added Zechariah
This commit is contained in:
parent
231da4d3b4
commit
55adee605c
|
@ -0,0 +1,434 @@
|
|||
\id ZEC
|
||||
\ide UTF-8
|
||||
\h ዘካርያስ
|
||||
\toc1 ዘካርያስ
|
||||
\toc2 ዘካርያስ
|
||||
\toc3 zec
|
||||
\mt ዘካርያስ
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 1
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ እንዲህ የሚል የያህዌ ቃል መጣ፤
|
||||
\v 2 “ያህዌ በአባቶቻችሁ እጅግ ተቆጥቶ ነበር!
|
||||
\v 3 ለሕዝቡ ተናገር፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ወደ እኔ ተመለሱ! ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 “የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ “ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ! ” በማለት በቀድሞ ዘመን ነቢያት እንደ ሰበኩላቸው አባቶቻችሁ አትሁኑ። እነርሱ ግን አልሰሙም፤ እኔንም አላደመጡም ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
\v 5 ለመሆኑ፣ አባቶቻችሁ ወዴት አሉ? ነቢያትስ ለዘላለም በሕይወት ይኖራሉን?
|
||||
\v 6 ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? እነርሱም ንስሐ በመግባት እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ ያህዌ በወሰነው መሠረት ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 7 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ሳባጥ በመባለው በአሥራ አንደኛው ወር በሃያ አራተኛው ቀን ያይህዌ ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ዘካርያስ መጣ።
|
||||
\v 8 እነሆም በሌሊት ራእይ አየሁ፤ አንድ ሰው ቀይ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ነበር፤ እርሱም በሸለቆው ውስጥ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፤ ከበስተ ኋላውም ቀይ፣ ቀይ ቡናማና ነጭ ፈረሶች ቆመው ነበር።
|
||||
\v 9 እኔም፣ “ጌታ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው? ” አልሁ። ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክም፣ “እነዚህ፣ ምን እንደ ሆኑ፣ አሳይሃለሁ” አለኝ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 10 ዛፎች መካከል ቆሞየነበረውም ሰው “እነዚህ በምድር ሁሉእንዲመላለሱ ያህዌ የላካቸው ናቸው”በማለት መለሰ።
|
||||
\v 11 ከዚያም፣ በባርሰነትዛፎች መካከል ቆሞ ለነበረው የያህዌመልአክ፣ “በምድር ሁሉ ተመላለስን፤እነሆ መላዋ ምድር አርፋ ተቀምጣለች”አሉት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 12 ያኔ የያህዌ መልአክ መልሶ፣ “የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በእነዚህ ሰባ ዓመቶች ውስጥ የተቆጣሃቸውን ኢየሩሳላምንና የይሁዳን ከተሞች የማትራራላቸው እስከ መቼ ነው? ” አለ።
|
||||
\v 13 ያህዌም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ ለነበረው መልአክ ደስ በሚያሰኝ የሚያጽናና ቃል መለሰለት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 14 ስለዚህ፣ ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፤ “እንዲህ ብለህ ተናገር፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ ለኢየሩሳሌምና ለጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ!
|
||||
\v 15 ተደላድለውና ተመቻችተው በተቀመጡ ሕዝቦች ላይ በጣም ተቆጥቻለሁ። እኔ የተቆጣሁት በመጠኑ ቢሆንም፣ እነርሱ ግን ጥፋት እንዲባባስ አድርገዋል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 16 ስለዚህ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ በምሕረቴ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሻለሁ። በውስጧ ቤቴ እንደ ገና ይሠራል፤ መለኪያ ገመድም በኢየሩሳሌም ላይ ይዘረጋል! ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
\v 17 ደግሞም፣ እንዲህ በማለት ተናገር፣ ‘የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ከተሞቼ እንደ ገና በመልካም ነገሮች ይሞላሉ፤ ያህዌ እንደ ገና ጽዮንን ያጽናናል፤ እንደ ገና ኢየሩሳሌምን ይመርጣታል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 18 ከዚያ ዐይኖቼን ወደ ላይ አንሥቼ አራት ቀንዶች ተመለከትሁ!
|
||||
\v 19 ከእኔ ጋር እየተነጋገረ ለነበረውም መልአክ፣ “እነዚህ ምንድን ናቸው? ” አልሁት። እርሱም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ ቀንዶች ናቸው” አለኝ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 20 ከዚያም ያህዌ አራት የእጅ ባለ ሙያዎች አሳየኝ።
|
||||
\v 21 እኔም፣ “እነዚህ ይሁዳን፣ እስራኤልንና ኢየሩሳሌምን የበተኑ አራት ቀንዶች ናቸው፤ እነዚህ ሰዎች የመጡት ግን እነርሱን ለማስወጣትና ሕዝቡን ለመበታተን በይሁዳ ምድር ላይ ቀንዳቸውን ያነሡትን ሕዝቦች ቀንዶች ሰባብሮ ለመጣል ነው” በማለት መለሰልኝ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 2
|
||||
\p
|
||||
\v 1 እንደ ገና ዐይኖቼን ወደ ላይ አንሥቼ በእጁ መለኪያገመድ የያዘ ሰው አየሁ።
|
||||
\v 2 እኔም፣ “የት ልትሄድ ነው? ” አልሁት። እርሱም መልሶ፣ “የኢየሩሳሌም ስፋትና ርዝመት ምን ያህል እንደ ሆነ ለመለካት ነው” አለኝ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 3 ከዚያም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክ ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ።
|
||||
\v 4 ሁለተኛው መልአክ፣ ሩጥና ለዚያ ወጣት እንዲህ ብለህ ንገረው፣ ‘በውስጧ ካለው ሕዝብና እንስሶች ባት የተነሣ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች።
|
||||
\v 5 ምክንያቱም እኔ ራሴ፣ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር በመካከልዋም ክብር እሆናለሁ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 6 ኑ! ኑ! ከሰሜን ምድር አምልጡ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሶች በትኛችኋለሁ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
