initial upload; 21 books

This commit is contained in:
Larry Versaw 2018-09-24 13:54:20 -06:00
parent a5451f6e50
commit 53a19db62a
22 changed files with 17356 additions and 0 deletions

2908
01-GEN.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,2908 @@
\id GEN
\ide UTF-8
\h ኦሪት ዘፍጥረት
\toc1 ኦሪት ዘፍጥረት
\toc2 ኦሪት ዘፍጥረት
\toc3 gen
\mt ኦሪት ዘፍጥረት
\s5
\c 1
\p
\v 1 እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ።
\v 2 ምድርም ቅርፅ የሌላትና ባዶ ነበረች። ጥልቅ የሆነው ስፍራዋም በጨለማ ተውጦ ነበር። የእግዚአብሔርም መንፈስ በውሃው ላይ ሰፍፎ ነበር።
\s5
\v 3 እግዚአብሔርም፦ “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።
\v 4 እግዚአብሔርም ብርሃኑ መልካም እንደሆነ አየ፤ ብርሃንኑም ከጨለማ ለየው።
\v 5 እግዚአብሔርም ብርሃኑን ‘ቀን’ ጨለማውን ደግሞ ‘ሌሊት’ ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ ሌሊቱም ነጋ አንድ ቀን ሆነ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔርም፦ “በውሆች መካከል ጠፈር ይሁን፣ ውሆችንም ይለያዩ” አለ።
\v 7 እግዚአብሔር ጠፈርን አደረገና ከጠፈር በላይና ከጠፈር በታች ያሉትን ውሆች ለየ። እንደዚያም ሆነ።
\v 8 እግዚአብሔር ጠፈሩን ‘ሰማይ’ብሎ ጠራው። ቀኑ መሸ ሌሊቱም ነጋ ሁለተኛ ቀን።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር፦ “ከሰማይ በታች ያለው ውሃ ወደ አንድ ስፍራ ይሰብሰብ፣ ምድሩም ይገለጥ” አለ። እንደዚያም ሆነ።
\v 10 እግዚአብሔርም ምድሩን ‘የብስ’፣ ወደአንድ ስፍራ የተሰበሰበውንም ውሃ ‘ባሕር’ ብሎ ጠራው። ይህም መልካም መሆኑን ተመለከተ።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር፦ እንደ ዓይነታቸው ዘርን የሚያፈሩ ተክሎችን፣ በውስጣቸው ዘርን ያዘሉ የፍራፍሬ ዛፎችን እንደዓይነታቸው የሚያፈሩ አዝርዕትን ታብቅል” አለ። እንደዚያም ሆነ።
\v 12 ምድር እንደአይነታቸው የሚያፈሩ አዝርዕትን አበቀለች። ይህም መልካም እንደሆነ እግዚአብሔር ተመለከተ።
\v 13 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ ሶስተኛ ቀን ሆነ።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር፦ “ቀኑን ከሌሊቱ ይለዩ ዘንድ በሰማይ ብርሃናት ይሁኑ። እነዚህ ብርሃናት የዓመት ወቅቶችን፣ ቀናትንና ዓመታትን የሚለዩ ምልክቶች ይሁኑ።
\v 15 ለምድርም ብርሃን ይሰጡ ዘንድ በሰማይ ላይ የሚገኙ ብርሃናት ይሁኑ” አለ። እንደዚያም ሆነ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ታላቁ ብርሃን በቀን፣ ታናሹ ብርሃን በሌሊት ይሠለጥኑ ዘንድ ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን አደረገ። ከዋክብትንም ደግሞ አደረገ።
\v 17 ለምድርም ብርሃን ይሰጡ ዘንድና
\v 18 በቀንና በሌሊት ላይ እንዲሠለጥኑ እንደዚሁም ብርሃንን ከጨለማ እንዲለዩ በሰማይ አኖራቸው። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ ተመለከተ።
\v 19 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ አራተኛ ቀን ሆነ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር፦ “ውሆች በሕያዋን ፍጡራን የተሞሉ ይሁኑ፣ ወፎችም ከምድር በላይ ባለው በሰማይ ጠፈር ይብረሩ” አለ።
\v 21 እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር ፍጥረታትን እንደዚሁም በምድር የሚንቀሳቀሱ፣ በውሆች ውስጥ የሚርመሰመሱና በክንፎቻቸው የሚበሩ ወፎችን እንደዓይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔር ይህ መልካም እንደሆነ ተመለከተ።
\s5
\v 22 እግዚአብሔርም፦ “ብዙ ተባዙ የባሕርን ውሆች ሙሉአቸው፣ ወፎችም በምድር ላይ ይብዙ” ብሎ ባረካቸው።
\v 23 ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ አምስተኛ ቀን ሆነ።
\s5
\v 24 እግዚአብሔርም፦ “ምድር እንደወገናቸው ሕያው ፍጥረታትን ማለትም ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡትንና የምድር አራዊትን ታስገኝ” አለ። እንደዚያም ሆነ።
\v 25 እግዚአብሔር በየዓይነታቸው የምድር አራዊትን፣ በየዓይነታቸው ማናቸውንም በምድር የሚሳቡትን ፈጠረ።
\s5
\v 26 እግዚአብሔርም፦ “ሰውን በመልካችን እንደ አምሳላችን እንፍጠር፣ ሰዎችም በባሕር ዓሣዎች፣ በሰማይ በሚበሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚሳቡ ማናቸውም ተሳቢ ፍጥረቶች ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ።
\v 27 እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ፣ በራሱም አምሳል ፈጠረው። ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።
\s5
\v 28 እግዚአብሔር ባረካቸው እንደዚህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፣ ምድርንም ሙሉአት ግዟትም። በባሕር ውስጥ ባሉት ዓሣዎች፣ በሰማይ ላይ በሚበሩት ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱት ማናቸውም ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ”
\v 29 እግዚአብሔርም፦ “እነሆ፣ ምግብ ይሆኑላችሁ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ በውስጣቸው ዘርን ያዘሉ ማናቸውንም ተክሎችና በውስጣቸው ፍሬ ያላቸውን ማናቸውንም የፍራፍሬ ዛፎች ሰጥቻችኋለሁ።
\s5
\v 30 በምድር ላይ ለሚገኙ እንስሳት ሁሉ፣ በሰማይ ለሚበሩ ወፎች ሁሉ፣ እንዲሁም በምድር ላይ ለሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ማለትም የሕይወት እስትንፋስ ላለበት ማንኛውም ፍጡር ማንኛውም ለምለም ተክል ምግብ እንዲሆናቸው ሰጥቻለሁ። እንደዚሁም ሆነ።
\v 31 እግዚአብሔር የፈጠረውን ማንኛውንም ነገር ተመለከተ። እነሆ፣ እጅግ መልካም ነበረ። ቀኑ መሸ፣ ሌሊቱም ነጋ ስድስተኛ ቀን ሆነ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 የምድር በውስጣቸው ያሉትም ሕያዋን ፍጡራን አፈጣጠር በዚህ ሁኔታ ተከናወነ።
\v 2 እግዚአብሔር ይሠራ የነበረውን ሥራ በሰባተኛው ቀን ፈጽሞ በዚሁ ቀን ከሥራው ሁሉ አረፈ።
\v 3 እግዚአብሔር የመፍጠር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ ያረፈው በዚህ ቀን ስለሆነ ሰባተኛውን ቀን ባረከው ቀደሰውም።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን በፈጠረበት ወቅት የሰማይና የምድር የአፈጣጠራቸው ታሪክ እንደዚህ ነበር።
\v 5 እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ ዝናብ እንዲዘንብ ስላደረገና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ በምድር ላይ ምንም ቡቃያ አልነበረም፣ በምድር ላይ የሚበቅል ተክልም ገና አልበቀለም።
\v 6 ነገር ግን ውሃ ከመሬት እየመነጨ የምድርን ገጽ ያረሰርስ ነበር።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።
\v 8 እግዚአብሔር አምላክም በስተምሥራቅ በኩል በዔደን የአትክልት ስፍራ አዘጋጀ፣ የአበጀውንም ሰው በዚያ አኖረው።
\s5
\v 9 ከምድር ውስጥም እግዚአብሔር አምላክ ለዓይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ። በአትክልት ስፍራው መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበር፣ መልካሙንና ክፉውን የሚያሳውቀውም ዛፍ በዚያ ነበር።
\v 10 የአትክልት ስፍራውንም የሚያጠጣ ወንዝ ከኤደን ይፈስ ነበር። ወንዙም ከኤደን ከወጣ በኋላ አራት ወንዞች ሆኖ ይከፋፈል ነበር።
\s5
\v 11 የመጀመሪያው ፊሶን የተባለው ወንዝ ነበር፣ ይህም ወርቅ ይገኝበት የነበረውን መላውን የሐዊላ ምድር አቋርጦ የሚፈስው ወንዝ ነበር።
\v 12 የዚያ አገር ወርቅ የጠራ ወርቅ ነበር፤ በተጨማሪም በዚያ አገር ሽቶና የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ።
\s5
\v 13 የሁለተኛው ወንዝ ስም ግዮን ይባል ነበር፣ እርሱም መላውን የኢትዮጵያ ምድር አቋርጦ ይፈስ ነበር።
\v 14 የሶስተኛው ወንዝ ስም ጤግሮስ ይባል ነበር፣ እርሱም በአሦር በስተምሥራቅ ይፈሳል። አራተኛው ወንዝ ኤፍራጥስ ነበር።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር አምላክም የኤደንን የአትክልት ስፍራ ያለማና ይንከባከብ ዘንድ ሰውን ወስዶ በዚያ አኖረው።
\v 16 እግዚአብሔር አምላክም እንዲህ በማለት አዘዘው፣ “በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም የፍሬ ዛፍ መብላት ትችላልህ።
\v 17 ነገር ግን መልካሙንና ክፉውን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፣ ምክንያቱም ከእርሱ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ።”
\s5
\v 18 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ፦ “ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም። ስለዚህ የምትመቸውን ረዳት እፈጥርለታለሁ” አለ።
\v 19 እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር የምድር እንስሶችንና የሰማይ ወፎችን አበጀ። ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ይመለከት ዘንድ ወደ አዳም አመጣቸው። ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር አዳም ያወጣለት ስም ያ ስሙ ሆነ።
\v 20 አዳም ለሁሉም ከብቶች፣ ለሁሉም የሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ሁሉ ስም አወጣላቸው። ነገር ግን ለአዳም ለራሱ የምትመች ረዳት አልተገኘለትም።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር አምላክ በአዳም ላይ ከባድ እንቅልፍ እንዲወስደው አደረገ፣ ስለሆነም አዳም አንቀላፋ። እግዚአብሔር አምላክ አዳም አንቀላፍቶ ሳለ ከጎድን አጥንቶቹ አንዱን ወስዶ አጥንቱን የወሰደበትን ስፍራ በሥጋ ዘጋው።
\v 22 እግዚአብሔር አምላክ ከአዳም ከወሰደው የጎድን አጥንት ሴት አድርጎ ሠራት። ወደ አዳምም አመጣት።
\v 23 አዳምም፦ “አሁን ይህቺ ከአጥንቴ የተገኘች አጥንት ከሥጋዬ የተገኘች ሥጋ ናት። ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል” አለ።
\s5
\v 24 ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።
\v 25 አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፤ ይሁን እንጂ አይተፋፈሩም ነበር።
\s5
\c 3
\p
\v 1 እግዚአብሔር በምድር ላይ ከፈጠራቸው ማናቸውም ሌሎች አራዊቶች ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኮለኛ ነበር። እርሱም ሴቲቱን፦ “በእርግጥ እግዚአብሔር ‘በአትክልቱ ስፍራ ካለው ከማንኛውም ዛፍ አትብሉ’ ብሎአልን? ” ብሎ ጠየቃት።
\v 2 ሴቲቱም ለእባቡ፦ “በአትክልቱ ስፍራ ካሉት የዛፎች ፍሬዎች መብላት እንችላለን፤
\v 3 ነገር ግን በአትክልቱ ስፍራ መካከል ስለሚገኘው ዛፍ እግዚአብሔር “እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም” ብሎአል።
\s5
\v 4 እባብም ለሴቲቱ፦ “በፍጹም አትሞቱም።
\v 5 ከእርሱ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንደሚከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካሙንና ክፉውን የምታውቁ እንደምትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው አላት።”
\v 6 ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት መልካም፣ ሲያዩት ደስ የሚያሰኝና ጥበብንም ለማግኘት የሚያጓጓ እንደሆነ ተመልክታ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ከእርሷ ጋር ለነበረውም ለባሏ ከፍሬው ሰጠችው፣ እርሱም በላ።
\s5
\v 7 የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፣ ራቁታቸውን እንደነበሩም አወቁ። የበለስ ቅጠሎችንም በማጋጠም ከሰፉ በኋላ ለራሳቸው መሸፈኛ ግልድም ሠሩ።
\v 8 ቀኑ ወደ ምሽት ሲቃረብ በአትክልት ስፍራው ሲመላለስ የእግዚአብሔር አምላክን ድምፅ ሰሙ፤ ስለዚህ አዳምና ሚስቱ ከእግዚአብሔር አምላክ ፊት በመሸሽ በአትክልቱ ስፍራ በነበሩት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር አምላክ አዳምን ጠራውና፣ “የት ነህ? ” አለው።
\v 10 አዳምም፣ “በአትክልቱ ስፍራ ውስጥ ድምፅህን ሰማሁና ራቁቴን ስለነበርሁ ፈራሁ፤ በዚህም ምክንያት ተሸሸግሁ።”
\v 11 እግዚአብሔርም፦ “ራቁትህን እንደሆንክ ማን ነገረህ? ከእርሱ እንዳትበላ ብዬ ካዘዝኩህ ከዛፉ ፍሬ በላህን? ” አለው።
\s5
\v 12 አዳምም፦ “አብራኝ እንድትሆን የሰጠኸኝ ሴት ከዛፉ ፍሬ ሰጠችኝ፣ እኔም በላሁት” አለ።
\v 13 እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ “ምንድነው ያደረግሽው? ” አላት። ሴቲቱም፦ “እባቡ አታለለኝና በላሁ” አለች።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር አምላክም ለእባቡ፦ “ይህንን በማድረግህ ከእንስሳት ሁሉና ከምድር አራዊት ሁሉ ተለይተህ የተረገምህ ትሆናለህ። በደረትህ እየተሳብክ ትሄዳለህ፣ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ አፈር ትበላለህ።
\v 15 በአንተና በሴቲቱ፣ በዘርህና በዘሯ መካካል ጠላትነትን አደርጋለሁ። የእርሷ ዘር ራስህን ይቀጠቅጣል፣ አንተም ተረከዙን ትነክሳለህ” አለው።
\s5
\v 16 ለሴቲቱም እንዲህ አላት፦ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በስቃይም ትወልጃለሽ። ፈቃድሽ ወደ ባልሽ ይሆናል፣ እርሱም ገዢሽ ይሆናል።”
\s5
\v 17 ለአዳምም እንደዚህ አለው፦ “የሚስትህን ቃል ሰምተህ ‘ከእርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ከዛፉ ፍሬ ስለበላህ ከአንተ የተነሳ ምድር የተረገመች ትሁን፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ በከባድ ድካም ምግብህን ከእርሷ ታገኛለህ።
\v 18 ምድር እሾህና አሜኬላ ታበቅልብሃለች፤ የምድርንም ቡቃያ ትበላለህ።
\v 19 ከተገኘህበት አፈር እስክትመለስ ድረስ በላብህ እንጀራን ትበላለህ። አፈር ነህና ወደ አፈር ተመልሰህ ትሄዳለህ”።
\s5
\v 20 የሕያዋን ሁሉ እናት በመሆኗ አዳም ለሚስቱ ‘ሔዋን’ የሚል ስም አወጣላት።
\v 21 እግዚአብሔር አምላክ ከቆዳ ልብስ አዘጋጅቶ አዳምንና ሚስቱን አለበሳቸው።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር አምላክ፦ “መልካምንና ክፉውን ለይቶ በማውቅ ረገድ አሁን ሰው ከእኛ እንደ አንዱ ሆኖአል። ስለዚህ አሁን እጁን ዘርግቶ ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ቀጥፎ እንዳይበላ ለዘላለምም እንዳይኖር ሊፈቀድለት አይገባም” አለ።
\v 23 በዚህም ምክንያት የተገኘባትን ምድር እንዲያለማ እግዚአብሔር አዳምን ከኤደን የአትክልት ስፍራ አስወጣው።
\v 24 ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ከአትክልት ስፍራው አባረረው፣ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ከኤደን የአትክልት ስፍራ በስተቀኝ በኩል ኪሩቤልን እንደዚሁም በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሰይፍ አኖረ።
\s5
\c 4
\p
\v 1 አዳምም ከሚስቱ ከሔዋን ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ። እርሷም ፀነሰች። ቃየንንም ወለደች። “በእግዚአብሔር ዕርዳታ ወንድ ልጅ ወለድሁ” አለች።
\v 2 ከዚያ በኋላም ወንድሙን አቤልን ወለደች። አቤል የበግ እረኛ ሲሆን ቃየን ግን ገበሬ ሆነ።
\s5
\v 3 ከዕለታት አንድ ቀን ቃየን ከምድር ፍሬ ለእግዚአብሔር መባ አቀረበ።
\v 4 አቤል ደግሞ መጀመሪያ ከተወለዱ በጎች መካከል ስባቸውን መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ። እግዚአብሔር በአቤልና በመሥዋዕቱ ደስ ተሰኘ፣
\v 5 በቃየንና በመሥዋዕቱ ግን ደስ አልተሰኘም። ስለዚህ ቃየን በጣም ተቆጣ፣ ፊቱም ተኮሳተረ።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር አምላክ ቃየንን፦ “ለምን ተቆጣህ፣ ፊትህስ ለምን ተኮሳተረ?
\v 7 መልካም ብታደርግ ፊትህ ያበራ አልነበረምን? ያደረግኸው መልካም ካልሆን ግን ኃጢአት በደጅህ እያደባች ናት፣ ልትቆጣጠርህም ትፈልጋለች፣ አንተ ግን በቁጥጥርህ ሥር አድርጋት” አለው።
\s5
\v 8 ቃየን ወንድሙን አቤልን፦ “ወደ ሜዳ እንውጣ” አለው፣ በዚያም ቃየን በወንድሙ በአቤል ላይ በቁጣ ተነሳበት፣ ገደለውም።
\v 9 ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር ቃየንን፦ “ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? ” አለው። እርሱም፦ “አላውቅም፣ እኔ የወንድሜ ጠባቂ ነኝን? ” አለ።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም፦ “ያደረግኸው ምንድን ነው? የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል” አለው።
\v 11 “አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።
\v 12 ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ፍሬዋን በሙላት አትሰጥህም። በምድር ላይ ኮብላይና ተንከራታች ትሆናለህ” አለው።
\s5
\v 13 ቃየንም ለእግዚአብሔር፦ ቅጣቴ ከምችለው በላይ ነው።
\v 14 በእርግጥም ዛሬ ከምድሪቱ አባርረኸኛል፣ እኔም ከፊትህ እሸሸጋለሁ። በምድር ላይ ኮብላይና ተንከራታች እሆናለሁ፣ የሚያገኘኝም ሁሉ ይገድለኛል” አለው።
\v 15 እግዚአብሔርም፦ “ቃየንን የሚገድል ማንኛውም ሰው ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ ይወሰድበታል” አለ። ከዚያ በኋላም የሚያገኘው ማንኛውም ሰው እንዳይገድለው እግዚአብሔር በቃየን ላይ ምልክት አደረገበት።
\s5
\v 16 ቃየንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፣ ከኤደን በስተምሥራቅ በነበረው ኖድ በተባለው ምድር ኖረ።
\v 17 ቃየንም ከሚስቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ፣ እርሷም ፀነሰች፣ ሄኖክንም ወለደች። ቃየን ከተማን መሠረተ፣ የመሠረታትንም ከተማ በልጁ ስም ሄኖክ ብሎ ጠራት።
\s5
\v 18 ሄኖክም አራድን ወለደ። አራድም መሑያኤልን ወለደ። መሑያኤልም መቱሳኤልን ወለደ። መቱሳኤልም ላሜክን ወለደ።
\v 19 ላሜክም ዓዳና ጺላ የተባሉ ሁለት ሚስቶችን አገባ።
\s5
\v 20 ዓዳ ያባልን ወለደች፣ እርሱም በድንኳን ለሚኖሩ ለከብት አርቢዎች አባት ነበር።
\v 21 የእርሱ ወንድም ዩባልም የበገና ደርዳሪዎችና የዋሽንት ነፊዎች አባት ነበር።
\v 22 ጺላም ከነሐስና ከብረት መሣሪያዎችን የሚሠራውን ቱባልቃይንን ወለደች። የቱባልቃይንም እህት ናዕማ ትባል ነበር።
\s5
\v 23 ላሜክ ለሚስቶቹ፦ “አዳና ጺላ ስሙኝ፣ እናንተ የላሜክ ሚስቶች የምላችሁን ስሙኝ ስለጎዳኝና ስላቆሰለኝ አንድ ሰው ገድያለሁ።
\v 24 ቃየንን የሚገድል ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ የሚወሰድበት ከሆነ የላሜክ ገዳይማ ሰባ ሰባት እጥፍ የበቀል እርምጃ ይወሰድበታል” አላቸው።
\s5
\v 25 አዳም ከሚስቱ ጋር እንደገና የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ፣ እርሷም ወንድ ልጅ ወለደች። “ቃየን በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ምትክ ሰጠኝ” በማለት ስሙን ሤት ብላ ጠራችው።
\v 26 ለሤትም ወንድ ልጅ ተወለደለት፣ ስሙንም ሄኖስ አለው። በዚያም ዘመን ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ጀመሩ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን በፈጠረው ጊዜ በራሱ አምሳያ ፈጠራቸው፤
\v 2 ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው፣ ባረካቸውም። በተፈጠሩም ጊዜ ‘ሰው’ ብሎ ጠራቸው።
\s5
\v 3 አዳም ዕድሜው 130 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እርሱን የሚመስል ወንድ ልጅ ወለደ፣ ስሙንም ‘ሤት’ ብሎ ጠራው።
\v 4 አዳም ሤትን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎችን ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ፤
\v 5 930 ዓመት ሲሆነውም ሞተ።
\s5
\v 6 ሤት ዕድሜው 105 ሲሆን ሄኖስን ወለደ።
\v 7 ሄኖስን ከወለደ በኋላ ሤት 807 ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 8 ሤት 912 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 9 ሄኖስ 90 ዓመት ሲሆነው ቃይናንን ወለደ።
\v 10 ሄኖስ ቃይናንን ከወለደ በኋላ 815 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 11 ሄኖስ 905 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 12 ቃይናን 70 ዓመት ሲሆነው መላልኤልን ወለደ።
\v 13 ቃይናን መላልኤልን ከወለደ በኋላ 840 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 14 ቃይናን 910 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 15 መላልኤል 65 ዓመት ሲሆነው ያሬድን ወለደ።
\v 16 መላልኤል ያሬድን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ። ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 17 መላልኤል 895 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 18 ያሬድ 162 ዓመት ሲሆነው ሄሮክን ወለደ።
\v 19 ያሬድ ሄኖክን ከወለደ በኋላ 800 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 20 ያሬድ 962 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 21 ሄኖክ 65 ዓመት ሲሆነው ማቱሳላን ወለደ።
\v 22 ሄኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 23 ሄኖክ 365 ዓመታት ኖረ።
\v 24 ሄኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል ኖረ፣ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ስለወሰደው አልተገኘም።
\s5
\v 25 ማቱሳላ 187 ዓመት ሲሆነው ላሜሕን ወለደ።
\v 26 ማቱሳላ ላሜሕን ከወለደ በኋላ 782 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 27 ማቱሳላ 969 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 28 ላሜሕ 182 ዓመት ሲሆነው አንድ ወንድ ልጅ ወለደ።
\v 29 “ይህ ልጅ እግዚአብሔር በረገማት ምድር ከልፋታችንና ከብርቱ ሥራችን ያሳርፈናል” ሲል ስሙን ‘ኖህ’ ብሎ ጠራው።
\s5
\v 30 ላሜሕ ኖህን ከወለደ በኋላ 595 ዓመታት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\v 31 ላሜሕ 777 ዓመታት ከኖረ በኋላ ሞተ።
\s5
\v 32 ኖህ 500 ዓመታት ሲሆነው ሴም፣ ካምንና ያፌትን ወለደ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 የሰው ልጆች በምድር ላይ እየበዙ ሲሄዱ ሴቶች ልጆች ተወለዱላቸው።
\v 2 የእግዚአብሔር ልጆችም የሰዎች ሴቶች ልጆች የሚስብ ውበት እንዳላቸው ተመለከቱ። ከእነርሱ መካከልም የመረጧቸውን ሚስቶች አድርገው ወሰዱ።
\v 3 እግዚአብሔርም፦ “እርሱ ሥጋ ስለሆነ መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜውም 120 ዓመት ይሆናል” አለ።
\s5
\v 4 የእግዚአብሔር ልጆች ከሰዎች ሴቶች ልጆች ጋብቻ በፈጸሙና ልጆችን በወለዱበት በዚያን ጊዜ ከዚያም በኋላ ኔፊሊም የተባሉ ግዙፍ ሰዎች በምድር ላይ ነበሩ። እነርሱም በጥንት ዘመን ዝናን ያተረፉ ኅያላን ነበሩ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር የሰው ልጆች ክፋት በምድር ላይ እየበዛ እንደሆነና የልቡም ሃሳብ ዘወትር ወደ ክፋት ብቻ ያዘነበለ መሆኑን ተመለከተ።
\v 6 እግዚአብሔር የሰው ልጆችን በምድር ላይ በመፍጠሩ ተጸጸተ ልቡም አዘነ።
\s5
\v 7 በዚህም ምክንያት እግዚአብሔር፦ “የፈጠርሁትን የሰው ልጅ ከምድር ገጽ አጠፋለሁ፤ ስለፈጠርኋቸው ተጸጽቻለሁና ከእነርሱም ጋር እንስሳትን፣ በደረታቸው የሚሳቡትን ፍጥረታትና የሰማይ ወፎችን ሁሉ አጠፋለሁ” አለ።
\v 8 ኖኅ ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አገኘ።
\s5
\v 9 የኖኅ ታሪክ እንደሚከተለው ነው። ኖኅ በዘመኑ ከነበሩት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ጻድቅና ከበደል የራቀ ሰው ነበር፤ የእግዚአብሔርንም መንገድ የሚከተል ሰው ነበር።
\v 10 ኖኅ ሴም፣ ካምና ያፌት የተባሉትን ሶስት ወንዶች ልጆች ወለደ።
\s5
\v 11 በእግዚአብሔር ፊት በክፉ ሥራ ረከሰች በዓመፅም ተሞላች።
\v 12 እግዚአብሔር ምድርን ተመለከተ፣ የተበላሸች እንደሆነችና በምድር የሚኖሩትም ሰዎች ሁሉ በክፋት እንደሚኖሩ አየ።
\s5
\v 13 እግዚአብሔርም ኖኅን፦ “ሥጋን የለበሰ ሁሉ ፍጻሜ ደርሶአል፣ ከእነርሱ የተነሳ ምድር በግፍ ተሞልታለችና። እኔም በእርግጥ ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ።
\v 14 አንተ ግን ከጥሩ እንጨት መርከብ ሥራ፤ መርከቧም ክፍሎች እንዲኖራት አድርግ፤ ውስጧንና ውጭዋንም በቅጥራን ለቅልቀው።
\v 15 እንደዚህ አድርገህ ሥራት፦ ርዝመቷ 140 ሜትር፣ ወርዷ 23 ሜትር፣ ከፍታዋ 13. 5 ሜትር ይሁን።
\s5
\v 16 ለመርከቧ ጣራ አብጅላት፣ ጣራና ግድግዳው በሚጋጠምበት ቦታ ግማሽ ሜትር ክፍተት ተው፤ ከጎኗ በር አውጣላት፤ ባለ ሦስት ፎቅ አድርገህ ሥራት።
\v 17 እኔም ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለባችውን ፍጡራን ሁሉ ለማጥፋት እነሆ በምድር ላይ የጥፋት ውሃ አወርዳለሁ፤ በምድር ላይ ያለ ሁሉ ይጠፋል።
\s5
\v 18 ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ።
\v 19 ከአንተ ጋር በሕይወት እንዲቆዩ ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ወንድና ሴት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ።
\s5
\v 20 ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቆዩ ዘንድ ወደ አንተ ይምጡ።
\v 21 ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዓይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።”
\v 22 ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።
\s5
\c 7
\p
\v 1 እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ትውልድ መካከል አንተን ጻድቅ ሆነህ አግኝቼሃለሁና ቤተሰብህን በሙሉ ይዘህ ወደ መርከቧ ግባ።
\v 2 ከንፁህ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ወንድና ሴት፣ ንፁሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ወንድና ሴት ከአንተ ጋር አስገባ።
\v 3 እንዲሁም ከሰማይ ወፎች ወገን ሰባት ወንዶችና ሰባት ሴቶች በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋር ታስገባለህ።
\s5
\v 4 ከሰባት ቀን በኋላ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁ፤ የፈጠርሁትንም ሕያው ፍጡር ሁሉ ከምድር ላይ አጠፋለሁ።”
\v 5 ኖኅም እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ አደረገ።
\s5
\v 6 የጥፋት ውሃ በምድር ላይ በወረደ ጊዜ ኖኅ የ600 ዓመት ሰው ነበር።
\v 7 ኖኅና ወንዶች ልጆቹ ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች ከጥፋት ውሃ ለማምለጥ ወደ መርከቡ ገቡ።
\s5
\v 8 ንፁሕ ከሆኑትና ንፁሕ ካልሆኑት እንስሳት ከወፎችና በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጡራን ሁሉ
\v 9 ጥንድ ጥንድ ወንድና ሴት ሆነው ወደ ኖኅ መጡ፤ እግዚአብሄር ኖኅን ባዘዘው መሠረትም ወደ መርከቧ ገቡ።
\v 10 ከሰባት ቀንም በኋላ የጠፋት ውሃ በምድር ላይ መጣ።
\s5
\v 11 ኖኅ በተወለደ በ600ኛው ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በአሥራ ሰባተኛው ቀን የታላቁ ጥልቅ ምንጮች በሙሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ።
\v 12 ዝናቡም መዝነብ ጀመረ፣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ባለማቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ።
\s5
\v 13 ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ጋር ከሴም ከካም ከያፌትና ከሶስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ።
\v 14 ከአራዊት ከእንስሳት በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዓይነት አብረዋቸው ገቡ።
\s5
\v 15 የሕይወት እስትንፋስ ያለባቸው ፍጡራን በሙሉ ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ከኖኅ ጋር ወደ መርከቡ ገቡ።
\v 16 ከሕያዋንም ፍጡራን ሁሉ እግዚአብሔር ኖኅን ባዘዘው መሠረት ወንድና ሴት እየሆኑ ገቡ፤ ከዚያም እግዚአብሔር የመርከቡን በር ከውጭ ዘጋ።
\s5
\v 17 የጥፋት ውሃም ለአርባ ቀናት ያለመቋረጥ በምድር ላይ ዘነበ ውሃው እየጨመረ በሄድ መጠን መርከቧን ከምድር ወደ ላይ አነሳት።
\v 18 ውሃው በምድር ላይ በጣም እየጨመረና ከፍ እያለ ሲሄድ፣ መርከቧ በውሃ ላይ ተንሳፈፈች።
\s5
\v 19 ውሃው በጣም ከፍ በማለቱ፣ ከሰማይ በታች ያሉትን ታላላቅ ተራሮች ሁሉ ሸፈናቸው።
\v 20 ውሃው ከተራሮች ጫፍ በላይ 7ሜትር ያህል ከፍ አለ።
\s5
\v 21 በምድር ላይ የነበሩ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፦ ወፎች፣ የቤት እንስሳት፣ አራዊት፣ በምድር የሚርመሰመሱ ፍጡራን ሰዎችም በሙሉ ጠፉ።
\v 22 የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው በምድር የነበሩ ፍጡራን ሁሉ ሞቱ።
\s5
\v 23 ሕይወት ያላቸው ፍጡራን ሁሉ ከሰዎች ጀምሮ እንስሳት፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጡራንና የሰማይ ወፎች ሁሉም ከምድር ገጽ ጠፉ። ኖኅና ከእርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ።
\v 24 ውሃውም ምድርን ሸፍኖ መቶ አምሳ ቀን ቆየ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቧ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሳት ሁሉ አሰበ። በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ ውሃውም ጎደለ።
\v 2 የጥልቁ ምንጮችና የሰማይ መስኮቶች ተዘጉ፣ ዝናቡም መዝነቡን አቆመ።
\v 3 ውሃው ከምድር ላይ ቀስ በቀስ እየቀነሰ መጣ፤ ከመቶ ሃምሳ ቀን በኋላም የውሃው ከፍታ እጅግ ቀነሰ።
\s5
\v 4 በሰባተኛው ወር፤ በአሥራ ሰባተኛው ቀን መርከቧ በአራራት ተራሮች ላይ አረፈች።
\v 5 ውሃው እስከ አሥረኛው ወር ድረስ ቀስ በቀስ እየጎደለ ሄደ። በአሥረኛው ወር መጀመሪያው ቀን የተራሮች ጫፎች ታዩ።
\s5
\v 6 ከአርባ ቀን በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቧን መስኮት ከፍቶ፣
\v 7 ቁራን ወደ ውጭ ላከ፤ ቁራውም ውሃው ከምድር ላይ እስኪደርቅ ድረስ ወዲያና ወዲህ ይበር ነበር።
\s5
\v 8 ከዚያም በኋላ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ ገጽ ጎድሎ እንደሆነ ለማወቅ ርግብን ላከ፤
\v 9 ነገር ግን ውሃው ገና ምድርን ሁሉ ሸፍኖ ስለነበር ርግቢቱ የምታርፍበት ቦታ አላገኘችም፤ ስለዚህ ኖኅ ወዳለበት መርከብ ተመልሳ መጣች፤ ኖኅም እጁን ዘርግቶ ወደ መርከቡ ውስጥ አስገባት።
\s5
\v 10 ሰባት ቀን ከቆየ በኋላ ኖኅ ርግቧን እንደገና ላካት።
\v 11 እርሷም ወደ ማታ ተመለሰች፤ እነሆም የለመለመ የወይራ ቅጠል በአፏ ይዛ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ኖኅ ውሃው ከምድር ላይ መጉደሉን አወቀ።
\v 12 ደግሞም ሰባት ቀን ከቆየ በኋላ ኖኅ ርግቢቱን እንደገና አውጥቶ ላካት፤ በዚህ ጊዜ ግን ርግቢቱ ወደ እርሱ አልተመለሰችም።
\s5
\v 13 ኖኅ በተወለደ 601ኛው ዓመት፣ በመጀመሪያው ወር፣ ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ውሃው ከምድር ላይ ደረቀ። ኖኅ የመርከቡን ክዳን አንሥቶ ዙሪያውን ተመለከተ፣ ምድሪቱም እንደደረቀች አየ።
\v 14 በሁለተኛው ወር፣ በሃያ ሰባተኛው ቀን ምድሪቱ ሙሉ በሙሉ ደረቀች።
\s5
\v 15 ከዚያም እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው።
\v 16 “አንተና ሚስትህ፣ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ከመርከቧ ውጡ።
\v 17 እንዲዋለዱ፣ እንዲራቡና በምድር ላይ እንዲበዙ ከአንተ ጋር ያሉትን ወፎች፣ እንስሳትና በምድር ላይ የሚሳቡ ሕያዋን ፍጡራንን ሁሉ ይዘሃቸው ውጣ።”
\s5
\v 18 ስለዚህ ኖኅ ከልጆቹ፣ ከሚስቱና ከልጆቹ ሚስቶች ጋር ወጣ።
\v 19 እንስሳቱ ሁሉ፣ ወፎችም፣ በምድር የሚሳቡት፣ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው ከመርከቧ ወጡ።
\s5
\v 20 ኖኅም ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ። ንፁሕ ከሆኑት እንስሳትና ንፁሕ ከሆኑት ወፎች አንዳንዶቹን ወስዶ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
\v 21 እግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን መዓዛ አሸተተ፣ በልቡም እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ሰው ገና ከልጅነቱ ጀምሮ ሐሳቡ ወደ ክፋት ያዘነበለ ቢሆንም በእርሱ ምክንያት ሁለተኛ ምድርን አልረግማትም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕያዋን ፍጡራንን ዳግመኛ አላጠፋም።
\v 22 ምድር እስካለች ድረስ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ፣ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት አይቋረጡም።”
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን እንዲህ ሲል ባረካቸው፦ “ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት፤
\v 2 አስፈሪነታችሁና አስደንጋጭነታችሁ በእንስሳት፣ በሰማይ ወፎች፣ በደረት በሚሳቡ ተንቀሳቃሽ ፍጡሮችና በባሕር ዓሦች፣ በምድር ላይ በሚገኙ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ላይ ይሁን። ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።
\s5
\v 3 ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፣ ለምለሙን ዕፅዋት እንደሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ።
\v 4 ነገር ግን ሕይወቱ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።
\s5
\v 5 ሰውን የገደለ ሁሉ ስለሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ።
\v 6 የሰውን ደም የሚያፈስ ሁሉ ደሙ በሰው እጅ ይፈሳል፤ በእግዚአብሔር አምሳል እግዚአብሔር ሰውን ሠርቶታልና።
\v 7 እናንተ ግን ብዙ ተባዙ፣ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ ይንሠራፋም።”
\s5
\v 8 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ለኖኅና ለልጆቹ እንዲህ አላቸው፦
\v 9 “እነሆ ከእናንተና ከእናንተ በኋላ ከሚመጣው ዘራችሁ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤
\v 10 እንዲሁም ከእናንተ ጋር ከነበሩት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ከወፎች፣ ከእንስሳት ከእናንተ ጋር ከመርከቧ ከወጡት በምድር ላይ ካሉት ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር ኪዳን እገባለሁ።
\s5
\v 11 ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋር ኪዳን እገባለሁ።”
\v 12 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “በእኔና በእናንተ መካከል ከእናንተም ጋር ካሉ ሕያዋን ፍጡራን ሁሉ፣ ከሚመጣው ትውልድ ሁሉ ጋር፣ የማደርገው የኪዳኑ ምልክት ይህ ነው፤
\v 13 ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አድርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል።
\s5
\v 14 ደመናን በምድር ላይ በጋረድሁና ቀስቴም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ
\v 15 ከእናንተና ከሕያዋን ፍጡራን ሁሉ ጋር የገባሁትን ኪዳን አስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም።
\s5
\v 16 ቀስቱ በደመና ላይ ተገልጦ በማይበት ጊዜ ሁሉ በእኔና በምድር ላይ ባሉ ሕያዋን ፍጡራን መካከል ያለውን ዘላለማዊ ኪዳን አስባለሁ።”
\v 17 ከዚያ በኋላም እግዚአብሔር ለኖኅ፦ “ይህ በእኔና በምድር ላይ በሚኖሩ ሕያዋን ሁሉ መካከል የገባሁት ኪዳን ምልክት ነው።” አለው።
\s5
\v 18 ከመርከቧ የወጡትም የኖኅ ልጆች ሴም፣ ካምና ያፌት ነበር፤ ካም የከነዓን አባት ነው።
\v 19 እነዚህ ሶስቱ የኖኅ ልጆች ሲሆኑ፣ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከነዚሁ ነው።
\s5
\v 20 ኖኅ ገበሬ መሆን ጀመረ፣ ወይንንም ተከለ።
\v 21 ከወይኑም ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ እርቃኑን ተኛ።
\s5
\v 22 የከንዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።
\v 23 ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በትከሻቸው ላይ አደረጉና የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ እንዳያዩ ፊታቸውን አዙረው የኋሊት በመሄድ የአባታቸውን ዕርቃነ ሥጋ ሸፈኑ።
\s5
\v 24 ኖኅ ከወይን ጠጁ ስካር ሲነቃ ታናሽ ልጁ ያደረገበትን አወቀ።
\v 25 ከዚህም የተነሣ፦ “ከነዓን የተረገመ ይሁን፤ ለወንድሞቹም አገልጋይ ይሁን።” አለ።
\s5
\v 26 ደግሞም፦ “የሴም አምላክ የሆነው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፣ ከነዓንም የሴም አገልጋይ ይሁን።
\v 27 እግዚአብሔር የያፌትን ግዛት ያስፋ፤ ያፌት በሴም ድንኳኖች ይኑር፤ ከነዓን የያፌት አገልጋይ ይሁን።” አለ።
\s5
\v 28 ኖኅ ከጥፋት ውሃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ።
\v 29 ኖኅ በአጠቃላይ 950 ዓመት ኖሮ ሞተ።
\s5
\c 10
\p
\v 1 የኖኅ ልጆች የሴም፣ የካምና የያፌት ዝርያዎች የሚከተሉት ናቸው። ከጥፋት ውሃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው።
\s5
\v 2 የያፌት ልጆች፦ ጋሜር፣ ማጎግ፣ ማዴ፣ ያዋን፣ ቶቤል፣ ሞሳሕና ቴራስ ነበሩ።
\v 3 የጋሜር ልጆች፦ አስከናዝ፣ ሪፋትና ቴርጋማ ነበሩ።
\v 4 የያዋን ልጆች፦ ኤሊሳ፣ ተርሴስ፣ ኪቲምና ሮዳኢ ነበሩ።
\v 5 ከእነዚህም በየነገዳቸው በየጎሳቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ።
\s5
\v 6 የካም ልጆች፦ ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥና ከነዓን ነበሩ።
\v 7 የኩሽ ልጆች፦ ሳባ፣ ኤውላጥ፣ ሰብታ፣ ራዕማና ሰበቀታ ነበሩ። የራዕማ ልጆች፦ ሳባና ድዳን ነበሩ።
\s5
\v 8 ኩሽ በምድር ላይ የመጀመሪያው ታላቅ ጦረኛ የነበረው የናምሩድ አባት ነበር።
\v 9 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ አዳኝ ነበር። ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ አዳኝ” ይባል ነበር።
\v 10 የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች በሰናዖር ምድር የነበሩት፡- ባቢሎን፣ አሬክ፣ አርካድና ካልኔ ነበሩ።
\s5
\v 11 ከዚያም ወደ አሦር ምድር ሄደና ነነዌን፣ ርሆቦትን፣ ካላሕን
\v 12 እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከል የነበረውን ታላቅ ከተማ ሬሴን የተባሉትን ከተሞች መሠረተ።
\v 13 ምጽራይም የሎዳማውያን፣የዐናሚማውያን፣ የላህሚማውያን፣ የነፍታሌማውያን፣
\v 14 የፈተሩሲማውያንና ፍልስጥኤማውያን የተገኙባቸው የካስሎሂማውያንና የቀፍቶርማውያን አባት ነበር።
\s5
\v 15 የከነዓንም የበኩር ልጅ ሲዶን ተከታዩም ሔት ይባሉ ነበር።
\v 16 ሌሎቹም የከነዓን ዝርያዎች ኢያቡሳውያን፣ አሞራውያን፣ ጌርጌሳውያን፣
\v 17 ኤውያውያንን፣ ዓርቃውያን፣ ሲናውያን፣
\v 18 ኤርዋዳውያን፣ አርዋዳውያን፣ ደማራውያን፣ ሐማታውያን የሚባሉ ነበሩ። ከጊዜ በኋላ የከነዓን ጎሣዎች በየስፍራው ተሠራጩ።
\s5
\v 19 የከነዓን ወሰን ከሲዶና አንሥቶ በጌራራ በኩል ገሞራን አዳማንና ሰቦይን ይዞ እስከ ላሣ ይዘልቃል።
\v 20 እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የካም ዝርያዎች ነበሩ።
\s5
\v 21 ለያፌት ታላቅ ወንድም ለሴም ደግሞ ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነበር።
\v 22 የሴም ልጆች ኤላም፣ አሦር፣ አርፋክስድ፣ ሉድ፣ አራም ነበሩ።
\v 23 የአራም ልጆች ዑፅ፣ ሁል፣ ጌቴር፣ ሞሶሕ ነበሩ።
\s5
\v 24 አርፋክስድ ሳላን ወለደ፤ ሳላም ኤቦርን ወለደ።
\v 25 ዔቦርም ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ። በዘመኑ ምድር ተከፍላ ስለነበር የአንደኛው ልጅ ስም ፍሌቅ ተባለ፤ ወንድሙም ዮቅጣን ተባለ።
\s5
\v 26 ዮቅጣንም የአልሞዳድ፣ የሼሌፍ፥ የሐጸርማዌት፣ የዮራሕ፣
\v 27 የዐዶራም፣ የኢዛል፣ የዲቅላ፣
\v 28 የዖባል፣ የአቢማኤል፣ የሳባ፣
\v 29 የኦፊር፣ የሐዊላና የዮባብ አባት ነበር። እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ዝርያዎች ነበሩ።
\s5
\v 30 መኖርያ ስፍራቸውም በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ስፋር ይደርስ ነበር።
\v 31 እነዚህም በየጎሣቸውና በየቋንቋቸው በየምድራቸውና በየነገዳቸው ይኖሩ የነበሩ የሴም ዝርያዎች ነበሩ።
\s5
\v 32 የኖኅ ወንዶች ልጆች ጎሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነበር።
\s5
\c 11
\p
\v 1 በዚያ ዘመን መላው ዓለም የሚናገረውና የሚግባባው በአንድ ቋንቋ ነበር።
\v 2 ወደ ምሥራቅ ሲጓዙ፣ በሰናዖር አንድ ሜዳማ ቦታ አግኝተው በዚያ ሰፈሩ።
\s5
\v 3 እርስ በርሳቸውም፣ “ኑ፣ ጡብ እንሥራና እስከበቃው ድረስ በእሳት እንተኩሰው” ተባባሉ። በድንጋይ ፈንታ ጡብ ተጠቀሙ፤ ጡቡን እርስ በርስ ለማያያዝም ቅጥራን ተጠቀሙ።
\v 4 ከዚያም፣ “ለስማችን መጠሪያ እንዲሆን ጫፉ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ። ያንን ካላደረግን በምድር ሁሉ ፊት መበታተናችን ነው” አሉ።
\s5
\v 5 የአዳም ልጆች የሠሩትን ለማየት ያህዌ ወደ ከተማውና ወደ ግንቡ ወረደ።
\v 6 ያህዌም፣ “አንድ ቋንቋ የሚናገሩ አንድ ሕዝብ በመሆናቸው ይህን ማድረግ ችለዋል! ከእንግዲህ ማድረግ የፈለጉትን ለማድረግ ምንም የሚያቅታቸው አይኖርም።
\v 7 ኑ እንውረድ፤ አርስ በርስ እንዳይግባቡም ቋንቋቸውን እንደበላልቀው” አለ።
\s5
\v 8 ስለዚህ ያህዌ ከዚያ ቦታ ወደ መላው ዓለም በታተናቸው፣ እነርሱም ከተማዋን መሥራት አቋረጡ።
\v 9 በዚያ የዓለምን ቋንቋ ስለ ደበላለቀ የከተማዋ ስም ባቤል ተባለ። ከዚያም ያህዌ በመላው ዓለም በተናቸው።
\s5
\v 10 የሴም ትውልድ ይህ ነው። የጥፋት ውሃ ከመጣ ሁለት ዓመት በኋላ ሴም መቶ ዓመት ሲሆነው አርፋድሰድን ወለደ።
\v 11 አርፋድሰድን ከወለደ በኋላ ሴም አምስት መቶ ዓመት ኖረ። ሌሎች ወንዶች እና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
\s5
\v 12 አርፋክሰድ በሰለሣ አምስት ዓመቱ ሰላን ወለደ፤
\v 13 ሰላን ከወለደ በኋላ አርፋክሰድ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ እርሱም ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 14 ሳላ ሰላሣ ዓመት ሲሆነው ዔቦርን ወለደ፤
\v 15 ዔቦርን ከወለደ በኋላ ሳላ አራት መቶ ሦስት ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
\s5
\v 16 ዔቦር አራት ዓመት ሲሆነው ፋሌቅን ወለደ፤
\v 17 ፋሌቅን ከወለደ በኋላ ዔቦር አራት መቶ ሰላሣ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 18 ፋሌቅ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ራግውን ወለደ፤
\v 19 ራግውን ከወለደ በኋላ ፋሌቅ ሁለት መቶ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 20 ራግው ሰለሣ ሁለት ዓመት ሲሆነው፣ ሴሮሕን ወለደ፤
\v 21 ሴሮሕን ከወለደ በኋላ ራግው ሁለት ሞት ሰባት ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 22 ሴሮሕ ሰለሣ ዓመት ሲሆነው፣ ናኮርን ወለደ፤
\v 23 ናኮርን ከወለደ በኋላ ሴሮሕ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።
\s5
\v 24 ናኮር ሃያ ዘጠኝ ዓመት ሲሆነው ታራን ወለደ፤
\v 25 ታራን ከወለደ በኋላ ናኮር አንድ መቶ አሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ፤ እርሱም እንዲሁ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ።
\v 26 ታራ ሰባ ዓመት ሲሆነው አብራምን፣ ናኮርንና ሐራንን ወለደ።
\s5
\v 27 የታራ ትውልድ ይህ ነው። ታራ፣ አብራምን፣ ናኮርንና ሐራን ወለደ። ሐራን ሎጥን ወለደ።
\v 28 ሐራን አባቱ ታራ በሕይወት እያለ በተወለደበት ከተማ በከለዳውያን ዑር ሞተ።
\s5
\v 29 አብራምና ናኮር ሁለቱም ሚስት አገቡ። የአብራም ሚስት ሦራ ስትባል፣ የናኮር ሚስት ደግሞ ሚልካ ትባል ነበር፤ ሚልካ የሐራን ልጅ ስትሆን፣ ሐራን የሚልካና የዮሳካ አባት ነበር።
\v 30 ሦራ ምንም ልጅ ያልነበራት መካን ነበረች።
\s5
\v 31 ታራ ልጁ አብራምን፣ የልጅ ልጁን ሎጥንና የአብራምን ሚስት ምራቱን ሦራን ይዞ ወደ ከነዓን ለመሄድ በከለዳውያን ምድር ከምትገኘው ዑር አብረው ወጡ። ሆኖም፣ ካራን በደረሱ ጊዜ በዚያ ተቀመጡ።
\v 32 ታራ ሁለት መቶ አምስት ዓመት ኖሮ በካራን ሞተ።
\s5
\c 12
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን፣ ወገንህንና የአባትህን ቤተ ሰብ ትተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ፤
\v 2 ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎችም በረከት አደርግሃለሁ።
\v 3 የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህንና የሚያዋርዱህን እረግማለሁ። በአንተ አማካይነት በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ይባረካሉ።”
\s5
\v 4 ስለዚህ አብራም ያህዌ እንዳዘዘው ወጣ፤ ሎጥም አብሮት ሄደ። አብራም ከካራን ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሰባ አምስት ዓመት ሰው ነበር።
\v 5 አብራም ሚስቱ ሦራን፣ የውንድሙ ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዞ በመጓዝ፣ ከነዓን ምድር ገቡ።
\s5
\v 6 አብራም በሞሬ ያለው ግዙፍ የወርካ ዛፍ እስካለበት እስከ ሴኬም ዘልቆ ሄደ። በዚያ ዘመን ከነሻናውያን በዚህ ምድር ይኖሩ ነበር።
\v 7 ያህዌ ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። ስለዚህ አብራም ለተገለጠለት ለያህዌ በዚያ መሠዊያ ሠራ።
\s5
\v 8 ከዚያ በመነሣት ከቤቴል በስተ ምሥራቅ ወዳለው ተራራማ አገር ሄደ፤ ቤቴል በስተ ምዕራብ፣ ጋይ በስተ ምዕራብ ባለችበት ቦታ ድንኳኑን ተከለ። እዚያ ለያህዌ መሠዊያ ሠራ፤ የያህዌንም ስም ጠርቶ ጸለየ።
\v 9 አብራም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ መጓዙን ቀጠለ።
\s5
\v 10 በዚያ ምድር ጽኑ ራብ ስለ ነበር አብራም እዚያ ጥቂት ጊዜ ለመቆየት ወደ ግብፅ ሄደ።
\v 11 ግብፅ በመግባት ላይ እያለ አብራም ሚስቱ ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ቆንጆ ሴት መሆንሽን አውቃለሁ።
\v 12 ግብፃውያን ሲያዩሽ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ይላሉ፤ እኔን ይገድሉኛል፤ አንቺን ግን ይተዉሻል።
\v 13 ስለዚህ በአንቺ ምክንያት ለእኔ መልካም እንዲሆልኝ ሕይወቴም እንዲተርፍ እኅቱ ነኝ’ በዪ አላት።
\s5
\v 14 አብራም ወደ ግብፅ ሲገባ፣ ሦራ ምን ያህል ቆንጆ እንደ ሆነች ግብፃውያኑ አዩ።
\v 15 የፈርሾን ሹማምንት ባዩአት ጊዜ እርሷን እያደነቁ ለፈርዖን ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ተወሰደች።
\v 16 በእርሷ ምክንያት ፈርኦን አብራምን በክብር አስተናገደው፤ በጎች፣ በሬዎች፣ ወንድ አህዮች ወንድና ሴት ባሪያዎች፣ ሴት አህዮችና ግመሎች ሰጠው።
\s5
\v 17 በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ያህዌ ፈርዖንና ቤተ ሰቡን በታላቅ መቅሠፍት መታ።
\v 18 ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ለመሆኑ ምን እያደረግህብኝ ነው? ሚስትህ መሆንዋን ለምን አልነገርከኝም?
\v 19 ለምን እኅቴ ናት አልከኝ? እኅቴ ናት ስላልከኝ ሚስቴ ላደርጋት ነበር። አሁንም ሚስትህ እቻት፤ ይዘሃት ሂድ”
\v 20 ከዚያም ፈርዖን አብራምን በተመለከተ ለባለሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋር አሰናበቱት።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ስለዚህ አብራም ሚስቱንና ያለውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከግብፅ ወደ ኔጌብ ሄደ። ሎጥም ከእነርሱ ጋር ነበረ።
\v 2 በዚህ ጊዜ አብራም በከብት፣ በብርና በወርቅ በልጽጎ ነበር።
\s5
\v 3 ከኔጌብ ተነሥቶ እስከ ቤቴል ተጓዘ፤ ቀድሞ ድንኳን ተክሎበት ወደ ነበረው በቤቴልና በጋይ መካከል ወደ ነበረው ቦታ ደረሰ።
\v 4 ይህ ቀድሞ መሠዊያ የሠራበት ቦታ ሲሆን በዚያ ያህዌን ጠራ።
\s5
\v 5 ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥ የራሱ በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት።
\v 6 ሁለቱ አንድ ላይ ይኖሩ ስለ ነበር ስፍራው አልበቃቸውም፤ በዚህ ላይ ንብረታቸውም በጣም ብዙ ስለ ነበር አብረው መኖር አልቻሉም።
\v 7 ይህም በመሆኑ በአብራምና በሎጥ እረኞች መካከል ጠብ ተፈጠረ። በዚያ ዘመን ከነኣናውያንና ፌርዛውያን በዚያው አገር ይኖሩ ነበር።
\s5
\v 8 አብራም ሎጥን እንዲህ አልው፤ “በእኔና በአንተ፣ በእኔ እረኞችና በአንተ እረኞች መካከል ግጭት መኖር የለበትም፤ በዚህ ላይ ደግሞ ቤተ ሰብ ነን።
\v 9 ይኸው እንደምታየው ምድሩ ሰፊ ነው፤ ብንለያይ ይሻላል። አንተ ግራውን ብትመርጥ፣ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ ወይም አንተ ቀኙን ብትመርጥ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።
\s5
\v 10 ስለዚህ ሎጥ ዙሪያውን ሲመለከት እስከ ዞዓር ድረስ ያለው የዮርዳኖስ ረባዳ ሜዳ ሁሉ እንደ ያህዌ ገነት እንደ የግብፅ ምድር በጣም ለም ሆኖ አገኘው። እንዲህ የነበረው እግዚአብሔር ሰዶምና ገሞራን ከማጥፋቱ በፊት ነበር።
\v 11 ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ ሁሉ መርቶ ወደ ምሥራቅ ተጓዘ፤ በዚህ ሁኔታ ዘመዳሞቹ ተለያዩ።
\s5
\v 12 አብራም መኖሪያውን በከነዓን ምድር አደረገ፤ ሎጥ ግን በረባዳው ሜዳ ባሉት ከተሞች መካከል ኖረ። እስከ ሰዶም ድረስ ባለው ቦታ ድንኳኖቹን ተከለ።
\v 13 የሰዶም ሰዎች በጣም ዐመፀኞችና በያህዌም ፊት እጅግ ኀጢአተኞች ነበሩ።
\s5
\v 14 ሎጥ ከእርሱ ከተለየው በኋላ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ካለህበት ቦታ ወደ ሰሜን፣ ወደ ደቡብ፣ ወደ ምሥራቅና ምዕራብ ተመልከት።
\v 15 ይህን የምታየውን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁ።
\s5
\v 16 ዘርህን እንደ ምድር ትቢያ አበዛዋለሁ፤ የምድር ትቢያ ሊቆጠር እንደማይቻል ሁሉ የአንተም ዘር ሊቆጠር አይችልም።
\v 17 እንግዲህ ምድሪቱን ስለምስጥህ ተነሣና በርዝመትና በስፋቱ ተመላለሰባት።”
\v 18 ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቀለና በኬብሮን ወዳሉት የመምሬ ወርካ ዛፎች መጥቶ ኖረ፤ እዚያም ለያህዌ መሠዊያ ሠራ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 አምራፌል የሰናዖር ንጉሥ፣ አርዮክ የአላሳር ንጉሥ፣ ከሎደጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ተድዓል የጎይም ንጉሥ፣
\v 2 በነበሩበት ዘመን፤ ከሰዶም ንጉሥ በላ፣ ከጎሞራ ንጉሥ ከብርሳ፣ ከአዳማ ንጉሥ ከሰነአብ፣ ከሰቦይ ንጉሥ ከሰሜበር፣ እንዲሁም ዞዓር ከተባለች ከቤላ ንጉሥ ጋር ለመዋጋት ወጡ።
\s5
\v 3 እነዚህ የኋለኞቹ አምስት ነገሥታት የጨው ባሕር እየተባለች በምትጠራው በሲዶም ሸለቆ ተሰበሰቡ።
\v 4 እነርሱም አሥራ ሁለት ዓመት ለኮሎዶጎምር ተገዙ፤ በአሥራ ሦስተኛው ዓመት ግን ዐመፁ።
\v 5 በአሥራ አራተኛው ዓመት ከሎዶጎምርና ከእርሱም ጋር የነበሩት ነገሥታት መጥተው ራፋይምን፣ በአስታሮት ቃርናይምን፣ በካም ዙዚምን፣ በሴዊ ኑሚምን፣ በሸቮት ኢምንን፣
\v 6 የሖር ሰዎችንም በተራራማው አገር በሴይ በረሐማ አጠገብ እስካለው እስከ አልፋራን ድረስ ድል አደረጋቸው።
\s5
\v 7 ከዚያም ተመልሰው ዓይንሚስፓጥ ወደሚባለው ወደ ቃዴስ መጡ፤ የአማሌዋውያንና በሐሴስ ታማር ይኖሩ የነበሩትን የአሞራውያን ግዛት በሙሉ ድል አድርገው ያዙ።
\v 8 ከዚያም የሶዶም፣ የገሞራ፣ የአዳማ፣ የሰቦይ እንዲሁም ዞዓር የተባለችው የቤላ ነገሥታት ወደ ሲዶም ሸለቆ ሄደው ለጦርነት ተዘጋጁ።
\v 9 እነዚህ አምስቱ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉስ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በአላሶር ንጉሥ በአርዮክ በእነዚህ ላይ ዘመቱባቸው።
\s5
\v 10 በሲዲም ሸለቆ ብዙ የቅጥራን ጉድጓዶች ነበሩ፤ የሰዶምና የጎመራ ነገሥታት ሲሸሹ ከሰዎቻቸው አንዳንዶቹ በእነዚህ ጉድጓዶች ውስጥ ወደቁ። የተረፉትም ወደ ተራሮች ሸሹ።
\v 11 አራቱ ነገሥታትም በሰዶምና በጎሞራ ያገኙትን ሀብትና ምግብ ሁሉ ዘርፈው ሄዱ።
\v 12 በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብርሃምን ወንድም ልጅ ሎጥንና የነበረውን ንብረት ሁሉ ይዘው ሄዱ።
\s5
\v 13 ከዚያ ያመለጠ አንድ ሰው መጥቶ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው። በዚያ ጊዜ ይኖር የነበረው የአስኮና የእውናን ወንድም በነበረው በአሞራዊው መምሬ ዋርካ ዛፎች አጠገብ ነበር፤ እነዚህ ሁሉ የአብራም አጋሮች ነበር።
\v 14 ጠላት ዘመዶቹን ማርኮ መውሰዱን አብራም ሲሰማ በቤቱ ተወልደው ያደጉ ሦስት መቶ አሥራ ስምንት ሰዎች ይዞ እስከ ዳን ድረስ ተከታተሏቸው።
\s5
\v 15 አብራም ጠላቶቹን ለማጥቃት ሰራዊቱን ሌሊቱን በቡድን በቡድን ከፋፍሎ ከደማስቆ በስተ ሰሜን እስከሚገኘው እስከ ሖባ ድረስ አሳደዳቸው።
\v 16 ጠላት የማረከውን በሙሉ አስጣለ፤ ዘመዱ ሎጥንና ንብረቱን፣ እንዲሁም ሴቶቹንና ሌሎች ሰዎችን አስመለሰ።
\s5
\v 17 አብራም የኮሎዶጎምርንና ከእርሱ ጋር የነበሩ ነገሥታትን ድል አድርጎ ሲመለስ የሰዶም ንጉሥ የንጉሥ ሸለቆ ተብሎ በሚጠራው በሴዊ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ።
\v 18 የሰሌም ንጉሥ መልከጼዴቅ እንጀራና ወይን ጠጅ ይዞ መጣ። እርሱ የልዑል አምላክ ካህን ነበር።
\s5
\v 19 አብራምም እንዲህ በማለት ባረከው፣ “ሰማይና ምድርን የፈጠረ ልዑል እግዚአብሔር አብራምን ይባርክ።
\v 20 ጠላቶችህን በእጅህ አሳልፎ የሰጠ ልዑል እግዚአብሔር ይባረክ።” አብራምም ይዞት ከነበረው ሁሉ አንድ አሥረኛውን ሰጠው።
\s5
\v 21 የሰዶም ንጉሥ አብራምን፣ “ሰዎቹን ለእኔ ስጠኝ፤ ንብረቱን ግን ለራስህ አስቀር” አለው።
\v 22 አብራምም ለሰዶም ንጉሥ እንዲህ አለው፤ “ከአንተ ብጣሽ ክርም ሆነ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ቢሆን፣
\v 23 ደግሞም ‘አብራምን ባለጸጋ አደረግሁት’ እንዳትል የአንተ ከሆነ ምንም ነገር እንዳልወስድ ሰማይና ምድርን ወደ ፈጠረ አምላክ ወደ ያህዌ እጄን አንሥቻለሁ።
\v 24 አብረውኝ ያሉት ሰዎች ከበሉትና የእነርሱ ድርሻ ከሆነው በቀር ምንም ነገር አልወስድም። አውናን፣ ኤስኩልና መምሬ ድርሻቸውን ይውሰዱ።”
\s5
\c 15
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፣ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ሽልማትህም እኔው ነን።”
\v 2 አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እኔ ልጅ የለኝም፤ የቤት ወራሽ የሚሆነው የደማስቆው ሰው ኤሊዔዘር ነው፤ ታዲያ አንተ ለእኔ የምትሰጠኝ ምንድን ነው? ” አለ።
\v 3 በመቀጠልም አብራም “አንተ ልጅ እስካልሰጠኸኝ ድረስ፣ ከቤቴ አገልጋይ አንዱ ወራሼ መሆኑ አይቀርም” አለ።
\s5
\v 4 በዚህ ጊዜ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እርሱ መጣ፤ “ይህ ሰው ወራሽህ አይሆንም፤ ይልቁንም ወራሽህ የሚሆነው ከአብራክህ የሚከፈል የራስህ ልጅ ይሆናል።”
\v 5 ከዚያም ወደ ውጭ አወጣውና እንዲህ አለው፤ “ቀና ብለህ ወደ ሰማይ ተመልከት፤ መቍጠር ከቻልህ ከዋክብቱን ቍጠር። ዘርህም እንዲሁ ይበዛል።”
\s5
\v 6 አብራም ያህዌን አመነ፤ እርሱም ጽድቅ አድርጎ ቆጠረለት።
\v 7 እንዲህም አለው፤ “ይህችን ምድር እንድትወርስ ልሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ከዑር ያወጣሁህ እኔ ያህዌ ነኝ።”
\v 8 አብራምም፣ “ጌታ ያህዌ ሆይ፣ ይህችን ምድር እንደምወርስ እንዴት አውቃለሁ? ” አለ።
\s5
\v 9 በዚህ ጊዜ፣ “እያንዳንዳቸው ሦስት ዓመት የሆናቸው አንዲት ጊደር፣ አንዲት ፍየልና አንድ በግ እንዲሁም ዋኖስና አንድ ርግብ አቅርብልኝ” አለው።
\v 10 እርሱም እነዚህን ሁሉ አቀረበለት፤ ቆርጦም ሁለት ቦታ ከከፈላቸው በኋላ እያንዳንዱን ክፍል በሌላው ወገን ትይዩ አስቀመጣቸው፤ ወፎቹን ግን አልከፈላቸውም።
\v 11 አሞሮች ሥጋውን ለመብላት ወረዱ፤ አብራምም አባረራቸው።
\s5
\v 12 ፀሓይ ልትጠልቅ ስትል አብራም ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ የሚያስፈራም ድቅድቅ ጨለማም መጣበት።
\v 13 በዚህ ጊዜ ያህዌ አብራምን እንዲህ አለው፤ “ዘሮችህ የራሳቸው ባልሆነ ምድር ባዕድ እንደሚሆኑና እዚያ ለአራቶ መቶ ዓመት በባርነት እንደሚኖሩ በእርግጥ ዕወቅ።
\s5
\v 14 እኔም ባሪያዎች ባደረጓቸው ሕዝብ እፈርዳለሁ፤ በኋላም ብዙ ሀብት ይዘው ይወጣሉ።
\v 15 አንተ ግን በሰላም ወደ አባቶችህ ትሄዳለህ፤ ዕድሜም ጠግበህ ትቀበራለህ።
\v 16 በአራተኛውም ትውልድ እንደ ገና ወደዚህ ይመጣሉ፤ ምክንያቱም የአሞራውያን ኀጢአት ጽዋው ገና አልሞላም።”
\s5
\v 17 ፀሓይ ገብታ ከጨለመ በኋላ የምድጃ ጢስና የሚንበለበል ፋና በተቆራረጡት ሥጋዎች መካከል አለፈ።
\v 18 በዚያን ቀን ያህዌ እንዲህ በማለት ከአብራም ጋር ኪዳን አደረገ፤ “ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤
\v 19 የምሰጣቸውም የቄናውያንን፣ የቄንፌዛውያንን፣ የቃድሞናውያንን፣
\v 20 የኬጢያውያንን፣ የፌርዛውያንን፣ የራፋይምን፣
\v 21 የአሞራውያንን፣ የከነዓናውያን፣ የጌርሳውያንንና የኢያቡሳውያን ምድር ነው።”
\s5
\c 16
\p
\v 1 የአብራም ሚስት ሦራ ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል ግብፃዊት አገልጋይ ነበረቻት።
\v 2 አብራምንም፣ "ያህዌ ልጅ እንዳልወደልድ አድርጎኛል። ምናልባት በእርሷ በኩል ልጅ አገኝ ይሆናልና ክአገልጋዬ ጋር ተኛ" አለችው። አብራም ሦራ በነገረችው ተስማማ።
\v 3 የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት አገልጋይዋ ሚስት እንድትሆነው ለአብራም የሰጠችው አብራም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከኖረ በኋላ ነበር።
\v 4 አብራም ክአጋር ግን'ኡንት አደረገ እርሷም ፀነሰች። አጋር መፅነሷን ባወቀች ጊዜ እመቤቷን በንቀት ማየት ጀመረች።
\s5
\v 5 በዚህ ጊዜ ሦራ አብራምን፣ "ይህ በደል የደረሰብኝ በአንተ ምክንያት ነው። ኅቅፍህ ውስጥ እንድትሆን አገልጋዬን ሰጠሁ፤ እርሷ ግን መፅነሷን ስታውቅ እኔን መናቅ ጀመረች። ያህዌ በእኔና በአንተ መካከ ይፍረድ" አለችው።
\v 6 አብራምም መልሶ ሦራን፣ "አገልጋይሽ እኮ በእጅሽ ውስጥ ናት እርሷ ላይ የፈለግሽውን ማድረግ ትችያልለሽ" አላት። ስለዚህ ሦራ ስላሠቃየቻት፣ አጋር ከቤት ጠፍታ ሄደች።
\s5
\v 7 የያህዌ መልአክ አጋርን ምድረ በዳ ውስጥ በነበረ አንድ ምንጭ አጠገብ አገኛት፤ ያ ምንጭ ወደ ሱር በሚወስደው መንገድ ላይ ነበር።
\v 8 መልአኩም፣ "የሦራ አገልጋይ አጋር ሆይ፣ ከየት መጣሽ ወዴትስ እየሄድሽ ነው?" አላት። እርሷም፣ "ከእመቤቴ ከሦራ ኮብልዬ እየሄድሁ ነው" አለችው።
\s5
\v 9 የያህዌ መልአክ፣ "ወደ እመቤትሽ ተመለዒ፤ ራስሽንም ለሥልጣንዋ አስገዢ" አላት።
\v 10 ከዚያም የያህዌ መልአክ፣ "ዘርሽን እጅግ አበዛዋለሁ፤ ከበምዛቱም የተነሣ ሊቆጠር አይቻልም" አላት።
\s5
\v 11 የያህዌም መልአክ በተጨማሪ እንዲህ አላት፤ "እነሆ ፀንሰሻል ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ያህዌ ችግርሽን ሰምቷልና ስሙን እስማኤል ትዪዋለሽ።
\v 12 እርሱ እንደ ዱር አህያ ይሆናል። ከሰው ሁሉ ጋር ይጣላል፤ ሰው ሁሉም ከእርሱ ጋር ይጣላል፤ ከወንድሞቹ ሁሉ ተነጥሎ ይኖራል።"
\s5
\v 13 እርሷም ይሚያናግራትን ያህዌን፣ "አንተኮ እኔን የምታይ አምላክ ነህ"በማለት ጠራችው፤ ምክንያቱም፥ "እርሱ እኔን እንዳየ ሁሉ እኔም እርሱን አየው ይሆን?" ብላ ነበር።
\v 14 ስለዚህ ያ ምንጭ ብኤርልያህሮኢ ተባለ፤ የሚገኘው በቃዴስና በባሬድ መካከ ልነው።
\s5
\v 15 አጋር ለአብራም ወድን ልጅ ወለደችለው፤ አብራምም አጋር የወለደችለትን ልጅ እስማኤል ብሎ ጠራው።
\v 16 አጋር እስማኤልን በወለደች ጊዜ አብራም ሰማንያ ስድስት ዓመት ሆኖት ነበር።
\s5
\c 17
\p
\v 1 አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው እያለ ያህዌ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ "እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ ነቀፋም አይኑርብህ።
\v 2 በእኔና በአንተ መካከል የተደረገውን ኪዳን አጸናለሁ፤ አንተንም እጅግ አበዛሃለሁ።"
\s5
\v 3 አብራም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ እግዚአበሔርም እንዲ አለው፤
\v 4 "እነሆ ኪዳኔ ክአንተ ጋር ነው። የብዙ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።
\v 5 ከእንግዲህ ስምህ አብራም መባል የለበትም፤ ስምህ አብርሃም መባል እለበት፤ ምክንያቱም የብዙ ሕዝብ አባት አድርጌሃለሁ።
\v 6 እጅግ አበዛሃለሁ፣ ሕዝቦች ክአንተ ይገኛሉ፤ ነገሥታትም ክአንተ ይወጣሉ።
\s5
\v 7 በእኔና በአንተ፣ ክአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ ለአንተ ከአንተም በኋላ ለዘርህ በዘላለም ኪዳን አምላክ እሆናችኋለሁ።
\v 8 ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ይህች አሁን የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣላለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።"
\s5
\v 9 ከዚያም እግዚአብሔር አብርሃምን፣ "በአንተም በኩል፣ አንተና ከአንተ በኋላ የሚመጣው ዘርህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን መጠበቅ አለባችሁ።
\v 10 በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ በእኔና በዘርህ መካከል መጠበቅ ያለባችሁ ኪዳኔ ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ።
\v 11 እናንተ ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእናንተ መካከል ያለው ኪዳን ምልክት ይሆናል።
\s5
\v 12 በመካከላችሁ ያለው ማንኛውም ስምንት ዓመት የሞላው ወንድ የሚመጣው ትውልድ ሁሉ ይገረዝ። ይህ በቤትህ የተወለደውን በገንዘብህ የተገዛውን ሁሉ ይጨምራል።
\v 13 ቤትህ ውስጥ የተወለደና በገንዘብህ የገዛኸው መገረዝ አለባቸው። ስለሆነም ኪዳኔ በዘላለም ኪዳን ሥጋችሁ ላይ ይሆናል።
\v 14 ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን አፍርሷልና ከወገኖቹ ይወገድ።"
\s5
\v 15 እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ሚስትህ ሦራን ክአንግዲህ ሥራ እንጂ ሦራ ብለህ አትጥራት።
\v 16 እባርክሃለሁ፤ ከእርሷ ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ። እባርካታለሁ። እርሷም የብዙ ሕዝብ እናት ትሆናልች፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ክአርሷ ይወጣሉ።
\s5
\v 17 በዚህ ጊዜ አብርሃም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፍቶ እየሳቀ በሉ እንዲህ አለ፤ "ለመሆኑ የመቶ ዓመት ሽማግሌ ልጅ መውልደድ ይችላል? የዘጠና ዓመቷ አሮጊት ሥራስ ብትሆን ልጅ መውለድ ይሆንላታል?"
\v 18 አብርሃም እግዚአብሔርን፣ "ይልቅ፣ እስማኤልን ብቻ ባኖርህልኝ!" አለ።
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም፣ "እንደዚያ አይደለም፤ ሚስትህ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ። የዘላለም ኪዳኔን ከእርሱ ጋር፣ ከእርሱም በኋላ ከዘሩ ጋር እመጸርታለሁ።
\v 20 እስማኤልን በተመለከተም ልምናህን ሰምቻለሁ። እነሆ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ፍሬያማም አደርገዋለሁ፤ እጅግም አበዛዋለሁ። የአሥራ ሁለት ነገዶች አባት ይሆናል፤ ታላቅ ሕዝብ እንዲሆንም አደርጋለሁ።
\v 21 ኪዳኔን ግን፣ የዛሬ ዓመት በዚህ ጊዜ ሣራ ከምትወልድህል ከይስሐቅ ጋር እመሠርታለሁ።"
\s5
\v 22 ከእርሱ ጋር መነጋገሩን ከጨረሰ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ላይ ወጣ።
\v 23 በዚያኑ ዕለት አብርሃም ልጁ ይስሐቅን፣ በቤቱ ውስጥ የተወለዱትን በሙሉ፣ በገንዘቡ የገዛቸውን ሁሉ፣ ቤቱ ውስጥ ያለ ማንኛውንም ወንድ ሁሉ እግዚአብሔር በነገረው መሠረት ገረዛቸው።
\s5
\v 24 አብርሃም በተገረዘ ጊዜ እድሜው ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ነበር።
\v 25 ልጁም እስማኤል በተገረዘ ጊዜ እድሜው አሥራ ሦስት ነበር።
\v 26 በዚያው ቀን አብርሃምና ልጁ እስማኤልም ተገረዙ።
\v 27 ቤቱ ውስጥ የተወለዱትን፣ ከውጭ በገንዘብ የተገዙትን ጨምሮ ቤቱ ውስጥ የነበሩ ወንዶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ተገረዙ።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ቀኑ በጣም ሞቃት በሆነ ጊዜ አብርሃም በመምሬ ወርካ ዛፎች አቅራቢይ ኣድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ እያለ ያህዌ ተገለጥለት።
\v 2 እርሱም ቀና ብሎ ሦስት ሰዎች ፊት ለፊቱ ቆመው አየ። ባያቸውም ጊዜ ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ፈጥኖ ወደ እነርሱ ሄዶ፣ ወደ መሬት ዝቅ ብሎም እጅ ነሣ።
\s5
\v 3 አብርሃም እንዲህ አለ፤ "ጌታዬ፣ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ባሪያህን አልፈህ አትሂድ።
\v 4 ጥቂት ውሃ ትምጣላችሁና እግራችሁን ታጠቡ፤ ከዚያም ዛፉ ሥር ዐረፍ በሉ።
\v 5 ወደ እኔ ወዳገልጋያችሁ ከመጣችሁ የደከመ ሰውነታችሁ እንዲበረታ እስቲ ጥቂት እህል ላምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም. "እንዳልኸው አድርግ" አሉት።
\s5
\v 6 ያኔውኑ አብርሃም በፍጥነት ሣራ ወደ ነበረችበት ድንኳን ገብቶ፣ "ቶሎ ብለሽ ሦስት መስፈሪያ ስልቅ ዱቄት አቡኪና ቂጣ ጋግሪ" አላት።
\v 7 ከዚያም ወደ መንጋው በፍጥነት ሄዶ አንድ ፍርጥም ያለ ሥጋው ግን ገር የሆነ ጥጃ መረጠና ለአገልጋዩ ሰጠው፤ እርሱም በአስቸኳይ አደረሰው።
\v 8 አብርሃምም እግሮ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀበላቸው፤ እነርሱ እየበሉ እያለ እርሱ ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር።
\s5
\v 9 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ "ሚስትህ ሥራ የታለች?" እርሱም፣ "ድንኳን ውስጥ ናት" አለ።
\v 10 እነርሱም፣ "የዛሬ ዓመት በፀደይ ወቅት ልክ በዚሁ ጊዜ በእርግጥ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሥራ ልጅ ትወልዳለች" አለ። ሥራ ከጀርባ በነበረው ድንኳን ደጃፍ ሆና ታዳምጥ ነበር።
\s5
\v 11 በዚህ ጊዜ አብርሃምና ሥራ በጣም አርጅተው ነበር፤ ሥራማ ልጅ የመውለጃ ጊዜ አልፎባት ነበር።
\v 12 ስለዚህ ሣራ በልቧ፣ "ይህን ያህል ካረጀሁና ጌታዬም ከደከመ በኋላ በዚህ ነገር መደሰት ይሆንልኛልን?" ብላ ሳቀች።
\s5
\v 13 ያህዌ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ "ካረጀሁ በኋላ እንዴት አድርጌ ልጅ እወልዳለሁ ስትል ሣራ የሳቀችው ለምንድን ነው?
\v 14 ለመሆኑ ለያህዌ የሚሳነው ነገር አለ? እኔ በወሰንሁት የፀደይ ወቅት ወደ እናንተ እመለሳለህ፤ በሚመጣው ዓመት በዚህ ጊዜ ሥራ ወንድ ልጅ ትወልዳለች።"
\v 15 ሣራ ግን ፈርታ ስል ነበር፣ "ኧረ እልሳቅሁም" በማለት ካደች። እርሱም፣ "የለም፤ ስቀሻል እንጂ" አላት።
\s5
\v 16 ሰዎቹ ለመሄድ ሲነሡ ቁልቁል ወደ ሰዶም ተመለከቱ። አብርሃምም ሊሸኛቸው ከእነርሱ ጋር ሄደ።
\v 17 በዚህ ጊዜ ያህዌ እንዲህ አለ፤ "እኔ የማደርገውን ክአብርሃም መደበቅ አለብኝን?
\v 18 አብርሃም በእርግጥ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይህሆናል፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉ።
\v 19 ትክክለኛና ቀና የሆነውን በማድረግ የያህዌን መንገድ እንዲጠብቁ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤተ ሰቡን እንዲያስተምር እኔ አብርሃምን መርጬዋለሁ፤ ይኸውም ለአብርሃም የነገረውን ሁሉ ያህዌ እንዲፈጽምለት ነው።"
\s5
\v 20 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ "በሰዶምና በገሞራ ላይ የሚሰማው ክስ በጣም ስለ በዛ፣ ኀጢአታቸውም በጣም ትልቅ ስል ሆነ፤
\v 21 ወደ እኔ የመጡ ክሶች ምን ያህል እውነት መሆናቸውን ለማየት ወደዚያ እወርዳለሁ፤ እንደዚይ ካልሆነም አውቃለሁ።"
\s5
\v 22 ሰዎቹም ፊታቸውን ወደ ሰዶም አቅንተው ሄዱ፤ አብርሃም ግን ያህዌ ፊት እንደ ቆመ ነበር።
\v 23 አብርሃም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ፣ "በእርግጥ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር ታጠፋለህን?
\s5
\v 24 ምናልባት በከተማዋ ሃምሳ ጻድቃን ቢገኙስ? እዚያ ባሉ ጻድቃን ስትል ከተማዋን ሳታድን ታጠፋታለህን?
\v 25 ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋር በመግደል፣ ኀጢአተኛ ላይ የደረሰው በእርሱም እንዲደርስ ማድረግን የመሰለ ንገር ከአንተ ይራቅ! እንዲህ ያለው ከአንተ ይራቅ! የምድር ሁሉ ዳኛ እውነተኛ ጻድቅ የሆነውን አያደርግምን?
\v 26 ያህዌም እንዲህ አለ፤ "በሰዶም ከተማ ውስጥ ሃምሳ ጻድቃን ካገኘሁ ፣ ለእነርሱ ስል ያንን ቦታ እምራለሁ።"
\s5
\v 27 አብርሃምም መልሶ እንዲህ አለ፤ "እኔ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታዬ ጋር ለመናገር አንዴ ደፍሬአለሁ፤
\v 28 ለመሆኑ ከአምሳዎቹ ጻድቃን አምስት ቢጎድሉ፣ በጎደሉት አምስቱ ምክንያት ከተማዋን በሙሉ ታጠፋለህን?" እርሱም፣ "እዚያ አርባ አምስ ጻድቃንካገኘሁ አላጠፋትም" አለ።
\s5
\v 29 አብርሃምም እንደ ገና፣ "ምናልባት አርባ ጻድቃን ቢገኙስ?" እለ፤ እርሱም፣ "ለአርባዎቹ ስል አላደርገውም" እለ።
\v 30 አብርሃምም፣ "እባክህን ጌታዬ ይህን ያህል በመናገሬ አትቆጣኝ። እንደው ምናልባት ሰለሣ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፣ "ሰላሣ ጻድቃን ካገኘሁ አላደርገውም" በማለት መለሰ።
\v 31 አብርሃምም፣ "መቼም አንዴ ከጌታዬ ጋር መናገር ጀምሬአለሁ! እንደው ምናልባት ሃያ ቢገኙስ" አለ። እርሱም መልሶ፥ "ለሃያዎቹ ስል አላደርገውም" አለ።
\s5
\v 32 በመጨረሻም እንዲህ አለ፤ "እባክህ ጌታዬ አትቆጣኝ፤ አንዴ ብቻ ልናገር፤ ምናልባት አሥር ቢገኙስ። እርሱም፣ "ለአሥሩ፣ ሲል አላጠፋትም" አለ።
\v 33 ከአብርሃም ጋር መነጋገሩን እንደ ጨረሰ ያህዌ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ቤቱ ተመለሰ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ወደ ሰዶም መጡ፤ በሰዶም ከተማ መግቢያበር ላይ ተቀምጦ ነበር። ሎጥ ሲያያቸው ሊቀበላቸው ተነሣ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።
\v 2 እርሱም፣ "እባካችሁ ጌቶቼ ወደ እኔ ወደ ባሪያችሁ ቤት ጎራ በሉ፤ እግራችሁን ታጠቡ፤ ሌሊቱንም ከእኛ ጋር አሳልፉ፤ ከዚያ ጧት በማለዳ ተነሥታችሁ ጕዞአችሁን ትቀጥላላችሁ።" እነርሱም፣ "የለም፤ እዚሁ አደባባዩ ላይ እናድራለን" አሉት።
\v 3 ሎጥ ግን አጥብቆ ስለ ለመናቸው እርሱ ቤት ለማደር አብረውት ገቡ። ከዚያም ቂጣ ጋግሮ አቀረበላቸው፤ እነርሱም በሉ።
\s5
\v 4 ሆኖም፣ ገና ከመተኛታቸው በፊት የሰዶም ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ ወጣቶችና ሽማግሌዎች ከየአካባቢው መጥተው ቤቱን ከበቡት።
\v 5 ሎጥን በመጣራት፣ "በዚህ ምሽት ወደ ቤትህ የመጡ ሰዎች የታሉ? ሩካቤ ሥጋ እንድንፈጽምባቸው ወደ ውጭ አውጣልን" አሉት።
\s5
\v 6 ሎጥ ሊያነጋግራቸው ወደ ውጭ ወጣ መዝጊያውን ከበስተ ኋላው ዘጋ።
\v 7 እንዲህም አለ፤ "ወንድሞቼ እንዲህ ያለ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ እለምናችሏለሁ።
\v 8 ከወንድ ጋር ተኝተው የማያውቁ ሁለት ሴቶች ልጆች አሉኝ፤ እነርሱን ላውጣላችሁና የወደዳችሁትን አድርጉባቸው። በእነዚህ ሰዎች ላይ ግን ምንም ነገር አታድርጉባቸው፤ እኔን ብለው ወደ ቤቴ ተብተዋልና።"
\s5
\v 9 እነርሱ ግን፣ "ዞር በል!" ይኸ ሰውዬ ስደተኛ ሆኖ እዚህ ለመኖር መጣ፤ ደግሞ ዳኛ ሆነብን! ይልቁ በእነርሱ ላይ ካሰብነው የከፋ እንዳይደርስብህ ዘወር በልልን" አሉት ሎጥንም እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተቃርበው ነበር።
\s5
\v 10 ሰዎቹ እጃቸውን ዘርግተው ሎጥን ወደ ቤት አስገቡትና በሩን ዘጉ።
\v 11 ከቤቱ ውጪ የነበሩትን ውጣቶችንም ሆን ሽማግሌዎችን ግን የሎጥ እንግዶች ዐይናቸውን አሳወሩአቸው፤ እነርሱም በሩን ለማግኘት ይደነባበሩ ጀመር።
\s5
\v 12 ከዚያም ሰዎቹ ሎጥን እንዲህ አሉት፤ "በከተማዋ የሚኖሩ የአንተ የሆኑ ሰዎች አሉህ? ወንዶችና ሴቶች ልጆችህን፣ የወንዶች ልጆችህን ሚስቶች፣ የሴቶች ልጆችህን ባሎችና ሌሎች ዘመዶችህን ሁሉ ከዚህ አውጣ።
\v 13 ምክንያቱም ይህን ቦታ ልናጠፋ ነው፤ በያህዌ ፊት ከተማዋ ላይ የሚቀርቡ ክሶች በጣም እየጮኹ በመሆናቸው እንድናጠፋት እርሱ ልኮናል።"
\s5
\v 14 ሎጥ ከቤቱ ወጥቶ የሴት ልጆቹን ባሎች፣ የሴት ልጆቹን እጮኞች፣ "ቶሎ ከዚህ ቦታ ውጡ፤ ያህዌ ከተማዋን ሊያጠፋ ነው" አላቸው። የሴት ልጆቹ ባሎች ግን የሚቀልድ መሰላቸው።
\v 15 ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥኝ፣ "ከተተማዋ ላይ በሚመጣው ቅጣት አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱ ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ" እያሉ አቻኮሉት።
\s5
\v 16 ሎጥ አመነታ፤ ያህዌ ምሕረት ስላደረገላቸው ሰዎቹ የእርሱ፣ የሚስቱንና የሁለት ሴት ልጆቹን እጅ ይዘው ከከተማዋ አወጣቸው።
\v 17 ከከተማው ካወጧቸው በኋላ ከሰዎቹ አንዱ፣ "ሕይወታችሁን ለማዳን ሩጡ! ወደ ኋላችሁ አትመልከቱ፤ ወይም ረባዳው ስፍራ ላይ አትቆዩ። ወደ ተራሮች ሽሹ፤ አለበለዚያ ትጠፋላችሁ።"
\s5
\v 18 ሎጥም እንዲህ አላቸው፤ "ጌቶቼ ሆይ፣
\v 19 እኔ ባሪያችሁ በፊታችሁ ሞገስ አግኝቻለሁ፤ ሕይወቴን ለማዳን ታላቅ ርኅራኄ አድርጋችሁልኛል፤ እኔ እንደ ሆንኩ ወደ ተራሮቹ ሸሽቼ ማምለጥ ስለማልችል የሚወርደው መዓት ደርሶ ያጠፋኛል።
\v 20 ወደዚያ ሸሽቶ ለማምለጥ ቅርብ ቦታ ያለች ትንሽ ከተማ አለች ሸሽቼ ወደዚያ ብሄድ ሕይወቴን ማዳን እችላለሁ።"
\s5
\v 21 እርሱም፣ "ይሁን እሺ፤ ልመናህን ተቀብብያለሁ፤ ያክካትንም ከተማ አላጠፋትም።
\v 22 አንተ እዚያ እስክትደርስ ምንም ማድረግ ስለማልችል በል ቶሎ ፍጠንና ወደዚያ ሽሽ" አለው። ስለዚህ ያቺ ከተማ ዞዓር ተባለች።
\s5
\v 23 ሎጥ ዞዓር ሲደርስ ፀሓይ በምድሩ ወጥታ ነበር።
\v 24 ከዚያ ያህዌ ሰዶምና ጎሞራ ላይ ድኝና እሳት አዘነበ።
\v 25 እነዚያን ከተሞችና ረባዳ ቦታዎቹን፣ የከተሞቹ ነዋሪዎችንና እዚይ ኣያሉ ለምለም ነገሮችን ሁሉ አጠፋ።
\s5
\v 26 ከኋላው የነበረችው የሎጥሚስት ግን ወደ ኋላዋ ስለ ተመለከተች የጨው ዐምድ ሆና ቀረች።
\v 27 አብርሃም ጠዋት ማለዳ ተነሥቶ ያህዌ ፊት ቆሞ ወደ ነበረበት ቦታ ሄደ።
\v 28 ቁልቁል ሰዶምና ጎሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የነበረውን ምድር ተመለከተ። ከምድጃ የሚወጣ የመሰለ ጢስ ከምድሩ እየወጣ ነበር።
\s5
\v 29 እግዚአብሔር በረባዳው ቦታ የነበሩ ከተሞችን ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው። ሎጥ የነበረበትን ከተሞች ቢያጠፋም፣ እርሱ ግን ከጥፋት መሐል አወጣው።
\s5
\v 30 ሎጥ ግን በዞዓር መኖር ስለ ፈራ ከሁለት ሴቶች ልጆቹ ጋር ተራሮቹ ላይ ለመኖር ከዞዓር ወደ ላይ ወጣ። ስለዚህ እርሱና ሁለት ሴቶች ልጆቹ ዋሻ ውስጥኖሩ።
\s5
\v 31 ታላቋ ልጅ ታናሿን እንዲህ አለቻት፣ "አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ከእኛ ጋር የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም።
\v 32 ስለዚህ አባታችንን የወይን ጠጅ እናጠጣውና ከእርሱ ጋር እንተኛ፤ የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር እናትርፍ።"
\v 33 ስለዚህ በዚያ ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት። ታላቂቱ ልጅ ሄዳ ክአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቅም።
\s5
\v 34 በሚቀጥለው ቀን ታላቂቱ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ "ትናንት ሌሊት እኔ ከእባቴ ጋር ተኛሁ። ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፣ ከዚያ አንቺ ሄደሽ ከእርሱ ጋር ትተኛለሽ፣ የአባታችንንም ዘር እናተርፋለን።"
\v 35 ስለዚህ በዚያም ምሽት አባታቸውን ወይን ጠጅ አጠጡት፤ ታናሺቱ ልጅ ሄዳ ከእርሱ ጋር ተኛች፤ እርሷ ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም።
\s5
\v 36 ሁለቱ የሎጥ ልጆች ክአባታቸው አረገዙ።
\v 37 ታላቂቱ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሞዓብ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት ሞዓባውያን አባት ሆነ።
\v 38 ታናሺቱም እንዲሁ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ቤንአሚ አለችው። እርሱም ዛሬ ያሉት አሞናውያን አባት ሆነ።
\s5
\c 20
\p
\v 1 አብርሃም ከዚያ ተነሥቶ ወደ ኔጌብ አካብቢ ሄደ፤ በቃዴስና በሱር መካከልም መኖር ጀመረ። ለጥቂት ጊዜ በጌራራ ተቀመጠ።
\v 2 አብርሃም ሚስቱ ሥራራን፣ "እኅቴ ናት" ይል ነበር፤ ስለዚህ ይጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክ ሰዎች ልኮ ሣራን ወሰዳት።
\v 3 እግዚአብሔር ግን በሕልም ወደ እቢሜሌክ መጥቶ፣ "እነሆ በወሰድካት ሴት ምክንያት አንተ ምውት ነህ፤ ምክንያቱም እርሷ ባለ ባል ናት" አለው።
\s5
\v 4 አቢሜሌክ ገና አልሰረሰባትም ነበርና እንዲህ አለ፤ "ጌታ ሆይ፣ በደል ያልተገኘበትን ሕዝብ ልታጠፋ ነውን?
\v 5 'እኅቴ ናት' ያለኝ እርሱ ራሱ አይደለምን? እርሷም ብትሆን 'ወንድሜ ነው' ብላኛለች። እኔ እንዲህ ያደረግሁት በቅን ልቦናና በንጹሕ እጅ ነው።"
\s5
\v 6 በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር በሕልም እንዲህ አለው፤ "አዎን፣ ይህን ያደረግኸው በልብ ቅንነት እንደ ነበር እኔም አውቃለሁ፤ እኔ ላይ ኀጢአት እንዳትፈጽም የጠበቅሁህና እንዳትነካትም ያደረግሁት በዚህ ምክንያት ነው፤
\v 7 ስለዚህ የሰውየውን ሚስት መልስለት፤ እርሱ ነቢይ ስለ ሆነ ይጸልይልሃል አንትም ትድናለህ። እርሷን ካልመለስህ፣ እንተና የአንተ የሆነው ሁሉ በእርግጥ እንደምትጠፉ ዐውቃለሁ።"
\s5
\v 8 አቤሜሊክ ጧት በማለዳ ተነሥቶ ሹማምንቶቹን ሁሉ ጠራ። የሆነውን ሁሉ ሲነግራቸው በጣም ፈሩ።
\v 9 ከዚያም አቤሜሌ አብርሃምን አስጠርቶ፣ "ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህብን ነው? በእኔና በግዛቴ ላይ እንዲህ ያለውን ትልቅ መዘዝ ያመጣህብኝ ምን ብበድልህ ነው? መደረግ ያልነበረትን አድርገህብኛል" አለው።
\s5
\v 10 በመቀጠልም፣ አብርሃምን፣ "እንዲህ እንድታደርግ ያነሣሣህ ምንድን ነው?" ሲል ጠየቀው።
\v 11 አብርሃምም፣ "በዚህ ቦታ እግዚአብሔርን መፍራት የለም፤ ለሚስቴ ሲሉ ይገድሉኛል በማለት ስላሰብሁ ነው።
\v 12 በዚህ ላይ ደግሞ ከእናቴ ባትወለድም የአባቴ ልጅ እኅቴ ናት፤ በኋላም ሚስቴ ሆነች።
\s5
\v 13 የአባቴን ቤት ትቼ በየአገሩ እንድዞር እግዚአብሔር ሲያዝዘኝ፣ "ለእኔ ለባልሽ ያለሽን ታማኝነት በዚህ አሳዪኝ፤ በምንሄድበት ቦታ ሁሉ 'ወንድሜ ነው' በዪ አልኳት።"
\v 14 ከዚያ አቤሜሊክ በጎችና በሬዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ለአብርሃም ሰጠው። ሚስቱ ሣራንም ለአብርሃም መለሰለት።
\s5
\v 15 አቤሜሌክ እንዲህ አለ፤ "አገሬ አገርህ ነው፤ ደስ በሚያሰኝህ ቦታ ተቀመጥ።"
\v 16 ሣራንም፣ "ለወንድምሽ አንድ ሺህ ጥሬ ብር እሰጠዋለሁ። ይህም፣ በአንቺ ላይ ለተፈጸመው በደል ካሣ እንዲሆንና አብረውሽ ያሉ ሁሉ አንቺ ንጹሕ ሴት መሆንሽን እንዲያውቁ ነው።"
\s5
\v 17 ከዚያም አብርሃም ለአቤሜሌክ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክን፣ ሚስቱንና ሴት አገልጋዮቹን ፈወሳቸው፤ ልጅ ለመውለድም በቁ።
\v 18 ከአብርሃም ሚስት ከሣራ የተነሣ በአቢሜሌክ ቤት የሚገኙ ሴቶችን ሁሉ ያህዌ ማኅፀናቸውን ዘግቶ ነበር።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ለአብርሃም በሰጠው የተስፋ ቃል መሰረት እግዚአብሔር ሳራን አሰባት፤ እንደገባላት የተስፋ ቃልም አደረገ ፤
\v 2 ስለዚህም ሳራ አርግዛ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው «በዚህ ጊዜ ይወለዳል» ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው።
\v 3 አብርሃም ሚስቱ ሳራ የወለደችለትን ልጅ «ይስሐቅ» ብሎ ስም አወጣለት።
\v 4 ይስሐቅ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ እግዚአብሔር ባዘዘው መሰረት አብርሃም ገረዘው።
\s5
\v 5 ልጁ ይስሐቅ በተወለደለት ጊዜ አብርሃም መቶ ዓመት ሆኖት ነበር።
\v 6 ሳራም «እግዚአብሔር ሳቅ አደረገልኝ ስለዚህ ይህንን ነገር የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋር ይስቃል»አለች።
\v 7 ቀጥላም «ሳራ ለአብርሃም ልጆችን ወልዳ ታጠባለች» ብሎ የሚናገር ከቶ ማን ነበር አሁን ግን እነሆ በእርጅናው ዘመን ወንድ ልጅ ወለድሁለት» አለች።
\s5
\v 8 ልጇም አድጎ ጡት መጥባት ተወ፤ ጡት ባስጣሉበትም ቀን አብርሃም ታላቅ ግብዣ አደረገ።
\v 9 ግብጻዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለት እስማኤል ከዕለታት አንድ ቀን በሳራ ልጅ በይስሐቅ ላይ ሲያሾፍበት ሳራ አየች።
\s5
\v 10 ስለዚህ ሳራ አብርሃምን«ይህችን አገልጋይ ከነ ልጅዋ ወዲያ አባርልኝ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም» አለችው።
\v 11 እስማኤልም ልጁ ስለሆነ ይህ ጉዳይ አብርሃምን በብርቱ አስጨነቀው
\s5
\v 12 እግዚአብሔር ግን አብርሃምን «ስለ ልጁና ስለ አገልጋይቱ ስለ አጋር አትጨነቅ። ዘር የሚወጣልህ በይስሃቅ በኩል ስለሆን እርሳ የምትልህን ሁሉ አድርግ።
\v 13 የአገልጋይቱም ልጅ የአንተ ዘርያ ስልሆን ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ» አለው
\s5
\v 14 አብርሃም በማለዳ ተነሳ ጥቂት ምግብ ውሃም በአቁማዳ ለአጋር በትከሻዋ አደረገላት። ልጁንም በጀርባዋ አሳዝሎ ከቤት አስወጣት፤ እርስዋም በቤርሳቤህ በረሃ ትንከራተት ጀመር።
\v 15 በአቁማዳ የነበረው ውሃ ባለቀ ጊዜ ልጁን በቁጥቋጦ ስር አስቀምችጠችው።
\v 16 እርስዋም «ልጄ ሲሞት ማየት አልፈልግም» በማለት ጥቂት ከልጅዋ ርቃ ተቀመጠች፤ እዚያም ሆና ድምጻን ከፍ አድርጋ ታለቅስ ጀመር።
\s5
\v 17 እግዚአብሔሬም ልሉ ምርር ብሎ ሲያለቅስ ሰማ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን «አጋር ሆይ የምትጨነቂበት ነገር ምንድር ነው? እግዚአብሔር የልጂን ለቅሶ ሰምቶአልና አትፍሪ።
\v 18 ተነሺ ሂንና ልጁን አንስተስ አባብይው፤ የእርሱንም ዘር አበዛለሁ ታላቅ ሕዝብም አደርገዋለሁ።
\s5
\v 19 በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ዓይኖችዋን ከፈተላትና አንድ የውኃ ጉድጋድ አየች፤ ሄዳም በአቁማዳ ውሃ ሞላች ለልጅዋም አጠጣችው።
\v 20 ልጁ እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር።
\v 21 በፋራንም በረሓ ኖረ፤ ቀስት በመወርወርም የታወቀ አዳኝ ሆነ። እናቱም ከአንዲት ግብጻዊት ጋር አጋባችው።
\s5
\v 22 በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሄደና አብርሃምን «በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤
\v 23 እኔንም ሆነ ልጆቼን ወይም ዝርያዎቼን እንዳትዋሸኝ አሁን በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ። እኔ ለአንተ ታማኝነትን አሳይቻለሁ፤ አንተም ለእኔና ለዚህች ለምትኖርባትአገር ታማኝንትን እንደምታሳይ ማልልኝ» አለው።
\v 24 አብርሃምም «እሺ እምላለሁ» አለ።
\s5
\v 25 አብርሃም የአቢሜሌክ አገልጋዮች ስለ ወሰዱበት የውሃ ጉድጋድ ለአቤሜሌክ አቤቱታ አቀረበ፤
\v 26 አቤሜሌክም «ይህን ያደረገ ማን እንደሆን አላውቅም። አንተም አልነገርኸኝም ይህንን ነገር ገና ዛሬ መስማቴ ነው» አለው።
\v 27 ከዚህ በኋላ አብርሃም ብዙ በጎችና ከብቶች አምጥቶ ለአቢሜሌክ ሰጠው፤ በዚያን ቀን ሁለቱም የስምምነት መሀላ አደረጉ።
\s5
\v 28 በዚያን ጊዜ አብርሃም ሰባት እንስት የበግ ጠቦቶችን ከመንጋው ለየ፤
\v 29 አቤሜሌክም «እንዚህን ሰባት ጠቦቶች ለይተህ ያቆምሃቸው ለምንድር ነው? » አለው።
\v 30 አብርሃምም «እነዚህን ሰባት እንስት ጠቦቶች ተቀበለኝ እነርሱን ከተቀበልከኝ ይህን ጉድጋድ የቆፈርሁ እኔ መሆኔን ምስክር እንዲሆን ነው» አለው፤
\s5
\v 31 ሁለቱ ተማምለው የተስማሙበት ስፍራ በመሆኑ የዚያ ቦታ ስም ቤርሳቤህ ተባል፤
\v 32 ይህን ስምምንት በቤርሳቤህ ተስማምተው ካደረጉ በኋላ አቤሜሌክና የሰራዊቱ አለቃ ፊኮል ወደ ፍልስጥኤም ምድር ተመለሱ
\s5
\v 33 ከዚህ ብኃላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከልና የዘላለም አምላክ ለሆነው ሰገደ፤
\v 34 አብርሃም በፍልስጥኤም ምድር በእንግድነት ለረዥም ጊዜ ኖረ።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ሁሉ ነገር በኋላ እግዚአብሔር አብርሃምን ፈተነው፤ እግዚአብሔርም «አብርሃም »ብሎ ጠራው፤ «እነሆ አለሁኝ» ብሎ መለሰ።
\v 2 እግዚአብሔርም «የምትወደውን አንድ ልጅህን ወደ ሞሪያ ምድር ሂድ። እዚያ በማሳይህ አንድ ኮረብታ ላይ እርሱን የሚቃጠል መስዋዕት አድርገህ አቅርብልኝ» አለው፤
\v 3 አብርሃም በማለዳ ተነስቶ ለመስዋዕት የሚሆን እንጨት ቆረጠና በአህያው ላይ ጫነው፤ከእርሱ ጋር ልጁን ይስሐቅን ና ሁለት ወጣት ሰዎችን ይዞ እግዚአብሔር ወደ ነገረው ቦታ ለመሄድ ጉዞ ጀመረ።
\s5
\v 4 በሦስተኛው ቀን አብርሃም ቀና ብሎ ሲመለከት ቦታውን በሩቅ አየ።
\v 5 ከዚህ በኃላ አብርሃም የርሱን ወጣቶች «እናንተ ከአህያው ጋር በዚህ ቆዩ እኔና ልጄ ወደዚያ ሄደን ከሰገድን በኃላ እንመለሳለን፤
\v 6 አብርሃምም የሚቃጠለውን መስዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንስቶ ለልጁ ለይስአቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢላዋውንና እሳቱን ያዘ ሁለቱም አብረው ሄዱ።
\s5
\v 7 ይስሐቅ አብርሃምን «አባባ» አለው፤ እርሱም «እነሆ አለሁ ልጄ» አለው፤ ይስሐቅም «እነሆ እሳትና እንጨት ይዘናል ታዲያ ለመስዋዕት የሚሆነው በግ የት አለ? » በማለት አብርሃምን ጠየቀው።
\v 8 አብርሃምም «ልጄ ሆይ ለመስዋዕት የሚሆነውን በግ እግዚአብሔር እራሱ ያዘጋጃል» አለው። ሁለቱም አብረው መንገዳቸውን ቀጠሉ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ነገረው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሰዊያ ሰርቶ እንጨቱን ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሰዊያው ላይ አጋደመው።
\v 10 ልጁን ለማረድ ቢላዋ አንስቶ እጁን ዘረጋ።
\s5
\v 11 ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ «አብርሃም! አብርሃም! » ብሎ ጠራው። እርሱም «እነሆኝ አለሁኝ» አለ።
\v 12 እርሱም «በልጁ ላይ እጅህን አትጫንበት፣ ምንም ዓይነት ጉዳትም አታድርስበት፣ እነሆ እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆንህን ተረድቻለሁ፤ አንድ ልጅህን እንኳ ለእኔ ከመስጠት አልተቆጠብህም» አለው።
\s5
\v 13 አብርሃም ዙሪያውን በተመለከት ጊዜ ከበስተጀርባው ቀንዶቹ በቁጥቋጥ ዛፍ የተያዙ አንድ በግ አየ፤ አብርሃምም ሄዶ በጉን አመጣና በልጁ ፋንታ የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበው።
\v 14 አብርሃምም ያን ቦታ «እግዚአብሔር ያዘጋጃል» ብሎ ጠራው። ዛሬም ቢሆን ሠዎች «እግዚአብሔር በተራራው ላይ ያዘጋጃል» ይላሉ።
\s5
\v 15 የእግዚአብሔር መልአክ ለሁለተኛ ጊዜ አብርሃምን ከሰማይ ጠራውና፤
\v 16 እንዲህ አለው፤ «እግዚአብሔር ብዙ በረከት እንድምሰጥህ በራሴ ስም እምላለሁ» ይላል፤ ይህን ስላደረግህና አንድ ልጅህንም ለእኔ ለመስጠት ስላልተቆጠብህ፤
\v 17 እኔም ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባህር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዝርያዎችህም ጠላቶቻቸውን ድል ነስተው፤ ከተሞቻቸውን ይይዛሉ።
\s5
\v 18 ትዕዛዜን ስለ ፈጸምህ የዓለም ህዝቦች ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ»፤
\v 19 ከዚህ በኋላ አብርሃም ወደ ወጣቶችሁ ተመለሰና በአንድነት ሆነው ወደ ቤርሳቤህ ሄዱ፤ አብርሃምም በቤርሳቤህ ተቀመጠ።
\s5
\v 20 ከዚህ ሁሉ በኋላ እንዲህ ተብሎ ለአብርሃም ተነገረው «ሚልካ ልጆችን ለወንድምህ ለናኮር ወልዳለች፤
\v 21 እነርሱም የመጀመሪያው ልጅ ዑፅ ወንድሙም ቡዝ የአራም አባት ቀሙኤል፤
\v 22 ኬሰድ፣ ሐዞ፣ ፊልዳሽ፤ ይድላፍና በቱኤል ናቸው።
\s5
\v 23 በቱኤል ርብቃን ወለደ። ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለንኮር ወለደችለት፤
\v 24 ረኡማ የተባለች የናኮር ቁባት ደግሞ ጤባሕን፣ ገሐምን፣ ተሐሽና ማዕካን ወለደችለት።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ሣራ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ኖረች። እነዚህን ዓመታት ነበር ሳራ የኖረችው።
\v 2 በከነዓን ምድር ባለችው ቂርያት አርባ ተብላ በምትጠራው በኬብሮን ከተማ ሞተች፤ አብርሃም በሣራ ሞት ምክንያት እጅግ ሃዘነ አለቀሰም።
\s5
\v 3 ከዚያም አብርሃም ከተቀመጠበት ከሚስቱ ሬሳ አጠገብ ተነሳ፣ ኬጢያውያንን እንዲህ አላቸው፤
\v 4 «እኔ በመካከላችሁ በእንግድነት የምኖር ነኝ። እባካችሁ የመቃብር ቦታ ስጡኝ፤ የሚስቴንም ሬሳ ልቅበርበት።»
\s5
\v 5 የኬጢ ልጆችም ለአብርሃም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤
\v 6 «ጌታ ሆይ ስማን፣ አንተ በእኛ መካከል ከእግዚአብሔር አለቃ ነህ። ከመቃብር ቦታችን በመረጥከው ስፍራ ሬሳህን መቅበር ትችላለህ፣ ማናችንም ብንሆን የሞተብህን ሰው እንዳትቀብርበት የምቃብር ቦታችንን አንከለክልህም።»
\s5
\v 7 አብርሃም ተነሣ በኬጢያውያን ልጆች ፊት እጅ ነስቶ እንዲህ አለ።
\v 8 የሚስቴን አስከሬን እዚህ እንድቀብር ከፈቀዳችሁልኝ የጾሐር ልጅ ዔፍሮምን ስለ እኔ ሆናችሁ ልምኑልኝ፤
\v 9 በእርሻው ዳር ያለችውን መክፈል የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፣ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንት ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።»
\s5
\v 10 ኤፍሮንም በኬጢ ልጆች መካከል ተቀምጦ ነበር፤ የኬጢም ሰው ኤፍሮንም የኪጥ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሲስሙ ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤
\v 11 «አይደለም ጌታዬ፣ ስማኝ። እርሻውን፣ በርሱም ዳር ያለውን ዋሻ፤ በወገኔ ልጆች ፊት ሰጥቼአለሁ። ሬሳህን ቅበር።»
\s5
\v 12 አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ።
\v 13 የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፤ «እባክህ ፈቃደኛ ብትሆን አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ። አንተም ከእኔ ዘንድ ውሰድ፤ ሬሳዬንም በዚያ እቀብራለሁ
\s5
\v 14 ኤፍሮንም ለአብርሃም እንዲህ ሲል መለሰለት፤
\v 15 «ጌታዬ ሆይ እኔን ስማኝ፤ የመሬቱ ዋጋ እራት መቶ ሰቅል ቢሆን ነው፤ ታዲያ ይሄ በእኔና በአንተ መካከል ምንድር ነው? ሬሳህንም ቅበር»
\v 16 አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬት ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው፤ ብሩንም በወቅቱ የንግድ መለኪያ መሰረት መዘነለት።
\s5
\v 17 በዚህም ሁኔታ በመምሬ አጠገብ በመክፈላ ያለውን የኤፍሮንን እርሻ ቦታ ከነዋሻው በከልሉ ካሉት ዛፎች ሁሉ ጭምር ለአብርሃም በርስትነት ተላለፈ፤
\v 18 እርሻው በእርሱ ያለውን ዋሻው በእርሻውም ውስጥ በዙሪያውም ያለው እንጨት ሁሉ በኬጢ ልጆችና በከተማይቱ በር በሚገቡ ሁሉ ፊት ለአብርሃም ርስቱ ሆነ።
\s5
\v 19 ከዚያም በኋላ ኬብሮን በምትባል በምምሬ ፊት በከነአን ፊት ባለው እርሻ ባለ ድርብ ክፍሌ በሆነው ዋሻ ውስጥ ሚስቱን ሳራን ቀበረ።
\v 20 እርሻውና በርሱ ያለው ዋሻው በኪጥ ልጆች ዘንድ ለአብርሃም የመቃብር ርስት ሆኖ ጸና።
\s5
\c 24
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ አብርሃም ሸመገለ፤ ዕድሜውም ገፋ፤ እግዚአብሔርም አብርሃምን በሁሉ ነገር ባረከው።
\v 2 አብርሃምም የንብረቱ ሁሉ ኀላፊ የቤቱ ሁሉ አዛዥ የሆነውን አገልጋይ እንዲህ አለው፤ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ
\v 3 እኔም በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናዊያን ለልጄ ሚስት እንዳታጭለት በሰማይና በምድር አምላክ እግዚአብሔር አስምልሃለሁ።
\v 4 ነገር ግን ወደ ገዛ ሀገሬ እና ወደ ወገኖቼ ሄደህ ለልጄ ለይስሐቅ ሚስትን ታጭለታለህ።
\s5
\v 5 አገልጋዩም «ምናልባት የምመርጥለት እጮኛ ከእንይ ጋሬ ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደ ነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገው? » ብሎ ጠየቀ።
\v 6 አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ «በምንም ዓይነት ምክንያት ቢሆን ልጄን ወደዚያ አገር መልሰህ እንዳትወስድ ተጠንቀቅ፤
\v 7 የሰማይ አምክክ እግዚአብሔር ከአባቴ ቤትና ከትውልድ አገሬ አውጥቶ አምጥቶኛል፤ ይህንንም ምድር ለዝርያዎቼ እንደሚሰጥ በመሃላ ቃል ገብቶልኛል፤ ከዚያ ለልጄ ሚስት ማግኘት እንድትችል እግዚአብሔር መልአኩን በፊትህ ይልካል።
\s5
\v 8 ልጅትዋ ከአንተ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንከዚህ መሓላ ነፃ ትሆናለህ፤ ልጄን ግን በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደዚያ አትመልሰው።»
\v 9 ከዚህ በኋላ አገልጋዩ እጁን በጌታው በአብርሃም ጉልበት ላይ አድርጎ አብርሃም ያዘዘውን ሁሉ እንደሚፈፅም በመሐላ ቃል ገባ።
\s5
\v 10 የአብርሃም ንብረት ኀላፊ የነበረው መጋቢ ከጌታው ቤት ምርጥ የሆኑ የስጦታ ዕቃዎችን በዕሥር ግመሎች ጭኖ በሰሜን መስጴጦምያ ናኮር ወደሚኖርበት ከተማ ሄደ።
\v 11 እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጭ ባለ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፣ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበትን ጊዜ ነበር፤
\s5
\v 12 አገልጋዩ እንዲህ ብሎ ጸለየ፣ ''የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ዛሬ የእኔን አሳብ በመፈፀም ለጌታዬ ለአብርሃም ዘላለምዊ ፍቅርህን ግለጥ።
\v 13 እነሆ፣ እኔ በዚህ የውሃ ጉድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማይቱም ልጃገረዶች ውሃ ሊቀዱ ወደዚህ ይመጣሉ፤
\v 14 ከእነሱም አንድዋ ልጃገረድ 'እንስራሽን ዘንበል አድርገሽ ውሃ አጠጪኝ' እላታለሁ፤ 'አንተም ጠጣ፤ ግመሎችህም እንዲጠጡ ውጃ ቀድቼ አመጣለሁ' ካለችኝ ለአገልጋይህ ለይስሐቅ ፍቅርህን እንዳሳየኸው ዐውቃለሁ።''
\s5
\v 15 ገና ጸሎቱን ሳፅቸርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት ባቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው።
\v 16 ርብቃ ገና ወንድ ያልደረሰባት በጣም ቆንጆ ልጃገረድ ነበረች፤ እርስዋ ወደ ውሃው ጉድጓድ ወርዳ በእንስራዋ ውሃ ከቀዳች በኋላ ተመለሰች።
\s5
\v 17 አገልጋዩም ወደ እርስዋ ሮጦ ሄዳና ''እባክሽ ከእንስራሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ''አላት።
\v 18 እርስዋም ''እሺ ጌታዬ ጠጣ'' አለችና እንስራዋን ከትከሻዋ አውርዳ ዘንበል አድርጋ ያዘችለት።
\s5
\v 19 ጠጥቶም ከረካ በኋላ ''ለግመሎችህም ውሃ እቀዳላቸዋለሁ፤ እስኪበቃቸውም ድረስ ይጠጡ'' አለችው።
\v 20 ወዲያውኑ፤ በእንስራዋ የያዘችውን ውሃ ግመሎቹ በሚጠጡበት ገዳን ላይ ገልብጣ ግመሎቹ ሁሉ ጠጥተው እስከሚረኩ ድረስ እየተጣደፈች ከጉድጓድ ውሃ መቅዳት ቀጠለች።
\s5
\v 21 ሰውየውም እግዚአብሔር የሄደበትን ተልእኮ አቃንቶለት እንደሆን ለማረጋገጥ የምታደርገውን ሁሉ ዝም ብሎ ይመለከት ነበር።
\v 22 ግመሎቹ ጠጥተው በኋላ ሰውየው አምስት ግራም ያህል የሚመዝን የወርቅ ጎታቻ አውጥቶ በጆሮዋ ላይ አደረገላት፤ መቶ ዐሥር ግራም ያህል የሚመዝን ሁለት የወርቅ አምባሮችንም አውጥቶ በእጆችዋ ላይ አደረገላትና፤
\v 23 ''የማን ልጅ ነሽ? እስቲ እባክሽ ንገሪኝ፤ ለእኔና አብረውኝ ቤት ይገኛልን?'' ብሎ ጠየቃት።
\s5
\v 24 እርስዋም ''የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር፣ እናቱም ሚልካ ይባላሉ፤
\v 25 በቤታችን ብዙ ገለባና ድርቆሽ አለ፤ ለእናንተም ማደሪያ ቦታ ይገኛል'' አለችው።
\s5
\v 26 ሰውየምውም በመንበርከክ ለእግዚአብሔር ሰግዶ፣
\v 27 ''ለጌታዬ የገባውን ቃል ኪዳንና ዘላለማዊ ፍቅሩን የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው'' አለ።
\s5
\v 28 ልጅትዋ ወደ ቤት ሮጣ ሄደችና የሆነውን ሁሉ ለእናትዋና ለእርስዋ ጋር ላሉት ሁሉ ነገረቻቸው።
\v 29 ርብቃ ላባ የተባለ ወንድም ነበራት፤ እርሱ የአብርሃም አገልጋይ ወዳለበት ውሃ ጉድጓድ እየሮጠ ሄደ።
\v 30 ላባ ወደ ሰውየው የሄደው እኅቱ በጆሮዋ ላይ ያደረገችውን ጉትቻና በእጆችዋ ላይ ያደረገቻቸውን አንባሮች ስላየና ርብቃ ሰውየው ጉድጓድ አጠገብ ከግመሎቹ ጋር ቆሞ አገኘው።
\s5
\v 31 ስለዚህ ላባ ''አንተ እግዚአብሔር የባረከህ ሰው! ና ወደ ቤት እንሂድ፤ በውጭ የቆምኸው ለምንድን ነው? በቤታችን ለአንተ ማደሪያ የተዘጋጀ ቦታ አለ'' አለው።
\v 32 ከዚህ በኋላ ሰውየው ወደ ቤት ሄደ፤ ላባም በግመሎቹ ላይ የነበረውን ጭነት አረግፎ ገለባና ድርቆሽ አቀረበላቸው፤ ቀጥሎም የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩት ሰዎች እግራቸውን የሚታጠቡበትን አመጣላቸው።
\s5
\v 33 ገበታ በቀረበው ጊዜ ጊዜ ሰውየው ''የተላክሁበትን ጎዳይ ከመናገሬ በፊት እህል አልቀምስም''አለ። ላባም '' ይሁን ተናገር'' አለው።
\v 34 እርሱም ''እኔ የአብርሃም አገልጋይ ነን፤
\v 35 እግዚአብሔር ጌታዬ እጅግ ባርኮል፤ ባለጸጋም አድርጎታል፤ ብዙ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋ፣ ብርና ወርቅ፣ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል።
\s5
\v 36 የጌታዬ ሚስት ሣራ በእርጅናዋ ዘምን ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሀብት ሁሉ ለዚሁ ልጅ አውርሶታል።
\v 37 ጌታዬ አብርሃም 'እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናዊያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳላጭለት፤
\v 38 ነገር ግን ወደ አባቴ ቤተሰብና ወደ ዘመዶቼ ሄደህ ለልጄ ሚስት እጭለት' ሲል በመሐላ ቃል ኪዳን አስገብቶኛል።'
\s5
\v 39 እኔም ጌታዬን 'ልጅቷ ከእኔ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ ምን ላድርግ?' ብዬ ጠየኩት።
\v 40 እርሱም እንዲህ አለኝ 'ዘውትር የማገለግለው እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፤ ጉዞህም የተቃና እንዲሆን ያደርጋል፤ በዚህ ሁኔታ አንተም ከአባትቴ ቤተሰብና ከዘመዶቼ መካከል ለልጄ ሚስት ልታጭለት ትችላለህ፤
\v 41 ከመሐላህ ነፃ የምትሆነው ወደ ዘመዶቼ ሄደህ እነርሱ ልጅትዋን አንሰጥም ብለው የከለከሉህ እንደሆነ ብቻ ነው።'
\s5
\v 42 ''ከዚያም በኋላ ዛሬ ወደ ውሃው ጉድጓድ ስመጣ እንዲህ ብዬ ጸለይሁ 'የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ የመጣሁበት ጉዳይ እንዲቃና አድርግልኝ፣
\v 43 እነሆ በዚህ ውሃ ጉድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ አንዲት ልጃገረድን ውሃ ልትቀዳ ስትመጣ፣ 'እባክሽ ከእንስራሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ' ብዬ እጠይቃታለሁ፤
\v 44 እርስዋም 'እሺ ጠጣ፤ ለግመሎችህም እቀዳቸዋለሁ'የምትለኝ ብትሆን፣ ለጌታዬ ልጅ ሚስት እንድትሆን አንተ የመረጥሃት እርስዋ ትሁን።
\s5
\v 45 የኅሊና ጸሎትን ገና ሳልጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ ብቅ አለች፤ ወደ ጉድጓዱም ሄዳ ውሃ ቀዳች፤ እኔም 'እባክሽ ጥቂት ውሃ አጠጪኝ አልኋት።
\v 46 እርስዋም እንስራዋን በፍጥነት ከጀርባዋ አወረደችና ዘንበል አድርጋ 'እሺ ጠጣ፤ ግመሎችህንም አጠጣልሃለሁ' አለችኝ፤ ስለዚህ እኔም ጠጣሁ፤ ግመሎቼንም አጠጣችልኝ።
\s5
\v 47 እኔም 'የማን ልጅ ነሽ?' ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም 'የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር እናቱም ሚልካ ይባላሉ' አለችኝ። ከዚህ በኋላ ጉትቻ በጆሮዋ ላይ፣ አንባሮቹንም በእጅዎችዋ ላይ አደረግሁላት፤
\v 48 ከዚህ በኋላ በጉልበቴ ተንበርክኬ ለእግዚአብሔር ሰገድሁ፤ የጌታዬን የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር አመሰገንሁ፤ ምክንያቱም ለጌታዬ ልጅ ሚስት የምትሆነዋን ሴት ወዳገኘሁበት ወደ ጌታዬ ወንድም ቤት በቀና መንገድ የመራኝ እርሱ ነው።
\s5
\v 49 እንግዲህ የጌታዬን ዐደራ በእውነት ተቀብላችሁ እርሱን ደስ ለማሰኘት የምትፈቅዱ እንደሆነ ንገሩኝ፤ የማትፈቅዱም እንደሆነ ቁርጡን ነገሩኝ፤ እኔም እግዚአብሔር ወደሚመራኝ እሄዳለሁ።''
\s5
\v 50 ላባና ባቱኤልም ''ይህ ነገር ከእግዚአብሔር የመጣ ስለሆነ፣ መከልከል አልችልም፤
\v 51 ርብቃ ይችውልህ፤ እነሆ ይዘሃት ሂድ፤ እግዚአብሔር ራሱ እንደተናገረው ለጌታዬ ልጅ ሚስት ትሁን'' አሉት።
\s5
\v 52 የአብርሃም አገልጋይ ይህን በሰማ ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤
\v 53 ከውርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፣ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው።
\s5
\v 54 ከዚህ በኋላ የአብርሃም አገልጋይና አብረውት የነበሩ ሰዎች በልተው ጠጥተው እዚያው አደሩ፤ ጠዋት በተነሡ ጊዜ የአብርሃም አገልጋይ ''እንግዲህ ወደ ጌታዬ እንድመለስ ፍቀዱልኝ'' አለ።
\v 55 ነገር ግን የርብቃ ወንድምና እናትዋ ''ልጅትዋ ዐሥር ቀን ያህል ከእኛ ጋር ትቆይ፤ ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር ልትሄድ ትችላለች'' አሉት።
\s5
\v 56 እርሱ ግን ''እባካችሁ አታቆዩኝ፤ እግዚአብሔር የመጣሁበትን ጉዳይ ስላቃናልኝ ቶሎ ብፄ ወደ ጌታዬ ልመለስ'' አላቸው።
\v 57 እነርሱም ''እስቲ ልጅቷን እንጥራትና እርስዋ የምትለውን እንስማ'' አሉ።
\v 58 ስለዚህ ርብቃን ጠሩና ''ከዚህ ሰው ጋር መሄድ ትፈልጊያለሽ?'' ብለው ጠየቅዋት። እርስዋም ''አዎ እሄዳለሁ''አለች።
\s5
\v 59 ስለዚህ ርብቃ ሞግዚትዋን አስከትላ፣ ከአብርሃም አገልጋይና ከእርሱ ሰዎች ጋር እንድትሄድ ፈቀዱላት።
\v 60 ''አንቺ እኅታችን የብዙ ሺ ሕዝብ እናት ሁኚ፤ ዝርያዎችሽም የጠላቶችሽን ከተሞች ይውረሱ'' ብለው ርብቃን መረቁአት።
\s5
\v 61 ከዚህ በኋላ ርብቃ ከተከታዮችዋ ጋር ለመሄድ ተነሣች፤ በግመሎቹ ላይ ተቀምጠው ከአብርሃም አገልጋይ ጋር ለመሄድ ተዘጋጁ። በዚህ ዐይነት የአብርሃም አገልጋይ ርብቃን ይዞ ሄደ።
\v 62 በዚህ ጊዜ ይስሐቅ ''ብኤር ላሐይ ሮኤ ወይም የሚያየኝን ሕያው አምላክ''የተባለው ኩሬ ወዳለበት በረሓ መጥቶ በኔጌብ ተቀምጦ ነበር።
\s5
\v 63 ከለዕታት አንድ ቀን ወደ ማታ ጊዜ እያሰላሰለ በመስክ ውስጥ ሲዘዋወር ሳለ ግመሎች ሲመጡ በሩቅ አየ።
\v 64 ርብቃ ይስሐቅ ባየች ጊዜ ከግመሏ ወረደችና፣
\v 65 ''ያ በመስክ ውስጥ ወደ እኛ የሚመጣው ሰው ማን ነው?'' ስትል የአብርሃምን አገልጋይ ጠየቀችው። አገልጋዩም ''እርሱ ጌታዬ ነው!'' አላት። ስለዚህ በጥፍነት በሻሽ ፊትዋን ሸፈነች።
\s5
\v 66 አገልጋዩም ያደረገውም ነግር ሁሉ ለይስሐቅ ነገረው።
\v 67 ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና።
\s5
\c 25
\p
\v 1 አብርሃም ቀጡራ የምትባል ሌላ ሚስት አገባ፤
\v 2 እርስዋም ዚምራንን፣ ዮቅሻንን፣ መዳንን፣ ምድያምን፣ ዩሽባቅንና ሹሐን ወለደችለት።
\v 3 ዮቅሻንም ሳባንና ደዳንን ወለደ፤ የዳደንም ዝርያዎች አሹራውያን፣ ሌጡሻውያንና ሌአማውያን ናቸው።
\v 4 የምድያም ልጆች ዔፋ፣ ዔፈር፣ ሐኖክ፣ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚሁ ሁሉ የቁጠራ ዝርያዎች ናቸው።
\s5
\v 5 አብርሃም ያለው ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤
\v 6 ከሌሎች ሴቶች ለተወለዱትም ልጆች ገና በሕይወት ሳለ ስጦታ ሰጣቸው፤ ከዚህ በኋላ እነዚህ ሌሎች ልጆች ከይስሐቅ ርቀው ወደ ምሥራቅ አገር እንዲሄዱ አደረጋቸው።
\s5
\v 7 የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤
\v 8 በዚህም ዐይነት አብርሃም በቂ ዕድሜ አግኝቶ ካረጀ በኋላ ሞተ፤
\s5
\v 9 ልጆቹ ይሰሐቅና እስማኤል ማክጴላ በተባለ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ ከመምሬ በስተምሥራቅ በሒታዊ በጶሐር ልጅ በዔፍሮን እርሻ ውስጥ የሚገኘው ነው።
\v 10 እነሱም አብርሃም ከሒታዊያን ላይ የገዛው የመቃብር ቦታ ነው፤ በዚህ ዐይነት አብርሃም ሚስቱ ሣራ በተቀበረችበት ዋሻ ተቀበረ።
\v 11 አብርሃም ከሞተ በኋላ ልጁን ይስሐቅን እግዚአብሔር ባረከው፤ ይስሐቅ ''ብኤርላሐይሮኢ ወይም የሚያየኝ ሕያው አምላክ'' ተብሎ በመጠራት ኩሬ አጠገብ ይኖር ነበር።
\s5
\v 12 የሣራ አገልጋይ ግብፃዊትዋ አጋር ለአብርሃም የወለደችለትን እስማኤል፤
\s5
\v 13 ከዚህ በታች በዕድሜአቸው ቅደም ተከተል ተራ የተዘረዘሩትን ልጆች ወለደ፤ እነርሱም፦ ነባዮት፣ ቄዳር፣ አድብኤል፣ ሚብሣም፣
\v 14 ሚሽማዕ፣ ዱማ፣ ማሣ፣
\v 15 ሐዳድ፣ ቴማ፣ ይጡር፣ ናፊሽና ቄድማ ናቸው።
\v 16 እነዚህ የእስማኤል ልጆች ለአሥራ ሁለት ነገዶች ቅድመ አያቶች ነበሩ፤ ስማቸውም በኖሩባቸው ከተሞችና ስፍራዎች ሲጠራ ይኖራል።
\s5
\v 17 እስማኤል መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ሲሆነው ሞተ።
\v 18 የእስማኤል ዝርያዎች ከግብፅ በስተምጅራቅ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ በሐዊላና በሹር መካከል ይኖሩ ነበር። የኖሩበትም ከሌሎቹ የአብርሃም ዝርያዎች ጋር በጥላቻ ተራርቀው ነበር።
\s5
\v 19 የአብርሃም ልጅ ይስሐቅ ታሪክ ይህ ነው። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ።
\v 20 ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሞኖሩ ሶሪያውያን ነበሩ።
\s5
\v 21 ርብቃ መኻን ስለ ነበረች ይስሐቅ ስለ እርስዋ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ስለ ሰማ ርብቃ ፀነሰች፤
\v 22 የተፀነሱትም መንትያዎች ስለነበሩ እርስ በርሳቸው በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋ ነበር፤ እርስዋም ''ይህን ዐይነት በገር ለምን ደረሰብኝ?'' በማለት ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ተነሣሣች።
\s5
\v 23 እግዚአብሔርም ያሉት ሁለት ሕዝቦች ናቸው፤ እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ሁለት ወገኖች ትወልጃለሽ፤ አንዱም ከሌላው የበረታ ይሆናል፤ ታላቁም ታናሹ አገልጋይ ይሆናል'' አላት።
\s5
\v 24 የመውለጃዋም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ሁለት ወንዶች ልጆች ወለደ።
\v 25 የመጀመሪያው ልጅ መልኩ ቀይ፣ ሰውነቱ ጠጉራም ነበር፤ ስለዚህ ዔሳው ተባለ።
\v 26 ሁለተኛው ልጅ ሲወለድ የዔሳውን ተገረዝ ይዞ በመውጣቱ ያዕቆብ ተባለ፤ ልጆቹ በተወለዱ ጊዜ ይስሐቅ ስልሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
\s5
\v 27 ሁለቱም ልጆች አደጉ፤ ዔሳው በዱር መዋል የሚወደ ብልኅ አዳኝ ሆነ፤ ያዕቆብ ግን በቤት መዋል የሚወድ ጭምት ሰው ነበር።
\v 28 ይስሐቅ ዔሳውን ይወድ ነበር። ምክንያቱም ዔሳው እያደነ ሥጋ ያበላው ነበር።ርብቃ ግን ያዕቆብን ትንን ነበር።
\s5
\v 29 ለዕለታት አንድ ቀን ያዕቆብ ቀይ የምስር ወጥ በመሥራት ላይ እንዳለ ዔሳው ከአደን መጣ፤ በጣም እርቦት ነበር፤
\v 30 ስለዚህም ያዕቆብ ''ከዚህ ከቀይ ወጥ ሰጠኝ'' አለው። ኤዶም የተባለውም ነዚሁ ምክንያት ነበር።
\s5
\v 31 ያዕቆብም ''በመጀመሪያ ብኩርናህን ሽጥልኝ'' አለው።
\v 32 ዔሳውም ''እኔ በረሀብ መሞቴ ነው፤ ታዲያ ብኩርና ምን ያደርግልኛል?'' አለው።
\v 33 ያዕቆብም ''እንግዲያውስ ብኩርናህን እንደምትሸጥልኝ መጀመሪያ ማልልኝ'' አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኩርናውን ለያዕቆብ ሸጠ።
\v 34 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ የምስሩን ወጥ በእንጀራ አድርጎ ሰጠው፤ ዔሳውም ከበላና ከጠጣ በኋላ ተነሥቶ ሄደ፤ በዚህ ዐይነት ዔሳው ብኩርናውን በመናቅ አቃለላት።
\s5
\c 26
\p
\v 1 በአብርሃም ዘመን ከደረሰው ረሀብ ሌላ ዳግመኛ ረሀብ በምድር ላይ መጣ፤ በዚህ ምክንያት ይስሐቅ የፍልስጥኤማዋን ንጉሥ አቢሜሌክ ወዳለበት ወደ ገራር ሄደ፤
\s5
\v 2 በዚህም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፣ ''ወደ ግብፅ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበትም በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤
\v 3 እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁ፤ ይህም ምድር ለአንተና ለዝርይዎችህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈፅማለሁ፤
\s5
\v 4 ዘርህን አንደ ሰማይ ክዋክብት አበዛዋልለሁ፤ ይህንንም ሁሉ ምድር አወርሳቸዋለሁ፤ ይህንንም ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ።
\v 5 አንተን የምባርክበትንም ምክንያት አባትህ አብርሃም ለእኔ ታዛዥ በመሆን የሰጠሁት ሕግና ሥርዓት ሁሉ ስለ ጠበወ ነው።
\s5
\v 6 ስለዚህ ይስሐቅ መኖሪያውን በገራር አደረገ፤
\v 7 በዚያ አገር ስሰዎችም ስለ ርብቃ ''ምንህናት'' ብለው በጠየቁት ጊዜ ''እኅቴ ናት'' አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቆንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው።
\v 8 ይስሐቅ እዚያ አገር ብዙ ጊዜ ከቆያ በኋላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌክ በመስኮት ወደ ውጪ ሲመለከት ይስሐቅና ርብቃ እንደባልና ሚስት በመዳራት ሲጫወቱ አየ።
\s5
\v 9 ስለዚህ አቢሜሌክ ይስሐቅን አስጠርቶ ''ለካስ ርብቃ ሚስትህ ናት! ታዲያ ''እኅቴ ናት' ያልከው ለምንድን ነው?'' ሲል ጠየቀው። እርሱም ''ሚስቴ ነች ያልኩ እንደሆን ሰዎች ይገድሉኝል ብዬ አስፈራሁ ነው'' ብሎ መለሰ።
\v 10 አቢሜሌክ ''ይህ በእኛ ላይ ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው? ከእኛ ሰዎች አንዱ በቀላሉ ሚስትህን ለመድፈር በቻለ ነበር፤''
\v 11 ቀጥሎም አቢሜሌክ ''ይህን ሰው ወይም ሚስቱን የሚነካ ሰው በሞቱ ይቀጣል''የሚል ማስጠንቀቂያ ለሕዝቡ ሰጠ።
\s5
\v 12 ይስሐቅ በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፤ እግዚአብሔር ስለባረከውም በዚያኑ ዓመት መቶ እጥፍ አመረተ፤
\v 13 ሀብት በሀብት ላይ እየተጨመረበት ዘመን የእርሱ አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን የውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው።
\v 14 ብዙ የበግና የከብት መንጋ፤ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት።
\s5
\v 15 ስለዚህ የይስሐቅ አባት አብርሃም በሕይወት በነበረበት ዘመን የእሱን አገልጋዮች ቁፍረዋቸው የነበሩትን ውሃ ጉድጓዶች ሁሉ ዐፈር ሞልተው ደፈኑአቸው።
\v 16 በዚያን ጊዜ አቢሜሌክ ይስሐቅን ''ኅይልህ ከእኛ ይልቅ እየበረታ ስለሄደ፤ አገራችንን ለቀህ ውጣ'' አለው።
\v 17 በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ያንን ቦታ ለቆ በገራር ሸለቆ ውስጥ ሰፈረ፤ እዚያም ተቀመጠ።
\s5
\v 18 አብርሃም በሕይወት ሳለ አስቆፍሮአቸው የነበሩትን አብርሃም ከሞተ በኋላ ግን ፍልስጥኤማውያን የደፈኑአቸውን የውሃ ጉድጓዶች ይስሐቅ እንደገና እንዲቆፍሩ አደረገ፤ አባቱ ባወጣላቸ ስሞችም ጠራቸው።
\s5
\v 19 የይስሐቅ አገልጋዮች በሸለቆው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ቁፍሩና ጥሩ የምንጭ ውሃ አገኙ፤
\v 20 የገራር እረኞች ግን ''ይህ ውሃ የእኛ ነው'' በማለት ከይስሐቅ እረኞች ጋር ተጣሉ።በዚህ ምክንያት ይስሐቅ ጉድጓዱን ''ዔሤቅ'' ብሎ ሰየመው።
\s5
\v 21 የይስሐቅ አገልጋዮች ሌላ የውሃ ጉድጓድ ቁፈሩ፤ በዚህኛውም ጉድጓድ ምክንያት ሌላ ጠብ ተነሣ፤ ስለዚህ ይስሐቅ ይህን ጉድጓድ ''ስጥና'' ብሎ ሰየመው።
\v 22 ከዚያም እልፍ ብሎ ሌላ የውሃ ጉድጓድ ምክንያት ምንም ጠብ ስላልተናሳ ''እነሆ አሁን እግዚአብሔር ሰፊ ቦታ ሰጠን፤ በምድር ላይም እንበዛለን ሲል ያንን ቦታ 'ረሖቦት'' ብሎ ሰየመው።
\s5
\v 23 ከዚያ በኋላ ይስሐቅ ወደ ቤርሳቤህ ወጣ፤
\v 24 በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና ''እኔ የአባትህ አምላክ ነኝ፤እኔ ከአንተ ጋር ስለሆንኩ አትፍራ! ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ'' አለው።
\v 25 ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጉድጓድ ቆፈሩ።
\s5
\v 26 አቢሜሌክ ከአማካሪው ከአሑዘትና ከሠራዊቱ ኣዥ ኮፊኮል ጋር ይስሐቅን ለመጎብኘት ከገራር ወት፤
\v 27 ስለዚህ ይስሐቅ ''ከዚህ በፊት ጠልታችሁን አገራችሁ እንድወጣ አድርጋችሁኛል፤ ታዲያ አሁን ልትጎበኝ የመጣችሁት ለምንድን ነው?'' አላቸው።
\s5
\v 28 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፣ ''እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን በግልጥ ዐውቀናል፤ ስለዚህ በእኛና በአንተ መካከል በሰላም ለመኖር የሚያስችል ስምምነት በመሐላ ለመፈፀም አስበናል፤ በዚህም መጀረት ቃል ኮዳን እንድትገባልን የሚንፈለገው፣
\v 29 በእኛ ላይ ምንም ዐይነት በደል እንዳታደርስብን ነው፤ ምክንያቱም እኛ በአንተ ላይ ምንም ግፍ አልሠራንም፤ ዘውትር መልካም ነገር አደረግንልህ እንጂ ክፉ አላደረግብህም፤ ከአገራችንም የወጣኸው በሰላም ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ባርኮሃል።''
\s5
\v 30 ከዚህ በኋላ፣ ይስሐቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ እነሱም በሉ፣ ጠጡ።
\v 31 በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ።
\s5
\v 32 ከዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቁፈሩት ጉድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ ''ውሃ አገኘን'' ብለውም አበሠሩት።
\v 33 እርሱም የውሃን ጉድጓድ ''ሳቤህ''ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ ''ቤርሳቤህ'' እየተባለ ይጠራል።
\s5
\v 34 ዔሳው አርባ ዓመት ሲሆንው የብኤሪን ልጅ ዮዲትንና የኤሎንን ልጅ ባሴማትን አገባ፤ ሁለቱም ሒታውያን ነበሩ።
\v 35 ይህም ጋብቻ ይስሐቅንና ርብቃን ሲያዝናቸው ይኖር ነበር።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ታውረው ነበር፤ ታላቁ ልጁን ዔሳውን፤ "ልጄ ሆይ!'' ብሎ ጠራው፤ ልጁም ''እነሆ አለሁ'' አለ።
\v 2 ይስሐቅም እንዲህ አለው፣ ''እንደምታየኝ አርጅቻለሁ፤ የምሞትበትንም ቀን አላውቅም፤
\s5
\v 3 ስለዚህ የምታድንበትን ቀስትና ፍላጻ ያዝ፤ ወደ ዱር ሂድና አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤
\v 4 ልክ እንደምወደው አድርገህ ምግብ ሥራልኝ ከበላሁም በኋላ ከመሞቴ በፊት የመጨረሻ ምርቃቴን እሰጥሃለሁ።''
\s5
\v 5 ይስሐቅ ለልጁ ለዔሳው ወደ አደን ከሄደ በኋላ፣
\v 6 ርብቃ ልጅዋን ያዕቆብን ''አባትህ ዔሳውን እንዲህ ሲለው ሰማሁ፣
\v 7 አውሬ አድነህ ሥጋ አምጣልኝ፤ ልክ እንደምወደው አድርገህ የጣፈጠ ምግብ ሥራልኝ፤ ሳልሞትም በእግዚአብሔር ፊት እነርቅሃለሁ፤
\s5
\v 8 አሁንም ልጄ ሆይ! የምነግርህን አድምጥ፤ የማዝህንም አድርግ፤
\v 9 አባትህ እንደሚወደው አጣፋጩ ጥሩ ምግብ እንድሠራለት፣ ወደ መንጋዎች ሂድና ሁለት የሰቡ የፍየል ጥቦቶች አምጣልኝ፤
\v 10 አንተም ያዘጋጀሁትን ምግብ እንዲበላ ለአባትህ ወስደህ ታቀርብለታለህ፤ በዚህ ዐይነት አባትህ ከመሞቱ በፊት ይመርቅሃል።''
\s5
\v 11 ያዕቆብ ግን እናቱን ርብቃን ''የወንድሜ የዔሳው ገላ ጠጉራም ነው፤ የ እኔ ገላ ግን ምንም ጠጉር የሌለው ለስላሳ ነው፤
\v 12 ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝና እንዳታለልኩህ ቢያውቅ በምርቃት ፈንታ እርግማን እንደማተርፍ ታውቂ የለምን?'' አላት።
\s5
\v 13 እናቱም ''ልጄ ሆይ! የአንተ እርግማን በእኔ ላይ ይሁን፤ አሁንም እንደነገርሁህ አድርግ፤ ሄድህ ጥቦቶቹን አምጣልኝ'' አለችው።
\v 14 ስለዚህ ሄዶ ጥቦቶቹን አመጣለት እርስዋም ልክ አባቱ እንደሚወደው እድርጋ ጥሩ ወጥ ሠራች፤
\s5
\v 15 የታላቁ ልጅዋን የዔሳውን የክት ልብስ ከተቀመጠበት ቦታ አውጥታ ለያዕቆብ አለበሰችው።
\v 16 የፍየሎቹንም ቆዳ በክንዶቹ ላይና ጠጉር በሌለበት በአንገቱ ላይ አለበሰችው።
\v 17 ያዘጋጀውንም ጥሩ ወጥ ከጋገረችው እንጀራ ጋር ልልጅዋ ለያዕቆብ ሰጠችው።
\s5
\v 18 ያዕቆብ ወደ አባቱ ሄደና ''አባባ!'' አለው፤ እርሱም ''እነሆ አለሁ! ለመሆኑ አንተ የትኛው ልጄ ነህ!'' አለ።
\v 19 ያዕቆብም ''የበኩር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ እነሆ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ፤ እንድትመርቀኝ እስቲ ቀና በልና ያመጣሁልህን የአደን ሥጋ ተመገብ'' አለው።
\s5
\v 20 ይስሐቅም ''ልጄ ሆይ! እንዴት ቶሎ ልታገኝ ቻልህ?'' አለው። ያዕቆብም ''አምላክህ እግዚአብሔር ስለረዳኝ በቶሎ ለማግኘት ቻልሁ'' አለው።
\v 21 ይስሕቅም ''እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በልና ልዳብስህ፤ በእርግጥ አንተ ዔሳው ነህን?'' አለው።
\s5
\v 22 ያዕቆብም ወደ አባቱ ተጠጋ፤ አባቱም ዳሰሰውና ''ድምፅህ የያዕቆብ ድምፅ ይመስላል፤ ክንድህ ግን የዔሳውን ክንድ ይመስላል'' አለው።
\v 23 ክንዶቹ እንደ ዔሳው ክንዶች ጠጉራም ስለ ነበሩ ይስሐቅ ያዕቆብን ለይቶ ማውቅ አልቻለም፤ ሊመርቀው ከዝዘጋጀ በኋላ፣
\s5
\v 24 ''እርግጥ አንተ ልጄ ዔሳው ነህን?'' ሲል እንደገና ጠየቀው፤ እርሱም ''አዎ ነን'' አለ።
\v 25 ይስሐቅም ''ልጄ! በል ከአደንከው ሥጋ አቅርብልኝ፤ ከበላሁም በኋላ እመርቅህለሁ'' አለው። ያዕቆብም ምግቡን አቀረበለት፤ የወይን ጠጅም እንዲጠጣ አመጣለት።
\s5
\v 26 ከዚህ በኋላ አባቱ ይስሐቅ ''ልጄ ሆይ! ቀረብ በልና ሳመኝ'' አለው፤
\v 27 ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብ ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፣ ''እነሆ የልጄ መልካም ሽታ እግዚአብሔር እንደባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤
\s5
\v 28 እግዚአብሔር ከሰማይ የሚያረሰርሰው ተል ይስጥህ፤ ምድርህን ያለምልምልህ፤ እህልንና የወይን ጠጅህን ያብዛልህ፤
\s5
\v 29 መንግሥታት ይገዙልህ፤ ሕዝቦችህም ያገልግሉህ፤ በወንድሞችህ ሁሉ ላይ አለቃ ሁን፤ የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ፤ የሚረግሙህ የተረገሙ ይሁኑ፤ የሚመርቁህ የተመረቁ ይሁኑ።''
\s5
\v 30 ይስሐቅ ያዕቆብን መርቆ እንዳበቃና ያዕቆብም አባቱን ፊት እንደወጣ ወዲያውኑ ዔሳው ከአደን ተመልሶ መጣ።
\v 31 እርሱም በበኩሉ የጣፈጠ ወጥ ሠርቶ ለአባቱ አቀረበለትና ''አባቴ ሆይ እንድትመርቀኝ፣ እስቲ ቀና ብለህ ካመጣሁልህ የአደን ሥጋ ብላ'' አለው።
\s5
\v 32 ይስሐቅም 'አንተ ማን ነህ?'' አለው፤ እርሱም ''እኔ የበኩር ልጅ ዔሳው ነኝ'' አለ።
\v 33 ይስሐቅም እጅግ ደንግጦ እየተነቀጠቀጠ ''ታዲያ አውሬ አድኖ ያመጣልኝ ማን ነበረ? ልክ አንተ ከመምጣትህ በፊት ተመገብሁ የመጨረሻ ምርቃቴንም ሰጠሁት፤ ምርቃቱም ተእርሱ ሆኖ ይኖራል''አለው።
\s5
\v 34 ዔሳው ይህን በሰማ ጊዜ ድምፁን ከፍ በማድረግ ምርር ብሎ እያለቀሰ ''አባቴ ሆይ! እኔንም መርቀኝ!'' አለ።
\v 35 ይስሐቅም ''ወንድምህ መጥቶ እኔን በማታለል የአንተን ምርቃት ወስዶብሃል''አለው።
\s5
\v 36 ዔሳውም ''እርሱ እኔን ሲያሰናክለኝ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ያዕቆብ መባሉ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፊት ብኩርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ፤ ታዲያ ለእኔ ያስቀረከው ምንም ምርቃት የለምን? አለው።
\v 37 ይስሐቅም ''ቀድሞ ብዬ እርሱን የአንተ ጌታ አድርጌዋለሁ፤ ወንድሞቹ ሁሉ የእርሱ አገልጋዮች እንዲሆኑ አድርጌአለሁ፤ እህልና የወይን ጠጅ እንዲበዛለት አድርጌአለሁ፤ ልጄ ሆይ! እንግዲህ ለአንተ ምን ላደርግልህ እችላለሁ?'' አለው።
\s5
\v 38 ዔሳውም ''አባቴ ሆይ! ምርቃትህ እንዲት ብቻ ናትን? እባክህ እኔንም መርቀኝ'' እያለ ለማልቀስ አባቱን ነዘነዘው።
\s5
\v 39 ይስሐቅም አንዲህ አለው። ''በረከት ከሞላበት ለምለም ምድር ርቀህ ትኖራለህ፤ የሰማይ ጠልም አታገኝም፤
\v 40 በሰይፍም ኅይል ትኖራለህ፤ የወንድምህም አገልጋይ ትሆናለህ፤ በተቃወምከውም ጊዜ ግን ከእርሱ ጭቁና ትላቀቃለህ።''
\s5
\v 41 አባቱ ስለመረቀው ዔሳው ያዕቆብን አጥብቆ ጠላው፤ በልቡም ''አባቴ በቅርብ ቀን ይሞታል፤ ከዚህ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ''ብሎ አሰበ።
\v 42 ነገር ግን ርብቃ የዔሳውን ዕቅድ ስለ ሰማች፣ ያዕቆብን ጠርታ እንዲህ አለችው፣ ''አድምጠኝ፤ ወንድምህ ዔሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ አስቦአል፤
\s5
\v 43 አሁንም ልጄ ሆይ! የምልህን አድርግ፤ ተነሥተህ በካራን ወደሚገኘው ወደ ወንድሜ ወደ ላባ ሽሽ፤
\v 44 የወንድምህ ቁጣ እስኪበርድ ድረስ ለጥቂት ጊዜ እዚያው ቆይ፤
\v 45 ቁጣውም ሲበርድ ያደረግህበትን ነገር ይረሳል፤ ከዚያ በኋላ ሰው ልኬ አስመጣሃለሁ፤ ሁለታችሁም በአንድ ቀን ማጣት አልፈልግም።
\s5
\v 46 ርብቃ ይስሐቅን ''ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሖታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱ ከገባ ለመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ''አለችው።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ መረቀው፤ እንዲህም ሲል አዘዘው፣ ''ከነዓናዊት ሴት እንድታገባ፤
\v 2 ይልቅስ ተነሥተህ በመስጴጦምያ ወዳለው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጎትህ ከገባ ሴቶች ልጆች አንዷን አግባ፤
\s5
\v 3 ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ይባርክህ፤ ብዙ ልጆችም ይስጥህ፤ የብዙ ሕዝቦችም አባት ያድርግህ፤
\v 4 አብርሃምን እንደባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ፤ ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ደስተኛ ሆነህ የኖርክበት ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ።''
\s5
\v 5 በዚህ ሁኔታ ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ ያዕቆብም በመስጴጦምያ ወደሚያኖረው ወደ ላባ ሄደ፤ ላባ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ነበረ፤ አባቱም ሶርያዊው ባቱኤል
\s5
\v 6 ይስሐቅ ያዕቆብን እንደመረቀና ሚስት እንደሚፈልግ ወደ መስጴጦምያ እንደላከው ዔሳው ተረዳ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ሲመርቀው ''ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ'' ብሎ ያዘዘው መሆኑንም ሰማ፤
\v 7 ያዕቆብ ለአባቱና ለእናቱ በመታዘዝ ወደ መስጴቶምያ መሄዱንም ተረዳ፤
\s5
\v 8 በዚህም አባቱ ይስሐቅ የከነዓንያውያንን ሴቶች እንደማይወድ ዔሳው ተገነዘበ፤
\v 9 ስለዚህ ከዚህ በፊት ከገባቸው ሌላ በተጨማሪ ወደ አብርሃም ልጅ ወደ እስማኤል ሄዶ ልጁን ማሕላትን አገባ፤ እርስዋም የነባዮት እኅት ናት።
\s5
\v 10 ያዕቆብ ቤርሳቤህን ትቶ ወደ ካራን ለመሄድ ተነሣ፤
\v 11 ፀሐይ በጠለቀች ጊዜ ወደ አንድ ስፍራ መጥቶ ዐፈር፤ በዚያም አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ተኛ፤
\s5
\v 12 በሕልሙም ከመሬት እስከ ሰማይ የሚደርሰው መሰላል አየ፤ በመሰላሉም የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይ ይውጡና ወደ ታች ይውረዱ ነበር።
\v 13 እግዚአብሔር በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፣ ''እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለዝርያዎችህ እንዲሆን ይህን የተገኘበት ምድር እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 14 ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ።
\v 15 አይዞህ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚያም ምድር በደህና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈፅምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።''
\s5
\v 16 ያዕቆብም ከእንቅልፉ ነቃና ''በእርግጥ እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ አለ፤ እኔ ግን ይህን አላወቅሁም ነበር''አለ።
\v 17 በጣም ፈርቶም ስለነበር ''ይህ እንዴት የሚያስፈራ ቦታ ነው፤ ይህ የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ ወደ ሰማይ የሚያስገባው በር ይህ ነው''አለ።
\s5
\v 18 ያዕቆብ በማግሥቱም ጠዋት በማለዳ ተነሣ፤ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ መታሰቢያ እንዲሆን እንደ ሐውልት አቆመው፤በላዩ ላይም የወይራ ዘይት አፈሰሰበት።
\v 19 ይህንንም ስፍራ ''ቤትኤል''ብሎ ሰየመው፤ ይህ ስፍራ ከዚያ በኋላ ሎዛ እየተባለ ይጠራ ነበር።
\s5
\v 20 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ ለእግዚአብሔር ተሳለ ''ከእኔ ጋር ሆነህ በምትሄድበት መንገድ ብትጠብቀኝ፣ የሚያስፈልገኝን ምግብና ልብስ ብትሰጠኝ፣
\v 21 ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብትመልሰኝ፤ አንተ አምላኬ ትሆናለህ፤
\v 22 ይህ ለመታሰቢያነት ያቆምሁት ድንጋይ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሁሉ ከዐሥር አንዱን እጅ ለአንተ እሰጣለሁ።''
\s5
\c 29
\p
\v 1 ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በስተ ምሥራቅ ወዳለው አገር ደረሰ፤
\v 2 እዚያም በሜዳ ላይ አንድ የውሃ ጉድጓድ አየ፤ በሦስት የተከፈሉ የበግ መንጋዎች በጉድጓድ ዙሪያ ነበሩ፤ መንጋዎቹ ውሃ የሚጠጡት ከዚሁ ጉድጓድ ነበር፤ ጉድጓዱም የሚዘጋበት ድንጋይ ትልቅ ነበር፤
\v 3 መንጋዎቹ ሁሉ እዚያ ከተሰበሰቡ በኋላ እረኞቹ ድንጋዩን አንከባለው ከጉድጓዱ ውሃ ያጠቱአቸው ነበር፤ መንጋዎቻቸውን ካጠጡ በኋላ ግን ድንጋዩንም መልሰው በጉድጓዱ አፍ ላይ ይከዱኑታል።
\s5
\v 4 ያዕቆብም እረኞቹን ''ወዳጆቼ ሆይ! ከየት ነው የመጣችሁት?'' ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም ''እኛ የመጣነው ከካራን ነው'' አሉት።
\v 5 እርሱም ''የናኮርን የልጅ ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?'' ብሎ ጠየቃቸው። እነሱም ''አዎ እናውቀዋለን'' አሉት።
\v 6 እርሱም ''ለመሆኑ እርሱ ደኅና ነውን?'' አላቸው። እነርሱም ''አዎ፣ ደኅና ነው፤ እንዲያውም ልጁ ራሔል ያችውልህ! በጎች እየነዳች በመምጣት ላይ ነች'' አሉት።
\s5
\v 7 ያዕቆብም ''ጊዜው ገና ቀን ነው፤ መንጋዎቻቸውንም ወደ ቤት የምታስገቡበት ሰዓት ገና አልደረሰም፤ ታዲያ ለምን ውሃ አጠጥታችሁ አታሰማሩአቸውም? ፤ አለ።
\v 8 እነርሱም ''እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን'' አሉት።
\s5
\v 9 ያዕቆብም ከእረኞቹ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ወደዚያ መጣች፤ ምክንያቱም እርስዋ የበጎች እረኛ ነበረች።
\v 10 ያዕቆብ ያጉቱን የላባን በጎች እየነዳች ስትመጣ ራሔልን አይቶ ወደ ጉድጓድ ሄደ፤ ጉድጓዱ የተከደነበትንም ድንጋይ አንከባሎ በጎቹን አጠጣቸው።
\s5
\v 11 ከዚያ በኋላ ራሔልን ሳማት። ከደስታውም ብዛት የተነሣ አለቀሰ፤
\v 12 ''እኔ የአባትሽ እኅት የሆነችው የርብቃ ልጅ ሄደች።
\s5
\v 13 ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ አቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤
\v 14 ላባም ''በእርግጥ አንተ ቅርብ የሥጋ ዘመዴ ነህ'' አለው፤ ያዕቆብም አንድ ወር ያህል ከአጎቱ ጋር ተቀመጠ።
\s5
\v 15 ላባ ያዕቆብን ''ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነፃ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያህል ደመወዝ ላስብልህ? አለው።
\v 16 ላባ ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ታላቂቱ ልያ፤ ታናሽቱ ራሔል ይባሉ ነበር።
\v 17 ልያ ዐይነ ልም ስትሆን፣ ራሔል ግን ቁመናዋ የሚያምር የደስ ደስ ያላት ነበረች።
\v 18 ያዕቆብ ራሔልን እጅግ ስለወደዳት ''ራሔልን ብትድርልኝ ሰባት ዓመት አገለግልሃለሁ'' አለ።
\s5
\v 19 ላባም ''ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለአንተ ብሰጥህ ይሻለኛል፤ እሺ ተስማምቼአለሁ፤ እዚሁ ከእኔ ጋር ኑር'' አለው።
\v 20 ያዕቆብ ራሔልን ለማግባት ሰባት ዓመት አገለገለ፤ ይሁን እንጂ ራሔልን በጣም ይወዳት ስለነበር የቆየበት ጊዜ ጥቂት ቀን ብቻ መስሎ ታየው።
\s5
\v 21 ከዚያ በኋላ ያዕቆብ ላባን ''እነሆ የአገልግሎት ዘመኔ ተፈፅሞአል፤ ሚስት እንድትሆነኝ ልጅህን ስጠኝ'' አለው።
\v 22 ላባም የሠርግ ድግስ አዘጋጅቶ በአቅራቢያው የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ ጠራ።
\s5
\v 23 ነገር ግን ላባ በራሔል ምትክ ልያን ለያዕቆብ ሰጠው፤ ያዕቆብም ከልያ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ።
\v 24 ላባ ሴት አገልጋዩን ዚልፋን አገልጋያዋን እንድትሆን ለልጁ ለልያ ሰጣት።
\v 25 በማግስቱ ጠዋት ያዕቆብ አብራው ያደረችው ልያ መሆንዋን ባወቀ ጊዜ ወደ ላባ ሄዶ ''ይህ ያደረግህብኝ ነገር ምንድን ነው? ያገለገልሁህ ራሔልን ለማግኘት አልነበረም? ታዲያ ለምን አታለልከኝ''አለው።
\s5
\v 26 ላባም ''ታላቂቱ ሳትዳር፤ ታናሺቱን መዳር የአገራችን ልማድ አይደለም፤
\v 27 የልያ ሠርግ ሰባት ቀን እስኪሞላው ድረስ ጠብቅ፤ ከእንግዲህ ወዲይ ሰባት ዓመት የምታገለግለኝ ከሆነ ራሔልን እሰጥሃለሁ'' አለው።
\s5
\v 28 ያዕቆብም ነገሩ ተስማማ፤ ከልያ ጋር ሰባት ቀን ተሞሽሮ ከቆየ በኋላ፤ ላባ ልጁን ራሔልን ለያዕቆብ ሳረለት።
\v 29 ላባ ሴት አገልጋዩን ባላን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለራሔል ሰጣት።
\v 30 ያዕቆብ ከራሔልም ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ከልያም አብልጦ ወደዳት፤ ከዚያ በኋላ ላባን ሰባት ዓመት አገለገለው።
\s5
\v 31 ልያ የራሔልን ያህል እንዳልተወደደች እግዚአብሔር ባየ ጊዜ መውለድ እንድትችል ማሕፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መኻን ሆነች፤
\v 32 ልያ ርርግዛ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ''እግዚአብሔር መከራዬን ተመለከተ፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ባሌ ይወደኛል'' ስትል ስሙን ሮቤል አለችው።
\s5
\v 33 እንደገና አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወደች፤ ''እግዚአብሔር እንዳልተወደድሁ ሰማ፤ ይህንንም ልጅ ደግሞ ሰጠኝ' ስትል ስሙን ስምዖን አለችው።
\v 34 እንደገና 'አረገዘችና ሌላ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ''እንግዲህ ሦስት ወንዶች ልጆች ስለ ወለድሁለት ባሌ ከእኔ ጋር በፍቅር ይጠመዳል'' ስትል ስሙን ሌዊ አለችው፤
\s5
\v 35 እንደገና አረገዘችና ውንድ ልጅ ወለደች፤ ''አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ'' ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች።
\s5
\c 30
\p
\v 1 ራሔል ለያዕቆብ አንድም ልጅ እንዳልወለደችለት ባየች ጊዜ በእኅቷ ቀናች። ያዕቆብንም፣ “ልጅ ስጠኝ አለበለዚያ እሞታለሁ” አለችው።
\v 2 ያዕቆብም ራሔልን ተቆጥቶ፤ “እኔ የሆድሽን ፍሬ በነሳሽ በእግዚአብሔር ቦታ ነኝን? ” አላት።
\s5
\v 3 እርሷም፣ “እነሆ፣ አገልጋዬ ባላ አለችልህ፣ ልጆች እንድትወልድልኝና እኔም ደግሞ በእርሷ አማካይነት ልጆች እንዳገኝ ከእርሷ ጋር ተኛ” አለችው።
\v 4 ስለዚህ ባላን እንደሚስት አድርጋ ሰጠችው፤ ያዕቆብም ከእርሷ ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት አደረገ።
\s5
\v 5 ባላም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደችለት።
\v 6 ራሔልም፦ “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፣ ልመናዬንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጥቶኛል” አለች። ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው።
\s5
\v 7 የራሔል አገልጋይ ባላ ዳግመኛ አረገዘችና ለያዕቆብ ሁለተኛ ወንድ ልጅ ወለደች።
\v 8 ከእኅቴ ጋር ብርቱ ትግል ታግዬ አሸነፍኋት” አለች። ስለዚህ ስሙን ንፍታሌም ብላ ጠራችው።
\s5
\v 9 ልያም ልጅ መውለድ ማቆሟን እንደተረዳች፣ አገልጋይዋን ዘለፋን ሚስት እንድትሆነው ለያዕቆብ ሰጠችው።
\v 10 የልያ አገልጋይ ዘለፋም ለያዕቆብ ወንድ ልጅ ወለደችለት፣
\v 11 ልያም፣ “እንዴት የታደልሁ ነኝ! ” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው።
\s5
\v 12 የልያም አገልጋይ ዘለፋ ለያዕቆብ ሁለተኛ ልጅ ወለደችለት፤
\v 13 ልያም፣ “እጅግ ደስ ብሎኛል፣ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ‘ደስተኛዋ’ ይሉኛል አለች፤ ስሙንም ‘አሴር’ ብላ ጠራችው።
\s5
\v 14 በስንዴ መከር ወራት ሮቤል ወደ ዱር ሄዶ እንኮይ አገኘ፤ ለእናቱ ለልያም አመጣላት፤ ራሔልም ልያን፣ “እባክሽን ልጅሽ ካመጣልሽ እንኮይ ስጪኝ” አለቻት።
\v 15 ልያም፦ “ባሌን የቀማሽኝ አነሰና የልጄን እንኮይ ደግሞ ልትወስጂ አማረሽ? ” አለቻት። ራሔልም፣ “ስለልጅሽ እንኮይ ዛሬ ያዕቆብ ከአንቺ ጋር ይደር” አለቻት።
\s5
\v 16 በዚያ ምሽት ያዕቆብ ከእርሻ ሲመለስ፣ ልያ ወጥታ ተቀበለችውና፣ “በልጄ እንኮይ ስለተከራየሁህ የዛሬው አዳርህ ከእኔ ጋር ነው” አለችው። ያዕቆብም በዚያች ሌሊት ከእርሷ ጋር አደረ።
\v 17 እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፣ ስለዚህ አረገዘችና ለያዕቆብ አምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት።
\v 18 ልያም፦ “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ደመወዜን ከፈለኝ” አለች። ስሙንም ይሳኮር አለችው።
\s5
\v 19 ልያ አሁንም ደግማ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ስድስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች።
\v 20 እርሷም፣ “እግዚአብሔር በከበረ ስጦታ አድሎኛል፣ ስድስት ወንዶች ልጆች ስለወለድሁለት ከእንግዲህ ባሌ አክብሮ ይይዘኛል” አለች፤ ስሙንም ዛብሎን አለችው።
\v 21 ከዚያም በኋላ ሴት ልጅ ወለደች ስምዋንም ዲና አለቻት።
\s5
\v 22 እግዚአብሔርም ራሔልን አሰበ፤ ጸሎትዋንም ሰምቶ ልጅ እንድትወልድ አደረጋት፤
\v 23 አርግዛም ወንድ ልጅ ወለደችና፣ “እግዚአብሔር ዕፍረቴን አስወገደልኝ” አለች፤
\v 24 ደግሞም ሌላ ወንድ ልጅ ይጨምርልኝ ስትል ስሙን ዮሴፍ ብላ ጠራችው።
\s5
\v 25 ራሔል ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ “ወደ ተወለድሁበት አገር እንድመለስ አሰናብተኝ፤
\v 26 አንተን በማገልገል ያገኘኋቸውን ሚስቶቼንና ልጆቼን ስጠኝና ልሂድ፤ ምን ያህል አገልግሎት እንዳበረከትኩልህ ታውቃለህ።”
\s5
\v 27 ላባም፣ “በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር እንደባረከኝ በንግርት መረዳቴን ልነግርህ እወዳለሁ፤
\v 28 የምትፈልገውን ደመወዝ ንገረኝና እከፍልሃለሁ” አለው።
\s5
\v 29 ያዕቆብም እንዲህ አለው፦ “እንዴት እንዳገለገልሁህና የከብትህም መንጋ በእኔ ጠባቂነት እንዴት እንደረባልህ አንተ ታውቃለህ፤
\v 30 እኔ ከመምጣቴ በፊት ጥቂት የነበሩት መንጋዎችህ አሁን እጅግ በዝተዋል፤ በተሰማራሁበት ሁሉ እግዚአብሔር በረከቱን አብዝቶልሃል። ታዲያ፣ ለራሴ ቤት የሚያስፈልገኝን የማቀርበው መቼ ነው?”
\s5
\v 31 ላባም፣ “ታዲያ ምን ያህል ልክፈልህ? ” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ የምልህን አንድ ነገር ብቻ ብታደርግልኝ መንጋህን ማሰማራቴንና መጠበቄን እቀጥላልሁ፤
\v 32 ዛሬ በመንጋዎችህ መካከል ልለፍና ዝንጉርጉርና ነቁጣ ጥቁርም የሆኑትን በጎች ሁሉ ልለይ፤ እንዲሁም ነቁጣና ዝንጉርጉር የሆኑትን ፍየሎች እመርጣለሁ፤ እነርሱም ደመወዜ ይሆናሉ፤
\s5
\v 33 ወደፊት ደመወዜን ለመቆጣጠር በምትመጣበት ጊዜ ታማኝነቴ ይታወቃል፤ ደመወዜን ለመቆጣጠር ስትመጣ ዝንጉርጉር ያልሆነ ወይም ነቁጣ የሌለበት ፍየል ብታገኝ፣ እንዲሁም ጥቁር ያልሆነ በግ ብታገኝ የተሰረቀ መሆኑን መረዳት ትችላልህ” አለው።
\v 34 ላባም፣ “እሺ አንተ ባልከው እስማማለሁ” አለ።
\s5
\v 35 ነገር ግን በዚያኑ ዕለት ከተባት ፍየሎች ሽመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቁጣ ያለባቸውን ሁሉ እንዲሁም ከእንስት ፍየሎች ነቁጣ ያለባቸውን ዝንጉርጉር የሆኑትን ሁሉ መረጠ፤ ደግሞም ጥቋቁር የሆኑትንም በጎች ሁሉ ለየና ወንዶች ልጆቹን አስጠበቃቸው።
\v 36 ከዚህ በኋላ ላባ መንጋውን ነድቶ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ከያዕቆብ ርቆ ሄደ፤ ያዕቆብም የቀሩትን የላባን መንጋዎች መጠበቁን ቀጠለ።
\s5
\v 37 ያዕቆብም ልብን፣ ለውዝና ኤርሞን ከሚባሉ ዛፎች እርጥብ በትሮችን ወሰደ፤ በበትሮቹ ያለው ነጭ እንዲታይ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው፤
\v 38 መንጋዎቹ ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ ከፊት ለፊት እንዲያዩአቸው የተላጡትን በትሮች በውሃ ማጠጫዎቹ ውስጥ አደረጋቸው። መንጎቹም ስሜታቸው ሲነሣሣና ውሃ ለመጠጣት ሲመጡ፣
\s5
\v 39 በትሮቹን ፊት ለፊት እያዩ ይሳረሩ ነበር፤ ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ የጣለባቸውንም ግልገሎች ወለዱ።
\v 40 ያዕቆብ እነዚህን ግልገሎች ለብቻ ለየ፤ የቀሩትን ግን ዝንጉርጉርና ጥቁር በሆኑት በላባ መጋዎች ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በዚህ ዓይነት የራሱን መንጋ ከላባ መንጋ ጋር ሳይቀላቅል ለብቻ አቆማቸው።
\s5
\v 41 ያዕቆብም ብርቱ እንስቶች አውራ ፈልገው በሚቅበጠበጡበት ጊዜ በትሮቹ አቅራቢያ እንዲጠቁ በትሮቹን በውሃ ገንዳዎች ውስጥ ፊት ለፊታቸው ያስቀምጥ ነበር፤
\v 42 ደካማ በሆኑት እንስቶች ፊት ግን በትሮቹን አያስቀምጥም ነበር፤ ስለዚህ ደካሞቹ ለላባ ሲሆኑ፣ ብርቱዎቹ ለያዕቆብ ሆኑ።
\s5
\v 43 በዚህም ሁኔታ ያዕቆብ እጅግ ባለጸጋ ሆነ፤ ብዙ መንጋዎች፤ ሴቶችና ወንዶች አገልጋዮች፣ ብዙ ግመሎችና አህዮችም ነበሩት።
\s5
\c 31
\p
\v 1 የላባ ወንዶች ልጆች፣ “ያዕቆብ የአባታችንን ሀብት እንዳለ ወስዶታል፤ ይህ ሁሉ እርሱ ያከማቸውም ሀብት ከአባታችን የተገኘ ነው” እያሉ ሲያወሩ ያዕቆብ ሰማ።
\v 2 በላባም ዘንድ እንደቀድሞ ተወዳጅ አለመሆኑን ተረዳ።
\v 3 እግዚአብሔርም ያዕቆብን፣ “ወደ አባቶችህ ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው።
\s5
\v 4 ስለዚህ ያዕቆብ መንጋዎቹ ወደ ተሰማሩበት መስክ እንዲመጡ ራሔልንና ልያን አስጠራቸው፤
\v 5 እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ ስለ እኔ ያለው አመለካከት እንደ ቀድሞ አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ ቢሆንም የአባቴ አምላክ አልተለየኝም፤
\v 6 መቼም ባለኝ አቅም አባታችሁን ማገልገሌን እናንተ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 7 አባታችሁ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ እየለዋወጠ አታልሎኛል፣ ሆኖም እንዲጎዳኝ እግዚአብሔር አልፈቀደለትም።
\v 8 እርሱ፣ ‘ደመወዝህ ዝንጉርጉሮቹ ይሆናሉ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ዝንጉርጉር ወለዱ’፤ ደግሞም፣ ‘ደመወዝህ ሽመልመሌዎቹ ይሆናሉ ሲለኝ፣ መንጎቹ ሁሉ ሽመልመሌ መልክ ያላቸውን ወለዱ፤
\v 9 ስለዚህ እግዚአብሔር የአባታችሁን ከብቶች ወስዶ ለእኔ ሰጠኝ።
\s5
\v 10 እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ መሆናቸውን በሕልም አየሁ።
\v 11 በዚያው ሕልም የእግዚአብሔር መልአክ፦ ‘ያዕቆብ’ ብሎ ጠራኝ፣ እኔም ‘እነሆ አለሁ’ አልሁ።
\s5
\v 12 እርሱም እንዲህ አለኝ፦ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፣ ዝንጉርጉርና ነቁጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፣ ላባ የፈጸመብህን በደል አይቻለሁ።
\v 13 የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።”
\s5
\v 14 ራሔልና ልያም እንዲህ ብለው መለሱለት፦ “ከአባታችን የምንወርሰው ድርሻ አለን?
\v 15 እርሱ እኛን የሚያየን እንደ ባዕዳን አይደለምን? ደግሞም እኮ እኛን ሽጦናል፣ የተሸጥንበትንም ዋጋ ራሱ በልቶታል።
\v 16 እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ።”
\s5
\v 17 ከዚያም ያዕቆብ ተነሥቶ ልጆቹንና ሚስቶቹን በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤
\v 18 በመስጴጦምያ ካፈራው ሀብት ሁሉ ጋር ከብቶቹን በሙሉ ወደፊት አስቀደመ፣ ወደ አባቱም ወደ ይስሐቅ አገር፣ ወደ ከነዓን ምድር ጉዞውን ቀጠለ።
\s5
\v 19 ላባ በጎቹን ሊሸልት ሄዶ ስለነበር፣ እርሱ በሌለበት ራሔል ከቤት የነበሩትን የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ ሄደች።
\v 20 ያዕቆብ መሄዱን ለላባ ሳይገልጥለት አታሎት ሄደ፣
\v 21 የራሱ የሆነውን ሀብት ይዞ በፍጥነት ታጓዘ፤ የኤፍራጥስንም ወንዝ ተሻግሮ ወደ ኮረብታማው አገር ወደ ገለዓድ ሄደ።
\s5
\v 22 ያዕቆብ መኮብለሉን ለላባ በሦስተኛው ቀን ተነገረው።
\v 23 ከዘመዶቹ ጋር ሆኖ ያዕቆብን ተከታተለው፤ ሰባት ቀን ከተጓዙ በኋላ ገለዓድ በተባለው ተራራማ አገር ላይ ሊደርስበት ተቃረበ።
\s5
\v 24 በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ለላባ በሕልም ተገለጠለትና “ያዕቆብን ክፉም ሆን ደግ እንዳትናገረው ተጠንቀቅ” አለው።
\v 25 ያዕቆብ ገለዓድ በተባለው ኮረብታማ ስፍራ ድንኳኑን በመትከትል ሰፍሮ ሳለ ላባ ደረሰበት፤ ላባና ዘመዶቹም እዚያው ድንኳናቸውን ተክለው ሰፈሩ።
\s5
\v 26 ከዚህ በኋላ ላባ ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ስለምን እንዲህ አድርገህ አታለልኸኝ፤ ሴቶች ልጆቼንስ በጦርነት እንደተማረኩ ያህል ይዘሃቸው ለምን ሄድህ?
\v 27 ሳትነግረኝ ተሰውረህ በመሄድ ለምን አታለልኽኝ? ነግረኸኝ ቢሆን በከበሮና በመስንቆ እየተዘፈነ በደስታ በሸኘሁህ ነበር።
\v 28 ልጆቼንና የልጅ ልጆቼን በመሳም እንድሰናበታቸው ባለማድረግህ የሞኝነት ተግባር ፈጽመሃል።
\s5
\v 29 ጉዳት ሳደርስብህ እችል ነበር፣ ነገር ግን ባለፈው ሌሊት የአባትህ አምላክ፣ ‘ያዕቆብን ክፉም ሆነ ደግ አንድ ቃል እንዳትናገረው’ ብሎ አስጠነቀቀኝ፣
\v 30 ወደ ትውልድ አገርህ ለመመለስ ባለህ ብርቱ ፍላጎት እንደተለየኸኝ አውቃለሁ፣ ታዲያ የቤቴን ጣዖቶች የሰረቅኽብኝ ለምንድነው?”
\s5
\v 31 ለላባ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ሴቶች ልጆችህን በኃይል ነጥቀህ ታስቀርብኛለህ ብዬ ስለ ፈራሁ ነው በድብቅ የሄድኩት።
\v 32 ነገር ግን ከእኛ መካከል የአንተን የጣዖት ምስል የሰረቀ ሰው ካለ ይሙት። የአንተ የሆነ አንዳች ነገር ከኔ ዘንድ ቢገኝ፣ አንተው ራስህ ዘመዶቻችን ባሉበት ፈልግና ውሰድ።” እንደዚህ ሲል ራሔል የጣዖታቱን ምስል መስረቋን ያዕቆብ አያውቅም ነበር።
\s5
\v 33 ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን እንዲሁም ወደ ሁለቱ ደንገጡሮቹ ድንኳን ገባ፤ ነገር ግን ምንም አላገኘም። ከልያ ድንኳን ከወጣ በኋላ ወደ ራሔል ድንኳን ገባ።
\s5
\v 34 ራሔል ግን ጣዖቱቹን ወስዳ በግመሉ ኮርቻ ሥር በመሰወር በላያቸው ተቀምጣባቸው ነበር። ላባ በድንኳኑ ውስጥ ያለውን ጓዝ ሁሉ በርብሮ ምንም ነገር አላገኘም።
\v 35 ራሔልም አባቷን፦ “በፊትህ ተነሥቼ መቆም ስላልቻልሁ፣ ጌታዬ አትቆጣ የወር አበባዬ መጥቶ ነው” አለችው፤ ስለዚህ በረበረ፤ የጣዖቱን ምስል ግን ማግኘት አልቻለም።
\s5
\v 36 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ ተቆጣ፤ ላባንም እንዲህ ሲል ወቀሰው፦ “እስቲ ወንጀሌ ምንድን ነው? ይህን ያህል የምታሳድደኝ ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው?
\v 37 ዕቃዬን አንድ በአንድ በርብረሃል፤ ታዲያ የአንተ ሆኖ ያገኘኸው ዕቃ የትኛው ነው? ካለ፣ እስቲ በአንተም በእኔም ዘመዶች ፊት አቅርብና እነርሱ ያፋርዱን።
\s5
\v 38 ሃያ ዓመት አብሬህ ኖሬአለሁ፤ በጎችህና ፍየሎችህ አልጨነገፉም፤ ከመንጋህም አንድ ጠቦት እንኳ አልበላሁም።
\v 39 አውሬ የሰበረውንም ቢሆን እተካ ነበር፣ በቀንም ሆነ በሌሊት የተሰረቁትን ሁሉ ስታስከፍለኝ ኖረሃል።
\v 40 ብዙ ጊዜ በቀን ሐሩርና በሌሊት ቁር እሠቃይ ነበር፤ በቂ እንቅልፍ ያገኘሁበት ጊዜ አልነበረም።
\s5
\v 41 ሃያ ዓመት በቤትህ የኖርሁት በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ዐሥራ አራት ዓመት ለሁለቱ ልጆችህ ብዬ አገለገልሁ፤ ስድስት ዓመት ስለመንጋዎችህ ስል አገለገልሁ፤ ይህም ሆኖ ደመወዜን ዐሥር ጊዜ ለዋውጠኽብኛል።
\v 42 የአባቴ አምላክና እርሱም የሚፈራው የአብርሃም አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን ሰድደኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን መከራዬን ዐይቶ፣ ልፋቴን ትመልክቶ ትናንት ሌሊት ገሠጸህ።”
\s5
\v 43 ላባም ለያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እነዚህ ሴቶች የእኔው ልጆች ናቸው፤ ልጆቻቸውም የእኔ ናቸው፤ እነዚህም መንጋዎች የእኔ ናቸው፤ ይህ የምታየው ሁሉ የራሴ ነው፤ ታዲያ በእነዚህ ሴቶች ልጆቼና በወለዷቸው ልጆቻቸው ላይ ዛሬ ምን ማድረግ እችላለሁ?
