና በርካታ ሞልቷል።"
\v 18 ጳውሎስና በርናባስ እንደዚህ እየተናገሩም እንኳ፣ ሕዝቡ እንዳይሠዉላቸው መከልከሉ ቀላል አልነበረም።
\s5
\v 19 ይልቁንም አንዳንድ አይሁድ ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጥተው ሕዝቡን በማግባባት ጳውሎስን በድንጋይ ወገሩት፤ የሞተ ስለ መሰላቸውም በመሬት ላይ ጎትተው ከከተማው አወጡት።
\v 20 ይሁን እንጂ፣ ደቀ መዛሙርቱ አብረውት ቆመው ሳሉ፣ ተነሥቶ ወደ ከተማው ገባ። በማግስቱም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤ ሄደ።
\s5
\v 21 በዚያም ከተማ ወንጌልን ሰብከው ብዙ ደቀ መዛሙርትን ካፈሩ በኋላ፣ ወደ ልስጥራ፣ ወደ ኢቆንዮንና ወደ አንጾኪያ ተመለሱ።
\v 22 የደቀ መዛሙርቱንም ልብ እያበረቱ በእምነት እንዲጸኑ መከሯቸው። ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በብዙ መከራ ውስጥ ማለፍ እንዳለብንም ነገሯቸው።
\s5
\v 23 ጳውሎስና በርናባስ በአማኞች ጉባኤ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ከሾሙ በኋላ፣ ላመኑበት ጌታ በጾምና በጸሎት ዐደራ ሰጡአቸው።
\v 24 ከዚያም በጲስድያ አድርገው ወደ ጵንፍልያ መጡ።
\v 25 ቃሉን በጴርጌን ከተናገሩ በኋላም ወደ አጣሊያ ወረዱ።
\v 26 ለፈጸሙት ሥራ ከዚህ ቀደም ለእግዚአብሔር ጸጋ ወደ ተሰጡበት፣ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ።
\s5
\v 27 አንጾኪያ ደርሰው፣ ጉባኤውን በአንድነት ከሰበሰቡ በኋላም፣ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉና ለአሕዛብም የእምነትን በር እንዴት እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።
\v 28 በዚያም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ረጅም ጊዜ ቆዩ።
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 አንዳንድ ሰዎች ከአይሁድ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ «በሙሴ ሥርዓት መሠረት ካልተገረዛችሁ መዳን አትችሉም» በማለት ወንድሞችን አስተማሯቸው።
\v 2 ጳውሎስና በርናባስም ከእነርሱ ጋር ጥልና ክርክር በገጠሙ ጊዜ፣ ጳውሎስና በርናባስ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ጉዳይ በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች እንዲወጡ ወንድሞች ወሰኑ።
\s5
\v 3 ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ተልከው፣ በፊንቄና በሰማርያ በኩል አድርገው ሲሄዱ፣ የአሕዛብን መለወጥ እያወጁ ዐለፉ፤ ይህም ወንድሞችን ሁሉ እጅግ ደስ አሰኛቸው።
\v 4 ወደ ኢየሩሳሌም በመጡ ጊዜም፣ ቤተ ክርስቲያን፣ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች በደስታ ተቀበሏቸው፤ እነ ጳውሎስም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ የሠራውን ሁሉ ነገሯቸው።
\s5
\v 5 ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑ አንዳንድ ሰዎች ግን ተነሥተው፣ «እነርሱን መግረዝና የሙሴንም ሕግ እንዲጠብቁ ማዘዝ ያስፈልጋል» አሉ።
\v 6 ስለዚህ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ይህን ጉዳይ ለማየት ተሰበሰቡ።
\s5
\v 7 ከብዙ ጭቅጭቅ በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ ቆመና እንዲህ አለ፦ «ወንድሞች ሆይ፣ አሕዛብ የወንጌልን ቃል ከአፌ እንዲሰሙና እንዲያምኑ፣ እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜያት በፊት ከእናንተ መካከል እኔን እንደ መረጠኝ ታውቃላችሁ።»
\v 8 ልብን የሚያውቅ አምላክ፣ ለእኛ እንዳደረገው ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤
\v 9 በእኛና በእነርሱ መካከልም ልባቸውን በእምነት በማንጻት ልዩነት አላደረገም።
\s5
\v 10 እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ መሽከም ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?
\v 11 ነገር ግን እኛም በጌታ በኢየሱስ ጸጋ እንደ እነርሱ እንደምንድን እናምናለን።»
\s5
\v 12 በርናባስና ጳውሎስ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት በአሕዛብ መካከል ስለ ሠራው ምልክትና ድንቅ ሲናገሩ፣ ሕዝቡ ሁሉ በጸጥታ አደመጡ።
\s5
\v 13 ንግግራቸውንም በጨረሱ ጊዜ፣ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ «ወንድሞች ሆይ፣ አድምጡኝ።
\v 14 እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ሕዝብ ከእነርሱ መካከል ይወስዱ ዘንድ፣ አሕዛብን በመጀመሪያ በጸጋ እንደ ረዳ ስምዖን ተናግሮአል።
\s5
\v 15 የነቢያት ቃል ከዚህ ጋር ይስማማል እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤
\v 16 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እመለሳለሁ፤ ፍርስራሹንም መልሼ እተክላለሁ፤ እንደገናም ዐድሳለሁ፤
\v 17 ይኸውም የተረፉት ሰዎችና በስሜ የተጠሩ አሕዛብ፣ እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ ነው።
\v 18 እነዚህ ጥንታዊ ነገሮች እንዲታወቁ የሚያደርግ ጌታ የሚለው ይህን ነው።
\s5
\v 19 ስለዚህ የእኔ ዐሳብ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን እንዳናስጨንቃቸው ነው፤
\v 20 ነገር ግን በጣዖታት ከመርከስ፣ ከዝሙት፣ ከታነቀና ከደም እንዲርቁ እንጻፍላቸው።
\v 21 ሙሴስ ከጥንት ዘመናት ጀምሮ በከተሞች ሁሉ በየሰንበታቱ በምኵራብ የሚሰብኩና የሚያነቡ ሰዎች አሉትና።»
\s5
\v 22 ስለዚህ በርስያን የተባለው ይሁዳንና ሲላስን የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አድርገው እንዲመርጡና፣ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ እንዲልኳቸው ለሐዋርያትና ለሽማግሌዎች፣ ከቤተ ክርስቲያን ሁሉ ጋር መልካም መስሎ ታያቸው።
\v 23 እንዲህም ብለው ጻፉ፤ «ለሐዋርያት፣ ለሽማግሌዎችና ወንድሞች፣ እንዲሁም በአንጾኪያ፣ በሶርያና በኪልቅያ ለሚገኙ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 24 እኛ ያላዘዝናቸው አንዳንድ ሰዎች ከእኛ ዘንድ መጥተው ነፍሳችሁን በሚያስጨንቅ ትምህርት እንዳስቸገሩአችሁ ሰምተናል።
\v 25 ስለዚህ በአንድ ልብ ሆነን ሰዎችን መርጠን ከወዳጆቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ መላክ ለሁላችንም መልካም መስሎ ታየን፤
\v 26 እነዚህ ሰዎች ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲሉ ለሕይወታቸው እንኳ ያልሣሡ ናቸው።
\s5
\v 27 ይህንኑ እንዲነግሯችሁ ይሁዳንና ሲላስን ወደ እናንተ ልከናል፤
\v 28 ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች በላይ ከባድ ሸክም እንዳንጭንባችሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስና ለእኛ መልካም መስሎ ታይቶናልና፤
\v 29 ይኸውም ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ከታነቀ፣ ከዝሙትም እንድትርቁ ነው። ራሳችሁን ከእነዚህ ብትጠብቁ መልካም ይሆንላችኋል፤ ደኅና ሁኑ።»
\s5
\v 30 ከዚያም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው።
\v 31 ደብዳቤውንም አንብበው ስለ ተጽናኑ በጣም ደስ አላቸው።
\v 32 ደግሞም ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ስለ ነበሩ፣ወንድሞችን በብዙ ቃል በመምከር አበረታቱአቸው።
\s5
\v 33 በዚያም ጥቂት ጊዜ ከተቀመጡ በኋላ፣ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ላኳቸው ሄዱ።
\v 34 ሲላስ ግን እዚያው መቆየት መልካም መስሎ ታየው።
\v 35 ጳውሎስና በርናባስ ግን የጌታን ቃል ባስተማሩበትና በሰበኩበት በአንጾኪያ ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋር ተቀመጡ።
\s5
\v 36 ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ጳውሎስ በርናባስን፣ «ተመልሰን የጌታን ቃል በሰበክንበት ከተማ ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ በምን ሁኔታ እንዳሉም እንወቅ» አለ።
\v 37 በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነሱ ጋር ይዞ ለመሄድ ፈለገ።
\v 38 ጳውሎስ ግን ማርቆስን ይዞ መሄድ አልፈለገም፤ ምክንያቱም ማርቆስ ከዚህ ቀደም ከእነርሱ ጋር ለሥራ በመሄድ ፈንታ፣ በጵንፍልያ ተለይቶአቸው ቀርቶ ነበር።
\s5
\v 39 በመካከላቸው ከፍተኛ አለምስማማት ስለ ተፈጠረም፣ ተለያዩ፤ በርናባስም ማርቆስን ይዞ ወደ ቆጵሮስ በመርከብ ሄደ።
\v 40 ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞች ለጌታ ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ፣ ተለይቶአቸው ሄደ።
\v 41 ከዚያም አብያተ ክርስቲያናትን እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ መጣ፤ እነሆም፣ እናቱ አይሁዳዊት አማኝ የሆነች፣ አባቱ ግን ግሪክ የሆነ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር አገኘ።
\v 2 በልስጥራና በኢቆንዮን የነበሩ ወንድሞችም ስለ እርሱ ጥሩ ምስክርነት ነበራቸው።
\v 3 ጳውሎስም እርሱን ይዞ መጓዝ ፈለገ፤ በዚያ አካባቢ ስለ ነበሩ አይሁድ ሲልም ጢሞቴዎስን ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉም ያውቁ ነበርና።
\s5
\v 4 በየከተሞቹ በሚዞሩበት ጊዜ፣ አብያተ ክርስቲያናት እንዲጠብቁት በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የጻፉትን መመሪያ ሰጡአቸው።
\v 5 ስለዚህ አብያተ ክርስቲያናቱ በእምነት እየበረቱ፣ ቍጥራቸውም በየዕለቱ እየጨመረ ነበር።
\s5
\v 6 በእስያ አውራጃ ቃሉን እንዳይሰብኩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው፣ ጳውሎስና ባልደረቦቹ በፍርግያና በገላትያ አውራጃዎች አድርገው ዐለፉ።
\v 7 ወደ ሚስያ አካባቢ በደረሱ ጊዜ፣ ቢታንያ ለመግባት ሞከሩ፤ የኢየሱስ መንፈስ ግን ከለከላቸው።
\v 8 ስለዚህ ሚስያን ዐልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።
\s5
\v 9 ጳውሎስም አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ፣ “ወደ መቄዶንያ ተሻግረህ ርዳን” እያለ ሲለምነው ሌሊት በራእይ ታየው።
\v 10 ራእዩንም ካየ በኋላ፣ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወንጌልን ለእነርሱ እንድንሰብክ እንደ ጠራን ዐሰብን።
\s5
\v 11 ከጢሮአዳ ተነሥተንም ቀጥታ በመርከብ ወደ ሳሞትራቄ ሄድን፤ በማግስቱም ናጱሌ ደረስን፤
\v 12 ከዚያም የመቄዶንያ ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ ሄድን፤ ከተማዋ የወረዳው ዋና ከተማና የሮም ቅኝ ግዛት ነበረች፤ በዚችም ከተማ ብዙ ቀን ተቀመጥን።
\v 13 በሰንበት ቀንም፣ በወንዝ አጠገብ በነበረው በር በኩል ወደ ውጭ ወጣን፤ ይህም ስፍራ የጸሎት ቦታ እንደ ሆነ ዐሰብን። በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩ ሴቶች ተናገርን።
\s5
\v 14 ከትያጥሮን ከተማ የመጣችና የሐምራዊ ሐር ሻጭ የነበረች፣ ልድያ የምትባል፣ እግዚአብሔርን የምታመልክ አንድ ሴት ትሰማን ነበር። ጳውሎስ እየተናገረ የነበረውን በሚገባ እንድታደምጥ፣ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
\v 15 ከቤተ ሰብዋ ጋር በተጠመቀች ጊዜም፣ “በጌታ ማመኔን ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ ግቡና ተቀመጡ” ብላ ለመነችን፤ አስገደደችንም።
\s5
\v 16 አንድ ቀን ጸሎት ቦታ ስንሄድ የጥንቈላ መንፈስ ያደረባት አንዲት ወጣት አገኘችን፤ በዚህ የጥንቈላ ሥራዋም ለአሳዳሪዎችዋ ከፍተኛ ገቢ ታስገኝ ነበር።
\v 17 ይህችው ሴት ጳውሎስንና እኛን ከኋላ እየተከተለች፣ “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፤ የመዳንን መንገድ ይነግሯችኋል” እያለች ትጮኽ ነበር።
\v 18 ይህንም ብዙ ቀን ደጋገመች። ጳውሎስ ግን በዚህ እጅግ ተበሳጨ፤ ዘወር ብሎም መንፈሱን፣ “ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው፤ በዚያው ቅጽበትም መንፈሱ ወጣ።
\s5
\v 19 አሳዳሪዎችዋም ተስፋ የሚያደርጉበት የገቢያቸው ምንጭ እንደ ጠፋ ባዩ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው በምድር ላይ እየጎተቱ በገበያ ስፍራ ባለ ሥልጣኖቹ ፊት አቀረቡአቸው።
\v 20 ወደ ገዢዎችም አምጥተዋቸው፣ “እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ሳሉ በከተማችን ውስጥ ከፍተኛ ሁከት እየፈጠሩ ነው።
\v 21 እኛ ሮማውያን ለመቀበል ያልተፈቀዱልንን ነገሮች ያስተምራሉ” አሉ።
\s5
\v 22 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ በጳውሎስና በሲላስ ላይ በአንድነት ተነሡ፤ ገዦቹም ልብሳቸውን አስወልቀው በዱላ እንዲደበድቡአቸው አዘዙ።
\v 23 ብዙ ድብደባ ካደረሱባቸው በኋላ፣ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፤ የወኅኒ ጠባቂውም በጥንቃቄ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።
\v 24 የወኅኒ ጠባቂውም ይህን ትእዛዝ ተቀብሎ፣ ወደ ውስጠኛው እስር ቤት ጣላቸው፤ እግራቸውንም ከግንድ ጋር አጣብቆ አሰራቸው።
\s5
\v 25 እኩለ ሌሊት አካባቢም፣ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ በዝማሬ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎች እስረኞችም አደመጡአቸው።
\v 26 ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስከሚናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ተከሠተ፤ ወዲያውም የወኅኒው በሮች ሁሉ ተከፈቱ፤ የታሳሪዎችም ሁሉ ሰንሰለቶች ተፈቱ።
\s5
\v 27 የወኅኒ ጠባቂውም ከእንቅልፉ ነቅቶ በሮቹ እንደ ተከፈቱ አየ፤ እስረኞቹ ያመለጡ ስለ መሰለውም፣ ሰይፉን መዞ ራሱን ሊገድል ቃጣ።
\v 28 ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፣ “ራስህን አትጉዳ! እኛ ሁላችን እዚሁ አለን” ብሎ ጮኸ።
\s5
\v 29 የወኅኒ ጠባቂውም መብራት ለምኖ ሮጦ ወደ ውስጥ ገባ፤ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ ፊት ተደፋ፤
\v 30 ወደ ውጭም አስወጥቶአቸው፣ “ጌቶች ሆይ፣ ለመዳን ምን ማድረግ አለብኝ?” አላቸው።
\v 31 እነርሱም፣ “በጌታ ኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።
\s5
\v 32 ጳውሎስና ሲላስ ለእርሱና አብረውት በቤት ለነበሩ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ተናገሩ።
\v 33 የወኅኒ ጠባቂውም ሌሊት፣ በዚያው ሰዓት ወስዶአቸው ቍስላቸውን አጠበላቸው። እርሱና ቤተ ሰዎቹም ሁሉ ወዲያው ተጠመቁ።
\v 34 ጳውሎስንና ሲላስንም ወደ ቤቱ ይዞአቸው ወጣ፤ ምግብም አቀረበላቸው። ሁሉም በእግዚአብሔርም በማመናችው ከቤተ ሰዎቹ ጋር እጅግ ደስ አለው።
\s5
\v 35 ሲነጋም ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ልቀቋቸው” የሚል ትእዛዝ ለጠባቂዎቹ ላኩ።
\v 36 የወኅኒ ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ ትእዛዝ ለእኔ ልከዋል፤ ስለዚህ ውጡና በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው።
\s5
\v 37 ጳውሎስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ሮማውያን የሆንነውን እኛን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበውናል፤ ወደ ወኅኒም አስገብተውናል፤ ታዲያ፣ አሁን በድብቅ ያስወጡናል? በፍጹም አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን።”
\v 38 ጠባቂዎቹም ይህንኑ አባባል ለገዦቹ ነገሯቸው፤ ገዦቹም ጳውሎስና ሲላስ ሮማውያን እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ።
\v 39 መጥተውም ተማጸኑአቸው፤ ከወኅኒም ካስወጡአቸው በኋላ፣ ከከተማው እንዲወጡ ጳውሎስንና ሲላስን ለመኑአቸው።
\s5
\v 40 ጳውሎስና ሲላስም ከወኅኒው ወጥተው ወደ ልድያ ቤት ገቡ። ወንድሞችንም ባዩአቸው ጊዜ፣ አበረታቱአቸው፤ ከዚያም ከከተማዪቱ ወጥተው ሄዱ።
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 አንፊጶልና አጶሎንያ በተባሉ ከተሞች በኩል ካለፉ በኋላም፣ ተሰሎንቄ ወደ ተባለች ከተማ መጡ፤ በዚያም ከተማ የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።
\v 2 ጳውሎስም እንደ ልማዱ፣ ወደ አይሁድ ሄዶ፣ ለሦስት ሰንበታት ያህል ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር።
\s5
\v 3 ቅዱሳት መጻሕፍትንም እየገለጠ፣ ክርስቶስ መከራን መቀበልና ከሙታን መነሣት እንደ ነበረበት እያስረዳም፣ «ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው» ይላቸው ነበር።
\v 4 ከአይሁድም አንዳንዶቹ መልእክቱን ተቀብለው ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤ በተጨማሪም ለእግዚአብሔር ያደሩ ግሪኮች፣ የከበሩ ብዙ ሴቶችና ከፍተኛ ቍጥር ያላቸው ሰዎች ከእነርሱ ጋር ሆኑ።
\s5
\v 5 ሌሎች ያላመኑ አይሁድ ግን፣ በቅንዓት በመነሣሣትና ክፉ ሰዎችን ከጎዳና ላይ በማሰባሰብ ሕዝብን አከማችተው ከተማዋን አወኩአት። የኢያሶንን ቤት በዐመፅ በመክበብም፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ለሕዝቡ ለማስረከብ ፈለጉ።
\v 6 ሊያገኙአቸው ባልቻሉ ጊዜም፣ ኢያሶንንና ሌሎች ወንድሞችን ይዘው መሬት ለመሬት እየጎተቱ ወደ ከተማዋ ባለ ሥልጣናት ፊት አወጡአቸው፤ እንዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ «እነዚህ ዓለምን የገለባበጡ ሰዎች ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል፤
\v 7 ኢያሶን በቤቱ የተቀበላቸው እነዚህ ሰዎች የቄሣርን ሕግ የሚቃወሙ ናቸው፤ ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ ነው።»
\s5
\v 8 ሕዝቡና የከተማው ሹሞች እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ፣ ታወኩ።
\v 9 ከኢያሶንና ከሌሎቹም የዋስትና ገንዘብ ተቀብለው ለቀቁአቸው።
\s5
\v 10 ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በዚያው ሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው። እነርሱም እዚያ በደረሱ ጊዜ፣ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ።
\v 11 እዚህ የሚኖሩ ሰዎች በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ሰፊ አስተሳሰብ ስለ ነበራቸው፣ ነገሩ እንዲህ ይሆንን በማለት ቅዱሳት መጻሕፍትን በየዕለቱ እየመረመሩ፣ ልባቸው ቃሉን ለመቀበል ዝግጁ ነበር።
\v 12 ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎች አመኑ፤ በተጨማሪ አንዳንድ ተደማጭነት ያላቸው የግሪክ ሴቶችና ሌሎች ወንዶችም አመኑ።
\s5
\v 13 በተሰሎንቄ የነበሩ አይሁድም ጳውሎስ በቤርያም ደግሞ ቃሉን እንደ ሰበከ ባወቁ ጊዜ፣ ወደዚያ ሄደው ሕዝቡን በማነሣሣት አወኩ።
\v 14 ወንድሞችም ወዲያው ጳውሎስን ወደ ባሕሩ አካባቢ እንዲሄድ አደረጉ ፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቆዩ።
\v 15 ጳውሎስን ይሸኙ የነበሩት ሰዎችም እስከ አቴና ድረስ ወሰዱት። ከዚያም ሲነሡ፣ ሲላስና ጢሞቴዎስ በተቻለው ፍጥነት ወደ እነሱ እንዲመጡ የሚል መልእክት ከጳውሎስ ተቀብለው ሄዱ።
\s5
\v 16 ጳውሎስ አቴና ተቀምጦ እየጠበቃቸው ሳለ፣ ከተማዋ በጣዖት የተሞላች መሆንዋን ሲያይ፣ መንፈሱ በውስጡ ተበሳጨበት።
\v 17 ስለዚህም ነገር በምኵራብ ከሚያገኛቸው አይሁድ፣ እግዚዘብሔርንም ከሚያመልኩ ሌሎች ሰዎችና ዘወትር በገበያ ቦታ ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይነጋገር ነበር።
\s5
\v 18 ከኤፌቆስና ከኢስጦኢኮች ወገን የሆኑ አንዳንድ ፈላስፎችም ደግሞ ጳውሎስን አገኙት። ከእነርሱም አንዳንዶች፣ «ይህ ለፍላፊ ምን እያለ ነው?» አሉ። ሌሎቹም፣ ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤው ሲሰብክ ስለ ሰሙት፣ «ስለ እንግዳ አማልክት የሚሰብክ ይመስላል» አሉ።
\s5
\v 19 ከዚያም፣ «አንተ የምትናገረውን ይህን ዐዲስ ትምህርት ማወቅ እንችላለን ወይ?
\v 20 ምክንያቱም እየሰማናቸው ያሉ ነገሮች እንግዳ ናቸው። ስለዚህ፣ የእነዚህን ነገሮች ትርጕም ማወቅ እንሻለን» አሉት።
\v 21 አቴናውያንና ሌሎች በዚያ የሚኖሩ እንግዶች ሁሉ ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት በሌላ ጉዳይ ሳይሆን፣ ስለ ዐዳዲስ ነገሮች በማውራት ወይም በመስማት ነበር።
\s5
\v 22 ስለዚህ ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፤ «እናንተ የአቴና ሰዎች ሆይ፣ በየትኛውም መልክ እጅግ ሃይማኖተኞች እንደ ሆናችሁ እመለከታለሁ።
\v 23 ምክንያቱም ወዲያ ወዲህ እየተመላለስሁ የምታመልኳቸውን ስመለከት፣ ላልታወቀ አምላክ የሚል ጽሑፍ የተጻፈበት አንድ መሠዊያ አይቻለሁ። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን አምላክ እኔ እነግራችኋለሁ።
\s5
\v 24 ዓለምንና በውስጧ የሚገኙትን ሁሉ የፈጠረ አምላክ፣ የሰማይና የምድር ጌታ በመሆኑ፣ በእጅ በተሠራ መቅደስ ውስጥ አይኖርም።
\v 25 ለሰዎች ሕይወት፣ እስትንፋስንና ሁሉንም ነገር የሚሰጠው እርሱ ራሱ ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር አንዳች እንደሚያስፈልገው በሰው እጅ አይገለገልም።
\s5
\v 26 በምድር ገጽ ላይ የሚኖሩትንም ሕዝቦች ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ የሚኖሩባቸውንም ስፍራዎች ወሰን፣ ወቅቶችንም የወሰነላቸው እርሱ ነው።
\v 27 ስለዚህ እግዚአብሔርን ቢፈልጉ ሊያገኙት ይችላሉ፤ እንደ እውነቱ ከሆነ፣ እርሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።
\s5
\v 28 ምክንያቱም የምንኖረው፣ የምንንቀሳቀሰውና በሕይወት የቆምነው በእርሱ ነው፤ ከእናንተ ባለ ቅኔዎች አንዱ እንዳለውም፣ 'እኛ ልጆቹ ነን።'
\v 29 እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን፣ መለኮትን በሰው ጥበብና እንደ ተቀረጸ ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ አድርገን ማሰብ የለብንም።
\s5
\v 30 ስለዚህ እግዚአብሔር የአለማወቅ ጊዜያትን አሳልፎ፣ አሁን ግን በየትኛውም ስፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ ያዛል።
\v 31 ምክንያቱም በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ የሚፈርድበትን ቀን አዘጋጅቶአል። እግዚአብሔር ይህን ሰው ከሙታን በማስነሣቱ ለሁሉ ሰው ማረጋገጫ ሰጥቶአል።"
\s5
\v 32 የአቴና ሰዎች ስለ ሙታን ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ፣ አንዳንዶቹ በጳውሎስ ላይ አፌዙ፤ሌሎች ግን፣ «ስለዚህ ጉዳይ ዳግመኛ እንሰማሃለን» አሉት።
\v 33 ከዚህ በኋላ፣ ጳውሎስ ተለይቶአቸው ሄደ፤
\v 34 አንዳንድ ወንዶች ግን ከእርሱ ጋር ተባብረው አመኑ፤ በእነዚህም ውስጥ የአርዮስፋጎስ አመራር አባል ዲዮናስዮስ፣ ደማሪስ የተባለች ሴትና ሌሎችም ይገኛሉ።
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 18
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ፣ ጳውሎስ ከአቴና ወደ ቆሮንቶስ ሄደ።
\v 2 እዚያም ከጳንጦስ ወገን የሆነ አቂላ የሚባል አይሁዳዊ አገኘ። እርሱም አይሁድ ሁሉ ከሮም እንዲወጡ ቀላውዴዎብ ባዘዘው መሠረት፣ ከሚስቱ ከጵርቅላ ጋር በቅርብ ከኢጣሊያ የመጣ ሰው ነበር። ጳውሎስም ከእነርሱ ጋር ተቀራረበ።
\v 3 ሥራቸው አንድ ዓይነት ስለ ሆነም፣ በእነርሱ ዘንድ እየኖረ ዐብሮአቸው ይሠራ ነበር። ሥራቸውም ድንኳን መስፋት ነበር።
\s5
\v 4 በየሰንበቱም በምኵራብ ውስጥ በመገኘት እየተከራከረ፣ አይሁድንም ግሪኮችንም ያሳምን ነበር።
\v 5 ሲላስና ጢሞቴዎስ ከመቄዶንያ እርሱ ወዳለበት በወረዱ ጊዜ ግን፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እንዲመሰክር መንፈስ ቅዱስ ጳውሎስን ገፋፋው።
\v 6 አይሁድ በተቃወሙትና በተሳደቡ ጊዜ፣ ጳውሎስ ልብሱን እያራገፈባቸው፣ «ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ይሁን፤ እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ከአሁን ጀምሮ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ» አላቸው።
\s5
\v 7 ከዚያም ወጥቶ ቲቶ ኢዮስጦስ ወደሚባል፣ እግዚአብሔርን ወደሚያመልክ ሰው ቤት ሄደ። ቤቱም በምኵራብ አጠገብ ነበር።
\v 8 ቀርስጶስ የተባለም የምኵራብ አለቃ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር በጌታ አመነ። ጳውሎስ ሲናገር ከሰሙት ከቆሮንቶስ ሰዎች መካከልም ብዙዎቹ አምነው ተጠመቁ።
\s5
\v 9 ጌታም ሌሊት በራእይ ጳውሎስን እንዲህ አለው፤ "አትፍራ ተናገር፣ ዝምም አትበል።
\v 10 ምክንያቱም እኔ ከአንተ ጋር አለሁ፤ ሊጎዳህ የሚነሣብህ ማንም የለም፤ እንዲያውም በዚህ ከተማ ብዙ ሰዎች አሉኝ።"
\v 11 ጳውሎስም በመካከላቸው የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማረ አንድ ዓመት ከስድስት ወር እዚያ ተቀመጠ።
\s5
\v 12 ነገር ግን ጋልዮስ የአካይያ አገረ ገዢ በሆነ ጊዜ፣ አይሁድ በጳውሎስ ላይ በአንድነት ተነሡ፤ ይዘውም ፍርድ ፊት አቀረቡት።
\v 13 ከዚያም፣ “ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዲያመልክ ይህ ሰው ከሕግ ውጪ እየቀሰቀሰ ነው” አሉ።
\s5
\v 14 ጳውሎስ ሊናገር ሲልም፣ ጋልዮስ አይሁድን፣ “አይሁድ ሆይ፣ ጉዳዩ በርግጥ የበደል ወይም የወንጀል ቢሆን ኖሮ፣ ልታገሣችሁ በተገባኝ ነበር።
\v 15 ነገር ግን ክርክሩ ስለ ቃላትና ስለ ስሞች፣ ደግሞም ስለ ገዛ ሕጋችሁ ስለ ሆነ፣ እናንተው ራሳችሁ ተነጋገሩበት። እኔ ስለ እንደዚህ ዐይነት ጉዳይ ፈራጅ መሆን አልፈልግም” አለ።
\s5
\v 16 ከዚያም ጋልዮስም ከችሎቱ አስወጣቸው።
\v 17 እነርሱ ሁሉ ግን የምኵራቡን አለቃ ሶስቴንስን በጉልበት ይዘው በፍርድ ወንበሩ ፊት ደበደቡት። ይሁን እንጂ፣ ይህ ድርጊታቸው ለጋልዮስ ደንታም አልሰጠውም።
\s5
\v 18 ጳውሎስም ብዙ ቀናት ከተቀመጠ በኋላ፣ ወንድሞችን ተሰናብቶ ከጵርስቅላና ከአቂላ ጋር በመርከብ ወደ ሶርያ ሄደ። ስእለት ስለ ነበረበትም፣ ከወደቡ ከክንክራኦስ ከመነሣቱ በፊት ራሱን ተላጨ።
\v 19 ኤፌሶን በደረሱ ጊዜ፣ ጳውሎስ ጵርስቅላንና አቂላን ትቶአቸው ወደ ምኵራብ ሄዶ ከአይሁድ ጋር ይነጋገር ነበር።
\s5
\v 20 እነርሱም ረዘም ላለ ጊዜ ዐብሮአቸው እንዲቆይ ሲለምኑት፣ ጳውሎስ እንቢ አለ።
\v 21 ከዚያም፣ “እግዚአብሔር ቢፈቅድ እንደ ገና ተመልሼ እመጣለሁ” ብሎ ተሰናበታቸው። ከኤፌሶንም ተነሥቶ በመርከብ ሄደ።
\s5
\v 22 ጳውሎስ ቂሣርያ በደረሰ ጊዜ፣ በኢየሩሳሌም ወደ ነበረችው ቤተ ክርስቲያን ወጥቶ ሰላምታ አቀረበላቸውና ወደ አንጾኪያ ወረደ።
\v 23 በዚያም ጥቂት ጊዜ ከተቀመጠ በኋላ፣ ጳውሎስ ተለያቸው፤ በገላትያና በፍርግያ አካባቢ በማለፍም ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ አበረታታ።
\s5
\v 24 ትውልዱ እስክንድርያዊ የሆነ፣ አጵሎስ የሚባል አንድ አይሁዳዊ ወደ ኤፌሶን መጣ፤ እርሱም የንግግር ችሎታና በቂ የቅዱሳት መጻሕፍት ዕውቀት ያለው ሰው ነበር።
\v 25 አጵሎስ የጌታን ትምህርት በሚገባ የተማረ በመሆኑ፣ በመንፈሱ ተነቃቅቶ ስለ ኢየሱስ በትክክል ይናገርና ያስተምር ነበር፤ የሚያውቀው ግን ስለ ዮሐንስ ጥምቀት ብቻ ነበር።
\v 26 አጵሎስ ምኵራብ ውስጥ በድፍረት መናገር ጀመረ። ነገር ግን ጵርስቅላና አቂላ በሰሙት ጊዜ፣ ወደ እርሱ ቀርበው የእግዚአብሔር መንገድ ይበልጥ በትክክል አብራሩለት።
\s5
\v 27 እርሱም ወደ አካይያ ማለፍ በፈለገ ጊዜ፣ ወንድሞች አበረታቱት፤ በአካይያ የነበሩ ደቀ መዛሙርት እንዲቀበሉትም ጻፉላቸው። እዚያ በደረሰ ጊዜም፣ በጸጋ ያመኑትን እጅግ ረዳቸው።
\v 28 አጵሎስ ከቅዱሳት መጻሕፍት እያስደገፈ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ በማሳየት በኀይሉና በችሎታው አይሁድን ተከራክሮ ረታቸው።
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 አጵሎስ በቆሮንቶስ በነበረ ጊዜ፣ ጳውሎስ በላይኛው አገር አድርጎ ወደ ኤፌሶን ከተማ መጣ፤ በዚያም አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን አገኘ።
\v 2 ጳውሎስም፣ “ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችኋል?” አላቸው። እነርሱም፣ “አልተቀበልንም፤ እንዲያውም መንፈስ ቅዱስ መኖሩን አልሰማንም” አሉት።
\s5
\v 3 ጳውሎስም፣ “ታዲያ፣ በምን ተጠመቃችሁ?” አላቸው። እነርሱም፣ “የተጠመቅነው በዮሐንስ ጥምቀት ነው” አሉት።
\v 4 ጳውሎስም መልሶ፣ “ዮሐንስ ያጠመቀው በንስሓ ጥምቀት ነው። ሰዎች ከእርሱ በኋላ በሚመጣው፣ በኢየሱስ ማመን እንደሚገባቸውም ነገራቸው” አለ።
\s5
\v 5 ሕዝቡ ይህን ሲሰሙ፣ በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠመቁ።
\v 6 ጳውሎስም እጆቹን በሰዎቹ ላይ በጫነ ጊዜ፣ መንፈስ ቅዱስ ወረደባቸው፤ እነርሱም በልዩ ቋንቋ መናገርና መተንበይ ጀመሩ።
\v 7 ቍጥራቸውም ዐሥራ ሁለት ያህል ነበረ።
\s5
\v 8 ጳውሎስ ከዚህ በኋላ ወደ ምኵራብ እየገባ ሦስት ወር ያህል በድፍረት ይናገር ነበር፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየገለጠ ሰዎችን ያስረዳ ነበር።
\v 9 አንዳንድ አይሁድ ግን ልባቸውን አደንድነው በመቃወም፣ በሕዝቡ ፊት የክርስቶስን መንገድ ተሳደቡ፤ ስለዚህ ጳውሎስ ትቶአቸው ሄደ፤ ያመኑትንም ከእነርሱ አራቀ። ጢራኖስ በሚባል የትምህርት አዳራሽም በየዕለቱ ንግግር ያደርግ ጀመር።
\v 10 ይህም፣ በእስያ የሚኖሩ አይሁድና ግሪኮችም ሁሉ የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ፣ ሁለት ዓመት ቀጠለ።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር በጳውሎስ እጅ ታላላቅ ተአምራትን ያደርግ ነበር፤
\v 12 ስለዚህ የጳውሎስ አካል የነካው ጨርቅ ወይም መሐረብ ሲወሰድ፣ የታመሙት ይፈወሱ፣ አጋንንትም ከሰዎች ይወጡ ነበር።
\s5
\v 13 አጋንንት እናስወጣለን እያሉ ከቦታ ቦታ የሚዞሩ አይሁድ ነበሩ፤ እነርሱም የኢየሱስን ስም ለገዛ ጥቅማቸው ለማዋል፣ በክፉ መናፍስት ላይ እየጠሩ፣ “እንድትወጡ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናዛችኋለን” ይሉ ነበር።
\v 14 ይህን ያደረጉትም የአይሁድ የካህናት አለቃ የነበረው የአስቄዋ ሰባት ወንድ ልጆች ነበሩ።
\s5
\v 15 ክፉው መንፈስም፣ “ኢየሱስን ዐውቀዋለሁ፤ ጳውሎስንም ዐውቃለሁ፤ ለመሆኑ እናንተ እነማን ናችሁ?” ብለው መለሱላቸው።
\v 16 ክፉ መንፈስ ያለበትም ሰው ዘሎ ያዛቸው፤ አሸንፏቸውም ደበደባቸው። ከዚያም ቤት ቈስለው ዕራቁታቸውን ሸሹ።
\v 17 ይህም በኤፌሶን ይኖሩ በነበሩ አይሁድና ግሪኮችም ዘንድ ሁሉ ታወቀ። እነርሱም ሁሉ በፍርሀት ተዋጡ፤ የጌታ ኢየሱስም ስም ተከበረ።
\s5
\v 18 ደግሞም ካመኑት ብዙዎቹ መጥተው ቀደም ሲል ያደረጉትን ክፉ ነገር ሳይሸሽጉ ይናዘዙ ነበር።
\v 19 አስማተኞችም የጥንቈላ መጻሕፍታቸውን ሰብስበው እያመጡ በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉ፤ ዋጋቸውም ሲተመን ሃምሳ ሺህ ብር ሆነ።
\v 20 በዚህም መሠረት የጌታ ቃል በስፋትና በኀይል ተሠራጨ።
\s5
\v 21 ጳውሎስ በኤፌሶን የነበረውን አገልግሎቱን ከፈጸመ በኋላ፣ በመቄዶንያና በአካይያ አድርጎ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ በመንፈስ ቅዱስ ሆኖ ወሰነ፤ ደግሞም፣ “እዚያ ከደረስሁ በኋላም፣ ሮሜን ማየት ይገባኛል” አለ።
\v 22 ሲረዱት ከነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን፣ ጢሞቴዎስንና ኤርስጦንን ወደ መቄዶንያ ላካቸው። እርሱ ራሱ ግን ጥቂት ጊዜ በእስያ ቆየ።
\s5
\v 23 በዚህ ጊዜ የጌታን መንገድ በተመለከተ በኤፌሶን ትልቅ ሁከት ተነሣ።
\v 24 ድሜጥሮስ የሚባል አንድ ብር ሠሪም የዲያናን ምስል ከብር እያበጀ ለአንጥረኞች ትልቅ ገቢ ያስገኝላቸው ነበር።
\v 25 ስለዚህ በዚህ ሙያ ላይ የተሰማሩትን ብዙ ሠራተኞች አንድ ላይ ሰብስቦ፣ “ሰዎች ሆይ፤ በዚህ ሙያችን ብዙ ገንዘብ እንደምናገኝ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 26 ይህ ጳውሎስ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን፣ ከብዙ በጥቂቱ በእስያ ሁሉ አብዛኛውን ሕዝብ በቃላት እያባበለ ከእኛ ማራቁን እያያችሁና እየሰማችሁ ነው። በእጅ የሚሠሩ አማልክት የሉም እያላቸው ነው።
\v 27 የእኛ ሞያዊ ጥበብ አላስፈላጊ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ የታላቅዋ አምላክ የዲያና ቤተ መቅደስም እንደ ከንቱ ነገር የመቍጠር አደጋ ያሠጋል፤ እስያ ሁሉና ዓለሙ የሚያመልካት ይህች አምላክም ዝናዋን ታጣለች።”
\s5
\v 28 ሕዝቡም ይህን በሰሙ ጊዜ፣ በቍጣ ተሞልተው፣ “የኤፌሶንዋ ዲያና ታላቅ ናት” እያሉ ጮኹ።
\v 29 ከተማው ሁሉ ድብልቅልቁ ወጣ፤ ሕዝቡም በአንድ ላይ ገንፍለው ወደ ቲያትር ማሳያው ቦታ ገቡ። ከመቄዶንያ የመጡትንም የጳውሎስን የጕዞ ባልደረቦች፣ ጋይዮስንና አርስጥሮኮስን ያዙአቸው።
\s5
\v 30 ጳውሎስ ወደ ሕዝቡ ሊደባለቅ ፈልጎ ነበር፤ ደቀ መዛሙርቱ ግን ከለከሉት።
\v 31 ደግሞም፣ የጳውሎስ ወዳጆች የነበሩ አንዳንድ የአካባቢ ሹሞች ጳውሎስ ወደ ቲያትር ማሳያ ቦታ እንዳይገባ መልእክት ላኩበት።
\v 32 ሕዝቡ ሁሉ ግራ ተጋብቶ ነበርና፣ አንዳንዶቹ ስለ አንድ ነገር ሲጮኹ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ስለ ሌላ ነገር ይጮኹ ነበር። አብዛኛዎቹ ደግሞ ለምን ተሰብስበው እንደ ወጡ እንኳ አያውቁም ነበር።
\s5
\v 33 አይሁድም እስክንድሮስን ገፋፍተው ወደ ሕዝቡ ፊት አወጡት። እስክንድሮስ ለሕዝቡ በእጅ ምልክት እያሳየ ሊያስረዳቸው ሞከረ።
\v 34 ሕዝቡም አይሁዳዊ መሆኑን በተረዱ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ፣ “የኤፌሶንዋ ዲያና ታላቅ ናት” እያሉ ለሁለት ሰዓት ያህል ጮኹ።
\s5
\v 35 የከተማዋ ጸሓፊ ሕዝቡን ዝም ካሰኘ በኋላ፣ እንዲህ አለ፤ “እናንተ የኤፌሶን ሰዎች ሆይ፣ የኤፌሶን ከተማ የታላቅዋ ዲያና ቤት መቅደስና ከሰማይ የወረደው ምስል ጠባቂ መሆንዋን የማያውቅ የትኛው ሰው ነው?
\v 36 እንግዲህ ይህ የማይካድ ነገር መሆኑ ከታያችሁ፣ ጸጥ ልትሉ፣ አንዳች ነገርም በችኰላ ልታደርጉ አይገባም፤
\v 37 ምክንያቱም አብያተ መቅደስን ያልሰረቁ፣ አማልክታችንንም ያልሰደቡ እነዚህን ሰዎች ወደዚህ ፍርድ ቤት አምጥታችኋል።
\s5
\v 38 ስለዚህ ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉ አንጥረኞች የሚከሱት ሰው ካለ፣ ፍርድ ቤቱ ክፍት ነው፤ ዳኞችም አሉ፤ እዚያ እርስ በርስ ይካሰሱ።
\v 39 ስለ ሌላ ጉዳይ የምትፈልጉት ነገር ካለ ግን፣ ችግሩ በመደበኛው ጉባኤ ይፈታል፤
\v 40 ምክንያቱም በዛሬው ቀን የነበረው ዐመፅ ሳያስጠይቀን አይቀርም። የነበረው ግርግር መንሥኢ የለውም፤ እንዲህ ነው ብለን ልንገልጸውም አንችልም።”
\v 41 ጸሓፊው ይህን ተናግሮ ጉባኤውን አሰናበተው።
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 ሁከቱ ካበቃ በኋላ፣ ጳውሎስ ደቀ መዛሙርቱን አስጠርቶ አበረታታቸው። ከዚያም ተሰናበታቸውና ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣ።
\v 2 በእነዚያም አካባቢዎች እያለፈ ያመኑትን እጅግ ካበረታታ በኋላ፣ ወደ ግሪክ ገባ።
\v 3 በዚያም ሦስት ወር ከቈየ በኋላ፣ ወደ ሶርያ በመርከብ ለመሄድ እያሰበ ሳለ፣ አይሁድ አሤሩበት፤ ስለዚህ በመቄዶንያ አድርጎ ለመመለስ ወሰነ።
\s5
\v 4 እስከ እስያ የሸኙትም የቤርያው ሱሲጳጥሮስ፣ ከተሰሎንቄ የመጡት አርስጥሮኮስና ሲኮንዱስ፣ የደርቤኑ ጋይዮስ፣ ጢሞቴዎስ፣ እንዲሁም ከእስያ የመጡት ቲኪቆስና ጥሮፊሞስ ነበሩ።
\v 5 እነዚህ ሰዎች ግን ቀድመውን በጢሮአዳ ጠበቁን።
\v 6 እኛም ከቂጣ በዓል ቀን በኋላ፣ ከፊልጵስዩስ በመርከብ ተነሥተን በዐምስት ቀን ውስጥ ጢሮአዳ ደረስንባቸው፤ እዚያም ሰባት ቀን ተቀመጥን።
\s5
\v 7 በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እንጀራ ለመቊረስ በተሰበሰብን ጊዜ፣ ጳውሎስ ለምእመናኑ ንግግር አደረገ። በሚቀጥሉት ቀናት ለመሄድ ዐቅዶ ስለ ነበረ፣ እስከ እኩለ ሌሊት መናገሩን ቀጠለ።
\v 8 በተሰበሰብንበትም ሰገነት ላይ ብዙ መብራቶች ነበሩ።
\s5
\v 9 አውጤኪስ የሚባል ወጣትም በመስኮት ተቀምጦ ሳለ፣ እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወሰደው። ጳውሎስ ንግግሩን ባስረዘመ ጊዜ፣ ይህ ወጣት ገና ተኝቶ እንዳለ ከሦስተኛው ፎቅ ወደቀ፤ ሲያነሡትም ሞቶ ነበር።
\v 10 ጳውሎስ ግን ወርዶ በላዩ ተዘረጋበት፣ ዐቀፈውም። ከዚያም፣ “በሕይወት ስላለ ከዚህ በኋላ አትታወኩ” አለ።
\s5
\v 11 እንደ ገናም በደረጃ ወደ ላይ ወጣ፤ እንጀራ ቈርሶም በላ። እስኪነጋ ድረስም ለረዥም ጊዜ ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ፣ ተለይቶአቸው ሄደ።
\v 12 ወጣቱንም በሕይወት እያለ አመጡት፤ በዚህም እጅግ ተጽናኑ።
\s5
\v 13 እኛም ራሳችን ጳውሎስን በመርከብ ለማሳፈር ወዳሰብንበት ወደ አሶን ቀድመን በመርከብ ሄድን። እርሱም ያሰበው ይህንኑ ነበር፤ በመርከብ ለመሄድ ዐቅዶ ነበርና።
\v 14 በአሶን ሲያገኘንም፣ ወዳለንበት መርከብ አስገብተነው ወደ ሚሊጢን ጕዞአችንን ቀጠልን።
\s5
\v 15 ከዚያም በመርከብ ተነሣንና በማግስቱ ኪዩ በምትባለዋ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ደሴት ጎራ ብለን፣ በማግስቱ ወደ ሚሊጢን ከተማ ገባን፤
\v 16 ጳውሎስም በእስያ ውስጥ ጊዜ ሳያባክን፣ ኤፌሶንን ዐልፎ በመርከብ ለመሄድ ወስኖ ነበርና፤ ምክንያቱም በተቻለው መጠን ሁሉ ለበዓለ ኀምሳ በኢየሩሳሌም ለመገኘት ቸኵሎ ነበር።
\s5
\v 17 ሰዎችንም ከሚሊጢን ወደ ኤፌሶን ልኮ፣ የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ወደ ራሱ አስጠራቸው።
\v 18 ወደ እርሱ በመጡም ጊዜ፣ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ እስያ ከገባሁበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ፣ ዘወትር እንዴት ከእናንተ ጋር እንደ ኖርሁ እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
\v 19 ራሴን እጅግ ዝቅ በማድረግና በእንባ፣ ከአይሁድ ሤራ የተነሣ በገጠመኝ መከራም ውስጥ ጌታን ማገልገል አላቋረጥሁም።
\v 20 ጠቃሚ የሆነውን ነገር ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽና በአደባባይም ሆነ ቤት ለቤት በመዞር እናንተን ከማስተማር ወደ ኋላ እንዳላልሁ ታውቃላችሁ።
\v 21 በንስሓ ወደ እግዚአብሔር ስለ መመለስና በጌታችን በኢየሱስ ስለ ማመን አይሁድንና ግሪኮችን እንዴት ሳስጠነቅቃቸው እንደ ነበር ታውቃላችሁ።
\s5
\v 22 እንግዲህ ተመልከቱ፤ እዚያ ምን እንደሚጠብቀኝ ሳላውቅ፣ በመንፈስ ቅዱስ ታስሬ ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ፤
\v 23 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ እስራትና መከራ እንደሚቆየኝ በየከተማው ይመሰክርልኛል።
\v 24 ነገር ግን ሩጫዬንና ከጌታ ኢየሱስ የተቀበልሁትን የእግዚአብሔርን ጸጋ ወንጌል የመመስከር አገልግሎት እስከምጨርስ ድረስ፣ እንደ ውድ ነገር በመቍጠር፣ ለሕይወቴ አልሳሳላትም።
\s5
\v 25 እንግዲህ ተመልከቱ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበክሁ በመካከላችሁ የዞርሁትን የእኔን ፊት ሁላችሁ ዳግመኛ እንደማታዩ ዐውቃለሁ።
\v 26 ስለዚህ ከማንም ሰው ደም ንጹሕ እንደ ሆንሁ ዛሬ እመሰክርላችኋለሁ፤
\v 27 ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ሁሉ ለእናንተ ከመግለጽ ወደ ኋላ ብዬ አላውቅም።
\s5
\v 28 ስለዚህ በገዛ ራሱ ደም የገዛትን የጌታን ጉባኤ ትጠብቁ ዘንድ፣ ስለ ራሳችሁና መንፈስ ቅዱስ ጠባቂ አድርጎ እናንተን ለሾመበት፣ ለመንጋው ሁሉ ተጠንቀቁ።
\v 29 እኔ ከሄድሁ በኋላ፣ ለመንጋው ርኅራኄ የሌላቸው አጥፊ ተኵላዎች በመካከላችሁ እንደሚገቡ ዐውቃለሁ።
\v 30 ከእናንተ መካከልም እንኳ ደቀ መዛሙርትን የራሳቸው ተከታዮች ለማድረግ አንዳንድ ሰዎች መጥተው ጠማማ ነገሮችን እንደሚናገሩ ዐውቃለሁ።
\s5
\v 31 ስለዚህ ተጠንቀቁ። ሳላቋርጥ ቀንና ሌሊት፣ ሁላችሁንም ሦስት ዓመት በእንባ እንዳገለገልኋችሁም አስታውሱ።
\v 32 አሁንም ለእግዚአብሔርና ሊያንጻችሁ፣ እንዲሁም በቅዱሳን ሁሉ መካከል ርስትን ሊሰጣችሁ ለሚችለው ለጸጋው ቃል ዐደራ እሰጣችኋለሁ።
\s5
\v 33 የማንንም ብር፣ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም።
\v 34 እነዚህ እጆቼ የእኔንም፣ ከእኔ ጋር የነበሩትንም ሰዎች ፍላጎት ሲያሟሉ እንደ ነበር እናንተ ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
\v 35 ደካሞችን በሥራ እንዴት እንደምትረዱ፣ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው” የሚለውንም የጌታ ኢየሱስን ቃል እንዴት እንደምታስታውሱ በሁሉም ረገድ አርኣያ ሆንኋችሁ።
\s5
\v 36 ጳውሎስ ይህን ሁሉ ካለ በኋላ፣ ተንበርክኮ ከሁሉም ጋር ጸለየ።
\v 37 ሁሉም እጅግ በማልቀስ ዐንገቱ ላይ ተጠምጥመው ሳሙት።
\v 38 ፊቱን ዳግመኛ እንደማያዩ መናገሩም ከሁሉ በላይ አሳዘናቸው። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 ከእነርሱም ተለይተን የባሕር ላይ ጕዞአችንን በቀጠልን ጊዜ፣ ቀጥታ ወደ ቆስ ከተማ አመራን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ ከተማ፣ ከዚያም ወደ ጳጥራ ከተማ ሄድን።
\v 2 ወደ ፊንቄ የሚሻገር መርከብ ባገኘን ጊዜም ተሳፍረን መጓዝ ጀመርን።
\s5
\v 3 የቆጵሮስን ደሴት ከሩቅ ባየን ጊዜ፣ ወደ ግራ ትተናት በባሕር ወደ ሶርያ ተጓዝን፤ መርከብዋ ጭነቷን የምታራግፈው በዚያ ስለ ነበር፣ ጢሮስ ወደብ ላይ ደረስን።
\v 4 ደቀ መዛሙርቱን ካገኘን በኋላም፣ በዚያ ሰባት ቀን ተቀመጥን። እነዚህም ደቀ መዛሙርት ጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይገባ በመንፈስ ቅዱስ ተናገሩት።
\s5
\v 5 የምንቈይበት ጊዜ ሲገባደድ፣ ተነሥተን ጕዞአችንን ቀጠልን። ሁሉም፣ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ከከተማ እስክንወጣ ድረስ በመንገዳችን ሸኙን። ከዚያም እወደቡ ላይ ተንበርክከን ጸለይን፤ እርስ በርስም ተሰነባበትን።
\v 6 እኛ በመርከቡ ተሳፈርን፤ እነርሱም ወደ ቤታቸው ተመልሰው ሄዱ።
\s5
\v 7 ከጢሮስ የተነሣንበትን ጕዞ በጨረስን ጊዜ፣ አካ ደረስን። በዚያም ወንድሞችን አገኘንና አንድ ቀን ከእነርሱ ጋር ቈየን።
\v 8 በሚቀጥለው ቀን ከዚያ ተነሥተን ወደ ቂሣርያ ሄድን። ከዚያም ከሰባቱ አንዱ ወደ ሆነው፣ ወደ ወንጌል ሰባኪው ወደ ፊልጶስ ቤት ገብተን ከእርሱ ጋር ሰነበትን።
\v 9 ይህም ሰው ትንቢት የሚናገሩ አራት ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት።
\s5
\v 10 የተወሰኑ ቀናት እንደ ተቀመጥንም፣ አጋቦስ የሚሉት ነቢይ ከይሁዳ ወደ ነበርንበት ወረደ።
\v 11 ወደ እኛም መጥቶ፣ የጳውሎስን መታጠቂያ ወሰደ፤ የገዛ ራሱን እጆችና እግሮችም አስሮ፣ “መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ ‘በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት እንደዚህ አድርገው ያስሩታል፤ አሳልፈውም ለአሕዛብ እጅ ይሰጡታል’” አለ።
\s5
\v 12 እነዚህን ነገሮች በሰማን ጊዜ፣ እኛና በዚያ ስፍራ የሚኖሩ ሰዎችም ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይወጣ ለመንነው።
\v 13 ጳውሎስም፣ “እያለቀሳችሁ ልቤን የምትሰብሩት ምን ማድረጋችሁ ነው? እኔኮ መታሰር ብቻ ሳይሆን፣ ለጌታችን ለኢየሱስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞት ዝግጁ ነኝ” ብሎ መለሰ።
\v 14 ጳውሎስ ምክር ለመቀበል እንዳልፈለገ በተረዳን ጊዜ፣ “የጌታ ፈቃድ ይሁን” ብለን መለመኑን አቆምን።
\s5
\v 15 ከእነዚህ ቀናት በኋላ፣ እኛም የጕዞ ዕቃዎቻችንን ይዘን ወደ ኢየሩሳሌም ወጣን።
\v 16 ደግሞም ከቂሣርያ የነበሩ አንዳንድ ደቀ መዛሙርት ከእኛ ጋራ መጡ። ምናሶን የሚባለውንም ሰው ይዘውት መጡ፤ እርሱም የቆጵሮስ ሰው፣ ወደ ፊት ከእርሱ ጋር እንድንቀመጥ የታሰበ የቀድሞ ደቀ መዝሙር ነበረ።
\s5
\v 17 ኢየሩሳሌም በደረስን ጊዜ፣ ወንድሞች በደስታ ተቀበሉን።
\v 18 በማግስቱም ጳውሎስ ከእኛ ጋር ወደ ያዕቆብ ሄደ፤ ሽማግሌዎችም ሁሉ በዚያ ነበሩ።
\v 19 ሰላምታ ካቀረበላቸው በኋላ፣ እግዚአብሔር በእርሱ አገልግሎት አማካይነት በአሕዛብ መካከል የሠራቸውን ነገሮች አንድ በአንድ ዘርዝሮ ነገራቸው።
\s5
\v 20 እነርሱም ስለ ሰሙት ነገር እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ እንዲህም አሉት፤ “ወንድም ሆይ፣ ከአይሁድ ያመኑት ስንትና ስንት ሺህ እንደ ሆኑ ታያለህ። ሁላቸውም ሕግን ለመጠበቅ የወሰኑ ናቸው።
\v 21 በአሕዛብ መካከል የሚኖሩት አይሁድ ሁሉ ሙሴን እንዲተዉ እንደምታስተምራቸው፣ ልጆቻቸውንም እንዳይገርዙ እንደምትነግራቸውና በቀድሞው ልማድ እንዳይሄዱ እንደምታደርግ፣ ስለ አንተ ተነግሮአቸዋል።
\s5
\v 22 እንግዲህ ምን እናድርግ? መምጣትህን እንደሚሰሙ ርግጠኞች ነን።
\v 23 ስለዚህ አሁን እኛ የምንልህን አድርግ፤ ስለት ያለባቸው አራት ሰዎች እዚህ አሉን።
\v 24 እነዚህን ሰዎች ይዘህ ከእነርሱ ጋር ራስህን አንጻ፤ ጠጕራቸውን ለመላጨት የሚያስፈልጋቸውንም ገንዘብ ክፈልላቸው። በዚህም ስለ አንተ የተነገራቸው ሁሉ ውሸት እንደ ሆነ ያውቃሉ፤ አንተም ልማዱን ጠብቀህ እንደምትኖር ይረዳሉ።
\s5
\v 25 ስላመኑ አሕዛብ ግን ለጣዖት ከተሠዋ፣ ከደም፣ ከታነቀ፣ እንዲሁም ከዝሙት ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጽፈን ትእዛዝ ሰጥተናል።”
\v 26 ጳውሎስም ሰዎቹን ይዞ በሚቀጥለው ቀን ራሱን ከእነርሱ ጋር እያነጻ ወደ መቅደሱ ገባ፤ ይኸውም መሥዋዕቱ ስለ እያንዳንዳቸው እስከሚቀርብ ድረስ መንጻቱ የሚወስደውን ጊዜ በመንገር ነው።
\s5
\v 27 ሰባቱ ቀናት ወደ መገባደዱ ሲቃረቡ፣ ከእስያ የመጡ አንዳንድ አይሁድ ጳውሎስን በቤተ መቅደስ ውስጥ አዩት፤ ሕዝቡንም ሁሉ በእርሱ ላይ አነሣሡ፤ ያዙትም።
\v 28 እንዲህም እያሉ ይጮኹ ነበር፤ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፣ ርዱን። ሰዎችን ሁሉ ከሕዝቡ፣ ከሕጉና ከዚህ ስፍራ ጋር የማይስማሙ ነገሮችን የሚያስተምር ይህ ሰው ነው። ከዚህም በላይ የግሪክን ሰዎች ወደ ቤተ መቅደሱ በማስገባት፣ ይህን ቅዱስ ስፍራ የሚያረክሰውም እርሱ ነው።”
\v 29 ምክንያቱም ቀደም ሲል የኤፌሶኑን ሰው ጥሮፊሞስን ከእርሱ ጋር በከተማ ስላዩት፣ ጳውሎስ ወደ ቤተ መቅደስ ያስገባው መሰላቸው።
\s5
\v 30 ከተማውም ሁሉ ታወከ፤ ሕዝቡም በአንድነት ተሰባስበው ጳውሎስን ያዙት፤ ጐትተውም ከቤተ መቅደስ አስወጡት፤ በሮቹም ወዲያው ተዘጉ።
\v 31 ሊገድሉት ሲሞክሩም፣ መላዋ ኢየሩሳሌም እጅግ ታውካለች የሚል ወሬ ወደ ጭፍሮቹ አለቃ ደረሰ።
\s5
\v 32 እርሱም ወዲያው ወታደሮችንና የመቶ አለቆችን ይዞ ሕዝቡ ወዳሉበት በሩጫ ወረደ። ሰዎቹም ሻለቃውንና ወታደሮችን ሲያዩ፣ ጳውሎስን መደብደብ አቆሙ።
\v 33 ከዚያም ሻለቃው ወደ ጳውሎስ ሄዶ ያዘው፤ በሁለት ሰንሰለቶች እንዲታሰርም አዘዘ። ስለ ማንነቱና ስለ ፈጸመው ድርጊትም ጠየቀው።
\s5
\v 34 ከሕዝቡም ግማሾቹ ስለ አንድ ነገር ሲጮኹ፣ የቀሩት ደግሞ ስለ ሌላ ነገር ይንጫጩ ነበር። ሻለቃውም ከጫጫታው ሁሉ የተነሣ፣ ስለ ምን እንደሚጮኹ እንኳ መለየት አልቻለም፤ ስለዚህ ጳውሎስን ወደ ወታደሮች ምሽግ እንዲያገቡት አዘዘ።
\v 35 ጳውሎስ ወደ መወጣጫው ደረጃ በደረሰ ጊዜ፣ ከሕዝቡ ረብሻ የተነሣ፣ ወታደሮቹ ተሸክመውት ሄዱ።
\v 36 ሕዝቡ “አስወግደው!” እያሉና እየጮኹ ከኋላ ይከተሉ ነበር።
\s5
\v 37 ጳውሎስም ወደ ምሽጉ ሊገባ ጥቂት ሲቀረው፣ ሻለቃውን፣ “አንድ ነገር እንድናገርህ ትፈቅድልኛለህ?” አለው። ሻለቃውም፣ “የግሪክ ቋንቋ መናገር ትችላለህ ወይ?
\v 38 አንተ ከዚህ በፊት ዐመፅ አስነሥተህ፣ አራት ሺህ ሰዎችን በማስሸፈት፣ ወደ ምድረ በዳ የገባህ ግብፃዊ አይደለህምን?” አለው።
\s5
\v 39 ጳውሎስም፣ “እኔስ በኪልቅያ ከምትገኘው ከጠርሴስ ከተማ የመጣሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ የታዋቂዋ ከተማ ዜጋ ነኝ። አንድ ነገር እለምንሃለሁ፤ ለሰዎቹ እንድናገር ፍቀድልኝ” አለው።
\v 40 ሻለቃው በፈቀደለት ጊዜም፣ ጳውሎስ መወጣጫ ደረጃው ላይ ቆሞ፣ በእጁ ወደ ሕዝቡ አመለከተ። ሕዝቡ ጸጥ እረጭ ሲልም፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
\s5
\c 22
\cl ምዕራፍ 22
\p
\v 1 “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፣ አሁን ስለ ራሴ ለእናንተ የማቀርበውን መከላከያ አድምጡኝ።”
\v 2 ሕዝቡም ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ሲያናግራቸው በሰሙ ጊዜ፣ ጸጥ አሉ። ጳውሎስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤
\s5
\v 3 “እኔ በኪልቅያዋ ጠርሴስ የተወለድሁ አይሁዳዊ ነኝ፤ የተማርሁትም በዚሁ ከተማ በገማልያል እግር ሥር ተቀምጬ ነው። የአባቶቻችንንም ጥብቅ የሕግ መንገድ በሚገባ ተምሬአለሁ። ዛሬ እናንተ ሁላችሁ እንደ ሆናችሁት፣ እኔም ለእግዚአብሔር ቀናተኛ ነኝ።
\v 4 ይህን መንገድ እስከ ሞት አሳድጄዋለሁ፤ ሴቶችንና ወንዶችን አስሬ ለወኅኒ አሳልፌ ሰጠኋቸው።
\v 5 ደግሞም ከእነርሱ ደብዳቤ ተቀብዬ፣ በደማስቆ ስለሚገኙ ወንድሞች ወደዚያ ለመጓዝ እንደ ተነሣሁ፣ ሊቀ ካህናቱና ሽማግሌዎች ሁሉ መመስከር ይችላሉ። ከዚያ መንገድ የሆኑትን አስሬ ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣትና ለማስቀጣት ስንቀሳቀስም ነበር።
\s5
\v 6 እየተጓዝሁ ወደ ደማስቆ ስቃረብ፣ ቀትር ላይ ድንገት ታላቅ ብርሃን ከሰማይ በዙሪያዬ በራ፤
\v 7 እኔም መሬት ላይ ወደቅሁ፤ ከዚያም፣ 'ሳውል፣ ሳውል፣ ለምን ታሳድደኛለህ?' የሚለኝን ድምፅ ሰማሁ።
\v 8 እኔም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ?' ብዬ መለስሁለት። እርሱም፣ 'አንተ የምታሳድደኝ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ' አለኝ።
\s5
\v 9 ከእኔ ጋር የነበሩትም ብርሃኑን አዩ፤ ነገር ግን የተናገረኝን ድምፅ አልሰሙም።
\v 10 እኔም፣ ‘ጌታ ሆይ፣ ምን ላድረግ? አልሁ። ጌታም፣ ‘ተነሥና ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ማድረግ የሚገባህን ሁሉ እዚያ ይነግሩሃል’ አለኝ።
\v 11 ከዚያ ብርሃን ድምቀት የተነሣም አንዳች ማየት አልቻልሁም፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር በነበሩት ሰዎች እጅ እየተመራሁ ወደ ደማስቆ ገባሁ።
\s5
\v 12 ለሕጉ በትጋት የሚታዘዝና በዚያ የሚኖሩ አይሁድ ሁሉ መልካምነቱን የመሰከሩለት፣ ሐናንያ የሚባል አንድ ሰው አገኘሁ።
\v 13 እርሱም ወደ እኔ መጥቶ አጠገቤ በመቆም፣ ‘ወንድሜ ሳውል፣ ዐይንህን ገልጠህ እይ’ አለኝ። እኔም በዚያው ቅጽበት አየሁት።
\s5
\v 14 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘ቅዱሱን እንድታይና ከገዛ አፉ የሚወጣውን ድምፅ እንድትሰማ፣ የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን እንድታውቅ መርጦሃል፤
\v 15 ምክንያቱም ስለ አየኸውና ስለ ሰማኸው ነገር ለሰዎች ሁሉ ምስክር ትሆንለታለህ።
\v 16 ስለዚህ አሁን ለምን ታመነታለህ? ተነሥ፤ ስሙን እየጠራህ ተጠመቅና ከኃጢአትህ ታጠብ።’
\s5
\v 17 ወደ ኢየሩሳሌም ከተመለስሁ በኋላም፣ በቤተ መቅደስ እየጸለይሁ ሳለሁ፣ ሸለብ አድርጎኝ ሰመመን ውስጥ ገባሁ።
\v 18 እርሱም፣ ‘ከኢየሩሳሌም ቶሎ ብለህ ውጣ፤ ምክንያቱም ስለ እኔ የምትናገረውን ምስክርነትህን አይቀበሉህም’ ሲለኝ አየሁ።
\s5
\v 19 እኔም እንዲህ አልሁ፤ ‘ጌታ ሆይ፣ በምኵራብ ሁሉ በአንተ ያመኑትን ሳስርና ስደበድብ እንደ ነበርሁ እነርሱ ራሳቸው ያውቃሉ።
\v 20 የሰማዕትህን የእስጢፋኖስንም ደም በሚያፈሱበት ጊዜ፣ በመስማማት እዚያው ቆሜ ነበር፤ የገዳዮቹንም ልብሶች እጠብቅ ነበር።’
\v 21 እርሱ ግን፣ ‘ተነሥተህ ሂድ፤ ምክንያቱም ወደ አሕዛብ እልክሃለሁ’ አለኝ።”
\s5
\v 22 ሕዝቡም እስከዚህ ድረስ እንዲናገር ፈቀዱለት፤ ከዚህ በኋላ ግን፣ “እንደዚህ ያለ ሰው ከምድር ይወገድ፤ በሕይወትም ይኖር ዘንድ አይገባውም” እያሉ ይጮኹ ጀመር።
\v 23 እየጮኹም ሳለ፣ ልብሳቸውን እያወለቁና አቧራም ወደ ላይ ይበትኑ ነበር፤
\v 24 ሻለቃውም ጳውሎስን ወደ ወታደራዊው ምሽግ እንዲወስዱት አዘዘ። እርሱ ራሱ ሕዝቡ ለምን እንደዚያ እንደ ጮኹበት ለማወቅ ስለ ፈለገ፣ እየገረፉ ጳውሎስን እንዲመረምሩት ትእዛዝ ሰጠ።
\s5
\v 25 ሰዎቹ በጠፍር ወጥረው ባሰሩት ጊዜ፣ ጳውሎስ በአጠገቡ የቆመውን መቶ አለቃ፣ “ሮማዊ የሆነን ሰው፣ ገና ሳይፈረድበት እንዲህ መግረፍህ ሕጋዊ ነው ወይ?” አለው።
\v 26 መቶ አለቃውም ይህን ሲሰማ፣ ወደ ሻለቃው ሄዶ፣ “ምን ማድረግህ ነው? ሰውየውኮ የሮማ ዜጋ ነው” በማለት ነገረው።
\s5
\v 27 ሻለቃውም መጥቶ፣ “አንተ የሮማ ዜጋ ነህን? እስቲ ንገረኝ” አለው። ጳውሎስም፣ “አዎ፣ ነኝ” አለ።
\v 28 ሻለቃውም፣ “እኔኮ ይህን ዜግነት ያገኘሁት በብዙ ገንዘብ ነው” ብሎ መለሰለት። ጳውሎስም፣ “እኔ ግን ከመወለዴ ጀምሮ ሮማዊ ነኝ” አለ።
\v 29 ሊመረምሩት የመጡ ሰዎችም ወዲያው ትተውት ሄዱ። ሻለቃውም ጳውሎስ የሮም ዜጋ መሆኑን ባወቀ ጊዜ ፈራ፤ ምክንያቱም ጳውሎስን አሳስሮት ነበር።
\s5
\v 30 በማግስቱም ሻለቃው፣ አይሁድ ጳውሎስን የከሰሱበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅ ፈለገ። ስለዚህ ጳውሎስን ከእስራት አስፈታውና የካህናት አለቆችና ሸንጎው በሙሉ እንዲሰበሰቡ አዘዘ። ከዚያም ጳውሎስን አስመጥቶ በመካከላቸው አቆመው።
\s5
\c 23
\cl ምዕራፍ 23
\p
\v 1 ጳውሎስም ትኵር አድርጎ ወደ ሸንጎው በመመልከት፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እኔ እስካሁን ድረስ፣ በእግዚአብሔር ፊት በንጹሕ ኅሊና ሁሉ ኖሬአለሁ” አለ።
\v 2 ሊቀ ካህናቱ ሐናንያም ጳውሎስ አጠገብ የነበሩትን ሰዎች አፉን እንዲመቱት አዘዛቸው።
\v 3 በዚህ ጊዜ ጳውሎስ፣ “አንተ ነጭ ቀለም የተቀባህ ግድግዳ፣ እግዚአብሔር ይመታሃል። በሕጉ መሠረት ልትፈርድብኝ የተቀመጥህ፣ ሕጉን ጥሰህ እኔ እንድመታ ታዛለህን?” አለው።
\s5
\v 4 በአጠገቡ ቆመው የነበሩትም፣ “የእግዚአብሔርን ሊቀ ካህናት እንዴት ትሰድባለህ?” አሉ።
\v 5 ጳውሎስም፣ “ወንድሞች ሆይ፣ ሊቀ ካህናት መሆኑን አላወቅሁም፤ ምክንያቱም፣ በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል ከአፍህ አይውጣ ተብሎ ተጽፎአል።”
\s5
\v 6 ጳውሎስም ከሸንጎው አባላት ከፊሉ ሰዱቃውያን፣ ሌሎቹም ፈሪሳውያን መሆናቸውን ሲያይ፣ በሸንጎ መካከል ሆኖ በከፍተኛ ድምፅ፣ “ወንድሞች ሆይ፣ እኔ የፈሪሳዊ ልጅ የሆንሁ፣ ፈሪሳዊ ነኝ። ፍርድ ፊት የቀረብሁትም የሙታን ትንሣኤ እንዳለ ስለማምን ነው” አላቸው።
\v 7 ይህን በተናገረ ጊዜ፣ በፈሪሳውያንና በሰዱቃውያን መካከል ክርክር ተነሣ፤ ጉባኤውም ተከፋፈለ።
\v 8 ምክንያቱም ሰዱቃውያን ትንሣኤ ሙታን የለም፤ መላእክትም የሉም፤ መናፍስትም የሉም ስለሚሉና፣ ፈሪሳውያን ግን እነዚህ ሁሉ አሉ ስለሚሉ ነው።
\s5
\v 9 በዚህ ጊዜ፣ ታላቅ ውካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ ጸሐፍትም ተነሥተው፣ “በዚህ ሰው ላይ አንድም ጥፋት አላገኘንም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት እንደ ሆነስ ማን ያውቃል?” በማለት ተከራከሩ።
\v 10 ክርክሩም እየጋለ ሲሄድ፣ ጳውሎስን ይዘው እንዳይቦጫጭቁት ሻለቃው ፈራ፤ ስለዚህ ወታደሮቹ ወርደው ጳውሎስን በኀይል ይዘው ከሸንጎ አባላት መካከል እንዲወስዱትና ወደ ምሽጉ አምጥተው እንዲያስገቡት አዘዘ።
\s5
\v 11 በሚቀጥለውም ሌሊት ጌታ በጳውሎስ አጠገብ ቆሞ፣ “አትፍራ፤ በኢየሩሳሌም ስለ እኔ እንደ መሰከርኸው፣ በሮማም ደግሞ ልትመሰክር ይገባሃል” አለው።
\s5
\v 12 በነጋም ጊዜ፣ አንዳንድ አይሁድ ጳውሎስን ሳንገድል እኽል ውሃ አንቀምስም በማለት በመሐላ ተስማሙ።
\v 13 ይህን የዶለቱትም ሰዎች ቍጥር ከአርባ በላይ ነበር።
\s5
\v 14 ወደ ካህናት አለቆችና ወደ ሽማግሌዎችም ሄደው እንዲህ አሉ፤ “ጳውሎስን እስከምንገድል ድረስ፣ እኽል እንዳንቀምስ በታላቅ ርግማን ተማምለናል።
\v 15 ስለዚህ አሁን ሻለቃው ጳውሎስን ወደ እናንተ እንዲያወርደውና እናንተ የእርሱን ጉዳይ ይበልጥ በትክክል እንደምታዩለት አስመስላችሁ፣ ሸንጎው ለሻለቃው ያመልክት። በእኛ በኩል ግን እዚህ ከመምጣቱ በፊትም ቢሆን ልንገድለው ዝግጁ ነን።”
\s5
\v 16 የጳውሎስ እኅት ወንድ ልጅም ጳውሎስን አድፍጠው እንደሚጠብቁት ዐወቀ፤ ሄዶም ወደ ምሽጉ ገብቶ ለጳውሎስ ነገረው።
\v 17 ጳውሎስም አንዱን መቶ አለቃ ጠራና፣ “ይህን ወጣት ወደ ሻለቃው ውሰደው፤ የሚናገረው ነገር አለውና” አለ።
\s5
\v 18 መቶ አለቃውም ወጣቱን ይዞ ወደ ሻለቃው አመጣውና እንዲህ አለ፤ “ጳውሎስ የተባለው እስረኛ ወደ ራሱ ጠርቶኝ፣ ይህን ወጣት ወደ አንተ እንዳቀርበው ለመነኝ፤ ወጣቱ ለአንተ የሚነግርህ ነገር አለው።”
\v 19 ሻለቃውም እጁን ይዞ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ ወስዶት፣ “ልትነግረኝ የፈለግኸው ነገር ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀው።
\s5
\v 20 ወጣቱም እንዲህ አለ፤ “አይሁድ ስለ ጉዳዩ ትክክለኛነት ይበልጥ ለመረዳት የፈለጉ አስመስለው፣ ነገ ጳውሎስን ወደ ሸንጎው እንድታወርደው አንተን ለመለመን ተስማምተዋል።
\v 21 ነገር ግን እሺ አትበላቸው፤ ምክንያቱም ከአርባ በላይ የሚሆኑ ሰዎች አድፍጠው እየጠበቁት ነው። ጳውሎስን ካልገደሉም እኽል ውሃ እንደማይቀምሱ ተማምለዋል። አሁንም እንኳ የአንተን መስማማት እየጠበቁ ነው እንጂ ዝግጁ ናቸው።”
\s5
\v 22 ስለዚህ ሻለቃው ወጣቱን ልጅ፣ “ስለ እነዚህ ነገሮች ለእኔ መግለጥህን ለማንም እንዳትናገር” ብሎ ካስጠነቀቀው በኋላ፣ አሰናበተው።
\v 23 ከመቶ አለቆቹም ሁለቱን ወደ ራሱ ጠርቶ፣ “እስከ ቄሣርያ ለመሄድ የሚችሉ ሁለት መቶ ወታደሮችን፣ ሰባ ፈረሰኞችንና ሁለት መቶ ባለ ጦሮችን አዘጋጁ፤ ከሌሊቱም በሦስተኛው ሰዓት ትንቀሳቀሳላችሁ” አላቸው።
\v 24 ጳውሎስ ወደ ሀገረ ገዡ፣ ወደ ፊልክስ የሚሄድበትንም ከብት እንዲያዘጋጁና በሰላም እንዲያደርሱት አዘዛቸው።
\s5
\v 25 ከዚያም እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፈ፤
\v 26 “ከቀላውዴዎስ ሉስዮስ፣ ወደ ተከበረው ሀገረ ገዢ ፊልክስ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን።
\v 27 ይህን ሰው አይሁድ ይዘው ሊገድሉት ሲሉ፣ ከወታደሮች ጋር ደርሼባቸው አዳንሁት፤ ይህን ያደረግሁትም ሮማዊ ዜጋ መሆኑን ስለ ተረዳሁ ነው።
\s5
\v 28 ለምን እንደ ከሰሱት ለማወቅ ስለ ፈለግሁም፣ ወደ ሸንጎአቸው ይዤው ወረድሁ።
\v 29 የገዛ ራሳቸውን ሕግ በሚመለከት በተነሣ ጥያቄ ምክንያት ተከሶ እንጂ፣ ሞት ወይም እስራት የሚገባው ክስ እንደሌለበት ዐውቄአለሁ።
\v 30 በዚህ ሰው ላይ ሤራ እንደ ተካሄደበትም ደርሼበታለሁ፤ ስለዚህም ፈጥኜ ወደ አንተ ላክሁት፤ ከሳሾቹም በእርሱ ላይ ያላቸውን ክስ አንተ ባለህበት እንዲያቀርቡ መመሪያ ሰጥቻቸዋለሁ። በደኅና ሰንብት።”
\s5
\v 31 ስለዚህ ወታደሮቹ በታዘዙት መሠረት፣ ጳውሎስን ይዘው በሌሊት ወደ አንቲጳጥሪስ ወሰዱት።
\v 32 በሚቀጥለውም ቀን፣ አብዛኞቹ ወታደሮች ፈረሰኞቹን ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ ትተው፣ ወደ ምሽግ ተመለሱ።
\v 33 ፈረሰኞቹም ቂሣርያ በደረሱና ደብዳቤውን ለሀገር ገዡ ሲሰጡ፣ ጳውሎስንም ለእርሱ አስረከቡት።
\s5
\v 34 ሀገረ ገዡም ደብዳቤውን ካነበበ በኋላ፣ ጳውሎስ ከየትኛው አውራጃ እንደ መጣ ጠየቀ፤ ከኪልቅያ እንደ መጣ ባወቀ ጊዜም፣
\v 35 “ከሳሾችህ ወደዚህ ሲመጡ፣ በሚገባ እሰማሃለሁ” አለው። ከዚያም በኋላ፣ በሄሮድስ ቅጥር ግቢ እንዲጠብቁት አዘዘ።
\s5
\c 24
\cl ምዕራፍ 24
\p
\v 1 ከዐምስት ቀናት በኋላ፣ ሊቀ ካህናቱ ሐናንያ፣ አንዳንድ ሽማግሌዎችና ጠርጠሉስ የተባለ አንድ የሕግ ባለ ሙያ ወደዚያ ሄዱ። እነዚህ ሰዎች ለገዡ አመልክተው ጳውሎስን ከሰሱት።
\v 2 ጳውሎስ በገዡ ፊት በቆመ ጊዜ፣ ጠርጠሉስ ይከሰው ጀመር፤ ገዡንም እንዲህ አለው፤ «ክቡር ፊልክስ ሆይ፣ በአንተ ምክንያት ብዙ ሰላም አግኝተናል፤ የአንተ ማስተዋልም ለሕዝባችን ጥሩ መሻሻልን ያመጣለታል፤
\v 3 ስለ ሆነም አንተ የምታደርገውን ሁሉ በፍጹም ምስጋና እንቀበለዋለን።
\s5
\v 4 ብዙ እንዳላቈይህ፣ በቸርነትህ በዐጭሩ እንድትሰማኝ እለምንሃለሁ።
\v 5 ይህ ሰው ቅንቅን ሆነና በመላው ዓለም ላይ ያሉትን አይሁዶች ሲያሳምፅ አግኝተነዋልና። የናዝራውያን ወገን መሪ ነው።
\v 6 ቤተ መቅደሱንም እንኳ ሊያረክስ ሞክሯል፤ ስለዚህ ያዝነው።
\s5
\v 7 ነገር ግን ወታደራዊው መኰንን ሉስዮስ መጥቶ፣ ጳውሎስን በኀይል ከእጃችን ወሰደው።
\v 8 አንተም ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ጳውሎስን በምትጠይቀው ጊዜ ለምን እንደምንከሰው ልታውቅ ትችላለህ።»
\v 9 አይሁድም አንድ ላይ ሆነው ጳውሎስን ከሰሱት፤ ነገሮቹም ሁሉ እውነት መሆናቸውን ተናገሩ።
\s5
\v 10 ገዡ ግን እንዲናገር ሲጠይቀው፣ ጳውሎስ እንዲህ ብሎ መልስ ሰጠ፤ «አንተ ለብዙ ዓመታት ለዚህ ሕዝብ ፈራጅ መሆንህን ዐውቃለሁ፤ ስለ ሆነም ደስ እያለኝ ስለ ራሴ እገልጽልሃለሁ።
\v 11 ለማምለክ ወደ ኢየሩሳሌም ከወጣሁ ከዐሥራ ሁለት ቀን እንደማይበልጥ አንተ መርምረህ ልትደርስበት ትችላለህ፤
\v 12 እነርሱ በቤተ መቅደስ ባገኙኝ ጊዜም፣ ከማንም ጋር አልተከራከርሁም፤ በምኵራቦችም ሆነ በከተማው ሕዝብን አልቀሰቀስሁም፤
\v 13 አሁን በእኔ ላይ የሚያቀርቡት ክስ እውነተኛ ለመሆኑ ማስረጃ የላቸውም።
\s5
\v 14 ነገር ግን ለአንተ ይህን እነግርሃለሁ፤ እነርሱ የእምነት ክፍል ብለው እንደሚጠሩት እኔም በዚያ ተመሳሳይ መንገድ የአባቶቻችንን አምላክ አገለግላለሁ። በሕግና በነቢያት ለተጻፈው ሁሉ የታመንሁ ነኝ።
\v 15 ልክ እነዚህ ሰዎች ደግሞ እንደሚጠብቁት፣ ስለሚመጣው የሙታን ማለትም የጻድቃንና የኀጥአን ትንሣኤ በእግዚአብሔር ላይ እምነት አለኝ።
\v 16 በዚህም በሁሉም ነገር በእግዚአብሕርና በሰዎች ፊት ነቀፋ የሌለበት ኅሊና እንዲኖረኝ እሠራለሁ።
\s5
\v 17 ከብዙ ዓመታትም በኋላ ለሕዝቤ ርዳታና የገንዘብ ስጦታ ለመስጠት መጣሁ።
\v 18 ይህንም ባደረግሁ ጊዜ ከእስያ የሆኑ አንዳንድ አይሁድ፣ ሕዝብም ጩኸትም ሳይኖር በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዓት ላይ አገኙኝ።
\v 19 እነዚህ ሰዎች በእኔ ላይ አንዳች ነገር ካላቸው፣ በፊትህ መጥተው ክሱን ሊያቀርቡብኝ ይገባቸዋል።
\s5
\v 20 አለበለዚያም፣ እነዚሁ ሰዎች በአይሁድ ሸንጎ ፊት በቆምሁ ጊዜ፣ ምን እንዳጠፋሁ መናገር ነበረባቸው፤
\v 21 «ዛሬ አንተ የምትፈርድብኝ ስለ ሙታን ትንሣኤ ነው» ብዬ በመካከላቸው ቆሜ ድምፄን ከፍ በማድረግ ከተናገርሁት ከዚህ አንድ ነገር በቀር፣ ምንም የተናገርሁት የለም።
\s5
\v 22 ፊልክስ ግን ስለ መንገዱ በሚገባ ያውቅ ነበር፤ ስለ ሆነም፣ «አዛዡ ሉስዮስ ከኢየሩሳሌም በሚወርድበት ጊዜ ለክሳችሁ ውሳኔ እሰጣለሁ» ብሎ አይሁድን እንዲጠብቁ አደረጋቸው።
\v 23 ከዚያም ጳውሎስን እንዲጠብቀው፣ ነገር ግን እንዲያደላለት፣ እርሱንም ከመርዳት ወይም ከመጎብኘት ማንም ወዳጆቹን እንዳይከለክል የመቶ አለቃውን አዘዘው።
\s5
\v 24 ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ፊልክስ ድሩሲላ ከምትባል አይሁዳዊት ሚስቱ ጋር ተመልሶ መጣ፤ ጳውሎስንም በማስጠራት በክርስቶስ ኢየሱስ ስላለው እምነት ከእርሱ ሰማ።
\v 25 ነገር ግን ጳውሎስ ስለ ጽድቅ፣ ራስን ስለ መግዛት፣ ስለሚመጣውም ፍርድ ከእርሱ ጋር በተነጋገረ ጊዜ፣ ፊልክስ ፈራ፤ «ለአሁኑ ሂድ፤ እንደ ገና ጊዜ ሲኖረኝ ግን፣ አስጠራሃለሁ» አለው።
\s5
\v 26 በዚሁ ጊዜ፣ ጳውሎስ ገንዘብ ይሰጠኛል ብሎ ፊልክስ ተስፋ ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ ብዙ ጊዜ እያስጠራ ያነጋግረው ነበር።
\v 27 ከሁለት ዓመት በኋላ ግን፣ ከፊልክስ ቀጥሎ ጶርቅዮስ ፊስጦስ ገዢ ሆነ፤ ፊልክስ ግን አይሁድን ለማስደሰት ፈልጎ ጳውሎስን በጥበቃ ሥር እንዲቆይ አደረገ።
\s5
\c 25
\cl ምዕራፍ 25
\p
\v 1 ፊስጦስም ወደ ክፍለ ሀገሩ ገባ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ።
\v 2 የካህናት አለቃውና ታዋቂ የሆኑት አይሁድ ጳውሎስን ፊስጦስ ላይ ከሰሱት፤ ለፊስጦስም በኀይል ተናገሩ።
\v 3 በመንገድም ላይ ሊገድሉት ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስጠራው ፊስጦስን ለመኑት።
\s5
\v 4 ፊስጦስ ግን መልሶ ጳውሎስ በቂሣርያ እስረኛ እንደ ሆነ፣ እርሱ ራሱም ወደዚያ እንደሚመለስ ተናገረ።
\v 5 “ስለዚህ፣ የሚችሉ ከእኛ ጋር ወደዚያ መሄድ አለባቸው። ሰውየው ያጠፋው ነገር ካለ፣ ክሰሱት” አለ።
\s5
\v 6 ፊስጦስም ስምንት ወይም ዐሥር ቀን ከቆየ በኋላ፣ ወደ ቂሣርያ ወረደ። በማግስቱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ጳውሎስን ወደ እርሱ እንዲያመጡት አዘዘ።
\v 7 ጳውሎስም በደረሰ ጊዜ፣ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ በአጠገቡ ቆሙ፤ በማስረጃ ማረጋገጥ ያልቻሉትን ብዙ ከባድ ክስም አቀረቡ።
\v 8 ጳውሎስ፣ “በአይሁድ ስምም ላይ፣ በቤተ መቅደሱም ላይ፣ በቄሣርም ላይ በደል አልፈጸምሁም” ብሎ ራሱን ተከላከለ።
\s5
\v 9 ፊስጦስ ግን አይሁድን ለማስደሰት ፈለገ፤ ስለሆነም፣ “እስከ ኢየሩሳሌም መውጣትና ስለ እነዚህ ነገሮች በዚያ ፍርድ እንድሰጥህ ትፈልጋለህን?” ብሎ ጳውሎስን ጠየቀው።
\v 10 ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “ፍርድ ሊሰጠኝ በሚገባኝ በቄሣር የፍርድ ወንበር ፊት እቆማለሁ። አንተም ደግሞ በሚገባ እንደምታውቀው፣ አንድንም አይሁዳዊ አልበደልሁም።
\s5
\v 11 ብበድልና ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ ቢሆን እንኳ፣ አልሞትም አልልም። እነርሱ በእኔ ላይ የሚያቀርቡት ክስ ከንቱ ከሆነ ግን፣ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም። ለቄሣር ይግባኝ ብያለሁ።”
\v 12 ከዚያም ፊስጦስ ከሸንጎው ጋር ተነጋግሮ፣ “ለቄሣር ይግባኝ ብለሃልና ወደ ቄሣር ትሄዳለህ” ብሎ መለሰ።
\s5
\v 13 ከጥቂት ቀናትም በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ፊስጦስን ለመጐብኘት ቂሣርያ ደረሱ።
\v 14 ንጉሥ አግሪጳ በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፣ ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለንጉሡ አቀረበ፤ እንዲህም አለ፤ “ፊልክ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ።
\v 15 እኔ በኢየሩሳሌም በነበርሁ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች ክስ መሥርተውበት ለእኔ አመለከቱ፤ እንድፈርድበትም ለመኑኝ።
\v 16 ለዚህም፣ የተከሰሰው ሰው በከሳሾቹ ፊት ቀርቦ ለተከሰሰበት ነገር እንዲከላከል ዕድል ሳይሰጠው አንድን ሰው አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ አይደለም ብዬ መልስ ሰጠሁ።”
\s5
\v 17 ስለዚህ፣ እነርሱ በአንድ ላይ ወደዚህ በመጡ ጊዜ፣ አልዘገየሁም፤ ነገር ግን በማግስቱ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ ሰውዬውን እንዲያመጡት አዘዝሁ።
\v 18 ከሳሾቹ ቆመው በከሰሱት ጊዜ፣ ካቀረቡበት ክሶች ማንኛቸውም ከባድ አይደሉም ብዬ ዐሰብሁ።
\v 19 ይልቁንም ስለ ገዛ ራሳቸው ሃይማኖትና ጳውሎስ ሕያው ነው ስለሚለው ሞቶ ስለ ነበረው ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ነበር።
\v 20 ይህን ጉዳይ እንዴት እንደምመረምር ግራ ገብቶኝ ነበር፤ ስለ እነዚህ ነገሮችም በዚያ ለመፋረድ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ እንደ ሆነ ጳውሎስን ጠየቅሁት።
\s5
\v 21 ጳውሎስ ግን የንጉሠ ነገሥቱን ውሳኔ እስኪያገኝ፣ በዘብ እንዲጠበቅ ይግባኝ ባለ ጊዜ፣ ወደ ቄሣር እስክሰደው ድረስ በጥበቃ ሥር እንዲሆን አዘዝሁት።”
\v 22 አግሪጳ፣ “እኔ ደግሞ ይህን ሰው ልሰማው እፈልጋለሁ” ብሎ ፊስጦስን አነጋገረው። ፊስጦስም፣ “ነገ ትሰማዋለህ” አለው።
\s5
\v 23 ስለ ሆነም፣ በማግስቱ፣ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ሥነ ሥርዓት ከወታደራዊ መኮንኖችና ከከተማዋ ታዋቂ ሰዎች ጋር ወደ አዳራሹ ገቡ። በፊስጦስ ትእዛዝም ጊዜ ጳውሎስን ወደ እነርሱ አመጡት።
\v 24 ፊስጦስም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ እዚህ ከእኛ ጋር ያላችሁትም ሰዎች ሁሉ፣ ይህን ሰው ተመልከቱት፤ በኢየሩሳሌምና እዚህም ያሉት የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ከእኔ ጋር ተማከሩ፤ ይህ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ በሕይወት መኖር የለበትም ብለውም ጮኹብኝ።
\s5
\v 25 እኔ ግን ለሞት የሚያበቃው ምንም በደል አለመፍጸሙን ዐወቅሁ፤ ነገር ግን ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ልሰደው ወሰንሁ።
\v 26 ሆኖም ለንጉሠ ነገሥቱ ለመጻፍ አሳማኝ ነገር የለኝም። በዚህ ምክንያት ስለ ጉዳዩ የምጽፈው ነገር እንዲኖረኝ፣ በተለይ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ወደ አንተ አምጥቼዋለሁ።
\v 27 አንድን እስረኛ መስደድና የቀረበበትን ክስም አለመግለጽ ለእኔ ምክንያታዊ ያልሆነ ይመስለኛልና።”
\s5
\c 26
\cl ምዕራፍ 26
\p
\v 1 አግሪጳም ጳውሎስን፣ «አንተ ለራስህ ተናገር» አለው። ከዚያም በኋላ፣ ጳውሎስ እጁን ዘርግቶ መከላከያውን አቀረበ።
\v 2 «ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ዛሬ በፊትህ አይሁድ ስለ ከፈቱብኝ ክስ ሁሉ መከላከያዬን ሳቀርብ ራሴን ደስተኛ አድርጌ እቈጥረዋለሁ፤
\v 3 ምክንያቱም በተለይ አንተ የአይሁድን ልማድና ጥያቄ ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ። ስለዚህ በትግዕሥት እንድታደምጠኝ እለምንሃለሁ።
\s5
\v 4 በእውነት ከልጅነቴ ጀምሮ በሕዝቤ መካከልና በኢየሩሳሌም እንዴት እንደ ኖርሁ አይሁድ ሁሉ ያውቃሉ።
\v 5 ከመጀመሪያው አንሥቶ እኔን ያውቁኛል፤ የሃይማኖታችን በጣም ወግ አጥባቂ ክፍል ፈሪሳዊ ሆኜ እንደ ኖርሁም ሊያምኑ ይገባል።
\s5
\v 6 አሁን እዚህ ለፍርድ የቆምሁት እግዚአብሔር ለአባቶቻችን የሰጠውን ተስፋ የምፈልግ በመሆኔ ነው።
\v 7 በዚህ ምክንያት ዐሥራ ሁለቱ ነገዶቻችን ቀንና ሌሊት በቅንነት እግዚአብሔርን ያገለግላሉ፤ እኛም ወደ እርሱ ለመድረስ ተስፋ እናደርጋለን። ንጉሥ ሆይ፣ አይሁድ እኔን የሚከሱኝ ስለዚህ ተስፋ ነው!
\v 8 እግዚአብሔር ሙታንን እንደሚያስነሣ አይታመንም ብላችሁ ለምን ታስባላችሁ?
\s5
\v 9 አንድ ጊዜ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስን ስም በመቃወም ብዙ ነገር ማድረግ አለብኝ ብዬ ዐሰብሁ።
\v 10 በኢየሩሳሌምም ይህንኑ አደረግሁ፤ ከምእመናን ብዙዎችን ወኅኒ እንዲገቡ አደረግሁ፤ ለዚህም ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተቀብዬ ነበር፤ በሚገደሉበት ጊዜም፣ ተስማምቻለው።
\v 11 ብዙ ጊዜም በምኵራቦች ሁሉ እንዲቀጡ አድርጌአለሁ፤ የስድብ ቃል እንዲናገሩም ጥረት አድርጌአለሁ። ምእመናኑን እጅግ እቈጣቸውና ሌሎች ከተሞች እንኳ አሳድዳቸው ነበር።
\s5
\v 12 ይህን እያደረግሁ፣ ከካህናት አለቆች ሥልጣንና ትእዛዝ ተቀብዬ ወደ ደማስቆ ሄድሁ፤
\v 13 ወደዚያ በመጓዝ ላይ እያለሁም ንጉሥ ሆይ፣ እኩለ ቀን ላይ ከፀሐይ ይልቅ የሚያበራ ብርሃን ከሰማይ አየሁ፤ በእኔና አብረውኝ ይጓዙ በነበሩት ሰዎች ዙሪያም አበራ።
\v 14 ሁላችንም በመሬት ላይ በወደቅን ጊዜ፣ በዕብራይስጥ ቋንቋ፣ «ሳውል፣ ሳውል፣ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይከፋብሃል» የሚል ድምፅ ሲናገረኝ ሰማሁ።
\s5
\v 15 እኔም፣ 'ጌታ ሆይ፣ አንተ ማን ነህ?' አልሁ። ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰልኝ፤ 'አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ።
\v 16 ተነሣና በእግርህ ቁም፤ እኔ የተገለጥሁልህ አሁን ስለ እኔ ስለምታውቃቸውና ኋላ ላይ ስለማሳይህ ነገሮች አገልጋዬና ምስክር እንድትሆን ልሾምህ ነው፤
\v 17 ወደ እነርሱ ከምልክህ ሕዝብና ከአሕዛብም አድንሃለሁ ፤
\v 18 ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሰይጣን ኃይልም ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ ይኸውም በእኔ በማመናቸው ለራሴ የለየኋቸው እነርሱ፣ ከእግዚአብሔር የኃጢአትን ይቅርታና ርስትን እንዲቀበሉ ነው።'
\s5
\v 19 ስለዚህ፣ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ለሰማያዊው ራእይ አልታዘዝም አላልሁም፤
\v 20 ነገር ግን መጀመሪያ በደማስቆ ላሉት፣ ከዚያም በኢየሩሳሌም፣ በመላው ይሁዳ፣ ደግሞም ለአሕዛብ ንስሓ እንዲገቡ፣ ወደ እግዚአብሔር ዘወር እንዲሉና ለንስሓ የሚገባ ሥራ እንዲሠሩ ሰበክሁ።
\v 21 በዚህ ምክንያት አይሁድ በቤተ መቅደስ ያዙኝና ሊገድሉኝ ሞከሩ።
\s5
\v 22 እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶኛል፤ ስለዚህ ለታናናሾችና ለታላላቆች ለመመስከር እዚህ ቆሜአለሁ፤ ምስክርነቴም ሙሴና ነቢያት ይሆናል ብለው ከተናገሩት የሚያልፍ አይደለም፤
\v 23 ይኸውም ክርስቶስ መከራ ይቀበላል፤ ከሙታን ለመነሣትና ለአይሁድ ሕዝብ፣ ለአሕዛብም ብርሃንን ለመስበክ የመጀመሪያው ይሆናል የሚል ነው።
\s5
\v 24 ጳውሎስም መከላከያውን እንደ ጨረሰ ፊስጦስ፣ «ጳውሎስ፣ አንተ ዕብድ ነህ፤ ብዙ መማርህ አሳብዶሃል» ሲል ጮኾ ተናገረ።
\v 25 ጳውሎስ ግን እንዲህ አለ፤ «እጅግ የተከበርህ ፊስጦስ ሆይ፣ እኔ ዕብድ አይደለሁም፤ ነገር ግን እውነተኛውንና ትክክለኛውን ቃል በድፍረት እናገራለሁ።
\v 26 ንጉሡ ስለ እነዚህ ነገሮች ያውቃልና እንደ ልብ እነግረዋለሁ፤ በመሆኑም ከእነዚህ ነገሮች አንዱም ከእርሱ የተሰወረ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ።
\s5
\v 27 ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ በነቢያት ታምናለህን? እንደምታምን ዐውቃለሁ።»
\v 28 አግሪጳም ጳውሎስን፣ «በአጭር ጊዜ ልታሳምነኝና ክርስቲያን ልታደርገኝ ትፈልጋለህን?» አለው።
\v 29 ጳውሎስም፣ «በአጭር ይሁን ወይም በረዥም ጊዜ፣ አንተ ብቻ ሳትሆን፣ ዛሬ የሚሰሙኝ ሁሉ፣ ከእነዚህ የወኅኒ ሰንሰለቶች በቀር እንደ እኔ እንድትሆኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ» አለ።
\s5
\v 30 ከዚያም ንጉሡ፣ ገዥውም፣ በርኒቄም ደግሞ፣ ከእነርሱ ጋር ተቀምጠው የነበሩትም ተነሡ፤
\v 31 ከአዳራሹም በወጡ ጊዜ፣ እርስ በርስ ተነጋግረው ፣«ይህ ሰው ለሞት ወይም ለእስራት የሚያበቃ ምንም አላደረገም» አሉ።
\v 32 አግሪጳ ፊስጦስን፣ «ይህ ሰው ወደ ቄሣር ይግባኝ ባይል ኖሮ በነጻ ሊለቀቅ ይችል ነበር» አለው።
\s5
\c 27
\cl ምዕራፍ 27
\p
\v 1 ወደ ኢጣሊያ በመርከብ እንድንሄድ በተወሰነ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሌሎችን እስረኞች የአውግስጦስ ክፍለ ጦር አባል ለሆነ ዩልዮስ ለተባለ የመቶ አለቃ አስረከቡአቸው።
\v 2 እኛም ከአድራሚጥዮን ተነሥተን በእስያ ጠረፍ ሊሄድ በተዘጋጀ መርከብ ላይ ተሳፍረን ወደ ባሕር ተጓዝን። በመቄዶንያ ካለችው ተሰሎንቄ የሆነው አርስጥሮኮስም ከእኛ ጋር ሄደ።
\s5
\v 3 በማግስቱ ወደ ሲዶን ከተማ ደርሰን፣ ከመርከብ ወረድን፤ እዚያም ዩልዮስ ለጳውሎስ ቸርነት አደረገለት፤ ወደ ወዳጆቹ እንዲሄድና እንክብካቤ እንዲያደርጉለትም ፈቀደለት።
\v 4 ከዚያም ተነሥተን ወደ ባሕር ሄድን፤ ነፋስ ይነፍስብን ስለ ነበር፣ በመርከብ ሆነን ነፋሱ በማያገኛት በቆጵሮስ ደሴት ዙሪያ ተጓዝን።
\v 5 በኪልቅያና በጵንፍልያ አጠገብ ያለውን ባሕር ከተሻገርን በኋላም፣ የሉቅያ ከተማ ወደ ሆነው ወደ ሙራ ደረስን።
\v 6 በዚያም፣ የመቶ አለቃው ከእስክንድርያ ወደ ኢጣሊያ የሚሄድ መርከብ አግኝቶ አሳፈረን።
\s5
\v 7 ብዙ ቀንም በዝግታ ተጓዝንና በመጨረሻ በችግር ወደ ቀኒዶስ ደረስን፤ ነፋሱም በዚያ መንገድ እንዳንሄድ ስለከለከለን፣ በሰልሙና አንጻር ያለችውን ቀርጤስን ተገን አድርገን ተጓዝን።
\v 8 በላሲያ ከተማ አጠገብ ወዳለው መልካም ወደብ ወደ ተባለው ስፍራ እስከምንደርስ ድረስ በችግር በጠረፉ በኩል ተጓዝን።
\s5
\v 9 ብዙ ጊዜም አሳለፍን፤ የአይሁድ የጾም ወራት ደግሞ ዐልፎ ነበር፤ ጕዞውን መቀጠልም አደጋ የሚያስከትል ነበር። ስለዚህ ጳውሎስ አስጠነቀቃቸው፤
\v 10 እንዲህም አለ፤ “እናንተ ሰዎች፣ አሁን የምናደርገው ጕዞ አደጋና ብዙ ጉዳት እንደሚኖርበት ይታየኛል፤ አደጋውም በመርከቡና በጭነቱ ብቻ ሳይሆን፣ በእኛም ሕይወት ላይ የሚደርስ ነው።”
\v 11 የመቶ አለቃው የሰማው ግን ጳውሎስ የተናገረውን ሳይሆን፣ በይበልጥ የመርከቡ አዛዥና ባለቤት ያሉትን ነው።
\s5
\v 12 ክረምቱን ለማሳለፍ ወደቡ ተስማሚ ስላልነበረ፣ አብዛኛዎቹ ተጓዦች የሚቻል ከሆነ ከዚያ ተነሥተን ፊንቄ ወደ ተባለችው ከተማ እንድንሄድና ክረምቱን እዚያ እንድናሳልፍ ምክር ሰጡን። ፊንቄ በሰሜን ምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ አንጻር የምትገኝ የቀርጤስ ወደብ ነች።
\v 13 የደቡቡ ነፋስ በቀስታ መንፈስ በጀመረ ጊዜ፣ መርከበኞቹ የፈለጉት እንደተከናወነላቸው ዐሰቡ። ስለዚህ ሸራውን አውርደው በባሕሩ ዳርቻ አቅራቢያ፣ በቀርጤስ በኩል አለፉ።
\s5
\v 14 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን፣ የሰሜን ምሥራቅ ዐውሎ ነፋስ የተባለ ኃይለኛ ነፋስ ደሴቲቱን አቋርጦ በመምጣት ይነፍስብን ጀመረ፤
\v 15 መርከቡም ወደ ፊት በተገፋና ነፋሱን መቋቋም ባልቻለ ጊዜ፣ ዝም ብለነው በነፋሱ እየተነዳን ሄድን።
\v 16 ቄዳ የተባለችውን ትንሽ ደሴት ተተግነን ተጓዝን፤ በትልቅ ችግርም ሕይወት አድን ጀልባው ላይ መውጣት ቻልን።
\s5
\v 17 መርከበኞቹ ጀልባውን ወደ መርከቡ ጎትተው አወጡት፤ ገመዱንም የመርከቡን ዙሪያ ለማሰር ተጠቀሙበት። ስርቲስ በምትባል አሸዋማ ስፍራ እንዳንወድቅ ፈርተው ነበር፤ ስለዚህ የባሕር ሸራውን አውርደው እየተነዱ ሄዱ።
\v 18 ዐውሎ ነፋሱ በጣም ስላየለብን፣ በማግስቱ መርከበኞቹ የመርከቡን ጭነት ወደ ባሕር መጣል ጀመሩ።
\s5
\v 19 በሦስተኛው ቀን መርከበኞቹ በመርከቡ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን እያነሡ ጣሉ።
\v 20 ለብዙ ቀንም ፀሐይና ከዋክብት ብርሃናቸውን ባልሰጡንና ትልቁ ማዕበልም በወረደብን ጊዜ፣ አንድንም ብለን ተስፋ ቈረጥን።
\s5
\v 21 ተጓዦቹ ምግብ ሳይበሉ ብዙ ቀን ቈይተው ነበር፤ በዚያን ጊዜ ጳውሎስ በተጓዦቹ መካከል ቆሞ እንዲህ አለ፤ “እናንተ ሰዎች፣ ይህ አደጋና ጉዳት እንዳይደርስባችሁ፣ ከቀርጤስ አትነሡ ብዬ የነገርኋችሁን መስማት ነበረባችሁ፤
\v 22 አሁንም መርከቡ ብቻ ይጎዳል እንጂ ከመካከላችሁ የሚሞት አይኖርምና አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ።
\s5
\v 23 ምክንያቱም ባለፈው ሌሊት የእርሱ የሆንሁትና ደግሞም የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በአጠገቤ ቆሞ እንዲህ ብሏል፤
\v 24 “ጳውሎስ ሆይ፣ አትፍራ። በቄሣር ፊት ልትቆም ይገባሃል፤ ተመልከት፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ ዐብረውህ የሚጓዙትን ሁሉ ሰጥቶሃል።
\v 25 ስለዚህ እናንተ ሰዎች፣ አይዞአችሁ፤ ልክ እንደ ተናገረኝ እንደሚሆን እግዚአብሔርን አምነዋለሁ።
\v 26 ነገር ግን ወደ አንዲት ደሴት ደርሰን ልናርፍ ይገባል።”
\s5
\v 27 በዐሥራ አራተኛውም ሌሊት፣ በአድርያቲክ ባሕር ወዲያና ወዲህ እየተንገላታን እያለን፣ እኩለ ሌሊት ገደማ፣ መርከበኞቹ ወደ መሬት የቀረቡ መሰላቸው።
\v 28 የባሕር ጥልቀት መለኪያ ገመድ ጣሉና ጥልቀቱን አርባ ሜትር ሆኖ አገኙት፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ መለኪያውን ሲጥሉም ሠላሳ ሜትር ሆኖ አገኙት።
\v 29 ከዐለቶቹ ጋር እንጋጫለን ብለውም ፈሩ፤ ስለዚህ ከኋላ አራት መልሕቆችን አውርደው ቶሎ እንዲነጋ ጸለዩ።
\s5
\v 30 መርከበኞቹ መርከቡን ትተው ለመሄድ መንገድ ይፈልጉና ሕይወት አድን ጀልባውን ወደ ባሕሩ ውስጥ ያወርዱ ነበር፤ መልሕቆቹንም ከቀስቱ የሚወረውሩ መሰሉ።
\v 31 ጳውሎስ ግን መቶ አለቃውንና ወታደሮቹን፣ “እነዚህ ሰዎች በመርከቡ ካልቆዩ በቀር፣ እናንተ መዳን አትችሉም” አላቸው።
\v 32 ከዚያም ወታደሮቹ የጀልባውን ገመዶች ቈረጡት፤ እንዲንሳፈፍም አደረጉት።
\s5
\v 33 ቀኑ ሊነጋ ሲልም፣ ምግብ እንዲበሉ ጳውሎስ ሁሉንም መከራቸው። እንዲህም አላቸው፤ “ምንም ሳትበሉ ከቈያችሁ ይህ ዐሥራ አራተኛ ቀናችሁ ነው።
\v 34 ስለዚህ በሕይወት እንድትኖሩ፣ ጥቂት ምግብ እንድትበሉ እለምናችኋለሁ፤ ከራሳችሁ ላይ አንዲቱም ጠጕር አትጠፋም።”
\v 35 ይህን ተናግሮ፣ እንጀራ አነሣና በሁሉም ፊት እግዚአብሔርን አመሰገነ። ከዚያም እንጀራውን ቈርሶ መብላት ጀመረ።
\s5
\v 36 በዚያን ጊዜ ሁሉም ተጽናንተው ምግብ በሉ።
\v 37 በመርከቡ ውስጥ 276 ሰዎች ነበርን።
\v 38 በልተው በጠገቡ ጊዜም፣ ስንዴውን ወደ ባሕሩ በመጣል የመርከቡን ጭነት አቃለሉ።
\s5
\v 39 በነጋታውም፣ የነበሩበትን ምድር አላወቁትም፤ ነገር ግን በዳርቻ ያለውን የባሕር ሰርጥ አዩ፤ መርከቡን ወደ ሰርጡ መግፋት ይችሉ እንደሆነም ተነጋገሩ።
\v 40 ስለዚህ መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕሩ ላይ ተዉአቸው። በዚሁ ጊዜም የመቅዘፊያዎቹን ገመዶች ፈትተው ሸራውን ወደ ነፋሱ ከፍ አደረጉና ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ።
\v 41 ነገር ግን ሁለት ማዕበሎች ወደ ተገናኙበት ስፍራ መጡ፤ መርከቡም ወደ መሬት ገባ፤ የመርከቡ ቅስትም በዚያ ተተከለና የማይነቃነቅ ሆነ፤ የኋላ ክፍሉ ግን ከማዕበሉ ነውጥ የተነሣ ይሰባበር ጀመር።
\s5
\v 42 የወታደሮቹ ዕቅድ ከመካከላቸው ማንም ዋኝቶ እንዳያመልጥ እስረኞቹን ለመግደል ነበር።
\v 43 የመቶ አለቃው ግን ጳውሎስን ለማዳን ፈለገ፤ ስለዚህ ዕቅዳቸውን አልተቀበለም፤ መዋኘት የሚችሉትም በመጀመሪያ ከመርከቡ ላይ እየዘለሉ ወደ የብስ እንዲወጡ አዘዘ።
\v 44 ከዚያም የቀሩት ሰዎች በሳንቃዎችና ከመርከቡ በተገኙ ስብርባሪዎች ላይ ሆነው ተከትለው እንዲወጡ አደረገ። በዚህ ዐይነት ሁላችንም በደኅና ወደ የብስ ወጣን።
\s5
\c 28
\cl ምዕራፍ 28
\p
\v 1 ወደ መሬት በደኅና በደረስን ጊዜም፣ ደሴቲቱ ማልታ የምትባል መሆንዋን ዐወቅን።
\v 2 የዚያች ደሴት ሰዎችም የተለመደውን ደግነት እንኳ አላሳዩንም፤ ሆኖም፣ በማያቋርጠው ዝናብና ብርድ ምክንያት እሳት አንድደው ሁላችንንም ተቀበሉን።
\s5
\v 3 ነገር ግን ጳውሎስ ጭራሮ ሰብስቦ እሳቱ ላይ በጨመረው ጊዜ፣ ከሙቀቱ የተነሣ አንድ እፉኝት ወጣና በእጁ ላይ ተጣበቀ።
\v 4 የደሴቲቱ ሰዎችም እፉኝቱ ከእጁ ላይ ተንጠልጥሎ ባዩ ጊዜ፣ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ሰው በእርግጥ ከባሕር ያመለጠ ነፍሰ ገዳይ ስለ ሆነ፣ ፍትሕ በሕይወት እንዲኖር አልፈቀደለትም” ተባባሉ።
\s5
\v 5 ጳውሎስ ግን እፉኝቱን በእሳቱ ላይ አራገፈው፤ አልተጐዳምም።
\v 6 ሰዎቹም ሰውነቱ በትኵሳት ያብጣል ወይም በድንገት ይሞታል ብለው ይጠባበቁ ነበር። ነገር ግን ረዘም ላለ ጊዜ ተጠባብቀውት ምንም እንዳልደረሰበት ካዩ በኋላ፣ ዐሳባቸውን ለውጠው አምላክ ነው አሉ።
\s5
\v 7 በአቅራቢያው ባለ አንድ ስፍራም ፑብልዮስ የተባለ የደሴቲቱ ገዢ መሬት ነበር፤ እርሱም ተቀብሎን ሦስት ቀን በደግነት አስተናገደን።
\v 8 የፑብልዮስ አባት ትኵሳትና ተቅማጥ ይዞት ታሞ ነበር። ጳውሎስ ወደ እርሱ ሄዶ ጸለየ፤ እጆቹን ጫነበት፤ ፈወሰውም።
\v 9 ይህ ከሆነ በኋላ፣ በደሴቲቱ የሚኖሩ ታመው የነበሩ ሌሎች ደግሞ መጡና ተፈወሱ።
\v 10 ሰዎቹም እጅግ አከበሩን። ለመሄድ በምንዘጋጅበት ጊዜም፣ የሚያስፈልገንን ሰጡን።
\s5
\v 11 ከሦስት ወር በኋላ፣ አፍንጫው ላይ የመንታ ወንድማማች ዓርማ በነበረበት፣ ክረምቱን በደሴቲቱ ባሳለፈ የእስክንድርያ መርከብ ላይ ተሳፍረን ጕዞ ጀመርን።
\v 12 ወደ ሲራኩስ ከተማ ከደረስን በኋላም፣ እዚያ ሦስት ቀን ቈየን።
\s5
\v 13 ከዚያም ተጕዘን ወደ ሬጊዩም ከተማ ደረስን። ከአንድ ቀን በኋላ የደቡብ ነፋስ ተነሣ፤ በሁለት ቀንም ወደ ፑቲዮሉስ ከተማ መጣን።
\v 14 እዚያም አንዳንድ ወንድሞችን አገኘንና ከእነርሱ ጋር ሰባት ቀን እንድንቈይ ተጋበዝን። በዚህ ዐይነት ወደ ሮም መጣን።
\v 15 ከዚያም ወንድሞች ስለ እኛ ከሰሙ በኋላ፣ ሊቀበሉን አፍዩስ ገበያና ሦስቱ ማደሪያዎች ድረስ መጡ። ጳውሎስ ወንድሞችን ባየ ጊዜ፣ እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ ተጽናናም።
\s5
\v 16 ወደ ሮም በገባን ጊዜ፣ ጳውሎስ ከሚጠብቀው ወታደር ጋር ብቻውን እንዲኖር ተፈቀደለት።
\v 17 ቀን በኋላ፣ ጳውሎስ በአይሁድ መካከል መሪዎች የነበሩትን ሰዎች አንድ ላይ ጠራ። በተሰበሰቡ ጊዜም፣ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፣ በሕዝቡ ወይም በአባቶች ሥርዓት ላይ የፈጸምሁት ስሕተት ባይኖርም እንኳ፣ ከኢየሩሳሌም በእስረኝነት ለሮማውያን እጅ ተላልፌ ተሰጠሁ።
\v 18 እነርሱ ከመረመሩኝ በኋላ ለሞት የሚያበቃኝ ምክንያት ስላልነበረብኝ፣ በነጻ ሊለቁኝ ፈልገው ነበር።
\s5
\v 19 ነገር ግን አይሁድ የሮማውያንን ፍላጎት ተቃውመው በተናገሩ ጊዜ፣ በሕዝቤ ላይ የማቀርበው ክስ ባይኖረኝም እንኳ፣ ወደ ቄሣር ይግባኝ ለማለት ተገደድሁ።
\v 20 በዚህ ምክንያት፣ ላያችሁና ላነጋግራችሁ ልመና አቅርቤአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ በዚህ ሰንሰለት የታሰርሁት ለእስራኤል ስለ ተሰጠው እምነት ነው።”
\s5
\v 21 ከዚያም እነርሱ እንዲህ አሉት፤ “ከይሁዳ ስለ አንተ ደብዳቤ አልደረሰንም፤ ከወንድሞች መካከልም ስለ አንተ ያወራ ወይም ክፉ የተናገረ የለም።
\v 22 ነገር ግን በሁሉም ስፍራ ተቃውሞ እየተወራበት መሆኑን እኛ ስለምናውቅ፣ ስለዚህ የሃይማኖት ወገን ምን እንደምታስብ ከአንተ መስማት እንፈልጋለን።”
\s5
\v 23 ለጳውሎስ ቀን በቀጠሩለት ጊዜም፣ ብዙ ሰዎች ወደ መኖሪያ ቤቱ መጡ። እርሱም ጉዳዩን ገለጠላቸው፤ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም መሰከረላቸው። ከጠዋት እስከ ማታም ከሙሴ ሕግና ከነቢያት እየጠቀሰ፣ ስለ ኢየሱስ ሊያሳምናቸው ጥረት አደረገ።
\v 24 አንዳንዶች የተናገረውን ቃል ሲያምኑ፣ ሌሎች ግን አላመኑም።
\s5
\v 25 እርስ በርሳቸው ሳይስማሙ ሲቀሩ፣ ጳውሎስ ይህን አንድ ቃል ከተናገረ በኋላ ሄዱ፤ “መንፈስ ቅዱስ በነቢዩ ኢሳይያስ አማካይነት ለአባቶቻችሁ በትክክል ተናገረ።
\v 26 እንዲህም አለ፤ ‘ወደዚህ ሕዝብ ሂድና እንደዚህ በላቸው፤ ‘መስማትስ ትሰማላችሁ፤ ነገር ግን አታስተውሉም፤ ማየትስ ታያላችሁ፤ ነገር ግን ልብ አታደርጉም።
\s5
\v 27 በዐይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸው እንዳይሰሙ፣ በልባቸው እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፣ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍኖአል።’
\s5
\v 28-29 ስለዚህ፣ ይህ የእግዚአብሔር ድነት ወደ አሕዛብ እንደ ተላከ፣ እነርሱም እንደሚቀበሉት ዕወቁ።
\s5
\v 30 ጳውሎስ በተከራየው በራሱ ቤት ሁለት ዓመት ሙሉ ኖረ፤ ወደ እርሱ የሚመጡትንም ሁሉ ይቀበል ነበር።
\v 31 የእግዚአብሔርን መንግሥት ይሰብክ፣ ያስተምርም ነበር። ይህንም ሲያደርግ ማንም አልከለከለውም።