\v 7 እናንት ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሩ፣ ወደ ጽዮን አምልጡ!”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 8 የሰራዊት ጌታ ያህዌ ካከበረኝና በዘረፉአችሁ ሕዝቦች ላይ ከላከኝ በኋላ፣ እናንተን የሚነካ የእግዚአብሔርን ዐይን ይነካል! ያህዌ ይህን ካደረገ በኋላ፣
|
||||
\v 9 “እኔ ራሴ እጄን በእነርሱ ላይ አንሣለሁ፤ ባርያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል” ያኔ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 10 እኔ ራሴ መጥቼ በመካከልሽ እኖራለሁና የጽዮን ልጅ ሆይ በደስታ ዘምሪ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
\v 11 ከዚያም ቀን ብዙ ሕዝቦች ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ፤ በመካከልሽ እኖራለሁ” እናንተም ወደ እናንተ የላከኝ ያህዌ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 12 ያህዌም በተቀደሰች ምድር ይሁዳን ርስቱ ያደርገዋል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደ ገና ለራሱ ይመርጣታል።
|
||||
\v 13 ከተቀደሰ ማደሪያው ተነሥቷልና፤ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በያህዌ ፊት ጸጥ በል!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 3
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ከዚያም ሊቀ ካሁኑ ኢያሱ በያህዌ መልአክ ፊት ቆሞ ያህዌ አሳየኝ፤ እርሱን በኃጢአት ልመክሰሰ ሰይጣን በቀኙ በኩል ቆሞ ነበር።
|
||||
\v 2 የያህዌ መልአክ ሰይጣንን፣ “አንተ ሰይጣን ያህዌ ይገሥጽህ፣ ኢየሩሳሌምን የመረጠ ያህዌ ይገሥጽህ! ይህ ሰው ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይድለምን? ” አለው።
|
||||
\v 3 መልአኩ ፊት ቆሞ በነበረ ጊዜ ኢያሱ ያደፉ ልብሶች ለብሶ ነበር።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 ስለዚህ መልአኩ በፊቱ ቆመው የነበሩትን፣ “ያደፉ ልብሶቹን አውልቁለት” አላቸው። ከዚያም ኢያሱን፣ “እነሆ፣ ርኩሰትህን ከአንተ አስወግጃለሁ፤ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው።
|
||||
\v 5 መልአኩም፣ “ራሱ ላይ ንጹሕ መጠምጠሚያ ያድርጉለት! አለ። እነርሱም የያህዌ መልአክ አጠገቡ ቆሞ እያለ በኢያሱ ራስ ላይ ንጹሕ መጠምጠሚያ አደረጉለት፤ ንጹሕ ልብስም አለበሱት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 6 በመቀጠል የያህዌ መልአክ ለኢያሱ ይህን ማስጠንቀቂያ ሰጠው፤
|
||||
\v 7 “የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ያኔ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ በእነዚህ በፊቴ በቆሙት መካከል እንድትገባና እንድትወጣ አደርግሃለሁ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 8 ሊቀ ካሁኑ ኢያሱ ሆይ ስማ፤ ከአንተ ጋር ያሉት ጓደኞችህም ፊት ለሚመጡት ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፤ እነሆ፣ ባርያዬን ቁጥቋጡን አመጣለሁ።
|
||||
\v 9 ኢያሱ ፊት ያኖሩትን ድንጋይ ተመልከቱ። በዚያ አንድ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖች አሉ፤ በእርሱም ላይ ቅርጽ እቀርጻለሁ፤ የዚህችንም ምድር ኀጢአት በአንድ ቀን አስወግዳለሁ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 10 በዚያን ቀን እያንዳንዱ ሰው በገዛ ወይኑና በለስ ዛፉ ሥር እንዲቀመጥ ባልንጀራውን ይጋብዛል” ይላል ያህዌ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 4
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ከእኔ ጋር ይነጋገር የነበረው መልአክም ተመልሶ፣ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው አንቃኝ።
|
||||
\v 2 እርሱም፣ “ምን ይታይሃል? ” አለኝ። እኔም፣ “በዐናቱ ላይ፣ የዘይት ማሰሮ ያለበት ሁለመናው ወርቅ የሆነ መቅረዝ አየሁ። መቅረዙም ላይ በእያንዳንዱ ጫፍ ሰባት ክሮች ያሏቸው ሰባት መብራቶች ነበር።
|
||||
\v 3 ደግሞም አንዱ ከዘይት ማሰሮው በስተ ቀኝ፣ ሌላውም በስተ ግራ ሁለት የወይራ ዛፎች አሉ።”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 እኔም፣ ያነጋገረኝ የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ እነዚህ ምንድን ናቸው? ” አልሁት።
|
||||
\v 5 ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክም መልሶ፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅም? ” አለኝ። እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” አልሁት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 6 ከዚያም እንዲህ አለኝ፤ “ለዘሩባቤል የመጣው የያህዌ ቃል ይህ ነው፤ ‘በመንፈሴ እንጂ፣ በኀይልና በብርታት አይደለም፤ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ።
|
||||
\v 7 አንተ ታላቅ ተራራ ምንድነህ? በዘሩባቤል ፊት ደልዳላ ሜዳ ትሆናለህ፤ ሰዎች “ሞገስ! ሞገስ ይሁንለት! ” ብለው እየጮኹ እርሱ መደምደሚያውን ድንጋይ ያወጣል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 8 የያህዌ ቃል ወደ እኔ መጣ፤
|
||||
\v 9 “የዘሩባቤል እጆች የዚህን ቤት መሠረት እንደ ጣሉ ሁሉ፣ የእርሱ እጆች ይፈጽሙታል። ያኔ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።
|
||||
\v 10 የጥቂቱን ቀን ነገሮች የናቀ ግን ነው? እነዚህ ሰዎች በዘሩባቤል እጅ ቱንቢውን ሲያዩ በጣም ደስ ይላቸዋል። እነዚህ ሰባት መብራቶች በምድር ሁሉ የሚመላለሱ የያህዌ ዐይኖች ናቸው።
|
||||
\v 11 ከዚያም መልአኩን፣ “ከመቅረዙ ግራና ቀኝ የቆሙት እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድን ናቸው? ” በማለት ጠየቅሁት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 12 እንደ ገናም፣ “በሁለት የወርቅ ቧንቧዎች አጠገብ የወርቅ ዘይት የሚያፈስሱት እነዚህ ሁለት የወይራ ቅንርንጫፎችስ ምንድን ናቸው? ” አልሁት።
|
||||
\v 13 እርሱም፣ “እነዚህ ምን እንደ ሆኑ አታውቅም? ” አለኝ፤ እኔም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ አላውቅም” አልሁት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 14 እርሱም፣ “እነዚህ የምድርን ሁሉ ጌታ ለማገለል የሚቆሙ ሁለቱ የወይራ ዛፎች ናቸው” አለኝ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 5
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ከዚያም ዘወር ብዬ ዐይኖቼን አነሣሁ፤ እነሆም፣ የሚበር መጽሐፍ ተመለከትሁ!