\v 44 በል አሁን ቃል ኪዳን እንጋባ፤ ኪዳኑም በአንተና በእኔ መካከል ምስክር ይሁን።”
\s5
\v 45 ያዕቆብም ድንጋይ ውስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፤
\v 46 ከዚያም ዘመዶቹን “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው። እነርሱም ድንጋይ እያመጡ ከመሩ፤ በክምሩም አጠገብ ምግብ በሉ።
\v 47 ላባም ክምር ድንጋዩን ይጋርሠሀዱታ ብሎ ጠራው፤ ያዕቆብ ደግሞ ገለዓድ አለው።
\s5
\v 48 ላባም “ይህ ክምር ድንጋይ በእኔና በአንተ መካከል ዛሬ ምስክር ነው” አለው። ገለዓድ ተብሎ የተጠራውም በዚሁ ምክንያት ነው፤
\v 49 ደግሞም ምጽጳ ተባለ ምክንያቱም ላባ እንዲህ ብሎአልና፤ “እንግዲህ ከዚህ በምንለያይበት ጊዜ እግዚአብሔር እኔንና አንተን ይጠብቀን፤
\v 50 ልጆቼን ብትበድላቸው ወይም ሌሎችን በላያቸው ብታገባ፣ ማንም ከእኛ ጋር ባይኖርም እንኳ እግዚአብሔር በአንተና በእኔ መካከል ምስክር መሆኑን አትርሳ።”
\s5
\v 51 ላባም ያዕቆብን እንዲህ አለው፦ “ክምር ድንጋዩ እነሆ፤ በአንተና በእኔ መካካል ያቆምሁትም ሐውልት እነሆ፤
\v 52 ይህን ክምር ድንጋይ አልፌ አንተን ለማጥቃት ላልመጣ፣ አንተም ይህን ክምር ድንጋይና ይህን ሐውልት አልፈህ እኔን ለማጥቃት ላትመጣ፤ ይህ ክምር ድንጋይ ምስክር ነው፤ ይህም ሐውልት ምስክር ነው።
\v 53 የአብርሃም አምላክ፣ የናኮር አምላክ፣ የአባታቸውም አምላክ በመካከላችን ይፍረድ።” ስለዚህ ያዕቆብ አባቱ ይስሐቅ በሚፈራው በእግዚአብሔር ማለ።
\s5
\v 54 ያዕቆብ በኮረብታማው አገር ላይ መሥዋዕት አቀረበ፤ ዘመዶቹንም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው፤ እነርሱም ከበሉ በኋላ እዚያው አደሩ።
\v 55 በማግስቱም ማለዳ ላባ የልጅ ልጆቹን እንዲሁም ሴቶች ልጆችን ስሞ መረቃቸው፤ ከዚያም ወደ አገሩ ተመለሰ።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ያዕቆብ በጉዞ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መላእክት በመንገድ ተገናኙት።
\v 2 ባያቸውም ጊዜ፤ “ይህ የእግዚአብሔር ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦት ስም መሃናይም አለው።
\s5
\v 3 ያዕቆብም በኤዶም አገር ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤
\v 4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፤ “ጌታዬን ዔሳውን እንዲህ ትሉታላችሁ፤ ‘አገልጋይህ ያዕቆብ እንዲህ ብሎአል በሉት፤ ከላባ ዘንድ ተቀምጬ እስካሁን ድረስ እዚያው ኖርሁ፤
\v 5 ከብቶች፣ አህዮች፣ የበግና የፍየል መንጎች እንደዚሁም የወንድን የሴት አገልጋዮች አሉኝ፤ አሁንም ይህን መልእክት ለጌታዬ መላኬ በአንተ ዘንድ ሞግስ አገኛለሁ በሚል ተስፋ ነው።’”
\s5
\v 6 የተላኩትም ሰዎች ወደ ያዕቆብ ተመልሰው፣ “ወደ ወንድምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እርሱም ከአንት ጋር ለመገናኘት በመምጣት ላይ ነው፤ ከእርሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ” አሉት።
\v 7 በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እጅግ በመፍራት ተጨነቀ፤ አብረውት የነበሩትንም ሰዎች በሁለት ክፍል መደባቸው፤ እንዲሁም በጎቹን፣ ፍየሎቹን፣ ከብቶቹንና ግመሎቹን በሁለት በሁለት መደባቸው።
\v 8 ይህንንም ያደረገው፦ “ዔሳው የመጀመሪያውን ክፍል ቢያጠቃ፣ ሌላው ክፍል ሊያመልጥ ይችላል” ብሎ በማሰብ ነው።
\s5
\v 9 ያዕቆብ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ፣ የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ሆይ፣ ‘ወደ አገርህና ወደ ዘመዶችህ ተመልስ፣ እኔም በጎ ነገር አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፣
\v 10 እኔ ባሪይህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በስተቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሠራዊት ሆኛለሁ።
\s5
\v 11 ከወንድሜ ከዔሳው እጅ እንድታድነኝ እለምንሃለሁ፤ መጥቶ እኔንም ሆነ እነዚህን እናቶች ከነልጆቻቸው ያጠፋናል ብዬ ፈርቻለሁኝ፤
\v 12 ነገር ግን አንተ ራስህ፣ ‘አበለጽግሃለሁ፤ ዘርህንም ሊቆጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ አበዛዋለሁ’ ብለኸኛል።”
\s5
\v 13 በዚያችም ሌሊት ያዕቆብ እዚያው አደረ፤ ካለው ሀብት ለወንድሙ ለኤሳው እጅ መንሻ እንዲሆኑ እነዚህን መረጠ፦
\v 14 ሁለት መቶ እንስት ፍየሎችና ሃያ አውራ ፍየሎች፣ ሁለት መቶ እንስት በጎችና ሃያ አውራ በጎች፣
\v 15 ሠላሳ የሚያጠቡ ግመሎች ከነግልገሎቻቸው፣ አርባ ላሞችና ዐሥር ኮርማዎች፣ ሃያ እንስት አህዮችና ዐሥር ተባት አህዮች።
\v 16 እነዚህንም በየመንጋው ለይቶ፣ የሚነዱአቸውን ጠባቂዎች መደበላቸው፤ ጠባቂዎችንም እናንተ ቀድማችሁ ሂዱ፣ መንጋዎቹንም አራርቃችሁ ንዱአቸው” አላቸው።
\s5
\v 17 ቀድሞ የሚሄደውንም እንዲህ ሲል አዘዘው፤ ዔሳው አግኝቶህ ‘የማን ነህ? ወዴትስ ትሄዳለህ? የምትነዳውስ ይህ ሁሉ ከብት የማን ነው? ብሎ ቢጠይቅህ፣
\v 18 ‘የአገልጋይህ የያዕቆብ ናቸው፤ ለጌታዬ ለዔሳው እጅ መንሻ የሰደዳቸው ናቸው፤ እርሱም ከበስተኋላችን እየመጣ ነው’ ብለህ ንገረው
\s5
\v 19 እንዲሁም ሁለተኛውን፣ ሦስተኛውንና መንጎቹን የሚነዱትን ሌሎቹንም ሁሉ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ ‘ዔሳውን ስታገኙት ይህንኑ ትነግሩታላችሁ፤
\v 20 በተጨማሪም ‘አገልጋይህ ያዕቆብ ከኋላችን እየመጣ ነው’ በሉት። ይህንንም ያዘዘው፣ ‘ዔሳው ከእኔ ጋር ከመገናኘቱ በፊት እጅ መንሻዬ አስቀድሞ ቢደርሰው ምናልባት ልቡ ይራራና በሰላም ይቀበለኛል’ ብሎ ስላሰበ ነበር።
\v 21 ስለዚህ የያዕቆብ እጅ መንሻ ከእርሱ አስቀድሞ ተላከ፤ እርሱ ራሱ ግን እዚያው በሰፈሩ ቦታ አደረ።
\s5
\v 22 በዚያኑ ሌሊት ያዕቆብ ተነሣ ሁለቱን ሚስቶቹን፣ ሁለቱን ሴት አገልጋዮቹንና ዐሥራ አንዱን ልጆቹን ይዞ የያቦቅን ወንዝ ተሻገረ።
\v 23 ወንዙን አሻግሮ ከሸኛቸው በኋላ፣ ጓዙን ሁሉ ሰደደ።
\s5
\v 24 ያዕቆብም ብቻውን እዚያ ቀረ፤ አንድ ሰውም እስኪነጋ ድረስ ሲታገለው አደረ።
\v 25 ያም ሰው ያዕቆብን ታግሎ ማሸነፍ እንዳቃተው በተረዳ ጊዜ፣ የጭኑን ሹልዳ መታው፣ ያዕቆብም በሚታገልበት ጊዜ ጭኑ ከመገጣጠሚያው ላይ ተለያየ፤
\v 26 በዚያን ጊዜ ሰውዬው፣ “እንግዲህ መንጋቱ ስለሆን ልቀቀኝና ልሂድ” አለው። ያዕቆብም፣ “ካልባረክኸኝ አልለቅህም” አለው።
\s5
\v 27 ሰውዬውም፣ “ስምህ ማን ነው? ” አለው። እርሱም፣ “ያዕቆብ ነው” አለ።
\v 28 ሰውዬውም፣ “ከእግዚአብሔርም ከሰዎችም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና ከእንግዲህ ስምህ እስራኤል እንጂ ያዕቆብ አይባልም” አለው።
\s5
\v 29 ያዕቆብም፣ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። ሰውዬውም፣ “ስሜን ለማወቅ ለምን ፈለግህ? ” አለው፤ በዚያም ስፍራ ባረከው።
\v 30 ስለዚህ ያዕቆብ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ዐይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል አለው።
\s5
\v 31 ጵኒኤልንም እንዳለፈ ፀሐይ ወጣችበት፣ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።
\v 32 ከዚህም የተነሣ የእስራኤል ልጆች ሹልዳን ከጭኑ ጋር የሚያገናኘውን ሥጋ አይበሉም፤ ምክንያቱም ያዕቆብ ከሰውዬው ጋር ሲታገል ሰውዬው ሹልዳውን መትቶት ስለነበር ነው።
\s5
\c 33
\p
\v 1 ያዕቆብ አሻግሮ ተመለከተ፤ እነሆ፣ ዔሳው አራት መቶ ሰዎች አስከትሎ እየመጣ ነበር። ስለዚህ ያዕቆብ ልጆቹን ለልያ ለራሔልና ለሁለቱ አገልጋዮቹ አከፋፈላቸው።
\v 2 ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ።
\v 3 እርሱ ራሱም ቀድሞአቸው ሄደ፤ ወንድሙም ዘንድ እስኪደርስ ድረስ ሰባት ጊዜ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ።
\s5
\v 4 ዔሳው ግን ሊገናኘው ወደ እርሱ ሮጦ ሄዶ አቀፈው፤ በአንገቱም ላይ ተጠምጥሞ ሳመው፤ ሁለቱም ተላቀሱ።
\v 5 ከዚያም ዔሳው ቀና ብሎ ሲመለከት ሴቶቹንና ልጆቹን ዐየ፤ እርሱም፣ “እነዚህ አብረውህ ያሉ እነማን ናቸው? ” ብሎ ጠየቀው። ያዕቆብም መልሶ፣ “እነዚህማ እግዚአብሔር በቸርነቱ ለእኔ ለአገልጋይህ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” አለው።
\s5
\v 6 በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሴት አገልጋዮችና ልጆቻቸው ቀርበው እጅ ነሡ፤
\v 7 ከዚያም ልያና ልጆቿ መጥተው እጅ ነሡ፤ በመጨረሻም ዮሴፍና ራሔል መጡ፤ እነርሱም ቀርበው እጅ ነሡ።
\v 8 ዔሳውም፣ “ወደ እኔ ተነድቶ የመጣው ይህ ሁሉ መንጋ ምንድነው? ” አለው። ያዕቆብም፣ “ጌታዬ ሆይ፣ በአንተ ዘንድ ሞገስ ባገኝ ብዬ ነው” አለው።
\s5
\v 9 ዔሳው ግን፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እኔ በቂ አለኝ፤ የራስህን ለራስህ አድርገው” አለው።
\v 10 ያዕቆብም፣ “የለም፣ እንዲህ አይደለም፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፣ እጅ መንሻዬን ተቀበል፤ በመልካም ሁኔታ ተቀብለኸኝ ፊትህን ማየት መቻሌ ራሱ፣ የእግዚአብሔርን ፊት የማየት ያህል እቆጥረዋለሁ።
\v 11 እግዚአብሔር በቸርነቱ አሟልቶ ስለ ሰጠኝ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝና ያቀረብሁልህን እጅ መንሻ እባክህ ተቀበለኝ” አለው። ያዕቆብ አጥብቆ ስለለመነው፣ ዔሳው እጅ መንሻውን ተቀበለ።
\s5
\v 12 ዔሳውም፣ “እንግዲህ እንሂድ፤ እኔም ከአንተ ቀድሜ እሄዳለሁ” አለው።
\v 13 ያዕቆብ ግን እንዲህ አለው፤ “ጌታዬ እንደምታየው ልጆቹ ይህን ያህል የጠኑ አይደሉም፣ ለሚያጠቡት በጎችና ጥገቶች እንክብካቤ ማድረግ አለብኝ፤ እንስሳቱ ለአንዲት ቀን እንኳ በጥድፊያ ቢነዱ በሙሉ ያልቃሉ።
\v 14 ስለዚህ ጌታዬ፣ አንተ ቀድመኸኝ ሂድ፤ እኔም በምነዳቸው እንስሳትና በልጆቹ ጉዞ አቅም ልክ እያዘገምሁ ሴይር ላይ እንገናኛለን”
\s5
\v 15 ዔሳው፣ “እንግዲያስ ከሰዎቼ ጥቂቶቹን ልተውልህ” አለው። ያዕቆብ ግን፣ “ለምን ብለህ? በአንተ ዘንድ ሞገስ ማግኘቴ ይበቃኛል” አለው።
\v 16 ስለዚህ ዔሳው በዚሁ ዕለት ወደ ሴይር ለመመለስ ተነሣ።
\v 17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ።
\s5
\v 18 ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሴኬም በሰላም ደረሰ፤ በከተማይቱም ፊት ለፊት ሰፈረ።
\v 19 ድንኳኑን የተከለበትንም ቦታ የሴኬም አባት ከነበረው ከኤሞር በመቶ ጥሬ ብር ገዛው፤
\v 20 በዚያም መሠዊያ አቁሞ፤ ኤል ኤሎሄ እስራኤል ብሎ ጠራው።
\s5
\c 34
\p
\v 1 ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ሴት ልጅ ዲና፤ አንድ ቀን የዚያን አገር ሴቶች ለማየት ወጣች።
\v 2 የአገሩ ገዥ የኤዊያዊ የኤሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ።
\v 3 ልቡ በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ልጅቷንም በጣም ወደዳት፤ በጣፈጠም አንደበት አናገራት።
\s5
\v 4 ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፣ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው።
\v 5 ያዕቆብ የልጁን የዲናን ክብረ-ንጽሕና ሴኬም እንደደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለነበር፣ እነርሱ እስኪመጡ ዝም ብሎ ቆየ፤
\s5
\v 6 ከዚያም የሴኬም አባት ኤሞር፣ ያዕቆብን ሊያነጋግረው ወጣ።
\v 7 የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም የተፈጸመውን ድርጊት እንደሰሙ ወዲያውኑ ከመስክ መጡ፤ ሴኬም መደረግ የማይገባውን አስነዋሪ ነገር በእስራኤል ላይ በመፈጸም የያዕቆብን ልጅ ስለደፈረ አዘኑ እጅግም ተቆጡ።
\s5
\v 8 ኤሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዶአታል፤ ስለዚህ እንዲያገባት ፍቀዱለት፤
\v 9 በጋብቻ እንተሳሰር፣ ሴት ልጃችህን ስጡን፣ የእኛንም ሴቶች አግቡ።
\v 10 አብራችሁንም መኖት ትችላላችሁ፤ አገራችን አገራችሁ ናት፣ ኑሩባት፤ ነግዱባት፣ ሀብት ንብረትም አፍሩባት።
\s5
\v 11 ሴኬም ደግሞ የዲናን አባትን ወንድሞች እንዲህ አላቸው። “በእናንተ ዘንድ ሞገስ ላግኝ እንጂ የተጠየቅሁትን ሁሉ እሰጣለሁ፤
\v 12 ለሙሽራዋም ጥሎሽ የፈለጋችሁትን ያህል ጠይቁኝ፤ እርሷን እንዳገባ ፍቀዱልኝ እንጂ፣ የፈለጋችሁትን ሁሉ ለመጠት ዝግጁ ነኝ።”
\v 13 ሴኬም እኅታቸውን ዲናን አስነውሮ ስለነበር የያዕቆብ ልጆች ለእርሱና ለአባቱ በተንኮል እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፣
\s5
\v 14 እንዲህ አሉአቸው፤ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ብንሰጥ ውርደት ስለሚሆንብን፣ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም።
\v 15 ሆኖም የምንስማማበት አንድ መንገድ ብቻ አለ፤ ይኸውም አንተና በእናንተ ዘንድ ያሉት ወንዶች ሁሉ እንደኛ የተገረዛችሁ እንደሆነ ነው።
\v 16 እንዲህ ከሆነ እናንተ የእኛን ሴቶች ልጆች ታገባላችሁ፣ እኛም የእናንተን ሴቶች ልጆች እናገባለን፣ አንድ ሕዝብ ሆነንም አብረን እንኖራለን።
\v 17 ዐሳባችንን ባትቀበሉና ባትገረዙ ግን እኅታችንን ይዘን እንሄዳለን።
\s5
\v 18 ያቀረቡትም ዐሳብ ለኤሞርና ለልጁ ለሴኬም መልካም መስሎ ታያቸው።
\v 19 ከአባቱ ቤተሰብ ሁሉ እጅግ የተከበረው ይህ ወጣት የያዕቆብን ልጅ እጅግ ወዶአት ስለነበር፣ ያሉትን ለማድረግ ጊዜ አልወሰደበትም።
\s5
\v 20 ስለዚህ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ይህንኑ ለወገኖቻቸው ለመንገር ወደ ከተማቸው በር ሄዱ፤
\v 21 እንዲህም አሏቸው፤ “እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር የሚኖሩት በሰላም ነው፣ በምድሪቱ ላይ አብረው ይቀመጡ፣ ተዘዋውረውም እንዲነግዱ እንፍቀድላቸው፤ ምድሪቱ እንደሆን ለእኛም ለእነርሱም ትበቃለች። ሴቶች ልጆቻቸውን እናገባለን፤ እነርሱም የእኛን ሴቶች ልጆች ያገባሉ፤
\s5
\v 22 ሆኖም ሰዎቹ ከእኛ ጋር እንደ አንድ ሕዝብ ሆነው አብረውን ለምኖር ፈቃደኞች የሚሆኑት፣ የእኛ ወንዶች እንደ እነርሱ የተገረዙ እንደሆነ ብቻ ነው።
\v 23 ታዲያ እንዲህ ብናደርግ ከብታቸው ንብረታቸው፣ እንስሶቻቸውም ሁሉ የእኛው ይሆኑ የለምን? ስለዚህ ባሉት እንስማማ፣ እነርሱም አብረውን ይኑሩ።”
\s5
\v 24 የከተማይቱ ነዋሪዎች ሁሉ ኤሞርና ሴኬም ባቀረቡት ዐሳብ ተስማምተው ወንዶቹ ሁሉ ተገረዙ።
\v 25 በሦስተኛውም ቀን የሁሉም ቁስል ገና ትኩስ ሳለ ከያዕቆብ ልጆች ሁለቱ፣ የዲና ወንድሞች ስምዓንና ሌዊ፣ ሰይፋቸውን መዘው ሳይታሰብ ወደ ከተማይቱ ገብተው ወንዶቹን በሙሉ ገደሏቸው።
\v 26 ኤሞርንና ሴኬምንም በሰይፍ ገድለው፣ እኅታቸውን ዲናን ከሴኬም ቤት አውጥተው ይዘዋት ተመለሱ።
\s5
\v 27 የቀሩትም የያዕቆብ ልጆች እኅታቸውን ስለደፈሩባቸው ወደ ሞቱት ሰዎች ቤት እየገቡ ከተማይቱን በሙሉ ዘረፉ።
\v 28 የበግና የፍየል መንጎቻቸውን፣ ከብቶቻቸውንና አህዮቻቸውን እንዲሁም በከተማይቱና በአካባቢው የሚገኘውን ንብረታቸውን ሁሉ ወሰዱባቸው፤
\v 29 ሀብታቸውን ሁሉ ዘርፈው ሴቶቻቸውንና ሕፃናቶቻቸውን ሁሉ ማርከው በየቤቱ ያገኙትን ሁሉ ይዘው ሄዱ።
\s5
\v 30 ያዕቆብ ስምዖንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ፣ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፌርዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቁጥር አነስተኞች ነን፣ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።”
\v 31 ስምዖንና ሌዊ ግን፣ “ታዲያ ሴኬም እኅታችንን እንደዝሙት አዳሪ ይድፈራትን? ” አሉት።
\s5
\c 35
\p
\v 1 እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሣና ወደ ቤቴል ሂድ፣ እዚያም ኑር። ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ አለው።
\v 2 ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና አብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ።
\v 3 ተነሥተን ወደ ቤቴል እንሂድ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።
\s5
\v 4 ስለዚህ በእነርሱ ዘንድ የነበሩትን ባዕዳን አማልክት ሰብስበው፣ የጆሮ ጉትቾቻቸውን አውልቀው ለያዕቆብ ሰጡት። ያዕቆብም ወስዶ ሴኬም አጠገብ ካለው ዋርካ ዛፍ ሥር ቀበራቸው።
\v 5 ያንንም ቦታ ለቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሃትና ድንጋጤ ስለለቀቀባቸው ያሳደዳቸው አልነበረም።
\s5
\v 6 ያዕቆብና አብረውት የነበሩት ሰዎች ሁሉ በከነዓን ወደምትገኘው፣ ቤቴል ወደተባለችው ወደ ሎዛ ደረሱ።
\v 7 ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል ቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር።
\v 8 በዚህ ጊዜ የርብቃ ሞግዚት ዲቦራ ሞተች፣ ከቤቴል ዝቅ ብሎ በሚገኘው የዋርካ ዛፍ ሥር ተቀበረች። ከዚህ የተነሣም ያ ቦታ አሉንባኩት ተባለ።
\s5
\v 9 ያዕቆብ ከመስጴጦምያ በተመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ዳግመኛ ተገለጠለትና ባረከው።
\v 10 እግዚአብሔርም፣ “እስካሁን ስምህ ያዕቆብ ነበር፤ ከእንግዲህ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም፤ ነገር ግን ስምህ እስራኤል ይባላል” አለው። ስለዚህም እስራኤል ብሎ ጠራው።
\s5
\v 11 ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉም ማድረግ የሚችል አምላክ ነኝ፤ ብዙ ልጆች ይኑሩህ፤ ዘርህም ይብዛ፤ የብዙ ሕዝብ አባት ሁን፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወለዱ።
\v 12 ለአብርሃምና ለይስሐቅ የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ፤ ከአንተም በኋላ ይህችን ምድር ለዘርህ አሰጣለሁ።”
\v 13 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ከዚያ ስፍራ ወደ ላይ ወጣ።
\s5
\v 14 ያዕቆብ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ስፍራ የድንጋይ ሐውልት አቆመ፣ በሐውልቱ ላይ የመጠጥ ቁርባን አፈሰሰ፤ ዘይትም አፈሰሰበት።
\v 15 ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው።
\s5
\v 16 ከዚያም ከቤቴል ተነሥተው ሄዱ፤ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፣ ምጡም ጠናባት።
\v 17 ምጧ እየበረታ በሄደ ጊዜ አዋላጅቱ፣ “አይዞሽ አትፍሪ፤ ሌላ ወንድ ልጅ ልትወልጂ ነው” አለቻት።
\v 18 እርስዋ ግን ልትሞት ታጣጥር ስለነበር ከመሞቷ በፊት ልጅዋን ‘ቤንኦኒ’ አለችው፤ አባቱ ግን ‘ብንያም’ አለው።
\v 19 ራሔል ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ በሚወስደው መንገድ በቤተልሔም ተቀበረች።
\v 20 ያዕቆብም በራሔል መቃብር ላይ ሐውልት አቆመ፤ እስከዛሬም የራሔል መቃብር ምልክት ይኸው ሐውልት ነው።
\s5
\v 21 ያዕቆብ ጉዞውን ቀጥሎ በዔዴር ግንብ ባሻገር ድንኳን ተክሎ ሰፈረ።
\v 22 ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፣ ሮቤል ከአባቱ ቁባት ከባላ ጋር የግብረሥጋ ግንኙነት አደረገ፤ ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆች ነበሩት፣ እነርሱም፦
\s5
\v 23 የልያ ልጆች፦ የያዕቆብ የበኩር ልጅ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤
\v 24 የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍ፣ ብንያም፤
\v 25 የራሔል አገልጋይ የባላ ልጆች፦ ዳን፣ ንፍታሌም፤
\s5
\v 26 የልያ አገልጋይ የዘለፋ ልጆች፦ ጋድ፣ አሴር፣ ናቸው። እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በመስጴጦምያ ሳለ የተወለዱለት ናቸው።
\v 27 ያዕቆብ በቂርያት አርባቅ (በኬብሮን) አጠገብ መምሬ በምትባል ስፍራ ወደሚኖረው አባቱ ወደ ይስሐቅ ሄደ፤ ይህም ስፍራ አብርሃምና ይስሐቅ የኖሩበት ነው።
\s5
\v 28 ይስሐቅ መቶ ሰማንያ ዓመት ኖረ፤
\v 29 አርጅቶ ዕድሜ ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገኖቹ ተሰበሰበ፤ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
\s5
\c 36
\p
\v 1 ኤዶም የተባለው የዔሳው የትውልድ ታሪክ የሚከተለው ነው፤
\v 2 ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የኬጢያዊው የዔሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤውያዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳት አህሊባማ፣
\v 3 እንዲሁም የነባዮት እኅት የሆነችውን የእስማኤል ልጅ ቤስሞት ነበሩ።
\s5
\v 4 ዓዳ ለዔሳው ኤልፋዝን ወለደችለት።
\v 5 እንደዚሁም አህሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆቹ ናቸው።
\s5
\v 6 ዔሳው ሚስቶቹንና ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።
\v 7 ብዙ ሀብት ስለነበራቸው አብረው መኖር አልቻሉም፣ የነበሩበትም ስፍራ ከከብቶቻቸው ብዛት የተነሣ ሊበቃቸው አልቻለም።
\v 8 ስለዚህ ዔዶም የተባለው ዔሳው መኖሪያውን በተራራማው አገር በሴይር አደረገ።
\s5
\v 9 በተራራማው አገር በሴይር የሚኖሩ የኤዶማውያን አባት፣ የዔሳው ዝርያዎች እነዚህ ናቸው፤
\v 10 የዔሳው ልጆች ስም፦ የዔሳው ሚስት የዓዳ ልጅ ኤልፋዝና የዔሳው ሚስት የቤሴሞት ልጅ ራጉኤል፤
\v 11 የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤
\v 12 የዔሳው ልጅ ኤልፋዝ ትምናዕ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ እርሷም አማሌቅን ወለደችለት፤ የዔሳው ሚስት የዓዳ የልጅ ልጆች እነዚህ ናቸው።
\s5
\v 13 የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሣማና ሚዛህ፤ እነዚህም ደግሞ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ናቸው።
\v 14 የፅብዖን የልጅ ልጅ፤ የዓና ልጅ የዔሳው ሚስት አህሊባማ ለዔሳው የወለደቻቸው ልጆች፦ የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤
\s5
\v 15 ከዔሳው ዝርያዎች እነዚህ የነገድ አለቆች ነበሩ፤ የዔሳው የበኩር ልጅ የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ቄኔዝ
\v 16 ቆሬ፣ ጎቶምና አማሌቅ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከኤልፋዝ የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዓዳ የልጅ ልጆች ነበሩ።
\s5
\v 17 የዔሳው ልጅ የራጉኤል ልጆች፦ ናሖት፣ ዛራ፣ ሃማና፣ ሚዛህ፤ እነዚህ በኤዶም ምድር ከራጉኤል የተገኙ የነገድ አለቆች፣ የዔሳው ሚስት የቤሴሞት የልጅ ልጆች ነበሩ።
\v 18 የዔሳው ሚስት የአሕሊባማ ልጆች፦የዑስ፣ የዕላማና ቆሬ፤ እነዚህ ከዓና ልጅ ከዔሳው ሚስት አሕሊባማ የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ።
\v 19 እነዚህም ኤዶም የተባለው የዔሳው ልጆችና የነገድ አለቆቻቸው ነበሩ።
\s5
\v 20 በኤዶም ምድር ነዋሪዎች የነበሩት የሴይር ልጆች የነበሩ የሖራውያን አለቆች፦ ሎጣን፣ ሦባል፣ ፅብዖን፣ ዓና፣
\v 21 ዲሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በኤዶም የነበረው የሴይር ልጆች፣ በሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
\v 22 የሎጣን ልጆች፦ ሖሪና ሔማም የሎጣንም እኅት ቲምናዕ ትባል ነበር።
\s5
\v 23 የሦባል ልጆች፦ ዓልዋን፣ ማኔሐት፣ ዔባልና ስፎና አውናንም፤
\v 24 የፅብዖን ልጆች፦ አያና፣ ዓና፤ ይህ ዓና የአባቱን የፅባዖንን አህዮች ሲጠብቅ፣ የፍልውሃ ምንጮችን በምድረበዳ ያገኘ ሰው ነው።
\s5
\v 25 የዓና ልጆች፦ዲሶንና የዓና የሴት ልጅ አህሊባማ፤
\v 26 የዲሶን ልጆች፦ ሔምዳን፣ ሴስባን፣ ይትራንና ክራን፤
\v 27 የኤድር ልጆች፦ ቢልሐን፣ ዛዕዋንና ዓቃን፤
\v 28 የዲሳን ልጆች፦ዑፅና አራን።
\s5
\v 29 የሖራውያን የነገድ አለቆች እነዚህ ነበሩ፦ሎጣን፣ ሦባል፣ፅዖን፥ ዓና፣
\v 30 ዶሶን፣ ኤድርና ዲሳን፤ እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖራውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።
\s5
\v 31 ንጉሥ በእስራኤል ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ነበሩ፦
\v 32 የቢዖር ልጅ ባላቅ በኤዶም ነግሦ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር።
\v 33 ባላቅ ሲሞት፣ በስፍራውም የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ነገሠ።
\s5
\v 34 የባሶራው የዛራ ልጅ ኢዮባብ ሲሞት የቴማኒው ሑሳም ነገሠ።
\v 35 ሑሳም ሲሞት፣ የምድያምን ሰዎች በሞዓብ ምድር ድል ያደረጋቸው የባዳድ ልጅ ሃዳድ በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ዓዊት ይባል ነበር።
\v 36 ሃዳድ ሲሞት፣ የመሥሬቃው ሠምላ በምትኩ ነገሠ።
\s5
\v 37 ሠምላ ሲሞት፣ በወንዙ አጠገብ ያለው የርሆቦቱ ሳኦል በምትኩ ነገሠ።
\v 38 ሳኦል ሲሞት፣ የዓክቦር ልጅ በልሐናን በምትኩ ነገሠ።
\v 39 የዓክቦር ልጅ በልሐናን ሲሞት፣ ሃዳር በምትኩ ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፋዑ ይባል ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣብዔል ሲሆን፣ እርሷም መጥሬድ የወለደቻት የሜዛሃብ ልጅ ነበረች።
\s5
\v 40 ከዔሳው የተገኙት የነገድ አለቆች ስም፣ እንደየነገዳቸውና እንደየአገራቸው ይህ ነው፦ ቲምናዕ፣ ዓለዋ፣ የቴት፣
\v 41 አህሊባማ፣ ኤላ፣ ፌኖን፣
\v 42 ቄኔዝ፣ ቴማን፣ ሚብሳር፣
\v 43 መግዲኤልና ዒራም፣ እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው ከኤዶም የተገኙ የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነበር።
\s5
\c 37
\p
\v 1 የዕቆብ አባቱ በኖረበት በከነዓን ምድር ተቀመጠ።
\v 2 የያዕቆብ ትውልድ ታሪክ ይህ ነው። ዮሴፍ የዐሥራ ሰባት ዓመት ወጣት በነበረ ጊዜ፣ ከአባቱ ሚስቶች ከባላቅና ከዘለፋ ከተወለዱት ወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎችና ፍየሎች ይጠብቅ ነበር። እርሱም ስለወንድሞቹ ድርጊት ለአባቱ መጥፎ ወሬ ይዞለት መጣ።
\s5
\v 3 እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፣ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም ሰፋለት።
\v 4 ወንድሞቹም አባታቸው ከእነርሱ አብልጦ የሚወደው መሆኑን ሲያዩ ዮሴፍን ጠሉት፤ በቅን አንደበት ሊያናግሩት አልቻሉም።
\s5
\v 5 ዮሴፍ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ ሲነግራቸው የባሰ ጠሉት፤
\v 6 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ”
\s5
\v 7 ‘እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት’ ”
\v 8 ወንድሞቹም፣ “ታዲያ በእኛ ላይ ንጉሥ ሆነህ ልትገዛን ታስባለህን? ” ብለው ጠየቁት። ስለ ሕልሙና ስለተናገረው ቃል ከፊት ይልቅ ጠሉት።
\s5
\v 9 እንደ ገናም ሌላ ሕልም አለመ፤ ለወንድሞቹም እነሆ፣ ሌላ ሕልም አለምሁ፣ ፀሐይና ጨረቃ፣ ዐሥራ አንድ ክዋክብትም ሲሰግዱልኝ ዐየሁ” ብሎ ነገራቸው።
\v 10 ይህንኑ ለወንድሞቹ የነገራቸውን ሕልም ለአባቱም በነገረው ጊዜ፣ አባቱ፣ “ይህ ምን ዐይነት ሕልም ነው? እኔና እናትህ ወንድሞችህም በፊትህ ወደ ምድር ተጎንብሰን በርግጥ ልንሰግድልህ ነው? ” ሲል ገሠጸው።
\v 11 ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው።
\s5
\v 12 አንድ ቀን የዮሴፍ ወንድሞች የአባታቸውን መንጋዎች ይዘው ወደ ሴኬም ተሰማሩ፤
\v 13 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “እንደምታውቀው ወንድሞችህ መንጎቹን በሴኬም አካባቢ አሰማርተዋል፤ በል ተነሥ፣ ወደ እነርሱ ልላክህ” አለው። ዮሴፍም፣ “እሺ እሄዳለሁ” አለ።
\v 14 አባቱም፣ “በል እንግዲህ ሄድና የወንድሞችህንና የመንጋዎቹን ደኅንነት አይተህ ንገረኝ” አለው። በዚህ ዓይነት እስራኤል ዮሴፍን ከኬብሮን ሸለቆ ላከው። ዮሴፍም ሴኬም በደረሰ ጊዜ፣
\s5
\v 15 ሜዳ ላይ ወዲያ ወዲህ ሲባዝን አንድ ሰው አግኝቶት፣ “ምን እየፈለግህ ነው? ” ሲል ጠየቀው።
\v 16 ዮሴፍም፣ “ወንድሞቼን እየፈለግኋቸው ነው፤ መንጎቻቸውን የት እንዳሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህ? ” አለው።
\v 17 ሰውዬውም፣ “ከዚህ ሄደዋል፤ ደግሞም ‘ወደ ዶታይን እንሂድ’ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ” አለው። ከዚያም ዮሴፍ ወንድሞቹን ፍለጋ ሄደ፣ በዶታይን አቅራቢያም አገኛቸው።
\s5
\v 18 ወንድሞቹም ዮሴፍ ወደ እነርሱ ሲመጣ በሩቅ ዐዩት፣ ወደ ነበሩበትም ስፍራ ከመድረሱ በፊት ሊገድሉት ተማከሩ።
\v 19 እነርሱ እንዲህ ተባባሉ፦ “ያ ሕልም አላሚ መጣ፤
\v 20 ኑ እንግደለውና ከጉድጓዶቹ በአንዱ ውስጥ እንጣለው፤ ከዚያም፣ ‘ክፉ አውሬ ነጥቆ በላው’ እንላለን፤ እስቲ ሕልሞቹ ሲፈጸሙ እናያለን።”
\s5
\v 21 ሮቤል ግን ይህን ምክር ሲሰማ ከእጃቸው ሊያድነው ፈለገ እንዲህም አለ፤ “አንግደለው፤
\v 22 የሰው ደም አታፍስሱ፣ ከምትገድሉት ይልቅ በዚህ በበረሃ ባለው ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት” አላቸው። ሮቤል ይህን ያለው ሕይወቱን ከእጃቸው አትርፎ ወደ አባቱ ሊመልሰው ዐስቦ ነበር።
\s5
\v 23 ዮሴፍ ወደ ወንድሞቹ እንደደረሰ፣ የለበሳትን በኅብረ ቀለማት የጌጠች እጀ ጠባቡን ገፈፉት፤
\v 24 ይዘውም ወደ ጉድጓድ ጣሉት፤ ጉድጓዱም ውሃ የሌለበት ደረቅ ነበር።
\s5
\v 25 ምግባቸውን ለመብላት ተቀመጡ፤ አሻግረው ሲመለከቱም ከገለዓድ የሚመጡ እስማኤላውያን ነጋዴዎች ጓዛቸውን በግመሎች ላይ ጭነው ተመለከቱ። ነጋዴዎቹ ሽቶ፣ በለሳን፣ ከርቤ በግመሎቻቸው ጭነው ወደ ግብፅ የሚወርዱ ነበሩ።
\v 26 ይሁዳም ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “ወንድማችንን መግደልና አሟሟቱን መደበቅ ምን ይጠቅመናል?
\s5
\v 27 ከዚህ ይልቅ ለእስማኤላውያን ነጋዴዎች እንሽጠው፤ እጃችንን ግን በእርሱ ላይ አናንሳ። ምንም ቢሆን የሥጋ ወንድማችን ነው” ወንድሞቹም በሃሳቡ ተስማሙ።
\v 28 የምድያም ነጋዴዎች የሆኑ እስማሴላውያን በዚያ በኩል ያልፉ ነበር፤ ስለዚህ ወንድሞቹ ዮሴፍን ከጉድጓድ ጎትተው በማውጣት ለእነዚህ እስማኤላውያን በሃያ ብር ሸጡላቸው፣ እነርሱም ወደ ግብፅ ይዘውት ሄዱ።
\s5
\v 29 ሮቤል ወደ ጉድጓዱ ተመልሶ ሲያይ፣ ዮሴፍን በማጣቱ ልብሱን በሐዘን ቀደደ።
\v 30 ወደ ወንድሞቹም ተመልሶ፣ “እነሆ፣ ልጁ እዚያ የለም! እንግዲህ እኔ ወዴት ብሄድ ይሻለኛል? ” አለ።
\s5
\v 31 ከዚህ በኋላ አንድ ፍየል አረዱና የዮሴፍን ልብስ በደም ነከሩት።
\v 32 በኅብረ ቀለማት ያጌጠችውን እጀ ጠባብ ወደ አባታቸው ወስደው፣ “ይህን ወድቆ አገኘነው፤ የልጅህ እጀ ጠባብ መሆን አለመሆኑን እስቲ እየው” አሉት።
\v 33 እርሱ የልጁ ልብስ መሆኑን ተረድቶ፣ “ይህማ የልጄ እጀ ጠባብ ነው! ፤ ክፉ አውሬ በልቶታል፣ በእርግጥም ዮሴፍ ተቦጫጭቆአል” አለ።
\s5
\v 34 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤
\v 35 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና አልቻለም፣ “በሐዘን እንደተኮራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ።
\v 36 በዚህ ጊዜ የምድያም ነጋዴዎች ዮሴፍን ወደ ግብፅ ወስደው፣ ከፈርዖን ሹማምንት አንዱ ለነበረው ለዘበኞች አለቃ፣ ለጲጥፋራ ሸጡት።
\s5
\c 38
\p
\v 1 በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ሒራ ወደተባለ ዐዱላማዊ ሰው ዘንድ ሄደ፣ መኖሪያውንም
\v 2 እዚያም ሳለ፣ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ ዐየ፤ እርሷንም አግብቶ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ፈጸመ።
\s5
\v 3 እርሷም አርግዛ ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም ዔር ብላ ጠራችው።
\v 4 እንደገናም አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ስሙንም አውናን አለችው።
\v 5 አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው፣ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።
\s5
\v 6 ይሁዳ የመጀመሪያ ልጁን ዔርን ትዕማር ከምትባል ልጃገረድ ጋር አጋባው።
\v 7 የይሁዳ የበኩር ልጅ ዔር ግን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነበር፤ እግዚአብሔርም ቀሠፈው።
\s5
\v 8 ይሁዳ አውናንን፣ “ዋርሳዋ እንደመሆንህ ከወንድምህ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በመፈጸም የወንድምህን ስም የሚያስጠራለት ዘር ተካለት አለው።
\v 9 አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት በፈጸመ ቁጥር የወንድሙን ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወለድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስ ነበር።
\v 10 ይህም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሆኖ ስለተገኘ፣ እርሱንም እግዚአብሔር በሞት ቀሠፈው።
\s5
\v 11 ከዚያም ይሁዳ ምራቱን ትዕማርን፣ “ልጄ ሴሎም ለአካለ መጠን እስኪደርስ ድረስ ወደ አባትሽ ቤት ሄደሽ መበለት ሆነሽ ብትኖሪ ይሻላል” አላት፤ ይህን ያለውም፤ ሴሎም እንደወንድሞቹ ተቀሥፎ ይሞትብኛል ብሎ ስለፈራ ነበር። ትዕማርም እንዳላት ሄደች፤ በአባቷም ቤት ተቀመጠች።
\s5
\v 12 ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፣ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደተምና ሄደ።
\v 13 ሰዎቹም ለትዕማር፣ “አማትሽ የበጎቹን ጠጉር ወደሚሸልቱ ሰዎች ዘንድ ወደተምና እየሄዱ ነው” አሏት። ይህን እንድሰማች
\v 14 የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፣ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ በር ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፣ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፣ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።
\s5
\v 15 ፊቷ በሻሽ ተሸፋፍኖ ሲያያት፣ ይሁዳ ዝሙት አዳሪ መሰለችው።
\v 16 ምራቱ መሆኗን ባለማወቁ፣ እርሷ ወዳለችበት ወደ መንደሩ ዳር ጠጋ ብሎ፣ “እባክሽን አብሬሽ ልተኛ” አላት። እርሷም፣ “አብሬህ ብተኛ ምን ትሰጠኛለህ? ” ብላ ጠየቀችው።
\s5
\v 17 “ከመንጋዬ መካከል አንድ የፍየል ጠቦት እልክልሻለሁ” አላት። እርሷም “ጠቦቱን እስክትልክልኝ ድረስ ምን መያዣ ትሰጠኛለህ? ” ብላ ጠየቀችው።
\v 18 “ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ? ” አላት። እርሷም፣ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፣ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም አረገዘችለት።
\s5
\v 19 ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሽዋን አውልቃ እንደወትሮዋ የመበለት ለብሷን ለበሰች።
\v 20 ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፣ እርሱ ግን ሊያገኛት አልቻለም።
\s5
\v 21 “በኤናይም ከተማ መግቢያ ከመንገዱ ዳር የነበረች ያቺ ዝሙት አዳሪ የት ደረሰች? ” ብሎ ዓዶሎማዊው ሰውዬ ጠየቀ። ሰዎቹም፣ “በዚህ አካባቢ እንደዚህ ያለች ዝሙት አዳሪ የለችም” አሉት።
\v 22 ስለዚህ ወደ ይሁዳ ተመልሶ ሄደና፣ “ላገኛት አልቻልሁም፤ በዚያ የሚኖሩትም ሰዎች፥ ‘እንደዚህ ያለች ዝሙት አዳሪ እዚህ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው።
\v 23 ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደያዘች ትቅር አለዚያ መሳቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፣ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።
\s5
\v 24 ከሦስት ወር ያህል በኋላ፣ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፣ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።
\v 25 እርሷም ተይዛ በምትወሰድበት ጊዜ ለአማትዋ፣ “እኔ ያረገዝሁት የእነዚህ ዕቃዎች ባለቤት ከሆነ ሰው ነው” ስትል ላከችበት፤ ደግሞም፣ “የማኅተሙ ቀለበት ከነማንጠልጠያውና በትሩ የማን እንደሆነ እስቲ ተመልከት” አለችው።
\v 26 ይሁዳም ዕቃዎቹን አውቆ፣ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፣ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም።
\s5
\v 27 የመውለጃዋ ጊዜ እንደደረሰም ፅንሷ መንታ መሆኑ ታወቀ።
\v 28 በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፣ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤
\s5
\v 29 ነገር ግን፣ እጁን መልሶ ሲያስገባ ወንድሙ ተወለደ። አዋላጂቱም፣ “አንተ እንዴት ጥሰህ ወጣህ! ” አለች፣ ከዚያም ስሙ ፋሬስ ተባለ።
\v 30 ከዚያ በኋላ እጁ ላይ ቀይ ክር የታሰረለት ወንድሙ ተወለደ፣ ስሙም ዛራ ተባለ።
\s5
\c 39
\p
\v 1 ዮሴፍ ወደ ግብፅ ተወስዶ ነበር፤ ከፈርዖንም ሹማምንት አንዱ የነበረውም የዘበኞች አለቃ፣ ግብፃዊው ጴጥፋራ ወደዚያ ከወሰዱት ከእስማኤላውያን ነጋዴዎች እጅ ገዛው።
\v 2 እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ስለነበረ ኑሮው ተቃናለት፤ እርሱም በግብፃዊው አሳዳሪው ቤት ኖረ።
\s5
\v 3 አሳዳሪው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለና ሥራውንም ሁሉ እንዳከናወነለት ባየ ጊዜ፣
\v 4 ዮሴፍ በእርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፣ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፣ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኃፊነት ሰጠው።
\s5
\v 5 ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ እግዚአብሔር የግብፅዊውን ቤት ባረከ፣ የእግዚአብሔርም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
\v 6 ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፣ የቀረበለትንም ከመመገብ በስተቀር፣ ማናቸውንም ጉዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ-መልካም ነበር፤
\s5
\v 7 ከጊዜ በኋላ የጌታው ሚስት ዮሴፍን ተመልክታ ስላፈቀረችው፣ “ና ከእኔ ጋር አብረን እንተኛ” አለችው።
\v 8 እርሱ ግን ይህን ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኃላፊነት ስለሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላልው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።
\v 9 በዚህ ቤት ላይ ከእኔ የበለጠ ኃላፊነት ያለው ማንም የለም፣ ከአንቺ በቀር በእኔ ቁጥጥር ሥር ያላደረገው ምንም ነገር የለም፤ ይኸውም ሚስቱ ስለሆንሽ ነው፤ ታዲያ፣ እኔ ይህን ክፉ ድርጊት በእግዚአብሔር ፊት እንዴት እፈጽማለሁ?”
\s5
\v 10 ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርሷ ጋር ይተኛ ዘንድ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም።
\v 11 አንድ ቀን ዮሴፍ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤት ሲገባ በቤት ውስጥ አንድም ሠራተኛ አልነበረም፤
\v 12 እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ፣ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጅዋ ላይ ትቶላት ከቤት ሸሽቶ ወጣ።
\s5
\v 13 እርሷም ልብሱን በእጅዋ ላይ ትቶ ከቤት ሸሽቶ መውጣቱን በተመለከተች ጊዜ፣
\v 14 አገልጋዮችዋን ጠርታ እንዲህ አለቻቸው፣ “እነሆ፣ ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ ሊያዋርደኝ ነበር፤ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፤ እኔ ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ።
\v 15 ዕርዳታ ለማግኘትም መጮኼን በሰማ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።”
\s5
\v 16 የዮሴፍ አሳዳሪ እስኪመጣ ድረስ ልብሱን በእርስዋ ዘንድ አቆየችው።
\v 17 በመጣም ጊዜ የሆነውን ታሪክ እንዲህ ስትል ዘርዝራ ነገረችው፤ “አንተ ወደዚህ የመጣኸው ዕብራዊ አገልጋይ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊያዋርደኝ ነበር።
\v 18 ነገር ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ በጮኽሁ ጊዜ ልብሱን በአጠገቤ ትቶ ከቤት ሸሽቶ ወጣ።”
\s5
\v 19 “የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቆጣ።
\v 20 ዮሴፍንም ወስዶ፣ የንጉሥ እስረኞች ወደታሠሩበት እስር ቤት አስገባው።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር ዘላለማዊ ፍቅሩን ዐሳየው፣ በእስር ቤት አዛዡም ዘንድ ሞገስን ሰጠው።
\v 22 ስለዚህ የእስር ቤቱ አዛዥ ዮሴፍን የእስረኞች ሁሉ አለቃ አደረገው፤ በእስር ቤት ላለውም ነገር ሁሉ ኃላፊ ሆነ።
\v 23 እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋር ሆኖ የሚያደርገው ነገር ሁሉ እንዲቃናለት ስላደረገ የእስር ቤት አዛዥ በዮሴፍ ቁጥጥር ሥር በነበረው ነገር ምንም ዐሳብ አልነበረበትም።
\s5
\c 40
\p
\v 1 ከዚህም በኋላ የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኃላፊው ንጉሡን የሚያሳዝን በደል ፈጸሙ።
\v 2 ፈርዖንም በመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ ቤቱ አዛዡ፣ በሁለቱም ሹማምንቱ ላይ እጅግ ተቆጣ፤
\v 3 በዘበኞቹ አለቃ ቤት ወዳለው ዮሴፍ ወደታሠረበት እስር ቤት አስገባቸው።
\s5
\v 4 የዘበኞቹም አለቃ እስረኞቹን ለዮሴፍ አስረከባቸው፤ በእስር ቤትም ለጥቂት ጊዜ ቆዩ።
\v 5 ታስረው የነበሩት የግብፅ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም ዐዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው።
\s5
\v 6 በማግስቱ ጥዋት ዮሴፍ እነርሱ ወዳሉበት ክፍል በገባ ጊዜ ተክዘው አገኛቸውና፤
\v 7 “ዛሬ በፊታችሁ ላይ ሐዘን የሚታየው ለምንድን ነው? ” አላቸው።
\v 8 እነርሱም፣ “ሁለታችንም ሕልም ዐየን፤ ነገር ግን የሚተረጉምልን ሰው አጣን” ሲሉ መለሱለት። ዮሴፍም፣ “ሕልም የመተርጎም ችሎታ የሚሰጥ እግዝአብሔር ነው፣ ስለዚህ የእያንዳንዳችሁን ሕልም ንገሩኝ” አላቸው።
\s5
\v 9 ስለዚህ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ሲል ሕልሙን ለዮሴፍ ነገረው፤ “ከፊት ለፊቴ አንዲት የወይን ተክል ዐየሁ፤
\v 10 ተክሏም ሦስት ሐረጎች ነበሯት፤ ወዲያው እቆጥቁጣ አበበች፤ የወይን ዘለላውም ወዲያው በሰለ።
\v 11 የፈርዖንንም ጽዋ ይዤ ነበር፣ የወይኑን ፍሬ ለቅሜ በጽዋው ውስጥ ጨምቄ ጽዋውን በእጁ ሰጠሁት።”
\s5
\v 12 ዮሴፍም እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ የሕልሙ ትርጓሜ ይህ ነው፤ ሦስቱ ሐረግ ሦስት ቀን ነው፤
\v 13 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፣ ወደ ቀድሞ ሹመትህም ይመልስሃል፤ በፊት የመጠጥ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ታደርግ እንደነበረው ኡሉ የፈርዖንን ጽዋ በእጁ ትሰጠዋለህ።
\s5
\v 14 እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፣ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤
\v 15 ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።”
\s5
\v 16 የእንጀራ ቤት አዛዡም፣ ለመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ሕልም የተሰጠው ፍቺ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን ሲሰማ፣ የራሱን ሕልም ለዮሴፍ እንዲህ ሲል ነገረው፤ “እኔም ደግሞ ሕልም አይቻለሁ፣ ሦስት መሶቦች በራሴ ላይ ተሸክሜ ነበር፤
\v 17 በላይኛው መሶብ ውስጥ ለፈርዖን የተዘጋጀ የተለያየ ምግብ ነበረበት፣ ነገር ግን ወፎች ምግቡን ከመሶቡ እያነሱ የበሉት ነበር።”
\s5
\v 18 ዮሴፍም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “የሕልሙ ፍቺ ይህ ነው፤ ሦስቱ መሶብ ሦስት ቀን ነው፤
\v 19 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ራስህን ካስቆረጠ በኋላ በእንጨት ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን የበሉታል።”
\s5
\v 20 በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለነበር ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምንቱ ካሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው።
\v 21 የመጠጥ አሳላፊዎቹን አለቃ ወደ ቀድሞ ሹመቱ መለሰው፤ እርሱም እንደ ቀድሞው ጽዋውን ለፈርዖን በእጁ ይሰጠው ጀመር፤
\v 22 የእንጀራ ቤት አዛዡን ግን ልክ ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው ሰቀለው።
\v 23 የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው።
\s5
\c 41
\p
\v 1 ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለም፤ ሕልሙም በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤
\v 2 እነሆ፣ መልካቸው ያማረ፣ ሥጋቸው የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ይበሉ ጀመር።
\v 3 ቀጥሎም መልካቸው የከፋ አጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው አስቀድመው ከወጡት ላሞች አጠገብ ቆሙ።
\s5
\v 4 እነዚህ መልካቸው የከፋና አጥንታቸው የወጣ ላሞች፥ እነዚያን ያማሩና የወፈሩ ላሞች ሲውጡአቸው ዐየ፤ ከዚያም ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ።
\v 5 ፈርዖንም እንደገና እንቅልፍ ወስዶት ሳለ ሌላ ሕልም ዐየ። በሕልሙም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዐየ፤
\v 6 ቀጥሎም የቀጨጩና ከበረሐ በተነሣ የምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁ ሰባት የእሸት ዛላዎች ወጡ።
\s5
\v 7 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎች፤ ሰባቱን የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጡአቸው፤ በዚህ ጊዜ ፈርዖን ከእንቅልፉ ነቃ፣ ነገሩ ሕልም ነበር።
\v 8 በነጋታውም ፈርዖን መንፈሱ ታወከበት፣ ስለዚህ በግብፅ አገር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች በሙሉ አስጠርቶ ሕልሞቹን ነገራቸው፣ ይሁን እንጂ፣ ሕልሞቹን ሊተረጉምለት የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም።
\s5
\v 9 በዚያን ጊዜ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ፈርዖንን እንዲህ አለው፤ “የሠራሁት በደል ዛሬ ታወሰኝ።
\v 10 ፈርዖን ሆይ! አንተ በእኔና በእንጀራ ቤት ኃላፊው ላይ ተቆጥተህ በዘበኞች አለቃ ቤት እንድንታሰር አድርገህ ነበር፤
\v 11 በዚያ ሳለን በአንድ ሌሊት ሁለታችንም የተለያየ ሕልም ዐየን፤ የእያንዳንዳችንም ሕልም የተለያየ ትርጉም ነበረው።
\s5
\v 12 በዚያን ጊዜ የዘበኞች አለቃ አገልጋይ የሆን አንድ ዕብራዊ ወጣት ከእኛ ጋር እስር ቤት ነበር። ሕልማችንን በነገርነው ጊዜ፣ ፍቺውን ነገረን፤ ለእያንዳንዳችንም እንደ ሕልማችን ተረጎመልን፤
\v 13 ነገሩም ልክ እርሱ እንደተረጎመልን፤ እኔ ወደ ቀድሞ ሹመቴ ተመለስሁ፤ የእንጀራ ቤት አዛዡም ተሰቀለ።
\s5
\v 14 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲያመጡት ትዕዛዝ ሰጠ፤ ከእስር ቤትም በጥድፊያ ይዘውት መጡ፤ ጠጉሩንም ከተላጨና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ፈርዖን ፊት ቀረበ
\v 15 ፈርዖንም ዮሴፍን፣ “ሕልም ዐይቼ ነበር፣ ሕልሜን ሊተረጉምልኝ የቻለ አንድም ሰው አልተገኘም፣ አንተ ግን ሕልም ሲነገርህ የመተርጎም ችሎታ እንዳለህ ሰማሁ” አለው።
\v 16 ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ይህ በእኔ አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በበጎነት ይመልስለታል”
\s5
\v 17 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሕልሜ በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሜ ነበር።
\v 18 ሥጋቸው የወፈረና መልካቸው የማረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጥተው በወንዙ ዳር የበቀለውን ሣር ሲበሉ ዐየሁ።
\s5
\v 19 ከእነርሱም በኋላ ዐቅመ ደካማ፣ መልካቸው እጅግ የከፋና አጥንታቸው የወጣ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ እነዚያን የመሰሉ የሚያስከፋ መልክ ያላቸው ላሞች በግብፅ ምድር ከቶ ዐይቼ አላውቅም።
\v 20 አጥንታቸው የወጣና አስከፊ መልክ ያላቸው ላሞች መጀመሪያ የወጡትን፣ ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጧቸው።
\v 21 ከዋጧቸውም በኋላ፣ ያው የበፊቱ መልካቸው ስላልተለወጠ እንደዋጧቸው ማንም ሊያውቅ አይችልም ነበር፤ ከዚያም ከእንቅልፌ ነቃሁ
\s5
\v 22 ደግሞም በአንድ የእህል አገዳ ላይ ሰባት የዳበሩና ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዐየሁ፤
\v 23 ቀጥሎም የቀጨጩና የደረቁ ሌሎች ሰባት ዛላዎች ወጡ።
\v 24 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ያየኋቸውንም ሕልሞች ለአስማተኞች ነገርሁ፣ ነገር ግን ሕልሞቹን ማንም ሊተረጉምልኝ አልቻለም።”
\s5
\v 25 ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ አለው፤ “ሁለቱም የፈርዖን ሕልሞች ተመሳሳይና አንድ ዓይነት ናቸው፤ እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውን ለፈርዖን ገልጦለታል።
\v 26 ሰባቱ የሚያምሩ ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፣ ሰባቱም የሚያማምሩ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙም አንድና ተመሳሳይ ነው።
\s5
\v 27 ከእነርሱም በኋላ አጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፣ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው።
\v 28 አስቀድሜ ለፈርዖን እንደተናገርሁት እግዚአብሔር ወደፊት የሚያደርገውን ነገር ለፈርዖን ገልጦለታል።
\v 29 በመላው የግብፅ ምድር እጅግ የተትረፈረፈ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ።
\s5
\v 30 በዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጎዳት በግብፅ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም።
\v 31 ከጥጋብ ዓመታት በኋላ የሚመጣው የራብ ዘመን እጅግ ጽኑ ከመሆኑ የተነሣ፣ ቀደም ሲል የነበረው የጥጋብ ዘመን ፈጽሞ ይረሳል።
\v 32 ሕልሙ ለፈርዖን በድጋሚ መታየቱ፣ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቆረጠ ስለሆነ ነው፤ ይህንንም እግዚአብሔር በቅርብ ጊዜ ይፈጽመዋል፤
\s5
\v 33 እንግዲህ ፈርዖን ብልኅና አስተዋይ ሰው ፈልጎ፣ በመላው የግብፅ ምድር ላይ አሁኑኑ ይሹም።
\v 34 እንደዚሁም በሰባቱ የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት፣ አንድ አምስተኛው እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ ኃላፊዎችን ይሹም።
\s5
\v 35 እነርሱም በሚመጡት የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ምርት ሁሉ ይሰብስቡ፤ በፈርዖንም ሥልጣን ሥር ያከማቹ፤ ለምግብ እንዲሆኑም በየከተማው ይጠበቁ።
\v 36 የሚከማቸው እህል፣ ወደፊት በግብፅ አገር ላይ ለሚመጣው የሰባት ዓመት ራብ መጠባበቂያ ይሁን፤ በዚህም ሁኔታ አገሪቱ በራብ አትጠፋም።
\s5
\v 37 ዕቅዱም ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ መልካም ሆኖ አገኙት።
\v 38 ፈርዖንም፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት እንደዚህ ያለ ሰው ልናገኝ እንችላለን? ” ብሎ ጠየቃቸው።
\s5
\v 39 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ “እግዚአብሔር ይህን ሁል ገለጠለህ እንዳንተ ያለ አስተዋይና ብልህ ሰው የለም።
\v 40 አንተ በቤተ መንግሥቴ የበላይ ትሆናለህ፤ ሕዝቤም ሁሉ ለሥልጣንህ ይገዛል፤ እኔ ከአንተ የምበልጠው በዙፋኔ ብቻ ይሆናል።”
\v 41 ከዚያም፣ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “በመላይቱ የግብፅ ምድር ላይ ኃላፊ አድርጌሃለሁ” አለው።
\s5
\v 42 ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በአንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።
\v 43 በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው።
\s5
\v 44 ከዝህ በኋላ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “እኔ ፈርዖን ነኝ፤ ሆኖም በመላይቱ ግብፅ ያለ አንተ ፈቃድ ማንም ሰው እጁን ወይም እግሩን ማንቀሳቀስ አይችልም” አለው።
\v 45 ፈርዖን ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም አስናት ተብላ የምትጠራውን ኦን ተብሎ የሚጠራው ከተማ ካህን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው።
\s5
\v 46 ዮሴፍ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖንን ማገልገል ሲጀምር፣ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ የግብፅን ምድር በሙሉ ዞረ።
\v 47 በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ምድሪቱ የተትረፈረፈ ሰብል ሰጠች።
\s5
\v 48 በእነዚያ ሰባት የጥጋብ ዓመታት፣ ዮሴፍ በግብፅ አገር የተገኘውን ምርት ሰብስቦ በየከተሞቹ አከማቸ፣ በእያንዳንዱ ከተማ ከየአቅራቢያው የተመረተውን እህል እንዲከማች አደረገ።
\v 49 ዮሴፍ ብዛቱ እንደ ባሕር አሸዋ የሚሆን የእህል ሰብል አከማቸ፤ ሰብሉ እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ ልኩን መስፈርና መመዝገብ አልቻለም ነበር።
\s5
\v 50 ሰባቱ የራብ ዓመታት ከመምጣታቸው በፊት የኦን ከተማ ካህን የጶጢፌራ ልጅ አስናት ለዮሴፍ ሁለት ወንድ ልጆች ወለደችለት።
\v 51 ዮሴፍም፣ “እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት እንድረሳ አድርጎኛል” በማለት የመጀመሪያ ልጁን ስም ምናሴ አለው።
\v 52 እንደዚሁም “መከራ በተቀበልሁበት ምድር እግዚአብሔር ፍሬያማ አደረገኝ” ሲል ሁለተኛ ልጁን ኤፍሬም አለው።
\s5
\v 53 በግብፅ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን አለፈና
\v 54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብፅ ምድር መስፋፋት ሲጀመር፣
\s5
\v 55 ሕዝቡ ምግብ ይሰጠን በማለት ወደ ፈርዖን ጮኸ። ፍርዖንም ግብፃውያኑን፣ “ወደ ዮሴፍ ሂዱና የሚላችሁን አድርጉ” አላቸው።
\v 56 ራቡ በአገሩ ላይ እየተስፋፋ ስለሄደ፣ ዮሴፍ ጎተራዎቹን ከፍቶ እህሉ ለግብፃውያን እንዲሸጥ አደረገ፤ ምክንያቱም ራቡ በመላይቱ ግብፅ ጸንቶ ነበር።
\v 57 ራቡ በመላው ዓለም ጸንቶ ስለነበር፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ ከዮሴፍ ዘንድ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ምድር መጡ።
\s5
\c 42
\p
\v 1 በግብፅ እህል መኖሩን ሲሰማ፣ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ለምን እርስ በርስ ትተያያላችሁ? ”
\v 2 በግብፅ አገር እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ በራብ ከመሞታችን በፊት ወደዚያ ሂድና እህል ግዙልን” አላቸው።
\v 3 ስለዚህ ዐሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመግዛት ወደ ግብፅ ሄዱ።
\v 4 ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሃት ከወንድሞቹ ጋር አልላከውም።
\s5
\v 5 ራቡ በከነዓንም በመበርታቱ፣ እህል ለመሸመት ወደ ግብፅ ከሄዱት መካከል የእስራኤል ልጆችም ነበሩ።
\v 6 በዚህ ጊዜ ዮሴፍ የምድሪቱ ገዢ ነበር፣ ለአገሩ ሰዎች ሁሉ እህል የሚሸጥላቸው እርሱ ነበር። የዮሴፍ ወንድሞችም እንደደረሱ ከፊቱ ቀርበው ወደ ምድር ለጥ ብለው ሰገዱለት።
\s5
\v 7 ዮሴፍም ወንድሞቹን ባየ ጊዜ ዐወቃቸው፣ ነገር ግን የማያውቃቸው በመምሰል በቁጣ ቃል፣ “ከየት ነው የመጣችሁት? ” ብሎ ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እህል ለመሸመት ከከነዓን ምድር የመጣን ነን" ብለው መለሱለት።
\v 8 ዮሴፍ ወንድሞቹን ቢያውቃቸውም እንኳ እነርሱ ግን አላወቁትም።
\s5
\v 9 በዚህ ጊዜ ስለወንድሞቹ ያየው ሕልም ትዝ አለውና፣ “ሰላዮች ናችሁ፣ የመጣችሁት አገራችን በየትኛው በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው።
\v 10 እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን ሆይ፣ እንዲህስ አይደለም፤ እኛ አገልጋዮችህ የመጣነው እህል ለመሸመት ነው፤
\v 11 ሁላችንም የአንድ አባት ልጆች ነን፤ አገልጋዮችህም የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።”
\s5
\v 12 እርሱም መልሶ፣ “አይደለም፣ ግብፅ በየት በኩል ለጥቃት የተጋለጠች መሆኗን ለመሰለል ነው” አላቸው።
\v 13 እነርሱ ግን መልሰው፣ “እኛ አገልጋዮችህ በከነዓን አገር ከሚኖር ከአንድ ሰው የተወለድን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን። ትንሹ ወንድማችን አባታችን ዘንድ ሲሆን አንዱ ወንድማችን ሞቷል።
\s5
\v 14 ዮሴፍም እንዲህ አላቸው፤ “ነገርኋችሁ እኮ፤ ሰላዮች ናችሁ
\v 15 ታናሽ ወንድማችሁ እዚህ እስካልመጣ ድረስ ከዚህ ንቅንቅ እንደማትሉ በፈርዖን ስም እምላልሁ፤ ማንነታችሁ የሚረጋገጠውም በዚህ ነው።
\v 16 ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁትም እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስት ቤት ትቆያላችሁ፤”
\v 17 ሁሉንም ሦስት ቀን በእስር አቆያቸው።
\s5
\v 18 በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ።
\v 19 ታማኝ ሰዎች ከሆናችሁ፣ ከመካከላችሁ እንዱ እዚህ እስር ቤት ሲቆይ፣ የቀራችሁት ግን ለተራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ትወስዱላቸዋላችሁ፤
\v 20 ታናሽ ወንድማችሁን ግን ይዛችሁ መምጣት አለባችሁ፤ በዚህም የተናገራችሁት ቃል እውነተኛነት ይረጋገጣል፤ እናንተም ከመሞት ትተርፋላችሁ።” እነርሱም ይህንኑ ለመፈጸም ተስማሙ።
\s5
\v 21 እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፤ “በእርግጥ በወንድማችን ላይ ስላደረስነው በደል ቅጣታችንን እየተቀበልን ነው። እርሱ እንደዚያ ተጨንቆ ስለ ሕይወቱ ሲማጠነን፣ እኛ አልሰማነውም ነበር፤ ይህ መከራ የደረሰብንም በዚሁ ምክንያት ነው” ተባባሉ።
\v 22 ሮቤልም መልሶ፣ “በዚህ ልጅ ላይ ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
\s5
\v 23 ዮሴፍ የሚያነጋግራቸው በአስተርጓሚ ስለሆነ የሚነጋገሩትን እንደሚሰማባቸው ዐላወቁም ነበር።
\v 24 ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደእነርሱ ትመልሶ እንደገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዓይናቸው እያየ አሰረው፤
\v 25 ዮሴፍ ለአገልጋዮቹ በስልቻዎቻቸው እህል እንዲሞሉላቸው፤ ብሩንም በያንዳንዱ ሰው ስልቻ ውስጥ መልሰው እንዲያስቀምጡና ለጉዞአቸው ስንቅ እንዲያሲዟቸው ትእዛዝ ሰጠ። ይህም ተደረገላቸው።
\s5
\v 26 እነርሱም እህላቸውን በአህዮቻቸው ጭነው ጉዞአቸውን ቀጠሉ።
\v 27 በመንገድም ለአዳር ሰፍረው ሳለ፣ ከእነርሱ አንዱ ከያዘው እህል ላይ ለአህያው ለመስጠት ስልቻውን ሲፈታ፣ በስልቻው አፍ ላይ ብሩን አገኘ።
\v 28 እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን? ” አሉ።
\s5
\v 29 በከነዓን ምድር ወዳለው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ከደረሱ በኋላ ያጋጠማቸውን ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩት፤
\v 30 “የግብፅ አገር አስተዳዳሪ ‘አገሬን ልትሰልሉ የመጣችሁ ናችሁ’ በማለት በቁጣ ቃል ተናገረን፤
\v 31 እኛ ግን እንዲህ አልነው፤ “እኛ የታመንን ሰዎች እንጂ ሰላዮች አይደለንም።
\v 32 እኛ የአንድ አባት ልጆች የሆንን ዐሥራ ሁለት ወንድማማቾች ነን፣ አንዱ የለም፣ ታናሽ ወንድማችን ግን ከአባታችን ጋር በከነዓን ይገኛል።’
\s5
\v 33 ከዚህ በኋላ የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው እንዲህ አለን፣ “ታማኝ ሰዎች መሆናችሁን የማውቀው በዚህ ነው ከእናንተ መካከል አንዱን ወንድማችሁን እዚህ እኔ ዘንድ ትታችሁ የተቀራችሁት ለትራቡት ቤተ ሰቦቻችሁ እህል ይዛችሁላቸው ሂዱ።
\v 34 ነገር ግን ታናሽ ወንድማችሁን ወደ እኔ አምጡት። በዚያን ጊዜም ታማኝ ሰዎች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁን ዐውቃለሁ፤ ወንድማችሁንም መልሼ እሰጣችኋለሁ፤ እናንተም በምድሪቱ እንደፈለጋችሁ እየተዘዋወራችሁ መነገድ ትችላላችሁ።
\s5
\v 35 እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፣ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ።
\v 36 አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፣ ዮሴፍ የለም፣ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ” አለ።
\s5
\v 37 በዚህን ጊዜ ሮቤል አባቱን፣ “ብንያምን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ወስደህ ግደላቸው፣ ስለዚህ በእኔ ኃላፊነት ላከው፤ እኔም መልሼ አመጣዋለሁ” እለው።
\v 38 ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፣ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጉዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
\s5
\c 43
\p
\v 1 አሁንም በምድሪቱ ላይ እንደጸና ነበር፤
\v 2 ከግብፅ ያመጡትንም እህል በልተው ከጨረሱ በኋላ፣ አባታቸው፣ “እስቲ እንደገና ወርዳችሁ፣ ጥቂት እህል ሸምቱልን” አላቸው።
\s5
\v 3 ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ ያ ሰው ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤
\v 4 ወንድማችን ከእኛ ጋር እንዲወርድ ከፈቀድህ ወደዚያ ሄደን እህል እንሸምትልሃለን፤
\v 5 እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም’ ብሎናል።”
\s5
\v 6 እስራኤልም፣ “ሌላ ወንድም አለን ብላችሁ ለዚያ ሰው በመንገር ለምን ይህን ችግር እንዲደርስብኝ አደረጋችሁ? ” ሲል ጠየቃቸው።
\v 7 እነርሱም፣ “ሰውዬው ስለ ራሳችንና ስለ ቤተ ሰባችን አጥብቆ ጠየቀን፤ እንደገናም ‘አባታችሁ አሁንም በሕይወት አለ? ሌላስ ወንድም አላችሁ? ሲል ጠየቀን። እኛም ለጥያቄው መልስ ሰጠነው። ታዲያ፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ወደዚህ እንድትመጡ’ እንደሚል እንዴት ማወቅ እንችል ነበር? ” ብለው መለሱለት።
\s5
\v 8 ይሁዳም አባቱን እስራኤልን እንዲህ አለው፣ “ልጁን ከእኔ ጋር ስደደው፤ እኛም በቶሎ እንሂድ፣ ይህ ከሆነ አንተም፣ እኛም፣ ልጆቻችንም አንሞትም፣ እንተርፋለን።
\v 9 ስለ ልጁ ደኅንነት እኔ ራሴ ኃላፊ ነኝ፤ ስለ እርሱም በግል ተጠያቂ እሆናለሁ፤ እርሱንም በደኅና መልሼ ባላመጣውና እዚህ በፊትህ ባላቆመው ለዘላለም በደለኛ እኔ ልሁን።
\v 10 ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፣ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።”
\s5
\v 11 ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፣ ምድሪቱ ከምታፈራቸው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው ስጦታ ውሰዱለት።
\v 12 በየስልቾቻችሁ አፍ ላይ የተገኘውን ብር መመለስ ስላለባችሁ፣ ዕጥፍ ገንዘብ ያዙ፤ ያ በየስልቾቻችሁ ውስጥ የተገኘው ብር ምናልባት በስሕተት የመጣ ሊሆን ይችላል።
\s5
\v 13 ወንድማችሁንም ይዛችሁ ወደ ሰውዬው በቶሎ ሂዱ።
\v 14 ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ይዛችሁ ለመመለስ እንድትችሉ ሁሉን የሚችል አምላክ በምሕረቱ የዚያን ሰው ልብ ያራራላችሁ። እኔ በበኩሌ ልጆቼን ካጣሁ፣ ባዶ እጄን መቅረቴ ነው።”
\v 15 ስለዚህ ወንድማማቾቹ ገጸ በረከቱንና ዕጥፍ ገንዘብ ይዘው ከብንያም ጋር ወደ ግብፅ ለመሄድ ጉዞ ጀመሩ፤ እዚያም በደረሱ ጊዜ ዮሴፍ ፊት ቀረቡ።
\s5
\v 16 ዮሴፍ ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ባየው ጊዜ የቤቱን አዛዥ፣ “እነዚህን ሰዎች ወደ ቤት ይዘሃቸው ሂድ፣ ዛሬ ቀትር ላይ አብረውኝ ስለሚበሉ አንድ ከብት እረድና አዘጋጅ” አለው።
\v 17 አዛዡም ዮሴፍ የነገረውን አደረገ፣ ሰዎቹንም ወደ ዮሴፍ ቤት ወሰዳቸው።
\s5
\v 18 ሰዎቹም ወደ ዮሴፍ ቤት በመወሰዳቸው ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ወደዚህ የመጣነው ቀደም ሲል እዚህ መጥተን ስንመለስ በየስልቾቻችን ውስጥ ተመልሶ በተጨመረው ብር ሰበብ ነው። ሰውዬው ሊያስረንና ባሪያዎች ሊያደርገን አህዮቻችንንም ሊወስድ ይችላል።”
\v 19 ወደ ዮሴፍ ቤት አዛዥ ቀርበው፣ በቤቱ መግቢያ ላይ አነጋገሩት፤
\v 20 እንዲህም አሉት፤ “ለመጀመሪያ ጊዜ እህል ለመሸመት ወደዚህ መጥተን ነበር፤
\s5
\v 21 ነገር ግን ለአዳር በሰፈርንበት ቦታ የየስልቾቻችንን አፍ ስንከፍት እያንዳንዳችን በስልቾቻችን አፍ ላይ ብራችንን ሙሉውን አገኘነው። ገንዘቡንም ይኸው መልሰን ይዘን መጥተናል።
\v 22 አሁንም እህል መሸመት የሚሆነን ተጨማሪ ብር ይዘን መጥተናል፤ በዚያን ጊዜ ገንዘቡን በየስልቾቻቸን ውስጥ ማን መልሶ እንዳስቀመጠው ግን አናውቅም” አሉት።
\v 23 የቤቱ አዛዥም፣ “አይዞአችሁ አትፍሩ፣ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደሆንሁ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው። ከዚያም ስምዖንን አውጥቶ አገናኛቸው።
\s5
\v 24 የቤቱ አዛዥ ሰዎቹን ወደ ዮሴፍ ቤት አስገብቶ እግራቸውን የሚታጠቡበት ውሃ አቀረበላቸው፤ ለአህዮቻቸውም የሚበሉት ገፈራ ሰጣቸው።
\v 25 ምሳ በዚያ እንደሚበሉ ተነገሯቸው ስለነበር፣ ዮሴፍ በቀትር ከመግባቱ በፊት እጅ መንሻዎቻቸውን ለማበርከት ተዘጋጁ።
\s5
\v 26 ዮሴፍም ወደ ቤቱ ሲገባ የመጧቸውን ስጦታዎች አበረከቱለት፤ ወደ መሬት ዝቅ ብለውም እጅ ነሡት።
\v 27 ዮሴፍም ስለ ደኅንነታቸው ጠየቃቸው፣ ከዚያም፣ “ሽማግሌ አባት እንዳላችሁ ነግራችሁኝ ነበር፤ ደኅና ነው? አሁንም በሕይወት አለ? ” አላቸው።
\s5
\v 28 እነርሱም መልሰው፣ “አገልጋይህ አባታችን አሁንም በሕይወት አለ፤ ደኅና ነው” በማለት ወደ መሬት ዝቅ ብለው እጅ ነሡት።
\v 29 ዮሴፍ በዓይኑ ሲቃኝ የእናቱን ልጅ ብንያምን ዐየና፣ “ያ የነገራችሁኝ ታናሽ ወንድማችሁ ይህ ነው? ” ብሎ ጠየቃቸው። ብንያምንም፣ “ልጄ እግዚአብሔር ይባርክህ” አለው።
\s5
\v 30 ዮሴፍ ወንድሙን በማየቱ ስሜቱ በጥልቅ ስለተነካ፣ ፈጥኖ ከፊታቸው ገለል አለ፤ ሰውር ያለ ቦታም ፈልጎ፣ ዕልፍኙ ውስጥ አለቀሰ።
\v 31 ፊቱንም ከታጠበ በኋላ ወጣ፤ ስሜቱንም በመቆጣጠር ምሳ እንዲቀርብ አዘዘ።
\s5
\v 32 ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደጸያፍ ይቆጥሩት ነበር።
\v 33 ወንድማማቾቹ ከታላቁ አንስቶ እስከታናሹ እንደየዕድሜአቸው በዮሴፍ ፊት በተርታ ተቀምጠው ነበር፤ በመገረምም እርስ በርሳቸው ተያዩ።
\v 34 ከዮሴፍ ገበታ ላይ እየተነሣ ለእያንዳንዳቸው ምግብ ሲቀርብ የብንያም ድርሻ ከሌሎቹ አምስት ዕጥፍ ነበር። እነርሱም እንዲህ ባለ ሁኔታ አብረውት ተደሰቱ እስኪረኩም ጠጡ።
\s5
\c 44
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ለቤቱ አዛዥ እንዲህ ሲል መመሪያ ሰጠው፤ የሰዎቹ ስልቻ የሚይዘውን ያህል እህል በየስልቻቸው ሙላላቸው፤ የእያንዳንዱንም ገንዘብ በየስልቻው አፍ አስቀምጠው።
\v 2 ከዚያም የብር ዋንጫዬን በታናሹ ወንድማቸው ስልቻ አፍ ከእህሉ ዋጋ ጋር ጨምረው።” አዛዡም ዮሴፍ እንዳለው አደረገ።
\s5
\v 3 ጠዋት በማለዳ ወንድማማቾቹ አህዮቻቸውን ይዘው እንዲሄዱ ተደረገ።
\v 4 ከከተማውም ምንም ያህል ርቀው ሳይሄዱ፣ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፤ “እነዚያን ሰዎች ቶሎ ድረስባቸውና፣ ‘በመልካም ፋንታ ክፉ የመለሳችሁት ስለ ምንድን ነው?
\v 5 የጌታዬን የብር ዋንጫ የሰረቃችሁት ለምንድነው? ዋንጫው ጌታዬ የሚጠጣበትና ሁሉን ነገር መርምሮ የሚያውቅበት እንደሆነ አታውቁምን? ይህ ያደረሳችሁት በደል እጅግ ከባድ ነው’ ብለህ ነገራቸው።”
\s5
\v 6 የቤቱ አዛዥም እንደደረሰባቸው፣ ልክ እንደተባለው ተናገራቸው።
\v 7 እነርሱ ግን እንዲህ አሉት፤ “ጌታችን እንዲህ ያለ ነገር ለምን ይናገራል? እኛ አገልጋዮችህ እንዲህ ያለውን ነገር አናደርገውም።
\s5
\v 8 ከዚህ ቀደምም በየስልቾቻችን አፍ የተገኘውን ብር ከከነዓን እንኳ መልሰን አምጥተናል፤ ታዲያ አሁን ብር ወይም ወርቅ ከጌታህ ቤት እንዴት እንሰርቃለን?
\v 9 የጠፋው ዕቃ ከአገልጋዮችህ የተገኘበት ይሙት፤ የቀረነው የጌታችን ባሮች እንሁን።”
\v 10 አዛዡም መልካም ነው፤ እንዳላችሁት ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው ባሪያዬ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን ከበደል ነጻ ትሆናላችሁ” አላቸው።
\s5
\v 11 ስለዚህ በፍጥነት ስልቻዎቻቸውን አወረዱ፤ እያንዳንዱም የራሱን ስልቻ ከፈተ።
\v 12 ከዚያም አዛዡ ፍተሻውን ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ ቀጠለ። በመጨረሻም ጽዋው በብንያም ስልቻ ውስጥ ተገኘ።
\v 13 በዚህ ጊዜ ልብሶቻቸውን በሐዘን ቀደዱ፤ ሁሉም ስልቾቻቸውን በየአህዮቻቸው ጭነው ወደ ከተማይቱ ተመለሱ።
\s5
\v 14 ይሁዳና ወንድሞቹ ወደ ዮሴፍ ቤት ሲገቡ፣ ዮሴፍ ገና ከቤቱ አልወጣም ነበር። እነርሱም በፊቱ ተደፍተው ሰገዱ።
\v 15 ዮሴፍም፣ “ለምን እንዲህ ያለ ነገር አደረጋችሁ? እንደ እኔ ያለ ሰው ስውር ነገርን የሚያውቅበት ልዩ ጥበብ እንዳለው አታውቁምን? ” ሲል ጠየቃቸው።
\s5
\v 16 ይሁዳም፣ “ከእንግዲህ ለጌታችን ምን ማለት እንችላለን? ምንስ እንመልሳለን? እንዲህ ካለው በደል ንጹሕ መሆናችንን ማስረዳትስ እንዴት ይቻለናል? ምክንያቱም እግዚአብሔር የሠራነውን በደል ገልጦታል፤ እንግዲህ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሪያዎችህ እንሁን” አለ።
\v 17 ዮሴፍም፣ “ይህንስ አላደርገውም፣ ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ መሆን አለበት፤ ሌሎቻችሁ በሰላም ወደ አባታችሁ መመለስ ትችላላችሁ” አለ።
\s5
\v 18 ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፣ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፣ ምንም እንኳ የፈርዖን ያህል የተከበርክ ብትሆንም እባክህ አትቆጣኝ።
\v 19 ጌታዬ፣ ‘አባት ወይም ወንድም አላችሁ? ብሎ አገልጋዮቹን ጠይቆ ነበር።
\s5
\v 20 እኛም፣ ‘አዎን ሽማግሌ አባት አለን፤ አባታችንም በስተርጅና የወለደው ትንሽ ልጅ አለው፣ ወንድምዬው ሞቶአል፣ ከአንድ እናት ከተወለዱት ልጆች መካከል የተረፈው እርሱ ብቻ ነው፤ አባቱም በጣም ይወደዋል’ ብለንህ ነበር።
\v 21 ከዚያም አንተ አገልጋዮችህን፣ ‘እንዳየው ወደ እኔ አምጡት’ አልኸን።
\v 22 እኛም ለጌታዬ፣ ‘ልጁ ከአባቱ ሊለይ አይችልም፤ ከተለየው ደግሞ አባትዬው ይሞታል’ አልንህ።
\s5
\v 23 አንተ ግን እኛን አገልጋዮችህን፣ ‘ታናሽ ወንድማችሁ አብሮአችሁ ወደዚህ ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን ዐታዩም’ አልኸን።
\v 24 እኛም ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ በተመለስን ጊዜ አንተ ጌታዬ ያልኸንን ነገርነው።
\v 25 ከዚያም አባታችን፣ ‘እስቲ ተመልሳችሁ ጥቂት እህል ሸምቱልን’ ሲለን
\v 26 ‘መሄድ አንችልም፤ መሄድ የምንችለው ታናሽ ወንድማችን አብሮን ሲሄድ ብቻ ነው። ታናሽ ወንድማችንን ይዘን ካልሄድን በስተቀር የሰውዬውን ፊት ማየት አንችልም’ አልነው።
\s5
\v 27 አገልጋይህ አባቴም እንዲህ አለን፤ ‘ሚስቴ ሁለት ወንዶች ልጆች እንደወለደችልኝ ታውቃላችሁ፤
\v 28 አንዱ በወጣበት በመቅረቱ በእርግጥ አውሬ በልቶት ይሆናል አልሁ፣ ከዚያ በኋላ ዐላየሁትም።
\v 29 አሁን ደግሞ ይህን ልጅ ወስዳችሁ አንዳች ጉዳት ቢደርስበት ሽበቴን በመራር ሐዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።’
\s5
\v 30 እንግዲህ አሁን ልጁን ሳንይዝ ወደ አገልጋይህ ወደ አባቴ ብመለስ ሕይወቱ ከልጁ ሕይወት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ስለሆነ፣
\v 31 የልጁን ከእኛ ጋር አለመኖር ሲያይ አባቴ ይሞታል። ከዚህም የተነሣ እኛ አገልጋዮችህ የአባታችንን ሽበት በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እናወርደዋለን።
\v 32 እኔ አገልጋይህ፣ “ልጅህን መልሼ ሳላመጣ ብቀር ለዘላለም በደለኛ አድርገህ ቁጠረኝ’ በማለት ስለ ልጁ ደህንነት በአባቴ ፊት ራሴን ዋስ አድርጌአለሁ።
\s5
\v 33 ስለዚህ አሁን፣ አገልጋይህ በልጁ ፋንታ የአንተ የጌታዬ ባሪያ ሆኜ እዚሁ ልቅር ልጁ ግን ከወንድሞቹ ጋር ይመለስ።
\v 34 ልጁን ሳልይዝ እንዴት ተመልሼ ወደ አባቴ እሄዳለሁ? እባክህ በአባቴ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዳይ አታድርገኝ።”
\s5
\c 45
\p
\v 1 በዚያን ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩ ሰዎች ፊት ስሜቱን ሊገታ ባለመቻሉ፣ “እዚህ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፤ ስለዚህም ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ጊዜ ከእርሱ ጋር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም።
\v 2 ዮሴፍም ድምፁን ከፍ አድርጎ በማልቀሱ ግብፃውያን ሰሙት፣ ወሬውም ወደ ፈርዖን ቤተ ሰዎች ደረሰ።
\v 3 ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ? ” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም።
\s5
\v 4 ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በሉ” አላቸው፣ ወደ እርሱም በቀረቡ ጊዜ እንዲህ አለ፤ “ወደ ግብፅ የሸጣችሁኝ እኔ ዮሴፍ ነኝ፤
\v 5 አሁንም በመሸጣችሁ አትቆጩ፤ በራሳችሁም አትዘኑ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወት ለማዳን ሲል ከእናንተ አስቀድሞ እኔን ወደዚህ ልኮኛል።
\v 6 በምድር ላይ ራብ ከገባ ይኸው ሁለት ዓመት ሆነ፣ ከዚህ በኋላም የማይታረስባቸውና ሰብል የማይሰበሰብባቸው አምስት ዓመታት ገና አሉ።
\s5
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ሕይወታችሁን በታላቅ ማዳን ለመታደግና ዘራችሁ ከምድር ላይ እንዳይጠፋ በማሰብ ከእናንተ አስቀድሞ ወደዚህ ላከኝ።
\v 8 ስለዚህ አሁን ወደዚህ የላከኝ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፣ እርሱም ለፈርዖን እንደ አባት፤ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታ፣ እንዲሁም በግብፅ ምድር ላይ ገዢ አደረገኝ።
\s5
\v 9 አሁንም ‘በፍጥነት ወደ አባቴ ተመልሳችሁ እንዲህ በሉት፤ “ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይላል፤ ‘እግዚአብሔር የመላው ግብፅ ጌታ አድርጎኛል፤ ስለዚህ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና።
\v 10 ልጆችህን የልጅ ልጆችህን በጎችህን፣ ፍየሎችህን ከብቶችህንና ያለህን ሁሉ ይዘህ በአቅራቢያዬ በጌሤም ትኖራለህ።
\v 11 ገና ወደ ፊት የሚመጣ የአምስት ዓመት ራብ ስላለ፣ በዚያ የሚያስፈልጋችሁን እኔ እሰጣችኋለሁ፤ ያለበልዚያ ግን አንተና ቤተ ስዎችህ ያንተም የሆነው ሁሉ፣ ችግር ላይ ትወድቃላችሁ።’
\s5
\v 12 ፊታችሁ ሆኜ የማናግራችሁ እኔ ዮሴፍ ራሴ መሆኔን እናንተም ሆናችሁ ወንድሜ ብንያም በዓይናችሁ የምታዩት ነው።
\v 13 በግብፅ ስላሏኝ ክብርና ስላያችሁትም ሁሉ ለአባቴ ንገሩት፣ አባቴንም በፍጥነት ይዛችሁት ኑ።
\s5
\v 14 ከዚያም በወንድሙ በብንያም አንገት ላይ ተጠምጥሞ አለቀሰ፤ ብንያምም እያለቀሰ ዮሴፍን አቀፈው።
\v 15 የቀሩትምንም ወንድሞቹን አንድ በአንድ እየሳመ አለቀሰ። ከዚያም ወንድሞቹ ከእርሱ ጋር መጨዋወት ጀመሩ።
\s5
\v 16 የዮሴፍ ወንድሞች መምጣት በፈርዖን ቤተ መንግሥት በተሰማ ጊዜ፣ ፈርዖንና ሹማምንቱ ሁሉ ደስ አላቸው።
\v 17 ፈርዖን ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ለወድሞችህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘እንዲህ አድርጉ እህዮቻችሁን ጭናችሁ ወደ ከነዓን ምድር ተመለሱ።
\v 18 ከዚያም አባታችሁንና ቤተ ሰባችሁን ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም እጅግ ለም ከሆነው የግብፅ ምድር እሰጣችኋለሁ፤ በምድሪቱ በረከት ደስ ብሎአችሁ ትኖራላችሁ።’
\s5
\v 19 ደግሞም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፤ ‘ይህን አድርጉ፣ ከግብፅ ምድር ልጆቻችሁንና ሚስቶቻችሁን የምታጓጉዙባቸው ሠረገላዎች ወስዳችሁ፤ አባታችሁን ይዛችሁ ኑ።
\v 20 ስለ ንብረታችሁ ምንም አታስቡ፣ ከግብፅ ምድር እጅግ ለም የሆነው የእናንተ ይሆናልና።’”
\s5
\v 21 የእስራኤልም ልጆች ይህንኑ አደረጉ። ዮሴፍም ፈርዖን ባዘዘው መሠረት ሠረገላዎች አቀረበላቸው፤ የመንገድም ስንቅ አስያዛቸው።
\v 22 ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት የክት ልብስ ሰጣቸው፤ ለብንያም ግን ሶስት መቶ ጥሬ ብርና አምስት የክት ልብስ ሰጠው።
\v 23 ለአባቱም በግብፅ ምድር ከሚገኘው የተመረጠ ነገር በዐሥር አህዮች፣ እንደዚሁም በዐሥር እንስት አህዮች ዳቦና ሌላ ምግብ አስጭኖ ሰደደለት።
\s5
\v 24 ከዚህ በኋላ ወንድሞቹን አሰናበታቸው፤ ከእርሱም ሲሰናበቱ፣ መንገድ ላይ እንዳትጣሉ” አላቸው።
\v 25 እነርሱም ከግብፅ ወጥረው በከነዓን ምድር ወደሚኖረው ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ መጡ።
\v 26 አባታቸውንም፣ እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብፅ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኖአል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።
\s5
\v 27 ነገር ግን ዮሴፍ ያላቸውን ሁሉ በነገሩት ጊዜና እርሱን ወደ ግብፅ የሚወስዱበትን ዮሴፍ የላከለትን ሠረገላ ባየ ጊዜ የአባታቸው የያዕቆብ መንፈስ ታደሰ።
\v 28 ከዚያም እስራኤል፣ “ልጄ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ ከመሞቴ በፊት ሄጄ ዐየዋለሁ” አለ።
\s5
\c 46
\p
\v 1 እስራኤልም ጓዙን ሁሉ ጠቅልሎ ተነሣ፤ ቤርሳቤህም ሲደርስ፣ ለአባቱ ለይስሐቅ አምላክ መሥዋዕት ሠዋ።
\v 2 እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ፣ “ያዕቆብ፣ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፣ አለሁ” አለ።
\v 3 እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ወደ ግብፅ ለመውረድ አትፍራ፤ በዚያ ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁና፤
\v 4 አብሬህ ወደ ግብፅ እወርዳለሁ፣ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፣ የዮሴፍ የራሱ እጆች በምትሞትበት ጊዜ ዓይኖችህን ይከድናል።
\s5
\v 5 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሣ፤ የእስራኤል ወንዶች ልጆችም አባታቸውን ያዕቆብን ልጆቻቸውንና ሚስቶቻቸውን ፈርዖን ለያዕቆብ በላከላቸው ሠረገላ ላይ አወጧቸው።
\v 6 ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብፅ ወረዱ።
\v 7 ወደ ግብፅም የወረደው፤ ወንዶች ልጆቹንና ወንዶች የልጅ ልጆቹን፣ ሴቶች ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን ማለት ዘሮቹን ሁሉ ይዞ ነው።
\s5
\v 8 ወድ ግብፅ የወረዱት የእስራኤል ልጆች፣ የያዕቆብ ዘሮቹ እነዚህ ናቸው፦ የያዕቆብ የበኩል ልጆ ሮቤል።
\v 9 የሮቤል ልጆች፦ ሄኖኅ፣ ፈሉሶ፣ አስሮን እና ከርሚ ናቸው።
\v 10 የስሞዖን ልጆች፦ ይሙኤል፣ ያሚን፣ ኦሃድ፣ ያኪን፣ ጸሐርና ከከነዓናዊቷ ሴት የተወለደው ሳኡል ናቸው።
\v 11 ልጆች፦ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው።
\s5
\v 12 የይሁዳ ልጆች፦ ዔር አውናን፣ ሴሎም፣ ፋሬስ እና ዛራ ናቸው። ነገር ግን ዔርና አውናን በከነዓን ምድር ሞቱ።
\v 13 የይሳኮር ልጆች፦ ቶላ፣ ፉዋ፣ ዮብና ሺምሮን ናቸው፤
\v 14 የዛብሎን ልጆች፦ ሴሬድ፣ ኤሎንና ያሕልኤል ናቸው፤
\v 15 እነዚህ ወንዶች ልጆች ያዕቆብ በሰሜን ምዕራብ መሰጴጦምያ ሳለ፣ ልያ የወለደችለት ናቸው። ሴቷን ዲናን ጨምሮ፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆቹ ቁጥር ሠላሳ ሦስት ነው።
\s5
\v 16 የጋድ ልጆች፦ ጽፎን፣ ሐጊ፣ ሹኒ፣ ኤስቦን፣ ዔሪ፣ አሮዲና አርኤሊ ናቸው፤
\v 17 የአሴር ልጆች፦ ዩምና፣ የሱዋ፣ የሱዊና በሪዓ ናቸው፤ እኅታቸውም ሤራሕ ናት፤ የበሪዓ ልጆች፦ ሐቤርና መልኪኤል ናቸው፤
\v 18 እነዚህ ዐሥራ ስድስት ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለልያ ከሰጣት ከዘለፋ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።
\s5
\v 19 የያዕቆብ ሚስት የራሔል ልጆች፦ ዮሴፍና ብንያም ናቸው፤
\v 20 በግብፅም የኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናት፣ ምናሴንና ኤፍሬምን ለዮሴፍ ወለደችለት።
\v 21 የብንያም ልጆች፦ቤላ፣ ቤኬር፣ አስቤል፣ ጌራ፣ ንዕማን፥ አኪ፣ ሮስ፥ ማንፌን፣ ሑፊምና አርድ ናቸው።
\v 22 እነዚህ ዐሥራ አራቱ፣ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ልጆችና የልጅ ልጆች ናቸው።
\s5
\v 23 የዳን ልጅ፦ ሑሺም ነው፤
\v 24 የንፍታሌም ልጆች፦ ያሕጽኤል፣ ጉኒ፣ ዮጽርና ሺሌም ናቸው፤
\v 25 እነዚህ ሰባቱ ልጆች ሁሉ ላባ ለልጁ ለራሔል ከሰጣት ከባላ ላይ ያዕቆብ የወለዳቸው ናቸው።
\s5
\v 26 ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የሄዱት የገዛ ዘሮቹ ብዛት ስድሳ ስድስት ሲሆን የልጆቹን ሚስቶች አይጨምርም።
\v 27 ዮሴፍ በግብፅ የወለዳቸውን ሁለት ልጆች ጨምሮ ወደ ግብፅ የወረደው የያዕቆብ ቤተ ሰብ ቁጥር ሰባ ነበር።
\s5
\v 28 ያዕቆብም ወደ ጌሤም ለመሄድ መመሪያ ይቀበል ዘንድ፣ ይሁዳን አስቀድሞ ወደ ዮሴፍ ላከው። እርሱም ጌሤም ሲደርሱ፣
\v 29 ዮሴፍ ሠረገላውን አዘጋጅቶ፤ አባቱን እስራኤልን ለመቀበል ወደ ጌሤም አመራ። ዮሴፍ አባቱ ዘንድ እንደደረሰ አንገቱ ላይ ተጠምጥሞ ለረጅም ጊዜ አለቀሰ።
\v 30 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “በሕይወት መኖርህን ስላየሁ፣ ከእንግዲህ ብሞትም አይቆጨኝም” አለው።
\s5
\v 31 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ እነግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል።
\v 32 ሰዎቹ ከብት የሚጠብቁ ስለሆኑ እረኞች ናቸው፣ ሲመጡም በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውንና ከብቶቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው መጥተዋል።
\s5
\v 33 ፈርዖን አስጠርቶአችሁ፣ ‘ሥራችሁ ምንድን ነው? ብሎ ቢጠይቃችሁ፤
\v 34 እናንተ፣ ‘እኛ አገልጋዮችህ ሥራችን ከልጅነታችን ጀምሮ ልክ እንደ አባቶቻችን ከብት ማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። ከብት አርቢዎች በግብፃውያን ዘንድ እንደ ጸያፍ ስለሚቆጠሩ፣ በጌሤም ምድር እንድትኖሩ ይፈቅድላችኋል።”
\s5
\c 47
\p
\v 1 ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ፣ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውን፣ ፍየሎቻቸውን እንዲሁም ያላቸውን ሁሉ ይዘው ከከነዓን አገር መጥተው በጌሤም ሰፍረዋል” አለው።
\v 2 ከወንድሞቹም መካከል አምስቱን መርጦ፣ ፈርዖን ፊት አቀረባቸው።
\s5
\v 3 ፈርዖን የዮሴፍን ወንድሞች፣ “ሥራችሁን ምንድነው? ” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም ፈርዖንን፣ “እኛ አገልጋዮችህ ልክ እንደአባቶቻችን ከብት አርቢዎች ነን” አሉት።
\v 4 ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት።
\s5
\v 5 ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “አባትንህና ወንድሞችህ ወደ አንተ መጥተዋል፤
\v 6 የግብፅ ምድር እንደሆነ በእጅህ ነው፤ አባትህንና ወንድሞችህን ምርጥ በሆነው ምድር አስፍራቸው፤ በጌሤም ይኑሩ። ከመካከላቸው ልዩ ችሎታ ያላቸው መኖራቸውን የምታውቅ ከሆነ፣ የከብቶቼ ኅላፊዎች አድርጋቸው።”
\s5
\v 7 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ አባቱን ያዕቆብን ቤተ መንግሥት አግብቶ በፈርዖን ፊት አቀረበው፤ ያዕቆብ ፈርዖንን ከመረቀው በኋላ
\v 8 ፈርዖን፣ “ለመሆኑ ዕድሜህ ምን ያህል ነው? ” ሲል ያዕቆብን ጠየቀው።
\v 9 ያዕቆብም ለፈርዖን፣ “በምድር ላይ በእንግድነት ያሳለፍሁት ዘመን 130 ዓመት ነው፤ ይህም አባቶቼ በእንግድነት ከኖሩበት ዘመን ጋር ሲነጻጸር አጭር ነው፤ ችግር የበዛበትም ነበር” ሲል መለሰለት።
\v 10 ከዚያም ያዕቆብ ፈርዖንን መርቆ፣ ተሰናብቶት ወጣ።
\s5
\v 11 ዮሴፍም አባቱንና ወንድሞቹን በግብፅ እንዲኖሩ አደረገ፤ ፈርዖን በሰጠውም ትእዛዝ መሠረት ምርጥ ከሆነው ምድር ራምሴን በርስትነት ሰጣቸው።
\v 12 ዮሴፍም ለአባቱ፣ ለወንድሞቹና ለመላው የአባቱ ቤተ ሰዎች በልጆቻቸው ቁጥር ልክ ቀለብ እንዲሰፈርላቸው አደረገ።
\s5
\v 13 በመላው ምድር እህል ባለመኖሩ ራቡ እየጸና ሄደ፤ ከዚህ የተነሣም ግብፅና ከነዓን በራብ እጅግ ተጎዱ፤
\v 14 ዮሴፍ የግብፅና የከነዓን ሰዎች እህል በመሸመት የከፈሉትን ገንዘብ ሁሉ ሰብስቦ ወደ ፈርዖን ቤተ መንግሥት አስገባ።
\s5
\v 15 የግብፅና የከነዓን ሕዝቦችም ገንዘባቸው ባለቀ ጊዜ፣ ግብፃውያን ሁሉ ወደ ዮሴፍ ቀርበው፣ “የምንበላው እህል ስጠን፣ ገንዘባችን አልቆብናል፤ ዓይንህ እያየ እንዴት በራብ እንለቅ? ” አሉት።
\v 16 ዮሴፍም ከብቶቻችሁን አምጡ፣ ገንዘባችሁ ካለቀ በከብቶቻችህ ለውጥ እህል እሰጣችኋለሁ አለ።
\v 17 ስለዚህ ከብቶቻቸውን ወደ ዮሴፍ አምጡ፤ እርሱም በፈረሶቻቸው፣ በበጎቻቸው፣ በፍየሎቻቸው፣ በከብቶቻቸውና በአህዮቻቸው ለውጥ እህል ሰጣቸው። በከብቶቻቸው ልዋጭ ባገኙት ምግብ በዚያ ዓመት ሳይራቡ እንዲያልፉ አደረጋቸው።
\s5
\v 18 ያም ዓመት ካለፈ በኋላ ሕዝቡ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ዮሴፍ መጥተው እንዲህ አሉት፣ “እንግዲህ ከጌታችን የምንሰውረው ምንም ነገር የለም፤ ገንዘባችን አልቆአል፤ ከብቶቻችንንም አስረክበንሃል፤ እንግዲህ ለጌታችን የምንሰጠው፣ ከሰውነታችንና ከመሬታችን በቀር ሌላ ምንም ነገር የለንም።
\v 19 ታዲያ እያየኸን እንዴት እንለቅ? መሬታችንም ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንና መሬታችንን ውሰድና በለውጡ እህል ስጠን፤ እኛ የፈርዓን አገልጋዮች እንሆናለን፤ መሬታችንም የእርሱ ይሁን፣ እኛም እንዳንሞት መሬታችንም ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው ዘር ስጠን።
\s5
\v 20 ስለዚህ ዮሴፍ የግብፅን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛለት፤ ራቡም እጅግ ስለጸናባቸው ግብፃውያን ሁሉ መሬታቸውን ሸጡ፣ ምድሪቱም የፈርዖን ርስት ሆነች።
\v 21 ዮሴፍ በግብፅ አገር ዳር እስከ ዳር ያሉት ሰዎች ሁሉ የንጉሡ አገልጋዮች እንዲሆኑ አደረገ።
\v 22 ሆኖም ዮሴፍ የካህናቱን መሬት አልገዛም፤ ምክንያቱም ካህናቱ ከፈርዖን ቋሚ አበል ስለሚያገኙ እርሱም ከሚሰጣቸው አበል ምግብ ያገኙ ስለነበረ መሬታቸውን አልሸጡም።
\s5
\v 23 ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፣ “እነሆ፣ ዛሬ እናንተንም መሬታችሁንም ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁና ይህን ዘር ወስዳችሁ በመሬት ላይ ዝሩ።
\v 24 መከሩ በሚሰበሰብበት ጊዜ ግን ከአምስት እጅ አንዱን ለፈርዖን ታስገባላችሁ፣ ከአምስት እጅ አራቱን ደግሞ ለመሬታችሁ ዘር፣ እንዲሁም ለራሳችሁ፣ ለቤተ ሰቦቻችሁና ለልጆቻችሁ ምግብ ታደርጉታላችሁ።”
\s5
\v 25 እነርሱም፣ “እንግዲህ ሕይወታችንን አትርፈህልናል፤ በጌታችን ፊት ሞገስ ካገኘን ለፈርዖን ገባሮች እንሆናለን” አሉት።
\v 26 ስለዚህ ዮሴፍ የምርቱ አንድ አምስተኛ ለፈርዖን እንዲገባ የሚያዝ የመሬት ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ይሠራበታል። በፈርዖን እጅ ያልገባው መሬት የካህናቱ ብቻ ነው።
\s5
\v 27 በዚህ ጊዜ እስራኤላውያን በግብፅ አገር በጌሤም ይኖሩ ነበር፣ በዚያም ሀብት ንብረት አፈሩ፤ ቁጥራቸውም እጅግ እየበዛ ይሄድ ጀመር።
\v 28 ያዕቆብ በግብፅ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ፣ ዕድሜውም አንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነበር።
\s5
\v 29 እስራኤልም የሚሞትበት ጊዜ መቃረቡን እንደተረዳ ልጁን ዮሴፍን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “በአንተ ዘንድ ሞገስ ካገኘሁ እጅህን በጭኔ ላይ አኑረህ፣ በጎነትንና ታማኝነትን ልታደርግልኝ ቃል ግባልኝ፤ በምሞትበት ጊዜ በግብፅ አትቅበረኝ፤
\v 30 እኔም ከአባቶቼ ጋር ሳንቀላፋ ከግብፅ አውጥተህ እነርሱ በተቀበሩበት ቦት ቅበረኝ” ዮሴፍም፣ “እሺ፣ እንዳልኸኝ አደርጋለሁ” አለ።
\v 31 ያዕቆብ፤ “በል ማልልኝ” አለው። ዮሴፍም ማለለት፣ እስራኤልም በአልጋው ራስጌ ላይ ሆኖ ጎንበስ አለ።
\s5
\c 48
\p
\v 1 ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ስለተነገረው ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ።
\v 2 ለያዕቆብ፣ “ልጅህ ዮሴፍ ወደ አንተ መጥቶአል” ተብሎ በተነገረው ጊዜ፣ እስራኤል ተበረታትቶ አልጋው ላይ ተቀመጠ።
\s5
\v 3 ያዕቆብም ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር ሎዛ በምትባል ቦታ ተገለጠልኝ፤ ባረከኝም፤
\v 4 እንዲህም አለኝ፤ ‘ፍሬያማ አደርግሃለሁ፣ ዝርያዎችህም ብዙ ሕዝቦች ይሆናሉ፣ ይህችንም ምድር ለዝርያዎችህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ’ አለኝ።”
\s5
\v 5 ወደዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ የወለድሃቸው ሁለቱ ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ሆነው ይቆጠራሉ፤ ሮቤልና ስምዖን ልጆቼ እንደሆኑ ሁሉ፣ ኤፍሬምና ምናሴም ልጆቼ ይሆናሉ።
\v 6 ከእነርሱ በኋላ የሚወለዱልህ ልጆች ግን፣ የአንተ ይሁኑ፤ በርስት ድልድላችው ግን በወንድሞቻቸው ስም ይቆጠራሉ።
\v 7 ከሰሜን ምዕራብ መስጴጦምያ ስመለስ ኤፍራታ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረኝ፤ እናትህ ራሔል በከነዓን ምድር ሞታብኝ አዘንሁ። እኔም ወደ ኤፍራታ ማለት ወደ ቤተ ልሔም በሚወስደው መንገድ ዳር ቀበርኋት።”
\s5
\v 8 እስራኤልም የዮሴፍን ልጆች ባየ ጊዜ፣ “እነዚህ እነማን ናቸው? ” ሲል ጠየቀ፤
\v 9 ዮሴፍም፣ “እነዚህ እግዚአብሔር የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ብሎ መለሰለት፤ እስራኤልም “አቅርባቸውና ልመርቃቸው” አለ።
\v 10 በዚህ ጊዜ እስራኤል ዓይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ አቀፋቸው።
\s5
\v 11 እስራኤልም ዮሴፍን፣ “ዓይንህን እንደገና ዐያለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ልጆችህን ጭምር ለማየት አበቃኝ” አለው።
\v 12 ዮሴፍም ልጆቹን ከእስራኤል ጉልበት ፈቀቅ በማድረግ አጎንብሶ በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ።
\v 13 ከዚያም ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ይዞ ኤፍሬምን ከራሱ በስተቀኝ ከእስራኤል በስተግራ፣ ምናሴን ደግሞ ከራሱ በስተግራ ከእስራኤል በስተቀኝ በኩል አቀረባቸው።
\s5
\v 14 እስራኤል ግን ቀኝ እጁን በታናሹ በኤፍሬም ራስ ላይ አኖረ፣ ግራ እጁንም በቀኝ እጁ ላይ አስተላልፎ በበኩሩ በምናሴ ላይ አኖረ።
\v 15 ከዚህ በኋላ ዮሴፍን ባረከ፤ እንዲህም አለው፤ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና ለእኔም እስከ ዛሬ ድረስ በዘመኔ ሁሉ እረኛ የሆነኝ አምላክ፣
\v 16 ከጉዳትም ሁሉ የታደገኝ ምልአክ፣ እርሱ እነዚህን ልጆች ይባርክ፤ እነርሱም በስሜ፣ በአባቶቼ በአብርሃምና በይስሐቅ ስም ይጠሩ፣ በምድር ላይ እጅግ ይብዙ።
\s5
\v 17 ዮሴፍ አባቱ ቀኝ እጁን በኤፍሬም ራስ ላይ ማድረጉን ሲያይ ቅር ተሰኘ፤ ከኤፍሬም ራስ ላይ አንስቶ በምናሴ ራስ ላይ ለማኖር የአባቱን እጅ ያዘ፤
\v 18 ዮሴፍም፣ “አባቴ ሆይ፣ እንዲህ አይደለም በኩሩ ይህኛው ስለሆነ፣ ቀኝ እጅህን እርሱ ራስ ላይ አድርግ” አለው።
\s5
\v 19 አባቱ ግን፣ “ዐውቃለሁ፣ ልጄ ዐውቃለሁ፣ እርሱም እኮ ሕዝብ ይሆናል፤ ታላቅም ይሆናል፤ ይሁን እንጂ፣ ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል፤ ዘሮቹም ታላቅ ሕዝቦች ይሆናሉ” ብሎ እምቢ አለው።
\v 20 በዚያን ዕለት ባረካቸው፣ እንዲህም አላቸው፤ “እስራኤላውያን በሚመርቁበት ጊዜ የእናንተን ስም በማስታወስ፤ ‘እግዚአብሔር እንደ ኤፍሬምና እንደ ምናሴ ያድርጋችሁ’ ይላሉ” በዚህ ሁኔታም ኤፍሬምን ከምናሴ አስቀደመው።
\s5
\v 21 ከዚህ በኋላ እስራኤል ዮሴፍን እንዲህ አለው፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ወደ አባቶቻችሁም ምድር መልሶ ያገባችኋል።
\v 22 እነሆ በሰይፌና በቀስቴ ከአሞራውያን እጅ የወሰድኋትን ምድር ከወንድሞችህ ድርሻ አብልጬ ለአንተ ሰጥቼሃለሁ።”
\s5
\c 49
\p
\v 1 ያዕቆብ ልጆቹን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “በአንድነት ተሰብሰቡና ወደፊት የሚገጥማችሁን ነገር ልንገራችሁ፣
\v 2 እናንተ የያዕቆብ ልጆች፣ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፣ አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ።
\s5
\v 3 ሮቤል፣ ኃይልና የጎልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ የወለድሁህ የበኩር ልጄ ነህ። ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኃይል የምትበልጥ አንተ ነህ።
\v 4 ይሁን እንጂ እንደ ውሃ የምትዋልል ስለሆንህ የበላይ አለቅነት ለአንተ አይገባም፣ ምክያንቱም የአባትህን መኝታ ደፍረሃል ምንጣፌንም አርክሰሃል።
\s5
\v 5 “ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው፣ ዓመፅ ለመፈጸም የጦር መሣሪያዎቻቸውን ያነሳሉ።
\v 6 ወደ ሸንጎአቸው አልግባ፣ ጉባኤያቸው ውስጥ አልገኝ፣ በቁጣ ተነሣስተው ወንዶችን ገድለዋል፣ የበሬዎችንም ቋንጃ እንደፈለጉ ቆራርጠዋል።
\s5
\v 7 እጅግ አስፈሪ የሆነ ቁጣቸው፣ ጭከና የተሞላ ንዴታቸው የተረገመ ይሁን፤ በያዕቆብ እበትናቸዋለሁ፣ በመላው እስራኤልም አሠራጫቸዋለሁ።
\s5
\v 8 ይሁዳ ወንድሞችህ ያመሰግኑሃል፣ እጅህም የጠላቶችህን አንገት አንቆ ይይዛል፣ የአባትህ ልጆች በፊትህ ተደፍተው ይስግዱልሃል።
\s5
\v 9 ይሁዳ እንደ ደቦል አንበሳ ነው፣ ከዐደንህ የምትመለስ ልጄ፣ እንደ አንበሳ ያደፍጣል በምድርም ላይ ይተኛል፤ እንደ እንስት እንበሳም ያደባል፣ ታዲያ ማን ሊቀሰቅሰው ይደፍራል?
\s5
\v 10 በትረ መንግስሥት ከይሁዳ እጅ አይወጣም፤ የገዥነት ምርኩዝም ከእግሮቹ መካከል፣ ሕዝቦች ሁሉ የሚታዘዙለት ‘ሴሎ’ እስኪመጣ ድረስ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይታዘዙለታል።
\s5
\v 11 አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፣ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጎናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።
\v 12 ዓይኖቹ ከወይን ጠጅ የቀሉ፣ ጥርሶቹም ከወተት ይልቅ የነጡ ይሆናሉ።
\s5
\v 13 ዛብሎን በባሕር ዳርቻ ይኖራል፣ የመርከቦቹ መጠጊያም ይሆናል፣ ወሰኑም እስከ ሲዶና ይደርሳል።
\s5
\v 14 ይሳኮር፣ አጥንተ ብርቱ አህያ በጭነት መካከል የሚተኛ፣ ማረፊያ ቦታው መልካም፣
\v 15 ምድሪቱም አስደሳች መሆኗን ሲያይ፣ ትከሻውን ለሸክም ዝቅ ያደርጋል ከባድ የጉልበት ሥራም ይሠራል።
\s5
\v 16 ዳን ከእስራኤል ነገዶች እንደ አንዱ ሆኖ በራሱ ሕዝብ ላይ ይፈርዳል።
\v 17 ዳን የመንገድ ዳር እባብ፣ የመተላለፊያም መንገድ እፉኝት ነው፤ ጋላቢው የኋሊት እንዲወድቅ፣ የፈረሱን ሰኮና ይነክሳል።
\v 18 እግዚአብሔር ሆይ፣ ማዳንህን እጠባበቃለሁ።
\s5
\v 19 ጋድን ወራሪዎች አደጋ ይጥሉበታል፣ እርሱ ግን ዱካቸውን ተከታትሎ ብድሩን ይመልሳል።
\v 20 አሴር ማዕደ ሰፊ ይሆናል፤ ለነገሥታትም የሚስማማ ምግብ ያቀርባል።
\v 21 ነጻ እንደተለቀቀች ሚዳቋ ነው፣ የሚያማምሩ ግልገሎች ይኖሩታል።
\s5
\v 22 ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣ በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው። ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ።
\v 23 ቀስተኞች በብርቱ ያጠቁታል፤ በቀስታቸውም እየነደፉ ያሳድዱታል፤
\s5
\v 24 ነገር ግን በያዕቆብ ኃያል አምላክ ክንድ፣ እረኛም በሆነው በእስራኤል አለት ቀስቱ ጸና ጠንካራ ክንዱም ቀልጣፋ ሆነ።
\s5
\v 25 አንተን በሚረዳህ በአባትህ አምላክ፣ በሚባርክህ ሁሉን በሚችል አምላክ፣ ከላይ ከሰማይ በሚገኝ ረድኤት፣ ከምድር ጥልቅ በሚገኝ በረከት፣ ከማኅፀንና ከጡት በሚገኝ ምርቃት ይባርክሃል።
\s5
\v 26 ከጥንት ተራሮች በረከት፣ ከዘላለም ኮረብቶች ምርቃት ይልቅ፣ የአባትይ በረከት ይበልጣል፤ ይህ ሁሉ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ፤ በወንድሞቹ መካከል አለቃ በሆነውም ግንባር ላይ ይረፍ።
\s5
\v 27 ብንያም ነጣቂ ተኩላ ነው፤ ያደነውን ማለዳ ይበላል፤ የማረከውን ማታ ያከፋፍላል።
\s5
\v 28 እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።
\v 29 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ “እኔ የምሞትበትና ወደ ወገኖቼ የምሰበሰብበት ጊዜ ደርሶአል፤ ስለዚህ በኬጢያዊው በኤፍሮን እርሻ ውስጥ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ዘንድ ቅበሩኝ፤
\v 30 ይህንን በከነዓን ምድር በመምሬ አጠገብ በማክፌል እርሻ ውስጥ ያለውን ዋሻ የመቃብር ቦታ እንዲሆን ከኬጢያዊው ኤፍሮን ላይ የገዛው አብርሃም ነው።
\s5
\v 31 በዚያ አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ተቀብረዋል፤ በዚያ ይስሐቅና ሚስቱ ርብቃ ተቀብረዋል፤ እኔም ልያን የቀበርኋት እዚያው ነው፤
\v 32 እርሻውና ዋሻው የተገዙት ከኬጢያውያን ላይ ነው።”
\v 33 ያዕቆብ እነዚህን ቃላት ለልጆቹ ተናግሮ እንዳበቃ እግሮቹን በአልጋው ላይ ሰብስቦ የመጨረሻ ትንፋሹን ተንፍሶ ሞተ፣ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።
\s5
\c 50
\p
\v 1 ዮሴፍ እጅግ ከማዘኑ የተነሣ በአባቱ ፊት ተደፍቶ አለቀሰ ሳመውም።
\v 2 ከዚያም የአባቱ የእስራኤል አስከሬን እንዳይፈርስ ባለ መድኃኒት የሆኑ አገለጋዮች በመድኃኒት እንዲያሹት አዘዘ። ባለ መድኃኒቶቹም አስከሬኑ እንዳይፈርስ በመድኃኒት አሹት።
\v 3 በአገሩ ልማድ መሠረት አስከሬኑ እንዳይፈርስ ማሸቱ አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ገብፃውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት።
\s5
\v 4 የለቅሶው ወራት በተፈጸመ ጊዜ ዮሴፍ የፈርዖንን ባለሥልጣኖች እንዲህ አላቸው፤ “መልካም ፈቃዳችሁ ቢሆን እባካችሁ ለፈርዖን፣
\v 5 ‘አባቴ ለመሞት ሲቃረብ በከነዓን ምድር ባዘጋጀው መቃብር እንድቀብረው በመሐላ ቃል አስገብቶኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ቀብሬ እንድመለስ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቆአል’ ብላችሁ ንገሩልኝ” አላቸው።
\v 6 ፈርዖንም፣ “ባስማለህ መሠረት ሄደህ አባትህን ቅበር” አለው።
\s5
\v 7 ስለዚህ ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ሄደ፣ የፈርዖን ሹማምንት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የግብፅ ከፍተኛ ባለ ሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት።
\v 8 እንደዚሁም የዮሴፍ ቤተ ሰቦች ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተ ሰቦች ሁሉ ከዮሴር ጋር ሄዱ፣ በጌሤም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፣ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋዎቻቸው ብቻ ነበሩ።
\v 9 እንዲሁም ሠረገሎች፣ ፈረሰኞች አብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበር።
\s5
\v 10 እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አጣድ ከተባለው ዐውድማ ሲደርሱ ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ ምርር ብለው አለቀሱ፤ ዮሴፍም በዚያ ለአባቱ ሰባት ቀን ለቅሶ ተቀመጠ።
\v 11 በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ ዐውድማ የተደረገውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፣ “ይህ ለግብፃውያን መራራ ልቅሶአቸው ነው” አሉ። በዮርዳኖስ አጠገብ ያለው የዚያ ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ተብሎ መጠራቱም ከዚሁ የተነሣ ነበር።
\s5
\v 12 በዚህ ሁኔታ የያዕቆብ ልጆች አባታቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ፤
\v 13 አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦት እንዲሆን ከኬጢያዊው ከኤፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።
\v 14 ዮሴፍ አባቱን ከቀበረ በኋላ ከወንድሞቹና ለቀብር አጅበውት ከሄዱት ሰዎች ሁሉ ጋር ሆኖ ወደ ግብፅ ተመለሰ።
\s5
\v 15 የዮሴፍ ወንድሞች ከአባታቸው ሞት በኋላ፣ “ከፈጸምንበት በደል የተነሣ ዮሴፍ ቂም ይዞ በበቀልን ምን እናደርጋለን ተባባሉ።
\v 16 ስለዚህ እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ፣ አባትህ ከመሞቱ በፊት፣
\v 17 ‘ለዮሴፍ ወንድሞችህ በአንተ ላይ የፈጸሙትን ኃጢአትና ክፉ በደል ይቅር በላቸው’ ብላችሁ ንገሩት የሚል ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። አሁንም የአባትህን አምላክ አገልጋዮች ኃጢአት ይቅር በለን።” ዮሴፍ ይህን በሰማ ጊዜ አለቀሰ።
\s5
\v 18 ከዚያም ወንድሞቹ መጡና በፊቱ ተደፍተው፣ “እኛ የአንተ አገልጋዮች ነን” አሉት።
\v 19 ዮሴፍ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፣ እኔ በእግዚአብሔር ምትክ የተቀመጥሁ አይደለሁም፣
\v 20 እናንተ እኔን ለመጉዳት አስባችሁ አድርጋችሁት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደሚታየው ሁሉ የብዙዎችን ሕይወት ለማዳን ለበጎ ነገር አዋለው።
\v 21 አሁንም ቢሆን አትፍሩ፤ ለእናንተና ለልጆቻችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አደርግላችኋለሁ” በማለት በመልካም ንግግር አረጋጋቸው።
\s5
\v 22 ዮሴፍ ከአባቱ ቤተ ሰቦች ጋር በግብፅ ተቀመጠ፤ አንድ መቶ ዐሥር ዓመትም ኖረ፤
\v 23 የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ ዐየ። ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች በጭኑ ላይ አድርጎ አቀፋቸው።
\s5
\v 24 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተ ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጎበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል።
\v 25 እግዚአብሔር በሚጎበኛችሁና ወደዚያች ምድር በሚመልሳችሁ ጊዜ ዐጽሜን ከዚህ ይዛችሁ የምትወጡ መሆናችሁን በማረጋገጥ ቃል ግቡልኝ” ብሎ አስማላቸው።
\v 26 ዮሴፍም ዕድሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሞላው ሞተ፣ አስከሬኑንም መድኃኒት ቀብተው በሬሳ ሳጥን ካስገቡት በኋላ በግብፅ ምድር አስቀመጡት።

1664
03-LEV.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1664 @@
\id LEV
\ide UTF-8
\h ኦሪት ዘሌዋውያን
\toc1 ኦሪት ዘሌዋውያን
\toc2 ኦሪት ዘሌዋውያን
\toc3 lev
\mt ኦሪት ዘሌዋውያን
\s5
\c 1
\p
\v 1 ያህዌ ከመገናኛው ድንኳን ሆኖ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤላዊያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ከእናንተ መሃል ማንም ሰው ለያህዌ መባ በሚያቀርብበት ጊዜ ከከብቶቻችሁ ወይም ከመንጋው እንስሳት መሃል አንዱን ያቅርብ፡፡
\s5
\v 3 መባው ከመንጋው መሃል የሚቃጠል መስዋዕት ከሆነ፣ ነውር የሌለበት ወንድ መስዋዕት ያቅርብ፡፡ መስዋዕቱ በያህዌ ፊት ተቀባይነት ያለው ይሆን ዘንድ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያቅርበው፡፡
\v 4 በሚቃጠለው መስዋዕት ራስ ላይ እጁን ይጭናል፣ ይህም በእርሱ ምነትክ ያስተሰርይለት ዘንድ ተቀባይነት ያገኛል፡፡
\s5
\v 5 ከዚያ በያህዌ ፊት ወይፈኑን ይረድ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ካህናቱ የአሮን ልጆች ደሙን ያቀርቡና በመሰዊያው ላይ ይረጩታል፡፡
\v 6 ከዚያም ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ቆዳ መግፈፍና ብልቶችንም ማውጣት ይኖርበታል፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ላይ ዕሳት ይለኩሱና እንጨት ይጨምሩበታል፡፡
\v 8 ካህናቱ የአሮን ልጆች የስጋውን ብልቶች፣ የከብቱን ጭንቅላትና ስቡን በመስዋዕቱ ምድጃ ላይ በሚገኘው እንጨት ላይ በስርዓት ይደረድሩታል፡፡
\v 9 ነገር ግን ካህኑ የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ማጠብ ይኖርበታል፡፡ በመስዋዕቱ ላይ የሚገኘውን ሁሉ የሚቃጠል መስዋዕት አብርጎ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለእኔ ጣፋጭ ሽታ ይሆናል፤ ይህም ለእኔ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡
\s5
\v 10 ለመስዋዕት የሚያቀርበው የሚቃጠል መስዋዕት ከመንጋው ከሆነ፣ ከበጎች ወይም ከፍየሎች መሃል ነውር የሌለበት ተባዕት መስዋዕት ማቅረብ አለበት፡፡
\v 11 በያህዌ ፊት መስዋዕቱን ከመሰዊያው በስተቀኝ በኩል ይረደው፡፡ ካህናቱ የአሮን ልጆች የመስዋዕቱን ከብት ደም በመሰዊያው ዙሪያ ሁሉ ይርጩት፡፡
\s5
\v 12 ከዚያ ካህኑ የመስዋዕቱን ከብት ጭንቅላቱንና ስቡን እንዲሁም ብልቶቹን ይቆራርጥ፡፡ ከዚያም በመሰዊያው በሚገኘው የሚነድ እንጨት ላይ በስርዓት ይደርድረው፡፡
\v 13 ነገር ግን የመስዋዕቱን ሆድቃና እግሮቹን በውሃ ይጠብ፡፡ ከዚያ ካህኑ መባውን በሙሉ ያቅርብና በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህም የሚቃጠል መስዋዕት ነው፣ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፤ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡
\s5
\v 14 “ካህኑ ለያህዌ የሚያቀርበው የሚቃጠል የወፎች መስዋዕት ከሆነ፣አንድ ወፍ ወይም ዕርግብ ማቅረብ አለበት፡፡
\v 15 ካህኑ መስዋዕቱን ወደ መሰዊያው ያመጣና አንገቱን ይቆለምመዋል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ደሙም በመሰዊያው ጎን ተንጠፍጥፎ ይፈሳል፡፡
\s5
\v 16 የወፉን ማንቁርትና በውስጡ ያሉትን ያስወግድ፣ ከዚያም አመድ በሚደፉበት ከመሰዊያው በስተ ምስራቅ ይወርውረው፡፡
\v 17 ክንፎቹን ይዞ ይሰንጥቀው፣ ነገር ግን ለሁለት አይክፈለው፡፡ ከዚያ ካህኑ በዕሳቱ ላይ ባለው እንጨት መሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ ለእርሱ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፡፡”
\s5
\c 2
\p
\v 1 ማንኛውም ሰው ለያህዌ የእህል ቁርባን ሲያቀርብ፣ መባው መልካም ዱቄት ይሁን፣ ዘይት ያፈስበታል ደግሞም ዕጣን ያድርግበት፡፡
\v 2 ቁርባኑን ወደ ካህናቱ ወደ አሮን ልጆች ይወስደዋል፣ ካህኑ ከዘይቱና በላዩ ካለው ዕጣን ጋር ከመልካሙ ዱቄት እፍኝ ይወስዳል፡፡ ከዚየም ካህኑ የያህዌን በጎነት ለማሰብ መስዋዕቱን በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ነው፣ ለእርሱ በዕሳት የቀረበ መስዋዕት ይሆናል፡፡
\v 3 ከእህል መስዋዕቱ የተረፈው ሁሉ ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ በዕሳት ከተዘጋጀው መስዋዕት ለእርሱ የተለየ ነው፡፡
\s5
\v 4 በምድጃ የተጋገረ እርሾ የሌለበት የእህል ቁርባን ስታቀርብ፣ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ለስላሳ ዳቦ መሆን አለበት፣ ወይም እርሾ የሌለበት በዘይት የተቀባ ቂጣ መሆን አለበት፡፡
\v 5 የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ ላይ የተጋገረ ከሆነ፣ እርሾ ያልገባበት በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን፡፡
\s5
\v 6 ቆራርሰህ በላዩ ዘይት ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡
\v 7 የእህል ቁርባንህ በመጥበሻ የሚዘጋጅ ከሆነ ከመለካም ዱቄትና ዘይት ይዘጋጅ፡፡
\s5
\v 8 ከእነዚህ ነገሮች የተዘጋጀውን የእህል ቁርባን ወደ ያህዌ ማቅረብ አለብህ፣ እናም ይህ ወደ መሰዊያው ወደሚያመጣው ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡
\v 9 ከዚያም የያህዌን በጎነት ለማሰብ ካህኑ ከእህል ቁርባኑ ጥቂት ይወስዳል፣ ቀጥሎም በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ይህ በዕሳት የተዘጋጀ መስዋዕት ይሆናል፣ እናም ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ይሆናል፡፡
\v 10 ከእህል ቁርባኑ የሚተርፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፡፡ ይህ ለያህዌ በዕሳት ከሚዘጋጀው ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየ ነው፡፡
\s5
\v 11 ለያህዌ በምታቀርቡት የእህል ቁርባን ውስጥ እርሾ አይግባበት፣ ለያህዌ በዕሳት በምታዘጋጁት ቁርባን ውስጥ ምንም እርሾ፣ ወይም ማር አታቃጥሉ፡፡
\v 12 እነዚህን እንደ በኩራት ፍሬዎች ለያህዌ ታቀርባላችሁ፣ ነገር ግን በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ ለመስጠት አታቀርቧቸውም፡፡
\v 13 የእህል ቁርባንህን ሁሉ በጨው አጣፍጠው፡፡ ከእህል ቁርባንህ በፍጽም የአምላክህ የቃል ኪዳን ጨው አይታጣ፡፡ በመስዋዕቶችህ ሁሉ ጨው ማቅረብ አለብህ፡፡
\s5
\v 14 ለያህዌ ከፍሬህ በኩራት የእህል ቁርባን ስታቀርብ ከእሸቱ በእሳት የተጠበሰውንና የተፈተገውን አቅርብ፡፡
\v 15 ከዚያ በላዩ ላይ ዘይትና እጣን ጨምርበት፡፡ ይህ የእህል ቁርባን ነው፡፡
\v 16 ከዚያ ካህኑ የተፈተገውን እህል እና ዘይት እንዲሁም ዕጣን የያህዌን በጎነት በአንክሮ ለማሰብ ከፊሉን ያቃጥለዋል፡፡ ይህም ለያህዌ የሚቀርብ የዕሳት መስዋዕት ነው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ማንኛውም ሰው ከመንጋው መሃል ወንድም ሆነ ሴት እንስሳ የህብረት መስዋዕት እንስሳ ቢያቀርብ፣በያህዌ ፊት ነውር የሌለበት እንስሳ ያቅርብ፡፡
\v 2 እጁን በመስዋዕቱ እንስሳ ራስ ላይ ይጭናል፣ ከዚያም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ያርደዋል፡፡ ከዚያ ካህናቱ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ይረጩታል፡፡
\s5
\v 3 የህብረት መስዋዕቱን ለያህዌ በዕሳት ያቀርባል፡፡ ሆድቃውን የሸፈነውን ወይም ከዚያ ጋር የተያያዘውን ስብ፣
\v 4 እና ሁለቱን ኩላሊቶች እንዲሁም በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን ስብ፣ እና የጉበቱን መረብ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\v 5 የአሮን ልጆች ከሚቃጠለው መስዋዕት ጋር እነዚህን በዕሳቱ ላይ በሚገኘው እንጨት በመሰዊያው ላይ ያቃጥሉታል፡፡ ይህም ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ ይሆናል፣ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ይሆናል፡፡
\s5
\v 6 ለያህዌ የሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት ወንድም ይሁን ሴት እንስሳ ነውር የሌለበት ይሁን፡፡
\v 7 መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ከሆነ፣ በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡
\v 8 እጁን በመስዋዕቱ ራስ ላይ ይጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ይረደው፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡
\s5
\v 9 የህብረት መስዋዕቱን በእሳት እንደሚቀርብ መስዋዕት አድርጎ ለያህዌ ያቀርባል፡፡ ስቡን፣ላቱን እስከ ጀርባ አጥንቱ ድረስ፣እንዲሁም የሆድ እቃውን የሸፈነውን ስብ ሁሉ፣በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ፣
\v 10 እና ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር ያለውን ስብ፣ በጎድኑ አጠገብ የሚገኘውን እና የጉበቱን መሸፈኛ ከኩላሊቶቹ ጋር እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\v 11 ከዚያም ካህኑ ሁሉንም ለያህዌ በመሰዊያው ላይ በእሳት የመበል ቁርባን አድርጎ ያቃጥላል፡፡
\s5
\v 12 የሚያቀርበው መስዋዕት ፍየል ከሆነ፣በያህዌ ፊት ያቅርበው፡፡
\v 13 እጁን በፍየሉ ራስ ላይ መጫንና በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት ማረድ ይኖርበታል፡፡ ከዚያ አሮን ልጆች በመሰዊያው ጎንና ጎኖች ደሙን ይረጩታል፡፡
\v 14 በእሳት የተዘጋጀውን መስዋእቱን ለያህዌ ያቀርባል፡፡ የሆድ እቃውን የሸፈነውንና በሆድ እቃው ዙሪያ የሚገኘውን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\s5
\v 15 እንዲሁም ሁለቱን ኩላሊቶችና ከእነዚህ ጋር የሚገኘውን ስብ፣ በጎድኖች እና ከኩላሊቶቹ ጋር በጉበቱን መሸፈኛው ላይ የሚገኘውን ስብ እነዚህን ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\v 16 ካህኑ እነዚህን ሁሉ በመሰዊያው ላይ መልካም መዓዛ እንዲሆን እንደ መብል መስዋዕት አድርጎ ሁሉንም ያቃጥለዋል፡፡ ስቡ ሁሉ የያህዌ ነው፡፡
\v 17 “‘ይህ ለእናንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቀዋሚ መታሰቢያ ነው፣ እናንተ ስብ ወይም ደም አትብሉ፡፡’”
\s5
\c 4
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‘ማንም ሰው ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር በማድረግ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ደግሞም የተከለከለ አንዳች ነገር ቢያደርግ፣ እንዲህ ይደረግ፡፡
\v 3 ኃጢአት የሰራው ሊቀ ካህኑ ቢሆንና በህዝቡ ላይ በደል የሚያስከትል ኃጢአት ቢሰራ ስለ ሰራው ኃጢአት ለያህዌ ነውር የሌለበት ወይፈን የኃጢአት መስዋእት አድርጎ ያቅርብ፡፡
\s5
\v 4 ወይፈኑን በያህዌ ፊት ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣ፤ ካህኑ እጆቹን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጫንና በያህዌ ፊት ይረደው፡፡
\v 5 የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውድና ወደ መገናኛው ድንኳን ያምጣው፡፡
\s5
\v 6 ካህኑ ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ ሰባት ጊዜ በቅድስተ ቅዱሳኑ መጋረጃ ላይ ከደሙ ጥቂት በያህዌ ፊት ይረጫል፡፡
\v 7 ደግሞም ካህኑ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በያህዌ ፊት ከደሙ ጥቂት ወስዶ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሰዊያው ቀንዶች ይጨምራል፤ የቀረውን ወይፈኑን ደም ሁሉ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡
\s5
\v 8 የሆድ ዕቃውን የሸፈነውንና ከሆድ ዕቃው ጋር የተያያዘውን የበደል መስዋዕቱን የሆነውን ወይፈን ስብ ሁሉ አውጥቶ ያቀርባል፡፡
\v 9 (ቁጥር 9?)
\v 10 ለህብረት መስዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን አውጥቶ እንዳቀረበ ሁሉ ይንንም አውጥቶ ያቀርባል፡፡ ከዚያም ካህኑ እነዚህን ክፍሎች ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡
\s5
\v 11 የወይፈኑን ቆዳና ማንኛውንም ስጋ ከጭንቅላቱና ከእግሮቹ እንዲሁም ከሆድዕቃው ክፍሎችና ከፈርሱ ጋር፣
\v 12 የቀረውን የወይፈኑን ክፍሎች ሁሉ ከእነዚህ ክፍሎች ሁሉ ከመንደር ተሸክሞ አመዱን ወደ ደፉበት ለእኔ ወደሚነጹበት ስፍራ ወስዶ እነዚያን ክፍሎች በእንጨት ላይ ያቃጥላቸው፡፡ እነዚያን የከብቱን ክፍሎች አመዱን በደፉበት ስፍራ ያቃጥለው፡፡
\s5
\v 13 መላው የእስራኤል ጉባኤ ኃጢአት መስራት ሳይፈልግ ኃጢአት ቢሰራ፣ ጉባኤውም ኃጢአት መስራቱን ባያውቅና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ፈጽሞ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣
\v 14 ከዚያም፣ የፈጸሙት በደል በታወቀ ጊዜ፣ ጉባኤው ለኃጢአት መስዋዕት ወይፈን ይሰዋና ወደ መገናኛው ድንኳን ፊት ያምጣው፡፡
\v 15 የጉባኤው ሽማግሌዎች በያህዌ ፊት በወይፈኑ ላይ እጃቸውን ይጫኑና በያህዌ ፊት ይረዱት፡፡
\s5
\v 16 የተቀባው ካህን ከወይፈኑ ደም ወደ መገናኛው ድንኳን ያመጣል፣
\v 17 ከዚያ ካህኑ ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ በመጋረጃው ላይ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጨዋል፡፡
\s5
\v 18 በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፣በያህዌ ፊት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ከደሙ ጥቂት ይጨምርበታል፤ ደግሞም ለሚቃጠል መስዋዕት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በመሰዊያው ታች ደሙን በሙሉ ያፈሳል፡፡
\v 19 ስቡን ሁሉ ከእንስሳው ቆርጦ ያወጣና በመሰዊያው ላይ ያቃጥላል፡፡
\s5
\v 20 ወይፈኑን በዚህ መልክ ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለኃጢአት መስዋዕት እንዳቀረበው ወይፈን ሁሉ፣ በዚህኛውም ወይፈን ይህንኑ ያደርጋል፣ እናም ካህኑ ለህዝቡ ማስተስረያ ያደርጋል፣ እናም ጉባኤው ይቅር ይባላል፡፡
\v 21 ካህኑ ወይፈኑን ከመንደር ያወጣና የመጀመሪያውን ወይፈን እንዳቃጠለ ይህኛውንም ያቃጥለዋል፡፡ ይህ ለጉባኤው የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
\s5
\v 22 የህዝቡ መሪ ኃጢአት ለመስራት ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ አምላኩ ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ማናቸውም ነገሮች አንዱን አድርጎ ቢገኝና በደለኛ ቢሆን፣
\v 23 ከዚያም የሰራው ኃጢአት ቢታወቀው፣ ነውር የሌለበት ተባዕት ፍየል ለመስዋዕት ያቀርባል፡፡
\s5
\v 24 እጁን በፍየሉ ራስ ላይ ይጭንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርዱበት ስፍራ በያህዌ ፊት ይረደው፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
\v 25 ካህኑ ያኃጢአት መስዋዕቱን ደም በጣቱ ይውሰድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረው፣ ደግሞም ደሙን ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ስር ያፍስሰው፡፡
\s5
\v 26 ልክ እንደ ሰላም መስዋዕት ሁሉ ስቡን በሙሉ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡ ካህኑ የህዝቡ መሪ ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያድርግለታል፣ መሪውም ይቅር ይባላል፡፡
\s5
\v 27 ከተራው ህዝብ መሃል አንድ ሰው ኃጢአት ለማድረግ ሳያስብ ኃጢአት ቢሰራ፣ያህዌ እንዳይደረግ ካዘዘው ከእነዚህ ነገሮች መሃል አንዱን ቢፈጽም፣ እናም በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣
\v 28 ከዚያም የፈጸመው በደል ቢታወቀው፣ ለበደሉ መስዋዕት ነውር የሌለበት ሴት ፍየል ያቅርብ፡፡
\s5
\v 29 በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጭናል ከዚያም በሚቃጠል መስዋዕቱ ስፍራ የኃጢአት መስዋዕቱን ያርዳል፡፡
\v 30 ካህኑ በጣቱ ጥቂት ደም ወስዶ ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ የተቀረውን ደም ሁሉ በመሰዊያው ስር ያፈሰዋል፡፡
\s5
\v 31 መስዋዕቱ በተወሰደበት ሁኔታ ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፡፡ ካህኑ ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለዋል፣የሰውየውንም ኃጢአት ያስተሰርያል፡፡
\s5
\v 32 ለኃጢአት መስዋዕቱ የበግ ጠቦት ቢያቀርብ ነውር የሌለባት ሴት ጠቦት ያምጣ፡፡
\v 33 በኃጢአት መስዋዕቱ ራስ ላይ እጁን ይጫንና የሚቃጠል መስዋዕት በሚያርድበት ስፍራ ለኃጢአት መስዋዕት ያርዳል፡፡
\s5
\v 34 ካህኑ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና ለሚቃጠል መስዋዕት በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ይጨምረዋል፡፡ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን ሁሉ ያፈሰዋል፡፡
\v 35 ከሰላም መስዋዕቱ የጠቦቱ ስብ በወጣበት ሁኔታ፣ከዚህኛውም ሁሉንም ስብ ይወስዳል፣ከዚያ ካህኑ በያህዌ መስዋዕቶች ላይ በእሳት በሚቀርበው መሰዊያ ላይ ያቃጥለዋል፡፡ ካህኑ መስዋእት አቅራቢው የሰራውን ኃጢአት ያስተሰርይለታል፣ እናም ሰውየው ይቅር ይባላል፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ማንም ሰው ያየውንም ሆነ የሰማውን አንዳች ነገር መምስከር ሲገባው ባለመመስከር ኃጢአት ቢሰራ፣ ይጠየቅበታል፡፡
\v 2 ወይም ማንም ሰው እግዚአብሔር ንጹህ አይደለም ያለውን ማናቸውንም ነገር ቢነካ፣ ይህ ንጹህ ያልሆነ ነገር የዱር እንስሳ ስጋ ወይም የሞተ የቤት እንስሳ ቢሆን፣ ወይም ማናቸውንም ያልነጻ ሰው ቢነካ፣ ደግሞም ይህን ማድረጉን ባያውቅ፣ ስለ ነገሩ ባወቀ ጊዜ ኃጢአጠኛ ይሆናል፡፡
\s5
\v 3 ቁጥር 3 (?)
\v 4 ወይም ማንም ሰው በችኮላ ክፉ ወይም በጎ ለማድረግ በከንፈሮቹ ቢምል፣በችኮላ የማለው መሀላ ምንም አይነት ይሁን፣ ስለ ነገሩ ባያውቅ እንኳን፣ ነገሩን ባወቀ ጊዜ ከእነዚህ በማናቸውም ነገር ኃጢአተኛ ይሆናል፡፡
\s5
\v 5 አንድ ሰው ከእነዚህ ነገሮች በማንኛውም በደለኛ ሆኖ ሲገኝ፣የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት መናዘዝ አለበት፡፡
\v 6 ከዚያም ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕቱን ወደ ያህዌ ማምጣት አለበት፣ ለኃጢአት መስዋዕት ሴት ጠቦት በግ ወይም ሴት ፍየል ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፡፡
\s5
\v 7 ጠቦት መግዛት ካልቻለ፣ ለኃጢአቱ የበደል መስዋዕት ለያህዌ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች ማምጣት ይችላል፤ አንዱ ለኃጢአት መስዋዕት እና ሌላኛው ለሚቃጠል መስዋዕት ያመጣል፡፡
\v 8 እነዚህን ወደ ካህኑ ያመጣል፣ እርሱም በመጀመሪያ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ያቀርባል - እርሱም የመስዋዕቱን ራስ ከአንገቱ ይቆለምማል ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ አይለያየውም፡፡
\v 9 ከዚያ ከኃጢአት መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በመሰዊያው ጎን ይረጫል፣ ከዚያ የቀረውን ደም በመሰዊያው ስር ደሙን ያንጠፈጥፈዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ ሁለተኛውን ወፍ በህጉ መሰረት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል፣ እናም ካህኑ ሰውየው ለሰራው ኃጢአት ማስተስረያ ያደርገዋል፤ ይቅር ይባላል፡፡
\s5
\v 11 “ነገር ግን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት እርግቦች መግዛት ሳይችል ቢቀር፣ ለሰራው ኃጢአት የኢፍ መስፈሪያ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄት መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ያኃጢአት መስዋዕት ስለሆነ ዘይት ወይም ዕጣን አይጨምርበት፡፡
\s5
\v 12 መስዋዕቱን ወደ ካህኑ ያቅርበው፣ካህኑም ለያህዌ በጎነት ምስጋና ለማቅረብ ከዱቄቱ እፍኝ ይወስዳል፣ ከዚያም በመሰዊያው ላይ ለያህዌ በመስዋዕቱ ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፡፡ ይህ የኃጢአት መስዋዕት ነው፡፡
\v 13 ካህኑ ሰውየው የሰራውን ማንኛውንም ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ይቅር ይባላል፡፡ ከመስዋዕት የተረፈው እንደ እህል ቁርባኑ ሁሉ የካህኑ ይሆናል፡፡’”
\s5
\v 14 ከዚያም ያህዌ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣
\v 15 “ማንም ሰው የያህዌን ትዕዛዝ በመጣስ እርሱ ካለው ውጭ ሆኖ ኃጢአት ቢሰራ፣ ነገር ግን ይህንን ሁን ብሎ ባያደርግ ለያህዌ የበደል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ይህ መስዋዕት ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ዋጋውም ለኃጢአት መስዋዕት በቤተ መቅድስ ገንዘብ በጥሬ ብር መገመት አለበት፡፡
\v 16 ቅዱስ ከሆነው በማጉደል ለሰራው በደል ዕዳውን በመክፈል ያህዌን ደስ ማሰኘት አለበት፣ እናም አንድ አምስተኛውን በዚህ ላይ ጨምሮ ለካህኑ ይስጥ፡፡ ከዚያ ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጠቦት ጋር ያስተሰርይለታል፤ እናም ይቅር ይባላል፡፡
\s5
\v 17 ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና ያህዌ እንዳይደረግ ያዘዘውን ማናቸውንም ነገር ቢያደርግ፣ ምንም እንኳን ነገሩን ሳያውቅ ቢያደርገውም በደለኛ ነው፤ ስለዚህም በበደሉ ጥፋተኛ ነው፡፡
\v 18 ከመንጋው ውስጥ ነውር የሌለበት ጠቦት ያቅርብ ለካህኑ ለበደል መስዋዕት ተመጣጣኝ ዋጋ ያምጣ፡፡ ከዚያም ካህኑ ሳያውቅ ከሰራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፤ ይቅር ይባላል፡፡
\v 19 ይህ የበደል መስዋዕት ነው፣ በያህዌ ፊት በእርግጥ ኃጢአተኛ ነው፡፡”
\s5
\c 6
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ ማንም ሰው ኃጢአት ቢሰራና የያህዌን ትዕዛዝ ቢተላለፍ፣ ታማኝነቱን አፍርሶ ሃሰተኛ ቢሆን፣ ወይም ጎረቤቱ በአደራ የሰጠውን ቢክድ፣ ወይም ቢያታልል ወይም ቢሰርቀው፣ወይም ጎረቤቱን ቢበድል
\v 3 ወይም ከጎረቤቱ የጠፋ ነገር አግኝቶ ቢዋሽ፣ እናም በሃሰት ቢምል፣ ወይም እነዚህን በመሰሉ ሰዎች በሚበድሉባቸው ጉዳዮች ኃጢአት ቢሰራና፣
\v 4 በደለኛ ሆኖ ቢገኝ፣ በስርቆት የወሰደውን ይመልስ ወይም የበደለውን ይካስ፣ ወይም ታማኝነቱን አጉድሎ የወሰደውን ጠፍቶ ያገኘውን ነገር ይመልስ፡፡
\s5
\v 5 ወይም በማንኛውም ጉዳይ ላይ ቢዋሽ፣ ሙሉ ለሙሉ ይመልስ፤ እንዲሁም ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ለባለንብረቱ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይክፈል፡፡
\v 6 ከዚያም የበደል መስዋዕቱን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ነውር የሌለበት ጠቦት ከመንጋው የኃጢአት መስዋእት ለያህዌ ወደ ካህኑ ያምጣ፡፡
\v 7 ካህኑ የኃጢአት ማስተስረያ በያህዌ ፊት ያቀርባል፣ እናም በዳዩ ለሰራው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል፡፡”
\s5
\v 8 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 9 “አሮንን እና ልጆቹን እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፣ ‘የሚቃጠል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የሚቃጠለው መስዋዕት በመሰዊያው ምድጃ ላይ ሌሊቱን ሁሉ እስከ ማለዳ ይገኝ፣ ደግሞም የመሰዊያው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡
\s5
\v 10 ካህኑ የበፍታ ልብሱን ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ ቀሚን ይልበስ፡፡ እሳቱ በመሰዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠለውን መስዋዕት ከበላ በኋላ አመዱን ይፈስ፣ ከዚያም አመዱን ከመሰዊያው ጎን ይድፋው፡፡
\v 11 አመዱን ከሰፈር ውጭ ንጹህ ወደ ሆነ ስፍራ ለመውሰድ የለበሰውን አውልቆ ሌላ ልብስ ይልበስ፡፡
\s5
\v 12 በመሰዊው ላይ ያለው እሳት ሳያቋርጥ ይንደድ፡፡ መጥፋት የለበትም፣ እናም ካህኑ በየማለዳው እንጨት ይጨምርበት፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ በላዩ የሚቃጠል መስዋዕት ያድርግበታል፣ ደግሞም የሰላም መስዋዕት ስብ በላዩ ያቃጥልበታል፡፡
\v 13 እሳቱ ሳያቋርጥ በመሰዊያው ላይ ይንደድ፤መጥፋት የለበትም፡፡
\s5
\v 14 የእህል ቁርባን ህግ ይህ ነው፡፡ የአሮን ልጆች ከያህዌ ፊት በመሰዊያው ላይ ያቀርቡታል፡፡
\v 15 ካህኑ የእህል ቁርባን አድርጎ እፍኝ መልካም የእህል ዱቄትና ዘይት እንዲሁም ዕጣን ለመስዋዕት ይውሰድና የያህዌን በጎነት ምስጋና ለማቅረብ በመሰዊያው ላይ ያቃጥለው፡፡
\s5
\v 16 አሮንና ልጆቹ ከመስዋዕቱ የቀረውን ይመገቡት፡፡ ይህም እርሾ ሳይገባበት በተቀደሰው ስፍራ ይብላ፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረ ግቢ ይመገቡት፡፡
\v 17 በእርሾ መጋገር የለበትም፡፡ እኔ በእሳት የተዘጋጀ ድርሻ አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ የኃጢአት መስዋዕትና የበደል መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ነው፡፡
\v 18 ለሚመጣው ተውልድ ሁሉ ለዘመናት ሁሉ ወንድ የሆነ የአሮን ትውልድ ድርሻው አድርጎ ከያህዌ ከሚቀርበው የእሳት ቁርባን ሊበላው ይችላል፡፡ ማናቸውም እርሱን የሚነካ ቅዱስ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 19 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 20 “ይህ አሮንና ልጆቹ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፣ እያንዳንዳቸው የአሮን ልጆች በሚቀቡበት ቀን ለያህዌ የሚያቀርቡት መስዋዕት ነው፡፡ እንደ ተለመደው የእህል ቁርባን የኢፍ አንድ አስረኛ ክፍል መልካም ዱቄት፤ በጠዋት ግማሹን የተቀረውን ግማሽ ደግሞ ምሽት ያቀርቡታል፡፡
\s5
\v 21 በመጥበሻ ላይ በዘይት ይጋገራል፡፡ በእርጥቡ ሳለ፣ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ታቀርበዋለህ፡፡ የእህል ቁርባኑን ለያህዌ ጣፋጭ መዓዛ እንዲሆን ቆራርሰህ ታቀርበዋለህ፡፡
\v 22 ከሊቀ ካህኑ ልጆች መሃል ተተኪ ካህን የሚሆነው ወንድ ልጅ መስዋዕቱን ያቀርባል፡፡ ለዘለዓለም እንደታዘዘው፣ መስዋዕቱ በሙሉ ለያህዌ ይቃጠላል፡፡
\v 23 ካህኑ የሚያቀርበው እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ሙሉ ለሙሉ ይቃጠላል፤አይበላም፡፡”
\s5
\v 24 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 25 “አሮንና ወንዶች ልጆቹን እንዲህ በላቸው፣ ‘የኃጢአት መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡ የኃጢአት መስዋዕት የሚታረደው የሚቃጠል መስዋዕት በሚታረድበት ስፍራ ያህዌ ፊት ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\v 26 የኃጢአት መስዋዕት የሚያቀርበው ካህን ይመገበዋል፡፡ በመገናኛው ድንኳን ቅጽረግቢ በተቀደሰው ስፍራ ይበላ፡፡
\s5
\v 27 የመስዋዕቱን ስጋ የሚነካ ሁሉ ይቀደሳል፣ደሙ በየትኛውም ልብስ ላይ ቢረጭ ደሙ የነካውን የጨርቁን ስፍራ በተቀደሰ ቦታ እጠበው፡፡
\v 28 የተቀቀለበት የሸክላ ማሰሮ ግን ይሰበር፡፡
\s5
\v 29 ከካህናቱ መሀል ማናቸውም ወንድ ከዚህ መብላት ይችላል ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\v 30 በተቀደሰው ስፍራ ወደ መገናኛው ድንኳን ለማስተስረይ ደሙ ከቀረበው የኃጢአት መስዋዕት ምንም አይበላ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 የበደል መስዋዕት ህግ ይህ ነው፡፡ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\v 2 የበደል መስዋዕቱን በሚታረድበት ስፍራ የበደሉንም መስዋዕ ይረዱት፣ ደሙን በመሰዊያው እያንዳንዱ ጎን ይርጩት፡፡
\v 3 በመስዋዕቱ ከብት ውስጥ ያለው ስብ ሁሉ ይቃጠል፤ ላቱ፣የሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነው ስብ በመሁሉ፣
\v 4 በጎድኑ አጠገብ ያለው ስብ፣ ሁለቱ ኩላሊቶችና በላያቸው ያለው ስብ፣ ጉበቱን የሸፈነው ስብ፣ ከኩላሊቶቹ ጋር - እነዚህ ሁሉ ይቅረቡ፡፡
\s5
\v 5 ካህኑ እነዚህን ክፍሎች በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት አድርጎ በመሰዊያው ላይ ለያህዌ ያቃጥል፡፡ ይህ የበደል መስዋዕት ነው፡፡
\v 6 እያንዳንዱ ካህን ከዚህ መስዋዕት መብላት ይችላል፡፡ በተቀደሰ ስፍራ ይበላ ምክንያቱም እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 7 የኃጢአት መስዋዕት ልክ እንደ በደል መስዋዕት ነው፡፡ የሁለቱም ህግ ተመሳሳይ ነው፡፡ እነዚህ ህጎች የማስተስረይ አገልግሎት ለሚሰጡ ካህናት ያገለግላሉ፡፡
\v 8 የየትኛውንም ሰው የሚቃጠል መስዋዕት የሚያቀርብ ካህን የመስዋዕቱን ቆዳ መውሰድ ይችላል፡፡
\s5
\v 9 በምድጃ የሚዘጋጅ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን፣ እና በመጥበሻ የሚዘጋጅ እንዲህ ያለው እያንዳንዱ መስዋዕት ወይም በመጋገሪያ መጥበሻ ላይ የሚዘጋጅን መስዋዕት፣ መስዋዕቱን የሚያሳርገው ካህን ይወስደዋል፡፡
\v 10 ደረቅም ሆነ በዘይት የተለወሰ እያንዳንዱ የእህል ቁርባን ለአሮን ትውልዶች እኩል የእነርሱ ነው፡፡
\s5
\v 11 ይህ ሰዎች ለያህዌ የሚያቀርቡት የሰላም መስዋዕት ህግ ነው፡፡
\v 12 ማንም ሰው ምስጋና ለማቅረብ ይህን ቢያደርግ፣ እርሾ የሌለበት መስዋዕት አድርጎ ያቅርበው፣ ነገር ግን ቂጣውን በዘይት ይለውሰው፣ ቂጣው በመልካም ዱቄት የተዘጋጀ በዘይት የተለወሰ ይሁን፡፡
\s5
\v 13 ደግሞም ምስጋና ለማቅረብ፣ ከሰላም መስዋዕቱ ጋር በእርሾ የተዘጋጀ ህብስት ያቅርብ፡፡
\v 14 ከእነዚህ መስዋዕቶች ከእያንዳንዳቸው አንድ አይነት መስዋዕት ለያህዌ ያቅርብ፡፡ ይህ የሰላም መስዋዕቱን ደም በመሰዊያው ላይ ለሚረጩት ካህናት ይሰጥ፡፤
\s5
\v 15 ምስጋና ለማቅረብ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርበው ሰው መስዋዕቱ በሚቀርብበት ዕለት የመስዋዕቱን ስጋ ይብላ፡፡ ከስጋው እስከ ማግስቱ አይደር፡፡
\v 16 ነገር ግን መስዋዕቱ የሚያቀርበው ለስዕለት ከሆነ፣ ወይም በበጎ ፈቃድ የሚቀርብ መስዋዕት ከሆነ ስጋው መስዋዕቱን ባቀረበበት ዕለት ባያልቅ በማግስቱ ሊበላ ይችላል፡፡
\s5
\v 17 ሆኖም፣ ከመስዋዕቱ የተረው ስጋ በሶስተኛው ቀን ይቃጠል፡፡
\v 18 አንድ ሰው ካቀረበው የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አንዳች ስጋ በሶስተኛው ቀን ቢበላ ይህ ተቀባይነት የለውም፤ መስዋዕቱን ላቀረበውም ዋጋ የለውም፡፡ ደስ የማያሰኝ ነገር ይሆናል፣ ስጋውን ለሚበላውም ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል፡፡
\s5
\v 19 ንጹህ ያልሆነ ነገር የነካ ከዚህ ስጋ አይበላም፡፡ ስጋው መቃጠል ይኖርበታል፡፡ የተረውን ስጋ፣ ማንኛውም ንጹህ የሆነ ሰው ሊበላው ይችላል፡፡
\v 20 ሆኖም፣ ለያህዌ የሚቀርበውን የሰላም መስዋዕት ስጋ የበላ ንጹህ ያልሆነ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
\s5
\v 21 ማንኛውም ሰው ንጹህ ያልሆነ ነገር ቢነካ - ንጹህ ያልሆነን ሰው፣ ወይም ንጹህ ያልሆነን አውሬ፣ ወይም ንጹህ ያልሆነ እና ደስ የማያሰኝ ነገር ቢነካ፣ እና ከዚያም ለያህዌ ከቀረበው የሰላም መስዋዕት ስጋ ቢበላ ያሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
\s5
\v 22 ቀጥሎም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 23 “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘የበሬ ወይም የበግ ወይም የፍየል ስብ አትብሉ፡፡
\v 24 ሳይታረድ ሞቶ የተገኘ እንስሳ ስብ፣ ወይም በዱር አውሬ የተገደለ እንስሳ ስብ ለሌላ ተግባር ሊውል ይችላል፣ ነገር ግን የዚያን እንስሳ ስብ በፍጹም አትብሉ፡፡
\s5
\v 25 ሰዎች በእሳት ለያህዌ መስዋዕት አድርገው ሊያቀርቡ የሚችሉትን እንስሳ ስብ የሚላ ማንኛውም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይወገድ፡፡
\v 26 በቤቶቻችሁ የወፍም ሆነ የእንስሳ ማናቸውም ዐይነት ደም አትብሉ፡፡
\v 27 ማናቸውንም ደም የበላ ማንም ሰው፣ ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡’”
\s5
\v 28 ደግሞም ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 29 “የእስራኤልን ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‘ለያህዌ የሰላም መስዋዕት የሚያቀርብ ከመስዋዕቱ ላይ ወስዶ ለያህዌ ያቅርብ፡፡
\v 30 ለያህዌ በእሳት የሚዘጋጀውን መስዋዕት፣ በእርሱ በራሱ እጅ ያቅረበው፡፡ ስቡን ከፍርምባው ጋር ያቅርበው፣ ስለዚህ ፍርምባውን በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ያቅርበው፡፡
\s5
\v 31 ካህኑ ስቡን በመሰዊያ ላይ ያቃጥለው፣ ነገር ግን ፍርምባው የአሮንና የትውልዱ ነው፡፡
\v 32 የቀኙን ወርች ከሳለም መስዋዕታችሁ የቀረበ ስጦታ አድርጋችሁ ለካህኑ ስጡት፡፡
\s5
\v 33 የሰላም መስዋዕቱንና ስቡን ደም የሚያቀርበው ከአሮን ትውልድ ውስጥ የሆነው ካህን ከመስዋዕቱ ውስጥ የቀኝ ወርቹ የእርሱ ድርሻ ነው፡፡
\v 34 ለእኔ የተወዘወዘውንና የቀረበውን የፍርምባውንና የወርቹን መስዋዕት እኔ ስለ ወሰድኩ፣ እነዚህን ሊቀካህን ለሆነው ለአሮንና ለዘሩ ሰጥቻለሁ፣ ይህ ሁልጊዜም በእስራኤል ህዝብ ከሚዘጋጀው የሰላም መስዋዕት ድርሻቸው ይሆናል፡፡
\s5
\v 35 ሙሴ በካህናት አገልግሎት ያህዌን እንዲያገለግሉ እነርሱን ባቀረበ ቀን ይህ ለአሮንና ለዘሮቹ በእሳት ለያህዌ ከሚቀርበው መስዋዕት ድርሻቸው ነው፡፡
\v 36 እርሱ ካህናትን በቀባ ቀን ያህዌ ከእስራኤል ህዝብ ድርሻቸው ሆኖ ለእነርሱ እንዲሰጥ ያዘዘው ይህ ነው፡፡ ይህ ሁልጊዜም በትውልዶች ሁሉ ድርሻቸው ይሆናል፡፡
\s5
\v 37 ይህ የሚቃጠል መስዋዕት፣ የእህል ቁርባን፣ የኃጢአት መስዋዕት፣ በደል መስዋዕት፣ የክህነት ሹመት መስዋዕት እና የሰላም መስዋዕት ስርዓት ነው፤
\v 38 ይህ ያህዌ ለሙሴ በሲና ተራራ ላይ የእስራኤል ህዝብ መስዋዕታቸውን በሲና ምድረበዳ የሚያቀርቡበትን ህግጋት ለሙሴ በሰጠበት ቀን የተሰጠ ስርዓት ነው፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “አሮንንና ልጆቹን፣ የክህነት ልብሶቹን፣ የቅባት ዘይቱን፣የኃጢአት መስዋዕቱን ወይፈኖች፣ ሁለቱን ጠቦቶች፣ እርሾ የሌለበትን ህብስት መሶብ ከእርሱ ጋር ውሰድ፡፡
\v 3 በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሁሉንም ጉባኤ ሰብስብ፡፡”
\s5
\v 4 ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፣ ጉባኤውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ተሰበሰበ፡፡
\v 5 ከዚያም ሙሴ ለጉባኤው እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው፡፡”
\s5
\v 6 ሙሴ አሮንንና ልጆቹን አቀረበና በውሃ አጠባቸው፡፡
\v 7 አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰውና በወገቡ ዙሪያ መቀነት አስታጠቀው፣ ቀሚ አጠለቀለትና ኤፉድ ደረበለት፣ ከዚያም ኤፉዱን በጥበብ በተጠለፈ መቀነት አስታጠቀው፡፡
\s5
\v 8 በቀሚሱ ላይ ደረት ኪስ አደረገለት፣ በደረት ኪሱ ውስጥ ኡሪምና ቱሚም አደረገበት፡፡
\v 9 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው በራሱ ላይ ጥምጥሙን ጠመጠመለት፣ በጥምጥሙ ላይ ከፊት በኩል ወርቃማ ቅብና ቅዱስ አክሊል አደረገለት፡፡
\s5
\v 10 ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወሰደ፣ ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀባው፤ እናም ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡
\v 11 በመሰዊያው ላይ ዘይቱን ሰባት ጊዜ ረጨው፣ እናም መሰዊያውንና መገልገያዎቹን ሁሉ ቀባቸው፣ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳህኑንና ማስቀመጫውን፣ ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡
\s5
\v 12 አሮንን ያህዌ ለመለየት ከቅባቱ ዘይት ጥቂቱን በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፡፡
\v 13 ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው የአሮንን ወንድ ልጆች አቅርቦ እጀጠባብ አለበሳቸው፣ በወገባቸው ዙሪያ መታጠቂያ አሰረላቸው፣ በራሳቸው ላይ በፍታ ጨርቅ ጠቀለለላቸው፡፡
\s5
\v 14 ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት በሬ አመጣ፣ አሮንና ልጆቹ ለኃጢአት መስዋዕት ባመጡት በሬ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፡፡
\v 15 በሬውን አርዶ ደሙን በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ በጣቱ ጨመረ፣ በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፣ ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር ለየው፡፡
\s5
\v 16 በመስዋዕቱ ሆድ ዕቃ ውስጥ ያለውን ስብ ሁሉ አወጣ፣ በጉበቱ መሸፈኛና በሁለቱ ኩላሊቶች ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሰዊያው ላይ ሁሉንም አቃጠለው፤
\v 17 ነገር ግን በሬውን፣ ቆዳውን፣ ስጋውን እና ፈርሱን ያህዌ እንዳዘዘው ከሰፈር አውጥቶ አቃጠለው፡፡
\s5
\v 18 ሙሴ ለሚቃጠል መስዋዕት ጠቦቱን አቀረበ፣ አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፡፡
\v 19 ሙሴም ጠቦቱን አርዶ በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ረጨ፡፡
\s5
\v 20 ጠቦቱን ቆራርጦ ራሱንና ቁርጥራጩን እንዲሁም ስቡን አቃጠለ፡፡
\v 21 የሆድ ዕቃውን ክፍሎችና እግሮቹን በውሃ አጠበ፣ ከዚያም ጠቦቱን በሙሉ በመሰዊያው ላይ አቃጠለ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፤ ደግሞም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ ጣፋጭ መዓዛ ነው፡፡
\s5
\v 22 ከዚያም ሙሴ ሌላውን ጠቦት ያቀርባል፣ ይህም የክህነት ሹመት መስዋዕት ነው፣ እናም አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ይጭናሉ፡፡
\v 23 አሮን ጠቦቱን ያርዳል፣ ሙሴም ከደሙ ጥቂት ወስዶ በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ያደርጋል፡፡
\v 24 የአሮንን ልጆች አቅርቦ፣ በቀኝ ጆሯቸው ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጃቸው አውራ ጣት ላይ እና በቀኛ እግራቸው አውራ ጣት ላይ ከደሙ ጥቂት ወስዶ ያደርጋል፡፡ ከዚያ ሙሴ የበጉን ደም በመሰዊያው ጎኖች ሁሉ ይረጫል፡፡
\s5
\v 25 ስቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃ ክፍሎች ውስጥ ሁሉ የሚገኘውን ስብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኩላሊቶች እና በላያቸው የሚገነውን ስብ እንዲሁም ቀኝ ወርቹን ወሰደ፡፡
\v 26 በያህዌ ፊት ከነበረው መሶብ እርሾ የሌለበት አንድ ህብስት ይወስዳል፣ደግሞም በዘይት ተለውሶ ከተሰራው ዳቦ አንዱን እና አንድ ስስ ቂጣ ይውሰድና በስቡና በቀኝ ወርች ላይ ያኖረዋል፡፡
\v 27 ሁሉንም በአሮን እጆችና በአሮን ወንድ ልጆች እጆች ላይ ያስቀምጠዋል፣ ይህንንም ለሚወዘወዝ መስዋዕት በያህዌ ት ያቀርባሉ፡፡
\s5
\v 28 ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ይወስድና የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበው፡፡ እነዚህ የክህነት ሹመት መስዋዕት ናቸው፤ ጣፋጭ መዓዛ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ነው፡፡
\v 29 ሙሴ ፍርምባውን ወስዶ ለያህዌ መስዋዕት አድርጎ ይወዝውዘው፡፡ ያህዌ እንዳዘዘው ይህ ከጠቦቱ የክህነት ሹመት የሙሴ ድርሻ ነው፡፡
\s5
\v 30 ሙሴ በመሰዊያው ላይ ካለው ከቅባት ዘይቱና ከደሙ ጥቂት ወስዶ እነዚህን በአሮን ላይ፣ በልብሶ ላይ፣ በወንድ ልጆቹ ላይ እና ከእርሱ ጋር በልጆቹ ልብሶች ላይ ይረጫል፡፡ በዚህ መንገድ አሮንና የክህነት ልብሱን እንዲሁም ልጆቹንና ልብሳቸውን ለያህዌ ይቀድሳል፡፡
\s5
\v 31 ደግሞም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ አለ፣ “በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ስጋውን ቀቅሉት፣ በዚያም ስፍራ በሹመት መስጫው መሶብ ውስጥ ያለውን ህብስትም ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ብዬ እንዳዘዝኩት ብሉት፡፡
\v 32 ከስጋውና ከህብስቱ የተረፈውን በሙሉ አቃጥሉት፡፡
\v 33 የሹመት ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሰባት ቀናት ከመገናኛው ከመገናኛው ድንኳን መግቢያ አትለፉ፡፡ ያህዌ በሰባት ቀናት ውስጥ ይሾማችኋል፡፡
\s5
\v 34 በዚህ ቀን የሚሆነው እናንተን ለማስተረይ ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ነው፡፡
\v 35 ለሰባት ቀናት ቀንም ሆነ ሌሊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ትቆያላችሁ፣ ደግሞም የያህዌን ትዕዛዝ ትጠብቃላችሁ፣ ይህን ካደረጋችሁ አትሞቱም፣ ምክንያቱም የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡”
\v 36 ስለዚህም አሮንና ልጆቹ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ሁሉንም ነገር አደረጉ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 በስምንተኛው ቀን ሙሴ አሮንንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጠራ፡፡
\v 2 አሮንን እንዲህ አለው፣ “ለኃጢአት መስዋዕት ከመንጋው እምቦሳ እና ነውር የሌለበትን አውራ በግ ወስደህ በያህዌ ፊት ሰዋቸው፡፡
\s5
\v 3 እስራኤል ሰዎች እንዲህ ባላቸው፣ ‘ለኃጢአት መስዋዕት ወንድ ፍየል ውሰድ እንደዚሁም ነውር የሌለባቸው የአንድ አመት እምቦሳና ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዓት ውሰድ፤
\v 4 እንዲሁም በያህዌ ፊት የሰላም መስዋት ለመስዋዕት አንድ በሬና አንድ አውራ በግ ውሰድ፣ በዘይት የተለወሰ የእህል ቁርባንም አቅርብ፣ ምክንያቱም ዛሬ ያህዌ ይገለጥላችኋል፡፡”
\v 5 ስለዚህም ሙሴ ያዘዘውን ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን አመጡ፣ የእስራኤል ጉባኤም ሁሉ ቀርበው በያህዌ ፊት ቆሙ፡፡
\s5
\v 6 ከዚያም ሙሴ እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንድታደርጉት ያዘዘው ይህንን ነው፣ስለዚህም ክብሩ ይገለጥላችኋል፡፡”
\v 7 ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፣ “ወደ መዊያው ቀርበህ የኃጢአት መስዋዕትህንና የሚቃጠል መስዋዕትህን አቅርብ፣ ደግሞም ያህዌ እንዳዘዘው ለራስህና ለህዝቡ አስተስርይ፣ ለህዝቡ ማስተስረያ ለማቅረብ መስዋዕቱን ሰዋ፡፡” 8ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡
\s5
\v 8 ስለዚህም አሮን ወደ መሰዊያው ቀርቦ ለራሱ የሆነውን መስዋዕት ለኃጢአት መስዋዕት እምቦሳውን አረደ፡፡
\v 9 የአሮን ልጆቸ ደሙን አቀረቡለት፣ እርሱም ጣቱን ደሙ ውስጥ እየነከረ በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ ጨመረ፤ ከዚያም በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፡፡
\s5
\v 10 ሆኖም ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ስቡን፣ ኩላሊቶቹን እና በመሰዊያው ላይ የጉበቱን ሽፋን የኃጢአት መስዋዕት አድርጎ አቃጠላቸው፡፡
\v 11 ስጋውንና ቆዳውን ከሰፈር ውጭ አቃጠለው፡፡
\s5
\v 12 አሮን የሚቃጠለውን መስዋዕት አረደ፣ ልጆቹ በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደም ሰጡት፡፡
\v 13 ከዚያ የሚቃጠለውን መስዋዕት ከከብቱ ራስ ጋር እየቆራረጡ ሰጡት፣ እርሱም በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡
\v 14 የሆድ ዕቃዎቹንና እግሮቹን አጥቦ በመሰዊያው ላይ በሚቃጠል መስዋዕቱ ላይ አቃጠላቸው፡፡
\s5
\v 15 አሮን አንድ ፍየል የህዝቡን መስዋዕት አቀረበ፣ ከዚያ ለኃጢአታቸው መስዋዕት አድርጎ አረደው፤ በመጀመሪያው ፍየል ላይ እንዳደረገው ሁሉ ለኃጢአት መስዋዕትነት ሰዋው፡፡
\v 16 ያህዌ እንዳዘዘው የሚቃጠል መስዋዕቱን አቅርቦ ሰዋው፡፡
\v 17 የእህል ቁርባኑን፣ ከእህል ቁርባኑ እፍኝ ሙሉ ወስዶ ከማለዳው የሚቃጠል መስዋዕት ጋር በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡
\s5
\v 18 እንዲሁም ለህዝቡ የሰላም መስዋዕት የሆነውን መስዋዕት በሬውንና አውራ በጉን አረደ፡፡ የአሮን ልጆች በመሰዊያው ዙሪያ የሚረጨውን ደሙን ሰጡት፡፡
\v 19 ሆኖም፣ የበሬውንና የአውራ በጉን ስብ፣ ላቱን፣ ሆድ ዕቃውን ክፍሎች የሸፈነውን ስብ፣ ኩላሊቶቹን፣ የጉበቱን ሽፋን
\s5
\v 20 እነዚህን በፍርምባው ላይ አደረጉ፣ ከዚያም አሮን ሙሴ ባዘዘው መሰረት ስቡን በመሰዊያው ላይ አቃጠለው፡፡
\v 21 አሮን ፍርምባውንና የቀኝ ወርቹን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ይወዝስዘውና እነዚህን ለያህዌ ያቅርብ፡፡
\s5
\v 22 ከዚያ አሮን አጆቹን ወደ ህዝቡ አንስቶ ይባርካቸው፤ ቀጥሎ የኃጢአት መስዋዕቱን፣ የሚቃጠል መስዋዕቱንና የሰላም መስዋዕቱን አቅርቦ ይወርዳል፡፡
\v 23 ሙሴና አሮን ወደ መገናኛው ድንኳን ይሂዱ፣ ከዚያ ተመልሰው ይውጡና ህዝቡን ይባርኩ፣ እናም የያህዌ ክብር ለህዝቡ ሁሉ ይገለጣል፡፡
\v 24 ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥቶ የሚቃጠል መስዋዕቱንና በመሰዊያው ላይ ያለውን ስብ ሁሉ በላ፡፡ ህዝቡ ሁሉ ይህንን ባዩ ጊዜ ጮኸው በፊታቸው ተደፉ፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩድ እያንዳንዳቸው ጥናዎቻቸውን ወስደው እሳት አደረጉበት ከዚያም ዕጣን ጨመሩበት፡፡ ከዚያ በያህዌ ፊት እርሱ እንዲያቀርቡ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ ዕሳት አቀረቡ፡፡
\v 2 ስለዚህም ከያህዌ ዘንድ እሳት ወጥታ በላቻቸው፣ እነርሱም በያህዌ ፊት ሞቱ፡፡
\s5
\v 3 ከዚያም ሙሴ አሮንን፣ “ያህዌ ‘ወደ እኔ በሚቀርቡ ላይ ቅድስናዬን እገልጻለሁ፡፡ በሰዎች ሁሉ ፊት እከብራለሁ’ ሲል ይህን ማለቱ ነው” አለው፡፡ አሮንም ምንም አልመለሰም፡፡
\v 4 ሙሴ የአሮን አጎት የሆነውን የዑዝኤልን ልጆች ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፣ “ወደዚህ ኑና ከመቅደሱ ደጃፍ ወንድሞቻችሁን ተሸክማችሁ ከሰፈር አውጣቸው፡፡”
\s5
\v 5 ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው ቀርበው የክህነት ቀሚሳቸውን እንደለበሱ ተሸክመው ከሰፈር አወጧቸው፡፡
\v 6 ከዚያም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምር እንዲህ አላቸው፣ “እንዳትቀሰፉ ፀጉራችሁን አትንጩ፣ ልብሳችሁንም አትቅደዱ፣ ያህዌ በህዝቡ ላይ ሁሉ እንዳይቆጣ ተጠንቀቁ፡፡ ነገር ግን ቤተዘመዶቻችሁና መላው የእስራኤል ቤት የያህዌ እሳት ለበላቻቸው ያልቅሱ፡፡
\v 7 እናንተ ግን ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትለፉ፣ የያህዌ የቅባት ዘይት በእናንተ ላይ ነውና ትሞታላችሁ፡፡ ስለዚህም ሙሴ እንዳዘዘው አደረጉ፡፡
\s5
\v 8 ያህዌ አሮንን እንዲህ አለው፣
\v 9 “አንተ፣ ወይም ከአንተ ጋር የሚሆኑ ልጆችህ ወደ መገናኛው ድንኳን ስትገቡ እንዳትሞቱ ወይን ጠጅ ወይም የሚያሰክር መጠጥ አትጠጡ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፣
\v 10 ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው መሃል ለመለየት፣ ንጹህ በሆነውና ንጹህ ባልሆነው መሃል ለመለየት፣
\v 11 ለእስራኤል ህዝብ ሁሉ በሙሴ በኩል ያህዌ ያዘዘውን ስርዓት ሁሉ አስተምሩ፡፡”
\s5
\v 12 ሙሴ ለአሮንና ለተረፉት ልጆቹ ለአልአዛርና ለኢታምርን እንዲህ አላቸው፣ “በእሳት ለያህዌ ከቀረበው የእህል ቁርባን የተረፈውን መስዋዕት ውሰድ፣ እጅግ ቅዱስ ነውና እርሾ ሳይገባበት ከመሰዊያው አጠገብ ብሉት፡፡
\v 13 በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፣ ምክንያቱም በእሳት ለያህዌ ከቀረበው መስዋዕት ይህ የአንተና የልጆችህ ድርሻ ነው፣ እንድነግርህ የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡
\s5
\v 14 ለመስዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና ለያህዌ የቀረበውን ወርች እግዚአብሔር ደስ በሚሰኝበት በተቀደሰው ስፍራ ብሉት፡፡ እነዚህን ድርዎቻችሁን አንተ፣ እንዲሁም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ብሉት፣ እነዚህ የእስራኤል ህዝብ ከሚያቀርበው የህብረት መስዋዕት የአንተና የልጆችህ ድርሻ ሆነው ተሰጥተዋል፡፡
\v 15 ለያህዌ መስዋዕት ሆኖ የቀረበውን ወርች እና መስዋዕት ሆኖ የተወዘወዘውን ፍርምባ በእሳት ከተዘጋጀው የስብ መስዋዕቶች ጋር ከፍ አድርገው ለመወዘወዝና ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ በአንድነት ያቅርቧቸው፡፡ ይህም ያህዌ እንዳዘዘው ለዘለዓለም የአንተና የልጆችህ ድርሻ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 16 ከዚያ ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት ስለሚሆነው ፍየል ጠየቀ፣እናም በእሳት እንደተቃጠለ አወቀ፡፡ ስለዚህም በአልአዛርና በኢታምር በተቀሩትም የአሮን ልጆች ላይ ተቆጣ፤ እንዲህም አላቸው፣
\v 17 “ይህ የኃጢአት መስዋዕት እጅግ የተቀደሰ ሆኖ ሳለና የጉባኤውን በደል በእረሱ ፊት እንድታስወግዱበትና ኃጢአታቸውንም እንድታስተረዩላቸው ሰጥቷችሁ ሳለ ስለምን በቤተ አምልኮው ስፍራ አልበላችሁትም?
