added 6 more books

This commit is contained in:
Larry Versaw 2019-04-29 19:55:28 -06:00
parent 53a19db62a
commit 231da4d3b4
8 changed files with 10655 additions and 7 deletions

2242
02-EXO.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,2242 @@
\id EXO
\ide UTF-8
\h ዘጸአት
\toc1 ዘጸአት
\toc2 ዘጸአት
\toc3 exo
\mt ዘጸአት
\s5
\c 1
\p
\v 1 እያንዳንዳቸው ቤተ ሰባቸውን በመያዝ፣ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት የእስራኤል ልጆች ስሞች እነዚህ ናቸው፦
\v 2 ሮሜል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣
\v 3 ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ብንያም፣
\v 4 ዳን፣ ንፍታሌም፣ ጋድና አሴር።
\v 5 ከያዕቆብ ዘር የተገኙት ሰዎች ሰባ ነበር። ዮሴፍ ቀድሞውኑ በግብፅ ውስጥ ነበረ።
\s5
\v 6 ከጊዜ በኋላ ዮሴፍ፣ ወንድሞቹ ሁሉና ያ ትውልድ በሙሉ ሞቱ።
\v 7 ነገር ግን እስራኤላውያን እየተዋለዱ ሄዱ፤ ቊጥራቸውም እጅግ ጨምሮ በጣም ብርቱዎች ሆኑ፤ ምድሪቱንም ሞሏት።
\s5
\v 8 በግብፅ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ ዐዲስ ንጉሥ ተነሣ።
\v 9 ለሕዝቡም እንደዚህ አለ፤ “እስራኤላውያንን ተመልከቷቸው፤ ከእኛ ይልቅ በቍጥር በዝተዋል፤ እጅግም በርትተዋል።
\v 10 በቍጥር እየበዙ እንዳይሄዱ፣ ጦርነት ቢነሣም ከጠላቶቻችን ጋር ዐብረው እንዳይወጉንና ምድሪቱ ጥለው እንዳይሄዱ ኑ በዘዴ እርምጃ እንውሰድባቸው።”
\s5
\v 11 በከባድ ሥራ የሚያስጨንቋቸው አሠሪ አለቆችን በላያቸው ሾሙ። እስራኤላውያን ለፈርዖን ፊቶምና ራምሴ የተባሉ የንብረት ማከማቻ ከተሞችን ሠሩ።
\v 12 ግን ግብፃውያን እስራኤላውያንን ባስጨነቋቸው ቊጥር፣ እስራኤላውያን በቊጥር እየበዙና በምድሪቱ እየተስፋፉ ሄዱ። ስለዚህ ግብፃውያን እስራኤላውያን መፍራት ጀመሩ።
\s5
\v 13 ግብፃውያን እስራኤላውያንን በጥብቅ እንዲሠሩ አደረጓቸው።
\v 14 በሸክላ ሥራና ጭቃ በማስቦካት፣ በዕርሻ ውስጥም ሁሉን ዐይነት ከባድ ሥራ በማሠራት አስመረሯቸው (ሕይወታቸውን መራራ አደረጉባቸው) ። የሚጠበቅባቸው ሥራ ሁሉ ከባድ ነበር።
\s5
\v 15 ከዚያም በኋላ የግብፅ ንጉሥ ሲፓራና ፉሐ የሚባሉ ዕብራውያት አዋላጆችን እንዲህ አላቸው፤
\v 16 “ዕብራውያት ሴቶችን በማማጫው ላይ ስታዋልዱ፣ በሚወልዱበት ጊዜ ተመልከቱ። ወንድ ከተወለደ ግደሉት፤ ሴት ከሆነች ግን በሕይወት ትኑር።”
\v 17 ነገር ግን አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ፈሩ፣ ንጉሡ ያዘዛቸውንም አልፈጸኩም፤ ትእዛዙን በመፈጸም ፈንታ ሕፃናት ወንዶችን በሕይወት እንዲኖሩ አደረጉ።
\s5
\v 18 የግብፅ ንጉሥ አዋላጆቹን ጠርቶ፣ “ለምን ይህን አደረጋችሁ፣ ሕፃናት ወንዶችንስ ለምን አልገደላችኋቸውም? ” አላቸው።
\v 19 አዋላጆቹም ለፈርዖን፣ “ዕብራውያት ሴቶች እንደ ግብፃውያት ሴቶች አይደሉም። እነርሱ ብርቱዎች ናቸው፣ የሚወልዱትም አዋላጅ ወደ እነርሱ ከመምጣቱ በፊት ነው” በማለት መለሱለት፥
\s5
\v 20 እግዚአብሔር እነዚህን አዋላጆች ጠበቃቸው። ሕዝቡ በቍጥር በዙ፣ እጅግ ብርቱዎችም ሆኑ።
\v 21 አዋላጆቹ እግዚአብሔርን ስለ ፈሩ፣ እግዚአብሔር ቤተ ሰቦችን ሰጣቸው።
\v 22 ፈርዖን፣ “የተወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወንዝ ውስጥ ጣሉ፣ ሴትን ልጅ ግን በሕይወት እንድትኖር ታደርጋላችሁ” በማለት ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ከሌዊ ወገን የሆነ አንድ ሰው ሌዋዊት ሴት አገባ፡፡
\v 2 ሴትዮዋ ፀነሰች ወንድ ልጅም ወለደች፡፡ ሕፃኑ መልከ መልካም መሆኑን ስታይ፣ ሦስት ወር ሸሸገችው፡፡
\s5
\v 3 ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፣ የደንገል ቅርጫት ወስዳ በዝፍትና በቅጥራን ለቀለቀችው፡፡ ከዚያም ልጁን በውስጡ አስተኝታ ውሃው ውስጥ በቄጠማው መካከል በወንዙ ዳርቻ አስቀመጠችው፡፡
\v 4 የሚያጋጥመውን ለማየት የሕፃኑ እኅት በርቀት ቆማ ነበር፡፡
\s5
\v 5 ጠባቂዎቿ በወንዙ ዳር እየሄዱ ሳለ፣ የፈርዖን ልጅ በወንዙ ለመታጠብ ወረደች፡፡ ልዕቲቱ ቅርጫቱን በቄጠማዎች መካከል አየችው፡፡ ቅርጫቱን እንዲያመጣላት ጠባቂዋን ላከች፡፡
\v 6 ቅርጫቱን ስትከፍተው፣ ሕፃኑን አየች፡፡ እነሆ፣ ሕፃኑ ያለቅስ ነበር፡፡ ራራችለትና፣ ‹‹ይህ በእርግጥ ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው›› አለች፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም በኋላ የሕፃኑን እኅት የፈርዖንን ልጅ፣ ‹‹ልሂድና ሕፃኑን የምታሳድግልሽ ዕብራዊት ሴት ልፈልግልሽ? አለቻት፡፡
\v 8 የፈርዖንም ልጅ ‹‹ሂጂ›› አለቻት፡፡ ወጣቷም ልጅ ሄዳ የሕፃኑን እናት አመጣች፡፡
\s5
\v 9 የፈርዖን ልጅ የሕፃኑን እናት፣ ‹‹ይህ ሕፃን ውሰጅና አሳድጊልኝ፤ ደሞዝ እከፍልሻለሁ›› አለቻት፡፡ ሴትዮዋም ሕፃኑን ወስዳ አሳደገችው፡፡
\v 10 ሕፃኑ ባደገ ጊዜም ወደ ፈርዖን ልጅ አመጣችው፤ የልዕልቲቱም ልጅ ሆነ፡፡ ‹‹ከውሃ አውጥቼዋለሁና›› ብላም ስሙን ሙሴ አለችው፡፡
\s5
\v 11 ሙሴ ባደገ ጊዜ ወደ ወገኖቹ ሄዶ የሚሠሩትን ከባድ ሥራ ተመለከተ፡፡ ከገዛ ወገኖቹ መካከል አንዱን ዕብራዊ አንድ ግብፃዊ ሲደበድበው አየ፡፡
\v 12 ግራና ቀኙን ተመልክቶ ማንም አለመኖሩን ሲያረጋግጥ፣ ግብፃዊውን ገድሎ በአሸዋ ውስጥ ደበቀው፡፡
\s5
\v 13 ቀን ሙሴ ወደ ውጭ ወጣ፤ እነሆም ሁለት ዕብራውያን ወንዶች እየተጣሉ ነበር፡፡በደለኛ የነበረውን ሰውየ፣ ‹‹ባልንጀራህ ለምን ትደበድበዋለህ? አለው፡፡
\v 14 ሰውየው ግን፣ ‹‹አንተን በእኛ ላይ አለቃና ዳኛ ማን አደረገህ? ያን ግብፃዊ እንድ ገደልኸው እኔንም ልትገድለኝ ታስባለህ? አለ፡፡ ሙሴም ፈራና፣ ‹‹ያደረግሁት በሌሎች ሰዎች ዘንድ በእርግጥ ታውቋል›› አለ፡፡
\s5
\v 15 ስለ ጉዳዩ ሲሰማ ሙሴን ሊገድለው ፈለገ፡፡ ነገር ግን ከፈርዖን ሸሽቶ በምድያም አገር ኖረ፡፡ እዚያም በአንድ የውሀ ጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፡፡
\v 16 ካህን ሰባት ሴት ልጆች ነበሩት፡፡ እነርሱም ወደ ጉድጓዱ መጥተው ውሀ ቀዱ፣ የአባታቸውን መንጋ ለማጠጣትም ገንዳውን ሞሉት፡፡
\v 17 መጥተው ሊያባርሯቸው ሞከሩ፣ ነገር ግን ሙሴ ሄዶ ዐገዛቸው፡፡ መንጋቸውንም አጠጣላቸው፤
\s5
\v 18 ወደ አባታቸው ወደ ራጉኤል ሲሄዱም፣ አባታቸው፣ ‹‹ዛሬ እንዴት ቶሎ ወደ ቤት መጣችሁ? አለ፡፡
\v 19 ‹‹አንድ ግብፃዊ ከእረኞች አዳነን፤ ውሀም ቀድቶ መንጋውን አጠጣልን›› አሉ፡፡
\v 20 ልጆቹን፣ ‹‹ታዲያ የት አለ? ሰውየውን ለምን ተዋችሁት? ምግብ ከእኛ ጋር እንዲበላ ጥሩት›› አላቸው፡፡
\s5
\v 21 ሲፓራን እንዲያገባትም እንኳ ከሰጠው ሰውየ ጋር ለመኖር ሙሴ ተስማማ፡፡
\v 22 ወንድ ልጅ ወለደች፤ ሙሴም፣ ‹‹የባዕድ ምድር ኗሪ ነኝ›› ሲልም ስሙን ጌርሳም አለው፡፡
\s5
\v 23 ከረጅም ጊዜ በኋላ፣ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፡፡ እስራኤላውያን ከባርነት ሥራ የተነሣ አለቀሱ፣ ለርዳትም ጮኹ፤ ከባርነት ቀበራቸው የተነሣም ያሰሙት ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ወጣ፡፡
\v 24 እግዚአብሔር ልቅሶአቸውን ሲሰማ ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር የገባውን ቃል ኪዳኑን ዐሰበ፡፡
\v 25 እግዚአብሔር እስራኤላውያንን አየ፤ ሁኔታቸውንም ተረዳ፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ሙሴ የምድያምን ካህን፣ የዐማቱን የየቶርን በጎች ጠብቅ ነበር፡፡ በጎቹን ወደ ምድረ በዳው ዳርቻ ነድቶ ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ኮሬብ ደረሰ፡፡
\v 2 በዚያም የእግዚአብሔር መልአክ በቊጥቋጦ ውስጥ በእሳት ነበልባል ተገለጠለት፡፡ ሙሴ ተመለከተ፣ እነሆም ቊጥቋጦው እየተቀጣጠለ ነበር፤ ነገር ግን ቊጥቋጦው አልተቃጠለም፡፡
\v 3 ሙሴም፣ ‹‹ልቅረብና ቊጥቋጦው ለምን እንዳልተቃጠለ ይህን አስደናቂ ነገር ልይ›› አለ፡፡
\s5
\v 4 ሊመለከት እንደ ቀረበ እግዚአብሔር ሲያየው፣ ከቊጥቋጦው ውስጥ ጠራው፤ ‹‹ሙሴ፣ ሙሴ›› አለውመ፡፡ ሙሴም፣ ‹‹እነሆኝ›› አለ፡፡
\v 5 እግዚአብሔር፣ ‹‹አትቅረብ! የቆምህበት ምድር ለእኔ ተቀድሶአልና ጫማህን አውልቅ›› አለው፡፡
\v 6 ደግሞም፣ ‹‹እኔ የአባትህ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ነኝ›› አለው፡፡ ከዚያም በኋላ ሙሴ እግዚአብሔርን ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ፡፡
\s5
\v 7 እንዲህ አለ፤ ‹‹በግብፅ የሚኖሩትን የሕዝቤን ሥቃይ በእርግጥ አይቻለሁ፡፡ አሠሪ አለቆቻቸው ከሚያደርሱባቸው ጭቈና የተነሣ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ስለ ሥቃያቸው ዐውቃለሁና፡፡
\v 8 ከግብፃውያን አገዛዝ ነጻ ላወጣቸውና ከዚያም ጋር አውጥቼ ማርና ወተት ወደምታፈሰው መልካምና ለም ወደሆነችው፤ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያንን፣ ፌርዛውያን፣ ኤውያውያንና ኢያቡሳውያን ምድር ላሰገባቸው ወርጃለሁ አለ፡፡
\s5
\v 9 የእስራል ሕዝብ ጩኸት ወደ እኔ ደርሶአል፡፡ ይልቁንም ግብፃውያን ያደረሱባቸውን ጭቈና አይቻለሁ፡፡
\v 10 ስለዚህ ሕዝቤን፣ እስራኤላውያንን ከግብፅ እንድታወጣ ወደ ፈርዖን እልክልሃለሁ፡፡››
\s5
\v 11 ግን፣ እግዚአብሔርን ‹‹ወደ ፈርዖን የምሄድና እስራኤላውያንን ከግብፅ የማወጣቸው እኔ ማን ነኝ? አለው፡፡
\v 12 ሙሴን መልሶ፣ ‹‹እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ ይህ እኔ እንደ ላክሁህ ምልክት ይሆናል፡፡ ሕዝቡን ከግብፅ ስታወጣቸው፣ በዚህ ተራራ ላይ ታመልኩኛላችሁ›› አለው፡፡
\s5
\v 13 ሙሴም እግዚአብሔርን፣ ‹‹ወደ እስራኤላውያን ስሄድና ‹የአባቶቻችሁ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል› ብዬ ስነግራቸው፣ እነርሱም፣ ‹‹ስሙ ማን ነው? ሲሉኝ ምን እነግራቸዋሉ? አለው፡፡
\v 14 እግዚአብሔርም ሙሴን፣ ‹‹እኔ ያለሁ የምኖርም ነኝ፡፡ ያለና የሚኖር ወደ እናንተ ልኮኛል ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው›› አለው፡፡
\v 15 ደግሞም እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ ወደ እናንተ ልኮኛል፡፡ ስሜ ለዘለዓለም ይህ ነው፤ ለትውልዶች ሁሉ የታስበውም በዚህ ነው ብለህ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፡፡››
\s5
\v 16 ሂድና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሰብስብ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ የአባቶቻችሁ አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ለእኔ ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ፣ ‹‹ጐብኝቻችኋለሁ፤ በግብፅ ውስጥ የደረሰባችሁንም አይቻለሁ፡፡
\v 17 በግብፅ ከደረሰባችሁ ጭቈና ነጻ ላወጣችሁና ማርና ወተት ወደምታፈሰው ወደ ከነዓናውያን፣ ወደ ኬጢያውያን፣ ወደ አሞራውያን፣ ወደ ፌርዛውያን፣ ወደኤዊያውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ላገባችሁ ቃል ገብቻለሁ፡፡››
\v 18 ሽማግሌዎቹም ይሰሙሃል፡፡ አንተና የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ሂዱና፣ የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገለጠልን፡፡ ስለዚህም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት እንድንችል በምድረ በዳው ውስጥ የሦስት ቀን ጕዞ እንሂድ በሉት፡፡
\s5
\v 19 ነገር ግን የግብፅ ንጉሥ እጁ ካልተገደደ በቀር ለመሄድ እንደማይፈቅድላችሁ ዐውቃለሁ፡፡
\v 20 በመካከላቸው በማድረጋቸው ተአምራት ሁሉ ግብፃውያንን እመታቸዋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ፣ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል፡፡
\v 21 ሕዝብ ከግብፃውያን ዘንድ መወደድን እንዲያገኝ አደርጋለሁ፣ ስለዚህ ስትወጡ፣ ባዶ እጃችሁን አትወጡም፡፡
\v 22 ሴት ከግብፃውያት ጎረቤቶቿና በጎረቤቶቿ ቤቶች ውስጥ ከምትኖር ማንኛውም ሴት የብርና የወርቅ ጌጣጌጦች፣ ልብስም እንዲሰጣት ትጠይቃለች፡፡ እነርሱንም በወንዶችና በሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ታደርጓቸዋላችሁ፡፡ ግብፃውያንን በዚህ መንገድ ትበዘብዟቸዋላችሁ፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ሙሴም መልሶ፣ ‹‹ባያምኑኝስ ወይም ባይሰሙኝ ነገር ግን በምትኩ፣ እግዚአብሔር አልተገለጠልህም›› ቢሉኝስ?
\v 2 እግዚአብሔር ሙሴን፣ ‹‹በእጅህ ያለው ምንድን ነው? አለው፡፡ ሙሴም ‹‹በትር›› አለ፡፡
\v 3 እግዚአብሔር፣ ‹‹መሬት ላይ ጣለው›› አለው፡፡ ሙሴም በትሩን መሬት ላይ ጣለው፤ በትሩም እባብ ሆነ፡፡ ሙሴ ከእባቡ ሸሸ፡፡
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ሙሴን፣ ‹‹እጅህን ዘርግተህ የእባቡን ጅራት ያዝ›› አለው፡፡ ሙሴም እጁን ዘረገና እባቡን ያዘው፡፡ እባቡ በእጁ ላይ እንደ ገና በትር ሆነ፡፡
\v 5 ‹‹ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይስሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር የተገለጠልህ መሆኑን እነዲያምኑ ነው፡፡
\s5
\v 6 ደግሞም እግዚአብሔር ሙሴን፣ ‹‹እጅህን በብትህ ውስጥ አግባ›› አለው፡፡ እጁን ሲያወጣው እነሆ፣ እንደ በረዶ ነጽቶ ለምጽ ሆኖአል፡፡
\v 7 እግዚአብሔር፣ ‹‹እጅህን እንደ ገና በብብትህ ውስጥ አግባ›› አለው፡፡ ሙሴም እጁን በብብቱ ውስጥ አገባ፣ ከብብቱ ሲወጣውም እንደ ሌላው ሰውነቱ ጤናማ ሆኖ አየው፡፡
\s5
\v 8 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ ‹‹ባያምኑህ፣ የመጀመሪያውን የተአምር ምልክት ባይቀበሉ ወይም ባያምኑበት፣ ሁለተኛውን ያምናሉ፡፡
\v 9 እነዚህን ሁለት የተአምር ምልክቶች ባያምኑም እንኳ፣ ወይም ባይሰሙህ፣ ከወንዙ ጥቂት ውሀ ወስደህ በደረቁ መሬት ላይ አፍስሰው፡፡ ያፈሰስኸውም ውሀ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል፡፡››
\s5
\v 10 እግዚአብሔርን፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ በፊትም፣ አንተ ለባሪያህ ከተናገርህ ወዲህም ርቱዕ አንደበት ያለኝ አይደለሁም፡፡ ኮልታፋና ንግግር የማልችል ሰው ነኝ›› አለው፡፡
\v 11 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹የሰውን አንደበት የፈጠረ ማን ነው? ሰውን ዲዳ ወይም ደንቈሮ ወይም እንዲያይ ወይም እንዲታወር የሚያደርግስ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር አይደለምን?
\v 12 አሁን ሂድ፤ እኔም ከአፍህ ጋር እሆናለሁ፤ ምን እንደምትናገርም አስተምርሃለሁ፡፡››
\v 13 ሙሴ ግን፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ እባክህ ልትልከው የምትፈልገውን ሌላ ሰው ላክ›› አለ፡፡
\s5
\v 14 በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን ተቈጣው፡፡ እንዲህም አለው፤ ‹‹ሌዋዊው ወንድምህ አሮንስ? እርሱ በሚገባ መናገር እንደሚችል ዐውቃለሁ፡፡ እንዲያውም ከአንተ ጋር ለመገናኘት እየመጣ ነውና ሲያይህ በልቡ ደስ ይሰኛል፡፡
\v 15 አንተ ለእርሱ ትናገራለህ፤ የሚናገራቸውንም ቃላት በአፉ ውስጥ ታስቀምጣለህ፡፡ እኔ በአፍህና በአፉ እሆናለሁ፣ ምን እነደምታደርጉም አሳያችኋለሁ፡፡
\v 16 ለሕዝቡ ይናገርልሃል፡፡ እርሱ የአንተ አፍ ይሆናል፤ አንተም ለእርሱ እንደ እኔ፣ አምላክ ትሆነዋህ፡፡
\v 17 ይህን በትር በእጅህ ትይዛለህ፣ በእርሱም ተአምራትን ታደርጋለህ፡፡››
\s5
\v 18 ሙሴም ወደ ዐማቱ ወደ የቶር ተመልሶ ሄደ፤ ‹‹ግብፅ ውስጥ ወዳሉት ዘመዶቼ ተመልሼ እንድሄድና አሁንም ድረስ በሕይወት መኖራቸውን እንዳይ ፍቀድልኝ›› አለው፡፡ ዮቶርም ሙሴን፣ ‹‹በሰላም ሂድ›› አለው፡፡
\v 19 ምድያም ውስጥ እያለ እግዚአብሔር ‹‹ሂድ፣ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ ሊገድሉህ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ሞተዋል›› አለው፡፡
\v 20 መሴም ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ፣ በአህያ ላይም አስቀምጦ ወደ ግብፅ ተመለሰ፤ የእግዚአብሔርን በትርም በእጁ ይዞ ነበር፡፡
\s5
\v 21 ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹ወደ ግብፅ ተመልሰህ ስትሄድ፣ በእጅህ ያስቀመጥኋቸውን ተአምራት ሁሉ በፈርዖን ፊት እንደምታደርግ ዐስብ፡፡ ነገር ግን እኔ ልቡን አደነድነዋለሁ፤ ሕዝቡ እንዲሄዱም አይፈቅድም፡፡
\v 22 እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‹‹እግዚአብሔር እየተናገረ ያለው ይህን ነው፤ እስራኤል ልጄ፣ በኵሬ ነው፤
\v 23 ‹‹እንዲያመልከኝ ልጄን ልቀቅ ብዬ እነግርሃለሁ፡፡›› ነገር ግን ለመልቀቅ እምቢ ስላለህ፣ በኵር ልጅህን እገድላለሁ፡፡››
\s5
\v 24 ላይ ለምሽቱ ዐርፈው ሳለ፣ እግዚአብሔር ሙሴን አግንኝቶ ሊገድለው ነበር፡፡
\v 25 ግን ስለታም ቢላዋ ይዛ የልጇን ሸለፈት ገረዘች፤ እግሩንም አስነካችው፡፡ ከዚያም በኋላ ‹‹አንተ ለእኔ በእውነት የደም ሙሽራዬ ነህ›› አለች፡፡
\v 26 እግዚአብሔር ሙሴን ተወው፡፡ ‹‹አንተ የደም ሙሽራ ነህ›› ብላ የተናገረችው በግርዘቱ ምክንያት ነው፡፡
\s5
\v 27 አሮንን፣ ‹‹ወደ ምድረ በዳ ሂድና ከሙሴ ጋር ተገናኝ›› አለው፡፡ አሮን ሄደ፣ ሙሴንም በእግዚአብሔር ተራራ ላይ አግኝቶ ሳመው፡፡
\v 28 እንዲናገር የላከለትን የእግዚአብሔር ቃሎች ሁሉና እንዲፈጽማቸው ያዘዘውን ተአምራት በሙሉ ለአሮን ነገረው፡፡
\s5
\v 29 በኋላ ሙሴና አሮን ሄደው የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰቡ፡፡
\v 30 እግዚአብሔር ተአምራትም በሕዝቡ ፊት አሳየ፡፡
\v 31 አመኑ፡፡ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን የጐበኛቸውና የደረሰባቸውን ጭቈና የተመለከተ መሆኑን ሲሰሙም ሰገዱ፣ አመለኩትም፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 እነዚህ ነገሮች ከሆኑ በኋላ፣ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እንደዚህ አሉ፤ ‹‹የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹በምድረ በዳው ለእኔ በዓል እንዲያደርጉ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡›››
\v 2 ፈርዖንም፣ ‹‹እግዚአብሔር ማን ነው? ቃሉን የምሰማው፣ እስራኤልንስ የምለቅ ለምንድን ነው? እግዚአብሔርን አላውቀውም፤ እስራኤልንም አልለቅም›› አለ፡፡
\s5
\v 3 ሙሴና አሮንም፣ ‹‹የዕብራውያን አምላክ ከእኛ ጋር ተገናኝቶአል፡፡ በመቅሠፍትና በሰይፍ እንዳይመታን፣ ወደ ምድረ በዳው የሦስት ቀን ጕዞ እንድናደርግና ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ፍቀድልን›› አሉት፡፡
\v 4 የግብፅ ንጉሥ ግን፣ ‹‹አንተ ሙሴ አንተም አሮን! ሕዝቡን ሥራቸውን አስፈትታችሁ የምትወስዷቸው ለምንድን ነው? ወደ ሥራችሁ ሂዱ›› አላቸው፡፡
\v 5 እንዲህ አላቸው፤ ‹‹በምድራችን አሁን ብዙ ዕብራውያን አሉ፤ እናንተም ሥራ ታስፈቷቸዋላችሁ፡፡››
\s5
\v 6 በዚያው ቀን ፈርዖን ለሕዝቡ አሠሪዎችና ተቈጣጣሪዎች ትእዛዝ ሰጠ፡፡ እንዲህም አለ፤
\v 7 ‹‹እንደ ቀድሞው፣ ከእንግዲህ ወዲያ ለሸክላ ሥራ ጭድ አታቅርቡ፡፡ እነርሱ ራሳቸው ይሂዱና ጭድ ይሰብስቡ፡፡
\v 8 ሆኖም በፊት የሚሠሩትን አንድ ዐይነት የሸክላ ቊጥር አሁንም ሠርተው እንዲያቀርቡ ማድረግ አለባችሁ፡፡ ከዚያ ያነሰ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ሰነፎች ናቸው፡፡ ‹እንሂድ ፍቀድልንና ለአምላካችን እንሠዋ› እያሉ የሚጮኹትም ለዚህ ነው፡፡
\v 9 እንዲተጉና ለማይረባ ንግግር ትኵረት እንዳይሰጡ ሥራውን ጨምራችሁ አክብዱባቸው፡፡››
\s5
\v 10 ስለዚህ የሕዝቡ አሠሪ አለቆችና ተቈጣጣሪዎች ወጥተው ሄዱ፤ ለሕዝቡም ነገሯቸው፡፡ እንዲህም አሉ፤ ‹‹ፈርዖን የሚለው ይህ ነው፡- ‹ከእንግዲህ ወዲያ ምንም ጭድ አልሰጣችሁም፡፡
\v 11 ሂዱና ማግኘት ከምትችሉበት ፈልጋችሁ አምጡ፤ የሥራችሁ መጠንም አይቀላለም፡፡››
\s5
\v 12 ሕዝቡ በጭድ ፈንታ ገለባ ለመሰብሰብ በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፡፡
\v 13 አለቆቹ፣ ‹‹ጭድ በሚቀርብላችሁ ጊዜ የምትሠሩትን ሥራችሁን ጨርሱ›› ይሏቸውና ያስጠነቅቋቸው ነበር፡፡››
\v 14 ፈርዖን የመደባቸው አሠሪ አለቆች የሠራተኞች ተቈጣጣሪ ያደረጓቸውን እስራኤላውያን ኀላፊዎች ገረፏቸው፡፡ አሠሪ አለቆቹ፣ ‹‹በፊት ታደርጉት እንደ ነበረው፣ ትናንትናም ዛሬም የሚጠበቅባችሁን ሸክላ በሙሉ ሠርታችሁ ያላቀረባችሁ ለምንድን ነው? እያሉ ይጠይቋቸው ነበር፡፡
\s5
\v 15 እስራኤላውያን ተቈጣጣሪዎቹም ወደ ፈርዖን መጥተው አቤቱታ አቀረቡ፡፡ እንደዚህም አሉት፤ ‹‹ባሪያዎችህን በዚህ መንገድ ለምን እንድንኖር ታደርጋለህ?
\v 16 ጭድ አይሰጡንም፤ ነገር ግን አሁንም ‹ሸክላ ሥሩ! ይሉናል፡፡ እኛ ባሪያዎችህ ተገርፈናልም፤ ስሕተቱ ግን የገዛ ሕዝብህ ነው፡፡››
\v 17 ግን እንዲህ አለ፤ ‹‹እናንተ ሰነፎች! እናንተ ሰነፎች! ‹ለእግዚአብሔር እንድንሠዋ ፍቀድልን› ትላላችሁ፡፡
\v 18 ወደ ሥራ ተመለሱ፡፡ አንዳችም ጭድ አይሰጣችሁም፤ ነገር ግን አሁንም ያንኑ የሸክላ ቊጥር መሥራት አለባችሁ፡፡››
\s5
\v 19 ‹‹የየቀኑን የሸክላ ቊጥር መቀነስ የለባችሁም›› የሚለው ሲነገራቸው፣ እስራኤላውያን ተቈጣጣሪዎች ችግር ውስጥ እንደ ነበሩ አስተዋሉ፡፡
\v 20 ከፈርዖን ዘንድ ሲወጡ፣ ከቤተ መንግሥቱ ውጭ ቆመው ከነበሩት ከሙሴና ከአሮን ጋር ተገናኙ፡፡
\v 21 ለሙሴና ለአሮንም እንዲህ አሏቸው፣ ‹‹እግዚአብሔር ይይላችሁ፣ ይፍረድባችሁም፤ ምክንያቱም በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት አስጸያፊዎች እንድንሆን አድርጋችሁናል፡፡››
\s5
\v 22 ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ፣ ‹‹ጌታ ሆይ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ እንዲደርስበት ያደረግህ ለምንድን ነው? እኔንስ ቀድሞውኑ ለምን ላክኸኝ?
\v 23 ስም ልነግረው ወደ ፈርዖን ከመጣሁበት ጊዜ ጀምሮ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ መከራ አምጥቶአል፤ አንተም ሕዝብህን ከቶ ነጻ አላወጣኸውም›› አለው፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን፣ ‹‹በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ይለቃቸዋልና፣ ይህን ታያለህ፡፡ ከጽኑዕ እጄ የተነሣ ሕዝቡን ከምድሩ ያስወጣቸዋል›› አለው፡፡
\s5
\v 2 ለሙሴ እንዲህ አለው፤ ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡
\v 3 እኔ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁላቸው፤ ነገር ግን በስሜ፣ በእግዚአብሔር ለእነርሱ አልታወቅሁላቸውም ነበር፡፡
\v 4 የተሰደዱባትን፣ በእንግድነት የኖሩባትን የከነዓንን ምድር ልሰጣቸው፣ ከእነርሱ ጋር ኪዳን አጽንቻለሁ፡፡
\v 5 ደግሞም ግብፃውያን ባሪያ ያደረጓቸውን የአስራኤላውያንን ጩኸት ሰምቻለሁ፤ ኪዳኔንም አስታውሻለሁ፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ በግብፃውያን ሥር ከምትኖሩባት ባርነት እታደጋችኋለሁ፤ ከአገዛዛቸውም ነፃ አወጣችኋለሁ፡፡ በታላቅ ፍርድና ኀይሌን በማሳየት እታደጋችኋለሁ፡፡
\v 7 አድርጌ ወደ ራሴ እወስዳችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፡፡ ግብፃውያን ከጫኑባችሁ ባርነት ነፃ ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\v 8 ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ልሰጥ ቃል ወደገባሁባት ምድር አስገባችኋለሁ፡፡ ምድሪቱን ርስት አድርጌ እሰጣችኋለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡››
\v 9 ይህን ለእስራኤላውያን በነገራቸው ጊዜ፣ በአስከፊው ባርነታቸው ተስፋ ከመቊረጣቸው የተነሣ አላደመጡትም፡፡
\s5
\v 10 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 11 ሂድና ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን የእስራኤልን ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቅ ንገረው፡፡
\v 12 ሙሴም እግዚአብሔርን፣ ‹‹ተብታባ በመሆኔ እስራኤላውያን ካልሰሙኝ፣ ፈርዖን እንዴት ይሰማኛል?
\v 13 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አናገራቸው፡፡ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር እንዲያስወጡ ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖንና ስለ እስራኤላውያንም ትእዛዝ ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 14 የአባቶቻቸውም ቤት አለቆች እነዚህ ነበሩ፤ የእስራኤል በኵር ልጅ የሮቤል ልጆች ሄኖኅ፣ ፈሉስ፣ አስሮንና ከርሚ ነበሩ፡፡ እነዚህ የሮቤል ነገድ ናቸው፡፡
\v 15 የስምዖን ልጆች ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ዱሐርና የከነዓናዊቷ ሴት ልጅ ሳኡል ነበሩ፡፡ እነዚህ የስምዖን ነገድ አባቶች ናቸው፡፡
\s5
\v 16 የሌዊ ልጆች ስሞች ከትውልዶቻቸው ጋር እነዚህ ናቸው፤ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ነበሩ፡፡ ሌዊ መቶ ሠላሳ ዓመት ኖረ፡፡
\v 17 የጌድሶን ልጆች ሉቤኒና ሰሜኢ ነበሩ፡፡
\v 18 የቀዓት ልጆች እንበረም፣ ይሰዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩ፡፡ ቀዓት መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ኖረ፡፡
\v 19 የሜራሪ ልጆች ሞሖሊና ሙሲ ነበሩ፡፡ እነዚህ በትውልዶቻቸው መሠረት፣ የሌዋውያን የነገድ አባቶች ሆኑ፡፡
\s5
\v 20 የአባቱን እኅት ዮካብድን አገባ፤ እርሷምአሮንንና ሙሴን ወለደችለት፡፡ እንበረም መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖሮ ሞተ፡፡
\v 21 የይስዓር ልጆች ቆሬ፣ ናፌግና ዝክሪ ነበሩ፡፡
\v 22 ልጆች ሚሳኤል፣ ኤልዳፋንና ሥትሪ ነበሩ፡፡
\s5
\v 23 የአሚካዳብን ልጅ፣ የነኦሶንን እኅት ኤልሳቤጥን አገባ፡፡ እርሷም ናዳብንና አብዩድን፣ አልዓዛርንና ኢተምርን ወለደችለት፡፡
\v 24 የቆሬ ልጆች አሴር፣ ሕልቃናና አብያሳፍ ነበሩ፡፡ እነዚህ የቆሬ ነገድ አባቶች ናቸው፡፡
\v 25 ልጅ አልዓር ከፏትኤል ልጆች አንዲቱን አገባ፡፡ እርሷም ፊንሐስን ወለደችለት፡፡ እነዚህ በየትውልዶቻቸው የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናቸው፡፡
\s5
\v 26 ሁለት ሰዎች፣ ‹‹እስራኤላውያንን በየተዋጊ ሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አውጡ›› ብሎ እግዚአብሔር ያዘዛቸው አሮንና ሙሴ ነበሩ፡፡
\v 27 ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብፅ ለማውጣት እንዲፈቅድላቸው ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ተናገሩ፡፡ እነዚህ ሙሴና አሮን እነዚያው ራሳቸው ነበሩ፡፡
\s5
\v 28 እግዚአብሔር በግብፅ ውስጥ ሙሴን ባናገረው ጊዜ፣
\v 29 ‹‹እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡ የምነግርህን ሁሉ ለግብፅ ንጉሥ ለፈርዖን ንገረው›› አለው፡፡
\v 30 ግን እግዚአብሔርን፣ ‹‹እኔ ተብታባ ነኝ፤ ፈርዖን ታዲያ እንዴት ይሰማኛል? አለው፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹ልብ በል፤ አንተን ለፈርዖን እንደ አምላክ አድርጌሃለሁ፡፡ ወንድምህ አሮን ነቢይህ ይሆናል፡፡
\v 2 እንድትናገር ያዘዝሁህን ሁሉ ትናራለህ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲለቀ፣ ወንድምህ አሮን ለፈርዖን ይናገራል፡፡
\s5
\v 3 ነገር ግን እኔ የፈርዖንን ለብ አደነድነዋሁ፤ የተአምራቴን ብዙ ምልክቶች፣ ብዙ ድንቆችም በግብፅ ምድር አሳያለሁ፡፡
\v 4 ነገር ግን ፈርዖን አይሰማችሁም፤ ስለዚህ እጄን በግብፅ ላይ አደርጋሁ፤ ሰራዊቱን፣ ሕዝቤን፣ የእስራኤልን ልጆች በታላቅ ፍርድ ከግብፅ ምድር አወጣለሁ፡፡
\v 5 በግብፅ ላይ ስዘረጋና እስራኤላውያንን ከመካከላቸው ሳወጣ፣ ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፡፡››
\s5
\v 6 አሮን እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ፈጸሙ፡፡
\v 7 ባጋገሩት ጊዜ፣ የሙሴ ዕድሜ ሰማንያ፣ የአሮን ደግሞ ሰማንያ ሦስት ነበር፡፡
\s5
\v 8 ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤
\v 9 ‹ተአምር አሳዩ› ሲላችሁ፣ አሮንን እንዲህ በለው፤ ‹በትርህን ውሰድና በፈርዖን ፊት ጣለው፤ እባብም ይሀናል፡፡›››
\v 10 ሙሴ አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው፣ እግዚአብሔር አዝዞአቸው የነበረውን አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት ጣለው፤ እባብም ሆነ፡፡
\s5
\v 11 ደግሞ ለጥበበኛ ሰዎቹና ለጠንቋዮቹ ጥሪ አደረገ፡፡ እነርሱም በምትሀታቸው ያንኑ አደረጉ፡፡
\v 12 እያንዳንዱ ሰው በትሩን ጣለ፤ በትሮቹም እባብ ሆኑ፣ ነገር ግን የአሮን በትር የእነርሱን እባቦች ዋጣቸው፡፡
\v 13 አስቀድሞ እንደ ተናገረው፣ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ አልሰማምም፡፡
\s5
\v 14 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹የፈርዖን ልብ ደንድኖአል፤ ሕዘቡም እንዲሄዱ አይፈቅድም፡፡
\v 15 ወደ ውሃው በሚሄድበት ጊዜ፣ በጠዋት ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እንዳገኘውም በወንዙ ዳር ቁም፤ ወደ እባብነት ተለውጦ የነበረውን በትርህን ውሰድ፡፡
\s5
\v 16 እንዲህ በለው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን እንድናገር ወደ አንተ ላከኝ፤ ‹‹በምድረ በዳ እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፤ እስካሁን ድረስ አልሰማህም፡፡››
\v 17 የሚናገረው ይህ ነው፤ ‹‹እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታውቃለህ፡፡ የአባይን ወንዝ ውሀ በእጄ በያዝሁት በትር እመታዋለሁ፣ ወንዙም ወደ ደምነት ይለወጣል፡፡
\v 18 ውስጥ የሚገኙት ዓሦች ይሞታሉ፤ ወንዙ ይከረፋል፡፡ግብፃውያኑም ከወንዙ ውሀ መጠጣት አይችሉም፡፡››
\s5
\v 19 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ አሮንን፣ ‹በትርህን ውሰድና ውሀቸው ደም እንዲሆን፣ በግብፅ ውሀዎች ላይ፣ በወንዞቻቸውም፣ በምንጮቻቸውም፣ በውሀ ማጠራቀሚያዎቻቸውና በኩሬዎቻቸው ሁሉ ላይ እጅህን ዘርጋ ብለህ ንገረው፡፡ በመላው የግብፅ ምድር፣ ከዕንጨትና ከድንጋይ በተሠሩ ውሀ መያዣዎች ያለው ውሀም እንኳ ደም እንዲሆን ይህን አድርግ፡፡›››
\s5
\v 20 ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፡፡ አሮን በትሩን አንሥቶ በፈርዖንና በአገልጋዮቹ ፊት የወንዙን ውሀ መታው፡፡ የወንዙ ውሀ በሙሉ ወደ ደምነት ተለወጠ፡፡
\v 21 ውስጥ ያለው ዓሣ ሞተ ወንዙም መከርፋት ጀመረ፡፡ ግብፃውያኑ ከወንዙ ውሀ መጠጣት አልቻም፤ ደሙም በግብፅ ምድር በየትኛውም ስፍራ ነበረ፡፡
\v 22 የግብፅ ጠንቋዮችም በምትሀታቸው ያንኑ ዐይነት ነገር አደረጉ፡፡ ስለዚህ የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እግዚአብሔር ይሆናለ ብሎ ተናግሮት እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን ለመስማት እምቢ አለ፡፡
\s5
\v 23 ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡ ለዚህ ጉዳይ ትኵረትም እንኳ አልሰጠም፡፡
\v 24 ግብፃውያኑ ሁሉ በወንዙ ዙሪያ የሚጠጣ ውሀ ለማግኘት ቈፈሩ፤ ነገ ርግን የወንዙን ውሀ መጠጣት አልቻሉም፡፡
\v 25 እግዚአብሔር ወንዙን ከመታው በኋላ ሰባት ቀን ዐለፈ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ በለው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ ‹‹እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
\v 2 ካልህ፣ አገርህን በሙሉ በጓጕንቸው መቅሠፍት እመታዋለሁ፡፡
\v 3 ጓጕንቸር ይርመሰመሳል፡፡ ጓጕንቸሮቹ ከወንዙ ይወጡና ወደ ቤትህ፣ ወደ መኝታ ክፍልህና ወደ ዐልጋህ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ አገልጋዮችህም ቤቶች ውስጥ ይገባሉ፡፡ ወደ ሕዝብህ፣ ወደ ምድጆችህና ወደ ቡሃቆችም ይዛመታሉ፡፡
\v 4 ጓጕንቸሮቹ አንተን፣ ሕዝብህንና አገልጋዮችህን ሁሉ ይመታሉ፡፡››
\s5
\v 5 ለሙሴ እንዲህ አለ፤ ‹‹አሮንን፣ እጅህንና በትርህን በወንዞች፣ በምንጮችና በቦዮች ላይ ዘርጋና በግብፅ ምድር ላይ ጓጕንቸሮች እንዲወጡ አድርግ›› በለው፡፡
\v 6 በግብፅ ውሆች ላይ እጁን ዘረጋ፤ ጓጕንቸዎቹም ወጥተው የግብፅን ምድር ሸፈኑት፡፡
\v 7 ጠንቋዮቹም በምትሃቸው ያንኑ አደረጉ፤ ጓጕንቸሮቹ በግብፅ ምድር ላይ እንዲወጡ አደረጉ፡፡
\s5
\v 8 ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ ‹‹ጓጕንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ላይ አንዲያስወግድ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ፡፡ ከዚያም ለእግዚአብሔር እንዲሠዉ ሕዝቡን እለቃቸዋለሁ›› አላቸው፡፡
\v 9 ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ ‹‹ጓጕንቸሮቹ ከአንተና ከቤቶችህ እንዲወገዱ፣ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን እንዲቈዩ፣ ለአንተ፣ ለአገልጋዮችህና ለሕዝብህ የምጸልይበትን ጊዜ ለእኔ መንገሩ የአንተ ድርሻ ነው፡፡››
\s5
\v 10 ‹‹ነገ›› አለው፡፡ ሙሴም ፈርዖንን መልሶ፣ ‹‹እንደ አምላካችን እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ እንድታውቅ አንተ እንደምትለው ይሁን፡፡
\v 11 ጓጕንቸሮቹ ከአንተ፣ ከቤቶችህ ከአገልጋዮችህና ከሕዝብህ ይወገዳሉ፡፡ በወንዙ ውስጥ ብቻ ግን ይቈያሉ›› አለው፡፡
\v 12 አሮን ከፈርዖን ወጥተው ሄዱ፡፡ ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፡፡
\s5
\v 13 ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- ጓጕንቸሮቹ በየቤቱ፣ በየግቢውና በየሜዳው ሞቱ፡፡
\v 14 ሕዝቡ የሞቱትን ሰብስበው ከመሯቸው፤ ምድሩም ከረፋ፡፡
\v 15 ነገር ግን ፈርዖን ፋታ መገኘቱን ሲያይ፣ ልቡን አደነደነ፤ እንደዚህ ያደርጋል ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮ እንድ ነበረ፣ ሙሴንና አሮንንም አልሰማቸውም፡፡
\s5
\v 16 ለሙሴ እንዲህ አለ፤ ‹‹አሮንን እንዲህ በለው ‹በመላው የግብፅ ምድር ተባይ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ በበትርህ ምታ፡፡››
\v 17 እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡- አሮን እጁን ዘርግቶ በበትሩ የምድሩን ትቢያ መታው፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባይ መጣ፡፡ የምድሩ ትቢያ ሁሉ በመላው የግብፅ ምድር ተባይ ሆነ፡፡
\s5
\v 18 በምትሃቸው ተባይ እንዲመጣ ሙከራ አደረጉ፤ ነገር ግን አልቻም፡፡ በሰውና በእንስሳ ላይ ተባዮች ነበሩ፡፡
\v 19 ጠንቋዮቹ ታዲያ ፈርዖንን፣ ‹‹ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው›› አሉት፡፡ ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደነደነ፤ እነርሱንም ለማድመጥ እምቢ አለ፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንዲህ እንደሚያደርግ እግዚአብሔር ተናግሮት በነበረው መሠረት ነው፡፡
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹በማለዳ ተነሣና ፈርዖን ወደ ወንዙ ሲወጣ በፊት ለፊቱ ቁም፡፡ እንደዚህም ብለህ ንገረው፤ ‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹‹እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
\v 21 የማትለቅ ከሆነ ግን፣ በአንተ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ፣ ወደ ቤቶችህም ውስጥ የዝንብ መንጋ እልካለሁ፡፡ የግብፃውያን ቤቶች በዝንብ መንጋ ይሞላሉ፤ የሚቆሙበት ምድርም እንኳ ዝንብ ብቻ ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 ግን በዚያ ቀን የዝንብ መንጋ እንዳይገኝባ፣ ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሤምን ምድር በተለየ ሁኔታ እይዛታለሁ፡፡ እኔ እግዚአብሔር በዚህ ምድር እንዳለሁ እንድታውቅ ይህ ይሆናል፡፡
\v 23 በሕዝቤና በሕዝብህ መካከል ልዩነት እንዲኖር አደርጋለሁ፡፡ ይህ ተአምራዊ ምልክት ነገ ነው የሚሆነው፡፡››
\v 24 እግዚአብሔር እንዲሁ አደረገ፤ ጥቅጥቅ ያለ የዝንብ መንጋም ወደ ፈርዖን ቤትና ወደ አገልጋዮቹ ቤቶች መጣ፡፡ በመላው የግብፅ ውስጥ ምድሩ ከዝንቡ መንጋ የተነሣ ተበላሽቶ ነበር፡፡
\s5
\v 25 ሙሴንና አሮንን አስጠርቶ፣ ‹‹ሂዱና በምድራችሁ ለአምላካችሁ ሠዉ›› አላቸው፡፡
\v 26 እንዲህ ለማድረግ ለእኛ ትክክል አይደለም፤ ለአምላካችን በእግዚአብሔር የምንሠዋቸው መሥዋዕቶች ለግብፃውያን አስጸያፊዎች ናቸውና፡፡ ለግብፃውያን አስጸያፊ የሆኑትን መሥዋዕቶች እያን በፊታቸው ብንሠዋ፣ በድንጋይ አይወግሩንም?
\v 27 ባዘዘን መሠረት፣ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሠዋት ያለብን ወደ ምድረ በዳወ የሦስት ቀን ጕዞ ሄደን ነው›› አለ፡፡
\s5
\v 28 ‹‹እንድትሄዱና በምድረ በዳው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንድትሠዉ እፈቅድላችኋለሁ፡፡ ርቃችሁ መሄድ ግን የለባችሁም፡፡ ለእኔም ጸልዩልኝ›› አለ፡፡
\v 29 ‹‹ከአንተ ወጥቼ እንደ ሄድሁ፣ የዝንቦቹ መንጋ አንተን ፈርዖንን፣ አገልጋዮችህንና ሕዝብህን ነገ ለቀው እንዲሄዱ ወደ እግዚአብሔር እጸልይልሃለሁ፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ሕዝባችን እንዲሄድ ባለመፍቀድ ከእንግዲህ ወዲያ ልታታልለን አይገባም›› አለ፡፡
\s5
\v 30 ከፈርዖን ወጥቶ ሄደና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡
\v 31 እግዚአብሔር ሙሴ እንደ ለመነው አደረገ፡- የዝንቡን መንጋ ከፈርዖን፣ ከአገልጋዮቹና ከሕዝቡ ላይ አስወገደ፡፡ አንድም አልቀረም፡፡
\v 32 ነገር ግን ፈርዖን በዚህም ጊዜ ልቡ አደነደነ፤ ሕዝቡም እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ ‹‹ወደ ፈርዖን ሂድና እንዲህ ብለህ ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ይናገራል፡፡ ‹‹እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡››
\v 2 ብትልና አሁንም ከልክለህ ብታስቀራቸው፣
\v 3 የእግዚአብሔር እጅ መስክ ላይ ባለው ከብትህ፣ በፈረሶችህ፣ በአህዮችህ፣ በግመሎችህ፣ በፍየሎችህና በበጎችህ ላይ ይሆናል፤ አስከፊ በሽታም ያመጣል፡፡
\v 4 እግዚአብሔር በእስራኤል ከብትና በግብፅ ከብት መካከል ልዩነት አድርጓል፡- የእስራኤል ከብት አይሞትም፡፡
\s5
\v 5 ጊዜ ወስኖአል፤ ‹‹በምድሪቱ ላይ ይህን የማደርገው ነገ ነው›› ብሎአል፡፡
\v 6 ይህን በሚቀጥለው ቀን አደረገው፡- የግብፅ ከብት ሁሉ ሞተ፡፡ ከእስራኤል ከብት ግን አንድም አልሞተም፡፡
\v 7 ተከታትሎ አጣራ፣ ከእስራኤል ከብት አንድም እንኳ አለመሞቱን ተረዳ፡፡ ነገር ግን ልቡ ደንድኖ ነበር፤ ስለዚህ ሕዝቡ እንዲሄድ አልፈቀደም፡፡
\s5
\v 8 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን አላቸው፤ ‹‹ከምድጃ ላይ እፍኝ ዐመድ ውሰዱና አንተ ሙሴ ወደ ሰማይ ፈርዖን እያየ ዐመዱን በትነው፡፡
\v 9 በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ትቢያ ይሆናል፡፡ ይህም በመላው የግብፅ ምድር በሰውና በእንስሳት ላይ ዕባጭና ቊስል ያመጣል፡፡››
\v 10 ስለዚህ ሙሴና አሮን ከምድጃ ዐመድ ወስደው ከፈርዖን ፊት ለፊት ቆሙ፡፡ ከዚያም ሙሴ ዐመዱን ወደ ሰማይ በተነው፡፡ ዐመዱ በሰውና በእንስሳ ላይ የሚወጣ ዕባጭና ቊስልን አመጣ፡፡
\s5
\v 11 በእነርሱና በሌች ግብፃውያን ሁሉ ላይ ወጥቶ በነበረው ዕባጭ ምክንያት ጠንቋዮቹ በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፡፡
\v 12 እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስለ አደነደነው፣ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን እንደዚህ እንደሚደርግ እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት እንድ ነበረው ነው፡፡
\s5
\v 13 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹በጠዋት ተነሣና ከፈርዖን ፊት ለፊት ቁም፤ እንደዚህ ብለህም ንገረው፤ ‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናገሯል፡- ‹‹እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
\v 14 ጊዜ በአንተ በራስህ፣ በአገልጋዮችህና በሕዝብህ ላይ መቅሠፍቴን ሁሉ እልካለሁ፡፡ ይህን የማየደርገውም በድምር ሁሉ እንደ እኔ ያለ እንደሌለ እንድታውቅ ነው፡፡
\s5
\v 15 ጊዜ እጄን ዘርግቼ አንተንና ሕዝብህን በበሽታ በመምታት ከምድር ባጠፋኋችሁ ነበር፡፡
\v 16 ግን በሕይወት እንድትቈይ ያደረግሁህ፣ ኀይሌን እንድገልጥብህና ስሜም በምድር ሁሉ እንዲታወቅ ነው፡፡
\v 17 ሕዝቤን እንዳይሄድ በማድረግ በሕዝቤ ላይ ራስህን እያሳበይህ ነው፡፡
\s5
\v 18 ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብፅ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የበረዶ ማዕበል አመጣለሁ፡፡
\v 19 አሁን ሰው ላክና ከብትህን፣ በመስክ ላይ ያለህን ማንኛውንም ነገር ወደ ጠለያ ስፍራ ሰብስብ፡፡ መስክ ላይ የቀረና ወደ ቤት ያልመጣ ማንኛውም ከብትና ሰው ሁሉ በረዶው ይወርድባቸውና ይሞታሉ፡፡››
\s5
\v 20 አገልጋዮች የእግዚአብሔር ቃል የተቀበሉት ባሮቻቸውንና ከብቶቻቸውን ወደ ቤት ለማምጣት ተጣደፉ፡፡
\v 21 የእግዚአብሔርን ቃል ከምር ያልተቀበሉት ግን ባሮቻቸውንና ከብታቸውን መስክ ላይ ተዉ፡፡
\s5
\v 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹በሁሉም የግብፅ ምድር፣ በሕዝብ፣ በእንስሳትና በመላው የግብፅ ምድር መስክ ላይ ባሉ ተክሎች ሁሉ ላይ በረዶ እንዲወርድ እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ፡፡››
\v 23 በትሩን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድ፣ በረዶና መብረቅ ወደ ምድር ላከ፡፡በግብፅም ምድር ላይ በረዶ አዘነበ፡፡
\v 24 ግብፅ አገር ከሆነችበት ጊዜ ጀምሮ በምድሪቱ ሁሉ ያልታየ እጅግ ከባድ የበረዶና የመብረቅ ቅልቅል ነበር የዘነበው፡፡
\s5
\v 25 የግብፅ ምድር፣ በረዶው መስክ ላይ ያለውን ማንኛውንም ነገር፣ ሰውንም እንስሳቱንም መታ፡፡ በመስክ ያለውን ተክል ሁሉ መታው፣ ዛፉንም ሁሉ ሰባበረው፡፡
\v 26 እስራኤላውያን በሚኖሩበት በጌሤም ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም፡፡
\s5
\v 27 በኋላ ፈርዖን ሙሴንና አሮንን እንዲጠሩ ሰዎችን ላከ፡፡ እንዲህም አላቸው፤ ‹‹በዚህ ጊዜ ኀጢአት ፈጽሜአለሁ፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ እኔና ሕዝቤ ግን ኀጢአተኞች ነን፡፡
\v 28 እግዚአብሔር ጸልዩ፤ ምክንያቱም ከባዱ ነጐድጓድና በረዶ እጅግ በዝቶብናል፡፡ እለቅቃችኋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ እዚህ አትቆዩም፡፡
\s5
\v 29 ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ ‹‹ከከተማዪቱ እንደ ወጣሁ፣ እጆቼን ወደ እግዚአብሔር እዘረጋለሁ፡፡ ነጐድጓዱ ያቆማል፣ በረዶም አይኖርም፡፡ በዚህ መንገድ አንተ ምድር የእግዚአብሔር መሆኗን ታውቃለህ፡፡
\v 30 ግን አንተንና አገልጋዮችህን በሚመለከት እግዚአብሔር አምላክን ገና በእውነት እንደማታከብሩ ዐውቃለሁ፡፡››
\s5
\v 31 ጊዜ ተልባው አብቦ፣ ገብሱም ፍሬ በመያዝ ላይ ነበረ፣ ተልባውና ገብሱ ከጥቅም ውጭ ሆነዋል፡፡
\v 32 አጃው ግን ቈይተው የሚደርሱ ሰብሎች በመሆናቸው አልተጐዱም፡፡
\v 33 ሙሴ ከፈርዖንና ከከተማዪቱ ሲወጣ፣ እጆቹን ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ቆሙ፤ ዝናብም አልዘነበም፡፡
\s5
\v 34 ፈርዖን ዝናቡ፣ በረዶውና ነጐድጓዱ መቆሙን ሲያይ፣ እንደ ገና ኀጢአት አደረገ፤ ከአገልጋዮቹ ጋርም በአንድነት ልቡን አደነደነ፡፡
\v 35 የፈርዖን ልብ ስለ ደነደነ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንዲሄዱ አልፈቀደም፡፡ ይህም የሆነው ፈርዖን ልቡን እንድሚያደነድን እግዚአብሔር ለሙሴ ነግሮት የነበረው መንገድ ነው፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ ‹‹የፈርዖንና የአገልጋዮቹን ልብ አደነድናለሁና ወደ ፈርዖን ሂድ፡፡ እነዚህን የተአምራቴን ምልክቶች ለማሳየት ይህን አድርጌአለሁ፡፡
\v 2 ይህን ያደረግሁት ግብፃውያንን እንዴት በከባድ አያያዝ እንደያዝኋቸውና በመካከላቸውም የተአምራትን ልዩ ልዩ ምልክቶች እንዳሳየሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሯቸው ነው፡፡ በዚህ መንገድ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፡፡
\s5
\v 3 አሮንም ወደ ፈርዖን ሄደው እንዲህ አሉት፤ ‹‹የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ‹ራስህን በፊቴ ለማዋረድ እምቢ የምትለው እስከ መቼ ነው? እንዲያመልኩኝ ሕዝቤን ልቀቅ፡፡
\v 4 ግን ሕዝቤን አልለቅም ብትል፣ እነሆ፣ በነገው ቀን በአገርህ ላይ አንበጣዎችን አመጣለሁ፡፡
\s5
\v 5 ማንም ሰው መድሩን ማየት እስከማይችል ድረስ የምድሩን ገጽ ይሸፍኑታል፡፡ ከበረዶው አምልጦ የቀረውን ሁሉ ይበሉታል፡፡ መስክ ላይ የሚያድግላችሁንም ዛፍ ሁሉ ይበሉታል፡፡
\v 6 አንበጣዎቹ የአንተን፣ የአገልጋዮችህን ቤቶች ሁሉ ይሞሏቸዋል፤ ይህም፣ አባትህም አያትህም በዚህ ምድር ላይ መኖር ከጀመሩበት ቀን አነሥቶ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ታይቶ የማይታወቅ ነው፡፡›› ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ሄደ፡፡
\s5
\v 7 ፈርዖንን፣ ‹‹ይህ ሰው ወጥመድ የሚሆንብን እስከ መቼ ነው? አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲያመልኩት እስራኤላውያን ይሂዱ፡፡ ግብፅ መጥፋቷን ገና አልተገነዘብህምን? አሉት፡፡
\v 8 ሙሴና አሮን፣ ‹‹ሂዱ አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፡፡ ነገር ግን የሚሄዱት የትኞቹ ናቸው? ወዳላቸው ወደ ፈርዖን እንደገና እንዲመጡ ተደረገ፡፡
\s5
\v 9 የምንሄደው ከወጣቶቻችንና ከሽማግሌዎቻችን፣ ከወንድና ከሴት ልጆችን ጋር ነው፡፡ ለእግዚአብሔር በዓል ማክበር ስለሚገባን፣ የበግና የፍየል መንጎቻችንን፣ የቀንድ ከብቶቻችንንም ይዘን እንሄዳለን›› አለ፡፡
\v 10 ፈርዖንም እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እናንተንና ታናናሽ ልጆቻችሁን ስለችሁ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ ነገር ግን ተመልከቱ፣ ክፉ ነገር ዐስባችኋል፡፡
\v 11 ከመካከላችሁ ወንዶች ብቻ ይሂዱና እግዚአብሔርን ያምልኩ፤ የምትፈልጉት ያንን ነውና፡፡›› ከዚያም በኋላ ሙሴና አሮን ከፈርዖን ዘንድ እንዲወጡ ተደረገ፡፡
\s5
\v 12 እግዚአብሔርም ሙሴን፣ ‹‹አንበጣዎች የግብፅን ምድር እንዲወርሩትና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን፣ በምድሩ ያለውን ተክል ሁሉ እንዲበሉት እጅህን በግብፅ ምድር ላይ ዘርጋ›› አለው፡፡
\v 13 ሙሴም በትሩን በግብፅ ምድር ላይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም በዚያ ቀንና ሌሊት ሁሉ የምሥራቅ ነፋስ በምድሩ ላይ እንዲነፍስ አደረገ። ማለዳ ላይ የምሥራቁ ነፋስ አንበጣዎቹን አምጥቶ ነበር።
\s5
\v 14 በግብፅ ምድር ሁሉ ተሠራጩ፤ አገሩንም ሁሉ ወረሩት። እንደዚህ እጅግ የበዙ አንበጣዎች በምድሩ ውስጥ ከዚህ በፊት አልነበሩም፤ ወደፊትም አይኖሩም።
\v 15 ጨለማ እስኪሆን ድረስ የምድሩን ሁሉ ገጽ ሸፈኑት። በምድሩ ላይ ያለውን ማንኛውንም ተክልና ከበረዶው ተርፎ የቀረውን የዛፍ ፍሬ ሁሉ በሉት። በግብፅ ምድር ሁሉ ለምለም ቅጠል ያለው ተክል አልቀረም፤ በመስክም ላይ ምንም ዛፍ አልነበረም።
\s5
\v 16 ሙሴንና አሮንን በፍጥነት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአምላካችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ ላይ ኀጢአት ሠርቻለሁ።
\v 17 እንግዲህ አሁን ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ሞት ከእኔ እንዲያስወግድልኝ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ።”
\v 18 ስለዚህ ሙሴ ከፈርዖን ዘንድ ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
\s5
\v 19 አንበጣዎቹን ለቃቅሞ ወደ ቀይ ባሕር የሚከትታቸውን ብርቱ የምዕራብ ነፋስ አመጣ፤ በግብፅ ግዛት ሁሉ የቀረ አንድም አንበጣ አልነበረም።
\v 20 ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን እስራኤላውያንን አልለቀቃቸውም።
\s5
\v 21 ሙሴን፣ “በግብፅ ምድር ላይ የሚዳስስ ከባድ ጨለማ እንዲሆን እጅህን ወደ ሰማይ ዘርጋ” አለው።
\v 22 እጁን ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ በግብፅም ምድር ሁሉ ለሦስት ቀን ድቅድቅ ጨለማ ሆነ።
\v 23 ቀኖች አንዱ ሌላውን ማየት አልቻለም፤ ከቤቱም የወጣ ማንም የለም። ለእስራኤላውያን ግን በሚኖሩበት ስፍራ ብርሃን ነበራቸው።
\s5
\v 24 ፈርዖን ሙሴን አስጠርቶ፣ “ሂዱ እግዚአብሔርን አምልኩ። ቤተ ሰቦቻችሁም እንኳ ዐብረዋችሁ መሄድ ይችላሉ፤ በጎቻችሁና ከብቶቻችሁ ግን እዚህ መቅረት አለባቸው” አለው።
\v 25 እንዲህ አለው፤ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር እንድንሠዋቸው ለመሥዋዕትና ለሚቃጠል መሥዋዕት እንስሳቱንም ልትሰጠን ይገባል።
\v 26 ከብቶቻችንም ከእኛ ጋር መሄድ አለባቸው፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለማምለክ ልንወስዳቸው ይገባልና ከእነርሱ ሰኮናም እንኳ እዚህ አይቀርም። ምክንያቱም እግዚአብሔርን በምን እንደምናመልከው እዚያ እስክንደርስ ድረስ አናውቅም።”
\s5
\v 27 ግን የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው ፈርዖን ሕዝቡን አልለቀቃቸውም።
\v 28 ሙሴን፣ “ሂድ ከእኔ ዘንድ! ፊቴን እንዳታይ ተጠንቀቅ፤ ፊቴን ባየህበት ቀን ትሞታለህና” አለው።
\v 29 ሙሴም፣ “አንተ ራስህ ተናግረሃል። ፊትህን እንደ ገና አላየውም” አለው።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ አለ፤ “በፈርዖንና በግብፅ ላይ የማመጣው ገና አንድ መቅሠፍት አለ። ከዚያ በኋላ ከዚህ እንድትሄዱ ይፈቅድላችኋል። በመጨረሻ እንድሄድ ሲያደርግም፣ ሙሉ በሙሉ ያባርራችኋል።
\v 2 ወንድና እያንዳንዱ ሴት ከጎረቤቱ ወይም ከጎረቤቱ የብርና የወርቅ ዕቃዎችን ስጡን ብለው እንዲጠይቁ ለሕዝቡ ተናገር።”
\v 3 እስራኤላውያንን ደስ ለማሰኘት ግብፃውያን እንዲነሣሡ አደረገ። ሙሴም በፈርዖን አገልጋዮችና በግብፅ ሕዝብ ዘንድ እጅግ የሚደነቅ ሰው ሆነ።
\s5
\v 4 እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ይህን ተናግሯል፦ ‘እኩለ ሌሊት ላይ በመላው ግብፅ ዐልፋለሁ።
\v 5 ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ ወፍጮ ላይ እስከምትፈጨዋ እስከ ባሪያዪቱ በኵር ልጅና እስከ እንስሳቱ በኵር ሁሉ ድረስ በግብፅ ምድር ያሉ በኵር በሙሉ ይሞታል።
\s5
\v 6 በቀድሞው ጊዜ ያልነበረ እንደገናም የማይደገም ታላቅ ዋይታ በግብፅ ምድር ሁሉ ይሆናል።
\v 7 ሕዝብ ላይ ግን፣ በሰውም ሆነ በእንስሳ ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽም። በዚህም ግብፃውያንንና እስራኤላውያንን የማስተናግድበት መንገድ የተለያየ እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።’
\v 8 እነዚህ አገልጋዮችህ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ ለእኔም ይሰግዳሉ። ‘አንተና ተከታዮችህ ሁሉ ሂዱ! ብለውም ይናገራሉ። ከዚያ በኋላ እወጣለሁ።” ከዚያም ሙሉ ከፈርዖን ዘንድ በትልቅ ቊጣ ወጥቶ ሄደ።
\s5
\v 9 ሙሴን፣ “ፈርዖን እናንተን አይሰማችሁም። ይህም የሆነው ብዙ አስደናቂ ነገሮችን በግብፅ ምድር ላይ እንዳደርግ ነው” አለው።
\v 10 አሮን እነዚህን ድንቆች ሁሉ በፈርዖን ፊት አደረጉ። ነገር ግን እግዚአብሔር የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ፈርዖን የእስራኤል ሕዝብ ከምድሩ እንዲወጡ አልፈቀደም።
\s5
\c 12
\p
\v 1 በግብፅ ምድር ለሙሴና ለአሮን እንዲህ ብሎ ነገራቸው፤
\v 2 ወር ለእናንተ የወሮች መጀመሪያ፣ የዓመቱም የመጀመሪያ ወር ይሁናችሁ።
\s5
\v 3 ጉባኤ ይህን ንገሩ፤ ‘በዚህ ወር ዐሥረኛ ቀን ላይ እያንዳንዳቸው ለራሳቸው አንድ ጠቦት የሚያንስ ከሆነ፣
\v 4 የቅርብ ጎረቤቱ ከቊጥራቸው ጋር የሚመጣጠን ጠቦት ያዘጋጁ። የሚመገቡትን በቂ ሥጋ መውሰድ እንዲችሉ፣ ጠቦቱ ለሁሉም የሚበቃ መሆን አለበት።
\s5
\v 5 ወይም የፍየል ጠቦታችሁ እንከን የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ሊሆን ይገባል። ከበጎቹ ወይም ከፍየሎቹ አንዱን ልትወስዱ ትችላላችሁ።
\v 6 እስከ ወሩ ዐሥራ አራተኛ ወር ድረስ አቆዩአቸው። ከዚያም መላው የእስራኤል ጉባኤ እነዚህን እንስሳት ፀሐይ ስትጠልቅ ይረዷቸው።
\v 7 ከዚያም ከደሙ ጥቂት ውሰዱና ሥጋውን በምትበሉበት ቤት በር መቃንና ጉበን ላይ አድርጉት።
\v 8 በእሳት ከጠበሳችሁት በኋላ፣ በዚያው ሌሊት ከቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ብሉት።
\s5
\v 9 ወይም ቅቅሉን አትብሉት። ይልቁን ከጭንቅላቱ፣ ከእግሮቹና ከሆድ ዕቃው ጋር በእሳት ጠብሳችሁ ብሉት።
\v 10 ድረስ ከሥጋው አንዳችም አታስቀሩ። የተራረፈ ነገር ቢኖር፣ በእሳት ይቃጠል።
\v 11 ወገባችሁን ታጥቃችሁ፣ ጫማችሁን አጥልቃችሁና በትራችሁን በእጃችሁ ይዛችሁ ነው። ተጣድፋችሁ ልትበሉት ይገባል። የእግዚአብሔር ፋሲካ ነው።
\s5
\v 12 በዚያ ሌሊት በግብፅ ምድር ሁሉ ዐልፋለሁ፤ በግብፅ ምድርም የሰውንና የእንስሳትን በኵር በሙሉ እመታለሁ። በግብፅ አማልክት ሁሉ ላይ እፈርድባቸዋለሁ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
\v 13 ደሙ እኔ ወደ እናንተ በቤቶቻችሁ ላይ ምልክት ይሆናል። ደሙንም በማይበት ጊዜ የግብፅን ምድር ስመታ እናንተን ዐልፌአችሁ እሄዳለሁ። ይህ መቅሠፍት በእናንተ ላይ አይመጣም፤ አያጠፋችሁምም።
\v 14 ቀን የእግዚአብሔር በዓል ቀን አድርጋችሁ የምታከብሩት የመታሰቢያ ቀን ይሆንላችኋል። ቀኑን እንድታከብሩት ለእናንተ፣ ለትውልዶቻችሁም ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ይሆናችኋል።
\s5
\v 15 ቀን ቂጣ ትበላላችሁ። በመጀመሪያው ቀን እርሾውን ከቤታችሁ ታስወግዳላችሁ። ከመጀመሪያው ቀን እስከ ሰባተኛው ቀን እርሾ ያለበትን እንጀራ የበላ ሰው ሁሉ ከእስራኤል ይወገድ።
\v 16 በመጀመሪያው ቀን ለእኔ የተቀደሰ ጉባኤ ይደረጋል፤ በሰባተኛውም ቀን እንደዚሁ ያለ ሌላ ጉባኤ ይሆናል። ሁሉም የሚበላውን ከመቀቀል በቀር፣ በእነዚህ ቀኖች ሥራ አይሠራም። የምትሠሩት የምግብ ዝግጅቱን ሥራ ብቻ ነው።
\s5
\v 17 በዓልን አክብሩት ምክንያቱም ሕዝባችሁን ሰራዊት በሰራዊት አድርጌ ከግብፅ ምድር ያወጣሁት በዚህ ቀን ነው። ስለዚህ ይህን ቀን በትውልዶቻችሁ ሁሉ አክብሩት፤ ለእናንተ ቋሚ ሥርዓት ይሆናችኋል።
\v 18 የመጀመሪያ ወር ዐሥራ አራተኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ አንሥቶ፣ እስከ ወሩ ሃያ አንደኛ ቀን ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ቂጣ ትበላላችሁ።
\s5
\v 19 በሰባቱ ቀኖች በቤታችሁ ውስጥ እርሾ መገኘት የለበትም። እርሾ ያለበት እንጀራ የሚበላ እንግዳም ሆነ በምድራችሁ የተወለደ ሰው ከእስራኤል ማኅበረ ሰ ይወገዳል።
\v 20 የተጋገረ አንዳችም መብላት የለባችሁም። የትም ብትኖሩ፣ መብላት የሚገባችሁ እርሾ የሌለበትን ነው።”
\s5
\v 21 በኋላ ሙሴ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ሂዱና ቤተ ሰቦቻችሁን ለመመገብ የሚበቁ ጠቦቶችን ወይም ግልገሎችን መርጣችሁ የፋሲካን በግ ዕረዱ።
\v 22 ጭብጥ የሂሶጵ ቅጠል ያዙና በሳሕን ውስጥ በሚቀመጠው ደም ውስጥ በመንከር፣ የቤታችሁን ጉበን ዐናትና ሁለቱን መቃኖች እርጩ። እስኪነጋ ድረስ ከእናንተ አንድም ከቤቱ አይወጣ።
\s5
\v 23 ለመቅሠፍት እግዚአብሔር ስለሚያልፍ፣ ደሙን በጉበኑ ዐናትና በሁለቱ መቃኖች ላይ ሲያይ፣ በበራፋችሁ ላይ ያልፋል፣ ቀሣፊውም ወደ ቤታችሁ እንዲገባና እናንተን እንዲቀሥፋችሁ አይፈቅድም።
\s5
\v 24 ይህ ሥርዐት ለእናንተም ለልጆቻችሁም የሁልጊዜ ሥርዐት ስለ ሆነ ልታከብሩት ይገባል።
\v 25 ቃል በገባላችሁ መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ ይህን የአምልኮ ሥርዐት ጠብቁት።
\s5
\v 26 ‘ይህ የአምልኮ ሥርዐት ምን ትርጕም አለው? ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ፣
\v 27 እንደዚህ ብላችሁ ልትነግሯቸው ይገባል፤ ‘ይህ የእግዚአብሔር ፋሲካ መሥዋዕት ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ግብፃውያንን ሲቀሥፍ፣ በግብፅ ውስጥ በእስራኤላውያን ቤቶች ዐልፎ ሄዶአል። ቤተ ሰቦቻችንን ነጻ አውጥቷቸዋል።” ከዚያም ሕዝቡ ሰገዱ፣ እግዚአብሔርንም አመለኩት።
\v 28 ሄደው እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዝዛቸው አደረጉ።
\s5
\v 29
እኩለ ሌሊት ላይ በዙፋኑ ላይ ከሚቀመጠው ከፈርዖን በኵር ልጅ ጀምሮ፣ በእስር ቤት ውስጥ እስካለው ሰው በኵር ልጅና እስከ እንስሳት በኵር ሁሉ ድረስ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር የሚገኝን በኵር በሙሉ ቀሠፈ።
\v 30 አገልጋዮቹ ሁሉና ግብፃውያን በሙሉ ሌሊት ላይ ተነሡ። በግብፅ ውስጥ ጕልሕ የልቅሶ ጩኸት ነበረ፤ ሰው ያልሞተበት እንደም ቤት አልነበረምና።
\s5
\v 31 ሙሴንና አሮንን በሌሊት አስጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ተነሡ፤ እናንተና እስራኤላውያን ከሕዝቤ መካከል ውጡ። ማድረግ የምትፈልጉትን እንደ ተናገራችሁ ሂዱ፣ እግዚአብሔርን አምልኩ።
\v 32 እንደ ተናገራችሁት፣ የበግና የፍየል መንጎቻችሁን፣ የቀንድና የጋማ ከብቶቻችሁንም ይዛችሁ ሂዱ፤ እኔንም ባርኩኝ።”
\v 33 እስራኤላውያንን ከአገራቸው ለማባረር በትልቅ ጥድፊያ ላይ ነበሩ፤ “ሁላችንም ማለቃችን ነው” ብለው ነበርና።
\s5
\v 34 ሕዝቡ እርሾ ያልተጨመረበትን ሊጣቸውን ያዙ። የቡሆ እቃዎቻቸውን ቀድሞውኑ በጨርቃቸው አስረው በትከሾቻቸው ተሸክመዋቸዋል።
\v 35 ሕዝብ ሙሴ እንደ ነገራቸው አደረጉ። የወርቅና የብር ዕቃዎችን፣ ልብስም እንዲሰጧቸው ግብፃውያንን ጠየቁ።
\v 36 ደስ ለማሰኘት እግዚአብሔር ግብፃውያንን አነሣሣ። ስለዚህ እስራኤላውያን የጠየቋቸውን ሁሉ ግብፃውያን ሰጧቸው። በዚህ መንገድ፣ እስራኤላውያን ግብፃውያንን በዘበዟቸው።
\s5
\v 37 ከራምሴ በመነሣት ወደ ሱኮት ተጓዙ። ቊጥራቸው ከሕፃናቱና ከሴቶቹ ሌላ ስድስት መቶ ሺሕ ያህል እግረኛ ነበር።
\v 38 እስራኤላዊ ያልሆነ ድብልቅ ሕዝቤም፣ ከበግና ከፍየል፣ እጅግ ብዙ ከሆነ የከብት መንጋ ጋር ዐብሯቸው ሄደ።
\v 39 ከግብፅ ያመጡትን እርሾ ተባርረው ስለ ወጡና ምግብ ማዘጋጀት ስላልቻሉ ነው።
\v 40 እስራኤላውያን በግብፅ ውስጥ የኖሩት አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር።
\s5
\v 41 መቶ ሠላሳው ዓመት ፍጻሜ፣ በዚያው ቀን፣ ሁሉም የእግዚአብሔር ሰራዊት ከግብፅ ምድር ወጣ።
\v 42 ሌሊት እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር እንዲያወጣቸው ለእስራኤላውያን ነቅቶ የመቆያ ሌሊት ነበር። ይህ ሌሊት እስራኤላውያን ሁሉ፣ መላ ትውልዶቻቸው ሊያከብሩት የሚገባ ሌሊት ነው።
\s5
\v 43 እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤ “የፋሲካ ሕግ እነሆ፦ ባዕድ ሰው ፋሲካን አይበላውም።
\v 44 የተገዛ እያንዳንዱ የእስራኤል ባሪያ ግን ከገረዛችሁት በኋላ መብላት ይችላል።
\s5
\v 45 ቅጥር አገልጋዮች መብላት አይገባቸውም።
\v 46 ምግቡ በአንድ ቤት ውስጥ መበላት አለበት። ሥጋ ከቤት ማውጣት፣ ዐጥንትም መስበር የለባችሁም።
\s5
\v 47 የእስራኤል ማኅበረ ሰብ በዓሉን ሊያከብር ይገባል።
\v 48 ባዕድ ሰው ከእናንተ ጋር ቢኖርና ፋሲካን ለእግዚአብሔር ለማክበር ቢፈልግ፣ ወንድ ዘመዶቹ ሁሉ መገረዝ አለባቸው። ከዚያም በኋላ፣ ሰውየው መምጣትና በዓሉን ማክበር ይችላል። በምድሩ እንደ ተወለዱት ሰዎች ይሆናል። ይሁን እንጂ፣ ያልተገረዘ ሰው የፋሲካን ምግብ አይበላም።
\s5
\v 49 አንድ ዐይነት ሕግ ተግባራዊ የሚሆነው በሁለቱም ማለት በአገሬው ተወላጅና በመካከላችሁ በሚኖረው ባዕድ ሰውም ላይ ነው።”
\v 50 እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዛቸው አደረጉ።
\v 51 በዚያው ቀን እግዚአብሔር እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብፅ ምድር አወጣቸው።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 2 ‘በእስራኤላውያን ዘንድ ከሰውም ሆነ ከእንስሳት በመጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ። በኵር የእኔ ነው።”
\s5
\v 3 ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጣችሁበትን ይህን ቀን አስታውሱት፤ በዚህ ቀን እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከዚህ ስፍራ አውጥቶአችኋልና። እርሾ ያለበት ምግብ አይበላም።
\v 4 በዚህ ቀን፣ በአቢብ ወር ከግብፅ ወጥቷችኋል።
\v 5 ለእናንተ ለመስጠት ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው፣ ወደ ከነዓናውያን፣ ኬጢያውያን፣ አሞራውያን፣ ኤውያውያን፣ ኢያቡሳውያን ምድር እግዚአብሔር ሲያስገባችሁ፣ ይህን አምልኮ በዚህ ወር ትፈጽማላችሁ።
\s5
\v 6 ቀን ቂጣ ትበላላችሁ፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔርን የምታከብሩበት በዓል ይሆናል።
\v 7 ቀን ሁሉ መበላት ያለበት ቂጣ ነው፤ እርሾ ያለበት እንጀራ በእናንተ ዘንድ መታየት የለበትም። በአዋሳኞቻችሁም ዘንድ እርሾ አይኑር።
\s5
\v 8 ቀን፣ ‘ይህ እንዲህ የሚሆነው ከግብፅ ስወጣ እግዚአብሔር ለእኔ ካደረገው የተነሣ ነው’ ብላችሁ ለልጆቻችሁ ትነግሯቸዋላችሁ።’
\v 9 ይህም በእጃችሁና በግንባራችሁ ላይ መታሰቢያ ይሆናል። ይኸውም እግዚአብሔር በብርቱ እጁ ከግብፅ ስላወጣችሁ፣ የእግዚአብሔር ሕግ በአፋችሁ እንዲሆን ነው።
\v 10 ይህን ሕግ በየዓመቱ በተወሰነለት ጊዜ ልትጠብቁት ይገባል።
\s5
\v 11 ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በማለው መሠረት፣ እግዚአብሔር ወደ ከነዓናውያን ምድር ሲያስገባችሁ፣
\v 12 በመጀመሪያ የተወሰደውን፣ የእንስሶቻችሁንም በኵር ሁሉ ለእግዚአብሔር ቀድሱ። ወንዶች የእግዚአብሔር ናቸው።
\v 13 ከአህያ በመጀመሪያ የተወለደውን ሁሉ በጠቦት ትዋጁታላችሁ። ካልዋጃችሁት፣ ዐንገቱን ስበሩት። ከወንድ ልጆቻችሁ መካከል በኵር የሆኑትን ሁሉ ዋጇቸው።
\s5
\v 14 ልጅህ፣ ‘ይህ ምን ማለት ነው? ብሎ ወደፊት ቢጠይቅህ፣ እንደዚህ ትነግረዋለህ ‘ከባርነት ቤት፣ ከግብፅ እግዚአብሔር ያወጣን በብርቱ እጅ ነበር።
\v 15 እኛን ለመልቀቅ በግትርነት እንቢ ባለ ጊዜ፣ እግዚአብሔር በግብፅ ምድር ያለውን በኵር ሁሉ፣ የሰውንም ሆነ የእንስሳትን በኵር በሙሉ ገደለ። ከእንስሳት ሁሉ በመጀመሪያ የተወለደውን ለእግዚአብሔር የምሠዋውና ከወንድ ልጆችም በኵር የሆነውን የምዋጀውን በዚህ ምክንያት ነው።’
\v 16 ከግብፅ ያወጣን በብርቱ እጅ ነውና፣ ይህ በእጅህና በግንባር ላይ ማስታወሻ ይሆናል።”
\s5
\v 17 ሕዝቡን ሲለቅቃቸው፣ እግዚአብሔር ምንም እንኳ ቅርብ ቢሆንም፣ በፍልስጥኤማውያን ምድር ባለው መንገድ አልመራቸውም። እግዚአብሔር፣ “ሕዝብ ጦርነት ቢያጋጥማቸው፥ ምናልባት ሐሳባቸውን ይለውጣሉ፣ ወደ ግብፅም ይመለሳሉ” ብሎ ነበርና።
\v 18 እግዚአብሔር ሕዝቡን በምድረ በዳው ዙሪያ ውደ ቀይ ባሕር መራቸው። እስራኤላውያን ለውጊያ ተዘጋጅተው ከግብፅ ምድር ወጥተው ሄዱ፣
\s5
\v 19 ሙሴ የዮሴፍን ዐፅም ይዞ ሄደ፤ ምክንያቱም ዮሴፍ፣ “እግዚአብሔር በእርግጥ ይታደጋችኋልና ዐፅሜን ይዛችሁ እንድትሄዱ” በማለት እስራኤላውያንን አስምሎአቸው ነበር።
\v 20 ከሱኮት በመጓዝ ምድረ በዳው ዳር ላይ በሚገኘው በአታም ሰፈሩ።
\v 21 እግዚአብሔር ሕዝቡን በመንገድ ላይ ሊመራቸው ቀን ቀን በደመና ዐምድ በፊታቸው ሄደ። ሌሊት ሌሊት ደግሞ ብርሃን ሊሰጣቸው በእሳት ዐምድ ሄደ። በዚህ ዐይነት ሕዝቡ በቀንም በሌሊትም መጓዝ ቻሉ።
\v 22 እግዚአብሔር የቀኑን የደመና ዐምድ ወይም የሌሊቱን የብርሃን ዐምድ ከሕዝቡ ፊት አላነሣም።
\s5
\c 14
\p
\v 1 ለሙሴ እንዲህ ብሎ ተናገር፤
\v 2 በሚግዶልና በባሕሩ መካከል ባለው በፊሀሒሮት ፊት፣ በበኣልዛፎንም አንጻር እንዲሰፍሩ ለእስራኤላውያን ንገር። በፊሀሒሮት ትይዩ በባሕሩ አጠገብ ትሰፍራላችሁ።
\v 3 ፈርዖን ስለ እስራኤላውያን፣ ‘በምድሪቱ እየተንከራተቱ ነው፤ ምድረ በዳውም ዘግቶባቸዋል’ ይላል።
\s5
\v 4 የፈርዖንን ልብ እኔ አደነድነዋለሁ፤ እርሱም እስራኤላውያንን ይከታተላቸዋል። በፈርዖንና በመላው ሰራዊቱ ምክንያት እኔ እከብራለሁ። ግብፃውያን እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።” ስለዚህ እስራኤላውያን በተነገራቸው መሠረት ሰፈሩ።
\v 5 ንጉሥ እስራኤላውያን እንደ ሄዱ ሲነገረው፣ ፈርዖንና አገልጋዮቹ ሐሳባቸውን በመለወጥ፣ እስራኤላውያን ለእኛ ከመሥራት ነጻ ሆነው እንዲሄዱ መፍቀዳችን ምን ማድረጋችን ነው? አሉ።
\s5
\v 6 ሠረገላዎቹ እንዲዘጋጁለት አደረገ፤ ሰራዊቱንም ከእርሱ ጋር ይዞ ሄደ።
\v 7 መቶ ምርጥ ሠረገሎችንና የግብፅን ሌሎች ሠረገሎች በሙሉ፣ በያንዳንዳቸው ላይ መኮንኖች ያሉባቸውን ይዞ ተንቀሳቀሰ።
\v 8 እግዚአብሔር የግብፅን ንጉሥ፣ የፈርዖንን ልብ ስላደነደነው፣ ንጉሡ እስራኤላውያንን ተከታተላቸው። አሁን እስራኤላውያን በድል ወጥተው ሄደዋል።
\v 9 ነገር ግን ግብፃውያን፣ ሁሉም የፈርዖን ፈረሶችና ሠረገሎች፣ የፈርዖን ፈረሰኞችና ሰራዊቱ እስራኤላውያንን አሳደዷቸው። በበኣልዛፎን አንጻር በባሕሩ አጠገብ ፊሀሒሮት ጥግ ሰፍረው እንዳሉ ደረሱባቸው።
\s5
\v 10 ፈርዖን በቀረ ጊዜ፣ እስራኤላውያን ወደ ላይ ተመለከቱ፣ ተደነቁም። ግብፃውያን ከኋላ እየተከተሏቸው ነበርና ፈሩ። እስራኤላውያን ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
\v 11 እንዲህ አሉት፤ “እዚህ ያመጣኸንና በምድረ በዳ እንድንሞት ያደረግኸው በግብፅ መቃብር ታጥቶ ይህን ነግረንህ አልነበረምን?
\v 12 ሠራተኞች እንድንሆን ተወን’ ብለንህ ነበር። በምድረ በዳ ከምንሞት፣ ለእነርሱ ሠራተኞች ሆነን ብንቀር ይሻል ነበር።’”
\s5
\v 13 እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ። ጸንታችሁ ቁሙና ዛሬ እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርግላችሁን ትድግና ታያላችሁ። ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ዳግም አታዩአቸውም።
\v 14 እግዚአብሔር ለእናንተ ይዋጋል፤ እናንተ መታገሥ ብቻ ነው ያለባችሁ።”
\s5
\v 15 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሙሴ ለምን ትጮኽብኛለህ? እስራኤላውያን ወደ ፊት እንዲሄዱ ንገራቸው።
\v 16 የእስራኤል ስዎች በባሕሩ ውስጥ በደረቅ መሬት እንዲሻገሩ በትርህን አንሣና እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርግተህ ለሁለት ክፈለው።
\v 17 ተከትለዋቸው እንዲገቡ እኔ የግብፃውያንን ልብ የማደነድን መሆኔን ዕወቅ። ከፈርዖንና ከሰራዊቱ ሁሉ፣ ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ የተነሣ እኔ እከብራለሁ።
\v 18 በፈርዖን፣ ሠረገሎቹና በፈረሰኞቹ ምክንያት ክብርን ሳገኝ፣ ግብፃውያኑ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
\s5
\v 19 ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ በስተ ኋላቸው ሄደ። የደመናውም ዐምድ ከፊታቸው ተንቀሳቅሶ በስተኋላቸው ሄዶ ቆመ።
\v 20 በግብፅ ሰራዊትና በእስራኤል መካከል መጣ። ለግብፃውያን የጨለማ ደመና ሲሆን፣ ለእስራኤላውያን ግን ሌሊቱን ብሩህ ያደረገ ደመና ነበር፤ ይህም ሌሊቱን ሙሉ አንደኛው ወገን ወደ ሌላው እንዳይጠጋ አደረገ።
\s5
\v 21 እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ። እግዚአብሔርም በዚያ ሌሊት ባሕሩን በብርቱ የምሥራቅ ነፋስ ወደ ኋላ እንዲሄድ በማድረግ ባሕሩን ደረቅ መሬት አደረገው። በዚህ መንገድ ውሃው ተከፈለ።
\v 22 እስራኤላውያን በባሕሩ መካከል ገብተው በደረቅ መሬት ዐለፉ። ውሃው በቀኛቸውና በግራቸውና በኩል ግድግዳ ሆነላቸው።
\s5
\v 23 ተከታትለዋቸው መጡ። እነርሱ፣ የፈርዖን ፈረሶች ሠረገሎችና ፈረሰኞች ሁሉ እስራኤላውያኑ ተከትለው በባሕሩ መካከል ገቡ።
\v 24 ላይ እግዚአብሔር በእሳቱና በደመናው ዐምድ ውስጥ የግብፃውያንን ሰራዊት ወደ ታች ተመለከተ። በግብፃውያን መካከልም ሽብር እንዲፈጠር አደረገ።
\v 25 የሠረገሎቻቸው መንኯራኵሮች ተቆላለፉ፤ ፈረሰኞችም ለመንቀሳቀስ እጅግ ተቸገሩ። ስለዚህ ግብፃውያኑ፣ እግዚአብሔር እኛን እየወጋላቸው ነውና፣ ከእስራኤል እንሽሽ” አሉ።
\s5
\v 26 ሙሴን፣ “ውሃው በግብፃውያኑ፣ በሠረገሎቻቸውና በፈረሰኞቻቸው ላይ ተመልሶ እንዲመጣባቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ” አለው።
\v 27 እጁን በባሕሩ ላይ ዘረጋ፤ ንጋት ላይም ባሕሩ ወደ ተለመደ ስፍራው ተመለሰ። ግብፃውያኑ ከባሕሩ ሸሹ፤ እግዚአብሔር ግን ወደ ባሕሩ መካከል አስገባቸው።
\v 28 ውሃው ተመስሎ በመምጣት የፈረዖንን ሠረገሎች፣ ፈረሰኞችን ሠረገሎቹን ተከትለው ወደ ባሕሩ የገቡትን ጠቅላላ ሰራዊቱን ሸፈናቸው። አንድም ሳይሰምጥ የቀረ አልነበረም።
\s5
\v 29 ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ላይ ተራምደው ሄዱ። ውሃው በቀኛቸውም በግራቸውም በኩል ለእነርሱ ግድግዳ ሆናላቸዋል።
\v 30 እግዚአብሔር በዚያ ቀን እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ ታደጋቸው፤ እስራኤላውያኑም የግብፃውያኑን ሬሳ በባሕሩ ዳር አዩ።
\v 31 እግዚአብሔር በግብፃውያኑ ላይ የገለጠውን ታላቅ ኀይል ሲያዩ፣ ሕዝቡ እግዚአብሔርን አከበሩ፣ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴም ታመኑ።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ጊዜ ሙሴና የእስራኤል ሕዝብ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል።
\s5
\v 2 ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ ድነቴም ሆኖልኛል። እርሱ አምላኬ ነው፣ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴ አምላክ ነው፣ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።
\v 3 ተዋጊ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 4 ሠረገሎችና ሠራዊት በባሕር ውስጥ ጥሎአል። የፈርዖን ምርጥ መኮንኖች በቀይ ባሕር ውስጥ ሰመጡ።
\v 5 ማዕበሎቹ ሽፈናቸው፤ እንደ ድንጋይ ወደ ጥልቆቹ ወረዱ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ሆይ፣ ቀኝ እጅህ ጠላትን ሰባበረ።
\v 7 ላይ የተነሡትን በታላቅ ግርማ ገለበጥሃቸው። ቊጣህን ላክህ፤ እንደ ገለባም አርጎ በላቸው።
\v 8 በአፍንጫህ እስትንፋስ ውሆች ተከመሩ፤ ፈሳሾች እንደ ክምር ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ በባሕሩ ውስጥ ረጋ።
\s5
\v 9 ጠላት፣ ‘አሳድዳቸዋለሁ፣ እይዛቸዋለሁ፣ ምርኮም እካፈላለሁ፤ ፍላጎቴ በእነርሱ ርዳታ ያገኛል፤ ሰይፌን እመዝዛለሁ፤ እጄም ታጠፋቸዋለች’ አለ።
\v 10 ግን በነፋስህ እፍ አልህ፣ ባሕሩም ሸፈናቸው፤ በኀይለኛ ውሆች ውስጥ እንደ ብረት ሰመጡ።
\v 11 ሆይ፣ ክአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና የከበረ፣ ተአምራትን በማድረግ በምስጋና ከፍ ያለ፣ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?
\s5
\v 12 እጅህን ዘረጋህ፤ ምድርም ዋጠቻቸው።
\v 13 ፍቅርህ የታደግሃቸውን ሕዝብህን መራህ። በብርታትህ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ መራሃቸው።
\s5
\v 14 ይሰማሉ፣ ይንቀጠቀጣሉም፤ የፍልስጥኤምን ኗሪዎች ሽብር ይይዛቸዋል።
\v 15 ጊዜ የኤዶም እለቆች ይደነግጣሉ፤ የሞዓብ መሪዎች ይርበደበዳሉ፤ የከነዓን ኗሪዎች ሁሉ ይቀልጣሉ።
\s5
\v 16 ሆይ፣ ሕዝብህ እስከሚያልፉ፣ የታደግሃቸው ሕዝብህ ዐልፈው እስከሚሄዱ ድረስ፣ ሽብርና ድንጋቴ ይወድቅባቸዋል፤ ከክንድህ ብርታት የተነሣ፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
\s5
\v 17 ሆይ፣ ማደሪያህ ባደረግኸው ስፍራ፣ ጌታችን ሆይ፣ እጆችህ በሠሩት መቅደስ፣ በርስትህ ተራራ ላይ ሕዝብህን ታመጣቸዋለህ፣ ትተክላቸዋለህም።
\v 18 ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል።”
\s5
\v 19 ፈረሶች ከሠረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕሩ ውስጥ ሲገቡ፣ እግዚአብሔር የባሕሩን ውሀ መልሶ በላያቸው አመጣባቸው። እስራኤላውያን ግን በባሕሩ መካከል በደረቅ መሬት ሄዱ።
\v 20 ይአሮን እኅት፣ ነቢይቱ ማርያም ከበሮ አነሣች፤ ሌሎቹ ሴቶችም በሙሉ ከበሮ ይዘው ከእርሷ ጋር እያሸበሸቡ ወጡ።
\v 21 “ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ውስጥ ጥሎአል፤ በክብር ከፍ ከፍ ብሎአልና፣ ለእግዚአብሔር ዘመሩ” እያለች ዘመረችላቸው።
\s5
\v 22 ሙሴ እስራኤላውያንን ከቀይ ባሕር እየመራቸው ወደ ሱር ምድረ በዳ ሄዱ። በምድረ በዳው ውስጥ ሦስት ቀን ሲጓዙ ውሀ አላገኙም።
\v 23 ማራም ደረሱ፤ ነገር ግን እዚያ የሚገኘው ውሀ መራራ ስለ ነበረ ሊጠጡት አልቻሉም። ቦታውን ማራ ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው።
\s5
\v 24 ሕዝቡ፣ “ምን እንጠጣ? ” ብለው በሙሴ ላይ አጕረመረሙ።
\v 25 ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፣ እግዚአብሔርም አንድ ዛፍ አሳየው። ሙሴም የዛፉን ዕንጨት ወደ ውሀው ውስጥ ጣለው፣ ውሀውም ጣፋጭ ሆነ። እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሕግና ሥርዐት የሰጣቸውና የፈተናቸው በዚያ ስፍራ ነበር።
\v 26 እንዲህ አለ፤ “የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፥ ትክክለኛ የሆነውንም በፊቱ ብታደርጉ፣ ትእዛዛቱንም ብታስተውሉና ሕግጋቱን ሁሉ ብትጠብቁ፣ ግብፃውያን ላይ ካመጣኋቸው በሽታዎች አንዱንም በእናንተ ላይ አላመጣም፤ እኔ ፈዋሻችሁ እግዚአብሔር ነኝና።”
\s5
\v 27 በኋላ ሕዝቡ ዐሥራ ሁለት ምንጮችና ሰባ የዘንባባ ዛፎች ወደ ነበሩበት ወደ ኤሊም መጡ። በዚያም በውሀው አጠገብ ሰፈሩ።
\s5
\c 16
\p
\v 1 የእስራኤል ማኅበር አባላት ከኤሊም ተንሥተው፣ ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ወር ዐሥራ አምስተኛ ቀን በኤሊምና በሲና መካከል ወዳለው ወደ ሲን ምድረ በዳ መጡ።
\v 2 በዳው ውስጥም ጠቅላላ የማኅበሩ አባላት በሙሴና በአሮን ላይ አጕረመረሙ።
\v 3 ሙሴንና አሮንንም፣ “በሥጋ ምንቸቶች ዙሪያ ተቀምጠን እስክንጠግብ ምግብ በምንበላበት በግብፅ ምድር በእግዚአብሔር እጅ ምነው በሞትን ኖሮ፤ ከዚያ አውጥታችሁ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁን መላውን ማኅበራችንን በረኃብ ልትጨርሱ ነውና” አሏቸው።
\s5
\v 4 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንጀራ ከሰማይ አዘንብላችኋለሁ። በሕጌ የሚመሩ ወይም የማይመሩ መሆናቸውን እንድፈትናቸው፣ ሕዝቡ ይውጡና በየቀኑ ለአንድ ቀን የሚሆነውን ይሰብስቡ።
\v 5 ቀን በየቀኑ ከሚሰበስቡት ዕጥፍ ይሰብስቡ፤ ያመጡትንም ያዘጋጁ።”
\s5
\v 6 ከዚያም ሙሴና አሮን ለእስራኤል ሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አሉ፤ “ከግብፅም ምድር ያወጣችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ማታ ታውቃላችሁ።
\v 7 በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶአልና፣ የእግዚአብሔርንም ክብር ጠዋት ታያላችሁ። በእኛ ላይ ልታጕረመርሙ እኛ ለእናንተ ምንድን ነን? ”
\v 8 ደግሞ እንዲህ አለ፤ በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶታልና፣ እግዚአብሔር ማታ ሥጋ፣ ጠዋትም ምግብ እስክትጠግቡ ሲሰጣችሁ፣ ይህን ታውቁታላችሁ። አሮንና እኔ ምንድን ነን? የምታጕረመርሙት በእኛ ላይ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ ነው።”
\s5
\v 9 ሙሴ አሮንን፣ “‘ጕርምርምታችሁን ሰምቶታልና ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ’ በልህ ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ ተናገር’” አለው።
\v 10 አሮን ለእስራኤል ሕዝብ ማኅበር ሁሉ እንደ ተናገረ፣ ወደ ምድረ በዳው ተመለከቱ፤ እነሆም፣ የእግዚአብሔር ክብር በደመናው ውስጥ ታየ።
\v 11 እግዚአብሔርም ለሙሴ እንዲህ ብሎ ነገረው፤
\v 12 “የእስራኤልን ሕዝብ ጕርምርምታ ሰምቻለሁ። እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ማታ ሥጋ ትበላላችሁ፤ ጠዋት ደግሞ እንጀራ ትበሉና ትጠግባላችሁ። ከዚያም በኋላ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።
\s5
\v 13 ላይ ድርጭቶች መጡና ሰፈሩን ሸፈኑት። በጠዋቱም የሰፈሩን ዙሪያ ጤዛ ተኝቶበታል።
\v 14 ሲጠፋ፣ እንደ ዐመዳይ ያለ ስስ ቅርፊት በምድረ በዳው ላይ ታየ።
\v 15 ሰዎች ሲያዩት፣ አንዳቸው ለአንዳቸው፣ “ምንድን ነው? ” ተባባሉ። ምን እንደ ነበረ አላወቁም። ሙሴም እንዲህ አላቸው፤ “ይህ እንድትበሉት እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶአል፦ ‘ለመብላት የምትፈልጉትን መጠን በሕዝባችሁ ቊጥር ለያንዳንዱ ሰው አንድ ጎሞር ሰብስቡ። የምትሰበስቡት እንደዚህ ነው፦ በድንኳናችሁ ውስጥ ለሚኖር ለእያንዳንዱ ሰው ለመብላት የሚበቃውን ሰብስቡ።”
\v 17 የተነገራቸውን አደረጉ። አንዳንዶች የበለጠ፣ አንዳንዶችም ያነሰ ሰበሰቡ።
\v 18 በጎሞር መጠን ሲለኩት፣ ብዙ የሰበሰቡት የተረፈ አላገኙም፤ ትንሽ የሰበሰቡትም ያጡትናየጎደለባቸው አልነበረም። እያንዳንዱ ሰው የሰበሰበው ለፍላጎቱ የሚበቃውን ያህል ነበር።
\s5
\v 19 “ማንም ሰው ለነገ ከእርሱ ምንም ማስተረፍ የለበትም” አላቸው።
\v 20 ግን ሕዝቡ ሙሴን አልሰሙትም። አንዳንዶቻቸው ከሰበሰቡት እስከሚቀጥለው ጠዋት የተወሰነ አስቀሩ፤ ያስቀሩት ምግብ ግን ተላ፣ ሸተተም። ሙሴ ተቆጣቸው።
\v 21 የሰበሰቡት ጠዋት ጠዋት ነበር። እያንዳንዱ ሰው ለቀኑ የሚበቃውን ሰበሰበ። ፀሐይ ስትሞቅ ቀለጠ።
\s5
\v 22 ቀን ለያንዳንዱ ሰው ሁለት ሁለት ጎሞር እንጀራ አድርገው ዕጥፍ ሰበሰቡ። የማኅበረ ሰቡ አለቆችም በሙሉ መጥተው ለሙሴ ነገሩት።
\v 23 “እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘ነገ ፍጹም ዕረፍት፣ ለእግዚአብሔር ክብር የተቀደሰ ሰንበት ነው። መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትንም ቀቅሉ። ተርፎ የሚቀረውን ሁሉ እስከ ጠዋት ለራሳችሁ አስቀምጡት’” አላቸው።
\s5
\v 24 የተረፈውን ሙሴ በነገራቸው መሠረት እስከ ጠዋት አቆዩት። አልሸተተም፤ ትልም አልነበረበትም።
\v 25 እንዲህ አለ፤ “ዛሬ እግዚአብሔርን ለማክበር የተቀደሰ ሰንበት ነውና፣ ያስተረፋችሁትን ያን ምግብ ዛሬ ብሉት። ዛሬ ሜላ ላይ አታገኙትም።
\s5
\v 26 ቀኖች ትሰበስቡታላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን የሰንበት ቀን ነው። በሰንበት ቀን መና የለም።”
\v 27 ቀን አንዳንዶች መና ሊሰበስቡ ወጡ፣ ነገር ግን ምንም አላገኙም።
\s5
\v 28 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ትእዛዛቴንና ሕገጋቴን ለመጠበቅ እንቢ የምትሉት እስከ መቼ ነው?
\v 29 በሉ፤ እግዚአብሔር ሰንበትን ሰጥቶአችኋል። ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሰጣችሁ ለሁለት ቀን የሚሆን እንጀራ ነው። ከእናንተ እያንዳንዱ በገዛ ስፍራው ይቆይ፤ በሰባተኛው ቀን ማንም ሰው ከስፍራው መውጣት የለበትም።”
\v 30 በሰባተኛው ቀን ዐረፉ።
\s5
\v 31 ምግቡን “መና” ብለው ጠሩት። ምግቡም እንደ ድንብላል ዘር ነጭ፣ ጣዕሙም በማር በስሱ እንደ ተጋገረ ቂጣ ነበረ።
\v 32 ሙሴም፣ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፦ ‘ከግብፅ ምድር ካወጣኋችሁ በኋላ በምድረ በዳ ያበላኋችሁን እንጀራ ልጆቻችሁ ማየት እንዲችሉ፣ አንድ ጎመር መና ለትውልዶቻችሁ ሁሉ ይቀመጥ” አለ።
\s5
\v 33 አሮንን፣ “አንድ ማሰሮ ውሰድና አንድ ጎሞር መና አስቀምጥበት፤ ለትውልዶች ሁሉ ተጠብቆ እንዲቆይም በእግዚአብሔር ፊት አስቀምጠው” አለው።
\v 34 ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ አሮን መናውን በምስክሩ ፊት አስቀመጠው።
\v 35 ወደሚኖሩበት ምድር እስከሚመጡ ድረስ አርባ ዓመት መና በሉ። ወደ ከነዓን ምድር ድንበር እስከሚመጡ ድረስ የተመገቡት እርሱን ነው።
\v 36 አንድ ጎመር የኢፍ አንድ ዐሥረኛ ነው።
\s5
\c 17
\p
\v 1 የእስራኤል ማኅበር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመከተል ከሲን ምድረ በዳ ተነሡ፤ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሀ አልነበረም።
\v 2 ሕዝቡ ሙሴን ወቀሡት፤ “የምንጠጣው ውሀ ስጠን” ብለውም ተናገሩት። ሙሴም፣ “ለምን እኔን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ? ” አላቸው።
\v 3 ያ ሕዝቡ ውሀ በጣም ጠምቷቸው ስለ ነበር በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እንዲህም አሉት፤ “እኛንና ልጆቻችንን፣ ከብቶቻችንንም በውሀ ጥም ለመፍጀት ከግብፅ ለምን አወጣኸን?”