|
||||
\v 2 መልአኩም፣ “ምን ይታይሃል? ” አለኝ። እኔም፣ “ርዝመቱ ሃያ ክንድ፣ ወርዱ አሥር ክንድ የሆነ መጽሐፍ ሲበር ይታየኛል” በማለት መለስሁ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 3 እርሱም፣ “ይህ በምድር ሁሉ ላይ የሚመጣ መርገም ነው፤ የሚሰርቅ ሁሉ፣ በአንዱ በኩል በተጻፈው መሠረት ይጠፋል፤ በሐሰት የሚምል ሁሉ እንደ ተናገረው ቃል በሌላው ወገን በተጻፈው መሠረት ይጠፋል።
|
||||
\v 4 እኔ መርገሙን አመጣዋለሁ፤ ይህ የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ዐዋጅ ነው። ወደ ሌባው ቤትና በስሜ በሐሰት ወደሚምለው ሰው ቤት ይገባል፤ በዚያም ይቀመጣል፤ ቤቱን፣ እንጨቱንና ድንጋዩን ያጠፋል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 5 ከዚያም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረው መልአክ መጥቶ፣ “ዐይንህን አንሥተህ እየመጣ ያለውን ተመልከት! አለኝ።
|
||||
\v 6 እኔም፣ “ምንድን ነው? ” አልኩት። እርሱም፣ “ይህ እየመጣ ያለውን ኢፋ የያዘ መስፈሪያ ነው፤ ይህ የምድሪቱ ሁሉ በደል ነው” አለኝ።
|
||||
\v 7 ከዚያም ከእርሳስ የተሠራው ክዳን ተነሣ፤ የአፍ መስፈሪያው ውስጥ አንዲት ሴት ተቀምጣ ነበር!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 8 መልአኩም፣ “ይህች ዐመፃ ናት! ” ብሎ መልሶ ወደ መስፈሪያው አስገባትና የእርሳሱን ክዳን አጋው።
|
||||
\v 9 እነሆም፣ ዐይኔን አንሥቼ ሁለት ሴቶች ወደ እኔ ሲመጡ አየሁ፤ በክንፎቻቸውም ነፋስ ነበር፤ የሽመላ ክንፎችን የመሰሉ ክንፎች ነበሯቸው። መስፈሪያውን በምድርና በሰማይ መካከል አነሡት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 10 በእኔም ጋር እየተነጋገረ የነበረውን መልአክ፣ “መስፈሪያውን ወዴት እየወሰዱት ነው? ” አልሁት።
|
||||
\v 11 እርሱም፣ “ቤተ መቅደስ ሊሠሩለት ወደ ባቢሎን ምድር ይወስዱታል፤ ቤተ መቅደሱ ዝግጁ ሲሆን፣ እዚያ በተዘጋጀለት ቦታ ይቀመጣል” አለኝ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 6
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ከዚያም ዘወር ብዬ ዐይኖቼን ወደ ላይ ሳነሣ አራት ሰረገሎች ከሁለት ተራሮች መካከል ሲመጡ አየሁ፤ ሁለቱ ተራሮች የናስ ተራሮች ነበር።
|
||||
\v 2 የመጀመሪያው ሰረገላ ቀይ ፈረሶች ነበሩት፤ ሁለተኛው ሰረገላ ጥቁር ፈረሶች ነበሩት።
|
||||
\v 3 ሦስተኛው ሰረገላ ነጭ ፈረሶች ነበሩት፤ አራተኛው ሰረገላ ዝንጉርጉር ፈረሶች ነበሩት።
|
||||
\v 4 እኔም ከእኔ ጋር እየተነጋገረ የነበረውን መልአክ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እነዚህ ምንድን ናቸው? ” አልሁት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 5 መልአኩም እንዲህ አለኝ’ “እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ቆመው ከነበሩበት ቦታ የወጡ አራቱ የሰማይ ነፋሶች ናቸው! ” አለኝ።
|
||||
\v 6 ጥቁር ፈረሶች ያሉት ወደ ሰሜን፣ ነጭ ፈረሶች ያሉት ወደ ምዕራብ፣ ዝንጉርጉር ፈረሶች ያሉት ወደ ደቡብ ይሄዳሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 7 ጠንካሮች ፈረሶች ሲወጡ፣ በምድር ሁሉ ፊት ለመመላለስ አቆብቁበው ነበር፤ ስለዚህም መልአኩ፣ “ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ! ” አላቸው። እነርሱም ወጥተው ወደ ምድር ሁሉ ሄዱ።
|
||||
\v 8 ከዚያም ወደ እኔ ጮኾ እንዲህ አለኝ፤ “ወደ ሰሜን እየሄዱ ያሉትን ተመልከት፣ መንፈሴን በሰሜን ምድር አሳርፈውታል።”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 9 የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
|
||||
\v 10 ከምርኮኞቹ ከሔልዳይና፥ ከጦቢያ፣ ከዮዳኤም ወርቅና ብር ወስደህ በዚያው ቀን ከምርኮ ወደ መጣው ወደ ሶፎንያስ ልጅ ወደ ኢዮስያስ ቤት ሂድ።
|
||||
\v 11 ወርቁንና ብሩን ወስደህ አክሊል ሥራ በኢዮሴዴቅ ልጅ በሊቀ ካህኑ ኢያሱ ራስ ላይ አድርገው።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 12 እንዲህም በለው፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እነሆ፣ ስሙ ቁጥቋጥ የተባለው ሰው ይህ ነው! እርሱም በቦታው ይንሰራፋል፤ የያህዌንም ቤተ መቅደስ ይሠራል!
|
||||
\v 13 የያህዌን ቤተ መቅደስ የሚሠራው እርሱ ነው፤ ክብሩን ይጎናጸፋል፤ ከዚያም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል። በዙፋኑ ላይ ካህን ይሆናል፤ በሁለቱም መካከል ስምምነት ይኖራል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 14 ለሔልዳይና፣ ለጦቢያና ለዮዳኤ ክብር አክሊል ቤተ መቅደሱ ውስጥ ይቀመጣል፤ ለሶፎንያስ ልጅ ቸርነት መታሰቢያ ይሆናል።
|
||||
\v 15 ያኔ በሩቅ ያሉት መጥተው የያህዌን ቤተ መቅደስ ይሠራሉ፤ ወደ እናንተ የላከኝ ያህዌ እንደ ሆነም ታውቃላችሁ፤ የአምላካችሁን የያህዌን ድምፅ ከልባችሁ ብትሰሙ ይህ ይሆናል!”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 7
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ንጉሥ ዳርዮስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ካሴሉ በተባለው በዘጠነኛው ወር የያህዌ ቃል ወደ ዘካርያስ መጣ።
|
||||
\v 2 የቤቴል ሰዎች እግዚአብሔርን ለመለመን ሳራሳርንና ሬጌሜሌክን አብረዋቸው ከነበሩ ሰዎች ላኩ።
|
||||
\v 3 በሰራዊት ጌታ በያህዌ ቤት የነበሩትን ካህናትና ነቢያት፣ “ብዙ ዓመት እንዳደርግሁት በአምስተኛው ወር ማዘንና መጾም ይገባኛልን? ” አሏቸው።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 ስለዚህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
|
||||
\v 5 “በምድሩ ላሉት ሕዝብ ሁሉ፣ ለካህናቱም እንዲህ በላቸው፤ በእነዚህ ሰባ ዓመታት አምስተኛና ሰባተኛ ወሮች የጾማችሁትና ያዘናችሁት በእውነት ለእኔ ነውን?