880
46-ROM.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,880 @@
\id ROM
\ide UTF-8
\h ሮሜ
\toc1 ሮሜ
\toc2 ሮሜ
\toc3 rom
\mt ሮሜ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 የእግዚአብሔርን ወንጌል በሐዋርያነት እንዲያገለግል ተለይቶ ከተጠራው ከኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ከጳውሎስ።
\v 2 ወንጌሉም በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በነቢያቱ አስቀድሞ ተስፋ የሰጠው ነው።
\v 3 ይህም ወንጌል በስጋ ከዳዊት ዘር ስለተወለደው ስለ ልጁ ነው።
\s5
\v 4 እርሱም በቅድስና መንፈስ ኃይል ከሙታን በመነሳት የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑ የተነገረለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር።
\v 5 በስሙ ምክንያት ከእምነት የሚገኝ መታዘዝ በሕዝቦች ሁሉ መካከል እንዲሆን በእርሱ በኩል ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን።
\v 6 እናንተም በእነዚህ ሕዝቦች መካከል የኢየሱስ ክርስቶስ ለመሆን ተጠራችሁ።
\s5
\v 7 ይህ መልዕክት የተጻፈው በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱስ ሕዝብ ለመሆን ለተጠራችሁ በሮም ላላችሁት ሁሉ ነው። ከእግዚአብሔር ከአባታችንና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 8 ስለ እምነታችሁ በመላው ዓለም በመነገሩ ምክንያት አስቀድሜ ስለሁላችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል አምላኬን አመሰግናለሁ።
\v 9 ባለማቋረጥ እንደማስባችሁ የልጁን ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
\v 10 አሁን በተቻለኝ መጠን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሳክቶልኝ ወደ እናንተ እንድመጣ ሁልጊዜ በጸሎቴ እለምናለሁ።
\s5
\v 11 የሚያበረታችሁን ጥቂት መንፈሳዊ ስጦታ እንዳካፍላችሁ ላያችሁ እናፍቃለሁ፥
\v 12 ይኸውም የእኔና የእናንተ በሆነ የእርስ በርሳችን እምነት አማካይነት እንድንበረታታ ስለምጓጓ ነው።
\s5
\v 13 ወንድሞች ሆይ፥ ብዙ ጊዜ ወደ እናንተ ለመምጣት እንደ ሞከርኩኝና እስካሁን እንደተስተጓጎልኩኝ ሳታውቁ እንድትቀሩ አልፈልግም። ወደ እናንተ መምጣት የፈለግሁበት ምክንያት ከተቀሩት አሕዛብ እንዳገኘሁት ሁሉ ከእናንተ ደግሞ ጥቂት ፍሬ እንዳገኝ ነው።
\v 14 ለግሪኮችና ግሪኮች ላልሆኑት፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉ ዕዳ አለብኝ።
\v 15 ስለዚህ፥ በበኩሌ በሮም ለምትገኙት ለእናንተ ደግሞ ወንጌልን ለመስበክ ተዘጋጅቻለሁ።
\s5
\v 16 በወንጌል አላፍርም! ምክንያቱም እርሱ አስቀድሞ ለአይሁድ ደግሞም ለግሪኮች የሚያምኑትን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ኃይል ስለሆነ ነው።
\v 17 "ጻድቅ በእምነት ይኖራል" ተብሎ እንደተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ በወንጌል ከእምነት ወደ እምነት ተገልጧልና።
\s5
\v 18 በአመጻቸው እውነትን በሚያፍኑ አመጸኞችና ክፉዎች ሰዎች ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ከሰማይ ተገልጧል።
\v 19 ይኽውም እግዚአብሔር ስላስታወቃቸው ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚገባው ነገር ለእነርሱ ግልጥ ነው።
\s5
\v 20 የማይታዩት ገጽታዎቹ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ግልጥ ሆነው ይታያሉ። እነዚህም በተፈጠሩት ነገሮች አማካይነት ይታወቃሉ። ገጽታዎቹም የዘላለም ኃይሉና የመለኮት ባህርዩ ናቸው። በመሆኑም እነዚህ ሰዎች የሚያመካኙት አይኖራቸውም።
\v 21 ምክንያቱም ስለ እግዚአብሔር ቢያውቁም እንደ እግዚአብሔርነቱ ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት ነው። ይልቁንም በሀሳባቸው ሞኞች ሆኑ፥ የማያስተውለው ልባቸውም ጨለመ።
\s5
\v 22 ጥበበኞች ነን ቢሉም የማያስተውሉ ሆኑ።
\v 23 የማይጠፋውን የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰው አምሳል፥በወፎች፥ አራት እግር ባላቸው አራዊትና በደረታቸው በሚሳቡ ፍጥረታት መልክ ለወጡ።
\s5
\v 24 ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሰውነታቸውን እንዲያዋርዱ እግዚአብሔር ለልባቸው የክፋት ምኞት ለእርኩሰት አሳልፎ ሰጣቸው።
\v 25 እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት የለወጡና በፈጣሪ ፈንታ ፍጥረትን ያመለኩና ያገለገሉ ናቸው፤ እርሱ ግን ለዘላለም የተመሰገነ ነው።አሜን።
\s5
\v 26 ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር ለአስነዋሪ ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፥ ሴቶቻቸውም ለተፈጥሮአቸው የሚገባውን ተግባር ተገቢ ባልሆነው ለወጡ።
\v 27 እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለተፈጥሮአቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወተ-ሥጋ ምኞት ተቃጠሉ። እነዚህ ወንዶች የማይገባውን ነገር ከወንድ ጋር በማድረጋቸው ስለ ነውራቸው ቅጣትን የተቀበሉ ናቸው።
\s5
\v 28 እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈቀዱ እነዚያን ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች እንዲያደርጉ ለማይረባ አዕምሮ አሳልፎ ሰጣቸው።
\s5
\v 29 እነርሱ በአመጻ ሁሉ፥ በጨካኝነት፥ በክፉ ምኞትና በምቀኝነት፥ በቅናት፥ በነፍስ መግደል፥ በጸብ፥ በማታለልና በክፉ ሃሳብ የተሞሉ ናቸው።
\v 30 ሐሜተኞች፥ የሰው ስም አጥፊዎችና እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ቁጡዎች፥ ዕብሪተኞችና ትዕቢተኞች ናቸው። ክፉ ነገሮችን የሚያመነጩና ለወላጆቻችው የማይታዘዙ፥
\v 31 ማስተዋል የሌላቸው፤ እምነት የማይጣልባቸው፥ ፍቅር የሌላቸውና የማይምሩ ናቸው።
\s5
\v 32 እንደዚህ ያሉትን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት እንደሚገባቸው የሚናገረውን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ያውቃሉ፥እነርሱ ግን እነዚህኑ ነገሮች ራሳቸው የሚያደርጉ ብቻ ሳይሆኑ የሚያደርጉትን ሌሎችን የሚያበረታቱ ናቸው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ስለዚህ አንተ ሰው፥ አንተው ፈራጁ እነዚያኑ ነገሮች ስለምታደርግ በሌላው በምትፈርድበት ራስህን ትኮንናለህና የምታመካኘው የለህም።
\v 2 ነገር ግን እነዚያን ነገሮች በሚያደርጉት ላይ ቁጣው በሚወርድባቸው ጊዜ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ እንደሆነ እናውቃለን።
\s5
\v 3 ነገር ግን አንተው ራስህ ያንኑ እያደረግህ እንደነዚያ ያሉትን በሚያደርጉት ላይ የምትፈርድ አንተ ሰው፥ይህንን አስተውል። ከእግዚአብሔር ፍርድ ታመልጣለህን?
\v 4 ወይስ የቸርነቱን ባለጠግነት፥የቅጣቱን መዘግየትና ትዕግስቱን ታቃልላለህን? ቸርነቱ ወደ ንስሐ ሊመራህ እንደሆነ አታውቅምን?
\s5
\v 5 ነገር ግን በፍርድ ቀን ያም የእግዚአብሔር የጽድቅ ፍርድ በሚገለጥበት ጊዜ በድንዳኔህና ንስሐ በማይገባው ልብህ መጠን ለራስህ ቁጣን ታከማቻለህ።
\v 6 እርሱ ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይከፍለዋል፤
\v 7 በበጎ ተግባር በመጽናት ምስጋናን፥ክብርንና የማይጠፋውን ሕይወት ለሚፈልጉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸዋል።
\s5
\v 8 የራሳቸውን ጥቅም በሚፈልጉት፥ለአመጻ እንጂ ለእውነት በማይታዘዙት ላይ ግን መቅሰፍትና ብርቱ ቁጣ ይመጣባቸዋል።
\v 9 አስቀድሞ በአይሁዳዊ ቀጥሎም በግሪክ ሰው፥ክፋትን ባደረገ ነፍስ ሁሉ ላይ እግዚአብሔር መከራና ጭንቀትን ያመጣባቸዋል።
\s5
\v 10 አስቀድሞ ለአይሁድ ቀጥሎም ለግሪክ መልካም ላደርጉ ሁሉ ግን ምስጋና፥ክብርና ሰላም ይሆንላቸዋል።
\v 11 እግዚአብሔር ስለማያዳላ
\v 12 ሕግ እያላቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ በሕግ ይፈረድባቸዋል፥ሕግ ሳይኖራቸው ኃጢአት ያደረጉ ሁሉ ደግሞ ያለ ሕግ ይጠፋሉ።
\s5
\v 13 በእግዚአብሔር ፊት የሚጸድቁት ሕጉን የሚሰሙት ሳይሆኑ ሕጉን የሚያደርጉት ናቸው።
\v 14 ሕግ የሌላቸው አሕዛብ በተፈጥሮአቸው የሕጉን ነገሮች በሚፈጽሙበት ጊዜ ሕግ ባይኖራቸውም እንኳ ለእነርሱ ለራሳቸው ሕግ ናቸው።
\s5
\v 15 በዚህም ሕጉ የሚጠይቃቸው ድርጊቶች በልቦናቸው መጻፋቸውን ያሳያሉ። ሃሳባቸው ሲከሳቸው ወይም ሲደግፋቸው ኅሊናቸው ደግሞ ለራሳቸውና
\v 16 ለእግዚአብሔር ይመሰክራል። ይህም እኔ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደምሰብከው ወንጌል ሰዎች ሁሉ በስውር ስላደረጉት ነገር እግዚአብሔር በሚፈርድበት ቀን በዚያን ጊዜ ይሆናል።
\s5
\v 17 በሕጉ በመመራትህ አይሁዳዊ ነኝ ትላለህ፥ በሕጉ ትደገፋለህ፥ በእግዚአብሔር በመመካት ደስ ትሰኛለህ፥
\v 18 ፈቃዱን ታውቃለህ፥ ከእርሱ ውጪ የሆኑትን ነገሮች መርምረህ ትረዳ ይሆናል።
\v 19 አንተ ራስህ የዕውሩ መሪ፥ በጨለማ ላሉት ብርሃን፥
\v 20 የሰነፎች አስተማሪ፥ የሕጻናትም መምህር በመሆንህ በሕግ የእውቀትና የእውነት መልክ እንዳለህ ትታመን ይሆናል።
\s5
\v 21 እንግዲህ አንተ ሌላውን የምታስተምር ራስህን አታስተምርምን? አትስረቅ ብለህ የምትሰብክ ትሰርቃለህን?
\v 22 አታመንዝር የምትል አንተ ታመነዝራለህን? ጣዖታትን የምትጸየፍ ቤተመቅደሶችን ትዘርፋለህን?
\s5
\v 23 አንተ በሕጉ በመመካት የምትደሰተው ሰው ሕጉን በመተላለፍ እግዚአብሔርን ትንቃለህን? ይህ ልክ "በእናንተ
\v 24 ምክንያት በአሕዛብ መካከል የእግዚአብሔር ስም ይናቃል" ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
\s5
\v 25 ሕጉን ብትፈጽም በርግጥ መገረዝ ይጠቅማል፥ የሕጉ ተላላፊ ብትሆን ግን መገረዝህ እንደ አለመገረዝ ይሆናል።
\v 26 እንግዲህ ያልተገረዘው ሰው የሕጉን ትዕዛዛት ቢጠብቅ አለመገረዙ እንደ መገረዝ አይቆጠርለትምን?
\v 27 በፍጥረቱ ያልተገረዘው ሰው ሕጉን ቢፈጽም አይፈርድባችሁምን? ይህም እናንተ ቅዱሳት መጻሕፍትና መገረዝ እያላችሁ ሕጉን ተላለፊ ስለሆናችሁ ነው።
\s5
\v 28 በውጫዊ ማንነቱ ብቻ አይሁዳዊ የሆነ እርሱ አይሁዳዊ አይደለም፥ የሥጋ ውጫዊ መገረዝ ብቻም መገረዝ አይደለም።
\v 29 ነገር ግን በውስጣዊ ማንነቱ አይሁዳዊ የሆነ እርሱ አይሁዳዊ ነው፥ መገረዝም በፊደል ሳይሆን በመንፈስ በልብ የተደረገው ነው። እንዲህ ላለ ሰው ከሰዎች ሳይሆን ከእግዚአብሔር ምስጋና ይሆንለታል።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድነው? የመገረዝስ ጥቅሙ ምንድነው?
\v 2 በሁሉም አቅጣጫ ብልጫው ታላቅ ነው። አስቀድሞ ክእግዚአብሔር ዘንድ መገለጥ በአደራ የተሰጠው ለአይሁድ ነበር።
\s5
\v 3 አንዳንድ አይሁድ ባያምኑስ? ያለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀረዋልን?
\v 4 በምንም ዓይነት አያስቀረውም፤ ይልቁንም ሰው ሁሉ ውሸተኛ ቢሆንም እንኳ እግዚአብሔር እውነተኛ ነው። "በቃልህ ጸድቅ ሆነህ ትገኝ ዘንድ፥ ወደ ፍርድ በመጣህ ጊዜም ትረታ ዘንድ" ተብሎ ተጽፏልና።
\s5
\v 5 የእኛ አመጻ የእግዚአብሔርን ጽድቅ የሚያሳይ ከሆነ ግን ምን ማለት እንችላለን? እግዚአብሔር ቁጣውን በሚያመጣበት ጊዜ አመጸኛ አይደለም፥ ነወይ? ። ይህንን የምለው እንደ ሰው አስተሳሰብ ነው።
\v 6 በፍጹም አይደለም። እንዲህ ከሆነማ እግዚአብሔር እንዴት በዓለም ላይ ይፈርዳል?
\s5
\v 7 ነገር ግን የእግዚአብሔር እውነት በእኔ ውሸት አማካይነት ለእርሱ ብዙ ምስጋና ካመጣ ለምን አሁንም እንደ ኃጢአተኛ ይፈረድብኛል?
\v 8 "መልካም እንዲመጣ ክፉን እናድርግ" ስለማለታችን በሐሰት እንዳስወሩብንና አንዳንዶችም እንዳመኑት ታዲያ ለምን አንልም? የሚደርስባቸው ፍርድ ትክክለኛ ነው።
\s5
\v 9 እንግዲህ ምን ይሁን? በዚህ ጉዳይ ራሳችንን ነጻ እያደረግን ነውን? በጭራሽ። አይሁድና ግሪኮች ሁሉም ከኃጢአት በታች ስለመሆናቸው አስቀድመን ወንጅለናቸዋልና።
\v 10 እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ "አንድም እንኳን ጻድቅ የለም።
\s5
\v 11 አንድ እንኳን የሚያስተውል የለም። እግዚአብሔርን የሚፈልግ አንድም የለም።
\v 12 ሁሉም ተሳስተዋል። በአንድ ላይ የማይጠቅሙ ሆነዋል። መልካም የሚያደርግ የለም፥አንድም እንኳን የለም።
\s5
\v 13 ጉሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው። ምላሳቸው አታሏል። የእባብ መርዝ በከንፈሮቻቸው ሥር አለ።
\v 14 አፋቸው እርግማንና መራራነትን ተሞልቷል።
\s5
\v 15 እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው።
\v 16 በመንገዶቻቸው ላይ ጥፋትና መከራ አለ።
\v 17 እነዚህ ሰዎች የሰላምን መንገድ አላወቁትም።
\v 18 በዓይኖቻቸው ፊት እግዚአብሔርን መፍራት የለም።"
\s5
\v 19 ሕጉ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንደሆነ እናውቃለን። ይህም አፍ ሁሉ እንዲዘጋና መላው ዓለም ለእግዚአብሔር መልስ እንዲሰጥ ነው።
\v 20 ይህ የሆነበት ምክንያት ሥጋን የለበሰ ሁሉ ሕግን በመፈጸም በእግዚአብሔር ዓይን ስለማይጸድቅ ነው። ኃጢአት የሚታወቀው በሕግ አማካይነት ነውና።
\s5
\v 21 አሁን ግን የእግዚአብሔር ጽድቅ ያለ ሕግ ተገልጧል። ልዩነት ሳይደረግ
\v 22 በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር ጽድቅ ለሚያምኑ ሁሉ ይሆንላቸው ዘንድ በሕግና በነቢያት የተመሰከረ ነው።
\s5
\v 23 ሁሉም ኃጢአትን ሠርተዋል፥ከእግዚአብሔር ክብርም ጎድለዋል።
\v 24 በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በተደረገው ቤዛነት በነጻ በጸጋው ይጸድቃሉ።
\s5
\v 25 በደሙ በማመን የኃጢአት ማስተሰሪያ ይገኝ ዘንድ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ሰጥቷልና። በትዕግስቱ የቀደመውን ኃጢአት ስለመተዉ ለጽድቁ ማረጋገጫ እንዲሆን ክርስቶስን መስዋዕት አድርጎ
\v 26 አቀረበው። በዚህ በአሁኑ ዘመን የእርሱ ጽድቅ እንዲታይ ይህ ሁሉ ሆነ። እንዲህም የሆነው እርሱ ጻድቅ መሆኑንና በኢየሱስ የሚያምነውን ሁሉ የሚያጸድቅ ራሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው።
\s5
\v 27 እንግዲህ ትምክህት ወዴት አለ? እርሱ ተወግዷል። ምን ላይ ተመሥርቶ? በሥራ ላይ ነውን? አይደለም፥በእምነት ላይ እንጂ።
\v 28 ስለዚህ ማንኛውም ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት ይጸድቃል እንላለን።
\s5
\v 29 ወይስ እግዚአብሔር የአይሁድ አምላክ ብቻ ነውን? የአሕዛብስ አምላክ አይደለምን? አዎን፥የአሕዛብም ደግሞ ነው።
\v 30 እግዚአብሔር አንድ ከሆነ የተገረዙትንም ሆነ ያልተገረዙትን ስለ እምነታቸው ያጸድቃቸዋል።
\s5
\v 31 እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? እንዲህስ አይሁን። ይልቁንም ሕግን እናጸናለን።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 እንግዲህ በስጋ አባታችን የሆነው አብርሃም ምን አገኘ እንበል?
\v 2 አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን ኖሮ ለመመካት ምክንያት በኖረው ነበር፥ትምክህቱ ግን በእግዚአብሔር ፊት አይደለም።
\v 3 ቅዱሱ መጽሐፍ ምን ይላል? "አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፥ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት" ይላል።
\s5
\v 4 ለሚሠራ ሰው ደሞዙ እንደ ተገቢ መብቱ እንጂ እንደ ነጻ ስጦታ አይቆጠርለትም።
\v 5 ነገር ግን ለማይሠራ ይልቁንም ኃጢአተኛውን በሚያጸድቅ ለሚያምን ለእርሱ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል።
\s5
\v 6 ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን በሚቆጥርለት ሰው ላይ በረከትን ይናገራል።
\v 7 እርሱም፤ "መተላለፋቸው የተተወላቸው፥ ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው እነርሱ የተባረኩ ናቸው።
\v 8 ጌታ ኃጢአቱን የማይቆጥርበት ያ ሰው የተባረከ ነው።" ብሏል።
\s5
\v 9 እንግዲህ ይህ በረከት የተነገረው በተገረዙት ላይ ብቻ ነው ወይስ ደግሞ ባልተገረዙትም ላይ? "ለአብርሃም እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት" እንላለን።
\v 10 ታዲያ እንዴት ነበር የተቆጠረለት? አብርሃም ከመገረዙ በፊት ወይስ በኋላ? ከመገረዙ በፊት እንጂ ከተገረዘ በኋላ አልነበረም።
\s5
\v 11 አብርሃም የመገረዝን ምልክት ተቀበለ። ይህም ከመገረዙ በፊት አስቀድሞ በእምነት ላገኘው ጽድቅ ማኅተም ነበር። የዚህ ምልክት ውጤት ምንም እንኳን ባይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት መሆኑ ነው። ይኸውም ጽድቅ ይቆጠርላቸዋል ማለት ነው።
\v 12 በተጨማሪም ይህ ማለት አብርሃም አባት የሆነው በመገረዝ በኩል ለሚመጡት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የአባታችን የአብርሃምን ምሳሌነት ለሚከተሉትም ነው። ይህም ሳይገረዝ በፊት በነበረው እምነት ነው።
\s5
\v 13 ዓለምን የሚወርሱበት ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው ይህ ተስፋ በሕግ በኩል የተሰጠ አልነበረም። ይልቅ ይህ በእምነት በኩል የተገኘ ጽድቅ ነበር።
\v 14 በሕግ በኩል የሆኑት ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኗል፥ተስፋም ባዶ ሆኗል ማለት ነው።
\v 15 ሕግ ቁጣን ያመጣልና ሕግ ከሌለ አለመታዘዝም የለም።
\s5
\v 16 በዚህ ምክንያት በጸጋ ይሆን ዘንድ ይህ የሚደረገው በእምነት ነው። በመሆኑም ተስፋው ለዘሩ ሁሉ የተረጋገጠ ነው። ይህ ዘር ሕጉን የሚያውቁትን ብቻ ሳይሆን ደግሞም እንደ አብርሃም የሚያምኑትን ያካትታል።
\v 17 "ለሕዝቦች ሁሉ አባት አድርጌሃለሁ" ተብሎ ስለተጻፈ እርሱ የሁላችንም አባት ነው። አብርሃም ለሙታን ሕይወትን በሚሰጥና የሌሉትን ነገሮች ወደ መኖር በሚጠራ በታመነበት በእግዚአብሔር ፊት ነበረ።
\s5
\v 18 ውጫዊ ሁኔታዎች ሁሉ ተስፋ ሰጪዎች ባይሆኑም አብርሃም ስለ ወደፊቱ ሳይጠራጠር በእግዚአብሔር ታመነ። እንዲሁም "ዘርህ እንዲህ ይበዛል" ተብሎ እንደተነገረለት የብዙ ሕዝብ አባት ሆነ።
\v 19 በእምነት ደካማ አልነበረም። አብርሃም በመቶ አመቱ ገደማ የራሱን ሰውነትና የሣራም ማህጸን ምውት መሆኑን ተገነዘበ።
\s5
\v 20 ነገር ግን አብርሃም ከእግዚአብሔር ተስፋ የተነሣ በእምነት ዕጦት አላመነታም። ከዚህ ይልቅ በእምነት በረታ፥ ለእግዚአብሔርም ምስጋናን ሰጠ።
\v 21 እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ሊፈጽመው ደግሞ እንደሚችል በጥብቅ ተረዳ።
\v 22 ስለዚህ ይህም ጽድቅ ሆኖ ተቆጠረለት።
\s5
\v 23 ተቆጠረለት የባለው ለእርሱ ጥቅም ብቻ የተጻፈ አይደለም።
\v 24 ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛም ደግሞ ይቆጠርልን ዘንድ ተጽፏል።
\v 25 እርሱም ስለ መተላለፋችን ተላልፎ የተሰጠውና እኛን ለማጽደቅ ከሙታን የተነሣው ነው።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 በእምነት ስለ ጸደቅን በጌታችን በኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን።
\v 2 እኛም ደግሞ በእርሱ በኩል አሁን ወደቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መቅረብ አለን። በእግዚአብሔር ክብር ውስጥ ተካፋዮች እንሆን ዘንድ እግዚአብሔር ስለወደፊቱ በሰጠን ተስፋ በመተማመን ደስ ይለናል።
\s5
\v 3 ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን በመከራዎቻችን ደግሞ ደስ ይለናል። መከራ መጽናትን እንደሚያደርግ እናውቃለን።
\v 4 መጽናት ተቀባይነትን፥ ተቀባይነትም ስለ ወደፊቱ መተማመኛን ያስገኛል።
\v 5 በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር ወደ ልባችን ውስጥ ስለፈሰሰ ይህ ተስፋ ሐዘን የለበትም።
\s5
\v 6 ክርስቶስ በትክክለኛው ጊዜ ለኃጢአተኞች የሞተው እኛ ገና ደካሞች እያለን ነበር።
\v 7 ስለ ጻድቅ ሰው የሚሞት ከስንት አንዱ ነው። ይህም ማለት ስለ ደግ ሰው ለመሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።
\s5
\v 8 ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች እያለን ክርስቶስ ስለ እኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያረጋግጣል።
\v 9 እንግዲህ አሁን በደሙ ስለ ጸደቅን ይበልጡኑ በእርሱ ከእግዚአብሔር ቁጣ እንድናለን።
\s5
\v 10 ጠላቶች እያለን በልጁ ሞት ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቅን ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን።
\v 11 ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን ይህንን ዕርቅ ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እኛ ደግሞ በእግዚአብሔር ደስ ይለናል።
\s5
\v 12 ስለዚህ በአንድ ሰው አማካይነት ኃጢአት ወደ ዓለም ገባ፥እንደዚሁም ሞት በኃጢአት አማካይነት ገባ። ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ወደ ሰው ሁሉ ደረሰ።
\v 13 ሕግ እስኪመጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረ፥ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኃጢአት አይቆጠርም።
\s5
\v 14 ይሁንና ሊመጣ ላለው ምሳሌ የሆነው የአዳምን አይነት ያለመታዘዝ ኃጢአት ባላደረጉት ላይ እንኳን ሳይቀር ከአዳም እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ።
\v 15 ነጻ ስጦታው ግን እንደ መተላለፉ አይደለም። በአንዱ መተላለፍ ብዙዎች ከሞቱ የእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ በኩል የሆነው ስጦታ ከዚያ ይልቅ ለብዙዎች በዛ።
\s5
\v 16 ስጦታው እንደተሰራው ኃጢአት ውጤት አይደለም። በአንድ ወገን በአንዱ ሰው መተላለፍ ምክንያት የኩነኔ ፍርድ መጣ። በሌላ ወገን ግን ጽድቅን የሚያስገኘው ነጻ ስጦታው ከብዙ መተላለፍ በኋላ መጣ።
\v 17 በአንዱ ሰው መተላለፍ ሞት በእርሱ በኩል ከነገሠ የጸጋን ብዛትና በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት በኩል የጽድቅን ስጦታ የተቀበሉት አብልጠው ይነግሳሉ።
\s5
\v 18 እንግዲህ በአንዱ መተላለፍ በኩል ሰዎች ሁሉ ወደ ኩነኔ እንደመጡ እንዲሁ በአንዱ የጽድቅ ሥራ ለሰዎች ሁሉ የሕይወት መጽደቅ መጣ።
\v 19 በአንድ ሰው አለመታዘዝ በኩል ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደሆኑ እንዲሁ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።
\s5
\v 20 ነገር ግን ሕግ ከጎን በመግባቱ መተላለፍ በዛ። ይሁን እንጂ ኃጢአት በበዛበት በዚያ ጸጋ ይበልጡኑ በዛ።
\v 21 ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለዘላለም ሕይወት ጸጋው በጽድቅ አብልጦ እንዲነግሥ ይህ ሆነ።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1-3 እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ በኃጢአት ውስጥ መኖራችንን እንቀጥልን? እንዲህ አይሁን። ለኃጢአት የሞትን እኛ እንዴት በእርሱ ውስጥ መኖር እንቀጥላለን? ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የተጠመቁ ሁሉ ወደ ከሞቱ ጋር ለመተባበር እንደተጠመቁ አታውቁምን?
\s5
\v 4 እንግዲህ ከሞቱ ጋር ለመተባበር በጥምቀት አማካይነት ከእርሱ ጋር ተቀብረናል። ይህም የሆነው ልክ ክርስቶስ በአብ ኃይል ከሙታን እንደ ተነሣ እኛ ደግሞ በታደሰ ሕይወት እንድንመላለስ ነው።
\v 5 ሞቱን በሚመስለው ከእርሱ ጋር ከተባበርን ከትንሣኤው ጋር ደግሞ እንተባበራለን።
\s5
\v 6 የኃጢአት ሰውነት ይጠፋ ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ ይህንን እናውቃለን። ይህም የሆነው ከዚህ በኋላ ለኃጢአት እንዳንገዛ ነው።
\v 7 ከኃጢአት አኳያ ሲታይ የሞተ ሰው መጽደቁ ታውጆለታል።
\s5
\v 8 ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር አብረን እንደምንኖር ደግሞ እናምናለን።
\v 9 ክርስቶስ ከሙታን እንደ ተነሣና ሞቶ እንዳልቀረ እናውቃለን። ከዚህ በኋላ ሞት አይገዛውም።
\s5
\v 10 ስለኃጢአት የሞተው ሞት ለዘላለም የሚሠራ የአንድ ጊዜ ሞት ነው። ይሁንና የሚኖረውን ሕይወት ለእግዚአብሔር ይኖራል።
\v 11 ልክ እንደዚሁ እናንተ ደግሞ ለኃጢአት እንደሞታችሁ ነገር ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር እንደምትኖሩ መቁጠር ይገባችኋል።
\s5
\v 12 ስለዚህ ለክፉ ምኞቱ እንድትታዘዙ በሚፈልግ የሚሞት ሥጋችሁ ላይ ኃጢአት እንዲነግሥ አትፍቀዱለት።
\v 13 ከሙታን ሕያው እንደመሆናችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ እንጂ የሰውነት ክፍሎቻችሁን የአመጻ መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ። የሰውነት ክፍሎቻችሁን ለእግዚአብሔር የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ አቅርቡ።
\v 14 ኃጢአት እንዲገዛችሁ አትፍቀዱለት። ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና።
\s5
\v 15 እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ባለመሆናችን ኃጢአት መሥራት አለብን? ከቶ እንዲህ አይሁን።
\v 16 ትታዘዙት ዘንድ ራሳችሁን እንደ አገልጋይ ለምታቀርቡለት ለእርሱ አገልጋዮች እንደሆናችሁ አታውቁምን? ወደ ሞት የሚመራችሁ የኃጢአት አገልጋዮች ወይም ወደ ጽድቅ የሚመራችሁ የመታዘዝ አገልጋዮች ናችሁ።
\s5
\v 17 ቀድሞ የኃጢአት አገልጋዮች ነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁ ትምህርት ከልባችሁ ስለ ታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
\v 18 ከኃጢአት ነጻ ተደርጋችኋል፥የጽድቅም አገልጋዮች ሆናችኋል።
\s5
\v 19 በሥጋችሁ ድካም ምክንያት እንደ ሰው ልማድ እናገራለሁ። ልክ የሰውነታችሁን ክፍሎች ለእርኩሰትና ለክፋት እንደ ባሪያ አድርጋችሁ እንዳቀረባችሁ እንደዚያው አሁን የሰውነት ክፍሎቻችሁ ሊቀደሱ የጽድቅ ባሪያዎች አድርጋችሁ አቅርቡ።
\v 20 የኃጢአት ባሪያዎች በነበራችሁበት ጊዜ ከጽድቅ ውጪ ነበራችሁ።
\v 21 አሁን በምታፍሩባቸው በእነዚያ ነገሮች ያን ጊዜ ምን ተጠቀማችሁባቸው? ምክንያቱም የእነዚያ ነገሮች ውጤት ሞት ነው።
\s5
\v 22 አሁን ግን ከኃጢአት ነጻ ስለተደረጋችሁና ለእግዚአብሔር ባሪያዎች ስለሆናችሁ ለመቀደስ ፍሬ ታፈራላችሁ። ውጤቱም የዘላለም ሕይወት ነው።
\v 23 የኃጢአት ደሞዝ ሞት ሲሆን የእግዚአብሔር ነጻ ስጦታ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የዘላለም ሕይወት ነው።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ፥ሰው በሕይወት እስካለ ድረስ ሕግ እንደሚገዛው አታውቁምን? ይህንን የምለው ስለ ሕግ ለሚያውቁት ነው።
\s5
\v 2 ያገባች ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ለእርሱ በሕግ የታሰረች ነች፥ባሏ ቢሞት ግን ከጋብቻ ሕግ ነጻ ትሆናለች።
\v 3 እንግዲህ ባሏ በሕይወት እያለ ከሌላ ወንድ ጋር ብትኖር አመንዝራ ትባላለች። ባሏ ቢሞት ግን ከሕጉ ነጻ ስለሆነች ከሌላ ወንድ ጋር ብትኖርም አመንዝራ አትሆንም።
\s5
\v 4 ስለዚህ ወንድሞቼ ሆይ፥እናንተም በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ምውት ተደርጋችኋል። ይኸውም ለእግዚአብሔር ፍሬ እናፈራ ዘንድ ከሌላው ማለትም ከሙታን ከተነሣው ጋር እንድትተባበሩ ነው።
\v 5 በሥጋ በነበርንበት ጊዜ ኃጢአታዊ ምኞት በሕግ በኩል ሞትን ሊያፈራ በሰውነታችን ክፍሎች ይሠራ ነበር።
\s5
\v 6 አሁን ግን ከሕግ ነጻ ተደርገናል። ተይዘን ለነበርንበት ለዚያ ሞተናል።ይኸውም በአሮጌው ፊደል ሳይሆን በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ እንድናገለግል ነው።
\s5
\v 7 እንግዲህ ምን እንላለን? ሕጉ ራሱ ኃጢአት ነውን? አይደለም። ይሁንና በሕግ በኩል ባይሆን ኖሮ ኃጢአትን አላውቅም ነበር። ሕጉ "አትጎምጅ" ባይል ኖሮ መጎምጀትን አላውቅም ነበር።
\v 8 ነገር ግን ኃጢአት በትዕዛዛት አማካይነት ዕድል አገኘና መጎምጀትን ሁሉ በውስጤ አመጣ። ምክንያቱም ኃጢአት ያለ ሕግ ምውት ስለሆነ ነው።
\s5
\v 9 በአንድ ወቅት ያለ ሕግ ሕያው ነበርኩ፥ትዕዛዝ በመጣ ጊዜ ግን እኔ ሞትኩኝና ኃጢአት ህያው ሆነ።
\v 10 ሕይወትን እንዲያመጣ የተሰጠው ትዕዛዝ ለእኔ ሞት ሆነ።
\s5
\v 11 ምክንያቱም ኃጢአት በሕግ አማካይነት ዕድል አግኝቶ አታሎኛል። በትዕዛዝ አማካይነትም ገደለኝ።
\v 12 በመሆኑም ሕጉ ቅዱስ ነው፥ትዕዛዙም ቅዱስ፥ጻድቅና በጎ ነው።
\s5
\v 13 ስለዚህ በጎ የሆነው እርሱ ለእኔ ሞት ሆነብኝን? አይደለም። ነገር ግን ኃጢአት በጎ በሆነው በእርሱ አማካይነት ኃጢአትነቱ ይታወቅ ዘንድ በእኔ ሞትን አመጣብኝ። ይህ የሆነው በሕግ አማካይነት ኃጢአት ያለ ልክ ኃጢአታዊ ይሆን ዘንድ ነው።
\v 14 ሕጉ መንፈሳዊ መሆኑን እናውቃለንና እኔ ግን ሥጋዊ ነኝ። ለኃጢአት ባርነት ተሽጫለሁ።
\s5
\v 15 በርግጥ የማደርገውን አላውቅም። ለማድረግ የምፈልገውን አላደርግም፥ለማድረግ የምጠላውን ግን ያንኑ አደርጋለሁ።
\v 16 ለማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆንሁ ሕጉ መልካም ስለመሆኑ እስማማበታለሁ።
\s5
\v 17 አሁን ግን ያንን የሚያደርገው በእኔ የሚኖረው ኃጢአት ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።
\v 18 በእኔ ማለትም በሥጋዬ ውስጥ ምንም መልካም ነገር እንደሌለ አውቃለሁ። መልካም የማድረግ ፍላጎቱ አለኝ፥ነገር ግን ላደርገው አልችልም።
\s5
\v 19 የምፈልገውን ያንን መልካሙን አላደርግም ክፉውን፥ያንን የማልፈልገውን ግን አደርጋለሁ።
\v 20 ለማድረግ የማልፈልገውን የማደርግ ከሆነ እንግዲህ አሁን ያንን የሚያደርገው በእኔ ውስጥ የሚኖረው ኃጢአት እንጂ እኔ አይደለሁም።
\v 21 እንግዲህ መልካም የሆነውን ለማድረግ የሚፈልግ ሕግ በውስጤ እንዳለ አያለሁ፥ነገር ግን በተግባር በውስጤ ያለው ክፋት ሆኖ አገኘዋለሁ።
\s5
\v 22 በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል።
\v 23 ነገር ግን በሰውነቴ ክፍሎች ውስጥ ሌላ ሕግ አያለሁ። እርሱም በአዕምሮዬ ውስጥ ያለውን አዲሱን ሕግ በመቃወም ይዋጋል። በሰውነት ክፍሎቼ ውስጥ ባለ የኃጢአት ሕግ ይማርከኛል።
\s5
\v 24 እኔ ምስኪን ሰው ነኝ! ለሞት ከሚዳርገኝ ከዚህ ሰውነት ማን ይታደገኛል?
\v 25 እንግዲያውስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኔ ራሴ በአእምሮዬ የእግዚአብሔርን ሕግ አገለግላለሁ። ሆኖም በሥጋ የማገለግለው የኃጢአትን ሕግ ነው።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም።
\v 2 ምክንያቱም በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ያለው የመንፈስ ቅዱስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶኛል።
\s5
\v 3 በሥጋ ድካም ምክንያት ሕግ ሊፈጽመው ያልተቻለውን እግዚአብሔር ፈጽሞታል። እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአታዊ ሥጋ ምሳሌ ለኃጢአት መሥዋዕት ይሆን ዘንድ ልኮ ኃጢአትን በሥጋው ኮነነ።
\v 4 ይህንንም ያደረገው እንደ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ፈቃድ በማንመላለስ በእኛ የሕጉ ትዕዛዛት ይፈጸሙ ዘንድ ነው።
\v 5 እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ ስለሥጋዊ ነገሮች ያስባሉ፥እንደ መንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን ስለመንፈስ ቅዱስ ነገሮች ያስባሉ።
\s5
\v 6 የሥጋ አስተሳሰብ ሞት ሲሆን የመንፈስ ቅዱስ አስተሳሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።
\v 7 ይህ የሆነበት ምክንያት የሥጋ አስተሳሰብ ለእግዚአብሔር ሕግ ስለማይገዛ፥መገዛትም ስለማይችል የእግዚአብሔር ጠላት በመሆኑ ነው።
\v 8 በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ለማስደሰት አይችሉም።
\s5
\v 9 ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ውስጥ መኖሩ እውነት ከሆነ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። ነገር ግን የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ማንም ቢሆን ይህ የእርሱ ወገን አይደለም።
\v 10 ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢኖር ሥጋ በኃጢአት ምክንያት ምውት ነው፥ መንፈስ ግን በጽድቅ ምክንያት ህያው ነው።
\s5
\v 11 ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው የእርሱ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ ቢኖር ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው እርሱ በውስጣችሁ በሚኖረው በቅዱስ መንፈሱ አማካይነት ለሚሞተው ሰውነታችሁ ደግሞ ሕይወትን ይሰጠዋል።
\s5
\v 12 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ ዕዳ አለብን፥ነገር ግን እንደ ሥጋ ፈቃድ ልንኖር ለሥጋ አይደለም።
\v 13 እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ መሞታችሁ አይቀርም፥የሥጋን ሥራ በመንፈስ ቅዱስ ብትገድሉ ግን በሕይወት ትኖራላችሁ።
\s5
\v 14 በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
\v 15 ተመልሳችሁ እንድትፈሩ የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም። ይልቅ የተቀበላችሁት "አባ፥አባት" ብለን የምንጮህበትን የልጅነትን መንፈስ ነው።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን መንፈስ ቅዱስ ራሱ ከመንፈሳችን ጋር ይመሰክራል።
\v 17 ልጆች ከሆንን ወራሾችም ነን፥ማለትም የእግዚአብሔር ወራሾች ነን። ከእርሱ ጋር እንድንከብር በርግጥ አብረነው ደግሞ መከራን ብንቀበል ከክርስቶስ ጋር አብረን የምንወርስ ነን።
\s5
\v 18 የአሁኑ ዘመን መከራ ሊገለጥልን ካለው ክብር ጋር ሊነጻጸር እንደማይገባው አስባለሁ።
\v 19 ምክንያቱም ፍጥረት የእግዚአብሔርን ልጆች መገለጥ በናፍቆት ስለሚጠባበቅ ነው።
\s5
\v 20 ፍጥረት ለከንቱነት ተገዝቷልና ይህም ባስገዛው ፈቃድ እንጂ በራሱ ፈቃድ አይደለም። አስተማማኙ ተስፋም
\v 21 ፍጥረት ራሱ ከመበስበስ ባርነት ነጻ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ልጆች የክብር ነጻነት ይደርስ ዘንድ ነው።
\v 22 አሁን እንኳን መላው ፍጥረት አብሮ በመቃተትና በምጥ ጣር ላይ መሆኑን እናውቃለን።
\s5
\v 23 ይህም ብቻ አይደለም፥ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ የመጀመሪያው ፍሬ ያለን እኛ፥የሰውነታችን ቤዛ የሚሆነውን ልጅነታችንን እየተጠባበቅን እኛ ራሳችን እንኳን በውስጣችን እንቃትታለን።
\v 24 የዳንነው በዚህ ተስፋ ነው። ነገር ግን ተስፋ የምናደርገው የማይታየውን ነው፥የሚያየውንማ ማን በተስፋ ይጠባበቃል?
\v 25 ገና ያላየነውን ተስፋ የምናደርግ ከሆነ ግን እንግዲያው በትዕግስት እንጠባበቀዋለን።
\s5
\v 26 እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በድካማችን ውስጥ ያግዘናል። እንዴት መጸለይ እንደሚገባን ስለማናውቅ መንፈስ ቅዱስ ራሱ በቃላት ሊገለጥ በማይቻል መቃተት ስለ እኛ ይማልድልናል።
\v 27 መንፈስ ቅዱስ ስለ አማኞች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለሚማልድ ልብን የሚመረምረው እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ሃሳብ ያውቃል።
\s5
\v 28 እግዚአብሔርን ለሚወዱት፥ በዓላማው ለተጠሩት ለእነርሱ ሁሉን ነገር አጣጥሞ ለመልካም እንደሚሠራላቸው እናውቃለን።
\v 29 ምክንያቱም አስቀድሞ ያወቃቸውን እነርሱን በብዙ ወንድሞች መካከል በኩር ይሆን ዘንድ የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወሰነ።
\v 30 አስቀድሞ የወሰናቸውን ደግሞ ጠራቸው። የጠራቸውን ደግሞ አጸደቃቸው። ያጸደቃቸውን ደግሞ አከበራቸው።
\s5
\v 31 እንግዲህ ስለእነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?
\v 32 ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ እንዴት ሁሉን ነገር ደግሞ ከልጁ ጋር በነጻ አይሰጠንም?
\s5
\v 33 እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይኮንናቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።
\v 34 የሚኮንንስ ማነው? ስለ እኛ የሞተው፥ ይልቁንም ደግሞ ከሞት የተነሣው ክርስቶስ ነው። እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር በክብር ሥፍራ ይገዛል፥ስለ እኛም እየማለደልን ያለው እርሱ ነው።
\s5
\v 35 ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ወይስ ጭንቀት ወይስ ስደት ወይስ ራብ ወይስ ራቁትነት ወይስ አደጋ ወይስ ሰይፍ ይለየናልን?
\v 36 "ቀኑን ሙሉ ስለአንተ ብለን እንገደላለን። እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን" ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
\s5
\v 37 በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ውስጥ በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።
\v 38 ሞት ቢሆን ሕይወት፥ መላእክት ቢሆኑ መንግሥታት፥አሁን ያሉት ነገሮች ወይም ሊመጡ ያሉት ቢሆኑ፥ ኃይላት ቢሆኑ፥
\v 39 ከፍታም ቢሆን ዝቅታ፥ የትኛውም ሌላ ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየኝ እንደማይችል ተረድቻለሁ።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 በክርስቶስ እውነትን እናገራለሁ እንጂ አልዋሽም፣ ህሊናዬ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሆኖ ይመሰክርልኛል፣
\v 2 ከፍተኛ ሀዘንና የማያቋርጥ ህመም በልቤ ውስጥ አለ።
\s5
\v 3 በሥጋ ዘሮቼ ስለሆኑት ወንድሞቼ ሲባል እኔ እራሴ በተረገምኩና ከክርስቶስ በተለየሁ ብዬ እመኛለሁ።
\v 4 እነርሱ እስራኤላውያን ናቸው። የልጅነት መብት ፥ክብሩ፥ቃል ኪዳኑ፥የህግ ስጦታው፥የአምልኮ ሥርዓቱ፥ የተስፋው ቃል አላቸው።
\v 5 ከሁሉ በላይና ለዘላለም የእግዚአብሔር ብሩክ የሆነው ክርስቶስ በሥጋ የመጣው ከአባቶቻቸው ነው። ለእርሱ ለዘላለም ምስጋና ይሁን። አሜን!
\s5
\v 6 ነገር ግን የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል ተሻረ ማለት አይደለም። ምክንያቱም በእስራኤል የሚኖር ሁሉ እስራኤላዊ አይደለም።
\v 7 ወይም የአብርሀም ዘር ሁሉ የአብርሀም ልጆች አይደሉም። ነገር ግን «ዘርህ በይስሀቅ ይጠራልሀል» ተባለ።
\s5
\v 8 ይህም ማለት የሥጋ ልጆች የሆኑ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም። የተስፋው ቃል ልጆች ግን ዘሮቹ ሆነው ተቆጠሩ።
\v 9 የተስፋው ቃል «በዚህ ጊዜ ተመልሼ እመጣለሁ ለሳራም ልጅ ይሰጣታል» የሚል ነው።
\s5
\v 10 ይህ ብቻ አይደለም፣ ርብቃ ከአባታችን ከይስሀቅ
\v 11 ከጸነሰች በኋላ በምርጫ የሆነው የእግዚአብሔር ዓላማ ከሥራ የተነሳ ሳይሆን ከእርሱ ጥሪ የተነሳ ይጸና ዘንድ ልጆቹ ገና ሳይወለዱና ክፉም ሆነ ደግ ሳያደርጉ
\v 12 «ታላቁ ለታናሹ ይገዛል» ተብሎ ተነግሯት ነበር።
\v 13 ልክ «ያዕቆብን ወደድኩ ኤሳውን ጠላሁ» ተብሎ እንደተጻፈው ማለት ነው።
\s5
\v 14 እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ የጽድቅ መጓደል አለ ማለት ነው? በጭራሽ አይደለም።
\v 15 ምክንያቱም ለሙሴ «የምምረውን እምራለሁ ለምራራለትም እራራለሁ» ብሎታል።
\v 16 ስለዚህም ምህረት ለፈለገ ወይም ለሮጠ ሳይሆን ምህረትን ከሚያሳይ ከእግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 17 ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ስለፈርዖን ሲናገር «ኃይሌን በአንተ ላይ አሳይ ዘንድ ስሜም በምድር ሁሉ ይታወቅ ዘንድ ለዚህ ዋና ዓላማ አስነሳሁህ» ይላል።
\v 18 ስለዚህም ከፈለገ ለአንዱ ምህረትን ይሰጠዋል ሌላውን ደግሞ ግትር ያደርገዋል።
\s5
\v 19 «ታዲያ ሁልጊዜ ፈቃዱን የሚያደርግ ከሆነ ለምን ስህተትን ይፈልግብናል?» ትሉኝ ይሆናል።
\v 20 በአንጻሩ ለእግዚአሔር መልስ የምትስጥ አንተ ማን ነህ? የሸክላ ጭቃ ቅርጽ ያወጣለትን ሰው ለምን እንደዚህ አድርገህ ሰራኽኝ ሊለው ይችላልን? ።
\v 21 ሸክላ ሰሪው ከዚያው ጭቃ አንዱን ለየት ባለ ቀን አገልግሎት ላይ የሚውል ዕቃ ሌላውን ደግሞ በየቀኑ አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ አድርጎ ሊሰራው በሸክላ ጭቃው ላይ ሥልጣን የለውም እንዴ?
\s5
\v 22 ቁጣውን ሊያሳይና ኃይሉ እንዲታወቅ የሚፈልገው እግዚአብሔር ለጥፋት የተዘጋጁትን የቁጣ ዕቃዎችአብዝቶ ሊታገሳቸው ቢፈልገስ?
\v 23 ይህን ያደረገው አስቀድሞ ለክብር ባዘጋጃቸው የምህረት ዕቃዎቹ ላይ ክብሩን ሊያሳይ ቢሆንስ?
\v 24 ይህንን ለአይሁድ ብቻ ሳይሆን ከአህዛብ ለተጠራን ለእኛም ቢያደርገውስ?
\s5
\v 25 በትንቢት ሆሴዕም ላይ «ህዝቤ ያልሆነውን ህዝቤ ብዬ ያልተወደደችውንም የተወደደች ብዬ እጠራለሁ።
\v 26 'ህዝቤ አይደላችሁም በተባሉበት በዚያው ቦታ 'የህያው እግዚአብሔር ልጆች' ይባላሉ» እንደሚለው ነው።
\s5
\v 27 ኢሳያስ ስለእስራኤል «የእስራኤል ልጆች ብዛት እንደ ባህር አሸዋ ቢሆን እንኳ የሚድኑት ግን ትሩፋን ናቸው» ብሎ ይጮኸል።
\v 28 ምክንያቱም እግዚአብሔር ቃሉን በምድር ላይ ሙሉ በሙሉ ፈጥኖ ይፈጽማል።
\v 29 ይህም ኢሳያስ ቀደም ሲል «የሠራዊት ጌታ ዘር ባያስቀርልን ኖሮ እንድ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በሆነብን ነበር» እንዳለው ነው።
\s5
\v 30 እንግዲህ ምን እንላለን? ለጽድቅ ያልሮጡት አህዛብ በእምነት የሆነውን ጽድቅ አገኙ።
\v 31 ለጽድቅ ህግ የተጉት እስራኤል ግን ወደዚያ ሊደርሱ አልቻሉም።
\s5
\v 32 ለምን አልደረሱም? ምክንያቱም ጽድቅን የፈለጉት በእምነት ሳይሆን በሥራ ስለሆነ ነው። በማሰናከያው ድንጋይ ተሰናከሉበት።
\v 33 «በጽዮን የማሰናከያ ድንጋይና የዕንቅፋት ዐለት አስቀምጣለሁ በእርሱ የሚያምን አያፍርም» ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ስለእነርሱ ለእግዚአብሔር የማቀርበው ልመና እንዲድኑ ነው።
\v 2 በእውቀት የሆነ ባይሆንም ለእግዚአብሔር እንደሚቀኑ እኔ ራሴ ስለእነርሱ እመሰክራለሁ።
\v 3 የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁምና የራሳቸውን ጽድቅ ሊመሰርቱ ይጥራሉ፤ለእግዚአብሔርም ጽድቅ ራሳቸውን አያስገዙም።
\s5
\v 4 ምክንያቱም ክርስቶስ ለሚያምን ሁሉ ለጽድቅ የሚሆን የህግ ፍጻሜ ነው።
\v 5 ሙሴ ከህግ ስለሚመጣ ጽድቅ ሲናገር «ከህጉ የሆነውን ጽድቅ የሚያደርግ በዚያው ጽድቅ ይኖራል።» ይላልና።
\s5
\v 6 በእምነት ስለሚሆን ጽድቅ ግን «በልብህ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል አትበል (ይህ ክርስቶስን ማውረድ ነውና)
\v 7 ወይም ወደ ሲዖል ማን ይወርዳል አትበል (ይህ ክርስቶስን ከሙታን መካከል ማውጣት ነውና)።» ይላል።
\s5
\v 8 ነገር ግን ቃሉ ምን ይላል? «ቃሉ ለአፍህና ለልብህ ቅርብ ነው።» ይላል። የምንሰብከው የእምነት ቃል ይህ ነው።
\v 9 ስለዚህም ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ።
\v 10 ምክንያቱም ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃል በአፉ መስክሮ ደግሞ ይድናል።
\s5
\v 11 ምክንያቱም መጽሀፍ እንደሚል «በእርሱ የሚያምን አያፍርም» ።
\v 12 በዚህ ጉዳይ በአይሁድና በግሪክ ልዩነት የለም። ያው አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና ለሚጠሩትም ሁሉ ባለጠጋ ነው።
\v 13 የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።
\s5
\v 14 ታዲያ ያላመኑበትን እንዴት ይጠሩታል? ስለእርሱ ሳይሰሙስ እንዴት ያምኑበታል?
\v 15 ያለ ሰባኪስ ከየት ይሰማሉ? «በመልካም ነገር የተሞላ ደስታን የሚሰብኩ እግሮች እንዴት ያማሩ ናቸው» ተብሎ እንድተጻፈ፣ ሳይላኩስ እንዴት ይሰብካሉ?
\s5
\v 16 ነገር ግን ኢሳያስ «ጌታ ሆይ መልዕክታችንን ማን አምኗል» እንዳለው ሁሉም ወንጌልን አልተቀበሉም።
\v 17 ስለዚህ እምነት የሚመጣው ከመስማት ሲሆን መሰማት ያለበትም የክርስቶስ ቃል ነው።
\s5
\v 18 ነገር ግን «አልሰሙ ይሆንን?» እላለሁ። በሙሉ እርግጠኝነት ሰምተዋል።«ድምጻቸው በምድር ሁሉ ላይ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ደርሷል።»
\s5
\v 19 በተጨማሪም «እስራኤል አያውቁምን?» እላለሁ። ሙሴ አስቀድሞ «ህዝብ ባልሆነ በእሱ በቅናት አነሳሳችኋለሁ። በማያስተውልም ህዝብ በቁጣ አናውጣችኋለሁ» ይላል።
\s5
\v 20 ደግሞም ኢሳያስ በድፍረት «ላልፈለጉኝ ተገኘሁ ላልጠየቁኝም ተገለጥኩ» ይላል።
\v 21 ስለእስራኤል ግን «ለዚህ የማይታዘዝና ደንዳና ህዝብ ቀኑን ሙሉ እጄን ዘረጋሁ» ይላል።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 ታዲያ እግዚአብሄር ህዝቡን ጣላቸውን? ፥በጭራሽ። ምክንያቱም እኔ ራሴ ከቢንያም ወገን የሆንኩ የአብርሀም ዘር እስራኤላዊ ነኝ።
\v 2 እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ህዝቡን አልጣላቸውም። ኤልያስ እስራኤልን በመቃወም ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት እንደተከራከረ መጽሀፍ የሚለውን አታውቁምን?
\v 3 «ጌታ ሆይ ነቢያትህን ገድለዋል፣ መሰዊያዎችህንም አፍርሰዋል፣ እኔም ብቻዬን ቀርቻለሁ ሊገድሉኝም እየፈለጉኝ ነው።»
\s5
\v 4 ነገር ግን እግዚአብሔር ምን ብሎ መለሰለት? «ለበዓል ያልሰገዱ ሰባት ሺ ሰዎችን ለራሴ ጠብቄ አቆይቻለሁ።»
\v 5 በዚህም በአሁኑ ዘመንም ከጸጋ ምርጫ የተነሳ ትሩፋን አሉ።
\s5
\v 6 ነገር ግን በጸጋ ከሆነ ከእንግዲህ በሥራ አይደለም።አለዚያ ጸጋ ከእንግዲህ ጸጋ መሆኑ ቀርቷል።
\v 7 እንግዲህ ምን ይሁን፣ እስራኤል ይፈልገው የነበረውን ነገር አላገኘም ፥ የተመረጡት ግን አግኝተውታል፥ የቀሩት ግን ደንዳኖች ሆነዋል።
\v 8 ይህም ልክ «እያዩ እንዳያዩ እየሰሙ እንዳይሰሙ እስከ አሁን እግዚአብሔር ያለማስተዋልን መንፈስ ሰጣቸው» ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
\s5
\v 9 ዳዊትም «ገበታቸው መረብ፥ወጥመድ፥የእንቅፋት ድንጋይና የበቀል ይሁንባቸው» ይላል።
\v 10 እንዳያዩ አይናቸው ይጨልም፥ ሁልጊዜ ጀርባቸው እንደጎበጠ ይቅር።» ይላል።
\s5
\v 11 «እስኪወድቁ ድረስ ተሰናከሉ» እላለሁን? ፈጽሞ አይሁን። በቅናት ሊያነሳሳቸው በእነርሱ ውድቀት ለአህዛብ ድነት ሆነ።
\v 12 እንግዲህ ውድቀታቸው ለዓለም ሙላት ከሆነ ጉድለታችው ለአህዛብም ሙላት ከሆነ ሙላታቸው እንዴት ታላቅ ይሆን?
\s5
\v 13 አሁን ለእናንተ ለአህዛብ እናገራለሁ። የአህዛብ ሀዋሪያ እንደመሆኔ በአገልግሎቴ እመካለሁ።
\v 14 ምናልባት የገዛ ሥጋዬ የሆኑትን አስቀናና አንዳንዶቹን እናድን ይሆናል።
\s5
\v 15 የእነኚያ መጣል ለዓለም የመታረቅ ምክንያት ከሆነ ተቀባይነት ማግኘታቸው ከሞት ወደ ህይወት ማምለጥ ካልሆን ምን ሊሆን ይችላል?
\v 16 በኩሩ ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ነው። ሥሩ ቅዱስ ከሆነ ቅርንጫፉ ቅዱስ ነው።
\s5
\v 17 ነገር ግን አንዳንዶቹ ቅርንጫፎች በመሰበራቸው ምክንያት አንተ የበረሀ ወይራ ዛፍ ቅርንጫፍ ባልወደቁት ቅርንጫፎች መካከል ብትጣበቅና የወይራ ዛፉን ሥር ብልጽግና ተካፋይ ብትሆን
\v 18 በቅርንጫፎቹ ላይ አትኩራራ። ብትኩራራ ግን ሥሩ አንተን ተሸከምህ እንጂ አንተ ሥሩን አልተሸከመከውም።
\s5
\v 19 «ቅርንጫፎቹ ስለተሰበሩ እኔ ተተካሁ» ትላለህ።
\v 20 እውነት ነው ባለማመናቸው ምክንያት እነርሱ ተቆርጠው ወድቀዋል አንተ ደግሞ በእምነት ቆመሀል። ፍራ እንጂ ራስህ ከፍ አድርገህ አታስብ።
\v 21 እግዚአብሔር ለመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ካልራራ ለአንተም አይራራልህም።
\s5
\v 22 እንግዲህ የእግዚአብሔርን የምህረት ሥራና ጭካኔ አስተውል። በአንድ በኩል ጭካኔው በወደቁት በአይሁድ ላይ መጣ፥በሌላ በኩል ደግሞ ጸንታችሁ ከቆያችሁ ምህረቱ ወደ እናንተ መጥቷል። አለበለዚያ ግን እናንተም ተቆርጣችሁ ትጣላላችሁ።
\s5
\v 23 ደግሞም እነርሱ ባለማመናቸው ካልጸኑ እንደገና በዛፉ ላይ ሊተከሉ ይችላሉ። እግዚአብሔር እንደገና በዛፉ ላይ ሊተክላቸው ይችላልና።
\v 24 እናንተ መነሻችሁ የበረሀ የወይራ ዛፍ የሆነና ተቆርጣችሁ የነበራችሁ ቅርንጫፎች ከተፈጥሮ ህግ ውጪ በመልካሙ የወይራ ዛፍ ላይ እንደገና ከተተከላችሁ የመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች እነኝህ አይሁድ ወደገዛ ዛፋቸው እንዴት እንደግና አይጣበቁም?
\s5
\v 25 ወንድሞች ሆይ በራሳችሁ አስተሳሰብ ጥበበኞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ስለዚህ ምስጢር እንግዳ እንድትሆኑ አልፈልግም፡ የአህዛብ ሙላት እስኪፈጸም ድረስ ከፊል ድንዛዜ በእስራኤል ላይ ወድቋል።
\s5
\v 26 ስለዚህም እስራኤል በሙሉ እንደተጻፈው ይድናሉ። «ከጽዮን ነጻ አውጪ ይነሳል ከያዕቆብም የማይገባ አካሄድን ያስወግዳል።
\v 27 ኃጢአታቸውን በማስወግድላቸው ጊዜ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው።»
\s5
\v 28 በአንድ በኩል ወንጌልን በተመለከተ ስለእናንተ የተጠሉ ናቸው፣ በሌላ በኩል ደግሞ በእግዚአብሔር ምርጫ ምክንያት ስለአባቶቻቸው የተወደዱ ናቸው።
\v 29 ምክንያቱም የእግዚአብሔር ስጦታና ጥሪ አይለወጥም።
\s5
\v 30 እናንተ ቀድሞ ለእግዚአብሔር የማትታዘዙ የነበራችሁ አሁን ግን በእነርሱ አለመታዘዝ ምክንያት ምህረትን አግኝታችኋል።
\v 31 ልክ እንደዚያው ዘንድ እነዚህ አይሁድ አሁን የማይታዘዙ ሆነዋል። በውጤቱም ለእናንት በተሰጠው ምህረት እነርሱ ደግሞ እንዲቀበሉ ነበር።
\v 32 ምህረቱን ለሁሉ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ሁሉን ባለመታዘዝ ዘግቶታልና።
\s5
\v 33 ኦ የእግዚአብሔር ጥበብና እውቀት ባለጠግነት ምን ያህል ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር መንገዱም እንዴት ከመታወቅ ያለፈ ነው!
\v 34 «የጌታን ልብ የሚያውቅ ማነው? አማካሪውስ የሆነ ማነው?
\s5
\v 35 ወይስ መልሶ ይከፍለው ዘንድ ለእግዚአብሔር ያበደረ ማነው?»
\v 36 ሁሉም ነገር ከእርሱ በእርሱና ለእርሱ ነው። ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 ስለዚህም ወንድሞች ሆይ ሥጋችሁን ህያው መስዋዕት፥ቅዱስ፥ ለእግዚአብሔር የሚገባ አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ምህረት እለምናችኋለሁ፥ ያም ተገቢ የሆነ አገልግሎታችሁ ነው።
\v 2 መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።
\s5
\v 3 ከእናንተ ማንም ስለራሱ ሊያስብ ከሚገባው በላይ እንዳያስብ በተሰጠኝ ጸጋ አሳስብለሁ። ይልቁኑም ለእያንዳንዱ ከእግዚአብሔር በተሰጠው እምነት ልክ በጥበብ ሊያስብ ይገባል።
\s5
\v 4 ልክ እኛ በአንድ አካል ላይ ብዙ የአካል ክፍሎች ቢኖሩንም ተግባራቸው ግን ተመሳሳይ አይደለም።
\v 5 እንዲሁ እኛም ብዙዎች ሳለን በክርስቶስ አንድ አካል ነን እያንዳንዳችንም አንዳችን የሌላችን የአካል ክፍል ነን።
\s5
\v 6 በተሰጠን ጸጋ በኩል ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉን። የአንድ ሰው ስጦታ ትንቢት መናገር ከሆነ ባመነው መጠን ያድርገው።
\v 7 የአንዱ ስጦታ ደግሞ ቸርነት ማድረግ ከሆነ ቸርነት ያድርግ። የማስተማር ስጦታ ያለው ያስተምር።
\v 8 የማጽናናት ስጦታ ያለው ያጽናና፤ የመስጠት ስጦታ ያለው በልግስና ያድርገው፤ የመምራት ስጦታ ያለው በጥንቃቄ ይፈጽመው፤ምህረት የማድረግ ስጦታ ያለው በደስታ ያድርገው።
\s5
\v 9 ፍቅራችሁ ያለግብዝነት ይሁን። ክፉ የሆነን ነገር ተጸየፉ፤መልካም የሆነውን ያዙ።
\v 10 እውነተኛ የወንድማማች ፍቅር ይኑራችሁ፤ እርስ በእርሳችሁ ተከባበሩ።
\s5
\v 11 ልግምተኞች አትሁኑ፤በመንፈሳችሁ ንቁ ሁኑ ፥ ጌታንም አገልግሉ።
\v 12 ስላላችሁ የወደፊት ተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ጊዜ ትዕግስተኞች ሁኑ፥ጸሎታችሁ የማያቋርጥ ይሁን፤
\v 13 ቅዱሳንን በችግራቸው እርዱ፤ መልካም ለማድረግ የሚያስችላቹሁን መንገዶች ፈልጉ።
\s5
\v 14 የሚያሳድዷችሁን ባርኳቸው፥ባርኩ እንጂ አትርገሙ።
\v 15 ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።
\v 16 አንድ ልብ ይኑራችሁ፥ትሁት ሰዎችን ተቀበሉዋቸው እንጂ በትዕቢት አታስቡ። በራሳችሁ አመለካከት ጥበበኞች እንደሆናችሁ አታስቡ።
\s5
\v 17 ክፉ ላደረገባችሁ ለማንም ክፉ አትመልሱ። በሰዎች ሁሉ ፊት መልካምን ነገር አድርጉ።
\v 18 በተቻላችሁ መጠን በእናንተ በኩል ከሰዎች ሁሉ ጋር በሠላም ኑሩ።
\s5
\v 19 የተወደዳችሁ ሆይ ስለራሳችሁ አትበቀሉ ይልቁኑ ለእግዚአብሔር ቁጣ ዕድል ስጡ።ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦ «ጌታ 'በቀል የኔ ነው ብድራትን የምከፍለው እኔ ነኝ' ይላል»።
\v 20 «ነገር ግን ጠላትህ ከተራበ መግበው። ከተጠማ ደግሞ የሚጠጣ ስጠው። ይህን ስታደርግ የእሳት ፍም በአናቱ ላይ ትከምራለህ።
\v 21 ክፉን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።»
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ካልተሰጠ በቀር ሥልጣን የለምና ሰው ሁሉ ለመንግስት ባለሥልጣናት ይገዛ። አሁን በሥልጣን ላይ ያለውም የተሾመው በእግዚአብሔር ነው።
\v 2 ስለዚህም ይህን ሥልጣን የሚቃወም የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ይቃወማል፥ የሚቃወሙትም ሁሉ በራሳችው ላይ ፍርድን ያመጣሉ።
\s5
\v 3 ምክንያቱም ገዢዎች ክፉ ለሚያደርጉ እንጂ መልካም ለሚያደርጉ የሚያስፈሩ አይደሉም። ባለሥልጣንን አለመፍራት ትፈልጋለህ? መልካምን አድርግ ከእርሱ ሽልማትን ታገኛለህ።
\v 4 ለመልካም ለአንተ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነውና። ክፉ የምታደርግ ከሆነ ግን ያለምክንያት ሠይፍ አልታጠቀምና ልትፈራ ይገባሀል። ምክንያቱም ክፉ የሚያደርገውን በቁጣ የሚበቀል የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው።
\v 5 ስለዚህ ስለ ቁጣው ብለህ ብቻ ሳይሆን ስለህሊናህ ብለህ ልትገዛ ይገባሀል።
\s5
\v 6 በዚህ ምክንያት ግብርም ትከፍላላችሁ። ምክንያቱም ባለሥልጣናት ይህንን ጉዳይ ያለመታከት የሚቆጣጠሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው።
\v 7 ለእያንዳንዱ የሚገባውን ስጡ፥ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፣ አክብሮት ለሚገባው አክብሮትን ስጡ።
\s5
\v 8 እርስ በእርስ ከመዋደድ በቀር የማንም ዕዳ አይኑርባችሁ። ምክንያቱም ባልንጀራውን የሚወድ ህግን ፈጽሟል።
\v 9 ምክንያቱም «አታመንዝር፥ አትግደል፥ አትስረቅ፥ አትመኝ» የሚሉትና ሌሎቹም ትዕዛዛት «ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ» በሚለው ትዕዛዝ ተጠቃለዋል።
\v 10 ፍቅር ያለው ባልንጀራውን አይጎዳም። ስለዚህ ፍቅር የህጉ ፍጻሜ ነው።
\s5
\v 11 በዚህም ምክንያት ከእንቅልፍ የምትነቁበት እንደደረስ ታውቃላችሁ። መዳናችን መጀመሪያ ካመንበት ጊዜ ይልቅ ቅርብ ነው።
\v 12 ሌሊቱ እያለፈ ቀኑም እየቀረበ ነው። ስለዚህ የጨለማን ሥራ ጥለን የብርሀንን የጦር ዕቃ እንልበስ።
\s5
\v 13 ቅጥ ባጣ ፈንጠዝያና በስካር ሳይሆን በቀን እንደሚመላለስ ሰው በተገቢው ሁኔታ እንመላለስ። በዝሙት ወይም በማይገታ ክፉ ምኞት፥ በጭቅጭቅና በቅናት አንመላለስ ።
\v 14 ይልቁኑ ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት ለሥጋችሁና ለክፉ ምኞቱም ዕድል አትስጡ።
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 በእምነት ደካማ የሆነውን በጥያቄዎቹ ላይ በመፍረድ ሳይሆን በፍቅር ተቀበሉት።
\v 2 አንዳንዱ ማንኛውንም ነገር በእምነት ይበላል፥በእምነቱ ደካማ የሆነው ደግሞ አትክልት ብቻ ይበላል።
\s5
\v 3 ስለዚህ ማንኛውንም ዓይነት ምግብ የሚበላው የማይበላውን አይናቀው። የማይበላውም በሚበላው ላይ አይፍረድ። ምክንያቱም እግዚአብሔር ተቀብሎታል።
\v 4 በሌላው አገልጋይ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? በገዛ ጌታው ፊት ወይ ይቆማል አሊያም ይወድቃል። ነገር ግን ጌታ ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።
\s5
\v 5 አንደኛው አንዱን ቀን ከሌላው ቀን የሚበልጥ አድርጎ ይቆጥራል። ሌላው ደግሞ ሁሉም ቀናት አንድ ናቸው ብሎ ያምናል። እያንዳንዱ ሰው የራሱ መረዳት ይኑረው።
\v 6 ቀንን የሚያከብር ለእግዚአብሔር ብሎ ያከብራል፥ የሚበላውም እግዚአብሔርን ያመሰግናልና ለእግዚአብሔር ብሎ ይበላል። የማይበላውም ራሱን ከመብላት ያቅባል። እርሱም እግዚእብሔርን ያመሰግናል።
\s5
\v 7 ምክንያቱም ከእኛ ማንም ለራሱ የሚኖር ወይም የሚሞት የለም።
\v 8 ብንኖር ለጌታ እንኖራልንና ብንሞትም ለጌታ እንሞታለንና። እንግዲያውስ ብንኖርም ብንሞትም የጌታ ነን።
\v 9 ምክንያቱም በሙታንና በህያዋን ላይ ጌታ ይሆን ዘንድ ለዚህ ዓላማ ክርስቶስ ሞቷል ደግሞም ህያው ሆኗል።
\s5
\v 10 ግን አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? አንተስ ወንድምህን ለምን ትንቃለህ? ሁላችንም በእግዚአብሔር የፍርድ ዙፋን ፊት እንቆማለን።
\v 11 ምክንያቱም «እኔ ህያው ነኝና ጉልበት ሁሉ በፊቴ ይንበረከካል ምላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል» ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፏል።
\s5
\v 12 ስለዚህም እያንዳንዳችን ስለ ስራችን በእግዚአብሔር ፊት መልስ እንሰጣለን።
\v 13 ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ አንዳችን በሌላችን ላይ አንፍረድ በዚያ ፋንታ ማንም በወንድሙ ፊት መሰናክል ወይም ወጥመድ እንዳያስቀምጥ እንወስን።
\s5
\v 14 ምንም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ በጌታ በኢየሱስ አውቃለሁ ተረድቻለሁም። ማንኛውም ነገር ርኩስ ነው ብሎ ለሚያስብ ለእርሱ ብቻ ያ ነገር እርኩስ ነው።
\v 15 በምግብ ጉዳይ ወንድምህን የምታሰናክል ከሆነ አንተ በፍቅር እየተመላለስክ አይደለም። ስለምግብህ ብለህ ክርስቶስ የሞተለትን ሰው አታጥፋ።
\s5
\v 16 ስለዚህ መልካም ስራዎቻችሁን ለሰዎች መቀለጃ አታድርጉ።
\v 17 ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚሆን ጽድቅ፥ ሠላምና ደስታ እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም።
\s5
\v 18 ክርስቶስ እንዲህ ባል ሁኔታ የሚያገለግለውን እግዚአብሔር ይቀበለዋል በሰዎችም ይመሰገናል።
\v 19 ስለዚህ ሠላም የሚገኝበትንና እርስበእርሳችን የምንተናነጽባቸውን ነገሮች እንፈልግ።
\s5
\v 20 በምግብ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሥራ አታበላሹ። በእርግጥም ሁሉ ነገር ንጹህ ነው፥ ነገር ግን እየተጠራጠረ ለሚበላ ለዚያ ሰው ክፉ ነው፣ እንዲሰናከልም ያደርገዋል።
\v 21 ወንድምህን የሚጎዳ ከሆነ ሥጋ ባትበላም ወይን ባትጠጣም ወይም ምንም ባታደርግ መልካም ነው።
\s5
\v 22 አንተ በግልህ ያለህ መረዳት ባንተና በእግዚአብሔር መሀል ይቅር። አምኖ የተቀበለውን ነገር በማድረጉ ራሱን የማይወቅስ የተባረከ ነው።
\v 23 እየተጠራጠረ የሚበላ ግን በእምነት ስላልሆነ ይፈረድበታል። ምክንያቱም ያለ እምነት የሆነ ነገር ሁሉ ኃጢአት ነው።
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 እንግዲህ ብርቱዎች የሆንን እኛ የደካሞቹን ድካም ልንሸከም እንጂ ራሳችንን ብቻ ልናስደስት አይገባም።
\v 2 መልካም ነውና እንድናንጸው እያንዳንዳችን ባልንጀራችንን ደስ እናሰኝ።
\s5
\v 3 ምክንያቱም ክርስቶስ እንኳን እራሱን ደስ አላሰኘም። ይልቁንም «አንተን የሰደቡበት ስድብ በኔም ላይ ደረሰ» ተብሎ እንደተጻፈው ነው።
\v 4 አስቀድሞ የተጸፈው ሁሉ በትዕግስትና በቅዱሳት መጽሀፍት እየተበረታታን ድፍረት እንድናገኝ ለትምህርታችን ተጽፎአል።
\s5
\v 5 እንግዲህ የትዕግስትና የመጽናናት አምላክ ለእርስ በእርሳችሁ በክርስቶስ አንድ ልብ ይስጣችሁ።
\v 6 በአንድ ልብና በአንድ አፍ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክና አባት እንድታመስግኑ ይህን ያድርግ።
\v 7 ልክ ክርስቶስ እንደተቀበላችሁ ለእግዚአብሔር ክብር እርስ በእርሳችሁ ተቀባበሉ።
\s5
\v 8 ስለ እግዚአብሔር እውነት ክርስቶስ የመገረዝ አገልጋይ ሆነ እላለሁ። ይህን ያደረገው ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ ሊያጸና
\v 9 አህዛብ ደግሞ ስለምህረቱ እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ነው። ይህም «በአህዛብ መካከል አመሰግንሀለሁ፣ለስምህም እዘምራለሁ» ተብሎ በተጻፈው መሰረት ነው።
\s5
\v 10 እንደገናም ደግሞ «እናንተ አህዛብ ከህዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ» ይላል።
\v 11 ደግሞም እንደገና «አህዛብ ሁላችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግኑት» ይላል።
\s5
\v 12 ኢሳያስ ደግሞ «አህዛብን ሊገዛ የሚነሳ የእሴይ ሥር ይወጣል፥ አህዛብም በእርሱ ይመካሉ።» ይላል።
\s5
\v 13 በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ ትሞሉ ዘንድ የተስፋ አምላክ በማመናችሁ ምክንያት በደስታና በሰላም ሁሉ ይሙላችሁ።
\s5
\v 14 ወንድሞቼ ሆይ እናንተ ራሳችሁ በመልካምነትና በእውቀት እንደተሞላችሁ እርስ በእርሳችሁም ልትማማሩ እንደምትችሉ ስለእናንተ ተረድቻለሁ።
\s5
\v 15 ነገር ግን ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ስጦታ ስለአንድ ጉዳይ ላሳስባችሁ በድፍረት ጽፌላችኋለሁ።
\v 16 ይኸም ስጦታ የእግዚአብሔርን ወንጌልን እንደ ካህን እንዳቀርብላቸው ወደ አህዛብ የተላክሁ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ መሆኔ ነው። ይህን ማድረግ ያለብኝ የአህዛብ መስዋዕት ተቀባይነት እንዲያገኝና በመንፈስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር እንዲቀርብ ነው።
\s5
\v 17 እንግዲህ ደስታዬ በክርስቶስ ኢየሱስና ከእግዚአብሔር በሚሆኑ ነገሮች ነው።
\v 18 አህዛብ ወደ መታዘዝ እንዲመጡ ክርስቶስ በእኔ ካከናወነው ነገር በቀር ስለምንም ነገር ለመናገር አልደፍርም። እነዚህም ነገሮች በቃልና በሥራ
\v 19 በምልክትና በድንቆች ኃይል በመንፈስ ቅዱስም ኃይል የተከናወኑ ናቸው። ይህም በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እስከ አልዋሪቆን ድርስ የክርስቶስን ወንጌል በሙላት እንዳደርስ ነበር።
\s5
\v 20 በዚህ መንገድ ፍላጎቴ ወንጌልን መስበክ ነው፥ ነግር ግን የምሰብከው በሌላው ሰው መሠረት ላይ እንዳልገነባ የክርስቶስ ስም በሚታወቅበት አካባቢ አይደለም።
\v 21 ይህም «ስለእርሱ ያልተነገራቸው ያዩታል፥ ያልሰሙም ያስተውላሉ» ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው።
\s5
\v 22 ስለዚህም ወደ እናንተ እንዳልመጣ ብዙ ጊዜ እንቅፋት ገጠመኝ።
\v 23 አሁን ግን በዚህ ባሉ ክልሎች እንብዛም የምሰራው ነገር የለኝም ወደ እናንተም ለመምጣት ለበርካታ ዓመታት ስናፍቅ ነበር።
\s5
\v 24 ስለሆነም ወደ እስፔን በምሄድበት ጊዜ ከእናንተ ጋር ደስ የሚያሰኝ ጥቂት ጊዜ አሳልፌ በጉዞዬ እንድትረዱኝ ወደናንተ ጎራ ብዬ እንደማያችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
\v 25 አሁን ግን በጌታ ያመኑትን ለማገልገል ወደ ኢየሩሳሌም እሄዳለሁ።
\s5
\v 26 ምክንያቱም በመቄዶኒያና በአካይያ ያሉ አማኞች በኢየሩሳሌም ባሉ አማኞች መካከል ለሚገኙ ድሆች የተወሰነ ድጋፍ ለማድረግ በደስታ ፈቅደዋል።
\v 27 አዎ በደስታ ሊያደርጉት መልካም ፈቃዳቸው ነበር፥ ለነገሩ የእነርሱ ባለዕዳዎች ናችው። አህዛብ ከእነርሱ መንፈሳዊ ነገርን ከተካፈሉ እነርሱ ደግሞ በቁሳዊ ነገር ሊያገለግሏቸው ይገባል።
\s5
\v 28 ስለዚህም ይህን ስጦታውን የማድረስ ተግባሬን ከፈጸምኩ በኋላ በእናንተ በኩል ወደ እስፔን አልፋለሁ።
\v 29 ወደ እናንተ ስመጣ በክርስቶስ በረከት ተሞልቼ እንደምመጣ አውቃለሁ።
\s5
\v 30 እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ ስለኔ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት አብራችሁኝ እንድትጋደሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ፣ በመንፈስ ቅዱስም ፍቅር እለምናችኋለሁ።
\v 31 በይሁዳ ካሉ የማይታዘዙ ሰዎች እንድጠበቅ አገልግሎቴም በኢየሩሳሌም ባሉ አማኞች ተቀባይነት እንዲያገኝ ጸልዩ።
\v 32 በእግዚአብሔር ፈቃድ ወደ እናንተ በደስታ መጥቼ አብሬያችሁ እንዳርፍ ጸልዩ።
\s5
\v 33 የሠላም አምላክ ከሁላችሁም ጋር ይሁን። አሜን።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 በክንክራኦስ ያለችው ቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነችውን እህታችንን ፌበንን
\v 2 በጌታ እንድትቀበሏት አደራ ሰጥቻችኋለሁ። ይህንንም ከአማኞች በሚጠበቅ መልኩ አድርጉት፣ የእናንተን እርዳታ በምትፈልግበት በማንኛውም ነገር ከጎኗ ቁሙ። ምክንያቱም እርሷ እራሷ እኔን ጨምሮ ብዙዎችን የምትርዳ ነች።
\s5
\v 3 በክርስቶስ የአግልግሎቴ አጋሮች ለሆኑት ለአቂላና ለጵርስቅላ ሠላምታ አቅርቡልኝ፥
\v 4 እነርሱ ስለእኔ ህይወታቸውን ለአደጋ ያጋለጡ ናቸው። አመሰግናቸዋለሁ፥ እኔ ብቻ ሳልሆን የአህዛብ አብያተክርስቲያናትም ሁሉ ያመስግኗቸዋል።
\v 5 በቤታቸው ላለች ቤተክርስቲያን ሠላምታ አቅርቡልኝ። በእስያ ለክርስቶስ የመጀምሪያው ፍሬዬ የሆነውን የምወደውን አጤኔጦንን ሠላም በሉልኝ።
\s5
\v 6 ለእናንተ በሥራ ለደከመችው ለማሪያ ሠላምታ አቅርቡልኝ።
\v 7 ዘመዶቼ ለሆኑትና አብረውኝ ታስረው ለነበሩት ለአንዲራኒቆንና ለዩልያን ሠላምታ አቅርቡልኝ። እነርሱ በክርስቶስ በመሆን የቀደሙኝና ከሐዋሪያት መካከል በመልካም የተመሰከረላቸው ናቸው።
\v 8 በጌታ ለምወደው ለጵልያጦን ሠላምታ አቅርቡልኝ።
\s5
\v 9 በክርስቶስ አብሮን የሚሠራውን ኢሩባኖንና የተወደደውን ስንጣክን ሠላም በሉልኝ።
\v 10 በክርስቶስ መሆኑ ለተመሰከረለት ለኤጤሌን ሠላምታ አቅርቡልኝ። የአርስጣባሉን ቤተሰቦች ሠላም በሉልኝ።
\v 11 ለዘመዴ ለሄሮድዮና ሠላምታ አቅርቡልኝ። ከንርቀሱ ቤተሰቦች መካከል በጌታ ላመኑት ሠላምታ አቅርቡልኝ።
\s5
\v 12 በጌታ ሥራ ለሚደክሙት ለፕሮፊሞንና ለጢሮፊሞስ ሠላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ ሥራ በብዙ የምትደክመውን የተወደደች ጠርሲዳን ሠላም በሉልኝ።
\v 13 በጌታ ልተመረጠው ለሩፎን እና ለእርሱም ለእኔም እናት ለሆነችው ለእናቱ ሠላምታ አቅርቡልኝ።
\v 14 አስቀራጦንን፥ አፍለሶንጳን፥ ሄሮሜንን፥ ጳጥሮባን፥ ሄርማንን እንዲሁም አብረዋቸው ያሉትን ወንድምች ሠላም በሉልኝ።
\s5
\v 15 ለፍሌጎን፥ ለዩልያ፥ ለኔርያ ለእህቱም ለአልንጦን አብረዋቸውም ላሉት በጌታ ላመኑት ሁሉ ሠላምታ አቅርቡልኝ።
\v 16 በተቀደሰ መሳሳም ሠላምታ ተለዋወጡ። የክርስቶስ አብያተክርስቲያናት ሁሉ ሠላምታ ያቀርቡላችኋል።
\s5
\v 17 ወንድሞቼ ሆይ በመካከላችሁ የመለያየትንና የመሰናክል ምክንያት ስለሆኑት ሰዎች እንድታስቡ እለምናችኋለሁ። እነርሱ እናንተ ከተማራችሁት የወጣ ነገር ያስተምራሉና ከእነርሱ ተለዩ።
\v 18 እንደነዚህ ያሉ ሰዎች የገዛ ሆዳቸውን እንጂ ክርስቶስን ጌታችንን አያገለግሉም። በለስላሳና በሚያባብል ቃላቸው የየዋሀንን ልብ ያታልላሉ።
\s5
\v 19 የመታዘዛችሁ ምሳሌነታችሁ ለብዙዎች ደርሷል። ስለዚህም በእናንተ ደስ ይለኛል፥ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር ደግሞ የዋሀን እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።
\v 20 የሠላም አምላክ ሠይጣንን በፍጥነት ከእግራችሁ በታች ይቀጠቅጠዋል። የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሠላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
\s5
\v 21 የሥራ አጋሬ ጢሞቴዎስና ዘመዶቼ ለቂዮስ፥ኢያሶንና ሱሲጴጥሮስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 22 ይህን ደብዳቤ በእጄ የጻፍኩ እኔ ጤርጥዮስ ሰላምታ አቀርብላችኋለሁ።
\s5
\v 23 እኔና ቤተክርስቲያንን በሙሉ በቤቱ ያስተናገደን ጋይዮስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። የከተማው ገንዘብ ያዥ ኤርስጦስ ወንድማችንም ቁአስጥሮስ ሰላም ብለዋችኋል።
\v 24
\s5
\v 25 እንግዲህ በወንጌሌ በኢየሱስ ክርስቶስም ስብከት ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ ተሰውሮ በነበረውና
\v 26 አሁን ግን በዘላለማዊ አምላክ ትዕዛዝ በአህዛብ ሁሉ መካከል በተገለጠውና የእምነት መታዘዝ እንዲገኝ በትንቢታዊ መጽሀፍት አማካኝነት በታወቀው ሚስጥር መሠረት ሊያቆማችሁ ለሚችለው
\s5
\v 27 ብቻውን ጥበበኛ አምላክ ለሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።