\s5
\v 4 እነዚህን ሰዎች ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” በማለት ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።
\v 5 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከእስራኤል ሽማግሌዎች አንዳንዶችን፣ ወንዙን የመታህበትንም በትር ያዝና ከሕዝቡ ፊት ቀድመህ ሂድ።
\v 6 ኮሬብ ባለው ዐለት ላይ እኔ ከፊትህ እቆማለሁ፤ ዐለቱንም ትመታዋለህ። ከእርሱም ሕዝቡ የሚጠቱት ውሀ ይወጣል።” ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት የታዘዘውን አደረገ።
\v 7 ስላጕረመረሙና “እግዚአብሔር በመካከላችን አለ ወይስ የለም? ” በማለት እግዚአብሔርን ስለ ተፈታተኑት ያን ስፍራ ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው።
\s5
\v 8 መጥተው እስራኤልን ራፊዲም ላይ ወጉ።
\v 9 ስለዚህም ሙሴ ኢያሱን፣ “ጥቂት ሰዎችን ምረጥና ውጣ፤ ከአማሌቃውያን ጋርም ተዋጋ። ነገ እኔ የእግዚአብሔን በትር ይዤ በኮረብታው ዐናት ላይ እቆማለሁ” አለው።
\v 10 ሙሴ ባዘዘው መሠረት አማሌቃውያን ተዋጋቸው፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኮረብታው ዐናት ወጡ።
\s5
\v 11 እጁን ወደ ላይ ሲያነሣ፣ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር፤ እጁን ሲያወርድ ግን አማሌቃውያን ለማሸነፍ ይጀምሩ ነበር።
\v 12 የሙሴ እጆች እየደከሙ ሲሄዱ፣ አሮንና ሖር ድንጋይ ወስደው እንዲቀመጥበት ከእርሱ ሥር አስቀመጡለት። በዚያውም ጊዜ አሮንና ሖር አንዳቸው በአንድ ጎኑ፣ የቀረውም በሌላው ጎኑ በኩል በመሆን የሙሴን እጆች ወደ ላይ ደግፈው ያዙ። የሙሴ እጆችም ፀሐይ እስክትገባ ድረስ ጠንክረው ቆዩ።
\v 13 ስለዚህም ኢያሱ አማሌቃውያንን በሰይፍ ድል አደረጋቸው።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “የአማሌቃውያንን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ሙሉ በሙሉ ስለምደመስስ፣ ይህን በመጽሐፍ ጽፈህ ኢያሱ እየሰማ አንብበው” አለው።
\v 15 ሙሴም መሠዊያ ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር አርማዬ ነው” ብሎ ሰየመው።
\v 16 “እጅ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተነሥቶአልና፣ እግዚአብሔር በአማሌቃውያን ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ጦርነት ያደርጋል” አለ።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ካህን፣ የሙሴ ዐማት ዮቶር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ሰማ። እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከግብፅ ያወጣቸው መሆኑን ዮቶር ሰምቶ ነበር።
\v 2 ሙሴ ወደ ቤት ከመለሳት በኋላ፣ የሙሴ ዐማት ዮቶር የሙሴን ሚስት ሲፓራን፣
\v 3 ምድር ባዕድ ነበርሁ” ሲል ጌርሳም ብሎ የጠራውንና ሌላውንም ልጅ ተቀብሏቸው ነበር።
\v 4 “የአባቶቼ አምላክ ረድቶኛል፤ ከፈርዖንም ሰይፍ አድኖኛል” ብሎ ነበርና፣ የሌላው ልጁ ስም አልዓዛር ነው።
\s5
\v 5 ዐማት ዮቶር ከሙሴ ልጆችና ከሚስቱ ጋር በምድረ በዳው ውስጥ በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ ሰፍሮ ወደ ነበረው ወደ ሙሴ መጣ።
\v 6 ሙሴን፣ “እኔ ዐማትህ፣ ዮቶር ከሚስትህና ከልጆችህ ጋር ወደ አንተ እየመጣሁ ነው” አለው።
\s5
\v 7 ዐማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ ሰገደ፤ ሳመውም። ስለ እያንዳንዳቸው ደኅንነት ተጠያይቀው ወደ ድንኳኑ ውስጥ ገቡ።
\v 8 ሙሴም እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ሲል በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ያደረገውን በሙሉ፣ በመንገድም በእነርሱ ላይ የደረሰባቸውን ችግር ሁሉና እግዚአብሔር እንዴት እንደታደጋቸው ለዐማቱ ነገረው።
\s5
\v 9 ዮቶር እስራኤላውያንን ከግብፃውያን እጅ በመታደግ እግዚአብሔር ባደረገው መልካም ነገር ሁሉ ተደሰተ።
\v 10 እንዲህ አለ፤ “ከግብፃውያን እጅና ከፈርዖን እጅ አድኖአችኋል፤ ሕዝቡንም ከግብፃውያን እጅ ታድጎአቸዋልና እግዚአብሔር ይመስገን።
\v 11 እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ ታላቅ እንደ ሆነ አሁን ዐውቃለሁ፤ ምክንያቱም ግብፃውያን እስራኤላውያንን በትዕቢት ይዘዋቸው በነበረ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን ታድጎአል።”
\s5
\v 12 ዐማት ዮቶር የሚቃጠል መሥዋዕቶችን ለእግዚአብሔር አቀረበ። አሮንና የእስራኤል አለቆች ሁሉ ከሙሴ ዐማት ጋር በእግዚአብሔር ለመብላት መጡ።
\s5
\v 13 በሚቀጥለው ቀን ሙሉ ሕዝቡን ሊዳኝ ተቀመጠ። ሕዝቡ ከጠዋት እስከ ማታ ድረስ በእርሱ ዙሪያ ቆሙ።
\v 14 የሙሴ ዐማት ሙሴ ለሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ተመልክቶ፣ “ምን እያደረግህ ነው? ብቻህን ለምን ትቀመጣለህ? ሰዎችስ ሁሉ ከጧት እስከ ማታ ድረስ ለምን በአንተ ዙሪያ ይቆማሉ? ” አለው።
\s5
\v 15 ዐማቱን እንዲህ አለው፤ “ሰዎቹ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ።
\v 16 ሲኖራቸው፣ ወደ እኔ ይመጡና በመካከላቸው ላለው ችግር ውሳኔ እሰጣለሁ፤ የእግዚአብሔርን ሕገጋትና ሥርዐትም አስተምራቸዋለሁ።”
\s5
\v 17 ዐማቱም ሙሴን መልሶ እንዲህ አለው፤ “የምታደርገው ተገቢ አይደለም።
\v 18 ዐብረውህ ያሉ ሰዎች በእውነት ራሳችሁን ታደክማላችሁ። ይህ ለአንተ ከባድ ሸክም ነው። ይህን ተግባር ብቻህን ማከናወን አትችልም።
\v 19 ስማኝ። ምክር እሰጥሃለሁ፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ ምክንያቱም አንተ በእግዚአብሔር ፊት የሕዝቡ ወኪል ነህ፤ አቤቱታቸውንም ወደ እግዚአብሔር ታቀርባለህ።
\v 20 ሥርዐታትና ሕገጋት ልታስተምራቸው፣ የሚሄዱበትን መንገድና የሚሠሩትን ሥራም ልታሳያቸው ይገባል።
\s5
\v 21 እግዚአብሔርን የሚፈሩ ችሎታቸውን፣ ኢፍትሓዊ ጥቅምን የሚጠሉ የእውነት ሰዎችንከሕዝቡ ሁሉ ምረጥ። ዕነርሱን መሪዎች እንዲሆኑ በሕዝቡ ላይ ሸለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች አድርገህ ሹማቸው።
\v 22 ጉዳዮችን ሁሉ በሚመለከት ሕዝቡን የሚዳኙት እነርሱ ይሆናሉ፤ ከባድ ከባድ ጉዳዮችን ግን ወደ አንተ ያቀርባሉ። አነስተኛ ጉዳዮችን ሁሉ በሚመለከት፣ እነርሱ ራሳቸው ውሳኔ ሊሰጡባቸው ይችላሉ። በዚህ መንገድ ሥራው ለአንተ ይቀልልሃል፤ እነርሱም ሸክሙን ከአንተ ጋር ይሸከማሉ።
\v 23 ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም እንደዚሁ እንድታደርግ ቢያዝዝህ፣ በርትተህ መሥራት ትችላለህ፤ መላው ሕዝብም ረክቶ ወደ ቤት መሄድ ይችላል።”
\s5
\v 24 የዐማቱን ምክር በመስማት የነገረውን ሁሉ አደረገ።
\v 25 ሙሴ ከእስራኤል ሁሉ ችሎታ ያላቸውን ሰዎች መረጠ፤ ሸለቆች፣ መቶ አለቆች፣ ዐምሳ አለቆችና ዐሥር አለቆች አድርጎም የሕዝቡ መሪዎች እንዲሆኑ ሾማቸው።
\v 26 በቀላላል ጉዳዮች ሕዝቡን ይዳኙ ነበር። ከበባድ ጉዳዮችን ለሙሴ አቀረቡ፤ ትንንሽ ጉዳዮችን ሁሉ ግን እነርሱ ለራሳቸው ብያኔ ሰጡባቸው።
\v 27 በኋላ ሙሴ ዐማቱን አሰናበተው፤ ዮቶርም ወደ ገዛ ምድሩ ተመልሶ ሄደ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ወር፣ እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡበት በዚያው ቀን ወደ ሲና ምድረ በዳ መጡ።
\v 2 ከራፊዲም ከተነሡ በኋላ፣ ወደ ሲና ምድረ በዳ መጥተው በምድረ በዳው ውስጥ ከተራራው ፊት ለፊት ሰፈሩ።
\s5
\v 3 ወደ እግዚአብሔር ወጣ። እግዚአብሔርም ከተራራው ጠርቶት እንዲህ አለው፤
\v 4 “ለያዕቆብ ቤት፣ ለእስራኤል ሕዝብ እንደዚህ ብለህ ተናገር፦ በግብፃውያን ላይ ምን እንዳደረግሁ ፣ እናንተንም በርግም ክንፎች እንዴት እንደ ተከከምኋችሁና ወደ ራሴ እንዴት እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።
\v 5 ቃሌን በታዛዥነት ብትሰሙና ኪዳኔንም ብትጠብቁ፣ ከሕዝብ ሁሉ መካከል የእኔ ርስት ትሆናላችሁ፤ ምድር ሁሉ የእኔ ነውና።
\v 6 እናንተ ለእኔ የካህናት መንግሕትና ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው።
\s5
\v 7 መጣ፤ የሕዝቡንም ሽማግሌዎች ጠርቶ እግዚአብሔር ያዘዘውን እነዚህን ቃሎች ሁሉ በፊታቸው ተናገረ።
\v 8 ሁሉ በአንድነት፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉ እናደርጋለን” በማለት መልስ ሰጡ። ሙሴ ሕዝቡ የተናገሩትን ወደ እግዚአብሔር ለማቅረብ መጣ።
\v 9 ሙሴን፤ “እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር፣ መስማት እንዲችሉና አንተንም ሁልጊዜ እንዲያምኑህ፣ ወደ አንተ በከባድ ደመና እመጣለሁ” አለው። ሙሴም ሕዝቡ የተናገሯቸውን ቃሎች ለእግዚአብሔር ነገረው።
\s5
\v 10 ሙሴን፣ “ወደ ሕዝቡ ሂድ። ዛሬና ነገ ለእኔ ቀድሳቸው፤ ልብሳቸውንም እንዲያጥቡ አድርግ።
\v 11 ቀንም ይዘጋጁ፤ በሦስተኛው ቀን እኔ እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ እወርዳለሁና።
\s5
\v 12 ዙሪያ ሁሉ ለሕዝቡ ወሰን አብጅና ለሕዝቡ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም የተራራውን ግርጌ ጫፍ እንዳትነኩ ተጠንቀቁ። ተራራውን የነካ ይሞታል።’
\v 13 ዐይነቱን ሰው ማንም አይንካው። እንዲያውም የነካው በድንጋይ ይወገራል ወይም በቀስታ ይወጋል። ሰውም ሆነ እንስሳ ይሞታል። መለከቱ የማያቋርጥ ድምፅ ሲያሰማ፣ ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት ይችላሉ” አለው።
\s5
\v 14 ሙሴም ከተራራው ወደ ሕዝቡ ወረደ። ሕዝቡን ለእግዚአብሔር ቀደሳቸው፤ ልብሳቸውንም አጠቡ።
\v 15 “በሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ፤ ወደ ሚስቶቻችሁም አትጠጉ” አላቸው።
\s5
\v 16 ቀን ጠዋት ላይ ነጏድጓድና የመብረቅ ብልጭታ፣ ከባድ ደመና እና ጉሉሕ የመለከት ድምፅ በተራራው ላይ ነበሩ። በሰፈሩ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ሁሉ ተንቀጠቀጡ።
\v 17 ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኙ ሕዝቡን ከሰፈር አወጣቸው፤ በተራራው ግርጌም ቆሙ።
\v 18 እግዚአብሔር በእሳትና በጢስ ወርዶበት ስለ ነበረ፣ የሲና ተራራ ሙሉ በሙሉ በጢስ ተሸፈነ። ጢሱ እንደ ምድጃ ጢስ ይወጣ ነበር፤ ጠቅላላ ተራራውም በኀይል ተናወጠ።
\s5
\v 19 ድምፅ እየጨመረና እየጎላ ሲሄድ፣ ሙሴ ተናገረ፤ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት።
\v 20 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ጫፍ ላይ ወርዶ፣ ሙሴን ወደ ተራራው ጫፍ እንዲወጣ ጠራው። ሙሴም ወጣ።
\v 21 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለማየት ዐልፈው ወደ እኔ እንድይመጡ፣ ሂድና ሕዝቡን አስጠንቅቃቸው፤ አለዚያ ብዙዎች ይሞታሉ።
\v 22 ወደ እኔ የሚቀርቡ ካህናትም ራሳቸውን ይቀድሱ፤ እንዳላጠፋቸውም ለእኔ መምጣት ራሳቸውን ያዘጋጁ።”
\s5
\v 23 እግዚአብሔርን፣ “ሕዝቡ ወደ ተራራው መውጣት አይችሉም፤ ምክንያቱም ‘በተራራው ዙሪያ ወሰን አብጅና ለእግዚአብሔር ቀድሰው’ ብለህ አዝዘኸናል” አለው።
\v 24 ሙሴን፣ “ከተራራው ወርደህ ሂድና አሮንን ክአንተ ጋር ይዘኸው ና፤ ካህናቱና ሕዝቡ ግን ወሰን ዐልፈው ወደ እኔ እንዲመጡ አትፍቀድላቸው፤ አለዚያ አጠፋቸዋለሁ” አለው።
\v 25 ስለዚህ ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው።
\s5
\c 20
\p
\v 1 እነዚህን ቃሎች እንዲህ በማለት ተናገረ፦
\v 2 ከግብፅ ምድር፣ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።
\v 3 ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።
\s5
\v 4 በላይ በሰማይ ያለውን፣ ወይም በታች በምድር ያለውን፣ ከምድርም በታች በውሀ ውስጥ ያለውን የማንኛውንም ነገር የተቀረጸ ምስልና ሥዕል ለራስህ ጣዖት አታብጅ።
\v 5 አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። የሚጠሉኝን ሦስትና አራት ትውልድ በልጆች ላይ ቅጣት በማምጣት የአባቶችን ኀጢአት እቀጣለሁ።
\v 6 በሚወዱኝና ትእዛዛቴን በሚጠብቁት በሺዎች ላይ ግን የኪዳን ታማኝነት አሳያለሁ።
\s5
\v 7 የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ ስሜን በከንቱ የሚያነሣውን በደል ዐልባ አላደርገውምና።
\s5
\v 8 እንድትቀድሰው፣ የሰንበትን ቀን ዐስብ።
\v 9 ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን።
\v 10 ቀን ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በሰንበት ቀን አንተም ወንድ ልጅህም፣ ሴት ልጅህም፣ ወንድ አገልጋይህም፣ ሴት አገልጋይህም፣ እንስሳትህም፣ በግቢህ ያለ እንግዳም ሥራ አትሠሩም።
\v 11 እግዚአብሔር ሰማያትን፣ ምድርንና ባሕርን፣ በእነርሱ ውስጥ ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሬ በሰባተኛው ቀን ዐርፌአለሁና። ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባረክሁት፤ ለራሴም ቀደስሁት።
\s5
\v 12 እኔ እግዚአብሔር አምላክህ በምሰጥህ ምድር ብዙ ጊዜ እንድትቆይ፣ አባትህንና እናትህን አክብር።
\v 13 አትግደል።
\v 14 አታመንዝር።
\s5
\v 15 አትስረቅ።
\v 16 በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።
\v 17 የባልንጀራህን ቤት አትመኝ፤ የባልንጀራህን ሚስት፣ ወንድ አገልጋዩን፣ ሴት አገልጋዩን፣ በሬውን፣ አህያውን፣ ወይም የባልንጀራህ የሆነውን ማንኛውንም ነገር አትመኝ።”
\s5
\v 18 ሰዎች ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን አዩ፤ የመለከቱን ድምፅም ሰሙ፤ የሚጨሰውንም ተራራ ተመለከቱ። ሕዝቡ ይህን ሲያዩ፣ ተንቀጠቀጡ፤ ርቀውም ቆሙ።
\v 19 ሙሴን፣ “አንተ ተናገረን፤ እኛም እንሰማሃለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እንዲናገረን አታድርግ፤ አለዚያ እንሞታለን” አሉት።
\v 20 ሙሴም ሕዝቡን፣ “አትፍሩ፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር በእናንተ ዘንድ እንዲገኝና ኀጢአት እንዳትሠሩ ሊፈትናችሁ እግዚአብሔር መጥቶአልና” አላቸው።
\v 21 ስለዚህ ሕዝቡ ርቀው ቆሙ፤ ሙሴም እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ጨለማው ተጠጋ።
\s5
\v 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ይህ ነው፦ ‘እኔ ከሰማይ ከእናንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል።
\v 23 በቀር ሌሎች አማልክትን፣ የብር ወይም የወርቅ አማልክትን ለራሳችሁ አታብጁ።
\s5
\v 24 የጭቃ መሠዊያ ሥራልኝ፣ በእርሱም ላይ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶችህን፣ የኅብረት መሥዋዕቶችህን፣ በጎችህንና በሬዎችህን ሠዋበት። ስሜ እንዲከበር በማደርግበት ስፍራ ሁሉ፣ ወዳንተ እመጣለሁ፤ እባርክሃለሁም።
\v 25 መሠዊያ የምትሠራልኝ ከሆነ፣ በተጠረበ በድንጋይ አትሥራው፤ ለመጥረብ ስትል መሣሪያህን በላዩ ካሳረፍህበት ታረክሰዋለህና።
\v 26 ሆነህ እንዳትጋለጥ፣ በመሠዊያዬ ላይ በደረጃ አትውጣ።”
\s5
\c 21
\p
\v 1 የምትመሠርታቸው ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፦
\s5
\v 2 አገልጋይ ብትገዛ፣ ስድስት ዓመት ያገልግልህና በሰባተኛው ዓመት ያለ ክፍያ ነጻ ይውጣ።
\v 3 ከመጣ፣ ብቻውን ነጻ ይውጣ፤ ሚስት ያገባ ከሆነ፣ ሚስቱም ዐብራው ነጻ ትውጣ።
\v 4 ጌታው ሚስት አጋብቶት ከሆነና እርሷም ወንዶች ወይም ሴቶች ልጆችን ከወለደችለት፣ ሚስቲቱና ልጆቿ የጌታዋ ይሆናሉ፤ ባልዮው ግን ብቻውን በነጻ ይሂድ።
\s5
\v 5 ግን አገልጋይ፣ “ጌታዬን፣ ሚስቴንና ልጆቼን እወድዳለሁ፤ ነጻ ወጥቼ አልሄድም” ቢል፣
\v 6 ውደ ዳኞች ይውስደው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ ወስዶም ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ከዚያም አገልጋይ ጌታውን ለዘለዓለም ያገለግለዋል።
\s5
\v 7 ሰው ሴቶ ልጁን በአገልጋይነት ቢሸጣት፣ እንደ ወንዶቹ አገልጋዮች በነጻ መሄድ የለባትም።
\v 8 ለራሱ የመረጣትን ጌታዋን ደስ ባታሰኝ፣ በዎጆ ይልቀቃት። ለባዕዳን እንዲሸጣት መብት የለውም፤ ምክንያቱም አታልሎአታል።
\s5
\v 9 ለልጁ አያያዝ ያድርግለት።
\v 10 ሌላ ሚስት ቢያጋባውም፣ የመጀመሪያዋን ሚስቱን ምግብ፥ ልብስ፣ ወይም ቊሳዊ መብት ማጕደል የለበትም።
\v 11 ነገር ግን እነዚህን ሦስት ነገሮች የማይሰጣት ቢሆን፣ ያለ ምንም የገንዘብ ክፍያ በነጻ መሄድ ትችላለች።
\s5
\v 12 ሰው ሰውን ቢደበድብና ቢገድል፣ ሊሞት ይገባዋል።
\v 13 ሰውየው ዐስቦ ሳይሆን ድንገት አድርጎት ከሆነ፣ የሚሸሽበት ስፍራ አዘጋጃለሁ።
\v 14 አንድ ሰው ባልንጀራውን ሆነ ብሎ በተንኮል ቢያጠቃውና ቢገድለው፣ ከእግዚአብሔር መሠዊያም እንኳ ተወስዶ ይገደል።
\s5
\v 15 ወይም እናቱን የሚመጣ ይገደል።
\v 16 የሚጠልፍና የሚሸጥ፣ ወይም የተጠለፈው ሰው በእጁየሚገኝበት ይገደል።
\v 17 ወይም እናቱን የሚሳደብ ይገደል።
\s5
\v 18 ቢጣሉና እንደኛው ሌላውን በድንጋይ ወይም በቡጢ ቢመታው፣ የተመታው ሰውም ባይሞትና ዐልጋው ላይ ቢቀር፤
\v 19 በኋላም ቢያገግምና በትሩን ተደግፎ በአካባቢው መንቀሳቀስ ቢችል፣ ለባከነበት ጊዜ የመታው ሰውን ይክፈል፤ ያገገመበትንም በሙሉ ይክፈል። ነገር ግን ያ ሰው የነፍስ ተጠያቂ አይደለም።
\s5
\v 20 አንድ ሰው ወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን በበትር ሲመታና አገልጋዩም ከድብደባው የተነሣ ቢሞት፥ ያ ሰው መቀጣት አለበት።
\v 21 ነገር ግን አገልጋዩ አንድ ወይም ሁለት ቀን በሕይወት ቢቆይ፣ ጌታው መቀጣት የለበትም፤ አገልጋዩ የግል ንብረቱ ነውና።
\s5
\v 22 ሰዎች ቢጣሉና ነፍሰ ጡር ሴት ቢጎዱ፣ እርሷም ብትጨነግፍ፣ ሆኖም ሌላ ጉዳት ባይደርስባት፣ በደለኛው ሰውዬ የሴትዮዋ ባል የሚጠብቅበትንና ዳኞቹ የሚወስኑትን መክፈል አለበት።
\v 23 ጉዳት ካደረሰ ግን፣ ሕይወትን ለሕይወት፣
\v 24 ዐይንን ለዐይን፣ ጥርስን ለጥርስ፣ እጅን ለእጅ፣ እግርን ለእግር፣
\v 25 ቃጠሎን ለቃተሎ፣ ቊስልን ለቊስል፣ ወይም ግርፋትን ለግርፋት በቅጣት ታስከፍላለህ።
\s5
\v 26 አንድ ሰው የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ዐይን ቢመታና ቢያጠፋው፣ አገልጋዩን ስለ ዐይኑ ካሣ ነጻ ሊያደርገው ይገባል።
\v 27 የወንድ ወይም የሴት አገልጋዩን ጥርስ ቢያወልቅ፣ አገልጋዩን ለጥርሱ ካሣ ነጻ ሆኖ እንዲሄድ ማድረግ አለበት።
\s5
\v 28 በሬ አንድን ሰው ወይም ሴት ቢወጋና የሞት አደጋ ቢያደርስ፣ በሬው በድንጋይ ይወገር፣ ሥጋውም አይበላ፤ የበሬው ባለቤት ግን ከተጠያቂነት ነጻ ይሁን።
\v 29 ግን በሬው የመዋጋት ልማድ ከቀድሞ ጀምሮ ካለበትና ባለቤቱ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በሬውን ሳይጠብቀው ቀርቶ፣ በሬው አንድ ወንድ ወይም ሴት ወግቶ ቢገድል፣ ያ በሬ በድንጋይ ይወገር፤ ባለቤቱም በሞት ይቀጣ።
\v 30 ለሕይወቱ ካሣ እንዲከፍል ካስፈለገ፣ የተጠየቀውን ይክፈል።
\s5
\v 31 በሬው የአንድን ሰው ወንድ ወይም ሴት ልጅ ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ይህ ሕግ የሚጠብቅበትን ያድርግ።
\v 32 ወንድ ወይም ሴት አገልጋይን ቢወጋ፣ የበሬው ባለቤት ሠላሳ የብር ሰቅል ለአገልጋዩ ጌታ መክፈልና በሬውም በድንጋይ መወገር አለበት።
\s5
\v 33 ሰው ጕድጓድ ቢከፍት ወይም ቢቆፍርና ሳይደፍነው ቀርቶ በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣
\v 34 ባለቤት ለጠፋው መክፈል ይኖርበታል። ለሞተው እንስሳ ባለቤት ገንዘብ መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።
\s5
\v 35 የአንድ ሰው በሬ የሌላ ሰውን በሬ ቢወጋና ቢሞት፣ የበሬዎቹ ባለቤቶች በሕይወት ያለውን በሬ ሽጠው የተሸጠበትንና የሞተውንም በሬ ይካፈሉ።
\v 36 ነገር ግን በሬው ከቀድሞ ጀምሮ የመውጋት ልማድ ያለበት መሆኑ ከታወቀና ባለቤቱም ያልጠበቀው ከሆነ፣ በበሬው ፈንታ በሬውን መክፈል አለበት፤ የሞተው እንስሳም የእርሱ ይሆናል።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅና ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፣ ለአንድ በሬ ዐምስት በሬ፣ ለአንድ በግም ዐምስት በግ መክፈል አለበት፥
\v 2 ሌባ በር ሰብሮ ሲገባ ቢገኝና ተደብድቦ ቢሞት፣ በማንም ሰው ላይ የደም ዕዳ አይኖርም።
\v 3 ነገር ግን ሰብሮ ከመግባቱ በፊት ፀሐይ ከወጣ፣ በገደለው ሰው ላይ የደም ተጠያቂነት ይኖራል። ሌባ የሰረቀውን መመለስ አለበት። ምንም ነገር ከሌለው፣ የሰረቀውን እንዲከፍል እርሱ ራሱ መሸጥ ይኖርበታል።
\v 4 ሆነ አህያ ወይም በግ ቢሆን የተሰረቀው እንስሳ በሕይወት እርሱ ዘንድ ከተገኘ፣ ዕጥፉን መልሶ መክፈል አለበት።
\s5
\v 5 ሰው ከብቱን መስክ ላይ ወይም የወይን ዕርሻ ውስጥ አሰማርቶ ቢለቅቀውና በሌላ ሰው ዕርሻ ውስጥ ገብቶ ቢግጥ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክና የወይን ዕርሻ መካስ ይኖርበታል።
\s5
\v 6 እሳት ቢነሣና በእሾኾችም ውስጥ ቢዛመት፣ ክምሩም፣ ያልታጨደውም እህል ወይም ዕርሻው ቢቃጠል፣ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይካሥ።
\s5
\v 7 ሰው እንዲጠበቅለት ገንዘቡን ወይም ዕቃውን ለጎረቤቱ ቢሰጥ፣ በዐደራ ያስቀመጠውንም ከሰውዬው ቤት ሌባ ቢሰርቀውና ሌባውም ቢገኝ፣ ያ ሌባ ዕጥፍ መክፈል አለበት፤
\v 8 ባይገኝ ግን፣ የቤቱ ባለቤት እጁን በጎረቤቱ ንብረት ላይ መዘርጋቱንና አለመዘርጋቱን ለማየት፣ በዳኞች ፊት ሊቀርብ ይገባል።
\v 9 ስለ በሬ፣ ስለ አህያ፣ ስለ በግ፣ ስለ ልብስ ወይም አንድ ሰው፣ “ይህ የእኔ ነው” ስለሚለው ስለ ማንኛውም የጠፋ ነገር የሚነሣ ክርክር ሁሉ፣ የሁለቱም ወገን አቤቱታ በዳኞች ፊት መቅረብ አለበት። ዳኞች በደለኛ ሆኖ ያገኙት ሰው ለጎረቤቱ ዕጥፍ መክፈል ይኖርበታል።
\s5
\v 10 አንድ ሰው አህያ፣ በሬ፣ በግ፣ ወይም ማንኛውም እንስሳ እንዲጠበቅለት ለጎረቤቱ በዐደራ ቢሰጥና እንስሳው ቢሞት፣ ወይም ጕዳይ ቢደርስበት፣ ወይም ማንም ሳያይ ቢወሰድ፣
\v 11 ሰው በጎረቤቱ ንብረት ላይ እጁን መዘርጋቱን ወይም አለመዘርጋቱን ለመለየት፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት መማል አለባቸው። ባለቤቱ ይህን ሊቀበል ይገባል፤ ሌላውም ሰው ካሣ አይክሥም።
\v 12 ነገር ግን እንስሳው ከእርፍሱ ተሰርቆ ከሆነ፣ ሌላው ሰው ለባለቤቱ ካሣ መካሥ አለበት።
\v 13 አንድን እንስሳ አውሬ ቢዘነጥለው፣ ሌላው ሰውዬ እንስሳውን ማስረጃ አድርጎ ያቅርብ። ለተዘነጣጠለው እንስሳ ካሣ መክፈል የለበትም።
\s5
\v 14 አንድ ሰው ከጎረቤቱ እንስሳ ቢዋስና እንስሳው ባለቤቱ በሌለበት ቢጎዳ ወይም ቢሞት፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መካሥ አለበት።
\v 15 ባለቤቱ ካለበት ከሆነ ግን፣ ሌላው ሰውዬ ካሣ መክፈል የለበትም፤ እንስሳ ተከራይቶ የነበረ ከሆነ፣ በተከራየበት ዋጋ ይከፈላል።
\s5
\v 16 አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድን ቢያታልልና ዐብሯት ቢተኛ፣ ለዚህ ተገቢ የሆነውን ማጫ ከፍሎ ሚስቱ ሊያደርጋት ይገባል።
\v 17 አባቷ በሚስትነት አልሰጥህም ካለው፣ ልጃገረዶች ማጫ ከሚከፈለው ጋር እኩል የሆነ ገንዘብ መክፈል አለበት።
\s5
\v 18 መተተኛ ሴት በሕይወት እንድትኖር አትፍቀድ።
\v 19 ከእንስሳት ጋር የወሲብ ግንኙነት የሚያደርግ መምት አለበት።
\s5
\v 20 ከእግዚአብሔር በቀር ለማንኛውም ባዕድ አምላክ መሥዋዕት የሚሠዋ ፈጽሞ መጥፋት ይኖርበታል።
\v 21 መጻተኛውን አትበድሉት ወይም አታስጨንቁት፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና።
\s5
\v 22 ማንኛዋንም መበለት ወይም አባትና እናት የሌለውን ልጁ ማስጨነቅ የለባችሁም።
\v 23 የምታስጨንቋቸው ከሆነና እነርሱም ወደ እኔ ከጮኹ፤ እኔ እግዚአብሔር ጩኸታቸውን እሰማለሁ።
\v 24 ቊጣዬ ይቀጣጠላል፤ በሰይፍም እገድላችኋለሁ፤ ሚስቶቻችሁ መበለታት፣ ልጆቻችሁም አባት ዐልባዎች ይሆናሉ።
\s5
\v 25 ከሕዝቤ መካከል ድኻ ከሆኑት ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ አራጣ አበዳሪ አትሁኑበት ወይም ወለድ አታስከፍሉት።
\v 26 የጎረቤትህን ልብስ በመያዣነት ብትወስድ፣ ፀሐይ ከመግባቷ በፊት ልትመልስለት ይገባል።
\v 27 ሰውነቱን የሚሸፍንበት ልብሱ እርሱ ብቻ ነውና። ምን ሌላ ልብስ ለብሶ መተኛት ይችላል? ወደ እኔ ሲጮኽ፣ ርኅሩኅ ነኝና እሰማዋለሁ።
\s5
\v 28 ፈራጆችንም አትስደብ፤ የሕዝብህን አለቃም አትርገም።
\s5
\v 29 ወይም ከወይን ጭማቂዎችህ የምታቀርባቸውን ስጦታዎች ማዘግየት የለብህም። የወንድ ልጆችህንም በኵር ለእኔ መስጠት አለብህ።
\v 30 በበጎችህ ላይም ይህንኑ ማድረግ ይኖርብሃል። ልጆቹ ሰባት ቀን ክአእናቶቻቸው ጋር መቆየት ይችላሉ፤ በስምንተኛው ቀን ግን ለእኔ መስጠት አለብህ።
\v 31 ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ። ስለዚህ መስክ ላይ አውሬ የዘነጣጠለውን ሥጋ ለውሾች ጣሉት፣ ልትበሉት አይገባም።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ማንም ሰው የሐሰት ወሬ እትናገር። ሐሰተኛ ምስክር ለመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር።
\v 2 ክፋት ለመፈጸም ሕዝብን አትከተል፤ ወይም ፍትሕን ለማጣመም ከሰዎች ጋር ተባብረህ ምስክርነት አትስጥ።
\v 3 ድኻውን በሙግቱ አታድላለት።
\s5
\v 4 በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው መልስለት።
\v 5 የሚጠላህን ሰው አህያ እንደ ተጫነ ከጭነቱ ሥር ወድቆ ብታየው፣ ያን ሰው ትተኸው አትሂድ። አህያውን ለማንሣት ልታግዘው ይገባል።
\s5
\v 6 ጊዜ ለድኻው ወገንህ የሚሰጠውን ፍትሕ አታጣምም።
\v 7 በሐሰት ክስ ከሌሎች ጋር አትተ ባበር፤ ንጹሑንም ወይም ጻድቁንም አትግደል፤ እኔ ኀጢአተኛውን ንጹሕ አላደርግምና።
\v 8 አትቀበል፤ ጕቦ የሚያዩ ሰዎችን ያሳውራል፤ የታማኝ ሰዎችን ቃልም ያጣምማልና።
\v 9 የመጻተኛነትን ስለምታውቁት፣ መጻተኛን አታስጨንቁ፤ እናንተም በግብፅ ምድር መጻተኞች ነበራችሁና።
\s5
\v 10 ስድስት ዓመት በመሬትህ ላይ ዘር ዝራ፤ መከሩንም ሰብስብ።
\v 11 በሰባተኛው ዓመት ግን በሕዝብህ መካከል ያሉ ድኾች መብላት እንዲችሉ ሳታርሰው ዕዳሪውን ተወው። ከድኾች የሚተርፈውንም የዱር እንስሳት ይበሉታል። በወይን ቦታዎችህና በወይራ ዛፎችህም ይህንኑ ታደርጋለህ።
\s5
\v 12 ቀን ሥራህን ትሠራለህ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ታርፋለህ። ይህን የምታደርገውም፦ በሬህ፣ አህያህ፣ የሴት አገልጋይህ ወንድ ልጅና መጻተኛው ሁሉ ዕረፍት እንዲያገኙና እንዲዝናኑ ነው።
\v 13 የነገርኋችሁን ሁሉ ጠብቁ። የሌሎች አማልክትን ስም አትጥሩ፤ ወይም ስማቸው ከአፋችሁ አይሰማ።
\s5
\v 14 በየዓመቱ ሦስት ጊዜ ልአእኔ በዓል ታከብራላችሁ።
\v 15 በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት ሰባት ቀን ቂጣ ትበላለህ። በዚያ ጊዜ፣ ለዚህ በተወሰነው በአቢብ ወር በፊቴ ትቀርባለህ። ከግብፅ የወጣኸው በዚህ ወር ነበር። ነገር ግን በፊቴ ባዶ እጅህን መቅረብ የለብህም።
\s5
\v 16 ላይ የዘራኸውን የእህልህን በኵራት፣ የመከርን በዓል አክብር። በዓመቱ መጨረሻ ምርትህን ከማሳ ስትሰበስብ፣ የመክተቻውን በዓል አክብር።
\v 17 ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይቅረብ።
\s5
\v 18 የመሥዋዕቱን ደም እርሾ ካለበት ዳቦ ጋር ለእኔ አታቅርብ። በበዓሎቼ የሚቀርበው የመሥዋዕቴ ሥብ እስከ ንጋት ድረስ መቆየት የለበትም።
\v 19 የመሬትህን ምርጥ ፍሬ በኵራት ወደ እኔ፣ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
\s5
\v 20 በመንገድ የሚጠብቅህንና ወዳዘጋጀሁልህ ስፍራ መርቶ የሚያስገባህን መልአክ በፊትህ እልካለሁ።
\v 21 ተከተለው፤ ታዘዝለትም። ኀጢአትህን ይቅር አይልህምና አታስቆጣው። ስሜ በእርሱ ላይ ነው።
\v 22 ድምፁን በእውነት ብትሰማና የምነግርህን ሁሉ ብታደርግ፣ ለጠላቶችህ ጠላት እሆናለሁ፤ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ።
\s5
\v 23 መልአክ በፊትህ ይሄዳል፤ አንተንም ወደ አሞራውያንና ወደ ኢያቡሳውያን ምድር ያስገባሃል። እኔ እነርሱን አጠፋቸዋለሁ።
\v 24 ለአማልክታቸው አትስገድ፤ አታምልካቸውም፤ ወይም ሕዝቡ እንደሚያደርጉት አታድርግ፤ ይልቁን ፈጽመህ ልታፈራርሳቸው፣ የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም ልትሰባብራቸው ይገባል።
\v 25 እኔን አምላክህን እግዚአብሔርን አምልክ። ይህን ካደረግህ፣ የምትባውንና የምትጠጣውን እባርካለሁ። በሽታንም ከመካከልህ አጠፋለሁ።
\s5
\v 26 የምትጨነግፍ ወይም የምትመክን ሴት አትምርም። ለአንተ ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ።
\v 27 ምድር ሕዝብ ላይ ማስፈራቴን እልካለሁ። የሚያጋጥሙህን ሰዎች ሁሉ እገድላለሁ። ጠላቶችህን ሁሉ ከፍርሀት የተነሣ ጀርባቸውን ወደ አንተ እንዲያዞሩ አደርጋለሁ።
\v 28 ከነዓናውያንና ኬጤያውያንን ከፊትህ እንዲያበሯቸው ተርቦችን በፊትህ እሰድዳለሁ።
\v 29 ወና እንዳትሆንና የዱር አራዊትም እጅግ እንዳበዙብህ፣ የምድሪቱን ኗሪዎች በአንድ ዓመት ውስጥ ከፊትህ አላባርራቸውም።
\s5
\v 30 ነገር ግን አንተ እስክትበዛና ምድሪቱን እስክትወርሳት ድረስ በትንሽ በትንሹ አስወጣቸዋለሁ።
\v 31 ከቀይ ባሕር እስከ ፍልስጥኤም ባሕር፣ ከምድር በዳውም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ አደርገዋለሁ። በምድሪቱ ኗሪዎች ላይ ድል እንድትጎናጸፍ አደርጋለሁ፤ ከፊትህም ታባርራቸዋለህ።
\v 32 ወይም ከአማልክታቸው ጋር ኪዳን አታድርግ።
\v 33 እነርሱ በምድርህ ውስጥ መኖር አይገባቸውም፤ አልዚያ በእኔ ላይ ኀጢአት እንድትሠራ ያደርጉሃል። አማልክታቸውን ብታመልክ፣ ይህ በእውነት ወጥመድ ይሆንብሃል።”
\s5
\c 24
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተ፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ እኔ ኑ፤ በርቀት ሆናችሁም ስገዱልኝ።
\v 2 ሙሴ ብቻ ወደ እኔ መቅረብ ይችላል። ሌሎች መቅረብ የለባቸውም፤ ወይም ሕዝቡ ከሙሴ ጋር መምጣት አይችሉም።”
\s5
\v 3 ሙሴ ወደ ሕዝቡ ሄዶ እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎችና ሕጎቹን ሁሉ ነገራቸው። ሕዝቡም ሁሉ በአንድ ድምፅ፣ “እግዚአብሔር የተናገራቸውን ቃሎች ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ።
\v 4 ሙሴም የእግዚአብሔርን ቃሎች ሁሉ ጻፈ። ማለዳ ላይም በተራራው ግርጌ መሠዊያ ሠራ፤ ዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች እንዲወክሉም፣ ዐሥራ ሁለት የድንጋይ ዐምዶችን አቆመ።
\s5
\v 5 የሚቃጠልና የኅብረት መሥዋዕቶችን ከበሬዎች ለእግዚአብሔር እንዲያቀርቡም፣ ጥቂት የእስራኤል ወጣት ወንዶችን ላከ።
\v 6 ሙሴ የደሙን እኩሌታ በሣህን አደረገው፣ የቀረውንም እኩሌታ በመሠዊያው ላይ ረጨው።
\s5
\v 7 መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ ጮኽ ብሎ አነበበላቸው። ሕዝቡም፣ “እግዚአብሔር የተናገረውን ሁሉእናደርጋለን፤ እንታዘዛለንም” ብለው ተናገር።
\v 8 ሙሴ ደሙን ወስዶ በሕዝቡ ላይ ረጨው። “ይህ፣ ይህን የተስፋ ቃል ከእነዚህ ቃሎች ጋር ለእናንተ በመስጠት፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባው የኪዳኑ ደም ነው” በማለትም ተናገረ።
\s5
\v 9 ከዚያም በኋላ ሙሴ፣ አሮን፣ ናዳብ፣ አብድዩና ሰባው የእስራኤል ሽማግሌዎች ወደ ተራራው ወጡ።
\v 10 የእስራኤልን አምላክ አዩት። ከእግሮቹ ሥርም እንደ ንጹሕ ሰማይ ከጠራ የሰንፒር ድንጋይ የተሠራ ወለል ነበረ።
\v 11 በእስራኤላውያን ሽማግሌዎች ላይ ተቆጥሮ እጅ አላሳረፈባቸውም። እነርሱ እግዚአብሔርን አዩ፤ በሉ፣ ጠጡም።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ተራራው ላይ ወደ እኔ ና፤ በዚያም ቆይ። የድንጋይ ጽላቱን ሕዝቡን እንድታስተምራቸውም የፋጽሏቸውን ሕጉንና ትእዛዛቱን እሰጥሃለሁ” አለው።
\v 13 ስለዚህ ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋር ወደ እግዚአብሔር ተራራ ሄደ።
\s5
\v 14 ሙሴ ሽማግሌዎቹን፣ “ተመልሰን ወደ እናንተ እስክንመጣ ድረስ እዚህ ቆዩን። አሮንና ሖር ከእናንተ ጋር ናቸው። ክርክር የሚኖርበት ሰው ካለ፣ ወደ እነርሱ ይቅረብ” አላቸው።
\v 15 ወደ ተራራው ወጣ፤ ደመናውም ተራራውን ሸፈነው።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ተራራውን ስድስት ቀን ሸፈነው። በሰባተኛው ቀን እግዚአብሔር ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።
\v 17 የእግዚአብሔርን ክብር እስራኤላውያን ሲያዩት እንደሚያጋይ እሳት ነበር።
\v 18 ሙሴ ደመናው ውስጥ ገብቶ ወደ ተራራው ወጣ። በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።
\s5
\c 25
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 2 “እያንዳንዱ ሰው ልቡ በፈቀደለት መሠረት ስጦታ ለእኔ እንዲያመጣ ለእስራኤላውያን ንገር። እነዚህን ስጦታዎች ተቀበልልኝ።
\s5
\v 3 ከእነርሱ የምትቀበላቸውም ስጦታዎች እነዚህ ናቸው፦ ወርቅ፣ ብርና ነሐስ፤
\v 4 ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የበፍታ ድር ልብስ፣ የፍየል ጠጕር፣
\v 5 ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቁርበት፣ የግራር ዕንጨት፤
\v 6 ለመቅደሱ መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያው ዘይት ቅመሞችና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፤
\v 7 ለኤፉድና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችና ሌሎች ዕንቆች።
\s5
\v 8 እንዳድር ሕዝቡ መቅደስ ይሥሩልኝ።
\v 9 ለመገናኛው ድንኳንና ለዕቃዎቹ ሁሉ እኔ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ሥሩት።
\s5
\v 10 ሁለት ክንድ ተኩል፣ ስፋቱ አንድ ክንድ ተኩል፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦት ከግራር ዕንጨት ይሠሩ።
\v 11 ውስጡንም ውጭውንም በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
\s5
\v 12 የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህለት በታቦቱ አራት እግሮች ላይ፣ ሁለቱን በአንድ ጎኑ፣ ሁለቱን ደግሞ በሌላው ጎኑ አስቀምጣቸው።
\v 13 መሎጎያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና አወርቅ ለብጣቸው።
\v 14 ታቦቱን ለመሸከም መሎጊያዎቹን በታቦቱ ጎን ባሉ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ።
\s5
\v 15 መሎጊያዎቹ ምንጊዜም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ይቀመጣሉ እንጂ ከዚያ አይወጡም።
\v 16 የኪዳኑን ምስክሮች በታቦቱ ውስጥ ታስቀምጣለህ።
\v 17 ሁለት ክንድ ተኩል፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሥራ።
\v 18 ለሁለቱ የስርየት መክደኛ ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ ትሠራለህ።
\s5
\v 19 ኪሩብ ለስርየት መክደኛው አንድ ጫፍ፣ ሌላውን ኪሩብ ደግሞ ለሌላው ጫፍ በማድረግ ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው መሠራት አለባቸው።
\v 20 ክንፎቻቸውን ወደ ላይ መዘርጋትና የስርየት መክደኛውን በክንፎቻቸው መጋረድ ይኖርባቸዋል። እርስ በርሳቸው መተያየትና ወደ ስርየት መክደኛውም መመልከት አለባቸው።
\v 21 መክደኛውን በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ በታቦቱ ውስጥም የምሰጥህን የኪዳኑን ምስክሮች ታስቀምጣለህ።
\s5
\v 22 እኔ ከአንተ ጋር የምገናኘው በታቦቱ ነው። በስርየት መክደኛው ላይ ሆኜ ከአንተ በተናገርሁበት በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ነው።
\s5
\v 23 እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ወርዱ አንድ ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሥራ።
\v 24 ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አድርግለት።
\s5
\v 25 አንድ ስንዝር ስፋት ያለው ጠርዝ ለጠርዙ በዙሪያው ከሚኖረው የወርቅ ክፈፍ ጋር አብጅለት።
\v 26 አራት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራለትና ቀለበቶችን አራቱ እግሮቹ ባሉበት ከሚገኙት አራት ማዕዘኖች ጋር አያይዛቸው።
\v 27 ለማስቀመጥና ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል፣ ቀለበቶቹ ከክፈፉ ጋር መያያዝ አለባቸው።
\s5
\v 28 የጠረጴዛው መሸከሚያ እንዲሆኑም መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው።
\v 29 ቊርባኑን ለማፍሰስ ጥቅም እንዲሰጡ ወጭቶችን፣ ጭልፋዎችን፣ ማንቆርቆሪያዎችንና ጎድጓዳ ሣህኖችን ከንጹህ ወርቅ ሥራ።
\v 30 በጠረጴዛውም ላይ የገጽ ኅብስት ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።
\s5
\v 31 መቆሚያና ዘንግ አበጅተህበት ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ መቅረዝ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ ሁሉ ወጥ ሆነው ከመቅረዙ ጋር ይሠራሉ።
\v 32 ሦስት ቅርንጫፎች በአንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፍ ደግሞ በሌላው ጎን፣ ስድስት ቅርንጫፎች ለመቅረዙ ይውጡለት።
\s5
\v 33 የመጀመሪያው ቅርንጫፍ የለውዝ አበቦችን መስለው የተሠሩ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ክአበባ ጋር፣ በሌላው ቅርንጫፍም እንደዚሁ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች የተቀረጹበት ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ሊኖሩት ይገባል። ከመቅረዙ በሚወጡት በስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ ላይ የሚሆነውም እንደዚሁ አንድ ዐይነት ነው።
\v 34 ላይ የለውዝ አበባ መስለው የተቀረጹ አራት ጽዋዎች ከቀንበጦቹና ከአበባዎቹ ጋር ሊኖሩበት ይገባል።
\s5
\v 35 በመጀመሪያዎቹ ቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ፣ በሁለተኛው የቅርንጫፎች ጥንድ ሥርም እንደዚሁ ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይኖረዋል። በሦስተኛው የቅርንጫፎቹ ጥንድ ሥርም ወጥ ሆኖ ዐብሮ የተሠራ ቀንበጥ ይበጅለታል። ከመቅረዙ በሚወጡ በስድስቱ ቅርንጫፎች ሁሉ የሚሆነውም ይኸው አንድ ዐይነት ነው።
\v 36 ቀንበጦቻቸውና ቅርንጫፎቻቸው ሁሉ አንድ ወጥና ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መሆን አለባቸው።
\s5
\v 37 መቅረዙንና ሰባት መብራቶችን ሠርተህ ፊት ለፊት ላለው ስፍራ ብርሃን እንዲሰጥ አድርግ።
\v 38 የኵስታሪ መሰብሰቢያ ሣህኖቻቸው ከንጹሕ ወርቅ መሠራት አለባቸው።
\v 39 መቅረዙንና የመቅረዙን ዕቃ ሁሉ ለመሥራት አንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ተጠቀም።
\v 40 ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት የሠራሃቸው ስለ መሆንህ እርግጠኛ ሁን።
\s5
\c 26
\p
\v 1 ከተፈተለ በፍታ ድር፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከተሠሩና ኪሩቤል ከተጠለፉባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ጋር ማደሪያ ድንኳኑን ሥራ። ይህም ብልኅ ሠራተኛ የሚሠራው ሥራ ነው።
\v 2 የያንዳንዱ መጋረሣ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። መጋረጃዎቹ ሁሉ እኩል መጠን ይኑራቸው።
\v 3 ዐምስቱ መጋረጃዎች እርስ በርስ መያያዝ አለባቸው፤ ሌሎቹ ዐምስት መጋረጃዎችም እንደዚሁ እርስ በርሳቸው መገጣጠም ይኖርባቸዋል።
\s5
\v 4 በአንደኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ ግምጃ ቀለበቶችን አድርግ። ለሁለተኛው ወገን የመጨረሻ መጋረጃ የውጭ ጠርዝም ይህንኑ አበጅለት።
\v 5 ዐምሳ ቀለበቶችን በአንደኛው የመጋረጃ ወገን፣ ዐምሳ ቀለበቶችን በሌላው የመጨረሻ መጋረጃ ላይ አድርግ። ይህን የምትሠራውም ቀለበቶቹ እርስ በርስ እንዲተያዩ በማድረግ ነው።
\v 6 ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዊችብ ሠርተህ ማደሪያ ድንኳኑ አንድ እንዲሆን፣ መጋረጃዎቹን በእነርሱ አያይዛቸው።
\s5
\v 7 ከማደሪያው በላይ ለድንኳን የሚሆኑ ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሥራ።
\v 8 መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱ አራት ክንድ ይሁን። ዐሥራ አንዱም መጋረጃዎች እኩል መጠን ይኑራቸው።
\v 9 ዐምስት መጋረጃዎችን በአንድነት፣ ስድስት መጋረጃውችንም እንዲሁ እርስ በርስ አያይዛቸው። ስድስተኛውን መጋረጃ በድንኳኑ ፊት ዕጠፈው።
\s5
\v 10 በመጀመሪያ ተገጣጣሚ የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን፣ ሁለተኛውን የመጋረጃ አካል በሚያገጣጥመው የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አድርግ።
\v 11 ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሥራና በቀለበቶቹ ውስጥ አስገ ባቸው። ከዚያም አንድ ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን አገጣጥመው።
\s5
\v 12 መጋረጃዎች ተንጠልጥሎ ያለው ቀሪ ግማሽ መጋረጃ ከማደሪያ ድንኳኑ ጀርባ ይንጠልጠል።
\v 13 ከመጋረጃዎቹ እርዝመት የተረፈው በአንድ በኩል አንድ ክንድ ምጋረጃ፣
\v 14 በሌላው ጎንም አንድ ክንድ መጋረጃ ማደሪያው ድንኳን መሸፈኛ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና ከዚያም በላይ የሚሆን የአስቆጣ ቁርበት አዘጋጅ።
\s5
\v 15 ለማደሪያው ድንኳን የሚሆኑ ወጋግራዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅ።
\v 16 ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።
\v 17 በርስ የሚያገናኗቸው ሁለት ጕጣጕጦች በያንዳንዱ ወጋግራ ላይ ይኑር። የመገናኛ ድንኳኑን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሥራ።
\v 18 ድንኳን ወጋግራዎችን ስታበጅ፣ በደቡብ መኩል ላለው ሃያ ወጋግራዎችን አብጅ።
\s5
\v 19 ወጋግራዎች የሚሆኑ አርባ የብር መቆሚያዎችን አብጅ። ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መጋጠሚያዎች እንዲሆኑ ሁለት መቆሚያዎች ይኑሩ። በሌሎች ወጋግራዎች በያንዳንዳቸው ሥርም ለሁለት መጋጠሚያዎቻቸው ሁለት መቆሚያዎች ይዘጋጁ።
\v 20 በሰሜን በኩል ላለው ለሁለተኛው የመገናኛው ድንኳን ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና አርባ የብር መቆሚያዎቻቸውን ሥራ።
\v 21 በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች. በእያንዳንዱ ሥር ይሁኑ።
\s5
\v 22 በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳኑ የኋላ ጎን ስድስት ወጋግራዎችን አብጅ።
\v 23 ለኋላ ማእዘኖቹም ሁለት ወጋግራዎችን አብጅ።
\v 24 እነዚህ ወጋግራዎች ከታች ጥንድ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የተያያዙ መሆን አለባቸው። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የሚሆነው በዚህ መንገድ ነው።
\v 25 ወጋግራዎች ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ሊኖሩ ይገባል። በሁሉም ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ናቸው ያሉት፤ በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋራ ሥርም ሁለት መቆሚያዎችና በእያንዳንዱም ሥር እንዲሁ።
\s5
\v 26 ድንኳኑ አንደኛ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን ከግራር ዕንጨት አዘጋጅ፤
\v 27 ለማደሪያ ድንኳኑ ሌላ ጎንም ወጋግራዎች ዐምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛ ድንኳኑ የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን እንዲሁ አብጅ።
\v 28 በወጋግራዎቹ መካከል ላይ ያለው አግዳሚ ከዳር እስከ ዳር መድረስ አለበት።
\s5
\v 29 ወጋግራዎቹን በወርቅ ለብጣቸው። አግዳምዎችን ደግፍ በመያዝ እንዲያገለግሉም የወርቅ ቀለበቶቻቸውን ሥራላቸው፤ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለብጣቸው።
\v 30 ድንኳኑን መትከል ያለብህ በተራራው ላይ ያየኸውን ምሳሌ በመተከትል ነው።
\s5
\v 31 ብልኅ ሠራተኛ ኪሩቤልን የጠለፈበት፣ የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ግምጃና አምሮ የተፈተለ በፍታ መጋረጃ አብጅ።
\v 32 በወርቅ በተለበጡ የግራር ዕንጨት አራት ዐምዶች ላይ ልትሰቅለው ይገባል። እነዚህ ዐምዶች በአራት የብር መቆሚያዎች ላይ የተቀመጡ የወርቅ ኵላቦች ይኖሯቸዋል።
\v 33 መጋረጃውን በማያያዣዎቹ አንጠልጥለው፤ የምስክሩንም ታቦት አግባው። መጋረጃው ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳን ይለየዋል።
\s5
\v 34 በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ባለ ውበምስክሩ ታቦት ላይ የስርየት መክደኛውን አስቀምጥ።
\v 35 ከመጋረጃው ውጭ፣ መቅረዙንም ከመገናኛው ድንኳን ደቡባዊ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ አስቀምጥ። ጠረጴዛው በሰሜናዊ ጎኑ በኩል መቀመጥ ይኖርበታል።
\s5
\v 36 መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ በጥልፍ ብሚያስጌጥ ሠራተኛ የተሠራ መጋረጃ አብጅለት።
\v 37 ዐምስት ምሰሶዎችን ከግራር ዕንጨት አብጅና በወርቅ ለብጣቸው። ኵላቦቻቸውም የውርቅ መሆን እላቸው፤ ዐምስት የነሐስ መቆሚያዎችንም ሥራላቸው።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ዐምስት ክንድ ወርዱም ዐምስት ክንድ የሆነ መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ። መሠዊያው አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ከፍታ ይኑረው።
\v 2 ማእዘኖች የበሬ ቀንድ ቅርጽ እንዲኖራቸው ታደርጋለህ። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር አንድ ወጥና በነሐስ የተለበጡ ይሆናሉ።
\s5
\v 3 የመሠዊያውን ዕቃዎች፦ የዐምድ ማስወገጃ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ የሥጋ ሜንጦዎችንና የፍም መያዣዎችን ሁሉ ከነሐስ አብጃቸው።
\v 4 ለመሠዊያው ከነሐስ እንደ መረብ የተሠራ ፍርግርግ አብጅለት። በፍርግርጉ አራት ማእዘኖች በያንዳንዳቸው ላይም የነሐስ ቀለበት አድርግ።
\s5
\v 5 አጋማሽ ወገብ እስከ ታች እንዲደርስ ፍርግርጉን ከመሠዊያው እርከን ሥር አድርገው።
\v 6 ለመሠዊያው መሎጊያዎችን ከግራር ዕንጨት አበጅተህ በነሐስ ለብጣቸው።
\s5
\v 7 በቀለበቶቹ ውስጥ መግባትና መሠዊያውን ለመሸከም በሁለቱ ጎኖቹ ላይ መቀመጥ አለባቸው።
\v 8 ባዶ እንዲሆን ከሳንቃዎች አብጀው። በተራራው ላይ ባየኸው መሠረት ልትሠራው ይገባል።
\s5
\v 9 ድንኳን አደባባይ ሥራለት። በአደባባዩ ደቡብ ጎንም አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው የአማረ በፍታ መጋረጃዎች ይደረጉ።
\v 10 መጋረጃዎቹ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች ጋር ሃያ ምሰሶዎች ይኑሯቸው። ከምስሶዎቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎችም መኖር አለባቸው።
\s5
\v 11 በሰሜን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎች፣ ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎችም ጋር ከምሰሶውቹ ጋር የተያያዙ የብር ኵላቦችና ዘንጎች ሊኖሩ ይገባል።
\v 12 በአደባባዩ ምዕራብ ጎንም ዐምሳ ክንድ ርዝመት ያለው መጋረጃ ይደረግ። ዐሥር ምሰሶዎችና ዐሥር መቆሚያዎችም ይኑሩት።
\v 13 በምሥራቅም በኩል አደባባዩ ዐምሳ ክንድ እርዝመት ይኑረው።
\s5
\v 14 የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ሊኖራቸው ይገባል። ሦስት ምሰዎችም ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ይኖሯቸዋል።
\v 15 ሌላው ጎንም ዐሥራ ዐምስት ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ይኖሩታል። የራሳቸው ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ይኖሯቸዋል።
\v 16 መግቢያ መጋረጃ ሃያ ክንድ እርዝመት ያለው፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ጠላፊ ጠልፎበት የተሠራ ይሁን። አራት ምሰሶዎች ከአራት መቆሚያዎች ጋር ሊኖሩት ይገባል።
\s5
\v 17 የአደባዩ ምሰሶዎች ሁሉ የብር ዘንጎችና ኵላቦች፣ የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሯቸው።
\v 18 የአደባባዩ እርዝመት አንድ መቶ ክንድ፣ ወርዱ ዐምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ዐምስት ክንድ ይሁን፤ የበፍታ መጋረጃዎችና የነሐስ መቆሚያዎችም ይኑሩት።
\v 19 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አገልግሎት የሚሰጥ ዕቃ ሁሉ፣ የድንኳኑ ካስማዎችም በሙሉ፣ አደባባዩም ከነሐስ መሠራት አለባቸው።
\s5
\v 20 ሁልጊዜ እንዲበሩ ለመብራቶቹ የወይራ ጭማቂ ንጹሕ ዘይት እንዲያመጡ እስራኤላውያንን እዘዛቸው።
\v 21 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣ ከመጋረጃው ውጭ በምስክሩ ታቦት ፊት፣ አሮንና ልጆቹ መብራቶቹን ከማታ እስከ ንጋት ድረስ በእግዚአብሔር ፊት እንዲበሩ ያድርጉ። ይህም ለእስራኤል ትውልድ ሁሉ የዘለዓለም ሥርዐት ይሆናል።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ሆነው እንዲያገለግሉኝ ወንድምህን ዘሮንንና ልጆቹን ናዳብን፣ አብድዩን፣ አልዓዛርንና ኢታምርን ከእስራኤል መካከል ወደ አንተ ጥራ።
\v 2 ለወንድምህ ለአሮን ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን አዘጋጅ። እነዚህ ልብሶች ለአሮን ክብርና ማዕርግ የሚሆኑ ናቸው።
\v 3 ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግለኝ የአሮንን ልብሶች የሚሠሩለትን፣ በልባቸው ጥበበኛ የሆኑትን፣ የጥበብን መንፈስም የሞላሁባቸውን ሰዎች ሁሉ አነጋግር።
\s5
\v 4 የሚሠሯቸው ልብሶችም የደረት ኪስ፣ ኤፉድ፣ ቀሚስ፣ ጥልፍ የተጠለፈበት ሸሚዝ፣ መጠምጠሚያና መታጠቂያ ናቸው። ለእኔ የተቀደሱትን እነዚህን ልብሶች መሥራት አለባቸው። ልብሶቹ ካህናት ሆነው እንዲያግለግሉኝ ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናሉ።
\v 5 ወርቅ፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊ፣ ቀይ ማግና የአማረ በፍታ ይጠቀሙ።
\s5
\v 6 ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግን ኣአምሮ ከተፈተለ በፍታ ይሥሩት። ሥራው የብልኀተኛ ሙያተኝ ሥራ ሊሆን ይገባል።
\v 7 ኤፉዱ ከሁለቱ ጠርዞቹ ጋር የሚያያዙ ሁለት የትከሻ ንጣዮች ይኑሩት።
\v 8 በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉድ መሆን አለበት፦ ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ወጥ ሆኖ የተሠራ ይሁን።
\v 9 ሁለት የመረግድ ድንጋዮችን ወስደህ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅረጽባቸው።
\s5
\v 10 ስድስቱ ስሞቻቸው በአንድ ድንጋይ፣ ስድስቱ ሌሎች ደግሞ በሌላው ድንጋይ ላይ እንደየልጁ ልደት ቀደም ተከተል ይቀረጹ።
\v 11 ሠራተኛ ማኅተም እንደሚቀርጽ የእስራኤልን ዐሥራ ሁለት ልጆች ስሞች በሁለቱ ድንጋዮች ላይ ቅረጽ። ድንጋዮቹንም በወርቅ ክፈፋቸው።
\v 12 ሁለቱን ድንጋዮች የእስራኤልን ልጆች አምላክ የሚያስታውሱ ድንጋዮች እንዲሆኑ በኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ አስቀምጥ። መታሰቢያ እንዲሆኑ አሮን ስሞቻቸውን በሁለቱ ትከሻዎቹ ላይ በእግዚአብሔር ፊት ይሸከማል።
\s5
\v 13 ፈርጦችንና
\v 14 እንደ ገመድ የተጎነጎኑ የንጹሕ ወርቅ ድሪዎችን አበጅተህ ከፈርጦቹ ጋር አያይዛቸው።
\s5
\v 15 ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ ኤፉዱ በተሠራበት መንገድ ፍርድ የሚሰጥበትን የደረት ኪስ አብጅ። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሥራው።
\v 16 አራት ማእዘን ያለ ውይሁን። የደረት ኪሱን ዐጥፈህ ድርብ አድርገው። አንድ ስንዝር እርዝመት፣ አንድ ስንዝር ስፋትም ይኑረው።
\s5
\v 17 ዕንቆችን በአራት ረድፍ አስቀምጥ። የመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶነዝዮንና አብረቅራቂ ዕንቊ ሊኖሩት ይገባል።
\v 18 ሁለተኛው ረድፍ በሉር፣ ሰንፔርና አልማዝ ይኑሩት።
\v 19 ሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶንና አማቴስጢኖስ ይገኙበታል።
\v 20 አራተኛው ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ይኑሩት። በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ ሊደረግላቸው ይገባል።
\s5
\v 21 ድንጋዮቹ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት መቀመጥ፣ ከእስራኤል ነገዶች አንዱን በመወከልም በቀለበት ማተሚያ እንደሚቀረጽ እያንዳንዱ ስም የተቀረጸባቸው መሆን አለባቸው።
\v 22 ኪሱ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አብጅለት።
\v 23 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከደረት ኪሱ ሁለት ጎኖች ጋር አያይዛቸው።
\v 24 የወርቅ ድሪዎች ከደረት ኪሱ ሁለት ማእዘኖች ጋር አያይዛቸው።
\s5
\v 25 ጕንጕን ድሪዎች ሌሎች ጎኖች ከሁለቱ የወርቅ ፈርጦች ጋር አገናኛቸው። ከኤፉፉ የትከሻ ንጣዮች ጋርም በፊቱ በኩል አያይዛቸው።
\v 26 የወርቅ ቀለበቶችን ሥራና ከውስጠኛው የኤፉዱ ጎን ቀጥሎ ባለው ጠርዝ ላይ፣ በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጎኖች ላይ አድርጋቸው።
\s5
\v 27 ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን አብጅና በብልኀት ከተጠለፈው ከሴፉዱ መታጠቂያ በላይ፣ መጋጠሚያው አጠገብ ከኤፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያይዛቸው።
\v 28 ከኤፉዱ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችሉ፣ የደረት ኪሱን ቀለበቶቹ ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ገመድ ማሰር አለባቸው። ይህም የሚሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋር ሳይያያዝ እንዳይቀር ነው።
\s5
\v 29 አሮን ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ፣ የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች በደረት ኪሱ ላይ ለፍርድ በልቡ ላይ ይሸከም። ይህም በእግዚአብሔር ፊት የዘለዓለም መታሰቢያ ሆኖ ያገለግላል።
\v 30 በፍርድ መስጫው የደረት ኪስ ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አስቀምጥ። አሮን ወደ እግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ፣ ኡሪምና ቱሚም በደረቱ ላይ መኖር አለባቸው፤ አሮንም ለእስራኤል ፍርድ መስጫውን በእግዚአብሔር ፊት ሲቀርብ ሁልጊዜ መሸከም ይኖርበታል።
\s5
\v 31 ቀሚስ ሙሉ በሙሉ ሰማያዊ ይሁን።
\v 32 ለራስ ማስገቢያ ክፍተት ይኑረው፤ ክፍተቱም እንዳይቀደድ ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ይኑረው። ይህ ሥራ የሸማኔ ሥራ መሆን አለበት።
\s5
\v 33 የግርጌ ጠርዝ ላይ የሰማያዊ፣ የሐምራዊና የቀይ ማግ ሮማኖችን በዙሪያው አድርግ። በመካከላቸውም ዙሪያውን የወርቅ ሻኵራዎችን አብጅ።
\v 34 የወርቅ ሻኵራዎቹና ሮማኖቹ በቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ እየተፈራረቁ መቀመጥ አለባቸው።
\v 35 ወደ መቅደሱ ሲገባና በእግዚአብሔር ፊት ሲሆን፣ ከመቅደስ ሲወጣም፣ ድምፁ እንዲሰማ ቀሚሱን አሮን ሲያገለግል ይልበሰው። ይህም የሚደረገው አሮን እንዳይሞት ነው።
\s5
\v 36 ከንጹሕ ወርቅ ሳሕን አብጅና በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ፣ “ቅዱስ ለእግዚአብሔር” ብለህ በላዩ ቅርጽበት።
\v 37 ሳሕን ከመጠምጠሚያው ፊት ጋር በሰማያዊ ገመድ አያይዘው።
\v 38 ሁልጊዜም በአሮን ግንባር ላይ ይሁን፤ አሮን እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ለይተው ከሚያቀርቧቸው የተቀደሱ ስጦታዎች ጋር የሚያያዝ ማንኛውንም በደል ይሸከማል። እግዚአብሔር ስጦታዎቻቸውን እንዲቀበል፣ መጠምጠሚያ ሁልጊዜ በአሮን ግንባር ላይ መሆን አለበት።
\s5
\v 39 ሸሚዙንም፣ መጠምጠሚያውንም ከአማረ በፍታ ትሠራለህ። መታጠቂያውም በጥልፍ ጠላፊ እንዲሠራ ታደርጋለህ።
\s5
\v 40 ለአሮን ልጆችም ሸሚዞቹን፣ መታጠቂያዎችንና የራስ ማሰሪያዎችን ለክብራቸውና ለማዕረጋቸው ታደርጋለህ።
\v 41 ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው። ቅባቸው፣ ሹማቸውም፤ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝም ለእኔ ቀድሳቸው።
\s5
\v 42 እስከ ጭን የውስጥ ሰውነታቸውን የሚሸፍን የውስጥ ልብሶችን ከበፍታ ሥራ።
\v 43 ልጆቹ ውደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ፣ ወይም መቅደሱ ውስጥ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ እነዚህን የውስጥ ልብሶች መልበስ አልባቸው። በደል እንዳይገኝባቸውና እንዳይሞቱ ይህን ማድረግ ይገባቸዋል። ይህ ለአሮንና ከእርሱም በኋላ ለሚመጡት ዘሮቹ የዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ሆነው እንዲያገለግሉኝ እነርሱን ለእኔ ለመቀደስ አሁን የምታደርገው ይህ ነው። ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና ሁለት አውራ በጎች፣
\v 2 የሌለበትን እንጀራና ዘይት የተቀላቀለበትን እንጎቻ ውሰድ፤ ዘይት የተቀባ ስስ ቂጣም አድርግ።
\s5
\v 3 በአንድ ሌማት አድርጋቸውና ከወይፈኑና ከአውራ በጎቹ ጋር አቅርባቸው።
\v 4 አሮንንና ልጆቹንም ወደ መገናኛ ድንኳኑ መግቢያ አቅርባቸው። በውሀም እጠባቸው።
\s5
\v 5 ውሰድና፦ ሸሚዙን፣ የኤፉዱን ቀሚስ፣ ኤፉዱን፣ የደረት ኪሱን፣ በብልኀት የተጠለፈውን የኤፉዱን መታጠቂያ በወገቡ ዙሪያ በማስታጠቅ አሮን አልብሰው።
\v 6 ቅዱሱን አክሊል በላዩ አስቀምጠህ መጠምጠሚያውን በአሮን ራስ አድርግ።
\v 7 ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ቅባው።
\s5
\v 8 አምጥተህ ሸሚዞችን አልብሳቸው።
\v 9 መታጠቂያዎችን ለአሮንና ለልጆቹ ታስታጥቃቸዋለህ፤ የራስ ማሰሪያዎችንም ታደርግላቸዋለህ። የክህነቱ ሥራ በዘለዓለማዊ ሕግ የእነርሱ ይሆናል። እኔን እንዲያገለግሉኝ አሮንና ልጆቹን ትክናቸዋለህ።
\s5
\v 10 በመገናኛው ድንኳን ፊት አቅርብ፤ አሮንና ልጆቹም በወይፈኑ ራስ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑ።
\v 11 በእኔ በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ዕረደው።
\s5
\v 12 ከወይፈኑ ደም ጥቂት በጣትህ ወስደህ በመሠዊያው ቀንዶች ላይ ታደርጋለህ፤
\v 13 የሆድ እቃዎችን የሚሸፍነውን ስብ ሁሉ ጉበቱን የሚሸፍነውንና ሁለቱን ኩላሊቶች በላያቸው ካለው ስብ ጋር ወስደህ ሁሉንም በመሰዊያው ላይ ታቃጥላቸዋለህ።
\v 14 ነገር ግን የወይፈኑን ሥጋ ግን ቁርበቱንና ፈርሱን ጭምር ከሰፈር ውጭ አውጥተህ ታቃጥላለህ። ያ የኀጢአት መሥዋዕት ይሆናል።
\s5
\v 15 የአውራ በግም ውሰድና አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን ይጫኑበት።
\v 16 በጉን ዕረደው፤ ደሙንም ወስደህ በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው።
\v 17 በጉን ለሁለት ክፈልና የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን እጠብ፤ የሆድ ዕቃውንም ከተቆራተጡ ብልቶችና ከራሱ ጋር
\v 18 ላይ አስቀምጥ። ከዚያም እውራ በጉን ሙሉ በሙሉ አቃጥለው። ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል። ይህም ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል።
\s5
\v 19 ሌላውንም አውራ በግ ወስደህ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት።
\v 20 በኋላ አውራ በጉን ዕረደው፤ ከደሙም ጥቂት ውሰድና በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍና በልጆቹ ቀኝ ጆሮዎች ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጆቻቸውና በቀኝ እግሮቻቸው አውራ ጣቶች ላይ አድርግ። ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን እርጨው።
\s5
\v 21 ካለው ደም፣ ከመቅቢያው ዘይትም ጥቂት ውሰድና በአሮንና በልብሶቹ፣ በልጆቹና በልብሶቻቸውም ላይ እርጨው። አሮንና ልብሶቹ፣ ልጆቹና ልብሶቻቸው ከእርሱ ጋር ይቀደሱልኛል።
\s5
\v 22 በጉን ሥብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኵላሊቶችና በላያቸው የሚገኘውን ሥብ፣ የቀኙን ወርችም ውሰድ፤ ይህ አውራ በግ ካህኑ ለእኔ የሚቀደስበት ነውና።
\v 23 እንጀራ፣ አንድ በዘይት የተጋገረ እንጎቻና አንድ ስስ ቂጣ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ከሚሆነው ያለ እርሾ ከተጋገረው ኅብስት ሌማት ትወስዳለህ።
\s5
\v 24 እነዚህን በአሮን እጆችና በልጆቹ እጆች ታስቀምጣለህ። እነርሱ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዟቸው፤ መሥዋዕት አድርገውም ለእኔ ያቅርቧቸው።
\v 25 ከእጆቻቸው ወስደህ ከሚቃጠለው መሥዋዕት ጋር በመሠዊያው ላይ አቃጥለው። ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያለው፣ በእሳት የቀረበልኝ መሥዋዕት ይሆናል።
\s5
\v 26 የአሮንን የክህነት አውራ በግ ፍርምባ ወስደህ ወዝውዘውና መሥዋዕት አድርገህ ለእኔ ለእግዚአብሔር አቅርበው። ይህም አንተ የምትበላው የአንተ ድርሻ ይሆናል።
\v 27 የመሥዋዕቱን ፍርምባና የቀረበውን የመሥዋዕቱን ወርች ለእኔ ቀድስልኝ፤ ሁለቱም አሮንና ልጆቹ ለእኔ ካህናት መሆናቸውን ለማረጋገጥ ከአውራ በጉ የሚገኙ ናቸው።
\v 28 የሚሰጧቸው እነዚህ የሥጋ ክፍሎች ምንጊዜም የአሮንና የልጆቹ ናቸው። በኅብረቱ መሥዋዕቶች ሥርዐት፣ ከእስራኤላውያን ለካህናቱ፣ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ይሆናሉ።
\s5
\v 29 የአሮን የተቀደሱ ልብሶች ከእርሱ በኋላ ለልጆቹም ይሆናሉ። በልብሶቹ የአሮን ልጆች ለእኔ መቀባትና መካን አለባቸው።
\v 30 በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እኔን ለማገልገል ወደ መገናኛው ድንኳን የሚገባ፣ አሮንን ከልጆቹ መካከል የሚተካ እነዚያን ልብሶች ሰባት ቀን ይልበስ።
\s5
\v 31 የክህነቱን አውራ በግ ውሰድና ሥጋውን በተቀደሰ ስፍራ ቀቅለው።
\v 32 ልጆቹ የአውራ በጉን ሥጋና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር ባለው ሌማት የተቀመጠውን ኅብስት ይብሉት።
\v 33 ለማስተስረይና ለእኔ እንዲቀደሱ የቀረቡትን ሥጋውንና ኅብስቱን መብላት አለባቸው። ሌላ ሰው መብላት አይችልም፤ ምክንያቱም ምግቡን ለእኔ የተቀደሰ አድርገው ሊይዙት ይገባል።
\v 34 መሥዋዕቱ ሥጋ፣ ወይም ከኅብስቱ እስከሚቀጥለው ጠዋት ድረስ አንዳች የሚተርፍ ከሆነ፣ አቃጥለው። ለእኔ የተቀደሰ ስለ ሆነ መበላት የለበትም።
\s5
\v 35 በዚህ መንገድ እንድታደርገው ያዘዝሁህን ሁሉ በመከተል ለአሮንና ለልጆቹ ትፈጽምላቸዋለህ። እነርሱን ሰባት ፍቀን ቀድስልኝ።
\v 36 ለስርየት የሚሆን የኀጢአት መሥዋዕት በየቀኑ አንድ ወይፈን አቅርብ። ማስተሰረያውን በማድረግም መሠዊያውን አንጻ፤ ለእኔ ለመቀደስም ቅባው።
\v 37 ሰባት ቀን ማስተሰረያ አድርግለትና ለእግዚአብሔር ቀድሰው። ከዚያ በኋላ መሠዊያው ሙሉ በሙሉ የተቀደሰ ይሆናል፤ መሠዊያውን የሚነካውም ሁሉ ይቀደሳል።
\s5
\v 38 የአንድ ዓመት ጠቦቶችን ዘወትር በየቀኑ በመሠዊያው ላይ አቅርብ።
\v 39 ጠቦት ማለዳ፣ ሌላውን ደግሞ ምሽት ላይ ታቀርበዋህ።
\s5
\v 40 ከመጀመሪያው ጠቦታ ጋር የኢፍ አንድ ዐሥረኛን ያማረ ዱቄት ተወቅጦ ከተጠለለ ሩብ ኢፍ ዘይት ጋር በመለወስ፣ ሩብ ወይንንም የመጠጥ ቍርባን በማድረግ አቅርብ።
\s5
\v 41 ሁለተኛውን ጠቦት በምሽት ሠዋው። በማለዳ እንደ ተሠዋው ጠቦት ተመሳሳይ የእህልና የመጠት ቍርባን ማቅረብ አለብህ። እነዚህ መሥዋዕቶች ለእኔ ጣፋጭ መዐዛ ያላቸው በእሳት የቀረቡልኝ መሥዋዕቶች ናቸው።
\v 42 ትውልዶች ሁሉ ዘወትር የሚቀርቡ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ናቸው። ላናግራችሁ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በእኔ በእግዚአብሔር ፊት መሥዋዕቶቹን አቅርቧቸው።
\s5
\v 43 ከእስራኤላውያን ጋር የምገናኝበት ቦታ ያ ነው፤ ድንኳኑ በክብሬ ይቀደስልኛል።
\v 44 የመገናኛውን ድንኳንና መሠዊያውን የእኔ ብቻ እንዲሆኑ እቀድሳቸዋለሁ። ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን እለያቸዋለሁ።
\s5
\v 45 በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁ፤ አምላካችውም እሆናለሁ።
\v 46 በመካከላቸው እንድኖር፣ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው እኔ እግዚአብሔር አምላካችው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
\s5
\c 30
\p
\v 1 ዕጣን የሚጤስበት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሥራ።
\v 2 እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ይሁን። አራት ማእዘንና ሁለት ክንድ ከፍታ ይኑረው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ይሁኑ።
\s5
\v 3 የዕጣን መሠዊያውን ላይኛ ክፍል፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለብጣቸው። የመሠዊያውን ዙሪያ በወርቅ ክፈፈው።
\v 4 ከክፈፉ በታች በሁለቱ ትይዩ ጎኖቹ ላይ እንዲያያዙ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አብጅ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ደግፈው የሚይዙ ናቸው።
\s5
\v 5 ከግራር ዕንጨት ሥራና በወርቅ ለብጣቸው።
\v 6 የዕጣን መሠዊያውን ከመጋረጃው ፊት በምስክሩ ታቦታ አጠገብ አስቀምጠው። ይህም እኔ ከአንተ ጋር በምገናኝበት፣ በምስክሩ ታቦታ ላይ ካለው ከስርየት መክደኛው ፊት ይሆናል።
\s5
\v 7 ደስ የሚያሰኝ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሁልጊዜ ጧት ቷት ያጢስ። ማጤስ ያለበትም መብራቶቹን በሚያዘጋጅበት ጊዜ ነው።
\v 8 መብራቶቹን በምሽት ሲያበራም፣ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን ማጤስ አለበት። ይህ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር በትውልዶች ሁሉ የሚጤስ ዕጣን ይሆናል።
\v 9 ነገር ግን ሌላ ዕጣን፣ አንዳችም የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የእህል ቍርባን በዕጣን መሠዊያው ላይ አታቅርብ፤ ምንም ዐይነት የመጠጥ ቍርባንም አታፍስስበት።
\s5
\v 10 መሠዊያው ቀንዶች ላይ አሮን በዓመት አንድ ጊዜ ማስተስረያ ያድርግ ይህንም የሚያደርገው የኀጢአት ስርየት ደሙን በመጠቀም ነው። ሊቀ ካህናቱ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ይህን ያድርገው። ይህ መሥዋዕት ሙሉ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል።”
\s5
\v 11 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 12 ስትቆጥራቸው፣ እያንዳንዱ ሰው ለራሱ ሕይወት ቤዛ ለእግዚአብሔር መክፈል አለበት። ስትቆጥራቸውና ከቆጠርሃቸውም በኋላ በመካከላቸው መቅሠፍት እንዳይኖር ይህን አድርግ።
\v 13 የተመዘገበ እያንዳንዱ ሰው በመቅደሱ ሰቅል ክብደት መሠረት የብር ግማሽ ሰቅል ይክፈል። ይህ ግማሽ ሰቅልም ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ መሥዋዕት ይሆናል።
\v 14 ከሃያ እና ከዚያ በላይ ዕድሜ ያለው የተቆጠረ ሁሉ ይህን መሥዋዕት ለእኔ ማቅረብ አለበት።
\s5
\v 15 ለሕይወታቸው ማስተስረያ ለማድረግ ይህን መሥዋዕት ለእኔ ሲያቀርቡ፣ ባለጠጋው ከግማሽ ሰቅል የበለጠ፣ ድኻውም ከዚያ ያነሰ መስጠት የለባቸውም።
\v 16 የማስተስረያ ገንዘብ ከእስራኤላውያን ተቀበልና ለመገናኛ ድንኳኑ ሥራ አውለው። ለሕይወታችሁ ማስተስረያ ማድረግ በፊቴ ለእስራኤላውያን መታሰቢያ ይሁን።”
\s5
\v 17 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 18 ትልቅ የናስ ሳሕን ከናስ መቆሚያ ጋር አብጅ። በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠውና ውሀ አድርግበት።
\s5
\v 19 ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ውስጡ ባለው ውሀ ይታጠቡ።
\v 20 መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም የሚቃጠል መሥዋዕት በማቅረብ እኔን ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ እንዳይሞቱ በውሀ መታጠብ አለባቸው።
\v 21 እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ሊታጠቡ ይገባል። ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በትውልዶቻቸው ሁሉ የሁልጊዜ ሕግ ይሁን።”
\s5
\v 22 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 23 ምርጥ ቅመሞች፦ ዐምስት መቶ ሰቅል ፈሳሽ ከርቤ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጣፋጭ ሽታ ያለው ቀረፋ፣ ሁለት መቶ ዐምሳ ሰቅል ጠጅ ሣር፣
\v 24 ዐምስት መቶ ሰቅል ብርጕድ በመቅደሱ ሰቅል ክብደት ተለክቶ፣ አንድ የኢን መስፈሪያ ወይራ ዘይትም ውሰድ።
\v 25 ቅመሞች በሽቶ ቀማሚ ሥራ የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት አዘጋጅ። ይህ ለእኔ የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት ይሆናል።
\s5
\v 26 ዘይት የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦትም፣
\v 27 ጠረጴዛውንና ዕቃውንም ሁሉ፣ መቅረዙንና ዕቃውን፣ የዕጣን መሠዊያውንም፣
\v 28 የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረቢያ መሠዊያውን ከዕቃው ሁሉ ጋር፣ መታጠቢያ ሳሕኑንም ከመቆፕሚያው ጋር ቅባ።
\s5
\v 29 ለእኔ የተቀደሱ እንዲሆኑ እነርሱን ለይልኝ። እነርሱን የሚነካ ማንኛውም ነገርም የተቀደሰ ይሆናል።
\v 30 ሆነው እንዲያገለግሉኝ አሮንንና ልጆቹን ቅባቸው፣ ለእኔም ለያቸው።
\v 31 እንዲህ በላቸው፤ ‘ይህ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ መቅቢያ ዘይት መሆን አለበት።
\s5
\v 32 የሰው ቆዳ ሊቀባበት አይገባም፤ እንደዚህ ያለ አንዳችም ዘይት በአንድ ዐይነት ቀመር መሥራት የለባችሁም ምክንያቱም ይህ ዘይት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዘይት ነው። እናንተም ቅዱስ መሆኑን ዐስቡ።
\v 33 እንደዚህ የሚሠራ ሁሉ፣ ወይም ከዚህ ዘይት ጥቂት በሰው ላይ የሚያፈስስ ሁሉ፣ ከወገኑ ይወገድ።’”
\s5
\v 34 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “የጣፋጭ ሽቶ ቅመሞችን፦ የሚንጠባጠብ ሙጫ፣ በዛጎል ውስጥ ያለ ሽቶ፣ የሚሸት ሙጫ ከንጹሕ ዕጣን ጋር፣ እያንዳንዱን በእኩል መጠን ውሰድ፥
\v 35 በሽቶ ቀማሚ እንደ ተሠራ፣ በጨው የተቀመመ፣ ንጹሕና ለእኔ የተቀደሰ ዕጣን አድርገው።
\v 36 አድቅቀህ ትወቅጠዋለህ። ከፊሉን ከአንተ ጋር በምገናኝበት፣ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ባለው በምስክሩ ታቦት ፊት ለፊት አስቀምጥ። ለእኔ የተቄደሰ መሆኑንም ዐስብ።
\s5
\v 37 እንደምትዘጋጀው ዕጣን በአንድ ዐይነት ቀመር ለራስህ ምንም አታድርግ። ለአንተ እጅግ ቅዱስ ይሁን።
\v 38 እንደ ሽቶ ለመጠቀም እንደዚህ አድርጎ የሚሠራ ሁሉ ከገዛ ወገኑ ይወገድ።”
\s5
\c 31
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 2 “የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስሙ ጠርቼዋለሁ።
\s5
\v 3 ለሁሉም ዐይነት የእጅ ሞያ ጥበብን፣ ማስተዋልንንና ዕውቀትን እንዲሰጠው፣ ባስልኤልን በመንፈስ ሞልቼዋለሁ፤
\v 4 ይኸውም ጥበባዊ ሥራዎችን በወርቅ፣ በብርና በነሐስ እንዲሠራ፣
\v 5 ዐይነት የእጅ ሞያ ለማከናወንም ድንጋይ እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው።
\s5
\v 6 ከእርሱም በተጨማሪ የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ከዳን ነገድ መርጬዋለሁ። ያዘዝሁህንም ሁሉ እንዲሠሩ የእጅ ሞያ ዐዋቂዎች በሆኑት ልብ ውስጥ ብልኀትን አስቀምጫለሁ።
\v 7 የመገናኛውን ድንኳን፣ የምስክሩን ታቦት፣ በታቦቱ ላይ ያለውን የስርየት መክደኛና የድንኳኑን ዕቃ ሁሉ፦
\v 8 ጠረጴዛውንና ዕቃውን፣ ንጹሑን መቅረዝ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር፣ የዕጣኑን መሠዊያ:
\v 9 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋርና ትልቁን ሰን ከነመቆሚያው የሚያካትት ይሆናል።
\s5
\v 10 የተሠሩትን ልብሶች፦ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉኝ ለእኔ የተለዩትን የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም ይጨምራል።
\v 11 ዘይቱንና የመቅደሱን ጣፋጭ ዕጣንም ያካትታል። እነዚህ የእሥ ሞያ ዐዋቂዎች እነዚህን ሁሉ እኔ ባዘዝሁህ መሠረት ይሥሯችው።”
\s5
\v 12 ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 13 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የእግዚአብሔርን የሰንበት ቀኖች ጠብቁ፤ እናንተን ለራሱ የለያችሁ እርሱ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ፣ ይህ በእርሱና በእናንተ መካከል በትውልዶቻችሁ ሁሉ ምልክት ነውና።
\v 14 ስለዚህ ለእናንተ የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰንበት ነውና አክብሩት። ሰንበትን የሚያረክስ ሁሉ ይሞታል። በሰንበት የሚሠራም ከወገኑ ተነጥሎ ይጥፋ።
\v 15 ስድስት ቀን ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ክብር የተጠበቀና የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት ሰንበትን ያክብሩ።
\s5
\v 16 በትውልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ ሕግ አድረገው ሰንበትን ሊያከብሩት ይገባል።
\v 17 እግዚአብሔር በስድስት ቀን ሰማይንና ምድርን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐርፎአልና፣ ሰንበት በእግዚአብሔርና በእስራኤላውያን መካከል ሁልጊዜ ምልክት ይሆናል።”
\s5
\v 18 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ከሙሴ ጋር የሚያደርገውን ንግግር ከጨረሰ በኋላ፣ በገዛ እጁ የጻፈባቸውን የምስክሩን ሁለት የድጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ከተራራው ሳይወርድ እንደ ዘገየ ሕዝቡ ሲመለከቱ፣ በአሮን ዙሪያ ተሰብስበው እንዲህ አሉት፤ “በፊታችን የሚሄድ ጣዖት ሥራልን። ከግብፅ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳጋጠምው አናውቅም።”
\v 2 እንዲህ አላቸው፤ “በሚስቶቻችሁ ጆሮዎች፣ በወንድና በሴት ልጆቻችሁ ጆሮዎችም ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቁና ወደ እኔ እምጧቸው።”
\s5
\v 3 ሁሉም በጆሮዎቻቸው ላይ ያሉ የወርቅ ቀለበቶችን አውልቀው ወደ አሮን አመጧቸው።
\v 4 ወርቁን ከእነርሱ ተቀብሎ በማቅለጥ ቅርጽ ሰጠው፤ የጥጃ ምስልም አደረገው። ሕዝቡም፣ “እስራኤል፣ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣህ አምላክህ ነው” አሉ።
\s5
\v 5 ይህን ባየው ጊዜ፣ በጥጃው ምስል ፊት መሠዊያ ሠራ፤ “ነገ ለእግዚአብሔር ክብር በዐል ይሆናል” ብሎም ዐወጀ።
\v 6 ሕዝቡ በማግስቱ ማልደው በመነሣት የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን አቀረቡ። ሊበሉና ሊጠጡም ተቀመጡ፤ ለመዝፈንም ተነሡ።
\s5
\v 7 ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ራሳቸውን በክለዋልና ቶሎ ሂድ።
\v 8 መንገድ ፈጥነው ወጥተዋል። ለራሳቸው የጥጃ ምስል ሠርተው ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለታል። ‘እስራኤል፣ ከግብፅ ያወጣህ አምላክህ ይህ ነው ብለውም ተናግረዋል።’”
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ አይቼዋለሁ። ተመልከት፣ ዐንገተ ደንዳናዎች ናቸው።
\v 10 በእነርሱ ላይ እንዲቀጣጠልና እንዳጠፋቸው ተወኝ። ከአንተም ታላቅ ሕዝብ አደርጋለሁ (አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ) ።”
\v 11 ግን አምላኩ እግዚአብሔር ዝም እንዲልለት ፈለገ፤ እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ሆይ፣ በታላቁ ኀይልና በኀያል እጅ ከግብፅ ባወጣሃው ሕዝብህ ላይ ቊጣህ ለምን ይቀጣጠላል?
\s5
\v 12 ‘እግዚአብሔር በተራሮች ላይ ሊገድላቸውና ከገጸ ምድር ሊያጠፋቸው ዐስቦ ነው ያወጣቸው’ ለምን ይበሉ? ከሚነድደው ቊጣህ ተመለስ፤ በሕዝብህ ላይ ይህን ቊጣ ከማምጣትም ታገሥ።
\v 13 ‘ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፣ የተናገርሁትን ይህንም ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጠዋለሁ፤ የዘለዓለም ርስታቸው ይሆናል’ ያልሃቸውንና በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህ አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን ዐስብ።”
\v 14 ከዚያም እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ አመጣባቸዋለሁ ካለው ቊጣ ታገሠ።
\s5
\v 15 ተመለሰ፤ የምስክሩን ሁለት ጽላት በእጁ ይዞ ከተራራው ወረደ። ጽላቱ በሁለቱም ጎኖቻቸው፣ በፊትም በኋላም ተጽፎባቸው ነበር።
\v 16 የእግዚአብሔር ሥራ ነበር፤ በጽላቱ ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር።
\s5
\v 17 ላይ የተቀረጸው ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር። 17 ኢያሱ የሕዝቡን ጫጫታ ሲሰማ፣ ሙሴን፣ “በሰፈር ውስጥ የጦርነት ድምፅ አለ” አለው።
\v 18 ሙሴም “የድል አድራጊ ድምፅ አይደለም፤ ድል የተደረገ ሕዝብ ድምፅም አይደለም፤ የምሰማው የዘፈን ድምፅ ነው” ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 19 ወደ ሰፈሩ ሲቀርብ፣ ጥጃውንና የሚጨፍረውን ሕዝብ አይቶ በጣም ተናደደ። ጽላቱን ከእጁ ወርውሮ በተራራው ግርጌ ሰበራቸው።
\v 20 ሠርተውት የነበረውን ጥጃም ወስዶ አቃጠለው፤ ዱቄት እስከሚሆን ድረስ በመፍጨትም በውሀ ውስጥ በተነው። ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ እንዲጠጣው አደረገ።
\s5
\v 21 “እንደዚህ ያለ ታላቅ ኀጢአት ያመጣህበት ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው? ” አለው።
\v 22 እንዲህ ብሎ መለሰለት፤ “ጌታዬ ሆይ ቊጣህ አይንደድ። እነዚህ ሰዎች ለክፋት የተዘጋጁ እንደ ሆኑ ታውቃለህ።
\v 23 እንደዚህ ብለውኛል፤ ‘በፊታችን የሚሄድ አምላክ አብጅልን። ከግብፅ ያወጣን ሰውየ ይህ ሙሴ ምን እንዳጋጠመው አናውቅም።’
\v 24 እኔም፣ ‘ወርቅ ያለው ሰው ሁሉ ያውልቀው’ አልኋቸው። እነርሱም ወርቁን ሰጡኝ። በእሳት ውስጥም ጣልሁትና ይህ ጥጃ ወጣ።”
\s5
\v 25 መዘባበቻ እንዲሆኑ አሮን መረን ስለ ለቀቃቸው፣ ሕዝቡ ከቊጥጥር ውጭ መሆናቸውን ሙሴ አስተዋለ።
\v 26 በሰፈሩ መግቢያ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ። ሌዋውያን ሁሉ በሙሴ ዙሪያ ተሰበሰቡ።
\v 27 ሌዋውያኑን እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአል፦ ‘እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ይታጠቅና በሰፈሩ ሁሉ ከበር እስከ በር ወደ ኋላና ወደ ፊት እየተመላለሰ ወንድሙን፣ ጓደኛውንና ጎረቤቱን ይግደል።’”
\s5
\v 28 ሌዋውያኑ ሙሴ ያዘዘውን ፈጸሙ። በዚያ ቀን ከሕዝቡ ሦስት ሺሕ ያህል ሰዎች ሞቱ።
\v 29 ሌዋውያኑን፣ “ዛሬ ከእናንተ እያንዳንዱ በልጁና በወንድሙ ላይ እርምጃ ስለ ወሰደ፣ ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተቀድሳችኋል። ስለዚህም እግዚአብሔር ዛሬ ባርኳችኋል” አላቸው።
\s5
\v 30 በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን፣ “ታላቅ ኀጢአት ሠርታችኋል። አሁን ወደ እግዚአብሔር እወጣለሁ። ምናልባት ለኀጢአታችሁ ማስተሰረያ ማድረግ እችል ይህናል” አላቸው።
\v 31 ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ተመልሶ ሄደ፤ እንዲህም አለ፤ “ወዮ! እነዚህ ስዎች ታላቅ ኀጢአት ሠርተዋል፤ ለራሳቸውም ከወርቅ ጣዖት አበጅተዋል።
\v 32 ግን እባክህ ኀጢአታቸውን ይቅር በል፤ ይቅር የማትላቸው ከሆነ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍ እኔን ደምስስልኝ።”
\s5
\v 33 ሙሴን እንዲህ አለው፤ እኔን የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ።
\v 34 ሂድ፤ ሕዝቡን ወደ ነገርኋችሁ ስፍራ ምራው። እነሆ፣ የእኔ መልአክ በፊትህ ይሄዳል። ሕዝቡን በምቀጣበት ቀን ግን ስለ ኀጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”
\v 35 አሮን በሠራው ጥጃ ስላደረጉት፣ እግዚአብሔር በሕቡ ላይ መቅሠፍት ላከባቸው።
\s5
\c 33
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “አንተና ከግብፅ ያወጣሃው ሕዝብ ከዚህ ሂድ። ‘ለዘርህ እሰጠዋለሁ’ ባልሁ ጊዜ፣ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማልሁበት ምድር ሂድ።
\v 2 በፊትህ መልአክ እሰድዳለሁ፤ ከነዓናውያንን፣ አሞራውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኤዊያውያንና ኢያቡሳውያንንም አስወጣቸዋለሁ።
\v 3 ማርና ወተት ወደምታፈስሰዋ ምድር ሂዱ፤ ነግር ግን እናንተ ግትሮች ስለ ሆናችሁ፣ እኔ ከእናንተ ጋር አልወጣም። በመንገድ ላይ ላጠፋችሁ እችላለሁ።”
\s5
\v 4 እነዚህን አስጨናቂ ቃሎች ሲሰሙ፣ አለቀሱ፤ ምንም ዐይነት ጌጥ ያደረገ ሰውም አልነበረም።
\v 5 ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበር፤ “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘እናንተ ግትር ሰዎች ናችሁ። ለአፍታ እንኳ ዐብሬአችሁ ብሄድ፣ አጠፋችኋለሁ። ስለዚህ ምን እንደማደርግባችሁ ለመወሰን ጌጣጌጦቻችሁን አውልቁ።”
\v 6 እስራኤላውያንም ከኮሬብ ተራራ ጀምረው ጌጦቻቸውን አወለቁ።
\s5
\v 7 አንድ ድንኳን ወሰደና በተወሰነ ርቀት ላይ ከሰፈር ውጭ ተከለው። የመገናኛ ድንኳን ብሎ ጠራው። ስለ ማንኛውም ጕዳይ እግዚአብሔርን የሚጠይቅ ሰው ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ ወደሚገኘው የመገናኛ ድንኳን ይሄድ ነበር።
\v 8 ወደ ድንኳኑ ሲሄድ፣ ሕዝቡ ሁሉ በየድንኳኑ መግቢያ ላይ ቆሞ ወደ ድንኳኑ ሲገባ ሙሴን ይመለከት ነበር።
\v 9 ወደ ድንኳኑ በሚገባበት ጊዜ ሁሉ፣ የደመና ዐምድ ይወርድና በድንኳኑ መግቢያ ላይ ይቆማል። እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር ይነጋገራል።
\s5
\v 10 ሕዝቡ በድንኳኑ መግቢያ ላይ የደመናውን ዐምድ ቆሞ ሲያዩት፣ እያንዳንዱ ሰው በራሱ ድንኳን መግቢያ ላይ ይነሣና ይሰግዳል።
\v 11 እግዚአብሔር አንድ ሰው ጓደኛውን እንደሚያነጋግር፣ ሙሴን ፊት ለፊት ያነጋግረዋል። ከዚያም በኋላ ሙሴ ወደ ሰፈሩ ይመለሳል፤ አገልጋዩና ወጣት የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ከድንኳኑ አይለይም ነበር።
\s5
\v 12 ሙሴ እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “ይህን ሕዝብ ምራው ብለኸኝ ነበር፤ ከእኔ ጋር ማንን እንደምትልክ ግን አላሳወቅኸኝም። ‘በስም ዐውቅሃለሁ፤ በፊቴም ሞገስ አግኝተሃል’ ብለሃል።
\v 13 በፊትህ ሞገስ ካገኘሁ፣ እንዳውቅህና በፊትህ ሞገስን በማግኘት እንድቀጥል መንገዶችህን አሳየኝ። ይህ ሕዝብ የአንተ ሕዝብ እንደ ሆነም አስታውስ።”
\s5
\v 14 እግዚአብሔርም መልሶ፣ “የእኔ ሀልዎት ከአንተ ጋር ዐብቶ ይሄዳል፤ ዕረፍትም እሰጥሃለሁ” አለው።
\v 15 እግዚአብሔርን እንዲህ አለው፤ “የአንተ ሀልዎት ዐብሮን የማይሄድ ከሆነ፣ ከዚህ አታውጣን።
\v 16 ከእኛ ጋር ካልሄድህ፣ እኔና ሕዝብህ በፊትህ ሞገስ ያገኘን መሆናችን እንዴት ሊታወቅ ይችላል? እኔና ሕዝብህ በምድር ገጽ ካለው ሕዝብ ሁሉ የተለየን የምንሆነው አንተ ከእኛ ጋር ብትሄድ ብቻ አይደለምን?”
\s5
\v 17 ሙሴን፣ “በፊቴ ሞገስን ስላገኘህና በስምም ስለማውቅህ፣ የጠየቅኸውን አድረጋለሁ” አለው።
\v 18 “እባክህ ክብርህን አሳየኝ” አለ።
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መልካምነቴ ሁሉ በፊትህ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ ስሜን እግዚአብሔርንም በፊትህ ዐውጃለሁ። የምምረውን እምረዋለሁ፤ የምራራለትንም እራራለታለሁ።”
\v 20 ነገር ግን እግዚአብሔር፣ ፊቴን ማየትና በሕይወት መኖር የሚችል ሰው ስለሌለ፣ አንተ የእኔን ፊት ማየት አትችልም” ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 21 እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ በእኔ ዘንድ ስፍራ አለ፤ አንተ በዚህ ዐለት ላይ ትቆማለህ።
\v 22 ክብሬ በዚያ ሲያልፍ፣ እኔ እስከማልፍ ድረስ አንተን በዐለቱ ስንጥቅ ውስጥ በእጄ እሸፍንያለሁ።
\v 23 ከዚያም እጁን አነሣውና ጀርባዬን ታያለህ፤ ፊቴ ግን አይታይም።”
\s5
\c 34
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንደ መጀመሪያዎቹ ጽላት አድርገህ ጥረብ። በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላት ላይ ተጽፈው የነበሩ ቃሎችን በእነዚህ ጽላት ላይ እጽፍባቸዋለሁ።
\v 2 ማለዳ ላይ ተዘጋጅተህ ወደ ሲና ተራራ ውጣና በዚያ በተራራው ዐናት ላይ በፊቴ ቁም።
\s5
\v 3 ከአንተ ጋር ማንም ሰው አይምጣ። በተራራው ላይ በየትኛውም ስፍራ ማንም እንዲታይ አታድርግ። የበግና የፍየል መንጋዎች፣ የቀንድ ከብቶችም እንኳ በተራራው ፊት ለፊት ሣር መጋጥ የለባቸውም።”
\v 4 ሁለት የድንጋይ ጽላትን እንድ መጀመሪያዎቹ አድርጎ ጠረበ፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ሲና ተራራ ወጣ። ሙሴ ሁለቱን የድንጋይ ጽላት በእጁ ይዞ ነበር።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር በደመና ወርዶ ከሙሴ ጋር በእዚያ ቆመ፤ ስሙን እግዚአብሔርንም ዐወጀ።
\v 6 በሙሴ ፊትም እንዲህ እያለ በማወጅ ዐለፈ፤ “እግዚአብሔር፣ ርኅሩኅም ቸርም አምላክ እግዚአብሔር፣ ለቊጣ የዘገየ፣ በጽኑዕ ፍቅርና በታማኝነት ባለ ጸጋ፣
\v 7 ጽኑዕ ፍቅሩን ለሺሕ ትውልድ የሚጠብቅ፣ ክፋትን፣ ዐመፅንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፤ በደለኛውን ግን ከቶ ንጹሕ አያደርገውም። ለአባቶች ኀጢአት ልጆቻቸውንና የልጅ ልጆቻቸውን እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ይቀጣል።”
\s5
\v 8 ሙሴ ወዲያውኑ ወደ መሬት ዝቅ ብሎ ሰገደ።
\v 9 አለ፤ “ጌታዬ ሆይ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ እባክህ ዐብረኸን ሂድ፤ ይህ ሕዝብ ግትር ሕዝብ ቢሆንም፣ ክፋታችንና ኀጢአታችንን ይቅር በለን፤ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”
\s5
\v 10 እንዲህ አለ፤ “እነሆ፣ ኪዳን እገባለሁ። በምድር ሁሉ አየትኛውም ሕዝብ ዘንድ ተደርገው የማያውቁ ድንቆችን በሕዝብህ ሁሉ ፊት አደርጋለሁ። በአንተ ዘንድ የማደርገው የሚያስፈራ ነውና፣ ዐብሮህ ያለው ሕዝብ ሁሉ ሥራዬን ያያል።
\v 11 የማዝዝህን ፈጽም። አሞራውያንን፣ ከነዓናውያንን፣ ኬጤያውያንን፣ ፌርዛውያንን፣ ኢዊያውያንንና ኢያቡሳውያንን በፊትህ አስወጣቸዋለሁ።
\s5
\v 12 አገር ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ አለዚያ በመካከልህ ወጥመድ ይሆኑብሃል።
\v 13 ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐምዶቻቸውን አድቅቋቸው፤ የአሼራ ዐፀዶቻቸውንም ቍረጡ።
\v 14 ስሜ ‘ቀናተኛ’ የሆነ እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነኝና ሌላ አምላክ አታምልክ።
\s5
\v 15 ስለዚህም ከምድሪቱ ኗሪዎች ጋር ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤ ምክንያቱም አማልክታቸውን በመከተልያመነዝራሉና፣ መሥዋዕትም ያቀርቡላቸዋልና አንተንም አንዱ ስለሚጋብዝህና ከመሥዋዕቱም ጥቂት ስለምትበላ፣
\v 16 ከዚያም ከሴቶች ልጆቹ የተወሰኑትን ለወንዶች ልጆችህ ትወስዳለህ፤ ሴት ልጆቹም አማልክታቸውን በመከተል ያመነዝራሉ፤ ወንዶች ልጆችህንም ለአማልክታቸው እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል።
\v 17 የተሠሩ አማልክትን ለራስህ አታብጅ።
\s5
\v 18 የቂጣ በዓልን አክብር። ባዘዝሁህ መሠረት እርሾ ያልገባበትን ዳቦ በተወሰነው ጊዜ በአቢብ ወር ሰባት ቀን ብላ፤ ከግብፅ የወጣሃው በአቢብ ወር ነበርና።
\s5
\v 19 በኵር ሁሉ፣ የከብትህም እንኳ ተባዕት በኵር በሙሉ፣ የበሬዎችህም የበጎችም በኵር የእኔ ነው።
\v 20 የአህያውን በኵር በጠቦት ዋጀው፤ ካልዋጀኸው ግን ዐንገቱን ስበረው። በኵር ወንድ ልጆችህን ሁሉ ዋጃቸው። ባዶ እጁን በፊቴ የሚቀርብ ማንም እይኑር።
\s5
\v 21 ቀን ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍ። በዕርሻና በመከር ጊዜም እንኳ ዕረፍ።
\v 22 ሱባዔ በዓል ከስንዴው በኵራት ጋር፣ የመክተቻውንም በዓል በዓመቱ መጨረሻ አክብር።
\s5
\v 23 በአንተ ዘንድ ያለ ወንድ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በእስራኤል አምላክ ፊት ይቅረብ።
\v 24 በፊትህ አስወጣቸዋለሁ፤ ወሰንህንም አሰፋዋለሁ። በዓመት ሦስት ጊዜ በእኔ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ለመውረርና ለመቆጣጠር ማንም አይመኝም።
\s5
\v 25 ደም ከእርሾ ጋር አታቅርብ፤ ወይም በፋሲካ በዓል የቀረበው መሥዋዕት ሥጋ እስከ ማለዳ ተርፎ አይቆይ።
\v 26 የዕርሻህ ምርጥ በኵራት ወደ ቤቴ አምጣ። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።”
\s5
\v 27 እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በተናገርሏቸው በእነዚህ ቃሎች ክአንተና ከእስራኤል ጋር ኪዳን አድርጌአለሁና አለው።
\v 28 አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር እዚያው ነበረ። ምግብም አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም።
\s5
\v 29 ሁለቱን የምስክሩን ጽላት በእጁ ይዞ ከሲና ተራራ ወረደ። ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገረ ሳለ፣ ፊቱ የሚያበራ ምሆኑን አላወቀም።
\v 30 እስራኤላውያን ሙሴን ሲያዩት፣ ፊቱ ይበራ ነበር፤ ስለዚህም ወደ እርሱ ለመጠጋት ፈሩ።
\v 31 ግን ጠራቸው፤ አሮንና የሕዝቡ መሪዎችም ወደ እርሱ መቱ፣ ሙሴም ከእነርሱ ጋር ተነጋገረ።
\s5
\v 32 ከዚያ በኋላም፣ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ሙሴ መጡ፤ እርሱም በሲና ተራራ ላይ እግዚአብሔር ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ ነገራቸው።
\v 33 ንግግሩን ከጨረሰ በኋላ፣ በፊቱ ላይ መሸፈኛ አደረገ።
\s5
\v 34 ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር በፊቱ በሚቀርብበት ጊዜ ሁሉ፣ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ መሸፈኛውን ያወልቀው ነበር። ሲወጣ ምን እንዲል እንደታዘዘ ለእስራኤላይዋን ይነግራቸዋል።
\v 35 እስራኤላውያን የሚያበራውን ፊቱን ሲያዩ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ተመልሶ እስኪሄድ ድረስ መሸፈኛውን እንደ ገና በፊቱ ላይ ያደርገዋል።
\s5
\c 35
\p
\v 1 የእስራኤልን ማኅበረ ሰብ ሁሉ ሰብስቦ እንዲህ አላቸው፤ “እንድትፈጽሟቸው እግዚአብሔር የሰጣችሁ ትእዛዝት እነዚህ ናቸው።
\v 2 ስድስት ቀን ሥራ ትሠራላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የፍጹም ዕረፍት የሰንበት ቀን ይሁንላችሁ። በዚያ ቀን ሥራ የሚሥዐራ ሁሉ ይሞታል።
\v 3 በሰንበት ቀን በማንኛችሁም ቤት ውስጥ እሳት አይንደድ።”
\s5
\v 4 ሁሉን የእስራኤል ማኅበረ ሰብ እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው።
\v 5 ከልብ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቅርቡ። ሁሉም ለእግዚአብሔር የወርቅ፣ የብር፣ የነሐስ መባያምጣ፤
\v 6 ሐምራዊና ቀይ ማግ፣ ቀጭን በፍታ፣ የፍየል ጠጒር፣
\v 7 በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳና የአቆስጣ ቆዳ፣ የግራር ዕንጨት፣
\v 8 መብራቶች ዘይት፣ ለመቅቢያ ዘይቱ ቅመምና ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን፣
\v 9 መረግዶችና ለኤፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ ሌሎች ዕንጨቶችንም መባ አድርጎ ያቅርብ።
\s5
\v 10 በመካከላችሁ ያሉ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ይምጡና እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ይሥሩ፦
\v 11 ከድንኳኑ ጋር፣ መደሪያውን፣ ማያያዣዎቹን፣ ክፈፎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ቋሚዎቹንና መሠረቶቹን፤
\v 12 ታቦቱንም ከነመሎጊያዎቹ፣ የስርየት መክደኛውንና የሚሸፍነውን መጋረጃ፤
\s5
\v 13 ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ ዕቃዎቹንም ሁሉን ኣየገጽ ኅብስቱን፤
\v 14 የመብራቶቹን መቅረዝ ከዐባሪ ዕቃዎቹ ጋር፣ መብራቶቹንና የመብራቶቹን ዘይት፤
\v 15 የዕጣኑን መሠዊያ ከመሎጊያዎቹ ጋር፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዓዛ ያለውን ዕጣን፣ የመገናኛ ድንኳኑን መግቢያ መጋረጃ፣
\v 16 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ ከነሐስ መጫሪያው፣ ከመሎጊያዎቹና ከዕቃዎቹ ጋር፤ ትልቁን የመታጠቢያ ሰን እስከ ማስቀመጫው፤
\s5
\v 17 የአድደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመሠረቶቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢይ ኣመጋረጃ፤
\v 18 የማደሪያውን ድንኳን ካስማዎች ከነገመዶቻቸው፤
\v 19 ውስጥ ለማገልገል በብልኀት የተሠሩ ልብሶችን፣ ካህናት ሆነው ለማገልገል ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ የሚሆኑ የተቀደሱ ልብሶችን ያምጡ።”
\s5
\v 20 ከዚያም ሁሉም የእስራኤል ነገዶች ሁሉ ከሙሴ ፊት ወጥተው ሄዱ።
\v 21 ልቡ የተነሣሣና ፈቃደኛ የሆነ ሁሉ በመምጣት ለመገናኛው ድንኳን ሥራ፣ ለውስጡም ለሚደረገው አገልግሎትና ለተቀደሱ ልብሶች የሚሆን ስጦታን ሰጡ።
\v 22 ፈቃደኛ የነበሩ ወንዶችም ሴቶችም መጥተው የአፍንጫ ጌጦችን፣ የጆሮ ጌጦችን፣ ቀለበቶችን፣ ድሪዎችንና ሁሉንም ዓይነት የወርቅ ጌጣጌጦች አመጡ።
\s5
\v 23 ሐምራዊ፣ ቀይም ቀይ ማግ፣ ያማረ በፍታ፣ የፍየል ጠጕር፣ በቀይ ቀለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ወይም የአስቆጣ ቆዳ የነበራቸውም አመጡ።
\v 24 ለማንኛውም ተግባር የሚጠቅም የግራር ዕንጨት የነራቸው፣ የብርና የነሐስ ስጦታ ማድረግ የሚፈልጉ ሁሉ በስጦታነት ለእግዚአብሔር አቀረቡ።
\s5
\v 25 ብልኀተኛ ሴቶችም ሁሉ ማግ ፈትለው፣ የፈተሉትን ሰማያዊ፣ ሕዐምራዊ፣ ወይም ቀይ ማግ አመጡ።
\v 26 ያነሣሣቸውና ብልኀተኛ የሆኑ ሴቶች ሁሉ የፍየል ጠጕር ፈተሉ።
\s5
\v 27 ለአፉዱና ለደረት ኪሱ የሚሆኑ መረግዶችንና ሌሎች ዕንቆችን አመጡ፤
\v 28 ለመቅቢያው ዘይትና ጣፋጭ መዐዛ ላለው ዕጣን ዘይትና ቅመምም አመጡ።
\v 29 የነጻ ፈቃድ ስጦታ ለእግዚአብሔር በሙሴ በኩል እንዲፈጸም አዝዞት ለነበረው ሥራ ሁሉ ቍሳቍሶችን አመጡ።
\s5
\v 30 እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እግዚአብሔር የሖር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባስልኤልን ከይሁዳ ነገድ በስም ጠርቶታል።
\v 31 ለሁሉም ዐይነት የጥበብ ሥራ ጥበብን፣ ማስተዋልንና ዕውቀትን ሊሰጠው ባስልኤልን በመንፈሱ ሞልቶታል፤
\v 32 የወርቅ፣ የብርና የነሐስ ጥበባዊ ሥራዎችን ለመሥራት፣
\v 33 የጥበባዊ ሥራ ዐይነቶችን ሁሉ ለመሥራት ድንጋዮችን እንዲጠርብና ዕንጨትም እንዲቀርጽ ነው።
\s5
\v 34 እግዚአብሔር በባስልኤልና ከዳን ነገድ በሆነው በአሂሳሚክ ልጅ በኤልያብ ልብ ይህን ችሎታ አስቀመጠ።
\v 35 ጥበበኛ ሰዎች፣ እንደ ቀራጺዎች፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊና በቀይ ማግ፣ ባማረ በፍታም እንደ ጥልፍ ጠላፊዎችና እንደ ሸመና ሠራተኞች እንዲሠሩም ብልኀትን ሞላባቸው። እነርሱ በሥራ ዐይነቶች ሁሉ ጥበበኞች የሆኑ የጥበብ ባለሙያዎች ናቸው።
\s5
\c 36
\p
\v 1 ስለዚህ ባስልኤልና ኤልያብ፣ የልብ ጥበበኞች የነበሩና እንዲፈጽሙት እግዚአብሔር ያዘዘውን በመከተል መቅደሱ እንዴት እንደሚሠራ ለማወቅ ብልኀትንና ማስተዋልን ያስቀመጠባቸውም ሁሉ ይሠራሉ።
\s5
\v 2 ባስልኤልንና ኤልያብን፣ እግዚአብሔር በልቡ ብልኀትን አስቀምጦበት የነበረ ጥበበኛ ስውን ሁሉ፣ መጥቶ ሥራውን ለመሥራት ልቡ ያነሣሣውንም ጠራ።
\v 3 የጠራቸውም ለመቅደሱ ሥራ እስራኤላውያን አምጥተውት የነበረውን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ተቀበሉ። ሕዝቡ የነጻ ፈቃድ ስጦታዎችን ጠዋት ጠዋት ወደ ሙሴ ማምጣት አላቋረጡም ነበር።
\v 4 ስለዚህ በመቅደሱ ሥራ ላይ የተሰማሩ ብልኀተኛ ሰዎች ሁሉ ከሚሠሩት ሥራ ተነሥተው መጡ።
\s5
\v 5 ሙሴን፣ “እግዚአብሔር እንድንሠራው ላዘዘን ሥራ ከሚበቃው በጣም የሚበልጥ ሕዝቡ እያመጡ ነው” አሉት።
\v 6 ሙሴም በሰፈሩ ውስጥ ያለ ማንም ሰው ለመቅደሱ ሥራ ሌላ ስጦታ እንዳያመጣ ትእዛዝ ሰጠ። ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ስጦታ ማምጣቱን አቆሙ።
\v 7 ለሥራው ሁሉ ከሚበቃው በላይ ቍሳቍሶች ነበሯቸው።
\s5
\v 8 ያሉ ጥበበኞችም ሁሉ ከአማረ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግም ከተሠሩትና ኪሩቤልም ከተጠለፉባቸው ዕሥር መጋረጃዎች ጋር የመገናኛውን ድንኳን ሠሩት። ይህም እጅግ ጥበበኛ የነበረው የባስልኤል ሥራ ነው።
\v 9 መጋረጃ እርዝመት ሃያ ስምንት ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ሁሉም መጋረጃዎች እኩል መጠን ነበራቸው።
\v 10 ባስልኤል ዐምስት ዐምስቱን መጋረጃዎች በአንድ ላይ አድርጎ እርስ በርስ አገጣጠማቸው።
\s5
\v 11 መጋረጃዎች የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይና በሁለተኛውም ተገጣጣሚ መጋረጃ የመጨረሻ የውጭ ጠርዝ ላይ ሰማያዊ ቀለበቶችን አደረገ።
\v 12 በሁለተኛው መጋረጃ ጠርዞች ዐምሳ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ። ስለሆነም ቀለበቶቹ እርስ በርስ ትይዩ ሆነው የተደረጉ ነበር።
\v 13 ባስልኤል ዐምሳ የወርቅ ማያያዣዎችን ሠርቶ የመገናኛው ድንኳን ወጥ እንዲሆን መጋረጃዎቹን አያያዛቸው።
\s5
\v 14 ባስልኤል በማደሪያው ላይ ላለው ድንኳን ዐሥራ አንድ የፍየል ጠጕር መጋረጃዎችን ሠራ።
\v 15 የእያንዳንዱ መጋረጃ እርዝመት ሠላሳ ክንድ፣ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ። ዐሥራ አንድ መጋረጃዎች እያንዳንዳቸው እኩል መጠን ነበራቸው።
\v 16 መጋረጃዎች እርስ በርሳቸው፣ ስድስቱንም መጋረጃዎች እንደዚሁ እርስ በርሳቸው አያያዛቸው።
\v 17 ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይ ዐምሳ ቀለበቶችን በሁለተኛዎቹ ተገጣጣሚ መጋረጃዎች የመጨረሻ መጋረጃ ጠርዝ ላይም እንደዚሁ ዐምሳ ቀለበቶችን አበጀ።
\s5
\v 18 ባስልኤል ወጥ እንዲሆን ድንኳኑን ለማገጣጠም ዐምሳ የነሐስ ማያያዣዎችን ሠራ።
\v 19 ለድንኳኑ መሸፈኛ በቀይ ቅለም የተነከረ የአውራ በግ ቆዳ፣ ከበላዩም የሚህን የአቆስጣ ቆዳ ሠራ።
\s5
\v 20 ባስልኤል ከግራር ዕንጨት ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ።
\v 21 ወጋግራ እርዝመት ዐሥር ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበር።
\v 22 እርስ በርስ ለማያያዝ በያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ማያያዣዎች ነበር። የመገናኛውን ድንኳን ወጋግራዎች ሁሉ በዚህ መንገድ ሠራ።
\v 23 ባስልኤል በዚህ መንገድ ወጋግራዎችን ለመገናኛው ድንኳን ሠራ። ለደቡቡ ጎንም ሃያ ወጋግራዎችን አበጀ።
\s5
\v 24 ባስልኤል ከሃያዎቹ ወጋግራዎች ሥር የሚሆኑ አራ የብር መቆሚያዎችን አበጀ። ማያያዣዎች ለመሆን ከመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ከያንዳንዱ ሌላ ወጋግራ በታችም እንደዚሁ ሁለት መቆሚያዎች ነበሩ።
\v 25 ጎን ላለው ለመገናኛው ድንኳን ሁለተኛ ጎን ሃያ ወጋግራዎችንና
\v 26 የብር መቆሚያዎቻቸውን አበጀ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለው ወጋግራ ሥርም እንዲሁ ሁለት ሁለት መቆሚያ አበጅቶአል።
\s5
\v 27 በስተ ምዕራብ ላለው ለመገናኛው ድንኳን ጀርባ ባስልኤል ስድስት ወጋግራዎችን ሠራ።
\v 28 ድንኳን የኋላ ማእዘኖች ሁለት ወጋግራዎችን አበጀ።
\s5
\v 29 እነዚህ ወጋግራዎች ከታች የተነጣጠሉ፣ ከላይ ደግሞ በአንድ ቀለበት የየያያዙ ነበር። ለሁለቱም የኋላ ማእዘኖች የተደረገው በዚህ መንገድ ነበር።
\v 30 ከብር መቆሚያዎቻቸው ጋር ስምንት ወጋግራዎች ነበሩ። በመጀመሪያው ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች፣ በሚቀጥለውም ወጋግራ ሥር ሁለት መቆሚያዎች ለያንዳንዱ ወጋግራ ሁለት ሁለት በመሆን ዐሥራ ስድስት መቆሚያዎች ነበሩ።
\s5
\v 31 ባስልኤል የግራር ዕንጨት አግዳሚዎችን አበጀ፦ ለመገናኛው ድንኳን አንድ ጎን ወጋግራዎች ዐምስት፣ አግዳሚዎችን፣
\v 32 የመገናኛው ድንኳን ጎን ወጋግራዎች አምስት አግዳሚዎችን፣ በምዕራብ በኩል ላለው ለመገናኛው ድንኳን የኋላ ጎን ወጋግራዎችም ዐምስት አግዳሚዎችን ሠራ።
\v 33 አግዳሚዎቹን የሥራቸውም በወጋግራዎች መካከል ላይ ከዳር እስከ ዳር እንዲደርሱ አድርጎ ነው።
\v 34 ወጋግራዎቹን በወርቅ ለበጣቸው። አግዳሚዎችን ለማያያዝ የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ፣ አግዳሚዎችንም በወርቅ ለበጣቸው።
\s5
\v 35 በብልኀተኛ ሠራተኛ ሥራ ኪሩቤል የተጠለፉበትን መጋረጃ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም ሠራው።
\v 36 አራት የግራር ዕንጨት ምሰሶዎችን አበጅቶ በውርቅ ለበጣቸው። ለምሰሶዎችም የወርቅ ኵላቦችን ሠርቶ አራት የብር መቆሚያዎችን አደረገላቸው።
\s5
\v 37 ለድንኳኑ መግቢያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ ካማረ በፍታም በጥልፍ ጠላፊ ሥራ የተዘጋጀ መጋረጃ አበጀለት።
\v 38 የመጋረጃውን ዐምስት ምሰሶዎች ከኵላቦች ጋር ሠራ። የምሰሶዎችን ዐናትና ዘንግ በወርቅ ለበጣቸው። ዐምስት መቆሚያዎቻቸውም ከነሐስ የተሰሩ ነበሩ።
\s5
\c 37
\p
\v 1 ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱ አንድ ተኩል ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ታቦታ ከግራር ዕንጨት ሠራ።
\v 2 ውስጡንና ውጩንም በንጹሕ ወርቅ ለበጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።
\v 3 ለአራት እግሮቹም አራት የወርቅ ቀለበቶችን፣ በአንዱ ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን፣ በሌላውም ጎኑ ላይ ሁለት ቀለበቶችን ጨምሮ ሠራ።
\s5
\v 4 ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
\v 5 ታቦቱን ለመሸከም በታቦቱ ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ መሎጊያዎቹን አስገባቸው።
\v 6 ሁለት ተኩል ክንድ፣ ወርዱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ የስርየት መክደኛ ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
\s5
\v 7 ባስልኤል ለስርየት መክደኛው ሁለት ጫፎች ሁለት ኪሩቤልን ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ።
\v 8 አንዱ ኪሩብ ለአንዱ የስርየት መክደኛ፣ ሌላውም ለሌላው የስርየት መክደኛ ጫፍ ነበረ። ኪሩቤል ከስርየት መክደኛው ጋር ወጥ ሆነው ተበጅተው ነበር።
\v 9 ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ወደ ላይ በመዘርጋት የስርየት መክደኛውን በድንፎቻቸው ጋረዱት። እርስ በርስ ትይዩ ሆነውም ወደ ስርየት መክደኛው መካከል ይመለከቱ ነበር።
\s5
\v 10 ባስልኤል እርዝመቱ ሁለት ክንድ፣ ቁመቱም አንድ ተኩል ክንድ የሆነ ጠረጴዛ ከግራር ዕንጨት ሠራ።
\v 11 ወርቅ ለበጠው፤ ዙሪያውንም በንጹሕ ወርቅ ከፈፈው።
\v 12 አንድ ስንዝር ጠርዝ ከወርቅ ክፈፍ ጋር አበጀለት።
\v 13 የወርቅ ቀለበቶችንም ሠርቶ የጠረጴዛው እግሮች ካሉበት ማእዘኖች ጋር አያያዛቸው።
\s5
\v 14 ለመሸከም መሎጊያዎችን ማስገባት እንዲቻል ቀለበቶቹ ከጠርዙ ጋር ተያይዘው ነበር።
\v 15 ጠረጴዛውን መሸከም እንዲቻል መሎጊያዎቹን ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
\v 16 በጠረጴዛው ላይ የሚቀመጡ ዕቃዎችን፦ ድስቶችን፣ ዝርግና ጎድጓዳ ሳሕኖችን ጭልፋዎችን፣ ወጭቶችንና የመጠጥ መሥዋዕቱን ማፍሰሻ ማንቆርቆሪያዎች ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
\s5
\v 17 ከነማቆሚያውና ከነዘንጉ ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ ሠራ። ጽዋዎቹ፣ ቀንበጦቹና አበባዎቹ በሙሉ ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ነበር የተሠሩት።
\v 18 ቅርንጫፎች በመቅረዙ አንድ ጎን፣ ሦስት ቅርንጫፎች ደግሞ በሌላው የመቅረዙ ጎን ተሠርተው ስድስት ቅርንጫፎች ነበር።
\v 19 ቅርንጫፍ ከቀንበጥና ክአበባ ጋር የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ነበሩት፤ በሌላውም ቅርንጫፍ እንደዚሁ የለውዝ አበባ የሚመስሉ ሦስት ጽዋዎች ከቀንበጥና ከአበባ ጋር ነበር። ከመቅረዙ ለሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር።
\s5
\v 20 በመቅረዙ መካከል ላይ ባለው ዘንግ ላይ የለውዝ አበቦችን የሚመስሉ እራት ጽዋዎች ከቀንበጦቻቸውና ከአበቦቻቸው ጋር ተሠርተዋል።
\v 21 በመጀመሪያ የቅርንጫፎች ጥንድ ሥር ወጥ ሆኖ ዐብሮት የተሠሩ ቀንበጦች ነበር። ከመቅረዙ በሚወጡ ስድስት ቅርንጫፎች ሁሉ የተደረገው አንድ ዐይነት ነበር።
\v 22 ቅርንጫፎቻቸው ከመቅረዙ ጋር ወጥ ሆነው ከተቀጠቀጠ ንጹሕ ወርቅ የተሠሩ ነበር።
\s5
\v 23 መቅረዙንና ሰባቱን መብራቶች፣ መኮስተሪያዎቹንና የኵስታሪ ማስቀመጫዎቻቸውን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ።
\v 24 መቅረዙንና ዐባሪ ዕቃዎቹን ከአንድ መክሊት ንጹሕ ወርቅ ሠራቸው።
\s5
\v 25 እርዝመቱ አንድ ክንድ፣ ወርዱም አንድ ክንድ የሆነውን የዕጣኑን መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። አራት ማእዘንና ቁመቱም ሁለት ክንድ ነበር። ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበር።
\v 26 የዕጣኑን መሠዊያ፦ ዐናቱን፣ ጎኖቹንና ቀንዶቹን በንጹሕ ወርቅ ለበጣቸው። ለዙሪያውም የወርቅ ክፈፍ አበጀለት።
\s5
\v 27 በሁለቱ ተነጻጻሪ ጎኖቹ ላይ ከክፈፉ ሥር እንዲያያይዙት ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠራ። ቀለበቶቹ መሠዊያውን ለመሸከም መሎጊያዎችን ለመያዝ የሚያገለግሉ ናቸው።
\v 28 ከግራር ዕንጨት ሠርቶ በወርቅ ለበጣቸው።
\v 29 የተቀሰውን የመቅቢያ ዘይትና የሽቶ ቀማሚ ሥራ የሆነውን፣ ንጹሕና ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን ሠራ።
\s5
\c 38
\p
\v 1 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያ ከግራር ዕንጨት ሠራ። ዐምስት ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ስፋት፣ አራት ማእዘንና ሦስት ክንድ ቁመት ነበረው።
\v 2 ማእዘኖችም የበሬ ቀንዶችን የሚመስሉ ቅርጾችን በመሥራት አስረዘማቸው። ቀንዶቹ ከመሠዊያው ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ መሠዊያውንም በነሐስ ለበጠው።
\v 3 ለመሠዊያው የሚያስፈልገውን ዕቃ ሁሉ፦ ለዐመድ ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ጎድጓዳ ሳሕኖችን፣ ሜንጦዎችንና ማንደጃዎችን በሙሉ ከነሐስ ሠራ።
\s5
\v 4 ከደረጃው ሥር ከመሠዊያው እኩሌታ እስከ ታች የሚደርስ እንደ መረብ የተሠራ የነሐስ ፍርግርግ ለመሠዊያው አበጀ።
\v 5 ፍርግርግ አራት ማእዘኖች ለመሎጊያዎቹ መያዣ አራት ቀለበቶችን ሠራላቸው።
\s5
\v 6 ዕንጨት መሎጊያዎችን ሠርቶ በነሐስ ለበጣቸው።
\v 7 መሎጊያዎቹን መሠዊያውን ለመሸከም በመሠዊያው ጎኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። መሠዊያውን ክፍት አድርጎ በሳንቃዎች ሠራው።
\s5
\v 8 ባስልኤል ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን ከነሐስ መቆሚያ ጋር ሠራ። ሳሕኑን የሠራውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ የሚያገለግሉት ሴቶች ይጠቀሙባቸው ከነበሩ መስተዋቶች ነው።
\s5
\v 9 ሠራው። በአደባባዩ ደቡብ ጎን ላይ የነበሩት መጋረጃዎች ከአማረ በፍታ የተሠሩና አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው ነበሩ።
\v 10 መጋረጃዎቹ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ መቆሚያዎች ነበሯቸው። ከምሰሶዎቹና ከብር ዘንጎቹ ጋር የተያያዙ ኵላቦችም ነበሩ።
\s5
\v 11 ጎን በኩልም እንደዚሁ አንድ መቶ ክንድ እርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች ከሃያ ምሰሶዎችና ከሃያ የነሐስ መቆሚያዎች፣ ከምሰሶዎቹ ጋር ከተያያዙ ኲላቦችና ከብር ዘንጎች ጋር ነበር።
\v 12 የምዕራቡ ጎን መጋረጃዎች ዐምሳ ክንድ የሚረዝሙ፣ ዐሥር ምሰስዎችና መቆሚያዎች ያሏቸው ነበሩ። የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎች ብር ነበሩ።
\s5
\v 13 አደባባዩም በምሥራቁ ጎን ላይ ዐምሳ ክንድ ይረዝም ነበር።
\v 14 የመግቢያው አንድ ጎን መጋረጃዎች እርዝመት ዐሥራ ዐምስት ክንድ ነበረ። ሦስት ምሰሶዎች ከሦስት መቆሚያዎች ጋር ነበሯቸው።
\v 15 በአደባባዩ መግቢያ ሌላ ጎን ላይም ዐሥራ ዐምስት ክንድ የሚረዝሙና ሦስት ምሰሶዎችና ሦስት መቆሚያዎች ያሏቸው መጋረጃዎች ነበሩ።
\v 16 በአደባባዩ ዙሪያ ያሉት መጋረጃዎች ሁሉ አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ ነበሩ።
\s5
\v 17 የምሰሶዎቹ መቆሚያዎች ከነሐስ፣ የምሰሶዎቹ ኵላቦችና ዘንጎቻቸው፣ የዐናታቸውም መሸፈኛ ከብር የተሠሩ ነበሩ። የአደባባዩ ምሰሶዎች ሁሉ በብር የተለበጡ ነበር።
\v 18 የአደባባዩ በር መጋረጃቅ እርዝመት ሃያ ክንድ ነበረ። ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ የተሠራ ነበረ። እንደ አደባባዩ መጋረጃዎች ሃያ ክንድ እርዝመትና ዐምስት ክንድ ቁመት ነበረው።
\v 19 የነሐስ መቆሚያዎችና የብር ኵላቦች ነበሩት። የዐናታቸው መሸፈኛና ዘንጎቹ ከብር የተሠሩ ነበሩ።
\v 20 የመገናኛው ድንኳን ካስማዎች ሁሉ የተሠሩት ከነሐስ ነበር።
\s5
\v 21 የሙሴን ትእዛዝ በመከተል በተመዘገበው መሠረት የመገናኛው ድንኳን፣ ይኸውም የምስክሩ ድንኳኝ ቆጠራ ይህ ነው። በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት ይህ የሌዋውያኑ ሥራ ነበረ።
\v 22 ከይሁዳ ነገድ የሆነው፣ የሖር የልጅ ልጅ፣ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ትእዛዝ ሁሉ ፈጸመ።
\v 23 ከባስልኤልም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ቅርጽ አውጪ ሠራተኛ፣ የእጅ ጥበብ ሙያተኛ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ግምጃና በአማረ በፍታ ጥልፍ ጠላፊም ሆኖ ዐብሮት ሠራ።
\s5
\v 24 ከመቅደሱ ሥራ ጋር ለተያያዘው ተግባር ሁሉ ጥቅም ላይ የዋለው ወርቅ ማለትም፣ ከስጦታው የተገኘው ወርቅ ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል መጠን መሠረት ሃያ ዘጠኝ መክሊትና ሰባት መቶ ሠላሳ ሰቅል ነበረ።
\v 25 ማኅበረ ሰቡ የሰጠው ብር በመቅደሱ ሰቅል መጠን ተመዝኖ አንድ መቶ መክሊትና አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰባ ዐምስት ሰቅል፣
\v 26 በአንድ ሰው አንድ ቤካ ይኸውም በመቅደሱ ሰቅል መጠን ግማሽ ሰቅል ነበረ። ይህ ቍጥር የተደረሰበት በሕዝብ ቆጠራው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆናቸው ተቆጥረው በተገኘው ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ወንዶች ቍጥር በያንዳንዱ ሰው ተሰልቶ ነው።
\s5
\v 27 የመቅደሱንና የመጋረጃዎችን መቆሚያዎች ለመሥራት አንድ መቶ የብር መክሊት ወጪ ሆኖአል፦ መቆሚያዎቹ በጠቅላላ አንድ መቶ ሆነው፣ ለያንዳንዱ መቆሚያ አንድ መክሊት ተከፍሎአል ማለት ነው።
\v 28 በቀሩት አንድ ሺሕ ሰባቶ መቶ ሰባ ዐምስት የብር ሰቅሎች ባስልኤል የምሰሶዎቹን ኵላቦች ሠርቶ ዐናታቸውን ሸፈነባቸው፤ ዘንጎችንም ለምሰሶዎቹ ሠራባቸው።
\v 29 ከስጦታ የተገኘው ነሐስ ተመዝኖ ሰባ ታለንትና ሁለት ሺሕ አራት መቶ ሰቅል ሆነ።
\s5
\v 30 በዚህም የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የነሐስ መሠዊያውን፣ የእርሱንም የነሐስ ፍርግርግ፣ የመሠዊያውን ዕቃ ሁሉ፣
\v 31 የአደባባዩን መቆሚያዎች፣ የአደባባዩን መግቢያ መቆሚያዎች፣ የመገናኛውን ድንኳንና የአደባባዩን ድንኳን ካስሞች ሁሉ ሠራበት።
\s5
\c 39
\p
\v 1 በመቅደሱ ውስጥ ለሚከናወነው አገልግሎት ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ የተሠሩ ልብሶችን አበጁ። እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለቤተ መቅደሱ የሚሆኑ የአሮንን ልብሶች ሠሩ።
\s5
\v 2 ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና አምሮ ከተፈተለ በፍታ ሠራ።
\v 3 ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በአማረ በፍታ ለመ|ሥራት ወርቁን ቀጥቅጠው ወደ ሽቦነት ቆራረጡት።
\s5
\v 4 የትከሻ ንጣዮችን ሠርተው ከላይኛዎቹ ጠርዞቹ ጋር አያያዙት።
\v 5 በብልኀት የተጠለፈው የወገብ መታጠቂያም እንደ ኤፉዱ ሲሆን፣ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ አምሮ ከተፈተለ በፍታ ይኸውም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ከኤፉድ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበረ።
\s5
\v 6 የመረግድ ድንጋዮችን በወርቅ ፈርጥ ክፈፍ አበጁላቸው፤ እንደ ማኅተምም የዐሥራ ሁለቱን የእስራኤል ልጆች ስሞች ቀረጹባቸው።
\v 7 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት፣ ባስልኤል በሴፉዱ የትከሻ ንጣዮች ላይ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች የመታሰቢያ ድንጋዮች አድርጎ አስቀመጣቸው።
\s5
\v 8 ኪሱንም ብልኅ ሠራተኛ እንደሚሠራው፣ እንደ ኤፉዱ አበጀው። ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከአማረ በፍታ ሠራው።
\v 9 ኪሱ አራት ማእዘን ነበረ። ርዝመቱም ወርዱም አንድ ስንዝር ሆኖ የተደረበ ዕጥፍ ነበረ።
\s5
\v 10 በውስጡም አራት የዕንቍ ድንጋዮች ፈድፎች አበጅተዋል። በመጀመሪያው ረድፍ ሰርድዮን፣ ቶጳዝዮንና አብራቅራቂ ዕንቍ ነበሩት።
\v 11 ረድፍ በሉር፣ ሰንፔር፣ አልማዝ፤
\v 12 በሦስተኛው ረድፍ ያክንት፣ ኬልቄዶን፣ አሜቴስጢኖስ፤
\v 13 በአራተኛውም ረድፍ ቢረሌ፣ መረግድና ኢያስጲድ ነበሩ። ድንጋዮቹ በወርቅ ፈርጥ ዙሪያቸውን የተከፈፉ ነበር።
\s5
\v 14 እያንዳንዳቸው በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ልጆች ስሞች ቅደም ተከተል መሠረት የተቀመጡ ነበር። እያንዳንዱ ስም ከዐሥራ ሁለቱ ነገዶች አንዱን በመወከል በማተሚያ ቀለበት ላይ እንደሚቀረጽ የተቀረጸባቸው ነበሩ።
\v 15 ኪሱ ላይ ከንጹሕ ወርቅ እንደ ገመድ የተጎነጎኑ ድሪዎችን አበጁ።
\v 16 ሁለት የወርቅ ፈርጦችንና ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ሁለቱን ቀለበቶች ከደረት ኪሱ ሁለት ጠርዞች ጋር አያያዟቸው።
\s5
\v 17 ሁለቱን የተጎነጎኑ የወርቅ ድሪዎች በደረት ኪሱ ጠርዞች ሁለት ቀለበቶች ውስጥ አስቀመጧቸው።
\v 18 ሌሎች ሁለት ጫፎች ከሁለት ፈርጦች ጋር አያያዟቸው። ከኤፉዱ የትከሻ ንጣዮች ጋር በኤፉዱ ፊት አገናኗቸው።
\s5
\v 19 የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው ከውስጠኛው ጠርዝ ቀጥሎ በሚገኘው ጎን በደረት ኪሱ ሌሎች ሁለት ጠርዞች ላይ አስቀመጧቸው።
\v 20 ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተው፣ በመያዣው አጠገብ በብልኀት ከተሠራው የወገብ መታጠቂያ በላይ፣ ከአፉዱ ፊት ሁለት የትከሻ ንጣዮች ግርጌ ጋር አያያዟቸው።
\s5
\v 21 በብልኀት ከተሠራው ከኤፉዱ የወገብ መታጠቂያ በላይ መያያዝ እንዲችል፣ የደረት ኪሱን በራሱ ቀለበቶች ከኤፉዱ ቀለበቶች ጋር በሰማያዊ ፈትል አሰሩት። ይህ የሆነው የደረት ኪሱ ከኤፉዱ የተነጠለ እንዳይሆን ነው። የተደረገውም እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
\s5
\v 22 የኤፉዱን ቀሚስ ሙሉ በሙሉ የሸማኔ ሥራ ከሆነው ከሐምራዊ ጨርቅ ሠራው።
\v 23 መካከሉ ላይ ዐንገት ማስገቢያ ነበረው። እንዳይቀደድም ዙሪያውን የተዘመዘመ ጠርዝ ነበረው።
\v 24 በታችኛው የቀሚሱ ዘርፍ ላይም የሰማያዊ፣ የሐምራዊ፣ የቀይ ማግና የአማረ በፍታ ሮማኖችን አበጁ።
\s5
\v 25 ሻኵራዎችን ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በታችኛው የቀሚሱ ጠርዝ ዙሪያ ላይ በሮማኖቹም መካከል፣
\v 26 አገልግሎት በቀሚሱ ጠርዝ ላይ ሻኵራን ሮማን፣ ሻኵራና ሮማን እያደረጉ አስቀመጧቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
\s5
\v 27 ለአሮንና ለልጆቹ ሸሚዞችን ከአማረ በፍታ ሠሩ።
\v 28 የራስ መጠምጠሚያዎችን፣ ቆቦችንና ሱሪዎችን ከአማረ በፍታ፣
\v 29 መታጠቂያዎችንም ከአማረ በፍታ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ጥልፍ ጠላፊ እንደሚሠራው አድርገው አበጇቸው። ይህም የሆነው እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት በነበረው መሠረት ነው።
\s5
\v 30 አክሊል ሠሌዳ ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው በቀለበት ላይ ማኅተም እንደሚቀረጽ በላዩ ቅዱስ ለእግዚአብሔርን ቀረጹበት።
\v 31 እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ በመጠምጠሚያው ዐናት ላይ ለማንጠልጠል ሰማያዊ ፈትል አሰሩበት።
\s5
\v 32 ድንኳን፣ የማደሪያው ሥራ ተጠናቀቀ። የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጣቸውን መመሪያዎች በመከተል ሁሉንም አደረጉ።
\v 33 ድንኳኑንና ዕቃዎቹን ሁሉ፣ ካስማዎቹን፣ ወጋግራዎቹን፣ አግዳሚዎቹን፣ ምሰሶዎቹንና መቆሚያዎቹን፣
\v 34 በቀይ ቀለም የተነከረውን የአውራ በግ ቆዳ መሸፈኛ፣ የአስቆጣ ቆዳዊን መሸፈኛና የሚሸፍነውን መጋረጃ፣
\v 35 የምስክሩን ታቦት፣ መሎጊያዎቹንና የስርየት መክደኛውን ወደ ሙሴ አመጡ።
\s5
\v 36 ጠረጴዛውን፣ የጠረጴዛውን ዕቃዎች ሁሉና የገጽ ኅብስቱን፤
\v 37 የንጹሑን ወርቅ መቅረዝና የረድፍ መብራቶችን ከዐባሪ ዕቃዎቹና ከመብራቶቹ ዘይት ጋር፤
\v 38 መሥዐዊያውን፣ መቅቢያ ዘይቱንና ጣፋጭ መዐዛ ያለን ዕጣን፣ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃ፤
\v 39 የነሐስ መሠዊያውን ከነሐስ ፍርግርጉና ከመሎጊያዎቹ፣ ከዕቃዎቹ፣ ከትልቁ የመታጠቢያ ሳሕንና ከመቆሚያው ጋር አመጡ።
\s5
\v 40 የአደባባዩን መጋረጃዎች ከምሰሶዎቹና ከመቆሚያዎቹ ጋር፣ የአደባባዩን መግቢያ መጋረጃም፣ ገመዶቹንና የድንኳን ካስማዎችን፣ ለመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ዕቃ ሁሉ አመጡ።
\v 41 አገልግሎት በጥበብ የተሠሩትን ልብሶች፣ ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ የካህኑን የአሮንንና የልጆቹን የተቀደሱ ልብሶችም አመጡ።
\s5
\v 42 ስለዚህም የእስራኤል ሰዎች እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ሥራውን በሙሉ አከናወኑ።
\v 43 ሙሴ ሥራውን ሁሉ ሲፈትሽ፣ እነሆ ሁሉን አከናውነውታል። ያከናወኑትም እግዚአብሔር አዝዞት በነበረው በዚያው መንገድ ነው። ሙሴም ሕዝቡን ባረካቸው።
\s5
\c 40
\p
\v 1 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤
\v 2 “በዐዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ወር የመጀመሪያ ቀን ማደረያውን፣ የመገናኛውን ድንኳን ትከለው።
\s5
\v 3 ታቦት በውስጡ አስቀምጠው፤ ታቦቱንም በመጋረጃ ከልለው።
\v 4 ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አምጣና በላዩ የሚቀመጡትን ዕቃዎች በሥርዐት አስቀምጥ። ከዚያም መቅረዙን አስገብተህ መብራቶቹን አስተካክል።
\s5
\v 5 የወርቅ የዕጣን መሠዊያውን በምስክሩ ታቦት ፊት አስቀምጥ፤ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃም አድርግ።
\v 6 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አስቀምጥ።
\v 7 ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠው፤ ውሀም አድርግበት።
\s5
\v 8 በዙሪያውም አደባባይ ሥራለትን በአደባባዩ መግቢያ ላይ መጋረጃውን ስቀል።
\v 9 መቅቢያ ዘይቱን ውሰድና መገናኛውን ድንኳንና አውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ቅባ። እርሱንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም የተቀደሰ ይሆናል።
\v 10 የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያና የመሠዊያውን ዕቃዎች ሁሉ ቅባቸው።
\v 11 መሠዊያውን ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም ለእኔ እጅግ የተቀደሰ ይሆንልኛል።
\s5
\v 12 ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ አምጣና በውሀ እጠባቸው።
\v 13 ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን ለአሮን አልብሰው፤ ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግልም ቅባው፤ ቀድሰውም።
\s5
\v 14 ልጆቹንም አምጣና ሸሚዞችን አልብሳቸው።
\v 15 ካህናቴ ሆነው እንዲያገለግሉኝ፣ አባታቸውን እንደ ቀባኸው እነርሱንም ቅጣቸው። የእነርሱ መቀባት በትውልዶች ሁሉ የዘለቄታ ካህንነትን ለእነርሱ ያስገኛል።”
\v 16 ሙሴ ያደረገው ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ተከተለ። እነዚህንም ሁሉ አደረገ።
\s5
\v 17 በሁለተኛው ዓመት የመጀመሪያ ወር አንደኛ ቀን ላይ የመገናኛው ድንኳን ተተከለ።
\v 18 ሙሴ መገናኛውን ድንኳን ተከለ፤ መቆሚያዎቹንም በስፍራቸው አስቀመጠ፤ ወጋግራዎቹን አቁሞ አግዳሚዎቹን አያያዘ፤ ምሰሶዎቹንም አቆመ።
\v 19 በማደሪያው ላይ መሸፈኛውን ዘረጋ፤ ድንኳኑንም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ከበላዩ አስቀመጠው።
\v 20 ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው።
\s5
\v 21 ወደ መገናኛው ድንኳን አመጣው። እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ የምስክሩን ታቦት ለመከለል መጋረጃውን አደረገ።
\v 22 ሰሜን ጎን ከመጋረጃው ውጭ ጠረጴዛውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ።
\v 23 እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው፣ ኅብስቱን በጠረጴዛው ላይ በሥርዐት በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው።
\s5
\v 24 መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ደቡብ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠው።
\v 25 መብራቶቹን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእግዚአብሔር ፊት አበራቸው።
\s5
\v 26 የተሠራውን የዕጣን መሠዊያም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ፊት ለፊት አደረገው።
\v 27 ላይም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን አቀጣጠለ።
\s5
\v 28 መጋረጃውን በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለ።
\v 29 የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ አስቀመጠ። በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እግዚአብሔር እንዳዘዘው አቀረበ።
\v 30 የመታጠቢያ ሳሕኑን በመገናኛው ድንኳንና በመሠውያው መካከል አኖረው፤ የመታጠቢያ ውሀም በውስጡ አደረገ።
\s5
\v 31 ሙሴ፣ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በመታጠቢያው ውሀ ይታጠቡ ነበር፤
\v 32 መገናኛው ድንኳን ውስጥ በሚገቡትና መሠዊያው ወዳለበት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ታጥበውታል።
\v 33 ሙሴ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን አቆመ። መጋረጃውንም በአደባባዩ መግቢያ ዘረጋ። ሙሴ በዚህ መንገድ ሥራውን ፈጸመ።
\s5
\v 34 ደመናውም የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፤ የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ሞላው።
\v 35 ደመናው በላዩ ስላረፈና የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ስለ ሞላው፣ ሙሴ መገናኛው ድንኳን ውስጥ መግባት አልቻለም ነበር።
\s5
\v 36 ከማደሪያው ድንኳን በተነሣ ጊዜ ሁሉ፣ የእስራኤል ሰዎች ይጓዛሉ።
\v 37 ግን ደመናው ከማደሪያው ላይ ካልተነሣ፣ ሕዝቡ አይጓዙም። ደመናው እስከሚነሣበት ቀን ድረስ ይቆያሉ።
\v 38 በሁሉም የእስራኤል ሕዝብ ፊት በጕዟቸው ሁሉ ቀን የእግዚአብሔር ደመና፣ ማታ ደግሞ እሳቱ በማደሪያው ላይ ነበረ።

769
16-NEH.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,769 @@
\id NEH
\ide UTF-8
\h ነህምያ
\toc1 ነህምያ
\toc2 ነህምያ
\toc3 neh
\mt ነህምያ
\s5
\c 1
\p
\v 1 እኔ የሐካልያ ልጅ ነህምያ ነኝ፡፡ ንጉስ አርጤክስስ የፋርስን መንግስት መግዛት በጀመረበት በሃያኛው አመት፣ ካሴሉ በተባለው ወር፤ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሼ ያደረግሁትን ይህን ነገር ጻፍሁ፡፡ እኔም በፋርስ ዋና ከተማ በሱሳ ነበርሁ፡፡
\v 2 ወንድሜ አናኒ እኔን ለማየት መጣ፡፡ እርሱና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ከይሁዳ መጥተው ነበር፡፡ ከባቢሎን ምርኮ ስላመለጡ ጥቂት አይሁዶች፣ እና ስለ ኢየሩሳሌም ከተማ ጥያቄዎችን ጠየቅኳቸው፡፡
\s5
\v 3 እነርሱም እንዲህ አሉኝ፣ “ከምርኮ ያመለጡት አይሁዶች በዚያ በታላቅ መከራ እና ውርደት እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ የከተማዋ ቅጥሮች በብዙ ስፍራዎች ተገፍተው ስለወደቁ ጠላት በቀላሉ ይገባባታል፣ ይህም ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን የከተማዋ በሮች ሙሉ በሙሉ በእሳት ተቃጥለዋል፡፡”
\s5
\v 4 ይህንን በሰማሁ ጊዜ፣ ተቀምጬ አለቀስኩ፡፡ ለብዙ ቀናት በሰማይ ወዳለው አምላክ በለቅሶ ጾምኩ ጸለይኩ፡፡
\v 5 እንዲህ ስል ጸለይኩ፣ “ያህዌ፣ አንተ በሰማይ ያለህ አምላክ ነህ፡፡ አንተ ታላቅና አስደናቂ አምላክ ነህ፣ ለሚወዱህና ህግጋትህንና ትዕዛዛትህን ለሚጠብቁ ሁሉ የተቀደሰውን አብሮነትህንና ቃልኪዳንህን ትጠብቃለህ፡፡
\s5
\v 6 እባክህ አሁን ወደ እኔ ተመልከት ወደ ጸሎቴም አድምጥ፡፡ በቀንና በለሊት ለህዝብህ ለእስራኤል እጸልያለሁ፡፡ ኃጢአት መስራታችንን እናዘዛለሁ፡፡ እኔና ቤተሰቤ ጭምር አንተን በድለናል፡፡
\v 7 በጣም ክፉ አድርገናል፡፡ ከብዙ አመታት አስቀድሞ ባሪያህ ሙሴ አንተ እናደርገው ዘንድ ያዘዝከውን ህግጋትና ስርዓቶች ሰጥቶናል፣ እኛ ግን ህግጋትህን አልጠበቅንም፡፡
\s5
\v 8 እባክህ ለአገልጋይህ ለሙሴ የተናገርከውን አስብ፡፡ እንዲህ ብለሃል፣ ‘በፊቴ በታማኝነት እና በመታዘዝ ባትመላለሱ በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፡፡
\v 9 ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ እና ትዕዛዞቼን ብትጠብቁ፣ ወደ ሩቅ ሥፍራዎች ብትጋዙም እንኳን፣ ሁላችሁንም ሰብስቤ የእኔን ታላቅነትና ክብር ወደማሳያችሁ ወደዚህ ስፍራ እመልሳችኋለሁ፡፡
\s5
\v 10 እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን፡፡ በታላቁ ሀይልህ ከባርነት ነጻ ያወጣኸን ህዝብ ነን፡፡ አንተ ያንን ያደረግከው ማድረግ የምትፈልገውን ሁሉ ማድረግ ስለምትችል ነው፡፡
\v 11 ያህዌ፣እባክህ የእኔን የአገልጋይህን ፀሎት ስማ፡፡ እባክህ በማንነትህና በስራህ አንተን ሲያከብሩ፣ ታላቅ ሀሴት የሚያደርጉትን የህዝብህን ሁሉ ጸሎት ስማ፡፡ ወደ ንጉሱ ፊት ስቀርብ መከናወንን እንድትሰጠኝ እጸልያለሁ፤ ለንጉሱ ጥያቄዬን ሳቀርብ ህይወቴ አደጋ ላይ እንዳትወድቅ ጠብቃት፡፡ ምህረትህ ይከተለኝ፡፡” እኔ ለንጉሱ እጅግ ከታመኑት አገልጋዮች አንዱ ሆኜ አገለግል ነበር፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 በንጉስ አርጤክስ፣ አገዛዝ ሃያኛ ዓመት፣ ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር፣ በክብረ በዓሉ ለንጉሱ ወይን ጠጅ የሚቀርብበት ሰዓት ነበር፡፡ ወይን ወስጄ ለንጉሱ አቀረብኩ፡፡ ከዚያ አስቀድሞ በንጉሱ ፊት እንዲህ አዝኜ ቀርቤ አላውቅም ነበር፡፡
\v 2 በዚያን ቀን ግን፣ ንጉሱ እኔን ተመልክቶ እንዲህ አለኝ፣ “ለምን እንዲህ እጅግ አዘንህ? የታመምክ አትመስልም፡፡ ምናልባት መንፈስህ ታውኮ ይሆንን? ” እኔም በጣም ፈርቼ ነበር፡፡
\s5
\v 3 እንዲህ ስል መለስኩ፣ “ንጉስ ሆይ፣ ለዘለዓለም ንገስ! ያዘንኩት ያለ ምክንያት አይደለም፣ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፍርስራሽ ሆናለች፣ በከተማዋ ዙሪያ ያሉ በሮቿ በሙሉ ተቃጥለው አመድ ሆነዋል፡፡”
\s5
\v 4 ንጉሱ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ? ” እናም ለእርሱ መልስ ከመስጠቴ አስቀድሞ፣ በሰማይ ወዳለው አምላክ ጸለይኩ፡፡
\v 5 ከዚያ እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠሁ፣ “ታደርገው ዘንድ ፈቃድህ ከሆነ፣ እኔም አንተን ደስ አሰኝቼ ከሆነ፣ አባቶቼ የተቀበሩባትን ከተማ ኢየሩሳሌምን መልሼ እንድገነባ ወደዚያ እንድሄድ ፈቀድልኝ፡፡”
\v 6 ንጉሱ (ንገስቲቱ አጠገቡ ተቀምጣ ሳለ) እንደህ ሲል ጠየቀኝ፣ “እንድትሄድ ብፈቅድልህ፣ ለስንት ጊዜ በዚያ ትቆያለህ? ደግሞስ መቼ ትመለሳለህ? ” እርሱም፣ ወደዚያ የምሄድበትንና ተመልሼ የምመጣበትን ቀን እንዳሳወቅሁት፣ ወዲያውኑ እንድሄድ ፈቃድ ሰጠኝ፡፡
\s5
\v 7 ደግሞም ለንጉሱ እንዲህ አልኩት፣ “ለአንተ ለሰጠሁት ታማኝ አገልግሎቴ እንደ ሽልማት አድርገህ፣ ከአፍራጦስ ወንዝ ባሻገር ለሚያስተዳድሩ ገዥዎች ደብዳቤ ስጠኝ፡፡ ወደ ይሁዳ ስገባና ስወጣ በግዛቶቻቸው በደህንነት መጓዝ እችል ዘንድ እንዲፈቅዱልኝ እባክህን ትዕዛዝ ስጣቸው፡፡
\v 8 እንዲሁም፣ እባክህን ደኖችህን ለሚያስተዳድረው ለአሳፍ ደብዳቤ ፃፍልኝ፣ ደግሞም በቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚገኘውን ግንብ በሮች አምዶቹን ለማበጀት፣ የከተማዋን ቅሮች ለመጠገን፣ እና የምኖርበትን ቤት እንዲሰጠኝ ፃፍለት፡፡” እግዚአብሔር ለዚህ ስራ የሚያስፈልገኝን እንዳገኝ እየረዳኝ ስለነበር፣ ንጉሱ እንዲያደርግ የጠየቅኩትን አደረገልኝ ፡፡
\s5
\v 9 ወደ ይሁዳ ለመሄድ ተነሳሁ፡፡ ንጉሱ፣ እኔን እንዲያጅቡኝና እንዲጠብቁኝ አንዳንድ ፈረሰኛ የጦር መኮንኖችንና ወታደሮችን ላከ ፡፡ ገዥዎቹ ወደሚያስተዳድሩት ግዛት ስንደርስ፣ ከንጉሱ ዘንድ የተላከውን ደብዳቤ ሰጠኋቸው፡፡
\v 10 ነገር ግን ሁለቱ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ሖሮናዊው ሰንበላጥና አሞራዊው አገልጋይ ጦቢያ፣ እኔ መድረሴን ሲሰሙ የእስራኤልን ህዝብ የሚረዳ በመምጣቱ በጣም ተቆጡ፡፡
\s5
\v 11 ስለዚህም እኔ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቼ በዚያ ለሶስት ቀናት ቆየሁ፡፡
\v 12 በምሽት ከከተማ ወጣሁ፣ ከእኔ ጋርም ጥቂት ሰዎች ነበሩ፡፡ እኛ የነበረን እኔ የተቀመጥኩበት አንድ እንስሳ ብቻ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ እግዚአብሔር በልቤ ስላስቀመጠው ነገር ለማንም ሰው ምንም አልተናገርኩም፡፡
\s5
\v 13 በሸለቆው መግቢያ አለፍኩና ከከተማው ቅጥር ውጭ ሄድኩ፡፡ ከዚያ በከተማዋ ዙሪያ ተዟዙሬ የቀበሮዎች ጉድጓድ በሚባለው ጉድጓድ በኩል አለፍኩ፡፡ ከዚያ ወደ ፋንድያ መድፊያ በር አለፍኩ፡፡ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የሚገኙ ቅጥሮችን ሁሉ ዞሬ ተመለከትኩ፣ እናም ሁሉም በሮች ተሰባብረው ቅጥሮቹ ክፍት መሆናቸውን አየሁ፣ ደግሞም በቅጥሩ ዙሪያ የነበሩ የእንጨት በሮች ሁሉ አመድ እስኪሆኑ ተቃጥለው ነበር፡፡
\v 14 ከዚያ ወደ ፏፏቴ በር እና የንጉስ ገንዳ ወደሚባለው ገንዳ ሄድኩ፣ ነገር ግን የተቀመጥኩበት አህያ በጠባቡ መተላለፊያ ማለፍ አልቻለችም፡፡
\s5
\v 15 ስለዚህ ወደ ኋላ ዞሬ ወደ በቄድሮን ሸለቆ አጠገብ እያለፍኩ ወደ ኋላ ከመመለሴና ወደ ሸለቆው በር ወደ ከተማዋ ከመግባቴ አስቀድሞ በዚያ የነበሩ ቅጥሮችን ተመለከትኩ፡፡
\v 16 የከተማዋ ባለስልጣናት እኔ ወዴት እንደሄድኩ ወይም ምን እንዳደረግኩ አላወቁም ነበር፡፡ ለአይሁድ መሪዎች ወይም ለባለስልጣናቱ ወይም ለካህናቱ ወይም በእድሳቱ ስራ ለሚሳተፉ ለማናቸው ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ምንም ነገር አልተናገርኩም፡፡
\s5
\v 17 እንዲህ አልኩ፣ “በከተማችን ላይ የደረሰውን መጥፎ ነገሮች ሁሉ ሁላችሁም በሚገባ ታውቃላችሁ፡፡ ከተማዋ ፍርስራሽ ሆናለች፣ ሌላው ቀርቶ በሮቿ ተቃጥለው ወድቀዋል፡፡ ኑ፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደገና ለመገንባት ስራውን እንጀምር፡፡ እኛ ያንን ብናደርግ፣ ከዚህ በኋላ በከተማችን አናፍርም፡፡”
\v 18 ከዚያ ከንጉሱ ጋር በተነጋገርኩ ጊዜ እግዚአብሔር እንዴት በመልካምነቱ እንዲረዳንና ንጉሱ ምን እንዳለኝ ነገርኳቸው፡፡ እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ተነስተን የእድሳቱን ስራ እንጀምር! ” ስለዚህም ይህን መልካም ሥራ ለመስራት ተነሱ፡፡
\s5
\v 19 ነገር ግን ሰንበላጥ፣ አሞናዊው አገልጋይ ጦቢያ፣ እና አረባዊው ጌሻም፣ እኛ ለመስራት ያቀድነውን ሰሙ፡፡ በእኛ ላይ ቀለዱ አፌዙብንም፡፤ እንዲህም አሉ፣ “ይህ እናንተ የምትሰሩት ስራ ምንድን ነው? በንጉሱ ላይ እያመጻችሁ ነውን? ”
\v 20 እኔ ግን እንዲህ አልኳቸው፣ “በሰማይ ያለው አምላክ ስኬት ይሰጠናል፡፡ እናንተ ግን በዚህ ከተማ ላይ መብት የላችሁም፣ ተሳትፎ የላችም፣ በዚህ ላይ ህጋዊ መብት የላችሁም፣ በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ ምንም ታሪካዊ መታሰቢያ የላችሁም፡፡”
\s5
\c 3
\p
\v 1 ከዚያ የእስራኤል ሊቀ ካህን የሆነው ኤልያብ፣ ከሌሎች ካህናት ጋር የበጎች በር የተባለውን እንደገና ሰሩ፡፡ ይህንንም ለያህዌ ክብር ለዩት፣ እናም የመግቢያውን በሮች በስፍራው አቆሙ ቀጥሎ ቅጥሩን የመቶ ማማ እስከሚባለው ድረስ መልሰው ገነቡ፣ እናም ያህዌን ለማክበር ለዩት፡፡ እንዲሁም የሐንኤልን ማማ መልሰው ገነቡ፡፡
\v 2 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የኢያሪኮ ሰዎች መልሰው ይገነቡ ነበር፡፡ ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የአምሪ ልጅ ዘኩር መልሶ ይገነባ ነበር፡፡
\s5
\v 3 የአሳ በር የሚባለውን የሃስና ልጆች ገነቡት፡፡ እነርሱ የእንጨት አምዶቹን ከመግቢያዎቹ በላይ አጋደሙ፣ ደግሞም በሮቹን በስፍራቸው አኖሩ፡፡ ከዚያ ጠንካራ ቁልፍ እንዲኖር መቀርቀሪያ እና መወርወሪያዎችን አበጁ፡፡
\v 4 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የአቆስ የልጅ ልጅ፣ የአርዮ ልጅ የሆነው ሜርሞት ቅጥሮቹን ለማጠናከር ጠገናቸው፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሜሴዜቤል የልጅ ልጅ፣ የበራክየ ልጅ የሆነው ሜሱላም የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ የበዓና ልጅ ሳዶቅ የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፡፡
\v 5 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የተቁሖ ሰዎች ቅጥሩን በከፊል ጠገኑ፣ ነገር ግን የቴቁ መሪዎች አሰሪዎቻቸው እንዲሰሩ የሰጣቸውን ለመስራት አልፈለጉም፡፡
\s5
\v 6 የፋሴሐ ልጅ ዮዳሄ እና የበሶድያ ልጅ ሜሱላም አሮጌውን መግቢያ ጠገኑ፡፡ ከመግቢያው በላይ ያሉትን አምዶችም በስፍራቸው አደረጉ፣ እንዲሁም መቀርቀሪያዎችንና መወርወሪያዎችን መግቢያውን ለመቆለፍ አስገቡ፡፡
\v 7 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የገባኦንና ከምጽጳ ሰዎች የሆኑት ገባኦናዊው መልጥያ እና ሜሮኖታዊው ያዶን፣ ከባህሩ ማዶ የሚገኘው አውራጃ ገዢ የሚኖርበትን ክፍል ጠገኑ፡፡
\s5
\v 8 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሖርሃያ ልጅ ዑዝኤል፣ እና ሐናንያ ነበሩ፣ ነገር ግን እነርሱ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ያለውን ክፍል ሰሩ፡፡ ሐርሃያ ወርቅ አንጥረኛ፣ ሐናንያ ደግሞ ሽቶ ቀማሚ ነበሩ፡፡
\v 9 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የኢየሩሳሌምን ከፊል አውራጃ የሚገዛው የሆር ልጅ ረፋ የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡
\v 10 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የኤርማፍ ልጅ ይዳያ ከቤቱ አጠገብ የሚገኘውን ቅጥር ከፊሉን መልሶ ሰራ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ የአሰቦንያ ልጅ ሐጡስ የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 11 የሃሪም ልጅ መልክያ፣ እና የፈሐት ሞዓብ ልጅ አሱብ የቅጥሩን ከፊል ጠገነ፣ እንዲሁም የእቶን ማማ የተባለውን መልሶ ሰራ፡፡
\v 12 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ሌላውን የኢየሩሳሌም ከፊል አውራጃ የሚገዛው የአጦሎኤስ ልጅ ሰሎም የቅጥሩን ከፊል መልሶ ሰራ፡፡ ሴት ልጆቹ በስራው ረዱት፡፡
\s5
\v 13 ሐኖንና የዛኖ ከተማ ሰዎች የሸለቆ መግቢያ ተብሎ የሚጠራውን መልሰው ሰሩ፡፡ እነርሱም መግቢያዎቹን መልሰው በስፍራቸው አቆሙ፣ ደግሞም መወርወሪያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን በሮቹን ለመቆለፊያ አበጁ፡፡ ቅጥሩን የቆሻሻ መጣያ በር እስከሚባለው ድረስ 460 ሜትር መልሰው ሰሩ፡፡
\s5
\v 14 የበት ሐካሪም አውራጃ ገዢ የሆነው የረካብ ልጅ መልክያ የቆሻሻ መጣያ በር ተብሎ የሚጠራውን መልሶ ሰራ፡፡ መግቢያውን ለመቆለፊያ መወርወሪያዎቹንና ፍርግርጎቹን መልሶ ሰራ፡፡
\v 15 የምጽጳ አውራጃን የሚገዛው የኮልሐዜ ልጅ ሰሎም የፏፏቴ በር ተብሎ የሚጠራውን መግቢያ መልሶ ሰራ፡፡ ከመግቢያው በላይ ጣራ አበጀ፣ በሩን ለመቆለፍ መግቢያዎቹንና መቀርቀሪያዎቹን እንዲሁም ፍርግርጎቹን አበጀ፡፡ ከዳዊት ከተማ ተነስቶ ቁልቁል እስከ ሼላን ገንዳ አጠገብ ከንጉሱ መናፈሻ ቀጥሎ ቅጥሩን ገነባ፡፡
\s5
\v 16 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የቤት ዱር አውራጃን በከፊል የሚገዛው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ፣ በዳዊት ከተማ ውስጥ እስከ መቃብር ስፍራ ያለውን ቅጽር፣ ሰው ሰራሽ እስከ ሆነው መዋኛ እና እስከ ፈረስ ቤቶች ድረስ መልሶ ሰራ፡፡
\v 17 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ካህናቱን የረዱት ብዙ የሌዊ ትውልዶች የቅጥሩን ክፍሎች መልሰው ሰሩ፡፡ የባኒ ልጅ ሬሁ አንዱን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ የቅኢላን ግማሽ አውራጃ የሚገዛው ሐሽብያ የአውራጃውን ህዝብ ወክሎ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 18 የቅዒሊን ቀሪውን ግማሽ አውራጃ የሚገዛው የኤንሐዳድ ልጅ በዋይና ከሌሎች የሌዊ ትውልዶች ጋር ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 19 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የምጽጳ ከተማን የሚገዛው የኢያሱ ልጅ ኤጽር እስከ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት ደጃፍ፣ መአዘን ላይ እስከ ሚገኘው የቅጥሩ ቅስት ድረስ ያለውን ሌላውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 20 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የዘባይ ልጅ ባሮክ የቀረውን የቅጥሩን ክፍል በታላቅ ትጋት መልሶ ሰራው፡፡ ከሊቀ ካህኑ ከኤልያሴብ ቤት በር እስከ ራሱ እስከ ባሮክ ቤት መጨረሻ ድረስ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 21 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የአቆስ የልጅ ልጅ፣ የኦርዮ ልጅ የሆነው ሜሪሞት ከኤልያሴብ ቤት በር እስከ ራሱ እስከ ሜሪምት ቤት መጨረሻ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 22 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ብዙ ካህናት የቅጽሩን ክፍሎች መልሰው ሰሩ፡፡ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ያሉ ካህናት አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡
\v 23 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ ብንያምና አሱብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ የሖናንያ የልጅ ልጅ፣ የመፅሤያ ልጅ የሆነው ዓዛርያስ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 24 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ከዓዛርያስ ቤት ቅጽሩ በጥቂቱ ዞር እስከሚልበት ድረስ ያለውን አንዱን ክፍል የኤንሐዳድ ልጅ ቢንዊ መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 25 ከእርሱ ቀጥሎ፣ ቅጥሩ ከሚዞርበትና የመጠበቂያ ማማው ከላይኛው ቤተ መንግስት ከፍ ብሎ እስከሚታይበት ድረስ ያለውን አንድ ክፍል የኡዛይ ልጅ ፉላል መልሶ ሰራ፡፡ መጠበቂያ ማማው ጠባቂዎቹ ከሚኖሩበት አደባባይ አጠገብ ይገኛል፡፡ ከፉላል ቀጥሎ፣ የፋሮስ ልጅ ፈዳ ቅጥሩን መልሶ ሰራ፡፡
\v 26 ከእርሱ ቀጥሎ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች በትልቁ ማማ ምስራቅ አቅጣጫ ፊቱን ወደ ውሃ በር ያደረገውን አንድ ክፍል መልሰው ጠገኑ፡፡
\v 27 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የተቁሐ ሰዎች ከትልቁ ማማ ፊት ለፊት እስከ ኦፌል ቅጥር ድረስ ያለውን ሁለተኛውን ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡
\s5
\v 28 ከፈረስ መግቢያ ሰሜን አንስቶ ያለውን ቅጽር አንድ የካህናት ቡድን መልሶ ሰራው፡፡ እያንዳንዱ ካህን ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 29 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ የኢሜር ልጅ ሳዶቅ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡ ከእርሱ ቀጥሎ፣ በስተምስራቅ የሚገኘው በር ጠባቂ የነበረው የሴኬንያ ልጅ ሸማያ ቀጣዩን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 30 ከእርሱ ቀጥሎ፣ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያ፣ እና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ አንድ ክፍል መልሰው ሰሩ፡፡ ያም እነርሱ መልሰው የጠገኑት ሁለተኛው ክፍል ነበር፡፡ ከእርሱ በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም እርሱ ይኖርበት በነበረው ቤት ፊት ለፊት የሚገኙትን ቅጥሮች ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\s5
\v 31 ከእነርሱ ቀጥሎ፣ ወርቅ አንጣሪው መልክያ ከቀጠሮ በር ማዕዘን ላይ እስከሚገኘው የላይኛው መኖሪያዎች የሚገኙትን የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና ነጋዴዎች እስከ ሚገለገሉባቸው ህንጻዎች ድረስ ያለውን ክፍል መልሶ ሰራ፡፡
\v 32 ሌሎች ወርቅ አንጥረኞች፣ ከነጋዴዎች ጋር ሆነው የቅጥሩን የመጨረሻ ክፍያ እስከ በጎች በር ድረስ መልሰው ሰሩ፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ሰንበላጥ የከተማዋን ቅጥር እንደገና እየሰራን መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ እኛ ኢየሩሳሌምን እንደ ገና መገንባታችን በውስጡ እንደ እሳት አቃጠለው፣ እናም በጣም ተቆጥቶ በአይሁዶች ላይ በጥላቻ ተሞልቶ ተናገረ፡፡
\v 2 ከሰማርያ በመጡት አማካሪዎቹና የጦር አለቆቹ ፊት እንዲህ አለ፣ “እነዚህ አይሁዶች ራሳቸውን ችለው መቆም አይችሉም፣ ምን እያደረጉ ያሉ መስሏቸዋል? ከተማዋን እንደገና ገንብተው ራሳቸው ሊኖሩባት ነውን? ቤተ መቅደሱን እንደገና ገንብተው ካህናቱ ለያህዌ የሚያቀርቡትን መስዋእት ሁሉ ሊያቀርቡ ነውን? በአንዲት ቀን እንዲህ ያለውን ታላቅ ሥራ ይጨርሳሉን? እነዚህን የተቃጠሉና ከጥቅም ውጭ የሆኑ ድንጋዮች ቅጥሩን እንደገና ለመገንባት ሊጠቀሙበትና ለከተማዋ ዳግም ሕይወት ሊሰጧት ይችላሉን?
\v 3 ጦቢያ ከሰንበላጥ አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፣ “ያ እነርሱ የሚገነቡት ቅጥር እጅግ ደካማ ነው፤ ትንሽ ቀበሮዎች ቢወጡበት እንኳን ይፈርሳል፤ የእነርሱ የድንጋይ ቅጥር ቀበሮ ቢወጣበት ይፈርሳል!”
\s5
\v 4 ከዚያ እኔ እንዲህ ስል ጸለይኩ፣ “አምላካችን ሆይ፣ ስማን፣ እነርሱ እየቀለዱብን ነው! የስድባቸውን ቃል ወደ ራሳቸው እንዲመለስ አድርግ! ጠላቶቻቸው እንዲመጡባቸውና እንዲይዟቸው ወደ ባዕድ ምድርም እንዲያሳድዷቸው አድርግ!