|
||||
\v 6 የምትበሉትና የምትጠጡትስ ለራሳችሁ አይደለምን?
|
||||
\v 7 በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች በሰላምና በብልጽግና ትኖር በነበረ ጊዜ የኔጌቭና የምዕራብ ተራሮች ግርጌ የሰው መኖሪያ በነበሩ ዘመን በቀደሙት ነቢያት የተነገረው የያህዌ ቃል ይኸው አልነበረምን?”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 8 የያህዌ ቃል እንደ ገና ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
|
||||
\v 9 “የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ‘በእውነተኛ ፍትሕና የኪዳን ታማኝነት፣ በምሕረትም ፍረዱ። እያንዳንዱ ሰው ለወንድሙ እንዲህ ያድረግ።
|
||||
\v 10 መበለቶችንና ድኻ አደጎችን፣ መጻተኞችንና ድኻውን አታስጨንቋቸው፤ በልባችሁም አንዳችሁ በሌላው ክፉ አታስቡ!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 11 እነርሱ ግን መስማት አልፈለጉም፤ በእልኽኝነት ትከሻቸውን አሳበጡ። እንዳይሰሙ ጆሮአቸውን ደፈኑ።
|
||||
\v 12 ሕጉንና የሰራዊት ጌታ የያህዌን ቃል ላለመስማት ልባቸውን እንደ ዐለት አጠነከሩ። በቀደሙት ዘመኖች በመንፈሱ፣ በነቢያትም አንደበት እነዚህን መልእክቶች ወደ ሕዝቡ ላከ። ሕዝቡ ግን መስማት አልፈለጉም፤ ስለዚህ ያህዌ በእነርሱ ላይ በጣም ተቆጣ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 13 እርሱ ሲጠራቸው አልሰሙም። በተመሳሳይ መንገድ፣ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ “ወደ እኔ ይጣራሉ፤ እኔ ግን አልሰማም።”
|
||||
\v 14 አይተዋቸው ወደማያውቁ ሕዝቦች ሁሉ በዐውሎ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፤ ምድሪቱም በኋላቸው ባድማ ትሆናለች። ሕዝቡ መልካሚቱ ምድራቸውን ባድማ አድርገዋልና ማንም በምድሪቱ አያልፍም ወደዚያም አይመለስም።”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 8
|
||||
\p
|
||||
\v 1 የሰራዊት ጌታ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
|
||||
\v 2 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ “ስለ ጽዮን እጅግ ቀንቻለሁ፤ ስለ እርሷ በታላቅ ቁጣ ነድጃለሁ!
|
||||
\v 3 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል ወደ ጽዮን እመለሳለሁ፤ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌም የእውነት ከተማ ትባላለች፤ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ተራራም ቅዱሱ ተራራ ይባላል!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል ሽማግሌዎችና አሮጊቶች እንደ ገና በኢየሩሳሌም አደባባዮች ይሆናሉ፤ እያንዳንዱ ሰው በጣም ስለሚያረጅ በእጁ ምርኩዝ ይይዛል።
|
||||
\v 5 የከተማዋ አደባባዮች በሚቦርቁ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 6 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ በዚያን ጊዜ ይህ ከተቀሩት ሕዝብ የማይቻል መስሎ ቢታይ እንኳ፣ በእኔ ዐይን ፊት የማይቻል ይመስላልን? ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
\v 7 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል። እነሆ እኔ ሕዝቤን ከፀሐይ መውጫና ከፀሐይ መጥለቂያ ምድር አድናለሁ!
|
||||
\v 8 እንደ ገና አመጣቸዋለሁ፤ በኢየሩሳሌም መካከልም ይኖራሉ፤ እንደ ገና ሕዝቤ ይሆናሉ እኔም በእውነትና በጽድቅ አምላካቸው እሆናለሁ!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 9 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ እናንተ ከነቢያት አፍ የወጡ ቃሎችን አሁን እየሰማችሁ ያላችሁ፣ የእኔ ቤት፣ የሰራውቲ ጌታ የእኔ የያህዌ ቤት መሠረት በተጣለ ጊዜ ቤተ መቅደሱ መሠራት እንዲችል እጆቻችሁን አበርቱ።
|
||||
\v 10 ከእነዚያ ቀኖች በፊት ማንም እህል አልሰበሰበም ነበር፤ ለሰውም ሆነ ለእንስሳት የሚጠቅም ነገር አልነበረም፤ ከጠላት የተነሣ ለሚወጣም ሆነ ለሚገባ ሰው ሰላም አልነበረም ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው በባልንጀራው ላይ እንዲነሣ አድርጌ ስለ ነበር ነው።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 11 አሁን ግን እንደ ቀድሞው ዘመን አይሆንም፤ ከተረፈው ሕዝብ ጋር እሆናለሁ፤ ይህ የሰራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
\v 12 የሰላም ዘር ይዘራል፤ ያንሰራራው ወይን ፍሬውን ይሰጣል፤ ምድሪቱም አዝመራዋን ታበረክታለች፤ ሰማያት ጠል ይሰጣሉ፤ የተፈረው ሕዝብ ይህን ሁሉ እንዲወርስ አድርጋለሁ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 13 የይሁዳና የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለሌሎች ሕዝቦች የመርገም ምሳሌ ሆናችሁ ነበር። ስለዚህ አድናችኋለሁ፤ በረከትም ትሆናላችሁ። አትፍሩ፤ እጃችሁም ይበርታ!