848
47-1CO.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,848 @@
\id 1CO
\ide UTF-8
\h 1ኛ ቆሮንቶስ
\toc1 1ኛ ቆሮንቶስ
\toc2 1ኛ ቆሮንቶስ
\toc3 1co
\mt 1ኛ ቆሮንቶስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ ሐዋርያ ሊሆን በክርስቶስ ኢየሱስ የተጠራ ጳውሎስና ወንድማችን ሶስቴንስ በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት።
\v 2 የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት ደግሞ እንጽፍላቸዋለን።
\v 3 ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 4 ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰጣችሁ ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ሁልጊዜ ስለእናንተ አምላኬን አመሰግናለሁ።
\v 5 በነገር ሁሉ፤በንግግርና በዕውቀት ሁሉ ባለጸጋ እንድትሆኑ አድርጎአችኋልና።
\v 6 ስለክርስቶስ የተሰጠው ምስክርነት በመካከላችሁ እውነት ሆኖ እንደጸና ሁሉ ባለጸጎች አድርጎአችኋል።
\s5
\v 7 ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ አንድም መንፈሳዊ ስጦታ አይጎድልባችሁም።
\v 8 እርሱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።
\v 9 ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።
\s5
\v 10 ስለዚህ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ ሁላችሁም በአንድ አሳብ እንድትስማሙ እንጂ በመካከላችሁ መለያየት እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ድርስቶስ ስም አሳስባችኋለሁ። እንዲሁም በአንድ ልብና በአንድ ዓለማ የተባበራችሁ እንድትሆኑ አሳስባችኋለሁ።
\v 11 በመካከላችሁ መከፋፈል እንደተፈጠረ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛል።
\s5
\v 12 ይህን የምላችሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ "እኔ ከጳውሎስ ጋር ነኝ፥ ወይም ከአጵሎስ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከኬፋ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከክርቶስ ጋር ነኝ" ትላላችሁ።
\v 13 ለመሆኑ ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይም የተጠመቃችሁት በጳውሎስስ ስም ነውን?
\s5
\v 14 ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ማናችሁንም ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 15 ስለዚህ ማናችሁም በእኔ ስም እንደተጠመቃችሁ ለመናገር አትችሉም። (የእስጢፋኖስን ቤተ ሰብ ደግሞ አጥምቄአለሁ።
\v 16 ከዚህ ውጪ ሌላ ማንን አጥምቄ እንደሆነ አላውቅም።)
\s5
\v 17 ክርስቶስ ወንጌልን እንድሰብክ እንጂ እንዳጥምቅ አላከኝም። በሰው ጥበብ እንድሰብክ አልላከኝም፤ እንዲሁም የክርስቶስ መስቀል ኃይሉ ከንቱ መሆን ስለሌለበት በሰው የንግግር ጥበብ አልሰብክም ።
\s5
\v 18 ስለመስቀሉ ያለው መልእክት ለሚጠፉት ሞኝነት፤ ነገር ግን ለምንድን ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው።
\v 19 "የጥበበኖችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል ከንቱ አደርጋለሁ" ተብሎ ተጽፎአልና።
\s5
\v 20 ጥበበኛ ሰው የት አለ? ፈላስፋስ የት አለ? የዚህ ዓለም መርማሪስ የት አለ? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ሞኝነት እንዲሆን አላደረገምን?
\v 21 ዓለም በጥበብዋ እግዚአብሔርን ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል።
\s5
\v 22 አይሁድ ታዓምራትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ።
\v 23 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን። ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለግሪክ ሰዎችም ሞኝነት ነው።
\s5
\v 24 ነገር ግን እግዚአብሔር ለጠራቸው ለአይሁዶችም ሆነ ለግሪክ ሰዎች የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ የሆነውን ክርስቶስን እንሰብካለን።
\v 25 ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሞኝነት የሚመስለው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድካም የሚመስለው ነገር ከሰዎች ብርታት ይበልጣል።
\s5
\v 26 ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ በእናንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ተመልከቱ። ብዙዎቻችሁ በሰው መስፈርት ጥበበኞች አልነበራችሁም። ብዙዎቻችሁ ኃያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከመሳፍንት አልነበራችሁም።
\v 27 ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ። ብርቱንም ነገር ለማሳፈር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ።
\s5
\v 28 ዓለም እንደ ከበረ ነገር የምትቆጥረውን ከንቱ ለማድረግ እግዚአብሔ የዓለምን ምናምንቴ ነገር መረጠ። የተናቀውንና ያልሆነውን ነገር መረጠ።
\v 29 ይህን ያደረገው ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመመካት ምክንያት እንዳይኖረው ነው።
\s5
\v 30 በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።
\v 31 እንግዲህ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፦"የሚመካ በጌታ ይመካ" ነው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ወንድሞችና እህቶች ሆይ፦ወደ እናንተ ስመጣ ስለ እግዚአብሔር የተሰወረውን የእውነት ምስጢር ሲሰብክላችሁ በሚያባብል የንግግር ችሎታ ወይም በላቅ ጥበብ አልመጣሁም።
\v 2 በመካከላችሁ ሳለሁ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀርና፥ እርሱም እንደተሰቀለ ሌላ እንዳላውቅ ወስኜ ነበርና።
\s5
\v 3 ወደ እናንተ የመጣሁት በድካምና በፍርሃት፤ እንዲሁም በብዙ መንቀጥቀጥ ነበር።
\v 4 መልእክቴና ስብከቴም የመንፈስን ኃይል በመግለጥ እንጂ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤
\v 5 ይህም እምነታችሁ በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በሰው ጥበብ ላይ እንዳይመሠረት ነው።
\s5
\v 6 በእምነታቸው በሰሉት ሰዎች መካከል በጥበብ እንናገራለን፤ ነገር ግን የምንናገረው የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ከጊዜ በኋላ የሚሻሩትን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም።
\v 7 ይልቁን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን ያዘጃውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን የጥበብ እውነት እንናገራለን።
\s5
\v 8 የዚህም ዓልም ገዢዎች አንዳቸውም ይህን ጥበብ አላወቁትም፤ በዚያን ጊዜ ይህን አውቀውስ ቢሆን ኖሮ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር።
\v 9 ነገር ግን፦ "ዓይን ያላየውን፤ ጆሮም ያልሰማውን፤ በሰውም ልብ ያልታሰበውን፤ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀውን ነገር" ተብሎ ተጽፎአልና።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካይነት የተሰወሩትን ነገሮች ገልጦናን ። ምክንያቱም መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራል። በሰው ውስጥ ካለው ከእርሱ መንፈስ በቀር የሰውን አሳብ የሚያውቅ ማን ነው?
\v 11 እንዲሁም ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር የሚያውቅ ማንም የለም።
\s5
\v 12 እኛ ግን ክእግዚአብሔር በነፃ የተሰጠንን እንድናውቅ ከእግዚአብሔር የሆነውን መንፈስ እንጂ የዓለምን መንፈስ አልተቀበለንም።
\v 13 የሰው ጥበብ ሊያስተምር የማይችለውን ነገር ግን የእግዚአብሔር መንፈስ የሚያስተምረውን ስለ እነዚህ ነገሮች በቃላት እንናገራለን። መንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊውን ቃላት በመንፈሳዊ ጥበብ ይገልጥልናል።
\s5
\v 14 የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ስለሚሆንበት አይቀበለውም ። በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም።
\v 15 የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ሰው ሁሉን ይመረምራል፤ እርሱ ግን በማንም አይመረመርም።
\v 16 "የጌታን አሳብ ማን አወቀው፤ ማንስ ሊያስተምረው ይችላል?" እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ እንደ ሥጋውያን፤ በክርስቶስም እንደ ሕፃናት እንጂ መንፈሳውያን እንደ ሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።
\v 2 ገና ጠንካራ ምግብ ለመብላት ስላልቻላችሁ ጠንካራ ምግብ ሳይሆን ወተት ጋትኋችሁ። እስከ አሁን ስንኳ ጠንካራ ምግብ ለመብላት ገና አልበቃችሁም።
\s5
\v 3 ምክንያቱም ገና ሥጋውያን ናችሁና። ቅናትና ክርክር ስለ ሚገኝባችሁ በሥጋ ፈቃድ እየኖራችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰውስ ልማድ እየተመላለሳችሁ አይደለምን?
\v 4 አንዱ፦ "እኔ ጳውሎስን እከተላለሁ" እንዲሁም ሌላውም፦ "እኔ የአጵሎስ ተከታይ ነኝ" ሲል እንደ ሰዎች ልማድ መመላለሳችሁ አይደለምን?
\v 5 ታዲያ አጵሎስ ማን ነው? ጳውሎስስ ማን ነው? በእነርሱ እጅ ያመናችሁ እንደ ተሰጣቸው አገልጋዮች ናቸው።
\s5
\v 6 እኔ ተክልሁ አጽሎስም አጠጣ፤ ግን ያሳደገው እግዚአብሔር ነው።
\v 7 እንግዲህ የሚተክል ወይም የሚያጠጣ ምንም አይደለም። ነገር ግን የሚያሳድግ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 8 የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው። እንዲሁም እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መሠረት የራሱን ደመወዝ ይቀበላል።
\v 9 ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነን። የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔርም ሕንፃ ናችሁ። ።
\s5
\v 10 ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ጸጋ እንደ ዋና ሙያተኛ መሐንድስ መሠረትን ጠልሁ፤ ሌላውም ሰው በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ሰው ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንደሚያንጽ ይጠንቀቅ።
\v 11 ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልም፤ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
\s5
\v 12 ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን፤ በብር፤ በከበረ ድንጋይ፤ በእንጨት፤ በሣር ወይም በአገዳ ቢያንጽ፤
\v 13 የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ የቀን ብርሃንም ይገልጠዋልና። የእያንዳንዱም ሥራ ጥራት እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።
\s5
\v 14 አንድ ሰው ማንኛውንም ነገር ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል። ነገር ግን የማንም ሥራ የተቃጠለበት ከሆነ ይከስራል።
\v 15 ነገር ግን እርሱ ራሱ ከእሳት እንደሚያመልጥ ሆኖ ይድናል ።
\s5
\v 16 እናንተ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደሚኖርባችሁ አታውቁምን?
\v 17 ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል። የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ እንደሆነ እናንተም እናንተም ቅዱሳን ናችሁ።
\s5
\v 18 ማንም ራሱን አያታልል። ከእናንተ መካከል ማንም በዚህ ዘመን ጥበበኛ እንደሆነው ቢያስብ፤ ጥበበኛ ይሆን ዘንድ እንደ ሞኝ ራሱን ይቁጠር።
\v 19 የዚህ ዓለም ጥበብ በእግዚአብሔር ፊት ሞኝነት ነውና። ምክንያቱም "እርሱ ጥበበኞችን በተንኮላቸው ይይዛል" ተብሎ ተጽፎአል።
\v 20 ደግሞም፦ "ጌታ የጥበበኞችን አሳብ ከንቱ እንደ ሆን ያውቃል" ተብሎ ተጽፎአል።
\s5
\v 21 ስለዚህ ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤
\v 22 ጳውሎስ ቢሆን፥ ወይም አጵሎስ ቢሆን፥ ወይም ኬፋ ቢሆን፥ ወይም ዓለምም ቢሆን፥ወይም ሕይወት ቢሆን፥ ወይም ሞት ቢሆን፥ ወይም ያለውም ቢሆን፥ ወይም የሚመጣውም ቢሆን
\v 23 ሁሉ የእናንተ ነው፤ እናንተም የክርስቶስ ናችሁ፤ ክርስቶስም የእግዚአብሔር ነው።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 እንግዲህ ማንም ሰው እኛን የክርስቶስ አገልጋዮችና የእግዚአብሔር የተሰወረው ምሥጢር መጋቢዎች እንደሆነን ሊቆጥረን ይገባል።
\v 2 በዚህ መሠረት መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይገባቸዋል።
\s5
\v 3 ነገር ግን በእናንተ ወይም በየትኛውም ፍርድ ቤት መፈረድ ካለብኝ ለእኔ በጣም ትንሽ ነገር ነው።
\v 4 እኔ በራሴ እንኳ አልፈርድም። እኔ ምንም ክስ የለብኝም ግን ፍጹም ነኝ ማለቴ አይደለም። በእኔ የሚፈርድ ጌታ ነው።
\s5
\v 5 ስለዚህ ጊዜ ሳይደርስ፥ ጌታ ከመምጣቱ በፊት ስለምንም ነገር አትፍረዱ።እርሱም በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን ያወጣል፤ የልብንም አሳብ ይገልጣል። በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ሰው የሚገባውን ምስጋና ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።
\s5
\v 6 እንግዲህ ወንድሞችና እህቶች ሆይ፦ "ከተጻፈው አትለፍ" የሚለውን ትርጉሙ ከእኛ መማር እንድትችሉ ስለ እናንተ ስል ለራሴና ለአጵሎስ እንደ ምሳሌ ተናገርሁ። ይህ ማናችሁም አንዳችሁ በሌላኛችሁ እንዳትታበዩ ነው።
\v 7 በእናንተና በሌሎች መካከል ምን ልዩነት አለ? በነጻ ያልተቀበልከውስ ምን አለህ? በነጻ የተቀበልከው ከሆንህ እንዳልተቀበልህ የምትመካ ስለ ምንድን ነው?
\s5
\v 8 አሁን የምትፈልጉት ሁሉ አላችሁ! አሁንስ ባለ ጠጎች ሆናችኋል! ከእኛ ተለይታችሁ መንገሥ ጀምራችኋል! በርግጥ እኛ ከእናንተ ጋር መንገሥ እንድንችል እናንተ ብትነግሡ በተመኘሁ ነበር።
\v 9 እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች ያደረገን ይመስለኛል። ለዓለም፥ ለመላእክትና ለሰዎች መታያ ሆነናልና።
\s5
\v 10 እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ናችሁ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ፤እኛ ግን የተዋረድን ነን።
\v 11 እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፤ እንጥማለን፤ እንራቆታለን፤ ያለርኅራኄ እንደበደባለን፤ ራሳችንን የምናስጠጋበት ስለሌለን እንክራተታለን።
\s5
\v 12 በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፤ ሲያሳድዱን እንታገሣለን።
\v 13 ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።
\s5
\v 14 እነዚህን ነገሮች የጻፍኩላችሁ ላሳፍራችሁ ሳይሆን እንደ ተወደዱ ልጆቼ አድርጌ እንድትታርሙ ልገስጻችሁ ነው።
\v 15 በክርስቶስ ብዙ እልፍ አዕላፋት አሳዳጊዎች ቢኖሩአችሁ እንኳ ብዙ አባቶች የሉአችሁም። እኔ ግን በኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ልጆቼ ናችሁ።
\v 16 እንግዲህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ።
\s5
\v 17 እንግዲህ የተወደደና ታማኝ የሆነውን በጌታ ልጄን ጢሞቲዎስን የላክሁላችሁ ለዚህ ነው ። እኔም በየስፍራውና በየአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንደማስተምር፤ በክርስቶስ ያሉትን መንገዶቼ እርሱ ያሳስባችኋል።
\v 18 አንዳንዶቻችሁ ግን ወደ እናንተ የማልመጣ መስሎአችሁ በትዕቢት የምትመላለሱ አላችሁ።
\s5
\v 19 ነገር ግን ጌታ ቢፈቅድ ፈጥኜ ወደ እናንተ እመጣለሁ። እነዚህ በትዕቢት የሚመላለሱት የሚናገሩትን ብቻ ሳይሆን ኃይላቸውንም ለማወቅ እሞክራለሁ።
\v 20 ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ነው እንጂ በቃል ብቻ አይደለምና። ምን ትፈልጋላችሁ?
\v 21 በበትር ወይስ በፍቅርና በትህትና መንፈስ እንድመጣባችሁ ትፈልጋላችሁ?
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 በእናንተ መካከል ዝሙት እንዳለ ሰምተናል፤የዚያም ዓይነት ዝሙት በአሕዛብ መካከል እንኳ ተሰምቶ የማይታወቅ ነው። እንደሰማነው ከእናንተ አንዱ ከእንጀራ እናቱ ጋር የሚተኛ አለ።
\v 2 ስለዚህ በትዕቢት የምትመላለሱ አይደላችሁምን? በዚህም ልታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ያደረገ ሰው ከመካከላችሁ ሊወገድ ይገባል።
\s5
\v 3 እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር አለሁ፤ከእናንተም ጋር እንዳለሁ ሆኜ ይህን ባደረገው ሰው ላይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ፈርጄበታለሁ።
\v 4 እናንተ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምትሰበሰቡበት ጊዜ መንፈሴም ከጌታችን ኢየሱስ ኃይል ጋር እዚያው በመካከላችሁ አለ።
\v 5 ይህ ሰው በጌታ በኢየሱስ ቀን ይድን ዘንድ፤ ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው።
\s5
\v 6 መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካ አታውቁምን?
\v 7 እንግዲህ እርሾ የሌለ እንጀራ ሆናችሁ አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ ከአሮጌው እርሾ ራሳችሁን አንጹ። ምክንያቱም የፋሲካችን በግ የሆነው ክርስቶስ ታርዶአል።
\v 8 ስለዚህ በአሮጌ እርሾ በመጥፎ አስተሳሰብና በክፋት ሳይሆን በቅንነትና በእውነት በዓልን እርሾ በሌለ ቂጣ እናድርግ።
\s5
\v 9 ዝሙትን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር ኅብረት እንዳታደርጉ በመልእክቴ ጽፌላችሁ ነበር።
\v 10 በምንም ነገር የዚህን ዓለም ዝሙት ከሚያደርጉትን ወይም ገንዘብን ከሚመኙትን፥ ከነጣቂዎችንም፤ወይም ጣዖትን ከሚያመልኩትን ከማያምኑት አትተባበሩ። እንዲህ ቢሆን ኖሮ ከዓለም መውጣት በተገባችሁ ነበር።
\s5
\v 11 አሁን ግን በክርስቶስ ወንድሞች ወይም እህቶች ተብለው ከሚጠሩት ከማናቸውም ዝሙትን ከሚያደርግ ወይም ገንዘብን ከሚመኝ ወይም ጣኦትን ከሚያመልክ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም ወይም ነጣቂ ቢሆኑ ከእነርርሱ ጋር እንዳትተባበሩ እጽፍላችኋለሁ። እንደነዚህ ካሉት ጋር አብራችሁ እንኳን አትብሉ።
\v 12 ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉ ሰዎች ላይ ለመፍረድ እንዴት እደፍራለሁ? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱምን?
\v 13 ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ባሉቱ ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል። "ክፉውን ከመካከላችሁ አውጡት።"
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ከእናንተ አንድ ሰው ከሌላ ሰው ጋር ክርክር ቢኖረው፤ በቅዱሳን ፊት ስለጉዳዩ ከመነጋገር ይልቅ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ወደ ፍርድ ቤት ለመሄድ ይደፍራልን?
\v 2 ቅዱሳን በዓለም ላይ እንደሚፈርዱ አታውቁምን? በዓለም ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፤ በትናንሽ ጉዳዮችን መፍረድ እንዴት ይሳናችኋል?
\v 3 በመላእክት ላይ እንኳ እንደምንፈርድ አታውቁምን? እንግዲህ በዚህ ዓለም ሕይወት ጉዳዮች ላይ የበለጠ ለመፍረድ እንዴት አንችልም?
\s5
\v 4 ለዕለታዊ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ መፍረድ ካለባችሁ በቤተ ክርስቲያን መካከል ለሚነሱ ክርክሮች የማያምኑ ሰዎችን እንዲፈርዱ ታስቀምጣላችሁን?
\v 5 አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ። እንደዚህ ነውን? በወንድሞችና እህቶች መካከል ክርክሮችን ሊፈታ የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን?
\v 6 ነገር ግን አንዱ አማኝ ሌላውን አማኝ ለመክሰስ በማያምን ዳኛ ፊት ለመቆም ይሄዳልን?
\s5
\v 7 እንግዲህ በክርስቲያኖች መካከል የእርስ በርስ ማንኛውም ክርክር ቢኖርባችሁ ለእናንተ ሽንፈት ነው። ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ እይሻልምን?
\v 8 ነገር ግን እናንተ ወድሞቻችሁንና እህቶቻችሁን ትበድላላችሁ ታታልሉማላችሁ።
\s5
\v 9 ዓመጸኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? በሐሰት አታምኑ። ዝሙት አድራጊዎች ቢሆኑ፣ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመዝሮች ወይም ግብረ ሶዶማውዎች ቢሆኑ፤ ወይም ሌቦች፥ ወይም ስግብግቦች፤ ወይም ሰካራሞች፣ ወይም ተዳዳቢዎች፥
\v 10 ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
\v 11 ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ። ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችሁማል።
\s5
\v 12 ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ነገር ግን ሁሉም የሚጠቅም አይደለም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን በእኔ ላይ ምንም ነገር አይሠለጥንብኝም።
\v 13 "መብል ለሆድ ነው፤ ሆድም ለመብል ነው።" እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም። ይልቁን ሥጋችንም ለጌታ ነው፤እንዲሁም ጌታ ለሥጋ ያዘጋጃል።
\s5
\v 14 እግዚአብሔርም ደግሞ ጌታን አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል።ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን?
\v 15 እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የሴተኛ አዳሪ ሴት ብልቶች ላድርጋቸውን? ሊሆን አይችልም።
\s5
\v 16 ከሴተኛ አዳሪ ጋር የሚተባበር ከእርስዋ ጋር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? "ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ" በእግዚአብሔር ቃል ተጽፎአል።
\v 17 ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን ከእርሱ ጋር አንድ መንፈስ ነው።
\s5
\v 18 ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ሌላ ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚያደርግ ሰው ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ያድርጋል።
\s5
\v 19 ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁትና በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን?
\v 20 በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም። ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 እንግዲህ ስለጻፋችሁኝ ነገር ሰው ከሴት ጋር አለመገናኘት መልካም ነው።
\v 2 ነገር ግን ስለ ዝሙት ፈተና ምክንያት እንዳይሆን እያንዳንዱ ሰው የራሱ ሚስት ይኑረው፤ እንዲሁም ለእያንዳንዱ ሴት የራስዋ ባል ይኑራት።
\s5
\v 3 ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፤ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ የሚገባትን ታድርግ።
\v 4 ሚስት በገዛ ሰውነትዋ ላይ ሥልጣን ያላትም፤ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ባል በገዛ ሰውነቱ ላይ ሥልጣን የላውም ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።
\s5
\v 5 በጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለጊዜው ካልሆነ በቀር እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ። ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ ደግሞ አብራችሁ መሆን ትችላላችሁ።
\v 6 ዳሩ ግን ይህን እንደ ፈቃድ እላለሁ እንጂ እንደ ትእዛዝ አይደለም።
\v 7 ሰው ሁሉ እንደ እኔ ቢሆን እወዳለሁ። ነገር ግን እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ከእግዚአብሔር የተቀበለ አንዱ አንድ ዓይነት ሌላው ሌላ ዓይነት ስጦታ አለው።
\s5
\v 8 ላላገቡትና ባሎቻቸው ለሞተባቸው ሴቶች ግን እላለሁ፦ እንደ እኔ ሳያገቡ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው።
\v 9 ነገር ግን ራሳቸውን መግዛት የማይችሉ ከሆነ መጋባት ይሻላል። በምኞት ከመቃጠል ይልቅ መጋባት ይሻላቸዋልና።
\s5
\v 10 ደግሞ የተጋቡትን እንዲ ብዬ አዛቸዋለሁ ይህንም እኔ ሳልሆን ጌታ ነው፦ "ሚስት ከባልዋ አትለይ፥
\v 11 ብትለይ ግን ሳታገባ ትኑር" ወይም "ከባልዋ ጋር ትታረቅ፥እንዲሁም" ባልም ሚስቱን አይፍታት።"
\s5
\v 12 ነገር ግን ሌሎችንም ጌታ ሳይሆን እኔ እላለሁ፦ ማንም ያላመነች ሚስት ያለው ወንድም፥ ከእርሱ ጋር ለመኖር ብትስማማ አይፍታት፤
\v 13 እንዲሁም ያላመነ ባል ያላት ሚስትም ብትኖር፥ ከእርስዋ ጋር ለመኖር ቢስማማ አትፍታው። ያላመነች ሚስት በአማኙ ባልዋ ተቀድሳለችል፤
\v 14 እንዲሁም ያላመነ ባል በአማኝ ሚስቱ ተቀድሶአል። አለዚያ ልጆቻቸውሁ ርኩሳን ይሆኑ ነበር፤ አሁን ግን የተቀደሱ ናቸው።
\s5
\v 15 የማያምን የትዳር ጓደኛ ግን የሚለይ ከሆነ ይለይ። እንዲህ በሚመስል ነገር ወንድም ወይም እህት በቃል ኪዳን መታሰር የለባቸውም። እግዚአብሔር ግን በሰላም እንድንኖር ጠርቶናል።
\v 16 አንቺ ሴት ባልሽን ታድኚ እንደ ሆንሽ ምን ታውቂአሽ? ወይስ አንተ ሰው ሚስትህን ታድናት እንደ ሆንህ ምን ታውቃለህ?
\s5
\v 17 እያንዳንዱ ሰው እንደተጠራው ዓለማና ጌታ በሰጠው ሕይወት ብቻ ይመላለስ። ይህ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የእኔ ድንጋጌ ነው።
\v 18 ማንም ተገርዞ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? ወደ አለመገረዝ መመለስ የለበትም። እንዲሁም ማንም ሳይገርዝ ወደ እምነት ተጠርቶአልን? መገረዝ የለበትም።
\v 19 የእግአብሔርን ትእዛዛት መጠበቅ ነው እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ የሚያመጠው ችግር የለም።
\s5
\v 20 እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ለእምነት በጠራበት ጊዜ እንደነበረ ይመላለስ።
\v 21 እግዚአብሔር ሲጠራህ ባሪያ ነበርን? ይህ ሊገድህ አይገባም። ነፃ የምትወጣ ከሆንህ ተቀበለው።
\v 22 አንድ ሰው በጌታ ባሪያ ሆኖ የተጠራ የጌታ ነፃ ሰው ነው፤ እንደዚሁም ነፃ ሆኖ ለእምነት የተጠራ የክርስቶስ ባሪያ ነው።
\v 23 በዋጋ ተገዝታችልኋልና የሰው ባሪያ አትሁኑ።
\v 24 ወድሞችና እህቶች ሆይ፤ እያንዳንዳችን በተጠራንበት እንደዚሁ ሆነን በእግዚአብሔር ዘንድ እንኑር።
\s5
\v 25 ላላገቡት የጌታ ትእዛዝ የለኝም። ነገር ግን በጌታ ምሕረት እንደ ታመነ ሰው ሆኜ የራሴን ምክር እሰጣለሁ።
\v 26 ስለዚህ ለችግር ጊዜ መፍትሔ እንዲሆን ሰው ሳያገባ መኖር ከቻለ መልካም ይመስለኛል።
\s5
\v 27 በጋብቻ ቃል ኪዳን በሚስት ታስረሃልን? እንዲህ ከሆነ ከዚህ ነፃ ለመሆን አትሻ። በበጋብቻ በሚስት አልታሰርህ ወይም ያላገባህ ነህ? ሚስትን አትሻ።
\v 28 ነገር ግን ካገባህ ኃጢአት አይሆንብህም። እንዲሁም ያላገባች ሴት ብታገባ ኃጢአት አይሆንባትም። ሆኖም ግን የሚያገቡ በኑሮአቸው ብዙ ችግር ይሆንባቸዋል፤ ከእንዲ ዓይነት ሕይወት እንድትርቁ እመኛለሁ።
\s5
\v 29 ዳሩ ግን ወንድሞ ሆይ፤ ይህን እላለሁ፤ ዘመኑ አጭር ነው። ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸ እንደሌላቸው ይኑሩ።
\v 30 የሚያላቅሱም እንደማያለቅሱ ይሁኑ፤ እንዲሁም የሚደሰቱ ደስታ እንደሌላቸው ይሁኑ፤
\v 31 ደግሞ ማንኛውንም ነገር የሚገዙ ምንም እንደሌላቸ ይሁኑ፤ በዚህች ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደ ማይጠቀሙ ይሁኑ ምክንያቱም የዚች ዓለም አሠራር ሁሉ አላፊ ነውና።
\s5
\v 32 ነገር ግን ያለ ጭንቀት እንድትኖሩ እወዳለሁ። ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንደሚያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል።
\v 33 ያገባው ግን ሚስቱን እንዴት ደስ እንዲያሰኛት የዓለምን ነገር ያስባል፥ ልቡም ተከፍሎአልና።
\v 34 ያላገባች ሴት ወይም ድንግል በሥጋና በመንፈስ እንዴትምትቀደስ የጌታን ነገር ታስባለች። ያገባች ሴት ግን ባልዋን እንዴት ደስ እንደምታሰኘው የዓለምን ነገር ታስባለች።
\s5
\v 35 ሌላ ሸክም ሊጭንባችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ጥቅም ይህን እላለሁ። ያለ ምንም ጉዳት በጌታ እንድትጸኑ ስለእውነት ይህን እላለሁ።
\s5
\v 36 ዳሩ ግን ማንም ሰው ያጫትን ድንግል በአግባቡ ካልያዘ የእርስዋም ዕድሜ እየገፋ ከሄደ ሊያገባት ካሰበ ያግባት። ይህ ኃጢአት የለበትም።
\v 37 ነገር ግን አንድ ሰው ላለማግባት ቢወስንና ስሜቱንም ለመቆጣጠር ከቻለ እርስዋን ባለማግባቱ መልካም ያደርጋል።
\v 38 የእርሱንም እጮኛ የሚያገባት መልካም ያደርጋል፤እርስዋንም ለማግባት የማይመርጥ የበለጠ መልካም ያድርጋል።
\s5
\v 39 አንዲት ሴት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ ከባልዋ ጋር የታሰረች ናት። ነገር ግን ባልዋ ቢሞት በጌታ የሆነውን ብቻ ለማግባት ነጻነት አላት።
\v 40 እንደ እኔ ውሳኔ ግን ሳታገባ ብትኖር ደስተኛ ትሆናለች። እኔም የእግዚአብሔር መንፈስ ያለኝ ይመስለኛል።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ለጣዖት ስለተሰዋ ሥጋ፦ "ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን" እናውቃለን።ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።
\v 2 አንድ ሰው አንድ ነገር እንደሚያውቅ ቢያስብ፥ ያ ሰው ፥እንደሚገባ እንደሚያውቅ ገና አለወቀም።
\v 3 ነገር ግን ማንም ሰው እግዚአብሔርን ቢወድ እርሱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይታወቃል።
\s5
\v 4 እንግዲህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት በተመለከተ፦ "የዚህ ዓለም ጣዖት ከንቱ ነው፤" እና "ከአንዱም ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ የለም" ይህንን እናውቃለን።
\v 5 ብዙ "አማልክትና ጌቶች" እንዳሉ ሁሉ፥ ምንም እንኳ በሰማይና በምድር አማልክት የተባሉ ቢኖሩ ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ
\v 6 እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ ብቻ አለን፤ እንዲሁም ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ አለን።
\s5
\v 7 ይሁን እንጂ ይህ ዕውቀት በሁሉም አይገኝም። በዚህ ፈንታ፥ አንዳንዶች ግን እስካሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ፦ ለጣዖት እንደ ተሠዋ አድርገው ይበላሉ። ሕሊናቸው ደካማ ስለ ሆነ ይረክሳሉ።
\s5
\v 8 መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያደርሰንም። ስላልበላምንም አንረክስም፤ ወይም ስለበላንም የተሻለን አንሆንም።
\v 9 ነገር ግን ይህ ነጻነታችሁ በእምነት ደካማ ለሆኑት ምክንያት ሆኖ መሰናከያ እንዳይሆን ተጠንቃቁ።
\v 10 አንተ ዕውቀት ያለህ በጣዖት ቤት በማዕድ ተቀምጠህ ስትበላ አንድ ሰው ቢያይህ፤ በእምነቱ ያልጠነከረ ሰው ለጣዖት የተሠዋውን ለመብላት አይደፋፈርምን?
\s5
\v 11 ስለ ጣዖት ባሕርይ በአንተ ዕውቀት የተነሣ ክርስቶስ የሞተላቸው ደካማ ወንድም ወይም እህት ይጠፋሉ።
\v 12 ስለዚህም ወንድሞችንና እህቶችን ስትበድሉና ደካማ ሕሊናቸውንም ስታቆሽሹ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።
\v 13 ስለዚህም መብል ወንድሜንና እህቴን የሚያሰናክል ከሆን ወንድሜንና እህት እንዳላሰናክል ለዘላለ ከቶ ሥጋን አልበለም።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 እኔ ነፃ አይደለሁም? እኔ ሐዋርያስ አይደለሁም? ጌታችን ኢየሱስን አላየሁትም? እናንተስ በጌታ የሥዬ ፍሬዎች አይደላችሁም?
\v 2 ለሌሎች ሐዋርያ ባልሆን እንኳ ቢያንስ ለእናንተ ሐዋርያ ነኝ። በጌታ ሐዋርያ ለመሆኔ እናንተ ማረጋገጫ ናችሁና።
\s5
\v 3 ለሚጠይቁኝ መልሴ ይህ ነው።
\v 4 እኛስ ለመብላትና ለመጠጣት መብት የለንም?
\v 5 እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት፣ እንደ ጌታ ወንድሞች፣ እና እንደ ኬፋ፣ አማኝ የሆነች ሚስት ይዞ ለመሄድ መብት የለንም?
\v 6 ወይስ የመሥራት ግዴታ ያለብን እኔና በርናባስ ብቻ ነን?
\s5
\v 7 በራሱ ወጪ በውትድርና የሚያገለግል ማን ነው? የወይን ተክል ተክሎ ከፍሬው የማይበላ ማን ነው? ወይስ ከሚጠብቀው መንጋ ወተት የማይጠጣ ማን ነው?
\v 8 እነዚህን ነገሮች የምናገረው በሰው ሥልጣን መሠረት ነው? ሕጉስ ይህን አይልም?
\s5
\v 9 በሙሴ ሕግ፦ "የሚያበራየውን በሬ፣አፉን አትሰር" ተብሎ ተጽፎአል። በእርግጥ እግዚአብሔር ስለ በሬዎች አስቦ ነው?
\v 10 እየተናገረ ያለው ስለ እኛ አይደለም? የተጸፈው ስለ እኛ ነው፣ምክንያቱም የሚያርስ በተስፋ ሊያርስ፣የሚያበራይም ከመከሩ ለመካፈል ተስፋ በማድረግ ሊያበራይ ይገባዋል።
\v 11 በመካከላችሁ መንፈሳዊ ነገር ዘርተን ከሆነ፣ከእናንተ ቁሳዊ ነገሮችን ብናጭድ ይበዛብናል?
\s5
\v 12 ሌሎች ይህን መብት ከእናንተ የሚያገኙ ከሆነ፣እኛስ የበለጠ መብት የለንም? ሆኖም ግን ይህን መብት ይገባናል አላልንም፣ይልቁንም ለክርስቶስ ወንጌል እንቅፋት እንዳንሆን ሁሉን ታገስን።
\v 13 በመቅደስ የሚያገለግሉ ምግባቸውን ከመቅደስ እንደሚያገኙ አታውቁም፣በመሠዊያው ላይ የሚያገልግሉስ መሠዊያው ላይ ከሚሠዋው እንደሚካፈሉ አታውቁም?
\v 14 እንዲሁም ደግሞ ወንጌልን የሚያውጁ ከወንጌል በሚገኝ እንዲኖሩ ጌታ አዟል።
\s5
\v 15 እኔ ግን ከእነዚህ መብቶች አንዱንም ይገባኛል አላልሁም። ይህንንም የጻፍሁት አንዳች እንዲደረግልኝ አይደለም። ይህን ትምክህቴን ማንም ከሚወስድብኝ ሞትን እመርጣለሁ።
\v 16 ይህ ግዴታዬ ስለሆነ ወንጌል ብሰብክ የምታበይበት ምክንያት የለኝም፣ ወንጌልን ባልሰብክ ግን ወዮልኝ!
\s5
\v 17 ይህን በፈቃደኝነት ባደርገው ግን ሽልማት አለኝ። በፈቃደኝነት ባላደርገው ግን በአደራ የተሰጠኝ ኃላፊነት አለብኝ።
\v 18 ታዲያ ሽልማቴ ምንድነው? በወንጌል ውስጥ ያለ ሙሉ መብቴን ትቼ ያለምንም ክፍያ ወንጌልን ስሰብክ ነው።
\s5
\v 19 ምንም እንኳ ከሁሉም ነፃ ብሆንም፣ ብዙዎችን ለመማረክ እንድችል፣የሁሉ አገልጋይ ሆንሁ።
\v 20 አይሁድን ለመማረክ እንድችል፣ እንደ አይሁዳዊ ሆንሁ። ምንም እንኳ በሕግ ስር ባልሆንም፣ በሕግ ስር ያሉትን መማረክ እንድችል፣ ከሕግ ስር እንዳለ ሰው ሆንሁ።
\s5
\v 21 ከሕግ ውጭ ያሉትን መማረክ እንድችል፣እኔ ራሴ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ ሳልሆን፣ ነገር ግን ከክርስቶስ ሕግ ስር እያለሁ፣ ከሕግ ውጭ እንዳለ ሰው ሆንሁ።
\v 22 ደካማውን መማረክ እንድችል፣እንደ ደካማ ሆንሁ። አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፣ ለሰዎች ሁሉ ብዬ ሁሉን ሆንሁ።
\v 23 ይህን ሁሉ ያደረግሁት ከወንጌል በረከት መካፈል እንድችል፣ ስለ ወንጌል ብዬ ነው።
\s5
\v 24 በሩጫ ውድድር የሚሳተፉ ሯጮች ሁሉ እንደሚሮጡ፣ ነገር ግን ሽልማት የሚቀበል አንዱ ብቻ እንደሆነ አታውቁም? ስለዚህ ሽልማት ለማግኘት ሩጡ።
\v 25 ለውድድር የሚዘጋጅ ሰው ሥልጠና ጊዜ ሁሉ ራሱን መቆጣጠር ይለማመዳል። እነርሱ የሚጠፋውን ሽልማት ለማግኘት ይሮጣሉ፣ እኛ ግን የማይጠፋውን ሽልማት ለማግኘት እንሮጣለን።
\v 26 ስለዚህም ያለ ዓላማ አልሮጥም፣ወይም ንፋስ በቦክስ አልመታም።
\v 27 ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ከውድድሩ ውጭ እንዳልሆን ሥጋዬን በመቆጣጠር አስገዛዋለሁ።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ወንድሞች እና እህቶች፣ይህን እንድታውቁ እወዳለሁ፣አባቶቻችን ከዳመና በታች እና በባሕር ውስጥ አለፉ።
\v 2 ሁሉም በዳመና እና በባሕር ውስጥ በሙሴ ተጠመቁ፣
\v 3 መንፈሳዊ ምግብ ተመገቡ፣
\v 4 ሁሉም አንድ ዓይነት መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ። እነርሱም ይከተላቸው ከነበረው መንፈሳዊ ዓለት ጠጡ፣ያም ዓለት ክርስቶስ ነበር።
\s5
\v 5 ነገር ግን እግዚአብሔር በብዙዎች አልተደሰተምና ሬሳቸው ምድረ በዳ ውስጥ ወድቆ ቀረ።
\v 6 እኛም እነርሱ እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን ተጽፈውልናል።
\s5
\v 7 "ሕዝቡ ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፣በዝሙት ፍላጎት በመነሳሳት ሊጨፍሩ ተነሡ።" ተብሎ እንደተጻፈ፣ከእነርሱ አንዳንዶች እንዳደረጉት ጣዖት አምላኪዎች አትሁኑ።
\v 8 ከእነርሱ ብዙዎች ዝሙት በመፈጸማቸው ምክንያት ሃያ ሦስት ሺ ሰዎች በአንድ ቀን እንደሞቱ፣እኛም ዝሙት አንፈጽም።
\s5
\v 9 ከእነርሱም ብዙዎች ክርስቶስን እንደፈተኑት እና በእባብ እንደጠፉ፣እኛም ጌታን እንፈታተን።
\v 10 በማጉረምረማቸው ምክንያት የሞት መልአክ እንዳጠፋቸው፣እኛም አናጉረምርም።
\s5
\v 11 በእነርሱ ላይ የሆኑት እነኚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን የተጻፈው፣ የዘመን ፍጻሜ ለደረሰብን ለእኛ ትምህርት እንዲሆንልን ነው።
\v 12 ስለዚህ ማንም ቆሜአለሁ ብሎ የሚያስብ፣ እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።
\v 13 በሰው ሁሉ ላይ ከሚደርሰው በላይ የሆነ ፈተና አልደረሰባችሁም። ነገር ግን እግዚአብሔር ታማኝ ነውና ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አያደርግም። ይልቁን ፈተናውን መወጣት እንድትችሉ ከፈተናው ጋር ማምለጫ መንገዱንም ያዘጋጅላችኋል።
\s5
\v 14 ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፣ከጣዖት አምልኮ ሽሹ።
\v 15 ይህን የምናገራችሁ አስተዋዮች በመሆናችሁ ነው፤የምለውን አመዛዝኑ።
\v 16 የምንባርከው የበረከት ጽዋ፣የክርስቶስን ደም መካፈል አይደለም? የምንቆርሰው እንጀራ የክርስቶስን ሥጋ መካፈል አይደለም?
\v 17 እንጀራው አንድ እንደሆነ፣ብዙዎች ሆነን ሳለ አንዱን እንጀራ በመካፈል አንድ አካል ነን።
\s5
\v 18 የእስራኤልን ሕዝብ ተመልከቱ፦ ከመሥዋዕቱ የሚበሉ ከመሠዊያው ተካፋዮች አይደሉም?
\v 19 ስለዚህ ምን እያልሁ ነው? ጣዖት ምንም አይደለም እያልሁ ነው? ወይስ ለጣዖት የተሠዋ ምግብ ምንም አይደለም ማለቴ ነው?
\s5
\v 20 እያልሁ ያለሁት፣አሕዛብ የሚሠዋቸው ነገሮች፣ለአጋንንት እንጂ ለእግዚአብሔር አይደለም። ከአጋንንት ጋር ተካፋዮች እንድትሆኑ አልፈልግም! የጌታንም ጽዋ፣ የአጋንንትንም ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም።
\v 21 በጌታም ማዕድ፣ በአጋንንትም ማዕድ ኅብረት ልታደርጉ አትችሉም።
\v 22 ይህን ብማድረግ ጌታን ለቅናት እናነሳሳዋለን? ከእርሱ የምንበረታ ነን?
\s5
\v 23 "ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፣" ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚጠቅም አይደልም። "ሁሉም ነገር ተፈቅዷል፣" ነገር ግን ሁሉም ነገር ሰዎችን የሚያንጽ አይደለም።
\v 24 ማንም ለራሱ መልካም የሆንውን ብቻ አያስብ። ይልቁን፣እያንዳንዱ ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም የሆነውን ይፈልግ።
\s5
\v 25 በገበያ ቦታ የሚሸጥ ማንኛውንም ነገር፣የኅሊና ጥያቄ ሳታነሱ መብላት ትችላላችሁ።
\v 26 "ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የጌታ ነውና።"
\v 27 አንድ አማኝ ያልሆነ ሰው ምግብ ቢጋብዛችሁና ግብዣውን ተቀብላችሁ መሄድ ብትፈልጉ፣ በፊታችሁ የቀረበላችሁን ማንኛውንም ነገር የኅሊና ጥያቄ ሳታነሱ ብሉ።
\s5
\v 28 ነገር ግን እንድ ሰው፣"ይህ ምግብ ለጣዖት የተሠዋ ነው።" ብሎ ቢነግራችሁ አትብሉ። ይህን ማድረግ የሚገባችሁ፣ ለነገራችሁ ሰው እና ለኅሊና ስትሉ ነው።
\v 29 ይህን ስል ስለ እናንተ ኅሊና ሳይሆን ስለ ሌላው ሰው ኅሊና ነው። ስለ ሌላው ኅሊና ሲባል ለምን በነፃነቴ ላይ ይፈረዳል?
\v 30 ምግቡን በአክብሮት ከተቀበልሁ፣አመስግኜ ለበላሁት ነገር ለምን እሰደባልሁ?
\s5
\v 31 ስለዚህ፣ስትበሉ እና ስትጠጡ፣ወይም በምታደርጉት ሁሉ፣ሁሉን ለጌታ ክብር አድርጉት።
\v 32 ለአይሁዶች ወይም ለግሪኮች፣ እንዲሁም ለእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን መሰናከያ አታድርጉ።
\v 33 እኔ ሰዎችን ሁሉ በሁሉ ነገር ደስ ለማሰኘት እንደምፈልግ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ። የራሴን ጥቅም ሳይሆን፣ለብዙዎች ጥቅም የሚሆነውን እፈልጋለሁ። ይህን የማደርገው ወደ ድነት እንዲመጡ ብዬ ነው።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 እኔ ክርስቶስን እንደምመስል፣እናንተም እኔን ምሰሉ።
\v 2 አሁን የማመሰግናችሁ በሁሉ ነገር ስለምታስቡኝ ነው። ለእናንተ ያስተላለፍኳቸውን ልምዶች ልክ እንደዚያው እንዳሉ አጥብቃችሁ በመያዛችሁ አመሰግናችኋለሁ።
\v 3 ክርስቶስ የወንድ ሁሉ ራስ ፣ወንድ ደግሞ የሴት ራስ ፣ እግዚአብሔር የክርስቶስ ራስ እንደሆነ እንድትረዱ እፈልጋለሁ።
\v 4 ራሱን ሸፍኖ የሚጸልይ ወይም ትንቢት የሚናገር ወንድ የእርሱ ራስ የሆነውን ክብር ያሳጣል።
\s5
\v 5 ነገር ግን ራሷን ሳትሸፍን የምትጸልይ ወይም ትንቢት የምትናገር ሴት ራሷን ክብር ታሳጣለች። ይህን ማድረግ ልክ ጠጉሯን እንደመላጨት ነው።
\v 6 ሴት ራሷን ካልሸፈነች፣ጠጕሯን አሳጥራ መቆረጥ ይኖርባታል። ሴት ጠጕሯን አሳጥራ መቆረጧ ወይም መላጭቷ አሳፋሪ ከሆነ፣ ራሷን ትሸፍን።
\s5
\v 7 ወንድ ራሱን መሸፈን የለበትም፣ ምክንያቱም እርሱ የእግዚአብሔር መልክ እና ክብር ነውና።
\v 8 ሴት ግን የወንድ ክብር ነች። ወንድ ከሴት አልተገኘምና። ይልቁንስ፣ሴት ከወንድ ተገኝታለች።
\s5
\v 9 ወንድ ለሴት አልተፈጠረም፣ሴት ግን ለወንድ ተፈጥራለች።
\v 10 ለዚህ ነው፣ ከመላእክቱ የተነሳ፣ ሴት በራሷ ላይ የሥልጣን ምልክት ሊኖራት የሚገባው።
\s5
\v 11 የሆነ ሆኖ፣በጌታ ሴት ከወንድ፣ ወንድም ከሴት የተነጣጠሉ አይደሉም።
\v 12 ሴት የተገኘችው ከወንድ እንደሆነ ሁሉ፣ወንድም የተገኘው ከሴት ነው። ሁሉም ነገር ደግሞ የተነኘው ከእግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 13 ራሳችሁ ፍረዱ፦ሴት ራሷን ሳትሸፈን ወደ እግዚአብሔር ብትጸልይ ተገቢ ነው?
\v 14 ወንድስ ረጅም ጠጕር ቢኖረው አሳፋሪ እንደሆነ ተፈጥሮ ራሱ አያስተምራችሁም?
\v 15 ሴት ግን ረጅም ጠጕር ቢኖራት ክብሯ እንደሆነ ተፈጥሮ ራሱ አያስተምራችሁም? ለእርሷ ጠጕር የተሰጣት እንደ መሸፈኛ ነውና።
\v 16 ነገር ግን በዚህ ማንም ክርክር ሊያስነሳ ቢፈልግ፣እኛም ሆንን የእግዚአብሔር አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ የተለየ ልምምድ የላቸውም።
\s5
\v 17 በሚከተሉት መመሪያዎቼ ግን፣አላመሰግናችሁም። ምክንያቱም በምትሰበሰቡበት ጊዜ፣ ለተሻለ ነገር ሳይሆን እጅግ ለከፋ ነገር ትሰበሰባላችሁ።
\v 18 በመጀመሪያ፣ በቤተክርስቲያን ስትሰበሰቡ በመካከላችሁ መከፋፈል እንዳለ ሰምቼአለሁ፣ ደግሞም ይህ እንደሚሆን በመጠኑም ቢሆን አምኜበታልሁ።
\v 19 ምክንያቱም በእናንተ መካከል ተቀባይነትያላቸው እንዲለዩ የተለያዩ ቡድኖች መኖራቸው ግድ ነው።
\s5
\v 20 በአንድነት በምትሰብሰቡበት ጊዜ፣የምትበሉት የጌታን ማዕድ አይደለምና።
\v 21 በምትበሉበት ጊዜ፣ሌሎች ምግብ ከማግኘታቸው በፊት እያንዳንዱ ቀድሞ የየራሱን ምግብ ይበላል። አንዱ ተርቦ ሳለ ሌላው ይሰክራል።
\v 22 የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁም? የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን በመናቅ ምንም የሌላቸውን ታዋርዳላችሁ? ምን ልበላችሁ? ታዲያ ላመስግናችሁ? ለዚህ አላምሰግናችሁም!
\s5
\v 23 ከጌታ የተቀበልሁትን ለእናንተ አሳልፌ ሰጥቼአለሁ፣ ጌታ ኢየሱስ ታልፎ በተሰጠበት ምሽት፣እንጀራ አንሳ።
\v 24 ካመሰገነ በኋላ ቆረሰውና፣"ለእናንተ የሆነ ሥጋዬ ይህ ነው፣ይህን እኔን ለማስታወስ አድርጉት፣" አለ።
\s5
\v 25 እንዲሁም ከእራት በኋላ ጽዋን አንስቶ፣"ይህ በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።ይህን በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ እኔን ለማስታወስ አድርጉት።"
\v 26 ይህን እንጀራ በበላችሁ እና ይህን ጽዋ በጠጣችሁ ጊዜ ሁሉ፣ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሞቱን ታውጃላችሁ።
\s5
\v 27 ስለዚህ ማንም፣ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ የጌታን እንጀራ ቢበላ ወይም የጌታን ጽዋ ቢጠጣ፣ለጌታ ሥጋ እና ለጌታ ደም ተጠያቂ ይሆናል።
\v 28 አንድ ሰው ራሱን ከመረመረ በኋላ እንጀራውን ይብላ ጽዋዉንም ይጠጣ።
\v 29 የጌታ ሥጋ መሆኑን ሳይረዳ የሚበላ እና የሚጠጣ፣በራሱ ላይ ፍርድን ይበላል ይጠጣልም።
\v 30 በመካከላችሁ ብዙዎች የታመሙ እና በሽተኞች የሆኑት ስለዚህ ነው፣ አንዳንዶችም ደግሞ ሞተዋል።
\s5
\v 31 ነገር ግን ራሳችንን ብንመረምር አይፈረድብንም።
\v 32 በጌታ ስንፈረድ ግን፣ከዓለም ጋር እንዳንኮነን እንገሠጻለን።
\s5
\v 33 ስለዚህ፣ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ለመብላት ስትሰበሰቡ፣እርስ በርሳችሁ ተጠባበቁ።
\v 34 ማንም የተራበ ቢኖር፣እቤቱ ይብላ፣እንዲያ ሲሆን ስትሰበሰቡ ለፍርድ አይሆንባችሁም። ስለ ጻፋችሁልኝ ሌሎች ነገሮች፣ስመጣ መመሪያዎችን እሰጣለሁ።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 ወንድሞች እና እህቶች መንፈሳዊ ስጦታዎችን በተመለከተ፣የማታውቁት ነገር እንዲኖር አልፈልግም።
\v 2 አረማውያን በነበራችሁበት ወቅት፣መናገር እንኳ በማይችሉ ጣዖታት ወደማታውቁት መንገድ ተመርታችሁ እንደነበር ታውቃላችሁ።
\v 3 ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር መንፈስ፣"ኢየሱስ የተረገመ ነው፣" የሚል እንደሌለ ሁሉ፤ እንዲሁም በእግዚአብሔር መንፈስ ካልሆነ በቀር፣"ኢየሱስ ጌታ ነው፣" ሊል የሚችል እንደሌለ እወቁ።
\s5
\v 4 ልዩ ልዩ ስጦታዎች አሉ፣መንፈስ ቅዱስ ግን አንድ ነው።
\v 5 አገልግሎቶች ልዩ ልዩ ናቸው፣ጌታ ግን አንድ ነው።
\v 6 ልዩ ልዩ ሥራዎች አሉ፣ነገር ግን ለእያንዳንዱ ሰው ችሎታን የሚሰጥ አንዱ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 7 ደግሞም ለእያንዳንዱ መንፍስ ቅዱስን መግለጥ የተሰጠው ለሁሉም ጥቅም ሲባል ነው።
\v 8 ለአንዱ የጥበብ ቃል በመንፈስ ቅዱስ ይሰጣል፣ለሌላው ደግሞ የእውቀት ቃል በዚያው መንፈስ ይሰጣል።
\s5
\v 9 ለሌላው በዚያው መንፈስ እምነት ይሰጠዋል፣ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የፈውስ ስጦታ ይሰጠዋል።
\v 10 ለሌላው ደግሞ የኃይል ሥራዎች፣ለሌላው ትንቢት መናገር። ለሌላው ደግሞ መናፍስትን መለየት፣ለሌላው በልዩ ልዩ ልሳኖች መናገር፣እና ለሌላው ልሳኖችን የመተርጎም ስጦታ ይሰጠዋል።
\v 11 ነገር ግን፣ለእያንዳንዳቸው እንደወደደ ልዩ ልዩ ስጦታዎችን በመስጠት በእነዚህ ሁሉ የሚሠራው ያው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው።
\s5
\v 12 አካል አንድ ሆኖ ሳለ ብዙ ብልቶች እንዳሉት ሁሉ፣ ሁሉም ብልቶች የእንዱ አካል ክፍል እንደሆኑ፣በክርስቶስም እንዲሁ ነው።
\v 13 በአንድ መንፈስ በአንድ አካል እንደተጠመቅን፣አይሁድ ይሁኑ ግሪኮች፣ባሪያ ይሁን ነጻ፣ሁሉ ከአንዱ መንፈስ ጠጥተዋል።
\s5
\v 14 አካል አንድ ብልት ብቻ ሳይሆን ብዙ ብልቶች አሉት።
\v 15 እግር፣"እኔ እጅ አይደለሁም፣ስለዚህ የአካሉ ክፍል አይደለሁም፣" ቢል የአካሉ ክፍል መሆኑ አይቀርም።
\v 16 ጆሮም ተነስቶ፣"ዓይን ስላይደለሁ፣የአካሉ ክፍል አይደለሁም፣" ቢል የአካሉ ክፍል ከመሆን አይቀነስም። አካል ሁሉ ዓይን ቢሆን፣ መስማት ወዴት ይሆናል?
\v 17 አካል ሁሉ ጆሮ ቢሆን፣ማሽተት ወዴት ይሆናል?
\s5
\v 18 እግዚአብሔር ግን እያንዳንዱን የአካል ክፍል እንደወደደ ሠርቶታል።
\v 19 ሁሉም አንድ ብልት ቢሆኑ ኑሮ፣አካል ወዴት በሆነ ነበር?
\v 20 አሁን ግን ብዙ ብልቶች ያሉት፣ አንድ አካል ነው።
\s5
\v 21 ዓይን እጅን፣"አንተ አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም። ራስም እግርን፣"አታስፈልገኝም፣" ሊል አይችልም።
\v 22 ነገር ግን ዝቅተኛ ግምት የሚሰጣቸው ብልቶች አስፈላጊ ናቸው፣
\v 23 ዝቅተኛ ግምት የምንሰጣቸውን የሰውነት ክፍሎች ትልቅ ክብር እንሰጣቸዋለን፣እምናፍርባቸውን ብልቶች ደግሞ በአክብሮት እንይዛለን።
\v 24 የማናፍርባቸውን ብልቶች ደግሞ በአክብሮት መያዝ አያስፈልገንም ምክንያቱም ቀድሞዉኑ ክብር አግኝተዋል። እግዚአብሔር ግን ብልቶችን ሁሉ በአንድነት በማያያዝ ክብር ላልተሰጣቸው የበለጠ ክብርን ሰጥቷል።
\s5
\v 25 እግዚአብሔር እንዲህ ያደረገው በአካል ውስጥ መከፋፈል እንዳይኖርና ይልቁን ብልቶች በበለጠ ፍቅር እርስ በርሳቸው አንዳቸው ሌላቸውን እንዲከባከቡ ነው።
\v 26 እናም አንዱ ብልት ሲሰቃይ ሁሉም ብልቶች አብረው ይሰቃያሉ። አንዱ ብልት ሲከብር፣ሁሉም ብልቶች አብረው ሐሴት ያደርጋሉ።
\v 27 እንግዲህ እናንተ የክርስቶስ አካል ስትሆኑ እያንዳንዳችሁ የአካሉ ብልቶች ናችሁ።
\s5
\v 28 እግዚአብሔርም በቤተክርስቲያን በመጀመሪያ ሐዋርያትን፣ሁለተኛ ነቢያትን፣ሦስተኛ አስተማሪዎችን፣ከዚያም ተአምራት ማድረግን፣በመቀጠል የፈውስ ስጦታዎችን፣እርዳታ የሚያደርጉትን፣ የአስተዳደር ሥራ የሚሠሩትን፣ እና ልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችን የሚናገሩትን ሰጥቷል።
\v 29 ታዲያ ሁላችን ሐዋርያት ነን? ሁላችንስ ነቢያት ነን? ወይስ ሁላችን አስተማሪዎች ነን? ሁላችን ተአምራቶችን እናደርጋለን?
\s5
\v 30 ሁላችን የፈውስ ስጦታዎች አሉን? ሁላችን በልሳኖች እንናገራለን? ሁላችን ልሳኖችን እንተረጉማለን?
\v 31 የሚበልጡትን ስጦታዎች በከፍተኛ ጉጉት ፈልጉ። እጅግ የሚበልጠውንም መንገድ አሳያችኋልሁ።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በሰዎች እና በመላእክት ልሳኖች ብናገር፣ግን ፍቅር ከሌለኝ፣የሚንጫጫ ቃጭል ወይም የሚጮህ ታንቡር ነኝ።
\v 2 የትንቢት ስጦታ ቢኖረኝ፣ የተሰወሩ እውነቶችን እና እውቀት ሁሉ ቢኖረኝ፣ተራሮችን ከስፍራቸው የሚያስወግድ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ፣ ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም የማይጠቅም ነኝ።
\v 3 ድሆችን ለመመገብ ያለኝን ሁሉ ብሰጥ፣ ሰውነቴንም እንዲቃጠል ብሰጥ፣ፍቅር ከሌለኝ ግን ምንም አይጠቅመኝም።
\s5
\v 4 ፍቅር ታጋሽና ደግ ነው። ፍቅር አይመቀኝም ደግሞም አይመካም። አይታበይም
\v 5 ወይም ትህትና የጎደለው አይደለም። ራስ ወዳድ አይደለም። በቀላሉ አይበሳጭም፤ወይም በደልን አይቆጥርም።
\v 6 ፍቅር በአመጽ ደስ አይሰኝም፣በእውነት ግን ደስ ይለዋል።
\v 7 ፍቅር ሁሉን ይታገሳል፤ሁሉን ያምናል፤በሁሉም ድፍረት አለው በሁሉ ይጸናል።
\s5
\v 8 ፍቅር ፍጻሜ የለውም። ትንቢቶች ያልፋሉ፤ልሳኖችም ቢሆኑ ያበቃሉ፤ዕውቀትም ቢሆን ጊዜ ያልፍበታል።
\v 9 ከዕውቀት የተወሰነውን እናውቃልን፣ትንቢትም በከፊል እንተነቢያለን።
\v 10 ነገር ግን ፍጹም የሆነው ሲመጣ፣ፍጹም ያልሆነው ወደ ፍጻሜ ይደርሳል።
\s5
\v 11 ልጅ በነበርሁበት ጊዜ፣እንደ ልጅ እናገር ነበር፣እንደ ልጅም አስብ ነበር፣የመረዳት ችሎታዬም እንደ ልጅ ነበር። ጎልማሳ ስሆን ግን የልጅነት ነገሮችን አስወገድሁ።
\v 12 አሁን በጨለማ ውስጥ ያለን ምስል በመስታዋት እንደሚያይ እንመለከታለን፣የዚያን ጊዜ ግን ፊት ለፊት እናያለን። አሁን ዕውቀትን በከፊል አውቃለሁ፣የዚያን ጊዜ ግን ልክ እኔ ሙሉ በሙሉ እንደምታወቀው ሙሉ በሙሉ አውቃለሁ።
\v 13 ነገር ግን እምነት፣ ተስፋ፣ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ግን ጸንተው ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጠው ፍቅር ነው።
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 ፍቅርን ተከታተሉ ለመንፈሳዊ ስጦታዎችም ከፍተኛ ጉጉት ይኑራችሁ፣
\v 2 በተለይም ደግሞ ትንቢት የመናገር ስጦታን በብርቱ ፈልጉ። በልሳን የሚናገር ለሰው ሳይሆን ለእግዚአብሔር ይናገራል፣በመንፈስ የተሰወሩ ነገሮችን ይናገራልና ማንም አይረዳውም።
\v 3 ትንቢት የሚናገር ግን ሰዎችን ለማነጽ፣ለማበረታታትና፣ ለማጽናናት፣ ይናገራል።
\v 4 በልሳን የሚናገር ራሱን ያንጻል፣ትንቢት የሚናገር ግን ቤተክርስቲያንን ያንጻል።
\s5
\v 5 እንግዲህ ሁላችሁም በልሳኖች ብትናገሩ ምኞቴ ነበር። ከዚያ ይበልጥ ትንቢት ብትናገሩ እወዳለሁ። በልሳን የተነገረውን የሚተረጉም ከሌለ፣ ቤተክርስቲያን እንድትታነጽ ልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር ይበልጣል።
\v 6 ወንድሞች እና እህቶች፣ልሳን እየተናገርሁ ወደ እናንተ ብመጣ ምን እጠቅማችኋለሁ? በመገለጥ፣ወይም በእውቀት፣ወይም በትንቢት፣ወይም በማስተማር ካልሆነ ልጠቅማችሁ አልችልም።
\s5
\v 7 ሕይወት የሌላቸው እንደ ዋሽንት ወይም ክራር ያሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች መለየት የሚቻሉ ድምፆችን ካላወጡ፣አንድ ሰው የትኛው የሙዚቃ መሣሪያ እንደተጫወተ እንዴት ማወቅ ይችላል?
\v 8 መለከት ሊለይ በማይቻል ድምፅ ቢነፋ፣አንድ ሰው ለጦርነት ለመዘጋጀት ጊዜው እንደሆነ እንዴት ሊያውቅ ይችላል?
\v 9 እናንተንም በተመለከተ እንዲሁ ነው። ሊታወቅ የማይችል ንግግር ብትናገሩ አንድ ሰው ምን እንደተናገራችሁ እንዴት ሊያውቅ ይችላል? እናንተ ትናገራላችሁ ነገር ግን ማንም አይረዳችሁም።
\s5
\v 10 በዓለም ውስጥ ብዙ ልዩ ልዩ ቋንቋዎች እንዳሉ ጥርጥር የለውም፣
\v 11 አንዳቸውም ግን ትርጉም የሌላቸው አይደሉም። የአንድን ቋንቋ ትርጉም የማላውቅ ከሆን ለሚናገረው ሰው እንግዳ እሆንበታለሁ፣ተናጋሪውም እንግዳ ይሆንብኛል።
\s5
\v 12 ለእናንተም እንዲሁ ነው። ለመንፈስ ቅዱስ መገለጦች ከፍተኛ ፍላጎት ስላላችሁ፣ቤተክርስቲያንን ለማነጽ ጉጉት ይኑራችሁ።
\v 13 ስለዚህ በልሳን የሚናገር መተርጎም እንዲችል ይጸልይ።
\v 14 በልሳን በምጸልይበት ጊዜ መንፈሴ ይጸልያል፣አእምሮዬ ግን ያለ ፍሬ ነው።
\s5
\v 15 ታዲያ ምን ላድርግ? በመንፈሴም እጸልያልሁ፣በአእምሮዬም እጸልያለሁ። በመንፈሴ እዘምራለሁ፣በአእምሮዬም እዘምራለሁ።
\v 16 እንደዚያ ካልሆነ ግን እግዚአብሔርን በመንፈሳችሁ ብታመሰግኑና ሌላው ሰው በምታመሰግኑበት ሰዓት ምን እያላችሁ እንደሆነ ካላወቀ እንዴት "አሜን" ይላል?
\s5
\v 17 በእርግጠኝነት በሚገባ እያመሰገናችሁ ነው፣ሌላው ሰው ግን እየታነጸበት አይደለም።
\v 18 ከሁላችሁም የበለጠ በልሳን ስለምናገር እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 19 በቤተክርስቲያን ውስጥ ግን ሰዎችን ማስተማር እንድችል፥ በልሳን አሥር ሺ ቃላትን ከምናገር፣ በአእምሮዬ አምስት ቃላትን መናገር እመርጣለሁ።
\s5
\v 20 ወንድሞች እና እህቶች፣በአስተሳሰባችሁ ልጆች አትሁኑ። ይልቁን ክፋትን በተመለከተ እንደ ሕፃናት ሁኑ። ነገር ግን በአስተሳሰባችሁ ይበልጥ የበሰላችሁ ሁኑ።
\v 21 በሕጉ እንደተጻፈው፣"የማያውቁት ቋንቋ ባላቸው ሰዎችና እንግዳ በሆነ ንግግር ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ። እንደዚያም ሆኖ አይሰሙኝም፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 22 ስለዚህ ልሳኖች ለአማኞች ሳይሆን አማኝ ላልሆኑ ሰዎች ምልክት ናቸው። ትንቢት መናገር ግን ለማያምኑ ሰዎች ሳይሆን ለአማኞች ምልክት ነው።
\v 23 ስለዚህ፣ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ሰው ሁሉ ቢሰበሰብ እና በልሳኖች በመናገር ላይ እያሉ ከውጭ ያሉና የማያምኑ ሰዎች ቢገቡ አብደዋል አይሉምን?
\s5
\v 24 ነገር ግን ሁላችሁም ትንቢት እየተናገራችሁ ባለበት ሰዓት አማኝ ያልሆነ ወይም የውጭ ሰው ቢገባ በሚሰማው ነገር ሁሉ ኃጢአተኝነቱ ይሰማዋል። በሚነገረው ነገር ሁሉ ይፈረድበታል።
\v 25 የልቡም ምስጢር ሁሉ ይገልጣል። ከዚህም የተነሳ፣ በግንባሩ ተደፍቶ እግዚአብሔርን ያመልካል። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው! ብሎ ያውጃል።
\s5
\v 26 ታዲያ ምን ይሁን፣ወንድሞች እና እህቶች? በአንድነት በምትሰበሰቡበት ጊዜ፣እያንዳንዳችሁ መዝሙር፣ትምህርት፣መገለጥ፣ልሳን፣ወይም ልሳን መተርጎም አላችሁ። የምታደርጉትን ሁሉ ቤተክርስቲያንን ለማንጽ አድርጉት።
\v 27 ማንም በልሳን ቢናገር ሁለትም ሦስትም ብትሆኑ ተራ በተራ አድርጉት። ሌላው ሰው ደግሞ በልሳን የተነገረውን ይተርጉም።
\v 28 የሚተረጉም ከሌለ ግን፣ሁሉም ሰው ድምፁን ሳያሰማ ለራሱ እና ለእግዚአብሔር ብቻ ይናገር።
\s5
\v 29 ሁለት ወይም ሦስት ነቢያቶች በሚናገሩበት ጊዜ ሌሎች የሚነገረውን በመመርመር ያዳምጡ።
\v 30 ነገር ግን በስብሰባው ውስጥ አንድ ሰው መረዳት ከመጣለት በመናገር ላይ ያለው ዝም ይበል።
\s5
\v 31 ትንቢት ስትናገሩ ሁሉም ሰው እንዲበረታታ እያንዳንዳችሁ ተራ በተራ መናገር ትችላላችሁ።
\v 32 የነቢያቶች መንፈስ ለነቢያት ይገዛል።
\v 33 እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ ግራ የመጋባት አምላክ አይደለም። በሁሉም የአማኞች አብያተክርስቲያናት ውስጥ፦
\s5
\v 34 ሴቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ዝም ይበሉ። እንዲናገሩ አይፈቀድላቸውም። ሕጉ ይህን ይላልና ይልቁንስ ይገዙ ።
\v 35 ሊያውቁ የሚፈልጉት ነገር ቢኖር፣ባሎቻቸውን በቤት ውስጥ ይጠይቁ። ሴት በቤተክርስቲያን ውስጥ መናገሯ አሳፋሪ ነውና።
\v 36 የእግዚአብሔር ቃል የመጣው ከእናንተ ነውን? ወይስ ወደ እናንተ ብቻ ደርሷልን?
\s5
\v 37 ማንም ሰው ራሱን ነቢይ እንደሆነ ወይም መንፈሳዊ እንደሆነ ቢያስብ፣የጻፍሁላችሁ ነገሮች የጌታ ትዕዛዛት እንደሆኑ ሊያውቅ ይገባዋል።
\v 38 ነገር ግን ማንም ይህን ባያውቅ እርሱም ዕውቅና አያግኝ።
\s5
\v 39 እንግዲህ ወንድሞች እና እህቶች፣ትንቢትን መናገር በቅንነት ፈልጉ፣ ማንንም ልሳኖችን እንዳይናገር አትከልክሉ።
\v 40 ነገር ግን ማንኛውም ነገር በመልካም ምግባር እና በሥርዓት ይደረግ።
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 ወንድሞች እና እህቶች፣ ስላወጅሁላችሁ እና እናንተም ጸንታችሁ ስለቆማችሁበት ወንጌል አሳስብባችኋለሁ።
\v 2 የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣በዚህ ወንጌል መዳን ይሆንላችኋል፣አለዚያ ግን ማመናችሁ ምንም ጥቅም የለውም።
\s5
\v 3 ለእናንተ ያስተላለፉሁት በቀዳሚነት አስፈላጊ የሆነውን እና እኔም የተቀበልሁትን ነው፤ መጽሐፍት እንደሚሉት ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፣
\v 4 ተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን ተነሳ፣መጽሐፍትም ይህን ያረጋግጣሉ።
\s5
\v 5 ለኬፋ ታየ፣ከዚያም ለእሥራ ሁለቱ።
\v 6 እንደገና ከአምስት መቶ ለሚበልጡ ወንድሞች እና እህቶች በእንድ ጊዜ ታየ። አብዛኛዎቹ እስካሁን ድረስ በሕይወት አሉ፣የተወሰኑት ደግሞ አንቀላፍተዋል።
\v 7 ከዚያም ለያዕቆብ፣ደግሞም ለሐዋርያቱ ሁሉ ታየ።
\s5
\v 8 ከሁሉም በኋላ፣ያለ ጊዜው እንደተወለደ ልጅ ለሆንሁት ለእኔ ታየ።
\v 9 ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና። የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን አሳድጃለሁና ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም።
\s5
\v 10 ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁትን ሆኜአለሁ፣በእኔ ውስጥ የነበረው ጸጋም በከንቱ አልነበረም። ይልቁን ከሁሉም በላይ ጠንክሬ ሠራሁ። ሆኖም ይህ የሆነው ከእኔ ሳይሆን ከእኔ ጋር ካለው የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ነው።
\v 11 ስለዚህ እኔም ሆንሁ እነርሱ ስንሰብክላችሁ አመናችሁ።
\s5
\v 12 አሁን ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ ከተሰበከ፣ከእናንተ አንዳንዶች ታዲያ እንዴት የሙታን ትንሣኤ የለም ይላሉ?
\v 13 ሙታን ትንሣኤ ከሌለ እንግዲያው ክርስቶስም ከሙታን አልተነሳማ።
\v 14 ክርስቶስም ካልተነሳ ስብከታችንም፣የእናንተም እምነት ዋጋ የሌለው ሆኗላ።
\s5
\v 15 እንግዲህ እኛም ስለ እግዚአብሔር የሐሰት ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፣ ምክንያቱም እርሱ ክርስቶስን ሳያስነሳ እኛ አስነስቶታል በማለታችን በእግዚአብሔር ላይ በሐሰት መስክረንበታል።
\v 16 ሙታን ካልተነሱ፣ክርስቶስም አልተነሳም ማለት ነው።
\v 17 ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ፣ እምነታችሁ ምንም ዋጋ የለውምናም አሁንም በኃጢአታችሁ አላችሁ።
\s5
\v 18 ስለዚህ በክርስቶስ ሆነው የሞቱ ደግሞ ጠፍተዋል ማለት ነው።
\v 19 ክርስቶስ ተስፋ ያደረግነው ለዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ከሰዎች ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን።
\s5
\v 20 አሁን ግን ክርስቶስ ከሙታን ሁሉ በኩር ሆኖ ተነስቷል።
\v 21 ሞት በአንድ ሰው በኩል እንደመጣ፣ የሙታን ትንሣኤም በአንድ ሰው በኩል መጥቷል።
\s5
\v 22 በአዳም ሁሉም እንደሞቱ፣ሁሉም ደግሞ በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ።
\v 23 ግን እያንዳንዱ በቅደም ተከተሉ መሠረት፦ ክርስቶስ በኩር፣ ቀጥሎ የክርስቶስ የሆኑት እርሱ ተመልሶ ሲመጣ ሕያዋን ይሆናሉ።
\s5
\v 24 ከዚያም ክርስቶስ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ ፍጻሜ ይሆናል። ይህም የሚሆነው ግዛትን ሁሉ፣ ሥልጣንን ሁሉ፣ እና ኃይልን ሁሉ ሲደመስስ ነው።
\v 25 ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሮቹ ስር እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋል።
\v 26 ሊደመሰስ የሚገባው የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው።
\s5
\v 27 "ሁሉን ከእግሮቹ በታች አደረገ።" ነገር ግን፣"ሁሉን አደረገ፣" ሲል፣ሁሉን እንዲገዛለት ያደረገውን እንደማይጨምር ግልጽ ነው።
\v 28 ሁሉም ሲገዛለት፣ ልጁ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ይገዛል። ይህ የሚሆነው እግዚአብሔር አብ ሁሉ በሁሉ እንዲሆን ነው።
\s5
\v 29 አለበዚያ ግን ፤ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ሰዎች ለምን ያደርጉታል? ሙታን ፈጽሞ የማይነሱ ከሆነ፣ስለምን ያጠምቁላቸዋል?
\v 30 ስለምንስ በየሰዓቱ አደጋ ውስጥ እንወድቃለን?
\s5
\v 31 ወንድሞች እና እህቶች፣ ስለ እናንተ በክርስቶስ ባለኝ ትምክህት ይህን እናገራለሁ፦ በየቀኑ እሞታለሁ ።
\v 32 በሰው ዓይን ሲታይ፣ በኤፌሶን ከአውሬዎች ጋር መጋደሌ፣ ሙታን የማይነሱ ከሆነ ምን ይጠቅመኛል? "ነገ መሞታችን ስለማይቀር፣እንብላ፣ እንጠጣ።"
\s5
\v 33 አትታለሁ፦ "መልካም ያልሆነ ግንኙነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።"
\v 34 ራሳችሁን ተቆጣጠሩ! የጽድቅ ሕይወት ኑሩ! ኃጢአት ማድረግን አትቅጠጥሉ። አንዳንዶቻችሁ ስለ እግዚአብሔር ዕውቀት የላችሁም። ይህን የምላችሁ ላሳፍራችሁ ነው።
\s5
\v 35 አንዳንዶች ግን እንዲህ ይላሉ፣"ሙታን የሚነሱት እንዴት ነው? በምን ዓይነት አካል ይመጣሉ?"
\v 36 ዕውቀት የጎደላችሁ ናችሁ! የዘራችሁት ዘር ካልሞተ አይበቅልም።
\s5
\v 37 የዘራችሁት አካል ተምልሶ አይበቅልም፣ይልቁን ዘር ነው እንጂ። ስንዴ ወይም የተዘራውን ሌላ ዓይነት ዘር ሆኖ ይበቅላል።
\v 38 እግዚአብሔር እንደወደደ አካልን ይሰጠዋል፣ለእያንዳንዱም ዘር የራሱን አካል ይሰጠዋል።
\v 39 ሥጋ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም። ይልቁን፣ የሰው ሥጋ አለ፣ እንዲሁም የእንሰሳት ሥጋ አለ፣ የአእዋፍት ሥጋም እንዲሁ፣ ዓሣም ደግሞ ሌላ ዓይነት ሥጋ አለው።
\s5
\v 40 እንዲሁም ደግሞ ሰማያዊ አካልና ምድራዊ አካል አለ። ነገር ግን የሰማያዊ አካል ክብር አለ የምድራዊ አካል ክብር ደግሞ ሌላ ነው።
\v 41 የፀሐይ ክብር አለ፣ የጨረቃ ክብር ደግሞ ሌላ ነው፣ ከዋክብት ደግሞ ሌላ ክብር አላቸው። የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ይለያል።
\s5
\v 42 የሙታን ትንሣኤም ልክ እንደዚሁ ነው። የተዘራው የሚጠፋ ነው፣ የሚነሳው ደግሞ የማይጠፋ ነው።
\v 43 ሲዘራ በውርደት ሲነሳ ግን በክብር ነው። ሲዘራ በድካም፣ሲነሳ ግን በኃይል ነው።
\v 44 የተዘራው ፍጥረታዊ አካል፣የሚነሳው ግን መንፈሳዊ አካል ነው። ፍጥረታዊ አካል እንዳለ ሁሉ መንፈሳዊ አካልም አለ።
\s5
\v 45 እንዲህም ተብሎ ተጽፎአል፣ "የመጀመሪያው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ።" የመጨረሻው አዳም ግን ሕይወት ሰጭ መንፈስ ሆነ።
\v 46 መጀመሪያ የመጣው መንፈሳዊው ሳይሆን ፍጥረታዊው ነው፣ከዚያም መንፈሳዊው ተከተለ።
\s5
\v 47 የመጀመሪያው ሰው ከምድር ሲሆን የተሠራውም ከአፈር ነው። ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው።
\v 48 አንዱ ከአፈር እንደተሠራ፣ከአፈር የተሠሩ ሁሉ እንዲሁ ናችው። እንዲሁም ከሰማይ እንደሆነው ሰው፣ ከሰማይ የሆኑትም እንዲሁ ናቸው።
\v 49 ልክ እኛ ከአፈር የተሠራውን ሰው እንደምንመስል፣ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩን ሰው መልክ እንይዛለን።
\s5
\v 50 ወንድሞች እና እህቶች፣ አሁን እንዲህ እላለሁ፣ሥጋ እና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ አይችልም። እንዲሁም የሚጠፋው የማይጠፋውን ሊወርስ አይችልም።
\v 51 ምስጢር የሆነ እውነት እነግራችኋለሁ፦ ሁላችን አንሞትም፣ግን ሁላችን እንለወጣለን።
\s5
\v 52 የመጨረሻው መለከት ሲነፋ፣ዐይን ተጨፍኖ እስኪገለጥ ባለ ፍጥነት ድንገት እንለወጣለን። መለከቱ ሲነፋ፣ ሙታን የማይጠፋውን አካል ለብሰው ይነሳሉ፣ እኛም እንለወጣለን።
\v 53 ይህ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይለብሳል፣ ሟቹ ደግሞ የማይሞተውን ይለብሳል።
\s5
\v 54 የሚጠፋው የማይጠፋውን ሲለብስ፣እና ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሲለብስ፣ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ይፈጸማል፣"ሞት በድል ተዋጠ።"
\v 55 ሞት ሆይ ድል ማድረግህ የት አለ? ሞት ሆይ መንደፊያህ የት አለ?"
\s5
\v 56 የሞት መንደፊያ ኃጢአት ነው፣ የኃጢአት ኃይል ደግሞ ሕጉ ነው።
\v 57 ነገር ግን በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ድል የሚሰጠን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
\s5
\v 58 ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የጸናችሁ እና የማትነቃነቁ ሁኑ። ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ሥራ ይብዛላችሁ፣ምክንያቱም በጌታ የምትደክሙት ድካም በከንቱ አይደለም።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 አሁን ደግሞ ለአማኞች የሚሰበሰበውን ገንዘብ በተመለከተ፣የገላትያ አብያተክርስቲያናትን እንዳዘዝሁት ሁሉ፣እናንተም እንደዚሁ አድርጉ።
\v 2 እኔ ስመጣ ገንዘብ ከመሰብሰብ፣ በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን፣እያንዳንዳችሁ እንደቻላችሁት መጠን የተወሰነ ገንዘብ አጠራቅሙ።
\s5
\v 3 ወደ እናንተ በደረስሁ ጊዜ በመረጣችሁት ሰው በኩል ከደብዳቤ ጋር መባችሁን ወደ እየሩሳሌም እልከዋለሁ።
\v 4 የእኔም መሄድ አስፈላጊ ከሆነ ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።
\s5
\v 5 ነገር ግን ወደ መቄዶንያ መሄዴ ስለማይቀር፣ በመቄዶንያ በኩል ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ። በምሄድበት ሁሉ ለጉዞዬ እንድትረዱኝ፣
\v 6 ምናልባትም ከእናንተ ጋር ልቆይና ክረምቱንም ከእናንተ ጋር ላሳልፍ እችላልሁ።
\s5
\v 7 አሁን ግን ጊዜው ስለሚያጥር ላያችሁ አላስብም። ጌታ ቢፈቅድና ብመጣ ግን ከእናንተ ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ለመቆየት ተስፋ አደርጋልሁ።
\v 8 ግን በኤፌሶን እስከ በዓለ ኅምሳ ቀን ድረስ እቆያልሁ፣
\v 9 ሰፊ በር የተከፈተልኝ ቢሆንም ብዙ ተቃዋሚዎች አሉብኝ።
\s5
\v 10 ጢሞቴዎስ ልክ እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና ወደ እናንተ ሲመጣ፣ያለ አንዳች ስጋት ከእናንተ ጋር እንዲቀመጥ አድርጉ።
\v 11 ማንም አይናቀው። ወደ አኔ ሲመጣ በሰላም እንዲሄድም እርዱት። ምክንያቱም ከሌሎች ወንድሞች ጋር እንዲመጣ እጠብቃለሁ።
\v 12 አጵሎስን በተመለከተ፣ከወንድሞች ጋር በመሆን እንዲጎበኛችሁ አበረታትቼው ነበር። አሁን ለመምጣት አልወሰነም፣ይሁን እንጂ ዕድሉን ሲያገኝ ይመጣል።
\s5
\v 13 ተጠንቀቁ፣በእምነትም ጸንታችሁ ቁሙ፣ቆራጦች ሁኑ፣በርቱ።
\v 14 የምታደርጉት ሁሉ በፍቅር ይሁን።
\s5
\v 15 የእስጢፋኖስን ቤተሰቦች ታውቃላችሁ። እነርሱ በአካይያ የመጀመሪያ አማኞች እንደሆኑና አማኞችን ለማገልገል ራሳችውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ። ወንድሞች እና እህቶች
\v 16 እንደዚህ ላሉ ሰዎች፣ በሥራ እየረዱንና አብረውን እየደከሙ ላሉ ሰዎች ሁሉ እንድትገዙ አሳስባችኋለሁ።
\s5
\v 17 በእስጢፋኖስ፣በፈርዶናጥስ፣ እና በአካይቆስ መምጣት ተደስቼአልሁ። የእናንተን በዚህ ያለመኖር ጉድለት ሞልተውልኛል።
\v 18 የእኔን እና የእናንተን መንፈስ አድሰዋል። እንዲህ ላሉ ሰዎችን እውቅና ስጧቸው።
\s5
\v 19 በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፣ እንዲሁም በቤታቸው ያለችው ቤተክርስቲያን በጌታ ስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 20 ወንድሞች እና እህቶች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተለዋወጡ።
\s5
\v 21 እኔ ጳውሎስ፣ ይህን በእጄ ጽፌአለሁ።
\v 22 ማንም ጌታን የማይወድ ቢኖር፣ የተረገመ ይሁን። ጌታ ሆይ ና!
\v 23 የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
\v 24 በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅሬ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