\v 5 እነርሱ በደለኞች ናቸው፡፡ በደላቸውን ከእነርሱ አታርቅ በፊትህ ለሰሩት ኃጢአት ዋጋ ይክፈሉ፡፡ በስድቦቻቸው፣ ቅጥሩን መልሰው የሚገነቡትን በጣም አስቆጥተዋል! ”
\v 6 ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን፣ ሰራተኞቹ ከጠቅላላው በከተማይቱ ዙሪያ ከሚገኘው የቅጥሩ ከፍታ ግማሽ ያህሉን ሰሩ፡፡ ይህን ማከናወን የቻሉት ሊሰሩ የሚችሉትን በሙሉ ልባቸው ለመስራት ስለፈለጉ ነበር፡፡
\s5
\v 7 ነገር ግን ሰንበላጥ፣ ጦብያ፣ ዐረቦች፣ አሞናዊያን፣ እና አሽዶዳዊያን የቅጥሩ ስራ መሰራቱ እንደ ቀጠለና የፈረሰውን ቅጥር እየጠገንን መሆኑን ሲሰሙ በጣም ተቆጡ፡፡
\v 8 እነርሱም መጥተው የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለመውጋት እና በከተማይቱ ውስጥ ሀብት ለመፍጠር በአንድነት ዕቅድ አወጡ፡፡
\v 9 እኛ ግን ቅጥሩን መልሰን በመገንባታችን እጅግ በተቆጡት በእነዚህ ሰዎች ምክንያት ወደ አምላካችን ጸለይን፣ ደግሞም ከተማዋን ቀንና ሌሊት ይጠብቁ ዘንድ ወንዶችን በቅጥሮቹ ዙሪያ አቆምን፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ የይሁዳ ሰዎች እንዲህ ማለት ጀመሩ፣ “ቅጥሩን የሚሰሩት ወንዶች መላ አቅማቸውን እየተጠቀሙ ነው፡፡ ልናነሳው የሚገባ እጅግ ብዙ ፍርስራሽ አለ፤ እኛ ይህን ስራ መጨረስ አልቻልንም ስራው እጅግ በዝቶብናል፡፡
\v 11 ከዚህም ባሻገር፣ ጠላቶቻችን እንዲህ እያሉ ነው! ‘አይሁዶች እኛን ከማየታቸው አስቀድሞ፣ በእነርሱ ላይ እንውጣባቸውና እንግደላቸው፣ የቅጥሩን ስራቸውንም እናስቁማቸው!”
\s5
\v 12 በጠላቶች አቅራቢያ ይኖሩ የነበሩ አይሁዶች ብዙ ጊዜ ወደ እኛ እየመጡ ጠላቶቻችን በእኛ ላይ ሊፈጽሙ የሚያስቡትን ክፉ እቅድ ይነግሩን ነበር፡፡
\v 13 ስለዚህ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ ቅጥሩን እንዲጠብቁ ሰዎችን አቆምኩ፡፡ እነዚህ ሰዎች ቅጥሩን በቀላሉ መሻገር በሚቻልባቸው በቅጥሩ ዝቅተኛ ስፍራዎች እንዲቆሙ ተደረገ፡፡ እነርሱም ሰይፎቻቸውን ጦሮቻቸውን፣ እና ደጋኖቻቸውንና ቀስቶቻቸውን ይዘው ይጠብቁ ነበር፡፡
\v 14 ከዚያ እያንዳንዳቸውን ከተመለከትኩ በኋላ፣ መሪዎችንና ሌሎች ሹማምንቶችን እንዲሁም ሌሎች ብዙ ሰዎችን ሰብስቤ እንዲህ አልኳቸው፣ “ጠላቶቻችንን አትፍሯቸው! እግዚአብሔር ታላቅና በክብር የተሞላ እንደሆነ አስቡ! እናም ቤተሰባችሁን፣ ወንድና ሴቶች ልጆቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን እና ቤቶቻችሁን ለመጠበቅ ተዋጉ!”
\s5
\v 15 ጠላቶቻችን፣ ዕቅዶቻቸውን እንደሰማን አወቁ፣ እግዚአብሔርም ስራችንን ለማስቆም ያወጡትን ዕቅድ ከንቱ አደረገባቸው፡፡ ስለዚህ እኛ ሁላችንም ወደ ፊት እንሰራበት ወደነበረው ወደዚያው ስፍራ ቅጥሩን ለመገንባት ተመለስን፡፡
\v 16 ነገር ግን ከዚያ በኋላ፣ በዚያ ከነበሩት ወንዶች ግማሾቹ ብቻ የቅጥሩን ሥራ ይሰሩ ነበር፡፡ ሌሎቹ ጦሮቻቸውን፣ ጋሻዎቻቸውን፣ ደጋኖቻቸውንና ቀስቶቻቸውን ይዘውና የጦር ልብሶቻቸውን ለብሰው ይጠብቁ ነበር፡፡ መሪዎቹ የይሁዳን ሕዝብ ይጠብቁ ነበር፡፡
\s5
\v 17 መሪዎች ቅጥሩን የሚሰሩትንና የጉልበት ሥራ የሚሰሩትን ይጠብቁ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ሰው በአንድ እጁ ቅጥሩን ሲገነባ በሌላው እጁ መሳሪያ ይይዛል፡፡
\v 18 ቅጥሩን የሚገነባ ሁሉ በወገቡ ሰይፍ ይታጠቃል፡፡ ጠላቶቻችን ቢመጡ መለከት የሚነፋው ሰው ከእኔ አጠገብ ይሆናል፡፡
\s5
\v 19 ከዚያ ለባለስልጣናቱ፣ ለሌሎች ታላላቅ ሰዎች፣ እና ለሌሎች ሰዎች እንዲህ አልኳቸው፣ “ይህ ሥራ ታላቅ ነው፣ እኛ በቅጥሩ ዙሪያ የምንገኝ አንዳችን ከሌላችን ተራርቀን እንገኛለን፡፡
\v 20 የመለከት ድምጽ ስትሰሙ፣ መለከቱ በሚነፋበት ስፍራ ተሰብስቡ፡፡ አምላካችን ለእኛ ይዋጋልናል!”
\s5
\v 21 ስለዚህም ስራችንን መስራት ቀጠልን፡፡ ከህዝቡ እኩሌታው ቀኑን ሙሉ ጦሩን ይዞ፣ ጠዋት ጸሀይ ስትወጣ አንስቶ ምሽት ከዋክብት እስኪታዩ ድረስ ጥበቃ ያደርጋል፡፡
\v 22 በዚያን ጊዜ፣ እኔ ለህዝቡ፣ “ለእያንዳንዱ ሰራተኛ እና ለረዳቱ በምሽት ኢየሩሳሌም ውስጥ እንዲቆዩ ይነገራቸው፡፡ ያንን በማድረግ፣ በምሽት እኛን መጠበቅና በቀን ቅጥሩን መገንባት ይችላሉ” በማለት እናገራሁ፡፡
\v 23 በእነዚያ ጊዜያት፣ ልብሴን አላወልቅም፣ የጦር መሳሪያዬንም ሁልጊዜ እይዛለሁ፡፡ ወንድሞቼ፣ አገልጋዮቼ እና እኔን የሚከተሉ ወንዶች እና ዘብ ሆነው የሚያገለግሉ ሁሉ ይህንኑ ያደርጋሉ፡፡ ሁላችንም ውሃ ለመጠጣት ስንሄድ እንኳን የጦር መሳሪያዎችንን እንደያዝን ነበር፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ቆይቶ፣ ሌሎቹ አንዳንድ አይሁዶች በሚያደርጉት ብዙዎቹ ወንዶችና ሚስቶቻቸው ፍትህ ለማግኘት ጮኹ፡፡
\v 2 አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፣ “እኛ ብዙ ልጆች አሉን፡፡ በልተን ለማደርና በህይወት ለመቆየት እንኳን ብዙ እህል ያስፈልገናል፡፡”
\v 3 ሌሎቹ ደግሞ እንዲህ አሉ፣ “በዚህ የረሃብ ወቅት የምንበላው እህል ለማግኘት የእርሻ መሬታችንን፣ የወይን ተክላችንንና ቤቶቻችንን ማስያዝ ግድ ሆኖብናል፡፡
\s5
\v 4 ሌሎቹም እንዲህ አሉ፣ “ለእርሻ መሬቶቻችንና ለወይን ተክላችን ለንጉሱ ግብር ለመክፈል ገንዘብ መበደር የግድ ሆኖብናል፡፡
\v 5 እኛም እንደ ሌሎቹ አይሁዶች አይሁዳውያን ነን፡፡ የእነርሱ ልጆች ለእነርሱ ጠቃሚ እንደሆኑ ሁሉ፤ የእኛም ልጆች ለእኛ እንደዚያው ናቸው፡፡ ነገር ግን መክፈል የሚገባንን ለመክፈል ስንል ልጆቻችንን ለባርነት ለመሸጥ ተገደናል፡፡ አንዳንድ ሴት ልጆቻችንን አሁን ለባርነት ሸጠናል፡፡ የእርሻ መሬቶቻችንና የወይን ተክሎቻችን ከእኛ ተወስደዋል፣ ስለዚህም መክፈል ያለብንን ገንዘብ ለመክፈል ገንዘቡ የለንም፡፡”
\s5
\v 6 እነዚህን እነርሱ የተጨነቁባቸውን ነገሮች በሰማሁ ጊዜ በጣም ተቆጣሁ፡፡
\v 7 ስለዚህም ማድረግ ያለብኝን ነገር አሰብ፡፡ ለመሪዎችና ለሹማምንቱ እንዲህ አልኳቸው፣ “ገንዘብ ሲበደሯችሁ የገዛ ዘመዶቻችሁን ወለድ ታስከፍላላችሁ፡፡ ይህ ልክ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ! ” ከዚያም ክስ እንዲያቀርቡባችሁ ብዙ ሰዎችን በእነርሱ ላይ ሰብስቤ ጠራሁ፡፡
\v 8 እንዲህም አልኳቸው፣ “አንዳንድ አይሁዳዊ ወገኖቻችን የአህዛብ ባሪያዎች ለመሆን ራሳቸውን ለመሸጥ ተገደው ነበር፡፡ የቻልነውን ያህል፣ መልሰን ገዝተናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን እናንተ የገዛ ወገኖችሁን እንኳን እየሸጣችሁ ነው፤ ይኸውም የገዛ ወገኖቻቸው ወደ ሆኑ አይሁዶች ተመልሰው ይሸጡ ዘንድ ነው! ” ይህን ስናገራቸው፣ ምላሽ አልሰጡም፡፡ አንዲት ቃል እንኳን አልመለሱም፡፡
\s5
\v 9 ከዚያ እንዲህ አልኳቸው፣ “የምታደርጉት ነገር ክፉ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ልትታዘዙና ትክክል የሆነውን ልታደርጉ አይገባችሁምን? ይህን ብታደርጉ፣ ጠላቶቻችን በንቀት እንዳያዩን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
\v 10 እኔና አይሁዳዊ ወገኖቼ እንዲሁም አገልጋዮቼ ለህዝቡ ገንዘብና እህል አበደርን፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ከእነዚህ ብድሮች በአንዱም ወለድ መቀበል እናቁም፡፡
\v 11 እንደዚሁም፣ የወሰዳችሁባቸውን የእርሻ መሬቶቻቸውን፣ የወይን ስፍራቸውን፣ የወይራ ዛፍ ቦታቸውን እንዲሁም ቤቶቻቸውን ልትመልሱላቸው ይገባል፡፡ እንደዚሁም ገንዘብ፣ እህል፣ ወይን፣ እና የወይራ ዘይት ሲበደሯችሁ ያስከፈላችኋቸውን ወለዶች ልትመልሱላቸው ይገባል፡፡ ይህን ዛሬውን ልታደርጉ ይገባል!”
\s5
\v 12 መሪዎች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ያልከንን እናደርጋለን፡፡ እንዲሰጡን ያስገደድናቸውን ነገር ሁሉ እንመልስላቸዋለን፣ ደግም ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዲሰጡን አንጠይቅም፡፡” ከዚያ ካህናቱን ሰበሰብኩ፣ እናም ቃል የገቡትን እንዲያደርጉት አስማልኳቸው፡፡
\v 13 የክህነት ልብሴን እጥፋት አራግፌ እንዲህ አልኳቸው፣ “ልታደርጉት አሁን ቃል የገባችሁትን ባታደርጉ፣ እኔ ልብሴን እንዳራገፍኩ እግዚአብሔር ያራግፋችኋል፡፡” እነርሱም “አሜን እንዳልከው ይሁን! ” ሲሉ መለሱ፤ ደግሞም ያህዌን አወደሱ፡፡ ከዚያ ለማድረግ ቃል የገቡትን አደረጉ፡፡
\s5
\v 14 አርጤክስስ የፋርስ ንጉስ በነበረበት በሀያኛው ዓመት የይሁዳ ገዥ ሆኜ ተሹሜ ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከ ሰላሳ ሁለተኛው የንግስናው አመት ድረስ እኔም ሆንኩ የእኔ ሹማምንት ገዥ በመሆኔ ለቀለብ የተፈቀደልኝን ገንዘብ አልተቀበልንም፡፡
\v 15 ከእኔ አስቀድሞ ገዥ የነበሩ ሰዎች በየቀኑ አርባ የብር ሳንቲሞች ለምግብና ለወይን በመጠየቅ በህዝቡ ላይ ሸክም አክብደውበት ነበር፡፡ አገልጋዮቻቸው ጭምር ህዝቡን ይጨቁኑ ነበር፡፡ እኔ ግን ያን አላደረግኩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት እፈልግ ነበር፡፡
\s5
\v 16 በዚህ ቅጥር ላይ መስራቴንም ቀጠልኩ፣ እኛም ከህዝቡ ምንም መሬት አልገዛንም፡፡ ለእኔ የሚሰሩት ሁሉ በቅጥሩ ስራ ተባበሩን፡፡
\v 17 እንዲሁም፣ በየዕለቱ ከገበታችን አይሁዶችንና ሹማምንቱን፣ አንድ መቶ ሀምሳ ሰዎችን፣ እና በዙሪያችን ካሉ አገሮች የመጡ ጎብኚዎችን እንመግብ ነበር፡፡
\s5
\v 18 በየቀኑ አገልጋዮቼ አንድ በሬ፣ ስድስት ሙክቶች እና የዶሮዎች ስጋ እንዲያቀርቡ አደርግ ነበር፡፡ በየአስሩ ቀን ብዙ የሆነ አዲስ ወይን ጠጅ አቀርብላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡ እጅግ ብዙ ግብር በመክፈል ጫና እንደሚበዛበት አውቅ ነበር፣ ስለዚህም እንደ አገረ ገዥ የተፈቀደልኝን ገንዘብ እንኳን አልቀበልም ነበር፡፡
\v 19 አምላኬ፣ አስበኝ፣ እናም ለዚህ ህዝብ ላደረግኩት ሽልማት ስጠኝ፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ምንም እንኳን እስከ አሁን በሮቹን በመግቢያዎቹ ላይ ገና ባንገጥምም፣ የቅጥሩን ሥራ መጨረሳችንንና ያልተጠገነ የፈረሰ ስፍራ አለመኖሩን ሰንበላጥ፣ ጦቢያ፣ ጌሳምና ሌሎች ጠላቶቻችን ሰሙ፡፡
\v 2 ስለዚህ ሰንበላጥና ጌሳም እንዲህ የሚል መልዕክት ወደ እኔ ላኩ፣ “ከኢየሩሳሌም በስተሰሜን በሚገኘው ኦኖ በሚባለው ሜዳ መጥተህ እንነጋገር፡፡” ነገር ግን ይህን ያሉት እኔን ለመጉዳት አስበው እንደነበር ግልጽ ነው፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህም እንዲህ ብለው እንዲነግሯቸው መልዕክተኞችን ላክሁ፣ “ከፍ ያለ ስራ እየሰራሁ ነው፣ እናም ወደዚያ ልሄድ አልችልም፡፡ እኔ ከእናንተ ጋር ለመነጋገር ወደዚያ በመሄድ ይህ ስራ መስተጓጎል አይኖርበትም፡፡
\v 4 እነርሱ ይህንኑ መልዕክት አራት ጊዜ ወደ እኔ ላኩ፣ እኔም በእያንዳንዱ ወቅት ተመሳሳይ መልስ ሰጠኋቸው፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ሰንበላጥ አምስተኛውን መልዕክት አስይዞ አንዱን አገልጋዩን ወደ እኔ ላከ፡፡ ይህኛው መልዕክት በጽሁፍ ነበር፣ በእርግጥ ማህተም ያልተደረገበትና ያልታሸገ ደብዳቤ ነበር፡፡
\v 6 በመልዕክቱ የተጻፈው ይህ ነበር፡ “በባቢሎን ንጉስ ላይ አመጽ ለማስነሳትና አንተም የእስራኤል ንጉስ ለመሆን አቅደህ አንተና ሌሎች አይሁዶች ቅጥሩን እንደገና እየገነባችሁ እንደሆነ በአቅራቢያ ባሉ አገሮች ያሉ አንዳንድ ሰዎች ወሬ ሰምተዋል፡፡ እውነቱ ይህ መሆኑን ጌሳም ነግሮናል፡፡
\s5
\v 7 ደግሞም ሰዎች፣ አንተ ነህምያ፣ አሁን የአይሁድ ንጉስ መሆንህን እንዲያውጁ ነቢያትን መሾምህን እየተናሩ ነው፡፡ ንጉስ አርጤክስስ በእርግጥ ይህን ወሬ መስማቱ አይቀርም፣ ያን ጊዜ ትልቅ ችግር ላይ ትወድቃለህ፡፡ ስለዚህ ተገናኝተን በዚህ ጉዳይ ላይ መነጋገር እንደሚኖርብን አሳስባለሁ፡፡”
\s5
\v 8 ያን መልዕክት ካነበብኩ በኋላ መልዕክተኛው ወደ ሰንበላጥ ይህን መልዕክት መልሶ እንዲያደርስ ላክሁ፣ “ከምትናገረው ውስጥ አንዱም እውነት አይደለም፡፡ ይህን የምትለው ከገዛ ልብህ ፈጥረህ ነው፡፡”
\v 9 ይህንን የምለው እነርሱ እኛን ለማስፈራራት እየሞከሩ እንደነበር ስለማወቅ ነው፣ ስለዚህም እንዲህ ብለው ያስባሉ፣ “ከዚህ በኋላ ቅጥሩን ለመስራት ፍጹም ተስፋ ይቆርጣሉ፣ ስራውም በፍጹም ከፍጻሜ አይደርስም፡፡” ስለዚህም እኔ፣ “አምላኬ ሆይ፣ ብርታትን ስጠኝ፡፡” ስል ጸለይኩ፡፡
\s5
\v 10 አንድ ዕለት የመሔጣብኤል የልጅ ልጅ፣ የድልያ ልጅ፣ ከሆነው ከሸማያ ጋር ለመነጋገር ሄድኩ፡፡ ከእርሱ ጋር ለመነጋገር ወደ ቤቱ ሄድኩ፡፡ ከቤቱ እንዳይወጣ ትዕዛዝ ተሰጥቶት ነበር፡፡ እርሱም እንዲህ አለኝ፣ “አንተና እኔ ከቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍሎች ወደ አንዱ መግባትና በሮቹን መቆለፍ አለብን፡፡ ዛሬ ምሽት ሊገድሉህ ይመጣሉ፡፡”
\v 11 እኔም እንዲህ ስል መለስኩለት፣ “እኔ እንዲያ ያለ ሰው አይደለሁም! ህይወቴን ለማትረፍ ራሴን ቤተመቅደስ ውስጥ ሸሽቼ ገብቼ አልደብቅም! አይ፣ ያንን አላደርግም!”
\s5
\v 12 የተናገረውን አሰላሰልኩ፣ ሸማያ እግዚአብሔር ያላለውን እንደነገረኝ አወቅሁ፡፡ ጦቢያ እና ሰንበላጥ ቀጥረውት ነበር፡፡
\v 13 እንዲያስፈራራኝ እነርሱ ቀጥረውት ነበር፡፡ እነርሱ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንዳልጠብቅ በመቅደስ ውስጥ በመደበቅ እንድበድል ይፈልጉ ነበር፡፡ ያንን ባደርግ፣ ስሜን ያጠፉና ከዚያም ያዋርዱኛል፡፡
\v 14 ስለዚህም እንዲህ ስል ጸለይኩ “አምላኬ ሆይ፣ ጦቢያና ሰንበላጥ ያደረጉትን አትርሳ፡፡ ነቢይቱ ኖዓድያ እና ሌሎች ነቢያት ሊያስፈራሩን የሞከሩትን አትርሳ፡፡”
\s5
\v 15 በኤሉል ወር በወሩ ሃያ አምስተኛው ቀን የቅጥሩን ጥገና አጠናቀቅን፡፡ ጠቅላላውን ስራ በሀምሳ ሁለት ቀናት አጠናቀቅን፡፡
\v 16 በአቅራቢያችን በሚገኙ አገሮች የሚኖሩ ጠላቶቻችን ይህንን ሲሰሙ፣ በጣም ፈሩ፣ ዕፍረትም ተሰማቸው ምክንያቱም ይህን ሥራ እንድናጠናቅቅ የረዳን እግዚአብሔር እንደሆነ አውቀው ነበር፡፡
\s5
\v 17 በዚህ ጊዜ ውስጥ፣ የአይሁድ መሪዎች ብዙ መልዕክቶችን ወደ ጦቢያ ይልኩ ነበር፣ ጦቢያም መልሶ መልዕክቶችን ወደ እነርሱ ይልክ ነበር፡፡
\v 18 በይሁዳ ያሉ ብዙ ሰዎች ታማኝታቸውን በመሀላ ለጦቢያ አረጋግጠውለት ነበር፡፡ እርሱም የኤራ ልጅ የሴኬንያ አማት ሲሆን፣ የጦቢያ ወንድ ልጅ የቤሪክያን ልጅ የሆሐና የሚሹ ሀላምን ሴት ልጅ አግብቶ ነበር፡፡
\v 19 ሰዎች ብዙ ጊዜ እኔ ባለሁበት ጦቢያ ስለ ሰራቸው መልካም ስራዎች ይናገሩና፣ ከዚያ እኔ የተናገርኩትን እያንዳንዱን ነገር ይነግሩታል፡፡ ስለዚህም ጦቢያ እኔን ለማስፈረራት በርካታ ደብዳቤዎችን ወደ እኔ ይልክልኝ ነበር፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ቅጥሩ ተሰርቶ ከተጠናቀቀና በሮቹም በስፍራቸው ከቆሙ በኋላ፣ የቤተ መቅደሱ ጠባቂዎችና የዝማሬ አባላቱ እንዲሁም የተቀሩት የሌዊ ትውልዶች በየስራ መደባቸው ተመደቡ፡፡
\v 2 ወንድሜን አናኒን የኢየሩሳሌም ገዥ አድርጌ ሾምኩት፡፡ እርሱ ከብዙ ሌሎች ሰዎች ይልቅ ታማኝና እግዚአብሔርን የሚፈራና የሚያከብር ሰው ነበር፡፡ በተጨማሪም ሐናንያ በኢየሩሳሌም ለሚገኘው የከተማይ ግንብ አዛዥ ሆኖ ተሾሙ፡፡
\s5
\v 3 እነርሱን እንዲህ አልኳቸው፣ “ፀሀይ ሞቅ እስክትል የኢየሩሳሌምን መግቢያ በሮች አትክፈቱ፡፡ በሮችን የምትቆልፉትና የበሮችን መቀርቀሪያዎች የምትዘጉት በር ጠባቂዎች መግቢያዎችን እየጠበቁ ሳለ ነው፡፡” አንዳንድ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎችን ዘቦችና በከተማዋ ዙሪያ ያሉ ማረፊያዎችን ጠባቂዎች እንዲያደረጓቸው፤ እንዲሁም አንዳንዶችን ከራሳቸው ቤቶች አቅራቢያ ጠባቂ እንዲያደረጓቸው ነገርኳቸው፡፡
\v 4 የኢየሩሳሌም ከተማ ሰፊ ናት፣ ነገር ግን በዚያን ጊዜ በከተማዋ ብዙ ህዝብ አይኖርም ነበር፣ እንዲሁም ከቤቶቹ አንዱንም እንደገና አልገነቡም ነበር፡፡
\s5
\v 5 እግዚአብሔር መሪዎችንና ሹማምንቱን እንዲሁም ሌሎች ሰዎችን እንድሰበስብ እና በየቤተሰባቸው መዛግብት እንድጽፍ አሳብ በልቤ አኖረ፡፡ እንደዚሁም ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱትን የመጀመሪያዎቹን ተመላሾች ዝርዝር አገኘሁ፡፡ በእዚያ መዛግብት ተጽፎ ያገኘሁት ይህንን ነው፡፡
\s5
\v 6 ”ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ሌሎች ስፍራዎች የተመለሱ ሰዎች ዝርዝር ይህ ነው፡፡ እነርሱ ባቢሎን ውስጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ናቡከደነጾር ወደዚያ ወስዷቸው ነበር፡፡ እነርሱ ወደ ኢየሩሳሌምና ይሁዳ ተመለሱ፡፡ እያንዳንዱ ተመላሽ አባት ከልደት በፊት ይኖርበት ወደነበረበት ወደ ራሱ ከተማ ተመልሶ ሄደ፡፡
\v 7 እነርሱ ከዘሩባቤል፣ ከኢያሱ፣ ከነህምያ፣ ከአዛርያስ፣ ከረዓምያ፣ ከነሐማኒ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከላሶን፣ ከሚስጴሬት፣ ከጉዋይ፣ ከነሑም፣ እና ከዓና ጋር ተመልሰው መጡ፡፡ ከህዝቡ የተመለሱት የወንዶች ቁጥር ዝርዝር እንደሚከተለው ነበር፡
\s5
\v 8 ከፋሮስ ትውልዶች 2172
\v 9 ከሰፋጥያስ ትውልዶች 372
\v 10 ከኤራ ትውልዶች፣ 652
\s5
\v 11 ሞዓብ ትውልዶች፣ የኢያሱና ኢዮብአብ ትውልዶች 2818
\v 12 ከኤላም ትውልዶች 1254፣
\v 13 ከዛቱዕ ትውልዶች፣ 845፣
\v 14 ከዘካይ ትውልዶች፣ 845፣
\s5
\v 15 ትውልዶች፣ 648፣
\v 16 ከቤባይ ትውልዶች፣ 628፣
\v 17 ከዓዝጋድ ትውልዶች፣ 2322፣
\v 18 ከአዶኒቃም ትውልዶች፣ 667፣
\s5
\v 19 ከበጉዋይ ትውልዶች፣ 2067፣
\v 20 ከዓዲን ትውልዶች፣ 655፣
\v 21 ከአጤር ትውልዶች ሌላ ስማቸው ሕዝቅያስ ከሚባለው፣ 98፣
\v 22 ከሐሱም ትውልዶች፣ 328
\s5
\v 23 ከቤሳይ ትውልዶች፣ 324፣
\v 24 ከሐሪፍ ትውልዶች፣ ሌላ ስማቸው ጆራህ ከሚባለው፣ 112
\v 25 ከገባዖን ትውልዶች 95
\v 26 አባቶቻቸው በእነዚህ ከተሞች የኖሩ ወንዶችም ደግሞ ተመለሱ ከቤተልሔምና ከነጦፉ የመጡ ወንዶች፣ 188፡፡
\s5
\v 27 ከዓናቶት የመጡ ወንዶች፣ 128 ነበሩ
\v 28 ከቤት አዛምት የመጡ ወንዶች 42፣
\v 29 ከቂርያት ይዓሪም ከከፈሪና ከብኤሮት 743 ወንዶች
\v 30 ኮራማና ከጌባ 621 ወንዶች
\s5
\v 31 122 ወንዶች ነበሩ
\v 32 ከቤቴልና ከጋይ፣ 123 ወንዶች
\v 33 ከናባው፣ 52 ወንዶች
\v 34 ከኤላም፣ 1254 ወንዶች
\s5
\v 35 ከካሪም 320 ወንዶች ነበሩ
\v 36 ከኢያሪኮ፣ 345 ወንዶች
\v 37 ከሎድ፣ ሐዲድና አኖ 721 ወንዶች ነበሩ እነዚህ ካህናትም ደግሞ ተመልሰዋል
\v 38 ከሴናዓ ትውልድ 3930 ነበሩ
\s5
\v 39 የኢያሱ ቤተሰብ የሆኑ፣ የዮዳኤ ትውልዶች፣ 973
\v 40 ከኢሜር ትውልዶች 1052፣
\v 41 ከፋስኮር ትውልዶች፣ 1247፣
\v 42 ከካሪም ትውልዶች፣ 1017
\s5
\v 43 ከሌዋውያን ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ፣ የኢያሱ፣ ቀደምኤል፣ ቤትኢ እና የሆዳይዋ ትውልዶች 74 ናቸው
\v 44 ከመዘምራኑ ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ ከኤሳፍ ትውልድ 148
\v 45 እንዲሁም ከሰሎም፣ አጤር፣ ጤልሞን፣ ዓቁብ፣ ሐጢጣ፣ እና ሶባይ ትውልዶች የተመለሱ 138 የቤተ መቅደሱ በር ጠባቂዎች ናቸው፡፡
\s5
\v 46 የተመለሱት የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች የእነዚህ ሰዎች ትውልዶች ነበሩ የሲሐ፣ ሐሡፋ፣ ጠብዖት
\v 47 የኬረስ፣ ሲዓዓ ሩዶን
\v 48 የልባና አገባ፣ ሰሞላይ
\v 49 የሐናን ጌዱል፣ ጋሐር፣
\s5
\v 50 ራያ፣ ራአሰን፣ ኔቆዳ
\v 51 ጋሴም፣ አዛ፣ ፋሴሐ
\v 52 ቤሳይ፣ ምዑኒም፣ ንፉሰሊም፣ እነዚህ ንፉሰሲም ተብለውም ይጠራሉ
\s5
\v 53 በቅቡቅ፣ ሐቀፋ፣ ሐርሑር፣
\v 54 በሰሎት፣ እነዚህ በሰሉት ተብለውም ይጠራሉ ምሒዳ፣ ሐርሻ
\v 55 ቦርቆስ፣ ሲሣራ፣ ቴማ
\v 56 ንስያ፣ ሐጢፋ
\s5
\v 57 ከንጉስ ዳዊት አገልጋዮች ትውልዶች የተመለሱት እነዚህ ነበሩ፣ ሶጣይ፣ ሶፌሬት፣ ፍሩዳ
\v 58 የዕላ፣ ደርቆን፣ ጊዴል
\v 59 ሰፋጥያስ፣ ሐጢል፣ ፈከራት፣ ሐፂቦይምና አሞን
\v 60 በአጠቃላይ፣ 392 የቤተ መቅደስ ሰራተኞችና የሰለሞን ትውልዶች አገልጋዮች ተመላሾች ነበሩ፡፡
\s5
\v 61 ከዳላያ፣ ጦብያ እና ኔቆዳ ጎሣዎች
\v 62 ሰዎች ያሉት ሌላ ቡድን ከቴልሜላ ቴላሬሳ፣ ከክሩብ፣ አዳን፣ በባቢሎን አዳን እና ኢሜር ተብሎም ይታወቃል፤ ከእነዚህ ከተሞች ይመለሳሉ፡፡ ነገር ግን እነርሱ እስራኤላዊያን መሆናቸውን ማረጋገጥ አልቻሉም፡፡
\v 63 የኤብያ፣ አቆስ፣ እና ቤርዜሊ ትውልድ የሆኑ ካህናትም ደግሞ ተመለሱ፡፡ ቤርዜሊ ከገለዓድ አካባቢ የቤርዜሊ ትውልድ የሆነችን አንዲት ሴት አገባ፤ እርሱም የሚስቱን ቤተሰቦች ስም መጠሪያው አድርጎ ወሰደ፡፡
\s5
\v 64 እነዚህ የአባቶችን ስሞች በያዙ መዛግብቶች ውስጥ የትውልድ ሀረጋቸውን ፍለጋ አደረጉ፣ ነገር ግን የቤተሰቦቻቸውን ስሞች ማግኘት አልቻሉም፤ ስለዚህ ካህናት ያሏቸውን መብቶችና ግዴታዎች ማግኘት አልተፈቀደላቸውም፡፡ በመሆኑም ንጹህ እንዳልሆኑ ስተቆጠረ ካህናት ለመሆን አልበቁም ምክንያቱም የትውልድ ሀረጋቸውን ማመላከት አልቻሉም፡፡
\v 65 ስለዚህ አገረ ገዥው በኡሪምና ቱሚም የሚያገለግል ከህን እስኪነሳ ድረስ ከመስዋዕቱ ከተወሰደው እጅግ ከተቀደሰው ከካህናቱ ድርሻ ምግብ እንዳይበሉ አዘዛቸው፡፡
\s5
\v 66 በአጠቃላይ፣ ከይሁዳ የተመለሱት ሰዎች 42360 ነበሩ፡፡
\v 67 እንደዚሁም 7337 አገልጋዮቻቸውና 245ዘማሪዎች ከወንዶችም ከሴቶችም በአንድነት ተቆጠሩ፡፡
\s5
\v 68 እስራኤላዊያኑ ከባቢሎን 736 ፈረሶችና 245 በቅሎዎች፣
\v 69 አራት መቶ ሰላሳ አምስት ግመሎችና 6720 አህዮችንም ጭምር ይዘው ተመለሱ፡፡
\s5
\v 70 አንዳንዶቹ የጎሣው መሪዎች ለመቅደሱ ግንባታ ሠራተኞች ስጦታዎችን ሰጡ፡፡ አገረ ገዥው 8. 5 ኪሎግራም ወርቅ ለመቅደስ አገልግሎት ሀምሳ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ እና 530 የክህነት ልብሶችን ለካህናቱ ሰጠ፡፡
\v 71 ሌሎቹ መሪዎች ለግምጃ ቤት ሀላፊው 170 ኪሎግራም ወርቅ ሰጡ፣ የጎሣው መሪዎች በአጠቃላይ 1. 2 ሜትሪክ ቶን ብር ሰጡ፡፡
\v 72 ሌላው ህዝብ 170 ኪሎግራም ወርቅ፣ እና 1. 1 ሜትሪክ ቶን ብር እንዲሁም 67 የክህነት ልብስ ለካህናቱ ሰጡ፡፡
\s5
\v 73 ስለዚህም ካህናቱ፣ ካህናቱን የሚረዱ ሌዋውያን፣ የቤተመቅደሱ ጠባቂዎች፣ ዘማሪዎቹ፣ የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች፣ እና በርካታው ተራ ህዝብ እንዲሁም እስራኤላዊ የሆኑ ሁሉ አባቶቻቸው ይኖሩባቸው በነበሩ በይሁዳ ከተሞች መኖር ጀመሩ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ህዝቡ ሁሉ በውሃ በር አጠገብ በሚገኘው አደባባይ በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ የሚነገረውን መረዳት የሚችሉ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ልጆች በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ እነርሱም ህግጋቱንና ትዕዛዛቱን ይጠብቁ ዘንድ፣ ያህዌ ለእስራኤል ህዝብ መመሪያ አድርጎ የሰጠውን ሙሴ የፃፈውን የህግ ጥቅልል መጽሐፍ እንዲመያጣ ዕዝራን ጠየቁት፡፡
\v 2 በቤተ መቅደስ መስዋዕቶችን በማቅረብ እግዚአብሔርን የሚያገለግለው ዕዝራ፣ ለወንዶችና ለሴቶች እንዲሁም ለማናቸውም የሚነበበውን መረዳት ለሚችሉ ህጉን አውጥቶ በህዝቡ ሁሉ ፊት አነበበ፡፡ ይህንን በዚያ አመት በሰባተኛው ወር በወሩ በመጀመሪያው ቀን አደረገ፡፡
\v 3 ስለዚህም መጽሐፉን አውጥቶ ለህዝቡ አነበበ፡፡ ጠዋት ከማለዳ አንስቶ እስከ እኩለ ቀን ድረስ የህጉን መጽሐፍ አነበበ፡፡ ወንዶና ሴቶች እንዲሁም የሚያነበውን መረዳት የሚችሉ ሁሉ ሰሙት፡፡ ዕዝራ ከህጉ መጽሐፍ የሚያነበውን፣ ህዝቡ በታላቅ ፍላጎት አደመጠ፡፡
\s5
\v 4 ዕዝራ ለዚህ ተግባር በህዝቡ በተዘጋጀ ከፍ ያ የእንጨት መድረክ ላይ ቆመ፡፡ ከእርሱ በስተቀኝ መቲትያ፣ ሽማዕ፣ ዓናያ፣ ኦርዮ፣ ኬልቅያስ እና መዕሤያ ቆመው ነበር፡፡ በስተግራው በኩል ደግሞ ፈዳያ፣ ሚሳኤል፣ መልክያ፣ ሐሱም፣ ሐሽበዳ፣ ዘካርያስና ሜሱላም ቆመው ነበር፡፡
\v 5 ዕዝራ በመድረኩ ላይ ሁሉም ሰዎች ሊያዩት በሚችሉት ቦታ ቆሞ ጥቅልሉን ተረተረው፣ እርሱ መጽሐፉን ሲከፍት ህዝቡ ሁሉ ተነስቶ ቆመ፡፡
\s5
\v 6 ከዚያም ዕዝራ ታላቁን አምላክ ያህዌን አመሰገነ፣ ህዝቡም ሁሉ እጆቻቸውን አንስተው፣ “አሜን! አሜን! ” አሉ፡፡ ከዚያም ሁሉም በግምባራቸው ወደ ምድር እየሰገዱ ያህዌን አመለኩ፡፡
\v 7 ኢያሱ፣ ባኒ፣ ሰራብያ፣ ያሚን፣ ዓቁብ፣ ሳባታይ፣ ሆዲያ፣ መዕሤያ፣ ቆሊጣስ፣ ዓዛርያስ፣ ዮዛባት፣ ሐናን እና ፌልያ ሁሉም ሌዋውያን ነበሩ፡፡ እነርሱም የሙሴን ህግጋት ትርጉም በዚያ ቆመው ለነበሩ ህዝቦች አብራሩ፡፡
\v 8 እንደዚሁም እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ህግ ከመጽሐፉ ጥቅልሎች አነበቡ፣ ደግም ወደ አረማይክ ቋንቋ እየተረጎሙ ህዝቡ ሊረዱት እንዲችሉ ትርጉሙን ግልጽ አደረጉ፡፡
\s5
\v 9 ከዚያ አገረ ገዥው ነህምያ እና ጸሓፊውና ካህኑ ዕዝራ፣ እንዲሁም የተነበበውን ለህዝቡ ይተረጉሙ የነበሩ ሌዋውያን፣ እንዲህ አሏቸው፣ “ያህዌ አምላካችሁ ይህን ቀን ከሌሎች ቀናት ለይቶታል፡፡ ስለዚህ በዚህ ቀን አትዘኑ ወይም አታልቅሱ! ” ይህን የተናገሩት፣ ዕዝራ ህጉን ሲያነብ፤ የሚሰሙት ሁሉ ያለቅሱ ስለነበር ነው፡፡
\v 10 ከዚያም ነህምያ እንደዚህ አላቸው፣ “አሁን ወደየቤታችሁ ሄዳችሁ መልካም ምግብ ተመገቡ ደስ የሚያሰኝ ጣፋጭ መጠጥም ጠጡ፡፡ ከምትበሉትና ከምትጠጡት የሚበሉትና የሚጠጡት ለሌላቸው አካፍሉ፡፡ ይህ ቀን፣ ጌታችንን ለማምለክ የተለየ ቀን ነው፡፡ ሀዘን አይሙላባችሁ! ያህዌ የሚሰጣችሁ ደስታ ብርቱ ያደርጋችኋል፡፡”
\s5
\v 11 ሌዋውያኑም ህዝቡን “ዝም በሉ አታልቅሱ፣ ይህ ቀን ለያህዌ የተለየ ቀን ነው፡፡ አትዘኑ! ” በማለት ፀጥ አሰኙ፡፡
\v 12 ስለዚህም ህዝቡ ተነስቶ ሄደ፤ በሉም ጠጡም፣ እንዲሁም ምንም ለሌላቸው ከምግባቸው አካፈሉ፡፡ የተነበባላቸውን ቃላት ትርጉሙን ስለተረዱ በጣም ደስተኞች ነበሩ፡፡
\s5
\v 13 በማግስቱ፣ የየቤተሰቡ አባወራዎች እና ካህናቱ እንዲሁም ሌዋውያኑ የህጉን ቃላት ይበልጥ ለመረዳት በአንድነት ወደ ዕዝራ መጡ፡፡
\v 14 አያቶቻቸው በበረሃ ሲጓዙ በዳሶች ውስጥ እንደኖሩ ያስታውሱ ዘንድ፣ በእነዚያ ወራት ሁሉ የእስራኤል ህዝብ እንዴት በጊዜያዊ ዳሶች ውስጥ መኖር እንደሚገባቸው ያህዌ ለሙሴ የሰጠውን ተዕዛዝ በህጉ ውስጥ ተጽፎ አገኙ፡፡
\v 15 እንደዚሁም ህዝቡ ወደ ኮረብቶች ሄዶ፤ ከወይራ ዛፎች ቅርንጫፎችን፣ ከበረሃ ወይራ ዛፎችና ከባርሰነት ዛፎች፣ ከዘንባባ ዛፎችና ሰፊ ጥላ ከሚሰጡ ዛፎች ዝንጣፊዎችን እየቆረጡ እንዲያመጡና በኢየሩሳሌምና በሌሎች ከተሞች ማወጅ እንዳለባቸው ተረድተዋል፡፡ ሙሴ እንደፃፈው፣ በበዓላቱ ወቅቶች ለመኖሪያነት የሚገለገሉባቸውን እነዚህን ዳሶች ከእነዚህ ዛፎች ቅርንጫፎች ማበጀት አለባቸው፡፡
\s5
\v 16 ስለዚህም ህዝቡ ከከተማ ወጥቶ ቅርንጫፎችን ቆርጦ ዳሶችን ለመስራት ተጠቀመባቸው፡፡ ዳሶችንም በየቤቶቻቸው ሰገነቶችች በየአደባባዮቻቸው፣ በቤተ መቅደስ አደባባዮች፣ እና በውሃ በር አጠገብ በሚገኘው አደባባይና በኤፍሬም መግቢያ ሰሩ፡፡
\v 17 ከባቢሎን የተመለሱ እስራኤላዊያን ሁሉ ዳሶችን ገንብተው ለአንድ ሳምንት ኖሩባቸው፡፡ እስራኤላዊያን ያንን በዓል ከኢያሱ ዘመን አንስቶ እስከዚያ ጊዜ ድረስ እንዲህ አላከበሩም፡፡ ህዝቡ በጣም ተደስቶ ነበር፡፡
\s5
\v 18 ዕዝራ በዚያን ሳምንት በየዕለቱ ከእግዚአብሔር ህግ ለህዝቡ ያነብ ነበር፡፡ ከዚያ በስምንተኛው ቀን፣ ድንጋጌውን ተከትለው ህዝቡ እንዲሰበሰብ አደረጉ፣ ይህም የበዓሉ ፍጻሜ ነበር፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 በዚያው ወር በሃያ አራተኛው ቀን፣ ህዝቡ በአንድነት ተሰበሰበ፡፡ ለጥቂት ጊዜ አልበሉም፣ ሰንዴና ሌላ እህል ለመያዣ የተዘጋጁ ጆንያዎችን ልብስ አደርገው ለበሱ፣ በራሳቸው ላይ የምድር ትቢያ ነሰነሱ፡፡
\v 2 የእስራኤል ትውልዶች ራሳቸውን ከሌሎች መጻተኞች ሁሉ ለዩ፡፡ በዚያ ቆመው የራሳቸውን ኃጢአትና አባቶቸው የሰሯቸውን ክፉ ነገሮች ተናዘዙ፡፡
\s5
\v 3 ቆመው ለሶስት ሰዓቶች ከያህዌ ህግ አነበቡ፣ ደግሞም ለሌላ ሶስት ሰዓቶች በያህዌ ፊት ኃጢአቶቻቸውን ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ፣ ከዚያ በመሬት ላይ ተደፍተው እርሱን አመለኩ፡፡
\v 4 ሌዋውያኑ በደረጃው ላይ ቆመው ነበር፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ባኒ፣ ቀድምኤል፣ ሰበንያ፣ ቡኒ፣ ሰራብያ፣ ባኒ፣ እና ከናኒ ነበሩ፡፡
\s5
\v 5 ከዚያ የሌዋውያኑ መሪዎች በህዝቡ ፊት ተሰየሙ፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ባኒ፣ አሰበንያ፣ ሰራብያ፣ ሆዲያ፣ ሰበንያና ፈታያ ነበሩ፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉ፣ “ቁሙና ከዘለዓም እስከ ዘለዓለም ለነበረውና ለሚኖረው ለአምላካችሁ ለያህዌ ምስጋና አቅርቡ! ያህዌ፣ የከበረውን ስምህን እናወድሳለን! መልካምና ድንቅ ከሆነው ነገር ሁሉ ስምህ የበለጠ ጠቃሚ ነው!
\v 6 አንተ ያህዌ ነህ፣ ሌላ ማንም ዘለዓለማዊና በራሱ ህልውና ያለው የለም፡፡ አንተ ሰማይንና ሰማያትን ከሁሉም በላይ ሰራህ፣ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽሙትን መላዕክት ሁሉ ፈጠርህ፡፡ ምድርንና በላይዋ ያሉትን አንተ አበጀህ፣ ባህሮችንና በውስጣቸው የሚገኙትን ሰራህ፡፡ አንተ ለሁሉም ነገር ህይወት ሰጠህ፡፡ በሰማይ ያሉ የመላዕክት ሰራዊት ሁሉ አንተን ያመልኩሃል፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ፣ አንተ እግዚአብሔር ነህ፡፡ አንተ አብራምን መርጠህ ከኡር ከከለዓድ አወጣኸው፡፡ አብርሃም የሚል ስም ሰጠኸው፡፡
\v 8 አንተ የእርሱን ልብ አየህ፣ የታመነ ሰው እንደነበረ ታውቅ ነበር፡፡ ከዚያ ከእርሱ ጋር በደም ቃል ኪዳን አደረግህ፣ የከነዓናዊያንን፣ የኬጢያውያንን፣ የአሞራውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የኢያቡሳውያንንና የጌርሳውያንን ምድር ለትውልዶች እንደምትሰጠው ቃል ገባህለት፡፡ እና አንተ ያህዌ፣ ቃል የገባኸውን ፈጸምክ፣ ምክንያቱም አንተ ሁልጊዜም ትክክል የሆነውን ታደርጋለህ፡፡
\s5
\v 9 አባቶቻችን በግብጽ ምን ያህል ይሰቃዩ እንደ ነበር አንተ አይተሃል፡፡ ቀይ ባህር አጠገብ በነበሩ ጊዜ ወደ አንተ ለእርዳታ ሲጮኹ ሰማሃቸው፡፡
\v 10 ንጉሱ፣ አገልጋዮቹና የእርሱ ህዝቦች ሁሉ እንዲጨነቁ የሚያደርግ ብዙ አይነት ተአምራቶችን አደረግህ፡፡ በዚህም፣ አንተ፣ ያህዌ፣ ለራስህ ስም አደረግህ፣ እናም ዛሬም ድረስ ስምህ ታላቅ መሆኑ ይታወቃል!
\s5
\v 11 ለሁለት ክፍል ከፈልህ፣ እናም ህዝብህ በደረቅ ምድር በመሀሉ ተራመደ፡፡ አንተ የግብጽን ወታደሮች በውሃዎች ስር አሰመጥክ፣ ድንጋይ በጥልቅ ውሃ እንደሚሰምጥ ሰመጡ!
\s5
\v 12 በቀን ደመና እንደ አምድ እየተከተላቸው መራሃቸው፣ በምሽት ወዴት እንደሚሄዱ ልታሳያቸው የእሳት አምድ ብርሃን ሰጠሃቸው፡፡
\v 13 አንተ ከሰማይ ወርደህ በሲና ተራራ ላይ አናገርካቸው፡፡ የታመኑና እውነተኛ የሆኑ ብዙ ድንጋጌዎችንና ደንቦችን ሰጠሃቸው፣ መልካም የሆኑ ትዕዛዛትንና ህግጋትንም ሰጠሃቸው፡፡
\s5
\v 14 ስለ ቅዱሱ ሰንበትህ አስተማርካቸው፣ ትዕዛዛትንና ህግጋትን እንዲሁም ይፈጽሟቸው ዘንድ የህግጋት አይቶችን በአገልጋይህ በሙሴ በኩል ሰጠሃቸው፡፡ እርሱ ለህዝቡ ይነግራቸዋል፡፡
\v 15 በተራቡ ጊዜ፣ ከሰማይ እንጀራ ሰጠሃቸው፡፡ በተጠሙ ጊዜ፣ ከአለት ውሃ አጠጣሃቸው፡፡ ትሰጣቸው ዘንድ በመሀላ ቃል የገባህላቸውን ምድር ሄደው እንዲወርሱ ነገርካቸው፡፡
\s5
\v 16 ነገር ግን አባቶቻችን በጣም ኩራተኞችና ግትሮች ነበሩ፡፡ እንዲያደርጉት ያዘዝካቸውን ለማስማት እንኳን ተቃወሙ፡፡
\v 17 አንተን ለመስማት አልወደዱም፡፡ ለእነርሱ ያደረግከውን ተአምራቶች ሁሉ ረሱ፡፡ ደንዳኖች ሆኑ፣ በአንተ ላይ ስላመጹ፣ ዳግም ባሪያዎች ወደሚሆኑበት! ወደ ግብጽ የሚመልሳቸውን መሪ መረጡ፡፡ ነገር ግን አንተ ደግመህ ደጋግመህ ይቅር የምትል አምላክ ነህ፡፡ ለመቆጣት አትቸኩልም፣ ለእነርሱ ያለህ ፍቅርም በፍጹም የማያልቅና ታላቅ ነው፡፡ እነርሱን አልተውካቸውም፡፡
\s5
\v 18 ስለዚህ፣ ምንም እንኳን የከበሩ ማዕድናትን አቅልጠው ጥጃ የሚመስል ጣኦት ቢቀርጹም ሙሉ ለሙሉ አልተወካቸውም፡፡ እግዚአብሔርን በመራገምና እርሱ የከለከለውን በማድረግ፣ ይህን ጥጃ ወደ ህዝቡ አቅርበው፣ ‘ይህ እናንተን ከግብጽ ያወጣችሁ አምላካችሁ ነው’ አሉ፡፡
\v 19 አንተ ሁልጊዜም መሃሪ ነህ፣ በበረሃ በነበሩ ጊዜም አልተውካቸውም፡፡ እንደ ታላቅ አምድ የሆነው ብሩህ ደመና በቀን ይመራቸው ነበር፣ የእሳት ደመናው በምሽት የሚሄዱበትን ይመራቸው ነበር፡፡
\s5
\v 20 መልካሙን መንፈስህን እንዲመራቸው ላክህላቸው፡፡ በተራቡ ጊዜ መናውን አልከለከልካቸውም፣ በተጠሙ ጊዜ ውሃ ሰጠሃቸው፡፡
\v 21 ለአርባ አመታት በበረሃ ተጠነቀቅክላቸው፡፡ በነዚያ ጊዜያት ሁሉ፣ የአንዳች ነገር ጉድለት አልነበረባቸውም፡፡ ልብሳቸው አላረጀም፣ እግሮቻቸው አላበጡም፡፡
\s5
\v 22 የአህዛብን ነገስታትና መንግስታት ሰጠሃቸው፡፡ በዚህ ምድር እጅግ ሩቅ የሆነውን ስፍራ እንኳን ርስት አድርገው ወሰዱ፡፡ ንጉስ ሴዎን የሚገዛውን ምድር ከሐሴቦን ወሰዱ እንዲሁም የንጉስ ዐግን ግዛት ባሳንን ወረሱ፡፡
\s5
\v 23 አባቶቻችንን በሰማይ እንዳሉ ከዋክብት እንዲበዙ ረዳሃቸው፣ አባቶቻቸው ይገቡባትና ይኖሩባት ዘንድ ወደ ነገርካቸው ወደዚህ ምድር አመጣሃቸው፡፡
\v 24 የእስራኤል ህዝቦች ገብተው በዚያ ከሚኖሩ ህዝቦች ምድሪቱን ወሰዱ፡፡ አንተ ከነአናዊያንንና ነገስታቶቻውን እንዲያሸንፉ ረዳሃቸው፣ አንተም በዚይ ምድር ህዝቦች ላይ ገዛህ፡፡ በእነዚያ ህዝቦች ላይ ማድረግ የሚፈልጉትን ሁሉ እንዲያደርጉ አንተ ረዳሃቸው፡፡
\s5
\v 25 አባቶቻችን ዙሪያቸው የተቀጠሩትን ከተሞች ያዙ፡፡ የለምለሚቱን ምድር ሀብት ወረሱ፡፡ በመልካም ነገሮች የተሞሉትን ቤቶችና የተቆፈሩ የውሃ ጉድጓዶችን ወረሱ፡፡ የወይን እርሻዎችን፣ የወይራ ዛፎችን እና የፍራፍሬ ዛፎችን ወረሱ፡፡ የፈለጉትን ሁሉ በልተው ረኩ፡፡ አንተ በሰጠሃቸው ብዙ ስጦታዎች ራሳቸውን ደስ አሰኙ፡፡
\s5
\v 26 ነገር ግን አልታዘዙህም በአንተ ላይም አመጹ፡፡ በህግጋትህ ላይ ጀርባቸውን ሰጡ፡፡ ወደ አንተ መመለስ እንዳለባቸው ያስጠነቀቋቸውን ነቢያት ገደሉ፡፡ ስምህን ተራገሙ፡፡
\v 27 ስለዚህም ያሸንፏቸው ዘንድ ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ሰጠሃቸው፡፡ ነገር ግን ጠላቶቻቸው ባሰቃይዋቸው ጊዜ፣ ወደ አንተ ጮኹ፡፡ አንተ ከሰማይ ጩኸታቸውን ሰማህ፣ አንተ እጅግ መሃሪ ስለሆንክ ከጠላቶቻቸው ነጻ የሚያወጧቸውን ሁሉ ላክህላቸው፡፡ እነርሱም ነፃ አወጧቸው፡፡
\s5
\v 28 ነገር ግን እንደገና የሰላም ጊዜ ከሆነ በኋላ፣ አባቶቻችን ዳግም አንተ የምትጠላውን ክፉ ነገሮች አደረጉ፡፡ ስለዚሀ ጠላቶቻቸው እንዲያሸንፏቸውና እንዲገዟቸው ፈቀድህ፡፡ ነገር ግን እንደገና እንድትረዳቸው በጮኹ ጊዜ ሁሉ አንተ ከሰማይ ሆነህ ትሰማቸዋለህ፣ አንተ በምህረት የተሞላህ ስለሆንክ ትታደጋቸዋለህ፡፡
\v 29 አንተ እንደገና ህግጋትህን እንዲታዘዙ ታስጠነቅቃቸዋለህ፣ ነገር ግን እነርሱ ኩራተኞችና ግትሮች ይሆናሉ፣ ድንጋጌዎችህንም ይጥሳሉ፡፡ እንዲያደርጉ ያዘዝካቸውን ሳይታዘዙ ይቀራሉ፡፡ ለትዕዛዛትህ አንዳች ትኩረት አይሰጡም፡፡ አንተን መስማትን በግትርነት ይቃወማሉ፡፡
\s5
\v 30 አንተ ለብዙ አመታት ታግሰሃቸው ነበር፡፡ መንፈስህ ለነቢያት በሚሰጣቸው መልዕክት አማካይነት ታስጠነቅቃቸዋለህ፡፡ ነገር ግን እነርሱን እነዚያን መልዕክቶች አይሰሙም፡፡ ስለዚህ እንደገና በአጠገባቸው ያሉ የአህዛብ ነገስታት እንዲያሸንፏቸው ትፈቅዳለህ፡፡
\v 31 ነገር ግን አንተ በይቅርታ ስለተሞላህ ሙሉ ለሙሉ አታጠፋቸውም ወይም ለዘለዓለም አትተዋቸውም አንተ መሀሪና ይቅር ባይ አምላክ ነህ!
\s5
\v 32 አምላካችን ሆይ፣ አንተ ታላቅ ነህ! አንተ ሃያል ነህ! አንተ አስደናቂ ነህ! አንተ እንደምታደርግልን በኪዳንህ ቃል እንደ ገባህልን በታማኝነት ትወደናለህ! ነገር ግን እኛ በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ታላቅ ችግሮች አሉብን፡፡ መከራችን በፊትህ እንደ ቀላል አይታይ! ይህ በእኛ ነገስታት ልዑላን፣ ካህናት፣ ነቢያት፣ አባቶች እና በመላው ህዝብህ ላይ ከአሶር ነገስታት ዘመን አንስቶ እስከ ዛሬ ደርሷል፡፡
\v 33 በቀጣኸን ጊዜ ሁሉ በጥፋታችን እንደተቀጣን እናውቃለን፡፡ እጅግ በድለናል፣ አንተ ግን በምህረትህ አይተኸናል እኛ ክፉ አድርገናል፡፡
\v 34 ንጉሶቻችን እና ሌሎች መሪዎች፣ ካህኖቻችን እና የእኛ አባቶች ህግህን አልጠበቁም፡፡ እነርሱ ትዕዛዛትን ወይም የሰጠኃቸውን ማስጠንቀቂያዎች አልሰሙም፡፡
\s5
\v 35 የራሳቸው ነገስታት በኖራቸው ጊዜ እንኳን፣ በዚህ በሰጠሃቸው ሰፊና ለም ምድር ለእነርሱ ባደረግካለቸው መልካም ነገሮች በተደሰቱ ጊዜ እንኳን፣ አንተን አላገለገሉህም ደግሞም ክፉ ማድረጋቸውን አላቆሙም፡፡
\s5
\v 36 ስለዚህ አሁን ምድሪቱ በምታበቅለው መልካም ነገሮች ሁሉ ደስ እንዲሰኙ ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው በዚህች ምድር ባሮች ነን፡፡ እነሆ ዛሬም በዚህ ባሮች ነን!
\v 37 ስለበደልን ምድሪቱ የምታበቅለውን ነገሮች መብላት አልቻልንም፡፡ አሁን እኛን የሚገዙ ነገስታት በዚህ በሚበቅሉ ነገሮች ደስ እየተሰኙ ነው፡፡ እነርሱ ይገዙናል ከብቶቻችንንም ይወስዳሉ፡፡ እኛ እነርሱን የማገልገልና ደስ የሚያሰኛቸውን ነገሮች የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡ በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እንገኛለን፡፡
\s5
\v 38 ከዚህ ሁሉ የተነሳ፣ እኛ የእስራኤል ሰዎች በጥቅልል ጽሁፍ ታላቅ ስምምነት እናደርጋለን፡፡ በጥቅልሉ ላይ የመሪዎቻችንን፣ የሌዋውያንን፣ የካህናትን ስሞች እንጽፍና ማህተም እናደርግበታለን፡፡”
\s5
\c 10
\p
\v 1 በስምምቱ ላይ የፈረሙት የስማቸው ዝርዝር ይህ ነው፡
\v 2 በጽሁፉ ላይ የፈረሙ ካህናት እነዚህ ናቸው፡ ሠራያ፣ ዓዛርያስ፣ ኤርምያስ
\v 3 ፉስኮር፣ አማርያ፣ መልክያ፣
\s5
\v 4 ሐጡስ፣ ሰበንያ፣ መሉክ
\v 5 ካሪም፣ ሜሪምት፣ አብድዩ
\v 6 ዳንኤል፣ ጌንቶን፣ ባሮክ
\v 7 ሜሱላም፣ አብያ፣ ሚያሚን፣
\v 8 መዓዝያ፣ ቤልጋይ፣ ሸማያ እነዚህ ካህናት ነበሩ፡፡
\s5
\v 9 የፈረሙት ሌዋውያን ትውልዶች እነዚህ ነበሩ፡ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፣ ቤንዊ፣ ከኤንሐዳድ፣ ቀድምኤል፣
\v 10 ሰባንያ፣ ሆዲያ፣ ቆሊጣስ፣ ፌልያ፣ ሐናን
\v 11 ሚካ፣ ሪአብ፣ ሐሽብያ፣
\v 12 ዘኩርር ሰራብያ፣ ሰበንያ፣
\v 13 ሆዲያ፣ ባኒ፣ ብኒኑ፡፡
\v 14 በመጽሐፍ ጥቅሉ ላይ የፈረሙት የእስራኤል መሪዎች እነዚህ ነበሩ፡ ፋሮስ፣ ፈሐት፣ ሞዓብ፣ ኤላም፣ ዛቱዕ፣ ባኒ፡፡
\s5
\v 15 ቡኒ፣ ዓዝጋድ፣ ቤባይ፣
\v 16 አዶንያስ፣ በጉዋይ፣ ዓዲን
\v 17 አጤር፣ ሕዝቅያስ፣ ዓዙር፣
\v 18 ሆዲያ፣ ሐሱም፣ ቤሳይ
\v 19 ሐሪፍ፣ ዓናቶት፣ ኖባይ፣
\v 20 መግጲዓስ፣ ሜሱላም፣ ኤዘር
\v 21 ሜሴዜቤል፣ ሳዶቅ፣ ያጹአ፣
\s5
\v 22 ፈላጥያ፣ ሐናን፣ ዓናያ፣
\v 23 ሆሴዕ፣ ሐናንያ፣ አሱብ፣
\v 24 አሎኤስ፣ ፈልሃ፣ ሶቤቅ
\v 25 ሬሁም፣ ሐሰብና፣ መዕሤያ፣
\v 26 አኪያ፣ ሐናን፣ ዓናን፣
\v 27 ሙሉክ፣ ካሪምና በዓና፡፡
\s5
\v 28 ካህናቱን በር ጠባቂዎቹን፣ ዘማሪዎቹን እና የመቅደስ ሰራተኞቹን ጨምሮ የቀረው ሕዝብ የከበረ ስምምነት አደረጉ፡፡ እንደዚሁም አገራቸውን ለቀው የወጡትንና በእስራኤል ይኖሩ የነበሩትን ጎረቤቶቻቸው ከሆኑ ከሌሎች ህዝቦች ወንዶችን ሁሉ ጨመሩ፡፡ እነዚህ ወንዶች ከሚስቶቻቸውና የሚያደርጉትን ለይተው ከሚያውቁ ከፍ ካሉ ወንድና ሴት ልጆቻቸው ጋር ሆነው የእግዚአብሔርን ህግ እንደሚጠበቁ ቃል ገቡ፡፡
\v 29 ይህን የከበረ ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም ከመሪዎቻቸው ጋር ተባበሩ፡፡ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ህግጋት ሁሉ ለመታዘዝ ተስማሙ፡፡ ያህዌ አምላካችን ያዘዘውን፣ ድንጋጌዎቹንና ትዕዛዛቱን ሁሉ ለመከተልና ለመፈፀም ተስማሙ፡፡ ተከታዩን ለማድረግ ቃል ገቡ፡፡
\s5
\v 30 “ሴቶች ልጆቻችን ያህዌን የማያመልኩትን የዚህ ምድር ሰዎች እንዲያገቡ አንሰጥም፣ ወንድ ልጆቻችን ሴት ልጆቻቸውን እንዲያገቡም አንፈቅድም፡፡
\v 31 ምድር የሚኖሩ የሌላ አገር ሰዎች በሰንበት ወይም በሌላ በተቀደሰ ቀን እህል ወይም ሌሎች ነገሮችን ሊሸጡልን ቢያመጡ፣ አንዳች ነገር አንገዛቸውም፡፡ እናም በየሰባት አመቱ አንዴ ለምድሪቱ እረፍት እንሰጣለን፤ በዚያን አንድ አመት ምንም አይነት እህል አንዘራም፤ እንዲሁም ለሌሎች አይሁዶች እዳቸውን ሁሉ እንሰርዛለን፡፡
\s5
\v 32 እንዲሁም እያንዳንዳችን ቤተ መቅደሱን ለሚያገለግሉና ለሚንከባከቡ በየአመቱ 5 ግራም ብር ለመክፈል ቃል ገባን፡፡
\v 33 በዚያ ገንዘብ እነዚህን ነገሮች መግዛት ይችላሉ፡ በእግዚአብሔር ፊት በገበታው ላይ የሚቀርብ ዳቦ፣ በእያንዳንዱ ቀን በመሰዊያው ላይ የሚቀርብ የእህል ቁርባን፣ በመሰዊያ ላይ ታርደው ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠሉ እንስሳት፣ ለእግዚአብሔር በሰንበት የሚርቡ የተቀደሱ መስዋዕቶች እና የአዲስ ጨረቃ በዓልን ለማክበርና ለሌሎች በዓላት መስዋዕቶች፣ ለእስራኤል ህዝቦች ኃጢአት መስዋዕት የሚሆኑ እንስሳት፣ እና ማናቸውም የቤተመቅደሱን ሥራ ለመንከባከብ የሚያስፈልጉ ሌሎች ነገሮች መግዛት ይችላሉ፡፡
\s5
\v 34 በየአመቱ ካህናቱ፣ ካህናቱን የሚረዱ የሌዊ ትውልዶች እና የተቀረነው በእግዚአብሔር ሕግ እንደተፃፈው በዚያ አመት ከሌዋውያን መሃል የትኛው ቤተሰብ በአምካላችን በእግዚአብሔር ቤት መስዋዕቶቹን ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ የሚነደውን እንጨት እንደሚያቀርቡ ለመወሰን እጣዎችን እንጥላለን፡፡
\v 35 በእያንዳንዱ አመት እያንዳንዱ ቤተሰብ በእርሻችን ካበቀልነውና ለምግብ ካጨድነው እንዲሁም በዚያ አመት ከፍራፍሬ ዛፎች የተገኘውን በኩራት መስዋዕት አድረገን ወደ ቤተ መቅደስ ለማምጣት ቃል እንገባለን፡፡
\v 36 የበኩር ወንድ ልጆችንና የላም፣ የበግና የፍየል በኩሮችን ለእግዚአብሔር መታሰበያ አድርገን ወደ እግዚአብሔር ቤት እናመጣለን፡፡ ማድረግ የሚገባን፣ በእግዚአብሔር ሕግጋት የተፃፈው ይህ ነው፡፡
\s5
\v 37 በየአመቱ ካመረትነው እህል ከበኩራቱ የተዘጋጀ ዱቄት ለካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ እናመጣለን፣ እንዲሁም ሌሎች የወይን፣ የወይራ ዘይትና የፍራፍሬ መስዋዕቶችንም ከበኩራቱ እናመጣለን፡፡ ካህናቱን ለሚረዱ የሌዊ ትውልዶች አስራቶችንም እናመጣለን፡፡
\v 38 የአሮን ትውልድ የሆነ አንድ ካህን፣ ከሌዋውያን ጋር ሆኖ አስራቶችን ሲሰበስቡ አብሮ ይገኛል፡፡ ከዚያ የሌዊ ትውልዶች ድርሻቸውን ይወስዳሉ፤ ህዝቡ ካመጣው ነገሮች አንድ አስረኛውን ይወስዱና በቤተ መቅደስ በግምጃ ቤት ያስቀምጣሉ፡፡
\s5
\v 39 የሌዊ ትወልዶችና አንዳንድ የእስራኤል ሰዎች በቤተ መቅደስ ለሚያገለግሉ የእህል፣ የወይን፣ እና የወይራ ዘይት ስጦታዎችን የተለያዩ መገልገያዎች ወደ ሚከማቹበት ግምጃ ቤቶች መውሰድ አለባቸው፡፡ በዚያን ጊዜ የሚያገለግሉ ካህናት፣ በር ጠባቂዎች፣ እና በቤተ መቅደስ የሚዘምሩ የዝማሬ ቡድን የሚኖሩበት ስፍራ ይህ ነው፡፡ “የአምላካችንን ቤተ መቅደስ ከመጠበቅ ቸል እንደማንል ቃል እንገባለን፡፡”
\s5
\c 11
\p
\v 1 የእስራኤል መሪዎችና ቤተሰቦቻቸው በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ ለእግዚአብሔር በተለየችው ከተማ የሚኖሩትን ከአስሩ ቤተሰብ አንዱን ለመለየት የተቀሩት ሰዎች እጣ ተጣጣሉ፡፡
\v 2 በኢየሩሳሌም ለመኖር ፈቃደኛ የሆኑትን ሰዎች እግዚአብሔር እንዲባርካቸው ጸለዩላቸው፡፡
\s5
\v 3 እነዚህ ቢየሩሳሌም ለመኖር የመጡት የአውራጃው ባለስልጣናት ናቸው፡፡ ነገር ግን በይሁዳ ከተሞች እያንዳንዱ በየራሱ ቤተሰብ ንብረት በየራሱ ከተማ ኖረ፡፡ አንዳንዶች ካህናት፣ ሌዋውያን፣ የቤተመቅደስ አገልጋዮች እና የሰለሞን አገልጋዮች ትውልዶች የሆኑ እስራኤላውያን በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመኖር መጡ፡፡
\v 4 ነገር ግን አንዳንድ የይሁዳ ሰዎች እና የብንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም ቆዩ በዚያም ኖሩ፡፡ እነዚህ ከይሁዳ ወገን ናቸው፡፡ የፋሬስ ትውልድ፣ የመላልኤል ልጅ፣ የሶፋጥያስ ልጅ፣ የአማርያ ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ፣ የኦዝያ ልጅ አታያ ናቸው፡፡
\s5
\v 5 እና የይሁዳ ልጅ ሴሎ ትውልድ የሆነው የዘካርያስ ልጅ፣ የዮያሪብ ልጅ፣ የዓዳያ ልጅ፣ የኦዛያ ልጅ፣ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ ነበር፡፡
\v 6 በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ትውልዶች 468 ወንዶች ነበሩ፡፡
\s5
\v 7 ከብንያም ትውልድ በኢየሩሳሌም ለመኖር ከወሰነው ጎሳ ሰዎች መሀል አንዱ የየሻያ ልጅ፣ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ፣ የቆላያ ልጅ፣ የፈዳያ ልጅ፣ የዮእድ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ ነው፡፡
\v 8 የሳሉ ሁለቱ ቤተ ዘመዶች ጌቤ እና ሳላይም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ በአጠቃላይ ከብንያም ጎሣ 928 ሰዎች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡
\v 9 መሪያቸው ዝክሪ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም በሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሹም ሐስኑአ ነበር፡፡
\s5
\v 10 በኢየሩሳሌም የተቀመጡት ካህናት የዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፣
\v 11 አስቀድሞ የካህናቱ ሁሉ መሪ የነበረው የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ፣ የሳዶቅ ልጅ የሜሱላም ልጅ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ ነበር፡፡
\v 12 በአጠቃላይ ከዚያ ነገድ የቤተ መቅደሱ ሠራተኞች 822 ሰዎች ናቸው፡፡ በኢየሩሳሌም የተቀመጠ ሌላው ካህን የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የዘካርያስ ልጅ የአማሲ ልጅ፣ የፈላልያ ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ ነበር፡፡
\s5
\v 13 በኢየሩሳሌም የተቀመጡ የዚያ ነገድ መሪዎች በጠቅላላው 242 አባላት ነበሩ፡፡ በኢየሩሳሌም የተቀመጠው ሌላው ካህን የኢሜር ልጅ፣ የምሺሌሞት ልጅ፣ የአሕዛይ ልጅ፣ የኤዝርኤል ልጅ፣ አማስያ ነበር፡፡
\v 14 ከዚያ ነገድ ደፋር የሆኑ 128 ወታደሮች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡ የእነርሱ መሪ የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበር፡፡
\s5
\v 15 በኢየሩሳሌም የተቀመጠው ሌላው የሌዊ ትውልድ የቡኒ ልጅ የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሻማያ ነበር፡፡
\v 16 ከቤ ተመቅደሱ ውጭ ያለውን ሥራ የሚከታተሉ ሁለቱ ሌዋውያን ታላላቅ ሰዎች ሳባታይ እና ዮዛባት ነበሩ፡፡
\s5
\v 17 ሌላው የአሳፍ ልጅ፣ የዘብዲ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ ነበር፡፡ መታንያ የቤተ መቅደሱ የመዘምራን ቡድን እግዚአብሔርን ለማመስገን ዝማሬ ሲያቀርብ ቡድኑን ይመራ ነበር፡፡ ረዳቱ በቅበቃር ነበር፡፡ ሌላው በኢየሩሳሌም የተቀመጠው የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ አብድያ ነበር፡፡
\v 18 በጠቅላላው፣ ለእግዚአብሔር በተለየችው ከተማ 284 ሌዋውያን ነበሩ፡፡
\s5
\v 19 በኢየሩሳሌም የተቀመጡት በር ጠባቂዎች ዓቁብ እና ጤልሞን ነበሩ፡፡ እነርሱና በአጠቃላይ በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ቤተሰቦቸው 172 ነበሩ፡፡
\v 20 ሌሎቹ የእስራኤል ትውልዶች የሌዊና ካህናትን ትውልዶች ጨምሮ በገዛ ይዞታቸውና በሌሎች ከተሞችና በይሁዳ ከተማዎች ተቀመጡ፡፡
\v 21 የቤተ መቅደሱ ሰራተኞች ግን በኦፌል ኮረብታ ኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀመጡ፡፡ እነርሱን የሚያዙት ሲሐ እና ጊሽጳ ነበሩ፡፡
\s5
\v 22 በኢየሩሳሌም የሚኖሩት የሌዊ ትውልዶች አለቃ የሚካ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሐሻብ ልጅ፣ የባኒ ልጅ ኦዚ ነበር፡፡ ኦዚ የአሳፍ ነገድ፣ በቤተ መቅደስ የዝማሬ ክፍሉ ሀላፊ ወገን ነበር፡፡
\v 23 የፋርስ ንጉስ እያንዳንዱ ነገድ በእያንዳንዱ ቀን በቤተ መቅደስ በሚቀርበው ዝማሬ እያንዳንዱ ነገድ የሚሰራውን ነገዶቹ እንዲወስኑ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡
\v 24 የይሁዳ ትውልድ የዛራ ነገድ የሆነው የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ በፋርስ መንግስት የእስራኤል አምባሳደር ነበር፡፡
\s5
\v 25 በኢየሩሳሌም ያልተቀመጡት አንዳንድ ሰዎች በእርሻቸው አቅራቢያ በሚገኙ መንደሮች ይኖሩ ነበር፡፡ ከይሁዳ ነገድ የሆኑ አንዳንዶች በቂርያት አርባቅ፣ በዲቦን፣ እና በይቀብጽኤል አጠገብ በሚገኙ መንደሮች ኖሩ፡፡
\v 26 አንዳንዶቹ በኢያሱ፣ በምላዳ፣ በቤትጳሌጥ፣
\v 27 በሐጸርሹዓል እና በቤርሳቤህ እንዲሁም በአቀራቢያው ባሉ መንደሮች ኖሩ፡፡
\s5
\v 28 ሌሎቹ በጺቅላግ፣ በምኮና እና በአካባቢው ባሉ መንደሮች፣
\v 29 በዓይንሪሞን፣ በጸርዓ፣ በየርሙት፣
\v 30 በዛኖዋ፣ በዓዶላም፣ እና በእነዚያ ከተሞች አቅራቢያ ተቀመጡ፡፡ አንዳንዶቹ በለኪሶ እና በአካባቢ ባሉ መንደሮች፣ እንዲሁም አንዳንዶች በዓዜቃና በአካባቢዋ ባሉ መንደሮች ተቀመጡ፡፡ እነዚህ ሁሉ ህዝቦች በደቡብ በቤርሳቤህ መሀል ባሉ ስፍራዎች እና በሰሜን ቦኖም ሸለቆ በኢየሩሳሌም ዳርቻ በይሁዳ ተቀመጡ፡፡
\s5
\v 31 የብንያም ጎሣ ሰዎች በጌባ፣ ማክማስ፣ በጋያ ይህ አይ ቤቴል ተብሎም ይታወቃል፣ እና በአካባቢው ባሉ መንደሮች፣
\v 32 በዓናቶች፣ በኖብ፣ በሐናንያ፣
\v 33 በሐጾር፣ በራማ፣ በጊቴም፣
\v 34 በሐዲድ፣ በስቦይም፣ በንቦላት፣
\v 35 በሎድ፣ በአኖ፣ እና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች ሸለቆ በሚባሉ ቦታዎች ተቀመጡ፡፡
\v 36 በይሁዳ የኖሩ አንዳንድ ሌዋውያን ከብንያም ሰዎች ጋር ለመኖር ሄዱ፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 ብዙ ካህናትና የሌዊ ትውልዶች ከዘሩባቤል እና ከኢያሱ ጋር ከባቢሎን ተመለሱ፡፡ እነዚህም፡ ሠራያ፣ ኤርምያስ፣ ዕዝራ፣
\v 2 አማርያ፣ ሙሉክ፣ ሐጡስ፣
\v 3 ሴኬንያ፣ ሬሁም፣ ሜሪሞት፣
\s5
\v 4 አዶ፣ ጌንቶን፣ አብያ፣
\v 5 ሚያሚን፣ መዓድያ፣ ቢልጋ፣
\v 6 ሸማያ፣ ዮያሪብ፣ ዮዳኤ፣
\v 7 ሰሉ፣ ዓሞቅ፣ ኬልቅያስና ዮዳኤ ነበሩ፡፡ እነዚህ በኢያሱ ዘመን የካህናቱና የወንድሞቸው አለቆች ነበሩ፡፡
\s5
\v 8 የተመለሱት የሌዊ ትውልዶች ዝርዝር ይህ ነው፡፡ እነርሱም ኢያሱ፣ ቢንዊ፣ ቀድምኤል፣ ሰራብያ፣ ይሁዳ እና መታንየ ነበሩ፡፡ የእነዚሀ ሀላፊነት ለእግዚአብሔር የምስጋና ዝማሬ ማቅረብ ነበር፡፡
\v 9 በቅቡቅያ፣ ዑኒም እና ሌሎች የሌዊ ትውልዶች በዝማሬ ወቅት በትይዩ የሚቆሙ የዝማሬ ቡድን አበጁ፡፡
\s5
\v 10 ከብዙ አመታት አስቀድሞ አያሱ ሊቀ ካህን ነበር፡፡ ኢያሱ የዩአቂም አባት ነበረ፣ ዮአቄም የኤልያሴብ አባት ነበረ፣ ኤልያሴብ የዩአዳን አባት ነበረ፣
\v 11 ዩአዳ የዮናታን አባት ነበረ፣ ዮናታን የያዱአን አባት ነበረ፡፡
\s5
\v 12 ዮአቂም የካህናቱ ሁሉ መሪ ነበረ፡፡ የካህናቱ ቤተሰቦች መሪዎች እነዚህ ነበሩ፡ የሠራያ ቤተሰብ መሪ ምራያ፣ የኤርምያስ ቤተሰብ መሪ ሐናንያ፣
\v 13 የዕዝራ ቤተሰብ መሪ ሜሱላም፣ የአማርያ ቤተሰብ መሪ ይሆሐናን
\v 14 የሙሊኪ ቤተሰብ መሪ ዮናታን፣ የሰብንያ ቤተሰብ መሪ ዮሴፍ
\s5
\v 15 ከካሪም ቤተሰብ ብዙዎቹ መሪዎች ዓድና ነበሩ፣ ከመራዮት ቤተሰብ ሔልቃይ
\v 16 ከአዶ ቤተሰብ ዘካርያስ ከጌንቶን ቤተሰብ ሜሱላም
\v 17 ከአብያ ቤተሰብ ዝክሪ መሪዎች ነበሩ፡፡ ከሚያሚን ቤተሰብም አንድ መሪ ነበር፡፡ ከሞዓድያ ቤተሰብ ፈልጣይ ነበር፡፡
\v 18 ከቢልጋ ቤተሰብ ሳሙስ፣ ከሸማያ ቤተሰብ ዮናታን
\v 19 ከዮያሪብ ቤተሰብ መትናይ፣ ከዮዳኤ ቤተሰብ ኦዚ፣
\v 20 ከሳላይ ቤተሰብ ቃላይ፣ ከዓምቅ ቤተሰብ ዔቤር፣
\v 21 ከኬልቅያስ ቤተሰብ ሐሽብያ፣
\s5
\v 22 ኤሊያሴብ ሌዋውያንን በሚመራበት ወቅት፣ የእነርሱ ሁሉ ዝርዝር ይህ ነው፡ ኤሊያሴብ፣ ዮአዳ፣ ዮሐና እና ያዱአ የካህናቱ ሁሉ መሪዎች ነበሩ፡፡ እነርሱ የሌዊ ትውልድ የሆኑትን ቤተሰቦች ስሞች መዘገቡ፡፡ዳርዮስ የፋርስ ንጉስ በነበረበት ዘመን የየቤተሰቡን መሪዎች የመመዝገቡ ሀላፊነት የካህናቱ ነበር፡፡
\v 23 የሌዊ ትውልድ የሆኑ የቤተሰብ መሪዎችን ስሞች ዝርዝር በታሪክ መጽሐፍ ጽፈው ነበር፡፡ የኤልያሴብ የልጅ ልጅ የሆነው ዮሐና የካህናት ሁሉ መሪ እስከ ሆነበት ጊዜ ድረስ ያሉትን ክንዋኔዎች መዝግበው ነበር፡፡
\s5
\v 24 እነዚህ የሌዋውያን መሪዎች ነበሩ፡ ሐሽብያ፣ ሰራብያ፣ የቀድመኤል ልጅ ኢያሱ፣ እና ለእግዚአብሔር ውዳሴና ምስጋና ለማቅረብ ከእነርሱ ፊት ለፊት የቆሙ ወንድሞቸው፡፡ ይህንንም የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነው ንጉስ ዳዊት እንዳዘዛቸው እንደዚያው አደረጉ፡፡
\v 25 በር ጠባቀዎቹ፣ መታንያ፣ በቅቡቅያ፣ አብድዩ፣ ሜሱላም ጤልሞንና ዓቁብ ነበሩ፡፡
\v 26 አገረ ገዢው ነህምያ እና ካህኑ ዕዝራ በነበሩበት ወቅት፣ በኢዮሴዴቅ የልጅ ልጅ በኢያሱ ልጅ በዮቂም ዘመን ይህንን ሥራ ሰሩ፡፡ ዕዝራ የአይሁድን ህግጋትም በሚገባ ያውቅ ነበር፡፡
\s5
\v 27 የኢየሩሳሌምን ቅጥር ስንመርቅ፣ የሌዊን ትወልዶች ከሚኖሩባቸው የእስራኤል አካባቢዎች የቅጥሩን ምርቃት ያከብሩ ዘንድ ጠራናቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ብዙዎቹም በጽናጽልና፣ በበገና፣ በክራርና በሌሎች የክር ሙዚቃ መሳሪያዎች በመጫወት ይዘምሩ ነበር፡፡
\v 28 በህብረት ያለማቋረጥ የሚዘምሩትን የሌዊ ወገኖች ሰበሰብን፡፡ ከሰፈሩበት ከኢየሩሳሌም ዙሪያ ከነጦፋውያን መንደሮችና ከደቡብ ምስራቅ ኢየሩሳሌም ወደ መሃል ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
\s5
\v 29 ከሰሜን ምስራቅ የኢየሩሳሌም ሶስት ቦታዎችም ከቤት ጌልገላ፣ ከጌባ አካባቢና ከዓዝሞት አካባቢ መጡ፡፡ መዘምራኑ ኢየሩሳሌም አቅራቢያ መንደሮችን መሰረቱ፡፡
\v 30 ካህናቱና የሌዊ ወገኖች ራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት የመንጻት ሥርዓት አደረጉ፣ ለህዝቡም ይህንኑ ስርዓት አደረጉ፣ ለከተማዋ መግቢያዎችና በመጨረሻም ለቅጥሩ ጭምር ስርዓቱን ፈጸሙ፡፡
\s5
\v 31 ከዚያ በቅጥሩ ጫፍ የይሁዳ መሪዎችን በአንድነት ሰበሰብኩ፣ እግዚአብሔርን እያገገኑ በቅጥሩ ላይ በከተማዋ ዙሪያ በሰልፍ እንዲዞሩ ሁለት ትላልቅ ቡድኖችን እዲመሩ ሾምኳቸው፡፡ በከተማይቱ ትይዩ ሲሆኑ፣ አንዱ ቡድን ወደ ቀኝ የቆሻሻ መጣያው በር ወደሚባለው ሄደ፡፡
\s5
\v 32 ከመሪዎቻቸው በኋላ ሆሻያና የይሁዳ እኩሌቶቹ መሪዎች ተሰለፉ፡፡
\v 33 ከእነርሱ በኋላ የተከተሏቸው ዓዛርያስ፣ ዕዝራ፣ ሜሱላም፣
\v 34 ይዳ፣ ብንያም፣ ሸማያ፣ ኤርምያስ፣
\v 35 እና መለከት የሚጫወቱ አንዳንድ የክህናቱ ወንዶች ልጆች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የአሳፍ ትውልድ የሆኑት የዘኩር ልጅ፣ የሚካያ ልጅ፣ የመታንያ ልጅ፣ የሸማያ ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ዘካርያስ ይገኙበታል፡፡
\s5
\v 36 ከእነዚህ በኋላ የሚገዙት የዘካርያስ ቤተሰቦች ሌሎች አባላት ነበሩ፡፡ ከእነዚህም ሸማያ፣ ኤዝርኤል፣ ሚላላይ፣ ጊላላይ፣ መዓይ፣ ናትናኤል፣ ይሁዳ፣ እና አናኒምን ያካትታል፡፡ ሁሉም ንጉስ ዳዊት ከብዙ አመታት አስቀድሞ ይጫወትበት የነበሩ እነዚያኑ አይነት የሙዚቃ መሳሪያዎችን ይጫወቱ ነበር፡፡ የአይሁድን ህግጋት በሚገባ የሚያውቀው ሰው ዕዝራ፣ ከዚህ ቡድን ፊት ሰልፉን ይመራ ነበር፡፡
\v 37 የፋፏቴ በር ሲደርሱ፣ ወደ ዳዊት ከተማ ደረጃዎችን ወጡ፣ የዳዊትን ቤተ መንግስት አልፈው፣ ከዚያ ውሃ በር አጠገብ ወደሚገኘው ቅጥር በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ሄዱ፡፡
\s5
\v 38 ለያህዌ ይዘምርና ያመሰግን የነበረው ሌላው የዝማሬ ቡድን በቅጥሩ ላይ በግራ በኩል በሰልፍ አለፈ፡፡ እኔ ከህዝቡ ከፊሉን ይዤ ተከተልኳቸው፡፡ እኛ የእቶን ግንቡን አልፈን ወደ ሰፊው ቅጥር አለፍን፡፡
\v 39 ከዚያ ተነስተን የኤፍሬምን በር፣ የጄቫናን በር፣ የአሣን በር፣ የሐናንኤልን ግንብ፣ የመቶ ወታደሮችን በር አልፈን ወደ በጎች በር ተጓዝን፡፡ ወደ ቤተ መቅደሱ በር ስንቃረብ ሰልፋችንን ጨረስን፡፡
\s5
\v 40 ሁለቱም ቡድኖች እየዘመሩና እርሱን እያመሰገኑ ወደ እግዚአብሔር ቤት ደረሱ፡፡ በዚያም በየስፍራቸው ቆሙ፡፡ እኔና ከእኔ ጋር የነበሩ መሪዎችም በስፍራችን ቆምን፡፡
\v 41 የእኔ ቡድን መለከት የሚነፉትን እነዚህን ካህናት ያጠቃልላል፡ ኤልያቄም፣ መዕሤያ፣ ሚንያሚን፣ ሚካያ፣ ኤልዮዔናይ፣ ዘካርያስ እና ሐናንያ፣
\v 42 ሌሎቹም መዕሤያ፣ ሸማያ፣ አልዓዛር፣ ኦዚ፣ ይሆሐናን፣ መልክያ፣ ኤላም እና ኤድር ናቸው፡፡ መሪያቸው ይዝራሕያ የሆነው መዘምራኑ ድምቸውን ከፍ አድርገው ዘመሩ፡፡
\s5
\v 43 ከቤተ መቅደሱ ውጭ ከሄድን በኋላ ብዙ መስዋዕቶችን አቀረብን፡፡ እኛ ወንዶች ሁላችን እግዚብሔር በጣም ደስተኞች ስላደረገን ደስ አለን፡፡ ሴቶቹና ልጆችም እንደዚሁ ደስ አላቸው፤ በሩቅ ያሉ ሰዎች እኛ በኢሩሳሌም ውስጥ ሆነን የምናሰማውን ድምጽ መስማት ይችሉ ነበር፡፡
\s5
\v 44 በዚያን ቀን ህዝቡ ለቤተ መቅደስ የሰጠውን ገንዘብ ለሚያስቀምጡበት ግምጃ ቤት ሀላፊ የሚሆኑ ወንዶች ተሾሙ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለአስራትና በየአመቱ ለሚሰበሰበው እህልና ፍራፍሬ በኩራቶችም ሀላፊዎች ነበሩ፡፡ እነዚሁ ሰዎች ወደ ግምጃ ቤቶቹ ከእርሻዎች ምርት ለካህናቱና ለሌዊ ትውልዶች ያመጡ ነበር፡፡ ይህ የተደረገው የይሁዳ ሰዎች በያህዌ ቤት የሚያገለግሉ አገልጋዮች እንዲኖር ይፈልጉ ስለነበር ነው፡፡
\v 45 ካህናቱና ሌዋውያኑ ነገሮችን ለማንጻት፣ በማንጻት ስርዓቱ ያህዌን ያገለግሉ ነበር፤ መዘምራኑ በቤተ መቅደስ፣ እንዲሁም በር ጠባቂዎቹ ንጉስ ዳዊትና ልጁ ሰለሞን እንዲደረግ እንደ ደነገጉት ስራቸውን ያከናውኑ ነበር፡፡
\s5
\v 46 ከዳዊትና ከአሳፍ ዘመን አንስቶ፣ የዘማሪዎች መሪዎች ነበሩ፤ መዘምራኑም እግዚአብሔርን ለማወደስና ለማመስገን ይዘምሩ ነበር፡፡
\v 47 ዘሩባቤል በነበረበት አመታትና በአገረ ገዥው ነህምያ ዘመን፣ ዘማርያኑና የቤተ መቅደስ በር ጠባቂዎች በየዕለቱ የሚያስፈልጋቸውን ምግብ መላው እስራኤል ያወጣ ነበር፡፡ ህዝቡ ለሌዋውያን ኑሮ የሚያስፈልገውን ያስቀምጡላቸውና ሌዋውያኑ ደግሞ ከካህናቱ ቀዳሚ መሪ ለሆኑት ለአሮን ትውልዶች የሚያስፈልገውን ያስቀምጡላቸው ነበር፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 በዚያን ቀን እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን አሞናዊያን ወይም ሞአባዊያን የእግዚአብሔር ህዝቦች ወደሚያመልኩበት ስፍራ አይግቡ የሚለውን የህጉን ክፍል ካህናቱ ለህዝቡ አነበቡ፤ ህዝቡም አደመጠ፡፡
\v 2 ይህ የሆነው የአሞንና የሞአብ ሰዎች እስራኤላዊያን ከግብጽ ወጥተው ወደሚገቡበት አገር ሲጓዙ ምንም ምግብ ወይም ውሃ ስላልሰጧቸው ነበር፡፡ ይልቁንም፣ የአሞንና የሞብ ሰዎች በለዓም እስራኤላዊያንን እንዲረግም ገንዘብ ከፈሉት፡፡ እግዚአብሔር ግን እስራኤልን ለመርገም የተደረገውን ያን ጥረት ወደ በረከት ለወጠው፡፡
\v 3 ስለዚህም ህዝቡ እነዚያ ህጎች ሲነበቡላቸው በሰሙ ጊዜ፣ አባቶቻቸው ከሌሎች አገሮች የሆኑትን ሰዎች ሁሉ አስወጡ፡፡
\s5
\v 4 አስቀድሞ፣ ካህኑ ኤልያሴብ በቤተ መቅደሱ የግምጃ ቤቱ ኃላፊ ሆኖ ተሹሞ ነበር፡፡ እርሱም የጦቢያ ቤተዘመድ ነበር፡፡ እነርሱም የእህል ቁርባኖቹንና እጣኑን በዚያ ስፍራ አከማቹ፡፡
\v 5 ለቤተ መቅደስ የሚያገለግሉ ዕቃዎችን በዚያ አስቀመጡ፡፡ ህዝቡ ለሌዋውያን የሰጠውን ስጦታዎች በግምጃ ቤት አስቀመጡ፡፡ እግዚአብሔር ለሌዋውያኑ፣ ለዘማሪዎቹና ለበር ጠባቂዎች እንዲሰጡ ያዘዘውን የእህል፣ የወይንና የወይራ ዘይት አስራት አመጡ፡፡ ሌሎች ካህናትን ለመደገፍም ስጦታዎቹን አመጡ፡፡
\s5
\v 6 በዚያን ጊዜ እኔ ኢየሩሳሌም ውስጥ አልነበርኩም፡፡ አርጤክስስ የባቢሎን ንጉስ በነበረበት በሰላሳ ሁለተኛው አመት ያከናወንኩትን ለንጉሱ ለመናገር ተመለስኩ፡፡ ለጥቂት ጊዜ በዚያ ከቆየሁ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም እንድመለስ እንዲፈቅደልኝ ንጉሱን ጠየቅሁት፡፡
\v 7 ስመለስ፣ ኤልያሴብ ያደረገውን ክፉ ነገር አወቅሁ፡፡ ጦቢያ ለእግዚአብሔር የተለየውን አንድ ክፍል ቤት ለገዛ ጥቅሙ እንዲያውለው ትቶለት ነበር፡፡
\s5
\v 8 እኔም በጣም ተቆጣሁ፡፡ ወደዚያ ክፍል ገብቼ የጦቢያ የሆኑትን ነገሮች ሁሉ አውጥቼ ጣልኩ፡፡
\v 9 ከዚያ ያንን ክፍል እንደገና ለማንጻት የማንጻት ሥርኣት እንዲደረግ አዘዝኩ፡፡ እንደዚሁም ደግሞ ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውሉ ማናቸውም ዕቃዎችና የእህል ቁርባኖችን እንዲሁም እጣኑ ወደነበሩበት ወደዚያ ክፍል እንዲመለሱ አዘዝኩ፡፡
\s5
\v 10 የእስራኤል ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ቀለብ ወደ ግምጃ ቤት ስላላመጡአቸው፣ የቤተ መቅደሱ ዘማሪዎችና ሌሎች ሌዋውያን ኢየሩሳሌምን ለቀው ወደ እርሻዎቻቸው መመለሳቸውን ተረዳሁ፡፡
\v 11 ስለዚህ ሹማምንቱን እንዲህ ስል ገሰጽኳቸው፣ “በቤተ መቅደስ ለሚካሄደው አገልግሎት ጥንቃቄ ያላደረጋችሁት ለምንድን ነው? ” ስለዚህም እነርሱን በአንድነት ሰብስቤ ወደ መጀመሪያ ስፍራቸው መለስኳቸው፡፡
\s5
\v 12 ከዚያ የይሁዳ ሰዎች በሙሉ የእህል፣ የወይንና የወይራ ዘይት አስራታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ግምጃ ቤት ዳግም ማምጣት ጀመሩ፡፡
\v 13 እኔም እነዚህን ሰዎች የግምጃ ቤቶቹ ሀላፊዎች አድርጌ ሾምኳቸው፡፡ እነርሱም ካህኑ ሰሌምያ፣ የአይሁድ ህግ አዋቂው ሳዶቅ፣ እና ከሌዊ ወገን የሆነው ፈዳያ ናቸው፡፡ እነርሱን እንዲረዳ የመታንያን የልጅ ልጅ የዘኩርን ልጅ ሐናን ሾምኩት፡፡ እነዚያ ሰዎች ለሠራተኞቹ ወገኖቸው ስጦታዎችን በትክክል እንደሚያከፋፍሉ ልተማመንባቸው እንደምችል አውቅ ነበር፡፡
\v 14 አምላኬ ሆይ፣ ለአንተ ቤተ መቅደስ የሰራኋቸውን እነዚህን መልካም ሥራዎችና እዚህ ለተሰራው ሰራ ሁሉ ያደረኩትን አትርሳ!
\s5
\v 15 በእነዚያ ጊዜያት፣ ይሁዳ ውስጥ አንዳንዶች በሰንበት ቀን ሲሰሩ አየሁ፡፡ አንዳንዶች ወይን ለመጥመቅ የወይን ፍሬ ይረግጡ ነበር፡፡ ሌሎች እህል፣ የወይን አቁማዳዎች፣ የወይን ፍሬ የሞሉ ቅርንጫቶች፣ በለስ፣ እና ሌሎች ብዙ ነገሮች በአህዮቻቸው ጭነው ወደ ኢየሩሳሌም ይወስዱ ነበር፡፡ በሰንበት ለይሁዳ ሰዎች ምንም ነገር እንዳይሸጡ አስጠነቀቅኳቸው፡፡
\s5
\v 16 ደግሞም በኢየሩሳሌም የሚኖሩ አንዳንድ የጢሮስ ሰዎች በሰንበት ቀን አሳና ሌሎች ነገሮችን ለአይሁድ ሰዎች ለመሸጥ ወደ ኢየረሳሌም ሲያመጡ አይሁ፡፡
\v 17 ስለዚህ የአይሁድን መሪዎች በመገሰጽ እንዲህ አልኳቸው፣ “ይህ የምታደርጉት በጣም ክፉ ነገር ነው! በሰንበት ቀን እግዚአብሔር በፍጹም እንዲሆን የማይወደውን ነገር እያደረጋችሁት ነው፡፡
\v 18 አባቶችሁ እንደዚህ ያለ ነገሮችን አደረጉ፣ ስለዚህም እግዚአብሔር ቀጣቸው፡፡ በእነርሱ ኃጢአት ምክንያት ይህች ከተማ እንድትጠፋ ፈቅዶ ነበር! እና አሁን የሰንበት ቀን ህግጋትን በመተላፍ እግዚአብሔር በእኛ ላይ እንዲቆጣ ምክንያት እየሆናችሁ ነው፣ እናም የከፋ ቅጣት ይቀጣናል!”
\s5
\v 19 ቀኑ ሲመሽ በኢየሩሳሌም መግቢያ ላይ አንዳንድ የራሴን ሰዎች አቆምኩ፣ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች በዚያን ቀን ምንም አይነት የሚሸጥ ዕቃ ማንም ሰው ወደ ከተማይቱ እንዳያስገባ ያደርጋሉ፡፡
\v 20 ነጋዴዎችና ሻጮች የተለያዩ አይነት ዕቃዎችና ሸቀጦች እንዲሁም አንዳንድ ነገሮችን በማግስቱ ለመሸጥ ተስፋ አድርገው ሰንበት ከሚጀምርበት ከአርብ ምሽት አንስቶ ከኢየሩሳሌም ውጭ ለጥቂት ጊዜ ይሰፍራሉ፡፡
\s5
\v 21 እኔም እንዲህ ስል አስጠነቀቅኳቸው፣ “ዓርብ ምሽት ከቅጥሩ ውጭ በዚህ ማደራችሁ አይጠቅማችሁም! ይህን ደግማችሁ ብታደርጉ፣ እኔ ራሴ አስወጣችሁና አባርራችኋለሁ! ” ስለዚህ ከዚያ በኋላ፣ ዳግመኛ በሰንበት ቀናት ተመልሰው አልመጡም፡፡
\v 22 እንደዚሁም ደግሞ የሌዊ ትውልዶች፤ ራሳቸውን ለማንጻት የማንጻት ሥርዓቱን እንዲፈጽሙና የከተማዋን በሮች ለመጠበቅ ስፍራቸውን እንዲይዙ፣ በዚያ የተቀደሰ ቀን ነጋዴዎች እንዳይገቡ በመከልከል ሰንበት ቅዱስ ሆኖ መጠበቁን እንዲያረጋግጡ አዘዝኳቸው፡፡ አምላኬ ሆይ፣ ስለዚህም ደግሞ አሰበኝ! እንደ ታላቅ ፍቅርህ መጠን ምህረትህን አድርግልኝ፡፡
\s5
\v 23 በዚያን ጊዜ ብዙዎቹ የአይሁድ ወንዶች ከአሽዶድ፣ አሞንና ሞዓብ ሴቶች ጋር መጋባታቸውን አወቅሁ፡፡
\v 24 ከልጆቻቸው እኩሌቶቹ የኖሩበትን ህዝብ የአሽዶድ ሰዎችን ቋንቋ ወይም ሌላ ቋንቋ ይናገሩ እንጂ የአይድን ቋንቋ መናገር አይችሉም ነበር፡፡
\s5
\v 25 ስለዚህም እነዚያን ሰዎች ገስጽኳቸው፣ እግዚአብሔር የተረገሙ እንዲያደርጋቸው ጠየቅኩት፤ አንዳንዶቹን በቡጢ መታኋቸው፤ የአንዳንዶቹንም ጸጉር ነጨሁ! ከዚያ እግዚአብሔር እንደሚሰማ በማወቅ ዳግመኛ ባዕዳንን እንዳያገቡና ልጆቻቸውም ከባዕዳን ጋር እንዲጋቡ እንዳይፈቅዱ ጥብቅ ቃል ኪዳን እንዲገቡ አስገደድኳቸው፡፡
\v 26 እንዲህ አልኳቸው፣ “የእስራኤል ንጉስ፣ ሰለሞን፣ ከባዕድ ሴቶች ጋር በመጋባቱ ምክንያት ኃጢአት ሰራ፡፡ እርሱ ከሌሎች መንግስታት ነገስታት ሁሉ ታላቅ ነበር፡፡ እግዘአብሔር ወዶት በመላው የእስራኤል ህዝብ ላይ ንጉስ አደረገው፡፡ ነገር ግን ባዕዳን የሆኑት ሚስቶቹ ኃጢአት እንዲሰራ ምክንያት ሆኑ፡፡
\v 27 እናንተ ስህተት መሆኑን እያወቃችሁ ባዕድ ሚስቶችን እንዳገባችሁና ጣኦት አምላኪ የሆኑ ባዕድ ሴቶችን በማግባት በአምላካችሁ ላይ ታላቅ ኃጢአት እንደፈፀማችሁ እኛም ያንን ማድረግ ያለብን ይመስላችኋልን?”
\s5
\v 28 ከዮአዳ ልጆች አንዱ፣ የሊቀ ካህኑ የአልያሴብ ልጅ የሰንበላጥን ልጅ አገባ፡፡ ስለዚህ የዮአዳን ልጅ ከኢየሩሳሌም አባረርኩት፡፡
\v 29 አምላኬ ሆይ በክህነት ማዕረግ ላይ ዕፍረት ያስተሉትን አስብ፣ እናም በስራቸው የክህነትንና የሌዋዊነትን ቃል ኪዳን ተላልፈዋል!
\s5
\v 30 ከሌሎች አገሮችና ሀይማኖቶች ካመጧቸው ማናቸውም ነገር አነፃኋቸው፣ እንደዚሁም ለካህናቱና ለሌዊ ወገኖች ደንቦችን ሰጠሁ፣ ስለዚህም እያንዳንዳቸው ማድረግ የለባቸውን ያውቃሉ፡፡
\v 31 በተወሰነው ጊዜና ቀናት በመሰዊያው ላይ የሚነድ ማገዶ ስለመኖሩ አረጋገጥሁ፡፡ ህዝቡ ከምርቱ በኩራቱን ወደ ግምጃ ቤት እንዲያመጣ መመሪያ ሰጠሁ፡፡ አምላኬ ሆይ፣ እዚህን ሁሉ ነገሮች ማድረጌን አትርሳ፣ እነዚህን በማድረጌም ባርከኝ፡፡

1866
20-PRO.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1866 @@
\id PRO
\ide UTF-8
\h ምሳሌ
\toc1 ምሳሌ
\toc2 ምሳሌ
\toc3 pro
\mt ምሳሌ
\s5
\c 1
\p
\v 1 የእስራኤል ንጉስ፣ የዳዊት ልጅ የሰለሞን ምሳሌዎች፡፡
\v 2 እነዚህ ምሳሌዎች የተጻፉት ጥበብንና ተግሳጽን፣ አርቆ ለማስተዋል የሚያስችሉ ቃላትን፣
\v 3 እርማትን በመቀበል ጽድቅ፣ ፍትሕና ሚዛናዊ የሆነ ብያኔን በማድረግ እንድትኖር ለማስተማር ነው፡፡
\s5
\v 4 ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ ምሳሌዎች የተጻፉት ላልተማሩ ጥበብን፣ ለወጣቶች ደግሞ እውቀትንና ልባምነትን ለመስጠት ነው፡፡
\v 5 ጥበበኞች ያድምጡና ትምህርታቸውን ያዳብሩ፣ አስተዋዮች ደግሞ ምሪትን ያግኙበት፣
\v 6 ይህ ደግሞ የጠቢባንን ምሳሌዎች፣ አባባሎችና ቃላቶች እንደዚሁም እንቆቅልሾቻቸውን እንዲረዱ ነው፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመርያ ነው፣ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ፡፡
\v 8 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ምክር ስማ፣ የእናትህንም ሕግ አትተው፤
\v 9 ለራስህ የሞገስ አክሊል፣ ለአንገትህ ደግሞ ውበት የሚሰጥ ጌጥ ይሆኑልሃል፡፡
\s5
\v 10 ልጄ ሆይ፣ ኃጢአተኞች በኃጢአታቸው እንድትሳተፍ ሊያባብሉህ ቢሞክሩ፣ እሺ አትበላቸው፡፡
\v 11 “ከእኛ ጋር ና፣ ነፍስ ለመግደል ተደብቀን እንጠብቅ፣ ንጹሐን ሰዎችን ያለ ምንም ምክንያት ለማትፋት እንሸምቅበት፡፡
\s5
\v 12 ሲኦል ጤናማ ሰዎችን እንደሚውጣቸው፣ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱ፣ እንዲሁ በሕይወት እያሉ እንዋጣቸው፡፡
\v 13 ሁሉም አይነት ውድ የሆኑ ነገሮች እናገኛለን፤ ከሌሎች ሰዎች በሰረቅናቸው ነገሮች ቤቶቻችንን እንሞላለን፡፡
\v 14 ከእኛ ጋር ዕጣህን ጣል፤ ሁላችንም አንድ የጋራ ቦርሳ ይኖረናል፡፡” ቢሉህ፣
\s5
\v 15 ልጄ ሆይ፣ ከእነርሱ ጋር በዚያ መንገድ አትሂድ፤ እነርሱ በሚሄዱበት መንገድ እግርህ አይርገጥ፤
\v 16 እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፣ ደም ለማፍሰስም ይቸኩላሉ፡፡
\v 17 ወፍ ፊት ለፊት እያየች ወፍን ለመያዝ ወጥመድ መዘርጋት ጥቅም የለውም፡፡
\s5
\v 18 እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ለመግደል ተደብቀው ይጠብቃሉ፣ በራሳቸው ላይ ወጥመድን ይዘረጋሉ፡፡
\v 19 ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ሀብትን ያከማቹ ሰዎች መንገዳቸው እንደዚህ ነው፣ ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ የተከማቸ ሃብት የባለቤቱን ሕይወት ያጠፋል፡፡
\s5
\v 20 ጥበብ በጎዳና ላይ ጮኻ ትጣራለች፣ በአደባባይም ድምጿን ከፍ ታደርጋለች፤
\v 21 ጩኸት በበዛባቸው ጎዳናዎች ላይ ትጣራለች፣ በከተማ መግቢያ በሮች ላይ እንዲህ በማለት ትናገራለች፣
\v 22 እናንተ ጥበብ የሌላችሁ አላዋቂነትን የምትወዱት እስከ መቼ ነው? እናንተ ፌዘኞች በፌዝ የምትደሰቱት እስከ መቼ ነው? እናንተ ሞኞች እውቀትን የምትጠሉት እስከ መቼ ነው?
\s5
\v 23 ለዘለፋየ ትኩረት ስጡ፤ ሃሳቤን ሁሉ ለእናንተ አፈስሳለሁ፤ ቃሎቼን አሳውቃችኋለሁ፡፡
\v 24 ጠራኋችሁ፣ እናንተ ግን ለመስማት እምቢ አላችሁ፤ እጄን ለእናንተ ዘረጋሁ፣ ነገር ግን አንድም ሰው ትኩረት አልሰጠውም፡፡
\v 25 ነገር ግን እናንተ ተግሳጼን በሙሉ ችላ አላችሁ፣ ለዘለፋየ ደግሞ ትኩረት አልሰጣችሁም፡፡
\s5
\v 26 እኔ ደግሞ በመከራችሁ እስቃለሁ፣ ሽብር በመጣባችሁ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ፣
\v 27 አስፈሪ ድንጋጤ እንደ ማዕበል በእናንተ ላይ ሲመጣባችሁ፣ ጥፋት እንደ አውሎ ነፋስ እናንተን ሲጠራርጋችሁ፣ ጭንቅና ችግር በእናንተ ላይ በመጣ ጊዜ፡፡
\s5
\v 28 በዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፣ እኔም አልመልስላቸውም፤ አጥብቀው ይፈልጉኛል፣ ነገር ግን አያገኙኝም፡፡
\v 29 እውቀትን ስለ ጠሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራት ስላልመረጡ፣
\v 30 ምክሬን አልተከተሉምና፣ ዘለፋየንም ሁሉ ናቁ፡፡
\s5
\v 31 የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፣ በእቅዳቸው ፍሬ ይጠግባሉ፡፡
\v 32 እነዚህ ያልተማሩ ሰዎች ከእውቀት መራቃቸው ይገድላቸዋል፣ ሞኞችንም ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል፡፡
\v 33 ነገር ግን የሚያደምጠኝ ሁሉ በሰላም ይኖራል፣ ከመከራም ስጋት ያርፋል፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ብትቀበልና ትእዛዛቴን በአንተ ዘንድ ብታኖር፣
\v 2 ጥበብን ብታደምጥና ልብህን ወደ እውቀት ብትመልስ፡፡
\s5
\v 3 እውቀትን ለማግኘት ብትጣራና ድምጽህን ከፍ አድርገህ ለማስተዋል ብትጮህ፣
\v 4 ብርን አጥብቀህ እንደምትፈልግ እርስዋንም ብትፈልጋት፣ የተሰወረ ሃብትን እንደምትፈልግ እንደዚሁ ማስተዋልን ብትሻት፣
\v 5 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፣ እውቀትና ማስተዋል ከአንደበቱ ይወጣሉ፡፡
\v 7 እርሱ ደስ ለሚያሰኙት ጥልቅ ጥበብን ያከማቻል፣ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱ ጋሻ ነው፣
\v 8 የፍትህን መንገድ ይጠብቃል፣ ለእርሱ ታማኞች ለሆኑት ደግሞ መንገዳቸውን ያጸናል፡፡
\s5
\v 9 በዚያን ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትህንና ሚዛናዊነትን እንደዚሁም ማንኛውንም መልካም መንገድ ትገነዘባለህ፡፡
\v 10 ጥበብ ወደ ልብህ ትመጣለችና፣ እውቀትም ነፍስህን ደስ ታሰኛለች፡፡
\s5
\v 11 የመለየት ችሎታ ይጠብቅሃል፣ ማስተዋል ይጋርድሃል፡፡
\v 12 እነዚህ ከክፋት መንገድ፣ ጠማማ ንግግር ከሚናገሩ ሰዎች፣
\v 13 ትክክለኛውን መንገድ ከተዉና በጨለማ መንገድ ከሚሄዱ ይጠብቁሃል፡፡
\s5
\v 14 እነዚህ ክፋትን ሲያደርጉ ደስ ይላቸዋል፣ በጠማማነት ሃሴት ያደርጋሉ፡፡
\v 15 ጠማማ መንገድን ይከተላሉ፣ አካሄዳቸውን ደግሞ በአታላይነታቸው ይደብቃሉ፡፡
\s5
\v 16 ጥበብና ልባምነት ከአመንዝራ፣ ከጀብደኛና በንግግሯ ከምታታልል ሴት ያድኑሃል፡፡
\v 17 ይህች ሴት የወጣትነት በልዋን የተወችና የአምላክዋን ቃል ኪዳን የረሳች ናት፡፡
\s5
\v 18 ቤቷ ወደ ሞት ያዘነበለ ስለሆነ አካሄዷ በመቃብር ወዳሉት ሙታን ይመራሃል፡፡
\v 19 ወደ እርስዋ የሚገቡ ሁሉ እንደገና አይመለሱም፣ የሕይወትንም መንገድ አያገኙም፡፡
\s5
\v 20 ስለዚህ አንተም በመልካም ሰዎች መንገድ ትሄዳለህ፣ የጻድቃንን መንገድ ትከተላለህ፡፡
\v 21 ጻድቃን ቤታቸውን በምድሪቱ ይሰራሉና፣ እነዚህ ነቀፋ የሌለባቸው ደግሞ በእርሷ ጸንተው ይኖራሉና፡፡
\v 22 ክፉዎች ግን ከምድሪቱ ይቆረጣሉ፣ ታማኝነት የሌላቸውም ከእርሷ ይወገዳሉ፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ትእዛዛቴን አትርሳ፣ ትምህርቴንም በልብህ ጠብቅ፣
\v 2 በሕይወትህ ብዙ ቀኖችንና ዓመቶችን እንደዚሁም ሰላምን ይጨምሩልሃል፡፡
\s5
\v 3 በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት አይለዩህ፣ በአንገትህ ዙርያ በአንድ ላይ እሰራቸው፣ በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው፡፡
\v 4 በዚያን ጊዜ ሞገስና መልካም ስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ታገኛለህ፡፡
\s5
\v 5 በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤
\v 6 በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም መንገድህን ቀና ያደርገዋል፡፡
\s5
\v 7 በራስህ አስተያየት ጥበበኛ አትሁን፤ እግዚብሔርን ፍራ፣ ከክፉም ራቅ፡፡
\v 8 ይህም ለስጋህ ፈውስ፣ ለሰውነትህም መታደስ ይሆንልሃል፡፡
\s5
\v 9 እግዚአብሔርን በሀብትህና በምርትህ ሁሉ በኩራት አክብረው፣
\v 10 ጎተራህ ሙሉ ይሆናል፣ ገንዳህ ደግሞ በአዲስ ወይን ጠጅ ተትረፍርፎ ይሞላል፡፡
\s5
\v 11 ልጄ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቅጣት አትናቅ፣ ተግሳጹንም አትጥላ፣
\v 12 አባት ደስ የሚሰኝበትን ልጁን እንደሚቀጣ እንደዚሁ እግዚአብሔርም የሚወዳቸውን ይቀጣልና፡፡
\s5
\v 13 ጥበብን የሚያገኛት ሰው ደስተኛ ነው፣ እውቀትንም ያገኛል፡፡
\v 14 ከጥበብ የምታገኘው ጥቅም ብር ከሚሰጥህ ትርፍ ይልቅ እጅግ ይበልጣል፣ የጥበብ ትርፍ ከወርቅም ይበልጣል፡፡
\s5
\v 15 ጥበብ ከከበረ ዕንቁ ይልቅ እጅግ ውድ ናት፣ አንተ ከምትመኘው ነገር ሁሉ እርሷን የሚተካከላት ምንም ነገር የለም፡፡
\v 16 በቀኝ እጇ ረጅም ዕድሜ አለ፤ በግራ እጇ ደግሞ ባለጠግነትንና ክብርን ይዛለች፡፡
\s5
\v 17 መንገዷ የደግነት መንገድ ነው፣ ጎዳናዋም ሰላም ነው፡፡
\v 18 እርሷ አጥብቀው ለሚይዟት የሕይወት ዛፍ ናት፣ የሚደገፉባትም ደስተኞች ናቸው፡፡
\s5
\v 19 እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሰረተ፣ ሰማያትን ደግሞ በማስተዋል አጸና፡፡
\v 20 በእወቀቱ ጥልቆች ተሰንጥቀው ተከፈቱ፣ ደመናትም ጠልን አንጠበጠቡ፡፡
\s5
\v 21 ልጄ ሆይ፣ ትክክለኛ ፍርድንና ነገሮችን በሚገባ መለየትን ጠብቅ፣ እነዚህ ከእይታህ አይራቁ፡፡
\v 22 እነዚህ ለነፍስህ ሕይወት፣ በአንገትህ ዙርያ የምታስራቸው የሞገስ ጌጥ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 23 በዚያን ጊዜ በመንገድህ ተማምነህ በሰላም ትራመዳለህ፣ እግርህም አይሰናከልም፤
\v 24 በምትተኛበት ጊዜ አትፈራም፤ ስትተኛ እንቅልፍህ ጣፋጭ ይሆናል፡፡
\s5
\v 25 በድንገተኛ ሽብርና በክፉዎች አማካይነት በሚደርስ ጥፋት አትፍራ፣
\v 26 እግዚአብሔር በአጠገብህ ይሆናልና፣ እግርህም በወጥመድ እንዳያያዝ ይጠብቅሃልና፡፡
\s5
\v 27 ልታደርግ የሚቻልህ ሲሆን፣ ለሚገባቸው ሰዎች መልካምን ነገር ከማድረግ አትከልክል፡፡
\v 28 አሁን በእጅህ ገንዘብ እያለ ለጎረቤትህ “አሁን ሂድ፣ እንደገና ተመልሰህ ና፣ ነገ እሰጥሃለሁ” አትበለው፡፡
\s5
\v 29 በአጠገብህ የሚኖረውንና በአንተ የሚተማመነውን ጎረቤትህን ለመጉዳት አትምከርበት፡፡
\v 30 አንድ ሰው አንተን ለመጉዳት ክፉ ካልሰራብህ ያለ በቂ ምክንያት ከዚህ ሰው ጋር አትከራከር፡፡
\s5
\v 31 በክፉ ሰው አትቅና፣ የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ፡፡
\v 32 ጠማማ ሰው በእግዚብሔር ፊት የተጠላ ነውና፣ ቅን ሰውን ግን ወዳጁ ያደርገዋል፡፡
\s5
\v 33 የእግዚአብሔር እርግማን በክፉ ሰዎች ቤት ላይ ነው፣ የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል፡፡
\v 34 እርሱ በፌዘኞች ላይ ያፌዛል፣ ለትሁታን ግን ሞገሱን ይሰጣቸዋል፡፡
\s5
\v 35 ጥበበኞች ክብርን ይወርሳሉ፣ የሞኞች ከፍታ ግን ውርደታቸው ነው፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ልጆች ሆይ፣ የአባትን ተግሳጽ አድምጡ፣ ማስተዋል ምን እንደሆነ እንድታውቁ ልብ በሉ፡፡
\v 2 እኔ መልካም ትምህርት እሰጣችኋለሁ፣ ትምህርቴን አትተዉ፡፡
\s5
\v 3 የአባቴ ልጅ ሳለሁ፣ ለእናቴም ተወዳጅና ብቸኛ ልጅ ሳለሁ፣
\v 4 አባቴ አስተማረኝ፣ እንዲህም አለኝ፡- “ቃሎቼን ሁሉ በልብህ ያዝ፤ ሕግጋቴን ጠብቅ በሕይወትም ኑር፡፡”
\s5
\v 5 ጥበብንና ማስተዋልን አግኝ፤ የአፌን ቃላቶች አትርሳ፣ እነርሱንም አትተው፤
\v 6 ጥበብን አትተዋት፣ እርሷ ከለላ ትሆንሃለች፤ ውደዳት፣ ትጠብቅሃለች፡፡
\s5
\v 7 ጥበብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ናት፣ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፣ ያለህን ሀብት ሁሉ ከፍለህ ማስተዋልን የራስህ አድርጋት፡፡
\v 8 ለጥበብ ከፍተኛ ስፍራ ስጣት፣ እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ እርሷን አጥብቀህ ስትይዛት ታከብርሃለች፡፡
\v 9 በራስህ ላይ የክብር አክሊል ታስቀምጥልሃለች፤ ውብ የሆነ ዘውድም ትሰጥሃለች፡፡
\s5
\v 10 ልጄ ሆይ፣ አድምጠኝ፣ ለቃሎቼም ትኩረት ስጥ፣ በሕይወት ዘመንህም ብዙ አመታት ይጨመሩልሃል፡፡
\v 11 በጥበብ ጎዳና አስተምርሃለሁ፤ በቀጥተኛ መንገዶችም እመራሃለሁ፡፡
\v 12 በምትራመድበት ጊዜ ማንም በመንገድህ ላይ አይቆምም፣ በሮጥህ ጊዜ አትሰናከልም፡፡
\s5
\v 13 ምክርን ያዝ፣ አትልቀቀው፤ ጠብቀው፣ እርሱ ሕይወትህ ነውና፡፡
\v 14 የክፉዎችን መንገድ አትከተል፣ ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፡፡
\v 15 ከእርሷ ራቅ፣ በዚያ አትሂድ፤ ከዚያ ተመለስ፣ በሌላ መንገድ ሂድ፡፡
\s5
\v 16 ክፋትን እስኪፈጽሙ ድረስ መተኛት አይችሉምና፣ አንድ ሰው እስኪያሰናክሉ ድረስ እንቅልፋቸው አይመጣምና፡፡
\v 17 የክፋትን እንጀራ ይበላሉና፣ የአመጽንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና፡፡
\s5
\v 18 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው መንገድ ግን እየፈካ እንደሚሔድ የንጋት ብርሃን ነው፤ ሙሉ ቀን እስከሚሆን ድረስ ብርሃኑ የበለጠ እየጨመረ ይሄዳል፡፡
\v 19 የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ጨለማ ነው፣ምን እንደሚያሰናክላቸው በፍጹም አያውቁም፡፡
\s5
\v 20 ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ልብ በል፣ ንግግሮቼን አድምጥ፡፡
\v 21 ከአይኖችህ አይራቁ፣ በልብህ ውስጥ ጠብቃቸው፡፡
\s5
\v 22 ቃሎቼ ለሚያገኘኟቸው ሰዎች ሕይወት፣ ለመላው ሰውነታቸውም ፈውስ ናቸውና፡፡
\v 23 ልብህን በጥንቃቄ ጠብቅ፣ በትጋትም ከልለው፣ የሕይወት ምንጭ የሚፈልቀው ከእርሱ ነውና፡፡
\s5
\v 24 ጠማማ ንግግርን ከአንተ አስወግድ፣ ብልሹ ወሬ ከአንተ አርቅ፡፡
\v 25 ዓይኖችህ ወደ ፊት በቀጥታ ይመልከቱ፣ በቀጥታ ፊት ለፊት አተኩረህ እይ፡፡
\s5
\v 26 ለእግርህ ደልዳላ ጎዳና አበጅለት፤ ከዚያ በኋላ መንገድህ በሙሉ አስተማማኝ ይሆናል፡፡
\v 27 ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ አትበል፤ እግርህን ከክፉ መልስ፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ለጥበቤ ትኩረት ስጥ፤ የማስተዋል ቃሌንም በጥንቃቄ አድምጥ፡፡
\v 2 ይህም ልባምነትን ትማር ዘንድ፣ ከንፈሮችህም እውቀትን ይጠብቁ ዘንድ ነው፡፡
\s5
\v 3 የአመንዝራ ሴት ከንፈር ማርን ያንጠባጥባልና፣ አንደበቷም ከዘይት ይልቅ የለሰለሰ ነውና፣
\v 4 ነገር ግን ፍጻሜዋ እንደ እሬት መራራ ናት፣ እንደ ስለታም ሰይፍ የምትቆርጥ ናት፡፡
\s5
\v 5 እግሮቿ ወደ ሞት ይወርዳሉ፣ እርምጃዎቿም ወደ ሲኦል መንገድ ይሄዳሉ፡፡
\v 6 ስለ ሕይወት መንገድ ምንም አታስብም፡፡ አረማመዷ የተቅበዘበዘ ነው፣ ወዴት እንደምትሄድም አታውቅም፡፡
\s5
\v 7 አሁንም ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፣ የአፌን ቃል ከማድመጥ ፈቀቅ አትበሉ፡፡
\v 8 መንገድህን ከእርሷ አርቅ፣ ወደ ቤቷም በር አትቅረብ፡፡
\s5
\v 9 እንዲህ ካደረግህ ክብርህን ለሌሎች ሰዎች፣ የሕይወት ዘመንህንም ለጨካኝ ሰው አሳልፈህ አትሰጥም፤
\v 10 ባዕዳን በሀብትህ አይፈነጥዙም፣ የደከምክበት ነገር ወደ ባዕዳን ቤት አይገባም፡፡
\s5
\v 11 በሕይወትህ መጨረሻ ስጋህና ሰውነትህ ሲጠፋ ታቃስታለህ፡፡
\v 12 እንዲህም ትላለህ፡- “ተግሳጽን እንዴት ጠላሁ፣ መታረምን ልቤ ናቀ!
\s5
\v 13 አስተማሪዎቼን አልታዘዝሁም፣ አሰልጣኞቼንም አላደመጥሁም፡፡
\v 14 በጉባኤና ሰዎች በተሰበሰቡበት መካከል ሙሉ በሙሉ ወደ ጥፋት ተቃርቤ ነበር፡፡”
\s5
\v 15 ከማጠራቀሚያህ ውሃ ጠጣ፣ ከጉድጓድህም የሚፈልቀውን ውሃ ጠጣ፡፡
\v 16 ምንጮችህ በሁሉም ቦታ ያለገደብ ሊፈስሱ፣ ወንዞችህስ በአደባባዩ ሁሉ ሊጎርፉ ይገባልን?
\v 17 እነርሱ ለአንተ ብቻ ይሁኑ፣ ከአንተ ጋር ላሉ ባዕዳን አይሁኑ፡፡
\s5
\v 18 ምንጭህ የተባረከ ይሁን፣ በወጣትነት ሚስትህም ደስ ይበልህ፡፡
\v 19 ምክንያቱም እርሷ በፍቅር እንደተሞላች ዋላ፣ ግርማ ሞገስ እንዳላትም ሚዳቋ ናት፡፡ ጡቷም ሁልጊዜ ያስደስትህ፣ ሁልጊዜም በፍቅሯ ተማረክ፡፡
\s5
\v 20 ልጄ ሆይ፣ ስለምን በጋለሞታ ሴት ትማረካለህ፤ የሌላይቱንስ ሴት ሰውነት ለምን ታቅፋለህ?
\v 21 እግዚአብሔር ሰው የሚሰራውን በሙሉ ያያል፣ የሚሄድበትንም መንገድ ሁሉ ይመለከታል፡፡
\s5
\v 22 ክፉ ሰው በራሱ ኃጢአት ይጠመዳል፤ የኃጢአቱም ገመድ አጥብቆ ይይዘዋል፡፡
\v 23 አልተቀጣምና ይሞታል፤ ከሞኝነቱም ብዛት የተነሳ መንገድ ይስታል፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ጎረቤትህ ለወሰደው ብድር ዋስ ብትሆንና ገንዘብህን ለዋስትና ብታስይዝ፣ የማታውቀው ሰው ለወሰደው ብድር መተማመኛ ሰጥተህ ከሆነ፣
\v 2 የዚያን ጊዜ በቃልህ ምክንያት በራስህ ላይ ወጥመድ ዘርግተሃል፣ በአፍህም ቃል ተጠምደህ ተይዘሃል፡፡
\s5
\v 3 ልጄ ሆይ፣ ይህን አድርግ፣ ራስህንም አድን፣ አንተ በጎረቤትህ ምህረት ስር ነህና፡፡ ሂድ፣ ጎረቤትህም እንዲተውህ ሄደህ በትህትና ለምነው፡፡
\s5
\v 4 ለአይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፡፡
\v 5 የሜዳ ፍየል ከአዳኝ እጅ፣ ወፍም ከአጥማጅ እጅ እንደምታመልጥ እንዲሁ ራስህን አድን፡፡
\s5
\v 6 አንተ ሰነፍ ሰው፣ ወደ ጉንዳን ተመልከት፣ መንገዷን አስተውል፣ ጥበበኛም ሁን፡፡
\v 7 አዛዥ፣ አለቃ ወይም ገዥ የላትም፣
\v 8 ይሁን እንጂ ምግቧን በበጋ ታዘጋጃለች፣ በመኸር ደግሞ የምትበላውን ታከማቻለች፡፡
\s5
\v 9 አንተ ሰነፍ፣ የምትተኛው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህስ የምትነሣው መቼ ነው?
\v 10 “ጥቂት ማንቀላፋት፣ ጥቂት ማንጎላቸት፣ ጥቂት እጅን አጣጥፎ ማረፍ”
\v 11 ድህነትህ እንደ ወንበዴ፣ ችግርህም መሳርያ እንደ ታጠቀ ወታደር ይመጣብሃል፡፡
\s5
\v 12 የማይረባ፣ ክፉ ሰው፣ በጠማማ ንግግሩ ይኖራል፣
\v 13 በዓይኑ ይጠቅሳል፣ በእግሩም ምልክት ያስቀምጣል፣ በጣቶቹም ይጠቁማል፡፡
\s5
\v 14 በልቡ ውስጥ ባለው አጭበርባሪነት ክፋትን ይዶልታል፣ ግጭትንም ሁልጊዜ ይጭራል፡፡
\v 15 ስለዚህ ጥፋቱ ሳይታሰብ በቅጽበት ይደርስበታል፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደማይድን ሆኖ ይሰበራል፡፡
\s5
\v 16 እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች አሉ፣ የሚጸየፋቸውም ሰባት ናቸው፡-
\s5
\v 17 የትዕቢተኛ ሰው አይን፣ ሐሰትን የሚናገር ምላስ፣ የንጹሃን ሰዎችን ደም የሚያፈስስ እጅ፣
\v 18 ክፋትን የሚፈጥር ልብ፣ ክፋት ለማድረግ በፍጥነት የሚሮጥ እግር፣
\v 19 ውሸትን የሚለፈልፍ ምስክር፣ በወንድማማቾች መካከል ብጥብጥ የሚዘራ ሰው፡፡
\s5
\v 20 ልጄ ሆይ፣ የአባትህን ትዕዛዝ ፈጽም፣ የእናትህንም ትምህርት አትተው፡፡
\v 21 ሁልጊዜ በልብህ አኑራቸው፣ በአንገትህም ዙርያ እሰራቸው፡፡
\s5
\v 22 ስትሄድ፣ ይመሩሃል፤ በተኛህ ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በነቃህም ጊዜ ያስተምሩሃል፡፡
\v 23 ትዕዛዛቱ መብራት ናቸው፣ ትምህርቱም ብርሃን ነው፤ የተግሳጽም ዘለፋዎች የሕይወት መንገድ ናቸውና፡፡
\s5
\v 24 ከምግባረ ብልሹ ሴት፣ ከአመንዝራ ሴትም ጣፋጭ ቃላት ይጠብቅሃል፡፡
\v 25 በልብህ ውበቷን አትመኝ፣ በሽፋሽፍትዋም አትጠመድ፡፡
\s5
\v 26 ከጋለሞታ ሴት ጋር መተኛት የአንድ ቁራሽ ዳቦ ዋጋ ያሳጣሃል፤ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር መተኛት ግን ሕይወትህን ያሳጣሃል፡፡
\v 27 አንድ ሰው ልብሱ ሳይቃጠል በደረቱ እሳት መያዝ ይችላልን?
\s5
\v 28 አንድ ሰው እግሩ ሳይቃጠል በፍም ላይ መራመድ ይችላልን?
\v 29 ከጎረቤቱ ሚስት ጋር የሚተኛም ሰው እንዲሁ ነው፤ ከእርሷ ጋር የሚተኛም ሳይቀጣ አይቀርም፡፡
\s5
\v 30 ሌባ በተራበ ጊዜ ፍላጎቱን ለማሟላት ቢሰርቅ ሰዎች አይንቁትም፡፡
\v 31 ሆኖም ሌባው ሲሰርቅ ከተያዘ፣ የሰረቀውን ሰባት እጥፍ ይመልሳል፤ በቤቱም ያለውን ንብረት ሁሉ መስጠት አለበት፡፡
\s5
\v 32 የሚያመነዝር ሰው አእምሮው አያመዛዝንም፤ እንዲህ የሚያደርግ ራሱን ያጠፋል፡፡
\v 33 ቁስልና ውርደት ይገባዋል፣ ውርደቱም አይደመሰስለትም፡፡
\s5
\v 34 ቅናት ሰውን ቁጡ ያደርገዋልና፤ በሚበቀልበት ጊዜ ምህረትን አያደርግም፡፡
\v 35 እርሱ ምንም ዓይነት ካሳ አይቀበልም፣ ብዙ ስጦታዎችን ብታቀርብለትም እሺ አይልም፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ልጄ ሆይ፣ ቃሎቼን ጠብቅ፣ ትእዛዜንም በአንተ ውስጥ አኑር፡፡
\v 2 ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ኑር፣ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፡፡
\v 3 በጣቶችህም ላይ እሰራቸው፤ በልብህም ጽላት ጻፋቸው፡፡
\s5
\v 4 ጥበብ “አንቺ እህቴ ነሽ” በላት፣ ማስተዋልን ደግሞ ዘመዴ ብለህ ጥራው፣
\v 5 ከአመንዝራ ሴት፣ ቃሏንም ከምታለዝብ ከዘማዊም ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፡፡
\s5
\v 6 በቤቴ መስኮት ላይ ሆኜ ወደ ውጭ ተመለከትሁ፣
\v 7 ብዙ እውቀት አልባ ወጣቶች ተመለከትሁ፡፡ ከመካከላቸው አንድ የማያስተውል ወጣት ተመለከትሁ፡፡
\s5
\v 8 ያ ወጣት በቤቷ ማዕዘን አጠገብ ባለው መንገድ አለፈ፣ ከዚያም ወደ ቤቷ አቅጣጫ ሄደ
\v 9 ብርሃን ደንገዝገዝ፣ ቀኑ መሸትሸት ብሎ ነበር፣ በምሽትና በሌሌት ጨለማ፡፡
\s5
\v 10 በዚያ አንዲት ሴት አገኘችው፣ እንደ ሴተኛ አዳሪ የለበሰች፣ እዚያ ለምን እንደ መጣች በሚገባ ታውቃለች፡፡
\v 11 ጯኺና እምቢተኛ ናት፣ እግሮቿ በቤት አይቀመጡም
\v 12 አንዴ በመንገድ፣ አንዴ በገበያ፣ በየማዕዘኑም ተጋድማ ታደባለች፡፡
\s5
\v 13 ስለዚህም ትይዘዋለች፣ ትስመውማለች፣ ፊቷም እፍረት ሳይታይበት እንዲህ አለችው፣
\v 14 ዛሬ የሰላም መስዋዕቴን አቅርቤአለሁ፣ ስእለቴንም ፈጽሜአለሁ፣
\v 15 ስለዚህ አንተን ለማግኘት፣ ፊትህን ለመፈለግ ወጣሁ፣ አግኝቼሃለሁም፡፡
\s5
\v 16 በአልጋየ ላይ መሸፈኛ ዘርግቼበታለሁ፣ ከግብጽ የመጣ ባለቀለም የአልጋ ልብስ አንጥፌበታለሁ፡፡
\v 17 አልጋየን ከርቤ፣ አልሙንና ቀረፋ ረጭቼበታለሁ፡፡
\v 18 ና፣ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፤ ፍቅራችንን በምንገልጥባቸው የተለያዩ መንገዶች በታላቅ ደስታ እንፈንድቅ፡፡
\s5
\v 19 ባሌ በቤት የለም፤ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዷል፡፡
\v 20 በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ ሙሉ ጨረቃ በወጣበት ቀን ይመለሳል፡፡”
\v 21 በሚያባብል ንግግሯ ታሳስተዋለች፣ በለሰለሰ ንግሯም ታታልለዋለች፡፡
\s5
\v 22 ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፣ ፍላጻ ጉበቱን እስኪወጋው ድረስ በወጥመድ እንደተያዘ አጋዘን፣
\v 23 ወደ ወጥመድ በርራ እንደምትገባ ወፍ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ እርሷን ይከተላታል፡፡
\s5
\v 24 አሁን፣ ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፤ የምናገረውንም ልብ ብላችሁ ስሙኝ፡፡
\v 25 ልባችሁ ወደ መንገዷ እንዲያዘነብል አትፍቀዱ፤ በጎዳናዋም አትሳቱ፡፡
\s5
\v 26 ብዙ ተጎጂዎችን አጥምዳ ጥላለች፤ ቁጥራቸውም እጅግ ብዙ ነው፡፡
\v 27 ቤቷ ወደ ሲኦል በሚወስደው መንገድ ነው፤ ወደ ሞት ማደርያም የሚያወርድ ነው፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ጥበብ እየጮኸች አይደለምን? ማስተዋልስ ድምጿን ከፍ አላደረገችምን?