\v 18 ተመልከቱ፣ ደሙ ወደ ቤተመቅደስ ውስጥ አልመጣም፤ እንዳዘዝኳችሁ በቤተ መቅደሱ አካባቢ ለትበሉት ይገባ ነበር፡፡”
\s5
\v 19 ከዚያም አሮን ለሙሴ እንደህ ሲል መለሰለት፣ “እነሆ፣ ዛሬ የኃጢአት መስዋዕታቸውን እና የሚቃጠል መስዋዕታቸውን በያህዌ ፊት አቀርቡ፣ እናም ይህ ነገር በእኔ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ እኔ የኃጢአት መስዋዕቱን ብበላ ኖሮ ይህ በያህዌ ፊት ደስ ያሰኝ ነበርን? ”
\v 20 ሙሴ ያንን ሲሰማ መልሱ አረካው፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በሏቸው፣ ‘በምድር ላይ ከሚገኙ እንስሳት ሁሉ የምትመገቧቸው ህያዋን ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡
\s5
\v 3 የተሰነጠቀ ሰኮና ያላቸውንና የሚያመሰኩትን ትመገባላችሁ፡፡
\v 4 ሆኖም፣ የሚያመሰኩ ቢሆኑም ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የሌላቸውን እንደ ግመል ያሉትን አትብሉ፤ምክንያቱም ያመሰኳሉ ነገር ግን ሰኮናው አልተሰነጠቀም፡፡ ስለዚህ ግመል ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 5 እንዲሁም ሽኮኮ ያመሰኳል ነገር ግን የተሰነጠቀ ሰኮና የለውም፣ ይህም ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 6 ጥንቸል ቢያመሰኳም የተሰነጠቀ ሰኮና ስለሌለው ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 7 አሳማ የተሰነጠቀ ሰኮና ቢኖረውም፣ አያመሰኳም ስለዚህ ለእናንተ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 8 የእነዚህን ስጋ ፈጽሞ አትብሉ፣ ጥንባቸውንም አትንኩ፡፡ እነርሱ ለእናንተ ንጹህ አይደሉም፡፡
\s5
\v 9 በውቂያኖስም ሆነ በባህር በውሃ ውስጥ ከሚኖሩ እንስሳት የምትበሏቸው ክንፍና ቅርፊት ያላቸው ናቸው፡፡
\v 10 ነገር ግን በውቂያኖስ ወይም በባህር የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ህያዋን ፍጥረታት ሁሉ፣በውሃ ውስጥ የሚንቀሳቀሱትን ጨምሮ እንዲሁም በውሃ ውስጥ ያሉት እንዲህ ያሉ ህያዋን ፍጥረታት በሙሉ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡
\s5
\v 11 ጸያፍ ሊሆኑ ስለሚገባቸውም፣ ስጋቸውን ልትበሉ አይገባም፣ እንደዚሁም በድናቸውም ጸያፍ ነው፡፡
\v 12 በውሃ ውስጥ የሚኖሩ ቅርፊት የሌላቸው እንስሳት ሁሉ፣በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ናቸው፡፡
\s5
\v 13 ልትጸየፏቸው የሚገቡና የማትበሏቸው ወፎች እነዚህ ናቸው፤ ንስር፣ ጥንብ አንሳ፣
\v 14 ጭላት፣ ማንኛውም አይነት የሎስ
\v 15 ማንኛውም አይነት ቁራ፣
\v 16 የተለያ አይነት ጉጉት፣ የባህር ወፍ እና ማንኛውም ዐይነት ጭልፊት፡፡
\s5
\v 17 ትናንሽና ትላልቅ ጉጉቶችን ትጸየፋላችሁ፣ርኩምና ጋጋኖ፣
\v 18 የተለያዩ ጉጉቶች፣ ይብራ፣
\v 19 ሽመላ፣ ማናቸውም ዐይነት የውሃ ወፍ፣ ሳቢሳ፣ ጅንጁላቲ ወፍና የለሊት ወፍ፡፡
\s5
\v 20 በእግራቸው የሚራዱ ክንፍ ያላቸው በራሪ ነፍሳት በሙሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው፡፡
\v 21 ሆኖም ግን ከእግራቸው በላይ በምድር ላይ የሚፈናጠሩበት አንጓ ያላቸውን ማናቸውንም የሚበሩ ነፍሳት መብላት ትችላላችሁ፡፡
\v 22 እንደዚሁም ደግሞ ማናቸውንም ዐይነት አንበጣ፣ ትልቅ የአንበጣ ዝርያ፣ ፌንጣና ዝንቢት መብላት ትችላላችሁ፡፡
\v 23 ነገር ግን አራት እግር ያላቸው የሚበሩ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጠሉ ናቸው፡፡
\s5
\v 24 ከእነዚህ እንስሳት ውስጥ የአንዱን በድን ብትነኩ እስከ ማታ ድረስ የረደሳችሁ ናችሁ፡፡
\v 25 ከእነዚህ የአንዱን በድን ያነሳ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ነው፡፡
\s5
\v 26 ማንኛውም ሙሉ ለሙሉ ያልተሰነጠቀ ሰኮና ያለው እንስሳ ወይም የማያመሰኳ እንስሳ በእናንተ ዘንድ ጸያፍ ነው፡፡ እነዚህን የነካ ሁሉ ይረክሳል፡፡
\v 27 በአራት እግሩ ከሚራመድ እንስሳ መሃል በመዳፋቸው የሚሄዱ ሁሉ በእናንተ ዘንድ እርሱስ ናቸው፡፡ እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን የነካ እስከ ማታ እርኩስ ነው፡፡
\v 28 እንደነዚህ ያሉትን በድናቸውን ያነሳ ልብሱን ይጠብ እስከ ማታ ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡ እነዚህ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ ናቸው፡፡
\s5
\v 29 በምድር ላይ ከሚሳቡ እንስሳት መሃል፣ በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡ አቁስጣ፣ አይጥ፣ ማናቸውም አይነት እንሽላሊት
\v 30 ትንሽ የቤት ላይ እንሽላሊት እና እስስት
\s5
\v 31 ከሚሳቡ እንስሳት በእናንተ ዘንድ እርኩስ የሆኑት እነዚህ ናቸው፡፡ ከእነዚህ የሞቱትን አንዳቸውን የነካ ሰው እስከ ምሽት እርሱስ ይሆናል፡፡
\v 32 ከእነዚህ መሃል አንዱ ሞቶ በማናቸውም ከእንጨት፣ ከጨርቅ፣ ከቆዳ ወይም ከበርኖስ በተሰራ ነገር ላይ ቢወድቀቅ ያዕቃ እርኩስ ይሆናል፡፡ ዕቃው ምንም ይሁን ለምንም አይነት ተግባር ይዋል ውሃ ውስጥ ይነከር እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\v 33 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ የገባበት ወይም የነካው የሸክላ ማሰሮ እንዲሁም በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ እርኩስ ይሆናል፤ ያንን ማሰሮ ሰባብረው፡፡
\s5
\v 34 ማናቸውም ለመበላት የተፈቀደ ምግብ፣ ንጹህ ካልሆነ ማሰሮ ውሃ ቢገባበት እርኩስ ይሆኖል፡፡ እንዲህ ካለው ማሰሮ ማንኛውም ነገር ቢጠጣ ያረክሳል፡፡
\v 35 እርኩስ ከሆነ እንስሳ በድን ማናቸውም አካሉ የወደቀበት ምድጃም ሆነ የማብሰያ ሸክላ እንዲሁም ማንኛውም ነገር ይረክሳል፡፡ ይሰባበር፡፡ እርኩስ ነው፣ በእናንተም ዘንድ የተጠላ ይሁን፡፡
\s5
\v 36 የመጠጥ ውሃ የሚገኝበት ምንጭ ወይም የውሃ ጉድጓድ እንዲህ ያሉ እንስሳት ቢገኙበትም ንጹህ ነው፡፡ ነገር ግን ማንም ሰው በውሃው ውስጥ የሚገኘውን እርኩስ የሆነውን በድን ቢነካ እርኩስ ይሆናል፡፡
\v 37 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ በድን በዘር ላይ ቢወድቅ፣ እነዚያ ዘሮች የረከሱ ይሆናሉ፡፡
\v 38 ነገር ግን በዘሮቹ ላይ ውሃ ቢፈስ ንጹህ ያልሆነው እንስሳ በድን ማንኛውም አካል የተክል ዘሩ ላይ ቢወድቅ ዘሩ በእናንተ ዘንድ እርኩስ ይሆናል፡፡
\s5
\v 39 ለመበላት ከተፈቀደው እንስሳ አንዱ ቢሞት፣ በድኑን የነካው ሰው እስከ ምሽት እርኩስ ይሆናል፡፡
\v 40 ደግሞም እንዲህ ያለውን በድን ያነሳ ሰው ልብሱን ያጥባል፣ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ይሆናል፡፡
\s5
\v 41 ማንኛውም በምድር ላይ የሚሳብ እንስሳ ጸያፍ ነው፤ አይበላም፡፡
\v 42 በሆዱ የሚሳብ እንስሳ ሁሉ፣ እና በአራቱም እግሮቹ የሚራመድ፣ወይም ማንኛውም ብዙ እግሮች ያሉት - በምድር የሚሳብ እንስሳን ሁሉ፣ አትብሉ፤ እነዚህ ጸያፍ ናቸው፡፡
\s5
\v 43 በደረቱ በሚሳብ ማናቸውም ህያው ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፤ እነዚህ እናንተን ያረክሳሉ፡፡
\v 44 እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ በምድር በሚንቀሳቀስ በማናቸውም አይነት እንስሳ ራሳችሁን አታርክሱ፡፡
\v 45 እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ያህዌ ነኝ፡፡ ስለዚህ እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱስ መሆን አለባችሁ፡፡
\s5
\v 46 ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በውሃ ውስጥ ስለሚንቀሳቀሱ ማናቸውም ህያዋን ፍጥረታት፣ እንዲሁም በምድር ላይ ስለሚሳቡ ፍጥረታት ህጉ ይህ ነው፤
\v 47 ንጹህ ባልሆኑና ንጹህ በሆኑት መካከል ልዩነት ለመፍጠር፣ እና በሚበሉ ህያዋን ነገሮችና በማይበሉ ህያዋን ነገሮች መሃል ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡’”
\s5
\c 12
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንደህ በላቸው፣ ‘አንዲት ሴት ብታረግዝና ወንድ ልጅ ብትወልድ፣ ልክ እንደ ወር አበባዋ ወቅት ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለችም፡፡
\v 3 በስምንተኛው ቀን ህጻኑ ልጅ መገረዝ አለበት፡፡
\s5
\v 4 ከዚያ የእናቲቱ ከደሟ መንጻት ለሰላሳ ሶስት ቀናት ይቆያል፡፡ ምንም አይነት የተቀደሰ ነገር መንካት የለባትም ወይም የመንጻቷ ቀናት እስኪፈጸም ድረስ ወደ ቤተመቅደስ አትምጣ፡፡
\v 5 ሴት ልጅ ከወለደች፣ በወር አበባዋ ወቅት እንደነበረችው ለሁለት ሳምንታት ንጹህ አትሆንም፡፡ ከዚያ የእናትየው የመንጻት ስርዓት ለስድስት ቀናት ይቀጥላል፡፡
\s5
\v 6 ወንድ ልጅም ሆነ ሴት ልጅ ከወለደች በኋላ የመንጻቷ ቀናት ሲያበቃ ለካህኑ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ የአንድ አመት ጠቦት ለሚቃጠል መስዋዕት እንዲሁም ለኃጢአት መስዋዕት ዋኖስ ወይም ዕርግብ ታቅርብ፡፡
\s5
\v 7 ከዚያ ካህኑ መስዋዕቱን በያህዌ ፊት ይሰዋና ያስተሰርይላታል፣ እናም ከደሟ መፍሰስ ንጹህ ትሆናለች፡፡ ወንድም ይሁን ሴት ልጅ ለወለደች ሴት ህጉ ይህ ነው፡፡
\v 8 ጠቦት ማቅረብ ባትችል፣ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት ርግቦች ትውሰድ፣ አንዱን ለሚቀጠል መስዋዕት ሌላውን ለኃጢአት መስዋዕት ታቅርብ እናም ካህኑ ያስተሰርይላታል፣ ከዚያም ንጹህ ትሆናለች፡፡’”
\s5
\c 13
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፣
\v 2 “ማንኛውም ሰው በሰውነቱ ቆዳ ላይ እባጭ ወይም ችፍታ ወይም ቋቁቻ ቢወጣና ቢቆስል በሰውነቱ ላይ የቆዳ በሽታ ይሆናል፣ በዚህ ጊዜ ወደ ሊቀካህኑ አሮን ይምጣ፣ አሊያም ካህናት ከሆኑት ልጆቹ ወደ አንዱ ይምጣ፡፡
\s5
\v 3 ከዚያ በሰውነቱ ቆዳ ላይ ያለውን በሽታ ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ በበሽታው ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት ከተለወጠ፣ እና በሽታው በቆዳው ላይ ከሚታየው ይልቅ የከፋ ሆኖ ከተገኘ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ካህኑ ከመረመረው በኋላ፣ ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡
\v 4 በቆዳው ላይ የታየው ቋቁቻ ነጭ ከሆነ፣ እና ወደ ቆዳው ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ እንዲሁም በህመሙ አካባቢ የሚገኘው ጸጉር ወደ ነጭነት ካልተለወጠ፣ ካህኑ በሽታው ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያገልግለው፡፡
\s5
\v 5 በሰባተኛው ቀን፣ ካህኑ በእርሱ እይታ በሽታው አየከፋ በቆዳው ላይ እየሰፋ አለመሄዱን ለማየት ይመርምረው፡፡ በሽታው ለውጥ ካላሳየ፣ ካህኑ ለተጨማሪ ሰባት ቀናት ሰውየውን አግልሎ ያቆየው፡፡
\v 6 በሰባተኛው ቀን በሽታው እየተሻለው እንደሆነና በቆዳው ላይ እየሰፋ እንደላሆነ ለማየት ካህኑ ሰውየውን ደግሞ ይመረምረዋል፡፡ በሽታው ለውጥ ካለው፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆነኑን ይገልጻል፡፡ ይህ ሽፍታ ነው፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚህ በኋላ ንጹህ ነው፡፡
\s5
\v 7 ነገር ግን ሰውየው ራሱን ለካህን ካሳየ በኋላ ሽፍታው በቆዳው ላይ ከተስፋፋ፣ እንደገና ራሱን ለካህን ያሳይ፡፡
\v 8 ሽፍታው ይበልጥ በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ መሆኑን ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ከተስፋፋ፣ ከዚያ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አይደለም ይላል፡፡ ይህ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ነው፡፡
\s5
\v 9 ተላላፊ የቆዳ በሽታ በአንድ ሰው ላይ ሲገኝ፣ ይህ ሰው ወደ ካህን ይምጣ፡፡
\v 10 ካህኑ በሰውየው ቆዳ ላይ ነጭ ዕብጠት መኖሩን ለማየት ይመረምረዋል፣ ጸጉሩ ወደ ነጭነት መቀየሩን፣ ወይም በዕብጠቱ ላይ የስጋ መላጥ መኖሩን ይመልከት፡፡
\v 11 እንዲህ ያለ ነገር ካለ፣ ይህ ጽኑ የቆዳ ህመም ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፡፡ ሰውየውን አያገለውም፣ ምክንያቱም ቀድሞውኑም ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 12 በሽታው በቆዳው ላይ በሰፊው ጎልቶ ከታየና የሰውየውን ቆዳ ከአናቱ እስከ እግሩ ከሸፈና፣ ካህኑ ይህ እስከ ታየው ድረስ፣ በሽታው የሰውየውን አካል ሸፍኖት እንደሆነ ለማየት ይመርምረው፡፡
\v 13 እንዲህ ሆኖ ከተገኘ፣ በሽታው ያለበት ሰው ንጹህ አለመሆኑን ካህኑ ይግለጽ፡፡ ሁሉም ወደ ንጣት ተለውጦ ከሆነ ንጹህ ነው፡፡
\v 14 ነገር ግን የስጋ መላጥ ከታየበት፣ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 15 ካህኑ የስጋውን መላጥ ማየትና ንጹህ አለመሆኑን ይግለጽ፣ ምክንያቱም የተላጠ ስጋ ንጹህ አይደለም፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\v 16 ነገር ግን የተላጠው ስጋ መለልሶ ነጭ ቢሆን፣ ሰውየው ወደ ካህኑ ይሂድ፡፡
\v 17 ካህኑ ስጋው ወደ ነጭነት ተመልሶ እንደሆነ ይመረምረዋል፡፡ እንዲህ ከሆነ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ይገልጻል፡፡
\s5
\v 18 አንድ ሰው በቆዳው ላይ እባጭ ወጥቶ ሲድን፣
\v 19 እና በዕባጩ ስፍራ እብጠት ወይም ቋቁቻ፣ ቀላ ያለ ንጣት፣ ሲኖር ይህን ካህኑ ሊያየው ይገባል፡፡
\v 20 ካህኑ ይህ ወደ ታማሚው ቆዳ ዘልቆ የገባ መሆኑን እና በዚያ ዙሪያ ያለው ጸጉር ወደ ነጭነት መለወጡን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቃል፡፡ እብጠቱ በነበረበት ስፍራ እየሰፋ ከሄደ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\s5
\v 21 ነገር ግን ካህኑ ይህንን መርምሮ በውስጡ ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ከተመለከተ፣ እና ይህም ከቆዳው ስር ካልሆነ ሆኖም ከደበዘዘ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
\v 22 በቆዳው ላይ በሰፊው ከተስፋፋ፣ ካህኑ ታማሚው ንጹህ አይደለም ይበል፡፡ ይህ የሚተላለፍ በሽታ ነው፡፡
\v 23 ነገር ግን ቋቁቻው በቦታው ከሆነና ካልተስፋፋ፣ ይህ የእባጩ ጠባሳ ነው፣ እናም ካህኑ ንጹህ ነው ብሎ ያስታውቅ፡፡
\s5
\v 24 አንድ ሰው ቆዳው ቃጠሎ ሲኖርበትና የስጋው መላጥ ቀላ ያለ ንጣት ወይም ነጭ ጠባሳ ሲሆን፣
\v 25 ካህኑ ያጠባሳ ስፍራ ወደ ንጣት መለወጡን እና ወደ ቆዳው ዘልቆ መግባቱን ለማየት ይመረምራል፡፡ እንደዚህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ ከቃጠሎው አልፎ ከውስጥ የመጣ ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\s5
\v 26 ነገር ግን ካህኑ በሚመረምርበት ጊዜ በስፍራው ነጭ ጸጉር አለመኖሩን ቢደርስበትና ቁስሉ ከቆዳው ስር ሳይሆን ቢቀር እየከሰመ ቢመጣ ካህኑ ታማሚውን ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
\v 27 ከዚያም ካህኑ በሰባተኛው ቀን ይመርምረው፡፡ ምልክቱ በሰፊው በቆዳው ላይ ቢስፋፋ፣ ካህኑ ንጹህ አይደለም ብሎ ያሳውቅ፡፡ ይህ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\v 28 ምልክቱ በስፍራው ከቆየና በቆዳው ላይ እየሰፋ ካልሄደ ነገር ግን ከከሰመ ይህ በቃጠሎው የመጣ እብጠት ነው፣ እናም ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፣ ይህ ከቃጠሎው የመጣ ጠባሳ እንጂ ሌላ ነገር አይደለም፡፡
\s5
\v 29 በአንድ ወንድ ወይም ሴት ራስ ወይም አገጭ ላይ ተላላፊ በሽታ ቢኖር፣
\v 30 ችግሩ ከቆዳው ስር የዘለቀ መሆኑና በላዩ ቢጫ ስስ ጸጉር እንዳለ ለማየት ካህኑ ካህኑ የተላላፊ በሽታ ምርመራ ያድርግለት፡፡ ይህ ከተገኘ፣ ካህኑ ሰውየው ንጹህ አለመሆኑን ያሳውቅ፡፡ ይህ የሚያሳክክ በሽታ ነው፣ በራስ ወይም አገጭ ላይ የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው፡፡
\s5
\v 31 የሚያሳክከውን በሽታ መርምሮ ከቆዳ ስር ያልዘለቀ መሆኑን ቢያይ፣ ደግሞም በውስጡ ጥቁር ጸጉር ባይኖር፣ ካህኑ ሰውየውን በሚያሳክክ በሽታው ምክንያት ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
\s5
\v 32 በሰባተኛው ቀን በሽታው ተስፋፍቶ እንደሆነ ለማየት ካህኑ ይመረምረዋል፡፡ ቢጫ ጸጉር ከሌለና፣ በሽታው ላይ ላዩን ብቻ ከታየ፣
\v 33 ሰውየው ይላጭ፣ ነገር ግን በሽታው የሚገኝበት ዙሪያ መላጨት የለበትም፣ እናም ካህኑ የሚያሳክክ በሽታ ያለበትን ሰው ለሰባት ቀናት ያግልለው፡፡
\s5
\v 34 በሰባተኛው ቀን በሽታው በቆዳው ላይ መስፋፋቱን ማቆሙን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያደርጋል፡፡ በሽታው ቆዳውን ዘልቆ የገባ ካልሆነ፣ ካህኑ የሰውየውን ንጹህ መሆን ያሳውቅ፡፡ ሰውየው ልብሱን ይጠብ፣ እናም ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 35 ነገር ግን ካህኑ ንጹህ መሆኑን ካሳወቀ በኋላ የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ ከሄደ ፣
\v 36 ካህኑ ዳግም ይመርምረው፡፡ በሽታው በሰውየው ቆዳ ላይ እየሰፋ ከሄደ፣ካህኑ ቢጫ ጸጉር መኖሩን መፈለግ አይኖርበትም፡፡ ሰውየው ንጹህ አይደለም፡፡
\v 37 ነገር ግን ካህኑ ሰውየውን የሚያሳክከው በሽታ እየሰፋ መሄዱን እንዳቆመ ከተመለከተ ንጹህ መሆኑን ያሳውቅ፡፡
\s5
\v 38 አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት በቆዳቸው ላይ ነጭ ምልክቶች ቢወጣ
\v 39 ምልክቱ ዳለቻ መልክ ያለው በቆዳ ላይ የወጣ ሽፍታ ብቻ መሆኑን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግ፡፡ ሰውየው ንጹህ ነው፡፡
\s5
\v 40 የሰውየው ጸጉር ከራሱ ላይ ካለቀ፣መላጣ ነው፣ ነገር ግን ንጹህ ነው፡፡
\v 41 ደግሞም ከፊት ለፊት ጸጉሩ ተመልጦ ራሰ በራ ቢሆንም ንጹህ ነው፡፡
\s5
\v 42 ነገር ግን በህመም ምክንያት ፈዘዝ ያለ ቅላት በተመለጠው ራሱ ላይ ወይም በግምባሩ ላይ ቢኖር፣ ይህ በተላላፊ በሽታ ምክንያት የመጣ ነው፡፡
\v 43 በቆዳ ላይ ተላላፊ በሽታ ሲኖር እንደሚታየው በመላጣው ወይም በበራው ላይ በህመሙ ዙሪያ ፈዘዝ ያለ ቅላት መኖሩን ለማየት ካህኑ ምርመራ ያድርግለት፡፡
\v 44 ይህ ከሆነ፣ ተላላፊ በሽታ አለበት እናም ንጹህ አይደለም፡፡ በእርግጥ ካህኑ ሰውየው በራሱ ላይ ካለበት በሽታ የተነሳ ንጹህ እንደልሆነ ያስታውቅ፡፡
\s5
\v 45 ተላላፊ በሽታ ያለበት ሰው የተቀደደ ልብስ ይልበስ፣ ጸጉሩን በከፊል ይሸፍን፣ እስከ አፍንጫው ይከናነብና ‘እርኩስ ነኝ፣ እርኩስ ነኝ’ እያለ ይጩህ፡፡
\v 46 ተላላፊው በሽታ ባለበት ቀናት ሁሉ እርኩስ ነው፡፡ እየሰፋ ሊሄድ በሚችል በሽታ ምክንያት ንጹህ ስላልሆነ፣ ለብቻው ይኑር፡፡ ከሰፈር ውጭ ይኑር፡፡
\s5
\v 47 በማናቸውም ነገር የተበከለ የሱፍም ሆነ የተልባ ዕግር ጨርቅ፣
\v 48 ወይም ከሱፍም ሆነ ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ፣ ወይም ቆዳም ሆነ ከቆዳ በተሰራ ልብስ -
\v 49 በልብሱ ላይ አረንጓዴ ወይም ቀላ ያለ ብክለት ቢገኝበት፤ በቆዳው፣ በተጠለፈው ወይም በተሰፋው ነገር፣ ወይም ማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ለይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ካህኑ ይህን ይመልከት፡፡
\s5
\v 50 ካህኑ የሚበከለውን ዕቃ ይመርምር፣ የተበከለውን ማናቸውንም ነገር ለሰባት ቀናት ይለየው፡፡
\v 51 በሰባተኛው ቀን እንደገና ብክለቱን ይመርምር፡፡ በልብሱ ወይም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ በተሸመነው ወይም በተጠለፈው ማናቸውም ልብስ ላይ ብክለቱ እየሰፋ ቢሄድ ወይም በቆዳ ወይም ከቆዳ በተሰራ ማናቸውም ነገር ላይ ብክለቱ ቢሰፋ ጎጁ ነው፣ እናም ዕቃው ንጹህ አይደለም፡፡
\v 52 ካህኑ ያንን ልብስ ያቃጥል፣ ወይም ማናቸውም ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተፈተለ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ነገር፣ ማናቸውም ጎጂ ብክለት የተገኘበት ነገር በሽታ ያመጣልና ያቃጥለው፡፡ ዕቃው ሙሉ ለሙሉ ይቃጠል፡፡
\s5
\v 53 ካህኑ ዕቃውን መርምሮ ብክለቱ በልብ ወይም በተሸመነው ወይም በተለጠፈው ልብስ ወይም በቆዳ ዕቃዎቹ ላይ እየሰፋ የሚሄድ አለመሆኑን ካወቀ፣
\v 54 ብክለቱ የተገኘባቸውን ዕቃዎች እንዲያጥቡ ያዛቸዋል፤ ደግሞም ዕቃውን ለሰባት ቀናት ያግልል፡፡
\v 55 ከዚያ ካህኑ የተበከለውን ዕቃ ከታጠበ ከሰባት ቀናት በኋላ ይመረምረዋል፡፡ ብክለቱ ቀለሙን ካልቀየረውና እየሰፋ ባይሄድ እንኳን ንጹህ አይደለም፡፡ ብክለቱ የትም ላይ ይሁን ዕቃዎቹን አቃጥሏቸው፡፡
\s5
\v 56 ካህኑ ዕቃውን ከመረመረና ልብሱ ከታጠበ በኋላ ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ከተበከለው የልብሱ ወይም የቆዳው ክፍል ወይም ከተሸመነው ወይም ከተጠለፈው ዕቃ ቀድዶ ያውጣው፡፡
\v 57 እንዲህም ሆኖ ብክለቱ አሁንም በተሸመነው ወይም በተጠለፈው፣ ወይም በማናቸውም ከቆዳ በተሰራው ነገር ላይ ከተገኘ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው፡፡ ብክለት ያለበትን ማናቸውንም ነገር አቃጥለው፡፡
\v 58 ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ የተሰራ ወይም የተለጠፈ ልብስ ወይም ማናቸውም ነገር፣ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ የተሰራ ማናቸውም ነገር - ስታጥበው ብክለቱ እየለቀቀ ከሄደ፣ ዕቃው ዳግመኛ ይታጠብ እናም ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 59 ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ለተሸመነ ወይም ለተጠለፈ፣ከሱፍ ወይም ከተልባ ዕግር ጨርቅ ወይም ቆዳ ወይም ከቆዳ ለተሰራ ማናቸውም ነገር ብክለት ህጉ ይህ ነው፣ ስለዚህ ንጹህ ነው ወይም እርኩስ ነው ብለህ ማሳወቅ ትችላለህ፡፡”
\s5
\c 14
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “የታመመ ሰው በሚነጻበት ቀን ህጉ ይህ ነው፡፡ ወደ ካህኑ ይቅረብ፡፡
\s5
\v 3 ካህኑ የሰውየው ተላላፊ የቆዳ በሽታ መዳኑን ለመመርመር ከሰፈር ይወጣል፡፡
\v 4 ከዚያም ካህኑ የሚነጻው ሰው ህይወት ያላቸው ሁለት ንጹህ ወፎችን፣ የጥድ ዕንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድርና ሂሶጵ እንዲያመጣ ያዘዋል፡፡
\v 5 ካህኑ የታመመው ሰው ከወፎቹ አንዱን አርዶ በሸክላ ማሰሮ ውስጥ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
\s5
\v 6 ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ፣የጥዱን እንጨትና፣ ደማቁን ቀይ ድርና ሂሶጵ ይቀበለውና ህይወት ያለውን ወፍ ጨምሮ እነዚህን ነገሮች በሙሉ ቀደም ሲል በታረደው ወፍ ደምና ንጹህ ውሃ ውስጥ ይከታቸዋል፡፡
\v 7 ከዚያ ካህኑ ይህንን ውሃ ከበሽታው በሚነጻው ሰው ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል፣ ከዚያ በኋላ ካህኑ ሰውየው ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡ ከዚያ ካህኑ ህይወት ያለውን ወፍ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡
\s5
\v 8 የነጻው ሰው ልብሱን ያጥባል፣ ፀጉሩን በሙሉ ይላጫል፣ገላውንም ይታጠባል፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር ይመለስ፣ ነገር ግን ከድንኳኑ ውጭ ለሰባት ቀናት ይቆያል፡፡
\v 9 በሰባተኛው ቀን የራሱን ፀጉር በሙሉ ይላጭ፣ ልብሶቹን ይጠብ፣ ገላውን በውሃ ይታጠብ፤ ከዚህ በኋላ ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 10 በስምንተኛው ቀን ነውር የሌለባቸው ሁለት ወንድ የበግ ጠቦቶች፣አንድ ነውር የሌለበት የአንድ አመት የበግ ጠቦት ያምጣ፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሶስት አስረኛ የላመ ዱቄት እና አንድ ሊትር ዘይት ለእህል ቁርባን ያቅርብ፡፡
\v 11 የመንጻት ስርዓቱን የሚያስፈጽመው ካህን የሚነጻውን ሰው ከእነዚህ ነገሮች ጋር ይዞ፣ በያህዌ ፊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ይቆማል፡፡
\s5
\v 12 ካህኑ ወንዱን ጠቦት ወስዶ ለኃጢአት መስዋዕት ከአንዱ ሊትር ዘይት ጋር ያቀርባል፤ እነዚህንም በያህዌ ፊት ለመስዋዕት ይወዘውዘዋል፤ ለእርሱም ያቀርበዋል፡፡
\v 13 ወንዱን ጠቦት የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ባቀረቡበት ስፍራ በቤተ መቅደስ ያርደዋል፤ እንደ በደል መስዋዕቱ ሁሉ የኃጢአት መስዋዕቱም ለካህኑ ይሰጥ፣ ምክንያቱም ይህ እጅግ ቅዱስ ነው፡፡
\s5
\v 14 ካህኑ ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ወስዶ በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባ፡፡
\v 15 ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ወስዶ በእርሱ በራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣
\v 16 ከዚያም በግራ እጁ መዳፍ ላይ በፈሰሰው ዘይት ውስጥ የቀኝ እጁን ጣት ያጠልቃል፣ በጣቱ ላይ ካለው ዘይት በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡
\s5
\v 17 ካህኑ በእጁ ላይ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት፣ እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡ ይህንን ዘይት በበደል መስዋዕቱ ደም ላይ ያድርገው፡፡
\v 18 ካህኑ በእጁ የቀረውን ዘይት፣ በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፍስስ፣ እናም ካህኑ በያህዌ ፊት የሚነጻውን ሰው ያሰርይለታል፡፡
\s5
\v 19 ከዚያ ካህኑ የኃጢአት መስዋዕቱን ይሰዋል፤ ደግሞም ንጹህ ባለመሆኑ ምክንያት መንጻት ላለበት ሰው ያሰርይለታል፣ እናም ከዚህ በኋላ የሚቃጠል መስዋዕቱን ይሰዋል፡፡
\v 20 ካህኑ የሚቃጠለውን መስዋዕትና የእህል ቁርባኑን በመሰዊያ ላይ ያቀርባል፡፡ ካሁኑ ለሰውየው ማስተስረያ ያቀርብለታል፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 21 ሆኖም ሰውየው ደሃ ከሆነና እነዚህን መስዋዕቶች ማቅረብ ካልቻለ ለኃጢአቱ ማስተስረያ የበደል መስዋዕት አንድ ወንድ ጠቦት፣ በዘይት የተለወሰ የኢፍ አንድ አስረኛ መልካም ዱቄትና አንድ ሊትር ዘይት ያቅርብ፣
\v 22 ሰውየው በአቅሙ ከሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ጋር፣ አንደኛውን ወፍ የኃጢአት መስዋዕት ሌላኛው ደግሞ የሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል፡፡
\v 23 በስምንተኛው ቀን ስለ መንጻቱ ወደ መገናኛው ድንኳን በያህዌ ፊት ያምጣቸው፡፡
\s5
\v 24 ከዚያ ካህኑ ጠቦቱን ለበደል መስዋዕት ደግሞም አንዱን ሊትር ዘይት፣ይወስድና ለያህዌ የበደል መስዋዕት ይወዘውዛል፣ እናም ለእርሱ እነዚህን ያቀርባቸዋል፡፡
\v 25 ለበደል መስዋዕት ጠቦቱን ያርዳል፣ እናም ከበደል መስዋዕቱ ጥቂት ደም ይወስድና በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ይቀባል፡፡
\s5
\v 26 ከዚያ ካህኑ ከዘይቱ ጥቂቱን በገዛ ራሱ ግራ እጅ መዳፍ ላይ ያፈሳል፣
\v 27 በቀኝ ጣቱ ከዘይቱ በግራ እጁ በያህዌ ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል፡፡
\s5
\v 28 ከዚያ ካህኑ በእጁ ካለው ዘይት ጥቂቱን በሚነጻው ሰው ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት ላይና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ የበደል መስዋዕቱን ደም ባደረገበት ተመሳሳይ ስፍራዎች ይቀባል፡፡
\v 29 የተረፈውን በእጁ ያለውን ዘይት ያስተሰርይለት ዘንድ በያህዌ ፊት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያፈሳል፡፡
\s5
\v 30 ሰውየው በአቅሙ ካቀረበው ከእርግቦቹ ወይም ከዋኖሶቹ አንዱን ይሰዋ -
\v 31 ከእህል ቁርባኑ ጋር፣ አንዱን ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፡፡ ከዚያም ካህኑ ለሚነጻው ሰው በያህዌ ፊት ያስተሰርይለታል፡፡
\v 32 ለመንጻት ዋናውን መስዋዕት ማቅረብ ለማይችል ተላላፊ የቆዳ በሽታ ላለበት ሰው የመንጻት ህጉ ይህ ነው፡፡”
\s5
\v 33 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣
\v 34 “ርስት አድርጌ ወደሰጠኋችሁ ወደ ከነዓን ምድር ስትመጡ፣ ርስት በሆናችሁ ምድር በቤታችሁ እየሰፋ የሚሄድ ብክለት ባደርግባችሁ፣
\v 35 የቤቱ ባለቤት ወደ ካህኑ መጥቶ ይናገር፡፡ እንዲህም ይበል፣ “በቤቴ ብክለት ያለ ይመስለኛል፡፡’
\s5
\v 36 ከዚያ ካህኑ በቤቱ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም ነገር እርኩስ እንዳይሆን ብክለት መኖሩን ለማየት ወደዚያ ቤት ከመግባቱ አስቀድሞ ቤቱን ባዶ እንዲያደርጉ ያዛል፣ ከዚህ አስቀድሞ ካህኑ ያንን ቤት ለማየት ይገባል፡፡
\v 37 ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መኖሩን፣ ደግሞም አረንጓዴ ሆኖ ወይም ቀላ ብሎ በግርግዳዎቹ ላይ መታየቱን ይመርምር፡፡
\v 38 ቤቱ ሻጋታ ካለው፣ ካህኑ ከዚያ ቤት ይወጣና ለሰባት ቀናት በሩን ይዘጋዋል፡፡
\s5
\v 39 በሰባተኛው ቀን ካህኑ ተመልሶ ይመጣና ሻጋታው በቤቱ ግድግዳዎች ላይ መስፋፋቱን ለማየት ይመረምራል፡፡
\v 40 እንዲያ ከሆነ፣ ካህኑ ሻጋታ የተገኘባቸውን ድንጋዮች ከግድግዳው ላይ እየፈነቀሉ እንዲያወጡና ከከተማ ውጭ ቆሻሻ ስፍራ መጣያ እንዲጥሏቸው ያዛል፡፡
\s5
\v 41 የቤቱ የውስጥ ግድግዳዎች ሁሉ እንደዲፋቁ ይጠይቃል፣ እነርሱም እየተፋቁ የተነሱትን የተበከሉትን ቁሶች ከከተማ አውጥተው በቆሻሻ መጣያ ስፍራ ይጥላሉ፡፡
\v 42 ባስወገዷቸው ድንጋዮች ስፍራ ሌሎች ድንጋዮች ወስደው ያስቀምጡ፣ ቤቱን ለመምረግ አዲስ ጭቃ ይጠቀሙ፡፡
\s5
\v 43 ድንጋዮቹ ተነስተውና ግርግዳው ተፍቆ እንዲሁም ተለስኖ ዳግም ብክለቱ ከወጣና ከታየ፣
\v 44 ካህኑ ብክለቱ መስፋፋቱን ለመመልከት ቤቱን ይመርምር፡፡ እንዲያ ከሆነ፣ ይህ ጎጂ ብክለት ነው፤ ቤቱ ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 45 ቤቱ ይፍረስ፡፡ የቤቱ ድንጋዮች፣ በሮች፣ እና ፍርስራሾች ከከተማ ውስጥ በቆሻሻ መጣያ ይጣል፡፡
\v 46 በተጨማሪም፣ ቤቱ በተዘጋባቸው ጊዜያት ወደዚያ ቤት የሄደ ሁሉ እስከ ምሽት ድረስ እርኩስ ነው፡፡
\v 47 ማንም በዚያ ቤት ውስጥ የተኛ ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እንዲሁም በዚህ ቤት ውስጥ የተመገበ ሰው ልብሱን ይጠብ፡፡
\s5
\v 48 ቤቱ ከተለሰነ በኋላ ብክለቱ ወዴት እንደተስፋፋ ለመመርመር ካህኑ ወደዚያ ቤት ቢገባ፣ እናም ብክለቱ ተወግዶ ቢሆን ቤቱ ንጹህ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
\s5
\v 49 ከዚያ ካህኑ ቤቱን ለማንጻት ሁለት ወፎች፣ የጥድ እንጨት፣ ደማቅ ቀይ ድር እና ሂሶጵ ይውሰድ፡፡
\v 50 ከወፎቹ አንዱ ንጹህ ውሃ በያዘ በሸክላ ዕቃ ውስጥ ያርደዋል፡፡
\v 51 የጥድ እንጨት፣ሂሶጵደማቅ ቀይ ድር እና በህይወት ያለ ወፍ ይውድና በታረደው ወፍ ደም ውስጥ እና በንጹህ ውሃ ውስት ይነክራቸዋል፣ከዚያም ቤቱን ሰባት ጊዜ ይርጨው፡፡
\s5
\v 52 ቤቱን በወፉ ደምና በንጹህ ውሃ፣ በህይወት በሚገኘው ወፍ፣ በጥድ እንጨት፣በሂሶጵና በደማቅ ቀይ ድር ያነጻዋል፡፡
\v 53 በህይወት የሚገኘውን ወፍ ግን ከከተማ ውጭ ወደ ሜዳ ይለቀዋል፡፡ በዚህ መንገድ ቤቱን ያስተሰርያል፣ ቤቱም ንጹህ ይሆናል፡፡
\s5
\v 54 ለሁሉም አይነት ተላላፊ የቆዳ በሽታና እንዲህ ያለውን በሽታ ለሚያመጡ ነገሮች፣ እንዲሁም ለሚያሳክክ ህመም፣
\v 55 እንዲሁም ለልብስና ለቤት ብክለት፣
\v 56 ለእብጠት፣ ለሚያሳክክ ህመም፣ እና ለቋቁቻ፣
\v 57 በእነዚህ ሁኔታዎች እርኩስና ንጹህ የሚሆነውን ለመለየት ህጉ ይህ ነው፡፡”
\s5
\c 15
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴንና አሮንን እንዲህ ሲል ተናገራቸው፣
\v 2 ‹ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብላችሁ ንገረቸው፣ ‹ማንም ሰው ከሰውነቱ የሚወጣ የሚመረቅዝ ፈሳሽ ሲኖርበት፣ ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 3 ንጹኅ የማይሆነ ከሚመረቅዝ ፈሳሽ የተነሳ ነው፡፡ ከሰውነቱ የሚወጣ ፈሳሽ ቢቀጥል ወይም ቢቆም ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 4 የሚተኛበት አልጋ ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፣ የሚቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይሆንም፡፡
\v 5 አልጋን የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ ሰውየውም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹኅ አይደለም፡፡
\s5
\v 6 የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበት ሰው በተቀመጠበት ማናቸውም ነገር ላይ የተቀመጠ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 7 የሚመረቅዝ ፈሳሽ ያለበትን ሰው አካል የነካ ማንኛውም ሰው ልብሱን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፡፡ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 8 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ሰው ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ንጹኅ በሆነ ሰው ላይ ቢተፋ፣ ያ ሰው ልብሱን ማጠብና እርሱም በውሃ መታጠብ አለበት፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 9 ፈሳሽ ያለበት ሰው የተቀመጠበት ማንኛውም ኮርቻ ንጹኅ አይደለም፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ ሰው በታች ያለን ማንኛውንም ነገር የነካ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፣ እነዚያን ነገሮች የተሸከመ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 11 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበት ማንም ቢሆን አስቀድሞ እጆቹን በውሃ ሳያጠራ ቢነካ፣ የተነካው ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 12 እንዲህ ያለ ፈሳሽ ያለበትን ሰው የነካ ማናቸውም አይነት የሸክላ ዕቃ ይሰበር፣ የእንጨት የተሰራ ማጠራቀሚያ ሁሉ በውሃ ይንጻ፡፡
\s5
\v 13 ፈሳሽ ያለበት ሰው ከፈሳሹ ሲነጻ ለመንጻቱ ለእራሱ ሰባት ቀናትን ይቁጠር፤ ከዚያ ልብሶቹን ይጠብ ሰውነቱን በምንጭ ውሃ ይታጠብ፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\v 14 በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ኖሶች ይውሰድና ወደ መገናኛ ድንኳን ያህዌ ፊት ይቅረብ፣ በዚያ ወፎቹን ለካህኑ ይስጥ፡፡
\v 15 ካህኑ አንዱን ለሀጢአት መስዋዕት እና ሌላውን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርባቸው፣ እናም ካህኑ ለሰውዬው ስለ ፈሳሹ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡
\s5
\v 16 የማንንም ሰው የዘር ፈሳሽ ሳይታሰብ በድንገት ከእርሱ ቢወጣ፣ መላ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 17 ማናቸውም የዘር ፈሳሽ የነካ ልብስ ወይም ሌጦ በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 18 አንዲት ሴትና አንድ ወንድ አብረ ቢተኙና ወደ እርሷ የዘር ፈሳሽ ቢተላለፍ ሁለቱም በውሃ ይታጠቡ፣ እስከ ምሽት ንጹኅ አይደሉም፡፡
\s5
\v 19 አንዲት ሴት የወር አበባ ሲፈሳት፣ ያለመንጻቷ ለሰባት ቀናት ይቀጥላል፣ እርሷን የነካ ሁሉ እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 20 በወር አበባ ወቅት የምትተኛበት ማንኛውም ነገር ንጹህ አይደለም፤ እንደዚሁም የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ንጹኅ አይደለም፡፡
\s5
\v 21 አልጋውን የነካ ማንኛም ሰው ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ ያሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 22 የተቀመጠችበትን ማናቸውንም ነገር የነካ ሁሉ ልብሱን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ ያ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\v 23 በአልጋም ይሁን በማንኛም ነገር ላይ ብትቀመጥ የተቀመጠችበትን ነገር የነካ ሰው እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 24 ከእርሷ ጋር የተኛ ንጹህ ያልሆነ ፈሳሽ ቢነካ፣ ለሰባት ቀናት ንጹህ አይደለም፡፡ የሚተኛበትም አልጋ ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 25 አንዲት ሴት ከወር አበባ ቀናት በኋላ ለብዙ ቀናት ደም መፍሰሱን ቢቀጥል፣ ይህም ከወር አበባ ጊዜያት በኋላ ፈሳሽ ቢኖርባት፣ ንጹኅ ባልሆነችባቸው ፈሳሽ ባለባት ጊዜያት ሁሉ፣ በወር አበባ ወቅት ላይ እንዳለች ሁሉ እርኩስ ይሆናል ንጹህ አይደለችም፡፡
\v 26 ደሟ በሚፈስባቸው ጊዜያት የምትተኛበት አልጋ ሁሉ በወር አበባ ወቅት እንደምትተኛበት እርኩስ ይሆናል፣ የምትቀመጥበት ነገር ሁሉ ልክ በወር አበባ ወቅት እንደሚሆነ ንጹህ አይደለም፡፡
\v 27 ደግሞም ከእነዚህ ነገሮች ማናቸንም የነካ ሁሉ ንጹህ አይደለም፤ ልብሶቹን ይጠብ እርሱም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ምሽት ድረስ ንጹህ አይደለም፡፡
\s5
\v 28 ነገር ግን ከደም መፍሰሳ ብትነጻ፣ ለራስዋ ሰባት ቀናትን ትቆጥራለች፣ እናም ከዚያ በኋላ ንጹኅ ናት፡፡
\v 29 በስምንተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ትወሰድና ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለካህኑ ትስጥ፡፡
\v 30 ካህኑ አንዱን ወፍ ለሀጢአት መስዋእት ሌላውን ለሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፣ ስለ ፈሳሽም እርኩሰት በያህዌ ፊት ያስተሰርይላታል፡፡
\s5
\v 31 የእስራኤል ሰዎች ከእርኩሰታቸው የምትይች እንደዚህ ነ፣ ይህ ከሆነ በመካከላቸ የምኖርበትን ቤተ መቅደሴን በማርከስ በእርኩሰታቸ አይሞቱም፡፡
\s5
\v 32 ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚጣ፣ የዘረ ፈሳሹ ከእርሱ ለሚጣና ለሚያረክሰ ማንኛም ሰ ህግጋቱ እነዚህ ናቸ፡፡
\v 33 ለማንኛም በር አበባ ላይ ላለች ሴት፣ ከሰነቱ ፈሳሽ ለሚፈሰ ሰ ሁሉ፣ ንድም ይሁን ሴት፣ እንዲሁም ንጹህ ካልሆነች ሴት ጋር ለሚተኛ ንድ ህጉ ይህ ነ፡፡”
\s5
\c 16
\p
\v 1 ያህ እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረ፡ - ይህ የሆነ የአሮን ሁለቱ ልጆች ¨ደ ያህ« ከቀረቡና ከሞቱ በሀላ ነበር፡፡
\v 2 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለ፣ “ለ¨ንድምህ ለአሮን እንዲህ ብለህ ተናገረ፣ በፈለገ¬ ጊዜ ሁሉ በመጋረጃ ¬ስጠኛ ¨ዳለ ¨ደ ቅድስተ ቅዱሳኑ፣ በታቦቱ ላይ ወዳለ ወደ ማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ፊት እንዳይቀርብ ንገረው፡፡ ይህንን ካደረገ፣ ይሞታል፣ ምክንያቱም እኔ በደመና በማስተሰርያ ክዳን ላይ እገለጣለሁ፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህም አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ መቅረብ ያለበት እንደዚህ ነው፡፡ ለሀጢአት መስዋዕት ወይፈን፣ ለሚቃጠል መስዋዕት አ¬ራ በግ ይዞ መግባት አለበት፡፡
\v 4 ቅዱሱን በፍታ ቀሚስ ይልበስ፣ እንዲሁም የበፍታ የስጥ ሱሪ ይልበስ፣ ደግሞም የበፍታ መጠምጠሚያ የበፍታ ቀሚስ ይልበስ፡፡ ቅዱሳኑ አልባሳት እነዚህ ናቸው፡፡ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብና እነዚህን ልብሶች ይልበስ፡፡
\v 5 ከእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁለት ወንድ ፍየሎችን ለሀጢአት መስዋዕት እንዲሁም አንድ አ¬ራ በግ ለሚቃጠል መስዋዕት ይውሰድ፡፡
\s5
\v 6 ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማ¬ን ለኃጢአት መስዋዕት ያቅርብ፣ ይህም ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ነው፡፡
\v 7 ቀጥሎም ሁለቱም ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ¬ ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ ፊት ያቁማቸው፡፡
\s5
\v 8 ከዚያ አሮን በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጣል፣ አንዱን ዕጣ ለያህዌ ሌላ¬ን ዕጣ ለሚለቀቀው ፍየል ይጣል፡፡
\v 9 ከዚያም አሮን ዕጣ ለያህ« የ¨ጣለትን ፍየል ያቀርባል፣ ያንን ፍየልም ለኃጢአት መስªዕት ያቀርበªል፡፡
\v 10 ለመለቀቅ ዕጣ የጣትን ፍየል ግን ወደ ምድረበዳ በመልቀቅ ለስርየት ከነህይ¨ት ለያህዌ መቅረብ አለበት፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም አሮን ለእራሱ ኮርማን ለሀጢአት መስዋዕት ያቀርባል፡፡ ለራሱና ለቤተሰቡ ማስተሰርያ ማድረግ አለበት፣ ስለዚህ ኮርማን ለራሱ የሀጢአት መስዋዕት አድርጎ ይረዳ፡፡
\s5
\v 12 አሮን በያህዌ ፊት ከመሰዊያ የከሰል እሳት የሞላውን ማጠንት ይውሰድ፣ በእጆቹ ሙሉ የላመ ጣፋጭ ዕጣን ይያዝና እዚህንም ነገሮች ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡
\v 13 በዚያም በያህ« ፊት ዕጣኑን በእሳቱ ላይ ይጨምር፣ ከእጣኑ የሚ¨ጣ ጢስ በምስክሩ ላይ ያለ የማስተሰርያን ክዳን ይሸፍናል፡፡ እንዳይሞት ይህንን ያድርግ፡፡
\s5
\v 14 ከዚያም ከወይፈኑ ጥቂት ደም ይውሰድና በጣቱ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ ከደሙ ጥቂት ¨ስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ በማስተሰርያ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም ለህዝቡ ኃጢአት የኃጢአት መስªዕት ፍየሉን ይረድና ደሙን ¨ደ መጋረጃ ¬ስጥ ይዞ ይግባ፡፡ በዚያም በኮርማ ደም እንዳደረገ ሁሉ ያድርግ በማስተሰርያ¬ ክዳን ላይ ደሙን ይርጭ ከዚያም በማስተሰርያ¬ ክዳን ፊት ይርጭ፡፡
\v 16 በእስራኤል ህዝብ ያልተቀደሱ ተግባራት፣ በአመጻቸ¬ና በኃጢአቶቻቸ¬ ሁሉ ምክንያት ለተቀደሰ ስፍራ ማስተሰርያ ያድርግ፡፡ ንጹህ ያልሆኑ ተግባሮቻቸ¬ በታዩ ጊዜያት፣ ያህ በመካከላቸ¬ ለሚያድርበት ለመገናኛ¬ ድንኳንም ይህን ያድርግ፡፡
\s5
\v 17 አሮን ለማስተሰርይ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚገባበት ሰዓትና እንዲሁም ለእርሱ፣ ለቤተሰቡና ለእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ማስተሰርዩን እስከሚጨርስ ድረስ ማንም ሰው በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አይገኝም፡፡
\v 18 በያህ« ፊት ወዳለ መሰዊያ ይሂድና መሰዊያን ያስተሰርይ፣ ከኮርማ ደም ጥቂት እንዲሁም ከፍየሉ ደም ጥቂት ይ¬ስድና በመሰዊያ ዙሪያ ባሉ ቀንዶች ሁሉ ¬ስጥ ያስነካ፡፡
\v 19 መሰዊያዉን ንጹህ ካልሆነ የእስራኤል ሰዎች ድርጊቶች ለማንጻትና ለያህዌ ለመለየት በላዩ ካለ ጥቂት ደም ወስዶ በጣቱ ሰባት ጊዜ ይርጭ፡፡
\s5
\v 20 ቅድስተ ቅዱሳኑን፣ የመገናኛን ድንኳንና መሰዊያን ማስተሰርያ¬ን ሲጨርስ በህይወት የሚገኘ¬ን ፍየል ያቅርብ፡፡
\v 21 አሮን ህይወት ባለው ፍየል ላይ ሁለቱንም እጆቹን ይጫንና የእስራኤልን ህዝብ በደልን ሁሉ፣ አመጻቸውን ሁሉ፣ እና ሀጢአታቸውን ሁሉ በላዩ ላይ ይናዘዝበት፡፡ ከዚያም ያንን ሃጢአተኛነት በፍየሉ ራስ ላይ አድርጎ ፍየሉን ወደ በረሃ ለመስደድ ኃላፊነት ባለበት ሰው አማካይነት ወደ በረሃ ያባው፡፡
\v 22 ፍየሉ የሰ­ቹን በደል ሁሉ ይሸከምና ገለልተኛ ¨ደ ሆነ ስፍራ ይሄዳል፡፡ በበረሃ ስፍራም፣ ሰ¬ዬ¬ ፍየሉን ይለቀªል፡፡
\s5
\v 23 ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳን ይመለስና ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ከመሄዱ አስቀድሞ የለበሰን የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፣ እነዚያን ልብሶችም በዚያ ስፍራ ያስቀምጣቸዋል፡፡
\v 24 በተቀደሰ ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያም የዘወትር ልብሱን ይልበስ፣ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መስዋዕቱን የህዝቡን የሚቃጠል መስዋዕት ያቅርብ፤ በዚህ መንገድ ለራሱና ለህዝቡ ማስተሰርያ ያቀርባል፡፡
\s5
\v 25 በመሰዊያ ላይ የኃጢአት መስዋዕቱን ስብ ያቃጥል፡፡
\v 26 የሚሰደደውን ፍየል የለቀቀው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡
\s5
\v 27 በተቀደሰው ስፍራ ለማስተሰርያው ደማቸው የቀረበው የኃጢአት መስªዕቱ ኮርማ እና የኃጢአት መስªዕቱ ፍየል ከሰፈር ውጭ ይውስዳቸው። በዚያም ቆዳቸውን፣ ስጋቸውንና ፈርሳቸውን ያቃጥላFቸው፡፡
\v 28 እነዚህን የእንስሳውን ክፍሎች የሚያቃጥለው ሰው ልብሶቹንና ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፣ ከዚያ በኋላ፣ ወደ ሰፈር መመለስ ይችላል፡፡
\s5
\v 29 በሰባተኛው ወር፣ በወሩ በአስረኛው ቀን ራሳችሁን ትሁት ታደርጋላችሁ ስራም አትሰሩበትም ለእናንተም ሆነ ለመጻተኛው ይህ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\v 30 ይህ የሚሆነው በዚህ ዕለት በያህዌ ፊት ቅዱስ ትሆኑ ዘንድ ከኃጢአቶቻችሁ ሁሉ እንድትነጹ ማስተሰርያ ስለሚደረግላችሁ ነው፡፡
\v 31 ይህ ለእናንተ ክቡር ሰንበት ዕረፍት ነው፣ ራሳችሁን ትሁት ማድረግ አለባችሁ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡ይህ በእናንተ መሀል ሁልጊዜም መታሰቢያ ነው
\s5
\v 32 ሊቀ ካህኑ፣ በአባቱ ስፍራ ሊቀካህን ሊሆን የሚቀባውና የሚሾመው፣ ይህን ማስተሰርያ ማስፈጸምና ቅዱስ የሆነውን የበፍታ ልብሶች መልበስ አለበት፡፡
\v 33 ለቅድስተ ቅዱሳኑ፣ ለመገናኛው ድንኳንና ለመስዋዕቱ፣ ማስተሰርያ ያደርጋል፤ እንደዚሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሰዎች በሙሉ ማስተሰርያ ያደርጋል፡፡
\s5
\v 34 "ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም መታሰቢያ ይሆናል፣ ለእስራኤል ሰዎች ለኃጢአቶቻቸው ሁሉ ማስተሰርያ ለማቅረብ ይህ በየአመት አንድ ጊዜ ይደረግ፡፡” ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ተደረገ፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 እንዲህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣
\v 2 ”አሮንና ልጆቹን እንዲሁም የእስራኤል ህዝብ ሁሉ እንዲህ በላቸው፡፡ ያህዌ ያዘዘውን ንገራቸው፡፡
\v 3 ”ከእስራኤል ሰዎች መሀል ማንም ለመስዋዕት በሰፈር ውስጥ ወይም ከሰፈር ውጭ በሬ፣ በግ፣ ወይም ፍየል ያረደ ሰው፣
\v 4 ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ በመቅደሱ ፊት ለያህዌ መስዋዕት ለማድረግ ባመጣው ውሃ ያ ሰው ስላፈሰሰው ደም በደለኛ ነው” ደም አፍስሷልና ያ ሰው ከህዝቡ መሃል ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\s5
\v 5 የዚህ ትእዛዝ ዓላማ የእስራኤል ሰዎች ለያህዌ በሜዳ ላይ የሚያቀርቧቸውን መስዋዕቶች ወደ ካህናት ለያህዌ የህብረት መስዋዕት አድርገው በመገናኛው ድንኳን መግቢያ እንዲያቀርቡ ነው፡፡
\v 6 ካህኑ የመስዋዕቱን ደም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ በያህዌ መሰዊያ ላይ ይረጫል፤ ስቡን ለያህዌ ጣፋጭ ማዕዛ አድርጎ ያቃጥለዋል፡፡
\s5
\v 7 ሕዝቡ ከእንግዲህ መስዋዕቱን ለጣኦት አይሰዋ፣ እንዲህ ያለው ተግባር ምንዝርና ነው፡፡ ይህ በትወልዶቻቸው ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 እንዲህ በላቸው፣ “ማንኛውም እስራኤላዊ፣ ወይም ማንኛውም በእነርሱ መሀል የሚኖር መጻተኛ፣ የሚቃጠል መስዋዕት የሚሰዋ ወይም መስዋዕት የሚያቀርብ
\v 9 እና ለያህዌ ለመሰዋት ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ የማያመጣው ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\s5
\v 10 ደግሞም ከእስራኤል አንዱ፣ ወይም በእነርሱ መሀል ከሚኖር መጻተኛ አንዱ፣ ደም ቢበላ፣ ፊቴን ከዚያ ሰው አስቆጣለሁ፣ ማንንም ደም የሚበላን ሰው ከህዝቡ መሃል አጠፋዋለሁ፡፡
\v 11 የእንስሳ ህይወቱ በደሙ ውስጥ ነው፡፡ በመሰዊያ ላይ ማስተሰርያ ይሁናችሁ ዘንድ ደሙን ለሕይወታችሁ ሰትቻችኋለሁ፣ ምክንያቱም ማስተሰርያ የሚሆነው ደም ነው፣ ለሕይወት ስርየት የሚያስገኘው ደም ነው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህም ለእስራኤላውያን ከመሀላችሁ ማንም ደም አይብላ እላለሁ፣ በመሀላችሁ የሚኖር ማንም ሙያተኛም ቢሆን ደም አይብላ፡፡
\v 13 ከእስራኤል ሰዎች መሀል ማንም ቢሆን፣ ወይም በእነርሱ መሃል የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣ የሚበላ እንስሳ ቢያርድ ወይም ወፍ ቢያጠምድ ደሙን ያፍስና በአፈር ይሸፍነው፡፡
\s5
\v 14 የእያንዳንዱ ፍጥረት ነፍስ ደሙ ነውና፡፡ ስለዚህም ነው ለእስራኤላውያን፣ የማንኛውም ፍጥረት ደም አትብሉ፣ የእያንዳንዱ ሕያው ፍጥረት ሕይወት ደሙ ነው፡፡ ማንም ይህን የሚበላ ተቆርጦ ይጥፋ” ብዬ የተናገርኩት፡፡
\s5
\v 15 እያንዳንዱ የሞተ፣ ወይም በዱር አውሬ የተዘነጠለ እንስሳ የበላ ሰው የአገር ተወላጅ ይሁን በመሀላችሁ የሚኖ መጻተኛ ልብሶቹን ይጠብ፣ እርሱም በውሃ ይታጠብ፣ እስ ምሽት ድረስ ንጹህ አይሆንም፡፡ ከዚያ ንጹህ ይሆናል፡፡
\v 16 ነገር ግን ልብሱን ባያጥብ ወይም ሰውነቱን ባይታጠብ፣ በበደሉ ተጠያቂ ነው፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\v 3 እኔ በማስገባችሁ ምድር፤ ቀድሞ ትኖሩበት በነበረው በግብጽ የነበሩ ሰዎች ያደርጓቸው የነበሩ ነገሮችን አታድርጉ፣ ደግሞም በከነአን ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ያደርጓቸው የነበሩ ነገሮችን አታድርጉ፡፡ የእነርሱን ልምዶች አትከተሉ፡፡
\s5
\v 4 እናንተ መፈጸም ያለባችሁ የእኔን ህጎች ነው መጠበቅ ያለባችሁ የእኔን ትዕዛዛት ነው፣ ስለዚህም በእነርሱ ትኖራላችሁ፣ ምክንያቱም እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 5 ስለዚህም እኔን ትዕዛዛትና ህጎች ትጠብቀላችሁ፡፡ አንድ ሰው እነዚህን ቢጠብቅ፣ በእነርሱ ምክንያት በህይወት ይኖራል፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 6 ማንም ሰው ከቅርብ ዘመዱ ጋር አይተኛ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 7 ከእናትህ ጋር በመተኛት አባትህን አታዋርድ፡፡ እርሷ እናትህ ናት! እርሷን ማዋረድ የለብህም፡፡
\v 8 ከአባትህ ሚስት ከየትኛዋም ጋር አትተኛ፤ አባትህን በዚያን አይነት ማዋረድ የለብህም፡፡
\s5
\v 9 የአባትህ ልጅ ወይም የእናትህ ልጅ ብትሆን በቤት ውስጥ አብራህ ብታድግ ወይም ርቃ ብታድግም ከየትኛዋም እህትህ ጋር አትተኛ፡፡
\v 10 ከወንድ ልጅህ ሴት ልጅ ጋር ወይም ከሴት ልጅህ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ ይህ እፍረት ይሆንብሃል፡፡
\v 11 ከአባትህ ከተወለደች ከእንጀራ እናትህ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ እህትህ ናት፣ እናም ከእርሷ ጋር መተኛት የለብህም፡፡
\s5
\v 12 ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፡፡ ለአባትህ የቅርብ ዘመድ ናት፡፡
\v 13 ከእናትህ እህት ጋር አትተኛ፡፡ ለእናትህ የቅርብ ዘመድ ናት፡፡
\v 14 ወንድም ከሚስቱ ጋር በመተኛት አታዋርደው” ለዚያ ተግባር ወደ እርሷ አትቅረብ፣ አክስትህ ናት፡፡
\s5
\v 15 ከምራትህ ጋር አትተኛ፡፡ የወንድ ልጅህ ሚስት ናት፣ ከእርሷ ጋር አትተኛ፡፡
\v 16 ከወንድምህ ሚስት ጋር አትተኛ፣ በዚህ መንገድ አታዋርደው፡፡
\s5
\v 17 ከአንዲት ሴትና ከልጇ ጋር ወይም ከወንድ ልጇ ሴት ልጅ ጋር ወይም ከሴት ልጇ ሴት ልጅ ጋር አትተኛ፡፡ እነርሱ ለእርሷ የቅርብ ዘመዶች ናቸው፣ እናም ከእነርሱ ጋር መተኛት ጸያፍ ነው፡፡
\v 18 የሚስትህን እህት ሁለተኛ ሚስት አድርገህ አታግባ፤ ሚስትህ በህይወት ሳለች ከእህቷ ጋር አትተኛ፡፡
\s5
\v 19 አንዲት ሴት በወር አበባዋ ወቅት ላይ ሳለች አብረሃት አትተኛ፡፡ በዚያን ጊዜ ንጹኅ አይደለም፡፡
\v 20 ከጎረቤትህ ሚስት ጋር አትተኛ፣ በዚህ መንገድ ራስህን አታርክስ፡፡
\s5
\v 21 ከልጆችህ አንዳቸውንም በእሳት ውስጥ እንዲያልፉ አትስጥ፣ በዚህ ድርጊት ለሞሎክ መስዋዕት አድርህ ትሰጣቸዋለህ፣ የአምላክህን ስም ማቃለል የለብህም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 22 ከወንዶች ጋር ከሴት ጋር እንደምትተኛው አትተኛ፡፡ ይህ ጻያፍ ነው፡፡
\v 23 ከማናቸውም እንስሳ ጋር አትተኛ ራስህን አታርክስ፡፡ ማንም ሴት ከማናቸውም እንስሳ ጋር መተኛት የለባትም፡፡ ይህ አስጸያፊ ወሲብ ነው፡፡
\s5
\v 24 ከእነዚህ መንገዶች በየትኛውም ራስህን አታርክስ፣ ከአንተ አስቀድሞ ያባረርኳቸው ህዝቦች በእነዚህ ሁሉ መንገዶች ረክሰዋል፡፡
\v 25 ምድሪቱ ረከሰች፣ ስለዚህም በኃጢአታቸው ቀጣኋቸው፣ ምድሪቱም በላይዋ የሚኖሩትን ተፋቻቸው፡፡
\s5
\v 26 ስለዚህ እናንተ የእኔን ትዕዛዛትና ህግጋቴን መጠበቅ አለባችሁ፣ እናንተ ተወላጅ እስራኤላዊያንም ሆናችሁ በእንተ መሀል የሚኖሩ እንግዶች ከእነዚህ ያልተገቡ ነገሮች የትኞቹንም ማድረግ የለባችሁም፡፡
\v 27 ከእናንተ አስቀድሞ በዚህ ምድር የኖሩ ሰዎች የሰሩት ጸያፍነት ይህ ነው፣ እናም አሁን ምድሪቱ ረከሰች፡፡
\v 28 ስለዚህም ምድሪቱ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ሰዎች እንደተፋች እናንተንም ካረከሳችኋት በኋላ እንዳትተፋችሁ ተጠንቀቁ፡፡
\s5
\v 29 ከእነዚህ አስነዋሪ ነገሮች መሀል የትኛውንም ነገር ያደረገ፣ እንዲህ ያለ ነገሮችን ያደረገው ሰው ከህዝቡ መሀል ተለይቶ ይጠፋል፡፡
\v 30 ስለዚህ በእነዚህ ነገሮች እንዳታረክሱ ከእናንተ አስቀድሞ በዚህ ስፍራ ይፈፀሙ የነበሩትን ጸያፍ ልምዶች ባለማድረግ ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለባችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሙሴን እንዲህ አለው
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች ጉባኤ ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ቅዱስ እንደሆንኩ እናተም ቅዱሳን ሁኑ፡፡
\v 3 እያንዳንዱ እናቱንና አባቱን ያክብር፣ እናንተም ሰንበቴን ጠብቁ፡፡ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡
\v 4 ጥቅም ወደሌላቸው ጣኦታት ዘወር አትበሉ፣ ከቀለጠ ብረት ለራሳችሁ አማልዕክትን አታብጁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 5 ለያህዌ የህብረት መስዋእቶችን ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ልታገኙ በምትችሉበት መንገድ አቅርቡ፡፡
\v 6 መስዋዕቱ ባቀረባችሁበት ቀን አሊያም በማግስቱ ይበላ፡፡ አንዳች ነገር እስ ሶተኛው ቀን ቢተርፍመ ይቃጠል፡፡
\v 7 በሶስተኛው ቀን ቢበላ የረከሰ ነው፡፡ ተቀባይነት አያገኝም፣
\v 8 ነገር ግን የበላው ሁሉ በበደለኛነቱ ይጠየቅበታል ምክንያቱም ለያህዌ የተለየውን አርክሷል፡፡ ያ ሰው ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\s5
\v 9 የምድራችሁን ሰብል በምትሰበስቡበት ጊዜ፤ የእርሻችሁን ቀርጢያ ሁሉ አትልቀሙ፣ አሊያም የአዝመራችን ምርት ሁሉ አትሰብስቡ፡፡
\v 10 ከወይን ተክልህ እያንዳንዱን ወይን ፍሬ አትሰብስብ፣ አሊያም በወይን ስፍራ የወዳደቁትን የወይን ፍሬዎች አትልቀም፡፡ ለድሆችና ለመጻተኞች እነዚህን ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 11 አትስረቁ፡፡ አትዋሹ፡፡ አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ፡፡
\v 12 በሃሰት በስሜ አትማሉ የአምላካችን ስም አታርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 13 ጎረቤትህን አትበድል ወይም አትዝረፈው፡፡ የቀን ሰራተኛውን ክፍያ በአንተ ዘንድ አታሳድር፡፡
\v 14 መስማት የተሳነውን ሰው አትርገመው ወይም ከእውሩ ፊት ማሰናከያ ድንጋይ አታስቀምጥ ይልቁንም አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 15 ፍትህን አታጣም፡፡ አንድ ሰው ድሃ ስለሆነ ልታደላለት አይገባም፣ እንደዚሁም አንድ ሰው ባለጸጋ ስለሆነ አታዳላለት፡፡ ይልቁንም ለጎረቤትህ በጽድቅ ፍረድ 16በሰዎች መሃል በሀሳት ሃሜትን አታሰራጭ
\v 16 በሰዎች መሃል ሀሜትን እያሰራጨህ አትዙር፣ ይልቁንም የጎረቤትህን ሕይወት አቅና፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 17 በልብህ ወንድምህን አትጥላ፡፡ በእርሱ ምክንያት የኃጢአቱ ተካፋይ እንዳትሆን ጎረቤትህን በቅንነት ገስጸው፡፡
\v 18 ከህዝብህ ማንንም አትቀበል ወይም በማንም ላይ ቂም አይኑርህ፣ ነገር ግን በዚህ ፈንታ ጎረቤትህን እንደራስህ ውደድ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 19 ትዕዛዛቴን መጠበቅ አለብህ፡፡ እንስሳትህን ከሌሎች ልዩ ዝርያ ካላቸው እንስሳት ጋር አታዳቅል፡፡ በእርሻህ ላይ ስትዘራ የተለያየ የዘር ዐይነቶችን አትደባልቅ፡፡ ከሁለት የተለያዩ አይነት ነገሮች ተደባልቆ የተሰራ ልብስ አትልበስ፡፡
\s5
\v 20 ቤዛ ካልተከፈለላት ወይም ነጻ ካልወጣች ለባል ከታጨት ባሪያ ከሆነች ልጃገረድ የተኛ ሁሉ ይቀጡ፡፡ ሊገደሉ ግን አይገባም ምክንያቱም ነጻ አልወጣችም፡፡
\v 21 ሰውዬው ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ለበደል መስዋዕት ለያህዌ አውራ በግ ያምጣ፡፡
\v 22 ከዚያ ካህኑ በያህዌ ፊት ሰውዬው ለሰራው ኃጢአት የበደል መስዋዕት አውራ በግ በማቅረብ ያስተሰርይለታል፡፡ ከዚያ የሠራው ኃጢአት ይቅር ይባልለታል፡፡
\s5
\v 23 ወደምድሪቱ ስትገቡና ለምግብ የሚሆን ሁሉንም ዐይነት ዛፎች ስትተክሉ፣ ዛፎቹ ያፈሩትን ፍሬ ለመብላት እንደተከለከለ ቁጠሩት፡፡ ፍሬው ለእናንተ ለሶስት ዓመታት የተከለከለ ነው፡፡ አይበላም፡፡
\v 24 ነገር ግን በአራተኛው አመት ፍሬው ሁሉ ለያህዌ ለምስጋና የሚሰዋ ቅዱስ ይሆናል፡፡
\v 25 አመት ፍሬውን መብላት ትችላላችሁ፡፡ በመጠበቃችሁ ዛፎቹ ብዙ ያፈራሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 26 ደሙ በውስጡ ያለበትን ስጋ አትብሉ፡፡ ስለ ወደፊቱ መናፍስትን አታማክሩ፣ ደግም ከተፈጥሮ በላይ በሆኑ ኃይላት ሌሎችን ለመቆጣጠር አትፈልጉ፤፡፡
\v 27 እንደ ጣኦት አምላኪዎች የጸጉራችሁን ዙሪያ አትላጩ ወይም የጺማችሁን ዙሪያ አትቆረጡ፡፡
\v 28 ለሙታን ሰውነታችሁን በስለት አትቁረጡ ወይም በሰውነታችሁ ላይ ንቅሳት አታድርጉ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 29 ሴት ልጅህን ሴተኛ አዳሪ በማድረግ አታወርዳት፣ በዚህ ነገር አገረ ወደ ግልሙትና ትገባለች ምድሪቱም በእርኩሰት ትሞላለች፡፡
\v 30 ጠብቁ የቤተመቅደሴን ቅድስና አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 31 ወደ ሙታን ጠሪዎችና መናፍስትን ወደሚያነጋግሩ ዘወር አትበሉ፡፡ እነዚህን አትፈልጉ፣ ካልሆነ ያረክሷችኋል፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 32 ፀጉሩ ለሸበተ ሰው ተነስለት ደግሞም በዕድሜ የገፋውን ሰው አክብር፡፡ አምላክህን ፍራ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 33 በምድርህ በመካከልህ መጻተኛ ቢኖር፣ አትግፋው፡፡
\v 34 በመካከላችሁ የሚኖረው መጻተኛ እንደ ተወላጅ እስራኤላዊ ወገናችሁ ቁጠሩት ደግሞም እንደ ራሳችሁ ውደዱት፣ ምክንያቱም እናንተም በግብጽ ምድር መጻተኞች ነበራችሁ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 35 ርዝመትን፣ ክብደትን፣ ወይም ብዛትን ስትለኩ፡፡ ሀሰተኛ መለኪያ አትጠቀሙ፡፡
\v 36 ትክክለኛ መስፈሪያን፣ ትክክለኛ ሚዛኖችን፣ ትክክለኛ የኢፍ እና የኢን መለኪያዎችን ተጠቀሙ፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\v 37 ትዕዛዛቴንና ህግጋቴን ሁሉ ጠብቁ፣ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\s5
\c 20
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእስራኤል ሰዎች መሃል ማንም ሰው፣ ወይም ማንኛውም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ከልጆቹ መሃል አንዱን ለሞሎክ ቢሰጥ በዕርግጥ ይገደል፡፡ በምድሪቱ የሚኖሩ ሰዎች በድንጋይ ይውገሩት፡፡
\s5
\v 3 እኔም በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አዞርበታለሁ፣ ከህዝቡም መሃል እቆርጠዋለሁ ምክንያቱም የተቀደሰውን ስፍራዬን ለማርከስና ቅዱሱን ስሜን ለማቃለል ልጁን ለሞሎክ ሰጥቷል፡፡
\v 4 ያ ሰው ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ ሲሰጥ ዚያች ምድር ሰዎች እንዳላዩ ቢሆን፣ ባይገድሉት፣
\v 5 እኔ ራሴ በዚያ ሰውና በቤቱ ላይ ፊቴን አዞራለሁ፣ እኔ ቆርጬ እጥለዋለሁ እንደዚሁም ከሞሎክ ጋር በሚያመነዝረው በማንኛውም ላይ ይህን አደርጋለሁ፡፡
\s5
\v 6 ወደ ሙታን ጠሪዎች ዘወር የሚል፣ ወይም ከመናፍስት ጋር ከሚነጋገሩ ጋር የሚመነዝርን ሰው ፊቴን አዞርበታለሁ፤ ከህዝቡም መሃል አጠፋዋለሁ፡፡
\v 7 ስለዚህ ራሳችሁን ለያህዌ ስጡ ተቀደሱም፣ ምክንያቱም እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 8 ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ ለራሴ የመረጥኳችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 9 ወይም እናቱን የሚረግም ሁሉ ይገደል፡፡ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና በደለኛ ነው ሞት ይገባዋል፡፡
\s5
\v 10 ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ዝሙት የፈጸመ ሰው፣ ከጎረቤቱ ሚስት፣ ጋር ያመነዘረ ይገደል አመንዝራውና አመንዝራይቱም ሁለቱም ይገደሉ፡፡
\v 11 ከአባቱ ሚስት ጋር ሊተኛት የወደቀ የገባ አባቱን ያዋርዳል፡፡ ልጅየውም የአባቱ ሚስትም ሁለቱም ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
\v 12 አንድ ሰው ከልጁ ሚስት ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ሊገደሉ ይገባል ያልገባ ፍትወት ፈጽመዋል በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
\s5
\v 13 አንድ ወንድ ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከሌላ ወንድ ጋር ቢተኛ፣ ሁለቱም ጸያፍ ነገር አድርገዋል፡፡ በእርግጥ ሞት ይገባቸዋል፡፡ ይገደሉ፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
\v 14 አንድ ሰው አንዲትን ሴትና እናቲቱንም ቢያገባ፣ ይህ አሳፋሪ ነው፡፡ እርሱና ሴቲቱ ሁለቱም በእሳት ይቃጠሉ፣ ይህ ሲደረግ በመሀላችሁ ክፋት አይኖርም፡፡
\s5
\v 15 አንድ ሰው ከእንስሳ ጋር ቢተኛ፣ በእርግጥ ይገደል፣ እንስሳይቱንም ግደሏት፡፡
\v 16 አንዲት ሴት ለመገናኘት ወደ ማንኛውም አይነት እንስሳ ብተቀርብ ሴትየዋንም እንስሳውንም ግደሏቸው፡፡ በእርግጥ ሊገደሉ ይገባል፡፡ በደለኞች ናቸው ሞት ይገባቸዋል፡፡
\s5
\v 17 አንድ ሰው የአባቱ ልጅ ከሆነችውም ሆነ የእናቱ ልጅ ከሆነች እህቱ ጋር ቢተገኛ እህትም ከእርሱ ጋር ብትተኛ ይህ አሳፋሪ ነገር ነው፡፡ ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፤ ምክንያቱም ከእህቱ ጋር ተኝቷል፡፡ በደሉን ይሸከማል፡፡
\v 18 አንድ ሰው አንዲትን ሴት በወር አበባዋ ወቅት አብሯት ቢተኛና ቢገናኛት፣ የደሟ ምንጭ የሆነውን የደም መፍሰሷን ገልጧል፡፡ ወንዱም ሴቷም ሁለቱም ከህዝባቸው መሃል ተለይተው ይውጡ፡፡
\s5
\v 19 ከእናትህ ወይም ከአባትህ እህት ጋር አትተኛ፣ ምከንያቱም የቅርብ ቤተ ዘመድህን ታዋርዳለህ፡፡ በደልህን ልትሸከም ይገባሃል፡፡
\v 20 አንድ ሰው ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ አጎቱን አዋርዷል፡፡ በደላቸውን ሊሸከሙ ይገባል ያለ ልጅ ይቀራሉ፡፡
\v 21 አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ይህ እርኩስ ነው ምክንያቱም ዘመዱ ሆኖ ሳለ የወንድሙን ትዳር አፍርሷል፣ ልጅ አልባ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 22 ስለዚህም ስርአቶቼንና ህግጋቶቼን ሁሉ መጠበቅ አለባችሁ፤ እንድትኖርባት ያመጣኋቸው ምድር እንዳትተፋችሁ ህግጋቴንና ሥርዓቶቼን ጠብቁ፡፡
\v 23 ከፊታችሁ በማባርራቸው ህዝቦች ልምዶች አትመላለሱ፣ እነርሱ እነዚህን ነገሮች ሁሉ አድርገዋል፣ እኔም እነርሱን ጠላሁ፡፡
\s5
\v 24 እኔ እንዲህ እላችኋለሁ፣ “ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፣ ምድሪቱን እንድትወርሷት ለእናንተ እሰጣችኋለሁ፣ ወተትና ማር የምታፈስ ምድር ናት፡፡ ከሌላው ህዝብ የለየኋችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ”
\v 25 ስለዚህ እናንተ ንጹህ በሆኑና ንጹኅ በሆኑ እንስሳት መሃል፣ ንጹኅ በሆኑና ንጹህ ባልሆኑ ወፎች መሃል ልዩነት አድርጉ፡፡ ለእናንተ ርኩስ ናቸው ብዬ በለየኋቸው ንጹኅ ባልሆኑ እንስሳት ወይም ወፎች ወይም በማንኛውም በምድር ላይ በሚሳብ ፍጥረት ራሳችሁን አታርክሱ፡፡
\s5
\v 26 እኔ ያህዌ ቅዱስ እንደሆንኩ፣ ደግሞም ለእኔ ትሆኑ ዘንድ ከሌሎች ህዝቦች እንደለየኋችሁ ቅዱሳን ሁኑ፡፡
\s5
\v 27 ከሙታን ጋር የሚነጋገር አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ወይም ከመናፍስት ጋር የሚነጋገር በእርግጥ ይገደል፡፡ ህዝቡ በድንጋይ ወግፎ ይግደላቸው በደለኞች ናቸውና ሞት ይገባቸዋል፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው “ለካህናቱ፣ ለአሮን ልጆች እንዲህ በላቸው፣ ‹ከእናንተ መሃል ማንም በመካከላችሁ በሞተ ሰው አይርከስ፣
\v 2 ለቅርብ ዘመድ ካልሆነ በስተቀር ማንም አይርከስ ለእናቱ እና አባቱ፣ ለወንድ ልጁና ለሴት ልጁ፣ ወይም ለወንድሙ
\v 3 ወይም በቤቱ ከምትኖር ባል ካላገባች ልጃገረድ እህቱ በስተቀር አይርከስ፡፡ ለእርሷ ግን ራሱን ንጹህ ላያርግ ይችላል፡፡
\s5
\v 4 ለሌሎች ዘመዶቹ ግን እስኪረክስ ድረስ ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡
\v 5 ካህናት ራሳቸውን አይላጩ ወይም የጺማቸውን ዳርቻ አይላጩ፣ አሊያም ሰውነታቸውን በስለት አይቁረጡ፡፡
\v 6 እነርሱ ለአምላካቸው የተለዩ ይሆኑ፣ የአምላካቸውን ስም አያቃሉ፣ ምክንያቱም ካህናቱ የአምላካቸውን “ምግብ” መስዋዕቱን ለያህዌ በእሳት ያቀርባሉ፡፡ ስለዚህም እነርሱ የተለዩ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 7 ለአምላካቸው የተለዩ ስለሆኑ ማናቸውንም ጋለሞታ እና የረከሰች ሴት እንደዚሁም ከባሏ የተፋታችን ሴት ማግባት የለባቸውም፡፡
\v 8 የአምላክህን “ምግብ” የሚያቀርብ ነውና እርሱን መለየት አለብህ፡፡ በፊትህ ቅዱስ መሆን አለበት፣ ምክንያቱም ለራሴ የለየሁህ እኔ፣ ያህዌ ቅዱስ ነኝ፡፡
\v 9 ማንኛዋም የማንኛውም ካህን ሴት ልጅ ጋለሞታ ብትሆን አባቷን ታሳፍራለች፡፡ በእሳት ትቃጠል፡፡
\s5
\v 10 ከወንድሞቹ መሃል ሊቀ ካህን የሆነው፣ የሹመቱ ዘይት በራሱ ላይ የፈሰሰበት፣ ደግሞም የሊቀ ካህኑን ልዩ ልብሶች ለመልበስ የተጾመ ጸጉሩን ይሸፍን ልብሱን አይቅደድ፡፡
\v 11 ለአባቱ ወይም ለእናቱም ቢሆን እንኳን የሞተ ሰው በሚገኝበትና ራሱን በሚያረክስበት ማናቸውም ስፍራ አይሂድ፡፡
\v 12 ሊቀካህኑ የቤተ መቅደሱን የተቀደሰ ስፍራ ትቶ አይሂድ ወይም የአምላኩን ቅድስና አያቃል፣ ምክንያቱም በአምላኩ የቅባት ዘይት ሊቀ ካህን ሆኖ ተሾሞ ነበርና፡፡እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 13 ካህኑ ድንግሊቱን ሚስቱ አድርጎ ያግባት፡፡
\v 14 ባሏ የሞተባትን ሴት፣ የተፋታችን ሴት፣ ወይም ጋለሞታን ሴት አያግባ፡፤ እንዲያ ካሉት ሴቶች መሃል አያግባ፡፡ ከራሱ ህዝብ መሃል ድንግሊቱን ብቻ ማግባት ይችላል፡፡
\v 15 እነዚህን ህጎች ይጠብቅ፣ በህዝቡ መሃል ልጆቹን እንዳያረክስ ህግጋቱን ይጠብቅ፣ እርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 16 ያህዌ እንደህ ሲል ሙሴን ተናገረው፣
\v 17 “አሮንን እንዲህ ብለህ ንገረው፣ ማናቸውም ከወገንህ መሀል በትወልዳቸው ውስጥ አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ የአምላኩን ‹ምግብ› ለመሰዋት መቅረብ የለበትም፡፡
\s5
\v 18 ማናቸውም አካላዊ እንከን ያለበት ሰው ወደ ያህዌ መቅረብ የለበትም፣ እንደ ዐይነ ስውር፣ ሽባ የሆነ ሰው፣ አካሉ የጎደለ ወይም አካሉ የተወላገደ፣
\v 19 እጆቹ ወይም እግሮቹ ሽባ የሆነ፣
\v 20 መጻጉ ወይም ድንክ ሰው፣ ወይም በዐይኖቹ ላይ እንከን ያለበት ሰው፣ ወይም በሽታ የያዘው፣ ሞጭሟጫ፣ እከክ ያለበት ወይም ጃንደረባ ወደ ያህዌ አይቅረብ፡፡
\v 21 ከካህኑ ከአሮን መሃል ምንም አካላዊ ጉድለት ያለበት ሰው ለያህዌ የእሳት መስዋዕቶች ለመሰዋት አይቅረብ፡፡ አካላዊ ጉድለት ያለበት እንዲህ ያለው ሰው የአምላኩን ‹ምግብ ለማቅረብ መቅረብ የለበትም፡፡
\s5
\v 22 ከቅድስተ ቅዱሳኑም ሆነ ከቅዱሱ የአምላኩ ምግብ ሊበላ ግን ይችል፣
\v 23 ሆኖም፣ ወደ መጋረጃው መግባት የለበትም ወይም ወደ መሰዊያው አይቅረብ፣ ምክንያቱም አካላዊ ጉድለት ያለበት፣ ስለዚህም ቅዱሱን ስፍራዬን አያርክስ፣ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\v 24 ሙሴ እነዚህን ቃላት ለአሮን፣ ለልጆቹ፣ እና ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ ተናገረ፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ የእስራኤል ሕዝብ ለእኔ ከለይዋቸው የተቀደሱ ነገሮች እንዲጠበቁ ንገራቸው፡፡ የተቀደሰው ስሜን አያርክሱ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 3 እንዲህ በላቸው፣ በዘመን ሁሉ ከትውልዳችሁ መሀል ማንም ንጹህ ያልሆነ ሰው የእስራኤል ህዝብ ለያህዌ ወደ ለየው ቅዱስ ነገሮች ቢቀርብ፣ ያ ሰው እኔ ፊት ከመቅረብ የተከለከለ ነወ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 4 ከአሮን ትውልድ ውስጥ ተላላፊ የቆዳ በሽታ ያለበት፣ ወይም ከሰውቱ ፈሳሽ የሚወጣ ንጹኅ እስኪሆን ድረስ ለያህዌ ከሚቀርብ መስዋዕት አይብላ፡፡ማንም ከሞተ ጋር በመነካካት ንጹህ ያልሆነውን ማንኛውንም ነገር የነካ፣ ወይም የዘር ፈሳሽ ካለበት ሰው ጋር በመነካካት፣
\v 5 ወይም የሚያረክሰውን ማናቸውንም በሆዱ የሚሳብ እንስሳ የነካ፣ ወይም ማናቸውንም የሚያረክሰውን ሰው የነካ፣ ማንኛውም አይነት እርኩሰት የሚያስከትል ነገር የነካ
\v 6 ማናቸውንም እርኩስ ነገር የነካ ካህን እስከ ምሽት ንጹህ አይደለም፡፡ ሰውነቱን በውሃ ካልታጠበ በቀር ከተቀደሱት ነገሮች አንዳች አይብላ፡፡
\s5
\v 7 ፀሐይ ስትጠልቅ፣ በዚያን ሰዓት ንጹህ ይሆናል፡፡ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ከተቀደሱት ነገሮች መብላት ይችላል፣ ምክንያቱም ለእርሱ የተፈቀዱ ምግብ ናቸው፡፡
\v 8 ሞቶ የተገኘን ማናቸውም ነገር አይብላ ወይም እርሱን የሚያረክሰውን በዱር እንስሳ የተገደለውን አይብላ፡፡
\v 9 ካህናት ትእዛዛቴን ይጠብቁ፣ ይህን ካላደረጉ በኃጢአት በደለኛ ይሆናሉ ደግም ስሜን በማቃለል ይሞታሉ፡፡ ለራሴ የለየኋቸው እኔ ያህዌ ነኝ፣
\s5
\v 10 ማንም የካህኑ ቤተሰብ ያልሆነ ሰው፣ የካህኑን እንግዶች ጨምሮ፣ ወይም ቅጥር አገልጋዮቹ ጭምር ቅዱስ ከሆነው አንዳች አይብሉ፡፡
\v 11 ነገር ግን ካህኑ በገንዘቡ ባሪያ ቢገዛ ያ ባሪያ ለያህዌ ከተለዩ ነገሮች መብላት ይችላል፡፡ የካህኑ ቤተሰብ አባላት እና በቤቱ የተወለዱ ባሪያዎች ከእርሱ ጋር ከእነዚህ የተቀደሱ ነገሮች መብላት ይችላሉ፡፡
\s5
\v 12 የካህኑ ሴት ልጅ ካህን ያልሆነ ሰው ብታገባ ለመስዋዕት ከመጣው ውስጥ አንዳች አትበላም፡፡
\v 13 ነገር ግን የካህኑ ሴት ልጅ ባሏ የሞተባት ከሆነች፣ ወይም ከባሏ ከተፋታች፣ እና ልጅ ያልወለደች ከሆነች እንደ ልጅነቷ ዘመን ለመኖር ወደ አባቷ ቤት ብትመለስ ከአባቷ ምግብ መብላት ትችላለች፡፡ ነገር ግን ማንም የካህን ቤተሰብ ያልሆነ ከካህናት ምግብ መብላት አይችልም፡፡
\s5
\v 14 አንድ ሰው ሳያውቅ ቅዱሱን ምግብ ቢበላ፣ ከወሰደው አንድ አምስተኛ ጨምሮ ለካህኑ ይመልስ፡፡
\v 15 የእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የወዘወዙትንና ያቀረቡትን ቅዱስ ነገሮች ማቃለል የለባቸውም፣
\v 16 ያልተፈቀደላቸውን ቅዱሱን ምግብ በመብላት ራሳቸውን በደለኛ የሚያደርጋቸውን ኃጢአት እንዲሸከሙ ማድረግ የለባቸውም እነርሱን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ”
\s5
\v 17 ያህዌ እንዲህ አለው፣
\v 18 “ለአሮንና ልጆቹ እንዲሁም ለእስራኤል ሰዎች ሁሉ እንዲህ በላቸው፣ ‹ማንኛውም እስራኤላዊ፣ ወይም በእስራኤል የሚኖር ባይተዋር፣ ለስዕለትም ይሁን፣ ወይም ለበጎ ፈቃድ መስዋዕት ሲያቀርቡ፣ ወይም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ሲያቀርቡ፣
\v 19 ተቀባይነትን እንዲያገኝ ከቀንድ ከብታቸው፣ ከበግ ወይም ፍየሎች ውስጥ ነውር የሌለበትን ተባዕት እንስሳ ያቅርቡ፡፡
\s5
\v 20 ነውር ያለበትን ግን አታቅርቡ፡፡ ይህን እኔ አልቀበልም፡፡
\v 21 ከከብቱ ወይም ከመንጋው ለስዕለት የህብረት መስዋዕት ለያህዌ የሚሰዋ ሁሉ፣ ወይም የበጎ ፍቃድ መስዋዕት የሚያቀርብ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ነውር የሌለበትን መስዋዕት ያቅርብ፡፡ በእንስሳው ላይ እንከን አይኑርበት፡፡
\s5
\v 22 ዕውር፣ አንካሳ ወይም ሰንካላ፣ ወይም ኪንታሮት፣ ህመም፣ ወይም ቁስል ያለበትን እንስሳ አትሰዉ፡፡ እዚህን በእሳት መስዋዕት አድርጋችሁ በመሰዊያ ላይ ለያህዌ አታቅርቡ፡፡
\v 23 የበጎ ፈቃድ መስዋዕት አድርጋችሁ ጎደሎ ወይም ትንሽ በሬ ወይም በግ ማቅረብ ትችላላችሁ፣ እንዲህ ያለው መስዋዕት ግን ለስዕለት ተቀባይነት የለውም፣
\s5
\v 24 ለያህዌ ሰንበር ያለበት፣ የተሰበረ፣ የተዘነጠለ፣ ወይም የዘር ፍሬው የተቀጠቀጠ እንስሳ አታቅርቡ፡፡ እነዚህን በምድራችሁ አታቅርቡ፣
\v 25 ለእግዚአብሔር ለምግብ የሚቀርብ አድርጋችሁ ከመጻተኛው እጅ አትቀበሉ፣ ምክንያቱም በእነዚህ ላይ ጉድለቶች ወይም ነውሮች አሉባቸው እነዚህን ከእናንተ አልቀበለም፡፡›”
\s5
\v 26 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 27 “አንድ ጥጃ ወይም አንድ የበግ ወይም የፍየል ግልገል ሲወለድ፣ ከእናቱ ጋር ሰባት ቀናት ይቆይ፡፡ ከዚያም ከስምንተኛው ቀን አንስቶ፣ ለያህዌ በእሳት መስዋዕት ሆኖ መቅረብ ይችላል፡፡
\s5
\v 28 አንዲትን ላም ወይም ሴት በግ ከጥጃዋ ወይም ከግልገሏ ጋር በአንድ ቀን አትረዱ፡፡
\v 29 ለያህዌ የምስጋና መስዋዕት ስታቀርቡ፣ ተቀባይነት ባለው መንገድ አቅርቡ፡፡
\v 30 መስዋዕቱ በቀረበበት ቀን ይበላ፡፡ እስከ ማለዳው አንዳች አታስቀሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 31 ትዕዛዛቴን ጠብቁ አድርጓቸውም፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\v 32 ቅዱስ ስሜን አታቃሉ፡፡ በቅድስናዬ በእስራኤል ህዝብ መታወቅ አለብኝ፡፡ እናንተን ለራሴ የለየሁት እኔ ያህዌ ነኝ፣
\v 33 አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\s5
\c 23
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “ለእስራኤል ህዝብ እንዲህ በላቸው፣ ‹ለያህዌ የተለዩ የተቀደሱ ባዕሎቻችሁ፣ እንደ ቅዱስ ጉባኤዎቻችሁ የምታውጇቸው፣ የእኔ መደበኛ በዓላት ናቸው፡፡
\s5
\v 3 ስድስት ቀናት ትሰራላችሁ፣ ሰባተኛው ቀን ግን ሙሉ እረፍት የሚደረግበት ሰንበት ነው፣ የተቀደሰ ጉባኤ ዕለት ነው በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለያህዌ ሰንበት ስለሆነ ምንም ስራ አትስሩበት፡፡
\s5
\v 4 እነዚህ ለያህዌ የተመረጡ በዓላት ብላችሁ በተወሰነላቸው ጊዜ የምታውጇቸው የተቀደሱ ስብሰባዎች ናቸው፡፡
\v 5 በመጀመሪያው ወር በወሩ በአስራ አራተኛው ቀን ጸሀይ ስትጠልቅ የያህዌ ፋሲካ ነው፡፡
\v 6 በዚያው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን የያህዌ የቂጣ በዓል ነው፡፡ ለሰባት ቀናት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ትበላላችሁ፡፡
\s5
\v 7 በመጀመሪያው ቀን ለያህዌ የተለየ ጉባኤ ይኖራችኋል፣ የተለመደ ተግባራችሁን አትሰሩበትም፡፡
\v 8 ለሰባት ቀናት በእሳት የሚቀርብ መስዋዕት ለያህዌ ታቀርባላችሁ ሰባተኛው ቀን የተለመደ ተግባራችሁን የማታከናውኑበት ለያህዌ የተለየ ጉባኤ የሚደረግበት ነው›”
\s5
\v 9 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 10 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ ብለህ ንገራቸው ‹ወደምሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፣ እና የመጀመሪያውን አዝመራ ስትሰበስቡ፣ ከበኩራቱ ፍሬዎች ለካህኑ አንድ ነዶ ታመጣላችሁ፡፡
\v 11 ነዶው ተቀባይነትን እንዲያገኝ ካህኑ በያህዌ ፊት ይወዘውዘውና ለእርሱ ያቀርበዋል፡፡ ካህኑ ነዶውን የሚወዘውዘውና ለእኔ የሚያቀርበው በሰንበት ቀን ማግስት ነው፡፡
\s5
\v 12 ነዶውን በምትወዘውዙበትና ለእኔ በምታቀርቡበት ቀን ለያህዌ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
\v 13 የእህል ቁርባን ለያህዌ መልካም መዓዛ የሚሆን በዘይት የተለወሰ የኢፍ ሁለት አስረኛ መልካም ዱቄት፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት፣ እና ከነዚህም ጋር የኢን አንድ አራተኛ ወይን የመጠጥ ቁርባን መቅረብ አለበት፡፡
\v 14 ለአምላካችሁ ይህን መስዋዕት እስከምታቀርቡበት ቀን ድረስ ምንም ዓይነት ዳቦ፣ አሊያም የተጠበሰ እሸት ወይም ለምለሙን እሸት አትብሉ፡፡ ይህ ለትወልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 15 ከዚያ ሰንበት ቀን ማግስት አንስቶ ነዶውን ለመወዝወዝና ለያህዌ ለማቅረብ ካመጣችሁት ቀን ጀምራችሁ ሰባት ሙሉ ሳምንታት፣ ሰባት ሰንበት ትቆጥራላችሁ፣
\v 16 እስከ ሰባተኛው ሰንበት ማግስት ድረስ ትቆጥራላሁ፡፡ ያም ማለት ሀምሳ ቀናት ትቆጥራላችሁ፡፡ ከዚያ ለያህዌ የአዲስ አዝመራ መስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
\s5
\v 17 ከየቤቶቻችሁ ከኢፍ ሁለት አስረኛ የተጋገሩ ሁለት ዳቦዎች ታመጣላችሁ፡፡ ከመልካም ዱቄት የሚዘጋጅና በእርሾ የተጋገሩ ይሁኑ፤ ከበኩራት ፍሬዎች የሚቀርቡ የሚወዘወዙና ለያህዌ የሚቀርቡ መስዋዕቶች ይሆናሉ፡፡
\v 18 ከዳቦው ጋር ነውር የሌለባቸው የአንድ ዓመት እድሜ ያላቸው ሰባት ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈን በሬ፣ እና ሁለት አውራ በጎች ታቀርባላችሁ፡፡ እነርሱም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ይሆናሉ፣ ከእህል ቁርባን ከመጠጥ ቁርባን ጋር፣ በእሳት የተዘጋጀ መስዋዕት እና ለያህዌ መልካም መዓዛ ያለው መስዋዕት ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 19 ለኃጢአት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል ታቀርባላሁ፣ እንዲሁም ለህብረት መስዋዕት የአንድ አመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወንድ ጠቦቶች ለመስዋዕት ታቀርባላችሁ፡፡
\v 20 ካህኑ ከበኩራት ፍሬዎች ዳቦ ጋር በያህዌ ፊት ይወዘወዛቸው፣ እነርሱንም መስዋዕት አድርጎ ለእርሱ ከሁለት ጠቦቶች ጋር ያቅርብ፡፡ ለያህዌ ቅዱስ መስዋዕቶች ሲሆኑ የካህኑ ድርሻ ናቸው፡፡
\v 21 በዚያው ቀን ማወጅ አለባችሁ፡፡ የተቀደሰ ጉባኤ ይኖራል፣ እናም የተለመደ ስራችሁን አትሰሩም፡፤ ይህ የህዝባችሁ በትውልዶች ሁሉ በምትኖሩበት ሥፍራ ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 የምድራችሁን ፍሬ ስትሰበስቡ፣ የእርሻችሁን ጥግጋት ሁሉ ሙሉ ለሙሉ አትሰብስቡ፣ የሰብላችን ቃርሚያ ሁሉ አትሰብስቡ፡፡ እነዚህን ለድሆችና ለመጻተኛው ተዉላቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
\s5
\v 23 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 24 ”ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር፣ የወሩ የመጀመሪያው ቀን ለእናንተ ታላቅ እረፍት ይሆናል፣ በመለኮት ድምጽ መታሰቢያ የሚደረግበት፣ እና የተቀደሰ ጉባኤ ይሆናል፡፡
\v 25 የተለመደ ሥራ አትሰሩበትም፣ ለያህዌ የእሳት መስዋዕት አቅርቡበት፡፡›”
\s5
\v 26 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 27 “አሁን የዚህ የሰባተኛው ወር አስረኛ ቀን የስርየት ቀን ይሆናል፡፡ ለያህዌ የተለየ ጉባኤ መሆን አለበት፣ ራሳችሁን ማዋረድና ለያህዌ በእሳት መስዋዕት መሰዋት አለባችሁ፡፡
\s5
\v 28 በዚያን ቀን ምንም ሥራ አትስሩ ምክንያቱም በአምላካችሁ በያዌ ፊት ለራሳች ማስታሰርያ የምታቀርቡበት የስርየት ቀን ነው፡፡
\v 29 በዚያን ቀን ራሱን የማያዋርድ ማንም ቢሆን ከህዝቡ ተለይቶ ይጥፋ፡፡
\s5
\v 30 በዚያን ቀን ማናቸውንም ሥራ የሚሰራውን ማንንም ቢሆን፣ እኔ ያህዌ ከህዝቡ መሀል አጠፋዋለሁ፡፡
\v 31 በዚያ ቀን ማናቸውንም ዐይነት ሥራ አትሰሩም፡፡ ይህ በህዝባችሁና ትውልዶቻችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡
\v 32 ይህ ቀን ለእናንተ የከበረ የሰንበት ዕረፍት ይሁንላችሁ፣ እናንተም በወሩ በዘጠነኛው ቀን ራሳችን አዋርዱ፡፡ ከምሽት እስከ ምሽት ሰንበትን ጠብቁ፡፡”
\s5
\v 33 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 34 “ለእስራኤል ሰዎች እንዲህ በላቸው፣ ‹በሰባተኛው ወር አስራ አምስተኛው ቀን ለያህዌ የዳስ በዓል ይሆናል፡፡ ይህም ሰባት ቀናት ይወስዳል፡፡
\s5
\v 35 በመጀመሪያው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይኖራል፡፡ የተለመደውን ሥራ አትስሩበት፡፡
\v 36 ለሰባት ቀናት ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡበት፡፡ በስምንተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ይሁን፣ እናንተም ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት አቅርቡ፡፡ ይህ ክቡር ጉባኤ ነው፣ እናም አንዳች የተለመደ ሥራ አትስሩበት፡፡
\s5
\v 37 እነዚህ ለያህዌ የተለዩ በአላት ናቸው፣ ለያህዌ የሚቃጠል መስዋዕት ለማቅረብ ቅዱስ ጉባኤ የምታውጁበት፣ የሚቃጠል መስዋዕትና የእህል ቁርባን፣ የመስዋዕቶችና የመጠጥ ቁርባች እያንዳንዱን በየራሱ ቀን ለይታችሁ ለእግዚአብሔር የምታውጁባቸው በዓላት ናቸው፡፡
\v 38 እነዚህ በአላት ከያህዌ ሰንበታትና ከእናንተ ስጦታዎች ተጨማሪ ናቸው፣ ስጦቻችሁ ሁሉ፣ እና ለያህዌ የምትሰጧቸው የበጎ ፈቃድ መስዋዕቶቻችሁ ሁሉ ናቸው፡፡
\s5
\v 39 የዳስ በዓልን በሚመለከት፣ በሰባተኛው ወር በአስራ አምስተኛው ቀን፣ እናንተ የምድሪቱን ፍሬዎች ስትሰበስቡ ይህን የያህዌ በዓል ለሰባት ቀናት ማክበር አለባችሁ፡፡ የመጀመሪያው ቀን የፍፁም ዕረፍት ቀን ይሆናል፣ ስምንተኛው ቀንም እንደዚሁ የፍጹም ዕረፍት ቀን ይሆናል፡፡
\s5
\v 40 በመጀመሪያው ቀን ከዛፎቹ መልካሞቹን ፍሬዎች ውሰዱ፣ የዘንባባ ዛፎች ዝንጣፊዎች፣ እና የለምለሙ ዛፎች ቅርንጫፎች፣ ከወንዝ ዳርቻ ለምለም ዛፎች ቅርንጫፎች ወስዳችሁ በአምላካችሁ በያህዌ ፊት ለሰባት ቀናት ሃሴት ታደርጋላችሁ፡፡
\v 41 በየአመቱ ለሰባት ቀናት፣ ይህን በዓል ለያህዌ ታከብራላችሁ፡፡ ይህ በትውልዳችሁ ሁሉ በምትኖሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ቋሚ መታሰቢያ ይሆናል፡፡ ይህን በዓል በሰባተኛው ወር አክብሩ፡፡
\s5
\v 42 ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ትኖራላችሁ፡፡ እስራኤላዊ የሆነ ሁሉ ለሰባት ቀናት በትንንሽ ዳሶች ውስጥ ይቀመጥ፣
\v 43 ከእናንተ በኋላ የሚመጣው ትውልድ፣ የልጅ ልጆቻችሁ፣ እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ሳወጣ በእንደዚህ ዐይነት ዳሶች ውስጥ እንዴት እንዲኖሩ እንዳደረግኩ ያውቃሉ፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡›”
\v 44 በዚህ መንገድ፣ ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ ለያህዌ የተለዩትን በዓላት አስታወቁ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣
\v 2 “የእስራኤል ሰዎች መቅረዞች ሁልጊዜም እንዲነዱና ብርሃን እንዲሰጡ ከወይራ ፍሬ የተጠመቀ ንጹኅ ዘይት ለመቅረዞችህ ወደ አንተ እንዲያመጡ እዘዛቸው፡፡
\s5
\v 3 አሮን ያለማቋረጥ ከምሽት እስከ ማለዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ውጭ በቃልኪዳኔ ድንጋጌ ፊት መቅረዙን በያህዌ ፊት ያለማቋረጥ ያብራ፡፡ ይህ በትወልዳች ሁሉ ቋሚ ስርዓት ይሆናል፡፡
\v 4 ሊቀ ካህኑ በንጹኅ ወርቅ በተሰራው የመቅረዝ መያዣ ላይ መቅረዞቹ ሁልጊዜም በያህዌ ፊት እንዲበሩ ያደርጋል፡፡
\s5
\v 5 መልካም ዱቄት ወስደህ አስራ ሁለት ዳቦዎች ጋግር፡፡ ለእያንዳንዱ ዳቦ የኢፍ ሁለት እስረኛ መጠን ተጠቀም፡፡
\v 6 ከዚያ በሁለት ረድፍ ደርድራቸው፣ በአንዱ መስመር ስድስቱን በንጹኅ ወርቅ በተሰራ ጠረጴዛ ላይ በያህዌ ፊት ደርድር፡፡
\s5
\v 7 በእያንዳንዱ የዳቦዎቹ ረድፍ እንደ ዳቦዎቹ ምልክት ንጹኅ ዕጣን አድርግበት፡፡ ይህ ዕጣን ለያህዌ በእሳት የሚቀርብ መስዋእት ይሆናል፡፡
\v 8 በእያንዳንዱ የሰንበት ዕለት ሊቀ ካህኑ የእስራኤልን ህዝብ ወክሎ የዘላለም ቃልኪዳን ምልክት አድርጎ ህብስቱን በመደበኛነት ለያህዌ ያቀርባል፡፡
\v 9 ይህ መስዋዕት የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሆናል፡፡ ሙሉ ለሙሉ ለእርሱ የተለየና ለያህዌ በእሳት ከሚቀርበው መስዋዕት የተወሰደ ስለሆነ ቅዱስ በሆነው ስፍራ ይብሉት፡፡”
\s5
\v 10 እናቱ እስራኤላዊ የሆነች እና አባቱ ግብፃዊ የሆነ ልጅ በእስራኤል ህዝብ መሀል ወጣ፡፡ ይህ እስራኤላዊት ሴት ልጅ በሰፈር ውስጥ ከእስራኤላዊ ሰው ጋር ተጣላ፡፡
\v 11 የእስራኤላዊቷ ሴት ልጅ የያህዌን ስም ሰደበ እግዚአበሔርንም ረገመ፣ ስለዚህም ህዝቡ ወደ ሙሴ አመጡት፡፡ የእናቱ ስም ሰሎሚት ነበር፣ የደብራይ ልጅ ስትሆን ከዳን ወገን ነበረች፡፡
\v 12 ያህዌ ራሱ ፈቃዱን እስኪገልጽላቸው ድረስ በጥበቃ ስር አቆዩት፡፡
\s5
\v 13 ከዚያ ያህዌ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 14 “እግዚአብሔርን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር አውጡት የሰሙት ሁሉ እጆቻቸውን በላዩ ይጫኑ፣ ከዚያም መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገረው፡፡
\s5
\v 15 ለእስራኤል ሰዎች ብለህ ግለጽላቸው፣ ‹አምላኩን የተሳደበ ማንኛውም ሰው በደሉን ይሸከም፡፡
\v 16 ተወላጅ የሆነ እስራኤላዊም ቢሆን ወይም መጻተኛ የያህዌን ስም በስድብ ያቃለለ መላው ጉባኤ በድንጋይ ይውገሩትና ይገደል፡፡ ማንም ሰው የያህዌን ስም ቢሳደብ፣ ይገደል፡፡
\s5
\v 17 ሌላ ሰው የገደለ ይገደል፡፡
\v 18 የሌላውን ሰው እንስሳ የገደለ በገደለው ፈንታ ይክፈል፣ ህይወት ስለ ህይወት ነው፡፡
\s5
\v 19 አንድ ሰው ጎረቤቱን ቢጎዳ፣ እርሱ በጎረቤቱ ላይ ያደረገው ነገር ይደረግበት፡፡
\v 20 ስብራት ስለ ስብራት፣ አይን ስለ አይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ፡፡ በአንድ ሰው ላይ ጉዳት እንዳደረሰ፣ በእርሱም ላይ እንደዚያው ይደረግበት፡፡
\v 21 ማንም እንስሳ የገደለ ሰው መልሶ ይክፈል ማንም ሰው የገደለ ይገደል፡፡
\s5
\v 22 ለመጻተኛውም ይሁን ለተወላጅ እስራኤላዊው አንድ አይነት ህግ ይኑራችሁ፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝና፡፡”
\v 23 ሙሴ ለእስራኤል ሰዎች ይህን ነገራቸው፣ ሰዎቹም ያህዌን የተሳደበውን ሰው ከሰፈር ውጭ አመጡት፡፡ በድንጋይ ወገሩት፡፡ የእስራኤል ሰዎች የያህዌን ትዕዛዝ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ፈጸሙ፡፡
\s5
\c 25
\p
\v 1 ያህዌ በሲና ተራራ ላይ ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፣
\v 2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹እኔ ወደሰጠኋችሁ ምድር ስትገቡ፣ ምድሪቱ ለያህዌ የሰንበት ዕረፍት ታክብር፡፡
\s5
\v 3 እርሻህን ለስድስት አመታት ታርሳለህ፣ ለስድስት አመታት የወይን ተክልህን እየገረዝህ ምርቱን ትሰበስባህ፡፡
\v 4 በሰባተኛው አመት ግን፣ ለምድሪቱ የከበረ የሰንበት ረፍት ይሁንላት፣ ለያህዌ ሰንበት ነው፡፡ እርሻህን አታርስም፡፡ ወይም የወይን ተክልህን አትገርዝም፡፡
\s5
\v 5 ሳትዘራው የበቀለውን አትጨደው፣ ያልገረዝከውን የወይን ተክል ፍሬ አትለቅመውም፡፡ ይህ ለምድሪቱ የከበረ የእረፍት አመት ነው፡፡
\v 6 ያልሰራህበት ምድር በሰባተኛው ዓመት ያፈራችው ሁሉ ለአንተ ምግብ ይሆናል፡፡ አንተ፣ ወንድና ሴት ባሮችህ፣ ለቅጥረኛ አገልጋዮችህ እና ከአንተ ጋር ለሚኖሩ መጻተኞች ምግብ ይሁን፡፡
\v 7 ምድሪቱ ያፈራችውን ሁሉ የቤት እንስሳትህና የዱር እንስሳት ይመገቡት፡፡
\s5
\v 8 ሰባት የሰንበት አመታትን ቁጠር፣ ይህም ማለት፣ ሰባት ጊዜ ሰባት አመታት ነው፣ ስለዚሀ ሰባት የሰንበት አመታት ይሆናሉ፣ ድምሩ አርባ ዘጠኝ አመታት ነው፡፡
\v 9 በሰባተኛው ወር በአስረኛው ቀን ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ በሁሉም ስፍራ ንፉ፡፡ በማስተሰርያ ቀን በምድራችሁ ላይ ሁሉ መለከት ንፉ፡፡
\s5
\v 10 አምሳኛውን አመት ለያህዌ ለዩና በምድሪቱ ላይ ለሚኖሩ ነዋሪዎች ሁሉ ነጻነትን አውጁ፡፡ ይህ ለእናንተ ንብረትና ባሮች ወደየቤተሰቦቻቸው የሚመለሱበት ኢዩቤልዩ ይሆንላችኋል፡፡
\s5
\v 11 አምሳኛው አመት ለእናንተ ኢዮቤልዮ ይሆናል፡፡ አትተክሉም ወይም አዝመራ አትሰበስቡም፡፡ ሳትዘሩ የበቀለውን ብሉ፣ ሳትገርዙት ወይናችሁ ያፈራውን ፍሬ ሰብስቡ፡፡
\v 12 ኢዮቤልዩ ነውና፣ ለእናንተ ቅዱስ ይሆናል፡፡ በሜዳ ሳትዘሩት የበቀለውን ምርት ብሉ፡፡
\s5
\v 13 በዚህ የኢዮቤልዩ አመት የእያንዳንዱን ሰው ንብረት መልሱለት፡፡
\v 14 ለጎረቤትህ ማናቸውንም መሬት ሸጠህለት ቢሆን ወይም ከጎረቤትህ ማንኛውንም መሬት ገዝተህ ቢሆን አንዱ ሌላውን አያታል ወይም እርስ በእርሱ ያልተገባ ነገር አታድርጉ።
\s5
\v 15 ከጎረቤትህ መሬት ብትገዛ፣ እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ድረስ ያሉትን አመታት እና ሊሰበሰብ የሚችለውን ሰብል ከግምት አስገባ፡፡ መሬቱን የሚሸጠው ጎረቤትህም እነዚህን ነገሮች ከግምት ያስገባል፡፡
\v 16 እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ብዙ አመታት የሚቀር ከሆነ ይህ የመሬቱን ዋጋ ከፍ ያደርገዋል፣ እስከ መጪው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ጥቂት አመታት የሚቀር ከሆነ ይህ የመሬቱን ዋጋ ዝቅ ያደርገዋል፣ ምክንያቱም ለአዲሱ የመሬቱ ባለቤት መሬቱ የሚሰጠው አዝመራ መጠን ለሚቀጥለው ኢዮቤልዩ ለመድረስ ከቀረው አመታት ቁጥር ጋር የተያያዘ ነው፡፡
\v 17 አንዳችሁ ሌላችሁን አታታሉ ወይም አንዳች ሌላችሁን አታሳስቱ፤ ይልቁንም አምላካችን አክብሩ፣ እኔ አምላካች ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 18 ስለዚህ ትዕዛዛቴን ጠብቁ፣ ህግጋቴን ፈጽሙ እናም አድርጓቸው፡፡ ይህን ካደረጋችሁ በምድሪቱ ላይ በሰላም ትቀመጣላችሁ፡፡
\v 19 ምድሪቱ ምርቷን ትሰጣለች፣ እናንተም ትጠግባላችሁ በዚያም በሰላም ትኖራላችሁ፡፡
\s5
\v 20 እንዲህ ልትሉ ትችላላችሁ “በሰባተኛው አመት ምን እንበላለን አንዘራም፣ ምርታችንንም አንሰበስብምና፡፡”
\v 21 በስድስተኛው አመት በረከቴ እንዲሆንላችሁ በእናንተ ላይ አዛለሁ፣ ምድሪቱ ለሶስት አመታት የሚሆን ምርት ትሰጣለች፡፡
\v 22 በስምንተኛው አመት ትተክላላችሁ፣ በቀደሙት አመታት ካመረታችሁትና ከሰበሰባችሁት ምግብ መብላት ትቀጥላላችሁ፡፡
\s5
\v 23 መሬት ለአዲስ ጊዜያዊ ባለቤቶች አይሸጥ፣ ምክንያቱም መሬቷ የእኔ ናት፡፡ እናንተ ሁላችሁም በምድሬ ላይ እንግዶችና ጊዜያዊ ነዋሪዎች ናችሁ፡፡
\v 24 የያዛችሁትን ምድር ሁሉ የመቤዠት መብት እንዳላችሁ ማስተዋል አለባችሁ፤ በገዛችሁት ቤተሰብ መሬቱ ተመልሶ እንዲገዛ መፍቀድ አለባችሁ፡፡
\v 25 እስራኤላዊ ወገናችሁ ደሃ ቢሆንና በዚህም ምክንያት ከንብረቱ ቢሸጥ፣ የቅርብ ዘመዱ ለአንተ የሸጠልህን ንብረት መልሶ ይግዛ፡፡
\s5
\v 26 ሰውዬው ንብረቱን የሚቤዥለት ምንም ዘመድ ባይኖረው፣ ነገር ግን ሀብት ቢያፈራና ንብረቱን መልሶ መቤዠት ቢችል፣
\v 27 መሬቱ ከተሸጠበት ጊዜ አንስቶ ያሉትን አመታት ያሰላና ለሸጠለት ሰው ቀሪ ሂሳቡን ይክፈል፡፡ ከዚያ ወደ ራሱ ንብረት ይመለስ፡፡
\v 28 ነገር ግን መሬቱን ለራሱ ማስመለስ ባይችል፣ የሸጠው መሬት እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ በገዛው ሰው ባለቤትነት ስር ይቆያል፡፡ በኢዮቤልዩ አመት፣ መሬቱ ለሸጠው ሰው ይመለስለታል፣ ከመሰረቱ ባለቤት የነበረው ወደ ንብረቱ ይመለሳል፡፡
\s5
\v 29 አንድ ሰው በተቀጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ቤቱን ቢሸጥ፣ በተሸጠበት በአመት ጊዜ ውስጥ መልሶ ሊገዛው ይችላል፡፡
\v 30 ለአንድ ሙሉ አመት ውስጥ ካልተቤዠ፣ በተቀጠረ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቤት፣ የገዛው ሰው ትውልድ የልጅ ልጅ ቋሚ ንብረት ይሆናል፡፡ ያ ቤት በኢዮቤልዩ ተመላሽ አይሆንም፡፡
\s5
\v 31 ነገር ግን በዙሪያቸው ቅጥር የሌላቸው መንደሮች ቤቶች ከአገሩ የእርሻ መሬት ጋር የሚታዩ ንብረቶች ይሆናሉ፡፡ ተመልሰው ሊዋጁ ይችላሉ፣ በኢዮቤልዩ ተመላሽ ይሆናሉ፡፡
\v 32 ሆኖም፣ የሌዋውያን ንብረት የሆኑ ቤቶች በማንኛውም ጊዜ ሊዋጁ ይችላሉ፡፡
\s5
\v 33 ከሌዋዊያን አንዱ የሸጠውን ቤት መልሶ ባይቤዥ፣ በከተማ ውስጥ የሚኘው የተሸጠው ቤት በኢዮቤልዩ ተመላሽ ይሆናል፣ በከተማ የሚገኝ የሌዋዊ ቤቶች በእስራኤል ሰዎች መሀል የእነርሱ ንብረት ነው፡፡
\v 34 በከተማዎቻቸው ዙሪያ የሚገኙ እርሻዎች ግን አይሸጡም ምክንያቱም እነዚህ የሌዋዊያን ቋሚ ንብረት ናቸው፡፡
\s5
\v 35 የአገራቸው ሰው ወገናችሁ ደሃ ቢሆን፣ ስለዚህም ራሱን መቻል ቢያቅተው፣ መጻተኛውን እንደምትረዱ እርዱት ወይም በመሀከላችሁ የሚኖርን ባዕድ እንደምትረዱ ዕርዱት፡፡
\v 36 ወለድ አታስከፍሉት ወይም በማናቸውም መንገድ ከእርሱ ትርፍ ለማግኘት አትሞክሩ፣ ነገር ግን እግዚአብሔርን አክብሩ በመሆኑም ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር አብሮ መኖር ይችላል፡፡
\v 37 በወለድ ገንዘብ አታበድሩት፣ ወለድም አታስከፍሉት፣ ትርፍ ለማግኘት ምግባችሁን አትሽጡለት፡፡
\v 38 የከነዓንን ምድር እሰጣችሁና አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡
\s5
\v 39 የአገርህ ሰው ወገንህ ደሃ ቢሆንና ራሱን ለአንተ ቢሸጥ፣ እንደ ባሪያ አታሰራው፡፡
\v 40 እንደ ተቀጣሪ አገልጋይ አስተናግደው፡፡ ከአንተ ጋር በጊዜያዊነት እንደሚኖር ሰው ይሁን፡፡ እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ በአንተ ዘንድ ያገለግል፡፡
\v 41 ከዚያ ከአንተ ዘንድ ይሄዳል፣ እርሱና ከእርሱ ጋር ያሉ ልጆቹ፣ ወደ ራሱ ቤተሰቦችና ወደ አባቱ ይዞታ ይመለሳሉ፡፡
\s5
\v 42 እነርሱ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ናቸውና፡፤ እንደ ባሪያዎች አይሸጡም፡፡
\v 43 በጭካኔ ልትገዛቸው አይገባም፣ ነገር ግን አምላክህን አክብር፡፡
\v 44 በዙሪያህ ከሚኖሩ ህዝቦች ወንድና ሴት ባሪያዎችን ከእነርሱ መሀል መግዛት ትችላለህ፡፡
\s5
\v 45 በመሀልህ ከሚኖሩ መጻተኞችም ባሪያዎችን መግዛት ትችላለህ፣ ይህም ማለት፣ ከአንተ ጋር ካሉ ቤተሰቦቻቸው፣ በምድርህ ከተወለዱ ልጆች ባሪያዎችን መግዛት ትችላለህ፡፡ እነርሱ የአንተ ሀብት ይሆናሉ፡፡
\v 46 እንዲህ ያሉትን ባሪያዎች ንብረት አድርገው እንዳይዟቸው ከአንተ በኋላ ለልጆችህ ውርስ አድርገህ መስጠት ትችላለህ፡፡ ከእነርሱ ሁልጊዜም ባሪያዎችህን መግዛት ትችላለህ ነገር ግን ከእስራኤላዊያን መሀል በወንድሞችህ ላይ በጭካኔ መግዛት የለብህም፡፡
\s5
\v 47 መጻተኛው ወይም ከአንተ ጋር በጊዜያዊነት ከሚኖረው እንግዳ መሃል አንዱ ባለጸጋ ቢሆንና ከእስራኤላዊ ወገንህ መሃል አንዱ ደሃ ቢሆን፣ ለራሱም ለዚያ ባዕድ ቢሸጥ፣ ወይም ከባዕዳን ቤተሰብ መሃል ለአንዱ ቢሸት፣
\v 48 እስራኤላዊ ወገንህ ከተገዛ በኋላ ተመልሶ ይገዛ፡፡ ከቤተሰቡ መሃል አንዱ ይቤዠው፡፡
\s5
\v 49 የሚቤዠው አጎቱ፣ የአጎቱ ልጅ፣ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ከቤተሰቡ ውስጥ ማንኛውም የቅርብ ዘመዱ ሊቤዠው ይችላል፡፡ ወይም፣ እርሱ ራሱ ባለፀጋ ቢሆን፣ ራሱን መቤዠት ይችላል፡፡
\v 50 ከገዛው ሰው ጋር ይደራደር፣ ለገዛው ሰው ራሱን ከሸጠበት አመት ጀምረው እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ይቁጠሩ፡፡ የመቤዣው ዋጋ ለገዛው ሰው መስራቱን መቀጠል በሚኖርበት አመታት ቁጥር ለተቀጣሪ አገልጋይ በሚከፍለው ክፍያ ይሰላል፡፡
\s5
\v 51 እስከ ኢዮቤልዩ ለመድረስ ብዙ አመታት የሚኖር ከሆነ፣ ለቤዣው መልሶ የሚከፍለው የገንዘብ መጠን ከእነዚያ ቀሪ አመታት ጋር የተመጣጠነ ይሁን፡፡
\v 52 ለኢዮቤልዩ አመት የቀሩት አመታት ጥቂት ከሆኑ፣ ከገዛው ሰው ጋር ለኢዮቤልዩ በቀሩት አመታት ልክ ይደራደር፣ ለመቤዣው በቀሩት አመታት ውስጥ ይክፈለው፡፡
\s5
\v 53 በየዓመቱ እንደ ቅጥር ሰው ይኑር፡፡ በግፍ አለመስተናገዱን ማረጋገጥ ይገባሃል፡፡
\v 54 በእነዚህ መንገዶች ካልተዋጀ፣ እስከ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ እርሱና ከእርሱ ጋር ልጆቹም አብረው ያገልግሉ፡፡
\v 55 እስራኤላውያን የእኔ አገልጋዮቼ ናቸው፡፡ ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ናቸው፡፡ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፡፡”
\s5
\c 26
\p
\v 1 “እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፤ ጣኦታትን አታብጁ፣ የተቀረጸ ምስልንም አታቁሙ፣ ወይም ለአምልኮ የድንጋይ አምዶችን አታቁሙ፣ እንደዚሁም ልትሰግዱላቸው ማናቸውንም የቀረፀ የድንጋይ ምስል በምድራችሁ አታድርጉ፡፡
\v 2 ሰንበቴን ጠብቁ የተቀደሰውን ስፍራዬን አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡
\s5
\v 3 በህጌ ብትኖሩና ትዕዛዛቴን ብትጠብቁ ብትታዘዟቸውም፣
\v 4 ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድር ምርቷን ትሰጣችኋለች፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬያቸውን ይሰጧችኋል፡፡
\s5
\v 5 የወቃችሁት እስከ ወይን አዝመራችሁ ድረስ ይቆያል፣ የወይን ፍሬ አዝመራችሁም እስከምትዘሩበት ወቅት ድረስ ይቆያል፡፡ እንጀራችሁን በምድሪቱ ቤታችን በሰራችሁበት ጠግባችሁ ትበላላችሁ በእረፍት ትኖራላችሁ፡፡
\v 6 በምድሪቱ ሰላምን እሰጣለሁ፣ ምንም ነገር ሳያስፈራችሁ ተዘልላችሁ ትቀመጣላችሁ፡፡ ከምድሪቱ አደገኛ እንስሳትን አስወጣለሁ፣ በምድራች ሰይፍ አያልፍም፡፡
\s5
\v 7 ጠላቶቻችሁን ታሳድዳላችሁ፣ እነርሱም በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡
\v 8 ከእናንተ አምስታችሁ መቶውን ታሳድዳላችሁ፣ ከእናንተ መቶው አስር ሺኅ ያሳድዳል፤ ጠላቶቻች በፊታችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡
\s5
\v 9 ወደ እናንተ በሞገስ እመለከታለሁ፣ ፍሬያማም አደርጋችኋለሁ፣ አበዛችሁማለሁ፤ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳኔን አደርጋለሁ፡፡
\v 10 ለረጅም ጊዜ የተከማቸ እህል ትበላላችሁ፡፡ ለአዲሱ ምርታችሁ ስፍራ ስለሚያስፈልጋችሁ የተከማቸውን እህል ታወጣላችሁ፡፡
\s5
\v 11 ማደሪያዬን በመካከላችሁ አደርጋለሁ፣ እኔም እናንተን አልጣላችሁም፡፡
\v 12 በመካከላችሁ እሆናለሁ አምላካችሁም እሆናለሁ፣ እናንተም የእኔ ህዝብ ትሆናላችሁ፡፡
\v 13 ከግብጽ ምድር ያወጣኋቸው፣ እኔ ያህዌ አምላካችሁ ነኝ፣ ስለዚህም የእነርሱ ባሮች አትሆኑም፡፡ የቀንበራችሁን ብረት ሰብሬያሁ፣ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌያለሁ፡፡
\s5
\v 14 ነገር ግን እኔን ባትሰሙኝ፣ እነዚህን ትዕዛዛቴን ሁሉ ባትጠብቁ፣
\v 15 ትዕዛዛቴን ብትተዉና ህግጋቴን ብትጠሉ፣ እናም ትዕዛዞቼን ሁሉ ሳትፈጽሙ ብትቀሩ፣ ነገር ግን ቃልኪዳኔን ብታፈርሱ
\s5
\v 16 እነዚህን ነገሮች ብታደርጉ፣ እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፡ ፍርሃትን እሰድባችኋለሁ፣ ዐይኖችንና ሕይወታችሁን የሚያጠፋ በሽታና ትሳት አደርስባችኋለሁ፡፡ በከንቱ ትዘራላችሁ፣ ምክንያቱም ፍሬያቸውን ጠላቶቻችሁ ይበሉታል፡፡
\v 17 ፊቴን በጠላትነት ወደ እናንተ እመልሳለሁ፣ ከጠላቶቻችሁ ሀይል በታች ትወድቃላችሁ፡፡ የሚጠሏችሁ ሰዎች ይገዙዋችኋል፣ ማንም ሳያሳድዳችሁ እንኳን ትሸሻላችሁ፡፡
\s5
\v 18 ትዕዛዛቴን ባትሰሙ፣ ከዚህ በኋላ ስለ ሀጢአታችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
\v 19 የትእቢታችሁን ኃይል እሰብራለሁ፡፡ ሰማይን በላያችሁ እንደ ብረት ምድራችሁንም እንደ ናስ አደርጋለሁ፡፡
\v 20 ብርታታችሁ ለአንዳች ነገር አይጠቅምም፣ ምክንያቱም ምድራችሁ አዝመራዋን አትሰጥም፣ በምድራችሁ ዛፎቻችሁ ፍሬያቸውን አይሰጡም፡፡
\s5
\v 21 በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ ብትመላለሱና ከኃጢአታችሁ በላይ እኔን ባትሰሙኝ፣ በእናንተ ላይ ሰባት ዕጥፍ ድንጋጤ አመጣለሁ፡፡
\v 22 ልጆቻችን የሚነጥቁ፣ ከብቶቻችሁን የሚያጠፉ፣ እናንተን በቁጥር ጥቂት የሚያደርጉ አደገኛ አውሬዎችን እሰድባችኋሉሁ፡፡ ስለዚህም ጎዳናዎቻችሁ በረሃ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 23 በእነዚህ ሁሉ ነገሮች ትምህርቶቼን ባትሰሙ ነገር ግን በእኔ ላይ ጠላት ሆናችሁ መመላለሳችሁን ብትቀጥሉ፣
\v 24 እኔም በእናንተ ላይ ጠላት እሆናለሁ፡፡ እኔ ራሴ በሀጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
\s5
\v 25 ቃልኪዳን በማፍረሳችሁ በእናንተ ላይ የበቀል ሰይፍ አመጣለሁ፡፡ በከተሞቻችሁ ውስጥ በአንድነት ትሰበሰባላችሁ፣ በዚያም በማህላችሁ በሽታን እልካለሁ፣ እናንተም በጠላቶቻችሁ ሀይል ትሸነፋላችሁ፡፡
\v 26 የምግብ አቅርቦታችሁን ስቆርጥ፣ አስር ሴቶች በአንድ ምድጃ እንጀራችሁን ይጋግራሉ፣ እንጀራችሁንም በሚዛን ያካፍሏችኋል፡፡ ትበላላችሁ ነገር ግን አትጠግቡም፡፡
\s5
\v 27 እነዚህ ነገሮች ሁሉ ሆነው ባትሰሙት፣ ነገር ግን በእኔ ላይ በጠላትነት መመላሳችሁን ብትቀጥሉ፣
\v 28 እኔ በቁጣ እመጣባችኋለሁ፣ በኃጢአቶቻችሁ ሰባት እጥፍ እቀጣችኋለሁ፡፡
\s5
\v 29 ወንድ ልጆቻችሁን ስጋና የሴት ልጆቻችሁን ስጋ ትበላላችሁ፡፡
\v 30 የአምልኮ ሥፍራችሁን አጠፋለሁ፣ የእጣን መሰዊያዎቻችሁን እቆርጣለሁ፣ በድኖቻችሁን በድን በሆኑ በጣኦቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፣ ደግሞም እኔ ራሴ እጸየፋችኋለሁ፡፡
\s5
\v 31 ከተሞቻችሁን ፍርስራሽ አደርጋለሁ የተቀደሱ ቦታዎቻችሁን አጠፋለሁ፡፡ በመስዋዕቶቻችሁ መዓዛ ደስ አልሰንም፡፡
\v 32 ምድሪቱን አጠፋለሁ፡፡ በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁ በጥፋቱ ይደነግጣሉ፡፡
\v 33 በአገራት መሃል እበትናችኋለሁ፣ ሰይፌን መዝዤ አሳድዳችኋለሁ፡፡ ምድራችሁ ባድማ ትሆናለች፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 34 ከዚያም ምድሪቱ ባድማ ሆኖ እስከቆየች ድረስና እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር እስከቆያችሁ ድረስ የሰንበት ዕረፍቷን ታገኛለች፡፡ በነዚያ ጊዜያት፣ ምድሪቱ ታርፋለች ሰንበቶቿንም ታገኛለች፡፡
\v 35 ፍርስራሽ ሆና እስከቆየች ድረስስ እረፍት ይሆንላታል፣ እናንተ በውስጧ ስትኖሩ በሰንበቶቻችሁ ያላገኘችውን ዕረፍት ታገኛች፡፡
\v 36 እናንተ በጠላቶቻችሁ ምድር በቀራችሁት ላይ በልቦቻችሁ ውስጥ ፍርሃት እሰዳለሁ፣ ስለዚህም የቅጠል ኮሰሽታ እንኳን ያስደነግጣችኋል፣ ከሰይፍ እንደሚሸሽ ትሆናላች፡፡ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትወድቃላች፡፡
\s5
\v 37 ማንም ባያሳድዳችሁም እንኳን ከሰይፍ እንደሚሸሽ ሰው አንዳችሁ በሌላችሁ ላይ ትደነቃቀፋላችሁ፡፡ በጠላቶቻችሁ ፊት ለመቆም ምንም ሀይል አይኖራችሁም፡፡
\v 38 ከአገራት መሀል ተለይታችሁ ትጠፋላችሁ፣ የጠላቶቻችሁ ምድር ራሱ በፍርሃት ይሞላችኋል፡፡
\v 39 ከእናንተ መሃል የቀሩት በዚያ በጠላቶቻችሁ ምድር በሀጢአቶቻቸው ይጠፋሉ፣ እንዲሁም በአባቶቻቸው ሀጢአቶች ምክንያት ይጠፋሉ፡፡
\s5
\v 40 ሆኖም የእነርሱንና የአባቶቻቸውን ሀጢአቶች ቢናዘዙ፣ ለእኔ ታማኝ ካልሆኑበት ክህደታቸው ቢመለሱ፣ ከእኔ ጋር ተላት ከሆኑበት አካሄዳቸው ቢመለሱ
\v 41 እኔ በእነርሱ ላይ እንድነሳ ካደረገንና ለጠላቶቸው ምድር አሳልፌ እንድሰጣቸው ካደረገ አካሄዳቸው ቢመለሱ ያልተገረዙ ልቦቻቸው ዝቅ ቢሉ፣ እናም በሀጢአቶቻቸው የደረሰባቸውን ቅጣታቸውን ቢቀበሉ፣
\v 42 ከያዕቆብ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባለሁ፤ እንዲሁም፣ ምድሪቱን አስባለሁ፡፡
\s5
\v 43 ምድሪቱ ለቀዋት ስለሄዱ ባዶ ትቀራለች፣ ስለዚህ ካለእነርሱ በተተወችበት ጊዜ በሰንበቶቿ ታርፋለች፡፡ እነርሱ በሀጢአታቸው ቅጣታቸውን ይቀበላሉ ምክንያቱም እነርሱ ራሳቸው ስርአቴን ትተዋል ህግጋቴንም ጠልተዋል፡፡
\s5
\v 44 ሆኖም ከዚህ ሁሉ ባሻገር፣ በጠላቶቸው ምድር ውስጥ ሲሆኑ፣ እኔ አልተዋቸውም ሙሉ በሙሉ እስካጠፋቸውም ድረስ አልጠላቸውም፣ ደግሞም ከእነርሱ ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አልረሳም፣ እኔ አምላካቸው ነኝ፡፡
\v 45 ነገር ግን ስለ እነርሱ ስል አምላካቸው እሆን ዘንድ አሕዛብ እያዩ ከግብጽ ምድር ካወጣኋቸው ከአባቶቻቸው ጋር የገባሁትን ኪዳኔን አስባሁ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡”
\s5
\v 46 በሙሴ በኩል ያህዌ በሲና ተራራ ላይ በራሱና በእስራኤል ህዝብ መሃል ያደረጋቸው ትዕዛዛት፣ ደንቦችና ህጎች እነዚህ ናቸው፡፡
\s5
\c 27
\p
\v 1 ያህዌ ሙሴን ተናገረው እንዲህም አለ፣
\v 2 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፣ ‹አንድ ሰው ለያህዌ ሰውን ለመስጠት የተለየ ስዕለት ቢሳል ተመጣጣን ዋጋ ለመክፈል ተከታዮን ዋጋዎች ተጠቀም፡፡
\s5
\v 3 ከዚያ እስከ ስልሳ አመት ዕድሜ ላለው ወንድ መደበኛው ዋጋ በቤ መቅደሱ ሰቅል መለኪያ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ይሁን፡፡
\v 4 ለተመሳሳይ ዕድሜ ክልል ለሴቷ መደበኛው ዋጋ ሰላሳ ሰቅሎች ይሁን፡፡
\s5
\v 5 ከአምስት አመት እስከ ሀያ አመት ዕድሜ ለወንድ መደበኛው ዋጋ ሀያ ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴቷ አስር ሰቅሎች ነው፡፡
\v 6 ከአንድ ወር ዕድሜ እስከ አምስት አመት ለወንድ መደበኛው ዋጋ አምስት የብር ሰቅሎች ይሁን፣ ለሴት ሶስት የብር ሰቅሎች ነው፡፡
\s5
\v 7 ከስልሳ አመት በላይ ለወንድ መደበኛው ዋጋ አስራ አምስት ሰቅሎች፣ ለሴት አስር ሰቅሎች ይሁን፡፡
\v 8 ነገር ግን ስዕለቱን የገባው ሰው መደበኛውን ዋጋ መክፈል ባይችል፣ በስለት የተሰጠው ሰው ወደ ካህኑ ይቅረብ፣ ካህኑም ያንን ሰው የተሳለው ሰው ሊከፍል በሚችል ዋጋ ይተምነዋል።
\s5
\v 9 አንድ ሰው ለያህዌ እንስሳ መሰዋት ቢፈልግ፣ ያህዌ ያንን ቢቀበል፣ ከዚያ ያ እንስሳ ለእርሱ ይለያል፡፡
\v 10 ሰውዬው እንዲህ ያለውን እንስሳ መለወጥ ወይም መቀየር የለበትም፣ መልካሙን በመጥፎው ወይም መጥፎውን በመልካሙ አይቀይርም፡፡ አንዱን እንስሳ በሌላው ቢለውጥ፣ ያ እንስሳና የተለወጠው ሁለቱም ንጹህ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 11 ሆኖም፣ ሰውዬው ለያህዌ ሊሰጥ የተሳለው ንጹህ ካልሆነ ስለዚህ ምክንያት ያህዌ ያንን አይቀበልም፣ ከዚያ ሰውዬው እንስሳውን ወደ ካህኑ ማምጣት አለበት፡፡
\v 12 ካህኑ በገበያው የእንስሳ ዋጋ ይተምነዋል፡፡ ማናቸውም ካህኑ ለእንስሳው የሰጠው ዋጋ፣ ያ የእንስሳው ዋጋ ይሆናል፡፡
\v 13 እናም ባለቤቱ እንስሳውን ሊዋጅ ቢፈልግ፣ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛውን ጨምሮ ይዋጀው፡፡
\s5
\v 14 አንድ ሰው ቤቱን ለያህዌ መቀደስ ሲፈልግ፣ ካህኑ የቤቱን ዋጋ ይተምናል፡፡ ማናቸውም ካህኑ የተመነው ዋጋ ያ የዚያ ቤት ዋጋ ነው፡፡
\v 15 ነገር ግን ባለቤቱ ቤቱን ቢለይና በኋላ ሊዋጀው ቢፈልግግ በሚዋጅበት ዋጋ ላይ አንድ አመስተና ይጨመር፣ እናም ከዚያ እንደገና የእርሱ ይሆናል፡፡
\s5
\v 16 አንድ ሰው ከመሬቱ ለያህዌ ለመለየት ቢፈልግ፣ የመሬቱ ዋጋ ግምት ለመዝራት በሚያስፈልገው ፍሬ መጠን ይተመናል፡፡ አንድ ሆሜር መስፈሪያ ገብስ ሃምሳ የብር ሰቅሎች ያወጣል፡፡
\s5
\v 17 እርሻውን በኢዮቤልዩ አመት ቢለይ፣ የተገመተው ዋጋ ይፀናል፡፡
\v 18 እርሻውን ከኢዮቤልዩ በኋላ ቢለይ ግን፣ ካህኑ የእርሻ መሬቱን ዋጋ እስከ ቀጣዩ የኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባሉ አመታት ቁጥር ያሰላና የተገመተው ዋጋ ይቀነሳል፡፡
\s5
\v 19 እርሻውን የለየው ሰው ሊዋጀው ቢፈልግ፣ በተገመተው ዋጋ ላይ አንድ አምስተኛ ይጨምራ፣ እናም መሬቱ ተመልሶ የእርሱ ይሆናል፡፡
\v 20 እርሻውን ካልዋጀ ወይም ለሌላ ሰው ሸጦት ከሆነ፣ ከዚያ በኋላ ተመልሶ ሊዋጅ አይችልም፡፡
\v 21 ይልቁንም፣ እርሾው፣ በኢዮቤልዩ ተመልሶ ሲለቀቅ ሙሉ ለሙሉ ለያህዌ እንደተሰተ እርሻ ሁሉ ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ ይሆናል፡፡ የካህናቱ ንብረት ይሆናል፡፡
\s5
\v 22 አንድ ሰው የገዛውን መሬት ለያዌ ቢለይ፣ ነገር ግን መሬቱ ከሰውዬው ቤተሰቦች መሬት ውስጥ ባይሆን፣
\v 23 ካህኑ የእርሻውን ዋጋ እስ ኢዮቤልዩ አመት ድረስ ባለው ጊዜ መተን ይተምናል፣ ሰውዬውም ዋጋውን በዚያ ቀን ለያህዌ ቅዱስ ስጦታ አድርጎ ይከፍላል፡፡
\s5
\v 24 በኢዮቤልዮ አመት፣ እርሻው ከገዛው ሰው ተወስዶ ወደ መሬቱ የቀድሞ ባለቤት ይመለሳል፡፡
\v 25 የሚተመኑ ዋጋዎች ሁሉ በመቅደሱ ሰቅል ዋጋ ሊተመኑ ይገባል፡፤ ሃያ ጌራ ከአንድ ሰቅል ጋር እኩል ነው፡፡
\s5
\v 26 ከእንስሳት በመጀመሪያ የሚወለደው ግን አስቀድሞም ቢሆነ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው፣ ማንም ሰው ሊቀድሰው አይችልም በሬም ይሁን በግ የያህዌ ነው
\v 27 ንጹህ ያልሆነ እንስሳ ከሆነ፣ ባለቤቱ በተመገተው ዋጋ መልሶ ይግዛውው ደግሞም ከዋጋው በላይ አንድ አምስተኛ ይጨምርበት፡፡ እንስሳው ካልተዋጀ፣ በተተመነው ዋጋ ይሸጥ፡፡
\s5
\v 28 ሆኖም፣ አንድ ሰው ለያህዌ ከለየው ሰውም ሆነ ወይም እንስሳ፣ ወይም የቤተሰቡ ርዕስት ምንም ነገር አይሽጥ ወይም አይዋጅ ማናቸውም የተለየ ነገር ለያህዌ ቅዱስ ነው፡፡
\v 29 እንዲጠፋ ለተለየ ሰው ምንም መዋጃ አይከፈልለትም፡፡ ያ ሰው መገደል አለበት፡፡
\s5
\v 30 አስራት ሁሉ፣ በምድሪቱ ላይ የበቀለ ሰብልም ሆነ ወይም የዛፍ ፍሬ የያህዌ ነው፡፡ ለያህዌ የተቀደሰ ነው፡፡
\v 31 አንድ ሰው ከአስራቱ አንዳች ቢዋጅ፣ በዋጋው ላይ አንድ አምስተኛ ይቸምር፡፡
\s5
\v 32 ከመንጋ ወይም ከከብት አስራት ሁሉ፣ ከእረኛው በትር ስር የሚያልፍ ሁሉ፣ ከአስር አንዱ ለያህዌ ይለይ፡፡
\v 33 እረኛው የተሸለውን ወይም የከፋውን እንስሳ አይፈልግም፣ ደግሞም አንዱን በሌላው አይተካ፡፡ ቢለውጠው እኗን፣ የተለወጠውና የሚለወጠው ሁለቱም የተቀደሱ ይሆናሉ፡፡ ሊዋጅ አይችልም፡፡”
\s5
\v 34 ያህዌ በሲና ተራራ ለሙሴ የሰጣቸው ለእስራኤላውያን የተሰጡ ትእዛዛት እነዚህ ናቸው፡፡

1994
05-DEU.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1994 @@
\id DEU
\ide UTF-8
\h ኦሪት ዘዳግም
\toc1 ኦሪት ዘዳግም
\toc2 ኦሪት ዘዳግም
\toc3 deu
\mt ኦሪት ዘዳግም
\s5
\c 1
\p
\v 1 ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ በምድር በዳ በዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሜዳ በዓረባ፥ በፋራን፥ በጦፌል፥ በላባን፥ በሐጼሮት፥ በዲዛሃብ መካከል ሳሉ፥ ለአስራኤል ሁሉ የተናገራቸው እነዚህ ቃላት ናቸው።
\v 2 በሴይር ተራራ መንገድ ከኮሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የአሥራ አንድ ቀን ጉዞ ነው።
\s5
\v 3 በአርባኛው ዓመት በአሥራ አንደኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሙሴ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያዘዘውውን ሁሉ ለእስራኤል ሕዝብ ነገራቸው።
\v 4 ይህም እግዚአብሔር በሐሴቦን ይኖር የነበረውን የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ በአስታዎትና በኤድራይ ይኖር የነበረውንም የባሳንን ንጉሥ ዐግን ከመታ በኋላ ነበር።
\s5
\v 5 በዮርዳኖስ ማዶ በሞዓብ ምድር ሙሴ እንዲህ ብሎ እነዚህን መመሪያዎች ይናገር ጀመር፦
\v 6 እግዚአብሔር አምላካችን በኮሬብ እንዲህ ብሎ ተናገረን፦ በዚህ ተራራ የኖራችሁበት ይብቃችሁ።
\s5
\v 7 ጉዞኣችሁን ወደ ኮረብታማው ወደ አሞራውያን አገር ወደ ድንበሮቹም፥ ሁሉ በዓረባም በደጋውና በቆላው፥ በደቡብና በባሕር ዳር ወዳሉ ወደ ከነዓናውያን ምድር፥ ወደ ሊባኖስ ወንዝ ሸለቆ እስከ ታላቁ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ሄዱ።
\v 8 እነሆ ምድሪቱን በፊታችሁ አድርጌአለሁ፤ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣቸው ዘንድ የማለላቸውን ምድር ሂዱና ውረሱ።
\s5
\v 9 በዚያን ጊዜ እንዲህ ብዬ ተናግሬአችሁ ነበር፦ እኔ በራሴ ብቻዬን ልሸከማችሁ አልችልም።
\v 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ አብዝቶአችኋል፥ እነሆም እናንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዙ ናችሁ።
\v 11 የአባቶቻችሁ እግዚአብሔር አምላክ ሺህ ጊዜ ሺህ ያድርጋችሁ፤ ተስፋ እንደሰጣችሁም ይባርካችሁ።
\s5
\v 12 ነገር ግን እኔ በራሴ ድካማችሁን፥ ሸክማችሁንና ክርክራችሁን እሸከም ዘንድ ብቻዬን እንዴት እችላለሁ?
\v 13 ከእናንተ መካከል ከየነገዶቻችሁ ጥበበኞች፥ አስተዋዮችና አዋቂዎች የሆኑትን ሰዎች ምረጡ፤ እኔም እነርሱን የእናንተ አለቆች አደርጋቸዋለሁ ብዬኣችሁ ነበረ።
\v 14 እናንተም እንዲህ ብላችሁ መለሳችሁ፦ የተናገርከንን ነገር ለማድረግ ለእኛ መልካም ነው።
\s5
\v 15 ስለዚህም ጥበበኞችና አዋቂዎች የሆኑትን የነገዶቻችሁን ወሰድሁ፥ በእናንተም ላይ አለቆች እንዲሆኑ የሺህ አለቆች፥ የመቶ አለቆች፥ የአምሳ አለቆች፥ የአሥር አለቆችና ሹማምንት በየገዶቻችሁ አደረግኋቸው።
\v 16 በዚያን ጊዜም ፈራጆቻችሁን እንዲህ ብዬ አዘዝኳቸው፦ በወንድሞቻችሁ መካከል፤ በሰውና በወንድሙ መካከልና በመጻተኛ ላይ በጽድቅ ፍረዱ።
\s5
\v 17 በክርክርም ጊዜ ለማንም ፊት አድልዎ አታድርጉ፥ ታላቁን እንደምትሰሙ፥ ታናሹንም ስሙ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለሆነ የሰው ፊት መፍራት አይገባችሁም። ከክርክርም አንድ ስንኳ ቢከብዳችሁ ወደ እኔ አምጡት እኔም እሰማዋለሁ።
\v 18 በዚያን ጊዜም ልታደርጉት የሚገባችሁን ነገር ሁሉ አዘዝኋችሁ።
\s5
\v 19 ከኮሬብም ተነስተን፥እግዚአብሔር አምላካችን እንዳዘዘን እንዳያችሁትም በታላቁና እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ምድረ በዳ ሁሉ ተጉዘን በተራራማው በአሞራውን አገር ሄድን፥ ወደ ቃዴስ በርኔም መጣን።
\s5
\v 20 እኔም እንዲህ አልኋችሁ፦ እግዚአብሔር አምላካችን ወደ ሚሰጠን ወደ ተራራማው አሞራውያን አገር መጣችኋል።
\v 21 እነሆ እግዚአብሔር አምላካችሁ ምድሪቱን በፊታችሁ አድርጎአል፤ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንዳላችሁ ውጡ፥ ውረሱአት፥ አትፍሩ አትደንግጡም።
\s5
\v 22 ከእናንተም ሁላችሁ ወደ እኔ መጥታችሁ እንዲህ አላችሁ፦ ምድሪቱን እንዲሰልሉልንና እናጠቃቸው ዘንድ የሚገባንን የመንገዱንና የምንገባባቸውን ከተሞች ሁኔታ ተመልሰው እንዲነግሩን ከፊታችን ሰዎችን እንድስደድ።
\v 23 ነገሩም ደስ አሰኘኝ፤ ከእናንተም ከየነገዱ ሁሉ አንድ አንድ ሰው፥ አሥራ ሁለት ሰዎችን መረጥሁ።
\v 24 እነርሱም ወደ ተራራማው አገር ሄዱ፥ ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጥተው ሰለሉአት።
\s5
\v 25 እነርሱም ከምድሪቱ ፍሬ በእጃቸው ወሰዱ፥ ወደ እኛም ይዘውት መጡ። እነርሱም ደግሞ፦ እግዚአብሔር አምላካችን የሚሰጠን ምድር መልካም ናት ብለውም አወሩልን።
\s5
\v 26 ምድሪቷንም ማጥቃት እንቢ ብላችሁ፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፥ ።
\v 27 በድንኳናችሁም ውስጥ እንዲህ እያላችሁ አጉረመረማችሁ፦ እግዚአብሔር ስለ ጠላን እንዲያጠፋን በአሞራውያን እጅ አሳልፎ ይሰጠን ዘንድ ከግብፅ ምድር አወጣን።
\v 28 አሁን ወዴት መሄድ እንችላለን? ሕዝቡ ብዙ ነው፥ ቁመቱም ከእኛ ይረዝማል ከተሞቹም ታላላቆች፥ የተመሽጉና እስከ ሰማይም የደረሱ ናችው፥ የዔናቅንም ልጆች ደግሞ በዚያ አየናቸው፤ ብለው ወንድሞቻችን ልባችንን እንዲቀልጥ አደረጉ።
\s5
\v 29 እኔም አልኋችሁ፦ አትደንግጡ፥ እነርሱንም አትፍሩአቸው።
\v 30 በፊታችሁ የሚሄደው እግዚአብሔር አምላካችሁ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ በፊታችሁም በግብፅና በምድረ በዳ እንዳደረገላችሁ ሁሉ፤
\v 31 ወደዚህም ስፍራ እስክትመጡ ድረስ በሄድዳችሁበት መንገድ ሁሉ ሰው ልጁን እንደሚሸከም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ተሸከማችሁ እናንተ አይታችኋል።
\s5
\v 32 ዳሩ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁን በዚህ ነገር አላመናችሁትም፤
\v 33 በፊታችሁም ሆኖ በምትሄዱበት መንገድ ድንኳናችሁን እንድታቆሙ ቦታ እንድታገኙና በሌሊት በእሳት፥ በቀንም በደመና እንድትሄዱ መንገዱን ያሳታችሁ እርሱ ነው።
\s5
\v 34 እግዚአብሔርም የቃላችሁን ድምፅ ሰምቶ ተቆጣ፥ ምሎም፥ እንዲህ አለ፦
\v 35 በርግጥ ለአባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ የማልሁላቸውን መልካሚቱን ምድር ከዮፎኒ ልጅ ከካሌብ በቀር ከእነዚህ ሰዎች ከዚህ ክፉ ትውልድ ማንም አያይም።
\v 36 እርሱም እግዚአብህሔርን ፈጽሞ ተከትሎአልና የረገጣትን ምድር ለእርሱና ለልጆቹ እሰጣለሁ ብሎ ማለ።
\s5
\v 37 እግዚአብሔርም ደግሞ በእናንተ ምክንያት እኔን ተቆጣኝ እንዲህም አለ፦ አንተ ደግሞ ወደዚያ አትገባም
\v 38 በፊትህ የሚሄድ አገልጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደዚያ ይገባል፥ እርሱም እስራኤላውያን ምድሪቱን እንዲወርሱ ይመራቸዋልና፤ አደፋፍረው።
\s5
\v 39 ከዚህም በተጨማሪ፦ ለጉዳት ይዳረጋሉ፥ ዛሬም መልካሙንና ክፉውን መለየት የማይችሉ ናቸው ያላችኋችሁ ታናናሽ ሕፃናታችሁ ልጆቻችሁ እነርሱ ወደዚያ ይገባሉ። ምድሪቱንም ለእነርሱ እሰጣለሁ ይወርሱታልም።
\v 40 እናንተ ግን ተመልሳችሁ በኤርትራ ባሕር መንገድ ወደ ምድረ በዳ ሂዱ።
\s5
\v 41 እናንተም፦ እግዚአብሔርን በድለናል፥ እግዚአብሔር አምላክችሁ እንዳዘዘን ሁሉ እንወጣለን፥ እንዋጋማለን ብላችሁ መለሳችሁልኝ። ከእናንተም ሰው ሁሉ የጦር መሣሪያውን ያዘ፥ ወደ ተራራማውም አገር ለመውጣትና ለማጥቃት ተዘጋጀ።
\v 42 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ እኔ በእናንተ መካከል ስለማልገኝ፥ በጠላቶቻችሁ ፊት እንዳትሸነፉ አትውጡ፥ አትዋጉም በላቸው አለኝ።
\s5
\v 43 እኔም ተናገርኋችሁ እናንተም አልሰማችሁም። በእግዚአብሔር ትእዛዝ ላይ ዐመፃችሁ፥ አልሰማችሁም በትዕቢታችሁም ወደ ተራራማው አገር ለማጥቃት ወጣችሁ።
\v 44 ነገር ግን በተራራማው አገር ይኖሩ የነበሩ አሞራውያን በእናንተ ላይ ወጥተው እንደ ንብ አሳደዱአችሁ፥ እስከ ሔርማም ድረስ በሴይር መቱአችሁ።
\s5
\v 45 ተመልሳችሁም በእግዚአብሔር ፊት አለቀሳችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ድምፃችሁን አልሰማም፥ ወደ እናንተም አላዳመጠም።
\v 46 ሁሉም ቀናት በቆያችሁባችሁ ለብዙ ቀን በቃዴስ ተቀመጣችሁ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ከዚያም እግዚአብሔርም እንደተናገረኝ ተመልሰን በኤርትራ ባሕር መንገድ ጉዞአችንን በምድረ በዳ ውስጥ ተመለስን፤
\v 2 በሴይርም ተራራ ዙሪያ ለብዙ ቀናት ተጓዝን።
\v 3 እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረኝ፦ ይህን ተራራ የዞራችሁበት ይበቃችኋል፤ ተመልሳችሁ ወደ ሰሜን ሄዱ።
\s5
\v 4 ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዛቸው፦ በሴይር በሚኖሩ በወንድሞቻችሁ በዔሳው ልጆች ድንበር ታልፋላችሁ፤ እነርሱም ይፈሩአችኋል።
\v 5 ስለዚህ የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ያህል እንኳ አልሰጣችሁም፥ ከእነርሱም ጋር እንዳትዋጉ እጅግ ተጠንቀቁ።።
\s5
\v 6 የምትበሉትንም ምግብ ከእነርሱም በገንዘብ ትገዛላችሁ፤ የምትጠጡትንም ውኃ ደግሞ በገንዘብ ትገዛላችሁ።
\v 7 አምላካችሁ እግዚአብሔር ፤ በዚህ በታላቅ ምድረ በዳ መጓዛችሁን ስላወቀ የእጃችሁን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና። በእነዚህ አርባ ዓመት ውስጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነበረ፥ አንዳችም አልጎደለባችሁም።
\s5
\v 8 በሴይርም ከሚኖሩት ከወንድሞቻችሁ ከዔሳው ልጆች በዓረባ መንገድ ከኤላትና ከዔጽዮን ጋብር አለፍን። ተመልሰንም በሞዓብ ምድረ በዳ መንገድ አለፍን።
\s5
\v 9 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ሞዓብን አታስጨንቁአቸው፤ አትውጋቸውም። ምክንያቱም የእነርሱን ምድር ርስት እንዲሆንላችሁ አልሰጣችሁም፤ ዔርን ለሎጥ ልጆች ርስት አድርጌ ሰጠኋችሁ።
\s5
\v 10 አስቀድሞ ታላቅና ብዙ ሕዝብ ሆነው እንደ ዔናቅምልጆች በቁመት የረዘሙ ኤሚማውያን በዚያ ይኖሩ ነበር፤
\v 11 እነርሱም ደግሞ እንደ ዔናቅ ልጆች ራፋይም ይባሉ ነበር፤ ሞዓባውያን ግን ኤሚም ይሉአቸዋል።
\s5
\v 12 ሖራውያንም ደግሞ አስቀድሞ በሴይር ላይ ይኖሩ ነበር፥ የዔሳው ልጆች ግን አሳደዱአቸው። እግዚአብሔርም በሰጠው በርስቱ ምድር እስራኤል እንዳደረገ፥ ከፊታቸው አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም መኖር ጀመሩ።
\s5
\v 13 እግዚአብሔርም፦ ተነሡ የዘሬድንም ወንዝ ተሻገሩ አለ። የዘሬድንም ወንዝ ተሻገርን።
\v 14 ከቃዴስ በርኔ ከመጠንበት ዘሬድን ወንዝን እስከ ተሻገርንበት ቀኖች ድረስ ሠላሳ ስምንት ዓመታት ነበሩ። እግዚአብሔር እንደ ማለላቸው ለመዋጋት ብቁ የሆኑ ሰዎች ትውልድ ሁሉ ከሕዝብ መካከል የጌድይት በዚያን ጊዜ ነበር።
\v 15 ከዚህ በተጨማሪ፥ ከመሄዳቸው በፊት ከሕዝቡ መካከል ለማጥፋት የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ከብዶ ነበረ።
\s5
\v 16 ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ሁሉ ከሕዝቡ መካከል በሞቱና በጠፉ ጊዜ
\v 17 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦
\v 18 አንተ ዛሬ የሞዓብን ዳርቻ ዔርን ታልፋለህ።
\v 19 ለሎጥም ልጆች ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ በአሞን ልጆች አቅረቢያ ስትደርስ አታስጨንቁአቸው አትውጋቸውም፤ ምክንያቱም ከአሞን ልጆች ምድር ርስት አልሰጥህምና ።
\s5
\v 20 ያም ደግሞ የራፋይም ምድር ተብሎ ተቆጠረ። ራፋይምም አስቀድሞ በዚያ ይኖሩ ነበር፤
\v 21 አሞናውያን ግን ዛምዙማውያን ብለው የሚጠሩአቸው እንደ ዔናቅም ልጆች ቁመታቸው ረጅም ነበር።
\v 22 እግዚአብሔር ከአሞራውያን ፊት አጠፋቸው፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው ይኖሩ ነበር። ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍተው በሴይር ለሚኖሩት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፤እነርሱም አሳድደው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።
\s5
\v 23 እስከ ጋዛ ድረስ ባሉ መንደሮች ይኖሩ የነበሩትን ኤዋውያንን ከከፍቶር የወጡ ከፍቶራውያን አጠፉአቸው፥ በስፍራቸውም ኖሩ።
\s5
\v 24 ደግሞም አለ፦ ተነሥታችሁ ሂዱ፥ የአርኖንንም ሸለቆ ተሻገሩ፤ እነሆ አሞራዊውን የሐሴቦንን ንጉሥ ሴዎንንና ምድሪቱን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻለሁ። እርስዋን ለመውረስ ጀምር፥ ከእርሱም ጋር ተዋጋ።
\v 25 ከሰማይ በታች ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ማስደንገጥህንና ማስፈራትህን እሰድድ ዘንድ ዛሬ እጀምራለሁ፤ ወሬህን በሰሙ ጊዜ በፊትህ ይንቀጠቀጣሉ፥ ድንጋጤም ይይዛቸዋል።
\s5
\v 26 ከቅዴሞትም ምድረ በዳ የሰላምን ቃል ይነግሩት ዘንድ ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁ፦
\v 27 ወደ ቀኝና ግራ ሳልል በአገርህ ላይ በአውራ ጎዳና ልለፍ።
\s5
\v 28 የምበላውን ምግብ በገንዘብ ሽጥልኝ፥ የምጠጣውንም ውኃ በገንዘብ እንድገዛ ስጠኝ፤
\v 29 በሴይር የሚኖሩ የዔሳው ልጆች፥ በዔርም የሚኖሩ ሞዓባውያን እንዳደረጉልኝ አምላካችን እግዚአብሔር ወደሚሰጠን ምድር ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ ብቻ በእግሬ ልለፍ።
\s5
\v 30 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ዛሬው ሁሉ በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ ልቡን ስላደነደነና ስላጸና የሐሴቦን ንጉሥ ሴዎን ግን ያሳልፈን ዘንድ አልፈቀደም ።
\v 31 እግዚአብሔርም፦ እነሆ ሴዎንንና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ መስጠት ጀመርሁ ምድሩን ትገዛት ዘንድ መውረስ ጀምር አለኝ።
\s5
\v 32 ሴዎንም ሕዝቡም ሁሉ ሊጋጠሙን ወደ ያሀጽ ወጡ።
\v 33 እግዚአብሔር አምላካችንም አሳልፎ ስለሰጠን አሸነፈነው፥እርሱንና ልጆቹን፥ ሕዝቡንም ሁሉ እስኪሞቱ ድረስ አሸነፍን፤መታንም።
\s5
\v 34 በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ወሰድን የተቀመጡባቸውንም ሰዎች ሁሉ ሴቶችንና ሕፃናትን አንዳችም ሳናስቀር አጠፋን።
\v 35 ከብቶቻቸውንና በከተሞቻቸው ያሉትን ብቻ ብዝበዛ ለራሳችን ወሰድን።
\s5
\v 36 በአርኖን ቆላ ጫፍ ካለው ከአሮዔር ከሸለቆውም ውስጥ ካለው ከተማ ጀምረን እስከ ገለዓድ ድረስ ማናቸውም ከተማ ከእኛ በላይ አልሆነም። እግዚአብሔር አምላካችን በፊታችን ባሉት ጠላቶቻችን ላይ ድልን ሰጠን።
\v 37 ዳሩ ግን አምላካችን እግዚአብሔር ወደ ከለከለን ወደ አሞን ልጆች ምድር በያቦቅም ወንዝ አጠገብ ወዳለው ስፍራ ሁሉ በተራራማው አገር ወዳሉት ከተሞች አልደረስንም።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ተመልሰን በባሳን መንገድ ሄድን፥ የባሳን ንጉሥ ዐግና ሕዝቡ ሁሉ በኤድራይ ሊዋጉን መጡ።
\v 2 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ እርሱንና ሕዝቡን ሁሉ ምድሩንም በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼአለሁና አትፍራው። በሐሴቦን ይኖር በነበረው በአሞራውያን ንጉሥ በሴሶን ላይ እንዳደረግህ በእርሱም ታደርግበታለህ አለኝ።
\s5
\v 3 እግዚአብሔር አምላካችንም በባሳን ንጉሥ በዐግ ሕዝቡንም ሁሉ በእጃችን ድልን ሰጠን። እኛም አንድ እንዳይቀር እስኪሞቱ ድረስ መታነው።
\v 4 በዚያን ጊዜም አንድም ያልወሰድነው ሳይቀር ሁሉንም ስድሳ ከተሞችን፦ በባሳን ያለውን የዐግን መንግሥት፥ የአርጎብን አገር ሁሉ ከተሞችን ወሰድን።
\s5
\v 5 እነዚህም ከተሞች ሁሉ ዙሪያቸው በረጅም ቅጥር፥ በበሮቻቸውና በመወርወሪያዎች የተመሸጉ ነበር፤ በአጠገባቸውም ብዙ ያልተመሸጉት ከተሞች ነበሩ።
\v 6 በሐሴቦንም ንጉሥ በሴዎን እንዳደረግን ከወንዶችና ሴቶች ከሕፃናትም ጋር ፈጽሞ አጠፋናቸው።
\v 7 ነገር ግን ከአጠፋናቸው ከተሞች ሁሉ ከብቶቹን ሁሉ ምርኮም ለራሳችን ወሰድን።
\s5
\v 8 በዚያም ጊዜ ከአርኖን ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ ምድሪቱን ከዮርዳኖስ ማዶ ከነበሩ ከሁለቱ ከአሞራውያን ነገሥታት እጅ ወሰድን፤
\v 9 (ሲዶናውያን አርሞንዔምን ሢርዮን ብለው ይጠሩታል፥ አሞራውያንም ሳኔር ብለው ይጠሩታል) ፤
\v 10 በሜዳውም ያሉትን ከተሞች ሁሉ፥ ገለዓድንም ሁሉ፥ በባሳንም ያሉትን የዐግን መንግሥት ከተሞች እስከ ስልካና፤እስከ ኤድራይ ድረስ ባሳንን ሁሉ ወሰድን።
\s5
\v 11 ከራፋይም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ተርፎ ነበር፤ እነሆም አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች አገር በረባት አልኖረምን? ይህም በሰው ክንድ ልክ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ፥ ወርዱም አራት ክንድ ነበረ።
\s5
\v 12 በዚያን ጊዜ በአርሞን ሸለቆ ከአሮዔር ርስት አድርገን የወሰደነውን ይህን የገለዓድን ተራራማ ምድር እኩልታ ከተሞቹንም ለሮቤልና ለጋድ ነገድ ሰጠኋቸው።
\v 13 ከገለዓድም የቀረውን የዐግንም መንግሥት ባሳንን ሁሉ የአጎብንም ምድር ሁሉ ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ሰጠሁ። (ይህም ተመሳሳይ አገር የራፋይም ምድር ተብሎ ይቆጠራል።)
\s5
\v 14 የምናሴ ነገድ አንዱ ኢያዕር እስከ ሄሸራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ ድረስ የአርጎብን አካባቢ ሁሉ ወሰደ። ይህንም የባሳንን ምድር እስከ ዛሬ ድረስ የሚጠራውን በስሙ የኢያዕር መንደሮች ብሎ ጠራ።
\s5
\v 15 ለማኪርም ገለዓድን ሰጠሁት።
\v 16 ለሮቤል ነገድና ለጋድም ነገድ ከገለዓድ ጀምሮ እስከ አርግኖን ሸለቆ ድረስ የሸለቆውን እኩሌታ ዳርቻውንም እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ሰጠኋቸው።
\s5
\v 17 ከኪኔሬት እስከ ዓርባ ባሕር (እርሱም የጨው ባሕር) ድረስ ከፈስጋ ተራራ በታች ወደ ምሥራቅ ያለውን የዮርዳኖስን ሸለቆ ዳቻውንም ሰጠኋቸው።
\s5
\v 18 በዚያም ጊዜ እንዲህ ብዬ አዘዝኋችሁ፦ እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን ምድር ርስት አድርጎ ሰጥቶአችኋል፤ እናንተ የጦር ሰዎች መሣሪያችሁን ታጥቃችሁ በወንድሞቻችሁ ከእስራኤል ልጆች ፊት ታልፋላችሁ።
\s5
\v 19 ነገር ግን ሚስቶቻችሁ፥ ልጆቻችሁና ከብቶቻችሁ (ብዙ ከብቶች እንዳሉአችሁ አውቃለሁ) በሰጠኋችሁ ከተሞች ይቀመጣሉ፤
\v 20 ይኸውም እግዚአብሔር እናንተን እንዳሳረፈም ወንድሞቻችሁን እስኪያሳርፍ ድረስ እነርሱም ደግሞ በዮርዳኖስ ማዶ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣቸውን ምድር እስኪወርሱ ድረስ ነው፤ ከዚያም በኋላ እናንተ ሁላችሁ ወደ ሰጠኋችሁ ርስት ትመለሳላችሁ።
\s5
\v 21 በዚያም ጊዜ ኢያሱን እንዲህ ብዬ አዘዝሁት፦አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነዚህ በሁለቱ ነገሥታት ያደረገውን ሁሉ ዓይኖችህ አይተዋል፤ እንዲሁ በምታልፍባቸው መንግሥታትም ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ያደርጋል።
\v 22 አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ ስለ እናንት ስለሚዋጋ አትፈራቸውም ብዬ አዘዝሁት።
\s5
\v 23 በዚያም ጊዜ እኔ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ለመንሁ፦
\v 24 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህንና ብርቱ እጅህን ለእኔ ለባሪያህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይ ወይም በምድር እንደ አንተ፥ እንደ ኃይልህ፥ ያደርግ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው?
\v 25 እኔም ወደዚያ ልሂድና በዮርዳኖስም ማዶ ያለውን መልካሙን ምድርና መልካሙን ተራራማውን አገር ሊባኖስንም ለመየት እለምንሃለሁ።
\s5
\v 26 እግዚአብሔር ግን እናንተ ባለመስማታችሁ ምክንያት ተቆጣኝ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ስለዚህም ነገር ደግመህ እንዳትናገረኝ ይበቃሃል።
\v 27 ይህን ዮርዳኖስን ስለማትሻገር ወደ ፈስጋ ራስ ውጣና ዓይንህንም ወደ ምዕራብ፥ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብምና ወደ ምሥራቅ ዓይንህን አንሥተህ ተመልከት።
\s5
\v 28 በዚህ ፈንታ ኢያሱን አስተምራው፥ አደፋፍረው እንዲሁም አጽናው፤ ምክንያቱም እርሱ በዚህ ሕዝብ ፊት ይሄዳል፥ አንተም የምታየውን ምድር ያወርሳቸዋል።
\v 29 ስለዚህም በቤተ ፌጎርም በሸለቆው ውስጥ ቆየን።
\s5
\c 4
\p
\v 1 አሁንም እስራኤል ሆይ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወት እንድትኖሩና የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ሄዳችሁ እንድትወርሱ የማስተምራችሁን ሥርዓትንና ድንጋጌን ስሙ።
\v 2 እኔ የማዛችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዛትን ሁሉ ሳትጨምሩና ሳታጎሉ ትጠብቃላችሁ።
\s5
\v 3 ከብዔልፌጎርም የተነሣ፥ ብዔልፌጎርን የተከተሉትን ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከመካከላችሁ እንዳጠፋ ዓይኖቻችሁ አይተወል።
\v 4 እናንተ ግን እግዚአብሔር አምላካችሁን የተከተላችሁ እስከ ዛሬ ድረስ በሕይወት አላችሁ።
\s5
\v 5 እነሆ እናንተ ለመውረስ በምትሄዱባቸው ምድር ሰዎች መካከል ታደርጉ ዘንድ እግዚአብሔር አምላኬ እንዳዘዘኝ ሥርዓትንና ድጋጌን አስተማርኋችሁ።
\v 6 ስለዚህ ጠብቁአቸው፥ አድርጉአቸውም፤ ምክንያቱም ስለእነዚህ ሥርዓት ሰምተው፦ 'በእውነት ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው' በሚሉ ሰዎች ሁሉ ፊት ይህ ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ነው።
\s5
\v 7 በምንጠራው ጊዜ ሁሉ እንደምቀርበን እንደ እግዚአሔር አምላካችን፥ ወደ እነርሱ የቀረበ አምላክ ያለው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?
\v 8 ዛሬ በፊታችሁ እንደማኖራው ሥርዓት ሁሉ ጽድቅ የሆነው ሥርዓትና ድንጋጌ ያለው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ማን ነው?
\s5
\v 9 ዓይኖቻችሁ ያዩትን ነገር እንዳትረሱ በሕይወታችሁም ዘመን ሁሉ ከልባችሁ እንዳይጠፋ ብቻ አስታውሉ፤በጥንቃቄም ራሳችሁን ጠብቁ። እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ እንደተናገረኝ፥
\v 10 በእግዚአብሔር አምላካችሁ ፊት በኮሬብ በቆማችሁ ቀን እንደሰማችሁ፥ይህን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ዘንድ እንዲታውቅ አድርጉ።
\s5
\v 11 እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር። እስከ ሰማይም መካከል ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፤ ጨለማና ደመና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ።
\v 12 እግዚአብሔርም በእሳት ውስጥ ሆኖ ተናገራችሁ፤ ድምፅን በቃል ሰማችሁ መልክን ግን አላያችሁም፤ ድምፅን ብቻ ሰማችሁ።
\s5
\v 13 ታደርጉትም ዘንድ ያዘዛችሁን ቃል ኪዳን አሥሪቱን ቃላት አስታወቃችሁ። በሁለቱም በድንጋይ ጽላቶች ላይ ጻፋቸው።
\v 14 በዚያን ጊዜ ትወርሱአት ዘንድ በምትሄዱባት ምድር የምታዳርጉትን ሥርዓትና ድንጋጌ አስተምራችሁ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዝኝ።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር በኮሬብ በእሳት መካከል ሆኖ በተናገራችሁ ጊዜ መልክን ከቶ እንዳላያችሁ፤ለራሳችሁ እጅግ ተጠንቀቁ።
\v 16 የማናቸውንም ፍጥረት ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል በወንድ ወይም በሴት፥
\v 17 ወይም በማናቸውም በምድር ባለው በዱር እንስሳ መልክ፥ ወይም ከሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ምሳሌ፥
\v 18 ወይም በምድር ላይ የሚሳበውን ሁሉ ምሳሌ፥ ወይም ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ በማድረግ እንዳትረክሱ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 19 ዓይኖቻችሁን ወደ ሰማይ አንሥታችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሰማይ ሁሉ በታች ላሉት ሕዝብ ሁሉ የመደባቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊት ሁሉ ባያችሁ ጊዜ አምልኮና ስግደት በማቅረብ እንዳትስቱ ተጠንቀቁ።
\v 20 እናንተን ግን እግዚአብሔር እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ ትሆኑለት ዘንድ ወስዶ ከብረት እሳት ከግብፅ አወጣችሁ።
\s5
\v 21 ከዚህም በተጨማሪ እግአብሔር በእናንተ ምክንያት ተቆጣኝ፣ ዮርዳኖስንም እንዳልሻገር ፥እግዚአብሔር አምላካችሁም ርስት አድርጎ ወደሚሰጣችሁ ወደመልካሚቱ ምድር እንዳልገባ ማለ።
\v 22 እኔ ግን በዚህች ምድር እሞታለሁ፥ ዮርዳኖስንም አልሻገርም፥ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር አምላካችሁም ከእናንተ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን እንዳትረሱ እግዚአብሔር አምላካችሁም የከለከለውን በማናቸውም ቅርጽ የተቀረጸውን ምስል እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ።
\v 24 እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚበላ እሳት ቀናተኛም አምላክ ነውና።
\s5
\v 25 ልጆችን የልጅ ልጆችንም በወለዳችሁ ጊዜ፥ በምድሪቱም ብዙ ዘመን በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ በማናቸውም ምስል የተቀረጸውን ምስል አድርጋችሁ በረከሳችሁም ጊዜ፥ ታስቆጡትም ዘንድ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር በሠራችሁ ጊዜ ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ፤
\v 26 ከምትገቡባት ምድር እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆኑ እጠራለሁ፤ ዘመናችሁም አይረዝምም፥ ፈጽሞም ትጠፋላችሁም።
\s5
\v 27 እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ በአሕዛብም መካከል ጥቂት ትሆናላችሁ፥እግዚአብሔርም ያስወጣችሁኋል።
\v 28 በዚያም የማያዩትን፥ የማይሰሙትን፥ የማይበሉትን፥ የማያሸቱትንም በሰው እጅ ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን አማልክት ታመልካላችሁ።
\s5
\v 29 ነገር ግን ከዚያ እግዚአብሔር አምላካችሁን ትሻላችሁ፤ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም የፈለጋችሁት እንደ ሆነ ታገኛላችሁ።
\s5
\v 30 በተጨነቃችሁና ይህም ሁሉ በደርሰባችሁ ጊዜ በዘመኑ ፍጻሜ ወደ እግዚአብሔር አምላካችሁ ትመለሳላችሁ፥ ድምፁንም ትሰማላችሁ።
\v 31 እግዚአብሔር አምላካችሁ መሓሪ አምላክ ነውና፥ አይተዋችሁም፥ አያጠፋችሁምም፤ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን ቃል ኪዳኑን አይረሳም።
\s5
\v 32 እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ከፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ ከሰማይ እስከ ዳርቻዋ ድረስ ከቶ እንዲህ ያለ ታላቅ ነገር ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰምቶ እንደ ሆነ ከእናንተ በፊት የነበረውምን የቀደመውን ዘመን ጠይቁ።
\v 33 እናንተ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የእግዚአብሔርን ድምፅ እንደሰማችሁት ሌላ ሕዝብ ሰምቶአልን?
\s5
\v 34 ወይም እግዚአብሔር አምላካችሁ በዓይናችሁ ፊት በግብፅ ለእናንተ እንዳደረገው ሁሉ በፈተናና በተአምራት በድንቅና በጦርነት በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ በታላቅም ማስፈራት እግዚአብሔር ከሌላ ሕዝብ መካከል ለራሱ ሕዝብን ይወስድ ዘንድ በዐይናችሁ ፊት አድርጎ ያውቃልን?
\s5
\v 35 እግዚአብሔርም አምላክ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ እነዚህ ነገሮች ለእናንተ የተገለጡ ናቸው፤ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም።
\v 36 ያስተምራችሁ ዘንድ ከሰማይ ድምፁን አሰማችሁ፥ በምድርም ላይ ታላቁን እሳት አሳያችሁ፤ ድምፁንም ከእሳት መካከል ሰማችሁ።
\s5
\v 37 አባቶቻችሁን ስለወደደ ከእነሱም በኋላ ዘራቸውን መረጠ፥ ከግብፅም በታላቁ ኃይል በመገኘቱ አወጣችሁ፤
\v 38 ዛሬ እንደ ሆነ ከእናንተ የጸኑትን ታላላቆችን አሕዛብ ከፊታችሁ ሊስያወጣቸውና ለእናንተም ምድራቸውንም ርስት አድርጎ ሊሰጣችሁ ነው።
\s5
\v 39 እንግዲህ እግዚአብሔር በላይ በሰማይ በታችም በምድር አምላክ እንደ ሆነ፥ ሌላም እንደሌለ ዛሬ እወቁ፤ በልባችሁም ያዙት።
\v 40 ለእናንተ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችሁም ለዘላለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዓቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።
\s5
\v 41 በዚያን ጊዜ ሙሴ አስቀድሞ ጠላት ያልነበረውን ሰው ሳያውቅ የገደለው ሰው
\v 42 ወደ አንዲቱ ሸሽቶ በሕይወት ይኖር ዘንድ በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ ሦስት ከተሞች መረጠ።
\v 43 ከተሞቹም ለሮቤል ነገድ በምድረ በዳ በደልዳላ ስፍራ ያለ ቦሶር፥ ለጋድም ነገድ በገለዓድ ያለ ራሞት፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ያለ ጎላን ነበሩ።
\s5
\v 44 ሙሴ በእስራኤል ልጆች ፊት ያኖራት ሕግ ይህች ናት።
\v 45 ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ከወጡ በኋላ እግዚአብሔር የተናገራቸው የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች፥ ሥርዓቶች፥ ሌሎችም ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤
\v 46 በቤተ ፌጎር አንጻር ባለው ሸለቆ፥ በሴዎን ምድር፣ ከዮርዳኖስ በስትምሥራቅ፥ በነበሩበት ጊዜ፥ሙሴና የእስራኤል ልጆች ከግብፅ በወጡበት ጊዜ ድል ያደረጉአቸው በሐሴቦን ተቀምጦ በነበረው በአራውያን ንጉሥ ነበር።
\s5
\v 47 የእርሱንና የባሳንን ንጉሥ የዐግን ምድር ወሰዱ፤
\v 48 በምሥራቅ በኩል በዮርዳኖስ ማዶ የነበሩትን የሁለቱ የአሞራያን ነገሥታት እነዚህ ናቸው። ይህም ምድር ከአርኖን በአሮዔር ዳርቻ እስከ ሴዎን ተራራ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ፥
\v 49 በምሥራቅ በኩል የዮርዳኖስ ወንዝ ሸለቆ ሜዳ በሙሉ ጨምሮ በዮርዳኖስ ማዶ ከፈስጋ ተራራ በታች ያለውን ዓረባ ሁሉ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ ያለው ነው።
\s5
\c 5
\p
\v 1 ሙሴም የእስራኤል ልጆችን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአቸውና እንድትጠብቁአቸው ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራውን ሥርዓቶችንና ድንጋጌዎችን ስሙ።
\v 2 እግዚአብሔር አምላካችን ከእኛ ጋር በኮሬብ ቃል ኪዳን አድርጎአል።
\v 3 እግዚአብሔር ከአባቶቻችን ቃል ኪዳን አላደረገም ዛሬ በሕይወት ካለነው ከእኛ ጋር ነው።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ፊት ለፊት በተራራው ላይ በእሳት መካከል ተናገረ፥
\v 5 (በዚያን ጊዜ ከእሳቱም የተነሣ ፈርታችሁ ወደ ተራራው ባልቀረባችሁ ጊዜ ቃሉን ልገልጥላችሁ በእግዚአብሔርና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር) ። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦
\v 6 ከባርነት ቤት፥ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
\s5
\v 7 ከእኔ በቀር በፊቴ ሌሎች አማልክት አይኑራችሁ።
\v 8 በላይ በሰማይ፥ወይም በታች በምድር፣ወይም ከምድርም በታች በውኃ፥ ማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን ምስል ለራሳችሁ አታድርጉ።
\s5
\v 9 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ ስለሆንኩ ለአማልክት አትስገዱላቸው፥ ወይም እነርሱን አታገልግሉአችሁ። በሚጠሉኝ ላይ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የእባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ ቅጣትን ያመጣል፥
\v 10 ለቃል ኪዳኔም ታማኝነት ለሚያሳዩኝና ለሚወዱኝ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ አምላክ ነኝ።
\s5
\v 11 የአምላካችሁን ስም በከንቱ አትጠቀሙ፥ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠቀመውን ከበደል አያነጻውምና።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ የሰንበትን ቀን ትቀድሱት ዘንድ ጠብቁ።
\v 13 ስድስት ቀን ሥሩ ተግባራችሁንም ሁሉ አድርጉ፤
\v 14 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ሰንበት ነው። እናንተ እንደምታርፉ ሁሉ አገልጋያችሁና የቤት ሠራተኛችሁ ያርፉ ዘንድ እናንተ ወንድ ልጆቻችሁ፥ ሴት ልጆቻችሁም ፥ አገልጋዮቻችሁ፥ የቤት ሠራተኞቻችሁም በፊታችሁ፥ አህዮቻችሁም፥ ከብቶቻችሁም፥ ሁሉ በደጆቻችሁ ውስጥ ያለው እንግዳም ጭምር በሰንበት ምንም ሥራ አትሥሩ።
\s5
\v 15 እናንተም በግብፅ በሪያ እንደ ነበራችሁ አስቡ፥ እብዚአብሔር አምላካችሁ በጸናች እጅና በተዘረጋች ክንድ ከዚያ አውጣችሁ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሰንበትን ቀን ትጠብቁ ዘንድ አዘዛችሁ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ምድር ላይ ዕድሜአችሁ እንዲረዝምና መልካም እንዲሆንላችሁ አባታቸውንና እናታቸውን አክብሩ።
\s5
\v 17 አትግደሉ።
\v 18 አታመንዝሩ።
\v 19 አትስረቁ።
\v 20 በባልንጀራችሁ ላይ በሐሰት አትመስክሩ።
\s5
\v 21 የባልንጀራችሁን ሚስት አትመኙ፤ የባልጀራችሁን ቤት፥ እርሻውንም፥ አገልጋዩንም፥ የባልጀራችሁንም በሬውንም፥ አህያውንም፥ ከባልጀራችሁ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኙ።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳትና በደመና በጨለማም ውስጥ ሆኖ በታላቅ ድምፅ፥ እነዚህን ቃሎች ለጉባኤአችሁ ሁሉ ከተናገረው ምንም አልጨመረም። በሁለቱም የድንጋይ ጽላችቶች ላይ ጻፋቸው ለእኔም ሰጠኝ።
\s5
\v 23 ተራራው በእሳት ሲነድድ ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ እናንተ የነገዶቻችሁ አለቆች ሽማግሌዎቻችሁም ወደ እኔ ቀረባችሁ።
\v 24 አላችሁም፦ እነሆ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳትም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰዎች ጋር ሲነጋገር ሰዎችም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።
\s5
\v 25 አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን እንሞታለን? እኛ የእግዚአብሔርን የአምላካችንን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን።
\v 26 ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን ንው?
\v 27 አንተ ቅረብ፤ እግዚአብሔር አምላካችን የሚለውን ሁሉ ስማ፤ እግዚአብሔር አምላካችንም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን አላችሁ።
\s5
\v 28 በተናገራችሁኝም ጊዜ እግዚአብሔር የእናንተን ቃል ሰማ። እግዚአብሔርም አለኝ፦ይህ ሕዝብ የተናገሩህን ቃል ሰምቼአለሁ፤ የተናገሩትም ሁሉ መልካም ነው።
\v 29 ለእነርሱ ለዘላለምም ለልጆቻቸው መልካም ይሆንላቸው ዘንድ፥ እንዲፈሩኝ፥ ሁልጊዜም ትእዘዜን ሁሉ እንዲጠብቁ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው በነበራቸው!
\v 30 ሄደህ እንዲህ በላቸው፦ ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ።
\s5
\v 31 አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁሙ፥ ርስት አድርጌ በምሰጣቸውም ምድር ላይ ያደርጉአት ዘንድ የምታስተምራቸውን ትእዛዜንና ሥርዓቴን፥ ድንጋጌንም ሁሉ እነግርሃለሁ።
\s5
\v 32 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳዘዛችሁ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፥ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ አትበሉ።
\v 33 በሕይወት እንድትኖሩ መልካምም እንዲሆንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መንገድ ሁሉ ሄዱ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ከዮርዳኖስ ማዶ በምትውርሱአት ምድር የምትጠብቃችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዳስተምራችሁ ያዘዘኝ እነዚህ ትእዛዘት፥ ሥርዓትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው፤
\v 2 እኔ የማዛችሁን ሥርዓትንና ትእዛዘትን በመጠበቅ እናንተ፥ ልጆቻችሁ፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዘመናችሁ ዕድሜአችሁ እንዲረዝም እግዚአብሔር አምላካችሁን አክብሩ።
\s5
\v 3 እንግዲህ እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ መልካምም እንዲሆንላችሁ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ተስፋ እንደሰጣችሁ ወተትና ማር በምታፈስሰው ምድር እጅግ እንድትበዙ ነው።
\s5
\v 4 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፥ እግዚአብሔር አምላካችን አንድ እግዚአብሔር ነው።
\v 5 እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ በፍጹም ኃይላችሁ ውደዱ።
\s5
\v 6 እኔም ዛሬ እናንተን የማዝዘው ቃል በልባችሁ ይሁን፤
\v 7 በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድም ስትሄዱ፥ ስትተኙም፥ ስትነሡም፥ ልጆቻችሁን አስተምሩአቸው።
\s5
\v 8 በእጃችሁም ምልክት አድርጋችሁ እሰሩት፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁንላችሁ።
\v 9 በቤታችሁም መቃኖች በደጃፋችሁም በሮች ላይ ጻፉት።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ ለእናንተ ሊሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባገባችሁ ጊዜ፥ ያልሠራሃችኋቸውን ታላላቅና መልካም ከተሞች፥
\v 11 በመልካም ነገሮች ሁሉ የተሞሉ ቤቶች ያልማስሃችኋቸውን የተማሱ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃችኋቸውን ወይንና ወይራ በሰጣችሁ ጊዜ፥
\v 12 በበላችሁና በጠገባችሁ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 13 አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ፤ እርሱንም አምልኩት በስሙም ማሉ።
\v 14 በዙሪያችሁ ያሉትን አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት ፍለጋ እንዳትሄዱ፥ እንዳከተከተሉ፤
\v 15 ምክንያቱም በመካከላችሁ ያለው እግዚአብሔር አምላካችሁ ቀናተኛ አምላክ ስለሆነ፥ ቁጣው እንዳይነድባችሁና ከምድር ገጽ እንዳያጠፋችሁ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 16 በማሳህ እንደተፈታተናችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁን አትፈታተኑት።
\v 17 ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዘትንና ሥርዓቱን አጥብቃችሁ ጠይቁ።
\s5
\v 18 መልካምም ይሆንላችሁ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን ነገር አድርጉ፤ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥
\v 19 እግዚአብሔርም እንደተናገረ ጠላቶቻችሁን ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣላችሁ ዘንድ።
\s5
\v 20 በኋለኛው ዘመንም ልጆቻችሁ እንዲህ ብለው በጠየቃችሁ ጊዜ፦ እግዚአብሔር አምላካችን ያዘዛችሁ የቃል ኪዳን ድንጋጌዎች፥ ሥርዓትና ሌሎችስ ድንጋጌዎች እነዚህ ምንድን ናቸው?
\v 21 እናንተም ለልጆቻችሁ እንዲህ በሉአችው፦ በግብፅ አገር የንጉሥ ፈርዖን አገልጋዮች ነበርን፥ እግዚአብሔርም በጽኑ እጅ ከግብፅ አወጣን፥
\v 22 እግዚብብሔርም በግብፅና በፈርዖን፥ በቤቱም ሁሉ ላይ በዓይናችን ፊት ታላቅና ክፉ፥ ምልክትና ተአምራትን አደረገ።
\v 23 ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር አምጥቶን እርስዋን ይሰጠን ዘንድ ከዚያ አወጣን።
\s5
\v 24 እንደ ዛሬም በሕይወት እንዲያኖረን ሁልጊዜም መልካም እንዲሆንልን እግዚአብሔር አምላካችንን እንፈራ ዘንድ ይህችንም ሥርዓት ሁሉ እናደርግ ዘንድ እግዚአብሔር አዘዘን።
\v 25 እርሱም እንዳዘዘን በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት እንፈጽመው ዘንድ ይህን ትእዛዝ ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።
\s5
\c 7
\p
\v 1 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወሱአት ወደምትገቡባት ምድር ባመጣችሁ ጊዜ፤ ከፊታችሁም ብዙ አሕዛብ ከእናንተ የበለጡትንና የበረቱትን ሰባቱን አሕዛብ ኬጢያዊውን፥ ጌርጌሳውያንን፥ አሞራውያንብ፥ ከነዓናውያንን፥ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውንና ኢያቡሳዊውን አወጣቸው።
\s5
\v 2 እንዲሁም ጦርነት በገጠማችሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁ ድል በሰጣችሁ ጊዜ፥ እነርሱን ማጥቃት አለባችሁ፥ ከዚያም ፈጽሞ ማጥፋት ይኖርባችኋል።
\v 3 ከእርሱም ጋር ቃል ኪዳን ማድረግ ወይም ምሕረት አለማድረግ፥ ከእነርሱም ጋር አትጋቡም፤ ሴት ልጆቻችሁን ለወንድ ልጆቻቸው አትስጡ፥ ሴት ልጃቸውንም ለወንድ ልጃችሁ አትውሰዱ።
\s5
\v 4 ሌሎች አማልክትን እንዳያመልኩ፥ ልጆቻችሁን እኔን እንዳይከተሉ ይመልሳሉ፥ የእግዚአብሔርም ቁጣ ይነድድባችኋል ፈጥኖም ያጠፋችኋል።
\v 5 በእነርሱ ላይ የምታደርጉባቸው እንደዚህ ነው፥ መሠዊያቸውን አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቻቸውንም ቁረጡ፥ የተቀረጸውን ምስላቸውንም በእሳት አቃጥሉ።
\s5
\v 6 እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የተለያችሁ ሕዝብ ናችሁ። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምድርም ገጽ ከሚኖሩ ሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ መረጣችሁ።
\s5
\v 7 እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቁጥር ስለ ባዛችሁ አይደለም፤ እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቁጥር ጥቂቶች ነበራችሁና፤
\v 8 ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን ቃል ኪዳን ስለ ጠበቀ ነው። እግዚአብሕር በጽኑ እጅ ያወጣችሁ፥ ከባሪነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ ለዚህ ነው።
\s5
\v 9 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እርሱ አምላክ እንደ ሆነ ለሚወድዱትና ትእዛዘትንም ለሚጠብቁት፥ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆን እወቁ፥
\v 10 ነገር ግን የሚጠሉትን በፊታቸው ሊያጠፋቸው ብድራትን ይመልሳል፤እንዲሁም ብድራትን ለመመለስ አይዘገይም።
\v 11 እንግዲህ ታደርጉት ዘንድ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘት፥ ሥርዓቶችና ድንጋጌዎችን ጠብቁ።
\s5
\v 12 እነዚህን ድንጋጌዎችን ሰምታችሁ ብትጠብቁና ብታደርጉ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ለአባቶቻችሁ የማለላችውን ቃል ኪዳን በታማኝነት ለእናንተ ይጠብቅላችኋል።
\v 13 እርሱም ይወድዳችኋል፥ ይባርካችኋል፥ ያበዛላችኋል፤ እንዲሁም የሆዳችሁንና የምድራችሁን ፍሬ፥ እህላችሁን፥ ወይናችሁን፥ ዘይታችሁን፥ የከብቶቻችሁንና የበጎቻችሁን መንጋ ይባርካል።
\s5
\v 14 ከአሕዛብም ሁሉ ይልቅ የተባረካችሁ ትሆናላችሁ፥ በሰዎቻችሁና በከብቶቻችሁ ዘንድ ወንድ ወይም ሴት ቢሆኑ መካን አይሆንባችሁም።
\v 15 እግዚአብሔርም ሕመምን ሁሉ ከእናንተ ያርቃል፥ የምታውቁአችሁን ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በእናንተ ላይ አያደርስባችሁም በሚጠሉባችሁም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር አምላካችሁም በእጃችሁ አሳልፎ የሚሰጣችሁን አሕዛብ ሁሉ ታጠፋቸዋላችሁ፥ ዓይናችሁም አያዝኑላቸውም። ወጥመድ እንዳይሆኑባችሁአማልክታቸውንም አታምልኩአችሁም።
\s5
\v 17 በልብህም እንዲህ ብትሉ፦ እነዚህ አሕዛብ ከእኔ ይልቅ ይበዛሉና አወጣቸው ዘንድ እንዴት እችላለሁ?