|
||||
\v 14 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ አባቶቻችሁ ቁጣዬን ባነሳሡ ጊዜ ያላንቻች ርኅራኄ ጥፋት ላመጣባቸው እንደ ወሰንሁ፣ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ
|
||||
\v 15 አሁን ደግሞ ለኢየሩሳሌምና ለይሁዳ እንደ ገና መልካም ለማድረግ ወስኛለሁ፤ አትፍሩ!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 16 እናንተ ማድረግ ያለባችሁ እነዚህን ነው፤ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባዮቻችሁም እውነትን፣ ፍትሕንና ሰላምን አስፍኑ።
|
||||
\v 17 በባልንጀራችሁ ላይ በልባችሁ ክፋትን አታውጠንጥኑ፤ የሐሰት መሓላን አትውደዱ፣ ምክንያቱም እኔ እነዚህን ሁሉ እጠላለሁ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 18 እንደ ገናም የሰራዊት ጌታ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤
|
||||
\v 19 አሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ የአራተኛው ወር፣ የአምስተኛው ወር፣ የሰባተኛውና የአሥረኛው ወር ጾሞች ለይሁዳ ቤት የደስታ፣ የተድላና የሐሤት በዓሎች ይሆናሉ! ስለዚህ እውነትንና ሰላምን ውደዱ!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 20 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ያላል፤ በተለያዩ ብዙ ከተሞች ያሉት እንኳ ሳይቀሩ እንደ ገና ሰዎች ይመጣሉ።
|
||||
\v 21 የአንዱ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ሌላው ከተማ እየሄዱ፣ “ያህዌን ለመለመንና የሰራዊት ጌታ ያህዌን ለመፈለግ ኑ በፍጥነት እንሂድ፤ እኛ ራሳችንም ደግሞ እንሄዳለን” ይላሉ።
|
||||
\v 22 ብዙ ሕዝብና ኀያላይ መንግሥታት የሰራዊት ጌታ ያህዌን ለመፈለግ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣሉ፤ የያህዌንም ሞገስ ይለምናሉ!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 23 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል በእነዚያ ቀኖች ከየወገኑና ከየቋንቋው አሥር ሰዎች የእናንተን ልብስ ዘርፍ አጥብቀው በመያዝ፣ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና፤ ከእናንተ ጋር እንሂድ! ይላሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 9
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ይህ በሴድራክና በደማስቆ ላይ የተነገረ የያህዌ ቃል ዐዋጅ ነው። የያህዌ ዐይኖች በሰው ልጆች ሁሉ እና በእስራኤል ነገዶች ሁሉ ላይ ናቸው።
|
||||
\v 2 ይህ ዐዋጅ ደማስቆን የምታዋስናትን ሐማትንም ይመለከታል፤ በጣም ጥበበኞች ቢሆኑም ጢሮስንና ሲዶናንም ይመለከታል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 3 ጢሮስ ለራሷ ምሽግ ሠርታለች፤ ብሩን እንደ ዐፈር፣ ንጹሑን ወርቅ እንደ መንገድ ላይ ትቢያ ቆልላለች።
|
||||
\v 4 እነሆ፣ ጌታ ሀብቷን ይወስዳል፤ በባሕሩ ላይ ያላትንም ኀይል ይደመስሳል፤ እርሷም ፈጽማ በእሳት ትጸፋለች።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 5 አስቀሎና አይታ ትፈራለች! ጋዛም እጅግ ትሸበራለች! የአቃሮና ተስፋ ይጨነግፋል! ንጉሥ ከጋዛ ይጠፋል፤ አስቀሎና ከእንግዲህ መኖሪያ አትሆንም!
|
||||
\v 6 ባዕዳን ቤታቸውን በአሽዶድ ያደርጋሉ፤ የፍልስጥኤማውያንን ትዕቢት አጠፋለሁ።
|
||||
\v 7 ደሙን ከአፋቸው፣ የተከለከለውንም ምግብ ከጥርሶቻቸው መካከል አወጣለሁ። ያኔ እንደ ይሁዳ ነገድ የአምላካችን ትሩፋን ይሆናሉ፤ አቃሮንም እንደ ኢያቡሳዊ ይሆናል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 8 እኔ ግን ቤቴን ከዘራፊዎች እጠብቃለሁ፤ ጨቋኝ እንግዲህ ምድሬን አይወርስም፤ አሁን ነቅቼ እጠብቃለሁና!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ በደስታ ጩኺ! እነሆ ንጉሥሽ በጽድቅ ወደ አንቺ መጥቶ ያድንሻል። እርሱ ትሑት ነው፤ በእህያ ላይ ይቀመጣል፤ በአህያ ግልገል በውርንጫዋ ላይ ይቀመጣል።
|
||||
\v 10 ከዚያም ከኤፍሬም ሰረገላን፣ ከኢየሩሳሌም ፈረስን አጠፋለሁ፤ ቀስት ከጦርነት ይሰበራል፤ ሰላምን ለሕዝቦች ይናገራል፤ ግዛቱ ከባሕር እስከ ባሕር ይሆናል፤ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ይሆናል!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 11 ለአንቺ ደግሞ፣ ከአንቺ ጋር ካደረግሁት የደም ኪዳን የተነሣ እስረኞችሽን ውሃ ከሌለበት ጉድጓድ ነጻ እለቃቸዋለሁ።
|
||||
\v 12 እናንተ የተስፋ እስረኞች ወደ ምሽጋችሁ ተመለሱ! አሁንም ቢሆን ዕጥፍ አድርጌ እንደምመልስላችሁ እናገራለሁ፤
|
||||
\v 13 እንደ እኔ ቀስት ይሁዳን አጉብጫለሁ። ኤፍሬምን በፍላጻ ሞልቻለሁ። ጽዮን ሆይ፣ ልጆችሽን አስነሣለሁ፤ ግሪክ ሆይ በአንቺ ልጆች ላይ ይነሣሉ፤ እንደ ተዋጊ ሰይፍም አደርግሻለሁ!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 14 ያህዌ ለእነርሱ ይገለጣል፤ ፍላጻውም እንደ መብረቅ ይፈነጠራል! ጌታ ያህዌ መለከት ይነፋል፤ በቴማን ዐውሎ ነፋስ ይገሰግሣል።
|
||||
\v 15 የሰራዊት ጌታ ያህዌ ይከልላቸዋል፤ ጠላቶቻቸውን ይደመስሳሉ፤ በድንጋይ ወንጭፍም ያሸንፋሉ። ይጠጣሉ፤ በወይን ጠጅ እንደ ሰከረ ሰው ይጮኻሉ፤ መሠዊያው ላይ እንዳሉ ዕቃዎች፣ እንደ መሠዊያው ማእዘኖች በወይን ይሚላሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 16 በዚያ ቀን አምላካቸው ያህዌ ያድናቸዋል፤ ሕዝቡን የራሱ መንጋ ያደርጋቸዋል። አክሊል ላይ እንዳለ ዕንቁ፣ በገዛ ምድሩ ላይ ያብለጨልጫሉ።
|
||||
\v 17 ምንኛ መልካም፣ ምንኛ ቆንጆ ይሆናሉ! እህል ወጣቶችን፣ ጣፋጭ ወይን ጠጅ ቆነጃጅቱን ያሳምራል!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 10
|
||||
\p
|
||||
\v 1 የበልግ ወራት ዝናብ እንዲሰጣችሁ ጠይቁ፣ ዝናብ ያዘለ ደመናን የሚልክ ያህዌ ነው እርሱ ዝናብንና የመስክ አትክልትን ለሁሉም ይሰጣል።
|
||||
\v 2 የቤተ ሰብ ጣዖቶች ውሸት ይናገራሉ፤ ሟርተኞች የሐሰት ራእይ ያያሉ አሳሳች ሕልም ይናገራሉ፤ ባዶ መጽናኛ ይሰጣሉ ስለዚህ ሕዝቡ እንደ በጎች ይባዝናሉ፣ እረኛ በማጣጥም ይጨነቃሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 3 ጽኑ ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዶአል፤ መሪዎችንም እቀጣለሁ። የሰራዊት ጌታ ያህዌ ለመንጋው ለይሁዳ ቤት ይጠነቀቃል፤ በጦርነት ጊዜ እንደ ኩሩ የጦር ፈረሱ ያደርጋቸዋል!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 ከይሁዳ ሕዝብ የማእዘን ድንጋይ ይወጣል፤ ከእነርሱ የድንኳን ካስማ ይገኛል፤ ከእነርሱ የጦር ቀስት ይመጣል፤ ከእነርሱ ገዥ ሁሉ ይወጣል።
|
||||
\v 5 በጦርነት ጊዜ ጠላቶቹን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንደሚረግጥ ሰራዊት ይሆናሉ፤ ያህዌ ከእነርሱ ጋር ስለሆነ ተዋግተው የጦር ፈረሰኞችን ያሸንፋሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 6 የይሁዳን ቤት አበረታለሁ፤ የዮሴፍንም ቤት አድናለሁ፤ እምራቸዋለሁ፤ ወደ ቦታቸውም እመልሳቸዋለሁ። ከዚህ በፊት በፍጹም ጥዬአቸው እንደማላውቅ ይሆናሉ፤ እኔ አምላካቸው ያህዌ ነኝ፤ ጸሎታቸውንም እሰማለሁ።
|
||||
\v 7 በዚያ ጊዜ ኤፍሬም እንደ ብርቱ ጦረኛ ይሆናል፤ ወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ልባቸውን ደስ ይለዋል፤ ልጆቻቸውም አይተው ሐሤት ያደርጋሉ። ልባቸው በእኔ ሐሤት ያደርጋል!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 8 በፉጨት ጠርቼ እሰበስባቸዋለሁ፤ በእርግጥ እታደጋቸዋለሁ፤ እንደ ቀድሞው ዘመን ይበዛሉ!