\v 2 ከመንገድ አጠገብ ባሉት ኮረብታዎች ጫፍ ላይ፣ መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ፣ ጥበብ ትቆማለች፡፡
\v 3 ወደ ከተማይቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣ በከተማይቱ መግቢያ አጠገብ፣ ትጣራለች፡፡
\s5
\v 4 እናተ ሰዎች፣ ወደ እናንተ እጣራለሁ፣ ድምጼንም ከፍ አድርጌ ወደ ሰው ልጆች እጮኸለሁ፡፡
\v 5 እናንተ ትምህርት ያላገኛችሁ፣ ጠንቃቃነትን ተማሩ፣ እናንተ እውቀትን የምትጠሉ፣ የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁ፡፡
\s5
\v 6 የከበሩ ነገሮችን እናገራለሁና አድምጡኝ፣ ከንፈሮቼ ሲከፈቱ ቀና የሆነውን ነገር እናገራለሁ
\v 7 አንደበቴ እውነትን ይናራልና፣ ከንፈሮቼም ክፋትን ይጠላሉና፡፡
\s5
\v 8 ከአንደበቴ የሚወጡ ቃሎች ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ በእነርሱ ውስጥ ጠማማ ወይም አሳሳች ነገር የለውም፡፡
\v 9 ለሚያስተውል ሰው ቃሎቼ በሙሉ ቀና ናቸው፤ እውቀትን ለሚያገኙ ቃሎቼ ትክክለኛ ናቸው፡፡
\s5
\v 10 ከብር ይልቅ ተግሳጼን ምረጡ፣ ከንጹህ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ምረጡ፡፡
\v 11 እኔ ጥበብ፣ ከከበረ ዕንቁ እበልጣለሁና፤ ከምትመኙት ነገር በሙሉ ከእኔ ጋር የሚስተካከል የለም፡፡
\s5
\v 12 እኔ ጥበብ፣ ከጥንቃቄ ጋር እኖራለሁ፣ እውቀትና ነገሮችን ለይቶ ውሳኔ የመስጠት ኃይልም አለኝ፡፡
\v 13 እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢት፣ እብሪት፣ ክፉ መንገድና ጠማማ ንግግር እጠላለሁ፣ ፈጽሞም እጠላቸዋለሁ፡፡
\s5
\v 14 እኔ መልካም ምክርና እውነተኛ ጥበብ አለኝ፤ ማስተዋል አለኝ፣ ብርታትም የእኔ ነው፡፡
\v 15 ነገስታት፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትሃዊነት ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡
\v 16 መሳፍንቶች፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትህ ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡
\s5
\v 17 የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፣ ተግተው የሚፈልጉኝም ያገኙኛል፡፡
\v 18 ባለጠግነትና ክብር፣ ዘላቂነት ያለው ሃብትና ጽድቅም በእኔ ዘንድ አሉ፡፡
\s5
\v 19 ፍሬየ ከወርቅ ይበልጣል፣ ከነጠረ ወርቅም ይበልጣል፤ ስጦታየም ከንጹህ ብር ይበልጣል፡፡
\v 20 እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፣ ወደ ፍትህ በሚወስድ ጎዳና እጓዛለሁ፣
\v 21 ስለዚህ ለሚወዱኝ ሀብትን እሰጣቸዋለሁ፣ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ፡፡
\s5
\v 22 እግዚአብሄር ከመጀመርያ ፈጠረኝ፣ በቀድሞ ዘመን የስራው መጀመርያ ነኝ፡፡
\v 23 ከመጀመርያ፣ ምድር ከመፈጠሯ በፊት፣ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ተሾምሁ፡፡
\s5
\v 24 ውቅያኖሶች ሳይኖሩ፣ የውኃ ምንጮች ሳይፈልቁ በፊት፣ እኔ ተወልጄ ነበር፣
\v 25 ተራሮች ገና ሳይመሰረቱ፣ ከኮረብቶችም በፊት፣ እኔ ተወለድሁ፡፡
\s5
\v 26 እግዚአብሔር ምድርንና ሜዳዎቿን፣ የመጀመርያውን የዓለም አፈር እንኳ ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ፡፡
\v 27 እርሱ ሰማያትን ሲመሰርት፣ በውቅያኖስ ገጽ የአድማስን ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
\s5
\v 28 እርሱ በላይ ያሉትን ደመናት ባጸና ጊዜ፣ የውቅያኖስን ምንጮች በመሰረተ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
\v 29 ውሆች የእርሱን ትዕዛዝ አልፈው እንዳያጥለቀልቁ እርሱ ለባህር ድንበርን ባበጀለት ጊዜ፣ የምድርም መሰረት የት መሆን እንዳለበት በወሰነበት ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡
\s5
\v 30 እኔ ዋና ሰራተኛ ሆኜ በአጠገቡ ነበርሁ፣ እኔ ዕለት በዕለት እርሱን ደስ አሰኘው ነበርሁ፣ ሁልጊዜ በፊቱ ደስ ይለኝ ነበር፡፡
\v 31 የእርሱ በሆነው በመላው ዓለም ደስ ይለኝ ነበር፣ ደስታየም በሰው ልጅ ነበር፡፡
\s5
\v 32 አሁንም፣ ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ሁሉ ደስተኞች ይሆናሉና፡፡
\v 33 ምክሬን አድምጡ፣ ጥበበኞችም ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት፡፡
\v 34 እኔን የሚያደምጠኝ ደስተኛ ይሆናል፣ ዕለት በዕለት በመግቢያየ የሚተጋ፣ በቤቴም በሮች አጠገብ የሚጠብቀኝ፡፡
\s5
\v 35 እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፣ የእግዚአብሔርንም ሞገስ ያገኛል፡፡
\v 36 እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጎዳል፤ እኔን የሚጠሉኝ በሙሉ ሞትን ይወድዳሉ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ጥበብ ቤቷን ሰራች፤ ሰባት ምሰሶዎችን ከድንጋይ ጠርባ አቆመች፡፡
\v 2 ለእራት እንስሳዎቿን አረደች፤ የወይን ጠጇንም ደባለቀች፤ ማዕዷንም አዘጋጀች፡፡
\s5
\v 3 በሴት ሰራተኞቿ በኩል የጥሪ ወረቀት ላከች፣ ከከተማይቱ ከፍተኛ ቦታ ተጣራች፡፡
\v 4 እርሷም አእምሮ ለጎደላቸው “እውቀትን ያላገኙ ሁሉ ወደዚህ ይምጡ! ” አለች፡፡
\s5
\v 5 “ኑ፣ ምግቤን ተመገቡ፣ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጄን ጠጡ፡፡
\v 6 የአላዋቂነት መንገዳችሁን ወደኋላ በመተው በሕይወት ኑሩ፤ በማስተዋል መንገድ ተመላለሱ፡፡
\s5
\v 7 ፌዘኛን የሚገስጽ ሰው በራሱ ላይ ስድብን ያመጣል፣ ክፉን ሰው የሚገስጽ ደግሞ ይጎዳል፡፡
\v 8 ፌዘኛን ሰው አትገስጽ፣ ይጠላሃል፤ ጥበበኛን ሰው ገስጽ፣ ይወድድሃል፡፡
\v 9 ለጥበበኛ ሰው ትምህርትን ስጠው፣ ይበልጥ ጥበበኛ ይሆናል፤ ጻድቅን ሰው አስተምረው፣ እርሱም ይበልጥ እውቀትን ይጨምራል፡፡
\s5
\v 10 የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፡፡
\v 11 በእኔ ዘመንህ ይበዛልና፣ በሕይወትህም ዓመታት ይጨመሩልሃል፡፡
\v 12 ጥበበኛ ከሆንህ፣ ጥበበኛ የምትሆነው ለራስህ ነው፣ ነገር ግን የምታፌዝ ከሆንህ፣ ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከመዋለህ፡፡”
\s5
\v 13 ሞኝ ሴት ለፍላፊ ናት፣ ትምህርት የሌላትና ምንም የማታውቅ ናት፡፡
\v 14 በከተማዋ ከፍተኛ ስፍራ በቤቷ በር በመቀመጫ ላይ ትቀመጣለች፡፡
\v 15 እርሷ በመንገድ የሚያልፉትን፣ በመንገዳቸውም ቀጥ ብለው የሚሄዱትን ሰዎች ትጣራለች፡፡
\s5
\v 16 እርሷም አእምሮ ለጎደላቸው “እነዚህ ትምህርት የሌላቸው ሰዎች ወደዚህ ይምጡ! ” አለች፡፡
\v 17 “የተሰረቀ ውኃ ጣፋጭ ነው፣ በምስጢር የበሉት እንጀራም አስደሳች ነው፡፡”
\v 18 ነገር ግን እርሱ ሙታን በዚያ እንዳሉ አያወቅም፣ ተጋባዦቿ በሲዖል ጥልቀት ውስጥ እንዳሉ አያውቅም፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 የሰሎሞን ምሳሌዎች፡፡ ጥበበኛ ልጅ አባቱን ደስ ያሰኛል፣ ሞኝ ልጅ ግን ለእናቱ ሃዘንን ያመጣል፡፡
\v 2 በክፋት የተከማቸ ሃብት ምንም ጥቅም የለውም፣ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል፡፡
\v 3 እግዚአብሔር በጽድቅ የሚሄዱትን እንዲራቡ አያደርግም፣ የክፉዎችን ምኞት ግን ያከሽፋል፡፡
\s5
\v 4 የሰነፍ እጅ ድሃ ታደርጋለች፣ የትጉ እጅ ግን ብልጽግናን ታመጣለች፡፡
\v 5 ጥበበኛ ልጅ በበጋ ምርትን ይሰበስባል፣ በመከር መተኛት ግን ለእርሱ ውርደት ነው፡፡
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር ስጦታ በጻድቃን ራስ ላይ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል፡፡
\v 7 ጻድቅ ሰው ስለ እርሱ ስናስብ ደስ እንድንሰኝ ያደርገናል፣ የክፉ ሰው ስም ግን ይጠፋል፡፡
\s5
\v 8 አዋቂዎች ትእዛዛትን ይቀበላሉ፣ ለፍላፊ ሞኝ ግን ወደ ጥፋት ይሄዳል፡፡
\v 9 በሀቀኝነት የሚሄድ ሰው ተማምኖ ይሄዳል፣ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይጋለጣል፡፡
\s5
\v 10 በዓይኑ የሚጠቅስ መከራን ያመጣል፣ ለፍላፊ ሞኝ ግን ወደ ይጠፋል፡፡
\v 11 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋትን ይደብቃል፡፡
\s5
\v 12 ጥላቻ ጠብን ያነሳሳል፣ ፍቅር ግን ስህተትን ሁሉ ይሸፍናል፡፡
\v 13 በአስተዋይ ሰው ከንፈር ጥበብ ትገኛለች፣ በትር ግን አእምሮ ለጎደለው ሰው ጀርባ ነው፡፡
\s5
\v 14 ጥበበኛ ሰዎች እውቀትን ይሰበስባሉ፣ የሞኝ አፍ ግን ጥፋትን ያመጣል፡፡
\v 15 የባለጠጋ ሰው ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው፤ የድሆች ድህነት ግን መጥፊያቸው ነው፡፡
\s5
\v 16 የጻድቅ ሰው ደመወዝ ወደ ሕይወት ይመራል፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ወደ ኃጢአት ይመራቸዋል፡፡
\v 17 እርምትን ለሚከተል ሰው ወደ ሕይወት የምትመራ ጎዳና አለች፣ ተግሳጽን የማይቀበል ሰው ግን ይስታል፡፡
\s5
\v 18 ጥላቻን የሚደብቅ ሰው ሐሰተኛ ከንፈሮች አሉት፣ ሐሜትን የሚያስፋፋ ሞኝ ነው፡፡
\v 19 በብዙ ቃላቶች ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፣ ለሚናገረው ነገር ጥንቃቄ የሚደርግ ሰው ግን ጥበበኛ ነው፡፡
\s5
\v 20 የጻድቅ ሰው ምላስ የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ዋጋ የለውም፡፡
\v 21 የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ያንጻሉ፣ ሞኞች ግን ባለማማዛዘናቸው ምክንያት ይሞታሉ፡፡
\s5
\v 22 የእግዚአብሔር መልካም ስጦታዎች ሃብትን ያመጣሉ፣ መከራንም አያክልበትም፡፡
\v 23 ክፋት የሞኞች ጨዋታ ነው፣ ጥበብ ግን ለአስተዋይ ሰው ደስታ ነው፡፡
\s5
\v 24 የክፉ ሰው ፍርሃት ድንገት ይደርስበታል፣ የጻድቅ ሰው ምኞት ግን ይፈጸማል፡፡
\v 25 ክፉ ሰዎች እንደሚያልፍ አውሎ ነፋስ ናቸው፣ ከዚያም በኋላ አይገኙም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን ለዘላለም የሚኖሩ መሰረት ናቸው፡፡
\s5
\v 26 በጥርስ ላይ ያለ ሆምጣጤ፣ በዓይንም ውስጥ ያለ ጢስ እንደሚጎዳ፣ ሰነፍ ሰው ለሚልኩት እንዲሁ ነው፡፡
\v 27 እግዚአብሔርን መፍራት ዕድሜን ያረዝማል፣ የክፉዎች ዕድሜ ግን አጭር ይሆናል፡፡
\s5
\v 28 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ተስፋ ደስታቸው ነው፣ የክፉዎች ዕድሜ ግን አጭር ይሆናል፡፡
\v 29 የእግዚአብሔር መንገድ ሃቀኞችን ይጠብቃቸዋል፣ ለክፉዎች ግን መጥፊያቸው ነው፡፡
\v 30 ጽድቅን የሚያደርጉ ፈጽሞ አይወድቁም፣ ክፉዎች ግን በምድሪቱ አይቀሩም፡፡
\s5
\v 31 ከጻድቃን አፍ የጥበብ ፍሬ ይወጣል፣ ጠማማ ምላስ ግን ይቆረጣል፡፡
\v 32 የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢ የሆነውን ነገር ያውቃሉ፣ የክፉዎች አፍ ግን የሚያውቀው ጠማማ የሆነውን ነገር ብቻ ነው፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 እግዚአብሔር ትክክለኛ ያልሆነ ሚዛን ይጠላል፣ በትክክለኛ ሚዝን ግን ሚዛን ደስ ይለዋል፡፡
\v 2 ትዕቢት ከመጣች ውርደት ትመጣለች፣ ከትህትና ጋር ግን ጥበብ ትመጣለች፡፡
\s5
\v 3 የቅኖች ሀቀኝነታቸው ይመራቸዋል፣ የከዳተኞች ጠማማ መንገድ ግን ራሳቸውን ያጠፋቸዋል፡፡
\v 4 በቁጣ ቀን ሀብት ዋጋ ቢስ ነው፣ ጽድቅ ግን ከሞት ታድንሃለች፡፡
\s5
\v 5 ነቀፋ የሌለበት ሰው ጽድቅ መንገዱን ያቀናለተል፣ ክፉዎች ግን በክፋታቸው ይወድቃሉ፡፡
\v 6 እግዚብሔርን ደስ የሚያሰኙ ሰዎች ጽድቃቸው ትታደጋቸዋለች፣ ከዳተኞች ግን በክፉ ምኞታቸው ይጠመዳሉ፡፡
\s5
\v 7 ክፉ ሰው ሲሞት ተስፋው ይጠፋል፣ በብርታቱ የተመካበት ተስፋም ከንቱ ይሆናል፡፡
\v 8 ጽድቅን የሚያደርግ ከመከራ ይድናል፣ ይልቁንም መከራው በክፉው ይመጣበታል፡፡
\s5
\v 9 አምላክ የለሽ ሰው በአንደበቱ ጎረቤቱን ያጠፋል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን በእወቀት ይድናሉ፡፡
\v 10 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ሲበለጽጉ ከተማ ትደሰታለች፤ ክፉዎች ሲጠፉ የደስታ ጩኸት ይሆናል፡፡
\v 11 እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኙ ሰዎች መልካም ስጦታ ከተማ ታላቅ ትሆናለች፤ በክፉዎች አንደበት ግን ከተማ ትፈርሳለች፡፡
\s5
\v 12 ጓደኛውን የሚንቅ ሰው አእምሮ የጎደለው ነው፣ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል፡፡
\v 13 ለሐሜት የሚሄድ ሰው ምስጢርን ይገልጣል፣ ታማኝ ሰው ግን ምስጢርን ይሰውራል፡፡
\s5
\v 14 በጥበብ አልባ አመራር ሕዝብ ይወድቃል፣ የመካሮች ብዛት ባለበት ግን ድል ይመጣል፡፡
\s5
\v 15 ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሚሆን መከራን ይቀበላል፣ በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ዋስ ለመሆን የሚጠላ ሰው ግን ይድናል፡፡
\v 16 ሞገስ ያላት ሴት ክብር ታገኛለች፣ ጨካኝ ሰዎች ግን ሀብትን ብቻ ያገኛሉ፡፡
\s5
\v 17 ደግ ሰው ራሱን ይጠቅማል፣ ጨካኝ ሰው ግን ራሱን ይጎዳል፡፡
\v 18 ክፉ ሰው ደመወዙን ለማግኘት ይዋሻል፣ ጽድቅን የሚዘራ ግን የእውነትን ደመወዝ ይሰበስባል፡፡
\s5
\v 19 ጽድቅን የሚያደርግ ታማኝ ሰው በሕይወት ይኖራል፣ ክፋትን የሚያደርግ ግን ይሞታል፡፡
\v 20 እግዚአብሔር ጠማማ ልብ ያላቸውን ይጠላል፣ በመንገዳቸው ነቀፋ በሌለባቸው ሰዎች ግን ደስ ይሰኛል፡፡
\s5
\v 21 ክፉ ሰዎች ሳይቀጡ እንደማይቀሩ ይህን እርግጠኛ ሁን፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ዘሮች ግን ይድናሉ፡፡
\v 22 በአሳማ አፍንጫ እንደተሰካ የወርቅ ቀለበት፣ ማስተዋል የሌላትም ቆንጆ ሴት እንዲሁ ናት፡፡
\s5
\v 23 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ምኞት መልካም ውጤት ያመጣል፣ ክፉ ሰዎች ግን ተስፋ ሊያደርጉት የሚችሉት መቅሰፍት ብቻ ነው፡፡
\v 24 ዘርን የሚዘራ አንድ ሰው አለ፣ እርሱ ይበልጥ ይሰበስባል፤ ሌላ ደግሞ የማይዘራ አለ፣ እርሱ ይደኸያል፡፡
\s5
\v 25 ለጋስ ሰው ይበለጽጋል፣ ለሌሎች ውኃ የሚሰጥ ደግሞ ለራሱም ውኃ ያገኛል፡፡
\v 26 እህል ለመሸጥ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰው ሕዝብ ይረግመዋል፣ በሚሸጠው ግን መልካም ስጦታዎችን በራሱ ላይ እንደ አክሊል ይጎናጸፋል፡፡
\s5
\v 27 መልካምን ነገር ተግቶ የሚፈልግ ሞገስን ይፈልጋል፣ ክፉን የሚፈልግ ግን ክፉ በራሱ ላይ ይመጣበታል፡፡
\v 28 በባለጠግነታቸው ላይ የሚታመኑ ሰዎች ይወድቃሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ፡፡
\s5
\v 29 በቤተሰቡ ላይ ሁከትን የሚያመጣ ሰው ነፋስን ይወርሳል፣ ሞኝም ሰው በልቡ ጥበበኛ ለሆነው ሰው አገልጋይ ይሆናል፡፡
\s5
\v 30 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች እንደ ሕይወት ዛፍ ይሆናሉ፣ ሁከት ግን ሕይወትን ያጠፋል፡፡
\v 31 ጽድቅን የሚደርጉ ሰዎች ለሰሩት ስራ የሚገባቸውን የሚቀበሉ ከሆነ፣ ይልቁንስ ክፉዎችና ኃጢአተኞች እንዴት አይቀበሉ!
\s5
\c 12
\p
\v 1 ተግሳጽን የሚወድ እውቀትን ይወዳል፣ እርምትን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው፡፡
\v 2 እግዚአብሔር ለመልካም ሰው ሞገስን ይሰጠዋል፣ ክፉ እቅድ ለሚያወጣ ሰው ግን ይፈርድበታል፡፡
\s5
\v 3 ሰው በክፋት ላይ ተመስርቶ ጸንቶ ሊቆም አይችልም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን ከመሰረታቸው አይነቀሉም፡፡
\v 4 መልካም ሴት ለበሏ ዘውድ ናት፣ አሳፋሪ ሴት ግን አጥንቱን እንደሚያበሰብስ በሽታ ናት፡፡
\s5
\v 5 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች እቅድ ጽድቅ ነው፣ የክፉዎች ምክር ግን ተንኮል ነው፡፡
\v 6 የክፉ ሰዎች ቃል ድንገት ለመግደል አድፍጦ ያደባል፣ የቅኖች ቃል ግን ይታደጋቸዋል፡፡
\s5
\v 7 ክፉ ሰዎች ይገለበጣሉ፣ አይገኙምም፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ቤት ግን ጸንቶ ይቆማል፡፡
\v 8 ሰው በጥበቡ ብዛት ይመሰገናል፣ ጠማማ ምርጫዎች የሚያደርግ ግን ይናቃል፡፡
\s5
\v 9 የሚበላው ምግብ ሳይኖረው ከሚኩራራ ሰው ይልቅ ራሱን ዝቅ አድርጎ አገልጋይ መሆን ይሻላል፡፡
\v 10 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው እንስሳቱ ስለሚያስፈልጋቸው ነገር ግድ ይለዋል፣ ክፉ ሰው ግን ርህራሄ አደረገ ቢባል እንኳ ስራው ጭካኔ የተሞላ ነው፡፡
\s5
\v 11 መሬቱን በሚገባ የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፣ ዋጋ ቢስ ስራዎችን የሚያሳድድ ሰው ግን አእምሮ አልባ ነው፡፡
\v 12 ኃጢአተኞች ክፉ ሰዎች ከሌሎች የሰረቁትን ይመኛሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ፍሬ ግን ከገዛ ራሳቸው ይመጣል፡፡
\s5
\v 13 ክፉ ሰው በክፉ ንግግሩ ይጠመዳል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ግን ከመከራ ያመልጣሉ፡፡
\v 14 ሰው ከቃሎቹ ፍሬ የተነሳ መልካም ነገርን ይጠግባል፣ እንደ እጁ ስራም ዋጋውን ይቀበላል፡፡
\s5
\v 15 የሞኝ መንገድ ለራሱ ትክክል መስሎ ይታየዋል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ምክርን ይሰማል፡፡
\v 16 ሞኝ ቁጣውን በቶሎ ይገልጣል፣ ስድብን ንቆ የሚተው ግን አስተዋይ ነው፡፡
\s5
\v 17 እወነትን የሚናገር ትክክለኛውን ነገር ይናራል፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይናገራል፡፡
\v 18 የለፍላፊ ሰው ቃሎች እንደሚዋጋ ሰይፍ ነው፣ የጥበበኛ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል፡፡
\s5
\v 19 እውነተኛ ከንፈሮች ለዘላለም ይኖራሉ፣ ሀሰተኛ ከንፈር ግን ለቅጽበት ብቻ ነው፡፡
\v 20 ክፋትን ለማድረግ በሚያቅዱ ሰዎች ልብ ውስጥ ተንኮል አለ፣ ሰላምን ለሚመክሩ ሰዎች ግን ደስታ ይመጣል፡፡
\s5
\v 21 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች በሽታ አያገኛቸውም፣ ክፉ ሰዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው፡፡
\v 22 እግዚአብሔር ሀሰተኛ ከንፈሮችን ይጠላል፣ በእውነተኛነት በሚኖሩ ሰዎች ግን ደስ ይለዋል፡፡
\s5
\v 23 አስተዋይ ሰው እወቀቱን ይሰውራል፣ የሞኞች ልብ ግን ከንቱነትን ያወራል፡፡
\v 24 የትጉ ሰዎች እጅ ይገዛል፣ ሰነፍ ሰዎች ግን ለጉልበት ስራተኝነት ታልፈው ይሰጣሉ፡፡
\s5
\v 25 በሰው ልብ ውስጥ የሚገኝ ጭንቀት ያዋርደዋል፣ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል፡፡
\v 26 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ለጓደኛው መንገድን ያሳያል፣ የክፉ መንገድ ግን ታስታቸዋለች፡፡
\s5
\v 27 ሰነፍ ሰዎች አድነው ያመጡትን እንስሳ እንኳ አይጠብሱም፣ ትጉ ሰው ግን የከበረ ሀብት ያገኛል፡፡
\v 28 በጽድቅ መንገድ የሚሄዱ ሰዎች ሕይወትን ያገኛሉ፣ በጎዳናዋም ሞት የለም፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 ጥበበኛ ልጅ የአባቱን ምክር ይሰማል፣ ፌዘኛ ግን ተግሳጽን አያዳምጥም፡፡
\v 2 ሰው ከአፉ ፍሬ መልካምን ነገር ይጠግባል፣ ጠማማ ሰው ግን ዓመጽን ይመኛል፡፡
\s5
\v 3 አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፣ ከንፈሮቹን ያለ ልክ የሚከፍት ግን ይጠፋል፡፡
\v 4 ሰነፍ ሰው ይመኛል ነገር ግን አንዳችም አያገኝም፣ የትጉ ሰው ምኞት ግን በሙላት ይረካል፡፡
\s5
\v 5 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ውሸትን ይጠላል፣ ክፉ ሰው ግን ራሱ ጥላቻን ይፈጥራል፣ አሳፋሪ ተግባርንም ይፈጽማል፡፡
\v 6 በመንገዳቸው ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን ጽድቅ ትጠብቃቸዋለች፣ ክፋት ግን ኃጢአተኞችን ትጥላቸዋለች፡፡
\s5
\v 7 ራሱን ባለጠጋ የሚያስመስል ሰው አለ፣ ነገር ግን አንዳች የለውም፣ ምንም እንደሌለው መስሎ የሚታይ ሰው ደግሞ አለ፣ ይሁን እንጂ እጅግ ባለጠጋ ነው፡፡
\v 8 ባለጠጋ ሰው ሀብቱን ለሕይወቱ ቤዛ አድርጎ ያቀርብ ይሆናል፣ ድሀ ግን እንዲህ ዓይነት ሥጋት በፍጹም የለበትም፡፡
\s5
\v 9 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ብርሃን ደምቆ ይበራል፣ የክፉዎች መብራት ግን ይጠፋል፡፡
\v 10 ትዕቢት ጠብን ብቻ ያስፋፋል፣ መልካም ምክርን ለሚያደምጡ ግን ጥበብ አለ፡፡
\s5
\v 11 ብዙ ከንቱነት ሲኖር ሀብት እየመነመነ ያልቃል፣ በእጁ እየሰራ ገንዘብ የሚያከማች ሰው ግን ገንዘቡ እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡
\v 12 ተስፋ ሲዘገይ ልብን ይሰብራል፣ የተሳካ ምኞት ግን የሕይወት ዛፍ ነው፡፡
\s5
\v 13 ትእዛዝን የሚንቅ በትእዛዝ ይቀጣል፣ ትእዛዝን የሚያከብር ግን ወሮታን ያገኛል፡፡
\v 14 የጥበበኛ ሰው ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው፣ ከሞት ወጥመድ እንድታመልጥ ያደርግሃል፡፡
\s5
\v 15 መልካም እውቀት ሞገስ ያስገኛል፣ የከዳተኛ ሰው መንገድ ግን አያልቅም፡፡
\v 16 ጥንቃቄ የተሞሉ ሰዎች ማንኛውንም ውሳኔ የሚያደርጉት በጥበብ ነው፣ ሞኝ ግን ከንቱነቱን ይገልጣል፡፡
\s5
\v 17 ክፉ መልእክተኛ መከራ ውስጥ ይገባል፣ ታማኝ መልእክተኛ ግን እርቅን ያመጣል፡፡
\v 18 ተግሳጽን የሚንቅ ድህነትና ኃፍረት ይመጣበታል፣ ከእርምት የሚማር ግን ክብር ወደ እርሱ ይመጣል፡፡
\s5
\v 19 ምኞት ሲፈጸም የውስጥ ፍላጎትን ደስ ያሰኛል፣ ሞኞች ግን ከክፋት መመለስን ይጠላሉ፡፡
\v 20 ከጥበበኞች ጋር ሂድ አንተም ጥበበኛ ትሆናለህ፣ የሞኞች ባልንጀራ ግን እጅግ ይጎዳል፡፡
\s5
\v 21 መቅሰፍት ኃጢአተኞችን ይከታተላቸዋል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን መልካምን ነገር ይቀበላሉ፡፡
\v 22 መልካም ሰው ለልጅ ልጆቹ የሚያወርሰውን ይተዋል፣ የኃጢአተኛ ሀብት ግን ጽድቅን ለሚያደርጉ ይከማቻል፡፡
\s5
\v 23 የድሆች እርሻ ያልታረሰም ቢሆን ብዙ ምግብ ሊያመርት ይችላል፣ ነገር ግን በፍትህ መጓደል ምክንያት ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡
\v 24 ልጁን የማይቀጣ ይጠላዋል፣ ልጁን የሚወድ ግን በጥንቃቄ ይቀጣዋል፡፡
\s5
\v 25 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ፍላጎቱን እስከሚያረካ ድረስ ጠግቦ ይበላል፣ የክፉዎች ሆድ ግን ሁልጊዜ እንደተራበ ነው፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 ጥበበኛ ሴት ቤቷን ትሰራለች፣ ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጇ ታፈርሰዋለች፡፡
\v 2 በጽድቅ የሚሄድ ሰው እግዚአብሔርን ይፈራል፣ በመንገዱ ታማኝ ያልሆነ ግን ይንቀዋል፡፡
\s5
\v 3 ከሞኝ አፍ የትዕቢት በትር ይወጣል፣ የጥበበኛ ከንፈሮች ግን ይጠብቋቸዋል፡፡
\v 4 ከብቶች በሌሉበት የመመገቢያ ገንዳ ባዶ ይሆናል፣ በበሬ ጉልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል፡፡
\s5
\v 5 እውነተኛ ምስክር አይዋሽም፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይለፈልፋል፡፡
\v 6 ፌዘኛ ጥበብን ይፈልጋል ሆኖም አያገኛትም፣ እውቀት ግን ወደ አስተዋይ ሰው በቀላሉ ትመጣለች፡፡
\s5
\v 7 ከሞኝ ሰው ራቅ፣ ከከንፈሮቹ እውቀትን አታገኝምና፡፡
\v 8 የጠንቃቃ ሰው ጥበብ መንገዱን ማስተዋል ነው፣ የሞኞች ከንቱነት ግን ማታለል ነው፡፡
\s5
\v 9 ሞኞች የኃጢአት መስዋዕት በሚቀርብበት ጊዜ ያፌዛሉ፣ በጻድቃን መካከል ግን ቸርነት ይገኛል፡፡
\v 10 ልብ የራሱን ምሬት ያውቃል፣ ደስታውንም ሌላ ሰው አይጋራውም፡፡
\s5
\v 11 የክፉ ሰዎች ቤት ይጠፋል፣ የጻድቃን ድንኳን ግን ይስፋፋል፡፡
\v 12 ለሰው ቅን የምትመስል መንገድ አለች፣ ፍጻሜዋ ግን ወደ ሞት ይመራል፡፡
\s5
\v 13 ልብ በሐዘን ውስጥ ሆኖ ሊስቅ ይችላል፣ የደስታም ፍጻሜ ሐዘን ሊሆን ይችላል፡፡
\v 14 ታማኝ ያልሆነ ሰው ለመንገዱ የሚገባውን ዋጋ ያገኛል፣ መልካም ሰው ግን የራሱ የሆነውን ያገኛል፡፡
\s5
\v 15 እውቀት አልባ ሰው ሁሉንም ነገር ያምናል፣ አስተዋይ ሰው ግን አካሄዱን ያስተውላል፡፡
\v 16 ጥበበኛ ሰው ይፈራል ከክፉም ይርቃል፣ ሞኝ ግን ራሱን ታምኖ ማስጠንቀቂያን ችላ ይላል፡፡
\s5
\v 17 ለቁጣ የሚቸኩል ሰው ከንቱ ነገሮችን ይፈጽማል፣ ክፋትን የሚያሴር ሰው ደግሞ ይጠላል፡፡
\v 18 እውቀት አልባ ሰዎች ሞኝነትን ይወርሳሉ፣ አስተዋይ ሰዎች ግን በእውቀት ይከበባሉ፡፡
\s5
\v 19 ክፉዎች በመልካም ሰዎች ፊት ይሰግዳሉ፣ ኃጢአተኞች ደግሞ በጻድቃን ደጅ ይሰግዳሉ፡፡
\v 20 ድሃ ሰው በራሱ ባልንጀሮችም ጭምር ይጠላል፣ ባለጠጋ ሰዎች ግን ብዙ ወዳጆች አሏቸው፡፡
\s5
\v 21 ለጎረቤቱ ንቀትን የሚያሳይ ኃጢአትን ያደርጋል፣ ለድሃ በጎነትን የሚያሳይ ግን ደስተኛ ነው፡፡
\v 22 ክፋትን የሚያሴሩ አይስቱምን? መልካምን ለማድረግ የሚያቅዱ ግን በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ይቀበላሉ፡፡
\s5
\v 23 በብዙ ድካም ትርፍ ይገኛል፣ ወሬ ግን ወደ ድህነት ይመራል፡፡
\v 24 የጥበበኞች ዘውድ ባለጠግነታቸው ነው፣ የሞኞች ሞኝነት ግን ተጨማሪ ከንቱነትን ያመጣባቸዋል፡፡
\s5
\v 25 እውነተኛ ምስክር ሕይወት ያድናል፣ ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸትን ይለፈልፋል፡፡
\s5
\v 26 ሰው እግዚአብሔርን ሲፈራ፣ በእርሱ ይታመናል፤ እነዚህ ነገሮች ደግሞ ለልጆቹ እንደ ብርቱ መጠጊያ ስፍራ ይሆኗቸዋል፡፡
\v 27 እግዚአብሔርን መፍራት የሕይወት ምንጭ ነው፣ ሰውን ከሞት ወጥመድ እንዲያመልጥ ያደርገዋል፡፡
\s5
\v 28 የንጉስ ክብር የሚገኘው ከሕዝቡ ብዛት ነው፣ ሕዝብ በሌለበት ግን ልዑል ይጠፋል፡፡
\v 29 ትዕግስተኛ ሰው ታላቅ ማስተዋል አለው፣ ለቁጣ የሚቸኩል ሰው ግን ሞኝነትን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡
\s5
\v 30 በሰላም የተሞላ ልብ ለሰውነት ሕይወት ነው፣ ቅናት ግን አጥንትን ያበሰብሳል፡፡
\v 31 ድሀን የሚያስጨንቅ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ ለድሀ ቸርነትን የሚያሳይ ግን ፈጣሪውን ያከብራል፡፡
\s5
\v 32 ክፉ ሰው በክፉ ስራው ይወድቃል፣ ጻድቅ ግን በሞት ጊዜ እንኳ መጠጊያ አለው፡፡
\v 33 ጥበብ በአስተዋይ ሰው ዘንድ ትኖራለች፣ በሞኞች መካከል እንኳ ራሷን ታሳውቃለች፡፡
\s5
\v 34 ጽድቅን ማድረግ ህዝብን ከፍ ከፍ ያደርጋል፣ ኃጢአት ግን ለማንኛውም ሕዝብ ውርደት ነው፡፡
\v 35 የንጉስ ሞገስ ተግተው በሚሰሩ አገልጋዮቹ ላይ ነው፣ ቁጣው ግን በአሳፋሪ አገልጋይ ላይ ነው፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 የለዘበ መልስ ቁጣን ይመልሳል፣ መጥፎ ቃል ግን ቁጣን ያስነሳል፡፡
\v 2 የጥበበኛ ሰዎች ምላስ እውቀትን የተላበሰ ነው፣ የሞኞች አፍ ግን ሞኝነትን ያንቆረቁራል፡፡
\s5
\v 3 የእግዚአብሔር ዓይኖች በሁሉም ስፍራ ናቸው፣ ክፉውንና መልካሙን ሁሉ ነቅተው ይመለከታሉ፡፡
\v 4 ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፣ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ይሰብራል፡፡
\s5
\v 5 ሞኝ የአባቱን ተግሳጽ ይንቃል፣ ከእርምት የሚማር ግን አስተዋይ ነው፡፡
\v 6 ጽድቅን በሚያደርጉ ሰዎች ቤት ብዙ ሀብት አለ፣ ክፉ ሰዎች የሚያገኙት ገቢ ግን መከራ ያመጣባቸዋል፡፡
\s5
\v 7 የጥበበኛ ሰዎች ከንፈሮች እውቀትን ያስፋፋሉ፣ የሞኞች ልብ ግን እንዲህ አይደለም፡፡
\v 8 እግዚአብሔር የክፉዎችን መስዋዕት ይጠላል፣ የቅኖች ጸሎት ግን ደስ ያሰኘዋል፡፡
\s5
\v 9 እግዚአብሔር የክፉዎችን መንገድ ይጠላል፣ ጽድቅን የሚከታተለውን ግን ይወደዋል፡፡
\v 10 ከመንገድ የሚወጣ ሰው ከባድ ቅጣት ይጠብቀዋል፣ እርምትን የሚጠላም ይሞታል፡፡
\s5
\v 11 ሲኦልና ጥፋት በእግዚአብሔር ፊት የተገለጡ ናቸው፤ የሰው ልጆች ልብማ ምንኛ የተገለጠ ይሆን?
\v 12 ፌዘኛ እርምትን ይንቃል፤ ወደ ጥበበኛም አይሄድም፡፡
\s5
\v 13 ደስተኛ ልብ ፊትን ያፈካል፣ የልብ ሐዘን ግን መንፈስን ይሰብራል፡፡
\v 14 የአስተዋይ ልብ እውቀትን ይፈልጋል፣ የሞኞች አፍ ግን ከንቱነትን ይመገባል፡፡
\s5
\v 15 የተጨቆኑ ሰዎች ቀናት በሙሉ አሰቃቂ ናቸው፣ ደስተኛ ልብ ግን የማይቋረጥ ግብዣ አለው፡፡
\v 16 እግዚአብሔርን ከመፍራት ጋር ያለ ጥቂት ነገር ከሁከት ጋር ካለ ትልቅ ሃብት ይሻላል፡፡
\s5
\v 17 ፍቅር ባለበት የአትክልት ምግብ መብላት ጥላቻ ባለበት የሰባ ጥጃ ከመብላት ይሻላል፡
\v 18 ቁጡ ሰው ጭቅጭቅን ያነሳሳል፣ ለቁጣ የዘገየ ሰው ግን ጠብን ጸጥ ያሰኛል፡፡
\s5
\v 19 የታካች ሰው መንገድ በእሾህ እንደ ታጠረ ስፍራ ነው፣ የቅን መንገድ ግን በሚገባ የተገነባ አውራ ጎዳና ነው፡፡
\v 20 ጥበበኛ ልጅ ለአባቱ ደስታን ያመጣለታል፣ ሞኝ ሰው ግን እናቱን ይንቃል፡፡
\s5
\v 21 ከንቱ ነገር አእምሮ ለጎደለው ሰው ደስ ያሰኛል፣ አስተዋይ ሰው ግን በቅን መንገድ ይሄዳል፡፡
\v 22 ምክር በሌለበት እቅድ ይበላሻል፣ በአማካሪዎች ብዛት ግን ይከናወናል፡፡
\s5
\v 23 ሰው ተገቢ የሆነ መልስ ሲሰጥ ደስታን ያገኛል፤ የጊዜው ቃል ምንኛ መልካም ነው!
\v 24 የሕይወት መንገድ አስተዋይ ሰዎችን ወደ ላይ ይመራቸዋል፣ በታች ካለው ከሲኦል ያመልጥ ዘንድ፡፡
\s5
\v 25 እግዚአብሔር የትዕቢተኛውን ውርስ ያፈራርሳል፣ የመበለቲቱን ንብረት ግን ይጠብቃል፡፡
\v 26 እግዚአብሔር የክፉ ሰዎችን ሐሳብ ይጠላል፣ የርኅራኄ ቃሎች ግን ንጹሐን ናቸው፡፡
\s5
\v 27 ዘራፊ ለቤተሰቡ መከራን ያመጣል፣ ጉቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል፡፡
\v 28 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ልብ መልስ ከመስጠቱ በፊት አጥብቆ ያስባል፣ የክፉ ሰዎች አፍ ግን ክፋትን ሁሉ ያጎርፋል፡፡
\s5
\v 29 እግዚአብሔር ከክፉ ሰዎች እጅግ ሩቅ ነው፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎችን ጸሎት ግን ይሰማል፡፡
\v 30 የዓይን ብርሃን ለልብ ደስታን ያመጣል፣ መልካም ወሬ ደግሞ ለሰውነት ጤና ነው፡፡
\s5
\v 31 አንድ ሰው እንዴት መኖር እንዳለብህ እርምትን ሲሰጥህ ትኩረት ሰጥተህ የምትሰማ ከሆንህ፣ በጥበበኛ ሰዎች መካከል ትቆያለህ፡፡
\v 32 ተግሳጽን የማይቀበል ራሱን ይንቃል፣ እርምትን የሚያደምጥ ግን ማስተዋልን ያገኛል፡፡
\s5
\v 33 የእግዚአብሔር ፍርሃት ጥበብን ያስተምራል፣ ትህትናም ከክብር በፊት ትመጣለች፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 የልብ እቅድ የሰው ነው፣ መልስ ግን ከእግዚአብሔር አንደበት ይመጣል፡፡
\v 2 የአንድ ሰው መንገዶች ሁሉ ለእርሱ ንጹህ ሆኖ ይታየዋል፣ እግዚአብሔር ግን መንፈስን ይመዝናል፡፡
\s5
\v 3 ስራህን ለእግዚአብሔር አስረክብ፣ እቅድህም ይሳካልሃል፡፡
\v 4 እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ለራሱ ዓላማ ፈጠረ፣ ሃጢአተኛውንም እንኳ ለክፉ ቀን፡፡
\s5
\v 5 እግዚአብሔር እምቢተኛ ልብ ያለውን ሁሉ ይጠላል፣ ተባብረው ቢቆሙም ከቅጣት አያመልጡም፡፡
\v 6 በኪዳን በተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ኃጢአት ስርየት ያገኛል፣ እግዚአብሔርን በመፍራትም ሰዎች ከክፋት ይርቃሉ፡፡
\s5
\v 7 የሰው መንገዶቹ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙ ሲሆኑ፣ እግዚአብሔር የዚያን ሰው ጠላቶች እንኳ ከእርሱ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡
\v 8 ፍትህ በጎደለው መንገድ ከተገኘ በርካታ ገቢ ይልቅ፣ በጽድቅ የተገኘ ጥቂት ገቢ ይሻላል፡፡
\s5
\v 9 ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፣ እግዚአብሔር ግን እርምጃውን ያቀናለታል፡፡
\v 10 ውሳኔ በንጉስ ከንፈሮች ላይ አለ፣ በፍርድም ጊዜ አፉ በማታለል አይናገርም፡፡
\s5
\v 11 እውነተኛ ሚዛን ከእግዚአብሔር ይመጣል፤ በከረጢትም ውስጥ ያሉት መመዘኛዎች ሁሉ የእርሱ ስራዎች ናቸው፡፡
\v 12 ነገስታት ክፋትን ሲሰሩ፣ እርሱ አጸያፊ ነገር ነው፣ ዙፋን የሚጸናው ጽድቅን በማድረግ ነውና፡፡
\s5
\v 13 ንጉስ እውነትን በሚናገሩ ከንፈሮች ደስ ይለዋል፣ በግልጽነት የሚናገረውንም ሰው ይወደዋል፡፡
\v 14 የንጉስ ቁጣ የሞት መልእክተኛ ነው፣ ጥበበኛ ሰው ግን የንጉሱን ቁጣ ያበርዳል፡፡
\s5
\v 15 የንጉስ ፊት ሲያበራ ሕይወት አለ፣ መልካም ፈቃዱም የጸደይን ዝናብ እንደሚያመጣ ደመና ነው፡፡
\v 16 ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት ምንኛ ይበልጣል፡፡ ከብርም ይልቅ ማስተዋል ይመረጣል፡፡
\s5
\v 17 የጻድቃን መንገድ ከክፋት ትርቃለች፤ ሕይወቱን የሚጠብቅም መንገዱን ይጠብቃል፡፡
\v 18 ትዕቢት ከጥፋት በፊት ትመጣለች፣ ኩሩ መንፈስም ከውድቀት በፊት፡፡
\s5
\v 19 ከትዕቢተኞች ጋር ዝርፊያን ከመካፈል ይልቅ ከድሆች ጋር ራስን ዝቅ ማድረግ ይሻላል፡፡
\v 20 የተማሩትን የሚያሰላስሉ ሰዎች መልካምን ነገር ያገኛሉ፣ በእግዚአብሔር የሚታመኑም ደስተኛ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 21 በልቡ ጥበበኛ የሆነ ሰው አስተዋይ ይባላል፣ ጣፋጭ ንግግርም የማስተማር ችሎታን ያዳብራል፡፡
\v 22 ገንዘብ ላደረገው ማስተዋል የሕይወት ምንጭ ነው፣ የሞኞች ቅጣት ግን ሞኝነታቸው ነው፡፡
\s5
\v 23 የጥበበኛ ሰው ልብ ለአፉ ትምህርትን ይሰጠዋል፣ ለከንፈሮቹም ትምህርትን ይጨምራል፡፡
\v 24 ደስ የሚያሰኙ ቃላት የማር ወለላ ናቸው፣ ለነፍስ የሚጣፍጡ አጥንትንም የሚፈውሱ ናቸው፡፡
\s5
\v 25 ለሰው ትክክል የሚመስል መንገድ አለ፣ ፍጻሜው ግን ወደ ሞት የሚወስድ ነው፡፡
\v 26 የሰራተኛ ረሃብ ለእርሱ ይሰራል፤ ረሃቡም ያነሳሳዋል፡፡
\s5
\v 27 የማይረባ ሰው ክፋትን ይቆፍራል፣ ንግግሩም እንደሚያቃጥል እሳት ነው፡፡
\v 28 ጠማማ ሰው ጥልን ያነሳሳል፣ ሐሜትም የቅርብ ወዳጆችን ያለያያል፡፡
\s5
\v 29 በጥባጭ ሰው ጎረቤቱን ይዋሻል፣ መልካም ወዳልሆነ መንገድም ይመራዋል፡፡
\v 30 በዓይኑ የሚጠቅስ ሰው ጠማማ ነገሮችን ያስባል፤ ከንፈሮቻቸውን የሚነክሱም ክፋትን ይጎትታሉ፡፡
\s5
\v 31 ሽበት የክብር ዘውድ ነው፤ በጽድቅ መንገድ በመኖር ይገኛል፡፡
\v 32 ጦረኛ ከመሆን ይልቅ ትዕግስተኛ መሆን ይሻላል፣ መንፈሱን የሚገዛም ከተማን ከሚቆጣጠር ይልቅ ይበረታል፡፡
\s5
\v 33 እጣ በጉያ ይጣላል፣ ውሳኔው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 ጥል ባለበት ግብዛ ከሞላበት ቤት ይልቅ ሰላም ባለበት ደረቅ ቁራሽ ዳቦ ይሻላል፡፡
\v 2 ጥበበኛ ባርያ አስነዋሪ ስራ የሚሰራውን ልጅ ይገዛል፣ ከወንድማማቾችም መካከል እንደ አንዱ ውርስን ይካፈላል፡፡
\s5
\v 3 ማቅለጫ ለብር ነው እቶንም ለወርቅ ነው፣ እግዚአብሔር ግን ልብን ያነጥራል፡፡
\v 4 ክፋትን የሚያደርግ ሰው ክፋትን የሚናገሩ ሰዎች ምክር ይሰማል፤ ውሸታምም ክፉ ነገሮች የሚያወሩ ሰዎችን ያዳምጣል፡፡
\s5
\v 5 በድሃ የሚቀልድ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ በጥፋትም የሚደሰት ከቅጣት አያመልጥም፡፡
\v 6 የልጅ ልጆች ለሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፣ ወላጆችም ለልጆቻቸው ክብር ናቸው፡፡
\s5
\v 7 መልካም ንግግር ለሞኝ ሰው አይስማማውም፤ ውሸታም ከንፈሮችም ለንጉሳውያን አይመቹም፡፡
\v 8 ጉቦ ለሰጪው እንደ አስማት ድንጋይ ነው፤ በሄደበት ስፍራ ሁሉ ስኬትን ያገኛል፡፡
\s5
\v 9 በደልን የሚሸፍን ፍቅርን ይፈልጋል፣ ነገርን የሚደጋግም ግን የቅርብ ወዳጆችን ይለያያል፡፡
\v 10 መቶ ግርፋት ወደ ሞኝ ጠልቆ ከሚገባ ይልቅ ተግሳጽ ወደ አስተዋይ ሰው ጠልቆ ይገባል፡፡
\s5
\v 11 ክፉ ሰው አመጽን ይፈልጋል፣ ጨካኝ መልዕክተኛም ወደ እርሱ ይላክበታል፡፡
\v 12 ሞኝን በሞኝነቱ ከመገናኘት ይልቅ ግልገሎቿ የተነጠቀችን ድብ መገናኘት ይሻላል፡፡
\s5
\v 13 አንድ ሰው በበጎ ፈንታ ክፋትን ሲመልስ፣ ክፋት ከቤቱ ፈጽሞ አይርቅም፡፡
\v 14 የጠብ መጀመርያ በሁሉም ስፍራ ውኃ እንደሚለቅ ሰው ነው፣ ስለዚህ ከመበርታቱ በፊት ከግጭት ራቅ፡፡
\s5
\v 15 ክፉ ሰዎችን ነጻ የሚለቅም ሆነ ጽድቅን የሚያደርጉትን ደግሞ የሚኮንን ማንኛውም ሰው፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠሉ ናቸው፡፡
\v 16 ሞኝ ጥበብን ለመማር የማይችል ሆኖ ሳለ፣ ጥበብን ለመማር ለምን ገንዘብ ይከፍላል?
\s5
\v 17 ጓደኛ በዘመኑ ሁሉ ወዳጅ ነው፣ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል፡፡
\v 18 አእምሮ የጎደለው ሰው ቃል በመግባት ግዴታ ውስጥ ይገባል፣ ለጎረቤቱም ብድር ዋስ ይሆናል፡፡
\s5
\v 19 ጠብ የሚወድ ኃጢአትን ይወዳል፤ መግቢያ በሩን እጅግ ከፍ አድርጎ የሚሰራ አጥንቶች እንዲሰበሩ ያደርጋል፡፡
\v 20 ጠማማ ልብ ያለው ሰው አንዳችም መልካም ነገር አያገኝም፤ ጠማማ ምላስ ያለውም ወደ መከራ ይወድቃል፡፡
\s5
\v 21 ሞኝን የወለደ ሐዘንን ወደራሱ ያመጣል፣ የሞኝም አባት ደስታን አያገኝም፡፡
\v 22 ደስተኛ ልብ ጥሩ መድሃኒት ነው፣ የተሰበረ መንፈስ ግን አጥንትን ያደርቃል፡፡
\s5
\v 23 ክፉ ሰው የፍትህን መንገድ ለማጣመም በሚስጥር ጉቦን ይቀበላል፡፡
\v 24 አስተዋይ ሰው ፊቱን ወደ ጥበብ ያዘነብላል፣ የሞኝ አይኖች ግን ወደ ምድር ዳርቻ ያዘነብላሉ፡፡
\s5
\v 25 ሞኝ ልጅ ለአባቱ ሐዘን ነው፣ ለወለደችውም እናቱ ምሬትን ያመጣል፡፡
\v 26 ጽድቅ የሚያደርግን ሰው መቅጣት በፍጹም መልካም አይደለም፤ በሐቀኝነት የሚሄዱትን የተከበሩ ሰዎችን መግረፍም መልካም አይደለም፡፡
\s5
\v 27 እውቀት ያለው ሰው ጥቂት ቃላትን ይናገራል፣ አስተዋይ ሰውም ለቁጣ የዘገየ ነው፡፡
\v 28 ሞኝ እንኳ ዝም ሲል ጥበበኛ እንደሆነ ይታሰባል፤ አፉንም ዘግቶ ዝም ሲል፣ እንደ ምሁር ይቆጠራል፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ራሱን ከሰው የሚለይ የራሱን ምኞት ይፈልጋል፣ ትክክለኛውንም ፍርድ ሁሉ ይቃወማል፡፡
\v 2 ሞኝ ሰው በማስተዋል ደስታን አያገኝም፣ በራሱ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር በመግለጥ እንጂ፡፡
\s5
\v 3 ክፉ ሰው ሲመጣ፣ ንቀት ከእፍረትና ከስድብ ጋር አብረውት ይመጣሉ፡፡
\v 4 ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሃ ናቸው፤ የጥበብ ምንጭም የሚፈስ ወንዝ ነው፡፡
\s5
\v 5 ለክፉው ማድላት፣ ጽድቅን ለሚያደርጉም ፍትህን ማጉደል መልካም አይደለም፡፡
\v 6 የሞኝ ከንፈሮች ጥልን ያመጡበታል፣ አፉም በትርን ትጠራለች፡፡
\s5
\v 7 የሞኝ አፍ መጥፊያው ነው፣ በከንፈሮቹም ራሱን ወጥመድ ውስጥ ይጥላል፡፡
\v 8 የሐሜት ቃላት እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፣ ወደ ሰውነት ውስጣዊ ክፍሎች ጠልቀው ይገባሉ፡፡
\s5
\v 9 በስራው ችላ የሚልም ብዙውን የአጥፊ ሰው ወንድም ነው፡፡
\v 10 የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ይድናል፡፡
\s5
\v 11 የባለጸጋ ሐብት የእርሱ የተመሸገ ከተማ ነው፣ ሃሳቡም እንደ ረዥም ግንብ ነው፡፡
\v 12 ከውድቀቱ በፊት የሰው ልብ ትዕቢተኛ ይሆናል፣ ትህትና ግን ክብርን ቀድሞ ይመጣል፡፡
\s5
\v 13 ከማድመጡ በፊት የሚመልስ ሰው ሞኝነትና ዕፍረት ይሆንበታል፡፡
\v 14 የሰው መንፈስ ሕመምን ትታገሳለች፣ የተሰበረን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?
\s5
\v 15 የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፣ የጠቢብም ጆሮ ይፈልገዋል፡፡
\v 16 የሰው ስጦታ መንገዱን ትከፍትለታለች በተከበሩም ሰዎች ፊት ታቆመዋለች፡፡
\s5
\v 17 ወደ ፍርድ ቀድሞ በመምጣት ጉዳዩን የሚያሰማ ጻድቅ ይመስላል፣ ይህ ግን የሚሆነው ተቀናቃኙ መጥቶ እስከሚጠይቀው ድረስ ነው፡፡
\v 18 እጣ ማውጣት ክርክርን ያቆማል፣ ሃይለኛ ጠላቶችንም ትለያለች፡፡
\s5
\v 19 የተበደለ ወንድምን መርታት ጠንካራ ከተማን ከማሸነፍ ይልቅ በጣም የከበደ ነው፣ ጠብም እንደ ግንብ ብረት ነው፡፡
\v 20 የሰው ሆድ ከአፉ ፍሬ ይሞላል፤ በንፈሮቹም ምርት ይረካል፡፡
\s5
\v 21 ሞትና ሕይወት በምላስ ላይ ናቸው፣ የሚወዱትም ፍሬዋን ይበላሉ፡፡
\v 22 ሚስትን ያገኘ መልካምን ነገር አግኝቷል፣ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ሞገስን አግኝቷል፡፡
\s5
\v 23 ድሃ ሰው ምህረትን ይለምናል፣ ሃብታም ግን በማመናጨቅ ይመልሳል፡፡
\v 24 ብዙ ጓደኞች ያለው ሰው በእነርሱ አማካኝነት ወደ ጥፋት ይመጣል፣ ከወንድም የቀረበ ጓደኛ ግን አለ፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 በንግግሩ ጠማማ ከሆነና ከሞኝ ሰው ይልቅ በሃቀኝነት የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡
\v 2 ደግሞም ያለ እውቀት አንድን ነገር መመኘት መልካም አይደለም፣ በችኮላ የሚሮጥም መንገዱን ይስታል፡፡
\s5
\v 3 የሰው ጅልነት ሕይወቱን ያበላሸዋል፣ ልቡም በእግዚአብሔር ላይ ይቆጣል፡፡
\v 4 ሐብት ብዙ ጓደኞችን ይጨምራል፣ ድሃ ሰው ግን ከወዳጆቹ የተለየ ነው፡፡
\s5
\v 5 ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይታለፍም፣ ውሸትንም የሚያሰራጭ አያመልጥም፡፡
\v 6 ብዙዎች ከቸር ሰው ውለታን ይጠይቃሉ፣ ስጦታን ለሚሰጥም ሁሉ ጓደኛ ይሆነዋል፡፡
\s5
\v 7 ድሃ ሰው ወንድሞቹ ሁሉ ይጠሉታል፤ ከእርሱ ብዙ ርቀው የሚገኙ ጓደኞቹማ ምንኛ ይጠሉት! ወደ እነርሱ ይጣራል፣ እነርሱ ግን አይገኙም፡፡
\v 8 ጥበብን የሚያገኝ ሕይወቱን ይወዳል፤ ማስተዋልንም ገንዘቡ ያደረገ መልካም ነገር ያገኛል፡፡
\s5
\v 9 ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፣ ውሸትን የሚያሰራጭ ግን ይጠፋል፡፡
\v 10 ለሞኝ በቅንጦት መኖር አይገባውም፣ ባርያ መሳፍንትን ሲገዛ ደግሞ ምንኛ የከፋ ይሆን፡፡
\s5
\v 11 ጠቢብ አእምሮ ሰውን ታጋሽ ያደርገዋል፣ በደልንም መተው ክብር ይሆንለታል፡፡
\v 12 የንጉስ ቁጣ እንደ ጎረምሳ አንበሳ ግሳት ነው፣ በፊቱ ሞገስ ማግኘት ግን ሳር ላይ እንዳለ ጤዛ ነው፡፡
\s5
\v 13 ሞኝ ልጅ ለአባቱ መጥፊያ ነው፣ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ የውኃ ነጠብጣብ ናት፡፡
\v 14 ቤትና ሐብት ከወላጆች ይወረሳል፣ ጠንቃቃ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ናት፡፡
\s5
\v 15 ስንፍና ሰውን ወደ እንቅልፍ ይጥለዋል፣ ለመስራት የማይፈቅድ ግን ይራባል፡፡
\v 16 ትእዛዛትን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፣ ስለ መንገዶቹ የማያስብ ሰው ግን ይሞታል፡፡
\s5
\v 17 ለድሃ ቸር የሆነ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል፣ ለሰራውም ቸርነት መልሶ ይከፍለዋል፡፡
\v 18 ተስፋ ሳለ ልጅህን ስርዓት አስይዘው፣ ሞቱንም እየተመኘህ ዝም ብለህ አትየው፡፡
\s5
\v 19 ንዴቱን መቆጣጠር የማይችል ሰው ቅጣቱን ማግኘት አለበት፤ ብታድነውም ለሁለተኛ ጊዜ ማድረግህ አይቀርም፡፡
\v 20 ምክርን ስማ ተግሳጽንም ተቀበል፣ በሕይወትህ መጨረሻ ጥበበኛ እንድትሆን፡፡
\s5
\v 21 በሰው ልብ ብዙ እቅዶች አሉ፣ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው፡፡
\v 22 ሰው የሚመኘው ታማኝ ሆኖ መገኘት ነው፣ ድሃም ሰው ከውሸታም ይሻላል፡፡
\s5
\v 23 እግዚአብሔርን ማክበር ሰዎችን ወደ ሕይወት ይመራል፤ እንዲህ ያለውም ሰው ይረካል በመከራም አይጎዳም፡፡
\v 24 ሰነፍ ሰው እጁን በሳህን ውስጥ ያጠልቃል፤ ወደ አፉም እንኳ እንደገና መልሶ አያመጣውም፡፡
\s5
\v 25 ፌዘኛን ብትመታው፣ ያልተማረው ጠንቃቃ ይሆናል፤ አስተዋዩን ብታርመው እውቀትን ያገኛል፡፡
\s5
\v 26 ከአባቱ የሚሰርቅ እናቱንም የሚያሳድድ ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው፡፡
\v 27 ልጄ ሆይ፣ ተግሳጽን አልሰማ ብትል፣ ከእውቀት ቃሎች ትስታለህ፡፡
\s5
\v 28 ምግባረ ብልሹ ምስክር በፍትህ ላይ ያፌዛል፣ የክፉ ሰው አፍም በደልን ይውጣል፡፡
\v 29 ለፌዘኞች ፍርድ፣ ለሞኞች ጀርባም ጅራፍ ተዘጋጅቶላቸዋል፡፡
\s5
\c 20
\p
\v 1 ወይን ጠጅ ፌዘኛ፣ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በመጠጥ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም፡፡
\v 2 የንጉስ ቁጣ እንደሚያገሳ ደቦል አንበሳ ቁጣ ነው፤ የሚያስቆጣውም ሰው ሕይወቱን ይከፍላል፡፡
\s5
\v 3 ጥልን መራቅ ለማንም ሰው ቢሆን ክብር ነው፣ ሞኝ ሰው ግን ወደ ጭቅጭቅ ይገባል፡፡
\v 4 ሰነፍ ሰው በመከር ወቅት አያርስም፤ በምርት ጊዜ እህል ይለምናል ነገር ግን ምንም አያገኝም፡፡
\s5
\v 5 በሰው ልብ ውስጥ ያለ አሳብ እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፣ አስተዋይ ሰው ግን ከዚያ ቀድቶ ያወጣዋል፡፡
\v 6 ብዙ ሰው ታማኝ እንደሆነ ይናገራል፣ ታማኝ የሆነውን ግን ማን ሊያገኘው ይችላል?
\s5
\v 7 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው በሐቀኝነቱ ይራመዳል፣ ፍለጋውን የሚከተሉ ልጆቹም ደስተኞች ናቸው፡፡
\v 8 የዳኛን ተግባር በማከናወን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠ ንጉስ በፊቱ ያለውን ክፋት ሁሉ በዓይኖቹ አበጥሮ ይለያል፡፡
\s5
\v 9 “ልቤን በንጽህና ጠብቄያለሁ፤ ከኃጢአቴ ንጹህ ነኝ” ብሎ መናገር የሚችል ማን ነው?
\v 10 1የተለያዩ ሚዛኖችና እኩል ያልሆኑ መስፈሪያዎች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ይጠላቸዋል፡፡
\s5
\v 11 ወጣት እንኳ ባህርዩ ንጹህና ቅን መሆኑ በስራው ይታወቃል፡፡
\v 12 የሚሰሙ ጆሮዎችና የሚያዩ ዓይኖች፣ ሁለቱንም እግዚአብሔር ሰራቸው፡፡
\s5
\v 13 እንቅልፍን አትውደድ ወደ ድህነት ትመጣለህና፤ ዓይኖችህን ክፈት፣ የተትረፈረፈ መብል ይኖርሃል፡፡
\v 14 ዕቃ የሚገዛ ሰው “መጥፎ ነው! መጥፎ ነው! ” ይላል፣ በሄደ ጊዜ ግን ይኩራራል፡፡
\s5
\v 15 ወርቅና ብዙ ውድ ድንጋዮች አሉ፣ የእውቀት ከንፈሮች ግን የከበረ ጌጥ ናቸው፡፡
\v 16 ለማይታወቅ ሰው ብድር በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው ልብስ ውሰድበት፣ ዝሙት ለምትፈጽም ሴት ዋስትና አስይዞ ከሆነ ውሰድበት፡፡
\s5
\v 17 በማጭበርበር የተገኘ ዳቦ ይጣፍጣል፣ ከዚያ በኋላ ግን አፉ ጠጠር ይሞላል፡፡
\v 18 እቅዶች በምክር ይጸናሉ፣ በጠቢብ ምክርም ብቻ ጦርነት አድርግ፡፡
\s5
\v 19 ሐሜት ሚስጥርን ያባክናል፣ ስለዚህ ወሬን ከሚያበዙ ሰዎች ጋር አንድነት አትፍጠር፡፡
\v 20 አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን ከሰደበ፣ መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ መካከል ይጠፋል፡፡
\s5
\v 21 በመጀመርያ በጥድፊያ የተገኘ ሀብት በመጨረሻ ላይ በረከት አይኖረውም፡፡
\v 22 “ለፈጸምክብኝ በደል ብድራትህን እመልስልሃለሁ” አትበል! እግዚአብሔርን ጠብቅ እርሱም ያድንሃል፡፡
\s5
\v 23 እኩል ያልሆኑ ሚዛኖችን እግዚአብሔር ይጠላል፣ ሐሰተኛ መስፈሪያም መልካም አይደለም፡፡
\v 24 የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይመራል፤ ታዲያ ሰው የራሱን መንገድ እንዴት ሊያስተውል ይችላል?
\s5
\v 25 ሰው በችኮላ “ይህ ነገር የተቀደሰ ነው” ቢሎ ስእለት ቢሳል፣ ከተሳለም በኋላ ስለ ነገሩ ምንነት ማሰላሰል ቢጀምርና ቢጸጸት ወጥመድ ይሆንበታል፡፡
\v 26 ጥበበኛ ንጉስ ክፉውን አበጥሮ ያወጣል፣ ከዚያም የመውቂያ ጋሪውን በላያቸው ላይ ይነዳል፡፡
\s5
\v 27 የሰው መንፈስ የእግዚአብሔር መብራት ነው፣ ውስጣዊ ማንነቱንም ይመረምራል፡፡
\v 28 በኪዳን የተመሰረተ ታማኝነትና እውነተኛነት ንጉስን ይጠብቁታል፤ ዙፋኑም በፍቅር ይጸናል፡፡
\s5
\v 29 የወጣት ወንዶች ክብር ጥንካሬያቸው ነው፣ የሽማግሌዎችም ውበት ሽበታቸው ነው፡፡
\v 30 የሚያቆስል ምት ክፋትን ያስወግዳል፣ ግርፋትም ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችን ያነጻል፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 የንጉስ ልብ በእግዚአብሔር እጅ እንዳለ የውኃ ፈሳሽ ነው፤ እርሱ ደስ ወዳሰኘው ይመራዋል፡፡
\v 2 ለሰው መንገዱ በራሱ ዓይን ፊት ቀና ሊመስለው ይችላል፣ ልብን የሚመዝን ግን እግዚአብሔር ነው፡፡
\s5
\v 3 ከመስዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት አለው፡፡
\v 4 ትቢተኛ ዓይንና ኩሩ ልብ፣ የክፉ ሰውም መብራት፣ ኃጢአት ናቸው፡፡
\s5
\v 5 የትጉ ሰው እቅዶች ወደ ብልጽግና ይመራሉ፣ በችኮላ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ግን ወደ ድህነት ይመጣል፡፡
\v 6 በሐሰተኛ ምላስ ሀብትን ማግኘት በኖ የሚጠፋ ተን፣ የሚገድልም ወጥመድ ነው፡፡
\s5
\v 7 የክፉዎች አመጽ ራሳቸውን ይጠራርጋቸዋል፣ ፍትሕን ማድረግ አይፈቅዱምና፡፡
\v 8 የበደለኛ ሰው መንገድ ጠማማ ነው፣ ንጹሕ ሰው ግን ጽድቅን ያደርጋል፡፡
\s5
\v 9 ከጠበኛ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር በጣራ ማእዘን ላይ ተጠግቶ መኖር ይሻላል፡፡
\v 10 የክፉ ሰው ምኞት ክፋትን አጥብቆ ይመኛል፤ ጎረቤቱም በዓይኖቹ ውስጥ ምንም ደግነት አያይም፡፡
\s5
\v 11 ፌዘኛ ሲቀጣ ፣ እውቀት አልባ ሰው ጥበበኛ ይሆናል፣ ጥበበኛ ሰው ሲገሰጽ፣ እውቀትን ይጨምራል፡፡
\v 12 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው የክፉውን ቤት ልብ ብሎ ይመለከታል፤ እርሱ ክፉውን ወደ ጥፋት ያወርደዋል፡፡
\s5
\v 13 የድሆችን ጩኸት የማይሰማ ሰው፣ እርሱም ሲጮህ ማንም አይሰማውም፡፡
\v 14 በምስጢር የተደረገ ስጦታ ቁጣን ያበርዳል፣ የተሸሸገ ስጦታም ታላቅ ቁጣን ያጠፋል፡፡
\s5
\v 15 ፍትሕ በተደረገ ጊዜ ጽድቅን ላደረገው ሰው ደስታን ያመጣለታል፣ ለክፉ አድራጊዎች ግን ሽብር ያመጣባቸዋል፡፡
\v 16 ከማስተዋል መንገድ የሳተ ሰው፣ በሙታን ጉባኤ ውስጥ ያርፋል፡፡
\s5
\v 17 ቅንጦት የሚወድ ሰው ድሃ ይሆናል፤ የወይን ጠጅና ዘይት የሚወድ ደግሞ ባለጠጋ አይሆንም፡፡
\v 18 ክፉ ሰው ጽድቅን ለሚያደርግ ሰው ቤዛ ይሆናል፣ ከዳተኛ ሰው ደግሞ ለጻድቅ ቤዛ ነው፡፡
\s5
\v 19 ጠብ ከምታነሳሳና ያለማቋረጥ ከምታማርር ሴት ጋር ከመኖር በምድረ በዳ መኖር ይሻላል፡፡
\v 20 የከበረ ሀብትና ዘይት በጥበበኛ ቤት ይገኛሉ፣ ሞኝ ሰው ግን ያባክናቸዋል፡፡
\s5
\v 21 ጽድቅን የሚያደርግና ደግ ሰው፣ ይህ ሰው ሕይወትን፣ ጽድቅንና ክብርን ያገኛል፡፡
\v 22 ጥበበኛ ሰው ወደ ኃያላን ከተማ ይገባል፣ የምትታመንበት ምሽጓንም ያፈርሳል፡፡
\s5
\v 23 አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ሰው ራሱን ከመከራ ይጠብቃል፡፡
\v 24 ኩሩና ትዕቢተኛ ሰው ስሙ “ሞኝ” ይባላል፣ እርሱም በእብሪትና በትዕቢት ያደርጋል፡፡
\s5
\v 25 የሰነፍ ምኞት ራሱን ይገድለዋል፣ እጆቹ ለመስራት አይፈቅዱምና፡፡
\v 26 እርሱ ቀኑን በሙሉ ይመኛል፣ ተጨማሪ ይመኛል፣ ጽድቅን የሚያደርግ ግን ይሰጣል፣ አይሰስትምም፡፡
\s5
\v 27 የክፉዎች መስዋዕት አስጸያፊ ነው፤ በክፉ ሃሳብ ሲያቀርበው ደግሞ የበለጠ አስጸያፊ ነው፡፡
\v 28 ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፣ የሚያዳምጥ ሰው ግን ለሁልጊዜ የሚሆን ይናገራል፡፡
\s5
\v 29 ክፉ ሰው ራሱን ጠንካራ አስመስሎ ያቀርባል፣ ጻድቅ ሰው ግን ስለ ድርጊቶቹ ይጠነቀቃል፡፡
\s5
\v 30 እግዚአብሔርን ሊቋቋም የሚችል ጥበብ፣ ማስተዋል ወይም ምክር የለም፡፡
\v 31 ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፣ ድል ግን የእግዚአብሔር ነው፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 ከብዙ ሐብት ይልቅ ጥሩ ስም ይመረጣል፣ ሞገስም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል፡፡
\v 2 ሃብታምና ድሃ ሰዎች የሚጋሩት አንድ ነገር አለ፤ ይህም እግዚአብሔር የሁሉም ፈጣሪ መሆኑ ነው፡
\s5
\v 3 ጠንቃቃ ሰው ችግር ሲያይ ራሱን ይሸሽጋል፣ አላዋቂዎች ግን በዚያው ገፍተው ይሄዳሉ በሱም ምክንያት ይጎዳሉ፡፡
\v 4 የትህትናና እግዚአብሔርን የመፍራት ሽልማት ባለጠግነት፣ ክብርና ሕይወት ነው፡፡
\s5
\v 5 እሾህና አሜኬላ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፤ ሕይወቱን የሚጠብቅም ከእነርሱ ይርቃል፡፡
\v 6 ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፣ በሸመገለም ጊዜ ከነገርከው መንገድ ፈቀቅ አይልም፡፡
\s5
\v 7 ባለጠጎች ድሆችን ይገዛሉ፣ ተበዳሪም ለአበዳሪው ባርያ ነው፡፡
\v 8 ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፣ የቁጣውም በትር አይጠቅመውም፡፡
\s5
\v 9 ቸር አይኖች ያሉት ሰው ይባረካል፣ እንጀራውን ከድሆች ጋር ይካፈላልና፡፡
\v 10 ፌዘኛን ከአንተ አርቀው፣ ጠብም ከአንተ ይርቃል፤ ግጭትና ስድብም ይቆማሉ፡፡
\s5
\v 11 ንጹህ ልብ የሚወድድና ንግግሩም ሞገስ ያለው ሰው፣ ንጉስ ጓደኛው ይሆናል፡፡
\v 12 የእግዚአብሔር ዓይኖች እውቀትን ይከታተላሉ፣ የከዳተኞችን ቃሎች ግን ይገለብጣል፡፡
\s5
\v 13 ሰነፍ ሰው “አንበሳ በመንገድ ላይ አለ! በውጪ ላይ እገደላለሁ” ይላል፡፡
\v 14 የአመንዝራ ሴት አፍ ጥልቅ ጉድጓድ ነው፤ ወደ እርሱም በሚወድቅ ሰው ሁሉ የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይሆናል፡፡
\s5
\v 15 ሞኝነት በሕጻን ልብ ላይ ታስሯል፣ የስርዓት በትር ግን ከእርሱ ያርቀዋል፡፡
\v 16 ሀብቱን ለማካበት ወይም ለሀብታሞች ለመስጠት ሲል ድሆችን የሚያስጨንቅ፣ ወደ ድህነት ይመጣል፡፡
\s5
\v 17 የጠቢብን ቃላት ልብ በል አስተውለህም ስማ፣ ልብህንም ወደ ከእውቀቴ አዘንብል፣
\v 18 በውስጥህ ብትጠብቃቸውና ሁሉም በከንፈሮችህ ላይ ዝግጁ ቢሆኑ ለአንተ ደስ ያሰኙሃልና፡፡
\v 19 እምነትህ በእግዚአብሔር ላይ ይሆን ዘንድ፣ እነዚህን ለአንተ ዛሬ አስተምርሃለሁ፣ ለአንተም ቢሆን አስተምርሃለሁ፡፡
\s5
\v 20 ሰላሳ የተግሳጽና የእውቀት ቃሎችን ለአንተ አልጻፍኩልህምን፣
\v 21 በእነዚህ ታማኝ ቃሎች እውነትን አስተምርህ ዘንድ፣ አንተም ለላኩህ ታማኝ መልስ ትሰጥ ዘንድ?
\s5
\v 22 ድሃ በመሆኑ ምክንያት ድሃ ሰው አትዝረፍ፣ ችግረኛውንም በበር ላይ አትግፋው፣
\v 23 እግዚአብሔር ለእነርሱ ይፈርድላቸዋልና፣ የዘረፏቸውንም ሰዎች ሕይወት እርሱ ይነጥቃል፡፡
\s5
\v 24 ግልፍተኛ ሰውን ጓደኛ አታድርግ፣ ቁጣም ካለበት ሰው ጋር አብረህ አትሂድ፣
\v 25 አለበለዚያ መንገዱን ትማራለህ፣ ራስህንም በወጥመድ ታጠላልፋለህ፡፡
\s5
\v 26 ገንዘብን በተመለከተ ግዴታ የሚያስገባ ውል የምትሰጥ አትሁን፣ ለሌሎችም ብድር ዋስ አትሁን፡፡
\v 27 መክፈል ካልቻልህ፣ ያንን ሰው አልጋህን ከስርህ ከመውሰድ ሊያቆመው የሚችል ምን ነገር አለ?
\s5
\v 28 አባቶችህ ያስቀመጡትን የጥንቱን የድንበር የምልክት ድንጋይ አታንሳ፡፡
\v 29 በስራው ስልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገስታት ፊት ይቆማል፤ በተራ ሰዎች ፊትም አይቆምም፡፡
\s5
\c 23
\p
\v 1 ከገዢ ጋር ለመብላት ስትቀመጥ፣ በፊት ያለውን በጥንቃቄ አስተውል፣
\v 2 ከመጠን ያለፈ ምግብ መብላት የምትወድ ዓይነት ሰው ከሆንህ በጉሮሮህ ላይ ካራ አድርግ፡፡
\v 3 የእርሱ ጣፋጭ ምግቦች አያስጎምጁህ፣ በውሸት የመጣ ምግብ ነውና፡፡
\s5
\v 4 ባለጠጋ ትሆን ዘንድ ከመጠን በላይ አትልፋ፤ መቼ ማቆም እንዳለብህም ታውቅ ዘንድ ብልህ ሁን፡፡
\v 5 አይንህን በገንዘብ ላይ በጣልክ ጊዜ፣ እርሱ ይጠፋል፣ በድንገት ክንፍ ያወጣል እንደ ንስርም ወደ ሰማይ እየበረረ ይሄዳል፡፡፤
\s5
\v 6 የክፉ ሰውን፣ እጅግ በጣም ከርቀት በምግብህ ላይ በቅናት የሚመለከተውን ሰው ምግብ አትብላ፣ ጣፋጭ መብሎቹንም አትጎምጅ፣
\v 7 እርሱ የምግቡን ዋጋ የሚቆጥር ሰው ነውና፡፡ “ብላ፣ ጠጣ! ” ይልሃል፣ ልቡ ግን ከአንተ ጋር አይደለም፡፡
\v 8 ትንሽ የበላኸው ያስታውክሃል፣ የምስጋና ቃልህንም ከንቱ ታደርጋለህ፡፡
\s5
\v 9 ሞኝ ሰው ባለበት ንግግር አታድርግ፣ እርሱ የቃሎችህን ጥበብ ያንኳስሳልና፡፡
\v 10 የጥንቱን የድንበር የምልክት ድንጋይ አታንሳ፣ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች እርሻ አትግፋ፣
\v 11 ታዳጊያቸው ብርቱ ነውና፣ እርሱ ጉዳያቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳል፡፡
\s5
\v 12 ልብህን ለተግሳጽ ጆሮህንም ለእውቀት ቃሎች ስጥ፡፡
\s5
\v 13 ልጅን ከመቅጣት ወደ ኋላ አትበል፣ በበትር ብትመታው አይሞትምና፡፡
\v 14 በበትር ብትመታው ነፍሱን ከሲኦል ታድናታለህ፡፡
\s5
\v 15 ልጄ ሆይ፣ ልብህ ጥበበኛ ቢሆን፣ ያኔ ልቤ ደግሞ ደስተኛ ይሆናል፤
\v 16 ከንፈሮችህ ትክክለኛ የሆነውን በሚናገሩበት ጊዜ ውስጣዊ ሰውነቴ ሁሉ ደስ ይለዋል፡፡
\s5
\v 17 ልብህ በኃጢአተኞች እንዲቀና አትፍቀድ፣ ነገር ግን ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ተመላለስ፡፡
\v 18 ለወደፊት እርግጠኛ አለኝታ አለህ፣ ተስፋህም አይጠፋም፡፡
\s5
\v 19 ልጄ ሆይ፣ ስማኝ፣ ጥበበኛ ሁን ልብህንም በትክክለኛው መንገድ ላይ አዘንብል፡፡
\v 20 ከሰካራሞች ወይም በሆዳምነት ስጋ ከሚበሉ ጋር አትተባበር፣
\v 21 ሰካራሞችና ሆዳሞች ድሃ ይሆናሉ፣ እንቅልፋምነትም ቁራጭ ጨርቅ ያስለብሳቸዋል፡፡
\s5
\v 22 የወለደህን አባትህን ስማ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት፡፡
\v 23 እውነትን የራስህ አድርጋት፣ አትሽጣትም፤ ጥበብን፣ ስርዓትንና ማስተዋልንም ገንዘብህ አድርግ፡፡
\s5
\v 24 የጻድቅ አባት በደስታ ይሞላል፣ ጥበበኛ ልጅንም የወለደ በልጁ ይደሰታል፡፡
\v 25 አባትህና እናትህን ደስ አሰኛቸው፣ የወለደችህ እናትህም ሐሴት ታድርግ፡፡
\s5
\v 26 ልጄ ሆይ፣ ልብህን ስጠኝ፣ አይኖችህም የእኔን መንገድ ያስተውሉ፡፡
\v 27 ዝሙት አዳሪ ሴት ጥልቅ ጉድጓድ፣ የሌላ ሰውም ሚስት ጠባብ ጉድጓድ ናትና፡፡
\v 28 እንደ ሌባ አድፍጣ ጥጠብቃለች፣ በሰዎችም መካከል የከዳተኞችን ቁጥር ታበዛለች፡፡
\s5
\v 29 ዋይታ የማን ነው? ሃዘን የማን ነው? ጠብስ የማን ነው? ማጉረምረም የማን ነው? ያለ ምክንያት መቁሰል የማን ነው? የዓይን መቅላት የማን ነው?
\v 30 ወይን ጠጅ በመጠጣት የሚቆዩ፣ ድብልቅ ወይን ጠጅ የሚቀምሱ ሰዎች ነው፡፡
\s5
\v 31 በቀላ ጊዜ ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት፣ በብርጭቆ ውስጥ መልኩ ባንጸባረቀ ጊዜ የሚያንጸባርቅ በሆነ ጊዜ፣ ስትጠጣውም ያለ ምንም ችግር በገባ ጊዜ፡፡
\v 32 በመጨረሻ እንደ እባብ ይናከሳል፣ እንደ እፉኝትም ይናደፋል፡፡
\v 33 አይኖችህ አዲስ ነገሮችን ያያሉ፣ ልብህም ጠማማ ነገሮችን ይናገራል፡፡
\s5
\v 34 በባህር ከፍታ ላይ እንደተኛ፣ በመርከብ ምሰሶ ጫፍ ላይ እንደተጋደመ ሰው ትሆናለህ፡፡
\v 35 “መቱኝ! ” “ነገር ግን አልተጎዳሁም፡፡ ደበደቡኝ፣ ነገር ግን አልተሰማኝም፡፡ መቼ ይሆን የምነቃው? ሌላ መጠጥ እፈልጋለሁ፡፡” ትላለህ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 ክፉ በሆኑ ሰዎች አትቅና፣ ከእነርሱም ጋር ለመተባበር አትፈልግ፣
\v 2 ምክንያቱም ልባቸው ግጭትን ያሴራል፣ ከንፈራቸውም ችግርን ያወራል፡፡
\s5
\v 3 ቤት በጥበብ ይሰራል፣ በማስተዋልም ይጸናል፡፡
\v 4 በእውቀትም ውድና ባማሩ እቃዎች ክፍሎቹ ይሞላሉ፡፡
\s5
\v 5 ጥበበኛ ሰው ብርቱ መሆኑን ያረጋግጣል፣ እውቀት ያለውም ሰው ከጠንካራ ሰው ይልቅ ይሻላል፣
\v 6 በጥበበኛ ምክር ጦርነትህን መዋጋት ትችላለህ፣ በብዙ አማካሪዎችም ድል ይገኛልና፡፡
\s5
\v 7 ለሞኝ ሰው ጥበብ እጅግ ትርቃለች፤ በበርም አፉን አይከፍትም፡፡
\s5
\v 8 ክፋትን ለማድረግ የሚያስብ አንድ ሰው አለ፣ ሰዎችም የተንኮል አለቃ ብለው ይጠሩታል፡፡
\v 9 የስንፍና እቅድ ኃጢአት ነው፣ ሰዎችም ፌዘኛን ይንቁታል፡፡
\s5
\v 10 በችግር ጊዜ ፍርሃትህን ካሳየህ፣ እንግዲያው አቅምህ ትንሽ ነው፡፡
\s5
\v 11 ወደ ሞት የሚወሰዱትን አድናቸው፣ እየተጎተቱ ለመታረድ የሚነዱትንም ይዘህ መልሳቸው፡፡
\v 12 አንተም “እዚያ! ስለዚህ ነገር ምንም አናውቅም” ብትል ልብን የሚመረምረው እርሱ ንግግርህን አያስተውለውምን? ሕይወትህን የሚጠብቀው እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ እንደ ስራው መጠን እግዚአብሔር አይሰጠውምን?
\s5
\v 13 ልጄ ሆይ፣ መልካም ነውና ማር ብላ፣ የማር ወለላ ጠብታዎች ለጣዕምህ ጣፋጭ ናቸው፡፡
\v 14 ጥበብም ለነፍስህ እንዲህ ነው፣ ካገኘኸውም፣ ወደፊት ዋስትና ይኖርሃል፣ ተስፋህም አይጠፋም፡፡
\s5
\v 15 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎችን ቤት እንደሚዘርፉ ክፉ ሰዎች አድፍጠህ አትጠብቅ፡፡ የጻድቁንም ቤት አታፍርስ፡፡
\v 16 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ሰባት ጊዜ ቢወድቅ፣ እንደገና ከወደቀበት ይነሳልና፣ ክፉዎች ግን ይቀሰፋሉ፡፡
\s5
\v 17 ጠላትህ በወደቀ ጊዜ ደስ አይበልህ፣ በተሰናከለም ጊዜ ልብህ ደስ አይበለው፣
\v 18 እግዚአብሔር ያያል፣ ተመልሶም ቁጣውን ከእርሱ ይመልሳልና፡፡
\s5
\v 19 ክፋትን በሚያደርጉ ሰዎች አትጨነቅ፣ በክፉዎችም አትቅና፣
\v 20 ክፉ ሰው ተስፋ የለውምና፣ የክፉ ሰውም መብራት ይጠፋልና፡፡
\s5
\v 21 እግዚአብሔርን ፍራ፣ ንጉስንም ፍራ፣ ልጄ ሆይ፤ በእነርሱ ላይ ከሚያምጹ ሰዎችም ጋር አትተባበር፣
\v 22 ጥፋታቸው በድንገት ይመጣልና፣ ከሁለቱም የሚመጣባቸውን ጥፋት ምን ያህል እንደሆነ ማን ያውቃል?
\s5
\v 23 እነዚህ ደግሞ የጥበበኛ ሰው ንግግር ናቸው፡፡ በዳኝነት አድልዎ ማድረግ መልካም አይደለም፡፡
\s5
\v 24 ወንጀለኛውን “ጻድቅ ነህ” የሚለው በሕዝብ ዘንድ ይረገማል፣ በመንግስታትም ዘንድ ይጠላል፡፡
\v 25 ነገር ግን በደለኛውን የሚገስጹ ደስታ ይሆንላቸዋል፣ የደግነት ስጦታዎችም ወደ እነርሱ ይመጣሉ፡፡
\s5
\v 26 እውነተኛ መልስ የሚሰጥ ሰው ከንፈሮችን ይስማል፡፡
\v 27 የውጪ ስራህን አዘጋጅ፣ በመስክም ሁሉንም ነገር ለራስህ ዝግጁ አድርግ፣ ከዚያም በኋላ ቤትህን ስራ፡፡
\s5
\v 28 ያለ ምክንያት በጎረቤትህ ላይ አትመስክር፣ በከንፈሮችህም አታታልል፡፡
\v 29 “እርሱ በእኔ ላይ ያደረገውን እኔም በእርሱ ላይ አደርግበታለሁ፤ በእኔ ላይ ላደረገው ነገር ዋጋውን እከፍለዋለሁ” አትበል፡፡
\s5
\v 30 በሰነፍ ሰው እርሻ በኩል ሄድሁ፣ አእምሮ በሌለውም ሰው የወይን እርሻ አለፍሁ፡፡
\v 31 እሾህም በየቦታው በቅሎ ነበር፣ መሬቱም በሳማ ተሸፍኖ ነበር፣ የድንጋይ ካቡም ፈርሶ ነበር፡፡
\s5
\v 32 ከዚያም አየሁና አሰብኩኝ፤ ተመለከትሁና ተግሳጽን ተቀበልሁ፡፡
\v 33 ጥቂት መተኛት፣ ጥቂት እንቅልፍ፣ ጥቂት ለማረፍ እጅን ማጣጠፍ፣
\v 34 ድህነት እንደ ሌባ በአንተ ላይ ይመጣል፣ ችግርህም መሳርያ እንደታጠቀ ወታደር ይመጣብሃል፡፡
\s5
\c 25
\p
\v 1 እነዚህ የይሁዳ ንጉስ፣ የሕዝቅያስ ሰዎች የቀዷቸው ተጨማሪ የሰለሞን ምሳሌዎች ናቸው፡፡
\v 2 ነገርን መሰወር የእግዚአብሔር ክብር ነው፣ የነገስታት ክብር ግን ነገርን መርምሮ ማውጣት ነው፡፡
\v 3 ሰማያት ከፍ ያሉ እንደሆኑ፣ ምድርም ጥልቅ እንደሆነች ሁሉ፣ የነገስታት ልብም አይመረመርም፡፡
\s5
\v 4 ቆሻሻውን ከብር አስወግድ፣ የብረት ሰራተኛውም ብሩን ለእጅ ሙያው ሊጠቀምበት ይችላል፡፡
\v 5 እንደዚሁ ክፉ ሰዎችን ከንጉስ ፊት አርቃቸው፣ ዙፋኑ ጽድቅን በማድረግ ይጸናል፡፡
\s5
\v 6 በንጉስ ፊት ራስህን ከፍ ከፍ አታድርግ፣ ለታላቅ ሰዎች መቆሚያ በተዘጋጀም ስፍራ ላይ አትቁም፡፡
\s5
\v 7 በተከበሩ ሰዎች ፊት ከምትዋረድ ይልቅ፣ እርሱ “ወደዚህ ና” ቢልህ ይሻላል፡፡ ያየኸውን ነገርም፣
\v 8 ወደ ፍርድ ፈጥነህ አታምጣው፡፡ ጎረቤትህ ባሳፈረህ ጊዜ በመጨረሻ ምን ታርጋለህ?
\s5
\v 9 ጉዳይህን በአንተና በጎረቤትህ መካከል ተከራከር፣ የሌላ ሰው ምስጢር ግን አታውጣ፣
\v 10 አለበለዚያ ግን አንተን የሰማ ሰው በአንተ ላይ ሃፍረትን ያመጣብሃል፣ ስለ አንተም ልትመልሰው የማትችለው መጥፎ ወሬ ይወራብሃል፡፡
\s5
\v 11 በጥንቃቄ የተመረጠ ቃል መናገር፣ በብር ላይ እንደተቀረጻ የወርቅ ንድፍ ነው፡፡
\v 12 ለሚሰማ ጆሮ የጥበበኛ ተግሳጽ እንደ ወርቅ ቀለበት፣ ከንጹህ ወርቅም እንደተሰራ ጌጥ ነው፡፡
\s5
\v 13 በምርት መሰብሰቢያ ወቅት እንዳለ የበረዶ ቅዝቃዜ ታማኝ መልዕክተኛ ለላኩት ሰዎች እንዲሁ ነው፤ የጌቶቹን ሕይወት ይመልሳል፡፡
\v 14 የማይሰጠውን ስጦታ እሰጣለሁ ብሎ የሚመካ ሰው ዝናብ እንደሌለው ደመናና ንፋስ ነው፡፡
\s5
\v 15 በትዕግስት ገዢን እንዲለዝብ ማድረግ ይቻላል፣ መልካም ምላስም አጥንትን ትሰብራለች፡፡
\s5
\v 16 ማር ካገኘህ፣ ለአንተ በቂ የሆነውን ብላ፣ አለበለዚያ ግን ከመጠን በላይ ከበላህ ትተፋዋለህ፡፡
\v 17 ወደ ጎረቤትህ ቤት እግር አታብዛ፣ ሊሰለችህና ሊጠላህ ይችላልና፡፡
\s5
\v 18 በጎረቤቱ ላይ በሐሰት የሚመሰክር ሰው በጦርነት ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል ዱላ፣ ሰይፍ ወይም የተሳለ ቀስት ነው፡፡
\v 19 በችግር ጊዜ የታመንከው ወስላታ ሰው እንደ ተበላሸ ጥርስ ወይም እንደሚያነክስ እግር ነው፡፡
\s5
\v 20 ላዘነ ልብ መዝሙር የሚዘምር፣ በብርድ ጊዜ ልብሱን እንደሚያወልቅ ወይም በሶዳ ላይ ኮምጣጤ እንደሚጨምር ነው፡፡
\s5
\v 21 ጠላትህ ቢራብ እንዲበላ ምግብ ስጠው፣ ቢጠማም እንዲጠጣ ውኃ ስጠው፣
\v 22 በራሱ ላይ ፍም ትከምራለህና፣ እግዚአብሔርም ዋጋህን ይከፍልሃልና፡፡
\s5
\v 23 የሰሜን ንፋስ በእርግጠኝነት ዝናብን ይዞ እንደሚመጣ፣ ሚስጥርን የሚያባክን ሰው ሰዎችን ያስቆጣል፡፡
\v 24 ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር በጣራ ማእዘን ላይ ተጠግቶ መኖር ይሻላል፡፡
\s5
\v 25 ለተጠማ ሰው ቀዝቃዛ ውሃ እንደሚያረካው ሁሉ፣ ከሩቅ አገር የመጣ የምስራችም እንዲሁ ነው፡፡
\v 26 በክፉ ሰዎች ፊት የሚንበረከክ መልካም ሰው፣ እንደ ተበከለ ፈሳሽና እንደተበላሸ ምንጭ ነው፡፡
\s5
\v 27 እጅግ በጣም ብዙ ማር መብላት ጥሩ አይደለም፤ በክብር ላይ ክብር እንደመፈለግ ነው፡፡
\v 28 ራሱን መግዛት የማይችል ሰው እንደፈረሰችና ቅጥር እንደሌላት ከተማ ነው፡፡
\s5
\c 26
\p
\v 1 በበጋ ጊዜ እንደሚወርድ በረዶና በመከር ጊዜ እንደሚዘንብ ዝናብ፣ ክብርም ለሞኝ ሰው አይገባውም፡፡
\v 2 ድንቢጥ ከቦታ ቦታ እንደምትበርር፣ ጨረባም እንደምትሸመጥጥ፣ ያልተገባ እርግማን ማንም ላይ አይደርስም፡፡
\s5
\v 3 ጅራፍ ለፈረስ፣ ልጓምም ለአህያ እንደሆነ፣ በትርም ለሞኞች ጀርባ ነው፡፡
\v 4 ለሞኝ መልስ አትስጠው፣ በሞኝነቱም አትተባበር፣ አለዚያ እንደ እርሱ ትሆናለህ፡፡
\s5
\v 5 ሞኝን እንደ ሞኝነቱ መልስለት፣ በሞኝነቱም ተባበረው፣ አለዚያ በዓይኖቹ ጥበበኛ የሆነ ይመስለዋል፡፡
\v 6 በሞኝ ሰው እጅ መልዕክትን የሚልክ ሁሉ የራሱን እግር ይቆርጣል ሁከትንም ይጠጣል፡፡
\s5
\v 7 የሰለሉ የሽባ እግሮች በሞኝ አፍ እንዳለ ምሳሌ ናቸው፡፡
\v 8 ለሞኝ ክብር መስጠት ድንጋይን በወንጭፍ እንደ ማሰር ነው፡፡
\s5
\v 9 በሰካራም እጅ ላይ ያለ እሾህ በሞኞች አፍ እንዳለ ምሳሌ ነው፡፡
\v 10 ሁሉንም ሰው የሚያቆስል ቀስተኛ፣ ሞኝን ወይም አላፊ አግዳሚውን እንደሚቀጥር ሰው ነው፡፡
\s5
\v 11 ውሻ ወደ ትውከቱ እንደሚመለስ፣ ሞኝነቱን የሚደጋግም ሞኝም እንዲሁ ነው፡፡
\v 12 በራሱ ዓይን ጥበበኛ እንደሆነ የሚያስብን ሰው አይተሃልን? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የተሻለ ተስፋ አለው፡፡
\s5
\v 13 ሰነፍ ሰው እንዲህ ይላል፣ “አንበሳ በመንገድ አለ! በውጭ በአውራ ጎዳና አንበሳ አለ፡፡”
\v 14 በር በማጠፊያው ላይ እንደሚዞር፣ ሰነፍም በአልጋው ላይ ይዟዟራል፡፡
\s5
\v 15 ሰነፍ ሰው እጁን ወደ ሳህኑ ያስገባል፣ ነገር ግን እጁን ወደ አፉ ለመመለስ ጉልበት የለውም፡፡
\v 16 ሰነፍ ሰው ማስተዋል ካላቸው ከሰባት ሰዎች የበለጠ ጥበበኛ እንደሆነ በራሱ ዓይን ያስባል፡፡
\s5
\v 17 የውሻን ጆሮ እንደሚይዝ ሰው፣ የራሱ ባልሆነ ጥል ላይ የሚገባ መንገድ አላፊ ሰውም እንዲሁ ነው፡፡
\s5
\v 18 ተቀጣጣይ ቀስት እንደሚወራወር እብድ ሰው፣
\v 19 “የተናገርሁት እኮ ቀልዴን ነበር? ” በማለት ጎረቤቱን የሚያታልል ሰው እንዲሁ ነው፡፡
\s5
\v 20 በእንጨት እጦት እሳት ይጠፋል፣ ሐሜት በሌለበትም ጥል ያቆማል፡፡
\v 21 ከሰል ፍምን እንጨትም እሳትን እንደሚያቀጣጥል፣ ጠበኛ ሰውም ሁከትን ያቀጣጥላል፡፡
\s5
\v 22 የሐሜት ቃላቶች እንደ ጣፋጭ ጉርሻ ናቸው፤ ወደ ውስጣዊ የሰውነት ክፍሎችም ይወርዳሉ፡፡
\v 23 እንሚያቃጥሉ ከንፈሮችና እንደ ክፉ ልብ በብር ፈሳሽ የተለበጠ የሸክላ ድስት እንዲሁ ነው፡፡
\s5
\v 24 ሌሎችን የሚጠላ ሰው ስሜቱን በከንፈሮቹ ይሸነግላል፣ ተንኮሉን ግን በውስጡ ያኖራል፡፡
\v 25 ማራኪ የሆነ ንግግር ይናገራል፣ ነገር ግን አትመነው፣ በልቡ ውስጥ ሰባት ርኩሰቶች አሉና፡፡
\v 26 ምንም እንኳ ጥላቻው በሽንገላ የተሸፈነ ቢሆንም፣ ክፋቱ ግን በጉባኤ ይገለጣል፡፡
\s5
\v 27 ጉድጓድን የሚቆፍር ሰው እርሱ ይገባበታል፣ ድንጋይንም የሚያንከባልል ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል፡፡
\v 28 ውሸታም ምላስ የጎዳቸውን ሰዎች ይጠላል፣ ሸንጋይ አፍም ጥፋትን ያመጣል፡፡
\s5
\c 27
\p
\v 1 ነገ በሚሆነው አትመካ፣ ቀኑ የሚያመጣው ምን እንደሆነ አታውቅምና፡፡
\v 2 ሌላ ያመስግንህ እንጂ በራስህ አፍ ራስህን አታመስግን፤ የማያውቅህ ሰው እንጂ የራስህ ከንፈሮች አያመስግኑህ፡፡
\s5
\v 3 የድንጋይን ክብደትና የአሸዋንም ክብደት አስብ፣ የሞኝ ሰው ትንኮሳ ግን ከሁለቱም እጅግ የከበደ ነው፡፡
\v 4 የንዴት ጨካኝነትና የቁጣ ጎርፍ አለ፣ በቅናት ፊት መቆም የሚችል ግን ማን ነው?
\s5
\v 5 ከተሰወረ ፍቅር ይልቅ የተገለጠ ተግሳጽ ይሻላል፡፡
\v 6 የጓደኛ ማቁሰል የታመኑ ናቸው፣ ጠላት ግን ከመጠን በላይ ይስማል፡፡
\s5
\v 7 በጣም ጠግቦ የበላ ሰው የማር ወለላንም አይቀበልም፣ ለራበው ሰው ግን ማንኛውም መራራ ነገር እንኳ ጣፋጭ ነው፡፡
\v 8 ከጎጆዋ ወጥታ የምትንከራተት ወፍ ከመኖሪያው አካባቢ ወጥቶ እንደሚባዝን ሰው ናት፡፡
\s5
\v 9 ሽቶና እጣን ልብን ደስ ያሰኛሉ፣ የጓደኛ ጣፋጭነት ግን ከምክሩ ይበልጣል፡፡
\v 10 በችግርህ ጊዜ ጓደኛህንና የጓደኛህን አባት ትተህ ወደ ወንድምህ ቤት አትሂድ፡፡ በቅርብ ያለ ወዳጅ በሩቅ ካለ ወንድም ይሻላልና፡፡
\s5
\v 11 ልጄ ሆይ፣ ጥበበኛ ሁን፣ ልቤንም ደስ አሰኛት፤ በዚያን ጊዜ ለሚያፌዝብኝ ሰው እኔ መልስ እሰጣለሁ፡፡
\v 12 ጥንቁቅ ሰው ችግር ሲያይ ራሱን ይሸሽጋል፣ አላዋቂዎች ግን ቀድመው ሄደው በችግሩ ምክንያት ይጎዳሉ፡፡
\s5
\v 13 ለማይታወቅ ሰው ብድር በዋስትና ገንዘብ ያስያዘውን ሰው ልብስ ውሰድበት፤ ዝሙት ለምትፈጽም ሴት ዋስትና አስይዞ ከሆነ ውሰድበት፡፡
\v 14 ጎረቤቱን በማለዳ ድምጹን በጣም ከፍ አድርጎ የሚባርክ ሰው፣ ባርኮቱ እንደ እርግማን ይቆጠራል!
\s5
\v 15 ጠበኛ ሚስት በዝናብ ቀን እንደማያቋርጥ ነጠብጣብ ናት፤
\v 16 እሷን ማቆም ንፋስን እንደማቆም ወይም ዘይትን በቀኝ እጅህ ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው፡፡
\s5
\v 17 ብረት ብረትን ይስለዋል፤ በተመሳሳይ መንገድ ሰው ጓደኛውን ይስለዋል፡፡
\v 18 የበለስ ዛፍ የሚጠብቅ ፍሬውን ይበላል፣ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል፡፡
\s5
\v 19 ውኃ የሰውን ፊት እንደሚያሳይ፣ የሰው ልብ ሰውየውን ያሳያል፡፡
\v 20 ሲዖልና የሙታን ዓለም መቼም እንደማይጠግቡ፣ የሰውም ዓይኖች መቼም አይጠግቡም፡፡
\s5
\v 21 ማቅለጫ ለብር ከውርም ለወርቅ ነው፣ ሰውም በሚመሰገንበት ጊዜ ይፈተናል፡፡
\v 22 ሰነፍን ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠውም፣ ሞኝነቱ ግን እርሱን አይለቀውም፡፡
\s5
\v 23 የመንጋህን ሁኔታ በእርግጠኝነት እወቅ፣ ስለ ከብቶችህም ግድ ይበልህ፣
\v 24 ሐብት ለዘላለም አይኖርምና፡፡ ዘውድ ለትውልድ ሁሉ ይጸናልን?
\v 25 የነበረው ሳር ጠፍቶ፣ አዲሱ ቡቃያ አድጎ ሲታይ፣ በተራሮች ደግሞ ለከብቶች የሚሆን መብል ተሰብስቦ ይገባል፡፡
\s5
\v 26 ለልብስህ የሚሆን ከበጎች ታገኛለህ፣ ለእርሻህ ዋጋ የሚሆን ደግሞ ከፍየሎችህ ታገኛለህ፡፡
\v 27 ለአንተና ለቤተሰብህ መብል፣ ሴት አገልጋዮችህንም ለመመገብ የሚበቃ የፍየሎች ወተት ይኖራል፡፡
\s5
\c 28
\p
\v 1 ኃጢአተኛ ማንም ሳያባርረው ይሸሻል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ አንበሳ ደፋር ናቸው፡፡
\v 2 በአገር አመጽ ምክንያት ብዙ ገዢዎች አሏት፣ ማስተዋልና እውቀት ባለው ሰው ግን፣ አገር ለረዥም ዘመን ትቆያለች፡፡
\s5
\v 3 ድሃ ሆኖ ሌሎች ድሆችን የሚያስጨንቅ ሰው፣ ሰብልን እንሚያጠፋ ዶፍ ዝናብ ነው፡፡
\v 4 ሕግን የሚተዉ ሰዎች ክፉዎችን ያመሰግናሉ፣ ሕግን የሚጠብቁ ግን ከእነርሱ ጋር ይዋጋሉ፡፡
\s5
\v 5 ክፉ ሰዎች ፍትህን አያውቁም፣ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ግን ሁሉን ነገር ያውቃሉ፡፡
\v 6 በመንገዱ ጠማማ ከሆነ ባለጠጋ ይልቅ፣ በሐቀኝነቱ የሚራመድ ድሃ ሰው ይሻላል፡፡
\s5
\v 7 ሕግን የሚጠብቅ ማስተዋል ያለው ልጅ ነው፣ የሆዳሞች ጓደኛ ግን አባቱን ያሳፍራል፡፡
\v 8 ከፍተኛ ወለድ በመሰብሰብ ሀብቱን የሚያከማች ለድሀዎች ለሚራራ ለሌላ ሰው ሀብቱን ይሰበሰብለታል፡፡
\s5
\v 9 አንድ ሰው ሕግን ከማድመጥ ጆሮውን የሚያዞር ከሆነ፣ ጸሎቱ እንኳ የተጠላ ነው፡፡
\v 10 ቅኑን ሰው ወደ ክፋት መንገድ የሚመራ ሁሉ ራሱ በቆፈረው ጉድጓድ ይገባል፣ ንጹሐን ግን መልካምን ነገር ይወርሳሉ፡፡
\s5
\v 11 ባለጠጋ ሰው በራሱ ዓይኖች ጥበበኛ ሊሆን ይችላል፣ አስተዋይ የሆነ ድሃ ሰው ግን እርሱን ይመረምረዋል፡፡
\v 12 ጽድቅን የሚያደርጉ ድል በሚያገኙበት ጊዜ፣ ታላቅ ክብር አለ፣ ክፉዎች በሚነሱበት ጊዜ ግን ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ፡፡
\s5
\v 13 ኃጢአቱን የሚሸሽግ አይሳካለትም፣ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምህረትን ያገኛል፡፡
\v 14 ዘወትር እግዚአብሔርን እየፈራ የሚኖር ሰው ደስተኛ ነው፣ ልቡን የሚያደነድን ግን ወደ መከራ ይወድቃል፡፡
\s5
\v 15 እንደሚያገሳ አንበሳ ወይም እንደ ተቆጣ ድብ በድሆች ላይ የሚገዛ ክፉ ገዥም እንዲሁ ነው፡፡
\v 16 ማስተዋል የሌለው ገዥ በጭካኔ የሚያስጨንቅ ነው፣ ማታለልን የሚጠላ ግን እድሜውን ያረዝማል፡፡
\s5
\v 17 አንድ ሰው የሌላውን ደም በማፍሰሱ ምክንያት በደለኛ ከሆነ፣ እስከ ሞቱ ቀን ድረስ ኮብላይ ይሆናል፣ ማንም ሰው አይረዳውም፡፡
\v 18 በሐቀኝነት የሚራመድ ሰው በደህና ይጠበቃል፣ መንገዱ በጠማማነት የተሞላ ግን በድንገት ይወድቃል፡፡
\s5
\v 19 መሬቱን የሚያርስ ሰው ብዙ መብል ይኖረዋል፣ የማይጠቅም ሞያ የሚከተል ግን እጅግ በጣም ይደኸያል፡፡
\v 20 ታማኝ ሰው ታላቅ በረከት ያገኛል፣ በጥድፊያ ሃብታም የሆነ ግን ሳይቀጣ አይቀርም፡፡
\s5
\v 21 አድልዎን ማሳየት መልካም አይደለም፣ ነገር ግን ለቁራጭ ዳቦ ሲል ሰው ስህተትን ይሰራል፡፡
\v 22 ስስታም ሰው ሐብትን ያሳድዳል፣ ድህነት በላዩ ላይ እንደሚመጣ ግን አያውቅም፡፡
\s5
\v 23 ሰውን በምላሱ ከሚያሞግስ ይልቅ የሚገስጽ ሰው በኋላ ውሎ አድሮ ከገሰጸው ሰው ብዙ ሞገስ ያገኛል፡፡
\v 24 አባቱንና እናቱን ሰርቆ “ኃጢአት አይደለም” የሚል ሰው የአጥፊ ተባባሪ ነው፡፡
\s5
\v 25 ስግብግብ ሰው ግጭትን ያነሳሳል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይባረካል፡፡
\v 26 በራሱ ልብ የሚታመን ሰው ሞኝ ነው፣ በጥበብ የሚራመድ ግን ከአደጋ ይርቃል፡፡
\s5
\v 27 ለድሃ የሚሰጥ ምንም ነገር አይጎድልበትም፣ በድሆች ላይ ዓይኖቹን የሚከድን ሰው ግን ብዙ እርግማን ይቀበላል፡፡
\v 28 ክፉ ሰዎች ሲነሱ፣ ሰዎች ራሳቸውን ይሸሽጋሉ፣ ክፉ ሰዎች ሲጠፉ ግን፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ይበዛሉ፡፡
\s5
\c 29
\p
\v 1 ብዙ ተግሳጽን ተቀብሎ አንገቱን ያደነደነ ሰው እንደማይድን ሆኖ በቅጽበት ይሰበራል፡፡
\v 2 ጽድቅን የሚያደርጉ ሰዎች ሲበዙ፣ ሕዝብ ደስ ይለዋል፣ ክፉ ሰው ገዢ ሲሆን ግን ሕዝብ ያቃስታል፡፡
\s5
\v 3 ጥበብን የሚወድ ሁሉ አባቱን ደስ ያሰኛል፣ አመንዝራዎች ወዳጅ ግን ሀብቱን ያጠፋል፡፡
\v 4 ንጉስ አገሩን በፍትህ ያጸናል፣ ጉቦን የሚፈልግ ግን ያፈራርሳታል፡፡
\s5
\v 5 ጎረቤቱን የሚሸነግል ሰው ለገዛ እግሩ መረብ እየዘረጋ ነው፡፡
\v 6 ክፉ ሰው በራሱ ኃጢአት በወጥመድ ይያዛል፣ ጽድቅን የሚያደርግ ግን ይዘምራል፣ ይደሰታልም፡፡
\s5
\v 7 ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ለድሆች ፍትሕ ይጨነቃል፤ ክፉ ሰው ግን እንዲህ ዓይነት እውቀት የለውም፡፡
\v 8 ፌዘኞች ከተማን ያቃጥላሉ፣ ጥበበኞች ግን ቁጣን ይመልሳሉ፡፡
\s5
\v 9 ጥበበኛ ሰው ከሞኝ ጋር በሚከራከርበት ጊዜ፣ ሞኝ ይቆጣል ይስቃልም፣ እረፍትም አይኖርም፡፡
\v 10 ደም የተጠማ ሰው ንጹሐንን ይጠላሉ፣ ቅን የሆነውንም ሕይወት ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡
\s5
\v 11 ሞኝ ቁጣውን ሁሉ ይገልጣል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ይቆጣጠራል፣ ራሱንም ያረጋጋል፡፡
\v 12 ገዢ ለሐሰተኛ ወሬ ትኩረት የሚሰጥ ከሆነ፣ ሹማምንቶቹ ሁሉ ክፉ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 13 ድሃና ጨቋኝን አንድ የሚያደርጋቸው አለ፣ እግዚአብሔር ለሁለቱም የዓይን ብርሃንን ሰጥቷቸዋልና፡፡
\v 14 ንጉስ ለድሃ በእውነት ከፈረደ፣ ዙፋኑ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል፡፡
\s5
\v 15 በትርና ተግሳጽ ጥበብን ይሰጣሉ፣ ያልተቀጣ ልጅ ግን እናቱን ያሳፍራል፡፡
\v 16 ክፉ ሰዎች ስልጣን ሲይዙ፣ አመጸኝነት ይጨምራል፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን የክፉዎችን ውድቀት ያያሉ፡፡
\s5
\v 17 ልጅህን ቅጣው እረፍትም ይሰጥሃል፤ ለሕይወትህም ደስታን ያመጣል፡፡
\v 18 ትንቢታዊ ራዕይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፣ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው፡፡
\s5
\v 19 አገልጋይ በቃል አይታረምም፣ ቢገባውም ምላሽ አይሰጥም፡፡
\v 20 በቃሎቹ የሚቸኩለውን ሰው ተመልክተሃል? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የበለጠ ተስፋ አለው፡፡
\s5
\v 21 አገልጋዩን ከወጣትነቱ ጀምሮ የሚያሞላቅቅ፣ በመጨረሻ ችግር ይገጥመዋል፡፡
\v 22 ቁጡ ሰው ሁከትን ያነሳሳል፣ ቁጣ የሞላበትም ሰው ብዙ ኃጢአቶችን ይሰራል፡፡
\s5
\v 23 የሰው ትዕቢት ያዋርደዋል፣ ትሁት መንፈስ ያለው ግን ይከበራል፡፡
\v 24 ከሌባ ጋር የሚካፈል ሰው ሕይወቱን ይጠላል፤ እርግማንን ይሰማል መልስ ግን አይሰጥም፡፡
\s5
\v 25 ሰውን መፍራት ወጥመድ ውስጥ ይከትታል፣ በእግዚአብሔር የሚታመን ግን ይጠበቃል፡፡
\v 26 ብዙዎች የገዢን ፊት ይሻሉ፣ ፍትህ ለሰው የሚመጣው ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡
\s5
\v 27 ፍትህን የሚያጓድል ሰው ጽድቅን በሚያደርጉ ሰዎች ፊት የተጠላ ነው፣ መንገዱ ቅን የሆነ ሰው ግን በክፉዎች የተጠላ ነው፡፡
\s5
\c 30
\p
\v 1 የያቄ ልጅ የአጉር ቃል፡- ይህ ሰው ለኢቲኤል፣ ለኢቲኤልና ለኡካል ተናገረ፡-
\v 2 በእርግጠኝነት እኔ ከሰው ሁሉ ይልቅ እንደ እንስሳ ሞኝ ነኝ፣ የሰው ልጅ ማስተዋልም የለኝም፡፡
\v 3 ጥበብን አልተማርሁም፣ ስለ ቅዱሱም እውቀት የለኝም፡፡
\s5
\v 4 ወደ ሰማይ ከፍ ብሎ የሄደና ወደታች የተመለሰ ማን ነው? ነፋሳትን በእጁ መዳፍ ሰብስቦ የያዘ ማን ነው? ውሆችንስ በካባው ላይ የሰበሰበ ማን ነው? የምድርን ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ስሙ ማን ነው፣ የልጁስ ስም ማን ነው? አንተ በእርግጠኝነት ታውቃለህ!
\s5
\v 5 የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትኗል፣ በእርሱ ለሚታመኑ ጋሻ ነው፡፡
\v 6 በቃሉ ላይ ምንም አትጨምር፣ አለዚያ ይገስጽሃልና፣ ሐሰተኛም ትሆናለህ፡፡
\s5
\v 7 ሁለት ነገር እጠይቅሃለሁ፣ ከመሞቴም በፊት እነዚህን ነገሮች አትከልክለኝ፡
\v 8 ከንቱነትንና ውሸትን ከእኔ አርቅ፡፡ ድህነትንም ብልጽግናንም አትስጠኝ፣ የሚያስፈልገኝን መብል ብቻ ስጠኝ፡፡
\v 9 ብዙ ሃብት ካለኝ፣ አንተን ከድቼ “እግዚአብሔርን ማን ነው? ” እላለሁና፣ ድሃ ከሆንኩኝ ደግሞ እሰርቃለሁ፣ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁና፡፡
\s5
\v 10 አገልጋዩን በጌታው ፊት ስሙን አታጥፋ፣ ይረግምሃል አንተም በደለኛ ሆነህ ትገኛለህና፡፡
\s5
\v 11 አባቱን የሚረግም፣ እናቱንም የማይባርክ ትውልድ፣
\v 12 ይህ ትውልድ ራሱን ንጹህ አድርጎ የሚያይ፣ ነገር ግን ከእድፉ ያልጸዳ ትውልድ ነው፡፡
\s5
\v 13 ይህ ትውልድ ዓይናቸው ምንኛ ትዕቢተኛ ነው፣ ሽፋሽፍቶቻቸውም ምንኛ ወደ ላይ ከፍ ያሉ ናቸው!
\v 14 ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ ትውልድ ናቸው፣ ድሆችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ልጆች መካከል ያጠፉ ዘንድ፡፡
\s5
\v 15 አልቅት “ስጡን፣ ስጡን” እያሉ የሚጮሁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉት፡፡ ፈጽሞ የማይጠግቡ ሦስት ነገሮች አሉ፣ ፈጽሞ “በቃኝ” የማይሉ አራት፤
\v 16 እነርሱም ሲኦል፣ የማትወልድ ማህጸን፣ ውሃ የተጠማች መሬትና፣ “በቃኝ” የማትል እሳት ናቸው፡፡
\v 17 በአባት ላይ የሚያፌዝ ለእናት መታዘዝን የሚንቅ ዓይን፣ ዓይኑ በሸለቆ አሞራዎች ይጎጠጉጡአታል፣ በአሞራዎችም ይበላል፡፡
\s5
\v 18 እጅግ የሚያስደንቁኝ ሦስት ነገሮች አሉ፣ አራት ደግሞ ፈጽሞ የማላስተውለው፡-
\v 19 የንስር መንገድ በሰማይ ውስጥ፤ የእባብ መንገድ በቋጥኝ ላይ፤ የመርከብ መንገድ በባህር ልብ ውስጥ፤ የሰውም መንገድ ከወጣት ሴት ጋር ናቸው፡፡
\s5
\v 20 ይህም የአመንዝራ ሴት መንገድ ነው፣ ትበላለች አፏንም ትጠርጋለች፣ “ምንም ስህተት አልሰራሁም” ትላለች፡፡
\s5
\v 21 በሶስት ነገሮች ምድር ትናወጣለች፣ አራተኛውንም መቋቋም አትችልም፡-
\v 22 ባርያ ንጉስ ሲሆን፤ ሞኝ በመብል በጠገበ ጊዜ፤
\v 23 የተጠላች ሴት ትዳር ስትይዝና፤ የቤት ሰራተኛ የእመቤቷን ቦታ ስትወስድ፡፡
\s5
\v 24 በምድር ላይ አራት ነገሮች ትንሽ ናቸው፣ ሆኖም እጅግ ጥበበኞች ናቸው፡-
\v 25 ጉንዳኖች ጠንካራ ያልሆኑ ፍጡራን ናቸው፣ ነገር ግን ምግባቸውን በበጋ ያዘጋጃሉ፤
\v 26 ሽኮኮዎች ብርቱ ያልሆኑ ፍጡሮች ናቸው፣ ነገር ግን ቤታቸውን በአለት ውስጥ ይሰራሉ፡፡
\s5
\v 27 አንበጣዎች ንጉስ የላቸውም፣ ነገር ግን ሁሉም በሰልፍ ይሄዳሉ፡፡
\v 28 እንሽላሊቶችም በሁለት እጅህ ልትይዛቸው ትችላለህ፣ ይሁን እንጂ በነገስታት ቤተ መንግስታት ውስጥ ይገኛሉ፡፡
\s5
\v 29 ግርማ ሞገስ ያለው አረማመድ ያላቸው ሶስት ነገሮች አሉ፣ በአካሄዳቸው ግርማ ሞገስ ያላቸው አራት አሉ፡-
\v 30 አንበሳ፣ ከዱር እንስሳት ሁሉ ብርቱ የሆነና ከምንም ነገር ወደኋላ የማይመለስ ነው፤
\v 31 እየተንጎራደደ የሚሄድ አውራ ዶሮ፤ ፍየል፤ እና በወታደሮቹ የታጀበ ንጉስ ናቸው፡፡
\s5
\v 32 ሞኝ ከሆንህ፣ ራስህንም ከፍ ከፍ የምታደርግ ከሆነ ወይም ክፉ ሃሳብን እያሰብክ ከሆነ፣ እጅህን በአፍህ ላይ አድርግ፡፡
\v 33 የተናጠ ወተት ቅቤ እንደሚወጣው፣ በጣም የታሸ አፍንጫም ደም እንደሚወጣው፣ በቁጣ የሚፈጸሙ ድርጊቶችም ጠብን ያመጣሉ፡፡
\s5
\c 31
\p
\v 1 እናቱ ያስተማረችው የንጉስ ልሙኤል ቃሎች፣
\v 2 ልጄ ሆይ፣ ምንድን ነው? የማሕጸኔ ልጅ ሆይ ምንድን ነው? የስእለቴ ልጅ ሆይ ምንድን ነው?
\v 3 ብርታትህን ለሴቶች አትስጥ፣ ነገስታትን ለሚያጠፉም መንገድህን፡፡
\s5
\v 4 ለነገስታት አይደለም፣ ልሙኤል ሆይ፣ የወይን ጠጅ መጠጣት ለነገስታት አይደለም፣ “ብርቱ መጠጥ የት ነው” ብለው ይጠይቁ ዘንድ ለገዢዎችም አይደለም፡፡
\v 5 ምክንያቱም እነርሱ መጠጥ ከጠጡ የተደነገገውን ሕጉን ይረሳሉ፣ የተጨቆኑ ሰዎችንም መብት ያጣምማሉ፡፡
\s5
\v 6 እየጠፉ ላሉ ሰዎች ብርቱ መጠጥ ስጧቸው፣ መራራ ችግር ውስጥ ላሉትም ወይን ስጧቸው፡፡
\v 7 ይጠጣል ድህነቱንም ይረሳል፣ ችግሩንም አያስታውስም፡፡
\s5
\v 8 መናገር ለማይችሉ ተናገርላቸው፣ እየጠፉም ላሉት ሁሉ ስለ ጉዳያቸው ተናገር፡፡
\v 9 ትክክል ስለሆነው ነገር ጮህ ብለህ ተናገር፣ ፍርድም ስጥ፣ ስለ ድሆችና ስለ ተቸገሩም ሰዎች ጉዳይ መልስ ስጥ፡፡
\s5
\v 10 ችሎታ ያላትን ሴት ማን ሊያገኛት ይችላል? የእርሷ ዋጋ ከእንቁ የበለጠ ነው፡፡
\v 11 የባሏ ልብ በእርሷ ይተማመናል፣ ድሃም አይሆንም፡፡
\v 12 በሕይወት ዘመኗ ሁሉ ለእርሱ መልካም ነገር ታደርግለታለች፣ ክፋትንም አታደርግበትም፡፡
\s5
\v 13 የበግ ጠጉርና የተልባ ትመርጣለች፣ በእጆቿም ደስ ብሏት ትሰራለች፡፡
\v 14 እርሷ እንደ ነጋዴ መርከብ ናት፤ መብሏን ከሩቅ ታመጣለች፡፡
\v 15 በሌሊት ተነስታ ለቤተሰቧ መብልን ታቀርባለች፣ ስራዋንም ለሴት አገልጋዮቿ ታከፋፍላለች፡፡
\s5
\v 16 እርሻን ተመልክታ ትገዛለች፣ በእጆቿም ፍሬ የወይን ተክል ትተክላለች፡፡
\v 17 ራሷን በብርታት ታለብሳለች፣ ክንዶቿንም ታጠነክራለች፡፡
\s5
\v 18 ለእርሷ ጥሩ ትርፍ የሚያመጣላትን ታውቃለች፤ ሌሊቱንም ሙሉ መብራቷ አይጠፋም፡፡
\v 19 እጆቿን በእንዝርቱ ላይ ታስቀምጣለች፣ የሚሽከረከረውንም ክር ትይዛለች፡፡
\s5
\v 20 እጇን ለድሆች ትዘረጋለች፤ ለተቸገሩትም እጆቿን ትዘረጋለች፡፡
\v 21 በረዶም ቢዘንብ ስለ ቤተሰቧ አትፈራም፣ ቤተሰቧ ሁሉ ቀይ ልብስ ለብሰዋልና፡፡
\s5
\v 22 ለመኝታዋ የአልጋ ልብስ ትሰራለች፣ ቀጭን ሐምራዊ ልብስም ትለብሳለች፡፡
\v 23 ባለቤቷም ከአገሩ ሽማግሌዎች ጋር ሲቀመጥ በበሮቹ የታወቀ ይሆናል፣ ፡፡
\s5
\v 24 የሊኖ ልብሶችን ትሰራለች፣ ትሸጣለችም፣ ለነጋዴዎችም መቀነቶችን ታስረክባለች፡፡
\v 25 ጥንካሬንና ክብርን ተላብሳለች፣ ወደፊት የሚመጣውን ጊዜ እያሰበች ትስቃለች፡፡
\s5
\v 26 አፏን በጥበብ ትከፍታለች፣ የደግነት ሕግም በምላሷ ላይ አለ፡፡
\v 27 የቤተሰቦቿን መንገዶች ትመለከታለች፣ የስንፍናንም እንጀራ አትበላም፡፡
\s5
\v 28 ልጆቿም አድገው የተባረክሽ ነሽ ይሏታል፤ ባለቤቷም እንዲህ ብሎ ያመሰግናታል፣
\v 29 “ብዙ ሴቶች መልካምን አድርገዋል፣ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡”
\s5
\v 30 ቁንጅና አሳሳች ነው፣ ውበትም ጠፊ ነው፣ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች፡፡
\v 31 የእጆቿን ፍሬ ስጧት፣ ስራዋቿም በአደባባዮች ያስመሰግኗት፡፡

2811
23-ISA.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,2811 @@
\id ISA
\ide UTF-8
\h ኢሳይያስ
\toc1 ኢሳይያስ
\toc2 ኢሳይያስ
\toc3 isa
\mt ኢሳይያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 የይሁዳ ነገሥታት በሆኑት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ።
\s5
\v 2 ስሙ፣ ምድርም አድምጪ፤ "ልጆችን ወለድሁ አሳደግሁም፣ እነርሱም አመጹብኝ።" ሲል እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\v 3 በሬ የገዢውን፣ አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቀም፥ እስራኤል አልተገነዘበም"
\s5
\v 4 ወዮላችሁ! ኃጢአተኛ ወገንና በደል የተሞላበት ሕዝብ፣ የክፉ አድራጊዎች ልጆች፣ ርኵሰትን የምታደርጉ ልጆች ሆይ! እግዚአብሔርን ትተዋል፣ የእስራኤልንም ቅዱስ አቃልለዋል ወደ ኋላቸውም እየሄዱ ተለይተዋል።
\s5
\v 5 አሁን ድረስ ለምን ትቀሰፋላችሁ? አሁንም አሁንም ዓመፃ ለምን ትጨምራላችሁ? ራስ ሁሉ ለሕመም፣ ልብም ሁሉ ለድካም ሆኗል።
\v 6 ከእግር መርገጫ አንስቶ እስከ ራስ ድረስ ያልታመመ የለውም፤ ቍስልና እበጥ፣ የሚደማ ቊስል ነው፤ አልፈረጠም፣ አልተጠገነም፣ በዘይትም አልለዘበም።
\s5
\v 7 ምድራችሁ ባድማ ናት፤ ከተሞቻችሁ በእሳት ተቃጠሉ፤ እርሻችሁንም በፊታችሁ እንግዶች ይበሉታል፤ ባዕድ እንዳፈረሳት ምድር ባድማ ሆነች።
\v 8 የጽዮንም ሴት ልጅ በወይን ቦታ እንዳለ ዳስ፣ በዱባ አትክልትም እንዳለ ጎጆ፣ እንደተከበበችም ከተማ ሆና ቀረች።
\s5
\v 9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጥቂት ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፣ እንደ ሰዶም በሆንን፣ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።
\s5
\v 10 የሰዶም አለቆች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፣ የአምላካችንን ሕግ አድምጡ።
\v 11 "የመሥዋዕታችሁ ብዙ ጋጋታ ለእኔ ምን ይጠቅመኛል?" ይላል እግዚአብሔር። "የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤያለሁ፤ የበሬና የበግ ጠቦት የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም።
\s5
\v 12 በእኔ ፊት ልትታዩ ብትመጡ፣ ይህን የመቅደሴን አደባባይ መርገጣችሁን ከእጃችሁ የሚሻ ማን ነው?
\v 13 ምናምንቴውን ቍርባን ጨምራችሁ አታምጡ፤ ዕጣን በእኔ ዘንድ አጸያፊ ነው፤ መባቻችሁንና ሰንበታችሁን በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወድድም - እነዚህን የረከሱ ጉባዔዎች አልታገሥም።
\s5
\v 14 መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሣቸውም ደክሜያለሁ።
\v 15 ስለዚህም እጃችሁን በጸሎት ወደ እኔ ብትዘረጉ ዓይኔን ከእናንተ እሰውራለሁ፣ ልመናንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደም ተሞልተዋል።
\s5
\v 16 ታጠቡ፣ ሰውነታችሁንም አንጹ፤ የሥራችሁን ክፋት ከዓይኔ ፊት አስወግዱ፤ ክፉ መሆንን ተዉ፤
\v 17 መልካም ማድረግን ተማሩ፣ ፍርድን ፈልጉ፣ የተጨቆነውን እርዱ፣ አባት ለሌለው ፍረዱለት፣ ስለ መበለቲቱም ተምዋገቱ።"
\s5
\v 18 "አሁን ኑና በአንድ ላይ እንዋቀስ" ይላል እግዚአብሔር፤ "ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን፣ እንደ በረዶ ትነጻለች፤ እንደ ደምም ብትቀላ፣ እንደ ባዘቶ ትጠራለች።
\s5
\v 19 እሺ ብትሉ ብትታዘዙ፣ የምድርን በረከት ትበላላችሁ።
\v 20 ነገር ግን እምቢ ብትሉ፣ ብታምፁም፣ ሰይፍ ይበላችኋል፣" የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
\s5
\v 21 ፍርድ ሞልቶባት የነበረችው የታመነችይቱ ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ ሞልቶባት ነበር፣ አሁን ግን ገዳዮች ሞልተውባታል።
\v 22 ብርሽ ወደ ዝገት ተለወጠ፣ የወይን ጠጅሽ ከውሃ ጋር ተደባለቀ።
\s5
\v 23 አለቆችሽ አመጸኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፣ ዋጋም ለማግኘትም ይሮጣሉ። ለድሀ አደጉ አይፈርዱም፣ የመበለቲቱም ሙግት ወደ እነርሱ አይደርስም።
\s5
\v 24 ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወዮላቸው! የሚቋቋሙኝ ላይ ቍጣዬን እፈጽማለሁ፣ በጠላቶቼ ላይ እበቀላለሁ።
\v 25 እጄንም በአንቺ ላይ አመጣለሁ፣ ዝገትሽንም በጣም አነጻለሁ፣ አለመንጻትሽንም ሁሉ አወጣለሁ፤
\s5
\v 26 ፈራጆችሽንም እንደ ቀድሞ፣ አማካሪዎችሽንም እንደ መጀመሪያው ጊዜ መልሼ አስነሣለሁ፤ ከዚያም በኋላ የጽድቅ ከተማ፣ የታመነችም ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።"
\s5
\v 27 ጽዮን በፍርድ፣ ከእርሷም በንስሃ የሚመለሱ በጽድቅ ይድናሉ።
\v 28 በደለኞችና ኃጢአተኞች ግን በአንድነት ይሰበራሉ፣ እግዚአብሔርንም የሚተዉ ይጠፋሉ።
\s5
\v 29 "በተመኛችኋት የተቀደሰች የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፣ በመረጣችኋትም አትክልት ስፍራ ላይ እፍረት ይይዛችኋልና፤
\v 30 ቅጠልዋ እንደ ረገፈ ዛፍ፣ ውሃም እንደሌለባት አትክልት ትሆናላችሁና።
\s5
\v 31 ኃይለኛውም እንደ ተልባ ጭረት፣ ሥራውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ አብረውም ይቃጠላሉ፣ እነርሱንም የሚያጠፋ የለም።"
\s5
\c 2
\p
\v 1 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም በራእይ ያያቸው ነገሮች።
\v 2 በኋለኞቹ የፍጻሜ ቀናት፣ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ከፍታ ላይ ጸንቶ ይቆማል፣ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይጎርፋሉ።
\s5
\v 3 ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፣ "ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።"
\s5
\v 4 በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፣ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፣ ጦርነትንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም።
\s5
\v 5 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፣ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ።
\v 6 የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፣ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፣ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ፣ የሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃል።
\s5
\v 7 ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፣ ለመዛግብቶቻቸውም ፍጻሜ የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፣ ለሠረገሎቻቸውም ፍጻሜ የለውም።
\v 8 ምድራቸው ደግሞ በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸውም ላደረጉት ለእጃቸው ሥራ ይሰግዳሉ።
\s5
\v 9 ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፣ ግለሰቦችም ይዋረዳሉ፤ ስለዚህ አትቀበላቸው።
\v 10 ከእግዚአብሔር ማሸበርና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግቡ፣ በመሬትም ውስጥ ተሸሸጉ።
\v 11 ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፣ የሰዎችም ኵራት ተጎትታ ትወድቃለች፣ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ይላል።
\s5
\v 12 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፣ እርሱም ይዋረዳል፤
\v 13 ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለው በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፣ በባሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ ይሆናል፣
\s5
\v 14 በረጅሞቹም ተራራዎች ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣
\v 15 በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፣ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፣
\v 16 በተርሴስም መርከቦች ሁሉ ላይ፣ በሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 17 የሰው ሁሉ ክብር ይዋረዳል፣ የሰውም ኵራት ይወድቃል፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
\v 18 ጣዖቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ።
\v 19 እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ፣ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብሩ የተነሣ፣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ይገባሉ።
\s5
\v 20 በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላሉ።
\v 21 እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ይገባሉ።
\v 22 እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፣ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል?
\s5
\c 3
\p
\v 1 ተመልከቱ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ድጋፍንና ብርታትን፡ የእንጀራን ድጋፍ ሁሉ የውኃውንም ድጋፍ ሁሉ ይወስዳል፤
\v 2 ኃያሉንም፣ ተዋጊውንም፣ ፈራጁንም፣ ነቢዩንም፣ ምዋርተኛውንም፣ ሽማግሌውንም፤
\v 3 የአምሳ አለቃውንም፣ ከበርቴ የሆነውን ዜጋ፣ አማካሪውንም፣ የብልኃት ሠራተኛውንም፣ አስማት አዋቂውንም ይነቅላል።
\s5
\v 4 "አለቆቻቸው እንዲሆኑ ተራ ወጣቶችን አስነሣባቸዋለሁ፣ ብላቴናውም ይገዛቸዋል።
\v 5 ሕዝቡም ይጨቆናሉ፣ ሰው በሰው ላይ፣ ሰውም በባልንጀራው ላይ ይገፋፋል፤ ብላቴናውም በሽማግሌው ላይ የተጠቃውም በከበርቴው ላይ ይኰራል።
\s5
\v 6 ሰውም በአባቱ ቤት ውስጥ ወንድሙን ይዞ፣ 'አንተ ልብስ አለህ፤ አለቃም ሁንልን፣ ይህችም ባድማ ከኃላፊነትህ በታች ትሁን' ይለዋል።
\v 7 በዚያ ቀን ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ ይላል፣ 'እኔ በቤቴ ውስጥ እንጀራ ወይም ልብስ የለኝምና ባለ መድኃኒት አልሆንም። በሕዝቡም ላይ አለቃ አታደርጉኝም" ይላል።
\s5
\v 8 ንጉሣዊ ሥልጣኑን ያረክሱ ዘንድ ንግግራቸውና ሥራቸው በእግዚአብሔር ላይ ነውና ኢየሩሳሌም ተፈታች ይሁዳም ወደቀ።
\v 9 የፊታቸውም እፍረት ይመሰክርባቸዋል፤ እንደ ሰዶምም ኃጢአታቸውን ያወራሉ፤ አይሠውሩአትም። በራሳቸው ላይ ጥፋትን ሠርተዋልና ለነፍሳቸው ወዮ!
\s5
\v 10 የሥራውን ፍሬ ይበላልና፣ ጻድቁን መልካም ይሆንልሃል በሉት።
\v 11 እንደ እጁ ሥራ ፍዳው ይደረግበታልና ለበደለኛ ወዮ! ክፉም ደርሶበታል።
\v 12 ሕዝቤን አስገባሪዎቻቸው ይገፉአቸዋል፣ ሴቶችም ይሠለጥኑባቸዋል። ሕዝቤ ሆይ፣ መሪዎቻችሁ ያስቱአችኋል የምትሄዱበትንም መንገድ አቅጣጫ ያጠፋሉ።
\s5
\v 13 እግዚአብሔር በፍርድ ቤት ሊፈርድ ተነሥቶአል፣ በሕዝቡም ላይ ሊፈርድ ቆሞአል።
\v 14 እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ይፋረዳል፡ "የወይኑን ቦታ የበላችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድሆች የበዘበዛችሁት በቤታችሁ አለ፤
\v 15 ሕዝቤንስ ለምን ታደቅቁአቸዋላችሁ? የድሆችንስ ፊት ለምን ትፈጫላችሁ?" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 16 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፣ የጽዮን ቈነጃጅት ኰርተዋልና፣ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፣ ፈንጠርም እያሉ፣ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉ።
\v 17 ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት አናት በበሽታ ቡሀነት ይመታል፣ እግዚአብሔርም መላጣ ያደርጋቸዋል።
\s5
\v 18 በዚያም ቀን ጌታ የእግር አልቦውን ክብር፣ መርበብንም፣ ጨረቃ የሚመስለውንም ጌጥ፣
\v 19 የጆሮ እንጥልጥሉንም፣ አንባሩንም፣ መሸፈኛውንም፣
\v 20 ቀጸላውንም፣ የቁርጭምጭሚት ሰንሰለቱንም፣ መቀነቱንም፣ የሽቱውንም ዕቃ።
\s5
\v 21 አሸንክታቡንም፣ የእጅና የአፍንጫ ቀለበቱንም ያስወግዳል፤
\v 22 የዓመት በዓል ልብሶችን፣ መጐናጸፊያውንም፣ መሸፈኛውንም፣ ከረጢቱንም፤
\v 23 የእጅ መስተዋቱንም፣ ከጥሩ በፍታ የተሰራውንም ልብስ፣ ራስ ማሰሪያውንም፣ ዓይነ ርግቡንም ያስወግዳል።
\s5
\v 24 በሽቱ ፋንታ ግማት፣ በመታጠቂያውም ፋንታ ገመድ፣ ጠጕርንም በመንቀስ ፋንታ ቡሀነት፣ በመጐናጸፊያ ፋንታ ማቅ፣ በውበትም ፋንታ ጠባሳ ይሆናል።
\v 25 ጕልማሶችሽ በሰይፍ፣ ኃያላንሽም በውጊያ ይወድቃሉ።
\v 26 በሮችዋ ያዝናሉ ያለቅሱማል፤ እርስዋም ብቻዋን በምድር ላይ ትቀመጣለች።
\s5
\c 4
\p
\v 1 በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች "የገዛ እንጀራችንን እንበላለን የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፥ ውርደታችንንም አርቅ" ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።
\v 2 በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ቍጥቋጥ ውብና የከበረ ይሆናል፣ ከእስራኤልም ወገን ላመለጡ ሰዎች የምድሪቱን ፍሬ ለትምክሕትና ለውበት ይሆናል።
\s5
\v 3 ከዚያም፣ ጌታ የጽዮንን ቈነጃጅት እድፍ ባጠበ ጊዜ፣ የኢየሩሳሌምንም ደም በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስ ከመካከልዋ ባነጻ ጊዜ፣
\v 4 በጽዮን የቀረ በኢየሩሳሌምም የተረፈ፣ በኢየሩሳሌም ለሕይወት የተጻፈ ሁሉ፣ ቅዱስ ይባላል።
\s5
\v 5 እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ማደሪያ ሁሉ በጉባኤያቸውም ላይ፣ በቀን ዳመናንና ጢስን፣ በሌሊትም የሚቃጠለውን የእሳት ብርሃን ይፈጥራል፤ በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።
\v 6 በቀን ከሙቀት ለጥላ፣ ከዐውሎ ነፋስና ከዝናብም ለመጠጊያና ለመሸሸጊያ ጎጆ ይሆናል።
\s5
\c 5
\p
\v 1 አሁን ስለ ወዳጄና ስለ ወይን ቦታው ለወዳጄ ቅኔ እቀኛለሁ። ለወዳጄ በለመለመው ኮረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው።
\v 2 በዙሪያው ቈፈረ፣ ድንጋዮችንም ለቅሞ አወጣ፣ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት። በመካከሉም ግንብ ሠራ፣ ደግሞም የመጥመቂያ ጕድጓድ ማሰበት። ወይንንም ያፈራ ዘንድ ጠበቀ፣ ዳሩ ግን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ።
\s5
\v 3 ስለዚህ አሁን፣ እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ የይሁዳ ሰዎች ሆይ፤ በእኔና በወይኑ ቦታዬ መካከል ፍረዱ።
\v 4 ለወይኔ ያላደረግሁለት፥ ከዚህ በተጨማሪ አደርግለት ዘንድ የሚገባኝ ምንድር ነው? መልካም ወይንን ያፈራል ብዬ ስትማመን፣ ስለ ምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ?
\s5
\v 5 አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን አስታውቃችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለማሰማርያም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፣ ለመራገጫም ይሆናል።
\v 6 ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይቈረጥም፣ አይኰተኰትም፤ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ዳመናዎችን አዝዛለሁ።
\s5
\v 7 የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፣ የደስታውም አትክልት የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ይጠብቅ ነበር፣ እነሆም ግድያ ሆነ፤ ጽድቅንም ይተማመን ነበር፣ ይልቅ እርዳታ የሚለምን ጩኸት ሆነ።
\s5
\v 8 ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፣ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
\v 9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ ታላላቆቹና መልካም የሆኑት ቤቶች ሳይቀሩ ባድማ ይሆናሉ፣ የሚኖርባቸውም አይገኝም።
\v 10 ከወይኑ ቦታ ዐሥር ጥማድ በሬ ካረሰው አንድ የባዶስ መስፈሪያ ብቻ ይወጣል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር አንድ የኢፍ መስፈሪያ ብቻ ይሰጣል።
\s5
\v 11 ጠንካራ መጠጥን ለማፈላለግ በጠዋት ለሚነቊ፣ የወይን ጠጅም እስኪያቃጥላቸው እስከ ሌሊት ድረስ ለሚዘገዩ ወዮላቸው!
\v 12 መሰንቆና በገና፣ ከበሮና እምቢልታም፣ የወይን ጠጅም በግብዣቸው አለ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ ግን አልተመለከቱም፣ እንዲሁም እጁ ያደረገችውን አላስተዋሉም።
\s5
\v 13 ስለዚህ ሕዝቤ ባለማወቃቸው ወደ ምርኮ ሄዱ፣ መሪዎቻቸውም ተራቡ፣ ሕዝባቸውም የሚጠጡት የላቸውም።
\v 14 ስለዚህም ሲኦል የመዋጥ ፍላጎትዋን አስፍታለች፣ አፍዋንም ያለ ልክ ከፍታለች፤ ከበርቴዎቻቸውና አዛውንቶቻቸው፣ ባለጠጎቻቸውም ደስተኞቻቸውም ወደ ሲዖል ይወርዳሉ።
\s5
\v 15 ሰውም ይጐሰቍላል፣ ሰውም ይዋረዳል፣ የትዕቢተኞችም ዓይን ትዋረዳለች።
\v 16 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍርድ ከፍ ከፍ ብሎአል፣ ቅዱሱም አምላክ በጽድቅ ተቀድሶአል።
\v 17 የበግ ጠቦቶች በገዛ መሰማርያቸው ውስጥ፣ እንዲሁም በባለጠጋ ሰዎች ጥፋት ውስጥ ይሰማራሉ፣ ጠቦቶችም ይግጣሉ።
\s5
\v 18 በደልን በምናምንቴ ገመድ፣ ኃጢአትንም በሰረገላ ማሰሪያ ወደ ራሳቸው ለሚስቡ፣ እናይ ዘንድ ይቸኵል፣
\v 19 "ሥራውንም ያፋጥን፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ምክር ትቅረብ፣ ትምጣ ለሚሉ ወዮላቸው!"
\s5
\v 20 ክፉውን መልካም፣ መልካሙን ክፉ ለሚሉ፤ ጨለማውን ብርሃን፣ ብርሃኑንም ጨለማ ለሚያደርጉ፤ ጣፋጩን መራራ፣ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
\v 21 በገዛ ዓይናቸው ዘንድ ጥበበኞች፣ በነፍሳቸውም አስተዋዮች ለሆኑ ወዮላቸው!
\s5
\v 22 የወይን ጠጅ ለመጠጣት ኃያላን፣ የሚያሰክረውንም ብርቱ መጠጥ ለማደባለቅ ጨካኞች ለሆኑ፤
\v 23 በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፣ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!
\s5
\v 24 ስለዚህ የእሳት ወላፈን ቃርሚያን እንደሚበላ፣ እብቅም በነበልባል ውስጥ እንደሚጠፋ፣ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፣ ቡቃያቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፣ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ገፍተዋልና፣ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።
\s5
\v 25 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ ነድዶአል፣ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ ቀጥቷቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፣ ሬሳቸውም በአደባባይ ላይ እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ በድጋሚ ለመምታት ገና ተዘርግታለች።
\s5
\v 26 ለአሕዛብም በሩቅ ምልክትን ያቆማል፣ ከምድርም ዳርቻ በፉጨት ይጠራቸዋል። ተመልከቱ፣ እየተጣደፉ ፈጥነው ይመጣሉ።
\s5
\v 27 በመካከላቸው ደካማና ስንኵል የለባቸውም፣ የሚያንቀላፋና የሚተኛም የለም፤ የወገባቸውም መቀነት አይፈታም፣ የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም፤
\v 28 ፍላጾቻቸው ተስለዋል፣ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፤ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ፣ የሰረገሎቻቸውም መንኰራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ነው።
\s5
\v 29 ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፣ እንደ አንበሳ ደቦሎችም ያገሣሉ። ንጥቂያንም ይዘው ያገሣሉ፣ ይወስዱትማል፣ የሚታደግም የለም።
\v 30 በዚያም ቀን እንደ ባሕር መትመም ይተምሙባቸዋል፤ ወደ ምድርም ቢመለከቱ፣ ጨለማና መከራ ይመለከታል፤ ብርሃንም በደመናዎችዋ ውስጥ ጨልሞአል።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት፣ እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፣ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።
\v 2 ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፣ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፣ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር።
\s5
\v 3 አንዱም አንደኛውን በመጥራት፣ "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር! ምድር ሁሉ በክብሩ ተሞልታለች" እያለ ይጮኽ ነበር።
\s5
\v 4 የመድረኩም መሠረት ከሚጮኹት ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፣ ቤቱም ጢስ ሞላበት።
\v 5 ከዚያ እኔ፣ "ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፣ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ፣ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!" አልሁ።
\s5
\v 6 ከዚያም ከሱራፌል አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፤ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ።
\v 7 በዚያም አፌን ዳሰሰበትና። "ተመልከት፣ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፣ ኃጢአትህም ተሰረየልህ።" አለኝ።
\s5
\v 8 የጌታንም ድምፅ፣ "ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል?" ሲል ሰማሁ። እኔም፣ "እኔ አለሁ፤ እኔን ላከኝ።" አልሁ።
\v 9 እርሱም፣ "ሂድና ይህን ሕዝብ፣ ትሰማላችሁ፣ አታስተውሉምም፤ ታያላችሁ፣ አትመለከቱምም" በላቸው።
\s5
\v 10 በዓይናቸው እንዳያዩ፣ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፣ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፣ ተመልሰውም እንዳይፈወሱ፣ የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፣ ጆሮአቸውንም አደንቍር፣ ዓይናቸውንም አሳውር" አለኝ።
\s5
\v 11 ከዚያም እኔ፣ "ጌታ ሆይ፣ እስከ መቼ ድረስ ነው?" አልሁ። እርሱም ሲመልስ፣ "ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፣ ቤቶችም ሰው የሌለባቸው እስኪሆኑ፣ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ፣
\v 12 እግዚአብሔርም ሰዎችን እስኪያርቅ፣ በምድርም መካከል ውድማው መሬት እስኪበዛ ድረስ ነው።" አለ።
\s5
\v 13 በእርስዋም ዘንድ አንድ ዐሥረኛ ሰው ቀርቶ እንደ ሆነ እነርሱ ደግሞ በድጋሚ ይቃጠላሉ፤ በተቈረጡ ጊዜ ጉቶቻቸው እንደ ቀሩ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሆኖ፣ ጉቶው የተቀደሰ ዘር ይሆናል።"
\s5
\c 7
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የሶርያ ንጉሥ ረአሶን፣ የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ፣ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፣ ሊያሸንፉአትም አልቻሉም።
\v 2 ለዳዊትም ቤት፣ ሶርያ ከኤፍሬም ጋር እንደተባበሩ ወሬ ተነገረ። የእርሱም ልብ፣ እንዲሁም የሕዝቡም ልብ፣ የዱር ዛፍ በነፋስ እንድትናወጥ ተናወጠ።
\s5
\v 3 ከዚያም እግዚአብሔር ኢሳይያስን፣ "አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ።
\v 4 እንዲህም በለው፣ 'ተጠንቀቅ፣ ዝምም በል፣ ስለ እነዚህ ስለሚጤሱ ስለ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፣ ስለ ሶርያና ስለ ረአሶን፣ ስለ ሮሜልዩም ልጅ ቍጣ አትፍራ፣ ልብህም አይድከም።
\s5
\v 5 ሶርያና ኤፍሬም የሮሜልዩም ልጅ፣
\v 6 "ወደ ይሁዳ እንውጣ እናስጨንቃትም፣ እንስበራትም፣ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥባት" ብለው ክፋት ስለ መከሩብህ፤
\s5
\v 7 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም፣
\v 8 የሶርያ ራስ ደማስቆ ስለሆነ፣ የደማስቆም ራስ ረአሶን ስለሆነ አይከናወንም። በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ ኤፍሬም ይሰባበራልና ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ አይሆንም፤
\v 9 የኤፍሬምም ራስ ሰማርያ ነው፣ የሰማርያም ራስ የሮሜልዩ ልጅ ነው። በእምነት ባትጸኑ፣ በእርግጥም በዋስትና አትጸኑም።"
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም ደግሞ አካዝን እንዲህ ብሎ ተናገረው፣
\v 11 "ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለምን።"
\v 12 አካዝ ግን፣ "አልለምንም፣ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም" አለ።
\s5
\v 13 ስለዚህ ኢሳይያስ ሲመልስ፣ "እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፣ ስሙ። በውኑ የሰውን ትእግሥት መፈታተናችሁ ቀላል ነውን? ዩአምላኬን ትእግሥት ደግሞ ልትፈታተኑ ይገባችኋልን?