523
48-2CO.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,523 @@
\id 2CO
\ide UTF-8
\h 2ኛ ቆሮንቶስ
\toc1 2ኛ ቆሮንቶስ
\toc2 2ኛ ቆሮንቶስ
\toc3 2co
\mt 2ኛ ቆሮንቶስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ እና ወንድማችን ከሆነው ጢሞቲዎስ፥ በቆሮንቶስ ለምትገኝ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን እንዲሁም በመላው አካይያ ላሉ አማኞች ሁሉ፡
\v 2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን እንዲሁም ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ለናንተ ይሁን።
\s5
\v 3 የምህረት አባት፥ የመፅናናት አምላክ እና በመከራችን ሁሉ የሚያፅናናን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።
\v 4 እግዚአብሔር በመከራችን ሁሉ ያፅናናል፥እኛም ራሳችን በእርሱ በእግዚአብሔር በተፅናናንበት መፅናናት ልክ ሌሎችን ማፅናናት እንችላለን።
\s5
\v 5 ምክንያቱም የክርስቶስ መከራ በእኛ ላይ እንደበዛ፥ መፅናናታችንም በክርስቶስ በኩል እንዲሁ ይበዛልናል።
\v 6 ነገር ግን መከራን ብንቀበል፥ስለናንተ መፅናናት እና ድነት ነው። ወይንም ደግሞ የእኛ መፅናናት የእናንተም መፅናናት ማለት ነው፤ይህም እኛ በምንቀበለው መከራ እናንተም በተመሳሳይ መልኩ በትእግስት አብራችሁን ስለምትካፈሉ ነው።
\v 7 በናንተም ያለን መታመን ፅኑ ነው፥በመከራችን እንደምትካፈሉ ሁሉ በመፅናናታችንን ደግሞ እንደምትካፈሉ እናውቃለን።
\s5
\v 8 ወንድሞች ሆይ፥በእስያ ስለደረሰብን መከራ እንድታውቁ እንወዳለን፤ በህይወት ለመኖር ተስፋ እስክንቆርጥ ድረስ ከአቅማችን በላይ ከብዶን ነበር።
\v 9 በርግጥም ሞት ተፈርዶብን ነበር። ሆኖም ግን ያ የደረሰብን መከራ ሙታንን በሚያስነሳ በእግዚአብሔር እንጂ በራሳችን እንዳንታመን አደረገን።
\v 10 ከብርቱ ጥፋት አዳነን እንዲሁም ያድነናል። መታመናችንን በእርሱ ላይ አድርገናል፤እርሱም ይታደገናል።
\s5
\v 11 በእናንተም የፀሎት ድጋፍ አምላካችን ስራውን ይሰራል። በመቀጠልም በብዙዎች ፀሎት አማካኝነት ለእኛ ስለተሰጠው ሞገስ በርካቶች ምስጋናን ያቀርባሉ።
\s5
\v 12 የምንመካው በህሊናችን ምስክርነት ላይ ነው። ምክንያቱም በዚህ ዓለም ስንመላለስ የነበረው በንፁህ ህሊና እና ከእግዚአብሔር በሚሰጥ ቅንነት ነበር። በተለይም ከናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት የተመሰረተው በእግዚአብሔር ፀጋ ላይ እንጂ በምድራዊ ጥበብ ላይ አልነበረም።
\v 13 ልታነቡትና ልትረዱት የማትችሉትን አንዳችም ነገር አንዳልፃፍንላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ፤
\v 14 እናንተም በከፊል እንደተረዳችሁን በጌታችን በኢየሱስ ቀን እናንተ በእኛ እንደምትመኩ እኛም እንዲሁ በእናንተ እንመካለን።
\s5
\v 15 ስለዚህ ርግጠኛ ስለነበርሁ፥ በመጀመሪያ ወደናንተ መምጣት ፈለግሁ፤ ይህ ደግሞ በሁለቱም ጉብኝቶቼ ተጠቃሚዎች እንድትሆኑ ነው።
\v 16 ወደ መቄዶንያ ስሄድ ልጎበኛችሁ ፤ከዚያ ደግሞ ክመቄዶንያ ስመለስ ላያችሁ፤በኋላ ግን እናንተው ወደ ይሁዳ እንደምትልኩኝ አቅጄ ነበር።
\s5
\v 17 ይህንን ሳስብ ታዲያ የወላወልኩ ይመስላችኋልን? ወይስ በአንድ ጊዜ እንደ ሰው መስፈርት "አዎን፥ አዎን" እና "አይደለም፥አይደለም" በማለት አቀድኩን?
\v 18 ነገር ግን እግዚአብሔር የታመነ እንደሆነ፣ እኛም በሁለት ቃል "አዎን" እና "አይደለም" ብለን አንናገርም።
\s5
\v 19 ምክንያቱም በእናንተ መካከል በእኔ፥ በስልዋኖስ እና በጢሞቲዎስ የተሰበከው የእግዚአብሔር ልጅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በአንድ ጊዜ "አዎን" እና "አይደለም" አልነበረም፥ይልቅስ ሁልጊዜም በእርሱ "አዎን" ነው።
\v 20 በእርሱ የእግዚአብሔር ተስፋዎች ሁሉ "አዎን" ናቸው። ስለዚህ እኛም በእርሱ በኩል ለእግዚአብሔር ክብር "አሜን" እንላለን።
\s5
\v 21 እንግዲህ እኛንም ከእናንተ ጋር በክርስቶስ የሚያፀናን እንዲሁም የሾመን እግዚአብሔር ነው።
\v 22 ለዚህም ወደፊት ለሚሰጠን ዋስትና እንዲሆነን መንፈሱን በልባችን የሰጠን ማህተሙንም ያደረገብን እርሱ ነው።
\s5
\v 23 ሆኖም ግን ወደ ቆሮንቶስ ያልመጣሁት እንዳላሳዝናችሁ አስቤ እንደሆነ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
\v 24 እኛም እምነታችሁ ምን መምሰል እንዳለበት በናንተ ላይ ልናዝዝ ሳይሆን በእምነታችሁ ፀንታችሁ እንድትቆሙ ለደስታችሁ የምንሰራ ነን።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ስለዚህም በበኩሌ እንደገና ላስከፋችሁ ተመልሼ መምጣት አልፈለግሁም።
\v 2 ባስከፋችሁ እንኳ ሊያስደስተኝ የሚችለው ያው ያስከፋሁት ሰው አይደለምን?
\s5
\v 3 እንደፃፍኩላችሁ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ ደስ ሊያሰኙኝ የሚገባችው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ ነው። ስለሁላችሁም እርግጠኛ የምሆንበት በእኔ ያለ ደስታ በተመሳሳይ መልኩ በእናንተም ዘንድ ያለ መሆኑ ነው።
\v 4 የፃፍኩላችሁም በታላቅ ጭንቀት፥ በልብ መናወጥ እንዲሁም በብዙ እንባ ነበር፥ ምክንያቱ ደግሞ ለናንተ ያለኝን ጥልቅ ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳላሳዝናችሁ ነው።
\s5
\v 5 ማንም ያሳዘነ ሰው ቢኖር እኔን ብቻ ያሳዘነ ሳይሆን በተወሰነ መልኩ ሁላችሁንም ነው።
\v 6 ለዚያም ሰው በብዙዎች የደረሰበት ቅጣት ይበቃዋል።
\v 7 ግን ይህን ሰው በብዙ ሐዘን እንዳይዋጥ ከመቅጣት ይልቅ ይቅር ልትሉትና ልታፅናኑት ይገባል።
\s5
\v 8 ስለዚህም ለዚህ ሰው ፍቅራችሁን በይፋ እንድታረጋግጡለት አደፋፍራችኋለሁ።
\v 9 የፃፍኩላችሁ በሁሉ ነገር ታዛዦች መሆናችሁን እንድፈትንና እንዳውቅ ነው።
\s5
\v 10 አንድን ሰው ይቅር ብትሉት፣ እኔም ያንን ሰው ይቅር እለዋለሁ። እኔ ይቅር የምለው አንዳች ነገር ቢኖር ይቅርታ የማደርግለት በክርስቶስ ፊት ስለ እናንተ ስል ነው።
\v 11 ይህን የማደርገውም ሰይጣን እንዳያታልለን ነው። ምክንያቱም የርሱን እቅድ አንስተውምና።
\s5
\v 12 ምንም እንኳ ወደ ጥሮአዳ ስመጣ የክርስቶስን ወንጌል ለመስበክ በጌታ በር ተከፍቶልኝ ነበር። ሆኖም ወንድሜን ቲቶን በዚያ ስላላገኘሁት በአዕምሮዬ አላረፍኩም ነበር።
\v 13 ስለሆነም እነርሱን ትቼ ወደ መቄዶንያ ተመለስኩ።
\s5
\v 14 ነገር ግን ሁልጊዜ በክርስቶስ በድል ለሚመራን፥ ጣፋጭ የእውቀት ሽታ በየስፍራውም ለሚናኘው ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
\v 15 ምክንያቱም በሚድኑትና በሚጠፉት መካከል ለእግዚአብሔር የክርስቶስ ጣፋጭ ሽታ ነን።
\s5
\v 16 ለሚጠፉት ሰዎች፥ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ ስንሆን ለሚድኑት ደግሞ ለህይወት የሚሆን የህይወት ሽታ ነን። ለነዚህ ነገሮች የበቃ ማነው?
\v 17 የእግዚአብሔርን ቃል ለትርፋቸው እንድሚነግዱበት እንደ ብዙዎች አይደለንም። በዚያ ፈንታ በክርስቶስ ሆነን በእግዚአብሔር ፊት፥ ከእግዚአብሔር እንደተላክን በቅን ልቦና እንናገራለን።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ራሳችንን እንደገና ልናወድስ እንጀምራለንን? አንዳንድ ሰዎች እንደሚያደርጉት ለናንተም ሆነ ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን? አያስፈልገንም።
\v 2 እናንተ ራሳችሁ በልባችን ላይ የተፃፋችሁ፥በሁሉም ሰዎች የምትታውቁ እና የምትነበቡ የድጋፍ ደብዳቤያችን ናችሁ።
\v 3 በእኛ የቀረባችሁ የክርስቶስ መልዕክት ከመሆናችሁም በላይ በህያው የእግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም ያልተፃፋችሁ፤በሰዎች የልብ ፅላት ላይ እንጂ በድንጋይ ፅላት ላይ ያልተቀረፃችሁ ናችሁ።
\s5
\v 4 እንግዲህ በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ላይ ይህ መታመን አለን።
\v 5 ከእኛ የሆነ ብለን ልናስበው የምንችል አንዳች ችሎታ የለንም፤ነገር ግን ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው።
\v 6 እርሱም የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች አደረገን። ይህ ኪዳን የፊደል ሳይሆን የመንፈስ ነው። ምክንያቱም ፊደል ይገድላል፣ መንፈስ ግን ህይወትን ይሰጣል።
\s5
\v 7 የእስራኤል ህዝብ ከፊቱ ክብር የተነሳ እያደር የሚደበዝዘውን የሙሴን ፊት መመልከት እስኪያቅታቸው ድረስ በፊደላት በድንጋይ ላይ የተቀረፀው የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፤
\v 8 የመንፈስ አገልግሎት እጅግ በክብር አይልቅምን?
\s5
\v 9 የኩነኔ አገልግሎት ክብር ከነበረው፥የፅድቅ አገልግሎት እንደምን በክብር ይብዛ!
\v 10 በርግጥም ቀድሞ በክብር የነበረው ከሱ በሚበልጥ ክብር ተሽሯል።
\v 11 አላፊው በክብር ከሆነ ፀንቶ የሚኖረው በክብር እንዴት ይበልጥ!
\s5
\v 12 እንግዲያውስ እንዲህ ያለ ትምክህት ስላለን እጅግ በድፍረት እንናገራለን።
\v 13 እኛ የእስራኤል ህዝቦች የሚያልፈውን ክብር ትኩር ብለው መመልከት እንዳልቻሉት፤ ፊቱን በመሸፈኛ እንደ ከለለው እንደ ሙሴ አይደለንም።
\s5
\v 14 ሆኖም ግን አእምሮዋቸው ተሸፈነባቸው። እስከዛሬም አሮጌው ኪዳን ሲነበብ ያው መሸፈኛ ይኖራል፤ሊገለጥም አይችልም፤ ምክንያቱም ሊወገድ የሚችለው በክርስቶስ ነው።
\v 15 ሆኖም ግን እስከዛሬ ድረስ የሙሴ ህግ ሲነበብ በልባቸው ላይ መሸፈኛው ይኖራል።
\v 16 ሰው ግን ወደ ጌታ መለስ ሲል ፥መሸፈኛው ይነሳል።
\s5
\v 17 ጌታም መንፈስ ነው፤የጌታም መንፈስ ባለበት ነፃነት አለ።
\v 18 እኛም ሁላችን ባልተሸፈነ ፊት የጌታን ክብር እያየን እርሱን ወደሚመስል ከአንድ ክብር ደረጃ ወደ ሌላ ክብር ደረጃ እንለወጣለን፤ይህም የሚሆነው መንፈስ ከሆነው ጌታ ነው።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 እንግዲህ፥ይህ አገልግሎት ስላለን እንዲሁም ምህረት እንደተቀበልን መጠን፥ ተስፋ አንቆርጥም።
\v 2 በዚያ ፈንታ ግን አሳፋሪ እና ድብቅ የሆኑ መንገዶችን ክደናል። የተንኮል ህይወት አንኖርም፥የእግዚአብሔርንም ቃል ያለ አግባብ አንጠቀምበትም። እውነትንም እየተናገርን ራሳችንን ለሰው ሁሉ ህሊና በእግዚአብሔር ፊት እናቀርባለን።
\s5
\v 3 ሆኖም ግን ወንጌላችን የተሸፈነ ቢሆን፥የተሸፈነው ለሚጠፉት ሰዎች ብቻ ነው።
\v 4 በእነርሱ ሁኔታ ታዲያ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምን አዕምሮዋቸውን አሳውሮታል። በዚህም የእግዚአብሔር መልክ የሆነውን የክርስቶስን የክብር ወንጌል ብርሃን እንዳያዩ አደረጋቸው።
\s5
\v 5 ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ እንጂ ራሳችንን አንሰብክም፥እንዲሁም ስለ ኢየሱስ ስንል የእናንተ አገልጋዮች ነን።
\v 6 ውስጥ ብርሃን ይብራ" ያለው ራሱ እግዚአብሔር ነው፤እናም በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔር ክብር የእውቀት ብርሃን እንዲሰጠን በልባችን ውስጥ አበራልን።
\s5
\v 7 ነገር ግን እጅግ ታላቅ የሆነው ሃይሉ ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳልሆነ ለማሳየት ይህ ሃብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን።
\v 8 በሁሉ መንገድ መከራን እንቀበላለን፥ሆኖም በዚያ አንዋጥም። እናመነታለን ነገር ግን ተስፋ በማጣት አንረበሽም።
\v 9 ቢሆንም ግን ተረስተን አንቀርም።
\v 10 የኢየሱስ ህይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ የእርሱን ሞት ሁልጊዜ በሰውነታችን እንሸከማለን።
\s5
\v 11 ይህም የኢየሱስ ህይወት በሰብዓዊ ሰውነቶቻችን እንዲገለጥ እኛ ህያዋን የሆንን በየዕለቱ ስለ ኢየሱስ ምክንያት ለሞት ታልፈን እንሰጣለን።
\v 12 በዚህም ምክንያት ሞቱ በእኛ፥ ህይወቱም በእናንተ ይሰራል።
\s5
\v 13 ነገር ግን "አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ"ተብሎ እንደተፃፈ፡ ሁላችንም አንድ አይነት የእምነት መንፈስ አለን። ስለምናምንም እንናገራለን።
\v 14 ጌታ ኢየሱስን ከሞት ያስነሳው እኛንም ከእርሱ ጋር ያስነሳናል። ከእናንተም ጋር ወደ ፊቱ እንዲያመጣን እናውቃለን።
\v 15 የሚሆነው ለእናንተ ጥቅም ሲሆን ፀጋ ለብዙዎች ሲበዛ ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆን ምስጋናም ይጨምራል።
\s5
\v 16 ስለዚህም ተስፋ አንቆርጥም። ምንም እንኳ ውጫዊው ማንነታችን እየደከም ቢመጣም ውስጣዊው ማንነታችን ዕለት በየዕለት ይታደሳል።
\v 17 ይህ ጊዜያዊ፣ ቀላል መከራችን መለኪያ ለሌለው፥ ለላቀው ዘላለማዊ ክብር የሚያዘጋጀን ነው።
\v 18 የሚታዩትን ነገሮች ሳይሆን የማይታዩትን ነገሮች እንመለከታለን። የምናያቸው ነገሮች ጊዜያዊ ሲሆኑ የማይታዩት ነገሮች ግን ዘላለማዊ ናቸው።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ምድራዊው መኖሪያችን ቢፈርስ እንኳ በሰማይ በሰው እጅ ያልተሰራ ዘላለማዊ ቤት በእግዚአብሔር እንደተሰራልን እናውቃለን።
\v 2 ድንኳን ውስጥ ሆነን እንቃትታለን፥ሰማያዊ መኖሪያችንንም ልንለብስ እንናፍቃለን።
\v 3 ምክንያቱም ያን ለብሰን ስንገኝ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም ።
\s5
\v 4 በርግጥ በዚህ ድንኳን ውስጥ ሆነን ከብዶን እንቃትታለን፤ምክንያቱ ደግሞ ሟች የሆነው ሰውነት በህይወት መዋጥ ስላለበት እኛም ለብሰን እንጂ ራቁታችንን መሆን አንፈልግም።
\v 5 ወደ ፊት ሊመጣ ላለው የመንፈሱን ዋስትና የሰጠን ለዚህም ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 6 እንግዲህ በሰውነታችን በዚህ ምድር በምንኖርበት ጊዜ በሰማይ ካለው ጌታ ርቀን እንዳለን ይህን እርግጠኛ ሁኑ
\v 7 ምክንያቱም በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና።
\v 8 ስለዚህ ይህ ድፍረት አለን፤ከሰውነታችን ተለይተን ከጌታ ጋር በሰማይ ቤት መሆንን እንመርጣለን።
\s5
\v 9 ስለሆነም በምድርም ብንሆን ወይም ከምድር ብንለይ ግባችን እርሱን ማስደሰት ነው።
\v 10 እያንዳንዳችን በሰውነታችን በዚህ ምድር ላይ የሰራነውን መልካምም ሆነ ክፉ እንቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረባችን ግድ ነው።
\s5
\v 11 እንግዲህ ጌታን መፍራት ምን ማለት እንደሆን ስለምናውቅ ሰዎችን ግድ እንላለን። ማንነታችን በእግዚአብሔር ፊት የተገለጠ ስለሆነ ለናንተም ህሊና ግልፅ እንደሚሆን ተስፋ አለኝ።
\v 12 ራሳችንን ደግመን እንድታወድሱን አናቀርብላችሁም፥ ሆኖም በልብ ሳይሆን በውጫዊው መልክ ለሚመኩ መልስ መስጠት እንዲቻላችሁ እኛን ምክንያት አድርጋችሁ እንድትመኩ እናስታውቃችኋለን።
\s5
\v 13 እንደ እብድ ቢያረገን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤እንደ ባለአዕምሮ ብንሆን ደግሞ ለእናንተ ስንል ነው።
\v 14 የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፥ በዚህ ነገር እርግጠኞች ነን፡አንዱ ሰው ስለሁሉ ሞተ፥ ስለሆነም ሁሉም ሞቱ ማለት ነው።
\v 15 በህይወት ያሉትም ስለእነርሱ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ለራሳቸው እንዳይኖሩ ክርስቶስ ስለሁሉ ሞተ።
\s5
\v 16 ስለዚህም ምክንያት ክርስቶስን ከዚህ ቀደም በሰዋዊ መንገድ አይተነው ቢሆን፥ካሁን ጀምሮ ማንንም በሰዋዊ መስፈርት አንፈርድም። በማንም ላይ ከዚህ በኋል በዚህ መንገድ አንፈርድም።
\v 17 ስለሆነም ማንም በክርስቶስ ውስጥ ቢሆን እርሱ አዲስ ፍጥረት ነው። አሮጌ ነገሮች አልፈዋል። ተመልከቱ፥ ሁሉ አዲስ ሆኗል።
\s5
\v 18 እነዚህ ነገሮች ሁሉ የሆኑት እኛን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ባስታረቀንና የዕርቅ አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው።
\v 19 እግዚአብሔርም በደላቸውን ሳይቆጥርባቸው ዓለሙን በክርስቶስ ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበር። እኛንም ለዚህ የዕርቅ መልዕክት ታማኝ አድርጎ ሾመን።
\s5
\v 20 ስለዚህም እግዚአብሔር በእኛ ሆኖ ልመናውን እንደሚያቀርብ፥ የክርስቶስ ተወካዮች ሆነን ተሹመናል። ከእናንተም ጋር በመሆን ስለ ክርስቶስ "ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!" ብለን ልመና እናቀርባለን።
\v 21 እኛም በእርሱ የእግዚአብሔር ፅድቅ እንድንሆን ሃጢያት ሰርቶ የማያውቀውን ክርስቶስን እግዚአብሔር የሃጢያት መስዋዕት አደረገው።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 እንደዚሁም፥ አብሮ እንደሚሰራ የእግዚአብሔርን ፀጋ እንዲሁ እንዳትቀበሉ እለምናችኋለሁ።
\v 2 ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሏልና "በምቹ ጊዜ ሰማሁህ በድነትም ቀን ረዳሁህ።" ልብ በሉ፥ ምቹ ጊዜም ሆነ የድነት ቀን አሁን ነው።
\v 3 አገልግሎታችን እንዳይነቀፍ በማንም ፊት ማሰናከያ አናኖርም።
\s5
\v 4 ከዚያ ይልቅ፥ በድርጊቶቻችን ሁሉ የእግዚአብሔር አገልጋዮች መሆናችንን እናረጋግጣለን። ይህም በመፅናት፥በመከራ፥ በስቃይ፥በችግር
\v 5 በመገረፍ፥ በእስራት፥ጥላቻ በተሞላ አመፅ፥ ፥በከባድ ስራ ፥እንቅልፍ በማጣት፥በርሃብ፥
\v 6 በንፅህና፥በእውቀት፥በትዕግስት፥በርህራሄ፥በመንፈስ ቅዱስ፥በእውነተኛ ፍቅር፥
\v 7 በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ሃይል ማለትም ለቀኝ እና ለግራ ለሚሆን ለፅድቅ የጦር ዕቃ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን።
\s5
\v 8 በክብርም ሆነ በውርደት፥ በሃሜትም ሆነ በሙገሳ ውስጥ እንሰራለን። በሃሰት ብንከሰስም እውነተኞች ሆነን ተገኝተናል።
\v 9 ያልታወቅን ሆነን ስንሰራ፥እንታወቃለን፤ የምንሞት ስንመስል ህያዋን ነን። በጥፋታችን እንደሚቅጣ ሰው ብንሆንም፥ሞት አልተፈረደብንም።
\v 10 እንደ ሃዘንተኞች ስንሰራ ሁልጊዜም ግን ደስተኞች ነን፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለፀጎች እናደርጋለን፥ ምንም የሌለን ስንሆን፥ ሁሉም አለን።
\s5
\v 11 የቆሮንቶስ ሰዎች ሆይ፥ ሁሉን ነገር በግልፅ ነግረናችኋል፥ልባችንንም ለእናንተ ከፍተንላችኋል።
\v 12 ልባችሁ በራሳችሁ መሻት እንጂ በእኛ ምክንያት አልተዘጋም።
\v 13 ተገቢ በሆነ ሁኔታ እኔም እንደ ልጆች እናገራችኋለሁ፤ልባችሁን ክፈቱልን።
\s5
\v 14 ከማያምኑ ጋር በማይሆን መንገድ በአንድ ላይ አትተሳሰሩ። ፅድቅ ከአመፀኝነት ጋር ምን መዛመድ አለው? ብርሃንስ ከጨለማ ጋር ምን ህብረት አለው?
\v 15 ክርስቶስስ ከቤልዖር ጋር ምን ስምምነት አለው? የሚያምንስ ከማያምን ጋር ምን ድርሻ አለው?
\v 16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስስ ከጣዖታት ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔር "ከእነርሱም ጋር አድራለሁ፥በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፥ እነርሱም ህዝብ ይሆኑኛል" ብሎ ስለተናገረ እኛ የህያው እግዚአብሔር መቅደሶች ነን።
\s5
\v 17 ስለዚህም "ከመካከላቸው ውጡ፤የተለያችሁም ሁኑ" ይላል ጌታ፥ "እርኩሱን አትንኩ፥እኔም እቀበላችኋለሁ።
\v 18 አባት እሆናችኋለሁ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ትሆኑኛላችሁ።" ብሏል ሁሉን የሚችል ጌታ።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 የተወደዳችሁ ሆይ፥ እነዚህ ተስፋዎች ስላሉን በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን እየተከተልን ስጋችንን እና መንፈሳችንን ከሚያረክስ ከማናቸውም ነገር ራሳችንን እናንፃ።
\s5
\v 2 ለእኛ በልባችሁ ስፍራ ስጡን! ማንንም አልበደልንም፥ማንንም አልጎዳንም፥ ማንንም ለራሳችን ጥቅም አልበዘብዝንም።
\v 3 ይህንን የምላችሁ ልኮንናችሁ ብዬ አይደለም፤ምክንያቱም አብረን ለመሞትም ሆነ ለመኖር በልባችን ውስጥ አላችሁና ነው።
\v 4 በእናንተም ታላቅ መታመን አለኝ፣ትምክህቴም ናችሁ። በመከራዎቻችን እንኳ መፅናናት እና የተትረፈርፈ ደስታ ሞልቶኛል።
\s5
\v 5 ወደ መቄዶንያ በመጣን ጊዜ ሰውነታችን እረፍት አልነበረውም። ይልቁንስ በውጭ ግጭት እና በውስጥ ፍርሃት ስለነበረብን በሁሉ አቅጣጫ ተጨነቅን ።
\v 6 ነገር ግን ተስፋ የቆረጡትን የሚያፅናና አምላክ በቲቶ መምጣት አፅናናን።
\v 7 የእርሱ መምጣት ብቻ ሳይሆን እናንተም እርሱን ያፅናናችሁት ማፅናናት እኛን አፅናናን። ለእኔም ያላችሁን ታላቅ ፍቅር፥ርህራሄ እና ጥልቅ ሃሳብ ሲነግረን በይበልጥ ተደሰትሁ።
\s5
\v 8 ምንም እንኳ በመልዕክቴ ባሳዝናችሁም ለምን ፃፍኩ ብዬ አልፀፀትም። ነገር ግን፥የምፀፀተው መልዕክቴ ለጥቂት ጊዜም እንዳሳዘናችሁ ስለማውቅ ነው።
\v 9 አሁን የምደሰትበት ምክንያት ስላዘናችሁ ሳይሆን ሃዘናችሁ ወደ ንስሃ ስለመራችሁ ነው። እግዚአብሔር የሚወደው አይነት ሃዘን እየተለማመዳችሁ ስለሆነ በእኛ ምክንያት ያጣችሁት ነገር የለም።
\v 10 እግዚአብሔር የሚወደው ሃዘን ፀፀት የሌለበት፥ ወደ ድነት የሚመራ ንስሃን ያመጣል። ዓለማዊ ሃዘን ግን ሞትን ያመጣል።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር የሚወደው ሃዘን ምን አይነት ታላቅ ቁርጠኝነት እንዳመጣላችሁ እዩ። ይህም ታላቅ ቁርጠኝነት ምን ያህል ንፁህ መሆናችሁን፥ ምን ያህል በሃጢያት ላይ እንድትቆጡ እንዳደረጋችሁ፥ ምን አይነት ናፍቆት እንዳሳደረባችሁ፥ ምን አይነት በጎ ቅንዓት እንደፈጠረባችሁ ፥ፍትህ እንድታደርጉም ምን አይነት ጥልቅ መሻት እንዳደረገላችሁ ተመልከቱ! በዚህ በኩል በሁሉም ንፁህ መሆናችሁን አስመስክራችኋል።
\v 12 ምንም እንኳ ብፅፍላችሁም የፃፍኩት ለክፉ አድራጊ ወይም በክፉ አድራጎቱ መከራ ለሚቀበል ሳይሆን ለእኛ ምን ያህል እንደምታስቡ በእግዚአብሔር ፊት እንዲታወቅ ነው።
\s5
\v 13 በዚህ እንበረታታለን። እኛ ከመፅናናታችን በተጨማሪ በቲቶ ደስታ ሃሴት አድርገናል፤ መንፈሱ በሁላችሁ ምክንያት አርፏልና ነው።
\v 14 ስለናንተ በመመካት ለእርሱ ተናግሬ ነበር፣እናንተም አላሳፈራችሁኝም። በሌላ አንፃር ስለናንተ የተናገርነው ሁሉ እውነት ነበር፥ለቲቶም ስለናንተ የተናገርነው ሁሉ ትክክል መሆኑ ተረጋግጧል።
\s5
\v 15 እርሱም በፍርሃት እና በመንቀጥቀጥ ያደረጋችሁለትን አቀባበል እንዲሁም የሁላችሁንም መታዘዝ በሚያስብበት ጊዜ ለእናንተ ያለው ፍቅር ታላቅ ነው።
\v 16 በናንተ ሙሉ መታመን ስላለኝ፥ሃሴት አደርጋለሁ።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 ወንድሞችና እህቶች ሆይ ለመቄዶንያ ለአብያተ ክርስቲያናት ስለ ተሰጠው የእግዚአብሔር ጸጋ እንድታውቁ እንፈልጋለን
\v 2 እጅግ የሚፈትናቸው መከራ በደረሰባቸው ጊዜ የደስታቸው መብዛትና የደህንነታቸው አስከፊነት የልግስናቸውን መትረፍረፍ አብዝቷል።
\s5
\v 3 የሚቻላቸውን ያህል ከሚቻላቸውም እንደ ሰጡ እኔ እመሰክርላቸዋለው። በፈቃዳቸውም ለቅዱሳን በሚሰጠው በዚህ አገልግሎት የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸው ዘንድ
\v 4 እኛን በብዙ ልመና ለመኑን።
\v 5 ይህም የሆነው እኛ እንደጠበቅነው አይደለም ነገር ግን በመጀመሪያ ራሳቸውን በጌታ ከዚያም በእግዘአብሔር ፈቃድ ለእኛ ሰጡ።
\s5
\v 6 ስለዚህ አስቀድሞ ከእናንተ ጋር የጀመረውን ተግባር በእናንተ ዘንድ ያለውን ይህን የልግስና ስራ ከፍጻሜ እንዲደርስ ቲቶን ግድ ብለነው ነበር።
\v 7 ነገር ግን እናንተ በሁሉም ነገር በእምነት፥ በንግግር ፣በዕውቀት በትጋት ሁሉ እንዲሁም ለእኛ ባላችሁ ፍቅር እንደሚልቁ በዚህ በበጎ ስራ ደግሞ የምትልቁ ሁኑ።
\s5
\v 8 ከሌሎች ሰዎች ትጋት ጋር በማወዳደር የፍቅራችሁን ቅንነት ለማረጋገጥ እንጂ ይህንን እንደ ትዕዛዝ አልልም እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና።
\v 9 በእርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ ፥ እርሱ ባለ ጠጋ ቢሆንም እንኳ ስለ እናንተ ደኸየ።
\s5
\v 10 በዚህ ጉዳይ እናንተን ስለሚጠቅማችሁ ነገር ምክር እለግሳችኋለው። ከአንድ ዓመት በፊት አንድን ነገር ለማድረግ መጀመር ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ልታደርጉት መሻት በውስጣችሁ ነበር።
\v 11 አሁን ያንኑ ማድረጋችሁን ፈጽሙ። እንግዲህ ልክ በዚያን ጊዜ ልታደርጉት ጉጉትና ጠንካራ ፍላጎት እንደ ነበራችሁ፣ወደ ፍጻሜ ልታመጡት ደግሞ ትችላላችሁ።
\v 12 ይህን ስራ ለመስራት ጉጉት ካለ፣ አንድ ሰው በሌለው ሳይሆን ባለው ነገር ላይ ተመስርቶ ሲሰራ መልካምና ተቀባይነት ያለው ነው።
\s5
\v 13 ይህ ተግባር ሚዛናዊነት እንዲኖር ነው እንጂ ሌሎች እንዲቀልላቸው እናንተም ሸክም እንዲበዛላችሁ አይደለም።
\v 14 አሁን ያለው የእናንተ መትረፍ ለእነርሱ የሚያስፈልጋቸውን ይሞላል። ይህም ደግሞ ሚዛናዊነት ይኖር ዘንድ የእነርሱ መትረፍረፍ የእናንተ ፍላጎት ደግሞ እንዲሞላ ነው።
\v 15 እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ «ብዙ ያለው ምንም አልተረፈውም ፣ጥቂት ያለው ግን ምንም አልጎደለውም።»
\s5
\v 16 ነገር ግን እኔ ለእናንተ ያለኝን ቅን ሃሳብ በቲቶ ልብ ያኖረው እግዚአብሔር ይመስገን።
\v 17 እርሱ ልመናችንን መቀበል ብቻ ሳይሆን ፣ ትጋትን በማሳየት በራሱ ፈቃድ ወደ እናንተ መጥቷልና።
\s5
\v 18 ከእርሱ ጋርም ወንጌልን በማወጅ ስራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የተመሰገነውን ወንድም ልከናል።
\v 19 ይህ ብቻ አይደለም ነገር ግን ለራሱ ለጌታ ክብርና እኛ ለመረዳት ያለንን ጉጉት ለመግለጥ ይህን የጸጋ ስራ እንዲያከናውን አብሮን ይጓዝ ዘንድ አብያተ ክርስቲያናት ደግሞ መርጠውት ነበር።
\s5
\v 20 ስለምንሰበስበው ስለዚህ የልግስና ስጦታ ማንም ትችት ለማቅረብ ምክንያት እንዳያገኝ እንጠነቀቃለን።
\v 21 በጌታ ፊት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በሰዎች ፊት ደግሞ የከበረውን ነገር ለማድረግ እንተጋለን።
\s5
\v 22 ብዙ ጊዜ ፈትነን በበርካታ ተግባራት ተነሳሽነት ያለው ሆኖ ያገኘውን ፣አሁን ግን በእናንተ ላይ ትልቅ መታመን ምክንያት የበለጠ ትጋት የሚያሳየው ሌላ ወንድም ከእነርሱ ጋር እንልካለን።
\v 23 ቲቶን በሚመለከት ግን ስለ እናንተ ከእኔ ጋር የሚሰራ አጋሬ ነው። ወንድሞቻችንን በሚመለከት አብያተ ክርስቲያናት የላኳቸው የክርስቶስ ክብር ናቸው።
\v 24 ስለዚህ ፍቅራችንን ፣ በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ዘንድም ስለ እናንተ ለምን እንደ ተመካን ግለጡላቸው።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 ለቅዱሳን ስለ ሚሆነው አግልግሎት ለእናንተ ልጽፍላችሁ አያስፈልገኝም ።
\v 2 ለመቄዶንያ ሰዎች ስለተመካሁት በውስጣችሁ ስላለው መሻት አውቃለው። በአካዶያ የሚነግሩት ካለፈው ዓመት ጀምሮ መዘጋጀትቱን ነገርኋቸው። የእናንተ ቅንዓት ብዙዎቻቸውን ለስራ አነሳስቷል።
\s5
\v 3 እንግዲህ የተዘጋጃችሁ ትሆናላችሁ እንዳልኩት የተዘጋጃችሁ ትሆኑ ዘንድ፣ ስለ እናንተ መመካታችን ከንቱ እንዳይሆን ወድሞችን ልኬአለው።
\v 4 ምናልባት አንዳቸው ከ እኔ ጋር ከሜቄዶንያ በመጡ፣ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ ሁላችንም ሀፍረት ይሰማናል ነገር ግን በእናንተ ስለምተማመን ፣ ስለ እናንተ የምለው ምንም የለኝም።
\v 5 ስለዚህ ወደ እናንተ እንዲመጡና እናንተ ተስፋ ለሰጣችሁት ስጦታ በቅድሚያ ዝግጅት እንዲያደርጉ ወንድሞችን መለመን አስፈላጊ እንደሆነ አሰብሁ። ይህም እንድትሰጡ ስለ ተገደዳችሁ ሳይሆን በነጻ እንደተሰጠ ስጦታ ዝግጁ ይሆን ዘንድ ነው።
\s5
\v 6 ፍሬ ነገሩ ይህ ነው ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂቱ ያጭዳል ፣ አትረፍርፎ የሚዘራ አትረፍርፎ ያጭዳል።
\v 7 እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ ስትሰጡ በሐዘን ወይም በግድ አይደለም።
\s5
\v 8 እግኢአብሔር ሁልጎዜ በነገር ሁሉ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝቷችሁ በብጎ ስራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።
\v 9 እንዲህ ተብሎ እንደተፃፈ «ሀብቱን በተነ ፣ለድሆችም አከፋፈለ።»
\s5
\v 10 ለዘሪን ዘርን ለምግብ እንጀራን የሚሰጥ ፣የሚዘራ ዘርን ደግሞ ይሰጣል ያበዛውማል፣ ምርት ይጨምራል።
\v 11 ለጋሶች እንድትሆኑ በሁሉም ረገድ መበልጸግ ትላላችሁ፣ ይህም በእኛ በኩል ለእግኢአብሔር ምስጋና ምክንያት ይሆናል።
\s5
\v 12 ይህ የመስጠት አገልግሎት ለቅዱሳን ይሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚሰጥ ብቻ አይደለምና፣ ነገር ግን ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ብዙ ምስጋና ደግሞ ይበዛል።
\v 13 በዚህ አገልግሎት ተፈትናችሁ አልፋችኋል ደግሞም በክርስቶስ ወንጌል ምስክርነት በመታዘዛችሁ ፣እንዲሁም ለእነርሱና ለሁሉ ባደረጋችሁት የስጦታችሁ ልግስና እግዚአብሔርን ታከብራላችሁ።
\v 14 በእናንተ ላይ ካለው እጅግ ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ስለ እናንተ ሲጸልዩ ይናፍቁአችኋል።
\v 15 ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 እኔ ራሴ ጳውሎስ ፣ በፊታችሁ ትሁት የሆንሁ በክርስቶስ ገርነትና የዋህነት እለምናችኃለሁ።
\v 2 እንደ ስጋ ፈቃድ እንደምንኖር የሚያስቡትን በምቃወምበት ጊዜ ፣ ከእናንተ ጋር ሳለሁ መሆን እንደሚገባኝ በራስ በመተማመን የምደፍር መሆን የለብኝም ብዬ እለምናችኃለው ።
\s5
\v 3 ምንም እንኳ በስጋ የምንመላለስ ብንሆን፣ እንደ ስጋ አንዋጋም።
\v 4 የምንዋጋባቸው የጦር መሳሪያዎች ሥጋዊ አይደሉምና ይልቁንም ምሽጎችን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለቸው ፥ አሳሳች የሆኑ ክርክሮችንም ያፈርሳሉ።
\s5
\v 5 ደግሞም በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ፥ እንዲሁም ለክርስቶስ ለመታዘዝ ሀሳብን ሁሉ እንማርካለን።
\v 6 መታዘዛችሁም በተፈጸመ ጊዜ ፣ ይለመታዘዝን ተግባር ሁሉ ለመቅጣት እንዘጋጃለን።
\s5
\v 7 በግልጽ ከፊታችን ያለውን ተመልከቱ ፥ ማንም የክርስቶስ እንደሆነ ቢያምን ልክ እርሱ የክርስቶስ እንደሆነ እኛ ደግሞ እንዲሁ መሆናችንን ራሱ ያሰበው።
\v 8 ሊያንጻችሁ እንጂ ሊያጠፋችሁ የይደለ ጌት ኣስለ ሰለ ሰጠው ስልጣናችን ጥቂት አብዝቼ ብመካም እንኳ፥ አላፍርም።
\s5
\v 9 በመልዕክቶቼም ላስደነግጣችሁ አልፈልግም።
\v 10 አንዳንድ ሰዎች ፥«መልእቶቹ ጠንከር ያሉና ኃይለኛ ናቸው፥ ነገር ግን በአካል ደካማ ነው፥ ንግግሩም ሊሰማ የሚገባ አይደለም»ይሉናል።
\s5
\v 11 እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ስንርቅ በመልዕክት የምንለው፥እዚያ ስንሆን ከምናደርገው ጋር አንድ መሆኑን ይረዱ።
\v 12 ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ጋር ራሳችንን እስከ ማስተያየት ወይም እስከ ማወዳደር ድረስ አንሔድም። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከሌላ ጋር ሲመዝኑና ራሳቸውን እርስ በእርስ ሲያወዳድሩ ፥ ማስተዋል ተላቸውም።
\s5
\v 13 ይሁን እንጂ እኛ ከልክ በላይ አንመካም፥ ነገር ግን ወደ እናንተ እንኳ እስክንደርስ እግዚአብሔር በወሰነልን ስራ እንሆናለን።
\v 14 ወድ እናንተ ስንደርስ ከመጠን አላለፍንምንና በክርስቶስ ወንጌል ወደእናንተ ለመድረስ የመጀመሪያዎች ነበርን።
\s5
\v 15 በሌሎች ድካም ከልክ ያለፈ አንመካም ፥ ነገር ግን ከእናንተ አካባቢ አልፎ እንኳ
\v 16 ወንጌልን እንሰብክ ዘንድ እምነታችሁ ሲያድግ ስራችን እጅግ እንደሚስፋፋ ተስፋ እናደርጋለን ። በሌላ ስፍራ እየተሰራ ስላለው ሥራ አንመካም።
\s5
\v 17 «ነገር ግን የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ።»
\v 18 ጌታ የሚያመሰግነው እንጂ፣ ራሱን የሚያመሰግን ተፈትኖ የሚወጣ አይደለምና።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 በጥቂት ሞኝነቴ ልትታገሱኝ ብትችሉ እመኝ ነበር፣ እናንተ ግን በእርግጥ ታግሳችሁኛል!
\v 2 እኔ ስለ እናንተ እቀናለሁና እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል ለክርስቶስ ላቀችርባችሁ ለአንድ ባል ስላጨዋችሁ በእግዚአብሔር ቅንአት እቀናላችኃለው ።
\s5
\v 3 ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳታለላት ፣ ሐሳባችሁ ለክርስቶስ ካልችሁ ቅንና ንጹህ ታማኝነት መረን እንዳትወጡ ብዬ እፈራለው።
\v 4 አንድሰው መጥቶ እኛ ከሰበክበው የተለየ ሌላ ኢየሱስ ቢያውጅላችሁ፣ ወይም ቀድሞ ከተቀበላችሁት የተለየ መንፈስ ብትቀበሉ ወይም እናንተ ከተቀበላችሁት የተለየ ወንጌል ቢደርሳችሁ ደህና ትታገሱታላችሁና።
\s5
\v 5 ከነዚያ «ገናና ሐዋርያት» በጥቂቱ እንኳ የማንስ አይደለሁም ብዬ አስባለውና።
\v 6 ነገር ግን በአነጋገር ያልሰለጠንሁ አይደለሁም። በሁሉም መንገድና በሁሉም ነገር ይህን አሳውቀናችኋል።
\s5
\v 7 የእግዚአብሔርን ወንጌል በነፃ ስለሰበኩለችሁ፥ እናንተ ከፍ እንድትሉ እኔ ራሴን በማዋረዴ ኋጢያት ሰራሁን?
\v 8 እናንተን ማገልገል እችል ዘንድ ከእነርሱ እርዳታ በመቀበል ሌሎችን አብያተ ክርስቲያናት«ጎዳሁ»።
\v 9 አብሬአችሁ በሆንኩና በተቸገርሁ ጊዜም በማንም ላይ ሸክም አልሆንሁም። ከመቄዶንያ የመጡት ወንድሞች የሚያስፈልገኝን ሰጥተዋልና። በሁሉም ረገድ ለእናንተ ሸክም ከመሆን ተጠንቅቄአለሁ፣ይህን ማድረጌንም እቀጥላለው ።
\s5
\v 10 የክርስቶስ እውነት በእኔ ውስጥ ያለ እንደ መሆኑ፣ ይህ የእኔ ትምህርት?
\v 11 ለምንስ እንዲህ ይሆናል? ለማልወደችሁ ነውን? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል። እንደነዚህ ያሉ ሰዎችን ራሳቸውን እንደ ክርስቶስ ሐዋርያት በማስመሰል ሐሰተኞች ሐዋርያት፣ አታላይ ሰራተኞች ናቸውና ።
\s5
\v 12 እኔን የሚነቅፉትንና እኛ የምናደርገውን እነርሱም እያደረጉ እንደ ሆነ እየተናገሩ የሚመኩበትን ምክንያት ለማሳጣት አሁን የሚደረገውን ወደ ፊትም አደርጋለሁ።
\v 13 እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች ሐሰተኛ ሐዋርያትና አታላይ ሸራተኞች ናቸው።
\s5
\v 14 ይህም የሚያስደንቅ አይደለም፣ ሰይጣን እንኳ ራሱን የብርሓን መልአክ በማስመሰሉ ርሱን ይለውጣልና።
\v 15 የእርሱ አግልጋዮች ደግሞ የጽድቅ አገልጋዮች በማስመሰል ራሳቸውን ቢለውጡ እጅግ የሚያስደንቅ አይደለም። ዕጣ ፈንታቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።
\s5
\v 16 ደግሜ እላለሁ፦ እኔ ሞኝ እንደሆንሁ ማንም አያስብ ። ሞኝ እንደሆንሁ ብታስቡ ግን በጥቂቱ እመካ ዘንድ እንደ ሞኝ ተቀበሉኝ።
\v 17 እንደዚህ ታምኜ በመመካት የምናገረው፣ ጌታ የፈቀደው አይደለም፣ እኔ ግን እንደ ሞኝ እናገራለው።
\v 18 ብዙ ሰዎች በሥጋ ሰለሚመኩ፣ እኔም ደግሞ እመካለው።
\s5
\v 19 እናንተ ብልሆች ሆናችሁ ሞኞችን በደስታ ትታገሣላችሁና!
\v 20 ማንም ባሪያዎች ቢያደርጋችሁ፣ ማንም በመካከላችሁ መለያየትን ቢፈጥር፣ ማንም መጠቀሚያ ቢያደርጋችሁ፣ ማንም ቢቀማችሁ ፣ወይም ፊታችሁን በጥፊ ቢመታችሁ ትታገሱታላችሁና.
\v 21 ይህንን ስናደርግ በጣም ደካሞች እንደ ነበርን እያፈርሁ እናገራለ። ሆኖም ማንም በሚመካበት ጊዜ ሁሉ እንደ ሞኝ እላለው፣ እኔ ደግሞ እመካለሁ።
\s5
\v 22 እነርሱ ዕብራውያን ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ እስራኤላውያን ናቸውን እኔ ደግሞ ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ።
\v 23 የክርስቶስ አግልጋዮች ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ (እንደ እብድ እናገራለው) እኔ እበልጣለሁ፣ በከባድ ሥራ አብዝቼ በመታሰር አብዝቼ፣ በመደብደብ ከልክ በላይ፣ ብዙ የሞት አደጋዎችን በመጋፈጥ ብዙ ጊዜ ሆንሁ።
\s5
\v 24 አይሁድ «አንድ ሲጎድል አርባ ጅራፍ»አምስት ግዜ ገረፉኝ።
\v 25 ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ። አንድ ግዜ በድንጋይ ተወገርሁ። ሦስት ጊዜ የተሳፈርኩበት መርከብ ተሰበረ። አንድ ሌሊትና አንድ ቀን በባህር ላይ አሳለፍሁሁሁ፣
\v 26 በተደጋጋሚ በመንገድ ተጓዝሁ። በወንዞች አደጋ፣ በወንበዴዎች አደጋ በወገኖቼ በኩል አደጋ፣ በአሕዛብ በኩል አደጋ፣ በከተማ አደጋ በምድረ በዳ አደጋ፣ በባሕር አደጋ፣ በሐሰተኞች በኩል አደጋ ነበረብኝ።
\s5
\v 27 በከባድ ስራና በችግር፣ እንቅልፍ ባጣሁባቸው ብዙ ሌሊቶች፣ በረሃብና በጥም ፣ እንዲሁም የሚበላ በማጣት፣በብርድባ በራቁትነት ነበርሁ።
\v 28 ከሌላውም ሁሉ በተለይ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ ለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያለኝ ጭንቀት ነው።
\v 29 ደካማ ምን ነው እኔስ አልደክምምን? ኃጢአት እንዲሠራ ሌላውን ያሰናከለ ማን ነው፣ እኔስ በውስጤ አልናደድምን?።
\s5
\v 30 መመካት ካለብኝ፣ ድካሜን ስለሚያሳየው ነገር እመካለው።
\v 31 እንደማልዋሽ፣ ለዘላለም የተመሰገነው የጌታ ኢየሱስ አምላክና አባት ያውቃል።
\s5
\v 32 በደማስቆ ከንጉስ አርስጦስዮስ በታች የሆነ ገዢ እኔን ይዞ ለማሰር ከተማዋን እየጠበቀ ነበር፣
\v 33 ነገር ግን በቅጥሩ ባለ መስኮት በቅርጫት አወረዱኝ፣ ከእጆቹም አመለጥሁ።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 መመካት አለብኝ፤ ነገር ግን በመመካት ጥቅም አይገኝም። ከጌታ ወዳሉት ራዕዮችና መገለጦች ግን እሄዳለው።
\v 2 በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ አላውቅም፤ እግዚአብሔር ግን ያውቃል። ከዐሥራ አራት ዓመታት በፊት በክርስቶስ የሆነ አንድ ሰው ወደ ሦስተኛ ሰማይ ተነጠቀ። እንደዚህ ያለውን ሰው ዐውቃለው።
\s5
\v 3 በሥጋ ይሁን ወይም ከሥጋ ውጭ እኔ አላውቅም፣ እግዚአብሔ ግን ያውቃል፣
\v 4 ይህ ሰው ወደ ገነት ተነጠቀ፤ ማንኛውም ሰው የማይናገራቸው እጅግ የተቀደሰ ነገሮችን ሰማ።
\v 5 እንደዚህ ስላለው ሰው እመካለው ስለራሴ ግን ከድካሜ በቀር አልመካም።
\s5
\v 6 ልመካ ከፈለግሁ፣ ሞኝ አይደለሁም፣ እውነትን እናገራለሁና፤ ነገር ግን ማንም በእኔ ከታየው ወይም ከእኔ ከተሰማው ፣
\v 7 ወይም በመገልጦቹ ልዩ ባሕርይ ምክንያት የምበልጥ አድርጎ እንዳያስብ አልመካም።ስለዚህ እንዳልታበይ፣ እጅግ እንዳልኩራራ የሥጋ መውጊያ፣የሚነዘንዘኝ የሰይጣን መልዕክተኛ ተሰጠኝ።
\s5
\v 8 መውጊያውን ከእኔ እንዲያነሣው ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።
\v 9 እርሱም፣ «ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይል በድካም ይፈጸማልና» አለኝ። ስለሆነም የክርስቶስ ኃይል ያርፍብኝ ዘንድ አብዝቼ ስለ ድካሜ እመካለው።
\v 10 ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በችግር፣ በስደት ፣ በጭንቀትም እርካታ ይሰማኛል በምደክምበት ጊዜ ሁሉ ብርቱ ነኝና።
\s5
\v 11 ሞኝ ሆኜአለሁ! እንዲህ እንድሆን ያስገደዳችሁኝ እናንተ ናችሁ፣እናንተ እኔን ልታመሰግኑኝ ይገባችሁ ነበር፥ምክንያቱም እኔ ምንም ባልሆን እንኳ ከ«ገናና ሐዋርያት» የማንስ አልነበርሁም።
\v 12 የአንድ ሐዋርያ እውነተኛ ምልክቶች በሁሉ ትዕግሥት፦ በምልክቶችና በድንቆች በብርቱ ተግባራትም በእናንተ መካከል ተደረጉ።
\v 13 እኔ ሸክም ካልሆንሁባችሁ በቀር ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የምታንሱት እንዴት ነበር? ይህን ስሕትቴን ይቅር በሉኝ!
\s5
\v 14 አስተውሉ! ለሦስተኛ ጊዜ ወደ እናንተ ለመምጣት ተዘጋጅቻለው፤ ሸክም አልሆንባችሁም፤ እናንተን እንጂ፣ የእናንተ የሆነውን አልፈልግም። ወላጆች ለልጆች እንጂ ልጆች ለወላጆች ገንዘብ አያስቀምጡምና።
\v 15 እኔ እጅግ በጣምታልቅ በሆነ ደስታ ስለ ነፍሳችሁ እከፍላለው። እናንተን የበለጠ ብወዳችሁ፣ እኔ ከዚህ ያነሰ መወደድ አለብኝን?
\s5
\v 16 ልክ እንደዚህ፣ እኔ አልከበድሁባችሁም፤ነገር ግን በጣም በተንኮልና በጥበብ ያታለልኃችሁ መሰላችሁ።
\v 17 ወደ እናንተ በላክሁት በማንም ተጠቀምሁባችሁን?
\v 18 ወደ እናንተ እንዲመጣ ቲቶን የግድ አልኩት ፤ ከእርሱ ጋርም ሌላውን ወንድም ላክሁት። ቲቶስ ተጠቀመባችሁን? በአንድ መንገድ አልተጓዝንምን? በአንድ ፈለግስ አልተራመድንምን?
\s5
\v 19 በዚህ ጊዜ ሁሉ ለእናንተ ራሳችንን የምንከላከል ይመስላችኃልን? በእግዚአብሔር ፊት ስለእናንተ ድፍረት በክርስቶስ ብዙ ነገር እየተናገርን ነበር።
\s5
\v 20 ስመጣ እንደምፈልገው ሆናችሁ አላገኛችሁምብዬ እፈራለው። እናንተም እንደምትፈልጉት ሆኜ አታግኙኝም ብዬ እፈራለው ምናልባት ክርክር፣ ቅንዓት፣ የቁጣ መግንፈል፣ራስ ወዳድነት ያለበት ምⶉት፣ ሐሜት፣ ኩራትና ሁከት ይሆናሉ።
\v 21 ተመልሼ ስመጣ፣ አምላኬ በፊታችሁ ዝቅ እንዳያደርገኝ ብዬ እፈራለው ፣ከዚህ በፊትም ኃጢያ ስለሠሩት፣ እንዲሁም ስለ ፈጸሙት ርኩሰትና ዝሙት መዳራትም ስለ ብዙዎቻቸው አዝናለው ብዬ እፈራለው።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው። «ክስ ሁሉ በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች መጽናት አለበት።»
\v 2 ሁለተኛ ስመጣ በፊት ኃጢያት ለሰሩትና ለሌሎች ሁሉ ተናግሬአለው፥ አሁንም ደግሞ እላለው ተመልሼ ስመጣ እንዲሁ አላልፋቸውም።
\s5
\v 3 ክርስቶስ በእኔ በኩል እየተናገረ ስለ መሆኑ ማስረጃ ስለምትሹ ይህን እነግራችሏለው። ክርስቶስ ስለ እናንተ አይደክምም፥ ይልቁንም እርሱ በእናንተ ኃይለኛ ነው።
\v 4 እርሱ በድካም ተሰቅሏልና፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል ሕያው ነው። እኛ ደግሞ በእርሱ ደካሞች ነንና፤ ነገር ግን በመካከላችሁ ብለው የእግዚአብሔር ኀይል ሕያዋን ነን።
\s5
\v 5 በእምነት መሆናችሁን ለማየት ራሳችሁን መርምሩ። ራሳችሁን ፈትኑ። ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ እንደሚኖር አትገነዘቡምን? ተፈትናችሁ ካላለፋችሁ በቀር፣ እርሱ በእናንተ ይኖራል።
\v 6 እኛ ግን ተፈትነን ያለፍን መሆናችንን እንደምታውቁ እተማመናለው።
\s5
\v 7 እንግዲህ እናንተ ክፉ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፥ ይህንም የምናደርገው ፈተናውን ያለፍን መሰለን ለመታየት አይደለም፥ ነገር ግን ፈተናውን ያላለፍን ብንመስልም እንኳ፣ እናንተ ትክክል የሆነውን ታደርጉ ዘንድ እጸልያለው።
\v 8 ስለ እውነት እንጂ የእውነት ተቃራኒ የሆነ ነገር መሥራት አንችልምና።
\s5
\v 9 እኛ ደካሞች ሆነን እናንተ ብርቱዎች ስትሆኑ ደስ ይለናልና። እናንተ ፍጹማን እንድትሆኑ እንኛ ደግሞ እንጸልያለን።
\v 10 ከእናንተ ርቄ እያለው እነዚህን ነገሮች ጻፍሁላችሁ፤ ከእናንተ ጋር ሳለው እናንተ ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ ያይደለ ጌታ የሰጠኝ ሥልጣንን በመጠቀም እንዳላመናጭቃችሁ ንችው።
\s5
\v 11 በመጨረሻ፣ ወንድሞችና እኅቶች፣ ደስ ይበላችሁ! ለተሐድሶ ሥሩ፤ተበረታቱ፤እርስ በርሳችሁ ተስማሙ፤በሰላም ኑሩ፤ የፍቅርና የሰላም አምልክም ከእናንተ ጋር ይሆናል።
\v 12 በተቀደሰ አሳሳም ሰላም ተባባሉ።
\s5
\v 13 ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 14 የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ፍቅር፣የመንፈስ ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

294
49-GAL.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,294 @@
\id GAL
\ide UTF-8
\h ገላቲያ
\toc1 ገላቲያ
\toc2 ገላቲያ
\toc3 gal
\mt ገላቲያ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በሰው በኩል ወይም ከሰው ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞም እርሱን ከሞት ባስነሳው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆንኩት ጳውሎስ
\v 2 አብረውኝ ካሉ ወንድሞች ጋር በገላትያ ለምትገኙ አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ
\s5
\v 3 ከአባታችን ከእግዚአብሔር አብ ከጌታም ከኢየሱስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ
\v 4 ይሁን፣እርሱ እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከአሁኑ ክፉ ዘመን ያድነን ዘንድ እራሱን ስለ ኃጢአታችን ሰጥቶአልና
\v 5 ለእርሱ ከዘላለም እስከዘላለም ክብር ይሁን። አሜን!
\s5
\v 6 ወደሌላ ወንጌል በዚህ ፍጥነት በመዞራችሁ እጅግ ተገርሜአለሁ። በክርስቶስ ጸጋ ከተጠራችሁ ከእርሱ ፊታችሁን ማዞራችሁ አስገርሞኛል።
\v 7 ሌላ ወንጌል የለም፣ ነገር ግን የሚያውኩዋችሁና የክርስቶስን ወንጌል ሊያጣምሙ የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ።
\s5
\v 8 ነገር ግን እኛም ሆንን የሰማይ መልአክ አስቀድመን ከሰበክንላችሁ ሌላ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።
\v 9 አስቀድመን እንዳልን እንደገና እላለሁ «ማንም ከተቀበላችሁት ወንጌል የተለየ ወንጌል ቢሰብክላችሁ የተረገም ይሁን»
\v 10 ለመሆኑ እኔ የምጥረው ከሰው ወይስ ከእግዚአብሔር ይሁንታን ለማግኘት ነው? ጥረቴ ሰውን ለማስደሰት ነው? እስከአሁን ድረስ ሰውን ለማስደሰት እየጣርኩ ከሆነ እውነት እኔ የክርስቶስ አገልጋይ አይደለሁም።
\s5
\v 11 ወንድሞች ሆይ የሰብኩላችሁ ወንጌል ከሰው እንዳልሆን እንድታውቁ እፈልጋለሁ።
\v 12 ከጌታ ከኢየሱስ ከተሰጠኝ መገለጥ እንጂ ከሰው አልተቀበልኩትም ከሰውም አልተማርኩትም።
\s5
\v 13 የይሁዲ እምነት ተከታይ በነበርኩበት በቀድሞው ህይወቴ ወቅት እንዴት ቤተክርስቲያንን በአመፅ አሳድድና አጠፋ እንደነበረ ስለእኔ ሰምታችኋል።
\v 14 በይሁዲነት ከአብዛኛዎቹ አብረውኝ ከነበሩ አይሁዶች እየላቅሁ ነበር። ለአባቶቼም ወግ ከመጠን ያለፈ ቀናኢ ነበርኩ።
\s5
\v 15 ነገር ግን እግዚአብሔር ገና በማህጸን ሳለሁ ሊመርጥኝ ወደደ፣
\v 16 በአረማውያን መካከል አውጀው ዘንድ ልጁን በእኔ ለመግለፅ በጸጋው ጠራኝ። በጠራኝ ጊዜ ወዲያውኑ ከስጋና ከደም ጋር አልተማከርኩም
\v 17 ፣ከእኔ አስቀድመው ሃዋሪያት የሆኑት ወደሚገኙበት ወደ ኢየሩሳሌምም አልሄድኩም። ነገር ግን ወደ አረቢያ በኋላም ደግሞ ወደ መቄዶኒያ ተመለስኩ።
\s5
\v 18 ከዚያም ከሶስት አመት በኋላ ኬፋን ለመጠየቅ ወደኢየሩሳሌም ሄጄ ከእርሱ ጋር አስራአምስት ቀናት ቆየሁ።
\v 19 ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በስተቀር ሌሎች ሃዋሪያትን አላገኘሁም።
\v 20 በምፅፍላችሁ በእነዚህ ነገሮች በእግዚአብሔር ፊት እንዳልዋሸሁ እወቁ።
\s5
\v 21 ቀጥሎም ወደ ሶሪያና ኪልቂያ አውራጃዎች ሄድኩኝ።
\v 22 እስከዚያን ጊዜ ድረስ በይሁዳ ላሉት አብያተክርስቲያናት በአካል አልታወቅም ነበር፣
\v 23 ነገር ግን «ያ ቀድሞ ያሳድደን የነበረው ሰው አሁን ሊያጠፋው ሲጥር የነበረውን እምነት እየሰበከ ነው» የሚል ወሬ ብቻ ይሰሙ ነበር፣
\v 24 ስለ እኔም እግዚአብሔርንም ያከብሩ ነበር።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ከአስራ አራት ዓመት በኋላ ቲቶን ይዤ ከበርናባስ ጋር እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ሄድኩ።
\v 2 የሄድኩበትም ምክንያት መሄድ እንዳለብኝ እግዚአብሔር ስላመለከተኝ ነበር። ሄጄም በአህዛብ መካከል እየሰበኩት ስላለው ወንጌል ነገርኳቸው፣ ነገር ግን በከንቱ እንዳልሮጥኩ ወይም እየሮጥኩ እንዳልሆን እርግጠኛ ለመሆን ይህን የተናገርኩት በሌሎቹ ዘንድ እንደ ዋና ለሚታሰቡት ብቻ ነበር።
\s5
\v 3 ግሪካዊ የሆነው ሲላስ እንኳ እንዲገረዝ አልተገደደም።
\v 4 ይህ ጉዳይ የተንሳው በክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነት ለመሰለል ሾልከው በገቡ ውሸተኞች ወንድሞች ምክንያት ነበር።
\v 5 የህግ ባሪያዎች ሊያደርጉን ይመኙ ነበር። ነገር ግን ለእናንተ ወንጌሉ ሳይለወጥ ይቆይላችሁ ዘንድ ለአንድ ሰዓት እንኳ ለሀሳባቸው አልተገዛንም።
\s5
\v 6 ነገር ግን ሌሎች መሪዎች ናቸው ያልዋቸው ምንም አስተዋፅኦ አላደርጉልኝም። ማንም ይሁኑ ለእኔ ትርጉም አልነበረውም። ሆኖም ግን ልክ ጴጥሮስ ለተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተሰጠው ሁሉ
\v 7 እኔም ላልተገረዙት ወንጌልን ለማድረስ አደራ እንደተቀበልኩ አዩ፥
\v 8 ምክንያቱም ለተገረዙት ሃዋሪያ ይሆን ዘንድ በጴጥሮስ የሰራ እግዚአብሔር ላልተገረዙት ሃዋሪያ እሆን ዘንድ በእኔም ስለሚስራ ነው።
\s5
\v 9 እንደመሪዎች የሚታወቁት ያዕቆብ፥ኬፋና ዮሀንስ በእኔ ላይ ያለውን ፀጋ ባዩ ጊዜ እኛ ወደ አህዛብ እነርሱ ደግሞ ወደተገረዙት ይሄዱ ዘንድ የማህበራቸውም ተካፋዮች እንድንሆን ሙሉ መብት ሰጡን።
\v 10 እኔ ለማድረግ የምናፍቀውን ድሆችን እንድናስብም አሳሰቡን።
\s5
\v 11 ከዚያም ኬፋ ወደ አንፆኪያ በመጣ ጊዜ ሥራው ትክክል ስላልነበረ ፊት ለፊት ተቃወምኩት።
\v 12 ምክንያቱም ከያዕቆብ ዘንድ ሰዎች ከመምጣታቸው በፊት ኬፋ ከአህዛብ ጋር ይበላ ነበር። ሰዎቹ በመጡ ጊዜ ግን እነኚህን የተገረዙ ሰዎች ፈርቶ ከአህዛብ ጋር መብላቱን አቆመ እንዲያውም ተለያቸው።
\s5
\v 13 በርናባስ እንኳ በግብዝነታቸው እስኪሳብ ድረስ ሌሎቹም አይሁድ በኬፋ ግብዝነት ተካፋዮች ነበሩ።
\v 14 ወንጌልን በሚፃረር መንገድ መሄዳቸውን ባየሁ ጊዜ ኬፋን በሁሉም ፊት «አንተ አይሁዳዊ ሆንህ በአህዛብ ስርአት የምትኖር ከሆነ አህዛብ በአይሁድ ስርአት እንዲኖሩ ለምን ታስገድዳቸዋልህ?» አልኩት።
\s5
\v 15 እኛ«አህዛብ ኃጢአተኞች» ያልሆንን ነገር ግን በትውልድ አይሁዳዊ የሆንን በክርስቶስ ኢየሱስ ላይ ባለ እምነት እንጂ ማንም ህግን በመፈፀም እንደምይፀድቅ እናውቃለን።
\v 16 በህግ ሥራ ማንም ሊፀድቅ ስለማይችል በህግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነት እንፀድቅ ዘንድ ወደ ክርስቶስ ኢየሱስ እምነት ተጠርተናል።
\s5
\v 17 ነገር ግን እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲያፀድቀን እየፈለግን ሳለ ራሳችንን ኃጢአተኞች ሆነን እናገኛለን፥
\v 18 ታዲያ ክርስቶስ የኃጢአት አገልጋይ ሆነ ማለት ነው? በፍፁም አይደለም።
\v 19 ምክንያቱም አውልቄ የጣልኩትን ህግን የመፈፀም ትምክህት እንደገና ብገነባ ራሴን ህግ ተላላፊ ሆኜ አገኘዋለሁ። በህግ በኩል ለህግ ሞቼአለሁ።
\s5
\v 20 ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።
\v 21 የእግዚአብሔርን ፀጋ አላቃልልም፥ ህግን በመጠበቅ ፅድቅ የሚገኝ ቢሆን ኖሮ ክርስቶስ መሞቱ ከንቱ በሆነ ነበር።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 እናንተ ማስተዋል የጎደላችሁ የገላቲያ ሰዎች ማነው በክፉ ዓይኑ ያያችሁ፥ ክርስቶስ እንደተሰቀል ሆኖ በፊታችሁ ተስሎ አልነበረምን?
\v 2 ይህን ብቻ ከእናንተ ማወቅ እፈልጋለሁ። መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት በህግ ሥራ ነው ወይስ የሰማችሁትን በማመናችሁ?
\v 3 ይህን ያህል ሞኞች ናችሁ እንዴ፥ በመንፈስ ጀምራችሁ በሥጋ ትጨርሳላችሁ?
\s5
\v 4 በእርግጥ ይህ ከንቱ ከተባለ ያን ሁሉ መከራ የተቀብላችሁት በከንቱ ነውን?
\v 5 መንፈስ ቅዱስን የሰጣችሁና በመካከላችሁ ኃይለኛ ነገርን ያደረገው እርሱ ይህን ያደረገው በህግ ሥራ ነው ወይስ ከእምነት በሆነ እምነታችሁ ነው?
\s5
\v 6 ልክ አብርሀም «እንዳመነና እምነቱ እንደ ፅድቅ እንደተቆጠረለት»
\v 7 የሚያምኑ ሁሉ የአብርሀም ልጆች እንደሆኑ አስተውሉ።
\v 8 ቅዱሳት መፅሀፍት እግዚአብሔር አህዛብን እንደሚያፀድቅ አስቀድመው አመልክተዋል። ወንጌል «አህዛብ ሁሉ በአንተ ይባረካሉ» ተብሎ በመጀመሪያ ለአብርሀም ተሰብኳል።
\v 9 ስለዚህም የሚያምኑ እምነት ከነበረው ከአብርሀም ጋር የተባረኩ ናቸው።
\s5
\v 10 «ህግን ሁሉ ይፈፅም ዘንድ ለህግ የማይታዘዝ ሁሉ የተረገመ ነው» ተብሎ ተፅፎአልና በህግ ስራ የሚታመን ሁሉ በእርግማን ስር ነው።
\v 11 «ጻድቅ በእምነት ይኖራልና» እግዚአብሔር ማንንም በህግ እንደማያጸድቅ ግልጽ ነው።
\v 12 ህግ ከእምነት የመነጨ አይደለም፥ ይልቁኑም «በህግ ውስጥ ያሉትን እነዚያን ነገሮች የሚያደርግ በህግ ይኖራል»
\s5
\v 13 «በእንጨት ላይ የሚሰቀል የተረገመ ነው» ተብሎ በተጻፈው መሰረት እርሱ ስለኛ እርግማን በመሆን ከህግ እርግማን ዋጀን።
\v 14 የዚህ ተግባር ዓላማ የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ በእምነት እንቀበል ዘንድ በአብርሀም ላይ የነበረው በረከት በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በአህዛብም ላይ እንዲሆን ነው።
\s5
\v 15 የምናገረው በሰው ቋንቋ ነው። ልክ በሰዎች መካከል እንደተደረገ ውል ማንም ከዚህ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር አይችልም።
\v 16 እንግዲህ ተስፋዎቹ የተነገሩት ለአብርሀምና ለዘሩ ነው። ብዙ ሰዎችን እንደሚያመለክት «ለዘሮቹ» አላለም። ነገር ግን አንድ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ«ለዘሩ» ብሎ ይናገራል። ያም ለዘሩ የተባለለት ክርስቶስ ነው።
\s5
\v 17 እንግዲህ እንዲህ ልበል። አስቀድሞ በእግዚአብሔር የተረጋገጠው ቃል ኪዳን ተስፋ ከ430 ዓመት በኋላ በተሰጠ ህግ አልተሻረም።
\v 18 ምክንያቱም ውርሱ በህግ የመጣ ቢሆን ኖሮ በተስፋ በኩል ባልመጣ ነበር፥ ነገር ግን እግዚአብሔር ለአብርሃም በተስፋ አማካኝነት ርስትን እንዲያው ሰጠው።
\s5
\v 19 ታዲያ ህግ ለምን አስፈለገ? የአብርሃም ዘር ተስፋ ወደተሰጣቸው እስኪመጣ ድረስ በመተላለፍ ምክንያት ህግ ተሰጠ፤ ህጉ በመካከለኛ አማካኝነት በመላዕክት አማካኝነት ተግባራዊ ሆኗል።
\v 20 መካከለኛ ሲል ከአንድ ሰው በላይ እንደሆነ ያመለክታል፥ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው።
\s5
\v 21 ታዲያ ህግ የእግዚአብሔርን ተስፋ ይቃረናል ማለት ነው? በፍጹም አይደለም። ህይወትን ሊሰጥ የሚችል ህግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጠኝነት ጽድቅ በህግ በኩል ይመጣ ነበር።
\v 22 ነገር ግን ይልቁኑ መጽሀፍ ሁሉን ነገር ከኃጢአት በታች እስርኛ አድርጓል። ስለዚህም እኛን በክርስቶስ ኢየሱስ ለማዳን እግዚአብሔር የሰጠው ተስፋ ለሚያምኑ ተሰጠ።
\s5
\v 23 ነገር ግን በክርስቶስ ማመን ከመምጣቱ በፊት እምነት እስከተገለጠበት ጊዜ ድረስ በህግ ታስረንና ታግደን ነበር።
\v 24 ስለዚህ በእምነት እንድንጸድቅ ህግ ወደ ክርስቶስ ዘመን የሚያደርሰን ሞግዚት ሆነ።
\v 25 አሁን እምነት ስለመጣ ከዚህ በኋላ በሞግዚት ሥር አይደለንም።
\v 26 ምክንያቱም ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ።
\s5
\v 27 በክርስቶስ ስም የተጠምቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታል።
\v 28 ሁላችሁ በክርስቶስ አንድ ስለሆናችሁ በዚህ ጉዳይ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች፥ በባሪያና ነጻ በሆነ፥በሴትና በወንድ መካከል ልዩነት የለም።
\v 29 እንግዲህ የክርስቶስ ከሆናችሁ የአብርሀም ዘሮች እንደተስፋ ቃሉም ወራሾች ናችሁ።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ያን የምለው ህጻን ሳለ ምንም እንኳ ሁሉም የእርሱ ቢሆንም ወራሹ ከባሪያ አይለይም።
\v 2 ነገር ግን አባቱ የወሰነልት ቀን እስኪደርስለት ድረስ በተንከባካቢዎቹና በሞግዚቶቹ ስር ይቆያል።
\s5
\v 3 እኛም ልጆች ሳለን በዚህ ዓለም ዋና ትምህርቶች እስራት ሥር ነበርን።
\v 4 ነገር ግን በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር በህግ ሥር ያሉትን
\v 5 ነጻ እንዲያወጣና የልጅነትን መብት እንዲኖረን ከሴት የተወለደውንና በህግ ሥር የተወለደውን ልጁን ላከ።
\s5
\v 6 ልጆች ስለሆናችሁ «አባ አባት» እያለ የሚጣራውን የልጁን መንፈስ ወደ ልባችን ላከ።
\v 7 በዚህም ምክንያት ከእንግዲህ ልጆች እንጂ ባሮች አይደላችሁም፥ ልጆች ከሆናችሁ ደግሞ የእግዚአብሔር ወራሾች ናችሁ።
\s5
\v 8 ነገር ግን እግዘአብሔርን በማታውቁበት በቀድሞው ዘመን በባህሪያቸው ፈጽሞ አማልክት ላልሆኑት ተገዝታችሁ ኖራችሁ።
\v 9 አሁን ግን እግዚአብሔርን አውቃችኋል ይልቁኑም በእግዚአብሔር ታውቃችኋል፥ ታዲያ እንዴት ወደ ደካማና ዋጋ ወደሌለው የዚህ ዓለም ዋና ትምህርት ተመለሳችሁ።እንደገና ባሮች መሆን ትፈልጋላችሁ?
\s5
\v 10 ልዩ ቀናትን፥አዳዲስ ጨረቃዎችን፥ ወራትና ዓመታትን ታመልካላችሁ።
\v 11 ስለ እናንተ የደከምኩት ድካም ከንቱ ሆኖብኝ እንዳይሆን ብዬ እፈራለሁ።
\s5
\v 12 ወንድሞች ሆይ ልክ እኔ ለእናንተ እንደምሆነው እናንተም ለእኔ እንደዚያው እንድትሆኑ እለምናችኋለሁ።
\v 13 ምንም ክፉ አላደርጋችሁብኝም ነገር ግን ወንጌልን በመጀመሪያ በሰብኩላችሁ ጊዜ የሥጋ ህመም አሞኝ እንደነበረ ታውቃላችሁ።
\v 14 በሥጋዬ ላይ የነበረው ለእናንተ ከባድ ፈተና ቢሆንም አልተጸየፋችሁኝም አልጣላችሁኝምም፥ ይልቁኑ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ወይም ክርስቶስን በተቀበላችሁብት አቀባበል ተቀበላችሁኝ።
\s5
\v 15 አሁን ደስታችሁ በምንድነው? ዓይናችሁን እንኳ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ፈቃደኛ እንደነበራችሁ እኔ ራሴ ምስክር ነኝ።
\v 16 ታዲያ እውነትን ስለነገርኳችሁ የእናንተ ጠላት ሆንኩ ማለት ነው?
\s5
\v 17 አጥበቀው ይፈልጓችኋል ነገር ግን ለመልካም አይደለም። እነርሱን እንድትከተሉ ከእኔ ሊለዩዋችሁ ይፈልጋሉ።
\v 18 እኔ ከእናንተ ጋር ስሆን ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ ለመልካም ነገር መትጋት ተገቢ ነው።
\s5
\v 19 ጨቅላ ልጆቼ ሆይ ክርስቶስ በውስጣችሁ እስኪቀረጽ ድረስ ስለእናንተ ምጥ ይዞኛል!
\v 20 የእናንተ ነገር ግራ ስለገባኝ በመካከላችሁ ተገኝቼ በቁጣ ልናገራችሁ እመኛለሁ።
\s5
\v 21 እስኪ እናንተ በህግ ሥር ለመሆን የምትፈልጉ ንገሩኝ ህጉ ምን እንደሚል አልሰማችሁምን?
\v 22 አብርሃም አንድ ባሪያ ከነበረች ሴት አንድ ደግሞ ነጻ ከነበረች ሴት የተወለዱ ሁለት ልጆች እንደነበሩት ተጽፏል።
\v 23 ነገር ግን ከባሪያይቱ የተወለደው በሥጋ ብቻ የተወለደ ነው፥ ከነጻይቱ የተወለደው ግን በተስፋ የተወለደ ነው።
\s5
\v 24 እነዚህ ነገሮች እንደ ምሳሌ ሊገለጹ ይችላሉ።እነኚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ቃል ኪዳኖች ናቸው፥ አንደኛዋ በሲና ተራራ የተሰጠውንና ባርነትን የወለደውን ታመለክታለች፥ እርሷም አጋር ናት።
\v 25 እንግዲህ አጋር በአረቢያ ምድር የሚገኘው የሲና ተራራ ስትሆን ከልጆቿ ጋር በባርነት የምትኖረውን የአሁኗን ኢየሩሳሌምን ትወክላለች።
\s5
\v 26 ነገር ግን እናታችን የሆነችው ላይኛይቱ ጽዮን ነጻ ነች።
\v 27 ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል «አንቺ ያልወለድሽና መካን የሆንሽ ሴት ሀሴት አድርጊ፥አንቺ መውለድን ያልተለማምድሽ ውጪና በደስታ ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የመካኗ ልጆች በዝተዋልና»።
\s5
\v 28 እንግዲህ እናንተ ወንድሞቼ እንደ ይስሀቅ የተስፋ ልጆች ናችሁ።
\v 29 ነገር ግን እንደ ሥጋ ፈቃድ የተወለደው እንደ መንፈስ ፈቃድ የተወለደውን እንዳሳደደው አሁንም እየሆነ ያለው እንደዚያው ነው።
\s5
\v 30 መጽሀፍ ስለዚህ ነገር ምን ይላል«የባሪያይቱ ልጅ ከነጻይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱንና ልጇን አስወጣ»።
\v 31 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ እኛ የነጻይቱ እንጂ የባሪያይቱ ልጆች አይደለንም።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ክርስቶስ ነጻ ያወጣን በነጻነት እንድንኖር ነው ። ስለዚህ ጸንታችሁ ቁሙ፥ እንደገና በባርነት ቀንበር አትጠመዱ።
\v 2 እኔ ጳውሎስ የምለውን ተመልከቱ ብትገረዙ ክርስቶስ በምንም ዓይነት መልኩ አይጠቅማችሁም።
\s5
\v 3 የተገረዘ ሁሉ ህግን ሁሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት ብዬ እንደገና እመሰክራለሁ።
\v 4 በህግ ልትጸድቁ የምትደክሙ ሁላችሁ የእግዚአብሔር ጠላቶች ሆናችኋል፤ከጸጋም ርቃችኋል።
\s5
\v 5 ምክንያቱም እኛ በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት የጽድቅን ዋስትና ስለምንጠብቅ ነው።
\v 6 በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍቅር የሆነ እምነት እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም ትርጉም የለውም።
\v 7 በጥሩ ሁኔታ ትሮጡ ነበር። ታዲያ ለእውነት ከመታዘዝ ያስቆማችሁ ማነው?
\v 8 ይህን እንድታደርጉ የሚያደርግ ጉትጎታ ከጠራችሁ የመጣ አይደለም።
\s5
\v 9 ትንሽ እርሾ ሊጡን በሙሉ እንዲቦካ ያደርጋል።
\v 10 በሌላ መልኩ እንደማታስቡ በጌታ እተማመንባችኋለሁ። ግራ የሚያጋባችሁ ማንም ይሁን ማን ፍርዱን ይቀበላል።
\s5
\v 11 ወንድሞች ሆይ እስከአሁን ተገረዙ እያልኩ የምሰብክ ቢሆን ለምን እሰደድ ነበር? እንግዲያውስ የመስቀሉ እንቅፋት ይደመሰሳል።
\v 12 የሚያስቷችሁ እራሳቸው ሄደው በተሰለቡ ብዬ እመኛለሁ።
\s5
\v 13 ወንድሞች ሆይ እግዚአብሔር የጠራችሁ ለነጻነት ነው። ብቻ ነጻነታችሁን ለሥጋ ፈቃድ አትጠቀሙበት፥ በዚያ ፈንታ እርስ በእርሳችሁ በፍቅር አንዳችሁ አንዳችሁን አገልግሉ።
\v 14 ምክንያቱም ህግ ሁሉ «ባልንጀራህን እንደራስህ ልትወድ ይገባል»
\v 15 በሚለው ትዕዛዝ የተጠቀለለ ነው።
\s5
\v 16 በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋን ክፉ ምኞት አትፈጽሙ እላችኋለሁ።
\v 17 ምክንያቱም ሥጋ ከመንፈስ ተቃራኒ መንፈስም ከሥጋ ተቃራኒ ነገር ይመኛሉና ነው።
\v 18 እነዚህ እርስ በእርሳቸው ስለሚቀዋወሙ በውጤቱ እናንተ የምትፈልጉትን ለማድረግ አትችሉም።
\s5
\v 19 እንግዲህ የሥጋ ስራዎች የተገለጡ ናቸው። እነዚህም አስቀድሜ እንዳስጠነቀኩዋችሁ
\v 20 ዝሙት፣እርኩሰት፣ክፉ ምኞት፣ጣዖትን ማምለክ፣ምዋርት፣ጥል፣ክርክር፣ቅናት፣ በቁጣ መገንፈል፣አድመኛነት፣መለያየት፣
\v 21 መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ስካር፥ ዘፋኝነትና የመሳሰሉት ናቸው፥ ፥አስቀድሜ እንደነገርኳችሁ እነዚህን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።
\s5
\v 22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥
\v 23 የውሃት፥ ራስን መግዛት ናቸው። ህግ እነዚህን አይቃወም።
\v 24 የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ስሜቱና መሻቱ ጋር ሰቅለውታል።
\s5
\v 25 በመንፈስ የምንኖር ከሆነ በመንፈስ እንመላለስ።
\v 26 አንታበይ፣ እርስ በእርሳችን ለክፉ አንነሳሳ፣ አንቀናና።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ አንድ ሰው ስቶ ቢገኝ መንፈሳዊያን የሆናችሁ እናንት በጨዋነት መንፈስ ልታቀኑት ይገባል።ወደ ፈተና እንዳትገቡ ለራሳችሁም ተጠንቀቁ።
\v 2 የእርስ በእርሳችሁን ሸክም በመሸካከም የክርስቶስን ህግ ፈጽሙ።
\s5
\v 3 ምክንያቱም ማንም ምንም ሳይሆን ምንም እንደሆነ ቢያስብ ራሱን ያታልላል።
\v 4 እያንዳንዱ ከሌላው ጋር ሳያነጻጽር የራሱን ሥራ ሊመዝን ይገባል፥ያን ጊዜ የሚመካበት ሊያገኝ ይችላል።
\v 5 እያንዳንዱ የየራሱን ሸክም ይሸከማልና።
\s5
\v 6 ቃሉን የሚማር ከመምህሩ ጋር ሁሉን ነገር ይካፈል ዘንድ ይገባዋል።
\v 7 አትታለሉ እግዚአብሔር አይቀለድበትም።ሰው ምንም ነገር ቢዘራ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል።
\v 8 በሥጋው የሚዘራ ከሥጋው ውድቀትን ያጭዳል፤በመንፈስ የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ህይወት ያጭዳል።
\s5
\v 9 በተገቢው ጊዜ ፍሬውን እናጭዳለንና መልካምን ከመስራት አንቦዝን።
\v 10 ስለዚህም ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ለሰው ሁሉ በተለይም ለእምነት ቤተሰቦች መልካምን እናድርግ።
\s5
\v 11 በገዛ እጅ ጽህፈቴ ምን ዓይነት ትልልቅ ቃላት እንደጻፍኩላችሁ ተመልከቱ።
\v 12 እነዚያ በሥጋ መልካም መስለው የሚታዩ ስለክርስቶስ መስቀል መከራ ላለመቀበል ብለው እንድትገረዙ ያስገድዱዋችኋል።የተገረዙት እራሳቸው ህጉን አይጠብቁ፣
\v 13 ነገር ግን እናንተን እንድትገረዙ በማድረጋቸው ጉራ ለመንዛት እንድትገረዙ ይፈልጋሉ።
\s5
\v 14 ዓለም ለእኔ ከተሰቀለበት እኔም ለዓለም ከተሰቀልኩበት ከክርስቶስ መስቀል በስተቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ።
\v 15 አዲስ ፍጥረት መሆን እንጂ መገረዝም ሆነ አለመገረዝ ምንም አይጠቅምም።
\v 16 በዚህ ሥርዓት ለሚሄዱ ሁሉ እንዲሁም የእግዚአብሔር ለሆነችው ለእስራኤል ሠላምና ምህረት ይሁን።
\s5
\v 17 የክርስቶስን ምልክት በሥጋዬ ተሸክሜአለሁና ከእንግዲህ ማንም አይረብሸኝ።
\v 18 ወንድሞች ሆይ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁጋር ይሁን። አሜን!