|
||||
\v 9 በሕዝቦች መካከል ብበትናቸው እንኳ፣ በሚኖሩባቸው ሩቅ አገሮች ሆነው ያስታውሱኛል፤ እነርሱና ልጆቻቸው ተርፈው ይመለሳሉ።
|
||||
\v 10 ከግብፅ ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ ከአሦርም እሰበስባቸዋልሁ። ቦታ እስኪጠባቸው ድረስ በገልዓድና በሊባኖስ አሰፍራቸዋለሁ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 11 በመከራቸው ባሕር ውስጥ አልፋለሁ፤ ምክንያቱም የባሕሩን ማዕበል እመታለሁ፤ የዐባይም ጥልቅ ሁሉ ይደርቃል። የአሦር ግርማ ይወገዳል፤ የግብፅ በትረ መንግሥት ከግብፃውያን ይወገዳል።
|
||||
\v 12 በእኔ በራሴ አበረታቸዋለሁ፤ በስሜ ይመላለሳሉ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 11
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ሊባኖስ ሆይ፣ እሳት ዝግባሽን እንዲበላው በሮችሽን ክፈቺ!
|
||||
\v 2 የጥድ ዛፍ ሆይ፣ ዝግባ ውድቋልና አልቅስ! ግርማ የነበራቸው ዛፎች ጠፍተዋል! ጥቅጥቅ ያለው ደን ተመንጥሯልና እናንት የባሳን ወርካዎች ሆይ አልቅሱ።
|
||||
\v 3 ክብራቸው ጠፍቷልና እረኞች ሆይ ጩኹ!
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 አምላኬ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ “ለእርስ የተለዩትን በጎች እንደ እረኛ አሰማራ!
|
||||
\v 5 የሚገዟቸው ያርዷቸዋል ሳይቀጡም ይቀራሉ፤ የሚሸጧቸውም፣ “ሀብታም ሆኛለሁና ያህዌ ይመስገን” ይላሉ። እረኞቻቸው እንኳ አይራሩላቸውም።
|
||||
\v 6 ከእንግዲህ እኔም በምድሪቱ ለሚኖረው ሕዝብ አልራራም! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። እኔ ራሴ ሰውን ሁሉ ለባልንጀራውና ለንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እነርሱ ምድሪቱን ያስጨንቃሉ። ይሁዳንም ከእጃቸው አልታደገውም።”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 7 ስለዚህ እኔ ለእርድ ለተለዩትና ለተጨቆኑት እረኛ ሆንሁ። ሁለት በትሮች ወስጄ እንዱን፣ “ሞገስ” ሌላውንም፣ “አንድነት” ብዬ ጠራኋቸው። መንጋውንም አሰማራሁ።
|
||||
\v 8 በአንድ ወር ውስጥ ሦስቱን እረኞች አስወገድሁ፤ ትዕግሥቴ አለቀ፤ እነርሱም እንዲሁ እኔን ጠሉኝ።
|
||||
\v 9 ከዚያም ለበጎቹ ባለቤቶች፣ “ከእንግዲህ እረኛችሁ አልሆንም፤ የሚሞቱ በጎች ይሙቱ፤ የሚጠፉት በጎች ይጥፉ። የቀሩትም አንዱ የሌላውን ሥጋ ይብላ” አልኋቸው።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 10 ከዚያም፣ ከነገዶቼ ሁሉ ጋር ያደረግሁት ኪዳን መቋረጡን ለማመልከት፣ “ሞገስ” የተባለው በትሬን ሰበርሁ።
|
||||
\v 11 በዚያ ቀን ኪዳኑ ፈረስ፣ ብጎቹን ያስጨነቁትና ሲመለከቱኝ የነበሩትም ያህዌ እንደ ተናገረ አወቁ።
|
||||
\v 12 እኔም፣ “መልካም መስሎ ከታያችሁ ደመወዜን ክፈሉኝ፤ ካልመሰላችሁም ተዉት” አልኋቸው። ስለዚህ ሰላሣ ብር ከፈሉኝ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 13 ያህዌም፣ “ሊከፍሉህ የተስማሙትን ጥሩ ዋጋ ሰላሣ ብሩን ግምጃ ቤት ውስጥ አኑረው” አለኝ። ስለዚህም ሰላሣውን ብር ወስጄ በሃህዌ ቤት ባለው ግምጃ ቤት ውስጥ አኖሩሁት።
|
||||
\v 14 ከዚያም በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መፍረሱን ለማመልከት፣ “አንድነት” የተባለው ሁለተኛውን በትሬን ሰበርሁት።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 15 ያህዌም እንዲህ አለኝ፤ “እንደ ገና የሰነፍ እረኛ ዕቃ ውሰድ፣
|
||||
\v 16 እነሆ እኔ በምድሪቱ ላይ እረኛ ላስነሣ ነው። እርሱም ለጠፋው በግ አያስብም፤ የባዘነውን በግ አይፈልግም፤ የተሰበረውን አይጠግንም፤ ጤነኛውን አይመግብም፤ ሆኖም፣ የሰባውን ሥጋ ይበላል፤ ሰኮናው እንኳ ሳይቀር ይቀለጣጥማል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 17 መንጋውን ለሚተው እረኛ ወዮለት! ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዐይኑን ይውጋ! ክንዱ ፈጽማ ትሰልል፤ ቀኝ ዐይኑም ጨርሳ ትታወር!”