\v 14 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ ተመልከቱ፣ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
\v 15 ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሲያውቅ ቅቤና ማር ይበላል።
\s5
\v 16 ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙን ለመምረጥ ከማወቊ በፊት፣ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት አገር ባድማ ትሆናለች።
\v 17 እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።"
\s5
\v 18 በዚያም ጊዜ እግዚአብሔር በግብጽ ወንዝ ርቀት ያለውን ዝምብ፣ በአሦርም አገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል።
\v 19 ሁሉም ይመጡና በበረሃ ሸለቆ፣ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ በእሾህ ቍጥቋጦ ሁሉ ላይ፣ በማሰማርያውም ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ።
\s5
\v 20 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይላጫል።
\v 21 በዚያም ቀን፣ ሰው አንዲት ጊደርንና ሁለት በጎችንም በሕይወት ያቆያል፣
\v 22 ደግሞም ከሚሰጡት ወተት ብዛት የተነሣ ቅቤ ይበላል፤ በአገሪቱም መካከል የቀረ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል።
\s5
\v 23 በዚያም ቀን፣ ሺህ ብር የተገመተ ሺህ የወይን ግንድ በነበረበት ስፍራ ሁሉ ለኵርንችትና ለእሾህ ብቻ ይሆናል።
\v 24 ኵርንችትና እሾህ በምድር ሁሉ ላይ ነውና በፍላጻና በቀስት ወደዚያ ይገባሉ።
\v 25 በመቈፈርያም ወደ ተቈፈሩ ኮረብቶች ሁሉ ከኵርንችትና እሾህ ፍርሃት የተነሣ ወደዚያ አትሄድም፤ ነገር ግን የበሬ ማሰማርያና የበግ መራገጫ ይሆናል።
\s5
\c 8
\p
\v 1 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ታላቅ ሰሌዳ ወስደህ፣ 'ምርኮ ፈጠነ፣ ብዝበዛ ቸኰለ' ብለህ ጻፍበት።
\v 2 የታመኑትን ሰዎች፣ ካህኑን ኦርዮንና የበራክዩን ልጅ ዘካርያስን ምስክሮች አድርግልኝ" አለኝ።
\s5
\v 3 ወደ ነቢይቱም ቀረብሁ፣ እርስዋም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች።
\v 4 ከዚያም እግዚአብሔር፣ "ሕፃኑ 'አባባ' እና 'እማማ' በማለት መጣራት ከማወቊ በፊት የደማስቆን ሀብትና የሰማርያን ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወስዳልና ስሙን ምርኮ ፈጠነ፣ ብዝበዛ ቸኰለ ብለህ ጥራው፤" አለኝ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር በድጋሚ ተናገረኝ፣ እንዲህም አለኝ፣
\v 6 "ይህ ሕዝብ በቀስታ የሚሄደውን የሰሊሆምን ውኃ ጠልቶአልና፣ ረአሶንንና የሮሜልዩንም ልጅ ወዶአልና፣
\v 7 ስለዚህ እግዚአብሔር ብርቱና ብዙ የሆነውን የወንዝ ውኃ፣ የአሦርን ንጉሥና ክብሩን ሁሉ፣ ያመጣባቸዋል። መስኖውንም ሁሉ ሞልቶ ይወጣል፣ በዳሩም ሁሉ ላይ ይፈስሳል፤
\s5
\v 8 እስከ አንገት እስኪደርስ ድረስ እየጐረፈ ወደ ይሁዳ ይገባል፣ እያጥለቀለቀም ያልፋል። አማኑኤል ሆይ፣ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች።"
\s5
\v 9 አሕዛብ ሆ፣ እወቁና ደንግጡ፣ እናንተም አገራችሁ የራቀ ሁሉ፣ አድምጡ፤ ታጠቁም፣ ደንግጡ፤ ታጠቁ፤ ደንግጡ።
\v 10 ዕቅድን አብጁ፣ ነገር ግን አይከናወንም፤ ትእዛዙን ተናገሩ፣ ነገር ግን አይከናወንም፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር በጽኑ እጁ ጭምር እንዲህ ተናገረኝ፣ በዚህም ሕዝብ መንገድ አንዳልሄድ አስጠነቀቀኝ፣ እንዲህም አለኝ።
\v 12 ይህ ሕዝብ፣ አድማ ነው የሚሉትን ሁሉ፣ አድማ ነው አትበሉ፤ ማስፈራታቸውንም አትፍሩ፣ አትደንግጡ።
\v 13 ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፤ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።
\s5
\v 14 እርሱም ለመቅደስ ይሆናል፤ ነገር ግን ለሁለቱ ለእስራኤል ቤቶች ለዕንቅፋት ድንጋይና ለማሰናከያ ዓለት ይሆናል። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለወጥመድና ለአሽክላ ይሆናል።
\v 15 ብዙዎችም በእርሱ ይሰናከላሉ፣ ይወድቁማል፣ ይሰበሩማል፣ ይጠመዱማል፣ ይያዙማል።
\s5
\v 16 ምስክሬን እሰር፣ በደቀ መዛሙርቶቼም መካከል ሕጉን አትም።
\v 17 ከያዕቆብም ቤት ፊቱን የሰወረውን እግዚአብሔርን እጠብቃለሁ፣ እጠብቀዋለሁም።
\v 18 ተመልከቱ፣ እኔና እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ለእስራኤል በጽዮን ተራራ ከሚኖረው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክትና ተአምራት ነን።
\s5
\v 19 እነርሱ፣ "የሚጮኹትንና ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው የሚናገሩትን መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ጠይቁ" ባሉአችሁ ጊዜ፣ ሕዝቡ ከአምላኩ መጠየቅ አይገባውምን? ወይስ ለሕያዋን ሲሉ ሙታንን ይጠይቃሉን?
\v 20 ስለዚህ ለሕግና ለምስክር ትኩረት ልትሰጡ ይገባል! እንዲህም ያለውን ቃል ባይናገሩ፣ የንጋት ብርሃን ስለሌላቸው ነው።
\s5
\v 21 እነርሱም ተጨንቀውና ተርበው ያልፋሉ። በተራቡም ጊዜ፣ ተቈጥተው ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይረግማሉ፣ ፊታቸውን ወደ ላይያቀናሉ።
\v 22 ወደ ምድርም ይመለከታሉ፣ ተመልከቱ፣ መከራና ጨለማ፣ የሚያስጨንቅም ጭጋግ አለ። ወደ ድቅድቅም ጨለማ ይሰደዳሉ።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ነገር ግን ተጨንቃ ለነበረች ጨለማ አይሆንም። በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ፣ በኋለኛው ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል።
\v 2 በጨለማ የሄደ ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤ በሞት ጥላ አገርም ለኖሩ ብርሃን በራላቸው።
\s5
\v 3 ሕዝቡን አብዝተሃል፣ ደስታንም ጨምረህላቸዋል፤ በመከር ደስ እንደሚላቸው፣ ሰዎችም ምርኮን ሲካፈሉ ደስ እንደሚላቸው በፊትህ ደስ ይላቸዋል።
\s5
\v 4 በምድያም ጊዜ እንደ ሆነ የሸክሙን ቀንበር የጫንቃውንም በትር የአስጨናቂውንም ዘንግ ሰብረሃል።
\v 5 የሚረግጡ የሰልፈኞች ጫማ ሁሉ፣ በደምም የተለወሰ ልብስ ለቃጠሎ ይሆናል፣ እንደ እሳት ማቃጠያም ሆኖ ይቃጠላል።
\s5
\v 6 ሕፃን ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
\v 7 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፣ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።
\s5
\v 8 ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃልን ሰደደ፣ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።
\v 9 በትዕቢትና በልብ ኵራት የሚናገሩ በኤፍሬምና በሳርያ የሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ።
\v 10 "ጡቡ ወድቆአል፣ ነገር ግን በተወቀረ ድንጋይ እንሠራለን፤ የሾላ ዛፎች ተቈርጠዋል፣ ነገር ግን ዝግባን እንተካባቸዋለን" የሚሉት ሁሉ ያውቃሉ።
\s5
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር በረአሶን ላይ በጽዮን ተራራ ተቋቋሚ ያስነሣበታል፣
\v 12 ጠላቶቹን ሶርያውያንንም ከምሥራቅ፣ ፍልስጥኤማውያንንም ከምዕራብ ያንቀሳቅስበታል፤ እስራኤልንም በተከፈተ አፍ ይበሉታል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
\s5
\v 13 ሕዝቡ ግን ወደ ቀሠፋቸው አልተመለሱም፣ የሠራዊትንም ጌታ እግዚአብሔርን አልፈለጉም።
\v 14 ስለዚህ እግዚአብሔር ራስና ጅራትን፣ የሰሌኑን ቅርንጫፍና እንግጫውን በአንድ ቀን ከእስራኤል ይቆርጣል።
\v 15 ሽማግሌውና ከበርቴው እርሱ ራስ ነው፤ በሐሰትም የሚያስተምር ነቢይ እርሱ ጅራት ነው።
\s5
\v 16 ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፤ በእነርሱ የሚመሩትም ይዋጣሉ።
\v 17 ስለዚህም ሰው ሁሉ ዝንጉና ክፉ ሠሪ ነውና፣ አፍም ሁሉ ስንፍናን ይናገራልና ስለዚህ ጌታ በጕልማሶቻቸው ደስ አይለውም፥ ለድሀ አደጎቻቸውና ለመበለቶቻቸውም አይራራም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
\s5
\v 18 ክፋት እንደ እሳት ይቃጠላል፤ ኵርንችቱንና እሾሁን ይበላል፤ ጭፍቅ የሆነውንም ዱር ያቃጥላል፥ ጢሱም ተትጐልጕሎ እንደ ዓምድ ይወጣል።
\v 19 በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ቍጣ ምድር ተቃጥላለች፤ ሕዝቡም እሳት እንደሚበላው እንጨት ሆኖአል፤ ሰውም ለወንድሙ ራርቶ አያድንም።
\s5
\v 20 ሰው ከቀኙ በኩል ሥጋ ቆርጦም ይራባል፤ ሥጋውን በግራ በኩል ይበላል አይጠግብምም። እያንዳንዱም የገዛ ራሱን ክንድ ሥጋ ይበላል፤
\v 21 ምናሴ ኤፍሬምን፣ ኤፍሬምም ምናሴን ይበላል፤ እነርሱም በአንድነት የይሁዳ ጠላቶች ይሆናሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ልትመታ ትዘረጋለች።
\s5
\c 10
\p
\v 1 መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፣ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፣ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፣
\v 2 የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፣ ክፉንም ጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!
\s5
\v 3 በፍርድ ቀን፣ መከራም ከሩቅ በሚመጣበት ዘመን ምን ታደርጉ ይሆን? ለእርዳታስ ወደ ማን ትሸሻላችሁ? ብልጥግናችሁንስ ወዴት ትተዉታላችሁ?
\v 4 ከእስረኞች በታች ይጐነበሳሉ፣ ከተገደሉትም በታች ይወድቃሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፣ ነገር ግን እጁ ገና ልትመታ ተዘርግታለች።
\s5
\v 5 ለቍጣዬ በትር ለሆነ፣ የመዓቴም ጨንገር በእጁ ላለ ለአሦር ወዮለት!
\v 6 እርሱንም በዝንጉ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፣ ምርኮውንና ብዝበዛውንም ይወስድ ዘንድ እንደ አደባባይም ጭቃ የተረገጡ ያደርጋቸው ዘንድ በምቈጣቸው ሰዎች ላይ አዝዘዋለሁ።
\s5
\v 7 እርሱ እንዲሁ አያስብም፣ በዚህ ሁኔታ አይወጥንም። ነገር ግን በልቡ በርካታ አሕዛብን ለማጥፋትና ለመቍረጥ በልቡ አለ።
\v 8 እንዲህ ብላልና፣ "መሳፍንቴ ሁሉ ነገሥታት አይደሉምን?
\v 9 ካልኖ እንደ ከርከሚሽ አይደለችምን? ሐማትስ እንደ አርፋድ አይደለችምን? ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደለችምን?
\s5
\v 10 የተቀረጹ ምስሎቻቸው ከኢየሩሳሌምና ከሰማርያ ምስሎች የበለጡትን የጣዖቶችን መንግሥታት እጄ እንደረታች፣
\v 11 በሰማርያና በጣዖቶችዋም እንዳደረግሁ፣ እንዲሁስ በኢየሩሳሌምና በጣዖቶችዋ አላደርግምን?"
\s5
\v 12 ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ፣ "የአሦርን ንጉሥ የኩሩ ልብ ፍሬን የዓይኑንም ከፍታ ትምክሕት እቀጣለሁ።"
\v 13 እርሱ እንዲህ ብሎአልና፣ "አስተዋይ ነኝና በእጄ ኃይልና በጥበቤ አደረግሁት፤ የአሕዛብን ድንበሮች አራቅሁ፣ ሀብታቸውንም ዘረፍሁ፣ እንደ ጀግናም ሆኜ በምድር የተቀመጡትን አዋረድሁ፤
\s5
\v 14 እጄም የአሕዛብን ባለጠግነት እንደ ወፍ ቤት አገኘች፤ የተተወም እንቍላል እንደሚሰበሰብ፣ እንዲሁ እኔ ምድርን ሁሉ ሰበሰብሁ። ክንፉን የሚያራግብ አፉንም የሚከፍት የሚጮኽም የለም።"
\s5
\v 15 በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ስለ ራሱ ይመካልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ላይ ራሱን ይክባልን? ይህስ፣ በትር የሚያነሣውን እንደ መነቅነቅ ዘንግም እንጨት ያይደለውን እንደ ማንሣት ያህል ነው።
\v 16 ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወፍራሞች ጦረኞቹ ላይ ክሳትን ይልካል፤ ከክብሩም በታች ቃጠሎው እንደ እሳት መቃጠል ይነድዳል።
\s5
\v 17 የእስራኤልም ብርሃን እንደ እሳት፣ ቅዱሷም እንደ ነበልባል ይሆናል፤ እሾሁንና ኵርንችቱን በአንድ ቀን ያቃጥላል ይበላውማል።
\v 18 ከነፍስም እስከ ሥጋ ድረስ የዱሩንና የሚያፈራውን እርሻ ክብር ይበላል፣ ይህም የታመመ ሰው እንደሚሰለስል ይሆናል።
\v 19 ታናሽ ብላቴናም ይጽፋቸው ዘንድ እስኪችል ድረስ የቀሩት የዱር ዛፎች በቍጥር ጥቂት ይሆናሉ።
\s5
\v 20 በዚያም ቀን፣ የእስራኤል ቅሬታ ከያዕቆብም ቤት ያመለጡት ከእንግዲህ ወዲህ በመቱአቸው ላይ አይደገፉም፣ ነገር ግን በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይደገፋሉ።
\v 21 የያዕቆብም ቅሬታ ወደ ኃያል አምላክ ይመለሳሉ።
\s5
\v 22 እስራኤል ሆይ፣ የሕዝብህ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይመለሳል። ጽድቅ የተትረፈረፈበትም ጥፋት ተወስኖአል።
\v 23 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ያለቀ የተቈረጠ ጥፋትን በምድር ሁሉ መካከል ይፈጽማል።
\s5
\v 24 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በጽዮን የምትኖር ሕዝቤ ሆይ አሦርን አትፍራ። አሦር በበትር ይመታሃል፣ ግብጽም እንዳደረገ ዘንጉን ያነሣብሃል።
\v 25 ቍጣዬ እስኪፈጸም መዓቴም እስኪያጠፋቸው ድረስ በጣም ጥቂት ጊዜ ቀርቶአልና አትፍራው።"
\s5
\v 26 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ምድያምን በሔሬብ ዓለት በኩል እንደ መታው ጅራፍ ያነሣበታል፤ በትሩንም በባሕር ላይ ያነሣል፣ በግብጽም እንዳደረገ ያነሣዋል።
\v 27 በዚያም ቀን፣ ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከአንገትህ ላይ ይወርዳል፤ ቀንበሩም ከአንገትህ ከፍተኛ ውፍረት የተነሣ ይሰበራል።
\s5
\v 28 ጠላት ወደ አንጋይ መጥቶአል፤ በመጌዶን በኩል አልፎአል፤ በማክማስ ውስጥ ዕቃውን አኑሮአል፤
\v 29 በመተላለፊያ አልፎአል፤ በጌባ ማደሪያው ነው፤ ራማ ደንግጣለች፤ የሳኦል ጊብዓ ኰብልላለች።
\s5
\v 30 አንቺ የጋሊም ልጅ ሆይ፥ በታላቅ ድምፅሽ ጩኺ፤ ላይሳ ሆይ፥ አድምጪ! አንቺ ምስኪን ዓናቶት ሆይ፣ መልሽላት!
\v 31 መደቤና እየሸሸች ናት፣ በግቤርም የሚኖሩ ቤተሰቦቻቸውን አሽሽተዋል።
\v 32 ዛሬ በኖብ ይቆማል፤ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ በኢየሩሳሌም ኮረብታ ላይ ቡጢውን ይንጣል።
\s5
\v 33 ተመልከቱ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅርንጫፎቹን በሚያስፈራ ኃይል ይቈርጣል፤ በቁመት የረዘሙትም ይቈረጣሉ፣ ከፍ ያሉትም ይዋረዳሉ።
\v 34 ጭፍቅ የሆነውንም ዱር በመጥረቢያ ይቈርጣል፣ ሊባኖስም በኃያሉ እጅ ይወድቃል።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፣ የሥሩም ቍጥቋጥ ፍሬን ያፈራል።
\v 2 የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኃይል መንፈስ፣ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
\s5
\v 3 እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል፤ ዐይኑም እንደምታይ አይፈርድም፣ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤
\v 4 ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፣ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል። በአፉም በትር ምድርን ይመታል፣ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።
\v 5 የወገቡ መታጠቂያ ጽድቅ፣ የጎኑም መቀነት ታማኝነት ይሆናል።
\s5
\v 6 ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋር ይኖራል፣ ነብርም ከፍየል ጠቦት ጋር ይተኛል፤ ጥጃና የአንበሳ ደቦል፣ ፍሪዳም በአንድነት ያርፋሉ፤ ትንሽም ልጅ ይመራቸዋል።
\v 7 ላምና ድብ አብረው ግጦሽ ይውላሉ፣ ግልገሎቻቸውም በአንድነት ያርፋሉ። አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል።
\s5
\v 8 ሕፃን በእባብ ጕድጓድ ላይ ይጫወታል፣ ጡት የጣለውም ሕፃን በእፉኝት ቤት ላይ እጁን ይጭናል።
\v 9 በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይ አይጐዱም አያጠፉምም፤ ውኃ ባሕርን እንደሚከድን ምድር እግዚአብሔርን በማወቅ ትሞላለችና።
\s5
\v 10 በዚያም ቀን፣ ለአሕዛብ ምልክት ሆኖ ይቆማል። የእሴይን ሥር አሕዛብ ይፈልጉታል፣ ማረፊያውም የተከበረ ይሆናል።
\v 11 በዚያም ቀን፣ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብጽ፣ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፣ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፣ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደ ገና እጁን ይገልጣል።
\s5
\v 12 ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል፣ ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል፣ ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱ የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል።
\v 13 የኤፍሬምንም ምቀኝነት ያቆማል፣ ይሁዳንም የሚጠሉ ይቆረጣሉ። ኤፍሬምም በይሁዳ አይቀናም፣ ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም።
\s5
\v 14 በምዕራብም በኩል በፍልስጥኤማውያን ጫንቃ ላይ እየበረሩ ይወርዳሉ፣ የምሥራቅንም ልጆች በአንድነት ይበዘብዛሉ። በኤዶምያስና በሞዓብም ላይ እጃቸውን ይዘረጋሉ፣ የአሞንም ልጆች ለእነርሱ ይታዘዛሉ።
\v 15 እግዚአብሔርም የግብጽን ባሕር ያጠፋል፤ በትኩሱም ነፋስ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ያነሣል፣ ሰባት ፈሳሾች አድርጎም ይከፋፍለዋል፣ ስለዚህም በጫማ ሊሻገሩት የሚችሉት ይሆናል።
\s5
\v 16 ከግብጽም በወጣ ጊዜ ለእስራኤል እንደ ነበረው ሁሉ ለቀረውም ሕዝብ ቅሬታ ከአሦር የሚወጣበት ጐዳና እንዲሁ ይሆናል።
\s5
\c 12
\p
\v 1 በዚያም ቀን፣ "እግዚአብሔር ሆይ፣ አመሰግንሃለሁ። ተቈጥተኸኛልና፣ ቍጣህንም ከእኔ መልሰሃልና፣ አጽናንተኸኛልምና።
\v 2 ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌና ዝማሬዬ ነውና፣ አዎን፣ በእርሱ ታምኜ አልፈራም። መድኃኒቴም ሆኖአልና" ትላለህ።
\s5
\v 3 ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።
\v 4 በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፣ "እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ሥራውን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ ተናገሩ።
\s5
\v 5 ታላቅ ሥራ ሠርቶአልና ለእግዚአብሔር ተቀኙ፤ ይህንም በምድር ሁሉ ላይ የታወቀ እንዲሆን አድርጉ።
\v 6 አንቺ በጽዮን የምትኖሪ ሆይ፣ የእስራኤል ቅዱስ በመካከልሽ ከፍ ከፍ ብሎአልና ደስ ይበልሽ እልልም በዪ።"
\s5
\c 13
\p
\v 1 የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ያየው ስለ ባቢሎን የተነገረ ሸክም።
\v 2 ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምልክትን አቁሙ፣ ድምፅንም ከፍ አድርጉባቸው፤ በአለቆችም ደጆች እንዲገቡ እጃችሁን አንስታችሁ አሳዩ።
\v 3 ቍጣዬን ይፈጽሙ ዘንድ ቅዱሳኔን አዝዣለሁ፣ እኔ ኃያላኔንና በታላቅነቴ ደስ የሚላቸውን ጠርቻለሁ።
\s5
\v 4 በተራሮች ላይ እንደ ታላቅ ሕዝብ ድምፅ የሆነ የብዙ ሰው ድምፅ አለ! የተከተማቹት የአህዛብ መንግሥታት የውካታ ጫጫታ አለ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊትን ለሰልፍ አሰልፎአል።
\v 5 እግዚአብሔርና የቍጣው የጦር ዕቃ ምድርን ሁሉ ያጠፉአት ዘንድ ከሩቅ አገር፣ ከሰማይ ዳርቻ ይመጣሉ።
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፣ አልቅሱ፤ ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ እንደሚመጣ ጥፋት ይመጣል።
\v 7 ስለዚህ፣ እጅ ሁሉ ትዝላለች፣ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል፤
\v 8 ይደነግጣሉ፤ ምጥና ሕማም ይይዛቸዋል፣ እንደምትወልድ ሴትም ያምጣሉ። አንዱም በሌላው ይደነቃል፣ ፊታቸውም የነበልባል ፊት ነው።
\s5
\v 9 ተመልከቱ፣ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፣ ኃጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ ጨካኝ ሆኖ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
\v 10 የሰማይም ከዋክብትና ሠራዊቱ ብርሃናቸውን አይሰጡም፣ ፀሐይም በወጣች ጊዜ ትጨልማለች፣ ጨረቃም በብርሃኑ አያበራም።
\s5
\v 11 ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ። የእብሪተኞችንም ኵራት፣ የጨካኞቹንም ትዕቢት አዋርዳለሁ።
\v 12 የቀሩትም ከጥሩ ወርቅ ይልቅ የከበሩ ይሆናሉ፣ ሰውም ከኦፊር ወርቅ ይልቅ የከበረ ይሆናል።
\s5
\v 13 ስለዚህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት፣ በጽኑ ቍጣ ቀንም ሰማያትን አነቃንቃለሁ፣ ምድርም ከስፍራዋ ትናወጣለች።
\v 14 እንደ ተባረረም ሚዳቋ፣ ማንም እንደማይሰበስበው እንደ በግ መንጋ፣ ሰው ሁሉ ወደ ወገኑ ይመለሳል፣ ሁሉም ወደ አገሩ ይሸሻል።
\s5
\v 15 የተገኘ ሁሉ ይገደላል፣ የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይሞታል።
\v 16 ሕፃናቶቻቸውም በዐይናቸው ፊት እስኪቆራረጡ ድረስ ይጨፈጨፋሉ። ቤቶቻቸውም ይበዘበዛሉ፣ ሚስቶቻቸውም ተይዘው ይነወራሉ።
\s5
\v 17 ተመልከቱ፣ ብር የማይሹትን፣ ወርቅም የማያምራቸውን ሜዶናውያንን በላያቸው አናውጣለሁ።
\v 18 ፍላጾቻቸውም ጎበዞችን ይወጋሉ። ጨቅላዎችን አይምሩም፣ ዓይኖቻቸውም ለሕፃናት አይራሩም።
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም ሰዶምንና ገሞራን ባፈረሰ ጊዜ እንደ ነበረው፣ የመንግሥታት ክብር፣ የከለዳውያንም ትዕቢት ጌጥ ባቢሎን እንዲሁ ትሆናለች።
\v 20 ከትውልድ እስከ ትውልድ ድረስ ማንም ሰው አይኖርባትም፤ ዓረቦቹ ድንኳንን በዚያ አይተክሉም፣ እረኞችም መንጎቻቸውን በዚያ አያሳርፉም።
\s5
\v 21 በዚያም የምድረ በዳ አራዊት ያርፋሉ። ጕጕቶችም በቤቶቻቸው ይሞላሉ፤ ሰጎኖችና የበረሃ ፍየሎች በዚያ ይኖራሉ።
\v 22 ጅቦችም በግንቦቻቸው፣ ቀበሮችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይጮኻሉ። ጊዜዋም ለመምጣት ቀርቦአል ቀንዋም አይዘገይም።
\s5
\c 14
\p
\v 1 እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል፣ እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል፣ በገዛ አገራቸውም ያኖራቸዋል። መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል፣ ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል።
\v 2 አሕዛብም ይዘው ወደ ስፍራቸው ያመጡአቸዋል። የእስራኤልም ቤት በእግዚአብሔር ምድር እንደ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች አድርገው ይገዙአቸዋል። የማረኩአቸውን ይማርካሉ፣ አስጨናቂዎችንም ይገዛሉ።
\s5
\v 3 በዚያም ቀን፣ እግዚአብሔር ከኀዘንህና ከመከራህ ከተገዛህለትም ከጽኑ ባርነት ያሳርፍሃል።
\v 4 ይህንም ምሳሌ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ታነሣለህ፣ "አስጨናቂ እንዴት በፍጻሜው ዐረፈ፣ ኩሩውስ እንዴት ጸጥ አለ!" ይላሉ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር የአሕዛብ ገዢዎችን በትር በመዓትና በማያቋርጥ መምታት መታ፣
\v 6 አሕዛብንም ባልተከለከለ መከራ፣ በቍጣው የገዛውን የኀጥኣንን በትር የአለቆችንም ዘንግ እግዚአብሔር ሰብሮአል።
\s5
\v 7 ምድርም ሁሉ ዐርፋ በጸጥታ ተቀምጣለች፤ በዝማሬ ክብረ-በዓላቸውን ማድረግ ጀምረዋል።
\v 8 ጥድና የሊባኖስ ዝግባ፣ 'አንተ ከተዋረድህ ጀምሮ ማንም ይቈርጠን ዘንድ አልወጣብንም' ብለው በአንተ ደስ አላቸው።
\v 9 ሲኦል በመምጣትህ ልትገናኝህ በታች ታወከች፤ የሞቱትንም፣ የምድርን ታላላቆች ሁሉ፣ ለአንተ አንቀሳቀሰች፣ የአሕዛብንም ነገሥታት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው አስነሣች።
\s5
\v 10 እነዚህ ሁሉ ተናግረው፣ 'አንተ ደግሞ እንደ እኛ ደክመሃል። እኛን መስለሃል። ጌጥህና የበገናህ ድምፅ ወደ ሲኦል ወረደ፤
\v 11 በበታችህም ብል ተነጥፎአል። ትልም ይሸፍንሃል' ብለው ይመልሱልሃል።
\s5
\v 12 አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፣ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፣ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ!
\v 13 አንተ በልብህ፣ 'ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፣ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፣ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤
\v 14 ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፣ በልዑልም እመሰላለሁ' አልህ።
\s5
\v 15 ነገር ግን ወደ ሲኦል፣ ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።
\v 16 የሚያዩህ አፍጥጠው ይመለከቱሃልና። በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፣ መንግሥታትንም ያናወጠ፥
\v 17 ዓለሙን ሁሉ ባድማ ያደረገ፣ ከተሞችንም ያፈረሰ ምርከኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።
\s5
\v 18 የአሕዛብ ነገሥታት ሁሉ፣ በየመቃብራቸው በክብር አንቀላፍተዋል።
\v 19 አንተ ግን እንደ ተጠላ ቅርንጫፍ ከመቃብርህ ተጥለሃል፤ በሰይፍም የተወጉት፣ ተገድለውም ወደ ጕድጓዱ ድንጋዮች የወረዱት ከድነውሃል፤ እንደ ተረገጠም ሬሳ ሆነሃል።
\v 20 ምድርህን አጥፍተሃልና፣ ሕዝብህንም ገድለሃልና ከእነርሱ ጋር በመቃብር በአንድነት አትሆንም፤ የክፉዎች ዘር ለዘላለም የተጠራ አይሆንም።"
\s5
\v 21 እንዳይነሡም፣ ምድርንም እንዳይወርሱ፣ የዓለሙንም ፊት በከተሞች እንዳይሞሉ ስለ አባቶቻቸው በደል ለልጆቹ ሞትን አዘጋጁላቸው።
\v 22 "በእነርሱ ላይ እነሣለሁ" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ከባቢሎን ስምንና ቅሬታን፣ ዘርንና ትውልድንም እቈርጣለሁ ይላል እግዚአብሔር።
\v 23 "የጃርት መኖርያ የውኃም መቋሚያ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 24 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሎአል፣ "እንደ ተናገርሁ በእርግጥ ይሆናል፣ እንደ አሰብሁም እንዲሁ ይቆማል።
\v 25 አሦርን በምድሬ ላይ እሰብረዋለሁ፣ በተራራዬም ላይ እረግጠዋለሁ። ከዚያም ቀንበሩ ከእነርሱ ላይ ይነሣል፣ ሸክሙም ከጫንቃቸው ላይ ይወገዳል።"
\s5
\v 26 በምድር ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያሰበው አሳብ ይህ ነው፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋች እጅ ይህች ናት።
\v 27 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቦአል፤ የሚያስጥለውስ ማን ነው? እጁም ተዘርግታለች፤ የሚመልሳትስ ማን ነው?
\s5
\v 28 ንጉሡ አካዝ በሞተበት ዓመት ይህ ዐዋጅ ወጣ።
\v 29 ፍልስጥኤም ሆይ፣ ከእባቡ ሥር እፉኝት ይወጣልና፣ ፍሬውም የሚበርርና እሳት የሚመስል እባብ ይሆናልና የመታሽ በትር ስለ ተሰበረ ሁላችሁም ደስ አይበላችሁ።
\v 30 የድሆችም የበኵር ልጆች ይሰማራሉ፣ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፤ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፣ ቅሬታህም ይገደላል።
\s5
\v 31 አንተ በር ሆይ፣ ወዮ በል አንቺም ከተማ ሆይ፣ ጩኺ፤ ፍልስጥኤም ሆይ፣ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይመጣል ከጭፍራውም ተለይቶ የሚቀር የለም።
\v 32 ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መመለስ ይገባል? እግዚአብሔር ጽዮንን እንደ መሠረተ፣ የሕዝቡም ችግረኞች በእርስዋ ውስጥ እንደሚጠጉ ነው።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ስለ ሞዓብ የተነገረ ሸክም፣ በእርግጥ፣ የሞዓብ ዔር በሌሊት ፈርሶ ጠፋ፤ ቂር የሚባልም የሞዓብ ምሽግ በሌሊት ፈርሶ ጠፋ።
\v 2 ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባው በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቶአል።
\s5
\v 3 በየመንገዳቸውም በማቅ ታጥቀዋል፤ በየሰገነቶቻቸውና በየአደባባዮቻቸው እንባ እጅግ እያፈሰሱ ሁሉም አልቅሰዋል።
\v 4 ሐሴቦንና ኤልያሊ ለእርዳታ ጮኹ፤ ድምፃቸው እስከ ያሀጽ ድረስ ይሰማል። ስለዚህ የሞዓብ ሰልፈኞች ጮኹ፤ ነፍስዋ በውስጥዋ ተንቀጠቀጠች።
\s5
\v 5 ልቤ ስለ ሞዓብ ጮኸ፤ ከእርስዋም የሚሸሹ ወደ ዞዓር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኰበለሉ፤ በሉሒት ዓቀበት ላይ እያለቀሱ ይወጣሉ፣ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኸት ያነሣሉ።
\v 6 የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፤ ሣሩም ደርቋል፣ ለጋውም ጠውልጓል፥ ልምላሜውም ሁሉ የለም።
\v 7 ስለዚህ የሰበሰቡትን ሀብትና መዝገባቸውን ወደ አኻያ ዛፍ ወንዝ ማዶ ይወስዱታል።
\s5
\v 8 ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ብኤርኢሊም ደረሰ።
\v 9 የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ በዲሞንም ላይ ሥቃይን እጨምራለሁ፣ ከሞዓባውያንም በሚያመልጡ፣ ከምድርም በሚቀሩ ላይ አንበሳን አመጣለሁ።
\s5
\c 16
\p
\v 1 በምድርም ላይ ለሠለጠነው አለቃ የበግ ጠቦቶችን በምድረ በዳ ካለችው ከሴላ ወደ ጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ስደዱ።
\v 2 እንደሚበርር ወፍ፣ እንደ ተበተኑም ጫጩቶች፣ እንዲሁ የሞዓብ ሴቶች ልጆች በአርኖን መሻገሪያዎች ይሆናሉ።
\s5
\v 3 "መመሪያን ስጪ፣ ፍርድን አድርጊ፣ በቀትር ጊዜ ጥላሽን እንደ ሌሊት አድርጊ፤ የተሰደዱትን ሸሽጊ፣ የሸሹትን አትግለጪ።
\v 4 ከሞዓብ የተሰደዱት ከአንቺ ጋር ይኑሩ፤ ከሚያጠፋቸው ፊት መጋረጃ ሁኛቸው።" ጭቆናው ይቆማልና፣ ጥፋትም ይቆማልና፣ ይጨቍኑ የነበሩ ከምድር ይጠፋሉና።
\s5
\v 5 ዙፋንም በኪዳን ታማኝነት ይመሠረታል፤ ከዳዊት ድንኳን የሆነው በታማኝነት በዚያ ይቀመጣል። ፍርድን የሚሻ ጽድቅንም የሚያደርግ እንደመሆኑ ይፈርዳል።
\s5
\v 6 ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ እብሪተኝነቱ፣ ስለ ኵራቱና፣ ስለ ቁጣው ሰምተናል። ትምሕክቱ ባዶ ቃላት ናቸው።
\v 7 ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ያለቅሳል፤ ሁሉም ያለቅሳል። ፈጽሞ ስለሚጠፋው ስለ ቂርሐራሴት የዘቢብ ጥፍጥፍ ታለቅሳላችሁ።
\s5
\v 8 የሐሴቦን እርሻዎችና የሴባማ ወይን ግንዶች ደርቀዋል። የአሕዛብ አለቆች የሰባበሩአቸው ቅርንጫፎች እስከ ኢያዜር ደርሰው ወደ ምድረ በዳ ተበትነዋል። ቍጥቋጦቹም ተንሰራፍተው ወደ ባሕር ሄደው ነበር።
\s5
\v 9 በእርግጥ በኢያዜር ልቅሶ ስለ ሴባማ ወይን ግንድ አለቅሳለሁ። ሐሴቦንና ኤልያሊ ሆይ፣ በእምባዬ አረሰርሳችኋለሁ። በበጋሽ ፍሬና በመከር ላይ የደስታን ጩኸት ትቻለሁና።
\v 10 ደስታና ሐሤትም ከፍሬያማው የእርሻ ደን ተወስዶአል፤ በወይኑም ቦታዎች ዝማሬና የደስታ እልልታ የለም። በመጥመቂያም ወይን የሚረግጥ የለም፤ የረጋጮቹን እልልታ አጥፍቻለሁ።
\s5
\v 11 ስለዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ አንጀቴም ስለ ቂርሔሬስ እንደ መሰንቆ ትጮኻለች።
\v 12 ሞዓብም መጥቶ በኮረብታ መስገጃ ላይ ራሱን በደከመና ለጸሎት ወደ መቅደሱ በገባ ጊዜ፣ ጸሎቱ ምንም ነገር አያሳካም።
\s5
\v 13 እግዚአብሔር በሞዓብ ላይ አስቀድሞ የተናገረው ነገር ይህ ነው።
\v 14 አሁን ግን እግዚአብሔር፣ "በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብርና የሕዝቡ ሁሉ ብዛት ይዋረዳል፣ ቅሬታውም እጅግ ያነሰና የተጠቃ ይሆናል" ይላል።
\s5
\c 17
\p
\v 1 ስለ ደማስቆ የተነገረ ሸክም። እነሆ፣ ደማስቆ ከእንግዲህ ከተማ አትሆንም፤ የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች።
\v 2 የአሮኤር ከተሞች ይጣላሉ። ለመንጋ ማሰማሪያ ሆናሉ፣ የሚያስፈራቸውም የለም።
\v 3 የተመሸጉ ከተሞች ከኤፍሬም ይጠፋሉ፣ መንግሥትም ከደማስቆ፤ የሶርያም ቅሬታ እንደ እስራኤል ልጆች ክብር ይሆናል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 4 በዚያም ቀን የያዕቆብ ክብር ይከሳል፣ የሥጋውም ውፍረት ይሸበሸባል።
\v 5 አጫጅ የቆመውን እህል በእጁ ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ ይሆናል። በራፋይም ሸለቆ ቃርሚያ እንደሚለቅም እንዲሁ ይሆናል።
\s5
\v 6 ወይራ በተመታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት በዛፊቱ ጫፍ እንደሚገኝ፣ በእርሱ ዘንድ ቃርሚያ ይቀራል ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።
\v 7 በዚያ ቀን ሰው ወደ ፈጣሪው ይመለከታል፣ ዐይኖቹም ወደ እስራኤል ቅዱስ ያያሉ።
\s5
\v 8 እጁም የሠራችውን መሠዊያ አይመለከትም፣ ጣቶቹም ወደ አበጁአቸው፣ ወደ አሼራ ዐምዶች ወይም ወደ ፀሐይ ምስሎች አያይም።
\v 9 በዚያም ቀን በእስራኤል ልጆች ፊት የአሞራውያንና የኤውያውያን ከተሞች እንደ ተፈቱ እንዲሁ ከተሞችህ ይፈታሉ ባድማም ይሆናሉ።
\s5
\v 10 የደኅንነትህን አምላክ ረስተሃልና፣ የብርቱነትህንም ዐለት አላሰብክምና። ስለዚህ ያማረውን ተክል ተክለሃል፣ እንግዳንም ዘር ዘርተሃል
\v 11 በዚያ ቀን ተክለህ ታጥርለትና ታበቅለዋለህ። ብዙም ሳይቆይ ዘርህ ያብባል፣ ነገር ግን መከሩ የሚሆነው በኀዘንና በጥልቅ ኃዘን ነው።
\s5
\v 12 ወዮላችሁ! እንደ ባሕር ሞገድ ድምፅ ለሚጮኹ፣ እንደ ኃይለኛም ውኃ ጩኸት ለሚጮኹ አሕዛብ!
\v 13 አሕዛብ እንደ ብዙ ውኃ ጩኸት ይጮኻሉ፣ እግዚአብሔር ግን ይገሥጻቸዋል። እነርሱም ወደ ሩቅ ይሸሻሉ፣ በተራራም ላይ እንዳለ እብቅ፣ በነፋስ ፊት ዐውሎ ነፋስ እንደሚያዞረው ትቢያ ይበተናሉ።
\v 14 በመሸ ጊዜ፣ ተመልከቱ፣ ድንጋጤ አለ፤ ከማለዳም በፊት አይገኙም። የዘረፉን ሰዎች እድል ፈንታ፣ የበዘበዙን ዕጣ ይህ ነው።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የክንፎች ድምፅ ለሚሰማባት አገር ወዮላት፤
\v 2 መልእክተኞችን ከደንገል በተሠራ ጀልባ በአባይ ወንዝ ላይ ለምትልከው አገር፤ ሕዝብዋ ረጃጅሞችና ቆዳቸው ለስላሳ፣ አገራቸው በወንዞች የተከፋፈለች፣ ጠንካሮችና ኃያላን በመሆናቸው በዓለም ሁሉ ወደሚፈሩት ሕዝቦች እናንት ፈጣን መልእክተኞች ሂዱ!
\s5
\v 3 በዓለም የምትኖሩ ሁሉ እና በምድር የምትኖሩ፣ በተራሮች ጫፍ ላይ የተተከለ የሰንደቅ ዓላማ ምልክት ሲውለበለብ አስተውሉ፤ መለከት ሲነፋ ስሙ።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ያለኝ ነገር እንዲህ ነው፣ "በቀትር ጊዜ በጸጥታ እንደምታበራ ፀሐይ፣ በመከርም ወራት በሞቃት ሌሊት እንደሚታይ ጤዛ ከሰማያዊ መኖሪያዬ ጸጥ ባለ መንፈስ ቊልቊል እመለከታለሁ።"
\v 5 የወይን መከር ከመሰብሰቡ በፊት አበቦች ረግፈው የወይን ፍሬ በሚበስልበት ጊዜ የወይን ሐረግ ቅርንጫፎች በስለት ተቈርጠው እንደሚጣሉ እርሱ የዚያችን አገር ሕዝብ ያጠፋል።
\s5
\v 6 በአንድነት ለተራራ ወፎችና ለምድረ በዳ አራዊት ይተዋሉ። በበጋ ወፎች፣ በክረምትም አራዊት ይቀራመቷቸዋል።
\v 7 የሠራዊት አምላክ በዓለም ሁሉ የመፈራት ግርማ ካላቸው፣ ቆዳቸው ለስላሳ፣ ቁመታቸው ረጅም ኀያላንና ብርቱዎች ከሆኑት፣ በወንዞች የተከፋፈለች ምድር ካላቸው ከእነዚያ ሕዝብ መባ የሚቀበልበት ጊዜ ይመጣል፤ እነርሱም የሠራዊት አምላክ ወደሚመለክባት ወደ ጽዮን ኰረብታ ይመጣሉ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ስለ ግብጽ የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል የሚከተለው ነው። ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ሆኖ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጻውያን ጣዖቶች በእርሱ ፊት ይናወጣሉ፤ የግብጽ ሕዝብም በፍርሃት ይቀልጣሉ።
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "ግብጻዊያንን በግብጻዊያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድም በወንድሙ ላይ፣ ጐረቤትም በጐረቤቱ ላይ በጠላትነት እንዲነሣ አደርጋለሁ፤ ከተሞች በከተሞች ላይ፣ ነገሥታት በነገሥታት ላይ በጠላትነት ተነሥተው ይዋጋሉ።
\s5
\v 3 የግብጻውያን መንፈስ በውስጡ ይዳከማል። የጣዖቶቻቸውን የጠንቋዮቻቸውን የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን ምክር ቢፈልጉም ምክሩን እደመስሳለሁ።
\v 4 እነርሱን በጭካኔ ለሚገዛቸው ጌታ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።"
\s5
\v 5 በዓባይ ውስጥ ያለው ውሃ ይደርቃል፣ ወንዙም እየደረቀ ሄዶ ባዶ ይሆናል
\v 6 ወንዞቹ ይገማሉ፤ የግብጽ ምንጭ እየጐደለ ይደርቃል፤ ደንገሎቹና ቄጤማዎቹ ይጠወልጋሉ።
\s5
\v 7 በዓባይ ወንዝ ዳርቻ ያለው ቄጤማ ሁሉ ይደርቃል፤ በወንዙ አጠገብ የተዘራውም ሰብል ሁሉ ደርቆ ወደ አፈርነት በመለወጥ ነፋስ ይወስደዋል።
\v 8 ዓሣ አጥማጆችና መንጠቆአቸውን ወደ አባይ ወንዝ የሚጥሉ ሁሉ ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ መረቦቻቸውንም በውሃ ላይ የሚዘረጉ ተስፋ ይቈርጣሉ፤
\s5
\v 9 የተበጠረውን የተልባ እግር የሚሠሩ እና ቀጭን ሐር የሚሠሩ ያፍራሉ።
\v 10 የግብጽ ሸማኔዎች ግራ ይጋባሉ፤ ደመወዝተኞችም በውስጣቸው ያዝናሉ።
\s5
\v 11 በጾዓን ያሉ ልዑላን ፍጹም ሞኞች ናቸው። ጠቢባን የሆኑት የፈርዖን አማካሪዎች ምክር ትርጉም የለሽ ይሆናል። ለፈርዖን "እኔ የብልኅ ሰው ልጅ ነኝ የጥንት ነገሥታት ልጅ ነኝ እንዴት ይላሉ?"
\v 12 እንግዲያው እነዚያ ጠቢባን ወዴት ናቸው? የሠራዊት አምላክ በግብጽ ላይ ያቀደውን ይንገሩህ፣ ደግሞም ያሳውቁህ።
\s5
\v 13 የጾዓን ልዑላን ሞኞች ሆኑ፤ የሜምፊስ ልዑሎችም ተታለሉ፤ የነገዶችዋ ማእዘናት የሆኑት ግብጽን አሳትዋት።
\v 14 የተቀያየጠ ምክር እንዲሰጡ ያደረጋቸውም እግዚአብሔር ነው፤ በመጨረሻም ግብጽ በሁሉ ነገር በመሳሳት የገዛ ትውከቱ አዳልጦት እንደሚጥለው ሰካራም ትንገዳገዳለች።
\v 15 በግብጽ ራስም ሆነ ጭራ፣ የዘንባባ ዝንጣፊ ቢሆን ወይም ቄጤማ የሆነ ምንም ነገር ማድረግ አይችልም።
\s5
\v 16 በዚያ ቀን፣ ግብጻዊያን እንደ ሴቶች ይሆናሉ። በእነርሱ ላይ ከሚነሣው የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር የቅጣት እጅ አንጻር ይሸበራሉ፣ ደግሞም ይፈራሉ።
\v 17 ይሁዳ ለግብጽ ሕዝብ የምታንገዳግድ ትሆናለች። ማንኛውም ሰው ስለ እርሷ ሲያስታውሳቸው፣ ከእግዚአብሔር የመቅጣት እቅድ የተነሣ ይሸበራሉ።
\s5
\v 18 በዚያን ቀን በግብጽ ምድር ውስጥ የሚገኙ አምስት የዕብራውያን ቋንቋ የሚናገሩ ከተሞች ይኖራሉ፤ በዚያም የሚኖሩ ሕዝቦች በሠራዊት አምላክ ስም ይምላሉ፤ ከእነዚህ ከተሞች አንዲቱ የፀሐይ ከተማ ተብላ ትጠራለች።
\s5
\v 19 በዚያን ቀን በግብጽ ምድር መካከል ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ እንዲሁም በግብጽ ጠረፍ ላይ ለእግዚአብሔር የተለየ የድንጋይ ዐምድ ይተከላል።
\v 20 እነርሱም የሠራዊት አምላክ በግብጽ ምድር ለመኖሩ ምልክትና ምስክር ይሆናሉ። ከጭቆና የተነሣ እግዚአብሔር እንዲረዳቸው በሚጠይቁበት ጊዜ፣ የሚታደጋቸውን አዳኝ ይልክላቸዋል፣ እርሱም ከጠላቶቻቸው ያድናቸዋል።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር ለግብጽ ሕዝብ የታወቀ ይሆናል፤ ደግሞም በዚያን ጊዜ እነርሱ ያውቁታል። መሥዋዕትና መባም ያቀርቡለታል፣ ለእግዚአብሔርም ስእለት ይሳላሉ፤ ስእለታቸውንም ሁሉ ይፈጽማሉ።
\v 22 እግዚአብሔር ግብጻውያንን ይቀጣል፤ ነገር ግን መልሶ ይፈውሳቸዋል፤ ወደ እርሱ ይመለሳሉ፤ እርሱም ጸሎታቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል።
\s5
\v 23 በዚያን ጊዜ በግብጽና በአሦር መካከል አውራ ጎዳና ይከፈታል፤ አሦራዊያን ወደ ግብጽ፣ ግብጻዊያንም ወደ አሦር ይመጣሉ፤ ደግሞም ግብጻዊያን ከአሦራዊያን ጋር ያመልካሉ።
\s5
\v 24 በዚያን ቀን፣ እስራኤል ከግብጽና ከአሦር ጋር ሦስተኛ አገር ትሆናለች፤ እነዚህም ሕዝቦች በዓለም መካከል በረከት ይሆናሉ።
\v 25 የሠራዊት አምላክም፣ "እናንተ በግብጽ የምትኖሩ ሕዝቤ፣ የፈጠርኳችሁ አሦራውያንና የመረጥኳችሁ የእስራኤል ሕዝብ የተባረካችሁ ሁኑ" ይላቸዋል።
\s5
\c 20
\p
\v 1 የአሦር ንጉሥ ሳርጎን ተርታንን በሰደደ ጊዜና ወደ አዛጦን በመጣ ጊዜ አዛጦንም ወግቶ በያዛት ጊዜ፥
\v 2 በዚያ ጊዜ እግዚአብሔር የአሞጽን ልጅ ኢሳይያስን፣ "ሂድና ማቅህን ከወገብህ አውጣ፣ ጫማህንም ከእግርህ አውልቅ" ብሎ ተናገረው። እንዲህም አደረገ፣ ራቁቱንም ባዶ እግሩንም ሄደ።
\s5
\v 3 እግዚአብሔርም አለ፣ "ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምልክትና ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፣
\v 4 በዚህ መንገድ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፣ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፣ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፣ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።
\s5
\v 5 እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል፤
\v 6 በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚኖሩ፣ "በእርግጥ፣ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?" ይላሉ።
\s5
\c 21
\p
\v 1 በባሕር አጠገብ ስላለው ስለ ምድረ በዳ የተነገረ ዐዋጅ። ዐውሎ ነፋስ ከኔጌቭ እንደሚወጣ፣ እንዲሁ ከሚያስፈራ አገር በምድረ በዳ አልፎ ይወጣል።
\v 2 የሚረብሽ ራእይ ተነገረኝ፤ ወንጀለኛው በወንጀል ይሠራል፣ አጥፊውም ያጠፋል። ኤላም ሆይ፣ ወደ ላይ ውጪ፣ ሜዶን ሆይ ክበቢ፤ ትካዜውን ሁሉ አስቀርቻለሁ።
\s5
\v 3 ስለዚህ ወገቤ በሕመም ተሞላ፤ እንደምትወልድ ሴት ምጥ ያዘኝ፤ ከሰማሁት የተነሣ ጎበጥኩ፤ ካየሁት ነገር የተነሣ ተረበሽኩ።
\v 4 ልቤ ተርበደበደ፣ መንቀጥቀጥ አስፈራኝ፤ የተመኘሁት ሌሊት የሚያንቀጠቅጠኝ ሆነብኝ።
\s5
\v 5 ማዕዱን ያዘጋጃሉ፣ ምንጣፉንም ይዘረጋሉ፣ ይበሉማል፣ ይጠጡማል፤ እናንተ ልዑላን ሆይ፣ ተነሡ፣ ጋሻውን በዘይት ቀቡ።
\s5
\v 6 ጌታ ያለኝ እንዲህ ነው፣ "ሂድ፣ ጉበኛም አቁም፣ የሚያየውንም ይናገር።
\v 7 በከብት የሚቀመጡትን፣ ሁለት ሁለት እየሆኑ የሚሄዱት ሠረገሎች፥ በአህዮች የሚጋልቡትንና በግመሎች የሚጋልቡትን ባየ ጊዜ፣ በጽኑ ትጋት አስተውሎ ተግቶም ያድምጥ።"
\s5
\v 8 ያየውም። ጌታ ሆይ፥ ቀኑን ሁሉ ዘወትር በማማ ላይ ቆሜአለሁ፥ ሌሊቱንም ሁሉ በመጠበቂያዬ ላይ ተተክያለሁ፣"
\v 9 እነሆም፣ በፈረሶች የሚቀመጡ፣ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፣ "ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች፣ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ" አለ።
\s5
\v 10 እናንተ በአውድማዬ ላይ የተወቃችሁ የአውድማዬ ልጆች ሆይ! ከእስራኤል አምላክ፣ ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሰማሁትን ነገርኋችሁ።
\s5
\v 11 ስለ ኤዶምያስ የተነገረ ዐዋጅ። አንዱ ከሴይር ይጣራል፣ "ጕበኛ ሆይ፣ ከሌሊቱ ምን ያክል ሰዓት ቀረ? ጕበኛ ሆይ፣ ከሌሊቱ ምን ያክል ሰዓት ቀረ?" ብሎ ጠራኝ።
\v 12 ጕበኛውም እንዲህ አለ፣ "ማለዳው ይመጣል፣ ድግሞም ምሽቱ፤ ብትጠይቁ፣ ጠይቁ፤ ተመልሳችሁም ኑ" አለ።
\s5
\v 13 ስለ ዓረብ የተነገረ ዐዋጅ። የዴዳናውያን ነጋዴዎች ሆይ፣ በዓረብ ዱር ውስጥ ታድራላችሁ።
\v 14 በቴማን የምትኖሩ ሆይ፣ ወደ ተጠሙት ሰዎች ውኃ አምጡ፣ እንጀራ ይዛችሁ የሸሹትን ሰዎች ተቀበሉአቸው።
\v 15 ከሰይፍ፣ ከተመዘዘው ሰይፍ፣ ከተለጠጠውም ቀስት ከጽኑም ሰልፍ ሸሽተዋልና።
\s5
\v 16 ጌታ ያለኝ እንዲህ ነውና፣ "ምንደኛ ለአንድ ዓመት እንደሚቀጠር፣ በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤
\v 17 ከቀስተኞች ቍጥር ጥቂቶቹ ብቻ፣ የቄዳር ልጆች ኃያላን፣ ያንሳሉ፤" የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ስለ ራእይ ሸለቆ የተነገረ ዐዋጅ፤ እናንተ ሁላችሁ ወደ ቤት ሰገነት መውጣታቸሁ ምን ሆናችኋል?
\v 2 ጩኸትና ፍጅት የተሞላብሽ ከተማ፣ ደስታ ያለሽ ከተማ ሆይ፣ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉም፣ በሰልፍም የሞቱ አይደሉም።
\s5
\v 3 ገዚዎችሽ ሁሉ በአንድነት ሸሹ፣ ያለ ቀስትም ተማረኩ፤ ከሩቅ ሸሽተው ከአንቺ ዘንድ የተገኙት ሁሉ በአንድነት ታሰሩ።
\v 4 ስለዚህም፣ "ወደ እኔ አትመልከቱ፣ መራራ ልቅሶ አለቅሳለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ታጽናኑኝ ዘንድ አትድከሙ" አልሁ።
\s5
\v 5 ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የድንጋጤና የመረገጥ የድብልቅልቅም ቀን፣ የቅጥርም መፍረስ ወደ ተራራም መጮኽ በራእይ ሸለቆ ውስጥ ሆኖአል።
\v 6 ኤላምም ከሰዎች ሠረገለኞችና ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ አፎቱን ተሸከመ፣ ቂርም ጋሻውን ገለጠ።
\v 7 መልካሞቹንም ሸለቆችሽን ሠረገሎች ሞሉባቸው፣ ፈረሰኞችም መቆሚያቸውን በበር ላይ አደረጉ።
\s5
\v 8 የይሁዳንም መጋረጃ ገለጠ፤ በዚያም ቀን በዱር ቤት የነበረውን የጦር ዕቃ ተመለከትህ።
\v 9 የዳዊትም ከተማ ፍራሾች እንደ በዙ አይታችኋል፣ የታችኛውንም ኵሬ ውኃ አከማችታችኋል።
\s5
\v 10 የኢየሩሳሌምን ቤቶች ቈጥራችሁ ቅጥሩንም ለማጥናት ቤቶችን አፈረሳችሁ።
\v 11 በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መጠባበቂያ ማከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፣ ቀድሞ የሠራውንም አላሰባችሁም።
\s5
\v 12 በዚያም ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ ልቅሶና ወደ ዋይታ ራስን ወደ መንጨትና ማቅንም ወደ መልበስ ጠራ።
\v 13 ነገር ግን ተመልከቱ፣ ሐሜትና ደስታ በሬውንና በጉንም ማረድ፣ ሥጋንም መብላት፣ የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል። እናንተ፣ ነገ እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል።
\v 14 ይህም ነገር በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተገለጠ፡- "እስክትሞቱ ድረስ ይህ በደል በእውነት አይሰረይላችሁም" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 15 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በቤቱ ውስጥ ወደ ተሾመው ወደዚህ አዛዥ ወደ ሳምናስ ሂድ እንዲህም በለው፣
\v 16 "መቃብር በዚህ ያስወቀርህ ከፍ ባለው ስፍራ መቃብር ያሠራህ በድንጋይም ውስጥ ለራስህ መኖርያ ያሳነጽህ በዚህ ምን አለህ? በዚህስ በአንተ ዘንድ ማን አለ?"
\s5
\v 17 እነሆ፣ እግዚአብሔር ወርውሮ ይጥልሃል፣ ኃያል ሰውም አጠንክሮ ይወረውርሃል፤ በኃይል ይጎትትሃል።
\v 18 ጠቅልሎም ያንከባልልሃል ወደ ሰፊይቱም ምድር እንደ ኳስ ይጥልሃል። በዚያ ትሞታለህ በዚያም የክብርህ ሰረገላዎች ይሆናሉ። አንተ የጌታህ ቤት እፍረት ትሆናለህ!
\v 19 ከአዛዥነትህና ከጣቢያ ሥራህ አሳድድሃለሁ። ከሹመትህም ትወርዳለህ።
\s5
\v 20 በዚያም ቀን ባሪያዬን የኬልቅያስን ልጅ ኤልያቄምን እጠራለሁ፥
\v 21 መጐናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፣ በመታጠቂያህም አስታጥቀዋለሁ፣ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።
\v 22 የዳዊትንም ቤት መክፈቻ በጫንቃው ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም።
\s5
\v 23 በአስተማማኝ ስፍራ እንደ ችንካር እተክለዋለሁ፣ ለአባቱም ቤት የክብር ዙፋን ይሆናል።
\v 24 የአባቱንም ቤት ክብር ሁሉ ልጆቹንም የልጅ ልጆቹንም፣ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፣ ታናናሹን ዕቃ ሁሉ ይሰቅሉበታል።
\s5
\v 25 በዚያ ቀን፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በታመነው ስፍራ የተከለው ችንካር ይወልቃል፤ ተሰብሮም ይወድቃል፣ በእርሱም ላይ የተሰቀለው ሸክም ይጠፋል እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ስለ ጢሮስ የተነገረ ሸክም። የተርሴስ መርከቦች ሆይ፣ አልቅሱ፤ ፈርሶአልና ቤት የለም፣ መግቢያም የለም፤ ከኪቲም አገር ጀምሮ ተገልጦላቸዋል።
\v 2 እናንተ በደሴት የምትኖሩ፣ በባሕርም የምትሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች፣ ወኪሎቻችሁ የሚያቀርቡላችሁ፣ ጸጥ በሉ።
\v 3 የሺሖር ዘርና የዓባይ ወንዝ መከር በብዙ ውኆች ላይ ገቢዋ ነበረ፤ እርስዋም የአሕዛብ መናገጃ ነበረች።
\s5
\v 4 እፈሪ፣ ሲዶና ሆይ፣ ባሕር ተናግሯልና፣ የባሕሩ ኃያል ተናግሯል። እንዲህ አለ፣ "አላማጥሁም፣ አልወለድሁምም፤ ጐበዛዝትንም አላሳደግሁም፤ ወጣት ሴቶችንም አላሳደግሁም" ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ።
\v 5 ወሬዋ ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ፣ በጢሮስ ወሬ ስለ እርሷ ምጥ ይይዛቸዋል።
\s5
\v 6 ወደ ተርሴስ ተሻገሩ፤ እናንተ በደሴት የምትኖሩ አልቅሱ።
\v 7 ደስተኛዋ ከተማ፣ ከቀድሞ ዘመን ጀምሮ የነበርሽ፣ ይህ ደርሶብሻልን፣ እንግዳ በሆነ ስፍራዎች ለመኖር እግሮችዋ ወደ ሩቅ ያፈለሱአት የደስታችሁ ከተማ ይህች ናትን?
\s5
\v 8 አክሊል ባስጫነች ከተማ ነጋዴዎችዋ ልዑላን በሆኑ፣ በእርስዋም የሚሸጡና የሚለውጡ የምድር ክቡራን የሆኑባት ጢሮስ ላይ ይህን የወጠነ ማን ነው?
\v 9 የክብርን ሁሉ ትዕቢት ይሽር ዘንድ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያስንቅ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል።
\s5
\v 10 የተርሴስ ልጅ ሆይ፣ የሚከለክልሽ የለምና እንደ ዓባይ ወንዝ በአገርሽ ላይ እረሺ።
\v 11 እግዚአብሔር በባሕር ላይ እጁን ዘረጋ፣ መንግሥታትንም አናወጠ፤ ምሽጎችዋንም ያጠፉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለ ከነዓን አገር አዘዘ።
\v 12 እርሱም፣ "አንቺ የተበደልሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፣ ተነሺ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በድጋሚ ደስ አይልሽም፤ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፣ በዚያም ደግሞ አታርፊም አለ።
\s5
\v 13 ተመልከቱ የከለዳውያን ሰዎች። ይህ ሕዝብ መኖሩ ይቆማል፤ አሦራውያን ለምድረ በዳ አራዊት ሰጥተውታል። የወረራ ግንቦቻቸውን ሠሩ፥ አዳራሾችዋንም አፈረሱ፣ የጥፋት ባድማም አደረጓት።
\v 14 እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፣ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ።
\s5
\v 15 በዚያም ቀን፣ ጢሮስ እንደ ንጉሥ ቀናት ሁሉ ሰባ ዓመት ያህል የተረሳች ትሆናለች። ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢሮስ በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል።
\v 16 አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፣ መሰንቆ ያዢ፣ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ።
\s5
\v 17 ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይረዳታል፣ ወደ ተቀጠረችበት ትመለሳለች። ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች።
\v 18 ንግድዋና ዋጋዋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል። ንግድዋም በልተው ይጠግቡ ዘንድ ማለፊያም ልብስ ይለብሱ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ ይሆናል እንጂ በዕቃ ቤትና በግምጃ ቤት ውስጥ አይከተትም።
\s5
\c 24
\p
\v 1 ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር ምድርን ባዶ ያደርጋታል፣ ባድማም ያደርጋታል፣ ይገለብጣትማል፣ በእርስዋም የሚኖሩትን ይበትናል።
\v 2 እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ፣ እንደ ባሪያውም እንዲሁ ጌታው፣ እንደ ባሪያይቱም እንዲሁ እመቤትዋ፣ እንደሚገዛም እንዲሁ የሚሸጠው፣ እንደ አበዳሪውም እንዲሁ ተበዳሪው፣ እንደ ዕዳ አስከፋዩም እንዲሁ ዕዳ ከፋዩ ይሆናል።
\s5
\v 3 ምድር ፈጽሞ ትጠፋለች፣ ፈጽማም ትበላሻላች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአልና።
\v 4 ምድር ደረቀች ረገፈችም፤ ዓለም ተናወጠች ረገፈችም፤ የምድርም ስመ-ጥር ሕዝብ ደከሙ።
\v 5 ሕጉን ተላልፈዋልና፣ ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፣ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና፣ ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች።
\s5
\v 6 ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች፣ የሚኖሩባትም ጥፋተኞች ይሆናሉ። ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይቃጠላሉ፣ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ።
\v 7 አዲስ የወይን ጠጅ ይደርቃል፣ የወይን ንግድ ደከመች፣ ልባቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ።
\s5
\v 8 የከበሮው ደስታ ቆሟል፣ የደስተኞች ድምፅ ዝም ብሎአል፣ የመሰንቆ ደስታ ቀርቶአል።
\v 9 እየዘፈኑም የወይን ጠጅን አይጠጡትም፣ የሚያሰክርም መጠጥ ለሚጠጡት መራራ ይሆናል።
\s5
\v 10 የተቃወሰችው ከተማ ፈረሰች፤ ቤት ሁሉ ተዘግቶ ባዶ ሆነ።
\v 11 ስለ ወይኑም ጠጅ በአደባባይ ለቅሶ ይሆናል፤ ደስታ ሁሉ ጨልሞአል፥ የምድርም ደስታ ጠፍቷል።
\s5
\v 12 ከተማይቱም ባድማ ሆናለች፣ በርዋም በጥፋት ተመትቶአል።
\v 13 የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፣ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም፣ እንዲሁ በምድር መካከል በአሕዛብም መካከል ይሆናል።
\s5
\v 14 እነዚህ ድምፃቸውን አሰምተው እልል ይላሉ፣ ስለ እግዚአብሔር ክብርም ከባሕር በደስታ ይጮኻሉ።
\v 15 ስለዚህ እግዚአብሔርን በምሥራቅ፣ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ።
\s5
\v 16 "ለጻድቁ ክብር ይሁን!" የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፣ "ባከንሁ፣ ባከንሁ፣ ወዮልኝ! ወንጀለኞች ወንጅለዋል፤ አዎን፣ ወንጀለኞች እጅግ ወንጅለዋል" አልሁ።
\s5
\v 17 በምድር ላይ የምትኖር ሆይ፣ ፍርሃትና ገደል ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ።
\v 18 ከፍርሃት ድምፅ የሸሸ፣ በገደል ይወድቃል፤ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል። የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋል፣ የምድርም መሠረት ተናውጣለች።
\s5
\v 19 ምድር ፈጽሞ ትሰባበራለች፣ ምድር ፈጽማ ደቀቀች፤ ምድር በኃይል ትነዋወጣለች።
\v 20 ምድር እንደ ሰካራም ሰው ትንገዳገዳለች፣ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች። መተላለፍዋ ይከብድባታል፣ ትወድቃለች ደግማም አትነሣም።
\s5
\v 21 በዚያም ቀን እንደዚህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በከፍታ ያለውን ሠራዊት በከፍታ ላይ፣ በምድርም ያሉትን ነገሥታት በምድር ላይ ይቀጣቸዋል።
\v 22 ግዞተኞች በጕድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ፣ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፣ ከብዙ ቀንም በኋላ ይፈረድባቸዋል።
\v 23 ከዚያም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ይነግሣልና፣ በሽማግሌዎቹም ፊት ክብር ይሆናልና ጨረቃ ያፍራል፣ ፀሐይም ይዋረዳል።
\s5
\c 25
\p
\v 1 እግዚአብሔር፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር፣ ከጥንት የታቀዱትን በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ።
\v 2 ከተማይቱን የድንጋይ ክምር፣ የተመሸገችውን ከተማ ውድማ እንድትሆን፣ የኀጥአንንም አዳራሽ ከተማ እንዳትሆን አድርገሃል፤ ከቶ አትሠራም።
\v 3 ስለዚህ ኃያላኑ ወገኖች ያከብሩሃል፤ የጨካኞች አሕዛብ ከተማም ትፈራሃለች።
\s5
\v 4 የጨካኞችም ቍጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ ዐውሎ ነፋስ በሆነ ጊዜ፣ ለድሀው መጠጊያ፣ ለችግረኛው በጭንቁ ጊዜ መጠጊያ፣ ከውሽንፍር መሸሸጊያ ከሙቀትም ጥላ ሆነሃል።
\v 5 እንደ በረሃ ሙቀት፣ የኀጥአንን ጩኸት ዝም ታሰኛለህ፤ ሙቀትም በደመና ጥላ እንዲበርድ እንዲሁ የጨካኞች ዝማሬ ይዋረዳል።
\s5
\v 6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፣ የተመረጠ የወይን ጠጅ፣ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፣ የጥሩና ያረጀ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።
\v 7 በዚህም ተራራ ላይ በወገኖች ሁሉ ላይ የተጣለውን መጋረጃ፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተዘረጋውን መሸፈኛ ያጠፋል።
\v 8 ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፣ የሕዝቡን ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\s5
\v 9 በዚያም ቀን፣ "ተመልከቱ፣ አምላካችን ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፣ ያድነንማል። እግዚአብሔር ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል ሐሤትም እናደርጋለን" ይባላል።
\v 10 የእግዚአብሔርም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፣ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በስፍራው ይረገጣል።
\s5
\v 11 ዋናተኛ ለመዋኘት እጁን እንደሚዘረጋ፣ እንዲሁ በመካከሉ እጁን ይዘረጋል፤ ነገር ግን ምንም ያክል እጆቹ ቢወራጭም እግዚአብሔር ትዕቢቱን ያዋርዳል።
\v 12 ከፍ ያሉት የተመሸገው ቅጥርህን እስከ ትቢያ ድረስ ዝቅ ያደርገዋል።
\s5
\c 26
\p
\v 1 በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ላይ ይዘመራል። የጸናች ከተማ አለችን፤ ለቅጥርና ለምሽግ መድኃኒትን አድርጎባታል።
\v 2 እውነትን የሚጠብቅ ጻድቅ ሕዝብ ይገባ ዘንድ በሮችን ክፈቱ።
\s5
\v 3 በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትጸና አእምሮ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
\v 4 ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና ለዘላለም በእግዚአብሔር ታመኑ።
\s5
\v 5 በኩራት የሚኖሩትን ሰዎች ዝቅ ያደርጋል፤ የተመሸገችውን ከተማ ወደ ምድር ያዋርዳል፤ እስከ መሬት ድረስ ያወርዳታል፤ እስከ አፈርም ድረስ ያርዳታል።
\v 6 በድሆች እንዲሁም በችግረኞች ረገጣ የምትረገጥ ትሆናለች።
\s5
\v 7 የጻድቃን መንገድ ደልዳላ ናት፣ አንተ ጻድቅ የሆንህ የጻድቃንን መንገድ ታቃናለህ።
\v 8 አዎን፣ በፍርድህ መንገድ ጠብቀንሃል፤ ስምህም መታሰቢያህም ምኞታችን ነው።
\v 9 ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፥ መንፈሴም በውስጤ ወደ አንተ ትገሠግሣለች። ፍርድህ ወደምድር በመጣ ጊዜ በዓለም የሚኖሩት ጽድቅን ይማራሉና።
\s5
\v 10 ለኃጢአተኛ ሞገስ ይደረግለት፣ ነገር ግን ጽድቅን አይማርም። በቅኖች ምድር ክፉን ነገር ያደርጋል፤ የእግዚአብሔርንም ግርማ አያይም።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር ሆይ፣ እጅህ ከፍ ብላ ተነሣች፣ ነገር ግን አላስተዋሉም። ነገር ግን በሕዝብህ ላይ ያለህን ቅንዓት አይተው ያፍራሉ፤ ምክንያቱም እሳትም ጠላቶችህን ትበላቸዋለች።
\v 12 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሥራችንን ሁሉ ሠርተህልናልና ሰላምን ትሰጠናለህ።
\s5
\v 13 አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ከአንተ በተጨማሪ ሌሎች ጌቶች ገዝተውናል፤ ነገር ግን የአንተን ስም ብቻ እናስባለን።
\v 14 እነርሱ ሞተዋል፣ በሕይወት አይኖሩም፤ ሞተዋል፣ አይነሡም፤ በእርግጥ፣ አንተ በፍርድ መጥተህ አጥፍተሃቸዋል፣ መታሰቢያቸውን ሁሉ እንዲጠፋ አድርገሃል።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝብን አበዛህ፣ ሕዝብን አበዛህ፤ አንተም ተከበርህ፣ የአገሪቱን ዳርቻ ሁሉ አሰፋህ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ሆይ፣ በመከራ ጊዜ ተመለከቱህ፤ ቅጣትህ በእነርሱ ላይ በሆነ ጊዜ ድግምታቸውን ሳይቀር በክፉው ላይ ተናገሩ።
\v 17 የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትታመምና በምጥ እንደምትጮኽ፣ አቤቱ፣ እንዲሁ በፊትህ ሆነናል።
\s5
\v 18 እኛ ፀንሰናል፣ ምጥም ይዞናል፣ ነገር ግን ነፋስን እንደምንወልድ ሆነናል፤ ድነትን ወደምድር አላመጣንም፣ በዓለምም የሚኖሩ አልወደቊም።
\s5
\v 19 ሙታንህ ሕያዋን ይሆናሉ፤ ሬሳዎችም ይነሣሉ። በምድር የምትኖሩ ሆይ፣ ጠልህ የመድሃኒት ጠል ነውና፣ ምድርም ሙታንን ታወጣለችና ንቁ ዘምሩም።
\s5
\v 20 ሂድ ሕዝቤ ሆይ፣ ወደ ክፍሎችህ ግባና ደጅህን በኋላህ ዝጋ፤ ቍጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ጊዜ ተሸሸግ።
\v 21 ተመልከት፣ በምድር በሚኖሩት ላይ በበደላቸው ምክንያት ቍጣውን ያመጣባቸው ዘንድ፣ እነሆ፣ እግዚአብሔር ከስፍራው ይወጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፣ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።
\s5
\c 27
\p
\v 1 በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ፣ በታላቅ፣ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፥ በባሕርም ውስጥ ያለውን አውሬ ይገድላል።
\v 2 በዚያም ቀን፣ ለተወደደው የወይን ቦታ ተቀኙለት።
\v 3 "እኔ፣ እግዚአብሔር ጠባቂው ነኝ፤ ሁልጊዜ አጠጣዋለሁ፤ ማንም እንዳይጐዳው በሌሊትና በቀን እጠብቀዋለሁ።
\s5
\v 4 እሾህና ኵርንችት ለሰልፍ በመኖራቸው አልተቈጣሁም! በውጊያ በእነርሱ ላይ ተራምጄ፣ በአንድነት ባቃጠልኋቸው ነበር።
\v 5 ከለላነቴን ካልያዙና ከእኔ ጋር ሰላም ካላደረጉ፣ ከእኔ ጋር ሰላም ያድርጉ።
\s5
\v 6 በሚመጣው ዘመን ያዕቆብ ሥር ይሰድዳል፣ እስራኤልም ያብባል ይጨበጭብማል፤ በፍሬያቸውም የዓለሙን ፊት ይሞላሉ።"
\s5
\v 7 በውኑ የመቱትን እንደ መታ እንዲሁ እርሱን መታውን? ወይስ እነርሱ እንደ ተገደሉበት መገደል ያዕቆብና እስራኤል ተገድሎአልን?
\v 8 ያዕቆብና እስራኤልን ለማባረር በታገልክበት መጠን፣ እርሱ ነዳቸው ሰደዳቸው ቀሠፋቸው፤ የምሥራቅ ነፋስ በሚነፍስበት ቀን በጠንካራ ዐውሎ ነፋስ አስወገዳቸው።
\s5
\v 9 ስለዚህም በዚህ መንገድ፣ የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፣ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፣ ይህም ከኀጢአት የመመለስ ፍሬ ሁሉ ነው።
\s5
\v 10 የተመሸገችው ከተማ ጠፋች፣ እንደ ምድረ በዳ የተፈታችና የተተወች መኖሪያ ናት። በዚያም ጥጃ ይሰማራል፣ በዚያም ይተኛል ቅርንጫፍዋንም ይበላል።
\v 11 ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ። ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
\s5
\v 12 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከኤፍራጥስ ወንዝ ምንጭ ጀምሮ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ሕዝቦች ሆይ፣ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
\v 13 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፣ በአሦርም የጠፉ፣ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፣ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ይሰግዳሉ።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ለኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል፣ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ በወፍራም ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮ!
\v 2 እነሆ፣ በጌታ ዘንድ ኃያል ብርቱ የሆነ አለ። እንደ በረዶ ወጨፎ፣ እንደሚያጠፋም ወጀብ፣ እንደሚያጥለቀልቅም እንደ ታላቅ ውኃ ፈሳሽ በጠነከረ እጅ ምድርን ያጠቃል።
\s5
\v 3 የኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል በእግር ይረገጣል፤
\v 4 በወፍራሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ፣ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ ሰው ባያት ጊዜ በእጁ እንዳለች ይበላታል።
\s5
\v 5 በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤
\v 6 በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍርድ መንፈስ፣ ሰልፉን ወደ በር ለሚመልሱም ኃይል ይሆናል።
\s5
\v 7 እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ። ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፣ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ። ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፤ በራእይ ይስታሉ፣ በፍርድም ይሰናከላሉ።
\v 8 በእውነት፣ ገበታው ሁሉ ትውከትን ተሞልቷል፤ ንጹሕ ስፍራ እንኳ የለም።
\s5
\v 9 እውቀትን ለማን ያስተምረዋል፣ ወይስ መልእክቱን ለማን ያስረዳል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?
\v 10 ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ደንብ በደንብ ላይ፣ እዚህ ጥቂት፣ ጥቂት በዚያ ነው።
\s5
\v 11 በእርግጥ፣ በፌዘኛ አፍ በሌሎችም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤
\v 12 "ይህች እረፍት ናት፣ የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም የምታድስ ማረፊያ ናት" አላቸው፤ እነርሱ ግን አልሰሙም።
\s5
\v 13 ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ሥርዓት በሥርዓት ላይ፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል።
\s5
\v 14 ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ይህንን ሕዝብ የምትገዙ ፌዘኞች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 15 እናንተም፣ "ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፣ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ስለዚህ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፣ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም" አላችሁ።
\s5
\v 16 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። "ተመልከቱ፡ በጽዮን የመሠረት ድንጋይን አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን ድንጋይ፣ የከበረውን፣ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ። የሚያምን እርሱ አያፍርም።
\s5
\v 17 ለገመድ ፍርድን፣ ለቱንቢም ጽድቅን አደርጋለሁ። በረዶውም የሐሰትን መሸሸጊያ ይጠርጋል፣ ውኆችም መሰወሪያውን ያሰጥማሉ።
\s5
\v 18 ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፣ ከሲኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይጸናም። የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ ትረገጡበታላችሁ።
\v 19 ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፤ ማለዳ ማለዳ ቀንና ሌሊት ያልፋል፤ መልእክቱ በገባቸው ጊዜ ድንጋጤ ይሆናል።
\s5
\v 20 ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ ብርድልብሱ እጅግ ጠባብ ነው።"
\v 21 እግዚአብሔርም ሥራውን፣ ማለትም እንግዳ የሆነ ሥራውን ይሠራ ዘንድ፣ አድራጎቱንም ማለት ያልታወቀውን አድራጎቱን ያደርግ ዘንድ በፐራሲም ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፣ በገባዖንም ሸለቆ እንደ ነበረ ይቈጣል።
\s5
\v 22 አሁንም እስራት እንዳይጸንባችሁ አታፊዙ። በምድር ሁሉ ላይ የሚጸናውን የጥፋት ትእዛዝ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና።
\s5
\v 23 በትኩረት አድምጡና ድምፄን ስሙ፤ ልብ አድርጉ ንግግሬንም ስሙ።
\v 24 በውኑ ገበሬ ሊዘራ ሁልጊዜ ያርሳልን? ወይስ ሁልጊዜ እርሻውን ይጎለጉላልን?
\s5
\v 25 እርሻውን ባስተካከለ ጊዜ ጥቁሩን አዝሙድ፣ ከሙኑንም፣ ስንዴውንም፣ በተርታ፣ ገብሱንም በስፍራው፣ አጃንም በደረጃው የሚዘራ አይደለምን?
\v 26 አምላኩ ያስታውቀዋል፣ በብልሃት ያስተምረውማል።
\s5
\v 27 በተጨማሪም፣ ጥቁሩ አዝሙድ በተሳለች መሄጃ አያስኬድም፣ የሰረገላም መንኰራኵር በከሙን ላይ አይዞርም፤ ነገር ግን ጥቁሩ አዝሙድ በሽመል ከሙኑም በበትር ይወቃል።
\v 28 የእንጀራ እህል ይደቅቃል፣ ነገር ግን ለዘላለም አያኬደውም፤ የሰረገላውን መንኰራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቅቀውም።
\s5
\v 29 ይህም ደግሞ ድንቅ ምክር ከሚመክር በግብሩም ማለፊያ ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ዳዊት ሰፍሮባት ለነበረችው ከተማ ለአርኤል፣ ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፣ በዓላትም ተመልሰው ይምጡ።
\v 2 ነገር ግን አርኤልንም እከብባለሁ፣ ለቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ ለእኔም እንደ አርኤልም ትሆንልኛለች።
\s5
\v 3 በዙሪያሽም እሰፍራለሁ፣ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቅሻለሁ፣ አምባም በላይሽ አቆማለሁ።
\v 4 ትዋረጂማለሽ፣ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፣ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምፅሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፣ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ በደካማነት ይጮኻል።
\s5
\v 5 ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፣ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል። በድንገት፣ በፍጥነትም ይሆናል።
\v 6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፣ በምድርም መናወጥ፣ በታላቅም ድምፅ፣ በዐውሎ ነፋስም፣ በወጨፎም፣ በምትባላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።
\s5
\v 7 በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፣ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፣ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል። ሊያስጨንቋት እርሷንና ምሽጎቿን ያጠቃሉ።
\v 8 የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ እንደሚያይ፣ ነገር ግን ሲነቃ ሆዱ ባዶ እንደሆነው ያክል ነው። የተጠማም ሰው በሕልሙ እየጠጣ እንደሚያይ፣ ነገር ግን ሲነቃ ጥሙ ሳይቆርጥለት ይዝላል። እንዲሁ የጽዮንን ተራራ የሚወጉ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት ይሆናል።
\s5
\v 9 ለራሳችሁ ተደነቁ፣ ተገረሙም፤ ራሳችሁን አሳውሩ፣ የታወራችሁ ሁኑ! በወይን ጠጅ አይሁን እንጂ ሰከሩ፤ በሚያሰክር መጠጥ አይሁን እንጂ ተንገደገዱ።
\v 10 እግዚአብሔር የጥልቅ እንቅልፍ መንፈስ አፍስሶባችኋል። ዐይኖቻችሁን አጨፍኗል፣ ራሶቻችሁን ደግሞ ነቢያት አጨፍነውባችኋል።
\s5
\v 11 ራእይ ሁሉ እንደ ታተመ መጽሐፍ ቃል ሆኖባችኋል፤ ማንበብንም ለሚያውቅ። ይህን አንብብ ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ። ታትሞአልና አልችልም ይላቸዋል፤
\v 12 ደግሞም መጽሐፉን ማንበብን ለማያውቅ "ይህን አንብብ" ብለው በሰጡት ጊዜ እርሱ፣ "ማንበብ አልችልም" ይላቸዋል።
\s5
\v 13 ጌታም አለ፣ "ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባልና፣ በከንፈሮቹም ያከብረኛልና፣ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው። የሚያከብሩኝ ሰዎች ባስተማሩት ትእዛዝ ነው።
\v 14 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ድንቅ ነገርን በዚህ ሕዝብ መካከል ለማድረግ እቀጥላለሁ፤ ድንቅ ነገርን በድንቅ ነገር ላይ አደርጋለሁ። የጥበበኞቻቸውም ጥበብ ትጠፋለች፣ የአስተዋዮችም ማስተዋል ትሰወራለች።"
\s5
\v 15 ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ፣ ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፣ "ማን ያየናል፣ ወይስ ማን ያውቀናል?" ለሚሉ ወዮላቸው!
\s5
\v 16 ነገሮችን ገለባብጣችኋል! የተሠራው ነገር የሠራውን "አልሠራኝም፣" ይለው ዘንድ ሸክላ ሠሪው እንደ ጭቃው ሊቆጠር ይገባልን? ወይስ የተበጀው ነገር ያበጀውን "አታስተውልም" ይለዋልን?
\s5
\v 17 ሊባኖስ እንደ ፍሬያማ እርሻ ሊለወጥ ፍሬያማውም እርሻ እንደ ዱር ሊቈጠር ጥቂት የቀረው አይደለምን?
\v 18 በዚያም ቀን ደንቆሮች የመጽሐፍን ቃል ይሰማሉ፣ የዕውሮችም ዓይኖች ከጭጋግና ከጨለማ ተለይተው ያያሉ።
\v 19 የተጨቆኑ ደስታቸውን በእግዚአብሔር ያበዛሉ፣ በሰዎች መካከል ያሉ ድሆችም ሐሤትን በእስራኤል ቅዱስ ያደርጋሉ።
\s5
\v 20 ጨካኙ ይቋረጣልና፣ ፌዘኛውም ይጠፋልና። ክፋትን ማድረግ የሚወድዱ ይወገዳሉ።
\v 21 እነዚህም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ። በበርም ለሚገሥጸው ወጥመድ የሚያኖሩ፣ ጻድቁንም በከንቱ ውሸት የሚያስቱ ናቸው።
\s5
\v 22 ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፣ "ያዕቆብ ከእንግዲህ አያፍርም፣ ፊቱም አይገረጣም።
\v 23 ነገር ግን የእጄ ሥራ የሆኑትን ልጆቹን ባያቸው ጊዜ ስሜን ይቀድሳሉ። የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፣ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።
\v 24 በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያገኛሉ፣ የሚያጕረመርሙም ትምህርትን ይቀበላሉ።"
\s5
\c 30
\p
\v 1 "ለዓመፀኞች ልጆች ወዮላቸው፣" ይላል እግዚአብሔር። "ከእኔ ዘንድ ያልሆነን ዕቅድ ይመክራሉ፣ ኃጢአትንም በኃጢአት ላይ ይጨምሩ ዘንድ በመንፈሴ ያልተመራውን የትብብር ኪዳን ያደርጋሉ።
\v 2 ከእኔም ምሪትን ሳይጠይቁ ወደ ግብጽ ይሄዱ ዘንድ ይወጣሉ። በፈርዖን ኃይል ይጸኑ ዘንድ በግብጽም ጥላ ይታመኑ ዘንድ ይፈልጋሉ።
\s5
\v 3 ስለዚህ የፈርዖን ከለላ እፍረት፣ በግብጽም ጥላ መታመን ውርደት ይሆንባችኋል።
\v 4 አለቆቻቸው በጣኔዎስ ቢሆኑ እንኳን፣ መልክተኞቻቸውም ወደ ሓኔስ ቢደርሱ እንኳን።
\v 5 ሁላቸው ይጠቅሙአቸው ዘንድ ስለማይችሉ፣ እፍረትና ስድብ እንጂ ረድኤትና ረብ ስለማይሆኑ ሕዝብ ያፍራሉ።
\s5
\v 6 በኔጌቭ ስላሉ አውሬዎች የተነገረ ሸክም፦ ተባትና እንስት አንበሳ እፉኝትም ነዘር እባብም በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።
\v 7 የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምናምን ነው፤ ስለዚህ ስሙን፣ ተረጋግጦ የሚቀመጥ ረዓብ ብዬ ጠርቼዋለሁ።
\s5
\v 8 አሁንም ሂድ፣ ለሚመጣውም ዘመን ለምስክርነት እንዲሆን በሰሌዳ ላይ በመጽሐፍም ውስጥ ጻፍላቸው።
\v 9 እነዚህ ዓመፀኛ ሕዝብ ናቸውና፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ለመስማት የማይወድዱ የሐሰት ልጆች ናቸውና።
\s5
\v 10 ለባለ ራእዮች፣ "አትመልከቱ፤" ይላሉ፣ ለነቢያትም፣ "የለዘበውን ነገር፣ አታላዩን ነገር እንጂ፣ ቀጥተኛውን እውነት አትንገሩን፤
\v 11 ከመንገድ ፈቀቅ በሉ፤ ከጐዳናውም ዘወር በሉ፤ የእስራኤልንም ቅዱስ ከእኛ ዘንድ አስወግዱ" ይሉአቸዋል።
\s5
\v 12 ስለዚህ የእስራኤል ቅዱስ እንዲህ ይላል፣ "ይህችን ቃል አቃልላችሁ፣ በግፍና በጠማምነት ታምናችኋልና፣ በእርሱም ተደግፋችኋልና፣
\v 13 ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፣ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።"
\s5
\v 14 የሸክላ ሠሪ ማድጋ እንደሚሰበር ይሰብረዋል፤ ሳይራራም ያደቅቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት ወይም ውኃ ከጕድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።
\s5
\v 15 የእስራኤል ቅዱስ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ኃይል ይሆንላችኋል። እናንተም እንቢ አላችሁ።
\v 16 ነገር ግን፣ 'አይሆንም፣ በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም' አላችሁ፣ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፣ 'በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን' አላችሁ፣ ስለዚህም የሚያሳድዱአችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።
\s5
\v 17 ከአንድ ሰው ዛቻ የተነሣ ሺህ ሰዎች ይሸሻሉ፤ እናንተም በተራራ ራስ ላይ እንዳለ ምሰሶ፣ በኮረብታም ላይ እንዳለ ምልክት ሆናችሁ እስክትቀሩ ድረስ፣ ከአምስት ሰዎች ዛቻ የተነሣ ትሸሻላችሁ።"
\s5
\v 18 ይሁን እንጂ እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፣ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብሩካን ናቸው።
\v 19 በኢየሩሳሌም ውስጥ በጽዮን የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ፣ ከእንግዲህ ወዲህ አታለቅሱም፤ በጩኸትም ድምፅ ይራራላችኋል፣ በሰማችሁም ጊዜ ይመልስላችኋል።
\s5
\v 20 ጌታም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ቢሰጥህም፣ አስተማሪህ ከእንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፣ ነገር ግን አስተማሪህን በገዛ ራስህ ዐይኖች ታያለህ።
\v 21 ወደ ቀኝም ወደ ግራም ብትዞር ከበስተኋላህ ጆሮችህ "መንገዱ ይህች ናት፣ በእርስዋም ሂድ" የሚለውን ቃል ይሰማሉ።
\s5
\v 22 በብርም የተለበጡትን የተቀረጹትን ምስሎችህን በወርቅም የተለበጡትን ቀልጠው የተሠሩትን ምስሎችህን ታረክሳለህ፤ እንደ ርኩስ ጨርቅ ትጥላቸዋለህ። "ከዚህ ውጡ" ትላቸውማለህ።
\s5
\v 23 በምድርም ለተዘራው ዘርህ ዝናብ ይሰጣል፣ ከምድርም ፍሬ የሚወጣ እንጀራ ወፍራምና ብዙ ይሆናል። እህሉም ብዙ ይሆናል። በዚያም ቀን ከብቶችህ በሰፊ መስክ ይግጣሉ።
\v 24 መሬትንም የሚያርሱ በሬዎችና አህዮች በመንሽና በወንፊት የነጻውን ጨው ጨው የሚለውን ገፈራ ይበላሉ።
\s5
\v 25 በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ በረጅሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።
\v 26 እግዚአብሔርም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፣ መቅሰፍቱ ያቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፣ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፣ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።
\s5
\v 27 ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር ስም ከሚነድድ ቍጣ ከሚትጐለጐልም ጢስ ጋር ከሩቅ ይመጣል፤ ከንፈሮቹም ቍጣን የተሞሉ ናቸው፣ ምላሱም እንደምትበላ እሳት ናት።
\v 28 እስትንፋሱም አሕዛብን በአጥፊ ወንፊት ሊነፋቸው እንደሚያጥለቀልቅ እስከ አንገትም እንደሚደርስ ወንዝ ነው፣ በሕዝብም መንጋጋ የሚያስት ልጓም ይሆናል።
\s5
\v 29 ዝማሬ በተቀደሰች የዐውደ ዓመት ሌሊት እንደሚሆን ዝማሬ ይሆንላችኋል፤ ወደ እግዚአብሔርም ተራራ ወደ እስራኤል አምባ ይመጣ ዘንድ እንቢልታ ይዞ እንደሚሄድ ሰው የልብ ደስታ ይሆንላችኋል።
\s5
\v 30 እግዚአብሔርም ክቡር ድምፁን ያሰማል፣ የክንዱንም መውረድ በሚነድድ ቍጣውና በምትባላ እሳት ነበልባል፣ በዐውሎ ነፋስም በወጨፎም፣ በበረዶ ጠጠርም ይገልጣል።
\s5
\v 31 አሦርም በበትር ከመታው ከእግዚአብሔር ድምፅ የተነሣ ይደነግጣል።
\v 32 እግዚአብሔር በላዩ በሚያወርድበት የታዘዘበቱ የበትር ድብደባ ሁሉ በከበሮና በመሰንቆ ይሆናል፤ በጦርነትም ክንዱን አንሥቶ ይዋጋቸዋል።
\s5
\v 33 ከጥንት ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች። በእርግጥ፣ ለንጉሥም ተበጅታለች፣ እግዚአብሔርም ጥልቅና ሰፊ አድርጎአታል። እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፣ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፣ (እጅግ ብርቱዎችም) ስለ ሆኑ፣ በፈረሰኞች ለሚታመኑ (የማይቆጠሩ ስለሆኑ) ፣ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ፣ እግዚአብሔርንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!
\v 2 እርሱ ደግሞ ጠቢብ ነው፣ ክፉንም ነገር ያመጣል፣ ቃሉንም አይመልስም። በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።
\s5
\v 3 ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፣ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም። እግዚአብሔርም እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፣ ሁለቱም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር የሚለኝ እንዲህ ነውና፣ "አንበሳ ወይም የአንበሳ ደቦል በንጥቂያው ላይ ሲያገሳ፣ ብዙ እረኞች ቢከማቹበት ከቃላቸው እንደማይፈራ፣ ከድምፃቸውም እንደማይዋረድ፣ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጽዮን ተራራና በኮረብታዋ ላይ ይዋጋ ዘንድ ይወርዳል።
\s5
\v 5 እንደሚበርር ወፍ፣ እንዲሁ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ይጋርዳታል፤ ይከልላታል፥ በላይዋ ሲያልፍ ይታደጋታል ያድናታልም።
\v 6 እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ፣ አጥብቃችሁ ወደ ዐመፃችሁበት ተመለሱ።
\v 7 በዚያም ቀን እያንዳንዳቸው እጆቻቸው ለኃጢአት የሠሩላቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ይጥላሉና።
\v 8 አሦርም በሰይፍ፣ የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃል፣ የሰውም ያልሆነ ሰይፍ ይበላዋል፤ ከሰይፍም ይሸሻሉ ጐበዛዝቱም ገባሮች ይሆናሉ።
\v 9 አምባው ከፍርሃት የተነሣ ያልፋል፣ መሳፍንቱም ከዓላማው የተነሣ ይደነግጣሉ፤" ይላል እሳቱ በጽዮን፣ እቶኑም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ተመልከቱ፣ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፣ መሳፍንትም በፍርድ ይገዛሉ።
\v 2 ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ፣ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፣ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፣ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ድንጋይ ጥላ ይሆናል።
\v 3 ከዚያም፣ የሚያዩትም ሰዎች ዓይኖች አይደበዝዙም፣ የሚሰሙትም ጆሮች በትኩረት ያደምጣሉ።
\s5
\v 4 ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፣ የተብታቦችም ምላስ በቀላሉ አድርጋ ትናገራለች።
\v 5 ከእንግዲህ ወዲህ ሰነፍ ከበርቴ ተብሎ አይጠራም፣ አታላዩም የተገራ አይባልም።
\v 6 ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፣ ልቡም ዝንጉነትን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔርም ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፣ የተራበችውንም ሰውነት ባዶ ያደርግ ዘንድ፣ ከተጠማም ሰው መጠጥን ይቈርጥ ዘንድ በደልን ይሠራል።
\s5
\v 7 የንፉግም ዕቃ ክፉ ናት። ችግረኛ ትክክል ነገርን በተናገረ ጊዜ እንኳ እርሱ በሐሰት ቃል ድሀውን ያጠፋ ዘንድ ክፉን አሳብ ያስባል።
\v 8 ነገር ግን፣ ከበርቴው ሰው ለመከበር ያስባል፤ በመከበርም ጸንቶ ይኖራል።
\s5
\v 9 እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፣ ተነሡ፣ ድምፄንም ስሙ፤ እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ንግግሬን አድምጡ።
\v 10 እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፣ ወይንን መሰብሰብ ይቀራልና፣ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ።
\s5
\v 11 እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፣ ተጠንቀቁ፤ ተማምናችሁም የምትቀመጡ ሆይ፣ ተንቀጥቀጡ፤ የቅምጥል ልብሳችሁን አውልቁ፣ ዕራቁታችሁን ሁኑ፣ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።
\v 12 ስለ ተወደደችውም እርሻ፣ ስለሚያፈራውም ወይን ደረታችሁን ድቁ።
\v 13 በሕዝቤ ምድር ላይ፣ በደስታ ከተማ ባሉት በደስታ ቤቶች ሁሉ ላይ እሾህና ኵርንችት ይወጣባቸዋል፤
\s5
\v 14 አዳራሹ ወና ትሆናለችና፣ የብዙ ሰውም ከተማ ትለቅቃለችና፣ አምባውና ግንቡም ለዘላለም ዋሻ፣ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፣ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናልና፤
\v 15 ይህም፣ መንፈስ ከላይ እስኪፈስስልን፣ ምድረ በዳውም ፍሬያማ እርሻ እስኪሆን፣ ፍሬያማውም እርሻ ጫካ ተብሎ እስኪቈጠር ድረስ ይሆናል።
\s5
\v 16 ከዚያ በኋላ ፍርድ በምድረ በዳ ይኖራል፤ ጽድቅም በፍሬያማው እርሻ ያድራል።
\v 17 የጽድቅም ሥራ ሰላም፣ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።
\v 18 ሕዝቤም በሰላም ማደሪያ፣ በታመነም ቤት በጸጥተኛ ማረፊያ ይቀመጣል።
\s5
\v 19 በረዶ ግን በዱር ላይ ይወርዳል፣ ከተማም ፈጽማ ትዋረዳለች፣
\v 20 እናንተ የበሬና የአህያ እግር እየነዳችሁ በውኃ ሁሉ አጠገብ የምትዘሩ ትባረካላችሁ።
\s5
\c 33
\p
\v 1 አንተ ሳትጠፋ የምታጠፋ፣ በአንተም ላይ ወንጀል ሳይደረግ ወንጀል የምታደርግ ወዮልህ! ማጥፋትን በተውህ ጊዜ ትጠፋለህ፣ አሳልፎ መስጠትንም በተውህ ጊዜ አሳልፈው ይሰጡሃል።
\s5
\v 2 እግዚአብሔር፣ ማረን፤ አንተን ተማምነናል፤ በየጠዋቱ ክንድ፣ በመከራም ጊዜ ማዳን ሁነን።
\s5
\v 3 ከታላቅ ጫጫታ ወገኖች ሸሹ፣ ስትነሣም አሕዛብ ተበትነዋል።
\v 4 አንበጣ እንደሚሰበስብ፣ ምርኮአችሁ ትሰበሰባለች፣ ኩብኩባም እንደሚዘልል፣ ሰዎች ይዘልሉበታል።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር ገነነ። እርሱ በአርያም ይኖራል። ጽዮንን በፍትህና በጽድቅ ሞላት።
\v 6 የዘመንህም ጸጥታ፣ የመድኃኒት ብዛት፣ ጥበብና እውቀት ይሆናል፤ እግዚአብሔርን መፍራት መዝገቡ ነው።
\s5
\v 7 ተመልከቱ፣ ባለሥልጣናቶቻቸው በጎዳና ይጮኻሉ፤ የሰላም መልእክተኞች መራራ ለቅሶ ያለቅሳሉ።
\v 8 መንገዶች ተራቆቱ፣ ተላላፊም ቀረ፤ እርሱም ቃል ኪዳንን አፈረሰ፣ ከተሞችንም ናቀ ሰውንም አልተመለከተም።
\s5
\v 9 ምድሪቱ አለቀሰች ከሳችም፤ ሊባኖስ አፈረ ጠወለገም፤ ሳሮን እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ባሳንና ቀርሜሎስ ቅጠላቸውን አረገፉ።
\s5
\v 10 "አሁን እነሣለሁ" ይላል እግዚአብሔር፤ "አሁን እከበራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ።"
\v 11 ገለባን ትፀንሳላችሁ፣ እብቅንም ትወልዳላችሁ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት።
\v 12 አሕዛብም እንደ ተቃጠለ ኖራ፣ ተቈርጦም በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ ይሆናሉ።
\s5
\v 13 እናንተ በሩቅ ያላችሁ፣ የሠራሁትን ስሙ፣ እናንተም በቅርብ ያላችሁ ኃይሌን እወቁ።"
\v 14 በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ፈሩ፣ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎቹን ያዘ፤ ከምትበላ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ? ለዘላለምም ከምትነድድ እሳት ጋር መኖርን የሚችል ከእኛ ማን አለ?
\s5
\v 15 በጽድቅ የሚሄድ ቅን ነገርንም የሚናገር፤ በሽንገላ የሚገኝ ትርፍን የሚንቅ፥ መማለጃ ጉቦን ከመጨበጥ እጁን የሚያርቅ፣ ደም የማፍሰስ ወንጀልን ከመስማት ጆሮቹን የሚያደነቍር፣ ክፋትንም ከማየት ዓይኖቹን የሚጨፍን ነው።
\v 16 እርሱ ከፍ ባለ ስፍራ ይቀመጣል፣ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፣ እንጀራም ይሰጠዋል፣ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።
\s5
\v 17 ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ሰፊ ምድርን ያዩአታል።
\v 18 ልብህም፣ ጸሐፊ ወዴት አለ? ገንዘቡንስ መዛኝ ወዴት አለ? ግንቦቹንስ የቈጠረ ወዴት አለ? ብሎ የሚያስፈራ ነገር ያስባል።
\v 19 ጨካኝን ሕዝብ፣ ቋንቋው ለማስተዋል ጥልቅ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ፣ አታይም።
\s5
\v 20 የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፣ ዓይኖችህ የሰላም ማደሪያ፣ ካስማውም ለዘላለም የማይነቀል፣ አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ፣ የማይወገድ ድንኳን የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
\v 21 ይልቅ፣ እግዚአብሔር በዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ ከእኛ ጋር በግርማ ይሆናል። የሚቀዘፉ መርከቦች አይጓዙባትም፣ ታላላቆችም መርከቦች አያልፉባትም።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር ፈራጃችን ነውና፣ እግዚአብሔር ሕግን የሰጠን ነውና፣ እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።
\s5
\v 23 ገመዶችህ ላልተዋል፣ ደቀላቸውንም አላጸኑም፣ ሸራውንም መዘርጋት አልቻሉም፤ በዚያም ጊዜ የብዙ ምርኮ ብዝበዛ ተከፈለ፤ አንካሶች እንኳ ብዝበዛውን በዘበዙ።
\v 24 በዚያም የሚኖር፣ "ታምሜአለሁ፣" አይልም፤ በእርስዋም ለሚቀመጡ ሰዎች በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋል።
\s5
\c 34
\p
\v 1 እናንተ አሕዛብ ሆይ፣ ቅረቡ፣ ስሙ፤ እናንተ ሕዝቦች ሆይ፣ አድምጡ! ምድርና ሞላዋ፣ ዓለምና ከእርስዋ የሚወጣ ሁሉ ይስሙ።
\v 2 የእግዚአብሔር ቍጣ በአሕዛብ ሁሉ ላይ፣ መዓቱም በሠራዊታቸው ሁሉ ላይ ነው፤ ፈጽሞ አጠፋቸው፣ ለመታረድም አሳልፎ ሰጣቸው።
\s5
\v 3 ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ፣ የሬሳቸውም ግማት በሁሉ ቦታ ይሸታል፣ ተራሮችም በደማቸው ይርሳሉ።
\v 4 የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ይበሰብሳሉ፣ ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ፣ ከወይንና ከበለስም ቅጠል እንደሚረግፍ፣ ሠራዊታቸው ሁሉ ይረግፋል።
\s5
\v 5 ሰይፌ በሰማይ ሆና እስክትረካ ድረስ ጠጥታለች፤ ተመልከቱ፣ በኤዶምያስና በረገምሁት ሕዝብ ላይ አሁን ለፍርድ ትወርዳለች።
\v 6 የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፣ በስብም፣ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፣ በአውራም በግ ኵላሊት ስብ ወፍራለች። እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፣ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና።
\s5
\v 7 ጎሽ ከእነርሱ ጋር፣ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትረካለች፣ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች።
\s5
\v 8 የእግዚአብሔር የበቀሉ ቀን፣ ስለ ጽዮንም ክርክር የብድራት ዓመት ነው።
\v 9 የኤዶምያስም ምንጮች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፣ አፈርዋም ዲን ይሆናል፣ መሬትዋም የሚቀጠል ዝፍት ትሆናለች።
\v 10 በሌሊትና በቀንም ይቃጠላል፣ ጢስዋም ለዘላለም ይወጣል፤ ከትውልድ እስከ ትውልድም ድረስ ባድማ ሆና ትኖራለች፤ ለዘላለም ዓለም ማንም አያልፍባትም።
\s5
\v 11 ነገር ግን፣ ጭልፊትና ጃርት ግን ይኖሩባታል፤ ጕጕትና ቍራም መረባቸውን ይሠሩባታል። በላይዋም የመፍረስ ገመድና የባዶነት ቱንቢ ይዘረጋባታል።
\v 12 መሳፍንቶችዋን ወደ መንግሥት ይጠራሉ፣ ነገር ግን ማንም አይገኝባትም፤ አለቆችዋም ሁሉ ምናምኖች ይሆናሉ።
\s5
\v 13 በቤተ መንግሥቶቿ እሾህ፣ በቅጥሮችዋም ሳማን፣ አሜከላ ይበቅሉባታል፤ የቀበሮም ማደሪያና የሰጐን ስፍራ ትሆናለች።
\v 14 የምድረ በዳም አራዊት ከተኵሎች ጋር ይገናኛሉ፣ አጋንንትም እርስ በርሳቸው በጩኸት ይጠራራሉ፤ ጅንም በዚያ ትኖራለች ለእርስዋም ማረፊያ ታገኛለች።
\v 15 በዚያም ዋሊያ ቤትዋን ትሠራለች፣ እንቍላልም ትጥላለች ትቀፈቅፈውማለች ልጆችዋንም በጥላዋ ትሰበስባለች፤ በዚያም ደግሞ አሞራዎች እያንዳንዳቸው ከባልንጀሮቻቸው ጋር ይሰበሰባሉ።
\s5
\v 16 በእግዚአብሔር የመጽሐፍ ጥቅልል ውስጥ ፈልጉ፣ አንዳቸውም አይጠፉም። አፌ አዝዞአልና፣ መንፈሱም ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፣ ባልንጀራውንም የሚያጣ የለም።
\v 17 እርሱም ዕጣ ጣለባቸው፣ እጁም በገመድ ከፈለችላቸው፤ ለዘላለም ይገዙአታል፣ ከትውልድም እስከ ትውልድ ድረስ ይቀመጡባታል።
\s5
\c 35
\p
\v 1 ምድረ በዳውና ደረቁ ምድር ደስ ይላቸዋል፣ በረሀውም ሐሤት ያደርጋል እንደ ጽጌ ረዳም ያብባል።
\v 2 እጅግ ተትረፍርፎ ያብባል፣ በደስታና በዝማሬ ሐሤትን ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብር፥ የቀርሜሎስና የሳሮን ግርማ ይሰጠዋል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር የአምላካችንንም ግርማ ያያሉ።
\s5
\v 3 የደከሙትን እጆች አበርቱ፣ የላሉትንም ጕልበቶች አጽኑ።
\v 4 ፈሪ ልብ ላላቸው፣ "ተመልከቱ፣ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፣ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፣ አትፍሩ" በሉአቸው።
\s5
\v 5 በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ያያል፣ የደንቆሮችም ጆሮ ይሰማል።
\v 6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፣ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፣ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
\v 7 ደረቂቱ ምድር ኵሬ፣ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆ ደንገልም ይሆንበታል።
\s5
\v 8 በዚያም ጐዳናና መንገድ ይሆናል እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል። ንጹሐንም ያልሆኑ አይጓዙበትም። ነገር ግን ለሚጓዙበት ይሆናል፤ ተላላፊዎችና ሰነፎች አይጓዙበትም።
\v 9 አንበሳም አይኖርበትም፣ ነጣቂ አውሬም አይወጣበትም፣ ከዚያም አይገኙም፤ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ፤
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ፣ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።
\s5
\c 36
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፣ በንጉሡ ሕዝቅያስ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ይሁዳ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ ወጥቶ ያዛቸው።
\v 2 ከዚያም፣ የአሦርም ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፣ እርሱም በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛይቱ ኵሬ መስኖ አጠገብ ቆመ።
\v 3 የቤቱም አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ወደ እርሱ ወጡ።
\s5
\v 4 ራፋስቂስም እንዲህ አላቸው፣ "ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፣ "ይህ የምትታመንበት መተማመኛ ምንድር ነው?
\v 5 እኔ፣ ለሰልፍ የሆነው ምክርህና ኃያልህ ከንቱ ነገር ነው አልሁ፤ አሁንም በእኔ ላይ ያመፅኸው በማን ተማምነህ ነው?
\s5
\v 6 ተመልከት፣ እየታመንክ ያለኸው በዚህ በተቀጠቀጠ በሸምበቆ በትር በግብጽ ነው። ሰው ቢመረኰዘው ተሰብሮ በእጁ ይገባል ያቈስለውማል። የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚታመኑበት ሁሉ አንዲሁ ነው።
\v 7 አንተም፣ "በአምላካችን በእግዚአብሔር እንታመናለን ብትለኝ፣ ሕዝቅያስ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን፣ "በዚህ መሠዊያ ፊት ስገዱ" ብሎ የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ይስፈረሰ ይህ አይደለምን?
\s5
\v 8 አሁን እንግዲህ፣ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋር በመልካም ተደራደር። የሚጋልቡባቸውንም ሰዎች ማግኘት ቢቻልህ እኔ ሁለት ሺህ ፈረሶች እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 9 ስለ ሰረገሎችና ስለ ፈረሶኞች በግብጽ ስትታመን፣ ከጌታዬ ባሪያዎች የሚያንሰውን የአንዱን አለቃ ፊት ትቃወም ዘንድ እንዴት ይቻልሃል?
\v 10 አሁንም በውኑ ያለ እግዚአብሔር ትእዛዝ ይህን አገር አጠፋ ዘንድ ወጥቻለሁን? እግዚአብሔር፣ "ወደዚህ አገር ወጥተህ አጥፋው" አለኝ።
\s5
\v 11 ከዚያም ኤልያቄምና ሳምናስ፣ ዮአስም ራፋስቂስን፣ "እኛ እንሰማለንና እባክህ፣ በሶርያ ቋንቋ ለባሪያዎችህ ተናገር፤ በቅጥርም ላይ ባለው ሕዝብ ጆሮ በአይሁድ ቋንቋ አትናገረን" አሉት።
\v 12 ራፋስቂስ ግን፣ "ጌታዬ ይህን ቃል እናገር ዘንድ ወደ አንተና ወደ ጌታህ ልኮኛልን? ከእናንተ ጋር ዐይነምድራቸውን ይበሉ ዘንድ ሽንታቸውንም ይጠጡ ዘንድ በቅጥር ላይ ወደ ተቀመጡት ሰዎች አይደለምን?" አላቸው።
\s5
\v 13 ራፋስቂስም ቆሞ በታላቅ ድምፅ በአይሁድ ቋንቋ እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ "የታላቁን የአሦርን ንጉሥ ቃል ስሙ፤
\v 14 ንጉሡ እንዲህ ይላል፣ 'ያድናችሁ ዘንድ አይችልምና ሕዝቅያስ አያታልላችሁ።
\v 15 ሕዝቅያስም፣ "እግዚአብሔር በእርግጥ ያድነናል ይህችም ከተማ በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም" ብሎ በእግዚአብሔር እንድትታመኑ አያድርጋችሁ።
\s5
\v 16 ሕዝቅያስንም አትስሙ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላልና፦ 'ከእኔ ጋር ታረቁ ወደ እኔም ውጡ። እያንዳንዳችሁም ከወይናችሁና ከበለሳችሁ ብሉ፣ ከጕድጓዳችሁም ውኃ ጠጡ።
\v 17 ይህም መጥቼ ምድራችሁን ወደምትመስለው ምድር፣ እህልና የወይን ጠጅ፣ እንጀራና ወይን ወዳለበት ምድር እስካፈልሳችሁ ድረስ ነው።'
\s5
\v 18 ሕዝቅያስም፣ 'እግዚአብሔር ያድነናል' ብሎ እንዳያታልላችሁ ተጠንቀቁ። በውኑ የአሕዛብ አማልክት አገሮቻቸውን ከአሦር ንጉሥ እጅ አድነዋቸዋልን?
\v 19 የሐማትና የአርፋድ አማልክት ወዴት አሉ? የሴፈርዋይም አማልክት ወዴት አሉ? ሰማርያን ከእጄ አድነዋታልን?
\v 20 እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ከእጄ ያድን ዘንድ ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ አገሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?"
\s5
\v 21 ነገር ግን ንጉሡ አንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና ሕዝቡ ዝም አሉ፣ አንዳችም አልመለሱለትም።
\v 22 ከዚያም የቤቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም ጸሐፊውም ሳምናስ ታሪክ ጸሐፊም የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፣ የራፋስቂስንም ቃል ነገሩት።
\s5
\c 37
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፣ ንጉሡ ሕዝቅያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፣ ማቅም ለበሰ፣ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገባ።
\v 2 የቤቱንም አዛዥ ኤልያቄምን፣ ጸሐፊውንም ሳምናስን የካህናቱንም ሽማግሌዎች ማቅ ለብሰው ወደ ነቢዩ ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ኢሳይያስ ይሄዱ ዘንድ ላካቸው።
\s5
\v 3 እነርሱም፣ "ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፣ 'ይህ ቀን የመከራና የተግሣጽ የዘለፋም ቀን ነው፤ ልጆች የሚወለዱበት ጊዜ ደርሶአል፣ እናታቸው ግን ለመውለድ ኃይል የላትም።
\v 4 ምናልባት በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ ጌታው የአሦር ንጉሥ የላከውን የራፋስቂስን ቃል አምላክህ እግዚአብሔር ይሰማ እንደ ሆነ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ስለ ሰማው ቃል ይገሥጸው እንደ ሆነ፣ ስለዚህ አሁን ድረስ እዚህ ላለው ቅሬታ ጸልይ" አሉት።
\s5
\v 5 ስለዚህ የንጉሡ የሕዝቅያስ ባሪያዎች ወደ ኢሳይያስ መጡ፣
\v 6 ኢሳይያስም እንዲህ አላቸው፣ ለጌታችሁ እንዲህ በሉት፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ የአሦር ንጉሥ ባሪያዎች ስለ ሰደቡኝ፣ ስለ ሰማኸው ቃል አትፍራ።
\v 7 ተመልከት፣ በላዩ መንፈስን እሰድዳለሁ፣ ወሬንም ይሰማል፣ ወደ ምድሩም ይመለሳል። በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ" በሉት" አላቸው።
\s5
\v 8 ከዚያም የአሦርም ንጉሥ ከለኪሶ እንደ ራቀ ሰምቶ ነበርና ራፋስቂስ ተመልሶ በልብና ሲዋጋ አገኘው።
\v 9 እርሱም፣ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ እና ግብጽ ሊወጉህ መጥቶአል የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፦
\v 10 እንዲህ ሲል፣ "ለይሁዳ ንጉሠ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፣ 'ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሥ እጅ አትሰጥም ብሎ የምትታመንበት አምላክህ አያታልልህ።'
\s5
\v 11 ተመልከት፣ የአሦር ነገሥታት በምድር ሁሉ ላይ ያደረጉትን፣ እንዴትስ ፈጽመው እንዳጠፉአቸው ሰምተሃል። አንተስ ትድናለህን?
\v 12 አባቶቼ ያጠፉአቸውን ጎዛንን፣ ካራንን፣ ራፊስን፣ በተላሳር የነበሩትንም የዔድንን ልጆች የአሕዛብ አማልክት አዳኑአቸውን?
\v 13 የሐማት ንጉሥ፣ የአርፋድ ንጉሥ፣ የሴፈርዋይም ከተማ ንጉሥ፣ የሄናና የዒዋ ንጉሥ ወዴት አሉ?"
\s5
\v 14 ሕዝቅያስም ደብዳቤውን ከመልእክተኞች እጅ ተቀብሎ አነበበው። ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው።
\v 15 ሕዝቅያስም ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ጸለየ፣
\v 16 "አቤቱ፣ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ሆይ፣ አንተ ብቻህን የምድር መንግሥታት ሁሉ አምላክ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን ፈጥረሃል።
\s5
\v 17 አቤቱ፣ ጆሮህን አዘንብልና ስማ። አቤቱ፣ ዐይኖችህን ክፈትና እይ፤ በሕያው አምላክ ላይ ይገዳደር ዘንድ የላከውን የሰናክሬም ቃል ስማ።
\v 18 አቤቱ፣ በእውነት የአሦር ነገሥታት ዓለሙን ሁሉ አገሮቻቸውንም አፍርሰዋል፣
\s5
\v 19 አማልክቶቻቸውንም በእሳት ላይ ጥለዋል፣ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራ ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
\v 20 እንግዲህም አምላካችን አቤቱ፣ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድነን።"
\s5
\v 21 ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ እንዲህ ብሎ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላከ፣ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስለ አሦር ንጉሥ ስለ ሰናክሬም ወደ እኔ ለምነሃልና
\v 22 እግዚአብሔር ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣ ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል ንቃሃለች፣ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።
\v 23 የተገዳደርኸው የሰደብኸውስ ማን ነው? ቃልህንስ ከፍ ከፍ ያደረግህበት ዓይንህንስ ወደ ላይ ያነሣህበት ማን ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው።
\s5
\v 24 አንተም፣ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፣ ወደ ሊባኖስ ጥግ ላይ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹንም ዝግባዎች የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፣ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ቀርሜሎስ ዱር እገባለሁ።
\v 25 ቈፈርሁም ውኃም ጠጣሁ የግብጽንም ወንዞች ሁሉ በእግሬ ጫማ አደርቃለሁ ብለህ በባሪያዎችህ እጅ በጌታ ላይ ተገዳደርህ።'
\s5
\v 26 እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፣ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? አሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ።
\v 27 ስለዚህ የሚኖሩባቸው ሰዎች እጃቸው ዝሎአል፣ ደንግጠውም ታውከዋል። እንደ ምድረ በዳ ሣር፣ እንደ ለመለመም ቡቃያ፣ በሰገነትም ላይ እንዳለ ሣር፣ ሳይሸት ዋግ እንደ መታው እህል ሆነዋል።
\s5
\v 28 ነገር ግን እኔ መቀመጫህንና መውጫህን፣ መግቢያህንም በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቍጣ አውቄአለሁ።
\v 29 ቍጣህና ትዕቢትህ ወደጆሮዬ ደርሶአልና ስለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፣ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።"
\s5
\v 30 ይህም ምልክት ይሆንሃል፦ በዚህ ዓመት የገቦውን፣ በሁለተኛውም ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ። በሦስተኛውም ዓመት ትዘራላችሁ ታጭዱማላችሁ፣ ወይንም ትተክላላችሁ ፍሬውንም ትበላላችሁ።
\s5
\v 31 ያመለጠው የይሁዳ ቤት ቅሬታ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፣ ወደ ላይም ያፈራል።
\v 32 ከኢየሩሳሌም ቅሬታ፣ ከጽዮንም ተራራ ያመለጡት ይወጣሉና።' የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል።"
\s5
\v 33 ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፣ "ወደዚህች ከተማ አይመጣም፣ ፍላጻንም አይወረውርባትም። በጋሻም አይመጣባትም፣ የአፈርንም ምሽግ አይደለድልባትም።
\v 34 በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፤ ወደዚችም ከተማ አይመጣም፤ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 35 ስለ እኔም፣ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት፣ ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ።"
\s5
\v 36 የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፣ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ። ማለዳም በተነሡ ጊዜ፣ እነሆ፣ ሁሉ በየሥፍራው በድኖች ተረፍርፈው ነበሩ።
\v 37 የአሦርም ንጉሥ ሰናክሬም ተነሥቶ ሄደ፣ ተመልሶም በነነዌ ተቀመጠ።
\s5
\v 38 ኋላ ላይ፣ በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ፣ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት። ወደ አራራትም አገር አመለጡ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
\s5
\c 38
\p
\v 1 በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ለሞት እስኪደርስ ድረስ ታመመ። ስለዚህ፣ ነቢዩ የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል' አለው።
\v 2 ከዚያም፣ ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፣
\v 3 "አቤቱ፣ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ።" ሕዝቅያስም እየጮኸ አለቀሰ።
\s5
\v 4 ከዚያም የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 5 "ሂድ፣ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፣ 'የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፣ እንባህንም አይቻለሁ። ተመልከት፣ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት አጨምራለሁ።
\v 6 አንተንና ይህችንም ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፣ ይህችንም ከተማ እጋርዳታለሁ።
\s5
\v 7 እግዚአብሔርም የተገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል፦
\v 8 ተመልከት፣ በአካዝ የጥላ ስፍረ-ሰዓት ላይ ከፀሐይ ጋር የወረደውን በደረጃዎች ያለውን ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደርጋለሁ።" ስለዚህ ፀሐይም በጥላ ስፍረ-ሰዓት ላይ የወረደበት ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።
\s5
\v 9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታምሞ ከደዌው በተፈወሰ ጊዜ የጻፈው ጽሕፈት ይህ ነው፦
\v 10 "እኔ፣ በሕይወት ዘመኔ መካከል ወደ ሲኦል በሮች እገባለሁ፤ የቀረው ዘመኔ ጐደለብኝ አልሁ።
\v 11 ደግሞም፣ በሕያዋን ምድር እግዚአብሔርን አላይም፤ በዓለምም ከሚኖሩ ጋር ሰውን እንግዲህ አልመለከትም አልሁ።
\s5
\v 12 ማደሪያዬ ተነቀለች፣ እንደ እረኛ ድንኳንም ከእኔ ዘንድ ተወገደች፤ ሕይወቴንም እንደ ሸማኔ ጠቀለልሁ፤ እርሱም ከመጠቅለያው ይቈርጠኛል፤ ከማለዳም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።
\v 13 እስኪነጋ ድረስ ቈይቼ ነበር፤ እርሱ እንደ አንበሳ አጥንቴን ሁሉ ሰበረ፤ ከማለዳ ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ታጠፋኛለህ።
\s5
\v 14 እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፣ እንደ ርግብም አጕረመረምሁ፤ ዓይኖቼ ወደ ላይ ከማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፣ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።
\v 15 ምን እላለሁ? እርሱ ተናግሮኛል፣ እርሱ ራሱም ይህን አድርጎአል፤ በዘመኔ ሁሉ ስለ ነፍሴ ምሬት ቀስ ብዬ እሄዳለሁ።
\s5
\v 16 ጌታ ሆይ፣ የላክኸው መከራ ለእኔ መልካም ነው፤ ሕይወቴ ተመልሶ ይሰጠኝ፤ አንተም ፈወስኸኝ ወደ ሕይወትም መለስኸኝ።
\v 17 ታላቅ ምሬት ለጥቅሜ ሆነ። አንተም ነፍሴን ከጥፋት ጕድጓድ አዳንሃት፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ወደ ኋላህ ጥለሃልና።
\s5
\v 18 ሲኦል አያመሰግንህምና፤ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጕድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም።
\v 19 እኔ ዛሬ አንደማደርግ ሕያዋን እነርሱ ያመሰግኑሃል፤ አባት ለልጆች እውነትህን ያስታውቃል።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ያድነኛል፣ ስለዚህ በዕድሜያችን ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ቅኔዎችን አውታር ባለው ዕቃ እንዘምራለን።"
\s5
\v 21 አሁን ኢሳይያስም፣ "የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተው በእባጩ ላይ ይለብጡት፣ እርሱም ይፈወሳል" ብሎ ነበር።
\v 22 ሕዝቅያስም፣ "ወደ እግዚአብሔር ቤት እወጣ ዘንድ ምልክቱ ምንድር ነው?" ብሎ ነበር።
\s5
\c 39
\p
\v 1 በዚያ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን፣ ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።
\v 2 ሕዝቅያስም በእነዚህ ነገሮች ደስ አለው፣ ግምጃ ቤቱንም፣ ብሩንና ወርቁንም፣ ቅመሙንና የከበረውንም ዘይት፣ መሣርያም ያለበትን ቤት ሁሉ፣ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።
\s5
\v 3 ከዚያም ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፣ "እነዚህ ሰዎች ምን አሉህ? ከወዴትስ መጡ?" አለው። ሕዝቅያስም፣ "ከሩቅ አገር ከባቢሎን መጡልኝ" አለው።
\v 4 እርሱም፣ "በቤትህ ያዩት ምንድር ነው?" አለው። ሕዝቅያስም፣ "በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም" አለው።
\s5
\v 5 ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፣ "የሠራዊትን ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።
\v 6 'ተመልከት፣ በቤትህ ያለው ሁሉ፣ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ፣ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል። ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 7 ከአንተም ከሚወለዱት ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ" አለው።
\v 8 ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፣ "የተናገርኸው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው" አለው። ደግሞም፣ "በዘመኔ ሰላምና እውነት ይሁን" አለ።
\s5
\c 40
\p
\v 1 "አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ" ይላል አምላካችሁ።
\v 2 ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፣ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፣ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ።
\s5
\v 3 የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪ ቃል፣ "የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ፤ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካክሉ።"
\v 4 ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፣ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፣ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤
\v 5 የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፣ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፣ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
\s5
\v 6 አንድ ድምጽ፣ "ጩኽ" ይላል፣ "ምን ብዬ ልጩኽ?" አልሁ። "ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፣ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።
\v 7 የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።
\v 8 ሣሩ ይደርቃል፣ አበባውም ይረግፋል፣ የአምላካችን ቃል ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።"
\s5
\v 9 የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፣ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ፣ የምስራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፣ አንሺ፣ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፣ "እነሆ፣ አምላካችሁ!" ብለሽ ንገሪ።
\v 10 ተመልከቱ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል። ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው።
\s5
\v 11 መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል።
\s5
\v 12 ውኆችን በእፍኙ የሰፈረ፣ ሰማይንም በስንዝር የለካ፣ የምድርንም አፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን ኮረብቶችንም በሚዛኖች የመዘነ ማን ነው?
\s5
\v 13 የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዘዘ፣ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው?
\v 14 ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው?
\s5
\v 15 ተመልከቱ፣ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፣ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ ተመልከቱ፣ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል።
\v 16 ሊባኖስ ለማንደጃ፣ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም።
\v 17 አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምናምን እንደሚያንሱ፣ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል።
\s5
\v 18 እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ?
\v 19 የተቀረጸውንስ ምስል! ሠራተኛ ሠርቶታል፤ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፣ የብሩንም ሰንሠለት አፍስሶለታል።
\v 20 ለዚህ መባዕ ገንዘቡ ያልበቃው ድሀ የማይነቅዘውን እንጨት ይመርጣል፤ ምስሉም እንዳይናወጥ ያቆመው ዘንድ ብልህ ሠራተኛን ይፈልጋል።
\s5
\v 21 አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?
\v 22 እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፣ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥
\s5
\v 23 አለቆችንም እንዳልነበሩ፣ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያሳንሳቸው እርሱ ነው።
\v 24 ተመልከቱ፣ ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፣ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፣ እነርሱም ደረቁ፣ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው።
\s5
\v 25 "እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ?" ይላል ቅዱሱ።
\v 26 ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፣ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም።
\s5
\v 27 ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ፣ "መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፣ ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች" ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ?
\v 28 አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፣ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፣ አይታክትም፣ ማስተዋሉም ወሰን የለውም።
\s5
\v 29 ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል።
\v 30 ብላቴኖች ይደክማሉ፣ ይታክቱማል፣ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤
\v 31 እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም።
\s5
\c 41
\p
\v 1 "ደሴቶች ሆይ በፊቴ ዝም ብላችሁ አድምጡ፣ አሕዛብም ኃይላቸውን ያድሱ፤ ይቅረቡም በዚያን ጊዜም ይናገሩ፤ ለፍርድ ለአንድነት እንቅረብ።
\v 2 ከምሥራቅ አንዱን ያስነሣ፣ በጽድቅም ወደ አገልግሎቱ የተጠራው ማን ነው? አሕዛብንም አሳልፎ በፊቱ ሰጠው፣ ነገሥታትንም አስገዛለት፤ ለሰይፉ እንደ ትቢያ ለቀስቱም እንደ ተጠረገ እብቅ አድርጎ ሰጣቸው።
\s5
\v 3 አሳደዳቸው፣ እግሮቹም አስቀድመው ባልሄዱባት ፈጣን መንገድ በደኅነት አለፈ።
\v 4 ይህን የሠራና ያደረገ፣ ትውልድንም ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ፣ እግዚአብሔር፣ ፊተኛው በኋላኞችም ዘንድ የምኖር እኔ ነኝ።
\s5
\v 5 ደሴቶች አይተው ፈሩ፣ የምድርም ዳርቾች ተንቀጠቀጡ፤ ቀረቡም ደረሱም።
\v 6 ሁሉም እያንዳንዱ ባልንጀራውን ይረዳው ነበር፣ ወንድሙንም፣ 'አይዞህ' ይለው ነበር።
\v 7 አናጢውም አንጥረኛውን፣ በመዶሻም የሚያሳሳውን መስፍ መችውን አጽናና፣ ስለ ብየዳ ሥራውም፣ 'መልካም ነው' አለ፤ እንዳይንቀሳቀስም በችንካር አጋጠመው።
\s5
\v 8 አንተ ግን፣ ባሪያዬ እስራኤል፣ የመረጥሁህ ያዕቆብ፣ የወዳጄ የአብርሃም ዘር ሆይ፣
\v 9 አንተ ከምድር ዳርቻ የያዝሁህ፣ ከማዕዘንዋም የጠራሁህና፣ 'አንተ ባሪያዬ ነህ፤' መርጬሃለሁ አልጥልህም ያልሁህ ሆይ።
\s5
\v 10 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
\s5
\v 11 ተመልከት፣ እነሆ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፣ ይዋረዱማል፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፣ ይጠፉማል።
\s5
\v 12 የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፣ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።
\v 13 እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፣ 'አትፍራ፣ እረዳሃለሁ' ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
\s5
\v 14 አንተ፣ ትል ያዕቆብ፣ የእስራኤልም ሰዎች ሆይ፣ አትፍሩ፤ እረዳሃለሁ፤" ይላል እግዚአብሔር፣ የሚቤዥህም የእስራኤል ቅዱስ ነው።
\v 15 "ተመልከቱ፣ እንደ ተሳለች እንደ አዲስ ባለ ሁለት ጎን ጥርስ ማሄጃ አድርጌሃለሁ፤ ተራሮችንም ታሄዳለህ ታደቅቃቸውማለህ፣ ኮረብቶችንም እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
\s5
\v 16 ታበጥራቸዋለህ፣ ነፋስም ይጠርጋቸዋል፣ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል። አንተም በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፣ በእስራኤልም ቅዱስ ትመካለህ።
\s5
\v 17 ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፣ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፣ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
\v 18 በወናዎቹ ኮረብቶች ላይ ወንዞችን፣ በሸለቆችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ መቆሚያ፣ የጥማትንም ምድር ለውኃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
\s5
\v 19 የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንደ ሠራች፣ የእስራኤልም ቅዱስ እንደ ፈጠረው ያዩ ዘንድ ያውቁም ዘንድ ያስቡም ዘንድ በአንድነትም ያስተውሉ ዘንድ፣
\v 20 በምድረ በዳ ዝግባውንና ግራሩን ባርሰነቱንና የዘይቱን ዛፍ አበቅላለሁ፣ በበረሀውም ጥዱንና አስታውን ወይራውንም በአንድነት አኖራለሁ።
\s5
\v 21 ክርክራችሁን አቅርቡ፣" ይላል እግዚአብሔር፤ "ማስረጃችሁን አምጡ፣" ይላል የያዕቆብ ንጉሥ።
\v 22 የገዛ ራሳቸውን ሙግት ያምጡ፣ የሚሆነውንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፣ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ተናገሩ፣ የሚመጡትንም አሳዩን።
\s5
\v 23 አማልክትም መሆናችሁን እናውቅ ዘንድ፣ በኋላ የሚመጡትን ተናገሩ፤ እንደነግጥም ዘንድ በአንድነትም እናይ ዘንድ መልካሙን ወይም ክፉውን አድርጉ።
\v 24 ተመልከቱ፣ እንዳልነበረ ናችሁ፣ ሥራችሁም ከንቱ ነው፤ የሚመርጣችሁም አስጻያፊ ነው።
\s5
\v 25 አንዱን ከሰሜን አነሣሁ፣ እርሱም መጥቶአል፤ አንዱም ከፀሐይ መውጫ ስሜን የሚጠራ ይመጣል፤ በጭቃ ላይ እንደሚመጣ ሰው አፈርም እንደሚረግጥ ሸክለኛ በአለቆች ላይ ይመጣል።
\v 26 እናውቅ ዘንድ ከጥንት የተናገረው። "እውነት ነው" እንልም ዘንድ ቀድሞ የተናገረው ማን ነው? የሚናገር የለም፣ የሚገልጥም የለም፣ ቃላችሁንም የሚሰማ የለም።
\s5
\v 27 በመጀመሪያ ለጽዮን፣ "ተመልከቱ እዚህ ናቸው፤" እላለሁ፤ ለኢየሩሳሌምም የምስራች ነጋሪን እሰጣለሁ።
\v 28 ብመለከት፣ ማንም አልነበረም፤ ብጠይቃቸውም የሚመልስልኝ አማካሪ በመካከላቸው የለም።
\v 29 ተመልከቱ፣ እነርሱ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፣ ሥራቸውም ምንምን ናት፤ ቀልጠው የተሠሩት ምስሎቻቸውም ነፋስና ኢምንት ናቸው።
\s5
\c 42
\p
\v 1 እነሆ፣ ደግፌ የያዝሁት ባሪያዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ። እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።
\v 2 አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፣ ድምፁንም በጎዳናዎች አያሰማም።
\s5
\v 3 የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል።
\v 4 በምድርም ፍትሕን እስኪያደርግ ድረስ ይበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም ሕጉን ይጠብቃሉ።
\s5
\v 5 ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፣ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፣ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፣ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣
\v 6 "እኔ፣ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፣ እጅህንም እይዛለሁ እጠብቅህማለሁ። እጠብቅሃለሁ፣ ለአሕዛብ ብርሃን እንደሆንክ ሁሉ፣ ለሕዝቡም እንደ ኪዳን አደርግሃለሁ።
\s5
\v 7 የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ፣ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 8 እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ስሜ ይህ ነው፤ ክብሬን ለሌላ፣ ምስጋናዬንም ለተቀረጹ ምስሎች አልሰጥም።
\v 9 ተመልከቱ፣ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፣ አዲስ ክስተቶችንም እናገራለሁ። አስቀድሞም ሳይከሰት ስለ እነርሱ አስታውቃችኋለሁ።"
\s5
\v 10 ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፣ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።
\v 11 ምድረ በዳውና ከተሞቹ የቄዳርም ሰዎች የሚቀመጡባቸው መንደሮች ድምፃቸውን በደስታ ያንሡ! በሴላ የሚኖሩ እልል ይበሉ፤ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።
\s5
\v 12 ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፣ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ።
\v 13 እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይወጣል፤ እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል፣ በጠላቶቹም ላይ ኃይሉን ያሳያል።
\s5
\v 14 ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፤ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።
\v 15 ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፣ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፣ ኵሬዎችንም አደርቃለሁ።
\s5
\v 16 ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፣ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፣ አልተዋቸውምም።
\s5
\v 17 በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፣ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፣ "አምላኮቻችን ናችሁ" የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፈጽመውም ያፍራሉ።
\s5
\v 18 እናንተ ደንቆሮች፣ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፣ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ።
\v 19 ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው?
\s5
\v 20 ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትገነዘቡትም፤ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል፣ ነገር ግን አትሰሙም።
\v 21 እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ።
\s5
\v 22 ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁላቸው በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፣ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ብዝበዛ ሆነዋል የሚያድንም የለም፣ ምርኮም ሆነዋል፣ ማንም፣ "መልሷቸው!" የሚል የለም።
\s5
\v 23 ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፣ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው?
\v 24 ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ይሄዱ ዘንድ ያልወደዱት ለሕጉም ያልታዘዙለት እግዚአብሔር እርሱ አይደለምን?
\s5
\v 25 ስለዚህ፣ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰበት። በዙሪያም አነደደው እርሱ ግን አላወቀም፣ አቃጠለውም እርሱ ግን ልብ አላደረገም።
\s5
\c 43
\p
\v 1 አሁንም ያዕቆብ ሆይ፣ የፈጠረህ፣ እስራኤልም ሆይ፣ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፣ አንተ የእኔ ነህ።
\s5
\v 2 በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፣ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።
\v 3 እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፣ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።
\s5
\v 4 በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፣ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።
\v 5 እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፣ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።
\s5
\v 6 ሰሜንን፣ 'መልሰህ አምጣ፣' ደቡብንም፣ 'ማናቸውንም አትከልክል፤' ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፣
\v 7 በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፣ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ።
\s5
\v 8 ዓይኖች ያሉአቸውን ዕውሮችን ሕዝብ፣ ጆሮችም ያሉአቸውን ደንቆሮቹን አውጣ።
\v 9 አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ይሰብሰቡ፣ ወገኖችም ይከማቹ። ከመካከላቸው፤ ይህን የሚናገር፣ የቀድሞዎቹንስ ክስተቶች የሚያሳየን ማን ነው? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፣ ሰምተውም 'እውነት ነው' ይበሉ።
\s5
\v 10 "ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፣ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ" ይላል እግዚአብሔር። ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።
\v 11 እኔ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።
\s5
\v 12 ተናግሬአለሁ፣ አድኜማለሁ፣ አውጄማለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም። ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፣" ይላል እግዚአብሔር። "እኔም አምላክ ነኝ።"
\v 13 ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ፣ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፣ የሚከለክልስ ማን ነው?"
\s5
\v 14 የእስራኤል ቅዱስ፣ የሚቤዣችሁ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ "ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፣ ከለዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።
\v 15 ቅዱሳችሁ፣ የእስራኤል ፈጣሪ፣ ንጉሣችሁ፣ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።"
\s5
\v 16 እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው (በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል፤
\v 17 እግዚአብሔር ሠረገላውንና ፈረሱን፣ ሠራዊቱንና አርበኛውን ያወጣል። እነርሱ ግን በአንድነት ተኝተዋል፤ መቼም አይነሡም፤ ቀርተዋል፣ እንደ ጥዋፍ ኩስታሪም ጠፍተዋል።)
\s5
\v 18 "የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፣ የጥንቱንም ነገር አታስቡ።
\v 19 ተመልከቱ፣ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፣ አታዩትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሀም ወንዞችን አደርጋለሁ።
\s5
\v 20 የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል።
\v 21 ምስጋናዬን እንዲናገሩ ለእኔ የፈጠርሁት ሕዝብ፣ የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን በበረሀም ወንዞችን ሰጥቻለሁና።
\s5
\v 22 ያዕቆብ ሆይ፣ አንተ ግን አልጠራኸኝም፣ አንተም እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ዘንድ ደክመሃል።
\v 23 ለሚቃጠል መሥዋዕት በጎችህን አላቀረብህልኝም፣ በሌላም መሥዋዕትህ አላከበርኸኝም፤ በእህልም ቍርባን አላስቸገርሁህም፣ በዕጣንም አላደከምሁህም።
\s5
\v 24 ጣፋጭ መዐዛ ያለው ዕጣን በገንዘብ አልገዛህልኝም፣ በመሥዋዕትህም ስብ አላጠገብኸኝም፤ ነገር ግን በኃጢአትህ አስቸገርኸኝ፣ በበደልህም አደከምኸኝ።
\s5
\v 25 አዎን፣ መተላለፍህን፣ ስለ እኔ ስል የምደመስስ እኔ ነኝ፤ ኃጢአትህንም ከእንግዲህ አላስብም።
\v 26 የተከሰተውን አሳስበኝ። በአንድነትም ሆነን እንከራከር፤ ስለ ንጹህነትህ እንድትጸድቅ ነገርህን ተናገር።
\s5
\v 27 የመጀመሪያው አባትህ ኃጢአት ሠርቶአል፣ መምህሮችህም በድለውኛል።
\v 28 ስለዚህ የመቅደሱን ቅዱሳን አለቆች አረከስሁ፣ ያዕቆብንም እርግማን፣ እስራኤልንም ስድብ አደረግሁ።"
\s5
\c 44
\p
\v 1 አሁንም ባሪያዬ ያዕቆብ፣ የመረጥሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማ።
\v 2 የፈጠረህ፣ ከማኅፀንም የሠራህ፣ የሚረዳህም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ባሪያዬ ያዕቆብ የመረጥሁህም ይሹሩን ሆይ፣ አትፍራ።
\s5
\v 3 በተጠማ ላይ ውኃን፣ በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈስሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፣ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈስሳለሁ፥
\v 4 በፈሳሾችም አጠገብ እንደሚበቅሉ እንደ አኻያ ዛፎች በሣር መካከል ይበቅላሉ።
\s5
\v 5 ይህ፣ 'እኔ የእግዚአብሔር ነኝ' ይላል፤ ሌላኛውም በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ይህም፣ 'እኔ የእግዚአብሔር ነኝ' ብሎ በእጁ ይጽፋል፣ በእስራኤልም ስም ይጠራል።"
\s5
\v 6 የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው - የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እኔ ፊተኛ ነኝ፣ እኔም ኋለኛ ነኝ፣ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።
\s5
\v 7 እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ይነሣና ይጥራ ይናገርም፤ ከጥንት የፈጠርሁትን ሕዝብ ያዘጋጅልኝ፣ የሚመጣውም ነገር ሳይደርስ ይንገሩኝ።
\s5
\v 8 አትፍሩ አትደንግጡም። ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርኋችሁምን? ወይስ አላሳየኋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፦ ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? ሌላ ዐለት የለም፤ ማንንም አላውቅም።"
\s5
\v 9 የተቀረጸውን ምስል የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች ናቸው፤ የወደዱትም ነገር አይረባቸውም፤ ምስክሮቻቸውም አያዩምና አያውቁም፤ ስለዚህ እንዲያፍሩ ይደረጋሉ።
\v 10 አምላክን የሠራ ወይስ ለምንም የማይረባ ምስልን የቀረጸ ማን ነው?