\v 18 እግዚአብሔር አምላካችሁ በፈዖንና በግብፅ ሁሉ ያደረገውን ትዝ ስለሚላችሁ እነሱን አትፍራቸው፤
\v 19 አምላካችሁ እግዚአብሔር ዓይናችሁ ፊት ታላቅን መቅሠፍት፥ ምልክትንና ተአምራትን በማድረግ በጸናችው እጅ፥ በተዘረጋውም ክንድ አወጣችሁ። እንዲሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተ በምትፈሩአችሁ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ያደርጋል።
\s5
\v 20 በተጨማሪም እግዚአብሔር አምላካችሁ ራሳቸውን የተሸሸጉትን ከፊታችሁ እስኪጠፉ ድረስ በመካከላችው ተርብ ይሰድድባቸዋል።
\v 21 እግዚአብሔር አምላካችሁ ታላቅና የተፈራ አምላክ በመካከላችሁ ስላለ፤ ከእነርሱ የተነሣ አትደንግጡ።
\v 22 እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን አሕዛብ ጥቂት በጥቂት ከፊታችሁ ያወጣቸዋል። ሁሉንም አንድ ጊዜ አታጠፋቸውም፤ ወይም የዱር አራዊት በዙሪያችሁ በጣም ብዙ ይሆናሉ።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር አምላካችሁ እነርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ እስኪጠፉም ድረስ በታላቅ ድንጋጤ ያስደነግጣቸዋል።
\v 24 ነገሥታታቸውንም በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣቸዋል፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች ታጠፋቸዋላችሁ። እስክታጠፏቸውም ድረስ ማንም በፊታችሁ ይቆም ዘንድ አይችልም።
\s5
\v 25 የተቀረጸውንም የአማልክታቸውን ምስል በእሳት ታቃጥላላችሁ፤ ከብር ወይም ከወርቅ የተሠሩትንም ለራሳችሁ ለመውሰድ አትመኙ፥ በእግዚአብሔር በአምላካችሁም ዘንድ ርኩስ ነውና እንዳትጠመዱበት ከእርሱ ምንም አትውሰዱ።
\v 26 እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆኑ ርኩስን ነገር ወደ ቤታችሁ አታግቡ ለማምለክም አትቃጡ፥ ለጥፋት የተለየ ስለ ሆነ ፈጽሞ ተጸየፉት፥ ጥሉትም።
\s5
\c 8
\p
\v 1 በሕይወት እንድትኖሩና እንድትበዙ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁ ወደ ማለላቸው ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱአት ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘትን ሁሉ ጠብቁ።
\v 2 እግዚአብሔር አምላካችሁ በልባችሁ ያለውን፥ ትእዛዘቱን መጠበቃችሁን ወይም አለመጠበቃችሁን ያውቅ ዘንድ ሊፈትናችሁና ትሁት እንድትሆኑ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራችሁን መንገድ ሁሉ አስቡ።
\s5
\v 3 አስጨነቃችሁ፥ እንድትራቡም አደረጋችሁ፥ እንዲሁም እናንተና ልጆቻችሁ፥ አባቶቻችምሁ የማያውቁአቸውን መና መገባችሁ። ይህም ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ነገር ሁሉ በሕይወት ይኖራል እንጂ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ያስታውቃችሁ ዘንድ ነው።
\s5
\v 4 በእነዚህ አርባ ዓመታት ውስጥ የለበሳችሁት ልብስ አላረጀም፥ እግራችሁም አላበጠም።
\v 5 ሰውም ልጁን እንደሚገሥጽ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን እንደሚገሥጽ በልባችሁ አስቡ።
\v 6 በመንገዱም እንድትሄዱ እርሱንም እንድትፈሩ የእግዚአብሔ የአምላካችሁን ትእዛዝ ጠብቁ።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደ መልካምና፥ ከሸለቆና ከኮረብታ የውኃ ጅረቶችና ፈሳሾች የሚመነጩ ምንጮች ወዳሉባት ምድር፤ ስንዴና ገብስ፤
\v 8 በለስና ሮማን፥ ወይራና ማር ወደ ሞሉባት፥
\s5
\v 9 ሳይጎድላችሁ እንጀራ ወደምትበሉባት ምድር፥ አንዳችም ወደማታጡባት፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር አመጣችሁ።
\v 10 እናንተም ትበላላችሁ፥ ትጠግባላችሁ፥ ስለ ሰጣችሁም ስለ መልካሚቱ ምድር እግዚአብሔር አምላካችሁን ትባርካላችሁ።
\s5
\v 11 ዛሬ እኔ እናንተን የማዝዛውን ትእዛዘትን፥ ድንጋጌዎችንና ሥርዓቶችን ባለመጠበቅ እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።
\v 12 ከበላችሁና ከጠገባችሁ ሙሉም ከሆናችሁ በኋላ መልካምም ቤት ሠርታችሁ በዚያ መኖር ከጀመራችሁ በኋላ እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 13 የላምና የበግ መንጋ ከበዛላችሁ በኋላ፥ ብራችሁና ወርቃችሁም፥ ያላችሁም ሁሉ ከበዛላችሁ በኋላ፥
\v 14 ልባችሁ እንዳይኮራ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣችሁን እግዚአብሔርን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 15 መርዛማ እባብና ጊንጥ፥ውኃ በሌለባትና ጥማትም ባለባት በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራችሁን፥ ከዐለት ድንጋይም ውኃን ያወጣላችሁን፥
\v 16 በመጨረሻም ዘመን መልካም ያደርግላችሁ ዘንድ ሊፈትናችሁ ሊያዋርዳችሁም አባቶቻችሁ ያላውቁትን መና በምድረ በዳ ያበላችሁን እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዳትረሱ፥
\v 17 በልባችሁም፦ ጉልባታችን የእጃችን ብርታት ይህን ሀብት አመጣልን እንዳትሉ።
\s5
\v 18 ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶቻችሁ የማለላችሁን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ሀብት ለማከማቸት ጉልበት ሰጥቶአችኋል፥ እግዚአብሔር አምላካችሁን አስቡ።
\v 19 አምላካችሁንም እግዚአብሔርን ብትረሳ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል፥ ብታመልካቸውም፥ ብትሰግድላቸውም ፈጽሞ እንደምትጥፉ እኔ ዛሬውኑ እመሰክርባችኋልለሁ።
\v 20 የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ቃል ስላልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፍታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ እንዲሁ እናንተ ትጠፋላችሁ።
\s5
\c 9
\p
\v 1 እስራኤል ሆይ፥ ስሙ፥ ከእናንተ የበለጡትንና የበረቱትን አሕዛብ፥ እስከ ሰማይም ድረስ የተመሸጉትን ታላላቅ ከተሞች ለመውረስ ትገቡ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ነው፤
\v 2 የኤናቅ ልጆች ፥ ታላቅና ረጅም ሕዝብ፥ እናንተም የምታውቃቸው ስለ እነርሱም እንዲህ ያላችኋቸው፦ በዔናቅ ልጆች ፊት ማን መቆም ይችላል?
\s5
\v 3 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊታችሁ ስለሚያልፍ፥ ዛሬ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊታችሁም ያዋርዳቸዋል፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገራችሁ እናንተ ታሳድዳቸዋላችሁ ፈጥናችሁም ታጠፋቸዋላችሁ።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ ካወጣቸው በኋላ ፦ እንወርሳት ዘንድ ወደዚህች ምድር እግዚአሔር ያመጠን፥ ስለ ጽድቄ ነው፥ እነዚህንም አሕዛብ እግዚአብሔር ከፊታችን ያወጣቸው ኃጢአተኞች ስለ ሆኑ ነው፥ ብላችሁ በልባችሁ እንዳትናገሩ።
\s5
\v 5 ምድራቸውን ትወርሱአት ዘንድ የምትገቡት ስለ ጽድቃችሁ ወይም ስለ ልባችሁ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ከፊታችሁ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኃጢአት ምክንያትና ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ይፈጽም ዘንድ ነው።
\s5
\v 6 እንግዲህ እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ስለ ሆናችሁና እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን መልካም ምድር ርስት አድርጎ የሰጣችሁ ስለጽድቃችሁ እንዳይደለ እወቁ።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር አምላካችሁን በምድረ በዳ እንዳስቁጣችሁት ከግብፅ አገር ከወጣችሁበት ቀን ጀምሮ ወደዚህ ስፍራ እስከ መጣችሁ ድረስ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፃችሁ አስቡ።
\v 8 በኮሬብ ደግሞ እግዚአብሔርን አስቆጣችሁ፤ እግዚእብሔርም ሊያጠፋችሁ ተቆጣባችሁ።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባውን የቃል ኪዳን፥ የድንጋዩን ጽላቶችን ከእግዚአብሔር ለመቀበል ወደ ተራራ ወጥቼ በተራራው ላይ ለአርባ ቀናትና አርባ ሌሊት በቆየሁበት ጊዜ እንጀራም አልበለሁም፥ ውኃም አልጠጠሁም።
\v 10 እግዚአብሔርም በእርሱ ጣት የተጻፉትን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶችን ሰጠኝ፤ በጽላቶቹም ላይ በተራራው ሥር በነበረው ጉበዔ እግዚአብሔር በእሳት መካከል ሆኖ የተናገራችሁ ቃል ሁሉ ተጽፎባቸው ነበር።
\s5
\v 11 ከአርባ ቀንና ከእርባ ሌሊትም በኋላ እግዚአብሔር ሁለቱን የድግንጋይ ጽላቶች፥ ያቃል ኪዳኑን ጽላቶች ሰጠኝ።
\v 12 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥተህ ከዚህ ፈጥነህ ውረድ ከግብፅ ያወጣሃቸው ሕዝብህ ረክሰዋል። ፈጥነው ካዘዝኋቸውም መንገድ ፈቀቅ ብለዋል። ቀልጦ የተሠራ ምስልም ለራሰቸው አድርገዋል።
\s5
\v 13 ከዚህም በተጨማሪ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ ይህ ሕዝብ አንገተ ደንዳና መሆኑን አይቼአለሁ።
\v 14 ስለዚህ አጠፋቸው፥ ስማቸውንም ከሰማይ በታች እደመስሳለሁ፥ አንተንም ከእነርሱ ለሚበረታና ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ።
\s5
\v 15 እኔም ተመልሼ ከተራራው ወረድሁ፥ ተራራውም በእሳት ይነድድ ነበር። ሁለቱም የቃል ኪንን ጽላቶች በእጆቼ ነበሩ።
\v 16 እናንተም እግዚአብሔር አምላካችሁን እንደበደላችሁ አየሁ። ለእናንተም ለራሳችሁ የጥጃ ምስል ሠርታችሁ ነበር። እግዚአብሔርም ካዘዛችሁ መንገድ ፈቀቅ ብላችሁ ነበር።
\s5
\v 17 ሁሉቱንም ጽላቶች ወስጄ፥ ከእጆቼ ጣልኋቸው። በዓይናችሁም ፊት ሰበርኋቸው።
\v 18 ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ከማድረጋችሁ የተነሣ እንደገና በእግዚአብሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ወደቅሁ፥ እንጀራም አልበላሁም፥ ውኃም አጠጣሁም ነበር።
\s5
\v 19 ምክንያቱም እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ ከተቆጣባችሁ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ስለ ፈራሁ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በዚያን ጊዜም ሰማኝ።
\v 20 እግዚአብሔርም አሮንን ሊያጠፋው እጅግ ተቆጣው፤ ስለ አሮንም ደግሞ በተመሳሳይ ሁኔታ ጸለይሁ።
\s5
\v 21 ያደረጋችሁትንም ኃጢአት ጥጃውን ወስድሁ በእሳትም አቃጠልሁት፥ አደቅዝቅሁትም፤ ዱቄትም እስኪሆን ድረስ ፈጨሁት። ዱቄቱንም ከተራራ በሚወርድ ወንዝ ጣልሁት።
\s5
\v 22 እግዚአብሔርንም በቀቤራ፥ በማሳህ፥ በምኞት መቃብርም አስቆጥታችሁት ነበር።
\v 23 እግዚአብሔርም ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ትእዛዝ ላይ አመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፤ወይም ድምፁንም አልሰማችሁም።
\v 24 እናንተን ካወቅሁበት ቀን ጀምሮ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፀኞች ነበራችሁ።
\s5
\v 25 እግዚአብሔር ያጠፋችሁ ዘንድ ስለ ተናገረ በእነዚያ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእግዚአብሔር ፊት ወደቅሁ።
\v 26 ጌታ በእግዚአብሔርም ፊት እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ በታላቅነትህና በኃያልነትህ ከግብፅ ያወጣቸውን፥ የተበዠሃቸውን ሕዝብህንና ርስትህን አታጥፋ ።
\s5
\v 27 አገልጋዮችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ደንዳናነት፥ ክፋቱንና ኃጢአቱን አትመልከት፤
\v 28 እኛንም ያወጣህባት ምድር ሰዎች እግዚአብሔር ተስፋ ወደ ሰጣቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ ስላልቻለ፤ ስለጠላቸውም በምድረ በዳ ሊገድላቸው አወጣቸው ይላሉ።
\v 29 እነርሱም በታላቅ ኃይልህ በጸነችውም ክንድህ ያወጣሃቸው ሕዛብህና ርስትህ ናቸው።
\s5
\c 10
\p
\v 1 በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ እንደ መጀመሪያ ያሉትን ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠርበህ ወደ እኔ ወደ ተራራ ውጣ፤ ለአንተም የእንጨት ታቦት ሥራ።
\v 2 በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት በእነዚህ ጽላቶች ላይ እጽፋለሁ፤ አንተም በታቦቱ ውስጥ ታደርጋቸዋለህ።
\s5
\v 3 ከግራርም እንጨት ታቦትን ሠራሁ፥ እንደፊተኞቹም ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ጠረብሁ፥ ሁለቱንም ጽላቶች በእጄ ይዤ ወደ ተራራው ወጣሁ።
\v 4 በተራራው ሥር የጉባዔው ቀን እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳት መካከል ሆኖ የተናገራችሁን አሥርቱን ቃላት በመጀመሪያ ተጽፈው እንደ ነበረ በጽላቶቹ ላይ ጻፈ፤ ከዚያም እግዚአብሔር እነርሱን ለእኔ ሰጠኝ።
\s5
\v 5 ተመልሼም ከተራራው ወረድሁ፤ ጽላችቶችንም በሠረሁት ታቦት ውስጥ አደረግኋቸው፤እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ በዚያ ሆኑ።
\s5
\v 6 የእስራኤልም ልጆች ከብኤሮት ብኔ ያዕቃን ወደ ሞሴራ ተጓዙ። በዚያ አሮን ሞተ፥ በዚያም ተቀበረ፥ በእርሱም ፋንታ ልጁ አልዓዛር ካህን ሆኖ አገለገለ።
\v 7 ከዚያም ወደ ጉድጎዳ ተጓዙ፤ከጉድጎዳም ወደ ውኃ ምንጮች ምድር ወደ ዮጥባታ ተጓዙ።
\s5
\v 8 በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር የሌዊን ነገድ እግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ይሸከሙና እርሱንም እንዲያገለግሉ፥ በፊቱም ይቆሙ ዘንድ በስሙም እንዲባርኩ መረጠ።
\v 9 ስለዚህ ለሌዊ ከወንድሞቹ ጋር ክፍልና ርስት የለውም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው እግዚአብሔር ርስቱ ነው።
\s5
\v 10 በተራራውም ላይ እንደ መጀመሪያውም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየሁ። እግዚአብሔርም እንደገናም ሰማኝ፤ እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ አልፈለገም።
\v 11 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ ተነሥተህ በሕዝቡ ፊት ሆነህ ሕዝቡን በጉዞው ምራው፤ ለአባቶቻቸው የማለሁላቸውን ምድር ሄደው ይገባሉ።
\s5
\v 12 እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትውድድ ዘንድ፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ መልካምም እንዲሆንልህ
\v 13 ዛሬ ለአንተ የማዘዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ከሆነ በቀር እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?
\s5
\v 14 እነሆ፥ ሰማይና ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ነው።
\v 15 ብቻ እግዚአብሔር ስለ አባቶቻችሁ ደስ ተሰኝቶአል፥ እነርሱንም ወድዶቸዋል፤ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራችሁን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዝብ ሁሉ መካከል መረጣችሁ።
\s5
\v 16 ስለዚህ እናንተ የልባችሁን ሸለፈት ግረዙ፥ አንገተ ደንዳኖች አትሁኑ።
\v 17 እግዚአብሔር አምላካችሁ የአማልክት አምላክ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ ኃያልም የሚያስፈራም በፍርድ የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል።
\s5
\v 18 እግዚአብሔር ለድሃ አደጉና ባል ለሞተባት ይፈርዳል፥ ምግብና ልብስም የሚሰጥ ነው።
\v 19 ስለዚህ እናንተም በግብፅ አገር ስደተኞች ስለ ነበራችሁ ስደተኛውን ውደዱ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር አምላካችሁን ፍሩ፥ እርሱንም አምልኩት። በእርሱም ተጣበቁ፤ በስሙም ማሉ።
\v 21 እርሱ ዓይኖቻችሁ ያዩትን እነዚህን ታላላቆችንና የሚያስፈሩትን ነገሮች ያደረገላችሁ ክብራችሁ ነው፤ አምላካችሁም ነው፤ ።
\s5
\v 22 አባቶቻችሁ ሰባ ሰዎች ሆነው ወደ ግብፅ ሄዱ፤ አሁንም እግዚአብሔር አምላካችሁ ብዛታችሁን እንደ ሰማይ ክዋክብት አደረገ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውዳዱት፥ ሁልጊዜም መመሪያዎቹን፥ ሥርዓቶቹን፥ ድንጋጌዎችንና ትእዛዛትን ጠብቁ።
\s5
\v 2 የእግዚአብሔርን የአምላካችሁን ቅጣት፥ታላቅነቱን፥ ኃያልነቱን፥ የተዘረጋውንም ክንዱን፥ ላላወቁት ወይም ላላዩት ልጆቻችሁ እየተናገርሁ እንዳልሆነ አስታውሉ፤
\v 3 በግብፅም መካከል በንጉሡ በፈርዖንና በአገሩ ሁሉ ላይ ያደረጋውን ተአምራቱንና ሥራውን፥
\s5
\v 4 በተከተሉአችሁም ጊዜ በግብፅ ጭፍራ፥ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ያደረገውን፥በኤርትራ ባሕር ውኃ እንዳሰጠማቸው፥ እግዚአብሔርም እስከ ዛሬ ድረስ እንዳጠፋቸው፥
\v 5 ወደዚህ ስፍራ እስከትመጡ ድረስ በምድረ በዳ ያደረገላችሁን፥አይተዋል።
\s5
\v 6 በእስራኤልም ሁሉ መካከል ምድር አፍዋን ከፍታ እነርሱንና ቤተ ሰቦቻቸውን ድንኳኖቻቸውንም ለእነርሱም የነበራቸውን ሁሉ በዋጠቻቸው በሮቤል ልጅ፥ በኤልያብ ልጆች፥ በዳታንና በአቤሮን እግዚአብሔር ያደረገውን አላዩም።
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ያደረገውን ታላቁ ሥራ ሁሉ ዓይኖቻቸው አይተዋል።
\s5
\v 8 እንግዲህ እንድትጠነክሩ ትወርሱአትም ዘንድ ወደምትሄዱባት ምድር እንድትሄዱ ዛሬ ለእናንተ የማዘዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤
\v 9 እግዚአብሔርም ለአባቶቻችሁና ለዘራቸው ይሰጣቸው ዘንድ በማለላቸው ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዘም ትእዛዘትን ጠብቁ።
\s5
\v 10 ትወሱአት ዘንድ የምትሄዱባት ምድር በመጣችሁበት በግብፅ አገር ዘር እንደዘራችሁና ውኃ በእግራችሁ ታጠጡ እንደነበረ፥ እንደ አትክልት ቦታ አይደለችም፤
\v 11 ነገር ግን ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ የምትገቡባት ምድር ኮረብታና ሸለቆ ያለባት በሰማይ ዝናብ ውኃ የምትጠጣ አገር ናት፤
\v 12 አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ የሆነ አገር ናት።
\s5
\v 13 እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ እግዚአብሔር አምላካችሁን ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ፥ ትወድዱና ታገለግሉት ዘንድ ዛሬ የማዝዛችሁን ትእዛዘትን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥
\v 14 እህላችሁን፥ ወይናችሁን፥ ዘይታችሁን ትሰበስቡ ዘንድ በየዚዜው ለምድራችሁ የመጀመሪያውንና የኋለኛውን የወቅቱን ዝናብ ይሰጣችኋል።
\v 15 በሜዳ ለእንስሶቻችሁም ሣርን እሰጣለሁ፤ትበላላችሁ፣ ትጠግባላችሁም።
\s5
\v 16 ልባችሁ እንዳይስት ፈቀቅ እንዳትሉ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም፥
\v 17 የእግዚአብሔርም ቁጣ እንዳይነድድባችሁ ዝናብ እንዳይዘንብ ምድሪቱም ፍሬዋን እንዳትሰጥ ሰማይን እንዳይዘጋባችሁ፤ እግዚአብሔርም ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ እንዳትጠፉ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 18 ስለዚህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደ ክታብ ይሁኑላችሁ። ፥
\v 19 በቤታችሁም ስትቀመጡ፥ በመንገድ ላይም ስትሄዱ፥ ስትተኙ፥ ስትነሡም ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው።
\s5
\v 20 በቤታችሁ መቃኖችና በከተሞቻችሁ በሮች ላይ ጻፈው፥
\v 21 እግዚአብሔርም እንዲሰጣቸው ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር፥ እንደ ሰማይ ቀኖች በላይ በምድር ከፍ ያሉና የልጆቻችሁም ዘመን የረዘመ ይሁን ።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር አምላካችሁን ትወድዱ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዘት ሁሉ ብትጠብቁ፥ ብታደርጉአቸውም፥
\v 23 እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣል፤ ከእናንተም የሚበልጡትን፥ የሚበረቱትንም አሕዛብ ትወርሳላችሁ።
\s5
\v 24 የእግራችሁ ጫማ የሚረግጥበት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስ ወንዝ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል።
\v 25 በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር እርሱ እንደ ተናገራችሁ ማስፈራታችሁና ማስደንገጣችሁ በምትረግጡበት ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል።
\s5
\v 26 እነሆ፥ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤
\v 27 በረከትም የሚሆነው፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ትእዛዝ ብትሰሙ
\v 28 እንዲሁም መርገም የሚሆነው የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ትአዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬም ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቋቸውን አምልክት ብትከተሉ ነው።
\s5
\v 29 እግዚአብሔር አምላካችሁ ትወሱአት ዘንድ እናንተም ወደምትሄዱባት ምድር ባገባሃችሁ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙንም በጌባል ተራራ ይሆናል።
\v 30 እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ከምዕራብ ካለው መንገድ በኋላ በዓረባ በሚኖሩት በከነዓናውያን ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ አይደለምን?
\s5
\v 31 እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁ፥ ትቀመጡባታላችሁም።
\v 32 እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራውን ሥርዓትና ድንጋጌዎች ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።
\s5
\c 12
\p
\v 1 የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንድትወርሱ በሚሰጣችሁ ምድር፥ ሁልጊዜ በምድር እያላችሁ የምትጠብቁአችሁ ሥርዓትና ድንጋጌዎች እነዚህ ናቸው።
\v 2 እናንተ የምትወርሱአቸው አሕዛብ አማልክታቸውን ያመለኩባቸውን በረጅም ተራሮች በኮረብቶችም ከለምለምም ዛፍ በታች ያለውን ስፍራ ሁሉ ፈጽማችሁ አጥፉአቸው።
\s5
\v 3 መሠዊያቸውንም አፍርሱ፥ ሐውልቶቻቸውንም ሰባብሩ፥የማልመኪያ ዐፀዶቻችቸውንም በእሳት አቃጥሉ፥የአማልክታቸውንም የተቀረጹ ምስሎች ቆራርጡአቸው፥ ከዚያም ስፍራ ስማቸውን አጥፉ።
\v 4 እግዚአብሔር አምላካችሁን እንዲህ ባለ ሁኔታ አታምልኩ።
\s5
\v 5 ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ ከነገዶቻችሁ ሁሉ ስሙን በዚያ ያኖር ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ ትመጣላችሁ፥ ማደሪያውንም ትሻላችሁ።
\v 6 ወደዚያም የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላም መሥዋዕታችሁንም፥ አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቁርባን፥ ስእለታችሁንም በፈቃዳችሁ የምታቀርቡትን፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት ውሰዱ።
\s5
\v 7 በዚያም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ብሉ፥ እጃችሁንም በምትዘረጉበት እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ ነገር ሁሉ እናንተና ቤተ ሰባችሁ ደስ ይበላችሁ።
\s5
\v 8 ሰው ሁሉ በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን፥ እኛ በዚህ ዛሬ የምናደርገውን ሁሉ አታደርጉም፥
\v 9 እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ዕረፍትና ርስት እስከ ዛሬ ድረስ አልገባችሁምና።
\s5
\v 10 ነገር ግን ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁም በሚያወርሳችሁ ምድር በተቀመጣችሁ ጊዜ ያለ ፍርሃትም እንድትኖሩ፥ ከከበቡአችሁ ጠላቶች ሁሉ ዕረፍት በሰጣችሁ ጊዜ በዚያ ጊዜ
\v 11 እግዚአብሔር አምላካችሁ ፥ ስሙ ይጠራበት ዘንድ ወደዚያ ወደ መረጠው ስፍራ እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን፥ ሌላም መሥዋዕታችሁን አሥራታችሁንም፥ በእጃችሁ ያነሣችሁትንም ቁርባን፥ ለእግዚአብሔርም ተስላችሁ የመረጣችሁትን ስእልታችሁን ሁሉ ውሰዱ።
\s5
\v 12 እናንተም፥ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ አገልጋዮቻችሁና የቤት አገልጋዮቻችሁ፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ የተቀመጠው ሌዋዊም፥ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።
\s5
\v 13 የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን በሚታያችሁ ስፍራ ሁሉ እንዳታቀርቡ ተጠንቀቁ።
\v 14 ነገር ግን እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ከአንዱ ዘንድ በመረጠው ስፍራ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አቅርቡ፥ በዚያም የማዝዛችሁን ሁሉ አድርጉ።
\s5
\v 15 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሰጣችሁ በረከት ሰውነታችሁ እንደ ፈቀደ በደጆቻችሁ ሁሉ ውስጥ አርዳችሁ ብሉ፤ንጹሕም ያልሆነ ሰው እንደ ሚቋና እንደ ዋላ ያለውን ይብላው።
\v 16 ደሙን ግን እንደ ውኃ በምድር ላይ ያፍስሰው፤ ደሙን አትብሉ።
\s5
\v 17 የእህላችሁን፥ የወይናችሁን፥ የጠጃችሁን የዘይታችሁንም፥ አሥራት፥ የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት የተሳላችሁትንም ስእለት ሁሉ በፈቃዳችሁም ያቀረባችሁትን፥ በእጃችሁም ያነሣችሁትን ቁርባን በደጆቻችሁ መብላት አትችሉም።
\s5
\v 18 በዚህ ፈንታ እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም አገልጋዮቻችሁና የቤት አገልጋዮቻችሁ፥በአገራችሁ ደጅ ያለው ሌዋዊ እግዚአብሔር አምላካችሁ በመረጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ብሉት፥ እጃችሁንም በምትዘረጉባችሁ ነገር ሁሉ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ።
\v 19 በምድራችሁ ላይ በምትኖሩባት ዘመን ሁሉ ሌዋዊውን ቸል እንዳትሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ነገራችሁ አገራችሁን ባሰፋ ጊዜ፥ ሰውነታችሁም ሥጋ መብላት ስለ ወደደ፦ ሥጋ እንብላ፥ ስትሉ እንደ ሰውነታችሁ ፈቃድ ሥጋን ብሉ።
\s5
\v 21 እግዚአብሔር አምላካችሁ በዚያ ስሙን ያኖር ዘንድ የመረጠው ስፍራ ከእናንተ ሩቅ ቢሆንም እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከላምና ከበግ መንጋችሁ እንዳዛዝኋችሁ እረዱ፥ እንደ ሰውነታችሁም ፈቃድ ሁሉ በአገራችሁ ደጅ ብሉ።
\v 22 ሚዳቋና ዋላ እንደሚበሉ እንዲሁ ብሉ፥ ንጹሕ ሰው ንጹሕ ያልሆነም ይብለው።
\s5
\v 23 ደሙ ሕይወት ነውና፥ ነፍሱንም ከሥጋው ጋር መብላት አይገባችሁምና፥ ደሙን እንዳትበሉ ተጠንቀቁ።
\v 24 በምድር ላይ እንደ ውኃ አፍስሱት እንጂ አትብሉ።
\v 25 በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን ነገር ስታደርጉ ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላችሁ አትብሉ።
\s5
\v 26 ነገር ግን የተቀደሰውን ነገራችሁን ስእለታችሁንም ይዛችሁ እግዚአብሔር ወደ መረጠው ስፍራ ሂዱ።
\v 27 የሚቃጠለውንም መሥዋዕታችሁን ሥጋውንና ደሙን በአምላካችሁ በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ አቅርቡ፤ የመሥዋዕታችሁም ደም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ መሠዊያ ላይ ይፍሰስ፥ ሥጋውንም ብሉ።
\s5
\v 28 በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት መልካምና ቅን የሆነውን ነገር ስታደርጉ ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ ለዘላለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ የማዝዛችሁን እነዚህን ቃሎች ሁሉ ሰምታችሁ ጠብቁ።
\s5
\v 29 እግዚአብሔር አምላካችሁ ትወርሱአቸው ዘንድ የምትሄዱባቸውን አሕዛብን ፊታችሁ ባጠፋ ጊዜ፥ እናንተም በወረሳችሁ ጊዜ፥ በምድራቸውም በተቀመጣችሁ ጊዜ፥
\v 30 ከፊታችሁ ከጠፉ በኋላ እነርሱን ለመከተል እንዳትጠመዱ፦ እነዚህ አሕዛብ አማልክታቸውን የሚያመልኩት እንዴት ነው? እንዲሁ ደግሞ እኔም አደርጋለሁ ብላችሁ ስለ አማልክታቸው እንዳትጠይቁ ተጠንቀቁ።
\s5
\v 31 እግዚአብሔር የሚጠላውን ርኩሰት ሁሉ እነዚህን ለአማልክታቸው አድርገዋል፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውንም ለአማልክታቸው በእሳት አቃጥሎአቸዋል፥ እናንተም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ እንዲሁ አታድርጉ።
\v 32 እኔ የማዝዛችሁን ነገር ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ፤ ምንም በእርሱ ላይ አትጨምሩ ከእርሱም ምንም አታጉድሉ።
\s5
\c 13
\p
\v 1 በመካከላችሁም፦ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክት ወይም ተአምራት ቢሰጣችሁ፥ እንደ ነገራችሁም
\v 2 ምልክቱ ወይም ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም፦ የማታውቃቸውን ሌሎች አማልክት ሄደን እንከተል እናምልካቸውም ቢላችሁ፥
\v 3 እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁ ትወድዱት እንደሆነ ያውቅ ዘንድ እግዚአብሔር አማላካችሁ ሊፈትናችሁ ነውና፥ የዚያን ነቢይ ቃል ወይም ያን ሕልም አላሚ አትስሙ።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር አምላካችሁን ተከተሉ፥ እርሱንም አክብሩ፥ ትእዛዘትንም ጠብቁ፥ ድምፁንም ስሙ፥ እርሱንም አምልኩት፥ ከእርሱም ጋር ተጣበቁ።
\v 5 ከግብፅ ምድር ካወጣችሁና ከባርነት ቤት ካዳናችሁ ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ሊያስታችሁ ስለተናገረ ያ ነቢይ ወይም ያ ሕልም አላሚ ይገደል። ያም ነቢይ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትሄዱበት ካዘዛችሁ መንገድ ሊያወጣችሁ ነው። ስለዚህ ክፉውን ነገር ከመካከላችሁ አርቁ።
\s5
\v 6 የእናታችሁ ልጅ፥ ወንድማችሁ ወይም ወንድ ልጃችሁ ወይም ሴት ልጃችሁ ወይም በብብታችሁ ያለች ሚስታሁ ወይም እንደ ነፍሳችሁ የምትቆጥሩት ወዳጃችሁ በስውርም ሊፈትናችሁ፦ ኑ፥ እናንተ ወይም አባቶቻችሁ የማታውቁአችሁን አማልክት ሄደን እናምልክ ብሉአችሁ፥
\v 7 ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ሌላኛው ምድር ዳር ድረስ ወደ እናንተ የቀረቡት ከእናንተም የራቁት በዙሪያችሁ ያሉ አሕዛብ ከሚያመልኩአቸው አማልክት ቢያስታችሁ እሺ አትበሉ።
\s5
\v 8 አትስማሙአቸው፤አትስማቸውም። ዓይናችሁም አይራራላቸው፥ አትምራቸውም፥ አትሸሽጋቸውም።
\v 9 በዚህ ፈንታ ፈጽማችሁ ግደሉአቸው፤ እርሱን ለመግደል የእናንተ እጅ በእርሱ ላይ ይሁን፤ ከዚያም በኋላ የሕዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ይሁን።
\s5
\v 10 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ካወጣችሁ ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ሊያርቃችሁ ወድዶአልና፥ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገሩት።
\v 11 እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምተው ይፈራሉ፥ በመካከላችሁም እንዲህም ያለ ክፉ ሥራ ለማድረግ አይቀጥሉም።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር አምልካችሁ ልትኖሩባችሁ በሚሰጣችሁ በአንዲቱ ከተማችሁ እንዲህ ሲባል ብትሰሙ፡-
\v 13 አንዳንድ ክፉ ሰዎች ከእናንተ መካከል ወጥተው፦ የማታውቋቸውን ሌሎችን አማልክት ሄደን እናምልክ ብለው የከተማቸውን ሰዎች አሳቱ፥ ሲሉ ብትሰሙ፤
\v 14 ታጣራላችሁ፥ ትመረምራላችሁ፥ በሚገባም ትጠይቃላችሁ። እነሆም፥ ይህም ክፉ ነገር በመካከላችሁ እንደ ተደረገ እውነት ሆኖ ቢገኝ።
\s5
\v 15 የዚያችን ከተማ ሰዎች በሰይፍ ስለት ፈጽሞ ትመታቸዋላችሁ፤ ከተማይቱን በእርስዋም ያለውን ሁሉ እንስሳውንም በሰይፍ ስለት ታጠፉአቸዋላችሁ።
\v 16 ዕቃዋንም ሁሉ ወደ አደባባይዋ ትሰበስባላችሁ፥ ከተማይቱንም ዕቃዋንም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በእሳት ፈጽማችሁ ታቃጥላላችሁ፤ እንደ ገና የማትሠራ ሆና ለዘላለም እንደ ፈረሰች ትቀራለች።
\s5
\v 17 ለጥፋት ከተለዩ ነገሮች ምንም እርም ነገር በእጃችሁ አይገኙ። እግዚአብሔር ከቁጣ ትኩሳት ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶቻችሁም እንደማለላቸው ይምራችሁና ይራራላችሁ ዘንድ፥ ያበዛላችሁም ዘንድ ነው።
\v 18 ዛሬ እኔ የማዝዛችሁን ትእዛዘት ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኘውን ታደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ቃል ስሙ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 እናንተ የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ሕዝብ ናችሁ። ስለ ሞተው ሰው አካላችሁን አታቆስሉ፥ የትኛውንም የፊታችሁን ክፍል አትላጩ።
\v 2 ምክንያቱም እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ፤ በምድርም ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለራሱ ሕዝብ ትሆኑ ዘንድ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን መርጦአልና።
\s5
\v 3 ርኩስን ነገር ሁሉ አትብሉ።
\v 4 የምትበሉአቸው እንስሶች እነዚህ ናቸው፦ በሬ፥ በግ፥ ፍየል፥
\v 5 ዋላ፥ ሚዳቋ፥ የበረሃ አጋዘን፥ አጭ፥ በራይሌ፥ የተራራ በግ (ድኩላ)።
\s5
\v 6 ከእንስሶች ሰኮናው የተሰነጠቀውን ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን የሚያመነዥከውንም እንስሳ ሁሉ ትበላላችሁ።
\v 7 ነገር ግን ከማያመሰኩ ወይም ሰኮናቸው ካልተሰነጠቀ፥ እነዚህን አትበሉም፤ ግመል፥ ጥንቸል፥ ሽኮኮን፥ አትበሉም። የሚያመነዥኩና ነገር ግን ሰኮናቸው ያልተሰነጠቀም እነዚህ ለእናንተ ርኩሶች ናቸው።
\s5
\v 8 እርያም ሰኮናው ስለ ተሰነጠቀ ነገር ግን ስለማያመነዥክ፥ እርሱ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ ሥጋውን አትብሉ በድኑንም አትንኩ።
\s5
\v 9 በውኃ ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው፤ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ።
\v 10 ነገር ግን ክንፍና ቅርፊትም የሌላቸውን አትበሉም፥ ለእናንተ ርኩስ ናቸው።
\s5
\v 11 ንጹሕ የሆኑትን ወፎችን ሁሉ ትበላላችሁ።
\v 12 ነገር ግን ከወፎች ሊበሉ የማይገባቸው እነዚህ ናቸው። ንስር፥ ገዴ፥ ዓሣ አውጭ፥
\v 13 ጭልፊት፥ ጭላት፥ በየወገኑ፥
\s5
\v 14 ቁራም ሁሉ በየወገኑ፥
\v 15 ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቃል፥ በየወገኑ፥
\v 16 ጉጉት፥ ጋጋኖ፥
\v 17 የውኃ ዶሮ ይብራ፥
\s5
\v 18 ጥምብ አንሣ፥ አሞራ፥ እርኩም ሽመላ ሳቢሳ፥ በየወገኑ፥ ጅንጅላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ፥።
\v 19 የሚበርርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ አይበሉም።
\v 20 ንጹሕ የሆኑትን ወፎች ሁሉ ብሉ።
\s5
\v 21 የበከተውን ሁሉ አትብሉ፥ ይበላው ዘንድ በአገራችሁ ደጅ ለተቀመጠ፥ መጻተኛ ትሰጠዋላችሁ፥ ወይም ለእንግዳ ትሸጣላችሁ። ምክንያቱም እናንተ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የተቀደሰ ሕዝብ ናችሁ። የፍየሉን፥ ጠቦት፥ በእናቱ ወተት አትቀቅሉ።
\s5
\v 22 ከእርሻችሁ በየዓመቱ ከምታገኙት ከዘራችሁ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣላችሁ።
\v 23 ሁልጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁን መፍራት ትማሩ ዘንድ ስሙ፤ እንዲጠራበት በመረጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት የእህላችሁን የወይን ጠጃችሁንም የዘይታችሁንም አሥራት የላማችሁንና የበጋችሁንም በኩራት ብሉ።
\s5
\v 24 እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ ጊዜ መንገዱ ሩቅ ቢሆን፥ እግዚአብሔር አምላካችሁም ስሙን ያኖርበት ዘንድ የመረጠው ስፍራ ቢርቅባችሁ ግን ወደዚያ ለመሸከም ባትችሉ ትሸጣላችሁ፥
\v 25 የዋጋውንም ገንዘቡ በእጃችሁ ይዛችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደ መረጠው ስፍራ ትሄዳላችሁ።
\s5
\v 26 በዚያም በገንዘቡ የፈለጋችሁትን በሬ ወይም፥ በግ ወይም፥ የወይን ጠጅ፥ ወይም ብርቱ መጠጥ፥ ወይም የፈለጋችሁትን ሁሉ ትገዛላችሁ፤ በዚያም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ትበላላችሁ፥ እናንተና ቤተ ሰባችሁም ደስ ይላችኋል።
\v 27 ድርሻና ርስት ከእናንተ ጋር ስለሌለው በአገራችሁ ደጅ ውስጥ ያለውን ሌዋዊውን ቸል አትበሉ።
\s5
\v 28 በየሦስተኛው ዓመት መጨረሻ በዚያ ዓመት ሌዋዊው ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለ የፍሬአችሁን አሥራት ሁሉ አምጥታችሁ በአገራችሁ ደጅ ታኖራላችሁ፤
\v 29 በአገራችሁም ደጅ ያለ መጻተኛ፥ ድሀ አደግ፥ ባል የሞተባት መጥተው ይበላሉ፤ ይጠግባሉም። ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደርጉት በእጃችሁ ሥራ ሁሉ ይባርካችሁ ዘንድ ነው።
\s5
\c 15
\p
\v 1 በየሰባት ዓመት የዕዳ ምሕረት ታደጋላችሁ።
\v 2 ይህ ዕዳ ምሕረት አፈጻጸም እንከሚከተለው ነው፤ አበዳሪ ሁሉ ለባልንጀራው ላበደረው እንዲተውዋውና ከባልጀራው ወይም ወንድሙ መልሶ እንዳይጠይቅ እግዚአብሔር ያወጀው ይህ ነው።
\v 3 ለእንግዳ ያበደራችሁትን መጠየቅ የምትችሉ ሲሆን፥ ለእስራኤላዊ ወንድማችሁ ያበደራችሁትን ግን ምሕረት አድርጉለት።
\s5
\v 4 ይሁን እንጂ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ትወርሱአት ዘንድ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ውስጥ አብዝቶ ስለሚባርካችሁ በመካከላችሁድኻ አይኖርም።
\v 5 ይህ የሚሆነው የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ድምፅ ፈጽማችሁ ስትሰሙና ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዘትን ሁሉ ስትታዘዙ ብቻ ነው።
\v 6 እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ተሰፋ መሠረት ስለሚባርካችሁ እናንተ ለብዙ አሕዛብ ታበድራላችሁ እንጂ እናንተ አትበደሩም፤ብዙ አሕዛብን ትገዛላችሁ እንጂ ማንም እናንተን አይገዛችሁም።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ደኻ ቢኖር፥ በደኻ ወንድማችሁ ላይ ልባችሁ አይጨክን፥ለደኻ ወንድማችሁ ላይም እጃችሁን ከመዘርጋት አትቆጥቡ፤
\v 8 ነገር ግን እጃችሁን በትክክል ፍቱለት ለማያስፈልገውም ቅር ሳትሉ አበድሩት።
\s5
\v 9 ዕዳ የሚሠርዝበት ሰባተኛ ዓመት ቀርቦአል፥ በማለት ክፉ አሳብ አድሮባችሁ በችግረኛ ወንድማችሁ ላይ እንዳትጨክኑና ምንም ሳትሰጡት እንዳይቀር እርሱ በእናንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኾ በደለኞች እንዳትሆኑ ተጠንቀቁ።
\v 10 በቅን ልቦና ስጡት፥ ስትሰጡትም ልባችሁ አይጸጸት፥ከዚያም የተነሣ ግዚአብሔር አምላካችሁ ሥራችሁንና እጃችሁን ያረፈበትን ሁሉ ይባርክላችኋል።
\s5
\v 11 በምድሪቱ ላይ ሁልጊዜ ድኾች አይጠፉም፥ስለዚህ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞቻችሁ ለድኾችና ለችግራኞች እጃችሁን እንድትዘረጉ አዛችኋለሁ።
\s5
\v 12 እናንተም ወንድማችሁን ዕብራዊውን ወይም ዕብራዊቱን ብትገዙ ስድስት ዓመት ያገልግላችሁ በሰባተኛውም ዓመት ከእናንተ ዘንድ አርነት አውጡት።
\v 13 ከእናንተም ዘንድ አርነት በሚታወጣበት ጊዜ ባዶውን አትስደዱት።
\v 14 ነገር ግን ከመንጋህ፥ ከአውድማችሁም፥ ከወይራችሁም መጥመቂያም ትለግሱታላችሁ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን ትሰጡት ዘንድ ይገባል።
\s5
\v 15 እናንተም በግብፅ አገር ባሮች እንደ ነበራችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁም እንደ ነበራችሁ አስቡ፤ስለዚህ እኔ ዛሬ ይህን እንድታደርጉ አዛችሁኋለሁ።
\v 16 ነገር ግን አገልጋያችሁ እናንተንና ቤተ ሰቦቻችሁን በመውደዱና ከእናንተ ጋር ደስተኛ ሆኖ ከመኖሩ የተነሣ፦ ከእናንተ መለየት አልፈልግም ቢላችሁ፦
\v 17 ጆሮውን ከቤታችሁ መዝጊያ ላይ በማስደግፍ በወስፌ ትበሳላችሁ፤ከዚያም ዕድሜ ልኩን አገልጋያችሁ ይሆናል። በቤት አገልጋዮችሁም ላይ እንዲሁ አድርግ።
\s5
\v 18 አገልጋያችሁን አርነት ማውጣት ከባድ መስሎ አይታያችሁ፤ ምክንያቱም የስድስት ዓመት አገልግሎቱ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር አምላካችሁ በምታደጉት ነገር ሁሉ ይባርካችኋልና።
\s5
\v 19 የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን ተባዕት በኩር ሁሉ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቀድሱ። የበሬአችሁን በኩር አትሥሩባቸው፥ የበጋችሁንም በኩር አትሸልቱ፥
\v 20 እርሱ በሚመርጠው ስፍራ እናንተና ቤተ ሰባችሁ በየዓመቱ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ትበሉታላችሁ።
\v 21 አንድ እንስሳ እንከን ካለበት፤ አንካሳ ወይም ዕውር ወይም ደግሞ ማናቸውም ዓይነት ከባድ ጉድለት ያለበት ከሆነ፤ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር አትሠዉ።
\s5
\v 22 የከተሞቻችሁ ትበላላችሁ፤ በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነውም ሆነ ያልሆነው ሰው፥ እንደ ድኩላ እንደ ዋላ ያሉትን ይበላዋል።
\v 23 ደሙን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሱት እንጂ አትብሉት።
\s5
\c 16
\p
\v 1 እግዚአብሔር አምላካችሁ በአቢብ ወር ከግብፅ በሌሊት ስላወጣችሁ የአቢብ ወር ጠብቁ፥ የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ፋሲካ አክብሩበት።
\v 2 እግዚአብሔር ለሰሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ በሚመርጠው ስፍራ ከበግና ከፍየል ወይም ከመንጋችሁ አንዱን እንስሳ እግዚአብሔር በአምላካችሁ ፋሲካ አድርጋችሁ ሠዉ።
\s5
\v 3 ከቦካ ቂጣ ጋር አትብሉ፤ ከግብፅ የወጣችሁ በችኮላ ነውና፥ ከግብፅ የወጣችሁበትን ጊዜ በሕይወታችሁ ዘመን ሁሉ ታስቡ ዘንድ ያልቦካ ቂጣ ሰባት ቀን ብሉ።
\v 4 ከምድራችሁ ሁሉ ላይ በእናንተ ዘንድ ለሰባት ቀን እርሾ አይገኝ በመጀመሪያው ዕለት ምሽት ከምትሠዉም ላይ ማናቸውም ሥጋ እስከ ጧት ድረስ እንዲቆዩ አታድርጉ።
\s5
\v 5 እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ በማናቸውም ከተማ በሮች ላይ ፋሲካን መሠዋት አይገባችሁም።
\v 6 በዚህ ፈንታ፥ ለስሙ ማደሪያ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር አምላካችን በመረጠው ስፍራ ፀሐይ ስትጠልቅ በምሽት ላይ ከግብፅ ከወጣችሁበት ሰዓት ላይ በዚያ ፋሲካ ሰዉ።
\s5
\v 7 ሥጋውንም ጠብሳችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚመርጠው ስፍራ ብሉ፥ ሲነጋም ወደ ድንኳናችሁ ተመልሳችሁ ሂዱ።
\v 8 ለስድስት ቀንም ያልቦካ ቂጣ ብሉ፤ በሰባተኛው ቀን በእግዚአብሔር በአምላካችሁ የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ሥራም አትሥሩበት።
\s5
\v 9 እህላችሁን ማጨድ ከምትጀምሩበት ዕለት አንሥቶ ለራሰችሁም ሰባት ሳምንታትን ቁጠሩ።
\v 10 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን በፈቃዳችሁ የምታመጡትን ስጦታ በማቅረብ በመከሩ በዓል እግዚአብሔር አምላካችሁን አክብሩ።
\s5
\v 11 እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ወንዶችና ሴቶች አጋልጋዮቻችሁ በከተሞቻችሁ ያለ ሌዋዊና መጻተኛ በመካከላችሁ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና ባል የሞተባቸው እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን በሚመርጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ።
\v 12 እናንተም በግብፅ ባሪያዎች እንደ ነበራችሁ አስታውሱ፥ እነዚህንም ሥርዓቶች በጥንቃቄ ጠብቁ አድርጉም።
\s5
\v 13 የእህላችሁን ምርት ከዐውድማችሁ ፤ ወይናችሁንም ከመጭመቂያችሁ ከሰበሰባችሁ በኋላ የዳስን በዓል ሰባት ቀን አክብሩ።
\v 14 በበዓላችሁ እናንተና ወንድና ሴት ልጆቻችሁ፥ ወንድና ሴት አገልጋዮቻችሁ፥ በከተማው ያለ ሌዋዊ መጻተኛ፥ አባት አልባውና ባል የሞተባት ደስ ይበላችሁ።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በዓሉን ሰባት ቀን አክብሩ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በእህል ምርታችሁና በእጆቻችሁ ሥራ ሁሉ ይበርካችኋል፤ ደስታችሁም ፍጹም ይሆናል።
\s5
\v 16 ወንዶቻችሁ ሁሉ በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በመከር በዓልና በዳስ በዓል ላይ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ይቅረቡ፥ ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ባዶ እጁን አይቅረብ፥
\v 17 በዚህ ፈንታ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ።
\s5
\v 18 እግዝዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ከተማ ሁሉ ለየነገዶቻችሁ ዳኞችንና አለቆችን ሹሙ፥ እነርሱም ሕዝቡን በቅን ፍርድ ይዳኙ፥
\v 19 ፍርድ አታዛቡ፥ አድልዎ አታደርጉ፥ ጉቦም አትቀበሉ፥ ጉቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና።
\v 20 በሕይወት እንድትኖሩና እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚሰጣችሁን ምድር እንድትወርሱ ቅን ፍርድን ብቻ ተከተሉ።
\s5
\v 21 ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በምታደርጉት መሠዊያ አጠገብ የአሼራን ምስል የእንጨት ዐምድ አታቁሙ።
\v 22 እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚጠላውን ማምለኪያ ዐምድ ለእናንተ አታቁሙ።
\s5
\c 17
\p
\v 1 እንከን ወይም ጉድለት ያለበትን በሬ ወይም በግ እግዚአብሔር ለአምላክችሁ አትሠዉ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነውና።
\s5
\v 2 እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ከተሞች በሮች አብሮአችሁ የሚኖር ወንድ ወይም ሴት ኪዳኑን በማፍረስ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ሲፈጽም ቢገኝ፥
\v 3 ትእዛዜንም በመተላለፍ ባዕዳን አማልክትን ያመለከ፥ ለእርሱም ማለትም ለፀሐይ ወይምለጨረቃ ወይም ለሰማይ ከዋክብት የሰገደ፥
\v 4 እናንተ ይህ መደረጉን ብትሰሙ ነገሩን በጥንቃቄ መርምሩ፥ የተባለውም እውነት ከሆንና እንዲህ ያለ አስጸያፊ ነገር በእስራኤል ዘንድ መፈጸሙ ከተረጋገጠ፥
\s5
\v 5 ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስዳችሁ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገሩት።
\v 6 ሞት የሚገባው ሰው በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፥ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል።
\v 7 ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት ክፉን ከመካከላችሁ አስወግዱ።
\s5
\v 8 በአንድ የነፍስ ግድያ ዓይነትና በሌላ በአንድ ዓይነት ሕጋዊ ክርክርን በሌላ ወይም በአንድ የክስ ዓይነትና በሌላ መካከል ውሳኔ የሚጠይቅ ማንኛውም ጉዳይ ቢነሣ፥ ከአቅማችሁ በላይ የሆነ ጉዳይ በከተሞቻችሁ ውስጥ ቢያጋጥማችሁ፥ ተነሥታችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚመርጠው ስፍራ ውጡ።
\v 9 ካህናት ወደ ሆኑት ሌዋውያንና በዚያን ጊዜ ዳኛ ወደ ሆነው ሰው ሄዳችሁ ስለ ጉዳዩ ጠይቁአቸው፥ እነርሱም ውሳኔውን ይነግሩአችኋል።
\s5
\v 10 እናንተም እግዚአብሔር በሚመርጠው ስፍራ እነርሱ በሚሰጡአችሁ ውሳኔ መሠረት ፈጽሙ። እንድፈጽሙ የሚሰጡአችሁን መመሪያ ሁሉ በጥንቃቄ አድርጉ፥
\v 11 በሚያስተምሩአችሁ ሕግና በሚሰጡአችሁ መመሪያዎች መሠረት ፈጽሙ፥ እነርሱ ከሚነግሩአችሁ ቀኝም ግራም አትበሉ።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር አምላካችሁን ለማገልገል በዚያ የሚቆመውን ካህን ወይም ዳኛ የሚንቅ ይገደል፥ ከእስራኤልም መካከል ክፉውን አስወግዱ።
\v 13 ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲሰማ ይፈራል፤ ከዚያ ወዲያም እንዲህ ያለውን የንቀት ድርጊት አይደግመውም።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፥ በምትወርሱአትና በምትቀመጡባት ምድር በዙርያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ ብትሉ፥
\v 15 ከዚያ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ የሚመርጠውን ንጉሥ በላይህ ታነግሣለህ፥ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንጂ እስራኤላዊ ወንድምህ ያልሆነውን ባዕድ በላይህ አታንግሥ።
\s5
\v 16 ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቁጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስ፤
\v 17 እግዚአብሔር በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ፥ ብሎአችኋልና፤ ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፥ ብዙ ብር ወይም ወርቅ ለራሱ አያብዛ።
\s5
\v 18 በመንግሥቱ ዙፋን ላይ በሚቀመጥበትም ጊዜ የዚህን ሕግ ቅጅ ከሌዋውያን ካህናት ወስዶ በጥቅልል መጽሐፍ ለራሱ ይጻፍ።
\v 19 እግዚአሔር አምላኩን ማክበር ይማር ዘንድ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉና ይህን ሥርዓት በጥንቅቄ ይጠብቅ ዘንድ ከእርሱ ጋር ይሁን፤በሁሉም ቀኖች ያንብበው።
\s5
\v 20 ይህን የሚያደርገው ከወንድሞቹ ላይ ልቡ እንዳይኮራ፥ ከትእዛዘትም ወደ ኋላ እንዳይመለስ፥ እርሱና ልጆቹም ረጅም ዘመን ይገዙ ዘንድ፥ ከሕጉ ቀኝ ወይም ግራም አበል።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ሌዋውን ካህናት፥ የሌዊ ነገድ ሁሉ ከእስራኤል ጋር የመሬት ድርሻ ወይም ርስት ስለማይኖራቸው ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርበው ድርሻቸው ነውና ይብሉ።
\v 2 እግዚአብሔር በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እርሱ ራሱ ርስታቸው ስለሆነ በወንድሞቻቸው መካከል ርስት አይኖራቸውም።
\s5
\v 3 ኮርማ ወይም በግ የሚሠዋው ሕዝብ ለካህኑ የሚሰጠው ድርሻ ወርቹን፥ ሁለት ጉንጮችንና የሆድ ዕቃውን ነው።
\v 4 የእህላችሁን፥ የአዲሱን ወይናችሁንና የዘይታችሁን በኩራት እንዲሁም ከበጎቻችሁ በመጀመሪያ የተሸለተውን ጠጉር ትሰጣላችሁ።
\v 5 በእግዚአብሔር ስም ቆሞ ለዘላለም ያገለግል ዘንድ እግዚአብሔር አምላክህ ከነገዶቻችሁ ሁሉ እርሱንና ዘሮቹን መርጦአል።
\s5
\v 6 አንድ ሌዋዊ ከሚኖርበት ከየትኛውም በእስራኤል ካሉት ከተሞቻችሁ መካከል በፍጹም ፈቃድ እግዚአብሔር ወደሚመርጠው ስፍራ ቢመጣ፥
\v 7 በእግዚአብሔር ፊት ቆመው እንደሚያገለግሉት ሌዋውያን ወንድሞቹ፥ እርሱም በእዚግአብሔር በአምላኩ ስም ያገልግል።
\v 8 ከቤተ ሰቡ ንብረት ሽያጭ ላይ ገንዘብ ቢቀበል እንኳ ባልንጀሮቹ ከሚያገኙት ጥቅም እኩል ይካፈላል።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር አምላካችሁ ወደሚሰጣችሁ ምድር በምትገቡበትጊዜ በዚያ የሚኖሩት አሕዛብ የሚፈጽሙትን አስጸያፊ መንገድ አትከተሉ።
\v 10 በመካከላችሁ ወንድ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሥዋ ሟርተኛ፥ ወይም መተተኛ፥ ሞራ ገለጭ፥ ጠንቋይ፥ ወይም በድግምት የሚጠነቁል፥
\v 11 መናፍስት ጠሪ ወይም ሙት አነጋጋሪ በመካከላችሁ ከቶ አይገኝ።
\s5
\v 12 እነዚህን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ ከእነዚህ አጸያፊ ልምዶች የተነሣ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚያን አሕዛብ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል።
\v 13 በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ነውር የሌላው ይሁን።
\v 14 ምድራቸውን የምታስለቅቃቸው አሕዛብ፥ መተተኞችን ወይም ሟርተኞችን ያዳምጣሉ፤ እናንተ ግን ይህን እንድታደርጉ እግዚአብሔር አምላካችሁ አልፈቀደላችሁም።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር አምላካችሁ ከገዛ ወንድሞቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣላችኋል። እርሱን አድምጡ።
\v 16 በኮሬብ ጉባኤ በተደረገበት ዕለት እንዳልሞት የእግዚአብሔር የአምላካችሁን ድምፅ አንስማ፤እንዲህ ያለውንም አስፈሪ እሳት ደግመን አንይ ብላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁን የጠየቃችሁት ይህ ነውና።
\s5
\v 17 እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ የተናገሩት መልካም ነው።
\v 18 ከወንድሞቻቸው መካከል እንደ አንተ ያለ ነቢይ አስነሣላቸዋለሁ። ቃሌን በአፉ አደርጋለሁ፤ የማዘውንም ሁሉ ይነግራቸዋል።
\v 19 ማንም ሰው ነቢዩ በስሜ የሚናገረውን ቃሌን ባይሰማ፤ እኔ ራሴ ተጠያቂነት አደርገዋለሁ።
\s5
\v 20 ነገር ግን እንዲናገር እኔ ያላዘዝሁትን ቃል በድፍረት በስሜና በሌሎች አማልክት ስም የሚናገር ነቢይ ይገደል።
\v 21 እናንተም በልባችሁ እግዚአብሔር ያልተነገረውን መልእክት እንዴት ማወቅ እንችላለን? ብትሉ፥
\s5
\v 22 ነቢዩም በእግዚአብሔር ስም የተናገርው ካልተፈጸመ ወይም እውነት ሆኖ ካልተገኘ፤ መልእክቱ እግዚአብሔር የተናገርው አይደለም። ያ ነቢይ በድፍረት ተናግሮታልና እርሱን አትፍራው።
\s5
\c 19
\p
\v 1 እግዚአብሔር አምላካችሁ ምድራቸውን ለእናንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ በሚደመስሳቸው ጊዜና እናንተም እነርሱን አስለቅቃችሁ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጡበት ጊዜ፥
\v 2 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር አማካይ ስፍራ ሦስት ከተሞችን ለራሳችሁ ምረጡ፥
\v 3 ሰው የገደለ ሁሉ እንዲሸሽባቸው እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር መንገዶችን ሠርታችሁ በሦስት ክፈሉአቸው።
\s5
\v 4 በተንኮል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ገድሎ ሕይወቱን ለማትረፍ ለሚሸሽ ሰው መመሪያው የሚከተለው ነው።
\v 5 እነሆ፥ አንድ ሰው ከባልንጀራው ጋር እንጨት ለመቁረጥ ወደ ጫካ ቢሄድ፥ ዛፉን ለመጣል መጥረቢያውን በሚሰነዝርበት ጊዜ ብረቱ ከእጀታው ወልቆ ባልንጀራውን በመምታት ቢገድለው፥ ያ ሰው ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ በመሸሽ ሕይወቱን ማትረፍ ይችላል።
\s5
\v 6 አለበለዚያ በተንኮል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፥ መንገዱ ረጅም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል። ይህ ከመሆኑ በፊት ባልንጀራውን ያልጠላ ከሆነ መሞት አይገባውም።
\v 7 ሦስት ከተሞችን ለራሳችሁ እንድትመርጡ ያዘዙአችሁ በዚሁ ምክንያት ነው።
\s5
\v 8 ለአባቶቻችሁ በመሐላ በገባላቸው ቃል መሠረት አምላካችሁ እግዚአብሔር ወሰናችሁን ሲያሰፋውና ለእነርሱ በሰጣቸው መሠረት ምድሪቷን ሁሉ ሲሰጣችሁ፤
\v 9 እግዝክአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱና ምን ጊዜም በመንገዱ እንድትሄዱ ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ሕግጋት ሁሉ በጥንቃቄ የምትጠብቁ ከሆነ በእነዚህ ላይ ሌሎች ሦስት ከተሞችን ትጨምራላችሁ።
\v 10 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር የንጹሕ ሰው ደም እንዳይፈስና በሚፈሰውም ደም በደለኛ እንዳትሆኑ ይህን አድርጉ።
\s5
\v 11 ነገር ግን አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፥ ቢገድለውና ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥
\v 12 የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፥ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት።
\v 13 አትራራለት፥ ነገር ግን መልካም እንዲሆንላችሁ የንጹሑን ደም በደል ከእስራኤል አስወግዱ።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት በሚሰጣችሁ ምድር ውስጥ ለእናንተ በሚተላለፍላችሁ ርስት ላይ የቀድሞ ሰዎች ያስቀመጡትን የባልጀራችሁን የድንበር ምልክት አታንሡ።
\s5
\v 15 በማንኛውም ወንጀል ወይም ሕግ በመተላለፍ ሰውን ጥፋተኛ ለማድረግ አንድ ምስክር አይበቃም፥ጉዳዩ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት መረጋገጥ አለበት።
\v 16 ተንኮለኛ የሆነ ምስክር አንድን ሰው በሐሰት ለመመስከር ቢነሣ፤
\s5
\v 17 ክርክሩ የሚመለከታቸው ሁለቱ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ።
\v 18 ፈፋጆችም ጉዳዩን በጥልቅ ይመርምሩት፥
\v 19 ያም ምስክሩ በወንድሙ ላይ በሐሰት የመሰከረ መሆኑ ከተረጋገጠ በወንድሙ ላይ ለማድረግ ያሰበውን በእርሱ ላይ አድርጉበት ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግዱ።
\s5
\v 20 የቀሩትም ሰዎች ይህን ሰምተው ይፈራሉ፤ እንዲህ ያለው ክፉ ነገርም ለወደፊቱ በመካከላችሁ ከቶ አይደገምም።
\v 21 ርኅራኄ አታድርጉ ሕይወት ለሕይወት፥ ዐይን ለዐይን፥ ጥርስ ለጥርስ፥ እጅ ለእጅ፥ እግር እግር ይመለስ።
\s5
\c 20
\p
\v 1 ጠላቶቻችሁን ለመውጋት ወደ ጦርነት ስትሄዱ ሠርገሎችንና ፈረሶችን ከእናንተ የሚበልጥ ሰራዊትንም በምታዩበት ጊዜ፥ አትፍሩአቸው፥ ከግብፅ ያወጣችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንተ ጋር ነውና።
\s5
\v 2 ወደ ውጊያው ቦታ ስትቃረቡ፥
\v 3 ካህኑ ወደ ፊት ወጣ ብሎ ለሠራዊቱ ይናገር፥ እንዲህም ይበል እስራኤል ሆይ ስማ በዛሬው ቀን ጠላቶቻችሁን ለመግጠም ወደ ጦርነት ልትገቡ ነው። ልባችሁ አይባባ፤ አትፍሩ፤ አትደግጡ፤ በጠላቶቻችሁ ፊት አትሸበሩ።
\v 4 ድልን ያቀዳጃችሁ ዘንድ ስለ እናንተ ጠላቶቻችሁን ሊወጋ አብሮአችሁ የሚወጣው አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና።
\s5
\v 5 አለቆቹም ለሠራዊት እንዲህ ይበሉ፥ አዲስ ቤት ሠርቶ ያላስመረቀ አለን? ወደ ቤቱ ተመልሶ ይሂድ፥ ያለበለዚያ በጦርነቱ ላይ ሲሞት፥ ቤቱን የሚያስመርቀው ሌላ ሰው ይሆናል።
\s5
\v 6 ወይን ተክሎ ገና ያልበላለት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፣ ያለበለዚያ በጦርነቱ ሲሞት፥ ሌላ ሰው ይበለዋል።
\v 7 ሚስት አጭቶ ያላገባት አለን? ወደ ቤቱ ይመለስ፥ ያለበለዚይ በጦርነቱ ሲሞት ሌላ ሰው ያገባታል።
\s5
\v 8 በዚያም አለቆቹ፦ የሚፈራ ወይም ልቡ የሚባባ ሰው አለን? የወንድሞችም ልብ እንዳይባባ፥ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ በማለት ጨምረው ይናገሩ።
\v 9 አለቆቹ ለሰራዊቱ ተናግረው ሲያበቁ አዛዦችን በሰራዊቱ ላይ ይሹሙ።
\s5
\v 10 አንድን ከተማ ለመውጋት በምትዘምቱበት ጊዜ አስቀድማችሁ ለሕዝቧ የሰላም ጥሪ አስተላልፉ፥
\v 11 ከተቀበሉአችሁና ደጃቸውን ከከፊቱላችሁ በከተማዋ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ የጉልበት ሥራ ይሥሩ፥ ያገልግላችሁም።
\s5
\v 12 ዕርቀ ሰላምን ባለመቀበል ውጊያ ከመረጡ፥ ከተማዪቱን ክበቡአት።
\v 13 እግዚአብሔር አምላካችሁ አሳልፎ በእጃችሁ በሰጣችሁ ጊዜ በውስጧ ያሉትን ወዶች በሙሉ በሰይፍ ግደሉአቸው።
\s5
\v 14 ነገር ግን ሴቶቹን ሕፃናትን እንስሳትንና በከተምዩቱ ውስጥ የሚገኘውን ማናቸውንም ነገር በምርኮ ለራሳችሁ አድርጉ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከጠላቶቻችሁ የሚሰጣችሁን ምርኮ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
\v 15 እንግዲህ የአካባቢያችሁ አሕዛብ ከተሞች ባልሆኑትና ከእናንተ እጅግ ርቀው በሚገኙት ከተሞች ሁሉ ላይ የምታደርጉት ይኸው ነው።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ በአሕዛብ ከተሞች ውስጥ እስትንፋስ ያለውን ነገር አታስተርፉ።
\v 17 በዚህ ፈንታ፥ ኬጢያዊውን፥ አሞራዊውን፥ ከነዓናዊውን፥ ፌርዛዊውን፥ ኤዊያዊውን፥ ኢያቡሳዊውን እግዚአብሔር አምላካችሁ ባዘዛችሁ መሠረት ፈጽማችሁ ደምስሱአቸው።
\v 18 አለበለዚያ አማልክታቸውን በሚያመልኩበት ጊዜ የሚፈጽሟቸውን አስጻያፊ ተግባራት ሁሉ ታደርግ ዘንድ ያስተምሩአችኋል፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ላይ ኃጢአት ትሠራላችሁ።
\s5
\v 19 አንድን ከተማ ተዋገታችሁ ለመያዝ የረጅም ጊዜ ከበባ በምታድርጉበት ጊዜ፥ ዛፎቹን በመጥረቢያ ጨፍጭፋችሁ ማጥፋት የለባችሁም። የዛፎችን ፍሬ መብላት ስለምትችሉ አትቁረጡአቸው። ከባችሁ የምታጠፉአችሁ የሜዳ ዛፎች ሰዎች ናቸውን?
\v 20 የሚበላ ፍሬ እንደማያፈራ የምታውቁትን ዛፍ ግን ልትቆርጡና ጦርነት የምታካሄዱባትን ከተማ በድል እስክትቆጣጠሩአት ድረስ ለከበባው ምሽግ መሥሪያ ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ።
\s5
\c 21
\p
\v 1 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንድትወርሱአት በሚሰጣችሁ ምድር ላይ አንድ ሰው ተገድሎ ሜዳ ላይ ቢገኝና ገዳዩም ማን እንደ ሆነ ባይታወቁ፥
\v 2 ሽማግሌዎቻችሁና ዳኞቻችሁ ወጥተው የተገደለ ሰው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት አንሥቶ በአቅራቢያው እስካሉት ከተሞች ድረስ ያለውን ርቀት ይለኩ።
\s5
\v 3 ከዚያም የተገደለ ሰው ሬሳው ወድቆ ከተገኘበት ስፍራ በጣም ቅርብ የሆነችው ከተማ ሽማግሌዎች ለሥራ ያልደረሰችና ቀንበር ያልተጫነባትን ጊደር ይዘው፥
\v 4 ከዚያ በፊት ታርሶ ወይም ተዘርቶበት ወደማይታወቅ ወራጅ ውሃ ወዳለበት ሸለቆ ያምጡት። በዚያ ሸለቆም የጊደሪቱን አንገት ይስበሩ፥
\s5
\v 5 እንዲያገለግሉና በእግዚአብሔር ስም እንዲባርኩ፥ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።
\s5
\v 6 ከዚያም ሬሳው በተገኘበት አቅራቢያ ከተማ የሚኖሩ ሽማግሌዎች ሁሉ፥ በሸለቆው ውስጥ፥ አንገቷ በተሰበረው ጊደር ላይ እጃቸውን ይታጠቡ፤
\v 7 እንዲህም ብለው ይናገሩ፥ እጆቻችን ደም አላፈሰሱም፤ ድርጊቱ ሲፈጸምም ዐይኖቻችን አላዩም።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር ሆይ፥ ስለ ተቤዥኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፥ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ። ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል።
\v 9 በዚህም መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ቀና የሆነውን ስታደርጉ የንጹሑን ደም የማፍሰስ በደልን ከመካከላችሁ ታስወግዳላችሁ።
\s5
\v 10 ከጠላቶቻችሁ ጋር ጦርነት ልትገጥሙ ወጥታችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር እነርሱን በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአችሁ በማረካችሁ ጊዜ፥
\v 11 ከምርኮኞቹ መካከል ቆንጆ ሴት አይታችሁ ብትማርኩ፥ ሚስታችሁ ልታደርጉአት ትችላላችሁ፤
\v 12 ወደ ቤታችሁ ውሰዱአት፥ ጠጉሯን ትላጭ፥ ጥፍሯንም ትቁረጥ።
\s5
\v 13 ስትማርኩአት የለበሰችውንም ልብስ ታውልቅ፥ እቤታችሁ ተቀምጣ ለአባትና ለናቷ ወር ሙሉ ካለቀሰችላቸው በኋላ፥ ከእርሷ ጋር ለመተኛና ባል ልትሆለት፥ እርሷም ሚስት ልትሆናችሁ ትችላለች።
\v 14 ነገር ግን በእርሷ ደስተኛ ባትሆን፥ ወደምትፈልገው እንድትሄድ ነጻነት ስጡአት፥ ውርደት ላይ ስለ ጠላችኋት በገንዘብ ልትሸጡአት ወይም እንደ ባሪያ ልትቆጥሩአት አይገባችሁም።
\s5
\v 15 አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ቢኖሩት አንደኛዋን የሚወዳት፥ ሌላዋን ግን የሚጠላት ቢሆን፥ ሁለቱም ወንዶች ልጆችን ወልደውለት፥ በኩር ልጁ ግን የተወለደው ከማይወዳት ሚስቱ ቢሆን፥
\v 16 ንብረቱን ለልጆቹ በሚያወርስበት ጊዜ፥ የብኩርናን መብት ከማይወዳት ሚስቱ ከወለደው በኩር ልጅ ገፎ ከሚወዳት ሚስቱ ለተወለደው ልጁ በአድልዎ መስጠት አይገባውም፤
\v 17 በዚህ ፈንታ፥ ከተጠላችው ሚስቱ ለተወለደው ልጅ ካለው ሁብት ሁሉ ሁለት እጥፍ ድርሻውን በመስጠት ብኩርናውን ያስታውቅ ያ ልጅ የአባቱ ኃይል መጀመሪያ ነውና የብኩርና መብት የራሱ ነው።
\s5
\v 18 አንድ ሰው የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፥ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥
\v 19 አባትና እናቱ ይዘው በሚኖሩበት ከተማ በር ወዳሉት አለቆች ያምጡት፥
\s5
\v 20 ይህ ልጃችን እልከኛና ዐመፀኛ ነው፥ አይታዘዘንም አባካኝና ሰካራም ነው ብለው ለአለቆች ይንገሯቸው።
\v 21 ከዚያም በኋላ የከተማዪቱ ሰዎች ሁሉ እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ይወገሩት፥ ክፉውንም ከመካከላችሁ ታስወግዳላችሁ፥ እስራኤልም ሁሉ ይህን ሰምቶ ይፈራል።
\s5
\v 22 አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና ሬሳው በእንጨት ላይ ቢሰቀል፥
\v 23 ሬሳውን በእንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድሩት ምክንያቱም በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሚሰጣችሁን ምድር እንዳታረክሱ በዚያኑ ዕለት ቅበሩት።
\s5
\c 22
\p
\v 1 የእስራኤላዊ ወንድማችሁ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታዩ ወደ እርሱ መልሳችሁ አምጡለት እንጂ ዝም ብላችሁ አትለፉት፥
\v 2 ወንድማችሁ በአቅራቢያ ባይኖር፥ ወይም የማን መሆኑን የማታውቁ ከሆነ ባለቤቱ ፈልጎ እስኪ መጣ ድረስ ወደ ቤታችሁና ወስዳችሁ ከእናንተ ዘንድ አቆዩት፤ ከዚያም መልሳችሁ ስጡት።
\s5
\v 3 የእስራኤላዊ ወንድማችሁን አህያ ወይም ልብስ ወይም የጠፋበትን ማናቸውንም ነገር ስታገኙ እንደዚህ አድርጉ፥ በቸልታ አትለፉት።
\v 4 የወንድማሁ አህያ ወይም በሬ መንገድ ላይ ወድቆ ብታዩት በእግሩ እንዲቆም ርዳው እንጂ አልፋችሁ አትሂዱ።
\s5
\v 5 ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፤ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ እንዲህ የሚያደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ ይጸየፈዋልና።
\s5
\v 6 በመንገድ ስታልፉ አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ወይም ዕንቁላሎቿን የታቀፈችበትን ጎጆ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ብታገኙም እናቲቱን ከነጫጩቶቿ አትውሰፉ፤
\v 7 ጫጩቶቿን መውሰድ ትችላላችሁ እናቲቱን ግን መልካም እንዲህንላችሁና ዕድሜአችሁም እንዲርዝም ልቀቁት፤
\s5
\v 8 አዲስ ቤት በምትሠሩበት ጊዜ፥ ከጣራው ላይ ሰው ወድቆ ቤታችሁ ላይ የደም በደል እንዳታመጡ፥ በጣራው ዙሪያ መከታ አብጁለት።
\s5
\v 9 በወይን ተክል ቦታችሁ ውስጥ ሁለት ዓይነት ዘር አትዝሩ ይህን ካደረጋችሁም የዘራችሁት ሰብል ብቻ ሳይሆን የወይን ፍሬአችሁ ይጠፋል።
\v 10 በሬና አህያ በአንድ ላይ ጠምዳችሁ አትረሱ።
\v 11 ሱፍና ሐር አንድ ላይ ተፈትሎ የተሠራ ልብስ አትልበሱ።
\s5
\v 12 በምትለብሱት ልብስ ላይ በአራቱ ማእዘኖች ዘርፍ አድርጉ።
\s5
\v 13 አንድ ወንድ ሚስት አግብቶ አብሮአት ከተኛ በኋላ ቢጠላት፥
\v 14 ስሟንም በማጥፋት፥ ይህችን ሴት አገባኋት፥ዳሩ ግን በደረስሁባት ጊዜ ድንግልናዋን አላገኘሁም ቢል፥
\s5
\v 15 የልጂቱ አባትና እናት ድንግልናዋን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው በከተማዪቱ በር ወዳሉት አለቆች ይምጡ።
\s5
\v 16 የልጂቱም አባት ለአለቆቹ እንዲህ ይበል፥ ልጄን ለዚህ ሰው ዳርሁለት፥ እርሱ ግን ጠላት፤
\v 17 ስሟንም በማጥፋት ልጅህን ከነድንግልናዋ አላገኘኋትም ብሎኛል፤ ነገር ግን የልጄ ድንግልና ማረጋገጫ ይኸውላችሁ። ከዚያም ወላጆቿ የደሙን ሸማ በከተማዪቱ አለቆች ፊት ይዘርጉት።
\s5
\v 18 ከዚያም በኋላ አለቆቹ ሰውየውን ይዘው ይቅጡት፥
\v 19 ይህ ሰው የአንዲት እስራኤላዊት ድንግል ስም አጥፍቶአልና አንድ መቶ ሰቅል ብር ያስከፍሉት፥ ገንዘቡንም ለልጂቱ አባት ይስጡት፥ ሴቲቱም ሚስቱ ሆና ትኖራለች፤ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።
\s5
\v 20 ሆኖም ክሱ እውነት ሆኖ ሴቲቱ ድንግል ለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ ማቅረብ ካልተቻለ፥
\v 21 በአባቷ ቤት ሳለች በማመንዘር በእስራኤል ውስጥ አሳፋሪ ተግባር ፈጽማለችና ወደ አባቷ ቤት ደጃፍ ያምጣት፥ እዚያም የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሯት።
\s5
\v 22 አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አብሮአት የተኛው ሰውና ሴቲቱ ሁለቱም ይገደሉ። ክፉውን ከእስራኤል ማስወገድ አለባችሁ።
\s5
\v 23 አንድ ሰው የታጨች ድንግል በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርሷ ጋር ቢተኛ፥ ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፥ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስግድዶ ስለ ደፈረ፥
\v 24 ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከላችሁ ማስወገድ አለባችሁ።
\s5
\v 25 ነገር ግን አንድ ሰው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማ ውጭ አግኝቶ በማስገደድ ቢደፍራት፥ ይህን ድርጊት የፈጸመው ሰው ብቻ ይገደል።
\v 26 በልጃገረዲቱ ላይ ግን ምንም አታድርጉባት፥ ለሞት የሚያበቃ ኃጢአት ምንም አልሠራችም፥ ይህ ዓይነቱ ጉዳይ አደጋ ጥሎ ባልንጀራውን ከሚገድል ሰው አድራጎት ጋር የሚመሳሰል ነው።
\v 27 ምክንያቱም ሰውየው የታጨችውን ልጃገረድ ከተማ ውጭ ስላገኛትና ብትጮኽም እንኳ ለርዳታ የደረሰላት ምንም ሰው ስላልነበር ነው።
\s5
\v 28 አንድ ሰው ያልታጨች ልጃገረድ አግኝቶ በማስገደድ ቢደርስባትና ቢጋለጡ
\v 29 ሰውየው ለልጅቷ አባት አምሳ ስቅል ብር ይክፈል፥ ልጃገረዲቱን አስገድዶ ደፍሮአታልና እርሷን ማግባት አለበት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ሊፈታት አይችልም።
\s5
\v 30 አንድ ሰው አባቱን ሚስት ማግባት የለበትም፥ የአባቱንም መኝታ አያርክስ።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቆረጠ ማናቸውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።
\v 2 ዲቃላም ይሁን፥ የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።
\s5
\v 3 አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ አሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ።
\v 4 ምክንያቱም ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህልና ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም። በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም እናንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት።
\s5
\v 5 ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ በብዓምን አልሰማውም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለሚወዳችሁ ርግማኑን ወደ በረከት አደረገላችሁ።
\v 6 በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኙ።
\s5
\v 7 ወንድማችሁ ስለ ሆነ ኤዶማዊውን አትጸየፈው፤ መጻተኛ ሆናችሁ በአገሩ ኖራችኋልና ግብፃዊውን አትጥሉት።
\v 8 ለእነርሱ የተወለዳቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ መግባት ይችላሉ።
\s5
\v 9 ጠላታችሁን ለመውጋት ወጥታችሁ በሰፈራችሁ ጊዜ ከማናቸውም ርኩሰት ራሳችሁን ጠብቁ።
\v 10 ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከስሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቆይ።
\v 11 እየመሸ ሲመጣ ግን ገላውን ይታጠብ ፀሐይ ስትጠልቅም ወደ ሰፈሩ ይመለስ።
\s5
\v 12 ለመጸዳጃ የሚሆንህን ቦታ ከሰፈር ውጭ አዘጋጅ። ከትጥቅህም ጋር መቆፍሪያ ያዝ፥
\v 13 በምትጸዳዳበት ጊዜ አፈር ቆፍረህ በዐይነ ምድርህ ላይ መልስበት።
\v 14 እግዚአብሔር አምላክህ ሊጠብቅህ ጠላቶህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈር ውስጥ ስለሚዘዋወር በመካከልህ አንዳች ነውር አይቶ ከአንተ እንዳይመለስ፥ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን።
\s5
\v 15 አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኮብልሎ ወደ እናንተ ቢመጣ፥
\v 16 ለአሳዳሪው አሳልፋችሁ አትስጡት፥ ደስ በሚያሰኘው ቦታን ራሱ በመረጠው ከተማ በመካከላችሁ ይኑር፤ እናንተም አታስጨንቁት።
\s5
\v 17 ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይኑራችሁ።
\v 18 ለዝሙት አዳሪ ሴት ወይም ለወንድ ዝሙተኛ የተከፈለውን ዋጋ ለማናቸውም ስእለት አድርጋችሁ ለመስጠት ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ቤት አታምጡ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና።
\s5
\v 19 የገንዘብ፥ የእህል ወይም የማንኛውንም ነገር ወለድ ለማግኘት ለወንድማችሁ በወለድ አታበድሩ። ባዕድ ለሆነ ሰው በወለድ ማበደር ትችላላችሁ።
\v 20 ነገር ግን ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር እጃችሁ በሚነካው በማናቸውም ነገር እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲባርካችሁ ለእስራኤልዊ ወንድማችሁ በወለድ አታበድሩት።
\s5
\v 21 ለእግዚአብሔር ለአምልካችሁ ስእለት ከተሳላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ አጥብቆ ከእናንተ ይሻዋልና፤ ኃጢአት እንዳይሆንባችሁ ለመክፈል አትዘግዩ።
\v 22 ሳትሳሉ ብትቀሩ ግን በደለኛ አትሆኑም። በአንደበታችሁ የተናገራችሁትን ሁሉ ለመፈጸም ጠንቃቃ ሁኑ፥
\v 23 ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር በገዛ አንደበታችሁ ፈቅዳችሁ ስእለት ተስላችኋልና።
\s5
\v 24 ወደ ባልንጀራችሁ የወይን ተክል ቦታ በምትገቡበት ጊዜ ያሰኛችሁን ያህል መብላት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አንዳችም በዕቃችሁ አትያዙ።
\v 25 ወደ ባልንጀራችሁ እርሻ በምትገቡበት ጊዜ እሸት መቅጠፍ ትችላላችሁ፤ በሰብሉ ላይ ግን ማጭድ አታሳርፉበት።
\s5
\c 24
\p
\v 1 አንድ ሰው አንዲት ሴት ካገባ በኋላ አሳፋሪ ነገር አግኝቶባት ባይደሰትባት የፍቺ ወረቀት ጽፎ በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ይስደዳት።
\v 2 ከቤቱ ከወጣች በኋላ ሌላ ባል ሊታገባ ትችላለች።
\s5
\v 3 ሁለተኛ ባሏም እንደዚሁ ጠልቷት የፍቺ ወረቀት በመስጠት ከቤቱ አስወጥቶ ቢሰዳት፥ ወይም ቢሞት፥
\v 4 ከዚያ በኋላ ፈቶአት የነበረው የመጀመሪያ ባሏ፥ የረከሰች በመሆኗ እንደ ገና መልሶ ሊያገባት አይችልም፤ ይህ በእግዚአብሔር ፊት አስጸያፊ ነው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ኃጢአት አታምጡ።
\s5
\v 5 አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፥ ለጦርነት አይሂድ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሥራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ እቤቱ ይቆይ፥ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።
\s5
\v 6 ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም እንኳ ቢሆን፥ የብድር መያዣ አድርጋችሁ አትውሰዱ፤ የሰውን ነፍስ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆናልና።
\s5
\v 7 አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባሪያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። ክፉውን ከመካከላችሁ አስወግድ።
\s5
\v 8 የለምጽ ደዌን በተመለከተ ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡአችሁን መመሪያ በትክክል ለመፈጸም ጥንቃቄ አድርጉ። እኔ ለእነርሱ የሰጠሁትን ትእዛዝ በጥንቃቄ ተከተሉ።
\v 9 ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በመንገድ ላይ ሳላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሙሴ እህት በምርያም ላይ ያደረገባትን አስታውሱ።
\s5
\v 10 ማናቸውንም ነገር ለባልንጀራችሁ ስታበድሩ መያዣ አድርጎ የሚሰጣችሁን ለመቀበል ወደ ቤቱ አትግቡ።
\v 11 እንንተ ከውጭ ሆናችሁ ጠብቅ፥ ያበደራችሁም ሰው መያዣውን ከቤት ያምጣላችሁ።
\s5
\v 12 ሰውየው ድኻ ከሆነ መያዣውን ከእናንተ ዘንድ አታሳድሩበት።
\v 13 መደረቢያውን ለብሶት እንዲያድር ፀሐይ ሳትጠልቅ መልሱለት። ከዚያም ያመሰግናችኋል፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ፊትም የጽድቅ ሥራ ሆኖ ይቆጠርላችኋል።
\s5
\v 14 ድኻና ችግረኛ የሆነውን የምንዳ ሠራተኛ እስራኤላዊ ወንድማችሁም ሆነ፥ከከተሞቻችሁ ባንዲቱ የሚኖረውን መጻተኛ አትበዝብዙት፤
\v 15 የሠራበትን ሒሳብ በዕለቱ ፀሐይ ሳትጠልቅ ክፈሉት፤ ድኻ በመሆኑ በጉጉት ይጠባበቀዋልና። ያለበለዚያ ወደ እግዚአብሔር ይጮኸና ኃጢአት ይሆንባችኋል።
\s5
\v 16 አባቶች ስለ ልጆቻቸው፥ ልጆችም ስለ አባቶቻቸው አይገደሉ፤ እያንዳንዱ በራሱ ኃጢአት ይገደል።
\s5
\v 17 መጻተኛው ወይም አባት ለሌለው ልጅ ፍትሕ አትንፈጉት፤ ባል የሞትባትንም መደረቢያ መያዣ አታድርጉ።
\v 18 እናንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበራችሁና እግዚአብሔር አምላካችሁ ከዚያ እንደ ተቤዣችሁ አስታውሱ፤ ይህን እንድታደርጉ ያዘዙአችሁ ለዚህ ነው።
\s5
\v 19 የእርሻችሁን ሰብል በምታጭዱበት ጊዜ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፥ ያን ለመውሰድ ተመልሳችሁ አትሂዱ፤እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ ሥራ ሁሉ እንዲባርካችሁ ነዶውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ።
\v 20 የወይራ ዛፋችሁን ፍሬ በምታራግፉበት ጊዜ በየቅርንጫፉ ላይ የቀረውን ለመቃረም ተመልሳችሁ አትሂዱ ለመጻተኛ፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ።
\s5
\v 21 የወይን ተክላችሁን ፍሬ ስትሰበስቡ ቃርሚያውን ለመሰብሰብ አትመለሱበት የቀረውን ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ተዉ።
\v 22 በግብፅ ባሮች እንደነበራችሁ አስታውሱ፤ ይህን እንድታደርጉ ያዘዙአሁን ለዚህ ነው።
\s5
\c 25
\p
\v 1 በሰዎች መካከል ጠብ ቢነሣ ወደ ፍርድ አደባባይ ቢሄዱ፥ ዳኞች ተበዳይን ነጻ፥ በዳይን ግን ጥፋተኛ፥ በማድረግ የፍርድ ውሳኔ ይስጡ።
\v 2 በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፥ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፥ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ።
\s5
\v 3 ሆኖም ግርፋቱ ከአርባ የሚበልጥ አይሁን፥ ከዚህ ካለፈ ግን እስራኤላዊ ወንድማችሁ በፊታችሁ የተዋረደ ይሆናል።
\s5
\v 4 እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰሩ።
\s5
\v 5 ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና፥ ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥የሟቹ ሚስት ከቤተ ሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።
\v 6 በመጀመሪያ የምትወልደውም ልጅ ስሙ ከእስራኤል ፈጽሞ እንዳይጠፋ በሟች ወንድሙ ስም ይጠራ።
\s5
\v 7 ሆኖም ግን አንድ ሰው የወንድሙን ሚስት ለማግባት ባይፈልግ ሴትዮዋ በከተማዋ በር ወዳሉት ሽማግሌዎች ሄዳ የባለቤቴ ወንድም የወንድሙን ስም በእስራኤል ለማስጠራት አልፈለገም፥ የዋርሳነት ግዴታውንም አልፈጸመልኝም ትበላቸው።
\v 8 ከዚያም የከተማው ሽማግሌዎች ያን ሰው ጠርተው ያነጋግሩት እርሱም እርሷን ላገባት አልፈልግም ብሎ በሐሳቡ ቢጸና፥
\s5
\v 9 የወንድሙንም ሚስት በሽማግሌዎች ፊት ወደ እርሱ ቀርባ፥ የአንድ እግሩን ጫማ በማውለቅ በፊቱ ላይ ትትፋበትና የወንድሙን ቤት ማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ያለው ድርጊት ይፈጸምበታል ትበል።
\v 10 የዚያም ሰው የዘር ሐረግ በእስራኤል ዘንድ ጫማው የወለቀበት ቤት ተብሎ ይታወቃል።
\s5
\v 11 ሁለት ሰዎች ቢደባደቡ፥ የአንደኛው ሚስት ባሏን ከደብዳቢው እጅ ለማስጣል መጥታ እጇን ዘርግታ ብልቱን ብትይዘው
\v 12 ፥እጇን ቁረጡ አትራሩላት።
\s5
\v 13 በከረጢታችሁ ውስጥ ከባድና ቀላል የሆኑ ሁለት የተለያዩ ሚዛኖች አይኑሩአችሁ።
\v 14 በቤታችሁም ውስጥ ትልቅና ትንሽ የሆኑ ሁለት የተለያዩ መስፈሪያዎች አይኑሩአችሁ።
\s5
\v 15 እግዚአብሔር አምላካችሁ በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም ትክክለኛና የታመነ ሚዛንና መስፈሪያ ይኑራችሁ።
\v 16 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲህ ያሉትን ጽድቅ ያልሆን ነገሮች የሚፈጽመውንና የሚያምታታውን ሁሉ ይጸየፈዋልና።
\s5
\v 17 ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ በእናንተ ላይ ያደረጉባችሁን አስታውሱ፤
\v 18 ደክማችሁና ዝላችሁ በነበራችሁበት ጊዜ በጉዞ ላይ አግኝቶአሁ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአቤርንም አልፈሩም።
\v 19 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ዙሪያ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ባሳረፋችሁ ጊዜ ከሰማይ በታች ያለውን የአማሌቅን መታሰቢያ ደምስሱ፤ ከቶ እንዳትረሱ!
\s5
\c 26
\p
\v 1 እግዚአብሔር አምላካችሁ ርስት አድርጎ ወደ ሚሰጣችሁ ምድር ስትገቡ፥ ስትወርሱአትና ስትኖሩባት፤
\v 2 እግዚአብሔር አምላካችሁ ከሚሰጣችሁ ምድር ከሁሉም የመጀመሪያ ፍሬ ውሰዱት። ከዚያም በቅርጫት ውስጥ አድርጉትና እግዚአብሔር አምላካችሁ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ሂዱ።
\s5
\v 3 በዚያን ወቅት ወደ ሚያገለግለው ካህን ሄዳችሁ ፦ እግዚአብሔር ለእኛ ሊሰጠን ለአባቶቻችን ወደ ማለላቸው ምድር እንደ ገባሁ ዛሬ እግዚአብሔር አምላካችሁን ለማምስገን እቀባለለሁ በለው።
\v 4 ካህኑም ቅርጫቱን ከእጃችሁ ተቀብሎ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ መሠዊያ ፊት ለፊት ያኖረዋል።
\s5
\v 5 እናንተም በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት እንዲህ ብላችሁ ትናገራላችሁ፦ አባቴ ዘላን ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብፅ ወረደ፤ በዚያም ተቀመጠ፤ ታላቅ፥ ኃያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።
\s5
\v 6 ግብፃውያንም በመጥፎ ሁኔታ እንገላቱን፥ አሠቃዩንም። እንደ ባሪያ ከባድ ሥራ እንድንሠራ አደረጉን።
\v 7 ከዚያ በኋላ ወደ አባቶቻችን አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኸን፥ እርሱም ጩኸታችንን ሰማ፤ መከራችንን፣ ድካማችንንና የተፈጸመብንን ግፍ ተመለከተ።
\s5
\v 8 ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር በብርቱ እጅና በተዘረጋው ክንዱ፥ በታላቅ ድንጋጤና ታምራት በምልክትና በድንቅ ከግብፅ አወጣን፤
\v 9 ወደዚህም ስፍራ አመጣን፥ ማርና ወተት የምታፈሰውን ይህችን ምድር ሰጠን።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር ሆይ እነሆ፥ አንተ ከሰጠኸኝ ከምድሪቱ የመጀመሪያ ፍሬ አምጥቻለሁ፤ ቅርጫቱንም በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት አኑራሃው አምልከው፤
\v 11 ለአንተና ለቤትህ ባደረገው መልካም ነገር አንተ፥ ሌዋውያንና መጻተኞች በእግአብሔር በአምላክህ ፊት ደስ ይበላችሁ።
\s5
\v 12 የአሥራት ዓመት የሆነውን የሦስተኛውን ዓመት ፍሬ አንድ አሥረኛ ለይታችሁ ካወጣችሁ በኃላ በየከተሞቻችሁ ውስጥ በልተው እንዲጠግቡ፥ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥አባት ለሌለውና ባል ለሞተባቸው ስጡአቸው።
\v 13 ከዚያ በኋላ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር እንዲህ በል፦ በሰጠኸኝ ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን ከቤቴ አምጥቼ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛው፥ አባት ለሌለውና ባል ለሞተባት ሰጥቻለሁ። ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ አንዱንም አልረሳሁም።
\s5
\v 14 በሐዘን ላይ ሳለሁ፥ ከተቀደሰው ክፍል ላይ ምንም አልበላሁም ባልነጻሁበትም ጊዜ ከዚህ ላይ ያነሣሁትምና ለሙታን ያቀረብሁት ምንም ነገር የለም። አምላኬን እግዚአብሔርን ታዝዣለሁ፥ ያዘዝኸኝንም ሁሉ ፈጽሜአለሁ።
\v 15 ከቅዱስ ማደሪያ ሆነህ ከሰማይ ተመልከት፥ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በማለህላቸው መሠረት፥ ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ባርክ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር አምላካችሁ ይህን ሥርዓትንና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ዛሬ ያዝዛችኋል፤ እናንተም በፍጹም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ትፈጽሙት ዘንድ ተጠንቀቁ።
\v 17 እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆነ በመንገዱም እንደምትሄዱ፥ ሥርዓቱን፥ ትእዛዙንና ሕጉን እንደምትጠብቁ እንደምትታዘዙለት በዛሬው ዕለት ተናግራችኋል።
\s5
\v 18 እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት እንንተ ሕዝቡና ርስቱ መሆናችሁን ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቁ በዛሬው ዕለት ተናግሮአል፤
\v 19 ከፈጠራቸው ሕዝቦች ሁሉ በላይ ለማመስገን፥ ለማክበረና ከፍ ለማድረግና በሰጠውም ተስፋ መሠረት ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ቅዱስ ሕዝብ እንደምትሆኑ ማረጋገጫ ሰጥቶአል።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ሙሴና የእስራኤል አለቆች ሕዝቡን እንዲህ ብለው አዘዙ፦ ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ።
\v 2 አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁሙና በኖራ ለስኑአቸው።
\v 3 የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማርና ወተት ወደምታፈሰው፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፉባቸው።
\s5
\v 4 ዮርዳኖስን እንደ ተሻገራችሁም ዛሬ ባዘዙአችሁ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከሉአቸው በኖራም ለስኑአቸው።
\v 5 እዚያም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የድንጋይ መሠዊያ ሥራ፥ በድንጋዮቹም ላይ ማናቸውንም የብረት መሣሪያ አታሳርፉባቸው።
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር የአምላካችሁን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥሩ፥ በላዩም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡበት።
\v 7 በላዩም የኅብረት መሥዋዕት ሠዉ፤ ብሉም፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ።
\v 8 በድንጋዮቹም ላይ የዚህ ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርጋችሁ ጻፉባቸው።
\s5
\v 9 ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም፥ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ እስራኤል ሆይ፥ ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! እናንተ ዛሬ የእግዚአብሔር የአላካችሁ ሕዝብ ሆናችኋል።
\v 10 ስለዚይም እግዚአብሔር አምላካችሁን ታዘዙ፥ ዛሬ የሚሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቁ።
\s5
\v 11 ሙሴ በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦
\v 12 ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ስምዖን ፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዮሴፍና ብንያም ወገኖች ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ።
\s5
\v 13 ሮቤል፥ ጋድ፥ አሴር፥ ዛብሎን፥ ዳንና ንፍታሌምወገኖች በጌባል ተራራ ላይ ለመርገም ይቁሙ።
\v 14 ሌዋውያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦
\s5
\v 15 ጥበበኛ የሠራውን በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ የሆነውን ምስል የሚቀርጽ ወይም ጣዖትን የሚያበጅ በስውርም የሚያቆም ሰው የተረገመ ይሁን። ሕዝብም ሁሉ፥ አሜን ይበል።
\s5
\v 16 አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገም ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
\v 17 የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
\s5
\v 18 ዐይነ ስዉርን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
\v 19 በመጻተኛው፥ አባት በሌለውና ባል በሞተባት ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
\s5
\v 20 ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
\v 21 ከማናቸውም እንስሳ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል።
\s5
\v 22 የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን።
\v 23 ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። ከሚስቱ እናት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
\s5
\v 24 በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
\v 25 ንጹሕውን ሰው ለመግደል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
\s5
\v 26 የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል።
\s5
\c 28
\p
\v 1 ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ በፍጹም ብትታዘዙና እኔ ዛሬ የምሰጣችሁን ትእዛዘትን ሁሉ በጥንቃቄ ብትከተሉ አምላካችሁ እግዝአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ አሕዝብ ሁሉ በላይ ከፍ ያደርጋችኋል።
\v 2 እግዚአብሔር አምላካችሁን ብትታዘዙ እነዚህ በረከቶች ሁሉ የእናንተ ይሆናሉ፤ አይለዩአችሁምም።
\s5
\v 3 በከተማና በእርሻ ትባረካላችሁ።
\v 4 የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ የምድራችሁ አዝመራ፥ የእንስሳታችሁ ግልገሎች፥ የክብታችሁ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎቻችሁም ይባረካሉ።
\s5
\v 5 እንቅባችሁና ቡሓቃያችሁም ይባረካሉ።
\v 6 ስትጓዙ ትበረካላችሁ፤ ስትወጡም ትባረካላችሁ።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚነሡ ጠላቶቻችሁን በፊታችሁ እንዲሸነፉ ያደርጋቸዋል፤በአንድ አቅጣጫ ቢመጡባችሁ በሰባት አቅጣጫም ከእናንተ ይሸሻሉ።
\v 8 እግዚአብሔር በጎተራችሁና እጃችሁ በነካው ሁሉ በረከቱን ይልካል። አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር ላይ ይባርካችኋል።
\s5
\v 9 የእግዚአብሔር የአምላካችሁ ትእዛዞች የምትጠብቁና በመንገዱ የምትሄዱ ከሆነ በማለላቸው ተስፋ መሠረት የተቀደሰ ሕዝቡ አድርጎ ያቆማችኋል።
\v 10 ከዚያ የምድር አሕዝብ ሁሉ በእግዚአብሔር ስም መጠራታችሁን ያያሉ፤ ይፈርሁማል።
\s5
\v 11 እግዚአብሔርም ሊሰጣችሁ ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ በእንስሳታችሁ፥ ግልገል፥ በምድራችሁም ሰብል፥ የተትረፈረፈ ብልጽግና ይሰጣችኋል።
\v 12 እግአብሔር ለምድራችሁ በወቅቱ ዝናብን ለመስጠትና የእጃችሁን ሥራ ሁሉ ለመባረክ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትላችኋል፤ እናንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራላችሁ እንጂ ከአንዳቸውም አትበደሩም።
\s5
\v 13 እግዚአብሔም ራስ እንጂ ድራት አያደርጋችሁም፤ ዛሬ የምሰጣችሁን የአምላካችሁ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በጥንቃቄ ብትጠብቁ መቼውንም ቢሆን በላይ እንጂ ፈጽሞ በታች አትሆኑም።
\v 14 ሌሎች አማልክት በመከተል እነርሱን በማገልገል ዛሬ ከምሰጣችሁ ትእዛዞች ቀኝም ግራም አትበሉ።
\s5
\v 15 ነገር ግን ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ ባትታዘዙ በዛሬዋ ዕለት የምሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ሁል በጥንቃቄ ባትከተሉአቸው እነዚህ ርግማኖች ሁሉ ይደርሱባችኋል፤ ያጥለቀልቁአችኋልም።
\s5
\v 16 በከተማ ትረገማላችሁ፤ በእርሻም ትረገማላችሁ።
\v 17 እንቅባችሁና ቡሓቃያችሁ የተረገሙ ይሆናሉ።
\s5
\v 18 የማሕፀናችሁ ፍሬ፥ የእርሻህ ሰብል፥ የመንጋችሁ ጥጆች፥ የበግና የፍየል ግልገሎቻችሁ ይረገማሉ።
\v 19 ስትገቡ ትረገማላችሁ፤ ስትወጡም ትረገማላችሁ።
\s5
\v 20 እርሱን በመተው ክፉ ድርጊት ከመፈለጋችሁ የተነሣ እስክትደመስሱ ፈጥናችሁም እስክትጠፉ ድረስ እጃችሁ በነካው ሁሉ ላይ እግዚአብሔር ርግማንን መደናገርንና ተግሣጽን ይሰድባችኋል።
\v 21 እግዚአብሔር ልትወርሱአት ከምትገቡባት ምድር ላይ እስኪያጠፋችሁ ድረስም በደዌ ይቀሥፋችኋል።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር እስክትጠፉ ድረስ በሚቀሥፍ ደዌ ትኩሳትና ዕባጭ ኃይለኛ ሙቀትና ድርቅ ዋግና አረማሞ ይመታችኋል።
\s5
\v 23 ከራሳችሁ በላይ ያለው ሰማይ ናስ ከእግራችሁ በታች ያለው ምድርም ብረት ይሆናል።
\v 24 እግዚአብሔር የምድራችሁን ዝናብ ወደ አቧራነትና ወደ ትቢያነት ይለወጠዋል፤ ይህም እስክትጠፉ ድረስ ከሰማይ ይወርድባችኋል።
\s5
\v 25 እግዚአብሔር በጠላቶቻችሁ ፊት እንድትሸነፉ ያደርጋችኋል፤ በአንድ አቅጣጫ ትመጣበቸዋላችሁ ነገር ግን በሰባት አቅጣጫ ከፊታቸው ትሽሻላችሁ ለምድር መንግሥታትም ሁሉ መሸማቀያ ትሆናላችሁ።
\v 26 ሬሳችሁ ለሰማይ አሞሮችና ለምድር አራዊት ሲሳይ ይሆናል፤ በማስፈራራትም የሚያባርሩአቸው አይኖርም።
\s5
\v 27 እግዚአብሔር በማትድኑበት በግብፅ ብጉጅ፥ በእባጭ በሚመግል ቁስልና በእከክ ያሠቃያችኋል።
\v 28 እግዚአብሔር በእብደት፥ በዕውርነትና ግራ በማጋባት ያስጨንኣቃችል።
\v 29 በእኩለ ቀን በጨለማ እንዳለ ዕውር በዳበሳ ትሄዳላችሁ። የምታደርጉት ሁሉ አይሳካላችሁም። በየዕለቱ ትጨቆናላችሁ፤ ትመዘበራላችሁም፤ የሚታደጋችሁም አይኖርም።
\s5
\v 30 ሚስት ለማግባት ልጃገረድ ታጫላችሁ ሌላው ግን ወስዶ በኃይል ይደፍራታል። ቤት ትሠራላችሁ፤ ግን እናንተ አትኖሩበትም። ወይን ትተክላላችሁ ፍሬውን ግን አትበሉም።
\v 31 በሬህ ዐይናችሁ እያየ ይታረዳል፤ ከሥጋውም አንዳች አትቀምሱም። አህያችሁም በግድ ይወሰድባችኋል፤ አትበሉም። በጎቻችሁ ለጠላቶቻችሁ ይሰጣሉ፤ የሚያሰጥላቸውም አይኖርም።
\s5
\v 32 ወዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ ለባዕድ ሕብብ ይሰጣሉ፤ እጃችሁንም ለማንሣት እቅም ታጣላችሁ፤ ይመጣሉ፤ በማለትም ዐይኖቻችሁ ሁልጊዜ እነርሱን በመጠባበቅ ይደክማሉ።
\s5
\v 33 የምድራችሁንና የድካማሁን ፍሬ ሁሉ የማታውቁት ሕዝብ ይበላዋል፤
\v 34 ሁልጊዜ በጭቆናና በጫን ትኖራላችሁ፤ በምታዩት ሁሉ ትጃጀላላችሁ።
\v 35 እግዚአብሔር ከእግራችሁ ጥፍር እስከ ራስህ ጠጉር በሚወርር ሊድን በማይችልና በሚያሠቃይ ቁስል ጉልበታችሁንና እግራችሁን ይመታችኋል።
\s5
\v 36 እግዚአብሔር እናንተንና በላያችሁ ያነገሣችሁትን ንጉሥ፥ እናንተና አባቶቻችሁ ወደ ማታውቁት ሕዝብ ይወሰዳችኋል፤ ከዚያም ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማክልትን ታመልካላችሁ።
\v 37 እግእብብሔር እንድትገቡ በሚመራችሁ ምድር ለአሕዛብ ሁሉ መሸማቀቂያ ማላገጫና መዘባበቻ ትሆናላችሁ።
\s5
\v 38 በእርሻ ላይ ብዙ ዘር ትዘራላችሁ አንበጣ ስለሚበላው የምትሰበስቡ ጥቂት ይሆናል። ወይን ትተክላላችሁ ትንከባከበዋላችሁ፤
\v 39 ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጡም ዘለላውንም አትሰበስቡም።
\s5
\v 40 በአገራችሁ ምድር ሁሉ የወይራ ዛፍ ይኖራችኋል፤ ፍሬው ስለሚረግፍባችሁ ግን ዘይቱን አትቀቡም።
\v 41 ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻችሁን ትወልዳላችሁ ነገር ግን በምርኮ ስለሚወሰዱ፤ አብረዋችሁ አይኖሩም።
\s5
\v 42 ዛፋችሁንና የምድራችሁን ሰብል ሁሉ አንበጣ መንጋ ይወረዋል።
\v 43 በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ከእናንተ በላይ ከፍ ከፍ ሲል እናንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላላችሁ።
\v 44 እርሱ ያበድራችኋል እንጂ እናንተ አታበድሩም። እርሱ ራስ ይሆናል፤ እናንተ ግን ጅራት ትሆናላችሁ።
\s5
\v 45 እነዚህ ርግማኖች እስክትጠፉ ድረስ ይከተሉአችኋል፤ ሁሉ በእናንተ ላይ ይመጣሉ፤ ይህም የሚሆነው አምላካችሁን እግዚአብሔርን ስላልታዘዛችሁና የሰጣኋችሁን ትእዛዝና ሥርዓት ስላልጠበቃችሁ ይወርዱባችኋልም።
\v 46 እነዚህ ርግማኖች እንደ ምልክትና ድንቅ ነገሮች ሆነው በእንንተና በዘራችሁ ለዘላለም ይሆናል።
\s5
\v 47 በብልጽግና ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችሁን በደስታና በሐሤት ስላላገለገችሁ በራብና በጥም በእርዛትና በከፋ ድኽነት
\v 48 እግዚአብሔር የሚያስነሣባችሁን ጠላቶቻችሁን ታገለግላላችሁ፤ እስኪያጠፉአችም ድረስ በአንገታችሁ ላይ የብረት ቀንበር ይጭንባችኃል።
\s5
\v 49 እግዚአብሔር እንደ ንስር በፈጣን የሚበሩና ቋንቋውን የማታውቁአችሁን ሕዝብ እጅግ ሩቅ ከሆነ፥ ከምድርም ዳርቻ ያስነሣነሰባችኋል፤
\v 50 ሽማግሌ የማያከብር፥ ለወጣትም መልካም ያልሆኑና የሚያስፈራና ጨካኝ ሕዝብ ነው።
\v 51 እስክትጠፉም ድረስ የእንስሳታችሁን ግልገልና የምድራችሁን ሰብል ይበላል፤ እስኪያጠፋችሁም ድረስ እህል፤አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት የመንጋችሁን ጥጃና የበግና ፍየል መንጋችሁን ግልገል አያስቀሩላችሁም።
\s5
\v 52 የምትታመኑባቸውን ታላላቅ የተመሸጉ ቅጥሮች እስኪወድቁ ድረስ በመላው አገራችሁ ያሉትን ከተሞቻችሁን ሁሉ ይከባል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጥጣችሁምድር ያሉትን ከተሞች በሙሉ ይወራቸዋል።
\v 53 ጠላቶቻችሁ ከበው በሚያስጨንቁአችሁ ጊዜ ከሥቃይ የተነሣ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችህን የአብራካችሁ ፍሬ የሆኑትን የወንዶችና የሴቶች ልጆቻችሁን ሥጋ ትበላላችሁ።
\s5
\v 54 ሌላው ይቅርና በመካከላችሁ በጣም ደግና ርኅሩኅ የሆነው ሰው እንኳ ለገዛ ወንድሙ ወይም ለሚወዳት ሚስቱ ወይም ለተረፉት ልጆቹ አይራራላቸውም።
\v 55 ከሚበላው ከልጆቹ ሥጋ ላይም ቅንጣት ያህል እንኳ ከእነርሱ ለአንዱ አያቀምስም፤ ከተሞቻችሁ ሁሉ በመከበባቸው ጠላቶቻችሁ ከሚያደርሱባችሁ ሥቃይ የተነሣ ለእርሱ የቀረለት ይህ ብቻ ነውና።
\s5
\v 56 በመካከላችሁ ተመቻችታና ተቀማጥላ የምትኖር ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ እግሯን አፈር ነክቶት የማያውቅ ሴት የምትወደውን ባሏን፥ የገዛ ወንድና ሴት ልጆቿን ትንቃለች።
\v 57 ከማሕፀኗ የወጣውን የምትወልዳቸውን ሕፃናት ትጠየፋለች፤ በመከራው ወቅት ጠላቶቻችሁ ከተሞቻችሁን ከበው በሚያስጨንቁአችሁ ጊዜ ሌላ የሚበላ ስለማይኖር እነርሱን ደብቃ ትበላለች።
\s5
\v 58 በዚህ መጽሐፍ የተጻፉትን የዚህን ሕግ ቃሎች ባትከተሉና የተከበረውና አስፈሪ የሆነውን የአምላካችሁን
\v 59 የእግዚአብሔርን ስም ባታከብሩ እግዚአብሔር አስፈሪ መቅሠፍት፥ አስጨናቂና ለብዙ ጊዜ የሚቋይ መዓት አሠቃቂና በቀላሉ የማይወገድ ደዌ በእናንተና በዘሮቻችሁ ላይ ይልክባችኋል።
\s5
\v 60 የምትፈሩአችሁንም የግብፅ በሽታዎች ሁሉ ያመጣባችኋል፤ በእናንተም ላይ ይጣበቃሉ።
\v 61 ደግሞም እግዚአብሔር በዚህ የሕግ መጽሐፍ ያልተጸፈውን ማንኛውንም ዓይነት ደዌና መከራ እስክትጠፉ ድረስ ያመጣባችኋል።
\v 62 ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ስላልታዛዝችሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝታችሁ ቢሆን እንኳ እናንተ ጥቂት ብቻ ትቀራላችሁ።
\s5
\v 63 እግዚአብሔር ለእናንተ መልካም በማድረግና ቁጥራችሁን በማብዛት ደስ እንዳተሰኘ ሁሉ ፤ እናንተን በመደምሰስና በማጥፋት ደስ ይለዋል። ከምትወርሱዋት ምድር ትነቀላላችሁ።
\v 64 ከዚያም እግዚአብሔር ከአንዱ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ዳርቻ በሕዝቦች ሁሉ መካከል ይበትናችኋል። በዚያም አባቶአኣችሁ የማታውቋቸውን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ።
\s5
\v 65 በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኙም፤ ለእግራችሁም ጫማ ማረገጫ አይኖርም፤ እዚያም እግዚአብሔር የሚጨነቅ አእምሮ፥ የሚደክም ዐይንና ተስፋ የሚቋርጥ ልብ ይሰጣችኋል።
\v 66 ዘመናችሁን በሙሉ ቀንና ሌሊት በፍርሃት እንደ ተዋጣችሁ ሕይወትታችሁ ዘወትር በሥጋት ትኖራላችሁ።
\s5
\v 67 ልባችሁ በፍርሃት ከመሞላቱና ዐይናችሁ ከሚያየው ነገር የተነሣ ሲነጋ ምነው አሁን ሲመሽ ፥ደግሞ ምነው አሁን በነጋ ትላላችሁ።
\v 68 ዳግመኛ አትመለሱባትም ባልሁ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልሳችኋል። እዚያም እንደ ወንድና ሴት ባሪያ ለጠላቶቻችሁ ለመሸጥ ራሳችሁን ታቀርባላችሁ የሚገዛችሁ ግን አይኖርም።
\s5
\c 29
\p
\v 1 እግዚአብሔር በኮሬብ ከገባው ቃል ኪዳን በተጨማሪ በሞዓብ ምድር ከእስራኤላውያን ጋር እንዲያደርግ ሙሴን ያዘዘው የኪዳኑ ቃሎች እነዚህ ናቸው።
\s5
\v 2 ሙሴ እስራኤላውያንን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ እግዚአብሔር በግብፅ በፈርዖን፥ በሹማምንቱ ሁሉና በመላ አገሩ ያደረተውን ሁሉ ዐይኖቻችሁ አይተዋል።
\v 3 እነዚያን ከባድ ፈተናዎች ታምራዊ ምልክቶችና ታላቅ ድንቆች በገዛ ዐኖቻችሁ አይታችኋል።
\v 4 ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ እግዚአብሔር የሚያስተውል አእምሮ ወይም የሚያይ ዐይን ወይም የሚሰማ ጆሮ አልሰጣችሁም።
\s5
\v 5 በምድረ በዳ በመራኋችሁ በእነዚያ አርባ ዓመታት ውስጥ ልብሳችሁ አላረጀም፥ የእግራችሁም ጫማ አላለቀም፥
\v 6 ቂጣ አልበላችሁም፥ የወይን ጠጅ ወይም ሌላ የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣችሁም፤ ይህን ያደረግሁት እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንህ ታውቁ ዘንድ ነው።
\s5
\v 7 ወደዚህ ስፍራ በደረሳችሁ ጊዜ የሐሴንቦን ንጉሥ ሴዎንና የባሳን ንጉሥ ዐግ ሊወጉን መጡ፤ ሆኖም ድል አደረግናቸው።
\v 8 ምድራቸውንም ወስደን ለሮቤላውያን ለጋዳውያንና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ርስት አድርገን ሰጠን።
\v 9 እንግዲህ የምታደርጉት ሁሉ እንዲከናወንላችሁ፤ የዚህ ኪዳን ቃሎች በጥንቃቄ ተከተሉ።
\s5
\v 10 እናንተ ሁላችሁ መሪዎቻችሁና አለቆቻችሁ፥ ሽማግሌዎቻችሁና ሹሞቻችሁ እንዲሁም ሌሎች የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዛሬ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቆማችኋል፤
\v 11 ልጆቻችሁና ሚስቶቻችሁ እንጨታችሁን እየፈለጡ ውሃዎቻችሁንም እየቀዱ በሰፈራችሁ የሚኖሩ መጻተኞችም አብረአችሁ ቆመዋል።
\s5
\v 12 እዚህ የቆማችሁ፥ እግዚአብሔር ዛሬ ከእናንተ ጋር ወደ ሚያደርገውና በመሐላ ወደሚያጸናው ኪዳን፥ከእግዚአብሔር ከአምላካችሁ ጋር ትገቡ ዘንድ ለእናንተ በሰጣችሁ ተስፋና፥
\v 13 ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በማለላቸው መሠረት እርሱ አምላካችሁ ይሆን ዘንድ እናንተም ሕዝቡ መሆናችሁን በዛሬው ዕለት ለማረጋገጥ ነው።
\s5
\v 14 እኔም ይህ የቃል ኪዳን የማደርገው ከእናንተ ጋር ብቻ አይደለም፤
\v 15 አብራችሁን በእግዚአብሔር በአምላካችን ፊት እዚህ ከቆማችሁት ጋር ብቻ ሳይሆን ዛሬ እዚህ ከሌሉትም ጋር ነው።
\v 16 በግብፅ ምድር እንዴት እንደኖርንና ወደዚህ ስንመጣም በየአገሮቹ ውስጥ እንዴት እንዳለፍን ራሳችሁ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 17 በመካከላቸውም አስጸያፊ ነገሮቻቸውን፦ የእንጨትና የድንጋይ፥ የብርና የወርቅ ጣዖቶቻቸውን አይታችኋል፤
\v 18 የእነዚህን ሕዝቦች አማልክት ለማምለክ ልቡን ከእግዚአብሔር ከአምላካችን የሚመልስ ወንድ፥ ሴት፥ቤተ ሰብ፥ ወይም ጎሣና ነገድ ዛሬ ከመካከላችሁ አይገኙ፤ ከመካከላችሁ እንዲህ ያለውን መራራ መርዝ የሚያወጣ ሥር እንዳይኖር ተጠንቀቁ።
\v 19 እንዲህ ያለው ሰው የዚህን ቃል ኪዳን በሚሰማበት ጊዜ በልቡ ራሱን በመባረክ፦ እንደ ልቤ ግትርነት ብመላለስም እንኳ ሰላም አለኝ ብሎ ያስባል። ይህም እርጥቡን ከደረቁ ጋር ያጠፋል።
\s5
\v 20 እግዚአብሔር ለዚህ ሰው ፈጽሞ ምሕረት አያደርግለትም፥ ቁጣውና ቅናቱ በእርሱ ላይ ይነድበታል፤ በዚህ መጽሐፍ የተጸፉት ርግማን ሁሉ ይወርድበታል፤ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።
\v 21 በዚህ የሕግ መጽሐፍ በተጻፈው የኪዳኑ ርግማን መሠረት እግዚአብሔር እርሱን ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ለጥፋት ይለየዋል።
\s5
\v 22 የሚቀጥለው ትውልድ ከእናንተ በኋላ የሚተኩት ልጆቻችሁና ከሩቅ አገር የሚመጡ እንግዶች በምድሩቱ የደረሰውን ታላቅ መቅሠፍትና እግዚአብሔር ያመጣባቸውን በሽታዎች ያያሉ፤
\v 23 ምድሩቱ በሙሉ የተቃጠለ ጨውና ዲን ዐመድ ትሆናለች፤ አንዳች ነገር አይተከልባት፤ ምንም ነገር አያቆጠቁጥባትም። የሚያድግ ተክል አይገኝባትም። የምደርስባት ውድመት እግዝክአብሔር በታላቅ ቁጣ እንደ ገለባበጣቸው እንደሰዶምና ገሞራ እንደ አዳማና ሊባዮ ጥፋት ይሆናል።
\v 24 አሕዛብም ሁሉ፤ እግዚአብሔር በዚች ምድር ላይ ይህን ለምን አደረገባት? ይህ አስፈሪና የሚነድ ቁጣስ ለምን መጣባት? ብለው ይጠይቃሉ።
\s5
\v 25 ሕዝቡም እንዲህ ይላሉ፦ የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ከግብፅ ምድር ያወጣቸውንና ከእነርሱም ጋር ያደረጉትን ቃል ኪዳን ሕዝቡ ስለ ተዉ ነው፤
\v 26 ወጥተውም የማያውቋቸውን እርሱም ያላዘዛቸውን ሌሎችን አማልክት ስለአመለኩአቸውና ስለሰገዱላቸውም ነው።
\s5
\v 27 ስለዚህ በዚህ መጽሐፍ የተጸፈውን ርግማን ሁሉ እስኪያመጣባት ድረስ የእግዚአብሔር ቁጣው በዚህች ምድር ላይ ነደደ።
\v 28 እግዚአብሔር በታላቅ አስፈሪነት፥በቁጣና በንዴት ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው የሚል ይሆናል።
\s5
\v 29 ምስጢር የሆነው ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ ለዘላለም እንድንተገብረው ዘንድ የኛና የልጆቻችን ነው።
\s5
\c 30
\p
\v 1 በፊታችሁ ያስቀመጥሁት ይህ በረከትና መርገም ሁሉ በእናንተ ላይ ሲመጣና አምላካችሁ እግዚአብሔር በትኖአችሁ ከምትኖሩበት አሕዛብ መካከል ሆናችሁ፤
\v 2 ወደ ልባችሁ ተመልሳችሁ ነገሮቹን በምታስተውሉበት ጊዜ፥ እንዲሁም ዛሬ እኔ በማዝዛችሁ ሁሉ መሠረት እናንተና ልጆቻችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመልሳችሁ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እርሱን ስትታዘዙ፤
\v 3 እግዚአብሔር አምላካችሁ ምርኮአችሁን ይመልስላችኋል፤ ይራራላችሁማል፤ እናንተን ከበተነበት አሕዛብ መካከል እንደ ገና ይሰበስባችኋል።
\s5
\v 4 ከሰማይ በታች እጅግ ሩቅ ወደ ሆነ ምድር ብትጋዙ እንኳ እግዚአብሔር አምላካችሁ ከዚያ ይሰበስባችኋል፤ መልሶም ያመጣችኋል።
\v 5 የአባቶቻችሁ ወደ ሆነችው ምድር ያመጣችኋል፤ እናንተም ትወርሱታላችሁ፤ ከአባቶቻችሁ ይበልጥ ያበለጽጋችኋል፤ያበዛችሁማል።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር አምላካችሁን በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እንድትወዱት፤በሕይወትም እንድትኖሩ እግዚአብሔር አምላካችሁ የእናንተንና የዘራችሁን ልብ ይገርዛል።
\v 7 አምላካችሁ እግዚአብሔር ይህን ርግማን ሁሉ በሚጠሉአችሁና በሚያሳድዱአችሁ ጠላቶቻችሁ ላይ ያደርገዋል።
\v 8 እናንተም ተመልሳችሁ ለእግዚአብሔር ትታዘዛላችሁ፥ ዛሬ እኔ የማዛችሁን ትእዛዛ ሁሉ ትጠብቃላችሁ።
\s5
\v 9 በዚያም እግዚአብሔር በእጃችሁ ሥራ ሁሉን በወገባችሁ ፍሬ በእንስሳታችሁ፥ ግልገሎችና በምድራችሁ ሰብል እጅግ ያበለጽጋችኋል። በአባቶቻችሁ ደስ እንደ ተሰኘ ሁሉ እግዚአብሔር እናንተንም በማበልጸግ ደስ ይለዋልና።
\v 10 ይህም የሚሆነው አምላካችሁን እግዚአብሔርን ከታዘዛችሁና በዚህ የሕግ መሕሐፍ የተጻፉትን ትእዛዙንና ሥርዓቱን በመጠበቅ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ስትመለሱ ነው።
\s5
\v 11 ዛሬ የምሰጣችሁ ትእዛዝ ይህን ያህል አስቸጋሪ ወይም ከእናንተ የራቀ አይደለም።
\v 12 እንድንፈጽሙት አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ወደ ሰማይ ይወጣል? እንዳትሉ በሰማይ አይደለም።
\s5
\v 13 ደግሞም እንድናደርገው አምጥቶ ይነግረን ዘንድ ማን ባሕሩን ይሻገራል? እንዳትሉም ከባሕር ማዶ አይደለም።
\v 14 ነገር ግን ቃሉ ለእናንተ በጣም ቅርብ ነው፤ ታደርጉትም ዘንድ በአፋችሁና በልባችሁ ውስጥ ነው።
\s5
\v 15 እነሆ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፥ ሞትንና ጥፋትን በፊታችሁ አኑሬአለሁ።
\v 16 እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ በመንገዱም እንድትሄና ትእዛዙን፥ ሥርዓቱንና ሕጉን እንድትጠብቁ አዝዛችኋል፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ ትበዛላችሁም፤ አምላካችሁም ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡበት ምድር ይባርካችህኋል።
\s5
\v 17 ዳሩ ግን ልባችሁን ወደ ኋላ በመለሰና ባትታዘዙ ለሌሎች አማልክት ለመስገድ ብትታለሉና ብታመልኩአችሁ፤
\v 18 በርግጥ እንደምትጠፉ እኔ በዛሬው ዕለት እነግራችኋለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ትወርሱአት ዘንድ በምትገቡባት ምድር ብዙ አትኖሩባትም።
\s5
\v 19 ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና ርግማንን በፊታችሁ እንዳስቀመጣችሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራችኋለሁ። እንግዲህ እናንተና ልጆቻችሁ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጡ፤
\v 20 ይኸውም እግዚአብሔር አምላካችሁን እንድትወዱ ቃሉን እንድታደምጥና ከእርሱ ጋር እንድትጣበቁ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወታችሁ ነው፤ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለሕስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረጅም ዕድሜ ይሰጣችኋል።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ሙሴም ወጥቶ እነዚህን ቃሎች ለእስራኤል በሙሉ ነገራቸው።
\v 2 እንዲህም አላቸው፦ መቶ ሃያ ዓመት ሆኖኛል ከእንግዲህ መወጣትና መግባት አልችልም፤ እግዚአብሔርም ዮርዳኖስን አትሻገርም ብሎኛል፥
\v 3 እግዚአብሔር አምላካችሁ ራሱ በፊታችሁ ቀድሞ ይሄዳል፤ እነዚህንም አሕዛብ ከፊታችሁ ያጠፋቸዋል፤ እናንተም ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው፤ ኢያሱም እናንተን ቀድሞ ይሻገራል።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር የአሞራውያንን ነገሥታት ሴዎንንና ዐግን ከነምድራቸው እንዳጠፋቸው እነዚህንም ያጠፋቸዋል።
\v 5 እግዚአብሔር እነርሱን በፊታችሁ አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ እናንተም ያዘዝኋችሁን ሁሉ በእነርሱ ላይ ታደርጋላችሁ።
\v 6 ብርቱና ደፋር ሁኑ፥ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡል አላቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንት ጋር ይሄዳልና አይተዋችሁም አይጥላችሁምም።
\s5
\v 7 ከዚያም ሙሴ ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው ሊሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ከዚህ ሕዝብ ጋር አብረህ ስለምትገባ፤ ምድሪቱን ርስታችው አድርገህ ስለምታከፋፍል በርታ፤ ደፋርም ሁን።
\v 8 እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋር ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አተውህምም አትፍራ ተስፋም አትቁረጥ።
\s5
\v 9 ሙሴም ይህን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት ለሚሸከሙ፥ ለሌዊ ልጆች፤ ለካህቱና ለእስራኤል አለቆች ሁሉ ሰጠ።
\v 10 ከዚያም በኋላ ሙሴ እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤ዕዳ በሚተውበት የዳስ በዓልም በሚከበርበት በየሰባቱ ዓመት መጨረሻ
\v 11 እስራኤል ሁሉ እርሱ በሚመርጠው ስፍራ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ሲታይ ይህ ሕግ በእነርሱ ፊት በጆሮአቸው ታነባቸዋላችሁ።
\s5
\v 12 እነርሱም ይስሙና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ይማሩ ዘንድ የዚህን ሕግ ቃል ሁሉ በጥንቃቄ እንዲከተሉ ሕዝቡን ይኸውም ወንዶችን፥ ሴቶችንና ልጆቻቸሁንና በከተሞቻችሁን የሚኖረውንም መጻተኛ ሰብስቡ።
\v 13 ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርሷት ምድር በምትኖሩበት ዘመን ሁሉ ይህን ሕግ የማያውቁት ልጆቻቸሁም መስማትና አምላካችሁን እግዚአብሔርን መፍራት ሊማሩ ይገባቸዋል።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር ሙሴን እነሆ የምትሞትበት ቀን ቀርቦአል፥ ትእዛዝ እንድሰጠው ኢያሱን ጥራውና ወደ መገናኛው ድንኳንም ቅረቡ።
\v 15 እግዚአብሔር በድንኳኑ ላይ በደመና ዐምድ ተገለጠ፤ የደመናውም ዐምድ ከድንኳኑ ደጃፍ ላይ ቆመ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ እነሆ ከአባቶቻችሁ ጋር ልታርፍ ነው፤ ይህም ሕዝብ በሚገባበት ምድር በሚገኙ አማልክት ወዲያውኑ ያመነዝራል፤ እኔን ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር የገባሁትን ኪዳን ያፈርሳሉ።
\s5
\v 17 በዚያም ቀን ቁጣዬ በእነርሱ ላይ ይነዳል፤ እተዋቸዋለሁም። ፊቴንም ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይጠፋሉ። ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር ይደርስባቸዋል፤ በዚያም ቀን ይህ ጥፋት የደረሰሰብን አምላካችን ከእኛ ጋር ባለመሆኑ አይደለምን? ይላሉ።
\v 18 ወደ ባዕዳን አማልክት በመዞር በፈጸሙት ክፋታቸው የተነሣ በዚያን ቀን ፊቴን ከእነርሱ ፈጽሞ እሰውራለሁ።
\s5
\v 19 እንግዲህ ይህን መዝሙር ለራሳችሁ ጻፉና ለእስራኤል ልጆች አስተምሩ። ስለ እኔ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ እንዲዘምሩ አድርጉ።
\v 20 ወተትና ማር ወደምታፈሰውና ለአባቶቻቸው በመሐላ ቃል ወደ ገባህላቸው ምድር ባመጣሃቸው ጊዜ ከበሉና ከጠገቡ፥ ከበለጸጉም በኋላ እኔን ንቀው ኪዳኔንም አፍርሰው ወደ ባዕዳን አማልክት ይዞራሉ፤ እነርሱንም ያመልካሉ።
\s5
\v 21 ብዙ ጥፋትና የከፋ ችግር በደረሰባቸው ጊዜ ይህ መዛሙር ምስክር ይሆንባቸዋል። በዘራቸውም አፍ የሚረሳ አይሆንም፤ ወደ ማልሁላቸው ምድር ሳላስገባቸው በፊት ምን ለማድረግ እንደሚያስቡ እንኳን አስቀድሜ አውቃለሁ።
\s5
\v 22 ስለዚህም ሙሴ ይህን መዝሙር በዚያን ቀን ጻፈና እስራኤላውያንን አስተማራቸው።
\v 23 እግዚአብሔርም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በር ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገባቸዋለህና እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ በማለት ትእዛዝ ሰጠው።
\s5
\v 24 ሙሴ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የዚህን ሕግ ቃል በመጽሐፍ ጽፎ እንዳበቃ፤
\v 25 የእስራኤልን የኪዳን ታቦት የሚሸከሙ ሌዋውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፤
\v 26 ይህን የሕግ መጽሐፍ ውሰዱ፤ በዚያም በእናንተ ላይ ምስክር እንዲሆን በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ቃል ኪዳን ታቦት አጠገብ አኑሩት።
\s5
\v 27 ዐመፀኞችና አንገተ ደንዳኖች እንደ ሆናችሁ አውቃለሁ፥ተመልከቱ እኔ ዛሬ በሕይወት ከእናንተ ጋር እያለሁ እንኳን በእግዚአሔር ላይ እንደህ ካመፃችሁ ከሞትሁ በኋላማ እንዴት አታደርጉም?
\v 28 ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ ጠርቼባቸው ይህን ቃል ይሰሙ ዘንድ ብጆሮኣቸው እንድናገር ፤ የነገድ አለቆቻችሁን በሙሉና ሹሞቻችሁን ሁሉ በፊቴ ሰብስቡ።
\v 29 እኔ ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንደምትረክሱ ካዘዝኋችሁም መንገድ ዘወር እንደምትሉ አውቃለሁና። በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ስለምትፈጽሙ፤ ይህ የሚሆነው እጆቻችሁ በሠሯቸውም ነገሮች እርሱን ለቁጣ ስለምታነሣሡት በሚመጡት ዘመናት ጥፋት ይደርስባችኋል።
\s5
\v 30 ሙሴ የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ ለተሰበሰበው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሮአቸው አሰማ።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ እኔም እናገራለሁ፤ ምድር ሆይ፥ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ።
\v 2 ትምህርቴም እንደ ዝናብ ይውረድ፤ ቃሌም እንደ ጤዛ ይንጠባጠብ፤ በቡቃያ ሣር ላይ እንደ ካፊያ፥ ለጋ ተክልም ላይ እንደ ከባድ ዝናብ ይውረድ።
\s5
\v 3 እኔ የእግዚአብሔርን ስም አውጃለሁ፤ የአምላካችንን ታላቅነት አወድሱ።
\v 4 እርሱ ዐለትና ሥራውም ፍጹም፥ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው። የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፤ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው።
\s5
\v 5 በእርሱ ላይ ክፋት ፈጽመዋል። ከነውራቸው የተነሣ ከእንግዲህ ልጆቹ አይደሉም። ወልጋዳና ጠማማ ትውልዶች ናቸው።
\v 6 እናንተ ተላላና ጥበብ የጎደላችሁ ሕዝብ፤ለእግዚአብሔር የምትመልሱለት በዚህ መንገድ ነውን? አባታችሁና ፈጣሪያችሁ የሠራችሁና ያበጃችሁእርሱ አይደለምን?
\s5
\v 7 የጥንቱን ዘመን፥ የብዙ ዓመቶችን አስታውሱ፤ አባቶቻችሁን ጠይቁ ይነግሩማልም፥ ሽማግሌዎቻችንም ጠይቁ ያስረዱአችኋል።
\v 8 ታላቁ አምላክ ለአሕዛብ ርስታቸውን በሰጠ ጊዜ የሰውንም ዘር በለያየ ጊዜ፤ በእስራኤል ልጆች ቁጥር ልክ፤ የአሕዛብን ርስት ድንበር ለየ።
\s5
\v 9 የእግዚአብሔር ድርሻ የገዛ ሕዝቡ ያዕቆብ የተለየ ርስቱ ነውና።
\v 10 እርሱን በምድረ በዳ፤ ባዶና ጭው ባለ በረሓ ውስጥ አግኘው፤እንደ ዐይኑ ብሌን ጠበቀው።
\s5
\v 11 ንስር ጎጆዋን እንደትጠብቅ፤ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፥ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፥ እግዚአብሔር ክንፎቹን ዘርግቶ፥ ተሸከሞ ወሰዳቸው።
\v 12 እግዚአብሔር ብቻ መራው ምንም ባዕድ አምላክ ከእርሱ ጋር አልነበረም።
\s5
\v 13 በምድር ከፍታ ላይ አስኬደው፤ የእርሻንም ፍሬ መገበው፤ ከዐለት ድንጋይ ማር አበላው፤ ከባልጩትም ድንጋይ ዘይት መገበው። በወንድና በሴት ልጆቹ ተቆጥቶአልና።
\s5
\v 14 የላሙንና የበጉን መንጋ ቅቤና ወትት የሰቡትን በጎችና ፍየሎች፤ የባሳንን ሙኩት በግ፤ መልካም የሆነውንም ስንዴ ማለፊያውንም የወይን ጠጅ ጠጠህ።
\s5
\v 15 ይሹሩን ወፈረ፥ ረገጠ፤ ስብ ጠገበ፥ ሰውነቱ ደነደነ፥ ለሰለሰም። የፈጠረውንም አምላክ ተወ፤ የመጠጊያ ዐለት የሆነውን አዳኙንም ናቀው።
\v 16 በባዕዳን አማልክታቸው አስቀኑት፤ በአስፈያፊ ጣዖቶቻቸውም አስቆጡት።
\s5
\v 17 አምላክ ላልሆኑ አጋንንት፥ ላላወቋቸው አማልክት፥ ከጊዜ በኋላ ለተነሡ አማልክት፥ አባቶቻችውም ላልፈሯቸው አማልክት ሠዉ።
\v 18 አባት የሆናችሁን ዐለት ከዳችሁት፤ የወለዳችሁን አምላክ ረሳችሁ።
\s5
\v 19 እግዚአብሔር ይህን አይቶ ተዋቸው፤ በወንድና በሴት ልጆቹ አስጥተውታልና።
\v 20 እርሱም እንዲህ ብሎአል፦ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፤ የማይታሙንም ልጆች ናቸውና።
\s5
\v 21 አምላክ ላልሆነው አስቀኑኝ፤ በከንቱ ጣዖቶቻቸውም አስቆጡኝ። እኔም ሕዝብ ባልሆነው አስቀናቸዋል፤ በማያስተውልም ሕዝብ አስቆጣቸዋለሁ።
\s5
\v 22 በቁጣዬ እሳት ተቀጣጥሎአልና፤እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነዳል፤ ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።
\s5
\v 23 በመዓት ላይ መዓት አመጣባቸዋለሁ። ፍላጻዬንም በእነርሱ ላይ እተኩሳለሁ። የሚያጠፋ ራብ፤በልቶ የሚጨርስ ቸነፈርና ከባድ መቅሠፍት እሰድባቸዋለሁ፤
\v 24 የአራዊትን ሹል ጥርስ፥ በምድር የሚሳብ የእባብ መርዝም እሰድባቸዋለሁ።
\s5
\v 25 ሰይፍ መንገድ ላይ ያስቀራቸዋል፤ በመኝታቸውም ድንጋጤ ይነግሣል፤ጎልማሳውና ልጃገረዷ፤ ሕፃኑና ሽማግሌው ይጠፋሉ።
\v 26 ከሰዎችም መካከል መታሰቢያቸውን አጠፋለሁ፥ እበትናቸዋለሁም፤አልሁ፤
\s5
\v 27 ድል ያደረገው እጃችን ነው ብለው፥ ጠላቶቻቸው በስሕተት እንዳይታበዩ፥ የጠላት ማስቆጣት እንዳይሆን እሠጋለሁ።
\s5
\v 28 እስራኤላውንም አእምሮ የጎደላቸው፤ ማስተዋልም የሌላቸው ናቸው።
\v 29 አስተዋዮች ቢሆኑ ኖሮ ይህን በተገነዘቡና መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን ባስተዋሉ ነብር።
\s5
\v 30 መጠጊያ ዐለታቸው ካልሸጣቸው እግዚአብሔር ካልተዋቸው በቀር፥ አንድ ሰው እንዴት ሺሁን ያሳድዳል፥ ሁለቱስ እንዴት አሥር ሺሁን እንዲሸሹ ያደጋሉ?
\v 31 የእነርሱ መጠጊያ ዐለታቸው እንደ እኛ መጠጊያ ዐለት አለመሆኑን፤ ጠላቶቻችንም እንኳ አይክዱም።
\s5
\v 32 ወይናቸው ከሰዶም ወይን ከገሞራም እርሻ ይመጣል፤ የወይናቸው ፍሬ በመርዝ፥ ዘለላቸውም መራራ ነው።
\s5
\v 33 ወይናቸው የእባብ መርዝ፤ መርዙም የጨካኝ እባብ ነው።
\v 34 ይህስ በእኔ ዘንድ ተጠብቆ ያለ፤ በመዝገቤስ የታተመ አይደለምን?
\s5
\v 35 በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፥ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቦአል፤ የሚመጣባቸውም ነገሮች ይፈጥንባቸዋል።
\s5
\v 36 ኃይላቸው መድከሙን ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል።
\s5
\v 37 እንዲህም ይላል፦ መጠጊያ ዐለት የሆኗቸው፤ አማልክታቸው ወዴት አሉ?
\v 38 የመሥዋዕታቸውን ስብ የበሉ፤ የመጠጥ ቁርባናችውንም የወይን ጠጅ የጠጡ አማልክት ወዴት ናቸው? እስቲ ይነሡና ይርዷችሁ! እስቲ መጠለያ ይስጧችሁ!
\s5
\v 39 እኔ ራሴ እርሱ እንደ ሆንሁ እዩ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤እገድላለሁ፤ አድናለሁ፤አቆስላለሁ፤ እፈውሳለሁም፤ ከእጄም የሚያስጥል ማንም የለም።
\v 40 እጄን ወደ ሰማይ አነሣለሁ፤ ለዘላለምም ሕያው እንደ ሆንሁ እናገራለሁ።።
\s5
\v 41 የሚያብራቀርቅ ሰይፌን ስዬ እጄ ለፍርድ ስይዘው፤ ባላጋራዎቼን እበቀላቸዋለሁ፤ ለሚጠሉኝም እንደሥራቸው እከፍላቸዋለሁ።
\s5
\v 42 ሰይፌ ሥጋ በሚበላበት ጊዜ፥ ፍላጾቼ በደም እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ደሙ የታረዱትና የምርኮኞች የጠላት አለቆችም ራስ ደም ነው።
\s5
\v 43 አሕዛብ ሆይ ከሕዝቡ ጋር ደስ ይበላችሁ፤ እርሱ የአገልጋዮቹን ደም ይመልሳል፤ጠላቶቹንም ይበቀላል። ምድሪቱንና ሕዝቡን ይቤዣቸዋል።
\s5
\v 44 ሙሴም ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ጋር መጥቶ የመዝሙር ቃሎችን በሕዝቡ ጆሮ ተናገረ።
\v 45 ሙሴም እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለመላው እስራኤል ተናገሮ ጨረሰ።
\s5
\v 46 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በጥንቃቄ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቻችሁን እንድታዟቸው እኔ ዛሬ በግልጥ የምነግራችሁን ቃሎች ሁሉ በልባችሁ አኑሩ።
\v 47 ቃሎቹ ለእናንተ ሕይወታችሁ ናቸው፥ ባዶ ቃሎች አይደሉም፥ በእነርሱ ዮርዳንስን ተሻገራችሁ በምትወርሷትም ምድር ረጅም ዘመን ትኖራላችሁ።
\s5
\v 48 በዚያችም ዕለት እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረ፦
\v 49 ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር ከዓብሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓን ምድር አሻግረህ ተመልከት።
\s5
\v 50 ወንድምህ አሮን በሖር ተራራ ላይ እንደ ሞተና ወደ ወገኖቹ እንደ ተስበስበ ሁሉ አንተም በወጣህበት በዚያ ተራራ ላይ ሙት፤ ወደ ወገኖችህም ተሰብሰብ።
\v 51 ይህ የሚሆንበት ምክንያት ሁለታችሁም በሲን ምድረ በዳ በቃዴስ በምሪባ ውሃ አጠገብ በእስራኤላውያን መካከል በእኔ ላይ ባለመታመናችሁ፤ እንዲሁም በእስራኤላውያን መካከል የሚገባውን አክብሮት ባለመስጠታችሁ ነው።
\v 52 ስለዚህ ምድሪቱን ከሩቅ ሆነህ ታያታለህ እንጂ ለእስራኤል ሕዝብ ወደምሰጣት ምድር አትገባም።
\s5
\c 33
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ከመሞቱ በፊት ለእስራኤላውያን የሰው ቃለ ቡራኬ ይህ ነው።
\v 2 እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ከሲና መጣ፤ በእነርሱም ላይ ከሴይር እንደ ማለዳ ፀሐይ ወጣ፤ ከፋራን ተራራ አበራላቸው፤ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጣ፤ በስተቀኙ የሚነድ እሳት ነበር።
\s5
\v 3 በእርግጥ ሕዝቡን የምትወድ አንተ ነህ፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው። ከእግርህ ሥር ሁሉ ይስገዳሉ፤ ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤
\v 4 ይህ ሙሴ የሰጠን ሕግ የያዕቆብ ጉባኤ ርስት ነው።
\s5
\v 5 የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋር ሆነው፤ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፤ እግዚአብሔር በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር። ሮቤል በሕይወት ይኑር፤ አይሙት።
\v 6 የወገኖቹ ቁጥርም ጥቂት ይሁን።
\s5
\v 7 ስለይሁዳ የተነገረው ባትኮት ይህ ነው። ሙሴም እንዲህ አለ፦ እግዚአብሔር ሆይ፥ የይዳን ጩኸት ስማ፤ ወደ ወገኖቹም እንደገና አምጣው። ስለእርሱ ተዋጋለት፤ አቤቱ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋ ረዳቱ ሁን!
\s5
\v 8 ስለ ሌዊም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ቱሚምህና ኡሪምህ ለምትወደው ሰው ይሁን፤ ማሳህ በተባለው ቦታ ፈተንኸው፤ በመሪባም ውሃ ከእርሱ ጋር ተከራከርህ።
\s5
\v 9 ስለ አባቱና ስለ እናቱ ሲናገርም፤ ስለ እነርሱ ግድ የለኝም አለ። ወንድሞቹን አልለያቸውም፤ ልጆቹንም አላወቃቸውም። ስለቃልህ ከለላ አደረገ፤ ኪዳንህንም ጠበቀ።
\s5
\v 10 ሥርዓትህን ለያዕቆብ፤ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራል። ዕጣን በፊትህ፤ ያሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ በምሠዊያህ ላይ ያቀርባል።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር ሆይ፥ ኃይሉን ሁሉ ባርክለት፤ በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤ በእርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቁረጠው፤ ጠላቶቹንም እንደገና እንዳይነሡ አድርገህ ምታቸው።
\s5
\v 12 ሙሴ ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወደውን ሰው በትክሻዎቹ መካከል ያርፋል።
\s5
\v 13 መሴ ስለ ዮሴፍ ደግሞ እንዲህ አለው፦ እግአብሔር ምድሩን ይባርክ፤ ውድ በሆኑ ሰማያዊ ነገሮች፥ ጠል ከላይ በማውረድ፤ ከታች በጥልቅ በተንጣለለው ነገሮች ይባርክ።
\s5
\v 14 ከፀሐይ በተሠሩ ምርጥ ፍሬ፤ ጨረቃም በምትሰጠው እጅግ መልካም ነገር፤
\v 15 ከጥንት ተራሮች በተገኘ ምርጥ ስጦታ፤ በዘላለማዊ ኮረብቶች ፍሬያማነት ይባርክ።
\s5
\v 16 ምድር በምታስገኘው ውድ ስጦታና በብዛት በቁጥቋጦም ውስጥ በነበረው በእርሱ መልካም ሞገስ። እነዚህ ሁሉ በረከቶች በወንድሞቹ መካከል ገዥ በሆነው፤ በዮሴፍ ራስ ላይ ይውረድ።
\s5
\v 17 በግርማው እንደ በኩር ኮርማ ነው፤ ዘንዶቹም የጎሽ ቀንዶች ናቸው። በእነርሱም ሕዝቦችን በምድር ዳርቻ ላይ ያሉትን እንኳ ሳይቀር ይወጋል፤ እነርሱም የኤፍሬም አሥር ሺዎቹ ናቸው።
\s5
\v 18 ስለ ዛብሎንም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ዛብሎን ሆይ፥ ወደ ውጭ በመውጣትህ፤ አንተም ይሳኮር በድንኳኖችህ ውስጥ ደስ ይበልህ።
\v 19 እነርሱም አሕዛብን ወደ ተራራው ይጠራሉ፤ በዚያም የጽድቅን መሥዋዕት ያቀርባሉ። እነርሱም ከባሕሮች በአሸዋ ውስጥ የተደበቀውን ሀብት ያወጡበታል።
\s5
\v 20 ስለ ጋድም ሙሴ እንዲህ አለ፦ የጋድን ግዛት የሚያሰፋ የተባረከ ይሁን! ክንድንና ራስን በመገነጣጠል፤ ጋድ እንደ አንበሳ በዚያ ይኖራል።
\s5
\v 21 ለአለቃን ድርሻ ሆኖ የተጠበቀለትን ለም የሆነውን መሬት ለራሱ መረጠ። ከሕዝብ አለቆች ጋር መጣ። በእስራኤል ላይ የወሰነውን የእግዚአብሔርን ሥርዓትንና ፍርዱን ፈጸመ።
\s5
\v 22 ስለ ዳንም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ዳን ከባሳን ዘሎ የሚወጣ፤ የአንበሳ ደቦል ነው።
\s5
\v 23 ስለ ንፍታሌምም ሙሴ እንዲህ አለ፦ ንፍታሌም በእግዚአብሔር ሞገስ ረክቶአል፤ በበረከቱም ተሞልቶአል፤ ባሕሩንና የደቡብን ምድር ይወርሳል።
\s5
\v 24 ስለ አሴርም ሙሴ እንዲህ አለ፦ አሴር ከሌሎች ልጆች ይልቅ የተባረከ ይሁን፤ በወንሞቹ ዘንድ ተወዳጅ ይሁን፤ እግሩንም በዘይት ውስጥ ያጥልቅ።
\v 25 በዘመንህና ደህንነትህ ሁሉ የደጃፍህ መቀርቀሪያ ብረትና ናስ ይሁን፤ ኃይልህም በዘመንህ ሁሉ ይኖራል።
\s5
\v 26 አንተን ለመርዳት በሰማያት ላይ በግርማው በደመናትም የሚገሠግሥ፤ እንደ ይሽሩን አምላክ ያለ ማንም የለም።
\s5
\v 27 ዘላለማዊ አምላክ መኖርያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከበታችህ ናቸው፤ እርሱን አጥፋው! በማለት፤ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።
\s5
\v 28 ስለዚህ እስራኤል በሰላም ይሆራል።። የሰማያት ጠል በሚወርድበት፤ እህልና የወይን ጠጅ ባለበት ምድር የያዕቆብን ምንጭ የሚነካው የለም።
\s5
\v 29 እስራኤል ሆይ፥ አንተ ቡሩክ ነህ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፤ እንዳንተ ያለ ማን ነው? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፤ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ ተሸብራው በፍርሃት፤ ወደ አንተ ይመጣሉ። አንተም ከፍታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።
\s5
\c 34
\p
\v 1 ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ ወደ ናባው ተራራ ሄደ። በዚያም እግዚአብሔር ከገለዓድ እስከ ዳን ያለውን ምድሪቱን ሁሉ፤
\v 2 ንፍታሌምን ሁሉ፥የኤፍሬምንና የምናሴን ግዛት እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ያለውን የይሁዳን ምድር ሁሉ አሳየው፤
\v 3 ኔጌብንና የዘንባባ ከተማ ከሆነችው ከኢያሪኮ ሸለቆ እስከ ዞዓር ያለውን ምድር ሁሉ አሳየው።
\s5
\v 4 ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ለአብርሃም፥ ለይስሐንና ለያዕቆብ ለአባቶቻችሁ እሰጣለሁ ብዬ በመሐላ ቃል የገባሁላቸው ምድር፥ በዐይንህ እንድታያት አድርጌአለሁ፤ ነገር ግን ወደዚያ አትሻገርም አለው።
\v 5 እግዚአብሔር እንደተናገረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ።
\v 6 በሞዓብ ምድር በቤተ ፌጎር ፊት ለፊት ባለው ሸለቆ እግዚአብሔር ቀበረው፤ ይሁን እንጂ መቃብሩ የት እንደ ሆን እስከ ዛሬ ማንም አያውቅም።
\s5
\v 7 ሙሴ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሃያ ዓመት ነበር፤ ሆኖም ዐይኑ አልፈዘዘም፤ ጉልበቱም አልደከመም።
\v 8 የልቅሶውና የሐዘኑ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ እስራኤላውያን በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን አለቀሱለት።
\s5
\v 9 ሙሴ እጆቹን ጭኖበት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ መንፈስ ተሞላ። ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ አደመጡት፤ እግዚአብሔር ሙሴን አዞት የነበረውንም ሁሉ አደረገ።
\s5
\v 10 እግዚብብሔር ፊት ለፊት ያወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል አልተነሣም።
\v 11 እግዚአብሔር ልኮት እነዚያን ታምራዊ ምልክቶችና ድንቆች ሁሉ በግብፅ በፈርዖን በሹማምንቱና በምድሪቱ ሁሉ ላይ እንዲያደርግ የላከውን ያደረገ ማንም ሰው አልነበረም።
\v 12 ሙሴ በእስራኤል ሁሉ ፊት ያሳየውን ታላቅ ኃይል ያሳየ ወይም ያደረገውን አስደናቂ ተግባር የፈጸመ ማንም ነቢይ የለም።

176
08-RUT.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,176 @@
\id RUT
\ide UTF-8
\h ሩት
\toc1 ሩት
\toc2 ሩት
\toc3 rut
\mt ሩት
\s5
\c 1
\p
\v 1 መሳፍንት ይገዙ በነበረበት ዘመን በምድሪቱ ላይ ራብ ነበረ። አንድ ከበተልሔም ይሁዳ የሆነ ሰው ከሚስቱና ከሁለቱ ልጆቹ ጋር ወደ ሞአብ አገር ሄደ፡፡
\v 2 የሰውዮው ስም አቤሜሌክ ይባል ነበር፣ የሚስቱም ስም ኑኃሚን ይባላል፡፡ የሁለቱም ወንዶች ልጆቹ ስም መሐሎንና ኬሌዎን፣ የይሁዳ ቤተልሔም ኤፍራታውያን ነበሩ፡፡ እነርሱም ወደ ሞዓብም አገር ደረሱና በዚያ ተቀመጡ፡፡
\s5
\v 3 የኑኃሚንም ባል አቤሜሌክ ሞተ እርስዋም ከሁለቱ ወንዶች ልጆችዋ ጋር ቀረች፡፡
\v 4 እነዚህ ወንዶች ልጆች ከሞዓባውያን ሴቶች ሚስቶችን ወሰዱ፤ የአንዷ ስም ዖርፋ ነበር፣ የሌላኛዋ ስም ደግሞ ሩት ነበረ። በዚያም ለአሥር ዓመታት ያህል ተቀመጡ፡፡
\v 5 ከዚያም መሐሎንና ኬሌዎን ሁለቱም ሞቱ፣ ኑኃሚንም ያለ ባልዋና ያለ ሁለቱ ልጆችዋ ብቻዋን ተለይታ ቀረች፡፡
\s5
\v 6 በዚያን ጊዜ ኑኃሚን ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ሞአብን ለመልቀቅና ወደ ይሁዳ ለመመለስ ወሰነች፡፡ እርስዋም በሞዓብ ምድር ሳለች እግዚአብሔር የተቸገሩትን ሕዝቡን እንደረዳቸውና መብልን እንደ ሰጣቸው ሰማች፡፡
\v 7 ስለዚህ እርስዋ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከነበረችበት ስፍራ ለቀቀች፣ ከዚያም ወደ ይሁዳ ምድር ለመመለስ መንገዱን ይዘው ወደታች ሄዱ፡፡
\s5
\v 8 ኑኃሚን ለምራቶችዋ “ሂዱ፣ እያንዳንዳችሁ ወደ እናታችሁ ቤት ተመለሱ፡፡ ለሞቱትና ለእኔ ታማኝነት እንዳሳያችሁን ሁሉ፣ እግዚአብሔር ለእናንተ ታማኝነቱን ያሳያችሁ፡፡
\v 9 ጌታ እያንዳንዳችሁን በሌላ ባል ቤት ዕረፍት ይስጣችሁ” አለቻቸው፡፡ ከዚያም ሳመቻቸው፣ እነርሱም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ፡፡
\v 10 እነርሱም “አይሆንም! ከአንቺ ጋር ወደ ሕዝብሽ እንመለሳለን” አሉአት፡፡
\s5
\v 11 ኑኃሚን ግን “ልጆቼ ሆይ፣ ተመለሱ! ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ ይሆኑ ዘንድ ለእናንተ የሚሆኑ ወንዶች ልጆች በማሕጸኔ አሁን አሉን?
\v 12 ልጆቼ ሆይ፣ ተመለሱ፣ በራሳችሁ መንገድ ሂዱ፤ ባል ለማግባት በጣም አርጅቻለሁና፡፡ ዛሬ ማታ ባል አገኛለሁ ብየ እንኳ ተስፋ ባደርግና ወንዶች ልጆችን ብወልድ፣
\v 13 እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትጠብቃላችሁን? እየጠበቃችሁ አሁን ባል ሳታገቡ ትቀራላችሁን? አይሆንም፣ ልጆቼ ሆይ! ከእናንተ ይልቅ ሁኔታው እኔን እጅግ በጣም ያስመርረኛል፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ወጥቶአልና፡፡
\s5
\v 14 በዚያን ጊዜ ምራቶችዋ ድምፃቸውንም ከፍ አደረጉና እንደገና አለቀሱ፡፡ ዖርፋም አማትዋን ሳመቻትና ተሰናበተቻት፣ ሩት ግን ተጠግታ ያዘቻት፡፡
\v 15 ኑኃሚንም “አድምጪኝ፣ እነሆ የባልሽ ወንድም ሚስት ወደ ሕዝብዋና ወደ አማልክትዋ ተመልሳለች፡፡ ከባልሽ ወንድም ሚስት ጋር አንቺም ተመለሽ” አለቻት፡፡
\s5
\v 16 ነገር ግን ሩት “ከአንቺ ርቄ እንድሄድ አታድርጊኝ፣ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፤ በምትቆይበትም እቆያለሁና፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ ይሆናል፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፡፡
\v 17 በምትሞችበትም እሞታለሁ፣ በዚያም እቀበራለሁ፡፡ ከሞት በቀር እኛን አንድም ነገር ቢለየን እግዚአብሔር ይቅጣኝ፣ ከዚህም በላይ ያድርግብኝ” አለቻት፡፡
\v 18 ኑኃሚን ሩት ከእርስዋ ጋር ለመሄድ እንደ ወሰነች ባየች ጊዜ፣ ከእርስዋ ጋር መከራከር አቆመች፡፡
\s5
\v 19 ስለዚህ ሁለቱም ወደ ቤተ ልሔም ከተማ እስኪመጡ ድረስ ተጓዙ፡፡ ወደ ቤተ ልሔምም በደረሱ ጊዜ፣ ከተማው በሙሉ ስለ እነርሱ እጅግ በጣም ተደነቁ፡፡ ሴቶችም “ይህች ኑኃሚን ናትን? ” አሉ፡፡
\v 20 እርስዋ ግን “ኑኃሚን ብላችሁ አትጥሩኝ፡፡ ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን መራራ አድርጎታልና፣ ማራ በሉኝ” አለቻቸው፡፡
\v 21 በሙላት ሄድሁ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ ቤቴ ባዶዬን እንደገና መለሰኝ፡፡ ታዲያ እግዚአብሔር አዋርዶኝ፣ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስጨንቆኝ እያያችሁ ለምን ኑኃሚን ትሉኛላችሁ? ” አለቻቸው፡፡
\s5
\v 22 ስለዚህ ኑኃሚንና ምራትዋ ሞአባዊት ሩት ከሞዓብ አገር ተመለሱ፡፡ እነርሱ የገብስ መከር በተጀመረ ጊዜ ወደ ቤተልሔም መጡ፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 የኑኃሚን ባል አቤሜሌክ፣ በጣም ባለጠጋና ኃያል ሰው የሆነ ቦዔዝ የሚባል ዘመድ ነበረው፡፡
\v 2 ሞዓባዊቱ ሩት ኑኃሚንን “አሁን ልሂድና ወደ እርሻዎች ገብቼ እህል ልቃርም፡፡ በፊቱ ሞገስ የማገኘውን ሰው እከተላለሁ” አለቻት፡፡ ኑኃሚንም “ልጄ ሆይ፣ ሂጂ” አለቻት፡፡
\s5
\v 3 ሩት ሄደችና ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፡፡ እርስዋም የአቤሜሌክ ዘመድ ወደሆነው ወደ ቦዔዝ እርሻ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ደረሰች።
\v 4 እነሆም፣ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣና ለአጫጆቹ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን” አላቸው፡፡ እነርሱም “እግዚአብሔር ይባርክህ” ብለው መለሱለት፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ቦዔዝ በአጫጆቹ ላይ ተቆጣጣሪ የነበረውን አገልጋዩን “ይህች ወጣት ሴት የማን ናት? ” አለው፡፡
\v 6 አጫጆቹንም የሚቆጣጠረው አገልጋይ “ይህች ወጣት ሞዓባዊት ከሞዓብ ምድር ከኑኃሚን ጋር የመጣች ናት” አለው፡፡
\v 7 እርስዋም ‘ከአጫጆቹ በኋላ እየተከተልሁ የእህል ቃርሚያ እንድቃርምና እንድለቅም እባክህ ፍቀድልኝ አለች’ አለው፡፡ ስለዚህ እርስዋም ወደዚህ መጣች፣ በቤት ጥቂት ከማረፍዋ በስተቀር፣ ከጠዋት ጀምራ እስከ አሁን ድረስ መቃረም ቀጥላለች፡፡”
\s5
\v 8 የዚያን ጊዜ ቦዔዝ ሩትን “ልጄ ሆይ፣ እኔን እያዳመጥሽኝ ነውን? ወደ ሌላ እርሻ ሄደሽ አትቃርሚ፤ ከእርሻየ አትሂጂ፣ ይልቁንም በዚህ ቆዪና ከወጠት ሴቶች ሰራተኞቼ ጋር አብረሽ ስሪ፡፡
\v 9 ዓይኖችሽ ሰዎቹ ወደሚያጭዱበት ስፍራ ብቻ ይመልከቱ፣ ሌሎቹንም ሴቶች ተከተያቸው፡፡ ሰዎቹን እንዳይነኩሽ አላዘዝኋቸውምን? ሲጠማሽ ወደ ውኃ ማሰሮዎቹ ሄደሽ ወንዶቹ ከቀዱት ውኃ መጠጣት ትችያለሽ” አላት፡፡
\s5
\v 10 ከዚያም በግንባርዋ መሬቱን በመንካት በቦዔዝ ፊት ሰገደች፡፡ እርስዋም “እኔ እንግዳ የሆንሁት ታስበኝ ዘንድ በአንተ ፊት ሞገስ ያገኘሁት ለምንድን ነው? ” አለችው፡፡
\v 11 ቦዔዝም ለእርስዋ “ባልሽ ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ የሰራሽው ስራ ሁሉ ለእኔ ተነግሮኛል፡፡ አማትሽን ለመከተልና ወደ ማታውቂው ሕዝብ ለመምጣት አባትሽንና እናትሽን የተወለድሽባትንም ምድር ትተሻል፡፡
\v 12 ስለ ስራሽ እግዚአብሔር ይክፈልሽ፡፡ ከክንፉ በታች መጠጊያ ካገኘሽበት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ሙሉ ደመወዝሽን ተቀበይ” አላት፡፡
\s5
\v 13 እርስዋም “ጌታዬ ሆይ፣ ምንም እንኳ እኔ ከሴት አገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ባልሆንም አጽናንተኸኛልና፣ እኔን በደግነት አናግረኸኛልና በፊትህ ሞገስን ላግኝ” አለቸው፡፡
\s5
\v 14 በምሳም ጊዜ ቦዔዝ ለሩት እንዲህ አላት፡- “ወደዚህ ነይ፣ እንጀራም ብዪ፣ ጉርሻሽንም በሆምጣጤው ወይን አጥቅሺው፡፡” በአጫጆቹም አጠገብ ተቀመጠች፣ እርሱም የተጠበሰ እህል ሰጣት፣ እርስዋም እስክትጠግብ ድረስ በላች፣ የቀረውንም አተረፈች፡፡
\s5
\v 15 ለመቃረም ስትነሳ፣ ቦዔዝ ወጣት አገልጋዮቹን “በነዶው መካከልም እንድትቃርም ፍቀዱላት፣ ምንም መጥፎ ነገር ለእርስዋ አትናገሩአት፡፡
\v 16 ደግሞም ከነዶው ዘለላዎች አስቀርታችሁ በእርግጠኝነት ልተተዉላት ይገባል፣ እንድትቃርም ለእርስዋ ተዉላት፡፡ እርስዋንም አትውቀሱአት” ብሎ አዘዛቸው፡፡
\s5
\v 17 ስለዚህ በእርሻው ውስጥ እስከ ማታ ድረስ ቃረመች፡፡ ከዚያም የቃረመችውን እህል ወቃችው፣ የወቃችውም እህል አንድ የኢፍ መስፈሪያ ያህል ገብስ ሆነ፡፡
\v 18 እርስዋም ተሸክማው ወደ ከተማ ሄደች፡፡ አማትዋም የቃረመችውን አየች፡፡ ሩትም በልታ ከጠገበች በኋላ የተረፋትን የተጠበሰ እህል አውጥታ ለእርስዋ ሰጠቻት፡፡
\s5
\v 19 አማትዋም ለእርስዋ እንዲህ አለቻት፡-“ዛሬ የቃረምሽው ወዴት ነው? ለመስራትስ ወዴት ሄድሽ? የረዳሽ ሰው የተባረከ ይሁን፡፡” ከዚያም ሩት ለአማትዋ የቃረመችበት እርሻ ባለቤት ስለሆነው ሰው ነገረቻት፡፡ እርስዋም “ዛሬ ቃርሚያ የቃረምሁበት እርሻ ባለቤት ስሙ ቦዔዝ ይባላል” አለቻት፡፡
\v 20 ኑኃሚንም ለምራትዋ “ታማኝነቱን በሕያዋንና በሙታን ላይ ባልተወው በእግዚአብሔር የተባረከ ይሁን” አለቻት፡፡ ኑኃሚንም ደግሞ “ይህ ሰው ለእኛ የቅርብ ዘመዳችን ነው፣ ከሚቤዡን አንዱ ነው” አለቻት፡፡
\s5
\v 21 ሞዓባዊቱ ሩትም “በእርግጥም፣ እንዲህ አለኝ፣ ‘መከሬን ሁሉ እስኪጨርሱ ድረስ ከወጣት ወንዶች ሰራተኞቼ አትራቂ፡፡’”
\v 22 ኑኃሚንም ለምራትዋ ለሩት “ልጄ ሆይ፣ ከወጣት ሴቶች ሰራተኞቹ ጋር ብትወጪ መልካም ነው፣ በሌላ በየትኛውም እርሻ ጉዳት እንዳያገኝሽ” አለቻት፡፡
\s5
\v 23 ስለዚህም እርስዋ እስከ ገብሱና ስንዴው መከር መጨረሻ ድረስ ልትቃርም ወደ ቦዔዝ ሴቶች ሰራተኞች ተጠግታ ቆየች፡፡ እርስዋም ከአማትዋ ጋር ትኖር ነበር፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 አማትዋም ኑኃሚን ለእርስዋ “ልጄ ሆይ፣ ታርፊ ዘንድ፣ ነገሮችም ለአንቺ መልካም ይሆኑልሽ ዘንድ፣ የምታርፊበትን ስፍራ አልፈግልሽምን? ” አለቻት፡፡
\v 2 አሁንም ቦዔዝ፣ ከወጣት ሴቶች ሰራተኞቹ ጋር የነበርሽበት ሰው፣ ዘመዳችን አይደለምን? ተመልከቺ፣ እርሱ ዛሬ ማታ በአውድማው ላይ ገብሱን በመንሽ ይበትናል፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህ፣ ታጠቢ፣ ሽቶሽን ተቀቢ፣ ልብስሽን ቀይሪ፣ ወደ አውድማውም ውረጂ፡፡ ነገር ግን መብላትና መጠጣት እስኪጨርስ ድረስ ለሰውዮው አትታወቂ፡፡
\v 4 በተኛም ጊዜ፣ ወደ እርሱ መሄድ እንድትችይ እርሱ የተኛበትን ስፍራ ማስታወስሽን እርግጠኛ ሁኚ፣ እግሩን ግለጪ፣ በዚያም ተጋደሚ፡፡ ከዚያም የምታደርጊውን እርሱ ይነግርሻል፡፡
\v 5 ሩትም ለኑኃሚን “የተናገርሽኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አለቻት፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ ወደ አውድማውም ወረደች፣ እርስዋም አማትዋ የሰጠቻትን ትዕዛዝ ተከተለች፡፡
\v 7 ቦዔዝም በበላና በጠጣ ጊዜ፣ ልቡም ደስ ባለው ጊዜ፣ በእህሉ ክምር ጫፍ ሊተኛ ሄደ፡፡ ከዚያም ሩት በቀስታ መጣች፣ እግሩንም ገለጠች፣ ተኛችም፡፡
\s5
\v 8 እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ ሰውዮው ደነገጠ፡፡ እርሱም ዘወር አለ፣ አንዲትም ሴት እዚያው እግርጌው ተኝታ ነበረች፡፡
\v 9 እርሱም “ማን ነሽ? አለ፡፡ እርስዋም “እኔ ሴት አገልጋይህ ሩት ነኝ” አለችው፡፡ አንተ የቅርብ ዘመዴ ነህና ልብስህን በሴት አገልጋይህ ላይ ዘርጋ አለችው፡፡
\s5
\v 10 ቦዔዝም፣ “ልጄ ሆይ፣ በእግዚአብሔር የተባረክሽ ሁኚ፡፡ ከመጀመርያው ይልቅ በመጨረሻ ብዙ ደግነት አሳይተሻል፣ ምክንያቱም ድሃም ይሁን ባለጠጋ ከወጣት ወንዶች ከአንዳቸውም ጋር አልሄድሽምና” አላት፡፡
\v 11 አሁንም፣ ልጄ ሆይ፣ አትፍሪ! ያልሽውን ሁሉ አደርግልሻለሁ፣ ምክንያቱም በከተማየ ያሉ ሕዝብ ሁሉ ምግባረ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ ያውቃሉ፡፡
\s5
\v 12 አሁን እኔ የቅርብ ዘመድ መሆኔ እውነት ነው፤ ይሁን እንጂ ከእኔ የበለጠ የሚቀርብ ዘመድ አለ፡፡
\v 13 ዛሬ ሌሊት እዚህ ቆዪ፣ ነገም ጠዋት የዋርሳነትን ግዴታ እርሱ የሚፈጽም ከሆነ፣ መልካም ነው፣ የዋርሳነትን ግዴታ ይፈጽም፡፡ ነገር ግን እርሱ ለአንቺ የዋርሳነትን ግዴታ ባይፈጽም፣ ሕያው እግዚአብሔርን እኔ አደርገዋለሁ፡፡ እስከ ማለዳ ድረስ ተኚ፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህ እስከ ማለዳ ድረስ በእግርጌው ተኛች፡፡ ነገር ግን አንዱ ሌላውን ማወቅ ከመቻሉ በፊት ተነሳች፡፡ ቦዔዝ “ሴት ወደ አውድማው መምጣትዋን ማንም እንዳያውቅ” ብሎ ነበርና፡፡
\v 15 ከዚያም ቦኤዝ “የለበስሽውን ልብስ አምጭና ያዢው” አላት፡፡ በያዘችም ጊዜ ስድስት ትልቅ መስፈሪያ ገብስ በልብሷ ላይ ሰፍሮ አሸከማት፡፡ የዚያን ጊዜ እርሱ ወደ ከተማ ሄደ፡፡
\s5
\v 16 ሩት ወደ አማትዋ በመጣች ጊዜ “ልጄ ሆይ፣ እንዴት ነሽ? ” አለቻት፡፡ ሩትም ሰውዮው ለእርስዋ ያደረገውን ሁሉ ነገረቻት፡፡
\v 17 እርስዋም “እነዚህ ስድስት መስፈሪያ ገብስ እርሱ የሰጠኝ ናቸው፣ ‘ወደ አማትሽ ባዶ እጅሽን አትሂጂ’” ብሏልና፡፡
\v 18 ኑኃሚንም “ልጄ ሆይ፣ ይህ ጉዳይ እንዴት እንደሚሆን እስከምታውቂ ድረስ በዚህ ቆዪ፣ ሰውዮው ይህን ነገር ዛሬ እስኪጨርስ ድረስ አያርፍምና” አለች፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ቦዔዝም ወደ ከተማይቱ በር ሄደና በዚያ ተቀመጠ፡፡ ወዲያውኑ ቦዔዝ ሲናገርለት የነበረው የቅርብ ዘመድ መጣ፡፡ ቦዔዝም ለእርሱ “ወዳጄ ሆይ፣ ና በዚህም ተቀመጥ” አለው፡፡ ሰውየውም መጣና ተቀመጠ፡፡
\v 2 ቦዔዝም ከከተማይቱ ሽማግሌዎች አሥር ሰዎች ወሰደ፣ “በዚህ ተቀመጡ” አላቸው፡፡ እነርሱም ተቀመጡ፡፡
\s5
\v 3 ቦዔዝም የቅርብ ዘመድ ለሆነው፣ “ከሞዓብ ምድር የተመለሰችው ኑኃሚን የወንድማችንን የአቤሜሌክን ቁራሽ መሬት ትሸጣለች፡፡
\v 4 እኔም ለአንተ አስታውቅህ ዘንድ አሰብሁ እንዲህም አልሁ፡- ‘ይህንን መሬት በዚህ በተቀመጡት በሕዝቤ ሽማግሌዎች ፊት ግዛው፡፡’ መቤዠት ብትፈልግ ተቤዠው፡፡ ነገር ግን መቤዠት የማትፈልግ ከሆነ ግን ከአንተ በቀር ሌላ የሚቤዥ የለምና፣ እኔም ከእአንተ በኋላ ነኝና እንዳውቀው ንገረኝ” አለው፡፡ የዚያን ጊዜ ሌላኛው ሰው “እቤዠዋለሁ” አለው፡፡
\s5
\v 5 ቦዔዝም “ከኑኃሚን እጅ እርሻውን በምትገዛበት ቀን፣ የሞተውን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንድታስነሣለት የምዋቹን ሰው ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ደግሞ መውሰድ አለብህ” አለ፡፡
\v 6 የቅርብ ዘመድ የሆነውም “የራሴን ርስት ሳልጎዳ እርሻውን ለራሴ መቤዠት አልችልም፡፡ እኔ ልቤዠው አልችልምና የእኔን የመቤዠት መብት ለራስህ ውሰድ” አለ፡፡
\s5
\v 7 በጥንት ዘመን መቤዠትና የሸቀጦች መለዋወጥ በተመለከተ በእስራኤል ዘንድ አንድ ልማድ ነበረ፡፡ ሁሉንም ነገር ለማጽናት ሰው ጫማውን ያወልቅና ለባልንጀራው ይሰጠዋል፤ በእስራኤል ውስጥ ሕጋዊ ስምምነት የሚኖረው በዚህ ሁኔታ ነበር፡፡
\v 8 ስለዚህ የቅርብ ዘመዱ ቦዔዝ፣ “አንተ ለራስህ ግዛው” አለው፡፡ እርሱም ጫማውን አወለቀ፡፡
\s5
\v 9 ቦዔዝም ለሽማግሌዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ፣ “ለአቤሜሌክ የነበረውን ሁሉ እንደዚሁም ለኬሌዎንና ለመሐሎንም የነበረውን ሁሉ ከኑኃሚን እጅ እኔ መግዛቴን እናንተ ዛሬ ምስክሮች ናችሁ፡፡
\v 10 ከዚህም በላይ ስለ መሐሎን ሚስት ስለ ሞዓባዊቷ ሩት፡- የምዋቹን ሰው ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ፣ ስሙ ከወንድሞቹ መካከልና ከአገሩም ደጅ እንዳይጠፋ፣ እኔ ደግሞ እርስዋ ሚስቴ እንድትሆን ወስጃታለሁ፡፡ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 11 በበሩ የነበሩ ሕዝብ ሁሉና ሽማግሌዎቹም እንዲህ አሉ፡- “እኛ ምስክሮች ነን፡፡ እግዚአብሔር ወደ ቤትህ የመጣችውን ሴት የእስራኤልን ቤት እንደ ገነቡት እንደ ሁለቱ እንደ ራሔልና ልያ ያድርጋት፡፡ አንተም በኤፍራታ ባለጠጋ ሁን፣ በቤተ ልሔምም እንደገና የታወቅህ ሁን፡፡
\v 12 ቤትህ እግዚአብሔር ከዚህች ወጣት ሴት በሚሰጥህ ዘር በኩል ትዕማር ለይሁዳ እንደወለደችለት እንደ ፋሬስ ቤት ይሁን” አሉት፡፡
\s5
\v 13 ስለዚህ ቦዔዝ ሩትን ወሰደ፣ ሚስቱም ሆነች፡፡ እርሱም ከእርስዋ ጋር ተኛ፣ እግዚአብሔርም ልጅ እንድትፀንስ ፈቀደላት፣ እርዋም ወንድ ልጅ ወለደች፡፡
\v 14 ሴቶችም ለኑኃሚን፣ “ዛሬ የሚቤዥ የቅርብ ዘመድ ያላሳጣሽ እግዚአብሔር ይባረክ፡፡ ይህ ሕጻን ስሙ በእስራኤል ውስጥ የገነነ ይሁን፡፡
\v 15 ይህ ልጅ ለአንቺ ሕይወትሽን የሚያድስ እርጅናሽንም የሚመግብ ይሁን፣ የምትወድሽ፣ ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ የምትሻል፣ ምራትሽ ይህን ልጅ ወልዳለችና፡፡
\s5
\v 16 ኑኃሚንም ሕፃኑን ወሰደችው፣ በእቅፍዋም አስቀመጠችው፣ እርሱንም ተንከባከበችው፡፡
\v 17 ጎረቤቶቿ የሆኑት ሴቶችም “ለኑኃሚን ወንድ ልጅ ተወለደላት” እያሉ ስም ሰጡት፡፡እነርሱም ስሙን ኢዮቤድ ብለው ጠሩት፡፡ እርሱም የዳዊት አባት የሆነው፣ የእሴይ አባት ሆነ፡፡
\s5
\v 18 አሁንም እነዚህ የፋሬስ ትውልድ ነበሩ፡- ፋሬስ የኤስሮም አባት ሆነ፣
\v 19 ኤስሮምም የአራም አባት ሆነ፣ አራምም የአሚናዳብ አባት ሆነ፣
\v 20 አሚናዳብም የነአሶን አባት ሆነ፣ ነአሶንም የሰልሞን አባት ሆነ፣
\v 21 ሰልሞንም የቦዔዝ አባት ሆነ፣ ቦዔዝም የኢዮቤድ አባት ሆነ፣
\v 22 ኢዮቤድ የእሴይ አባት ሆነ፣ እሴይም የዳዊት አባት ሆነ፡፡

1671
09-1SA.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1671 @@
\id 1SA
\ide UTF-8
\h 1ኛ ሳሙኤል
\toc1 1ኛ ሳሙኤል
\toc2 1ኛ ሳሙኤል
\toc3 1sa
\mt 1ኛ ሳሙኤል
\s5
\c 1
\p
\v 1 በተራራማው በኤፍሬም አገር በራማ መሴፋ የሚኖር አንድ ሰው ነበር፤ ስሙ ሕልቃና ይባላል፥ እርሱም የኤፍሬማዊው የናሲብ ልጅ፥ የቶሑ ልጅ፥ የኤሊዮ ልጅ፥ የኢያርምኤል ልጅ ነበር።
\v 2 እርሱም ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤ ስማቸውም የአንደኛዋ ሐና፥ የሁለተኛዋም ፍናና ነበር። ፍናና ልጆች ነበሯት፣ ሐና ግን አንድም ልጅ አልነበራትም።
\s5
\v 3 ይህም ሰው በየዓመቱ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ለመስገድና መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ሴሎ ይሄድ ነበር። የእግዚአብሔር ካህናት የሆኑት ሁለቱ የኤሊ ወንዶች ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ ነበሩ።
\v 4 በየዓመቱ ሕልቃና የሚሠዋበት ጊዜ ሲደርስ፥ ለሚስቱ ፍናና፥ ለወንዶችና ሴቶች ልጆችዋ በሙሉ ሁልጊዜ ከመሥዋዕቱ ሥጋ ድርሻቸውን ይሰጣቸው ነበር።
\s5
\v 5 ነገር ግን ሐናን ይወዳት ስለነበር ሁልጊዜም ድርሻዋን ሁለት ዕጥፍ አድርጎ ይሰጣት ነበር፤ እግዚአብሔር ግን ማኅፀንዋን ዘግቶት ነበር።
\v 6 እግዚአብሔር ማኅፀንዋን ዘግቶት ስለነበር ጣውንቷ እርስዋን ለማስመረር ክፉኛ ታስቆጣት ነበር።
\s5
\v 7 ስለዚህ በየዓመቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ከቤተሰብዋ ጋር በምትወጣበት ጊዜ ጣውንቷ ሁልጊዜ ታበሳጫት ነበር። በዚህ ምክንያት ታለቅስ ነበር፤ ምግብም አትበላም ነበር።
\v 8 ባሏ ሕልቃና ሁልጊዜ "ሐና ሆይ፥ ለምንድነው የምታለቅሽው? ምግብስ የማትበዪው ለምንድነው? ልብሽ የሚያዝነውስ ለምንድነው? ከዐሥር ወንዶች ልጆች ይልቅ ላንቺ እኔ አልሻልም?" ይላት ነበር።
\s5
\v 9 ከእነዚህ ወቅቶች በአንዱ፥ በሴሎ መብላታቸውንና መጠጣታቸውን ከጨረሱ በኋላ ሐና ተነሣች። ካህኑ ዔሊ በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በራፍ በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር።
\v 10 እርሷም እጅግ አዝና ነበር፤ ወደ እግዚአብሔር ጸለየች፥ አምርራም አለቀሰች።
\s5
\v 11 እንዲህ ስትልም ስዕለት ተሳለች፣ "የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ የአገልጋይህን ጉስቁልና ብትመለከትና ብታስበኝ፥ አገልጋይህን ባትረሳኝ፥ ነገር ግን ወንድ ልጅን ብትሰጠኝ፥ እኔም የሕይወት ዘመኑን ሁሉ ለእግዚአብሔር እሰጠዋለሁ፥ መቼም ቢሆን ጸጉሩ አይላጭም"።
\s5
\v 12 በእግዚአሔር ፊት ጸሎቷን ቀጥላ እያለች ዔሊ አፏን ይመለከት ነበር።
\v 13 ሐና በልቧ ትናገር ነበር። ከንፈሮችዋ ይንቀሳቀሱ ነበር፥ ድምፅዋ ግን አይሰማም ነበር። ስለዚህ ዔሊ ሰክራለች ብሎ አሰበ።
\v 14 ዔሊም "ስካርሽ የሚቆየው እስከ መቼ ነው? ወይንሽን ከአንቺ አርቂው" አላት።
\s5
\v 15 ሐናም፣ "ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፥ እኔ ልቤ በሐዘን የተጎዳብኝ ሴት ነኝ። ወይን ወይም የሚያሰክር መጠጥ አልጠጣሁም፥ ነገር ግን ነፍሴን በእግዚአብሔር ፊት እያፈሰስኩ ነው።
\v 16 አገልጋይህን እንደ ኃፍረተ ቢስ ሴት አትቁጠረኝ፤ ይህን ያህል ጊዜ የተናገርኩት እጅግ ከበዛው ሐዘኔና ጭንቀቴ የተነሣ ነው" በማለት መለሰችለት።
\s5
\v 17 ከዚያም ዔሊ፣ "በሰላም ሂጂ፤ የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ልመና ይስጥሽ" ብሎ መለሰላት።
\v 18 እርሷም፣ "አገልጋይህ በዐይንህ ፊት ሞገስን ላግኝ" አለችው። ከዚያም መንገዷን ሄደች፥ በላችም፤ ከዚያም በኋላ ፊቷ ሐዘንተኛ አልሆነም።
\s5
\v 19 እነርሱም ማልደው ተነሥተው በእግዚአብሔር ፊት ሰገዱ፥ ከዚያም ወደ መኖሪያቸው ወደ አርማቴም ተመለሱ። ሕልቃና ከሚስቱ ከሐና ጋር ተኛ፥ እግዚአብሔርም አሰባት።
\v 20 ጊዜው ሲደርስም ሐና አረገዘችና ወንድ ልጅ ወለደች። "ከእግዚአብሔር ስለ እርሱ ለምኜ ነበር" ስትል ስሙን ሳሙኤል ብላ ጠራችው።
\s5
\v 21 ሕልቃናና ቤተ ሰቡ በሙሉ ለእግዚአብሔር ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብና ስዕለታቸውን ለመፈጸም ዳግመኛ ወደ ሴሎ ወጡ።
\v 22 ሐና ባሏን "ልጁ ጡት መጥባት እስኪያቆም እኔ አልሄድም፤ ከዚያም በእግዚአብሔር ፊት እንዲታይና ለዘላለም በዚያ እንዲኖር አመጣዋለሁ" ብላው ስለነበረ አልሄደችም።
\v 23 ባሏም ሕልቃና፥ "መልካም መስሎ የታየሽን አድርጊ። ጡት መጥባቱን እስኪያቆም ቆዪ፥ ብቻ እግዚአብሔር ቃሉን ያጽና" አላት። ስለዚህ ልጇ ጡት መጥባቱን እስኪያቆም ድረስ በቤት በመቆየት ተንከባከበችው።
\s5
\v 24 ጡት መጥባቱን ባስቆመችው ጊዜ፥ እርሱን ከሦስት አመት ወይፈን፥ አንድ ኢፍ ዱቄትና አንድ ጠርሙስ ወይን ጋር በሴሎ ወደሚገኘው ወደ እግዚአብሔር ቤት ወሰደችው። ልጁ ገና ሕፃን ነበር።
\v 25 ወይፈኑን አረዱት፤ ልጁንም ወደ ዔሊ አመጡት።
\s5
\v 26 እርሷም፥ "ጌታዬ ሆይ፥ ሕያው እንደመሆንህ፥ እዚህ አጠገብህ ቆማ ወደ እግዚአብሔር የጸለየችው ሴት እኔ ነኝ።
\v 27 ስለዚህ ልጅ ጸለይኩኝ፥ እግዚአብሔርም የለመንኩትን ልመና ሰጥቶኛል።
\v 28 ለእግዚአብሔር ሰጥቼዋለሁ፤ በሕይወት በሚኖርበት ዘመን ሁሉ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ይሆናል"። እነርሱም በዚያ ለእግዚአብሔር ሰገዱ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ሐናም እንዲህ በማለት ጸለየች፥ “ልቤ በእግዚአሔር በደስታ ተሞላ። ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ አለ። በማዳንህ ደስ ብሎኛልና አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ።
\s5
\v 2 አንተን የሚመስልህ የለምና፥ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለም ዐለት የለም።
\s5
\v 3 ከእንግዲህ አትታበዩ፤ አንዳች የዕብሪት ንግግር ከአፋችሁ አይውጣ። እግዚአብሔር ዐዋቂ አምላክ ነውና፤ ሥራዎች ሁሉ በእርሱ ይመዘናሉ።
\v 4 የኃያላን ሰዎች ቀስት ተሰብሯል፥ የተሰናከሉት ግን ኃይልን ታጥቀዋል።
\s5
\v 5 ጠግበው የነበሩት እንጀራ ለማግኘት ሲሉ ለሥራ ተቀጠሩ፤ ተርበው የነበሩት ረሃብተኝነታቸው አብቅቷል። መካኒቱ እንኳን ሰባት ወልዳለች፥ ብዙ ልጆች የነበሯት ሴት ግን ጠውልጋለች።
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ይገድላል፥ ያድናልም። ወደ ሲዖል ያወርዳል፥ ያነሣልም።
\v 7 እግዚአብሔር ድሃ ያደርጋል፥ ባለጸጋም ያደርጋል። እርሱ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ያደርጋል።
\s5
\v 8 እርሱ ድሃውን ከመሬት ያነሣዋል። ምስኪኖችን ከልዑላን ጋር ሊያስቀምጣቸውና የክብርን ወንበር ሊያወርሳቸው ከአመድ ክምር ላይ ብድግ ያደርጋቸዋል። የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጓል።
\s5
\v 9 የታመኑ ሰዎችን እግር ይጠብቃል፥ ማንም በኃይሉ አያሸንፍም፤ ክፉዎች ግን በጨለማ ውስጥ ወዳለው ጸጥታ ይጣላሉ።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደቅቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጎደጉድባቸዋል። እግዚአብሔር በምድር ዳርቻዎች ላይ ይፈርዳል፤ የእርሱ ለሆነው ንጉሥ ኃይልን ይሰጠዋል፥ ለቀባውም ቀንዱን ከፍ ያደርግለታል።”
\s5
\v 11 ከዚያም ሕልቃና በራማ ወደሚገኘው ቤቱ ሄደ። ልጁም በካህኑ በዔሊ ፊት እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
\s5
\v 12 የዔሊ ወንዶች ልጆች ምንም የማይረቡ ነበሩ። እግዚአብሔርን አያውቁም ነበር።
\v 13 የካህናቱ ልማድ ከሕዝቡ ጋር እንደዚያ ነበርና፥ ማንኛውም ሰው መሥዋዕት ሲያቀርብ፥ ሥጋው እየተቀቀለ እያለ የካህኑ አገልጋይ ሦስት ጣት ያለው ሜንጦ ይዞ ይመጣ ነበር።
\v 14 እርሱም ወደ ድስቱ፥ ወይም ወደ አፍላሉ፥ ወይም ወደ ምንቸቱ ውስጥ ያጠልቀው ነበር። ሜንጦው ያወጣውንም ሁሉ ካህኑ ለራሱ ይወስደው ነበር። ይህንን ወደዚያ ወደ ሴሎ በሚመጡት እስራኤላውያን ሁሉ ላይ ያደርጉ ነበር።
\s5
\v 15 ይልቁንም ስቡን ከማቃጠላቸው በፊት የካህኑ አገልጋይ ይመጣና የሚሠዋውን ሰው፥ “ጥሬውን ብቻ እንጂ የተቀቀለውን ሥጋ ከአንተ አይቀበልምና ለካህኑ እንድጠብስለት ሥጋ ስጠኝ" ይለው ነበር።
\v 16 ሰውየው፥ "መጀመሪያ ስቡን ማቃጠል አለባቸው፥ ከዚያም የፈለከውን ያህል መውሰድ ትችላለህ" ካለው ያ ሰው መልሶ፥ "አይደለም፥ አሁኑኑ ስጠኝ፤ እምቢ ካልክም በግድ እወስደዋለሁ" ይለው ነበር።
\v 17 የእግዚአብሔርን መስዋዕት ንቀዋልና የእነዚህ ወጣቶች ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ታላቅ ነበር።
\s5
\v 18 ትንሹ ልጅ ሳሙኤል ግን ከተልባ እግር ጨርቅ የተሠራ ኤፉድ ለብሶ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
\v 19 እናቱም ዓመታዊውን መሥዋዕት ለማቅረብ ከባሏ ጋር በምትመጣበት ጊዜ በየዓመቱ አነስተኛ መደረቢያ ልብስ እየሠራች ታመጣለት ነበር።
\s5
\v 20 ዔሊም ሕልቃናን እና ሚስቱን እንዲህ በማለት ባረካቸው፥ ”ከእግዚአብሔር በለመነችው ልመና ምክንያት እግዚአብሔር ከዚህች ሴት ተጨማሪ ልጆችን ይስጥህ።“ ከዚያም ወደ ራሳቸው መኖሪያ ተመለሱ።
\v 21 እግዚአብሔር እንደገና ሐናን ረዳት፥ እንደገናም አረገዘች። እርሷም ሦስት ወንዶችና ሁለት ሴት ልጆችን ወለደች። እንዲሁም ትንሹ ልጅ ሳሙኤል በእግዚአብሔር ፊት አደገ።
\s5
\v 22 ዔሊ በጣም አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹ በእስራኤላውያን ሁሉ ላይ እያደረጉ ያሉትን በሙሉ እና በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደ ተኙ ሰማ።
\v 23 እርሱም እንዲህ አላቸው፥ ”ስለ ክፉ ሥራችሁ ከዚህ ሕዝብ ሁሉ ሰምቻለሁና እንደዚህ ያሉትን ነገሮች የምትፈጽሙት ለምንድነው?