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 12
|
||||
\p
|
||||
\v 1 ስለ እስራኤል የተነገረው የያህዌ ቃል ዐዋጅ ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፣ ምድርን የመሠረተ፣ የሰውን መንፈስ የሠራ ያህዌ እንዲህ ይላል፣
|
||||
\v 2 “ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ የሚያንገዳግድ ጽዋ አደርጋታለሁ። ኢየሩሳሌም በምትከበብበት ጊዜ ይሁዳም ላይ እንደዚያው ይሆናል።
|
||||
\v 3 በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን አሕዛብ ሁሉ ላይ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ። ያንን ድንጋይ ማንቀሳቀስ የሚሞክር ሁሉ ክፉኛ ይጎዳል፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ በዚያች ከተማ ላይ ይሰበሰባሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 በዚያ ቀን፣ ፍረሱን ሁሉ በሽብር፣ የተቀመጠበትንም ሁሉ በእብደት እመታለሁ። የይሁዳን ቤት በምሕረት አያለሁ፤ የጠላትን ፈረስ ሁሉ አሳውራለሁ።
|
||||
\v 5 በዚያ ጊዜ የይሁዳ መሪዎች በልባቸው፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ አምላካቸው ስለ ሆነ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ብርታታችን ናቸው! ” ይላሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 6 በዚያ ቀን የይሁዳን መሪዎች በእንጨት ክምር ውስጥ እንዳለ የእሳት ምድጃ በነዶም መካከል እንዳለ ችቦ ነበልባል አደርጋለሁ፤ በቀኝና በግራ ዙሪያውን ያሉትን ሕዝቦች ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌምም እንደ ገና ከምድሯ ትኖራልች።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 7 የዳዊት ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ክብር ከይሁዳ ክብር እንዳይበልጥ፣ በዚያ ቀን ያህዌ በመጀመሪያ የይሁዳን መኖሪያዎች ያድናል።
|
||||
\v 8 በዚያ ቀን ያህዌ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከለላ ይሆናል፤ በዚያ ቀን በመካከላቸው ያለው ደካማው እንደ ዳዊት፣ የዳዊት ቤትም በፊታቸው እንደ አምላክ፣ እንደ ያህዌም መልአክ ይሆናል።
|
||||
\v 9 በዚያ ቀን ኢየሩሳሌም ላይ የሚነሡ ሕዝቦችን ሁሉ ማጥፋት እጀምራለሁ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 10 በዚያ ቀን በዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ ወጉኝ ወደ እኔ ይመለክታሉ፤ እነርሱም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ሰው ያለቅሱልኛል፤ ለበኩር ልጁ ሞት እንደሚያለቅስ ሰው ምርር ብለው ያለቅሳሉ።
|
||||
\v 11 በዚያ ቀን ኢየሩሳሌም ውስጥ የሚሆነው ለቅስ በመጊዶ ሜዳ ለሐዳድ ሪሞን እንደ ተለቀሰው ታላቅ ለቅሶ ይሆናል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 12 ምድሪቱ ታለቅሳለች፤ የእያንዳንዱ ወገን ቤተ ሰብ ለየራሱ ያለቅሳል። የዳዊት ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የናታን ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣
|
||||
\v 13 የሌዊ ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣ የሰማኢ ቤት ወገን ወንዶች ከነሚስቶቻቸው፣
|
||||
\v 14 የቀሩትም ወገኖች ወንዶች ሁሉ ከነሚስቶቻቸው ያለቅሳሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 13
|
||||
\p
|
||||
\v 1 በዚያ ቀን የዳዊትን ቤትና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችን ኀጢአትና ርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።
|
||||
\v 2 በዚያ ቀን ከእንግዲህ አስታዋሽ እንዳይኖራቸው የጣዖቶችን ስሞች ከምድሪቱ አጠፋለሁ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። ሐሰተኛ ነቢያትንና ርኵሳን መናፍስቶቻቸውም ከምድሪቱ ይወገዳሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 3 ማንም ትንቢት ቢናገር ወላጅ አባት እናቱ፣ “በያህዌ ስም ሐሰት ተናግረሃልና ትሞታለህ! ” ይሉታል። ትንቢት ሲናገርም የገዛ ወላጆቹ ይወጉታል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 4 በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው ትንቢት ራእይ ያፍራል። እነዚህ ነቢያት ሕዝቡን ለማታለል ከእንግዲህ ጠጕራም ልብስ አይለብስም።
|
||||
\v 5 እያንዳንዱ፣ “እኔ ገበሬ እንጂ፣ ነቢይ አይደለሁም፤ ከልጅነቴ ጀምሮ ኑርዬ የተመሠረተውም በዚሁ ነበር! ” ይላል።
|
||||
\v 6 ሌላውም መልሶ፣ “ታዲያ፣ ክንዶችህ” መካከል ያሉት እነዚህ ቁስሎች ምንድናቸው? ” በማለት ቢጠይቀው፣ “በባልንጀሮቼ ቤት ሳለሁ ያቆሰልሁት ነው” በማለት ይመልሳል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 7 “ሰይፍ ሆይ፣ በእረኛ፣ ለእኔ ቅርብ በሆነው ላይ ተነሣ ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። እረኛውን ምታው በጎቹም ይበተናሉ! እኔም ክንዴን በታናናሾች ላይ አዘራለሁ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 8 የምድሩ ሁሉ ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል! ሰዎች ይሞታሉ አንድ ሦስተኛው ብቻ ይተርፋል ያላል ያህዌ።
|
||||
\v 9 እንደ ብር እንደነጹ፣ ያንን አንድ ሦስተኛ ሕዝብ በእሳት ውስጥ አሳልፋለሁ፤ ወርቅ እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ። ስሜን ይጠራሉ፣ እኔም እመልስላቸዋለሁ ‘ይህ ሕዝቤ ነው’ እላለሁ፤ እነርሱም፣ “ያህዌ አምላኬ ነው! ” ያላሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\c 14