\s5
\v 11 ተመልከቱ፣ ባልንጀሮቹ ሁሉ ያፍራሉ፤ ሠራተኞቹም ከሰዎች ወገን ብቻ ናቸው። ሁላቸው ተሰብስበው ይቁሙ፤ ይፈራሉ በአንድነትም ያፍራሉ።
\s5
\v 12 ብረት ሠሪ መጥረቢያውን ይሠራል፣ በፍምም ውስጥ ያደርገዋል፣ በመዶሻም መትቶ ቅርጽ ይሰጠዋል። በክንዱም ኃይል ይሠራዋል፣ እርሱም ይራባል፣ ይደክምማል፣ ውኃም አይጠጣም ይታክትማል።
\s5
\v 13 አናጢውም ገመድ ዘርግቶ በበረቅ ይለካዋል፣ በመቅረጫም ይቀርጸዋል። በመለኪያም ይለካዋል። በቤትም ውስጥ ይቀመጥ ዘንድ በሰው አምሳልና በሚስብ የሰው ውበት ያስመስለዋል።
\s5
\v 14 የዝግባን ዛፎች ይቈርጣል፣ የዞጲንና የኮምቦልን ዛፍ ይመርጣል። ከዱር ዛፎችም መካከል ይጠነክር ዘንድ ይተወዋል፤ የጥድንም ዛፍ ይተክላል ዝናብም ያበቅለዋል።
\s5
\v 15 ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፣ አዎን፣ አንድዶ እንጀራ ይጋግርበታል። ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፣ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል።
\v 16 ግማሹን በእሳት ያቃጥላል፣ በዚያ በግማሹ ሥጋ ይበላል። ሥጋም ይጠብስበትና ይጠግባል። ራሱን ያሞቅና፣ "እሰይ ሞቅሁ፣ እሳቱን አይቻለሁ" ይላል።
\s5
\v 17 የቀረውንም እንጨት አምላክ አድርጎ ምስል ይቀርጽበታል፤ በፊቱም ተጐንብሶ ይሰግዳል ወደ እርሱም እየጸለየ፣ "አምላኬ ነህና፣ አድነኝ" ይላል።
\s5
\v 18 አያውቁም፣ አያስቡም፣ እንዳያዩ ዓይኖቻቸውን፣ እንዳያስተውሉ ልቦቻቸውን ታውረዋል።
\s5
\v 19 በልቡም ማንም አያስብም፣ "ግማሽዋን በእሳት አቃጥያለሁ፣ በፍምዋም ላይ እንጀራን ጋግሬአለሁ፣ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ። የቀረውንም አስጸያፊ ነገር አደርጋለሁን? ለዛፍስ ግንድ እሰግዳለሁን? እንዲልም እውቀትና ማስተዋል የለውም።"
\s5
\v 20 አመድ ይበላል፤ የተታለለ ልብ አስቶታል። ነፍሱን ለማዳን አይችልም፣ ወይም፣ በቀኝ እጄ ሐሰት አለ" አይልም።
\s5
\v 21 ስለ እነዚህ ነገሮች አስብ፣ ያዕቆብ ሆይ፣ አንተም እስራኤል፣ ባሪያዬ ነህና ይህን አስብ፤ እኔ ሠርቼሃለሁ፤ አንተም ባሪያዬ ነህ፤ እስራኤል ሆይ፣ በእኔ ዘንድ ያልተረሳ ትሆናለህ።
\v 22 መተላለፍህን እንደ ደመና፣ ኃጢአትህንም እንደ ጭጋግ ደምስሼአለሁ፤ ተቤዥቼሃለሁና ወደ እኔ ተመለስ።
\s5
\v 23 ሰማያት ሆይ፣ እግዚአብሔር አድርጎታልና ዘምሩ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፣ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፣ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች፣ አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፣ እልል በሉ።
\s5
\v 24 ከማኅፀን የሠራህ፣ የሚቤዥህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሁሉን የፈጠርሁ፣ ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያጸናሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ማን ነበረ?
\v 25 የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፣ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፣ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ፣ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፤
\s5
\v 26 እኔ፣ እግዚአብሔር! የባሪያዬን ቃል አጸናለሁ፣ የመልእክተኞቼንም ምክር እፈጽማለሁ፤ ኢየሩሳሌምን፣ 'የሰው መኖሪያ ትሆኛለሽ፣' የይሁዳንም ከተሞች፣ 'ድጋሚ ትታነጻላችሁ፣ ፍራሾቻችሁንም አቆማለሁ' እላለሁ፤
\v 27 ቀላዩንም፣ 'ደረቅ ሁን፣ ፈሳሾችህንም አደርቃለሁ' እላለሁ፤
\s5
\v 28 ቂሮስንም፣ 'እርሱ እረኛዬ ነው፤ እርሱም ኢየሩሳሌምን፣ - 'ትታነጺያለሽ፣ ቤተ መቅደስም ይመሠረታል' ብሎ ፈቃዴን ሁሉ ይፈጽማል" እላለሁ።
\s5
\c 45
\p
\v 1 እግዚአብሔር ለቀባሁት፣ አሕዛብንም በፊቱ አስገዛ ዘንድ የነገሥታትንም ወገብ እፈታ ዘንድ፣ በሮቹም እንዳይዘጉ መዝጊያዎቹን በፊቱ እከፍት ዘንድ፣ ቀኝ እጁን ለያዝሁት ለቂሮስ እንዲህ ይላል፦
\s5
\v 2 "በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፤ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤
\v 3 በስምህም የምጠራህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ታውቅ ዘንድ፣ በጨለማ የነበረችውን መዝገብ በስውርም የተደበቀችውን ሀብት እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 4 ስለ ባሪያዬ ስለ ያዕቆብ፣ ስለ መረጥሁትም ስለ እስራኤል ብዬ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ በቍልምጫ ስምህ ጠራሁህ፤ አንተ ግን አላወቅኸኝም።
\v 5 እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም ሌላ ማንም የለም፤ ከእኔም በቀር አምላክ የለም፤
\v 6 በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ አስታጠቅሁህ፥ አንተ ግን አላወቅኸኝም፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።
\s5
\v 7 ብርሃንን ሠራሁ፣ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ደኅንነትን እሠራለሁ፣ ክፋትንም እፈጥራለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
\v 8 እናንተ ሰማያት ከላይ አንጠባጥቡ፣ ደመናትም ጽድቅን ያዝንቡ! ምድርም ትከፈት መድኃኒትንም ታብቅል፣ ጽድቅም በአንድነት ይብቀል። እኔ እግዚአብሔር ፈጥሬዋለሁ።
\s5
\v 9 ከሠሪው ጋር ለሚከራከር ወዮለት! በምድር ሸክላዎች መካከል ያለ ሸክላ ነው! ጭቃ የሚሠራውን፣ 'ምን ትሠራለህ?' ወይስ 'ሥራህ - እጅ የለውም' ይላልን?
\s5
\v 10 አባቱን፣ 'ምን ወልደሃል?' ወይም ሴትን፣ 'ምን አማጥሽ?' ለሚል ወዮ!
\s5
\v 11 የእስራኤል ቅዱስ፣ ሠሪውም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስለሚመጣው ነገር ጠይቁኝ፣ ስለ ልጆቼና ስለ እጄ ሥራም እዘዙኝ።'
\s5
\v 12 'እኔ ምድርን ሠርቻለሁ ሰውንም በእርስዋ ላይ ፈጥሬአለሁ። እኔ በእጄ ሰማያትን ዘርግቼአለሁ፣ ሠራዊታቸውንም ሁሉ አዝዣለሁ።
\s5
\v 13 እኔ ቂሮስን በጽድቅ አስነሥቼዋለሁ፣ መንገዱንም ሁሉ አቀናለሁ። እርሱ ከተማዬን ይገነባል፣ በዋጋም ወይም በደመወዝ ሳይሆን ምርኮኞቼን ያወጣል፣" ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 14 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፣ "የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ። እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፣ ለአንተም እየሰገዱ። 'በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፣ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም' ብለው ይለምኑሃል።"
\v 15 የእስራኤል አምላክ መድኃኒት ሆይ፣ በእውነት አንተ ራስህን የምትሰውር አምላክ ነህ።
\s5
\v 16 ሁሉም ያፍራሉ ይዋረዱማል፤ ጣዖታትንም የሚሠሩ በአንድነት ወደ ውርደት ይሄዳሉ።
\v 17 እግዚአብሔር ግን እስራኤልን በዘላለማዊ መድኃኒት ያድነዋል፤ እናንተም ለዘላለም አታፍሩምና አትዋረዱም።
\s5
\v 18 ሰማያትን የፈጠረ እግዚአብሔር፣ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፣ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፣ እንዲህ ይላል፣ "እኔ እግዚአብሔር ነኝ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
\s5
\v 19 በስውር ወይም በጨለማ ምድር ስፍራ አልተናገርሁም፤ ለያዕቆብ ዘር፣ 'በከንቱ ፈልጉኝ አላልሁም!' እኔ እግዚአብሔር ጽድቅን እናገራለሁ፣ ቅንንም አወራለሁ።
\s5
\v 20 እናንተ ከአሕዛብ ወገን ሆናችሁ ያመለጣችሁ ኑ! ተሰብስባችሁ ኑ፣ በአንድነትም ቅረቡ! የተቀረጸውን የምስላቸውን እንጨት የሚሸከሙና ያድን ዘንድ ወደማይችል አምላክ የሚጸልዩ እውቀት የላቸውም።
\s5
\v 21 ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ! ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፣ ከእኔም በቀር ማንም የለም።
\s5
\v 22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፣ እኔ አምላክ ነኝና፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።
\v 23 'ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፣ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፣ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።
\s5
\v 24 ስለ እኔም፣ "በእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ጽድቅና ኃይል አለ፣ ወደ እርሱም ሰዎች ይመጣሉ።" በእርሱም ላይ የተቈጡ ሁሉ ያፍራሉ።
\v 25 የእስራኤልም ዘር ሁሉ በእግዚአብሔር ይጸድቃሉ፤ ይመካሉም ይባላል።
\s5
\c 46
\p
\v 1 ቤል ተዋረደ፣ ናባው ተሰባበረ፤ ጣዖቶቻቸው በእንስሳና በከብት ላይ ተጭነዋል። ሸክሞቻችሁ ለደካማ እንስሳ ከባድ ጭነት ሆነዋል።
\v 2 ተጐነበሱ በአንድነትም ተዋረዱ፤ ሸክሙን ለማዳን አልቻሉም፣ ራሳቸው ግን ተማረኩ።
\s5
\v 3 እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ የእስራኤልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ ከሆድ ያነሣኋችሁ ከማኅፀንም የተሸከምኋችሁ፣ ስሙኝ።
\v 4 እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፣ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ።
\s5
\v 5 በማን ትመስሉኛላችሁ? ከማንስ ጋር ታስተካክሉኛላችሁ? እንመሳሰል ዘንድ ከማን ጋር ታስተያዩኛላችሁ?
\v 6 ወርቁን ከኮረጆ የሚያፈስሱ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፣ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራ ዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል።
\s5
\v 7 በጫንቃቸው ላይ አንሥተው ይሸከሙታል፤ በስፍራውም ያደርጉታል፣ በዚያም ይቆማል፣ ከስፍራውም ፈቀቅ አይልም፤ ሰውም ወደ እርሱ ቢጮኽ አይሰማውም ከመከራውም አያድነውም።
\s5
\v 8 ስለእነዚህ ነገሮች አስቡና አልቅሱ፤ ተላላፊዎች ሆይ፣ ንስሐ ግቡ! ልባችሁንም መልሱ።
\v 9 እኔ አምላክ ነኝና፣ ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።
\s5
\v 10 በመጀመሪያ መጨረሻውን፣ ከጥንትም ያልተደረገውን ሳይሆን በፊት እነግራለሁ፤ "ምክሬ ትጸናለች፣ ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ፤" እላለሁ።
\v 11 ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፣ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራዋለሁ፤ ተናግሬአለሁ፤ እፈጽማለሁ፤ አስቤአለሁ አደርግማለሁ።
\s5
\v 12 እናንተ ጽድቅን ከማድረግ የራቃችሁ፣ እልከኞች፣ ስሙኝ።
\v 13 ጽድቄን አቀርባለሁ፤ አይርቅም መድኃኒቴም አይዘገይም፤ ከጽዮን ለክብር እንዲሆን መድኃኒትን ለእስራኤል ሰጥቻለሁ።
\s5
\c 47
\p
\v 1 አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፣ ውረጂ በመሬት ትቢያም ላይ ያለ ዙፋን ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፤ ከዚህ በኋላ ቅልጣናምና ቅምጥል አትባይምና።
\v 2 ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ መሸፈኛሽን አውጪ፣ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣዪው፤ ባትሽን ግለጪ፣ ወንዙን ተሻገሪ።
\s5
\v 3 ኀፍረተ ሥጋሽ ይገለጣል እፍረትሽም ይታያል፤ አዎን፣ እኔ እበቀላለሁ፥ ለማንም አልራራም።
\v 4 ታዳጊያችን፣ ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ቅዱስ ነው።
\v 5 የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፣ ከዚህ በኋላ፣ የመንግሥታት እመቤት አትባይምና ዝም ብለሽ ተቀመጪ ወደ ጨለማም ውስጥ ግቢ።
\s5
\v 6 በሕዝቤ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ ርስቴንም አረከስሁ፣ በእጅሽም አሳልፌ ሰጠኋቸው፤ ለእነርሱ ምንም ምሕረት አላደረግሽም፣ በሽማግሌዎቻቸው ላይ ቀንበርሽን እጅግ አክብደሻል።
\v 7 አንቺም፣ "እኔ ለዘላለም እመቤት እሆናለሁ" ብለሻል፤ ይህንም በልብሽ አላደረግሽም ፍጻሜውንም አላሰብሽም።
\s5
\v 8 አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ "እኔ እኖራለሁ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም የወላድ መካንነትንም አላውቅም" የምትዪ ይህን ስሚ፤
\v 9 አሁን ግን በአንድ ቀን እነዚህ ሁለት ነገሮች፦ የወላድ መካንነትና መበለትነት፣ በድንገት ይመጡብሻል፤ ስለ መተቶችሽ ብዛትና ስለ አስማቶችሽ ጽናት ፈጽመው ይመጡብሻል።
\s5
\v 10 በክፋትሽ ታምነሻል፤ "የሚያየኝ የለም" ብለሻል፤ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፣ ነገር ግን በልብሽ፣ "እኔ እኖራለሁ፣ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።" ብለሻል።
\v 11 ስለዚህ ምክንያት ክፉ ነገር ይመጣብሻል፤ በምዋርትሽም እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም። ጉዳት ይውድቅብሻል ታስወግጅውም ዘንድ አይቻልሽም፤ የማትውቂያትም ጕስቍልና ድንገት ትመጣብሻለች።
\s5
\v 12 ምናልባትም መጠቀም ትችዪ ወይም ታስደነግጪ እንደ ሆነ፣ ከአስማቶችሽና ከሕፃንነትሽ ጀምረሽ ከደከምሽበት ከመተቶችሽ ብዛት ጋር ቁሚ።
\v 13 በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፣ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፣ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ።
\s5
\v 14 ተመልከቱ፣ እንደ እብቅ ይሆናሉ። እሳትም ያቃጥላቸዋል። ሰውነታቸውንም ከነበልባል ኃይል አያድኑም። እርሱም ሰው እንደሚሞቀው ፍም፣ ወይም በፊቱ ሰው እንደሚቀመጥበት እሳት ያለ አይደለም!
\v 15 የደከምሽባቸው ነገሮች እንዲህ ይሆኑብሻል፤ ከሕፃንነትሽ ጀምረው ከአንቺ ጋር ይነግዱ የነበሩ እያንዳንዳቸው ወደ ስፍራቸው ይሄዳሉ፣ የሚያድንሽም የለም።
\s5
\c 48
\p
\v 1 እናንተ በእስራኤል ስም የተጠራችሁ፣ ከይሁዳም ዘር የወጣችሁ፣ በእግዚአብሔር ስም የምትምሉ፣ በእውነት ሳይሆን በጽድቅም ሳይሆን የእስራኤልን አምላክ የምትጠሩ።
\v 2 በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፣ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፤ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ይህን ስሙ።
\s5
\v 3 የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፣ ከአፌም ወጥቶአል፣ አሳይቼውማለሁ፤ ድንገት አድርጌዋለሁ ተፈጽሞማል።
\v 4 አንተ እልከኛ፣ አንገትህም የብረት ጅማት፣ ግምባርህም ናስ እንደሆነ አውቄአለሁ፤
\v 5 ስለዚህ፣ አንተ፣ 'ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፣ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌ ይህን አዘዙኝ' እንዳትል፣ አስቀድሜ ነግሬህ ነበር ሳይሆንም አሳይቼህ ነበር።
\s5
\v 6 ስለ እነዚህ ነገሮች ሰምተሃል፤ ይህን ሁሉ ማረጋገጫ ተመልከት፤ እናንተም የምትናገሩት አይደላችሁምን? የተሰወሩትን ያላወቅሃቸውንም አዲሶች ነገሮችን ከዚህ ጀምሬ አሳይቼሃለሁ።
\v 7 እነርሱም አሁን እንጂ ከጥንት አልተፈጠሩም፤ አንተም፣ እነሆ፣ 'አውቄአቸዋለሁ' እንዳትል ከዛሬ በፊት አልሰማሃቸውም።
\s5
\v 8 አልሰማህም፣ አላወቅህም፣ ጆሮህ ከጥንት አልተከፈተችም። አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደተጠራህ አውቄአለሁና።
\s5
\v 9 ስለ ስሜ ቍጣዬን አዘገያለሁ፣ እንዳላጠፋህም ስለ ምስጋናዬ እታገሣለሁ።
\v 10 ተመልከት፣ አንጥሬሃለሁ፣ ነገር ግን እንደ ብር አይደለም፤ በመከራም እቶን ፈትኜሃለሁ።
\v 11 ስለ እኔ፣ ስለ ራሴ አደርገዋለሁ፣ ስሜ እንዲነቀፍ የምፈቅደው እንዴት ነው? ክብሬንም ለሌላ አልሰጥም።
\s5
\v 12 ያዕቆብ ሆይ፣ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፣ ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ፣ እኔም ኋለኛው ነኝ።
\v 13 አዎን፣ እጄ ምድርን መሥርታለች፣ ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች፤ በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ።
\s5
\v 14 እናንተ ሁሉ፣ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ ከእነርሱ ይህን የተናገረ ማን ነው? እግዚአብሔር የወደደው ፈቃዱን በባቢሎን ላይ ያደርጋል፣ ክንዱም በከለዳውያን ላይ ይሆናል።
\v 15 እኔ፣ እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ እኔ ጠርቼዋለሁ፤ አምጥቼዋለሁ፥ መንገዱም ትሳካለታለች።
\s5
\v 16 ወደ እኔ ቅረቡ፣ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፣ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ" ልከውኛል።
\s5
\v 17 ታዳጊህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። "እኔ የሚረባህን ነገር የማስተምርህ፣ በምትሄድባትም መንገድ የምመራህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ።"
\v 18 ትእዛዜን ብትፈጽም ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤
\s5
\v 19 ዘርህም እንደ አሸዋ፣ የሆድህም ትውልድ እንደ ምድር ትቢያ በሆነ ነበር፣ ስሙም ከፊቴ ባልጠፋና ባልፈረሰ ነበር።
\s5
\v 20 ከባቢሎን ውጡ! ከከለዳውያንም ኰብልሉ! በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፣ ይህንም ንገሩ፣ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፣ 'እግዚአብሔር ባሪያውን ያዕቆብን ታድጎታል' በሉ።
\s5
\v 21 በምድረ በዳ በኩል በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፣ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ።
\v 22 ለክፉዎች ሰላም የላቸውም" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 49
\p
\v 1 ደሴቶች ሆይ፣ ስሙኝ! እናንተም በሩቅ ያላችሁ አሕዛብ፣ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ከማኅፀን በስም ጠርቶኛል፣ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ።
\v 2 አፌንም እንደ ተሳለ ሰይፍ አድርጎአል፣ በእጁ ጥላ ሰውሮኛል፤ እንደ ተሳለ ፍላጻም አድርጎኛል፣ በሰገባውም ውስጥ ሽጎኛል።
\s5
\v 3 እርሱም፣ "እስራኤል ሆይ፣ አንተ ባሪያዬ ነህ፣ በአንተም እከበራለሁ" አለኝ።
\v 4 እኔ ግን፣ በከንቱ ደከምሁ፣ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጕልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ፣ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው አልሁ።
\s5
\v 5 አሁንም በእግዚአብሔር ዓይን ከብሬአለሁና፣ አምላኬም ጕልበት ሆኖኛልና ያዕቆብን ወደ እርሱ እንድመልስ እስራኤልንም ወደ እርሱ እንድሰበስብ፣ ባሪያ እሆነው ዘንድ ከማኅፀን ጀምሮ የሠራኝ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\v 6 እርሱ እንዲህ ይላል፣ "የያዕቆብን ነገዶች እንድታስነሣ፣ ከእስራኤልም የዳኑትን እንድትመስል፣ ባሪያዬ ትሆን ዘንድ እጅግ ቀላል ነገር ነውና እስከ ምድር ዳር ድረስ መድኃኒት ትሆን ዘንድ ለአሕዛብ ብርሃን አድርጌ ሰጥቼሃለሁ" ይላል።
\s5
\v 7 የእስራኤል ታዳጊ ቅዱሱም፣ እግዚአብሔር፣ ሰዎች ለሚንቁት ሕዝብም ለሚጠላው ለገዥዎች ባሪያ እንዲህ ይላል፣ "ስለ ታማኙ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለ መረጠህም ስለ እስራኤል ቅዱስ ነገሥታት አይተው ይነሣሉ፣ መሳፍንትም አይተው ይሰግዳሉ።"
\s5
\v 8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፣ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ እጠብቅህማለሁ፣ ምድርንም ታቀና ዘንድ፣ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፥
\s5
\v 9 የተጋዙትንም፣ 'ውጡ፤' በጨለማም የተቀመጡትን፣ 'ራሳችሁን ግለጡ' ትል ዘንድ ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ። በመንገድም ላይ ይሰማራሉ፣ ማሰማርያቸውም በወና ኮረብታ ሁሉ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 10 የሚራራላቸውም ይመራቸዋልና፣ በውኃም ምንጮች በኩል ይነዳቸዋልና አይራቡም፣ አይጠሙም፣ ትኩሳት ወይም ፀሐይ አይጐዳቸውም።
\v 11 ተራሮቼንም ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፣ ጎዳኖቼም ከፍ ከፍ ይላሉ።"
\s5
\v 12 ተመልከቱ፣ እነዚህ ከሩቅ፣ አንዳንዶቹም፣ ከሰሜንንና ከምዕራብ፣ እነዚህም፣ ከሲኒም አገር ይመጣሉ።
\v 13 እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፣ ለችግረኞቹም ራርቶአልና ሰማያት ሆይ፣ ዘምሩ፣ ምድር ሆይ፣ ደስ ይበልሽ ተራሮችም ሆይ፣ እልል በሉ።
\s5
\v 14 ጽዮን ግን፣ "እግዚአብሔር ትቶኛል፣ ጌታም ረስቶኛል" አለች።
\v 15 "በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም።
\s5
\v 16 ተመልከቱ፣ እኔ በእጄ መጻፍ ቀርጬሻለሁ፤ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።
\v 17 ልጆችሽ ተመልሰው ይፈጥናሉ፤ ያፈረሱሽና ያወደሙሽ ከአንቺ ዘንድ ይወጣሉ።
\v 18 ዓይንሽን አንሥተሽ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፣ እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊአቸዋለሽ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 19 ባድማሽና ውድማሽ ወናም የሆነው ምድርሽ ከሚኖሩብሽ የተሣ ዛሬ ጠባብ ትሆናለችና፣ የዋጡሽም ይርቃሉና።
\v 20 የወላድ መካን ከሆንሽ በኋላ የተወለዱልሽ ልጆችሽ በጆሮሽ፣ 'ስፍራ ጠብቦናልና፣ እንቀመጥ ዘንድ ቦታ አስፊልን' ይላሉ።
\s5
\v 21 አንቺም በልብሽ፣ 'የወላድ መካን ሆኛለሁና፣ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁና ተቅበዝበዤ አለሁምና እነዚህን ልጆች ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፣ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ከወዴት መጡ?" ትያለሽ።
\s5
\v 22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ እጄን ወደ አሕዛብ አነሣለሁ፣ ዓላማዬንም ወደ ወገኖች አቆማለሁ፤ ወንዶች ልጆችሽንም በብብታቸው ያመጡአቸዋል። ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሙአቸዋል።
\s5
\v 23 ነገሥታትም አሳዳጊ አባቶችሽ ይሆናሉ፣ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግምባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፥ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።"
\s5
\v 24 በውኑ ብዝበዛ ከኃያል እጅ ይወሰዳልን፣ ወይስ የጨካኙ ምርኮኞች ያመልጣሉን?
\v 25 እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፣ "አዎን፣ በኃያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፣ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል፤ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፣ ልጆችሽንም አድናለሁ።
\s5
\v 26 አስጨናቂዎችሽንም ሥጋቸውን አስበላቸዋለሁ፣ እንደ ጣፋጭም ወይን ጠጅ ደማቸውን ጠጥተው ይሰክራሉ፤ ሥጋ ለባሹም ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መድኃኒትሽና ታዳጊሽ፣ የያዕቆብ ኃያል እንደ ሆንሁ ያውቃል።"
\s5
\c 50
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እናታችሁን የፈታሁበት የፍችዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፣ ስለ ኃጢአታችሁ ተሽጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈትታለች።
\s5
\v 2 እኔ በመጣሁ ጊዜ ሰው ስለ ምን አልነበረም? በጠራሁስ ጊዜ የሚመልስ ስለ ምን አልነበረም? መታደግ እንዳትችል እጄ አጭር ሆናለችን? ወይስ ለማዳን ኃይል የለኝምን? እነሆ፣ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዓሦቻቸው ይገማሉ በጥማትም ይሞታሉ።
\v 3 ሰማያትን ጥቍረት አለብሳቸዋለሁ፣ መጋረጃቸውንም ማቅ አደርጋለሁ።"
\s5
\v 4 የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፣ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።
\s5
\v 5 ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬን ከፍቶአል፣ እኔም ዓመፀኛ አልነበርሁም ወደ ኋላዬም አልተመለስሁም።
\v 6 ጀርባዬን ለገራፊዎች፣ ጕንጬንም ለጠጕር ነጪዎች ሰጠሁ፣ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።
\s5
\v 7 ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና፣ ስለዚህ አልተዋረድሁም፤ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፣ እንዳላፍርም አውቃለሁ።
\s5
\v 8 የሚያጸድቀኝ ቅርብ ነው። ከእኔስ ጋር የሚከራከር ማን ነው? በአንድነት እንቁም፤ የሚከስሰኝ ማን ነው? ወደ እኔ ይቅረብ።
\v 9 ተመልከቱ፣ ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛል። ማን ይፈርድብኛል? ተመልከቱ፣ ሁሉ እንደ ልብስ ያረጃሉ ብልም ይበላቸዋል።
\s5
\v 10 ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ የባሪያውንም ቃል የሚሰማ፣ በጨለማም የሚሄድ፣ ብርሃንም የሌለው፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ስም የሚታመን፣ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?
\s5
\v 11 ተመልከቱ፣ እሳት የምታነድዱ የእሳትንም ወላፈን የምትታጠቁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ነበልባል ባነደዳችሁትም ወላፈን ሂዱ፤ ይህ ከእጄ ይሆንባችኋል፦ በኀዘን ትተኛላችሁ።
\s5
\c 51
\p
\v 1 እናንተ ጽድቅን የምትከተሉ እግዚአብሔርንም የምትሹ፣ ስሙኝ፤ ከእርሱ የተቈረጣችሁበትን ድንጋይ ከእርሱም የተቈፈራችሁበትን ጕድጓድ ተመልከቱ።
\s5
\v 2 ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፣ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፣ ባረክሁትም አበዛሁትም።
\s5
\v 3 አዎን፣ እግዚአብሔር ጽዮንን ያጽናናል፤ በእርስዋም ባድማ የሆነውን ሁሉ ያጽናናል፤ ምድረ በዳዋንም እንደ ዔደን፣ በረሀዋንም እንደ እግዚአብሔር ገነት ያደርጋል፤ ደስታና ተድላ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ ይገኝበታል።
\s5
\v 4 ወገኔ ሆይ፣ አድምጠኝ፤ ሕዝቤ ሆይ፣ ስማኝ! ሕግ ከእኔ ይወጣልና፣ ፍርዴም ለአሕዛብ ብርሃን ይሆናልና።
\v 5 ጽድቄ ፈጥኖ ቀርቦአል፣ ማዳኔም ወጥቶአል፣ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፣ በክንዴም ይታመናሉ።
\s5
\v 6 ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ፣ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያት እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፣ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፣ የሚኖሩባትም እንዲሁ ይሞታሉ። ማዳኔ ግን ለዘላለም ይሆናል፣ ጽድቄም አይፈርስም።
\s5
\v 7 ጽድቅን የምታውቁ ሕጌም በልባችሁ ያለ ሕዝብ ሆይ፣ ስሙኝ፤ የሰውን ተግዳሮት አትፍሩ፣ በስድባቸውም አትደንግጡ።
\v 8 እንደ ልብስም ብል ይበላቸዋል፣ እንደ በግ ጠጕርም ትል ይበላቸዋል፤ ጽድቄ ግን ለዘላለም ማዳኔም ለትውልድ ሁሉ ይሆናል።"
\s5
\v 9 የእግዚአብሔር ክንድ ሆይ፣ ተነሥ፣ ተነሥ፣ ኃይልንም ልበስ። በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
\v 10 ባሕሩንና የታላቁን ጥልቅ ውኃ ያደረቅኸው፣ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጠሊቁን ባሕር መንገድ ያደረግህ አንተ አይደለህምን?
\s5
\v 11 እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ፤ የዘላለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፣ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።
\s5
\v 12 "እኔ፣ የማጽናናችሁ እኔ ነኝ፣ እኔ ነኝ፤ የሚሞተውን ሰው እንደ ሣርም የሚጠወልገውን የሰው ልጅ ትፈራ ዘንድ አንተ ማን ነህ?
\s5
\v 13 ሰማያትንም የዘረጋው ምድርንም የመሠረተውን ፈጣሪህን እግዚአብሔርን ረስተሃል፤ ያጠፋ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቍጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሃል፤ የጨቋኙ ቍጣ የት አለ?
\s5
\v 14 ምርኮኛ ፈጥኖ ይፈታል፣ አይሞትም ወደ ጕድጓድም አይወርድም፣ እንጀራም አይጐድልበትም።
\v 15 ሞገዱም እንዲተምም ባሕርን የማናውጥ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፣ ስሜም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 16 ሰማያትን እዘረጋ ዘንድ ምድርንም እመሠርት ዘንድ፣ ጽዮንንም፣ 'አንቺ ሕዝቤ ነሽ' እል ዘንድ ቃሌን በአፍህ አድርጌአለሁ፣ በእጄም ጥላ ጋርጄሃለሁ።"
\s5
\v 17 ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ንቂ፣ ንቂ፣ ቁሚ፤ የሚያንገደግድን ዋንጫ ጠጥተሻል፣ ጨልጠሽውማል።
\v 18 ከወለደቻቸው ልጆች ሁሉ የሚመራት የለም፣ ካሳደገቻቸውም ልጆች ሁሉ እጅዋን የሚይዝ የለም።
\s5
\v 19 እነዚህ ሁለት ነገሮች ሆነውብሻል፣ ማንስ ያስተዛዝንሻል? መፈታትና ጥፋት ራብና ሰይፍ ናቸው፤ እንዴትስ አድርጌ አጽናናሻለሁ?
\v 20 ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደተያዘ ሚዳቋ በአደባባይ ሁሉ ራስ ላይ ተኝተዋል፤ በእግዚአብሔር ቍጣና በአምላክሽ ተግሣጽ ተሞልተዋል።
\s5
\v 21 አሁን ግን ይህንን ስሚ፣ ያለ ወይን ጠጅ የሰከርሽ አንቺ የተጨቆንሽ።
\v 22 ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ የሚያንገደግድን ጽዋ የቍጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም።
\s5
\v 23 ነፍስሽንም፣ 'እንሻገር ዘንድ ዝቅ በዪ፣ በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤' ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።"
\s5
\c 52
\p
\v 1 ጽዮን ሆይ፣ ተነሺ፣ ተነሺ፣ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።
\s5
\v 2 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትቢያን አራግፊ፤ ተነሺና ተቀመጪ፤ ምርኮኛይቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ የአንገትሽን እስራት ፍቺ።
\v 3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፣ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ።"
\s5
\v 4 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፣ አሦርም ቅርብ ጊዜ ላይ ያለ ምክንያት በደለው።
\s5
\v 5 ወገኔ በከንቱ ተወስዶአልና አሁን ከዚህ ምን አለኝ? ይላል እግዚአብሔር፤ የሚገዙአቸው ይጮኻሉ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ስሜም ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ይሰደባል።
\v 6 ስለዚህ ወገኔ ስሜን ያውቃል፤ ስለዚህም የምናገር እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያውቃሉ፤ አዎን፣ እኔ ነኝ!"
\s5
\v 7 የምስራች የሚናገር፣ ሰላምንም የሚያወራ፣ የመልካምንም ወሬ የምስራች የሚናገር፣ መድኃኒትንም የሚያወራ፣ ጽዮንንም፣ "አምላክሽ ነግሦአል!" የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
\v 8 አድምጪ፣ ጕበኞችሽ ጮኸዋል፤ እግዚአብሔር ወደ ጽዮን በተመለሰ ጊዜ ዓይን በዓይን ይተያያሉና ድምፃቸውን ያነሣሉ፣ በአንድነትም ይዘምራሉ።
\s5
\v 9 እናንተ የኢየሩሳሌም ፍርስራሾች ሆይ፣ እግዚአብሔር ሕዝቡን አጽናንቶአልና፤ ኢየሩሳሌምንም ታድጎአልና ደስ ይበላችሁ፣ በአንድነትም ዘምሩ።
\v 10 እግዚአብሔር የተቀደሰውን ክንዱን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ገልጦአል፤ በምድር ዳርቻ የሚኖሩትም ሁሉ የአምላካችንን መድኃኒት ያያሉ።
\s5
\v 11 እናንተ የእግዚአብሔር ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፣ ትታችሁ ውጡ፣ ትታችሁ ውጡ፤ ከዚያ ውጡ፣ ርኩስን ነገር አትንኩ፣ ከመካከልዋ ውጡ፣ ንጽሐን ሁኑ።
\v 12 እግዚአብሔር ይቀድማችኋልና፣ የእስራኤልም አምላክ ይከተላችኋልና በችኰላ አትወጡም በመኰብለልም አትሄዱም።
\s5
\v 13 ተመልከቱ፣ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፣ እጅግ ታላቅም ይሆናል።
\v 14 ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፣ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቍሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፣ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤
\s5
\v 15 ያልተነገረላቸውንም ያያሉና፣ ያልሰሙትንም ያስተውላሉና ነገሥታት ስለ እርሱ አፋቸውን ይዘጋሉ።
\s5
\c 53
\p
\v 1 የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
\v 2 በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፣ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
\s5
\v 3 የተናቀ ከሰውም የተጠላ፣ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው። ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፣ እኛም አላከበርነውም።
\s5
\v 4 በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
\s5
\v 5 እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፣ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፣ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
\s5
\v 6 እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
\s5
\v 7 ተጨቆነ፣ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፣ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፣ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
\s5
\v 8 በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
\v 9 ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፣ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፣ በአፉም ተንኮል አልተገንበትም ነበር።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፣ ዕድሜውም ይረዝማል፣ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
\v 11 ከነፍሱ መከራ በኋላ፣ ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፣ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።
\s5
\v 12 ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፣ ከብዙ ኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፣ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፣ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።
\s5
\c 54
\p
\v 1 "አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፣ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፣ እልል በዪ፣ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 2 የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፣ መጋረጃዎችሽንም ይዘርጉ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ ካስሞችሽንም አጽኚ።
\v 3 በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፣ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፣ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና።
\s5
\v 4 አታፍሪምና አትፍሪ፤ አተዋረጂምና አትደንግጪ፤ የሕፃንነትሽንም እፍረት ትረሺዋለሽ፣ የመበለትነትሽንም ስድብ ከእንግዲህ ወዲህ አታስቢም።
\s5
\v 5 ፈጣሪሽ ባልሽ ነው፣ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም ቅዱስ ታዲጊሽ ነው፣ እርሱም የምድር ሁሉ አምላክ ይባላል።
\v 6 እግዚአብሔር እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች በልጅነትዋም እንደ ተጣለች ሚስት ጠርቶሻል፣ ይላል አምላክሽ።
\s5
\v 7 "ለጥቂት ጊዜ ተውሁሽ፣ በታላቅም ምሕረት እሰበስብሻለሁ።
\v 8 በጥቂት ቍጣ ለቅጽበት ዓይን ፊቴን ከአንቺ ሰወርሁ፣ በዘላለምም ቸርነት እምርሻለሁ፣ ይላል ታዳጊሽ እግዚአብሔር።
\s5
\v 9 ይህ ለእኔ እንደ ኖኅ ውኃ ነው፤ የኖኅ ውኃ ደግሞ በምድር ላይ እንዳያልፍ እንደ ማልሁ፣ እንዲሁ አንቺን እንዳልቈጣ እንዳልገሥጽሽም ምያለሁ።
\v 10 ተራሮች ይፈልሳሉ፣ ኮረብቶችም ይወገዳሉ፤ ቸርነቴ ግን ከአንቺ ዘንድ አይፈልስም የሰላሜም ቃል ኪዳን አይወገድም፣ ይላል መሐሪሽ እግዚአብሔር።
\s5
\v 11 አንቺ የተቸገርሽ በዐውሎ ነፋስም የተናወጥሽ ያልተጽናናሽም፣ ተመልከቺ፣ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፣ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ።
\v 12 የግንብሽንም ጕልላት በቀይ ዕንቍ፣ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቍ፣ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ።
\s5
\v 13 ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፣ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል።
\v 14 በጽድቅ ትታነጺያለሽ፤ ከግፍ ራቂ፣ አትፈሪምም፣ ድንጋጤም ወደ አንቺ አትቀርብም።
\s5
\v 15 ተመልከቺ፣ ይሰበሰባሉ፣ ነገር ግን ከእኔ ዘንድ አይሆንም፤ በአንቺም ላይ ችግር የሚፈጥሩ ሁሉ ይሸነፋሉ።
\v 16 ተመልከቺ፣ ፍሙን በወናፍ የሚያናፋ ለሥራውም መሣሪያ የሚያወጣ ብረት ሠሪን እኔ ፈጥሬአለሁ፤ የሚያፈርሰውንም እንዲያጠፋ ፈጥሬአለሁ።
\s5
\v 17 በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም፤ በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፣ ጽድቃቸውም ከእኔ ዘንድ ነው፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 55
\p
\v 1 "እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፣ ወደ ውኃ ኑ፣ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም፤ ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ።
\s5
\v 2 ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፣ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? በጥንቃቄ አድምጡኝ በረከትንም ብሉ፣ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።
\s5
\v 3 ጆሮአችሁን አዘንብሉ ወደ እኔም ቅረቡ! ስሙ፣ ሰውነታችሁም በሕይወት ትኖራለች! የታመነችይቱን የዳዊትን ምሕረት፣ የዘላለምን ቃል ኪዳን ከእናንተ ጋር አደርጋለሁ።
\v 4 ተመልከቱ፣ ለአሕዛብ ምስክር፣ ለወገኖችም አለቃና አዛዥ እንዲሆን ሰጥቼዋለሁ።
\s5
\v 5 ተመልከቱ፣ የማታውቀውን ሕዝብ ትጠራለህ፤ የእስራኤልም ቅዱስ አክብሮሃልና ስለ አምላክህ ስለ እግዚአብሔር የማያውቁህ ሕዝብ ወደ አንተ ይሮጣሉ።"
\s5
\v 6 እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፣ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤
\v 7 ክፉ ሰው መንገዱን በደለኛም አሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ እርሱም ይምረዋል፣ ይቅርታውም ብዙ ነውና ወደ አምላካችን ይመለስ።
\s5
\v 8 አሳቤ እንደ አሳባችሁ፣ መንገዳችሁም እንደ መንገዴ፣ አይደለምና ይላል እግዚአብሔር።
\v 9 ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፣ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።
\s5
\v 10 ዝናብና በረዶ ከሰማይ እንደሚወርድ፣ ምድርን እንደሚያረካት፣ ታበቅልና ታፈራም ዘንድ እንደሚያደርጋት፣ ዘርንም ለሚዘራ እንጀራንም ለሚበላ እንደሚሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እንደማይመለስ፣
\v 11 ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል፤ የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።
\s5
\v 12 እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በፊታችሁ እልልታ ያደርጋሉ፣ የሜዳም ዛፎች ሁሉ ያጨበጭባሉ።
\v 13 በእሾህም ፋንታ ጥድ፣ በኩርንችትም ፋንታ ባርሰነት፣ ይበቅላል፤ ለእግዚአብሔርም መታሰቢያን ለዘላለምም የማይጠፋ፣ ምልክት ይሆናል።"
\s5
\c 56
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ማዳኔ ሊመጣ፣ ጽድቄም ሊገለጥ ቀርቦአልና ፍርድን ጠብቁ ጽድቅንም አድርጉ።
\v 2 ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፣ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።"
\s5
\v 3 ወደ እግዚአብሔርም የተጠጋ መጻተኛ፣ "በእውነት እግዚአብሔር ከሕዝቡ ይለየኛል" አይበል፤ ጃንደረባም፣ "ተመልከቱ፣ እኔ ደረቅ ዛፍ ነኝ አይበል።"
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፣
\v 5 "በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።"
\s5
\v 6 ያገለግሉት ዘንድ የእግዚአብሔርንም ስም ይወድዱ ዘንድ ባሪያዎቹም ይሆኑ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የሚጠጉትንም መጻተኞች፣ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን ቃል ኪዳኔንም የሚይዙትን ሁሉ፣
\v 7 "ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፣ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ።
\s5
\v 8 ከእስራኤል የተበተኑትን የሚሰበስብ ጌታ እግዚአብሔር፣ ወደ ተሰበሰቡት ዘንድ ሌሎችን እሰበስብለታለሁ" ይላል።
\s5
\v 9 እናንተ የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ፣ እናንተም የዱር አራዊት ሁሉ፣ ትበሉ ዘንድ ቅረቡ!
\v 10 ጕበኞቹ ዕውሮች ናቸው፣ ሁሉ ያለ እውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ።
\s5
\v 11 መብል ወዳጆች ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እነርሱም ያስተውሉ ዘንድ የማይችሉ እረኞች ናቸው፤ ሁሉ ወደ መንገዳቸው፣ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፣ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል።
\v 12 "ኑ፣ የወይን ጠጅ እንውሰድ፣ በሚያሰክርም መጠጥ እንርካ፤ ዛሬም እንደ ሆነ እንዲሁ ነገ ይሆናል፣ ከዛሬም ይልቅ እጅግ ይበልጣል" ይላሉ።
\s5
\c 57
\p
\v 1 ጻድቅ ይጠፋል፣ በልቡም ነገሩን የሚያኖር የለም፤ ምሕረተኞችም ይወገዳሉ፣ ጽድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።
\v 2 ወደ ሰላም ይገባል፤ በቅንነት የሄደ በአልጋው ላይ ያርፋል።
\s5
\v 3 እናንተ የአስማተኛይቱ ልጆች፣ የአመንዝራውና የጋለሞታይቱ ዘር፣ ወደዚህ ቅረቡ።
\v 4 በማን ታላግጣላችሁ? በማንስ ላይ አፋችሁን ታላቅቃላችሁ? ምላሳችሁንስ በማን ላይ ታስረዝማላችሁ?
\s5
\v 5 እናንተ በአድባር ዛፎች መካከል በለመለመም ዛፍ ሁሉ በታች በፍትወት የምትቃጠሉ፣ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ሕፃናትን የምታርዱ፣ የዓመፅ ልጆችና የሐሰት ዘር አይደላችሁምን?
\s5
\v 6 በሸለቆው ውስጥ ያሉ የለዘቡ ድንጋዮች እድል ፈንታሽ ናቸው፣ እነርሱም ዕጣሽ ናቸው፤ ለእነርሱም የመጠጥ ቍርባን አፍስሰሻል፣ የእህልንም ቍርባን አቅርበሻል። እንግዲህ በዚህ ነገር አልቈጣምን?
\s5
\v 7 ከፍ ባለውም በረዘመውም ተራራ ላይ መኝታሽን አደረግሽ፣ መሥዋዕትንም ትሠዊ ዘንድ ወደዚያ ወጣሽ።
\v 8 ከመዝጊያውና ከመቃኑ በኋላ መታሰቢያሽን አደረግሽ፤ እኔን ትተሽ ለሌላ ተገልጠሻል፣ ወጥተሽ መኝታሽን አስፍተሻል፤ ቃል ኪዳንም ተጋባሻቸው፣ ባየሽበትም ስፍራ ሁሉ መኝታቸውን ወደድሽ።
\s5
\v 9 ዘይትም ይዘሽ ወደ ንጉሡ ሄድሽ፣ ሽቱሽንም አበዛሽ፣ መልእክተኞችሽንም ወደ ሩቅ ላክሽ፣ እስከ ሲኦልም ድረስ ተዋረድሽ።
\v 10 በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፣ ነገር ግን፣ "ተስፋ የለም" አላልሽም፤ የጕልበትን መታደስ አገኘሽ፣ ስለዚህም አልዛልሽም።
\s5
\v 11 "ሐሰትን የተናገርሺው እኔንም ያላሰብሺው በልብሽም ነገሩን ያላኖርሺው ማንን ሰግተሽ ነው? ማንንስ ፈርተሽ ነው? እኔ ብዙ ጊዜ ዝም አልሁ፣ አንቺም አልፈራሽም።
\v 12 እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፣ ሥራሽም አይረባሽም።
\s5
\v 13 ወደ አንቺ የሰበሰብሻቸው በጮኽሽ ጊዜ ይታደጉሽ፤ ንፋስ ግን ይወስዳቸዋል ሽውሽውታም ሁሉን ያስወግዳቸዋል። በእኔ የታመነ ግን ምድሪቱን ይገዛል፣ የተቀደሰውንም ተራራዬን ይወርሳል።
\s5
\v 14 እርሱም፣ 'ጥረጉ፣ መንገድን አዘጋጁ! ከሕዝቤም መንገድ ዕንቅፋትን አውጡ!" ይላል።
\v 15 ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፣ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፣ "የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፣ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።
\s5
\v 16 መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘላለም አልጣላም፣ ሁልጊዜም አልቈጣም።
\v 17 ስለ ኃጢአቱ ጥቂት ጊዜ ተቈጥቼ ቀሠፍሁት፣ ፊቴን ሰውሬ ተቈጣሁ፤ እርሱም በልቡ መንገድ እያፈገፈገ ሄደ።
\s5
\v 18 መንገዱን አይቻለሁ እፈውሰውማለሁ፣ እመራውማለሁ፣ ለእርሱና ስለ እርሱም ለሚያለቅሱ መጽናናትን እመልሳለሁ።
\v 19 የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ። በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፣ እፈውሰውማለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 20 ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፣ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና።
\v 21 ለክፉዎች ሰላም የላቸውም" ይላል አምላኬ።
\s5
\c 58
\p
\v 1 "በኃይልህ ጩኽ፣ አትቈጥብ፣ ድምፅህን እንደ መለከት አንሣ፣ ለሕዝቤ መተላለፋቸውን ለያዕቆብ ቤትም ኃጢአታቸውን ንገር።
\v 2 ነገር ግን ዕለት ዕለት ይሹኛል መንገዴንም ያውቁ ዘንድ ይወድዳሉ፤ ጽድቅን እንዳደረጉ የአምላካቸውንም ፍርድ እንዳልተዉ ሕዝብ እውነተኛውን ፍርድ ይለምኑኛል። ወደ እግዚአብሔርም ለመቅረብ ይወድዳሉ።
\s5
\v 3 'ስለ ምን ጾምን፣' አንተም 'አልተመለከትኸንም? ሰውነታችንንስ ስለ ምን አዋረድን፣ አንተም አላወቅህም?' ይላሉ። ተመልከቱ፣ በጾማችሁ ቀን ፈቃዳችሁን ታደርጋላችሁ፣ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ታስጨንቃላችሁ።
\s5
\v 4 ተመልከቱ፣ ለጥልና ለክርክር ትጾማላችሁ በግፍ ጡጫም ትማታላችሁ፤ ድምፃችሁንም ወደ ላይ ታሰሙ ዘንድ ዛሬ እንደምትጾሙት አትጾሙም።
\v 5 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፣ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለህን?
\s5
\v 6 እኔስ የመረጥሁት ጾም ይህ አይደለምን? የክፋት በደልን እስራት ትፈቱ ዘንድ፣ የቀንበርንስ ጠፍር ትለቅቁ ዘንድ፣ የተገፉትንስ አርነት ትሰድዱ ዘንድ፣ ቀንበሩንስ ሁሉ ትሰብሩ ዘንድ አይደለምን?
\v 7 እንጀራህንስ ለተራበ ትቈርስ ዘንድ፣ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ ታገባ ዘንድ፣ የተራቈተውንስ ብታይ ታለብሰው ዘንድ፣ ከሥጋ ዘምድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
\s5
\v 8 የዚያን ጊዜ ብርሃንህ እንደ ንጋት ይበራል፣ ፈውስህም ፈጥኖ ይበቅላል፣ ጽድቅህም በፊትህ ይሄዳል፣ የእግዚአብሔርም ክብር በኋላህ ሆኖ ይጠብቅሃል።
\s5
\v 9 የዚያን ጊዜ ትጠራለህ፣ እግዚአብሔርም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፣ "እነሆኝ" ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፣ ጣትህንም መጥቀስ ብትተው፣
\v 10 ባታንጐራጕርም፣ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፣ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፣ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።
\s5
\v 11 እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል። አንተም እንደሚጠጣ ገነት፣ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ።
\s5
\v 12 ከዱሮ ዘመን የፈረሱት ስፍራዎች ይሠራሉ፣ የብዙ ትውልድም መሠረት ይታነጻል፤ አንተም፣ "ቅጥሩን ጠጋኝ፣" "የመኖሪያ መንገድን አዳሽ" ትባላለህ።
\s5
\v 13 ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ እግርህን ከሰንበት ብትመልስ፣ ሰንበትንም ደስታ፣ እግዚአብሔርም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህንም ከማድረግ ፈቃድህንም ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው።
\s5
\v 14 "በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ደስ ይልሃል፤ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፤ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ የእግዚአብሔር አፍ ተናግሮአልና።"
\s5
\c 59
\p
\v 1 ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር እጅ ከማዳን አላጠረችም፣ ጆሮውም ከመስማት አልደነቈረችም፤
\v 2 ነገር ግን፣ በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፣ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል።
\s5
\v 3 እጃችሁ በደም ጣታችሁም በበደል ረክሳለች፣ ከንፈራችሁም ሐሰትን ተናግሮአል፣ ምላሳችሁም ኃጢአትን አሰምቶአል።
\v 4 በጽድቅ የሚጠራ በእውነትም የሚፈርድ የለም፤ በምናምንቴ ነገር ታምነዋል ሐሰትንም ተናግረዋል፤ ጕዳትን ፀንሰዋል በደልንም ወልደዋል።
\s5
\v 5 የእባብን እንቍላል ቀፈቀፉ፣ የሸረሪትንም ድር አደሩ። እንቍላላቸውንም የሚበላ ሰው ይሞታል፣ እንቍላሉም ሲሰበር እፉኝት ይወጣል።
\v 6 ድሮቻቸውም ልብስ አይሆኑላቸውም፣ በሥራቸውም አይሸፈኑም፤ ሥራቸውም የበደል ሥራ ነው፣ የግፍም ሥራ በእጃቸው ነው።
\s5
\v 7 እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፣ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው። ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።
\v 8 የሰላምን መንገድ አያውቁም፣ በአካሄዳቸውም ፍርድ የለም፤ መንገዳቸውን አጣምመዋል፣ የሚሄድባትም ሁሉ ሰላምን አያውቅም።
\s5
\v 9 ስለዚህ ፍርድ ከእኛ ዘንድ ርቆአል፣ ጽድቅም አላገኘንም፤ ብርሃንን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር። እነሆም፣ ጨለማ ሆነ፤ ጸዳልን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፣ ነገር ግን በጨለማ ሄድን።
\v 10 እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፣ ዓይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፣ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።
\s5
\v 11 ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ እንለቃቀሳለን፤ ፍርድን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር። እርሱም የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።
\s5
\v 12 ዓመፃችን በአንተ ፊት በዝቶአልና፣ ኃጢአታችን መስክሮብናልና፣ ዓመፃችን ከእኛ ጋር ነውና፣ በደላችንን እናውቃለንና።
\v 13 ዐምፀናል፣ ሐሰትን ተናግረናል፣ አምላካችንንም ከመከተል ተመልሰናል፤ ግፍንና ዓመፅንም ተናግረናል፣ የኃጢአት ቃልንም ፀንሰን ከልብ አውጥተናል።
\s5
\v 14 ፍርድም ወደ ኋላ ተመልሶአል፣ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፣ ቅንነትም ሊገባ አልቻለምና።
\v 15 እውነትም ታጥቶአል፣ ከክፋትም የራቀ ሰው ለብዝበዛ ሆኖአል። እግዚአብሔርም አየ፣ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ።
\s5
\v 16 ሰውም እንደሌለ አየ፣ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፣ ጽድቁም አገዘው።
\s5
\v 17 ጽድቅንም እንደ ጥሩር ለበሰ፣ በራሱም ላይ የማዳንን ራስ ቍር አደረገ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፣ በቅንዓትም መጐናጸፊያ ተጐናጸፈ።
\v 18 እንደ ሥራቸው መጠን እንዲሁ ቍጣን ለባላጋራዎቹ፣ ፍዳንም ለጠላቶቹ ይከፍላል፤ ለደሴቶችም ፍዳቸውን ይከፍላል።
\s5
\v 19 እርሱ የእግዚአብሔር ነፋስ እንደሚነዳው እንደ ጐርፍ ፈሳሽ ይመጣልና በምዕራብ ያሉት የእግዚአብሔርን ስም፣ በፀሐይ መውጫም ያሉት ክብሩን ይፈራሉ።
\v 20 "ለጽዮን ታዳጊ ይመጣል፣ በያዕቆብም ዘንድ ከኃጢአት ለሚርቁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 21 ከእርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል እግዚአብሔር፣ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ ከአፍህ ከዘርህም አፍ ከዘር ዘርህም አፍ አያልፍም፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 60
\p
\v 1 ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፣ አብሪ።
\s5
\v 2 እነሆ፣ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል፣ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤
\v 3 አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ።
\s5
\v 4 ዓይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ። እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፣ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል።
\v 5 በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፣ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፣ አይተሽ ደስ ይልሻል፣ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል።
\s5
\v 6 የግመሎች ብዛት፣ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፣ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፣ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ።
\v 7 የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፣ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፣ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።
\s5
\v 8 ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፣ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው?
\v 9 እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል።
\s5
\v 10 በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፣ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል።
\v 11 በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ፤ ሰዎች የአሕዛብን ብልጥግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም።
\s5
\v 12 ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፣ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ።
\v 13 የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፣ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፣ ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ።
\s5
\v 14 የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፣ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል።
\s5
\v 15 ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ።
\v 16 የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፣ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃይል፣ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
\s5
\v 17 በናስ ፋንታ ወርቅን፣ በብረትም ፋንታ ብርን፣ በእንጨትም ፋንታ ናስን፣ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። አለቆችሽንም ሰላም፣ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ፤
\v 18 ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፣ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ
\s5
\v 19 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፣ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም።
\v 20 እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፣ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም።
\s5
\v 21 ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እከብር ዘንድ የአታክልቴን ቡቃያ፣ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ።
\v 22 ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ።
\s5
\c 61
\p
\v 1 የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፣ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፣ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
\s5
\v 2 የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፣ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤
\s5
\v 3 እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፣ በአመድ ፋንታ አክሊልን፣ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፣ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
\s5
\v 4 ከጥንትም ጀምሮ ባድማ የነበሩትን ይሠራሉ፤ ከቀድሞ የፈረሱትንም ያቆማሉ። ባድማ የነበሩትንና ከብዙ ትውልድ በፊት የፈረሱትን ከተሞች እንደ ገና ይሠራሉ።
\v 5 መጻተኞችም ቆመው በጎቻችሁን ያሰማራሉ፣ ሌሎች ወገኖችም አራሾችና ወይም ጠባቂዎች ይሆኑላችኋል።
\s5
\v 6 እናንተ ግን የእግዚአብሔር ካህናት ትባላላችሁ፣ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው ይጠሩአችኋል፤ የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ፣ በክብራቸውም ትመካላችሁ።
\v 7 በእፍረታችሁ ፋንታ ሁለት እጥፍ ይሆንላችኋል፣ በውርደታችሁም ፋንታ ዕድል ፈንታችሁ ደስ ይላቸዋል፤ ስለዚህ በምድራቸው ሁሉ እጥፍ ይገዛሉ፣ የዘላለምም ደስታ ይሆንላቸዋል።
\s5
\v 8 እኔ እግዚአብሔር ፍርድን የምወድድ፣ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፣ ከእነርሱም ጋር የዘላለም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።
\v 9 ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፣ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ እግዚአብሔር የባረካቸው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል።
\s5
\v 10 አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፣ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፣ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፣ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፣ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።
\v 11 ምድርም ቡቃያዋን እንደምታወጣ፣ ገነትም ዘሩን እንደሚያበቅል፣ እንዲሁ ጌታ እግዚአብሔር ጽድቅንና ምስጋናን በአሕዛብ ሁሉ ፊት ያበቅላል።
\s5
\c 62
\p
\v 1 ስለ ጽዮን ዝም አልልም፣ ስለ ኢየሩሳሌምም ጸጥ አልልም፣ ጽድቅዋ እንደ ጸዳል መዳንዋም እንደሚበራ ፋና እስኪወጣ ድረስ።
\v 2 አሕዛብም ጽድቅሽን ነገሥታትም ሁሉ ክብርሽን ያያሉ፤ የእግዚአብሔርም አፍ በሚጠራበት በአዲሱ ስም ትጠሪያለሽ።
\s5
\v 3 በእግዚአብሔር እጅ የክብር አክሊል፣ በአምላክሽም እጅ የመንግሥት ዘውድ ትሆኛለሽ።
\v 4 ከእንግዲህ ወዲህ፣ "የተተወች" አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፣ "ውድማ" አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፣ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፣ "ደስታዬ የሚኖርባት" ትባያለሽ ምድርሽም፣ "ባል ያገባች" ትባላለች።
\s5
\v 5 ጕልማሳም ድንግሊቱን እንደሚያገባ፣ እንዲሁ ልጆችሽ ያገቡሻል። ሙሽራም በሙሽራይቱ ደስ እንደሚለው፣ እንዲሁ አምላክሽ በአንቺ ደስ ይለዋል።
\s5
\v 6 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ጕበኞችን በቅጥርሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንና ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም፤ እናንተ እግዚአብሔርን የምታሳስቡ፣
\v 7 ኢየሩሳሌምን እስኪያጸና በምድርም ላይ ምስጋና እስኪያደርጋት ድረስ አትረፉ ለእርሱም ዕረፍት አትስጡ።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር፣ "ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፣ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም።
\v 9 ነገር ግን የሰበሰቡት ይበሉታል፣ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፣ ያከማቹትም በመቅደሴ አደባባይ ላይ ይጠጡታል" ብሎ በቀኙና በኃይሉ ክንድ ምሎአል።
\s5
\v 10 እለፉ፣ በበሮች በኩል እለፉ! የሕዝቡንም መንገድ ጥረጉ፤ አዘጋጁ፣ ጐዳናውን አዘጋጁ፣ ድንጋዮቹንም አስወግዱ፤ ለአሕዛብም ዓለማ አንሡ!
\s5
\v 11 ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር ለምድር ዳርቻ አዋጅ እንዲህ ብሎ ነግሮአል፣ "ለጽዮን ልጅ፣ እነሆ፥ መድኃኒትሽ ይመጣል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ሥራውም በፊቱ አለ" በሉአት።
\v 12 እግዚአብሔር፣ "የተቤዣቸው፣ የተቀደሰ ሕዝብ" ብለው ይጠሩአቸዋል፤ አንቺም፣ "የተፈለገች ያልተተወችም" ከተማ ትባያለሽ።
\s5
\c 63
\p
\v 1 ይህ ከኤዶምያስ፣ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፣ አለባበሱ ያማረ፣ በጕልበቱ ጽናት በራስ መተማመን የሚራመድ ማን ነው? በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።
\v 2 ቀሚስህ ስለ ምን ቀላ፣ ልብስህስ በወይን መጥመቂያ እንደሚረግጥ ሰው ልብስ ስለ ምን መሰለ?
\s5
\v 3 መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፣ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፣ ልብሴንም ሁሉ አስድፌአለሁ።
\v 4 የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፣ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና።
\s5
\v 5 ተመለከትሁ፣ የሚረዳም አልተገኘም፤ የሚያግዝም አልነበረምና ተደነቅሁ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዴ መድኃኒት አመጣልኝ፣ ቍጣዬም እርሱ አገዘኝ።
\v 6 በቍጣዬም አሕዛብን ረገጥሁ በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፣ ደማቸውንም ወደ ምድር አፈሰስሁት።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቸርነትና የእግዚአብሔርን ምስጋና፣ እንደ ምሕረቱና እንደ ቸርነቱም ብዛት ለእስራኤል ቤት የሰጠውን ትልቅ በጎነት አሳስባለሁ።
\v 8 እርሱም፣ "በእውነት ሕዝቤ፣ ሐሰትን የማያደርጉ ልጆች ናቸው" አለ፤ መድኃኒትም ሆነላቸው።
\s5
\v 9 በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፣ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፣ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።
\s5
\v 10 እነርሱ ግን ዐመፁ ቅዱስ መንፈሱንም አስመረሩ። ስለዚህ ተመልሶ ጠላት ሆነባቸው፣ እርሱም ተዋጋቸው።
\s5
\v 11 እርሱም እንዲህ ብሎ የቀደመውን ዘመን አሰበ። "የበጎቹን እረኛ ከባሕሩ ያወጣው ወዴት ነው ያለ? ቅዱስ መንፈሱንም በመካከላቸው ያኖረ ወዴት ነው ያለ?
\s5
\v 12 የከበረውንም ክንድ በሙሴ ቀኝ ያስሄደ፣ ለራሱም የዘላለምን ስም ያደርግ ዘንድ ውኃውን በፊታቸው የከፈለ፣
\v 13 በምድረ በዳም እንደሚያልፍ ፈረስ፣ በቀላይ ውስጥ ያለ ዕንቅፋት ያሳለፋቸው ወዴት ነው ያለ?
\s5
\v 14 ወደ ሸለቆ እንደሚወርዱ ከብቶች፣ እንዲሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ዕረፍት አመጣቸው። እንዲሁም ለራስህ የከበረ ስም ታደርግ ዘንድ ሕዝብን መራህ።
\s5
\v 15 ከሰማይ ቁልቊል ተመልከት፣ ከቅዱስነትህና ከክብርህም ማደሪያ ጐብኝ፤ ቅንዓትህና ኃይልህስ ወዴት ነው? ለእኔም የሆነው የልብህ ናፍቆትና ርኅራኄህ ተከለከለ።
\v 16 አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን፣ አንተ አባታችን ነህ፤ 'አቤቱ፣ አንተ አባታችን ነህ፣' ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው።
\s5
\v 17 አቤቱ፣ ከመንገድህ ለምን አሳትኸን? እንዳንፈራህም ልባችንን ለምን አጸናህብን? ስለ ባሪያዎችህ ስለ ርስትህ ነገዶች ተመለስ።
\s5
\v 18 የተቀደሰው ሕዝብህ መቅደስህን ጥቂት ጊዜ ወረሱት፤ ጠላቶቻችንም ረግጠውታል።
\v 19 ከዘላለም እንዳልገዛኸን በስምህም እንዳልተጠራን ሆነናል።
\s5
\c 64
\p
\v 1 "ሰማዮችን ቀድደህ ምነው ብትወርድ! ተራሮችም ምነው ቢናወጡ!
\v 2 እሳት ጭራሮውን እንደሚያቃጥል፥ እሳትም ውኃውን እንደሚያፈላ፥ ስምህ ለጠላቶችህ ይገለጥ ዘንድ፥ አሕዛብም በፊትህ ይንቀጠቀጡ ዘንድ!
\s5
\v 3 ያልተጠባበቅነውን የክብርህን ሥራ ባደረግህ ጊዜ፣ ወረድህ ተራሮችም በፊትህ ተንቀጠቀጡ።
\v 4 ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላቸው ከአንተ በቀር ሌላ አምላክን አልሰሙም በጆሮአቸውም አልተቀበሉም ዓይንም አላየችም።
\s5
\v 5 ጽድቅን የሚያደርገውን በመንገዶችህም የሚያስቡህን ትገናኛቸዋለህ። እነሆ፣ እነተ ተቈጣህ እኛም ኃጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።
\s5
\v 6 ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፣ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፣ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
\v 7 ስምህንም የሚጠራ፣ አንተንም ሊይዝ የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ ሰውረሃል፣ በኃጢአታችንም አጥፍተኸናል።
\s5
\v 8 አሁን ግን፣ አቤቱ፣ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ጭቃ ነን አንተም ሠሪያችን ነህ፣ እኛም ሁላችን የእጅህ ሥራ ነን።
\v 9 አቤቱ፣ እጅግ አትቈጣ፣ ለዘላለምም ኃጢአትን አታስብ፤ እነሆ፣ እባክህ፣ ተመልከት፣ እኛ ሁላችን ሕዝብህ ነን።
\s5
\v 10 የተቀደሱ ከተሞችህ ምድረ በዳ ሆነዋል፤ ጽዮን ምድረ በዳ ኢየሩሳሌምም ውድማ ሆናለች።
\v 11 አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፣ ያማረውም ስፍራችን ሁሉ ፈርሶአል።
\v 12 አቤቱ፣ በውኑ በዚህ ነገር ትታገሣለህን? ዝምስ ትላለህን? አጥብቀህስ ታስጨንቀናለህን?
\s5
\c 65
\p
\v 1 ላልጠየቁኝ ተገለጥሁ፣ ላልፈለጉኝም ተገኘሁ፤ በስሜም ያልተጠራውን ሕዝብ፣ 'እነሆኝ! እነሆኝ!' አልሁት።
\v 2 መልካም ባልሆነው መንገድ፣ አሳባቸውን እየተከተሉ፣ ወደሚሄዱ ወደ ዓመፀኛ ሕዝብ ቀኑን ሁሉ እጆቼን ዘረጋሁ!
\s5
\v 3 ይህ ሕዝብ ዘወትር የሚያስቈጡኝ ናቸው፤ እነርሱ በአትክልት ውስጥ የሚሠዉ በጡብም ላይ የሚያጥኑ፣
\v 4 በመቃብርም መካከል የሚቀመጡ፣ በስውርም ስፍራ የሚያድሩ፣ የእሪያ ሥጋም የሚበሉ ናቸው። የረከሰው መረቅ በዕቃቸው ውስጥ አለ።
\s5
\v 5 እነርሱም፣ 'ርቀህ ቁም፣ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና ወደ እኔ አትቅረብ' ይላሉ፤ እነዚህ በአፍንጫዬ ዘንድ ጢስ ቀኑንም ሁሉ የምትነድድ እሳት ናቸው።
\s5
\v 6 እነሆ፣ በፊቴ ተጽፎአል። ኃጢአታችሁና የአባቶቻችሁን ኃጢአት በአንድ ላይ ወደ ብብታቸው ፍዳ አድርጌ አመልሳለሁ እንጂ ዝም አልልም፣" ይላል እግዚአብሔር፤
\v 7 "በተራሮችም ላይ ስላጠኑ፣ በኮረብቶችም ላይ ስለ ሰደቡኝ፣ ስለዚህ አስቀድመው የሠሩትን ሥራቸውን በብብታቸው እሰፍራለሁ።"
\s5
\v 8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወይን በዘለላው በተገኘች ጊዜ፣ በረከት በእርስዋ ላይ አለና አታጥፉት" እንደሚባለው፣ ሁሉን እንዳላጠፉ ስለባሪያዎቼ እንዲሁ አደርጋለሁ።'
\s5
\v 9 ከያዕቆብ ዘርን ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሰውን አወጣለሁ፤ እኔም የመረጥኋቸው ይወርሱአታል፣ ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።
\v 10 ሳሮንም የበጎች ማሰማርያ፣ የአኮርም ሸለቆ የላሞች መመሰግያ ለፈልጉኝ ሕዝቤ ይሆናል።
\s5
\v 11 እናንተን ግን እግዚአብሔርን የተዋችሁትን፣ ቅዱሱንም ተራራዬን የረሳችሁትን፣ ጉድ ለተባለ ጣዖትም ማዕድ ያዘጋጃችሁትን፣ እድል ለተባለ ጣዖትም የወይን ጠጅ ለመጠጥ ቍርባን የቀዳችሁትን -
\s5
\v 12 እድላችሁን ለሰይፍ አደርገዋለሁ፣ ሁላችሁም ለመታረድ ትጐነበሳላችሁ፤ በፊቴም ክፉ ነገርን አደረጋችሁ፣ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝምና፣ በተናገርሁም ጊዜ አልሰማችሁኝምና።"
\s5
\v 13 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ይበላሉ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ደስ ይላቸዋል እናንተ ግን ታፍራላችሁ፤
\v 14 ተመልከቱ፣ ባሪያዎቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፣ እናንተ ግን ከልባችሁ ኀዘን የተነሣ ትጮኻላችሁ፣ መንፈሳችሁም ስለ ተሰበረ ወዮ ትላላችሁ።
\s5
\v 15 ስማችሁንም ለተመረጡት ሕዝቤ እርግማን አድርጋችሁ ትተዋላችሁ፣ ጌታ እግዚአብሔርም ይገድላችኋል፣ ባሪያዎቹንም በሌላ ስም ይጠራቸዋል።
\v 16 እንዲሁም በምድር ላይ የተባረከ በእውነት አምላክ ይባረካል፣ በምድርም ላይ የማለ በእውነት አምላክ ይምላል፤ የቀድሞው ጭንቀት ተረስቶአልና፣ ከዓይኔም ተሰውሮአልና።
\s5
\v 17 ተመልከቱ፣ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እፈጥራለሁና፤ የቀደሙትም አይታሰቡም፣ ወደ ልብም አይገቡም።
\v 18 ነገር ግን በፈጠርሁት ደስ ይበላችሁ፣ ለዘላለምም ሐሤት አድርጉ፤ ተመልከቱ፣ ኢየሩሳሌምን ለሐሤት፣ ሕዝብዋንም ለደስታ እፈጥራለሁና።
\v 19 እኔም በኢየሩሳሌም ሐሤት አደርጋለሁ በሕዝቤም ደስ ይለኛል፤ ከዚያም ወዲያ የልቅሶ ድምፅና የዋይታ ድምፅ አይሰማባትም።
\s5
\v 20 ከዚያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚኖር ሕፃን, ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም፤ ጕልማሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞታልና, ኃጢአተኛውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተረገመ ይሆናልና።
\v 21 ቤቶችንም ይሠራሉ ይቀመጡባቸውማል፤ ወይኑንም ይተክላሉ ፍሬውንም ይበላሉ።
\s5
\v 22 ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፣ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፣ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና።
\v 23 እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም።
\s5
\v 24 እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ አመልስላቸዋለሁ፣ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።
\v 25 ተኵላና ጠቦት በአንድነት ይሰማራሉ፣ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፣ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፣ አያጠፉምም፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 66
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሰማይ ዙፋኔ ነው፣ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድር ነው?
\s5
\v 2 እነዚህን ሁሉ እጄ ሠርታለችና እነዚህ ሁሉ የእኔ ናቸው ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን ወደዚህ ወደ ትሑት፣ መንፈሱም ወደ ተሰበረ፣ በቃሌም ወደሚንቀጠቀጥ ሰው እመለከታለሁ።
\s5
\v 3 በሬን የሚያርድልኝ ሰውን እንደሚገድል ነው፤ ጠቦትንም የሚሠዋ የውሻውን አንገት እንደሚሰብር ነው፤ የእህልን ቍርባን የሚያቀርብ የእርያን ደም እንደሚያቀርብ ነው፤ ዕጣንን የሚያጥን ጣዖትን እንደሚባርክ ነው። እነዚህ የገዛ መንገዳቸውን መረጡ፤ ነፍሳቸውም በርኵሰታቸው ደስ ይላታል፤
\s5
\v 4 እኔ ደግሞ የተሳለቀባቸውን እመርጣለሁ፣ የፈሩትንም ነገር አመጣባቸዋለሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገርን አደረጉ፣ ያልወደድሁትንም መረጡ እንጂ በጠራሁ ጊዜ አልመለሱልኝምና፣ በተናገርሁም ጊዜ አልሰሙኝምና።"
\s5
\v 5 በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ "የጠሉአችሁ ስለ ስሜም ያባረሩአችሁ ወንድሞቻችሁ፣ ደስታችሁን እናይ ዘንድ እግዚአብሔር ይክበር' ብለዋል፤ ነገር ግን ያፍራሉ።
\s5
\v 6 የጩኸት ድምፅ ከከተማ፣ ድምፅም ከመቅደስ፣ በጠላቶቹ ላይ ፍዳን የሚያመጣ የእግዚአብሔር ድምፅ ተሰምቶአል።
\s5
\v 7 ሳታምጥ ወለደች፤ ምጥም ሳያገኛት ወንድ ልጅን ወለደች።
\v 8 ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳልን? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።
\s5
\v 9 በውኑ ወደ መውለድ የማደርስ እኔ አላስወልድምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የማስወልድስ ማኅፀንን እኔ እዘጋለሁን?" ይላል አምላክሽ።
\s5
\v 10 እናንተ የምትወድዱአት ሁሉ፣ ከኢየሩሳሌም ጋር ሐሤትን አድርጉ፣ ስለ እርስዋም ደስ ይበላችሁ፤ እናንተም የምታለቅሱላት ሁሉ፣ ከእርስዋ ጋር በደስታ ሐሤትን አድርጉ፣
\v 11 ትጠቡ ዘንድ ከማጽናናትዋም ጡት ትጠግቡ ዘንድ፤ እጅግ ጠጥታችሁ በክብርዋ ሙላት ደስ ይላችሁ ዘንድ።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "እነሆ፣ ሰላምን እንደ ወንዝ፣ የአሕዛብንም ክብር እንደሚጐርፍ ፈሳሽ እመልስላታለሁ፤ ከዚያም ትጠባላችሁ፣ በጫንቃ ላይ ይሸከሙአችኋል በጕልበትም ላይ እያስቀመጡ ያቀማጥሉአችኋል።
\v 13 እናት ልጅዋን እንደምታጽናና እንዲሁ አጽናናችኋለሁ፣ በኢየሩሳሌምም ውስጥ ትጽናናላችሁ።"
\s5
\v 14 ታያላችሁ፣ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፣ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የእግዚአብሔርም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፣ በጠላቶቹም ላይ ይቈጣል።
\s5
\v 15 ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፣ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፣ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።
\v 16 እግዚአብሔርም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በእግዚአብሔርም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።
\s5
\v 17 በመካከላቸው ያለውን አንዱን ተከትለው ወደ ገነቱ ይገቡ ዘንድ ሰውነታቸውን የሚቀድሱና የሚያነጹ፣ የእሪያንም ሥጋ አስጸያፊ ነገርንም አይጥንም የሚበሉ በአንድነት ይጠፋሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 18 ሥራቸውንና አሳባቸውን አውቄአለሁና፤ አሕዛብንና ልሳናትን ሁሉ የምሰበስብበት ጊዜ ይደርሳል፣ እነርሱም ይመጣሉ ክብሬንም ያያሉ።
\v 19 በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፣ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፣ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ ወደ ፉጥ ወደ ሉድ ወደ ሞሳሕ ወደ ቶቤል ወደ ያዋን በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፣ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።
\s5
\v 20 የእስራኤል ልጆች ቍርባናቸውን በጥሩ ዕቃ አድርገው ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደሚያመጡ፣ እንዲሁ ለእግዚአብሔር ቍርባን ይሆን ዘንድ ወንድሞቻችሁን ሁሉ፣ በፈረሶችና በሰረገሎች፣ በአልጋዎችና በበቅሎች በጠያር ግመሎችም ላይ አድርገው፣ ከአሕዛብ ሁሉ ወደ ተቀደሰው ተራራዬ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡአቸዋል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 21 ካህናትና ሌዋውያን እንዲሆኑ ከእነርሱ እወስዳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 22 እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 23 እንዲህ ይሆናል፤ በየመባቻውና በየሰንበቱ ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቴ ይሰግድ ዘንድ ዘወትር ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 24 ወጥተውም በእኔ ያመፁብኝን ሰዎች ሬሳቸውን ያያሉ፤ ትላቸው አይሞትምና፣ እሳታቸውም አይጠፋምና፤ ለሥጋ ለባሽም ሁሉ አስጸያፊ ነገር ይሆናሉ።"

2615
24-JER.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,2615 @@
\id JER
\ide UTF-8
\h ኤርሚያስ
\toc1 ኤርሚያስ
\toc2 ኤርሚያስ
\toc3 jer
\mt ኤርሚያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ይህ የኬልቅያስ ልጅ የሆነው የኤርምያስ ቃል ነው፤ እርሱ በብንያም ምድር ከነበሩት ካህናት አንደኛው ነበር።
\v 2 የአሞጽ ልጅ በሆነው በይሁዳ ንጉሥ ዐሥራ ሦስተኛ ዓመት አገዛዝ ዘመን ላይ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።
\v 3 ቃሉ የመጣው በይሁዳ ንጉሥ የኢዮስያስ ልጅ በሆነው ኢዮአቄም ዘመን፣ የኢዮስያስ ልጅ በሆነው የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ የዐሥራ አንደኛው አመት አገዛዝ አምስተኛ ወር ድረስ፣ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ምርኮኛ ሆነው ሲወሰዱ ነበር።
\s5
\v 4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 5 "በማኅፀን ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብ ነቢይ አድርጌሃለሁ።"
\v 6 እኔም፣ "ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ ገና ብላቴና በመሆኔ እንዴት እንደምናገር አላውቅም" አልሁ።
\s5
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር "'ገና ብላቴና ነኝ' አትበል። ወደምልክህ ሁሉ ልትሄድ ይገባል፣ የማዝዝህንም ሁሉ ልትናገር ይገባል!
\v 8 ላድንህ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ - ይህ የእግዚአብሔር ንግግር ነው።" አለኝ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔርም እጁን ዘርግቶ አፌን ዳሰሰ፣ እንዲህም አለኝ "ቃሌን በአፍህ ውስጥ አኑሬአለሁ፤
\v 10 ትነቅልና ታፈርስ ዘንድ፥ ታጠፋና ትገለብጥ ዘንድ፥ ትሠራና ትተክል ዘንድ በአሕዛብና በመንግሥታት ላይ ዛሬ ሾሜሃለሁ" አለኝ።
\s5
\v 11 የእግዚአብሔር ቃል "ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ?" እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም "የለውዝ በትር አያለሁ" አልሁት።
\v 12 እግዚአብሔርም "መልካም አይተሃል፣ እፈጽመው ዘንድ በቃሌ እተጋለሁና" አለኝ።
\s5
\v 13 የእግዚአብሔር ቃል ለሁለተኛ ጊዜ "ምን ታያለህ?" እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም "ፊቱ ከሰሜን አቅጣጫ የሆነ የሚፈላ ማሰሮ አያለሁ" አልሁ።
\v 14 እግዚአብሔርም "በዚህች ምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ከሰሜን አቅጣጫ ክፉ ነገር ይገለጣል" አለኝ።
\s5
\v 15 በሰሜን ያሉትን የመንግሥታትን ወገኖች ሁሉ እጠራለሁና ይላል እግዚአብሔር። እነርሱም ይመጣሉ፣ እያንዳንዳቸውም በኢየሩሳሌም መግቢያ በራፍ ላይ፣ በዙሪያዋ ባሉት በአጥሮቿ ሁሉ ላይ፣ በይሁዳም ከተሞች ሁሉ ላይ ዙፋናቸውን ያኖራሉ።
\v 16 እኔን ስለተዉበት ክፋታቸው ሁሉ፣ ለሌሎችም አማልክት ስላጠኑ፣ በገዛ እጃቸው ለሠሯቸውም ስለሰገዱላቸው፣ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።
\s5
\v 17 አንተ ራስህን አዘጋጅ! ተነሥና ያዘዝሁህን ሁሉ ንገራቸው። በእነርሱ ፊት አትፍራ፣ አሊያ እኔ በእነርሱ ፊት አስፈራሃለሁ!
\v 18 ተመልከት! ዛሬ በምድሪቱ ሁሉ ላይ በይሁዳም ነገሥታት -በአለቆችዋና በካህናትዋ ላይ በምድሪቱም ሕዝብ ላይ እንደ ተመሸገ ከተማ እንደ ብረትም ዓምድ እንደ ናስም ቅጥር አድርጌሃለሁ።
\v 19 ይዋጉሃል፣ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 2
\p
\v 1 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ፣
\v 2 "ሂድና በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ። እንዲህም በል 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወጣትነትሽ የነበረሽን የኪዳን ታማኝነት፣ በታጨሽበት ጊዜ የነበረሽን ፍቅር፣ ዘር ባልተዘራበት ምድረ በዳ እንደ ተከተልሽኝ ስለአንቺ አስታውሳለሁ።
\v 3 እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፣ የእርሻው መከር በኩራትም ነበረ! ከበኩራቱ የበሉት ሁሉ ኃጢአት አድርገዋል! ክፉም ነገር ይመጣባቸዋል ይላል እግዚአብሔር።'"
\s5
\v 4 የያዕቆብ ቤትና የእስራኤልም ቤት ቤተሰቦች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "አባቶቻችሁ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው እኔን ከመከተል የራቁት፣ ከንቱ ጣዖታትንም የተከተሉት፣ እና ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት?
\v 6 እነርሱም 'ከግብጽ ምድር ያወጣን እግዚአብሔር፣ በምድረ በዳ ጉድጓድ ወዳለበት የአረባህ ምድር፣ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ?' አላሉም።
\s5
\v 7 ነገር ግን ፍሬዋንና ሌሎች መልካም ነገሮቿን እንድትበሉ ወደ ቀርሜሎስ ምድር አገባኋችሁ! ይሁን እንጂ በመጣችሁ ጊዜ፣ ምድሬን አረከሳችሁ፣ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ!
\v 8 ካህናቱም 'እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ የኦሪቶች ሊቅ የሆኑትም ስለ እኔ ግድ አላላቸውም! እረኞችም በደሉኝ፥ ነቢያትም ለበኣል ትንቢት ተናገሩ፣ ትርፍ የሌለውንም ነገር ተከተሉ።
\s5
\v 9 ስለዚህ እከስሳችኋለሁ - የልጆቻችሁንም ልጆች እከስሳለሁ።
\v 10 ወደ ኪቲም ደሴቶች እለፉና ተመልከቱ። ወደ ቄዳርም መልእክተኞችን ላኩና እንደዚህ ያለ ነገር ህኖ እንደ ሆነ መርምራችሁ እዩ።
\v 11 አማልክት ባይሆኑ እንኳን አማልክት ያልሆኑትን አማልክቱን የለወጣቸው አንድ ሕዝብ አለን? ነገር ግን ሕዝቤ ሊረዳቸው ለማይችለው ነገር ክብሩን ለወጠ።
\s5
\v 12 ሰማያት ከዚህ የተነሣ ተደነቁ! ተንቀጥቀጡ እና ደንግጡ ይላል እግዚአብሔር።
\v 13 ሕዝቤ ሁለቱን ክፉ ነገሮች በእኔ ላይ አድርገዋልና፦ ውሃ ለመያዝ የማይችሉትን የተቀደዱ ጉድጓዶች ለራሳቸው በመቆፈር እኔን የሕያውን ውኃ ምንጭ ትተውኛል!
\s5
\v 14 እስራኤል ባርያ ነውን? ወይስ በቤት የተወለደ አይደለምን? እናስ ብዝበዛ የሆነው ለምንድነው?
\v 15 የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ። ብዙ ድምጽ በማሰማት ምድሩን አስፈሪ አደረጉት! ከተሞቹም የሚኖርባቸው እንዳይኖር ሆኖ ተደመሰሰ።
\v 16 የሜምፎስና የጣፍናስ ልጆች የራስ ቅልሽን ላጭተው ባርያዎችን ከአንቺ ወሰዱ!
\v 17 ይህን ሁሉ በራስሽ ላይ ያደረግሽው በመንገድ ላይ ሲመራሽ አምላክሽን እግዚአብሔርን ስለተውሽ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር አምላክሽ።
\s5
\v 18 አሁንስ በግብጽ መንገድ ሄደሽ የሺሖርን ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው? በአሦርስ መንገድ ሄደሽ የኤፍራጥስንም ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው?
\v 19 ክፋትሽ ይገሥጽሻል፣ ክዳትሽም ይቀጣሻል፤ አምላክሽንም እግዚአብሔርን መተውሽ እኔንም መፍራት ማቆምሽ ክፉና መራራ ነገር እንደ ሆነ እወቂ፥ ተመልከቺ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 20 ከጥንት ጀምሮ የነበረብሽን ቀንበር ሰብሬአለሁና፣ እስራትሽንም ቈርጫለሁ። እንዲህም ሆኖ አንቺ 'አላገለግልም!' አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ተጋደምሽ፣ አንቺ አመንዝራ።
\v 21 እኔ ራሴ ግን የተመረጠች ወይን፣ ፈጽሞ እውነተኛ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር። አንቺ ግን ክፉ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ?
\v 22 በወንዝ ብትታጠቢ ወይም በብርቱ ሳሙና ብትታጠቢ፣ በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\v 23 'አልረከስሁም! በአሊምንም አልተከተልሁም' እንዴት ትያለሽ? በሸለቆዎች ያለውን ባህርይሽን ተመልከቺ! ያደረግሽውንም ተገንዘቢ፣ በመንገዷ ላይ እንደ ተለቀቀች ፈጣን ግመል ሆነሻል፤
\v 24 በምኞትዋ ከንቱ ነፋስን እንደምታሸትት፣ ምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ! ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚፈልጋት ሁሉ ራሱን አያደክምም። ወደ እርሷ ሄደው በትኩሳቷ ወራት ያገኟታል።
\v 25 እግርሽን ባዶ ከመሆን፣ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ! አንቺ ግን 'ተስፋ-ቢስ ነው! አይሆንም፣ እንግዶችን ወድጄአለሁና እከተላቸዋለሁ!' አልሽ።
\s5
\v 26 ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍረው ሁሉ፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት፣ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸው፣ አለቆቻቸው፣ ካህናቶቻቸውና ነብያቶቻቸውም ያፍራሉ።
\v 27 ለዛፉ፣ 'አንተ አባቴ ነህ፣' ድንጋዮንም 'አንተ ወለድከኝ' ይላሉ። ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ። በመከራቸው ጊዜ ግን 'ተነሥና አድነን!' ይላሉ።
\v 28 ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቊጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ!
\s5
\v 29 ስለዚህ እኔ እንዳጠፋሁ አድርጋችሁ የምትከስሱኝ ለምንድር ነው? ሁላችሁ በእኔ ላይ ኃጢአት ሠርታችሁብኛል ይላል እግዚአብሔር።
\v 30 ሕዝባችሁን በከንቱ ቀጥቼአቸዋለሁ፤ ተግሣጽን አልተቀበሉም፤ እንደሚሰብር አንበሳ ሰይፋችሁ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል!
\v 31 ከዚህ ትውልድ የሆናችሁ እናንተ! የእግዚአብሔር ቃል ለሆነው ለቃሌ ትኩረት ስጡ! በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ፣ ወይስ የጥልቅ ጨለማ ምድር ሆንሁባትን? ሕዝቤስ ስለ ምን 'እኛ እንቅበዝበዝ፣ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም' ይላል?
\s5
\v 32 ደናግሏ ጌጥዋን፣ ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠሩ ቀናት ረስቶኛል።
\v 33 ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት በደህና ታቀኛለሽ። እንደውም መንገድሽን ለክፉዎች ሴቶች እንኳ አስተምረሻል።
\v 34 የንፁሐን ሕይወት የሆነው ደም፣ የድሆችም ደም በልብሶችሽ ላይ ተገኝቷል። እነዚህ ሰዎች በስርቆሽ ተግባር የተያዙ አልነበሩም።
\s5
\v 35 ይልቊን፣ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ፣ 'ወቀሳ የለብኝም፤ በእውነት የእግዚአብሔር ቊጣ ከእኔ ተመልሶአል' አልሽ። ነገር ግን ተመልከቺ! 'ኃጢአት አልሠራሁም' ብለሻልና ይፈረድብሻል።
\v 36 መንገድሽን ትለዋውጪ ዘንድ ነገሩን ለምን ታቀልያለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ ያሳፍርሻል።
\v 37 እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ።
\s5
\c 3
\p
\v 1 በሰው ዘንድ፣ 'ሰው ሚስቱን በፍቺ ቢያባርራት፣ ከእርሱም ሄዳ የሌላ ሰው ሚስት ትሆናለች። በድጋሚ ወደ እርሷ ሊመለስ ይገባዋልን? እርሷ ፈጽሞ የረከሰች አይደለችምን?' ይባላል። ያቺ ሴት ማለት ይህች ምድር ናት! አንቺ እንደ ሴተኛ አዳሪ ከብዙ ውሽሞች ጋር አመንዝረሻል፣ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 2 ዓይንሽን ወደ ተራቆቱት ኮረብቶች አንሺና ተመልከቺ! ያልተነወርሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ዘላን በምድረ በዳ እንደሚቀመጠው፣ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ አፍቃሪዎችሽን ትጠብቂያቸው ነበር። በዘማዊነትሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።
\s5
\v 3 ስለዚህ የጸደይ ዝናብ ተከለከለ፣ የኋለኛውም ዝናብ አልመጣም። ነገር ግን እንደ ዘማዊት ሴት ፊት፣ ፊትሽ የእብሪተኛ ነበር። ልታፍሪም እንቢ ብለሻል።
\v 4 ከእንግዲህ ወዲህ 'አባቴ! የወጣትነቴ የቅርብ ወዳጅ ነህ።' ብለሽ ወደ እኔ አልጮኽሽልኝምን?
\v 5 እስከ ለዘላለም ትቆጣለህን? ቊጣህንስ እስከ ፍጻሜ ድረስ ትጠብቀዋለህን?' ብለሽ ተናገርሽ። ተመልከቺ! ክፋትን እንደምትፈጽሚ ተናገርሽ፣ አደረግሸውም። ስለዚህ ማድረግሽን ቀጥይ!"
\s5
\v 6 እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ "እስራኤል እኔን መክዳቷን ታያለህ? ከፍ ወዳለው ተራራ ሁሉ፣ ወደለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፣ በዚያም እንደ ዘማዊት ሴት ሆነች።
\v 7 'ይህንም ሁሉ ካደረገች በኋላ፣ ወደ እኔ ትመለሳለች' ብዬ ነበር፤ ነገር ግን አልተመለሰችም። ከዚያም እምነት የለሿ እኅቷ ይሁዳ እርሷ ያደረገችውን አየች።
\s5
\v 8 ስለዚህ፣ ለእነዚህ ምክንያቶች ሁሉ ማመንዘሯን አየሁ። ከዳተኛይቱ እስራኤል! ፈትቼያት አባርሬያታለሁ፣ ደግሞም የፍችዋንም ወረቀት ሰጥቻታለሁ። አታላይ እኅትዋ ይሁዳ ግን አልፈራችም፣ እርስዋም ደግሞ ሄዳ ዝሙትን ፈጸመች።
\v 9 በዝሙትዋ ምድሪቱ መርከሷ ምንም አልመሰላትም፣ ስለዚህ ከድንጋይና ከግንድ ጣዖታትን አደረጉ።
\v 10 ከዚያም ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ እምነት-የለሿ ይሁዳ በውሸት እንጂ በፍጹም ልብዋ ወደ እኔ አልተመለሰችም!"-ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 11 ከዚያም እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ከእምነት-የለሿ ይሁዳ ይልቅ እምነት-የለሿ እስራኤል ጸደቀች!
\v 12 ሂድና ይህን ቃል ለሰሜን ተናገር። 'እምነት የለሿ እስራኤል ሆይ፥ ተመለሽ! ይላል እግዚአብሔር፤ ለሁልጊዜ አልቈጣብሽምና። እኔ ታማኝ ስለሆንኩ - ለዘላለም እንደተቆጣሁ አልቆይም ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 13 በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኃጢአትሽን ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር።
\v 14 አግብቻችኋለሁና እምነት-የለሽ የሆናችሁት ሕዝቦች፣ ተመለሱ! ይላል እግዚአብሔር፤ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ! ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ!
\v 15 እንደ ልቤም የሆኑ እረኞችን እሰጣችኋለሁ፣ እነርሱም በዕውቀትና በማስተዋልም ይጠብቁአችኋል።
\s5
\v 16 በእነዚያ ቀናት ትበዛላችሁ፣ በምድሪቱም ላይ ታፈራላችሁ ይላል እግዚአብሔር። "የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት!" ብለው ከእንግዲህ ወዲህ አይናገሩም። ከእንግዲህ አያስቡትምና፣ ወይም አያስተውሉትምና ይህ ጉዳይ ከእንግዲህ በልባቸው አይመጣም። ከእንግዲህ ወዲህም ይህ ንግግር አይኖርም።'
\s5
\v 17 በዚያም ዘመን ስለ ኢየሩሳሌም 'ይህች የእግዚአብሔር ዙፋን ናት' ብለው ይናገራሉ፣ ደግሞም ሌሎች አሕዛብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም ኢየሩሳሌም ላይ ይሰበሰባሉ። ከእንግዲህም ወዲህ በእልከኛ ልባቸው አይሄዱም።
\v 18 በእነዚያም ቀናት፣ የይሁዳ ቤት ከእስራኤል ቤት ጋር ይሄዳል። በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
\s5
\v 19 እኔ ግን 'እንደ ወንድ ልጄ ላከብርሽና በሌሎች አሕዛብ ካለው ይልቅ የበለጠ ውብ የሆነውን አስደሳቹን ምድር ልሰጥሽ እንዴት ፈለግሁ!' ብዬ ነበር። "አባቴ" ብለሽ ትጠሪኛለሽ። እኔንም ከመከተል አትመለሽም' ብዬ ነበር።
\v 20 ነገር ግን ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሴት፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት የሆናችሁት ከዳችሁኝ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 21 "የእስራኤል ልጆች መንገዳቸውን ቀይረዋልና፣ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተውኛልና በወና ኮረብቶች ላይ የልመናቸውና ልቅሶአቸው ድምፅ ተሰማ።
\v 22 ከዳተኞች ሕዝቦች ሆይ ተመለሱ! ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ!" እነሆ! አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና ወደ አንተ እንመጣለን።
\s5
\v 23 የኮረብቶችና የብዙ ተራሮች ሐሰት ብቻ መጥቷል። በእርግጥም የእስራኤል መዳን በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው።
\v 24 ይሁን እንጂ አሳፋሪ ጣዖታት ለበጎቻቸውና ላሞቻቸው፣ ለወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው አባቶቻችን የሠሩትን በልተውባቸዋል።
\v 25 በእፍረት እንጋደም። በአምላካችን እግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና እፍረታችን ይሸፍነን። ከትንሽነታችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባቶቻችን በአምላካችን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርተናልና፣ የአምላካችንንም የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማንምና!"
\s5
\c 4
\p
\v 1 እስራኤል ሆይ፣ ብትመለሺ፣ የምትመለሺው ወደ እኔ ይሁን፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ከፊቴ ርኩሰትሽን ብታስወግጂ፣ በድጋሚም ከእኔ ባትርቂ
\v 2 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለሽ በእውነትና በፍትሕ፣ በጽድቅም ብትምይ፥ አሕዛብ በረከቴን ይጠይቃሉ፣ እኔንም ያመሰግኑኛል።
\v 3 ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ጥጋቱን እርሻ እረሱ፣ በእሾህም ላይ አትዝሩ።
\s5
\v 4 እናንተም የይሁዳ ሰዎች፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች፣ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቊጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳያቃጥል፥ ለእግዚአብሔር ተገረዙ፥ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
\v 5 ይሁዳ ውስጥ ተናገሩ፣ በኢየሩሳሌምም ላይ አውሩ። "በአገሪቱ ላይ መለከት ንፉ" በሉ፤ ጮኻችሁም "ሁላችሁ ተሰብሰቡ። ወደ ተመሸጉትም ከተሞች እንግባ" በሉ።
\v 6 ከሰሜን ክፉ ነገርንና ጽኑ ጥፋትን አመጣለሁና ወደ ጽዮን ሰንደቅ ዓላማን አንሡ፤ ሽሹ፥ አትዘግዩ።
\s5
\v 7 አንበሳ ከጥቅጥቅ ዱር እየወጣ ነው፣ አሕዛብንም የሚያጠፋ እየወጣ ነው። ምድርሽን ለማሸበር፣ ከተሞችሽም ሰው የሌለባቸው ፍርስራሾች ለማድረግ ከስፍራው ወጥቶአል።
\v 8 ከዚህ የተነሣ፣ ራስሽን በማቅ ልብስ ሸፍኚ፣ ሙሾ አውጪ፣ አልቅሺም። የእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ ከእኛ ዘንድ አልተመለሰምና።
\s5
\v 9 በዚያም ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ የንጉሡና የመኳንንቱ ልብ ይሞታል። ካህናቱም ይደነቃሉ ነቢያቱም ይደነግጣሉ።
\v 10 እኔም "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ፥ 'ሰላም ይሆንላችኋል' በማለት ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን በእርግጥም ፈጽመህ አታልለሃል። ሆኖም 'ሰይፉ እስከ ነፍስ ድረስ ያጠቃል።"
\s5
\v 11 በዚያ ጊዜ ለዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም፣"የሚያቃጥል ነፈሳስ በምድረበዳ ካሉት ወና ኮረብቶች ወደ ሕዝቤ ሴት ልጅ ይመጣል። እነርሱን አያበጥርም ወይም አያጠራም።
\v 12 ከዚያም ይልቅ እጅግ ብርቱ የሆነ ነፋስ በትእዛዜ ይመጣል፣ ደግሞም እኔ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።
\s5
\v 13 ተመልከቱ እንደ ደመና ያጠቃል፣ ሠረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው። ፈረሶቹም ከንስር ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። ጠፍተናልና ወዮልን!
\v 14 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ትድኚ ዘንድ ልብሽን ከክፉ ነገር እጠቢ። እንዴት ኃጢአት እንደምትሠሪ ክፉ አሳብ የሚኖርብሽ እስከ መቼ ድረስ ነው?
\v 15 የተናጋሪ ድምፅ ከዳን ይናገራል። የሚመጣውም ጥፋት ከኤፍሬምም ተራሮች ይሰማል።
\s5
\v 16 አሕዛብ ይህንን እንዲያስቡ አድርጉ፦ ተመልከቱ፣ ወራሪዎች በይሁዳ ከተሞች ላይ የጦርነት ጩኸት ለመጮኽ ከሩቅ ምድር እየመጡ ነው ብላችሁ አውሩ።
\v 17 በእኔ ላይ ዓመፀኛ ሆናለችና የለማ እርሻን ከብበው እንደሚጠብቊ ይሆናሉ ይላል እግዚአብሔር።
\v 18 ባሕርይሽና ሥራሽ ይህን አድርጎብሻል። ይህ ቅጣትሽ ይሆናል። እንዴት አስጨናቂ ይሆናል! የገዛ ልብሽም ይመታል።
\s5
\v 19 ልቤ! ልቤ! በልቤ ተጨንቄያለሁ። ልቤ በውስጤ ታውኮብኛል። የመለከትን ድምፅና የጦርነት ማንቂያን ሰምቻለሁና ዝም ልል አልችልም።
\v 20 በጥፋት ላይ ጥፋት ተጠርቶአል፣ መላዋ ምድርም ተበዝብዛለች። በድንገትም ድንኳኔንና መጋረጃዬን አጠፉ።
\s5
\v 21 መስፈርቱን የምመለከተው እስከመቼ ነው? የመለከቱንስ ድምፅ እሰማ ይሆን?
\v 22 ሕዝቤ ተሞኝተዋልና አላወቁኝም። ሰነፍ ሕዝብ ናቸው፣ ማስተዋልም የላቸውም። ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፣ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።
\s5
\v 23 ምድሪቱን አየሁ፣ እነሆም፥ ባዶ ነበረች አንዳችም አልነበረባትም፤ ለሰማያትም ብርሃንም አልነበረባቸውም።
\v 24 ተራሮችን አየሁ። እነሆም፣ ይንቀጠቀጡ ነበር፣ ኮረብቶችም ሁሉ ተናወጡ።
\v 25 አየሁ። እነሆ፣ ሰው አልነበረም፣ የሰማይም ወፎች ሁሉ ሸሽተው ነበር።
\v 26 ተመለከትሁ። እነሆ፣ ፍሬያማ እርሻ ምድረ በዳ ሆነች፣ ከተሞችም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ከጽኑ ቊጣው የተነሣ ፈርሰው ነበር።
\s5
\v 27 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል "ምድር ሁሉ ትጠፋለች፣ ነገር ግን ፈጽሜ አላጠፋቸውም።
\v 28 ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፣ ከላይ ያለው ሰማይ ይጠጨልማል። ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከመፈጸምም አልመለስም።
\v 29 ከፈረሰኞችና ከቀስተኞች ጫጫታ የተነሣ እያንዳንዱ ከተማ ሁሉ ይሸሻሉ፤ ወደ ጫካም ይገባሉ። እያንዳንዱ ከተማ በቋጥኝ ላይም ይወጣሉ። ከተሞቹ ይተዋሉ፣ የሚኖርባቸው ሰው አይኖርምና።
\s5
\v 30 አንቺም ባድማ ሆንሽ፥ ምን ታደርጊአለሽ? ቀይ በለበስሽ ጊዜ፥ በወርቅ አንባርም አጌጥሽ፣ ዓይንሽንም ተኳልሽ፣ የሚመኙሽ ወንዶች ገፉሽ። ይልቊን፣ ነፍስሽን ይሹአታል።
\v 31 ስለዚህ የምጥ፣ የበኩር ልጅ እንደሚወለድበት ያለ የጭንቅ ድምጽ፣ የጽዮን ሴት ልጅን ድምጽ ሰምቻለሁ። ለመተንፈስ ትታገላለች። እጆቿንም ትዘረጋለች፣ ከገዳዮቹ የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና 'ወዮልኝ!' አለች።
\s5
\c 5
\p
\v 1 በኢየሩሳሌም መንገድ እየተመላለሳችሁ ሩጡ፤ በአደባባዮችዋም ፈልጉ። ከዚያም ተመልከቱ፣ ስለዚህም አስቡ፦ ፍትሕን የሚያደርገውን በታማኝነትም ለማድረግ የሚሞክረውንም ሰው ታገኙ እንደሆነ፣ ይቅር እላታለሁ።
\v 2 እነርሱም 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ቢሉ የሚምሉት በሐሰት ነው።
\v 3 እግዚአብሔር ሆይ፣ ዓይንህ ታማኝነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፣ ነገር ግን አላመማቸውም። ሙሉ ለሙሉ አሸንፈሃቸዋል፣ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ። ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱ ዘንድ እንቢ አሉ።
\s5
\v 4 ስለዚህ እኔም "እነዚህ ድሆች ብቻ የሆኑ ሕዝቦች ናቸው። የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ አላወቁምና እነዚህ ሰነፎች ናቸው፤
\v 5 ወደ ጠቃሚዎቹ ሕዝቦች እሄዳለሁ የእግዚአብሔርን መልእክት እናገራቸዋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና። ነገር ግን እነርሱ በሙሉ ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፣ ለእግዚአብሔር ያሰራቸውንም ሰንሰለቶች ቈርጠዋል።
\v 6 ስለዚህ ኃጢአታቸው በዝቶአልና፣ የክዳታቸውም ብዛት አይቆጠርምና አንበሳ ከዱር ወጥቶ ይሰብራቸዋል፣ የበረሀም ተኵላ ያጠፋቸዋል፣ ነብርም በከተሞቻቸው ላይ ይተጋል፣ ከዚያም የሚወጣ ሁሉ ይነጠቃል።
\s5
\v 7 እነዚህን ሰዎች ይቅር የምላቸው ለምንድነው? ልጆችሽ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑትም ምለዋል። ሞልቼ መገብኳቸው፣ እነርሱ ግን አመነዘሩ የምንዝርና ቤትን ምልክቶችንም ወሰዱ።
\v 8 በትኩሳት እንዳሉ ፈረሶች ሆኑ፤ ወዳጅነት ፈልገው ተንከላወሱ። እያንዳንዱ ሰው ወደባልንጀሮቻቸው ሚስቶች አሽካኩ።
\v 9 ስለዚህ ልቀጣ አይገባኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?
\s5
\v 10 ወደ ወይን ከፍታዋ ወጥታችሁ አፍርሱ። ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፏቸው። ወይኖቻቸውን ቊረጡ፣ እነዚህ ወይኖች ከእግዚአብሔር አልመጡምና።
\v 11 የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ ፈጽሞ ከድተውኛልና ይላል እግዚአብሔር።
\v 12 እነርሱም ከድተውኛል። 'እርሱ እውነተኛ አይደለም። ክፉ ነገርም አይመጣብንም፣ ሰይፍንና ራብንም አናይም' አሉ።
\v 13 ነብያትም የነፋስን ያህል ጥቅም የለሽ ሆነዋል የእግዚአብሔርንም ቃል ለእኛ የሚነግረን የለም። ዛቻቸው በራሳቸው ላይ ይምጣባቸው።
\s5
\v 14 ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል "በዚህ ቃል ተናግራችኋልና ተመልከት፣ በአፍህ ውስጥ ቃሌን አኖራለሁ። እንደ እሳት ይሆናል፣ ይህም ሕዝብ እንደ እንጨት ይሆናል! እሳቱም ይበላቸዋል።
\v 15 ተመልከቱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው! ቋንቋቸውንም የማታውቋቸው፣ የሚናገሩትንም የማታስተውሉት ሕዝብ ነው።
\s5
\v 16 የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው። ሁሉም ኃያላን ናቸው።
\v 17 መከሮቻችሁንና እንጀራችሁን ይበላሉ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም ይበሏቸዋል፤ በጎችንና ላሞቻችሁንም ይበላሉ፤ ወይናችሁንና በለሶቻችሁንም ይበላሉ። የምትታመኗቸውን የተመሸጉ ከተሞችን በሰይፍ ይደበድባሉ።
\s5
\v 18 ነገር ግን በዚያ ዘመን እንኳን ይላል እግዚአብሔር፣ ፈጽሜ ላጠፋችሁ አላስብም።
\v 19 እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እስራኤል እና ይሁዳ፣ 'አምላካችን እግዚአብሔር ይህን ነገር ሁሉ ስለምን አደረገብን?' ስትሉ፣ አንተ ኤርምያስ ያን ጊዜ፣ 'እግዚአብሔርን እንደተዋችሁ እና በምድራችሁም ሌሎችን አማልክት እንዳመለካችሁ፣ እንዲሁ ለእናንተ ባልሆነ አገር ለሌሎች ሰዎች በባርነት ትገዛላችሁ' ትላቸዋለህ።
\s5
\v 20 ይህን ለያዕቆብ ቤት አውሩ፣ በይሁዳም ይሰማ።
\v 21 ይህን ስሙ፣ እናንተ ሰነፎች! ጣዖታት ፈቃድ የላቸውምና፤ ዐይን አለባቸው፣ ነገር ግን ሊያዩ አይችሉም። ጆሮዎችም አሉባቸው፣ ነገር ግን አይሰሙም።
\v 22 እኔን አትፈሩኝምን? በፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ የአሸዋን ድንበር እንዳይተላለፈው በማይቋረጥ ትእዛዝ በባሕሩ ላይ አድርጌአለሁ። የባህሩ ነውጥ ቢጮኽም አያቋርጠውም።
\s5
\v 23 ነገር ግን ይህ ሕዝብ ግን ዐመፀኛ ልብ አለው። በዐመፅ ሸፍቶ ሄዷል።
\v 24 በልባቸውም፣ 'የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በትክክለኛው ጊዜ የሚሰጠውን፣ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ አላሉም።
\v 25 በደላችሁ እነዚህ እንዳይሆኑ አስቀርታለች። ኃጢአታችሁም መልካምን ነገር ወደ እናንተ እንዳይመጣ አስቆመ።
\s5
\v 26 በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል። አንድ ሰው ወፎችን ለመያዝ ሲያደባ እንደሚመለከቱ፣ ወጥመድን ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ።
\v 27 ዋሻ ወፎችን እንደሚሞላ፣ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች። እንዲሁም ተልቀዋል፣ ባለ ጠጎችም ሆነዋል።
\v 28 ወፍረዋል፣ በደህንነታቸውም ያብረቀርቃሉ። ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል። ለሰዎች፣ ወይም ለወላጅ አልባዎች ነገር አልተምዋገቱላቸውም። ለችግረኞች ፍትሕን ባያደርጉም እንኳን በልጽገዋል።
\v 29 ስለእነዚህ ነገሮች አልቀጣምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ ለራሴ አልበቀልምን?
\s5
\v 30 በምድር ላይ የምታስደንቅና የምታስደነግጥ ነገር ሆናለች፤
\v 31 ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፣ ካህናትም በገዛ ኃይላቸው ይገዛሉ። ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፣ ነገር ግን በፍጻሜው ምን ይፈጠራል?
\s5
\c 6
\p
\v 1 እናንተ የብንያም ሕዝቦች፣ ከኢየሩሳሌም በመሸሽ ደህንነትን አግኙ። በቴቁሔ መለከትን ንፉ። ታላቅ ጥፋት የሆነ ክፉ ነገር ከሰሜን እየመጣ ነውና በቤትሐካሬም ላይ ምልክትን አንሡ።
\v 2 የተዋበችውና ሰልካካዋን የጽዮንን ልጅ እደመስሳለሁ።
\v 3 እረኞችና መንጐቻቸው ወደ እርስዋ ይሄዳሉ፣ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፣ እያንዳንዱም እረኛ በገዛ እጁ መንጋውን ይጠብቃል።
\s5
\v 4 ነገሥታት "ለአማልክቶቻችሁ እንድትዋጉ ራሳችሁን አስገዙ። ተነሡ፣ በቀጥርም እናጥቃ። ቀኑ እየመሸ መሆኑ፣ የማታውም ጥላ እየረዘመ መሆኑ እጅግ መጥፎ ነው።
\v 5 ነገር ግን በሌሊትም እናጥቃ፣ አምባዎችዋንም እናፍርስ።
\s5
\v 6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ የከበባ አፈርን ደልድሉ፤ ይህች በግፍ የተሞላች ከተማ በመሆኗ ለማጥቃት ትክክለኛዋ ከተማ ነች።
\v 7 ጕድጓድ ውኃ ማፍለቊን እንደሚቀጥል፣ እንዲሁ ይህች ከተማ ክፋትን ማፍለቋን ትቀጥላለች። ዐመጽና ሥርዓተቢስነት በእርስዋ ዘንድ ይሰማል። መከራና መቅሠፍትም ሳይቋረጥ በፊቴ አለ።
\v 8 ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ከአንቺ እንዳልለይ፣ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፣ ተግሣጽን ተቀበዪ።"
\s5
\v 9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሰው ወይኑን እንደሚለቅም፣ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን በእርግጥ ይቃርሟቸዋል፤ በድጋሚ እጅህን ዘርግተህ ወይንን ከግንዱ እንደሚለቅም አድርግ።
\v 10 ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ፣ ለማንስ አስጠነቅቃለሁ? ተመልከቱ! ጆሮአቸው ያልተገረዘ ነው፤ በትኩረት ለመስማት አይችሉም! ተመልከቱ! የእግዚአብሔር ቃል ሊያቀናቸው መጥቶባቸዋል፣ ነገር ግን አይፈልጉትም።"
\s5
\v 11 ነገር ግን በእግዚአብሔር ቍጣ ተሞልቻለሁ። በውስጤ ይዤ ልታገሠው ደክሜአለሁ። እንዲህ አለኝ፣ "በጎዳና ሕፃናት ላይ፣ እንዲሁም በወጣቶችም ስብስብ ላይ አፍስሰው። እያንዳንዱ ባል ከሚስቱ ጋር እድሜ ጠገቡ ሽማግሌም ከጎበዙ ጋር ይወሰዳልና።
\v 12 ቤቶቻቸው እርሻዎቻቸውም ሚስቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሆናሉ። በምድር የሚገኙ ነዋሪዎችን አጠቃለሁና ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 13 ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ እያንዳንዳቸው በኃቅ ላልሆነ ትርፍ ስስታሞች ናቸው። ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ እያንዳንዳቸው በተንኰል ይመላለሳሉ።
\v 14 የሕዝቤንም ስብራት የሚፈውሱት ግን በጥቂቱ ነው፣ ሰላም ሳይኖር 'ሰላም ሰላም!' ይላሉ።
\v 15 ርኩስን ነገር ስለሠሩ አፍረዋልን? በጭራሽ አልፈሩም፣ ማንኛውንም እፍረት አላወቁም። ስለዚህ በምቀጣቸው ጊዜ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ። ይገለበጣሉ፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በመንገድ ማቋረጫ ላይ ቁሙና ተመልከቱ፣ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ። 'መልካሚቱ መንገድ ወዴት ናት?' በሉና በእርስዋ ላይ ሄዳችሁ ለነፍሳችሁ ዕረፍትን አግኙ። ሕዝቡ ግን፣ 'አንሄድባትም' አሉ።
\v 17 እኔም የመለከቱን ድምፅ እንዲያደምጡ ጠባቂ ጉበኞችን ሾምሁላችሁ። እነርሱ ግን፣ 'አናደምጥም' አሉ።
\v 18 አሕዛብ ሆይ፥ አድምጡ! ተመልከቱ፣ በእነርሱ ላይ የሚደርስባቸውን ትመሰክራላችሁ።
\v 19 ምድር ሆይ፣ ስሚ! ተመልከቺ፣ የአሳባቸው ፍሬ የሆነ ጥፋትን በዚህ ህዝብ ላይ ላመጣ ነው። ለቃሌ ወይም ለህጌ ምንም ትኩረት አልሰጡም፣ ነገር ግን ከዚያ ይልቅ አጣጣሉት።"
\s5
\v 20 ከሳባ የሚቀርበው ዕጣን ለእኔ ምን ማለት ነው? ወይስ ከሩቅም አገር የሆነው ጣፋጭ ሽታ ምንድነው? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፣ እንዲሁም መስዋዕቶቻችሁን አልቀበለውም።
\v 21 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ በዚህ ሕዝብ ፊት ዕንቅፋቶችን አደርጋለሁ። አባቶችና ልጆች በአንድነት ይሰናከሉባቸዋል። ነዋሪዎችና ጎረቤቶቻቸው ይጠፋሉ።
\v 22 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ሕዝብ ከሰሜን ምድር ይመጣል። ታላቅ ሕዝብም ከምድር ዳርቻ ይነሣል።
\s5
\v 23 ቀስትንና ጦርን ያነሣሉ። ጨካኞች ናቸው፣ ምሕረትንም የላቸውም። ድምፃቸው እንደ ባሕር ጩኸት ነው፣ በጽዮን ሴት ልጅ ላይ እንደሚዋጉ በፈረሶችም ላይ ይጋልባሉ።"
\v 24 ስለ እነርሱ ወሬውን ሰምተናል። እጃችን በጭንቀት ዝላለች። ምጥ ወላድን ሴት እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል።
\s5
\v 25 የጠላት ሰይፍና ሽብር ስለከበባችሁ ወደ ሜዳ አትውጡ፣ በመንገድም ላይ አትሂዱ።
\v 26 የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣ ማቅ ልበሺና ለብቸኛ ልጅ መቀበሪያ አፈር ውስጥ ተንከባለዪ። አጥፊው በድንገት ይመጣብናልና ለራስሽ መራራ የሆነ የቀብር ለቅሶን አድርጊ።
\s5
\v 27 "ኤርምያስ፣ መንገዳቸውን እንድትመረምርና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን አድርጌሃለሁ።
\v 28 እነርሱ ሁሉ ሌሎችን የሚወነጅሉ እጅግ ዐመፀኞች ናቸው። በብልሹነት የሚመላለሱ ናስና ብረት ናቸው።
\v 29 ወናፍ በሚያቃጥላቸው እሳት አናፋ፣ እርሳሱም በእሳቱ ቀለጠ። ክፋት ስላልተወገደ፣ የማጥራቱ ሥራ በመካከላቸው ይቀጥላል።
\v 30 እግዚአብሔር ጥሎአቸዋልና የተጣለ ብር ብለው ይጠሯቸዋል።"
\s5
\c 7
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፣
\v 2 በእግዚአብሔር ቤት በራፍ ላይ ቁም! እንዲህ በል፣ 'ይሁዳ ሁሉ ሆይ፣ እግዚአብሔርን ልታመልኩ በእነዚህ በራፎች የምትገቡ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\s5
\v 3 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መንገዳችሁንና ሥራችሁን መልካም አድርጉ፣በዚህም ስፍራ መኖር እንድትቀጥሉ አደርጋችኋለሁ።
\v 4 ራሳችሁን አታላይ በሆኑ ቃሎች ላይ ታምናችሁ፣ "የእግዚአብሔር መቅደስ! የእግዚአብሔር መቅደስ! የእግዚአብሔር መቅደስ!" አትበሉ።
\s5
\v 5 መንገዳችሁንና ሥራችሁን ፈጽማችሁ መልካም ብታደርጉ፤ በሰውና በጎረቤቱ መካከል ቅን ፍርድ ብትፈርዱ፤
\v 6 በምድሪቱ የሚቆየውን እንግዳ፣ ወላጅ አልባውን፣ ወይም መበለቲቱንም ባትበዘብዙ፣ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደምን ባታፈስሱ፣ ለገዛ ጉዳታችሁ እንዲሆንባችሁ ሌሎች አማልክትን ባትከተሉ፤
\v 7 ያን ጊዜ ከጥንቱ ጊዜ ጀምሮ እስከ ለዘላለም ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር በዚህ ስፍራ አሳድራችኋለሁ።
\s5
\v 8 እነሆ! በማይረዳችሁ የሐሰት ቃል እየታመናችሁ ናችሁ።
\v 9 ትሰርቃላችሁ፣ ትገድላላችሁ፣ ታመነዝራላችሁ? ደግሞም በሐሰትም ትምላላችሁ፣ ለበኣልም ታጥናላችሁ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ትከተላላችሁ?
\v 10 ከዚያም መጥታችሁ ስሜም በተጠራበት በዚህ ቤት በፊቴ ቆማችሁ፣ እነዚህን ሁሉ ጥፋቶች ማድረግ እንድትችሉ "ድነናል፣" አላችሁ።
\v 11 ይህስ ስሜ የተጠራበት ቤት በዓይናችሁ ፊት የሌቦች ዋሻ ሆኖአልን? ነገር ግን፣ እነሆ፣ እኔ አይቻለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 12 'ስለዚህ በቀድሞ ዘመን ስሜን ከመጀመሪያ ወዳሳደርሁበት በሴሎ ወደ ነበረው ስፍራዬ ሂዱ፣ ከሕዝቤም ከእስራኤል ክፋት የተነሣ ያደረግሁበትን እዩ።
\v 13 ስለዚህ አሁንም፣ ይህን ሥራችሁን ሁሉ ስላደረጋችሁ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ ተናገርኳችሁ፣ እናንተ ግን አልሰማችሁም። በጠራኋችሁም ጊዜ፣ አልመለሳችሁም።
\v 14 ስለዚህ፣ በሴሎ እንዳደረግሁ፣ እንዲሁ ስሜ በተጠራበት በምትታመኑበት ቤት፣ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠኋችሁ ስፍራ ላይ እንዲሁ አደርጋለሁ።
\v 15 የኤፍሬምንም ዘር የሆኑትን ወንድሞቻችሁን ሁሉ እንደ ጣልሁ፣ እንዲሁ ከፊቴ እጥላችኋለሁ።
\s5
\v 16 ደግሞም አንተ፣ ኤርምያስ አልሰማህምና ለዚህ ሕዝብ አትጸልይ፣ ስለ እነርሱም ልመናና ጸሎት አታድርግ፣ አትማልድላቸው።
\v 17 እነርሱ በይሁዳ ከተሞች ውስጥና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የሚያደርጉትን አታይምን?
\v 18 ያስቈጡኝ ዘንድ፣ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቍርባን እንዲያፈስሱ፣ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፣ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፣ ሴቶችም ዱቄት ያቦካሉ።
\s5
\v 19 በእውነት እኔን ያስቈጣሉን? ይላል እግዚአብሔር፤ ለእነርሱስ እፍረት እንዲሆንባቸው የሚያስቆጡት ራሳቸውን አይደለምን?
\v 20 እንግዲያው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ ይፈስሳል፣ በሰውና በአውሬው ላይ፣ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል። ይነድዳል፣ መቼም አይጠፋም።'
\s5
\v 21 የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ለመሥዋዕታችሁ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን ጨምሩ፣ ከዚያም ላይ ሥጋውን ጨምሩ።
\v 22 አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ባወጣኋቸው ቀን፣ የትኛውንም ነገር ከእነርሱ አልጠየቅሁም። ስለሚቃጠል መሥዋዕትና ስለ ሌላ መሥዋዕት አላዘዝኋቸውምም።
\v 23 ይህንን ትእዛዝ ብቻ ሰጠኋቸው፣ "ቃሌን ስሙ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ ባዘዝኋችሁ መንገድ ሁሉ ሂዱ።"
\s5
\v 24 ነገር ግን በክፉ ልባቸው አሳብና እልከኝነት ሄዱ ወደ ፊትም ሳይሆን ወደ ፊታቸው ሳይሆን ወደ ኋላቸው ሄዱ እንጂ አልሰሙም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
\v 25 አባቶቻችሁ ከግብጽ ምድር ከወጡበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አገልጋዮቼን፣ ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። እነርሱን ተግቼ ላክሁባችሁ።
\v 26 ነገር ግን አልሰሙኝም። ምንም ትኩረት አልሰጡም። ይልቊን፣ አባቶቻቸውም ካደረጉት ይልቅ የባሰ አደረጉ።
\s5
\v 27 እነዚህን ቃሎች ሁሉ ንገራቸው፣ ነገር ግን አይሰሙህም። እነዚህን ነገሮች አውጅላቸው፣ ነገር ግን አይመልሱልህም።
\v 28 የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቃል ያልሰማ፣ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው። እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ተቈርጦአል በላቸው።
\s5
\v 29 ፀጕርሽን ቍረጪ፣ ተላጪው፣ ጣዪውም። በወናዎች ኮረብቶችም ላይ ሙሾን አውጪ። እግዚአብሔር በቍጣው ይህንን ትውልድ ጥሎአልና፣ ትቶታልምና ።
\v 30 የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉን ነገር ሠርተዋል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል።
\s5
\v 31 ከዚያም ቶፌት ውስጥ በቤን ሄኖም ሸለቆ መስገጃዎችን ገነቡ። እኔም ያላዘዝሁትንና ፈጽሞ በልቤ ያላሰብሁትን ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ ይህንን አድርገዋል።
\v 32 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ቶፌት ወይም የቤን ሄኖም ሸለቆ ተብሎ ዳግመኛ አይጠራም። የእርድ ሸለቆ ይባላል፤ የሚተርፍ ስፍራ እስኪታጣ ድረስ በቶፌት በድኖችን ይቀብራሉ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 33 የዚህም ሕዝብ ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል፣ የሚያስፈራራቸውም አይኖርም።
\v 34 ምድሪቱም ወና ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ አጠፋለሁ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 በዚያን ዘመን፥ የይሁዳን ነገሥታት አጥንትና የመኳንንቶቹን አጥንት፥ የካህናቱን አጥንትና የነቢያቱን አጥንት፥ የኢየሩሳሌምንም ሰዎች አጥንት ከመቃብራቸው ያወጣሉ ይላል እግዚአብሔር።
\v 2 በተከተሉአቸው፣ ባገለገሏቸውና በፈለጉአቸው፣ ባመለኳቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል። አጥንቶቻቸው አይሰባሰቡም ወይም በድጋሚ አይቀበሩም። በምድር ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
\v 3 እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩት፣ ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ቅሬታዎች ሁሉ፣ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ ይላል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር።
\s5
\v 4 እንዲህም ትላቸዋለህ፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የትኛውም የወደቀ ሰው አይነሣምን? የጠፋስ ለመመለስ አይሞክርምን?
\v 5 ይህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ ዘላቂ በሆነ አለመታመን ስለ ምን ወደ ኋላው ይመለሳል? ተንኰልን ይዞአል ንስሃ ለመግባትም እንቢ ብሎአል።
\s5
\v 6 አደመጥሁ ሰማሁም፣ ትክክለኛ ነገር አልተናገሩም፤ ማንም ስለ ክፋቱ ንስሃ አልገባም፣ ማንም "ምን አድርጌአለሁ?" አላለም። ወደ ጦርነት እንደሚሮጥ ፈረስ ሁላቸውም በየመንገዳቸው ሄዱ።
\v 7 ሽመላ በሰማይ ትክክለኛ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም ያውቃሉ። እነርሱ ወደ ሚሰደዱበት የሚሄዱት በትክክለኛ ጊዜ ነው፣ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም።
\s5
\v 8 እናንተስ፣ "ጥበበኞች ነን! የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው" እንዴት ትላላችሁ? በእርግጥ ተመልከቱ! የአታላይ ጸሐፊ ብዕር ማታለልን አድርጎአል።
\v 9 ጥበበኞች ያፍራሉ። ደንግጠውማል ተጠምደዋል። ተመልከቱ! የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፣ ስለዚህ ጥበባቸው ምን ጥቅም አለው?
\v 10 ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስታሞች ናቸውና፣ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ ያታልላሉና፣ ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
\s5
\v 11 ቀላል ነገር እንደሆነ በማድረግ የሕዝቤን ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ። ሰላም ሳይሆን፣ "ሰላም፣ ሰላም" ይላሉ።
\v 12 አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም። ትሕትናም አልነበራቸውም። ስለዚህ በሚቀጡ ጊዜ ቀድሞውኑ ከወደቊት ጋር ይወድቃሉ ይላል እግዚአብሔር።
\v 13 ፈጽሜ አጠፋችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በወይን ላይ ፍሬ፣ በበለስ ዛፍ ላይ በለስ አይሆንም። ቅጠልም ይረግፋልና የሰጠኋቸውም ያልፋልና።
\s5
\v 14 ለምን ዝም ብለን እንቀመጣለን? በአንድነት ኑ፤ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንሂድ፣ በዚያም በሞት ዝምተኞች እንሆናለን። እግዚአብሔር ዝም ያሰኘናልና። ስለ በደልነው መርዝ አጠጥቶናል።
\v 15 ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ነገር ግን መልካም ነገር አልተገኘም። የፈውስ ጊዜን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ነገር ግን ሽብር እንደሆነ ተመልከቱ።
\s5
\v 16 የፈረሰኞች ድምጽ ከዳን ተሰማ። ከአርበኞች ፈረሶች ማሽካካት የተነሣ ምድር ሁሉ ተንቀጠቀጠች። ምድሪቱንና በእርስዋም ያለውን ሁሉ፥ ከተማይቱንና የሚኖሩባትንም ሊበሉ ይመጣሉና።
\v 17 ተመልከቱ፣ አስማት የማይከለክላቸውን እባቦችንና እፉኝቶችን እሰድድባችኋለሁ። እነርሱም ይነድፉአችኋል" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 18 ኅዘኔ ፍጻሜ የለውም፣ ልቤም ታምሞአል።
\v 19 ተመልከቱ! እግዚአብሔር በጽዮን የለምን? ወይስ ንጉሥዋ በእርስዋ ዘንድ የለምን? የሚል የሕዝቤ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ምድር ተሰማ። በተቀረጹ ምስሎቻቸውና በባዕድ ከንቱ ጣዖታት ያስቈጡኝ ስለ ምንድር ነው?
\s5
\v 20 መከሩ አልፎአል፣ በጋው አብቅቷል። እኛ ግን አልዳንነም።
\v 21 በሕዝቤ ሴት ልጅ ስብራት እኔ ተሰብሬአለሁ። በደረሰባት ነገር በጭንቀት አለቅሳለሁ፤ ጠቁሬማለሁ።
\v 22 በገለዓድ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ፈዋሽ የለምን? የሕዝቤ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?
\s5
\c 9
\p
\v 1 ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፣ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!
\v 2 ሁሉም አመንዝሮች፣ የከዳተኞች ጉባኤ በመሆናቸው ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ!
\v 3 "አታላይ ቀስታቸው በሆነው በምላሳቸው ሐሰት ተናገሩ፣ ነገር ግን በምድር ላይ በታማኝነት ግሩም አይደሉም። ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉ። እኔንም አላወቁምና፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 4 እያንዳንዱ ወንድም ሁሉ ያታልላልና፣ እያንዳንዱ ጎረቤትም ሁሉ ሐሜተኛ ስለሆነ እናንተ ሁሉ ከጎረቤቶቻችሁ ተጠንቀቁ፣ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።
\v 5 እያንዳንዱ ሰውም ሁሉ ጎረቤቱን ያታልላል በእውነትም አይናገርም። ምላሶቻቸው የማታለል ነገሮችን ያስተምራል። በደልንም በማድረግ ይደክማሉ።
\v 6 በማታለል መካከል ትኖራላችሁ፣ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 7 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ እፈትናቸዋለሁ። እመረምራቸዋለሁ። ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው?
\v 8 ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ያልታመኑ ነገሮችን ይናገራሉ። ከጎረቤቶቻቸው ጋር በአንደበታቸው በሰላም ይናገራሉ፣ በልባቸው ግን ያደቡበታል።
\v 9 በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀጣቸውምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህስ ባለ ሕዝብ ላይ አልበቀልምን?
\s5
\v 10 ለተራሮች የልቅሶና የዋይታን ዝማሬ እዘምራለሁ፣ ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም የቀብር ዋይታን እዘምራለሁ። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የየትኛውንም ከብት ድምፅ አይሰሙም። የሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሁሉ ሸሽተው ሄደዋል።
\v 11 ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባት ወና አደርጋቸዋለሁ።
\v 12 ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ለሌሎች እንዲነግር የእግዚአብሔር አፍ ምን ተናገረው? ምድሪቱስ ስለምን ጠፋች? ማንም እንደማያልፍባት እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተደመሰሰች?
\s5
\v 13 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ "በፊታቸው የሰጠኋቸውን ሕጌን ስለተዉ፣ ድምጼንም አልሰሙምና ወይም አልተጓዙበትምና።
\v 14 አባቶቻቸው እንዳስተማሯቸው በልባቸውን ምኞት ተመላልሰዋልና፣ በኣሊምን ተከትለዋልና።
\s5
\v 15 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣዋለሁ።
\v 16 እነርሱና አባቶቻቸውም ባላወቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፣ እስካጠፋቸውም ድረስ በበስተኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።"
\s5
\v 17 የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህንን አስቡ፦ የቀብር አስለቃሾችን ጥሩ፤ ይምጡ። ወደ ብልሃተኛ አልቃሾች ላኩ።
\v 18 ይፍጠኑና ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ የለቅሶ ዝማሬን ይዘምሩልን።
\s5
\v 19 'እንዴት ተበዘበዝን። ቤቶቻችን ስለፈረሱ ምድሪቱንም ትተናልና እንዴት አፈርን!' የሚል የልቅሶ ድምፅ በጽዮን ተሰምቶአል።
\v 20 ስለዚህ እናንተ ሴቶች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ ከአፉ ለሚወጣው ቃል ትኩረት ስጡ። ከዚያም ለሴቶች ልጆቻችሁም የልቅሶውን ዝማሬ አስተምሩ፣ ለእያንዳንዷም የጎረቤታችሁ ሴት የቀብሩን ሙሾ አስተምሩ።
\s5
\v 21 ሞት ወደ መስኮታችን መጥቷልና፤ ወደ ቤተ መንግሥቶቻችን ሄዷል። ሕፃናቱን ከውጪ፣ ወጣቶቹንም ከከተማይቱ አደባባይ ያጠፋል።
\v 22 'የሰውም ሬሳ በሜዳ ላይ እንደ ጕድፍ፣ ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል፣ ማንምም አይሰበስበውም።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ጠቢብ በጥበቡ እንዲመካ አትፍቀዱ፣ ወይም ጦረኛ በኃይሉ አይመካ። ባለ ጠጋም በብልጥግናው እንዲመካ አትፍቀዱ።
\v 24 ሰው በየትኛውም ነገር የሚመካ ከሆነ፣ በዚህ ይሁን፣ ማስተዋል ያለውና የሚያውቀኝ በመሆኑ። የኪዳን ታማኝነት፣ ፍትሕንና ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 25 ተመልከቱ፣ በሰውነታቸው ብቻ የተገረዙትን እቀጣለሁ።
\v 26 ግብጽንና ይሁዳን፣ የአሞን ሕዝቦች የሆኑትን ኤዶምያስና ሞዓብንም፣ እንዲሁም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ፀጉራቸውን የተላጩትን ሁሉ፣ ባለመገረዛቸው ምክንያት የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል። እነዚህ ሁሉ ሕዝቦች ያልተገረዙ ናቸውና፣ ደግሞም የእስራኤል ልብ አልተገረዘምና" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 10
\p
\v 1 እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ የተናገረውን ቃል ስሙ።
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የአሕዛብን መንገድ አትማሩ፣ ከሰማይ በሚሆኑት ምልክቶችም አትፍሩ፣ አሕዛብ እነዚህን ይፈራሉና።
\s5
\v 3 የአሕዛብ ልማድ ከንቱ ነውና። አንድ ሰው ዛፍን ከጫካ ይቈርጣል፤ የሠራተኛም እጅ በመጥረቢያ ይህንን ይሠራል።
\v 4 ከዚያም በብርና በወርቅ ያስጌጡታል። እንዳይወድቅም በመዶሻና በሚስማር ይቸነክሩታል።
\v 5 እነዚህ ጣዖታት ምንም ማለት ስለማይችሉ፣ በዱባ ማሳ ላይ እንደ ተቀረጸ ዓምድ ናቸው። ጨርሶ መራመድ ስለማይችሉ ሊይሸከሟቸው ይገባል። ክፉ መሥራት አይቻላቸውምና፣ ደግምም የትኛውንም መልካም ነገር ይሠሩ ዘንድ አይችሉምና አትፍሩአቸው።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ሆይ እንደ አንተ ያለ የለም። አንተ ታላቅ ነህ፣ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው።
\v 7 የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ፣ የማይፈራህ ማነው? በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል ወይም በታማኝ መንግሥታቸውም ሁሉ መካከል እንደ አንተ ያለ ስለሌለ፣ አንተ ይህ ይገባሃል።
\s5
\v 8 እነርሱ ሁሉም ተመሳሳይ ናቸው፣ ደንዝዘዋል፣ ደንቍረውማል፤ እንጨት ብቻ እንጂ ምንም ላልሆኑ ጣዖቶቻቸው ደቀመዛሙርት ናቸው።
\v 9 ከጠርሴስ አንጥረኛ የቀጠቀጠውን ብር፣ ከአፌዝም ወርቅ ያመጣሉ። ልብሳቸውም ሰማያዊና ቀይ ግምጃ ነው። ብልሃተኞች ሰዎቻቸው እነዚህን ሁሉ ነገሮች ይሠራሉ።
\v 10 እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው። እርሱም ሕያው አምላክና የዘላለም ንጉሥ ነው። ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፣ አሕዛብም ቊጣውን መቋቋም አይችሉም።
\s5
\v 11 እናንተም "ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ ከሰማይም በታች ይጠፋሉ" ትሏቸዋላችሁ።
\v 12 ምድርን በኃይሉ የፈጠረው፣ ደረቊን ምድር በጥበቡ የመሠረተው ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።
\v 13 ድምፁ በሰማይ የውኾችን ድምፅ ይፈጥራል፣ ከምድርም ጠርዝ ደመናትን ከፍ ያደርጋል። ለዝናቡም መብረቅን ያደርጋል፣ ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ያወጣል።
\s5
\v 14 እያንዳንዱ ሰው እውቀት አጥቶ አላዋቂ ሆኗል። እያንዳንዱ አንጥረኛ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፣ ሕይወትም የለባቸውምና በቀረጸው ጣዖት አፍሮአል።
\v 15 እነርሱ ጥቅም የለሽ፣ የቀልደኞች ሥራ ናቸው፤ በሚቀጡበት ጊዜ ይጠፋሉ።
\v 16 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፣ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነውና፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስሙ ነው።
\s5
\v 17 በከበባ ውስጥ የምትኖሩ እናንተ ሕዝቦች፣ ዕቃችሁን ሰብስቡና ምድሪቱን ትታችሁ ውጡ።
\v 18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ተመልከቱ፣ በዚህ ጊዜ በምድሪቱ የሚኖሩትን ልወረውራቸው ነው። አስጨንቃቸዋለሁ፣ እንደዚያም ሆኖ ያገኙታል።
\s5
\v 19 ስለ ተሰበረው አጥንቴ ወዮልኝ! ቍስሌም መርቅዟል። ስለዚህ እኔ፣ "በእውነት ይህ የመከራ ጩኸቴ ነው ልሸከመውም ይገባኛል" አልሁ።
\v 20 ድንኳኔ ተበዘበዘ፣ አውታሬም ሁሉ ለሁለት ተቈረጠ። ልጆቼም ከእኔ ወሰዷቸው፣ ስለዚህ ከእንግዲህ የሉም። ድንኳኔንም ከእንግዲህ ወዲህ የሚዘረጋ መጋረጃዎችንም የሚያነሣ የለም።
\s5
\v 21 እረኞች ደንቆሮዎች ሆነዋል። እግዚአብሔርን አልፈለጉትምና። ስኬት አልሆነላቸውም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።
\v 22 የወሬን ድምፅ ስሙ፣ "ተመልከቱ! እየመጣ ነው! የይሁዳን ከተሞች ባድማና የቀበሮ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ጽኑ የምድር ነውጥ መጥቶአል።"
\s5
\v 23 እግዚአብሔር ሆይ፣ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳይመጣ አውቃለሁ። የሚራመድ የትኛውም ሰው የገዛ አካሄዱን አያቀናም።
\v 24 እግዚአብሔር ሆይ እንዳታጠፋኝ በቊጣህ ሳይሆን በፍትህ ቅጣኝ።
\v 25 በማያውቁህ አሕዛብ፣ ስምህንም በማይጠሩ ወገኖች ላይ መዓትህን አፍስስ። ያዕቆብን በልተውታልና፣ ፈጽመው ሊያጠፉት ውጠውታልና ማደሪያውንም አፍርሰዋልና።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ።
\v 2 የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስማ፣ ለእያንዳንዳቸው የይሁዳ ሰዎች፣ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩትም ተናገር፥
\s5
\v 3 እንደዚህም በላቸው 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል የማይሰማ ሰው ርጉም ይሁን።
\v 4 ከግብጽ አገር ከሚቀልጠው የብረት ምድጃ ባወጣኋቸው ቀን ለአባቶቻችሁ ያዘዝሁበት ኪዳን ይህ ነው። "ድምፄን ስሙ፣ ያዘዝኋችሁንም ነገሮች ሁሉ አድርጉ፣ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁና።"
\v 5 ይህም ዛሬ የምትኖሩባትን ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ የማልሁትን መሐላ አጸና ዘንድ ነው።" ከዚያ እኔ ኤርምያስ "አዎን፣ እግዚአብሔር ሆይ!' ብዬ መለስሁለት።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ "ይህችን ቃል ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ተናገር። እንዲህ በል፣ 'የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ ፈጽሙትም።
\v 7 አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ "ቃሌን ስሙ" በማለት በጽናት አስጠንቅቄአቸው ነበር።
\v 8 እነርሱ ግን አልሰሙም ወይም ትኩረት አልሰጡም። እያንዳንዱ ሰው በክፉ ልባቸው እልከኝነት ሄዱ። ስለዚህ እንዲመጡባቸው ያዘዝኋቸውን እርግማን ሁሉ አመጣሁ። ሕዝበ ግን እንደዚያም ሆኖ አልታዘዙም።"
\s5
\v 9 ቀጥሎ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፣ "በይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ዘንድ አድማ ተገኝቶአል።
\v 10 ቃሌንም ይሰሙ ዘንድ እንቢ ወዳሉ፣ ይልቊንም ያመልኩአቸው ዘንድ እንግዶችን አማልክት ወደተከተሉ ወደ አባቶቻቸው ኃጢአት ተመለሱ። የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት ከአባቶቻቸው ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን አፈረሱ።
\s5
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ሊያመልጡት የማይችሉትን ጥፋት አመጣባቸዋለሁ። ከዚያም ወደ እኔ ይጮኻሉ፣ እኔ ግን አልሰማቸውም።
\v 12 የይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ሄደው ወደሚሰዉላቸው አማልክት ይጮኻሉ፤ ነገር ግን በጥፋታቸው ጊዜ ከቶ አያድኑአቸውም።
\v 13 ይሁዳ፣ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ጨምረዋል። በኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ልክ አሳፋሪ መሠዊያ፣ ለበዓለም የማጠኛ መሠዊያ አድርጋችኋል።
\s5
\v 14 ስለዚህ አንተ ራስህ፣ ኤርምያስ፣ ለዚህ ሕዝብ ልትጸልይ አይገባም። ስለእነርሱ አታልቅስ ወይም አትጸልይ። በጥፋታቸው ጊዜ ወደ እኔ ሲጮኹ አልሰማቸውምና።
\v 15 እጅግ ብዙ ክፉ ፍላጎት የነበረው ተወዳጁ ሕዝቤ በቤቴ ውስጥ ያለው ለምንድነው? ለመስዋዕታችሁ የተጠበቀው ሥጋ ክፋትን አድርጋችኋልና ሊረዳችሁ አይችልም፣ ከዚያም በዚያ ደስተኛ አትሆኑም።
\v 16 በጥንቱ ጊዜ እግዚአብሔር በተወዳጅ ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራሽ። ሆኖም ግን እንደ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፣ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል።
\s5
\v 17 ለበኣልም በማጠናቸው ያስቈጡኝ ዘንድ ለራሳቸው ስለ ሠሩአት ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ ቤት ክፋት የተከለሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ክፉን ነገር ተናግሮብሻል።
\s5
\v 18 እግዚአብሔርም እነዚህን ነገሮች አውቃቸው ዘንድ አስታወቀኝ፤ አንተ እግዚአብሔር ሥራቸውን እንዳይ አደረግኸኝ።
\v 19 እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ የበግ ጠቦት ሆንሁ። እነርሱም፣ "ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ! ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው" ብለው ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
\v 20 ይሁን እንጂ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር አእምሮንና ልብን ይመረምራል፣ በቅንም ይፈርዳል። ጉዳዬን አቅርቤልሃለሁና በእነርሱ ላይ በቀልህን እመሰክራለሁ።
\s5
\v 21 ስለዚህም 'በእጃችን እንዳትሞት በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር' ብለው ነፍስህን ስለሚሹ ስለ ዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\v 22 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህንን ይላል፣ 'ተመልከት፣ እቀጣቸዋለሁ። ኃያላን ወጣቶቻቸው በሰይፍ ይሞታሉ። ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በረሃብ ይሞታሉ።
\v 23 በምቀጣቸውም ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁና ማንም ከእነርሱ የሚቀር የለም።
\s5
\c 12
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከአንተ ጋር በተሟገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ። የማጉረመርምበትን ምክንያት በእርግጥ ልነግርህ ይገባኛል። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይሳካል? እምነት-የለሽ የሆኑት ሁሉ ተሳክቶላቸዋል።
\v 2 አንተ ተክለሃቸዋል፣ እነርሱም ሥር ሰድደዋል። ፍሬ ማፍራታቸውን ቀጥለዋል። በአፋቸው አንተ ቅርብ ነህ፣ ከልባቸው ግን ሩቅ ነህ።
\s5
\v 3 ይሁን እንጂ አንተ እግዚአብሔር ታውቀኛለህ። አይተኸኛል፣ ልቤንም ፈትነሃል። እንደ ሚታረዱ በጎች ለያቸው። ለመታረድም ቀን ነጥላቸው።
\v 4 ምድሪቱ የምታለቅሰው፣ የአገሩ ሣርስ ሁሉ ከነዋሪዎቹ ክፋት የተነሣ የሚደርቀው እስከ መቼ ነው? አራዊት እና ወፎች ተወስደዋል። በእርግጥም ሕዝቡ "በእኛ ላይ የሚሆነውን እግዚአብሔር አያውቅም፤" ብለዋል።
\s5
\v 5 "አንተ ኤርምያስ ከእግረኛ ወታደሮች ጋር በሮጥህ ጊዜ እነርሱ ቢያደክሙህ፣ ከፈረሶች ጋር መወዳደር እንዴት ትችላለህ? በአስተማማኝ የገጠር ምድር ውስጥ ብትሰናከል፣ በዮርዳኖስ ጥሻዎች ውስጥ እንዴት ትሆናለህ?