\v 24 ልጆቼ ሆይ፥ የምሰማው መልካም ወሬ አይደለምና ልክ አይደላችሁም። የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲያምጽ ታደርጉታላችሁ።
\s5
\v 25 አንድ ሰው ሌላውን ቢበድል፥ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ ይፈርዳል፤ አንድ ሰው ግን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ቢሠራ ስለ እርሱ የሚናገር ማን ነው?" እነርሱ ግን እግዚአሔር ሊገድላቸው ፈልጓልና የአባታቸውን ቃል አልሰሙም።
\v 26 ትንሹም ልጅ ሳሙኤል አደገ፥ በእግዚአብሔርና በሰዎችም ፊት ደግሞ በሞገስ እያደገ ሄደ።
\s5
\v 27 አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'በግብፅ አገር፥ በፈርዖን ቤት ባሪያዎች በነበሩ ጊዜ ለአባትህ ቤት ራሴን ገለጥኩኝ፤
\v 28 ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ካህን እንዲሆነኝ፥ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ ዕጣን እንዲያጥንልኝ፥ በፊቴም ኤፉድ እንዲለብስ መረጥኩት። የእስራኤል ሕዝብ በእሳት የሚያቀርበውን መባ ሁሉ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።
\s5
\v 29 ታዲያ በማደሪያዬ ያዘዝኩትን መሥዋዕትና መባ የምትንቁት ለምንድነው? በሕዝቤ በእስራኤል ከሚቀርበው መስዋዕት ሁሉ በተመረጠው እየወፈራችሁ ልጆችህን ከእኔ በላይ ያከበርከው ለምንድነው?'
\v 30 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'ቤትህና የአባትህ ቤት ለዘላለም በፊቴ እንዲመላለስ ተስፋ ሰጥቼ ነበር'። አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ 'ይህንን ማድረግ ከእኔ ይራቅ፥ የሚያከብሩኝን አከብራለሁና የሚንቁኝ ግን ፈጽሞ ይናቃሉ።
\s5
\v 31 ተመልከት፥ ከእንግዲህ በቤትህ ሽማግሌ የሚሆን አንድም ሰው እንዳይኖር ያንተን ኃይልና የአባትህን ቤት ኃይል የምቆርጥበት ቀን ቀርቧል።
\v 32 በማድርበት ስፍራም መከራን ታያለህ። ለእስራኤል መልካም ነገር ቢሰጥም ከእንግዲህ በቤትህ ሽማግሌ የሚሆን አንድ ሰው አይኖርም።
\v 33 ያንተ የሆኑትና ከመሠዊያዬ የማልቆርጣቸው ማናቸውም ዐይኖችህን እንዲያፈዝዙና ሕይወትህን በሐዘን እንዲሞሉት አደርጋቸዋለሁ። በቤተ ሰብህ ውስጥ የተወለዱ ወንዶች ሁሉ ይሞታሉ።
\s5
\v 34 በሁለቱ ወንዶች ልጆችህ በአፍኒን እና በፊንሐስ የሚደርስባቸው ምልክት ይሆንሃል፤ ሁለቱም በአንድ ቀን ይሞታሉ።
\v 35 በልቤና በነፍሴ ውስጥ ያለውን የሚፈጽም ታማኝ ካህን ለራሴ አስነሣለሁ። የማያጠራጥር ቤት እሠራለታለሁ፤ ለዘላለምም በቀባሁት ንጉሥ ፊት ይሄዳል።
\s5
\v 36 ከቤተ ሰብህ የተረፈ ሁሉ ጥቂት ጥሬ ብርና ቁራሽ እንጀራ እንዲሰጠው ለመለመን በዚያ ሰው ፊት መጥቶ ይሰግዳል፥ 'ቁራሽ እንጀራ መብላት እንድችል እባክህ ከካህናቱ ኃላፊነቶች በአንዱ ስፍራ መድበኝ'" ይለዋል።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ትንሹ ልጅ ሳሙኤል በዔሊ ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር።
\v 2 በእነዚያ ቀናት የእግዚአብሔር ቃል እምብዛም አይገኝም ነበር፤ ትንቢታዊ ራዕይም አይዘወተርም ነበር። በዚያን ጊዜ፥ ዔሊ ዐይኖቹ ከመፍዘዛቸው የተነሣ አጥርቶ ማየት ባቃተው ጊዜ፥ በአልጋው ላይ ተኝቶ እያለ፥
\v 3 የእግዚአብሔር መብራት ገና አልጠፋም ነበር፥ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ታቦት ባለበት በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተኝቶ ነበር።
\v 4 እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው፥ እርሱም፥ “አቤት! ” አለው።
\s5
\v 5 ሳሙኤል ወደ ዔሊ ሮጠና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው፤ ዔሊም፥ “እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ ” አለው። ስለዚህ ሳሙኤል ሄደና ተኛ።
\v 6 እግዚአብሔር እንደገና፥ “ሳሙኤል” ብሎ ተጣራ። ሳሙኤልም እንደገና ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው። ዔሊም፥ "ልጄ ሆይ፥ እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 7 ሳሙኤል እግዚአብሔርን ገና አላወቀም ነበር፥ ከእግዚአብሔር ምንም ዓይነት መልዕክት ገና አልተገለጠለትም ነበር።
\v 8 እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ጠራው። ሳሙኤልም እንደገና ተነሥቶ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “ጠርተኸኛልና ይኸው መጥቻለሁ” አለው። ከዚያም ልጁን እግዚአብሔር እንደ ጠራው ዔሊ አስተዋለ።
\s5
\v 9 ዔሊም ሳሙኤልን፥ "ሂድና ተመልሰህ ተኛ፤ ደግሞ ከጠራህም፥ 'እግዚአብሔር ሆይ፥ አገልጋይህ እየሰማህ ነውና ተናገር' ማለት አለብህ" አለው። ስለዚህ ሳሙኤል እንደገና ወደ ስፍራው ተመልሶ ተኛ።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፤ እንደ ቀድሞው ሁሉ፥ "ሳሙኤል፥ ሳሙኤል" ብሎ ጠራው። ከዚያም ሳሙኤል፥ "አገልጋይህ እየሰማህ ነውና ተናገር" አለው።
\v 11 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፥ "ተመልከት፥ የሚሰማውን ሁሉ ጆሮውን ጭው የሚያደርግ አንድ ነገር በእስራኤል ላይ አደርጋለሁ።
\s5
\v 12 በዚያም ቀን፥ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ስለ ቤቱ የተናገርኩትን ሁሉ በዔሊ ላይ አመጣበታለሁ።
\v 13 ልጆቹ በራሳቸው ላይ እርግማንን ስላመጡና እርሱም ስላልከለከላቸው፥ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እርሱ ስለሚያውቀው ኃጢአት በቤቱ ላይ እንደምፈርድ ነግሬዋለሁ።
\v 14 በዚህ ምክንያት የቤቱ ኃጢአት በመሥዋዕት ወይም በመባ ይቅር እንዳይባል ለዔሊ ቤት ምያለሁ።"
\s5
\v 15 ሳሙኤል እስኪነጋ ተኛ፤ ከዚያም የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ። ሳሙኤል ግን ስላየው ራዕይ ለዔሊ ለመንገር ፈራ።
\v 16 ከዚያም ዔሊ ሳሙኤልን ጠርቶ፥ "ልጄ ሳሙኤል ሆይ" አለው። ሳሙኤልም፥ "አቤት!" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 17 እርሱም፥ "የነገረህ ቃል ምንድነው? እባክህ አትደብቀኝ። ከነገረህ ቃል ሁሉ አንዱን ብትደብቀኝ እግዚአብሔር ይህን ያድርግብህ፤ ከዚያም የባሰውን ጨምሮ ያድርግብህ" አለው።
\v 18 ሳሙኤል ሁሉንም ነገር ነገረው፤ ከእርሱም ምንም አልደበቀም። ዔሊም፥ "እርሱ እግዚአብሔር ነው። መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ" አለ።
\s5
\v 19 ሳሙኤል አደገ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበር፥ ከትንቢታዊ ቃሉ ሳይፈጸም የቀረ አንድም አልነበረም።
\v 20 ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያሉት እስራኤላውያን በሙሉ ሳሙኤል የእግዚአብሔር ነቢይ እንዲሆን መመረጡን ዐወቁ።
\v 21 እግዚአብሔር እንደገና በሴሎ ተገለጠ፥ እርሱም በቃሉ አማካይነት በሴሎ ራሱን ለሳሙኤል ገለጠለት።
\s5
\c 4
\p
\v 1 የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤላውያን ሁሉ መጣ። በዚህ ወቅት እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ጋር ለመዋጋት ሄዱ። የጦር ሰፈራቸውንም በአቤንኤዘር አደረጉ፥ ፍልስጥኤማውያንም የጦር ሰፈራቸውን በአፌቅ አደረጉ።
\v 2 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤላውያን ጋር ለመዋጋት ተሰለፉ። ውጊያው በተፋፋመ ጊዜ እስራኤላውያን አራት ሺህ ሰዎቻቸው በውጊያው ሜዳ በመገደላቸው በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ።
\s5
\v 3 ሕዝቡ ወደ ጦር ሰፈሩ በመጣ ጊዜ፥ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ "እግዚአብሔር ዛሬ በፍልስጥኤማውያን ፊት እንድንሸነፍ ያደርገን ለምንድነው? ከእኛ ጋር እንዲሆንና ከጠላቶቻችን ኃይል እንዲያድነን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከሴሎ እናምጣው" አሉ።
\v 4 ስለዚህ ሕዝቡ ወደ ሴሎ ሰዎችን ላኩ። ከዚያ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠውን የሠራዊቱን ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ። ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።
\s5
\v 5 የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ጦር ሰፈሩ በመጣ ጊዜ፥ የእስራኤል ሕዝብ በሙሉ በታላቅ ዕልልታ ጮኹ፥ ምድሪቱም አስተጋባች።
\v 6 ፍልስጥኤማውያን የዕልልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “ይህ በዕብራውያኑ የጦር ሰፈር የሚሰማው የዕልልታ ድምፅ ምን ማለት ይሆን? አሉ። ከዚያም የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ጦር ሰፈሩ እንደ መጣ ተገነዘቡ።
\s5
\v 7 ፍልስጥኤማውያኑ ፈሩ፤ እነርሱም፥ ”እግዚአብሔር ወደ ጦር ሰፈሩ መጥቷል" አሉ።
\v 8 እነርሱም፥ "ወዮልን! እንደዚህ ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልሆነም! ወዮልን! ከዚህ ኃያል አምላክ ክንድ ማን ያድነናል? ይህ በምድረ በዳ ግብፃውያንን በልዩ ልዩ ዓይነት መቅሠፍት የመታቸው አምላክ ነው።
\v 9 እናንተ ፍልስጥኤማውያን በርቱ፥ ወንድነታችሁንም አሳዩ፥ ካልሆነ እነርሱ ባሪያዎቻችሁ እንደነበሩ ባሪያዎቻቸው ትሆናላችሁ። ወንድነታችሁ ይታይ፥ ተዋጉም" አሏቸው።
\s5
\v 10 ፍልስጥኤማውያኑ ተዋጉ፥ እስራኤላውያንም ተሸነፉ። እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሸሸ፥ የተገደሉትም እጅግ ብዙ ነበሩ፤ ከእስራኤል ሠላሳ ሺህ እግረኛ ወታደር ወደቀ።
\v 11 የእግዚአብሔር ታቦት ተወሰደ፥ ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስም ሞቱ።
\s5
\v 12 በዚያው ቀን አንድ ብንያማዊ ከውጊያው መስመር ወደ ሴሎ በሩጫ መጣ፥ በደረሰ ጊዜ ልብሱን ቀድዶና በራሱ ላይ አፈር ነስንሶ ነበር።
\v 13 እርሱ በደረሰ ጊዜ፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት በመስጋት ልቡ ታውኮበት ስለነበረ በመንገዱ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር። ሰውየው ወደ ከተማ ገብቶ ወሬውን በነገራቸው ጊዜ፥ ከተማው በሙሉ አለቀሱ።
\s5
\v 14 ዔሊ የልቅሶውን ድምፅ በሰማ ጊዜ፥ “የዚህ ሁካታ ትርጉሙ ምንድነው? ” አለ። ሰውየው ፈጥኖ መጣና ለዔሊ ነገረው።
\v 15 በዚህ ጊዜ ዔሊ የዘጠና ስምንት ዓመት ሽማግሌ ነበር፤ ዓይኖቹ አጥርተው አያዩም ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር።
\s5
\v 16 ሰውየውም ዔሊን፥ “ከውጊያው መስመር የመጣሁት እኔ ነኝ። ዛሬ ከውጊያው ሸሽቼ መጣሁ” አለው። ዔሊም፥ “ልጄ ሆይ፥ ነገሩ እንዴት እየሆነ ነው? ” አለው።
\v 17 ወሬውን ያመጣው ያ ሰው መልሶ፥ “እስራኤላውያን ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ። ደግሞም በሕዝቡ መካከል ታላቅ ዕልቂት ሆኗል። ሁለቱ ወንዶች ልጆችህ፥ አፍኒን እና ፊንሐስ ሞተዋል፥ የእግዚአብሔር ታቦትም ተወስዷል” አለው።
\s5
\v 18 እርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ጠቅሶ በተናገረ ጊዜ፥ ዔሊ በመግቢያው በር አጠገብ ከተቀመጠበት ወንበር ላይ ወደ ኋላው ወደቀ። ስላረጀና ውፍረት ስለነበረው አንገቱ ተሰብሮ ሞተ። እርሱም በእስራኤላውያን ላይ ለአርባ ዓመታት ፈርዶ ነበር።
\s5
\v 19 በዚህ ጊዜ ምራቱ የፊንሐስ ሚስት አርግዛ የመውለጃ ሰዓቷ ደርሶ ነበር። የእግዚአብሔር ታቦት መማረኩን፥ ዐማቷና ባሏ መሞታቸውን በሰማች ጊዜ ተንበርክካ ወለደች፥ ነገር ግን ምጡ አስጨነቃት።
\v 20 ለመሞት በምታጣጥርበት ጊዜ ያዋልዷት የነበሩ ሴቶች፥ "ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ“ አሏት። እርሷ ግን አልመለሰችላቸውም ወይም የነገሯትን በልቧ አላኖረችውም።
\s5
\v 21 እርሷም የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከና ስለ ዐማቷና ስለ ባልዋ "ክብር ከእስራኤል ተለየ!" ስትል ልጁን ኤካቦድ ብላ ጠራችው።
\v 22 እርሷም፥ ”የእግዚአብሔር ታቦት ስለተማረከ ክብር ከእስራኤል ተለየ!" አለች።
\s5
\c 5
\p
\v 1 ፍልስጥኤማውያንም የእግዚአብሔርን ታቦት በመማረክ ከአቤንኤዘር ወደ አሽዶድ አመጡት።
\v 2 እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ማርከው ወደ ዳጎን ቤት ወስደው በዳጎን አጠገብ አቆሙት።
\v 3 የአሽዶድ ሰዎች በቀጣዩ ቀን ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። ስለዚህ ዳጎንን አንሥተው በስፍራው መልሰው አቆሙት።
\s5
\v 4 ነገር ግን በማግስቱ ማልደው በተነሡ ጊዜ፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፍቶ አዩ። በደጁ መግቢያ ውስጥ የዳጎን ራሱና እጆቹ ተሰብረው ወድቀው ነበር። የቀረው የዳጎን ሌላው የአካል ክፍሉ ብቻ ነበር።
\v 5 ለዚህ ነው እስካሁን እንኳን የዳጎን ካህናትና ሌላ ማንኛውም ሰው በአሽዶድ ወደሚገኘው ወደ ዳጎን ቤት በሚመጣበት ጊዜ የዳጎንን ደጅ መግቢያ ሳይረግጥ የሚያልፈው።
\s5
\v 6 የእግዚአብሔር እጅ በአሽዶድ ሰዎች ላይ ከብዶ ነበር። በአሽዶድና በዙሪያው ባሉት ላይ ጥፋትን በማምጣት በእባጭ መታቸው።
\v 7 የአሽዶድ ሰዎች የሆነባቸውን ባስተዋሉ ጊዜ፥ “እጁ በእኛና በአምላካችን በዳጎን ላይ ከብዳለችና የእስራኤል አምላክ ታቦት ከእኛ ጋር መቆየት የለበትም” አሉ።
\s5
\v 8 ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ልከው በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ "በእስራኤል አምላክ ታቦት ላይ ምን እናድርግ?" አሏቸው። እነርሱም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ ጌት ይምጣ” ብለው መለሱላቸው። የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደዚያ ወሰዱት።
\v 9 ነገር ግን ወደዚያ ካመጡት በኋላ የእግዚአብሔር እጅ በከተማዪቱ ላይ ሆነ፥ ታላቅ መደናገርንም አደረገባቸው። ልጅና ዐዋቂውን፥ የከተማውን ሰዎች አስጨነቀ፤ ሰውነታቸውም በእባጭ ተወረረ።
\s5
\v 10 ስለዚህ የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ አቃሮን ላኩት። ነገር ግን የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አቃሮን እንደ መጣ፥ አቃሮናውያን፥ "እኛንና ሕዝባችንን እንዲገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ወደ እኛ አምጥተዋል" በማለት ጮኹ።
\s5
\v 11 ስለዚህ ወደ ፍልስጥኤማውያን ገዢዎች በመላክ ሁሉንም በአንድ ላይ ሰበሰቧቸው፤ እነርሱም፥ “እኛንና ሕዝባችንን እንዳይገድል የእስራኤልን አምላክ ታቦት ላኩት፥ ወደ ስፍራውም ይመለስ" አሏቸው። በዚያ የእግዚአብሔር እጅ እጅግ ስለበረታባቸው በከተማው ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበረ።
\v 12 ከሞት የተረፉት ሰዎች በእባጮቹ ይሠቃዩ ስለነበር የከተማዪቱ ጩኸት ወደ ሰማያት ወጣ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 የእግዚአብሔር ታቦት በፍልስጥኤማውያን አገር ከተቀመጠ ሰባት ወር ሆነው።
\v 2 ከዚያም የፍልስጥኤም ሰዎች ካህናትንና ጠንቋዮችን ጠርተው፥ “የእግዚአብሔርን ታቦት ምን እናድርገው? ወደ አገሩ እንዴት አድርገን መመለስ እንዳለብን ንገሩን” አሉአቸው።
\s5
\v 3 ካህናቱና ጠንቋዮቹም፥ "የእስራኤልን አምላክ ታቦት መልሳችሁ የምትልኩ ከሆነ ያለስጦታ አትላኩት፤ በተቻለ መጠን የበደል መስዋዕትም ላኩለት። ከዚያም ትፈወሳላችሁ፥ እናንተም እስካሁን ድረስ እጁን ከላያችሁ ላይ ያላነሣው ለምን እንደሆነ ታውቃላችሁ"።
\v 4 ሕዝቡም፥ “የምንመልሰው የበደል መስዋዕት ምን መሆን አለበት? ”አሏቸው። እነርሱም እንዲህ በማለት መለሱላቸው፥ "አምስት የወርቅ እባጮችንና አምስት የወርቅ አይጦችን፥ በቁጥር አምስት መሆኑም የፍልስጥኤማውያንን ገዢዎች ቁጥር የሚወክል ነው። እናንተንና ገዢዎቻችሁን የመታው ተመሳሳይ መቅሰፍት ነውና።
\s5
\v 5 ስለዚህ ምድራችንን ባጠፋው በእባጮቻችሁና በአይጦቻችሁ አምሳል ማድረግ አለባችሁ፥ ለእስራኤል አምላክም ክብርን ስጡ። ምናልባት እጁን ከእናንተ፥ ከአማልክቶቻችሁና ከምድሪቱ ላይ ያነሣ ይሆናል።
\v 6 ግብፃውያንና ፈርዖን ልባቸውን እንዳደነደኑ ለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? ያን ጊዜ ነበር የእስራኤል አምላክ ክፉን ያደረገባቸው፤ ታዲያ ግብፃውያኑ ሕዝቡን አልለቀቋቸውም?እነርሱስ ከዚያ አልወጡም?
\s5
\v 7 እንግዲህ አዲስ ሠረገላና እስካሁን ቀንበር ያልተጫነባቸውን ሁለት የሚያጠቡ ላሞች አዘጋጁ። ላሞቹን በሠረገላው ጥመዷቸው፥ እምቦሳዎቻቸውን ግን ከእነርሱ ለይታችሁ በቤት አስቀሩአቸው።
\v 8 ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት ወስዳችሁ በሠረገላው ላይ አኑሩት። የበደል መስዋዕት አድርጋችሁ የምትመልሱለትን የወርቁን አምሳያዎች በሳጥን ውስጥ አድርጋችሁ በአንደኛው ጎኑ አስቀምጡ። ከዚያም ልቀቁትና በራሱ መንገድ እንዲሄድ ተዉት።
\v 9 ከዚያም ተመልከቱ፥ ወደ ራሱ ምድር፥ ወደ ቤት ሳሚስ በመንገዱ ከሄደ፥ ይህንን ታላቅ ጥፋት ያመጣው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ካልሆነ ግን፥ ይህ በአጋጣሚ የደረሰብን እንጂ የመታን የእርሱ እጅ እንዳልሆነ እናውቃለን"።
\s5
\v 10 ሰዎቹም እንደተነገራቸው አደረጉ፤ ሁለት የሚያጠቡ ላሞችን ወሰዱና በሠረገላው ጠመዷቸው፥ እምቦሳዎቻቸውንም ከቤት እንዳይወጡ አደረጉ።
\v 11 የወርቁን አይጥና የእባጮቻቸው ምሳሌ የሆነውን ከያዘው ሳጥን ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት በሠረገላው ላይ አደረጉት።
\v 12 ላሞቹም በቤት ሳሚስ አቅጣጫ ቀጥ ብለው ሄዱ። እነርሱም በዚያው ጎዳና፥ ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳይሉ ቁልቁል ሄዱ። የፍልስጥኤማውያን ገዢዎችም እስከ ቤት ሳሚስ ዳርቻ ድረስ ከበስተኋላቸው ተከተሏቸው።
\s5
\v 13 በዚህ ጊዜ የቤት ሳሚስ ሰዎች በሸለቆው ውስጥ ስንዴአቸውን በማጨድ ላይ ነበሩ። ቀና ብለው ባዩ ጊዜ ታቦቱን ተመለከቱ፥ ደስም አላቸው።
\s5
\v 14 ሠረገላው የቤት ሳሚስ ሰው ወደሆነው ወደ ኢያሱ እርሻ መጥቶ በዚያ ቆመ። በዚያም ትልቅ ቋጥኝ ነበር፥ የሠረገላውን እንጨት በመፍለጥ ላሞቹን ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።
\v 15 ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ታቦትና አብሮት የነበረውን፥ የወርቁ ምስሎች የነበሩበትን ሳጥን፥ ከሠረገላው አውርደው በትልቁ ቋጥኝ ላይ አስቀመጡት። በዚያው ቀን የቤት ሳሚስ ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አቀርቡ፥ መሥዋዕቶችንም ሠዉ።
\s5
\v 16 አምስቱ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች ይህንን ባዩ ጊዜ በዚያው ቀን ወደ አቃሮን ተመለሱ።
\s5
\v 17 የፍልስጥኤም ሰዎች ለእግዚአብሔር የበደል መስዋዕት አድርገው የመለሷቸው የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት እና አንዱ ስለ አቃሮን ነበር።
\v 18 የወርቁ አይጥ አምስቱ ገዢዎች ከሚገዟቸው የተመሸጉ የፍልስጥኤማውያን ከተሞችና መንደሮች ቁጥር ሁሉ ጋር ቁጥሩ ተመሳሳይ ነበር። የእግዚአብሔርን ታቦት ያስቀመጡበት ያ ታላቅ ቋጥኝ በቤት ሳሚስ በኢያሱ እርሻ ውስጥ እስከ ዛሬ ድረስ ምስክር ሆኖ ይኖራል።
\s5
\v 19 ወደ ታቦቱ ውስጥ ተመልክተዋልና እግዚአብሔር ከቤት ሳሚስ ሰዎች ጥቂቶቹን መታቸው። እርሱም ሰባ ሰዎችን ገደለ። እግዚአብሔር ሕዝቡን ክፉኛ ስለመታቸው ሕዝቡ አለቀሱ።
\v 20 የቤት ሳሚስ ሰዎችም፥ “በዚህ ቅዱስ አምላክ በእግዚአብሔር ፊት መቆም የሚችል ማነው? ከእኛስ ወደ ማን ይሄዳል? ” አሉ።
\s5
\v 21 በቂርያትይዓሪም ወደሚኖሩት መልዕክተኞች ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፤ ወደዚህ ውረዱና ውሰዱት” አሏቸው።
\s5
\c 7
\p
\v 1 የቂርያትይዓሪም ሰዎች መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት ወሰዱ፥ በኮረብታው ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አስገቡት። የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ለዚህ አገልግሎት ለዩት።
\v 2 ታቦቱ በቂርያትይዓሪም ከተቀመጠ ብዙ ዓመት አለፈው፥ ሃያ ዓመትም ሆነው። የእስራኤል ቤት ሁሉ አዘኑ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስም ፈለጉ።
\s5
\v 3 ሳሙኤል የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ እንዲህ አላቸው፥ "በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር የምትመለሱ ከሆነ እንግዶቹን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አስወግዱ፥ ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር መልሱ፥ እርሱንም ብቻ አምልኩት፥ ያን ጊዜ ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናችኋል"።
\v 4 ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ በኣልንና አስታሮትን አስወገዱ፥ እግዚአብሔርን ብቻም አመለኩ።
\s5
\v 5 ከዚያም ሳሙኤል፥ "እስራኤልን በሙሉ ምጽጳ ላይ ሰብስቡ፥ እኔም ስለ እናንተ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ“ አላቸው።
\v 6 እነርሱም በምጽጳ ተሰበሰቡ፥ ውሃም ቀድተው በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሱ። በዚያም ቀን ጾሙ፥ ”በእግዚአብሔር ላይም ኃጢአትን አድርገናል“ አሉ። ሳሙኤል በእስራኤል ሕዝብ ላይ የፈረደውና ሕዝቡን የመራው በዚያ ነበር።
\s5
\v 7 የእስራኤል ሕዝብ በምጽጳ መሰብሰባቸውን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፥ የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች እስራኤልን ለማጥቃት መጡ። የእስራኤል ሰዎች ይህንን በሰሙ ጊዜ ፍልስጥኤማውያንን ፈሩ።
\v 8 ከዚያም የእስራኤል ሕዝብ ሳሙኤልን፥ ”ከፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲያድነን፥ ስለ እኛ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር መጣራትህን አታቁም“ አሉት።
\s5
\v 9 ሳሙኤል የሚጠባ ግልገል ወስዶ ለእግዚአብሔር ሙሉውን የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ሠዋው። ከዚያም ሳሙኤል ስለ እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም መለሰለት።
\s5
\v 10 ሳሙኤል የሚቃጠለውን መስዋዕት በማቅረብ ላይ እያለ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለማጥቃት ቀረቡ። ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ላይ በታላቅ ድምፅ አንጎደጎደባቸው፥ አሸበራቸውም፥ በእስራኤልም ፊት ተሸንፈው ሸሹ።
\v 11 የእስራኤል ሰዎችም ከምጽጳ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን አሳደዱ፥ ከቤትካር በታች እስካለው ቦታ ድረስ ተከትለው ገደሏቸው።
\s5
\v 12 ከዚያም ሳሙኤል አንድ ድንጋይ አንሥቶ በምጽጳና በሼን መካከል አቆመው። ”እስካሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል“ በማለት አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።
\s5
\v 13 ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፥ የእስራኤልን ድንበርም አልፈው አልገቡም። በሳሙኤል የሕይወት ዘመን ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከብዳ ነበር።
\v 14 ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል የወሰዷቸው ከአቃሮን እስከ ጌት ያሉ መንደሮች ለእስራኤል ተመለሱላቸው፤ እስራኤላውያን ድንበሮቻቸውን ከፍልስጥኤማውያን አስመለሱ። በዚያን ጊዜ በእስራኤላውያንና በአሞራውያን መካከል ሰላም ነበረ።
\s5
\v 15 ሳሙኤል በሕይወት ዘመኑ ሁሉ በእስራኤል ላይ ፈረደ።
\v 16 በየዓመቱ ወደ ቤቴል፥ ወደ ጌልገላና ወደ ምጽጳ ይዘዋወር ነበር። በእነዚህ ስፍራዎች ሁሉ በእስራኤላውያን መካከል ባሉ አለመግባባቶች ላይ ይፈርድ ነበር።
\v 17 ከዚያም መኖሪያው በዚያ ነበርና ወደ ራማ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤላውያን አለመግባባት ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያም ደግሞ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ልጆቹን በእስራኤል ላይ ፈራጆች አድርጎ ሾማቸው።
\v 2 የመጀመሪያ ልጁ ስም ኢዮኤል፥ የሁለተኛው ስም አብያ ነበር። እነርሱም በቤርሳቤህ ፈራጆች ነበሩ።
\v 3 ነገር ግን ልጆቹ ነውረኛ ጥቅም ፈላጊዎች ሆኑ እንጂ በእርሱ መንገድ አልሄዱም። ጉቦ እየተቀበሉ ፍትሕን አዛቡ።
\s5
\v 4 ከዚያም የእስራኤል ሽማግሌዎች በአንድነት ተሰብስበው በራማ ወደሚኖረው ወደ ሳሙኤል መጡ።
\v 5 እነርሱም፥ "ተመልከት፥ አንተ ሸምግለሃል፥ ልጆችህም በመንገድህ አይሄዱም። እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ እንዲፈርድልን ንጉሥ አንግሥልን" አሉት።
\s5
\v 6 ነገር ግን፥ “እንዲፈርድልን ንጉሥ ስጠን” ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን ቅር አሰኘው። ስለዚህ ሳሙኤል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
\v 7 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን እንዲህ አለው፥ “በላያቸው ላይ ንጉሥ እንዳልሆን የተቃወሙት እኔን እንጂ አንተን አይደለምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ታዘዝ።
\s5
\v 8 ከግብፅ ካወጣዃቸው ጊዜ ጀምሮ እኔን ትተው ሌሎች አማልክቶችን በማምለክ ሲያደርጉት የነበረውን ያንኑ አሁን እያደረጉ ነው፤ በአንተም ላይ የሚያደርጉት እንደዚሁ ነው።
\v 9 አሁንም የሚሉህን ስማቸው፤ ነገር ግን በላያቸው የሚገዛው ንጉሥ የሚያደርግባቸውን እንዲያውቁ አጥብቀህ አስጠንቅቃቸው"።
\s5
\v 10 ስለዚህ ሳሙኤል ንጉሥ ለጠየቀው ሕዝብ የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ነገራቸው።
\v 11 እርሱም እንዲህ አላቸው፥ "ንጉሡ በላያችሁ ላይ የሚገዛው እንዲህ ነው። ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ፈረሰኞች እንዲሆኑና በሠረገላዎቹ ፊት እንዲሮጡ በሠረገላዎቹ ላይ ይሾማቸዋል።
\v 12 እርሱም ለራሱ ሻለቃዎችንና ሃምሳ አለቃዎችን ይሾማል። አንዳንዶቹ መሬቱን እንዲያርሱ፥ ሌሎቹም እህሉን እንዲያጭዱ፥ አንዳንዶቹ የጦር መሳሪያዎችንና ሌሎቹም የሠረገላ ዕቃዎችን እንዲሠሩለት ያደርጋቸዋል።
\s5
\v 13 ሴቶች ልጆቻችሁን ደግሞ ሽቶ ቀማሚዎች፥ ወጥ ሠሪዎችና እንጀራ ጋጋሪዎች እንዲሆኑ ይወስዳቸዋል።
\v 14 በጣም ምርጥ የሆነውን መሬታችሁን፥ የወይን ቦታችሁንና የወይራ ዛፋችሁን ወስዶ ለአገልጋዮቹ ይሰጣቸዋል።
\v 15 ከእህላችሁና ከወይናችሁ አንድ ዐሥረኛውን ወስዶ ለሹማምንቱና ለአገልጋዮቹ ይሰጣቸዋል።
\s5
\v 16 ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁን፥ ከወጣት ልጆቻችሁና ከአህዮቻችሁ የተመረጡትን ይወስዳል፤ ሁሉንም ለእርሱ እንዲሠሩ ያደርጋቸዋል።
\v 17 ከበግና ከፍየል መንጋዎቻችሁ አንድ ዐሥረኛውን ይወስዳል፥ እናንተም አገልጋዮቹ ትሆናላችሁ።
\v 18 በዚያም ቀን ለራሳችሁ ስለመረጣችሁት ንጉሥ ታለቅሳላችሁ፤ ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር አይመልስላችሁም”።
\s5
\v 19 ሕዝቡ ግን ሳሙኤልን ለመስማት እምቢ አሉ፤
\v 20 ሳሙኤልንም፥ “አይሆንም፥ ንጉሣችን እንዲፈርድልን፥ በፊታችን እንዲሄድና ጦርነቶቻችንን እንዲዋጋልን፥ እንደ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ለእኛም ንጉሥ ሊሆንልን ይገባል” አሉት።
\s5
\v 21 ሳሙኤል የሕዝቡን ቃል ሁሉ በሰማ ጊዜ እርሱም በእግዚአብሔር ጆሮ ደግሞ ተናገረው።
\v 22 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “ቃላቸውን ታዘዝና ንጉሥ አድርግላቸው” አለው። ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤልን ሰዎች፥ “እያንዳንዱ ወደገዛ ከተማው ይሂድ” አላቸው።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ከብንያም ወገን ጽኑ ኃያል የሆነ አንድ ሰው ነበር። ስሙ ቂስ ሲሆን እርሱም የአቢኤል ልጅ፥ የጽሮር ልጅ፥ የብኮራት ልጅ፥ የብንያማዊው የአፌቅ ልጅ ነበር።
\v 2 እርሱም ሳኦል የሚባል መልከ መልካም ወጣት ልጅ ነበረው። ከእርሱ የሚበልጥ መልከ መልካም ሰው በእስራኤል ሕዝብ መካከል አልነበረም። ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ ቁመቱ ረጅም ነበር።
\s5
\v 3 የሳኦል አባት የቂስ ሴት አህዮች ጠፍተው ነበር። ስለዚህ ቂስ ልጁን ሳኦልን፥ “ከአገልጋዮቻችን አንዱን ውሰድ፤ ተነሥናም አህዮቹን ፈልግ” አለው።
\v 4 ስለዚህ ሳኦል በኮረብታማው በኤፍሬም አገር በኩል አልፎ ወደ ሻሊሻ ምድር ሄደ፥ ነገር ግን አላገኟቸውም። ከዚያም በሻዕሊም ምድር በኩል አለፉ፥ ነገር ግን በዚያ አልነበሩም። ከዚያም በብንያማውያን ምድር በኩል አለፉ፥ ነገር ግን አላገኟቸውም።
\s5
\v 5 ወደ ጹፍ ምድር በመጡ ጊዜ፥ ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበረውን አገልጋዩን፥ "ና እንመለስ፥ አለበለዚያ አባቴ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ ስለ እኛ መጨነቅ ይጀምራል" አለው።
\v 6 ነገር ግን አገልጋዩ እንዲህ አለው፥ “ስማኝ፥ በዚህ ከተማ ውስጥ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ። እርሱም የተከበረ ሰው ነው፤ የሚናገረው ነገር ሁሉ ይፈጸማል። ወደዚያ እንሂድ፤ በየትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን ሊነግረን ይችል ይሆናል"።
\s5
\v 7 ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን፥ "ታዲያ ወደ እርሱ የምንሄድ ከሆነ ለዚያ ሰው ምን ልንሰጠው እንችላለን? እንጀራው ከከረጢታችን አልቋል፥ ለእግዚአብሔር ሰው የምናቀርበው ምንም ስጦታ የለንም። ምን አለን?"አለው።
\v 8 አገልጋዩም ለሳኦል፥ "ይኸውና፥ የሰቅል ጥሬ ብር አንድ አራተኛው አለኝ፥ በየትኛው አቅጣጫ መሄድ እንዳለብን እንዲነግረን ለእግዚአብሔር ሰው እሰጠዋለሁ" ሲል መለሰለት።
\s5
\v 9 (ቀደም ሲል በእስራኤል ውስጥ፥ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ በሚሄድበት ጊዜ፥ "ኑ፥ ወደ ባለ ራዕዩ እንሂድ" ይል ነበር። የዛሬው ነቢይ ቀደም ሲል ባለ ራዕይ ተብሎ ይጠራ
\v 10 ነበር።)ከዚያም ሳኦል አገልጋዩን፥ ”መልካም ብለሃል። ና፥ እንሂድ“ አለው። ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ወደነበረበት ከተማ ሄዱ።
\v 11 ኮረብታው ላይ ወዳለው ከተማ በመውጣት ላይ እያሉ ወጣት ሴቶች ውሃ ለመቅዳት ሲወጡ አገኟቸው፤ ሳኦልና አገልጋዩም፥ ”ባለ ራዕዩ በዚህ አለ? “ በማለት ጠየቋቸው።
\s5
\v 12 እነርሱም እንዲህ በማለት መለሱላቸው፥ "አዎን፤ ተመልከቱ፥ እንዲያውም ከፊታችሁ እየቀደመ ነው። ዛሬ ሕዝቡ በኮረብታው ራስ ላይ ስለሚሠዉ ወደ ከተማው ይመጣልና ፍጠኑ።
\v 13 ወደ ከተማው እንደገባችሁ ለመብላት ወደ ኮረብታው ራስ ከመውጣቱ በፊት ታገኙታላችሁ። መሥዋዕቱን የሚባርከው እርሱ ስለሆነ፥ እርሱ ከመምጣቱ በፊት ሕዝቡ አይበሉም፤ ከዚያ በኋላም የተጋበዙት ይበላሉ። ወዲያውኑ ታገኙታላችሁና አሁን ወደ ላይ ውጡ።”
\s5
\v 14 ስለዚህ ወደ ላይ ወደ ከተማው ወጡ። ወደ ከተማይቱ በመግባት ላይ እያሉም ሳሙኤል ወደ ኮረብታው ራስ ለመውጣት በእነርሱ አቅጣጫ ሲመጣ አዩት።
\s5
\v 15 ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት እግዚአብሔር ለሳሙኤል እንዲህ ሲል ገልጦለት ነበር፥
\v 16 “ነገ በዚህ ሰዓት ከብንያም ምድር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፥ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መስፍን እንዲሆን ትቀባዋለህ። እርሱም ሕዝቤን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ያድናቸዋል። እርዳታ በመፈለግ መጮኻቸው ወደ እኔ ደርሷልና ሕዝቤን በርኅራኄ ተመልክቻለሁ።”
\s5
\v 17 ሳሙኤል ሳኦልን ባየው ጊዜ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፥ ”ስለ እርሱ የነገርኩህ ሰው ይህ ነው! ሕዝቤን የሚገዛው ሰው እርሱ ነው።“
\v 18 ከዚያም ሳኦል በበሩ አጠገብ ወደ ሳሙኤል ቀረብ ብሎ፥ ”የባለ ራዕዩ ቤት የት እንደሆነ ንገረኝ“ አለው።
\v 19 ሳሙኤልም ለሳኦል እንዲህ በማለት መለሰለት፥ ”ባለ ራዕዩ እኔ ነኝ። ከእኔ በፊት ቀድማችሁ ወደ ኮረብታው ራስ ውጡ፥ ዛሬ ከእኔ ጋር ትበላላችሁና። ነገ ጠዋት በአዕምሮህ ያለውን ነገር ሁሉ እነግርህና አሰናብትሃለሁ።
\s5
\v 20 ከሦስት ቀን በፊት ጠፍተው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋልና ስለ እነርሱ አታስብ። የእስራኤል ሁሉ ምኞት የተቀመጠው በማን ላይ ነው? በአንተና በአባትህ ቤት ሁሉ ላይ አይደለም? “
\v 21 ሳኦልም፥ "ከእስራኤል ነገዶች ትንሹ የሆነው ብንያማዊ አይደለሁም? ጎሳዬስ ከብንያም ነገድ ጎሳዎች ሁሉ የመጨረሻው አይደለም? ታዲያ እንዲህ ባለ ሁኔታ ለምን ትናገረኛለህ?"ሲል መለሰለት።
\s5
\v 22 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልንና አገልጋዩን ወደ አዳራሹ አስገብቶ ሠላሳ ከሚያህሉ ከተጋበዙት ሰዎች ከፍ ባለው ስፍራ ላይ አስቀመጣቸው።
\s5
\v 23 ሳሙኤልም ወጥ ሠሪውን፥ " 'ለብቻ አስቀምጠው' ብዬ የሰጠሁህን ድርሻ አምጣው" አለው።
\v 24 ወጥ ሠሪውም በመሥዋዕቱ ጊዜ ያነሣውን ጭኑንና ከእርሱ ጋር ያለውን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ከዚያም ሳሙኤል፥ "የተቀመጠልህን ተመልከት! ለአንተ እስከተወሰነው ሰዓት ድረስ የቆየልህ ነውና ብላው። አሁን 'ሕዝቡን ጋብዣለሁ' ማለት ትችላለህ" አለው። ስለዚህ በዚያን ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ።
\s5
\v 25 ከኮረብታው ራስ ወደ ከተማው በወረዱ ጊዜ፥ በቤቱ የጣሪያ ወለል ላይ ሳሙኤል ከሳኦል ጋር ተነጋገረ።
\v 26 ከዚያም በነጋ ጊዜ ሳሙኤል በጣሪያው ወለል ላይ ሳኦልን ተጣርቶ፥ "መንገድህን እንድትሄድ አሰናብትህ ዘንድ ተነሥ" አለው። ስለዚህ ሳኦል ተነሣ፥ እርሱና ሳሙኤል ሁለቱም ወደ ጎዳናው ሄዱ።
\s5
\v 27 ወደ ከተማው ዳርቻ በመሄድ ላይ እያሉ፥ ሳሙኤል ሳኦልን፥ "አገልጋዩ ከፊታችን ቀድሞ እንዲሄድ ንገረው፥ (እርሱም ቀድሞ ሄደ) አንተ ግን የእግዚአብሔርን መልዕክት እንዳስታውቅህ እዚህ ጥቂት መቆየት አለብህ" አለው።
\s5
\c 10
\p
\v 1 ከዚያም ሳሙኤል የዘይቱን ጠርሙስ ወስዶ በሳኦል ራስ ላይ አፈሰሰው፤ ሳመውም። እርሱም እንዲህ አለው፥ "በርስቱ ላይ ገዢ እንድትሆን እግዚአብሔር ቀብቶሃል፤
\v 2 ዛሬ ከእኔ ተለይተህ ስትሄድ፥ የብንያም ወሰን በሆነው በጼልጻህ፥ በራሔል መቃብር አጠገብ ሁለት ሰዎች ታገኛለህ። እነርሱም፥ 'ስትፈልጋቸው የነበሩት አህዮች ተገኝተዋል። አሁን አባትህ ስለ አህዮቹ ማሰቡን ትቶ፥ "ስለ ልጄ ምን ባደርግ ይሻለኛል?" በማለት ተጨንቋል“ ይሉሃል።
\s5
\v 3 ከዚያ አልፈህ ትሄድና በታቦር ወደሚገኘው ወደ በሉጥ ዛፍ ትመጣለህ። ወደ ቤቴል፥ ወደ እግዚአብሔር የሚሄዱ አንደኛው ሦስት የፍየል ጠቦቶች ይዞ፥ ሌላኛው ሦስት ዳቦ ተሸክሞ፥ ሌላኛው ደግሞ ወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ ተሸክሞ ሦስት ሰዎች ይገናኙሃል።
\v 4 ሰላምታ ከሰጡህ በኋላ ሁለት ዳቦ ይሰጡሃል፥ ከእጃቸውም ትቀበላቸዋለህ።
\s5
\v 5 ከዚህ በኋላ የፍልስጥኤም የጦር ሠፈር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ። ወደ ከተማው በምትደርስበት ጊዜ፥ አንድ የነቢያት ቡድን በፊታቸው መሰንቆ፥ ከበሮ፥ እምቢልታና በገና ይዘው ከተራራው ሲወርዱ ትገናኛቸዋለህ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገራሉ።
\v 6 የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ይመጣብሃል፥ አንተም ከእነርሱ ጋር ትንቢት ትናገራለህ፥ እንደ ሌላ ሰው ሆነህም ትለወጣለህ።
\s5
\v 7 እነዚህ ምልክቶች በሚፈጸሙልህ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና እጅህ ያገኘውን ሁሉ አድርግ።
\v 8 ቀድመኸኝ ወደ ጌልገላ ውረድ። ከዚያም የሚቃጠለውን መባ ለማቅረብና የሰላሙን መባ ለመሠዋት ወደ አንተ እወርዳለሁ። ወደ አንተ እስክመጣና ልታደርገው የሚገባህን እስከማሳይህ ድረስ ሰባት ቀን ቆይ።”
\s5
\v 9 ሳኦል ከሳሙኤል ተለይቶ ለመሄድ ፊቱን ባዞረ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ሰጠው። እነዚህ ምልክቶች ሁሉ በዚያው ቀን ተፈጸሙ።
\v 10 እነርሱም ወደ ኮረብታው በመጡ ጊዜ፥ የነቢያት ቡድን ተገናኙት፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በኃይል መጣበት፥ ከእነርሱም ጋር ትንቢት ተናገረ።
\s5
\v 11 ቀድሞ ያውቁት የነበሩት ሁሉ እርሱም ከነቢያት ጋር ትንቢት ሲናገር ባዩት ጊዜ፥ እርስ በእርሳቸው፥ “የቂስን ልጅ ምን ነካው? አሁን ሳኦል ከነቢያት አንዱ መሆኑ ነው? ” ተባባሉ።
\v 12 በዚያው ስፍራ የነበረ አንድ ሰው፥ “አባታቸው ማነው? ” ሲል መለሰ። በዚህ ምክንያት፥ “ሳኦልም ከነቢያት አንዱ ነው? ” የሚል ምሳሌአዊ አባባል የተለመደ ሆነ።
\v 13 ትንቢት መናገሩን በጨረሰ ጊዜ ወደ ተራራው ራስ መጣ።
\s5
\v 14 ከዚያም የሳኦል አጎት፥ እርሱንና አገልጋዩን፥ “የት ነበር የሄዳችሁት? ” አላቸው። እርሱም፥ “አህዮቹን ለመፈለግ ነበር፤ ልናገኛቸው እንዳልቻልን ባየን ጊዜ ወደ ሳሙኤል ሄድን” ብሎ መለሰለት።
\v 15 የሳኦልም አጎት፥ “ሳሙኤል የነገረህን እባክህ ንገረኝ" አለው።
\v 16 ሳኦልም አጎቱን፥ "አህዮቹ መገኘታቸውን በግልጽ ነገረን" ብሎ መለሰለት። ሳሙኤል ነግሮት የነበረውን የንግሥና ጉዳይ ግን አልነገረውም።
\s5
\v 17 ሳሙኤል ሕዝቡን በአንድነት በእግዚአብሔር ፊት ወደ ምጽጳ ጠራቸው።
\v 18 እርሱም የእስራኤልን ሕዝብ እንዲህ አላቸው፥ ”የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፥ 'እስራኤልን ከግብፅ አወጣሁት፥ ከግብፃውያን እጅና ካስጨነቋችሁ መንግሥታት ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ'።
\v 19 ነገር ግን ዛሬ እናንተ ከመከራና ከጭንቃችሁ ሁሉ የሚያድናችሁን አምላካችሁን ተቃውማችኋል፤ እርሱንም፥ 'በላያችን ላይ ንጉሥ አንግሥልን' ብላችሁታል። አሁን በየነገዳችሁና በየጎሣችሁ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ"።
\s5
\v 20 ስለዚህ ሳሙኤል የእስራኤልን ነገዶች በሙሉ አቀረበ፥ የብንያም ነገድም ተመረጠ።
\v 21 ከዚያም የብንያምን ነገድ በየጎሣቸው አቀረበ፤ የማጥሪ ጎሣም ተመረጠ፤ የቂስ ልጅ ሳኦልም ተመረጠ። ነገር ግን በፈለጉት ጊዜ ሊያገኙት አልቻሉም።
\s5
\v 22 ከዚያም ሕዝቡ ”ገና የሚመጣ ሌላ ሰው አለ? “ በማለት እግዚአብሔርን ተጨማሪ ጥያቄዎች ለመጠየቅ ፈለጉ። እግዚአብሔርም፥ ”ራሱን በዕቃዎቹ መካከል ደብቋል" በማለት መለሰላቸው።
\v 23 ከዚያም ሮጠው ሄዱና ሳኦልን ከዚያ አመጡት። በሕዝቡ መካከል በቆመ ጊዜ፥ ከሕዝቡ ሁሉ ይልቅ ቁመቱ ረጅም ነበር።
\s5
\v 24 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ "እግዚአብሔር የመረጠውን ይህንን ሰው ታዩታላችሁ? በሕዝቡ ሁሉ መካከል እንደ እርሱ ያለ የለም! “ አላቸው። ሕዝቡም ሁሉ፥ ”ንጉሥ ለዘላለም ይኑር! “ በማለት ጮኹ።
\s5
\v 25 ከዚያም ሳሙኤል የንግሥናን ደንብና ልማዶች ለሕዝቡ ነገራቸው፥ በመጽሐፍ ጽፎም በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጣቸው። ከዚያም ሳሙኤል እያንዳንዱ ወደ ገዛ መኖሪያው እንዲሄድ ሕዝቡን ሁሉ አሰናበተ።
\s5
\v 26 ሳኦልም ደግሞ በጊብዓ ወደሚገኘው መኖሪያው ሄደ፥ እግዚአብሔር ልባቸውን የነካቸው አንዳንድ ኃያላን ሰዎችም ከእርሱ ጋር ሄዱ።
\v 27 አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች ግን፥ ”ይህ ሰው ሊያድነን እንዴት ይችላል? “ አሉ። እነዚህ ሰዎች ሳኦልን ናቁት፥ ምንም ዓይነት ስጦታዎችንም አላመጡለትም። ሳኦል ግን ዝም አለ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 አሞናዊው ናዖስ ሄዶ ኢያቢስ ገለዓድን ከበባት። የኢያቢስ ሰዎች ሁሉ ናዖስን፥ "ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፥ እኛም እናገለግልሃለን" አሉት።
\v 2 አሞናዊው ናዖስም፥ "የሁላችሁንም ቀኝ ዐይኖቻችሁን በማውጣት በመላው እስራኤል ላይ ኃፍረትን አመጣለሁ፥ በዚህ ቅድመ ሁኔታ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ" ብሎ መለሰላቸው።
\s5
\v 3 የኢያቢስ ሽማግሌዎችም፥ "ወደ እስራኤል ወገኖች ሁሉ መልዕክተኞችን እንድንልክ ለሰባት ቀናት ታገሰን። ከዚያም የሚያድነን አንድም ባይኖር ለአንተ እንገዛለን" በማለት መለሱለት።
\s5
\v 4 መልዕክተኞቹም ሳኦል ወደሚኖርበት ወደ ጊብዓ መጥተው የሆነውን ነገር ለሕዝቡ ነገሯቸው። ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።
\v 5 በዚህ ጊዜ ሳኦል ከእርሻ በሬዎቹን እየነዳ መጣ። ሳኦልም፥ "ሕዝቡ ምን ሆኖ ነው የሚያለቅሰው?" አለ። እነርሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሉትን ለሳኦል ነገሩት።
\s5
\v 6 ሳኦል የነገሩትን በሰማ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል መጣበት፥ እጅግም ተቆጣ።
\v 7 የበሬዎቹን ቀንበር ወስዶ ፈለጣቸውና ወደ እስራኤል ወሰኖች ሁሉ በመልዕክተኞች እጅ ላከው። እርሱም፥ "ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ በማይመጣው ሁሉ በበሬዎቹ ላይ እንዲህ ይደረግበታል" አለ። ከዚያም ከእግዚአብሔር ታላቅ ፍርሃት በሕዝቡ ላይ ወደቀ፥ እንደ አንድ ሰው ሆነው ተሰብስበው መጡ።
\v 8 ቤዜቅ በተባለ ስፍራ በሰበሰባቸው ጊዜ፥ የእስራኤል ሰዎች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይሁዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።
\s5
\v 9 እነርሱም ለመጡት መልዕክተኞች፥ "ለኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች፥ 'ነገ ፀሐይ ሞቅ በሚልበት ሰዓት እንታደጋችኋለን' ብላችሁ ንገሯቸው" አሏቸው። መልዕክተኞቹ ሄደው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሯቸው፥ እነርሱም እጅግ ደስ አላቸው።
\v 10 ከዚያም የኢያቢስ ሰዎች ናዖስን፥ ”ነገ እንገዛልሃለን፥ አንተም ደስ የሚያሰኝህን ልታደርግብን ትችላለህ“ አሉት።
\s5
\v 11 በቀጣዩ ቀን ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ቡድን ከፈላቸው። ሊነጋጋ ሲል ወደ ጦር ሠፈሩ መካከል መጡ፥ አሞናውያንንም አጠቁ፥ ቀኑ እስኪሞቅ ድረስም አሸነፏቸው። በሕይወት የተረፉትም ከእነርሱ ሁለቱ አንድ ላይ ሆነው እስከማይታዩ ድረስ ተበታተኑ።
\s5
\v 12 በዚያን ጊዜ ሕዝቡ ሳሙኤልን፥ " 'ሳኦል በእኛ ላይ እንዴት ይነግሣል?' ያለው ማን ነበር? እንድንገድላቸው ሰዎቹ ይምጡልን" አሉት።
\v 13 ነገር ግን ሳኦል፥ "ዛሬ እግዚአብሔር እስራኤልን ታድጎታልና በዚህ ቀን ማንም መገደል የለበትም" አላቸው።
\s5
\v 14 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ "ኑ፥ ወደ ጌልገላ እንሂድና በዚያ መንግሥቱን እናድስ" አላቸው።
\v 15 ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄደው በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ሳኦልን አነገሡት። በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የሰላምን መባ ሠዉ፥ ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ሁሉ እጅግ ደስ አላቸው።
\s5
\c 12
\p
\v 1 ሳሙኤል እስራኤላውያንን በሙሉ እንዲህ አላቸው፥ ”የነገራችሁኝን በሙሉ ሰምቻችኋለሁ፥ ንጉሥንም በላያችሁ ላይ አንግሼላችኋለሁ።
\v 2 አሁንም፥ በፊታችሁ የሚሄድላችሁ ንጉሥ ይኸውላችሁ፤ እኔ አርጅቻለሁ፥ ጸጉሬም ሸብቷል፤ ልጆቼም ከእናንተ ጋር ናቸው። ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በፊታችሁ ኖሬአለሁ።
\s5
\v 3 ይኸው በፊታችሁ ነኝ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ። የማንን በሬ ወስጃለሁ? የማንንስ አህያ ወስጃለሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? ዓይኖቼን ለማሳወር ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? መስክሩብኝና እመልስላችኋለሁ።“
\s5
\v 4 እነርሱም፥ ”አላታለልከንም፥ ግፍም አልሠራህብንም ወይም ከማንም እጅ ምንም ነገር አልሰረቅህም“ አሉ።
\v 5 እርሱም፥ ”በእጄ ላይ ምንም እንዳላገኛችሁ ዛሬ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ምስክር ነው፥ እርሱ የቀባውም ምስክር ነው“ አላቸው። እነርሱም፥ ”እግዚአብሔር ምስክር ነው“ ብለው መለሱ።
\s5
\v 6 ሳሙኤልም ሕዝቡን፥ ”ሙሴንና አሮንን የመረጣቸው፥ አባቶቻችሁንም ከግብፅ ምድር ያወጣቸው እግዚአብሔር ነው።
\v 7 አሁን እንግዲህ፥ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ ስለ ሠራላችሁ የጽድቅ ሥራ ሁሉ እንድሟገታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን አቅርቡ።
\s5
\v 8 ያዕቆብ ወደ ግብፅ በመጣ ጊዜ አባቶቻችሁ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔር፥ ከግብፅ ምድር እየመሩ አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲቀመጡ ያደረጓቸውን ሙሴንና አሮንን ላከ።
\v 9 እነርሱ ግን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ረሱ፤ እርሱም የሐጾር ሠራዊት አዛዥ በሆነው በሲሣራ እጅ፥ በፍልስጥኤማውያን እጅና በሞአብ ንጉሥ እጅ ሸጣቸው፤ እነዚህ ሁሉ አባቶቻችሁን ተዋጓቸው።
\s5
\v 10 እነርሱም ወደ እግዚአብሔር በመጮህ፥ ''እግዚአብሔርን ትተን በኣልንና አስታሮትን በማገልገላችን ኃጢአት አድርገናል። አሁን ግን ከጠላቶቻችን እጅ አድነን፥ እኛም እናገለግልሃለን' አሉት።
\v 11 ስለዚህ እግዚአብሔር ይሩበኣልን፥ ባርቅን፥ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ በሰላም እንድትኖሩ በዙሪያችሁ ባሉ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ላይ ድልን ሰጣችሁ።
\s5
\v 12 እናንተም የአሞን ሕዝብ ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ንጉሣችሁ ሆኖ እያለ፥ 'አይሆንም፥ ይልቁን በላያችን ላይ ንጉሥ መንገሥ አለበት' አላችሁኝ።
\v 13 አሁንም እናንተ የመረጣችሁት፥ እንዲሆንላችሁ የጠየቃችሁትና እግዚአብሔርም በእናንተ ላይ ንጉሥ እንዲሆን የመረጠው ንጉሥ ይኸውላችሁ።
\s5
\v 14 እናንተም እግዚአብሔርን ብትፈሩት፥ ብታገለግሉት፥ ድምፁንም ብትታዘዙና በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ባታምጹ ያን ጊዜ እናንተና በላያችሁ የሚገዛው ንጉሣችሁ የአምላካችሁ የእግዚአብሔር ተከታዮች ትሆናላችሁ።
\v 15 የእግዚአብሔርን ድምፅ ባትታዘዙ፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ላይ ብታምጹ፥ ያን ጊዜ በአባቶቻችሁ ላይ እንደነበረ የእግዚአብሔር እጅ በእናንተ ላይ ይሆናል።
\s5
\v 16 አሁንም፥ ራሳችሁን አቅርቡና እግዚአብሔር በዓይናችሁ ፊት የሚያደርገውን ይህንን ታላቅ ነገር ተመልከቱ።
\v 17 ዛሬ የስንዴ መከር ነው አይደል? ነጎድጓድና ዝናብን እንዲልክ እግዚአብሔርን እጠራለሁ። ከዚያም ለራሳችሁ ንጉሥ በመጠየቃችሁ በእግዚአብሔር ፊት ያደረጋችሁት ክፋት ታላቅ እንደሆነ ታውቃላችሁ፥ ታያላችሁም“።
\v 18 ስለዚህ ሳሙኤል እግዚአብሔርን ጠራ፤ በዚያው ቀን እግዚአብሔር ነጎድጓድንና ዝናብን ላከ። ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን በጣም ፈሩ።
\s5
\v 19 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ሳሙኤልን፥ "እንዳንሞት፥ ስለ አገልጋዮችህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ። ለራሳችን ንጉሥ በመጠየቃችን በኃጢአታችን ሁሉ ላይ ይህንን ክፋት ጨምረናልና” አሉት።
\v 20 ሳሙኤል እንዲህ ሲል መለሰላቸው፥ “አትፍሩ። ይህንን ሁሉ ክፋት አድርጋችኋል፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን በሙሉ ልባችሁ አገልግሉት እንጂ ከእግዚአብሔር ፊታችሁን አትመልሱ።
\v 21 የማይጠቅሙ ናቸውና ሊረዷችሁ ወይም ሊረቧችሁ የማይችሉትን ከንቱ ነገሮች አትከተሉ።
\s5
\v 22 እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ ሊያደርጋችሁ ስለ ወደደ፥ ስለ ታላቅ ስሙ ሲል ሕዝቡን አይጥላቸውም።
\v 23 ስለ እናንተ መጸለይን በመተው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ማድረግ ከእኔ ይራቅ። ይልቁንም፥ መልካሙንና ትክክለኛውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።
\s5
\v 24 ብቻ እግዚአብሔርን ፍሩት፥ በሙሉ ልባችሁም በእውነት አገልግሉት። ያደረገላችሁን ታላላቅ ነገሮች አስቡ።
\v 25 ክፉ በማድረግ ብትጸኑ ግን እናንተና ንጉሣችሁ ትጠፋላችሁ”።
\s5
\c 13
\p
\v 1 ሳኦል መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበር፤ በእስራኤል ላይ አርባ ዓመት በነገሠ ጊዜ፥
\v 2 ከእስራኤል ሦስት ሺህ ሰዎች መረጠ። አንዱ ሺህ ከዮናታን ጋር በብንያም ጊብዓ ሲሆኑ ሁለቱ ሺህ በኮረብታማው አገር በቤቴልና በማክማስ ከእርሱ ጋር ነበሩ። የቀሩትን ወታደሮች ወደየቤታቸው፥ እያንዳንዱንም ወደ ድንኳኑ አሰናበታቸው።
\s5
\v 3 ዮናታን በጊብዓ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ድል አደረገ፥ ፍልስጥኤማውያንም ይህንን ሰሙ። ከዚያም ሳኦል፥ “ዕብራውያን ይስሙ” በማለት በምድሪቱ ሁሉ ላይ መለከት አስነፋ።
\v 4 ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር እንዳሸነፈ፥ ደግሞም እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን እንደ ግም መቆጠራቸውን እስራኤላውያን በሙሉ ሰሙ። ከዚያም ወታደሮቹ በጌልገላ ሳኦልን ለመከተል በአንድ ላይ ተሰበሰቡ።
\s5
\v 5 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፤ ሦስት ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ሠረገላ ነጂዎችና የሠራዊቱም ቁጥር በባህር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ነበሩ። እነርሱም መጥተው ከቤትአዌን በስተምሥራቅ ማክማስ ላይ ሰፈሩ።
\s5
\v 6 የእስራኤል ሰዎች ችግር ውስጥ መግባታቸውንና ሕዝቡም መጨነቁን ባዩ ጊዜ፥ ሕዝቡ በዋሻዎች፥ በየቁጥቋጦ ሥር፥ በዐለቶች፥ በገደሎችና በጉድጓዶች ውስጥ ተደበቁ።
\v 7 አንዳንድ ዕብራውያንም የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ጋድና ገለዓድ ምድር ሄዱ። ሳኦል ግን ገና በጌልገላ ነበር፥ የተከተለው ሕዝብ በሙሉ በፍርሃት ይንቀጠቀጥ ነበር።
\s5
\v 8 እርሱም ሳሙኤል በሰጠው ቀጠሮ መሠረት ሰባት ቀን ቆየ። ነገር ግን ሳሙኤል ወደ ጌልገላ አልመጣም ነበር፥ ሕዝቡም ከሳኦል ተለይቶ መበታተን ጀምሮ ነበር።
\v 9 ሳኦልም፥ "የሚቃጠለውን መባና የሰላሙን መባዎች አምጡልኝ" አለ። ከዚያም የሚቃጠለውን መባ አቀረበ።
\v 10 የሚቃጠለውን መባ ማቅረቡን እንደ ጨረሰ ሳሙኤል ወደዚያ ደረሰ። ሳኦልም ሊገናኘውና ሰላምታ ሊሰጠው ሄደ።
\s5
\v 11 ከዚያም ሳሙኤል፥ "ያደረግከው ምንድነው?" አለው። ሳኦልም፥ "ሕዝቡ ትተውኝ እየሄዱ እንዳሉ፥ አንተም በቀጠሮው ሰዓት አለመምጣትህን፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን ባየሁ ጊዜ፥
\v 12 'አሁን ፍልስጥኤማውያን ወደ ጌልገላ በእኔ ላይ ሊወርዱብኝ ነው፥ እኔም የእግዚአብሔርን ሞገስ አልለመንኩም' ብዬ አሰብኩኝ። ስለዚህ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ ግድ ሆነብኝ“ ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 13 ሳሙኤልም ሳኦልን፥ ”ያደረግከው ስንፍና ነው። አምላክህ እግዚአብሔር የሰጠህን ትዕዛዝ አልጠበቅክም። በዚህ ቀን እግዚአብሔር መንግሥትህን በእስራኤል ላይ ለዘላለም ሊያጸናልህ ነበር።
\v 14 አሁን ግን አገዛዝህ አይቀጥልም። እግዚአብሔር ያዘዘህን አልታዘዝክምና እርሱ እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው ፈልጓል፥ እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ መስፍን እንዲሆን መርጦታል" አለው።
\s5
\v 15 ከዚያም ሳሙኤል ከጌልገላ ተነሥቶ ወደ ብንያም ጊብዓ ወጣ። ሳኦል ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ቆጠራቸው፥ ስድስት መቶ የሚያክሉ ነበሩ።
\v 16 ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ከእነርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች በብንያም ጊብዓ ቆዩ። ፍልስጥኤማውያን ግን በማክማስ ሰፍረው ነበር።
\s5
\v 17 ከፍልስጥኤም ጦር ሰፈር ወራሪዎች በሦስት ቡድን ተከፍለው መጡ። አንደኛው ቡድን ወደ ሦጋል ምድር ወደ ዖፍራ ታጠፈ።
\v 18 ሌላኛው ቡድን በቤትሖሮን አቅጣጫ ታጠፈ፥ ሌላኛውም ቡድን በምድረ በዳው አቅጣጫ ወደ ስቦይም ሸለቆ ቁልቁል ወደሚያሳየው ወሰን ዞረ።
\s5
\v 19 ፍልስጥኤማውያን፥ “ዕብራውያን ለራሳቸው ሰይፍ ወይም ጦር እንዳይሠሩ" ብለው ስለነበረ፥ በመላው እስራኤል ብረት ሠሪ አልተገኘም።
\v 20 ነገር ግን የእስራኤል ወንዶች ሁሉ፥ እያንዳንዱ የማረሻውን ጫፍ፥ ዶማውን፥ ጠገራውንና ማጭዱን ለማሳል ወደ ፍልስጥኤማውያን ይወርድ ነበር።
\v 21 የክፍያው ዋጋ ለማረሻው ጫፍና ለዶማው የሰቅል ሁለት ሦስተኛ፥ ጠገራ ለማሳልና መውጊያውን ለማቃናት የሰቅል አንድ ሦስተኛ ነበር።
\s5
\v 22 ስለዚህ በጦርነቱ ቀን ሰይፍና ጦር በሳኦልና በዮናታን እጅ ብቻ እንጂ ከእነርሱ ጋር ከነበሩት ወታደሮች በአንዱም እጅ ሰይፍ ወይም ጦር አልነበረም።
\v 23 የፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጣ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣቱን ጋሻ ጃግሬውን፥ ”ና፥ በፍልስጥኤማውያን ሠራዊት ላይ በሌላ አቅጣጫ እንሂድባቸው“ አለው። ለአባቱ ግን አልነገረውም።
\s5
\v 2 ሳኦል መጌዶን በሚባል በጊብዓ ዳርቻ በሮማኑ ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር።
\v 3 እርሱም በሴሎ የእግዚአብሔር ካህን የነበረው የዔሊ ልጅ፥ የፊንሐስ ልጅ፥ የኢካቦድ ወንድም የአኪጦብ ልጅ የሆነው፥ ኤፉድ ይለብስ የነበረውን አኪያን ጨምሮ ስድስት መቶ ያህል ሰዎች ከእርሱ ጋር ነበሩ። ዮናታን መሄዱን ሕዝቡ አላወቀም ነበር።
\s5
\v 4 ዮናታን ወደ ፍልስጥኤማውያኑ ጦር ሰፈር አቋርጦ ለመሄድ ባሰበባቸው በመተላለፊያዎቹ መካከል በግራና በቀኙ በኩል ሾጣጣ ድንጋዮች ነበሩ። የአንደኛው ሾጣጣ ድንጋይ ስም ቦጼጽ ሲሆን የሁለተኛው ስም ሴኔ ነበር።
\v 5 አንደኛው ቀጥ ያለው ድንጋይ የቆመው በስተሰሜን በሚክማስ ፊት ለፊት ሲሆን ሌላኛው በጊብዓ ፊት ለፊት በስተደቡብ ነበር።
\s5
\v 6 ዮናታንም ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ "ና፥ ወደእነዚህ ወዳልተገረዙት ጦር ሰፈር እንሻገር። እግዚአብሔር በብዙ ወይም በጥቂት ሰዎች ከማዳን ሊከለክለው የሚችል ነገር የለምና፥ ምናልባት እግዚአብሔር ይሠራልን ይሆናል" አለው።
\v 7 ጋሻ ጃግሬውም፥ "በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ። ወደፊት ቀጥል፥ ተመልከት፥ የምታዝዘኝን ሁሉ ለመፈጸም ከአንተ ጋር ነኝ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 8 ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፥ "ወደ እነርሱ ተሻግረን እንታያቸዋለን።
\v 9 እነርሱም፥ 'ወደ እናንተ እስክንመጣ እዚያው ቆዩ' ካሉን በስፍራችን እንቆያለን፥ ወደ እነርሱም አንሻገርም።
\v 10 ነገር ግን፥ 'ወደ እኛ ውጡ' ብለው ቢመልሱልን እግዚአብሔር በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ወደ እነርሱ እንሻገራለን።”
\s5
\v 11 ስለዚህ ሁለቱም ራሳቸውን ለፍልስጥኤማውያን ጦር ገለጡ። ፍልስጥኤማውያኑም፥ “ተመልከቱ፥ ዕብራውያኑ ከተደበቁባቸው ጉድጓዶች ወጥተው እየመጡ ነው" ተባባሉ።
\v 12 ከዚያም የጦር ሰፈሩ ሰዎች ወደ ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በመጣራት፥ ”ወደ እኛ ውጡ፥ አንድ ነገርም እናሳያችኋለን" አሏቸው። ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን፥ “እግዚአብሔር በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና ተከተለኝ" አለው።
\s5
\v 13 ዮናታን በእጁና በእግሩ ተንጠላጥሎ ወጣ፥ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው ተከተለው። ፍልስጥኤማውያኑ በዮናታን ተገደሉ፥ ጋሻ ጃግሬውም ከኋላው ተከትሎ ጥቂቶቹን ገደለ።
\v 14 ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በፈጸሙት በዚያ የመጀመሪያ ጥቃት አንድ ጥማድ በሬ ሊያርሰው በሚችለው የመሬት ስፋት ላይ ሃያ ያህል ሰዎችን ገደሉ።
\s5
\v 15 በጦር ሰፈሩ፥ በእርሻውና በሕዝቡ መካከል ሽብር ሆነ። የጦር ሰፈሩና ወራሪዎቹም እንኳን ተሸበሩ። ምድሪቱ ተንቀጠቀጠች፥ ታላቅ ሽብርም ሆነ።
\s5
\v 16 በብንያም ጊብዓ የነበሩ የሳኦል ጠባቂዎች፥ የፍልስጥኤም ወታደሮች ሲበተኑና ወዲያና ወዲህ ሲራወጡ ተመለከቱ።
\v 17 ከዚያም ሳኦል ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሰዎች፥ ”ቁጠሩና ከእኛ የጎደለ ማን እንደሆነ ዕወቁ“ አላቸው። በቆጠሩ ጊዜም ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው ታጡ።
\s5
\v 18 ሳኦልም አኪያን፥ "የእግዚአብሔርን ኤፉድ ወደዚህ አምጣው" አለው። በዚያ ቀን አኪያ ኤፉድ ለብሶ ከእስራኤል ወታደሮች ጋር ነበር።
\v 19 ሳኦል ከካህኑ ጋር በመነጋገር ላይ እያለ በፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር የነበረው ሁከት መጨመሩን ቀጠለ። ሳኦልም ካህኑን፥ "እጅህን መልስ" አለው።
\s5
\v 20 ሳኦልና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ሁሉ በሩጫ ወደ ጦርነቱ ሄዱ። የእያንዳንዱ ፍልስጥኤማዊ ሰይፍ በራሱ ዜጋ ላይ ነበር፥ ታላቅ ግራ መጋባት ውስጥ ነበሩ።
\v 21 ቀድሞ ከፍልስጥኤማውያን ጋር የነበሩና አብረዋቸው ወደ ጦር ሰፈሩ የገቡት ዕብራውያን እነርሱም እንኳን አሁን ከሳኦልና ከዮናታን ጋር ከነበሩት እስራኤላውያን ጋር ተባበሩ።
\s5
\v 22 በኤፍሬም አቅራቢያ በኮረብታዎቹ ውስጥ የተደበቁ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ፍልስጥኤማውያን መሸሻቸውን በሰሙ ጊዜ እነርሱም እንኳን ለውጊያ በኋላቸው አሳደዷቸው።
\v 23 ስለዚህ እግዚአብሔር በዚያን ቀን እስራኤልን አዳነ፥ ውጊያውም ቤትአዌንን አልፎ ሄደ።
\s5
\v 24 ሳኦል፥ ”ጠላቶቼን እስከምበቀልበት እስከ ምሽት ድረስ የትኛውንም ዓይነት መብል የሚበላ ቢኖር የተረገመ ይሁን“ ብሎ ሕዝቡን አምሎ ስለነበረ በዚያን ቀን የእስራኤል ሰዎች ተጨነቁ። ስለዚህ ከሠራዊቱ አንዱም ምግብ አልቀመሰም።
\v 25 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ጫካ ውስጥ ገባ፥ ማርም በምድሩ ላይ ነበር።
\v 26 ሕዝቡ ወደ ጫካ በገባ ጊዜ ማሩ ይፈስስ ነበር፥ ነገር ግን ሕዝቡ መሓላውን ስለፈራ በእጁ ጠቅሶ ወደ አፉ ያደረገ አንድም አልነበረም።
\s5
\v 27 ዮናታን ግን አባቱ ሕዝቡን በመሓላ ማሰሩን አልሰማም ነበር። በእጁ ላይ የነበረውን በትር ጫፉን በማሩ እንጀራ ውስጥ አጠቀሰው። እጁን አንሥቶ ወደ አፉ አደረገው፥ ዐይኖቹም በሩለት።
\v 28 ከዚያም ከሰዎቹ አንዱ፥ ”ሕዝቡ በረሃብ ቢደክምም እንኳን አባትህ፥ 'በዚህ ቀን ምግብ የሚበላ የተረገመ ይሁን' ብሎ ሕዝቡን ከመሓላ ጋር አጥብቆ አዝዞአል" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 29 ከዚያም ዮናታን፥ "አባቴ በምድሪቱ ላይ ችግር ፈጥሯል። ከዚህ ማር ጥቂት በመቅመሴ ዐይኖቼ እንዴት እንደበሩ ተመልከቱ።
\v 30 ሕዝቡ ከጠላቶቻቸው ከበዘበዙት ላይ ዛሬ በነጻነት በልተው ቢሆን ኖሮ ምንኛ በተሻለ ነበር? ምክንያቱም አሁን በፍልስጥኤማውያን መካከል የተገደሉት ያን ያህል ብዙ አይደሉም“ አለ።
\s5
\v 31 እነርሱም በዚያን ቀን ፍልስጥኤማውያንን ከሚክማስ ጀምሮ እስከ ኤሎን ድረስ መቱአቸው። ሕዝቡም እጅግ ደከሙ።
\v 32 ሕዝቡም ተስገብግበው ወደ ብዝበዛው ተጣደፉ፥ በጎችን፥ በሬዎችንና ጥጆችንም በመሬት ላይ አረዱ። ሕዝቡም ከነደሙ በሉ።
\s5
\v 33 ከዚያም ለሳኦል፥ "ተመልከት፥ ሕዝቡ ከነደሙ በመብላታቸው በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት በመሥራት ላይ ናቸው" አሉት። ሳኦልም፥ "ተላልፋችኋል፥ አሁንም ትልቅ ድንጋይ አንከባልላችሁ አምጡልኝ“ አለ።
\v 34 በመቀጠልም፥ "ወደ ሕዝቡ ሂዱና፥ 'እያንዳንዱ ሰው በሬውንና በጉን እዚህ አምጥቶ በማረድ ይብላ። ከነደሙ በመብላት በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን አታድርጉ' ብላችሁ ንገሯቸው" አለ። ስለዚህ በዚያ ምሽት እያንዳንዱ በሬውን እያመጣ በዚያ ዐረደው።
\s5
\v 35 ሳኦል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፥ ይኸውም ለእግዚአብሔር የሠራው የመጀመሪያው መሠዊያ ነበር።
\s5
\v 36 ከዚያም ሳኦል፥ "ሌሊቱን ፍልስጥኤማውያንን እናሳድ፥ እስኪነጋም ድረስ ሀብታቸውን እንበዝብዝ፤ ከእነርሱም አንድ በሕይወት አናስቀር“ አለ። እነርሱም፥ ”መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ“ ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥ ”እዚሁ እግዚአብሔርን እንጠይቅ“ አለ።
\v 37 ሳኦልም እግዚአብሔርን እንዲህ ሲል ጠየቀ፥ ”ፍልስጥኤማውያንን ላሳድዳቸው? በእስራኤል እጅ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ? “። ነገር ግን በዚያን ቀን እግዚአብሔር አልመለሰለትም።
\s5
\v 38 ከዚያም ሳኦል፥ ”የሕዝቡ አለቆች የሆናችሁ ሁሉ ወደዚህ ቅረቡ፤ ዛሬ ይህ ኃጢአት እንዴት እንደመጣብን መርምሩና ዕወቁ።
\v 39 እስራኤልን ያዳነ ሕያው እግዚአብሔርን! ልጄ ዮናታን ቢሆን እንኳን በእርግጥ እርሱ ይሞታል" አለ። ነገር ግን ከሕዝቡ ሁሉ አንዱም እንኳን አልመለሰለትም።
\s5
\v 40 እርሱም እስራኤልን በሙሉ፥ “እናንተ በአንድ በኩል ቁሙ፥ እኔና ልጄ ዮናታን በሌላው በኩል እንቆማለን” አላቸው። ሕዝቡም ሳኦልን፥ “መልካም መስሎ የታየህን አድርግ” አሉት።
\v 41 ስለዚህ ሳኦል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔርን፥ “በቱሚም አሳየኝ” አለው። ዮናታንና ሳኦል በዕጣ ተያዙ፥ ሕዝቡ ግን የተመረጠ ሆነና አመለጠ።
\v 42 ከዚያም ሳኦል፥ “በእኔና በልጄ በዮናታን መክከል ዕጣ ጣሉ” አለ። ዮናታንም በዕጣ ተያዘ።
\s5
\v 43 ሳኦልም ዮናታንን፥ “ያደረግኸውን ንገረኝ” አለው። ዮናታንም፥ “በእጄ በነበረው በትር ጫፍ ጥቂት ማር ቀምሻለሁ። ይኸው ለመሞት ዝግጁ ነኝ” አለ።
\v 44 ሳኦልም፥ “ዮናታን ሆይ፥ ባትሞት እግዚአብሔር በእኔ ላይ እንዲሁ ያድርግ፥ ይጨምርም” አለ።
\s5
\v 45 ሕዝቡም ሳኦልን፥ “ለእስራኤል ይህንን ታላቅ ድል ያመጣ ዮናታን መሞት ይገባዋል? ይህ ከእርሱ ይራቅ! እርሱ ዛሬ ከእግዚአብሔር ጋር ሠርቷልና ሕያው እግዚአብሔርን! ከራስ ጸጉሩ አንድ በምድር ላይ አይወድቅም" አሉት። ስለዚህ ሕዝቡ ዮናታንን ከመሞት አዳነው።
\v 46 ከዚያም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ማሳደዱን አቆመ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ስፍራቸው ሄዱ።
\s5
\v 47 ሳኦል እስራኤልን መግዛት በጀመረ ጊዜ፥ በየአቅጣጫው ከነበሩ ጠላቶቹ ሁሉ ጋር ተዋጋ። እርሱም ከሞዓብ፥ ከአሞን ሰዎች፥ ከኤዶም፥ ከሱባ ነገሥታትና ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ። በደረሰበት ሁሉ በቅጣት ያሰቃያቸው ነበር።
\v 48 ከአማሌቃውያን ጋር በጀግንነት ተዋግቶ ድል አደረጋቸው። እስራኤላውያንንም ከዘራፊዎቻቸው እጅ አዳናቸው።
\s5
\v 49 የሳኦል ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ የሱዊና ሜልኪሳ ነበሩ። የሁለቱ ሴቶች ልጆቹ ስም፥ የመጀመሪያ ልጁ ሜሮብና ታናሿ ሜልኮል ይባሉ ነበሩ።
\v 50 የሳኦል ሚስት ስም አኪናሆም ነበር፥ እርሷም የአኪማአስ ልጅ ነበረች። የሠራዊቱ አዛዥ ስም፥ የሳኦል አጎት የኔር ልጅ አበኔር ነበር።
\v 51 ቂስ የሳኦል አባት ነበር፤ የአበኔር አባት ኔርም የአቢኤል ልጅ ነበር።
\s5
\v 52 በሳኦል ዘመን ሁሉ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ከባድ ጦርነት ይካሄድ ነበር። ሳኦል ኃያል ወይም ብርቱ የሆነ ሰው ባየ ጊዜ ሁሉ ያንን ወደ ራሱ ይሰበስብ ነበር።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፥ ”እግዚአብሔር በሕዝቡ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ እንድቀባህ ላከኝ። አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።
\v 2 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው፥ 'እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ አማሌቅ እየተቃወመ በመንገዱ ላይ ያደረገበትን አስታውሻለሁ።
\v 3 አሁንም ሂድና አማሌቅን ምታ፥ ያላቸውን ሁሉ ፈጽመህ ደምስስ። አትራራላቸው፥ ወንድና ሴቱን፥ ልጅና ሕፃኑን፥ በሬና በጉን፥ ግመልና አህያውን ግደል።"
\s5
\v 4 ሳኦል ሕዝቡን በጥላኢም ከተማ ሰብስቦ ቆጠራቸው፤ እነርሱም ሁለት መቶ ሺህ እግረኞችና ዐሥር ሺህ የይሁዳ ሰዎች ነበሩ።
\v 5 ከዚያም ሳኦል ወደ አማሌቅ ከተማ መጥቶ በሸለቆው ውስጥ አደፈጠ።
\s5
\v 6 ከዚያም ሳኦል ቄናውያንን፥ "ከግብፅ በመጡ ጊዜ ለእስራኤል ሕዝብ በሙሉ ደግነትን አሳይታችኋልና ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ፥ ከአማሌቃውያን መካከል ተለይታችሁ ውጡና ሂዱ" አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለይተው ሄዱ።
\v 7 ሳኦልም አማሌቃውያንን ከኤውላጥ ጀምሮ ከግብፅ በስተምሥራቅ እስካለችው እስከ ሱር ድረስ መታቸው።
\s5
\v 8 የአማሌቃውያኑን ንጉሥ አጋግን ከነሕይወቱ ያዘው፤ ሕዝቡን ሁሉ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋቸው።
\v 9 ነገር ግን ሳኦልና ሕዝቡ አጋግን፥ እንዲሁም ምርጥ የሆኑትን በጎች፥ በሬዎች፥ የሰቡትን ጥጆችና የበግ ጠቦቶች በሕይወት ተዉአቸው። መልካም የሆነውን ሁሉ አላጠፉም። የተናቀውንና ዋጋ ቢስ የሆነውን ነገር ሁሉ ግን ፈጽመው ደመሰሱ።
\s5
\v 10 ከዚያም የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሳሙኤል መጣ፥
\v 11 "እኔን ከመከተል ስለተመለሰና ያዘዝኩትንም ስላልፈጸመ ሳኦልን በማንገሤ ተጸጽቻለሁ"። ሳሙኤልም ተቆጣ፤ ሌሊቱን በሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጮህ አደረ።
\s5
\v 12 ሳሙኤልም ሳኦልን በጠዋት ለመገናኘት ማልዶ ተነሣ። ለሳሙኤልም፥ "ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ መጥቶ ለራሱ ሐውልት አቆመ፥ ከዚያም ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወረደ" ብለው ነገሩት።
\v 13 ከዚያም ሳሙኤል ወደ ሳኦል መጣ፥ ሳኦልም፥ "አንተ በእግዚአብሔር የተባረክህ ነህ! የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ፈጽሜአለሁ" አለው።
\s5
\v 14 ሳሙኤልም፥ "ታዲያ ይህ በጆሮዬ የምሰማው የበጎች ድምፅና የበሬዎች ግሣት ምንድነው?" አለው።
\v 15 ሳኦልም፥ "ከአማሌቃውያኑ ያመጧቸው ናቸው። ሕዝቡ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ምርጥ የሆኑትን በጎችና በሬዎች በሕይወት አስቀሯቸው። የቀሩትን ፈጽመን አጥፍተናል" ብሎ መለሰለት።
\v 16 ከዚያም ሳሙኤል ሳኦልን፥ "አድምጠኝ፥ በዛሬው ሌሊት እግዚአብሔር የነገረኝን እነግርሃለሁ" አለው። ሳኦልም፥ "ተናገር!" አለው።
\s5
\v 17 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፥ "በራስህ ግምት ታናሽ ብትሆንም በእስራኤል ነገዶች ላይ አለቃ ተደረግህ። እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ ቀባህ፤
\v 18 እግዚአብሔርም፥ 'ሂድና ኃጢአተኞቹን አማሌቃውያንን ፈጽመህ አጥፋቸው፥ እስኪጠፉም ድረስ ተዋጋቸው' ብሎ በመንገድህ ልኮህ ነበር።
\v 19 ታዲያ የእግዚአብሔርን ድምፅ ያልታዘዝከው ለምንድነው? ከዚያ ይልቅ ግን ከምርኮው በመውሰድ በእግዚአብሔር ፊት ክፋትን አደረግህ።"
\s5
\v 20 ሳኦልም ሳሙኤልን፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ በትክክል ታዝዣለሁ፥ እግዚአብሔር በላከኝም መንገድ ሄጃለሁ። የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን ማርኬዋለሁ፥ አማሌቃውያንንም በሙሉ ፈጽሜ ደምስሻለሁ።
\v 21 ሕዝቡ ግን ከምርኮው ላይ ጥቂት በጎችንና በሬዎችን፥ ሊጠፉም የነበሩ ምርጥ ነገሮችን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በጌልገላ ሊሠዉአቸው ወሰዱ" አለው።
\s5
\v 22 ሳሙኤልም፥ "የእግዚአብሔርን ድምፅ ከመታዘዝ የበለጠ በሚቃጠል መባና መሥዋዕት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛል? ከመሥዋዕት መታዘዝ ይሻላል፥ ከአውራ በግ ስብም መስማት ይሻላል።
\v 23 እምቢተኝነት እንደ ምዋርተኝነት ኃጢአት ነው፥ እልኸኝነትም እንደ አመጸኝነትና እንደ ክፋት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እርሱም ደግሞ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃል“ አለው።
\s5
\v 24 ከዚያም ሳኦል ሳሙኤልን፥ ”ኃጢአትን ሠርቻለሁ፤ ሕዝቡን ስለፈራሁና ቃላቸውን ስለታዘዝኩ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝና የአንተን ቃል ተላልፌአለሁ።
\v 25 አሁንም እባክህን ኃጢአቴን ይቅር በለኝ፥ ለእግዚአብሔር እንድሰግድም ከእኔ ጋር ተመለስ“ አለው።
\s5
\v 26 ሳሙኤልም ሳኦልን፥ ”ከአንተ ጋር አልመለስም፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና አንተም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን እግዚአብሔር ንቆሃል" አለው።
\v 27 ሳሙኤል ለመሄድ ዘወር ባለ ጊዜ፥ ሳኦል የልብሱን ጫፍ ያዘ፥ እርሱም ተቀደደ።
\s5
\v 28 ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ዛሬ የእስራኤልን መንግሥት ከአንተ ቀደደው፥ ከአንተ ለሚሻለው ለጎረቤትህም አሳልፎ ሰጠው።
\v 29 ደግሞም የእስራኤል ኃይል አይዋሽም፥ አሳቡንም አይለውጥም፥ እርሱ አሳቡን መለወጥ ይችል ዘንድ ሰው አይደለምና“ አለው።
\s5
\v 30 ከዚያም ሳኦል፥ ”ኃጢአትን አድርጌአለሁ። አሁን ግን እባክህ በሕዝቤ ሽማግሌዎችና በእስራኤል ፊት አክብረኝ። ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እንድሰግድ ከእኔ ጋር ተመለስ“ አለው።
\v 31 ስለዚህ ሳሙኤል ከሳኦል ኋላ ተመለሰ፥ ሳኦልም ለእግዚአብሔር ሰገደ።
\s5
\v 32 ከዚያም ሳሙኤል፥ ”የአማሌቃውያንን ንጉሥ አጋግን አምጡልኝ“ አለ። አጋግ በሠንሠለት አንደታሠረ ወደ እርሱ መጣና፥ ”ለካስ ሞት እንዲህ መራራ ነው“ አለ።
\v 33 ሳሙኤልም፥ ”ሰይፍህ እናቶችን ልጅ ዐልባ እንዳደረጋቸው አሁን እናትህ በሴቶች መካከል ልጅ ዐልባ ትሆናለች“ ብሎ መለሰለት። ከዚያም ሳሙኤል አጋግን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ ቆራረጠው።
\s5
\v 34 ሳሙኤል ወደ ራማ ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ወደ ሳኦል ጊብዓ ሄደ።
\v 35 ሳሙኤል እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ሳኦልን አላየውም፥ ለሳኦልም አለቀሰለት። እግዚአብሔርም ሳኦልን በእስራኤል ላይ በማንገሡ አዘነ።
\s5
\c 16
\p
\v 1 እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ንጉሥ እንዳይሆን ለናቅኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? በወንዶች ልጆቹ መካከል ለራሴ ንጉሥ የሚሆነውን መርጫለሁና ወደ ቤተ ልሔማዊው ወደ እሴይ እልክሃለሁ። የዘይት መያዣ ቀንድህን በዘይት ሞልተህ ሂድ” አለው።
\s5
\v 2 ሳሙኤልም፥ “እንዴት መሄድ እችላለሁ? ሳኦል ከሰማ ይገድለኛል” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፥ 'ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ' በል።
\v 3 እሴይንም ወደ መሥዋዕቱ ጥራው፥ እኔም የምታደርገውን አሳይሃለሁ። የምነግርህንም እርሱን ትቀባልኛለህ” አለው።
\s5
\v 4 ሳሙኤልም እግዚአብሔር እንደተናገረው አደረገ፥ ወደ ቤተ ልሔምም ሄደ። የከተማይቱም ሽማግሌዎች እየተንቀጠቀጡ ሊገናኙት መጡና፥ “በሰላም ነው የመጣኸው? ” አሉት።
\v 5 እርሱም፥ “በሰላም ነው። ለእግዚአብሔር ልሠዋ መጥቻለሁ። ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱና ከእኔ ጋር ወደ መሥዋዕቱ ኑ”አላቸው። እሴይንና ወንዶች ልጆቹንም ቀደሳቸው፥ ወደ መሥዋዕቱም ጠራቸው።
\s5
\v 6 እነርሱ በመጡ ጊዜም፥ ወደ ኤልያብ ተመልክቶ እግዚአብሔር የሚቀባው በእርግጥ በፊቱ ቆሟል ብሎ በልቡ አሰበ።
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ሳሙኤልን፥ "እኔ ንቄዋለሁና ውጫዊ ገጽታውን ወይም የቁመቱን ዘለግታ አትመልከት። እግዚአብሔር ሰው እንደሚያይ አያይምና፤ ሰው ውጫዊ ገጽታን ያያል፥ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል" አለው።
\s5
\v 8 ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገው። ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ይኸኛውንም አልመረጠውም“ አለ።
\v 9 ከዚያም እሴይ ሳማን አሳለፈው። ሳሙኤልም፥ "እግዚአብሔር ይኸኛውንም አልመረጠውም“ አለ።
\v 10 እሴይ ሰባቱን ወንዶች ልጆቹን በሳሙኤል ፊት እንዲያልፉ አደረጋቸው። ሳሙኤልም እሴይን፥ ”እግዚአብሔር ከእነዚህ አንዳቸውንም አልመረጠም“ አለው።
\s5
\v 11 ሳሙኤልም እሴይን፥ ”ወንዶቹ ልጆችህ እነዚህ ብቻ ናቸው? “ አለው። እርሱም፥ ”የሁሉ ታናሽ የሆነው ገና ቀርቷል፥ እርሱ ግን በጎች እየጠበቀ ነው" ብሎ መለሰ። ሳሙኤልም እሴይን፥ "ልከህ አስመጣው፤ እርሱ እዚህ እስኪመጣ ድረስ አንቀመጥምና" አለው።
\v 12 እሴይም ልኮ አስመጣው። በመጣ ጊዜም ልጁ ቀይ፥ ዐይኖቹ የተዋቡና መልከ መልካም ገጽታ ነበረው። እግዚአብሔርም፥ "ያ ሰው እርሱ ነውና ተነሣ፤ ቀባውም" አለው።
\s5
\v 13 ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ አንሥቶ በወንድሞቹ መካከል እርሱን ቀባው። ከዚያን ቀን ጀምሮ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ በኃይል መጣበት። ሳሙኤልም ተነሥቶ ወደ አርማቴም ሄደ።
\s5
\v 14 የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ተለየ፥ በምትኩም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ክፉ መንፈስ አሠቃየው።
\v 15 የሳኦል አገልጋዮችም፥ "ተመልከት፥ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ እያሠቃየህ ነው።
\v 16 ደህና አድርጎ በገና መደርደር የሚችል ሰው እንዲፈልጉ ጌታችን በፊቱ ያሉትን አገልጋዮቹን ይዘዝ። ከዚያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሆነብህ ጊዜ እርሱ ይጫወትልሃል፥ አንተም ደኅና ትሆናለህ" አሉት።
\s5
\v 17 ሳኦልም አገልጋዮቹን፥ "በገና በደንብ መደርደር የሚችል ሰው ፈልጋችሁ አምጡልኝ" አላቸው።
\v 18 ከዚያም ከወጣቶቹ አንዱ እንዲህ ሲል መለሰ፥ "ደኅና አድርጎ በገና መደርደር የሚችለውን፥ ጽኑ፥ ኃያል፥ ተዋጊ፥ በንግግሩ ጠንቃቃና መልከ መልካም የሆነውን የቤተ ልሔማዊውን የእሴይን ልጅ አይቻለሁ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነው።"
\v 19 ስለዚህ ሳኦል መልዕክተኞችን ወደ እሴይ ልኮ፥ "ከበጎች ጋር ያለውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ" አለው።
\s5
\v 20 እሴይም እንጀራና ወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ የተጫነበትን አህያ፥ ከፍየል ጠቦት ጋር አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው።
\v 21 ከዚያም ዳዊት ወደ ሳኦል መጣና አገልግሎቱን መስጠት ጀመረ። ሳኦል እጅግ ወደደው፥ ዳዊትም ጋሻ ጃግሬው ሆነ።
\s5
\v 22 ሳኦልም፥ "በዐይኔ ፊት ሞገስን አግኝቷልና ዳዊት በፊቴ እንዲቆም ፈቃድህ ይሁን“ ብሎ ወደ እሴይ ላከ።
\v 23 በሳኦል ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ዳዊት በገና አንሥቶ ይደረድርለት ነበር። ስለዚህ ሳኦል ይታደስና ደኅና ይሆን ነበር፥ ክፉውም መንፈስ ከእርሱ ይርቅ ነበር።
\s5
\c 17
\p
\v 1 ፍልስጥኤማውያን ሠራዊታቸውን ለውጊያ አዘጋጁ። እነርሱም የይሁዳ በሆነችው በሰኮት ተሰበሰቡ። በሰኮትና በዓዜቃ መካከል በምትገኘው በኤፌስደሚምም ሰፈሩ።
\s5
\v 2 ሳኦልና የእስራኤል ሰዎችም ተሰብስበው በኤላ ሸለቆ ሰፈሩ፥ ፍልስጥኤማውያንን ለመግጠምም ስፍራቸውን ያዙ።
\v 3 ፍልስጥኤማውያን በአንደኛው ወገን ተራራ ላይ ቆሙ፥ በዚህኛው ወገን ባለው ተራራ ላይ እስራኤላውያኑ ቆሙ፥ በመካከላቸውም ሸለቆ ነበር።
\s5
\v 4 የጌት ሰው ጎልያድ የሚባል አንድ ጀግና ከፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር ወጣ፥ ቁመቱም ስድስት ክንድ ከስንዝር ነበር።
\v 5 በራሱ ላይ ከነሐስ የተሠራ የራስ ቁር ደፍቶ፥ ጥሩርም ለብሶ ነበር። ጥሩሩም አምስት ሺህ የነሐስ ሰቅል ይመዝን ነበር።
\s5
\v 6 በእግሮቹ ላይ የነሐስ ገምባሌዎች አድርጎ ነበር፥ በትከሻዎቹም መሓል ቀለል ያለ የነሐስ ጦር ነበር።
\v 7 የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ወፍራም ነበር። የጦሩ ጫፍ ስድስት መቶ የብረት ሰቅል ይመዝን ነበር። ጋሻ ጃግሬው በፊቱ ሄደ።
\s5
\v 8 እርሱም ተነሥቶ በእስራኤል ሠልፈኞች ላይ እንዲህ በማለት ጮኸ፥ “ለውጊያ የተሰለፋችሁት ለምንድነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ፥ እናንተ የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁም? ለራሳችሁ አንድ ሰው ምረጡና ወደ እኔ ይውረድ።
\v 9 እርሱ ሊዋጋኝ ቢችልና ቢገድለኝ እኛ አገልጋዮቻችሁ እንሆናለን። ነገር ግን ባሸንፈውና ብገድለው እናንተ አገልጋዮቻችን በመሆን ታገለግሉናላችሁ።”
\s5
\v 10 ፍልስጥኤማዊው ደገመና፥ “ዛሬ የእስራኤልን ሰልፈኞች እገዳደራቸዋለሁ። እንድንዋጋ አንድ ሰው ስጡኝ" አለ።
\v 11 ፍልስጥኤማዊው የተናገረውን ሳኦልና እስራኤላውያን ሁሉ በሰሙ ጊዜ እጅግ ፈሩ፥ ተስፋም ቆረጡ።
\s5
\v 12 ዳዊት በይሁዳ የሚኖረው የቤተ ልሔም ኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይ ስምንት ወንዶች ልጆች ነበሩት። በሳኦል ዘመን እሴይ በዕድሜው ያረጀና ከወንዶቹ ሁሉ በዕድሜ የገፋ ሰው ነበር።
\v 13 የእሴይ ሦስቱ ታላላቅ ልጆች ሳኦልን ተከትለው ወደ ጦርነቱ ሄደው ነበር። ወደ ጦርነት የሄዱት የሦስቱ ወንዶች ልጆች ስም፥ የመጀመሪያው ልጅ ኤልያብ፥ ተከታዩ አሚናዳብና ሦስተኛው ሣማ ይባሉ ነበር።
\s5
\v 14 ዳዊት የሁሉም ታናሽ ነበር። ትልልቆቹ ሦስቱ ሳኦልን ተከተሉት።
\v 15 ዳዊት በሳኦል ሠራዊትና በቤተ ልሔም የሚገኙትን የአባቱን በጎች በመጠበቅ ተግባር ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ናበር።
\v 16 ፍልስጥኤማዊው ኃያል ሰው ለአርባ ቀናት በየጠዋቱና በየምሽቱ ለጦርነት ዝግጁ መሆኑን ለማሳየት ይቀርብ ነበር።
\s5
\v 17 ከዚያም እሴይ ልጁን ዳዊትን እንዲህ አለው፥ ”ከዚህ ከተጠበሰው እሸት ዐሥር ኪሎና እነዚህን ዐሥር ዳቦዎች በጦር ሰፈሩ ውስጥ ላሉት ወንድሞችህ ፈጥነህ ውሰድላቸው።
\v 18 በተጨማሪም እነዚህን ዐሥር የአይብ ጥፍጥፎች ለሻለቃቸው ስጠው። ወንድሞችህ ያሉበትን ሁኔታ ተመልከትና ደኅና ስለመሆናቸው ማረጋገጫ አምጣልኝ።
\s5
\v 19 ወንድሞችህ ከሳኦልና ከእስራኤል ሰዎች ሁሉ ጋር ፍልስጥኤማውያንን እየተዋጉ በኤላ ሸለቆ ናቸው።“
\v 20 ዳዊት ማልዶ ተነሣና በጎቹን ለእረኛ ዐደራ ሰጠ። እርሱም እሴይ እንዳዘዘው የወንድሞቹን ስንቅ ይዞ ሄደ። ሠራዊቱ ወደ ውጊያው ግምባር እየፎከረ በመውጣት ላይ እያለ ዳዊት ወደ ጦር ሰፈሩ ደረሰ።
\v 21 እስራኤላውያንና ፍልስጥኤማውያን፥ ሠራዊት በሠራዊት ላይ ለውጊያ ተሰለፉ።
\s5
\v 22 ዳዊት የያዘውን ዕቃ ለስንቅ ጠባቂው ዐደራ ሰጥቶ ወደ ሠራዊቱ በመሮጥ ለወንድሞቹ ሰላምታ አቀረበ።
\v 23 ከእነርሱ ጋር እየተነጋገረ እያለ ጎልያድ ተብሎ የሚጠራው፥ ከጌት የመጣው ፍልስጥኤማዊ ከሰልፈኞች መካከል ወጥቶ የቀድሞውን የሚመስል ቃል ተናገረ። ዳዊትም ሰማቸው።
\v 24 የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ሰውዬውን ባዩት ጊዜ፥ ከእርሱ ሸሹ፥ እጅግም ፈርተውት ነበር።
\s5
\v 25 የእስራኤልም ሰዎች፥ "ይህን የሚወጣውን ሰው አያችሁት? እስራኤልን ለመገዳደር ነው የመጣው። እርሱን የሚገድለውን ሰው ንጉሡ እጅግ ያበለጽገዋል፥ ልጁን ይድርለታል፥ የአባቱንም ቤት በእስራኤል ውስጥ ከግብር ነጻ ያደርጋቸዋል" ይባባሉ ነበር።
\s5
\v 26 ዳዊትም በአጠገቡ የቆሙትን ሰዎች፥ "ይህንን ፍልስጥኤማዊ ለሚገድልና ከእስራኤል ኀፍረትን ለሚያስወግድ ሰው ምን ይደረግለታል? የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ሊንቅ ይህ ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ማን ሆነና ነው?" አላቸው።
\v 27 ከዚያም ሰዎቹ ቀደም ሲል የተናገሩትን ደግመው፥ "ስለዚህ እርሱን ለሚገድለው የሚደረግለት ይህ ነው" አሉት።
\s5
\v 28 ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሲነጋገር የሁሉ ታላቅ የሆነው ወንድምየው ኤልያብ ሰማው። ኤልያብም በዳዊት ላይ ቁጣው ነድዶ፥ "ወደዚህ የወረድከው ለምንድነው? እነዚያንስ ጥቂት በጎች በምድረ በዳ ውስጥ ለማን ተውካቸው? እኔ ትዕቢትህንና የልብህን ክፋት አውቃለሁ፤ ወደዚህ የወረድከው ውጊያውን ለማየት ነውና" አለው።
\v 29 ዳዊትም፥ "አሁን እኔ ምን አደረኩ? እንዲያው መጠየቄ ብቻ አልነበረም?" አለው።
\v 30 ከእርሱ ወደ ሌላው ዞር ብሎ በተመሳሳይ መንገድ ተናገረ። ሰዎቹም የቀድሞውን የሚመስል መልስ ሰጡት።
\s5
\v 31 ዳዊት የተናገረው ቃል በተሰማ ጊዜ፥ ወታደሮች ቃሉን ለሳኦል ነገሩት፥ እርሱም ዳዊትን አስጠራው።
\v 32 ከዚያም ዳዊት ሳኦልን፥ "በዚያ ፍልስጥኤማዊ ምክንያት የማንም ልብ አይውደቅ፤ አገልጋይህ ሄዶ ከፍልስጥኤማዊው ጋር ይዋጋል" አለው።
\v 33 ሳኦልም ዳዊትን፥ "አንተ ከዚህ ፍልስጥኤማዊ ጋር ለመዋጋት መሄድ አትችልም፤ አንተ ገና ልጅ ነህ፥ እርሱ ደግሞ ከወጣትነቱ ጀምሮ ተዋጊ ነው" አለው።
\s5
\v 34 ዳዊት ግን ሳኦልን፥ "አገልጋይህ የአባቴን በጎች እጠብቅ ነበር። አንበሳ ወይም ድብ መጥቶ ከመንጋው ጠቦት በሚወስድበት ጊዜ
\v 35 በኋላው ተከትዬ እመታውና ከአፉ አስጠለው ነበር። ሊያጠቃኝ በተነሣብኝ ጊዜም ጉሮሮውን ይዤ እመታውና እገድለው ነበር።
\s5
\v 36 አገልጋይህ አንበሳና ድብ ገድያለሁ። የሕያው እግዚአብሔርን ሠራዊት ስለተገዳደረ ይህም ያልተገረዘ ፍልስጥኤማዊ ከእነርሱ እንደ አንዱ ይሆናል" አለው።
\s5
\v 37 ዳዊትም፥ "እግዚአብሔር ከአንበሳና ከድብ መዳፍ አድኖኛል። ከዚህም ፍልስጥኤማዊ እጅ ያድነኛል" አለው።
\v 38 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ "ሂድ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሁን" አለው። ሳኦል የራሱን የጦር መሣሪያ ለዳዊት አስታጠቀው። በራሱ ላይ የነሐስ ቁር ደፋለት፥ ጥሩርም አለበሰው።
\s5
\v 39 ዳዊትም ሰይፉን በጦር ልብሱ ላይ ታጠቀው። ነገር ግን አልተለማመደውምና ለመራመድ አቃተው። ከዚያም ዳዊት ሳኦልን፥ "አልተለማመድኳቸውምና በእነዚህ መዋጋት አልችልም" አለው። ስለዚህ ዳዊት ከላዩ ላይ አወለቃቸው።
\v 40 በትሩን በእጁ ያዘ፥ ከጅረቱም አምስት ድቡልቡል ድንጋዮች መርጦ በእረኛ ኮሮጆው ውስጥ ጨመራቸው። ፍልስጥኤማዊውን በሚቀርብበት ጊዜ ወንጭፉን ይዞ ነበር።
\s5
\v 41 ፍልስጥኤማዊውም በፊት ለፊቱ ከሚሄደው ጋሻ ጃግሬው ጋር መጥቶ ወደ ዳዊት ቀረበ።
\v 42 ፍልስጥኤማዊው ዙሪያውን ሲመለከት ዳዊትን ባየው ጊዜ ቀይ፥ መልከ መልካም ገጽታ ያለው ትንሽ ልጅ ብቻ ስለነበረ ናቀው።
\v 43 ፍልስጥኤማዊው ዳዊትን፥ "በትር ይዘህ የምትመጣብኝ እኔ ውሻ ነኝ?" አለው። ፍልስጥኤማዊውም በአማልክቶቹ ስም ዳዊትን ረገመው።
\s5
\v 44 ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፥ "ወደ እኔ ና፥ እኔም ሥጋህን ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ" አለው።
\v 45 ዳዊትም ለፍልስጥኤማዊው እንዲህ ሲል መለሰለት፥ "አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ። እኔ ግን አንተ ባቃለልከው፥ የእስራኤል ሠራዊት አምላክ በሆነው፥ በእግዚአብሔር ስም እመጣብሃለሁ።
\s5
\v 46 ዛሬ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ድልን ይሰጠኛል፥ እገድልሃለሁ፥ ራስህንም ከሰውነትህ ላይ አነሣዋለሁ። ዛሬ የፍልስጥኤምን ሠራዊት ሬሳ ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ፥ ይኸውም ምድር ሁሉ በእስራኤል አምላክ እንዳለ እንዲያውቅና
\v 47 በዚህ የተሰበሰበው ሁሉ እግዚአብሔር በሰይፍ ወይም በጦር ድልን እንደማይሰጥ እንዲያውቁ ነው። ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነውና እናንተንም በእጃችን ላይ አሳልፎ ይሰጣችኋል።"
\s5
\v 48 ፍልስጥኤማዊው ተነሥቶ ዳዊትን በቀረበው ጊዜ ዳዊት ሊገናኘው ወደ ጠላት ጦር በፍጥነት ሮጠ።
\v 49 ዳዊት እጁን ወደ ኮሮጆው አስገብቶ አንድ ድንጋይ ከዚያ ወሰደ፥ ወነጨፈውና የፍልስጥኤማዊውን ግንባር መታው። ድንጋዩም በፍልስጥኤማዊው ግንባር ውስጥ ጠልቆ ገባ፥ እርሱም በግንባሩ በምድር ላይ ተደፋ።
\s5
\v 50 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን በወንጭፍና በድንጋይ አሸነፈው። ፍልስጥኤማዊውንም መትቶ ገደለው። በዳዊት እጅ ሰይፍ አልነበረም።
\v 51 ከዚያም ዳዊት ሮጠና በፍልስጥኤማዊው ላይ ቆመ፥ ከእርሱም ሰይፉን ወሰደ፥ ከሰገባው አወጣና ገደለው፥ በእርሱም ራሱን ቆርጦ አነሣው። ፍልስጥኤማውያን ጀግናቸው መሞቱን ባዩ ጊዜ ሸሹ።
\s5
\v 52 ከዚያም የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች እልል እያሉ ተነሥተው ፍልስጥኤማውያንን እስከ ሸለቆውና እስከ ኤቅሮን መግቢያ ድረስ አሳደዷቸው። የፍልስጥኤማውያኑ ሬሳ ከሸዓራይም እስከ ጌትና ዔቅሮን ድረስ በየመንገዱ ወድቆ ነበር።
\v 53 የእስራኤል ሰዎች ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ ተመለሱና የጦር ሰፈራቸውን በዘበዙ።
\v 54 ዳዊት የፍልስጥኤማዊውን ራስ ወስደ፥ ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣው፥ የጦር መሣሪያውን ግን በድንኳኑ ውስጥ አኖረው።
\s5
\v 55 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመጋጠም ሲሄድ ሳኦል ባየው ጊዜ፥ የሰራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ "አንተ አበኔር፥ ይህ ወጣት የማን ልጅ ነው?" አለው። አበኔርም፥ "ንጉሥ ሆይ፥ በሕያውነትህ እምላለሁ፥ አላውቅም" አለው።
\v 56 ንጉሡም፥ "የማን ልጅ እንደሆነ ምናልባት ሊያውቁት የሚችሉትን ጠይቅ" አለው።
\s5
\v 57 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ገድሎ በተመለሰ ጊዜ፥ አበኔር ወሰደው፥ የፍልስጥኤማዊውን ራስ በእጁ እንደያዘ ወደ ሳኦል አመጣው።
\v 58 ሳኦልም፥ "አንተ ወጣት፥ የማን ልጅ ነህ?" አለው። ዳዊትም፥ "እኔ የቤተ ልሔማዊው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\c 18
\p
\v 1 ለሳኦል መናገሩን በጨረሰ ጊዜ የዮናታን ነፍስ በዳዊት ነፍስ ታሰረች፥ ዮናታንም እንደ ራሱ ነፍስ አድርጎ ወደደው።
\v 2 በዚያ ቀን ሳኦል ዳዊትን ወደ ራሱ አገልግሎት ወሰደው፤ ወደ አባቱ ቤት እንዲመለስ አላሰናበተውም።
\s5
\v 3 ዮናታን ዳዊትን እንደ ራሱ ነፍስ አድርጎ ስለወደደው በመካከላቸው የወዳጅነት ቃል ኪዳን አደረጉ።
\v 4 ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከጦር ልብሱ ጋር፥ እንዲሁም ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ለዳዊት ሰጠው።
\s5
\v 5 ዳዊት ሳኦል ወደሚልከው ቦታ ሁሉ ይሄድ ነበር፥ ይከናወንለትም ነበር። ሳኦልም በተዋጊዎቹ ላይ ሾመው። ይህም በሕዝቡ ዓይን ሁሉ ደግሞም በሳኦል አገልጋዮች ፊት ደስ የሚያሰኝ ሆነ።
\s5
\v 6 ፍልስጥኤማውያንን ድል አድርገው ወደ መኖሪያቸው በመመለስ ላይ እያሉ ከእስራኤል ከተሞች ሁሉ ንጉሥ ሳኦልን ለመገናኘት፥ ሴቶች በከበሮና በሙዚቃ መሳሪያዎች በደስታ እየዘመሩና እየጨፈሩ መጡ።
\v 7 ሴቶቹም ሲጫወቱ እየተቀባበሉ ይዘምሩ ነበር፤ እነርሱም፥ "ሳኦል ሺዎችን ገደል፥ ዳዊትም ዐሥር ሺዎችን ገደለ" እያሉ ዘመሩ።
\s5
\v 8 ሳኦል እጅግ ተቆጣ፥ ይህም መዝሙር አስከፋው። እርሱም፥ "ለዳዊት ዐሥር ሺዎች አሉ፥ ለእኔ ግን ሺዎችን ብቻ። ታዲያ ከመንግሥት በቀር ምን ቀረው?" አለ።
\v 9 ሳኦል ከዚያን ቀን ጀምሮ ዳዊትን በጥርጣሬ ዐይን ተመለከተው።
\s5
\v 10 በቀጣዩ ቀን በሳኦል ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ክፉ መንፈስ መጣበት። እርሱም በቤት ውስጥ እንደ ዕብድ ይለፈልፍ ነበር። ስለዚህ ዳዊት በየቀኑ ያደርግ እንደነበረው በገናውን ይደረድር ነበር። ሳኦልም በእጁ ጦር ይዞ ነበር።
\v 11 ሳኦል፥ "ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ" ብሎ በማሰብ ጦሩን ወረወረበት። ነገር ግን ዳዊት ከሳኦል ፊት ሁለት ጊዜ እንዲህ ባለ መንገድ አመለጠ።
\v 12 እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንጂ ከእርሱ ጋር ስላልነበረ ሳኦል ዳዊትን ፈራው።
\s5
\v 13 ስለዚህ ሳኦል ከፊቱ አራቀው፥ ሻለቃም አድርጎ ሾመው። በዚህ ሁኔታ ዳዊት በሕዝቡ ፊት ይወጣና ይገባ ነበር።
\v 14 እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበረ ዳዊት የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር።
\s5
\v 15 እንደ ተከናወነለት ሳኦል ባየ ጊዜ እጅግ ፈራው።
\v 16 ነገር ግን በፊታቸው ይወጣና ይገባ ስለነበረ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ ዳዊትን ወደዱት።
\s5
\v 17 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ "ትልቋ ልጄ ሜሮብ ይቹት። እርሷን እድርልሃለሁ። ብቻ ጎብዝልኝ፥ የእግዚአብሔርን ጦርነቶችም ተዋጋ" አለው። ሳኦል፥ "እጄ በእርሱ ላይ አይሁን፥ ነገር ግን የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ ይሁን" ብሎ አስቦአልና።
\v 18 ዳዊትም ሳኦልን፥ "የንጉሥ አማች ለመሆን እኔ ማነኝ? ሕይወቴ ወይም የአባቴ ቤተ ሰብ በእስራኤል ውስጥ ምንድነው?" አለው።
\s5
\v 19 ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለዳዊት የምትዳርበት ጊዜ ሲደርስ ለመሓላታዊው ለኤድሪኤል ተዳረች።
\s5
\v 20 ነገር ግን የሳኦል ልጅ ሜልኮል ዳዊትን ወደደችው። ለሳኦል ነገሩት፥ ይህም እርሱን ደስ አሰኘው።
\v 21 ከዚያም ሳኦል፥ "ወጥመድ እንድትሆነውና የፍልስጥኤማውያን እጅ በእርሱ ላይ እንድትሆን እርሷን እድርለታለሁ" ብሎ አሰበ። ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን ለሁለተኛ ጊዜ፥ "አማቼ ትሆናለህ" አለው።
\s5
\v 22 ሳኦል አገልጋዮቹን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፥ "ዳዊትን በምስጢር እንዲህ በሉት፥ 'አስተውል፥ ንጉሡ በአንተ ደስ ብሎታል፥ አገልጋዮቹም ሁሉ ይወዱሃል። እንግዲያው የንጉሡ አማች ሁን'"
\s5
\v 23 ስለዚህ የሳኦል አገልጋዮች ይህንን ቃል ለዳዊት ነገሩት። ዳዊትም፥ "እኔ ድሃና ብዙም የማልታወቅ ሰው ሆኜ እያለሁ የንጉሥ አማች እንድሆን ማሰባችሁ ጉዳዩ እንዴት ቀልሎ ታያችሁ?" አላቸው።
\v 24 የሳኦል አገልጋዮችም ዳዊት የተናገረውን ቃል ነገሩት።
\s5
\v 25 ሳኦልም፥ "ለዳዊት እንዲህ ትሉታላችሁ፥ 'የንጉሡን ጠላቶች ለመበቀል ከአንድ መቶ የፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ብቻ በቀር ንጉሡ ምንም ጥሎሽ አይፈልግም''። ዳዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲወድቅ ለማድረግ ሳኦል አሰበ።
\v 26 አገልጋዮቹ ይህንን ቃል ለዳዊት በነገሩት ጊዜ የንጉሡ አማች መሆን ዳዊትን ደስ አሰኘው።
\s5
\v 27 እነዚያ ቀናት ከማብቃታቸው በፊት፥ ዳዊት ከሰዎቹ ጋር ሄዶ ሁለት መቶ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ። ዳዊት የንጉሡ አማች ይሆን ዘንድ ሸለፈቶቹን አመጣ፥ ለንጉሡም ሙሉውን ቁጥር አስረከቡ። ስለዚህ ሳኦል ልጁን ሜልኮልን ዳረለት።
\v 28 እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር እንደነበረ ሳኦል አየ፥ ዐወቀም። የሳኦል ልጅ ሜልኮልም ወደደችው።
\v 29 ሳኦልም ዳዊትን የበለጠ ፈራው። ሳኦል የዳዊት ጠላቱ እንደሆነ ቀጠለ።
\s5
\v 30 ከዚያም የፍልስጥኤም ልዑላን ብዙ ጊዜ ያደርጉት እንደነበረው ለጦርነት መጡ፥ ዳዊት ከሳኦል አገልጋዮች ሁሉ በበለጠ ሁኔታ የተሳካለት ሆነ፥ በመሆኑም ስሙ እጅግ የተከበረ ሆነ።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ሳኦል ልጁን ዮናታንን እና አገልጋዮቹን በሙሉ ዳዊትን እንዲገድሉት ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር።
\v 2 ስለዚህ ዮናታን ዳዊትን፥ "አባቴ ሳኦል ሊገድልህ ይፈልጋል። በመሆኑም ለራስህ ጥንቃቄ አድርግ፥ በነገውም ቀን በምስጢራዊ ቦታ ተደበቅ።
\v 3 አንተ ባለህበት አካባቢ ሄጄ በአባቴ አጠገብ እቆማለሁ፥ ስለ አንተም አነጋግረዋለሁ። አንዳች ነገር ካገኘሁኝም እነግርሃለሁ“ አለው።
\s5
\v 4 ዮናታንም ለአባቱ ለሳኦል ስለ ዳዊት መልካምን ነገር ተናገረ፥ እንዲህም አለው፥ ”ንጉሡ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ክፉ ነገር አያድርግ። እርሱ ክፉ አላደረገብህም፥ እርሱ የሠራው ሥራ ለአንተ መልካም ሆኖልሃልና።
\v 5 ነፍሱን በእጁ ላይ ጥሎ ፍልስጥኤማዊውን ገደለ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል በሙሉ ታላቅ ድልን ሰጠ። አንተም አይተህ ደስ ብሎህ ነበር። ያለምንም ምክንያት ዳዊትን በመግደልህ በንጹህ ደም ላይ ለምን ኃጢአት ትሠራለህ?“
\s5
\v 6 ሳኦልም ዮናታንን ሰማው። ሳኦልም፥ ”ሕያው እግዚአብሔርን! ዳዊት አይገደልም“ ብሎ ማለ።
\v 7 ከዚያም ዮናታን ዳዊትን ጠራው፥ ዮናታንም ይህንን ነገር ሁሉ ነገረው። ዮናታንም ዳዊትን ወደ ሳኦል አመጣው፥ እርሱም እንደቀድሞው በፊቱ ነበረ።
\s5
\v 8 እንደገናም ጦርነት ሆነ። ዳዊት ወጥቶ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፥ በታላቅ አገዳደልም ድል አደረጋቸው። እነርሱም ከፊቱ ሸሹ።
\v 9 ሳኦል በእጁ ጦሩን እንደያዘ በቤቱ ተቀምጦ እያለ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሳኦል ላይ መጣበት፥ ዳዊትም በገና ይደረድር ነበር።
\s5
\v 10 ሳኦል በጦሩ ዳዊትን ከግድግዳው ጋር ለማጣበቅ ሞከረ፥ ዳዊት ግን ከሳኦል ፊት ዘወር አለ፥ ስለዚህ የሳኦል ጦር በግድግዳው ላይ ተሰካ። በዚያ ምሽት ዳዊት ሸሽቶ አመለጠ።
\v 11 ሳኦልም በማግስቱ ይገድለው ዘንድ ከብበው እንዲጠብቁት ወደ ዳዊት ቤት መልዕክተኞች ላከ። የዳዊት ሚስት ሜልኮልም፥ ”በዚህ ሌሊት ሕይወትህን ካላዳንክ ነገ መገደልህ ነው“ አለችው።
\s5
\v 12 ስለዚህ ሜልኮል ዳዊትን በመስኮት እንዲወርድ አደረገችው። እርሱም ሄደ፥ ሸሽቶም አመለጠ።
\v 13 ሜልኮልም የቤተሰቡን የጣዖት ምስል ወስዳ በአልጋው ውስጥ አጋደመችው። በራስጌው ከፍየል ጸጉር የተሠራ ትራስ አስቀመጠች፥ በልብስም ሸፈነችው።
\s5
\v 14 ሳኦል ዳዊትን የሚወስዱ መልዕክተኞች በላከ ጊዜ እርሷ፥ "አሞታል" አለቻቸው።
\v 15 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን እንዲያዩት መልዕክተኞች ላከ፥ እርሱም፥ "እንድገድለው ከነዐልጋው አምጡልኝ" አላቸው።
\s5
\v 16 መልዕክተኞቹ ወደ ቤት በገቡ ጊዜ፥ በዐልጋው ውስጥ የቤተሰቡ የጣዖት ምስል፥ በራስጌውም ከፍየል ጸጉር የተሠራው ትራስ ነበር።
\v 17 ሳኦል ሜልኮልን፥ "ጠላቴ እንዲሄድና እንዲያመልጥ በማድረግ ለምን አታለልሽኝ?" አላት። ሜልኮልም ለሳኦል፥ "'ልሂድ፥ አለበለዚያ እገድልሻለሁ' ስላለኝ ነው" ብላ መለሰችለት።
\s5
\v 18 ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፥ ሳሙኤል ወዳለበት ወደ ራማም ሄደ፥ ሳኦል ያደረገበትንም ሁሉ ነገረው። ከዚያም እርሱና ሳሙኤል ሄዱ፥ በነዋትም ተቀመጡ።
\v 19 ለሳኦልም፥ "ዕወቀው፥ ዳዊት በራማ ነዋት ነው" ተብሎ ተነገረው።
\v 20 ሳኦልም ዳዊትን እንዲይዙት መልዕክተኞችን ላከ። እነርሱም ትንቢት የሚናገሩ የነቢያትን ጉባዔ፥ ሳሙኤልንም መሪያቸው ሆኖ ባዩ ጊዜ በሳኦል መልዕክተኞች ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ መጣባቸው፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።
\s5
\v 21 ይህ ሁኔታ ለሳኦል በተነገረው ጊዜ፥ ሌሎች መልዕክተኞችን ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። ስለዚህ ሳኦል እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ ሌሎች መልዕክተኞችን ላከ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።
\v 22 ከዚያም እርሱ ደግሞ ወደ አርማቴም ሄደ፥ በሤኩ ወዳለው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድም መጣ። እርሱም፥ ”ሳሙኤልና ዳዊት የት ነው ያሉት? “ ብሎ ጠየቀ። አንደኛው ሰው፥ ”በራማ ነዋት ናቸው“ ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 23 ሳኦልም በራማ ወዳለው ነዋት ሄደ። የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ መጣ፥ በራማም ወደሚገኘው ወደ ነዋት እስኪደርስ ድረስ በመንገድ ላይ ትንቢት ይናገር ነበር።
\v 24 እርሱም ደግሞ ልብሶቹን አወለቀ፥ በሳሙኤል ፊት እርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገረ፥ ያን ቀንና ሌሊቱን ሁሉ ራቁቱን ተጋደመ። እነርሱም፥ ”ሳኦል ከነቢያት አንዱ ሆነ እንዴ? “ ያሉት በዚህ ምክንያት ነው።
\s5
\c 20
\p
\v 1 ከዚያም ዳዊት በራማ ካለው ከነዋት ሸሽቶ መጣና ዮናታንን፥ ”ምን አድርጌአለሁ? ጥፋቴስ ምንድነው? በአባትህ ፊት ኃጢአቴ ምን ቢሆን ነው ሕይወቴን ለማጥፋት የሚፈልገው? “ አለው።
\v 2 ዮናታንም ዳዊትን፥ ”ይህ ከአንተ ይራቅ፥ አትሞትም። ነገሩ ትልቅም ይሁን ትንሽ ሳይነግረኝ አባቴ ምንም አያደርግም። አባቴ ይህንን ነገር ለምን ይደብቀኛል? ነገሩ እንዲህ አይደለም።
\s5
\v 3 ዳዊት ግን እንደገና ማለና፥ “በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አባትህ ያውቃል። እርሱም፥ 'ይህንን ዮናታን አይወቅ፥ ካልሆነ ያዝናል' ይላል። በሕያው እግዚአብሔር ስም፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፥ በእኔና በሞት መካከል የቀረው አንድ እርምጃ ነው" አለው።
\s5
\v 4 ዮናታን ዳዊትን፥ "የምትጠይቀኝን ሁሉ አደርግልሃለሁ" አለው።
\v 5 ዳዊትም ዮናታንን፥ "ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት ቀን ነው፥ ከንጉሡ ጋር ለመብላት መቀመጥ ይኖርብኛል። እስከ ሦስተኛው ቀን ምሽት ድረስ በመስኩ ውስጥ ሄጄ እንድደበቅ ፍቀድልኝ" አለው።
\s5
\v 6 አባትህ እኔን በማጣቱ ከጠየቀህ፥ "ዳዊት፥ መላው ቤተ ሰቡ ዓመታዊ መሥዋዕት ስለሚያቀርቡ ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ' በለው።
\v 7 እርሱም፥ 'መልካም ነው' ካለህ ነገሩ ለአገልጋይህ ሰላም ሆኗል ማለት ነው። ነገር ግን እርሱ እጅግ ከተቆጣ ክፉ ሊያደርግብኝ እንደወሰነ በዚህ ታውቃለህ።
\s5
\v 8 እንግዲህ አገልጋይህን በርኅራኄ ተመልከተኝ። በእግዚአብሔር ፊት ከአገልጋይህ ጋር ቃል ኪዳን አድርገሃልና። ኃጢአት ቢገኝብኝ ግን አንተው ግደለኝ፤ ለምንስ ወደ አባትህ ትወስደኛለህ?" አለው።
\v 9 ዮናታንም፥ "ይህ ከአንተ ይራቅ! አባቴ ክፉ ሊያደርግብህ መወሰኑን ባውቅ አልነግርህም?"
\s5
\v 10 ዳዊትም ዮናታንን፥ "አባትህ አንደ አጋጣሚ በቁጣ ቢመልስልህ ማን ይነግረኛል?" አለው።
\v 11 ዮናታንም ዳዊትን፥ "ና፥ ወደ መስኩ እንሂድ" አለው። ሁለቱም ወደ መስኩ ሄዱ።
\s5
\v 12 ዮናታንም ዳዊትን እንዲህ አለው፥ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ምስክር ይሁን። ነገ ወይም በሦስተኛው ቀን እንደዚህ ባለው ሰዓት አባቴን በምጠይቀው ጊዜ፥ ስለ ዳዊት በጎ አሳብ ካለው ልኬብህ አላሳውቅህም?
\v 13 አባቴ በአንተ ላይ ክፉ ማድረጉ የሚያስደስተው ከሆነ በሰላም እንድትሄድ ባላሳውቅህና ባላሰናብትህ እግዚአብሔር በዮናታን ላይ ይህንን እና ከዚህም የከፋውን ያድርግበት። ከአባቴ ጋር እንደነበረ እግዚአብሔር ከአንተም ጋር ይሁን።
\s5
\v 14 አንተስ በሕይወት በምኖርበት ዘመን እንዳልሞት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታማኝነት አታሳየኝም?
\v 15 እግዚአብሔር የዳዊትን ጠላቶች፥ እያንዳንዳቸውን ከምድር ላይ በሚያጠፋበት ጊዜ የቃል ኪዳን ታማኝነትህን ከቤቴ አታጥፋ"።
\v 16 ሰለዚህ ዮናታን ከዳዊት ቤት ጋር ቃል ኪዳን አደረገና ”እግዚአብሔር ከዳዊት ጠላቶች እጅ ይጠይቀው“ አለ።
\s5
\v 17 ዮናታን ነፍሱን እንደሚወዳት ዳዊትን ይወደው ስለነበረ፥ ለእርሱ ከነበረው ፍቅር የተነሣ ዳዊት እንደገና እንዲምልለት አደረገ።
\v 18 ከዚያም ዮናታን እንዲህ አለው፥ ”ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት የወር መጀመሪያ ቀን ነው። ወንበርህ ባዶ ስለሚሆን ላትኖር ነው።
\v 19 ለሦስት ቀናት ከቆየህ በኋላ፥ ፈጥነህ ውረድና በዚህ ጉዳይ ካሁን በፊት ወደተደበቅህበት ስፍራ መጥተህ በኤዜል ድንጋይ አጠገብ ቆይ።
\s5
\v 20 በዒላማ ላይ የምወረውር መስዬ ሦስት ፍላጻዎችን ወደዚያ አቅራቢያ እወረውራለሁ።
\v 21 ከእኔ ጋር ያለውን ታዳጊ ወጣት እልከውና፥ 'ሂድ ፍላጻዎቹን ፈልግ' እለዋለሁ። ታዳጊውን ልጅ፥ 'ተመልከት፥ ፍላጻዎቹ አጠገብህ ናቸው፤ ውሰዳቸው' ካልኩት ሕያው እግዚአብሔርን! ለአንተ ደኅንነት እንጂ ጉዳት አይሆንብህምና ትመጣለህ።
\s5
\v 22 ነገር ግን ታዳጊውን ወጣት፥ 'ተመልከት፥ ፍላጻዎቹ ከአንተ በላይ ናቸው' ካልኩት እግዚአብሔር አሰናብቶሃልና መንገድህን ሂድ።
\v 23 እኔና አንተ ያደረግነውን ስምምነት በሚመለከት እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ለዘላለም ምስክር ነው።"
\s5
\v 24 ስለዚህ ዳዊት በመስኩ ውስጥ ተደበቀ። አዲስ ጨረቃ በሆነ ጊዜ ንጉሡ ምግብ ለመብላት ተቀመጠ።
\v 25 ንጉሡ እንደተለመደው በግድግዳው አጠገብ በነበረው በመቀመጫው ላይ ተቀመጠ። ዮናታን ተነሣ፥ አበኔርም በሳኦል አጠገብ ተቀምጦ ነበር። የዳዊት ቦታ ግን ባዶ ነበር።
\s5
\v 26 በዚያን ቀን ሳኦል ገና ምንም አልተናገረም፥ ምክንያቱም፥ "አንድ ነገር ደርሶበት ይሆናል፥ ወይም በሕጉ መሰረት አልነጻም ይሆናል፤ በርግጥ ባይነጻ ነው" ብሎ ሳላሰበ ነው።
\v 27 ነገር ግን አዲስ ጨረቃ በታየችበት ማግስት፥ በሁለተኛው ቀን የዳዊት ስፍራ ባዶ ነበር። ሳኦል ልጁን ዮናታንን፥ "የእሴይ ልጅ ዳዊት ትላንትም ይሁን ዛሬ ወደ ማዕድ ያልመጣው ለምንድነው?" አለው።
\s5
\v 28 ዮናታንም ለሳኦል እንዲህ በማለት መለሰለት፥ "ዳዊት ወደ ቤተ ልሔም ለመሄድ እንድፈቅድለት አጥብቆ ለመነኝ።
\v 29 እርሱም፥ 'እባክህን እንድሄድ ፍቀድልኝ። በዚያ ከተማ ቤተሰባችን የሚያቀርበው መሥዋዕት አለ፥ እኔም በዚያ እንድገኝ ወንድሜ አዞኛል። አሁንም በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ፥ ወንድሞቼን አያቸው ዘንድ እንድሄድ እባክህን ፍቀድልኝ' አለኝ። ወደ ንጉሡ ማዕድ ያልመጣው በዚህ ምክንያት ነው።"
\s5
\v 30 ከዚያም የሳኦል ቁጣ በዮናታን ላይ ነደደ፥ እርሱም እንዲህ አለው፥ "አንተ የጠማማና አመጸኛ ሴት ልጅ! ለራስህ ኃፍረትና ለእናትህ የዕርቃንነት ኃፍረት የእሴይን ልጅ እንደ መረጥክ የማላውቅ መሰለህ?
\v 31 የእሴይ ልጅ በምድር ላይ እስካለ ድረስ አንተም ሆንክ መንግሥትህ አትጸኑም። አሁንም በእርግጥ መሞት የሚገባው ነውና ልከህ አስመጣልኝ።“
\s5
\v 32 ዮናታንም አባቱን ሳኦልን፥ ”የሚገደለው በምን ምክንያት ነው? ያደረገውስ ምንድነው? “ ሲል መለሰለት።
\v 33 በዚያን ጊዜ ሳኦል ሊገድለው ጦሩን ወረወረበት። ስለዚህ አባቱ ዳዊትን ለመግደል መወሰኑን ዮናታን ተረዳ።
\v 34 ዮናታን እጅግ ተቆጥቶ ከማዕድ ተነሣ፥ አባቱ ስላዋረደው ስለ ዳዊት አዝኖ ነበርና በወሩ በሁለተኛው ቀን ምንም ምግብ አልበላም።
\s5
\v 35 በማግስቱ ዮናታን ከዳዊት ጋር ወደተቀጣጠሩበት መስክ ሄደ፥ አንድ ታዳጊ ወጣትም አብሮት ነበር።
\v 36 እርሱም ታዳጊውን ወጣት፥ ”ሩጥ፥ የምወረውራቸውን ፍላጻዎች ሰብስብ“ አለው። ታዳጊው ወጣት በሚሮጥበት ጊዜ ፍላጻውን ከበላዩ ላይ ወረወረው።
\v 37 ታዳጊው ወጣት ዮናታን የወረወረው ፍላጻ ወደ ወደቀበት ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ ዮናታን ታዳጊውን ተጣርቶ፥ "ፍላጻው ከአንተ በላይ ነው" አለው።
\s5
\v 38 ዮናታንም ታዳጊውን፥ "ቶሎ በል፥ ፍጠን፥ አትዘግይ!" አለው። ስለዚህ የዮናታኑ ታዳጊ ወጣት ፍላጻዎቹን ሰብስቦ ወደ ጌታው መጣ።
\v 39 ታዳጊው ወጣት ግን አንዳች የሚያውቀው አልነበረም። ጉዳዩን የሚያውቁት ዮናታንና ዳዊት ብቻ ነበሩ።
\v 40 ዮናታን የጦር መሣሪያዎቹን ለታዳጊው ወጣት ሰጥቶ፥ "ሂድ፥ ወደ ከተማ ውሰዳቸው" አለው።
\s5
\v 41 ታዳጊው ወጣት እንደ ሄደ፥ ዳዊት ከጉብታው ኋላ ተነሣ፥ ወደ ምድርም ተጎንብሶ ሦስት ጊዜ ሰገደ። እርስ በእርሳቸው ተሳሳሙ፥ ተላቀሱም፥ ዳዊትም አብዝቶ አለቀሰ።
\v 42 ዮናታንም ዳዊትን፥ ”'እግዚአብሔር፥ በእኔና በአንተ፥ በዘሬና በዘርህ መካከል ለዘላለም ይሁን' ተባብለን በእግዚአብሔር ስም ተማምለናልና በሰላም ሂድ” አለው። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ሄደ፥ ዮናታንም ወደ ከተማ ተመለሰ።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ከዚያም ዳዊት ካህኑን አቢሜሌክን ለማግኘት ወደ ኖብ መጣ። አቢሜሌክም ዳዊትን ለመገናኘት እየተንቀጠቀጠ መጣና፥ “አንድም ሰው አብሮህ ያልሆነውና ብቻህን የሆንከው ለምንደነው? ” አለው።
\v 2 ዳዊትም ካህኑን አቢሜሌክን፥ “ንጉሡ ለአንድ ጉዳይ ልኮኛል። እርሱም፥ 'ስለምልክህ ጉዳይና ያዘዝኩህን ነገር ማንም እንዳያውቅ'ብሎኛል። ወጣቶቹንም የሆነ ቦታ ላይ እንዲጠብቁኝ ነግሬአቸዋለሁ።
\s5
\v 3 ታዲያ አሁን እጅህ ላይ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም ያለውን ነገር ስጠኝ” አለው።
\v 4 ካህኑም ለዳዊት መልሶ፥ “ማንኛውም ሰው የሚበላው እንጀራ የለኝም፥ ነገር ግን ታዳጊ ወጣቶቹ ራሳቸውን ከሴቶች ጠብቀው ከሆነ የተቀደሰ እንጀራ አለ” አለው።
\s5
\v 5 ዳዊትም ለካህኑ እንዲህ ሲል መለሰለት፥ “በእርግጥ በእነዚህ ሦስት ቀናት ከሴቶች ተጠብቀናል። ለተራ ተልዕኮ በሚወጡበት ጊዜ ራሳቸውን ካነጹ ለዚህ ተልዕኮማ ከእኔ ጋር ያሉት ወጣቶች ሰውነት ለእግዚአብሔር እንዴት የበለጠ የተቀደሰ አይሆንም? ”
\v 6 ስለዚህ ከተነሣ በኋላ በስፍራው ትኩስ እንጀራ ይደረግ ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ፊት ከተነሣው፥ ከገጸ ሕብስቱ በስተቀር ሌላ እንጀራ በዚያ አልነበረምና፥ ካህኑ ለእግዚአብሔር የተቀደሰውን እንጀራ ሰጠው።
\s5
\v 7 በዚያም ቀን ከሳኦል አገልጋዮች አንዱ በእግዚአብሔር ፊት በእዚያ ቆይቶ ነበር፤ ስሙ ዶይቅ የሚባል ኤዶማዊ፥ የሳኦል የእረኞቹ አለቃ ነበር።
\s5
\v 8 ዳዊት አቢሜሌክን፥ "እዚህ ጦር ወይም ሰይፍ ይኖርሃል? የንጉሡ ጉዳይ አስቸኳይ ስለነበረ ሰይፌንም ሆነ መሣሪያዬን ይዤ አልመጣሁም“ አለው።
\v 9 ካህኑም፥ ”በዔላ ሸለቆ የገደልከው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ በጨርቅ ተጠቅልሎ እዚህ ከኤፉዱ ኋላ አለ። ሌላ የጦር መሣሪያ በዚህ የለምና እርሱን ልትወስደው ብትፈልግ ውሰደው።" ዳዊትም፥ "እንደ እርሱ ያለ ሌላ ሰይፍ የለም፤ እርሱን ስጠኝ" አለው።
\s5
\v 10 በዚያን ቀን ዳዊት ተነሥቶ ከሳኦል ፊት ሸሸ፥ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስም ሄደ።
\v 11 የአንኩስ አገልጋዮችም ንጉሡን፥ "ይህ የምድሪቱ ንጉሥ የሆነው ዳዊት አይደለም? 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ' እያሉ ስለ እርሱ በዘፈን እየተቀባበሉ ዘምረውለት አልነበረም? አሉት።
\s5
\v 12 ዳዊት ይህንን ቃል በልቡ አኖረው፥ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው።
\v 13 በፊታቸውም አዕምሮውን ለወጠ፥ በያዙት ጊዜም እንደ ዕብድ ሆነ፤ የቅጥሩን በር እየቧጨረም ለሃጩን በጺሙ ላይ አዝረከረከ።
\s5
\v 14 አንኩስም አገልጋዮቹን፥ “ተመልከቱ፥ ሰውዬው ዕብድ እንደሆነ ታያላችሁ።
\v 15 ወደ እኔ ለምን አመጣችሁት? ይህንን ሰው በፊቴ እንዲያብድ ወደ እኔ ያመጣችሁት ያበዱ ሰዎችን ስላጣሁኝ ነው? በእርግጥ እንዲህ ያለው ሰው ወደ ቤቴ ይገባል? ” አላቸው።
\s5
\c 22
\p
\v 1 ስለዚህ ዳዊት ያንን ትቶ ወደ ዓዶላም ዋሻ አመለጠ። ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰብ በሙሉ ይህንን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ወደ እርሱ ወረዱ።
\v 2 የተጨነቁ፥ ዕዳ ያለባቸውና የተከፉ ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ። ዳዊትም አዛዣቸው ሆነ። ከእርሱም ጋር ወደ አራት መቶ የሚጠጉ ሰዎች ነበሩ።
\s5
\v 3 ዳዊት ከዚያ በሞዓብ ወዳለችው ወደ ምጽጳ ሄደ። እርሱም የሞዓብን ንጉሥ፥ “እግዚአብሔር የሚያደርግልኝን እስካውቅ ድረስ እባክህን አባቴና እናቴ አንተጋ እንዲኖሩ ፈቃድህ ይሁን” አለው።
\v 4 እነርሱንም በሞዓብ ንጉሥ ዘንድ ተዋቸው። ዳዊት በጠንካራው ምሽግ ውስጥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ አባቱና እናቱ ከንጉሡ ጋር ኖሩ።
\v 5 ከዚያም ነቢዩ ጋድ ዳዊትን፥ “በጠንካራው ምሽግ ውስጥ አትቆይ። እርሱን ትተህ ወደ ይሁዳ ምድር ሂድ” አለው። ስለዚህ ዳዊት ያንን ትቶ ወደ ሔሬት ጫካ ሄደ።
\s5
\v 6 ዳዊት ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሰዎች ጋር መገኘቱን ሳኦል ሰማ። ሳኦል በጊብዓ ከአጣጥ ዛፍ ስር በእጁ ጦሩን እንደያዘ ተቀምጦ ነበር፥ አገልጋዮቹም ሁሉ በዙሪያው ቆመው ነበር።
\s5
\v 7 ሳኦል በዙሪያው የቆሙትን አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የብንያም ሰዎች ሆይ፥ አሁን ስሙ! የእሴይ ልጅ ለእያንዳንዳችሁ እርሻና የወይን ቦታ ይሰጣችኋል? ሁላችሁም በእኔ ላይ ስላደማችሁበት ምትክ ሻለቆችና መቶ አለቆችስ አድርጎ ይሾማችኋል?
\v 8 ልጄ ከእሴይ ልጅ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ከእናንተ አንዱም አልነገረኝም። አንዳችሁም ስለ እኔ አላዘናችሁም። ልጄ አገልጋዬን ዳዊትን በእኔ ላይ ሲያነሣሣው ከእናንተ ማንም አልነገረኝም። ዛሬ ተደብቋል፥ እኔን ለማጥቃትም ይጠባበቃል።"
\s5
\v 9 ከዚያም በሳኦል አገልጋዮች መካከል ቆሞ የነበረው ኤዶማዊው ዶይቅ፥ "የእሴይን ልጅ ወደ ኖብ፥ ወደ አኪጦብ ልጅ ወደ አቢሜሌክ መጥቶ አይቼዋለሁ።
\v 10 አቤሜሌክም እግዚአብሔር ዳዊትን እንዲረዳው ጸለየለት፥ እርሱም ስንቅና የፍልስጥኤማዊውን የጎልያድን ሰይፍ ሰጠው" አለው።
\s5
\v 11 ንጉሡም የአኪጦብን ልጅ ካህኑን አቢሜሌክንና የአባቱን ቤተሰብ በሙሉ፥ እንዲሁም በኖብ ይኖሩ የነበሩትን ካህናት እንዲጠራ መልዕክተኛ ላከ። ሁሉም ወደ ንጉሡ መጡ።
\v 12 ሳኦልም፥ "የአኪጦብ ልጅ ሆይ፥ አሁን ስማ!" አለው። እርሱም፥ "ጌታዬ ሆይ፥ ይኸው አለሁ” ብሎ መለሰለት።
\v 13 ሳኦልም እንዲህ አለው፥ “አንተና የእሴይ ልጅ በእኔ ላይ ያሤራችሁት ለምንድነው? ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ በእኔ ላይ እንዲነሣና በምስጢራዊ ቦታ እንዲደበቅ እንጀራና ሰይፍ ሰጠኸው፥ ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር የጸለይክለት ለምንድነው?”
\s5
\v 14 አቢሜሌክም ለንጉሡ፥ “የንጉሡ አማችና በጠባቂዎቹ ላይ የበላይ የሆነ፥ በቤትህም የተከበረ፥ በአገልጋዮችህ ሁሉ መካከል እንደ ዳዊት የታመነ ማነው?
\v 15 እግዚአብሔር እንዲረዳው ስጸልይለት የዛሬው የመጀመሪያዬ ነውን? ይህ ከእኔ ይራቅ! ንጉሡ ምንም ነገር በአገልጋይህ ወይም በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር። አገልጋይህ ከዚህ ሁሉ ነገር አንዱንም አላውቅምና" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 16 ንጉሡም፥ "አቢሜሌክ ሆይ፥ አንተና የአባትህ ቤት በሙሉ በእርግጥ ትሞታላችሁ" ብሎ መለሰለት።
\v 17 ንጉሡም በዙሪያው የቆሙትን ጠባቂዎች፥ "መሸሹን እያወቁ አላስታወቁኝምና፥ እጃቸውም ከዳዊት ጋር ነውና፥ ዙሩና የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሏቸው” አላቸው። የንጉሡ አገልጋዮች ግን የእግዚአብሔርን ካህናት ለመግደል እጆቻቸውን አላነሡም።
\s5
\v 18 ከዚያም ንጉሡ ዶይቅን፥ "ዙርና ካህናቱን ግደላቸው" አለው። ስለዚህ ኤዶማዊው ዶይቅ ዞረና መታቸው፤ በዚያም ቀን ከተልባ እግር የተሠራ ኤፉድ የለበሱ ሰማንያ አምስት ሰዎችን ገደለ።
\v 19 እርሱም የካህናቱን ከተማ ኖብን፥ ወንዶችንና ሴቶችን፥ ልጆችንና ሕፃናትን፥ በሬዎችን፥ አህዮችንና በጎችን በሰይፍ ስለት መታቸው። ሁሉንም በሰይፍ ስለት ገደላቸው።
\s5
\v 20 ነገር ግን አብያታር የተባለው የአኪጦብ ልጅ፥ የአቢሜሌክ ልጅ አመለጠ፥ ወደ ዳዊትም ሸሸ።
\v 21 አብያታርም ሳኦል የእግዚአብሔርን ካህናት እንደ ገደለ ለዳዊት ነገረው።
\s5
\v 22 ዳዊትም አብያታርን፥ “ኤዶማዊው ዶይቅ በዚያ በነበረ ጊዜ በእርግጥ ለሳኦል እንደሚነግረው በዚያን ቀን ዐውቄ ነበር። ለአባትህ ቤተ ሰብ ሁሉ መሞት ተጠያቂው እኔ ነኝ! ።
\v 23 ከእኔ ጋር ተቀመጥ፥ አትፍራ። ያንተን ነፍስ የሚፈልግ የእኔንም ነፍስ የሚፈልግ ነው። ከእኔ ጋር በሰላም ትኖራለህ” አለው።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ለዳዊትም፥ "ፍልስጥኤማውያን ቅዒላን በመውጋት ላይ ናቸው፥ ዐውድማውንም እየዘረፉ ነው“ ብለው ነገሩት።
\v 2 ስለዚህ ዳዊት እግዚአብሔር እንዲረዳው ጸለየ፥ እርሱም፥ ”እነዚህን ፍልስጥኤማውያን ሄጄ ልምታቸው? “ ብሎ ጠየቀ። እግዚአብሔርም ዳዊትን፥ ”ሂድና ፍልስጥኤማውያንን ምታ፥ ቅዒላንም አድን“ አለው።
\s5
\v 3 የዳዊት ሰዎችም፥ ”ተመልከት፥ እዚሁ በይሁዳ ሆነን እየፈራን ነው። በፍልስጥኤማውያን ላይ ወደ ቅዒላ ለመውጣትማ ይልቁን እንዴት አስፈሪ አይሆንብንም? “ አሉት።
\v 4 ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔር እንዲረዳው እንደገና ጸለየ። እግዚአብሔርም፥ ”ተነሥ፥ ወደ ቅዒላ ውረድ። በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን እሰጥሃለሁ“ ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 5 ዳዊትና ሰዎቹም ሄደው ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጉ። የቀንድ ከብቶቻቸውን ወሰዱ፥ እነርሱንም በታላቅ አገዳደል መቷቸው። ስለዚህ ዳዊት የቅዒላን ነዋሪዎች አዳናቸው።
\v 6 የአቢሜሌክ ልጅ አብያታር ወደ ቅዒላ ወደ ዳዊት በሸሸ ጊዜ ኤፉዱን ይዞ ወርዶ ነበር።
\s5
\v 7 ዳዊት ወደ ቅዒላ መሄዱ ለሳኦል ተነገረው። ሳኦልም፥ "በሮችና መቀርቀሪያዎች ወዳሏት ከተማ በመግባቱ በራሱ ላይ ዘግቷልና እግዚአብሔር በእጄ ላይ ጥሎታል" አለ።
\v 8 ሳኦልም ወደ ቅዒላ ወርደው ዳዊትንና ሰዎቹን እንዲከቡ ሠራዊቱን ሁሉ ለጦርነት ጠራቸው።
\v 9 ዳዊትም ሳኦል ክፉ ሊያደርግበት እንዳቀደ ዐወቀ። እርሱም ካህኑን አብያታርን፥ "ኤፉዱን ወደዚህ አምጣው" አለው።
\s5
\v 10 ዳዊትም፥ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ሳኦል በእኔ ምክንያት ከተማይቱን ለማጥፋት ወደ ቅዒላ ለመምጣት እንደሚፈልግ አገልጋይህ በእርግጥ ሰምቷል።
\v 11 አገልጋይህ እንደ ሰማው፥ ሳኦል ወደዚህ ይወርዳል? የቅዒላ ሰዎችስ በእጁ አሳልፈው ይሰጡኝ ይሆን? የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እባክህን ለአገልጋይህ እንድትነግረኝ እለምንሃለሁ” አለ። እግዚአብሔርም፥ “አዎን፥ ወደዚህ ይወርዳል” አለው።
\s5
\v 12 ዳዊትም፥ “የቅዒላ ሰዎች እኔንና ሰዎቼን በሳኦል እጅ አሳልፈው ይሰጡናልን? ” ብሎ ጠየቀው። እግዚአብሔርም፥ “አሳልፈው ይሰጧችኋል" አለ።
\s5
\v 13 ከዚያም ዳዊትና ወደ ስድስት መቶ የሚደርሱ ሰዎቹ ተነሡ፥ ከቅዒላም ወጥተው ሄዱ፥ ከቦታ ቦታም እየተዘዋወሩ ሄዱ። ዳዊት ከቅዒላ መሸሹ ለሳኦል ተነገረው፥ እርሱም ማሳደዱን አቆመ።
\v 14 ዳዊትም በዚፍ ምድረ በዳ ውስጥ ባለው በኮረብታማው አገር፥ በምድረ በዳው ባለ ምሽግ ውስጥ ኖረ። ሳኦል በየቀኑ ይፈልገው ነበር፥ እግዚአብሔር ግን በእጁ ላይ አልጣለውም።
\s5
\v 15 ዳዊት በዚፍ ምድረ በዳ ሖሬሽ በተባለ ቦታ ነበር፤ ሳኦልም የእርሱን ሕይወት ለማጥፋት እንደ ወጣ አየ።
\v 16 ከዚያም የሳኦል ልጅ ዮናታን ተነሥቶ በሖሬሽ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት ሄደ፥ በእግዚአብሔር ስም አበረታታው።
\s5
\v 17 እንዲህም አለው፥ "የአባቴ የሳኦል እጅ አያገኝህምና አትፍራ። አንተ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆናለህ፥ እኔም ምክትልህ እሆናለሁ። አባቴ ሳኦልም ደግሞ ይህንን ያውቃል።"
\v 18 እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረጉ። ዳዊት በሖሬሽ ቆየ፥ ዮናታንም ወደ ቤቱ ተመለሰ።
\s5
\v 19 ዚፋውያንም በጊብዓ ወዳለው ወደ ሳኦል መጥተው፥ "ዳዊት ከየሴሞን በስተደቡብ በሚገኘው በኤኬላ ኮረብታ ላይ፥ በሖሬሽ ምሽጎች ውስጥ በመካከላችን ተደብቋል፤
\v 20 አሁንም ንጉሥ ሆይ! ወደዚህ ውረድ፥ ደስ ባለህ ጊዜ ወደዚህ ውረድ! በንጉሡ እጅ አሳልፎ የመስጠቱ ድርሻ የእኛ ይሆናል” አሉት።
\s5
\v 21 ሳኦልም፥ “ስለ እኔ ተቆርቁራችኋልና እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
\v 22 ሂዱና በይበልጥ እርግጠኛ ሁኑ። የት እንደ ተደበቀና በዚያ ማን እንዳየው መርምሩና ዕወቁ። እጅግ ተንኮለኛ ስለመሆኑ ተነግሮኛል።
\v 23 ስለዚህ ልብ በሉ፥ ራሱን የሚደብቅባቸውን ቦታዎች በሙሉ መርምሩ። የተረጋገጠ መረጃ ይዛችሁልኝ ተመለሱ፥ ከዚያ በኋላ እኔም ከእናንተ ጋር እሄዳለሁ። በምድሪቱ ላይ ካለ፥ በይሁዳ ሺዎች ሁሉ መካከል እፈልገዋለሁ” አላቸው።
\s5
\v 24 እነርሱም ተነሡ፥ ሳኦልንም ቀድመው ወደ ዚፍ ሄዱ። ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተደቡብ በዓረባ በምትገኘው በማዖን ምድረ በዳ ውስጥ ነበሩ።
\v 25 ሳኦልና ሰዎቹም እርሱን ሊፈልጉት ሄዱ። ይህም ለዳዊት ተነገረው፥ ስለዚህ ወደ ዐለታማው ኮረብታ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ውስጥ ኖረ። ሳኦል በሰማ ጊዜ ዳዊትን በማዖን ምድረ በዳ አሳደደው።
\s5
\v 26 ሳኦል በተራራው በአንዱ ወገን ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም በተራራው በወዲያኛው ወገን ይሄዱ ነበር። ዳዊት ከሳኦል ለማምለጥ ተቻኮለ። ሳኦልና ሰዎቹ ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመያዝ እየከበቧቸው በነበሩበት ጊዜ
\v 27 አንድ መልዕክተኛ ወደ ሳኦል መጥቶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ምድሪቱን ወረዋታልና ፈጥነህ ና" አለው።
\s5
\v 28 ስለዚህ ሳኦል ዳዊትን ከማሳደድ ተመልሶ ፍልስጥኤማውያንን ለመዋጋት ሄደ። በዚህ ምክንያት ያ ስፍራ የማምለጫ ዐለት ተብሎ ተጠራ።
\v 29 ዳዊት ከዚያ ወጥቶ በዓይንጋዲ ባሉ ምሽጎች ውስጥ ኖረ።
\s5
\c 24
\p
\v 1 ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ከማሳደድ በተመለሰ ጊዜ፥ "ዳዊት በዓይንጋዲ ምድረ በዳ ውስጥ ነው" ተብሎ ተነገረው።
\v 2 ከዚያም ሳኦል ከእስራኤል ሁሉ የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ ወደ ዓይንጋዲ ሄደ።
\s5
\v 3 እርሱም በመንገዱ በበጎች ማደሪያ አቅራቢያ ወደነበረ ዋሻ መጣ። ሳኦልም ለመጸዳዳት ወደዚያ ገባ። ዳዊትና ሰዎቹ በዋሻው ውስጥ ከኋላ ጥጉጋ ተቀምጠው ነበር።
\v 4 የዳዊት ሰዎችም፥ " 'ደስ ያሰኘህን እንድታደርግበት ጠላትህን በእጅህ ላይ አሳልፌ እሰጥሃለሁ' ባለህ ጊዜ እግዚአብሔር የተናገረው ስለዚህ ቀን ነው” አሉት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ በጸጥታ በደረቱ እየተሳበ ወደ ፊት በመሄድ የሳኦልን የካባውን ጫፍ ቆረጠው።
\s5
\v 5 ከዚህ በኋላ የሳኦልን የካባውን ጫፍ ስለ ቆረጠ ዳዊትን ኅሊናው ወቀሰው።
\v 6 እርሱም ሰዎቹን፥ "እግዚአብሔር በቀባው በጌታዬ ላይ እጄን በማንሣት እንዲህ ያለውን ነገር ማድረግን እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው" አላቸው።
\v 7 ስለዚህ ዳዊት የእርሱን ሰዎች በዚህ ቃል ገሰጻቸው፥ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲጥሉበት አልፈቀደላቸውም። ሳኦል ተነሥቶ ከዋሻው ወጣና መንገዱን ቀጠለ።
\s5
\v 8 ከዚህ በኋላ ዳዊት ተነሥቶ ከዋሻው በመውጣት ሳኦልን፥ "ጌታዬ፥ ንጉሥ ሆይ!" በማለት ተጣራ። ሳኦል ወደ ኋላው ዘወር ብሎ በተመለከተ ጊዜ፥ ዳዊት በመስገድ አክብሮትን አሳየው።
\v 9 ዳዊትም ሳኦልን፥ “ 'ዳዊት ሊጎዳህ ይፈልጋል' የሚሉህን ሰዎች ለምን ትሰማቸዋለህ?
\s5
\v 10 በዋሻው በነበርን ጊዜ እግዚአብሔር ዛሬ እጄ ላይ ጥሎህ እንደነበረ ዓይኖችህ አይተዋል። አንዳንዶቹ እንድገድልህ ነግረውኝ ነበር፥ እኔ ግን ራራሁልህ። እኔም፥ 'በእግዚአብሔር የተቀባ ስለሆነ፥ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም' አልኩኝ።
\v 11 አባቴ ሆይ ተመልከት፥ በእጄ ላይ ያለውን የካባህን ቁራጭ ተመልከት። የካባህን ጫፍ ቆረጥኩኝ እንጂ አልገደልኩህም፥ በመሆኑም በእጄ ላይ ክፋትና ክህደት እንደሌለ ዕወቅ፤ ምንም እንኳን ሕይወቴን ለማጥፋት ብታሳድደኝም፥ እኔ አልበደልኩህም።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ይፍረድ፥ እግዚአብሔር ይበቀልልኝ፥ እጄ ግን ባንተ ላይ አትሆንም።
\v 13 የጥንቱ ምሳሌ፥ 'ከክፉ ሰው ክፋት ይወጣል' ይላል። እጄ ግን ባንተ ላይ አትሆንም።
\s5
\v 14 የእስራኤል ንጉሥ የወጣው በማን ላይ ነው? የምታሳድደው ማንን ነው? የሞተን ውሻ! ቁንጫን!
\v 15 እግዚአብሔር ፈራጅ ይሁን፥ በእኔና በአንተ መካከል ይመልከት፥ ይፍረድም፥ ጉዳዬን ተመልክቶም ከእጅህ እንዳመልጥ ይርዳኝ።”
\s5
\v 16 ዳዊት ይህንን ቃል ለሳኦል ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፥ ሳኦል፥ “ልጄ ዳዊት! ይህ ድምፅህ ነው? ” አለው። ሳኦልም ድምፁን አሰምቶ አለቀሰ።
\s5
\v 17 እርሱም ዳዊትን እንዲህ አለው፥ "በክፋት ስመልስልህ በደግነት መልሰህልኛልና ከእኔ ይልቅ አንተ ጻድቅ ነህ።
\v 18 እግዚአብሔር በእጅህ ላይ በጣለኝ ጊዜ አልገደልከኝምና በጎነትን እንዳደረግህልኝ ዛሬ አሳይተሃል።
\s5
\v 19 አንድ ሰው ጠላቱን ቢያገኘው በሰላም ያሰናብተዋል? ዛሬ ስላደረግህልኝ ነገር እግዚአብሔር ቸርነትን ያድርግልህ።
\v 20 አሁንም፥ በእርግጥ ንጉሥ እንደምትሆንና የእስራኤል መንግሥት በእጅህ እንደሚጸና ዐውቃለሁ።
\s5
\v 21 ከእኔ በኋላ ዘሮቼን እንደማታጠፋና ስሜንም ከአባቴ ቤት እንደማትደመስሰው በእግዚአብሔር ማልልኝ።"
\v 22 ስለዚህ ዳዊት ለሳኦል ማለለት። ከዚያም ሳኦል ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹ ግን ወደ አምባው ወጡ።
\s5
\c 25
\p
\v 1 ሳሙኤል ሞተ። እስራኤላውያን ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በራማም በቤቱ ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።
\s5
\v 2 በማዖን አንድ ሰው ነበር፥ ንብረቱም በቀርሜሎስ ይኖር ነበር። ሰውዬው እጅግ ባለጸጋ ነበር። እርሱም ሦስት ሺህ በጎችና አንድ ሺህ ፍየሎች ነበሩት። በቀርሜሎስም በጎቹን ይሸልት ነበር።
\v 3 የሰውየው ስም ናባል፥ የሚስቱም ስም አቢግያ ነበር። ሴቲቱ ብልህና መልኳም የተዋበ ነበረች። ሰውየው ግን አስቸጋሪና በምግባሩ ክፉ ነበር። እርሱም የካሌብ ቤተ ሰብ ተወላጅ ነበር።
\s5
\v 4 ዳዊት በምድረ በዳ ውስጥ ሳለ ናባል በጎቹን እንደሚሸልት ሰማ።
\v 5 ስለዚህ ዳዊት ዐሥር ወጣቶችን ላከ። ዳዊትም ወጣቶቹን እንዲህ አላቸው፥ “ወደ ቀርሜሎስ ውጡ፥ ወደ ናባልም ሂዱና በስሜ ሰላምታ አቅርቡለት።
\v 6 እርሱንም እንዲህ በሉት፥ 'በብልጽግና ኑር፥ ሰላም ላንተ፥ ለቤትህና ያንተ ለሆነው ሁሉ ይሁን።
\s5
\v 7 ሸላቾች እንዳሉህ ሰምቻለሁ። እረኞችህ ከእኛ ጋር ነበሩ፥ ምንም ጉዳት አላደረስንባቸውም፥ በቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ አንድም አላጡም።
\v 8 ወጣቶችህን ጠይቃቸው፥ እነርሱም ይነግሩሃል። አሁንም በግብዣህ ቀን መጥተናልና ወጣቶቼ በዓይንህ ፊት ሞገስ ያግኙ። በእጅህ ያለውን ማንኛውንም ነገር ለአገልጋዮችህና ለልጅህ ለዳዊት እባክህን ስጠው።"
\s5
\v 9 የዳዊት ወጣቶች በደረሱ ጊዜ፥ በዳዊት ስም ይህንን ሁሉ ለናባል ነገሩትና ምላሹን ጠበቁ።
\v 10 ናባልም ለዳዊት አገልጋዮች፥ "ዳዊት ማነው? የእሴይስ ልጅ ማነው? በእነዚህ ቀናት ከጌቶቻቸው የሚኮበልሉ ብዙ አገልጋዮች አሉ።
\v 11 ታዲያ እንጀራዬን፥ ውሃዬንና ለሸላቾቼ ያረድኩትን ሥጋ ወስጄ ከየት እንደ መጡ ለማላውቃቸው ሰዎች መስጠት ይኖርብኛል?" ሲል መለሰላቸው።
\s5
\v 12 ስለዚህ የዳዊት ወጣቶች ዞረው በመመለስ የተባለውን ሁሉ ነገሩት።
\v 13 ዳዊትም ሰዎቹን፥ "ሁሉም ሰው ሰይፉን ይታጠቅ" አለ። ስለዚህ ሁሉም ሰይፎቻቸውን ታጠቁ። ዳዊትም ደግሞ ሰይፉን ታጠቀ። አራት መቶ የሚያህሉ ሰዎች ዳዊትን ተከተሉት፥ ሁለት መቶዎቹም ከስንቅና ትጥቃቸው ጋር ቆዩ።
\s5
\v 14 ነገር ግን ከወጣቶቹ አንዱ፥ ለናባል ሚስት ለአቢግያ እንዲህ ሲል ነገራት፥ ”ዳዊት ከምድረ በዳ ለጌታችን ሰላምታ ለማቅረብ መልዕክተኞች ላከ፥ ጌታችን ግን ሰደባቸው።
\v 15 ሰዎቹ ግን ለእኛ በጣም ጥሩዎች ነበሩ። በመስኩ ላይ እያለን ከእነርሱ ጋር በሄድንበት ጊዜ ሁሉ አንድም አልጎደለብንም፥ እነርሱም አልጎዱንም።
\s5
\v 16 በጎቹን እየጠበቅን ከእነርሱ ጋር በቆየንበት ጊዜ ሁሉ ቀንና ሌሊት አጥር ሆነውልን ነበር።
\v 17 በጌታችንና በቤተሰቡ ሁሉ ላይ ክፉ ታስቦአልና ይህንን ዕወቂ፥ ምን ማድረግ እንዳለብሽም አስቢበት። እርሱ የሚረባ ሰው አይደለምና ማንም ሊያነጋግረው አይችልም“።
\s5
\v 18 አቢግያም ፈጥና ሁለት መቶ እንጀራ፥ ሁለት ጠርሙስ የወይን ጠጅ፥ ቀደም ብሎ የተዘጋጀ አምስት በግ፥ አምስት መስፈሪያ የተጠበሰ እሸት፥ አንድ መቶ የወይን ዘለላና ሁለት መቶ የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ ወስዳ በአህዮች ላይ ጫነች።
\v 19 ከእርሷ ጋር የነበሩትንም ወጣቶች፥ "በፊቴ ቅደሙ፥ እኔም እከተላችኋለሁ" አለቻቸው። ለባልዋ ለናባል ግን አልነገረችውም።
\s5
\v 20 እርሷም በአህያዋ ላይ በመቀመጥ ተራራውን ተከልላ በመውረድ ላይ እያለች ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርሷ ወረዱ፥ እርሷም አገኘቻቸው።
\s5
\v 21 ዳዊትም፥ ”የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ እንኳን እንዳይጠፋበት፥ ይህ ሰው የነበረውን ሁሉ በምድረ በዳ መጠበቄ በእርግጥም በከንቱ ነበር፥ ስላደረግሁት በጎነት ክፋትን መልሶልኛልና።
\v 22 ነገ ጠዋት የእርሱ ከሆነው ሁሉ አንድ ወንድ እንኳን ባስቀርለት እግዚአብሔር በእኔ በዳዊት ላይ ይህንኑ ያድርግብኝ፥ ደግሞም ይጨምርብኝ" ብሎ ነበር።
\s5
\v 23 አቢግያ ዳዊትን ባየችው ጊዜ፥ ከአህያዋ ላይ ፈጥና ወረደች፥ በዳዊትም ፊት አጎንብሳ ወደ ምድር ሰገደች።
\v 24 በእግሩ ላይ ወድቃም እንዲህ አለችው፥ "ጌታዬ ሆይ፥ በደሉ በእኔ ላይ ብቻ ይሁን። እባክህን አገልጋይህ እንድናገርህ ፍቀድልኝ፥ የአገልጋይህንም ቃል ስማ።
\s5
\v 25 ጌታዬ ለዚህ ለማይረባው ናባል ትኩረት አይስጥ፥ እርሱ እንደ ስሙ ነው። ስሙ ናባል ነውና ጅልነትም ከእርሱ ጋር ነው። እኔ አገልጋይህ ግን የላካቸውን የጌታዬን ወጣቶች አላየሁም።
\v 26 አሁንም ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው እግዚአብሔር ስም፥ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ ደም ከማፍሰስና በራስህ እጅ ከመበቀል እግዚአብሔር አግዶሃልና፥ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ ለማድረግ የሚፈልጉ እንደ ናባል ይሁኑ።
\s5
\v 27 አሁንም አገልጋይህ ወደ ጌታዬ ያመጣሁት ይህ ስጦታ ጌታዬን ለሚከተሉ ወጣቶች ይሰጥ።
\v 28 እባክህን የአገልጋይህን መተላለፍ ይቅር በል፥ አንተ ጌታዬ፥ የእግዚአብሔርን ጦርነት በመዋጋት ላይ ስላለህ፥ እግዚአብሔር በርግጥ ለጌታዬ እውነተኛ የሆነን ቤት ይሠራል፥ በሕይወት ዘመንህም ሁሉ ክፋት አይገኝብህም።
\s5
\v 29 ሰዎች ተነሥተው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድዱህም የጌታዬ ሕይወት በአምላክህ በእግዚአብሔር በሕያዋን አንድነት የታሰረች ትሆናለች፤ እርሱም የጠላቶችህን ሕይወት ከወንጭፍ ኪስ እንደሚወረወር፥ በወንጭፍ ይወረውራል።
\s5
\v 30 ይህ በሆነ ጊዜ፥ እግዚአብሔር ተስፋ የሰጠህን መልካም ነገር ሁሉ ለጌታዬ በፈጸመ ጊዜ፥ በእስራኤልም ላይ መሪ ባደረገህ ጊዜ፥
\v 31 ይህ ጉዳይ ሐዘን አይሆንብህም፥ ለጌታዬም የልብ ጸጸት አይሆንም፥ ያለ ምክንያት ደም ያፈሰስክ፥ በራስህም እጅ የተበቀልክ አትሆንም። እግዚአብሔር ለጌታዬ ስኬትን ባመጣልህ ጊዜ አገልጋይህን አስበኝ።"
\s5
\v 32 ዳዊትም አቢግያን፥ "ዛሬ እንድታገኚኝ የላከሽ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን።
\v 33 ደም በማፍሰስ ከሚሆን በደልና በራሴ እጅ ስለ ራሴ ከመበቀል ጠብቀሽኛልና ጥበብሽ የተባረከ ነው፥ አንቺም የተባረክሽ ነሽ።
\s5
\v 34 በእውነት፥ አንቺን ከመጉዳት የጠበቀኝ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን፥ እኔን ለመገናኘት ፈጥነሽ ባትመጪ ኖሮ፥ ያለምንም ጥርጥር ነገ ጠዋት ለናባል አንድ ወንድ ሕፃን ልጅ አይቀርለትም ነበር“ አላት።
\v 35 ስለዚህ ዳዊት ያመጣችለትን ከእጇ ተቀበላት፤ እርሱም፥ "ወደ ቤትሽ በሰላም ሂጂ፤ ይኸው ቃልሽን ሰማሁ፥ ተቀበልኩሽም" አላት።
\s5
\v 36 አቢግያም ተመልሳ ወደ ናባል ሄደች፤ እርሱም የንጉሥ ግብዣን የመሰለ ግብዣ በቤቱ ያደርግ ነበር፤ ናባልም በጣም ሰከሮ፥ ልቡም ደስ ብሎት ነበር። ስለዚህ እስኪነጋ ድረስ ምንም ነገር አልነገረችውም።
\s5
\v 37 ከነጋ በኋላ፥ የናባል ስካር በበረደ ጊዜ፥ ሚስቱ እነዚህን ነገሮች ነገረችው፤ ልቡ ቀጥ አለ፥ እርሱም እንደ ድንጋይ ሆነ።
\v 38 ዐሥር ቀን ካለፈ በኋላ እግዚአብሔር ናባልን ስለመታው ሞተ።
\s5
\v 39 ናባል መሞቱን ዳዊት በሰማ ጊዜ፥ ”የመሰደቤን ምክንያት ከናባል እጅ የተቀበለና አገልጋዩን ከክፉ የጠበቀ ጌታ እግዚአብሔር ቡሩክ ይሁን። እርሱም የናባልን ክፉ ሥራ በራሱ ላይ መለሰበት“ አለ። ከዚያም ዳዊት ወደ አቢግያ መልዕክተኛ ልኮ ሚስት አድርጎ ሊወስዳት አናገራት።
\v 40 የዳዊት አገልጋዮች ወደ ቀርሜሎስ፥ ወደ አቢግያ በመጡ ጊዜ፥ "ሚስቱ እንድትሆኚው ልንወስድሽ ዳዊት ወዳንቺ ልኮናል" አሏት።
\s5
\v 41 እርሷም ተነሣች፥ በግምባርዋ ወደ ምድር ሰግዳ፥ "ይኸው፥ ሴት አገልጋይህ፥ የጌታዬን አገልጋዮች እግር የማጥብ አገልጋይ ነኝ" አለች።
\v 42 አቢግያም ፈጥና ተነሣች፥ ከተከተሏት ከአምስት ሴት አገልጋዮቿ ጋር በአህያ ተቀመጠች፥ የዳዊትን መልዕክተኞች ተከትላ ሄደች፥ ሚስትም ሆነችው።
\s5
\v 43 በተጨማሪም ዳዊት ኢይዝራኤላዊቱን አኪናሆምን ሚስት እንድትሆነው ወሰዳት፥ ሁለቱም ሚስቶቹ ሆኑ።
\v 44 ሳኦል የዳዊት ሚስት የነበረችውን ልጁን ሜልኮልን፥ በጋሊም ለሚኖረው ለሌሳ ልጅ ለፈልጢ ሰጥቶ ነበር።
\s5
\c 26
\p
\v 1 ዚፋውያን ወደ ሳኦል ወደ ጊብዓ መጥተው፥ “ዳዊት በምድረ በዳው ፊት ለፊት በኤኬላ ኮረብታ ላይ ተደብቋል? ” አሉት።
\v 2 ከዚያም ሳኦል ተነሣ፥ ከእስራኤል የተመረጡትን ሦስት ሺህ ሰዎች ይዞ ዳዊትን ለመፈለግ ወደ ዚፍ ምድረ በዳ ወረደ።
\s5
\v 3 ሳኦልም በምድረ በዳው ፊት ለፊት ባለው በኤኬላ ኮረብታ ላይ፥ በመንገዱ ዳር ሰፈረ። ዳዊት ግን በምድረ በዳው ቆይቶ ነበር፥ ሳኦል በምድረ በዳው ከበስተኋላው እንደመጣ አየ።
\v 4 ስለዚህ ዳዊት ሰላዮችን ላከና በርግጥም ሳኦል በመምጣት ላይ መሆኑን ዐወቀ።
\s5
\v 5 ዳዊት ተነሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈረበት ስፍራ ሄደ፤ ሳኦልና የሰራዊቱ አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር የተኙበትን ስፍራ አየ፤ ሳኦል በሰፈሩ ውስጥ ተኝቶ ነበር፥ ሕዝቡም በዙሪያው ሰፍሮ ነበር፥ ሁሉም እንቅልፍ ወስዷቸው ነበር።
\s5
\v 6 ከዚያም ዳዊት ኬጢያዊውን አቢሜሌክንና የኢዮአብን ወንድም የጽሩያን ልጅ አቢሳን፥ "ወደ ሳኦል ወደ ጦር ሰፈሩ ውስጥ ከእኔ ጋር የሚወርድ ማነው?" አላቸው። አቢሳም፥ " እኔ ከአንተ ጋር እወርዳለሁ" አለው።
\v 7 ስለዚህ ዳዊትና አቢሳ በሌሊት ወደ ሰራዊቱ ሄዱ። ሳኦል በሰፈሩ መካከል ተኝቶ፥ ጦሩም ከራስጌው በምድር ላይ ተተክሎ ነበር። አበኔርና ወታደሮቹ በዙሪያው ተኝተው ነበር።
\v 8 አቢሳም ዳዊትን፥ "እግዚአብሔር ዛሬ ጠላትህን በእጅህ ላይ ጣለው። አሁንም፥ በአንድ ምት ብቻ በጦር ከምድር ጋር እንዳጣብቀው ፍቀድልኝ፥ ሁለተኛ መምታትም አያስፈልገኝም" አለው።
\s5
\v 9 ዳዊትም አቢሳን እንዲህ አለው፥ "አትግደለው፤ እግዚአብሔር በቀባው ላይ እጁን ዘርግቶ ከበደል መንጻት የሚችል ማነው?
\v 10 ሕያው እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር ራሱ ይገድለዋል፥ ወይም ቀኑ ደርሶ ይሞታል፥ ወይም ወደ ጦርነት ሄዶ ይሞታል።
\s5
\v 11 እርሱ በቀባው ላይ እጄን ማንሣትን እግዚአብሔር ከእኔ ያርቀው፤ አሁን ግን፥ በራስጌው ያለውን ጦርና የውሃውን ኮዳ ይዘህ እንድንሄድ እለምንሃለሁ።"
\v 12 ስለዚህ ዳዊት በሳኦል ራስጌ የነበረውን ጦርና የውሃ ኮዳ ወሰደና ሄዱ። ከእግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ ስለወደቀባቸው ሁሉም አንቀላፍተው ነበርና አንድም የነቃ፥ ያየ ወይም ያወቀ አልነበረም።
\s5
\v 13 ከዚያም ዳዊት በሌላኛው ወገን ወጣ፥ በተራራው ጫፍ ላይም ርቆ ቆመ፤ በመካከላቸው ሰፊ ርቀት ነበረ።
\v 14 ዳዊትም ወደ ኔር ልጅ ወደ አበኔርና ወደ ሕዝቡ ጮኾ፥ "አበኔር ሆይ፥ አትመልስምን?" አለው። አበኔርም፥ "በንጉሡ ላይ የምትጮኸው አንተ ማነህ?" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 15 ዳዊትም አበኔርን፥ "አንተ ጀግና አይደለህም? በእስራኤልስ አንተን የሚመስልህ ማነው? ታዲያ ጌታህን ንጉሡን ያልጠበቅኸው ለምንድነው? አንድ ሰው ጌታህን ንጉሡን ለመግደል መጥቶ ነበርና።
\v 16 ይህ ያደረግኸው ነገር መልካም አይደለም። ሕያው እግዚአብሔርን! ሞት የሚገባህ ነህ፥ ምክንያቱም እግዚአብሔር የቀባውን ጌታህን አልጠበቅኸውም። አሁንም፥ የንጉሡ ጦርና በራስጌው የነበረው የውሃ ኮዳ የት እንዳለ ተመልከት" አለው።
\s5
\v 17 ሳኦልም የዳዊት ድምፅ መሆኑን ለየና፥ "ልጄ ዳዊት፥ ይህ ድምፅህ ነው?" አለው። ዳዊትም፥ "ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ድምፄ ነው" አለው።
\v 18 እርሱም እንዲህ አለው፥ "ጌታዬ አገልጋዩን የሚያሳድደው ለምንድነው? ምን አድርጌአለሁ? በእጄስ ያለው ክፋት ምንድነው?