302
50-EPH.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,302 @@
\id EPH
\ide UTF-8
\h ኤፌሶን
\toc1 ኤፌሶን
\toc2 ኤፌሶን
\toc3 eph
\mt ኤፌሶን
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፥ ለእግዚአብሔር ለተለዩት በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑ በኤፌሶን ለሚኖሩ ቅዱሳን፤
\v 2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 3 በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ።
\v 4 እግዚአብሔር በክርስቶስ የምናምነውን እኛን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት መርጦናል። ይህም በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እንሆን ዘንድ ነው
\s5
\v 5 እግዚአብሔር በፍቅር በኢየሱስ ክርስቶስ የራሱ ልጆች አድርጎ ሊቀበለን አስቀድሞ ወሰነን። ይህንንም የፈጸመው ሊያደርግ የፈለገውን ነገር ለማድረግ ደስ ስለተሰኘ ነበር።
\v 6 ይህ ሁሉ የተፈጸመው በሚወደው ልጁ እንዲያው በነጻ ስለ ተሰጠን ክቡር ጸጋው እግዚአብሔር ይመሰገን ዘንድ ነው።
\s5
\v 7 እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን በሚወደው ልጁ ደም ቤዛነትን ይኸውም የሐጢአት ይቅርታን አገኘን።
\v 8 ይህም ጸጋ በጥበብና በማስተዋል ሁሉ ተትረፍርፎ ተሰጠን።
\s5
\v 9 በክርስቶስ በተገለጠው ፈቃዱ መሠረት እግዚአብሔር በዕቅዱ ውስጥ ያለውን የተሰወረውን እውነት እንድናውቅ አድርጎናል፤
\v 10 ዕቅዱን የሚፈጽምበት ጊዜ ሲድርስ በሰማይና በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ በአንድ ላይ በክርስቶስ ስር ይጠቀልላል።
\s5
\v 11 ሁሉንም ነገር እንደ ገዛ ፈቃዱ በሚያደርገው ዕቅድ መሠረት በክርስቶስ ተመረጥን፤ አስቀድሞም ተወሰንን
\v 12 ይህም የሆነው በክርስቶስ በማመን ቀዳሚ የሆንነው እኛ ለክብሩ ምስጋና ይሆን ዘንድ እንድንኖር ነው።
\s5
\v 13 ባመናችሁበትና እንደ ተሰጠው ተስፋ በመንፈስ ቅዱስ በታተማችሁበት በክርስቶስ አማካይነት የመዳናችሁ ወንጌል የሆነውን የእውነት ቃል የሰማችሁት በክርስቶስ ነው
\v 14 ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን ተስፋ የተደረገው ሀብት በእጅ እስገሚገባ ድረስ መንፈስ ቅዱስ የርስታችን ዋስትና የሚሆን መያዣ ነው።
\s5
\v 15 ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለእርሱም ቅዱሳን ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ከሰማሁበት ጊዜ አንስቶ
\v 16 ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ማመስገንና እናንተንም በጸሎቴ ማስታወስ አላቋረጥሁም ።
\s5
\v 17 የክብር አባት፥የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን ለማወቅ የሚያስችላችሁን የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤
\v 18 የምጸልየውም የመጠራታችን አስተማማኝነት እና በእርሱ ቅዱሳን መካከል የርስቱ ክብር ባለጠግነት ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ
\s5
\v 19 እንዲሁም እንደ ኀይሉ ብርታት አሠራር በእኛ በምናምነው ውስጥ የሚሠራው የኀይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ እንድትረዱ ነው።
\v 20 ይህም እግዚአብሔር ከሙታን ባስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዲቀመጥ ባደረገው ጊዜ በክርስቶስ ውስጥ የታየው ኀይል ነው።
\v 21 ክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በአብ ቀኝ የተቀመጠውም ከማንኛውም ግዛት፥ ሥልጣን፥ኀይልና ጌትነት እንዲሁም በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚችለው ስም ሁሉ በላይ ነው።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር ሁሉም ነገር በክርስቶስ እግር ሥር እንዲገዛ አድርጓል፤ እርሱንም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሁሉም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾሞታል
\v 23 ቤተ ክርስቲያንም ሁሉንም ነገር በሁሉም መንገድ የሚሞላው የእርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 እንግዲህ እናንተ ከበደላችሁና ከሓጢአታችሁ የተነሳ የሞታችሁ ነበራችሁ።
\v 2 በዚያን ጊዜ የዚህን ዓለም ክፉ መንገድ በመከተል፥ በአየር ላይ ባሉት ኀይላት ላይ ገዥ ለሆነው እንዲሁም በማይታዘዙት ልጆች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር።
\v 3 በአንድ ወቅት እኛ ሁላችን ለሥጋችን ክፉ ምኞት እየታዘዝንና ፈቃዱን እየፈጸምን፥ የአእምሮአችንንም ሐሳብ እየተከተልን በእነዚህ በማያምኑት ሰዎች መካከል እንኖር ነበር፤ በተፈጥሮአችንም እንደሌሎቹ የቁጣ ልጆች ነበርን።
\s5
\v 4 ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት በማድረግ ባለጠጋ ስለሆነ፥ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ
\v 5 በበደላችን ሙታን በነበርንበት ጊዜ እንኳ ከክርስቶስ ጋር አዲስ ሕይወት ሰጠን፤የዳናችሁትም በጸጋ ነው፤
\v 6 ከእርሱም ጋር አስነሳን፤በሰማያዊ ስፍራም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር እንድንቀመጥ አደረገን።
\v 7 ይህንንም ያደረገው፥በክርስቶስ ኢየሱስ በቸርነቱ የገለጠውን የጸጋው ባለጠግነት ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ በሚመጣው ዘመን ለእኛ ያሳይ ዘንድ ነው።
\s5
\v 8 የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋ ነውና ፤ ይህ ከእግዚአብሔር ያገኛችሁት ስጦታ እንጂ ከእናንተ የሆነ ነገር አይደለም።
\v 9 ማንም ሰው እንዳይመካ በሥራ የተገኘ ነገር አይደለም
\v 10 ምክንያቱም እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት እንድንፈጽመው ያዘጋጀውን መልካም ሥራ ለመሥራት በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።
\s5
\v 11 ስለዚህ በአንድ ወቅት በአካል ላይ በሰው እጅ የሚከናወነውን መገረዝ ስላገኙ «የተገረዙ» በሚባሉት ዘንድ «ያልተገረዙ» ተብላችሁ የምትጠሩ በትውልድ አሕዛብ የነበራችሁ እንደሆነ አስታውሱ።
\v 12 በዚያን ጊዜ ከክርስቶስ ተለይታችሁ፥ የእስራኤል ወገን ከመሆን ርቃችሁ፥ለተስፋውም ኪዳን ባዕድ ሆናችሁ ያለ ተስፋ እና ያለ እግዚአብሔር በዓለም ላይ ትኖሩ እንደነበር ልብ በሉ።
\s5
\v 13 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁት በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆን በክርስቶስ ደም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር እንድትቀርቡ ተደርጋችኋል።
\v 14 አይሁድንና አሕዛብን ሁለቱን አንድ ሕዝብ ያደረገ እርሱ ሰላማችን ነውና ፤ በሥጋውም እርስ በርስ የለያየንን የጥል ግድግዳ አፈረሰ።
\v 15 ይኸውም ከሁለቱ ሕዝቦች አንድ አዲስ ሕዝብ በመፍጠር ሰላምን ያደርግ ዘንድ የትእዛዛትንና የሕግ ደንቦችን በሥጋው ሻረ።
\v 16 ይህንንም ያደረገው በመስቀሉ አማካይነት በመካከላቸው የነበረውን ጠላትነት ገድሎ ሁለቱን ሕዝቦች አንድ አካል በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ነው።
\s5
\v 17 ኢየሱስ መጥቶ ርቀው ለነበሩት እና ቀርበው ለነበሩት ለእነዚያ የምሥራቹን ወንጌል ሰበከ፤ ሰላሙንም አወጀ።
\v 18 በኢየሱስ አማካይነት እኛ ሁለታችንም በአንድ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና።
\s5
\v 19 ስለዚህ እናንተ አሕዛብ ከቅዱሳንና ከእግዚአብሔር ቤተ ሰብ አባላት ጋር የአንድ አገር ዜጎች ናችሁ እንጂ ከእንግዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም።
\v 20 እነዚህ በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ የተመሠረቱ ናቸው፤ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው።
\v 21 ቤተ ሰቡ የሆነው ሕንጻ ሁሉ በኢየሱስ ኀይል አንድ ላይ ተገጣጥሞ ለጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ለመሆን ያድጋል።
\v 22 እናንተም እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ሕንጻ እንድትሆኑ አብራችሁ በክርስቶስ እየታነጻችሁ ነው።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 በዚህ ምክንያት አሕዛብ ስለሆናችሁት ስለ እናንተ እኔ ጳውሎስ የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ሆኛለሁ።
\v 2 ለእናንተ ጥቅም ሲባል ስለ ተሰጠኝ የእግዚእብሔር ጸጋ መጋቢነት ሰምታችኋል ብዬ አስባለሁ።
\s5
\v 3 ቀደም ሲል እንደጻፍሁላችሁ እግዚአብሔር የተሰወረውን ምስጢር በመገለጥ እንዳውቅ አድርጓል።
\v 4 ይህን በምታነቡበት ጊዜ ስለ ክርስቶስ ምስጢር እኔ ያለኝን መረዳት መገንዘብ ትችላላችሁ።
\v 5 ምስጢሩም አሁን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለሓዋርያቱ እና ለነቢያቱ የተገለጠው ያህል ባለፉት ዘመናት ለነበሩ ሰዎች አልተገለጠም ነበር።
\s5
\v 6 ይህም ምስጢር አሕዛብ በወንጌል አማካይነት አብረው ወራሾች፥ አብረው የካሉ ብልቶች እንዲሁም በክርስቶስ በተገኘው ተስፋ አብረው ተካፋዮች መሆናቸው ነው።
\v 7 እንደ እርሱ ኀይል አሠራር በተሰጠኝ በእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ አገልጋይ ሆኛለሁ።
\s5
\v 8 ምንም እንኳ ከቅዱሳን ሁሉ ያነስሁ ብሆንም፥ የማይመረመረውን የክርስቶስ የባለጠግነት ወንጌል ለአሕዛብ እሰብክ ዘንድ ይህ ጸጋ ለእኔ ተሰጠኝ።
\v 9 እንዲሁም የሁሉን ነገር ፈጣሪ በሆነው በእግዚአብሔር ላለፉት ዘመናት ተሰውሮ ስለነበረው ምስጢር የእግዚአብሔር ዕቅድ ምን እንደሆነ ለሁሉም እገልጥ ዘንድ ተሰጠኝ።
\s5
\v 10 በዚህም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ብዙ ገጽታ ያለው የእግዚአብሔር ጥበብ በሰማያዊ ስፍራ ላሉት አለቆችና ባለ ሥልጣናት እንዲታወቅ ነው።
\v 11 ይህም የሆነው በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ በፈጸመው ዘላለማዊ ዕቅዱ መሠረት ነው።
\s5
\v 12 በክርስቶስ በማመናችን በእርሱ ሆነን በድፍረትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለንና።
\v 13 ስለዚህ ክብራችሁ በሆነው ለእናንተ ስል በምቀበለው መከራ ተስፋ እንዳትቆርጡ እለምናችኋለሁ።
\s5
\v 14 በዚህም ምክንያት በአብ ፊት እንበረከካለሁ፤
\v 15 እርሱም በሰማይና በምድር ላለ ቤተ ሰብ ሁሉ ስያሜ የሰጠ እና እነርሱንም የፈጠረ ነው።
\v 16 የምጸልየውም ትጠነክሩ ዘንድ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት እንደ ክብሩ ባለጠግነት መጠን ኀይል እንዲሰጣችሁ ነው።
\s5
\v 17 ይህም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲኖር፥ በፍቅሩ ሥር እንድትሰዱና እንድትታነጹ ነው፤
\v 18 ደግሞም የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱ፥ርዝመቱ፥ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር መረዳት ትችሉ ዘንድ ነው።
\v 19 እንዲሁም በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ ፥ ከሰው ዕውቀት ሁሉ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ታላቅ ፍቅር እንድታውቁ ነው።
\s5
\v 20 እንግዲህ በእኛ ውስጥ እንደሚሠራው ሀይሉ መጠን ሁሉንም ነገር እኛ ከምንለምነው ወይም ከምናስበው በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው
\v 21 በቤተ ክርስቲያንና በክርስቶስ ኢየሱስ በትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን፤አሜን።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ስለዚህ የጌታ እስረኛ እንደመሆኔ በእግዚአብሔር ለተጠራችሁለት መጠራት የሚገባውን ሕይወት ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ።
\v 2 ይኽውም እርስ በርስ በፍቅር ተቻችላችሁ በፍጹም ትሕትና፥በገርነትና በትዕግሥት እንድትኖሩ ነው።
\v 3 በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥረት ሁሉ አድርጉ።
\s5
\v 4 በተጠራችሁ ጊዜ በአንድ ተስፋ እንደተጠራችሁ ሁሉ፥ አንድ አካል እና አንድ መንፈስ አለ፤
\v 5 አንድ ጌታ፥አንድ እምነት፥አንድ ጥምቀት አለ ፤
\v 6 ደግሞም ከሁሉ በላይ የሆነ፥በሁሉ የሚሠራ፥ በሁሉ የሚኖር ፥የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ አለ።
\s5
\v 7 ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጥቶናል
\v 8 ይህም የእግዚአብሔር ቃል «ወደ ላይ በወጣ ጊዜ ምርኮኞችን ማረከ፤ለሰዎችም ስጦታ ሰጠ» በማለት እንደሚናገረው ነው።
\s5
\v 9 «ወደ ላይ ወጣ» ሲል ደግሞም «ወደ ምድር ጥልቅ ወረደ» ማለት ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ሊያመለክት ይችላል?
\v 10 ታች የወረደው ሁሉንም ይሞላ ዘንድ ከሰማያት ሁሉ በላይ የወጣው ያው እርሱ ራሱ ነው።
\s5
\v 11 ወንጌል ሰባኪዎችን፥እረኞችን እና አስተማሪዎችን ስጦታ አድርጎ የሰጠ ክርስቶስ ራሱ ነው።
\v 12 ያደረገው የክርስቶስን አካል ለማነጽና ለአገልግሎት ሥራ ቅዱሳንን ለማስታጠቅ ነው።
\v 13 የሚሆነው ሁላችንም የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እና በማወቅ ወደ ሚገኘው አንድነት እንዲሁም ወደ ክርስቶስ ሙላት ልክ እንዳደጉት ሰዎች ሙሉ ሰው ወደ መሆን ደረጃ እስከምንደርስ ድረስ ነው።
\s5
\v 14 በሰዎች ረቂቅ ተንኮል እና ማታለል በተዘጋጀ የትምህርት ነፋስ ወዲያና ወዲህ የምንነዳ ሕጻናት መሆን አይገባንም
\v 15 ይልቁንም እውነትን በፍቅር የምንናገር እና ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ በሁሉም መንገድ የምናድግ ሰዎች መሆን ይጠበቅብናል።
\v 16 የአማኞችን አካል ሁሉ በሚያገናኘው ጅማት እየተያያዘና እየተጋጠመ፥እያንዳንዱም ክፍል የራሱን ተግባር እያከናወነ በፍቅር ያድጋል።
\s5
\v 17 እየለመንኋችሁ ይህን የምናገረው፥ ከእንግዲህ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱት እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ነው።
\v 18 እነርሱም አእምሮአቸው ጨልሞአል፤ካለማወቃቸውና ከልባቸው ደንዳናነት የተነሳ ከእግዚአብሔር ሕይወት ርቀዋል፤
\v 19 ስግብግብነት ሁሉ ለሞላበት ቅጥ ላጣ ብልግና ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል።
\s5
\v 20 ግን ስለ ክርስቶስ የተማራችሁት እንደዚህ አይደለም።
\v 21 እርሱ የሰማችሁ እና የተማራችሁ ከሆነም በርግጥ የተማራችሁት ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት ነው።
\v 22 ክፉ ምኞት የጎደፈውን አስቀድሞ ትኖሩበት የነበረውን አሮጌውን ሰው ልታስወግዱ ይገባል።
\s5
\v 23 በአእምሮአችሁ መንፈስ እንድትታደሱ
\v 24 እውነተኛ በሆነው ጽድቅና ቅድስና በእግዚአብሔር የተፈጠረውን አዲሱን ሰው እንድትለብሱ ነው።
\s5
\v 25 ውሸትን አስወግዱ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ስለሆንን «እያንዳንዱ ከባልንጀራው ጋር እውነትን ይነጋገር»።
\v 26 «ተቆጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ» በቁጣችሁ ጸሓይ እስከሚገባ ድረስ አትቆዩ፤
\v 27 ዕድል አትስጡት።
\s5
\v 28 የነበረ ከእንግዲህ አይስረቅ፤ይልቁንም ለተቸገሩ ሰዎች ማካፈል ይችል ዘንድ በራሱ እጅ በተገቢው ሁኔታ እየሠራ ለማግኘት ጥረት ማድረግ ይገባዋል።
\v 29 ለማነጽ የሚያስፈልግ፥ ለሚሰሙትም ጸጋን የሚሰጥ ጠቃሚ ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።
\v 30 ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።
\s5
\v 31 ሁሉ፥ቁጣንና ንዴትን፥ጭቅጭቅንና ስድብን ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ጋር ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ።
\v 32 በርሳችሁ ቸሮች፥ ርኅሩሆች ሁኑ፤ ደግሞም እግዚአብሔር በክርስቶስ እንዲሁ ይቅር እንዳላችሁ እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 እንግዲህ እንደ ተወደዱ የእርሱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትመስሉ ሁኑ፤
\v 2 እንደ ወደደን፥ ራሱንም ስለ እኛ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር እንዳቀረበ ሁሉ እናንተም በፍቅር ኑሩ።
\s5
\v 3 የሚገባ ባለመሆኑ ዝሙት፥ማንኛውም ርኩሰትና ስስት በእናንተ ዘንድ ሊኖር አይገባም፤
\v 4 ጸያፍ ንግግር፥ዋዛ ወይም ውርደትን የሚያስከትል ቀልድ ለእናንተ ስለማይገባ ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ከዚህ ይልቅ የምታመሰግኑ ሁኑ።
\s5
\v 5 አመንዝራ፥ርኩስ፥ ስግብግብ የሆነ ይኽውም ጣዖት አምላኪ ሰው በክርስቶስና በእግዚአብሔር መንግሥት ርስት እንደማይኖረው ርግጠኛ ልትሆኑ ይገባል።
\v 6 ከንቱ በሆነ ንግግር ማንም አያታላችሁ፤በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ ይመጣል
\v 7 ስለዚህ የእነርሱ ተባባሪዎች አትሁኑ።
\s5
\v 8 ወቅት ጨለማ ነበራችሁና፤ አሁን ግን በክርስቶስ ብርሃን ናችሁ። ስለዚህ እንደ ብርሃን ልጆች ኑሩ።
\v 9 ምክንያቱም ከብርሃኑ የሚገኘው ፍሬ መልካም ነገር ሁሉ፥ ጽድቅና እውነት ነው
\v 10 እንዲሁም ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር ለማድረግ አስቡ፤
\v 11 ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፤ይልቁን ልትገልጡት ይገባል።
\v 12 በስውር ያደረጉትን ነገር ለመግለጽ እንኳ አሳፋሪ ነውና።
\s5
\v 13 በሚኖርበት ጊዜ ማንኛውም ነገር በግልጽ ይታያል።
\v 14 ብርሃኑ በላዩ ላይ ስለሚያበራ ነው። ስለዚህ፥ «አንተ የምትተኛ ንቃ፤ከሙታን ተነሳ፤ክርስቶስም ያበራልሃል» ተብሎ ተነግሯል።
\s5
\v 15 ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን፥እንደ ጥበብኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ።
\v 16 ክፉዎች ስለሆኑ ዘመኑን ዋጁ።
\v 17 ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።
\s5
\v 18 ሕይወታችሁን ለጥፋት ስለሚዳርግ፥በወይን ጠጅ አትስከሩ፤ይልቁንስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ።
\v 19 እርስ በርሳችሁ በመዝሙር፥በቅኔና በመንፈሳዊ ዝማሬ ተነጋገሩ፤ ጌታንም በልባችሁ አመስግኑ፤ለእርሱም ተቀኙ።
\v 20 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉም ነገር ሁልጊዜ እግዚአብሔር አብን አመስግኑ
\v 21 ክርስቶስን ለማክበር ስትሉ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተገዙ።
\s5
\v 22 ሚስቶች ሆይ! ለጌታ እንደምትገዙ ለባሎቻችሁ ተገዙ።
\v 23 ክርስቶስ አካሉ ለሆነችውና አዳኟ ለሆናት ቤተ ክርስቲያን ራስ እንደ ሆነ ሁሉ ባልም የሚስቱ ራስ ነውና።
\v 24 ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ ሁሉ ሚስቶችም በማንኛውም ነገር ለባሎቻቸው ሊገዙ ይገባል።
\s5
\v 25 ባሎች ሆይ፤ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ስለ እርስዋም ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ፥ እናንተም ሚስቶቻችሁን ውደዱ።
\v 26 ይህንንም ያደረገው በቃሉ አማካይነት በውሃ አጥቦ በማንጻት እንድትቀደስ፥
\v 27 ጉድፍ ወይም የፊት መጨማደድ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ሳይታይባት ቅድስት የሆነችና ነውር የሌለባት ክብርት ቤተ ክርስቲያን አድርጎ ለራሱ ሊያቀርባት ነው።
\s5
\v 28 ባሎች የገዛ ሥጋቸውን እንደሚወዱ ሚስቶቻቸውን መውደድ ይገባቸዋል። ሚስቱን የሚወድ ራሱን ይወዳል።
\v 29 የራሱን ሥጋ የሚጠላ ማንም የለም፤ ይልቁን ይመግበዋል፤ ይንከባከበዋልም። ይህም ክርስቶስ ልክ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚወድ ነው።
\v 30 እኛ የእርሱ ብልቶች ነን።
\s5
\v 31 ምክንያት ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል፤ከሚስቱም ጋር አንድ ይሆናል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
\v 32 ታላቅ ምስጢር ነው፤ እኔም ይህን የምናገረው ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያኑ ነው።
\v 33 ግን ከእናንተ እያንዳንዱ ደግሞ ሚስቱን እንደ ራሱ አድርጎ መውደድ ይገባዋል፤ ሚስትም ባልዋን ታክብር።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ልጆች ሆይ፤ በጌታ ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤ ይህ ተገቢ ነውና።
\v 2 «አባትህንና እናትህን አክብር» በሚለው የመጀመሪያ ትእዛዝ ውስጥ ያለው ተስፋ
\v 3 እንዲሆንልህ፥ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም» የሚል ነው።
\s5
\v 4 እናንተም አባቶች ሆይ፤ ልጆቻችሁን አታስቆጡአቸው፤ ይልቁንስ በጌታ ሥርዓትና ምክር አሳድጓቸው።
\s5
\v 5 ባሮች ሆይ፤ ለክርስቶስ እንደምትታዘዙት ለምድራዊ ጌቶቻችሁም በታላቅ አክብሮት፥ በመንቀጥቀጥና በልባችሁ ቅንነት ታዘዙ፤
\v 6 ለታይታ እነርሱን ደስ ለማሰኘት ብላችሁ ሳይሆን፥ እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ከልብ በመፈጸም ታዘዙአቸው።
\v 7 ሰውን ሳይሆን ጌታን እንደምታገለግሉ እያሰባችሁ በደስታ አገልግሉ።
\v 8 ባሪያም ይሁን ነጻ ሰው እያንዳንዱ ሰው ለሚያደርገው መልካም ነገር ከጌታ ሽልማት እንደሚቀበል ልብ በሉ።
\s5
\v 9 እናንተም ጌቶች ሆይ፤ ለባሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ የእነርሱና የእናንተም ጌታ የሆነው እርሱ በሰማይ እንዳለና ለሰው ፊትም እንደማያዳላ ተረድታችሁ አታስፈራሯቸው።
\s5
\v 10 በጌታና ብርቱ በሆነው ኀይሉ የበረታችሁ ሁኑ።
\v 11 የዲያብሎስን ተንኮል አዘል ዕቅድ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ።
\s5
\v 12 ውጊያችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከአለቆች፥ ከሥልጣናት፥ ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦችና በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ርኩሳን መናፍስት ጋር ነው።
\v 13 በክፉ ቀን ክፉውን በመቃወም ጸንታችሁ ትቆሙ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ፤ ጸንታችሁ ለመቆምም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።
\s5
\v 14 ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ ታጥቃችሁ፥የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ ጸንታችሁ ቁሙ፤
\v 15 የሰላምን ወንጌል ለማወጅ እግሮቻችሁ በዚያ ተጫምተው ዝግጁ ይሁኑ
\v 16 የሚንበለበሉትን የክፉውን ፍላጻዎች ማጥፋት ትችሉ ዘንድ ሁል ጊዜ የእምነትን ጋሻ አንሱ።
\s5
\v 17 የመዳንን ራስ ቁር አድርጉ፤የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ፤ይህም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
\v 18 ዓይነት ጸሎትና ልመና ሁልጊዜ በመንፈስ በመጸለይና መልሱን ከእርሱ በመጠበቅ፥ ለቅዱሳንም ልመና በማቅረብ ትጉ።
\s5
\v 19 ምስጢር በድፍረት ለመናገር አፌን በምከፍትበት ጊዜ ሁሉ ቃል ይሰጠኝ ዘንድ ለእኔም ጸልዩልኝ።
\v 20 መናገር እንደሚገባኝ በድፍረት እናገር ዘንድ በሰንሰለት የታሰረ መልእክተኛ የሆንሁት ለዚሁ ነውና።
\s5
\v 21 ሁኔታ እንዳለሁና ምን እያደረግሁ እንደምገኝ፥ የተወደደ ወንድምና በጌታ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ቲኪቆስ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል።
\v 22 ያለንበትን ሁኔታ እንድታውቁና እናንተንም እንዲያበረታታ በማለት ወደ እናንተ ልኬዋለሁ።
\s5
\v 23 ከአብ፥ ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር ከእምነት ጋር ለወንድሞች ይሁን።
\v 24 ኢየሱስ ክርስቶስን በማይጠፋ ፍቅር ከሚወዱ ጋር ሁሉ ጸጋ ይሁን።

197
51-PHP.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,197 @@
\id PHP
\ide UTF-8
\h ፊልጵስዩስ
\toc1 ፊልጵስዩስ
\toc2 ፊልጵስዩስ
\toc3 php
\mt ፊልጵስዩስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቲዎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ቅዱሳን ለሆኑ በፊልጵስዩስ ከተማ ከእረኞችና ከዲያቆናት ጋር ለሚኖሩ ሁሉ።
\v 2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ስላም ለአናንተ ይሁን።
\s5
\v 3 ስለእናንተ በማስብበት ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 4 ስለ ሁላችሁም በምጸልይበት ጊዜ ሁሉ በደስታ እጸልያለሁ።
\v 5 ከመጀመሪያ ጀምሮ እስካሁን ወንጌል በሚሰበክበት ሥራ ስላሳያችሁት ትብብራችሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 6 ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።
\s5
\v 7 እናንተ በልቤ ስላላችሁ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰብ ይኖርብኛል። በእስራቴና ስለ ወንጌል በመቆሜ ስለእርሱም በመመስከሬ ሁላችሁም በጸጋ ተባባሪዎች ሆናችኋል።
\v 8 በኢየሱስ ክርስቶስ ባለኝ ጥልቅ ፍቅር ሁላችሁንም እንድምናፍቃችሁ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው።
\s5
\v 9 ፍቅራችሁ በዕውቀትና በሙሉ መረዳት የበለጠ እንዲበዘላችሁ እጸልያለሁ።
\v 10 ይህን የምጸልይበት ምክንያት የተሻለውን ነገሮችን መርምራችሁ እንድታውቁ እንዲሁም ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ቀን ንጹኃንና ነውር የሌለባችሁ ሆናችሁ እንድትገኙ ነው።
\v 11 ይህ ደግሞ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሚገኘው የጽድቅ ፍሬ ተሞልታችሁ ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና እንዲሆን ነው።
\s5
\v 12 ወንድሞች ሆይ፥በእኔ ላይ የደረሰው ሁሉ ወንጌል በጣም እንዲስፋፋ እንዳደረገ እንድታውቁ እወዳለሁ።
\v 13 እኔም የታሰሁት በክርስቶስ ምክንያት መሆኑን የቤተ መንግሥት ጠበቂዎችና ሌሎችም እዚያ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ ሆኖአል።
\v 14 በእኔ መታሰር ምክንያት በጌታ ወንድሞች ከሆኑት ብዙዎቹ የበለጠ ከቀድሞ ይልቅ የእግዚአብሔርን ቃል ያለ ፍርሃት ለመናገር ድፍረት አግኝተዋል።
\s5
\v 15 በርግጥ አንዳንዶቹ የክርስቶስን ወንጌል የሚሰብኩት በቅናትና በፉክክር መንፈስ ነው፤ሌሎቹ ግን ክርስቶስን የሚሰብኩት በቅን ልቡና ነው።
\v 16 እነዚህ የእግዚአብሔርን ቃል በቅን ልቡና የሚሰብኩት ከፍቅር የተነሳ ነው፤እነርሱም እኔ ስለወንጌል ቆሜ በመከራከርይ መታሰሬን ያውቃሉ።
\v 17 እነዚያ ግን ስለ ክርስቶስ የሚሰብኩት በራስ ወዳድነትና ቅንነት በሌለበት አስተሳሰብ ነው። በእስራቴም ላይ ተጨማሪ መከራ ሊያመጡብኝ አስበው ነው።
\s5
\v 18 ታዲያ ምን ይደረግ? በርግጥ በዚህ ደስ ይለኛል፤በማስመሰል ወይም በእውነት በሁሉም መንገድ ክርስቶስ ይሰበካል።
\v 19 ምክንያቱም በእናንተ ጸሎትና በኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ርዳታ ነጻ እንደምወጣ አውቃለሁ።
\s5
\v 20 እንደማላፍርበት በሙሉ መተማመ እጠባበቃለሁ። ነገር ግን ዘወትር እንደማደርገውና በተለይም ዛሬም በሕይወት ብኖር ወይም ብሞት ክርስቶስ በሰውነቴ ይከብራል ብዬ በድፍረት እናገራለሁ።
\v 21 ስለዚህ ለእኔ ሕይወት ማለት በክርስቶስ መኖር ነው፤ ሞትም ማለት ማትፍረፍ ነው።
\s5
\v 22 ነገር ግን በሥጋ መኖር ለእኔ የሥራ ፍሬ ቢሆን የትኛውን እንደምመርጥ አላውቅም።
\v 23 ምክንያቱም በእነዚህ በሁለቱ አሳቦች መካከል ተወጥሬአለሁ። በአንድ በኩል ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለሆነ ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆንን እፈልጋለሁ።
\v 24 ሆኖም በሥጋ መኖሬ ለእናንተ የበለጠ አስፈላጊ ነው።
\s5
\v 25 እምነታችሁ እንዲያድግና ደስታን እንድታገኙ እንደምቆይና ከሁላችሁም ጋር እንደምቀጥል ስለዚህ ነገር እተማመናሉ።
\v 26 በዚህ ምክንያት እኔም እንደገና ወደ እናንተ ስመጣት ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ በእኔ ትመካላችሁ።
\v 27 እንግዲህ ከሁሉም በላይ ሕይወታችሁ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ይሁን፤ ይህም እኔ መጥቼ ባያችሁ ወይም ከእናንተ ብርቅ በአንድ መንፈስ ጸንታችሁ መቆማችሁንና ለወንጌልም እምነት በኅብረት መጋደላችሁን እሰማ ዘንድ ነው።
\s5
\v 28 ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን፤ ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳናችሁ ምልክት ነው።
\v 29 ምክንያቱም ከክርስቶስ የተነሳ ይህ የተሰጣችሁ አገልግሎት በእርሱ እንድታምኑ ብቻ ሳይሆን በእርሱ ምክንያት መከራ እንድትቅበሉም ጭምር ነው።
\v 30 ስለዚህ አሁን ከእኔ ጋር የመከራ ተካፋዮች ሆናችኋል፤ ይህም መከራ ከዚህ በፊት ደርሶብኝ ያያችሁትና አሁንም እየደረሰብኝ መሆኑን የሰማችሁት ነው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 በክርስቶስ መበረታታት ካላችሁ፤ከፍቅሩም መጽናናት ካላችሁ፤የመንፈስም ኅብረት ካላችሁ፤እርስ በእርሳችሁም ደግነትና ርኅራኄ ካላችሁ።
\v 2 ስለዚህ በአንድ አሳብ፤ በፍቅር፤ በመንፈስ አንድነት፤በአንድ ዓላማ እየተስማማችሁ ደስታዬ እንዲፈጸም አድርጉት።
\s5
\v 3 በራስ ወዳድነት ወይም በከንቱ ትምክህት ምንም አታድርጉ፤ነገር ግን በዚህ ፈንታ ሌሎች ሰዎች ከእናንተ እንደሚሻሉ በትህትና ቁጠሩ።
\v 4 እንዲሁም እያንዳንዳእሁ የራሳችሁን ጥቅም ብቻ ሳይሆን የሌላውንም ሰው ጥቅም አስቡ።
\s5
\v 5 በኢየሱስ ክርስቶስ የነበረ አሳብ በእናንተም ደግሞ ይኑር፤
\v 6 እርሱም የመለኮት ባሕር ነበረው፥ ነገር ግን ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሚያደርጋውን የመለኮት ባሕይ እንደ ያዘ አልቆጠረም። ክብሩን ትቶ ራሱን ባዶ አደረገ።
\v 7 የባሪያንም መልክ ያዘ፤ በሰው አምሳል ተገለጠ፤ እንደ ሰውም ሆኖ በትህትና ራሱን ዝቅ አደረገ።
\v 8 እንዲሁም እስከ ሞት፤ያውም እስከ መስቀል ሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
\s5
\v 9 ስለዚህም እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አደረገው፤ ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ሰጠው።
\v 10 በዚህም ምክንያት ጉልበት ሁሉ በሰማይና በምድር፤ ከምድርም በታች ሁሉ በኢየሱስ እግሮች በታች እንዲንበረከኩ ነው።
\v 11 አንደበትም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር እንዲሆን፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው ብሎ እንዲመሰክር ነው።
\s5
\v 12 ስለዚህ ወዳጆቼ ሆይ፤ እኔ ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ሁሉ እንደምትታዘዙ፥ይልቁንም አሁን ከእናንተ በራቅሁበት ጊዜ ይበልጥ ታዛዦች እንድትሆኑ ነው።
\v 13 በፍርሃትና በመንቀጥቅቀጥም መዳናችሁን ሥሩ። ምክንያቱም ለመልካምነቱ መፍቃዱንና ማድረግን በእናንተ የሚሠራ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 14 ማናቸውንም ነገር ሳታጉረምግሙና ሳትከራከሩ አድርጉ።
\v 15 ይህን በማድረግ ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ታማኝ የአግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ። በዚህ በጠማናና በመጥፎ ትውልድ መካከል በዚህ ዓለም እንደ ደማቅ ብርሃን ታበራላችሁ።
\v 16 ሕይወት የሚገኝበትን ቃል አጥብቃችሁ በምትይዙበት ጊዜ በከንቱ እንዳልሮጥሁና በከንቱም እንዳልደከምሁ ክርስቶስ በሚመለስበት ቀን ለማክበር ምክንያት ሊኖረኝ ይችላል።
\s5
\v 17 ነገር ግን ለእግዚአብሔር በእምነት በምታቀርቡት መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ የእኔም ሕይወት እንደ መሥዋዕት ሆኖ ቢቀርብ እንኳ ደስ ይለኛል። ከሁላችሁ ጋር ታላቅ ደስታ እደሰታለሁ።
\v 18 እንዲሁም በተመሳሳይ ሁኔታ እናንተም ከእኔ ጋር ደስተኞች ትሆናላችሁ።
\s5
\v 19 ነገር ግን እናንተ እንዴት እየሠራችሁ እንዳላችሁ ሰምቼ እንድጽናና ጢሞቲዎስን ወደ እናንተ ፈጥኜ እንደምልክ በጌታ በኢየሱስ ተስፋ አደርጋለሁ።
\v 20 ስለ እናንተ ሁኔታ ከልብ የሚያስብ ከጢሞቲዎስ በስተቀር ሌላ ሰው የለኝም።
\v 21 ሌሎቹ ግን የራሳቸውን ጥቅም ብቻ ስለሚፈልጉ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ግድ የላቸውም።
\s5
\v 22 ነገር ግን ጢሞቲዎስ ልጅ አባቱን እንደሚያገለግል ከእኔ ጋር ወንጌልን በማሠራጨት እንዳገለገለና ስለታማኝነቱም የተመሰከረለት መሆኑን እናንተም ታውቃላችሁ።
\v 23 ስለዚህ የእኔን ሁኔታ እንዳወቅሁ በፍጥነት ጢሞቲዎስን ወደ እናንተ እንደምልክላችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
\v 24 እንዲያውም እኔ ራሴ በቶሎ ወደ እናንተ እንደምመምጣት በጌታ እተማመናለሁ።
\s5
\v 25 ነገር ግን ኤጳፍሮዲቱስን መልሼ ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እርሱ እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜና ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ባልደረባዬ ነው።
\v 26 እርሱን ወደ እናንተ የምልከውም ሁላችሁንም ለማየት በመናፈቁና እናንተም መታመሙን በመስማታችሁ ስለ ተጨነቀ ነው። በእርግጥ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት አደረገለት።
\v 27 ከሕመሙ መዳኑ ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ሐዘን በሐዘን ላይ እንዳይደረርብኝ ለእኔም ጭምር ነው።
\s5
\v 28 ስለዚህ እናንተ እርሱን በማየት እንድትደሰቱና የእኔም ሐዘን እንዲቃለል እርሱን ወደ እናንተ ለመላክ ከፍተኛ ፍላጎት አድሮብኛል።
\v 29 እንግዲህ ኤጳፍሮዲቱስን በሙሉ ደስታ በጌታ ተቀበሉት። እንደ እርሱ ያሉትን ሰዎች አክብሩአቸው ።
\v 30 በቅርብ ተገኝታችሁ ልታደርጉልኝ ያልቻላችሁትን በእናንተ ቦታ ሆኖ ሲያገለግለኝና የሚያስፈልገኝን ለማሟላት ስለ ክርስቶስ ሥራ በማለት ለሕይወቱ ሳይሳሳ በማድረግ ለሞት ተቃርቦ ነበር።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 በጨረሻም ወንድሞቼ ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ። ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁን ተመሳሳይ ነግሮች አሁንም ደግሜ ብጽፍላችሁ አይታክተኝም። እነዚህ ነገሮች እናንተን ከስሕተት ይጠብቃችኋል።
\v 2 ከውሾች ተጠንቀቁ። ከክፉ ሠራተኞች ተጠንቀቁ፤ከሐሰተኞች መገረዝም ተጠንቀቁ።
\v 3 እኛ በእግዚአብሔር መንፈስ የምናመልክ፤ በሥጋም የማንታመን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ የምንታመን የተገረዝን ነን።
\s5
\v 4 በሥጋ ትምክሕት የሚያስፈልግ ቢሆን እኔ በብዙ ነገር ልመካ እችል ነበረ። ማንም በሥጋ የሚመካበት አለኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ቢኖር እኔ ከእርሱ የበለጠ የምመካበት ብዙ አለኝ።
\v 5 እኔ በተወለድኩ በስምንተኛው ቀን ተገርዤአለሁ፤ በትውልዴም ከብንያም ነገድ የሆንኩ እስራኤላዊ ነኝ፤ ከዚህም የተነሳ ጥርት ያልኩ ዕብራዊ ነኝ። የአይሁድን ሕግ ስለ መጠበቅም ቢሆን ፈሪሳዊ ነበርኩ።
\s5
\v 6 በቅንዓት ቤተ ክርስቲያን አሳድድ ነበር። ሕግን በመጠበቅ ስለ መጽደቅም ቢሆን ያለ ነቀፋ እኖር ነበር።
\v 7 ነገር ግን ከዚህ በፊት ጠቃሚዎች ናቸው ብዬ አምንባቸው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ ስለ ክርስቶስ ብዬ ዋጋ እንደሌላቸው እንደ ከንቱ ነገሮች አድርጌ ቆጥሬአቸዋለሁ።
\s5
\v 8 በርግጥ፥ ከሁሉ ይልቅ ስለሚበልጥ ስለ ክርስቶስ ጌታዬ ዕውቀት ነገር ሁሉ ጉዳት እንዲሆን እቆጥራለሁ። ስለ እርሱም ሁሉን ነገር አጥቻለሁ። ክርስቶስንም ለማግኝትና በእርሱም ለመገኝት ስል ሁሉን ነገር እንደ ቤት ጥራጊ እቆጥራለሁ።
\v 9 እንግዲህ በሕግ ላይ የተመሠረተው የራሴ ጽድቅ የለኝም። በዚህ ፈንታ በክርስቶስ በኩል በሚገኝ እምነት የእግዚአብሔር ጽድቅ አለኝ።
\v 10 ይኸውም እርሱን የማወቅ ጽድቅ፤ የእርሱ የትንሣኤ ኃይልና የመከራው ተካፋይ የመሆንና በሞቱም ክርስቶስን ለመምሰል ነው።
\v 11 ደግሞም ከሙታን ትንሣኤን አገኝ ዘንድ ነው።
\s5
\v 12 እነዚህን ነገሮች ገና አልጨበጥኩአቸውም ፤ ፍጹም ሆኜአለሁ ማለትም አልችልም። ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ያገኘሁትን አገኝ ዘንድ ወደ ፊት ጥረቴን እቀጥላለሁ።
\v 13 ወንድሞች ሆይ፤እኔ ራሴ ገና እንደጨበጥኩ አልቆጥርም። ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ይኸውም በስተኋላዬ የነበረውን እየረሰሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እተጋለሉ።
\v 14 እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ጠርቶ ሽልማቴን ለማግኘት በፊት ወዳለው ግብ እሮጣለሁ።
\s5
\v 15 ስለዚህ እኛ ብዙዎቻችን በመንፈሳዊ ሕይወት እንዳደጉ ሰዎች ነገሮችን ሁሉ ማሳብ ይኖርብናል። ደግሞ በማንኛውም ነገር የተለያየ አስተሳሰብ ቢኖራችሁ እግዚአብሔር ሁሉንም ግልጥ ያደርግላችኋል።
\v 16 ይሁን እንጂ በደረሰንበት በዚያው ሁኔታ እንመላለስ።
\s5
\v 17 ወንድሞች ሆይ፥ የእኔን ምሳሌነት ተከተሉ፤ በእኛም ምሳሌነት የሚመላለሱትን ሁሉ ልብ ብላችሁ ተመልከቱ።
\v 18 ከአሁን በፊት ብዙ ጊዜ እንደ ነገርኳችሁና አሁንም እንባዬን እያፈሰስኩ እንደምነግራችሁ ሁሉ ብዙዎቹ በአካሄዳቸው የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነዋል።
\v 19 የእነርሱ አምላክ ሆዳቸው ነው፤ አሳፋሪ የሆነ ነገርም ለእነርሱ ክብራቸው ነው፤ አሳባቸውም የሚያተኩረው በምድራዊ ነገር ላይ ነው ስለዚህ የእነርሱም መጨረሻ ጥፋት ነው፤
\s5
\v 20 ነገር ግን የሚመጣውን አዳኝ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን የምንጠብቅ የሰማይ መንግሥት ዜጎች ነን።
\v 21 እርሱ ይህን የተዋረደውን ሰውነታችንን በመለወጥ የእርሱን ክቡር ሰውነት እንዲመስል ያደርገዋል። ይህንንም የሚያደርገው ሁሉን በሥልጣኑ ሥር ለማድረግ በሚያስችለው ኃይል ነው።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ፤ ወዳጆቼም ሆይ፤ የምናፍቃችሁ፤ ደስታዬና አክሊሎቼ የሆናችሁ በዚህ መንገድ በጌታ ጸንታችሁ ቁሙ።
\v 2 ኤዎድያና ሲንጢኪ እርስ በርሳቸው በጌታ ተስማምተው እንዲኖሩ እለምናቸዋለሁ።
\v 3 በርግጥ አንተም እዚያ ያለኸው የሥራ ባልደርባዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ። እነርሱም ወንጌልን በማሰራጨት ከእኔና ከቅሌምንጦስ ጋር እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቼ ጋር ብዙ ተጋድለዋል።
\s5
\v 4 ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ።
\v 5 ደግነታችሁ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ይታወቅ።
\v 6 ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና።
\v 7 ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
\s5
\v 8 በመጨረሻም ወንድሞችሆይ፥ እውነት የሆነውን ሁሉ፤ ክቡር የሆነውን ሁሉ፤ ትክክል የሆነውን ሁሉ፤ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፤ ፍቅር የሆነውን ሁሉ፤ መልካም የሆነውን ሁሉ፤ በጎነት ቢሆን፤ ምስጋናም ቢሆን፤ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስቡ።
\v 9 ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፤ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ማናቸውንም ነገር አድርጉ። የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
\s5
\v 10 እንደገና በመጨረሻ ጊዜ ለእኔ ማሰብ ስለ ጀመራችሁ በጌታ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። በርግጥ ከዚህ በፊት ስለ እኔ ያሰባችሁ ቢሆንም እኔን ለመርዳት ዕድሉን አላገኝችሁም ነበር።
\v 11 ይህን የምለው ለራሴ ጥቅም አይደለም። ምክንያቱም በሁሉም ሁኔታ ባለኝ ነገር መርካትን ተምሬአለሁ።
\v 12 በማጣትም ሆነ በማግኘት እንዴት መኖር እንዳለብኝ ዐውቃለሁ። በማንኛውም መንገድ የመጥገብንና የመራብን፤ የማግኝትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ።
\v 13 ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።
\s5
\v 14 ይሁን እንጂ፤ እናንተ የችግሬ ተካፋዮች በመሆናችሁ መልካም አድርጋችኋል።
\v 15 እናንተ የፊልጵስዩስ ሰዎች የወንጌልን ተልዕኮ በጀመርኩበት ጊዜ ከመቄዶንያ ስወጣ ከእናንተ በቀር በመስጠትም ሆን በመቀበል ከእኔ ጋር የተባበረ ሌላ ቤተ ክርስቲያን እንዳልነበረ ታውቃላችሁ።
\v 16 በተሰሎንቄ በነበርኩበት ጊዜም ቢሆን ከአንድ ጊዜ በላይ ለሚያስፈልገኝ ርዳታ ልካችሁልኛል።
\v 17 ይህንንም ስል የእናንተን ስጦታ ለማግኝት በመፈለግ ሳይሆን የልግሥናችሁ ፍሬ እንዲበዛላችሁ በመመኘት ነው።
\s5
\v 18 ሁሉንም ነገር ተቀብያለሁ፤በዝቶልኛል፤ ሞልቶልኛልም። የላካችሁልኝን ስጦታ ከኤጳፍሮዲቱስ እጅ ተቀብዬአለሁ። ይህም ስጦታ በመልካም መዓዛ እንደ ተሞላ መሥዋዕት እግዚአንሔር የሚቀበለውና ደስ የሚሰኝበት ነው።
\v 19 ደግሞም አምላኬ እንደ ክብሩ ባለጠግነቱ በክርስቶስ ኢየሱስ አማካይነት የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይሰጣችኋል።
\v 20 እንግዲህ ለአባታችንና ለአምላካችን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
\s5
\v 21 በክርስቶስ ኢየሱስ ለሆኑት ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሰላምታ ያቀርቡላችሁኋል።
\v 22 እዚህ ያሉት አማኞች ሁሉ በተለይም የሮማ ቤተ መንግሥት ያሉ ሠራተኞች ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 23 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን።

184
52-COL.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,184 @@
\id COL
\ide UTF-8
\h ቆላስይስ
\toc1 ቆላስይስ
\toc2 ቆላስይስ
\toc3 col
\mt ቆላስይስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቲዎስ፤
\v 2 በቆላስይስ ለሚኖሩ ለእግዚአብሔር ለተለዩና በክርስቶስ ታማኝ ለሆኑ አማኞች፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ጸጋና ሰላም ይሁንላችሁ።
\v 3 ለእናንተ በምንጸልይበት ጊዜ ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን እናመሰግናለንን።
\s5
\v 4 በክርስቶስ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለእግዚአብሔር ለተለዩት ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምተናል።
\v 5 በሰማይ ከተጠበቀላችሁ ከመታመነ ተስፋ የተነሣ ይህ እምነትና ፍቅር አላችሁ። ስለዚህም ተስፋ በወንጌል የእውነት ቃል አስቀድማችሁ ሰማችሁ፤ ይህም ወደ እናንት ደርሶአል።
\v 6 ይህንም ወንጌል ከሰማችሁበትና የእግዚአብሔርን ጸጋ በእውነት ከተረዳችሁበት ቀን ጀምሮ በእናንተም ዘንድ እየሠራ እንዳለ ሁሉ በዓለም ዙሪያ ሁሉ ፍሬ እያፈራና እያደገ ነው።
\s5
\v 7 በእኛ ምትክ ለእናንተ የክርስቶስ ታማኝ አገልጋይ የሆነውና ከእኛም ጋር አብሮን ከሚያገለግል ከተወዳጁ ከኤጳፍራ ይህን ተምራችኋል።
\v 8 ደግሞም በእግዚአብሔር መንፈስ ያላችሁን ፍቅር ነግሮናል።
\s5
\v 9 ከዚህም ፍቅር የተነሣ ስለ እናንተ ከሰማንበት ቀን ጀምሮ ለእናንተ ከመጸለይ አላቋረጥንም። በፈቃዱ ዕውቀት፣ በጥበብ ሁሉና በመንፈሳዊ ማስተዋል እንድትሞሉ እንጸልይላችኋለን።
\v 10 ጌታን ደስ በሚያሰኝ መንገድ በሁሉም እንደሚገባ እንድትመላለሱ፤ በማናቸውንም መልካም ሥራ ፍሬ እንድታፈሩና በእግዚአብሔርም ዕውቀት እንድታድጉ እንጸልያለን።
\s5
\v 11 በሁሉም ነገር እንድትጽኑና ትእግሥት እንዲኖራችሁ ፣ከኅይሉ ክብር የተነሣም በሁሉ ብርታትና ጥንካሬ እንዲኖራችሁ እንጸልያለን።
\v 12 በብርሃን ከሚኖሩት አማኞች ጋር የርስቱ ተካፋይ እንድንሆን ላበቃን ለእግዚአብሔር በደስታ ምስጋና ማቅረብ እንድትችሉ እንጸልያለን።
\s5
\v 13 ከጨለማ ኅይል አዳነን፤ ወደ ተወደደውም ወደ ልጁ መንግሥት አሸጋገረን።
\v 14 በልጁም የኅጢአታችንን ይቅርታ፣ ድነትን አገኘን።
\s5
\v 15 ልጁ የማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው። እርሱ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው።
\v 16 ምክንያቱም በሰማያትና በምድር፤ የሚታዩትና የማይታዩት ነገሮች ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል። ዙፋናትም ሆኑ ኅይላት ወይም ግዛቶችች ወይም ሥልጣናት፤ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥረዋል።
\v 17 እርሱ ከሁሉ በፊት ነበረ፤ሁሉም ነገር የተያያዘው በእርሱ ነው።
\s5
\v 18 እርሱ አካሉ ለሆነችው ቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። እርሱ የሁሉም መገኛና የሁሉም የመጀመሪያ፣ከሙታንም በኩር ነው።
\v 19 በመሆኑም በሁሉም ነገሮች መካከል የመጀመሪያ ነው። በእርሱ የእግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ እንዲኖርና እግዚአብሔር በልጁ በኩል ሁሉን ነገር
\v 20 ከራሱ ጋር ያስታርቅ ዘንድ ስለ ወደደ ነው። እግዚአብሔር ልጁ በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም በሰማያትም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ አስታረቀ።
\s5
\v 21 እናንተም ቀድሞ ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ነበር፤ በአሳባችሁና በክፉ ሥራችሁም ምክንያት ጠላቶች ነበራችሁ።
\v 22 አሁን ግን ቅዱሳንና ንጹሓን፤ ነቀፋም የሌለባችሁ አድርጎ በፊቱ ሊያቀርባችሁ በልጁ ሞት እግዚአብሔር ከራሱ ጋር አስታረቃችሁ። ይህም በእርሱ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ
\v 23 በእምነት ጸንታችሁ እንድትኖሩ ነው። ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ ተሰብኮአል። እኔም ጳውሎስ አገልጋይ የሆንኩት ለዚህ ወንጌል ነው።
\s5
\v 24 አሁን ስለ እናንተ በምቀበለው መከራ ደስ ይለኛል። አካሉ ስለ ሆነችው ስለ ቤተ ክርስቲያንም ከክርስቶስ መከራ ከመካፈል የጎደለውን በሥጋዬ አሟላለሁ።
\v 25 የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ለእናንተ እንድገልጥ ከእግዚአብሔር በተሰጠኝ ኅላፊነት ቃሉን ለመፈጸም የማገለግለው ይህችን ቤተ ክርስቲያን ነው።
\v 26 ይህም ባለፉት ዘመናትና ትውልዶች ከሰው ልጆች ተሰውሮ የቆየውና አሁን ግን እግዚአብሔር ለሚያምኑት ሁሉ የገለጠው ምስጢር ነው።
\v 27 እግዚአብሔርም በእናንተ መካከል ለአሕዛብ ሊገልጥላቸው የፈለገው የዚህ ምስጢር የክብር ብልጽግና ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።
\s5
\v 28 የምንሰብከው እርሱን ነው። እያንዳንዱን ሰው በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ለማቅረብ ጥበብን ሁሉ በማስተማርና በመምክር ሰውን ሁሉ እንገስጻለን።
\v 29 በውስጤ በኅይል በሚሠራው መሠረት በብርቱ እየታገልኩ እደክማለሁ።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ስለ እናንተና በሎዶቅያ ስላሉት ሰዎች እንዲሁም ፊቴን በሥጋ አይተውት ስለማያውቁ ስለ ብዙዎች ምን ያህል ብርቱ ትግል እንዳደረግሁ እንድታውቁ እወዳለሁ።
\v 2 ልባቸው ተጽናንቶና በፍቅር ተሳሰረው ፍጹም የሆነ የመረዳት ብልጽግና እንዲኖራቸውና የእግዚአብሔርን ምስጢር የሆነውን እውነት ክርስቶስን እንዲያውቁ እታገላለሁ።
\v 3 የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የተሰወረው በእርሱ ነው።
\s5
\v 4 ይህን የምላችሁ ማንም በሚያታልል ንግግር እንዳያስታችሁ ነው።
\v 5 በሥጋ ከእናንተ ጋር ባልሆን እንኳ በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ። የእናንተን መልካም ሥርዐትና በክርስቶስ ያላችሁን ጽኑ እምነት እያየሁ ደስ ይለኛል።
\s5
\v 6 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ተቀበላችሁት በእርሱ ተመላለሱ።
\v 7 በእርሱም ተመሥርታችሁና ታንጻችሁ፤ እንደ ተማራችሁትም በእምነት ተደላድላችሁ ኑሩ፤ ምስጋናም ይብዛላችሁ።
\s5
\v 8 በክርስቶስ ላይ ባልተመሠረተ በሰው ሠራሽ ልማድና በዓለማዊ ነገሮች፥ በፍልስፍናና በከንቱ ሽንገላ ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።
\v 9 የእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት በእርሱ ይኖራልና።
\s5
\v 10 በእርሱም ተሞልታችኋል። እርሱ የአለቅነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ ነው።
\v 11 በእርሱም ተገርዛችኋል፤ ይህም መገረዛችሁ የሥጋዊ አካል በማስወገድ በሰው እጅ የተደረገ ሳይሆን በክርስቶስ የተደረገ ነው።
\v 12 በተጠመቃችሁ ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ተቀበራችሁ፤በእርሱም ክርስቶስን ከሞት ባስነሣው በእግዚአብሔር ኅይል በእምነት ተነሥታችኋል።
\s5
\v 13 እናንተም በበደላችሁና በሥጋችሁ ባለመገረዝ ሙታን ሳላችሁ፤ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ሕያዋን አድርጎ መተላለፋችንንም ሁሉ ይቅር ብሎአል።
\v 14 እርሱ ይከሰን የነበረውን የዕዳ ጽሑፍ ደመሰሰው። ሁሉንም በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከእኛ አስወገደው።
\v 15 ኅይላትንና ባለሥልጣናትን በመስቀሉ ድል አድርጎ በይፋ እንዲጋለጡ አደረጋቸው።
\s5
\v 16 እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም የበዓላትን ቀናት ወይም የወር መባቻን፤ ወይም ሰንበትን በማክበር ምክንያት ማንም አይፍረድባችሁ።
\v 17 እነዚሁ ሁሉ ወደ ፊት ሊመጡ ላሉት ነገሮች እንደ ጥላ ናቸው፤ እውነተኛው አካል ግን በክርስቶስ ነው።
\s5
\v 18 አስመሳይ በሆነ ትሕትና የመላእክትን አምልኮ በመፈለግ ማንም ዋጋ እንዳያሳጣችሁ። እንዲህ ያለው ሰው ስለሚያየው ነገር በሥጋዊ አስተሳሰቡ ይታበያል።
\v 19 እርሱም ራስ ከሆነ ከክርስቶስ ጋር አልተያያዘም። በእግዚአብሔር በተሰጠው እድገት በመገጣጠሚያና በጅማት አካልን በሙሉ አያይዞ የሚመግበውና ለአካል ሙሉ ዕድገት የሚሰጠው ራስ ነው።
\s5
\v 20 ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፣ ለዓለማዊ ነገሮች እየታዘዛችሁ ስለ ምን ትኖራላችሁ? ትእዛዞቹም፦
\v 21 «አትያዝ፤አትቅመስ፤ አትንካ!» የሚሉ ናቸው።
\v 22 እነዚህ ሁሉ የሰው ትእዛዛትና ትምህርቶች ሥራ ላይ ከዋሉ በኋላ የሚጠፉ ናቸው።
\v 23 እነዚህ ትእዛዞች ሰው ሰራሽ «ጥበብ» አምልኮና የሐሰት ትሕትና ሰውነትንም በማጎሳቆል ላይ የሚያተኩሩ፤ ነገር ግን ሥጋዊ ስሜትን በመቆጣጠር ረገድ ዋጋ ቢሶች ናቸው።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ከሞት ካስነሣችሁ፤ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያሉትን ነገሮች እሹ።
\v 2 በላይ ስላሉት ነገሮች እንጂ በምድር ስላሉት ነገሮች አታስቡ።
\v 3 ምክንያቱም ሞታችኋል፤ ሕይወታችሁንም እግዚአብሔር በክርስቶስ ውስጥ ሰውሮታልና።
\v 4 ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።
\s5
\v 5 ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፦ እነርሱም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞት፣ ስግብግብነትና ጣዖትን ማምለክ ናቸው።
\v 6 በእነዚህም ነገሮች ምክንያት በማይታዘዙ ልጆች ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ይመጣባቸዋል።
\v 7 እናንተም ራሳችሁ ከዚህ በፊት በማይታዘዙ ሰዎች መካከል ሳላችሁ እነዚህን ነገሮች እያደረጋችሁ ትመላለሱ ነበር።
\v 8 አሁን ግን ቁጣን፤ ንዴትን፤ ተንኮልን፤ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።
\s5
\v 9 አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ፣ አንዳችሁ በሌላው ላይ አትዋሹ።
\v 10 የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል ዕውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል።
\v 11 በዚህ ዕውቀት በግሪካዊና በአይሁዳዊ፣ በተገረዘና ባልተገረዘ፣ በሠለጠነና ባልሠለጠነ፣ በባሪያና በነጻ ሰው መካከል ልዩነት የለም፤ ክርስቶስ ግን ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።
\s5
\v 12 ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳንና የተወደዳችሁ ሆናችሁ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ ገርነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ።
\v 13 እርስ በርሳችሁ ታገሱ፤ እርስ በርሳችሁም ቸሮች ሆኑ። ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅርታ ቢኖረው፣ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።
\v 14 በዚህ ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነው ፍቅር ይኑራችሁ።
\s5
\v 15 የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
\v 16 የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ። በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤በመዝሙርና በውዳሴ፤ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ።
\v 17 በእርሱ እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
\s5
\v 18 ሚስቶች ሆይ፥ ለጌታ እንደሚገባ ለባሎቻችሁ ታዘዙ።
\v 19 ባሎች ሆይ፥ ሚስቶቻችሁን ውደዱ መራራም አትሁኑባቸው።
\v 20 ልጆች ሆይ፥ ይህ ጌታን ደስ የሚያሰኝ በመሆኑ ለወላጆቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ።
\v 21 አባቶች ሆይ፥ልጆቻችሁ ተስፋ እንዳይቆርጡ አታስመርሩአቸው።
\s5
\v 22 አገልጋዮች ሆይ፥ ሰውን ለማስደሰትና ለታይታ ሳይሆን በቅን ልብ ጌታን በመፍራት ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ነገር ታዘዙ።
\v 23 የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው እንደምታደርጉ ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።
\v 24 ከጌታ ዘንድ እንደ ዋጋ የምትቀበሉት ርስት እንዳለ ታውቃላችሁና።
\v 25 በዚህም የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነው። በእግዚአብሔር ዘንድ አድልዎ ስለሌለ ክፉ የሚሠራ ማንም ስለ ክፉ ሥራው ቅጣቱን ይቀበላል።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ጌቶች ሆይ፥ እናንተም በሰማይ ጌታ እንዳላችሁ ዐውቃችሁ ለአገልጋዮቻችሁ በትክክልና የሚገባቸውን ስጡአቸው።
\s5
\v 2 በንቃት እግዚአብሔርን እያመሰገናችሁ ሳታቋርጡ ጸልዩ።
\v 3 የክርስቶስ ምሥጢር የሆነውን የቃሉን እውነት መናገር እንድንችል እግዚአብሔር በር እንዲከፍትልን ለእኛም ደግሞ በአንድ ልብ ጸልዩልን፤ ምክንያቱም እስር የሆንኩት ስለእርሱ ነውና።
\v 4 እኔም እንደሚገባ ቃሉን መግለጥና መናገር እንድችል ጸልዩልኝ።
\s5
\v 5 በውጪ ካሉት ጋር በጥበብ ተመላለሱ፤ ዘመኑንም ዋጁ።
\v 6 ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መመለስ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።
\s5
\v 7 ቲኪቆስ መጥቶ እኔ ስላለሁበት ሁኔታ ሁሉንም ነገር ይነግራችኋል። እርሱም ተወዳጅ ወንድም፤ ታማኝ አገልጋይና በጌታ ሥራም የአገልግሎት ባልደረባዬ ነው።
\v 8 እርሱንም ወደ እናንተ የላክሁበት ምክንያት ስለ እኛ ሁኔታ ትክክል የሆነውን እንዲነግራችሁና ልባችሁንም እንዲያጽናና ነው።
\v 9 ከእርሱም ጋር የእናንተ ወገን የሆነውን የታመነውንና የተወደደውን ወንድም አናሲሞስን ወደ እናንተ ልኬዋለሁ። እነርሱ በዚህ ስፍራ የተደረገውን ነገር ሁሉ ይነግሩአችኋል።
\s5
\v 10 ከእኔም ጋር የታሰረው አርስጥሮኮስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል፤ አንድ ጊዜ፥ «ወደ እናንተ በሚመጣበት ጊዜ ተቀበሉት» ብዬ አሳስቤአችሁ የነበረው የበርናባስ የአጎት ልጅ ማርቆስም ሰላምታ ያቀርብላችኋል።
\v 11 ኢዮስጦስ ተብሎ የሚጠራው ኢያሱም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ከተገረዙ ወገኖች መካከል ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው የሚሠሩት ሰዎች እነዚህ ብቻ ናቸው፤ ለእኔም መጽናናት ሆነውኛል።
\s5
\v 12 የእናንተ ወገን የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ኤጳፍራም ሰላምታ ያቀርብላችኋል። እርሱም ፍጹም ጠንክራችሁና ሙሉ በሙሉ ተማምናችሁ በእግዚአብሔር ፈቃድ በሁሉ ጸንታችሁ እንድትቆሙ ዘወትር ስለ እናንተ በጸሎት እየተጋ ነው።
\v 13 ስለ እናንተ በሎዶቅያና በሂራፖሊስ ስላሉትም ሰዎች ተግቶ እንደሚሠራ እኔ ራሴ እመሰክርለታለሁ።
\v 14 የተወደደው ሐኪም ሉቃስና ዴማስም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\s5
\v 15 በሎዶቅያ ላሉት ወንድሞች ለንምፉና በቤትዋም ላለች ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ አቅርቡልኝ ።
\v 16 ይህን መልእክት እናንተ ካነበባችሁ በኋላ በሎዶቅያ ሰዎች ዘንድ ባለችው ቤተ ክርስቲያን እንዲነበብ አድርጉ፤እናንተም ከሎዶቅያ የሚላክላችሁን መልእክት አንብቡ።
\v 17 ለአርኪጳስም፥ «በጌታ አገልግሎት የተሰጠህን ሥራ በጥንቃቄ ፈጽም» ብላችሁ ንገሩልኝ።
\s5
\v 18 ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍኩት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ በሰንሰለት ታስሬ እንዳለሁ አስታውሱና ጸልዩልኝ። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

175
53-1TH.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,175 @@
\id 1TH
\ide UTF-8
\h 1 ተሰሎንቄ
\toc1 1 ተሰሎንቄ
\toc2 1 ተሰሎንቄ
\toc3 1th
\mt 1 ተሰሎንቄ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከጳውሎስ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ በእግዚአብሔር አብና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ለተሰሎንቄ ቤተክርስቲያን፤ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን!
\s5
\v 2 በጸሎታቻን እያሳሰብን እግዚአብሔርን ሁልጊዜ ስለ ሁላችሁም እናመሰግናለን።
\v 3 በእምነት ስለምትሠሩት ሥራ፣ በፍቅር ስለምትደክሙት ድካምና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ በመታመን ስለመጽናታችሁ በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ሳናቋርጥ እናስታውሳችኋለን።
\s5
\v 4 በእግዚአብሔር የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ! መመረጣችሁን እናውቃለን፣
\v 5 ወንጌላችን በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፥ ነገር ግን በኃይል፣ በመንፈስ ቅዱስና በብዙ መረዳትም እንጂ፥ ስለእናንተ ስንል በመካከላችሁ ደግሞ እንዴት እንደነበርን ታውቃላችሁ።
\s5
\v 6 በብዙ መከራ ውስጥ ቃሉን ከመንፈስ ቅዱስ ደስታ ጋር ስትቀበሉት እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ፣
\v 7 በመቄዶንያ ሁሉና በአካይያ ላሉ ለሚያምኑት ምሳሌ ሆናችሁላቸዋል።
\s5
\v 8 የጌታ ቃል ከእናንተ ተነሥቶ በመቄዶንያና አካይያ ብቻ ሳይሆን ምንም መናገር እስከማያስፈልገን ድረስ በእግዚአብሔር ላይ ያላችሁ እምነት በሁሉ ሥፍራ ተወርቷል።
\v 9 እኛን በሚመለከት እንዴት ያለ አቀባበል እንዳደረጋችሁልን፣ ሕያውና እውነተኛ የሆነውን አምላክ ታገለግሉ ዘንድ ከጣዖታት እንዴት ወደ እግዚአብሔር ዘወር
\v 10 እንዳላችሁ፣ደግሞም ከሰማይ የሚመጣውን ልጁን፣ ያም ከሙታን ያስነሳውን፣ ሊመጣ ካለው ቁጣ የሚያድነንን ኢየሱስን እንደምትጠባበቁ እነርሱ ራሳቸው ይመሰክራሉ።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ! ወደ እናንተ መምጣታችን ፍሬቢስ እንዳልነበረ እናንተው እራሳችሁ ታውቃላችሁ፣
\v 2 ነገር ግን እንደምታውቁት ቀደም ሲል በፊልጵስዩስ መከራና እንግልት ደረሰብን። በብዙ ተቃውሞ መካከል የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ ለመንገር አምላካችን ድፍረት ሰጥቶናል።
\s5
\v 3 የምንመክራችሁ ምክር ከስሕተት ወይም ከእርኩሰት ወይም ከማታለል የመነጨ አይደለም፣
\v 4 ነገር ግን ወንጌልን በአደራ ይሰጠን ዘንድ እግዚአብሔር ታማኞች አድርጎ እንደቆጠረን እንዲሁ ሰውን ሳይሆን ልባችንን የሚመረምረውን እርሱን ደስ ለማሰኘት እንናገራለን።
\s5
\v 5 እናንተው እንደምታውቁት መቼም ቢሆን የሽንገላን ቃል አልተጠቀምንም፣ ገንዘባችሁን በመመኘት እንዳልሆነም እግዚአብሔር ምስክር ነው፣
\v 6 የክርስቶስ ሐዋርያት እንደመሆናችን ልንጠቀምባችሁ መብት ቢኖረንም እንኳን ከእናንተ ወይም ከሌሎች ክብርን ከማንም ሰው አልፈለግንም።
\s5
\v 7 ይልቁንም እናት የራስዋን ልጆች እንደምትንከባከብ በመካከላችሁ የዋሆች ሆንን።
\v 8 ለእናንተ ካለን ፍቅር የተነሳ የእግዚአብሔርን ወንጌል ብቻ ሳይሆን የራሳችንን ሕይወት እንኳን ጨምረን ብንካፈላችሁ ደስ ይለን ነበር፣ ምክንያቱም ለእኛ እጅግ የተወደዳችሁ ሆናችኋልና።
\v 9 ወንድሞች ሆይ! የእግዚአብሔርን ወንጌል በሰበክንላችሁ ጊዜ በማናችሁም ላይ ሸክም ላለመሆን ቀንና ሌሊት እንደሠራን ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሳላችሁ።
\s5
\v 10 በእናንተ በምታምኑት መካከል እንዴት በቅድስና፣ በጽድቅና ነቀፋ በሌለበት ኑሮ ራሳችንን እንዳቀረብንላችሁ እግዚአብሔርና እናንተም ጭምር ምስክሮች ናችሁ፣
\v 11 እናንተው እንደምታውቁት አባት ለራሱ ልጆች እንደሚያደርገው እያንዳንዳችሁን መከርናችሁ፣ አበረታታናችሁና
\v 12 መሰከርንላችሁ፣ይኸውም ወደ ራሱ መንግሥትና ክብር ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ ነው።
\s5
\v 13 በዚህ ምክንያት እኛ ደግሞ ሳናቋርጥ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፣ የመልዕክቱን ቃል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ከእኛ በሰማችሁ ጊዜ እንደ ሰው ቃል ሳይሆን፣ ነገር ግን እውነት እንደሆነ፣ በእናንተ በምታምኑት ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል ተቀበላችሁት።
\s5
\v 14 እናንተም ወንድሞች ሆይ፣ በይሁዳ የሚኖሩ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑትን የእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት የምትመስሉ ሆናችኋል፣ እነርሱ ከአይሁድ መከራ እንደደረሰባቸው እናንተ ደግሞ ከገዛ ራሳችሁ ሕዝብ ያንኑ መከራ ተቀብላችኋልና፣
\v 15 አይሁድ ጌታ ኢየሱስንና ነቢያትን ገደሉ፣ እኛንም አሳደዱን፣ እነርሱ እግዚአብሔርን ደስ አያሰኙትም፥ ሰውን ሁሉ ይቃወማሉ።
\v 16 ዘወትር ኀጢአታቸውን ለማብዛትም ይድኑ ዘንድ ለአሕዛብ እንዳንናገር ይከለክሉናል። ቁጣው በላያቸው ላይ መጥቶባቸዋል።
\s5
\v 17 ወንድሞች ሆይ፣ እኛ ለጥቂት ጊዜ በልባችን ሳይሆን በአካል ተለይተናችሁ ነበር፣ በመሆኑም በነበረን ታላቅ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት የተቻለንን ያህል ጥረት አድርገናል፣
\v 18 ወደ እናንተ ለመምጣት ፈልገን ነበር፣ እኔ ጳውሎስም ከአንድም ሁለት ጊዜ ሞከርኩኝ፣ ነገር ግን ሰይጣን አዘገየን።
\v 19 ጌታችን ኢየሱስ በሚመጣበት ጊዜ በፊቱ ተስፋችን ወይም ደስታችን ወይም የመክበራችን አክሊል እንደሌሎቹ ሁሉ እናንተ አይደላችሁምን?
\v 20 ምክንያቱም እናንተ ክብራችንና ደስታችን ናችሁ።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ስለዚህ ከዚያ በላይ ልንታገስ ባልተቻለን ጊዜ በአቴና ለብቻችን መቅረታችን መልካም እንደሆነ አሰብን።
\v 2 በእምነታችሁ ያጸናችሁና ያበረታችሁ ዘንድ ወንድማችንንና በክርስቶስ ወንጌል የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን ጢሞቴዎስን ላክንላችሁ፣
\v 3 ይህንን ያደረግነውም በእነዚህ መከራዎቻችሁ ማንም እንዳይናወጥ ነው፣ ለዚህ እንደተመረጥን ራሳችሁ ታውቃላችሁና።
\s5
\v 4 በእርግጥ ከእናንተ ጋር በነበርንበት ወቅት መከራ ልንቀበል እንዳለን አስቀድመን ነግረናችሁ ነበር፣ እንደምታውቁት የሆነውም ይኸው ነው።
\v 5 በዚህ ምክንያት ወደፊት ልታገስ ባቃተኝ ጊዜ ምናልባት ፈታኙ ፈትኗችሁ ልፋታችንም ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር ስለ እምነታችሁ አውቅ ዘንድ ላክሁት።
\s5
\v 6 ጢሞቴዎስ ከእናንተ ዘንድ ተመልሶ ስለ እምነታችሁና ፍቅራችሁ የምሥራች ባመጣልን ጊዜ ሁልጊዜ በመልካም እንደምታስታውሱንና እኛ ደግሞ ልናያችሁ እንደምንናፍቅ ሁሉ ልታዩን እንደምትናፍቁ ሲነግረን
\v 7 በዚህ ምክንያት ወንድሞች ሆይ፣ በችግራችንና በመከራችን ሁሉ በእናንተ እምነት ተጽናንተናል።
\s5
\v 8 በጌታ ጸንታችሁ ብትቆሙ እኛ ደግሞ አሁን በሕይወት እንኖራለን።
\v 9 በእናንተ ምክንያት በአምላካችን ፊት ስላገኘነው ደስታ ሁሉ ስለ እናንተ ለእግዚአብሔር እንዴት ያለ ምስጋና ማቅረብ እንችል ይሆን?
\v 10 ፊታችሁን ለማየትና በእምነታችሁ የሚጎድላችሁን ለመሙላት ሌሊትና ቀን እጅግ አጥብቀን እንጸልያለን።
\s5
\v 11 ራሱ አምላካችንና አባታችን፣ ጌታችንም ኢየሱስ ወደ እናንተ እንድንመጣ መንገዳችንን ያቅና፣
\v 12 እኛ ደግሞ እንደምናፈቅራችሁ ጌታ ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ የሚሆን ፍቅራችሁን ያብዛ ያትረፍርፍም።
\v 13 ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር ሲመጣ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁን ነቀፋ በሌለበት ቅድስና ያጸና ዘንድ ይህንን ያድርግላችሁ።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፣ እንዴት መመላለስና እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንዳለባችሁ ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት አሁን እንደምትኖሩት ሁሉ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉ በጌታ በኢየሱስ እንመክራችኋለን እናደፋፍራችሁማለን።
\v 2 በጌታ በኢየሱስ በኩል እንዴት ያለውን ትዕዛዝ እንደሰጠናችሁ ታውቃላችሁና፤
\s5
\v 3 በቅድስና መኖራችሁ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣
\v 4 ከእናንተ እያንዳንዱ ከዝሙት በመራቅ የራሱን አካል በቅድስናና በክብር ማግኘት እንዳለበት ታውቃላችሁ፣
\v 5 እግዚአብሔርን እንደማያውቁ እንደ አሕዛብ የፍትወት ምኞት አይሁን፣
\v 6 በዚህ ጉዳይ ማንም አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል፣ ምክንያቱም አስቀድመን እንደነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ ስለነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚበቀል ነውና።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለእርኩሰት አልጠራንም።
\v 8 ስለዚህ ይህንን የማይቀበል ሰውን ሳይሆን የማይቀበለው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን ነው።
\s5
\v 9 የወንድማማች መዋደድን በተመለከተ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፣ እርስ በርስ ስለመዋደድ እናንተው ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና።
\v 10 በመቄዶንያ ላሉ ወንድሞች ሁሉ ይህንን ታደርጋላችሁ፣ ይሁን እንጂ ወንድሞች ሆይ፣ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉት ደግሞ እንመክራችኋለን።
\v 11 ደግሞም ልክ እንዳዘዝናችሁ በጸጥታ እንድትኖሩ፣ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩና በገዛ እጆቻችሁ እንድትሠሩ እንመክራችኋለን።
\v 12 በማያምኑት ዘንድ በአግባብ እንድትመላለሱና በኑሮአችሁ ምንም የሚጎድላችሁ እንዳይኖር ይህንን አድርጉ።
\s5
\v 13 ወንድሞች ሆይ፣አንቀላፍተው ስላሉት ባለማወቃችሁ ስለወደፊቱ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሀዘናችሁ መሪር እንዲሆን አንፈልግም።
\v 14 ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሳ ካመንን በእርሱ አምነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ያመጣቸዋል።
\v 15 በጌታ ቃል የምንነግራችሁ ይህንን ነው፣ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ እኛ ሕያዋን ሆነን የቀረነው አስቀድመው ያንቀላፉትን በርግጥ አንቀድምም።
\s5
\v 16 ጌታ ራሱ በታላቅ ድምፅ፣ በመላዕክት አለቃ ድምፅና በእግዚአብሔር መለከት ከሰማይ ይወርዳል፣ በክርስቶስ የሞቱትም አስቀድመው ይነሳሉ።
\v 17 ከዚያም እኛ ሕያዋን ሆነን የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፣ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን።
\v 18 ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በእነዚህ ቃላት ተጽናኑ።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ፣ አሁን ስለ ጊዜያትና ዘመናት ሊጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም።
\v 2 ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ የጌታ ቀንም እንደዚያው እንደሆነ እናንተ ራሳችሁ በሚገባ ታውቃላችሁና።
\v 3 እርጉዝን ሴት የምጥ ህመም እንደሚሆንባት ሁሉ “ሁሉ ሰላምና ደህና ነው” በሚሉበት በዚያን ጊዜ ድንገተኛ ጥፋት ይመጣባቸዋል፣ እነርሱም በምንም መንገድ አያመልጡም።
\s5
\v 4 ወንድሞች ሆይ፣ እናንተ ግን ያ ቀን እንደ ሌባ ይመጣባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም።
\v 5 ሁላችሁም የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ የሌሊት ወይም የጨለማ ልጆች አይደለንም።
\v 6 እንግዲያውስ ሌሎች እንደሚያደርጉት አናንቀላፋ፣ ነገር ግን እንንቃ በመጠንም እንኑር።
\v 7 የሚያንቀላፉ በሌሊት ያንቀላፋሉ፣ የሚሰክሩትም በሌሊት ይሰክራሉና።
\s5
\v 8 የብርሃን ልጆች እንደመሆናችን በመጠን እንኑር፣ የእምነትንና የፍቅርን ጥሩር፣ የድነታችንን ተስፋ እርግጠኝነትም እንደ ራስ ቁር እንልበስ።
\v 9 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ድነትን ልንቀበል እንጂ እግዚአብሔር ለቁጣ አልመደበንም፣
\v 10 የነቃን ወይም ያንቀላፋን ብንሆን ከእርሱ ጋር እንድንኖር ስለ እኛ ሞቶአልና።
\v 11 ስለዚህ አሁን እንደምታደርጉት ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ፣ አንዱም ሌላውን ያንጸው።
\s5
\v 12 ወንድሞች ሆይ፣በመካከላችሁ በማገልገል የሚለፉትንና በጌታ የሚያስተዳድሯችሁን፣ የሚመክሯችሁንም እንድታከብሯቸው እንጠይቃችኋለን።
\v 13 ደግሞም በሥራቸው ምክንያት ከፍ ያለ የፍቅር አክብሮት እንድታሳዩአቸው እንጠይቃችኋለን። እርስ በርሳችሁ በሰላም ኑሩ።
\v 14 ወንድሞች ሆይ እንመክራችኋለን፣ ያለ ሥርዓት የሚመላለሱትን ገስጹአቸው፣ ድፍረት ያጡትን አበረታቱአቸው፣ ደካሞችን ደግፉአቸው፣ሰውን ሁሉ ታገሱ።
\s5
\v 15 ማንም ስለተደረገበት ክፉ ነገር ለሌላው በክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፣ ነገር ግን ለእርስ በርሳችሁና ለሰው ሁሉ መልካም የሆነውን ለማድረግ ሁልጊዜ ትጉ።
\v 16 ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፣
\v 17 ባለማቋረጥ ጸልዩ፣
\v 18 ስለ ሁሉም ነገር አመስግኑ፣ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ነውና።
\s5
\v 19 የመንፈስ ቅዱስን ሥራ አታዳፍኑ።
\v 20 ትንቢትን አትናቁ።
\v 21 ሁሉን መርምሩ፣ መልካም የሆነውን ያዙ፣
\v 22 ማንኛውንም ዓይነት ክፋት አስወግዱ።
\s5
\v 23 የሰላም አምላክ ራሱ ፈጽሞ ይቀድሳችሁ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ መላው መንፈሳችሁ፣ ነፍሳችሁና ሥጋችሁ ያለ ነቀፋ ይጠበቅ።
\v 24 የጠራችሁ ታማኝ ነው፣ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።
\s5
\v 25 ወንድሞች ሆይ፣ ስለ እኛ ደግሞ ጸልዩ።
\v 26 ወንድሞችን ሁሉ በተቀደሰ አሳሳም ሰላም በሏቸው።
\v 27 ይህ መልዕክት ለወንድሞች ሁሉ እንዲነበብ በጌታ አደራ እላችኋለሁ።
\v 28 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።

99
54-2TH.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,99 @@
\id 2TH
\ide UTF-8
\h 2ኛ ተሰሎንቄ
\toc1 2ኛ ተሰሎንቄ
\toc2 2ኛ ተሰሎንቄ
\toc3 2th
\mt 2ኛ ተሰሎንቄ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከጳውሎስ፣ ስልዋኖስና ጢሞቴዎስ በእግዚአብሔር በአባታችን በጌታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ላሉ ለተሰሎንቄ ሰዎች ቤተክርስቲያን።
\v 2 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 3 ወንድሞች ሆይ፣ ስለ እናንተ ሁልጊዜ ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ አለብን፣ ይህ ተገቢ ነውና፣ ምክንያቱም እምነታችሁ እጅግ እያደገ ነውና፣ የእያንዳንዳችሁ ፍቅርም ለሌሎች የሚተርፍ ሆኗል።
\v 4 በመሆኑም በስደቶቻችሁና በመከራዎቻችሁ ሁሉ ስለ መጽናታችሁ ስለ ትዕግስታችሁና እምነታችሁ እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር አብያተክርስቲያናት መካከል በልበ ሙሉነት እንመሰክራለን።
\v 5 እናንተ ደግሞ መከራን ለምትቀበሉለት ለእግዚአብሔር መንግሥት ብቁ ሆናችሁ ትቆጠሩ ዘንድ ይህ የእግዚአብሔር ፍርድ ጻድቅ የመሆኑ ግልጽ ምልክት ነው።
\s5
\v 6 መከራን ለሚያመጡባችሁ መከራን ይመልስላቸው ዘንድ ይህ በእግዚብሔር ፊት ቅን ፍርድ ነው፣
\v 7 ጌታችን ኢየሱስ ከኀይሉ መላዕክት ጋር ከሰማይ በሚገለጥበት ጊዜ ከእኛ ጋር መከራን ለተቀበላችሁት ደግሞ እረፍትን ይሰጣችኋል።
\v 8 እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ግን በሚነድ እሳት ይበቀላቸዋል።
\s5
\v 9 ከጌታ ሀልዎትና ከኀይሉ ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት እየተቀጡ ይሰቃያሉ፣
\v 10 እርሱ በቅዱሳኑ ሊከበር በሚመጣበት በዚያን ቀን፣ ምስክርነታችንን አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ይገረምባቸዋል።
\s5
\v 11 በዚህ ምክንያት እኛ ደግሞ አምላካችን ለጥሪአችሁ የተገባችሁ አድርጎ ይቆጥራችሁና መልካሙን ምኞታችሁንና ማናቸውንም የእምነት ሥራ በኀይል ይፈጽምላችሁ ዘንድ ባለማቋረጥ እንጸልይላችኋለን።
\v 12 ይህም በአምላካችንና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ምክንያት የጌታችን የኢየሱስ ስም በእናንተ እንዲከበርና እናንተም በእርሱ ትከብሩ ዘንድ ነው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ፣ አሁን የምንለምናችሁ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለመሰብሰባችን ነው፣
\v 2 ከእኛ የሆነ በሚመስል በመንፈስ፣ በቃል ወይም በደብዳቤ እነሆ የጌታ ቀን ሆኗል ብላችሁ በማመን በቀላሉ በአዕምሮአችሁ እንዳትናወጡ ወይም እንዳትደነግጡ እንለምናችኋለን።
\s5
\v 3 በየትኛውም መንገድ ማንም አያስታችሁ። የመጨረሻው ክህደት ሳይመጣና የአመጽ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና።
\v 4 የሚቃወመውና አምላክ ከተባለው ወይም ከሚመለከው ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ የሚያደርገው እርሱ ነው፣ በእግዚአብሔር ቤተመቅደስ እስኪቀመጥም ድረስ ራሱን እንደ አምላክ ያስተዋውቃል።
\s5
\v 5 ከእናንተ ጋር በነበርኩበት ጊዜ ስለእነዚህ ነገሮች እንደነገርኳችሁ ትዝ አይላችሁምን?
\v 6 በትክክለኛው ጊዜ ብቻ ይገለጥ ዘንድ አሁን የሚከለክለው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ።
\v 7 የአመጽ ምስጢር በሥራ ላይ ነው፣ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክለው አንድ ብቻ አለ።
\s5
\v 8 ከዚያም ጌታ ኢየሱስ በአፉ እስትንፋስ የሚገድለውና በመምጣቱ መገለጥ የሚያጠፋው የአመጽ ሰው ይገለጣል።
\v 9 የአመጽ ሰው አመጣጥ እንደ ሰይጣን አሰራር በኀይል ሁሉ፣ በምልክቶችና በሐሰተኛ ድንቆች፣
\v 10 ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉት በአመጽ ማታለል ሁሉ ነው።
\s5
\v 11 በዚህ ምክንያት ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል፣
\v 12 ይኸውም እነዚያ እውነትን ያላመኑ ነገር ግን በአመጻ የተደሰቱ ሁሉ ይፈረድባቸው ዘንድ ነው።
\s5
\v 13 ነገር ግን ስለ እናንተ በጌታ ስለተወደዳችሁት ወንድሞች ለእግዚአብሔር ሁልጊዜ ምስጋና ልናቀርብ ይገባናል፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ መቀደስና እውነትን በማመን ለድነት እንደ በኩራት መርጧችኋልና፣
\v 14 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር እንድትካፈሉ በወንጌላችን ጠራችሁ።
\v 15 እንግዲያውስ ወንድሞች ሆይ፣ ጸንታችሁ ቁሙ፣ በቃልም ሆነ ወይም በደብዳቤአችን የተማራችኋቸውን ልማዶች አጥብቃችሁ ያዙ።
\s5
\v 16 አሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱና የወደደን፣ የዘላለምን መጽናናትና በጸጋው ተስፋ የምናደርግበትን መልካሙን መታመን የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን፣
\v 17 በቃልና በመልካም ሥራ ሁሉ ልባችሁን ያጽናኑት፣ ያበርቷችሁም።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፣ በእናንተ ዘንድ ደግሞ እንደሚሆነው የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲዳረስና እንዲከበር ስለ እኛ ጸልዩ፣
\v 2 ሁሉ እምነት ያላቸው አይደሉምና ከአመጸኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ጸልዩልን።
\v 3 ነገር ግን የሚያጸናችሁና ከክፉው የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።
\s5
\v 4 ያዘዝናችሁን ነገሮች እንደጠበቃችሁና ወደፊትም እንደምትጠብቁ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል።
\v 5 ጌታ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር ፍቅርና ወደ ክርስቶስ ጽናት ይምራው።
\s5
\v 6 ወንድሞች ሆይ፣ ከእኛ እንደተቀበላችሁት ልማድ ሳይሆን ሥራ በመፍታት ከሚኖር ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
\v 7 እንዴት ምሳሌነታችንን መከተል እንደሚኖርባችሁ እናንተው ታውቃላችሁ። በመካከላችሁ በስንፍና አልተመላለስንም፣
\v 8 ወይም ገንዘብ ሳንከፍል የማንንም ምግብ አልበላንም። ከዚያ ይልቅ ከእናንተ በማንም ላይ ሸክም ላለመሆን በድካምና በጥረት ሌሊትና ቀን ሠራን።
\v 9 ይህንን ያደረግነው እኛን ትመስሉ ዘንድ ምሳሌ ልንሆንላችሁ ብለን እንጂ ሥልጣን ስላልነበረን አይደለም።
\s5
\v 10 ከእናንተ ጋር በነበርንበት ጊዜ “ሊሠራ የማይወድ ማንም ቢኖር እርሱ መብላት የለበትም” ብለን አዝዘናችሁ ነበር።
\v 11 በመካከላችሁ ሥራ ፈት ሆነው የሚመላለሱ አንዳንዶች መኖራቸውን ሰምተናልና፤ ሥራ አይሠሩም ነገር ግን በሰው ጉዳይ ጣልቃ ይገባሉ።
\v 12 እንደነዚህ ያሉትን በጸጥታ እንዲሠሩና የራሳቸውን ምግብ እንዲበሉ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸዋለንም።
\s5
\v 13 እናንተ ግን ወንድሞች ሆይ፣ ትክክል የሆነውን ከማድረግ አትታክቱ፡፡
\v 14 በዚህ ደብዳቤ ውስጥ ያለውን ቃላችንን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር ይህንን ሰው ልብ በሉት፣ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር ኅብረት አታድርጉ፡፡
\v 15 እንደ ወንድም ገስጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቁጠሩት፡፡
\s5
\v 16 የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉ መንገድ ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
\v 17 እኔ ጳውሎስ፣ ሰላምታዬ እንዲህ ነው፣ በራሴ እጅ በምጽፋቸው ደብዳቤዎች ሁሉ ላይ ምልክቴ ይህ ነው።
\v 18 የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

228
55-1TI.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,228 @@
\id 1TI
\ide UTF-8
\h 1 ጢሞቴዎስ
\toc1 1 ጢሞቴዎስ
\toc2 1 ጢሞቴዎስ
\toc3 1ti
\mt 1 ጢሞቴዎስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 መታመኛችን በሆነው በክርስቶስ ኢየሱስ እና በአዳኛችን በእግዚአብሔር ትእዛዝ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ጳውሎስ፣
\v 2 በእምነት እውነታኛ ልጄ ለሆነው፣ ለጢሞቴዎስ፡፡ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ለአንተ ይሁን፡፡
\s5
\v 3 ወደ መቄዶንያን በሄደኩ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ልዩ ትምህርትን እናዳያስተምሩ፣
\v 4 በእምነት የሆነውን የእግዚአብሔርን እቅድ ለማያግዙ ለታሪኮችና መጨረሻ የሌላቸውን የትውልዶችን ሐረግ ለመቁጠር ትኩረት ወደ መስጠት እንዳያዘነብሉ ታስጠነቅቃቸው ዘንድ በኤፌሶን እንድትቀመጥ አዘዝኩህ፡፡
\s5
\v 5 ነገር ግን የትእዛዙ ግብ ከንጹህ ልብ፣ ከመልካም ኅሊና እና ከእውነተኛ እምነት የሚወጣ ፍቅር ነ|ው፡፡
\v 6 አንዳንድ ሰዎች ከእነዚህ ነገሮች ርቀው ወደ ባዶ ወሬ ዞረዋል፡፡
\v 7 የሕግ አስተማሪዎች ለመሆን ተመኝተዋል፤ ነገር ግን የሚናገሩትንና መሆን አለበት የሚሉትን ነገር አያውቁትም፡፡
\v 8 ሆኖም ሕግ በትክክል ቢጠቀምበት መልካም እንደሆነ እናወቃለን፡፡
\s5
\v 9 እንዲሁም ሕግ ለጻድቅ ሰው እንዳልተሠራ እናውቃለን፤ ነገር ግን ሕግ የተሰጠው፣ ሕገወጥ ለሆኑና ለአመጸኞች ሰዎች ፣ እግዚአብሔርን ለማይፈሩና ለኃጢአተኞች ፣
\v 10 ለአመንዝሮችና ለግብረ ሰዶማውያን፣ ሰዎችን ባርያ አድርገው ለሚሸጡ፣ ለውሸተኞች፣ ለሐሰት ምስክሮች፣ ከእውነተኛው ትምህርት ርቀው ለሚገኙ ሰዎች ነው፡፡
\v 11 ይህ እውነተኛ ትምህርት በተባረከው አምላካችን ለእኔ በአደራ የተሰጠው ወንጌል ነው፡፡
\s5
\v 12 ለዚህ አገልገሎት ታማኝ እንድሆን ያበቃኝንና የሾመኝን፣ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰግናለሁ፡፡
\v 13 ምንም እንኳ አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ ብሆንም፣ ባለማወቅና ባለማመን ስላደረግሁት ከጌታ ዘንድ ምሕረትን አግኝቼአለሁ፡፡
\v 14 ነገር ግን የጌታችንም ጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ ከእምነትና ከፍቅር ጋር ይበልጥ በዛ፡፡
\s5
\v 15 ‹‹ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም መጣ›› የሚለው መልዕክት ሁሉም ሊቀበሉት የተገባና አስተማማኝ ነው፡፡ እኔም ከእነዚህ ሁሉ የባስኩ ኃጢአተኛ ነኝ፡፡
\v 16 በዚህም ምክንያት ከኃጢአተኞች ዋነኛ በምሆን በእኔ ክርስቶስ ኢየሱስ ትእግስቱን ሁሉ ሊያሳይ ምሕረትን አገኘሁ፤ ይህም የሆነው በእርሱ ለሚያምኑና የዘላለም ሕይወት ለሚያገኙ ምሳሌ እሆን ዘንድ ነው፡፡
\v 17 ስለዚህ ለዘላለም ንጉሥ ፣ ለማይሞተው እና ለማይታየው፣ ብቻውን አምላክ ለሆነው፣ ክብርና ግርማ ለዘላለም ይሁን፡፡ አሜን፡፡
\s5
\v 18 ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ፣ ስለ አንተ አስቀድሞ በተነገረው ትንቢት ተስማምቼ ይህን አዝሃለሁ፤ መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፤
\v 19 ስለዚህም እምነትና መልካም ኅሊና ይኑርህ፡፡ አንዳንድ ሰዎች እነዚህን ክደው መርከብ አለመሪ እንደሚጠፋ በእምነት ነገር ጠፍተዋል፡፡
\v 20 ከእነዚህም መካከል በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል እንዳይናገሩ፣ ለሰይጣን አሳልፌ የሰጠኋቸው፣ ሄሜኔዎስ እና እስክንድሮስ ይገኙባቸዋል፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ስለዚህ ከሁሉ በፊት፣ ጸሎት፣ ምልጃና ምሥጋና ስለ ሰዎቸ ሁሉ እንዲደረግ እመክራለሁ፤ እግዚአብሔርን በመፍራትና በማክበር፣
\v 2 በጸጥታ ሕይወት ሰላማዊ ኑሮ እንድንኖር፣ ለነገሥታትና በሥልጣን ላይ ላሉ ሁሉ ጸልዩ፡፡
\v 3 ይህም በአዳኛችን በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ተቀባይነት ያለው ነገር ነው፡፡
\v 4 እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ሁሉ ወደ ማውቅ እንዲደርሱ ይፈልጋልና፡፡
\s5
\v 5 አንድ እግዚአብሔር አለና፣ እንዲሁም በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል፣ ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ አንድ መካከለኛ አለ፤
\v 6 እርሱም ለሁሉ ራሱን ቤዛ አድርጎ የሰጠ፣ በትክክለኛው ጊዜ የተገለጠ ምስክር ነው፡፡
\v 7 ለዚህም ዓላማ እኔ ራሴ፣ አወጅ ነጋሪና ሐዋርያ ሆኜአለሁ፡፡ እውነትን እናገራለሁ አልዋሽም፤ እኔ ለአሕዛብ የእምነትና የእውነት አስተማሪ ነኝ፡፡
\s5
\v 8 ስለዚህ፣ ወንዶች ሁሉ በየሥፍራው ያለ ጥርጥርና ያለ ቁጣ የተቀደሱ እጆቻቸውን እያነሱ እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ፡፡
\v 9 እንደዚሁም፣ ሴቶች አግባብ ያለው አለባበስ ይኑራቸው፣ ራሳቸውን በመግዛት ረጋ እንዲሉ እንጂ ጸጉራቸውን በወርቅ ወይም በዕንቁ በመሥራት ወይም ውድ የሆኑ ልብሶችን በመልበስ ሊያጌጡ አይገባም፡፡
\v 10 ነገር ግን እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ሴቶች አግባብ እንደሆነው፣ በመልካም ሥራ ተውበው ይታዩ፡፡
\s5
\v 11 ሴት በጸጥታና በመታዘዝ ትማር፡፡
\v 12 ሴት በጸጥታ እንድትኖር እንጂ፣ እንድታስተምርና በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም፡፡
\s5
\v 13 አስቀድሞ አዳም ተፈጥሮአልና፣ ከዚያም ሔዋን፡፡
\v 14 አዳም አልተታለለም፣ ነገር ግን ሴቲቱ ሙሉ ለሙሉ በመተላለፍ ተታልላለች፡፡
\v 15 ሆኖም፣ በእምነትና በፍቅር፣ በቅድስናም በመልካም አዕምሮ ጸንታ ብትኖር፣ ልጆችን በመውለድ ትድናለች፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 አንድ ሰው መሪነትን ቢፈልግ፣ መልካምን ሥራ ተመኝቶአል፣ የሚለው አባባል የታመነ ነው፡፡
\v 2 ስለዚህ መሪው ነቀፋ የሌለበት፣ የአንዲት ሚስት ባል፣ በመጠን የሚኖር፣ አስተዋይ፣ ሥርዓት ያለው፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ለማስተማር የሚበቃ፣
\v 3 የማይሰክር፣ የማይጨቃጨቅ፣ ነገር ግን፣ ለሌሎች የሚጠነቀቅ፣ ሰላማዊ፣ ገንዘብን የማያፈቅር መሆን አለበት፡፡
\s5
\v 4 ቤቱን በመልካም የሚያስተዳድርና ልጆቹም በሁሉም ረገድ የሚታዘዙለት ለሆን ይገባል፤
\v 5 ሰው የራሱን ቤት በመልካም ማስተዳደር የማያውቅ ከሆነ ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዴት ሊጠነቀቅ ይችላል?
\s5
\v 6 ዲያብሎስ በትእቢት እንደወደቀ እንዳይወድቅ አዲስ አማኝ የቤተ ክርስቲያን መሪ አይሁን፤
\v 7 በውጭ ባሉት ዘንድ መልካም ምስክርነት ያለው ሊሆን ይገባል፣ በመሆኑም በነቀፋ እና በዲያብሎስ ወጥመድ አይወድቅም፡፡
\s5
\v 8 ዲያቆናትም እንዲሁ፣ የተከበሩ፣ ቃላቸው አንድ የሆነ፣ ብዙ የወይን ጠጅ የማይጠጡ፣ የማይስገበገቡ መሆን አለባቸው፡፡
\v 9 በንጹህ ኅሊና የተገለጠውን የእምነት እውነት ሊጠብቁ ይገባቸዋል፡፡
\v 10 አስቀድመው ይገምገሙ፣ ከዚያም ያለነቀፋ ሆነው ከተገኙ በዲቁና አገልግሎት ይሾሙ፡፡
\s5
\v 11 እንዲሁም ሴቶች የተከበሩ፣ የማያሙ፣ ልከኞችና በሁሉ ነገር የታመኑ ሊሆኑ ይገባቸዋል፡፡
\v 12 ዲያቆናት እያንዳንዳቸው የአንዲት ሚስት ባል መሆን አለባቸው፤ ቤታቸውንና ልጆቻቸውንም በመልካም የሚያስተዳሩ ሊሆኑ ይገባል፡፡
\v 13 መልካም አገልግሎት የሚያበረክቱ እነርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ ባላቸው እምነት ለራሳቸውእውነተኛ መሠረትና ድፍረትን ያገኛሉ፡፡
\s5
\v 14 እነዚህን ነገሮች ስጽፍልህ ወደ አንተ በቅርቡ እንደምመጣ ተስፋ በማድረግ ነው፡፡
\v 15 ነገር ግን ብዘገይ፣ በእግዚአብሔር ቤት፣ ማለትም የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነው፣ በሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንዴት መኖር እንደሚገባህ ታውቅ ዘንድ እጽፍልሃለሁ፡፡
\s5
\v 16 እኛ ሁላችን በዚህ እንስማማለን፡- ‹‹የተገለጠው እግዚአብሔርን የመምሰል ምስጢር ታላቅ ነው፣›› ይህም በሥጋ የተገለጠው፣ በመንፈስ የጸደቀው፣ በመላእክት የታየው፣ በሕዝቦች መካከል የታወጀው፣ በዓለም የታመነው፣ በክብር ወደ ሰማይ ያረገ ነው፡፡
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 አሁን ግን መንፈስ በመጨረሻ ዘመን አንዳንድ ሰዎች የራሳቸውን ኅሊና በውሸት በተሞላ ግብዝነት በማደንዘዝ፤
\v 2 ለሚያስቱ መናፍስትና ለአጋንንት ትምህርት ትኩረት በመስጠት እምነትን ይክዳሉ በማለት በግልፅ ይናገራል፡፡
\s5
\v 3 እውነትን ለማወቅ የመጡትን አማኞች ከምሥጋና ጋር ከሚቀበሉትና እርስበርሳቸው ከሚካፈሉት እግዚአብሔር ከፈጠረው ምግብ እንዲርቁ፣ ጋብቻንም እንዳያደርጉ ይከለክላሉ፡፡
\v 4 በእግዚአብሔር የተፈጠረው ሁሉ መልካም ነውና፤ በምሥጋና የሚቀበሉት እንጂ የሚጣል የለውም፡፡
\v 5 በእግዚአብሔር ቃልና በጸሎት የተቀደሰ ነው።
\s5
\v 6 እነዚህን ነገሮች ለወንድሞች ብታስረዳ፣ በእምነት ቃሎች እና በተከተልከውም መልካም ትምህርት የምትመገብ የኢየሱስ ክርስቶስ መልካም አገልጋይ ትሆናለህ፡፡
\v 7 ራስህን እግዚአብሔርን ለመምሰል አሰልጥን እንጂ፣ አሮጊቶች የሚወዱአቸውን አለማዊ ተረቶችን አትቀበል፡፡
\v 8 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጥቂት ነገር ይጠቅማል፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን መምሰል ለአሁኑና ለሚመጣውም ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል፡፡
\s5
\v 9 ይህ መልእክት የታመነና ሁሉም ሊቀበሉት የተገባው ነው፡፡
\v 10 ለዚህም እንታገላለን ጠንክረንም እንሠራለን፣ ይህም የሚሆነው ሰዎችን ሁሉ በተለይም የሚያምኑትን በሚያድን በሕያው እግዚአብሔር ስለምንታመን ነው፡፡
\s5
\v 11 እነዚህን ነገሮች አውጅ አስተምርም፡፡
\v 12 ማንም ወጣትነትህን አይናቀው፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ፣ በቃልና በሥራ፣ በፍቅር፣ በእምነትና በንጽሕና የእምነት ምሳሌ ሁን፡፡
\v 13 እስክመጣ ድረስ፣ ማንበብህን፣ መምከርህን እና ማስተማርህን ቀጥል፡፡
\s5
\v 14 በትንቢት ከሽማግሌዎች የእጅ መጫን ጋር ለአንተ የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል፡፡
\v 15 ለእነዚሀ ነገሮች ተጠንቀቅ፣ በእነርሱም ጽና፣ ይህን በማድረግህ ማደግህ በሁሉም ዘንድ ይገለጻል፡፡
\v 16 ለራስህ እና ለትምህርቱ ተጠንቀቅ፣ በእነዚህም ጽና ይህን ብታደርግ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህ፡፡
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ሽማግሌ የሆነውን አትገስጸው፣ ነገር ግን እንደ አባት ለምነው፣ ወጣቶችን እንደ ወንድሞች፣
\v 2 አሮጊቶችን እንደ እናቶች፣ ቆነጃጅቶችን እንደ እኅቶች በሙሉ ንጽሕና ለምናቸው፡፡
\s5
\v 3 በትክክል መበለት የሆኑትን አክብር፤
\v 4 ነገር ግን ባሏ የሞተባት ልጆችና የልጅ ልጆች ከሏት፣ እነርሱ ራሳቸው በቤታቸው አክብሮትን፣ ለወላጆቻቸው ብድራት መክፈልን ይማሩ፣ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው፡፡
\s5
\v 5 ነገር ግን እውነተኛ መበለት ሁሉን ነገር ትታ በእግዚአብሔር ታምና ትኖራለች፣ ልመናዋን ሁል ጊዜ በእርሱ ፊት በማቅረብ ሌትና ቀን ትጠባበቃለች፡፡
\v 6 የሆነ ሆኖ፣ መቀማጠልን የምትወድ ሴት በሕይወትም ብትኖር የሞተች ነች፡፡
\s5
\v 7 ከወቀሳ የራቁ እንዲሆኑ እነዚህን ነገሮች ስበክ፡፡
\v 8 ነገር ግን ማንም ለዘመዶቹ የሚያስፈልጋቸውን የማይሰጥ፣ ይልቁንም ለገዛ ቤተሰቡ የማያስብ እምነትን የካደ ከማያምን ሰው ይልቅ የከፋ ነው፡፡
\s5
\v 9 ባሏ የሞተባት ሴት በመዝገብ ለመጻፍ እድሜዋ ከስድሳ ማነስ የለበትም፣ የአንድ ባል ሚስትም መሆን አለባት፡፡
\v 10 ልጆቿን በሥርዓት የምታሳድግ፣ እንግዶችን የምትቀበል፣ ወይም የቅዱሳንን እግር በማጠብ፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ በመልካም ሥራ ሁሉ የተመሰከረላት መሆን አለባት፡፡
\s5
\v 11 ወጣት መበለቶችን ግን እንደ መበለት አትመዝግባቸው፣ ምክንያቱም የክርስቶስ ተቃራኒ የሆነው ሥጋዊ ፍላጎታቸው ሲያይልባቸው ለማግባት ይፈልጋሉና፡፡
\v 12 በዚህ ሁኔታ የቀድሞ እምነታቸውን ስለተዉ በደለኞች ናቸው፡፡
\v 13 ለሥራ ፈትነትም ስለሚጋለጡ ከቤት ወደ በት የሚዞሩ ይሆናሉ፡፡ ሥራ ፈቶች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ሐሜተኞችና በሰው ጉዳይ ጣልቃ እየገቡ የማይገባውን የሚናገሩ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህ ወጣት ሴቶች እንዲያገቡ እና ልጆችን እንዲወልዱ ቤታቸውንም በመልካም እንዲያስተዳድሩ፣ ተቃዋሚውም ክፉ እንደምናደርግ የሚከስበትን ምክንያት እንዲያሳጡት እመክራለሁ፡፡
\v 15 አንዳንዶች ሰይጣንን ለመከተል ዞር ብለዋል፡፡
\v 16 መበለቶች ያሏት አንዲት የምታምን ሴት ብትኖር፣ ትርዳቸው፣ ስለሆነም የቤተ ክርስቲያን ሸክም ይቀልላታል እውነተኞቹን መበለቶች ለመርዳት ትችላለች፡፡
\s5
\v 17 በመልካም የሚያስተዳድሩ መሪዎች በተለይም በቃሉ ስብከትና በማስተማር የሚተጉ እጥፍ ክብር ይገባቸዋል፡፡
\v 18 የእግዚአብሔር ቃል ‹‹የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር›› እንዲሁም ‹‹ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል›› ይላል፡፡
\s5
\v 19 ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ሳታገኝ በሽማግሌ ላይ ክስ አትቀበል፡፡
\v 20 ሁሉም ይማሩ ዘንድ አጥፊዎችን በሁሉ ፊት ገስጻሳቸው፡፡
\s5
\v 21 በእግዚአብሔር ፊት፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ በተመረጡትም መላእክት ፊት አዝዝሃለሁ፣ አንዳች አድልኦ ሳታደርግ እነዚህን ደንቦች ጠብቅ፡፡
\v 22 በማንም ላይ ቸኩለህ እጅህን አትጫን፣ ከማንም ኃጢአት ጋር አትተባበር፣ ርስህን በንጽሕና መጠበቅ አለብህ፡፡
\s5
\v 23 በተደጋጋሚ ሆድህን ስለሚያምህ ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጣ እንጂ ለወደፊቱ ውኃ ብቻ አትጠጣ፡፡
\v 24 የአንዳንድ ሰዎች ኃጢአት በግልጽ የታወቀ ነው፣ ፍርድን ያስከትልባቸዋል፣ አንዳንዶች ግን ኋላ ይከተሉታል፡፡
\v 25 ልክ እንደዚሁ አንዳንድ መልካም ሥራዎች የተገለጡ ናቸው፣ ነገር ግን ሌሎቹ በጊዜው የተገለጡ ባይሆንም እንኳ የተሰወሩ አይደሉም፡፡
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ስምና ትምህርቱ እንዳይሰደብ ከቀንበር በታች ያሉ ባሪያዎች ለገዢዎቻቸው የሚገባቸውን ክብር ይስጡ፡፡
\v 2 አማኞች የሆኑ ገዢዎች ያሉአቸው ባሪያዎች፣ በእምነት ወንድሞቻቸው ስለሆኑ ገዢዎቻቸውን መናቅ የለባቸውም፡፡ ይልቁንም በመልካም ሥራቸው የሚጠቅሙ የተወደዱ ወንድሞች በመሆናቸው አብልጠው ያገልግሉአቸው፡፡ እነዚህን ነገሮች አስተምር ግለጽም፡፡
\s5
\v 3 ማንም ልዩ ትምህርትን ቢያስተምር፣ እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚረዳውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶሰን ቃል እና የእኛንም ጤናማ ቃል ባይቀበል፣
\v 4 በትእቢት ተነፍቶአል አንዳችም አያውቅም፡፡ ነገር ግን በክርክርና በቃል በመዋጋት የተለከፈ ነው፣ ከዚህም ምቀኝነት፣ ክርክር፣ መሳደብ፣ ክፉ አሳብና፣ እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉ፡፡
\v 5 እነርሱም አእምሮአቸው የተበላሸባቸው ከእውነትም የራቁ እግዚአብሔርን መምሰል ጥቅም ማግኛ የሚመስላቸው ናቸው፡፡
\s5
\v 6 ባለው ለሚረካ ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፡፡
\v 7 ወደ ዓለም ምንም አላመጣንምና፣ አንዳችም ይዘን መሄድ አይቻለንም፡፡
\v 8 ምግብ እና ልብስ ካለን ያ ይበቃናል፡፡
\s5
\v 9 ባለጠጋ ለመሆን የሚመኙ በፈተና ውስጥ ይወድቃሉ፣ በወጥመድ፣ ሞኝነት በመሰሉ አያሌ ጎጂ ምኞቶች፣ እንዲሁም ሰዎችን በሚያሰጥሙና በሚያጠፉ በሌሎች ነገሮች ላይ ይወድቃሉ፡፡
\v 10 የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲመኙ ከእምነት ስተው ራሳቸውን በብዙ ሐዘን ጎዱ፡፡
\s5
\v 11 አንተ ግን፣ የእግዚአብሔር ሰው፣ ከእነዚሀ ነገሮች ሽሽ፡፡ ጽድቅን፣ እግዚአብሔርን መምሰል፣ ታማኝነትን፣ ፍቅርን፣ ጽናትን እና ለሰዎች መጠንቀቅን ተከታተል፡፡
\v 12 መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል፡፡ የተጠራህለትን በብዙ ምሥክሮች ፊት ስለመልካምነቱ የመሰከርክለትን የዘላለምን ሕይወት ያዝ፡፡
\s5
\v 13 ሁሉን ነገር በፈጠረ፣ በእግዚአብሔር ፊት፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ፊት እውነትን በመሰከረው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት አዝዝሃለሁ፣
\v 14 ኢየሱስ ክርስቶስ እስኪገለጥ ድረስ ያለነቀፋ ሆነህ ትእዛዛቱን በፍጹምነት ጠብቅ፡፡
\s5
\v 15 እርሱም መገለጡን የተባረከውና፣ ብቻውን ኃያል የሆነው፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ በወሰነው በትክክለኛው ጊዜ ያሳያል፡፡
\v 16 እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ውስጥ ይኖራል፡፡ ማንም ሰው አላየውም ሊያየውም አይችልም፡፡ ለእርሱ ክብር የዘላለምም ኃይል ይሁን፡፡ አሜን፡፡
\s5
\v 17 በአሁኑ ዘመን ሀብታሞች ለሆኑት እንዳይታበዩ ንገራቸው፡፡ ደስ እንዲለን እግዚአብሔር በሚሰጠን እውነተኛ ብልጥግና እንጂ እርግጠኛ ባልሆነው በዚህ ምድራዊ ባለጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፡፡
\v 18 በመልካም ሥራ ባለጠጎች እንዲሆኑ፣ መልካም የሆነውን እንዲያደርጉ ለማካፈልም ፈቃደኞች እንዲሆኑ ንገራቸው፡፡
\v 19 በዚህ ሁኔታ በሚመጣው ዓለም ለራሳቸው መልካም መሠረትን ይጥላሉ፣ እውነተኛውንም ሕይወት ይይዛሉ፡፡
\s5
\v 20 ጢሞቴዎስ ሆይ፣ ለአንተ የተሰጠህን አደራ ጠብቅ፡፡ የማይረባውን ወሬ አስወግድ፣ በሐሰት እውቀት ከተባለ እርስ በርሱ ከሚጋጭ ነገር ጋር ከመከራከር ራቅ፡፡
\v 21 አንዳንድ ሰዎች ይህ እውቀት አለን በማለት ከእምነት ርቀዋል፡፡ ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡

162
56-2TI.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,162 @@
\id 2TI
\ide UTF-8
\h 2 ጢሞቴዎስ
\toc1 2 ጢሞቴዎስ
\toc2 2 ጢሞቴዎስ
\toc3 2ti
\mt 2 ጢሞቴዎስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነው የሕይወት ተስፋ፣ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ የሆነው፣ጳውሎስ
\v 2 ለተወደደው ልጄ፣ ለጢሞቴዎስ፣ ጸጋና ምሕረት ሰላምም በእግዚአብሔር አባታችን፣ ቤታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ ይሁን፡፡
\s5
\v 3 ሌትና ቀን በጸሎቴ ስለማስብህ፣ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹህ ኅሊና የማገለግለወን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣
\v 4 እምባህን እያሰብኩ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ፤
\v 5 ያለህንም እውነተኛ እምነት አስባለሁ፣ ይህም እምነት አስቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፣ በአንተም እንዳለ ተረድቼአለሁ፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔር የሰጠህን በአንተ ያለውን ስጦታ እንድታነሣሣ ስእጆቼን በመጫኔ አሳስብሃለሁ፡፡
\v 7 እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡
\s5
\v 8 በጌታ እና የእርሱ እስረኛ በሆንኩት በእኔም ምሥክርነት አትፈር፣ እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል መከራን ተቀበል፡፡
\v 9 ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ያዳነን፣ በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሆነው በራሱ እቅድና በጸጋወ ነው እጂ በእኛ ሥራ አይደለም፡፡
\v 10 አሁን ግን የእግዚአብሔር ማዳን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ እና፣ ሞትን በማጥፋቱ እና የዘላለምን ሕይወት ወደ ብርሃን በማውጣቱ በወንጌሉ ተገልጦአል፣
\v 11 ይህንንም ወንጌል ለማብሰር እኔ ሐዋርያ እና አስተማሪ ሆኜ ተሹሜአለሁ፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ ምክንያት እኔ መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን አላፍርበትም፣ ያመንኩትን አውቃለሁና፤ የሰጠሁትን አደራ እስከዚያች ቀን ድረስ እንደሚጠብቅ ተረድቼአለሁ፡፡
\v 13 ከእኔ የሰማኸውን ጤናማ ቃል፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር በምሳሌነት ጠብቅ፡፡
\v 14 በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ አድርገህ በእግዚአበሔር የተሰጠህንም አደራ ጠብቅ፡፡
\s5
\v 15 በእስያ ያሉት ሁሉ ከእኔ ፈቀቅ እንዳሉ ታውቃለህ፣ ከእነዚህም ጊሊጎስ እና ሄርዋጌኔስ ይገኙባቸዋል፡፡
\v 16 ጌታ ለሄኔሲፎሩ ቤተ ሰብ ምሕረትን ይስጣቸው፣ ብዙ ጊዜ አሳርፎኛልና፣ በሰንሰለቴም አላፈረበትም፡፡
\v 17 ነገር ግን በሮም በነበረ ጊዜ፣ በብርቱ ፈልጎ አገኘኝ፣
\v 18 ጌታ በዚያች ቀን ምሕረትን እንዲያገኝ ይስጠው፣ በኤፌሶን ምንያህል እንደረዳኝ አንተ በደኅና ታውቃለህ፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 እንግዲህ ልጄ ሆይ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጽጋ በርታ፡፡
\v 2 ከብዙ ምስክሮች ጋር ከእኔ የሰማኸውን፣ ሌሎችን ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ፡፡
\s5
\v 3 እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ መልካም ወታደር ሆነህ አብረኸኝ መከራ ተቀበል፡፡
\v 4 አለቃውን ማስደሰት የሚፈልግ ወታደር በምድራዊው ነገር ራሱን አያጠላልፍም፡፡
\v 5 ማንም በስፖርታዊ ውድድር የሚሳተፍ፣ በደንቡ መሠረት ካልተወዳደረ የድሉን አክሊል ሊያገኝ አይችልም፡፡
\s5
\v 6 በርትቶ የሚሠራው ገበሬ ምርቱን ከሚበሉት የመጀመሪያው ሊሆን ይገባል፡፡
\v 7 የምለወን ተመልከት ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ፡፡
\s5
\v 8 በወንጌል መልእክቴ የገለጽኩትን፣ ከሙታን የተነሣውንና ከዳዊት ዘር የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፡፡
\v 9 በዚህም ምክንያት እንደ ወንጀለኛ በመታሰር መከራ እቀበላለሁ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አይታሰርም፡፡
\v 10 ስለዚህ ስለተመረጡት ስል በሁሉ እጸናለሁ፣ እነርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን መዳን ከዘላለማዊ ክብር ጋር ያገኙ ዘንድ፡፡
\s5
\v 11 እንዲህ የሚለው ቃል የታመነ ነው ‹‹ከእርሱ ጋር ከሞትን፣ ከእርሱ ጋር እንኖራለን፡፡
\v 12 ብንጸና ከእርሱ ጋር እንነግሣለን፡፡ ብንከዳው እርሱ ደግሞ ይክደናል፡፡
\v 13 ባናምነው እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፣ ራሱን ሊክድ አይችልምና፡፡
\s5
\v 14 እነዚህን ነገሮች አስታውሳቸው፡፡ በቃል እንዳይጣሉ በእግዚአብሔርም ዘንድ አስጠንቅቃቸው፣ይህ ምንም ጥቅም የሌለው የሚሰሙትንም የሚጎዳ ነው፡፡
\v 15 የእውነትን ቃል በትክክል የሚይዝ፣ የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነሀ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብ ትጋ፡፡
\s5
\v 16 እግዚአብሔርን ከመምሰል የሚያርቅህን አለማዊ ተረቶቸን አስወግድ፡፡
\v 17 ቃላቸው እንደ ቆላ ቁስል ነው፣ ከእነርሱም ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ ይገኙባቸዋል፣
\v 18 እነዚህም ሰዎች ከእውነት ርቀው ትንሣኤ ሙታነ ካሁን ቀደም ሆናል ይላሉ፣ በዚህም የአንዳንዶችን እምነት ይገለብጣሉ፡፡
\s5
\v 19 ሆኖም፣ ‹‹ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል›› ደግሞም ‹‹የጌታን ስም የሚጠራ ከዓመፃ ይራቅ›› የሚለው ማኅተም ያለበት የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል፡፡
\v 20 በሀብታም ቤት ውስጥ የሚገኙት የወርቅ እና የብር ዕቃዎች ብቻ አይደሉም ነገር ግን የእንጨት እና የሸክላ ዕቃዎችም ይገኛሉ፣ አንዳንዶቹ ለክብር ሌሎቹም ክብር ለማይሰጣቸው ሥራዎች ይውላሉ፡፡
\v 21 ማንም ከማያስከብር ሥራ ራሱን ቢያነጻ፣ የተከበረ ዕቃ፣ የተቀደሰ፣ ለጌታውም የሚጠቅም፣ ለማንኛውም መልካም ሥራ የተዘጋጀ ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 ከወጣትነት ምኞት ራቅ፣ በንጹህ ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፣ እምነትን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን ተከታተል፡፡
\v 23 ነገር ግን ጠብን እንደሚያመጣ አውቀህ ከሰነፎችና ካልተማሩ ምርመራ ራቅ፡፡
\s5
\v 24 የጌታ አገልጋይ ሊጣላ አይገባውም፣ ከዚሀ ይልቅ ለሁሉ የሚጠነቀቅ፣ ለማስተማርም የሚበቃ በትእግስትም የሚጸና፣
\v 25 በትህትናም ለሚቃወሙት ትምህርት የሚሰጥ ሊሆን ይገባዋል፡፡ እውነትን በማወቃቸው እግዚአብሔር ምናልባት ንስሐን ይሰጣቸው ይሆናልና፣
\v 26 እንዲሁም ለዲያብሎስ እና ለፈቃዱ ከተያዙበት ወጥመድ ተላቀው ወደ ኅሊናቸው ሊመለሱ ይችሉ ይሆናል፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ነገር ግን ይህን እወቅ፣ በመጨረሻዎቹ ቀናት አደገኛ ዘመን ይመጣል፡፡
\v 2 ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ፣ ገንዘብን የሚወዱ፣ ትእቢተኞች፣ ትምክህተኞቸ፣ በእግዚአብሔር ላይ የስድብን ቃል የሚናገሩ፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ ቅድስና የሌላቸው፣
\v 3 ተፈጥሮአዊ ፍቅር የሌላቸው፣ ሰላምን የማይፈጥሩ፣ ሐሜተኞች፣ ራሳቸውን የማይገዙ፣ አመጸኞች፣ መልካም የሆነውን የማይወዱ፣
\v 4 ከዳተኞች፣ ምክርን የማይሰሙ፣ በትእቢት የተነፉ፣ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 5 እግዚአብሔርን የመምሰል መልክ አላቸው ነገር ግን ኃይሉን ይክዳሉ፣ ከእነዚህ ሰዎች ራቅ፡፡
\v 6 ከእነዚህም አንዳንዶች በቤተ ሰብ ውስጥ ሾልከው እየገቡ በኃጢአት የሚገረሙትንና በልዩ ልዩ ምኞትም የሚነዱትን ሞኞችን ሴቶች ይማርካሉ፡፡
\v 7 እነዚህ ሴቶች ሁል ጊዜ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር ይሞክራሉ፣ ነገር ግን ፈጽሞ ወደ እውነት እውቀት ሊደርሱ አይችሉም፡፡
\s5
\v 8 ኢያኔስ እና ኢያንበሬስ ሙሴን እንደተቃወሙት፣ እነዚህ የስህተት አስተማሪዎች እውነትን ይቃወማሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች አዕምሮአቸው የተበላሸባቸው፣ የእምነታቸውም እውነተኝነት ያልተረጋገጠ ነው፡፡
\v 9 ዳሩ ግን የእነዚያ የሁለቱ ሰዎች ሞኝነት እንደተጋለጠ፣ እነዚህም ሞኝነታቸው ይገለጣልና አይሳካላቸውም፡፡
\s5
\v 10 አንተ ግን ትምህርቴን፣ አካሄዴን፣ ዓላማዬን፣ እምነቴን፣ መጽናቴን፣ ፍቅሬን፣ ትእግስቴን፣
\v 11 ስደቴን፣ መከራዬን፣ በአንጾኪያ፣ በኢቆንዮን እና በልስጥራን የደረሰብኝን ሁሉ ተከትለሃል፡፡ ይህን ሁሉ ስደት በጽናት አልፌዋለሁ፣ ጌታም ከሁሉ አዳነኝ፡፡
\v 12 በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔር እንደሚወደው ሊኖሩ የሚፈልጉ ሁሉ ይሰደዳሉ፡፡
\v 13 ከፉ ሰዎች እና አታላዮች በክፋት እየባሱ ሌሎችንም እያሳቱና ራሳቸውም ችየሳቱ ይሄዳሉ፡፡
\s5
\v 14 አንተ ግን በተማርህበትና በምታምንበት ነገር ጸንተህ ኑር፣ ከማን እንደተማርከው ታውቃለህና፡፡
\v 15 ከሕፃንነትህ ጀምሮ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ስለሚገኘው መዳን ጥበብ ሊሰጡህ ስለሚችሉት ቅዱሳት መጻሕፍት አውቀሃል፡፡
\s5
\v 16 በእግዚአብሔር የተገለጡ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ለመሠረተ እምነት፣ በእምነትም ለመጽናት፣ በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማሉ፣
\v 17 በመሆኑም የእግዚአብሔር ሰው ለመልካም ሥራ የተዘጋጀ እና የታጠቀ እንዲሆን ያደርጉታል፡፡
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 በእግዚአብሔር ፊት፣ በሕያዋንና በሙታን ሊፈርድ ባለው በክርስቶስ ኢየሱስ ፊት፣ በመገለጡና በመንግስቱ፣ አዝዝሃለሁ፣
\v 2 ቃሉን ስበክ ሲመችህም ሳይመችህም የተዘጋጀህ ሁን፡፡ እየታገስክና እያስተማርክ ዝለፍ፣ ገስጽ፣ ምከርም፡፡
\s5
\v 3 ሰዎች እውነተኛውን ትምህርት የማይታገሱበት ዘመን ይመጣል፣ ይልቁን፣ ለፍላጎታቸው የሚስማማቸውን የሚሰብኩአቸውን አስተማሪዎችን በዙሪያቸው ይሰበስባሉ፡፡ ይህም ጆሮቻቸውን የሚያሳክክላቸው ይሆናል፡፡
\v 4 ጆሮቻቸውን እውነትን ከመስማት ይመልሳሉ፣ ወደ ስህተትም ያዘነብላሉ፡፡
\v 5 አንተ ግን፣ በነገር ሁሉ የነቃህ ሁን፣ መከራን ተቀበል፣ የወንጌላዊነትን ሥራ አድርግ፣ አገልግሎትህንም ፈጽም፡፡
\s5
\v 6 እኔ እንደ መስዋዕት ልሰዋ ነው፡፡ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል፡፡
\v 7 መልካሙን ገድል ተጋድያለሁ፣ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፣ እምነቱንም ጠብቄአለሁ፡፡
\v 8 የጽድቅም አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንንም ጻድቅ ፈራጅ፣ የሆነው ጌታ፣ በዚያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፣ ለእኔ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን መገለጡን ለሚወዱ ሁሉ ነው፡፡
\s5
\v 9 ወደ እኔ በቶሎ ልትመጣ ትጋ፣
\v 10 ዴማስ ትቶኛልና፣ ይህንንም ዓለም ወድዶ ወደ ተሰሎንቄ ሄዶአል፡፡ ቄርቂስ ወደ ገላትያ፣ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል፡፡
\s5
\v 11 ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፡፡ ማርቆስን ይዘኸው ና እርሱ በሥራው እጅግ ይጠቅመኛል፡፡
\v 12 ቲኪቆስን ወደ ኤፌሶን ልኬዋለሁ፡፡
\v 13 ስትመጣ በጢሮአዳ የተውኩትን ልብሴን፣ ይልቁንም በብራና የተጻፉትን መጻሕፍት ይዘህልኝ ና፡፡
\s5
\v 14 መዳብ አንጥረኛው አሌክሳንደር እጅግ ከፋብኝ፡፡ ጌታ ስለ ክፉ ሥራው ዋጋውን ይከፍለዋል፡፡
\v 15 አንተም ደግሞ ከእርሱ ተጠበቅ፣ ቃላችንን እጅግ ተቃውሞአልና፡፡
\v 16 በፊተኛው የፍርድ ቤት ክርክሬ ከአኔ ጋር ማንም አልቆመም፣ ነገር ግን ሁሉም ተዉኝ፡፡ ይህንንም አይቁጠርባቸው፡፡
\s5
\v 17 ነገር ግን፣ አሕዛብ ሁሉ እንዲሰሙት፣ የወንጌሉ ስብከት በእኔ እንዲፈጸም፣ ጌታ በአጠገቤ ቆሞ አበረታኝ፣ ከአንበሳም አፍ ዳንኩኝ፡፡
\v 18 ጌታ ከክፉ ሥራዎች ሁሉ አውጥቶኛል፣ ለሰማያዊውም መንግሥቱ ይጠብቀኛል፡፡ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
\s5
\v 19 ለጵርስቅላና ለአቂላ ለሄኔሲፎሩ በተ ሰብ ሰላምታ አቅርብልኝ፡፡
\v 20 ኤርስጦስ በቆሮንቶስ ቀረ፣ ነገር ግን ጥሮፊሞስ ስለታመመ በሚሊጢን ተውኩት፡፡
\v 21 ከክረምት በፊት ልትመጣ ትጋ፡፡ ኤውግሎስና ጱዴስ፣ ሊኖስና ቅላውዲያም ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል፡፡
\v 22 ጌታ ከመንፈስህ ጋር ይሁን፡፡ ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡ አሜን፡፡

110
57-TIT.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,110 @@
\id TIT
\ide UTF-8
\h ቲቶ
\toc1 ቲቶ
\toc2 ቲቶ
\toc3 tit
\mt ቲቶ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ባሪያና፣የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነው ጳውሎስ፣ በእግዚአብሔር የተመረጡት ሰዎች እምነት እንዲጸና፣ እግዚአብሔርን ከመምሰል ጋር የሚስማማውን የእውነት እውቀት ለማፅናት፣
\v 2 የማይዋሽ እግዚአብሔር፣ በተረጋገጠ ዘላለማዊ ሕይወት ከዘመናት በፊት ተስፋን ሰጠ፣
\v 3 እንደ መድሃኒታችን እግዚአብሔር ትዕዛዝ፣ በትክክለኛው ጊዜ፣ ቃሉን ለእኔ አደራ በሰጠኝ መልዕክት ገለጠ፡፡
\s5
\v 4 የጋራችን በሆነ እምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለቲቶ። ከእግዚአብሔር አብ፣ከመድሃኒታችን ክርስቶስ ኢየሱስ ፀጋ፣ምህረትና ሰላም ለአንተ ይሁን።
\v 5 አንተን በቀርጤስ የተውኩበት ምክንያት፣ ያልተጠናቀቁትን ነገሮች እንድታስተካክልና፣ በነገርኩህ መሠረት በየከተማው ሁሉ ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው፡፡
\s5
\v 6 የቤተክርስቲያን ሽማግሌ፣ ነቀፋ የሌለበት፣የአንዲት ሚስት ባል፣ ከክፍዎችና ካልታረሙ ጋር ስማቸው የማይነሳ ታማኝ ልጆች ያሉት ሊሆኑ ይገባዋል።
\v 7 የቤተክርስቲያን ሽማግሌ የእግዚአብሔርን ቤት የሚያስተዳድር መሪ ስለሆነ ነቀፋ የሌለበት፣ የማይጮህ፣ራሱን የሚገዛ ፣የማይቆጣ ፣ለወይን ጠጅ የማይገዛ፣ የማይጣላና ስስታም ያልሆነ ሊሆን ይገባል።
\s5
\v 8 ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፣ መልካምን የሚወድ፣ ጠንቃቃ፣ ጻድቅ፣ መንፈሳዊና ራሱን የሚገዛ መሆን አለበት።
\v 9 በጤናማ ትምህርት ሌሎችን ለማበረታታት፣ የሚቃወሙትን ለመገሠጽ እንዲችል እውነተኛውን ትምህር አጥብቆ መያዝ ይኖርበታል።
\s5
\v 10 ሥርዓት የሌላቸው በተለይም ከተገረዙት ወገን የሆኑ ብዙዎች አሉ። ቃላቸው ከንቱ ነው። ሰዎችን ያስታሉ፣ በተሳሳተ መንገድም ይመራሉ።
\v 11 እነዚህን ዝም ማሰኘት ይገባል። ለነውረኛ ትርፍ ብለው ማስተማር የማይገባቸውን እያስተማሩ፣ መላ ቤተሰብን ያፈርሳሉ።
\s5
\v 12 ከነሱ ከራሳቸው ነብያት መካከል አንዱ፣ "የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፣ ክፉና አደገኛ አውሬዎች፣ ሰነፍ ሆዳሞች ናቸው" ብሏል፡፡
\v 13 ይህም አባባል ትክክል ነው፣ ስለዚህ ጤነኛ እምነት እንዲኖራቸው አጥብቀህ ገሥጻቸው ።
\s5
\v 14 ጊዜያቸውን በአይሁድ ተረትና፣ ከእውነት በራቁ ሰዎች ትዕዛዛት ላይ አያባክኑ።
\s5
\v 15 ንጹሆች ለሆኑት፣ ሁሉም ንጹህ ነው፣ ለርኩሶችና ለማያምኑ ግን ንጹህ የሆነ ምንም የለም። ይልቁን፣ አዕምሯቸውና ሃሳባቸው እንኳ የረከሰ ነው፡፡
\v 16 እግዚአብሔር እንደሚውያቁ ይናገራሉ፣ በሥራቸው ግን ይክዱታል። የሚያስጸይፉ የማይታዘዙና፣ ለመልካም ስራም የማይበቁ ናቸው፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 አንተ ግን፣ ከጤናማው ትምህርት ጋር የሚስማማውን ተናገር።
\v 2 በእድሜ የገፋ ሰዎች ልከኞች፣ ጨዋዎች፣ ጠንቃቆች ጤናማ እምነት፣ ፍቅርና ጽናት ያላቸው ሊሆኑ ይገባችዋል፡፡
\s5
\v 3 በእድሜ የገፉ ሴቶችም እንዲሁ ጨዋዎችና፣ ከሃሜት የራቁ መሆን አለባቸው፡፡ ወይን ጠጅ ጠጪዎች መሆን አይገባቸውም። መልካም የሆነውን ማስተማር ይገባችዋል
\v 4 ወጣት ሴቶችን በአስተሳሰባቸው ሚዛናዊ እንዲሆኑ እንዲያሳስቧቸው፣ የገዛ ባሎቻቸውና ልጆቻቸውን የሚወዱ፣ ጠንቃቃ እንዲሆኑ እንዲያበርቷቷቸው፣
\v 5 የእግዚአብሔር ቃል እንዳይሰደብ ንፁህ፣ መልካም የቤት አስተዳዳሪና፣ ለባሎቻቸውም የሚታዘዙ ይሁኑ።
\s5
\v 6 በተመሳሳይ መንገድ፣ ወጣት ወንዶች ጠንቃቆች እንዲሆኑ አሳስባቸው።
\v 7 በነገር ሁሉ ራስህን የመልካም ሥራ ምሳሌ አድርገህ ተገኝ፤ በትምህርትም ንጽህናን፣ ጨዋነት፣ የማይነቀፍ ጤናማ ቃላት ይኑርህ።
\v 8 ስለ እኛ የሚናገረው ምንም ክፉ ነገር እንዳይኖር። የማይነቀፍ ስህተት የሌለበትን፣ ነገር ግን ሊቃወም የሚሞክረውን የሚያሳፍር ቃላትን ተናገር።
\s5
\v 9 ባሪያዎች በሁሉም ነገር ለጌቶቻቸው ይታዘዙ። ጌቶቻቸውን ደስ ሊያሰኟቸው ይሞክሩ እንጂ፣ አይከራከሯቸው።
\v 10 ስለ መድሃኒታችን እግዚአብሔር የምናስተምረው፣ በሁሉ መንገድ የሚማርክ እንዲሆን፣ ታማኝነትን ያሳዩ እንጂ አይስረቁ።
\s5
\v 11 ሰዎችን ሁሉ ሊያድን የሚችለው የእግዚአብሔር ፀጋ ተገልጧል፡፡
\v 12 ይህም ፀጋ ሃጢዓተኝነትና ዓለማዊ ምኞትን እንድንክድና፣ በአሁኑ ዘመን በጥንቃቄ፣ በጽድቅና፣ እግዚአብሔርን በመምሰል እንድንኖር ያስለምደናል
\v 13 ይህም የተባረከውን ተስፋችንን፣ የታላቁን አምላካችንና አዳኛችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ፣ ለመቀበል በደስታ እንድንጠባበቅ ነው።
\s5
\v 14 ኢየሱስ ራሱን ለእኛ የሰጠው፣ ከዓመፅ ነፃ ሊያወጣንና ሊያነፃን፣ ገንዘቡና መልካምን ለማድረግ የሚናፍቅ ሕዝብ፣ ለራሱ ሊያደርገን፣ ዋጋ ለመክፈል ነው።
\s5
\v 15 እነዚህን ነገሮች ተናገር፣ አበረታታ፣ በሙሉ ስልጣን ገስጽ፣ ማንም አይናቅህ።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ለገዢዎችና ለባለሥልጣኖች እንዲገዙ፣ እንደታዘዟቸው፣ ለበጐ ሥራ ሁሉ የተዘጋጁ እንዲሆኑ፣
\v 2 ማንንም እንዳይሳደቡ፣ የሌሎችንም ፈቃድ እንዲያከብሩ እንጂ እንዳይከራከሩ፣ ለሁሉም ሰው ትህትን እንዲያሳዩ አሳስባቸው።
\s5
\v 3 እኛም ቀድሞ የማናስተውልና የማንታዘዝ ነበርን። የሳትንና የተለያዩ ምኞቶቻችንና ፍላጐቶቻችን ባሪያዎች ነበርን። በክፋትና በምቀኝነት እንኖር ነበር። የተጠላንና እርስበርስ የምንጠላላ ነበርን።
\s5
\v 4 ነገር ግን፣ የመድሃኒታችን የእግዚአብሔር ርህራሔና ለሰው ልጅ ያለው ፍቅር በተገለጠ ጊዜ፣
\v 5 ከምህረቱ የተነሳ፣ በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታድስ አዳነን እንጂ፣ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ምክንያት አይደለም።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል፣ አብዝቶ መንፈስ ቅዱስን አፈሰሰልን።
\v 7 ይህም በፀጋው ፀደቅን፣ የዘላለም ህይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን ነው።
\s5
\v 8 እነዚህ ቃሎች የታመኑ ናቸው። በእግዚአብሔር የሚያምኑ እርሱ በፊታቸው ላኖረው መልካም ሥራ እንዲተጉ፣ እነዚህን ነገሮች በድፍረትት እንድትናገር እፈልጋለሁ። እነዚህ ነገሮች መልካምና ለሰዎች ሁሉ የሚጥቅሙ ናቸው።
\s5
\v 9 ነገር ግን ከከንቱ ክርክር፣ ከዘር ቆጠራና በህግ ጉዳይ ከሚሆን ጸብና ግጭት ራቅ። እነዚህ ነገሮች፣ የማይገቡና የማይጠቅሙ ናቸው፡፡
\v 10 አንዴ ወይም ሁለቴ ካስጠነቀቅከው በኋላ፥ በመካከሃላችሁ መከፋፈል የሚፈጥረውን ሰው አስወግደው፡፡
\v 11 እንዲህ ዓይነቱ ሰው፣ ከእውነተኛው መንገድ የወጣ፣ ሃጢያት የሚያደርግና በራሱ የፈረደ እንደሆነ እወቅ።
\s5
\v 12 አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፣ ክረምቱን ለማሳለፍ ወደ ወሰንኩበት ወደ ኒቆሊዎን ፈጥነህ ና።
\v 13 የህግ ባለሞያውን፣ ዜማስንና አጵሎስን የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ሰጥተህ ቶሎ ላካቸው።
\s5
\v 14 ወገኖቻችንም እለታዊ ፍላጎታቸውን ማግኛት እንዲችሉ ፍሬ ቢስም ሆነው እንዳይገኙ፣ መልካም ሥራ ማድረግን መማር አለባቸው።
\s5
\v 15 ከኔ ጋር ያሉት ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡልሃል ። የሚወዱንን አማኞችን ሁሉ ሰላም በልልን። ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፡፡አሜን።

51
58-PHM.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,51 @@
\id PHM
\ide UTF-8
\h ፊልሞና
\toc1 ፊልሞና
\toc2 ፊልሞና
\toc3 phm
\mt ፊልሞና
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ስለክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ የሆነው ጳውሎስ ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ ጋር ለተወደደው ወንድማችንና የሥራ አጋራችን ለሆነው ለፊሊሞና፣
\v 2 ለእህታችን ለአፒፊያ፣አብሮን ወታደር ለሆነው ለአክሪፋ እንዲሁም በቤትህ ላለችው ቤተክርስቲያን፡
\v 3 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሠላም ለእናንተ ይሁን።
\s5
\v 4 በጸሎቴ ሁሉ ስላንተ እያነሳሁ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ።
\v 5 ምክንያቱም በጌታ በኢየሱስ ስላለህ እምነት ለቅዱሳንም ሁሉ ስላለህ ፍቅር ሰምቻለሁ።
\v 6 በክርስቶስ በኩል የመልካም ነገር ሁሉ እውቀት በእኛ ውስጥ ስላለ በእምነት ያለህ ተካፋይነት ውጤታማ እንዲሆን እጸልያለሁ።
\v 7 ወንድሜ ሆይ፣ ለዚህም ምክንያቱ የቅዱሳን ሁሉ ልብ በአንተ በማረፉ ምክንያት በፍቅርህ በጣም ደስ ስላለኝና ስለተጽናናሁ ነው።
\s5
\v 8 ስለዚህም ምንም እንኳ ምን ማድረግ እንዳለብህ በክርስቶስ ለማዘዝ ድፍረት ቢኖረኝም
\v 9 በዚህ ፈንታ እንደ ሽማግሌው አሁን ደግሞ ስለ ክርስቶስ እስረኛ እንደሆነው ጳውሎስ በፍቅር እለምንሀለሁ።
\s5
\v 10 ልመናዬ በእስርቤት አባት ስለሆንኩት ስለ ልጄ ኦኖሲሞስ ነው።
\v 11 ምክንያቱም ቀድሞ ለአንተ የማይጠቅም አሁን ግን ለአንተም ለእኔም ጠቃሚ በመሆኑ ነው።
\v 12 የልቤ የሆነውን እርሱን ወደ አንተ ልኬዋለሁ።
\v 13 በእኔ በኩልስ አንተን ወክሎ ስለ ወንጌል በእስር ቤት ያለሁትን ያገለግለኝ ዘንድ እኔ ጋ ቢቀር እወድ ነበር።
\s5
\v 14 ነገር ግን መልካም ሥራህ በግድ ሳይሆን በፈቃድህ ይሆን ዘንድ ያለ አንተ ፈቃድ ምንም ማድረግ አልፈለግሁም።
\v 15 ለጥቂት ጊዜ ከአንተ ተለይቶ የነበረው ምናልባት ለዘላለም የአንተ ይሆን ዘንድ ነው ።
\v 16 ነገር ግን ከዚህ በኋላ ከባሪያ የተሻለ እንደተወደደ ወንድም እንጂ እንደባሪያ አይደለም፥ በተለይ ለእኔ የተወደደ ከሆነ ለአንተማ በሥጋም በጌታም የበለጠ ይሆናል።
\s5
\v 17 እንግዲህ እንደ አጋርህ ከቆጠርከኝ እንደኔ አድርገህ ተቀበለው።
\v 18 ነገር ግን በምንም መልኩ አሳዝኖህ ቢሆን ወይም ዕዳ ቢኖርበት በእኔ ላይ ቁጠረው።
\v 19 እኔ ጳውሎስ እኔ እከፍላለሁ ብዬ በገዛ እጄ ጽፌአለሁ።የገዛ ህይወትህ እንኳ የኔ ነው ብዬህ አላውቅም።
\v 20 አዎ ወንድሜ ሆይ እስኪ በጌታ ደስ ይበለኝ፥ ልቤም በክርስቶስ ይጽናና።
\s5
\v 21 እንደምትታዘዘኝ በመተማመን ካልኩህም በላይ እንደምታደርግ ስለማውቅ ጽፌልሀለሁ።
\v 22 በነገራችን ላይ ከጸሎታችሁ የተነሳ ወደ እናንተ እንደምመጣ ተስፋ ስለማደርግ አንድ የእንግዳ ክፍል አዘጋጅልኝ።
\s5
\v 23 ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ አብሮኝ የታሰረው ኤጳፍራ
\v 24 እንዲሁም የሥራ አጋሮቼ ማርቆስ፣አርስጥሮኮስ፣ዴማስና ሉቃስ ሠላምታ ያቀርቡልሀል።
\v 25 የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከመንፈሳችሁ ጋር ይሁን። አሜን!

591
59-HEB.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,591 @@
\id HEB
\ide UTF-8
\h ዕብራዊያን
\toc1 ዕብራዊያን
\toc2 ዕብራዊያን
\toc3 heb
\mt ዕብራዊያን
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከረጅም ጊዜ በፊት በተለያዩ ዘመናትና በተለያዩ መንገዶች እግዚአብሔር በነቢያት በኩል ለአባቶቻችን ተናግሮ ነበር።
\v 2 አሁን ግን የሁሉም ነገር ወራሽ ባደረገው፣ ዓለምንም በፈጠረበት በልጁ ተናገረን።
\v 3 ልጁ የክብሩ ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም አንድ ነው፤ በሥልጣን ቃል ሁሉን ደግፎ ይዞአል። የሰዎችንም ኃጢአት ካነዳ በኃላ በሰማይ በግርማው ቀኝ ተቀምጧል።
\s5
\v 4 እርሱ የወረሰው ስም ከሰማቸው እጅግ የላቀ በመሆኑ፣ ከመላእክትም የበለጠ ሆኖአል።
\v 5 ለመሆኑ፣ ከመላክት መካከል፣ “አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ” ደግሞስ፣ “እኔ አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል” ያለው ለማን ነው?
\s5
\v 6 የበኩር ልጁን ወደ ዓለም ሲያስገባ እግዚአብሔር፣ “የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት” ብሏል።
\v 7 ስለ መላእክቱ ግን፣"መላዕክቱን ነፋሳት፥ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል" ይላል።
\s5
\v 8 ስለ ልጁ ግን፣ “አምላክ ሆይ፣ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ነው፤ የመንግሥትህም በትር የጽድቅ በትር ነው።
\v 9 ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፅንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ” ብሏል።
\s5
\v 10 እንዲሁም፣ “ጌታ ሆይ፣ በመጀመሪያ ምድርን ፈጠርህ፤ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።
\v 11 እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ትኖራለህ። ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ።
\v 12 እንደ መጎናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።
\s5
\v 13 በየትኛውም ጊዜ ነበር እግዚአብሔር ከመላእክቱ ለአንዱ፣ “ጠላቶችህን ከእግርህ በታች እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው?
\v 14 ታድያ፣ መላእክት ሁሉ እኔን እንዲያመልኩና ድነት የሚወርሱትን ለመርዳት ተተላኩ መንፈሶች አይደሉምን?
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ስለዚህ ከሰማነው ነገር እንዳንወሰድ፣ ስለ ሰማነው ነገር ይበልጥ መጠንቀቅ አለብን።
\s5
\v 2 በመላእክት አማካይነት የመጣው መልእክት ጽኑ ከሆነና፣ ማንኛውም መተላለፍና ዐመፅ ተገቢውን ቅጣት የሚቀበል ከሆነ።
\v 3 ታዲያ፣ይህንን ታላቅ መዳን ቸል ካልን እንዴት ማምለጥ እንችላለን?
\v 4 እግዚአብሔርም ምልክቶችን፣ ድንቆችንና የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ፣እንደ ፈቃዱ በታደሉት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎች አማካይነት ምስክርነታቱን አጽንቶአል።
\s5
\v 5 ይህ እየተናገርንለት ያለውን ወደ ፊት የሚመጣውን ዓለም እግዚአብሔር ለመላእክት አላስገዛም።
\v 6 እንዲያውም በቅዱሳት መጻህፍት አንድ ሰው አንድ ስፍራ ሲናገር፣
\s5
\v 7 ሰውን ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው የክብርና የምስጋና ዘውድ ጫንህለት።
\f + \ft አንዳንድ ቅጆች “…በእጆችህ ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው” የሚል ይጨምራሉ። \f*
\v 8 ማንኛውንም ነገር ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት” ብሏል። እግዚአብሔር ከእግሩ በታች ሲያስገዛለት ምንም ያላስገዛለት ነገር የለም። ነገር ግን በእሁኑ ጊዜ ሁሉም ነገር ተገዝቶለት ገና አናይም።
\s5
\v 9 ይሁን እንጂ፣ ከመከራውና ከሞቱ የተነሣ ከመላእክቱ በጥቂቱ አንሶ የነበረውን ኢየሱስ፣ የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖለት እናያለን። በእግዚአብሔር ጸጋ እርሱ ለሰው ሁሉ ሞትን ቀምሷል።
\v 10 ሁሉም በእርሱና ለእርሱ የሚኖር ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ለማምጣት የድነታቸውን መሥራች በመከራው አማካይነት እግዚአብሔር ፍጹም ሊያደርገው ተገቢ ሆነ።
\s5
\v 11 የሚቀድሰውም ሆነ የሚቀደሱት ሁለቱም ከአንዱ ምንጭ፣ ከእግዚአብሔር ናቸው። በዚህም ምክንያት የሚቀድሳቸው እርሱን ወንድሞቼ ብሎ ሊጠራቸው አላፈረም።
\v 12 እንዲያውም፣
\s5
\v 13 እንዲሁም፣ “እኔ በእርሱ እታመናለሁ” ይላል። በተጨማሪ፣ “እነሆ እኔንና እግዚአብሔር የሰጠኝን ልጆች ተመልከቱ” ብሏል።
\v 14 ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በሥጋና ደም ስለሆኑ፣ በሞቱ አማካይነት ሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ማለትም ዲያብሎስን ለመሻር ኢየሱስም እንደ እነርሱ ሥጋ ለብሶ።
\v 15 ይህም የሆነው ዕድሜ ልካቸውን በሞት ፍርሃት ምክንያት ዕድሜ ልካቸውን ባርነት ውስጥ የነበሩትን ሁሉ ነጻ ለማውጣት ነው።
\s5
\v 16 እርግጥም እየረዳቸው ያለው መላእክትን ሳይሆን፣ የአብርሃም ዘሮችን ነው።
\v 17 ስለሆነም የእግዚአብሔር በሆነ ነገር ሁሉ መሓሪና ታማኝ ሊቀ ካህን ለመሆንና ለሰዎችም ሁሉ የኃጢአት ይቅርታን ለማስግገኘት በሁሉም ረገድ ወንድሞችን መምሰሉ አስፈላጊ ሆነ።
\v 18 ኢየሱስ ራሱ መከራ የተቀበለና የተፈተነ በመሆኑ፣ የሚፈተኑትን ሁሉ ሊረዳቸው ይችላል።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ስለዚህ የሰማያዊ ጥሪ ተከፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች የእምነታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት የሆነውን ኢየሱስን አስቡ።
\v 2 ሙሴ በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ ላይ ታማኝ እንደ ነበር ሁሉ፣ እርሱም ለሾመው ለእግዚአብሔር ታማኝ ነበር።
\v 3 ቤቱን የሚሠራው ከራሱ ከቤቱ የበለጠ ክብር እንዳለው ሁሉ፣ ኢየሱስም ከሙሴ ይልቅ የበለጠ ክብር እንደሚገባው ተቆጥሯል።
\v 4 ማንኛውም ቤት ሠሪ አለው፤ ሁሉም ነገር የሠራ ግን እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 5 ወደ ፊት መነገር ለሚገባው ነገር ምስክር እንዲሆን፣ ሙሴም በእግዚአብሔር ቤት ሁሉ እንደ አገልጋይ ታማኝ ነበር።
\v 6 ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ሥልጣን ያለው ልጅ ነው። የምንተማመንበትንና የመተማመናችንን ድፍረት አጥብቀን ብንይዝ ቤቱ ነን።
\s5
\v 7 ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ፣ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ
\v 8 በምድረበዳ በፈተና ቀን በአመጽ እንዳደረጋችሁት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ።
\s5
\v 9 ይህ የሆነው አባቶቻችሁ እኔን በመፈታተን ሲያምፁብኝና ዐርባ ዓመት ሙሉ ሥራዎቼን ባዩበት ጊዜ ነበር።
\v 10 ስለዚህ በዚያ ትውልድ ደስ አልተሰኘሁም። እንዲህም አልኩ፤ ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል መንገዴንም አላወቁም።
\v 11 ስለዚህ በቁጣዬ፥ "ወደ እረፍቴ አይገቡም" ብዬ ማልሁ።
\s5
\v 12 ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ማንም የማያምን ክፉና ከሕያው እግዚአብሔር ዘወር የሚል ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።
\v 13 ይልቁንስ ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልኸኛ እንዳይሆን ከዛሬ ጀምሮ በየዕለቱ እርስ በርሳችሁ ተበረታቱ።
\s5
\v 14 ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ በእርሱ ያለንን ድፍረት አጥብቀን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ተባባሪዎች እንሆናለን።
\v 15 ስለዚህም፣ "ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ በአመጽ ጊዜ እንደሆነው ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ" ተብሏል።
\s5
\v 16 ለመሆኑ፣እነዚያ ድምፁን ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ እየመራ ከግብፅ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን?
\v 17 ለአርባ ዓመት እግዚአብሔር የተቆጣባቸውስ እነማን ነበሩ? ኃጢአት ያደረጉና ሬሳቸው በበረሃ ወድቆ የቀረው አይደሉምን?
\v 18 ደግሞስ እነዚያ ያልታዘዙት ካልሆኑ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንደማይገቡ እግዚአብሔር የማለባቸው እነማን ሊሆኑ ነው?
\v 19 ባለማመናቸው ምክንያት ወደ ዕረፍቱ ሊገቡ እንዳልቻሉ እናያለን።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ከእናንተ ማንም የእግዚአብሔር ዕረፍት ከሆነው ዘላቂ ተስፋ የሚጎድል እንዳይመስለው በጣም መጠንቀቅ አለብን።
\v 2 ምክኒያቱም ለእስራኤላውያን እንደ ተነገረ ሁሉ ለእኛም ስለ እግዚአብሔር ዕረፍት መልካም ዜና ተነግሮናል፤ ሆኖም፣ የሰሙትን መልእክት ሰሞዎቹ በእምነት ስላልተቀበሉት አልጠቀማቸውም።
\s5
\v 3 “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም፣ ብዬ በቁጣዬ ማልሁ” እንዳለው ሳይሆን እኛ ያመንን ግን ወደ ዕረፍቱ እንገባለን። የእርሱ ፍጥረት ሥራ ከዓለም መፈጠር ጀምሮ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣
\v 4 ስለ ሰባተኛ ቀን በማመልከት አንድ ቦታ “በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከሥራው ሁሉ ዐረፈ” ይላል።
\v 5 ደግሞም፣ “ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ይላል።
\s5
\v 6 ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት ለመግባት ለአንዳንዶች አሁንም የተጠበቀባቸው በመሆኑና ፣ መልካሙን ዜና ከሰሙት እስራኤላውያን ብዙዎቹ ባለ መታዘዛቸው ምክንያት ወደ ዕረፍቱ ባለ መግባታቸው እግዚአብሔር በድጋሚ፣
\v 7 “ዛሬ” የተባለ ቀን ወስኖአል።
\s5
\v 8 ኢያሱ አሳርፎአቸው ቢሆን ኖሮ፣ እግዚአብሔር ስለ ሌላ ቀን አይናገርም ነበር።
\v 9 ስለዚህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ አሁንም ቢሆን የሰንበት ዕረፍት ተጠብቆላቸዋል።
\v 10 ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት የገባ ሰው እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ ሁሉ፣ እርሱም ከሥራው ያርፋል።
\v 11 ስለዚህ ማንም የእነዚያን ሰዎች ዐመፅ ተከትሎ እንዳይወድቅ ወደዚያ ዕረፍት ለመግባት እንናፍቅ።
\s5
\v 12 የእግዚአብሔር ቃል ሕያው፣ የሚሠራና፣ ሁለት አፍ ካለው ሰይፍ ይልቅ፣ ስለታም ነው። ነፍስንና መንፈስን፣ ጅማትንና ቅልጥምን እስኪለያይ ድረስ ይወጋል። የልብን ሐሳብና ውስጥን ይመረምራል።
\v 13 ከእግዚአብሔር ፊት የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም። እኛ ተጠያቂዎች በሆንንበት በእርሱ ዓይኖች ፊት ማንኛውም ነገር የተገለጠና የተራቆተ ነው።
\s5
\v 14 እንግዲህ በሰማያት ያለፈ ታላቅ ሊቀ ካህናት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ስላለን፣ እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ።
\v 15 ነገር ግን እርሱ ከኃጢአት በቀር በማንኛውም ነገር እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንምና።
\v 16 ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 እያንዳንዱ ሊቀ ካህን ከሰዎች መካከል ይመረጣል፤ ለኃጢአት መሥዋዕትንና መባን ለማቅረብ እግዚአብሔርን በሚመለከት ጉዳይ እነርሱን በመወከል ይሾማል።
\v 2 እርሱ ራሱም በድካም ውስጥ ያለ በመሆኑ ዐላዋቂዎችንና ከመንገድ የሳቱትን ሊራራላቸው ሊቀበላቸው ይችላል።
\v 3 ከዚህም የተነሣ ለሕዝቡ ኃጢአት እንደሚያድርገው ሁሉ እርሱም ለገዛ ራሱ ኃጥአት መሥዋዕት ማቅረብ ይኖርበታል።
\s5
\v 4 እንደ አሮን በእግዚአብሔር የተጠራ ካልሆነ በቀር ማንም ይህን ክብር በራሱ አያገኘውም።
\v 5 ክርስቶስ ራሱም ቢሆን ሊቀ ካህናት የመሆንን መብት በገዛ ራሱ አልወሰደም። ይልቁንም እግዚአብሔር ለእርሱ፣
\s5
\v 6 ይህም በሌላ ቦታ፣ እግዚአብሔር፣እንደመልከጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ" ይላል።
\s5
\v 7 ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በነበረ ዘመን ፣ ከሞት ሊያድነው ወደሚችለው አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ። እግዚአብሔርን በመፍራቱም ጸሎቱ ተሰማለት።
\v 8 ምንም እንኳ እርሱ ልጅ ቢሆንም፣ ከደረሰበት መከራ የተነሣ መታዘዝን ተማረ።
\s5
\v 9 በዚህ ሁኔታ ሁሉ የዘላለም ድነት ምክንያት ሆነላቸው፤
\v 10 እግዚአብሔርም እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት አድርጎ ሾመው።
\v 11 ስለ ኢየሱስ ብዙ የምንናገረው አለን፤ ሆኖም፣ ለመቀበል ዳተኞች ስለሆናችሁ፣ ለእናንተ ማስረዳት አዳጋች ነው።
\s5
\v 12 እስከ አሁን ድረስ መምህራን መሆን ሲገባችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረታዊ መርሖዎች የሚያስተምራችሁ ሰው ገና ትፈልጋላችሁ። እናንተ የምትፈልጉት ወተት እንጂ፣ ጠንካራ ምግብ አይደለም።
\v 13 ወተት ብቻ ሊጋት ማንኛውም ሰው ገና ሕፃን ስለሆነ የጽድቅ ትምህርት ልምምድ የለውም።
\v 14 በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ ምግብ ግን መልካምንና ክፉውን መለየት ለተማሩና ትክክል የሆነውን ካልሆነው የመለየት ልምድ ላላቸው ትልልቅ ሰዎች ነው።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ስለዚህ ስለ ክርስቶስ መልእክት በመጀመሪያ የተረዳነውን ተወት በማድረግ ወደ ብስለት ልንሻገር ይገባናል እንጂ ከሞተ ሥራ ንስሐ መግባትንና በእግዚአብሔር ማመንን፣
\v 2 ወይም ጥምቀቶችን፣እጆች መጫንን፣ የሙታን ትንሳኤን እንዲሁም የዘላለም ፍርድን ወደ ሚመለከት መሠረትን የመጣል ትምህርት መመለስ አይገባንም።
\v 3 እግዚአብሔር ከፈቀደ እነዚህንም እናደርጋለን
\s5
\v 4 ይህንን የምናደርገው አንድ ጊዜ ብርሃን በርቶላቸው ሰማያዊውን ስጦታ የተቀበሉትን፣ከመንፈስ ቅዱስ ተሳታፊዎች የነበሩትን፣
\v 5 መልካሙን የእግዚአብሔር ቃልና በመጪው ዘመን ሊመጣ ያለውን ኃይል ከቀመሱ በኃላ
\v 6 የካዱትን በንስሐ እንዲታደሱ ማድረግ የማይቻል በመሆኑ ነው። እነዚህ ለሕዝብ መሳለቂያ ይሆን ዘንድ ራሱን የእግዚአብሔርን ልጅ ራሳቸው እንደገና ይሰቅሉታል።
\s5
\v 7 በእርሷ ላይ ብዙ ጊዜ የሚዘንበውን ዝናብ ተቀብላ ለደከሙባት የሚጠቅም ፍሬን የምታፈራ መሬት ከእግዚአብሔር በረከትን ትቀበላለች።
\v 8 እሾህና አሜኬላ የምታበቅል ከሆነች ግን ዋጋ ቢስና እርግማን የሚጠብቃት ትሆናለች፣ ፍጻሜዋም መቃጠል ይሆናል።
\s5
\v 9 እንደዚህ የምንናገር ብንሆንም፣ ወዳጆች ሆይ፣ እናንተንና ድነታችሁን በሚመለከት ግን የተሻለ ነገር ስለ መኖሩ እርግጠኞች ነን።
\v 10 ምክንያቱም ቅዱሳንን በማገልገላችሁና አሁንም እያገለገላችኋቸው በመሆኑ ለስሙ ያላችሁን ፍቅር በማሳየት የሠራችሁትን ሥራ ይረሳ ዘንድ እግዚአብሔር ዓመፀኛ አይደለም።
\s5
\v 11 በፍጹም የመተማመን ዋስትና እያንዳንዳችሁ ይህንኑ ትጋት እስከመጨረሻ እንድታሳዩ በእጅጉ እንናፍቃለን።
\v 12 ከእምነትና ከትዕግሥት የተነሣ የተስፋ ቃሉን የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ቸልተኞች እንድትሆኑ አንፈልግም።
\s5
\v 13 ምክንያቱም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተስፋ ቃል በገባለት ጊዜ ከራሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ
\v 14 “በእርግጥ እባርክሃለሁ፣ ዝርያዎችህንም እጅጉን አበዛለሁ” በማለት በራሱ ምሎአልና።
\v 15 በዚህ መንገድ በትዕግሥት ከጠበቀ በኃላ ተስፋ የተገባለትን ተቀበለ።
\s5
\v 16 ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው ይምላሉና፣ በመካከላቸው ለሚፈጠርውም ለማንኛውም ሙግት መሐላ የመጨረሻው ማጽኛ ነው።
\v 17 የዓለማውን የማይለወጥ ባሕርይ ለተስፋው ወራሾች ይበልጥ ግልጽ አድርጎ ለማሳየት እግዚአብሔር በወሰነ ጊዜ በመሃላ አጸናው።
\v 18 ይህንን ያደረገው እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይችልባቸው ሁለት የማይለወጡ ነገሮች በፊታችን ያለውን መተማመኛ አጥብቀን ይዘን አምባ ፍለጋ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ነው።
\s5
\v 19 ከመጋረጃው በስተጀርባ ወዳለው ቅድስት የሚገባውና እኛ የያዝነው ይህ መተማመኛ፣ ሥጋት የሌለበትና አስተማማኝ የነፍሶቻችን መልሕቅ ነው።
\v 20 በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት ለዘላለም ሊቀ ካህናት በመሆን ኢየሱስ ወደዚህ ስፍራ ለእኛ ቀዳሚ በመሆን ገብቷል።
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 የሳሌም ንጉሥና የልዑል እግዚአብሔር ካህን የነበረው ይህ መልኬ ጼዴቅ የባረከው አብርሃምን ነገሥታቱን ድል አድርጎ ሲመለስ ነበር።
\v 2 አብርሃምም ከማረጀው ከማንኛውም ነገር አንድ አሥረኛውን ለእርሱ ሰጠው። ‘መልኬ ጼዴቅ’ የሚለውም የስሙ ትርጉም ‘የጽድቅ ንጉሥ’ ደግሞም ‘የሳሌም ንጉ’ ማለትም ‘የሰላም ንጉሥ’ ማለት ነው።
\v 3 እርሱ አባትም ሆነ እናት፣ የትውልድ ሐረግም ሆነ የጅማሬ ወይም የፍጻሜ አመን የሌለው ነው። ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ልጅ ሁሉ እርሱም ካህን ሆኖ ለዘላለም ይኖራል።
\s5
\v 4 ይህ ሰው እንግዲህ ምን ያህል ታላቅ እንደነበረ አስቡ። አባታችን አብርሃም በጦርነት ካገኛቸው ምርጥ ነገሮች አንድ አሥረኛ የሚሆነውን ሰጥቶታል።
\v 5 በእርግጥ የክህነቱን አገልግሎት የተቀበሉትም የሌዊ ዝርያዎች ከአብርሃም ዝርያ የተገኙ ቢሆኑም ከሕዝቡ ማለትም ከእስራኤላውያን ወገኖቻቸው አሥራትን ይሰበስቡ ዘንድ በሕጉ ታዘዋል።
\v 6 ይሁን እንጂ የሌዊ ዝርያ ያልነበረው መልኬ ጼዴቅ የተስፋ ቃሎች ከነበሩት ከአብርሃም አሥራትን ተቀበለ፣ ባረከውም።
\s5
\v 7 ታናሹ በታላቁ እንደሚባረክ የሚካድ ነገር አይደለም።
\v 8 በአንድ በኩል ስናየው አሥራትን የሚቀበሉ ሰዎች አንድ ቀን ይሞታሉ በሌላ በኩል ስንመለከተው ግን ከአብርሃም አሥራትን የተቀበለው ሕያው ሆኖ እንደሚኖር ተገልጿል።
\v 9 በሌላ አነጋገር አሥራትን ይቀበል የነበረው ሌዊ እንኳን በአብርሃም በኩል አሥራትን ሰጥቷል።
\v 10 ምክንያቱም መልኬ ጼዴቅ አብርሃምን ባገኘው ጊዜ ሌዊ በቀደምት አባቱ በአብርሃም አብራክ ውስጥ ነበረና።
\s5
\v 11 ሕዝቡ ሕጉን የተቀበሉት በዚህ ሥርዓት በነበሩ ጊዜ ነበርና ፍፁምና በሌዊ ክህነት ማግኘት የሚቻል ቢሆን ኖሮ በአሮን ሥርዓት ሳይሆን በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት የሚሾም ሌላ ካህን ወደፊት ይነሳ ዘንድ ምን ያስፈልግ ነበር?
\v 12 ክህነቱ የሚለውጥ ከሆነ ደግሞ ሕጉም መለወጥ ይገባዋል።
\s5
\v 13 እነዚህ ነገሮች እየተነገሩለት ያለው ከወገኖቹ ከቶ ማንም በመሠዊያው ላይ አገልግሎ የማያውቅ የሌላ ነገድ ወገን ነውና።
\v 14 እንግዲያውስ ጌታችን ካህናትን በሚመለከት ሙሴ ከቶውንም ምንም ካልተናገረለት ከይሁዳ ነገድ የመጣ መሆኑ ግልጽ ነው።
\s5
\v 15 መልከ ጼዴቅን የመሰለ ሌላ ካህን ቢነሳ የምንለው ይበልጥ ግልጽ ይሆናል።
\v 16 ይሄኛው ካህን ደግሞ ሰብዓዊ ዝርያን መሠረት በሚያደርገው ሕግ ሳይሆን የማይጠፋ የሕይወት ያይልን መሠረት ባደረገ ሕግ ካህን የሆነ ነው።
\v 17 ቅዱሳት መጻሕርትም ስለ እርሱ እንዲህ ሲሉ ይመሰክራሉ፦ “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘላለም ካህን ነህ”
\s5
\v 18 የቀደመው ትዕዛዝ ገለል የተደረገው ደካማና የማይጠቅም በመሆኑ ነውና።
\v 19 ሕጉ ፍጹም ያደረገው ምንም ነገር አልነበረምና። ይሁን እንጂ ከዚህ በኃላ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ መተማመኛ አለ።
\s5
\v 20 ይሄኛው የተሻለው መተማመኛ ግን ያለ መሃላ እውን አልሆነም፣ ምክንያቱም እነዚህ ሌሎቹ ካህናት ምንም መሃላ አልፈጸሙም።
\v 21 “ጌታ ምሎአል ሃሳቡንም አይቀይርም፤ ‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ’” ተብሎ እንደተጻፈ።
\s5
\v 22 በዚህም ደግሞ ኢየሱ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል።
\v 23 በእርግጥም ሞት ካህናቱን ለዘላለም ከማገልገል ያግዳቸዋል። እብንዱ ሌላውን እየተካ፣ ካህናት የሆኑት የበዙት ከዚህ የተነሣ ነው።
\v 24 ኢየሱስ ግን ለዘላለም ስለሚኖር የእርሱ ክህነት የማይለወጥ ነው።
\s5
\v 25 ስለዚይ ስለ እነርሱ ሊማልድ ምን ጊዜም በሕይወት ስለሚኖር በእርሱ በኩል ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ሙሉ በሙሉ ሊያድናቸው ይችላል።
\v 26 እንደዚህ ያለው ማለትም ኃጢአትና ነቀፋ የሌለበት፣ ንጡሕ፣ ከኃጢአተኞች የተለየ ከሰማያትም በላይ ከፍ ያለ ሊቀ ካህን ሊኖረን ይገባል።
\s5
\v 27 እርሱ ሊቀ ካህናቱ ሲያደርጉት እንደነበረው በመጀመሪያ ራሱ ለሠራቸው ኃጢአቶች ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ለፈፀሟቸው ኃጢአቶች በየቀኑ መሥዋዕቶችን ማቅረብ አያስፈልገውም። ራሱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ ይህንን ለአብዴና ለመጨረሻ ጊዜ አድርጎታል።
\v 28 ሕጉ ድካም ያለባቸውን ሰዎች ሊቀ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፣ ከሕጉ በኃላ የመጣው የመሐላው ቃል ግን ለዘላለም ፍጹም የተደረገውን ልጁን ሾሟልና።
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 እንግዲህ ልንናገር የፈለግነው ጉዳይ ዋና ነጥቡ ይሄ ነው፦ በሰማያት በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ ሊቀ ካህን አለን።
\v 2 እርሱ እግዚአብሔር በተከላት እውነተኛይቱ የማደሪያ ድንኳን፣ በተቀደሰው መቅደስ አገልጋይ የሆነ ነው እንጂ ማንኛውም ሟች ሰው አይደለም።
\s5
\v 3 ማንኛውም ሊቅቀ ካህናት የሚሾመው ስጦታዎችንና መሥዋዕቶችን ለማቅረብ በመሆኑ፣ የሚቀርብ ነገር ይዞ መገኘት አስፈላጊ ነው።
\v 4 ታዲያ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ የሚኖር ቢሆን በሕጉ መሠረት ስጦታዎችን የሚያቀርቡ ስላሉ እርሱ በፍጹም ካህን መሆን ባልቻለም ነበር።
\v 5 የማደሪያ ድንኳኑን ለመሥራት በተነሣ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን”አስተውል፣ በተራራው ላይ ባየኸው ምሳሌ መሰረት ማንኛውንም ነገር እንድትሠራ” በማለት እንዳስጠነቀቀው ሁሉ እነርሱ የሰማያዊ ነገሮች ጥላና ግልባጭ የሆኑ ነገሮችን የሚያገለግሉ ናቸው።
\s5
\v 6 ነገር ግን በተሻለ ተስፋ ላይ የተመሠረተ የተሻለ ኪዳን መካከለኛው በመሆኑ ክርስቶስ አሁን የላቀ አገልግሎት ተቀብሏል።
\v 7 ያ የመጀመሪያው ኪዳን ነቀፋ ካልነበረው ሁለተኛ ኪዳን የሚፈለግበት ምንም ምክንያት አይኖርም ነበር።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ነቀፋ ባገኘ ጊዜ እንደዚህ ብሎ ነበርና”አስተውሉ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ዘመን ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር።
\v 9 “ከግብፅ ምድር በእጆቼ መርቼ ባወጣኋቸው በዚያን ዘመን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት እንደዚያ ቃል ኪዳን አይሆንም። በዚያ ኪዳኔ አልጸኑምና እኔም ችላ አልኳቸው” ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 10 “ከእነዚያ ዘመናት በኃላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ይህንን ኪዳን ነው፥ ‘ሕጌን በልቦናቸው አኖራለሁ፣ በልቦቻቸውም ላይ እጽፈዋለሁ። አምላካቸው እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
\s5
\v 11 እያንዳንዱ ጎረቤቱን እያንዳንዱም ወንድሙን፥ ‘እግዚአብሔርን እወቅ እያለ አያስተምርም፣ እጅግ ታናሽ ከሆነው ጀምሮ እጅግ ታላቅ እስከሆነው ድረስ ሁሉም ያውቁኛልና።
\v 12 በዓመፅ ለፈጸሟቸው ድርጊቶች ሁሉ ምሕረት አደርጋለሁና ኃጢአቶቻቸውንም ከእንግዲህ አላስብምና”
\s5
\v 13 ‘አዲስ’ በማለቱም የመጀመሪያው ኪዳን አስረጅቷል። አሮጌ ነው ብሎ የገለጸውም ሊወገድ ተቃርቧል።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 የመጀመሪያው ኪዳን ቢሆን በዚህ ምድር ለሚከናወነው አምልኮም ሆነ ለአምልኮ ደንቦች ስፍራ ነበረው።
\v 2 በመገናኛው ድንኳን የተዘጋጀ ቅድስት የተባለ ውጨኛ ክፍል ነበር። በዚህ ስፍራ መቅረዙ፣ ጠረጴዛውና የመንግስቱ መገለጫ ኅብስት ነበሩበት።
\s5
\v 3 ከሁለተኛው መጋረጃም በስተጀርባ ቅድስተ ቅዱሳን የተባለ ሌላ ክፍል ነበረ።
\v 4 ዕጣን ለማጠን የሚሆን የወርቅ መሠዊያ ነበረው። ሙሉ በሙሉ በወርቅ የተለበጠ የኪዳን ታቦትም ነበረበት። በእርሱም ውስጥ መና ያለበት የወርቅ መሶብ፣ ያቆጠቆጠች የአሮን በትርና የኪዳኑ የድንጋይ ጽላቶች ነበሩት።
\v 5 በኪዳኑም ታቦት ላይ በስርየት መክደኛው ላ ያሰፈፉ የከበሩ የኩሩቤል ምስሎች ነበሩ። ይሁን እንጂ ስለ እነዚህ ሁሉ አሁን በዝርዝር መግለጽ አንችልም።
\s5
\v 6 እነዚህ ሁሉ ነገሮች ከተዘጋጁ በኃላ፣ ካህናቱ አገልግሎቶቻቸውን ለመፈጸም በመደበኛነት በማደሪያው ድንኳን ውጫዊው ክፍል በኩል ይገባሉ።
\v 7 ሊቀ ካህናቱ ግን በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ሁለተኛው ክፍል ይገባል፣ በሚገባበትም ጊዜ ለራሱና ሕዝቡም ባለማወቅ ለፈጸሟቸው በደሎች የደም መሥዋዕት ይዞ እንጂ እንደዚሁ አይደለም።
\s5
\v 8 የመጀመሪያይቱ የመገናኛ ድንኳን በስፍራዋ ቆማ እስካለች ድረስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያመራው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ በምሳሌ እያሳየ ነው።
\v 9 ይህም ለአሁኑ ጊዜ ተምሳሌት ነው። አሁን እየቀረአቡ ያሉት ስጦታዎችም ይሁኑ መሥዋዕቶች የአምላኪውን ሕሊና ፍጹም ማድረግ የሚችሉ አይደሉም።
\v 10 ከተለያዩ የመንፃት ሥርዓቶች ጋር የተያያዙ ምግቦችና መጠጦች ብቻ ናቸው። እነዚህ ሁሉ አዲሱ ሥርዓት በሥራ ላይ እስኪውል ድረስ በሥጋዊ ደረጃ እንዲከበሩ የተሰጡ ሥርዓቶች ናቸው።
\s5
\v 11 ክርስቶስ በሰው እጆች በተሠራችው ሳይሆን ላቅ ባለችውና ይበልጥ ፍጹምና ቅድስት በመሆነችው፣ ከዚህም ከፍጥረታዊው ዓለም ባልሆነችው ድንኳን በኩል ለመጡት መልካም ነገሮች ሊቀ ካህናት ሆኖ መጥቷል።
\v 12 ክርስቶስ እጅግ ቅድስት ወደሆነችው ስፍራ አንድ ጊዜ ለሰዎች ሁሉ የገባውና የዘላለም ቤዛችንን ያስገኘልን በፍየሎችና በጥጃዎች ደም ሳይሆን በራሱ ደም ነው።
\s5
\v 13 የፍየሎችና የኮርማዎች ደም እንዲሁም የጊደሮች አመድ በሥርዓታዊ ደረጃ ንፁሕ ባልሆኑት ላይ መረጨቱ የሚያጠራቸውና ሰውነቶቻቸውንም ንፁሕ የሚያደርገው ከሆነ፣
\v 14 ይልቁንም ነውር ሳይኖረው በዘላለማዊ መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም ሕያው እግዚአብሔርን እናገለግል ዘንድ ሕሊናችንን ከሞተ ሥራ ምን ያህል ያነጻን ይሆን?
\v 15 ከዚህም የተነሳ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት በእግዚአብሔር የተጠሩት ስለ ዘላለም ርስት የተሰጣቸውን የስፋ ቃል ይቀበሉ አንድ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር ከነበረባቸው የኃጢአት ቅጣት ነፃ እንዲወጡ የሞት ቅጣት ተፈጽሞ ስለነበረ ነው።
\s5
\v 16 ይህም የሆነው አንድ ሰው ኑዛዜ እንደተወ ሲገለጽ ኑዛዜ የተወውን ሰው መሞት ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።
\v 17 ምክንያቱም ኑዛዜ የሚጸናው ሞት ተከስቶ ከሆነ ብቻ ነው፣ ተናዛዡ በሕይወት እስካለ ሊጸና አይችልምና።
\s5
\v 18 እንደዚህም በመሆኑ የመጀመሪያው ኪዳን እንኳን ያለ ደም አልጸናምና።
\v 19 በሕጉ ውስጥ ያሉትን ማንኛቸውንም ትዕዛዛት ሙሴ ለሕዝቡ ሁሉ በሰጠ ጊዜ የጥጆችንና የፍየሎችን ደም ከውሃ፣ ከቀይ የበግ ፀጉርና ከሂሶጵ ጋር ቀላቅሎ በራሱ በሕጉ መጽሐፍና በሕዝብ ሁሉ ላይ ይረጭ ነበርና።
\v 20 ይህንንም ካደረገ በኃላ “እግዚቸብሔር ለእናንተ ሕግጋቱን የሰጠበት የኪዳኑ ደም ይህ ነው” ይል ነበር።
\s5
\v 21 በዚያው ዓይነት መንገድ ደሙን በመገናኛው ድንኳንና ለክህነት አገልግሎት በሚውሉት ዕቃዎች ሁሉ ላይ ይረጭ ነበር።
\v 22 ሕጉ በሚለውም መሠረት ሁሉም ነገር የሚነጻው በደም ነበር ማለት ይቻላል። ደምም ካልፈሰሰ በስተቀር ይቅርታ የለም።
\s5
\v 23 ስለሆነም በሰማይ ያሉት ነገሮች ግልባጮችም በእነዚህ የእንስሳት መሥዋዕቶች ይነጹ ዘንድ አስፈላጊ ነበር። ይሁን እንጂ ሰማያዊ የሆኑት ነገሮች ራሳቸው እጅግ በተሻሉ መሥዋዕት መንጻት ይገባቸዋል።
\v 24 ክርስቶስ በእጅ ወደተሠራው የእውነተኛውም ግልባጭ ብቻ ወደነበረው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባምና። ይልቁንም እርሱ የገባው እግዚአብሔር ባለበት ስለ እኛ አሁን እግዚአብሔር ፊት ወደሚቀርብበት ሰማይ በቀጥታ ገብቷል።
\s5
\v 25 ወደዚያም የገባው የሌላውን ደም ይዞ በየዓመቱ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንደሚገባው እንደ ሊቀ ካህናቱ በየጊዜው ራሱን ለማቅረብ አይደለም።
\v 26 እንደዚያ ቢሆን ኖሮ ከዓለም ጅማሬ አንስቶ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር። አሁን ግን ራሱን መሥዋዕት በማድረግ ኃጢአትን ለማስወገድ በዘመናት መጨረሻ የተገለጠው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።
\s5
\v 27 እያንዳንዱ ሰው አንድ ጊዜ መሞት ከዚያ በኃላም ወደ ፍርድ መቅረብ እንደሚገባው ሁሉ
\v 28 እንደዚሁም የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው ክርስቶስ ኃጢአትን ለማስወገድ ዓላማ ሳይሆን በትዕግሥት ለሚጠባበቁት ድነትን ያስገኝላቸው ዘንድ ዳግመኛ ይገለጣል
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ሕጉ ሊመጡ ላሉ መልካም ነገሮች ጥላ ብቻ እንጂ እውነተኛው አካል አይደለም። ሕጉ ካህናት ያለማቋረጥ በየዓመቱ በሚያቀርቧቸው በነዚያው መሥዋዕቶች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡትን ከቶ ፍጹም ሊያደርጋቸው አይችልም።
\v 2 ቢችል ኖሮ እነዚያ መሥዋዕቶች መቅረባቸው ይቀር አልነበረምን? እንደዚያ ቢሆን ኖሮ የሚያመልኩት አንድ ጊዜ ከኃጢአታቸው ከነጹ በኋላ ስለ ኃጢአታቸው የሚያስታውሱት ነገር ምንም አይኖርም ነበር።
\v 3-4 ነገር ግን በእነዚያ መሥዋዕቶች ውስጥ በየዓመቱ የተፈጸሙትን ኃጢአቶች የሚያስታውስ ነገር አለ። ለዚህ ምክንያቱ የኮርማዎችና የበጎች ደም ኃጢአትን ማስወገድ ባለመቻሉ ነው።
\s5
\v 5 ክርስቶስ ወደ ዓለም ሲመጣ፣ “አንተ መሥዋዕቶችን ወይም ስጦታዎችን አልፈለግህም። ይልቅ ለእኔ ሥጋን አዘጋጀህልኝ።
\v 6 አንተ በሚቃጠል መባ ወይም በኃጢአት መሥዋዕት ደስ አልተሰኘህም።
\v 7 ቀጥሎም፣ “እግዚአብሔር ሆይ በመጽሐፍ ስለ እኔ እንደተጻፈው እነሆ ፈቃድህን ለማድረግ እዚህ አለሁ” ብሏል።
\s5
\v 8 ከላይ እንደተጠቀሰው፡“አንተ መሥዋዕቶችን፣ ስጦታዎችን ወይም ለኃጢአት የሚቃጠሉ ሙሉ መሥዋዕቶችን ማለትም በሕጉ መሠረት የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን አልፈለግህ፣ በእነርሱም ደስ ስላልተሰኘህም” ብሏል።
\v 9 ደግሞም፣ “እነሆ ፈቃድህን ለማድረግ እዚህ አለሁ” አለ። ሁለተኛውን ሥርዓት ለመትከል የመጀመሪያውን ሥርዓት ወደ ጎን ያደርገዋል።
\v 10 በሁለተኛው ሥርዓት ለአንድ ጊዜና ለዘላለም በቀረበው በኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ አማካኝነት በእግዚአብሔር ፈቃድ ተቀድሰናል።
\s5
\v 11 በእርግጥ እያንዳንዱ ካህን ኃጢአትን ፈጽሞ ሊያስወግድ የማይችሉትን መሥዋዕቶች ለማቅረብ በየዕለቱ ለማገልገል ይቆማል።
\v 12 ነገር ግን ክርስቶስ ለኃጢአት ሁሉ ለዘላለም የሚሆን አንድ መሥዋዕት ካቀረበ በኋላ፣
\v 13 ጠላቶቹ እስኪዋረዱና የእግሩ መረገጫ እስኪሆኑ ድረስ እየተጠባበቀ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል።
\v 14 ይህም በአንድ መሥዋዕት የተቀደሱትን ለዘላለም ፍጹማን ስላደረጋቸው ነው።
\s5
\v 15 ደግሞም መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ይመሰክርልናል። ምክንያቱም በመጀመሪያ፣
\v 16 “ ከእነዚያ ቀኖች በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ቃልኪዳን ይህ ነው፡ ሕጎቼን በልባቸው ውስጥ አደርጋለሁ፣ ደግሞም በአእምሮአቸው ውስጥ እጽፈዋለሁ” ስላለ ነው።
\s5
\v 17 ቀጥሎም፣ “ኃጢአታቸውንና ዓመጻቸውን ከእንግዲህ አላስበውም” አለ።
\v 18 ለእነዚህ ነገሮች ይቅርታ በተረገበት በዚያ ለኃጢአት ከእንግዲህ ወዲያ መሥዋዕት አይቀርብም።
\s5
\v 19 ስለዚህ ወንድሞች፣ በኢየሱስ ደም አማካኝነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አለን።
\v 20 ይህም በመጋረጃው ማለትም በሥጋው አማካኝነት ለእኛ የከፈተልን አዲስና ሕያው መንገድ ነው።
\v 21 በእግዚአብሔር ቤት ታላቅ ካህን ስላለን፣
\v 22 ልባችን በመረጨት ከክፉ ኅሊና ሁሉ ነጽቶ፣ ሥጋችንም በንጹሕ ውኃ ታጥቦ ባገኘነው የእምነት ሙሉ ዋስትና በእውነተኛ ልብ እንቅረብ።
\s5
\v 23 ተስፋን የሰጠ እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ፣ አምነን የምንመሰክረውን ተስፋ ያለ ማወላወል አጥብቀን እንያዝ።
\v 24 ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እርስ በርስ እንዴት እንደምንነቃቃ እናስብ።
\v 25 አንዳንዶቹ ልማድ እንዳደረጉት በአንድነት መሰብሰባችንን አንተው። በዚህ ፈንታ ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስታዩ እርስ በርሳችሁ ይበልጥ ተበረታቱ።
\s5
\v 26 የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆን ብለን ኃጢአት ማድረጋችንን የምንቀጥል ከሆንን፣ ከእንግዲህ ለኃጢአት የሚሆን መሥዋዕት አይኖርም።
\v 27 ይልቅ የሚጠብቀን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች ሊበላ ያለ ብርቱ እሳት ብቻ ነው።
\s5
\v 28 የሙሴን ሕግ የናቀ ማናቸውም ሰው በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ያለ ምንም ምሕረት ይሞታል።
\v 29 ታዲያ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፣ የተቀደሰበትን የቃልኪዳኑን ደም እንደ እርኩስ የቆጠረ፣ የጸጋን መንፈስ የሰደበ ሰው ምን ያህል የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?
\s5
\v 30 “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ዋጋን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቃለንና። ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል።”
\v 31 በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነገር ነው!
\s5
\v 32 ነገር ግን ከበራላችሁ በኋላ በእንዴት ያለ ታላቅ ሥቃይ ውስጥ እንደታገሣችሁ እነዚያን የቀደሙ ወቅቶች አስታውሱ።
\v 33 በስድብና በስደት ለሕዝብ መሳለቂያ ተዳርጋችኋል፣ ደግሞም በዚህ ዓይነቱ ሥቃይ ውስጥ ካለፉ ሰዎችም ጋር አብራችሁ ነበራችሁ።
\v 34 ለእስረኞች ርኅራኄ አሳያችሁ፣ የተሻለና ዘላለማዊ ሀብት ለራሳችሁ እንዳላችሁ በመረዳትም የንብረታችሁን መነጠቅ በደስታ ተቀበላችሁ።
\s5
\v 35 ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን ድፍረታችሁን አትጣሉ።
\v 36 ፈቃዱን ካደረጋችሁ በኋላ እግዚአብሔር ለእናንተ ተስፋ የገባውን ነገር ለመቀበል መታገሥ ያስፈልጋችኋል።
\v 37 “በጣም በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚመጣው በእርግጥ ይመጣል፣ አይዘገይምም።
\s5
\v 38 የእኔ የሆነው ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል። ወደኋላ ቢመለስ በእርሱ ደስ አይለኝም።”
\v 39 እኛ ግን ለጥፋት ወደኋላ እንደሚያፈግፍጉት አይደለንም። ይልቅ እኛ ነፍሳቸውን ለማዳን ከሚያምኑት ነን።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 እንግዲህ እምነት ሰው በተስፋ ለሚጠበቀው ነገር ማረጋገጫ ያልታየውም ነገርም አስረጅ ነው።
\v 2 የቀድሞ አባቶቻችንም እምነታቸው የተረጋገጠው በዚሁ ነበር።
\v 3 ፍጥርተ-ዓለሙ በእግዚአብሔር ትእዛዝ መፈጠሩን፣ የሚታየውም ከሚታዩት ነገሮች የተፈጠረ አለመሆኑን በእምነት እንረዳለን።
\s5
\v 4 አቤል ከቃየል የበለጠ ተቀባይነት ያለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው በእምነት ነበር። ጻድቅ እንደሆነ የተመሰከረለትም በዚህ ምክንያት ነበር። ስላቀረባቸው መሥዋዕቶች እግዚአብሔር መስክሮለታል። ቢሞትም እንኳ አሁንም ይናገራል።
\s5
\v 5 ሄኖክ ሞትን ሳያይ ወደ ላይ የተወሰደው በእምነት ነበር። “እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም።” ከመወሰዱ በፊት እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘ ተነግሮለታና።
\v 6 ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ምክንያቱም፣ ወደ እግዚአብሔር የሚመጣ፣ እግዚአብሔር እንዳለና እርሱን ለሚሹትም ዋጋን እንደሚሰጥ ማመን ስለሚገባው ነው።
\s5
\v 7 ኖኅ ገና ስላልታዩ ነገሮች ከእግዚአብሔር ሲያስጠነቅቀው እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን የሚያድንበትን መርከብ የሠራው በእምነት ነበር። ይህን በማድረግ ዓለምን ኮንኖ በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።
\s5
\v 8 አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስትን ወደሚቀበልበት ቦታ ታዞ የሄደው በእምነት ነበር። የወጣው ወዴት እንደሚሄድ ሳያውቅ ነበር።
\v 9 በተስፋው ምድር እንደ ባዕድ የኖረውም በእምነት ነበር። ያን ተስፋ ከእርሱ አብረው ከሚወርሱት እንደ ይስሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ውስጥ ኖረ።
\v 10 ይሄውም እግዚአብሔር መሠረት ያላትን፣ ያቀዳትንና ያነጻትን ከተማ ይጠባበቅ ስለነበር ነው።
\s5
\v 11 አብርሃምና ሣራ እጅግ አርጅተው ሳሉ እንደሚወልዱ በተነገራቸው ጊዜ፣ ወንድ ልጅን እንደሚሰጣቸው ተስፋ የገባላቸውን እግዚአብሔር ታማኝ አድርገው ስለቆጠሩ ሣራ ለማርገዝ ኃይል ያገኘችው በእምነት ነበር።
\v 12 በመሆኑም፣ ሊሞት ከተቃረበ ከዚህ አንድ ሰው ቁጥር ስፍር የሌላቸው ዝርያዎች ተገኙ። እነርሱም በሰማይ እንዳሉ ከዋክብትና በባሕር ጠረፍ እንዳለ አሸዋ በዙ።
\s5
\v 13 እነዚህ ሁሉ የተሰጧቸውን ተስፋዎች ሳይጨብጡ እምነታቸውን እንደጠበቁ ሞቱ። ይልቁንም እነዚህን ተስፋዎች ከሩቅ አይተው ስለተቀበሏቸው በምድር ላይ እንግዶችና መጻተኞች መሆናቸውን ተገነዘቡ።
\v 14 እንደዚህ የሚሉ ሰዎች የራሳቸው የሆነ አገር እንዲሚሹ በግልጽ ያሳያሉ።
\s5
\v 15 በእርግጥ ለቀው የመጡትን አገር ቢያሰቡ ኖሮ ለመመለስ ዕድሉ ነበራቸው።
\v 16 አሁን ግን የሚፈልጉት የተሻለውን ሰማያዊ አገር ነው። ስለዚህም፣ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ አያፍርም።
\s5
\v 17 አብርሃም በተፈተነ ጊዜ ይስሐቅን ያቀረበው በእምነት ነበር። አዎን፣
\v 18 “ዝሮችህ የሚጠሩት በይስሐቅ ነው” የተባሉለትን ተስፋዎቹን በደስታ ስለተቀበለ አንድ ልጁን ለመሥዋዕት አቀረበ።
\v 19 አብርሃም፣ እግዚአብሔር ይስሐቅን ከሞት ሊያስነሣ እንደሚችል አምኖ ነበር። ይስሐቅን ከሞት የመነሣት አምሳያ አድርጎ መልሶ ተቀበለው።
\s5
\v 20 ይስሐቅ ገና ወደፊት የሚመጡትን ነገሮች አስቦ ያዕቆብንና ኤሳውን በእምነት ባረካቸው።
\v 21 ያዕቆብ ፍጻሜው በተቃረበ ጊዜ፣ የዮሴፍን ልጆች እያንዳንዳቸውን የባረካቸውና በምርኩዙ አናት ተደግፎ የሰገደው በእምነት ነበር።
\v 22 ዮሴፍ ሊሞት ሲቃረብ የእስራኤል ልጆች ከግብጽ እንደሚወጡ የተናገረውና የእርሱን አጽሙን እንዲወስዱ ያዘዘው በእምነት ነበር።
\s5
\v 23 ሙሴ ሲወለድ ወላጆቹ መልከ መልካም ሕፃን መሆኑን አይተው የንጉሡን ትእዛዝ ሳይፈሩ ለሦስት ወራት የደበቁት በእምነት ነበር።
\v 24 ሙሴም ካደገ በኋላ የፈርዖን የልጅ ልጅ፣ እንዳይባል እምቢ ያለው በእምነት ነበር።
\v 25 ለአጭር ጊዜ በኃጢአት ደስ ከመሰኘት ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራን መካፈልን መረጠ።
\v 26 ዓይኖቹ ወደፊት የሚቀበለውን ዋጋ አተኩረው ስለተመለከቱ፣ በግብጽ ከሚገኝ ሀብት ይልቅ ክርስቶስን መከተል የሚያስከትልበትን ውርደት የላቀ ብልጽግና አድርጎ አሰበ።
\s5
\v 27 ሙሴ ግብጽን ለቆ የወጣው በእምነት ነበር። የማይታየውን እርሱን ተመልክቶ በአቋሙ ስለጸና የንጉሡን ቁጣ አልፈራም።
\v 28 ቀሳፊው የእስራኤልን የበኩር ልጆች እንዳይነካ ሙሴ የፋሲካ በዓልንና የደም ርጭት ሥርዓትን ያካሄደው በእምነት ነበር።
\s5
\v 29 እስራኤላውያን በደረቅ መሬት ላይ እንደሚሄዱ ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነበር። ግብጻውያን ይህን ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ተዋጡ።
\v 30 የኢያሪኮ ግንብ በእምነት የወደቀው ለሰባት ቀናት ከተከበበ በኋላ ነበር።
\v 31 ሴተኛ አዳሪዋ ረዓብ ሰላዮቹን ለደህንነታቸው ተጠንቅቃ ስለተቀበለቻቸው ከማይታዘዙት ጋር ያልጠፋችው በእምነት ነበር።
\s5
\v 32-33 እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ምን ልበል? በእምነት መንግሥታትን ድል ስላደረጉት፣ ፍትህን ስላስከበሩትና የተስፋ ቃሎችን ስለተቀበሉት ስለነጌደዎን፣ ባርቅ፣ ሳምሶን፣ ዮፍታሄ፣ ዳዊት፣ ሳሙኤልና ነቢያት እንዳልናገር ጊዜ ያጥረኛል።
\v 34 እነርሱ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፣ የእሳትን ኃይል አጠፉ፣ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፣ ከበሽታ ተፈወሱ፣ በጦርነት ኃያላን ሆኑ፥ የባዕድን ሠራዊት አባረሩ።
\s5
\v 35 ሴቶች ሙታናቸው ከሞት ተነሡላቸው። ሌሎች የተሻለውን ትንሣኤ ያገኙ ዘንድ ከእስር መፈታታቸውን ለመቀበል እምቢ በማለት ተሠቃዩ።
\v 36 የተቀሩት ደግሞ በስድብና በግርፋት፣ እንዲያውም በሰንሰለት በመታሰር ተሠቃዩ።
\v 37 በድንጋይ ተወገሩ። በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ። በሰይፍ ተገደሉ። ይህ ዓለም ስላልተገባቸው
\v 38 በምድረበዳ፣ በተራሮች፣ በዋሻዎችና በየጉድጓዱ እየተጎሳቆሉ፣ መከራ እየተቀበሉና ግፍ እየተፈጸመባቸው የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው በመንከራተት ዞሩ።
\s5
\v 39 እነዚህ ሰዎች ሁሉ ስለ እምነታቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው ቢሆኑም የተሰጣቸውን ተስፋ አልተቀበሉም።
\v 40 እነርሱ ያለ እኛ ፍጹም ስለማይሆኑ እግዚአብሔር ለእኛ የተሻለውን ነገር አስቀድሞ ሰጠን።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 እንደነዚህ ያሉ እጅግ ብዙ ምስክሮች ስላሉን፣ የሚከብደንን ነገር ሁሉና በቀላሉ የሚጠላልፈንን ኃጢአት አሽቀንጥረን እንጣል። ከፊታችን ያለውንም ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ።
\v 2 በእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ ኢየሱስ ላይ ዓይኖቻችን እንትከል። እርሱ ከፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉንና መስቀሉ የሚያስከትለውን ውርደት ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።
\v 3 እንዳትደክሙ ወይም ልባችሁ እንዳይዝል፣ ከኃጢአተኞች የተሰነዘረበትን እንዲህ ያለውን የጥላቻ ንግግር የታገሠውን እርሱን አስቡ።
\s5
\v 4 ደም እስከማፍሰስ ድረስ ኃጢአትን አልተቃወማችሁም፣ አልታገላችሁትምም።
\v 5 ደግሞም እንደ ልጆች፡ “ልጄ ሆይ የጌታን ቅጣት አታቅልል፣ በሚቀጣህም ጊዜ ልብህ አይዛል።
\v 6 ጌታ የሚወደውን ይገሥጻል፣ የሚቀበለውን ማንኛውንም ልጅ ይቀጣል" በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ምክር ረስታችኋል።
\s5
\v 7 አባት በልጆቹ እንደሚደረግ እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ስለሚያደርግ፣ መከራን እንደ ተግሣጽ በመቁጠር ታገሡ። ለመሆኑ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው?
\v 8 ነገር ግን እኛ ሁላችን ከምንካፈለው ተግሣጽ ውጭ ከሆናችሁ፣ ዲቃሎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም።
\s5
\v 9 ከዚህም በላይ የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እኛም እናከብራቸው ነበር። ይልቁንስ መንፈስ ለሆነው አባት እየታዘዝን መኖር የቱን ያህል ይገባናል?
\v 10 በእርግጥ አባቶቻችን ለእነርሱ መልካም መስሎ እንደታያቸው ለጥቂት ጊዜ ይቀጡን ነበር፣ እግዚአብሔር ግን የእርሱን የቅድስናው ተካፋዮች እንድንሆን ለጥቅማችን ያቀጣናል።
\v 11 ቅጣት በወቅቱ የሚያም እንጂ አስደሳች አይደለም። ይሁን እንጂ፣ ለለመዱት በመጨረሻ ሰላማዊ የጽድቅ ፍሬን ያፈራል።
\s5
\v 12 ስለዚህ የዛሉ እጆቻችሁን ወደ ላይ አንሡ፣ የደከሙ ጉልበቶቻችሁንም እንደገና አበርቱ፤
\v 13 የሚያነክስ ማንም ቢኖር እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ እግሮቻችሁ የሚራመዱባቸውን መንገዶች ቀና አድርጉ።
\s5
\v 14 ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ፣ ቅድስናንም ተከታተሉ፣ ያለ ቅድስና ማንም ጌታን ሊያይ አይችልም።
\v 15 ማንም ከእግዚአብሔር ጸጋ እንዳይጎድል፣ መራራ ሥርም አድጎ እንዳያስጨንቅና ብዙዎችን እንዳይመርዝ ተጠንቀቁ።
\v 16 ለአንድ መብል ብሎ ብኩርናውን እንደሸጠ እንደ ኤሳው እግዚአብሔርን የማይፈራ፣ ወይም ሴሰኛ የሆነ ማንም እንዳይኖር ተጠንቀቁ።
\v 17 ከዚያ በኋላ በረከትን ለመውረስ እያለቀሰ በትጋት ቢፈልግም፣ ከአባቱ ዘንድ የይቅርታ እድል እንዳጣና እንደተጣለ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 18 የሚቃጠል እሳት፣ ጨለማ፣ ጭጋግና ማዕበል ወዳለበት በእጅ ሊነካ ወደሚችል ተራራ ገና አልመጣችሁም።
\v 19 የሰሙትም ሌላ ቃል እንዳይነገራቸው እስከሚለምኑ ወዳደረሳቸው ቃልን ወደሚያሰማ ድምጽ ወይም የመለከት ጩኹት ገና አልመጣችሁም።
\v 20 ይህም፣ “እንስሳም እንኳ ቢሆን ተራራውን ከነካ በድንጋይ ይወገር” ተብሎ የተሰጠውን ትእዛዝ ሊሸከሙት አልቻሉም።
\v 21 ሙሴ፣ “እጅግ ስለፈራሁ እየተንቀጠቀጥሁ ነኝ” እስከሚል ድረስ ይህ ስፍራ አስፈሪ ነበር።
\s5
\v 22 አሁን ግን፣ የሕያው እግዚአብሔር ከተማ ወደሆነችው ወደ ጽዮን ተራራ፣ አእላፋት መላእክት በደስታ ወደሚያመልኩባት ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም መጥታችኋል፤
\v 23 በሰማይ ወደሚገኙት የበኩራን ሁሉ ጉባኤ፣ የሁሉም ፈራጅ ወደሆነው እግዚአብሔርና ፍጹም የተደረጉ የጻድቃን መንፈሶች ወዳሉበት መጥታችኋል፤
\v 24 የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ወደሆነው ኢየሱስና ከአቤል ደም የተሻለውን ወደሚናገር ወደተረጨው ደም ደርሳችኋል።
\s5
\v 25 የሚናገራችሁን እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ። እነርሱ በምድር ላይ ሆኖ ያስጠነቀቃቸውን እምቢ በማለታቸው ካላመለጡ፣ በሰማይ ሆኖ ከሚያስጠነቅቀን በእርግጥ አናመልጥም።
\v 26 በዚያን ጊዜ ድምጹ ምድርን አናወጠ። ነገር ግን፣ “አንድ ጊዜ ደግሜ ምድርን ብቻ ሳይሆን ሰማያትንም አናውጣለሁ” በማለት አሁን ተስፋ ሰጥቷል።
\s5
\v 27 “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚል ቃል፣ ያልተናወጡ ነገሮች መጽናታቸውን፣ የተናወጡት ማለትም የተፈጠሩት ነገሮች መወገዳቸውን ያመላክታል።
\v 28 ስለዚህ፣ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ስለተቀብልን አምላካችንን እናመስግነው፣ ደግሞም እግዚአብሔርን ተቀባይነት ባለው በአክብሮትና በፍርሃት እናምልከው፣
\v 29 ምክንያቱም አምላካችን የሚባላ እሳት ነው።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 በወንድማማችነት ፍቅር መዋደዳችሁን ቀጥሉ።
\v 2 እንግዶችን መቀበል አትርሱ፣ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲያደርጉ ሳያውቁት መላእክትን አስተናግደዋል።
\s5
\v 3 ከእነርሱ ጋር እንደታሰረ ሆናችሁ፣ በሰውነታችሁም እንደ እነርሱ መከራን እንደሚቀበል ሆናችሁ በእስራት ያሉትን አስቡ።
\v 4 ጋብቻ በሁሉም ዘንድ የተከበረ መኝታውም ንጹሕ ይሁን፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር በሴሰኞችና በአመንዝራዎች ላይ ይፈርድባቸዋል።
\s5
\v 5 አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር የጸዳ ይሁን። እግዚአብሔር ራሱ፣ “እኔ ፈጽሞ አልተውህም፣ ደግሞም አልጥልህም” ስላለ፣ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ።
\v 6 ስለዚህ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰውስ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” ብለን በድፍረት እንናገራለን።
\s5
\v 7 የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን አስቡ፣ የምግባራቸውንም ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሏቸው።
\v 8 ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬና ለዘላለምም ያው ነው።
\s5
\v 9 በልዩ ልዩ እንግዳ ትምህርቶች አትወሰዱ፣ ለሚከተሏቸው ሰዎች ፋይዳ የሌላቸውን የአመጋገብ ሥርዓቶች በመጠበቅ ሳይሆን ልብ በጸጋ ሲጸና መልካም ነው።
\v 10 በመገናኛው ድንኳን የሚያገለግሉት ከእርሱ እንዲበሉ ያልተፈቀደላቸው መሠዊያ አለን።
\v 11 ሊቀካህናቱ ለኃጢአት ስርየት የተሠዋውን የእንስሳት ደም ወደ ቅድስት ያመጣል፣ የእንስሳቱ ሥጋ ግን ከሰፈር ውጭ ይቃጠላል።
\s5
\v 12 ደግሞም ኢየሱስ ሰዎችን በገዛ ደሙ ለመቀደስ ከከተማይቱ ቅጥር ውጭ መከራን ተቀበለ።
\v 13 ስለዚህ እኛም እርሱ የተሸከመውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደርሱ እንሂድ።
\v 14 በዚህ ምድር ምንም ዓይነት ዘላቂ ከተማ የለንም። ነገር ግን የምትመጣውን ከተማ እንጠብቃለን።
\s5
\v 15 የስሙን ታላቅነት የሚናገሩ የከንፈሮቻችንን ፍሬ፣ ማለትም የምስጋና መሥዋዕቶችን ያለማቋረጥ በኢየሱስ በኩል ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይገባናል።
\v 16 ደግሞም መልካም ማድረግንና እርስ በርስ መረዳዳትን አትርሱ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚደሰተው እንደነዚህ ባሉ መሥዋዕቶች ነው።
\v 17 ተጠያቂነት ስላለባቸው ለነፍሳችሁ እንክብካቤ ለሚያደርጉ ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፣ ተገዙላቸውም። ለእናንተ ስለማይጠቅም በሐዘን ሳይሆን በደስታ እንዲንከባከቧችሁ ታዘዟቸው።
\s5
\v 18 በሁሉም ነገር የከበረ ሕይወት ለመኖር የሚፈልግ ንጹሕ ኅሊና ስላለን ጸልዩልን።
\v 19 ወደ እናንተ ቶሎ መመለስ እንድችል ይበልጥ ይህን እንድታደርጉ አበረታታችኋለሁ።
\s5
\v 20-21 እንግዲህ በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን፣ ከሙታን ያስነሣው የሰላም አምላክ እግዚአብሔር፣በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በእኛ ውስጥ የሚሠራውን፣ በእርሱ ፊት ደስ የሚያሰኘውን ፈቃዱን እንድታደርጉ በማናቸውም መልካም ነገር ያስታጥቃችሁ። ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ክብር ይሁን። አሜን።
\s5
\v 22 ወንድሞች ሆይ፤ አሁን በዐጭሩ የጻፍሁላችሁን ማበረታቻ እንድትቀበሉ አደፋፍራችኋለሁ።
\v 23 ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደተፈታ ዕወቁ፣ ቶሎ ከመጣም ከእርሱ ጋር አብሬ አያችኋለሁ።
\s5
\v 24 ለመሪዎችና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በኢጣልያ ያሉት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
\v 25 ጸጋ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።