\v 6 ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አሳልፈው ሰጥተውሃልና፣ ጮኸው ክደውሃልና። መልካም ነገሮችንም ቢናገሩህ አትታመናቸው።
\s5
\v 7 ቤቴን ትቼአለሁ፣ ርስቴንም ጥያለሁ። ተወዳጁን የገዛ ሕዝቤን በጠላቶቹ እጅ አሳልፌ ሰጥቻለሁ።
\v 8 ርስቴ በጥሻ እንዳለ አንበሳ ሆናብኛለች፤ ድምፅዋን አንሥታብኛለችና ስለዚህ ጠልቻታለሁ።
\v 9 ርስቴ እንደ ጅብ ሆነችብኝ፣ ዝንጕርጕር አሞሮችም ለማጥመድ በላይዋ ይዞራሉ። ሂዱ፣ የምድር አራዊትን ሁሉ ከሜዳ ሰብስቡና ይበሉም ዘንድ አምጡአቸው።
\s5
\v 10 ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን ደምስሰዋል። እድል ፈንታዬ የሆነውን ምድር ሁሉ ረግጠዋል፤ የምደሰትበትን እድል ፈንታ ወና ምድረ በዳ አድርገውታል።
\v 11 ባድማ አድርገውታል። ፈርሳለችና አለቅስላታለሁ። ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም።
\s5
\v 12 በወና ኮረብቶች ሁሉ ላይ አጥፊዎች መጥተዋል፣ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከአንደኛው የምድር ዳር ጀምሮ እስከ ሌላኛው የምድር ዳር ድረስ ይበላልና። በሕይወት ላለ ሥጋ ለባሽ ሁሉ ደህንነት የለም።
\v 13 ስንዴን የዘሩ ቢሆንም እሾህን አጨዱ። በሥራቸው ደከሙ፣ ምንም አላገኙም። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባገኛችሁት ፍሬ ታፍራላችሁ።
\s5
\v 14 ሕዝቤ እስራኤል እንዲወርስ ያደረግሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ከገዛ ምድራቸው የምነቅላቸው እኔ ነኝ፣ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ።
\v 15 ከነቀልኋቸውም በኋላ መልሼ እራራላቸዋለሁ፣ እያንዳንዱንም ወደ ርስቱ እያንዳንዱንም ወደ ምድሩ እመልሳለሁ።
\s5
\v 16 በበኣል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩት ሁሉ እነዚያው ሕዝቦች 'ሕያው እግዚአብሔርን!' ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ በጥንቃቄ ቢማሩ፣ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ።
\v 17 ነገር ግን ማናቸውም ባይሰሙኝ ያንን ሕዝብ ፈጽሜ እነቅለዋለሁ። በእርግጥም ይነቀላል፣ ይጠፋማል" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\c 13
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "ሂድ፣ ከተልባ እግር የተሠራ የውስጥ ሱሪ ግዛና ወገብህን ታጠቅ፤ ነገር ግን አስቀድመህ በውኃ ውስጥ አትንከረው።
\v 2 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳለው የውስጥ ሱሪን ገዛሁና ወገቤን ታጠቅሁበት።
\v 3 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ እኔ መጣና እንዲህ አለኝ፣
\v 4 በወገብህ ያለውን የገዛሃውን መታጠቂያ ወስደህ ተነሥና ወደ ኤፍራጥስ ሂድ። በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽገው" አለኝ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁና በኤፍራጥስ ሸሸግሁት።
\v 6 ከብዙ ቀንም በኋላ፣ እግዚአብሔር፣ "ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ። በዚያም እንድትሸሽገው ያዘዝሁህን የውስጥ ሱሪ ከዚያ ውሰድ" አለኝ።
\v 7 እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄድሁ ቆፈርሁም፣ ከሸሸግሁበትም ስፍራ የውስጥ ሱሪውን ወሰድሁ። ነገር ግን እነሆ! የውስጥ ሱሪው ተበላሽቶ ነበር፣ ለምንም የማይጠቅም ሆኖ ነበር።
\s5
\v 8 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ በድጋሚ መጣና እንዲህ አለኝ፣
\v 9 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ታላቅ እብሪት አጠፋለሁ።
\v 10 ቃሌን ይሰሙ ዘንድ እንቢ የሚሉ፣ በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ፣ ያመልኩአቸውና ይሰግዱላቸው ዘንድ ሌሎችን አማልክት የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝብ አንዳች እንዳማይረባ እንደሆነው እንደዚ የውስጥ ሱሪ ይሆናሉ።
\v 11 የውስጥ ሱሪው በሰው ወገብ ላይ እንደሚጣበቅ፣ እንዲሁ ሕዝብና ስም ምስጋናና ክብር ይሆኑልኝ ዘንድ የእስራኤልን ቤት ሁሉ የይሁዳንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን አልሰሙኝም።
\s5
\v 12 ስለዚህ ይህንን ቃል ለእነርሱ ልትናገር ይገባል፣ 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ ይሞላል።' እነርሱም 'ማድጋ ሁሉ የወይን ጠጅ እንዲሞላ በውኑ እኛ አናውቅምን?' ይሉሃል።
\v 13 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፣ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት፣ ካህናቱን፣ ነቢያቱንና በኢየሩሳሌምም የተቀመጡትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ።'
\v 14 ሰውንም በሰው ላይ፣ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፣ እቀጠቅጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራም፣ አላዝንላቸውም፣ አልምርም።"
\s5
\v 15 ስሙ፣ አድምጡም። እግዚአብሔር ተናግሮአልና እብሪተኞች አትሁኑ።
\v 16 ሳትጨልም እግራችሁም በጨለመችው ተራራ ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨለማ ሳይለውጠው ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ።
\v 17 ይህን ባትሰሙ፣ ስለ ትዕቢታችሁ ብቻዬን አለቅሳለሁ። የእግዚአብሔርም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ ታነባለች፣ እንባንም ታፈስሳለች።
\s5
\v 18 ለንጉሡና ንግሥቲት ለሆነችው እናት፣ 'የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ' በል።
\v 19 የደቡብ ከተሞች ተዘግተዋል፣ የሚከፍታቸውም የለም። ይሁዳ ሁሉ ተማርኮአል፣ ፈጽሞ ተማርኮአል።
\s5
\v 20 ዓይናችሁን አንሥታችሁ እነዚህን ከሰሜን የሚመጡትን ተመልከቱ፤ ለአንቺ የሰጠው መንጋ፣ ለአንቺ የተዋበው መንጋሽ ወዴት አለ?
\v 21 ወዳጆችሽ እንዲሆኑ ያስተማርሻቸውን እግዚአብሔር በራስሽ ላይ አለቆች ባደረጋቸው ጊዜ ምን ትያለሽ? እንደ ወላድ ሴት ምጥ አንቺንም የሚይዝሽ የምጥ ስቃይ ጅማሬ አይደለምን?
\s5
\v 22 በልብሽም፣ 'እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ?' ብትዪ፣ የቀሚስሽ ዘርፍ ተገልጦ የተገፈፍሽው ከብዙ ኃጢአትሽ የተነሣ ነው።
\v 23 የኩሽ ሕዝቦች የቆዳ ቀለማቸውን፣ ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? ከሆነ፣ በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ መልካምን ማድረግ ትችላላችሁ።
\v 24 ስለዚህ እንደሚያልፍ እብቅ በምድረ በዳ ነፋስ እበትናቸዋለሁ።
\s5
\v 25 ረስተሽኛልና፣ በሐሰትም ታምነሻልና የሰጠኹሽ፣ የደነገግሁልሽም እድል ፈንታ ይህ ነው፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 26 ስለዚህም የቀሚስሽን ዘርፍ እኔ ራሴ በፊትሽ እገልጣለሁ፣ የእፍረት አካልሽም ይታያል።
\v 27 አስጸያፊ ሥራሽን፣ ምንዝርናሽን፣ ማሽካካትሽን፣ የግልሙትናሽንም መዳራት በኮረብቶች ላይ በሜዳም የሆኑትን እነዚህን አስፀያፊ ነገሮች እንዲታዩብሽ አደርጋለሁ! ወዮልሽ፣ ኢየሩሳሌም! አልነፃሽም። ይህስ እስከ መቼ ይቀጥላል?"
\s5
\c 14
\p
\v 1 ስለ ድርቅ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፣
\v 2 "ይሁዳ ታልቅስ፣ ደጆችዋም ይውደቊ። ስለ ምድራቸው እያለቀሱ ናቸው፤ ለኢየሩሳሌም የሚያለቅሱት ከፍ ብሎአል።
\v 3 ኃያላኖቻቸውም አገልጋዮቻቸውን ለውኃ ሰደዱ። ወደ ጕድጓድ ሲመጡ ውኃ ሊያገኙ አልቻሉም። ሁሉም ሳይሳካላቸው ተመለሱ፤ አፍረውና ተዋርደው ራሳቸውን ተከናነቡ።
\s5
\v 4 ከዚህ የተነሣ በምድሪቱ ላይ አልዘነበምና መሬቱ ስንጥቅጥቅ ሆነ። አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ።
\v 5 ዋላ በምድረ በዳ ወልዳ ሣር ባለመኖሩ ግልገልዋን ተወች።
\v 6 የሜዳ አህዮችም በወና ኮረብታ ላይ ቆመው እንደ ቀበሮ ወደ ነፋስ አለከለኩ። ልምላሜ የለምና ዓይኖቻቸው ፈዘዙ።
\s5
\v 7 ኃጢአታችን ቢመሰክርብንም፣ እግዚአብሔር ስለ ስምህ ሥራ። ያልታመንንባቸው ተግባራቶቻችን ጨምረዋልና፣ በአንተ ላይ ኃጢአት ሠርተናል።
\v 8 የእስራኤል ተስፋ ሆይ፣ በጭንቀት ጊዜ የምታድነው አምላክ ወደ ማደሪያ ዘወር እንደሚል መንገደኛ በምድሪቱ ላይ ለምን እንደ እንግዳ ትሆናለህ?
\v 9 ግራ እንደተጋባ ሰው፣ ያድንም ዘንድ እንደማይችል ኃያል ለምን ትሆናለህ? አንተ ግን፣ በመካከላችን ነህ፣ እግዚአብሔር ሆይ እኛም በስምህ ተጠርተናል። አትተወን።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፣ "መቅበዝበዝን ወድደዋልና፣ እግራቸውንም እንዲህ ከማድረግ አልከለከሉም፤" ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አላለውም። አሁን በደላቸውን ያስባል ኃጢአታቸውንም ይቀጣል።
\v 11 እግዚአብሔርም፣ "ለዚህ ሕዝብ መልካም እንዲሆንላቸው አትጸልይላቸው።
\v 12 ቢጾሙ ጸሎታቸውን አልሰማም፣ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን ባቀረቡ ጊዜ አልቀበላቸውም። በሰይፍና በራብ በቸነፈርም አጠፋቸዋለሁ አለኝ።
\s5
\v 13 ከዚያም፣ "ኦ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ወዮ! እነሆ! ነቢያት ለሕዝቡ፣ 'በዚህ ስፍራ በእውነት ሰላምን እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፣ ራብም አያገኛችሁም ይሉአቸዋል" እያሉ ናቸው።
\v 14 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ነቢያቱ በስሜ የውሸት ትንቢት ይናገራሉ። አልላክኋቸውም፣ አላዘዝኋቸውም፣ አልተናገርኳቸውምም። ነገር ግን፣ የውሸት ራእይና ጥቅም የለሽ የሆነ ከንቱ ምዋርትን፣ የልባቸውንም ሽንገላ ይተነብዩላችኋል።"
\s5
\v 15 ስለዚህ እግዚአብሔር፣ "በዚህች አገር ሰይፍና ራብ አይሆንም ስለሚሉ፣ ነገር ግን በስሜ ትንቢት ስለሚናገሩ ስላልላክኋቸው ነቢያት እንዲህ ይላል፦ እነዚህ ነብያት በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ።
\v 16 ትንቢት የሚናገሩላቸውም ሰዎች ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም አደባባይ ይበተናሉ፤ ክፋታቸውንም አፈስስባቸዋለሁ እነርሱንና ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም የሚቀብራቸው አይገኝም።
\s5
\v 17 ይህንን ቃል ንገራቸው፦ 'ዐይኖቼ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጡ እንባ ያፍስሱ። ድንግሊቱ የሕዝቤ ልጅ በታላቅ ስብራትና እጅግ ክፉ በሆነ ቍስል ተሰብራለችና ።
\v 18 ወደ ሜዳ ብወጣና ባይ! በሰይፍ የሞቱ አሉ። ወደ ከተማም ብገባ፣ ያኔም በራብ የታመሙ አሉ። ነቢዩና ካህኑም ወደማያውቋት አገር ሄደዋል።"
\s5
\v 19 በውኑ ይሁዳን ፈጽመህ ጥለኸዋልን? ጽዮንንስ ጠልተሃታልን? ፈውስ በማይኖረን ጊዜ ስለ ምን መታኸን? ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፣ መልካምም አልተገኘም፤ ፈውስን በተስፋ ተጠባበቅን፣ ተመልከቱ፣ ያለው ግን ድንጋጤ ብቻ ነው።
\v 20 እግዚአብሔር ሆይ፣ በአንተ ላይ ኃጢአትን ሠርተናልና ክፋታችንንና የአባቶቻችንን በደል እናውቃለን።
\s5
\v 21 አትጣለን! ስለ ስምህ፣ የክብርህንም ዙፋን አታስነውር። ከእኛ ጋር ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ እንጂ አታፍርስ።
\v 22 በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል የጸደይን ዝናብ ከሰማይ ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ይህንን የምታደርግ አምላካችን እግዚአብሔር አንተ አይደለህምን? እነዚህን ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን ተስፋ እናደርጋለን።
\s5
\c 15
\p
\v 1 እግዚአብሔርም እንደዚህ አለኝ፣ "ሙሴና ሳሙኤል በፊቴ ቢቆሙም እንኳን፣ ለዚህ ሕዝብ አላደላም። እንዲወጡ ከፊቴ አባርራቸው።
\v 2 እነርሱም፣ 'ወዴት እንሂድ?' ቢሉህ፣ ያኔ አንተ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለሞት የተወሰኑት ወደ ሞት፣ ለሰይፍም የተወሰኑት ወደ ሰይፍ፣ ለራብም የተወሰኑት ወደ ራብ፣ ለምርኮም የተወሰኑት ወደ ምርኮ' ትላቸዋለህ።
\s5
\v 3 አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፣ እነርሱም አንዳንዶችን የሚገድል ሰይፍ፣ አንዳንዶችን የሚጎትቱ ውሾችን፣ አንዳንዶችን የሚበሉ የሰማያትን ወፎች፣ የምድርንም አራዊት ናቸው ይላል እግዚአብሔር።
\v 4 የይሁዳም ንጉሥ የሕዝቅያስ ልጅ ምናሴ በኢየሩሳሌም ስላደረገው ሁሉ ለምድር መንግሥታት ሁሉ መጨነቂያ አደርጋቸዋለሁ።
\s5
\v 5 ኢየሩሳሌም ሆይ የሚራራልሽ ማን ነው? የሚያዝንልሽስ ማን ነው? ወይስ ስለ ደኅንነትሽ ይጠይቅ ዘንድ ዘወር የሚል ማነ ነው?
\v 6 አንቺ እኔን ጥለሻል፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል። ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ እመታሽና አጠፋሻለሁ። ለአንቺ ምሕረት ማድረግ አድክሞኛል።
\v 7 በአገርም ደጆች ውስጥ በመንሽ አበጥራቸዋለሁ። ልጆቻቸውንም እነጥቃለሁ። ከመንገዳቸውም አልተመለሱምና ሕዝቤን አጠፋለሁ።
\s5
\v 8 መበለቶቻቸውን ከባሕር አሸዋ ይልቅ አበዛለሁ። በቀትር ጊዜ ላይ በብላቴኖች እናት ላይ አጥፊውን እልካለሁ። ድንጋጤና ሽብር በድንገት እንዲወድቅባቸው አደርጋለሁ።
\v 9 ሰባት የወለደች ትደክማለች። ታለከልካለች። ገና ቀን ሳለ ፀሐይዋ ትገባባታለች። የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁና ታፍራለች፣ ትዋረድማለች።
\s5
\v 10 እናቴ ሆይ፣ ወዮልኝ! በምድሪቱ ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና። አላበደርሁም፣ ከማንም አልተበደርኩም፣ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።
\v 11 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ "በእውነት ለደኅንነትህ አልታደግህምን? በእርግጥ በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላቶችህ እንዲለምኑህ አደርጋለሁ።
\v 12 ሰው ብረትን ይሰብራልን? በተለይ ከሰሜን የሆነውን ከናስ ጋር የተቀየጠውን ብረት የሚሰብር አለን?
\s5
\v 13 ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለመበዝበዝ በነፃ እሰጣለሁ። ይህንንም የማደርገው በድንበሮችህ ሁሉ ስለፈጸምከው ኃጢአትህ ሁሉ ነው።
\v 14 ከዚያም፣ ጠላቶችህ ወደማታውቀው ምድር እንዲወስዱህ አደርጋለሁ፣ የምታቃጥላችሁ እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና።
\s5
\v 15 አንተ ራስህ ታውቃለህ፣ እግዚአብሔር ሆይ! አስበኝ እርዳኝም። የሚያሳድዱኝንም ተበቀላቸው። በትእግሥትህ አታርቀኝ። ስለ አንተ ነቀፌታን እንደ ጠገብሁ እወቅ።
\v 16 ቃሎችህ ተገኝተዋል እኔም በልቼያቸዋለሁ። የሠራዊት አምላክ ሆይ፣ በስምህ ተጠርቻለሁና ቃሎችህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆኑልኝ።
\s5
\v 17 በሚፈነድቁትና በደስተኞች ዙሪያ አልተቀመጥሁም። በቍጣህ ሞልተኸኛልና በኃይለኛው እጅህ ፊት ለብቻዬ ተቀመጥሁ።
\v 18 ስለ ምን ሕመሜ አዘወተረኝ፣ ቍስሌስ ስለ ምን ፈውስን የማይቀበልና የማይሽር ሆነ? በውኑ እንደ አታላይ ምንጭ፣ እንደደረቅ ውኃ ትሆናለህን?
\s5
\v 19 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ኤርምያስ ሆይ፣ ንስሃ ብትገባ፣ እንደ ቀድሞው እመልስሃለሁ፣ በፊቴም ቆመህ ታገለግለኛለህ። የተዋረደውንም ከከበረው ብትለይ፣ እንደ አፌ ትሆናለህ። ሕዝቡ ወደ አንተ ይመለሳሉ፣ አንተ ራስህ ግን ወደ እነርሱ አትመለስም።
\v 20 ለዚህም ሕዝብ የማይጣስ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፣ ይዋጉሃል። ነገር ግን እኔ ላድንህ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም ይላል እግዚአብሔር።
\v 21 ከክፉ ሰዎችም እጅ እታደግሃለሁ፣ ከጨካኞችም ቡጢ እቤዥሃለሁ።
\s5
\c 16
\p
\v 1 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 2 "በዚህ ስፍራ ሚስት አታግባ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም አይኑርህ።
\v 3 እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ስለ ተወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፣ ስለወለዱአቸውም ስለ እናቶቻቸው፣ በዚህችም ምድር እንዲወለዱ ስላደረጉ አባቶቻቸው እንዲህ ይላል፣
\v 4 በበሽታ ሞት ይሞታሉ። አይለቀስላቸውም ወይም አይቀበሩም። በመሬትም ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ። በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ፣ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናሉ።'
\s5
\v 5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ልቅሶ ወዳለበት የትኛውም ቤት አትግባ። ታለቅስም፣ ታዝንም ዘንድ አትሂድ። ሰላሜን፣ ቸርነትና ምሕረትን፣ ከዚህ ሕዝብ አስወግጄአለሁና!
\v 6 ታላላቆችና ታናናሾች በዚህች ምድር ይሞታሉ። አይቀበሩም፣ ሰዎችም አያለቅሱላቸውም። ስለ እነርሱም ገላን አይነጩላቸውም ራስንም አይላጩላቸውም።
\s5
\v 7 ሰዎችም ስለ ሞቱት ለማጽናናት የእዝን እንጀራን ሊካፈሉ አይገባም፣ ለአባታቸውና ለእናታቸውም ማንም የመጽናናት ጽዋ ሊሰጧቸው አይገባም።
\v 8 ትበላና ትጠጣ ዘንድ ከእነርሱ ጋር ለመቀመጥ ወደ ግብዣ ቤት አትግባ።'
\v 9 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ተመልከት፣ በዐይናችሁ ፊት በዘመናችሁም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስቆማለሁ።'
\s5
\v 10 ከዚያም ለዚህ ሕዝብ ይህን ቃል ሁሉ በተናገርህ ጊዜ፣ 'እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ታላቅ የሆነ ክፉ ነገር ለምን ተናገረብን? በደላችንስ ምንድር ነው? በአምላካችንስ በእግዚአብሔር ላይ የሠራነው ኃጢአታችን ምንድር ነው? ሲሉህ፣
\v 11 እንዲህ በላቸው፣ 'አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ሌሎችን አማልክት ተከተሉ አመለኩአቸውም ሰገዱላቸውም። እነርሱም ትተውኛል፣ ሕጌንም አልጠበቁም።
\s5
\v 12 ነገር ግን፣ እናንተ ራሳችሁ ከአባቶቻችሁ ይልቅ ክፉ አድርጋችኋል፤ ተመልከቱ፣ እያንዳንዱ ሰው በክፉ ልብ እልከኝነት ሄዷል፣ እኔንም የሚሰማ የለም።
\v 13 ስለዚህ ከዚህች ምድር እናንተና አባቶቻችሁ ወዳላወቃችኋት ምድር እጥላችኋለሁ፣ ሞገስን አላደርግላችሁምና በዚያ ሌሎችን አማልክት ቀንና ሌሊት ታመልካላችሁ።
\s5
\v 14 ስለዚህ ተመልከቱ! ከእንግዲህ 'የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!' የማይባልበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 15 ነገር ግን፣ የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር፣ ካሳደዳቸውም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ወደ ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ።
\s5
\v 16 ተመልከቱ! ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም ሕዝቡን ሊያወጡ ያጠምዱአቸዋል። ከዚህም በኋላ ብዙ አጥማጆችን እሰድዳለሁ፣ እነርሱም ከየተራራውና ከየኮረብታው ሁሉ ከየድንጋዩም ስንጣቂ ውስጥ ያጠምዷቸዋል።
\v 17 ዓይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነውና፤ ከፊቴም ሊሰወሩ አይችሉም። በደላቸውም ከዓይኔ ሊሰወር አይችልም።
\v 18 በተጠሉ ጣዖቶቻቸው ሬሳዎች ምድሬን አርክሰዋልና፣ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና፣ አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።"
\s5
\v 19 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ምሽጌ፣ አምባዬ፣ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ። አሕዛብ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ ሄደው፣ "በእርግጥ አባቶቻችን ውሸትን ወርሰዋል። ባዶ ናቸው፤ በእነርሱ ዘንድ ትርፍ የለም ይላሉ።
\v 20 በውኑ ሕዝቦች አማልክት ያልሆኑትን ለራሳቸው አማልክትን አድርገው ይሠራሉን?
\v 21 ስለዚህ ተመልከቱ! በዚህ ጊዜ አስታውቃቸዋለሁ፣ እጄንና ኃይሌን አስታውቃቸዋለሁ፤ ከዚህም የተነሣ ስሜ እግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቃሉ።"
\s5
\c 17
\p
\v 1 "የይሁዳ ኃጢአት የሾለ አልማዝ ባለው የብረት ብዕር ተጽፎአል። በልባቸው ጽላትና በመሠዊያቸው ቀንዶች ላይ ተቀርጾአል።
\v 2 ልጆቻቸውም ከለመለሙ ዛፎች በታችና በከፍተኞቹ ኮረብቶች ላይ ያሉትን መሠዊያቸውንና አሼራ የምትባለውን ጣዖታቸውን ያስባሉ።
\s5
\v 3 በገጠር ባሉት ተራሮች ላይ ያሉትን መሠዊያዎቻቸውን ያስታውሳሉ። ባለጠግነታችሁንና መዝገባችሁን ሁሉ፣ የኮረብታውን መስገጃዎቻችሁንም በኃጢአታችሁ ምክንያት እንዲበዘበዙ አደርጋለሁ።
\v 4 አናንተም የሰጠኋችሁን ርስት ትለቅቃላችሁ። በማታውቋትም ምድር ለጠላቶቻችሁ ባሪያ አደርጋችኋለሁ፤ ለዘላለም የሚነድደውን እሳት በቍጣዬ አንድዳችኋልና።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በሰው የሚታመን፣ ሥጋ ለባሹንም ብርታቱ የሚያደርግ፣ ልቡን ግን ከእግዚአብሔር የሚመልስ ሰው ርጉም ነው።
\v 6 በአረብ ምድር እንዳለ ትንሽ ቍጥቋጦ ይሆናል፣ የሚመጣውንም መልካም ነገር አያይም። ሰውም በሌለበት ዐለታማ ምድር ውስጥ ደረቅ በሆነ ምድረ በዳ ይቀመጣል።
\s5
\v 7 ነገር ግን በእግዚአብሔር የታመነ፣ የልበ-ሙሉነቱ ምክንያት እግዚአብሔር ነውና ቡሩክ ነው።
\v 8 በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፣ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ተክል ይሆናልና። ሙቀት ሲመጣ አያይም፣ ቅጠሉ ይለመልማልና። ከዚያም፣ በድርቅ ዓመት ላይ አይሠጋም፣ ማፍራቱንም አያቋርጥም።
\s5
\v 9 ልብ ከየትኛውም ነገር ይልቅ ተንኰለኛ ነው። በሽተኛ ነው፤ ማንስ ያስተውለዋል?
\v 10 ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፣ እንደ ሥራው ፍሬ ልሰጥ ልብን የምመረምር፣ ኵላሊትንም የምፈትን እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
\v 11 ያልጣለችውን እንቁላል እንደምታቅፍ ቆቅ፣ እንዲሁ አንድ ሰው ያለፍትህ ባለጠጋ ይሆን ይሆናል። ነገር ግን በእኩሌታ ዘመኑ ላይ ብልጥግናው ይተወዋል፣ በፍጻሜውም ሰነፍ ይሆናል።
\s5
\v 12 የመቅደሳችን ስፍራ ከመጀመሪያም ጀምሮ ክፍ ያለ የክብር ዙፋን ነው።
\v 13 እግዚአብሔር የእስራኤል ተስፋ ነው። አንተን የሚተዉህ ሁሉ ያፍራሉ። ከአንተም የሚለዩ የሕይወትን ውኃ ምንጭ እግዚአብሔርን ትተዋልና በምድር ላይ ይቆረጣሉ።
\v 14 እግዚአብሔር ሆይ፣ ፈውሰኝ እኔም እፈወሳለሁ! አድነኝ እኔም እድናለሁ። አንተ የምስጋናዬ ዝማሬ ነህና።
\s5
\v 15 ተመልከቱ፣ 'የእግዚአብሔር ቃል ወዴት ነው? ይምጣ!' ይሉኛል።
\v 16 እኔም አንተን ተከትዬ እረኛ ከመሆን አልሮጥሁም። የመከራንም ቀን አልታገሥሁም። ከከንፈሬ የመጣውን አንተ ታውቃለህ። በህልውናህ ፊት ተነግረዋል።
\s5
\v 17 መሸበሪያ አትሁንብኝ። በመከራ ቀን አንተ መጠጊያዬ ነህ።
\v 18 አሳዳጆቼ ይፈሩ፣ እኔ ግን አልፈር። እነርሱ ይደንግጡ፣ እኔ ግን አልደንግጥ። የጥፋትን ቀን አምጣባቸው፣ በሁለት እጥፍ ጥፋት አጥፋቸው።
\s5
\v 19 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ "ሂድና የይሁዳም ነገሥታት በሚገቡበትና በሚወጡበት የሕዝቡ በር፣ ከዚያም በኢየሩሳሌምም በሮች ሁሉ ቁም።
\v 20 እንዲህም በላቸው፣ 'በእነዚህ በሮች የምትገቡ እናንተ የይሁዳ ነገሥታት፣ የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ፣ የኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ለራሳችሁ ሕይወት ተጠንቀቁ፥ በኢየሩሳሌምም በሮች እንድታገቡ በሰንበት ቀን ሸክምን አትሸከሙ።
\v 22 በሰንበት ቀን ከቤቶቻችሁ ሸክምን አታውጡ። የትኛውንም ሥራ ሁሉ አትሥሩበት፣ ነገር ግን አባቶቻችሁንም እንዳዘዝሁት የሰንበትን ቀን ቀድሱ።"
\v 23 እነርሱ ግን ትኩረት ሰጥተው አልሰሙም፣ እንዳይሰሙና ተግሣጽን እንዳይቀበሉ አንገታቸውን አደነደኑ።
\s5
\v 24 እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ ይሆናል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ደግሞም በሰንበት ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም አታምጡ፣ ይልቊንም የሰንበትን ቀን ለእግዚአብሔር ቀድሱ የትኛውንም ሥራ አትሠሩበት፤
\v 25 በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታትና መሳፍንት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ እየተቀመጡ በዚህች ከተማ በሮች ይገባሉ፣ እነርሱና መሳፍንቶቻቸው የይሁዳም ነዋሪዎች በኢየሩሳሌምም የሚቀመጡ ይመጣሉ። ይህችም ከተማ ለዘላለም የሰው መኖሪያ ሆና ትቀራለች።
\s5
\v 26 የሚቃጠለው መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን የእህሉንም ቍርባን ዕጣኑንም የምስጋናውንም መሥዋዕት ይዘው ከይሁዳ ከተሞች ከኢየሩሳሌምም ዙሪያ ከብንያምም አገር ከቈላውም ከደጋውም ከኔጌቭም ወደ እግዚአብሔር ቤት ይመጣሉ።
\v 27 ነገር ግን የሰንበትን ቀን ልትቀድሱ፣ በሰንበትም ቀን ሸክምን ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች ልትገቡ የነገርኋችሁን ባትሰሙኝ፣ እሳትን በበሮችዋ ላይ እለኩሳለሁ፣ የኢየሩሳሌምንም ምሽጎች ትበላለች፣ እሳቱም አይጠፋም።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል እንዲህ አለው፣
\v 2 "ተነሥተህ ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ውረድ፣ በዚያም ቃሌን አሰማሃለሁና።
\v 3 ስለዚህም ወደ ሸክላ ሠሪው ቤት ወረድሁ፣ ሸክላ ሠሪውም ሥራውን በመንኵራኩር ላይ ይሠራ ነበር።
\v 4 ከጭቃም ይሠራው የነበረ ዕቃ በሸክላ ሠሪው እጅ ተበላሸ፣ ሸክላ ሠሪውም እንደ ወደደ መልሶ ሌላ ዕቃ አድርጎ ሠራው።
\s5
\v 5 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 6 "የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ይህ ሸክላ ሠሪ እንደሚሠራ በውኑ እኔ በእናንተ ዘንድ መሥራት አይቻለኝምን? ይላል እግዚአብሔር። ተመልከቱ! ጭቃው በሸክላ ሠሪ እጅ እንዳለ፣ እንዲሁ እናንተ በእኔ እጅ ውስጥ አላችሁ።
\v 7 በአንድ ወቅት፣ አባርር፣ አፈርስ፣ ወይም አጠፋ ዘንድ ስለ ሕዝብ ወይም ስለ መንግሥት አንዳች ነገር እናገር ይሆናል።
\v 8 ነገር ግን ያንን የተናገርኩበት ሕዝብ ከክፋቱ ቢመለስ፣ ያኔ እኔ ላደርግበት ያሰብሁትን ክፉ ነገር እተወዋለሁ።
\s5
\v 9 በሌላ ጊዜ፣ ስለ ሕዝብ ወይም ስለ መንግሥት እንደምሠራው ወይም እንደምተክለው እናገራለሁ።
\v 10 ነገር ግን ድምፄን ባለመስማት በፊቴ ክፉን ነገር ቢያደርግ፣ ያኔ እኔ ላደርግለት የተናገርሁትን መልካም ነገር አቆማለሁ።
\s5
\v 11 አሁን እንግዲህ፣ ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ተናገርና እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ ክፉ ነገር ልፈጥርባችሁ ነው። እቅድንም ላወጣባችሁ ነው። መንገዶቻችሁ እና ልምምዶቻችሁ መልካምን እንዲያመጡላችሁ፣ እያንዳንዱ ሰው ከክፉ መንገዱ ንስሃ ይግባ'
\v 12 እነርሱ ግን፣ 'ይህ ጥቅም የለውም። እንደ እቅዶቻችን እናደርጋለን። እያንዳንዳችን ክፉ የሆነው ልባችን እንደተመኘው እልከኝነትን እናደርጋለን' አሉ።
\s5
\v 13 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እንዲህ ያለውን ነገር ማን ሰምቷል ብላችሁ አሕዛብን ጠይቊ። የእስራኤል ድንግል አስደንጋጭ ነገርን አድርጋለች።
\v 14 በውኑ የሊባኖስ በረዶ በሜዳ ያሉትን ድንጋያማ ኮረብቶች ይተዋልን? ወይስ ከሩቅ የምትመጣው ቀዝቃዛይቱ ፈሳሽ ውኃ ትደርቃለችን?
\s5
\v 15 ሕዝቤ ግን ረስተውኛል። ጥቅም ለሌላቸው ጣዖታት ሠውተዋል፤ ከመንገዳቸውም ተሰናክለዋል፤ በአነስተኞቹ መንገዶች ለመሄድ ሲሉ የቀደሙትን መንገዶች ትተዋል።
\v 16 ምድራቸው ለመደንገጪያና ለዘላለም ማፍዋጫ ይሆናል። የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፣ ራሱንም ይነቀንቃል።
\v 17 እንደ ምሥራቅ ነፋስ በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ። በጥፋታቸውም ቀን ፊቴን ሳይሆን ጀርባዬን አሳያቸዋለሁ።"
\s5
\v 18 እነርሱም፣ "ሕግ ከካህናት፣ ወይም ምክር ከጠቢባን፣ ወይም ቃልም ከነቢያት አይጠፋምና ኑ፣ በኤርምያስ ላይ እናሲር። ኑ፣ በቃላችን እናጥቃው፣ የሚናገረውንም ሁሉ ትኩረት አንስጠው" አሉ።
\v 19 እግዚአብሔር ሆይ፣ አድምጠኝ! የጠላቴንም ድንፋታ ስማ።
\v 20 ጕድጓድ ቈፍረውልኛልና መልካም ስለሆንኩላቸው ከእነርሱ የሚሆን ጥፋት ክፍያዬ ይሆናልን? ለደህንነታቸው ለመናገር፣ ከእነርሱ ቊጣህን ለመመለስ በፊት እንደቆምኩ አስታውስ።
\s5
\v 21 ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፣ ለሰይፍም ኃይል አሳልፈህ ስጣቸው። ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፣ ወንዶቻቸውም ይገደሉ፣ ወጣቶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።
\v 22 ሊይዙኝ ጕድጓድ ቆፍረዋልና፣ ለእግሮቼም ድብቅ ወጥመድ አኑረዋልና በላያቸው ጭፍራን በድንገት ባመጣህ ጊዜ፣ ከቤታቸው ጩኸት ይሰማ።
\v 23 አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይገድሉኝ ዘንድ በላዬ ያቀዱትን ዕቅድ ሁሉ ታውቃለህ። በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር አትበል። ኃጢአታቸውንም ከአንተ ዘንድ አትደምስስ። ይልቅ፣ በፊትህ ይውደቁ። በቍጣህ ጊዜ እንዲሁ አድርግባቸው።
\s5
\c 19
\p
\v 1 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፣ "ሂድና ከሸክላ ሠሪ ገምቦ ግዛ፤ ከሕዝቡም ሽማግሌዎችና ከካህናት ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ።
\v 2 የገል በር በሚከፈትበት ወዳለው ወደ ሄኖም ልጅ ሸለቆ ሂድ፣ በዚያም የምነግርህን ቃል ተናገር።
\v 3 እንዲህም በል፣ 'ይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ! የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ! የሰማውን ሰው ጆሮ የሚያስጨንቅ ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ አመጣለሁ።
\s5
\v 4 ይህንን የማደርገው ስለተዉኝና ይህንን ስፍራ የባዕድ አማልክት አድርገውታልና ነው። እነርሱና አባቶቻቸው ለማያውቋቸው ለሌሎች አማልክት አጥነዋል፣ የይሁዳም ነገሥታት ይህንን ስፍራ በንጹህ ደም ሞልተዋል።
\v 5 እኔም ያላዘዝሁትን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ወንዶች ልጆቻቸውን ለበኣል በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋል። ይህንን እንዲያደርጉ አልተናገርኳቸውም፣ በልቤም አላሰብሁትም።
\s5
\v 6 ስለዚህም፣ ተመልከቱ፣ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ከእንግዲህ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ የማይባልበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር።
\v 7 በዚህ ስፍራ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን እቅድ ከንቱ አደርጋለሁ። በጠላቶቻቸው ፊት በሰይፍና ነፍሳቸውን ደግሞ በሚሹት እጅ እጥላቸዋለሁ። ከዚያም ሬሳቸውንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል አድርጌ እሰጣለሁ።
\v 8 ከዚያም ይህችን ከተማ አጠፋና መደነቂያ አደርጋታለሁ፣ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፣ ከንፈሩንም ይመጥጣል።
\v 9 የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፣ ሁሉም ጠላቶቻቸውንና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የጎረቤቶቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።
\s5
\v 10 ከዚያም ገምቦውን ከአንተ ጋር በሚሄዱ ሰዎች ፊት ትሰብራለህ።
\v 11 እንዲህም ትላቸዋለህ፣ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የሸክላ ሠሪውን ዕቃ ኤርምያስ እንደሰባበረው፣ ደግሞም በድጋሚ ይጠገን ዘንድ እንደማይቻል፣ እንዲሁ ይህን ሕዝብና ይህችን ከተማ እሰብራለሁ፤ የሚቀብሩበትም ስፍራ እስከማይኖር ድረስ በቶፌት ይቀበራሉ።
\s5
\v 12 ይህችንም ከተማ እንደ ቶፌት ሳደርግ ለዚህ ስፍራና በሚኖሩበት ላይ የማደርገው ይህንኑ ነው ይላል እግዚአብሔር።
\v 13 የረከሱትም የኢየሩሳሌም ቤቶችና የይሁዳ ነገሥታት ቤቶች፣ እነዚያ በሰገነታቸው ላይ ለሰማይ ከዋክብት ሁሉ ያጠኑባቸው ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቍርባን ያፈሰሱባቸው ቤቶች ሁሉ፣ እንደ ቶፌት ስፍራ ይሆናሉ።"
\s5
\v 14 ከዚያም ትንቢት እንዲናገር እግዚአብሔር ልኮት ከበረው ስፍራ፣ ከቶፌት ኤርምያስ መጣ። በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፣
\v 15 "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና፣ በዚህች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።"
\s5
\c 20
\p
\v 1 በእግዚአብሔርም ቤት የተሾመው አለቃ የካህኑ የኢሜር ልጅ ጳስኮር ኤርምያስ በዚህ ነገር ትንቢት ሲናገር ሰማ።
\v 2 ስለዚህ ጳስኮር ነቢዩን ኤርምያስን መታው፣ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ባለው በላይኛው የብንያም በር በእግር ግንድ አሰረው።
\s5
\v 3 በቀጣዩ ቀን ጳስኮር ኤርምያስን ከግንድ እስር አወጣው። ከዚያም ኤርምያስ እንዲህ አለው፣ "እግዚአብሔር ስምህን፣ ማጎርሚሳቢብ እንጂ ጳስኮር ብሎ አይጠራህም።
\v 4 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ተመልከት፣ ለራስህና ለወዳጆችህ ሁሉ ፍርሃት አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በጠላቶቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉና ዓይኖችህም ያንን ያያሉ። ይሁዳንም ሁሉ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እርሱም በባቢሎን ምርኮኛ ያደርጋቸዋል ወይም በሰይፍ ይገድላቸዋል።
\s5
\v 5 የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እነዚህን ነገሮች በጠላቶቻችሁ እጅ አኖራለሁ፣ እነርሱም ይይዟቸዋል። እነርሱም ይወስዷቸዋል ደግሞም ወደ ባቢሎን ያመጧቸዋል።
\v 6 አንተ ግን፣ ጳስኮር ሆይ፣ በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ። ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ ደግሞም በዚያ ትሞታለህ። አንተና የሚያታልሉ ነገሮችን የተነበይክላቸው ወዳጆችህ ሁሉ በዚያ ትቀበራላችሁ።"
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ሆይ፣ አሳመንኸኝ፣ እኔም አምኛለሁ። ያዝኸኝ ደግሞም አሸነፍኸኝ። መላገጫ ሆኛለሁ። ሕዝቡ በየቀኑ፣ ቀኑን ሁሉ ይሳለቊብኛል።
\v 8 በተናገርሁ ቍጥር፣ 'ግፍና ጥፋት' ብዬ እጮኻለሁ። የእግዚአብሔርም ቃል ቀኑን ሁሉ ነቀፌታና ዋዛ ሆኖብኛልና።
\v 9 እኔም፣ 'ከእንግዲህ ወዲህ የእግዚአብሔርን ስም አላስብም። ከእንግዲህ ወዲህም ስሙን አላውጅም' ብል፣ ያን ጊዜ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደሚነድድ፣ በልቤ ውስጥ እንዳለ እሳት ሆነብኝ። ስለዚህ ልሸከመው ታገልሁ፣ ነገር ግን አልቻልሁም።
\s5
\v 10 በዙሪያዬ ካሉ ብዙ ሰዎች የሚያሽብር አሉባልታን ሰምቻለሁ። የቅርቤ ሰዎች የሆኑት ውድቀቴን ለማየት ጠበቊ፣ 'ምናልባት እንበረታበት እንደ ሆነ፣ ከዚያም እንበቀለው እንደ ሆነ 'ክሰሱት፣ እኛም እንከስሰዋለን' ይላሉ።
\v 11 እግዚአብሔር ግን እንደ ኃያል ጦረኛ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ። አያሸንፉኝም። አይከናወንላቸውምና፣ በእጅጉ ያፍራሉ። መቼም የማይረሳ በሚሆን እፍረት የማያበቃ እፍረት ያፍራሉ።
\s5
\v 12 ጻድቅን የምትመረምር፣ አእምሮንና ልብን የምትመለከት የሠራዊት ጌታ ሆይ፣ ክርክሬን አሳይቼሃለሁና በላያቸው በቀልህን ልይ።
\v 13 ለእግዚአብሔር ዘምሩ! እግዚአብሔርን አመስግኑ! የተጨቆኑትን ሰዎች ሕይወት ከክፉ አድራጊዎች እጅ አድኖአልና።
\s5
\v 14 የተወለድሁባት ቀን የተረገመች ትሁን። እናቴ እኔን የወለደችባት ቀን የተባረከች አትሁን።
\v 15 'ወንድ ልጅ ተወልዶልሃል' ብሎ ለአባቴ የነገረው ሰው የተረገመ ይሁን።
\s5
\v 16 ያም ሰው እግዚአብሔር ያለምሕረት እንደ ገለበጣቸው ከተሞች ይሁን። በማለዳም እርዳታ የሚለምን ጩኸትን በቀትርም የጦርነት እሪታን ይስማ።
\v 17 እግዚአብሔር በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና ወይም እናቴን መቃብሬ አላደረገኝምና፣ ይህ ይከሰት።
\v 18 ችግርንና ጣርን አይ ዘንድ፣ ዘመኔም በእፍረት ይሞላ ዘንድ ለምን ከማኅፀን ወጣሁ?
\s5
\c 21
\p
\v 1 ንጉሥ ሴዴቅያስ የመልክያን ልጅ ጳስኮርንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስ ወደ ኤርምያስ በላከ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 2 "የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፣ እባክህ፣ እግዚአብሔርን ጠይቅ። ምናልባት ከእኛ ይመለስ ዘንድ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአምራቱ ሁሉ ያደርግ ይሆናል።"
\s5
\v 3 ስለዚህ ኤርምያስ እንዲህ አላቸው፣ "ለሴዴቅያስ እንዲህ በሉት፣
\v 4 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ የባቢሎንን ንጉሥ ከቅጥርም ውጭ የከበቡአችሁን ከለዳውያንን የምትወጉበትን በእጃችሁ ያለውን ዕቃ ጦራችሁን እመልሰዋለሁ! እነዚያንም ወደዚህች ከተማ አማከይ እሰበስባቸዋለሁ።
\v 5 ያን ጊዜ እኔ ራሴ በተዘረጋች እጅና በብርቱ ክንድ፣ በቍጣና በመዓት በታላቅም መቅሠፍት እወጋችኋለሁ።
\s5
\v 6 በዚህችም ከተማ የሚኖሩትን፣ ሰዎችንና እንስሶችን እመታለሁ፣ በጽኑም መቅሰፍት ይሞታሉ።
\v 7 ከዚህ በኋላ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስን፣ ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህች ከተማ የቀሩትንም ባሪዎቹንና ሕዝቡን፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ከዚያም እርሱ በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል። አያዝንላቸውም፣ አይራራላቸውም፣ ወይም አያዝንላቸውም።'
\s5
\v 8 ከዚያም ለዚህ ሕዝብ እንዲህ ልትል ይገባል፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ የሕይወትን መንገድና የሞትን መንገድ በፊታችሁ አደርጋለሁ።
\v 9 በዚህች ከተማ ውስጥ የሚቆይ የትኛውም ሰው በሰይፍ፣ በራብ፣ በመቅሠፍትም ይሞታል፤ ነገር ግን ወጥቶ ወደ ከበቡአችሁ ወደ ከለዳውያን የሚገባ ግን በሕይወት ይኖራል። በሕይወትም ያመልጣል።
\v 10 መልካምን ሳይሆን ጥፋትን ለማምጣት ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተሰጥታለች፣ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።'
\s5
\v 11 የይሁዳ ንጉሥ ቤትን በተመለከተ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 12 የዳዊት ቤት ሆይ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'በማለዳ ፍርድን አድርጉ። የተዘረፈውንም ከአጨቋኙ እጅ አድኑ፣ አሊያ ቍጣዬ እንደ እሳት ይወጣና ያቃጥላል። ከሥራችሁ ክፋት የተነሣ ሊያጠፋው የሚችል ማንም አይኖርም።
\s5
\v 13 ተመልከቱ፣ የሸለቆው ነዋሪዎች! በሜዳው ላይ ያለው ዓለት ሆይ በእናንተ ላይ ነኝ ይላል እግዚአብሔር። "ሊያጠቃን በእኛ ላይ የሚወርድ ማነው?" ወይም "ወደ ቤታችን የሚገባ ማን ነው?" ለምትሉት፣ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ።
\v 14 የሥራችሁ ፍሬ በእናንተ ላይ እንዲመጣባችሁ መድቤያለሁ ይላል እግዚአብሔር፤ በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፣ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።
\s5
\c 22
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወደ ይሁዳ ንጉሥ ቤት ውረድና በዚያም ይህን ቃል ተናገር።
\v 2 እንዲህም በል፣ 'በዳዊት ዙፋን የምትቀመጥ የይሁዳ ንጉሥ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ። አንተና የእርሱ ባርያዎች የሆናችሁ፣ በእነዚህም በሮች የመትገቡት ሕዝቦቹ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ፍርድንና ጽድቅን አድርጉ፣ የተዘረፈውንም ከጨቋኙ እጅ አድኑ። በምድራችሁ ያለውን እንግዳ፣ ወይም የትኛውንም ወላጅ አልባ ወይም መበለቲቱን አትበድሉ። አታምፁባቸው፣ ወይም በዚህ ስፍራ ንጹሕ ደምን አታፍስሱ።
\s5
\v 4 እነዚህንም ነገሮች ብታደርጉ፣ ያን ጊዜ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡ ነገሥታት በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ። እርሱም፣ ባርያዎቹም፣ ሕዝቡም እንዲሁ ይገባሉ!
\v 5 ነገር ግን ከእኔ የተነገሩትን እነዚህን ቃሎች ባትሰሙ፣ ይህ ንጉሣዊ ቤተመንግሥት እንደሚጠፋ በራሴ ምያለሁ" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ቤት እንዲህ ይላልና፣ 'አንተ በእኔ ዘንድ እንደ ገለዓድ፣ ወይም እንደ ሊባኖስ ራስ ነህ። ነገር ግን፣ በእርግጥ ምድረ በዳ፣ ማንም እንደማይቀመጥባቸው ከተሞች አደርግሃለሁ።
\v 7 እንዲመጡባችሁ አጥፊዎችን በእናንተ ላይ አዘጋጅቻለሁ! የተመረጡትንም የዝግባ ዛፎቻችሁን ይቈርጣሉ፣ በእሳትም ውስጥ ይጥሉአቸዋል።
\s5
\v 8 ከዚያም ብዙ አሕዛብ በዚህች ከተማ አጠገብ ያልፋሉ። ሁሉም ባልንጀሮቻቸውን፣ "እግዚአብሔር በዚህች ታላቅ ከተማ ለምን እንዲህ አደረገ?" ይላሉ።
\v 9 ሌላኛውም፣ "የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ ስላመለኩአቸውም ነው" ብለው ይመልሳሉ።
\s5
\v 10 ለሞተው አታንቡ። አታልቅሱለትም። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ አይመለስምና፣ የተወለደባትንም አገር አያይምና ወደምርኮ ለሚሄደው በእርግጥ አልቅሱ።
\s5
\v 11 በአባቱ በኢዮአስ ፋንታ ስለ ነገሠው ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\v 12 'በተማረከባት አገር ይሞታል እንጂ ወደዚህ አይመለስም፣ ይህችንም አገር ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።'
\s5
\v 13 ቤቱን ያለ ጽድቅ ሰገነቱንም በግፍ ለሚሠራ፣ ሌሎችንም አሠርቶ፣ ክፍያ ለማይሰጣቸው።
\v 14 'ለራሴ ሰፊ የላይኛ ቤት፣ ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፣ መስኮትንም ለሚያወጣ፣ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጥ፣ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት።'
\s5
\v 15 የዝግባ እንጨት እንዲኖርህ ስለፈለግህ መልካም ንጉሥ የሚያደርግህ ይህ ነውን? በውኑ አባትህ አይበላምና አይጠጣም ነበርን፣ ፍርድንና ጽድቅንስ አያደርግም ነበርን? በዚያም ጊዜ ነገሮች መልካም ሆነውለት አልነበረምን።
\v 16 ለድሀውና ችግረኛው ፍርድን ይፈርድ ነበር። በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር። እኔን ማወቅ ማለት ይህ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 17 ዓይንህና ልብህ ግን ለስስት፣ ንጹሕ ደምንም ለማፍሰስ፣ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ብቻ ካልሆነ በቀር ሌላ ነገር የለውም።
\v 18 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፦ "ወዮ፣ ወንድሜ ሆይ!" ወይም፣ "ወዮ፣ እኅቴ ሆይ!' እያሉ አያለቅሱለትም፣ ወይም 'ወዮ፣ ጌታዬ!' አሊያም 'ወዮ፣ ግርማዊነትዎ!' እያሉ አያለቅሱለትም።
\v 19 በአህያ ቀብር ይቀበራል፣ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።
\s5
\v 20 ወደ ሊባኖስ ወጥተሽ ጩኺ። በባሳን ድምፅሽን አንሺ። ውሽሞችሽ ሁሉ ይጠፋሉና ከበዓባሪም ተራሮች ሆነሽ ጩኺ።
\v 21 በደኅንነትሽ ጊዜ ተናገርሁሽ፣ አንቺ ግን 'አልሰማም' አልሽ። ከወጣትነትሽ ጀምሮ ቃሌን አለመስማትሽ ልማድሽ ነው።
\s5
\v 22 በግ ጠባቂዎችሽን ሁሉ ነፋስ ይጠብቃቸዋል፣ ውሽሞችሽም ተማርከው ይሄዳሉ። በዚያን ጊዜም ስለ ክፋትሽ ሁሉ ታፍሪያለሽ ትዋረጂማለሽ።
\v 23 አንቺ በሊባኖስ የምትቀመጪ፣ በዝግባ ዛፍም ውስጥ ጎጆሽን የምትሠሪ ሆይ፣ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ሕማም በያዘሽ ጊዜ እንዴት ታጓሪያለሽ።"
\s5
\v 24 "እኔ ሕያው ነኝና የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአቄም ልጅ ኢኮንያን የቀኝ እጄ ማኅተም ቢሆን ኖሮ እንኳ፣ ከዚያ እነቅልህ ነበር፤ ይላል እግዚአብሔር።
\v 25 ነፍስህንም ለሚሹት ለምትፈራቸውም እጅ፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር ለከለዳውያንም እጅ እሰጥሃለሁ።
\v 26 አንተንም የወለደችህንም እናትህን ወዳልተወለዳችሁባት ወደ ሌላ አገር እጥላችኋለሁ፣ በዚያም ትሞታላችሁ።
\s5
\v 27 ይመለሱባትም ዘንድ ወደሚመኟት ወደዚያች ምድር ተመልሰው አይመጡም።
\v 28 በውኑ ይህ ሰው ኢዮአቄም የተናቀና የተሰበረ የሸክላ ዕቃ ነውን? ወይስ እርሱ ለአንዳች የማይረባ የሸክላ ዕቃ ነውን? እርሱና ዘሩስ በማያውቋት ምድር ስለ ምን ተጥለው ወደቁ?
\s5
\v 29 ምድር ሆይ፣ ምድር ሆይ፣ ምድር ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ!
\v 30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወን በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ እንግዲህ አይገኝምና። መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።"
\s5
\c 23
\p
\v 1 "የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።"
\v 2 ስለዚህ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለሚጠብቁ እረኞች እንዲህ ይላል፣ "በጎቼን በትናችኋል ደግሞም አባርራችኋቸዋል። በጭራሽ አልተንከባከባችኋቸውም። ይህንን እወቊ! ለሥራችሁ ክፋት መልሼ እከፍላችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር
\s5
\v 3 እኔ ራሴ የመንጋዬን ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ እሰበስባለሁ፣ ፍሬያማ ወደሚሆኑበትና ወደሚበዙበት ወደ መሠማሪያቸው እመልሳቸዋለሁ።
\v 4 ከዚያም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይፈሩና እንዳይደነግጡ የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ። ከእነርሱ አንዳቸውም አይጐድሉም፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 5 ተመልከቱ፣ ለዳዊት ጻድቅ ቅርንጫፍን የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር። እርሱም እንደ ንጉሥ ይገዛል፤ ብልፅግናን ያመጣል፣ በምድሪቱም ላይ ፍትህንና ጽድቅን ይፈጽማል።
\v 6 በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፣ እስራኤልም በአስተማማኝ ደህንነት ይቀመጣል። የሚጠራበትም ስም፦ እግዚአብሔር ጽድቃችን ነው ተብሎ ነው።
\s5
\v 7 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ ከእንግዲህ 'የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!' የማይባልበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 8 ይልቊን፣ 'የእስራኤልን ቤት የዘር-ሐረግ ከሰሜን ምድርና ከተሰደዱባቸው ምድሮች ሁሉ ያወጣና የመራ ሕያው እግዚአብሔርን!' ይባላል፤ እነርሱም በገዛ ራሳቸው ምድር ይቀመጣሉ።"
\s5
\v 9 ስለ ነቢያት፣ ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል፣ አጥንቶቼም ሁሉ ታውከዋል። ከእግዚአብሔር እና ከቅዱስ ቃሉም የተነሣ እንደ ሰካራም ሰው፣ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈውም ሆኛለሁ።
\v 10 ምድር በአመንዝሮች ተሞልታለችና። ከዚህ መርገም የተነሣ ምድር አለቀሰች። የምድረ በዳ ማሰማርያዎች ደርቀዋል። የእነዚህ ነብያት አካሄድ ክፉ ነው፤ ኃይላቸውም በትክክለኛው መንገድ ጥቅም ላይ አልዋለም።
\s5
\v 11 "ነብያትና ካህናትም ረክሰዋል። እንደውም፣ በቤቴ ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ! ይላል እግዚአብሔር።
\v 12 ስለዚህ መንገዳቸው በጨለማ እንዳለች ድጥ ስፍራ ትሆንባቸዋለች። እነርሱም ይገፈተሩበታል። በውስጧም ይወድቁባታል። እኔም በምቀጣቸው ዓመት ክፉ ነገርን እልክባቸዋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 13 በሰማርያ ነቢያት ላይ የሚያስቀይም ነገርን አይቻለሁ። በበኣል ትንቢት ይናገራሉ፣ ደግሞም ሕዝቤንም እስራኤልን ያስታሉ።
\v 14 በኢየሩሳሌምም ነቢያት ላይ የሚያስደነግጥ ነገሮችን አይቻለሁ፦ ያመነዝራሉ ደግሞም በሐሰት ይመላለሳሉ። የክፉ አድራጊዎችን እጅ ያበረታሉ፤ ማንም ከክፋቱ አልተመለሰም። ሁሉም እንደ ሰዶም ነዋሪዎቿም እንደ ገሞራ ሆኑብኝ!"
\v 15 ስለዚህ ነብያትን በተመለከተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና እሬትን አበላቸዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣቸዋለሁ።"
\s5
\v 16 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ትንቢት የሚናገሩላችሁን የነቢያትን ቃል አትሰሙ። ሐሰተኝነትን ያስተምሩአችኋል! ከእግዚአብሔር አፍ ሳይሆን ከገዛ አሳባቸው የወጣውን ራእይ ይናገራሉ።
\v 17 ያለማቋረጥ ለሚንቁኝ እንዲህ ይላሉ፣ 'እግዚአብሔር ሰላም ይሆንላችኋል ብሎአል።' በገዛ ራሱ የልብ እልከኝነት ለሚሄድ ሁሉ፣ 'ክፉ ነገር አያገኛችሁም።' ይላሉ።
\v 18 ይሁን እንጂ ቃሉን ያይና ይሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር የቆመ ማን ነው? ለቃሉ አትኩሮት ሰጥቶ የሰማ ያደመጠስ ማን ነው?
\s5
\v 19 ተመልከቱ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እየመጣ ያለ ዐውሎ ነፋስ አለ! የእርሱም ቍጣና የሚገለባብጥ ዐውሎ ነፍስ ወጥቶአል። በዓመፀኞች ራስ ላይ ይገለባበጣል።
\v 20 የእግዚአብሔር ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም። በመጨረሻው ዘመን፣ ትገነዘቡታላችሁ።
\s5
\v 21 እነዚህን ነብያት እኔ አልላክኋቸውም። በድንገት ተገኙ። ምንም አልነገርኳቸውም፣ ነገር ግን እንደዚያም ሆኖ ትንቢትን ተናገሩ።
\v 22 በምክሬ ግን ቆመው ቢሆን ኖሮ፣ ለሕዝቤ ቃሌን ባሰሙ ነበር፤ ከክፉም ቃሎቻቸው እንዲሁም ከብልሹ ሥራቸው በመለሱአቸው ነበር።
\s5
\v 23 እኔ የቅርብ አምላክ ብቻ ነኝ ደግሞም የራቀ አምላክ አይደለሁም? ይላል እግዚአብሔር።
\v 24 ሰው ላየው እንዳልችል በስውር ሊሸሸግ ይችላልን? ሰማይንና ምድርንስ አልሞላምን? ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 25 በስሜ ሐሰትን የሚናገሩት የነብያት ያሉትን ነገር ሰምቻለሁ። እነርሱም 'ህልም አልሜ ነበር! ህልም አልሜ ነበር!' ብለዋል።
\v 26 ሐሰትን ከአሳባቸው በሚተነብዩ፣ የልባቸውንም ማታለል በሚተነብዩ ነቢያት ይህ የሚቀጥለው እስከ መቼ ነው?
\v 27 በሚናገሯቸው ሕልሞች ሕዝቤ ስሜን እንዲረሳ ለማድረግ ያቅዳሉ፣ እያንዳንዱ ለጎረቤቱ ልክ አባቶቻቸው ለበኣል ሲሉ ስሜን እንደ ረሱ ያደርጋሉ።
\s5
\v 28 የሚያልም ነቢይ ሕልሙን ይናገር። ነገር ግን ቃሌን የነገርኩት፣ ቃሌን በእውነተኝነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል እግዚአብሔር።
\v 29 ቃሌ እንደ እሳት፣ ድንጋዩም እንደሚያደቅቅ መዶሻ አይደለችምን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 30 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ እኔ ቃልን ከሌላኛው ሰው ሰርቆ ቃሉ ከእኔ ዘንድ መጥቷል በሚሉት ነብያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 31 ተመልከቱ፣ ትንቢትን ለማወጅ ምላሳቸውን በሚጠቀሙት ነብያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 32 ተመልከቱ፣ በሐሰት በሚያልሙ፣ ከዚያም በሚናገሩትና በዚህም መልኩ በሐሰታቸውና በትምክህታቸውም ሕዝቤን በሚያስቱ በነቢያት ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር። እኔም አልላክኋቸውምና ትእዛዛትንም አልሰጠኋቸውምና በእነርሱ ላይ ነኝ። ስለዚህም ለዚህ ሕዝብ በእርግጥም አይጠቅሟቸውም ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 33 ይህ ሕዝብ ወይም ነቢይ ወይም ካህን፣ 'የእግዚአብሔር ዐዋጅ ምንድር ነው?' ብለው ቢጠይቊህ፣ 'እናንተን ትቻችኋለሁና የምን ዐዋጅ ነው?' ይላል እግዚአብሔር ልትላቸው ይገባል።
\v 34 'የእግዚአብሔር ዐዋጅ ይህ ነው፣' የሚሉትን ነብያትን፣ ካህናትን እና ሕዝቡን በተመለከተ፣ ያን ሰውና ቤቱን እቀጣለሁ።
\s5
\v 35 እያንዳንዱ ሰው ለጎረቤቱ፣ እንዲሁም እያንዳንዱ ሰው ለወንድሙ፣ 'እግዚአብሔር የመለሰው ምንድር ነው?' ደግሞስ 'እግዚአብሔር ምን ዐወጀ?' ማለትህን ቀጥል።
\v 36 ከእያንዳንዱ ሰው የሆነው እያንዳንዱ ዐዋጅ የገዛ ራሱ መልእክት ይሆንበታልና፣ እንዲሁም የሕያው እግዚአብሔርን ቃል ለውጣችኋልና፣ ስለ እግዚአብሔር ዐዋጅ ከእንግዲህ ልትናገሩ አይገባችሁም።
\s5
\v 37 ለነቢዩ የምትጠይቀው ይህንን ነው፣ 'እግዚአብሔር ምን መለሰልህ? እግዚአብሔር ምን ዐወጀ?'
\v 38 ከዚያም፣ ከእግዚአብሔር የሆነውን ዐዋጅ ትናገራለህ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ይህንን ይላል፣ "ይህ የእግዚአብሔር ዐዋጅ ነው አትበሉ።" ብዬ ትእዛዝን የላክሁባችሁ ቢሆንም፣ እናንተ ግን "የእግዚአብሔር ዐዋጅ ይኸውላችሁ፣" አላችሁ።
\v 39 ስለዚህም፣ ተመልከቱ፣ አንሥቻችሁ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ከሰጠሁት ከተማ ጋር ከእኔ ዘንድ ልወረውራችሁ ነው።
\v 40 ከዚያም የማይረሳ ዘላለማዊ እፍረትን እና ስድብን አኖርባችኋለሁ።"
\s5
\c 24
\p
\v 1 እግዚአብሔር አንድ ነገር አሳየኝ። እነሆ፣ በእግዚአብሔር መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር። (ይህ ራእይ የታየው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፣ የይሁዳንም አለቆች፣ ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ ነበር።)
\v 2 በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደበሰለ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ ነገር ግን በሁለተኛው ቅርጫት ውስጥ ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት።
\v 3 እግዚአብሔርም፣ "ኤርምያስ ሆይ፣ ምንታያለህ?" አለኝ። እኔም፣ "በለስን። እጅግ መልካም የሆነ በለስ፣ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ በለስ አያለሁ።" አልሁ።
\s5
\v 4 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 5 "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንደዚህ እንደ መልካሙ በለስ፣ እንዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድሁትን የይሁዳን ምርኮ ለጥቅማቸው እመለከተዋለሁ።
\v 6 ዓይኔንም ለመልካም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፣ ወደዚህችም ምድር እመልሳቸዋለሁ። እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም። እተክላቸዋለሁ፣ እንጂ አልነቅላቸውም።
\v 7 ከዚያም፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ እንዲመለሱ፣ ሕዝብ ይሆኑኛል፣ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
\s5
\v 8 ነገር ግን ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉው በለስ፣ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አለቆቹንም በዚህችም አገር የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቅሬታ በግብጽም አገር የሚቀመጡትን እጥላቸዋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 9 በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ፣ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆኑ ዘንድ በምድር መንግሥታት ሁሉ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
\v 10 ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ከሰጠኋቸው ምድር እስኪጠፉ ድረስ በመካከላቸው ሰይፍንና ራብን፣ ቸነፈርንም እሰድዳለሁ።"
\s5
\c 25
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት፣ ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 2 ይህንም ቃል ነቢዩ ኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ።
\s5
\v 3 "ከይሁዳ ንጉሥ ከአሞጽ ልጅ ከኢዮስያስ አሥራ ሦስተኛው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ባሉት በእነዚህ በሀያ ሦስቱ ዓመታት፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ ሲመጣ ነበር። እነግራችሁም ነበር። እነግራችሁ ነበር፣ ነገር ግን አልሰማችሁም።
\v 4 እግዚአብሔርም ባርያዎቹን ነቢያትን ሁሉ ወደ እናንተ ላከ። እነርሱም ለመውጣት ጉጉዎች ነበሩ፣ ነገር ግን እናንተ አላደመጣችሁም ትኩረትም አልሰጣችሁትም።
\s5
\v 5 እነዚህ ነብያት፣ 'እያንዳንዱ ሰው ከክፉ መንገዱና ከሥራችሁ ብልሹነት ተመለሱና እግዚአብሔር ከጥንት ጊዜያት ጀምሮ ቋሚ ስጦታ አድርጎ ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣችሁ ምድር ተቀመጡ።
\v 6 ታመልኩአቸው፣ ትሰግዱላቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፣ ክፉም እንዳያደርግባችሁ በእጃችሁ ሥራ አታስቈጡኝ አለ።
\s5
\v 7 ለእናንተ ጕዳት እንዲሆን በእጃችሁ ሥራ ታስቈጡኝ ዘንድ አልሰማችሁኝም፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 8 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ቃሌን አልሰማችሁምና፣
\v 9 ተመልከቱ፣ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባርያዬ ከሆነው ከባቢሎን ንጉሥ ናብከደነዖር ጋር ለመሰብሰብ ትእዛዝን እልካለሁ፤ በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች፣ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ። ለማጥፋትም እለያቸዋለሁ። ለመጨነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
\s5
\v 10 ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ፣ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አጠፋለሁ።
\v 11 ከዚያም ይህች ምድር ሁሉ ባድማና መደነቂያ ትሆናለች፣ ከዚያም እነዚህ አሕዛብ ለባቢሎን ንጉሥ ሰባ ዓመት ይገዛሉ።
\s5
\v 12 ሰባው ዓመትም የሚፈጸምበት ጊዜ ይመጣል፣ የባቢሎንን ንጉሥና ያንን ሕዝብ፣ የከለዳውያንን ምድር ስለ ኃጢአታቸው እቀጣለሁ፣ የማያበቃ ባድማ አደርጋታለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 13 በዚያችም ምድር ላይ የተናገርሁትን ቃሌን ሁሉ፣ እንዲሁም፣ ኤርምያስ በአሕዛብ ሁሉ ላይ የተነበየውን በዚህች መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ በዚያች ምድር አመጣለሁ።
\v 14 ብዙ ሌሎች አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ከእነዚህ ሕዝቦች ውስጥ ባርያዎችን ያደርጋሉ። እኔም ስለ አደራረጋቸውና ስለ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።"
\s5
\v 15 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፣ አንተን ለምሰድድባቸው አሕዛብ ሁሉ አጠጣቸው።
\v 16 ከምሰድድባቸውም ሰይፍ የተነሣ ይጠጣሉ፣ ይሰናከላሉ፣ በእብደት ይለፈልፋሉ።
\s5
\v 17 ስለዚህ ጸዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ወሰድሁ፣ ከዚያም እግዚአብሔርም እኔን ለላከባቸው አሕዛብ ሁሉ አጠጣኋቸው።
\v 18 በዚህ ዛሬ እንደሆኑት ሁሉ ባድማና መደነቂያ፣ ማፍዋጫም፣ እርግማንም አደርጋቸው ዘንድ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣ ነገሥታትዋንም፣ አለቆችዋንም አጠጣኋቸው።
\s5
\v 19 ሌሎች ሕዝቦችም እንዲሁ ሊጠጡት ይገባል፦ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖንና ባርያዎቹ፤ አለቆቹና ሕዝቦቹ ሁሉ፤
\v 20 የተደባለቀ ቅርስ ሕዝቦች ሁሉ፣ የዖፅ ምድር ነገሥታት ሁሉ፣ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፣ አስቀሎና፣ ጋዛ፣ አቃሮን የአዞጦን ቅሬታ ሁሉ፤
\v 21 ኤዶምያስ፣ ሞዓብ፣ እና የአሞንም ሕዝቦች፤
\s5
\v 22 የጢሮስና ሲዶና ነገሥታ፣ በባህሩ ማዶ ያለች የደሴት ነገሥታትም፣
\v 23 ድዳን፣ ቴማን፣ ቡዝን፣ በራሳቸው ጎንና ጎን ጠጕራቸውን የሚቈርጡትን ሁሉ።
\s5
\v 24 እነዚህም ሕዝቦች እንዲሁ ሊጠጡት ይገባል፦ የዓረብ ነገሥታት ሁሉ፣ በምድረ በዳ የሚኖሩት የድብልቅ ቅርስ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣
\v 25 የዘምሪ ነገሥታት ሁሉ፣ የኤላም ነገሥታት ሁሉ፣ የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፤
\v 26 የቀረቡና የራቁ፣ አንዱ ከሌላው ጋር ያሉ የሰሜን ነገሥታትንም ሁሉ፣ በምድር ገጽ ላይ ያሉ የዓለም መንግሥታት ሁሉ አጠጣኋቸው። በመጨረሻም፣ የባቢሎን ንጉሥ ከእነርሱ በኋላ ይጠጣል።
\s5
\v 27 "'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመካከላችሁ ከምሰድደው ሰይፍ የተነሣ ጠጡ፣ ስከሩ፣ አስታውኩ፣ ውደቁ፣ ከእንግዲህም ወዲህ አትነሡ' በላቸው፤ አለኝ።
\v 28 እንዲጠጡ ጽዋውን ከእጅህ ለመቀበል እንቢ ቢሉ፣ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በእርግጥ ትጠጡታላችሁ፤ በላቸው።
\v 29 ተመልከቱ፣ ስሜ በተጠራባት ከተማ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፣ እናንተ ራሳችሁ ያልተቀጣችሁ ትሆናላችሁን? በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ሰይፍን እጠራለሁና ከቅጣት ነፃ አትሆኑም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።'
\s5
\v 30 ስለዚህ፣ አንተ ራስህ፣ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ትተነብይባቸዋለህ፣ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ 'እግዚአብሔር ከበላይ ሆኖ ይጮኻል፣ ከቅዱስ ማደሪያውም ሆኖ ድምፁን ያሰማል። በማደሪያው ላይ እጅግ ይጮኻል፣ ወይንን ሲሚጠምቁ እንደሚዘምሩት በምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ይጮኻል።
\v 31 እግዚአብሔር ከአሕዛብ ጋር ክርክር አለውና ድምፅ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይደርሳል። ከሥጋ ለባሽ ሁሉ ጋር በፍትህ ይፋረዳል። ኃጢአተኞችንም ለሰይፍ አሳልፎ ይሰጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።'
\s5
\v 32 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ጥፋት ከሕዝብ ወደ ሕዝብ ይወጣል፣ ደግሞም ጽኑም ዐውሎ ነፍስ ከሩቅ የምድር ዳርቻ ይነሣል።
\v 33 ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ግዳዩች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበዛሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ አይሰበሰቡም፣ ወይም አይቀበሩም። በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።
\s5
\v 34 እረኞች አልቅሱ፣ ለእርዳታም ጩኹ! በመንጋው ውስጥ አውራ የሆናችሁት ሕዝቦች በመሬት ላይ ተንከባለሉ። ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ መጥቷልና። እንደ ተመረጡ በጎች ትወድቃላችሁ።
\v 35 ወደእረኞች ለመሸሸግ ማምለጥ ይቀራል።
\v 36 እግዚአብሔር ማሰማርያቸውን አጥፍቶአልና የእረኞች ጩኸት ድምፅ፣ የመንጋ አውራዎችም ልቅሶ ሆኖአል።
\s5
\v 37 ከእግዚአብሔር ጽኑ ቊጣ የተነሣ የሰላም ማሰማሪያ ይፈርሳል።
\v 38 እንደ ታዳጊ አንበሳ መደቡን ለቅቆአል፣ ከአስጨናቂውም ሰይፍና ከጽኑ ቍጣው የተነሣ ምድራቸው አስፈሪ ሆናለችና።"
\s5
\c 26
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ መጣና እንዲህ አለ፣
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በቤቴ አደባባይ ቁም፣ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ንገራቸው። እንድትነግራቸው ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ንገራቸው። አንዲትም ቃል አትጉደል!
\v 3 ምናልባት ይሰሙ፣ ከክፉ መንገዳቸውም ይመለሱ ይሆናል፤ እኔም ስለ ሥራቸው ክፋት ያሰብሁባቸውን ክፉ ነገር እተዋለሁ።
\s5
\v 4 ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በፊታችሁ በሰጠኋት ሕጌ ትሄዱ ዘንድ ባትሰሙኝ፣
\v 5 በጽናት ወደ እናንተ የላክኋቸውን የባሪያዎቼን የነቢያትን ቃል ባትሰሙ፣ ነገር ግን አላደመጣችኋቸውም!
\v 6 ያኔ ይህንን ቤት እንደ ሴሎ አደርገዋለሁ፤ ይህችንም ከተማ ለምድር አሕዛብ ሁሉ እርግማን አደርጋታለሁ።"
\s5
\v 7 ኤርምያስ በእግዚአብሔር ቤት ይህንን ቃል ሲናገር ካህናቱ፣ ነቢያቱ፣ ሕዝቡም ሁሉ ሰሙ።
\v 8 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር ሁሉ በፈጸመ ጊዜ፣ ካህናት፣ ነቢያትና ሕዝቡም ሁሉ፣ ያዙትና "በእርግጥ ትሞታለህ!
\v 9 በእግዚአብሔር ስም ተንብየህ ይህ ቤት እንደ ሴሎ ይሆናል፣ ይህችም ከተማ ነዋሪ የማይገኝባት ወና ትሆናለች ብለህ ለምን ትንቢት ተናገርህ?" አሉት። ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በኤርምያስ ላይ በዐመጽ ተሰብስበው ነበር።
\s5
\v 10 ከዚያም የይሁዳ አለቆች ይህን ሰሙና ከንጉሥ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄዱ። በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ።
\v 11 ካህናቱና ነብያቱም ለአለቆቹና ለሕዝቡ ሁሉ ተናገሩ። እንዲህም አሉ፣ "በጆሮአችሁ እንደ ሰማችሁ በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት ተናግአልና ይህ ሰው ሞት የሚገባው ነው!" አሉ።
\v 12 ስለዚህ ኤርምያስ ለአለቆችና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ "በሰማችሁት ቃል ሁሉ፣ በዚህች ቤትና በዚህች ከተማ ላይ ትንቢት እናገር ዘንድ እግዚአብሔር ልኮኛል።
\s5
\v 13 አሁንም መንገዳችሁንና ሥራችሁን አሳምሩ፣ እግዚአብሔርም የተናገረባችሁን ጥፋት እንዲተው፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ድምፅ ስሙ።
\v 14 ተመልከቱኝ! እኔ ራሴ በእጃችሁ ነኝ። በዐይናችሁ ፊት መልካምና ቅን የመሰላችሁን አድርጉብኝ።
\v 15 ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነት እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚህች ከተማ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በእርግጥ እወቁ።"
\s5
\v 16 አለቆቹና ሕዝቡም ሁሉ ለካህናትና ለነቢያት፣ "ይህ ሰው በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ተናግሮናልና ሊሞት አይገባውም" አሉ።
\v 17 ከዚያም ከምድሪቱ ሽማግሌዎች ሰዎች ተነሥተው ለመላው የሕዝቡ ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ።
\s5
\v 18 እነርሱም፣ "ሞሬታዊው ሚክያስ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ዘመን ይተነብይ ነበረ። ለይሁዳም ሕዝብ ሁሉ ተንብዮ 'የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጽዮን እንደ እርሻ ትታረሳለች፣ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች፣ የቤተመቅደሱም ተራራ እንደ ዱር ከፍታ ይሆናል' ብሎ ተናገረ።
\v 19 በውኑ የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስና ሕዝቡ ሁሉ ገደሉትን? በውኑ እግዚአብሔርን አልፈራምን? ወደ እግዚአብሔርስ አልተማለሉምን? እግዚአብሔርስ የተናገረባቸውን ክፉ ነገር አይተውምን? እኛም በገዛ ሕይወታችን ላይ ታላቅ ክፋት እናደርጋለንን?"
\s5
\v 20 ደግሞም በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገረ አንድ ሰው ነበረ፣ እርሱም የቂርያትይዓሪም ሰው የሸማያ ልጅ ኦርዮ ይባል ነበር፤ በዚህችም ከተማ በዚህችም ምድር ላይ ከኤርምያስ ቃል ጋር የተስማማ ትንቢት ተናገረ።
\v 21 ነገር ግን ንጉሡ ኢዮአቄም እና ወታደሮቹ ሁሉ እንዲሁም አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ሞከረ፤ ነገር ግን ኦርዮም ይህን ሲሰማ ፈርቶ ሸሸ ወደ ግብጽም ገባ።
\s5
\v 22 ንጉሡም ኢዮአቄም የዓክቦርን ልጅ ኤልናታንን ከእርሱም ጋር ሌሎችን ሰዎች ወደ ግብጽ ላካቸው፤
\v 23 ኦርዮንን ከግብጽ አውጥተው ወደ ንጉሡ ኢዮአቄም ይዘውት መጡ። ከዚያም ኢዮአቄም በሰይፍ ገደለውና ሬሳውን ተራ በሆኑ ሰዎች መቃብር ውስጥ ጣለው።
\v 24 ነገር ግን በሕዝቡ እጅ እንዳይሰጥና እንዳይገድሉት የሳፋን ልጅ የአኪቃም እጅ ከኤርምያስ ጋር ነበረች።
\s5
\c 27
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም መንግሥት መጀመሪያ ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ።
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፣ "እስራትና ቀንበር ለራስህ ሥራ። በአንገትህም ላይ አድርግ።
\v 3 ከዚያም ወደ ይሁዳ ንጉሥም ወደ ሴዴቅያስ፣ ወደ ኢየሩሳሌም በመጡት መልእክተኞች እጅ ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፣ ወደ ሞዓብም ንጉሥ፣ ወደ አሞንም ልጆች ንጉሥ፣ ወደ ጢሮስም ንጉሥ፣ ወደ ሲዶናም ንጉሥ ላካቸው።
\v 4 ለጌቶቻቸውም እንዲነግሩ እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ 'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለጌቶቻችሁ ልትነግሯቸው የሚገባው ይህንን ነው፣
\s5
\v 5 እኔ ራሴ ምድሪቱን በታላቅ ኃይሌና በተዘረጋችው ክንዴ ፈጥሬአለሁ። በምድርም ፊት ላይ ያሉትን ሰዎችንና እንስሶችን ጭምር ፈጥሬያለሁ። በዐይኔም ዘንድ ትክክል ለሆነው ለማንኛውም ሰው እሰጣታለሁ።
\v 6 አሁንም፣ እነዚህን ምድሮች ሁሉ ለባርያዬ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣታለሁ። እንዲሁም ያገለግሉት ዘንድ በሜዳዎች ያሉትን ሕያዋን ነገሮችን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።
\v 7 የገዛ ራሱም ምድር ፍጻሜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጅ ልጅ ልጁም ይገዛሉ። ከዚያም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እርሱን ያስገዙታል።
\s5
\v 8 ለባቢሎን ንጉሥም ለናቡከደነፆር የማያገለግለውን፣ ከባቢሎንም ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የማያደርገውን ሕዝብና መንግሥት፣ ያን ሕዝብ በእጁ እስካጠፋው ድረስ በሰይፍና በራብ፣ በመቅሰፍትም እቀጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 9 እናንተ ደግሞ! 'ለባቢሎን ንጉሥ አታገልግሉ' የሚሉአችሁን ነቢያቶቻችሁን፣ ሟርተኞቻችሁን፣ ሕልም አላሚዎቻችሁንና ቃላተኞቻችሁን፣ መተተኞቻችሁንም መስማት አቊሙ።
\v 10 ከምድራቸሁ አርቀው ሊልኳችሁ፣ እኔም እንዳሳድዳችሁ፣ እናንተም እንድትሞቱ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና።
\v 11 ነገር ግን ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገቱን ዝቅ የሚያደርገውንና የሚያገለግለውን ሕዝብ በአገሩ ላይ እተዋቸዋለሁ፤ እነርሱም ያርሱአታል ቤቶችንም ይሠሩባታል።"
\s5
\v 12 ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስም በዚህ ቃል ተናገርሁ ይህንንም መልእክት ሰጠሁት፣ "ከባቢሎን ንጉሥ ቀንበር በታች አንገታችሁን ዝቅ አድርጉና ለእርሱና ለሕዝቡ አገልግሉ፣ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
\v 13 ለባቢሎን ንጉሥ ይገዛ ዘንድ እንቢ ስላለ ሕዝብ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ፣ አንተና ሕዝብህ በሰይፍና በራብ በመቅሰፍትም ለምን ትሞታላችሁ?
\s5
\v 14 ሐሰተኛን ትንቢት ይናገሩላችኋልና፣ 'ለባቢሎን ንጉሥ አታገልግሉ' የሚሉአችሁን የነቢያትን ቃል አትስሙ።
\v 15 'እኔ አልላክኋቸውምና፤ ነገር ግን እኔ እንዳሳድዳችሁ፣ እናንተና ትንቢት የሚናገሩላችሁ ነቢያትም እንድትጠፉ በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገራሉ፣' ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 16 ይህንን ለካህናትና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተንብየውላችሁ 'ተመልከቱ! የእግዚአብሔር ቤት ዕቃ አሁን ከባቢሎን ይመለሳል!' የሚሉአችሁን የነቢያቶቻችሁን ቃል አትስሙ። እነርሱ ውሸትን ይተነብዩላችኋል።
\v 17 እነርሱንም አትስሟቸው። የባቢሎንን ንጉሥ ልታገለግሉና በሕይወት ልትኖሩ ይገባችኋል። ይህችስ ከተማ ስለ ምን ባድማ ትሆናለች?
\v 18 እነርሱ ግን ነቢያት ከሆኑ፣ የእግዚአብሔርም ቃል በእውነት ወደእነርሱ ቢመጣ፣ በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም የቀረችው ዕቃ ወደ ባቢሎን እንዳትሄድ ወደ ሠራዊት ጌታ ወደ እግዚአብሔር ይለምኑ።
\s5
\v 19 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ከበርቴዎች ሁሉ ማርኮ
\v 20 ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ባፈለሳቸው ጊዜ ስላልወሰዳቸው ዓምዶች ስለ ኵሬውም፣ ስለ መቀመጫዎቹም በዚህችም ከተማ ስለ ቀረች ዕቃ ሁሉ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\s5
\v 21 በእግዚአብሔር ቤትና በይሁዳ ንጉሥ ቤት በኢየሩሳሌምም ስለ ቀረችው ዕቃ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣
\v 22 'እነርሱ ወደ ባቢሎን ትወሰዳለች እስከምጐበኛትም ቀን ድረስ በዚያ ትኖራለች፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ከዚያም አወጣታለሁ ወደዚህም ስፍራ እመልሳታለሁ።"
\s5
\c 28
\p
\v 1 በዚያም ዓመት በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ በአራተኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ነቢዩ የገባዖን ሰው የዓዙር ልጅ ሐናንያ በእግዚአብሔር ቤት በካህናትና በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረኝ።
\v 2 "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ይናገራል፣ የባቢሎን ንጉሥ ያኖረውን ቀንበር ሰብሬአለሁ።
\s5
\v 3 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከዚህች ስፍራ ወደ ባቢሎን ያጋዛትን የእግዚአብሔርን ቤት የሆኑትን ዕቃዎች ሁሉ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደዚህች ስፍራ እመልሳታለሁ።
\v 4 ከዚያም ወደ ባቢሎንም የሄዱትን የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንንና የይሁዳን ምርኮ ሁሉ ወደዚህች ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ የባቢሎንን ንጉሥ ቀንበር እሰብራለሁና።"
\s5
\v 5 ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በእግዚአብሔር ቤት በቆሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለነቢዩ ሐናንያ ተናገረ።
\v 6 ነብዩም ኤርምያስ እንዲህ አለ፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ያድርግ! የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ምርኮውንም ሁሉ ከባቢሎን ወደዚህ ስፍራ በመመለስ እግዚአብሔር የተናገረውን ትንቢት ይፈጽም።
\v 7 ይሁን እንጂ፣ በጆሮህና በሕዝብህ ጆሮ ሁሉ የምናገረውን ይህን ቃል ስማ።
\s5
\v 8 ከጥንት ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩ ነብያት በብዙ አገርና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ሰልፍና ስለ ክፉ ነገር፣ ስለ መቅሰፍትም ትንቢት ተናገሩ።
\v 9 ስለዚህም ሰላም እንደሚኖር የተናገረ ነቢይ፣ የነቢዩ ቃል በተፈጸመ ጊዜ፣ ያኔ እግዚአብሔር በእውነት የሰደደው ነቢይ እንደ ሆነ ይታወቃል።"
\s5
\v 10 ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ወስዶ ሰበረው።
\v 11 ከዚያም ሐናንያ በሕዝብ ሁሉ ፊት፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ልክ እንደዚሁ፣ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ" አለ። ከዚያም ነብዩ ኤርምያስ መንገዱን ሄደ።
\s5
\v 12 ነቢዩም ሐናንያ ቀንበሩን ከነቢዩ ከኤርምያስ አንገት ከሰበረ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 13 "ሂድና ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ የእንጨት ቀንበርን ሰብረሃል፣ እኔ ግን በእርሱ ፋንታ የብረትን ቀንበር እሠራለሁ።'
\v 14 የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እንዲያገለግሉ የብረትን ቀንበር በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ አንገት ላይ አድርጌአለሁ። እነርሱም ያገለግሉታል። እንዲገዛቸውም የምድረ በዳ አራዊትን ደግሞ ሰጥቼዋለሁ።"
\s5
\v 15 ቀጥሎ፣ ነብዩ ኤርምያስ ነብዩን ሐናንያን፣ "ሐናንያ ሆይ፣ አድምጥ! ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል እንጂ እግዚአብሔር አልላከህም።
\v 16 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት ከምድር ላይ እሰድድሃለሁ። በእግዚአብሔር ላይ ዐመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ።" አለው።
\v 17 ነብዩም ሐናንያ በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ሞተ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ነቢዩ ኤርምያስ ከምርኮ ሽማግሌዎች መካከል ወደ ተረፉት፣ ወደ ካህናቱም፣ ወደ ነቢያቱም፣ ናቡከደነፆር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ማርኮ ወዳፈለሰውም ሕዝብ ሁሉ ከኢየሩሳሌም የላከው የደብዳቤው ቃል ይህ ነው።
\v 2 ይህም የሆነው ንጉሡ ኢኮንያን፣ እቴጌይቱ እናቱ፣ ከፍተኛ መኮንኖቹ፣ የይሁዳና የኢየሩሳሌም አለቆች፣ ጠራቢዎችና ብረት ሠራተኞችም ከኢየሩሳሌም ከወጡ በኋላ ነው።
\v 3 ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን እንዲህ ሲል ላከው።
\s5
\v 4 ጥቅሉ እንዲህ ይላል፣ "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ላስማረክኋቸው ምርኮኞች ሁሉ እንዲህ ይላል፣
\v 5 'ቤት ሠርታችሁ ኑሩባቸው፣ አታክልትም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ፤
\s5
\v 6 ሚስቶችን ውሰዱ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፤ ከዚያም ለወንዶች ልጆቻችሁ ሚስቶችን ውሰዱ፣ ሴቶች ልጆቻችሁንም ለባሎቻቸው ስጡ። እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ።
\v 7 በእርስዋም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፣ ከእኔ ዘንድ ማልዱ።'
\s5
\v 8 የእስራኤልም አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'በመካከላችሁ ያሉት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፣ እናንተም ራሳችሁ የምታልሙትን ሕልም አትስሙ።
\v 9 በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና። እኔም አልላክኋቸውም። ይላል እግዚአብሔር።'
\s5
\v 10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ባቢሎን ለሰባ ዓመታት በገዛቻችሁ ጊዜ፣ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ እረዳችኋለሁ፣ ደግሞም መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
\v 11 ለእናንተ የማስባትን አሳብ እኔ ራሴ አውቃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ፍጻሜና ተስፋ እሰጣችሁ ዘንድ የሰላም አሳብ ነው እንጂ የጥፋት አይደለም።
\s5
\v 12 እናንተም ወደ እኔ ትጠራላችሁ፣ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፣ እኔም እሰማችኋለሁ።
\v 13 እናንተ ትሹኛላችሁ፣ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።
\v 14 ከእናንተም ዘንድ እገኛለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፤ ከአሕዛብም ሁሉ ዘንድ እናንተንም ከበተንሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።'
\s5
\v 15 እናንተም፣ እግዚአብሔር በባቢሎን ነቢያትን አስነሥቶልናል ብላችኋልና፣
\v 16 እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ስለ ተቀመጠ ንጉሥ፣ በዚያች ከተማ ለቆዩት ሕዝቦች ሁሉ፣ ከእናንተም ጋር ስላልተማረኩት ወንድሞቻችሁ፣ እንዲህ ይላል።
\v 17 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ሰይፍንና ራብን፣ በሽታንም እሰድድባቸዋለሁ። ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉ በለስ አደርጋቸዋለሁ።
\s5
\v 18 በሰይፍም፣ በራብም፣ በመቅሠፍትም አሳዳድዳቸዋለሁ፣ ባሳደድሁባቸውም አሕዛብ ሁሉ ዘንድ ለመጠላት፣ ለመደነቂያ፣ ለማፍዋጫም፣ ለመሰደቢያም እንዲሆኑ በምድር መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለመበተን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
\v 19 ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በማለዳ ተነሥቼ ባሪያዎቼን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፤ በተደጋጋሚ ላክኋቸው፣ እናንተ ግን አልሰማችሁም፣ ይላል እግዚአብሔር።'
\s5
\v 20 ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ ሆይ፣ እናንተ ራሳችሁ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣
\v 21 'የእስራኤል አምላክ፣ እኔ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ስለሚናገሩላችሁ ስለ ቆላያ ልጅ ስለ አክዓብና ስለ መዕሤያ ልጅ ስለ ሴዴቅያስ እንዲህ እላለሁ፦ ተመልከቱ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። በዓይኖቻችሁም ፊት ይገድላቸዋል።
\s5
\v 22 ከዚያም በባቢሎን ያሉ የይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ ስለ እነዚህ ሰዎች እርግማንን ይናገራሉ። እርግማኑም፦ እግዚአብሔር የባቢሎን ንጉሥ በእሳት እንደ ጠበሳቸው እንደ ሴዴቅያስና እንደ አክዓብ ያድርግህ የሚል ነው።
\v 23 በእስራኤል ዘንድ ስንፍና አድርገዋልና፣ ከጎረቤቶቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፣ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና ይህ ይሆናል። እኔም አውቃለሁ ምስክርም ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 24 "ለኔሔላማዊው ለሸማያ እንዲህ በል፦
\v 25 'የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ወዳለው ሕዝብ ሁሉ፣ ወደ ካህኑም ወደ መዕሤያ ልጅ ወደ ሶፎንያስ፣ ወደ ካህናቱም ሁሉ ደብዳቤዎችን በገዛ ስምህ እንዲህ ስትል ልከሃል፣
\v 26 "እያበደ ትንቢት የሚናገርን ሰው ሁሉ በእግር ግንድና በሠንሰለት ታኖረው ዘንድ በእግዚአብሔር ቤት አለቃ እንድትሆን እግዚአብሔር በካህኑ በዮዳሄ ፋንታ ካህን አድርጎሃል።
\s5
\v 27 አሁንስ፣ ትንቢት ተናጋሪውን የዓናቶቱን ሰው ኤርምያስን ስለ ምን አትገሥጸውም?
\v 28 እርሱ፣ 'ጊዜው የረዘመ ነው። ቤት ገንቡና በውስጡ ኑሩበት፣ አትክልትንም ተክላችሁ ፍሬዋን ብሉ' ብሎ ወደ እኛ ወደ ባቢሎን ልኮአል።"
\v 29 ካህኑም ሶፎንያስ ይህን ደብዳቤ ነብዩ ኤርምያስ እየሰማ አነበበው።
\s5
\v 30 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 31 "'እግዚአብሔር ስለ ኔሔላማዊው ስለ ሸማያ እንዲህ ይላል፣ ብለህ ወደ ምርኮኞች ሁሉ ላክ፦ 'እኔ ሳልልከው ሸማያ ትንቢት ተናግሮላችኋልና፣ በሐሰትም እንድትታመኑ አድርጎአችኋልና፤
\v 32 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ ኔሔላማዊውን ሸማያንና ዘሩን እቀጣለሁ። እኔም የማደርግላችሁን መልካሙን ነገር የሚያይ አንድም የእርሱ ሰው በመካከላችሁ አይኖርም። ለሕዝቤ የማደርገውን አንዱንም መልካም ነገር አያይም ይላል እግዚአብሔር። እርሱ በእኔ፣ በእግዚአብሔር ላይ በእምነት ያልሆነ ነገርን ተናግሯልና።"
\s5
\c 30
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣
\v 2 "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የነገርኩህን ቃል ሁሉ በጥቅልል ላይ ጻፈው።
\v 3 ተመልከት፣ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስባት ዘመን ይመጣልና፣ ይላል እግዚአብሔር። ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፣ እነርሱም ይገዙአታል።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣
\v 5 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የሚያስፈራ ድምፅ ሰምተናል፤ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም።
\s5
\v 6 ጠይቁ፣ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ። እያንዳንዱ ወጣት ሰው እጁን በወገቡ ላይ ያደረገው ለምንድነው? እንደ ወላድ ሴት፣ ፊታቸው ሁሉ ወደ ጥቁረት የተለወጠው ለምንድነው?
\v 7 ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ይሆናልና፣ እርሱንም የሚመስል የለምና። ያ የያዕቆብ የመከራ ዘመን ነው፣ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል።
\s5
\v 8 በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፣ እስራትህንም እበጥሳለሁ፣ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለሌላ አትገዛም።
\v 9 ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ በእነርሱ ላይ ንጉሥ ለማደርግላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ያገለግላሉ።
\s5
\v 10 ስለዚህ፣ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ፣ አትደንግጥ። ተመልከቱ፣ አንተን ከሩቅ፣ ዘርህንም ከምርኮ አገር አድናለሁና። ያዕቆብም ይመለሳል ሰላምም ይሆናል፤ ደህንነቱም ይጠበቃል፣ ከዚያም በኋላ ማንም አያስፈራውም።
\v 11 አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፣ ይላል እግዚአብሔር። አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብ ፍጹም ማብቂያቸው እንዲመጣ አደርጋለሁ። አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፣ በፍትህ እቀጣሃለሁ፣ ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።'
\s5
\v 12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስብራትህ የማይፈወስ፣ ቍስልህም ያመረቀዘ ነው።
\v 13 ጉዳይህን የሚሟገትልህ የለም፣ ቍስልህንም የሚፈውስ መድኃኒት የለህም።
\s5
\v 14 አፍቃሪዎችሽ ሁሉ ረስተውሻል። አይፈልጉሽምም፣ በደልሽ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትሽም ስለ በዛ፣ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ አሠሪ ቅጣት አቍስዬሻለሁና።
\v 15 ሕመምሽ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትሽ ለምን ትጮያለሽ? በደልሽ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትሽም ስለ በዛ፣ ይህን አድርጌብሻለሁ።
\s5
\v 16 ስለዚህ የሚበሉሽ ሁሉ ይበላሉ፣ ጠላቶችሽም ሁሉ ወደ ምርኮ ይወሰዳሉ። የዘረፉሽም ይዘረፋሉ፣ የበዘበዙሽንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ።
\v 17 እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ይህንንም የማደርገው፦ ማንም የማይሻት፤ የተጣለች ጽዮን" ብለው ጠርተውሻልና።
\s5
\v 18 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ለቤቱም እራራለሁ። ከተማይቱም በፍርስራሽ ጉብታዋ ላይ ትሠራለች፣ ምሽጉም እንደ ዱሮው ይሆናል።
\v 19 ከዚያም ከእርሱ ዘንድ የምስጋናና የዘፋኞች ድምፅ ይወጣል፣ እኔም አበዛቸዋለሁ አላሳንሳቸውም፤ እንዳይዋረዱ እኔ አከብራቸዋለሁ።
\s5
\v 20 ከዚያም ሕዝቦቻቸው እንደ ቀድሞ ይሆናሉ፣ ማኅበራቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፤ የሚያስጨንቋቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ።
\v 21 መሪያቸው ከእነርሱ ውስጥ ይወጣል። እኔ ሳቀርበውና እርሱም ሲቀርበኝ ከመካከላቸው ይወጣል። ይህንን ባላደርግ፣ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር።
\v 22 እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።
\s5
\v 23 ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፣ ቍጣው ወጥቷል። ሳይቋረጥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፋስ ወጥቶአል። የክፉዎችንም ራስ ይገለባብጣል።
\v 24 የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም። በመጨረሻው ዘመን ታስተውሉታላችሁ።"
\s5
\c 31
\p
\v 1 "በዚያን ዘመን፣ ይላል እግዚአብሔር፣ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።"
\v 2 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እስራኤልን ለማረድ ከመጣው ሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ።"
\v 3 እግዚአብሔር በኃላፊው ጊዜ ተገለጠልኝና እንዲህ አለኝ፣ "እስራኤል ሆይ፣ በዘላለም ፍቅር ወድጄሻለሁ። ስለዚህ በኪዳን ታማኝነት ወደራሴ ሳብሁሽ።
\s5
\v 4 የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ እንደ ገና እገነባሻለሁ አንቺም ትገነቢያለሽ። እንደ ገናም ከበሮሽን አንሥተሽ ከዘፋኞች ጋር ወደ ደስታ ጭፈራሽ ትወጫለሽ።
\v 5 እንደ ገናም በሰማርያ ተራሮች ላይ የወይን ቦታዎችን ትተክያለሽ፤ ገበሬዎች ይተክላሉ፣ ፍሬውንም በመልካም ይጠቀሙበታል።
\v 6 በኤፍሬምም ተራሮች ላይ ያሉ ተመልካቾች፣ 'ተነሡ፣ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ.' ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣልና።"
\s5
\v 7 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ስለ ያዕቆብ በደስታ ጩኹ! ስለ አሕዛብም አለቆች በደስታ ጩኹ! ምስጋና ይሰማ። 'እግዚአብሔር ሕዝቡን፣ የእስራኤልን ቅሬታ አድኖአል' በሉ።
\s5
\v 8 ተመልከቱ፣ ከሰሜን ምድር አመጣቸዋለሁ። ከምድርም ዳርቻ እሰበስባቸዋለሁ። በመካከላቸውም ዕውሩና አንካሳው፣ ያረገዙ ሴቶችና ሊወልዱ ያሉ ሴቶች በአንድነት ይሆናሉ። ታላቅ ጉባኤ ሆነው ወደዚህ ይመለሳሉ።
\v 9 በልቅሶ መጡ፤ ልመናቸውን ሲያደርጉ እመራቸዋልሁ። በወንዝ ዳር በቀጥተኛ መንገድ አስኬዳቸዋለሁ። በእርሱም አይሰናከሉም፣ እኔ ለእስራኤል አባት እሆናለሁና፣ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።"
\s5
\v 10 "አሕዛብ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩ። እናንተ አህዛብ፣ "እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስባታል፣ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቃታል" በሉ።
\v 11 እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቶታል፣ ከበረታበትም እጅ አድኖታል።
\s5
\v 12 ከዚያም ይመጡና በጽዮን ተራራ ይፈነድቃሉ። ወደ እግዚአብሔርም መልካምነት፣ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ፣ ወደ ዘይትም፣ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ይሰበሰባሉ። ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፣ ከእንግዲህም ወዲህ ኃዘን አይሰማቸውም።
\s5
\v 13 በዚያን ጊዜ ደናግሉ በዘፈን ደስ ይላቸዋል፣ ወጣቶቹና ሽማግሌዎቹም በአንድ ላይ ይሆናሉ። ለቅሷቸውን ወደ ክብረ-በዓል እለውጣለሁና። እራራላቸዋለሁ፣ ከኅዘናቸውም ይልቅ እንዲፈነድቁ አደርጋቸዋለሁ።
\v 14 ከዚያም የካህናቱን ነፍስ በብዛት አረካታለሁ። ሕዝቤም መልካምነቴን ይጠግባል ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 15 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "የዋይታና የመራራ ለቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ። ስለ ልጆችዋ የምታለቅሰው ራሔል ናት። ከእንግዲህ አይኖሩምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።"
\s5
\v 16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ድምፅሽን ከለቅሶ፣ ዐይንሽንም ከእንባ ከልክዪ፤ ምክንያቱም ለመከራሽ ካሳ አለ፤ ልጆችሽ ከጠላት ምድር ይመለሳሉ።
\v 17 ለፍጻሜሽ ተስፋ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ልጆችሽም ወደ ዳርቻቸው ይመለሳሉ።"
\s5
\v 18 "ኤፍሬም፣ 'ቀጣኸኝ፣ እኔም ተቀጣሁ። እንዳልተገራ ወይፈን መልሰህ አምጣኝ፣ አንተ እግዚአብሔር አምላኬ ነህና እኔም እመለሳለሁ።
\v 19 ወደ አንተ ከተመለስሁ በኋላ፣ ተጸጸትሁ፤ ከሠለጠንሁም በኋላ፣ በኃዘን ጭኔን መታሁ፤ በወጣትነቴ በደልን ተሸክሜአለሁና አፈርሁ፣ ተዋረድሁ።'
\v 20 ኤፍሬም ለእኔ የከበረ ልጅ አይደለምን? ወይስ የምደሰትበት ሕጻን ነውን? በእርሱ ላይ በተናገርሁ ቍጥር፣ እንደዚያም ሆኖ በፍቅር አስበዋለሁ። በዚህ መልኩ ልቤ ትናፍቀዋለች። በእርግጥም እራራለታለሁ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 21 ለራስሽ የመንገድ ምልክት አድርጊ። ለራስሽም መንገድን የሚመሩ ዓምዶችን ትከዪ። አሳብሽንም ልትሄጂበት ወደሚገባው ትክክለኛ መንገድ አድርጊ። የእስራኤል ድንግል ሆይ፣ ተመለሺ! ወደ እነዚህም ወደ ከተሞችሽ ተመለሺ።
\v 22 አንቺ እምነት የለሽ ልጅ ሆይ፣ እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና፤ ብርቱ ወንዶችን ለመጠበቅ ሴቶች ይከብባሉ።
\s5
\v 23 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ሕዝቡን ወደ ምድራቸው ባመጣኋቸው ጊዜ፣ በይሁዳ ምድርና በከተሞችዋ እንዲህ ይላሉ፣ 'እርሱ የሚኖርብሽ የጽድቅ ማደሪያ፣ የቅድስና ተራራ ሆይ፣ እግዚአብሔር ይባርክሽ።'
\v 24 ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ በአንድነት በእርስዋ ይኖራሉ። ገበሬዎችና እረኞች ከመንጎቻቸው ጋር በዚያ ይገኛሉ።
\v 25 ለደከሙት የሚጠጡትን ውሃ እሰጣለሁና፣ በጥማት የሚሰቃዩትን ሁሉ በእርካታ እሞላለሁ።
\v 26 ከዚህም በኋላ ነቃሁ፣ እንቅልፌ የሚያነቃ እንደሆነ አስተዋልኩኝ።
\s5
\v 27 "ተመልከቱ፣ የእስራኤልን ቤትና የይሁዳን ቤት በሰውና በእንስሳ ዘር የምዘራበት ዘመን፣ እንደሚመጣ ተመልከቱ ይላል እግዚአብሔር።
\v 28 እንዲህም ይሆናል፣ አፈርሳቸውና፣ ክፉ አድርግባቸው ዘንድ እንደ ተጋሁባቸው፣ ነገር ግን በሚመጡት ዘመናት፣ እንዲሁ እሠራቸውና፣ እተክላቸው ዘንድ እተጋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 29 በዚያ ዘመን ሰው ዳግመኛ እንዲህ አይልም፣ 'አባቶች መራራ የወይን ፍሬ በሉ፣ ነገር ግን የልጆች ጥርሶች ጠረሱ።'
\v 30 ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፤ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ።
\s5
\v 31 ተመልከቱ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 32 ከግብጽ ምድር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም። ምንም እንኳን እኔ ባላቸው ብሆንም፣ እነርሱ ኪዳኔ ላይ ዐምጸዋልና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 33 ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ግን ይህ ነውና፣ ይላል እግዚአብሔር፦ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፣ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።
\v 34 ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም እያንዳንዱ ሰው ወንድሙን፣ 'እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፣ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፣ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።"
\s5
\v 35 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው። እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ እርሱ ነው። ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። እርሱ እንዲህ ይላል፣
\v 36 "እነዚህ ቋሚ ነገሮች ከእይታዬ ቢወገዱ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ በዚያን ጊዜ ደግሞ የእስራኤል ዘር በፊቴ ሕዝብ እንዳይሆን ለዘላለም ይቀራል።"
\s5
\v 37 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ከፍ ያሉት ሰማያት ሊለኩ ቢችሉ፣ የምድርም መሠረት ከታች ቢመረመር፣ በዚያን ጊዜ ስላደረጉት ነገር ሁሉ የእስራኤልን ዘር ሁሉ እጥላለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 38 "ተመልከቱ፣ ከሐናንኤል ግንብ ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ ከተማ ለእግዚአብሔር የሚሠራበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 39 የተለካበትም ገመድ ወደ ጋሬብ ኮረብታ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄዳል፣ ወደ ጎዓም ይዞራል።
\v 40 የሬሳም ሸለቆ ሁሉ የአመድም እርሻ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረሰ በር ማዕዘን ድረስ ለእኔ፣ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል። ከእንግዲህም ወዲህ ለዘላለም አይነቀልም አይፈርስምም።"
\s5
\c 32
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዐሥረኛው ዓመት፣ በናቡክደነፆር በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 2 በዚያን ጊዜ፣ የባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከብቦ ነበር፤ ነቢዩም ኤርምያስ በይሁዳ ንጉሥ ቤት በነበረው በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ነበር።
\s5
\v 3 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በእስር አቆይቶት እንዲህ አለው፣ "ለምን እንዲህ ብለህ ትንቢት ትናገራለህ፣ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ይህችን ከተማ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ እርሱም ይይዛታል።
\v 4 የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፣ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፣ አፉ ለአፉ ይናገረዋል፣ ዐይኑም የንጉሡን ዐይን ያያል።
\v 5 ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ይሄዳል፣ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይሆናል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ከከለዳውያን ጋር ብትዋጉ አይሳካላችሁም።"
\s5
\v 6 ኤርምያስም እንዲህ አለ፣ "የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 7 'ተመልከቱ፣ የአጐትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፣ "ትገዛው ዘንድ መቤዠቱ የአንተ ነውና በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ ይልሃል።"
\s5
\v 8 ከዚያም፣ እግዚአብሔር እንደተናገረው ቃል፣ የአጐቴ ልጅ አናምኤል እኔ ወዳለሁበት ወደ ግዞቱ ቤት አደባባይ መጥቶ እንዲህ አለኝ፣ 'በብንያም አገር በዓናቶት ያለውን እርሻዬን፣ እባክህ ግዛ፤ የርስት መብቱ የአንተ ነውና፣ የመቤዠቱ መብትም የአንተ ነውና ለአንተ ግዛው።' ያን ጊዜ ይህ የእግዚአብሔር ቃል እንደ ሆነ አወቅሁ።
\v 9 ስለዚህ፣ በዓናቶት ያለውን እርሻ ከአጐቴ ልጅ ከአናምኤል ገዛሁ፣ ዐሥራ ሰባት ሰቅል ብርም መዘንሁለት።
\s5
\v 10 በውሉም ወረቀት ላይ ፈረምሁ አተምሁትም፣ ምስክሮችም እንዲመሰክሩ አስደረግሁ። ከዚያም ብሩን በሚዛን መዘንሁለት።
\v 11 ቀጥሎ፣ የታተመውንና የተከፈተውን የግዢ ውል ወረቀት ወሰድሁ፤
\v 12 የአጐቴም ልጅ አናምኤል፣ የውሉንም ወረቀት የፈረሙ ምስክሮች፣ በግዞትም ቤት አደባባይ የተቀመጡ አይሁድ ሁሉ እያዩ የውሉን ወረቀት ለመሕሤያ ልጅ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ ሰጠሁት።
\s5
\v 13 በፊታቸውም እንዲህ ብዬ ባሮክን አዘዝሁት።
\v 14 'የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፡- የታተመውንና የተከፈተውን ይህን የውል ወረቀት ውሰድ። ብዙ ቀን እንደተጠበቊ እንዲቆዩ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኑራቸው።
\v 15 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰዎች በዚህች ምድር ቤትን፣ እርሻን፣ የወይን ቦታንም እንደ ገና ይገዛሉ።'
\s5
\v 16 ለኔርያ ልጅ ለባሮክም የውሉን ወረቀት ከሰጠሁት በኋላ፣ እንዲህ ብዬ ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፣
\v 17 'ወዮ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ተመልከቱ! አንተ ብቻህን ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል። ለአንተም እንደሚያቅትህ የተናገርከው ነገር የለም።
\v 18 ለብዙ ሺህ ምሕረት ታደርጋለህ፣ የአባቶችንም በደል ከእነርሱ በኋላ በልጆቻቸው ጭን ላይ ትመልሳለህ። ስምህ ታላቅና ኃያል አምላክ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 19 በጥበብ ታላቅ በአደራረግም ብርቱ ነህ፣ ለሁሉም እንደ መንገዱና እንደ ሥራው ፍሬ ትሰጥ ዘንድ ዐይኖችህ በሰዎች መንገድ ሁሉ ላይ ተገልጠዋል።
\v 20 እስከ ዛሬም ድረስ ምልክትንና ድንቅን ነገር በግብጽ ምድር አድርገሃል። እስከዛሬ ድረስ፣ በዚህ በእስራኤልና በሌሎች ሰዎች ሁሉ መካከል ስምህን አግንነሃል።
\v 21 በምልክትና በድንቅ ነገር፣ በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ በታላቅም ግርማ ሕዝብህን እስራኤልን ከግብጽ ምድር አውጥተሃልና።
\s5
\v 22 ከዚያም ትሰጣቸውም ዘንድ ለአባቶቻቸው የማልህላቸውን፣ ወተትና ማርን የምታፈስሰውን ምድር፣ ሰጠሃቸው።
\v 23 እነርሱም ገብተው ወረሱአት። ነገር ግን ቃልህን አልሰሙም ለሕግህም በመታዘዝ አልሄዱም። ይደረግ ዘንድ ካዘዝሃቸው ሁሉ ምንም አላደረጉም፣ ስለዚህ ይህን ጥፋት ሁሉ አመጣህባቸው።
\s5
\v 24 ተመልከቱ! የአፈር ድልድል ሊይዙአት እስከ ከተማይቱ ድረስ ቀርበዋል። ከሰይፍ፣ ከራብና፣ ከመቅሠፍት የተነሣ፣ ከተማይቱ ለሚዋጓት ለከለዳውያን እጅ ተሰጥታለች። እንደሚሆን የተናገርኸው ሆኖአልና፣ ደግሞም ተመልከቱ፣ አንተ ታየዋለህ።
\v 25 ከዚያም አንተ ራስህ፣ "ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ምንም እንኳን ይህች ከተማ ለከለዳውያን እጅ ተላልፋ የምትሰጥ ቢሆንም፣ እርሻውን በብር ግዛ ምስክሮችንም ጥራ" አልኸኝ።
\s5
\v 26 ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣
\v 27 "ተመልከቱ! የሰው ዘር ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እፈጽመው ዘንድ የሚያቅተኝ ነገር አለን?
\v 28 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ ይህችን ከተማ ለከለዳውያን እጅና ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። እርሱም ይይዛታል።
\s5
\v 29 ይህችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን መጥተው በእሳት ያነድዱአታል፣ ያስቈጡኝም ዘንድ በሰገነታቸው ላይ ለበኣል ካጠኑባቸው፣ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቊርባን ካፈሰሱባቸው ቤቶች ጋር ያቃጥሉአታል።
\v 30 የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች ከወጣትነታቸው ጀምሮ በዐይኔ ፊት ክፉ ነገርን ብቻ አድርገዋል። የእስራኤልም ልጆች እኔን በእጃቸው ሥራ ከማስቈጣት በቀር ሌላ ሥራ አላደረጉምና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 31 ከፊቴ አስወግዳት ዘንድ ይህች ከተማ ከገነቧት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ቍጣዬንና መዓቴን ለማነሣሣት ሆናለችና። ስለዚህም ከፊቴ አስወግዳታለሁ።
\v 32 ምክንያቱም እኔን ያስቈጡኝ ዘንድ፣ እነርሱና ነገሥታቶቻቸው፣ አለቆቻቸውም፣ ካህናቶቻቸውም፣ ነቢያቶቻቸውም፣ የይሁዳም ሰዎች፣ በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ፣ ስላደረጉት ስለ እስራኤል ልጆችና ስለ ይሁዳ ልጆች ክፋት ሁሉ ነው።
\s5
\v 33 ምንም እንኳን በጉጉት ያስተማርኳቸው ቢሆንም፣ ፊታቸውን ሳይሆን ጀርባቸውን ወደ እኔ መለሱ። ላስተምራቸው ሞከርኩ፣ ነገር ግን ተግሣጽን ይቀበሉ ዘንድ አንዳቸውም እንኳን አልሰሙም።
\v 34 ከዚያም፣ ያረክሱት ዘንድ፣ ስሜ በተጠራበት ቤት ውስጥ ርኩሰታቸውን አኖሩ።
\v 35 ቀጥሎም ይሁዳን ኃጢአት እንዲሠራ ለማድረግ፣ ይህንን ርኩሰት ያደርጉ ዘንድ፣ እኔ ያላዘዝሁትንና በልቤ ያላሰብሁትን ነገር፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ያሳልፉ ዘንድ፣ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉትን የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠሩ።
\s5
\v 36 አሁን እንግዲህ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ አንተ ስለ እርስዋ፣ 'በሰይፍና በራብ በመቅሰፍትም ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ተሰጥታለች' ስለምትላት ከተማ እንዲህ ይላል።
\v 37 ተመልከቱ፣ በቍጣዬ፣ በመዓቴና በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ። ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፣ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ።
\s5
\v 38 ከዚያም እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፣ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።
\v 39 ለእነርሱም፣ ከእነርሱም በኋላ ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ ለዘላለም እንዲፈሩኝ አንድ ልብና አንድ መንገድ እሰጣቸዋለሁ።
\v 40 ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፣ ከእነርሱ ጋር የዘላለምን ቃል ኪዳን እገባለሁ። መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ። ከዚህ የተነሣ እኔን ከመከተል አይመለሱም።
\s5
\v 41 ከዚያም ለእነርሱ መልካምን በማድረግ ደስ ይለኛል። በታማኝነት በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
\v 42 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ 'ይህን እጅግ ክፉ ነገር ሁሉ በዚህ ሕዝብ ላይ እንዳመጣሁ፣ እንዲሁ እንደማደርግላቸው የተናገርሁላቸውን በጎነት ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።
\s5
\v 43 ከዚያም፣ እናንተ፣ "ይህች ያለ ሰውና ያለ እንሰሳ ያለች ባድማ ምድር ናት። ለከለዳውያንም እጅ ተሰጥታለች።" በምትሉአት ምድር እርሻን ይገዛሉ።
\v 44 ምርኮኞቻቸውንም እመልሳለሁና፣ በብንያም አገር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፣ በይሁዳም ከተሞች በደጋውም ባሉ ከተሞች በቈላውም ባሉ ከተሞች፣ በደቡብም ባሉ ከተሞች፣ ሰዎች እርሻውን በብር ይገዛሉ በውሉም ወረቀት ፈርመው ያትማሉ ምስክሮችንም ይጠራሉ።"
\s5
\c 33
\p
\v 1 ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ጊዜ መጣለትና እንዲህ አለው፣
\v 2 "ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፣ ያደረገው እግዚአብሔር፣ ያጸናውም ዘንድ የሠራው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።
\v 3 'ወደ እኔ ጩኽ፣ እኔም እመልስልሃለሁ። አንተም የማታስተውለውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ።'
\s5
\v 4 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር፣ ለአፈር ድልድልና ለምሽግ ስለ ፈረሱ ስለዚህች ከተማ ቤቶች፣ ስለ ይሁዳም ነገሥታት ቤቶች እንዲህ ይላልና።
\v 5 'ስለ ክፋታቸው ሁሉ ፊቴን ከዚህች ከተማ ስሰውር፣ ከለዳውያን ለመዋጋትና በቊጣዬ፣ እንዲሁም በመዓቴ በምገድላቸው ሰዎች ሬሳዎች ሊሞሏቸው እየመጡ ናቸው።
\s5
\v 6 ነገር ግን ተመልከቱ፣ ፈውስንና መድኃኒትን አመጣላታለሁ፣ እፈውሳቸውማለሁ፤ መትረፍረፍንም አመጣላቸዋለሁ፣ ሰላምንና የታማኝነትን ብዛት አመጣላቸዋለሁ።
\v 7 የይሁዳን ምርኮና የእስራኤልን ምርኮ መልሼ አመጣለሁ፣ ቀድሞም እንደ ነበሩ አድርጌ እሠራቸዋለሁ።
\v 8 እኔንም ከበደሉበት ኃጢአት ሁሉ አነጻቸዋለሁ። እኔንም የበደሉበትን ያመፀብኝንም ኃጢአታቸውን ሁሉ ይቅር እላለሁ።
\v 9 ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ እኔም ስላመጣሁላቸው መልካምነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ ስም ለምስጋናም ለክብርም ትሆናለች።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ እናንተ፣ "ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ያለች ባድማ ናት በምትሉአት በዚህች ስፍራ፣ የሚቀመጥባቸው በሌላ፣ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባድማ በሆኑ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ጥፋት ሆኗል።"
\v 11 የሐሤት ድምፅና የደስታ ድምፅ፣ የወንድ ሙሽራ ድምፅና የሴት ሙሽራ ድምፅ፣ "እግዚአብሔር ቸር ነውና፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና የሠራዊትን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኑ" የሚሉ ድምፅ በድጋሚ ይሰማል። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የምስጋናን መሥዋዕት አምጡ፣ የምድርን ምርኮ ቀድሞ እንደ ነበረ አድርጌ እመልሳለሁና፣' ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 12 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ባድማ ሆኖ፣ ያለ ሰውና ያለ እንስሳ ባለው በዚህ ስፍራ፣ በከተሞችም ሁሉ መንጎቻቸውን የሚያሳርፉት የእረኞች መኖሪያ ይሆናል።
\v 13 በደጋው ላይ ባሉ ከተሞች፣ በቈላውም ባሉ ከተሞች፣ በደቡብም ባሉ ከተሞች፣ እንዲሁም በብንያምም ምድር በኢየሩሳሌምም ዙሪያ ባሉ ስፍራዎች፣ በይሁዳም ከተሞች መንጎቹ በተቈጣጣሪው እጅ እንደ ገና ያልፋሉ፣' ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 14 'ተመልከቱ! ስለ እስራኤል ቤትና ስለ ይሁዳ ቤት የተናገርሁትን መልካም ቃል የምፈጽምበት ዘመን ይመጣል፤ ይላል እግዚአብሔር።
\v 15 በዚያም ዘመን በዚያም ጊዜ ለዳዊት የጽድቅን ቍጥቋጥ አበቅልለታለሁ፣ እርሱም ፍትህንና ጽድቅን በምድር ላይ ያደርጋል።
\v 16 በዚያም ዘመን ይሁዳ ይድናል ኢየሩሳሌምም በአስተማማኝ ሁኔታ ትቀመጣለች፤ የምትጠራበትም ስም፣ "እግዚአብሔር ጽድቃችን" ተብሎ ነው።
\s5
\v 17 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ 'በእስራኤል ቤት ዙፋን ላይ የሚቀመጥ ሰው ከዳዊት ዘንድ አይታጣም፤
\v 18 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት የሚያቀርብ፣ የእህሉንም ቍርባን የሚያቃጥል፣ ሁልጊዜም የሚሠዋ ሰው ከሌዋውያን ካህናት ዘንድ በእኔ ፊት አይታጣም።"
\s5
\v 19 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 20 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 'ቀንና ሌሊት በወራቱ እንዳይሆን የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፣
\v 21 ያኔ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ልጅ ከእንግዲህ እንዳይሆንለት ከባሪዬ ከዳዊት ጋር፣ ከአገልጋዮቼም ከሌዋውያን ካህናት ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ደግሞ ይፈርሳል።
\v 22 የሰማይ ሠራዊት መቍጠር፣ የባሕርንም አሸዋ መስፈር እንደማይቻል፣ እንዲሁ የባሪያዬን የዳዊትን ዘርና የሚያገለግሉኝን ሌዋውያንን አበዛለሁ።"
\s5
\v 23 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 24 "ይህ ሕዝብ፣ 'እግዚአብሔር መርጧቸው የነበሩትን ሁለቱን ወገን ጥሎአቸዋል፤' ያለውን ነገር አትመለከትምን? በዚህ መልኩ በፊታቸው ከእንግዲህ ወዲህ ሕዝብ እንዳይሆን ሕዝቤን አቃልለዋል።
\s5
\v 25 እኔ፣ እግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፣ 'የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔ የማይኖሩ ከሆነ፣ ወይም የሰማይንና የምድርንም ሥርዓት ያልጠበቅሁ እንደሆነ፣
\v 26 ያን ጊዜ በአብርሃም፣ በይስሐቅና፣ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዦች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እንዳልወስድ፣ የያዕቆብንና የባሪያዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ። ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፣ እምራቸውማለሁና።"
\s5
\c 34
\p
\v 1 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል የመጣው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፣ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ ነበር።
\v 2 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር እንዲህም በለው፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። በእሳትም ያቃጥላታል።
\v 3 አንተም በእርግጥ ትያዛለህ፣ በእጁም ተላልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም። ዐይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፤ ወደ ባቢሎን ስትሄድ፣ እርሱ ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይነጋገራል።'
\s5
\v 4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ! ስለ አንተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'በሰይፍ አትሞትም።
\v 5 በሰላም ትሞታለህ። እንደ አባቶችህ የቀብር መቃጠል፣ ከአንተ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት፣ እንዲሁ አካልህን ያቃጥላሉና። "ወየው፣ ጌታ ሆይ!" እያሉ ያለቅሱልሃል። አሁን እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 6 ነቢዩ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው።
\v 7 የባቢሎንም ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳን ከተሞች ሁሉ፦ ለኪሶንና ዓዜቃን ወጋ። እነዚህ የይሁዳ ከተሞች የተመሸጉ ከተሞች ሆነው ቀሩ።
\s5
\v 8 ንጉሡ ሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ነፃነትን ለማወጅ ስምምነት ካደረገ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 9 እያንዳንዱ ሰው እስራኤላዊ የሆነውን ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን ነፃነት ሊለቅ ይገባል። ማንም ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በይሁዳ ውስጥ መሰል እስራኤላዊን ባርያ ሊያደርግ አይገባም።
\s5
\v 10 ስለዚህም ስምምነቱን የተቀላቀሉት መሪዎች ሁሉ እና ሕዝቡ ታዘዙ። እያንዳንዱ ሰው ወንድ እና ሴት ባርያዎቻቸውን ከእንግዲህ ወዲህ ባርያ ላያደርጓቸው ነፃ አደረጓቸው። እነርሱም ሰሙ፣ ሰደዷቸውም።
\v 11 ነገር ግን ከዚህ በኋላ አሳባቸውን ቀየሩ። ነፃነት የለቀቋቸውን ባርያዎቻቸውን መልሰው አመጡ። በድጋሚ ባርያዎች እንዲሆኑ አስገደዷቸው።
\s5
\v 12 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 13 "የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ።
\v 14 "ሰባት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፣ ራሱን የሸጠላችሁን፣ ስድስትም ዓመት የተገዛላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ ነፃነት ልታወጡት ይገባል። ነፃ አድርጋችሁ ስደዱት።" ነገር ግን አባቶቻችሁ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
\s5
\v 15 እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት ዐዋጅ በመንገር ለዐይኔ ትክክል የሆነውን ነገር አድርጋችሁ ነበር። በስሜም በሚጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር።
\v 16 ነገር ግን ያን ጊዜ ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፤ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ ነፃነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባርያዎቻችሁን አስመለሳችሁ። በድጋሚ ወንዶችና ሴቶች ባርያዎች እንዲሆኑላችሁ አስገደዳችኋቸው።'
\s5
\v 17 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እናንተ ራሳችሁ አልሰማችሁኝም። እያንዳንዳችሁ፣ ለወንድሞቻችሁና ለመሰል እስራኤላውያን ነፃነትን ልታውጁ በተገባ ነበር። ስለዚህ ተመልከቱ! እኔ ለሰይፍ፣ ለመቅሰፍት፣ ለራብም የነፃነት ዐዋጅ እናገርባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል አስደንጋጭ ነገር አደርጋችኋለሁ።
\v 18 ከዚያም ቃል ኪዳኔን የተላለፉትን ሰዎች፣ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን እቀጣለሁ፤
\v 19 ከዚያም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ጃንደረቦችን ካህናትንም፣ በእንቦሳም ቍራጭ መካከል ያለፉትን የአገሩን ሕዝብ ሁሉ።
\s5
\v 20 ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
\v 21 የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት እጅ፣ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ።
\v 22 ተመልከቱ፣ ትእዛዝ እሰጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ጦርነትን እንዲከፍቱባትና እንዲወስዷት፣ እንዲያቃጥሏትም ወደዚህች ከተማ እመልሳቸዋለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።"
\s5
\c 35
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉስ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣
\v 2 "ወደ ሬካባውያን ወገን ሄደህ አነጋግራቸው። ወደ ቤቴ፣ ከክፍሎቹ ወደ አንዲቱ፣ አግባቸው የወይን ጠጅም አጠጣቸው።"
\s5
\v 3 የከባስንን ልጅ የኤርምያስን ልጅ ያእዛንያን፣ እንዲሁም ወንድሞቹን፣ ልጆቹንም ሁሉ፣ ብሎም የሬካባውያንን ወገን ሁሉ ወሰድኋቸው።
\v 4 ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጌዴልያ ልጅ ወደ ሐናን ልጆች ጓዳ ወሰድኳቸው። እነዚህ ክፍሎች የእግዚአብሔር ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በመዕሤያ ጓዳ በላይ ባለው የአለቆች ክፍል አጠገብ ነበሩ።
\s5
\v 5 በሬካባውያንም ልጆች ፊት የወይን ጠጅ የሞላባቸውን ማድጋዎችንና ጽዋዎችን አኑሬ፣ "ጥቂት የወይን ጠጅ ጠጡ፤" አልኳቸው።
\v 6 እነርሱ ግን እንዲህ አሉ፣ "የትኛውንም የወይን ጠጅ አንጠጣም፣ አባታችን የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ 'እናንተና ልጆቻችሁ ለዘላለም የወይን ጠጅ አትጠጡ' ብሎ አዝዞናልና።
\v 7 እንደ እንግዶች በምትኖሩባት ምድር ላይ ብዙ ዘመን እንድትኖሩ፣ በዕድሜአችሁ ሙሉ በድንኳን ውስጥ ተቀመጡ እንጂ ቤትን አትሥሩ፣ የትኛውንም ዘር አትዝሩ፣ የትኛውንም ወይን አትትከሉ፣ ይህ ለእናንተ አይደለም።'
\s5
\v 8 እኛም የአባታችንን የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብን ቃል ባዘዘን ነገር ሁሉ ታዝዘናል፤ እኛም፣ ሚስቶቻችንም፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም፣ ዕድሜአችንን ሙሉ የወይን ጠጅ አልጠጣንም።
\v 9 የምንቀመጥበትንም ቤት አልሠራንም፣ የወይን ቦታና እርሻ ዘርም የለንም።
\v 10 በድንኳንም ውስጥ ኖረናል፣ አድምጠናል፣ አባታችንም ኢዮናዳብ ያዘዘንን ሁሉ አድርገናል።
\v 11 ነገር ግን የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ምድሪቱን ባጠቃ ጊዜ፣ 'ኑ ከከለዳውያን ሠራዊትና ከሦርያ ሠራዊት ፊት የተነሣ ወደ ኢየሩሳሌም እንሂድ' አልን። ስለዚህ በኢየሩሳሌም እየኖርን ነን።"
\s5
\v 12 ከዚያም የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 13 "የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፣ 'ሂድና ለይሁዳ ሰዎችና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ተናገር እንዲህም በላቸው፣ "ቃሌን ትሰሙ ዘንድ ተግሣጽን አትቀበሉምን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 14 ልጆቹ የወይን ጠጅ እንዳይጠጡ የሬካብ ልጅ ኢዮናዳብ ያዘዛቸው ቃል እስከ ዛሬ ድረስ ተፈጸመ። ለአባታቸውም ትእዛዝ ታዝዘዋል። እኔ ግን በተደጋጋሚ ተናግሬአችኋለሁ፣ ሆኖም አልሰማችሁኝም።
\s5
\v 15 'እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ፣ ሥራችሁንም አሳምሩ፤ ታመልኩአቸውም ዘንድ ሌሎችን አማልክት አትከተሉ፣ ለእናንተና ለአባቶቻችሁም በሰጠሁት ምድር ትቀመጣላችሁ እያልሁ በተደጋጋሚ ባርያዎቼን፣ ነቢያትን ሁሉ ልኬባችሁ ነበር። እናንተ ግን ጆሯችሁን አላዘነበላችሁም፣ ወይም እኔንም አልሰማችሁኝም።
\v 16 የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብ ልጆች አባታቸው ያዘዛቸውን ትእዛዝ ፈጽመዋልና፣ ይህ ሕዝብ ግን ሊሰማኝ አልፈለገም።"
\s5
\v 17 ስለዚህ፣ የእስራኤል አምላክና የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ በተናገርኋቸው ጊዜ አልሰሙምና፣ በጠራኋቸውም ጊዜ አልመለሱልኝምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ፣ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ አመጣባቸዋለሁ።"
\s5
\v 18 ኤርምያስም ለሬካባውያን ቤተሰብ እንዲህ አላቸው፣ "የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ለአባታችሁ ለኢዮናዳብ ትእዛዝ ታዝዛችኋልና፣ ትእዛዙንም ሁሉ ጠብቃችኋልና፣ ያዘዛችሁንም ፈጽማችኋልና፤
\v 19 ስለዚህ፣ 'በፊቴ የሚቆም ሰው፣ ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ወገን ለዘላለም አይታጣም።" ይላል የሠራዊት አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\s5
\c 36
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፣ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጣ፣ እንዲህም አለው፣
\v 2 "ለራስህ አንድ የመጽሐፍ ጥቅልል ውሰድና በእስራኤልና በይሁዳ ላይ፣ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት። ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ለአንተ የተናገርሁትን ጻፍበት።
\v 3 ምናልባት የይሁዳ ሕዝብ እኔ አደርግባቸዋለሁ ያልሁትንና ያሰብሁትን ክፉ ነገር ሁሉ ይሰሙ ይሆናል። ከክፋ መንገዳቸው ይመለሱ፣ እኔም በደላቸውንና ኃጢአታቸውን ይቅር እል ዘንድ።
\s5
\v 4 ኤርምያስም የኔርያን ልጅ ባሮክን ጠራ፣ ባሮክም ከኤርምያስ አፍ እግዚአብሔር ለእርሱ የተናገረውን ቃል ሁሉ በመጽሐፉ ጥቅልል ላይ ጻፈ።
\v 5 ቀጥሎም ኤርምያስ ለባሮክ እንዲህ ሲል አዘዘው። "እኔ በእስር ላይ ስለሆንኩ ወደ እግዚአብሔር ቤት መሄድ አልችልም።
\v 6 ስለዚህ አንተ መሄድና ከአፌም የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል ልታነብብ ይገባል። በጾም ቀን፣ በእግዚአብሔር ቤት ሕዝቡ እየሰሙ አንብብ፣ ደግሞም ከከተሞቻቸው የሚወጡ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እየሰሙ አንብበው። እነዚህን ቃሎች አውጅላቸው።
\s5
\v 7 ምናልባት የምሕረት ልመናቸው በእግዚአብሔር ፊት ትመጣ ይሆናል። እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብ ላይ የተናገረው ቍጣውና መዓቱ ታላቅ ነውና፣ ሁሉም ከክፉ መንገዱ ይመለስ ይሆናል።"
\v 8 ስለዚህ የኔርያም ልጅ ባሮክ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። በእግዚአብሔርም ቤት የእግዚአብሔርን ቃል በመጽሐፉ አነበበ።
\s5
\v 9 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአምስተኛው ዓመት በዘጠነኛው ወር በኢየሩሳሌም የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ ከይሁዳም ከተሞች ወደ ኢየሩሳሌም የመጡ ሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ለመጾም አዋጅ ነገሩ።
\v 10 ባሮክም የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ በእግዚአብሔር ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ጓዳ ሕዝቡ ሁሉ እየሰሙ መጽሐፉን አነበበ።
\s5
\v 11 የሳፋንም ልጅ የገማርያ ልጅ ሚክያስ የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ከመጽሐፉ ጥቅልል ሰማ።
\v 12 ወደ ንጉሡ ቤት ወደ ጸሐፊው ክፍል ወረደ። በዚያም፣ አለቆች ሁሉ፦ ጸሐፊው ኤሊሳማ፣ የሸማያ ልጅ ድላያ፣ የዓክቦር ልጅ ኤልናታን፣ የሳፋን ልጅ ገማርያ፣ የሐናንያ ልጅ ሴዴቅያስ፣ እንዲሁም አለቆቹ ሁሉ በዚያ ተቀምጠው ነበር።
\s5
\v 13 ሚክያስም ሕዝቡ እየሰሙ ባሮክ ከመጽሐፉ ባነበበ ጊዜ የሰማውን ቃል ሁሉ ነገራቸው።
\v 14 አለቆቹም ሁሉ፣ "በሕዝቡ ጆሮ ያነበብኸውን ጥቅልል በእጅህ ይዘህ ና" የሚል መልእክት በኵሲ ልጅ፣ በሰሌምያ ልጅ፣ በናታንያ ልጅ፣ በይሁዲ እጅ፣ ወደ ባሮክ ላኩ። ስለዚህ የኔርያ ልጅ ባሮክ ጥቅልሉን በእጁ ይዞ ወደ እነርሱ ሄደ።
\v 15 ከዚያም፣ "ተቀመጥና እየሰማንህም ይህንን አንብብልን፤" አሉት። ባሮክም በጆሮአቸው አነበበው።
\s5
\v 16 እነዚህን ቃሎች ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈሩና እርስ በእርሳቸው ተመካከሩ፣ ባሮክንም፣ "ይህን ቃል ሁሉ በእርግጥ ለንጉሡ ልንናገር ይገባል" አሉት።
\v 17 ከዚያም ባሮክን፣ "ይህን ሁሉ ቃላት ከኤርምያስ አፍ እንዴት እንደ ጻፍኸው ንገረን" ብለው ጠየቁት።
\v 18 ባሮክም፣ "ይህን ቃል ከአፉ ይነግረኝ ነበር፣ እኔም በመጽሐፍ ጥቅልል ላይ በቀለም እጽፍ ነበር" ብሎ መለሰላቸው።
\v 19 አለቆቹም ለባሮክ፣ "አንተና ኤርምያስ ሄዳችሁ ተሸሸጉ። የት እንደሆናችሁ ማንም አይወቅ" አሉት።
\s5
\v 20 ወደ ንጉሡም ሸንጎ ገቡና ቃሉን ሁሉ ንጉሡ እየሰማ ተናገሩ። ነገር ግን አስቀድመው ጥቅልሉን በጸሐፊው በኤሊሳማ ክፍል አኑረውት ነበር።
\v 21 ከዚያም ንጉሡ ጥቅልሉን ያመጣ ዘንድ ይሁዲን ላከ። እርሱም ከጸሐፊው ከኤሊሳማ ክፍል ወሰደው። ከዚያም ይሁዲ ንጉሡና በንጉሡ አጠገብ የቆሙት አለቆች ሁሉ እየሰሙ አነበበው።
\v 22 ያኔ፣ ንጉሡ በዘጠነኛው ወር በክረምት ቤት ተቀምጦ ነበር፣ በፊቱም በምድጃ ውስጥ እሳት ይነድድ ነበር።
\s5
\v 23 ይሁዲ ሦስት ወይም አራት ዓምድ ያህል ባነበበ ቍጥር፣ ንጉሡ በካራ እየቀደደ ጥቅልሉ በምድጃ ውስጥ ባለው እሳት ፈጽሞ እስኪቃጠል ድረስ በምድጃ ውስጥ ወዳለው እሳት ጣለው።
\v 24 ነገር ግን ንጉሡ ወይም ይህንን ቃል ሁሉ የሰሙ ባሪያዎቹ ሁሉ አልፈሩም፣ ልብሳቸውንም አልቀደዱም።
\s5
\v 25 ነገር ግን ኤልናታን፣ ድላያና፣ ገማርያ ጥቅልሉን እንዳያቃጥል ንጉሡን ለመኑት፣ እርሱ ግን አልሰማቸውም።
\v 26 ንጉሡም ጸሐፊውን ባሮክንና ነብዩን ኤርምያስን ይይዙ ዘንድ የንጉሡን ልጅ ይረሕምኤልን፣ የዓዝርኤልን ልጅ ሠራያን፣ የዓብድኤልንም ልጅ ሰሌምያን አዘዘ፣ እግዚአብሔር ግን ሰውሯቸው ነበር።
\s5
\v 27 ከዚያም ንጉሡ ጥቅልሉንና ባሮክ ከኤርምያስ አፍ እየቀዳ የጻፈውን ቃል ካቃጠለ በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ።
\v 28 "ዳግመኛ ሌላ ጥቅልል ውሰድ፣ የይሁዳም ንጉሥ ኢዮአቄም ባቃጠለው ጥቅልል ላይ የነበረውን የቀድሞውን ቃል ሁሉ ጻፍበት።
\v 29 ከዚያም፣ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ አንተ፣ "የባቢሎን ንጉሥ በእርግጥ ይመጣል ይህችንም አገር ያፈርሳታል ከሰውና ከእንስሳም ባዶ ያደርጋታል" ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ጥቅልል አቃጥለሃል።"
\s5
\v 30 ስለዚህ፣ ስለ አንተ፣ የይሁዳ ንጉሥ፣ ስለ ኢዮአቄም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም። ሬሳውም በቀን ለትኩሳት፣ በሌሊትም ለውርጭ ይጣላል።
\v 31 ስለ ኃጢአታቸውም እርሱንና ዘሩን፣ ባሪያዎቹንም እቀጣለሁ። እነርሱም አልሰሙምና የተናገርሁባቸውን ክፉ ነገር ሁሉ በእነርሱ ላይና፣ በኢየሩሳሌም በሚቀመጡ፣ በይሁዳም ሰዎች ላይ አመጣለሁ።
\s5
\v 32 ሰለዚህ ኤርምያስ ሌላ ጥቅልል ወሰደ ለኔርያም ልጅ ለጸሐፊው ለባሮክ ሰጠው። እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ እየቀዳ ጻፈበት። በተጨማሪም፣ ከቀድሞው ቃል ጋር የሚመሳሰል ብዙ ቃል ተጨመረበት።
\s5
\c 37
\p
\v 1 የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር በይሁዳ ያነገሠው የኢዮስያስ ልጅ ሴዴቅያስ በኢዮአቄም ልጅ በኢኮንያን ፋንታ ነገሠ።
\v 2 ነገር ግን ሴዴቅያስም ሆነ ባርያዎቹ፣ የአገሩም ሕዝብ በነቢዩ በኤርምያስ እጅ የተናገረውን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
\s5
\v 3 ስለዚህ፣ ንጉሡ ሴዴቅያስ፣ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ። እነርሱም "ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ስለ እኛ ጸልይ" አሉት።
\v 4 በግዞት ቤት ገና አላገቡትም ነበርና ኤርምያስ በሕዝቡ መካከል ይወጣና ይገባ ነበር።
\v 5 የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፣ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።
\s5
\v 6 ከዚያም፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 7 "የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ ከእኔ ትጠይቁ ዘንድ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ 'ተመልከቱ፣ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደገዛ ምድሩ ወደ ግብጽ ይመለሳል።
\v 8 ከለዳውያንም ይመለሳሉ። ይህችን ከተማ ይዋጉአታል፣ ይይዟትማል፣ በእሳትም ያቃጥሉአታል።'
\s5
\v 9 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለማይሄዱ 'ከለዳውያን በእርግጥ ከእኛ ዘንድ ይሄዳሉ' ብላችሁ ራሳችሁን አታታልሉ።
\v 10 እናንተም የሚዋጉትን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ አሸንፋችሁ ቢሆን እንኳን፣ ከእነርሱም የቆሰሉት ብቻ በድንኳኖቻቸው ቀርተው ቢሆን ኖሮ፣ይህችን ከተማ በእሳት ባቃጠሉአት ነበር።
\s5
\v 11 ስለዚህ የከለዳውያን ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት ፊት የተነሣ ከኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ፣
\v 12 ያኔ ኤርምያስ ወደ ብንያም አገር ሊሄድ ከኢየሩሳሌም ወጣ። እርሱ የርስቱን እድል ፈንታ በዚያ ከሕዝቡ መካከል ይቀበል ዘንድ ፈለገ።
\v 13 በብንያምም በር በነበረ ጊዜ፣ የዘበኞች አለቃ በዚያ ነበር። ስሙም የሐናንያ ልጅ የሰሌምያ ልጅ የሪያ ነበረ። እርሱም "ወደ ከለዳውያን መኰብለልህ ነው" ብሎ ነቢዩን ኤርምያስን ያዘው።
\s5
\v 14 ኤርምያስ ግን፣ "ይህ እውነት አይደለም። ወደ ከለዳውያን መኰብለሌ አይደለም" አለ። ነገር ግን የሪያ አልሰማውም። ኤርምያስንም ይዞ ወደ አለቆች አመጣው።
\v 15 አለቆችም በኤርምያስ ላይ ተቈጡ። መቱትና የጸሐፊውንም የዮናታንን ቤት እስር ቤት አድርገውት ነበርና በዚያ አኖሩት።
\s5
\v 16 ስለዚህ ኤርምያስ ብዙ ቀናት በተቀመጠበት ከምድር በታች ባለ ክፍል ተጣለ፤
\v 17 ከዚያም ንጉሡ ሴዴቅያስ አንድ ሰው ልኮ ወደ ቤተመንግሥት አስመጣው። ንጉሡም በቤቱ፣ "በውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?" ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፣ "አዎን አለ፦ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፈህ ትሰጣለህ" አለ።
\s5
\v 18 ከዚያም ኤርምያስ ንጉሡን ሴዴቅያስን፣"በእስር ቤት የጣላችሁኝ አንተን፣ ወይስ ባርያዎችህን፣ ወይስ ሕዝብህን ምን በድያችሁ ነው?