\s5
\v 19 አሁንም ጌታዬ ንጉሡ የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማ እለምንሃለሁ። በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ከሆነ መስዋዕትን ይቀበል፤ ሰዎች ከሆኑ ግን በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ፥ 'ሄደህ ሌሎች አማልክቶችን አምልክ' ብለው የእግዚአብሔርን ርስት አጥብቄ እንዳልይዝ ዛሬ አባረውኛልና።
\v 20 ስለዚህ፥ አንድ ሰው በተራሮች ላይ ቆቅን እንደሚያድን፥ የእስራኤል ንጉሥ ቁንጫን ለመፈለግ መጥቷልና ደሜ ከእግዚአብሔር ፊት ርቆ በምድር ላይ እንዲፈስ አታድርግ።“
\s5
\v 21 ከዚያም ሳኦል፥ ”ኃጢአትን አድርጌአለሁ። ልጄ ዳዊት፥ ተመለስ፤ ዛሬ ሕይወቴ በዐይንህ ፊት ከብራለችና ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ አላደርግብህም። ስንፍናን አድርጌአለሁ፥ እጅግም ተሳስቻለሁ“ አለው።
\s5
\v 22 ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰለት፥ ”ንጉሥ ሆይ ተመልከት! ጦርህ ያለው እዚህ ነው፥ ከወጣቶቹ አንዱ ይምጣና ይውሰድልህ።
\v 23 ዛሬ እግዚአብሔር በእጄ ላይ ጥሎህ እያለ በእርሱ የተቀባውን አልመታሁትምና እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ እንደ ጽድቁና ታማኝነቱ ይክፈለው።
\s5
\v 24 ተመልከት፥ ዛሬ ሕይወትህ በዐይኔ ፊት እንደ ከበረች የእኔም ሕይወት በእግዚአብሔር ዐይን አብልጣ የከበረች ትሁን፥ ከመከራዬም ሁሉ ያድነኝ።“
\v 25 ከዚያም ሳኦል ዳዊትን፥ ”ልጄ ዳዊት፥ በርግጥ ታላላቅ ነገሮችን እንድታደርግና እንዲከናወንልህ የተባረክህ ሁን“ አለው። ስለዚህ ዳዊት መንገዱን ሄደ፥ ሳኦልም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ዳዊትም፥ ”አሁንም አንድ ቀን በሳኦል እጅ እሞታለሁ፤ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ከመሸሽ የሚሻል አማራጭ የለኝም፤ ያን ጊዜ ሳኦል በእስራኤል ወሰኖች ሁሉ ውስጥ እኔን መፈለጉን ያቆማል፤ በዚህ መንገድ ከእጁ አመልጣለሁ" ብሎ በልቡ አሰበ።
\s5
\v 2 ዳዊትም ተነሣ፥ እርሱና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አሜህ ልጅ ወደ አንኩስ ተሻገሩ።
\v 3 ዳዊትና ሰዎቹ እያንዳንዱ ከቤተሰቡ ጋር፥ እርሱም ከሁለቱ ሚስቶቹ፥ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ ከአቢግያ ጋር በጌት ከአንኩስ ጋር ኖሩ።
\v 4 ዳዊት ወደ ጌት መሸሹን ሳኦል ሰማ፥ ስለዚህ ከዚህ በኋላ አልፈለገውም።
\s5
\v 5 ዳዊትም አንኩስን፥ "በዐይንህ ፊት ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፥ በዚያ እኖር ዘንድ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ስፍራ ይስጡኝ፤ አገልጋይህ በንጉሣዊ ከተማ ከአንተ ጋር ለምን ይኖራል?" አለው።
\v 6 ስለዚህ በዚያን ቀን አንኩስ ጺቅላግን ሰጠው፤ እስከዛሬ ድረስ ጺቅላግ የይሁዳ ነገሥታት የሆነችው ለዚህ ነው።
\v 7 ዳዊት በፍልስጥኤም ምድር የኖረበት ቀን ሲቆጠር አንድ ዓመት ከአራት ወር ሆነው።
\s5
\v 8 ዳዊትና ሰዎቹ ጌሹራውያንን፥ ጌርዛውያንን እና አማሌቃውያንን በመውረር የተለያዩ ቦታዎችን አጠቁ፤ እነዚህ ሕዝቦች እስከ ሱርና እስከ ግብፅ ምድር ድረስ ባለው አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ናቸው። እነርሱም ከጥንት ጀምሮ በዚያ ምድር ይኖሩ ነበር።
\v 9 ዳዊትም ምድሪቱን መታ፥ ወንዱንም ሆነ ሴቱን በሕይወት አልተወም፤ በጎችን፥ በሬዎችን፥ አህዮችን፥ ግመሎችን እና ልብሶችን ወሰደ፤ ተመልሶም እንደገና ወደ አንኩስ መጣ።
\s5
\v 10 አንኩስ፥ "ዛሬ በማን ላይ ወረራ ፈጸማችሁ?" ብሎ ይጠይቅ ነበር፥ ዳዊትም፥ "በይሁዳ ደቡብ ላይ" ወይም "በደቡብ ይረሕምኤላውያን ላይ" ወይም "በደቡብ ቄናውያን ላይ" ብሎ ይመልስለት ነበር።
\s5
\v 11 "ስለዚህ ስለ እኛ፥ 'ዳዊት እንዲህና እንዲህ አደረገ' ለማለት እንዳይችሉ" ብሎ ነበርና ዳዊት ወደ ጌት ይዞ ለመምጣት በማሰብ ወንድ ወይም ሴት በሕይወት አያስቀርም ነበር። በፍልስጥኤም አገር በኖረበት ጊዜ ሁሉ ያደረገው እንደዚህ ነበር።
\v 12 አንኩስም፥ "የራሱ የሆነው የእስራኤል ሕዝብ አምርሮ እንዲጠላው አድርጓል፤ ስለዚህ ለዘላለም አገልጋዬ ይሆናል“ ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።
\s5
\c 28
\p
\v 1 በዚያም ዘመን ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት ሠራዊታቸውን ሁሉ በአንድ ላይ ሰበሰቡ። አንኩስም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ ያለ ጥርጥር ከእኔ ጋር ወደ ጦርነቱ እንደምትወጡ ዕወቅ” አለው።
\v 2 ዳዊትም አንኩስን፥ “ስለዚህ አገልጋይህ ምን ሊያደርግ እንደሚችል ታያለህ” አለው። አንኩስም ዳዊትን፥ “ስለዚህ እኔም በቋሚነት የግል ጠባቂዬ አደርግሃለሁ" አለው።
\s5
\v 3 ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤል ሁሉ አልቅሰውለት በከተማው በራማም ቀብረውት ነበር። ሳኦል ከሙታንና ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩትን ከምድሪቱ አጥፍቶ ነበር።
\v 4 ፍልስጥኤማውያን በአንድነት ተሰባስበው በመምጣት ሱነም ላይ ሰፈሩ፤ ሳኦልም እስራኤልን በሙሉ በአንድነት ሰብስቦ ጊልቦዓ ላይ ሰፈረ።
\s5
\v 5 ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ሰራዊት ባየ ጊዜ ፈራ፥ ልቡም እጅግ ተንቀጠቀጠ።
\v 6 ይረዳው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር በጸለየ ጊዜም እግዚአብሔር በህልም፥ ወይም በኡሪም፥ ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።
\v 7 ከዚያም ሳኦል አገልጋዮቹን፥ "ወደ እርሷ ሄጄ ምክሯን እንድጠይቅ ከሞተ ጋር መነጋገር እችላለሁ የምትል ሴት ካለች ፈልጉልኝ" አላቸው። አገልጋዮቹም፥ "ከሞተ ጋር መነጋገር እችላለሁ የምትል ሴት በዓይንዶር አለች" አሉት።
\s5
\v 8 ሳኦል ሌላ ልብስ በመልበስ ራሱን ቀይሮ ከሁለት ሰዎች ጋር ሄደ፤ እነርሱም በሌሊት ወደ ሴቲቱ ሄዱ። እርሱም፥ "የምነግርሽን ሰው አስነሥተሽ ከሞተው ጋር በመነጋገር እንድትጠነቁይልኝ እለምንሻለሁ" አላት።
\v 9 ሴቲቱም፥ "ሳኦል ከሙታንና ከመናፍስት ጋር የሚነጋገሩትን ከምድሪቱ በማጥፋት ያደረገውን ታውቃለህ። ታዲያ እንድሞት ለሕይወቴ ወጥመድ የምታዘጋጀው ለምንድነው?" አለችው።
\v 10 ሳኦልም በእግዚአብሔር ስም ምሎላት፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! በዚህ ጉዳይ ምንም ቅጣት አይደርስብሽም” አላት።
\s5
\v 11 ሴቲቱም፥ “ማንን ላስነሣልህ? ” አለችው። ሳኦልም፥ “ ሳሙኤልን አስነሽልኝ” አላት።
\v 12 ሴቲቱም ሳሙኤልን ባየችው ጊዜ በታላቅ ድምፅ ጮኻ ሳኦልን፥ "አንተ ራስህ ሳኦል ሆንህ ሳለ ለምን አታለልከኝ?" አለችው።
\s5
\v 13 ንጉሡም፥ "አትፍሪ፤ ምንድነው ያየሽው?" አላት። ሴቲቱም ሳኦልን፥ "አንድ መንፈስ ከምድር ሲወጣ አያለሁ" አለችው።
\v 14 እርሱም፥ “ምን ይመስላል? ” አላት። እርሷም፥ "አንድ ካባ የለበሰ ሽማግሌ እየመጣ ነው" አለችው። ሳኦልም ሳሙኤል እንደሆነ ዐወቀ፥ አክብሮቱን ለማሳየትም በምድር ላይ ሰገደለት።
\s5
\v 15 ሳሙኤልም ሳኦልን፥ "እኔን በማስነሣት የምታስቸግረኝ ለምንድነው?" አለው። ሳኦልም፥ "በጣም ተጨንቄአለሁ፥ ፍልስጥኤማውያን ጦርነት ዐውጀውብኛል፥ እግዚአብሔር ትቶኛል፥ በሕልምም ሆነ በነቢያት አይመልስልኝም። ምን ማድረግ እንዳለብኝ እንድታስታውቀኝ ለዚህ ነው የጠራሁህ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 16 ሳሙኤልም እንዲህ አለው፥ " ታዲያ እግዚአብሔር ከተወህና ጠላት ከሆነህ የምትጠይቀኝ ምንድነው?
\v 17 እግዚአብሔር አደርገዋለሁ ብሎ የነገረህን እርሱን ነው ያደረገብህ። እግዚአብሔር መንግሥትን ከእጅህ ቀዶ ለሌላ ሰው፥ ለዳዊት ሰጥቶታል።
\s5
\v 18 የእግዚአብሔርን ድምፅ ስላልታዘዝክና ጽኑ ቁጣውን በአማሌቅ ላይ ስላልፈጸምክ ዛሬ ይህንን አድርጎብሃል።
\v 19 በተጨማሪም እግዚአብሔር አንተንና እስራኤልን በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል። አንተና ልጆችህ ነገ ከእኔ ጋር ትሆናላችሁ። በተጨማሪም እግዚአብሔር የእስራኤልን ሰራዊት በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል።“
\s5
\v 20 ከዚያም ሳኦል በሳሙኤል ቃል ምክንያት እጅግ ስለፈራ ወዲያውኑ በቁመቱ ሙሉ በምድር ላይ ወደቀ። በዚያ ቀንና ሌሊት ምግብ ስላልበላ ምንም አቅም አልነበረውም።
\v 21 ሴቲቱም ወደ ሳኦል መጥታ እጅግ መጨነቁን አየች፥ እርሷም እንዲህ አለችው፥ "እኔ አገልጋይህ ቃልህን ሰምቻለሁ፤ ሕይወቴን በእጄ ላይ ጥዬ የነገርከኝን ቃል ሰምቻለሁ።
\s5
\v 22 አሁንም እንግዲህ አንተም ደግሞ የእኔን የአገልጋይህን ቃል እንድትሰማና ጥቂት ምግብ እንዳቀርብልህ እለምንሃለሁ። መንገድህን ለመሄድ ዐቅም እንድታገኝ ብላ።
\v 23 ሳኦል ግን፥ "አልበላም" በማለት እንቢ አለ። ነገር ግን አገልጋዮቹ ከሴቲቱ ጋር በመሆን ለመኑት፥ እርሱም ቃላቸውን ሰማ። ስለዚህ ከምድር ላይ ተነሥቶ ዐልጋ ላይ ተቀመጠ።
\s5
\v 24 ሴቲቱም በቤቷ የደለበ ጥጃ ነበራት፤ ፈጥና አረደችው፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰችው፤ ቂጣ አድርጋም ጋገረችው።
\v 25 እርሷም በሳኦልና በአገልጋዮቹ ፊት አቀረበችላቸው፥ እነርሱም በሉ። ከዚያም በዚያው ሌሊት ተነሥተው ሄዱ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ፍልስጥኤማውያንም ሰራዊታቸውን ሁሉ አፌቅ ላይ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።
\v 2 የፍልስጥኤማውያኑ መሳፍንት በመቶዎችና በሺዎች እየሆኑ አለፉ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር በደጀንነት አለፉ።
\s5
\v 3 ከዚያም የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?" አሉ። አንኩስም ለሌሎቹ የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "ይህ በእነዚህ ቀናት ሁሉ ከእኔ ጋር የነበረው፥ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ ዳዊት አይደለምን? ደግሞም በእነዚህ ዓመታት ሁሉ ወደ እኔ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁበትም” አላቸው።
\s5
\v 4 ነገር ግን የፍልስጥኤም መሳፍንት በእርሱ ላይ ተቆጥተው፥ “ያንን ሰው ወደ ሰጠኸው ወደ ስፍራው እንዲመለስ አሰናብተው፥ በውጊያው ውስጥ ጠላት እንዳይሆንብን ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አትላከው። ይህ ሰው ከጌታው ጋር ሰላምን የሚፈጥረው በምንድነው? የሰዎቻችንን አንገት በመቁረጥ አይደለምን?
\s5
\v 5 ይህ በዘፈን እየተቀባበሉ፥ 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ" ያሉለት ዳዊት አይደለምን?" አሉት።
\s5
\v 6 ከዚያም አንኩስ ዳዊትን ጠርቶ፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ ጥሩ ሰው ነህ፥ በእኔ አመለካከት በሰራዊቱ ውስጥ መውጣትህና መግባትህ መልካም ነው፤ ወደ እኔ ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬው ቀን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁብህም። ይሁን እንጂ መሳፍንቱ አልደገፉህም።
\v 7 ስለዚህ አሁን የፍልስጥኤም መሳፍንት ቅር እንዳይሰኙ ተመለስና በሰላም ሂድ" አለው።
\s5
\v 8 ዳዊትም አንኩስን፥ “ግን ምን አድርጌአለሁ፥ እንዳልሄድና ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ በእነዚህ በፊትህ በኖርኩባቸው ቀናት በአገልጋይህ ላይ ምን አግኝተህብኛል? ” አለው።
\v 9 አንኩስም ለዳዊት፥ “አንተ በእኔ ዕይታ ነቀፌታ እንደማይገኝበት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ ይሁንና የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ 'ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አይሄድም' ብለዋል።
\s5
\v 10 ስለዚህ ከአንተ ጋር ከመጡት ከጌታህ አገልጋዮች ጋር ማልዳችሁ ተነሡ፤ ማልዳችሁ ተነሡና ሲነጋላችሁ ሂዱ" ብሎ መለሰለት።
\v 11 ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ በጠዋት ለመሄድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ለመመለስ ማልደው ተነሡ። ፍልስጥኤማውያን ግን ወደ ኢይዝራኤል ወጡ።
\s5
\c 30
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፥ ዳዊትና ሰዎቹ በሦስተኛው ቀን ወደ ጺቅላግ በመጡ ጊዜ አማሌቃውያን በኔጌቭና በጺቅላግ ላይ ወረራ ፈጽመው ነበር። እነርሱም ጺቅላግን መቱ፥ አቃጠሏትም፥
\v 2 ሴቶችንና በውስጧ የነበረውን ትንሽና ትልቅ ሁሉ ማረኩ። ይዘዋቸው መንገዳቸውን ሄዱ እንጂ አንዱንም አልገደሉም።
\s5
\v 3 ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ከተማይቱ በመጡ ጊዜ ከተማይቱ በእሳት ተቃጥላ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው ተወስደው ነበር።
\v 4 ከዚያም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ለማልቀስ ኃይል እስከማይኖራቸው ድረስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።
\s5
\v 5 ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች፥ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያ ተማርከው ነበር።
\v 6 የሕዝቡም ሁሉ መንፈስ፥ እያንዳንዱም ስለ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ስላዘነ በድንጋይ ሊወግሩት ይነጋገሩ ስለነበር ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አበረታ።
\s5
\v 7 ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ "ኤፉዱን ወደዚህ እንድታመጣልኝ እለምንሃለሁ" አለው። አብያታር ኤፉዱን ለዳዊት አመጣለት።
\v 8 ዳዊትም ምሪት ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር፥ "ይህንን ወራሪ ብከተል እደርስበታለሁ?" ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም፥ "ተከተላቸው፥ ያለጥርጥር ትደርስባቸዋለህ፥ ሁሉንም ነገር ታስመልሳለህ" ብሎ መለሰለት።
\s5
\v 9 ስለዚህ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ስድስት መቶ ሰዎች ሄዱ፤ ከእነርሱ ወደ ኋላ የቀሩት ወደሚቆዩበት ወደ ባሦር ወንዝ መጡ።
\v 10 ነገር ግን ዳዊት ከአራት መቶ ሰዎች ጋር መከታተሉን ቀጠለ፤ ሁለት መቶዎቹ በጣም ስለ ደከሙ የባሦርን ወንዝ መሻገር አልቻሉምና ወደ ኋላ ቀሩ።
\s5
\v 11 እነርሱም በሜዳው ላይ አንድ ግብፃዊ አገኙና ወደ ዳዊት አመጡት፤ ምግብ ሰጡትና በላ፥ እንዲጠጣም ውሃ ሰጡት፤
\v 12 ደግሞም ከበለስ ጥፍጥፍ ቁራጭና ሁለት የወይን ዘለላ ሰጡት። ለሦስት ቀንና ሌሊት ምንም ምግብ አልበላም፥ ውሃም አልጠጣም ነበርና በበላ ጊዜ እንደገና ብርታት አገኘ።
\s5
\v 13 ዳዊትም፥ "አንተ የማን ነህ? ከየትስ ነው የመጣኸው?" አለው። እርሱም፥ "እኔ የአማሌቃዊ አገልጋይ፥ ግብፃዊ ወጣት ነኝ፤ ከሦስት ቀናት በፊት ታምሜ ስለነበር ጌታዬ ትቶኝ ሄደ።
\v 14 እኛም በከሊታውያን ኔጌቭ፥ የይሁዳ በሆነው ምድርና በካሌብ ኔጌቭ ላይ ወረራ ፈጸምን፥ ጺቅላግንም አቃጠልናት“ አለው።
\s5
\v 15 ዳዊትም፥ ”ወደዚህ ወራሪ አካል መርተህ ልታወርደኝ ትፈቅዳለህ? “ አለው። ግብፃዊውም፥ ”እንዳትገድለኝ ወይም በጌታዬ እጅ ላይ አሳልፈህ እንዳትሰጠኝ በእግዚአብሔር ማልልኝ እንጂ ወደ ወራሪው አካል መርቼ አወርድሃለሁ“ አለው።
\s5
\v 16 ግብፃዊው ዳዊትን እየመራው ወደ ታች ባወረደው ጊዜ፥ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያን ምድርና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ምርኮ ሁሉ የተነሣ እየበሉና እየጠጡ፥ እየጨፈሩም በምድሩ ሁሉ ተበትነው ነበር።
\v 17 ዳዊትም ደንገዝገዝ ሲል ጀምሮ እስከ ማግስቱ ምሽት ድረስ መታቸው። በግመሎች ተቀምጠው ከሸሹት ከአራት መቶ ወጣቶች በስተቀር አንድም ሰው አላመለጠም።
\s5
\v 18 ዳዊት አማሌቃውያን ወስደዋቸው የነበሩትን ሁሉ አስመለሰ፤ ሁለቱን ሚስቶቹንም አዳነ።
\v 19 ትንሽ ይሁን ትልቅ፥ ወንዶች ልጆች ይሁኑ ሴቶች ልጆች፥ ምርኮም ይሁን ወራሪዎቹ ለራሳቸው ከወሰዱት ማንኛውም ነገር አንዱም አልጠፋም። ዳዊት ሁሉን ነገር አስመለሰ።
\v 20 ዳዊትም ሰዎቹ ከሌሎች ከብቶች ፊት ይነዷቸው የነበሩትን የበጉን፥ የፍየሉንና የላሙን መንጋ ሁሉ ወሰደ። እነርሱም፥ "ይህ የዳዊት ምርኮ ነው" አሉ።
\s5
\v 21 ዳዊት ሊከተሉት እጅግ ደክሟቸው በባሦር ወንዝ አጠገብ እንዲቆዩ ወደተደረጉት ወደ ሁለት መቶዎቹ ሰዎች መጣ። እነዚህ ሰዎች ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ለመገናኘት ወጡ። ዳዊት ወደ እነዚህ ሰዎች በመጣ ጊዜ ሰላምታ ሰጣቸው።
\v 22 ከዚያም ከዳዊት ጋር ሄደው በነበሩት ሰዎች መካከል ክፉዎችና የማይረቡት ሁሉ፥ ”እያንዳንዱ ሚስቱንና ልጆቹን ይዞ ከመሄድ በስተቀር እነዚህ ሰዎች ከእኛ ጋር ስላልሄዱ፥ ካስመለስነው ምርኮ ምንም አንሰጣቸውም“ አሉ።
\s5
\v 23 ከዚያም ዳዊት፥ ”ወንድሞቼ ሆይ፥ እግዚአብሔር በሰጠን ነገር እንዲህ ልታደርጉ አይገባም። እርሱ ጠበቀን፥ በእኛ ላይ የመጡትንም ወራሪዎች በእጃችን ላይ አሳልፎ ሰጠን።
\v 24 በዚህ ጉዳይ ማን ይሰማችኋል? ወደ ጦርነት የሄደው የየትኛውም ሰው ድርሻ ስንቅና ትጥቅ ከጠበቀ ከየትኛውም ሰው ድርሻ ጋር እኩል ይሆናል፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ" አላቸው።
\v 25 ዳዊት ለእስራኤል ደንብና ሥርዓት ስላደረገው፥ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከዚህ ቀን ድረስ እንደዚሁ ሆነ።
\s5
\v 26 ዳዊት ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ፥ ከምርኮው ጥቂቱን፥ "ይህ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ካገኘነው ምርኮ ለእናንተ የተላከ ስጦታ ነው“ብሎ ለይሁዳ ሽማግሌዎችና ለወዳጆቹ ላከላቸው።
\v 27 የላከውም፥ በቤቴል፥ በደቡብ ራሞት፥ በየቲር፥
\v 28 በአሮኤር፥ በሢፍሞት፥ በኤሽትሞዓ ለነበሩ ሽማግሌዎች ነበር።
\s5
\v 29 እንዲሁም በራካል፥ በይረሕምኤላውያንና በቄናውያን ከተሞች፥
\v 30 በሔርማ፥ በቦራሣን፥ በዓታክ፥
\v 31 በኬብሮን፥ እንዲሁም ዳዊት ራሱና ሰዎቹ አዘውትረው ይሄዱባቸው በነበሩ ስፍራዎች ሁሉ ለሚኖሩ ሽማግሌዎች ላከላቸው።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር ተዋጉ። የእስራኤል ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይም ተገድለው ወደቁ።
\v 2 ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በቅርብ ርቀት ተከተሏቸው። ፍልስጥኤማውያንም ልጆቹን ዮናታንን፥ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሏቸው።
\v 3 ውጊያው በሳኦል ላይ በረታበት፥ ቀስተኞችም አገኙት። በእነርሱም ምክንያት በጽኑ ሕመም ላይ ነበር።
\s5
\v 4 ሳኦልም ጋሻ ጃግሬውን፥ ”ሰይፍህን ምዘዝና ውጋኝ። አለበለዚያ፥ እነዚህ ያልተገረዙ መጥተው ይሳለቁብኛል“ አለው።
\v 5 ጋሻ ጃግሬው ግን እጅግ ፈርቶ ስለነበረ እምቢ እለ። ስለዚህ ሳኦል የራሱን ሰይፍ ወስዶ በላዩ ላይ ወደቀበት። ጋሻ ጃግሬው ሳኦል መሞቱን ባየ ጊዜ እርሱም ደግሞ ሰይፉ ላይ ወድቆ አብሮት ሞተ።
\v 6 ስለዚህ ሳኦል፥ ሦስቱ ወንዶች ልጆቹና ጋሻ ጃግሬው ሞቱ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ በአንድ ቀን ሞቱ።
\s5
\v 7 ከሸለቆው በወዲያኛው ወገን የነበሩትና ከዮርዳኖስ በላይ የነበሩት የእስራኤል ሰዎች፥ የእስራኤል ሰዎች መሸሻቸውን፥ ሳኦልና ልጆቹ መሞታቸውን ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ትተው ሸሹ፥ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።
\v 8 በማግስቱ እንዲህ ሆነ፥ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ትጥቅ ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።
\s5
\v 9 እነርሱም ራሱን ቆረጡት፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈፉት፥ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር ሁሉ ለጣዖት መቅደሶቻቸውና ለሕዝቡ ወሬውን እንዲያደርሱ መልዕክተኞችን ላኩ።
\v 10 የጦር መሣሪያውን በአስታሮት መቅደስ ውስጥ አስቀመጡት፥ ሬሳውንም በቤትሳን ከተማ የግንብ አጥር ላይ አንጠለጠሉት።
\s5
\v 11 የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ፍልስጥኤማውያን በሳኦል ላይ ያደረጉትን በሰሙ ጊዜ
\v 12 ተዋጊ የሆኑ ሰዎች ሁሉ ተነሥተው ሌሊቱን ሁሉ ተጉዘው የሳኦልንና የልጆቹን ሬሳ ከአጥሩ ላይ ወሰዱ። ወደ ኢያቢስ ሄዱ፥ በዚያም አቃጠሏቸው።
\v 13 ከዚያም አጥንቶቻቸውን በመውሰድ በኢያቢስ ባለው የአጣጥ ዛፍ ሥር ቀበሯቸው፥ ሰባት ቀንም ጾሙ።

1364
10-2SA.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1364 @@
\id 2SA
\ide UTF-8
\h 2ኛ ሳሙኤል
\toc1 2ኛ ሳሙኤል
\toc2 2ኛ ሳሙኤል
\toc3 2sa
\mt 2ኛ ሳሙኤል
\s5
\c 1
\p
\v 1 ሳዖል ከሞተ በኋላ፣ ዳዊት በአማሌቃውያን ላይ ጥቃት ከማድረስ በመመለስ በጺቅላግ ሁለት ቀን ቆየ፡፡
\v 2 በሦስተኛው ቀን የተቀዳደደ ልብስ የለበሰ፣ በራሱም ላይ ትቢያ የነሰነሰ አንድ ሰው ከሳኦል ሰፈር መጣ፡፡ ወደ ዳዊት እንደ ደረሰም ወደ መሬት ለጥ ብሎ ሰገደለት፡፡
\s5
\v 3 ዳዊትም “ከወዴት መጣህ? ” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “ከእስራኤላውያን ሰፈር አምልጬ የመጣሁ ነኝ” ሲል መለሰ፡፡
\v 4 ዳዊትም፣ “እስቲ የሆነውን ሁሉ ንገረኝ” አለው፡፡ እርሱም “ሰዎቹ ከጦርነት ሸሽተዋል፤ ብዙዎቹ ወድቀዋል ደግሞም ሞተዋል፤ ሳዖልና ልጁ ዮናታንም ሞተዋል” አለ፡፡
\v 5 ዳዊትም ለወጣቱ፤ “ሳኦልና ልጁ ዮናታን መሞታቸውን እንዴት አወቅህ? ” ሲል ጠየቀው፡፡
\s5
\v 6 ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከታትለው ደረሱበት፤
\v 7 ወደ ኋላውም ዞር ሲል እኔን ስላየ ጠራኝ፤ እኔም ‘እነሆኝ አለሁ’ አልኩት፡፡
\s5
\v 8 እርሱም፣ ‘አንተ ማን ነህ? ሲል ጠየቀኝ፡፡ አኔም፣ ‘አማሌቃዊ ነኝ’ ብዬ መለስሁለት፡፡
\v 9 እርሱም አለኝ ‘እኔ በታላቅ ስቃይ ውስጥ እገኛለሁ፤ ነፍሴ ግን አልወጣችም፤ እባክህ በላዬ ቆመህ ግደለኝ’ አለኝ፡፡
\v 10 ስለሆነም፣ ከወደቀ በኋላ እንደማይተርፍ ስላወቅሁ፤ በላዩ ቆሜ ገደልሁት፤ በራሱ ላይ የነበረውን ዘውድና የክንዱን አንባር ወስጄ እነሆ፣ ለጌታዬ አምጥቻለሁ፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም ዳዊት ልብሱን ቀደደ፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሁሉ እንደዚሁ አደረጉ፡፡
\v 12 የወደቁት በሰይፍ ነበርና ለሳኦል ለልጁ ለዮናታንና ለእግዚአብሔር ሕዝብ አዘኑ፤ አለቀሱ፤ እስከ ማታም ድረስ ጾ፡፡
\v 13 ዳዊትም ወጣቱን ሰውዬ፣ “የየት አገር ሰው ነህ? ” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም፣ “በአገሪቱ ውስጥ በመጻተኛነት የሚኖር አማሌቃዊ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 14 ዳዊትም፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ንጉሥ በገዛ እጅህ ስትገድል ለምን አልፈራህም? ” ሲል ጠየቀው፡፡
\v 15 ዳዊትም ከጎልማሶቹ አንዱን ጠርቶ፣ “ግደለው” አለው፤ ጎልማሳው ሰው ሄዶ መታው፣ አማሌቃዊውም ሞተ፡፡
\v 16 ከዚያም ዳዊት ለሞተው አማሌቃዊ፣ “‘እግዚአብሔር የቀባውን ገድያለሁ’ ስትል አፍህ መስክሮብሃልና ደምህ በራስህ ላይ ነው” አለው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም ዳዊት ለሳዖልና ለልጁ ለዮናታን የሚከተለውን የሐዘን እንጉርጉሮ አንጎራጎረ፡፡
\v 18 እንዲሁም የቀስት እንጉርጉሮ የተባለውን ለይሁዳ ሕዝብ እንዲያስተምሩ አዘዘ፤ ይህም በያሸር መጽሐፍ ተጽፎአል፡፡
\v 19 “እስራኤል ሆይ፣ ክብርህ ሞቶአል፣ በተራሮችህ ላይ ተገድሎአል! ኃያላኑ እንዴት ወደቁ!
\v 20 የፍልስጥኤም ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፣ ያልተገረዙት ሴት ልጆች ፌሽታ እንዳያደርጉ ይህን በጌት አትናገሩ፣ በአስቆሎናም መንገዶች አታውጁት፡፡
\s5
\v 21 እናንት የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ ጠል አያረስርሳችሁ፣ ዝናብም አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች በዚያ አይኑሩ፤ በዚያ የኃያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፣ የሳዖል ጋሻ ከእንግዲህ በዘይት አይወለወልም፡፡
\v 22 ከሞቱት ሰዎች ደም፣ ከኃያላኑም ገላ የዮናታን ቀስት ተመልሶ አልመጣም፤ የሳዖልም ሰይፍ በከንቱ አልተመለሰም፡፡
\s5
\v 23 ሳዖልና ዮናታን በሕይወት እያሉ የሚዋደዱና ግርማ ያላቸው ነበሩ፤ ሲሞቱም አልተለያዩም፤ከንስርም ይልቅ ፈጣኖች ከአንበሳም ይልቅ ብርቱዎች ነበሩ፡፡
\v 24 እናንተ የእስራኤል ቆነጃጅት ሆይ፤ ሐምራዊ ቀሚስና ቀጭን ፈትል ላለበሳችሁ ፤ ልብሶቻችሁንም በወርቀ-ዘቦ ላስጌጠላችሁ ለሳዖል አልቅሱለት፡፡
\s5
\v 25 ኃያላን እንዴት እንዲህ በጦርነት መካከል ወደቁ! ዮናታን ከፍ ባሉ ስፍራዎቻችሁ ላይ ሞቶአል፡፡
\v 26 ወንድሜ ዮናታን ሆይ፤ እኔ ስለ አንተ አዘንሁ፤ አንተ ለእኔ እጅግ ውድ ነበርህ፤ ፍቅርህ ለእኔ ድንቅ ነበር፤ ከሴት ፍቅርም የላቀ ነበር፡፡
\v 27 ኃያላን እንዴት ወደቁ፤ የጦር መሣሪዎቹስ እንዴት ከንቱ ሆኑ!”
\s5
\c 2
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ዳዊት፤ “ከይሁዳ ከተሞች ወደ አንዲቱ ልውጣን? ” ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፣ እግዚአብሔርም፣ “ወደ ኬብሮን” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 2 ስለዚህ ዳዊት ከሁለቱ ሚስቶቹ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ ጋር ሄደ፡፡ ጠየቀ፡፡ እግዚአብሔርም፣ “ውጣ” ብሎ መለሰለት፡፡ ዳዊትም፣ “ወደ የትኛው ከተማ ልሂድ? ” ብሎ ጠየቀ፡፡
\v 3 ዳዊት ቤተ ሰቦቻቸውን ይዘው የመጡትን ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ኬብሮን ይዟቸው መጣ፡፡
\s5
\v 4 ከዚያ በኋላም የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጥተው ዳዊትን በይሁዳ ቤት ላይ ንጉሥ አድርገው ቀቡት፡፡ የኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ሳኦልን እንደቀበሩት ለዳዊት ነገሩት፡፡
\v 5 ስለዚህ ወደ ኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞች ልኮ እንደዚህ አላቸው፣ “ጌታችሁን ሳኦልን በመቅበር ይህንን በጎነት ስላሳያችሁ በእግዚአብሔር የተባረካችሁ ናችሁ፡፡
\s5
\v 6 አሁንም እግዚአብሔር ጽኑ ፍቅሩንና ታማኝነቱን ይገለጥላችሁ፤ እናንተ ይህን ስላደረጋችሁ እኔም እንደዚሁ በጎ ነገር አደርግላችኋለሁ፡፡
\v 7 እንግዲህ እጆቻችሁ ይጠንክሩ፣ በርቱ፤ ጌታችሁ ሳኦል ሞቶአልና፣ የይሁዳ ቤትም እኔን ቀብተው በላያቸው አንግሠውኛል፡፡”
\s5
\v 8 የሳኦል ሠራዊት አዛዥ፣ የኔር ልጅ አብኔር ግን የሳዖልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፤
\v 9 ኢያቡስቴንም በገለዓድ፣ በአሴር፣ በኢይዝራኤል፣ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ ላይ አነገሠው፡፡
\s5
\v 10 የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በእስራኤል ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው አርባ ዓመት ነበረ፣ ሁለት ዓመትም ገዛ፡፡ የይሁዳ ቤት ግን ዳዊትን ተከተለ፡፡
\v 11 ዳዊት በኬብሮን በይሁዳ ቤት ላይ ንጉሥ የሆነበት ዘመን ሰባት ዓመት ከስድስት ወር ነበር፡፡
\s5
\v 12 የኔር ልጅ አብኔርና የሳኦል ልጅ የኢያቡስቴ አገልጋዮች ከመሃናይም ተነሥተው ወደ ገባዖን ሄዱ፡፡
\v 13 እነርሱንም የጽሩይ ልጅ ኢዮአብና የዳዊት ሰዎች በገባዖን ኩሬ አጠገብ ተገናኟቸው፤ በዚያም አንዱ ወገን በኩሬው ወዲህ ማዶ፣ ሌላው ወገን ደግሞ በኩሬው ወዲያ ማዶ ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 14 አበኔርም ለኢዮአብ፣ “ጎልማሶች ይነሡና እርስ በርሳቸው ይጋጠሙ” አለው፡፡ ኢዮአብም፣ “እሺ፣ ይነሡ” አለ፡፡
\v 15 ከዚያ በኋላም ከብንያምና ከሳኦል ልጅ ከኢየቡስቴ ወገን አሥራ ሁለት፣ የዳዊት አገልጋዮች ከሆኑት ደግሞ አሥራ ሁለት ጎልማሶች ተነሥተው በአንድነት ተሰባሰቡ፡፡
\s5
\v 16 እያንደንዱም ሰው የባላጋራውን ራስ በመያዝ ሰይፉን በጎኑ እየሻጠበት ተያይዘው ወደቁ፡፡ ስለዚህ በገባዖን ያለው ያ ስፍራ በዕብራይስጥ ‘ሐልቃት አዙሪም’ ወይም ‘የሰይፍ ምድር’ ተባለ፡፡
\v 17 በዚያን ዕለት ጦርነቱ እጅግ ከባድ ነበር፣ አበኔርና የእስራኤል ሰዎች በዳዊት አገልጋዮች ድል ሆኑ፡፡
\s5
\v 18 ሦስቱ የጽሩይ ወንዶች ልጆች ኢዮአብ፣ አቢሳና አሣሄል እዚያው ነበሩ፡፡ አሣሄል እንደ ዱር ሚዳቋ በሩጫ ፈጣን ነበር፤
\v 19 አሣሄል በየትኛውም አቅጣጫ ዞር ሳይል አበኔርን በቅርበት ተከታተለው፡፡
\s5
\v 20 አበኔርም ወደ ኋላው ዞር ብሎ በመመልከት፣ “አሣሄል አንተ ነህን? ” አለው፡፡ እርሱም፣ “እኔ ነኝ” ሲል መለሰለት፡፡
\v 21 አበኔርም፣ “ወደ ቀኝህ ወይም ወደ ግራህ ዘወር በልና አንዱን ጎልማሳ ይዘህ መሣሪያውን ንጠቀው” አለው፤ አሣሄል ግን እርሱን መከታተሉን አልተወም ነበር።
\s5
\v 22 እንደገናም አቤኔር “እኔን መከታተል ብትተው ይሻልሃል፤ እኔስ ለምን ከመሬት ጋር ላጣብቅህ? ከዚያስ የወንድምህን የኢዮአብን ፊት ቀና ብዬ እንዴት አያለሁ? ” አለው።
\v 23 አሣሄል ግን ዘወር ለማለት እምቢ አለ፤ ስለዚህ አብኔር በጦሩ ጫፍ አከላቱን ወጋው፤ ጦሩም በአካሉ በሌላው ወገን ዘልቆ ወጣ፤ አሣሄልም ወደቀ፣ በዚያ ስፍራም ሞተ፡፡ ስለሆነም አሣሄል ወደ ወደቀበት ይመጣ የነበረ እያንዳንዱ ሰው በዚያ ስፍራ ሲደርስ ይቆም ነበር፡፡
\s5
\v 24 ኢዮአብና አቢሳ ግን አበኔርን አሳደዱት፤ ፀሐይም በምትጠልቅበት ጊዜ ወደ ገባዖን ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ከጋይ አጠገብ ወዳለው ወደ አማ ኮረብታ ደረሱ፡፡
\v 25 የብንያም ሰዎችም ከአበኔር በስተኋላ ተሰብስበው በተራራው ጫፍ ላይ ቆሙ፡፡
\s5
\v 26 ከዚያ በኋላም አበኔር ኢዮአብን ጠርቶ፣ “ሰይፍ ለዘላለም ማጥፋት አለበትን? ውጤቱ በመጨረሻ መራራ መሆኑን አንተ አታውቅምን? ሰዎችህ ወንድሞቻቸውን ማሳደድ እንዲያቆሙ የማትነግራቸውስ እስከ መቼ ድረስ ነው? ” አለው፡፡
\v 27 ኢዮአብም ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን፣ ይህን ባትናገር ኖሮ፣ ወታደሮቼ እስኪነጋ ድረስ ወንድሞቻቸውን ባሳደዱ ነበር” ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 28 ስለዚህ ኢዮአብ ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ ሰዎቹም ሁሉ ቆሙ፤ ከዚያ በኋላም እስራኤልን አላሳደዱም፣ መዋጋታቸውንም አልቀጠሉም፡፡
\v 29 አበኔርና ሰዎቹም ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ በኩል አለፉ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረው በማግሥቱ ጥዋት ሲጓዙ ቆይተው ከዚያ በኋላ ወደ መሃናይም ደረሱ፡፡
\s5
\v 30 ኢዮአብም አበኔር ከማሳደድ ተመለሰ፡፡ አሣሄልና ከዳዊት ወታደሮች አሥራ ዘጠኙ የጎደሉባቸውን ሰዎቹን ሁሉ ሰበሰበ፡፡
\v 31 የዳዊት ሰዎች ግን ከአበኔር ጋር ከነበሩት ሦስት መቶ ሥልሳ ብንያማውያንን ገድለዋል፡፡
\v 32 ከዚያ በኋላም አሣሄልን ከወደቀበት አንሥተው ቤተ ልሔም በነበረው በአባቱ መቃብር ቀበሩት፡፡ ኢዮአብና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ ገሥግሠው ኬብሮን ሲደርሱ ሌሊቱ ነጋላቸው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 በሳዖል ቤትና በዳዊት ቤት መካከል ለረጅም ጊዜ የቆየ ጦርነት ነበረ፡፡ ዳዊት እየበረታ ሲሄድ የሳዖል ቤት ግን እየደከመ ሄደ፡፡
\s5
\v 2 በኬብሮን ለዳዊት ወንዶች ልጆች ተወለዱለት፡፡ የበኩር ልጁ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆም የተወለደው አምኖን ነበር፡፡
\v 3 ሁለተኛው፣ የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቢግያ የተወለደው ኪልአብ ነበር፡፡ ሦስተኛ የነበረው፣ አቤሴሎም የጌሹር ንጉሥ ከነበረው ከተልማይ ልጅ ከመዓካ የተወለደው ነበር፡፡
\s5
\v 4 አራተኛው፣ ልጁ ከአጊት የተወለደው አዶንያስ፣ አምስተኛው፣ ከአቢጣል የተወለደው ሰፋጥያ፣
\v 5 ስድስተኛው፣ ከዳዊት ሚስት ከዔግላ የተወለደው ይትርኃም ነበር፤ እነዚህ ወንዶች ልጆች ለዳዊት በኬብሮን የተወለዱለት ነበሩ፡፡
\s5
\v 6 የሳኦል ቤትና የዳዊት ቤት በጦርነት ላይ በነበሩበት ጊዜ አበኔር በሳዖል ቤት ራሱን ጠንካራ አድርጎ ነበር፡፡
\v 7 ሳኦል የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ የተባለች ቁባት ነበረችው፤ ኢያቡስቴም አበኔርን፣ “ለምንድን ነው ከአባቴ ቁባት ጋር የተኛኸው? ” አለው፡፡
\s5
\v 8 አብኔርም በዚያን ጊዜ በኢያቡስቴ ንግግር እጅግ ስለተቆጣ እንዲህ አለ፣ “እኔ ለይሁዳ የተሰጠሁ የውሻ ራስ ነኝን? አንተን ለዳዊት አሳልፌ ባለመስጠቴ እኔ ዛሬ ለአባትህ ለሳኦል ቤት ለወንድሞቹና ለወዳጆቹ ታማኝነቴን አሳይቻለሁ፤ ይህም ሆኖ ሳለ አንተ ከዚህች ሴት ጋር በፈጸምሁት ነገር ትከሰኛለህን?
\s5
\v 9 እግዚአብሔር ለዳዊት መንግሥትን ከሳዖል ቤት አውጥቶ
\v 10 ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ባለው በእስራኤልና በይሁዳ ዙፋኑን እንደሚያጸና በመሐላ የገባለት ተስፋ እንዲፈጸም ባለደርግ እግዚአብሔር በእኔ በአበኔር ላይ ክፉ ያድርግብኝ ከዚያ የባሰም ያምጣብኝ፡፡”
\v 11 ኢያቡስቴም አበኔርን ፈርቶት ስለነበረ አንዲት ቃል ስንኳ ሊመልስለት አልቻለም፡፡
\s5
\v 12 ከዚያም አበኔር ለዳዊት፣ “ይህች ምድር የማን ናት? ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አድርግ፣ እነሆ፣ እስራኤል ሁሉ ወደ አንተ እንዲመለሱ ለማድረግ እጄ ከአንተ ጋር እንደሆነ ትመለከታለህ” ብለው እንዲነግሩለት መልእክተኞችን ላከ፡፡
\v 13 ዳዊትም፣ “መልካም ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ነገር ግን ከአንተ የምሻው አንድ ነገር፤ ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜ የሳዖልን ሴት ልጅ ሜልኮልን ይዘህልኝ ካልመጣህ ፊቴን ማየት እንደማትችል እንድታውቅ ነው፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 14 ከዚያም ዳዊት፣ “የመቶ ፍልስጥኤማውያን ሸለፈት ማጫ የከፈልሁባትን ሚስቴን ሜልኮልን ስጠኝ” ብሎ ወደ ሳኦል ልጅ ወደ ኢያቡስቴ መልእክተኞች ላከበት፡፡
\v 15 ስለዚህም ኢያቡስቴ መልእክተኛ ልኮ፣ ሜልኮልን ከባሏ ከሌሳ ልጅ ከፍልጢኤል ወሰዳት፡፡
\v 16 ባሏም እስከ ብራቂም ከተማ ድረስ እያለቀሰ ተከትሎአት ሄደ፤ ከዚያም አበኔር፣ “አሁን፣ ወደ ቤትህ ተመለስ” አለው፡፡ ስለዚህም ተመለሰ፡፡
\s5
\v 17 አበኔር ከእስራኤል ሽማግሌዎች ጋር እንደዚህ በማለት ተመካከረ፤ “ባለፈው ጊዜ ዳዊትን በላያችሁ ለማንገሥ ሞክራችሁ ነበር፤
\v 18 እግዚአብሔር ለዳዊት፣ ‘በባሪያዬ በዳዊት ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅና ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ እታደጋቸዋለሁ’ ብሎ ስለተናገረው፣ ይህን አሁኑኑ አድርጉት፡፡”
\s5
\v 19 አበኔርም ራሱ ሄዶ ለብንያማውያን ይህንን ነገራቸው፤ ከዚያም በኋላ አበኔር እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለገውን ሁሉ በመግለጽ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ፡፡
\v 20 ከሃያ ሰዎች ጋር አበኔር በዳዊት ፊት ለመቅረብ ወደ ኬብሮን በመጡ ጊዜ ዳዊት ግብዣ አደረገላቸው፡፡
\s5
\v 21 አበኔርም ለዳዊት፣ “ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን እንዲያደርጉና በፈለግኸውም ሁሉ ላይ እንድትገዛ ተነሥቼ እስራኤልን ሁሉ ወደ አንተ እሰበስባለሁ” በማለት ገለጸለት፡፡ ዳዊትም አሰናበተው፤ አበኔርም በሰላም ሄደ፡፡
\s5
\v 22 ከዚያ በኋላ የዳዊትና የኢዮአብ ወታደሮች ከዘመቻ ሲመለሱ ብዙ ምርኮ ይዘው መጡ፡፡ ዳዊት አሰናብቶት ስለነበረና እርሱም በሰላም ስለሄደ አበኔር በኬብሮን ከዳዊት ጋር አልነበረም፡፡
\v 23 ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ሁሉ እዚያ እንደ ደረሱ፣ “የኔር ልጅ አበኔር ወደ ንጉሡ መጣ ንጉሡም አሰናበተው እርሱም በሰላም ሄደ” ብለው ለኢዮአብ ነገሩት፡፡
\s5
\v 24 ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ገብቶ እንዲህ አለ፣ “ምን ማድረግህ ነው? እነሆ አበኔር መጥቶልህ ለምን ይሄድ ዘንድ አሰናበትኸው?
\v 25 የኔር ልጅ አበኔር የመጣው አንተን ሊያታልልህ፣ ዕቅድህን ለማወቅና የምታደርገውን ማንኛውንም ነገር ለማጥናት እንደሆነ አታውቅምን? ”
\v 26 ኢዮአብ ከዳዊት ዘንድ በወጣ ጊዜ አበኔር ዘንድ መልእክተኞችን ላከ እነርሱም ከሴይር የውሃ ጉድጓድ አጠገብ መለሱት፡፡ ዳዊት ግን ይህን አላወቀም ነበር፡፡
\s5
\v 27 አበኔር ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በቆይታ ለማነጋገር ወደ ቅጥሩ ዞር አደረገው በዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ በዚህም ዓይነት መንገድ የወንድሙን የአሣሄልን ደም ተበቀለ፡፡
\s5
\v 28 ዳዊት ይህንን በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ፣ “እኔም ሆንሁ መንግሥቴ ከኔር ልጅ ከአብኔር ደም በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ንጹሕ ነን፤
\v 29 ደሙ በኢዮአብ ራስና በአባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይሁን፤ ፈሳሽ ነገር የሚወጣው ወይም አሠቃቂ የቆዳ በሽታ ያለበት፣ በምርኩዝ የሚሄድ አንካሳ፣ ወይም በሰይፍ የሚገደል ወይም ምግብ አጥቶ የሚራብ ሰው ከኢዮአብ ቤት አይታጣ፡፡”
\v 30 ስለዚህ ወንድማቸውን አሣሄልን በገባዖን በተደረገው ጦርነት ገድሎባቸው ነበርና፣ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ አበኔርን ገደሉት፡፡
\s5
\v 31 ዳዊት ለኢዮአብና አብሮት ለነበረው ሕዝብ ሁሉ፣ “ልብሳችሁን ቀዳችሁ፣ ማቅ ለብሳችሁ በአበኔር አስከሬን ፊት አልቅሱ” አላቸው፤ ንጉሥ ዳዊትም አስከሬኑን ከሚያጅበው ሕዝብ ጋር አብሮ ይሄድ ነበር፡፡
\v 32 አበኔርንም በኬብሮን ቀበሩት፤ ንጉሡም በአበኔር መቃብር ላይ ጮኾ አለቀሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ እንደዚሁ አለቀሱ፡፡
\s5
\v 33 ንጉሡም በሐዘን እንጉርጉሮ ለአበኔር አለቀሰ፣ “አበኔር እንደ ተራ ሰው ሊሞት ይገባው ነበር?
\v 34 እጆችህ አልታሰሩም፤ እግሮችህ በእግር ብረት አልገቡም፤ ሰዎች በግፈኞች ፊት እንደሚወድቁ አንተም እንደዚሀ ወደቅህ፡፡” ሕዝቡም ሁሉ እንደገና አለቀሱለት፡፡
\s5
\v 35 ገና ቀን ሳለ ምግብ እንዲበላ ለማድረግ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ዳዊት መጡ፤ ዳዊት ግን፣ “ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት እንጀራ ወይም ማንኛውንም ነገር ብቀምስ እግዚአብሔር ክፉ ያድርግብኝ ከዚያም የባሰ ያምጣብኝ” ብሎ ማለ፡፡
\v 36 ሕዝቡም ሁሉ የዳዊትን ሐዘን ተመለከቱ፤ ንጉሡ የሚያደርገው ሁሉ በእርግጥ ደስ ያሰኛቸው ስለነበረ፣ በዚህም ደስ አላቸው፡፡
\s5
\v 37 ስለዚህ የኔር ልጅ አበኔር ይገደል ዘንድ የንጉሡ ፍላጎት እንዳልነበረ ሕዝቡ ሁሉና እስራኤል በሙሉ በዚያን ዕለት ዐወቁ፡፡
\v 38 ንጉሡ ለአገልጋዮቹ እንደዚህ አላቸው፣ “በዛሬይቱ ዕለት በእስራኤል መስፍንና ታላቅ ሰው መውደቁን አላወቃችሁምን?
\v 39 ምንም እንኳን የተቀባሁ ንጉሥ ብሆንም እኔ ደካማ ነኝ፤ እነዚህ የጽሩይ ልጆች እጅግ ጨካኞች ሆነውብኛል፡፡ እንደ ክፋቱ በመቅጣት እግዚአብሔር ለክፉ አድራጊው እንደ እጁ ሥራ መጠን ይክፈለው፡፡”
\s5
\c 4
\p
\v 1 አበኔር በኬብሮን መሞቱን የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ በሰማ ጊዜ እጆቹ ዛሉ፣ መላው እስራኤልም ተጨነቀ፡፡
\v 2 በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ የወታደር ጭፍራ መሪዎች የነበሩ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ የአንደኛው ስም በዓና ሲሆን የሌላኛው ስም ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር፡፡ እነርሱም ከብንያም ነገድ የብኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች ነበሩ (ብኤሮት ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ትቆጠር ነበር፤
\v 3 የብኤሮት ሕዝብ ወደ ጌቴም በመሸሽ እስከ ዛሬ በዚያ ይኖራሉ) ፡፡
\s5
\v 4 የሳኦል ልጅ ዮናታን ሁለት እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ ልጅ ነበረው፡፡ እርሱም የሳዖልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ሞግዚቱ ይዛው ለመሸሽ አነሣችው፣ ነገር ግን ይዛው በምትሮጥበት ጊዜ የዮናታን ልጅ ወደቀና ሽባ ሆነ፡፡ ስሙም ሜምፊቦስቴ ይባል ነበር፡፡
\s5
\v 5 በዚህ ጊዜ የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ሞቃት በነበረበት በቀትሩ ሰዓት እርሱ ዕረፍት እያደረገ ሳለ ወደ ኢያቡስቴ ቤት ሄዱ፡፡
\v 6 ትጠብቅ የነበረችው ሴት ስንዴ በምታበጥርበት ጊዜ እንቅልፍ ወስዷት ነበርና ሬካብና በዓና በቀስታ አልፈዋት ገቡ፡፡
\v 7 ስለዚህ ወደ ቤት ከገቡ በኋላ በክፍሉ ተኝቶ ሳለ አጠቁት ገደሉትም፡፡ ከዚያ በኋላ ራሱን ቆርጠው በመውሰድ ሌሊቱን ሁሉ በዓረባ መንገድ ተጓዙ፡፡
\s5
\v 8 የኢያቤስቴንም ራስ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት ዘንድ አምጥተው፣ “አንተን ሊገድል ይፈልግ የነበረው የጠላትህ የሳዖል ልጅ የኢያቡስቴ ራስ ይኸውልህ፤ እነሆ እግዚአብሔር በዛሬው ቀን ስለ ጌታዬ ስለ ንጉሡ ሳዖልንና ዘሩን ተበቅሎአል፡፡” አሉት፡፡
\v 9 ዳዊትም ለብኤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና ምላሽ በመስጠት እንዲህ አላቸው፣ “ከመከራ ሁሉ ያዳነኝ ሕያው እግዚአብሔርን፣
\v 10 የምሥራች ያመጣልኝ መስሎት ‘እነሆ ሳኦል ሞተ’ ብሎ የነገረኝን ሰው ይዤ ጺቅላግ ላይ ገደልሁት፤ እንግዲህ ወሬውን ላመጣው ለዚያ ሰው የሸለምሁት ይህንን ነበር፡፡
\s5
\v 11 ታዲያ በገዛ ዐልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው ክፉ ሰዎች የገደሉት ከሆነ እንዴት ይልቅ ደሙን ከእጃችሁ አልፈልግ፣ ከዚህ ምድርስ አልደመስሳችሁ? ”
\v 12 ስለዚህም ዳዊት ጎልማሶቹን አዘዘ፤ እነርሱም ገደሏቸው፤ እጅና እግራቸውንም ቆርጠው በኬብሮን ካለው ኩሬ አጠገብ ሰቀሏቸው፡፡ ነገር ግን የኢያቡስቴን ራስ ወስደው ኬብሮን በሚገኘው በአብኔር መቃብር ውስጥ ቀበሩት፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፣ “እነሆ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤
\v 2 ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረበት ባለፈው ጊዜ የእስራኤልን ሠራዊት የምትመራ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፣ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፣ በእስራኤልም ላይ ገዥ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር፡፡”
\s5
\v 3 ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፡፡
\v 4 ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረr፤ አርባ ዓመትም ገዛ፡፡
\v 5 በኬብሮን በይሁዳ ላይ ለሰባት ዓመት ከስድስት ወር፣ ኢየሩሳሌም ሆኖም በመላው እስራኤልና በይሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፡፡
\s5
\v 6 ንጉሡና ሰዎቹ የምድሪቱ ነዋሪዎች በሆኑት በኢያቡሳውያን ላይ ለመዝመት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡ እነርሱም ለዳዊት፣ “በዕውሮችና በአንካሶች ልትመለስ ካልሆነ በስተቀር አንተ ወደዚህ አትገባም፤ ዳዊት እዚህ መምጣት አይችልም” አሉት፡፡
\v 7 ይሁን እንጂ ዳዊት የጽዮንን አምባ ያዘ፤ ይህችም አሁን የዳዊት ከተማ የሆነችው ነች፡፡
\s5
\v 8 በዚያን ጊዜ ዳዊት እንደዚህ አለ፣ “ኢያቡሳውያንን የሚያጠቃ በውሃ መተላለፊያው ሽቅብ መውጣት አለበት፤ በዚያም ዳዊትን የሚጠሉትን ዕውሮችንና አንካሶችን ያገኛል፡፡” እንግዲህ ሰዎች፣ “አንካሶችና ዕውሮች ወደ ቤተ መንግሥት መግባት አይችሉም” ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው፡፡
\v 9 በመሆኑም ዳዊት በአምባይቱ ኖረ፤ የዳዊት ከተማም ብሎ ጠራት፡፡ ከሸንተረሩ አንሥቶ ወደ ውስጥ ዙሪያዋን ምሽግ ገነባባት፡፡
\v 10 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበረ፣ ዳዊት እጅግ እየበረታ ሄደ፡፡
\s5
\v 11 በዚህ ጊዜ የጢሮስ ንጉሥ ኪራም መልእክተኞችን፣ የዝግባ እንጨት፣ አናጢዎችንና ድንጋይ ጠራቢዎችን ወደ ዳዊት ላከ፤ እነርሱም ለዳዊት ቤት ሠሩለት፡፡
\v 12 እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገለት ዳዊት አወቀ፡፡
\s5
\v 13 ኬብሮንን ትቶ ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ቁባቶችን አስቀመጠ ሚስቶችንም አገባ፤ ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፡፡
\v 14 በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች ስም፣ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፣
\v 15 ኢያቤሔር፣ ኤሊሱዔ፣ ናፌቅ፣ ናፍያ፣
\v 16 ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባሉ ነበር፡፡
\s5
\v 17 ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ለመፈለግ በሙሉ ኃይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ግን ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ፡፡
\v 18 በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 19 ዳዊትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ ሲል ዕርዳታ ጠየቀ፣ “ፍልስጥኤማውያንን ወጥቼ ልውጋቸውን? በእነርሱስ ላይ ድል ትሰጠኛለህ? ” እግዚአብሔርም ለዳዊት፣ “በፍልስጥኤማውያን ላይ በእርግጥ ድል እሰጥሃለሁና ውጋቸው” አለው፡፡
\v 20 ስለዚህ ዳዊት በበአልፐራሲም ወጋቸው በዚያም ድል አደረጋቸው፡፡ እርሱም፣ “የጎርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” በማለት ስሜቱን ገለጸ፡፡ ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም በአልፐራሲም ተባለ፡፡
\v 21 ፍልስጥኤማውያን ጣዖቶቻቸውን እዚያ ትተው ስለነበር ዳዊትንና ሰዎቹን ወሰዷቸው፡፡
\s5
\v 22 ፍልስጥኤማውያን እንደ ገና መጥተው በራፋይም ሸለቆ በድጋሚ ተበታትነው ሰፈሩ፡፡
\v 23 ስለዚህ ዳዊት እንደገና ከእግዚአብሔር ዕርዳታ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “በፊት ለፊት በኩል አትውጋቸው፤ ይልቁኑ በስተኋላቸው በኩል በመክበብ በበለሳኑ ዛፎች ፊት ለፊት ግጠማቸው፡፡
\s5
\v 24 በበለሳኑ ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ጉዞ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመምታት እግዚአብሔር ቀድሞ ወጥቶአልና በዚያን ጊዜ በኃይል አጥቃ” አለው፡፡
\v 25 ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ፍልስጥኤማውያንን ከገባዖን እስከ ጌዘር ድረስ ገደላቸው፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ዳዊት እንደ ገና ከእስራኤል የተመረጡትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች ሰበሰበ፡፡
\v 2 ዳዊትና አብረውት ያሉት ሰዎች ሁሉ በኪሩቤል ላይ በዙፋኑ በተቀመጠው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም የተጠራውን የእግዚአብሔርን ታቦት ለማምጣት በይሁዳ ወዳለው ወደ በአል ሄዱ፡፡
\s5
\v 3 የእግዚአብሔርን ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ አኑረው በኮረብታ ላይ ካለው ከአሚናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፡፡ ልጆቹ ዖዛና አሒዩ አዲሱን ሠረገላ ይመሩ ነበር፡፡
\v 4 የእግዚአብሔርን ታቦት በላዩ ላይ አኑረው ሠረገላውን በኮረብታ ላይ ካለው ከአሚናዳብ ቤት አውጥተው አመጡ፤ አሒዩ ከታቦቱ ፊት ለፊት ይሄድ ነበር፡፡
\v 5 ዳዊትና የእስራኤል ቤት በሙሉ በጥድ እንጨት በተሠሩ የሙዚቃ መሣሪያዎች ማለትም በበገና፣ በመሰንቆ፣ በከበሮ፣ በጸናጽልና በቃጭል መጫወትና ደስታቸውን መግለጽ ጀመሩ፡፡
\s5
\v 6 ወደ ናኮን ዐውድማ ሲደርሱም በሬዎቹ ስለተደናቀፉ፤ ዖዛ የእግዚአብሔርን ታቦት ለመያዝ እጁን ዘረጋ በእጁም ያዘው፡፡
\v 7 ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፤ በዚያም ስፈራ እግዚአብሔር ስለ ኃጢአቱ መታው፡፡ ዖዛም በዚያ በእግዚአብሔር ታቦት አጠገብ ሞተ፡፡
\s5
\v 8 እግዚአብሔር ዖዛን ስለመታው ዳዊት ተቆጣ፤ የዚያን ቦታም ስም ፔሬዝ ዖዛ ብሎ ጠራው፡፡ ያም ቦታ እስከ ዛሬ ድረስ ፔሬዝ ዖዛ ተብሎ ይጠራል፡፡
\v 9 ዳዊት በዚያን ቀን እግዚአብሔርን ስለ ፈራ፣ “የእግዚአብሔር ታቦት ወደ እኔ እንዴት ሊመጣ ይችላል? ” ብሎ ጠየቀ፡፡
\s5
\v 10 ስለዚህ ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ከእርሱ ጋር ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈቀደም፤ በዚህ ፋንታ አቅጣጫ ለውጦ የጌት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ወሰደው፡፡
\v 11 የእግዚአብሔርም ታቦት የጌት ሰው በሆነው በአቢዳራ ቤት ሦስት ወር ተቀመጠ፤ እርሱንና ቤተሰቡንም ሁሉ እግዚአብሔር ባረካቸው፡፡
\s5
\v 12 በዚህ ጊዜ፣ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የአቢዳራን ቤተሰብና ያለውን ሁሉ እግዚአብሔር ባረከለት” ብለው ለዳዊት ነገሩት፡፡ ስለዚህ ዳዊት ወደዚያ ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከኦቤድ ኤዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በደስታ አመጣው፡፡
\v 13 የእግዚአብሔርን ታቦት ተሸክመው የነበሩት ሰዎች ስድስት እርምጃ በሄዱ ቁጥር አንድ በሬና አንድ የሰባ ጥጃ ይሠዋ ነበር፡፡
\s5
\v 14 ዳዊትም የበፍታ ኤፉድ ብቻ በወገቡ ታጥቆ በሙሉ ኃይሉ በእግዚአብሔር ፊት ይጨፍር ነበር፡፡
\v 15 ስለዚህ ዳዊትና መላው የእስራኤል ቤት እልል እያሉና ቀንደ መለከት እየነፉ የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘውት መጡ፡፡
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ እየገባ ሳለ የሳዖል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሥ ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልና ሲጨፍር አየችው፤ ከዚያ በኋላም በልቧ ናቀችው፡፡
\v 17 ከዚያም የእግዚአብሔርን ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን በተዘጋጀለት በማዕከላዊ ስፍራ አኖሩት፡፡ ከዚያ በኋላም ዳዊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት አቀረበ፡፡
\s5
\v 18 ዳዊት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት ማቅረብ በፈጸመ ጊዜ ሕዝቡን በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ስም ባረከ፡፡
\v 19 ከዚያ በኋላ ለመላው እስራኤል፣ ለሕዝቡ ሁሉ ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ ሰው አንዳንድ እንጀራ፣ አንዳንድ ሙዳ ሥጋና አንዳንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ፡፡ ከዚያ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ ወደየቤቱ ሄደ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያ በኋላ ቤተሰቡን ለመባረክ ተመለሰ፡፡ የሳዖል ልጅ ሜልኮልም ዳዊትን ልትቀበለው መጣችና እንደዚህ አለች፣ “ራሳቸውን ከሚያራቁቱ ባለጌዎች እንደ አንዱ ዛሬ የእስራኤል ንጉሥ በአገልጋዮቹ መካከል በነበሩት ገረዶች ፊት ራሱን በማራቆቱ ምን ያህል የተከበረ ነበር!”
\s5
\v 21 ዳዊትም ለሜልኮል እንዲህ ሲል መለሰላት፣ “እኔን ከአባትሽና ከቤተሰቡ ሁሉ በላይ በመረጠኝና በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ መሪ አድርጎ በሾመኝ በእግዚአብሔር ፊት ያንን አድርጌአለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ፊት ሐሴት አደርጋለሁ!
\v 22 እንዲያውም ከዚህም የበለጠ ራሴን ዝቅ አደርጋለሁ፣ ከዚህም የባሰ የተናቅሁ እሆናለሁ፤ ነገር ግን በጠቀስሻቸው ገረዶች ፊት እከብራለሁ፡፡”
\v 23 ስለዚህም የሳኦል ልጅ ሜልኮል እስከምትሞተችበት ጊዜ ድረስ ልጅ አልወለደችም ነበር፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ንጉሡ በቤቱ ተደላድሎ ከተቀመጠና እግዚአብሔርም በዙሪያው ካሉት ጠላቶቹ ሁሉ ካሳረፈው በኋላ፣
\v 2 ለነቢዩ ለናታን ንጉሡ እንደዚህ አለው፣ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው፡፡
\s5
\v 3 ከዚያ በኋላ ናታን ለንጉሡ፣ “እግዚአብሔር ካንተ ጋር ስለሆነ ያሰብኸውን ሁሉ አድርግ” አለው፡፡
\v 4 ነገር ግን በዚያች ሌሊት እንደዚህ የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ናታን መጣ፣
\v 5 “ሂድና ለባሪያዬ ለዳዊት እንደዚህ በለው፣ ‘እግዚአብሔር የሚልህ እንደዚህ ነው፣ የምኖርበትን ቤት አንተ ትሠራልኛለህን?
\s5
\v 6 የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ካወጣሁበት ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳን ማደሪያ ውስጥ ሆኜ እንቀሳቀስ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ ኖሬ አላውቅምና፤
\v 7 በመላው የእስራኤል ሕዝብ መካከል በተመላለስሁባቸው በሁሉም ስፈራዎች ሕዝቤን እስራኤልን እንዲጠብቁ ከሾምኋቸው መሪዎች ለአንዱ ስንኳ፣ ‘ከዝግባ እንጨት ለምን ቤት አልሠራህልኝም? ብያለሁን?
\s5
\v 8 እንግዲህ አሁን ለባሪያዬ ለዳዊት እንደዚህ በለው፣ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፣ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ገዥ ትሆን ዘንድ ከመስክ በጎችን ትከተል ከነበርህበት ስፍራ ወሰድሁህ፤
\v 9 በሄድህበት ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርሁ፤ ጠላቶችህንም ሁሉ ከፊትህ አጠፋሁልህ’፤ በምድር ላይ ስማቸው ታላቅ እንደሆነው እንደ አንዱ ለአንተ ታላቅ ስም አደርግልሃለሁ፡፡
\s5
\v 10 ከእንግዲህ ወዲያ በራሳቸው መኖሪያ እንዲኖሩ እንጂ እንዳይናወጡ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጣቸዋለሁ፣ በዚያም እተክላቸዋለሁ፡፡ ከዚህ በፊት እንደሆነውም ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ሕዝብ አይጨቁናቸውም፤
\v 11 መሳፍንትን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ባዘዝሁበት ጊዜ እንዳደረጉባቸው ከእንግዲህ ወዲህ አያደርጉባቸውም፤ ከጠላቶችህም ሁሉ አሳርፍሃለሁ፡፡ ከዚህም ባሻገር፣ እኔ እግዚአብሔር ቤት እንደምሠራልህ እነግርሃለሁ፡፡
\s5
\v 12 ዕድሜህ በሚጠናቀቅበት ጊዜና ከአባቶችህ ጋር በምታርፍበት ጊዜ ከአብራክህ የሚወጣ ዝርያ አስነሳልሃለሁ፣ መንግሥቱንም አጸናለሁ፡፡
\v 13 እርሱ ለእኔ ቤት ይሠራልኛል፤ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ፡፡
\v 14 እኔ አባት እሆነዋለሁ፣ እርሱም ልጄ ይሆናል፡፡ ኃጢአት በሚያደርግበት ጊዜ በሰዎች በትር እቀጣዋለሁ፣ የሰው ልጆች በሚገረፉበትም ግርፋት እገርፈዋለሁ፤
\s5
\v 15 ከፊትህ ካስወገድሁት ከሳኦል ላይ እንደወሰድሁ ኪዳናዊ ታማኝነቴ ከእርሱ አይርቅም፡፡
\v 16 ቤትህና መንግሥትህ በፊትህ ለዘላለም የጸና ይሆናል፤ ዙፋንህም ለዘላለም የጸና ይሆናል፡፡”
\v 17 ናታን ለዳዊት እንደዚህ ተናገረ፣ ይህንንም ሁሉ ነገር ነገረው፤ ጠቅላላውንም ራእይ ገለጸለት፡፡
\s5
\v 18 ከዚያም ንጉሥ ዳዊት ገባና በእግዚአብሔር ፊት ተቀመጠና እንደዚህ አለ፣ “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፣ እኔ ማን ነኝ? እስከዚህ ደረጃስ ታደርሰኝ ዘንድ ቤተሰቤስ ምንድን ነው?
\v 19 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህ በፊትህ ታናሽ ነገር ነው፡፡ ስለ ባሪያህ ቤተሰብ እንኳን ለረጅም ጊዜ የሚሆነውን ተናገርህ፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ከዚህ በኋላ የሚኖረውንም ትውልዴን አሳየኸኝ!
\v 20 እኔ ዳዊት ከዚህ በላይ ለአንተ ምን እላለሁ? ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ባሪያህን አክብረኸዋል፡፡
\s5
\v 21 ስለ ቃልህ ብለህ፣ ዓላማህንም ትፈጽም ዘንድ ይህን ታላቅ ነገር አድርገሃል፤ ለባሪያህም ገልጸህለታል፡፡
\v 22 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ታላቅ ነህና እንደ አንተ ያለም የለም፤ በገዛ ጆሮቻችንም እንደ ሰማን ከአንተም በቀር አምላክ የለም፡፡
\v 23 አንተ እግዚአብሔር መጥተህ ለራስህ እንዳዳንከው በምድር ላይ እንዳለው እንደ ሕዝብህ ያለ በምድር ላይ ምን ሕዝብ አለ? ይህንን ያደረግኸው ለራስህ ሕዝብን ታስነሳ ዘንድ፣ ለራስህም ስምህን ታስጠራ ዘንድና ታላቅና አስፈሪ ነገር በምድርህ ታደርግ ዘንድ ነው፡፡ ከግብፅ ከዋጀኸው ከሕዝብህ ፊት አሕዛብንና ጣዖቶቻቸውን አባረርህ፡፡
\s5
\v 24 እስራኤልን ሕዝብህ አድርገህ ለዘላለም አጸናህ፣ አንተም፣ እግዚአብሔር ሆይ አምላክ ሆንህላቸው፡፡
\v 25 አሁንም ባሪያህንና ቤተሰቡን በሚመለከት የሰጠኸውን ተስፋ ለዘላለም አጽናለት፤ እንደተናገርኸውም አድርግለት፡፡
\v 26 የእኔ፣ የባሪያህ የዳዊት ቤት በፊትህ በሚጸናበት ጊዜ ሕዝቦች፣ ‘የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የእስራኤል አምላክ ነው’ ይሉ ዘንድ ስምህ ለዘላለም ታላቅ ይሁን፡፡
\s5
\v 27 አንተ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል አምላክ ለባሪያህ ቤት እንደምትሠራለት ገልጸህለታልና፤ ለዚህ ነው እኔ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት ያገኘሁት፡፡
\v 28 አሁን፣ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ አምላክ ነህ፣ ቃሎችህም የታመኑ ናቸው፤ ይህንን መልካም የተስፋ ቃል ለባሪያህ ገብተህለታል፡፡
\v 29 በፊትህ ለዘላለም የሚቀጥል ይሆን ዘንድ፣ እንግዲህ አሁን የባሪያህን ቤት መባረክ አንተን ደስ ያሰኝህ፡፡ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፣ እነዚህን ነገሮች ተናግረሃልና በበረከትህ የባሪያህ ቤት ለዘላለም የተባረከ ይሆናል፡፡”
\s5
\c 8
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ዳዊት ፍልስጥኤማውያንን ወጋቸው ድልም አደረጋቸው፡፡ ስለዚህ ዳዊት ጋትና መንደሮችዋን ከፍልስጥኤማውያን ቁጥጥር ነጻ አወጣት፡፡
\s5
\v 2 ከዚያ በኋላም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፣ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር፡፡ ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፣ ግብርም ገበሩለት፡፡
\s5
\v 3 ከዚህ በኋላ ደዊት በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ ያለውን ግዛቱን ለማስመለስ ይጓዝ በነበረበት ጊዜ የሱባን ንጉሥ የረአብን ልጅ አድርአዛርን ድል አደረገው፡፡
\v 4 ዳዊትም ከእርሱ ላይ 1700 ሠረገሎችና 20, 000 እግረኞች ማረከ፡፡ ለመቶ ሠረገሎች የሚሆኑትን አስቀርቶ ዳዊት የሠረገሎቹን ፈረሶች ሁሉ ቋንጃዎች ቆረጠ፡፡
\s5
\v 5 ከደማስቆ አራማውያን የሱባን ንጉሥ አድርአዛርን ለመርዳት በመጡ ጊዜ ሃያ ሁለት ሺህ አራማውያን ሰዎችን ገደለ፡፡
\v 6 ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው በአራም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ አራማውያንም ለእርሱ አገልጋዮች ሆነው ተገዙለት፣ ግብርም ገበሩለት፡፡ ዳዊት በሄደበት ሁሉ እግዚአብሔር ድልን ሰጠው፡፡
\s5
\v 7 የአድርአዛር አገልጋዮች ይዘዋቸው የነበሩትን የወርቅ ጋሻዎች ዳዊት ወሰዳቸው ወደ ኢየሩሳሌምም አመጣቸው፡፡
\v 8 ቤጣህና ቤሮታይ ከተባሉ ከአድርአዛር ከተሞችም ዳዊት እጅግ ብዙ ናስ ወሰደ፡፡
\s5
\v 9 የሐማት ንጉሥ ቶዑ ዳዊት መላውን የአድርአዛርን ሠራዊት ድል ማድረጉን በሰማ ጊዜ፣
\v 10 ዳዊት ከአድርአዛር ጋር ስለ ተዋጋና ድል ስላደረገው ደግሞም አድርአዛር ከቶዑ ጋር ተዋግቶ ስለ ነበረ፣ ቶዑ ልጁን ዮራምን ሰላምታ ይሰጠው ዘንድና ይባርከው ዘንድ ወደ ዳዊት ላከው፡፡ ዮራምም ከእርሱ ጋር የብር፣ የወርቅና የናስ ዕቃዎች ይዞ መጣ፡፡
\s5
\v 11 ንጉሥ ዳዊትም ድል ካደረጋቸው መንግሥታት ሁሉ ማለትም
\v 12 ከአራም፣ ከሞዓብ፣ የአሞን ሕዝብ፣ ከፍልስጥኤማውያን ከአማሌቅ እንዲሁም ከሱባ ንጉሥ ከረአብ ልጅ ከአድርአዛር ከበዘበዛቸው ዕቃዎችና ካገኛቸው ብርና ወርቅ ጋር እነዚህን ለእግዚአብሔር ቀደሰ፡፡
\s5
\v 13 ዳዊት የጨው ሸለቆ በተባለው ስፍራ ከአሥራ ስምንት ሺህ ሰዎቻቸው ጋር የነበሩትን አራማውያንን ድል አድርጎ ከተመለሰ በኋላ ስሙ ገነነ፡፡
\v 14 በመላው ኤዶም የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ኤዶማውያን ሁሉ የዳዊት አገልጋዮች ሆኑ፤ እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ስፈራ ሁሉ ድልን ሰጠው፡፡
\s5
\v 15 ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ፤ ሕዝቡንም ሁሉ በፍትሐዊነትና በጽድቅ አስተዳደረ፡፡
\v 16 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የሠራዊቱ አለቃ ሲሆን፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥም ታሪክ ጸሐፊ ነበረ፡፡
\v 17 የአኪጦብ ልጅ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቢሜሌክ ካህናት ሲሆኑ፣ ሠራያ ጸሐፊ ነበር፡፡
\v 18 የዮዳሔ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አለቃ ሲሆን፣ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ የንጉሡ ተቀዳሚ አማካሪዎች ነበሩ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ዳዊትም፣ “ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳዖል ቤት የቀረ ሰው ይኖር ይሆን? ” በማለት ጠየቀ፡፡
\v 2 በሳኦል ቤተሰብ ውስጥ ሲባ የሚባል አንድ አገልጋይ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ዳዊት እንዲሄድ ነገሩት፡፡ ንጉሡም፣ “አንተ ሲባ ነህን? ” ብሎ ጠየቀው፡፡ ሲባም፣ “አዎን፣ እኔ አገልጋይህ ነኝ” ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 3 ንጉሡም፣ “የእግዚአብሔርን ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው የለምን? ” በማለት ጠየቀው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “ዮናታን እግሩ ሽባ የሆነ አንድ ልጅ አለው” ብሎ መለሰ፡፡
\v 4 ንጉሡም፣ “ወዴት ነው ያለው? ” አለው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “ሎዶባር በተባለ ስፍራ በዓሚኤል ልጅ በማኪር ቤት ይገኛል” ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 5 በዚህን ጊዜ ንጉሥ ዳዊት ሎደባር ወደሚገኘው ወደ ዓሚኤል ልኮ ከማኪር ቤት ሜምፊቦስቴን አስመጣው፡፡
\v 6 የሳኦል ልጅ፣ የዮናታን ልጅ ሜምፊቦስቴ ወደ ዳዊት መጥቶ ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት ለዳዊት አክብሮቱን ገለጠ፡፡ ዳዊትም፣ “ሜምፊቦስቴ” ብሎ ጠራው፡፡ እርሱም፣ “እነሆ፣ አገልጋይህ” አለ፡፡
\s5
\v 7 ዳዊትም፣ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል በእርግጥ ቸርነት አደርግልሃለሁና፡፡ የአያትህንም የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከገበታዬ ትበላለህ፡፡” አለው፡፡
\v 8 ሜምፊቦስቴም ለጥ ብሎ እጅ ነሣና፣ “እንደ ሞተ ውሻ የሆንኩትን እኔ አገልጋይህን በሞገስ ትመለከተኝ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?”
\s5
\v 9 ከዚያም ንጉሡ የሳኦልን አገልጋይ ሲባን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “የሳኦልና የቤተሰቡ የሆነውን ሁሉ ለጌታህ ልጅ ሰጥቼዋለሁ፡፡
\v 10 አንተ፤ ልጆችህና አገልጋዮችህ የጌታችሁ የልጅ ልጅ የሚበላውን እንዲያገኝ መሬቱን እረሱለት፣ ምርቱንም አግቡለት፡፡ የጌታህ የልጅ ልጅ ሜምፊቦስቴ ግን ምን ጊዜም ከገበታዬ ይበላል፡፡” በዚያን ጊዜ ሲባ ዐሥራ አምስት ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም ሲባ ንጉሡን፣ “ጌታዬ ንጉሥ፣ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፣ አገልጋይህ ይፈጽመዋል” አለው፡፡ ንጉሡም በተጨማሪ፣ “ሜምፊቦስቴ በበኩሉ ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከገበታዬ የሚበላ ይሆናል” አለ፡፡
\v 12 ሜምፊቦስቴ ሚካ የተባለ አንድ ትንሽ ልጅ ነበረው፤ የሲባ ቤተሰቦች በሙሉ የሜምፊቦስቴ አገልጋዮች ነበሩ፡፡
\v 13 ስለዚህ ሜምፊቦስቴ ይኖር የነበረው በኢየሩሳሌም ነበር፣ ሁለት እግሮቹም ሽባ ቢሆኑም ሁልጊዜ ከንጉሡ ገበታ ይበላ ነበር፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ሞተ፣ ልጁ ሐኖንም በእርሱ ምትክ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 2 ዳዊትም፣ “አባቱ ቸርነትን እንዳደረገልኝ ሁሉ እኔን ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነትን አደርግለታለሁ፡፡” አለ፡፡ ስለዚህ በአባቱ ምክንያት ከደረሰበት ኃዘን ያጽናኑት ዘንድ ዳዊት አገልጋዮቹን ላከ፡፡ አገልጋዮቹም ወደ አሞን ምድር ገቡ፡፡
\v 3 የአሞን ሕዝብ መሪዎች ግን ለጌታቸው ለሐኖን እንደዚህ አሉት፣ “አንተን እንዲያጽናኑ ሰዎቹን በመላኩ ዳዊት በእርግጥ አባትህን በማክበር ነው ብለህ ታስባለህን? ዳዊት ሰዎቹን የላከው ከተማይቱን እንዲመለከቱና ያጠፏትም ዘንድ እንዲሰልሏት አይደለምን?”
\s5
\v 4 ስለዚህ ሐኖን የዳዊትን ሰዎች ይዞ፤ የእያንዳንዳቸውን ጢም በከፊል ላጨ፣ ልብሳቸውንም እስከ ቂጣቸው ድረስ አሳጥሮ በመቁረጥ መልሶ ሰደዳቸው፡፡
\v 5 ይህንን ለዳዊት በገለጹለት ጊዜ፣ ሰዎቹ እጅግ አፍረው ነበርና መልእክተኞችን ወደ እነርሱ ላከ፡፡ ንጉሡም፣ “ጢማችሁ እስኪያድግ በኢያሪኮ ቆዩና ከዚያ በኋላ ተመለሱ” አላቸው፡፡
\s5
\v 6 የአሞን ሰዎች ለዳዊት መጥፎ ጠረን እንዳላቸው ሰዎች እንደሆኑበት ባወቁ ጊዜ የአሞን ሰዎች መልእክተኞችን ልከው ከቤትሮዖብና ከሱባ ሃያ ሺህ አራማውያን እግረኛ ወታደሮችን፣ ከንጉሥ መዓካ አንድ ሺህ ሰዎችን ደግሞም ከጦብ ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ፡፡
\v 7 ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮአብን ከመላው ተዋጊ ሠራዊት ጋር ላከው፡፡
\v 8 አሞናውያን ወጥተው በከተማቸው መግቢያ በር ላይ ሲሰለፉ፤ የሱባና የረአብ አራማውያን ሰዎች ለብቻቸው ሜዳው ላይ ቆሙ፡፡
\s5
\v 9 ኢዮአብም ከፊትና ከኋላው ጦር እንደ ከበበው ባየ ጊዜ፣ በእስራኤል በጀግንነታቸው ከታወቁት ጥቂቶቹን መርጦ በአራማውያን ግንባር አሰለፋቸው፡፡
\v 10 የቀሩትን ሰዎች ደግሞ በወንድሙ በአቢሳ ሥር መድቦ በአሞናውያን ሠራዊት ግንባር አሰለፋቸው፡፡
\s5
\v 11 ኢዮአብም እንዲህ አለ፤ “አራማውያን የሚያይሉብኝ ከሆነ አንተ መጥተህ ትረዳኛለህ፤ አሞናውያን የሚያይሉብህ ከሆነ እኔ መጥቼ እረዳሃለሁ፡፡
\v 12 እንግዲህ በርታ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ጠንካሮች መሆናችንን እናስመስክር፤ እግዚአብሔርም ለዓላማው መልካም መስሎ የታየውን ያደርጋል፡፡”
\s5
\v 13 ከዚያም ኢዮአብና አብሮት የነበረው ሠራዊት ከእስራኤል ሠራዊት ፊት እንዲሸሹ ወደ ተገደዱት ወደ አራማውያን በመገሥገሥ ወደ ጦርነቱ ሄዱ፡፡
\v 14 አራማውያን መሸሻቸውን አሞናውያን ባዩ ጊዜ፣ እነርሱም ከአቢሳ ፊት ሸሽተው ወደ ከተማይቱ ውስጥ ገቡ፡፡ ከዚህ በኋላ ኢዮአብ ከአሞናውያን ሕዝብ ተመልሶ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፡፡
\s5
\v 15 አራማውያን በእስራኤላውያን እየተሸነፉ እንደሆኑ ባዩ ጊዜ እንደ ገና ተሰባሰቡ፡፡
\v 16 አድርአዛር ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ወደነበሩት ወደ አራማውያን ሠራዊት መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም በአድርአዛር ሠራዊት አዛዥ በሶባክ መሪነት ወደ ዔላም መጡ፡፡
\s5
\v 17 ይሄ ነገር ለዳዊት በተነገረው ጊዜ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ፡፡ አራማውያን ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን ገጠሙት ተዋጉትም፡፡
\v 18 አራማውያን ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደለ፡፡ የሠራዊቱ አዛዥ ሶባክም ቆስሎ በዚያ ሞተ፡፡
\v 19 የአድርአዛር አገልጋዮች የነበሩት ነገሥታት ሁሉ በእስራኤል መሸነፋቸውን ባዩ ጊዜ ከእስራኤላውያን ጋር ሰላም መሠረቱ ተገዙላቸውም፡፡ ስለዚህም ሶርያውያን ከዚያ በኋላ አሞናውያንን መርዳት ፈሩ፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ነገሥታት ወደ ጦርነት መውጣታቸው የተለመደ በነበረበት በፀደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን፣ አገልጋዮቹንና መላውን የእስራኤል ሠራዊት ወደ ዘመቻ ላካቸው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ረባትንም ከበቡአት፡፡ ዳዊት ግን በኢየሩሳሌም ቀረ፡፡
\s5
\v 2 ከዚህም የተነሣ በአንድ የምሽት ወቅት ዳዊት ከዐልጋው ተነስቶ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ነበር፤ በዚያም ስፍራ ሆኖ አንዲት ሴት ገላዋን ስትታጠብ አየ፤ ሴቲቱም እጅግ በጣም ውብ ነበረች፡፡
\v 3 ዳዊትም ሰው ልኮ ስለ ሴቲቱ የሚያውቁ ሰዎችን አጠያየቀ፡፡ አንድ ሰውም፣ “ይህች የኤልያብ ልጅ፣ የኬጢያዊው የኦርዮን ሚስት አይደለችምን?”
\s5
\v 4 ከዚያም ዳዊት መልእክተኞች ልኮ አስመጣት፤ ወደ እርሱም ገባች፣ (ከወር አበባ ጊዜዋ የነጻችበት ወቅት ነበርና) አብሮአት ተኛ፡፡ ከዚያም ተመልሳ ወደ ቤቷ ሄደች፡፡
\v 5 ሴቲቱ ፀነሰች፣ “አርግዣለሁ” ብላም ወደ ዳዊት መልእክት ላከችበት፡፡
\s5
\v 6 ከዚያ በኋላም ዳዊት ለኢዮአብ፣ “ኬጢያዊውን ኦርዮንን ወደ እኔ ላክልኝ” ብሎ መልእክት ላከበት፡፡ ስለዚህም ኢዮአብ ኦርዮንን ወደ ዳዊት ላከው፡፡
\v 7 ኦርዮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብና ሠራዊቱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንዲሁም ጦርነቱ እንዴት እየተካሄደ እንዳለ ጠየቀው፡፡
\v 8 ዳዊትም ለኦርዮን፣ “ወደ ቤትህ ሄደህ እግርህን ተታጠብ” አለው፡፡ ኦርዮንም ከቤተ መንግሥቱ ወጣ፣ ንጉሡም ኦርዮን ከወጣ በኋላ ስጦታ አስከትሎ ላከለት፡፡
\s5
\v 9 ኦርዮን ግን ከጌታው አገልጋዮች ጋር በቤተ መንግሥቱ ቅጥር በር ተኛ እንጂ ወደ ቤቱ አልወረደም ነበር፡፡
\v 10 ለዳዊት “ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው በነገሩት ጊዜ፣ ዳዊት ኦርዮንን፣ “ከመንገድ መግባትህ አይደለምን? ለምን ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው? ” ሲል ጠየቀው፡፡
\v 11 ኦርዮም ዳዊትን፣ “ታቦቱ፣ እስራኤልና ይሁዳ በድንኳን ሆነው፣ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም አገልጋዮች ገላጣ ሜዳ ላይ ሰፍረው፤ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋር ለመተኛት እንዴት ወደ ቤቴ እሄዳለሁ? እንዲህ ያለውን ነገር እንደማላደርገው በነፍስህ እምላለሁ፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 12 ከዚህም የተነሣ ዳዊት ለኦርዮ፣ “ዛሬ ደግሞ በዚህ እደርና ነገ አሰናብትሃለሁ” አለው፡፡ ስለዚህ ኦርዮ በዚያ ዕለትና በማግሥቱ እዚያው ኢየሩሳሌም ቆየ፡፡
\v 13 ዳዊትም ባስጠራው ጊዜ በእርሱ ፊት በላ ደግሞም ጠጣ፣ ዳዊትም እንዲሰክር አደረገው፤ ሲመሽም ኦርዮን በአልጋው ላይ ለመተኛት የጌታው አገልጋዮች ወዳሉበት ሄደ፣ ወደ ቤቱ ግን አልሄደም፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህ በማግስቱ ሲነጋ ዳዊት ለኢዮአብ ደብዳቤ ጽፎ በኦርዮን እጅ ላከለት፡፡
\v 15 በደብዳቤውም ውስጥ ዳዊት፣ “ኦርዮንን ውጊያው በተፋፋመበት ግንባር መድበው፤ ከዚያም እንዲመታና እንዲሞት ከኋላው አፈግፍጉ” ብሎ ጻፈ፡፡
\s5
\v 16 ስለዚህ ኢዮአብ የከተማይቱን መከበብ እየተመለከተ ሳለ ጠንካሮቹ የጠላት ሠራዊት እየተዋጉ እንዳሉ በሚያውቅበት ግንባር ኦርዮንን መደበው፡፡
\v 17 የከተማይቱ ሰዎች ወጥተው ከኢዮአብ ጋር ጦርነት በገጠሙበት ጊዜ ከዳዊት ወታደሮች ጥቂቶቹ ሞቱ፣ እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮንም በዚያ ሞተ፡፡
\s5
\v 18 ኢዮአብም በጦርነቱ የሆነውን ሁሉ ለዳዊት በላከበት ጊዜ፣
\v 19 መልእክተኛውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፣ “ጦርነቱን በሚመለከት ሁሉንም ነገር ለንጉሡ ከጨረስክ በኋላ፣
\v 20 ምናልባት ንጉሡ ይቆጣና፣ ‘ለመዋጋት ስትሉ ወደ ከተማይቱ ይህን ያህል የተጠጋችሁት ስለምንድን ነው? በግንቡ ቅጥር ላይ ሆነው ፍላፃ እንደሚወርውሩባችሁ አታውቁም ኖሮአል?
\s5
\v 21 የይሩቤሼትን ልጅ አቤሜሌክን የገደለው ማነው? በቴቤስ እንዲሞት ያደረገችው አንዲት ሴት ከግንቡ ላይ የወፍጮ መጅ ስለለቀቀችበት አይደለምን? ወደ ግንቡ ቅጥር ይህን ያህል የተጠጋችሁት ለምንድን ነው? ’ይልህ ይሆናል፡፡ በዚያን ጊዜ፣ ‘አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞቶአል’ ብለህ ንገረው፡፡”
\s5
\v 22 ስለዚህ መልእክተኛው ተነሥቶ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄደ፣ ኢዮአብ እንዲናገር የላከውን ማንኛውንም ነገር ነገረው፡፡
\v 23 መልእክተኛውም ለዳዊት እንዲህ አለው፣ “እኛ በመጀመሪያ ከነበረው ይልቅ ጠላት በርትቶ ነበር ወደ ሜዳው ወደ እኛ ዘንድ መጡ፤ እኛም እስከ ቅጥሩ መግቢያ በር ድረስ አሳድደን መለስናቸው፡፡
\s5
\v 24 የእነርሱም ባለ ፍላጻዎች ከግንቡ ላይ ሆነው በወታደሮችህ ላይ ቀስት ወረወሩ፣ ከንጉሡ አገልጋዮችም ጥቂቶችን ገደሉ፤ አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ፡፡”
\v 25 ከዚያ በኋላ ዳዊት ለመልእክተኛው፣ “ለኢዮአብ፣ ‘መቼም ሰይፍ አንድ ጊዜ ይህን፣ ሌላ ጊዜም ሌላውን ይበላልና ይህ አያሳዝንህ፡፡ በከተማይቱ ላይ ውጊያህን አጠናክረህ አፍርሳት፡፡’ በለው፣ ኢዮአብን አበረታታው፡፡”
\s5
\v 26 ስለዚህ የኦርዮ ሚስት ባሏ መሞቱን በሰማች ጊዜ አምርራ አለቀሰችለት፡፡
\v 27 የሐዘኗም ጊዜ ካበቃ በኋላ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ ወሰዳት፣ ሚስቱም ሆነች፣ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር እግዚአብሔርን አሳዘነው፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 እግዚአብሔር ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፣ “በአንድ ከተማ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ባለጠጋ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ድኻ ነበረ፡፡
\v 2 ባለጠጋው እጅግ ብዙ መንጋዎችና የቀንድ ከብቶች ነበሩት፤
\v 3 ድኻው ግን ከገዛትን ካሳደጋት ከአንዲት መሲና በግ በስተቀር ሌላ አልነበረውም፡፡ ይህች በግ ከእርሱ ጋር ኖረች ከልጆቹም ጋር አደገች፡፡ በጊቱ እንዲያውም ከእርሱ ጋር ትበላ፣ ከጽዋውም ትጠጣ ነበር፤ በእቅፉም ትተኛ ነበር፣ ለእርሱም እንደ ሴት ልጁ ነበረች፡፡
\s5
\v 4 አንድ ቀን አንድ እንግዳ ወደ ባለጠጋው ቤት መጣ፤ ባለጠጋው ግን ለእንግዳው ምግብ ለማቅረብ ከራሱ መንጋ ወይም ከቀንድ ከብቶቹ አንድ እንሰሳ ለመውሰድ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ከዚያ ይልቅ የድኻውን መሲና ጠቦት ወስዶ ለእንግዳው ምግብ አድርጎ አዘጋጀለት፡፡”
\v 5 ዳዊትም በባለጠጋው ላይ ቁጣው ነደደ፣ በንዴትም ለናታን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል!
\v 6 እንዲህ ያለውን ነገር በማድረጉና ለደኻውም ባለመራራቱ ስለ በጊቱ አራት ዕጥፍ መክፈል አለበት፡፡”
\s5
\v 7 ከዚያ በኋላም ናታን ለዳዊት፣ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፣ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤
\v 8 የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፣ የጌታህንም ሚስቶች በብትህ አስታቀፍሁህ፤ የእስራኤልና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ብዙ ሌሎች ነገሮችንም ጨምሬ በሰጠሁህ ነበር፡፡
\s5
\v 9 ስለዚህ በእርሱ ፊት ክፉ የሆነውን ታደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሕግ ለምን አቃለልህ? ኬጢያዊውን ኦርዮንን በሰይፍ ገደለህ፣ ሚስቱንም ወስደህ የራስህ ሚስት አደረግኸት፡፡ ኦርዮንን በአሞናውያን ሠራዊት ሰይፍ ገደልኸው፡፡
\v 10 እኔን አቃለኸኛልና የኬጢያዊውንም የኦርዮንን ሚስት ሚስትህ አድርገህ ወስደሃልና ሰይፍ ከቤትህ በፍጹም አይርቅም፡፡’
\s5
\v 11 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ከራስህ ቤት ጥፋት አስነሳብሃለሁ፤ ዓይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለጎረቤትህ እሰጠዋለሁ፣ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል፡፡
\v 12 አንተ ኃጢአትህን በስውር እኔ ግን ይህንን ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ፡፡’”
\v 13 ከዚያም ዳዊት ለናታን፣ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው፡፡ ናታንም ለዳዊት መለሰለት፣ “እግዚአብሔር ኃጢአትህን አስወግዶልሃል፡፡ አንተ አትሞትም፤
\s5
\v 14 ይሁን እንጂ በዚህ ድርጊትህ እግዚአብሔርን ስላቃለልህ የተወለደልህ ልጅ በእርግጥ ይሞታል፡፡”
\v 15 ከዚያ በኋላ ናታን ወጥቶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ እግዚአብሔርም የኦርዮን ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ እግዚአብሔር አስጨነቀው እጅግም ታመመ፡፡
\s5
\v 16 ዳዊት ስለ ልጁ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም ከዚያም ወደ ክፍሉ ገብቶ ሌሊቱን ወለሉ ላይ ተኝቶ አደረ፡፡
\v 17 የቤተሰቡ ሽማግሌዎችም ከወለሉ ላይ ያነሱት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፣ እርሱ ግን አልተነሳም፣ ከእነርሱም ጋር አልበላም፡፡
\v 18 በሰባተኛውም ቀን ልጁ ሞተ፡፡ “እነሆ፣ ልጁ ገና በሕይወት ሳለ ስናነጋግረው ድምፃችንን አልሰማንም፣ ታዲያ፣ ልጁ ሞቶአል ብንለው በራሱ ላይ ምን ያደርግ ይሆን?! ” ብለው ስለነበረ፣ የዳዊት አገልጋዮች ልጁ እንደ ሞተ ለመንገር ፈርተው ነበር፡፡
\s5
\v 19 ነገር ግን እርስ በርሳቸው ሲንሾካሾኩ ዳዊት በተመለከተ ጊዜ፣ ልጁ እንደ ሞተ ዳዊት ተገነዘበ፤ ለአገልጋዮቹም፣ “ልጁ ሞተ? ” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም፣ “ሞቶአል” ብለው መለሱለት፡፡
\v 20 ከዚያም ዳዊት ከወለሉ ላይ ተነስቶ ታጠበ፣ ቅባት ተቀባ ደግሞም ልብሱን ለወጠ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤትም ሄዶ አምልኮ አቀረበ፣ ከዚያ በኋላም ወደ ራሱ ቤተ መንግሥት ተመለሰ፡፡ ምግብ እንዲያቀርቡለት በጠየቀ ጊዜ አቀረቡለት፣ እርሱም በላ፡፡
\s5
\v 21 ከዚያ በኋላ አገልጋዮቹ፣ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ልጁ በሕይወት እያለ ጾምህ አለቀስህም፤ ልጁ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” አሉት፡፡
\v 22 ዳዊትም፣ “ልጁ ገና በሕይወት ሳለ ጾምሁ አለቀስሁም፤ ‘ልጁ በሕይወት ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር ቸርነት ያደርግልኝ እንደሆነ ማን ያውቃል’ ብዬ ነበር፡፡
\v 23 አሁን ግን፣ እርሱ ሞቶአልና ለምን እጾማለሁ? መልሼ ላመጣው እችላለሁን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም፡፡”
\s5
\v 24 ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፡፡ ከዚህም የተነሣ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ልጁም ሰሎሞን የሚል ስም ተሰጠው፤ እግዚአብሔርም ወደደው፡፡
\v 25 ስለሆነም እግዚአብሔር ስለወደደው ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ፡፡
\s5
\v 26 በዚያን ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያን የንጉሥ ከተማ የነበረችውን ረባትን ወግቶ ምሽጉን ያዘ፡፡
\v 27 ስለሆነም ኢዮአብ ወደ ዳዊት መልእክተኞችን በመላክ እንዲህ አለው፣ “ረባትን ወግቼ የከተማይቱን የውሃ ማከፋፈያ ይዤአለሁ፡፡
\v 28 እንግዲህ አሁን፣ የቀረውን ሠራዊት አሰባስበህ በከተማይቱ ዙሪያ ሠፍረህ ያዛት፤ ምክንያቱም እኔ ከተማይቱን ከያዝኳት በስሜ መጠራቷ ነው፡፡”
\s5
\v 29 ስለዚህ ዳዊት መላውን ሠራዊት አሰባስቦ ወደ ረባት ሄዶ ከተማይቱን ወግቶ ያዛት፡፡
\v 30 ዳዊት ከሞሎክ ራስ ላይ ዘውዱን ወሰደ፤ የዘውዱም ክብደት አንድ መክሊት ወርቅ ሲሆን የከበረ ዕንቁም በላዩ ላይ ነበረበት፡፡ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ፡፡ ከዚያም እጅግ ብዙ የከተማይቱን ምርኮ አመጣ፡፡
\s5
\v 31 በከተማይቱ የነበሩትንም ሰዎች አውጥቶ በመጋዝ፣ በብረት መቆፈሪያና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አስገደዳቸው፤ የሸክላ ጡብም እንዲሠሩ አደረጋቸው፡፡ ዳዊት የአሞን ሕዝብ ከተሞች ሁሉ ይህንኑ ተግባር እንዲፈጽሙ አደረጋቸው፡፡ ከዚያም ዳዊትና ሠራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ የዳዊት ልጅ አምኖን የዳዊት ሌላ ልጅ የአቤሴሎም ሙሉ እኅት በነበረችው በውቧ ግማሽ እህቱ በትዕማር እጅግ ተማረከ፡፡
\v 2 በእኅቱ በትዕማር ምክንያት እስኪታመም ድረስ አምኖን እጅግ ተጨነቀ፡፡ ድንግል ስለነበረች በእርሷ ላይ ምንም ነገር ማድረግ ለአምኖን የማይቻል መሰለው፡፡
\s5
\v 3 አምኖን ግን የዳዊት ወንድም የሳምዕ ልጅ ኢዮናዳብ የተባለ ወዳጅ ነበረው፡፡ ኢዮናዳብ እጅግ ተንኮለኛ ሰው ነበር፡፡
\v 4 ኢዮናዳብም ለአምኖን፣ “የንጉሥ ልጅ ሆይ፣ በየጥዋቱ ጭንቀት የሚሰማህ ለምንድን ነው? አትነግረኝምን? ” ብሎ ጠየቀው፡፡ አምኖንም፣ “የወንድሜን የአቤሴሎምን እህት ትዕማርን አፍቅሬ ነው” ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 5 በዚህን ጊዜ ኢዮናዳብ፣ “የታመምህ መስለህ አልጋህ ላይ ተኛ፣ አባትህ ሊጠይቅህ ሲመጣም፣ ‘እህቴ ትዕማር የምበላውን ምግብ ታቀርብልኝ ዘንድ እባክህ ላክልኝ፤ ምግቡንም ዓይኔ እያየ ከእጇ እንድጎርስ እዚሁ መጥታ ታዘጋጅልኝ’ ብለህ ጠይቀው፡፡”
\v 6 ስለዚህ አምኖን የታመመ ሰው መስሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊጠይቀው በመጣ ጊዜ አምኖን ለንጉሡ፣ “ለሕመሜ የሚሆን ጥቂት ምግብ በፊቴ እንድታዘጋጅልኝና ከእጇም እንድበላ እባክህ እህቴን ትዕማርን ላክልኝ” ብሎ ጠየቀው፡፡
\s5
\v 7 ከዚያም ዳዊት፣ “አሁን ሂጂና ለወንድምሽ ለአምኖን ምግብ አዘጋጂለት” በማለት በቤተ መንግሥቱ ወደ ነበረችው ትዕማር መልእክት ላከባት፡፡
\v 8 ስለዚህም ትዕማር ወንድሟ አምኖን ወደተኛበት ቤት ሄደች፤ ጥቂት ሊጥ ወስዳ ካቦካችው በኋላ ቂጣ አደረገችው፣ ጋገረችውም፡፡
\v 9 ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ ቂጣውን አቀረበችለት፣ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም፡፡ ስለዚህ አምኖን በዘያ ለነበሩት ለሌሎቹ፣ “ማንኛውንም ሰው ከዚህ ከእኔ ዘንድ አስወጡልኝ” አላቸው፤ ስለዚህ ሰው ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ፡፡
\s5
\v 10 ከዚያም አምኖን ትዕማርን፣ “ምግቡን ከእጅሽ እበላ ዘንድ ወደዚህ ወደ ክፍሌ አምጭልኝ” አላት፡፡
\v 11 ምግቡን ባመጣችለት ጊዜ አምኖን እጇን ያዛትና፣ “እህቴ ሆይ፣ ነይ ከእኔ ጋር ተኚ” አላት፡፡
\v 12 እርሷም፣ “አይሆንም፣ ወንድሜ ሆይ፣ አታስገድደኝ፤ ይህን የመሰለ ነገር በእስራኤል ሊደረግ አይገባውምና፡፡ ይህን አሳፋሪ ነገር አታድርግ፡፡
\s5
\v 13 ይሄ ነገር ከሚያስከትልብኝ ዕፍረት ለማምለጥስ ወዴት መሄድ እችላለሁ? ይህም ድርጊት አንተን በመላው እስራኤል ኀፍረተ-ቢስ ጅል አድርጎ ያስቆጥርሃል፡፡ እባክህ፣ ለንጉሡ እንድትነግረው እጠይቅህሃለሁ፤ እንድታገባኝ ይፈቅድልሃል፡፡”
\v 14 ይሁን እንጂ አምኖን አልሰማትም፡፡ ከትዕማር ይልቅ ብርቱ ስለ ነበረ ይዟት ከእርሷ ጋር ተኛ፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም አምኖን ትዕማርን ከመጠን በላይ ጠላት፤ አፍቅሯት ከነበረውም ይልቅ ጠላት፡፡ አምኖንም፣ “ተነሺ፣ ውጭልኝ” አላት፡፡
\v 16 እርሷ ግን፣ “አይሆንም፣ ምክንያቱም እኔን በማስወጣት የምታደርገው ይህ ክፉ ነገር ቀድመህ ካደረግኸው ይልቅ የከፋ ነው፡፡” አምኖን ግን እርሷን አልሰማትም፡፡
\v 17 ከዚያ ይልቅ የግል አገልጋዩን ጠርቶ፣ “ይህችን ሴት ከእኔ ዘንድ አስወጥተህ፣ በሩን ቀርቅረው” አለው፡፡
\s5
\v 18 ከዚህ በኋላ አገልጋዩ አስወጣትና በሩን ከበስተኋላዋ ቀረቀረባት፡፡ ድንግል የሆኑት የንጉሡ ሴት ልጆች እንደዚያ ይለብሱ ነበርና፣ ትዕማር በጣም ያጌጠ ቀሚስ ለብሳ ነበር፡፡
\v 19 ትዕማር በራሷ ላይ ማቅ ነሰነሰች፣ ቀሚሷንም ቀደደች፡፡ እጇንም በራሷ ላይ አድርጋ ሄደች፣ በምትሄድበትም ወቅት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ አለቀሰች፡፡
\s5
\v 20 ወንድሟ አቤሴሎምም፣ “ወንድምሽ አምኖን ካንቺ ጋር ነበርን? ሆኖም፣ እህቴ ሆይ፣ አሁን ዝም በይ፡፡ ወንድምሽ ስለሆነ ነገሩን በልብሽ አትያዢው፡፡” ስለሆነም ትዕማር በወንድሟ በአቤሴሎም ቤት ብቸኛ ሆና ኖረች፡፡
\v 21 ነገር ግን ንጉሥ ዳዊት ይህንን ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፤
\v 22 አቤሴሎም ለአምኖን ምንም አልተናገረውም፤ ስላደረገባት ነገር እህቱንም ትዕማርን ስላስነወራት ጠልቶት ነበርና፡፡
\s5
\v 23 ከሁለት ሙሉ ዓመት በኋላ አቤሴሎም በጎቹን በኤፍሬም አጠገብ በነበረው በቤላሶር ከተማ በጎችን የሚሸልቱ ሰዎች አስመጥቶ ነበር፤ አቤሴሎምም የንጉሡን ልጆች ወደዚያ ስፍራ ጋበዛቸው፡፡
\v 24 አቤሴሎም ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “እነሆ፣ ባሪያህ በጎችን የሚሸልቱ አስመጥቷል፣ንጉሡና አገልጋዮቹ እባክህን ከባሪያህ ጋር ይምጡ” አለው፡፡
\s5
\v 25 ንጉሡም ለአቤሴሎም፣ “ልጄ ሆይ፣ ሁላችንም መሄድ የለብንም፤ ሸክም እንሆንብሃለን” ብሎ መለሰለት፡፡ አቤሴሎም ንጉሡን አደፋፈረው፣ እርሱ ግን መሄድ ባይፈልግም አቤሴሎምን ባረከው፡፡
\v 26 ከዚህ በኋላ አቤሴሎም፣ “ይሄ ካልሆነ፣ እባክህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር ይሂድ” አለው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ አቤሴሎምን፣ “አምኖን አብሮአችሁ የሚሄደው ለምንድን ነው? ” ብሎ ጠየቀው፡፡
\s5
\v 27 አቤሴሎም አጥብቆ ስለለመነው፣ አምኖንና የንጉሡ ልጆች አብረውት እንዲሄዱ ፈቀደ፡፡
\v 28 አቤሴሎም አገልጋዮቹን፣ “ልብ ብላችሁ አድምጡ፣ አምኖን ወይን ጠጅ ጠጥቶ መስከር ሲጀምርና እኔ ‘አምኖንን ምቱት’ ስላችሁ፣ በዚያን ጊዜ ግደሉት፤ አትፍሩ፡፡ ያዘዝኋችሁ እኔ ነኝና በርቱ፣ ጠንክሩ፡፡” ብሎ አዘዛቸው፡፡
\v 29 ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት፡፡ ከዚያ በኋላም የንጉሡ ልጆች በየበቅሎአቸው ላይ ተቀምጠው ሸሹ፡፡
\s5
\v 30 እነርሱም እየሄዱ በመንገድ ላይ ሳሉ፣ “አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ገደለ፣ አንድም የተረፈ የለም” የሚል ዜና ለዳዊት ደረሰው፡፡
\v 31 ከዚያ በኋላ ንጉሡ ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፣ በወለሉም ላይ ተጋደመ፣ አገልጋዮቹም ልብሳቸውን ቀደው በአጠገቡ ቆሙ፡፡
\s5
\v 32 የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ ግን፣ “የሞተው አምኖን ብቻ ነውና የንጉሡ ልጆች የሆኑትን ጎልማሶች ሁሉ ገድለዋቸዋል ብሎ ጌታዬ አይመን፡፡ አምኖን እህቱን ትዕማርን ከደፈራት ቀን አንስቶ አቤሴሎም ይህንን ሲያቅድ ነበር፤
\v 33 ስለሆነም የሞተው አምኖን ብቻ ነውና፣ የንጉሡ ልጆች ሁሉ ሞተዋል ብሎ እስከሚያምን ድረስ ጌታዬ ንጉሡ የሚለውን ዜና ወደ ልቡ አያስገባው፡፡”
\s5
\v 34 አቤሴሎም ሸሸ፡፡ ለጥበቃ የቆመውም አገልጋይ ቀና ብሎ ሲመለከት ከእርሱ በስተምዕራብ ካለው ኮረብታ ጥግ ባለው መንገድ ብዙ ሰዎች ሲመጡ አየ፡፡
\v 35 በዚያን ጊዜ ኢዮናዳብ ለንጉሡ፣ “እነሆ፣ የንጉሡ ልጆች እየመጡ ነው፤ ልክ ባሪያህ እንዳለው ነው፡፡”
\v 36 ስለሆነም ተናግሮ እንደጨረሰ፣ የንጉሡ ልጆች ደረሱ፣ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፡፡ ንጉሡና አገልጋዮቹም ሁሉ አምርረው አለቀሱ፡፡
\s5
\v 37 አቤሴሎም ኮብልሎ የጌሹር ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ፡፡ ዳዊትም ስለ ሞተው ልጁ ዘወትር ያለቅስ ነበር፡፡
\v 38 አቤሴሎም ለሶስት ዓመታት ወደ ቆየበት ወደ ጌሹር ሸሽቶ ሄደ፡፡
\v 39 በልጁ በአምኖን ሞት ከደረሰበት ሐዘን ተጽናንቶ ስለነበረ ንጉሥ ዳዊት በሃሳቡ ወደ አቤሴሎም የመሄድ ናፍቆት አደረበት፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ የንጉሡ ልብ አቤሴሎምን እንደ ናፈቀ ተረዳ፡፡
\v 2 ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ቴቁሔ ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጥቶ፣ “ሐዘንተኛ በመምሰል የሐዘን ልብስ ልበሺ፣ እባክሽን ዘይት አትቀቢ ነገር ግን ለብዙ ጊዜ እንዳዘነች መስለሽ ታዪ፡፡
\v 3 ከዚያም ወደ ንጉሡ ሄደሽ እኔ የምገልጽልሽን ንገሪው፡፡” ስለዚህ ኢዮአብ ለንጉሡ የምትናገረውን ነገር ነገራት፡፡
\s5
\v 4 ከቴቁሔ የመጣችውም ሴት ለንጉሡ ለመንገር በገባችበት ጊዜ በንጉሡ ፊት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት፣ “ንጉሥ ሆይ፣ እርዳኝ” አለች፡፡
\v 5 ንጉሡም፣ “ችግርሽ ምንድን ነው? ” አላት፡፡ ሴቲቱም፣ “እኔ በእውነቱ ባሏ የሞተባት ባልቴት ነኝ፡፡
\v 6 እኔ ባሪያህ ሁለት ልጆች ነበሩኝ፣ እነርሱም ሜዳ ላይ እርስ በርሳቸው ተጣሉ፣ የሚገላግላቸውም ሰው አልነበረም፡፡ አንደኛውም ሌላኛውን መታውና ገደለው፡፡
\s5
\v 7 መላው ቤተሰብም አሁን በባሪያህ ላይ ተነሥቶ፣ ’ስለገደለው ስለ ወንድሙ ዋጋ እንዲከፍልና እኛም እንድንገድለው ወንድሙን የገደለውን ሰው አውጥተሸ ስጪን’ አሉኝ፤ ወራሽ የሆነውንም ያጠፉ ዘንድ ይፈልጋሉ፡፡ በዚህም ዓይነት የቀረኝን አንድ የጋለ ፍም አጥፍተው፣ ባሌን በምድር ላይ ያለ ስምና ያለ ዘር ሊያስቀሩት ነው፡፡”
\s5
\v 8 ስለዚህ ንጉሡ ለሴቲቱ፣ “አንቺ ወደ ቤትሽ ሂጂ፣ አንድ ነገር እንዲደረግልሽ እኔ ትዕዛዝ እሰጣለሁ” አላት፡፡
\v 9 የቴቁሔዪቱም ሴት ለንጉሡ፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በደሉ በእኔና በአባቴ ቤተሰብ ላይ ይሁን፤ ንጉሡና ዙፋኑ ከበደል የነጹ ይሁኑ” አለች፡፡
\s5
\v 10 ንጉሡም፣ “ማንም ሰው ቢናገርሽ ወደ እኔ ዘንድ አምጪው ከዚያ በኋላም አያስቸግርሽም” በማለት መለሰላት፡፡
\v 11 ከዚያ በኋላ ሴቲቱ፣ “ደም ተበቃዩ ሌላ ሰው እንዳያጠፋና ልጄንም እንዳያጠፉት፣ እባክህን ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክህን አሳስብልኝ” አለችው፡፡ ንጉሡም፣ “ሕያው እግዚአብሔርን ከልጅሽ ራስ አንዲት ፀጉር እንኳ አትወድቅም” ብሎ መለሰላት፡፡
\s5
\v 12 ከዚያ በኋላም ሴቲቱ፣ “ባሪያህ ለጌታዬ ለንጉሡ ተጨማሪ ቃል እንድናገር እባክህ ፍቀድልኝ” አለችው፡፡ ንጉሡም፣ “ተናገሪ” አላት፡፡
\v 13 ስለዚህ ሴቲቱ፣ “ታዲያ፣ እንዲሀ ያለውን ነገር በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ያሰብኸው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይህንን በመናገሩ ንጉሡ ራሱን በደለኛ እንደሚያደርግ ሰው ነው፣ የኮበለለውን ልጁን ንጉሡ ወደ ቤቱ አልመለሰውምና፡፡
\v 14 ሁላችንም እንሞት ዘንድ ይገባናልና፣ እንደገናም ሊሰበሰብ እንደማይችል እንደ ፈሰሰ ውሃ ነንና፡፡ እግዚአብሔር ግን የሰውን ሕይወት አይወስድም ይልቁንም ከፊቱ ራሱን ያስኮበለለውን ሰው ወደ ራሱ የሚመልስበት መንገድ ይፈልጋል እንጂ፡፡
\s5
\v 15 እንግዲህ አሁን ለጌታዬ ለንገሡ ይህንን ልናገር የመጣሁት ሕዝቡ እንድፈራ ስላደረጉኝ ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ባሪያህ ለራሷ፣ ‘አሁን ለንጉሡ እናገራለሁ፣ ምናልባትም ንጉሡ የባሪያውን ጥያቄ ይቀበል ያደርግላት ይሆናል፡፡
\v 16 እኔንና ልጄን ከእግዚአብሔር ርስት ሊያጠፋን ካለው ሰው እጅ ያድን ዘንድ ባሪያውን ያወጣ ዘንድ ንጉሡ ይሰማኛልና፣’ አለች፡፡
\v 17 ከዚያ በኋላም ባሪያህ፣ ‘እግዚአብሔር ሆይ፣ የጌታዬ የንጉሡ ቃል እፎይታን የሚሰጠኝ ይሁን፣ ምክንያቱም መልካሙን ከክፉው በመለየት ጌታዬ ንጉሡ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነውና’ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡”
\s5
\v 18 ከዚያ በኋላም ንጉሡ ለሴቲቱ፣ “እኔ ለምጠይቅሽ ጥያቄ እባክሽ ምንም ነገር አትደብቂኝ” አላት፡፡
\v 19 ንጉሡም፣ “በዚህ ሁሉ የኢዮአብ እጅ ከአንቺ ጋር የለም? ” ሴቲቱም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ጌታዬ ንጉሡ ከተናገረው አንዳችም ነገር ማንም ሰው ወደ ቀኝም ወደ ግራም ማምለጥ አይችልም፡፡ ያዘዘኝና ባሪያህም የተናገረችውን እነዚህን ነገሮች እንድናገር የነገረኝ ባሪያህ ኢዮአብ ነው፡፡
\v 20 ባሪያህ ኢዮአብ ይህንን ያደረገው ነገሮች እየሄዱበት ያለውን አቅጣጫ ለመለወጥ ነው፡፡ እንደ እግዚአብሔር መልአክ ጥበብ ጌታዬ ጠቢብ ነው፤ በምድሪቱም የሚሆነውን ማንኛውንም ነገር ያውቃል፡፡”
\s5
\v 21 ስለዚህ ንጉሡ ለኢዮአብ፣ “እነሆ፣ እኔ አሁን ይህንን አደርጋለሁ፡፡ እንግዲህ ሂድና ወጣቱን አቤሴሎምን አምጣው” አለው፡፡
\v 22 ስለዚህ ኢዮአብ ለንጉሡ አክብሮቱንና ምስጋናውን ለመግለጽ ጎንበስ ብሎ እጅ ነሳ፡፡ ኢዮአብም፣ “ዛሬ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ፊት ሞገስ እንዳገኘ አወቅሁ፣ ንጉሡ የባሪያውን ጥያቄ ፈጽሞለታልና”
\s5
\v 23 ስለዚህ ኢዮአብ ተነሥቶ ወደ ጌሹር ሄደ፣ አቤሴሎምንም ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡
\v 24 ንጉሡም፣ “ወደ ራሱ ቤት መመለስ ይችላል፣ ነገር ግን ፊቴን አያይም” ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ቤቱ ተመለሰ፣ የንጉሡን ፊት ግን አላየም፡፡
\s5
\v 25 በመላው እስራኤል ከአቤሴሎም ይልቅ በመልከ መልካምነቱ የተመሰገነ ማንም አልነበረም፡፡ ከእግር ተረከዙ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ ምንም እንከን አልነበረበትም፡፡
\v 26 ይከብደው ስለ ነበረ የራሱን ፀጉር በሚቆረጥበት ጊዜ ፀጉሩን ይመዝነው ነበር፣ በንጉሡም የመመዘኛ ልክ ሁለት መቶ ሰቅል ይመዝን ነበር፡፡
\v 27 አቤሴሎምም ሦስት ወንዶች ልጆችና ትዕማር የምትባል አንድ ሴት ልጅ ነበሩት፡፡ ሴት ልጁም ውብ ነበረች፡፡
\s5
\v 28 አቤሴሎምም የንጉሡን ፊት ሳያይ ሁለት ሙሉ ዓመት በኢየሩሳሌም ኖረ፡፡
\v 29 ከዚህ በኋላ ወደ ንጉሡ ይወስደው ዘንድ አቤሴሎም ወደ ኢዮአብ መልእክት ላከ፣ ኢዮአብ ግን ሊመጣ አልፈለገም፡፡ ስለዚህ አቤሴሎም ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ኢዮአብ መልእክት ላከ፣ ኢዮአብ ግን አሁንም አልመጣም፡፡
\s5
\v 30 ስለዚህ አቤሴሎም ለአገልጋዮቹ፣ “ኢዮአብ በእኔ እርሻ አጠገብ እርሻ አለው፣ በዚያም ገብስ አለው፤ ሂዱና በገብሱ ላይ እሳት ልቀቁበት” አላቸው፡፡ ስለዚህ የአቤሴሎም አገልጋዮች በእርሻው ላይ እሳት ለቀቁበት፡፡
\v 31 ከዚያም ኢዮአብ ተነስቶ ወደ አቤሴሎም ቤት መጣና፣ “አገልጋዮችህ በእርሻዬ ላይ እሳት የለቀቁበት ለምንድን ነው? ” አለው፡፡
\s5
\v 32 አቤሴሎምም ለኢዮአብ፣ “እነሆ፣ ወደ አንተ ዘንድ፣ ‘ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ዘንድ መጥተህ ለንጉሡ፣ ከጌሹር ለምን መጣሁ? እዚያው ብቆይ ይሻለኝ ነበር’ ብለህ እንድትነግርልኝ መልእክት ልኬብህ ነበር፡፡ ስለዚህ አሁን የንጉሡን ፊት ልይ፣ በደለኛ ከሆንኩም ይግደለኝ” አለው፡፡
\v 33 ስለዚህ ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ዘንድ ሄዶ ነገረው፡፡ ንጉሡም አቤሴሎምን ባስጠራው ጊዜ አቤሴሎም በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፣ ንጉሡም አቤሴሎምን ሳመው፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ አቤሴሎም ሠረገላና ፈረሶች እንዲሁም ፊት ፊቱ የሚሮጡ ሃምሳ ሰዎች ለራሱ አዘጋጀ፡፡
\v 2 አቤሴሎም በማለዳ ተነሥቶ ወደ ከተማይቱ መግቢያ በር በሚወስደው መንገድ ዳር ይቆማል፡፡ ሙግት ያለበት ማንኛውም ሰው ዳኝነት ለማግኘት ወደ ንጉሡ ሲመጣ፣ በዚያን ጊዜ አቤሴሎም ወደ እርሱ ይጠራውና፣ “ከየትኛው ከተማ ነው የመጣኸው? ” ይለው ነበር፡፡ ሰውዬውም፣ “አገልጋይህ ከእስራኤል ነገዶች ከአንዱ ነው? ” ይለው ነበር፡፡
\s5
\v 3 ከዚህም የተነሣ አቤሴሎም፣ “ተመልከት፣ ጉዳይህማ ትክክልና ተገቢም ነው፤ ነገር ግን ጉዳይህን ለመመልከት ከንጉሡ ሥልጣን የተሰጠው ማንም ሰው የለም፡፡” ይለው ነበር፡፡
\v 4 ከዚህ ጋር በማያያዝ አቤሴሎም፣ “ሙግት ወይም ጉዳይ ያለው ማንኛውም ሰው ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም ፍትሕ እንድሰጠው በምድሪቱ ዳኛ ሆኜ መሾም እመኛለሁ” ይል ነበር፡፡
\s5
\v 5 ስለዚህ ክብርን ሊሰጠው ማንኛውም ሰው ወደ አቤሴሎም በሚመጣበት ጊዜ አቤሴሎም እጁን ዘርግቶ ይይዘውና ይስመው ነበር፡፡
\v 6 ከንጉሡ ፍትሕ ለማግኘት በሚመጡ እስራኤላውያን ሁሉ አቤሴሎም እንደዚህ ያደርግ ነበር፡፡ በዚህም ሁኔታ አቤሴሎም የእስራኤላውያንን ልብ ሰረቀ፡፡
\s5
\v 7 በአራተኛው ዓመት ፍጻሜ አቤሴሎም ለንጉሡ፣ “ለእግዚአብሔር የተሳልሁትን ስእለት ለማድረስ ወደ ኬብሮን እንድሄድ እባክህን ፍቀድልኝ፡፡
\v 8 ባሪያህ በአራም በጌሹር በነበርኩበት ጊዜ፣ ‘እግዚአብሔር በእርግጥ ወደ ኢየሩሳሌም ዳግመኛ የመለሰኝ እንደሆነ በኬብሮን እሰግዳለሁ’ ብዬ ተስዬ ነበር፡፡”
\s5
\v 9 ንጉሡም፣ “በሰላም ሂድ” አለው፤ ስለዚህ አቤሴሎም ወደ ኬብሮን ሄደ፡፡
\v 10 አቤሴሎም ግን ወደ መላው የእስራኤል ነገዶች፣ “የመለከትን ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ‘አቤሴሎም በኬብሮን ነገሠ’ ማለት ይገባችኋል” የሚሉ ሰላዮችን ላከ፡፡
\s5
\v 11 ከአቤሴሎምም ጋር ሁለት መቶ የተጋበዙ ሰዎች ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡ አቤሴሎም ምን እንዳቀደ ምንም ነገር ሳያውቁ በየዋህነት ነበረ የሄዱት፡፡
\v 12 አቤሴሎም መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ የዳዊት አማካሪ ለሆነው ለአኪጦፌል ወደሚኖርበት ወደ ጊሎ መልእክት ላከበት፡፡ አቤሴሎምን ይከተለው የነበረው ሕዝብ እየጨመረ ስለነበረ የአቤሴሎም ሤራ ጠንካራ ነበር፡፡
\s5
\v 13 “የእስራኤል ሰዎች ልብ አቤሴሎምን እየተከተለ ነው፡፡” የሚል መልእክተኛ ወደ ዳዊት መጣ፡፡
\v 14 ስለዚህ ዳዊት በኢየሩሳሌም ለነበሩት አገልጋዮቹ ሁሉ፣ “ተነሡ እንሽሽ፤ ያለበለዚያ አንዳችንም ከአቤሴሎም እጅ ማምለጥ አንችልም፤ አሁኑኑ ለመውጣት ተዘጋጁ አለዚያ እርሱ መጥቶ ይይዘናል በእኛም ላይ ጥፋት ያደርስብናል፣ ከተማይቱንም በሰይፍ ይመታታል፡፡” አላቸው፡፡
\v 15 የንጉሡም አገልጋዮች፣ “እነሆ፣ ጌታችን የወሰነውን ማንኛውንም ለማድረግ አገልጋዮችሀ ዝግጁ ነን” በማለት ለንጉሡ ነገሩት፡፡
\s5
\v 16 ንጉሡ ከእርሱም ጋር መላው ቤተሰቡ ሄዱ፣ ነገር ግን ቤተ መንግሥቱን ይጠብቁ ዘንድ ቁባቶች የነበሩ አሥር ሴቶችን እንዲቀሩ አደረገ፡፡
\v 17 ንጉሡና እርሱን ተከትሎ መላው ሕዝብ ከሄደ በኋላ ከመጨረሻው ቤተ ሲደርሱ ቆሙ፡፡
\v 18 ሠራዊቱ ሁሉ ከእርሱ ጋር ተጓዙ፣ ከሊታውያን፣ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡት ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፡፡
\s5
\v 19 ከዚያም ንጉሡ ጌታዊውን ኢታይን፣ “አንተ ደግሞ ከእኛ ጋር የመጣኸው ለምንድን ነው? እንግዳና ስደተኛ ነህና ተመልሰህ ሄደህ ከአቤሴሎም ጋር ቆይ፤ ወደ ራስህ አገር ሂድ፡፡
\v 20 የወጣኸው ገና ትላንት ስለሆነ፣ ከእኔ ጋር በየቦታው ለምን እንድትንከራተት ላድርግህ? ወዴት እንደምሄድ እንኳን አላውቅም፡፡ ስለዚህ ተመለስ የአገርህንም ሰዎች መልሳቸው፤ በጎነትና ታማኝነት ከአንተ ጋር ይሁን፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 21 ኢታይ ግን ለንጉሡ፣ “ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሁም በጌታዬ በንጉሡ እምላለሁ፤ ሕይወትም ይሁን ሞት ንጉሡ ወደሚሄድበት ወደየትኛውም ቦታ አገልጋይህም ይሄዳል፡፡” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 22 ስለዚህ ዳዊት ለኢታይ፣ “እንግዲያውስ፣ ከእኛ ጋር መሄድህን ቀጥል” አለው፡፡ ከእርሱ ጋር ከነበሩት ሰዎች ሁሉና አብረውት ከነበሩት ቤተሰቦቹ ሁሉ ጋር ጌታዊው ኢታይ ከንጉሡ ጋር ተጓዘ፡፡
\v 23 ሕዝቡ ሁሉ ንጉሡም ራሱ የቄድሮንን ወንዝ ሲሻገሩ የአገሩ ሕዝብ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ፡፡ ሕዝቡ ሁሉ ወደ ምድረ-በዳ በሚወስደው መንገድ ተጓዘ፡፡
\s5
\v 24 ሳዶቅም እንኳን የእግዚአብሔርን የኪዳን ታቦት ከተሸከሙት ሌዋውያን ጋር በዚያ ነበር፡፡ የእግዚአብሔርን ታቦት አስቀመጡትና አብያታር ከእነርሱ ጋር ሆነ፤ እነርሱም ሕዝቡ ሁሉ ከከተማይቱ እስኪወጡ ድረስ ጠበቁ፡፡
\v 25 ንጉሡም ሳዶቅን፣ “ታቦቱን ወደ ከተማይቱ ይዘህ ተመለስ፣ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ ካገኘሁ ወደዚህ መልሶ ያመጣኛል፣ ታቦቱንና እርሱም የሚኖርበትን ስፍራ እንደገና ያሳየኛል፡፡
\v 26 ነገር ግን እርሱ፣ ‘በአንተ አልተደሰትሁም’ ካለኝ፣ እነሆ፣ በፊቱ አለሁ፣ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግብኝ፡፡”
\s5
\v 27 ንጉሡ ለካህኑ ለሳዶቅ፣ “አንተ ነቢይ አይደለህምን? አንተ ከሁለቱ ልጆችህ፣ ከልጅህ አኪማአስና ከአብያታር ልጅ ከዮናታን ጋር ሆናችሁ በሰላም ወደ ከተማይቱ ተመለሱ፡፡
\v 28 ከአንተ ዘንድ መልእክት እስካገኝ ድረስ፣ እነሆ፣ እኔ በአረባ በሚገኘው በወንዙ መሻገሪያ እቆያለሁ፡፡”
\v 29 ስለዚህ ሳዶቅና አብያታር የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሰው እዚያው ቆዩ፡፡
\s5
\v 30 ዳዊት ግን እያለቀሰ በባዶ እግሩ የደብረ ዘይትን ተራራ ሽቅብ ወጣ፣ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፡፡ ከእርሱ ጋር የነበረውም እያንዳንዱ ሰው ራሱን ተከናንቦ ነበር፤ እየሄዱም ሳሉ ያለቅሱ ነበር፡፡
\v 31 አንድ ሰውም ለዳዊት፣ “በሤራው ውስጥ ከአቤሴሎም ጋር ካሉት አንደኛው አኪጦፌል ነው” ብሎ ነገረው፡፡ ስለዚህ ዳዊት፣ “እባክህ፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ የአኪጦፌልን ምክር ወደ ሞኝነት ለውጠው” ብሎ ጸለየ፡፡
\s5
\v 32 ዳዊት እግዚአብሔር ወደሚመለክበት ወደ መንገዱ ጫፍ በደረሰ ጊዜ፣ አርካዊው ኩሲ መጎናጸፊያውን ቀድዶ ትቢያ በራሱ ላይ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ፡፡
\v 33 ዳዊትም ለእርሱ፣ “አብረኸኝ ብትሄድ ሸክም ትህንብኛለህ፤
\v 34 ነገር ግን ወደ ከተማይቱ ተመልሰህ አቤሴሎምን ‘ንጉሥ ሆይ፣ አገልጋይህ እሆናለሁ፣ ቀድሞ የአባትህ አገልጋይ እንደ ነበርሁ ሁሉ አሁን ደግሞ የአንተ አገልጋይ እሆናለሁ’ ብትለው የአኪጦፌልን ምክር በማደናገር ትረዳኛለህ፡፡
\s5
\v 35 ካህናቱ ሳዶቅና አብያታር እዚያው ከአንተ ጋር አሉልህ አይደለምን? በንጉሡ ቤተ መንግሥት የምትሰማውን ማንኛውንም ነገር ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር መንገር አለብህ፡፡
\v 36 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስና የአብያታር ልጅ ዮናታን ሁለቱ ወንዶች ልጆች በዚያ አብረዋቸው መሆናቸውን አረጋግጥ፡፡ የምትሰማውን ማንኛውንም ነገር በእነርሱ በኩል ላክልኝ፡፡”
\v 37 ስለዚህ የዳዊት ወዳጅ ኩሲ አቤሴሎም ኢየሩሳሌም በገባበት በዚያው ወቅት ወደ ከተማይቱ መጣ፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 ዳዊት ከተራራው ጫፍ ባሻገር ጥቂት እልፍ ብሎ እንደሄደ ሲባ የተባለው የሜምፊቦስቴ አገልጋይ፣ ሁለት መቶ እንጀራ አንድ ሙሉ ጥፍጥፍ ዘቢብ አንድ መቶ ጥፍጥፍ በለስና አንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ የተጫኑ ሁለት አህዮች ይዞ ተገናኘው፡፡
\v 2 ንጉሡም ሲባን፣ “ይህን ሁሉ ያመጣኸው ለምንድን ነው? ” ሲል ጠየቀው፡፡ ሲባም፣ “አህዮቹን የንጉሡ ቤተ ሰቦች እንዲቀመጡባቸው፣ እንጀራውንና በለሱን ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች እንዲበሉት፣ የወይን ጠጁ ደግሞ በምድረ-በዳ የደከመ ማንኛውም ሰው እንዲጠጣው ነው” አለው፡፡
\s5
\v 3 ንጉሡም፣ “የጌታህ የልጅ ልጅ የት ነው? ” አለው፡፡ ሲባም ለንጉሡ፣ “’ዛሬ የእስራኤል ቤት የአባቴን መንግሥት ለእኔ ይመልስልኛል’ እያለ ስለነበረ፣ እነሆ፣ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 4 ከዚያም ንጉሡ ሲባን፣ “የሜምፊቦስቴ የነበረው ሁሉ ከእንግዲህ፣ እነሆ፣ የአንተ ሆኖአል” አለው፡፡ ሲባም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ በትሕትና በፊትህ እጅ እነሣለሁ፣ በፊትህ ሞገስ ላግኝ” አለው፡፡
\s5
\v 5 ንጉሥ ዳዊት ወደ ብራቂም ሲደርስ ከሳዖል ቤተሰብ ነገድ የሆነ የጌራ ልጅ ሳሚ ብቅ አለ፡ እርሱም እየመጣ ሳለ ይራገም ነበር፡፡
\v 6 የንጉሡ ወታደሮችና የክብር ዘቦቹ ሁሉ በዳዊትና ግራና ቀኝ ቢኖሩም እንኳን፣ በዳዊትና በሹማምንቱ ላይ ድንጋይ ይወረውርባቸው ነበር፡፡
\s5
\v 7 ሳሚም እንደዚህ ብሎ ተራገመ፣ “ውጣ፣ ከዚህ ውጣ፣ አንተ ወሮበላ፣ አንተ የደም ሰው፤
\v 8 በእርሱ ምትክ የነገሥህበትን የሳዖልን ቤተሰብ ደም ብድራት ሁሉ እግዚአብሔር እየከፈለህ ነው፡፡ እግዚአብሔር መንግሥቱን በልጅህ በአቤሴሎም እጅ አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ አሁንም አንተ የደም ሰው ስለሆንክ ጥፋት ደርሶብሃል፡፡”
\s5
\v 9 ከዚህ በኋላ የጽሩይ ልጅ አቢሳ፣ “ይህ የሞተ ውሻ ንጉሡ ጌታዬን ለምን ይራገማል? እባክህ፣ ተሻግሬ ልሂድና ራሱን ልቁረጠው” አለ፡፡
\v 10 ንጉሡ ግን፣ “እናንተ የጽሩያ ልጆች፣ እኔ ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? እርሱ የሚረግመኝ ምናልባት እግዚአብሔር፣ ‘ዳዊትን ርገመው’ ብሎት ይሆናል፡፡ ታዲያ እርሱን፣ ‘ንጉሡን ለምን ትረግማለህ? ሊለው የሚችለው ማን ነው?”
\s5
\v 11 ስለዚህ ዳዊት ለአቢሳና ለአገልጋዮቹ ሁሉ፣ “ከአብራኬ የወጣው ልጄ ነፍሴን ሊያጠፋት ከፈለገ፣ ይህ ብንያማዊ ምን ያህል ጥፋቴን አይፈልግ? እግዚአብሔር እንዲራገም አዞት ይሆናልና፣ ተዉት፣ ይራገም፡፡
\v 12 ምናልባት የተሰነዘረብኝን ውርደት እግዚአብሔር ተመልክቶ ስለ ዛሬው እርግማኑ በጎ ያደርግልኝ ይሆናል፡፡”
\s5
\v 13 ስለዚህም ዳዊትና ሰዎቹ በመንገዱ ጉዟቸውን ቀጠሉ፣ ሳሚም በኮረብታው ጥግ ጥግ እየሄደ ድንጋይ ይወረውር አቧራም ይበትንበት ነበር፡፡
\v 14 ከዚህ በኋላ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ደከሙ፣ እነርሱም ለምሽቱ በሚቆሙበት ጊዜ እርሱ ዕረፍቱ አደረገ፡፡
\s5
\v 15 አቤሴሎምና ከእነርሱ ጋር የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ በበኩላቸው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፣ አኪጦፌልም ከእርሱ ጋር ነበረ፡፡
\v 16 የዳዊት ወዳጅ፣ አርካዊው ኩሲም ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ፣ “ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ንገሥ! ንጉሥ ሆይ፣ ለዘላለም ንገሥ! ” አለው፡፡
\s5
\v 17 አቤሴሎምም ኩሲን፣ “ለወዳጅህ ያለህ ታማኝነት ይሄ ነው? ለምን ከእርሱ ጋር አልሄድህም? ” አለው፡፡
\v 18 ኩሲም አቤሴሎምን፣ “አይሆንም፣ ይልቁኑ እግዚአብሔርና ይህ ሕዝብ እንዲሁም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ከመረጡት ከእርሱ ጋር ነው እኔ የምሆነው፣ ከእርሱም ጋር እቆያለሁ፡፡
\s5
\v 19 ላገለግለው የሚገባኝ ሰው ማን ነው? በልጁስ ፊት ላገለግል አይገባኝምን? በአባትህ ፊት እንዳገለገልሁ በአንተም ፊት አገለግላለሁ፡፡”
\s5
\v 20 ከዚያ በኋላ አቤሴሎም ለአኪጦፌል፣ “ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክርህን ስጠን” አለው፡፡
\v 21 አኪጦፌልም ለአቤሴሎም፣ “ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ አባትህ ከተዋቸው ቁባቶቹ ጋር ግባና ተኛ፣ ከዚያም አንተ ለአባትህ መጥፎ ጠረን እንዳለው ሰው እንደሆንክበት እስራኤል ሁሉ ይሰማል፤ ከዚያም ከአንተ ጋር ያሉት ሰዎች ሁሉ እጅ ይበረታል፡፡”
\s5
\v 22 ስለዚህ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ ለአቤሴሎም ድንኳን ተከሉለት፤ አቤሴሎምም መላው እስራኤል እያየው ከአባቱ ቁባቶች ጋር ተኛ፡፡
\v 23 በዚያን ጊዜ አኪጦፌል ይሰጠው የነበረው ምክር ከእግዚአብሔር ከራሱ አፍ እንደ መስማት ያለ ነበር፡፡ ዳዊትም ሆነ አቤሴሎም ለአኪጦፌል ምክር የነበራቸው ግምት እንደዚህ ነበር፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ አኪጦፌል ለአቤሴሎም፣ “አሥራ ሁለት ሺህ ሰው መርጬ በዛሬይቱ ሌሊት አባትህን አሳድደዋለሁ፤
\v 2 በደከመውና ዐቅም ባነሰው ጊዜ ድንገት ደርሼ በማስፈራት አስደንቀዋለሁ፤ አብሮት ያለው ሕዝብም ይሸሻል፣ በንጉሡ ላይ ብቻ ጥቃት አደርስበታለሁ፡፡
\v 3 ሙሽራ ወደ ባሏ እንደምትመጣ ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፤ ሕዝቡም ሁሉ በአንተ ሥር በሰላም ይሆናል፡፡”
\v 4 አኪጦፌል የተናገረውም አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ሁሉ ደስ አሰኛቸው፡፡
\s5
\v 5 ከዚያ በኋላ አቤሴሎም፣ “አርካዊውን ኩሲን አሁን ጥሩትና እስቲ፣ እርሱ ደግሞ የሚለውን እንስማ” አለ፡፡
\v 6 ኩሲ ወደ አቤሴሎም በመጣ ጊዜ፣ አኪጦፌል ያለውን ከገለጸለት በኋላ፣ ኩሲን፣ “አኪጦፌል ያለውን እናድርግ? ካልሆነም የምትመክረንን አንተ ንገረን፡፡”
\v 7 ስለዚህ ኩሱ ለአቤሴሎም፣ “አኪጠፌል በዚህን ጊዜ የሰጠው ምክር መልካም አይደለም፡፡” ካለ በኋላ፣
\s5
\v 8 ኩሲ በመቀጠል፣ “አባትህና ሰዎቹ ብርቱ ተዋጊዎችና ግልገሎቿ በሜዳ እንደተነጠቁባት ድብ መራሮች እንደሆኑ አንተ ታውቃለህ፡፡ አባትህ የጦር ሰው ነው፣ በዛሬው ሌሊት ከሠራዊቱ ጋር አይተኛም፡፡
\v 9 እነሆ፣ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል፡፡ በውጊያው መጀመሪያ ላይ ከአንተ ሰዎች ጥቂቶቹ ቢሞቱ፣ ያንን የሰማ ማንኛውም ሰው፣ ‘አቤሴሎምን ይከተሉ በነበሩት ላይ እልቂት ተፈጽሟል’ ይላል፡፡
\v 10 ከዚያ በኋላ አባትህ ኃያል ሰው ስለሆነና ከእርሱም ጋር ያሉት በጣም ብርቱዎች መሆናቸውን መላው እስራኤል ስለሚያውቅ ልባቸው እንደ አንበሳ ልብ የሆነው እጅግ ጀግና የሆኑት እንኳን ይፈራሉ፡፡
\s5
\v 11 ስለዚህ እኔ የምመክርህ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ብዙ የሆነው ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ያለው መላው የእስራኤል ሕዝብ ወደ አንተ ይሰብሰብ፣ አንተም በግልህ ወደ ጦርነቱ ግባ፡፡
\v 12 ከዚያ በኋላ እርሱ በየትኛውም ቦታ ቢሆን እንመጣበታለን፣ ጤዛም ምድርን እንደሚሸፍን በላዩ ላይ እንወድቅበታለን፡፡ ከእርሱ ማንኛውንም ሰው ወይም እርሱን ራሱንም እንኳን ቢሆን በሕይወት አንተውም፡፡
\s5
\v 13 ወደ አንዲት ከተማ የሚያፈገፍግ እንኳ ቢሆን፣ እስራኤል ሁሉ ገመድ አምጥቶ አንድ እንኳ እስከማይቀር ድረስ ከተማይቱን ወደ ወንዝ ውስጥ ስበን እንከታታለን፡፡”
\v 14 ከዚያም አቤሴሎምና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ፣ “የአርካዊው ኩሲ ምክር ከአኪጦፌል ምክር ይልቅ የተሻለች ነች” አሉ፡፡ በአቤሴሎም ላይ ጥፋት ይመጣ ዘንድ እግዚአብሔር የአኪጦፌል መልካም ምክር ተቀባይነት እንዳያገኝ አደረገ፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም ኩሲ ለካህናቱ ለሳዶቅና ለአብያታር፣ “አኪጦፌል አቤሴሎምንና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ምን ምን ማድረግ እንዳለባቸው መክሮአቸው ነበር፣ እኔ ግን የተለየ ምክር ሰጠኋቸው፡፡
\v 16 እንግዲህ እናንተ ፈጥናችሁ ወደ ዳዊት ዘንድ ሂዱና ፣ ‘በአረባ ባለው የወንዙ መሻገሪያ እንዳታድር፣ ነገር ግን እንደ ምንም ብለህ ተሻገር፤ አለበለዚያ ንጉሡና አብሮት ያለው ሕዝብ በሙሉ ትዋጣላችሁ’ በሉት፡፡”
\s5
\v 17 በዚህ ጊዜ፣ ዮናታንና አኪማአስ በዓይንሮጌል ባለችው ምንጭ ይጠብቁ ነበር፣ ወደ ከተማ ሲገቡ እንዳይታዩ አንዲት ሴት አገልጋይ ወደ እነርሱ እየሄደች መልእከቶችን ታቀብላቸው ነበር፤ እነርሱም በዚያን ጊዜ ለዳዊት ሄደው ይነግሩት ነበር፡፡
\v 18 በዚህን ጊዜ ግን አንድ ወጣት አያቸውና ለአቤሴሎም ሄዶ ነገረ፡፡ ስለዚህ ዮናታንና አኪማአስ ፈጥነው በግቢው ውስጥ የውሃ ጉድጓድ ወደነበረው በብራቂም ወደ ነበረ ሰው ቤት መጡ፡፡
\s5
\v 19 የሰውዬው ሚስት የውሃ ጉድጓዱን መሸፈኛ ወስዳ በጉድጓዱ አፍ ላይ ዘረጋችው ከዚያ በኋላም ዮናታንና አኪማአስ በውሃ ጉድጓድ ዘንድ እንዳሉ ማንም እንዳያውቅ በላዩ ላይ እህል አሰጣችበት፡፡
\v 20 የአቤሴሎም ሰዎች በቤት ወደነበረችው ሴትዮ መጡና፣ “አኪማአስና ዮናታን ወዴት አሉ? ” አሏት፤ እርሷም፣ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” አለቻቸው፡፡ ስለዚህ ፈልገው ሊያገኟቸው ስላልቻሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
\s5
\v 21 እነርሱ ከሄዱ በኋላ አኪማአስና ዮናታን ከጉድጓዱ ወጡ፤ ወደ ዳዊትም ዘንድ ሄደው፣ “ተነሣና ፈጥነህ ወንዙን ተሻገር፣ ምክንያቱም አኪጦፌል አንተን በሚመለከት እንደዚህና እንደዚያ ብሎ ምክር ሰጥቶአል፡፡”
\v 22 ከዚያ በኋላ ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበረው ሕዝብ ተነሡ፣ የዮርዳኖስንም ወንዝ ተሻግረው ሄዱ፤ ሲነጋም ዮርዳኖስን መሻገር አቅቶት የቀረ አንድም ሰው አልነበረም፡፡
\s5
\v 23 አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተቀበሉት ባየ ጊዜ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወዳለበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፣ ጉዳዩንም መልክ ካስያዘ በኋላ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፡፡ በዚህ አኳኋን ሞተና በአባቱ መቃብር ተቀበረ፡፡
\s5
\v 24 ከዚያ በኋላ ዳዊት ወደ መሃናይም መጣ፤ አቤሴሎምም ከእርሱ ጋር ከነበሩት ከመላው የእስራኤል ሰዎች ጋር ዮርዳኖስን ተሻገረ፡፡
\v 25 ከዚህ በኋላም አቤሴሎም በኢዮአብ ምትክ አሜሳይን በሠራዊቱ ላይ ሾመ፤ አሜሳይ የእስራኤላዊው የዮቴር ልጅ ነበር፡፡ ዮቴር ከኢዮአብ እናት ከጽሩያ እህት ከናዖስ ልጅ ከአቢግያ ጋር ተኝቶ የነበረ ነው፡፡
\v 26 ከዚህ በኋላ እስራኤላውያንና አቤሴሎም ከበገለዓድ ምድር ሰፈሩ፡፡
\s5
\v 27 ዳዊት ወደ መሃናይም በመጣ ጊዜ ከአሞናውያን ከተማ ከራባ የመጣው፣ የናዖስ ልጅ ሾቢ፣ ከሎዶባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፣
\v 28 መተኛ ምንጣፎችና ብርድ ልብሶች፣ ጎድጓዳ ሳህኖችና ድስቶች እንዲሁም ዳዊትና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሰዎች ይበሉ ዘንድ ስንዴ፣ የገብስ ዱቄት፣ የተጠበሰ እሸት፣ ባቄላ፣ ምስር፣
\v 29 ማር፣ ቅቤ፣ በግና እርጎ አመጡ፡፡ እነዚህ ሰዎች፣ “ሕዝቡ በምድረ-በዳ ተርቦአል፣ ደክሞአል ደግሞም ተጠምቶአል” ብለው ነበር፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ዳዊት አብሮት የነበሩትን ወታደሮች ቆጠረ፤ በእነርሱም ላይ የሻለቆችንና የመቶ አለቆችን ሾመላቸው፡፡
\v 2 ከዚህ በኋላ ዳዊት ሠራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩይ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጌታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው፡፡ ንጉሡም ለሠራዊቱ፣ “እኔ ራሴም አብሬአችሁ በእርግጥ እወጣለሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 3 ሰዎቹ ግን፣ “አንተ መውጣት የለብህም፤ እንድንሸሽ ብንገደድ፣ ሰዎቹ ስለ እኛ ግድ አይኖራቸውም ወይም ከእኛ ግማሻችን እንኳን ብንሞት ደንታም የላቸውም፡፡ አንተ ግን ከእኛ አሥር ሺሁ ያህል ነህ፤ ስለዚህ በከተማ ሆነህ ልትረዳን ዝግጁ ብትሆን የተሻለ ነው፡፡” አሉት፡፡
\v 4 ስለዚህ ንጉሡ፣ “መልካም መስሎ የታያችሁን ሁሉ አደርጋለሁ” አላቸው፡፡ ስለዚህ ሠራዊቱ ሁሉ በመቶና በሺህ እየሆነ ተሰልፎ ሲወጣ ንጉሡ በከተማይቱ ቅጥር በር ቆሞ ነበር፡፡
\s5
\v 5 ንጉሡ ኢዮአብን፣ አቢሳንና ኢታይን፣ “ለእኔ ስትሉ ለወጣቱ ለአቤሴሎም ራሩለት” ብሎ አዘዛቸው፡፡ ሕዝቡ ሁሉ አቤሴሎምን በሚመለከት ንጉሡ ይህንን ትዕዛዝ ለአዛዦቹ ሲሰጣቸው ሰሙ፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ እስራኤልን ይወጋ ዘንድ ሠራዊቱ ከከተማ ወጣ፤ ውጊያውም እስከ ኤፍሬም ደን ተስፋፋ፡፡
\v 7 በዚያ የእስራኤል ሠራዊት በዳዊት ወታደሮች ድል ሆነ፤ በዚያ ሃያ ሺህ ሰው የሞተበት ታላቅ እልቂት በዚያ ቀን ነበረ፡፡
\v 8 ውጊያው በገጠሩ ሁሉ ተስፋፋ፣ በሰይፍ ካለቀውም ይልቅ ጫካ ውጦ ያስቀረበው ሰው በለጠ፡፡
\s5
\v 9 አቤሴሎም ከዳዊት ሰዎች ከጥቂቶቹ ጋር ተገናኘ፡፡ አቤሴሎምም በበቅሎው እየጋለበ ነበር፤ በቅሎውም ጥቅጥቅ ያሉ ቅርንጫፎች በነበሩት የወርካ ዛፍ ሥር ያልፍ ነበርና ራሱ በዛፉ ቅርንጫፎች ተያዘ፡፡ የተቀመጠበት በቅሎ ከሥሩ አልፎ ሲሄድ እርሱ በሰማይና በምድር ተንጠልጥሎ ቀረ፡፡
\v 10 አንድ ሰው ይህንን ተመልክቶ፣ “እነሆ፣ አቤሴሎም በወርካ ዛፍ ላይ ተንጥልጥሎ አየሁት” ብሎ ለኢዮአብ ነገረው፡፡
\v 11 ኢዮአብም ስለ አቤሴሎም ለነገረው ሰው፣ “እነሆ፣ አንተ አየኸው፣ ታዲያ መትተህ ለምን ወደ መሬት አልጣልከውም? እኔ አሥር የብር ሰቅልና ቀበቶ በሸለምኩህ ነበር፡፡”
\s5
\v 12 ሰውዬውም ለኢዮአብ፣ “አሥር ሺህ ሰቅል የምቀበል ብሆንም እንኳን እጄን ዘርግቼ የንጉሡን ልጅ ባልነካሁም ነበር፤ ምክንያቱም አንተን፣ አቢሳንና ኢታይን ንጉሡ፣ ‘አንድም ሰው ወጣቱን አቤሴሎምን እንዳይነካው’ ብሎ ሲያዛችሁ ሁላችንም ሰምተናል፡፡
\v 13 ውሸት በመናገር ሕይወቴን አደጋ ላይ ብጥል እንኳን (ከንጉሡ የሚደበቅ ምንም ነገር አይኖርምና) አንተ ታጋልጠኝ ነበር፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 14 ከዚህ በኋላ ኢዮአብ፣ “እኔ አንተን አልጠብቅም” አለ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብ ሦስት ጦር ወስዶ ገና በሕይወት እያለና በወርካው ዛፍ ላይ ተንጠልጥሎ ሳለ በአቤሴሎም ልብ ላይ ተከላቸው፡፡
\v 15 ከዚያ በኋላም ከኢዮአብ ጋሻ ጃግሬዎች አሥሩ አቤሴሎምን በመክበብ ወግተው ገደሉት፡፡
\s5
\v 16 ከዚያም ኢዮአብ ቀንደ-መለከቱን ነፋ፣ ኢዮአብም ከልክሏቸው ስለነበረ ሠራዊቱ እስራኤልን ከማሳደድ ተመለሰ፡፡
\v 17 አቤሴሎምን ወስደው በጫካ ውስጥ ወደነበረ አንድ ትልቅ ጉድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ እስራኤልም ሁሉ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ በሚሸሽበት ጊዜ በአስከሬኑ ላይ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፡፡
\s5
\v 18 አቤሴሎም፣ “የስሜን መታሰቢያ የሚያስጠራ ልጅ የለኝምና” በማለት ገና በሕይወቱ ሳለ ለራሱ አንድ ትልቅ የድንጋይ ሐውልት በንጉሡ ሸለቆ አቁሞ ነበር፡፡ ሐውልቱንም በስሙ ጠርቶት ስለነበረ፣ እስከዚህ ቀን ድረስ ‘የአቤሴሎም ሐውልት’ ተብሎ ይጠራል፡፡
\s5
\v 19 በዚህ ጊዜ የሳዶቅ ልጅ አኪማአስ እግዚአብሔር ከጠላቶቹ እንዳዳነው ሄጄ ለንጉሡ የምሥራች ልንገረው አለ፡፡
\v 20 ኢዮአብም፣ “ዛሬ የምሥራቹን የምታደርስለት አንተ አይደለህም፣ ሌላ ጊዜ ታደርስለታለህ፤ የንጉሡ ልጅ ስለሞተ ምንም የምሥራች አታደርስም፡፡”
\s5
\v 21 ከዚያም ኢዮአብ ለአንድ ኩሻዊ፣ “ሂድና ለንጉሡ ያየኸውን ተናገር” አለው፡፡ ኩሻዊውም ኢዮአብን እጅ ነሥቶ እየሮጠ ሄደ፡፡
\v 22 የሳዶቅ ልጅ አኪማአስም እንደገና ለኢዮአብ፣ “ምንም ዓይነት ነገር ይሁን፣ እባክህ፣ ኩሻዊውን ተከትዬው ልሩጥ” አለው፡፡ ኢዮአብም፣ “ለየምሥራቹ ምንም ብድራት እንደማታገኝ እያወቅህ፣ ልጄ ሆይ፣ ለምን ትሮጣለህ? ” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 23 “የሆነው ይሁን፣ እሮጣለሁ” አለ፣ አኪማአስ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብ ፣ “እንግዲያውስ፣ ሩጥ” ብሎ መለሰለት፡፡ ከዚያም አኪማአስ በሜዳው መንገድ በኩል ሮጠ፣ ኩሻዊውንም ቀደመው፡፡
\s5
\v 24 ዳዊት በውስጠኛውና በውጭኛው በሮች መካከል ተቀምጦ ነበር፡፡ ጠባቂው ቅጥሩ ላይ ወዳለው ወደ በሩ ሰገነት ጣራ ወጥቶ ወደ ውጭ ዓይኑን አንስቶ ሲመለከት አንድ ብቻውን የሚሮጥ ሰው እየተቃረበ ነበር፡፡
\v 25 ጠባቂው ተጣራና ለንጉሡ ነገረው፤ ከዚያም ንጉሡ፣ “ብቻውን ከሆነ መልካም ዜና በአንደበቱ አለ” አለ፡፡ ሯጩ እየተጠጋ መጥቶ ወደ ከተማይቱ ቀረበ፡፡
\s5
\v 26 ከዚያም ጠባቂው ሌላ የሚሮጥ ሰው አስተዋለ፤ ጠባቂውም ዘበኛውን ጠራና፣ “እነሆ፣ ብቻውን የሚሮጥ ሌላ ሰው አለ” አለው፡፡ ንጉሡም፣ “እርሱም መልካም ዜና አለው” አለ፡፡
\v 27 ስለዚህ ጠባቂው፣ “ከፊት እየሮጠ ያለው ሰው አሯሯጥ የሳዶቅን ልጅ የአኪማአስን ሩጫ ይመስለኛል” አለ፡፡ ንጉሡም፣ “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፣ እርሱም የሚመጣው የምሥራች ይዞ ነው” አለ፡፡
\s5
\v 28 ከዚያ በኋላ አኪማአስ ተጣርቶ ለንጉሡ፣ “ሁሉም ደኅና ነው” አለና በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሥቶ፣ ወደ መሬት እያቀረቀረ፣ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠህ እግዚአብሔር አምላክህ የተባረከ ይሁን” አለው፡፡
\v 29 ንጉሡም፣ “ወጣቱ አቤሴሎም ደህና ነውን? ሲል ጠየቀ፡፡ አኪማአስም፣ “ኢዮአብ እኔን የንጉሡን አገልጋይ በላከኝ ጊዜ ትልቅ ሁካታ ነበር፣ ምን እንደሆነ ግን እኔ አላወቅሁም” አለው፡፡
\v 30 ከዚያ በኋላ ንጉሡ፣ “እልፍ በልና ቁም” አለው፡፡ ስለዚህ አኪማአስ እልፍ ብሎ ዝም ብሎ ቆመ፡፡
\s5
\v 31 ከዚያ በኋላ ወዲያውኑ ኩሻዊው ደረሰና፣ “ለጌታዬ ለንጉሡ የምሥራች አለኝ፣ እግዚአብሔር በንጉሡ ላይ የተነሡብህን ሁሉ ዛሬ ተበቅሎልሃልና” አለው፡፡
\v 32 ንጉሡም ኩሻዊውን፣ “ወጣቱ አቤሴሎም ደህና ነውን? ” አለው፡፡ ኩሻዊውም፣ “የጌታዬ የንጉሡ ጠላቶች እንዲሁም በእርሱ ላይ ጉዳት ለማድረስ በአንተ ላይ የሚነሡብህ ሁሉ እንደዚያ ወጣት ይሁኑ” ብሎ መለሰለት፡፡
\v 33 በዚያን ጊዜ ንጉሡ ጥልቅ የሆነ ሐዘን አዘነ፤ በቅጥሩ በር ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ገብቶም አለቀሰ፡፡ እየሄደም ሳለ፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ልጄ፣ ልጄ! ” እያለ ያለቅስ ነበር፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 “እነሆ፣ ንጉሡ ለልጁ ለአቤሴሎም እያለቀሰ ነው” ተብሎ ለኢዮአብ ተነገረው፡፡
\v 2 “ንጉሡ ለልጁ እያለቀሰ ነው” የሚለውን ሠራዊቱ በዚያን ቀን ሰምቶ ስለነበረ፣ የዚያን ቀኑ ድል ለሠራዊቱ ወደ ኃዘን ቀንነት ተለወጠ፡፡
\s5
\v 3 ከጦርነት ሸሽተው የሚመጡ በኀፍረት ሹልክ ብለው እንደሚገቡ በዚያን ቀን ወታደሮቹ ሹልክ ብለው ወደ ከተማ ይገቡ ነበር፡፡
\v 4 ንጉሡ ፊቱን ሸፍኖና ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፣ አቤሴሎም፣ ልጄ፣ ልጄ! ” እያለ አለቀሰ፡፡
\s5
\v 5 ከዚያም ኢዮአብ ወደ ቤት ወደ ንጉሡ ዘንድ ገብቶ፣ “የሚወዱህን ትጠላለህና የሚጠሉህንም ትወዳለህና ዛሬ ሕይወትህን፣ የወንዶችና የሴቶች ልጆችህን ሕይወት፣ የሚስቶችህን ሕይወት እንዲሁም የቁባቶችህን ሕይወት ያዳኑትን የወታደሮችህን ሁሉ ፊት አሳፍረሃል፡፡
\v 6 የሚጠሉህን ትወዳለህ የሚወዱህን ትጠላለህ፤ የጦር አዛዦችና ወታደሮች ለአንተ ምንም እንዳይደሉ ዛሬ አሳይተሃልና፡፡ ዛሬ አቤሴሎም በሕይወት በኖረና እኛ ሁላችንም ብንሞት፣ ያ ደስ ያሰኝህ እንደነበረ አምናለሁ፡፡
\s5
\v 7 ስለዚህ አሁንም ተነሥተህ ውጣና ለወታደሮችህ በትሕትና ተናገራቸው፣ ባትሄድ ግን፣ በእግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ በዛሬው ሌሊት አንድም ሰው ከአንተ ጋር አይቀርም፡፡ ይሄ ደግሞ ከልጅነትህ ጀምሮ እስካሁን ከደረሰብህ መከራ ሁሉ የከፋ ይሆንብሃል፡፡”
\v 8 ስለዚህ ንጉሡ ተነሥቶ በከተማይቱ በር አጠገብ ተቀመጠ፣ ለሰዎችም ሁሉ፣ “እነሆ፣ ንጉሡ በበሩ ተቀምጦአል” ተብሎ ተነገራቸው፡፡ ከዚያ በኋላም ሰዎች ሁሉ በንጉሡ ፊት መጡ፡፡ በዚህን ጊዜ በእስራኤል ሰው ሁሉ ወደየቤቱ ሸሽቶ ነበር፡፡
\s5
\v 9 በመላው እስራኤል በየነገዱ ያሉ ሰዎች ሁሉ እርስ በርሳቸው፣ “ንጉሡ ከጠላቶቻችን እጅ አስጥሎናል፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ አድኖናል፤ አሁን ደግሞ ከአቤሴሎም ሸሽቶ ከአገር ወጥቷል፡፡
\v 10 በላያችን ላይ የቀባነውም አቤሴሎም በጦርነቱ ተገድሏል፡፡ ስለዚህ ንጉሡን መልሰን ስለማምጣት ለምን አንነጋገርም? ” እያሉ ይነጋገሩ ነበር፡፡
\s5
\v 11 ንጉሥ ዳዊት ወደ ካህናቱ ወደ ሳዶቅና ወደ አብያታር ልኮ፣ “ለይሁዳ ሽማግሌዎች፣ ‘ወደ ቤተ መንግሥቱ ይመልሰው ዘንድ የመላው የእስራኤል ልብ ለንጉሡ ድጋፍ የሚሰጥ ነውና፣ ንጉሡን ወደ ቤተ መንግሥቱ ለመመለስ እናንተ የመጨረሻዎቹ የምትሆኑት ለምንድን ነው?
\v 12 እናንተ የሥጋዬ ቁራጭ የአጥንቴ ፍላጭ ናችሁ፡፡ ታዲያ፣ ንጉሡን ለመመለስ እናንተ የመጨረሻዎቹ የሆናችሁት ለምንድን ነው?
\s5
\v 13 ለአሜስያም፣ ‘አንተስ የሥጋዬ ቁራጭ የአጥንቴ ፍላጭ አይደለህምን? ከአሁን ጀምሮ በኢዮአብ ምትክ የሠራዊቴ አዛዥ ባለደርግህ እግዚአብሔር ይህንን ያድርግብኝ፣ ከዚህም የባሰ ይጨምርብኝ’” በሉ ብሎ መልእክት ላከ፡፡
\v 14 “አንተና ሰዎችህ ሁሉ ተመለሱ” ብለው ወደ ንጉሡ መልእከት እስኪልኩ ድረስ የአንድ ሰው ልብ እንደነበራቸው ያህል የይሁዳን ሁሉ ልብ ማረከ፡፡
\v 15 ስለዚህ ንጉሡ ተመልሶ ወደ ዮርዳኖስ መጣ፡፡ የይሁዳም ሰዎች ዮርዳኖስን ሲሻገር ለማጀብ፣ ንጉሡን ለመገናኘት ወደ ጌልጌላ መጡ፡፡”
\s5
\v 16 ከብራቂም የሆነው የጌራ ልጅ ሳሚ ንጉሥ ዳዊትን ለመቀበል ከይሁዳ ሰዎች ጋር ፈጥኖ ወረደ፡፡
\v 17 ከእርሱ ጋር ከብንያም አንድ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤ ደግሞም ከሲባ ከሳዖል አገልጋይ ጋር አሥራ አምስት ልጆቹና ሃያ አገልጋዮቹ ነበሩ፡፡ በንጉሡ ፊት ዮርዳኖስን አቋረጠው ተሻገሩ፡፡
\v 18 የተሻገሩት የንጉሡን ቤተሰብ ለማምጣትና እርሱ መልካም ነው ያለውን ለማድረግ ነበር፡፡
\s5
\v 19 ሳሚ ለንጉሡ፣ “ጌታዬ እኔን በደለኛ አድርጎ አይቁጠረኝ ወይም ጌታዬ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም በወጣበት ቀን ባሪያህ በግትረኛነት ያደረገውን ትኩረት አይስጠው፡፡ ንጉሥ ሆይ፣ እባክህ ይህንን በልብህ አታኑረው፡፡
\v 20 ባሪያህ ኃጢአት ማድረጌን አውቃለሁ፡፡ ከመላው የዮሴፍ ቤት ጌታዬ ንጉሡን ለመቀበል የመጀመሪያ ሆኜ ዛሬ የመጣሁት እነሆ፣ ለዚህ ነው፡፡” አለ፡፡
\s5
\v 21 ነገር ግን የጽሩይ ልጅ አቢሳ፣ “እግዚአብሔር የቀባውን ተራግሟልና ስለዚህ ጉዳይ ሳሚ ሊገደል አይገባውምን? ”
\v 22 ከዚያ በኋላ ዳዊት፣ “ዛሬ ለእኔ ጠላቶች ትሆኑኝ ዘንድ እናንተ የጽሩያ ልጆች ከእናንተ ጋር ምን አለኝ? ዛሬ በእስራኤል አንድ ሰው ሊገደል ይገባዋል? በእስራኤል ላይ ንጉሥ መሆኔን ያወቅሁት በዛሬው ቀን አይደለምን? ”
\v 23 ስለዚህ ንጉሡ ለሳሚ፣ “አትሞትም” አለው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ በመሐላ ቃል ገባለት፡፡
\s5
\v 24 ከዚያ በኋላ የሳዖል ልጅ ሜምፊቦስቴ ንጉሡን ለመቀበል መጣ፡፡ ንጉሡ ከሄደበት ቀን ጀምሮ በሰላም ወደ ቤቱ እስከተመለሰበት ቀን ድረስ በእግሩ ሱሪ አላስገባም፣ ጢሙን አልተላጨም ወይም ልብሱን አላጠበም፡፡
\v 25 ስለዚህም ንጉሡን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም በመጣ ጊዜ፣ ንጉሡ፣ “ሜምፊቦስቴ ከእኔ ጋር ለምን አልሄድክም? ” አለው፡፡
\s5
\v 26 እርሱም፣ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ አገልጋዬ አታለለኝ፣ ምክንያቱም፣ ‘እኔ ባሪያህ ሽባ ስለሆንኩኝ እንድቀመጥበትና ከንጉሡ ጋር እንድሄድ አህያዬን እጭናለሁ’ ብዬ ነበርና፡፡
\v 27 አገልጋዬ ሲባ እኔን ባሪያህን ለጌታዬ ለንጉሡ አማ፤ ጌታዬ ንጉሡ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነው፡፡ ስለዚህ በዓይንህ ፊት መልካም መስሎ የታየህን አድርግብኝ፡፡
\v 28 የአባቴ ቤት ሰዎች ሁሉ በጌታዬ በንጉሡ ዘንድ የሞት ሰዎች ነበሩና፤ ነገር ግን ባሪያህን በገበታህ ከሚበሉት አንዱ አድርገህ አስቀመጥኸኝ፡፡ ስለዚህ አሁንም በንጉሡ ፊት ልቅሶዬን ለመቀጠል እኔ ምን መብት አለኝ?”
\s5
\v 29 ከዚያ በኋላም ንጉሡ፣ “ከዚህ በላይ መግለጫ መስጠት ምን ያስፈልጋል? እርሻውን አንተና ሲባ እንድትካፈሉት ወስኛለሁ፡፡”
\v 30 ስለዚህ ሜምፊቦስቴ ለንጉሡ፣ “ጌታዬ ንጉሡ ወደ ራሱ ቤት በሰላም ስለመጣ፣ ግድ የለም፣ እርሱ ሁሉንም ይውሰደው” አለው፡፡
\s5
\v 31 ከዚያም ገለዓዳዊው ቤርዜሊ ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን ለመሻገር ከሮግሊም መጣ፣ ንጉሡም ዮርዳኖስን ሲሻገር አጀበው፡፡
\v 32 ቤርዜሊ ሰማንያ ዓመት የሆነው ሽማግሌ ሰው ነበር፡፡ እጅግ ባለጠጋ ሰው ስለነበረ፣ ንጉሡ በመሃናይም በቆየበት ጊዜ ስንቅ አምጥቶለት ነበር፡፡
\v 33 ንጉሡም ለቤርዜሊ፣ “ከእኔ ጋር ና፣ እኔ በኢየሩሳሌም የምትመገበውን አቀርብልሃለሁ” አለው፡፡
\s5
\v 34 ቤርዜሊም ለንጉሡ፣ “ከንጉሡ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም እሄድ ዘንድ ከሕይወት ዘመኔ ምን ያህል ቢቀር ነው?
\v 35 እኔ ሰማንያ ዓመቴ ነው፤ መልካሙንና ክፉውን መለየት እችላለሁን? ባሪያህ የሚበላውንስ ሆነ የሚጠጣውን ጣዕም መለየት ይችላልን? የሚዘፍኑ ወንዶችንና የሚዘፍኑ ሴቶችን ከእንግዲህ መስማት እችላለሁን? ስለዚህ ባሪያህ በጌታዬ በንጉሡ ላይ ለምን ሸክም ይሆናል?
\v 36 ባሪያህ የሚፈልገው ከንጉሡ ጋር ዮርዳኖስን መሻገር ብቻ ነው፡፡ ንጉሡ ለባሪያው ይህንን ያህል ብድራት ለምን ይከፍለኛል?
\s5
\v 37 በአገሬ እሞት ዘንድ፣ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እቀበር ዘንድ፣ እባክህ ወደ አገሬ እንድመለስ ፍቀድልኝ፡፡ ነገር ግን አገልጋይህ ከመዓም ከዚህ አለ፣ እርሱ ከአንተ ጋር ይሻገር፣ የመሰለህን መልካም ነገር አድርግለት፡፡”
\s5
\v 38 ንጉሡም፣ “ከመዓም ከእኔ ጋር ይሻገራል፣ ለአንተም መልካም መስሎ የታየህን አደርግለታለሁ፤ ከእኔም የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር እኔ አደርግልሃለሁ፡፡”
\v 39 ከዚያም ሰዎቹ ሁሉ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፤ ከዚያም ንጉሡ ተሻገረ፣ ንጉሡም ቤርዜሊን ሳመው ባረከውም፡፡ ከዚህ በኋላ ቤርዜሊ ወደ ራሱ አገር ተመለሰ፡፡
\s5
\v 40 ስለዚህ ንጉሡ ወደ ጌልጌላ ተሻገረ፣ ከመዓምም ከእርሱ ጋር ተሻገረ፡፡ የይሁዳ ሠራዊት ንጉሡንና የእስራኤልን ግማሽ ሠራዊት ይዞ ተመለሰ፡፡
\v 41 ወዲያውም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ንጉሡ መጥተው ለንጉሡ፣ “ወንድሞቻችን የይሁዳ ሰዎች አንተን ዳዊትንና ቤተሰቡን እንዲሁም የዳዊትን ሰዎች ሰርቀው ዮርዳኖስን አሻግረው ለምን አመጧቸው?”
\s5
\v 42 ስለዚህ የይሁዳ ሰዎች ለእስራኤል ሰዎች፣ “ይህንን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለሆነ ነው፡፡ ታዲያ እናንተ በዚህ ለምን ትቆጣላችሁ? እኛ የበላነውና ንጉሡ መክፈል ያለበት አንዳች ነገር አለ? ለእኛስ አንዳች ስጦታ ሰጥቶናል? ”
\v 43 የእስራኤል ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች፣ “እኛ ከዳዊት ጋር የሚዛመዱ አሥር ነገዶች አሉን፣ ስለዚህ እኛ ከእናንተ ይልቅ በዳዊት ዘንድ መብት አለን፡፡ ታዲያ እናንተ እኛን ለምን ትንቁናላችሁ? ንጉሡን ለማምጣት ያቀረብነው ሃሳብ በመጀመሪያ ሊሰማ የሚገባው አልነበረምን? ነገር ግን የይሁዳ ሰዎች የሰጡት መልስ የእስራኤል ሰዎች ከሰጡት መልስ ይልቅ እጅግ የከረረ ነበር፡፡”
\s5
\c 20
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ በዚሁ ስፍራ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የተባለ አንድ ችግር ፈጣሪ ብንያማዊ ነበር፡፡ እርሱም መለከት ነፍቶ፣ “እኛ ከዳዊት ጋር ድርሻ የለንም፣ ከእሴይ ልጅም ጋር ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፣ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ ይመለስ” አለ፡፡
\v 2 ስለዚህ የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ዳዊትን ከድተው የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ተከተሉ፡፡ የይሁዳ ሰዎች ግን ከዮርዳኖስ አንስተው እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ንጉሣቸውን አጥብቀው ተከተሉ፡፡
\s5
\v 3 ዳዊት በኢየሩሳሌም ወዳለው ቤተ መንግሥቱ በመጣ ጊዜ ቤተ መንግሥቱን እንዲጠብቁ ትቶአቸው የነበሩትን ዐሥሩን ቁባቶች በአንድ ቤት ውስጥ አስገብቷቸው በአንድ ዘበኛ እንዲጠበቁ አደረገ፡፡ የሚያስፈልጋቸውን አቀረበላቸው፣ ነገር ግን ከዚያ በኋላ ከእነርሱ ጋር አልተኛም፡፡
\s5
\v 4 እስከ ዕለተ ሞታቸው ድረስ ተዘግቶባቸው እንደ መበለት ይኖሩ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ንጉሡ ለአሜሳይ፣ “በሦስት ቀን ውስጥ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ እንዲሰባሰቡ ጥራቸው፣ አንተም እዚህ መገኘት አለብህ” አለው፡፡
\v 5 ስለዚህ አሜሳይ የይሁዳ ሰዎች እንዲሰባሰቡ ለመጥራት ሄደ፣ ነገር ግን ንጉሡ ካዘዘው ቀነ-ገደብ በላይ ቆየ፡፡
\s5
\v 6 ስለዚህ ዳዊት ለአቢሳ፣ “አሁን የቤክሪ ልጅ ሳቤዔ አቤሴሎም ካደረሰው ይልቅ የባሰ ጉዳት ያደርስብናል፡፡ የጌታህን አገልጋዮች ወታደሮቼን ያዝና አሳደው፣ አለበለዚያ የተመሸጉ ከተሞችን ያገኝና ከዓይናችን ይሰወራል፡፡” አለው፡፡
\v 7 በዚያን ጊዜ የኢዮአብ ሰዎች ከከሊታውያን ከፈሊታውያን እንዲሁም ከሌሎች ኃያላን ጦረኞች ጋር ተከትለውት ወጡ፡፡ የቤክሪን ልጅ ሳቤዔን ያሳድዱ ዘንድ ከኢየሩሳሌም ወጡ፡፡
\s5
\v 8 ገባዖን ከሚገኘው ታላቅ ዐለት በደረሱ ጊዜ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፣ ኢዮአብ በሰገባው ውስጥ የገባ ሰይፍ በወገቡ የታጠቀበትን ቀበቶ የሚያካትት የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ነበር፡፡ ወደፊት እየተራመደ ሳለም ሰይፉ ወደቀ፡፡
\s5
\v 9 ኢዮአብም አሜሳይን፣ “ወንድሜ ሆይ፣ ደህና ነህን? ” አለው፡፡ ኢዮአብም አሜሳይን እንደሚያፈቅረው አድርጎ ለመሳም ጢሙን ይዞ ሳበው፡፡
\v 10 አሜሳይ ኢዮአብ በግራ እጁ ይዞት የነበረውን ጩቤ አላስተዋለም፡፡ ኢዮአብ አሜሳይን ሆዱን ወጋው፣ ሆድ-ዕቃውም በምድር ላይ ተዘረገፈ፡፡ ኢዮአብ እንደገና አልወጋውም፣ አሜሳይም ሞተ፡፡ ስለዚህ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቤክሪን ልጅ ሳቤዔን አሳደዱ፡፡
\s5
\v 11 ከዚያ በኋላ ከኢዮአብ ሰዎች አንዱ በአሜሳይ አጠገብ ቆመና፣ “ኢዮአብን የሚደግፍና የዳዊት የሆነ ኢዮአብን ይከተል” አለ፡፡
\v 12 በዚህን ጊዜ አሜሳይ በደም ተጨማልቆ በመንገዱ መካከል ወድቆ ነበር፡፡ ሰዎች ሁሉ ቆመው እንደቀሩ ሰውዬው ተመልክቶ የአሜሳይን ሬሳ ከመንገድ ጎትቶ ወደ እርሻ ውስጥ አስገባው፡፡ ወደ አጠገቡ የደረሰ ማንኛውም ሰው ቆሞ ይቀር እንደነበረ ተመልክቶ ልብስ በላዩ ጣል አደረገበት፡፡
\v 13 አሜሳይ ከመንገድ ዞር ከተደረገ በኋላ የቤክሪ ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ሰዎች ሁሉ ኢዮአብን ተከተሉ፡፡
\s5
\v 14 ሳቤዔአም በእስራኤል ነገዶች ሁሉ መካከል አልፎ ወደ አቤል ቤትማዓካና ተሰባስበው ሳቤዔን ያሳድዱ ወደነበሩት ወደ መላው የቤክሪያውያን ግዛት መጣ፡፡
\v 15 ደረሱበትና አቤል ቤትመዓካ ላይ ከበቡት፡፡ በከተማይቱም ላይ ግድግዳውን አስጠግተው የአፈር ድልድል ሠሩበት፡፡ ከኢዮአብ ጋር የነበረውም ሠራዊት ግንቡን ለመናድ ደበደበው፡፡
\v 16 ከዚያ በኋላ አንድ ብልህ ሴት ከከተማ ውስጥ ተጣራችና፣ “ስማኝ፣ እባክህን ስማኝ ኢዮአብ፤ እንዳነጋግርህ ወደዚህ ጠጋ በል” አለችው፡፡
\s5
\v 17 ስለዚህ ኢዮአብ ጠጋ አለ፣ ሴቲቱም፣ “አንተ ኢዮአብ ነህን? ” አለችው፡፡ እርሱም፣ “አዎን፣ ነኝ” አለ፡፡ እርሷም ከዚያ በኋላ ለእርሱ፣ “የባሪያህን ቃል ስማ” አለችው፡፡ እርሱም፣ “እየሰማሁ ነው” ብሎ መለሰላት፡፡
\v 18 ከዚያ በኋላም እርሷ፣ “በቀደሙት ጊዜያት ‘በእርግጥ ምክርን ከአቤል ጠይቅ ምክሩም ችግሮችን ይፈታል’ ይሉ ነበር፡፡
\v 19 እኛ በእስራኤል ውስጥ እጅግ ሰላማዊና ታማኝ ከሆኑት ከተሞች አንዱ ነን፡፡ በእስራኤል ውስጥ እናት የሆነችውን ከተማ ለማጥፋት እየሞከርክ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ርስት ለምን ለመዋጥ ትፈልጋለህ?”
\s5
\v 20 ስለዚህ ኢዮአብ፣ “መዋጥ ወይም ማጥፋት ከእኔ የራቀ ይሁን፣
\v 21 ያ እውነት አይደለም፡፡ ነገር ግን ከኮረብታማው ከኤፍሬም አገር የሆነ ሳቤዔ የተባለ የቤክሪ ልጅ እጁን በንጉሡ ላይ ፣ በዳዊት ላይ አንስቷል፤ እርሱን ብቻ አሳልፋችሁ ስጡኝ፣ ከተማውን ለቅቄ እወጣለሁ” ብሎ መለሰላት፡፡ ሴቲቱም ለኢዮአብ፣ “ራሱ በቅጥሩ ላይ ይወረወርልሃል” አለችው፡፡
\v 22 ከዚያም ሴቲቱ በጥበብዋ ወደ ሕዝቡ ሁሉ ሄደች፡፡ የቤክሪን ልጅ የሳቤዔን ራስ ቆርጠው በቅጥሩ ላይ ለኢዮአብ ወረወሩለት፡፡ እርሱም ቀንደ-መለከቱን ነፋ፣ የኢዮአብም ሰዎች ከተማይቱን ለቀው እያንዳንዱ ሰው ወደየቤቱ ሄደ፡፡
\s5
\v 23 በዚህን ጊዜ ኢዮአብ በሠራዊቱ ሁሉ ላይ የበላይ ነበር፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ ደግሞ በከሊታውያንና በፈሊያታውያን ላይ አለቃ ሆነ፡፡
\v 24 አዶኒራም በግዳጅ ሥራ ላይ ለተሰማሩት አለቃ ሆነ፣ የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ ደግሞ ታሪክ ጸሐፊ ሆነ፤
\v 25 ሱሳ ጸሐፊ፣ ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ፤
\v 26 እንዲሁም የኢያዕር ሰው ዒራስ የዳዊት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነ፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 በዳዊት ዘመን ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ራብ ሆነ፣ ዳዊትም የእግዚአብሔርን ፊት ፈለገ፡፡ስለዚህ እግዚአብሔር፣ “ሳዖልና ገዳይ ቤተሰቡ ገባዖናውያንን እንዲሞቱ ስላደረገ ይህ ረሃብ በአንተ ላይ ነው” አለ፡፡
\s5
\v 2 እንግዲህ ገባዖናውያን ከአሞራውያን የተረፉ እንጂ የእስራኤል ሕዝብ ወገን አልነበሩም፡፡ የእስራኤል ሕዝብ እንደማይገድሏቸው ምለውላቸው ነበር፣ ሳዖል ግን ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ ከነበረው ቅናት የተነሣ እንዲሁ ሁሉንም የመግደል ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡
\v 3 ስለዚህ ዳዊት ገባዖናውያንን በአንድነት ጠራቸውና፣ “ምን ላደርግላችሁ? የእርሱን በጎነትና ተስፋ ቃሉን የሚወርሱትን የእግዚአብሔርን ሕዝብ ትባርኩ ዘንድ ስርየትን እንዴት ማድረግ እችላለሁ? ” አላቸው፡፡
\s5
\v 4 ገባዖናውያንም፣ “በእኛና በሳዖል ወይም በቤተሰቡ መካከል ያለው የብርና የወርቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ በእስራኤልም ውስጥ ማንም ሰው እንየዲገደል የምናደርግ እኛ አይደለንም፡፡” ብለው መለሱለት፡፡ ዳዊትም፣ “የምትጠይቁትን ማንኛውንም ነገር ቢሆን እኔ ያንን አደርግላችኋለሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 5 እነርሱም ለንጉሡ፣ “እንድንጠፋና በእስራኤል ክልል ውስጥ ምንም ስፍራ እንዳይኖረን ሁላችንንም ለመግደል ሙከራ ካደረገውና በእኛ ላይ ሤራ ካውጠነጠነው
\v 6 ከእርሱ ዝርያዎች ሰባት ሰዎች ለእኛ ተላልፈው ይሰጡን እኛም በእግዚአብሔር በተመረጠው በሳዖል አገር በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” አሉት፡፡ ስለዚህ ንጉሡ፣ “እነርሱን እሰጣችኋለሁ” አላቸው፡፡
\s5
\v 7 ንጉሡ ግን በእርሱና በሳዖል ልጅ በዮናታን ስለነበረው የእግዚአብሔር መሐላ የሳዖልን ልጅ የዮናታንን ልጅ ሜምፊቦስቴን አዳነው፡፡
\v 8 ነገር ግን ንጉሡ የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳዖል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን ወሰዳቸው፣ በተጨማሪም ዳዊት የሳዖል ልጅ ሜልኮል ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደቻቸውን አምስት ወንዶች ልጆች ወሰዳቸው፣
\v 9 በገባዖናውያንም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡ እነርሱም በተራራው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰቀሏቸው፣ ሰባቱም አንድ ላይ ሞቱ፡፡ የተገደሉት በመከራ ወቅት፣ የገብስ መከር በሚሰበሰብባቸው የመጀመሪያዎቹ አምስት ቀናት ነበረ፡፡
\s5
\v 10 ከዚያ በኋላ የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ከመከር መሰብሰብ ጊዜ ጀምሮ ዝናብ በእነርሱ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ በአስከሬኖቹ አጠገብ ባለው ተራራ ለራሷ ማቅ ወስዳ ዘረጋች፡፡ የሰማይ ወፎች በቀን፣ የዱር አራዊት በማታ እንዲነኳቸው አልፈቀደችም፡፡
\v 11 የሳዖል ቁባት የኢዩሄል ልጅ ሪጽፋ ያደረገችው ለዳዊት ተነገረው፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ሳዖልን በጊልቦዓ ከገደሉት በኋላ ሰቅለውት ከነበረበት ከቤትሻን አደባባይ ከሰረቁት ከኢያቢስ ገለዓድ ሰዎች ዘንድ ዳዊት ሄዶ አመጣ፡፡
\v 13 ዳዊት ከዚያ ስፍራ የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት እንዲሁም በዚያ የተሰቀሉትን የሰባት ሰዎች አጥንትም ሰብስቦ ወሰደ፡፡
\s5
\v 14 የሳዖልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት በብንያም አገር በጼላ በአባቱ በቂስ መቃብር ቀበሩአቸው፡፡ ንጉሡም ያዘዘውን ነገር ሁሉ አከናወኑ፡፡ ከዚያ በኋላ ለምድሪቱ የተደረገውን ጸሎት እግዚአብሔር መለሰ፡፡
\s5
\v 15 ከዚያ በኋላ ፍልስጥኤማውያን ከእስራኤል ጋር እንደገና ውጊያ ገጠሙ፡፡ ስለዚህ ዳዊት ከሠራዊቱ ጋር ወርዶ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፡፡ ዳዊት በጦርነቱ የሰውነት መዛል አጋጠመው፡፡
\v 16 የኃላኑ ዝርያ የነበረውና የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝነው እንዲሁም አዲስ ሰይፍ የታጠቀው ይሽቢብኖብ ዳዊትን ለመግደል አቀደ፡፡
\v 17 ነገር ግን የጽሩይ ልጅ አቢሳ ፍልስጥኤማዊውን ወግቶ በመግደል ዳዊትንም ታደገው፡፡ ከዚያ በኋላም የዳዊት ሰዎች፣ “የእስራኤል መብራት እንዳታጠፋ ከእንግዲህ አንተ ከእኛ ጋር መውጣት የለብህም” ብለው ማሉለት፡፡
\s5
\v 18 ከዚህ በኋላ ጎብ በተባለ ስፍራ የራፋይም ዝርያ የነበረው ኩስታዊው ሴቦካይ ሳፋንን የገደለበት ጦርነት ከፍልስጥኤማውያን ጋር እንደገና ተደረገ፡፡
\v 19 ጎብ ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር በተደረገ ጦርነት የቤተልሔሙ የየዓሬዓርጊም ልጅ ኤልያናን የጦሩ ዘንግ እንደ ሸማኔ መጠቅለያ የሆነውን የጌት ሰው ጎልያድን ገደለ፡፡
\s5
\v 20 ጋዛ ላይ በተደረገ ሌላ ጦርነት በእጆቹ ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች በእግሮቹም ላይ ስድስት ጣቶች ባጠቃላይ ሃያ አራት ጣቶች የነበሩት ታላቅ ቁመት የነበረው ሰው ነበር፡፡ እርሱም የራፋይም ዝርያ ነበር፡፡
\v 21 እርሱም በእስራኤል ላይ ባፌዘ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሣማ ልጅ ዮናታን ገደለው፡፡
\v 22 እነዚህ የጋዛዋ ራፋይም ዝርያዎች ነበሩ፣ እነርሱም በዳዊት እጅና በወታደሮቹ እጅ ተገደሉ፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳዖል እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት በዚህ መዝሙር ያሉትን የቅኔ ቃላት ለእግዚአብሔር ዘመረ፡፡
\v 2 እንዲህም እያለ ጸለየ፣ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ አምባዬና ታዳጊዬ ነው፡፡
\s5
\v 3 እግዚአብሔር የምጠጋበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፡፡ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊዬና ከግፍ የሚያድነኝ ነው፡፡
\v 4 ሊመሰገን የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁ፡፡
\s5
\v 5 የሞት ማዕበል ከበበኝ፤ የከንቱነት ጎርፍም አጥለቀለቀኝ፡፡
\v 6 የሲዖል ገመድ ተጠመጠመብኝ፣ የሞትም ወጥመድ አጥምዶ ያዘኝ፡፡
\s5
\v 7 በጨነቀኝ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ተጣራሁ፣ አምላኬን ጠራሁት፣ ከመቅደሱ ድምፄን ሰማኝ፤ ለረድኤት ያደረግሁት ጥሪም ወደ ጆሮው ደረሰ፡፡
\s5
\v 8 በዚያን ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች እግዚአብሔር ተቆጥቶ ነበረና የሰማይ መሠረቶች ተናወጡ ተንቀጠቀጡም፡፡
\v 9 ከአፍንጫው ጢስ፣ ከአፉም ፍሙን የሚያግል የሚንበለበል እሳት፡፡
\s5
\v 10 ሰማይን ከፍቶ ወረደ፣ ድቅድቅ ጨለማም ከእግሩ በታች ነበር፡፡
\v 11 በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በንፋስም ክንፍ ተቀምጦ ሲበር ታየ፡፡
\v 12 በሰማይ ላይ ያሉ ከባድ የዝናብ ደመናዎችን በማሰባሰብ ጨለማን እንደ ድንኳን እንዲከበው አደረገ፡፡
\s5
\v 13 በፊቱ ካለው ነጎድጓድ የእሳት ፍም ወረደ፡፡
\v 14 እግዚአብሔር ከሰማይ አንጎደጎደ፣ የልዑልም ድምፅ አስተጋባ፡፡
\v 15 ፍላፃውን ወረወረ ጠላቶቹንም በተነ - መብረቁ እንዲበርቅ አደረገ፣ በታተናቸውም፡፡
\s5
\v 16 በዚያን ጊዜ የውሃ መውረጃዎች ታዩ፣ እግዚአብሔር ባስተጋባው የክተት ድምፅ፣ ከአፍንጫው በሚወጣ የእስትንፋስ ግፊት የምድር መሠረቶች ተጋለጡ፡፡
\s5
\v 17 ከላይ እጁን ዘርግቶ ያዘኝ፣ እየተንዶለዶለ ካለውም ውሃ አወጣኝ፡፡
\v 18 ብርቱ ከሆነው ጠላቴ፣ ከሚጠሉኝም ታደገኝ፣ በእኔ ላይ እጅግ በርትተውብኝ ነበርና፡፡
\s5
\v 19 በጭንቀቴ ጊዜ መጡብኝ፣ እግዚአብሔር ግን ድጋፍ ሆነኝ፡፡
\v 20 እርሱም ሰፋ ወዳለ ስፍራ አወጣኝ፡፡ በእኔ ደስ ተሰኝቶ ነበርና አዳነኝ፡፡
\v 21 እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ መጠን ብድራትን ከፍሎኛል፣ እንደ እጄም ንጽሕና መጠን ወደ ስፍራዬ መልሶኛል፡፡
\s5
\v 22 የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፣ ከአምላኬም ዞር በማለት ክፋትን አላደረግሁም፡፡
\v 23 የጽድቅ ሥርዓቱ በፊቴ ናቸውና፣ ከድንጋጌም ፈቀቅ አላልሁም፡፡
\s5
\v 24 ቅንነቴን በፊቱ ጠብቄ ነበርና፣ ራሴንም ከኃጢአት አርቄ ነበር፡፡
\v 25 ስለዚህ እግዚአብሔር ወደ ጽድቅ ደረጃዬ፣ በፊቱ ካለኝ የንፅሕና አቋሜ መልሶኛል፡፡
\s5
\v 26 ታማኝ ለሆነው ታማኝነትህን ታሳያለህ፣ ነቀፋ ለሌለበትም ሰው ነቀፋ የሌለብህ መሆንህን ታሳያለህ፡፡
\v 27 ከንጹሖች ጋር ንጹሕ መሆንህን ስታሳይ ለተጣመሙት ግን ጠማማ ነህ፡፡
\s5
\v 28 የተጎሳቆሉትን ታድናለህ፣ ዐይኖችህ ግን በትዕቢተኞች ላይ ነው፣ ታዋርዳቸውማለህ፡፡
\v 29 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ መብራቴ ነህና፣ እግዚአብሔር ጨለማዬን ያበራል፡፡
\s5
\v 30 በአንተ መሰናክሉን ጥሼ አልፋለሁ፣ በአምላኬ ቅጥሩን እዘላለሁ፡፡
\v 31 የእግዚአብሔር መንገድማ ፍጹም ነው፣ የእግዚአብሔር ቃል ንፁሕ ነው፡፡ ወደ እርሱ ለሚጠጋ ለማንኛውም ሰው ጋሻ ነው፡፡
\s5
\v 32 ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችንስ በቀር አምባ ማን ነው?