|
||||
\p
|
||||
\v 1 እነሆ፣ ብዝበዛሽን በውስጥሽ የሚከፋፈሉበት ቀን ይመጣል።
|
||||
\v 2 ሕዝብን ሁሉ ለጦርነት ኢየሩሳሌም ላይ አስነሣለሁ፤ ከተማዋም ትያዛለች። ቤቶች ይበዘበዛሉ፣ ሴቶች ይነወራሉ። የከተማው ግማሽ ሕዝብ በምርኮ ይወሰዳል፤ የተቀረው ሕዝብ ግን ከከተማው አይጠፋም።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 3 ነገር ግን በጦርነት ጊዜ እንደሚዋጋ ያህዌ እነዚያን ሕዝቦች ይዋጋል።
|
||||
\v 4 በዚያ ጊዜ እግሮቹ ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ባለው ደብረ ዘይት ተራራ ይቆማሉ። የደብረ ዘይት ተራራ በመካከሉ ባለው ታላቅ ሸለቆ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ለሁለት ይከፈልና እኩሌታው ወደ ሰሜን፣ እኩሌታው ወደ ደቡብ ይሄዳሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 5 እናንተም በያህዌ ተራሮች መካከል ባለው ሸለቆ በኩል ታመልጣላችሁ፤ በእነዚህ ተራሮች መካከል ያለው ሸለቆ እስከ አጸል ይደርሳል። በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን ከነበረው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደ ሸሻችሁ ትሸሻላችሁ። ያኔ አምላኬ ያህዌ ይመጣል፤ ከእርሱም ጋር ቅዱሳኑ ይመጣሉ።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 6 በዚያ ቀን ብርሃን አይኖርም፣ ብርድና ውርጭም አይኖርም።
|
||||
\v 7 በዚያ በእግዚአብሔር ብቻ በሚታወቅ ቀን ቀንም ሆነ ማታ ከኢየሩሳሌም ይፈስሳል።
|
||||
\v 8 ክረምትም ሆነ በጋ እኩሌታው ወደ ምሥራቅ ባሕር፣ እኩሌታው ወደ ምዕራብ ባሕር ይፈስሳል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 9 ያህዌ በመላው ምድር ይነግሣል። በዚያ ቀን አንድ አምላክ ያህዌ ብቻ ይሆናል፤ ስሙም አንድ ይሆናል።
|
||||
\v 10 ከጌባ አንሥቶ በኢየሩሳሌም ደቡብ እስካለችው ሬሞን ድረስ ምድር ሁሉ እንደ አረባ ትሆናለች። ኢየሩሳሌም ከፍ እንዳለች ትዘልቃለች። ከብንያም በር አንሥቶ የመጀመሪያው በር እስከ ነበረበት እስከ ማእዘኑ በር ድረስ፣ ከሐናንኤል ግንብ እስከ ንጉሡ ወይን መርገጫ ድረስ በቦታዋ ትኖራለች።
|
||||
\v 11 ሕዝቡም በኢየሩሳሌም ይኖራል፤ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከባድ ጥፋት አይመጣባቸውም፤ ኢየሩሳሌም በሰላም ትኖራለች።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 12 ኢየሩሳሌምን በወጉ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያህዌ የሚያመጣባቸው መቅሠፍቶች እነዚህ ናቸው፤ በእግራቸው ቆመው እያለ ሥጋቸው ይበሰብሳል። ዐይኖቻቸው ጉድጓዶቻቸው ውስጥ እያሉ ይበሰብሳሉ፤ ምላሳቸው አፋቸው ውስጥ ይበሰብሳል።
|
||||
\v 13 በዚያ ቀን ከያህዌ ዘንድ ታላቅ ፍርሃት ይመጣባቸዋል። እያንዳንዱ ሰው የባልንጀራውን እጅ ይይዛል፤ አንዱ ሌላውን ይወጋል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 14 ይሁዳም ኢየሩሳሌምን ይወጋል። የአካባቢውን ሕዝቦች ሁሉ ሀብት ይሰበስባሉ፤ ወርቅ፣ ብርና ልብስ በብዛት ይኖራል።
|
||||
\v 15 ፈረሶችና በቅሎዎች ላይ፣ ግመሎችና አይሆች ላይ መቅሠፍት ይወርዳል፤ ይኸው መቅሠፍት በየሰፈሩ ያሉ እንስሳትንም ሁሉ ይመታል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 16 ኢየሩሳሌምን ከወጓት ሕዝቦች ከሞት የተረፉት ለንጉሡ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ለመስገድና የዳስን በዓል ለማክበር በየዓመቱ ይወጣሉ።
|
||||
\v 17 በምድር ካሉ ሕዝቦች ሁሉ ለንጉሡ፣ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ለመስገድ ወደ ኢየሩሳሌም የማይወጣ ካለ፣ ያህዌ ደግሞ ዝናብ አያዘንብላቸውም።
|
||||
\v 18 የግብፅ ሕዝብ የማይወጣ ከሆነ ዝናብ አያገኝም። የዳስ በዓልን ለማክበር በማይወጡ ሕዝቦች ላይ መቅሠፍት ከያህዌ ዘንድ ይመጣባቸዋል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 19 የዳስ በዓልን ለማክበር በማይወጣው ግብፅና ማንኛውም ሕዝብ ላይ የሚመጣው ቅጣት ይህ ይሆናል።
|
||||
|
||||
\s5
|
||||
\v 20 በዚያ ቀን በፈረሶች ሻኩራ ላይ፣ “ለእግዚአብሔር የተቀደሰ” የሚል ጽሑፍ ይቀረጻል፤ በእግዚአብሔር ቤት ያሉት መታጠቢያዎች መሠዊያው ፊት እንዳሉት ሳህኖች የተቀደሱ ይሆናሉ፤
|
||||
\v 21 በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ያሉት ምንቸቶች ሁሉ ለሰራዊት ጌታ ለያህዌ ይቀደሳሉ፤ መሥዋዕት ለማቅረብ የሚመጡ ሁሉ በእነርሱ በማብሰል ይበሉባቸዋል። በዚያ ቀን በሰራዊት ጌታ በያህዌ ቤት ውስጥ ከእንግዲህ ነጋዴዎች አይኖሩም።
|
|
@ -42,7 +42,7 @@ dublin_core:
|
|||
subject: 'Bible'
|
||||
title: 'Unlocked Literal Bible'
|
||||
type: 'bundle'
|
||||
version: '7.2'
|
||||
version: '7.3'
|
||||
|
||||
checking:
|
||||
checking_entity:
|
||||
|
@ -236,6 +236,13 @@ projects:
|
|||
sort: 22
|
||||
path: ./22-SNG.usfm
|
||||
categories: [ 'bible-ot' ]
|
||||
-
|
||||
title: 'ዘካርያስ '
|
||||
versification: ufw
|
||||
identifier: 'zec'
|
||||
sort: 38
|
||||
path: ./38-ZEC.usfm
|
||||
categories: [ 'bible-ot' ]
|
||||
-
|
||||
title: 'ሶፎንያስ '
|
||||
versification: ufw
|
||||
|
|
Loading…
Reference in New Issue