\v 19 የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች ምድር አይመጣባችሁም ብለው ትንቢት ይናገሩላችሁ የነበሩ ነቢያቶቻችሁ ወዴት አሉ?
\v 20 ንጉሡ ጌታዬ ሆይ፣ እንድትሰማኝ እለምንሃለሁ! ልመናዬ ወደ አንተ ይድረስ። በዚያ እንዳልሞት ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ።"
\s5
\v 21 ስለዚህ ንጉሡ ሴዴቅያስ አዘዘ። አገልጋዮቹም ኤርምያስን በግዞት ቤት አደባባይ አኖሩት። እንጀራም ሁሉ ከከተማ እስኪጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እንጀራ ከጋጋሪዎች መንገድ ይሰጡት ነበር። ስለዚህ ኤርምያስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀምጦ ነበር።
\s5
\c 38
\p
\v 1 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ የተናገረውን ቃል የማታን ልጅ ስፋጥያስ፣ የጳስኮርም ልጅ ጎዶልያስ፣ የሰሌምያም ልጅ ዮካል፣ የመልክያም ልጅ ጳስኮር ሰሙ። ኤርምያስ እንዲህ ሲል ነበር፣
\v 2 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህች ከተማ የሚቀመጥ ማንኛውም ሰው በሰይፍ፣ በራብ፣ በመቅሠፍትም ይሞታል። ወደ ከለዳውያን የሚወጣ ግን በሕይወት ይኖራል። ሕይወቱንም ያስመልጣል፣ በሕይወትም ይኖራል።
\v 3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ በእርግጥ ትሰጣለች፣ እርሱም ይይዛታል።"
\s5
\v 4 ስለዚህ አለቆቹ ለንጉሡ እንዲህ አሉት፣ "ይህን የመሰለውን ቃል ሲነግራቸው በዚህች ከተማ የቀሩትን የሰልፈኞቹን እጅ የሕዝቡንም ሁሉ እጅ ያደክማልና ይህ ሰው ይገደል። ይህ ሰው ጥፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አያበጅለትምና እነዚህን ቃሎች እየተናገረ ነው።
\v 5 ስለዚህ ንጉሡ ሴዴቅያስ፣ "ተመልከቱ፣ እናንተን የሚቋቋም ንጉሥ የለምና፣ በእጃችሁ ነው" አለ።
\s5
\v 6 ከዚያም ኤርምያስን ወሰዱትና ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መልክያ ጕድጓድ ጣሉት። ጉድጓዱ በእስር ቤቱ አደባባይ ነበረ። ኤርምያስንም በገመድ አወረዱት። በጕድጓድም ውስጥ ውኃ አልነበረበትም፣ ነገር ግን ጭቃማ ነበርና ኤርምያስ ጭቃው ውስጥ ገባ።
\s5
\v 7 ኩሻዊ የሆነው አቤሜሌክ በንጉሡም ቤት ከነበሩት ጃንደረቦች አንዱ ነበር። ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።
\v 8 ስለዚህ አቤሜሌክ ከንጉሡ ቤት ወጥቶ ከንጉሡ ጋር ተነጋገረ።
\v 9 "ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ እነዚህ ሰዎች ነቢዮን ኤርምያስን በጕድጓድ ውስጥ በመጣላቸው ክፉ አድርገዋል። በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለሌለ በዚያ በራብ እንዲሞት ወደ ጉድጓድ ጥለውታል።"
\s5
\v 10 ከዚያም ንጉሡ ለኩሻዊው አቤሜሌክ ትእዛዝ ሰጠ። "ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፣ ነብዩ ኤርምያስ ሳይሞት በፊት ከጕድጓድ አውጣው" ብሎ አዘዘው።
\v 11 ስለዚህ አቤሜሌክ ከእርሱ ጋር ሰዎችን ይዞ ሄደና ከቤተ መዛግብቱም በታች ወደ ነበረው ወደ ንጉሥ ቤት ገባ። ከዚያም አሮጌ ጨርቅና እላቂ ልብስ ወሰደና ወደ ኤርምያስ ወደ ጉድጓድ ውስጥ በገመድ አወረደው።
\s5
\v 12 ኩሻዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን፣ "ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብብትህ እና ከገመዱ በታች አድርግ" አለው። ስለዚህ ኤርምያስ እንዲሁ አደረገ።
\v 13 ከዚያም ኤርምያስን በገመዱ ጐተቱት። በዚህ መልኩ ከጕድጓድ አወጡት። ስለዚህ ኤርምያስ በግዞት ቤት አደባባይ ተቀመጠ።
\s5
\v 14 ከዚያም ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ በእግዚአብሔር ቤት ወደ ነበረው፣ ወደ ሦስተኛው መግቢያ፣ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው። ንጉሡም ኤርምያስን፣ "አንዲት ነገር ልጠይቅህ እፈልጋለሁ። መልሱን አትደብቅብኝ" አለው።
\v 15 ኤርምያስም ሴዴቅያስን፣ "ብመልስልህ፣ በእርግጥ አትገድለኝምን? ምክር ብሰጥህም፣ አትሰማኝም" አለው።
\v 16 ንጉሡ ሴዴቅያስ ግን "እኛን የፈጠረንን ሕያው እግዚአብሔርን፣ አልገድልህም፣ ወይም ነፍስህን ለሚሹ ለእነዚህ ሰዎች እጅ አሳልፌ አልሰጥህም" ብሎ በድብቅ ለኤርምያስ ማለ።
\s5
\v 17 ስለዚህ ኤርምያስ ሴዴቅያስን፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት አምላክ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ብትወጣ፣ በሕይወት ትኖራለህ፣ ይህችም ከተማ አትቃጠልም። አንተና ቤተሰብህ በሕይወት ትኖራላችሁ።
\v 18 ነገር ግን ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፣ ይህች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች። በእሳትም ያቃጥሉአታል፣ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም" አለው።
\s5
\v 19 ንጉሡ ሴዴቅያስም ኤርምያስን፣ "ነገር ግን ወደ ከለዳውያን ክፉኛ እንዲያፌዙብኝ፣ በኰበለሉት በአይሁድ እጅ አሳልፈው ይሰጡኛል ብዬ እፈራለሁ" አለው።
\s5
\v 20 ኤርምያስም እንዲህ አለው፣ "ለእነርሱ አሳልፈው አይሰጡህም። እኔ እየነገርኩህ ያለሁትን የእግዚአብሔርን መልእክት ታዘዝ፤ ነገሮችም መልካም ይሆኑልሃል፣ በሕይወትም ትኖራለህ።
\v 21 ነገር ግን ትወጣ ዘንድ እንቢ ብትል፣ እግዚአብሔር ያሳየኝ ይህንን ነው፦
\s5
\v 22 ተመልከት! በይሁዳ ንጉሥ ቤት የቀሩትን ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ያወጣሉ። እነዚያም ሴቶች ለአንተ፣ "ወዳጆችህ አታልለውሃል፤ አበላሽተውህማል። እግሮችህ ግን አሁን በጭቃ ውስጥ ሰጥመዋል፣ ወዳጆችህም ይሸሻሉ።'
\v 23 ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፣ አንተም ራስህ አታመልጥም። በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።"
\s5
\v 24 ከዚያም ሴዴቅያስ ኤርምያስን እንዲህ አለው፣ "እንዳትሞት ስለእነዚህ ቃሎች ለማንም አትናገር።
\v 25 አለቆቹ ግን እኔ ከአንተ ጋር እንደ ተነጋገርሁ ከሰሙ፣ ወደ አንተ መጥተው፣ 'ለንጉሡ የነገርከውን ንገረን። ከእኛም አትሸሽገን፣ አሊያ እንገድልሃለን። ንጉሡ ደግሞ ያለህን ንገረን' ቢሉህ፣
\v 26 ያን ጊዜ 'በዚያ እሞት ዘንድ ወደ ዮናታን ቤት አትመልሰኝ' ብዬ በንጉሡ ፊት ለመንሁ" በላቸው።
\s5
\v 27 ከዚያም አለቆቹ ሁሉ ወደ ኤርምያስ መጥተው ጠየቁት፣ ንጉሡም እንዳዘዘው እንደዚህ ቃል ሁሉ ነገራቸው። በኤርምያስና በንጉሡ መካከል የነበረው ውይይት አልተሰማምና ከእርሱ ጋር መነጋገርን ተዉ።
\v 28 ስለዚህ፣ ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ቀን ድረስ ኤርምያስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ።
\s5
\c 39
\p
\v 1 ኢየሩሳሌምም በተያዘች ጊዜ፣ በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው ከበቡአት።
\v 2 በሴዴቅያስም በዐሥራ አንደኛው ዓመትና በአራተኛው ወር ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማይቱ ተሰበረች።
\v 3 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ፣ ኤርጌል ሳራስር፣ ሳምጋርናቦና፣ ዋና አለቃው ሠርሰኪም፤ ኤርጌል ሳራስር በከፍተኛ ደረጃ ያለ አለቃ ነበርና ከቀሩት የባቢሎን ንጉሥ አለቆች ሁሉ ጋር ገብተው በመካከለኛው በር ውስጥ ተቀመጡ።
\s5
\v 4 የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ ሰልፈኞቹም ሁሉ፣ ባዩአቸው ጊዜ ሸሹ። በሌሊትም በንጉሡ አትክልት መንገድ በሁለቱ ቅጥር መካከል ከነበረው ደጅ ከከተማይቱ ወጡ። ንጉሡ በዓረባ መንገድ ወጣ።
\v 5 ነገር ግን የከለዳውያን ሠራዊት ተከታተላቸውና ሴዴቅያስን በኢያሪኮ ሜዳ አቅራቢያ ባሉት የዮርዳኖስ ሸለቆ ሜዳዎች ላይ አገኙት። ከዚያም ይዘውት በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፣ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
\s5
\v 6 የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በገዛ ዐይኑ ፊት በሪብላ አረዳቸው። እርሱም የይሁዳን ከበርቴዎች ሁሉ ገደለ።
\v 7 ከዚያም የሴዴቅያስን ዐይን አወጣና ወደ ባቢሎን ሊወስደው በመዳብ ሰንሰለት አሰረው።
\s5
\v 8 ከዚያም ከለዳውያን የንጉሡንና የሕዝቡን ቤቶች በእሳት አቃጠሉ። የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ።
\v 9 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን በከተማይቱ የቀሩትን ሕዝብ፣ ወደ እርሱም የኰበለሉትን ሰዎች፣ የቀረውንም የሕዝቡን ቅሬታ ወደ ባቢሎን ማረካቸው።
\v 10 አንዳች የሌላቸውን የሕዝቡን ድሆች ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን በይሁዳ አገር ተዋቸው። የወይኑን ቦታና እርሻውን በዚያው ቀን ሰጣቸው።
\s5
\v 11 የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ፣
\v 12 "ውሰደውና በመልካም ተንከባከበው። አትጉዳው። የሚነግርህንም የትኛውንም ነገር አድርግለት።" ብሎ የዘበኞቹን አለቃ ናቡዘረዳንን አዘዘ።
\v 13 ስለዚህ የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ላከ፣ የጃንደረቦች አለቃ ናቡሽዝባን፣ ዋናው አለቃ ራፋስቂስም ኤርጌል ሳራስርም፣ ራብማግም የባቢሎንም ንጉሥ ዋና ዋና አለቆች ሁሉ ሰዎችን ላኩ።
\v 14 ሰዎቻቸውም ኤርምያስን ከግዞት ቤት አደባባይ አወጡት፣ ወደ ቤቱም ይወስደው ዘንድ ለሳፋን ልጅ ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ ሰጡት፤ ስለዚህ ኤርምያስ በሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
\s5
\v 15 በግዞትም ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ኤርምያስ መጣ፣
\v 16 "ለኩሻዊው ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፣ 'የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ለበጎነት ሳይሆን ለጥፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ። በዚያም ቀን በፊትህ እውነት ሆኖ ይፈጸማል።
\s5
\v 17 ነገር ግን በዚያ ቀን እታደግሃለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም።
\v 18 በእርግ አድንሃለሁ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች እንጂ በሰይፍ አትወድቅም። በእኔ ታምነሃልና፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\c 40
\p
\v 1 ወደ ባቢሎን በተማረኩት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ምርኮኞች መካከል የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን፣ከራማ ከለቀቀው በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ መጥቶ የነበረው ቃል ይህ ነው። ኤርምያስ ተወስዶ የነበረው ወደዚህ ቦታ የነበረ ሲሆን፣ እርሱም በሠንሰለት ታስሮ ነበር። እርሱ በምርኮ ከተወሰዱት የኢየሩሳሌም እና ይሁዳ ምርኮኞች ሁሉ መካከል አንዱ ነበር።
\v 2 የዘበኞቹም አለቃ ኤርምያስን ወሰደውና እንዲህ አለው፣ "አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር በዚህ ስፍራ ላይ ተናገረ።
\s5
\v 3 ስለዚህ እግዚአብሔር ነገሩን አመጣው። እናንተ ሕዝቦች በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርታችኋልና፣ እንደ ተናገረው አደረገ። ይህ ነገር እየሆነባችሁ ያለው፣ ቃሉን አልሰማችሁምና ነው።
\v 4 አሁን ግን ተመልከት! እጅህ የታሰረችበትን ሰንሰለት ዛሬ ፈታሁልህ። ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣት በዐይኖችህ ዘንድ መልካም መስሎ ቢታይህ፣ ና፣ እኔም እንከባከብሃለሁ። ነገር ግን ከእኔ ጋር ወደ ባቢሎን መምጣቱ በዐይኖችህ ዘንድ መልካም መስሎ ባይታይህ ግን፣ አትምጣ። በፊትህ ያለችውን ምድር ሁሉ ተመልከት። በዐይኖችህ ዘንድ ልትሄድበት መልካም መስሎ ወደሚታይህና ትክክል ወደሚመስልህ ስፍራ ሂድ።"
\s5
\v 5 እርሱም ገና መልስ ሳይሰጥ፣ ናቡከደነፆር "የባቢሎን ንጉሥ በይሁዳ ከተሞች ላይ ወደ ሾመው ወደ ሳፋን ልጅ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ተመለስ። ከእርሱም ጋር በሕዝቡ መካከል ተቀመጥ ወይም ልትሄድበት ደስ ወደሚያሰኝህ ስፍራ ሁሉ ሂድ" አለው። የዘበኞቹም አለቃ የምግብ ስንቅና ስጦታ ሰጥቶ አሰናበተው።
\v 6 ስለዚህ ኤርምያስ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ወዳለበት ወደ ምጽጳ ሄደ። ከእርሱም ጋር በአገሩ ውስጥ በቀሩት ሕዝብ መካከል ተቀመጠ።
\s5
\v 7 በየገጠሩ የነበሩት የጭፍራ አለቆችና ሰዎቻቸው ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምድር ላይ እንደ ሾመ ሰሙ። እንዲሁም ወደ ባቢሎን ያልተማረኩ የምድሪቱ ድሆች የሆኑት ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች ላይ እንደሾመው ሰሙ።
\v 8 ስለዚህ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ። እነዚህም ሰዎች የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናንና ዮናታን፣ የተንሑሜትም ልጅ ሠራያ፣ የነጦፋዊውም የዮፌ ልጆች፣ የማዕካታዊውም ልጅ ያእዛንያ፣ እነርሱና ሰዎቻቸው ነበሩ።
\s5
\v 9 የሳፋንም ልጅ የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ለእነርሱና ለሰዎቻቸው ማለ፣ እንዲህም አላቸው፣ "ለከለዳውያን አለቆች ለማገልገል አትፍሩ። በምድሪቱ ላይ ተቀመጡ ለባቢሎንም ንጉሥ አገልግሉ፣ መልካምም ይሆንላችኋል።
\v 10 ተመልከቱ፣ ወደ እኛ ከሚመጡት ከለዳውያን ጋር ለመገናኘት ምጽጳ ውስጥ እኖራለሁ፤ እናንተ ግን ወይንን፣ የበጋ ፍሬንና፣ ዘይትን በየዕቃዎቻችሁ አከማቹ። በያዛችኋቸውም ከተሞቻችሁ ውስጥ ኑሩ።"
\s5
\v 11 በሞዓብ፣ በአሞንም ልጆች መካከል፣ እንዲሁም በኤዶምያስና በእያንዳንዱ ምድር ሁሉ ላይ የነበሩ አይሁድ ሁሉ የባቢሎን ንጉሥ የይሁዳን ቅሬታ እንዳስቀረ፣ የሳፋንንም ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በላያቸው እንደ ሾመው ሰሙ።
\v 12 ስለዚህ አይሁድ ሁሉ ከተበተኑበት ስፍራ ሁሉ ተመለሱ። ጎዶልያስ ወዳለበት፣ ወደ ይሁዳ ምድር፣ ወደ ምጽጳ መጡ። ወይንና የበጋንም ፍሬ በመሰብሰብ እጅግ ብዙ አከማቹ።
\s5
\v 13 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ በየገጠሩም የነበሩ የጭፍራ አለቆች ሁሉ ወደ ጎዶልያስ ወደ ምጽጳ መጡ።
\v 14 "የአሞን ልጆች ንጉሥ በኣሊስ ይገድልህ ዘንድ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንደ ሰደደ ታውቃለህን?" አሉት። የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን አላመናቸውም።
\s5
\v 15 ስለዚህ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን ምጽጳ ላይ ጎዶሊያስን እንዲህ በማለት በሚስጢር አነጋገረው፣"ሄጄ ማንም ሳያውቅ የናታንያን ልጅ እስማኤልን እንድገድለው ፍቀድልኝ። ማንም አይጠረጥረኝም። ሊገድልህ የሚገባው ለምንድነው? ወደ አንተ የተሰበሰቡ አይሁድ ሁሉ እንዲበተኑ፣ የይሁዳም ቅሬታ እንዲጠፋ ለምን ትፈቅዳለህ?"
\v 16 ነገር ግን የአኪቃም ልጅ ጎዶልያስ ግን የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፣ "በእስማኤል ላይ ሐሰት ተናግረሃልና ይህን ነገር አታድርግ" አለው።
\s5
\c 41
\p
\v 1 በሰባተኛውም ወር ከመንግሥት ወገንና፣ ከንጉሡ ዋና ዋና አለቆች አንዱ የኤሊሳማ ልጅ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ወደ ምጽጳ ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ። በዚያም በምጽጳ በአንድ ላይ እንጀራ በሉ።
\v 2 የናታንያም ልጅ እስማኤል፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት ዐሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ። የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን እስማኤል ገደለው።
\v 3 ከዚያም እስማኤል ከጎዶልያስ ጋር በምጽጳ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፣ በዚያም የተገኙትን የከለዳውያንን ሰልፈኞች ሁሉ ገደላቸው።
\s5
\v 4 ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ ሁለት ቀን ሆነ፣ ነገር ግን ማንም አላወቀም ነበር።
\v 5 ጢማቸውን ላጭተው፣ ልብሳቸውንም ቀድደው፣ ገላቸውንም ነጭተው፣ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው እየያዙ፣ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬም፣ ከሴሎና፣ ከሰማርያ መጡ።
\s5
\v 6 የናታንያም ልጅ እስማኤል ከምጽጳ ወጥቶ እያለቀሰ ሊገናኛቸው ሄደ። ባገኛቸውም ጊዜ፣ "ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ ኑ!" አላቸው።
\v 7 ወደ ከተማም መካከል በመጡ ጊዜ፣ የናታንያ ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩ ሰዎች አረዷቸውና በጉድጓድ ውስጥ ጣሉአቸው።
\s5
\v 8 ነገር ግን በመካከላቸው እስማኤልን፣ "የምንሰጥህ በሜዳ የተሸሸገ ስንዴ፣ ገብስ፣ ዘይትና፣ ማር ስላለን አትግደለን" የሚሉት ዐሥር ሰዎች ነበሩ። እርሱም ከሌሎች ወዳጆቻቸው ጋር አልገደላቸውም።
\v 9 ጉድጓዱ እስማኤል ከጎዶልያስ ጋር የገደላቸውን የሰዎች ሬሳ ሁሉ የጣለበት ጕድጓድ ነበር። ይህ ጥልቅ ጉድጓድ ንጉሡ አሳ የእስራኤልን ንጉሥ ባኦስን ስለ ፈራ የሠራው ጉድጓድ ነበረ። የናታንያም ልጅ እስማኤል የገደላቸውን ሞላበት።
\s5
\v 10 ቀጥሎ እስማኤል በምጽጳ የነበረውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፣ የንጉሡን ሴቶች ልጆች፣ የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በምጽጳ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ ማረካቸው። ስለዚህ የናታንያም ልጅ እስማኤል ማርኮ ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።
\s5
\v 11 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ የናታንያ ልጅ እስማኤል ያደረገውን ክፋት ሁሉ ሰሙ።
\v 12 ስለዚህ ሰዎቻቸውን ሁሉ ይዘው ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ጋር ሊዋጉ ሄዱ። በገባዖንም ባለው በታላቁ የውኃ ጉድጓድ አጠገብ አገኙት።
\s5
\v 13 ከዚያም ከእስማኤል ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ የቃሬያን ልጅ ዮሐናንን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩትን የጭፍራ አለቆችን ሁሉ ሲያዩ እጅግ ደስ አላቸው።
\v 14 ስለዚህ እስማኤል ከምጽጳ የማረካቸው ሕዝብ ሁሉ ዞረው ወደ ቃሬያም ልጅ ወደ ዮሐናን ሄዱ።
\s5
\v 15 ነገር ግን የናታንያ ልጅ እስማኤል ከስምንት ሰዎች ጋር ከዮሐናን አመለጠ። ወደ አሞንም ሕዝቦች ሄደ።
\v 16 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ከእርሱም ጋር የነበሩት የጭፍራ አለቆች ሁሉ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በምጽጳ ከገደለው በኋላ ከናታንያ ልጅ ከእስማኤል ያስመለሱአቸውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፣ ከገባዖን ያስመለሱአቸውን ሰልፈኞች፣ ሴቶችንም፣ ልጆችንም፣ ጃንደረቦችንም፣ ወሰዱ።
\s5
\v 17 ከዚያም ሄደው ለተወሰነ ጊዜ በቤተልሔም አቅራቢያ ባለው በጌሮት ከመዓም ተቀመጡ። ሊሄዱ የነበረው ወደ ግብጽ ነበር።
\v 18 ይህም ከከለዳውያን ፍርሃት የተነሣ ነበር። የባቢሎን ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን እስማኤል ስለ ገደለው ፈሯቸው።
\s5
\c 42
\p
\v 1 ከዚያም የጭፍራ አለቆች ሁሉ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ የሆሻያም ልጅ ያእዛንያ፣ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ያሉት ሕዝብ ወደ ነብዩ ኤርምያስ ቀረቡ።
\v 2 እንዲህም አሉት፣ "ልመናችን በፊትህ ይድረስ። እንዳየኸው ከብዙዎቹ መካከል የቀረነው ጥቂቶች ነንና፣
\v 3 የምንሄድበትን መንገድና፣ የምናደርገውን ነገር እንዲያሳየን ስለ እኛና ስለዚህ ቅሬታ ሕዝብ ወደ አምላክህ እግዚአብሔር ጸልይ" አሉት።
\s5
\v 4 ስለዚህ ነቢዩ ኤርምያስ፣ "ሰምቻችኋለሁ። ተመልከቱ፣እንደጠየቃችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ። እግዚአብሔርም የሚመልስላችሁን ሁሉ እነግራችኋለሁ። ከእናንተ ምንም አልሸሽግም፤" አላቸው።
\v 5 እነርሱም ለኤርምያስ፣ "አምላክህ እግዚአብሔር ወደ እኛ የላከውን ነገር ሁሉ ባናደርግ፣ እግዚአብሔር በመካከላችን እውነተኛና ታማኝ ምስክር ይሁን።
\v 6 የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፣ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ እንሰማለን አሉት።"
\s5
\v 7 ከዚያም ከዐሥር ቀን በኋላ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ መጣ።
\v 8 ስለዚህ ኤርምያስ የቃሬያንም ልጅ ዮሐናንን ከእርሱም ጋር የነበሩትን የሠራዊቱን አለቆች ሁሉ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሕዝቡንም ሁሉ ጠራ።
\v 9 እንዲህ አላቸው፣ "ጸሎታችሁን በፊቱ አቀርብ ዘንድ ወደ እርሱ የላካችሁኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣
\v 10 'በእናንተ ላይ ያመጣሁባችሁን ጥፋት እመልሳለሁና ተመልሳችሁ በዚህች ምድር ብትኖሩ፣እሠራችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፣ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም።
\s5
\v 11 የምትፈሩትን የባቢሎን ንጉሥ አትፍሩ። አድናችሁ ዘንድ፣ ከእጁም አስጥላችሁ ዘንድ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና አትፍሩ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 12 ምሕረትን እሰጣችኋለሁና። እርሱ እንዲምራችሁ ወደ ምድራችሁም እንዲመልሳችሁ እኔ እራራላችኋለሁ።
\s5
\v 13 እናንተ ግን፣"በዚህች ምድር አንቀመጥም" ብትሉ፣ የእኔን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ባትሰሙ፣
\v 14 እናንተም፣ "አይሆንም! የትኛውንም ጦርነት ወደማናይባት፣ የመለከትም ድምፅ ወደማንሰማባት፣ ወደማንራብባት ወደ ግብጽ ምድር እንሄዳለን። በዚያ እንኖራለን" ብትሉ፣
\s5
\v 15 አሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ እናንተ የይሁዳ ቅሬታ የሆናችሁ። የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ወደ ግብጽ እንድትገቡ፣ በዚያም እንድትኖሩ በእርግጥ ፊታችሁን ብታቀኑ፣
\v 16 ያኔ የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብጽ ምድር ያገኛችኋል። የምትደነግጡበት ረሃብ በዚያ በግብጽ ይደርስባቸኋል። በዚያም ትሞታላችሁ።
\v 17 ስለዚህ ወደ ግብጽ እንዲገቡ፣ በዚያም እንዲኖሩ ፊታቸውን የሚያቀኑ ሰዎች ሁሉ በሰይፍ፣ በረሃብ፣ ወይም በመቅሠፍት፣ ይሞታሉ። እኔም ከማመጣባቸው ክፉ ነገር ማንም አይተርፍም፣ ማንም አያመልጥም።
\s5
\v 18 የእስራኤል አምላክ፣የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላልና፦ ቊጣዬና መዓቴ በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ላይ እንደ ፈሰሰ፣ እንዲሁ ወደ ግብጽ የምትገቡ ከሆነ መዓቴ ይፈስስባችኋል። እናንተም ለእርግማንና ለመደንገገጪያ፣ ለመረገሚያና ለመዋረጂያ ትሆናላችሁ። ደግሞም ይህንን ስፍራ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩትም።"
\v 19 ከዚያም ኤርምያስ እንዲህ አለ፣ "እናንተ የይሁዳ ቅሬታዎች፣ እግዚአብሔር፣ ወደ ግብጽ አትሂዱ ብሎ ተናግሯችኋልና ዛሬ ምስክር እንደሆንኩባችሁ በእርግጥ እወቁ።
\s5
\v 20 'ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። አምላካችንም እግዚአብሔር የሚናገርህን ሁሉ ንገረን፣ እኛም እንፈጽመዋለን' ብላችሁ ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ስትልኩኝ የሕይወት ዋጋ የሚያስከፍላችሁን ነገር አድርጋችኋልና።
\v 21 እኔም ዛሬ ነግሬአችኋለሁ፣ ወደ እናንተም በላከኝ ነገር ሁሉ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማችሁም።
\v 22 ስለዚህ፣ አሁንም ሄዳችሁ እንድትኖሩበት በወደዳችሁበት ስፍራ በሰይፍ፣ በራብ፣ በቸነፈር እንድትሞቱ በእርግጥ እወቁ።"
\s5
\c 43
\p
\v 1 ኤርምያስ አምላካቸው እግዚአብሔር ለእነርሱ የላከውን ይህንን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ፣ለሕዝቡ ሁሉ ተናግሮ ጨረሰ።
\v 2 የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ፣ የቃሬያም ልጅ ዮሐናን፣ ትዕቢተኞችም ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን፣ "ሐሰትን እየተናገርክ ነህ። አምላካችን እግዚአብሔር፣ 'በዚያ ትቀመጡ ዘንድ ወደ ግብጽ አትግቡ ብሎ አልላከህም፤'
\v 3 ነገር ግን ከለዳውያን እንዲገድሉን ወደ ባቢሎንም እንዲማርኩን በእጃቸው አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርያ ልጅ ባሮክ በላያችን ላይ አነሣሥቶሃል" አሉት።
\s5
\v 4 ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ የጦር ሠራዊቱ አለቆች ሁሉ፣ ሕዝቡም ሁሉ በይሁዳ ምድር ይኖሩ ዘንድ የእግዚአብሔርን ቃል አልሰሙም።
\v 5 የቃሬያም ልጅ ዮሐናን የጭፍራ አለቆችም ሁሉ በይሁዳ ምድር ለመኖር ከተሰደዱባቸው ከአሕዛብ ሁሉ የተመለሱትን የይሁዳን ቅሬታ ሁሉ ወሰዱ።
\v 6 እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆችን፣ የንጉሡንም ሴቶች ልጆች፣ የዘበኞቹንም አለቃ ናቡዘረዳን፣ ከሳፋን ልጅ፣ ከአኪቃም ልጅ ከጎዶልያስ ጋር የተዋቸውን ሰዎች ሁሉ፣ ነቢዩንም ኤርምያስን የኔርያንም ልጅ ባሮክን ወሰዱ።
\v 7 የእግዚአብሔርንም ቃል ስላልሰሙ ወደ ግብጽ ምድር ሄዱ፣ እስከ ጣፍናስ ድረስ መጡ።
\s5
\v 8 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል በጣፍናስ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 9 "ታላላቆችን ድንጋዮች በእጅህ ውሰድ፣ የይሁዳም ሰዎች እያዩ በጣፍናስ ባለው በፈርዖን የጡብ ቤት ደጅ መግቢያ ሸሽጋቸው።"
\v 10 ከዚያም እንዲህ በላቸው፣ "የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን አገልጋዬ ለማድረግ መልእክተኛ እልክበታለሁ። ዙፋኑንም አንተ፣ ኤርምያስ በሸሸግሃቸው በእነዚህ ድንጋዮች ላይ አኖራለሁ። ናቡከደነፆር ማለፊያ ድንኳኑን በላያቸው ይዘረጋል።
\s5
\v 11 መጥቶም የግብጽን ምድር ያጠቃል። ለሞት የተመደበውን ለሞት ይሰጣል። ለምርኮም የተመደበው ለምርኮ ይወሰዳል። ለሰይፍ የተመደበው ለሰይፍ ይሰጣል።
\v 12 ከዚያም፣ በግብጽ አማልክት ቤቶች ላይ እሳትን አነድዳለሁ። ናቡከደነፆር ያቃጥላቸዋል ወይም ይማርካቸዋል። እረኞች ከደበሏቸው ተባይን እንደሚያራግፉ፣ እንዲሁ የግብጽን አገር ያጸዳል። ከዚያም ስፍራ በድል ይወጣል።
\v 13 በግብጽም ምድር ያለውን የሄልዮቱን ከተማ ሐውልቶች ይሰብራል። የግብጽንም አማልክት ቤቶች በእሳት ያቃጥላል።"
\s5
\c 44
\p
\v 1 በግብጽ ምድር በሚግዶልና በጣፍናስ በሜምፎስም በጳትሮስም አገር ስለ ተቀመጡ አይሁድ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
\v 2 "የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ያመጣሁትን ክፉ ነገር ሁሉ እናንተ ራሳችሁ አይታችኋል። ተመልከቱ፣ ዛሬ ጠፍተዋል። የሚኖርባቸው የለም።
\v 3 ይህም የሆነው ለሌሎች አማልክት በማጠንና በማምለክ ያስቀይሙኝ ዘንድ ስላደረጉት ክፋት ነው። እነዚህም አማልክት እነርሱ ራሳቸው፣ አንተም ራስህ፣ እንዲሁም አባቶቻቸው የማያውቋቸው ናቸው።
\s5
\v 4 ስለዚህ በተደጋጋሚ ባርያዎቼን ነብያትን ሁሉ ሰደድሁባችሁ። 'እንደነዚህ ያሉ የጠላኋቸውን ርኩስ ነገሮች ማድረጋችሁን አቊሙ' ልላቸው ላክኋቸው።
\v 5 ነገር ግን አልሰሙም። ከክፋታቸው ተመልሰው ለሌሎች አማልክት እንዳያጥኑ አትኩሮታቸውን ለመስጠት አልፈለጉም።
\v 6 ስለዚህ መዓቴና ቍጣዬ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ ፈሰሱ፣ ደግሞም እንደ እሳት ተቀጣጠሉ። ዛሬም እንደ ሆነው ፈረሱ፣ ባድማም ሆኑ።"
\s5
\v 7 አሁንም ቢሆን፣ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ወንድንና ሴትን፣ ብላቴናንና ሕፃንን ከይሁዳ እንድታጠፉ ይህን ታላቅ ክፋት በራሳችሁ ላይ ለምን ታደርጋላችሁ? ከመካከላችሁ የአንዳችሁም ቅሬታ አይተርፍም።
\v 8 ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ፣ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፣ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብጽ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
\s5
\v 9 በይሁዳ ምድርና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያደረጉትን የአባቶቻችሁን ክፋት፣ የይሁዳንም ነገሥታት ክፋት፣ የሚስቶቻቸውንም ክፋት፣ የእናንተንም ክፋት፣ የሚስቶቻችሁንም ክፋት ረስታችሁታልን?
\v 10 እስከ ዛሬ ድረስ ትሑታን አልሆኑም። በእነርሱና በአባቶቻቸውም ፊት ያኖርሁትን ሕጌን ወይም ሥርዓቴን አላከበሩም፣ አልሄዱበትም።"
\s5
\v 11 ስለዚህም የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፦ "ተመልከቱ፣ በእናንተ ላይ ጥፋትን ለማድረግ እና ይሁዳን ሁሉ ላጠፋ ፊቴን በላያችሁ ላይ አደርጋለሁ።
\v 12 ወደ ግብጽ ሄደው በዚያ እንዲኖሩ ፊታቸውን ያቀኑትን የይሁዳን ቅሬታ እወስዳለሁና። ይህን የማደርገው ሁሉም በግብጽ ምድር እንዲጠፉ ነው። እነርሱ በሰይፍና በራብ ይጠፋሉ። ከታናሹም ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ በሰይፍና በራብ ይሞታሉ፤ ለጥላቻና ለመደነቂያ፣ ለመረገሚያና ለመሰደቢያ ይሆናሉ።
\s5
\v 13 ኢየሩሳሌምን በሰይፍ፣ በረሃብ እና በመቅሠፍት እንደ ቀጣሁ፣ እንዲሁ በግብጽ ምድር የሚኖሩትን እቀጣለሁ።
\v 14 በዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ ምድር ከሄዱ እንኳን ወደ ይሁዳ አገር ተመልሰው በዚያ ይኖሩ ዘንድ ከሚወድዱ ከይሁዳ ቅሬታ ወገን የሚያመልጥና የሚቀር፣ ወደዚያም የሚመለስ የለም። ከዚህ ከሚያመልጥ በቀር ማንም አይመለስም።"
\s5
\v 15 ከዚያም ሚስቶቻቸው ለሌሎች አማልክት ማጠናቸውን ያወቁ ሰዎች ሁሉ፣ በዚያም የቆሙ ሴቶች ሁሉ፣ በግብጽ ምድር በጳጥሮስ የተቀመጡ ሕዝብ ሁሉ፣ ታላቅ ጉባኤ ሆነው እንዲህ ሲሉ ለኤርምያስ መለሱለት።
\v 16 እነርሱም እንዲህ አሉ፣ "በእግዚአብሔር ስም የነገርኸንን ቃል አንሰማህም።
\v 17 እኛና አባቶቻችን፣ ነገሥታቶቻችን፣ አለቆቻችንም በይሁዳ ከተሞች በኢየሩሳሌም አደባባይ እናደርገው እንደ ነበረ፣ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቊርባን እንድናፈስስላት ከአፋችን የወጣውን ቃል ሁሉ በእርግጥ እናደርጋለን። ያን ጊዜ እንጀራ እንጠግባለን፣ ደግሞም የትኛውም ጥፋት ሳይደርስብን እንበለጽጋለን።
\s5
\v 18 ለሰማይ ንግሥት ማጠንን ለእርስዋም የመጠጥን ቍርባን ማፍሰስን ከተውን ወዲህ ግን፣በድህነት ተሰቃይተናል፣ ደግሞም በሰይፍና በረሃብ አልቀናል።"
\v 19 ሴቶቹም እንዲህ አሉ፣ "እኛስ ለሰማይ ንግሥት ባጠንንላት፣ የመጠጥንም ቍርባን ባፈሰስንላት ጊዜ፣ ባሎቻችን ሳያውቊ ምስልዋን ለማበጀት እንጐቻ አድርገንላት ኖሮአልን? የመጠጥንም ቍርባን አፍስሰንላት ኖሮአልን?"
\s5
\v 20 ኤርምያስም ይህን ቃል ለመለሱለት ሕዝብ ሁሉ፣ ለወንዶቹና ለሴቶቹ፣ ለሕዝቡም ሁሉ፣ መለሰላቸው እንዲህም አለ፣
\v 21 "እናንተና አባቶቻችሁ፣ ነገሥታቶቻችሁና አለቆቻችሁም፣ የምድርም ሕዝብ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ያጠናችሁትን ዕጣን እግዚአብሔር ያሰበው በልቡም ያኖረው አይደለምን?
\s5
\v 22 ከክፉ ልምምዳችሁ የተነሣ፣ ከእንግዲህ ወዲህ የሥራችሁን ክፋትና ያደረጋችሁትን ርኵሰት እግዚአብሔር ይታገሥ ዘንድ አልቻለም። ስለዚህ ምድራችሁ ባድማ፣ መደነቂያ፣ መረገሚያም ሆናለች ዛሬም እንደሆነው የሚኖርባት የለም።
\v 23 እጣን ስላጠናችሁና በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ስለሠራችሁ፣ ድምፁንም ስላልሰማችሁ፣ በሕጉ፣ በሥርዓቱና በምስክሩም ስላልሄዳችሁ፣ ዛሬ እንደሆነው ይህች ክፉ ነገር አግኝታችኋለች።"
\s5
\v 24 ከዚያም ኤርምያስ ለሕዝቡ ሁሉ፣ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፣ "በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
\v 25 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ፣ "ለሰማይ ንግሥት እንድናጥን፣ የመጠጥንም ቍርባን እንድናፈስስላት የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን።" ብላችሁ በእጃችሁ አደረጋችሁት፤ እንግዲህ ስእለታችሁን አጽኑ፣ ፈጽሙትም።'
\s5
\v 26 ስለዚህ፣ እናንተ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ 'ተመልከቱ፣ በግብጽ ምድር ሁሉ በሚኖር በይሁዳ ሰው ሁሉ አፍ ስሜ ከእንግዲህ ወዲህ፣ "ሕያው እግዚአብሔርን!" ተብሎ እንዳይጠራ በታላቅ ስሜ ምያለሁ፤" ይላል እግዚአብሔር።
\v 27 ተመልከቱ፣ ለመልካም ሳይሆን ለጥፋት እተጋባቸዋለሁ። በግብጽ ምድር ያሉት የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ያልቃሉ።
\v 28 ከዚያም ከሰይፍ የሚያመልጡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ሆነው ከግብጽ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ። ሊቀመጡም ወደ ግብጽ ምድር የገቡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንዲጸና ያውቃሉ።
\s5
\v 29 ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚህች ስፍራ እንድቀጣችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፣' ይላል እግዚአብሔር።
\v 30 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ጠላቱ ለሆነው፣ ነፍሱንም ለሚፈልገው ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደነፆር እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። ሁኔታው የግብጹን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራንን ለጠላቶቹ ነፍሱንም ለሚፈልጉ እጅ አሳልፌ እንደሰጠሁት ይሆናል።"
\s5
\c 45
\p
\v 1 ኤርምያስ ለኔርያ ልጅ ለባሮክ የነገረው ቃል ይህ ነበር። ይህም የሆነው በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት ኤርምያስ እየነገረው በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ ነበር፤ እርሱም እንዲህ አለ፣
\v 2 "ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይልሃል፦
\v 3 አንተ፣ 'እግዚአብሔር በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ። በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፤ ዕረፍትንም አላገኘሁም' ብለሃል።
\s5
\v 4 ልትለው የሚገባህ ይህንን ነው፦ 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ የሠራሁትን፣ አሁን እያፈረስኩ ነው። የተከልሁትንም፣ እየነቀልሁ ነው። ይኽም በምድር ሁሉ ላይ እውነት ነው።
\v 5 ነገር ግን ለራስህ ታላቅ ነገር ተስፋ ታደርጋለህን? ያንን ተስፋ አታድርግ። በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ክፉ ነገርን እንደማመጣ ትመለከታለህና አትፈልገው፣ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን በሄድህበት ስፍራ ሁሉ ነፍስህን እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።"
\s5
\c 46
\p
\v 1 ስለ አሕዛብ ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
\v 2 ስለ ግብጽ፦ "ይህ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በከርከሚሽ ስለ ነበረው ሠራዊት ነው። በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታው ስለ ግብጽ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ኒካዑ ሠራዊት፦
\v 3 ትንንሾቹን እና ትልልቆቹን ጋሻዎች አዘጋጁና ወደ ውጊያ ሂዱ።
\v 4 ፈረሰኞች ሆይ፣ ፈረሶችን ለጉሙና ውጡ፣ ራስ ቍርንም ደፍታችሁ ቁሙ። ጦርንም ሰንግሉ፣ የጦር ዕቃንም ልበሱ።
\s5
\v 5 በዚህ የማየው ምንድነው? ወታደሮቻቸው ተሸንፈዋልና፣ በፍርሃት ተሞልተው ወደ ኋላ ተመለሱ። ወደ ኋላቸውም ሳይመለከቱ ፈጥነው ሸሹ። ድንጋጤ በሁሉ ቦታ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 6 ፈጣኑ ሊሸሽ አይችልም፣ ወታደሮችም ሊያመልጡ አይችሉም። በሰሜን ተሰናከሉ፣ በኤፍራጥስ ወንዝ በኩል ደግሞ ወደቁ።
\s5
\v 7 ይህ እንደ አባይ ወንዝ የሚነሣ፣ ውኃውም እንደ ወንዝ የሚናወጥለት ማን ነው?
\v 8 ግብጽ እንደ አባይ ወንዝ ይነሣል፣ ውኃውም እንደ ወንዙ ይናወጣል። እርሱም፣' እነሣለሁ ምድርንም ሁሉ እከድናለሁ። ከተሞችንና የሚኖሩባቸውን አጠፋለሁ ብሎአል።
\v 9 ፈረሶች ሆይ፣ ውጡ። ሠረገሎችም ሆይ፣ ንጐዱ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፋጥ ኃያላን፣ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።'
\s5
\v 10 ያ ቀን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር የበቀል ቀን ነው፣ ደግሞም ጠላቶቹን እርሱ ራሱ ይበቀላቸዋል። ሰይፍ በልቶ ይጠግባል። ደማቸውንም ተሞልቶ ይጠጣል። ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር በሰሜን ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መሥዋዕት አለውና።
\s5
\v 11 ድንግሊቱ የግብጽ ሴት ልጅ ሆይ፣ ወደ ገለዓድ ውጪና መድኃኒት ውሰጂ። መድኃኒትን በራስሽ ላይ ማብዛትሽ ጥቅም የለሽ ነገር ነው። ለአንቺ የሚሆን ፈውስ የለም።
\v 12 ወታደሩ በወታደሩ ላይ ተሰናክሎ፣ ሁለቱ በአንድነት ወድቀዋልና አሕዛብ እፍረትሽን ሰምተዋል። ምድር በለቅሶሽ ተሞልታለች።"
\s5
\v 13 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር መጥቶ የግብጽን ምድር ሲያጠቃ እግዚአብሔር ለነብዩ ኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።
\v 14 "ለግብጽ ተናገሩ፣ በሚግዶልና በሜምፎስ ይሰማ። በጣፍናስ 'ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፣ ተነሥተህ ተዘጋጅ' ብለዋል።
\s5
\v 15 የከፍታ አምላክሽ ለምን ሸሸ? በበሬ የተመሰለው ጣዖትሽስ ለምን አይቆምም? እግዚአብሔር ገፍትሮ ጥሎታል።
\v 16 እርሱ የሚሰናከሉትን ቊጥር ያበዛል። እያንዳንዳቸው ወታደሮች አንዱ በሌላው ላይ ይወድቃል። እነርሱም፣ "ተነሡ። ወደቤት እንጂድ። ወደገዛ ሕዝባችን፣ ወደ ተወለድንባት ምድር እንሂድ። ይህንን እየቀጠቀጠን ያለውን ሰይፍ ትተን እንሂድ።" ይላሉ።
\v 17 በዚያም፣ ' የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ያገኘውን ዕድል የሚያሳልፍ ኁከተኛ ብቻ ነው" ብለው ይናገራሉ።
\s5
\v 18 "እኔ ሕያው ነኝና በተራሮች መካከል እንዳለ እንደ ታቦር፣ በባሕርም አጠገብ እንዳለ እንደ ቀርሜሎስ፣ እንዲሁ በእውነት ይመጣል፣ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።
\v 19 አንቺ በግብጽ የምትቀመጪ ልጅ ሆይ፣ ለምርኮ የምትሄጂበትን ዕቃ አዘጋጂ። ሜምፎስ የምትሸበር ትሆናለችና፣ ማንም በዚያ የማይኖርባት እንድትሆን ትፈራርሳለችና።
\s5
\v 20 ግብጽ እጅግ የተዋበች ጊደር ናት፣ ነገር ግን ከሰሜን በኩል የሚያሰቃይ መዥገር ይመጣባታል።
\v 21 በመካከሏም ያሉ ቅጥረኛ ወታደሮች እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፣ ነገር ግን እነርሱም እንዲሁ ይመለሱና ይሸሻሉ። የጥፋታቸው ቀን እየመጣባቸው ነውና፣ የቅጣታቸው ጊዜ መጥቶባቸዋልና በአንድነት አይቆሙም።
\v 22 ጠላቶቿ በእርሷ ላይ ይሰለፉባታልና ግብጽ እንደ እባብ ድምፅ ትጮኻለች፣ በደረቷም ተስባ ትሸሻለች። በመጥረቢያ እንደሚቆርጡ እንደ እንጨት ቈራጮች ሆነው ይመጡባታል።
\s5
\v 23 በጣም ጥቅጥቅ ያሉ ቢሆኑም እንኳን ጫካዎቿን ይቈርጣሉ፣ ይላል እግዚአብሔር። ጠላቶቿ ሊቆጠሩ እስከማይችሉ ድረስ ከአንበጣ ይልቅ ብዙ ይሆናሉና።
\v 24 የግብጽ ሴት ልጅ እንድታፍር ትደረጋለች። ከሰሜን ለሚሆኑ ሕዝቦች እጅ ተላልፋ ትሰጣለች።"
\s5
\v 25 የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እንዲህ ይላል፣ 'ተመልከቱ፣ የኖእ አሞንን፣ ፈርዖንንም፣ ግብጽንና አማልክቶችዋን፣ ፈርዖን ነገሥታቶችዋንና በእነርሱም የሚታመኑትን እቀጣለሁ።
\v 26 ነፍሳቸውንም በሚፈልጉ ሰዎች እጅ፣ በባቢሎን ንጉሥ በናቡክደነፆር እንዲሁም በባርያዎቹም እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ከዚያም በኋላ አንደ ቀድሞው ዘመን የሰው መኖሪያ ትሆናለች፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 27 "ነገር ግን፣ አንተ ባርያዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ። አንተም እስራኤል ሆይ፣ አትደንግጥ። እነሆ፥ አንተን ከሩቅ ዘርህንም ከተማረከባት ምድር አድናለሁ። ከዚያም፣ ያዕቆብ ይመለሳል፣ ሰላም ያገኛል፣ በዋስትናም ይቀመጣል፣ የሚያስፈራራው ማንም አይገኝም።
\v 28 አንተ፣ ባርያዬ ያዕቆብ፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተን ያሰደድሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁና አትፍራ ይላል እግዚአብሔር። ነገር ግን አንተን ፈጽሜ አላጠፋህም። በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም አልተውህም።"
\s5
\c 47
\p
\v 1 ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል ወደ እርሱ የመጣው ፈርዖን ጋዛን ሳይመታ በፊት ነው።
\v 2 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ውኃ ከሰሜን ይነሣል። እነርሱም እንደሚያጥለቀልቅ ፈሳሽ ይሆናሉ! ከዚያም በምድሪቱና በመላዋ ሁሉ፣ በከተማይቱና በሚኖሩባት ላይ ይጐርፋሉ! ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለእርዳታ ይጮኻል፣ በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
\s5
\v 3 ከኃይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፣ ከሰረገሎቹና ከጎማዎቻቸውም መሸከርከር ሁከት የተነሣ፣ አባቶች በገዛ ራሳቸው ድካም ምክንያት ልጆቻቸውን አይረዱም።
\v 4 ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ያጠፋ ዘንድ የቀሩትንም ረዳቶች ሁሉ ከጢሮስና ከሲዶና የሚቆርጥ ቀን ስለሚመጣ ነው። እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንና የከፍቶርን ደሴት ቅሬታ ያጠፋልና።
\s5
\v 5 ራሰ ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል። አስቀሎናን በተመለከተ፣ በሸለቋቸው የተተዉት ሕዝብ ዝም እንዲሉ ይደረጋሉ። እስከ መቼ ድረስ በለቅሶ ራሳችሁን ትነጫላችሁ?
\v 6 ወዮ፣ የእግዚአብሔር ሰይፍ! ዝም እስከምትል ምን ያክል ትቆያለህ? ወደ ሰገባህ ተመለስ! ቊም ደግሞም ጸጥ በል።
\v 7 እግዚአብሔር አዝዞሃልና እንዴት ዝም ልትል ትችላለህ። በአስቀሎናና በባሕር ዳር ላይ ጥቃት እንድትፈጽም አዘጋጅቶሃልና።"
\s5
\c 48
\p
\v 1 ስለ ሞዓብ፣ የእስራኤል አምላክ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ናባው ጠፍታለችና ወዮላት። ቂርያታይም ተይዛለች አፍራለችም። ምሽጓ ተደምስሷል፣ ተዋርዷልም።
\v 2 ከእንግዲህ ወዲህ ሞዓብ ትምክሕት የላትም። በሐሴቦን ያሉ ጠላቶቿ በእርሷ ላይ ጥፋትን አሲረዋል። 'ኑ ሕዝብ እንዳትሆን እናጥፋት። ማድሜንም እንዲሁ ትጠፋለች፣ ሰይፍም ይከታተልሻል።' ብለዋል።
\s5
\v 3 አድምጡ! መፍረስና ታላቅ ጥፋት ያለበት የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ።
\v 4 ሞዓብ ጠፍታለች። ልጆችዋም ጩኸታቸውን አሰምተዋል።
\v 5 በሉሒት ኮረብታ ለቅሶ እያለቀሱ ይወጣሉ፣ ከጥፋቱም የተነሣ፣ በሖሮናይምም ቍልቍለት ጩኸትን ሰምተዋል።
\s5
\v 6 ሸሹ! ሕይወታችሁን አድኑና በምድረ በዳ እንዳለ ቊጥቋጦ ሁኑ።
\v 7 በሥራሽና በኃብትሽ ታምነሻልና፣ አንቺ ደግሞ ትያዢያለሽ። ከዚያም፣ ካሞሽ ከካህናቱና ከመሪዎቹ ጋር በአንድነት ወደ ምርኮ ይሄዳል።
\s5
\v 8 አጥፊው ወደየከተማው ሁሉ ይመጣል፣ አንዲትም ከተማ አታመልጥም። ስለዚህ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ሸለቆው ይጠፋል፣ ሜዳውም ይበላሻል።
\v 9 በእርግጥም በርራ እንድትጠፋ ለሞዓብ ክንፍ ስጡአት። ከተሞችዋ በውስጣቸው አንድም የማይኖርባቸው ወና ይሆናሉ።
\v 10 የእግዚአብሔርን ሥራ በስንፍና የሚሠራ ርጉም ይሁን! ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚከለክል ርጉም ይሁን!
\s5
\v 11 ሞዓብ ከወጣትነቱ ጀምሮ ደህንነት ይሰማው ነበር። እርሱ ከዕቃ ወደ ዕቃ ተገላብጦ እንደማያውቀው ወይኑ ነው። ወደ ምርኮም ሄዶ አያውቅም። ስለዚህ ጣዕሙ ከመቼውም ጊዜ በላይ መልካም ነው፣ መዓዛውም አልተለወጠም።
\v 12 ስለዚህ ተመልከቱ፣ የሚያገላብጡትን ሰዎች የምልክበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ እነርሱም እያፈሰሱ ጋኖቹን ባዶ ያደርጋሉ፣ መስቴዎቹንም ይሰብራሉ።
\s5
\v 13 የእስራኤል ቤት ከታመነበት ቤተል እንዳፈረ ሁሉ፣ እንዲሁ ሞዓብ ከታመነበት ካሞሽ ያፍራል።
\v 14 እናንተ፣ 'እኛ ወታደሮች ነን፣ ጽኑዓን ተዋጊዎች ነን' እንዴት ትላላችሁ?
\s5
\v 15 ሞዓብ ይፈርሳል፣ ከተሞቹም ጥቃት ይፈጸምባቸዋል። የተመረጡትም ጕልማሶች ወደ መታረድ ወርደዋል። ይህ የንጉሡ አዋጅ ነው! ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
\v 16 የሞዓብ ጥፋት ሊመጣ ቀርቦአል፤ መከራውም እጅግ ይፈጥናል።
\v 17 በሞዓብ ዙሪያ ያላችሁ ሁሉ፣ አልቅሱ። ዝናውንም የምታውቁ ሁሉ፣ 'ብርቱው በትር፣ የከበረው ሽመል ተሰብሯልና ወዮለት' ብላችሁ አልቅሱለት።
\s5
\v 18 በዲቦን የምትኖሪ ሴት ልጅ ከክብር ስፍራሽ ውረጂና በደረቅ መሬት ላይ ተቀመጪ። ሞዓብን የሚያጠፋው፣ ምሽግሽንም የሚሰብረው ወጥቶብሻልና።
\v 19 በአሮዔር የምትኖሩ ሕዝቦች በመንገድ አጠገብ ቆማችሁ ተመልከቱ። እየሸሹ ያሉትንና የሚያመልጡትን ጠይቊ። 'ምን ተፈጠረ?' በሉ።
\v 20 ሞዓብም ፈራርሷልና አፈረ። አልቅሱ፣ ጩኹ፣ ለእርዳታም ተጣሩ። ሞዓብ እንደ ተዘረፈ በአርኖን አጠገብ ለሰዎች አውሩ።
\s5
\v 21 አሁን በኮረብታማው ገጠር ላይ ባሉት በሖሎን፣ በያሳ፣ በሜፍዓት ላይ፣
\v 22 በዲቦን፣ በናባው፣ በቤት ዲብላታይም ላይ፣
\v 23 በቂርያታይም፣ በቤትጋሙል፣
\v 24 በቤትምዖን ላይ፣ በቂርዮት፣ በባሶራ፣ እና በሞዓብ ምድር ባሉ የቅርብና ሩቅ ከተሞች ሁሉ ላይ ቅጣት መጥቶአል።
\v 25 የሞዓብ ቀንድ ተቈረጠ፤ ክንዱም ተሰበረ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 26 በእኔ በእግዚአብሔር ላይ ኰርቷልና አስክሩት። እንግዲህ ሞዓብ በገዛ ራሱ ትውከቱ ላይ በጥላቻ እጆቹን ያጨበጭባል፣ ደግሞም መሳለቂያ ይሆናል።
\v 27 እስራኤል ለአንተ መሳለቂያህ አልሆነምን? ወይስ ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ሁሉ ራስህን እንድትነቀንቅ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን?
\s5
\v 28 እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፣ ከተሞችን ትታችሁ በቋጥኝ ውስጥ ተቀመጡ። በዐለታማ ገደል አፋፍ ቤትዋን እንደምትሠራ ርግብ ሁኑ።
\v 29 እጅግ እንደ ታበየ ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ ስለ ትምክህቱም፣ ስለ ኩራቱም፣ ራሱን ስለማክበሩም፣ ስለ ልቡም ትዕቢት ሰምተናል።
\s5
\v 30 ምንም ሆኖ የማይቆጠረውን የድንፋታ ንግግሩን እኔ ራሴ አውቃለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ፉከራው ምንም አልሠራም።
\v 31 ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፣ በኃዘኔታ ለመላዋ ሞዓብ እጮኻለሁ። ለቂርሔሬስ ሰዎች አለቅሳለሁ።
\v 32 አንቺ የሴባማ ወይን ሆይ፣ ከኢያዜር ልቅሶ ይልቅ ለአንቺ አለቅሳለሁ! ቅርንጫፎችሽ የጨው ባሕርን ተሻግረው ወደ ኢያዜር ባሕር ደርሰዋል። አጥፊዎች በሰብልሽና በወይንሽ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል።
\s5
\v 33 ክብረ-በዓላዊ ሐሤትና ፍንደቃ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል። የወይን ጠጁን ከመጥመቂያው አጥፍቻለሁ። ጠማቂውም በደስታ እልልታ አይጠምቅም። እልልታቸውም የደስታ እልልታ አይሆንም።
\s5
\v 34 ከሐሴቦን ጩኸት እስከ ኤልያሊና፣ እስከ ያሀጽ ድረስ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፤ ከዞዓር እስከ ሖሮናይምና እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ ይደርሳል፤ የኔምሬም ውኃዎች ደርቀዋልና።
\v 35 በኮረብታው መስገጃ ላይ የሚሠዋውን ለአማልክቱም የሚያጥነውን ከሞዓብ ፍጻሜያቸውን አደርጋለሁ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 36 ልቤ ለሞዓብ እንደ እንቢልታ ይጮኻል። ልቤም ለቂርሔሬስ ሰዎች እንደ እንቢልታ ይጮኻል። ያገኙት ትርፋቸው ጠፍቶባቸዋልና።
\v 37 ራስ ሁሉ መላጣ፣ ጢምም ሁሉ የተላጨ ነውና። በእጅም ሁሉ ላይ ክትፋት በወገብም ላይ ማቅ አለና።
\s5
\v 38 በሞዓብ ሰገነት ሁሉ ላይ፣ በእያንዳንዱም የተደላደለ ጣራ እና በሁሉም የሞዓብ አደባባዮች ላይ ለቅሶ አለ። ሞዓብን ማንም እንደማይፈልጋቸው የሸክላ ዕቃዎች ሰብሬአለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 39 እንዴት ተገለበጠ! ከለቅሶም የተነሣ ሞዓብ እያፈረ ጀርባውን እንዴት መለሰ! ብላችሁ አልቅሱ። ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና ድንጋጤ ይሆናል።"
\s5
\v 40 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ ጠላት እንደ ንስር እየበረረ፣ ክንፉንም በሞዓብ ላይ እየዘረጋ ይመጣል።
\v 41 ከተሞቹ ተይዘዋል፣ ምሽጎቹም ተይዘዋል። በዚያም ቀን የሞዓብ ወታደሮች ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።
\s5
\v 42 ስለዚህ ሞዓብ በእኔ በእግዚአብሔር ላይ እብሪተኛ ሆኗልና ሕዝብ ከመሆን ይጠፋል።
\v 43 በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፣ ፍርሃትና ጉድጓድ፣ ወጥመድም በእናንተ ላይ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 44 በፍርሃት የሸሸ በጕድጓድ ውስጥ ይወድቃል፥ ከጉድጓድም የወጣ በወጥመድ ይያዛል፤ በሞዓብ ላይ የምበቀልበትን ዓመት አመጣበታለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 45 የሸሹ ያለ ምንም ብርታት ከሐሴቦን ጥላ በታች ቆመዋል፤ እሳት ከሐሴቦን፣ ነበልባልም ከሴዎን ወጥቶአልና፣ የሞዓብንም ማዕዘን የሤትንም ልጆች አናት በልቶአልና።
\s5
\v 46 ሞዓብ ሆይ፣ ወዮልህ! የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሰዋል፣ ወንዶች ልጆችህ ተማርከዋልና፣ ሴቶች ልጆችህም ወደ ምርኮ ሄደዋልና።
\v 47 ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የሞዓብን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።" የሞዓብ ፍርድ እዚህ ላይ ያበቃል።
\s5
\c 49
\p
\v 1 ስለ አሞን ልጆች፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "እስራኤል ልጆች የሏትምን? ወይስ የትኛውንም ነገር ከእስራኤል የሚወርስ የላትምን? ሚልኮም ጋድን ለምን ወረሰ? ሕዝቡስ በከተሞቿ ላይ ስለ ምን ተቀመጠ?
\v 2 ስለዚህ ተመልከቱ፣ በአሞን ልጆች ከተማ በረባት ላይ የጦርነት ውካታን የማሰማበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች፣ ሴቶች ልጆችዋም በእሳት ይቃጠላሉ። እስራኤልም የወረሷትን ትወርሳለች፣" ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 3 "ሐሴቦን ሆይ፣ ጋይ ፈርሳለችና አልቅሺላት! እናንተም የረባት ሴቶች ልጆች ጩኹ! ማቅ ልበሱ። ሚልኮም ካህናቱና አለቆቹም በአንድነት ይማረካሉና ጩኹ፣ ማቅም ታጠቁ፣ አልቅሱም፣ በቅጥሮችም መካከል ተሯሯጡ።
\v 4 ማን ይመጣብኛል ብለሽ በብርታትሽ የታመንሽ አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ፣ በሸለቆችሽ፣ ውኃ በሚያረካቸው ሸለቆችሽ፣ ስለ ምን በብርታትሽ ትመኪያለሽ?
\s5
\v 5 ተመልከቺ፣ ሽብርን አመጣብሻለሁ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ይህ ሽብር በዙሪያሽ ከከበቡሽ ሁሉ ዘንድ ይሆናል። እያንዳንዳችሁም በፊታችሁ ወዳለው ስፍራ ትበተናላችሁ። የሚሸሹትንም የሚሰበስብ አይኖርም።
\v 6 ነገር ግን ከዚያ በኋላ የአሞንን ልጆችን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 7 ስለ ኤዶምያስ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "በውኑ በቴማን ከእንግዲህ ጥበብ አይገኝምን? ማስተዋል ካላቸውስ መልካም ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸው ተበላሽቷልን?
\v 8 ሽሹ! ተመለሹ! እናንተ በድዳን የምትኖሩ ሆይ፣ በጥልቅ ውስጥ ተቀመጡ። የዔሳውን ጥፋት እርሱን በምቀጣበት ጊዜ አመጣበታለሁና
\s5
\v 9 የወይን አዝመራ ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ፣ቃርሚያውን አይተውልህምን? ሌቦችስ በሌሊት ቢመጡ፣ የሚሠርቁት እስኪበቃቸው ድረስ አይደለምን?
\v 10 እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት። የተሸሸገበትንም ስፍራዎች ገለጥሁ። ስለዚህ ይሸሸግ ዘንድ አይችልም። ልጆቹ፣ ወንድሞቹ፣ እንዲሁም ጎረቤቶቹ ጠፍተዋል፤ እርሱም የለም።
\v 11 ድሀ አደጎችህን ተዋቸው። እኔም ለሕይወታቸው እንክብካቤ አደርጋለሁ፤ መበለቶችህም በእኔ ሊታመኑ ይችላሉ።"
\s5
\v 12 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ "ተመልከቱ ያልተገባቸው ሰዎች ጽዋውን በእርግጥም ሊጠጡት ይገባቸዋል። አንተም ሳትቀጣ የምትቀር ይመስልሃልን? በእርግጥ ትጠጣለህ እንጂ ያለ ቅጣት አትቀርም።
\v 13 ባሶራ መደነቂያና መሰደቢያ፣ መረገሚያም እንድትሆን በራሴ ምያለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር። ከተሞችዋም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።
\s5
\v 14 ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ፣ መልእክተኛም በአሕዛብም መካከል ተልኳል፣ 'ተሰብሰቡ፣ እርስዋንም አጥቊ። ለጦርነትም ተነሡ' ይላል።
\v 15 "ተመልከቱ፣ በንጽጽር ስትታይ በአሕዛብ ዘንድ የተጠቃህ፣ በሰዎችም ዘንድ የተናቅህ አድርጌሃለሁ።
\s5
\v 16 በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትኖር፣ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ፣ ድፍረትህና የልብህ ኵራት አታልለውሃል። ቤትህን ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፣ ከዚያ አወርድሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 17 ኤዶምያስም የሚያልፉባት ሁሉ እስኪደነቁ ድረስ መሸበሪያ ትሆናለች። ስለ መጣባትም መቅሠፍት ሁሉ እንዲህ ያሉ ሰዎች ሁሉ ተደናግጠው ያፍዋጩባታል።
\v 18 "ሰዶምና ገሞራ፣ በእነርሱም አጠገብ የነበሩት ከተሞች እንደ ተገለበጡ፣" ይላል እግዚአብሔር፣ "እንዲሁ በዚያ ሰው አይቀመጥም የሰው ልጅም አይኖርባትም።
\s5
\v 19 ተመልከቱ፣ ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት እንደ አንበሳ ይወጣል፤ የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?
\s5
\v 20 "ስለዚህ እግዚአብሔር በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፣ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ አድም። በእውነት ትንንሽ መንጎች ሳይቀሩ ይጐተታሉ። በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል።
\s5
\v 21 ከመውደቃቸው ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች። የጩኸታቸውም ድምፅ በቀይ ባሕር ተሰማ።
\v 22 ተመልከቱ፣ አንዱ መጥቶ እንደ ንስር ወጥቶ ያጠቃል፣ እያንዣበበ ክንፉን በባሶራ ላይ ይዘረጋል። ያን ጊዜ በዚያ ቀን፣ የኤዶምያስ ወታደሮች ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።"
\s5
\v 23 ስለ ደማስቆ፣ "ክፉ ወሬ ሰምተዋልና ሐማትና አርፋድ አፈሩ። ቀለጡ! ሊረጋጋ በማይችል ባሕር ላይ ኅዘን አለ።
\v 24 ደማስቆ እጅግ ደከመች። ትሸሽም ዘንድ ዘወር አለች፤ ሽብር ያዛት፣ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።
\v 25 ሕዝቦቿም፣ 'የተመሰገነችው ከተማ፣ የደስታዬ ከተማ፣ ስፍራውን ሳትለቅቅ እንዴት ቀረች?' ይላሉ።
\s5
\v 26 ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፣ በዚያም ቀን ተዋጊዎቿ ሁሉ ይጠፋሉ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።"
\v 27 "በደማስቆም ቅጥር ላይ እሳት አነድዳለሁ፣ የወልደ አዴርንም አዳራሾች ትበላለች።"
\s5
\v 28 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ መታ ስለ ቄዳርና ስለ አሶር መንግሥታት፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፣ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።
\v 29 ጦር ሠራዊቱ ድንኳናቸውንና መንጋቸውን ይወስዳል፤ መጋረጆቻቸውንና ዕቃቸውን ሁሉ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው ይወስዳሉ። በዙሪያቸውም ሁሉ ጥፋትን ጥሩባቸው፣ 'ሽብር በዙሪያቸው ሁሉ አለ!"
\s5
\v 30 ሽሹ! በሩቅ ቦታም ተቅበዝበዙ! እናንተ በአሶር የምትኖሩ ሆይ፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ተማክሮባችኋልና፣ አሳብም አስቦባችኋልና በጥልቅ ውስጥ ተቀመጡ፣ ይላል እግዚአብሔር። ሽሹ! ዙሩና ተመለሱ!
\v 31 ዕርፊት ወዳለበት በዋስትናም ወደ ተቀመጠው፣ ደጅና መወርወሪያ ወደሌለው ብቻውንም ወደ ተቀመጠው ሕዝብ ውጡ፣ ተነሡ! አጥቊ!።
\s5
\v 32 ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ፣ የእንስሶቻቸውም ብዛት በጦርነት ይማረካል። ጠጉራቸውንም በዙሪያ የሚላጩትን ሰዎች ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከየዳርቻቸውም ሁሉ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
\v 33 አሶርም የቀበሮ መኖሪያና የዘላለም ባድማ ትሆናለች። በዚያም ሰው አይኖርም፣ የሰው ልጅም አይቀመጥባትም።"
\s5
\v 34 ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ይህ የሆነው በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ መንግሥት መጀመሪያ ነው። እንዲህም አለ፣
\v 35 "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዋና የኃይላቸው መሣሪያ የሆነውን የኤላምን ቀስት እሰብራለሁ።
\v 36 ከአራቱም ከሰማይ ማዕዘናት አራቱን ነፋሳት በኤላም ላይ አመጣለሁ፣ የኤላምን ሕዝብ ወደ እነዚያ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ። ከኤላም የተሰደዱ ሰዎች የማይበተኑበት ሕዝብ አይገኝም።
\s5
\v 37 ስለዚህ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን በሚሹአት ፊት ኤላምን አስደነግጣለሁ። ክፉ ነገርን እርሱም ጽኑ ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር። እስካጠፋቸውም ድረስ በኋላቸው ሰይፍ እሰድድባቸዋለሁ።
\v 38 ከዚያም፣ ዙፋኔንም በኤላም አኖርና ንጉሡን ከእነአለቆቹ አጠፋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 39 ነገር ግን በኋለኛው ዘመን የኤላምን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\c 50
\p
\v 1 እግዚአብሔር ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣
\v 2 "በአሕዛብ መካከል ተናገሩና እንዲሰሙ አድርጉ። ዓላማውን አንሡና እንዲሰሙ አውሩ። አትደብቁት። 'ባቢሎን ተወሰደች። ቤል አፈረ። ሜሮዳክ ደነገጠ። ጣዖቶችዋ አፈሩ። ምስሎችዋ ደነገጡ' በሉ።
\s5
\v 3 ሕዝብ ከሰሜን ወጥቶባታል ምድርዋንም ባድማ ያደርጋል፣ የሚቀመጥባት እንዳይገኝባት። ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ በውስጥዋ አይኖሩም። ሸሽተው ሄደዋል።
\v 4 በእነዚያም ወራት፣ በዚያም ጊዜ፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ሆነው እያለቀሱና አምላካቸውን እግዚአብሔርን እየፈለጉ ይመጣሉ።
\v 5 ፊታቸውንም ወደጽዮን አቅንተው ይሄዳሉ። ከቶ በማይረሳ በዘላለም ቃል ኪዳን ወደ እግዚአብሔር ሄደው ራሳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር ያገኛኛሉ።
\s5
\v 6 ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል። እረኞቻቸው በተራሮች ላይ አስተው አቅበዘበዟቸው፤ ከኮረብታ ወደ ኮረብታ አለፉ። ሄዱ፣ የኖሩበትንም በረታቸውን ረሱ።
\v 7 ሲሄዱባቸው ያገኙአቸው ሁሉ በሉአቸው። ጠላቶቻቸውም፣ 'በጽድቅ ማደሪያ በእግዚአብሔር ላይ፣ በአባቶቻቸው ተስፋ በእግዚአብሔር ላይ፣ ኃጢአት ስለ ሠሩ እኛ አልበደልንም' አሉ።
\s5
\v 8 ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ ወደ ከከለዳውያን ድር ውጡ፤ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።
\v 9 ተመልከቱ፣ ከሰሜን ምድር የታላላቅ አሕዛብን ጉባኤ አስነሣለሁ በባቢሎንም ላይ አመጣቸዋለሁ። በእርስዋም ላይ ይሰለፋሉ። ባቢሎን ከዚያ ስፍራ ትወሰዳለች። ፍላጾቻቸውም ባዶውን እንደማይመለስ እንደ ተካነ ተዋጊ ፍላጻ ናቸው።
\v 10 የከላውዴዎንም ምድር ትበዘበዛለች። የሚበዘብዙአትም ሁሉ ይጠግባሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 11 ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ፣ ደስ ይበላችሁ፤ በመስክ ላይም እንዳለች ጊደር ሆናችሁ ሐሤት እያደረጋችሁ ዝለሉ፤ እንደ ብርቱ ፈረሶች አሽካኩ።
\v 12 እንዲሁ እናታችሁ በእጅጉ ታፍራለች፤ የወለደቻችሁም ትጐሰቍላለች። ተመልከቱ፣ በአሕዛብ መካከል አነስተኛይቱ ትሆናለችና፣ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፣ በረሀም ትሆናለች።
\v 13 ከእግዚአብሔር ቍጣ የተነሣ ባድማ ትሆናለች እንጂ ሰው አይኖርባትም። በባቢሎንም በኩል የሚያልፍ ሁሉ ይደነቃል፣ በመጣባትም መቅሠፍት ሁሉ ያፍዋጫል።
\s5
\v 14 በባቢሎን ላይ በዙሪያዋ ተሰለፉ። እናንተ ቀስትን የምትገትሩ ሰዎች ሁሉ። በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርታለችና ወርውሩባት ፍላጾችንም አትመልሱ።
\v 15 የእግዚአብሔር በቀል ነውና ድል እያደረጋችሁ በዙሪያዋ ጩኹባት። እጅዋን ሰጠች፤ ግንቦችዋ ወደቁ፣ ቅጥሮችዋም ፈረሱ ይህ የእግዚአብሔር በቀል ነውና። እርስዋን ተበቀሉ! እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
\s5
\v 16 ዘሪውንና በመከር ጊዜ ማጭድ የሚይዘውን ከባቢሎን አጥፉ። ከሚያስጨንቅ ሰይፍ ፊት እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል።
\s5
\v 17 እስራኤል ባዝኖ የተበተነ በግ እና አንበሶች ያሳደዱት ነው። መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፤ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።
\v 18 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቱ፣ የአሦርን ንጉሥ እንደ ቀጣሁ፣ እንዲሁ የባቢሎንን ንጉሥና ምድሩን እቀጣለሁ።
\s5
\v 19 እስራኤልንም ወደ ማሰማርያ ምድሩ እመልሳለሁ፤ በቀርሜሎስና በባሳንም ላይ ይሰማራል። በኤፍሬም ተራራና በገለዓድ ላይ ይጠግባል።
\v 20 በእነዚያም ቀኖች፣ በዚያ ጊዜ፣ እነዚህን ያስቀረኋቸውን ይቅር እላቸዋለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር፣ የእስራኤል በደል የይሁዳም ኃጢአት ይፈለጋል ምንም አይገኝም።"
\s5
\v 21 "በምራታይም ምድር ላይ፣ በፋቁድም በሚኖሩት ላይ ተነሥና ውጣ፤ ግደላቸው ፈጽመህም አጥፋቸው፤ ይላል እግዚአብሔር፣ እንዳዘዝሁህም ሁሉ አድርግ።
\v 22 የሰልፍና የታላቅ ጥፋት ውካታ በምድሪቱ ላይ አለ።
\s5
\v 23 የምድር ሁሉ መዶሻ እንዴት ደቀቀ እንዴትስ ተደመሰሰ። ባቢሎንስ በአሕዛብ መካከል እንዴት መሸበሪያ ሆነች።
\v 24 ባቢሎን ሆይ፣ አጥምጄብሻለሁ። አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል።
\s5
\v 25 እግዚአብሔር ዕቃ ቤቱን ከፍቶ የቍጣውን ዕቃ ጦር አውጥቶአል። የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በከለዳውያን ምድር ይሠራ ዘንድ ሥራ አለውና።
\v 26 ከየበኩሉ በእርስዋ ላይ ጥቃትን ፈጽሙ። ጎተራዎችዋንም ክፈቱ። እንደ ክምርም አድርጓት፣ ፈጽማችሁም አጥፉአት። አንዳችም አታስቀሩላት።
\s5
\v 27 ወይፈኖችዋን ሁሉ እረዱ። ወደ መታረድም ስፍራ ላኳቸው። ቀናቸው፣ የመቀጣታቸው ጊዜ፣ ደርሶአልና ወዮላቸው!
\v 28 የአምላካችንን የእግዚአብሔርን በቀል፣ የመቅደሱንም በቀል በጽዮን ይነግሩ ዘንድ ሸሽተው ከባቢሎን አገር ያመለጡት ሰዎች ድምፅ ተሰምቶአል።"
\s5
\v 29 ቀስትን የሚገትሩትን ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩአቸው። በዙሪያዋ ስፈሩባት፣ አንድም አያምልጥ። በእስራኤል ቅዱስ ላይ በእግዚአብሔር ላይ ኰርታለችና እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት። እንዳደረገችም ሁሉ አድርጉባት።
\v 30 ስለዚህ ጐበዛዝትዋ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፣ በዚያም ቀን ሰልፈኞችዋ ሁሉ ይጠፋሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 31 ትዕቢተኛው ሆይ፣ አንተን የምቀጣበት ጊዜ፣ ቀንህ ደርሶአልና በአንተ ላይ ነኝ፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
\v 32 ስለዚህ ትዕቢተኞቹ ተሰናክለው ይወድቃሉ። የሚያነሣቸው ማንም አይኖርም። በከተሞቻቸውም ውስጥ እሳት አነድዳለሁ፤ በዙሪያቸው ያለውን ሁሉ ትበላለች።
\s5
\v 33 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤል ልጆችና የይሁዳ ልጆች በአንድነት ተጨቊነዋል። የማረኳቸውም ሁሉ አሁን ድረስ በኃይል ይዘዋቸዋል፤ ይለቅቁአቸውም ዘንድ እንቢ ብለዋል።
\v 34 የሚቤዣቸው ብርቱ ነው። ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው። ምድርንም ያሳርፍ ዘንድ፣ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ሙግታቸውን ፈጽሞ ይሟገታል።
\s5
\v 35 ሰይፍ በከለዳውያንና በባቢሎን በሚኖሩ ላይ፣ በአለቆችዋና በጥበበኞችዋ ላይ አለ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 36 ጥንቆላን በሚናገሩት ላይ ሰይፍ አለ፣ ራሳቸውን ሰነፎች አድርገው ይገልጣሉ። ሰይፍም በጦረኞችዋ ላይ አለ፣ እነርሱም በሽብር ይሞላሉ።
\v 37 ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ በመካከልዋም ባሉት በልዩ በልዩ ሕዝብ ሁሉ ላይ አለ፣ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ። ሰይፍ በቤተ መዛግብቷ ላይ አለ፣ ለብዝበዛም ይሆናል።
\s5
\v 38 እርስዋ የተቀረጹ ምስሎች ምድር ናት፣ እነርሱም በጣዖታት ይመካሉና ድርቅ በውኆችዋ ላይ ይሆናል እነርሱም ይደርቃሉ።
\v 39 ስለዚህ የምድረ በዳ አራዊት ከተኵላዎች ጋር ይኖሩባታል፣ ሰጐኖችም ይኖሩባታል፤ ሰውም ከዚያ ወዲያ ለዘላለም አይኖርባትም፣ እስከ ልጅ ልጅም ድረስ የሚኖርባት የለም።
\v 40 ሰዶምንና ገሞራን በአጠገባቸውም የነበሩትን ከተምች እግዚአብሔር እንደ ገለበጣቸው፣ ይላል እግዚአብሔር፣ እንዲሁ ሰው በዚያ አይኖርም የሰውም ልጅ አይኖርባትም።"
\s5
\v 41 "ተመልከቱ፣ ሕዝብ ከሰሜን ይመጣል፣ ታላቅ ሕዝብና ብዙ ነገሥታትም ከምድር ሩቅ ዳርቻዎች ይነሣሉ።
\v 42 ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ። ጨካኞች ናቸው ምሕረትም አያደርጉም። ድምፃቸው እንደ ባሕር ይተምማል፣ በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፣ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ።
\v 43 የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፣ እጁም ዝላ ደክማለች። ጭንቀትም ይዞታል፣ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።
\s5
\v 44 ተመልከቱ! ከእርስዋ ዘንድ በቶሎ አባርራቸዋለሁና በጠነከረው አምባ ላይ ከዮርዳኖስ ትዕቢት ውስጥ እንደ አንበሳ ይወጣል። የተመረጠውንም በእርስዋ ላይ እሾመዋለሁ። እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ወይስ ለእኔ ጊዜ የሚወስን ማን ነው? ወይስ ፊቴን የሚቃወም እረኛ ማን ነው?
\s5
\v 45 ስለዚህ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ የመከረባትን ምክር፣ በከለዳውያንም ምድር ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ። በእውነት የመንጋ ትናንሾች ሳይቀሩ ይጎተታሉ። በእውነት ማደሪያቸውን ባድማ ያደርግባቸዋል።
\v 46 ከባቢሎን መያዝ ድምፅ የተነሣ ምድር ተናወጠች፤ ጩኸትም በአሕዛብ መካከል ዘንድ ተሰማ።"
\s5
\c 51
\p
\v 1 "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ተመልከቱ፣ በባቢሎን ላይና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ አጥፊውን ነፋስ አስነሣለሁ።
\v 2 በባቢሎንም ላይ የውጪ ሰዎች እልካለሁ። እነርሱም ይበትኗታል፣ ምድርዋንም ባዶ ያደርጋሉ፤ በመከራም ቀን በዙሪያዋ ይከብቡአታል።
\s5
\v 3 በወርዋሪው ላይ በጥሩርም በሚነሣው ላይ ቀስተኛው ቀስቱን ይገትር፤ ለጐበዛዝትዋ አትዘኑ፣ መላውን ሠራዊትዋንም አጥፉ።
\v 4 የቆሰሉት ሰዎች በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፣ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉና።
\s5
\v 5 ምድራቸው በእስራኤል ቅዱስ ላይ በተሠራው በደል ምንም እንኳ የተሞላች ብትሆን፣ እስራኤልም ሆነ ይሁዳ በአምላኩ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ዘንድ አልተጣለም።
\v 6 ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ራሳችሁን አድኑ። በበደልዋ አትጥፉ። የእግዚአብሔር የበቀል ጊዜ ነውና። እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታል።
\s5
\v 7 ባቢሎን በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ምድርን ሁሉ ያሰከረች የወርቅ ጽዋ ነበረች፣ አሕዛብም ከጠጅዋ ጠጥተዋል፤ ስለዚህ አሕዛብ እብድ ሆነዋል።
\v 8 ባቢሎን በድንገት ወድቃ ጠፍታለች። ለእርሷ አልቅሱላት! ትፈወስም እንደ ሆነ ለቊስልዋ መድኃኒት ውሰዱላት።
\s5
\v 9 'ባቢሎንን ለመፈወስ ተመኘን፣ እርስዋ ግን አልተፈወሰችም። ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፣ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሎአልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ ምድራችን እንሂድ።'
\v 10 እግዚአብሔር ጽድቃችንን አውጥቶአል። ኑ፣ በጽዮን የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ሥራ እንናገር።'
\s5
\v 11 ፍላጾችን ሳሉ ጋሻዎችንም አዘጋጁ። እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ አሳቡ በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ነገሥታት መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚብሔር በቀል፣ የመቅደሱ መጥፊያ በቀል ነውና።
\v 12 በባቢሎን ቅጥር ዓላማውን አንሡበት፣ ጥበቃን አጽኑ። ተመልካቾችን አቁሙ፣ ከከተማዋ የሚወጡትን ለመያዝ ድብቅ ጦር አዘጋጁ። እግዚአብሔር በባቢሎን በሚኖሩት ላይ የተናገረውን አስቦአልና፣ አድርጎአልምና።
\s5
\v 13 አንቺ በብዙ ውኃ አጠገብ የተቀመጥሽ፣ በመዝገብም የበለጠግሽ፣ እንደ ስስትሽ መጠን ፍጻሜሽ ደርሶአል።
\v 14 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በራሱ ምሏል፣ 'በእውነት ሰዎችን እንደ አንበጣ እሞላብሻለሁ፣ እነርሱም የጦርነት ጩኸት ያነሡብሻል።'
\s5
\v 15 ምድርን በኃይሉ ፈጠረ፤ ዓለሙን በጥበቡ መሠረተ። ሰማያትንም በማስተዋሉ ዘረጋ።
\v 16 ድምጹን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፣ ከምድርም ዳር ደመናትን ከፍ ያደርጋል። ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፣ ነፍስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።
\s5
\v 17 ሰው ሁሉ እውቀት አጥቶ እንደ እንስሳ ሆኗል፤ እያንዳንዱ አንጥረኛ ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል። ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፤ እስትንፋስም የላቸውምና።
\v 18 እነርሱም ምናምንቴና፣ የቀልድ ሥራ ናቸው፤ በሚቀጡበት ጊዜ ይጠፋሉ።
\v 19 የያዕቆብ እድል ፈንታ እንደ እነዚህ አይደለም፣ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስራኤልም የርስቱ ነገድ ነው፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
\s5
\v 20 አንቺ መዶሻዬና የጦር መሣሪያዬ ነሽ። በአንቺ አሕዛብን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም መንግሥታትን አጠፋለሁ።
\v 21 በአንቺ ፈረሱንና ሠረገላውን እሰባብራለሁ፤
\s5
\v 22 በአንቺም በላዩ የሚቀመጡትን ወንድ እና ሴት እሰባብራለሁ፤ በአንቺም ሽማግሌውንና ብላቴናውን እሰባብራለሁ። በአንቺም ጐልማሳውንና ልጃገረዲቱን እሰባብራለሁ።
\v 23 በአንቺም እረኛውንና መንጋውን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አራሹንና ጥማጁን እሰባብራለሁ፤ በአንቺም አለቆችንና ሹማምቶችን አሰባብራለሁ።
\s5
\v 24 በጽዮን በዓይናችሁ ፊት ስለሠሩት ክፋታቸው ሁሉ በባቢሎንና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩ ሁሉ ላይ ፍዳቸውን እከፍላለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 25 "ተመልከት፣ አንተ ምድርን ሁሉ የምታጠፋ አጥፊ ተራራ ሆይ፣ እኔ በአንተ ላይ ነኝ፣ ይላል እግዚአብሔር። እጄንም እዘረጋብሃለሁ፣ ከድንጋዮችም ላይ አንከባልልሃለሁ። የተቃጠለም ተራራ አደርግሃለሁ።
\v 26 ከአንተም ለማዕዘንና ለመሠረት የሚሆን ድንጋይ አይወስዱም፣ ለዘላለምም ባድማ ትሆናለህ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\s5
\v 27 "በምድር ላይ ዓላማን አንሡ። በአሕዛብም መካከል መለከት ንፉ። እንዲያጠቋት አሕዛብን አዘጋጁባት፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት ሰብስቡባት፣ አለቃንም በላይዋ አቁሙ። እንደ ጠጉራም አንበጣ ኩብኩባ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ።
\v 28 አሕዛብን የሚዶንንም ነገሥታት አለቆችንም ሹማምቶችንም ሁሉ የግዛታቸውንም ምድር ሁሉ አዘጋጁባት።
\s5
\v 29 ማንም እንዳይቀመጥባት የባቢሎንን ምድር ባድማ ያደርጋት ዘንድ የእግዚአብሔር አሳብ በባቢሎን ላይ ጸንቶአልና ምድር ተናወጣለች ታመመችም።
\s5
\v 30 የባቢሎን ወታደሮች መዋጋትን ትተዋል፤ በምሽጎቻቸውም ውስጥ ተቀምጠዋል። ኃይላቸውም ጠፍቶአል እንደ ሴቶችም ሆነዋል። ማደሪያዎችዋም ነድደዋል፣ መወርወሪያዎችዋም ተሰብረዋል።
\v 31 ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች መልካምዎችዋም እንደ ተያዙ፣ ቅጥርዋም በእሳት እንደ ተቃጠለ፣ ሰልፈኞችም እንደ ደነገጡ
\v 32 ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ወሬኛው ወሬኛውን፣ መልእክተኛውም መልእክተኛውን ሊገናኝ ይሮጣል።"
\s5
\v 33 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፣ አውድማ እንደ ተረገጠ ጊዜ፣ እንዲሁ የባቢሎን ልጅ ናት። ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስላታል።
\s5
\v 34 ኢየሩሳሌም፣ 'የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ። አድርቆ አሟጠጠኝ፣ እንደ ባዶ የሸክላ ዕቃም አደረገኝ። እንደ ዘንዶም ዋጠኝ። ከሚጣፍጠውም ምግቤ ሆዱን ሞላ። እኔንም ወደ ውጪ ጣለኝ።' አለች።
\v 35 የጽዮን ነዋሪዎች እንዲህ ይላሉ፣ 'በእኔና በሥጋዬ የተደረገ ግፍ በባቢሎን ላይ ይሁን።' ኢየሩሳሌምም፣ 'የሚፈስሰው ደሜ ጥፋት በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ ይሁን" ትላለች።
\s5
\v 36 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከቺ፣ እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ። ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ፣ ምንጭዋንም አደርቀዋለሁ።
\v 37 ባቢሎንም የድንጋይ ቊልልና የቀበሮ ማደሪያ፣ መደነቂያም ማፍዋጫም ትሆናለች፤ የሚቀመጥባትም ሰው አይገኝም።
\s5
\v 38 በአንድነትም እንደ አንበሶች ያገሣሉ። እንደ አንበሳም ደቦሎች ያጕረመርማሉ።
\v 39 በስስት በሞቃቸው ጊዜ ደስ እንዲላቸው፣ ለዘላለምም አንቀላፍተው እንዳይነቁ፣ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ፣ አሰክራቸውማለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 40 እንደ ጠቦቶችና እንደ አውራ በጎች እንደ አውራ ፍየሎችም ወደ መታረድ አወርዳቸዋለሁ።"
\s5
\v 41 "ባቢሎን እንዴት ተያዘች! የምድርም ሁሉ ምስጋና እንዴት ተወሰደች። ባቢሎንም በአሕዛብ መካከል መደነቂያ እንዴት ሆነች።
\v 42 ባሕር በባቢሎን ላይ ወጣ! በሞገዱም ብዛት ተከደነች።
\s5
\v 43 ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፣ ሰውም የማይኖርበት፣ የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ።
\v 44 በባቢሎንም ውስጥ ቤልን እቀጣለሁ፤ የዋጠውንም ከአፉ አስተፋዋለሁ፣ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርሱ አይሰበሰቡም። የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።"
\s5
\v 45 "ሕዝቤ ሆይ፣ ከመካከልዋ ውጡ። እያንዳንዳችሁም ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ ራሳችሁን አድኑ።
\v 46 በምድርም ከሚሰማ ወሬ የተነሣ አትፍሩ፣ ልባችሁም የዛለ አይሁን፤ በአንድ ዓመት ወሬ ይመጣል፣ ከዚያም በኋላ በሌላው ዓመት ወሬ፣ በምድርም ላይ ግፍ ይመጣል፣ አለቃም በአለቃ ላይ ይነሣል።
\s5
\v 47 ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ የተቀረጹትን የባቢሎን ምስሎች የምቀጣበት ዘመን ይመጣል። ምድርዋም ሁሉ ታፍራለች፣ ተወግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።
\v 48 አጥፊዎች ከሰሜን ይመጡባታልና ሰማይና ምድር በእነርሱም ያለው ሁሉ ስለ ባቢሎን እልል ይላሉ፣ ይላል እግዚአብሔር።
\v 49 ባቢሎንም ከእስራኤል ተወግተው የሞቱት እንዲወድቁ እንዳደረገች፣ እንዲሁ በባቢሎን ከምድሩ ሁሉ ተወግተው የሞቱት ይወድቃሉ።"
\s5
\v 50 "ከሰይፍ ያመለጣችሁ፣ ሂዱ! ተረጋግታችሁ አትቁሙ። እግዚአብሔርን ከሩቅ ጥሩት፤ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።
\v 51 ስድብን ስለ ሰማን አፍረናል፤ ባዕዳን ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብተዋልና ነውር ፊታችንን ከድኖታል።"
\s5
\v 52 "ስለዚህ፣ ተመልከቱ፣ የተቀረጹትን ምስሎችዋ የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርዋም ላይ ሁሉ የተወጉት ያንቋርራሉ።
\v 53 ባቢሎን ምንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፣ የኃይልዋንም ምሽጎች ብታጸና፣ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፣ ይላል እግዚአብሔር።"
\s5
\v 54 ከባቢሎን ጩኸት፣ ከከለዳውያንም ምድር የታላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰምቶአል።
\v 55 እግዚአብሔር ባቢሎንን አጥፍቶአታልና፣ ከእርስዋም ታላቁን ድምፅ ዝም አሰኝቶአልና፤ ሞገዳቸውም እንደ ብዙ ውኆች ይተምማል፣ የድምፃቸውም ጩኸት በብርቱ ተሰምቶአል።
\v 56 አጥፊው በባቢሎን ላይ መጥቶባታልና፣ ኃያላኖችዋ ተያዙ፣ ቀስታቸውም ተሰባበረ፤ እግዚአብሔር ፍዳን የሚከፍል አምላክ ነውና፣ ፍዳንም በእርግጥ ይከፍላል።
\s5
\v 57 "መሳፍንቶችዋንና ጥበበኞችዋን፣ አለቆችዋንና ሹማምቶችዋን፣ ወታደሮችዋንም አሰክራለሁ፥ ለዘላለምም አንቀላፍተው አይነቁም፣ ይላል ስሙ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የተባለው ንጉሥ።"
\v 58 "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሰፊው የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ረጃጅሞችም በሮችዋም በእሳት ይቃጠላሉ፤ የወገኖችም ድካም ከንቱ ትሆናለች፣ የአሕዛብም ሥራ ሁሉ ለእሳት ትሆናለች፤ እነርሱም ይደክማሉ።"
\s5
\v 59 የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው፣ ያን ጊዜ ሠራያ የቤት አዛዥ ነበረ።
\v 60 በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፣ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፣ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው።
\s5
\v 61 ኤርምያስም ሠራያን እንዲህ አለው፣ "ወደ ባቢሎን በገባህ ጊዜ ይህ ቃል ሁሉ መነበቡን እርግጠኛ ሁን።
\v 62 አንተም ደግሞ፣ 'ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ማንም እንዳይቀመጥባት፣ ለዘላለምም ባድማ እንድትሆን ታጠፋት ዘንድ በዚህች ስፍራ ላይ ተናግረሃል' በል።
\s5
\v 63 ከዚያም ይህንን ጥቅልል መጽሐፍ ማንበብ ከፈጸምህ በኋላ፣ ድንጋይን እሰርበትና በኤፍራጥስ ወንዝ መሃከል ጣለው።
\v 64 አንተ፣ 'እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች፣ አትነሣምም" በል። የኤርምያስ ቃል እዚህ ላይ ያበቃል።
\s5
\c 52
\p
\v 1 ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። እናቱም አሚጣል የምትባል ነበረች፤ እርሷ የሊብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።
\v 2 ኢዮአቄምም እንዳደረገ ሁሉ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ።
\v 3 ከፊቱም አውጥቶ እስኪጥላቸው ድረስ ይህ በእግዚአብሔር ቍጣ፣ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ሆኖአልና። ከዚያም ሴዴቅያስ በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።
\s5
\v 4 ሴዴቅያስም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ በኢየሩሳሌም ላይ መጥተው ከበቡአት፤ በዙሪያዋም ቅጥር የሚሆን ግድግዳ ገነቡ።
\v 5 ስለዚህ ከተማይቱ እስከ ንጉሡ እስከ ሴዴቅያስ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ድረስ ተከብባ ነበር።
\s5
\v 6 በአራተኛውም ወር፣ በዐመቱ ዘጠነኛ ቀን፣ በከተማይቱ ራብ ጸንቶ ነበር። ለምድሪቱም ሰዎች እንጀራ ታጣ።
\v 7 ከተማይቱም ተሰበረች፣ ተዋጊዎች ሁሉ ሸሹ፣ በሁለቱም ቅጥር መካከል ባለው በር ወደ ንጉሡ አትክልት በሚወስደው መንገድ በሌሊት ከከተማይቱ ወጡ። ከለዳውያንም በከተማይቱ ዙሪያ ነበሩ። ስለዚህ በዓረባ መንገድ ሄዱ።
\v 8 ነገር ግን የከለዳውያን ሠራዊት ንጉሡን ተከታተሉት፣ በኢያሪኮም ሜዳ ሴዴቅያስን ያዙ። ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ተበትነው ነበር።
\s5
\v 9 ንጉሡንም ይዘው የባቢሎን ንጉሥ ወዳለባት በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
\v 10 የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በዐይኖቹ ፊት ገደላቸው፣ የይሁዳንም አለቆች ሁሉ ደግሞ በሪብላ ዐረዳቸው።
\v 11 ከዚያም የሴዴቅያስን ዐይኖች አወጣ፣ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው። ወደ ባቢሎንም ወሰደው፣ እስኪሞትም ድረስ በግዞት ቤት አኖረው።
\s5
\v 12 በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥረኛው ቀን፣ በባቢሎን ንጉሥ ፊት የቆመው የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
\v 13 የእግዚአብሔርን ቤትና የንጉሡን ቤት አቃጠለ፤ የኢየሩሳሌምንም ቤቶች ሁሉ፣ ታላላቆችን ቤቶች ሁሉ፣ በእሳት አቃጠለ።
\v 14 ከዘበኞቹም አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት ሁሉ የኢየሩሳሌምን ቅጥር ሁሉ ዙሪያዋን አፈረሱ።
\s5
\v 15 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን የሕዝቡን ድኆች፣ በከተማም ውስጥ የቀረውን ሕዝብ፣ ሸሽተውም ወደ ባቢሎን ንጉሥ የተጠጉትን፣ የሕዝቡንም ቅሬታ አፈለሰ።
\v 16 ነገር ግን የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአገሩ ድኆች ወይን ተካዮችና አራሾች እንዲሆኑ አስቀረ።
\s5
\v 17 ከለዳውያንም በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የናስ ዓምዶች፣ በእግዚአብሔርም ቤት የነበሩትን መቀመጫዎችና የናሱን ኵሬ ሰባበሩ፣ ናሱንም ወደ ባቢሎን ወሰዱ።
\v 18 ምንቸቶቹንና መጫሪያዎችንም፣ መኰስተሪያዎችንና ድስቶችን፣ ጭልፋዎችንም የሚያገለግሉበትንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ።
\v 19 የዘበኞቹም አለቃ ጽዋዎቹንና ማንደጃዎቹን፣ ድስቶቹንና ምንቸቶችን፣ መቅረዞችንና ጭልፋዎቹን፣ መንቀሎችንም፣ የወርቁን ዕቃ በወርቅ፣ የብሩንም ዕቃ በብር፣ አድርጎ ወሰደ።
\s5
\v 20 ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር ቤት ያሠራቸውን ሁለቱን ዓምዶች፣ አንዱንም ኵሬ፣ ከመቀመጫዎቹም በታች የነበሩትን ዐሥራ ሁለቱን የናስ በሬዎች ወሰደ፤ ለእነዚህ ዕቃዎች ሁሉ ናስ ሚዛን አልነበረም።
\v 21 ዓምዶቹም የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ። የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ። ውፍረቱም አራት ጣት ያህል ነበረ፣ ባዶም ነበረ።
\s5
\v 22 የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ። የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፣ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት። በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት።
\v 23 በስተውጭም ዘጠና ስድስት ሮማኖች ነበሩ። በመረበቡም ዙሪያ የነበሩ ሮማኖች ሁሉ አንድ መቶ ነበሩ።
\s5
\v 24 የዘበኞቹም አለቃ ታላቁን ካህን ሠራያን ሁለተኛውንም ካህን ሶፎንያስን ሦስቱንም በረኞች ወሰደ።
\v 25 ከከተማይቱም በሰልፈኞች ላይ ተሹመው ከነበሩት አንዱን ጀንደረባ፣ በከተማይቱም ከሚገኙት በንጉሡ ፊት ከሚቆሙት ሰባቱን ሰዎች፣ የአገሩንም ሕዝብ የሚያሰልፈውን የሠራዊቱን አለቃ ጸሐፊ፣ በከተማይቱም ከተገኙት ከአገሩ ሕዝብ ስድሳ ሰዎች ወሰደ።
\s5
\v 26 የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጣቸው።
\v 27 የባቢሎንም ንጉሥ ገደላቸው፣ በሐማትም ምድር ባለችው በሪብላ ገደላቸው። እንዲሁ ይሁዳ ከአገሩ ተማረከ።
\s5
\v 28 ናቡከደነፆር የማረከው ሕዝብ ይህ ነው፤ በሰባተኛው ዓመት፣ 3, 023 አይሁድ፤
\v 29 ናቡከደነፆርም በአሥራ ስምንተኛው ዓመት 832 ሰዎችን ከኢየሩሳሌም ማርኮአል፤
\v 30 በናቡከደነፆር በሀያ ሦስተኛው ዓመት የዘበኞቹ አለቃ ናቡዘረዳን ከአይሁድ 745 የይሁዳ ሰዎችን ማርኳል። የተማረኩት ሰዎች ሁሉ 4, 600 ነበሩ።
\s5
\v 31 እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፣ በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፣ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የዮአኪንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ ከወህኒም አወጣው።
\s5
\v 32 በመልካምም ተናገረውና ዙፋኑን ከእርሱ ጋር በባቢሎን ከነበሩት ነገሥታት ዙፋን በላይ አደረገለት።
\v 33 ክፉው ዮርማሮዴክ በወህኒ ውስጥ ዮአኪን ለብሶት የነበረውን ልብስ ለወጠለት፣ ዮአኪንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ በፊቴ ሁልጊዜ እንጀራ ይበላ ነበር።
\v 34 የባቢሎንም ንጉሥ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ እስኪሞት ድረስ የዘወትር ቀለብ ዕለት ዕለት ይሰጠው ነበር።

305
25-LAM.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,305 @@
\id LAM
\ide UTF-8
\h ሰቆቃው ኤርሚያስ
\toc1 ሰቆቃው ኤርሚያስ
\toc2 ሰቆቃው ኤርሚያስ
\toc3 lam
\mt ሰቆቃው ኤርሚያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በሰዎች ተሞልታ የነበረችው ከተማ አሁን ፈጽማ ብቻዋን ተቀምጣለች! ኃያል የነበረችው አገር እንደ መበለት ሆናለች! በሕዝቦች መካከል እንደ ልዕልት ነበረች፥ አሁን ግን በባርነት ውስጥ ወድቃለች!
\v 2 በሌሊት ታለቅሳለች፥ታነባለችም፤እንባዎቿም ጉንጮቿን ከድነዋል። ከፍቅረኞቿ መካከል የሚያጽናናት የለም። ጓድኞቿ ሁሉ አሳልፈው ሰጧት። ጠላቶቿም ሆነዋል።
\s5
\v 3 ከድህነቱና ከመከራዉ የተነሳ ይሁዳ ወደ ምርኮ ሄደች። በሕዝቦች መካከል ኖረች፥ ዕረፍትንም አላገኘችም። በጭንቀቷ ጊዜ አሳዳጆቿ ሁሉ በረቱባት።
\s5
\v 4 ወደ ተቀጠሩት በዓላት የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች ያለቅሳሉ። ደጆቿ ሁሉ ባዶ ናችው። ካህናቶቿ ይቃትታሉ። ደናግሎቿ ሐዘንተኞች ናቸዉ፥እራስዋም በፍጹም ጭንቀት ውስጥ አለች።
\v 5 ባላንጣዎቿ ጌቶቿ ሆኑ፥ጠላቶቿ በለጸጉ። ስለ ብዙ ኃጢአቷ እግዚአብሔር መከራን አመጣባት። ልጆቿ ለጠላቷ ተማርከው ወደ ግዞት ሄዱ።
\s5
\v 6 የጽዮን ሴት ልጅ ውበቷ ተለያት። ልዑላኖቿ መሰማሪያ እንዳላገኙ አጋዘኖች ሆኑ፥ በአሳዳጆቻቸው ፊት በድካም ሄዱ።
\s5
\v 7 በመከራዋና ቤት አልባ በሆነችባቸው ቀናት፥ ኢየሩሳሌም በቀደሙት ቀናት የነበሯትን የከበሩ ነገሮች ታስባለች፤ሕዝቦቿ በጠላት እጅ በወደቁ ጊዜ ማንም የረዳት አልነበረም። ጠላቶቿ ተመለከቷት፥ በጥፋቷም ሳቁ።
\s5
\v 8 ኢየሩሳሌም ታላቅ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ እንደ አደፈ ነገር ተንቃለች። ዕርቃናዋን ከተመለከቱበት ጊዜ አንስቶ ያከበሯት ሁሉ ናቋት። ታጉተመትማለች፥ ዘወር ለማለትም ትሞክራላች።
\v 9 ከቀሚሷ በታች አድፋለች። የወደፊቷን አላሰበችም። አወዳደቋ አስፈሪ ነበር። የሚያጽናት ማንም አልነበረም። « እግዚአብሔር ሆይ፥ መከራዬን ተመልከት፥ ጠላት እጅግ ታላቅ ሆኖአልና» እያለች ትጮኻለች!።
\s5
\v 10 ጠላት በከበረ ነገሯ ሁሉ ላይ እጁን አደረገ። ወደ ጉባዔህ እንዳይገቡ አዝዘህ የነበረ ቢሆንም እንኳን፥ ሕዝቦች ወደ መቅደሷ ሲገቡ አየች።
\s5
\v 11 ሕዝቦቿ ሁሉ ምግብ እየፈለጉ ይጮኻሉ። ሕይወታቸውን ለማቆየት የከበረ ኃብታቸውን ስለ ምግብ ይሰጣሉ። የማልጠቀም ሆኟለሁና፥ እግዚአብሔር ሆይ ተመልከት አስበኝም።
\v 12 እናንተ መንገደኞች ሁሉ ይህ ለእናንተ ምንም አይደለምን? እግዚአብሔር እኔን መቅጣት ከጀመረበት ከጽኑ ቁጣው ቀን አንስቶ፥ የደረሰብኝን ሐዘን የሚመስል የማንም የሌላ ሰው ሐዘን ካለ ተመልከቱ፥ እዩም።
\s5
\v 13 ወደ ዉስጥ ወደ አጥንቶቼ ከላይ እሳት ላከ፥ አሸነፋቸዉም። ለእግሮቼ መረብን ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ። ያለማቋረጥ ባዶና ደካማ አደረገኝ።
\v 14 የመተላለፌ ቀንበር በእጆቹ በአንድ ላይ ታስረዋል። በአንድ ላይ ተገምደዋል፥በአንገቴም ላይ ተደርገዋል። ብርታቴን ከንቱ አደረገው። ጌታ በእጃቸው አሳልፎ ሰጠኝ፥ መቆምም አልችልም።
\s5
\v 15 ጌታ፥የሚመክቱልኝን ኃያላን ወንዶች ሁሉ ወዲያ ጣላቸው። ጽኑዓን ወንዶቼን ለማድቀቅ ጉባዔን በላዬ ጠራብኝ። ጌታ ድንግሊቱን የይሁዳ ልጅ በወይን መጥመቂያ እንዳለ ወይን ረገጣት።
\s5
\v 16 ስለ እነዚህ ነገሮች አለቅሳልሁ። ሕይወቴን የሚያድሳት አጽናኙ ከእኔ ርቋልና ከዓይኖቼ ውኃ ይፈሳል፥ ከዓይኖቼ።
\v 17 ጽዮን እጆቿን እጅግ ዘረጋች፥ የሚያጽናናት ማንም የለም። እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉ ጠላቶቹ እንዲሆኑ አዘዘ። ኢየሩሳሌም በእነርሱ ዘንድ እንደ ርኩስ ነገር ተቆጠረች።
\s5
\v 18 በትዕዛዙ ላይ ዐመጽ አድርጌእለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ ሕዝቦች ሁሉ ስሙ፥ ሐዘኔንም ተመልከቱ። ደናግሎቼና ኃያላን ወንዶቼ ተማርከዉ ሄደዋል።
\v 19 ፍቅረኞቼን ጠራኋቸው፥ ነገር ግን ከዳተኞች ሆኑብኝ። ካህናቶቼና ሽማግሌዎቼ ሕይወታችውን ለማኖር ምግብ እየፈለጉ በከተማ ውስጥ ሞቱ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ሆይ ተጨንቄአለሁና ውስጤም ተንጦአልና ተመልከት። እጅግ ዓመጽ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ታውኮአል። በመንገዶች ላይ ሰይፍ ልጆቻችንን ይነጥቃል፥በቤትም እንደ ሙታን መንደር ነው።
\s5
\v 21 ሲቃዬን ስማ። የሚያጽናናኝ ማንም የለም። ጠላቶቼ ሁሉ ስለ መከራዬ ሰምተዋል። አንተ ስለ አደረግከው ደስ አላቸው። እነርሱም እንደ እኔ ይሆኑ ዘንድ ያወጅክባቸውን ቀን አምጣ።
\v 22 ክፋታቸው ሁሉ በፊትህ ይታይ። መቃተቴ ብዙ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፤ስለ መተላለፌ ሁሉ እንዳሰቃየኽኝ አሰቃያቸው።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ጌታ በቁጣው ጥቁር ደመና የጽዮንን ሴት ልጅ ፈጽሞ ከደናት! የእስራኤልን ውበት ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፥ በቁጣው ቀን የእግሩን መር ግጫ ችላ አለ።
\v 2 ጌታ የያዕቆብን ከተማዎች ሁሉ ዋጠ፥ ርኅራኄም አልነበረውም። በቁጣው የጽዮንን ሴት ልጅ የተመሸጉ ከተማዎች ጣለ፤ መንግሥቱ ንና ልዑላኗን አቃለለ፥አዋርዶ ወደ ምድር መትቶ ጣላችው።
\s5
\v 3 በብርቱ ቁጣው የእስራኤልን ብርታት ሁሉ ቆረጠ፥ ከጠላት ፊት ቀኝ እጁን ወደ ኋላ መለሰ፥ በዙሪያው ያለውን ሁሉ እንደሚበላ የሚንቦገቦግ እሳት ያዕቆብን አቃጠለ።
\v 4 እንደ ጠላት ቀስቱን በእኛ ላይ ገተረ፥ እንደ ባላጋራ ወርውሮ ሊገድል እጆቹ ተዘጋጅተው በተጠንቀቅ ቆመ። ለዓይን እጅግ የከበሩትን ሰዎች ሁሉ አረደ፥ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ውስጥ ቁጣውን እንደ እሳት አፈሰሰ።
\s5
\v 5 ጌታ እንደ ጠላት ሆነ። እስራኤልን ዋጠ። ቤተ መንግሥቶቿን ሁሉ ዋጠ፤ምሽጎቿን አጠፋ። በይሁዳ ሴት ልጅ ውስጥ ለቅሶንና ሰቆቃን አበዛ።
\v 6 ድንኳኑን እንደ አትክልት ቦታ አጠፋ። የታላቁን ጉባዔ ስፍራ አፈረሰ። በቁጣው ትኩሳት ንጉሡንና ካህኑን ንቋልና እግዚአብሔር በጽዮን ታላቁን ጉባዔና ሰንበትን እንዲረሱ አደረገ።
\s5
\v 7 ጌታ መሠዊያውን ጣለ፥ መቅደሱን አልተቀበለም። የቤተ መንግሥቶቿን ግንቦች በጠላት እጅ አሳልፎ ሰጠ። በታላቅ ጉባዔ ቀን እንደሚሆን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የድል ድምጽ አሰሙ።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ የከተማ ቅጥር ለማፍረስ ወሰነ። የመለኪያውን ገመድ ዘረጋ፥ቅጥሩን ከማፍረስ እጁን አልመለሰም። ምሽጎቿ እንዲያለቅሱ፥ቅጥሮቿ አቅመ አልባ እንዲሆኑ አደረገ።
\v 9 በሮቿ ወደ መሬት ሰመጡ፥ የበሮቿን መቀርቀሪያዎች አጠፋ፥ ሰበረም።ንጉሧና ልዑላኖቿ የሙሴ ሕግ በሌለበት በአሕዛብ መካከል ናቸው። ነቢያቶቿም እንኳን ሳይቀሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ ራዕይ አላገኙም።
\s5
\v 10 የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች መሬት ላይ ተቀምጥዋል፥ በዝምታም ይቆዝማሉ። በራሳቸው ላይ አቧራ ነሰነሱ፥ የሐዘንም ልብስ ለበሱ። የኢየሩሳሌም ደናግል ራሳቸውን ወደ መሬት ዝቅ አደረጉ።
\s5
\v 11 እንባዬ ደረቀ፥ዓይኖቼ ቀሉ፥ የውስጥ ሰዉነቴ ታወከ። ልጆችና የሚያጠቡ ሕጻናት በመንደሮች መንገዶች ላይ ያለ ምንም ተስፋ ደክመዋልና፥ የሕዝቤም ሴት ልጆች ደቅቀዋልና ጉበቴ በመሬት ላይ ተዘረገፈ።
\v 12 በከተማይቱ መንገዶች ላይ እንደ ቆሰለ ሰው ዝለው ሳሉ፥ በእናቶቻቸው እቅፍ ነፍሳቸው እየፈሰሰች ሳሉ፥ እናቶቻቸውን፦ « እሕሉና ወይኑ የት አለ? » ይላሉ።
\s5
\v 13 የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ስለ አንቺ ምን ማለት እችላለሁ? የጽዮን ድንግል ሆይ አጽናናሽ ዘንድ ከምን ጋር አመሳስልሻለሁ? ውድቀትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነው። ሊፈውስሽ የሚችል ማነው?
\v 14 ነቢያቶችሽ የሚያስትና ከንቱ ራዕይ አይተውልሻል። በረከትሽን ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አለገለጡም፤ ነገር ግን የሚያስት ትንቢትና የሚያጠምድ ራዕይ ተቀበሉ።
\s5
\v 15 በመንገድ የሚያልፉ ሁሉ እጃቸውን በአንቺ ላይ ያጨበጭባሉ። በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ይዝታሉ፥ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ፥ ደግሞም « 'የውበት ሁሉ መጨረሻ'፥ 'የምድር ሁሉ ደስታ' ብለው የሚጠሯት ከተማ ይህቺ ናትን? » ይላሉ።
\v 16 ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን እጅግ ይከፍታሉ፥ ያላግጡብሻልም። እያፏጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ «ዋጥናት! በእርግጥም የተጠባበቅናት ቀን ይህቺ ናት! አገኘናት! አየናትም! » ይላሉ።
\s5
\v 17 እግዚአብሔር የወሰነውን አደረገ። ከረዥም ጊዜ በፊት ያወጀውን ቃሉን ፈጸመ። አፈረሰ፥ርኅራኄም አልነበረውም፤ ጠላትሽ በአንቺ ላይ እንዲደሰት ፈቀደ፥ የጠላቶሽን ብርታት ከፍ ከፍ አደረገ።
\s5
\v 18 ልባቸው ወደ ጌታ ጮኽ፤የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ እንባሽ እንደ ወንዝ ቀንና ሌሊት ይፍሰስ። ለራስሽ የእፎይታ ጊዜ አትስጪ። የአይኖችሽን ማፍሰስ አታስቁሚ።
\v 19 በሌሊት ተነሺና ጩኺ፥ ከሌሊቱ መጀመሪያ አንስቶ በጌታ ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ። በየመንገዱ ራስ ላይ በረሀብ ደክመው ስለወደቁት ልጆችሽ ሕይወት እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ሆይ ተመልከት፥ ጽኑ መከራን ስላመጣህባቸው ስለ እነዚያ ሰዎች ግድ ይበልህ። ሴቶች የራሳቸውን ፍሬ፥ የሚሳሱላቸውን ልጆቻቸውን ይብሉን? ካህኑና ነቢዩ በጌታ መቅደስ ውስጥ ይታረዱን?
\s5
\v 21 ወጣቱና ሽማግሌው በአንድነት በየመንገዶቹ በመሬት ላይ ወደቁ። ደናግሎቼና ኃያላን ወንዶቼ በሰይፍ ወደቁ። በቁጣህ ቀን አረድሃቸው፥በጭካኔ ገደልካቸው፥ ርኅራኄም አልነበረህም።
\v 22 በከበረው ጉባዔ ቀን እንደሚሆን ከዙሪያው ሁሉ ሽብርን ጥራህብኝ፤ ማንም አላመለጠም፥ በእግዚአብሔር ቁጣ ቀን የተረፈ ማንምአልነበረም። የተንከባከብኳቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ አጠፋቸው።
\s5
\c 3
\p
\v 1 በእግዚአብሔር የቁጣ በትር መከራ ያየ ሰው እኔ ነኝ።
\v 2 አባረረኝ፥ በብርሃን ሳይሆን በጨለማ እንድሄድ አደረገኝ።
\v 3 በእርግጥ ሊቃወመኝ ወደ እኔ ዘወር አለ፥ ቀኑን ሙሉ እጁን በላዬ መለሰ።
\v 4 ሥጋዬንና ቆዳዬን ቀደደ፥ አጥንቶቼን ሰበረ።
\s5
\v 5 ቅጥር በዙሪያዬ ገነባብኝ፥ በምሬትና በመከራም ከበበኝ።
\v 6 ከሞቱ ረዥም ጊዜ እንደሆናቸው በጨለማ ስፍራ እንድኖር አደረገኝ።
\v 7 በዙሪያዬ ቅጥርን ገነባ፥ ማምለጥም አልችልም። የእግሬን ሰንሰለት አከበደ።
\v 8 ለርዳታ ብጮኽና ብጣራም ጸሎቴን ዘጋ።
\s5
\v 9 ከጥርብ ድንጋይ በተሰራ ቅጥር መንገዴን ዘጋ፤የምሄድብት የትኛውም መንገድ ጠማማ ሆን።
\v 10 መንገዴን ቀየረው።
\v 11 ገነጣጠለኝ፥ብቸኛም አደረገኝ።
\s5
\v 12 ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ።
\v 13 ቀስቱን ለጠጠ፥ ለፍላጻውም የዒላማ ምልክት አደረገኝ። ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ። ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ።
\v 14 ለሰዎች ሁሉ መሳለቂያ፥ ዘወትርም ለሽሙጥጯ ዝማሬያቸው ምክንያት ሆንኩ።
\v 15 ምሬት ሞላብኝ፥ እሬት እንድጠጣ አስገደደኝ።
\s5
\v 16 ጥርሴን በድንጋይ ሰበረ፥ ወደ መሬት ውስጥ ረገጠኝ።
\v 17 ሰላምን ከሕይወቴ አስወገድክ፤ ከእንግዲህ መቼም የትኛዉንም ደስታ አላስብም።
\v 18 ስለዚህም« ጽናቴ ጠፍቷል፥ በእግዚአብሔር ላይ ያለ ተስፋዬም ሄዷል» አልሁ።
\s5
\v 19 መከራዬንና እሬትና ምሬት ወደ አለበት መጥፋቴን አስባለሁ።
\v 20 በእርግጥ አስበዋለሁ፥ተስፋ በመቁረጥ በውስጤ አቀረቀርኩ ።
\v 21 ነገር ግን ይህን አስባልሁ፥ ተስፋ ሊኖረኝ የቻለውም ከዚህ የተነሳ ነው።
\s5
\v 22 ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና።
\v 23 የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!
\v 24 ለራሴ እንዲህ አልኩ « እግዚአብሔር ዕጣ ክፍሌ ነው» ስለዚህ ተስፋ አደርገዋለሁ።
\s5
\v 25 ለምጠብቀው፥ ለምትፈልገውም ሕይወት እግዚአብሔር መልካም ነው።
\v 26 የእግዚአብሔርን ማዳን በዝምታ መጠበቅ መልካም ነው።
\v 27 በወጣትነቱ ቀንበርን ቢሸከም ለሰው መልካም ነው።
\v 28 እግዚአብሔር አሸክሞታልና ለብቻው ይቀመጥ ዝምም ይበል።
\v 29 ምናልባት ተስፋ ሊኖር ይችላልና አፉን በአፈር ዉስጥ ያኑር።
\s5
\v 30 ለሚመታው ጉንጩን ይስጥ። ዉርደትንም ይጥገብ፤
\v 31 እግዚአብሔር ለዘላለም አይጥለውምና!
\v 32 ሐዘንን ቢያመጣም እንኳን ከታላቁ የኪዳኑ ታማኝነት በሚሆን ርኅራኄ ይራራል።
\v 33 ምክንያቱም ከልቡ አይጨቁንም፥ወይንም የሰዎችን ልጆች አያሰቃይም።
\s5
\v 34 በምድር ያሉ ምርኮኞችን ሁሉ ከእግሩ በታች ሲያደቅቅ፥
\v 35 በልዑል ፊት የሰውን ፍርድ ሲያጣምም፥
\v 36 ፍትህ ፈላጊውን ሲያፍን- ጌታ አያይምን?
\s5
\v 37 ጌታ ካላዘዘው በቀር የሚናገርና የሚፈጽመው ማን ነው?
\v 38 ጥፋትና ስኬት ከልዑል አፍ የሚወጡ አይደሉምን?
\v 39 ታዲያ ማንም ሕያው የሆነ ሰው እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል? ማንም ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል?
\s5
\v 40 መንገዳችንን እንፈትን እንመርምርም፥ ወደ እግዚአብሔርም እንመለስ።
\v 41 ልባችንንና እጃችንን በሰማይ ወደ አለው ወደ እግዚአብሔር እናንሣና እንዲህ ብለን
\v 42 እንጽልይ፦ተላልፈናል በአንተም ላይ ዐምፀናል፥ስለዚህ ይቅር አላልከንም።
\v 43 ራስህን በቁጣ ሸፈንክ አሳደድከንም። አረድከን፥ አራራህልንምም።
\s5
\v 44 ራስህን በደመና ሸፈንክ፥ስለዚህም ማለፍ የሚችል ጸሎት የለም።
\v 45 በአሕዛብም መካከል ቆሻሻና ውዳቂ አደረግኽን ።
\v 46 ጠላቶቻችን በእኛ ላይ በማላገጥ አፋቸውን ከፈቱ።
\v 47 የአሳር ጉድጓድ ፥የባዶነትና የጥፋት ፍርሃት መጣብን።
\s5
\v 48 ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋት ዓይኔ ያለማቋርጥ ውኃ አፈሰሰች።
\v 49 ዓይኖቼ ያፈሳሉ አያቆሙምም፥ለለቅሷቸውም ፍጻሜ የለውም፥
\v 50 እግዚአብሔር ውደ ታች እስኪመለከት ከሰማይም እስኪያይ ድረስ።
\s5
\v 51 ከከተማዬ ሴቶች ልጆች የተነሳ ዓይኔ ጽኑ ስቃይ በሕይወቴ ላይ አመጣች።
\v 52 ጠላቶቼ ያለ ምንም ምክንያት፥ያለመታከት እንደ ወፍ አደኑኝ።
\v 53 ሕይወቴን በጉድጓድ ዉስጥ አጠፉ፥ ድንጋይንም በላዬ ከመሩ።
\v 54 ውኆች በራሴ ላይ አለፉ፤እኔም፦ «ተቆርጬአለሁ! » አልኩ።
\s5
\v 55 እግዚአብሔር ሆይ፥ ከጥልቅ ጉድጓድ ስምህን ጠራሁ።
\v 56 «እርዳታ ፈልጌ ስጮህ፥እረፍት ፈልጌ ስጣራ ጆሮህን አትሰውር» ባልኩኝ ጊዜ ድምጼን ሰማህ።
\v 57 በጠራሁህ ቀን ወደ እኔ ቀርበህ «አትፍራ» አልከኝ።
\s5
\v 58 ጌታ ሆይ በተከሰስሁ ጊዜ ስለ ነፍሴ ተሟገትህ፤ ሕይወቴንም አዳንክ።
\v 59 እግዚአብሔር ሆይ እንዴት እንደ ጨቆኑኝ አይተሃል፥ ክርክሬን በጽድቅ ፍረድልኝ።
\v 60 በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉ፥የበቀላቸውን ሥራ ሁሉ አይተሃል።
\v 61 እግዚአብሔር ሆይ በእኔ ላይ የዶለቱትን ሁሉና እሽሙጥጫቸውን ሰምተሃል።
\s5
\v 62 በእኔ ላይ የተነሱብኝን ከንፈሮች ሰምተሃል፤ቀኑን ሁሉ እኔን በመቃወም የሚያስቡትን ጥልቅ አሳቦች ሰምተሃል።
\v 63 እግአብሔር ሆይ! ተመልከት፥ በመቀመጣቸውም ሆነ በመነሳታችው የስላቅ ዘፈናቸው ምክንያት ነኝ።
\s5
\v 64 እግዚአብሔር ሆይ እጆቻቸው እንዳደረጉት ክፉ ነገር እንደዚያው መልሰህ ክፈላቸው።
\v 65 ፍርሃትን በልባቸው አድርግ፥ ርግማንህንም በላይቸው አድርግ።
\v 66 እግዚአብሔር ሆይ! በቁጣህ አሳድዳችው፥ከሰማይት በታች በየስፍራው አጥፋቸው።
\s5
\c 4
\p
\v 1 ወርቁ ፈጽሞ ደበዘዘ፤ ንጹሁ ወርቅ ተለወጠ! የተቀደሱት ድንጋዮች በየመንገዱ ዳር ተበተኑ።
\v 2 የጽዮን ልጆች የከበሩ፥ከንጹህ ወርቅ በላይ የሚቆጠሩ ነበሩ። አሁን ግን በሸክላ ሠሪ እጅ እንደተሠሩ የሸክላ ዕቃዎች እንጂ ከምንም አልተቆጠሩም።
\s5
\v 3 ቀበሮዎች እንኳን ግልገሎቻቸውን ለማጥባት ጡቶቻቸውን ይገልጣሉ፥የሕዝቤ ሴት ልጅ ግን እንደ ምድረ በዳ ሰጎን ጨካኝ ሆነች።
\s5
\v 4 ከጥም የተነሳ የሚጠባው ሕጻን ምላስ ከላንቃው ጋር ተጣበቀ፤ሕጻናት እንጀራ ለመኑ፥ ነገር ግን የሚሰጣችው የለም።
\v 5 በውድ ዋጋ የሚገዛ ምግብ ይመገቡ የነበሩ ተጥለዋል፥ በየመንገዱ ተርበዋል፤ቀይ ግምጃ ይለብሱ የነበሩ አሁን በቆሻሻ ክምር መካከል ናቸው።
\s5
\v 6 ምንም እጅ ሳይወድቅባት በድንገት ከተገለበጠች ከሰዶም ኃጢአት ይልቅ የሕዝቤ ሴት ልጅ ኃጢአት ታላቅ ነው።
\s5
\v 7 መሪዎቿ እንደ በረዶ የሚያንጸባርቁ ነበሩ፥እንደ ወተትም ነጭ ነበሩ። ሰውነታቸው ከቀይ ዕንቁ ይልቅ ቀይ ነበረ፥ መልካቸውም እንደ ሰንፔር ነበረ።
\v 8 አሁን ጨለማው ገጽታቸውን አጥቁሮታል፥ ቆዳቸው ከመነመኑ አጥንቶቻቸው ጋር ስለተጣበቀም በመንገዶች ላይ ማንነታቸው አልታወቀም።
\s5
\v 9 በሰይፍ የተገደሉት በረሃብ ከሞቱት ይሻላሉ፥አንዳችም ሰብል ከእርሻ በመጥፋቱ በረሃብ ተወግተው ከተወገዱት ይሻላሉ።
\v 10 የርኁሩኆቹ ሴቶች እጆች የገዛ ልጆቻቸውን ቀቀሉ፤ በሕዝቤ ሴት ልጅ የጥፋት ቀን እነዚህ ልጆች መብል ሆኑአቸው።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር ቁጣውን አረካ። ጽኑ ቁጣውን አፈሰሰ፤ በጽዮን እሳትን አያያዘ፥ መሠረትዋንም በላ።
\s5
\v 12 የምድር ነገሥታት ወይም በዓለም ከሚኖሩ ማናቸውም፥ ባላጋራ ወይም ጠላት በኢየሩሳሌም በሮች ይገባል ብለው አላመኑም።
\v 13 ነገር ግን የጻድቅን ደም በመካከልዋ ካፈሰሱ ከነቢያቶቿ ኃጢአትና ከካህናቷ በደል የተነሳ ይህን አደረጉ።
\s5
\v 14 አሁን እነዚያ ነቢያትና ካህናት እንደ ዓይነ ስውራን ሰዎች በየጎዳናዎቹ ይቅበዘበዛሉ። ማንም ልብሶቻቸውን መንካት እስከማይችል ድረስ በደም ረክሰዋል።
\v 15 «እናንተ ርኩሳን ለቃችሁ ሂዱ! » እያሉ በነቢያቱና ካህናቱ ላይ ይጮሁባቸዋል።«ለቃችሁ ሂዱ፥ለቃችሁ ሂዱ! አትንኩን! » ይሏቸዋል። ስለዚህ ወደ ሌላ ምድር ይቅበዘበዛሉ፥ ነገር ግን አሕዛብ እንኳን፥«ከእንግዲህ ወድያ በዚህ እንደ እንግዳ መኖር አይችሉም» ይላሉ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ከማደሪያው በትኖአቸዋል፥ ከእንግዲህ ወድያ ወደ እነርሱ በርኅራኄ አይመለከትም። ማንም ከእንግዲህ ወድያ ካህናቱን በምንም መልኩ አክብሮ አይቀበላቸውም፥ ለሽማግሌዎቹም ግድ አልተሰኙም።
\s5
\v 17 የማይጠቅሙ ረዳቶችን እንኳ ለማግኘት ዓይኖቻችን ድከሙ፤ሊያድነን ወደማይችል ሕዝብ በጉጉት ተመለከቱ።
\v 18 በመንገዶቻችን ሁሉ እርምጃዎቻችንን ተከታተሉ። ፍፃሜያችን መጥቶአልና መጨረሻችን ቀርቦአል፥ ቀኖቻችንም አልቀዋል።
\s5
\v 19 አሳዳጆቻችን ከሰማይ ንስሮች ይልቅ ፈጣኖች ናቸው። በተራሮች ላይ አሳደዱን በምድረ በዳም ሸመቁብን።
\v 20 በእግዚአብሔር የተቀባው ንጉሣችን፥ የአፍንጫችን እስትንፋስ፥ በጉድጓቸው ተያዘ፤« በአሕዛብ መካከል በጥበቃው ሥር እንኖራልን» ብለን የተናገርንለት ንጉሣችን ነበር።
\s5
\v 21 በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶም ሴት ልጅ ሆይ፥ጽዋው ወደ አንቺም ያልፋልና ደስ ይበልሽ ሐሴትም አድርጊ። ትሰክሪያልሽ፥ እርቃንሽንም ትቀሪያልሽ።
\v 22 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ በደልሽ ተፈጸመ። ከእንግዲህ ወዲያ በምርኮ አያኖርሽም። ነገር ግን የኤዶም ሴትልጅ ሆይ በደልሽን ይቀጣል። ኃጢአትሽንም ይገልጣል።
\s5
\c 5
\p
\v 1 እግዚአብሔር ሆይ የሆነብንን አስብ። እፍረታችንን እይ፥ተመልከትም።
\v 2 ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለባዕዳን ታልፈው ተሰጡ።
\v 3 አባቶች ስለሌሉ፥ እናቶቻችንም መበለቶች ስለሆኑ ወላጅ አልባ ሆን።
\v 4 ለመጠጣት ውኃችን የብር ዋጋ ጠየቀ፥ የገዛ እንጨታችንም ተሸጠል ን።
\s5
\v 5 ጠላቶቻችን ያሳድዱናል፥ አንገታችንም ላይ ደርሰዋል። እኛ ደክመናል፥ ዕረፍትም የለንም።
\v 6 ምግብ ለመጥገብ ለግብፃውያንና ለአሦራውያን እጃችንን ሰጠን።
\v 7 አባቶቻችን ኃጢአት ሠሩ፤ እነርሱ የሉም፥እኛ ግን ኃጢአታቸውን ተሸከምን።
\s5
\v 8 ባሮች ይገዙናል፥ ከእጃቸውም የሚያድነን የለም።
\v 9 ከምድረ በዳው ሰይፍ የተነሳ እንጀራ ለማግኘት በሕይወታችን ፈረድን።
\v 10 ቆዳችን እንደ ምድጃ ሆኖአል፥ ከረሃቡ ትኩሳት የተነሳ ተቃጥሎአል።
\s5
\v 11 በጽዮን ሴቶችን፥ በይሁዳ ከተሞች ደናግላንን ደፈሩ።
\v 12 በገዛ እጆቻቸው ልዑላኑን ሰቀሉ፥ሽማግሌዎችንም አላከበሩም።
\s5
\v 13 ኃያላን ወንዶችን ወደ ወፍጮ ቤት አመጡአቸው፥ ወጣት ወንዶችም ከእንጨት በታች ተንገዳግዱ።
\v 14 ሽማግሌዎችን ከከተማይቱ ደጅ፥ ኃያላን ወንዶችንም ከዘፈናቸው አስወገዷቸው።
\s5
\v 15 የልባችን ደስታ ተወግዶአል፥ ጭፈራችንም ወደ ለቅሶ ተለውጦአል።
\v 16 አክሊል ከራሳችን ወድቋል! ወዮልን! ኃጢአት ሠርተናልና!
\s5
\v 17 ልባችን ታምሞአል፥ዓይኖቻችንም ፈዝዘዋል፤
\v 18 ምክንያቱም ባድማ በሆነችው በጽዮን ተራራ ላይ ቀበሮዎች ፈንጭተውበታልና።
\s5
\v 19 ነገር ግን አንተ እግዚአብሔር ነህ፤ ለዘላለም ትገዛለህ፥ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
\v 20 ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ለረዥም ዘመናትስ ትተወናለህን?
\v 21 እግዚአብሔር ሆይ፥ወደ አንተ መልሰን፥እኛም ንስሐ እንገባልን። ቀኖቻችንን እንደ ጥንቱ ዘመን አድስ፥
\v 22 ፈጽመህ ካልጣልከንና እጅግም ካልተቆጣኽን።

View File

@ -1,5 +1,3 @@
# am_ulb
Amharic ULB
# Amharic ULB
STR https://git.door43.org/unfoldingWord/SourceTextRequestForm/issues/206 for OT.

View File

@ -1,4 +1,4 @@
dublin_core:
dublin_core:
conformsto: 'rc0.2'
contributor:
- "Abera Wolde"
@ -22,12 +22,12 @@
description: 'An unrestricted literal Bible'
format: 'text/usfm'
identifier: 'ulb'
issued: '2018-09-24'
issued: '2019-04-29'
language:
direction: 'ltr'
identifier: 'am'
title: 'Amharic'
modified: '2018-09-24'
modified: '2019-04-29'
publisher: 'Door43'
relation:
- 'am/tw'
@ -42,7 +42,7 @@
subject: 'Bible'
title: 'Unlocked Literal Bible'
type: 'bundle'
version: '7.1'
version: '7.2'
checking:
checking_entity:
@ -96,6 +96,13 @@ projects:
sort: 21
path: ./21-ECC.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ዘጸአት '
versification: ufw
identifier: 'exo'
sort: 2
path: ./02-EXO.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኦሪት ዘፍጥረት '
versification: ufw
@ -124,6 +131,20 @@ projects:
sort: 28
path: ./28-HOS.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኢሳይያስ '
versification: ufw
identifier: 'isa'
sort: 23
path: ./23-ISA.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኤርሚያስ '
versification: ufw
identifier: 'jer'
sort: 24
path: ./24-JER.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኢዮብ '
versification: ufw
@ -145,6 +166,13 @@ projects:
sort: 32
path: ./32-JON.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ሰቆቃው ኤርሚያስ '
versification: ufw
identifier: 'lam'
sort: 25
path: ./25-LAM.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኦሪት ዘሌዋውያን '
versification: ufw
@ -173,6 +201,13 @@ projects:
sort: 34
path: ./34-NAM.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ነህምያ '
versification: ufw
identifier: 'neh'
sort: 16
path: ./16-NEH.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ትንቢተ አብድዩ '
versification: ufw
@ -180,6 +215,13 @@ projects:
sort: 31
path: ./31-OBA.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ምሳሌ '
versification: ufw
identifier: 'pro'
sort: 20
path: ./20-PRO.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ሩት '
versification: ufw