\v 33 እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነው፣ ነቀፋ የሌለበትንም ሰው በመንገዱ ይመራዋል፡፡
\s5
\v 34 እንደ ዋላ እግሮች እግሮቼን ፈጣን ያደርጋቸዋል፣ በተራራም ላይ ያቆመኛል፡፡
\v 35 እጆቼን ለውጊያ፣ ክንዴንም የናስ ቀስት ለመለጠጥ ያሠለጥናቸዋል፡፡
\s5
\v 36 የድነትን ጋሻ ሰጥተኸኛል፣ ሞገስህም ታላቅ አድርጎኛል፡፡
\v 37 በእግሮቼ ሥር ያለውን ስፍራ ሰፊ አድርገህልኛል፣ ስለዚህ እግሮቼ አልተንሸራተቱም፡፡
\s5
\v 38 ጠላቶቼን አሳደድኋቸው፣ አጠፋኋቸውም፡፡ እስካጠፋቸውም ድረስ አልተመለስሁም፡፡
\v 39 ፈጽሜ አጠፋኋቸው፣ አደቀቅኋቸውም፣ ተመልሰው መነሣት አይችሉም፡፡ በእግሬ ሥር ወድቀዋል፡፡
\s5
\v 40 እንደ ጦር መታጠቂያ ኃይልን በእኔ ላይ አደረግህ፣ በላዬ ላይ የተነሡትንም ከእኔ በታች አደረግኸቸው፡፡
\v 41 የጠላቶቼን ማጅራት ሰጠኸኝ፣ የሚጠሉኝንም አፈራረስኳቸው፡፡
\s5
\v 42 ዕርዳታ ለማግኘት ተጣሩ ነገር ግን ማንም አላዳነቸውም፣ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ እርሱ ግን አልመለሰላቸውም፡፡
\v 43 እንደ አቧራ መሬት ላይ ፈጨኋቸው፣ በመንገድ ላይ እንዳለ ጭቃም ረገጥኋቸው፡፡
\s5
\v 44 ከራሴ ሕዝብ ክርክር አድነኸኛል፣ የሕዝቦችም ራስ አድርገህ አጽንተኸኛል፣ የማላውቀው ሕዝብ ያገለግለኛል፡፡
\v 45 ባዕድ ሕዝቦች ለእኔ ለመስገድ ተገደዱ፣ ስለ እኔ እንደሰሙ ወዲያውኑ ታዘዙኝ፡፡
\v 46 ባዕዳን ከምሽጋቸው እየተንቀጠቀጡ ወጡ፡፡
\s5
\v 47 እግዚአብሔር ሕያው ነው! ዐለቴ የተመሰገነ ይሁን፣ የድነቴ ዐለት እግዚአብሔር ከፍ ይበል፡፡
\v 48 በቀልን የሚበቀልልኝ፣ ሕዝብንም ከእኔ ሥር የሚያደርግልኝ አምላክ ይሄ ነው፡፡
\v 49 ከጠላቶቼ ነፃ ያወጣኛል፡፡ እንዲያውም በእኔ ላይ ከተነሡት በላይ አውጥተኸኛል፡፡ ከግፍኞች ታድገኸኛል፡፡
\s5
\v 50 ስለዚህ እግዚብሔር ሆይ፣ በሕዝቦች መካከል ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ፣ ለስምህም ምስጋና መዝሙር እዘምራለሁ፡፡
\v 51 እግዚአብሔር ለንጉሡ ታላቅ ድልን ይሰጠዋል፣ ኪዳናዊ ታማኝነቱን እርሱ ለቀባው፣ ለዳዊትና ለዘሮቹ ለዘላለም ያሳየዋል፡፡”
\s5
\c 23
\p
\v 1 እነዚህ ተወዳጁ የእስራኤል ዘማሪ፣ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ እጅግ የተከበረው፣ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሎች ናቸው፡፡
\v 2 የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፣ ቃሉም በምላሴ ላይ ነበረ፡፡
\s5
\v 3 የእስራኤል አምላክ ተናገረ፣ የእስራኤልም ዐለት እንደዚህ አለኝ፣ “ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣ በፈሪሀ-እግዚአብሔር የሚያስተዳድር፣
\v 4 እርሱ ከዝናብ በኋላ ብሩሕ በሆነው የፀሐይ ብርሃን ከምድር እንደሚበቅል ለምለም ሣር፣ ደመና የሌለባት ፀሐይ ጥዋት ስትወጣ እንደሚፈነጠቅ የማለዳ ብርሃን ነው፡፡
\s5
\v 5 በእርግጥ የእኔ ቤተሰብ በእግዚአብሔር ፊት እንደዚህ አይደለምን? ከእኔስ ጋር ሥርዓት ያለውና በሁሉም መንገድ እርግጠኛ የሆነ የዘላለም ቃል ኪዳን አልገባምን? ድነቴን ከፍ ከፍ አድርጎ፣ ማንኛውንም ፍላጎቴን አይፈጽምልኝምን?
\s5
\v 6 ነገር ግን በእጅ ሊሰበሰቡ ስለማይችሉ ሁላቸውም እንደሚጣሉ እሾሆች ከንቱዎች ናቸው፡፡
\v 7 እነርሱን የሚነካ የብረት መሣሪያ መጠቀም ወይም የጦር ዘንግ መያዝ ስላለበት ባሉበት መቃጠል ይገባቸዋል፡፡”
\s5
\v 8 የዳዊት ምርጥ ወታደሮች ስም የሚከተለው ነው፡- የታህክሞን ሰው ዮሴብ የሦስቱ አለቆች አለቃና በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰዎችን የገደለ ነው፡፡
\s5
\v 9 ከእርሱ ቀጥሎ የአሆሃዊው የዱዲ ልጅ ኤልዔዘር ነበረ፣ እርሱም ከሶስቱ ኃያላን ሰዎች አንዱ ነበር፡፡ እርሱም ጦርነት ለመግጠም የተሰባሰቡ ፍልስጥኤማውያን በተገዳደሩ ጊዜና የእስራኤልም ሰዎች በፈገፈጉ ጊዜ በዚያ ነበር፡፡
\v 10 ኤልኤዘር እስኪዝልና እጁ ከሰይፉ ጋር ተጣብቆ እስኪቀር ድረስ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ቆሞ ተዋጋ፡፡ የዚያን ቀን እግዚአብሔር ታላቅ ድል አስገኘ፡፡ ከኤልኤዘር በኋላ ሠራዊቱ የተመለሰው አስከሬኖቹን ለመግፈፍ ብቻ ነበር፡፡
\s5
\v 11 ከእርሱም በኋላ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበር፡፡ ፍልስጥኤማውያኑ የምስር እርሻ በነበረበት ተሰብስበው ሳሉ ሠራዊቱ ከ እነርሱ ሸሸ፡፡
\v 12 ሣማ ግን በእርሻው መካከል ቆሞ ተቋቋማቸው ፍልስጥኤማዊውንም ገደለው እግዚአብሔርም ታላቅ ድል ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 13 ከሰላሳዎቹ ወታደሮች ሶስቱ በመከር ጊዜ ወደ አዶላም ዋሻ ወደ ዳዊት ዘንድ ሄዱ፡፡ የፍልስጥኤም ሠራዊት በራፋይም ሸለቆ ሰፍረው ነበር፡፡
\v 14 በዚያን ጊዜ ዳዊት በአንድ ዋሻ በምሽጉ ውስጥ ሲሆን ፍልስጥኤማውያን ግን በቤተልሔም ተደራጅተው ነበር፡፡
\s5
\v 15 ዳዊትም ውሃ ተጠምቶ፣ “በበሩ አጠገብ ካለችው ጉድጓድ የምጠጣውን ውሃ ምነው አንድ ሰው በሰጠኝ! ” አለ፡፡
\v 16 ስለዚህ እነዚህ ሶስቱ ኃያላን ፍልስጥኤማውያንን ጥሰው አልፈው በበሩ አጠገብ ካለችው ከቤተልሔም ጉድጓድ ውሃ ቀዱ፡፡ ውሃውንም ይዘው ለዳዊት አመጡለት፣ እርሱ ግን ሊጠጣው ስላልፈቀደ በእግዚአብሔር ፊት አፈሰሰው፡፡
\v 17 ከዚያ በኋላም፣ “እግዚአብሔር ሆይ፣ ይህንን እጠጣው ዘንድ ከእኔ ይራቅ፤ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የጣሉ ሰዎችን ደም ልጠጣ ይገባኛልን? ” ከዚህም የተነሣ ሊጠጣው አልፈቀደም፡፡ ሶስቱ ኃያላን ያደረጓቸው ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡
\s5
\v 18 የኢዮአብ ወንድምና የጽሩያ ልጅ አቢሳ የሶስቱ አለቃ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት ከሶስት መቶዎቹ ጋር በጦሩ ተዋግቶ ገደላቸው፡፡ ከሶስቱ ወታደሮች ጋር በተያያዘ ብዙውን ጊዜ ስሙ ይጠቀሳል፡፡
\v 19 እርሱ ከእነርሱም ይልቅ ዝነኛ አልነበረምን? እርሱ የሶስቱ አለቃ ሆኖ ተሾመ፡፡ ይሁን እንጂ የእርሱም ዝና ከሶስቱ እጅግ ዝነኛ ከነበሩት ወታደሮች ጋር የሚስተካከል አልነበረም፡፡
\s5
\v 20 የቀብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያስ ታላቅ ጀብዱ የሠራ ጠንካራ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም ሁለቱን የአርኤል ልጆች ገደለ፡፡ በረዶ በጣለበትም ወቅት በጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሎአል፡፡
\v 21 ደግሞም አንድ ግዙፍ ግብፃዊም ገድሎአል፡፡ ግብፃዊው በእጁ ጦር የያዘ ቢሆንም በናያስ በትር ብቻ ይዞ ገጠመው፡፡ ጦሩን ከግብፃዊው እጅ ቀምቶ በራሱ ጦር ገደለው፡፡
\s5
\v 22 በናያስ እነዚህን ጀብዱዎች ፈጸመ ከሶስቱም ኃያላን ጋርም ስሙ የተጠራ ሆነ፡፡
\v 23 በአጠቃላይ ከነበሩት ሰላሳ ወታደሮች ይልቅ ከፍ ያለ ግምት የተሰጠው ነበረ፣ ሆኖም የሶስቱ እጅግ ምርጥ ወታደሮችን ያህል ታላቅ ግምት የተሰጠው አልነበረም፡፡ ሆኖም ዳዊት የክቡር ዘበኞቹ አለቃ አደረገው፡፡
\s5
\v 24 ሰላሳዎቹ የሚከተሉትን ያካተተ ነበር፣ የኢዮአብ ወንድም አሣሄል፣ የቤተልሔሙ ሰው የዱዲ ልጅ ኤልያናን፣
\v 25 አሮዳዊው ሣማ፣ አሮዳዊው ኤሊቃ፣
\v 26 ፈሊጣዊው ሴሌስ፣ የቴቁሐዊው የዒስካ ልጅ ዒራስ፣
\v 27 ዓኖቶታዊው አቢዔዜር፣ ኩስታዊው ምቡናይ ፣
\v 28 አሆሃዊው ጸልሞን፣ ነጦፋዊው ማህራይ፣
\s5
\v 29 የነጦፋዊው የበዓና ልጅ ሔሌብ፣ ከብንያም ወገን የጊብዓ ሰው የሆነው የሪባይ ልጅ ኢታይ፣
\v 30 ጲርዓቶናዊው በናያስ፣ የገዓስ ሸለቆ ሰው ሂዳይ፣
\v 31 ዓረባዊው አቢዔልቦን፣ በርሑማዊው ዓዝሞት፣
\v 32 ሸዓልቦናዊው ኤሊያሕባ፣ የአሳን ልጆች፤ ዮናታን የተባለው፣
\s5
\v 33 የአሮዳዊው የሣማ ልጅ፣ የአሮዳዊው የሻራር ልጅ አሒአም፣
\v 34 የማዕካታዊው የአሐሰባይ ልጅ ኤልፋላት፣ የጊሎናዊው የአኪጦፌል ልጅ ኤሊኦም፣
\v 35 ቀርሜሎሳዊው ሐጽሮ፣ አርባዊው ፈዓራይ፣
\v 36 የሱባ ሰው የሆነው የናታን ልጅ ይግዓል፣
\s5
\v 37 አሞናዊው ጻሌቅ፣ የጽሩያ ልጅ የኢዮአብ ጦር መሣሪያ ያዥ የነበረው ብኤሮታዊው ነሃራይ፣
\v 38 ይትራዊው ዔራስ ፣ ይትራዊው ጋሬብ፣
\v 39 እንዲሁም ኬጢያዊው ኦርዮ፤ በጠቅላላው ሠላሳ ሰባት ነበሩ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 እንደገናም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ እጅግ ተቆጣ፤ ዳዊትንም በእነርሱ ላይ በማስነሳት፣ “ሂድ እስራኤልንና ይሁዳን ቁጠር” አለው፡፡
\v 2 ንጉሡ አብሮት ለነበረው ለኢዮአብ፣ “ከዳን እስከ ቤርሳቤህ ወደ እስራኤል ነገዶች ሁሉ ሂዱ፣ ለጦርነት ብቁ የሆኑትንም ጠቅላላ ብዛት ማወቅ እችል ዘንድ ሕዝቡን ሁሉ ቁጠሩ፡፡” አለው፡፡
\s5
\v 3 ኢዮአብም ለንጉሡ፣ “እግዚአብሔር አምላክህ የሕዝቡ ቁጥር መቶ እጥፍ ያብዛ፣ የጌታዬ የንጉሡ ዓይንም ይህንን ለማየት ያብቃው፡፡ ነገር ግን ጌታዬ ይህንን ለማድረግ ለምን ፈለገ? ”
\v 4 ይሁን እንጂ የንጉሡ ቃል የኢዮአብንና የሠራዊት አለቆችን ቃል የሚሽር የመጨረሻ ቃል ነበር፡፡ ስለዚህ የእስራኤልን ሕዝብ ይቆጥሩ ዘንድ ኢዮአብና የሠራዊቱ አለቆች ከንጉሡ ፊት ወጡ፡፡
\s5
\v 5 ዮርዳኖስን ተሻገሩና ከከተማው በስተደቡብ በሸለቆው ዘንድ ባለው በአሮዔር አጠገብ ሠፈሩ፡፡ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ኢያዜር ተጓዙ፡፡
\v 6 ወደ ገለዓድና ወደ ተባሶን አደሰይ፣ ቀጥሎም ወደ ዳንየዓን ከዚያም ዞረው ወደ ሲዶና ሄዱ፡፡
\v 7 ወደ ጢሮስ ምሽግና ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያን ከተሞች ደረሱ፡፡ ከዚያም በይሁዳ ቤርሳቤህ ወዳለችው ወደ ኔጌቭ ወጡ፡፡
\s5
\v 8 በመላው ምድሪቱ ከተዘዋወሩ በኋላ ከዘጠኝ ወር ከሃያ ቀናት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
\v 9 ከዚያም ኢዮአብ ለንጉሡ የተዋጊ ወንዶችን ጠቅላላ ቁጥር ዘገባ አቀረበ፡፡ በእስራኤል ሰይፍን መምዘዝ የሚችሉ ስምንት መቶ ሺህ ጀግኖች ሲኖሩ በይሁዳ ደግሞ አምስት መቶ ሺህ ሰዎች ነበሩ፡፡
\s5
\v 10 ሰዎቹን ከቆጠረ በኋላ ዳዊት በልቡ ተጨነቀ፡፡ ስለዚህ ለእግዚአብሔር፣ “ይህንን በማድረጌ ታላቅ ኃጢአት ሠርቻለሁ፡፡ የሠራሁት እጅግ የስንፍና ሥራ ነውና፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ የባሪያህ በደል አስወግድ፡፡”
\s5
\v 11 ዳዊት ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ፣ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ዳዊት ባለ ራእይ ወደ ነቢዩ ጋድ እንዲህ ሲል መጣ፣
\v 12 “ሂድና ለዳዊት፣ ‘እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፣ ሶስት ምርጫ እሰጥሃለሁ፣ አንዱን ምረጥ’”
\s5
\v 13 ስለዚህ ጋድ ወደ ዳዊት ሄደና፣ “የሦስት ዓመት ረሃብ ወደ ምድርህ ይምጣን? ወይስ እነርሱ እያሳደዱህ ከጠላቶችህ ለሶስት ወራት ብትሸሽ ይሻልሃል? ወይስ በአገርህ የሶስት ቀን ቸነፈር ይምጣብህ? ለላከኝ ምን መልስ እንደምሰጥ አሁን ወስን” አለው፡፡
\v 14 ዳዊትም ጋድን፣ “እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ ምሕረታዊ አደራረጉ እጅግ ታላቅ ስለሆነ በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ እንጂ በሰው እጅ አንውደቅ” አለው፡፡
\s5
\v 15 ስለዚህ እግዚአብሔር ህከጥዋት እስከ ተወሰነ ጊዜ ቸነፈሩን በእስራኤል ላይ ላከ፣ ከዳን እስከ ቤርሳቤህም ሰባ ሺህ ሰዎች ሞቱ፡፡
\v 16 መልአኩ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ስለደረሰው ጉዳት ተፀፀቶ ሕዝቡን እያጠፋ የነበረውን መልአክ፣ “ይበቃል፣ እጅህን ሰብስብ” አለው፡፡ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር፡፡
\s5
\v 17 ሕዝቡን እየቀሠፈ የነበረውን መልአክ ባየ ጊዜ ዳዊት ለእግዚአብሔር፣ “ኃጢአት ሠርቻለሁ፣ የማይገባም ነገር አድርጌአለሁ፡፡ ነገር ግን እነዚህ በጎች ምን ያደረጉት ነገር አለ? እባክህን የአንተ እጅ እኔንና የአባቴን ቤተሰብ ይቅጣ፡፡” ብሎ ለእግዚአብሔር ተናገረ፡፡
\s5
\v 18 ከዚያ በኋላ ጋድ በዚያን ቀን ወደ ዳዊት መጣና፣ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሥራ” አለው፡፡
\v 19 ስለዚህ ዳዊት ጋድ እንደ ነገረውና እግዚአብሔር እንዳዘዘው ወጣ፡፡
\v 20 ኦርና ሲመለከት ንጉሡና አገልጋዮቹ ሲደርሱ አየ፡፡ ስለዚህ ኦርና ወጣ ብሎ በንጉሡ ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፡፡
\s5
\v 21 ከዚያ በኋላም ኦርና፣ “ጌታዬ ንጉሡ ወደ ባሪያው ዘንድ ለምን መጣ? ” ዳዊትም መለሰ፣ “ቸነፈሩ ከሕዝቡ ይወገድ ዘንድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ የምሠራበትን የአንተን ዐውድማ እገዛ ዘንድ ነው፡፡”
\v 22 ኦርናም ለዳዊት፣ “ጌታዬ ንጉሡ የራስህ አድርገህ ውሰደው፡፡ በፊትህ ደስ ያሰኘህንም አድርግበት፡፡ እነሆ፣ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሬዎች፣ ለማገዶም የሚሆን የመውቂያ ዕቃና ቀንበር በዚህ አለ፡፡
\v 23 ይህንን ሁሉ ንጉሤ ሆይ፣ እኔ ኦርና ለአንተ እሰጣለሁ” አለና ከዚያ በኋላ፣ “እግዚአብሔር አምላክህ ይቀበልህ” አለው፡፡
\s5
\v 24 ንጉሡም ለኦርና፣ “አይሆንም፣ ይህንን በዋጋ መግዛት ይኖርብኛል፡፡ ምንም ነገር ያላወጣሁበትን አንድም ነገር ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አላቀርብም” አለው፡፡ ስለዚህ ዳዊት ዐውድማውንና በሬዎቹን በሃምሳ የብር ሰቅል ገዛ፡፡
\v 25 ዳዊት በዚያ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራና የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ምድሪቱ ተለመነው፣ በእስራኤል የነበረውም ቸነፈር ቆመ፡፡

1394
12-2KI.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1394 @@
\id 2KI
\ide UTF-8
\h 2ተኛ ነገስት
\toc1 2ተኛ ነገስት
\toc2 2ተኛ ነገስት
\toc3 2ki
\mt 2ተኛ ነገስት
\s5
\c 1
\p
\v 1 አክዓብ ከሞተ በኋላ ሞአብ በአስራኤል ላይ ዐመፀ፡፡
\v 2 በዚያን ጊዜ የአስራኤል ንጉሥ አካዝያስ በሰማርያ ቤተ መንግሥቱ ሳለ ከሰገነቱ ላይ ወድቆ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፤ እርሱም እኔ ከዚህ ሕመም እድን እንደሆነ በፍልስጥኤም የአቃሮን ከተማ አምላክ የሆነውን ብዔልዜቡል ጠይቁልኝ ብሎ መልእክተኞቹን ላከ፡፡
\s5
\v 3 ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ ቴስቢያዊውን ኤልያስን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ ተነሥተህ የሰማርያ ንጉሥ አካዝያስ የላካቸውን መልእክተኞች ለመገናኘት ውጣ፤ እንዲህም ብለህ ንገራቸው፤ የአቃሮንን አምላክ ብዔሌዜቡልን ለመጠየቅ የምትሄዱት በእስራኤል ዘንድ አምላክ የለም ብላችሁ ነውን?
\v 4 ስለዚህ እግዚአብሔር እነሆ አንተ ትሞታለህ እንጂ አትፈወስም፤ ከተኛህበት አልጋም አትነሣም፤ ብሎሃል በሉት፡፡ ከዚያም ኤልያስ ትቶ ሄደ፡፡
\s5
\v 5 መልእተኞቹም ወደ ንጉሡ ተመልሰው ሄዱ፤ ንጉሡም ስለምን ተመልሳችሁ መጣችሁ? ሲል ጠየቃቸው፡፡
\v 6 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤ አንድ ሰው በመንገድ አግኝቶን ወደ አንተ ተመልሰን እንድንመጣና እግዚአብሔር ስለ አንተ የተናገረውን እንድናስረዳህ አዘዘን፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፤ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ለመጠየቅ መልእክተኞች የላክህበት ምክንያት ምንድን ነው? ስለዚህ ትሞታለህ እንጂ ከዚህ ሕመም አትፈወስም፤ ከተኛህበትም አልጋ አትነሣም!
\s5
\v 7 ንጉሡም በመንገድ ያገኛችሁት ይህንን ቃል የነገራችሁ ያ ሰው እንዴት ያለ ነው? ሲል ጠየቃቸው፡፡
\v 8 እነርሱም ጠጉራም ልብስ ለብሶ በወገቡ ዙሪያ የጠፍር ቀበቶ የታጠቀ ነው ሲሉ መለሱለት፡፡ ንጉሡም እርሱማ ኤልያስ ነው! አለ፡፡
\s5
\v 9 ከዚህም በኋላ ንጉሡ አንዱን የጦር መኮንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሄዶ ኤልያስን ይዞ ያመጣለት ዘንድ አዘዘው፡፡ መኮንኑም ኤልያስን በአንድ ኮረብታ ላይ ተቀምጦ አገኘውና የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል አለው፡፡
\v 10 ኤልያስም እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ አለው፤ ወዲያውኑ እሳት ከሰማይ ወርዶ መኮንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ፡፡
\s5
\v 11 ንጉሡም እንደገና ሌላውን መኮንን ከኀምሳ ሰዎች ጋር ላከ፤ እርሱም ወደ ኤልያስ ወጥቶ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ አሁኑኑ ወርደህ ወደ እርሱ እንድትመጣ ንጉሡ አዞሃል አለው፡፡
\v 12 ኤልያስም እኔስ የእግዚአብሔር ሰው ከሆንኩ እሳት ከሰማይ ወርዶ አንተንና ኀምሳውን ሰዎችህን ይብላ አለው፤ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር እሳት መኮንኑንና ኀምሳዎቹን ሰዎች በላ፡፡
\s5
\v 13 ንጉሡም ለሦስተኛ ጊዜ ከኀምሳ ሰዎች ጋር ሌላ መኮንን ላከ፤ ይህኛው መኮንን ግን ወደ ኮረብታው በመውጣት በኤልያስ ፊት በጉልበቱ ተንበርክኮ እንዲህ ሲል ለመነ፤ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ ለእኔና ከእኔ ጋር ላሉት ሰዎች ምሕረት አድርግልን፤ ሕይወትችንንም ከሞት አድን፣
\v 14 ሌሎቹን ሁለት መኮንኖችና ተከታዮቻቸውን ሁሉ ከሰማይ የወረደ እሳት በልቶአቸዋል፤ ለእኔ ግን እባክህ ምሕረት አድርግልኝ፡፡
\s5
\v 15 የእግዚአብሔርም መልአክ ኤልያስን ከእርሱ ጋር አብረህ ውረድ፤ ከቶም አትፍራ አለው፡፡ ስለዚህም ኤልያስ ከመኮንኑ ጋር ወደ ንጉሡ ወረደ፡፡
\v 16 እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን እንዲጠይቁ መልእክተኞችን የላክህ በእስራኤል አምላክ እንደሌለ በመቁጠርህ ነውን? ስለዚህ ከተኛህበት አልጋ ሳትወርድ ትሞታለህ እንጂ አትድንም አለው፡፡
\s5
\v 17 ስለዚህ እግዚአብሔር በኤልያስ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት አካዝያስ ሞተ፡፡ አካዝያስ ወንዶች ልጆች ስላልነበሩት በእርሱ ፈንታ ተተክቶ ወንድሙ ኢዮራም ነገሠ። ይህም የሆነው የኢዮሣፍጥ ልጅ ኢዮራም በይሁዳ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት ነበር፡፡
\v 18 ንጉሥ አካዝያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\s5
\c 2
\p
\v 1 እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የሚወስድበት ጊዜ ደረሰ፤ ኤልያስና ኤልሳዕ ከጌልጌላ ተነሥተው ጉዞ ጀመሩ፡፡
\v 2 በመንገድም ሳሉ ኤልያስ ኤልሳዕን እነሆ አንተ በዚህ ቆይ እኔ ወደ ቤቴል እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡ ኤልሳዕ ግን እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ ከቶ ከአንተ አልለይም ሲል መለሰለት፤ ስለዚህም አብረው ወደ ቤቴል ሄዱ፡፡
\s5
\v 3 በዚያ የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው፣ እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን? ሲሉ ጠየቁት፡፡ ኤልሳዕም አዎን ዐውቃለሁ፣ ነገር ግን ዝም በሉ ሲል መለሰላቸው፡፡
\v 4 ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን እነሆ አንተ በዚህ ቆይ እኔ ወደ ኢያሪኮ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡ ኤልሳዕ ግን እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ ከቶ ከአንተ አልለይም፣ ሲል መለሰለት፡፡ ስለዚህም አብረው ወደ ኢያሪኮ ሄዱ፡፡
\s5
\v 5 በዚህም የሚኖሩ የነቢያት ጉባኤ ወደ ኤልሳዕ ሄደው እግዚአብሔር ዛሬ ጌታህን ከአንተ ለይቶ እንደሚወስደው ታውቃለህን? ሲሉ ጠየቁት፡፡ ኤልሳዕም አዎን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ዝም በሉ ሲል መለሰላቸው፡፡
\v 6 ከዚህም በኋላ ኤልያስ ኤልሳዕን እነሆ አንተ በዚህ ቆይ፤ እኔ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ እንድሄድ እግዚአብሔር አዞኛል አለው፡፡ ኤልሳዕ ግን እኔ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ ከቶ ከአንተ አልለይም፤ ሲል መለሰለት:: እነዚህም አብረው ጉዞአቸውን ቀጠሉ፡፡
\s5
\v 7 ከነቢያቱም ኀምሳው ተከትለዋቸው ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ፤ ኤልያስና ኤልሳዕም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ቆሙ፤ ኀምሳውም ነቢያት ደግሞ ጥቂት ራቅ ብለው ቆመው ነበር፤
\v 8 ከዚህ በኋላ ኤልያስ ካባውን አውልቆ በመጠቅለል ውሃውን መታው፤ ውሃው ወደ ቀኝና ወደ ግራ ተከፍሎላቸው ኤልያስና ኤልሳዕ በደረቅ ምድር ተሸገሩ፡፡
\s5
\v 9 በዚህም ኤልያስ ኤልሳዕን እኔ ከአንተ ከመወሰዴ በፊት ምን እንዳደርግልህ እንደምትፈልግ ንገረኝ አለው፡፡ ኤልሳዕም ያንተ ተተኪ እንድሆን የሚያስችለኝ መንፈስ በእጥፍ ይሰጠኝ ሲል መለሰለት፡፡
\v 10 ኤልያስም ‹‹ያቀረብከው ጥያቄ ከባድ ነው፤ ነገር ግን እኔ ከአንተ ተለይቼ ስወሰድ ብታየኝ ይህን የጠየከውን ስጦታ መቀበል ትችላልህ፤ ባታየኝ ግን ልታገኘው አትችልም›› ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 11 እየተነጋገሩ እርምጃቸውን ቀጠሉ፤ ከዚያም በኋላ ፈረሰኞች የሚስቡአቸው የእሳት ሠረገሎች ድንገት ገብተው ሁለቱን ለዩአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ ተወሰደ፡፡
\v 12 ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ ‹‹የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንከው አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም፡፡ ኤልሳዕም ከሐዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤
\s5
\v 13 ከኤልያስም የወደቀውን ካባ ከመሬት አነሣ፤ ከዚያም ሄዶ በዮርዳኖስ ወንዝ ደርቻ ቆመ፡፡
\v 14 ውሃውንም በኤልያስ ካባ መትቶ፣ ‹‹የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው? አለ፤ ከዚያም በኋላ እንደገና በመታው ጊዜ ውሃው ወደ ቀኝና ግራ ተከፍሎለት ወደ ማዶ ተሻገረ፡፡
\s5
\v 15 ከኢያሪኮ የመጡት ነቢያት እርሱን ባዩት ጊዜ፣ ‹‹በኤልያስ ላይ ዐድሮ የነበረው የመንፈስ ኀይል በኤልሳዕ ላይ አርፏል! አሉ፤ ወደ እርሱም በመቅረብ ጎንበስ ብለው እጅ ነሡት
\v 16 ‹‹እነሆ! በዚህ ጠንካራ የሆንን ኀምሳ ሰዎች አለን፤ እንሂድና ጌታህን እንፈልገው፤ ምናልባት የእግዚአብሔር መንፈስ አንሥቶ ወስዶ በአንድ ተራራ ወይም ሸለቆ ውስጥ አሳርፎት ይሆናል፡፡›› ኤልሳዕም “አትሂዱ” ሲል መለሰ፡፡
\s5
\v 17 እነርሱ ግን እምቢ በማለት እስኪያፍር ድረስ አጥብቀው ስለ ለመኑት በጉዳዩ ተስማማና ኀምሳ ሰዎች ሄደው ሦስት ቀን ሙሉ ኤልያስን ፈለጉት፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፡፡
\v 18 ከዚያም በኋላ በኢያሪኮ ሆኖ ወደሚጠብቃቸው ወደ ኤልሳዕ ተመለሱ፤ ኤልሳዕም ‹‹እኔ ቀድሞውንስ አትሂዱ ብያችሁ አልነበረምን? አላቸው፡፡
\s5
\v 19 ጥቂት ሰዎች ከኢያሪኮ ወደ ኤልሳዕ መጥተው ‹‹ጌታችን አንተ እንደምታውቀው ይህች ምድር መልካም ናት፤ ውሃው ግን መጥፎ በመሆኑ ምድሪቱ ምርት አትሰጥም፤ ስለሁኔታው እንለምንሃለን›› አሉት፡፡
\v 20 ኤልሳዕም ‹‹በአዲስ ሳህን ውስጥ ጨው ጨምራችሁ አምጡልኝ›› ብሎ አዘዘ፡፡ እነርሱም እንዳዘዛቸው አድርገው አመጡለት፡፡
\s5
\v 21 እርሱም ወደ ምንጩ ሄዶ በውሃ ውስጥ ጨው በመጨመር ‹‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው ‹እኔ ይህን ውሃ በመፈወስ ንፁህ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ የሞትና የምርት መጨንገፍ ምክንያት አይሆንም› ሲል ተናገረ፡፡
\v 22 ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ኤልሳዕ በተናገረው መሠረት ውሃው እስከ ዛሬ ድረስ ንጹሕ ሆነ፡፡
\s5
\v 23 ኤልሳዕም ወደ ቤቴል ለመሄድ ከኢያሪኮ ተነሣ፡፡ በመንገድ ሳለ ከከተማይቱ በርከት ያሉ ልጆች ወጥተው ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ አንተ ራሰ መላጣ! ራሰ መላጣ! ከዚህ ውጣ እያሉ ጮኹበት፡፡
\v 24 ኤልሳዕም መለስ ብሎ ዙሪያውን በመቃኘት አትኩሮ ተመለከታቸውና በእግዚአብሔር ስም ረገማቸው፤ በዚህም ጊዜ ሁለት እንስት ድቦች ከጫካ ወጥተው ከእነዚያ ልጆች መካከል አርባ ሁለቱን ሰባብረው ጣሉአቸው፡፡
\v 25 ኤልሳዕም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ ዘግየት ብሎ ግን ወደ ሰማርያ ተመለሰ፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በእስራኤል ላይ በሰማርያ ነገሠ፤ እርሱም ዐሥራ ሁለት ዓመት ገዛ፡፡
\v 2 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠራ፡፡ ነገር ግን እንደ አባቱና እናቱ አልነበረም፤ ምክንያቱም በዓል ተብሎ የሚጠራውን አባቱ አሠርቶት የነበረውን በዕድ አምላክ ምስል አስወገደ፡፡
\v 3 ይህም ሆኖ ከእርሱ በፊት እስራኤል ወደ ኃጢአት የመራው የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን አምልኮ ተከተለ እንጂ አላስወገደውም፡፡
\s5
\v 4 የሞአብ ንጉሥ ሞሳ በግ አርቢ ነበር፤ በየዓመቱም አንድ መቶ ሺህ ጠቦት የአንድ መቶ ሺህ በጎች ጠጉር ለእስራኤል ንጉሥ ይገብር ነበር፤
\v 5 ነገር ግን የእስራኤል ንጉሥ አካዓብ በሞተ ጊዜ የሞአብ ንጉሥ ሞሳ በእስራኤል ላይ ዐመፀ፡፡
\v 6 በዚያን ጊዜ ንጉሥ ኢዮራም ወዲያውኑ ከሰማርያ ወጥቶ ወታደርቹን ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ፤
\s5
\v 7 ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ኢዮሣፍጥም የሞአብ ንጉሥ በእኔ ላይ አምፆብኛል፤ በእርሱ ላይ በማደርገው ጦርነት ከእኔ ጋር ትተባበራለህን? የሚል መልእክት ላከ፡፡ ንጉሥ ኢሣፍጥም አዎን እተባበርሃለሁ፤ እኔን እንደ ራስህ፣ ሠራዊቴን እንደ ሠራዊትህ፣፣ ፈረሶቼንም እንደ ፈረሶችህ መቁጠር ትችላለህ ሲል መለሰለት፡፡
\v 8 እርሱም ልናጠቃ የምንችለው በየትኛው መንገድ ነው? ሲል ጠየቀው፡፡ ንጉሥ ኢዮራምም በኤዶም በረሓ የሚገኘውን ዙሪያ መንገድ ይዘን እንጓዛለን ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 9 ስለዚህም ንጉሥ ኢዮራም፣ እንዲሁም የይሁዳና የኤዶም ነገሥታት ለዘመቻ ወጡ፤ ከሰባት ቀን ጉዞም በኋላ ውሃ አለቀባቸው፤ ለሠራዊቱም ሆነ ለጭነት እንስሶቻቸው ምንም ውሃ አልነበረም፡፡
\v 10 የእስራኤል ንጉሥ ይህ ምንድን ነው? እግዚአብሔር ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞአብ ንጉሥ አሳልፎ ሊሰጠን ነውን? ወዮልን ሲል ጮኸ፡፡
\s5
\v 11 ንጉሥ ኢዮሣፍጥም በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔርን መጠየቅ እንድንችል በዚህ አንድ ነቢይ የለም? ሲል ጠየቀ፡፡ ከንጉሥ ኢዮራም ሠራዊት አዛዦች አንዱ፣ ቀድሞ የኤልያስ ረዳት የነበረው የሣፋጥ ልጅ ኤልሳዕ እዚህ አለ ሲል መልስ ሰጠ፡፡
\v 12 ንጉሥ ኢዮሣፍጥም የእግዚአብሔር ቃል በእርሱ ዘንድ ይገኛል አለ፤ ከዚያም በኋላ ሦስቱም ነገሥታት ወደ ኤልሳዕ ሄዱ፡፡
\s5
\v 13 ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ ኢዮራምን እኔ ለአንተ ማድረግ የሚገባኝ ምንድን ነው? ወደ አባትህና እናትህ ነቢያት ሂድ። ንጉሥ ኢዮራምም መልሶ አይደለም፣ ሦስታችንንም ነገሥታት ለሞአብ ንጉሥ አሳልፎ ለመስጠት የጠራን እግዚአብሔር ነው አለ፡፡
\v 14 ኤልሳዕም እኔ በማገልግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ አንተን ለመርዳት ለመጣው ለይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ክብር ስል ነው እንጂ ለአንተስ ምንም ነገር ላደርግልህ ባልተገባ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ነገር ግን በገና የሚደረድር ሰው አምጡልኝ አለ፡፡ ባለ በገናውም በሚደረድርበት ጊዜ የእግዚአብሔር ኃይል በኤልሳዕ ላይ ወርዶ እንዲህ አለ፡፡
\v 16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- በዚህ የደረቀ ሸለቆ ሁሉ የውሃ ጉድጓድ ቆፍሩ፡፡
\v 17 ምንም ዝናብና ነፋስ ባታዩም ይህ ሸለቆ በውሃ የተሞላ ይሆናል፡፡ እናንተ፣ የቀንድ ከብቶቻችሁና የጭነት እንስሶቻችሁ ሁሉ የምትጠጡት በቂ ውሃ ታገኛላችሁ፡፡
\s5
\v 18 ነገር ግን ይህን ማድረግ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀላል ነገር ነው፡፡ ከዚህ በላይ እርሱ በሞአባውያን ላይ ድልን ያጎናጽፋችኋል፡፡
\v 19 የተመሸጉና ምርጥ የሆኑ ከተሞቻቸውን ሁሉ ድል አድርጋችሁ ትይዛላችሁ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውን ሁሉ ትቆርጣላችሁ፤ ምንጮቻቸውን ትደፍናላችሁ፤ ለም የሆኑ የእርሻ ቦታዎቻቸውን በማበላሸት ድንጋይ ትከምሩባቸዋላችሁ፡፡
\s5
\v 20 በማግስቱም ጠዋት መሥዋዕት የሚቀርብበት ሰዓት ሲደርስ ከኤዶም በኩል የውሃ ምንጭ ፈልቆ ምድሩን ሸፈነው፡፡
\s5
\v 21 ሞአባውያንም ሦስቱ ነገሥታት አደጋ ሊጥሉባቸው መምጣታቸውን በሰሙ ጊዜ፣ ከሽማግሌ እስከ ወጣት መሣሪያ መያዝ የሚችሉ ሰዎች ሁሉ ተጠርተው ወጥተው ለጦርነት መጡ፡፡
\v 22 በማግስቱም ጠዋት ከእንቅልፋቸው ነቅተው ሲመለከቱ በውሃው ላይ የሚያበራው የፀሐይ ነጸብራቅ እንደ ደም ቀይ መስሎ ታያቸው፡፡
\v 23 ስለዚህም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ፣ ይህ ነገር ደም ነው፤ የሦስቱ ጠላቶቻችን ሠራዊቶች እርስ በርሳቸው በመተራረድ ተላልቀዋል፤ እንግዲህ ሄደን ሰፈራቸውን እንዝረፍ ተባባሉ፡፡
\s5
\v 24 እነርሱ ወደ ሰፈር በደረሱ ጊዜ እስራኤላውያን ተነሥተው አደጋ በመጣል ወደ ኋላ መለሱአቸው፤ እስራኤላውያን አገሪቱን ወርረው ሞአባውያንን ጨፈጨፉአቸው፡፡
\v 25 ከተሞቻቸውን ደመሰሱ፤ ለም በሆነው እርሻ ውስጥ በሚያልፉበትም ጊዜ እያንዳንዱ እስራኤላዊ አንዳንድ ድንጋይ ይወረውርበት ስለ ነበር በመጨረሻ እርሻዎቹ ሁሉ በድንጋይ ተሸፈኑ፤ ምንጮቻቸውን ደፈኑ፤ የፍራፍሬ ዛፎቻቸውንም ሁሉ ቆረጡ፤ በመጨረሻም የአገሪቱ ዋና ከተማ የነበረችው ቂርሔሬስ ብቻ ቀረች፤ እርስዋንም ድንጋይ የሚወነጭፉ ጦረኞች ከበው አደጋ ጣሉባት፡፡
\s5
\v 26 የሞአብ ንጉሥ ድል እንደ ተመታ ባረጋገጠ ጊዜ ሰይፍ የታጠቁ ሰባት መቶ ሰዎችን እስከትሎ የጠላት ጦር የተሰለፈበትን መስመር ጥሶ ለማምለጥና ወደ ሶሪያ ንጉሥ ለመሄድ ቢሞክርም ከቶ አልተሳካለትም፡፡
\v 27 ስለዚህ በእርሱ ምትክ መንገሥ የሚገባውን የመጀመሪያ ልጁን በከተማይቱ ግንብ ላይ ለሞአብ አምላክ መሥዋዕት አደርጎ አቀረበ፡፡ ስለዚህ በእስራኤል ዘንድ ከፍ ያለ ቁጣ ነበር፡፡ እስራኤላውያንም ለሞአብ ንጉሥ ከተማይቱን ለቀው ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 የነቢያት ጉባኤ አባል የነበረ፣ ባልዋ የሞተባት አንዲት ሴት ወደ ኤልሳዕ መጥታ፣ ጌታዬ ሆይ፣ ባሌ ሞቶብኛል፤ እርሱም አንተ እንደምታውቀው እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበር፡፡ ነገር ግን እነሆ ለባሌ ገንዘብ አበድሮት የነበረ አንድ ሰው በባሌ ዕዳ ፈንታ ሁለት ወንዶች ልጆቼን ወስዶ ባሪያ አደርጎ ሊገዛቸው ፈልጎአል አለችው፡፡
\v 2 ኤልሳዕም ታዲያ ምን እንዳደርግልሽ ትፈልጊያለሽ? በቤትሽ ምን እንዳለሽ ንገሪኝ? ሲል ጠየቃት፡፡ እርስዋም በትንሽ ማሰሮ ከሚገኝ የወይራ ዘይት በቀር ሌላ ምንም የለኝም ስትል መለሰችለት፡፡
\s5
\v 3 ኤልሳዕም እንዲህ አላት፡- ወደ ጎረቤቶችሽ ሄደሽ ማግኘት የምትችዪውን ያህል ባዶ ማድጋ ለምኚ፤
\v 4 ከዚህም በኋላ አንቺና ልጆችሽ ቤት ገብታችሁ በሩን ዝጉ፡፡ የማሰሮውንም ዘይት ወደ ማድጋዎቹ ማንቆርቆር ጀምሪ፤ እያንዳንዱ ማድጋ በሚሞላበት ጊዜ ለብቻው በማግለል አኑሩት፡፡
\s5
\v 5 ስለዚህም ሴትዮዋ ወደ ቤትዋ ሄዳ ከልጆችዋ ጋር በሩን ዘጋች፤ ዘይት የነበረበትን ትንሽ ማሰሮ አንሥታም ልጆችዋ እያቀረቡላት በማንቆርቆር በየማድጋዎቹ ሞላች፡፡
\v 6 ማድጋዎቹንም ሁሉ ከሞሉ በኋላ ሌላ ትርፍ የለም ወይ ስትል ጠየቀች፤ ከልጆችዋም አንዱ ሌላ ማድጋ የለም ሲል መለሰላት፡፡ ከዚያ በኋላ ዘይቱ መውረዱን አቆመ፡፡
\s5
\v 7 እርስዋም ተመልሳ ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄደች፤ እርሱም እንግዲህ ዘይቱን ሸጠሽ ዕዳሽን ክፈይ፤ ለአንቺና ለልጆችሽ መተዳደሪያ የሚሆንም ብዙ ገንዘብ ይተርፍሻል አላት፡፡
\s5
\v 8 አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርስዋም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፡፡
\v 9 እርስዋም ባልዋን እንዲህ አለችው፤ ብዙ ጊዜ ወደ ቤታችን የሚመጣው ይህ ሰው የተቀደሰ የእግዚአብሔር ሰው ስለ መሆኑ እርግጠኛ ነኝ፡፡
\s5
\v 10 ስለዚህም በሰገነቱ ላይ አንድ ትንሽ ክፍል ሠርተን በዚያች ውስጥ አል፣ ጠረጳዛ፣ ወንበርና የፋኖስ መብራት እናኑርለት፤ እርሱም ወደ እኛ በሚመጣበት ጊዜ እዚያ ያርፋል፡፡
\v 11 አንድ ቀን ኤልሳዕ ወደዚያ እንደገና ሄደ፤ ወደ ተሠራለት ክፍል ገብቶ እረፍት አደረገ፡፡
\s5
\v 12 ኤልሳዕም ለአገልጋዩ ግያዝ እንዲህ አለ፡- ‹‹ይህችን ሱናማዊት ጥራት›› በጠራትም ጊዜ መጥታ በፊቱ ቆመች፡፡
\v 13 ኤልሳዕም ግያዝን እንዲነግራት እንዲህ አለው፡- ‹‹እኛን ለመንከባከብ ይህን ሁሉ ተቸገረሽ፤ እኛ ደግሞ ለአንቺ ምን እናድርግልሽ? ለንጉሥ ወይም ለጦር አዛዥ ስለ አንቺ ልንነግርልሽ እንችላለን? በላት አለው፡፡ እርስዋም ‹‹በዘመዶቼ መካከል ስለምኖር በዚህ ስፍራ ምንም የሚቸግረኝ ነገር የለም›› ስትል መለሰችለት፡፡
\s5
\v 14 ኤልሳዕም ግያዝን ‹‹ታዲያ ምን ልናደርግላት እችላለን? ሲል ጠየቀው፡፡ ግያዝም “እነሆ ልጅ የላትም፣ ባሏም ሸምግሎአል” አለ፡፡
\v 15 ኤልሳዕም ጥራት አለው፡፡ ሲጠራትም መጥታ በበሩ አጠገብ ቆመች፡፡
\v 16 ኤልሳዕም አላት፡- በመጪው ዓመት በዚህ ጊዜ ወንድ ልጅ ትታቀፊያለሽ አላት፡፡ እርስዋም ጌታዬ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እባክህ አገልጋይህን አትዋሻት አለችው፡፡
\s5
\v 17 ሴቲቱም ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በዓመቱ ወንድ ልጅ ወለደች፡፡
\v 18 ሕፃኑም በአደገ ጊዜ አንድ ቀን አባቱ ከአጫጆች ጋር ወዳለበት ሄደ፡፡
\v 19 እርሱም በድንገት “ራሴን! ራሴን! ” ብሎ ወደ አባቱ ጮኸ፡፡ አባትየውም አንዱን አገልጋይ ጠርቶ፡- “ልጁን ወደ እናቱ ውሰድ” ሲል አዘዘው፡፡
\v 20 አገልጋዩም ልጁን ተሸክሞ ወደ እናቱ ባመጣው ጊዜ እርስዋም ተቀብላው በጉልበትዋ እንደታቀፈችው ቆይቶ እኩለ ቀን ላይ ሞተ፡፡
\s5
\v 21 ሴቲቱም ተነሥታ ልጁን በእግዚአብሔር ሰው አልጋ ላይ አስተኝታ በሩን ዘግታበት ተመልሳ ሄደች፡፡
\v 22 ባልዋንም ጠርታ “አንድ አገልጋይና አንድ አህያ ላክልኝ፤ ወደ እግዚአብሔር ሰው ዘንድ ሄጄ እመለሳለሁ አለችው፡፡
\s5
\v 23 ባልዋ “ለምን መሄድ ትፈልጊያለሽ? ዛሬ ሰንበት ወይም የጨረቃ በዓል የሚከበርበት ቀን አይደለም” አላት፡፡ እርስዋም “ግድ የለም፤ እንዳልኩህ አድርግ” አለችው፡፡
\v 24 እርስዋም አህያው እንዲጫንላት ካደረገች በኋላ አገልጋዩን “በተቻለ መጠን አህያው እንዲፈጥን አድርግ፤ እኔም ካልነገርኩህ በቀር ቀስ ብሎ እንዲሄድ ዕድል አትስጠው” ስትል አዘዘችው፡፡
\s5
\v 25 እርስዋም ከዚያ ተነሥታ ኤልሳዕ ወደነበረበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣች፡፡ የእግዚአብሔርም ሰው ገና በሩቅ ሳለች ወደ እርሱ ስትመጣ አይቶ አገልጋዩን ግያዝን ‹‹ተመልከት! ያቺ ሱነማዊት ወደዚህ እየመጣች ነው! አለው፡፡
\v 26 ፈጠን ብለህ ሂድና የእርስዋን፤ የባልዋንና የልጅዋን ደኅንነት ጠይቃት›› አለው፡፡ እርስዋም ግያዝን ‹‹ሁላችንም ደኅና ነን›› ስትል ነገረችው፡፡
\s5
\v 27 ወደ ኤልሳዕ ወደ ተራራው በመጣች ጊዜ እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ሊያርቃት ፈለገ፤ ኤልሳዕ ግን ‹‹ተዋት፤ እርስዋ ተጨንቃለች፣ እግዚአብሔርም ከእኔ ሰውሮታልና ምንም የነገረኝ ነገር የለም›› አለው፡፡
\s5
\v 28 ሴቲቱም ‹‹ጌታዬ፣ ልጅ እንድትሰጠኝ ጠይቄህ ነበርን? ‹አታሳስተኝ› ብዬ ነግሬህ አልነበረምን? አለችው፡፡
\v 29 ኤልሳዕም ግያዝን አለው፡- ለጉዞ በፍጥነት ተነሣና ምርኩዜን በእጅህ ያዝ፡፡ ወደ ቤትዋ ሂድ፡፡ በመንገድ ማንንም ብታገኝ ሰላምታ አትስጥ፤ ማንም ሰላምታ ቢሰጥህ መልስ አትስጥ፡፡ ምርኩዜን በልጁ ፊት ላይ አኑር! አለው፡፡
\s5
\v 30 የልጁ እናት ግን ኤልሳዕን ‹‹በምትተማመንበት በሕያው እግዚአብሔር ስምና በነፍስህ እምላለሁ፤ ከቶ አንተን ትቼ አልሄድም! አለችው፤ ስለዚህ እርስዋን ተከትሎ ለመሄድ ተነሣ፤
\v 31 ግያዝም ወደ ፊት ቀድሞአቸው የኤልሳዕን ምርኩዝ በልጁ ፊት ላይ አኖረ፤ ነገር ግን ልጁ ግን አልተናገረም፣ አልሰማም፡፡ ስለዚህም ተመልሶ ሄዶ ኤልሳዕን ‹‹ልጁ አልተነሣም›› አለው፡፡
\s5
\v 32 ኤልሳዕም ወደ ቤቱ በደረሰ ጊዜ ልጁ ሞቶ አልጋ ላይ ነበር፡፡
\v 33 ስለዚህ ኤልሳዕ ገባና በሩን በልጁና በራሱ ላይ ዘግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡
\v 34 ሄዶም በልጁ ላይ ተጋደመ፤ አፉን በአፉ ላይ፣ ዐይኖቹን በአይኖቹ ላይ፣ እጆቹን በእጆቹ ላይ አደረገ፤ ራሱን በልጁ ላይ ዘርግቶ ተጋደመ፤ የልጁም ሰውነት መሞቅ ጀመረ፡፡
\s5
\v 35 ከዚያም፣ ኤልሳዕ ተነሥቶ በክፍሉ ውስጥ ወዲያና ወዲህ ይመላለስ ጀመር፤ እንደገናም ተመለሰና በመዘርጋት በልጁ ላይ ተጋደመ፡፡ ልጁም ሰባት ጊዜ ካስነጠሰው በኋላ ዐይኖቹን ከፈተ፡፡
\v 36 ስለዚህ ኤልሳዕ ግያዝን ጠርቶ እንዲህ አለ፣ ሱነማይቱን ጥራት አለው፡፡ እርሱም ጠራት፣ እርስዋም በመጣች ጊዜ ኤልሳዕ ልጅሽ ይኸውልሽ አንሽው አላት፡፡
\v 37 እርስዋ ወደ መሬት ለጥ ብላ በኤልሳዕ ጫማ ላይ በመውደቅ እጅ ነሣች፤ ከዚያም በኋላ ልጅዋን ይዛ ሄደች፡፡
\s5
\v 38 ከዚያም ኤልሳዕ ወደ ጌልጌላ መጣ፡፡ በአገሪቱ ራብ በነበረበት ጊዜ የነቢያት ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፡፡ እርሱም አገልጋዩን እንዲህ አለው፡- ትልቅ ድስት ጥደህ ለነቢያቱ ልጆች ወጥ ሥራላቸው አለው፡፡
\v 39 ከነቢያቱም አንዱ ቅጠላ ቅጠል ለመልቀም ወደ ሜዳ ሄደ፡፡ እርሱም በጫካ ውስጥ የበቀለ የቅል ሐረግ አገኘ፤ መሸከም የሚችለውን ያህል በርከት ያለ ቅል ቆርጦ አመጣ፡፡ እርሱም ከተፈውና ወጡ ውስጥ ጨመረው፤ ነገር ግን ምን እንደሆነ ዐላወቁም፡፡
\s5
\v 40 እነርሱም ወጡን ለሰዎቹ እንዲመገቡት አወጡ፡፡ በኋላም እየበሉ ሳለ ጮኸው፣ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፣ በድስቱ ውስጥ ሞት አለ! አሉት፤ ስለዚህም ሊበሉት አልቻሉም፡፡
\v 41 ነገር ግን ኤልሳዕ እንዲህ አለ፡- ጥቂት ዱቄት አምጡልኝ፡፡ ያመጡትን ዱቄት በድስቱ ውስጥ ጨምሮ እንዲህ አለ፡- ለሰዎች እንዲበሉ ወጡን አውጡ፡፡ ከዚያ በወጡ ውስጥ የሚጎዳ ነገር አልተገኘም፡፡
\s5
\v 42 በዓል ሻሊሻ ተብሎ ከሚጠራው ስፍራ አንድ ሰው ወደ እግዚአብሔር ሰው መጥቶ በመከር ጊዜ በመጀመሪያ ከተወቃው ሃያ የገብስ የዳቦ ሙልሙሎችና አዲስ የተቆረጠ እሸት በከረጢቱ አመጣለት፡፡ እርሱም ይህን እንዲበሉ ለነቢያት ልጆች ስጡአቸው አለ፡፡
\v 43 አገልጋዩም እንዲህ አለ፡- በመቶ ሰዎች ፊት ይህን ምን ብዬ ማቅረብ አለብኝ? ነገር ግን ኤልሳዕ አለ፡- እንዲበሉ ለሰዎቹ ስጣቸው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ይበላሉ ያተርፉማል፡፡
\v 44 ስለዚህም አገልጋዩ ምግቡን አቀረበላቸው፣ እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት ሁሉም በልተው ከጠገቡ በኋላ የተረፈ ምግብ ነበር፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 የሶርያ ጦር አዛዥ የነበረው ንዕማን በሶርያ ንጉሥ ዘንድ ታላቅና የተከበረ ነበር፤ ምክንያቱም በእርሱ አማካይነት እግዚአብሔር ለሶርያ ሠራዊት ድልን አጎናጽፎ ነበር፡፡ እርሱም ደግሞ ጠንከራና ብርቱ ሰው ነበር፤ ነገር ግን ለምጻም ነበር፡፡
\v 2 ሶርያውያን በእስራኤላውያን ላይ ወረራ በፈጸሙበት ጊዜ አንዲት ትንሽ እስራኤላዊት ልጃገረድ ማርከው ወስደው ነበር፤ እርስዋም ለንዕማን ሚስት ሠራተኛ ሆና ታገለግል ነበር፡፡
\s5
\v 3 ልጃገረዲቱም እመቤትዋን እንዲህ አለቻት፡- ‹‹ጌታዬ በሰማርያ ወደሚገኘው ነቢይ ቢሄድ እወዳለሁ! እርሱም ጌታዬን ከዚህ ለምጽ ሊያነፃው ይችላል! አለቻት፡፡
\v 4 ንዕማንም ይህን በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ ቀርቦ ልጃገረዲቱ ያለችውን ሁሉ ነገረው፡፡
\s5
\v 5 ስለዚህ የሶርያ ንጉሥ እንዲህ አለ፣ ‹‹ለእስራኤል ንጉሥ ደብዳቤ እልካለሁ፤ አሁን አንተ ሂድ›› ብሎ ፈቀደለት፡፡ ንዕማንም ዐሥር መክሊት ብር፣ ስድስት ሺህ መሐለቅ ወርቅና ዐሥር መለወጫ ልብስ አስጭኖ፣ ጉዞውን ቀጠለ፡፡
\v 6 እርሱም ለእስራኤል ንጉሥ የተጻፈለትን ደብዳቤ ወሰደ፣ ደብዳቤውም እንዲህ ይላል፡- ‹‹ይህ ደብዳቤ የኔ አገልጋይ ስለሆነው ስለ ንዕማን ጉዳይ የሚገልጥ ነው፤ ከለምጹም እንድትፈውሰው ወደ አንተ ልኬዋለሁ›› የሚል ነበር፡፡
\s5
\v 7 የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ በቁጣ ልብሱን ቀደደ፤ እንዲህም አለ፡- ‹‹የሶሪያ ንጉሥ ይህን ሰው እንድፈውስለት እንዴት ይገምታል? እኔ ሰውን ከለምጽ እፈውስ ዘንድ የማዳንና የመግደል ሥልጣን ያለኝ እግዚአብሔር መሰልኩትን? ይህ አባባል ከእኔ ጋር ጠብ ለመጀመር የፈለገ ይመስላል! አለ፡፡
\s5
\v 8 ስለዚህ የእግዚአብሔር ሰው ነቢዩ ኤልሳዕ የእስራኤል ንጉሥ ልብሱን መቅደዱን በሰማ ጊዜ ወደ ንጉሡ እንዲህ ሲል መልእክት ላከ፡- ‹‹ስለምን ልብስህን ቀደድክ? ሰውየውን ወደ እኔ ላከው፤ እርሱም በእስራኤል ነቢይ መኖሩን ያውቃል! አለው፡፡
\v 9 ስለዚህም ንዕማን ከፈረሶችና ከሠረገላዎቹ ጋር ወደ ኤልሳዕ ቤት መጥቶ በር ላይ ቆመ፡፡
\v 10 ኤልሳዕም አንዱን አገልጋይ ልኮ ‹‹ሄደህ በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ራስህን በማጥለቅ ታጠብ፤ ሰውነትህም ይመለሳል፤ ንጹሕም ትሆናለህ› ብለህ ለዚህ ሰው ንገረው›› ሲል ተናገረው፡፡
\s5
\v 11 ንዕማን ግን ተቆጥቶ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም አለ፡- “እኔ ነቢዩ መጥቶ የአምላኩን የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ በሽታዬ ያለበትን ቦታ በእጆቹ በመዳሰስ ከለምጽ በሽታዬ ይፈውሰኛል ብዬ ነበር፡፡
\v 12 በእስራኤል ከሚገኙት ወንዞች ይልቅ በአገሬ በደማስቆ የሚገኙት አባናና ፋርፋ አይሻሉምን? በእነርሱ ታጥቤ ንጹሕ መሆን አልችልምን? ” ስለዚህ ተነሥቶ ሄደ፡፡›
\s5
\v 13 የንዕማንም አገልጋዮች ወደ እርሱ ቀርበው፡- ‹‹ጌታችን ሆይ፣ ነቢዩ ሌላ ከባድ ነገር እንድታደርግ ቢያዝህ ኖሮ ትፈፅመው ነበር፤ ታዲያ ነቢዩ ባዘዘህ መሠረት ታጥበህ ከበሽታህ መንጻት ምን ይከብድሃል? አሉት፡፡
\v 14 ከዚያም ንዕማን የእግዚአብሔር ሰው ባዘዘው መሠረት ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ወርዶ ሰባት ጊዜ በመነከር ታጠበ፤ ከበሽታውም ፈጽሞ ነጻ፡፡ ሰውነቱም እንደ ሕፃን ልጅ ገላ በመታደስ ፍፁም ጤናማ ሆነ፡፡
\s5
\v 15 ንዕማንና አጃቢዎቹ ወደ እግዚአብሔር ሰው ተመልሰው መጥተው በፊቱ ቆሙ፡፡ ንዕማንም እንዲህ አለ፡- ‹‹ከእስራኤል አምላክ በቀር በምድር ላይ ሌላ አምላክ እንደሌለ እነሆ አሁን ዐወቅሁ፡፡ ስለዚህም ከአገልጋይ ይህን ስጦታ እባክህ ተቀበለኝ›› አለው፡፡
\v 16 ኤልሳዕ ግን ‹‹በፊቱ ቆሜ በማገለግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ምንም ስጦታ አልቀበልህም›› ሲል መለሰለት፡፡ ንዕማንም ስጦታውን እንዲቀበል አጥብቆ ቢለምነውም ኤልሳዕ ሊቀበለው አልፈቀደም፡፡
\s5
\v 17 ስለዚህም ንዕማን እንዲህ አለ፡- ‹‹ስጦታዬን የማትቀበለኝ ከሆነ ለሌሎች ባዕዳን አማልክት የሚቃጠልም ሆነ ሌላ አይነት መሥዋዕት የማቀርበውን ከአሁን ጀምሮ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ብቻ ለማቅረብ ስለወሰንሁ የሁለት በቅሎ ጭነት አፈር ይዤ እንድሄድ ፍቀድልኝ፡፡››
\v 18 ስለዚህም የአገሬን ንጉሥ በማጀብ ሬሞን የተባለ ባዕድ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር በዚህ ጉዳይ ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም በዚህ ጉዳይ ይቅር ይለኛል፡፡››
\v 19 ኤልሳዕም ‹‹በሰላም ሂድ! አለው፤ ንዕማንም ተሰናብቶ ሄደ፡፡
\s5
\v 20 እርሱም ጥቂት ራቅ ብሎ እንደ ሄደ፣ የኤልሳዕ አገልጋይ ግያዝ ለራሱ እንዲህ አለ፡- ‹‹ጌታዬ ሶሪያዊው ንዕማን ካመጣው ስጦታ ሳይቀበል አሰናብቶታል፡፡ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፣ ተከትዬው ሄጄ ከእርሱ አንድ ነገር ማግኘት አለብኝ›› ሲል በልቡ አሰበ፡፡
\v 21 ስለዚህም ግያዝ ንዕማንን ከኋላው ተከተለው፡፡ ንዕማንም መለስ ብሎ አንድ ሰው እየሮጠ ሲከተለው ባየ ጊዜ እርሱን ለመገናኘት ከሠረገላው ወርዶ እንዲህ አለ፡- ‹‹ሁሉ ነገር ሰላም ነው?
\v 22 ግያዝም፡- ‹‹ሁሉ ነገር መልካም ነው፡፡ ጌታዬ በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የሚኖሩ ሁለት ወጣት የነቢያት ልጆች ድንገት መጡብኝ፤ አንድ መክሊት ብርና ሁለት መቀየሪያ ልብሶች ላክልኝ ብሎ ልኮኛል›› ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 23 ንዕማንም፡- ‹‹እባክህ ሁለት መክሊት ብር ለመስጠት በጣም ደስተኛ ነኝ›› ሲል መለሰለት፡፡ ብሩን በሁለት ከረጢት ሞልቶ ከሁለት መለወጫ ልብሶች ጋር በሁለት አገልጋዮች አስይዞ ከግያዝ ፊት እንዲሄዱ አደረገ፡፡
\v 24 ግያዝም ወደ ኮረብታው በደረሰ ጊዜ፣ ግያዝ ሁለቱን ከረጢት ብር ከእጃቸው ወስዶ ወደ ቤት አስገባ፡፡ እነርሱንም አሰናብቶአቸው ሄዱ፡፡
\v 25 ወደ ቤት ተመልሶ ገብቶ በጌታው በኤልሳዕ ፊት በቆመ ጊዜ ኤልሳዕ እንዲህ አለው፡- ‹‹ግያዝ ከወዴት መጣህ? እርሱም፡- ‹‹ጌታዬ፣ አገልጋይህ የትም አልሄድኩም›› ሲል መለሰ፡፡
\s5
\v 26 ኤልሳዕም ለግያዝ፡- ‹‹ሰውየው አንተን ለመገናኘት ከሠረገላው ሲወርድ እኔ በመንፈስ ከአንተ ጋር አልነበርኩምን? እነሆ አሁን ገንዘብና ልብስ፣ የወይራና የወይን ተክል ቦታ፣ በግና የቀንድ ከብት ወይም አገልጋዮችን ለመቀበል ጊዜው ነውን?
\v 27 ስለዚህ እነሆ የንዕማን ለምጽ ወደ አንተና ዘሮችህ ለዘላለም ይተላለፋል›› አለው፡፡ ግያዝም ከፊቱ ወጥቶ ሄደ፣ ለምጹም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 የነቢያት ልጆችም ኤልሳዕን፡- ‹‹ከአንተ ጋር የምንኖርበት ስፍራ ከሁላችንም ጠባብ ነው አሉት፡፡
\v 2 ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሄደን ዛፍ ቆርጠን የምንኖርበትን ቤት በዚያ እንድንሠራ ፍቀድልን! አሉት፡፡ ኤልሳዕም ‹‹መልካም ነው ቀጥሉ! በማለት መለሰላቸው፡፡
\v 3 ከእነርሱም አንዱ ኤልሳዕን አብሮአቸው እንዲሄድ ጠየቀው፤ ኤልሳዕም እሄዳለሁ አላቸው፡፡
\s5
\v 4 እርሱም አብሮአቸው ሄደ፤ ወደ ዮርዳኖስም በደረሱ ጊዜ ዛፍ የመቁረጥ ተግባራቸውን ጀመሩ፡፡
\v 5 ነገር ግን አንዱ ዛፍ በመቁረጥ ላይ ሳለ መጥረቢያው ወድቆ ውሃው ውስጥ ጠለቀ፤ እርሱም ድምፁን ከፍ አድርጎ: - ‹‹ጌታዬ ሆይ! መጥረቢያው የተዋስኩት ነው፣ ምን አደርጋለሁ? ሲል ጮኸ፡፡
\s5
\v 6 የእግዚአብሔርም ሰው፡- ‹‹በየት በኩል ነው የወደቀው? ሲል ጠየቀው፡፡ ሰውየውም መጥረቢያው የወደቀበትን ስፍራ አሳየው፡፡ እርሱም አንድ እንጨት ቆርጦ ወደ ውሃው በጣለ ጊዜ መጥረቢያው ተንሳፈፈ::
\v 7 ኤልሳዕም፡- ‹‹ውሰደው›› አለው፡፡ ሰውየውም ጎንበስ ብሎ አነሣው፡፡
\s5
\v 8 እነሆ፣ የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ጦርነት ከፍቶ ነበር፡፡ እርሱም ከጦር አዛዦቹ ጋር ተማክሮ የሚሰፍሩበትን ቦታ መረጠ፡፡
\v 9 የእግዚአብሔርም ሰው: - ‹‹ሶርያውያን ደፈጣ አድርገው ስለሚጠብቁህ ከዚህ ወደዚያ ስፍራ አትቅረብ›› ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ፡፡
\s5
\v 10 የእስራኤልም ንጉሥ ወታደሮቹ ወደሚኖሩበት፣ የእግዚአብሔር ሰው ወደተናገረበትና ወዳስጠነቀቀበት ስፍራ ላከ፡፡ ይህም ድርጊት ከአንድ ጊዜ ወይም ከሁለት ጊዜ በላይ ንጉሡ እዚያ ሲሄድ ከጥበቃ ጋር ነበር፡፡
\v 11 የሶርያ ንጉሥም፡- ‹‹ከእኛ መካከል ከእስራኤል ንጉሥ ጋር ግንኙነት ያለው ማን እንደሆነ አትነግሩኝምን? ሲል ጠየቃቸው፡፡
\s5
\v 12 ከእነርሱም አንዱ ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፣ ከእኛ መካከል ይህን የሚያደርግ ማንም የለም፤ በመኝታ ክፍልህ እንኳ ሆነህ የምትናገረውን ሁሉ ሳይቀር ለእስራኤል ንጉሥ ምሥጢሩን የሚገልጥለት ኤልሳዕ የተባለው ነቢይ ነው›› ሲል መለሰለት፡፡
\v 13 የሶርያው ንጉሥ፡- ‹‹እርሱ የሚገኝበትን ስፍራ ፈልጉ፤ እኔም ልኬ እማርከዋለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ በዶታይን እንደሚኖር ተነገረው፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህ ንጉሡ በፈረሶችና በሠረገሎች የተጠናከረ ብዙ ሠራዊት ወደ ዶታይን ላከ፡፡ እነርሱም በሌሊት ደርሰው ከተማዪቱን ከበቡ፡፡
\v 15 በማግስቱም ማለዳ የኤልሳዕ አገልጋይ ከመኝታው ተነሥቶ ከቤት ሲወጣ፣ በፈረሶችና በሠረገሎች የታጀቡ የሶርያ ወታደሮች ከተማዪቱን መክበባቸውን አየ፡፡ ወደ ኤልሳዕም ተመልሶ: - ‹‹ጌታዬ ወዮ! ምን ማድረግ ይሻለናል? ሲል ጠየቀው፡፡
\v 16 ኤልሳዕም ‹‹አይዞህ አትፍራ፤ ከእነርሱ ጋር ከተሰለፈው ይልቅ ከእኛ ጋር የተሰለፈው ሠራዊት ይበልጣል›› አለው፡፡
\s5
\v 17 ኤልሳዕም ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! ማየት እንዲችል ዐይኖቹን ክፈትለት! ሲል ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን አገልጋይ ዐይኖች ከፈተለት፤ በኮረብታው ብዙ የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ እንዳሉ ተመለከተ፡፡
\v 18 ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ እንዲህ ሲል ጸለየ፡- ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ! እግዚአብሔርም ኤልሳዕ እንደ ጸለየው፣ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ፡፡
\v 19 ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ሶርያውያንን፡- ‹‹መንገድ ተሳስታችኋል፤ የምትፈልጓት ከተማ ይህች አይደለችም፤ ይልቅስ ወደምትፈልጉት ሰው እኔ ልምራችሁ፣ ተከተሉኝ›› ብሎ ወደ ሰማርያ መራቸው፡፡
\s5
\v 20 ወደ ሰማርያም በደረሱ ጊዜ ኤልሳዕ፡- ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች ማየት እንዲችሉ ዐይኖቻቸውን ክፈት! ሲል ጸለየ፡፡ እግዚአብሔርም ዐይኖቻቸውን በከፈተላቸው ጊዜ በሰማርያ መካከል መሆናቸውን ተረዱ፡፡
\v 21 የእስራኤልም ንጉሥ ሶርያውያንን ባያቸው ጊዜ ‹‹ጌታዬ! ልግደላቸውን? ልግደላቸውን? ሲል ኤልሳዕን ጠየቀው፡፡
\s5
\v 22 ኤልሳዕም ‹‹አይሆንም! እንኳን እነዚህን በሰይፍህና በቀስትህ የማረካቸውን ወታደሮች መግደል አይገባህም፤ ይልቅስ የሚበሉትንና የሚጠጡትን ምግብ አቅርብላቸውና ወደ ንጉሣቸው ተመልሰው እንዲሄዱ አድርግ›› አለው፡፡
\v 23 ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ፡፡
\s5
\v 24 ከዚህ በኋላ የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ መላ ሠራዊቱን ሰብስቦ በእስራኤል ላይ በማዝመት ጉዳት አደረሰ፤ የሰማርያን ከተማም ከበበ፡፡
\v 25 ስለዚህ በሰማርያ ጽኑ ራብ ነበር:: ከዚህም የተነሣ የአንድ አህያ ራስ ሰማኒያ መክሊት ብር፣ ሁለት መቶ ግራም የሚያህል የርግብ ኩስ ዋጋ እስከ አምስት መክሊት ብር ይሸጥ ነበር፡፡
\v 26 አንድ ቀን የእስራኤል ንጉሥ በከታማዪቱ የቅጥር ግንብ ላይ በሚመላለስበት ጊዜ አንዲት ሴት: - ‹‹ንጉሥ ሆይ እባክህ እርዳኝ! ስትል ጮኸች፡፡
\s5
\v 27 ንጉሡም ‹‹እግዚአብሔር ካልረዳሽ እኔ እንዴት ልረዳሽ እችላለሁ? ከአውድማው ወይንስ ከወይን መጭመቂያው ይመጣልን?
\v 28 ለመሆኑ ችግርሽ ምንድን ነው? ሲል ጠየቃት፡፡ እርስዋም እንዲህ ስትል መለሰችለት፡- ‹‹ባለፈው ቀን ይህች ሴት ‹ዛሬ ያንቺን ልጅ እንብላ፤ በማግስቱ ደግሞ የእኔን ልጅ እንበላለን› ስትል አሳብ አቀረበች፡፡
\v 29 ስለዚህም የእኔን ልጅ ቀቅለን በላን፤ በማግስቱም ‹ልጅሽን አምጪና እንብላ› ብዬ ጠየቅኋት፤ እርስዋ ግን ደበቀችው፡፡››
\s5
\v 30 ንጉሡም ይህንን የሴትዮዋን ቃል በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ በግንቡ ላይ በመሆኑ በአቅራቢያው የነበረው ሕዝብ ንጉሡ በውስጡ ማቅ ለብሶ እንደ ነበር አዩ፡፡
\v 31 ንጉሡም ድምፁን ከፍ በማድረግ ‹‹የዛሬይቱ ጀምበር ከመጥለቅዋ በፊት የሳፋጥ ልጅ የኤልሳዕ ራስ ሳይቆረጥ ቢያድር እግዚአብሔር እኔን በሞት ይቅጣኝ! ሲል ተናገረ፡፡
\s5
\v 32 በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ ከሽማግሌዎች ጋር በቤቱ ተቀምጦ ነበር፡፡ ንጉሡም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ፡፡ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን፡- ‹‹ይህ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል›› አላቸው፡፡
\v 33 ገና ይህን ተናግሮ ሳይጨርስ ንጉሡ ድንገት ከተፍ ብሎ ‹‹ይህን መከራ ያመጣው እግዚአብሔር ነው፤ ታዲያ ከዚህ በላይ እግዚአብሔርን የምጠብቀው ለምንድን ነው? አለ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ኤልሳዕም፡- ‹‹እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ስማ! ነገ በዚህ ጊዜ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር በሰማርያ በር ይሸመታል›› አለ፡፡
\v 2 በዚህ ጊዜ የንጉሡ ባለሥልጣን ለእግዚአብሔር ሰው እንዲህ ሲል መለሰለት፡- እግዚአብሔር የሰማይ መስኮቶችን እንኳ ቢከፍት ይህ ሊሆን ይችላልን? ኤልሳዕም እንዲህ ሲል መለሰለት፡- ይህ ሲፈጸም በዐኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፤፤ አንተ ግን ከዚህ ምንም አትበላም፡፡
\s5
\v 3 አራት ለምጻሞች ከሰማርያ ከተማ በር ቆመው ነበር፡፡ እርስ በርሳቸውም እንዲህ ተባባሉ፡- እስክንሞት ለምን እዚህ እንቀመጣለን?
\v 4 ወደ ከተማ እንግባ ካልን በከተማው ራብ ስላለ እንሞታለን፡፡ ነገር ግን እዚህ ከተቀመጠንም መሞታችን ነው፤ ወደ ሶርያውያን ጦር ሰፈር እንሂድ፤ በሕይወት ካቆዩንም በሕይወት እንኖራለን፤ ከገደሉንም መሞት ብቻ ነው፡፡
\s5
\v 5 ስለዚህም ቀኑ ሊመሽ ሲል ወደ ሶርያውያን ጦር ሰፈር ሊሄዱ ተነሡ፤ ወደ ሰፈሩም በደረሱ ጊዜ እዚያ ማንም አልነበረም፡፡
\v 6 ይህም የሆነበት ምክንያት እግዚአብሔር የሶርያ ጦር የፈረሶች፣ የሠረገሎችና ሌሎችንም ከፍተኛ የሠራዊት ድምፅ እንዲሰሙ አድርጎ ስለነበረ ነው፤ እርስ በርሳቸውም እንዲህ አሉ፡- የእስራኤል ንጉሥ የሒታውያንና የግብፃውያንን ሠራዊት ቀጥሮ እኛን እያጠቃ ነው፡፡
\s5
\v 7 ስለዚህ ሠራዊቱ በሌሊት ተነሥቶ ሸሸ፤ ድንኳኖቻቸውን፣ ፈረሶቻቸውንና በሰፈሩ ያለውን ሁሉ ትተው ሕይወታቸውን ለማትረፍ ሸሹ፡፡
\v 8 ለምጻሞቹም ወደ ሶርያውያን ሰፈር ዳርቻ በደረሱ ጊዜ ወደ አንዱ ድንኳን በገቡ ጊዜ በሉ፣ ጠጡ፤ ብር፣ ወርቅና ልብስም ወስደው ደበቁ፡፡ እንደገና ተመልሰው ወደ ሌላ ድንኳን ገብተው ያለውን ወስደው እንደበፊቱ አደረጉ፡፡
\s5
\v 9 ከዚያም እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፡- መልካም አላደረግንም፡፡ ዛሬ የምሥራች የሚሆን ታላቅ ነገር አግኝተናል፤ ነገር ግን ዝም ብለናል፡፡ እስኪነጋም ዝም ብንል ቅጣት ይደርስብናል፡፡ አሁን ተነሥተን እንሂድና ለንጉሡ ቤተ ሰብ እንንገር፡፡
\v 10 ስለዚህ ሄደው የከተማውን በር ጠባቂዎች ተጣሩ፤ እንዲህ ብለውም ነገሩአቸው፡- ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ማንም አልነበረም፤ አንዲት ድምፅ እንኳን የለም፤ ነገር ግን ፈረሶችና አህዮች እንደታሰሩ አሉ፣ እንዲሁም ድንኳኖቹም እንዳሉ ናቸው፡፡
\v 11 ከዚያም የበር ጠባቂዎቹ ወሬውን ተናገሩ፤ ከዚያም እስከ ንጉሡ ቤተ ሰብ ድረስ ተሰማ፡፡
\s5
\v 12 ንጉሡም በሌሊት ተነሥቶ ለአገልጋዮቹ እንዲህ አለ፡- ሶርያውያን የደረጉብንን እነግራችኋለሁ፤ እንደተራብን ስለሚያውቁ ራሳቸውን ለመሰወር ሰፈሩን ለቀው ወደ ገጠር ሄደዋል፤ እንዲህም ይላሉ፡- ምግብ ፍለጋ ከከተማ ሲወጡ በሕይወት እንይዛቸዋለን፤ ወደ ከተማም እንወስዳቸዋለን፡፡
\v 13 ከንጉሡም ባለሥልጣናት አንዱ መልሶ እንዲህ አለ፡- ጥቂት ሰዎች ከሞት ከተረፉት አምስት ፈረሶች እንድንወስድ እለምንሃለሁ፡፡ በዚህ ከተማ የተረፈው ሕዝብ ከዚህ በፊት እንደሞቱ ሰዎች ሁሉ ከሞት የሚያመልጥ አይደለም፡፡ ስለዚህ የሆነውን ነገር ለማወቅ እንድንችል እነርሱን እንላክ፡፡
\s5
\v 14 ንጉሡም ሁለት ሠረገላዎችን ከፈረሶች ጋር ከሶርያውያን ሠራዊት በኋላ እንዲህ ሲል ላካቸው፡- ሂዱና ተመልከቱ፡፡
\v 15 እነርሱም ከሶርያውያን ኋላ ወደ ዮርዳኖስ ሄዱ፤ በየመንገዱም ሁሉ ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለው የሄዱትን ብዙ ልብስና መሣሪያ ሁሉ አገኙ፡፡ መልእክተኞቹም ተመልሰው ለንጉሡ ነገሩት፡፡
\s5
\v 16 ሕዝቡ ሄደው የሶርያውያንን ሰፈር ዘረፉ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ከዚህ በፊት እንደተናገረው ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም አምስት ኪሎ የገብስ ዱቄት በአንድ ብር ተሸመተ፡፡
\v 17 ንጉሡም የከተማዪቱ ቅጥር በር በባለሥልጣኑ ኃላፊነት እንዲጠበቅ አድርጎ ነበር፤ ነገር ግን ያንን አገልጋይ ሕዝቡ ረጋጦት በዚያው ሞተ፡፡ ይህም የሆነው ንጉሡ የእግዚአብሔርን ሰው ለማነጋገር በሄደ ጊዜ የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ነበር፡፡
\s5
\v 18 ስለዚህም የእግዚአብሔር ሰው ለንጉሡ፣ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ከተማ በር ሦስት ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ብር ይሸመታል ብሎት ነበር፡፡
\v 19 በዚያም ባለሥልጣኑ ለእግዚአብሔር ሰው እንዲህ ሲል መልሶ ነበር፡- እግዚአብሔር የሰማይ መስኮቶችን እንኳ ቢከፍት ይህ እንዴት ይሆናል? ኤልሳዕም፡- ይህ ሲሆን በዐይንህ ብቻ ትመለከታለህ፤ ነገር ግን ከዚህ ምንም አትበላም ብሎት ነበር፡፡
\v 20 እንግዲህ ያ የንጉሡ ባለሥልጣን በሰማርያ ከተማ ቅጥር በር ላይ ሕዝብ ረጋግጦት ለመሞት የበቃው ይህ ትንቢት ስለ ተፈጸመበት ነው፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ኤልሳዕም ልጅዋን ከሞት ያስነሣላትን፣ በሱነም የነበረችውን ሴት አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፡- እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቆይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተ ሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ፡፡
\v 2 ስለዚህም የኤልሳዕን ምክር ሰምታ ከነቤተ ሰብዋ ወደ ፍልስጥኤም አገር በመሰደድ እስከ ሰባት ዓመት ቆየች፡፡
\s5
\v 3 ሴቲቱም ከሰባቱ የራብ ዓመቶች ፍፃሜ በኋላ ከፍልስጥኤም አገር ተመልሳ መጣች፤ ስለ መኖሪያ ቤትዋና ስለ እርሻ መሬትዋ ለመጠየቅ ወደ ንጉሡ ሄደች፡፡
\v 4 ንጉሡም ከእግዚአብሔር ሰው አገልጋይ ከግያዝ ጋር፡- ‹‹ኤልሳዕ ስላደረጋቸው ታላላቅ ነገሮች ንገረኝ›› እያለ ይነጋገር ነበር፡፡
\s5
\v 5 ግያዝም ኤልሳዕ እንዴት የሞተውን ሕፃን እንዳስነሣው ለንጉሡ እየነገረ እያለ ኤልሳዕ ሕፃኑን ከሞተ ያስነሣላት ሴት ንጉሡን ስለ መኖሪያ ቤትዋና ስለ እርሻ መሬቷ ለመጠየቅ መጣች፡፡ ግያዝም እንዲህ አለ፡- ‹‹ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሴቲዮዋ እነሆ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣው ልጅዋም ይሄ ነው!
\v 6 ንጉሡም ሴቲቱን ስለ ሕፃኑ በጠየቃት ጊዜ በሚገባ አስረዳችው፡፡ ስለዚህ ንጉሡ አንዱን ባለሥልጣን ስለ እርስዋ እንዲህ ሲል አዘዘ፡- የእርስዋ የሆነውን ማናቸውንም ነገርና የእርሻ መሬትዋን ከሰባት ዓመት ጀምሮ አገሩን ከለቀቀችበት እስካሁን ያለውን ሰብል ጭምር እንዲመልስላት አዘዘው፡፡
\s5
\v 7 የሶርያ ንጉሥ ቤን ሀዳድ በታመመ ጊዜ ኤልሳዕ ወደ ደማስቆ ሄደ፡፡ ንጉሡም የእግዚአብሔር ሰው መምጣቱን ሰማ፡፡
\v 8 ንጉሡም አዛሄልን፡- ‹‹በእጅህ አንድ ስጦታ ይዘህ ወደ እግዚአብሔር ሰው ሂድና ከዚህ ሕመም እድናለሁን? ብለህ ጠይቅ አለው፡፡
\v 9 ስለዚህ አዛሄል በደማስቆ ከሚገኘው ምርጥ የምድር በረከት ሁሉ በአርባ ግመሎች ጭኖ ወደ ኤልሳዕ ሄደ፡፡ አዛሄልም መጥቶ በኤልሳዕ ፊት ቆመና፡- ‹‹ልጅህ ንጉሥ ቤን ሀዳድ ከሕመሙ ይድን እንደሆነ እንድትነግረው እጠይቅህ ዘንድ ልኮኛል›› አለው፡፡
\s5
\v 10 ኤልሳዕም፡- ‹‹ቤን ሀዳድን አንተ በርግጥ ትድናለህ ብለህ ንገረው፣ ነገር ግን እንደሚሞት እግዚአብሔር ገልጦልኛል፤›› አለው፡፡
\v 11 ከዚያም ኤልሳዕ ፊቱን በማጥቆር ትኩር ብሎ እስኪያፍር ድረስ አዛሄልን ተመለከተው፤ የእግዚአብሔርም ሰው እንባውን ማፍሰስ ጀመረ፡፡
\v 12 አዛሄልም፡- ‹‹ጌታዬ ስለምን ታለቅሳለህ? ሲል ጠየቀው፡፡ ኤልሳዕም፡- ‹‹በእስራኤል ሕዝብ ላይ የምትፈፅመውን አሰቃቂ ነገር ስለማውቅ ነው፡፡ ምሽጎቻቸውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ወጣቶቻቸውን በሰይፍ ትገድላለህ፤ ሕፃናቶቻቸውን በድንጋይ ትከሰክሳለህ፤ የእርጉዞች ሴቶችንም ሆድ ትሰነጥቃለህ›› ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 13 አዛሄልም፡- ‹‹ይህን ታላቅ ነገር የሚያደርግ አገልጋይህ ማን ሆኖ ነው? ይህ ሰው ውሻ ብቻ ነው ሲል ጠየቀው፡፡ ኤልሳዕም፡- ‹‹አንተ የሶርያ ንጉሥ እንደምትሆን እግዚአብሔር ገልጦልኛል›› ሲል መለሰለት፡፡
\v 14 ከዚያም አዛሄል ተመልሶ ወደ ጌታው ወደ ንጉሡ መጣ፡፡ ‹‹ኤልሳዕ ምን አለህ? ሲል ቤን ሀዳድ ጠየቀው፡፡ አዛሄልም፡- ‹‹አንተ በእርግጥ እንደምትድን ነግሮኛል›› ሲል መለሰለት፡፡
\v 15 ነገር ግን በማግስቱ አዛሄል ብርድ ልብስ ወስዶ ውሃ ውስጥ ነከረ፤ ከዚያም በቤን ሀዳድ ፊት ወረወረውና ታፍኖ ሞተ፡፡ አዛሄልም በቤን ሀዳድ ፈንታ ተተክቶ የሶርያ ንጉሥ ሆነ፡፡
\s5
\v 16 የእስራኤል ንጉሥ የአክአብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት ኢዮራም በይሁዳ መንገሥ ጀመረ፡፡ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ልጅ ነበር፡፡
\v 17 እርሱም በነገሠ ጊዜ ሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነበር፡፡ መቀመጫውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ስምንት ዓመት ነገሠ፡፡
\s5
\v 18 ሚስቱም የአክዓብ ልጅ ስለነበረች የእስራኤል ነገሥታት ይፈፅሙት የነበረውን እንደ አክዓብ ቤተ ሰብ የክፋት መንገድ ተከተለ፡፡ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ሥራ ሠራ፡፡
\v 19 ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከዘሩ መንግሥታትን እንደማያጠፋ ለአገልጋዩ ለዳዊት ተስፋ ሰጥቶት ስለ ነበር ይሁዳን ማጥፋት አልፈለገም፡፡
\s5
\v 20 በኢዮራም ዘመነ መንግሥት ኤዶም በይሁዳ ላይ ዐመፀ፤ ለራሳቸውም ንጉሥ አነገሡ፡፡
\v 21 ስለዚህም ኢዮራም ሠረገሎቹን በመላ አሰልፎ ወደ ጸዒር ዘመተ፡፡ የኤዶም ሠራዊትም ኢዮራምን በከበቡ ጊዜ፤ በሌሊት ተነሥተው የሠረገሎቹን አዛዦች አጠቁአቸው፤ ነገር ግን የኢዮራም ሠራዊት ሮጠው ወደየቤታቸው ተበታተኑ፡፡
\s5
\v 22 ስለዚህ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኤዶም በይሁዳ አገዛዝ ላይ አመፁ፡፡ በተመሳሳይ ጊዜም የልብና ከተማ አመፀች፡፡
\v 23 ኢዮራም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ የነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 24 ኢዮራም ሞተ፤ በዳዊት ከተማም በሚገኘው በአባቶቹ መካነ መቃብር ተቀበረ:: ከዚያም አካዝያስ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ ነገሠ፡፡
\s5
\v 25 የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 26 አካዝያስ በነገሠ ጊዜ የሃያ ሁለት ዓመት ወጣት ነበረ፡፡ እርሱም በኢየሩሳሌም አንድ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱ ጎቶልያ ተብላ የምትጥራው የእስራኤል ንጉሥ የዘንበሪ ልጅ ነበረች፡፡
\v 27 አካዝያስ የንጉሥ አክዓብን መንገድ ተከተለ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ አደረገ፡፡ ምክንያቱም አካዝያስ የንጉሥ አከዓብን ልጅ ስለሚያገባ ነበር፡፡
\s5
\v 28 አካዝያስም ከንጉሥ አከዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሆኖ ከሶርያ ንጉሥ ከአዛሄል ጋር ለመዋጋት ወደ ራሞት ገለዓድ ዘመተ፡፡ ሶርያውያንም ኢዮራምን አቆሰሉት፡፡
\v 29 ኢዮራምም ከሶሪያ ንጉሥ አዛሄል ጋር በሬማት በተደረገው ጦርነት የደረሰበትን ቁስሉን ለመታከም ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ተመለሰ፡፡ ስለዚህ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ የአከዓብ ልጅ ኢዮራም ስለደረሰበት ጉዳት ለመጠየቅ ወደ ኢይዝራኤል ከተማ ሄደ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 ነቢዩ ኤልሳዕም ከነቢያት ልጆች አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለ፡- ‹‹በገለዓድ ወደምትገኘው ወደ ሬማት ለመሄድ ተዘጋጅ፤ ይህንንም የዘይት ማሰሮ ያዝ፡፡
\v 2 እዚያም በደረስህ ጊዜ የኢዮሳፍጥ ልጅ የናሜሲ ልጅ የሆነውን ኢዩን ፈልግ፤ እርሱንም ከጓደኞቹ በመለየት ወደ ውስጥ አስገባው፡፡
\v 3 ይህን የወይራ ዘይት በራሱ ላይ አፍስስበትና እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- ‹አንተ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን ቀብቼሃለሁ›› ብለህ ንገረው አለው፡፡ ከዚያም በሩን ከፍተህ ከዚያ ስፍራ ተነሥተህ ሽሽ፤ አትዘገይም፡፡››
\s5
\v 4 ስለዚህም ወጣቱ ነቢይ ወደ ሬማት ሄደ፡፡
\v 5 እዚያም በደረሰ ጊዜ የጦር አዛዦች ተቀምጠው ነበር፡፡ ወጣቱም ነቢይ እንዲህ አለ፡- ‹‹ጌታዬ የምነግርህ መልእክት አለኝ›› አለው፡፡ ኢዩም፡ ‹‹ለማናችን ነው የምትነግረው? ሲል ጠየቀው፡፡ ወጣቱም ነቢይ፡- ‹‹የምናገረው ለአንተ ነው ጌታዬ›› ሲል መለሰለት፡፡
\v 6 ስለዚህ ኢዩ ተነሥቶ ወደ ቤት ገባ፤ ወጣቱ ነቢይም ዘይቱን በኢዩ ራስ ላይ አፈሰሰበትና እንዲህ አለው፡- ‹‹የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚናገረው ይህ ነው፡- ‹በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን ቀብቼሃለሁ፡፡
\s5
\v 7 አንተም የአክዓብን የጌታህን ቤተ ሰብ መግደል አለብህ፤ በዚህም በኤልዛቤል የተገደሉትን፣ የአገልጋዮቼን የነቢያቴንና የእግዚአብሔር አገልጋዮችን ደም በሙሉ እበቀላለሁ፡፡
\v 8 መላው የአክዓብ ቤተ ሰብና ትውልዱ ሁሉ ይጠፋሉ፤ ከእርሱ ቤተ ሰብ ወንድ የሆነውን ማንኛውንም ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አጠፋለሁ፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል ነገሥታት በነበሩት በናባጥ ልጅ በኢዮርብአምና በአኪያ ልጅ በባኦስ ቤተሰቦች ላይ ያደርግኹትን ሁሉ በአክዓብ ቤተ ሰብ ላይ እፈፅማለሁ፡፡
\v 10 ኤልዛቤል የመቀበር ዕድል እንኳ አታገኝም፤ የኤልዛቤልን ሬሳ በኢይዝራኤል ከተማ ውሾች ይበሉታል፤ ማንም አይቀብራትም፡፡›› ከዚያም ወጣቱ ነቢይ በሩን ከፍቶ ከዚያ ክፍል ወጥቶ ሸሸ፡፡
\s5
\v 11 ከዚያም ኢዩ ወደ ንጉሡ አገልጋዮች በመጣ ጊዜ አንዱ፡- ‹‹ሁሉ ነገር ሰላም ነውን? ለመሆኑ ይህ እብድ ወደ አንተ ለምን መጣ? ሲሉ ጠየቁት፡፡ ኢዩም ‹‹ሰውየውንም ሆነ እርሱ የሚናገረውን እናንተ ታውቁታላችሁ›› አላቸው፡፡
\v 12 እነርሱም ‹‹ይህ ሐሰት ነው፡፡ አንተ ንገረን›› ሲሉ መለሱለት፡፡ ኢዩም፡- ‹‹በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንድትሆን እግዚአብሔር ቀብቼሃለሁ››› አለኝ ሲል አስረዳቸው፡፡
\v 13 ከዚያም እነርሱ ወዲያውኑ ልብሳቸውን እያወለቁ ኢዩ በሚራመድበት ደረጃ ላይ አነጠፉ፡፡ በዚያም ላይ እንዲቆም አድርገው እምቢልታ ነፉ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው ‹‹ኢዩ ንጉሥ ነው! ሲሉ ጮኹ፡፡
\s5
\v 14 በዚህ ሁኔታ የኢዮሳፍጥ ልጅ የናሜሲ ልጅ ኢዩ በንጉሥ ኢዮራም ላይ ሤራ ማካሄድ ጀመረ፡፡ ኢዮራም ከሶርያ ንጉሥ አዛሄል ጋር በሬማት ገለዓድና እስራኤል በሙሉ ሲከላከሉ፤ ነገር ግን በዚያን ጊዜ በኢይዝራኤል ውስጥ በማገገም ላይ ነበር፡፡
\v 15 ስለዚህም ኢዩ የጦር መኮንኖች ‹‹እናንተ በእርግጥ ከእኔ ጋር ከሆናችሁ በኢይዝራኤል የሚኖረውን ሕዝብ ለማስጠንቀቅ አንድ ወሬ ከሬማት ወጥቶ እንዳያመልጥ አድርጉ›› አላቸው፡፡
\v 16 ከዚህም በኋላ ኢዩ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ገሠገሠ፤ በዚህ ጊዜ ኢዮራም ገና ከቁስሉ አልዳነም ነበር፤ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስም ሊጠይቀው መጥቶ በዚያ ነበር፡፡
\s5
\v 17 በኢይዝራኤል ከተማ መጠበቂያ ግንብ ላይ የነበረው ጠባቂ ኢዩና ተከታዩ ጭፍራ ሲመጡ ከሩቅ አይቶ ‹‹ሰዎች እየጋለቡ በቡድን ሲመጡ አያለሁ! አለ፡፡ ኢዮራምም ‹‹አንድ ፈረሰኛ ልከህ የሚመጡትን ሰዎች ሰላም ነውን? ብሎ እንዲጠይቅ አድርግ›› አለው፡፡
\v 18 መልእክተኛውም ጋልቦ ሄዶ ኢዩን፡- ‹‹ንጉሡ አመጣጥህ በሰላም ነውን? ይልሃል ሲል ጠየቀው፡፡ ኢዩም፣ ‹‹አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ! ሲል መለሰለት፡፡ ከዚያም ጠባቂው፡- ‹‹መልእክተኛው በመምጣት ላይ ወዳለው ጭፍራ ደርሶአል፤ ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም›› ሲል ለንጉሡ ነገረው፡፡
\s5
\v 19 ሌላም መልእክተኛ ተልኮ ያንኑ ተመሳሳይ ጥያቄ ለኢዩ አቀረበለት፡፡ ኢዩም፡- ‹‹አንተ ከሰላም ጋር ምን ግንኙነት አለህ? ይልቅስ ወደ ኋላ አልፈህ ተከተለኝ! ሲል መለሰለት፡፡
\v 20 ጠባቂውም እንደገና፡- ‹‹እርሱ ተገናኝቶአል ነገር ግን ተመልሶ አልመጣም›› አለ፡፡ ‹ምክንያቱም የሠረገላ አነዳዱ እንደ እብድ ሰው እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ ነው! ልክ ኢዩን ይመስላል! ሲል ተናገረ፡፡
\s5
\v 21 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮራም፡- ‹‹ሠረገላ አዘጋጁልኝ›› አለ፡፡ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት ኢዮራም የእስራኤል ንጉሥና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላችው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፡፡ እነርሱም ኢዩን የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት፡፡
\v 22 ኢዮራምም፡- ‹‹ኢዩ ሆይ አመጣጥህ በሰላም ነውን? ሲል ጠየቀ፡፡ ኢዩም፡- ‹‹የእናትህ የኤልዛቤል የአመንዝራይቱ ጣዖትና ጥንቆላ ሥራ በዝቶ እያለ ምን ሰላም አለ? ሲል መለሰለት፡፡
\s5
\v 23 በመሆኑም ኢዮራም፡- ‹‹አካዝያስ ሆይ! ይህ ክሕደት ነው! እያለ ሠረገላውን መልሶ ሸሸ፡፡
\v 24 ኢዩ ቀስቱን ስቦ ባለው ኀይል ሁሉ ፍላጻውን ባስፈነጠረ ጊዜ ኢዮራምን ወግቶ በትከሻዎቹ መካከል ወደ ልቡ ዘለቀ፤ ኢዮራምም ሞቶ በሠረገላው ውስጥ ወደቀ፡፡
\s5
\v 25 ኢዩም ቢድቃር ተብሎ የሚጠራውን የጦር አዛዥ ‹‹ሬሳውን አንሥተህ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ ወርውረህ ጣለው አለው፡፡ እኔና አንተ የንጉሥ ኢዮራም አባት ከነበረው ከአክዓብ በስተኋላ እየጋለብን ስንሄድ እግዚአብሔር በአክዓብ ላይ የተናገረውን ቃል አስታውስ፡፡
\v 26 ‹ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ› የሚል ነበር፡፡›› ስለዚህ ኢዩ ‹‹እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈፀም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው›› ሲል የጦር አዛዡን አዘዘው፡፡
\s5
\v 27 የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ይህን ባየ ጊዜ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ወደ ቤት ሀጋን ከተማ ሸሸ፡፡ ኢዩ ተከታትሎ እያሳደደው ‹‹እርሱንም ደግሞ በሠረገላው ውስጥ ግደሉት›› አለ፡፡ እነርሱም ተከታትለው በኢዮርብዓም ከተማ አጠገብ በጉር በሠረገላው ሳለ ወጉት፤ አካዝያስም ወደ መጊዶ ከተማ ሸሸ፤ በዚያም ሞተ፡፡
\v 28 አገልጋዮቹም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም ወስደው በዳዊት ከተማ በሚገኘው በአባቶቹ መካነ መቃብር ቀበሩት፡፡
\s5
\v 29 አካዝያስ የይሁዳ ንጉሥ የሆነው የእስራኤል ንጉሥ የአክዓብ ልጅ ኢዮራም በነገሠ በዐሥራ አንደኛው ዓመት ነበር፡፡
\s5
\v 30 ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል በደረሰ ጊዜ፣ ኤልዛቤል ይህን ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በመስኮት ትመለከት ነበር፡፡
\v 31 ኢዩም የቅጥሩን በር አልፎ ሲገባ ‹‹አንተ ዘምሪ! አንተ የጌታህ ገዳይ፣ እዚህ ደግሞ የመጣሃው በሰላም ነውን? አለችው፡፡
\v 32 ኢዩ ቀና ብሎ ወደ ላይ በመመልከት፡- ‹‹ከእኔ ጋር የሚተባበር ማን ነው? አለ፡፡ ቁጥራቸው ሁለት ወይም ሦስት የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በመስኮት ወደ እርሱ ተመለከቱ፡፡
\s5
\v 33 ኢዩም ‹‹ኤልዛቤልን ወደ ታች ወርውሯት! አላቸው፡፡ እነርሱም አንሥተው በወረወሯት ጊዜ ደምዋ በግንቡና በፈረሶች ላይ ተረጨ ኢዩም ሬሳዋን በፈረስና ሠረገላው ረጋገጠ፡፡
\v 34 ኢዩም ወደ ቤተ መንግሥቱ ገብቶ ተመገበ፤ ጠጣም፡፡ ከዚያም ‹‹የንጉሥ ልጅ ነችና ያችን የተረገመች ሴት ቅበሩአት›› አለ፡፡
\s5
\v 35 ሊቀብሩዋት የሄዱ ሰዎች ግን ከራስ ቅልዋ፣ ከእግሮችዋና ከእጆችዋ መዳፍ በቀር ምንም አላገኙም፡፡
\v 36 ይህንንም ለኢዩ በነገሩት ጊዜ ኢዩ እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህ ሁሉ የተፈፀመው እግዚአብሔር በአገልጋዩ በቴስቢያዊው በኤልያስ አማካይነት አስቀድሞ በተናገረው መሠረት ነው፤ ይኸውም ‹የኤልዛቤልን ሬሳ በኢይዝራኤል ውሾች ይበሉታል፡፡
\v 37 ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርሷነቷን ለየቶ በማወቅ፡- ይህች ኤልዛቤል ናት ሊል አይችልም፡፡››
\s5
\c 10
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ የአክዓብ ሰባ ትውልድ በሰማርያ ይገኝ ነበር፡፡ ኢዩ ደብዳቤ ጽፎ አንዳንድ ቅጂ ለከተማዪቱ ገዢዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የአክዓብ ትውልድ ጠባቂዎች ሁሉ ላከ፡፡ ደብዳቤውም እንዲህ ይላል፡-
\v 2 ‹‹እናንተ ለንጉሡ ትውልድ፣ ፈረሶችና ሠረገሎች የጦር መሣሪያዎችና የተመሸጉ ከተሞች በእናንተ በእጃችሁ ለሚገኙ ሁሉ ኃላፊዎች ናችሁ፡፡ እንግዲህ ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳችሁ ወዲያውኑ፡-
\v 3 ከንጉሡ ትውልድ የተሻለውን አንዱን መርጣችሁ በአባቱ ዙፋን አንግሡት፤ ለእርሱም ለሥርወ መንግሥቱ ተዋጉለት! የሚል ነበር፡፡
\s5
\v 4 ነገር ግን እነርሱም በፍርሃት ተሸብረው ‹‹ንጉሥ ኢዮራምና ንጉሥ አካዝያስ ሊቋቋሙት ያልቻሉትን እኛ እንዴት ኢዩን ልንቋቋመው እንችላለን? አሉ፡፡
\v 5 ስለዚህም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊና የከተማዪቱ ገዢ ከታወቁ የአገር ሽማግሌዎችና ከአሳዳጊ ሞግዚቶች ጋር በመተባበር ለኢዩ ‹‹እኛ አገልጋዮችህ ነን፤ አንተ የምታዘንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁዎች ነን፤ እኛ ማንንም አናነግሥም፤ አንተ መልካም መስሎ የታየህን አድርግ›› ሲሉ መልእክት ላኩ፡፡
\s5
\v 6 ኢዩም፡- ‹‹እናንተ ከእኔ ጋር ከተባበራችሁና ትእዛዜንም ለመፈፀም ዝግጁዎች ከሆናችሁ ነገ በዚህ ጊዜ የንጉሥ አክዓብን ዘሮች ሁሉ ራሶቻቸውን ቆርጣችሁ ወደ ኢይዝራኤል ይዛችሁልኝ እንድትመ›ጡ› ሲል ሌላ ደብዳቤ ጻፈላቸው፡፡ ሰባውም የንጉሥ አክዓብ ትውልድ በታወቁ የአገር ሽማግሌዎች ጥበቃ ሥር ነበሩ፡፡
\v 7 የኢዩ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው የሰማርያ መሪዎች ሰባውንም የአክዓብ ተወላጆች በሙሉ ገደሉ፤ ራሶቻቸውንም በመቁረጥ በቅርጫት ሞልተው በኢይዝራኤል ወደ ነበረው ወደ ኢዩ ላኩለት፡፡
\s5
\v 8 ኢዩም የአክዓብ ትውልድ ራሶች ተቆርጠው መምጣታቸውን በሰማ ጊዜ በከተማይቱ ቅጥር በር በሁለት ረድፍ ተከምረው እስከ ተከታዩ ቀን ጠዋት ድረስ እንዲቆዩ ትእዛዝ ሰጠ፡፡
\v 9 በማግስቱ ማለዳ ላይ ኢዩ ወደ ከተማይቱ ቅጥር በር ሄዶ በዚያ ለተሰበሰቡት ሕዝብ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ ‹‹በንጉሥ ኢዮራም ላይ በማሤር የገደልኩት እኔ ነበርኩ፤ ስለዚህም እናንተ በዚያ ጉዳይ አትጠየቁበትም፤ ነገር ግን እነዚህን ሁሉ የገደለ ማነው?
\s5
\v 10 ይህም ሁሉ እግዚአብሔር ስለ አክዓብ ትውልድ የተናገረው ቃል እውነት መሆኑን ያስረዳል፤ እግዚአብሔር በአገልጋዩ በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት የተናገረውን ቃል ፈፅሞታል፡፡››
\v 11 ከዚህም በኋላ ኢዩ በኢይዝራኤል የሚኖሩትን ሌሎቹን የአክዓብን ዘመዶችና ባለሥልጣናት የነበሩትን እንዲሁም የቅርብ ወዳጆቹንና ካህናቱን አንድም ሳይቀር ሁሉንም ገደለ፡፡
\s5
\v 12 ኢዩ ከኢይዝራኤል ተነሥቶ ወደ ሰማርያ ሄደ፤ በመንገድ ሳለም ‹‹የእረኞች ሰፈር›› ተብሎ በሚጠራው ቦታ ሲደርስ፡-
\v 13 ከሟቹ የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ዘመዶች መካከል ጥቂቶቹን አግኝቶ ‹‹እናንተ እነማን ናችሁ? ሲል ጠየቀ፡፡ እነርሱም ‹እኛ የአካዝያስ ዘመዶች ነን፤ አሁንም የንግሥት ኤልዛቤልን ልጆችና የቀሩትንም ንጉሣውያን ቤተ ሰብ እጅ ለመንሣት ወደ ኢይዝራኤል መሄዳችን ነው›› ሲሉ መለሱለት፡፡
\v 14 ኢዩም ‹‹እነዚህን ሰዎች ከነሕይወታቸው ያዙአቸው! ሲል ለጭፍሮቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ ጭፍሮቹም ያዙአቸው፤ ኢዩም በዚያው በቤት ኤክድ አጠገብ ገደላቸው፡፡ ብዛታቸውም በሙሉ አርባ ሁለት ሲሆን ከእነርሱ አንድ እንኳ በሕይወት አልተረፈም፡፡
\s5
\v 15 ኢዩ ተነሥቶ እንደገና ጉዞ ቀጠለ፤ በመንገድ ሳለም የሬካብን ልጅ ኢዮናዳብን አገኘ፤ ኢዩም ሰላምታ ከሰጠው በኋላ ‹‹የእኔ ልብ ከአንተ ጋር እንደ ሆነ የአንተ ልብ ከእኔ ጋር ነውን? ሲል ጠየቀው፡፡ ኢዮናዳብም ‹‹አዎን ከአንተ ጋር ነው›› ሲል መለሰለት፡፡ ኢዩም ‹‹እንግዲያውስ ጨብጠኝ›› ሲል መለሰለት፤ እጅ ለእጅ ተያይዘው ኢዩ ደግፎት በሠረገላው ላይ አስቀመጠው፡፡
\v 16 ‹‹ከእኔ ጋር ሆነህ እኔ ለእግዚአብሔር ምን ያህል ታማኝ እንደ ሆንኩ ራስህ ተመልከት›› አለው፤ አብረውም እየጋለቡ ወደ ሰማርያ ሄዱ፡፡
\v 17 ወደ ሰማርያ በደረሱ ጊዜ ኢዩ አንድም ሳያስቀር በሰማርያ ያሉትን የአክዓብን ዘመዶች በሙሉ ፈጀ፤ ይህም ሁሉ የሆነው እግዚአብሔር በነቢዩ ኤልያስ አማካይነት በተናገረው ቃል መሠረት ነበር፡፡
\s5
\v 18 ከዚያም ኢዩ የሰማርያን ሕዝብ በአንድነት ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ንጉሥ አክዓብ ባዓልን ያገለገለው በመጠኑ ነበር፤ እኔ ግን ከእርሱ ይበልጥ ላገለግለው እፈልጋለሁ፤
\v 19 ስለዚህም የባዓልን ነቢያት በሙሉ ባዓልን የሚያመልኩትንና ካህናቱን ጭምር በአንድነት ጠርታችሁ ሰብስቡልኝ፤ በምንም ምክንያት የሚቀር አይኑር፤ እኔ ለባዓል ታላቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ በዚያ የማይገኝ ማንም ሰው ቢኖር በሕይወት አይኖርም፡፡›› ይህም ሁሉ ባዓልን የሚያመልኩትን ሁሉ ለመግደል ኢዩ ያቀደው የተንኮል ዘዴ ነበር፡፡
\v 20 ከዚህም በኋላ ኢዩ ‹‹ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት ክብረ በዓል ይደረግ! ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ይህም በዐዋጅ ተነገረ፡፡
\s5
\v 21 ኢዩም በእስራኤል ምድርና ባዓልን ለሚያመልኩ ሁሉ መልእክት ላከ፡፡ ማንም ከጫፍ እስከ ጫፍ ሳይመጣ የቀረ አልነበረም፤ ሁሉም ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ገብተው ዳር እስከ ዳር ሞሉት፡፡
\v 22 ከዚያ ኢዩ የተቀደሱ አልባሳት ኀላፊ የሆነው ካህን አልባሳትን ሁሉ አውጥቶ ለባዓል አምላኪዎች እንዲያመጣላቸው አዘዘ፡፡ እንደታዘዘውም አልባሳቱን አመጣላቸው፡፡
\s5
\v 23 ስለዚህም ኢዩ ራሱ ከሬካብ ልጅ ከኢዮናዳብ ጋር አብሮ ወደ ባዓል ቤተ መቅደሱ ገባ፤ በዚያም ለሕዝቡ በዚህ የሚገኙት የባዓል አምላኪዎች ብቻ መሆናቸውንና እግዚአብሔርን የሚያመልክ አንድም አለመኖሩን በሚገባ አረጋግጡ ሲል ተናገረ፡፡
\v 24 ከዚያም እርሱና ኢዮናዳብ ለባዓል ልዩ ልዩ መሥዋዕትንና የሚቃጠል መሥዋዕትን ለማቅረብ ሄዱ፡፡ ኢዩም በባዓል ቤተ መቅደሱ ዙሪያ ሰማኒያ ወታደሮች በማሰለፍ እነዚህን ሁሉ ሰዎች እንድትገድሉ፣ ከእነርሱ አንድ እንኳ የሚያመልጥ ሰው ቢኖር በዚያ ሰው ምትክ እርሱ ራሱ ይገደላል ሲል መመሪያ ሰጥቶአቸው ነበር፡፡
\s5
\v 25 ኢዩ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ ወዲያውኑ ለጠባቂዎችና ለአዛዡ፡- ሂዱና ማንም ሰው እንዳያመልጥ ግደሉአቸው አለ፡፡ እነርሱም በሰይፍ ስለት ሁሉንም ገደሉአቸው፤ ሬሳቸውንም ሁሉ እየጎተቱ ወደ ውጪ ጣሉ፤ ጠባቂና የጦር አዛዦቹ ወደ ባዓል ቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ገቡ፡፡
\v 26 ከዚያም በባዓል ቤተ መቅደስ የነበረውን የድንጋይ ዐምዶች ወደ ውጪ አውጥተው በእሳት አቃጠሉት።
\v 27 ከዚያም የባዓል አምላኪዎቹን አጸድ አፍርሰው የባዓልን ቤተ መቅደስ አጠፉ፤ እስከዛሬ ድረስ ቤተ መቅደሱንም መጸዳጃ እንዲሆን አደረጉት፡፡
\v 28 ኢዩ በእስራኤል የነበረውን የባዓልን አምልኮ ያስወገደው በዚህ ዓይነት ነበር፡፡
\s5
\v 29 ነገር ግን ኢዩ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን፣ በቤተልና በዳን፣ የወርቅ ጥጃ የጣዖት ማምለኪያ ምስል ያቆመበትን የኃጢአት መንገድ አልተከተልም፡፡
\v 30 ስለዚህም እግዚአብሔር ኢዩን፡- በአክዓብ ትውልድ ሁሉ ላይ ልታደርግ የሚገባህን በዐይኖቼ ፊት ትክክል የሆነውን ፈጽመሃል፤ ከዚህም የተነሣ የአንተ ትውልድ እስከ አራት ትውልድ ድረስ በእስራኤል ላይ እንደሚነግሡ የተስፋ ቃል እስጥሃለሁ አለው፡፡
\v 31 ኢዩ ግን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ እርሱም እስራኤልን ወደ ኃጢአት ከመራበት ከኢዮርብዓም ኃጢአት አልተመለሰም፡፡
\s5
\v 32 በዚያም ዘመን እግዚብሔር የእስራኤልን ግዛት እንዲቀነስ አደረገ፤ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤልን ድል ነሥቶ የእስራኤልን ግዛት ድንበሮች ያዘ፡፡
\v 33 እርሱም የያዘው ግዛት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅ በስተ ደቡብ በኩል ከአርኖን ወንዝ በላይ እስከምትገኘው እስከ አሮዔር ከተማ የሚደርስ ሲሆን ይህም የጋድ የቶቤልና በምሥራቅ የሚገኘው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ይኖሩባቸው የነበሩትን ሸለቆ የገለዓድንና የባሳንን ግዛቶች ያጠቃልላል፡፡
\s5
\v 34 ኢዩ ያደረገው ሌላው ነገርና የጀግንነት ሥራውም ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 35 ከዚህም በኋላ ኢዩ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በሰማርያም ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮአካዝ ነገሠ፡፡
\v 36 ኢዩም በሰማርያ እስራኤልን ለሃያ ስምንት ዓመት ገዛ፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 የንጉሥ አካዝያስ እናት ጎቶልያ የልጅዋን መገደል እንደ ሰማች ተነሥታ የንጉሣውኑን ቤተ ሰብ አባላት በሙሉ ገደለች፡፡
\v 2 ከእርስዋም እጅ ማምለጥ የቻለ የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ ብቻ ነበር፤ ነገር ግን አክስቱ የነበረችው በአባትዋ በኩል የንጉሥ አካዝያስ እኅት የንጉሥ ኢዮራም ልጅ ዮሳቤት ከሞቱት ከንጉሥ ልጆች መካከል ወስዳ በመደበቅ ከሞት አዳነችው፤ እርሰዋም ሞግዚቱን ወስዳ በቤትዋ መኝታ ክፍል ውስጥ ስለደበቀችው በጎቶልያ እጅ ሳይገደል ቀረ፡፡
\v 3 ጎቶልያ በነገሠችበት ስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ዮሳቤት ሕፃኑን ኢዮአስን በመደበቅ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመንከባከብ አሳደገችው፡፡
\s5
\v 4 ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ካህኑ ዮዳሄ ለንጉሡ ክብር ዘቦችና ለቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ሁሉ ኃላፊ ወደሆኑት የጦር አዛዦች ሁሉ ልኮ ወደ ቤተ መቅደስ እንዲመጡ አስጠራቸው፤ በዚያም ሊያደርገው ያቀደውን ይስማሙበት ዘንድ በመሐላ እንዲያረጋግጡለት አደረገ፤ ከዚያም በኋላ የአካዝያስን ልጅ ኢዮአስን አሳያቸው፡፡
\v 5 የሚከተለውንም ትእዛዝ ሰጣቸው፤ በሰንበት ቀን ለጥበቃ በምትሰማሩበት ጊዜ ከእናንተ ከሦስት አንዱ እጅ ቤተ መንግሥቱን ይጠብቅ፤
\v 6 ሌላው አንድ ሦስተኛ እጅ የሱርን የቅጥር በር ይጠብቅ፤ የቀረው አንድ ሦስተኛ እጅ ደግሞ ከሌሎቹ ጥበቃዎች በስተኋላ ያለውን ቅጥር በር ይጠብቅ፡፡
\s5
\v 7 በሰንበት ቀን ከጥበቃ ነጻ የሆኑት ሁለቱ ቡድኖች ንጉሡን ለመከላከል ቤተ መቅደሱን ይጠብቁ፤
\v 8 ንጉሥ ኢዮአስን በዙሪያው በምትጠብቁበትም ጊዜ ሰይፋችሁን መዛችሁ ወደሚሄድበት ስፍራ ሁሉ አብራችሁ ሂዱ፤ ወደ እናንተ ለመቅረብ የሚደፍር ማንም ቢኖር ይገደል፡፡ ንጉሡ ሲወጣና ሲገባ ከእርሱ አትለዩ፡፡
\s5
\v 9 የጦር አዛዦቹም ካህኑ ዮዳሄ የሰጠውን መመሪያ በመቀበል በሰንበት ቀን ለጥበቃ የሚሰማሩትንና ከጥበቃም የሚወጡትን ጭፍሮቻቸውን ጭምር አሰልፈው ወደ ካህኑ ዮዳሄ አመጡ፡፡
\v 10 ዮዳሄም በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የንጉሥ ዳዊት ጦሮችና ጋሻዎች አውጥቶ ለጦር አለቆቹ ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 11 ጭፍሮቹም ሰይፋቸውን እንደ መዘዙ ንጉሡን ከበው በቤተ መቅደሱ በቀኝና በግራ በመሠዊያው አጠገብ እንዲቆሙ አደረጋቸው፡፡
\v 12 ከዚያም ዮዳሄ ኢዮአስን አቅርቦ በራሱ ላይ ዘውድ ጫነለት፤ ለመንግሥቱ መመሪያ የሆነውንም ሕግ አንድ ቅጂ አስረከበው፤ በዚህ ዓይነት ኢዮአስ ተቀብቶ ነገሠ፡፡ ሕዝቡም በእጃቸው እያጨበጨቡ፣ ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ አሉ፡፡
\s5
\v 13 ንግሥት ጎቶልያ የክብር ዘቦቹንና የሕዝቡን ጩኸት ድምፅ በሰማች ጊዜ ሕዝቡ ወደተሰበሰበበት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መጣች፡፡
\v 14 እዚያ እንደ ደረሰች አዲሱ ንጉሥ በተለመደው ባሕል መሠረት በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሚገኘው ዐምድ አጠገብ ቆሞ አየቸው፤ እርሱም በጦር አዛዦችና በእምቢልታ ነፊዎች ታጅቦ ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ በደስታ ተሞልተው እልል እያሉ እምቢልታ ይነፉ ነበር፤ ጎቶልያ በድንጋጤ ልብስዋን ቀዳ ይህ በክሕደት የተፈጸመ ሤራ ነው ስትል ጮኸች፡፡
\s5
\v 15 ዮዳሄም የጦር አለቆችን ግራና ቀኝ በተሰለፉት ዘቦች መካከል ጎቶልያን አውጥታችሁ ውሰዱአት፤ እርስዋን ለመከተል የሚሞክር ቢኖር ይገደል ሲል አዘዛቸው፡፡
\v 16 እነርሱም እርስዋን አፈፍ አድርገው በመያዝ ወደ ቤተ መንግሥት ወሰዱአት፤ እዚያ የፈረስ መግቢያ ቅጥር በር ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ገደሉአት፡፡
\s5
\v 17 ዮዳሄ፣ ንጉሡና ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ ከእግዘአብሔር ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፤ እንዲሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ፡፡
\v 18 ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ወደ ባዓል ቤተ መቅደስ ሄዶ አፈራረሰው፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበረ፤ ማታን ተብሎ የሚጠራውንም የባዓል ካህን በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት፡፡ ዮዳሄም ቤተ መቅደሱን በየተራ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ፤
\s5
\v 19 ከዚህም በኋላ እርሱ፣ የጦር አለቆች፣ የንጉሡ የክብር ዘብና የቤተ መንግሥቱ ጠባቂዎች ንጉሡን ከቤተ መቅደስ እስከ ቤተ መንግሥት አጅበው እንዲሄዱና ሕዝቡም ሁሉ ከኋላ እንዲከተል አደረገ፤ ኢዮአስም በዘብ ጠባቂዎች ቅጥር በር በኩል ገብቶ በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፡፡
\v 20 ጎቶልያ በቤተ መንግሥት በሰይፍ ስለ ተገደለች ሰው ሁሉ ተደሰተ፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች፡፡
\s5
\v 21 ኢዮአስም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 ኢዩ በእስራኤል በነገሠ በሰባተኛው ዓመት ኢዮአስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም በኢየሩሳሌም አርባ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ሳብያ ተብላ የምትጠራ የቤርሳቤህ ከተማ ተወላጅ ነበረች፡፡
\v 2 ካህኑም ዮዳሄ ይመክረውና ያስተምረው ስለ ነበር፣ ኢዮአስ በዕድሜው ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡
\v 3 ነገር ግን በየኮረብታዎቹ ላይ የሚገኙት የአሕዛብ ማምለኪያዎች ስላልተደመሰሱ ሕዝቡ በዚያ ዕጣን እያጠኑ መሥዋዕት ማቅረባቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፡፡
\s5
\v 4 ኢዮአስም ካህናትን ጠርቶ በቤተ መቅደስ ከሚቀርበው መሥዋዕት ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ መባ ሆኖ የሚገባውን ገንዘብ ሁሉ በጥንቃቄ እንዲጠብቁ አዘዘ፤ ይኸውም ቋሚ ከሆነው ከዘወትር መሥዋዕት ጋር መባ ሆኖ የሚቀርበውንና በበጎ ፈቃድ ሕዝቡ የሚያመጣውን ስጦታ ሁሉ የሚያጠቃልል ነበር፡፡
\v 5 እያንዳንዱ ካህን ከሚያገለግላቸው ሰዎች የሚገኘውን የገንዘብ መባ ሁሉ በጥንቃቄ የመጠበቅ ኃላፊነት ተሰጠው፡፡ ገንዘቡንም እንዳስፈላጊነቱ ለቤተ መቅደሱ ጥገና አገልግሎት እንዲያውሉት ነገራቸው፡፡
\s5
\v 6 ነገር ግን ኢዮአስ እስከ ነገሠበት እስከ ሃያ ሦስተኛው ዓመት ድረስ ካህናቱ በቤተ መቅደሱ ላይ ምንም ዓይነት እድሳት አላደረጉም፡፡
\v 7 ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ አላቸው፡፡
\v 8 ካናቱም በዚህ ተስማምተው ቤተ መቅደሱን በራሳቸው ለማደስ የነበራቸውን ተግባር አቆሙ፡፡
\s5
\v 9 በዚህ ፈንታ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀ፤ ሣጥኑንም ወስዶ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ በስተ ቀኝ በሚገኘው መሠዊያ አጠገብ አኖረው፤ የየዕለቱ ተረኞች የነበሩትም ካህናት ለአምልኮ የሚመጡት ሰዎች የሚሰጡትን የገንዘብ መባ እየተቀበሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡት ነበር፡፡
\v 10 ሣጥኑም በሚሞላበት ጊዜ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ እየመጡ ገንዘቡን በመቁጠር በከረጢት እያሰሩ ያኖሩት ነበር፡፡
\s5
\v 11 ትክክለኛውን ሒሳብ አጣርተው ከመዘገቡ በኋላ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሥራ ኃላፊዎች ያስረክቡ ነበር፤ እነርሱም ገንዘቡን ተረክበው ለአናጢዎችና ለግንበኞች ይሰጡ ነበር፡፡
\v 12 ለድንጋይ ጠራቢዎች፣ ለማደሻ አገልግሎት የሚውል እንጨትና ድንጋይ ለሚገዙና እንዲሁም ለልዩ ልዩ አስፈላጊ ነገሮች ለሚውል ተግባር ሁሉ ይከፍሉ ነበር፡፡
\s5
\v 13 ነገር ግን ከብር ለሚሠሩ ጎድጓዳ ሳሕኖች የዐመድ ማጠራቀሚያ ጎድጓዳ ወጭት፣፣ እምቢልታ ወይም ደግሞ ከብርና ከወርቅ ለሚሠሩ ንዋያተ ቅዱሳት ከዚያ ገንዘብ ላይ ተነሥቶ የሚከፈል ሒሳብ አልነበረም፡፡
\v 14 ያ ገንዘብ በሙሉ በቤተ መቅደሱ እድሳት ተግባር ላይ ለተሰማሩት ሠራተኞች ብቻ የሚውል ነበር፡፡
\s5
\v 15 ለሥራው ኃላፊነት የተመረጡትም ሰዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ነበሩ ገንዘቡን የሰጡአቸው ሰዎች አይቆጣጠሩአቸውም ነበር፡፡
\v 16 ስለ በደልና ስለ ኃጢአት መሥዋዕት የሚከፈለው ገንዘብ ግን ለካህናቱ ጥቅም የሚውል እንጂ ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጥ አይገባም ነበር፡፡
\s5
\v 17 በዚያ ጊዜ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል በጌት ከተማ ላይ አደጋ ጥሎ ያዛት፤ ቀጥሎም በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል ተመለሰ፡፡
\v 18 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስም ከእርሱ በፊት የነበሩትን ነገሥታት ማለትም ኢዮሳፍ፣ ኢዮራምና አካዝያስ ለእግዚአብሔር ለይተው ያኖሩትን መባና የራሱን መባ ጨምሮ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ግምጃ ቤቶች የነበረውን ወርቅ ሁሉ በመሰብሰብ ገጸ በረከት አድርጎ ለንጉሥ አዛሄል ላከለት፡፡ ሐዛሄልም ይህን ተቀብሎ ሠራዊቱን ከኢየሩሳሌም መለሰ፡፡
\s5
\v 19 ንጉሥ ኢዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኝ የለምን?
\v 20 ከዚህ በኋላ የንጉሥ ኢዮአስ ባለሥልጣኖች አንድ ላይ ተነሥተው አድመውበት ወደ ሲላ ሲሄድ በሚሎ ጥቃት አደረሱበት፡፡
\v 21 የሰምዓት ልጅ ዮዛካርና የሾሜር ልጅ ዮዛባት ኢዮአስን ገደሉት፡፡ በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አሜስያስ ነገሠ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስ በይሁዳ በነገሠ በሃያ ሦስተኛው ዓመት የኢዩ ልጅ ኢዮአካዝ በሰማርያ ለዐሥራ ሰባት ዓመት ለመግዛት የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 2 እርሱም ከእርሱ በፊት እንደ ነበረው እንደ ናባጥ ልጅ ንጉሥ ኢዮርብዓም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠራ፡፡ ከክፉ ሥራውም ከቶ አልራቀም፡፡
\s5
\v 3 ስለዚህም እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ ላይ ተቆጥቶ ለሶርያ ንጉሥ አዛሄል፣ እንዲሁም ለልጁ ለቤን ሀዳድ በተደጋጋሚ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል፡፡
\v 4 ከዚህ በኋላ ኢዮአካዝ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ የፈጸመባቸው ግፍ እጅግ ከባድ መሆኑን ተመልክቶ የኢዮአካዝን ጸሎት ሰማ፡፡
\v 5 ስለዚህም እግዚአብሔር እስራኤልን ከሶርያውያን እጅ ነጻ የሚያወጣቸውን መሪ ላከላቸው፤ እነርሱም ከዚያ በፊት በነበረው ዓይነት በሰላም ኖሩ፡፡
\s5
\v 6 ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ኢዮርብዓም እስራኤልን ወደ ኃጢአት ከመራበት ከክፉ ሥራቸው አልተመለሱም፤ እስካሁንም አሼራ ተብላ የምትጠራውን የሴት አምላክ ምስል በሰማርያ ማምለክ ቀጠሉ፡፡
\v 7 ንጉሥ ኢዮአካዝ ከኀምሳ ፈረሰኞች፣ ከዐሥር ሰረገሎችና ከዐሥር ሺህ ወታደሮች በቀር ሌላ የተደራጀ የጦር ኃይል አልነበረውም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሠራዊቱን የሶርያ ንጉሥ በአውድማ እንዳለ እብቅ አድርጎ ስለ ደመሰሰበት ነው፡፡
\s5
\v 8 ንጉሥ ኢዮአካዝ የፈጸመው ሌላው ተግባርና የጀግንነት ሥራው ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 9 ኢዮአካዝም ሞተ፤ በሰማርያም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ዮአስ ነገሠ፡፡
\s5
\v 10 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስ በነገሠ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በሰማርያ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፤ በዚያም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፡፡
\v 11 እርሱም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ ምሳሌነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡
\s5
\v 12 ዮአስ የፈጸመው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ላይ ባደረገው ጦርነት የፈጸመው ጀግንነት ጭምር በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 13 ከዚህ በኋላ ዮአስ ሞተ፤ በሰማርያም በሚገኘው መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነገሠ፡፡
\s5
\v 14 ነቢዩ ኤልሳዕ በብርቱ ደዌ ታሞ ነበር፤ ተኝቶም ሊሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ሄዶ፣ ድምፁን ከፍ በማድረግ ‹‹አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! አንተ እኮ የእስራኤል ሕዝብ ኀይላቸውና ጋሻ መከታቸው ነህ! እያለ አለቀሰለት፡፡
\v 15 ኤልሳዕም ንጉሡን ‹‹አንድ ቀስትና ፍላጻዎች ውሰድ›› ሲል አዘዘው፤ ዮአስም እንደታዘዘው አደረገ ኤልሳዕም
\v 16 ለማስፈንጠር ተዘጋጅ›› አለው፤ ንጉሡም እንደታዘዘው አደረገ፤ ኤልሳዕም እጆቹን በንጉሡ እጆች ላይ አኖረ፡፡
\s5
\v 17 ኤልሳዕ ‹‹የምሥራቁን መስኮት ክፈት›› አለ፤ ንጉሡም ከፈተው፤ ኤልሳዕም ‹‹ፍላጻውን አስፈንጥር! አለው፤ ንጉሡም ፍላጻውን እንዳስፈነጠረ ወዲያውኑ ኤልሳዕ፣ ‹‹ፍላጻ ነህ፤ በአንተም አማካይነት እግዚአብሔር ሶርያውያንን ድል ያደርጋል፤ ሶርያውያንን ድል እስክትነሣቸው ድረስ በአፌቅ ከተማ ትወጋቸዋለህ፡፡››
\v 18 ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ንጉሡን ‹‹ሌሎቹንም ፍላጻዎች አንሥተህ በእነርሱ ምድርን ምታ! አለው፡፡ ንጉሡም ምድርን ሦስት ጊዜ መትቶ አቆመ፡፡
\v 19 ይህም ኤልሳዕን አስቆጣው፤ ስለዚህም ንጉሡን ‹‹አምስት ወይም ስድስት ጊዜ መተህ ቢሆን ኖሮ በሶርያውያን ላይ ፍጹም ድልን ትቀዳጅ ነበር፤ አሁን ግን ሦስት ጊዜ ብቻ ድል ትነሣቸዋለህ›› አለው፡፡
\s5
\v 20 ኤልሳዕም ሞተ፤ ተቀበረም፡፡ ከሞአብ የመጡ አደጋ ጣዮች በየዓመቱ የእስራኤልን ምድር ይወጉ ነበር፡፡
\v 21 አንድ ጊዜ የአንድ ሰው ሥርዓተ ቀብር በሚፈጸምበት ሰዓት በእነዚያ አደጋ ጣዮች መካከል አንድ ቡድን ሲመጣ ስለታየ የሚቀበረውን ሬሳ ወደ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ በችኮላ በመወርወር ጥለውት ሸሹ፤ ያም ሬሳ ከኤልሳዕ አስክሬን ጋር በተገናኘበት ቅጽበት ወዲያውኑ ከሞት ተነሥቶ ቆመ፡፡
\s5
\v 22 ኢዮአካዝ በነገሠበት ዘመን ሁሉ የሶርያ ንጉሥ አዛሄል እስራኤላውያንን በመውረር ያስጨንቃቸው ነበር፤
\v 23 እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ ምሕረትን በማድረግ ረዳቸው እንጂ እንዲደመሰሱ አልፈቀደም፤ ይህንን ያደረገበት ምክንያት ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን ቃል ኪዳን በማሰብ ሕዝቡን ስላልረሳው ነው፡፡
\v 24 የሶርያ ንጉሥ አዛሄል በሞተ ጊዜ፣ በእርሱ ፈንታ ተተክቶ ልጁ ቤን ሀዳድ ነገሠ፡፡
\v 25 ከዚህም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ቤን ሀዳድን ሦስት ጊዜ ድል ነሥቶ በኢዮአካዝ ዘመነ መንግሥት ቤን ሀዳድ ይዞአቸው የነበሩትን ከተሞች አስመለሰ፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በእስራኤል ላይ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 2 እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ከኢየሩሳሌም ዮዓዳን ተብላ የምትጠራ ነበረች፡፡
\v 3 አሜስያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቶአል፤ ይሁን እንጂ እንደ ቀድሞ አያቱ እንደ ንጉሥ ዳዊት አልነበረም፤ እንደ ዳዊት በመሆን ፈንታ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ፡፡
\s5
\v 4 ይኸውም በየኮረብታዎቹ ላይ የተሠሩትን የአሕዛብ ማምለኪያዎችን አላፈረሰም፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ በየኮረብታዎቹ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጠኑን እንደቀጠለ ነበር፡፡
\v 5 አሜስያሰ መንግሥቱን አደላድሎ እንደ ያዘ ወዲያውኑ፣ ቀደም ሲል ነግሦ የነበረውን አባቱን የገደሉትን ባለሥልጣኖች በሞት ቀጣ፤
\s5
\v 6 ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር ‹‹ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣል›› ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል፡፡
\v 7 አሜስያስ ‹‹የጨው ሸለቆ›› እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ ‹‹ዮቅትኤል›› ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች፡፡
\s5
\v 8 ከዚህ በኋላ አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን በመላክ ‹‹እንግዲህ ና ፊት ለፊት ጦርነት እንግጠም! ሲል ለጦርነት አነሣሣው፡፡
\v 9 ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት ‹‹አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኩርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‹ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ› ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኩርንችት ሞተች፡፡
\v 10 አሜስያስ ሆይ! እነሆ አንተ ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ ባገኘኸውም ድል በመደሰት ዐርፈህ በቤትህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መከራና ውድቀት ስለ ምን ታስከትላለህ?
\s5
\v 11 አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቆጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤት ሳሚስ ጦርነት ገጠመው፡፡
\v 12 ይሁዳም ድል ተመታ፤ ወታደሮቹም ሁሉ ተበታትነው ወደየቤታቸው ተመለሱ፡፡
\s5
\v 13 ዮአስም የአካዝያስን ልጅ፣ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ለመድረስ ገሠገሠ፤ እዚያም እንደ ደረሰ ከኤፍሬም ቅጥር በር ‹‹የማዕዘን ቅጥር በር›› ተብሎ እስከሚጠራው በር ድረስ ጠቅላላ ርዝመቱ ሁለት መቶ ሜትር የሆነውን የቅጥር ግንብ አፈረሰ፡፡
\v 14 በዚያም ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ፣ የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅዱሳትና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ሁሉ ጭኖ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፤ በመያዣ ስም የተማረኩ ሰዎችንም ይዞ ሄደ፡፡
\s5
\v 15 ንጉሥ ዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ በአሜስያስ ላይ ባደረገው ጦርነት የፈጸመው የጀግንነት ሥራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 16 ዮአስ ሞተ፤ በሰማርያ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነገሠ፡፡
\s5
\v 17 የእስራኤል ንጉሥ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ ከሞተ በኋላ፣ የይሁዳ ንጉሥ የዮአስ ልጅ አሜስያስ ዐሥራ አምስት ዓመት ቆየ፡፡
\v 18 አሜስያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 19 አሜስያስን ለመግደል በኢየሩሳሌም ሤራ ተጠንስሶ ነበር፤ ስለዚህ አሜስያስ ሸሽቶ ወደ ለኪሶ ከተማ ሄደ፤ ነገር ግን ጠላቶቹ ወደ ለኪሶ ሰዎችን ልከው እዚያ አስገደሉት፡፡
\s5
\v 20 ሬሳውም በፈረስ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡
\v 21 የይሁዳም ሕዝብ የዐሥራ ስድስት ዓመት ልጁ የነበረውን ዓዛርያስን አነገሡት፤
\v 22 ዓዛርያስም ቀድሞ ተይዛ የነበረችውን ኤላትን ከአባቱ ሞት በኋላ በጦር ኃይል ድል ነሥቶ አስመልሶ እንደገና ሠራት፡፡
\s5
\v 23 የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓም በእስራኤል ነገሠ፤ እርሱም በሰማርያ አርባ አንድ ዓመት ገዛ፡፡
\v 24 ዳግማዊ ኢዮርብዓምም እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ ከእርሱ በፊት የነበረውን የናባጥ ልጅ የኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡
\v 25 ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነበር፡፡
\s5
\v 26 እግዚአብሔር የእስራኤላውያንን አሠቃቂ መከራ ተመለከተ፤ በእስራኤል ውስጥ ባርያዎችም ሆኑ ነጻ ሰዎች ረዳት አልነበራቸውም፡፡
\v 27 ይሁን እንጂ እነርሱ ለዘለዓለም ፈጽሞ እንዲደመሰሱ የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም፤ ስዚህ በዳግማዊ ኢዮርብዓም አማካይት አዳናቸው።
\s5
\v 28 ዳግማዊ ኢዮርብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ፣ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነት፣ እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩት ደማስቆና ሐማት ለእስራኤል እንዲመለሱ ያደረገበት ታሪካዊ ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 29 ከዚህ በኋላ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ሞተ፤ በነገሥታት መካነ መቃብርም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ዘካርያስ ነገሠ፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 ዳግማዊ ኢዮርብዓም በእስራኤል በነገሠ በሃያ ሰባተኛው ዓመት የአሜስያስ ልጅ ዓዛርያስ በይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 2 እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስድስት ዓመት ነበረ፤ እርሱም በኢየሩሳሌም ሃምሳ ሁለት ዓመት ገዛ፤ እናቱም ይኮልያ ተብላ የምትጠራ የኢየሩሳሌም ተወላጅ ነበረች፡፡
\v 3 እርሱም የአባቱን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡
\s5
\v 4 ነገር ግን በየኮረብቶቹ ላይ የነበሩትን የአሕዛብን የማምለኪያ ቦታዎች አላጠፋቸውም ነበር፤ ስለዚህም ሕዝቡ በየኮረብቶቹ ላይ መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤
\v 5 በኋላም እግዚአብሔር ዓዛርያስን በቆዳ በሽታ መታው፤ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ይህ በሽታ ስላልለቀቀው ከሥራው ሁሉ ተገልሎ በተለየ ቤት ውስጥ ለብቻው ይኖር ነበር፤ በዚህም ጊዜ መንግሥቱን ሲመራ የቆየው ልጁ ኢዮአታም ነበር፡፡
\s5
\v 6 ንጉሥ ዓዛርያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ውስጥ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 7 ዓዛርያስም ሞተ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በቀድሞ አባቶቹ መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮአታም ነገሠ፡፡
\s5
\v 8 ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ስምንተኛው ዓመት የዳግማዊ ኢዮርብዓም ልጅ ዘካርያስ በእስራኤል ነገሠ፤ እርሱም በሰማርያ ስድስት ወር ገዛ፡፡
\v 9 እርሱም ከእርሱ በፊት እንደ ነበሩት ነገሥታት ሁሉ ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ እዲሁም እስራኤልን ወደ ኃጢአት መራ፤ የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት ተከተለ፡፡
\s5
\v 10 ሰሎም ተብሎ የሚጠራው የኢያቤስ ልጅ ሤራ በማድረግ ይብልዓም ተብላ በምትጠራው ስፍራ ንጉሥ ዘካርያስን ገድሎ በእርሱ ፈንታ ነገሠ፡፡
\v 11 ንጉሥ ዘካርያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 12 በዚህም ዓይነት እግዚአብሔር ለንጉሥ ኢዩ ልጆችህ እስከ አራት ትውልድ በእስራኤል ይነግሣሉ ሲል የተናገው የተስፋ ቃል ተፈጸመ፡፡
\s5
\v 13 ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የኢያቤስ ልጅ ሰሎም የእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም በሰማርያ አንድ ወር ብቻ ገዛ፡፡
\v 14 ምናሔ ተብሎ የሚጠራው የጋዲ ልጅ ከቲርጻ ተነሥቶ ወደ ሰማርያ ሄደ፤ የኢያቤስን ልጅ ሰሎምን ገድሎም በእርሱ ፈንታ ነገሠ፡፡
\s5
\v 15 ሰሎም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም እርሱ የጠነሰሰው ሤራ ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 16 ምናሔም ከቲርጻ ተነሥቶ በሚያልፍበት ጊዜ የቲፍሳን ከተማ ነዋሪዎችና በዙሪያዋ የነበረውን ግዛት ሁሉ ደመሰሰ፡፡ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት የከተማይቱ ነዋሪዎች ለእርሱ እጃቸውን ለመስጠት ባለመፍቀዳቸው ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ነፍሰ ጡሮችን እንኳ ሳይምር ሆዳቸውን ቀደደ፡፡
\s5
\v 17 ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠነኛው ዓመት የጋዲ ልጅ ምናሔም በእስራኤል ነገሠ፡፡ እርሱም በሰማርያ ዐሥር ዓመት ገዛ፡፡
\v 18 እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ የኢርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት በመሥራቱም እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡
\s5
\v 19 የአሦር ንጉሠ ነገሥት ፎሐ እስራኤልን ወረረ፤ ምናሔም በአገሩ መንግሥት ላይ ሥልጣኑን እንዲያጸናለትና እንዲደግፈው ለመማጠን ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር እጅ መንሻ አድርጎ ለፎሐሰጠው፡፡
\v 20 ምናሔም ገንዘቡን የሰበሰበው የእስራኤል ከበርቴዎች እየንዳንዳቸው ኀምሳ ጥሬ ብር አዋጥተው እንዲሰጡ በማስገደድ ነበር፡፡ በዚህም ዓይነት ፎሐ በሰላም ወደ አገሩ ተመልሶ ሄደ፡፡
\s5
\v 21 ምናሔም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 22 ምናሔም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ፋቂስያስ ነገሠ፡፡
\s5
\v 23 ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በኀምሳኛው ዓመት የምናሔም ልጅ ፋቂስያስ በእስራኤል ነገሠ፤ እርሱም በሰማርያ ሁለት ዓመት ገዛ፡፡
\v 24 እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት ስለ ሠራ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡
\s5
\v 25 በፋቂስያስ ሠራዊት መካከል ፋቁሔ ተብሎ የሚጠራው የሮሜልዩ ልጅ የሆነ አንድ የጦር አዛዥ ከኀምሳ የገለዓድ ሰዎች ጋር ሆኖ ሤራ ጠነሰሰ፤ በሰማርያ በቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሚገኘው ምሽግ ውስጥ ዘልቆ በመግባትም ፋቂስያስን ከአርጎብና ከአርዬ ጋር ገድሎ በፋቂስያስ ፈንታ ተተክቶ ነገሠ፡፡
\v 26 ፋቂስያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\s5
\v 27 ዓዛርያስ በይሁዳ በነገሠ በኀምሳ ሁለተኛው ዓመት የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል ነገሠ፤ እርሱም በሰማርያ ሃያ ዓመት ገዛ፡፡
\v 28 እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራውን የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን መጥፎ አርአያነት በመከተል ኃጢአት ስለ ሠራ እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡
\s5
\v 29 የአሦር ንጉሠ ነገሥት ቴልጌልቴልፌልሶር ዒዮን፣ አቤልቤትመዓካ፣ ያኖዋ፣ ቃዴስና ሐጾር ተብለው የሚጠሩትን ከተሞች እንዲሁም የገለዓድን፣ የገሊላንና የንፍታሌምን ግዛቶች በመውረር ሕዝቡን ወደ አሦር ማርኮ የወሰደው ይኸው ፋቁሔ በነገሠበት ዘመን ነበር፡፡
\v 30 የዖዝያንም ልጅ ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠ በሃያኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በንጉሥ ፋቁሔ ላይ ሤራ ጠነሰሰ፤ እርሱንም ገድሎ በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡
\v 31 ፋቁሔ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\s5
\v 32 የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የዖዝያን ልጅ ኢዮአታም የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 33 በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ዐሥራ ስድሰት ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ኢየሩሳ ተብላ የምትጠራ የሳዶቅ ልጅ ነበረች፡፡
\s5
\v 34 የአባቱንም የዖዝያንን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡
\v 35 ነገር ግን በየኮረብቶቹ ላይ የነበሩትን የአሕዛብን መሠዊያዎች አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጥር በር ያሠራው ይኸው ኢዮአታም ነበር፡፡
\v 36 ኢዮአታም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 37 እግዚአብሔር በመጀመሪያ የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በይሁዳ ላይ አደጋ እንዲጥሉባት የላካቸው ይኸው ኢዮአታም በይሁዳ በነገሠበት ዘመን ነበር፡፡
\v 38 ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው የነገሥታት መካነ መቃብርም ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አካዝ ነገሠ፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በእስራኤል በነገሠ በዐሥራ ሰባተኛው ዓመት የኢዮአታም ልጅ አካዝ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 2 አካዝም በሚነግሠበት ጊዜ ዕድሜው ሃያ ዓመት ነበር፡፡ እርሱም በኢየሩሳሌም ዐሥራ ስድስት ዓመት ገዛ፡፡ እርሱም የቀድሞ አባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት አልተከተለም፡፡ በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ደስ የማያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡
\s5
\v 3 ይልቁንም የእስራኤልን ነገሥታት መጥፎ አርአያነት ተከተለ፡፡ የራሱን ልጅ እንኳ ሳይቀር ለጣዖታት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ ይህንንም ድርጊት የእስራኤል ሕዝብ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከመግባቱ በፊት እግዚአብሔር ከእስራኤል ምድር ያስወገዳቸውን አሕዛብ ይሠሩት የነበረውን አስጸያፊ ድርጊት በመከተል ነበር፡፡
\v 4 አካዝ በየኮረብቶቹ ላይ በተሠሩት የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችና በእያንዳንዱም ዛፍ ሥር መሥዋዕት በማቅረብ ዕጣን አጠነ፡፡
\s5
\v 5 የሶርያ ንጉሥ ረአሶንና የእስራኤል ንጉሥ ፋቁሔ በኢየሩሳሌም ላይ አደጋ ለመጣል መጡ፤ ከበቧትም፡፡ ነገር ግን አካዝን ድል ሊያደርጉት አልቻሉም፡፡
\v 6 በዚያን ጊዜ የሶርያ ንጉሥ ረአሶን የኤላትን ከተማ አስመልሶ በቁጥጥሩ ሥር በማድረግ በዚያ የነበሩትን አይሁድ አስወጣ፡፡ ከዚያም በኤላት የሰፈሩት ኤዶማውያን እስከ አሁንም በዚያ ይኖራሉ፡፡
\s5
\v 7 ስለዚህም ንጉሥ አካዝ ወደ አሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ቴልጌልቴልፌልሶር ‹‹እኔ ለአንተ ታማኝ አገልጋይህ ነኝ፤ አደጋ ከጣሉብኝ ከሶርያና ከእስራኤል ነገሥታት እጅ መጥተህ እኔን አድነኝ›› በማለት መልእክተኞችን ላከ፡፡
\v 8 አካዝም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤት የተገኘውን ብርና ወርቅ ሰብስቦ ለዚሁ ለአሦር ንጉሥ ገጸ በረከት በማድረግ ላከለት፡፡
\v 9 ከዚያም የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፡፡ ንጉሥ ረአሶንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው፡፡
\s5
\v 10 ንጉሥ አካዝም ከንጉሠ ነገሥት ቴልጌልቴልፌልሶር ጋር ለመገናኘት ወደ ደማስቆ ሄደ፡፡ በደማስቆም አንድ መሠዊያ አየ፡፡ ያንንም መሠዊያ በተመሳሳይ ሁኔታ መሥራት የሚያስችለውን ቅርጽ አዘጋጅቶ ለካህኑ ለኦሪያ ላከለት፡፡
\v 11 ስለዚህ ኦሪያ ንጉሥ አካዝ ከደማስቆ በላከለት ንድፍ መሠረት መሠዊያ ሠራ፡፡
\v 12 ንጉሡም ከደማስቆ በተመለሰ ጊዜ መሠዊያውን ተመለከተ፤ ወደ መሠዊያው ቀርቦም መሥዋዕት አቀረበ፡፡
\s5
\v 13 በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠል የእንስሶች መሥዋዕትና የእህል መባ አቀረበ፡፡ የመባውን ወይን ጠጅና የኅብረት መሥዋዕት ደም አፈሰሰበት፡፡
\v 14 ከነሐስ ተሠርቶ ለእግዚአብሔር የተለየውም መሠዊያ በዚያ አዲስ መሠዊያ፣ በቤተ መቅደሱ መካከል ነበር፤ ያንንም መሠዊያ አስነሥቶ እርሱ ባሠራው በአዲሱ መሠዊያ በስተሰሜን በኩል አኖረው፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም ካህኑን ኦሪያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ ይህንን የእኔን ታላቅ መሠዊያ ማለዳ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት በምሽት ለሚቀርበውም የእህል መባ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡ የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ የሚቀርብበትና የሕዝቡ የወይን ጠጅ መባ የሚፈስበት እንዲሆን አድርግ፤ የሚሠዉትንም የእንስሳት ደም ሁሉ በእርሱ ላይ አፍስስ፤ ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ግን እኔ ራሴ የምፈልገውን ነገር የምጠይቅበት እንዲሆን አድርግ፡፡
\v 16 ካህኑም ኦሪያን ንጉሡ አካዝ እንዳዘዘው አደረገ፡፡
\s5
\v 17 ንጉሥ አካዝም በቤተ መቅደስ ውስጥ መገልገያ የነበሩትን ከነሐስ የተሠሩ መንኩራኩሮች ቆርጦ ልሙጥ የሆነውን ነገር ከጎናቸው ወስደ፡፡ በእነርሱ ላይ የነበሩትንም የመታጠቢያ ሳሕኖች ወሰደ፤ ከነሐስ የተሠራውን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ከታች በኩል ተሸክመውት ከነበሩት ከነሐስ ከተሠሩት ከዐሥራ ሁለት የበሬ ቅርጾች ጀርባ ላይ አንሥቶ ከድንጋይ በተሠራ መሠረት ላይ አኖረው፡፡
\v 18 አካዝ ከአሦር ንጉሠ ነገሥት የተነሣ በቤተ መቅደሱ የሠሩትን የሰንበት መግቢያ መንገድ ንጉሡ ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በውጪው በኩል ከሚገባበት መግቢያ ጋር አስወገደው፡፡
\s5
\v 19 ንጉሥ አካዝ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 20 አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ በሚገኘው በአባቶቹ መካነ መቃበር ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ሕዝቅያስ ነገሠ፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 አካዝ በይሁዳ በነገሠ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል ንጉሥ ሆነ፡፡ እርሱም በሰማርያ ዘጠኝ ዓመት እስራኤልን ገዛ፡፡
\v 2 እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ፡፡ ሆኖም እርሱ ያደረገው ኃጢአት ከእርሱ በፊት የነበሩ የእስራኤል ነገሥታት የፈጸሙት አልነበረም፡፡
\v 3 የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር ጦርነት በገጠመው ጊዜ ተሸንፎ ሆሴዕ እጁን በመስጠት በየዓመቱ ይገብርለት ጀመር፡፡
\s5
\v 4 ነገር ግን ከጥቂት ዓመቶች በኋላ ንጉሥ ሆሴዕ ሴጎር ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ግብጽ ንጉሥ መልእክተኞች በመላክ ይረዳው ዘንድ ጠየቀው፤ በየዓመቱ ለአሦር ንጉሥ ይሰጠው የነበረውንም ግብር አቆመ፡፡ ስልምናሶር ይህን በሰማ ጊዜ ሆሴዕን አስይዞ ወህኒ ቤት አስገባው፡፡
\v 5 ከዚህ በኋላ ስልምናሶር አገሪቱን ወርሮ ሰማርያን ለሦስት ዓመት ከበባት፡፡
\v 6 ከዚያም ሆሴዕ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ስልምናሶር ድል አድርጎ ሰማርያን ያዘ፤ እስራኤላውያንንም ማርኮ ወደ አሦር ወሰዳቸው፤ ከእነርሱም ጥቂቶቹን በአላሔ ከተማ፣ ጥቂቶቹን በጎዛን አውራጃ ውስጥ በሚገኘው በአቦር ወንዝ አጠገብ፣ እንዲሁም ሌሎቹን በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፡፡
\s5
\v 7 ይህም ምርኮ የሆነው እስራኤላውያን በሠሩት ኃጢአት ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ በመታደግ አውጥቶ ወደ ተስፋይቱ ምድር የመራቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ኃጢአት በመሥራት በማሳዘናቸው ነበር፡፡ ሕዝቡም ባዕዳን አማልክትን አመለኩ፡፡
\v 8 ሕዝቡም ከፊታቸው ያጠፋላቸውን የአሕዛብን መጥፎ ልማድ ተከተሉ፤ እንዲሁም የእስራኤል ነገሥታት ያሠራጩትን መጥፎ ልማድ ተቀባዮች ሆኑ፡፡
\s5
\v 9 እስራኤላውያንም አምላካቸው እግዚአብሔር የሚጠላውን ነገር ሁሉ አደረጉ፡፡ ከዘብ ጠባቂዎች ማማ አንሥቶ እስከ ትልቅ ከተማ ድረስ በገጠር ከተሞቻቸው ሁሉ በየኮረብታዎቹ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሠሩ፡፡
\v 10 በኮረብቶች ሁሉ ላይና በየዛፉ ጥላ ሥር የድንጋይ አምዶችንና አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስሎች አቆሙ፡፡
\s5
\v 11 እግዚአብሔርም ከፊታቸው ያስወጣቸውን የአረማውያን ሕዝብ ልማድ በመከተል በአሕዛብ መሠዊያዎች ሁሉ ላይ ዕጣን አጠኑ፤ በዚህም ክፉ ሥራቸው ሁሉ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፤
\v 12 እግዚአብሔርም እንዳያደርጉ የተናገራቸውን ጣዖታትን አመለኩ፡፡
\s5
\v 13 እግዚአብሔርም እስራኤልንና ይሁዳን የሚያስጠነቅቁ መልእክተኞችንና ነቢያትን በመላክ፣ ከክፉ መንገዳችሁ ሁሉ ተመለሱ፤ አገልጋዮቼ በሆኑት ነቢያትና ባለ ራዕዮች አማካይነት ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለእናንተም በሰጠሁት ሕጎችና ትእዛዞች የተጻፈውን ሥርዓቱን ጠብቁ ብሎ ነግሮአቸው ነበር፡፡
\s5
\v 14 እነርሱ ግን መታዘዝ አልፈለጉም፤ በአምላካቸው በእግዚአብሔር እንዳልታመኑ እንደ ቀድሞ አባቶቻቸው እልከኞች ሆኑ፡፡
\v 15 የሰጣቸውንም ድንጋጌ አልተቀበሉም፤ ከቀድሞ አባቶቻቸው ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን አልጠበቁም፤ የሰጣቸውንም ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ ቸል አሉ፤ ለከንቱ ጣዖቶች በመስገድ ራሳቸውም ከንቱዎች ሆኑ፤ የእነርሱን መጥፎ ምሰሌነት እንዳይወርሱ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ ባለመስማት በዙሪያቸው የሚኖሩትን የአሕዛብ ልማድ ሁሉ ተከተሉ፡፡
\s5
\v 16 የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ቸል አሉ፡፡ የሚሰግዱላቸውን ከብረት የተሠሩ ሁለት ጥጆችን አቆሙ፡፡ እንዲሁም አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ሠሩ፣ ለከዋክብትም ሰገዱ፣ ባዓል ተብሎ ለሚጠራውም ባዕድ አምላክ አገልጋዮች ሆኑ፡፡
\v 17 ለእነዚያም አሕዛብ አማልክት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፤ ከሙታን ጠሪዎችና ከጠንቋዮችም ምክር ጠየቁ፤ እግዚአብሔር ለሚጠላው ክፉ ነገር ሁሉ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሡ፡፡
\v 18 ስለዚሀም እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ተቆጥቶ የይሁዳን መንግሥት ብቻ በማስቀረት እስራኤላውያንን ከፊቱ አስወገደ፡፡
\s5
\v 19 የይሁዳ ሰዎችም ቢሆኑ አምላካቸው እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዞች አልጠበቁም ነበር፡፡ እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ የተቀበሉትን ልማድ ተከታዮች ነበሩ፡፡
\v 20 ስለዚህም እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ሁሉ ተዋቸው፤ ከፊቱም እስኪወገዱ ድረስ ለጠላቶቻቸው አሳልፎ በመስጠት ቀጣቸው፡፡
\s5
\v 21 እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ከይሁዳ ከለየ በኋላ እስራኤላውያን የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓምን መርጠው አነገሡ፤ ኢዮርብዓምም እግዚአብሔርን እንዲተዉ በማድረግ አሠቃቂ ወደ ሆነ ኃጢአት መራቸው፡፡
\v 22 በአገልጋዮቹ ነቢያት ሁሉ አማካይነት እግዚአብሔር እስራኤልን ከፊቱ እስኪያስወግድ ድረስ እስራኤላውያን የኢዮርብዓምን ኃጢአት ሲሠሩ ኖሩ እንጂ ከዚያ አልራቁም፡፡
\v 23 ስለዚህ እስራኤላውያን ከአገራቸው ተማርከው በመወሰድ እስከ ዛሬ ድስ በአሦር ይኖራሉ፡፡
\s5
\v 24 የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን ኩታ፣ ዓዋና፣ ሐማትና ሴፈርዋይ ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ፡፡
\v 25 እነርሱም በዚያ ሰፍረው መኖር እንደ ጀመሩ እግዚአብሔርን አላመለኩትም ነበር፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አንበሶችን በመላክ ከእነርሱ ጥቂቶቹን ሰባብረው እንዲገድሉ አደረገ፡፡
\v 26 ለአሦርም ንጉሠ ነገሥት በሰማርያ ከተሞች ሰፍረው እንዲኖሩ ያደረግሃቸው ሕዝቦች የዚያችን አገር አምላክ ሕግ የሚያውቁ ሆነው አልተገኙም፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሰባብረው የሚገድሉ አንበሶችን ላከባቸው የሚል ወሬ ደረሰው፡፡
\s5
\v 27 ስለዚህ ንጉሠ ነገሥቱ ማርኮ ካመጣቸው ካህናት አንዱን ወደዚያ ላኩ፤ ወደዚያ ተመልሶ በመሄድ የዚያች አገር አምላክ ያዘዘውን ሕግ ለሕዝቡ እንዲያስተምራቸው አድርጉ ሲል አዘዘ፡፡
\v 28 ስለዚህም ከሰማርያ ተማርኮ የተወሰደ አንድ እስራኤላዊ ካህን ተመልሶ በመሄድ በቤተል ተቀመጠ፤ በዚያ ሕዝቡ እግዚአብሔርን እንዴት ማምለክ እንደሚገባቸው አስተማራቸው፡፡
\s5
\v 29 በሰማርያ የሰፈሩት ሕዝቦች ግን የየራሳቸውን ጣዖት መሥራት ቀጥለው እስራኤላውያን ባሠሩአቸው በከፍተኛ ማምለኪያ ቦታዎች አኖሩአቸው፤ እያንዳንዱ ቡድን በሚኖርበት ከተማ ሁሉ የየራሱን ጣዖት አቆመ፡፡
\v 30 በዚህም ዓይነት የባቢሎን ሰዎች ሱኮትበኖት በተባለው አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ እንዲሁም የኩታ ሰዎች ኤርጌል ተብሎ በሚጠራው ባዕድ አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤ የሐማት ሕዝብ አሲማት ተብሎ በሚጠራው ባዕድ አምላክ ስም ጣዖት ሠሩ፤
\v 31 የዓዋ ሕዝብ ኤልባዝርና ተርታቅ ተብለው በሚጠሩ አማልክቶቻቸው ስም ጣዖቶቻቸውን ሠሩ፤ የሴፈርዋይምም ሕዝብ አድራሜሌክና ዓናሜሌክ ተብለው ለሚጠሩ አማልክቶቻቸው ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፡፡
\s5
\v 32 እነዚሁ ሰዎች በተጨማሪ ለእውነተኛው አምላክ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ነበር፡፡ ከእያንዳዳቸውም ቡድን በአረማውያን የማምለኪያ ስፍራዎች የሚያገለግሉና መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸውን ካህናት መረጡ፡፡
\v 33 በዚህ ዓይነት እግዚአብሔርን ማክበርና ማምለክ ጀመሩ፡፡ በሌላ በኩል ግን ቀድሞ ይኖሩባቸው በነበሩት ሕዝቦች ይፈጽሙት በነበረው ልማድ መሠረት ለባዕዳን አማልክት ይሰግዱ ነበር፡፡
\s5
\v 34 ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን አያመልኩም ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፣ ሥርዓቶች፣ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም፡፡
\v 35 እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፡- ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፣ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፣ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፡፡
\s5
\v 36 በታላቅ ኃይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፡፡
\v 37 ጽፌ የሰጠኋችሁንም ድንጋጌና ሥርዓቱን ሕጎችና ትእዛዞቹን ሁልጊዜ ጠብቁ፣ ባዕዳን አማልክትንም አትከተሉ፡፡
\v 38 እኔ ከእናንተ ጋር የገባሁትንም ቃል ኪዳን አትርሱ፤ ባዕዳን አማልክትንም አታምልኩ፡፡
\s5
\v 39 እኔን አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፍሩ፤ እኔም ከኃይለኛው ጠላቶቻችሁ እጅ አድናችኋለሁ፡፡
\v 40 ነገር ግን እነዚያ ሕዝቦች ይህን መስማት ትተው አሮጌ ልማዳቸውን ተከተሉ፡፡
\v 41 እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዓይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዓይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል በነገሠ በሦስተኛው ዓመት የአካዝ ልጅ ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡
\v 2 ሕዝቅያስም ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፡፡ እርሱም በኢያሩሳሌም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም አቢያ የምትባል የዘካርያስ ልጅ ነበረች፡፡
\v 3 ሕዝቅያስም የአባቱን የንጉሥ ዳዊትን መልካም አርአያነት በመከተል እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠራ፡፡
\s5
\v 4 የአሕዛብን የማምለክያ ስፍራዎች አስወገደ፤ የድንጋይ ዐምዶችንም ሰባብሮ አጠፋ፤ ኣሼራ ተብላ በምትጠራው ሴት አምላክ ስም የተቀረጹትን ምስሎች ሁሉ አፈረሰ፡፡ ሙሴ ከነሐስ ሠርቶት የነበረውን ኔሑሽታን ተብሎ የሚጠራውን የእባብ ምስል ሰባብሮ አደቀቀ፤ ምክንያቱም እስከዚያን ጊዜ ድረስ እስራኤላውያን ለእርሱ ዕጣን ያጥኑለት ነበር፡፡
\v 5 ሕዝቅያስ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ተማመነ፤ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ ወዲህ እርሱን የመሰለ ሌላ ንጉሥ በይሁዳ አልተነሣም፡፡
\s5
\v 6 ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለ ሆነ ከእግዚአብሔር መንገድ የራቀበት ጊዜ የለም፤ ለሙሴ የሰጣቸውን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ይፈጽም ነበር፡፡
\v 7 ስለዚህም እግዚአብሔር ከሕዝቅያስ ጋር ስለነበረ የሚሠራው ሁሉ ይከናወንለት ነበር፡፡ ሕዝቅያስም በአሦር ንጉሠ ነገሥት ላይ ዐምፆ ለእርሱ መገዛትን አሻፈረኝ አለ፡፡
\v 8 ፍልስጥኤማውያንንም ድል ነሥቶ ከትንሽ እስከ ታላቅ የተመሸጉ ከተማ ጋዛንና በዙሪያው የሚገኘውን ግዛት፣ የሚኖሩበትን ስፍራ ሁሉ አጠቃ፡፡
\s5
\v 9 ሕዝቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ማለትም የኤላ ልጅ ሆሴዕ በእስራኤል በነገሠ በሰባተኛው ዓመት የአሦር ንጉሥ ስልምናሶር በእስራኤል ላይ አደጋ በመጣል ሰማርያን ከበበ፡፡
\v 10 በሦስተኛውም ዓመት መጨረሻ ሰማርያ በሙሉ ተያዘች፤ ይህም የሆነው ሕዝቅያስ በነገሠ በስድስተኛው ዓመት ሆሴዕም በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት ነበር፡፡
\s5
\v 11 የአሦር ንጉሠ ነገሥት እስራኤላውያንን ማርኮ ወደ አሦር በመውሰድ ከእነርሱ ጥቂቶቹን በአላሔ ከተማ፣ ጥቂቶቹን በጋዛ አውረጃ በሚገኘው በአቦር ወንዝ አጠገብ፣ ሌሎቹን ደግሞ በሜዶን ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፡፡
\v 12 ይህም የሆነበት ምክንያት እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛቸው ነበር፤ ይኸውም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን አፈረሱ፣ በእግዚአብሔር አገልጋይ በሙሴ አማካይነት ለተሰጠ ሕግ ሁሉ ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ለመስማትም ሆነ ሕጉን ለመጠበቅ አሻፈረን አሉ፡፡
\s5
\v 13 ከዚያም ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም አደጋ በመጣል የተመሸጉትን የይሁዳ ከተሞች ያዘ፡፡
\v 14 ስለዚህም የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ በለኪሶ ሰፍሮ ለነበረው ለሰናክሬም፣ እኔ በድያለሁ፤ እባክህን እኔን ተወኝ፤ የምትጠይቀኝን ሁሉ እልክልሃለሁ ሲል መልእክት ላከ፡፡ ንጉሠ ነገሥቱም ለይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ እኔ የምፈልገው ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ እንድትልክልኝ ነው ሲል መለሰለት፡፡
\v 15 ስለዚህም ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥተ ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረውን ብር ሁሉ ሰብስቦ ላከለት፡፡
\s5
\v 16 እንዲሁም በእግዚዚብሔር ቤተ መቅደስ መግቢያ በሮች ላይ ተለብጦ የነበረውን ወርቅና እርሱም ራሱ በቤተ መቅደሱ የበር ዐምዶች ላይ ለብጦት የነበረውን ወርቅ ጭምር ወደ ሰናክሬም ላከ፡፡
\v 17 ነገር ግን የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከለኪሶ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ሠራዊቱም ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፡፡ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኩሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፡፡
\v 18 ከዚያ ወደ ሕዝቅያስ መልእክት ላኩበት፤ ሕዝቅያስም አገልጋዮቹ የሆኑ ሦስት ባለሥልጣኖች ሄደው እንዲገናኙአቸው አዘዘ፡፡ እነርሱም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነው የኬልቂያስ ልጅ ኤልያቄም፣ የቤተ መንግሥት ጸሐፊ የሆነው ሳምናስና የቤተ መዛግብት ኃላፊ የሆነው የአሳፍ ልጅ ዮአስ ነበሩ።
\s5
\v 19 ስለዚህም የአሦር ዋና የጦር አዛዥ እንዲህ አላቸው፡- ለሕዝቅያስ እንዲህ በሉት፣ ‘ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፡- እንደዚህ የተማመንክበት ነገር ምንድን ነው?
\v 20 በጦርነት የሚረዳ ኃይል እንዳለህ የተናገርከው ከንቱ ቃላት ናቸው፤ በእኔ ላይ ለማመጽ የቻልከው በምን ተማምነህ ነው?
\v 21 የግብጽ ንጉሥ ይረዳኛል ብለህ አስበህ ከሆነ የተቀጠቀጠ ሸምበቆ እንደሚመረኮዝ ሰው መሆንህ ነው፤ እርሱ ተሰብሮ ስንጣሪው እጅህን ያቆስልሃል፤ እንግዲህ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ለሚተማመኑበት ሁሉ እንዲህ ነው’ ሲል ተናገረ፡፡
\s5
\v 22 የአሦር የጦር አዛዥ ንግግሩን በመቀጠል እንደገና እንዲህ አለ፡- አምላክህ እግዚአብሔር እንደሚረዳህ ታስብ እንደሆነ፣ ይህ እንዳይሆን አንተ የእግዚአብሔርን የተቀደሱ ስፍራዎችንና መሠዊያዎችን ደምስሰህ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ ማምለክ የሚገባቸው ኢየሩሳሌም ውስጥ በሚገኘው በአንድ መሠዊያ ብቻ ነው ብለህ ወስነሃል፡፡
\v 23 አሁንም በንጉሠ ነገሥቱ ስም ለፍልሚያ እጠይቅሃለሁ፤ መጋለብ የሚችሉ በቂ ሰዎች ታገኝ አንደ ሆነ እስቲ ሁለት ሺህ ፈረሶች ልስጥህ፡፡
\s5
\v 24 አንተ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ከሆነው ከአሦር ተራ የጦር መኮንን ጋር እንኳ መወዳደር አትችልም፤ ግብጻውያን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ይልኩልኛል ብለህ የምትጠባበቀውም በዚሁ ምክንያት ነው፡፡
\v 25 እኔ በአንተ አገር ላይ አደጋ የጣልኩባትና የደመሰስኳት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ይመስልሃልን? እግዚአብሔር ራሱ በዚህች አገር ላይ አደጋ እንድጥልባትና እንድደመስሳት አዞኛል፡፡
\s5
\v 26 ኤልያቄም፣ ሳምናስና ዮአስ ይህን የጦር አዛዥ ትርጉሙን ስለምናውቅ በሶርያ ቋንቋ እንድትነግረን እንለምንሃለን፤ በቅጥር ላይ ያሉት ሕዝብ ሁሉ በሚሰሙት በዕብራይስጥ ቋንቋ አትናገረን አሉት፡፡
\v 27 የጦር አዛዡም፣ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ይህን ሁሉ ለእናንተና ለንጉሣቸሁ ብቻ እንድናገር የላከኝ መሰላችሁን? እንደ እናንተ ኩሳቸውን ለመብላትና ሽንታቸውን ለመጠጣት ለሚገደዱ ሰዎችም ጭምር ስለ ሆነ እኔ የምናገረውን በቅጥር ላይ ያሉት ሰዎች ሁሉ እንዲሰሙት እንድናገር አልላከኝምን? ሲል መለሰላቸው፡፡
\s5
\v 28 ከዚያም የአሦር የጦር አዛዥ ከተቀመጠበት ተነሥቶ ቆመ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ በዕብራይስጥ ቋንቋ እንዲህ እያለ ጮኸ፡- የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚነግራችሁን ስሙ፤
\v 29 በሕዝቅያስ አትታለሉ፤ እርሱ ሊያድናችሁ ከቶ አይችልም፡፡
\v 30 ሕዝቅያስ፣ በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ ያድናችኋል፤ ከተማችንም በአሦርያውያን ሠራዊት እጅ እንዳትገባ ይከላከልልናል እያለ የሚሰብካችሁን አትስሙት፡፡
\s5
\v 31 ሕዝቅያስ የሚላችሁን አታዳምጡ፤ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ከከተማችሁ ወጥታችሁ እጃችሁን እንድትሰጡ አዞአችኋል፤ ይህን ብታደርጉ ሁላችሁም እያንዳንዳችሁ የወይን ተክሎቻችሁን ዘለላና የበለስ ዛፎቻችሁን ፍሬ ትበላላችሁ፤ ከጉድጓዶቻችሁም ውሃ ትጠጣላችሁ፡፡
\v 32 ይህም ሁሉ የሚሆነው ንጉሠ ነገሥቱ የእናንተን አገር ወደምትመስል ምድር ወስዶ እስከሚያሰፍራችሁ ድረስ ነው፤ በዚያችም ምድር ወይን ጠጅ የሚገኝባቸው የወይን ተክል ቦታዎችና በቂ የእንጀራ እህል የሚመረትባቸው እርሻዎች አሉ፤ ምድሪቱም የወይራ ፍሬና የወይራ ዘይት እንዲሁም ማር የሞላባት ናት። ንጉሠ ነገሥቱ የሚያዛችሁን ብትፈጽሙ በሕይወት ትኖራላችሁ እንጂ አትሞቱም፡፡ ስለዚህ ሕዝቅያስ፣ “እግዚአብሔር ይታደጋችኋል” እያለ በመስበክ አያሙኛችሁ፡፡
\s5
\v 33 ለመሆኑ ከሌሎች ሕዝቦች አማልክት አንዱ እንኳ ከአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አገሩን ያዳነ ይገኛልን?
\v 34 ታዲያ ይህ ከሆነ የሐማትና የአርፋድ አማልክት የት አሉ? የሴፈርዋይ፣ የሄናና የዒዋ አማልክትስ የት ደረሱ? ከእነርሱ አንዱ እንኳ ሰማርያን ከእጄ ማዳን ችሎአልን?
\v 35 የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ንጉሠ ነገሥቶቻቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እንግዲህ እናንተ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?
\s5
\v 36 ሕዝቡም ቀደም ሲል ንጉሥ ሕዝቅያስ ባዘዛቸው መሠረት አንዲት ቃል ሳይናገሩ ዝም አሉ፡፡
\v 37 ከዚያም ኤልያቄም፣ ሳምናስና ዮአስ በሐዘን ልብሳቸውን ቀደዱ፤ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ቀርበው የአሦራውያን የጦር አዛዥ የተናገረውን አስረዱት፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 ንጉሥ ሕዝቅያስ ይህን ሁሉ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ ማቅ ለብሶም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሄደ፡፡
\v 2 ወዲያውም የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን ኤልያቄምን፣ የቤተ መንግሥቱን ጸሐፊ ሳምናስንና ሽማግሌዎች ካህናትን ወደ አሞጽ ልጅ ወደ ነቢዩ ኢሳይያስ ላከ፤ እነርሱም ራሳቸው ማቅ ለብሰው ነበር፡፡
\s5
\v 3 ለኢሳይያስም እንዲነግሩት የላከው መልእክት ከዚህ የሚከተለው ነው፡- ዛሬ የታላቅ መከራ ቀን ነው፤ የሚያሳፍር ቅጣትና ውርደት እየደረሰብን ነው፤ የምትወልድበት ጊዜ ደርሶ ለማማጥ አቅም እንዳነሣት ሴት ሆነናል፡፡
\v 4 የአሦር ንጉሠ ነገሥት ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢው ይቀጣ ይሆናል። ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ለተረፉት ሰዎች እባክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡
\s5
\v 5 የንጉሥ ሕዝቅያስ መልእክተኞች ወደ ኢሳይያስ በመጡ ጊዜ፣
\v 6 ኢሳይያስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብላችሁ ለንጉሣችሁ ንገሩት አላቸው፣ የአሦር ንጉሥ አገልጋዮች ሲሰድቡኝ ስለ ሰማችሁት ቃል አትፍሩአቸው፡፡
\v 7 እነሆ እኔ የሽብር ወሬ የሚያሰማ መንፈስ እልክበታለሁ፤ ስለዚህ ወደ አገሩ ተመልሶ እንዲሄድ፣ እዚያ በገዛ ምድሩ በሰይፍ ተመትቶ እንዲሞት አደርጋለሁ፡፡
\s5
\v 8 ከዚያ የአሦር የጦር አዛዥ፣ የአሦር ንጉሥ ከሰፈሩ ከለኪሶ ተነሥቶ ልብናን ሊያጠቃ እንደ ሄደ በመስማቱ እርሱም ወደ ለኪሶ ሄደ፡፡
\v 9 በኢትየጵያ ንጉሥ በቲርሃቅ የሚመራ የግብጽ ሠራዊት እነርሱን ለመውጋት በመገሥገሥ ላይ መሆኑን ሰናክሬም ሰማ፤ ወዲያውኑ የአሦር ንጉሠ ነገሥት ወደ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል ደብዳቤ በመልእክተኞች እጅ ላከ፡-
\s5
\v 10 ‹‹የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሆይ፣ የምትታመንበት አምላክ ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አትወድቅም ብሎ አያታልልህ፤
\v 11 የአሦር ነገሥታት አገሮችን ሁሉ እንዴት ፈጽመው እንደ ደመሰሱ ሰምተሃል፤ አንተስ የምታመልጥ ይመስልሃልን?
\s5
\v 12 የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፣ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር የሚኖሩትን የዓዴንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን፣ ከአማልክቶቻቸው አንድ እንኳ ሊያድናቸው ችሎአልን?
\v 13 ለመሆኑ የሐማት፣ የአርፋድ፣ የሴፈርዋይም፣ የሄናዕና የዒዋ ከተሞች ነገሥታት የት አሉ?
\s5
\v 14 ንጉሥ ሕዝቅያስ ደብዳቤውን ከመልእክተኞች ተቀብሎ አነበበው፤ ወደ ቤተ መቅደስም ወስዶ ደብዳቤውን በእግዚአብሔር ፊት ዘረጋው፡፡
\v 15 እንዲህ ሲልም ጸለየ፡- ‹‹የሠራዊት አምላክ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ በኪሩቤል ላይ የተቀመጥህ፣ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፡፡
\s5
\v 16 አሁንም እግዚአብሔር ሆይ፤ የደረሰብንን ነገር ሁሉ ተመልከት፣ አንተን ሕያው የሆነከውን አምላክ በመስደብ ሰናክሬም የተናገረውን የዛቻ ቃል ሁሉ አድምጥ፤
\v 17 እግዚአብሔር ሆይ፣ የአሦር ነገሥታት ብዙ ሕዝቦችንና ምድራቸውን መደምሰሳቸው እርግጥ ነው፡፡
\v 18 ከእንጨትና ከድንጋይ ተጠርበው የተሠሩ የሰው እጅ ሥራ እንጂ አማልክት ስላልነበሩ በእሳት ላይ ጥለው አጠፉአቸው፡፡
\s5
\v 19 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፣ አንተ ብቻ አምላክ መሆንህን የዓለም መንግሥታት ሁሉ ያውቁ ዘንድ አሁን ከአሦር ንጉሥ አድነን፡፡››
\s5
\v 20 ከዚያም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፡- ‹‹የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‹ስለ አሦር ንጉሠ ነገሥት ስለ ሰናክሬም ዛቻ ወደ እኔ የጸለይከውን ጸሎት ሰምቻለሁ፡፡
\v 21 ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፡- የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፣ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል፡፡
\v 22 የሰደብከውና የተዳፈርከው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ያደረግኸው በማን ላይ ነው? በትዕቢትስ ዐይንህን ያነሳኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ ነው፡፡
\s5
\v 23 በመልእክተኞችህ አማካይነት፣ በእግዚአብሔር ላይ ስድብን አብዝተሃል፤ ‹በሠረገሎቼ ከፍተኛ ወደ ሆኑት ተራራዎች፣ ወደ ሊባኖስ ጫፍ ወጥቻለሁ፤ ረጃጅሞቹን የሊባኖስ ዛፎችዋንና ምርጦቹን ዝግባ ቆርጬአለሁ፤ ወደ ዳርቻዋና ውብ ወደሆነው ጫካዋ ደርሼአለሁ፤› ብለሃል፡፡
\v 24 ‹በባዕድ አገር ጉድጓድ ቆፍሬ ውሃ ጠጣሁ፤ በእግሬ ኮቴዎች የግብጽን ወንዞች አድርቄአለሁ› ብለህ ታብየሃል፡፡
\s5
\v 25 ሰናክሬም ሆይ! አስተውል፤ ጥንቱኑ እኔ እንደ ወሰንኩት፣ በቀድሞው ዘመን እንዳቀድኩትና አሁን በሥራ ላይ ባዋልኩት መሠረት የተጠናከሩ ከተሞችን ወደ ፍርስራሽ ክምርነት እንድትለውጥ ያደረግኹህ እኔ መሆኔን አልሰማህምን?