214
60-JAS.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,214 @@
\id JAS
\ide UTF-8
\h ያዕቆብ
\toc1 ያዕቆብ
\toc2 ያዕቆብ
\toc3 jas
\mt ያዕቆብ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር እስረኛና አገልጋይ የሆነ ያዕቆብ በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑና በመላው ዓለም ለተበተኑት ለአሥራ ሁለቱ ነገዶች ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡
\v 2 ወንድሞቼ ሆይ፣ በልዩ ልዩ ፈተናዎች ውስጥ ማለፋችሁን እጅግ ደስ እንደሚያሰኝ ነገር ቊጠሩት፡፡
\v 3 በፈተና ውስጥ ሳላችሁ በእግዚአብሔር ስታምኑ ይበልጥ ሌሎች ፈተናዎችን በትዕግሥት ለማሳለፍ የሚረዱዋችሁ መሆኑን ትረዳላችሁ፡፡
\s5
\v 4 ክርስቶስን በሁሉም መንገድ ትከተሉ ዘንድ እስከ መጨረሻው በፈተና ጽኑ፤ ያንጊዜ መልካም ማድረግ አይከብዳችሁም፡፡
\v 5 ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔርን ስትለምኑ፣ የምትጠይቁትን እንደሚሰጣችሁ እመኑ፤ መልስ እንደሚሰጣችሁና ሁልጊዜም እንደሚረዳችሁ አትጠራጠሩ፤ የሚጠራጠሩ ሰዎች እግዚአብሔርን ሊከተሉት አይችሉም፤ መጠራጠር ልክ ተመልሶ እንደሚመጣ፣ ደግሞም በዚያው አቅጣጫ መጓዝን እንደማይቀጥል የባሕር ማዕበል ያለ ነገር ነው፡፡
\v 7 በእርግጥ የሚጠራጠሩ ሰዎች የሚጠይቁትን ነገር ለመፈጸም እግዚአብሔር አንድ ነገር ሊያደርግ እንደሚችል አያምኑም፡፡
\v 8 እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን ለመከተል ወይም ላለመከተል ያልወሰኑ ናቸው፤ እነዚህም የሚናገሩትን ነገር የማያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡
\s5
\v 9 ድሀ የሆኑ አማኞች እግዚአብሔር ስላከበራቸው ደስ ሊሰኙ ይገባል፡፡
\v 10 ባለጠጋ የሆኑ አማኞችም እግዚአብሔር ትሑታን ስላደረጋቸው ደስ ሊሰኙ ይገባል፤ ልክ የበረሃ አበቦች እንደሚደርቁ ሁሉ፣ እነርሱም ሆኑ ሀብታቸው የሚያልፉ ናቸውና፡፡
\v 11 ፀሐይ በሚወጣ ጊዜ ሞቃታማ የሆነው ነፋስ ተክሎችን ያደርቃል፤ ደግሞም አበቦችን በምድር ላይ እንዲወድቁም ሆነ በውበታቸው እንዳይቀጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ባለ ጠጎች ልክ እንደሚሞቱ አበቦች ሁሉ ገንዘብን እየሰበሰቡ ሳሉ ይሞታሉ፡፡
\s5
\v 12 በመከራ የሚጸኑትን ሰዎች እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፤ ለሚወድዱት ሁሉ ተስፋ እንደ ሰጠው ለዘላለም እንዲኖሩ በማድረግ ብድራታቸውን ይከፍላቸዋል፡፡
\v 13 በኃጢአት ስንፈተን እግዚአብሔር እየፈተነን ነው ብለን ልናስብ አይገባም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ክፉን እንድንሠራ አይፈልግምና፤ ክፉን እንዲያደርግ ማንንም አይፈትንምና፡፡
\s5
\v 14 እያንዳንዱ ሰው የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲታለልና ሲሳብ ነው።
\v 15 ክፉ ምኞት ከተፀነሰ በኋላ ኀጢአት ይወለዳል፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞት ይወለዳል።
\v 16 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ አትታለሉ።
\s5
\v 17 ማንኛውም መልካምና ፍጹም ስጦታ እንደሚዘዋወር ጥላ ከማይለዋወጠው ከላይ ከሰማይ ከብርሃናት አባት ይወርዳል።
\v 18 በፍጥረታቱ መካከል እንደ በኵራት እንድንሆን እግዚአብሔር በእውነት ቃል ሕይወት ሊሰጠን ወደደ።
\s5
\v 19 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን ዕወቁ። ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገዬ፣ ለመቆጣትም የዘገዬ ይሁን!
\v 20 ምክንያቱም የሰው ቊጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣም።
\v 21 ስለዚህ ርኵሰትንና በየቦታው ሞልቶ ያለውን ክፋት አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁ የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።
\s5
\v 22 ለቃሉ ታዘዙ እንጂ፣ ሰሚዎች ብቻ በመሆን ራሳችሁን አታታልሉ።
\v 23 ማንም ቃሉን እየሰማ ቃሉ የሚለውን ባያደርግ፣ ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ ሰው ይሆናል።
\v 24 ፊቱን አይቶ ይሄዳል፤ ምን እንደሚመስል ግን ወዲያው ይረሳዋል።
\v 25 ፍጹሙንና ነጻ የሚያወጣውን ሕግ በጥንቃቄ የሚመለከትና የሚኖርበት እንጂ፣ ሰምቶ እንደሚረሳው ያልሆነ ሰው በሚያደርገው ሁሉ የተባረከ ይሆናል።
\s5
\v 26 አንድ ሰው ሃይማኖተኛ ነኝ እያለ፣ አንደበቱን ግን ባይቆጣጠር፣ ልቡን ያስታል፤ ሃይማኖቱም ከንቱ ነው።
\v 27 በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ንጹሕና ርኵሰት የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ አባት የሌላቸውንና መበለቶችን በችግራቸው መርዳት፤ በዓለም ካለ ርኵሰት ራስን መጠበቅ።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ፤ ለአንዳንዶች አድልዎ እያደረጋችሁ የክብር ጌታ የጌታችን አየሱስ ክርስቶስን እምነት እንከተላለን አትበሉ።
\v 2 የወርቅ ቀለበት ያደረገና የሚያማምሩ ልብሶች የለበሰ ወደ ስብሰባችሁ ሲገባና እንዲሁም አዳፋ ልብሶች የለበሰ ድኻ ቢገባ
\v 3 ትኵረታችሁ የሚያማምሩ ልብሶች የለበሰው ሰው ላይ ይሆንና፣ “እዚህ ደኅና ቦታ ላይ ተቀመጥ” ትሉታላችሁ፤ ድኻውን ግን፣ “እዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ በታች ተቀመጥ” ትሉታላችሁ
\v 4 ታዲያ፣ በመካከላችሁ አድልዎ ማድረጋችሁ አይደለምን፤ ደግሞስ በክፉ ዐሳብ የተያዛችሁ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለምን?
\s5
\v 5 የተወደዳችሁ ወንድሞች ስሙ፤ በእምነት ባለ ጸጋ እንዲሆኑና፣ እርሱን ለሚወዱ ቃል የገባላቸውን መንግሥት እንዲወርሱ እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ድኾችን አልመረጠምን?
\v 6 እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ! የሚጨቁኗችሁ ባለ ጸጎች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጎትቱዋችሁስ እነርሱ አይደሉምን?
\v 7 የተጠራችሁበትን መልካም ስም የሚሳደቡ ባለ ጸጎቹ አይደሉምን?
\s5
\v 8 ይሁን እንጂ፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ተብሎ እንደ ተጻፈው የከበረውን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤
\v 9 ለአንዳንዶች አድልዎ ብታደርጉ ግን፣ ኃጢአት ትሠራላችሁ፤ እንደ ሕግ ተላላፊዎችም ትቆጠራላችሁ።
\s5
\v 10 ምክንያቱም ሕጉን የሚፈጽም፣ በአንዱ ግን የሚሰናከል፣ ሕጉን ሁሉ እንደ ተላለፈ ይቆጠራል!
\v 11 “አታመንዝር” ያለው እግዚአብሔር፣ “አትግደልም” ብሎአልና። ባታመነዝር ሆኖም ግድያ ብትፈጽም፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ተላልፈሃል።
\s5
\v 12 ስለዚህ ነጻ በሚያወጣው ሕግ እንደሚፈረድባቸው ሰዎች ተናገሩ፤ ደግሞም ታዘዙ።
\v 13 ምክንያቱም ምሕረት በማያደርጉ፣ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይመጣባቸዋል። ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል!
\s5
\v 14 ወንድሞቼ ሆይ፣ አንድ ሰው እምነት እንዳለው ቢናገር፣ ሥራ ግን ባይኖረው ምን ይጠቅማል? ያ እምነት ሊያድነው ይችላልን?
\v 15 አንድ ወንድም ወይም እኅት ልብስና የዕለት ምግብ ባይኖራቸው
\v 16 ከእናንተ አንዱ፣ “በሰላም ሂዱ፤ አይብረዳችሁ፤ በደንብ ጥገቡ” ቢላቸው፤ ለአካል የሚያስፈልጉ ነገሮችን ግን ባትሰጧቸው፣ ምን ይጠቅማል?
\v 17 ሥራ የሌለው እምነትም እንዲሁ በራሱ የሞተ ነው።
\s5
\v 18 ምናልባትም አንዱ፣ “አንተ እምነት አለህ እኔ ደግሞ ሥራ አለኝ” ሥራ የሌለው እምነትህን አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይል ይሆናል።
\v 19 አንድ እግዚአብሔር መኖሩን ታምናለህ፤ ትክክል ነህ። አጋንንትም ይህን ያምናሉ፤ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ።
\v 20 አንተ ሞኝ፣ እምነት ያለ ሥራ ከንቱ መሆኑን ማወቅ ትፈልጋለህ?
\s5
\v 21 አባታችን አብርሃም፣ ልጁ ይስሐቅን መሠዊያው ላይ ባቀረበ ጊዜ በሥራ ጸድቆ አልነበረምን?
\v 22 እምነት በሥራው ታየ፤ በዚያው ሥራ እምነት ዓላማውን ፈጸመ።
\v 23 “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ። ስለዚህም አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ።
\v 24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን፣ በሥራ እንደሚጸድቅ ታያለህ።
\s5
\v 25 በተመሳሳይ ሁኔታ ጋለሞታዪቱ ረዓብ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቅችምን?
\v 26 ከመንፈስ የተለዬ አካል ሙት እንደ ሆነ ሁሉ፣ ከሥራ የተለዬ እምነትም የሞተ ነው።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ወንድሞቼ፣ እኛ የባሰውን ፍርድ እንደምንቀበል በመገንዘብ፣ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አትሁኑ።
\v 2 ሁላችንም በብዙ መንገድ እንሰናከላለን። በንግግሩ የማይሰናከል እርሱ ሰውነቱን ሁሉ መቆጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።
\s5
\v 3 ፈረሶች አፍ ውስጥ ልጓም ብናደርግ ይታዘዙልናል፤ መላ አካላቸውንም መቆጣጠር እንችላለን።
\v 4 ምንም እንኳ መርከቦች ግዙፍና በኃይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም፣ የመርከቡ ነጂ በትንሽ መሪ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንደሚመራቸው አስተውሉ።
\s5
\v 5 እንዲሁም አንደበት ትንሽ የሰውነት ክፍል ሆኖ፣ በታላላቅ ነገሮች ይኵራራል። ጫካ የቱንም ያህል ሰፊ ቢሆን፣ በትንሽ እሳት ፍንጣሪ እንደሚቃጠል ልብ አድርጉ!
\v 6 አንደበትም እንዲሁ እሳት ነው፤ ሰውነትን ሁሉ የሚያረክስና የሕይወትንም መንገድ የሚያቃጥል፣ እርሱ ራሱም በገሃነም እሳት የሚቃጠል ሰውነታችን ብልቶች መካከል ያለ ኃጢአተኛ ዓለም ነው።
\s5
\v 7 ማንኛውም እንስሳ፣ ወፎች፣ በምድር የሚሳቡና ባሕር ውስጥ ያሉ ፍጥረቶች በሰው ተገርተዋል፤
\v 8 ነገር ግን ከሰው መካከል ማንም አንደበትን መግራት አልቻለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ዕረፍት የለሽ ክፉ ነው።
\s5
\v 9 በአንደበት ጌታና አባታችንን እንባርካለን፤ በዚያው አንደበት በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን።
\v 10 ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣል። ወንድሞቼ፣ እንዲህ መሆን የለበትም።
\s5
\v 11 ከአንድ ምንጭ ጣፋጭና መራራ ውሃ ይወጣልን?
\v 12 ወንድሞቼ፣ የበለስ ዛፍ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ያበቅላልን? እንዲሁም ከጨው ውሃ ንጹሕ ውሃ ሊገኝ አይችልም።
\s5
\v 13 ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? ያ ሰው ከጥበብ በሚገኝ ትሕትና በሥራው መልካም ሕይወትን ያሳይ።
\v 14 በልባችሁ መራራ ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ካለ ግን አትኵራሩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።
\s5
\v 15 ይህ ከላይ የሚመጣ ጥበብ አይደለም፤ ይልቁንም ምድራዊ፣ መንፈሳዊ ያልሆንና አጋንንታዊም ነው።
\v 16 ምክንያቱም ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ባለበት ሁከትና ክፉ ሥራ ይኖራል።
\v 17 ከላይ የሚመጣው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላም ወዳድ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላበት፣ ለሰዎች አድልዎ የማያደርግ ቅን ነው።
\v 18 ሰላምን ለሚያደርጉ የጽድቅ ፍሬ በሰላም ይዘራል።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 በእናንተ መከከል ያለው ፀብና ጭቅጭቅ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ውጊያ ከገጠሙት ክፉ ምኞቶቻችሁ የመጣ አይደለምን?
\v 2 የሌላችሁን ትመኛላችሁ። ትገድላላችሁ፤ ማግኘት ያልቻላችሁትን በብርቱ ታሳድዳላችሁ። ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ፤ ይሁን እንጂ፣ ከእግዚአብሔር ስለማትለምኑ አታገኙም።
\v 3 ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፤ ምክንያቱም ክፉ ምኞቶቻችሁን ለማሳካት ክፉ ነገሮችን ስለምትለምኑ ነው።
\s5
\v 4 እናንት አመንዝሮች! የዓለም ወዳጅ መሆን፣ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን እንደ ሆነ አታውቁም? ስለዚህ ማንም የዓለም ወዳጅ መሆን ቢፈልግ፣ የእግዚአብሔር ጠላት ይሆናል።
\v 5 ወይስ እግዚአብሔር እኛ ውስጥ ያኖረው መንፈስ ለእርሱ ብቻ እንድንሆን አብዝቶ ይቀናል የሚለው የመጽሐፍ ቃል በከንቱ የተነገረ ይመስላችኋል?
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ግን አብዝቶ ጸጋውን ይሰጣል፤ መጽሐፍ፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው በዚህ ምክንያት ነው።
\v 7 ስለዚህ፣ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል።
\s5
\v 8 ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።
\v 9 እዘኑ፤ አልቅሱ፤ ጩኹ! ሳቃችሁን ወደ ሐዘን፣ ደስታችሁን ወደ ትካዜ ለውጡ።
\v 10 በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል።
\s5
\v 11 ወንድሞች ሆይ፣ እርስ በርስ አትወነጃጀሉ። ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙ ላይ የሚፈርድ ሕጉ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በእግዚአብሔርም ሕግ ላይ ይፈርዳል። ሕጉ ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ ፈራጆች እንጂ፣ ሕጉን አድራጊዎች አይደላችሁም።
\v 12 ሕጉን የሰጠና በሕጉም የሚፈርድ፣ ማዳንም መግደልም የሚቻለው አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ታዲያ፣ በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?
\s5
\v 13 “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ አገር እንሄዳለን፤ እዚያ አንድ ዓመት እንቆያለን፤ ነግደን እናተርፋለን” የምትሉ እናንተ ሰዎች ስሙ።
\v 14 ነገ የሚሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? ሕይወታችሁስ ምንድን ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ ጭጋግ አይደላችሁምን?
\s5
\v 15 ይልቁንም፣ “ጌታ ቢፈቅድ እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን” ማለት ይኖርባችኋል።
\v 16 አሁን ግን በዕቅዶቻችሁ ትመካላችሁ። እንዲህ ያለው ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው።
\v 17 ስለዚህ መልካም የሆነውን ማድረግ እንዳለበት እያወቀ ለማያደርግ ለዚያ ሰው ኃጢአት ይሆንበታል።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስለሚመጡባችሁ ክፉ ነገሮች አልቅሱ ዋይ ዋይም በሉ።
\v 2 ሀብታችሁ ሻግቶአል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል።
\v 3 ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም እናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል። ለመጨረሻው ቀን ሀብታችሁን አከማችታችኋል።
\s5
\v 4 ልብ በሉ፤ እርሻችሁን ላጨዱ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ ይጮኻል! የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።
\v 5 በምድር ላይ በምቾትና በመንደላቀቅ ኖራችኋል። ለዕርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል።
\v 6 እናንተን ያልተቃወመውን ጻድቅ ሰው ኮንናችሁታል፤ ገድላችሁታል።
\s5
\v 7 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፣ የመጀመሪያውና የኋለኛው ዝናብ እስኪመጣ ድረስ የምድርን ፍሬ በትዕግሥት እንደሚጠብቅ ገበሬ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ።
\v 8 እናንተም እንዲሁ ታገሡ፤ ልባችሁን አዘጋጁ፤ ምክንያቱም የጌታ መምጫ ቅርብ ነው።
\s5
\v 9 ወንድሞች ሆይ፤ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ። ልብ በሉ፤ ፈራጁ በሩ ላይ ቆሞአል።
\v 10 በጌታ ስም የተናገሩ ነቢያትን መከራና ትዕግሥት እንደ ምሳሌ ውሰዱት።
\v 11 ልብ በሉ፤ በትዕግሥት የጸኑትን፣ “የተባረኩ” እንላቸዋለን። ስለ ኢዮብ ትዕግሥት ሰምታችኋል፤ ጌታ ለኢዮብ የነበረውንም ዓላማ ታውቃላችሁ፤ ጌታ እጅግ ሩኅሩኅና መሐሪ ነው።
\s5
\v 12 ወንድሞቼ ሆይ፣ ከሁሉም በላይ አትማሉ፤ በሰማይም ሆነ በምድር ወይም በሌላ ነገር አትማሉ። ቃላችሁ “አዎን” ካላችሁ፣ “አዎን” ይሁን፤ “አይደለም” ካላችሁም፣ “አይደለም” ይሁን።
\s5
\v 13 በእናንተ መካከል መከራ የደረሰበት አለ? እርሱ ይጸልይ። ደስ ያለው አለ? እርሱ ይዘምር።
\v 14 በእናንተ መካከል የታመመ አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት እየቀቡ ይጸልዩለት፤
\v 15 የእምነት ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሳል፤ ጌታም ያስነሣዋል። ኃጢአት አድርጎ ከሆነም እግዚአብሔር ይቅር ይለዋል።
\s5
\v 16 እንዲሁ ጌታ ከበሽታ ሊፈውስና ኃጢአትን ይቅር ሊል ስለሚችል ያደረጋችሁትን ኃጢአት በተመለከተ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተናዘዙ፡፡ ጻድቃን ሰዎች ከጸለዩና አንድ ነገር እንዲያደርግላቸው ጌታን አጥብቀው ከጠየቁት፣ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ደግሞም በእርግጠኝነት ያን ነገር ያደርገዋል፡፡
\v 17 ነቢዩ ኤልያስ እንደኛው ያለ ሰው ቢሆንም፣ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፡፡ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወራት ጊዜ ያህልም ዝናብ አልነበረም፡፡
\v 18 ከዚያም ዝናብ እንዲዘንብ እግዚአብሔርን እየለመነ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ዝናብን ላከ፣ ተክሎችም ዐደጉና ሰብልን ሰጡ፡፡
\s5
\v 19 ወንድቼና እኅቶቼ ሆይ፥ ከእናንተ አንዱ ዕውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል መልእክት መታዘዝ ቢያቆም፣ ከእናንተ አንዱ ያደርገው ዘንድ እግዚአብሔር ለዚያ ሰው የነገረውን ነገር በመንገር ሊያሳምነው ይገባል፡፡
\v 20 የሚያሳምነው ሰውም ኃጢአት እየሠራ የነበረውን ሰው ተናግሮ ስሕተት ከመሥራት እንዲመለስ ስላስቻለው፣ እግዚአብሔር ያንን ሰው ከመንፈሳዊ ሞት ያድነዋል፤ ደግሞም ብዙ የሆኑት ኃጢአቶቹን ይቅር ይልለታል፡፡

213
61-1PE.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,213 @@
\id 1PE
\ide UTF-8
\h 1ኛ ጴጥሮስ
\toc1 1ኛ ጴጥሮስ
\toc2 1ኛ ጴጥሮስ
\toc3 1pe
\mt 1ኛ ጴጥሮስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጴጥሮስ፤ በጳንጦስ፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በእስያና በቢታንያ ተበትነው በመጻተኝነት ለሚኖሩ፤ ለተመረጡት፤
\v 2 እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ እንዳወቃቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመታዘዝ በደሙ ለተረጩትና በመንፈስ ቅዱስ ለተቀደሱት፤ ጸጋ ለእናንተ ይሁን፤ ሰላማችሁም ይብዛ።
\s5
\v 3 የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባትና አምላክ ይባረክ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት በመነሣቱ ምክንያት ላገኘነው ርስት ዋስትና እንዲሆነን በታላቅ ምሕረቱ አዲስ ልደትን ሰጠን፤
\v 4 ይህም የማይጠፋ፣ የማይበላሽ እና የማያረጅ ርስት በመንግሥተ ሰማይ ተጠብቆላችኋል።
\v 5 እናንተም በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀው መዳን በእምነት አማካይነት በእግዚአብሔር ኅይል ተጠብቃችኋል።
\s5
\v 6 ምንም እንኳን አሁን በብዙ ልዩ ልዩ ዐይነት መከራ ማዘናችሁ ተገቢ ቢሆንም፣ በዚህ እጅግ ደስ ይላችኋል።
\v 7 ይኸውም፣ በእሳት ተፈትኖ ቢጠራም፣ ጠፊ ከሆነው ወርቅ ይልቅ እጅግ የከበረው እምነታችሁ እንዲፈተን ነው። ይህ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ አምነታችሁ ምስጋናን ክብርንና፣ ውዳሴን እንዲያስገኝላችሁ ነው።
\s5
\v 8 ኢየሱስ ክርስቶስን ባታዩትም እንኳ ትወዱታላችሁ፤ አሁን ባታዩትም በእርሱ ታምናላችሁ፤ ሊነገር በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት በጣም ደስ ይላችኋል፤
\v 9 አሁን የእምነታችሁን ፍጻሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ ነውና።
\v 10 እናንተ ስለምትቀበሉት ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ይፈልጉና በጥልቅ ይመረምሩ ነበር፤
\s5
\v 11 የሚመጣው መዳን ምን ዐይነት እንደ ሆነ ለማወቅ ይመረምሩ ነበር፤ እንዲሁም በእነርሱ ውስጥ የነበረው የክርስቶስ መንፈስ ስለ ክርስቶስ መከራና ከመከራው በኋላ ስለሚሆነው ክብር አስቀድሞ የተናገራቸው በምን ጊዜና እንዴት እንደሚፈጸም ይመረምሩ ነበር። ነቢያቱ ያገለግሉ የነበሩት እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳልነበረ ተገልጦላቸዋል፤
\v 12 ይኸውም ከሰማይ በተላከው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወንጌልን ያበሠሩአችሁ ሰዎች የነገሩአችሁን በመግለጥ ነው፤ መላእክትም እንኳ ይህ ነገር ሲገለጥ ለማየት ይመኙ ነበር።
\s5
\v 13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጠቁ፤ ጠንቃቆች ሁኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ በምታገኙት ጸጋ ላይ ፍጹም መተማመን ይኑራችሁ።
\v 14 ታዛዦች ልጆች እንደ መሆናችሁ ባለማወቅ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ።
\s5
\v 15 ነገር ግን የጠራችሁ እርሱ ቅዱስ እንደ ሆነ፣ እናንተም በኑሮአችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ፤
\v 16 ምክንያቱም «እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ» ተብሎ ተጽፎአል።
\v 17 ሳያዳላ በእያንዳንዱ ሰው ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን «አባት» ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በእንግድነት ዘመናችሁ እርሱን በማክበር ኑሩ።
\s5
\v 18 ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከማይረባ ሕይወት የተዋጃችሁት በሚጠፋ ነገር ማለትም በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤
\v 19 ይልቁንም የተዋጃችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም፣ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው።
\s5
\v 20 ክርስቶስ የተመረጠው ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ነው፤ አሁን ግን በመጨረሻው ዘመን ለእናንተ ተገለጠ።
\v 21 በእርሱ አማካይነት፣ ከሞት ባስነሣውና ክብርን በሰጠው በእግዚአብሔር ታምናላችሁ። ይኸውም እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ላይ እንዲሆን ነው።
\s5
\v 22 ለእውነት በመታዘዝ ለእውነተኛ የወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልብ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
\v 23 ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፤ ነገር ግን በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው።
\s5
\v 24 ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል፤ አበባውም ይረግፋል፤
\v 25 የጌታ ቃል ግን ለዘላለም ይኖራል። የተሰበከላችሁም ወንጌል መልእክቱ ይህ ነው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 እንግዲህ ክፋትን ፣ ማታለልን ፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ።
\v 2 በድነታችሁ በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹህ የሆነውን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤
\v 3 ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ ከሆነ፣
\s5
\v 4 በሰው ዘንድ ወደ ተናቀው፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠውና ክቡር ወደ ሆነው ወደዚህ ሕያው ድንጋይ ቅረቡ።
\v 5 ደግሞም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕት የሚያቀርቡ ቅዱሳን ካህናት ትሆኑ ዘንድ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ትሠራላችሁ።
\s5
\v 6 በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈው «እነሆ፤ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም» ።
\s5
\v 7 እንግዲህ ለምታምኑት ለእናንተ እርሱ ክቡር ነው፤ ለማያምኑት ግን፣«ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ»
\v 8 እንደዚሁም ደግሞ «ሰዎችን የሚያሰናክልና የሚጥላቸውም ዐለት ሆነ»። የሚሰናከሉት ቃሉን ባለመታዘዛቸው ነው፤ የተመደቡት ለዚህ ነውና።
\s5
\v 9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ፣ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር የራሱ ያደረጋችሁ ሕዝብ ናችሁ።
\v 10 ቀድሞ የእርሱ ሕዝብ አልነበራችሁም፤ አሁን ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆናችኋል፤ ቀድሞ ምሕረትን አላገኛችሁም ነበር፤ አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።
\s5
\v 11 ወዳጆች ሆይ፤ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ መጠን፣ ነፍሳችሁን ከሚዋጉ ከኅጢኣት ምኞቶች እንድትርቁ እለምናችኋለሁ።
\v 12 ክፉ እንደምትሠሩ አድርገው ቢያሟችሁም፣ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ መልካሙን ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያከብሩ፣ በአሕዛብ መካከል አኗኗራችሁ መልካም መሆን አለበት።
\s5
\v 13 ስለ ጌታ ብላችሁ ለምድራዊ ባለ ሥልጣን ሁሉ ታዘዙ፤
\v 14 የበላይ ባለ ሥልጣን ስለ ሆነ ለንጉሥ ቢሆን፣ ወይም ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት፣ በጎ አድራጊዎችን ለማመስገን እርሱ ለሾማቸው ገዦች ታዘዙ፤
\v 15 ምክንያቱም፣ መልካም በማድረግ የአላዋቂዎችን ከንቱ ንግግር ዝም እንድታሰኙ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።
\v 16 እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ሆናችሁ በነጻነት ኑሩ እንጂ ነጻነታችሁን የክፋት መሸፈኛ አታድርጉት።
\v 17 ለሰው ሁሉ ተገቢውን አክብሮት ስጡ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።
\s5
\v 18 እናንተ አገልጋዮች ፤ ለመልካሞችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለክፉዎችም በፍጹም አክብሮት ታዘዙ።
\v 19 ስለ እግዚአብሔር ሲል የግፍ መከራን የሚቀበል ሰው ምስጋናን ያገኛል።
\v 20 ክፉ ሥራ ሠርታችሁ ስትቀጡ ብትታገሡ ምን ያስመሰግናችኋል? ነገር ግን መልካም ሥራ ሠርታችሁ መከራ ስትቀበሉ ብትታገሡ ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስመሰግናችኋል።
\s5
\v 21 የተጠራችሁት ለዚህ ነው፤ ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌ ሊተውላችሁ ነው።
\v 22 እርሱ ኅጢአት አላደረገም፥ ተንኵልም በአፉ አልተገኘበትም፤
\v 23 ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራንም ሲቀበል አልዛተም፤ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤
\s5
\v 24 ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በመስቀል ላይ ተሸከመ፤ በእርሱ ቊስል እናንተ ተፈውሳችኋል።
\v 25 ቀድሞ ሁላችሁም እንደ ጠፉ በጎች ትቅበዘበዙ ነበር፤ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ሚስቶች ሆይ፤ እናንተም እንደዚሁ ለባሎቻችሁ ተገዙ፤ አንዳንድ ለቃሉ የማይታዘዙ ቢኖሩ እንኳ፣ ሚስቶቻቸው ቃል ሳይናገሩ በመልካም አኗኗራቸው ሊማርኳቸው ይችላሉ፤
\v 2 ይህም የሚሆነው ለእነርሱ ያላችሁን አክብሮት በንጹሕ አኗኗራችሁ ሲመለከቱ ነው።
\s5
\v 3 ውበታችሁ በውጫዊ ነገሮች በመሽሞንሞን ይኸውም ሹሩባ በመሠራት፣ በወርቅ በመንቆጥቆጥ ወይም ጌጠኛ ልብስ በመልበስ አይሁን፤
\v 4 ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት የከበረ፣ ገርና ጭምት መንፈስ ያለበት፣ ምንጊዜም የማይጠፋ የውስጥ ሰውነት ውበት ይሁን።
\s5
\v 5 የቀድሞ ቅዱሳት ሴቶች የተዋቡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እነርሱ በእግዚአብሔር የሚደገፉና ለባሎቻቸ የሚታዘዙ ነበሩ።
\v 6 ሣራም እንደዚሁ አብርሃምን «ጌታዬ» እያለች ትታዘዘው ነበር፣ እናንተም መከራን ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ፣ አሁን የእርሷ ልጆች ናችሁ።
\s5
\v 7 እንዲሁም ባሎች ሆይ፤ ሚስቶቻችሁ ደካማ አጋር መሆናቸውን ዐውቃችሁ፣ የሕይወትን ጸጋ ከእናንተ ጋር አብረው የሚካፈሉ መሆናቸውንም ተገንዝባችሁ አብራችኋቸው ኑሩ። ጸሎታችሁ እንዳይከለከል ይህን አድርጉ።
\s5
\v 8 በመጨረሻም፣ ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ ተዛዘኑ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።
\v 9 ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም እናንተ የተጠራችሁት በረከትን ለመውረስ ነው።
\s5
\v 10 ስለዚህ «ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።
\v 11 ከክፉ ይራቅ፤ መልካምንም ያድርግ፤ ሰላምን ይፈልግ፤ ይከተላትም።
\v 12 የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።»
\s5
\v 13 መልካም ነገር ለማድረግ ብትቀኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?
\v 14 ነገር ግን በጽድቅ ምክንያት መከራ ቢደርስባችሁ ቡሩካን ናችሁ፤ ዛቻቸውን አትፍሩ፤ አትታወኩም።
\s5
\v 15 ይልቁንም፣ ክርስቶስ የከበረ መሆኑን ተረድታችሁ በልባችሁ ቀድሱት። እናንተ በእግዚአብሔር ላይ ስላላችሁ መታመን ምክንያቱን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁል ጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ፤ ነገር ግን ይህን ሁሉ በትሕትናና በአክብሮት አድርጉት፤
\v 16 በክርስቶስ ያላችሁን መልካም አናናራችሁን የሚያክፋፉ ሰዎች በሐሜታቸው እንዲያፍሩ በጎ ኅሊና ይኑራችሁ።
\v 17 እግዚአብሔር የሚፈልገው ይህን ከሆነ፣ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል፤
\s5
\v 18 እንዲሁም ክርስቶስ አንድ ጊዜ ስለ ኀጢአታችን ሞቷል። ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ፣ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ እኛ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤
\v 19 በመንፈስም ሄዶ በወህኒ ቤት ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው፤
\v 20 በወህኒ የነበሩት እነዚህ ነፍሳት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ይጠብቃቸው የነበሩ እምቢተኞች ናቸው፤ እግዚአብሔር ከውሃ ያዳናቸው ጥቂት ሰዎችን፣ ይኸውም ስምንት ሰዎችን ብቻ ነበር።
\s5
\v 21 ይህም ውሃ አሁን እናንተን የሚያድነው የጥምቀት ምሳሌ ነው፤ ይህ ጥምቀት የሰውነትን ዕድፍ ማስወገድ ሳይሆን ንጹሕ ኅሊናን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ልመና ነው፤ የሚያድናችሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ አማካይነት ነው፤
\v 22 እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ አለ፤ መላእክት፣ ሥልጣናትና ኀይላትም ተገዝተውለታል።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ክርስቶስ በሥጋው መከራን ስለ ተቀበለ፣ እናንተም በዚሁ ዐላማ ታጥቃችሁ ተነሡ፤ በሥጋው መከራን የሚቀበል ሰው ኀጢአትን ትቶአል።
\v 2 እንዲህ ያለው ሰው ከእንግዲህ በሚቀረው ዕድሜ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ እንደ ሥጋ ምኞት አይኖርም።
\s5
\v 3 አሕዛብ ፈልገው እንደሚያደርጉት በመዳራት፣ በሥጋ ምኞት፣ በስካር፣ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያ፣ በጭፈራና ርኵስ ከሆነ የጣዖት አምልኮ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።
\v 4 እነዚህን ነገሮች ለማድረግ ከአነርሱ ጋር አለመተባበራችሁ እንግዳ ሆኖባቸው ስለ እናንተ ክፉ ያወራሉ።
\v 5 ነገር ግን እነርሱ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ ለተዘጋጀው መልስ ይሰጣሉ።
\v 6 ወንጌል ለሙታን የተሰበከው በዚህ ምክንያት ነው፤ በሥጋቸው እንደ ሰው ሁሉ ይፈረድባቸዋል፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በመንፈስ ይኖራሉ።
\s5
\v 7 የሁሉም ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በአስተሳሰባችሁም ጠንቃቆች ሁኑ።
\v 8 ፍቅር ብዙ ኀጢአትን ይሸፍናልና ከሁሉ አስቀድሞ እርስ በርሳችሁ ከልብ ተዋደዱ፤
\v 9 ያለ ማጒረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ።
\s5
\v 10 እንደ ታማኝ የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ መጋቢ እያንዳንዱ ሰው በተቀበለው የጸጋ ስጦታ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤
\v 11 የሚናገር ቢኖር እንደ እግዚአብሔር ቃል ይናገር፤ የሚያገለግልም ቢኖር እግዚአብሔር በሚሰጠው ብርታት ያገልግል፤ ይኸውም እግዚአብሔር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት በሁሉም ነገር እንዲከብር ነው፤ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን፤ አሜን።
\s5
\v 12 ወዳጆች ሆይ፤ እንደ እሳት የሚፈትን ብርቱ መከራ ስትቀበሉ፣ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ በመቍጠር አትደነቁ፤
\v 13 ነገር ግን ክብሩ በሚገለጥበት ጊዜ ደስታችሁ ታላቅ እንዲሆን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች በመሆናችሁ ሐሴት አድርጉ።
\v 14 ስለ ክርስቶስ ስም ብትሰደቡ፣ የክብር መንፈስ የሆነው የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ላይ ስለሚያርፍ ቡሩካን ናችሁ።
\s5
\v 15 ከእናንተ ማንም እንደ ነፍሰ ገዳይ፣ እንደ ሌባ፣ እንደ ክፉ አድራጊ ወይም በሰው ነገር ጣልቃ እንደሚገባ ሰው ሆኖ መከራን አይቀበል፤
\v 16 ማንም ክርስቲያን በመሆኑ መከራ ቢደርስበት፣ በዚህ ስም እግዚአብሔርን ያመስግን እንጂ አይፈር፤
\s5
\v 17 ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት የሚጀምርበት ጊዜ ቀርቦአል። እንግዲህ ፍርድ የሚጀምረው በእኛ ከሆነ፣ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ ሰዎች መጨረሻቸው ምን ይሆን?
\v 18 እንግዲህ፣ ጻድቅ ሰው የሚድነው በጭንቅ ከሆነ፣ ዐመፀኛውና ኀጢአተኛው እንዴት ይሆን ይሆን?”
\v 19 ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ መልካም እያደረጉ ነፍሳቸውን ለታመነው ፈጣሪ ዐደራ ይስጡ። ።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 እንግዲህ እኔም ከእነርሱ ጋር ሽማግሌና የክርስቶስ መከራ ምስክር የሆንሁ እንዲሁም ወደ ፊት የሚገለጠው ክብር ተካፋይ የምሆን በመካከላችሁ ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤
\v 2 ስለዚህ፣ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ የምትጠብቋቸውም ማድረግ ስላለባችሁ በግዴታ ሳይሆን፣ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በደስታ ይሁን፤ ጥቅም ለማግኘት በመስገብገብ ሳይሆን፣ በበጎ ፈቃደኝነት ይሁን፤
\v 3 እንዲሁም በእናንተ ኀላፊነት ሥር ላለው መንጋ መልካም ምሳሌ ሁኑ እንጂ እንደ ዐለቃ በላያቸው አትሠልጥኑ።
\v 4 የእረኞች ዐለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይጠፋውን የክብር አክሊል ትቀበላላችሁ።
\s5
\v 5 ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ ምክንያቱም፣ «እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል» እንደ ተባለው፣
\v 6 እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤
\v 7 እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
\s5
\v 8 ጠንቃቆች ሁኑ፤ ንቁም፤ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሳ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል።
\v 9 በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እንደሚቀበሉ ዐውቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
\s5
\v 10 ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ ፣ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለማዊ ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ፍጹማን ያደርጋችኋል፤ ያጸናችኋል ፤ ያበረታችኋልም።
\v 11 የገዥነት ሥልጣን ከዘላለም እስከ ዘላለም ለእርሱ ይሁን! አሜን።
\s5
\v 12 እንደ ታማኝ ወንድም በምቈጥረው በስልዋኖስ አማካይነት ይህን ዐጭር መልእክት ጽፌላችኋለሁ፤ የጻፍሁላችሁም ልመክራችሁና ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልመሰክርላችሁ ነው። በዚህ ጸጋ ጸንታችሁ ቁሙ።
\v 13 ከእናንተ ጋር የተመረጠችው፣ በባቢሎን የምትገኘው ሰላምታ ታቀርብላችኋለች፤ እንዲሁም ልጄ ማርቆስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል።
\v 14 በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁም ሰላም ይሁን።

125
62-2PE.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,125 @@
\id 2PE
\ide UTF-8
\h 2ኛ ጴጥሮስ
\toc1 2ኛ ጴጥሮስ
\toc2 2ኛ ጴጥሮስ
\toc3 2pe
\mt 2ኛ ጴጥሮስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ስምዖን ጴጥሮስ፤ በአምላካችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ አማካይነት የተቀበልነውን ዐይነት ክቡር እምነት ለተቀበሉት፤
\v 2 እግዚአብሔርንና ጌታችንን ኢየሱስን በማወቅ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
\s5
\v 3 በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን እግዚአብሔርን በማወቅ እንድንኖር ለሕይወትና ለእውነተኛ መንፈሳዊነት የሚያስፈልገን ሁሉ በመለኮቱ ኀይል ተሰጥቶናል።
\v 4 በእነዚህ ነገሮች አማካይነት እጅግ የከበረና ታላቅ ተስፋ ሰጠን፤ ይህንም ያደረገው በክፉ ምኞቶች ሰበብ በዓለም ካለው ምግባረ ብልሹ ሕይወት አምልጣችሁ ከመለኮታዊ ባሕርይ ተካፋዮች እንድትሆኑ ነው።
\s5
\v 5 በዚህም ምክንያት፣ የሚከተሉትን ነገሮች ለመጨመር ትጉ፣ በእምነታችሁ ላይ ደግነትን፣ በደግነት ላይ ዕውቀትን፣
\v 6 በዕውቀት ላይ ራስን መግዛት፣ ራስን በመግዛት ላይ መጽናትን፣ በመጽናት ላይ እግዚአብሔርን መምሰልን፤
\v 7 እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣ በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ።
\s5
\v 8 እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና በውስጣችሁ ቢያድጉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ዳተኞችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ያደርጉአችኋል።
\v 9 እነዚህ ነገሮች የሌሉት ግን ዕውር ነው፤ በቅርብ ያለውን ብቻ ያያል፤ ከቀድሞው ኀጢአቱ መንጻቱንም ረስቶአል።
\s5
\v 10 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፤ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ለማጽናት ትጉ፤ ይህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉም፤
\v 11 በዚህም ወደ ጌታችንና አዳኛችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘላለማዊ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋል።
\s5
\v 12 ስለዚህ ምንም እንኳ እነዚህን ነገሮች ብታውቋቸውና በያዛችሁት እውነት ብትጸኑም፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ዘወትር እናንተን ከማሳሰብ ቸል አልልም።
\v 13 በዚህ ምድራዊ ድንኳን ውስጥ እስካለሁ ድረስ ስለ እነዚህ ነገሮች እናንተን ማሳሰብ ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ፤
\v 14 ምክንያቱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ገለጠልኝ ይህን ምድራዊ ድንኳን ቶሎ ለቅቄ እንደምሄድ ዐውቃለሁ፤
\v 15 ከተለየኋችሁም በኋላ እነዚህን ነገሮች ዘወትር እንድታስቡ የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ።
\s5
\v 16 ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ ዳግም መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ ግርማውን በዐይናችን አይተን መሰከርን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ተከትለን አይደለም።
\v 17 «በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው» የሚል ድምፅ ከግርማዊው ክብር በመጣለት ጊዜ፣ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ሞገስን ተቀብሎአል።
\v 18 ከእርሱ ጋር በተቀደሰው ተራራ ላይ በነበርንበት ጊዜ ይህን ከሰማይ የመጣውን ድምፅ ሰምተነዋል።
\s5
\v 19 ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል፤ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ በጨለማ ስፍራ ለሚያበራ መብራት እንደምትጠንቀቁ፣ የንጋቱ ኮከብ በልባችሁ እስኪበራ ድረስ ለዚህ ቃል ብትጠነቀቁ መልካም ታደርጋላችሁ።
\v 20 ይህን በመጀመሪያ ዕወቁ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት የሚገኘውን የትንቢት ቃል ማንም ሰው በራሱ መንገድ የሚተረጒመው አይደለም፤
\v 21 ምክንያቱም ትንቢት ከእግዚአብሔር የተላኩ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናገሩት እንጂ ከቶ በሰው ፈቃድ የመጣ አይደለም።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ሐሰተኞች ነቢያት በእስራኤላውያን መካከል ነበሩ፤ በእናንተ መካከል ደግሞ ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። ብዙዎች የእነርሱን መዳራት ይከተላሉ።
\v 2 ከእነርሱም አድራጎት የተነሣ የእውነት መንገድ ይሰደባል።
\v 3 እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ የሚያታልሉ ቃላትን በመጠቀም ይበዘብዙአችኋል። በእነርሱ ላይ ያለው ፍርድ አይዘገይም፤ መጥፊያቸውም የራቀ አይደለም።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሐነም ከጣላቸውና በሰንሰለት አስሮ እስከ ፍርድ ጊዜ ድረስ በጨለማ ውስጥ ካስቀመጣቸው፣
\v 5 የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ ለጥንቱ ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣
\v 6 ደግሞም ኀጢአት በሚያደርጉ ሁሉ ላይ የሚመጣው ጥፋት ምሳሌ እንዲሆኑ የሰዶምንና የገሞራን ከተሞች ዐመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጥሎ ከፈረደባቸው፣
\s5
\v 7 በሕገ ወጦች ሴሰኝነት ነፍሱ እየተጨነቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን ግን አዳነው፤
\v 8 ያ ጻድቅ ሰው በመካከላቸው ሲኖር በየቀኑ ያየውና ይሰማው በነበረው ሕገ ወጥ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱ ትጨነቅ ነበር።
\v 9 ጌታ፣ እግዚአብሔርን የሚመስሉትን ሰዎች ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል።
\s5
\v 10 በተለይም ብልሹ የሥጋ ምኞታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለ ሆኑ የከበሩትን ሲሳደቡ አይፈሩም፤
\v 11 መላእክት ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ብርታትና ችሎታ ያላቸው ሆነው ሳሉ፣ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ ዘለፋ ያዘለ የፍርድ ቃል አይሰነዝሩም።
\s5
\v 12 እነዚህ አእምሮ እንደ ጎደላቸው እንስሳት ለምርኮና ለጥፋት የተፈጠሩ ናቸው፤ የሚሳደቡትን ስለማያውቁ ይጠፋሉ።
\v 13 እነርሱ የዐመፃቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ በቀን በመስከርና ያለ ልክ በመፈንጠዝ ይኖራሉ ፤ እነርሱ አሳፋሪዎችና ነውረኞች ናቸው። ከእናንተ ጋር ግብዣ ላይ ሲገኙ፣ በአታላይ ፈንጠዝያቸው ሐሴት ያደርጋሉ።
\v 14 ዐይናቸው ቅንዝር የተሞላ በመሆኑ ኀጢአትን ከመሥራት ከቶ አይቈጠቡም፤ ጽኑ ያልሆኑትን ሰዎች ያስታሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 15 ቀናውን መንገድ ትተው፣ በክፉ ሥራ የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ስተዋል፤
\v 16 እርሱ ስለ መተላለፉ ተገሥጾአል፤ መናገር የማይችል አህያ በሰው ቋንቋ ተናግሮ የነቢዩን እብደት አስቍሟልና።
\s5
\v 17 እነዚህ ሰዎች እንደ ደረቁ ምንጮችና በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዱ ደመናዎች ናቸው፤ የሚጠብቃቸውም ድቅድቅ ጨለማ ነው፤
\v 18 ፍሬ ቢስ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወታቸው ሰዎችን ያጠምዳሉ፤ ከተሳሳተና ከብልሹ የሕይወት ዘይቤ ለማምለጥ የሚሞክሩትን ሰዎች ያጠምዳሉ።
\v 19 እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነጻ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለሚሸነፍለት ለማንኛውም ነገር ባሪያ ነውና።
\s5
\v 20 ጌታችንንና አዳኛችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በማወቅ ከዓለም ርኵሰት ካመለጡ በኋላ፣ እንደ ገና ወደ ቀደሞው የርኵሰት ሕይወት ቢመለሱ፣ ከመጀመሪያው ይልቅ የኋለኛው የከፋ ይሆንባቸዋል።
\v 21 የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ፣ ቀድሞውኑ የጽድቅን መንገድ ባያውቋት ይሻላቸው ነበር።
\v 22 «ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል» እንዲሁም «ዐሣማ ቢታጠብም ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል» የሚለው ምሳሌ እውን ይሆንባቸዋል።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ወዳጆች ሆይ! ይህን ሁለተኛ መልእክት የምጽፍላችሁ፣ ቅን ልቦናችሁን ለማነቃቃት ነው፤
\v 2 ደግሞም አስቀድሞ በቅዱሳን ነቢያት የተነገረውን ቃል እንዲሁም በሐዋርያቶቻችሁ አማካይነት በጌታችንና በአዳኛችን የተሰጠውን ትእዛዝ እንድታስታውሱ ነው።
\s5
\v 3 በቅድሚያ ይህን ዕወቁ፤ በመጨረሻዎቹ ቀኖች የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ዘባቾች እየዘበቱባችሁ ይመጣሉ።
\v 4 እነርሱም፣ «የመምጣቱ ተስፋ ወዴት አለ? አባቶቻችን ሞተዋል፤ ከፍጥረት መጀመሪያም አንሥቶ እስካሁን ድረስ ሁሉም ነገር እንዳለ ይኖራል» ይላሉ።
\s5
\v 5 እነዚህ ሰዎች ሰማያትና ምድር ከብዙ ዘመን በፊት በእግዚአብሔር ቃል ከውሃና በውሃ አማካይነት መፈጠራቸውን ፣ ሆን ብለው ይክዳሉ፤
\v 6 በቃሉና በውሃ እማካይነት በዚያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውሃ ተጥለቅልቆ ጠፋ።
\v 7 ደግሞም በዚያው ቃል አሁን ያሉት ሰማያትና ምድር ኀጢአተኞች እስከሚጠፉበት እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለእሳት ተጠብቀዋል።
\s5
\v 8 ወዳጆች ሆይ፤ ፤በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፣ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን መሆኑን ይህን አትዘንጉ ።
\v 9 አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዳችሁም እንድትጠፉ ስለማይፈልግና ሰው ሁሉ በቂ የንስሓ ጊዜ እንዲያገኝ ፈልጎ ስለ እናንተ ይታገሳል።
\s5
\v 10 ይሁን እንጂ የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ የሰማይም ፍጥረት በእሳት ይቃጠላል፤ በምድርና በእርሷም ውስጥ በተሠራው ነገር ሁሉ ላይ ይፈረድበታል።
\s5
\v 11 እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በዚህ ሁኔታ የሚጠፉ ከሆነ፣ ታዲያ እናንተ በቅድስናና እግዚአብሔርን በመምሰል ሕይወት ለመኖር እንዴት ዐይነት ሰዎች ልትሆኑ ይገባችኋል?
\v 12 ስለዚህ የእግዚአብሔርን ቀን መምጣት በናፍቆት የምትጠባበቁና የምታፋጥኑ ሁኑ፤ በዚያን ቀን ሰማያት በእሳት ተቃጥለው ይጠፋሉ፤ ፍጥረታትም በእሳት ግለት ይቀልጣሉ፤
\v 13 እኛ ግን እርሱ በሰጠን ተስፋ መሠረት፣ ጽድቅ የሰፈነበትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንጠባበቃለን።
\s5
\v 14 ስለዚህ ወዳጆች ሆይ፤ እነዚህን ነገሮች የምትጠባበቁ እንደ መሆናችሁ፣ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ ከእርሱም ጋር በሰላም እንድትገኙ ትጉ።
\v 15 እንዲሁም ወንድማችን ጳውሎስ በተሰጠው ጥበብ መጠን እንደ ጻፈላችሁ፤ የጌታችን ትዕግሥት እናንተ እንድትድኑ እንደ ሆነ አስቡ፤ ምንም እንኳ በመልእክቶቹ ውስጥ በቀላሉ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ነገሮች ቢኖሩም፣
\v 16 ጳውሎስ ስለ እነዚህ ነገሮች በመልእክቶቹ ሁሉ ጽፎአል፤ ዕውቀት የጐደላቸውና ጽናት የሌላቸው ሰዎች ሌሎችን የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች እንደሚያጣምሙ ሁሉ እነዚህም ለገዛ ጥፋታቸው ያጣምማሉ።
\s5
\v 17 እንግዲህ ወዳጆች ሆይ፤ ይህን አስቀድማችሁ ስላወቃችሁ፣ በዐመፀኞች ስሕተት ተስባችሁ ጽኑ መሠረታችሁን እንዳትለቅቁ ተጠንቀቁ።
\v 18 ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ፤ ለእርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን፤ አሜን!

208
63-1JN.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,208 @@
\id 1JN
\ide UTF-8
\h 1ኛ ዬሐንስ
\toc1 1ኛ ዬሐንስ
\toc2 1ኛ ዬሐንስ
\toc3 1jn
\mt 1ኛ ዬሐንስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከመጀመሪያው ስለ ነበረው፣ ስለ ሰማነው፣ በዓይኖቻች ስላየነው፣ ስለ ተመለከትነው ፣በእጆቻችንም ስለ ዳሰስነው ስለ ህይወት ቃል
\v 2 ህይወትም ተገልጦ ነበር ፤እኛም አይተናል፣ምስክሮችም ነን፤ በአብ ዘንድ ስለ ነበረው ለእኛም ስለ ተገለጠው፣ የዘላለም ሕይወት እንናገራለን፤
\s5
\v 3 ከእኛም ጋር ህብረት እንዲኖራቸሁ፣ ያየነውንና የሰማነውን እንነግራችኋለን፤ ህብረታችንም ከአብና፣ ከልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፡፡
\v 4 ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ፣እነዚህን ነገሮች እንጽፍላችኋለን።
\s5
\v 5 ከእርሱ የሰማነው፣ለናንተም የምንነግራችሁ መልዕክት፣ እግዚአብሔር ብርሃን ነው፤ በእርሱም ምንም ጨለማ የለም፤ የሚል ነው፡፡
\v 6 ከእርሱ ጋር ህብረት አለን እያልን፣ ነገር ግን በጨለማ ውስጥ ብንመላለስ፣እንዋሻለን ፣እውነትንም አናደርግም፡፡
\v 7 እርሱ ብርሃን እንደሆነ ፣ በብርሃን ብንመለላለስ እርስ በርሳችን ህብረት ይኖረናል፡፡የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስም ደም ከሃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
\s5
\v 8 ሃጢያት የለብንም ብንል፣ ራሳችንን እናስታለን፣ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
\v 9 ነገር ግን ሃጢያታችንን ብንናዘዝ፣ሃጢያታችንን ይቅር ሊለንና ከዓመጽ ሁሉ ሊያነጻን፣ የታመነና ፃድቅ ነው፡፡
\v 10 ሃጢአት አላደረግንም ብንል፣ ሃሰተኛ እናደርገዋለን፣ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም፡፡
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣ሃጢያት እንዳታደርጉ ይህን እፅፍላችኋላሁ። ግን ማንም ሃጢያት ቢያደርግ ፣ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን ፤እርሱም ፃድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡
\v 2 እርሱ የእኛ ብቻ ሳይሆን፣ የዓለሙም ሁሉ ሃጢዓት ማስተስረያ ነው፣፡፡
\v 3 ትዕእዛዙን የምንጠብቅ ከሆነ ፣በዚህ እርሱን እንዳወቅነው እናውቃለን።
\s5
\v 4 "እግዚአብሔርን አውቀዋለሁ" የሚል ፣ግን ትዕዛዛቱን የማይጠብቅ፣ ውሸታም ነው ፣እውነትም በውስጡ የለም፡፡
\v 5 ሆኖም ማንም ቃሉን ቢጠብቅ፣ በርግርጥ በዚያ ሰው ለእግዚአብሔር ያለው ፍቅር ተገልጧል፤ በዚህም በእርሱ እንደሆንን እናውቃለን።
\v 6 በእግዚአብሔር እኖራለሁ የሚል ፣ኢየሱስ ክርስቶስ እንደኖረ መኖር አለበት።
\s5
\v 7 የተወደዳችሁ፣የምጽፍላችሁ በመጀመሪያ የነበረውን አሮጌ ትዕዛዝ እንጂ አዲስ ትዕዛዝ አይደለም።አሮጌውም ትእዛዝ የሰማችሁት ቃል ነው፡፡
\v 8 ሆኖ በክርስቶስና በናንተ እውነት የሆነውን አዲሱን ትእዛዝ እጽፍላችኋለሁ።ምክንያቱም ጨለማው አልፎ እውነተኛው ብርሃን እያበራ ነው።
\s5
\v 9 በብርሃን አለሁ እያለ ፣ወንድሙን ግን የሚጠላ ፣አሁንም እንኳ በጨለማ ውስጥ ነው፡፡
\v 10 ወንድሙን የሚወድ በብርሃን ይኖራል። የሚያሰናክል ሁኔታም የለም፡፡
\v 11 ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው፣ በጨለማም ይኖራል፤ ወዴት እንደሚሄድም አያውቅም ፣ምክንያቱም ጨለማው ዓይኖች አሳውሮታል፡፡
\s5
\v 12 ልጆች ሆይ! ኃጢያታችሁ በክርስቶስ ስም ይቅር ስለተባለ እፅፍላችኋለሁ፡፡
\v 13 አባቶች ሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃኋልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ! ክፉውን ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡ ታናናሽ ልጆች ሆይ! አብን ስላወቃችሁ እጽፍላችኋለሁ፡፡
\v 14 አባቶችሆይ! ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ወጣቶች ሆይ! ብርቱዎች ስለሆናቹ ፣የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር፣ ክፉውንም አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ፡፡
\s5
\v 15 ዓለምን ወይም በዓለም ያሉት ነገሮች አትውደዱ። ማንም ዓለምን ቢወድ የአብ ፍቅር በርሱ ውስጥ የለም፡፡
\v 16 በዓለም ያለው ሁሉ፣ የሥጋ ምኞት፣ የዓይን አምሮትና ትምክህት ከዓለም እንጂ ከአብ አይደሉም፡፡
\v 17 ዓለሙና ምኞቱም ያልፋሉ፣የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል፡፡
\s5
\v 18 ታናናሾች ልጆች ሆይ! የክርስቶስ ተቀዋሚ ስለመምጣቱ እንደሰማችሁት ፣ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፡፡ አሁንም እንኳ፣ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፡፡
\v 19 ከእኛው መካከል ወጥተዋል ፣ከእኛ ወገን ግን አልነበሩም። ከእኛ ወገን ቢሆኑ ኖሮ፣ ከእኛ ጋር ፀንተው ይኖሩ ነበር። ሆኖም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ እንዲገለጥ ወጡ።
\s5
\v 20 እናንት ግን፣ከቅዱሱ የተቀበላችሁት ቅባት ስላላችሁ፣ሁላችሁም እውነትን ታውቃላችሁ።
\v 21 የምጽፍላችሁ እውነትን ስለማታውቁ አይደለም፤ነገር ግን ስለምታውቁትና፣ በእውነትም ምንም ሃሰት ስለሌለ ነው።
\s5
\v 22 ኢየሱስ ክርስቶስ መሆኑን ከሚክድ በስተቀር ሃሰተኛ ማነው ነው? አብና ወልድን ስለሚክድ፣እንዲህ ዓይነት ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
\v 23 ወልድን የሚክድ ሁሉ አብ የለውም፤ ወልድንን የሚያውቅ አብም ደግሞ አለው።
\s5
\v 24 እናንተ ግን ፣ከመጀመሪያው የሰማችሁት በውስጣችሁ ይኑር። ከመጀመሪያ የሰማችሁት፣በእናንተ ቢኖር፣እናንተም በወልድና በአብ ትኖራላችሁ።
\v 25 እርሱ የሰጠን ተስፋ ይህ ነው፤ እርሱም የዘላለም ሕይወት ነው።
\v 26 የሚያስቷችሁን በተመለከተ ፣ ይህን ፅፌላችኋለሁ፡፡
\s5
\v 27 እናንተ ግን የተቀበለች ቅባት በእናንተ ስለሚኖር ፣ማንም እንዲያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም። የርሱም ቅባት ስለ ሁሉም ነገሮች እውነት እንጂ ሃሰት ስለማያስተምራችሁ ፣ እንደተማራችሁት በርሱ ኑሩ፡፡
\v 28 አሁንም የተወዳዳችሁ ልጆች፣ በሚገለጥበለት ጊዜ ድፍረት እንዲኖረንና ፣በመምጣቱም እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ፡፡
\v 29 እርሱ ፃድቅ እንደሆነ ካወቃችሁ ፣ፅድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከርሱ እንደተወለደ ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።
\v 2 የተወደዳችሁ፣አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፤ምክንያቱም ትክክለኛ ማንንነቱን እናየዋለን።
\v 3 በእርሱም ላይ ይህ ጽኑ እምነት ያለው ሁሉ፣ እርሱ ንፁህ እንደሆነ ራሱን ያነፃል፡፡
\s5
\v 4 ኃጢያትን የሚሠራ ሁሉ ዐመጽን ያደርጋል፣ ኃጢአትም ዐመጽ ነው፡፡
\v 5 ኃጢያትን ለማስወገድ ክርስቶስ እንደተገለፀ ታውቃላችሁ፣ በእርሱም ኃጢያት የለም፡፡
\v 6 በእርሱ የሚኖር ኃጢያት አያደርግም፡፡ ኃጢያት የሚያደርግ እርሱን አላየውም ወይም አላወቀውም፡፡
\s5
\v 7 የተወደዳችሁ ልጆች፣ ማንም አያስታችሁ፡፡ ክርስቶስ ፃድቅ እንደሆነ ሁሉ፣ ፅድቅን የሚያደርግ ፃድቅ ነው።
\v 8 ኃጢያት የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፤ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያው ኃጢያት አድርጓል፡፡ በዚህም ምንክያት የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ፣የእግዚአብሔር ልጅ ተገልጧል፡፡
\s5
\v 9 የእግዚአብሔር ዘር በርሱ ስለሚኖር ፣ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢያትን አያደርግም፤ ከእግዚአብሔር ተወልዷልና ኃጢያትን ሊያደርግም አይችልም።
\v 10 በዚህም የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ይታወቃሉ፡፡ ፅድቅን የማያደርግ ወይም ወንድሙን የማይወድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡
\s5
\v 11 ከመጀመሪያው የሰማችኋት መልእክት፣ይህ እርስ በርሳችን እንድንዋደድ የሚለው ነው።
\v 12 ክፉ እንደሆነውና ወንድሙን እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም። የገደለው ለምንድን ነው? ምክንያቱ የራሱ ሥራ ክፉ፣ የወንድሙ ጽድቅ ስለነበረ ነው፡፡
\s5
\v 13 ወንድሞች፣ ዓለም ቢጠላችሁ፣አትደነቁ።
\v 14 ወንድሞችን ስለምንወድ ፣ከሞት ወደ ህይወት እንደተሻገርን እናውቃለን። ፍቅር የሌለው በሞት ውስጥ ይኖራል፡፡
\v 15 ወንድሙን የሚጠላ ነፍሰ ገዳይ ነው፡፡ ነፍሰ ገዳይ የሆነ ሁሉ፣ በውስጡ የዘላለም ህይወት እንደሌለው ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\v 16 ክርስቶስ ለእኛ ህይወቱን ሰጥቷልና፣በዚህ ፍቅርን እናውቃለን።እኛም ለወንድሞቻችን ህይወታችንን አሳልፈን መስጠት ይገባናል።
\v 17 ነገር ግን ማንም የዚህ ዓለም ንብረት ያለውና፣ወንድሙም የሚያስፈልገውን አውቆ፣ባይራራለት፣ እንዴት የእግዚአብሔር ፍቅር በርሱ ይኖራል?
\v 18 የተወደዳችሁ ልጆቼ ፣በሥራና በእውነት እንጂ ፣በቃል ወይም በአንደበት አንዋደድ።
\s5
\v 19 በዚህም ከእውነት እንደሆንንና፣ልባችንም በፊቱ ትክክል እንደሆነ እናረጋግጣለን።
\v 20 ልባችን ግን የሚፈርድብን ከሆነ፣ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነው፣ሁሉንም ያውቃል፡፡
\v 21 ወዳጆች ሆይ! ልባችን የማይፈርድብን ከሆነ፣በእግዚአብሔር ፊት ድፍረት አለን።
\v 22 ትዕዛዙን የምንጠብቅና፣በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆነ፣ የምንለምነውንና ሁሉ እንቀበላለን፡፡
\s5
\v 23 የርሱም ትዕዛዙ፣በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንድናምንና፣ ትእዛዙን እንደሰጠን እንደዚያው እርስ በርስ እንድንዋደድ ነው፡፡
\v 24 የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ፣በርሱ ይኖራል እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡በዚህም በሰጠን በመንፈሱ፣ በእኛ ውስጥ እንደሚኖር እናውቃለን።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ወዳጆች ሆይ! መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፣ ምክንያቱም ብዙ ሃሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ገብተዋል፡፡
\v 2 የእግዚአብሔርን መንፈስ በዚህ እናውቃለን፣- ጌታ ኢየሱስ በሥጋ እንደመጣ የሚቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው።
\v 3 ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። ይህ እንደሚመጣ የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፣ አሁን እንኳ በዓለም ውስጥ አለ፡፡
\s5
\v 4 የተወደዳችሁ ልጆች! እናንተ ከእግዚአብሔር ስለሆናችሁ፣ እነዚህን መናፍስት አሸንፋችኋል፣ ምክንያቱም በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ይበልጣል፡፡
\v 5 እነዚህ መናፍስት ከዓለም ናቸው፣ስለሆነም የሚናገሩት ሁሉ የዓለምን ነው፣ዓለምም ይሰማቸዋል፡፡
\v 6 እኛ ከእግዚአብሔር ነን። እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል። ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም። በዚህም የእውነት መንፈስንና ፣የስህተትን መንፈስን እናውቃለን፡፡
\s5
\v 7 ወዳጆች ሆይ! እርስ በርስ እንዋደድ፣ምክንያቱም ፍቅር ከእግዚአብሔር ነውና፣ ፍቅር ያለው ከእግዚአብሔር ተወልዷል፣ እግዚአብሔርንም ያውቃል፡፡
\v 8 ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፣እግዚአብሔር ፍቅር ነውና፡፡
\s5
\v 9 በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በመካከላችን ተገልጧል፣ እግዚአብሔር በርሱ እንድንኖር ፣አንድ ልጁን ወደ ዓለም ላከው፡፡
\v 10 ፍቅር እንደዚህ ነው፣እግዚአብሔርን ስለወደድነው ሳይሆን፣ እርሱ ስለወደደን ለኃጢያታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ላከ፡፡
\s5
\v 11 ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል።
\v 12 ማንም እግዚአብሔርን አላየውም። እርስ በርሳችን ብንዋደድ፣ እግዚአብሔር በኛ ይኖራል፣ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል፡፡
\v 13 መንፈሱን ሰጥቶናልና፣ በዚህም እኛ በእርሱ እንደምንኖር፣ እርሱም በኛ እንደሚኖር እናውቃለን።
\v 14 እኛም አይተናል፣እግዚአብሔር ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጐ እንደላከውም እንመሰክራለን፡፡
\s5
\v 15 ማንም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ቢቀበል፣ እግዚአብሔር በርሱ ይኖራል ፤እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል፡፡
\v 16 እኛም እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል ደግሞም አምነናል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡
\s5
\v 17 በፍርድ ቀን ድፍረት እንዲኖረን፣ይህም ፍቅር በመካከላችን ተፈጸሟል፣ እኛም በዚህ ዓለም እንደ እርሱ ነን ፡፡
\v 18 በፍቅር ፍርሃት የለም። ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፣ ምክንያቱም ፍርሃት የሚያመለክተው ቅጣት መኖሩን ነው። የሚፈራ ግን ፍቅሩ ፍፁም አይደለም፡፡
\s5
\v 19 አስቀድሞእግዚአብሔር ወዶናልና፣እኛም እንወደዋለን።
\v 20 አንድ ሰው "እግዚአብሔርን እወዳለሁ" እያለ ወንድሙን ግን ቢጠላ ሃሰተኛ ነው፤የሚያየውን ወንድሙን የማይወድ፣ የማያየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም።
\v 21 እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን መውደድ አለበት፣የሚል ትእዛዝ ከእግዚአብሔር ተቀብለናል።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዷል።አባት የሆነውን የሚወድ ሁሉ፣ከርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።
\v 2 እግዚአብሔርን ስንወድና ትዕዛዙን ስንፈጽም፣ የእግዚአብሔርን ልጆች እንደምንወድ በዚህ እናውቃለን።
\v 3 እግዚአብሔርን የምንወደው የርሱን ትእዛዙን በመጠበቃችን ነው። የርሱም ትእዛዛት ከባዶች አይደሉም።
\s5
\v 4 ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋል። ዓለምን የሚያሽንፈው እምነታችን ነው።
\v 5 ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ከሚያምን በቀር፣ ዓለምን የሚየሸንፍ ማነው?
\s5
\v 6 በውሃና በደም የመጣው እርሱም ነው፣እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፣ በውሃ ብቻ ሳይሆን፣ነገር ግን በውሃና በደም የመጣ ነው።
\v 7-8 የጥንቶችቹ የተሻሉት ቅጅዎች ይተውታል። ሦሶት ምስክሮች አሉ፤እነርሱም መንፈሱ ፣ውሃውና ደሙ ናቸው፤ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።
\s5
\v 9 የሰዎችን ምስክርነት የምንቀበል ከሆነ፣ የእግዚአብሔር ምስክርነት ደግሞ የበለጠ ነው። እግዚአብሔር ስለ ጁል የሰጠው ምስክር ይህ ነው።
\v 10 በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በውስጡ ምስክር አለው። በእግዚአብሔር የማያምን ፣እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስለማያምን ሐሰተኛ አድርጎታል።
\s5
\v 11 ምስክሩም ይህ ነው ፣እግዚአብሔር የዘላለምን ህይወት እንደሰጥንና፣ይህም ህይወት በልጁ መሆኑ ነው።
\v 12 ልጁ ያለው ሕይወት አለው፥ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
\s5
\v 13 በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ፣የዘላለም ህይወት እንዳላችሁ እንድታውቁ ፣እነዚህን ነገሮች እጽፍላችኋለሁ።
\v 14 በእርሱ ፊት ያለን ድፍረት ይህ ነው፣እንደ ፈቃዱ ማንኛውንም ነገር ብንጠይቀው፣ይሰማናል።
\v 15 የምንጠይቀውን ሁሉ እንደሚሰማን ካወቅን፣ከርሱ የጠየቅነውን ሁሉ እንደተቀበልን እናውቃለን።
\s5
\v 16 ማንም ወንድሙ ለሞት የማያበቃ ሃጢዓት ሲያደርግ ቢያይ፣ መጸለይ ይገባዋል፣ሞት የማይገባውን ሃጢዓት ለሚያደርጉት እግዚአብሔር ህይወትን ይሰጣል። ለሞት የሚያበቃ ኃጢዓት አለ። ያንን የተመለከተ ልመና እንዲያደርግ አላልኩም።
\v 17 ዓመጽ ሁሉ ኃጢዓት ነው፣ ነገር ግን ለሞት የማያበቃ ኃጢዓት አለ።
\s5
\v 18 ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢዓት እንደማያደርግ እናውቃለን፣ከእግዚአብሔር የተወለደውን፣እግዚአብሔር ከክፉ ይጠብቀዋል ፣ክፉውም አይነካውም።
\v 19 እኛ ከእግዚአብሔር እንደሆንን፣ዓለም ሁሉ በክፉው ቁጥጥር ሥር እንደሆነ እናውቃለን።
\s5
\v 20 እኛ ግን የእግዚአብሔር ልጅ እንደመጣና እውነት የሆነውን እንድናውቅ ማስተዋል እንደሰጠን እናውቃለን፤ እኛም እውነት በሆነው በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለን እናውቃለን። እርሱም እውነተኛ አምላክና የዘላለም ህይወት ነው።
\v 21 ልጆች ሆይ! ከጣዖታት ዓምልኮ ራሳችሁን ጠብቁ።

33
64-2JN.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,33 @@
\id 2JN
\ide UTF-8
\h 2ኛ ዮሐንስ
\toc1 2ኛ ዮሐንስ
\toc2 2ኛ ዮሐንስ
\toc3 2jn
\mt 2ኛ ዮሐንስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ከሽማግሌው በእውነት ለምወዳችሁና እኔም ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዱአችሁ ለተመረጥች እመቤትና ለልጆችዋ ።
\v 2 ይህም ፍቅር በውስጣችን ካለውና ለዘላለም ከእኛ ጋር ከሚሆነው እውነት የተነሳ ነው።
\v 3 በእውነትና በፍቅር ከእግዚአብሔር አብ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ምህረትና ሠላም ከሁላችን ጋር ይሁን።
\s5
\v 4 ከልጆችሽ መካከል ከአብ በተቀበልነው ትዕዛዝ መሠረት በእውነት ሲሄዱ በማግኘቴ እጅግ ሀሴት አደርጋለሁ።
\v 5 እንግዲህ እመቤት አሁን አዲስ ትዕዛዝ እንደምሰጥ ሳይሆን እርስ በእርሳችን እንዋደድ ብዬ ከመጀመሪያው በነበረን ትዕዛዝ እለምንሻለሁ።
\v 6 ይህም በትዕዛዛቱ መሰረት ልንጓዝበት የሚገባን ፍቅር ነው። ይህ ትዕዛዝ ከመጀመሪያው እንደሰማችሁት ልትራመዱበት የሚገባ ትዕዛዝ ነው።
\s5
\v 7 ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል። ይህም አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው።
\v 8 ሙሉ ዋጋችሁን እንድትቀበሉ እንጂ እኛ ሁላችን የደክምንባቸውን ነገሮች እንዳታጡ ስለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 9 በክርስቶስ ትምህርት ሳይጸና ዝም ብሎ ወደፊት የሚገሰግስ እግዚአብሄርን አያውቅም። በዚህ ትምህርት የሚጸና አብና ወልድ አሉት።
\v 10 ማንም ወደ እናንተ መጥቶ ይህን ትምህርት ባያስተምር ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አትፍቀዱለት ሠላምም አትበሉት።
\v 11 ምክንያቱም ሠላምታ የሚሰጠው ሁሉ በክፉ ሥራው ይካፈላል።
\s5
\v 12 የምጽፍላችሁ ብዙ ነገር ነበረኝ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈለግሁም። ነገር ግን ደስታችን ሙሉ ይሆን ዘንድ ወደ እናንተ ልመጣና ፊት ለፊት ላወራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
\v 13 የተመረጠችው እህትሽ ልጆች ሠላምታ ያቀርቡልሻል።

35
65-3JN.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,35 @@
\id 3JN
\ide UTF-8
\h 3ኛ ዮሐንስ
\toc1 3ኛ ዮሐንስ
\toc2 3ኛ ዮሐንስ
\toc3 3jn
\mt 3ኛ ዮሐንስ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ሽማግሌው በእውነት ለምወደውና ለተወደደው ጋይዮስ።
\v 2 የተወደድክ ሆይ በነፍስህ እንደበለጸግህ በሁሉ ነገር እንድትበለጽግና በመልካም ጤንነት እንድትሆን እጸልያለሁ።
\v 3 ወንድሞች መጥተው በእውነት እንደምትሄድ ሲመሰክሩልኝ እጅግ ሀሴት አደረግሁኝ።
\v 4 ልጆቼ በእውነት መንገድ እየሄዱ እንደሆነ ከመስማት የበለጠ ደስታ የለኝም።
\s5
\v 5 የተወደድክ ሆይ ለወንድሞችም ሆነ ለእንግዶች በምታድርገው ነገር ስላለህ ታማኝነት
\v 6 ሁሉም በጉባኤ ፊት ይመሰክሩልሀል።ለእግዚአብሔር እንደሚገባ በጉዞአቸው በመደገፍህ መልካም አድርገሀል።
\v 7 ምክንያቱም ለተጠሩለት ስም አገልግሎት ሲወጡ ከአህዛብ ምንም አልወሰዱም።
\v 8 ስለዚህም የእውነት ማህበርተኞች እንሆን ዘንድ እንደነዚህ ያሉትን መርዳት ይገባናል።
\s5
\v 9 ስለአንድ ጉዳይ ለቤተክርስቲያን ጽፌ ነበር ነገር ግን በመካከላቸውአለቃ ሊሆን የሚወደው ዲዮትሪፈስ አይቀበለንም።
\v 10 ስለዚህ በምመጣበት ጊዜ ያደረገውን ነገርና እንዴት ባሉ ክፉ ቃላት በእኛ ላይ እንደተናገረ አልረሳም።ይህም አልበቃ ብሎት ወንድሞችን አይቀበልም ሊቀበሉ የሚፈልጉትንም ይከለክላቸዋል ከቤተክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።
\s5
\v 11 የተወደድክ ሆይ መልካሙን እንጂ ክፉን አትምሰል። መልካም የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ እግዚአብሔርን አላየውም።
\v 12 ለዲሜጥሮስ ሁሉም ይመሰክሩለታል እውነት እራሷም ትመሰክርለታልች። እኛም እንመሰክርለታለን የኛ ምስክርነት ደግሞ እውነት እንደሆነ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 13 የምጽፍልህ ብዙ ነገር ነበረኝ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፍልህ አልፈለግሁም።
\v 14 ይልቁኑ ልጎበኝህ አስባለሁና በዚያን ጊዜ ፊት ለፊት እንነጋገራለን።
\v 15 ሠላም ለአንተ ይሁን። ወገኖችሰላምታ ያቀርቡልሀል። በአንተ ዘንድ ላሉት ወገኖች በስማቸው እየጠራህ ሠላምታ አቅርብልኝ።

57
66-JUD.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,57 @@
\id JUD
\ide UTF-8
\h ይሁዳ
\toc1 ይሁዳ
\toc2 ይሁዳ
\toc3 jud
\mt ይሁዳ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ፥ የያዕቆብ ወንድም ይሁዳ፤ ለተጠሩት፥ በእግዚአብሔር አብ ለተወደዱትና በኢየሱስ ክርስቶስ ለተጠበቁት፤
\v 2 ምሕረት ለእናንተ ይሁን፤ ሰላምና ፍቅርም ይብዛላችሁ።
\s5
\v 3 ወዳጆች ሆይ፤ አብረን ስለምንካፈለው ድነት ልጽፍላችሁ ጥረት እያደረግሁ ሳለ፥ ለቅዱሳን አንዴና ለመጨረሻ ስለተሰጠው እምነት ጸንታችሁ ትጋደሉ ዘንድ ለመምከር እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።
\v 4 ለፍርድ እንደሚዳረጉ ከብዙ ዘመን በፊት የተጻፈባቸው አንዳንድ ሰዎች ሾልከው ወደ እናንተ ገብተዋልና። እነዚህ ሰዎች ፈሪሃ እግዚአብሔር የሌላቸው፥ የእግዚአብሔርን ጸጋ በሴሰኝነት የሚለውጡ፥ እርሱ ብቻ ገዣችንና ጌታችን የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚክዱ ናቸው።
\s5
\v 5 ምንም እንኳ አስቀድማችሁ ሁሉን የምታውቁት ቢሆንም ጌታ አንድ ጊዜ ሕዝቡን ከግብጽ አውጥቶ እንደ አዳናቸው በኋላ ግን ያላመኑትን እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።
\v 6 እንዲሁም የነበራቸውን የሥልጣን ደረጃ ባለመጠበቅ ተገቢ የመኖሪያ ስፍራቸውን የተውትን መላእክት እግዚአብሔር እስከ ታላቁ የፍርድ ቀን ድረስ በዘላለም እስራት በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንዲቆዩ አድርጓል።
\s5
\v 7 እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸውም የነበሩት ከተሞች በተመሳሳይ ሁኔታ ራሳቸውን ለሴሰኝነትና ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ ለሆነ ግብረ ሥጋ ግንኙነት አሳልፈው ሰጡ፤ እነርሱም በዘላለም እሳት ተጥለው ለሚሰቃዩት ምሳሌ እንዲሆኑ ተደርገዋል።
\v 8 በዚህ ሁኔታ እነዚህ ደግሞ በሚያልሙት ሕልማቸው የራሳቸውን ሥጋ ያረክሳሉ፤ሥልጣንን ይቃወማሉ፤በሰማይ ክብር ያላቸውንም ይሳደባሉ።
\s5
\v 9 የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳ ዲያብሎስን በመቃወም ስለ ሙሴ ሥጋ በተከራከረው ጊዜ «ጌታ ይገሥጽህ» አለው እንጂ በእርሱ ላይ ሊፈርድ ወይም አንዳች የስድብ ቃል ሊናገር አልደፈረም።
\v 10 እነዚህ ሰዎች ግን የማያውቋቸውን ነገሮች ሁሉ ይሳደባሉ። እነርሱም አእምሮ የሌላቸው እንስሳት እንደሚያደርጉት በደመ ነፍስ በሚያውቋቸው ነገሮች ይጠፋሉ።
\v 11 ወዮላቸው፤ በቃየን መንገድ ሄደዋልና፤ለገንዘብ ሲሉ በበለዓም ስህተት ውስጥ ወድቀዋልና፤በቆሬም ዐመፅ ጠፍተዋልና።
\s5
\v 12 እነዚህ በፍቅር ግብዣችሁ ላይ አብረዋችሁ ሲጋበዙ ችግር የሚፈጥሩባችሁ ድብቅ እንቅፋቶች ናቸው፤ ደግሞም ያለ ሃፍረት ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው። እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ውሃ አልባ ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው፥ ከሥራቸው የተነቀሉና ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው።
\v 13 የራሳቸውን የነውር አረፋ የሚደፍቁ የተቆጣ የባሕር ማዕበል፥ ድቅድቅ ጨለማም ለዘላለም የተጠበቀላቸው ተንከራታች ከዋክብት ናቸው።
\s5
\v 14 ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ ትውልድ የሆነው ሄኖክ ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ በማለት ትንቢት ተናግሯል፤ «እነሆ፤ ጌታ ከብዙ ሺህ ቅዱሳኑ ጋር ይመጣል።
\v 15 የሚመጣውም በሰው ሁሉ ላይ ለመፍረድ እንዲሁም ዐመፀኞችንና ኀጢአተኞችን ክፋት በተሞላበት ሁኔታ በፈጸሙት የዐመፅ ሥራቸውና በእግዚአብሔር ላይ በተናገሩት የስድብ ቃል ለመውቀስ ነው።»
\v 16 እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ ሌላውን የሚከሱ፥ የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ፥ ጉራ የሚነዙና ጥቅም ለማግኘትም ሰዎችን የሚክቡ ናቸው።
\s5
\v 17 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፤የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት አስቀድመው የተናገሩትን ቃል አስታውሱ
\v 18 ለእናንተም ሲናገሩ፥«በመጨረሻው ዘመን የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ ዘባቾች ይመጣሉ» ብለዋል።
\v 19 እነዚህ በሰዎች መካከል መለያየትን የሚፈጥሩ፥የሥጋን ምኞት የሚከተሉና መንፈስ ቅዱስ የሌላቸው ናቸው።
\s5
\v 20 እናንተ ግን ወዳጆች ሆይ፤እጅግ ቅዱስ በሆነው እምነታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ ትጉ፤በመንፈስ ቅዱስም ጸልዩ።
\v 21 በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ፤የዘላለም ሕይወትም ታገኙ ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ፈልጉ።
\s5
\v 22 ለሚጠራጠሩ ሰዎች ርኅራኄ አድርጉላቸው፤
\v 23 ከእሳት ነጥቃችሁ በማውጣት አንዳንዶችን አድኑ፤ ለሌሎች ድግሞ በእርኩስ ሥጋ የተበከለውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ምህረት አሳዩአቸው።
\s5
\v 24 እንግዲህ ከመውደቅ ሊጠብቃችሁ፥ ነቀፋ ሳይኖርባችሁ በታላቅ ደስታ በክብሩ ፊት ሊያቀርባችሁ ለሚችለው
\v 25 በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት አዳኛችን ለሆነው ብቸኛ አምላክ ከዘመናት ሁሉ በፊት፥ አሁንና እስከ ዘላለም ድረስ ክብር፥ ግርማ፥ ኀይልና ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።

860
67-REV.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,860 @@
\id REV
\ide UTF-8
\h የዮሐንስ ራእይ
\toc1 የዮሐንስ ራእይ
\toc2 የዮሐንስ ራእይ
\toc3 rev
\mt የዮሐንስ ራእይ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 ይህ ፈጥኖ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳይ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ራእይ ነው። እርሱም ይህን ራእይ መልአኩን ወደ አገልጋዩ ወደ ዮሐንስ በመላክ እንዲታወቅ አድርጓል።
\v 2 ዮሐንስም የእግዚአብሔርን ቃል በሚመለከት ስላየው ማንኛውንም ነገር እና ክርስቶስን በሚመለከት ስለተሰጠው ምስክርነት ተናግሯል።
\v 3 ዘመኑ ስለ ቀረበ ፥ የዚህን የትንቢት ቃል የሚያነብ የተባረከ ነው፤እንዲሁም የሚሰሙት ሁሉ በውስጡም የተጻፈው ን ነገር የሚፈጽሙ የተባረኩ ናቸው።
\s5
\v 4 ከዮሐንስ፥በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ካለው፥ከነበረው፥ወደፊትም ከሚመጣውና በዙፋኑ ፊት ካሉት ከሰባቱ መንፈሶች
\v 5 እንዲሁም ታማኝ ምስክር፥ከሙታን በኩርና የምድር ነገሥታት ገዥ ከሆነው ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለሚወደንና ከኀጢአታችንም በደሙ ነጻ ላወጣን፥
\v 6 አባቱ ለሆነው እግዚአብሔር መንግሥትና ካህናት እንሆን ዘንድ ላደረገን ለእርሱ ክብርና ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሁን፤አሜን።
\s5
\v 7 እነሆ፤እርሱ በደመና ይመጣል፤የወጉትን ጨምሮ ዐይን ሁሉ ያየዋል። የምድርም ነገዶች ሁሉ በእርሱ ምክንያት ያለቅሳሉ፤እንደዚያም ይሆናል፤አሜን።
\v 8 ጌታ እግዚአብሔር፥«አልፋና ኦሜጋ፥ ያለሁና የነበርሁ፥ወደፊትም የምመጣው ሁሉን ቻይ እኔ ነኝ» ይላል።
\s5
\v 9 እኔ ከእናንተ ጋር በመከራው፥በመንግሥቱና በኢየሱስ በሚገኘው ትዕግሥት ተካፋይ የሆንሁ ወንድማችሁ ዮሐንስ፥ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።
\v 10 በጌታም ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤በኋላዬም የመለከትን ድምጽ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ።
\v 11 ድምፁም እንዲህ የሚል ነበር፤«የምታየውን በመጽሓፍ ጻፈው፤ ከዚያም በኤፌሶን፥ በሰምርኔስ፥ በጴርጋሞን፥ በትያጥሮን፥ በሰርዴስ፥ በፊለደልፍያና በሎዶቅያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላከው።
\s5
\v 12 ይናገረኝ የነበረው የማን ድምፅ እንደ ሆነ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወር በምልበትም ጊዜ ሰባት የወርቅ መቅረዞችን አየሁ።
\v 13 በመቅረዞቹም መካከል እስከ እግሩ ድረስ የሚደርስ ረጅም ልብስ የለበሰና ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ የሰው ልጅ የሚመስለው ነበር።
\s5
\v 14 ራሱና ጸጉሩ እንደ ነጭ የበግ ጸጉር ማለትም እንደ በረዶ ነጭ ነበሩ፤ዐይኖቹ የእሳት ነበልባል፥
\v 15 እግሮቹም በእቶን እሳት እንደ ነጠረ የጋለ ናስ፥ ድምፁም እንደ ብዙ ወራጅ ውኃ ድምፅ ነበር።
\v 16 በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት ይዞ ነበር፤ከአፉም በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ፊቱም ጸሐይ በሙሉ ኀይልዋ ስታበራ የምታበራውን ያህል ያበራ ነበር።
\s5
\v 17 ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅሁ፤ እርሱም ቀኝ እጁን በእኔ ላይ በመጫን እንዲህ አለኝ፤ «አትፍራ፤እኔ የመጀመሪያውና የመጨረሻው
\v 18 ሕያውም ሆኜ የምኖር ነኝ። ሞቼ ነበር፤እነሆም ለዘላለም ሕያው ነኝ፤የሞትና የሲዖል መክፈቻም አለኝ።
\s5
\v 19 ስለዚህ ያየኽውን፥አሁን ያለውን ሁኔታና ከዚህ በኋላ የሚሆነውን ነገር ጻፍ።
\v 20 በቀኝ እጄ ያሉት አንተም ያየሃቸውን የሰባቱን ከዋክብትና የሰባቱን የወርቅ መቅረዞች ምስጢር በተመለከተ ትርጉሙ ይህ ነው፤ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ሲሆኑ፥ ሰባቱ መቅረዞች ደግሞ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 “በኤፌሶን ወዳለው መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ ‘ሰባቱን ከዋክብት በቀኝ እጁ የያዘውና በሰባቱ የወርቅመቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፤
\v 2 ‘ሥራህን፣ ትዕግሥትህንና ጽናትህን አውቃለሁ። ክፉ ሰዎችን መታገሥ አለመቻልህንም አውቃለሁ። ሐዋሪያት ሳይሆኑ “ሐዋሪያት ነን” የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸውም አውቃለሁ።”
\s5
\v 3 በትዕግሥት እንደ ጸናህ፥ስለ ስሜ ብዙ መከራ ቢደርስብህም እንዳልደከመህ አውቃለሁ።
\v 4 ነገር ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ይኽውም የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃል።
\v 5 እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ ለይተህ እወቅ፤ንስሓ ግባ፤ቀደም ሲል ታደርገው የነበረውንም ነገር አድርግ። ንስሓ ካልገባህ እመጣብሃለሁ፤መቅረዝህንም ከስፍራው አስወግዳለሁ።
\s5
\v 6 ነገር ግን ይህ መልካም ነገር አለህ፤ እኔ የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ጠልተሃል።
\v 7 ጆሮያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ይስማ። ድል ለሚነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው የሕይወት ዛፍ የመብላትን መብት እሰጠዋለሁ።”
\s5
\v 8 «በሰምርኔስ ላለችው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "እነዚህ መጀመሪያም መጨረሻም የሆነው የእርሱ ቃሎች ናቸው፤ሞቶ የነበረው፥እንደ ገና ሕያው የሆነው እንዲህ ይላል፤
\v 9 '"መከራህንና ድኽነትህንም አውቃለሁ፤ነገር ግን ባለጠጋ ነህ፤የሰይጣን ማኅበር ሆነው እያለ፥አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን ብለው የሚናገሩ ሰዎች የሚሳደቡትን ስድብ አውቃለሁ።
\s5
\v 10 ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ። ተመልከት ከእናንተ አንዳንዶቹን እንድትፈተኑ ዲያብሎስ እስር ቤት ያስገባችኋል፤ ለአሥር ቀን መከራ ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ እኔም የሕይወትን አክሊል እሰጥሃለሁ።
\v 11 ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለው ይስማ። ድል የሚነሻ በሁለተኛው ሞት አይጎዳም።
\s5
\v 12 «በጴርጋሞን ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "እነዚህ በሁለት በኩል የተሳለ ስለታም ሰይፍ ካለው የተነገሩ ቃሎች ናቸው፤እርሱም እንዲህ ይላል፤
\v 13 '"የሰይጣን ዙፋን ባለበት በዚያ እንደምትኖር አውቃለሁ፤ነገር ግን ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል። ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ መካከል በተገደለው በታማኙ ምስክሬ በአንቲጳስ ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።
\s5
\v 14 ነገር ግን የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ፤የእስራኤል ልጆች ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉና እንዲሴስኑ በፊታቸው ማሰናከያ ያስቀምጥ ዘንድ ባላቅን የመከረው የበለዓምን ትምህርት አጥብቀው የሚከተሉ አንዳንድ ሰዎች በመካከልህ አሉ።
\v 15 እንደዚሁም የኒቆላውያንን ትምህርት አጥብቀው የያዙ ሰዎች እንኳ በአንተ ዘንድ አሉ።
\s5
\v 16 ስለዚህ ንስሓ ግባ፤አለበለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፤ከአፌም በሚወጣው ሰይፍ አዋጋቸዋለሁ።
\v 17 ጆሮ ካለህ፥መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ስማ። ድል ለሚነሳ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤እንደዚሁም ከሚቀበለው ሰው በስተቀር ማንም የማያውቀውን አዲስ ስም የተጻፈብትን ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።>
\s5
\v 18 በቲያጥሮን ወዳለው መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “የእሰት ነበልባል የመሰሉ ዐይኖችና በእሳት ፍም የነጠረ ናስ የሚመስሉ እግሮች ያሉት የእግዚአብሔር ልጅ እንዲህ ይላል።
\v 19 ሥራህን፣ ፍቅርህንና እምነትህን፣ አገልግሎትህንና በትዕግሥት መጽናትህን አውቃለሁ። አሁን በቅርቡ ያደረግኸው ቀድሞ ካደረግኸው የበለጠ መሆኑን አውቃለሁ።”
\s5
\v 20 ነገር ግን የምነቅፍብህ አንድ ነገር አለኝ፤ራሷን ነቢይት ብላ የምትጠራውን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል። ይህች ሴት በትምህርትዋ አገልጋዮቼ ሴሰኛ እንዲሆኑና ለጣዖት የተሰዋ ምግብ እንዲበሉ ታስታቸዋለች።
\v 21 ንስሓ እንድትገባ ጊዜ ሰጥቻት ነበር ፤ይሁን እንጂ ከርኩሰትዋ ንስሓ ለመግባት ፈቃደኛ አልሆነችም።
\s5
\v 22 እነሆ በሥቃይ አልጋ ላይ እጥላታለሁ፤ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩት እርስዋ ከፈጸመችው ነገር ንስሓ ካልገቡ በስተቀር በከባድ ሥቃይ እንዲወድቁ አደርጋለሁ።
\v 23 በሞት እቀጣለሁ፤በመሆኑም አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ የሰውን ሐሳብና ፍላጎትን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ። ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እከፍላለሁ።
\s5
\v 24 ዳሩ ግን ይህን ትምህርት ለማትከተሉ ሁሉ እንዲሁም አንዳንዶች የሰይጣን ጥልቅ ምስጢር ነው የሚሉትን ነገር ለማታውቁ በትያጥሮን ለምትኖሩ ለቀራችሁት ሌላ ሸክም አልጭንባችሁም።>
\v 25 ሆኖም እስክመጣ ድርስ ያላችሁን ነገር አጸንታችሁ ጠብቁ።
\s5
\v 26 ለሚነሣውና እስከ መጨረሻው እኔ የደረግሁትን ለሚያደርግ በሕዝቦች ላይ ሥልጣን እሰጠዋለሁ።
\v 27 በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እንደ ሸክላም ዕቃ የደቃቸዋል።
\v 28 እኔ ከአባቴ እንደ ተቀበልሁ የንጋትን ኮከብ እሰጠዋለሁ።
\v 29 ጆሮ ያለው መንፈስ መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ይስማ።”
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 «በሰርዴስ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ከዋክብት የያዘው እንዲህ በማለት ይናገራል፤«ሥራህን ዐውቃለሁ፤ሕያው እንደሆንህ የሚገልጽ ዝነኛ ስም አለህ፤ነገር ግን ሞተሃል።
\v 2 ሥራህን በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ሆኖ ስላላገኘሁት ንቃ፤ሊሞቱ የተቃረቡትን የቀሩትን ነገሮች አጽና።
\s5
\v 3 እንግዲህ ምን እንደተቀበልህና ምን እንደሰማህ አስታውስ፤ጠብቀው፤ንስሓም ግባ። ነገር ግን ባትነቃ ፥እንደ ሌባ እመጣለሁ፤በምን ሰዓት እንደምመጣብህም አታውቅም።
\v 4 ነገር ግን በሰርዴስ ልብሳቸውን ያላቆሸሹ ጥቂት ሰዎች አሉ። የተገባቸውም ስለ ሆነ፥ ነጭ ልብሳቸውን ለብሰው ከእኔ ጋር ይሄዳሉ።
\s5
\v 5 ድል የሚነሳ ነጭ ልብስ ይለብሳል፤ስሙን ከሕይወት መጽሐፍ ፈጽሞ አልደመስሰውም፤ይልቁን በአባቴና በመላእክቱ ፊት ለስሙ እመሰክራለሁ።
\v 6 ጆሮ ካለህም መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት ይሚናገረውን ስማ።»
\s5
\v 7 «በፊላደልፍያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ የዳዊት መክፈቻ ያለው፥የሚከፍት እርሱ የከፈተውን ማንም የማይዘጋ፥የሚዘጋ እርሱ የዘጋውን ማንም ሊከፍት የማይችል ቅዱስና እውነተኛ የሆነው እርሱ እንዲህ ይላል፤
\v 8 ሥራህን ዐውቃለሁ፤እነሆ፤ማንም ሊዘጋው የማይችል የተከፈተ በር በፊትህ አድርጌአለሁ። ዐቅምህ ትንሽ እንደሆነ አውቃለሁ፤ይሁን እንጂ ቃሌን ጠብቀሃል፤ስሜንም አልካድህም።
\s5
\v 9 እነሆ፤አይሁድ ሳይሆኑ አይሁድ ነን የሚሉት እነዚያ ከሰይጣን ማኅበር የሆኑት ውሸተኞች ናቸው። እነርሱንም እኔ እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ መጥተው በእግርህ እንዲወድቁ አደርጋለሁ።
\v 10 በትዕግሥ እንድትጸና የሰጠሁህን ትእዛዜን ስለ ጠበቅህ ፥በምድር የሚኖሩትን ይፈትን ዘንድ በዓለም ላይ ሁሉ ሊመጣ ካለው የፈተና ሰዓት እጠብቅሃለሁ።
\v 11 በቶሎ እመጣለሁ፤አክሊልህን ማንም እዳይወስድብህ፥ያለህን አጥብቀህ ያዝ።
\s5
\v 12 ድል የሚነሻውን በአባቴ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያ በፍጹም አይወጣም። እርሱ ላይ የአምላኬን ከተማ ስም፣ ማለት ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ የምትወጣውን የአዲሲቱ ኢዩሳሌምን ስም ደግሞ አዲሱ ስሜን እጽፋለሁ።
\v 13 ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን የስማ።”
\s5
\v 14 «በሎዶቅያ ላለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ "ይህም በእግዚአብሔር ፍጥረት ላይ ገዥ እንዲሁም እውነተኛና ታማኝ ምስክር ከሆነው ቃሉም አሜን ከሆነው የተነገረ ነው፤
\v 15 ሥራህን አውቃለሁ፤በራድ ወይም ትኩስ አይደለህም። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆን ኖሮ መልካም ይሆን ነበር።
\v 16 እንግዲህ ትኩስ ወይም በራድ ሳትሆን በመካከል ለብ ስላልህ ከአፌ ልተፋህ ነው።
\s5
\v 17 «እኔ ሀብታም ነኝ፤ብዙ ገንዘብ አለኝ፤የጎደለኝ ምንም ነገር የለም» ትላለህ፤ነገር ግን እጅግ ጎስቋላ፥ምስኪን፥ድኻ፥ዕውርና የተራቆትህ እንደሆንህ አታውቅም።
\v 18 ሀብታም ትሆን ዘንድ በእሳት የተፈተነውን ወርቅ ከእኔ እንድትገዛ፥የራቁትነትህን ሐፍረት ለመሽፈን ነጭ ልብስ እንድትለብስ፥አጥርተህ ለማየትም ዐይንህን እንድትኳል እመክርሃለሁ።
\s5
\v 19 እኔ የምወዳቸውን እንዴት መኖር እንደሚገባቸው ያውቁ ዘንድ እቀጣቸዋለሁ፤ አስተምራቸዋለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ንስሓም ግባ።
\v 20 እነሆ፤በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ። ማንም ድምጼን ሰምቶ ቢከፍትልኝ ወደ ቤቱ እገባለሁ፤ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።
\s5
\v 21 እኔ ድል እንደነሳሁና በዙፋኑ ላይ ከአባቴ ጋር እንደተቀመጥሁ፥ድል ለሚነሳም በዙፋኔ ላይ ከእኔ ጋር የመቀመጥን መብት እሰጠዋለሁ።
\v 22 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።»
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ እነሆ የተከፈተ በር በሰማይ አየሁ። እንደ መለከት ድምፅ ሆኖ ሲናገረኝ የነበረው የመጀመሪያው ድምፅ፥«ወደዚህ ና! ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በኋላ የሚሆነውን አሳይሃለሁ።» አለ።
\v 2 ወዲያው በመንፈስ ነበርሁ፤በሰማይ ዙፋን ተዘርግቶ አየሁ፤በዙፋኑም ላይ አንድ የተቀመጠ አካል ነበር።
\v 3 በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ የነበረው መልኩ የኢያስጲድንና የሰርዲኖን ዕንቁ ይመስል ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ የመረግድ ዕንቁ የመሰለ ቀስተ ደመና ነበር።
\s5
\v 4 በዙፋኑም ዙሪያ ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ፤በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ ሃያ አራት ሽማግሌዎች ተቀምጠው ነበር።
\v 5 ከዙፋኑም የመብረቅ ብልጭታና የነጎድጓድ ድምፅ ወጣ። በዙፋኑም ፊት ሰባት መብራቶች ይበሩ ነበር፤እነዚህም ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።
\s5
\v 6 እንደዚሁም በዙፋኑ ፊት እንደ መስተዋት እጅግ የጠራ ባሕር ነበር። በዙፋኑም ዙሪያ ሁሉ ከፊትና ከኋላ በዐይን የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።
\s5
\v 7 የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ሲመስል፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ጥጃ ይመስል ነበር፤ሦስተኛው ሕያው ፍጡር የሰውን ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤አራተኛው ሕያው ፍጡር ደግሞ የሚበር ንስር ይመስል ነበር።
\v 8 አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፍ ነበራቸው፤ከላይና ከሥርም በዐይኖች የተሞሉ ነበሩ። እነርሱም ቀንና ሌሊት፥ «ቅዱስ፥ቅዱስ፥ቅዱስ፥ በሁሉም ላይ የሚገዛ፥የነበረና ያለ፥ወደፊትም የሚመጣው ጌታ አምላክ» ማለትን አያቋርጡም ነበር።
\s5
\v 9 ሕያዋን ፍጡራኑም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ክብር፥ ሞገስና ምስጋና በሚሰጡበት ጊዜ፥
\v 10 ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ከዘላለም እስከ ዘላለም ለሚኖረው ሰገዱ፤አክሊላቸውንም በዙፋኑ ፊት አስቀምጠው፥
\v 11 «ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤አንተ ሁሉንም ነገር ስለፈጠርህ፥በፈቃድህ ስለፈጠርሃቸውና እንደዚያም ሆነው ስለተገኙ ክብር፥ሞገስ፥ኅይልም ልትቀበል ይገባሃል።» ይሉ ነበር።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 በዙፋኑም ላይ በተቀመጠው ቀኝ እጅ ከፊትና ከጀርባ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የታሸገ ጥቅልል መጽሓፍ አየሁ።
\v 2 አንድ ብርቱ መልአክ፥«መጽሓፉን ሊከፍት፥ ማኅተሙን ሊፈታ የተገባው ማን ነው?» ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ።
\s5
\v 3 በሰማይ ቢሆን በምድር ወይም ከምድር በታች መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ ማንም አልቻለም።
\v 4 መጽሓፉን ሊከፍት ወይም ሊያነብ የተገባው ማንም ስላልተገኘ፥አምርሬ አለቀስሁ።
\v 5 ነገር ግን ከሽማግሌዎች አንዱ፥«አታልቅስ፤እነሆ! ከዳዊት ሥር፥ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ መጽሓፉን ይከፍትና ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነስቷል» አለኝ።
\s5
\v 6 በዙፋኑና በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን መካከል እንዲሁም በሽማግሌዎች መካከል አንድ ታርዶ የነበረ የሚመስል በግ ቆሞ አየሁ። እርሱም ሰባት ቀንዶችና ሰባት ዐይኖች ነበሩት፤እነዚህም በምድር ሁሉ ላይ የተላኩ ሰባቱ የእግዚአብሔር መንፈሶች ናቸው።
\v 7 ሄዶም በዙፋን ላይ ከተቀመጠው ቀኝ እጅ ጥቅልል መጽሓፉን ወሰደ።
\s5
\v 8 ጥቅልል መጽሓፉንም በሚወስድበት ጊዜ አራቱ ሕያዋን ፍጡራን እና ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት በግምባራቸው ተደፉ፤ እያንዳንዳቸውም በገና እና የቅዱሳን ጸሎት የሆነው ዕጣን የሞላበት የወርቅ ዕቃ ይዘው ነበር።
\s5
\v 9 እነርሱም እንዲህ የሚል አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤«መጽሓፉን ትወስድ እና ማኅተሞቹን ተፈታ ዘንድ ይገባሃል፤ ታርደሃልና በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ፥ከቋንቋ ሁሉ፥ ከሕዝብና ከአገር ሁሉ ሰዎችን ዋጅተሃል።
\v 10 አምላካችንን ያገለግሉ ዘንድ መንግሥትና ካህናት አደረግሃቸው፤እነርሱም በምድር ላይ ይገዛሉ።»
\s5
\v 11 ከዚያም በኋላ ስመለከት፥በዙፋኑ፥በሕያዋኑ ፍጡራን እና በሽማግሌዎች ዙሪያ የብዙ መላእክት ድምፅ ሰማሁ፤ቁጥራቸውም ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።
\v 12 እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«የታረደው በግ ኀይልና ባለጠግነት፥ጥበብና ብርታት፥ምስጋና እና ክብር ሊቀበል ይገባዋል።» አሉ።
\s5
\v 13 በሰማይና በምድር፥ከምድር በታች እንዲሁም በባሕር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ ፥«ምስጋና፥ክብር፥ውዳሴ፥የመግዛትም ኀይል ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው እና ለበጉ ይሁን።» ሲሉ ሰማሁ፤
\v 14 አራቱ ሕያዋን ፍጡራን፥«አሜን» አሉ፤ሽምግሌዎችም በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱ።
\s5
\c 6
\cl ምዕራፍ 6
\p
\v 1 ከዚህም በኋላ በጉ ከሰባቱ ማኅተሞች አንዱን ሲከፍት አየሁ፤ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን አንዱ እንደ ነጎድጓድ ባለ ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ።
\v 2 አየሁም ፤እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ አየሁ፤ባላዩ ላይ የተቀመጠውም ቀስት ይዞ ነበር፤አክሊልም ተሰጠው። እንደ ድል አድራጊ ሆኖ ድል ይነሳ ዘንድ ወጣ።
\s5
\v 3 በጉ ሁለተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ሁለተኛው ሕያው ፍጡር«ና!» ሲል ሰማሁ።
\v 4 ከዚያም ደማቅ ቀይ ፈረስ ወጣ፤በፈረሱም ላይ ለተቀመጠው ሰዎች እርስ በርስ ይተራረዱ ዘንድ ሰላምን ከምድር እንዲያስወግድ ሥልጣን ተሰጠው፤ትልቅ ሰይፍም ተሰጠው።
\s5
\v 5 በጉ ሦስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ፥ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር «ና!» ሲል ሰማሁ፤ ጥቁር ፈረስ አየሁ፤በፈረሱም ላይ የተቀመጠው በእጁ ሚዛን ይዞ ነበር።
\v 6 ከአራቱ ሕያዋን ፍጡራን የመጣ የሚመስል ድምፅ፥«አንድ እርቦ ስንዴ በዲናር፥ሦስት እርቦ ገብስም በዲናር፤ ነገር ግን ዘይቱንና ወይኑን አትጉዳ» ሲል ሰማሁ።
\s5
\v 7 በጉ አራተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ የአራተኛው ሕያው ፍጡር ድምፅ «ና!» ሲል ሰማሁ።
\v 8 ከዚያም በኋላ ግራጫ ፈረስ አየሁ፤በላዩም ላይ የተቀመጠው ስሙ ሞት ተብሎ ይጠራ ነበር፤ሲኦልም ይከተለው ነበር። ሞትና ሲኦልም የምድርን አንድ አራተኛ በሰይፍ፥በረሃብ፥ በበሽታ፥በዱር አራዊት እንዲገድሉ ሥልጣን ተሰጣቸው።
\s5
\v 9 በጉ አምስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ ስለ እግዚአብሔር ቃልና በጽናት ስለ ጠበቁት ምስክርነት የተገደሉትን ሰዎች ነፍሶች ከመሠዊያው በታች አየሁ።
\v 10 እነርሱም በታላቅ ድምፅ፥«በሁሉም ላይ የምትገዛ ቅዱስና እውነተኛ የሆንህ ጌታ አምላክ ሆይ፤በምድር በሚኖሩት ላይ የማትፈርደው፥ ደማችንስ የማትበቀለው እስከ መቼ ድረስ ነው?» በማለት ይጮኹ ነበር።
\v 11 ከዚያም በኋላ ለእያንዳንዳቸው ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፤እነርሱ እንደ ተገደሉ፥ ገና የሚገደሉ አገልጋይ ጓደኞቻቸው፥ወንድሞቻቸውና እህቶቻቸው ቁጥር እስኪሞላ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እንዲታገሱ ተነገራቸው።
\s5
\v 12 በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በሚከፍትበት ጊዜ አየሁ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ። ፀሐይም እንደ ጥቁር ጨርቅ ጠቆረች፤ ጨረቃም ሙሉ በሙሉ እንደ ደም ቀላች።
\v 13 የበለስ ዛፍ ኀይለኛ ነፋስ በሚወዘውዛት ጊዜ በላይዋ ያለ ያልበሰለ ፍሬ እንደሚረግፍ ሁሉ የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ረገፉ።
\v 14 ሰማይም እንደ ብራና እየተጠቀለለ ተወገደ፤ እያንዳንዱ ተራራና ደሴት ከስፍራው ተነቀለ።
\s5
\v 15 ከዚያም በኋላ የምድር ነገሥታት፥ታላላቅ ሰዎች፥ የጦር መኮንኖች፥ ሀብታሞች፥ብርቱዎች፥ ባሮችና ጌቶች ሁሉ በዋሻዎችና በተራሮች ዐለት ውስጥ ተሸሸጉ።
\v 16 ለተራሮችና ለዐለቶችም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤«በላያችን ላይ ውደቁ፤ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ፊት፥ከበጉም ቁጣ ሰውሩን
\v 17 ታላቁ የቁጣቸው ቀን ስለ መጣ ማን መቆም ይችላል?»
\s5
\c 7
\cl ምዕራፍ 7
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ አራት መላእክት በአራቱም የምድር ማዕዘን ቆመው አየሁ፤ እነርሱም በምድር ቢሆን በባሕር ላይ ወይም በማንኛውም ዛፍ ላይ ፈጽሞ ነፋስ እንዳይነፍስ አራቱን የምድር ነፋሳትን አጥብቀው ይከለክሉ ነበር።
\v 2 የሕያው አምላክ ማኅተም የያዘ ሌላ መልአክ ከምስራቅ ሲመጣ አየሁ። እርሱም ምድርንና ባሕርን ይጎዱ ዘንድ ሥልጣን ወደ ተሰጣቸው ወደ አራቱ መላእክት በታላቅ ድምፅ እየጮኽ፥
\v 3 «በአምላካችን አገልጋዮች ግምባር ላይ ማኅተም እስክናደርግ ድረስ ምድርንም ሆነ ባሕርን ወይም ዛፎችን እንዳትጎዱ» አለ።
\s5
\v 4 ከእስራኤል ሕዝብ ነገድ ሁሉ የታተሙት ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ እንደ ሆነ ሰማሁ።
\v 5 ከይሁዳ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከሮቤል ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከጋድ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥
\v 6 ከአሴር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ ከንፍታሌም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከምናሴ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ
\s5
\v 7 ከስምዖን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ፥ከሌዊ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከይሳኮር ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥
\v 8 ከዛብሎን ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከዮሴፍ ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ፥ከብንያም ነገድ አሥራ ሁለት ሺህ ታተሙ።
\s5
\v 9 ከዚህ በኋላ ከሕዝብ፥ከነገድ፥ከወገንና ከቋንቋ ሁሉ የመጡ ቁጥራቸው ማንም ሊቆጥረው የማይችል አጅግ ብዙ ሕዝብ ነጭ ልብስ ለብሰው፥ በእጃቸውም የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆመው አየሁ።
\v 10 በታላቅ ድምፅም «ማዳን፥ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!» እያሉ ይጮኹ ነበር።
\s5
\v 11 መላእክቱም ሁሉ በዙፋኑ እና በሽማግሌዎች ዙሪያ እንዲሁም በአራቱ ሕያዋን ፍጡራን ዙሪያ ቆመው ነበር፤እነርሱም በመሬት ላይ ወድቀው በዙፋኑም ፊት በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ፥
\v 12 «አሜን! ውዳሴ፥ ክብር፥ጥበብ፥ምስጋና፥ኀይልና ብርታትም ከዘላለም እስከ ዘላለም ለአምላካችን ይሁን፤አሜን» ይሉ ነበር።
\s5
\v 13 ከዚያም በኋላ ከሽማግሌዎች አንዱ፥«እነዚህ ነጭ ልብስ የለበሱ እነማናቸው ከየትስ የመጡ ናቸው?» በማለት ጠየቀኝ፤
\v 14 እኔም «ጌታ ሆይ፥አንተ ታውቃለህ» አልሁት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤«እነዚህ በታላቁ መከራ ውስጥ አልፈው የመጡ ናቸው፤ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው በማንጻት ነጭ አድርገዋል።
\s5
\v 15 ክዚህም የተነሳ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት መሆን ችለዋል፤ እርሱንም በመቅደሱ ውስጥ ቀንና ሌሊት ያመልኩታል። በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው ድንኳኑን በእነርሱ ላይ ይዘረጋል።
\v 16 እነርሱም ከእንግዲህ አይራቡም፤አይጠሙምም። ፀሐይ አያቃጥላቸውም፤ ሙቀትም አያሰቃያቸውም።
\v 17 ምክንያቱም በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናል፤ወደ ሕይወት ውኃ ምንጭ ይመራቸዋል፤እግዚአብሔር እንባንም ሁሉ ከዐይኖቻቸው ያብሳል።»
\s5
\c 8
\cl ምዕራፍ 8
\p
\v 1 በጉ ሰባተኛውን ማህተም በፈታ ጊዜ በሰማይ ለግማሽ ሰዓት ያህል ጸጥታ ሆነ፤
\v 2 ከዚያም በእግዚአብሄር ፊት የቆሙ ስባት መላዕክትን አየሁ፡፤ሰባት መለከቶችም ተሰጣቸው።
\s5
\v 3 ሌላም መልኣክ መጣ፤በእጁም ከወርቅ የተሰራ ጥና ይዞ ነበር።እርሱም በመሰዊያው አጠገብ ቆሞ ነበር።በዙፋኑ ፊት ባለው በወርቅ በተሰራ መሰዊያ ላይ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር የሚያቀርበው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።
\v 4 የእጣኑ ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሄር ወጣ፤
\v 5 መልአኩም ጥናውን ወስዶ ከመሰዊያው በወስድው እሳት ሞላው ከዚያም በኃላ ወደ ምድር ወረወረው፤የነጎድጛድ ድምጽ፤መብረቅ፤የምድር መናወጥም ሆነ።
\s5
\v 6 ሰባት መለከቶችን የያዙ ስባት መላዕክት መለከቶቻቸውን ለመንፋት ተዘጋጁ።
\v 7 የመጀመሪያውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ደም የተቀላቀለበት እሳትና በረዶ ሆነ። ይህም ወደ ምድር ተጣለ፤ ከዚህም የተነሣ የምድርም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የዛፎችም አንድ ሦስተኛ ተቃጠለ፤ የለመለመ ሣር ሁሉ ተቃጠለ።
\s5
\v 8 ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ በእሳት የሚቃጠል ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር ወደ ባህር ተጣለ፤ የባህር አንድ ሦስተኛ ወደ ደም ተለወጠ።
\v 9 በባህር ውስጥ ካሉ ህያዋን ፍጥረታት አንድ ሦስተኛ ሞቱ፤ የመርከቦችም አንድ ሦስተኛ ተደመሰሱ።
\s5
\v 10 ሦስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ እንደ ችቦ የሚቃጠል ታላቅ ኮከብ ከሰማይ ወደቀ፤ የወደቀውም በወንዞች አንድ ሦስተኛ በውሃ ምንጮች ላይ ነው።
\v 11 የኮከቡም ስም እሬቶ ይባላል። የውኆችም አንድ ሦስተኛ መራራ ሆነ። ከውሃው መራራነት የተነሳ ብዙ ሰዎች ሞቱ።
\s5
\v 12 አራተኛውም መልአክ መልከቱን ነፋ፤የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፣ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ። ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛ ጨለመ፤ በዚህም ምክንያት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛው ያለ ብርሃን ሆነ።
\s5
\v 13 እነሆ በሰማይ መካከል ሲበርር የነበር አንድ ንስር በታላቅ ድምጽ፤ ሦስቱ መላእክት የቀሩትን መለከቶች ስለሚነፉ «በምድር ላይ ለሚኖሩ ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!» ሲል ሰማሁ።
\s5
\c 9
\cl ምዕራፍ 9
\p
\v 1 አምስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ አንድን ኮከብ ከሰማይ ወደ ምድር ሲወድቅ አየሁ። ኮከቡም የጥልቁ ጕድጓድ መክፈቻ ተሰጠው፤
\v 2 እርሱም ጥልቅ የሆነውን ጕድጓድ ከፈተው፤ ጢስም ከታላቅ ምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ሆኖ ከጕድጓዱ ወጣ፤ ከጕድጓዱ በሚወጣው ጢስ ምክንያት ፀሐይና አየር ወደ ጨለማነት ተለወጡ፤
\s5
\v 3 ከጢሱም ውስጥ አንበጣዎች በምድር ላይ ወጡ፤የምድር ጊንጦችን ኅይል የመሰለ ኅይል ተሰጣቸው፤
\v 4 የምድርንም ሣር ሆነ ማናቸውንም የለመለመ ተክል ወይም ማናቸውንም ዛፍ እንዳይጎዱ ተነገራቸው። መጉዳት የነበረባቸው ግን በግንባራቸው ላይ የእግዚአብሔር ማህተም የሌለባቸውን ሰዎች ብቻ ነው።
\s5
\v 5 እነርሱንም ቢሆን ለአምስት ወር ለማሰቃየት ብቻ እንጂ የመግደል ሥልጣን አልተሰጣቸውም። የእነርሱም ስቃይ ጊንጥ ሰውን ነድፎ እንደሚሰማው ስቃይ ዐይነት ነበር።
\v 6 በእነዚያ ቀናት ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ነገር ግን አያገኙትም። ለመሞት በብርቱ ይሻሉ፤ ነገር ግን ሞት ከእነርሱ ይሸሻል።
\s5
\v 7 አንበጦቹ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ፈረሶች ነበሩ። በራሳቸውም ላይ የወርቅ አክሊል የመሰለ ነገር ነበር፤ ፊታቸውም የሰው ፊት ይመስል ነበር።
\v 8 የሴቶች ጠጕር የሚመስል ጠጕር ነበራቸው። ጥርሳቸው የአንበሳ ጥርስ ይመስል ነበር።
\v 9 የብረት ጥሩር የሚመስልጥሩር ነበራቸው፤ የክንፎቻቸውም ድምፅ ወደ ጦርነት የሚጋልቡ ብዙ ፈረሶችና ሰረገሎች የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስል ነበር።
\s5
\v 10 እንደ ጊንጥ መንደፊያ ያለው ጅራት ነበራቸው። ሰዎችንም በጅራታቸው ባለ መንደፊያ ለአምስት ወር ለመጉዳት ስልጣን ነበራቸው።
\v 11 በእነርሱም ላይ የጥልቁ ጕድጓድ መልአክ የሆነ ንጉሥ ነበራቸው። ስሙም በዕብራይስጥ አብዶን ሲሆን በግሪክ ደግሞ አጶሊዮን ይባላል፥
\v 12 የመጀመሪያው ወዮ አልፎአል፥ልብ በል! ከዚህ በኋላ ሌላ ሁለት ጥፋቶች ይመጣሉ።
\s5
\v 13 ስድስተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፥ በእግዚአብሔር ፊት ካለው በወርቅ ከተሰራው መሰዊያ ከቀንዶቹ ድምጽ ሲወጣ ሰማሁ።
\v 14 ድምፁም መለከት የያዘውን ስድስተኛውን መልአክ፣ «በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ የታሰሩትን አራቱን መላእክት ፍታቸው» አለው።
\v 15 ለዚያ ሰዓትና ለዚያ ቀን ለዚያ ወርና ለዚያ ዓመት ተዘጋጅተው የነበሩት አራት መላእክት የሰዎችን አንድ ሦስተኛ እንዲገድሉ ተፈቱ።
\s5
\v 16 የፈረሰኛው ሰራዊት ብዛት ሁለት መቶ ሚሊዮን ነበር።ቍጥራቸውንም ሰማሁ።
\v 17 ፈረሶቹና በፈረሶቹ ላይ የሚጋልቡ በራእይ ያየኋቸው በዚህ ዐይነት ነበር፥ በደረታቸው ላይ የነበረው ጥሩር እንደ እሳት ቀይ፣ እንደ ያክንት (ጥቁር ሰማያዊ)፣ እንደ ዲንም ቢጫ ነበር፥ የፈረሶቹ ራስ የአንበሳ ራስ ይመስል ነበር። ከአፋቸው እሳትና ጢስ ዲንም ይወጣ ነበር።
\s5
\v 18 በእነዚህ ሦስት መቅሰፍቶች ማለትም ከአፋቸው በወጣው እሳት፤ ጢስና ዲን የሰዎች አንድ ሦስተኛ ተገደለ።
\v 19 የፈረሶቹ ኃይል በአፋቸውና በጅራታቸው ነበር፥ ምክንያቱም ጅራታቸው እባብ ይመስላል፥ ራስ አላቸው፥ ሰውን የሚጎዱትም በእርሱ ነበር።
\s5
\v 20 በእነዚያ መቅሰፍቶች ከመሞት የተረፉት ሰዎች ከክፉ ሥራቸው ንስሓ አልገቡም፤ አጋንንትንና ከወር፣ ከብር፣ ከናስ፣ ከድንጋይና ከእንጨት የተሠሩ፣ ማየት ወይም መሄድ የማይችሉትን ጣዖታት ማምለክንም አልተዉም።
\v 21 እንዲሁም ከነፍሰ ገዳይነት ወይም ከሟርት፥ ከሴስኛነትና፥ ከሌብነት ንስሓ አልገቡም።
\s5
\c 10
\cl ምዕራፍ 10
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ሌላ ብርቱ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። እርሱም ደመናን የለበሰ ነበር። በራሱም ዙሪያ ቀስተ ደመና ነበር። ፊቱ እንደ ፀሐይ እግሮቹ እንደ እሳት ዐምድ ነበሩ፤
\v 2 የተከፈተ ትንሽ ጥቅል መጽሐፍ በእጁ ይዞ ነበር፤ ቀኝ እግሩን በባህር ላይ ግራውንም በምድር ላይ አደረገ።
\s5
\v 3 ከዚያም እንደሚያገሳ አንበሳ በመሰለ ታላቅ ድምጽ ጮኸ፤ በጮኸ ጊዜ፣ ሰባቱም ነጎድጓዶች ድምፃቸውን አሰሙ ፤
\v 4 ሰባቱ ነድጓዶች በተናገሩ ድምፃቸውን ባሰሙ ጊዜ፣ እኔ ልጽፍ አሰብሁ። ነገር ግን «ሰባቱ ነጎድጓዶች የተናገሩትን በምስጢር ያዘው እንጂ አትጻፈው» የሚል ድምጽ ከሰማይ ሰማሁ።
\s5
\v 5 ከዚያም በባህርና በምድር ላይ ቆሞ ያየሁት መልአክ ቀኝ እጁን ወደ ሰማይ አነሣና
\v 6 ዘላለም በሚኖረው ሰማይንና በእርሱ ያሉትን፣ ምድርንና በእርስዋ ያሉትን፣ ባህርንና በርስዋ ያሉትን በፈጠረው አምላክ ስም ማለ። እንዲህም አለ፤«ከእንግዲህ ወዲህ አይዘገይም
\v 7 ነገር ግን ሰባተኛው መልአክ መለከቱን በሚነፋበት ቀን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት በገለጠላቸው መሰረት የእግዚአብሔር ምስጢር ይፈጸማል።»
\s5
\v 8 ከሰማይ የሰማሁት ድምጽ፣«በባህርና በምድር ላይ የቆመው መልአክ በእጁ የያዘውንና የተፈታውን ጥቅል መጽሐፍ ሂድና ውሰድ» ብሎ እንደገና ሲናገረኝ ሰማሁት»።
\v 9 ወደ መልእኩም ሄጄ «ትንሹን ጥቅል መጽሐፍ ስጠኝ?» አልሁት። እርሱም «ውሰድና ብላ በሆድህም ውስጥ መራራ ይሆናል፤ በአፍህ ግን እንደ ማር ይጣፍጣል»አለኝ።
\s5
\v 10 እኔም ትንሹን ጥቅል መጽሐፍ ከመልአኩ እጅ ወስጄ በላሁት፤ በአፌ እንደ ማር ጣፈጠ፤ ከበላሁት በኋላ ግን ሆዴ መራራ ሆነ።
\v 11 ከዚህም በኋላ «ስለብዙ ሕዝቦች፤ አገራት፤ ልዩ ልዩ ቋንቋ ስለሚናገሩ ሰዎችና ሰለ ነገሥታት እንደ ገና ትንቢት መናገር አለብህ» ተብሎ ተነገረኝ።
\s5
\c 11
\cl ምዕራፍ 11
\p
\v 1 ከዚያም ለመለኪያ የሚያገለግል አንድ ረዥም ዘንግ ተሰጠኝ፤እንዲህም ተባልሁ፣«ተነሥተህ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ፥ መሰዊያውንና በዚያ የሚያመለኩትንም ቍጠር።
\v 2 ከቤተመቅደሱ ውጭ ያለውን አደባባይ ግን ተወው፤ እርሱ ለአሕዛብ የተሰጠ ስለ ሆነ አትለካው፥አሕዛብ ቅድስቲቱን ከተማ አርባ ሁለት ወራት ይረግጧታል።
\s5
\v 3 ሁለቱ ምስክሮቼ ማቅ ለብሰው ለ1260 ቀን ትንቢት እንዲናገሩ ሥልጣን እሰጣቸዋለሁ።»
\v 4 እነዚህም በምድር ጌታ ፊት የቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎችና ሁለቱ መቅረዞች ናቸው፤
\v 5 ማንም እነርሱን ሊጎዳ ቢፈልግ እሳት ከአፋቸው ወጥቶ ጠላቶቻቸውን ይበላል፤ እነርሱን ሊጎዳ የሚፈልግ ሁሉ የሚሞተው በዚህ ዐይነት ነው፥
\s5
\v 6 እነዚህ ምስክሮች ትንቢት በሚናገሩባቸው ቀናት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ለመዝጋት ሥልጣን አላቸው፥ እንዲሁም ውሆችን ወደ ደም ለመለወጥና በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በማንኛውም ዓይነት መቅሰፍት ምድርን ለመምታት ሥልጣን አላቸው፡
\v 7 ምስክርነታቸውን በጨረሱ ጊዜ ከጥልቁ ጉድጛድ የሚወጣው አውሬ ከእነርሱ ጋር ይዋጋል፤ ያሸንፋቸዋል ይገድላቸውማል።
\s5
\v 8 ሬሳቸውም በምሳሌያዊ አጠራር ሰዶም ወይም ግብጽ ተብላ በምትጠራው በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይጋደማል፤ ከተማይቱም የእነርሱ ጌታ የተሰቀለባት ናት፤
\v 9 ከልዩ ልዩ ወገን፥ ነገድ፥ ከልዩ ልዩ ቋንቋና ሕዝብ የሆኑ ሰዎች ሶስት ቀን ተኩል ሬሳቸውን ይመለከታሉ፥ ሬሳቸውም እንዳይቀበር ይከለክላሉ።
\s5
\v 10 ሁለቱ ነቢያት የምድርን ሰዎች ሁሉ አስጨንቀው ስለ ነበር፣ በእነርሱ ሞት በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም በዓል ያደርጋሉ፤ ስጦታም ይለዋወጣሉ።
\v 11 ነገር ግን ሦስት ቀን ተኩል ካለፈ በኋላ፣ የሕይወት እስትንፋስ ከእግዚአብሔር መጥቶ ወደ ሬሳዎቹ ይገባል፤ በእግራቸውም ይቆማሉ፤ የሚመለከቷቸውም ሰዎች ታላቅ ፍርሃት ይወድቅባቸዋል።
\v 12 ከዚህ በኋላ ሁለቱ ነቢያት፣ «ወደዚህ ውጡ» የሚል ታላቅ ድምጽ ከሰማይ ሰሙ፤ ጠላቶቻቸውም እየተመለከቷቸው በደመና ወደ ሰማይ ወጡ።
\s5
\v 13 በዚያኑ ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ የከተማይቱም አንድ ዐሥረኛ ወደመ። በምድር መናወጥም ምክንያት ሰባት ሺህ ሰዎች ሞቱ፤ ከሞት የተረፉትም እጅግ ፈሩ፤ለሰማይም አምላክ ክብርን ሰጡ።
\v 14 ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ልብ በል! ሦስተኛው ወዮ ፈጥኖ ይመጣል።
\s5
\v 15 ሰባተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤በሰማይም«የዓለም መንግሥት የጌታ አምላካችንና የእርሱ ክርስቶስ ሆናለች፤ እርሱም ለዘላለም ይነግሣል» የሚል ታላቅ ድምጽ ሰማሁ።
\s5
\v 16 በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው ላይ የተቀመጡት ሃያ አራቱም ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤
\v 17 እነርሱም እንዲህ አሉ፣«ያለህና የነበርህ፣ ሁሉን የምትችል፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ትልቁን ሥልጣንህን በእጅህ አድርገህ ስለ ነገሥህ እናመሰግንሃለን።
\s5
\v 18 አሕዛብ ተቆጡ፤ ነገር ግን የአንተም ቁጣ መጣ ።በሙታን ላይ የምትፈርድበት ዘመንም መጣ፤ለአገልጋዮችህ፣ ለነቢያት፣ ለቅዱሳን፣ ስምህንም ለሚያከብሩት ለታናናሾችና ለታላላቆች ሽልማታቸውን የምትሰጥበት ጊዜ እንዲሁም ምድርን ያጠፏትን የምታጠፋበት ጊዜ ደረሰ።»
\s5
\v 19 በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ተከፈተ፤የእርሱም የቃል ኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ የመብረቅ ድምጽ፣ነጎድጓድም፣የምድር መናወጥና ታላቅም ማዕበል ሆነ።
\s5
\c 12
\cl ምዕራፍ 12
\p
\v 1 በሰማይም ታላቅ ምልክት ታየ ፤ ፀሐይን የለበሰችና ጨረቃን ከእግሯ በታች ያደረገች፣ ዐሥራ ሁለት ከዋክብት ያሉት አክሊልም በራስዋ ላይ የደፋች አንዲት ሴት ታየች።
\v 2 እርስዋም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ምጥ ይዟትም ተጨንቃ ትጮህ ነበር፥
\s5
\v 3 እንዲሁም ሌላ ምልክት በሰማይ ታየ፤እነሆ፤ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶች የነበሩት፤በራሶቹም ላይ ሰባት አክሊል የደፋ ትልቅ ቀይ ዘንዶ ታየ።
\v 4 በጅራቱ የኮከቦችን አንድ ሦስተኛ ከሰማይ ስቦ ወደ ምድር ጣለ፤ዘንዶውም ሴቲቱ በምትወልድበት ጊዜ ልጅዋን ለመዋጥ አስቦ ልትወልድ ወደ ተቃረበችው ሴት ፊት ቆመ።
\s5
\v 5 ሴቲቱም ሕዝቦችን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛ ወንድ ልጅ ወለደች። ልጅዋ ግን ወደ እግዚአብሔርና ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተወሰደ፤
\v 6 ሴቲቱም ወደ ምድረበዳ ሸሽታ ሄደች፤ በዚያም እግዚአብሔር ለ1260 ቀን በክብካቤ ተይዛ እንድትጠበቅ አደረጋት።
\s5
\v 7 በሰማይም ጦርነት ሆነ። ሚካኤልና መላእክቱ ከዘንዶው ጋር ተዋጉ፤ዘንዶውና መላእክቱ መልሰው ተዋጓቸው።
\v 8 ነገር ግን ዘንዶው የማሸነፍ ዐቅም አልነበረውም፤ከዚያም ወዲያ እርሱና መላእክቱ በሰማይ የነበራቸውን ስፍራ አጡ።
\v 9 ታላቁም ዘንዶ ወደ ምድር ተጣለ፤ እርሱም ሰዎችን ሁሉ የሚያስተው ዲያቢሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀደመው እባብ ነው።እርሱ ወደ ምድር ተጣለ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።
\s5
\v 10 ከዚህ በኋላ ታላቅ ድምፅ ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤«አሁን ማዳንና ኃይል መንግሥትም የአምላካችን ሆኖአል፤ሥልጣንም የእርሱ ክርስቶስ ሆኖአል።ምክንያቱም ወንድሞቻችንን በአምላካችን ፊት ቀንና ለሊት ሲከሳቸው የነበረ የወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአል።
\s5
\v 11 እነርሱም በበጉ ደምና በተናገሩት የምስክርነት ቃል ድል ነሡት፤ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ሰጥተዋልና።
\v 12 ስለዚህ ሰማይና በውስጣቸው የምትኖሩ ሁሉ ደስ ይበላችሁ፤ ምድርና ባህር ግን ወዮላችሁ፤ ምክንያቱም ጥቂት ጊዜ እንደ ቀረው ዐውቆ ዲያቢሎስ በታላቅ ቍጣ ወደ እናንተ ወርዷል።
\s5
\v 13 ዘንዶው ወደ ምድር እንደተጣለ ባስተዋለ ጊዜ፤ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት፤
\v 14 ሴቲቱ ከእባቡ ፊት ርቃ ለዘመን፣ ለዘመናትና ለዘመንም እኩሌታ በክብካቤ ተጠብቃ ወደ ምትኖርበት በምድረ በዳ ወደ ተዘጋጀላት ስፍራ በርራ እንድትሄድ ሁለት የታላቅ ንስር ክንፎች ተሰጧት።
\s5
\v 15 እባቡ የወንዝ ውሃ የሚያህል ውሃ ከአፉ ተፍቶ ሴቲቱ በጎርፍ እንድትወሰድ ብሎ በስተ ኋላዋ አፈሰሰ።
\v 16 ነገር ግን ምድር አፍዋን ከፍታ ዘንዶው በአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ በመዋጥ ረዳቻት።
\v 17 ከዚያም ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ ከትሩፋን ዝርያዎችዋ ጋር ሊዋጋ ሄደ። እነርሱም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁና ስለ ኢየሱስ በታማኝነት የሚመሰክሩት ናቸው።
\v 18 ዘንዶውም በባህር ዳር ባለው አሸዋ ላይ ቆመ።
\s5
\c 13
\cl ምዕራፍ 13
\p
\v 1 ከዚያም አንድ አውሬ ከባህር ሲወጣ አየሁ። እርሱም ዐስር ቀንዶችና ሰባት ራሶች ነበሩት። በቀንዶቹም ላይ አስር አክሊሎች ነበሩ፤ በራሶቹም ላይ እግዚአብሔርን የሚሰድብ ስሞች ነበሩት።
\v 2 ያየሁትም አውሬ ነብር ይመስል ነበር፤ እግሮቹ የድብ እግሮች፤ አፉ የአንበሳ አፍ ይመስል ነበር። ይገዛም ዘንድ ዘንዶው የራሱን ኅይልና የራሱን ዙፋን ትልቅም ስልጣን ለአውሬው ሰጠው።
\s5
\v 3 ከአውሬው ራሶቹ አንዱ ለሞት የሚያበቃ ቁስል እንደነበረው ሆኖ አየሁት፤ ነገር ግን ለሞት የሚያደርስው ቁስል ዳነ፤በዚህም ምክንያት ዓለም በሙሉ በመደነቅ አውሬውን ተከተለ።
\v 4 አውሬውም ስልጣኑን በመስጠቱ ሁሉም ለዘንዶው ሰገዱለት «አውሬውን ማን ይመስለዋል? ከእርሱስ ጋር ማን ሊዋጋ ይችላል?» እያሉ ለአውሬው ሰገዱለት።
\s5
\v 5 አውሬውም የትዕቢትና የስድብ ቃል የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፤ ለአርባ ሁለት ወራትም ስልጣኑን እንዲያሳይ ተፈቀደለት።
\v 6 አውሬው አፉን ከፍቶ እግዚአብሔርን፤ የእግዚአብሔርን ስም፤ መኖሪያውንና በሰማይ የሚኖሩትን መሳደብ ጀምረ።
\s5
\v 7 አውሬው ቅዱሳንን እንዲዋጋ ና፤ ድል እንዲነሳቸውም ስልጣን ተሰጠው። በነገድና በወገን በቃንቃና በህዝብ ሁሉ ላይ ስልጣን ተስጠው።
\v 8 ዓለም ሲፈጠር ጀምሮ ስሞቻቸው በታረደው በግ የህይወት መጽሀፍ ያልተጻፈ በዓለም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁ ሉ ለአውሬው ይሰግዳሉ።
\s5
\v 9 የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ።
\v 10 «የሚማረክ ማንም ቢኖር ወደ ምርኮ ይሄዳል፤ በሰይፍ የሚገደል ማንም ቢኖር በሰይፍ ይገደላል» እንግዲህ የቅዱሳን ትዕግስትና እምነት የሚታየው በዚህ ጊዜ ነው።
\s5
\v 11 ከዚህም በኃላ ሌላ አውሬ ደግሞ ከምድር ሲውጣ አየሁ፤ የበግ ቀንዶች የሚመስሉ ሁለት ቀንዶች ነበሩት አነጋግሩም እንደ ዘንዶው ነበር።
\v 12 የመጀመሪያውን አውሬ ስልጣን ሁሉ በመጀመሪያው አውሬ ፊት ሆኖ ይሰራበት ነበር፤ ምድርና በእርስዋ ላይ የሚኖሩት ሁሉ ለአውሬው እንዲሰግዱለት ያደርጋል፤ ይህም አውሬ ያ ለሞት የሚያድርስ ቁስል የዳነለት የመጀመሪያው አውሬ ነው።
\s5
\v 13 እርሱም በሰዎች ፊት እሳትን ከሰማይ እስከማውረድ ድረስ ታላላቅ ምልክቶችን ያደርግ ነበር፤
\v 14 እንዲያደርግ በተፈቀደለት ተዓምራት በሰይፍ ቁስሎ የዳነውን የአውሬውን ምስል እንዲሰሩ በማዘዝ በምድር ላይ የሚኖሩትን ሰዎች ያስት ነበር።
\s5
\v 15 እርሱም ምስሉ መናገር እንካ እስከሚችል ድረስ እስትንፋስ ለመስጠትና ለአውሬው የማይስግዱትን መግደል ይችል ዘንድ ለማድረግ ስልጣን ተሰጠው።
\v 16 እርሱም ታናናሾችም ሆኑ ታላላቆች፤ ሀብታሞችም ሆኑ ድኾች ጌቶችም ሆኑ አገልጋዮች ሁሉም በቀኝ እጃቸው ወይም በግምባራቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉ አስገደዳቸው።
\v 17 የአውሬው ስም የሆነው ምልክት ወይም የስሙ ቁጥር የሌለው ማንም ሰው መግዛትም ሆን መሸጥ አይችልም ነበር።
\s5
\v 18 ይህ ጥበብን የሚጠይቅ ነው።የሚያስተውል የአውሬውን ቁጥር ያስላው፤ ቁጥሩም የሰው ቁጥር ነው፤ የውሬውም ቁጥር 666 ነው፤
\s5
\c 14
\cl ምዕራፍ 14
\p
\v 1 አየሁም እነሆ በጉ በጽዮን ተራራ በፊቴ ቆሞ ነበር። ከእርሱ ጋር የእርሱ ስምና የአባቱ ስም በግንባራቸው ላይ የተጻፈባቸው አንድ መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።
\v 2 በሰማይ እንደ ብዙ ውኃ ድምጽና ና እንደታላቅ ነጎድጋድ ድምጽ የመሰለ ድምጽ ሰማሁ፤ የሰማሁትም ድምጽ በገና ደርዳሪዎች በገና እየደረደሩ የሚያሰሙትን ድምጽ ይመስል ነበር።
\s5
\v 3 እነርሱም በዙፋኑና በአራቱ እንስሶች በሽማግሌዎችም ፊት አዲስ መዝሙር ዘመሩ። ይህንም መዝሙር ከምድር ከተዋጁት ከአንድ መቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ማንም ሊማረው አልቻለም።
\v 4 እነርሱም ራሳቸውን ከሴቶች ጋር ካላረከሱት ናቸው፤ ራሳቸውንም በግብረ ስጋ ግንኙነት ካለማርከስ ጠብቀዋል። እነርሱ ናቸው በጉ ወደሚሄድበት ሁሉ የሚከተሉት እነዚህ ናቸው፤ እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኩራት ለመሆን ከሰዎች መካከል የተዋጁ ናቸው።
\v 5 በአንደበታቸውም ሀሰት ተናግረው አያውቁም። ነቀፋም የሌለባቸው ናቸው።
\s5
\v 6 በምድር ላይ ለሚኖሩ ለህዝብ፤ ለነገድ፤ ለቃንቃና ለወገን ሁሉ ለማብሰር ዘላለማዊውን የምስራች ቃል የያዘ ሌላ መልዓክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ
\v 7 እርሱም በታላቅ ድምጽ «እግዚአብሄርን ፍሩ፤ አክብሩትም። ምክንያቱም የእርሱ የፍርድ ሰዓት ደርሳል፤ ሰማይን፤ ምድርን፤ ባህርንና የውሃ ምንጮችን የፈጠረን አምላክ አምልኩ» አለ
\s5
\v 8 ሌላም ሁለተኛ መልአክ «የዝሙትዋ ፍትወት የሆነውን የሚያሰክር የወይን ጠጅ ለህዝቦች ሁሉ ያጠጣች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፤ ወደቀች» እያለ የመጀመሪያውን መልዓክ ተከተለው
\s5
\v 9 ሌላ ሶስተኛ መለዓክ በታላቅ ድምጽ እንዲህ እያለ ተከተላቸው «ለአውሬውና ለምስሉ ቢሰግዱ ምልክቱን በግምባሩ ወይም በእጁ ቢያደርግ፤
\v 10 የእግዚአብሔርን የቁጣ የወይን ጠጅ ይጠጣል፤ ይህም የወይን ጠጅ ሳይበረዝ በቁጣው ጽዋ የተዘጋጀ ነው፤ ፅሚጠጣውም ሰው በቅዱሳን መላዕክት ፊትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሰቃያል፤
\s5
\v 11 የስቃያቸውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ወደ ላይ ይወጣል፤ ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ የስሙንም ምልክት ያደረጉ ሁሉ ቀንና ለሊት ዕረፍት የላቸውም።
\v 12 የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የሚጠብቁና በኢየሱስ የሚያምኑማመኑ ቅዱሳን፤ ትዕግስታቸው የሚታየው እዚህ ላይ ነው።
\s5
\v 13 ከሰማይም እንዲህ የሚል ድምጽ ሰማሁ «ይህን ጻፍ ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ ሆነው የሚሞቱ የተባረኩ ናቸው» መንፈስም አዎ ስራቸው ስለሚከተላቸው ከድካማቸው ያርፋሉ» ይላል
\s5
\v 14 አየሁም እነሆ ነጭ ደመና ነበር በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦ ነበር። በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል አድርጎአል፤ በእጁም ስለታም ማጭድ ይዞአል።
\v 15 ከዚህም በኃላ ሌላ መልአክ ከመቅደሱ ወጣ በደመና ላይ የተቀመጠውን በታላቅ ድምጽ «የምድር መከር ደርሶአል የአጨዳ ሰዓትም ቀርቦአል፤ ስለዚህ ማጭድህን ስደድ» አለው።
\v 16 በደመናው ላይ የተቀመጠውም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደው ምድርም ታጨደች።
\s5
\v 17 ሌላ መልዓክ ከሰማይ ባለው መቅደስ ወጣ፤ እርሱም ስለታም ማጭድ ይዞ ነበር።
\v 18 በእሳትም ላይ ስልጣን ያለው ሌላ መልዓክ ከመሰዊያው አጠገብ ወጣና ስለታም ማጭድ የያዘውን መልዓክ በታላቅ ድምጽ «የዘለላዎቹ ፍሬዎች ስለበሰሉ የወይን ዘለላዎችን ሁሉ ከምድር ወይን ቁረጥ» አለው።
\s5
\v 19 መልዓኩም ማጭዱን ወደ ምድር ሰደደው፤ የምድርንም ወይን ዘለላ ቆረጠ፤ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር የቁጣ ወይን መጭመቂያ ውስጥ ጣለው።
\v 20 ከከተማው ውጭ ባለው በወይን መጥመቂያም ተጨመቀ ከመጭመቂያውም እስከ ፈረስ ልጋም ወደ ላይ ከፍ ያለና 300 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ደም ወጥቶ ፈሰሰ።
\s5
\c 15
\cl ምዕራፍ 15
\p
\v 1 ከዚህም በኃላ ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቁጣ የሚፈጽምባቸው የመጨረሻዎቹን ሰባት መቅሰፍት የያዙትን ሰባት መላዕክት አየሁ
\s5
\v 2 እኔም እሳት የተቀላቀለበት የሚመስል የመስተዋት ባህር አየሁ፤ አውሬውንና የአውሬውን ምስል የስሙንም ቁጥር ድል የነሱትን በባህሩ አጥገብ ቆመው ነበር። እግዚአብሔር የሰጣቸውንም በገና ይዘው ነበር።
\s5
\v 3 እነርሱም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሙሴን መዝሙርና የበጉን መዝሙር እንዲህ እያሉ ይዘምሩ ነበር «ሁሉን የምትችል ጌታ አምላክ ሆይ ስራህ ታላቅና አስደናቂ ነው። የእዝቦች ንጉስ ሆይ መንገድህ ትክክልና እውነት ነው።
\v 4 ጌታ ሆይ አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? ምክንያቱም አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ የጽድቅ ስራህ ስለተገለጠ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።»
\s5
\v 5 ከዚህም በኃላ አየሁ እነሆ የምስክር ድንካን የሆንው ቅድስተ ቅዱሳን በሰማይ ተከፈተ።
\v 6 ከቅድስተ ቅዱሳንም ሰባቱን መቅሰፍቶች የያዙት ሰባት መላዕክት ወጡ፤ የሚያንጸባርቅ ነጭ ልብስ ለብሰው ነበር። ደረታቸውንም በወርቅ መታጥቂያ ታጥቀው ነበር።
\s5
\v 7 ከአራቱ ህያዋን ፍጡራን አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚኖረው አምላክ ቁጣ የተሞሉትን ሰባት የውርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላዕክት ሰጣቸው።
\v 8 ቅድስተ ቅዱሳኑም ከእግዚአብሔር ክብርና ኃይል የተነሳ በጢስ ተሞላ፤ ሰባቱ መላዕክት የያዙእቸው ስባት መቅሰፍቶች እስኪፈጽሙ ድረስ ማንም ወደ ቅዱሰተ ቅዱሳኑ መገባት አልቻሉም።
\s5
\c 16
\cl ምዕራፍ 16
\p
\v 1 ሰባቱን መላእክት፣ “ሂዱና ሰባቱን የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች ምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሲወጣ ሰማሁ።
\s5
\v 2 የመጀመሪያው መልአክ ጽዋውን ምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬው ምልክት ባላቸውና ለምስሉ በሰገዱት አስከፊና የሚያሠቃይ ቁስል ወጣባቸው።
\s5
\v 3 ሁለተኛው መልአክ ጽዋውን ባሕር ላይ አፈሰሰ፤ ባሕሩ እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነ፤ ባሕር ውስጥ የነበረ ሕያው ፍጡር ሁሉ ሞተ።
\s5
\v 4 ሦስተኛው መልአክ ጽዋውን ወንዞችና የውሃ ምንጮች ላይ አፈሰሰ እነርሱም ደም ሆኑ።
\v 5 የውሃውም መልአክ፣ “ያለህና የነበርህ ቅዱስ ጌታ እንዲህ ስለ ፈረድህ ትክክል ነህ፣
\v 6 ምክንያቱም የቅዱሳንህና የነበያትን ደም ስላፈሰሱ፣ ደም አጠጣሃቸው፤ ይህም የሚገባቸው ነው” ሲል ሰማሁ።
\v 7 ከመሠዊያውም፣ “አዎን፣ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ፍርድህ እውነትና ትክክል ነው” የሚል ድምፅ ወጣ።
\s5
\v 8 አራተኛው መልአክ ጽዋውን ፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ለእርሷም ሰዎችን በግለትዋ የማቃጠል ሥልጣን ተሰጣት።
\v 9 ሰዎች በከባድ ሙቀቷ ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔር ስም ሰደቡ። ንሰሐ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም።
\s5
\v 10 አምስተኛው መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት በጨለማ ተዋጠ። ከሥቃያቸውም የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር።
\v 11 ከሥቃያቸውና ከደረሰባቸው ቁስል የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ያም ሆኖ ግን ስላደረጉት ክፉ ሥራ ንስሐ ለመግባት ፈቃደኞች አልሆኑም።
\s5
\v 12 ስድስተኛው መልአክ ጽዋውን ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለመጡ ነገሥታት መንገድ ለማዘጋጀት የወንዙ ውሃ ደረቀ።
\v 13 ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ እንዲሁም ከሐስተኛው ነቢይ አፍ እንቁራሪት የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ስወጡ አየሁ።
\v 14 እነዚህ ተአምራዊ ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው። ሁሉን በሚገዛ አምላክ ታላቅ ቀን ለሚደረገው ጦርነት የዓለም መንግሥታችን ሁሉ ለመሰብሰብ ወደ ወጥተው ሄዱ።
\s5
\v 15 “ልብ በሉ! እኔ እንደ ሌባ እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይገኝና ሰዎችም ሐፍረቱን እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ የተባረከ ነው።”
\v 16 መናፍስቱ ነገሥታቱን ሰብስበው በዕብራይስጥ አርማጌደን ወደሚባል ቦታ አመጧቸው።
\s5
\v 17 ሰባተኛው መልአክ ጽዋውን አየር ላይ አፈሰሰ። በዚያን ጊዜ፣ “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱና ከዙፋኑ ወጣ።
\v 18 ከዚያም የመብረቅ ብልጥታ፣ ሁካታ ነጎድጓድና ከባድ የመሬት መናወጥ ሆነ፤ የዚያ ዓይነት የምድር ነውጥ የሰው ልጅ ምድር ላይ መኖር ከጀመረ አንሥቶ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ከባድ ነበር።
\v 19 ታላቂቷ ከተማ ለሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ተደመሰሱ። እግዚአብሔር ታላቂቱ ባቢሎንን አስታወሰ፤ ለዚያች ከተማም የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንድትጠጣ ሰጣት።
\s5
\v 20 ደሴቶች ሁሉ ጠፋ፤ ተራሮችም በቦታቸው አልተገኙም።
\v 21 አንድ ታለንት የሚመዝን የበረዶ ድንጋይ ከሰማይ ወርዶ ሰዎች ላይ ወደቀ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሰቃቂ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች ስለ በረዶው ድንጋይ እግዚአብሔርን ተራገሙ።
\s5
\c 17
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ሰባቱን ጽዋዎች ይዘው ከነበሩት ሰባት መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ እንዲህ አለን፤ “በብዙ ውሆች ላይ የተቀመጠችውን ታላቂቱ አመንዝራ የፍርድ ቅጣት አሳይሃለሁ፤
\v 2 የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረሃል፤ ከዝሙቷ ወይን ጠጅ የምድር ነዋሪዎች ሰክረዋል።”
\s5
\v 3 መልአኩ በመንፈስ ወደ በረሐ ወስዶኝ፣ የስድብ ስሞች በሞሉበት ቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠች ሴት አየሁ። አወሬው ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ነበሩት።
\v 4 ሴትዬዋ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች እንዲሁም በዕንቁዎች አጊጣ ነበር። በእዛም ጸያፍ ነገሮችና የዝሙቷ ርኩሰት የሞላበት የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር።
\v 5 ግንባሯም ላይ፣ “ታላቂቱ ባቢሎን፣ የአመንዝሮችና የምድር ጸያፍ ነገሮች እናት” የሚል ምስጢራዊ ትርጉም ያለው ስም ተጽፎ ነበር።
\s5
\v 6 ሴትዬዋ በቅዱሳንና በኢየሱስ ሰማዕታት ደም ሰክራ አየሁ። ባየኋት ጊዜ በጣም ተደነቅሁ።
\v 7 መልአኩ ግን፣ “ለምን ትደነቃለህ? የሴትዮዋንና የተሸከማትን አውሬ (ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶች ያሉትን አውሬ) ምንነት እነግርሃለሁ።
\s5
\v 8 ያየኸው አውሬ ቀድሞ ነበረ፤ አሁን የለም፤ ሆኖም በኃላ ከጥልቁ ጉድጓድ ይመጣል። ከዚያም ወደ ጥፋት ይሄዳል። ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ሰማቸው በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፈ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ቀድሞ የነበረውን፣ አሁን የሌለውን በኃላ ግን የሚመጣውን አውሬ ሲያዩ ይደነቃሉ።
\s5
\v 9 ይህ አስተዋይ አእምሮን የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴትዬዋ የተቀመጠችባቸው ሰባት ኮረብቶች ናቸው።
\v 10 እነርሱም ሰባት ነገሥታት ናቸው። አምስቱ ወድቀዋል፤ አንድሱ አሁንም አለ፤ ሌለው ገና አልመጣም፤ በሚመጣበት ጊዜ ግን ለአጭር ጊዜ መቆየት ይገባዋል።
\s5
\v 11 ቀድሞ የነበረው አሁን ግን የሌለው አውሬ ራሱ ስምንተኛው ንጉሥ ነው ሆኖም፣ ከሰባቱ አንዱም ነው ወደ ጥፋትም ይሄዳል።
\s5
\v 12 ያዩኋቸው አሥር ቀንዶች ገና መንግሥት ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው፤ ነገር ግን ለአንድ ሰዓት ያህል ከአውሬው ጋር እንዲነግሡ ሥልጣን ይቀበላሉ።
\v 13 እነዚህ ነገሥታት ተመሳሳይ ሐሳብ አላቸው፤ ኅይልና ሥልጣናቸውን ሁሉ ለአውሬው ያስረክባሉ።
\v 14 በጉን ይዋጋሉ። ይሁን እንጂ፣ በጉ የጌቶች ጌታ የነገሥታት ንጉሥ በመሆኑ እርሱ ያሸንፋቸዋል የተጠሩት፣ የተመረጡትና ታማኝ የሆኑት ከእርሱ ጋር ድል ይነሣሉ።”
\s5
\v 15 መልአኩም፣ “አመንዝራዋ ተቀመጣባቸው የነበሩት ያየሃቸው ውሆች ሕዝቦችና ሰዎች፣ ወገኖችና ቋንቋዎች ናቸው” አለኝ።
\s5
\v 16 ያየሃቸው አሥር ቀንዶች ከአውሬው ጋር አንድ ላይ ሆነው አመንዝራዋን ይጠላሉ። ያጠፏታል፤ ራቁትዋን ያስቀሯታል፤ ሥጋዋን ይበላሉ፤ ጨርሶ እስክትጠፋ በእሳት ያቃጥሏታል።
\v 17 ምክንያቱም፣ የእግዚአብሔር ቃል እስኪፈጸም ድረስ ሥልጣናቸውን ለአውሬው ለመስጠት በመስማማት ዕቅዱን እንዲፈጽሙ እግዚአብሔር ይህን ሐሳብ በልባቸው ውስጥ አኑሮአል።
\s5
\v 18 ያይየሃት ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትገባ ታላቂቱ ከተማ ናት።”
\s5
\c 18
\cl ምዕራፍ 17
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። ታላቅ ሥልጣንም ነበረው፤ ምድርም በክብሩ አበራች።
\v 2 በታላቅ ድምፅም ጮኾ እንደኢህ አለ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ ማደሪያ፣ የማንኛውም ርኩስና ጠያፍ ወፍ መጠጊያ ሆነች
\v 3 ሕዝቦች ሁሉ ቁጣ በሚያመጣበት የዝሙቷ ወይን ጠጅ ሰክረዋል። የምድር ነገሥታት ከእርሷ ጋር አመንዝረዋል። የምድር ነጋዴዎች በምቾት ኑሮዋ በልጽገዋል።”
\s5
\v 4 ሌላ ድምጽም ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ፣ በኃጢአትዋ እንዳትካፈሉ የማመጣበትንም መቅሠፍት እንዳትቀበሉ ከእርሷ ውጡ።
\v 5 ኃጢአቷ እስከ ሰማይ ተከምሯል እግዚአብሔር ክፉ ሥራዋን አስታውሷል።
\v 6 በሰጠችው መጠን ስጧት፤ ባደረገችው መጠን ዕጥፍ አድርጉባት እርሷ በቀካቀከችው ጽዋ መጠን፣ ዕጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት።
\s5
\v 7 እርሷ ራስዋን እንዳከበረችውና በምቾት በኖረችው መጠን፣ የዚያኑ ያህል ስቃይና ሐዘን ስጧት እርሷ በልቧ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጫለሁ መበለትም አይደለሁም ሀዘንም አይደርስብኝም’ ብላለች።
\v 8 ስለዚህ፣ መቅሠፍቶችዋ በእብንድ ቀን ይደርሱባታል፣ ሞት፣ ሐዘንና ረሐብ ይመጡባታል። በእሳት ትቃጠላለች፤ እርሷ ላይ የሚፈርድ ጌታ እግዚአብሔር ብርቱ ነው”
\s5
\v 9 ከእርሷ ጋር ያመነዘሩና ቅጥ ያጣ ሕይወት የኖሩ፣ የቃጠሎዋ ጭስ ሲወጣ ሲያዩ ስለ እርሷ እየጮኹ ያለቅሳሉ።
\v 10 ሥቃይዋንም በመፍራት በሩቅ ቆመው፣ “ታላቂቱ ከተማ፣ አንቺ ብርቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ውስጥ ቅጣትሽ መጥቷልና ወዮልሽ ወዮልሽ” ይላሉ።
\s5
\v 11 ከእንግዲህ ሸቀጧን የሚገዛ ስለማይኖር የምድር ነጋዴዎች ለእርሷ ያለቅሳሉ፤ ያዝኑላታል፤
\v 12 ሸቀጦችዋ ወርቅ፣ ብር፣ የከበረ ድንጋይ፣ ዕንቁ፣ ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊ ጨርቅ፣ ሐር ጨርቅ፣ ቀይ ጨርቅ፣ ማንኛውም ዓይነት ጣፋጭ ሽታ ያለው እንጨት፣ ማንኛውም ከዝሆን ጥርስ የተሠራ ዕቃ፣ ማንኛውም ከከበረ ድንጋይ የተሠራ ዕቃ፣ ነሐስ፣ ብረት፣ እብነ በረድ
\v 13 ቀረፋ፣ ቅመም፣ የሚሸር እንጨት፣ ከርቤ፣ ዕጣን፣ ወይን ጠጅ፣ ዘይት፣ንጹሕ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ከብቶች፣ በጎች፣ ፈረሶችና ሰረገሎች ባሪያዎችና የሰዎች ነፍሶች ናቸው።
\s5
\v 14 አጥብቀሽ የተመኘሻቸው ነገሮች ከአንቺ አምልጠዋል። ምቾትና ውበትሽ ጠፍተዋል ከእንግዲህም አይገኙም።
\s5
\v 15 በእርሷ የበለጸጉ እነዚህን ዕቃዎች የሚነግዱ ሰዎች ሥቃይዋን በመፍራት ከእርሷ ርቀው በመቆም በታላቅ ድምፅ ያለቅሳሉ
\v 16 እንዲህም ይላሉ “ቀጭን ልብስ፣ ሐምራዊና ቀይ ልብስ ትለብስ ለነበች፤ በመርቅ፣ በከበረ ድንጋይና በዕንቁ ታጌጥ ለነበረች ታላቂቱ ከተማ ወዮ ወዮ!”
\v 17 በእብንድ ሰዓት ያ ሀብት ሁሉ ጠፍቷል። የመርከብ አዛዦች ሁሉ፣ በመርከብ የሚጓዙ ሰዎች ሁሉ፣ መርከበኞችና በባሕር ላይ የሚሠሩ ሁሉ ርቀው ቆሙ።
\s5
\v 18 ያቀጠሎዋን ጭስ ሲመለከቱ፣ “ ታላቂቱን ከተማ የሚመስላት ማነው?” እያሉ ጮኹ።
\v 19 በራሳቸውም ላይ ዐመጽ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ፣ መርከቦች ያሏቸውና በእርሷ ሀብት የበለጸጉ ሁሉ ታላቂቱ ከተማ በአንድ ሰዓት ስለ ወደመች ወዮላት ወዮላት” አሉ።
\v 20 “ ሰማይ ሆይ ደስ ይበልህ፤ እግዚአብሔር ስለ እናንተ እርሷ ላይ ፈርዷልና እናንት ቅዱሳን፣ ሐዋርያትና ነቢያት ደስ ይበላችሁ!”
\s5
\v 21 ከዚያም አንድ ብርቱ መልአክ ታላቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስልን ድንጋይ እንዲህ በማለት ወደ ባሕር ወረወሬ፣ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን በዚህ ሁኔታ በኅይል ተገፍታ ወደ ባሕር ትጣላለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ ጨርሶ አትታይም
\v 22 የበገና ደርዳሪዎች፣ የሙዚቀኞች፣ የዋሽንትና መለኮት ነፊዎች ድምፅ ከእንዲህ በአንቺ አይሰማም። ማንኛውንም ዓይነት የጥበብ ሥራ የሚሠራ በአንቺ አይገኝም። የወፍጮ ድምፅም በአንቺ አይሰማም።
\s5
\v 23 የመብራት ብርሃን፣ ከእንግዲህ በአንቺ አያበራም። የሙሽራውና የሙሽራይቱ ድምፅ ከእንግዲህ በአንቺ አይሰማም። ነጋዴዎችሽ የምድር ልዑላን ነበሩ ሕዝቦችን በመተትሽ አሳስተሻል።
\v 24 የነቢያትና የቅዱሳን ደም፣ በዚህ ምድር የተገደሉ ሰዎች ሁሉ ደም በእርሷ ተገኝቷል።
\s5
\c 19
\cl ምዕራፍ 19
\p
\v 1 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ የበዙ ሰዎች ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ከሰማይ ሰማሁ “ሃሌ ሉያ ማዳን፣ ክብርና ኃይል የአምላካችን ነው።
\v 2 በዝሙቷ ምድርን ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ ስለ ፈረደባት ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው። እርሷ ያፈሰሰችውን የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።
\s5
\v 3 በድጋሚ “ሃሌ ሉያ፤ ጢስዋ ከዘላለም እስከ ዘላለም ከእርሷ ይወጣል” በማለት ተናገሩ።
\v 4 ሃያ አራቱ ሽማግሌዎችና አራቱ ሕያዋን ፍጡራን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “አሜን ሃሌ ሉያ!” በማለት ዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው ሰገዱ።
\s5
\v 5 ከዚያ በኋላ፣ “ታናናሾችም ታላላቆችም እርሱን የምትፈሩ አገልጋዮቹ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ!” የሚል ድምፅ ከዙፋኑ ወጣ።
\s5
\v 6 ከዚያም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፣ እንደ ብዙ ውሆች ድምፅና የብርቱ ነጎድጓድ የሚመስል ድምፅ እንዲህ አለ፤
\s5
\v 7 ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ፤ የበጉ ሰርግ ስለ ደረሰ ሙሽራዋም ራስዋን ስላዘጋጀች፤ ደስ ይበለን፤ ሐሤት እናድርግ ፤ ክብርንም እንስጠው።”
\v 8 ደማቅና ቀጭን ንጹሕ ልብስ እንድትለብስ ገሰጣት። ቀጭኑ ልብስ የቅዱሳኑ የጽድቅ ሥራ ነው።
\s5
\v 9 መልአኩም፣ “ወደ በጉ ሰርግ እንደመጡ የተጋበዙ ሰዎች የተባረኩ ናቸው ብለህ ጻፍ” አለኝ። በተጨማሪም፣ “እነዚህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ቃሎች ናቸው” አለኝ።
\v 10 እኔም ልሰግድለት በእግሩ ሥር ተደፋሁ፤ እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከአንተና ስለ ኢየሱስ የተሰጠውን ምስክር ከያዙ ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ። ልችእግዚአብሔር ስገድ፤ ስለ ኢየሱስ የተሰጠው ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና” አልኝ።
\s5
\v 11 ከዚያም ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም አንድ ነጭ ፈረስ ተመለከትኩ ፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ ይባላል። በጽድቅ ይፈርዳል፤ ይዋጋል።
\v 12 ዐይኖቹ እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ ራሱም ላይ ብዙ አክሊሎች ነበሩ። ከእርሱ በቀር ማንም የማያውቀው ስም እርሱ ላይ ተጽፎ ነበር።
\v 13 ደም የተነከረ ልብስ ለብሶ ነበር፤ ስሙ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ ይጠራል።
\s5
\v 14 ቀጭን፣ ነጭና ንጹሕ ልብስ የለበሱ ሠራዊት በነጫጭ ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።
\v 15 ከአፉም ሕዝቦችን የሚመታበት የተሳለ ሰይፍ ይወጣ ነበር፤ በብረት በትር ይገዛቸዋል። ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን ቁጣ የወይን ጠጅ መጭመቂያ ይረግጣል።
\v 16 ልብሱና ጭኑ ላይ፣ የነገሥታት ንጉሥ፣ የጌቶችም ጌታ የሚል ስም ተጽፎበት ነበር።
\s5
\v 17 አንድ መልአክ ፀሐይ ላይ ቆሞ አየሁ። እርሱም በታላቅ ድምፅ፣ “ኑ፣ ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር ግብዣ ተሰብሰቡ።
\v 18 መጥታችሁ የነገሥታትን፣ የጦር አዛዦችን፣ ሥጋ የኅያላንን ሥጋ፣ የፈረሰኞችንና በላያቸው የተቀመጡትን ሥጋ፣ የጌቶችን የባሮችን፣ የታናናሾችንና የታላላቆችን ሥጋ፣ የሰዎችን ሁሉ ሥጋ ብሉ።”
\s5
\v 19 አውሬውንና ከእርሱም ጋር የምድር ነገሥታትንና ሰራዊታቸውን አየሁ። ፈረሱ ላይ ተቀምጦ ከነበረውና ከሰራዊቱ ጋር ውጊያ ለመግጠም ተዘጋጅተው ነበር።
\v 20 እነሆ አውሬው ተያዘ፤ ከእነርሱም ጋር በእርሱ ፊት ምልክቶችን የሚያደርገው ሐሰተኛ ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች አማካይነት የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳሳተ። ሁለቱም በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር በሕይወት እያሉ ተጣሉ።
\s5
\v 21 የተቀሩትም ፈረስ ላይ ከተቀመጠው አፍ በሚወጣው ሰይፍ ተገደሉ። ወፎችም ሁሉ ሥጋቸውን በልተው ጠገቡ።
\s5
\c 20
\cl ምዕራፍ 20
\p
\v 1 ከዚህ በኃላ የጥልቁ መክፈቻ ያለው አንድ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በእጁም ትልቅ ሰንሰለት ይዞ ነበር።
\v 2 ዘንዶውን ይዞ ሺህ ዓመት አሰረው፤ ይህ ዘንዶ ዶያብሎስ ሰይጣን የተባለው የቀድሞው እባብ ነው።
\v 3 ወደ ጥልቁ ጣለው፤ ዘግቶም በእርሱ ላይ ማኅተም አደረገበት። ይህን ያደረገው ሺህ ዓመቱ እስኮፈጸም ድረስ ከእንግዚህ ሕዝቦችን እንዳያሳስት ነው። ከዚያ በኋላ ለአጭር ጊዜ መፈታት ይኖርበታል።
\s5
\v 4 ከዚያም ዙፋኖች አየሁ። ዙፋኖቹም ላይ የመፍረድ ሥልጣን የተሰጣቸው ተቀምጠው ነበር። ለኢየሱስና ለእግዚአብሔር ቃል ምስክር የተሰየፉ ሰዎችን ነፍሶችንም አየሁ። ለአውሬው ወይም ለምስሉ አልሰገዱም፤ ምልክቱም ግንባራቸው ወይም እጃቸው ላይ እንዲያረግ አልፈቀዱም። ከሞት ተነሥተው፣ ለሺህ ዓመት ከክርስቶስ ጋር ነገሡ።
\s5
\v 5 የተቀሩት ሙታን ግን ሺሁ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ከሞት አልተነሡም። ይህ የመጀመሪያው ትንሣኤ ነው።
\v 6 በመጀመሪያው ትንሣኤ ድርሻ የሚኖራቸው ሁሉ የተባረኩና የተቀደሱ ናቸው! እነዚህን በመሳሰሉት ላይ ሁለተኛው ሞት ኅይል አይኖረውም። የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ሺህ ዓመት ይነግሣሉ።
\s5
\v 7 ሽው ዓመት ካበቃ በኃላ ሰይጣን ከእስራት ይፈታል።
\v 8 በአራቱ የምድር ማእዘን ያሉ ሕዝቦች ማለትም ጎግና ማጎግን ወደ ጦርነት ለማምጣት እያሳተ ወደ ጦርነት ለማምጣት ይወጣል ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ ያህል እጅግ ብዙ ነው።
\s5
\v 9 እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ ሄደው የቅዱሳንን ሰፈር፣ እንዲሁም የተወደደችውን ከተማን ከበቡ። ሆኖም፣ እሳት ከሰማይ ወርዶ በላቸው።
\v 10 እነርሱን ያሳሳተው ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወደ ተጣለበት በዲን ወደሚነደው የእሳት ባሕር ተጣሉ። ቀንና ሌሊት ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሰቃያሉ።
\s5
\v 11 ከዚያም አንድ ታላቅ ነጭ ዙፋንና በላዩ የተቀመጠውን አየሁ። ምድርና ሰማይ ከፊቱ ሸሹ፣ ሆኖም፣ መሄጃ ቦታ አልነበራቸውም።
\v 12 በዙፋኑ ፊት መታን፣ ታላላቆችና ታናናሾች ቆመው አየሁ፤ መጽሕፍትም ተከፈቱ። ከዚያም የሕይወት መጽሐፍ የተባለ ሌላም መጽሐፍ ተከፈተ። መታንም መጻሕፍቱም ውስጥ በተመዘገበው መሠረት እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው
\s5
\v 13 ባሕር ውስጡ ያሉ ሙታንን ሰጡ። ሞትና ሲኦል ውስጣቸው ያሉትን ሙታን ስጡ፤ ሙታንም እንደ ሥራቸው ተፈረደባቸው።
\v 14 ሞትና ሲኦል ወደ እሳቱ ባሕር ተጣሉ። የእሳቱም ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።
\v 15 ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳቱ ባሕር ተጣለ።
\s5
\c 21
\cl ምዕራፍ 21
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ ምክንያቱም የመጀመሪያው ሰማይና የመጀመሪያው ምድር አልፈው ነበር፤ ባሕርም ከእንግዲህ አልተገኘም።
\v 2 ቅድስቲቱ ከተማ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ለባልዋ እንዳጌጠች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አየሁ።
\s5
\v 3 ከዙፋኑም እንዲህ የሚል ታላዝ ድምፅ ሰማሁ፣ “እነሆ የእግዚአብሔር መኖሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱ ጋር ይኖራል። እነርሱ ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ራሱም ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል።
\v 4 እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ሞት፣ ወይም ሐዘን፣ ወይም ለቅሶ ወይም ሕመም አይኖርም። ምክንያቱም የቀድሞ ነገሮች አልፈዋል።
\s5
\v 5 በዙፋኑ የተቀመጠው፣ “እነሆ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ” አለ። “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛ ስለሆኑ ጻፍ” አለ።
\v 6 ለእኔም እንዲህ አለኝ፤”እነዚህ ሁሉ ተፈጽመዋል እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም ነኝ። ለተጠማ ሰው ከሕይወት ውሃ ምንጭ እንዲጠጣ ያለ ዋጋ እሰጣለሁ።
\s5
\v 7 ድል የነሣ እነዚህን ነገሮች ይወርሳል፤ አምላኩ እሆናለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል።
\v 8 ነገር ግን የፈሪዎች፣ የእምነተ ቢሶች፣ የርኩሶች፣ የነፍስ ገዳዮች፣ የአመንዝራዎች፣ የሟርተኞች፣ የጦዖት አምላኪዎችና የሐሰተኞኦች ቦታቸው በዲን በሚቃጠለው እሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።
\s5
\v 9 የመጨረሻዎቹ ሰባት መቅሠፍቶች የሞሉበትን ሰባት ድዋዎች ከያዙት ሰባት መላእክት አንዱ ወደ እኔ መጥቶ፣ “ወደዚህ ና፣ የበጉን ሚስት ሙሽራዋን አሳይሃለሁ” አለኝ።
\v 10 ከዚያም ወደ አንድ ታላቅና ከፍ ወዳለ ተራራ በመንፈስ ወሰደኝና ቅዱሳቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስትወርድ አሳየኝ።
\s5
\v 11 ኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ክብር ነበራት፤ የብርሃንዋ ፀዳል እጅግ እንደከበረ ድንጋይ፣ እንደ አያሰጲድ ድንጋይ ጥርት ያለ ነበር።
\v 12 አሥራ ሁለት በሮች ያሉት በጣም ታላቅ ረጅም ግምብ ነበራት በየበሮቹ አሥራ ሁለት መላእክት ነበሩ። በእነርሱም ላይ የአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ተጽፈው ነበር።
\v 13 በምሥራቅ ሦስት በሮች፣ በሰሜን ሦስት በሮች፣ በደቡብ ሦስት በሮች፣ በምዕራብ ሦስት በሮች ነበሩ።
\s5
\v 14 የከተማዋ ግምብ አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩት፤ በእነርሱም ላይ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።
\v 15 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክ ከተማዋን፣ በሮቹንና ቅጥሮቹን የሚለካበት የወርቅ ዘንግ ነበረው።
\s5
\v 16 ከተማዋ አራት ማእዘን ነበረች፤ ርዝመትና ስፋቱ ዕኩል ነበር። በመለኪያ ዘንጉ ሲለካ ርዝመቱ 12,000 ምዕራፍ ሆነ (ርዝመቱ፣ ስፋቱና ከፍታዋ ዕኩል ነበር)።
\v 17 ቅጥሯን ስለካ ስፋቱ በሰው መለኪያ (ይህም የመላእክት መለኪያም ነው) 144 ክንድ ሆነ
\s5
\v 18 ቅጥሩ ከኢያሰጲድ፣ ከተማዋም እንደ መስተዋት በጠራ ንጹሕ ወርቅ የተሠራች ነበረች።
\v 19 የቅጥሩ መሠረቶች በከበሩ ድንጋዮች ያጌጡ ነበር። የመጀመሪያው ኢያሰጲድ፣ ሁለተኛው ሶንፔር፣ ሦስተኛው ኬልቄዶን፣ አራተኛው መረግድ
\v 20 አምስተኛው ሰርደንክስ፣ ስድስተኛው ሰርድዮን፣ ሰባተኛው ክርስቲሎቤ፣ ስምንተኛው ቢረሌ፣ ዘጠነኛው ወራውሬ፣ አሥረኛው ክርስጵራስስ፣ አሥራ አንደኛው ያክንት፣ አሥራ ሁለተኛው አሜቴስ ቲኖስ ነበረ።
\s5
\v 21 አሥራ ሁለቱም በሮች፣ አሥራ ሁለት ዕንቁዎች ነበሩ፤ እያንዳንዱ በር ከአንድ ዕንቁ የተሠራ ነበር። የየከተማዋ መንገዶች ጥርት እንዳለ መስተዋት ንጽሕ ወርቅ ነበሩ።
\v 22 በከተማዋ ምንም መቅደስ አላየሁም፤ ምክንያቱም ሁሉን የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደሷ ነበሩ።
\s5
\v 23 የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራለት ከተማዋ የፀሐይ ወይም የጨረቃ ብርሃን አልነበራትም፤ ምክንያቱም በጉ ራሱ ብርሃንዋ ነው።
\v 24 ሕዝቦችም በዚያች ከተማ ብርሃን ይመላለሳሉ። የምድር ነገሥታት ክብራቸውን ወደ እርሷ ያመጣሉ።
\v 25 በሮቿ በቀን አይዘጉም፤ በዚያ ሌሊት የለም።
\s5
\v 26 የመንግሥታትን ግርማና ክብር ወደ እርሷ ያመጣሉ
\v 27 ርኩስ ነገር በፍጹም አይገባባትም። ጸያፍ ወይም አታላይ ወደዚያ አይገባም፤ ወደዚያ የሚገቡት ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፈ ብቻ ናቸው።
\s5
\c 22
\cl ምዕራፍ 22
\p
\v 1 ከዚያም መልአኩ፣ እንደ መስተዋት የጠራውን የሆነውን የሕይወት ውሃ ወንዝ አሳየኝ። ወንዙም የሚወጣው ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን ነበር
\v 2 በከተማዋ ዋና መንገድ መካከል ያልፍ ነበር። በወንዙ ግራና ቀኝ አሥራ ሁለት ወር ሙሉ አሥራ ሁለት ዓይነት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበር። የዛፉ ቅጠሎች ሕዝቦችን ሁሉ ይፈውሱ ነበር።
\s5
\v 3 ከእንግዲህ ምንም ዐይነት መርገም አይሆንም። የእግዚአብሔርና የበጉ ዚፋን ከተማው ውስጥ ይሆናሉ፤ አገልጋዮቹም ያገለግሉታል።
\v 4 ፊቱን ያያሉ፤ ስሙም ግንባሮቻቸው ላይ ይሆናል።
\v 5 ከእንግዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክ ስለሚያበራላቸው የመብራት ወይም የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም። ከዘላለም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።
\s5
\v 6 መልአኩም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛ ናቸው። ጌታ፣ የነቢያት መናፍቅ አምላክ ቶሎ መሆን ያለበትን ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው መልአኩን ላከ።”
\v 7 “እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ! ለዚህ መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች የሚታአእ የተባረከ ነው።
\s5
\v 8 እነዚህን ነገሮች የሰማሁና ያየሁ እኔ ዮሐንስ ነኝ። እነዚህን በሰማሁና ባይብሁ ጊዜ እነዚህን ነገሮች ላሳየኝ መልአክ ለመስገድ በፊቱ ተደፋሁ።
\v 9 እርሱ ግን፣ “እንዳታደርገው! እኔ ራሴ ከወንድሞችህ ከነቢያት ጋር፣ ለዚህ መጽሐፍ ቃል ከሚታዘዙት ጋር አብሬ አገልጋይ ነኝ። ይልቅ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ!”
\s5
\v 10 እንዲህም አለኝ፤ ጊዜው በጣም ቅርብ ስለሆነ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃሎች በማኅተም አትዝጋው።
\v 11 ዐመፀኛው ማመፁን ይቀጥል። ርኩሱም ርኩሰት ማድረጉን ይቀጥል። ጻድቁም ጽድቅ የሆነውን ማድረጉን ይቀጥል። ቅዱስም ቅዱስ መሆን ይቀጥል።
\s5
\v 12 “እነሆ፣ ቶሎ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው የምከፍለው ዋጋ ከእኔ ዘንድ አለ።
\v 13 እኔ አልፋና ዖሜጋ፣ ፊተኛውና ኋለኛው፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው ነኝ።
\s5
\v 14 ከሕይወት ዛፍ ለመብላትና በበሮቿ ወደ ከተማዋ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን የሚያጥቡ የተባረኩ ናቸው።
\v 15 ውሾች፣ ጠንቋዮች፣ አመንዝራዎች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎችና ሐሰትን የሚወዱና የሚያደርጉ ግን በውጭ አሉ።
\s5
\v 16 እኔ ኢየሱስ ለእናንተ እንዲመሰክር መልአኬን ወደ አብያተ ክርስቲያናት ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርጥ ዘር ነኝ፤ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”
\s5
\v 17 መንፈሱና ሙሽራይቱ፣ “ና!” ይላሉ፤ የሚሰማ ሁሉ፣ “ና!” ይበል። ማንም የተጠማ ቢኖር ይምጣ፣ የሚፈልግ የሕይወትን ውሃ በነጻ ይውሰድ።
\s5
\v 18 የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ለሚሰሙ ሁሉ እኔ እመሰክራለሁ፣ ማንም ትንቢቱ ላይ ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን መቅሠፍቶች ይጨምርበታል።
\v 19 ማንም ከዚህ መጽሐፍ ትንቢት ቢያጎድል እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ ከተጻፈው የሕይወት ዛፍና ቅድስት ከተማ ዕድሉን ያጎልበታል።
\s5
\v 20 ለእነዚህ ነገሮች የሚመሰክር እርሱ፣”አዎን! ቶሎ እመጣለሁ” አሜን! ጌታ ኢየሱስ ሆይ ና! ይላል።
\v 21 የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን

View File

@ -1,3 +1,6 @@
# Amharic ULB
STR https://git.door43.org/unfoldingWord/SourceTextRequestForm/issues/206 for OT.
STRs:
* https://git.door43.org/unfoldingWord/SourceTextRequestForm/issues/206 for OT
* https://git.door43.org/unfoldingWord/SourceTextRequestForm/issues/422 for NT

View File

@ -3,31 +3,48 @@ dublin_core:
contributor:
- "Abera Wolde"
- "Andarge Arega"
- "Barnabas"
- "Burje Duro"
- "Dagmawi Wube"
- "Daniel"
- "Dereje"
- "Deresse"
- "Ermias Gezahegn"
- "Feben Alemayehu"
- "Fekadu"
- "Fikerte"
- "Fitehamlak"
- "Getachew Wolde Amanuel"
- "Getachew Yohannes"
- "girso"
- "Girum"
- "Kaleab Getachew"
- "LD"
- "Mene"
- "Mesfin Tesfaye"
- "Minas"
- "Negassa"
- "Pr. Ashebir"
- "Rev. Endale Awgichew"
- "Tekalign Shiferaw Demissie"
- "Tensae Amdeyesus"
- "Tersit Zewde"
- "Tizita M"
- "Tizita Zenebe"
- "Worku"
- "Zekarias"
- "Zelalem Assefa"
- "ዘላለም ቸርነት"
creator: 'Door43 World Missions Community'
description: 'An unrestricted literal Bible'
format: 'text/usfm'
identifier: 'ulb'
issued: '2020-12-18'
issued: '2020-12-27'
language:
identifier: 'am'
title: 'Amharic'
direction: 'ltr'
modified: '2020-12-18'
modified: '2020-12-27'
publisher: 'Door43'
relation:
- 'am/obs'
@ -46,7 +63,7 @@ dublin_core:
subject: 'Bible'
title: 'Unlocked Literal Bible'
type: 'bundle'
version: '7.1'
version: '7.2'
checking:
checking_entity:
@ -331,3 +348,192 @@ projects:
sort: 39
path: './39-MAL.usfm'
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'የማቴዎስ'
versification: ufw
identifier: 'mat'
sort: 40
path: './41-MAT.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ማርቆስ'
versification: ufw
identifier: 'mrk'
sort: 41
path: './42-MRK.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ሉቃስ'
versification: ufw
identifier: 'luk'
sort: 42
path: './43-LUK.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ዮሐንስ'
versification: ufw
identifier: 'jhn'
sort: 43
path: './44-JHN.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'የሐዋርያት ሥራ'
versification: ufw
identifier: 'act'
sort: 44
path: './45-ACT.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ሮሜ'
versification: ufw
identifier: 'rom'
sort: 45
path: './46-ROM.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '1ኛ ቆሮንቶስ'
versification: ufw
identifier: '1co'
sort: 46
path: './47-1CO.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '2ኛ ቆሮንቶስ'
versification: ufw
identifier: '2co'
sort: 47
path: './48-2CO.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ገላቲያ'
versification: ufw
identifier: 'gal'
sort: 48
path: './49-GAL.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ኤፌሶን'
versification: ufw
identifier: 'eph'
sort: 49
path: './50-EPH.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ፊልጵስዩስ'
versification: ufw
identifier: 'php'
sort: 50
path: './51-PHP.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ቆላስይስ'
versification: ufw
identifier: 'col'
sort: 51
path: './52-COL.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '1 ተሰሎንቄ'
versification: ufw
identifier: '1th'
sort: 52
path: './53-1TH.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '2ኛ ተሰሎንቄ'
versification: ufw
identifier: '2th'
sort: 53
path: './54-2TH.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '1 ጢሞቴዎስ'
versification: ufw
identifier: '1ti'
sort: 54
path: './55-1TI.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '2 ጢሞቴዎስ'
versification: ufw
identifier: '2ti'
sort: 55
path: './56-2TI.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ቲቶ'
versification: ufw
identifier: 'tit'
sort: 56
path: './57-TIT.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ፊልሞና'
versification: ufw
identifier: 'phm'
sort: 57
path: './58-PHM.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ዕብራዊያን'
versification: ufw
identifier: 'heb'
sort: 58
path: './59-HEB.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ያዕቆብ'
versification: ufw
identifier: 'jas'
sort: 59
path: './60-JAS.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '1ኛ ጴጥሮስ'
versification: ufw
identifier: '1pe'
sort: 60
path: './61-1PE.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '2ኛ ጴጥሮስ'
versification: ufw
identifier: '2pe'
sort: 61
path: './62-2PE.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '1ኛ ዬሐንስ'
versification: ufw
identifier: '1jn'
sort: 62
path: './63-1JN.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '2ኛ ዮሐንስ'
versification: ufw
identifier: '2jn'
sort: 63
path: './64-2JN.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: '3ኛ ዮሐንስ'
versification: ufw
identifier: '3jn'
sort: 64
path: './65-3JN.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'ይሁዳ'
versification: ufw
identifier: 'jud'
sort: 65
path: './66-JUD.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]
-
title: 'የዮሐንስ ራእይ'
versification: ufw
identifier: 'rev'
sort: 66
path: './67-REV.usfm'
categories: [ 'bible-nt' ]