\v 26 የእነዚያ አገር ነዋሪዎች ኃይላቸው ተዳክሞ፣ ተስፋ በመቁረጥ እንዲያፍሩ ተደርገው በምሥራቅ ነፋስ እንደተመቱ የመስክ አትክልቶች፣ እንደ ቀጨጩ አረንጓዴ ቡቃያዎች፣ በጣራ ላይ እንደበቀሉ ሣር ናቸው፡፡
\s5
\v 27 እኔ ግን መነሣትህንና መቀመጥህን፣ መውጣትህንና መግባትህን፣ እንዲሁም እኔን መቃወምህን ዐውቃለሁ፡፡
\v 28 በእኔ ላይ ያለው ተቃውሞህና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአል፤ በአፍንጫህ ትናጋ፣ በአፍህም ልጓም አድርጌ፣ በመጣህበት መንገድ እመልስሃለሁ፡፡››
\s5
\v 29 ከዚያም ኢሳይያስ ንጉሥ ሕዝቅያስን አንዲህ አለው፤ ‹‹ይህ ሁሉ እንደሚፈጸም ምልክቱ ይህ ነው፣ በአሁኑና በሚቀጥለው ዓመት ሳይዘሩት የሚበቅለውንና የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን የራሳችሁን እህል ዘርታችሁ ታመርታላችሁ፤ ወይንም ተክላችሁ ፍሬውን ትበላላችሁ፤
\v 30 በይሁዳ ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ወደ መሬት ሥር ሰድዶ እንደሚያድግና እንደሚያፈራ ተክል ይሆናሉ፤
\v 31 ከኢየሩሳሌምና ከጽዮን ተራራ የተረፉት ወገኖች ይወጣሉ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ይፈጽማል፡፡››
\s5
\v 32 ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦራውያን ንጉሠ ነገሥት የተናገረውም ቃል ይህ ነው፡- ‹‹ሰናክሬም ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባባትም፤ አንድ ፍላጻ እንኳ አይወረውርባትም፤ ጋሻ ያነገበ ወታደርም ወደ እርስዋ አይቀርብም፤ በአፈር ቁልልም አትከበብም፡፡
\v 33 እርሱ ወደዚህች ከተማ ሳይገባ በመጣበት መንገድ ተመልሶ ይሄዳል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፡፡
\v 34 ስለ ራሴ ክብርና ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ይህችን ከተማ እኔ ራሴ ተከላክዬ አድናታለሁ፡፡››
\s5
\v 35 በዚያው ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወደ አሦራውያን ሰፈር አልፎ አንድ መቶ ሰማኒያ አምስት ሺህ ወታደሮችን ገደለ፤ በማግስቱ በማለዳ ሰዎች በሚነቁበት ጊዜ ሁሉም ሞተው ተገኙ፡፡
\v 36 ስለዚህ የአሦራውያን ንጉሠ ነገሥት ሰናክሬም ወደ ኋላው በማፈግፈግ ወደ ነነዌ ተመለሰ፡፡
\v 37 ከዕለታት በአንዱ ቀን ናሳራክ በሚል ስም በሚጠራው ባዕድ አምላኩ ቤተ መቅደስ ውስጥ በስግደት ላይ እንዳለ፣ ከልጆቹ ሁለቱ በተለይ አደራሜሌክና ሳራሳር ተብለው የሚጠሩት በሰይፍ ገደሉት፤ እነርሱም ወደ አራራት አምልጠው ሄዱ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ከልጆቹ አንዱ አስራዶን የተባለው ነገሠ፡፡
\s5
\c 20
\p
\v 1 በዚያን ዘመን ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበር፡፡ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጎበኘው ሄዶ፡- ‹‹እግዚአብሔር ‹ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህም ስለማይቀር ሁሉን ነገር አስተካክል› ብሎሃል›› ሲል ነገረው፡፡
\v 2 ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡-
\v 3 ‹‹እግዚአብሔር ሆይ! በታማኝነትና በቅንነት እንዳገለገልኩህ፣ አንተ የምትደሰትበትንም ነገር ለማድረግ ዘወትር እጥር እንደነበር ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ! እያለ በመጸለይ ምርር ብሎ አለቀሰ፡፡
\s5
\v 4 ኢሳይያስ ከንጉሡ ፊት ወጥቶ የቤተ መንግሥቱን መካከለኛ አደባባይ አልፎ ከመሄዱ በፊት፣ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጣለት፡-
\v 5 ‹‹ሕዝቤን ወደሚመራው ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ተመልሰህ በመግባት እንዲህ በለው፡- ‹እኔ የቀድሞ አባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ እንባህንም ተመልክቻለሁ፤ እኔ እፈውስሃለሁ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ትወጣለህ፡፡
\s5
\v 6 በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምርልሃለሁ፤ አንተንና ይህችን የኢየሩሳሌምን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ በመታደግ አድናለሁ፡፡ ስለ ክብሬና ለአገልጋዬ ለዳዊት ስለ ሰጠሁት የተስፋ ቃል ከተማይቱን በመከላከል እጠብቃታለሁ፡፡”
\v 7 ስለዚህ ኢሳይያስ የንጉሡን አገልጋዮች ‹‹የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ አምጡልኝ›› ብሎ አመጡለት፤ በቁስሉ ላይ ባደረጉለት ጊዜ የሕዝቅያስ ቁስል ተፈወሰ፡፡
\s5
\v 8 ንጉሥ ሕዝቅያስም ኢሳይያስን ‹‹እግዚአብሔር እንደሚፈውሰኝና ከሦስት ቀን በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ መሄድ እንደምችል በምን ምልክት ዐውቃለሁ? ሲል ጠየቀው፡፡
\v 9 ኢሳይያስም ‹‹እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል የሚፈጽም ስለ መሆኑ ራሱ ምልክት ይሰጥሃል፤ እንግዲህ አሁን የምትመርጠው ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ነው? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ? ሲል ጠየቀው፡፡
\s5
\v 10 ሕዝቅያስም ‹‹ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት እንዲሄድ ማድረግ ይቀላል፤ ስለዚህ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አድርግልኝ›› አለው፡፡
\v 11 ኢሳይያስም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ንጉሥ አካዝ ባሠራው ደረጃ ላይ ያረፈው ጥላ ዐሥር ደረጃ ላይ ያረፈው ጥላ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ እንዲመለስ አደረገ፡፡
\s5
\v 12 በዚያኑ ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባላዳን ልጅ መሮዳክ ባላዳን፣ ንጉሥ ሕዝቅያስ መታመሙን ሰምቶ ከገጸ በረከት ጋር ደብዳቤ ላከለት፡፡
\v 13 ሕዝቅያስ መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበላቸው፤ በቤተ መንግሥቱም የዕቃ ግምጃ ቤት ያለውን ሀብት በሙሉ፣ ብሩንና ወርቁን፣ ቅመማ ቅመሙንና ሽቶውን፣ የጦር መሣሪያውንም ሁሉ አሳያቸው፤ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤትም ሆነ በመንግሥቱ በማንኛውም ስፍራ ካለው ሀብት ሁሉ ያላሳያቸው አንድም አልነበረም፡፡
\s5
\v 14 በዚያን ጊዜ ነቢዩ ኢሳይያስ ወደ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሄዶ፣ ‹‹እነዚህ ሰዎች ከወዴት መጡ? ምንስ ነገሩህ? ብሎ ጠየቀው፡፡ ሕዝቅያስም ‹‹እነርሱ የመጡት ባቢሎን ከሚባል ከሩቅ አገር ነው›› ሲል መለሰለት፡፡
\v 15 ኢሳይያስም ‹‹በቤተ መንግሥቱ ምን አዩ›› ሲል ጠየቀው፡፡ ሕዝቅያስም ‹‹ሁሉን ነገር አይተዋል፤ በግምጃ ቤቱ ካለው ሀብት ሁሉ ለእነርሱ ያላሳየኋቸው አንድም ነገር የለም›› አለ፡፡
\s5
\v 16 ኢሳይያስም ንጉሡን እንዲህ አለው፡- ‹‹ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣
\v 17 ‹የቀድሞ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ድረስ ያከማቹት፣ በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርም።
\v 18 ከዘሮችህም አንዳንዶቹ ወደ ባቢሎን ተማርከው በመሄድ በባቢሎን ቤተ መንግሥት ጃንደረቦች ሆነው እንዲያገለግሉ ይደረጋል፡፡››
\s5
\v 19 ንጉሥ ሕዝቅያስም በተለይ በእርሱ ዘመን በሰላም የመኖር ዋስትና እንዳለው ስለ ተረዳ ‹‹ከእግዚአብሔር ተልከህ የተናገርከኝ ቃል መልካም ነው›› ሲል መለሰ፡፡
\v 20 ንጉሥ ሕዝቅያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ የጀግንነት ሥራው ጭምር፣ እንዲሁም የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ እንዴት እንደ ሠራና ወደ ከተማይቱ ውሃ ለማምጣት ያስቆፈረው የመሬት ውስጥ ቦይ አሠራር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 21 ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ምናሴ ነገሠ፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 ምናሴ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ሁለት ዓመት ነበር፤ እርሱም በኢየሩሳሌም ኀምሳ አምስት ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ሐፍሴባ ተብላ ትጠራ ነበረ፡፡
\v 2 እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ አገር በሚገቡበት ጊዜ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋቸውን የአሕዛብን አሳፋሪ ልማድ በመከተል ምናሴ የሠራው ኃጢአት እግዚአብሔርን አሳዘነ፡፡
\v 3 ምናሴ አባቱ ሕዝቅያስ አጥፍቶአቸው የነበሩትን የአሕዛብ መስገጃ ስፍራዎች እንደገና እንዲሠሩ አደረገ፡፡ የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ባደረገውም ዐይነት ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ መሠዊያዎችን፣ አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስልን ሠራ፤ የሰማይ ከዋክብትንም አመለከ፡፡
\s5
\v 4 እግዚአብሔር እንዲመለክበት ባዘዘው ስፍራ ማለትም በቤተ መቅደስ ውስጥ አረማዊ መሠዊያዎችን አቆመ፡፡
\v 5 በሁለቱም የቤተ መቅደሱ አደባባዮች የሰማይ ከዋክብት የሚመለኩባቸውን መሠዊያዎች ሠራ፡፡
\v 6 የገዛ ልጁንም መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት በመሥራቱ የእግዚአብሔርን ቁጣ አነሣሣ፡፡
\s5
\v 7 በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን ‹‹ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እንድመለክበት ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፡፡
\v 8 የእስራኤል ሕዝብ ትእዛዞቼን ቢጠብቁና ለአገልጋዬ ለሙሴ የሰጠሁትንም ሕግ ቢፈጽሙ፣ ለቀድሞ አባቶቻቸው ከሰጠኋቸው ከዚህች ምድር ተነቃቅለው እንዲጠፉ አላደርግም›› ሲል ነግሮአቸው የነበረው ነው፡፡
\v 9 የይሁዳ ሰዎች ግን ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዦች ሆነው አልተገኙም፤ ይልቁንም ምናሴ እስራኤላውያን ወደፊት እየገፉ ሲመጡ እግዚአብሔር ከፊታቸው ነቃቅሎ ያጠፋላቸው ሕዝቦች ይፈጽሙት ከነበረው ይበልጥ ወደ ክፉ ኃጢአት መራቸው፡፡
\s5
\v 10 ስለዚህ እግዚአብሔር በአገልገጋዮቹ በነቢያት አማካይነት እንዲህ ሲል ተናገረ፡-
\v 11 ‹‹የይሁዳ ንጉሥ ምናሴ ይህን ሁሉ አሳፋሪ ነገር አደረገ፤ ይኸውም ቀድሞ ከነዓናውያን ይፈጽሙት ከነበረው ሁሉ የከፋ ነው፤ በሠራቸውም ጣዖቶች የይሁዳን ሕዝብ ወደ ኃጢአት መራ፡፡
\v 12 ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ የመጣው በጣም ከባድ መቅሰፍት ይህ ነው፤ ስለ እርሱም የሚሰማ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ጆሮው ጭው ይላል፡፡
\s5
\v 13 ሰማርያንና የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን ከነዘሮቹ እንደ ቀጣሁ ኢየሩሳሌምንም እቀጣለሁ፤ ሳሕን ከተወለወለ በኋላ ተደፍቶ እንደሚቀመጥ፣ እኔም ኢየሩሳሌምን ከኃጢአት አጸዳታለሁ፡፡
\v 14 ከጥፋት የተረፈውን ሕዝቤን ለጠላቶቹ ተላልፎ እንዲሰጥ እተወዋለሁ፤ እርሱም ይማረካል፤ ንብረቱም ይዘረፋል፡፡
\v 15 በእነርሱም ላይ ይህን ሁሉ የማደርግበት ምክንያት የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ ከወጡበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን ድረስ ኃጢአት ሠርተው እኔን በማሳዘናቸውና ቁጣዬን በማነሣሣታቸው ነው፡፡››
\s5
\v 16 ከዚህም በተጨማሪ ምናሴ የይሁዳን ሕዝብ ወደ ጣዖት አምልኮና እግዚአብሔርን ወደሚያሳዝን ኃጢአት ከመምራት አልፎ፣ ንጹሓን የሆኑትን ብዙ ሰዎችን በመፍጀት የኢየሩሳሌምን መንገዶች በደም እንዲጥለቀለቁ አድርጎአል፡፡
\v 17 ምናሴ ያደረገው ሌላው ነገርና የፈጸመው ኃጢአት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሓፍ ተመዝቦ ይገኛል፡፡
\v 18 ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በቤተ መንግሥቱ ግቢ ‹‹የዖዛ አትክልት ስፍራ›› ተብሎ በሚጠራው ቦታ ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ አሞን ነገሠ፡፡
\s5
\v 19 አሞን በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሁለት ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ሜሶላም ተብላ የምትጠራ የዮጥባ ከተማ ተወላጅ የሐሩስ ልጅ ነበረች፡፡
\v 20 አሞን እንደ አባቱ እንደ ምናሴ ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሠራ፡፡
\s5
\v 21 የአባቱንም መጥፎ አርአያነት ሁሉ ተከተለ፤ አባቱ ይሰግድላቸውና ያመልካቸው የነበሩትንም ጣዖቶች ሁሉ አመለከ፡፡
\v 22 የቀድሞ አባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርንም ተወ፤ እግዚአብሔርንም አልተከተለም፡፡
\v 23 አገልጋዮቹ ባለሥልጣኖችም በአሞን ላይ አድመው በራሱ ቤት ውስጥ ገደሉት፡፡
\s5
\v 24 የይሁዳም ሕዝብ የአሞንን ገዳዮች ደምስሰው ልጁን ኢዮስያስን አነገሡ፡፡
\v 25 አሞን ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 26 አሞን ‹‹የዖዛ አትክልት ስፍራ›› ተብሎ በሚጠራው መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ልጁ ኢዮስያስ ነገሠ፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 ኢዮስያስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ገና ስምንት ዓመት ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም ይዲዳ ተብላ የምትጠራ የባሱሮት ከተማ ተወላጅ የሆነው የአዳያ ልጅ ነበረች፡፡
\v 2 ኢዮስያስ የቀድሞ አባቱን የዳዊትን መልካም ምሳሌነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፡፡ ወደ ግራም ቀኝም አላለም፡፡
\s5
\v 3 ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የሜሶላም የልጅ ልጅ፣ የኤዜልያስ ልጅ የሆነውን የቤተ መንግሥቱን ጸሓፊ ሳፋንን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በማለት መልእክት ወደ ቤተ መቅደስ ላከው፡፡
\v 4 ‹‹ኬልቂያስ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄደህ፣ ወደ ቤተ መቅደስ በሚያስገባው በር አጠገብ በየተራ ከሕዝቡ ገንዘብ የመሰብሰብ ኃላፊነት የተሰጣቸው ካህናት እስከ አሁን ምን ያህል ገንዘብ ከሕዝቡ እንደሰበሰቡ የሚገልጥ የሒሳብ ማስረጃ ይዘህ እንድትመጣ አለው፡፡
\v 5 የመቅደሱን እድሳት ለመቆጣጠር ለተሾሙት ሰዎች ያስረክቡ፤ እነርሱም የተረከቡትን ገንዘብ ቤተ መቅደሱን ለሚጠግኑ፣ ለአናጢዎች፣ ለግንበኞችና ለድንጋይ ጠራቢዎች ይክፈሉ፡፡
\s5
\v 6 እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ እድሳት ሳንቃዎችንና የተጠረቡ ድንጋዮችን ይግዙ፡፡
\v 7 ነገር ግን የሥራው ኃላፊዎች ፍጹም ታማኞች ስለ ሆኑ እነርሱን ስለ ገንዘቡ አወጣጥ መቆጣጠር አያስፈልግም፡፡››
\s5
\v 8 ጸሐፊው ሳፋን ከንጉሡ የተላከውን ትእዛዝ ለኬልቂያስ ሰጠው፤ ኬልቂያስም ‹‹የሕጉን መጽሐፍ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አገኘሁ›› ብሎ ለሳፋን ሰጠው፤ ሳፋንም ተቀብሎ አነበበው፡፡
\v 9 ጸሐፊውም ሄደና ‹‹አገልጋዮችህ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበረውን ገንዘብ ተቀብለው ለእድሳቱ ሥራ ኃላፊዎች ለሆኑት ሰዎች አስረክበዋል›› ሲል አስረዳ፡፡
\v 10 ከዚያም ጸሐፊው ሳፋን ለንጉሡ ‹‹ካህኑ ኬልቂያስ አግኝቶ የሰጠኝ መጽሐፍ›› ነው አለው፡፡
\s5
\v 11 ንጉሡም፣ የሕጉ መጽሐፍ ሲነበብ በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፡፡
\v 12 እርሱም ለካህኑ ለኬልቂያስ፣ የሳፋን ልጅ ለሆነው ለአኪቃም፣ የሚክያስ ልጅ ለሆነው ለዓክቦር፣ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊ ለሆነው ለሳፋንና የንጉሡ የቅርብ አገልጋይ ለሆነው ለዓሳያ የሚከተለውን ትእዛዝ ሰጠ፡፡
\v 13 ‹‹እንግዲህ ሂዱና እኔና የይሁዳ ነዋሪ ሕዝብ በዚህ በተገኘው መጽሐፍ ስላለው ትምህርት ማወቅ እንችል ዘንድ እግዚአብሔርን ጠይቁ፤ የቀድሞ አባቶቻችን በዚህ መጽሐፍ የተጻፈውን መመሪያ ስላልተከተሉ እግዚአብሔር በእኛ ላይ በጣም ተቆጥቶአል፡፡››
\s5
\v 14 ካህኑ ኬልቂያስ፣ አኪቃም፣ ዓክቦር፣ ሳፋንና ዓሳያ በኢየሩሳሌም አዲስ በተሠራው ሰፈር የምትኖረውን ሕልዳና ተብላ የምትጠራውን ነቢይቱን የሴሌም ሚስት ለመጠየቅ ሄዱ። የሐርሐስ የልጅ ልጅ የቲቅዋ ልጅ የሆነው የቤተ መቅደስ አልባሳት ኃላፊ ነበር፤ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ለነቢይቱ አስረዱአት፡፡
\v 15 እርስዋም እንዲህ አለቻቸው፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፡- ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፡-
\v 16 ‹‹እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፤ የይሁዳ ንጉሥ ባነበበው መጽሐፍ ውስጥ በተጻፈው መሠረት በዚህች ቦታና በሕዝብዋ ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፡፡
\s5
\v 17 እነርሱ እኔን ትተው ለባዕዳን አማልክት መሥዋዕት አቅርበዋል፤ በእጃቸው በሠሩአቸው ጣዖታት ሁሉ እኔን አስቆጥተውኛል፤ ቁጣዬም አይበርድም፡፡
\v 18 እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ እንዲህ በሉት፤ እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የምለው ይህ ነው፤ ‹አንተ በዚያ መጽሐፍ የተነገረውን ቃል ሰምተህ፡-
\v 19 ይህችን ቦታና ሕዝብዋን የተረገሙና ባድማ እንደማደርግ የተናገርኩትን ቃል በሰማህ ጊዜ ልብህ ተነክቶ ራስህን በማዋረድህ፣ ልብስህን በመቅደድና በፊቴም በማልቀስህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ፡፡
\s5
\v 20 ከዚህም የተነሣ በኢየሩሳሌም ላይ የማመጣውን ቅጣት በዐይንህ ሳታየው እስከምትሞትበት ጊዜ ድረስ ተፈጻሚ አይሆንም፤ ስለዚህም አንተ በሰላም እንድትሞት አደርጋለሁ፡፡›› ሰዎቹም ይህን መልእክት ይዘው ወደ ንጉሥ ኢዮስያስ ተመለሱ፡፡
\s5
\c 23
\p
\v 1 ስለዚህ ንጉሥ ኢዮስያስ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን የታወቁ ሽማግሌዎችን ሁሉ ጠርቶ ሰበሰባቸው፡፡
\v 2 እነርሱም ካህናት፣ ነቢያት፣ ሌሎችም ሰዎች ከታናሾች ጀምሮ እስከ ታላቆች ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ ንጉሡም በዚያ ጠፍቶ በነበረውና በቤተ መቅደስ በተገኘው መጽሐፍ የሰፈረውን ቃል በሙሉ ለሕዝቡ አነበበ፡፡
\s5
\v 3 ንጉሡም በዐምዱ አጠገብ ቆሞ በሙሉ ልቡና አሳቡ እግዚአብሔርን ለመከተልና ትእዛዞቹን፣ ደንቦቹንና ድንጋጌዎቹን ለመጠበቅ በእርሱ ፊት ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ስለዚህም በዚህ የተጻፈውን ቃል ኪዳን አረጋገጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በቃል ኪዳኑ ለመቆም ተስማሙ፡፡
\s5
\v 4 ንጉሡም ኢዮስያስ ሊቀ ካህናቱን ኬልቅያስን፣ ረዳቶቹ የሆኑትን ካህናትና የቤተ መቅደስ በር ዘብ የሚጠብቁ ተረኞችን ጠርቶ ለባዓልና አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ፣ እንዲሁም ለከዋክብት ማምለኪያ ያገለግሉ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፡፡ ንጉሡም እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ከኢየሩሳሌም ውጪ ባለው በቄድሮን ሸለቆ በእሳት አቃጥሎ ዐመዱን ወደ ቤቴል ወሰደው፡፡
\v 5 በይሁዳ ከተማዎችና በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ባሉት ስፍራዎች ሁሉ በየኮረብታው ላይ በነበሩት መሠዊያዎች መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ የይሁዳ ነገሥታት ሾመዋቸው የነበሩትን ካህናት ሁሉ ከሥራ አሰናበተ፤ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ፣ ለፕላኔቶች፤ ለፀሐይ፣ ለጨረቃ፣ ለፀሐይና ለሰማይ ከዋክብት ሁሉ መሥዋዕት በማቅረብ የሚያገለግሉ ካህናትን ሁሉ አስወገደ፡፡
\s5
\v 6 አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ከቤተ መቅደስ ነቅሎ ከከተማይቱ በማውጣት ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ትቢያ እስኪሆንም አድቅቆ፣ በሕዝብ መቃብር ላይ በተነው፡፡
\v 7 ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፣ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉ ሴቶች አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ መጋረጃ የሚፈትሉበትን ክፍል ሁሉ አጸዳ፡፡
\s5
\v 8 በይሁዳ ከተሞችና በመላ አገሪቱ ከጌባ እስከ ቤርሳቤህ የነበሩትን ካህናት ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አመጣ፡፡ መሥዋዕት ያቀርቡባቸው የነበሩትን መሠዊያዎች ሁሉ ርኩስ መሆናቸውን አወጀ፤ እንዲሁም የከተማይቱ ገዢ ኢያሱ ወደ ከተማይቱ ሲገቡ ከዋናው ቅጥር በር በስተግራ በኩል ባሠራው ቅጥር በር አጠገብ የሚገኙትን መስገጃዎች አፈራረሰ፡፡
\v 9 የከፍታ ቦታ ካህናት በቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ለማገልገል ያልተፈቀደላቸው ቢሆንም በወንድሞቻቸው ዘንድ የነበረውን እርሾ ያልነካውን ሕብስት በሉ፡፡
\s5
\v 10 ንጉሥ ኢዮስያስ በሔኖም ሸለቆ የነበረውን ‹‹ቶፌት›› ተብሎ የሚጠራውን የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ ‹‹ሞሌክ›› ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፡፡
\v 11 የይሁዳ ነገሥታት ለፀሐይ አምልኮ መድበዋቸው የነበሩትን ፈረሶች ሁሉ አስወገደ፡፡ ለዚሁ አምልኮ ያገለግሉ የነበሩትን ሠረገሎች አቃጠለ፡፡ እነዚህ ሁሉ ቀደም ሲል ታላቁ ባለሥልጣን ናታን ሜሌክ በሚኖርባቸው ክፍሎች አጠገብና በቤተ መቅደሱ አደባባይ ቅጥር በር አጠገብ ይገኙ ነበር፡፡
\s5
\v 12 ንጉሥ አካዝ ባሠራቸው መኖሪያ ክፍሎች ጣራ ላይ በሚገኘው ቤተ መንግሥት የይሁዳ ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን መሠዊያዎችና በቤተ መቅደሱ ሁለት አደባባዮች ንጉሥ ምናሴ አሠርቶአቸው የነበሩትን መስገጃዎቸ ሁሉ ኢዮስያስ ደመሰሳቸው፤ መሠዊያዎቹን ሰባብሮ ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ ጣላቸው፡፡
\v 13 ንጉሡም ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ ከርኩሰት ተራራ በስተ ደቡብ አስታሮት ተብሎ ለሚጠራው ለአሞን አምላክ ንጉሥ ሰሎሞን አሠርቶአቸው የነበሩትን አስጸያፊ ምስሎች፣ የሲዶናውያንና የሞዓባውያን አስጸያፊ የሆኑ ጣዖታትን ሁሉ ደመሰሰ፡፡
\v 14 ንጉሥ ኢዮስያስ የድንጋይ አምዶችን ሁሉ ሰባበረ፤ አሼራ ተብላ የምትጠራውንም የሴት አምላክ ምስሎች ሰባብሮ ጣለ፡፡ እነርሱም ቆመውበት የነበረውን የድንጋይ ዐምዶች ሰባብሮ ስፍራውንም የሙታን አጥንት ሞላበት፡፡
\s5
\v 15 እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም በቤቴል አሠርቶት የነበረውን የማምለኪያ ቦታ ኢዮስያስ አፈራርሶ ጣለው፤ መሠዊያውን ነቅሎ የተመሠረተበትን ድንጋይ ሁሉ ሰባብሮ በማድቀቅ እንደ ትቢያ አደረገው፤ የአሼራንም ምስል በእሳት አቃጠለ፡፡
\v 16 ከዚያም ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት፣ በኮረብቶች ላይ የተሠሩ መቃብሮች አየ፤ በእነዚያም መቃብሮች ውስጥ የነበረውን አፅም ሁሉ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በእሳት አቃጠለው፡፡ በዚህም ዓይነት መሠዊያው የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ኢዮስያስ ይህንን ሁሉ በማድረጉ ከብዙ ጊዜ በፊት በተደረገ የአምልኮ በዓል ላይ ንጉሥ ኢዮርብዓም በመሠዊያው አጠገብ ቆሞ ሳለ ነቢዩ የተናገረው የትንቢት ቃል ተፈጸመ፡፡ ንጉሥ ኢዮስያስ ዙሪያውን ሲመለከት ይህንን የእግዚአብሔር ቃል ተናግሮ የነበረው ነቢይ የተቀበረበትን መካነ መቃብር የማን ነው ሲል ጠየቀ፡፡
\s5
\v 17 የቤቴል ሕዝብ ከይሁዳ መጥቶ በዚህ መሠዊያ ላይ ይህንን አንተ ያደረግኸውን ነገር ሁሉ እንደሚፈጸምበት ተናግሮ የነበረው የነቢዩ መቃብር ነው ሲሉ መለሱለት፡፡
\v 18 ኢዮስያስም እንዳለ ይኑር፣ የእርሱ አፅም ከዚህ መንቀሳቀስ የለበትም ሲል መለሰ፡፡ ስለዚህም የእርሱም ሆነ የሰማርያው ነቢይ አፅሞች ከዚያ እንዲነሡ አልተደረገም፡፡
\s5
\v 19 ከዚያም ንጉሥ ኢዮስያስ በማንኛይቱም የእስራኤል ከተማ የእስራኤል ነገሥታት አሠርተዋቸው የነበሩትን የእግዚአብሔርን ቁጣ ለማነሣሣት ምክንያት የሆኑ የአሕዛብ ማምለኪያ ስፍራዎችን ሁሉ አፈራረሰ፡፡ በቤቴል ያደረገውን ሁሉ በእነዚያ መሠዊያዎች ላይ ፈጸመ፡፡
\v 20 በእነዚያ መሠዊያዎች ላይ ያገለግሉ የነበሩትንም የአሕዛብ ካህናት ሁሉ አረዳቸው፡፡ በመሠዊያዎቹም ላይ አጥንቶቻቸውን አቃጠለ፡፡ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ፡፡
\s5
\v 21 ከዚያም ንጉሥ ኢዮስያስ በቃል ኪዳን መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የፋሲካ በዓል ያከብሩ ዘንድ ሕዝቡን አዘዘ፡፡
\v 22 መሳፍንት የሕዝቡ ገዢዎች ከነበሩበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አሁን በማናቸውም የእስራኤል ወይም የይሁዳ ነገሥታት አማካይነት ይህንን የመሰለ የፋሲካ በዓል ተከብሮ አያውቅም፡፡
\v 23 ነገር ግን ኢዮስያስ በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት የእግዘአብሔር ፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ተከበረ፡፡
\s5
\v 24 ሊቀ ካህናቱ ኬልቂያስ በቤተ መቅደስ ባገኘው መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው ሕግ ሁሉ ተፈጻሚነት እንዲኖረው በማሰብ፣ ንጉሥ ኡዮስያስ ከኢየሩሳሌምና ከሌላውም የይሁዳ ከተማ ሁሉ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችን ሁሉ የቤተ ሰብ አማልክት ጣዖቶችንና ሌሎችም አረማዊ የአምልኮ መፈጸሚያ ዕቃዎችን ሁሉ አስወገደ፡፡
\v 25 ለኦሪት ሕግ በመታዘዝ በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱና በፍጹም ኃይሉ እግዚአብሔርን ያገለገለ እንደ ንጉሥ ኢዮስያስ ያለ ከእርሱም በፊት ሆነ ከእርሱ በኋላ ከቶ አልነበረም፡፡
\s5
\v 26 ይሁን እንጂ ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው የእግዚአብሔር ቁጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር፡፡
\v 27 ስለዚህ እግዚብሔር እንዲህ አለ፡- በእስራኤል ላይ ያደረግኹትን ነገር ሁሉ በይሁዳ ላይ አደርጋለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ሕዝብ ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኳትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራል ብዬ የነበረውንም ቤተ መቅደስ እተዋለሁ፡፡
\s5
\v 28 ንጉሥ ኢዮስያስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 29 በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ኒካዑ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፡፡ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፡፡
\v 30 አገልጋዮቹም ባለሥልጣኖች ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፡፡ የይሁዳም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን መረጡ፣ በአባቱም ፈንታ አነገሡት፡፡
\s5
\v 31 ኢዮአክስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ ሦስት ዓመት ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም አሚጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፡፡
\v 32 ኢዮአክስ የቀድሞ አባቶቹ እንዳደረጉት በእግዚብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
\v 33 እርሱንም ኒካዑ ተብሎ የሚጠራው የግብጽ ንጉሥ ኢዮአክስ በኢየሩሳሌም እንዳይነግሥ በሐማት ምድር በምትገኘው በሪብላ አስሮ ይሁዳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ ብር ሠላሳ አራት ኪሎ ወርቅ ግብር እንዲከፍል ባደረገው ጊዜ የኢዮአክስ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ሆነ፡፡
\s5
\v 34 ንጉሥ ኒካዑ የኢዮአክስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ ፈንታ ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፡፡ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፡፡ ኢዮአክስ በንጉሥ ኒካዑ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ፡፡
\v 35 ኢዮአቄም ለግብጽ ንጉሥ ለኒዑዑ የጠየቀውን ብርና ወርቅ ከፈለ፡፡ ይህንንም ለማድረግ እንደየችሎታቸው በሕዝቡ ላይ ግብር ጣለ፡፡
\s5
\v 36 ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ዘቢዳ ተብላ የምትጠራ የሩማ ከተማ ተወላጅ የሆነው የፈዳያ ልጅ ነበረች፡፡
\v 37 ኢዮአቄም የቀድሞ አባቶቹ እንዳደረጉት በእግዚብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይሁዳን ወረረ፤ ኢዮአቄምም ሦስት ዓመት ከገበረለት በኋላ እንደገና አመፀ፡፡
\v 2 እግዚብሔር በአገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፣ ሶርያውያንን፣ ሞአባውያንንና አሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት፡፡
\s5
\v 3 ይህም ሁሉ የሆነው ንጉሥ ምናሴ በፈጸመው ኃጢአት ምክንያት የይሁዳን ሕዝብ ከፊቱ ለማስወገድ እግዚብሔር ባዘዘው መሠረት ነው፡፡
\v 4 በተለይ ምናሴ የንጹሓንን ሰዎች ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓ ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፡፡ ከዚህም የተነሣ እግዚብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም፡፡
\s5
\v 5 ኢዮአቄም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡
\v 6 ኢዮአቄምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በእርሱም ፈንታ ልጁ ዮአኪን ነገሠ፡፡
\s5
\v 7 የባቢሎን ንጉሥ ከኤፍራጥስ ወንዝ እስከ ግብጽ ሰሜናዊ ጠረፍ ድረስ የግብጽ ይዞታ የነበረውን ሁሉ በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ ስለ ነበረ፣ የግብጽ ንጉሥና ሠራዊቱ ከዚያ በኋላ ከግብጽ ውጪ ዘመቻ አላደረጉም፡፡
\s5
\v 8 ዮአኪን በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ዐሥራ ስምንት ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌም ሦስት ወር ገዛ፡፡ እናቱም ኔስታ ተብላ የምትጠራው የኢየሩሳሌም ተወላጅ የሆነው የኤልናታን ልጅ ነበረች፡፡
\v 9 አባቱ እንዳደረገው ሁሉ በእግዚብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
\s5
\v 10 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን አጠቃ፤ ከተማይቱንም ከበባት፡፡
\v 11 ሠራዊቱ ከብቦ በነበረበት ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡
\v 12 የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ከእናቱ፣ ከልዑላን መሳፍንቱ፣ ከጦር አዛዦቹና ከባለሥልጣናቱ ጋር ወደ ባቢሎን ንጉሥ ተወሰዱ፡፡ የባቢሎን ንጉሥም በነገሠ በስምንተኛው ዓመት ዮአኪንን ማረከው፡፡
\s5
\v 13 ናቡከደነፆርም በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት የነበረውን ሀብት ሁሉ ጠራርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደ፡፡ ቀደም ሲል እግዚብሔር በተናገውም ቃል መሠረት ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚብሔር ቤተ መቅደስ አሠርቶት የነበረውን የወርቅ ዕቃ ሁሉ ሰባበረ፡፡
\v 14 ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ልዑላን፣ መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎች ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፡፡ ከእርሱም ጋር የዕደ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎቹን ድኾች ብቻ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ናቡከደነፆር ዮአኪንን አስሮ ከእናቱ፣ ከሚስቶቹ፣ ከአገልጋዮቹ፣ ከባለሥልጣኖቹና ከይሁዳ ታላላቅ ሰዎች ጋር በአንድነት ሰብስቦ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፡፡
\v 16 የባቢሎን ንጉሥ ሰባት ሺህ ለውጊያ ብቃት ያላቸው ወንዶችን እንዲሁም አንድ ሺህ ብረት ቀጥቃጮችንና ዕደ ጥበበኞችን ወደ ባቢሎን ወሰደ፡፡
\v 17 ናቡከደነፆርም በዮአኪን ምትክ ማታንያ ተብሎ የሚጠራውን የዮአኪንን አጎት በይሁዳ አነገሠው፤ ስሙንም በመለወጥ ሴዴቅያስ ብሎ ጠራው፡፡
\s5
\v 18 ሴዴቅያስ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፡፡ እናቱም አሚጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የነበረው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፡፡
\v 19 እርሱም አባቱ ኢዮአቄም ባደረገው ዓይነት በእግዚአብሔር ክፉ አደረገ፡፡
\v 20 እግዚብሔር ከፊቱ እስኪያስወግዳቸው ድረስ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሕዝብ ተቆጥቶ ነበር፡፡ ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ፡፡
\s5
\c 25
\p
\v 1 ናቡከደነፆር መላው ሠራዊቱን አስከትቶ ሴዴቅያስ በነገሠ በዘጠነኛው ዓመት፣ ዐሥረኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ከባቢሎን መጥቶ በኢየሩሳሌም ላይ ዘመተ፤ ወታደሮቹ ከከተማይቱ ውጪ ሰፍረው ዙሪያውን የሚከብብ አጥር ሠሩ፡፡
\v 2 ከበባው እስከ ሴዴቅያስ ዐሥራ አንደኛ ዓመት ዘመነ መንግሥት ድረስ ቆየ፡፡
\v 3 ስለዚህም አራተኛው ወር በገባ በዘጠነኛው ቀን ራቡ በጣም ስለ ጸና ሕዝቡ የሚመገበው እንዳችም ምግብ አልነበረም፡፡
\s5
\v 4 ከዚያም የከተማይቱ ቅጥር ተጣሰ፤ የባቢሎን ወታደሮች ከተማይቱን ዙሪያውን ከበው በመያዝ ቢጠብቁም እንኳ የይሁዳ ንጉሥ ወታደሮች በሌሊት አምልጠው ወጡ፤ ወደ ንጉሡ የአትክልት ቦታ ከሚያስገባው መንገድ ተነሥተው ሁለቱን ቅጥሮች በሚያያይዘው የቅጥር በር በኩል በማለፍ ወደ ዮርዳኖስ ሸለቆ አቅጣጫ ሸሹ፡፡
\v 5 ነገር ግን የከላደውያን ሠራዊት ንጉሥ ሴዴቅያስን በኢያሪኮ አጠገብ በሚገኝ ሜዳ ላይ አሳደደው፡፡ ወታደሮቹም ጥለውት ሸሹ፡፡
\s5
\v 6 ሴዴቅያስ ተይዞ በሪብላ ከተማ ወደሚገኘው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ተወሰደ፡፡ በዚያም ፍርድ አስተላለፉበት፡፡
\v 7 ሴዴቅያስም ዐይኑ እያየ ልጆቹ በፊቱ ታረዱ፡፡ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ አሳወረው፤ እጆቹንም በነሐስ ሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፡፡
\s5
\v 8 ናቡከደነፃር በባቢሎን በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት፣ አምስተኛው ወር በገባ በሰባተኛው ቀን ናቡዘረዳን ተብሎ የሚጠራው የናቡከደነፆር የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡
\v 9 እርሱም ቤተ መቅደሱን፣ ቤተ መንግሥቱን፣ በከተማው የሚኖሩትን የታላላቅ ሰዎች ቤት፣ በከተማው ውስጥ የሚገኙትንም ሌሎች ቤቶች ሁሉ በእሳት አቃጠለ፡፡
\v 10 በክብር ዘቡ አዛዥ ሥር የነበሩት የባቢሎናውያን ወታደሮች በሙሉ የኢየሩሳሌምን ዙሪያ አጥር ደመሰሱ፡፡
\s5
\v 11 ከዚህ በኋላ ናቡዘረዳን በከተማይቱ ቀርተው የነበሩትንና ሌሎችን ሰዎች እንዲሁም ከድተው ወደ ባቢሎናውያን የተጠጉትን ሁሉ ምርኮ አድርጎ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፡፡
\v 12 ነገር ግን ምንም ሀብት የሌላቸውን የመጨረሻ ድኾች አትክልት ኮትኳቾችና መሬት አራሾች እንዲሆኑ በይሁዳ ምድር ትቶአቸው ሄደ፡፡
\s5
\v 13 ባቢሎናውያን በቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩትን የነሐስ አምዶች፣ ባለ መንኮራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎችንና ከነሐስ የተሠራውን ታላቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ ሰባበሩ፤ ነሐሱንም ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰዱት፡፡
\v 14 እነርሱም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ መኮስተሪያዎችን፣ የዕጣን ማስቀመጫዎችንና ከነሐስ የተሠሩ የቤተ መቅደስ መገልገያ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰዱ፡፡
\v 15 ጽናዎችንና ዱካዎችን ከብርና ከወርቅ የተሠሩ በመሆናቸው ወሰዱአቸው፡፡
\s5
\v 16 ንጉሥ ሰሎሞን ለቤተ መቅደስ ያሠራቸውን ሁለቱን አምዶች፣ ባለመንኮራኩር የዕቃ ማስቀመጫዎችንና ታላቁን የውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳዎቸ፣ በክብደታቸው ምክንያት ሊመዝኑአቸው አልቻሉም፡፡
\v 17 አንዱ አምድ ስምንት ሜትር ነበረው፤ ጉልላቱ ከነሐስ የተሠራ ነበር፤ የጉልላቱም ቁመት አንድ ሜትር ከሠላሳ ሳንቲ ሜትር ነበር፤ በዙሪያውም ከነሐስ በተሠራ መረብ ላይ የሮማን ፍሬ ቅርጽ የመሰለ ባለፈርጥ ጌጥ ተሠርቶበት ነበር፡፡
\s5
\v 18 የሠራዊቱ አዛዥ ናቡዘረዳን ሊቀ ካህናቱን ሠራያን በማዕርግ የእርሱ ምክትል የሆነውን ካህኑን ሶፎንያስንና ሦስቱን የቤተ መቅደስ ዘበኞች እስረኛ አደርጎ ወሰዳቸው፡፡
\v 19 ከከተማይቱም የወታደሮች አዛዥ የሆነው አንድ ባለሥልጣን እስከዚያ ጊዜ ድረስ በከተማይቱ የነበሩትን አምስቱን የንጉሥ አማካሪዎች፣ የአገሩን ሕዝብ ለወታደርነት ይመለምል የነበረው መኮንንና ሌሎችንም ስልሳ ሰዎችን ወሰደ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያም ናቡዘረዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ በሐማት ግዛት በምትገኘው በሪብላ ከተማ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወሰዳቸው፡፡
\v 21 የባቢሎንም ንጉሥ በዚያ እነርሱን አስደብድቦ በማሠቃየት በሞት ቀጣቸው፡፡ በዚህም ዐይነት የይሁዳ ሕዝብ ከአገራቸው ተማርከው ተወሰዱ፡፡
\s5
\v 22 የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የሳፋን የልጅ ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን ወደ ባቢሎን ተማርከው ሳይወሰዱ ለቀሩት ሰዎች ሁሉ ኃላፊ ይሆን ዘንድ የይሁዳ ገዢ አድርጎ ሾመው፡፡
\v 23 እጃቸውን ያልሰጡ የይሁዳ የጦር መኮንኖችና ወታደሮች የባቢሎን ንጉሥ ጎዶልያስን ገዢ አድርጎ እንደ ሾመው በሰሙ ጊዜ ወደ ምጽጳ መጥተው ከእርሱ ጋር ተገናኙ፤ እነዚህም የጦር መኮንኖች የናታንያ ልጅ እስማኤል፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናን፣ የነጦፋ ከተማ ተወላጅ የሆነው የተንሑሜት ልጅ ሠራያና የማዕካ ተወላጅ የሆነው ያእዛንያ ነበሩ፡፡
\v 24 ጎዶልያስ እነርሱንና ወታደሮቻቸውን እንዲህ አላቸው፤ ከባቢሎናውያን ባለሥልጣኖች የተነሣ ምንም ዐይነት ፍርሃት ሊያድርባችሁ እንደማይገባ ቃል እገባላችኋለሁ፤ በዚህች ምድር ኑሮአችሁን መሥርቱ፤ ለባቢሎን ንጉሥ ገብሩ፤ ይህን ብታደርጉ ሁሉ ነገር ይቃናላችኋል፡፡
\s5
\v 25 ነገር ግን በዚያው ዓመት በሰባተኛው ወር ከንጉሣዊ ቤተ ሰብ የነበረውና የኤሊሳማ የልጅ ልጅ የሆነው የናታንያ ልጅ እስማኤል ከዐሥር ሰዎች ጋር ሆኖ ወደ ምጽጳ ሄደ፤ በዚያም አደጋ ጥሎበት ጎዶልያስን ገደለው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር የተገኙትን አይሁዳውያንንና ባቢሎናውያንን ሁሉ ገደለ፡፡
\v 26 ከዚህም የተነሣ ባቢሎናውያንን ስለፈሩ እስራኤላውያን ሀብታሞችና ድኾች ከጦር ሠራዊት መኮንኖች ጋር በአንድነት ተነሥተው ወደ ግብጽ ሸሹ፡፡
\s5
\v 27 ዮርማሮዴቅ በነገሠበት ዓመት የይሁዳን ንጉሥ ዮአኪንን ከእስራት በመፍታት ምሕረት አደረገለት፤ ይህም የሆነው ዮአኪን ተማርኮ በሄደ በሠላሳ ሰባት ዓመቱ፣ በዐሥራ ሁለተኛው ወር በሃያ ሰባተኛው ቀን ነበር፡፡
\s5
\v 28 ዮርማሮዴቅ ለዮአኪን መልካም ነገር አደረገለት፤ እንደ እርሱ ተማርከው በባቢሎን በስደት ከሚኖሩ ነገሥታት ሁሉ የላቀ የክብር ማዕረግ ሰጠው፡፡
\v 29 ስለዚህም ዮአኪን በእስር ቤት የነበረውን ልብስ ለውጦ እስከ ዕድሜው ፍጻሜ ድረስ ከንጉሡ ማዕድ እንዲመገብ ተፈቀደለት፡፡
\v 30 እርሱም በኖረበት ዘመን ሁሉ በየቀኑ ለማናቸውም ለሚያስፈልገው ነገር ያውለው ዘንድ የዘወትር ቀለብ ይሰጠው ነበር፡፡

1649
14-2CH.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,1649 @@
\id 2CH
\ide UTF-8
\h ሁለተኛ ዜና
\toc1 ሁለተኛ ዜና
\toc2 ሁለተኛ ዜና
\toc3 2ch
\mt ሁለተኛ ዜና
\s5
\c 1
\p
\v 1 የዳዊት ልጅ ሰለሞንም በመንግሥቱ በረታ፤ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበር፤ እጅግም ብርቱ ንጉሥ አደረገው።
\s5
\v 2 ሰለሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለዳኞችም፥ በመላው እስራኤልም ሁሉ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ፤
\v 3 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ በምድረ በዳ የሠራው የእግዚአብሔር መገናኛ ድንኳን በገባኦን ስለነበር ሰለሞንና ጉባኤው ሁሉ እዚያ ወደነበረው የአምልኮ ሥፍራ ሄዱ።
\v 4 ዳዊት ግን ለእግዚአብሔር ታቦት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ስለነበር ከቂርያት ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ሥፍራ አምጥቶት ነበር።
\v 5 በተጨማሪም በሆር ልጅ በኡሪ ልጅ በባስልኤል የተሠራው የናስ መሠዊያ በዚያ በእግዚአብሔር ማደሪያ ድንኳን ፊት ነበረ፤ ሰለሞንና ጉባኤውም ወደ እርሱ ሄዱ።
\s5
\v 6 ሰለሞንም በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ዘንድ ወደነበረው ወደ ናሱ መሰዊያ ወጣ። በዚያም አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ።
\v 7 በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር ለሰለሞን ተገልጦ ፦ እንድሰጥህ የምትፈልገውን ማንኛውንም ነገር ለምነኝ አለው።
\s5
\v 8 ሰለሞንም እግዚአብሔርን፦ ለአባቴ ለዳዊት ታላቅ የቃል ኪዳን ታማኝነት አሳይተሃል፤ እኔንም በእርሱ ምትክ ንጉሥ አድርገኸኛል፤
\v 9 አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፦ ቁጥራቸው እንደ ምድር ትቢያ በሆነው ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛልና ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም።
\v 10 አሁንም እንደዚህ ቁጥራቸው በበዛ ሕዝብህ ላይ ሊፈርድ የሚችል ማንም ስለሌለ ይህንን ሕዝብ እመራ ዘንድ ጥበብና እውቀት ስጠኝ አለው፡፡
\v 11 እግዚአብሔርም ሰለሞንን፡- በልብህ የነበረው ይህ ስለነበር ባለጠግነትን፥ ሀብትን፥ ወይም ክብርን ወይም የሚጠሉህን ሰዎች ነፍስ ወይም ለራስህ ረጅም እድሜ ስላልጠየቅህ ነገር ግን ባነገሥሁህ በህዝቤ ላይ ለመፍረድ ትችል ዘንድ ለራስህ ጥበብንና እውቀትን ስለጠየቅህ
\s5
\v 12 አሁን ጥበብና እውቀት ተሰጥተውሃል፤ ከአንተ በፊት የነበሩት ከነበራቸው እና ከአንተም በኋላ የሚመጡት ከሚኖራቸው ከየትኛውም ነገሥታት ይበልጥ ባለጠግነት፥ ሀብት፥ ክብርም እሰጥሃለሁ አለው፡፡
\v 13 ስለሆነም በገባኦን ከመገናኛው ድንኳን ፊት ከነበረው ከኮረብታው መስገጃ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ እዚያም በእስራኤል ላይ ነገሠ፡፡
\s5
\v 14 ሰለሞን ሰረገሎችን እና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፡፡ በሰረገሎች ከተማዎችና ከራሱ ከንጉሡ ጋር በኢየሩሳሌም ያኖራቸው አንድ ሺህ አራት መቶ ሰረገሎች እና አሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፡፡
\v 15 ንጉሡም ብርና ወርቅ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት በቆላ እንዳሉት የሾላ ዛፎች እንዲበዛ አደረገው፡፡
\s5
\v 16 ከግብጽና ከቀዌ ለሰለሞን ፈረሶችን ስለ ማስመጣት የእርሱ ነጋዴዎች በገንዘብ እየገዙ ያመጡአቸው ነበር፡፡
\v 17 ከግብጽ አንዱን ሰረገላ በስድስት መቶ ሰቅል ብር፥ አንዱን ፈረስ በመቶ ሃምሳ ሰቅል ብር ዋጋ ያስመጡ ነበር፡፡ ለኬጢያውያንና ለሶርያ ነገሥታትም ልከው ይሸጡአቸው ነበር፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 በዚህ ጊዜ ሰለሞን ለእግዚአብሔር ስም ቤት እንዲገነባ እና ለመንግሥቱ ቤተ መንግሥት እንዲገነባ አዘዘ፡፡
\v 2 ጭነት የሚሸከሙ ሰባ ሺህ ሰዎች እና ከተራሮች እንጨት የሚቆርጡትን ሰማንያ ሺህ ሰዎች እነርሱንም የሚቆጣጠሩ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎች መደበ፡፡
\v 3 ሰለሞንም ወደ ጢሮስ ንጉሥ ወደ ኪራም ፦የሚኖርበትን ቤት እንዲሠራ የዝግባ እንጨት በመላክ ከአባቴ ከዳዊት ጋር እንዳደረግህ ለእኔም እንደዚሁ አድርግልኝ፡፡
\s5
\v 4 እነሆ በእግዚአብሔር ፊት የጣፋጩን ቅመም ሽታ ለማጠን፥ የመገኘቱን ኅብስት ዘወትር ለማኖር፥ በጠዋትና በማታ፥ በሰንበታቱም ፥ በመባቻዎቹና ለአምላካችን ለእግዚአብሔር በተመደቡት ልዩ በዓላት የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤት ልገነባና ልቀድሰው ነው፡፡ ይህ ለእስራኤል ለሁልጊዜ ሕግ ነው፡፡
\v 5 አምላካችን ከአማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ ስለሆነ የምሠራው ቤት እጅግ ታላቅ ይሆናል፡፡
\s5
\v 6 ነገር ግን መላው አጽናፈ ዓለምና ሰማይ ራሱ ሳይቀር ሊይዘው ለማይችለው ለእርሱ ለእግዚአብሔር ቤት ይሠራ ዘንድ የሚችል ማን ነው? በፊቱ መሥዋዕት ከማቅረብ በስተቀር ለእርሱ ቤት እሰራ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
\v 7 በመሆኑም በወርቅ፥ በብር፥ በናስ፥ በብረት፥ እንዲሁም ሐምራዊውን፥ ቀዩን፥ ሰማያዊውን ግምጃ በመሥራት የተካነ ሰው፥ የእንጨት ቅርጻ ቅርጽ ዓይነቶችን ሁሉ መሥራት የሚያውቅ ሰው ላክልኝ፡፡ እርሱም አባቴ ዳዊት ካዘጋጃቸው በእኔ ዘንድ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ካሉት የተካኑ ሰዎች ጋር ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 አገልጋዮችህ እንጨት ከሊባኖስ መቁረጥ እንደሚያውቁ ስለማውቅ ከሊባኖስ የዝግባ እንጨቶች፥ የጥድ እንጨቶች፥ የሰንደልም እንጨቶች ላክልኝ፡፡ እነሆ ባሪያዎችህ ከባሪያዎቼ ጋር ይሆናሉ፡፡
\v 9 ልሠራ ያሰብኩት ቤት ታላቅና ድንቅ ይሆናልና የተትረፈረፈ ሳንቃ እንጨት እንዲያዘጋጁልኝ ነው፡፡
\v 10 እነሆ እንጨቱን ለሚቆርጡ ሰዎች ሀያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ የተፈጨ ስንዴ፥ ሀያ ሺህ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ፥ ሀያ ሺህ የባዶስ መስፈሪያ የወይን ጠጅ፥ ሀያ ሺህ የባዶስ መስፈሪያ ዘይት ለባሪያዎችህ እሰጣለሁ፡፡
\s5
\v 11 ንጉሥ ኪራም፦ እግዚአብሔር ሕዝቡን ስለሚወዳቸው በላያቸው አንግሦሃል ብሎ መልሶ ወደ ሰለሞን መልእክት ላከ፡፡
\v 12 በተጨማሪም ኪራም፦ ሰማይንን ምድርን የፈጠረ፥ ለእግዚአብሔር ቤት እና ለመንግሥቱ ቤት የሚሠራ ጥበበኛና ብልሃተኛ አስተዋይም ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት የሰጠ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን አለ፡፡
\s5
\v 13 አሁንም ማስተዋል የተሰጠውን የተካነውን ባለሙያዬን ሁራምን ልኬልሃለሁ፡፡
\v 14 ከዳን ሴት ልጆች የአንዲቱ ልጅ ነው፡፡ አባቱ የጢሮስ ሰው ነበር፡፡ ወርቁን፥ ብሩን፥ ናሱን፥ ብረቱን፥ ድንጋዩን እንዲሁም እንጨቱን፥ ሐምራዊውን፥ ሰማያዊንና ቀዩን ግምጃ ጥሩ በፍታውንም በመሥራት የተካነ ነው፡፡ የትኛውንም ዓይነት ቅርጽ በመሥራት እና የትኛውንም ዓይነት ንድፍ በማውጣትም የተካነ ነው፡፡ በተካኑት ሠራተኞችህ መካከል እና ከጌታዬ ከአባትህ ከዳዊት ብልሃተኞች ጋር ይሆን ዘንድ ስፍራ ይዘጋጅለት፡፡
\s5
\v 15 አሁንም ጌታዬ የተናገረውን ስንዴውንና ገብሱን ዘይቱንና የወይን ጠጁን እነዚህን ነገሮች ወደ አገልጋዮቹ ይላክ፡፡
\v 16 እኛም የሚያስፈልግህን ያህል እንጨት ከሊባኖስ እንጨት እንቆርጣለን፡፡ እንደ ታንኳ በባሕር ላይ ወደ ኢዮጴ እንወስድልሃለን፤ አንተም እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ታጓጉዘዋለህ፡፡
\s5
\v 17 ሰለሞንም ኣባቱ ዳዊት በእስራኤል ምድር የነበሩትን የውጪ አገር ዜጎች ሁሉ እንደቆጠረ እርሱ ያደረገበትን ዘዴ ተከትሎ ቆጠራቸው፡፡ እነርሱም አንድ መቶ ሃምሳ ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሆነው ተገኙ፡፡
\v 18 ሰባ ሺህው ጭነት እንዲሸከሙ ሰማንያ ሺህው በተራሮችም ላይ እንጨት እንዲቆርጡ እና ሦስት ሺህ ስድስት መቶው ደግሞ ሕዝቡን ለሥራ የሚያሰማሩ ተቆጣጣሪዎች እንዲሆኑ መደባቸው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ከዚህ በኋላ ሰለሞን እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠለት በሞሪያ ተራራ ላይ በኢየሩሳሌም የእግዚአብሔር ቤት መሥራት ጀመረ፡፡ ዳዊት እንዳቀደለት በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ሥፍራውን አዘጋጀ፡፡
\v 2 በነገሠ በአራተኛው ዓመት በሁለተኛው ወር በሁለተኛው ቀን መሥራት ጀመረ፡፡
\v 3 ሰለሞንም ለእግዚአብሔር ቤት የጣለው መሠረት ስፍሮች እነዚህ ናቸው፡፡ ርዝመቱ በድሮው መለኪያ ስልሳ ክንድ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፡፡
\s5
\v 4 በቤቱም ፊት የነበረው በረንዳ ርዝመቱ ከቤቱ ወርድ ተመሳሳይ ሆኖ ሃያ ክንድ ነበር፡፡ ቁመቱም ሃያ ክንድ ነበረ፡፡ ሰለሞንም ውስጡን በንጹህ ወርቅ ለበጠው፡፡
\v 5 የዋናውን ቤት ጣሪያ በጥድ እንጨት ሠራው፡፡ በንጹህ ወርቅም ለበጠው፡፡ የዘንባባ ዛፎችንና የሰንሰለቶችን አምሳል ቀረጸበት፡፡
\s5
\v 6 ቤቱንም በከበሩ ድንጋዮች አስጌጠው፤ ወርቁም የምሥራቅ ፈርዋይም ወርቅ ነበር፡፡
\v 7 አውታሮቹን፥ ሰረገሎቹን፥ ግድግዳዎቹንና በሮቹንም በወርቅ ለበጣቸው፡፡ በግድግዳዎቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረፀ፡፡
\s5
\v 8 ቅድስተ ቅዱሳኑንም ሠራ፤ ርዝመቱም ከቤቱ ወርድ ጋር ተመሳሳይ ሆኖ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፡፡ ስድስት መቶ መክሊት በሚያህል በጥሩ ወርቅም ለበጠው፡፡
\v 9 የሚስማሮቹም ክብደት ሃምሳ ሰቅል ወርቅ ነበር፡፡ ከፍ ያሉ ገጽታዎቹን/ሰሌዳዎቹን በወርቅ ለበጣቸው፡፡
\s5
\v 10 ለቅድስተ ቅዱሳን ሁለት የኪሩቤል አምሳያዎችን ሠራ፤ ባለሙያዎችም በወርቅ ለበጡዋቸው፡፡
\v 11 ክንፎቹ በአጠቃላይ ከዳር እስከ ዳር ሃያ ክንድ ይረዝሙ ነበር፡፡ የአንዱ ኪሩብ ክንፍ ክፍሉ ግድግዳ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ይረዝም ነበር፤ ሌላኛው ክንፍ እንደዚሁ እስከ ሌላኛው ኪሩብ ክንፍ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ነበር፡፡
\v 12 የሌላኛው ኪሩብ ክንፍም ክፍሉ ግድግዳ ድረስ የሚደርስ አምስት ክንድ ይረዝም ነበር፤ ሌላኛው ክንፉም እንደዚሁ የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ የሚነካ አምስት ክንድ ነበር፡፡
\s5
\v 13 የእነዚህም ኪሩቤሎች ክንፎች በአጠቃላይ ሃያ ክንድ ያህል ተዘርግተው ነበር፡፡ ኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ዋናው ቤት እየተመለከቱ በእግሮቻቸው ቆመው ነበር፡፡
\v 14 ከሰማያዊም፥ ከሐምራዊም፥ ከቀዩም፥ ሐር እና ከጥሩ በፍታ መጋረጃውን ሠራ፤ የኪሩቤሎችንም ቅርፅ ሠራባቸው፡፡
\s5
\v 15 ሰለሞንም ለቤቱ ፊት ለፊት እያንዳንዳቸው ሠላሳ አምስት ክንድ ከፍታ ያላቸውን ሁለት ምሰሶዎች ሠራ፡፡ በእያንዳንዳቸውም ጫፍ ላይ የነበሩት ርዕሰ አእማድ አምስት ክንድ ከፍታ ያላቸው ነበሩ፡፡
\v 16 ለምሰሶዎቹም ሰንሰለቶችን አድርጎ በጫፋቸው ላይ አኖራቸው፡፡ መቶም ሮማኖች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አገናኛቸው፡፡
\v 17 ምሰሶዎቹንም በቤት መቅደሱ ፊት ለፊት አንደኛውን በቀኝ ሌላኛውንም በግራ አቆማቸው፤ በስተቀኝ የነበረውን ምሰሶ የሚያቆም/ያኪን፥ የበስተግራውንም ምሰሶ የሚያበረታ/ቦኤዝ ብሎ ሰየመው፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 በተጨማሪም የናሱን መሠዊያ ሠራ፤ ርዝመቱ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ቁመቱም አሥር ክንድ ነበር፡፡
\v 2 ክፈፉ ከጫፍ እስከ ጫፉ አሥር ክንድ የሆነ ከቀለጠ ብረት ትልቅ ክብ ውሃ መያዣ ኩሬም ሠራ፡፡ ቁመቱም አምስት ክንድ ነበር፤ ዙሪያውም ሰላሳ ክንድ ነበር፡፡
\v 3 ውሃ መያዣው ቀልጦ ሲሰራ ከአርሱ ጋር አብረው የተሠሩ ከውሃ መያዣው ዙሪያ ከክፈፉ በታች በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት አሥር ኮርማዎች ነበሩበት፡፡
\s5
\v 4 ውሃ መያዣው ሦስቱ ወደ ሰሜን በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ምዕራብ በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ በሚመለከቱ በአሥራ ሁለት በሬዎች ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ውሃ መያዣው በላያቸው ላይ ሆኖ የጀርባ የሠውነት ክፍላቸው በስተ ውስጥ ነበር፡፡
\v 5 ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበር፡፡ የአፉ ክፈፍም እንደ ጽዋ ከንፈር እንደ ፈነዳ የሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፡፡ ሦስት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ውሃ ይይዝ ነበር፡፡
\v 6 ደግሞም የተለያዩ ነገሮችን ማጠቢያ አሥር ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፤ አምስቱን በስተግራ አምስቱንም በስተቀኝ አኖራቸው፤ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ለማቅረብ ጥቅም የሚሰጡ ነገሮች በውስጣቸው ይታጠቡባቸው ነበር፡፡ የውሃ መያዣው ኩሬ ግን ለካህናቱ መታጠቢያ ነበር፡፡
\s5
\v 7 ለንድፋቸው በተሰጠው መመሪያ መሠረት አሥሩን የወርቅ መቅረዞች ሠራ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተግራ አምስቱን በስተቀኝ አኖራቸው፡፡
\v 8 አሥሩንም ገበታዎች ሠርቶ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተግራ አምስቱን በስተቀኝ አኖራቸው፡፡ አንድ መቶ የወርቅ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡
\s5
\v 9 በተጨማሪም የካህናቱን አደባባይ እና ታላቁንም አደባባይ የአደባባዮቹንም በሮች ሠራ፤ በሮቻቸውንም በናስ ለበጠ፡፡
\v 10 የውሃ መያዣውንም ኩሬ በቤቱ በስተቀኝ በስተምስራቅ ፊቱን ወደ ደቡብ አዙሮ አኖረው፡፡
\s5
\v 11 ኪራምም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹንና መሠዊያውን መርጪያ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡ ኪራምም እንደዚህ ለንጉሥ ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ -
\v 12 ሁለቱን አዕማድ፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ጨረሰ፡፡
\v 13 በአዕማዱ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ለሚሸፍኑት ሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ተርታ ሮማኖች አድርጎ ለሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች አራት መቶ ሮማኖች ሠራ፡፡
\s5
\v 14 ማቆሚያዎቹንና በማቆሚያዎቹ ላይ የሚቀመጡትን የመታጠቢያ ሰሃኖችንም ሠራ፤
\v 15 አንድ የውሃ መያዣ ኩሬ እና ከስሩ የሚሆኑትን አስራ ሁለት ኮርማዎች፥
\v 16 እንዲሁም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ሜንጦዎቹን እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ቁሳቁሶችን ሁሉ ሠራ፤ ኪራም ለንጉሥ ሰለሞን ለእግዚአብሔር ቤት ከአንፀባራቂ ናስ ሠራቸው፡፡
\s5
\v 17 ንጉሡም በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና ዛሬታን መካከል በሸክላው መሬት ውስጥ ብረታ ብረቱ እንዲቀልጥ አስደረገ፡፡
\v 18 ሰለሞንም እነዚህን እቃዎች ሁሉ በብዛት እንዲሰሩ አስደረገ፤ በእርግጥም የናሱ ክብደት ሊታወቅ አይችልም ነበር፡፡
\s5
\v 19 ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የቤት ዕቃዎች፥ የወርቁን መሠዊያ፥ የመገኘቱ ሕብስት የሚቀመጥባቸውን ገበታዎች፥
\v 20 በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ያበሩ ዘንድ የታቀዱትን መቅረዞችን ከቀንዲሎቹ ጋር ሠራ፡፡እነዚህ ከንጹሕ ወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡
\v 21 አበባዎቹም፥ ቀንዲሎቹና መኮስተሪያዎቹም የጥሩ ወርቅ ነበሩ፡፡
\s5
\v 22 ጉጠቶቹም፥ ጎድጓዳ ሳህኖቹም፥ ማንኪያዎቹም ፥ እጣን ማጨሻዎቹም ሁሉ ከንጹህ ወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡ ወደ ቤቱ ውስጥ መግቢያዎቹን በተመለከተ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያስገቡት የውስጥ በሮች እና የቤቱ ማለትም የቤተ መቅደሱ በሮች ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡
\s5
\c 5
\p
\v 1 ሰለሞንም እንደዚህ ለእግዚአብሔር ቤት የሠራው ሥራ ሁሉ ተጠናቀቀ፡፡ ሰለሞንም አባቱ ዳዊት የቀደሳቸውን እቃዎች ብሩን፥ ወርቁንና የቤት እቃዎችን ሁሉ ጨምሮ አምጥቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩት ግምጃ ቤቶች ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡
\s5
\v 2 ከዚያም ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ማለትም ከጽዮን እንዲያመጡ የእስራኤልን ሽማግሌዎች ፥ የነገድ አለቆችን ሁሉ እና የእስራኤልን ሕዝብ ቤተሰብ መሪዎች ሰበሰበ፡፡
\v 3 የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ በሰባተኛው ወር በበዓሉ ወቅት በንጉሡ ፊት ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 4 የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ፤ ሌዋውያንም ታቦቱን አነሱ፡፡
\v 5 ታቦቱንም፥ የመገናኛውንም ድንኳን፥ በድንኳኑም ውስጥ የነበሩትን ቅዱሳት ዕቃዎች በሙሉ አመጡ፡፡ ከሌዊ ነገድ የነበሩት ካህናት እነዚህን ነገሮች ሁሉ አመጡ፡፡
\v 6 ንጉሥ ሰለሞንና የእስራኤል ማህበር ሁሉ ሊቆጠሩ የማይችሉትን በጎችና በሬዎች እየሰዉ በታቦቱ ፊት ተሰበሰቡ፡፡
\s5
\v 7 ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ከኪሩቤል ክንፍ በታች ወደ ቦታው አመጡት፡፡
\v 8 ኪሩቤልም በታቦቱ ስፍራ ላይ ክንፎቻቸውን ዘርግተው ነበር፤ ኪሩቤልም ታቦቱንና መሸከሚያዎቹን ምሶሶዎችም ይሸፍኑ ነበር፡፡
\s5
\v 9 መሸከሚያዎቹ ምሶሶዎችም እጅግ ረጅም ከመሆናቸው የተነሳ ጫፎቻቸው ከውስጠኛው ክፍል ፊት ለፊት ከቅዱሱ ሥፍራ ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ክውጪ መታየት አይችሉም ነበር፡፡ እስከዚህች ቀንም ድረስ በዚያ ይገኛሉ፡፡
\v 10 በታቦቱም ውስጥ የእስራኤል ሰዎች ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን ባደረገ ጊዜ ሙሴ በኮሬብ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በስተቀር ምንም ነገር አልነበረባቸውም፡፡
\s5
\v 11 ካህናቱም ከቤተ መቅደሱ ቅዱስ ስፍራ ወጡ፡፡ በዚያ የነበሩትም ካህናት በተመደቡበት ክፍል ላይ ሳያተኩሩ ሁሉም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀድሰው ነበር፡፡
\v 12 መዘምራን የነበሩትም ሌዋውያንም አሳፍን፥ ኤማንን፥ ኤዶታምን ልጆቻቸውንና ወንድሞቻቸውን ጨምሮ ሁሉም ጥሩ በፍታ ለብሰው ጸናጽል፥ በገና እና መሰንቆ/ክራር እየመቱ በመሠዊያው አጠገብ በስተምሥራቅ ቆመው ነበር፡፡ ከእነርሱም ጋር መቶ ሃያ መለከት የሚነፉ ካህናት ነበሩ፡፡
\s5
\v 13 መለከቱን የሚነፉትና መዘምራኑም ከመቅደሱ ሲወጡ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያወደሱ በአንድ ቃል ድምጻቸውን ያሰሙ ነበር፡፡ ከመለከቶቹና ከጸናጽሎቹ ከሌሎቹም መሳሪያዎች ጋር ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፡፡" ቸር ነውና የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም የሚጸና ነውና" ብለው ዘመሩ፡፡ በዚያን ጊዜ ቤቱ የእግዚአብሔር ቤት በደመና ተሞላ፡፡
\v 14 የእግዚአብሔር ክብር ቤቱን ሞልቶት ስለነበር ከደመናው የተነሳ ካህናቱ ለማገልገል መቆም አልቻሉም ነበር፡፡
\s5
\c 6
\p
\v 1 ሰለሞንም፦"እግዚአብሔር በድቅድቅ ጨለማ እንደሚኖር ተናግሯል፤
\v 2 እኔ ግን ለዘላለም እንድትኖርበት የላቀ መኖሪያ ቤት ሠራሁልህ" አለ፡፡
\v 3 ከዚያም የእስራኤል ጉባኤ ቆመው በነበሩበት ንጉሡ ፊቱን ዘወር አድርጎ የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ ባረከ፡፡
\s5
\v 4 እርሱም ፦ "ለአባቴ ለዳዊት የተናገረ እና በገዛ እጆቹ የፈጸመ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፤
\v 5 "ሕዝቤን እስራኤልን ከግብጽ ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ ስሜ በዚያ የሚሆንበት ቤት በዚያ ይሠራልኝ ብዬ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ማንኛውንም ከተማ አልመረጥኩም፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ አለቃ ይሆን ዘንድ አንድም ሰው አልመረጥኩም፤
\v 6 ነገር ግን ስሜ በዚያ እንዲሆንባት ኢየሩሳሌምን መርጫለሁ፤ በሕዝቤም በእስራኤል ላይ እንዲሆን ዳዊትን መርጫለሁ" ብሎአል፡፡
\s5
\v 7 አሁንም ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤት መስራት በአባቴ በዳዊት ልብ ነበር፡፡
\v 8 ነገር ግን እግዚአብሔር ለአባቴ ለዳዊት፦ "ለስሜ ቤት ትሠራ ዘንድ በልብህ ነበረ፤ ያ በልብህ የነበረ መሆኑ መልካም አደረግህ፡፡
\v 9 ነገር ግን ቤቱን አንተ ልትገነባው አይገባም፤ ይልቁንም ከወገብህ የሚወጣው ልጅህ እርሱ ለስሜ ቤትን ይሠራልኛል" አለው፡፡
\s5
\v 10 እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠ በአባቴ በዳዊት ፈንታ ስለተነሳሁ በእስራኤልም ዙፋን ላይ ስለተቀመጥሁ እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ፈጽሞአል፡፡ ለእስራኤል አምላክም ለእግዚአብሔር ስም ቤት ሠራሁ፡፡
\v 11 ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ያደረገው የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ያለበትን ታቦቱን በዚያ ውስጥ አኖርሁ፡፡
\s5
\v 12 ሰለሞን የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ባሉበት በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት እጆቹን ዘርግቶ ቆመ፡፡
\v 13 ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱ አምስት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መድረክ ሰርቶ ነበር፡፡ በአደባባዩም መሃል ላይ አድርጎት ነበር፡፡ በእርሱም ላይ በመቆም በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት ተንበርክኮ እጆቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ፡፡
\s5
\v 14 እንዲህም አለ፦ "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ በፍጹም ልባቸው በፊትህ ከሚሄዱ ባሪያዎችህ ጋር ኪዳንንና የቃል ኪዳን ታማኝነትን የምትጠብቅ በሰማይም ሆነ በምድር እንዳንተ ያለ አምላክ የለም፤ ለባሪያህ
\v 15 ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸውን ተስፋ የጠበቅህ አንተ፥ አዎ በአፍህ የተናገርኸውን ዛሬም እንደሆነው በእጅህ ፈጽመኸዋል፡፡
\s5
\v 16 አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት፦ "'አንተ በፊቴ እንደተመላለስህ ልጆችህ በሕጌ ይሄዱ ዘንድ ቢጠነቀቁ በእስራኤል ዙፋን የሚቀመጥ ሰው በፊቴ አታጣም' በማለት የሰጠኸውን ተስፋ ፈጽምለት፡፡
\v 17 እንግዲህ የእስራኤል አምላክ ሆይ ለባሪያህ ለዳዊት የሰጠኸው የተስፋ ቃል ይፈጸም፡፡
\s5
\v 18 በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ መላው አጽናፈ ዓለም እና ሰማየ ሰማያት ራሱ ሊይዝህ አይችልም - ይልቁንም እኔ የሠራሁት ቤት ምንኛ ያነሰ ይችላል!
\v 19 ነገር ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ የባሪያህን ይህንን ጸሎትና ልመናውን እባክህን ተቀበል፤ ባሪያህ በፊትህ የሚጸልየውን ጩኸትና ጸሎት ስማ፡፡
\v 20 ባሪያህ ወደዚህ ስፍራ የሚጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ስምህን እንደምታደርበት ወደተናገርከው ወደዚህ ስፍራ ዓይኖችህ ወደዚህ ቤተ መቅደስ በቀንና በሌሊት የተገለጡ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 21 ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ በሚጸልዩበት ጊዜ ልመናዎቻቸውን ስማ፤ ከማደሪያህ ስፍራ ከሰማያት ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል፡፡
\s5
\v 22 አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢበድልና እንዲምል ቢጠየቅ እርሱም መጥቶ በዚህ ቤት ውስጥ በመሠዊያህ ፊት ቢምል
\v 23 ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ አድርግም፤ በደሉን በራሱ ላይ በማድረግ በደለኛውን መልሰህ በመክፈል በባሪያዎችህ መካከል ፍረድ፡፡ ለጽድቁ ብድራትን ለመስጠት ጻድቁ ንጹህ መሆኑንም አስታውቅለት፡፡
\s5
\v 24 ሕዝብህ እስራኤል አንተን ከመበደላቸው የተነሳ በጠላት ድል ሲነሱ ወደ አንተ ቢመለሱ፥ በዚህም ቤተ መቅደስ ውስጥ በፊትህ ስምህን ቢጠሩ፥ ቢጸልዩና ምህረትን ቢለምኑ
\v 25 እባክህን ከሰማያት ስማና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፤ ለእነርሱና ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃቸው ምድር መልሳቸው፡፡
\s5
\v 26 አንተን ከመበደላቸው የተነሳ ሰማያት ቢዘጉና ምንም ዝናብ በማይኖርበት ጊዜ ወደዚህ ስፍራ ቢጸልዩ፥ ስምህን ቢጠሩና ስታስጨንቃቸው ከኃጢአታቸው ቢመለሱ
\v 27 ከሰማይ ስማ፤ ሊመላለሱበት ወደሚገባቸው መልካሙ መንገድ ስትመራቸው የባሪያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኃጢአት ይቅር በል፡፡ ለሕዝብህ ርስት አድርገህ በሰጠሃት በምድርህ ላይ ዝናብን ላክ፡፡
\s5
\v 28 በምድሪቱ ላይ ርሃብ ቢኖር ወይም ቸነፈር ወይም ዋግ ወይም አረማሞ ወይም አንበጣ ወይም ኩብኩባ ቢኖር ወይም ጠላቶች በምድራቸው ውስጥ የከተማ በሮችን ቢያጠቁ ወይም ማናቸውም መቅሰፍት ወይም ደዌ ቢኖር
\v 29 አንድም ሰው ወይም ሕዝብህ እስራኤል ሁሉ እያንዳንዱ መቅሰፍቱንና ሐዘኑን በልቡ አውቆ ወደዚህ ቤተ መቅደስ እጆቹን ዘርግቶ ጸሎትና ልመና ቢያቀርብ
\v 30 በሰማይ በምትኖርበት ሆነህ ስማ፤ ይቅርም በል፤ የሰውን ሁሉ ልብ የምታውቅ አንተ ብቻ ስለሆንክ ልቡን ታውቃለህ፤ ለእያንዳንዱ እንደ መንገዱ ሁሉ ብድራትን ስጠው፡፡
\v 31 ለአባቶቻችን በሰጠሃቸው ምድር ላይ በሚኖሩበት ጊዜ ሁሉ አንተን እንዲፈሩህ በመንገድህም ይሄዱ ዘንድ ይህንን አድርግ፡፡
\s5
\v 32 ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ ባእድ ሰው ደግሞ ከታላቁ ስምህ ፥ ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋችው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ሲመጣ፥ ወደዚህ ቤተ መቅደስ መጥተው በሚጸልዩበት ጊዜ
\v 33 በሰማይ በምትኖርበት ስፍራ ሆነህ ስማ፤ በምድር ላይ ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ስምህን እንዲያውቁ፥ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል እንዲፈሩህ እና ይህ የሠራሁት ቤት በስምህ የሚጠራ መሆኑን እንዲያውቁ ባእዱ ሰው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ፡፡
\s5
\v 34 ሕዝብህ አንተ በምትልካቸው በምንም መንገድ ከጠላቶቻቸው ጋር ለመዋጋት ቢወጡ ፥ አንተ ወደመረጥካት ወደዚች ከተማና ለስምህ ወደሠራሁት ወደዚህ ቤት ቢጸልዩ
\v 35 ከሰማያት ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማና በጉዳያቸው አግዛቸው፡፡
\s5
\v 36 ኃጢአት የማይሰራ ማንም የለምና አንተን በበደሉህ ጊዜ ተቆጥተሃቸውም ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው ጠላት ወደ ቅርብም ሆነ ሩቅ አገር ቢያግዛቸውና እንደ ምርኮኛ ወደ ምድራቸው ቢወስዳቸው
\v 37 በግዞት አገር ውስጥ መሆናቸውን ቢገነዘቡ፥ ንስሃ ቢገቡና በተማረኩበት ምድር ሞገስን ካንተ ቢፈልጉ፥ 'ጠማማን ነገር አድርገናል፤ በድለናል፤ እኩይ ምግባር ፈጽመናል፤' ቢሉ
\v 38 ምርኮኛ ተደርገው በተወሰዱባት በተማረኩባት ምድር በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ወዳንተ ቢመለሱና ለአባቶቻቸው ወደሰጠሃቸው ምድር፥ ወደ መረጥካት ከተማና ለስምህ ወደሠራሁት ቤት ቢጸልዩ
\v 39 በሰማያት በምትኖርበት ስፍራ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማና በጉዳያቸው አግዛቸው፡፡ የበደሉህን የሕዝብህን ኃጢአት ይቅር በል፡፡
\s5
\v 40 አሁንም አምላኬ ሆይ በዚህ ስፍራ ወደሚደረገው ጸሎት ዓይኖችህ የተገለጡና ጆሮዎችህ የሚያተኩሩ እንዲሆኑ እለምንሃለሁ፡፡
\v 41 አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ አንተና የኃይልህ ታቦት ወደ ማረፊያህ ስፍራ ተነስ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ካህናትህ ደህንነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በመልካምነትህ ደስ ይበላቸው፡፡
\v 42 እግዚአብሔር አምላክ ሆይ የቀባኸውን ሰው ፊት ካንተ አትመልሰው፡፡ ለባሪያህም ለዳዊት ያደረግህለትን የቃል ኪዳን ታማኝነት አስብ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ሰለሞን ጸሎቱን በፈጸመ ጊዜ እሳት ከሰማይ ወርዶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና መሥዋዕቶችን በላ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ቤቱን ሞላ፡፡
\v 2 የእርሱ ክብር ቤቱን ሞልቶት ስለነበር ካህናቱ ወደ እግዚአብሔር ቤት መግባት አልቻሉም፡፡
\v 3 የእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ እሳቱ ሲወርድና የእግዚአብሔር ክብር በቤቱ ላይ እንደነበር ያዩ ነበር፡፡ በድንጋዩ ወለል ንጣፍ ላይ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱ፤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና አቀረቡ፡፡ "መልካም ነውና የቃል ኪዳን ታማኝነቱም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና" አሉ፡፡
\s5
\v 4 ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ፡፡
\v 5 ንጉሥ ሰለሞንም ሃያ ሁለት ሺህ በሬዎችና መቶ ሃያ ሺህ በጎች በጎችና ፍየሎች ሰዋ፡፡ እንደዚህ ንጉሡና ሕዝቡ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት ቀደሱ፡፡
\v 6 ካህናቱም እያንዳንዳቸው በሚያገለግሉበት ቦታ ቆመው ሌዋውያኑም "የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራልና" በሚለው መዝሙር እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ ንጉሥ ዳዊት ያዘጋጀውን የእግዚአብሔር የዜማ መሳሪያዎች ይዘው ቆመው ነበር፡፡ ካህናቱ ሁሉ በፊታቸው መለከቶቻቸውን ሲነፉ እስራኤላውያን ሁሉ ቆሙ፡፡
\s5
\v 7 ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት ፊት ለፊት የነበረውን የአደባባዩን መካከል ቀደሰ፡፡ በዚያም የሠራው የናስ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህሉን ቁርባንና ስቡን መያዝ ስላልቻለ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የሕብረት መሥዋዕቱን ስብ በዚያ አቀረበ፡፡
\s5
\v 8 በዚያን ጊዜ ሰለሞን ከእርሱም ጋር እስራኤል ሁሉ ከሐማት መግቢያ እስከ ግብጽ ወንዝ ድረስ የመጡ እጅግ ታላቅ ጉባኤ ለሰባት ቀናት ለሰባት ቀናት በዓል አደረጉ፡፡
\v 9 መሠዊያውን ለሰባት ቀናት ቀድሰው እና በዓሉን ለሰባት ቀናት ጠብቀው ስለነበር በስምንተኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አደረጉ፡፡
\v 10 ሰለሞንም በሰባተኛው ወር በሃያ ሦስተኛው ቀን እግዚአብሔር ለዳዊት፥ ለሰለሞንና ለሕዝቡ ለእስራኤል ካሳየው በጎነት የተነሳ በደስታና በሐሴት ልብ ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ ሕዝቡን አሰናበተ፡፡
\s5
\v 11 በመሆኑም ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የገዛ ራሱን ቤት ጨረሰ፡፡ ለእግዚአብሔር ቤትና ለገዛ ራሱ ቤት ሰለሞን በልቡ ያሰበውን ማናቸውንም ነገር በስኬት አከናወነ፡፡
\v 12 እግዚአብሔርም በሌሊት ለሰለሞን ተገልጦ፦" ጸሎትህን ሰምቻለሁ፤ ይህንንም ስፍራ ለራሴ የመስዋዕት ቤት እንዲሆን መርጫለሁ" አለው፡፡
\s5
\v 13 ዝናብ እንዳይኖር ሰማያትን ብዘጋ ወይም ምድሪቱን እንዲበላ አንበጣን ባዝዘው ወይም በሕዝቡ መካከል ቸነፈርን ብሰድድ
\v 14 በስሜ የተጠሩት ህዝቤ ራሳቸውን ቢያዋርዱ፥ ቢጸልዩ፥ ፊቴን ቢፈልጉና ከክፉ መንገዳቸው ቢመለሱ ከሰማይ ሆኜ እሰማለሁ፤ ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፤ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ፡፡
\v 15 አሁንም በዚህ ስፍራ ለሚደረግ ጸሎት ዓይኖቼ ክፍት ይሆናሉ፤ ጆሮዎቼም ያደምጣሉ፡፡
\s5
\v 16 አሁንም ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ይህንን ቤት መርጫለሁ፤ ቀድሻለሁም፤ ዓይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ፡፡
\v 17 አንተ ደግሞ ያዘዝሁህን ሁሉ በመፈጸም እና ሥርዓቶቼንና ሕግጋቴን በመጠበቅ አባትህ ዳዊት እንደሄደ በፊቴ ብትሄድ፥
\v 18 ከአባትህ ከዳዊት ጋር በገባሁት በቃል ኪዳን " ከዘርህ በእስራኤል ላይ አለቃ የሚሆን አይታጣም" እንዳልኩት የመንግሥትህን ዙፋን አጸናለሁ፡፡
\s5
\v 19 ነገር ግን እኔን ከመከተል ብትመለሱና በፊታችሁ ያኖርኳቸውን ሥርዓቶቼንና ትዕዛዛቶቼን ብትተዉ፥ ሄዳችሁ ሌሎችንም አማልክት ብታመልኩ ብትሰግዱላቸውም፥
\v 20 ያን ጊዜ ከሰጠኋችሁ ምድሬ እነቅላቸዋለሁ፤ ለስሜ የቀደስኩትን ይህንን ቤት ከፊቴ እጥለዋለሁ፡፡ በሕዝቦችም ሁሉ መካከል ምሳሌና መቀለጃ አደርገዋለሁ፡፡
\s5
\v 21 ምንም እንኳን ይህ ቤተ መቅደስ እጅግ የላቀ ቢሆንም በአጠገቡ የሚያልፉ ሰዎች ይደነግጣሉ፤ በጥላቻ ይነጋገራሉ፡፡ " እግዚአብሔር በዚህ ምድርና በዚህ ቤት ላይ ይህንን እንዲህ ያደረገው ለምንድን ነው?" ብለው ይጠይቃሉ፡፡
\v 22 ሌሎችም፦ " ከግብጽ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክትን የሙጥኝ ከማለታቸው የተነሳ ፥ ስለሰገዱላቸው ስላመለኳቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው እግዚአብሔር ይህንን ሁሉ አደጋ ያመጣባቸው" ብለው ይመልሳሉ፡፡
\s5
\c 8
\p
\v 1 ሰለሞን የእግዚአብሔርን ቤትና የራሱን ቤት የሠራበትን ሃያው ዓመት መጠናቀቂያ ላይ
\v 2 ሰለሞን ኪራም የሰጠውን ከተሞች እንደገና ሠርቶ የእስራኤል ሰዎች እንዲኖሩባቸው አደረገ፡፡
\s5
\v 3 ሰለሞን ሐማትሱባን አጥቅቶ አሸነፋት፡፡
\v 4 በምድረ በዳም የነበረችውን ታድሞርን እና በሐማትም የሠራቸውን የዕቃ ቤቱን ከተሞች ሁሉ ሠራ፡፡
\s5
\v 5 በቅጥሮች፥ በበሮችና በመዝጊያዎች የተመሸጉትን የላይኛውን ቤትሆሮንን እና የታችኛዋን ቤትሆሮንን ከተሞች ሠራ፡፡
\v 6 የባዕላትንም ከተማ፥ ሰለሞንም የነበሩትን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ፥ የሰረገላዎቹንም ከተሞች፥ የፈረሰኞቹንም ከተሞች እንዲሁም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስ እና በግዛቱ ሥር በነበሩት ስፍራዎች ሊሠራ የተደሰተባቸውን ነገሮች ሁሉ ሠራ፡፡
\s5
\v 7 ከኬጢያውያን፥ ከአሞራውያን፥ ከፌርዜያውያን፥ ከኤዊያውያን እና ከኢያቡሳውያን የቀሩትን የእስራኤል ወገን ያልሆኑትን ሕዝብ ሁሉ፥
\v 8 የእስራኤል ሕዝብ ያላጠፉአቸውን በምድሪቱ ላይ ከእነርሱ በኋላ የቀሩትን ዝርያዎቻቸውን ሰለሞን እስከ ዛሬ ድረስ የግዳጅ የጉልበት ሠራተኞች አደረጋቸው፡፡
\s5
\v 9 ነገር ግን ሰለሞን የእስራኤል ሰዎችን አንድም የግዳጅ የጉልበት ሠራተኞች አላደረጋቸውም፤ ይልቁንም ወታደሮቹ፥ አዛዦቹ፥ ሹማምንቶቹ እና የሠረገሎቹና የፈረሰኞቹ አዛዦች አደረጋቸው፡፡
\v 10 እነዚህ ሁለት መቶ ሃምሳው፥ ሥራውን የሚሰሩትን ሰዎች የሚቆጣጠሩ የንጉሥ ሰለሞን ዋና ተቆጣጣሪዎችን የሚያስተዳድሩ ዋና ሹማምንቶችም ነበሩ፡፡
\s5
\v 11 ሰለሞንም፦ "የእግዚአብሔር ታቦት የደረሰበት ቦታ ሁሉ ቅዱስ ስለሚሆን ሚስቴ በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት ቤት መኖር አይገባትም" በማለቱ ምክንያት የፈርኦንን ልጅ ከዳዊት ከተማ ውጪ ለእርሷ ወደ ሰራላት ቤት አመጣት፡፡
\s5
\v 12 ከዚያም ሰለሞን በመተላለፊያው ፊት ለፊት በሠራው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፡፡
\v 13 ዕለታዊው መርሀ ግብር በሚጠይቀው መሰረት መሥዋዕቶች አቀረበ፤ በሙሴ ትዕዛዝ የሚገኙትን መመሪያዎች በመከተል በሰንበታቱ ቀናት፥ በየመባቻዎቹ እና በተደነገጉት በዓላት በየዓመቱ ሦስት ጊዜ በየቂጣው በዓል፥ በየሰባቱ ሱባኤ በዓል እና በየዳሱም በዓል አቀረባቸው፡፡
\s5
\v 14 ሰለሞን የአባቱን የዳዊትን ትዕዛዝ በመከተል ካህናቱን በየክፍላቸው፥ ሌዋውያንንም ዕለታዊው መርሀ ግብር እንደሚጠብቅባቸው እግዚአብሔርን ለማወደስና በካህናቱ ፊት ለማገልገል በየሥራቸው መደባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ሰው ዳዊት ይህንንም አዝዞ ስለነበር ደጅ ጠባቂዎችን ደግሞ በእያንዳንዱ በር በየክፍላቸው መደባቸው፡፡
\v 15 እነዚህ ሰዎች ንጉሡ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ማናቸውንም ጉዳይ ወይም መጋዘኖቹን በተመለከተ ከሰጠው ትዕዛዛቱ አላፈነገጡም፡፡
\s5
\v 16 እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ቤት መሠረት ከተጣለበት ቀን አንስቶ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ የሰለሞን ሥራ ተከናወነ፡፡ በዚህ ሁኔታ የእግዚአብሔር ቤት ተጠናቅቆ ጥቅም ላይ ዋለ ፡፡
\s5
\v 17 ከዚህ በኋላ ሰለሞን በኤዶምያስ ምድር የባሕር ዳርቻ ወዳሉት ወደ ዔጽዮንጋብር እና ኤላት ሄደ፡፡
\v 18 ኪራምም የባህርን ነገር በሚገነዘቡ መርከበኞች የሚታዘዙ መርከቦችን ላከለት፡፡እነርሱም ከሰለሞን አገልጋዮች ጋር ወደ ኦፊር ሄዱ፡፡ ከዚያም አራት መቶ ሃምሳ መክሊት ወርቅ ለንጉሥ ሰለሞን አመጡ፡፡
\s5
\c 9
\p
\v 1 የሳባም ንግሥት የሰለሞንን ዝና በሰማች ጊዜ በከባባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች፡፡ ቅመማ ቅመሞች፥ ብዙ ወርቆች እና በርካታ የከበሩ ማዕድናት ከተጫኑ ግመሎች ጋር ከብዙ ጓዝ ጋር መጣች፡፡ ወደ ሰለሞን በመጣች ጊዜ በልብዋ የነበረውን ሁሉ አጫወተችው፡፡
\v 2 ሰለሞንም ጥያቄዎችዋን ሁሉ መለሰላት፤ ለሰለሞንም የከበደው ምንም ነገር አልነበረም፡፡ ያልመለሰውም ምንም ጥያቄ አልነበረም፡፡
\s5
\v 3 የሳባም ንግሥት የሰለሞንን ጥበብ፥ ሠርቶትም የነበረውን ቤተ መንግሥት፥
\v 4 በጠረጴዛው ላይ የነበረውን ምግብ፥ የአገልጋዮቹን አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥራ እና አለባበሳቸውን፥ አስተናጋጆቹንና አለባበሳቸውንም፥ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥም መስዋዕት የሚያቀርብበትን ሁኔታ ባየች ጊዜ አንዳች መንፈስ አልቀረላትም፡፡
\s5
\v 5 ንጉሡንም ፦ "ስለምትናገረው ነገርና ስለ ጥበብህ በገዛ አገሬ የሰማሁት ዘገባ እውነት ነው፤
\v 6 እዚህ እስክመጣ ድረስ ግን የሰማሁትን አላመንኩም ነበር፤ አሁን ዓይኖቼ አይተውታል፡፡ ስለ ጥበብህና ሃብትህ ግማሹ እንኳን አልተነገረኝም ነበር! ከሰማሁት ዝና ትበልጣለህ፡፡" አለችው፡፡
\s5
\v 7 "ጥበብህን ስለሚሰሙ ህዝብህ ምንኛ የተባረኩ፥ ዘወትር በፊትህ የሚቆሙ አገልጋዮችህም ምንኛ የተባረኩ ናቸው፡፡
\v 8 ለአምላክህ እግዚአብሔር ንጉሥ ትሆን ዘንድ ባንተ ደስ የተሰኘ እና በዙፋን ላይ ያስቀመጠህ አምላክህ እግዚአብሔር ብሩክ ይሁን፡፡ አምላክህ እስራኤልን ለዘላለም ያፀናቸው ዘንድ ስለወደደ ፍትህንና ጽድቅን እንድታደርግላቸው በላያቸው ላይ አነገሠህ " አለችው፡፡
\s5
\v 9 ለንጉሡም መቶ ሃያ መክሊት ወርቅ እና ከፍተኛ መጠን ያላቸው ቅመሞችንና የከበሩ ድንጋዮችን ሰጠችው፡፡ የሳባም ንግሥት ለንጉሡ ለሰለሞን ከሰጠችው ከእደነዚህ የሚበልጥ መጠን ያላቸው ቅመሞች እንደገና ተሰጥቶት አያውቅም፡፡
\s5
\v 10 ከኦፊር ወርቅ ያመጡት የኪራም አገልጋዮችና የሰለሞን አገልጋዮች የሰንደል እንጨትና የከበሩ ድንጋዮችን አመጡ፡፡
\v 11 ንጉሡም ከሰንደሉ እንጨት ለእግዚአብሔር ቤትና ለራሱ ቤት ደረጃዎችን እንዲሁም ለሙዚቀኞቹ በገናዎችንና መሰንቆዎችን/ክራሮችን አስደረገ፡፡ እንደዚህ ያለ እንጨት ከዚያ በፊት በይሁዳ ምድር ታይቶ አይታወቅም ነበር፡፡
\v 12 የሳባም ንግሥት ወደ ንጉሡ ካመጣችው የበለጠ ንጉሥ ሰለሞን የተመኘችውን ሁሉ፥ የለመነችውንም ሁሉ ሰጣት፡፡ እርስዋም ተመልሳ ከአገልጋዮችዋ ጋር ወደ ራሷ ምድር ሄደች፡፡
\s5
\v 13 በአንድ ዓመት ለሰለሞን የመጣለት ወርቅ ክብደት ስድስት መቶ ስልሳ ስድስት መክሊት ወርቅ ነበር፡፡
\v 14 ይህም ነጋድራሶችና ነጋዴዎች ካመጡት ወርቅ በተጨማሪ ነው፡፡ የዓረብም ነገሥታት ሁሉ እና የአገሪቱ ሹማምንት ለሰለሞን ወርቅና ብር ያመጡ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ንጉሡም ሰለሞን በጥፍጥፍ ወርቅ ሁለት መቶ ትልልቅ ጋሻዎችን ሠራ፡፡ በእያንዳንዳቸውም ውስጥ ስድስት መቶ ሰቅል ጥፍጥፍ ወርቅ ገብቶባቸው ነበር፡፡
\v 16 ከጥፍጥፍ ወርቅም ሦስት መቶ ጋሻዎችን ሠራ፡፡ በእያንዳንዱም ጋሻ ውስጥ ሦስት ምናን ወርቅ ገብቶበት ነበር፡፡ ንጉሡም በሊባኖስ ዱር ቤተ መንግሥት ውስጥ አስቀመጣቸው፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም ንጉሡ ከዝሆን ጥርስ ታላቅ ዙፋን አሠርቶ ከሁሉ በበለጠ ወርቅ አስለበጠው፡፡
\v 18 ወደ ዙፋኑ የሚያደርሱ ስድስት ደረጃዎች ነበሩት፤ የዙፋኑም የላይኛው ክፍል ከጀርባው ክብ ነበር፡፡ በመቀመጫው በእያንዳንዱ ጎን በኩል የክንድ መደገፊያዎች እና ከመደገፊያዎቹም አጠገብ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፡፡
\s5
\v 19 በስድስቱም ደረጃዎች በእያንዳንዱ ላይ በእያንዳንዱ ጎን በኩል አንድ አንበሳ አስራ ሁለት አንበሶች ቆመው ነበር፡፡ በሌላ በየትኛውም መንግሥት እንደ እርሱ ያለ ዙፋን አልነበረም፡፡
\v 20 ንጉሥ ሰለሞን የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ የወርቅ ነበሩ፤ በሊባኖስ ዱር ቤተ መንግሥት ውስጥ የነበሩትም የሚጠጣባቸው ዕቃዎች በሙሉ ከንፁህ ወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡ በሰለሞን ዘመን ብር ዋጋ እንዳለው የማይቆጠር ስለነበር አንዳቸውም ብር አልነበሩም፡፡
\v 21 ከኪራም መርከቦች ጋር በመሆን በባሕር ላይ የሚሄዱ ብዙ መርከቦች ነበሩት፡፡ በየሦስት ዓመቱም አንድ ጊዜ መርከቦቹ ወርቅ፥ ብር እና የዝሆን ጥርስ እንዲሁም ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ይዘው ይመጡ ነበር፡፡
\s5
\v 22 በመሆኑም ንጉሥ ሰለሞን ከዓለም ነገሥታት ሁሉ በባለጠግነትና በጥበብ በለጠ፡፡
\v 23 ምድር ሁሉ እግዚአብሔር በልቡ ያኖረውን ጥበቡን ይሰሙ ዘንድ የሰለሞንን መገኘት ይፈልጉ ነበር፡፡
\v 24 ከዓመት ዓመት የሚጎበኙትም ግብር፥ የብርና የወርቅ ዕቃዎች፥ አልባሳት፥ የጦር መሣሪያዎች እና ቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ፈረሶችና በቅሎዎችን ያመጡ ነበር፡፡
\s5
\v 25 ሰለሞንም በሰረገሎች ከተሞችና ከራሱ ጋር በኢየሩሳሌም በተመደበላቸው ሥፍራ ለሚያኖራቸው ለፈረሶችና ለሰረገላዎች አራት ሺህ ጋጣዎች አስራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፡፡
\v 26 ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጤም ምድርና እስከ ግብፅ ዳርቻ ድረስ ባሉ ነገሥታት ሁሉ ላይ ይገዛ ነበር፡፡
\s5
\v 27 ንጉሡም በምድር ላይ እንዳለ ድንጋይ ያህል የበዛ ብር በኢየሩሳሌም ነበረው፡፡ የዝግባውንም እንጨት በቆላ እንዳሉት የሾላ ዛፎች የተትረፈረፈ እንዲሆን አደረገው፡፡
\v 28 ለሰለሞንም ከግብፅና ከየአገሩ ሁሉ ፈረሶችን ያመጡለት ነበር፡፡
\s5
\v 29 ሰለሞንን የሚመለከቱ ሌሎች ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው በነቢዩ በናታን ታሪክ፥ በሴሎናዊውም በአሒያ ትንቢት፥ ስለ ናባጥም ልጅ ስለ ኢዮርብዓም ባየው በባለ ራዕዩ በአዶ የተፃፉ አይደለምን?
\v 30 ሰለሞንም በኢየሩሳሌም በእስራኤል ሁሉ ላይ አርባ ዓመት ነገሠ፡፡
\v 31 ከአባቶቹም ጋር አንቀላፋ፤ ሕዝቡም በአባቱ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፤ ልጁም ሮብዓም በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
\s5
\c 10
\p
\v 1 እስራኤልም ሁሉ ሊያነግሡት ወደ ሴኬም እየመጡ ስለነበር ሮብዓም ወደ ሴኬም ሄደ፡፡
\v 2 የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ይህንን ሰማ (ከንጉሡ ከሰለሞን ፊት ሸሽቶ በግብፅ ይኖር ነበር፤ ነገር ግን ኢዮርብዓም ከግብፅ ተመለሰ)
\s5
\v 3 ልከውም አስጠሩት፤ ኢዮርብዓም እና እስራኤልም ሁሉ መጡ፤ ሮብዓምንም ተናገሩት፤
\v 4 "አባትህ ቀንበራችንን ከባድ አድርጎት ነበር፤ ስለዚህ አሁን አንተ ጽኑውን የአባትህን ሥራ ቀሊል፥ በእኛ ላይ ያደረገውንም ከባድ ቀንበር የማያስቸግር አድርግልን፤ እኛም እንገዛልሃለን" አሉት፡፡
\v 5 ሮብዓምም ፦ " ከሦስት ቀናት በኋላ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ኑ" አላቸው፤ ሕዝቡም ሄዱ፡፡
\s5
\v 6 ንጉሥ ሮብዓም፦ "ለእነዚህ ሰዎች መልስ እንድሰጣቸው እንዴት ትመክሩኛላችሁ?" ብሎ አባቱ ሰለሞን በሕይወት እያለ በፊቱ ይቆሙ የነበሩትን ሽማግሌዎች አማከራቸው፡፡
\v 7 እነርሱም ፦ "ለዚህ ሕዝብ መልካም ብታደርግላቸውና ብታስደስታቸው፥ በመልካም ቃል ብታናግራቸው ሁልጊዜ አገልጋዮችህ ይሆኑልሃል፤" ብለው ተናገሩት፡፡
\s5
\v 8 ሮብዓም ግን ሽማግሌዎቹ የመከሩትን ምክር ችላ ብሎ ከእርሱ ጋር ያደጉትን በፊቱም የሚቆሙትን ወጣቶች አማከራቸው፡፡
\v 9 "'አባትህ በእኛ ላይ ያደረገውን ቀንበር አቅልልልን' ላሉኝ ሰዎች መልስ እንድሰጣቸው ምን ምክር ትሰጡኛላችሁ?" አላቸው፡፡
\s5
\v 10 ከሮብዓም ጋር ያደጉት ወጣቶች ተናገሩት፦ "'አባትህ ሰለሞን ቀንበራችንን አከበደብን፤ አንተ ግን ልታቀልልን ይገባል' ብለው ለነገሩህ ሰዎች፦ 'ትንሿ ጣቴ ክአባቴ ወገብ ትወፍራለች' ልትላቸው ይገባል፡፡
\v 11 "በመሆኑም አሁን ምንም እንኳን አባቴ ቀንበር አክብዶባችሁ የነበረ ቢሆንም እኔ ቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ ነገር ግን እኔ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ" አላቸው፡፡
\s5
\v 12 በመሆኑም ንጉሡ፦ "በሦስተኛው ቀን ወደ እኔ ተመልሳችሁ ኑ" ባላቸው መሠረት ኢዮርብዓምና ሕዝቡ ሁሉ በሦስተኛው ቀን ወደ ሮብዓም መጡ፡፡
\v 13 ንጉሡም በጽኑ ምላሽ መለሰላቸው፤ ንጉሡም ሮብዓም የሽማግሌዎችን ምክር ቸል አለ፡፡
\v 14 የወጣቶቹን ምክር ተከትሎ ተናገራቸው፤ " ቀንበራችሁን ይበልጥ አከብድባችኋለሁ፤ እጨምርባችኋለሁ፡፡ አባቴ በአለንጋ ገርፏችሁ ነበር፤ ነገር ግን እኔ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ" አላቸው፡፡
\s5
\v 15 በመሆኑም ንጉሡ ሕዝቡን አልሰማም፤ እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብአም የተናገረውን ቃሉን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔር የተደረገ ክስተት ነበር፡፡
\s5
\v 16 እስራኤል ሁሉ ንጉሡ እንዳልሰማቸው ሲያዩ ሕዝቡ ፦ "ከዳዊት ምን ድርሻ አለን? ከእሴይም ልጅ ምንም ርስት የለንም! እስራኤል ሆይ እያንዳንዳችሁ ወደየድንኳኖቻችሁ ተመለሱ፡፡ ዳዊት ሆይ የገዛ ራስህን ቤት ተመልከት" ብለው መለሱለት፡፡ በመሆኑም እስራኤል ሁሉ ወደየድንኳኖቻቸው ተመለሱ፡፡
\s5
\v 17 በይሁዳ ከተሞች በሚኖሩት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ግን ሮብዓም ነገሠባቸው፡፡
\v 18 ከዚያም ንጉሡ ሮብዓም አስገባሪውን አዶኒራምን ላከው፤ ነገር ግን የእስራኤል ሕዝብ በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ንጉሥ ሮብዓም ፈጥኖ በሰረገላው ወደ ኢየሩሳሌም ሸሸ፡፡
\v 19 በመሆኑም እስራኤል እስከ ዛሬ ድረስ በዳዊት ቤት ላይ አመጸ፡፡
\s5
\c 11
\p
\v 1 ሮብዓም ኢየሩሳሌም ሲደርስ ከእስራኤል ጋር ተዋግተው መንግሥቱን ወደ ሮብዓም ለመመለስ ወታደሮች የሆኑ መቶ ሰማንያ ሺህ የተመረጡ ሰዎች ከይሁዳና ከቢንያም ቤት ሰበሰበ፡፡
\s5
\v 2 ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ሸማያ እንዲህ ሲል መጣ፤
\v 3 "ለይሁዳ ንጉሥ ለሰለሞን ልጅ ለሮብዓም በይሁዳና በቢንያምም ላሉት ለእስራኤል ሁሉ ተናገር፦
\v 4 እግዚአብሔር ይህንን ይላል፦ "ወንድሞቻችሁን ማጥቃት ወይም መዋጋት አይገባችሁም፡፡ ይህ ነገር በእኔ እንዲሆን የተፈቀደ ስለሆነ እያንዳንዱ ሰው ወደ ቤቱ መመለስ ይገባዋል፡፡" በመሆኑም የእግዚአብሔርን ቃል ሰሙ፤ በኢዮርብዓምም ላይ ለማጥቃት ከመውጣት ተመለሱ፡፡
\s5
\v 5 ሮብዓም በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ በይሁዳም ለምሽግነት ከተሞችን ገነባ፡፡
\v 6 ቤቴልሔምን፥ ኤጣምን፥ ቴቁሔን፥
\v 7 ቤትጹርን፥ ሦኮን፥ ዓዶላምን፥
\v 8 ጌትን፥ መሪሳን፥ ዚፍን፥
\v 9 አዶራይምን፥ ለኪሶን፥ ዓዜቃን፥
\v 10 ጾርዓን፥ ኤሎንን፥ ኬብሮንን ሠራ፡፡ እነዚህ በይሁዳና በብንያም ያሉት የተመሸጉት ከተሞች ናቸው፡፡
\s5
\v 11 ምሽጎቹንም አጠናክሮ ምግቡንም፥ ዘይቱንም፥ እና ከወይን ጠጁም መጋዘኖች ጋር አለቆቹንም አኖረባቸው፡፡
\v 12 በከተሞቹ ሁሉ ጋሻዎችና ጦሮችም አኖረባቸው፤ ከተሞቹንም እጅግ ጠንካራ አደረጋቸው፡፡ ይሁዳና ብንያምም የእርሱ ወገን ነበሩ፡፡
\s5
\v 13 በመላው እስራኤል የነበሩት ካህናትና ሌዋውያን ከነበሩባቸው ድንበሮች ወደ እርሱ መጡ፡፡
\v 14 ለእግዚአብሔር የክህነት ግዴታቸውን ከዚያ በኋላ መወጣት እንዳይችሉ ኢዮርብዓምና ልጆቹ አስለቅቀዋቸው ነበርና ሌዋውያንም ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም ለመምጣት መሠማሪያቸውንና ቦታቸውን ትተው ነበር፡፡
\v 15 ኢዮርብዓም ለመስገጃዎቹና ለሠራቸው የጥጆችና የፍየሎች ጣኦታት ለራሱ ካህናትን ሾመ፡፡
\s5
\v 16 የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልባቸው የቆረጠ ሰዎች ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ተከትለዋቸው መጡ፤ ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ለመሰዋት ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
\v 17 በመሆኑም ለሦስት ዓመታት በዳዊትና በሰለሞን መንገድ ስለሄዱ በሦስቱ ዓመታት ውስጥ የይሁዳን መንግሥት አበረቱ፤ የሰለሞንንም ልጅ ሮብዓምን ጠንካራ አደረጉ፡፡
\s5
\v 18 ሮብዓም የዳዊትን ልጅ የኢያሪሙትን እና የእሴይን ልጅ የኤልያብን ሴት ልጅ የአቢካኢልን ሴት ልጅ መሐላትን ለራሱ ሚስት አድርጎ ወሰደ፤
\v 19 እርስዋም ወንዶች ልጆችን የዑስን፥ ሰማራያን፥ እና ዘሃምን ወለደችለት፡፡
\s5
\v 20 ከመሐላት በኋላ ሮብዓም የአቤሴሎምን ሴት ልጅ መዓካን ወሰደ፤ እርስዋም አብያን፥ ዓታይን፥ ዚዛን እና ሰሎሚትን ወለደችለት፡፡
\v 21 ሮብዓምም ከሌሎቹ ሚስቶቹና ቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ሴት ልጅ መዓካን ወደደ፤ (አስራ ስምንት ሚስቶችና ስልሳ ቁባቶች ወስዶ የሃያ ስምንት ወንዶች ልጆችና የስልሳ ሴቶች የልጅ ልጆች አባት ሆኖ ነበር፡፡)
\s5
\v 22 ሮብዓምም ንጉሥ ሊያደርገው ስላሰበ የመዓካን ልጅ አብያን በወንድሞቹ መካከል መሪ እንዲሆን አለቃ አድርጎ ሾመው፡፡
\v 23 ሮብዓም በጥበብ ያስተዳድር ነበር፤ ልጆቹንም ሁሉ ወደ ይሁዳና ቢንያም ምድር ሁሉ ወደ ተመሸጉት ከተሞች ሁሉ በተናቸው፡፡ የተትረፈረፈም ምግብ ሰጣቸው፤ ብዙ ሚስቶችንም ፈለገላቸው፡፡
\s5
\c 12
\p
\v 1 እንዲህም ሆነ፤ የሮብዓም መንግሥት በጸናች ጊዜና እርሱም በበረታበት በዚያን ጊዜ እርሱና እስራኤል ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕግ ተዉ፡፡
\s5
\v 2 ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ታማኞች ባለመሆናቸው ንጉሥ ሮብዓም በነገሠ በአምስተኛው ዓመት የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ሊያጠቃ መጣባት፡፡
\v 3 ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ ሰረገሎችና ከስልሳ ሺህ ፈረሰኞች ጋር መጠባት፡፡ ከእርሱም ጋር ሊቆጠሩ የማይችሉ ወታደሮች ሊቢያውያን፥ ሱካውያን እና ኢትዮጵያውያን መጡ፡፡
\v 4 የይሁዳ ይዞታ የነበሩትን የተመሸጉ ከተሞች ወሰደና ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡
\s5
\v 5 ይሄኔ ነቢዩ ሸማያ ወደ ሮብዓምና ከሺሻቅ የተነሳ ወደ ኢየሩሳሌም በአንድነት ወደተሰበሰቡት መሪዎች መጣ፡፡ ሸማያ እንዲህ አላቸው፦ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔን ትታችሁኛል፤ ስለዚህ እኔ ደግሞ ለሺሻቅ እጅ አሳልፌ ሰጠኋችሁ፡፡"
\v 6 በዚያን ጊዜ የእስራኤል መሳፍንትና ንጉሡ ራሳቸውን አዋረዱ፤ "እግዚአብሔር ጻድቅ ነው" አሉ፡፡
\s5
\v 7 እግዚአብሔርም ራሳቸውን እንዳዋረዱ ባየ ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ሽማያ መጣ፦ "ሰውነታቸውን አዋርደዋል፡፡ አላጠፋቸውም፤ በተወሰነ ደረጃ አድናቸዋለሁ፡፡ ቁጣዬም በሺሻቅ እጅ በኢየሩሳሌም ላይ አይፈስስም፡፡
\v 8 ነገር ግን እኔን ማገልገል እና የሌሎች አገራትን ገዢዎች ማገልገል ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲገባቸው አገልጋዮቹ ይሆናሉ" አለ፡፡
\s5
\v 9 ስለሆነም የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን ሊያጠቃ መጥቶ የእግዚአብሔርን ቤት የከበሩ መዝገቦችና የንጉሡን ቤት የከበሩ መዝገቦች ወሰደ፡፡ ሁሉንም ነገር ወሰደ፤ ሰለሞን የሠራቸውን የወርቁን ጋሻዎችም ጭምር ወሰደ፡፡
\v 10 ንጉሥ ሮብዓም በእነርሱ ምትክ የናስ ጋሻዎች ሠርቶ የንጉሡን ቤት በሮች በሚጠብቁት ዘበኞች አለቃዎች እጅ አስቀመጣቸው፡፡
\s5
\v 11 ከዚያ በኋላ ንጉሡ ወደ እግዚአብሔር ቤት በገባ ቁጥር ዘበኞቹ ይሸከሙአቸው ነበር፤ ከዚያም ወደ ዘበኞቹ ቤት ይመልሷቸው ነበር፡፡
\v 12 ሮብዓም ሰውነቱን ባዋረደ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንዳያጠፋው የእግዚአብሔር ቁጣ ከእርሱ ተመለሰ፤ ደግሞም በይሁዳ የተወሰነ መልካምነት ገና ይገኝ ነበር፡፡
\s5
\v 13 ንጉሡም ሮብዓም ንግሥናውን በኢየሩሳሌም አጠናከረ፤ በዚህ ሁኔታም ገዛ፡፡ ሮብዓም መንገሥ ሲጀምር አርባ አንድ ዓመቱ ነበር፤ እግዚአብሔር ስሙን ያኖርባት ዘንድ ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጣት በኢየሩሳሌም ከተማ አስራ ሰባት ዓመታት ነገሠ፡፡ የአሞናዊቷ እናቱም ስም ናዕማ ነበር፡፡
\v 14 እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልቡን አላዘጋጀም ነበርና ክፉውን ነገር አደረገ፡፡
\s5
\v 15 ሮብዓምን የሚመለከቱ ሌሎች ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው የትውልዶች ስም ዝርዝርና በሮብዓምና በኢዮርብዓም መካከል የነበሩት ያልተቋረጡ ጦርነቶች በተመዘገቡበት በነቢዩ ሸማያና በባለ ራዕዩ በአዶ ጽሑፎች ውስጥ የተጻፉ አይደለምን?
\v 16 ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም አብያ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
\s5
\c 13
\p
\v 1 ንጉሥ ኢዮርብዓም በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት አብያ በይሁዳ ላይ መንገሥ ጀመረ፡፡
\v 2 በኢየሩሳሌም ለሦስት ዓመታት ገዛ፤ የገብዓው ሰው የኡርኤል ልጅ የነበረችው የእናቱ ስም ሚካያ ነበር፡፡ በአብያና በኢዮርብዓም መካከል ጦርነት ነበረ፡፡
\v 3 አብያም ከአራት መቶ ሺህ የተመረጡ ጠንካራ፥ ደፋር ሰዎች ሠራዊት ጋር ወደ ጦርነት ሄደ፡፡ ኢዮርብዓምም ከተመረጡት ስምንት መቶ ሺህ የተመረጡ ጠንካራ፥ ደፋር ወታደሮች ጋር ሊጋጠመው ተሰለፈ፡፡
\s5
\v 4 አብያም በተራራማው በኤፍሬም አገር ባለው በጽማራይም ተራራ ላይ ቆሞ፦ "ኢዮርብዓምና እስራኤል ሁሉ ስሙኝ!
\v 5 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ መንግሥት ለዳዊት ለዘላለም ለልጆቹ በደንብ በተጠበቀ ቃል ኪዳን እንዲገዙ እንደሰጠ አታውቁምን?" አለ፡፡
\s5
\v 6 የዳዊት ልጅ የሰለሞን ባሪያ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም ግን ተነሳና በጌታው ላይ ዐመፀ፡፡
\v 7 የማይረቡ ሰዎችም ጸያፍ ሰዎችም ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፡፡ የሰለሞን ልጅ ሮብዓም ወጣትና ልምድ የለሽ በነበረበትና ሊቋቋማቸው በማይችልበት ጊዜ በሮብዓም ላይ ተነሱበት፡፡
\s5
\v 8 አሁንም በዳዊት ዝርያዎች እጅ ውስጥ የሆነውን የእግዚአብሔር አገዛዝ ኃይል ልትቋቋሙ እንደምትችሉ ትናገራላችሁ፡፡ እናንተም ታላቅ ሠራዊት ናችሁ፤ ኢዮርብዓም አማልክት አድርጎ የሠራላችሁ የወርቅ ጥጃዎች ከእናንተ ጋር አሉ፡፡
\v 9 የአሮንን ትውልዶች የእግዚአብሔርን ካህናትና ሌዋውያን አላባረራችሁምን? እንደ ሌሎች ምድር ሕዝቦች ልማድ ለራሳችሁ ካህናት አላደረጋችሁምን? ከአንድ ወይፈንና ሰባት አውራ በጎች ጋር ራሱን ሊቀድስ የሚመጣው ሁሉ አማልክት ላልሆኑ ነገሮች ካህን ይሆናል፡፡
\s5
\v 10 ለእኛ ግን እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ እኛም አልተውነውም፡፡ የአሮን ዝርያዎች የሆኑት እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ካህናትና በሥራቸው ላይ የተሰማሩ ሌዋውያን አሉን፡፡
\v 11 በየማለዳውና በየምሽቱ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ጣፋጩን ዕጣን ያቃጥላሉ፤ የመገኘቱንም ሕብስት በንጹህ ገበታ ላይ ያዘጋጃሉ፤ በየምሽቱ እንዲያበሩ የወርቁን መቅረዝ ከቀንዲሎቹ ጋር ይንከባከባሉ/ይጠብቃሉ፡፡ እኛም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ እንጠብቃለን፤ እናንተ ግን ትታችሁታል፡፡
\s5
\v 12 እነሆ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር እንደ አለቃችን ነው፤ በእናንተ ላይ መለከቶቹን ለመንፋት የእርሱ ካህናትም እዚህ ይገኛሉ፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ ስለማይሳካላችሁ ከአባቶቻችሁ አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር አትዋጉ፡፡
\s5
\v 13 ኢዮርብዓም ግን ክጀርባቸው ድብቅ ጦር አዘጋጅቶ ነበር፤ የእርሱ ሠራዊት ከይሁዳ ፊት ለፊት ሆኖ ድብቁ ጦር ግን ክጀርባቸው ነበር፡፡
\v 14 ይሁዳ ከወደ ኋላ ሲመለከቱ እነሆ ውጊያው ከፊታቸውና ከኋላቸውም ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ፤ ካህናቱም መለከቶቹን ነፉ፡፡
\v 15 የይሁዳም ሰዎች ጮኹ፤ በጮኹም ጊዜ እግዚአብሔር ኢዮርብዓምንና እስራኤልን ሁሉ በአብያና በይሁዳ ፊት መታቸው፡፡
\s5
\v 16 የእስራኤል ሕዝብ ከይሁዳ ፊት ሸሹ፤ እግዚአብሔርም በይሁዳ እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፡፡
\v 17 አብያና ሠራዊቱ በታላቅ አገዳደል ገደሏቸው፤ አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ የእስራኤል ሰዎች ተገድለው ወደቁ፡፡
\v 18 በዚህ መንገድ በዚያን ጊዜ የእስራኤል ሕዝብ ተሸነፉ፤ የይሁዳ ሕዝብ በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ታምነው ስለነበር አሸነፉ፡፡
\s5
\v 19 አብያ ኢዮርብዓምን አሳደደ፤ ከእርሱም ከተሞችን ወሰደ፤ ቤቴልንና መንደሮችዋን፥ ይሻናንና መንደሮችዋን፥ እንዲሁም ዔፍሮንንና መንደሮችዋን ወሰደ፤
\v 20 ኢዮርብዓምም በአብያ ዘመን እንደገና ኃይሉ ከቶም አላገገመም፡፡ እግዚአብሔርም ቀሰፈው፤ እርሱም ሞተ፡፡
\v 21 አብያ ግን በረታ፤ ለራሱ አስራ አራት ሚስቶችን ወሰደ፤ ሃያ ሁለት ወንዶች ልጆችንና አስራ ስድስት ሴቶች ልጆችን ወለደ፡፡
\v 22 የተቀሩት የአቢያ ድርጊቶችና ባሕርዩ የተናገራቸው ነገሮችም በነቢዩ አዶ ትርጓሜ/አንድምታ ተጽፈዋል፡፡
\s5
\c 14
\p
\v 1 አብያም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡ ልጁም አሳ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡ በእርሱም ዘመን በምድሪቱ ላይ ለአሥር ዓመታት ፀጥታ ነበር፡፡
\v 2 አሳ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤
\v 3 የእንግዶቹን አማልክት መሠዊያ እና መስገጃዎቹን አስወገደ፤ የተቀደሱትን የድንጋይ ሐውልቶች ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ቆራረጠ፡፡
\v 4 የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ይሹ ዘንድ እና ሕጉንና ትዕዛዛቱን ይፈጽሙ ዘንድ ይሁዳን አዘዘ፡፡
\s5
\v 5 ከይሁዳም ከተሞች ሁሉ መስገጃዎቹንና ዕጣን የሚጨስባቸውን መሠዊያዎች አስወገደ፡፡ መንግሥቱም በእርሱ ሥር በሰላም ተቀመጠች፡፡
\v 6 በምድሪቱ ላይ ጸጥታ ስለነበርና እግዚአብሔርም ሰላም ስለሰጠው በእነዚያ ዓመታት ምንም ጦርነት ስላልነበረበት በይሁዳ የተመሸጉ ከተሞችን ሠራ፡፡
\s5
\v 7 አሳም ይሁዳን፡-"እነዚህን ከተሞች እንገንባ፤ በዙሪያቸው ቅጥር ፥ ማማዎች፥ መዝጊያዎች፥ እና መወርወሪያዎች እንሥራ፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ስለፈለግነው ምድሪቱ እስከ አሁንም የእኛ ናት፡፡ እኛም ፈልገነዋል እርሱም በሁሉም በኩል እረፍት ሰጥቶናል፡፡" አላቸው፡፡ እነርሱም ገነቡ፤ ተሰካላቸውም፡፡
\v 8 ለአሳም ጋሻና ጦር የሚይዙ ከይሁዳ ሦስት መቶ ሺህ ሰዎች፥ ጋሻ የሚይዙና ቀስት የሚስቡ ደግሞ ከቢኒያም ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች የያዘ ሠራዊት ነበረው፡፡
\s5
\v 9 ኢትዮጵያዊው ዝሪ አንድ ሚሊዮን ወታደሮችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ያሉት ሠራዊት ይዞ ሊያጠቃቸው መጣባቸው፤ ወደ መሪሳም መጣ፡፡
\v 10 አሳም ሊጋጠመው ወጣ፤ በመሪሳም በጽፋታ ሸለቆ ውስጥ በጦርነቱ ግንባር ተሰለፉ፡፡
\v 11 አሳም ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ፦ "እግዚአብሔር ሆይ ምንም ጉልበት የሌለው ሰው ብዙዎችን በሚጋፈጥበት ጊዜ ካንተ በቀር ማንም የሚረዳው የለም፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በአንተ ላይ ተማምነናልና እርዳን፤ ይህንን የመጣብንን ብዙ ቁጥር ያለው ሠራዊት በስምህ እንመጣባቸዋለን፡፡ እግዚአብሔር ሆይ አንተ አምላካችን ነህ፤ ሰውም አያሸንፍህ" ብሎ ጮኸ፡፡
\s5
\v 12 እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ፤ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ፡፡
\v 13 አሳና ወታደሮቹም እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው፡፡ ስለዚህ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ሙሉ በሙሉ ስለተደመሰሱ ማገገም እስከማይችሉ ድረስ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደቁ፡፡ሠራዊቱም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፡፡
\s5
\v 14 የእግዚአብሔር ድንጋጤ በነዋሪዎቹ ላይ ስለመጣባቸው ሠራዊቱ በጌራራ ዙሪያ ያሉ መንደሮችን ሁሉ ደመሰሱ፡፡ በውስጣቸውም እጅግ ብዙ ምርኮ ስለነበር ሠራዊቱ መንደሮቹን ሁሉ በዘበዙ፡፡
\v 15 የከብት አርቢ ዘላኖቹን የድንኳን ሰፈራዎችም ደመሰሱ፤ ከመጠን በላይ በጎችን እንዲሁም ግመሎችን ወስደው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡
\s5
\c 15
\p
\v 1 የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በዓዛርያስ ላይ መጣ፡፡
\v 2 አሳንም ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፦ "አሳ፥ ይሁዳ ሁሉና ቢኒያም ሆይ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፡፡ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፡፡
\s5
\v 3 እስራኤል ለረጅም ጊዜ ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪ ካህን እና ያለ ሕግ ይኖሩ ነበር፡፡
\v 4 በጭንቃቸው ጊዜ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ሲፈልጉት ይገኝላቸው ነበር፡፡
\v 5 በዚያን ዘመን ርቆ ለሚሄደውና ወደዚህ ቅርብ ለሚመጣው ሰላም አልነበረም፤ ይልቁንም በምድሪቱ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ታላቅ ጭንቅ ነበር፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔር በሁሉም ዓይነት መከራዎች ያስጨንቃቸው ስለነበር ፍርስርሳቸው ወጥቶ ነበር፤ ህዝብ ከህዝብ ጋር፥ ከተማም ከከተማ ጋር ይዋጋ ነበር፡፡
\v 7 እናንተ ግን ሥራችሁ ብድራት ስለአለው በርቱ እጃችሁም እንዲደክም አትፍቀዱ፡፡"
\s5
\v 8 ይህንን ቃል፥ የነቢዩን የዖዴድን ትንቢት በሰማ ጊዜ ብርታት አግኝቶ ከይሁዳና ከቢኒያም ምድር ሁሉ፥ ከተራራማው የኤፍሬም አገር ከያዛቸው ከተሞች ጸያፉን ነገር አስወገደ፤ በእግዚአብሔርም ቤት መተላለፊያ ፊት ለፊት የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ እንደገና ሠራ፡፡
\v 9 ይሁዳንና ቢኒያምን ሁሉ ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴም ከስምዖንም ወገን የሆኑትን ከእርሱም ጋር የዘለቁትን ሰበሰበ፡፡ እግዚአብሔር አምላኩ ከእርሱ ጋር እንደነበር ሲያዩ ከእስራኤል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡
\s5
\v 10 በመሆኑም አሳ በነገሠ በአስራ አምስተኛው ዓመት በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡
\v 11 በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ የተወሰነውን ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎችና ፍየሎች ለእግዚአብሔር ሠዉ፡፡
\s5
\v 12 የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ሊፈልጉት ቃል ኪዳን አደረጉ፡፡
\v 13 የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ማንም ቢኖር ሰውየው ታናሽ ይሁን ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ሊገደል እንደሚገባው ተስማሙ፡፡
\s5
\v 14 በታላቅ ድምጽና በጩኸት፥ በእምቢልታና በቀንደ መለከት ለእግዚአብሔር ማሉ፡፡
\v 15 በሙሉ ልባቸው መሐላውን ስለፈጸሙ፥ እግዚአብሔርንም በሙሉ ፍላጎታቸው ስለፈለጉት እርሱም ተገኝቶላቸው ስለነበር ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፡፡ እግዚአብሔር በዙሪያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፡፡
\s5
\v 16 ንጉሡም አሳ ሴት አያቱ መዓካ ከማምለኪያ አጸድ አስጸያፊ ምስል/ጣኦት ስላበጀች ከንግሥትነትዋ አስወገዳት፡፡ አሳም አስጸያፊ ምስሏን/ጣኦቷን ቆርጦ አቧራ አድርጎ ፈጨው፤ በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው፡፡
\v 17 መስገጃዎቹ ግን ከእስራኤል አልራቁም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፍጹም ታማኝና ታዛዥ ነበር፡፡
\s5
\v 18 የእግዚአብሔር የሆኑትን የአባቱን ነገሮችና የገዛ ራሱን ነገሮች፥ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ወደ እግዚአብሔር ቤት ውስጥ አስገባቸው፡፡
\v 19 አሳም እስከነገሠበት እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ ከዚያ ወዲያ ጦርነት አልነበረም፡፡
\s5
\c 16
\p
\v 1 አሳ በነገሠ በሠላሳ ስድስተኛው ዓመት የእስራኤል ንጉሥ ባኦስ በይሁዳ ላይ የጠብ ጫሪነት ድርጊት ፈጸመ፡፡ ወደ ይሁዳም ንጉሥ ወደ አሳ ምድር ማንም መውጣትና መግባት እንዳይፈቀድለት ራማን ዙሪያዋን ሠራ፡፡
\s5
\v 2 አሳም ከእግዚአብሔር ቤት እና ከንጉሡ ቤት መጋዘኖች ብርና ወርቅ አውጥቶ በደማስቆ ይኖር ወደ ነበረው ወደ አራም ንጉሥ ወደ ቤንሃዳድ ላከው፡፡
\v 3 "በአባትህና በአባቴ መካከል እንደነበረው በእኔና በአንተ መካከል የሰላም ስምምነት ይኑር፡፡ እነሆ ብርና ወርቅ ሰድጄልሃለሁ፤ ከእኔ ርቆ እንዲተወኝ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያደረግኸውን የሰላም ስምምነት አፍርስ" አለው፡፡
\s5
\v 4 ቤንሃዳድም ንጉሡን አሳን ሰማው፤ የእስራኤልን ከተሞች እንዲያጠቁም የሠራዊቱን አለቆች ላከ፡፡ እነርሱም ኦዮንን፥ ዳንን፥ አቤልማይምንና የንፍታሌምን የዕቃ ቤት ከተሞች ሁሉ መቱ፡፡
\v 5 ባኦስም ይህንን ሲሰማ የራማን ዙሪያዋን መሥራቱን አቆመ፤ ሥራውንም አቋረጠ፡፡
\v 6 በዚያን ጊዜ ንጉሡ አሳ ይሁዳን ሁሉ ሰበሰበ፤ ባኦስ ከተማይቱን ይሠራበት የነበረውን የራማን ድንጋዮችና ጣውላዎች ወሰዱ፡፡ ከዚያም ንጉሡ አሳ ያንን የግንባታ ዕቃ ጌባንና ምጽጳን ለመሥራት ተጠቀመበት፡፡
\s5
\v 7 በዚያን ጊዜ ባለ ራዕዩ አናኒ ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሳ ሄዶ፦ "በአራም ንጉሥ ስለታመንህና በአምላክህ በእግዚአብሔር ስላልታመንህ የአራም ንጉሥ ሠራዊት ከእጅህ አምልጦአል፡፡
\v 8 እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሯቸው ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ታላቅ ሠራዊት አልነበሩምን? ነገር ግን በእግዚአብሔር ስለታመንህ በእነርሱ ላይ ድልን ሰጠህ፡፡
\s5
\v 9 ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የተሰጠ የሆነውን ሰው በኃይሉ ያበረታ ዘንድ የእግዚአብሔር ዓይኖች በምድር ሁሉ ላይ ይዘዋወራሉ፡፡ ነገር ግን አንተ በዚህ ጉዳይ ስንፍና አድርገሃል፡፡ ከአሁን ጊዜ ጀምሮ ጦርነት ይሆንብሃል" አለው፡፡
\v 10 በዚያን ጊዜ ንጉሡ አሳ በባለ ራዕዩ ላይ ተቆጣ፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ተቆጥቶ ስለነበር እስር ቤት ውስጥ አኖረው፡፡ በዚያው ጊዜ አሳ ከሕዝቡ የተወሰኑትን አስጨነቀ፡፡
\s5
\v 11 እነሆ የአሳ ድርጊቶች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል፡፡
\v 12 አሳ በነገሠ በሠላሳ ዘጠኝ ዓመቱ እግሩን ታመመ፤ ሕመሙም እጅግ ጽኑ ነበር፡፡ እንዲህም ሆኖ ከባለ መድኃኒቶች ብቻ እንጂ ከእግዚአብሔር እርዳታ አልፈለገም፡፡
\s5
\v 13 አሳ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በነገሠም በአርባ አንደኛው ዓመት ሞተ፡፡
\v 14 በዳዊት ከተማ ለእርሱ ለራሱ በቆፈረው በራሱ መቃብር ቀበሩት፡፡ በተካኑ ቀማሚዎች በተሰናዳ ልዩ ልዩ የቅመም ዓይነቶች በጣፋጭ መዓዛ በተሞላ ቃሬዛ ላይ አኖሩት፡፡ ለክብሩም እጅግም ታላቅ የሆነ እሳት ለኮሱለት፡፡
\s5
\c 17
\p
\v 1 ልጁ ኢዮሳፍጥ በእርሱ ቦታ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ራሱን አጠነከረ፡፡
\v 2 በተመሸጉትም በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ወታደሮችን አስቀመጠ፤ በይሁዳም ምድር እና አባቱ አሳ በያዛቸው የኤፍሬም ከተሞች ውስጥ የጦር ሠፈር አደራጀ፡፡
\s5
\v 3 በአባቱ በዳዊት በፊተኛይቱ መንገድ ስለሄደና በአሊምንም ስላልፈለገ እግዚአብሔር ከኢዮሣፍጥ ጋር ነበረ፡፡
\v 4 በዚያ ፈንታ በአባቱ አምላክ ላይ ተደገፈ፤ እንደ እስራኤል ባህርይ ሳይሆን በአምላኩ ትዕዛዛት መሠረት ሄደ፡፡
\s5
\v 5 በመሆኑም እግዚአብሔር መንግሥቱን በእጁ አጸናለት፤ ይሁዳ ሁሉ ለኢዮሣፍጥ ግብር ያመጡለት ነበር፡፡ የተትረፈረፈ ባለጠግነትና ክብርም ነበረው፡፡
\v 6 ልቡም በእግዚአብሔር መንገድ የጸና ነበረ፡፡ መስገጃዎቹንና የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ከይሁዳ አስወገደ፡፡
\s5
\v 7 በነገሠም በሦስተኛው ዓመት ያስተምሩ ዘንድ ባለሥልጣናቱን ቤንኃይልን፥ አብድያስን፥ ዘካርያስን፥ ናትናኤልንና ሚኪያስን ወደ ይሁዳ ከተሞች ላካቸው፡፡
\v 8 ከእነርሱም ጋር ሌዋውያኑ ሸማያ፥ነታንያ፥ ዝባድያ፥ አሣኤል፥ ሰሚራሞት፥ዮናትን፥ አዶንያስ፥ ጦብያ እና ጠባዶንያ ነበሩ፡፡ ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ኤሊሳማና ኢዮራም ነበሩ፡፡
\v 9 እነርሱም የእግዚአብሔር የሕግ መጽሐፍ ከእነርሱ ጋር ስለነበር በይሁዳ አስተማሩ፡፡በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ተዘዋውረው በሕዝቡ መካከል አስተማሩ፡፡
\s5
\v 10 በይሁዳ ዙሪያ በነበሩት አገራት ነገሥታት ላይ የእግዚአብሔር ድንጋጤ ስለወደቀባቸው ከኢዮሣፍጥ ጋር ምንም ጦርነት አላደረጉም፡፡
\v 11 የተወሰኑት ፍልስጤማውያን ለኢዮሳፍጥ ስጦታዎችና ብር እንደ ግብር ያመጡለት ነበር፡፡ አረቦችም ሰባት ሺህ ሰባት መቶ የአውራ በጎችና ሰባት ሺህ ሰባት መቶ የፍየሎች መንጋዎችን አመጡለት፡፡
\s5
\v 12 ኢዮሣፍጥም እጅግ ብርቱ ሆነ፤ በይሁዳም ትልልቅ ምሽጎችንና የመጋዘን ከተሞችን ሠራ፡፡
\v 13 በይሁዳም ከተሞች በርካታ አቅርቦት እና በኢየሩሳሌምም ጠንካራና ደፋር ሰዎች - ወታደሮች ነበሩት፡፡
\s5
\v 14 በአባቶቻቸው ቤቶች ስም ቅደም ተከተል ዝርዝራቸው ይህ ነው፤ ከይሁዳ የሺዎች አዣዦች፥ አዣዡ ዓድና ከእርሱም ጋር ሦስት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች፤
\v 15 ከእርሱም ቀጥሎ አለቃው ይሆሐናን፥ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤
\v 16 ከእርሱም ቀጥሎ ራሱን በፈቃዱ እግዚአብሔርን ለማገልገል ያቀረበ የዝክሪ ልጅ ዓማስያ ከእርሱም ጋር ሁለት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች ነበሩ፤
\s5
\v 17 ከቢኒያም ኃይለኛ ደፋር ሰው የነበረው ኤሊዳሄ ከእርሱም ጋር ቀስትና ጋሻ የሚይዙ ሁለት መቶ ሺህ ተዋጊ ሰዎች ነበሩ፤
\v 18 ከእርሱም ቀጥሎ ዮዛባት ከእርሱም ጋር ለጦርነት የተዘጋጁ መቶ ሰማንያ ሺህ ሰዎች ነበሩ፤
\v 19 ንጉሡ በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞች ሁሉ ካስቀመጣቸው በተጨማሪ እነዚህ ንጉሡን የሚያገለግሉ ነበሩ፡፡
\s5
\c 18
\p
\v 1 ኢዮሣፍጥ ታላቅ ባለጠግነትና ክብር ነበረው፡፡ ከቤተሰቦቹ አንዱ ሴት ልጁን እንዲያገባ በማድረግ ከአክዓብ ጋር ራሱን አዛመደ፡፡
\v 2 ከተወሰኑ ዓመታት በኋላም ወደ አክዓብ ወደ ሰማርያ ወረደ፡፡ አክዓብም ለእርሱና ከእርሱ ጋር ለነበሩት ሕዝብ በርካታ በጎችንና በሬዎችን አረደላቸው፡፡ ከእርሱም ጋር ሬማት ዘገለአድን ለማጥቃት ይሄድ ዘንድም አክዓብ አሳመነው፡፡
\v 3 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ የይሁዳን ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ፦ "ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገለአድ ትሄዳለህን?" አለው፡፡ ኢዮሣፍጥም ፦"እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝቤም እንደ ሕዝብህ ናቸው፤ በጦርነቱ ውስጥ ካንተ ጋር አብረን እንሆናለን" ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 4 ኢዮሣፍጥም የእስራኤልን ንጉሥ ፦ "እባክህን ለመልስህ በመጀመሪያ የእግዚአብሔርን ቃል ጠይቅ" አለው፡፡
\v 5 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ ነቢያቱን አራት መቶ ሰዎች በአንድነት ሰብስቦ፦ "ወደ ሬማት ዘገለአድ ለጦርነት መሄድ ይገባናል ወይስ መሄድ አይገባኝም?" አላቸው፡፡ እነርሱም ፦" እግዚአብሔር ለንጉሡ ድል ይሰጠዋልና አጥቃት!" አሉት፡፡
\s5
\v 6 ኢዮሣፍጥ ግን፦ "ምክር የምንጠይቀው አሁንም ሌላ የእግዚአብሔር ነቢይ የሆነ ሰው በእዚህ የለምን?" አለ፡፡
\v 7 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን ፦" የእግዚአብሔርን ምክር የምንጠይቅበት አሁንም አንድ ሰው የይምላ ልጅ ሚክያስ አለ፤ ነገር ግን ችግር ብቻ እንጂ ስለእኔ ምንም ነገር መልካም ትንቢት ከቶም ተናግሮልኝ ስለማያውቅ እጠላዋለሁ" አለው፡፡ኢዮሣፍጥ ግን ፦ " ንጉሥ እንደዚያ አይበል" አለ፡፡
\v 8 ከዚያም የእስራኤል ንጉሥ አንድ ሹም ጠርቶ ፦"የይምላን ልጅ ሚክያስን በፍጥነት አምጣው" ሲል አዘዘው፡፡
\s5
\v 9 የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የአስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥ መጎናጸፊያቸውን እንደለበሱ እያንዳንዳቸው በዙፋን ላይ በሰማርያ በር መግቢያ በግልጽ ሥፍራ ላይ ተቀምጠው ነቢያቱም ሁሉ በፊታቸው ትንቢት እየተናገሩ ነበር፡፡
\v 10 የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስም ለራሱ የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ' በእነዚህ ቀንዶች አርመናውያን እስኪያልቁ ድረስ ትወጋቸዋለህ' " አለ፡፡
\v 11 ነቢያቱም ሁሉ፦" እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ስለሚሰጣት ሬማት ዘገለዓድን አጥቃና አሸንፍ" እያሉ ተመሳሳይ ትንቢት ይናገሩ ነበር፡፡
\s5
\v 12 ሚክያስን ሊጠራ የሄደው መልዕክተኛ ፦" እነሆ የነቢያቱ ቃላት በአንድ አፍ ለንጉሡ መልካም ነገሮች ያውጃሉ፡፡ እባክህን ያንተም ቃል ከእነርሱ የአንዱን ቃል ዓይነት ይሁንና መልካም ነገሮች ተናገር" ሲል ተናገረው፡፡
\v 13 ሚክያስም፦"ሕያው እግዚአብሔርን የምናገረው አምላኬ እርሱ የሚለውን ነው" ብሎ መለሰ፡፡
\v 14 ወደ ንጉሡም በመጣ ጊዜ ንጉሡ፦" ሚክያስ ሆይ ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለጦርነት መሄድ ይገባናል ወይስ መቅረት?"አለው፡፡ ሚክያስም፦" አጥቃና አሸንፍ! ታላቅ ድል ይሆንልሃልና!" ብሎ መለሰለት፡፡
\s5
\v 15 ከዚያም ንጉሡ ፦" በእግዚአብሔር ስም ከእውነቱ በቀር ሌላ ምንም ነገር እንዳትነግረኝ ስንት ጊዜ እንድትምል ላደርግህ ይገባኛል?" አለው፡፡
\v 16 ሚክያስም፦" እስራኤል ሁሉ እረኛ እንደሌላቸው በጎች በተራሮች ላይ ተበትነው አየኋቸው፤ እግዚአብሔርም፦ 'እነዚህ እረኛ የላቸውም፡፡ እያንዳንዱ ሰው በሰላም ወደ ቤቱ ይመለስ' አለ" ብሎ ተናገረ፡፡
\s5
\v 17 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ ለኢዮሳፍጥ ፦" እኔን በተመለከተ ጥፋት ብቻ እንጂ መልካም ትንቢት እንደማይናገርልኝ አልነገርኩምን?" አለው፡፡
\v 18 ከዚያም ሚክያስ፦" እንግዲህ ሁላችሁም የእግዚአብሔርን ቃል መስማት ይገባችኋል፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ የሰማይም ሰራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው እንደነበር አየሁ፡፡
\s5
\v 19 እግዚአብሔርም ፦" የእስራኤል ንጉሥ አክዓብ ወደ ሬማት ዘገለዓድ እንዲወጣና እንዲወድቅ የሚያታልለው ማነው?" አለ፡፡ አንዱ በእዚህ መንገድ ብሎ ሲመልስ ሌላውም በዚያ መንገድ ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 20 ከዚያም አንድ መንፈስ መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ፦" እኔ አታልለዋለሁ" አለ፡፡ እግዚአብሔርም ፦"እንዴት?" አለው፡፡
\v 21 መንፈሱም፡-" ወጥቼ በነቢያቱ ሁሉ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ እሆናለሁ" አለ፡፡ እግዚአብሔርም፦" ታታልለዋለህ፤ ይሳካልሃልም፤ አሁንም ሂድና እንደዚሁ አድርግ" ብሎ መለሰ፡፡
\s5
\v 22 አሁንም እነሆ እግዚአብሔር በእነዚህ ነቢያትህ አፍ ሐሰተኛ መንፈስ አስቀምጧል፤ እግዚአብሔርም ጥፋት እንዲመጣብህ ተናግሯል፡፡
\s5
\v 23 የክንዓና ልጅ ሴዴቅያስም ቀረብ ብሎ ሚክያስን በጥፊ መታውና ፦"የእግዚአብሔር መንፈስ ለአንተ ሊናገር በየትኛው መንገድ ከእኔ ሄደ?" አለው፡፡
\v 24 ሚክያስም፦" እነሆ በዚያ ቀን ልትሸሸግ ወደ አንድ የውስጥ ክፍል ስትሸሽ ታውቀዋለህ" አለው፡፡
\s5
\v 25 የእስራኤል ንጉሥም ለአገልጋዮቹ ፦" እናንተ ሰዎች ሚክያስን ያዙና ወደ ከተማይቱ አስተዳዳሪ ወደ አሞንና ወደ ልጄ ወደ ኢዮአስ ውሰዱት፤ "
\v 26 ንጉሡ፦' በደህና እስከምመለስ ድረስ ይህንን ሰው እስር ቤት ውስጥ አኑሩት፤ ጥቂት ምግብ ብቻ እና ጥቂት ውሃ ብቻ መግቡት' ይላል በሉት" አላቸው፡፡
\v 27 ሚክያስም፦" አንተ በደህና ከተመለስህ በእኔ የተናገረው እግዚአብሔር አይደለም" አለ፡፡ ጨምሮም፦"እናንተ ሕዝብ ሁሉ ይህንን ስሙ" አለ፡፡
\s5
\v 28 በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ አክዓብና የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ሬማት ዘገለዓድን ሊዋጉ ወጡ፡፡
\v 29 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮሳፍጥን፡-"እኔ እንዳልታወቅ አለባበሴን ለውጬ ወደ ጦርነቱ እገባለሁ፤ አንተ ግን ንጉሣዊ መጎናፊያህን ልበስ" አለው፡፡ በመሆኑም የእስራኤል ንጉሥ በአለባበሱ እንዳይታወቅ ራሱን ለውጦ ወደ ጦርነቱ ሄዱ፡፡
\v 30 የአራምም ንጉሥ የሰረገሎቹን አዛዦች፦ " ከፍተኛ ወይም ዝቅተኛ ወታደሮችን እንዳታጠቁ፤ ይልቁንም የእስራኤል ንጉሥን ብቻ አጥቁ" በማለት አዝዟቸው ነበር፡፡
\s5
\v 31 የሰረገሎቹ አለቆች ኢዮሳፍጥን ባዩ ጊዜ፦"የእስራኤል ንጉሥ ያ ነው ፤" አሉ፡፡ ሊያጠቁትም ወደ እርሱ ዞሩበት፤ ነገር ግን ኢዮሳፍጥ ሲጮህ እግዚአብሔር ረዳው፡፡ እግዚአብሔርም ከእርሱ ዞር አደረጋቸው፡፡
\v 32 የሰረገሎቹም አለቆች የእስራኤል ንጉሥ እንዳልነበረ ባዩ ጊዜ እርሱን ከመከታተል ተመለሱ፡፡
\s5
\v 33 አንድ ሰው ግን በዘፈቀደ ቀስቱን ሲስበው የእስራኤል ንጉሥን በጥሩር መገጣጠሚያዎቹ መካከል ወጋው፡፡ ያን ጊዜ አክዓብ የሰረገላውን ነጂ፦" ክፉኛ ተወግቻለሁና አቅጣጫህን ቀይርና ከጦርነቱ ውስጥ አውጣኝ፡፡
\v 34 በዚያን ጊዜ ጦርነቱ እጅግ የከፋ ሆነ፤ የእስራኤልም ንጉሥ አርመናውያንን እየተመለከተ እስኪመሽ ድረስ ሰረገላውን እንደተደገፈ ነበር፡፡ ፀሐይ በምታዘቀዝቅበት ጊዜ አካባቢ ሞተ፡፡
\s5
\c 19
\p
\v 1 የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥም ወደ ቤቱ ወደ ኢየሩሳሌም በደህና ተመለሰ፡፡
\v 2 ያኔ የባለ ራዕዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፤ ንጉሡንም ኢዮሳፍጥን፦"ክፉውን ልትረዳ ይገባሃልን? እግዚአብሔርን የሚጠሉትን ልትወድ ይገባሃልን? ለዚህ ድርጊትህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል፡፡
\v 3 ነገር ግን የማምለኪያ አፀዶቹን ከምድሪቱ ላይ አስወግደሃልና እግዚአብሔርን ለመፈለግ ቆርጠህ ልብህን አዘጋጅተሃልና በአንተ ዘንድ መልካምነት ተገኝቶብሃል" አለው፡፡
\s5
\v 4 ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ተቀመጠ፤ ከቤርሳቤህ እስከ ተራራማው የኤፍሬም አገር ድረስ እንደገና በሕዝቡ መካከል ወጥቶ ወደ አባቶቻቸው አምላክ መለሳቸው፡፡
\v 5 በምድሪቱ ላይ በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በእያንዳንዱ ከተማ ውስጥ ፈራጆችን አስቀመጠ፡፡
\s5
\v 6 ፈራጆቹንም፦"የምትፈርዱት ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው ስላልሆነ ምን ማድረግ እንደሚገባችሁ አጢኑ፤ በፍርድ ነገር እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፤
\v 7 አሁንም የእግዚአብሔር ፍርሃት በእናንተ ላይ ይሁን፡፡ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ምንም በደል የለምና፤ ለሰው ፊት ማድላት ወይም መማለጃ መውሰድ የለምና በምትፈርዱበት ጊዜ ተጠንቀቁ" አላቸው፡፡
\s5
\v 8 በተጨማሪም ኢዮሳፍጥ በኢየሩሳሌም ከሌዋውያኑንና ከካህናቱ የተወሰኑትንና ከእስራኤል የአባቶች ቤቶች መሪዎች የተወሰኑትን የእግዚአብሔርን ፍርድ እንዲያስፈጽሙና ጠቦችን እንዲፈቱ ሾማቸው፡፡ እነርሱም በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፡፡
\v 9 " እግዚአብሔርን በመፍራት፥ በታማኝነትና በፍጹም ልብ የምታደርጉት ይህ ነው፤
\s5
\v 10 በደም መፍሰስ ጉዳይ ቢሆን፥ በሕግና በትእዛዝ፥ በሥርዓት ወይም በድንጋጌ ጉዳዮች ቢሆን በከተሞቻቸው ከተቀመጡት ከወንድሞቻችሁ ምንም ኣይነት ጠብ ወደ እናንተ ቢመጣ እግዚአብሔርን እንዳይበድሉ፥ ቁጣ በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይወርድ ልታስጠነቅቋቸው ይገባል፡፡ እንደዚህ ብታደርጉ በኃጢአት በደለኛ አትሆኑም፡፡
\s5
\v 11 እነሆ ለእግዚአብሔር በሚሆኑት ነገሮች ሁሉ ላይ ሊቀ ካህናቱ አማርያ፥ በንጉሡ ጉዳዮች ሁሉ ላይ የተሾመው የይሁዳ ቤት መሪ የእስማኤል ልጅ ዝባድያ አለቆች ናቸው፡፡ ሌዋውያኑም ደግሞ የሚያገለግሏችሁ ባለሥልጣናት ይሆናሉ፡፡ በድፍረት አድርጉ፤ እግዚአብሔርም መልካም ከሆኑት ጋር ይሁን፡፡
\s5
\c 20
\p
\v 1 ከዚህ ጊዜ በኋላ የሞዓብና የአሞን ሕዝቦች ከእነርሱም ጋር ምዑናውያን ኢዮሳፍጥን ሊዋጉት መጡ፡፡
\v 2 አንዳንድ ሰዎች መጥተው፦"ከባሕሩ ማዶ ከሶሪያ ታላቅ ሠራዊት መጥቶብሃል፤ እነሆም ዓይንጋዲ በተባለች በሐሴሶን ታማር ናቸው" ብለው ነገሩት፡፡
\s5
\v 3 ኢዮሳፍጥም ፈራ፤ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ራሱን አቀና፤ በመላው ይሁዳ ፆምን አወጀ፡፡
\v 4 ይሁዳም እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ በአንድነት ተሰበሰበ፤ ከመላው የይሁዳ ከተሞች ሁሉ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ መጡ፡፡
\s5
\v 5 ኢዮሳፍጥም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ጉባዔ በአዲሱ አደባባይ ፊት ቆመ፡፡
\v 6 "የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ አንተ በሰማይ ያለህ አምላክ አይደለህምን? በሕዝቦች ነገሥታት ሁሉ ላይ ገዢ አይደለህምን? ኃይልና ብርታት በእጅህ ናቸው፤ በመሆኑም ማንም ሊቋቋምህ የሚችል የለም፡፡
\v 7 አምላካችን ሆይ በዚህ ምድር ላይ የነበሩትን ነዋሪዎች ከሕዝብህ ከእስራኤል ፊት አሳድደህ ለዘላለም ለአብርሃም ዝርያዎች አልሰጠሃትምን?" አለ፡፡
\s5
\v 8 እነርሱም በውስጧ ኖሩባት፤
\v 9 " አደጋ/መቅሰፍት ቢመጣብን - ሰይፍ፥ ፍርድ፥ ወይም በሽታ፥ ወይም ረሃብ - (ስምህ በዚህ ቤት ስላለ) በዚህ ቤት ፊትና በፊትህ እንቆምና በመከራችን ወደ አንተ እንጮሃለን፤ አንተም ሰምተህ ታድነናለህ" በማለት ለስምህም ቅዱስ ሥፍራ በውስጥዋ ሠሩ፡፡
\s5
\v 10 አሁንም እነሆ እስራኤል ከግብጽ ምድር በሚወጡበት ጊዜ እንዲወሩዋቸው ያልፈቀድክላቸው ይልቁንም ዞር ብለው ያላጠፏቸው የአሞን፥ የሞዓብና የሴይር ተራራ ሕዝቦች እዚህ ናቸው፤
\v 11 እነሆ ለወረታችን እንዴት እንደሚመልሱልን ተመልከት፤ እንድንወርሰው ከሰጠኸን ከምድርህ ሊያስወጡን መጥተዋል፡፡
\s5
\v 12 አምላካችን ሆይ አትፈርድባቸውምን? ይህንን ሊያጠቃን የመጣብንን ታላቅ ሠራዊት እንቋቋም ዘንድ ምንም ኃይል የለንም፡፡ የምናደርገውንም አናውቅም፤ ነገር ግን ዓይኖቻችን በአንተ ላይ ናቸው" አለ፡፡
\v 13 ይሁዳ ሁሉ ከሕጻናቶቻቸው፥ ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በእግዚአብሔር ፊት ቆመው ነበር፡፡
\s5
\v 14 በጉባዔው መካከል የእግዚአብሔር መንፈስ ከአሳፍ ልጆች አንዱ በነበረው በሌዋዊው በማታንያ ልጅ በይዒኤል ልጅ በበናያስ ልጅ በዘካርያስ ልጅ በየሕዚኤል ላይ መጣ፡፡
\v 15 የሕዚኤልም፦" ይሁዳ ሁሉ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እና ንጉሥ ኢዮሳፍጥ ስሙ፤ እግዚአብሔር የሚላችሁ ይህ ነው፦"ከዚህ ታላቅ ሠራዊት የተነሳ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ምክንያቱም ጦርነቱ የእግዚአብሔር እንጂ የእናንተ አይደለም፡፡
\s5
\v 16 ነገ በእነርሱ ላይ ለጦርነት ልትወጡ ይገባል፤ እነሆ በጺጽ መተላለፊያ መንገድ ይመጣሉ፡፡ በይሩኤል ምድረ በዳ ፊት ለፊት በሸለቆው መጨረሻ ታገኙዋቸዋላችሁ፡፡
\v 17 በዚህ ጦርነት እናንተ መዋጋት የሚያስፈልጋችሁ አይደላችሁም፡፡ ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ በቦታችሁ ቁሙ፤ ዝም ብላችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር ለእናንተ የሚያደርገውን ማዳን ተመልከቱ፡፡ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለሆነ አትፍሩ፤ አትደንግጡም፤ ነገ ለጦርነት ውጡባቸው" አለ፡፡
\s5
\v 18 ኢዮሳፍጥም በምድር ላይ በፊቱ ተደፋ፤ ይሁዳ ሁሉና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እግዚአብሔርን በማምለክ በፊቱ ወደቁ፡፡
\v 19 የቀዓትና የቆሬ ዝርያዎች ሌዋውያን የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን በታላቅ ድምጽ ለማወደስ ቆመው ነበር፡፡
\s5
\v 20 ጥዋት በማለዳ ተነስተው ወደ ቴቁሔ ምድረ በዳ ሄዱ፡፡ እየሄዱም እያለ ኢዮሳፍጥ ቆሞ፦" ይሁዳና እናንተ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ስሙኝ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፤ ድጋፍ ታገኛላችሁ፡፡ በነቢያቱም እመኑ፤ ይቃናላችኋልም" አለ፡፡
\v 21 ከሕዝቡ ጋር ከተማከረ በኋላም ከሠራዊቱ ፊት ቀድመው እየሄዱ " የቃል ኪዳን ታማኝነቱ ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ ለእግዚአብሔር ምሥጋናን ስጡ" በማለት ለእግዚአብሔር የሚዘምሩትንና ለቅዱስ ክብሩ ውዳሴ የሚሰጡትን ሾመ፡፡
\s5
\v 22 መዘመርና ማወደስ ሲጀምሩ ይሁዳን ሊዋጉ በመጡት በአሞን፥ በሞዓብና በሴይር ተራራ ሰዎች ላይ እግዚአብሔር ድብቅ ጦር አስነስቶ በድንገት እንዲያጠቋቸው አደረገ፡፡ እነርሱም ተሸነፉ፡፡
\v 23 የአሞንና የሞዓብ ሰዎች የሴይርን ተራራ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ እስኪገድሉዋቸውና እስኪያጠፏቸው ድረስ ሊዋጉዋቸው ተነስተው ነበር፡፡ የሴይርን ተራራ ነዋሪዎች በጨረሷቸው ጊዜ ሁሉም እርስ በእርስ ለመጠፋፋት ተረዳዱ፡፡
\s5
\v 24 ይሁዳ ምድረ በዳውን ወደሚመለከቱበት ቦታ ሲመጡ ሠራዊቱን ተመለከቱ፡፡ እነሆ ሞተው በምድሩም ላይ ወድቀው ነበር፤ አንድም ያመለጠ ሰው አልነበረም፡፡
\s5
\v 25 ኢዮሳፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ በመጡ ጊዜ ሊሸከሙት ከሚችሉት በላይ የተትረፈረፈ ባለጸግነትና የከበሩ ጌጦች አገኙ፤ ለራሳቸውም በዘበዙ፡፡ እጅግ ብዙ ስለነበርም ምርኮውን ለመውሰድ ሦስት ቀናት ፈጀባቸው፡፡
\v 26 በአራተኛው ቀን በበረከት ሸለቆ ውስጥ ተሰበሰቡ፡፡ በዚያም እግዚአብሔርን አወደሱ፤ ስለዚህም የዚያ ሥፍራ ስም እስከዛሬ ድረስ "የበረከት ሸለቆ" ነው፡፡
\s5
\v 27 የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሁሉ እግዚአብሔር በጠላቶቻቸው ላይ ደስ አሰኝቷቸዋልና በደስታ እንደገና ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ኢዮሳፍጥ እየመራቸው ተመለሱ፡፡
\v 28 በበገናና በመሰንቆ በመለከትም ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ እግዚአብሔር ቤት መጡ፡፡
\s5
\v 29 እግዚአብሔር የእስራኤልን ጠላቶች እንደተዋጋ በሰሙ ጊዜ በሕዝቦች ነገሥታት ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ፍርሃት ሆነ፡፡
\v 30 በመሆኑም አምላኩ በዙሪያው ሁሉ ሰላም ስለሰጠው የኢዮሳፍጥ መንግሥት ጸጥታ ሰፈነባት፡፡
\s5
\v 31 ኢዮሳፍጥ በይሁዳ ላይ ነገሠ፡፡ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሠላሳ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ለሃያ አምስት ዓመታት ነገሠ፡፡ የእናቱ የሺልሒ ሴት ልጅ ስም ዓዙባ ነበር፡፡
\v 32 በአባቱም በዓሳ መንገዶች ሄደ፤ ከእነርሱም ፈቀቅ አላለም፤ በእግዚአብሔር ፊት ቅን የነበረውን ነገር አደረገ፡፡
\v 33 ነገር ግን የኮረብታው መስገጃዎች ገና አልተወገዱም ነበር፡፡ ሕዝቡም ልባቸውን ወደ አባቶቻቸው አምላክ ገና አላቀኑም ነበር፡፡
\s5
\v 34 ኢዮሳፍጥን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ እንደተመዘገበው በአናኒ ልጅ በኢዩ ታሪክ ውስጥ ተጽፈዋል፡፡
\s5
\v 35 ከዚህ በኋላ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሳፍጥ እጅግ ክፋት ከፈጸመው ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝያስ ጋር ራሱን አዛመደ፡፡
\v 36 በባህር ላይ የሚሄዱ መርከቦችን ለመገንባት ከእርሱ ጋር ተባበረ፡፡ መርከቦቹንም በዔጽዮንጋብር ገነቡ፡፡
\v 37 የመሪሳም ሰው የዶዳያ ልጅ አልዓዛር ፦" ከአካዝያስ ጋር ተባብረሃልና እግዚአብሔር ሥራዎችህን አፍርሷል፤" ብሎ በኢዮሳፍጥ ላይ ትንቢት ተናገረበት፡፡ መርከቦቹም ተሰባበሩ፤ ጉዞ ለማድረግም አልቻሉም፡፡
\s5
\c 21
\p
\v 1 ኢዮሳፍጥም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ከእነርሱ ጋር ተቀበረ፤ ልጁም ኢዮራም በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
\v 2 ኢዮራም የኢዮሳፍጥ ልጆች የሆኑ ወንድሞች ዓዛርያስ፥ ይሒኤል፥ ዘካርያስ፥ ዔዛርያስ፥ ሚካኤልና ሰፋጥያስ ነበሩት፡፡ እነዚህ ሁሉ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮሳፍጥ ልጆች ነበሩ፡፡
\v 3 አባታቸው ብዙ የብር፥ የወርቅ እና የሌሎች የከበሩ ነገሮች እንዲሁም በይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን ሰጣቸው፤ ዙፋኑን ግን የመጀመሪያ ልጁ ስለነበር ለኢዮራም ሰጠው፡፡
\s5
\v 4 ኢዮራም በአባቱ መንግሥት ላይ በወጣና ራሱን እንደ ንጉሥ አጽንቶ በመሠረተ ጊዜ ወንድሞቹን ሁሉና የተለያዩ የእስራኤል ሌሎች መሪዎችን ጭምር በሰይፍ ገደላቸው፡፡
\v 5 ኢዮራምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሠላሳ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፡፡
\s5
\v 6 የአክዓብን ሴት ልጅ አግብቶ ስለነበር የአክዓብ ቤት ያደርግ እንደነበር በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ የነበረውን ነገር አደረገ፡፡
\v 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ካደረገው ቃል ኪዳን የተነሳ የዳዊትን ቤት ለማጥፋት አልፈለገም፤ ለአርሱና ለዝርያዎቹ ሁልጊዜ ሕይወት እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸው ነበር፡፡
\s5
\v 8 በኢዮራም ዘመን ኤዶምያስ በይሁዳ ኃይል ላይ ዐመፀ፤ በራሳቸውም ላይ ንጉሥ ሾሙ፡፡
\v 9 በዚያን ጊዜ ኢዮራም ከአዛዦቹና ከሠረገላዎቹ ሁሉ ጋር ተሻገረ፤ በሌሊትም ተነስቶ እርሱንና የሠረገላዎቹን አዛዦች ከብበው የነበሩትን ኤዶማውያንን መታ፡፡
\v 10 በመሆኑም እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ኤዶምያስ በይሁዳ ኃይል ላይ እንዳመፀ ነው፡፡ ኢዮራም የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ስለተወ የልብና ከተማ ጭምር በዚያው ጊዜ በኃይሉ ላይ ዐመጸ፡፡
\s5
\v 11 በተጨማሪም ኢዮራም በይሁዳ ተራራዎች ላይ መስገጃዎችን ሠርቶ ነበር፤ የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎችም እንደ አመንዝራ ሌሎች አማልክትን እንዲከተሉ አደረጋቸው፡፡ በዚህ መንገድ ይሁዳን ከትክክለኛው መስመር አስወጣቸው፡፡
\s5
\v 12 ከነቢዩም ከኤልያስ አንድ ደብዳቤ ወደ ኢዮራም መጣለት፤ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦" በአባትህ በኢዮሳፍጥ መንገድ ወይም በይሁዳ ንጉሥ በአሳ መንገድ ስላልሄድህ
\v 13 ነገር ግን በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ስለሄድህ ይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች የአክዓብ ቤት እንዳደረገ እንደ አመንዝራ ሌሎች አማልክትን እንዲከተሉ ስላደረግሃቸው፤ በአባትህ ቤተሰብም ውስጥ ከአንተ የሚሻሉ የነበሩትን ወንድሞችህን በሰይፍ ስለገደልካቸው
\v 14 እነሆ እግዚአብሔር ሕዝብህን፥ ልጆችህን፥ ሚስቶችህን እና ሀብትህንም ሁሉ በታላቅ መቅሰፍት ይመታል፡፡
\v 15 አንተም ራስህ ከበሽታው የተነሳ ከቀን ወደ ቀን አንጀትህ እስኪወጣ ድረስ በአንጀትህ ሕመም እጅግ ትታመማለህ፡፡"
\s5
\v 16 እግዚአብሔርም የፍልስጤማውያንን እና በኢትዮጵያውያን አጠገብ ይኖሩ የነበሩትን የዓረባውያንን መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሳበት፡፡
\v 17 እነርሱም ይሁዳን አጠቁ፤ ወረሩአትም፤ በንጉሡ ቤት ውስጥ የተገኘውን ሀብት ሁሉ ወሰዱ፤ ወንዶች ልጆቹንና ሚስቶቹንም ወሰዱ፡፡ ከታናሹ ልጁ ከአካዝያስ በስተቀር ምንም ልጅ አልቀረለትም፡፡
\s5
\v 18 ከዚህ ሁሉ በኋላ እግዚአብሔር ሊድን በማይችል በሽታ አንጀቱን መታው፤
\v 19 በተገቢው ጊዜ በሁለቱ ዓመት መጨረሻ ከሕመሙ የተነሳ አንጀቱ ወጣ፤ በብርቱ በሽታም ሞተ፡፡ ሕዝቡም ለእርሱ አባቶች እንዳደረገው ለክብሩ ምንም ችቦ አላበራም፡፡
\v 20 በሠላሳ ሁለት ዓመቱ ላይ መንገሥ ጀምሮ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ስምንት ዓመት ነገሠ፤ ማንም ሳያዝንለት ሞተ፡፡ በነገሥታቱ መቃብር ሳይሆን በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
\s5
\c 22
\p
\v 1 የኢየሩሳሌም ነዋሪዎችም የኢዮራምን ታናሽ ልጅ አካዝያስን በእርሱ ቦታ አነገሡት፤ ምክንያቱም ከአረቢያኖቹ ጋር ወደ ካምፑ የመጡባቸው የሽፍቶች ቡድን የእርሱን ታላላቆች ሁሉ ገድለዋቸው ስለነበር ነው፡፡ በመሆኑም የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ ነገሠ፡፡
\v 2 አካዝያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ አርባ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሁለት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱ ስም ጎቶልያ ነበረ፤ እሷም የዖምሪ ልጅ ነበረች፡፡
\v 3 እናቱ ክፉ ነገሮችን ለማድረግ መካሪው ስለነበረች እርሱም በአክዓብ ቤት መንገድ ሄደ፡፡
\s5
\v 4 ከአባቱ ሞት በኋላ ለገዛ ራሱ ጉዳት እስኪሆን የአክዓብ ቤት መካሪዎቹ ስለነበሩ የአክዓብ ቤት እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ፡፡
\v 5 ምክራቸውንም ተከተለ፤ የአራምን ንጉሥ አዛሄልን በሬማት ዘገለዓድ ሊዋጋ ከእስራኤል ንጉሥ ከአክዓብ ልጅ ከኢዮራም ጋር ሄደ፡፡ አርመናውያንም ኢዮራምን አቆሰሉት፡፡
\s5
\v 6 ኢዮራምም የአራምን ንጉሥ አዛሄልን በራማ በተዋጋ ጊዜ ካቆሰሉት ቁስል ይፈወስ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ተመለሰ፡፡ ኢዮራም ቆስሎ ስለነበር የይሁዳ ንጉሥ የኢዮራም ልጅ አካዝያስ የአክዓብን ልጅ ኢዮራምን ሊያየው ወደ ኢይዝራኤል ወረደ፡፡
\s5
\v 7 አካዝያስ ኢዮራምን በመጎብኘቱ አማካይነት እንዲጠፋ እግዚአብሔር ፈቅዶ ነበር፡፡ በመጣ ጊዜ የአክዓብን ቤት እንዲያጠፋ እግዚአብሔር የመረጠውን የናሚሴን ልጅ ኢዩን ለማጥቃት ከኢዮራም ጋር ሄደ፡፡
\v 8 ኢዩም የእግዚአብሔርን ፍርድ በአክዓብ ቤት ላይ እየፈጸመ በነበረበት ጊዜ የይሁዳን መሪዎችና አካዝያስን የሚያገለግሉትን የአካዝያስን ወንድሞች ልጆች አገኛቸው፡፡ ኢዩም ገደላቸው፡፡
\s5
\v 9 ኢዩ አካዝያስን ፈለገው፤ በሰማርያም ተሸሽጎ አገኙት፤ ወደ ኢዩም አመጡት፤ እርሱም ገደለው፡፡ ከዚያም "እግዚአብሔርን በፍጹም ልቡ የፈለገው የኢዮሳፍጥ ልጅ ነው" ብለው ቀበሩት፡፡ በመሆኑም የአካዝያስ ቤት መንግሥቱን ለመምራት ምንም የቀረ ኃይል አልነበረውም፡፡
\s5
\v 10 የአካዝያስ እናት ጎቶልያ ልጇ መሞቱን ባየች ጊዜ ተነስታ በይሁዳ ቤት ውስጥ የነገሥታቱን ዝርያ ልጆች ሁሉ ገደለች፡፡
\v 11 ነገር ግን የንጉሡ ልጅ ዮሳቤት የአካዝያስ ልጅ ኢዮአስን ከተገደሉት ከንጉሡ ልጆች መካከል ሰርቃ ወሰደችው፤ እርሱንና ሞግዚቱን በመኝታ ክፍል ውስጥ አስቀመጠቻቸው፡፡ ስለዚህ የንጉሡ የኢዮራም ልጅ የካህኑ የዮዳሄ ሚስት ዮሳቤት (የአካዝያስ እኅት ስለነበረች) ጎቶልያ እንዳትገድለው ከጎቶልያ ሸሸገችው፡፡
\v 12 ጎቶልያ በምድሪቱ ላይ ስትገዛ ሳለ እርሱ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለስድስት ዓመታት ተሸሽጎ ከእነርሱ ጋር ነበረ፡፡
\s5
\c 23
\p
\v 1 በሰባተኛውም ዓመት ዮዳሄ ውጤት ያለው ነገር አደረገ፡፡ የመቶ አለቆቹን የይሮሐምን ልጅ ዓዛርያስን፥ የይሆሐናንን ልጅ ይስማኤልን፥ የዖቤድን ልጅ ዓዛሪያስን፥ የዓዳያንም ልጅ መዕሴያን፥ የዝክሪንም ልጅ ኤሊሳፋጥን ወስዶ ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን እንዲገቡ አደረገ፡፡
\v 2 በይሁዳ ሁሉ ዞረውም ከይሁዳ ከተሞች ሁሉ ሌዋውያንንና የእስራኤልን ቤቶች አባቶች መሪዎች ሰብስበው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡
\v 3 ጉባኤውም ሁሉ ከንጉሡ ጋር በእግዚአብሔር ቤት ቃል ኪዳን አደረጉ፡፡ ዮዳሄም፦ "እነሆ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ዝርያዎች እንደተናገረው የንጉሡ ልጅ ይነግሣል" አላቸው፡፡
\s5
\v 4 "ማድረግ የሚገባችሁ ይህ ነው፤ በሰንበት ቀን ለማገልገል ከምትመጡት ከእናንተ ከካህናትና ከሌዋውያን አንድ ሦስተኛው በበሮቹ ላይ ጠባቂዎች ትሆናላችሁ፡፡
\v 5 አንድ ሦስተኛችሁ ደግሞ በንጉሡ ቤት ትሆናላችሁ፤ ሌላው አንድ ሦስተኛ በመሠረቱ በር ላይ ይሁኑ፤ ሕዝቡም ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ላይ ይሁኑ፡፡
\s5
\v 6 ከካህናቱና ከሚያገለግሉት ሌዋውያን በስተቀር ማንም ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲገባ አትፍቀዱ፤ እነርሱ ለዛሬው ሥራቸው ተለይተው ተመድበዋልና መግባት ይገባቸዋል፡፡ ሁሉም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መጠበቅ ይገባቸዋል፡፡
\v 7 ሁሉም ሰው የጦር መሣሪያውን በእጁ ይዞ ሌዋውያኑ ንጉሡን በሁሉም በኩል ሊከቡት ይገባቸዋል፡፡ ማንም ወደ ቤቱ ውስጥ ቢገባ ይገደል፡፡ ንጉሡም በሚገባበትና በሚወጣበት ጊዜ ሁሉ ከእርሱ ጋር ሁኑ፡፡
\s5
\v 8 በመሆኑም ሌዋውያኑና ይሁዳ ሁሉ በሁሉም መንገድ ካህኑ ዮዳሄ ባዘዘው መሠረት አገለገሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን በሰንበት ለማገልገል የሚገቡትንና በሰንበትም ከአገልግሎት ይወጡ የነበሩትን ሰዎች ወሰደ፤ ምክንያቱም ካህኑ ዮዳሄ የትኞቹንም የሥራ ክፍሎች አላሰናበተም ነበር፡፡
\v 9 ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የንጉሡን የዳዊትን ጦሮች፥ ትንንሽና ትልልቅ ጋሻዎች ለአለቆቹ አመጣላቸው፡፡
\s5
\v 10 ዮዳሄ እያንዳንዱ ሰው የጦር መሣሪያውን እንደያዘ ከቤተ መቅደሱ ቀኝ በኩል እስከ ቤተ መቅደሱ ግራ በኩል በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ አጠገብ ንጉሡን እንዲከቡ ሁሉንም ወታደሮች በቦታቸው አቆማቸው፡፡
\v 11 ከዚያም የንጉሡን ልጅ አውጥተው፥ ዘውዱን በላዩ ላይ ደፍተው የቃል ኪዳኑ ሕግጋት የተጸፈበትን ጥቅልል ሰጡት፡፡ ከዚያም አነገሡት፤ ዮዳሄና ልጆቹም ቀቡት፡፡ ከዚያም ፦" ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኑር!" ብለው ጮኹ፡፡
\s5
\v 12 ጎቶልያ የህዝቡን መሯሯጥና ንጉሡን ማወደስ ጫጫታ ስትሰማ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ሕዝቡ መጣች፡፡
\v 13 እነሆም ንጉሡ መግቢያው ላይ በራሱ ምሰሶ አጠገብ ቆሞ እንደነበርና አዛዦቹና መለከት ነፊዎቹ ከንጉሡ አጠገብ ቆመው እንደነበር አየች፡፡ የአገሩ ህዝብ ሁሉ ደስ እያላቸውና መለከት እየነፉ ነበር፡፡ ዘማሪዎቹም የሙዚቃ መሣሪያዎች እየተጫወቱ የውዳሴ መዝሙሮችን ይዘምሩ ነበር፡፡ ጎቶልያ ልብሷን ቀድዳ፦" አገር ከመክዳት የሚቆጠር ዓመፅ ነው! ዓመፅ ነው!" ብላ ጮኸች፡፡
\s5
\v 14 ካህኑ ዮዳሄ በሠራዊቱ ውስጥ መሪዎች የነበሩትን የመቶ አለቆች አውጥቶ፦ " ወደ ወታደሮቹ መካከል አውጡአት፤ የሚከተላትም በሰይፍ ይገደል" አላቸው፡፡ ካህኑ ፦"በእግዚአብሔር ቤት አትግደሉአት" ብሎ ነበር፡፡
\v 15 በመሆኑም ገለል ብለው ሲያሳልፏት ወደ ንጉሡ ቤት ፈረሱ በር በሚወስደው መንገድ ሄደች፤ እዚያም ገደሏት፡፡
\s5
\v 16 ከዚያም ዮዳሄ የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእርሱ፥ በሕዝቡና በንጉሡ መካከል ቃል ኪዳን አደረገ፡፡
\v 17 ሕዝቡም ሁሉ ወደ በኣል ቤት ሄደው አፈረሱት፡፡ የበኣል መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን አደቀቁ፤ የበኣል ካህንን ማታንን በእነዚያ መሠዊያዎች ፊት ገደሉት፡፡
\s5
\v 18 ዮዳሄም በሙሴ ሕግ ተጽፎ እንደነበረው በእግዚአብሔር ቤት ከደስታና ከመዝሙር ጋር የሚቃጠለውን መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ ዳዊት በእግዚአብሔር ቤት ላይ የሾማቸው ሌዋውያን ዳዊት በሰጠው መመሪያ መሠረት ከካህናቱ እጅ በታች እንዲያገለግሉ ለእግዚአብሔር ቤት ኃላፊዎችን ሾመ፡፡
\v 19 ርኩስ የሆነ ማንም በማናቸውም መንገድ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዳይገባ በበሮቹ ላይ ጠባቂዎችን አኖረ፡፡
\s5
\v 20 ዮዳሄ ከእርሱ ጋር የመቶ አለቆቹን፥ ባላባቶቹን ፥ የሕዝቡን አስተዳዳሪዎችና የአገሩንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፡፡ ንጉሡንም በኮረብታ ላይ ከነበረው ከእግዚአብሔር ቤት አወረደው፡፡ ሕዝቡም በላይኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት መጥተው ንጉሡን በመንግሥቱ ዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡
\v 21 የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አላቸው፤ ከተማይቱም ጸጥ አለች፡፡ ጎቶልያንም በሰይፍ ገድለዋት ነበር፡፡
\s5
\c 24
\p
\v 1 ኢዮስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሰባት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አርባ ዓመት ነገሠ፡፡ የቤርሳቤዋ እናቱ ስም ሳብያ ነበር፡፡
\v 2 ኢዮስያስ ካህኑ ዮዳሄ በነበረበት ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ፡፡
\v 3 ዮዳሄ ለኢዮስያስ ሁለት ሚስቶችን አጋባው፤ የወንዶችና የሴቶች ልጆች አባት ሆነ፡፡
\s5
\v 4 ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ የእግዚአብሔርን ቤት ለመጠገን ወሰነ፡፡
\v 5 ካህናቱንና ሌዋውያኑን በአንድነት ሰብስቦ ፦"በየዓመቱ ወደ ይሁዳ ከተሞች ውጡና የአምላካችሁን ለማደስ ከእስራኤል ሁሉ ገንዘብን ሰብስቡ፡፡ በፍጥነት መጀመራችሁን እርግጠኛ ሁኑ" አላቸው፡፡ ሌዋውያኑ በመጀመሪያ ምንም አላደረጉም፡፡
\s5
\v 6 በመሆኑም ንጉሡ ሊቀ ካህናቱን ጠርቶ፦"ሌዋውያኑ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ለቃል ኪዳኑ ድንኳን ድንጋጌ የእስራኤል ጉባኤ የተጣለባቸውን ግብር ከይሁዳና ከኢየሩሳሌም እንዲያስመጡ ለምን አላደረግሃቸውም?" አለው፡፡
\v 7 የዚያች ክፉ ሴት የጎቶልያ ልጆች የእግዚአብሔርን ቤት አፍርሰው እና የእግዚአብሔርንም ቤት የተቀደሱ ነገሮች ሁሉ ለበኣል ሰጥተው ነበር፡፡
\s5
\v 8 በመሆኑም ንጉሡ ስለአዘዘ የገንዘብ ሳጥን ሰርተው በእግዚአብሔር ቤት መግቢያ በስተውጪ አስቀመጡት፡፡
\v 9 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በምድረ በዳ በእስራኤል ላይ የጣለባቸውን ግብር ለእግዚአብሔር እንዲያመጡ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ሁሉ አዋጅ ነገሩ፡፡
\v 10 መሪዎቹ ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ደስ ብሎአቸው ገንዘብ አመጡ፤ እስኪሞሉትም ድረስ በገንዘብ ሳጥኑ ውስጥ አስቀመጡት፡፡
\s5
\v 11 የገንዘብ ሳጥኑ በሌዋውያኑ እጅ ወደ ንጉሡ ሹማምንት በሚመጣበት ጊዜ ሁሉና ብዙ ገንዘብ እንዳለበት ባዩ ጊዜ ሁሉ የንጉሡ ጸሐፊና የሊቀ ካህናቱ ሹም መጥተው ከገንዘብ ሳጥኑ ገንዘቡን አውጥተው በመውሰድ ሳጥኑን ወደ ሥፍራው ይመልሱት ነበር፡፡ ከፍ ያለ መጠን ያለው ገንዘብ በመሰብሰብ ይህንንም ዕለት ዕለት ያደርጉት ነበር፡፡
\v 12 ንጉሡና ዮዳሄ በእግዚአብሔር ቤት የማገልገል ሥራ ለሚሠሩት ሰዎች ገንዘቡን ይሰጡ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቤት ለሚያድሱት ድንጋይ ጠራቢዎችና አናጢዎች እንዲሁም የብረትና የነሃስ ሥራ የሚሠሩትን ቀጥረው ያሠሩበት ነበር፡፡
\s5
\v 13 በመሆኑም ሠራተኞቹ አብዝተው ሠሩ፤ የጥገናውም ሥራ በእጃቸው ተከናወነ፤ የእግዚአብሔርንም ቤት በመጀመሪያ ንድፉ አቁመው አጠናከሩት፡፡
\v 14 በጨረሱም ጊዜ የተረፈውን ገንዘብ ወደ ንጉሡና ዮዳሄ አመጡት፡፡ ይህ ገንዘብ የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ፥ ለአገልግሎትና መሥዋዕት ለማቅረብ የሚሆኑ ማንኪያዎችንና የወርቅና የብር ዕቃዎች ለማሟላት ጥቅም ላይ ዋለ፡፡ በዮዳሄ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚቃጠል መሥዋዕት ባለማቋረጥ ያቀርቡ ነበር፡፡
\s5
\v 15 ዮዳሄም ሸመገለ፤ ዕድሜም ጠግቦ ሞተ፡፡ በሚሞትበት ጊዜ ዕድሜው መቶ ሠላሳ ዓመት ነበር፡፡
\v 16 በእስራኤልም ለእግዚአብሔርና ለእግዚአብሔር ቤት መልካም ስላደረገ በነገሥታቱ መካከል በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
\s5
\v 17 ዮዳሄ ከሞተ በኋላ የይሁዳ መሪዎች መጥተው ለንጉሡ ክብርን ሰጡት፡፡ ንጉሡም አዳመጣቸው፡፡
\v 18 የአባቶቻቸውን አምላክ የእግዚአብሔርን ቤት ትተው የማምለኪያ ዐፀዶችንና ጣዖታቱን አመለኩ፡፡በዚህም ኃጢአታቸው ምክንያት የእግዚአብሔር ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ መጣ፡፡
\v 19 ሆኖም ግን ወደ እግዚአብሔር ወደ ራሱ እንደገና እንዲያመጧቸው ነቢያትን ይልክላቸው ነበር፤ ነቢያቱም በሕዝቡ ላይ ይመሰክሩባቸው ነበር፤ እነርሱ ግን ለመስማት እምቢ አሉ፡፡
\s5
\v 20 የእግዚአብሔር መንፈስ በካህኑ በዮዳሄ ልጅ በዘካርያስ ላይ መጣ፤ እርሱም ከሕዝቡ በላይ ቆሞ፦"እግዚአብሔር ይህንን ይላል፤ 'የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ለምን ትተላለፋላችሁ? መልካም ነገር ሊሆንላችሁ አይችልም፡፡ እግዚአብሔርን ስለተዋችሁ እርሱም ትቶአችኋል'" አላቸው፡፡
\v 21 እነርሱ ግን አሴሩበት፤ በንጉሡ ትዕዛዝም በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ውስጥ በድንጋይ ወገሩት፡፡
\v 22 በዚህ ሁኔታ ንጉሡ ኢዮአስ የዘካርያስ አባት ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት ችላ አለ፡፡ ይልቁንም የዮዳሄን ልጅ ገደለ፡፡ ዘካርያስም በሚሞትበት ጊዜ፦" እግዚአብሔር ይህንን ይየው፤ ይጠይቃችሁም" አለ፡፡
\s5
\v 23 በዓመቱ መጨረሻም የአራም ሠራዊት ሊያጠቁት በኢዮአስ ላይ መጡበት፡፡ ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፤ የሕዝቡን መሪዎች ሁሉ ገደሉ፤ ከእነርሱ የወሰዱትንም ምርኮ ሁሉ ወደ ደማስቆ ንጉሥ ላኩ፡፡
\v 24 የሶርያውያንም ሠራዊት የመጡት ከትንሽ ሠራዊት ጋር ነበር፤ ነገር ግን ይሁዳ የአባቶቻቸውን አምላክ ከመተዋቸው የተነሳ እግዚአብሔር እጅግ ታላቅ በነበረው ሠራዊት ላይ ድልን ሰጣቸው፡፡ በዚህ መንገድ የሶርያውያን ሠራዊት በኢዮአስ ላይ ፍርድን አመጡበት፡፡
\s5
\v 25 ሶርያውያን ከሄዱ በኋላ ኢዮአስ ክፉኛ ቆስሎ ነበር፡፡ ከካህኑ ከዮዳሄ ልጆች ግድያ የተነሳ የገዛ አገልጋዮቹ አሲረውበት ነበር፡፡ በአልጋው ላይ ገደሉት፤ እርሱም ሞተ፤ በነገሥታቱ መቃብር ሳይሆን በዳዊት ከተማ ቀበሩት፡፡
\v 26 ያሴሩበትም ሰዎች የአሞናዊቷ የሰምዓት ልጅ ዛባድ፥ የሞዓባዊቷ የሰማሪት ልጅ ዮዛባት ነበሩ፡፡
\s5
\v 27 የልጆቹ ነገርና ስለ እርሱ የተነገሩት ዋና ዋና ትንቢቶች እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቤት እንደገና መገንባቱ እነሆ በነገሥታቱ መጽሐፍ ማብራሪያ ተጽፈዋል፡፡ ልጁም አሜስያስ በእርሱ ቦታ ነገሠ፡፡
\s5
\c 25
\p
\v 1 አሜስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ፡፡ የኢየሩሳሌሟ እናቱ ስም ዮዓዳን ነበር፡፡
\v 2 በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን በፍጹምና በተሰጠ ልብ አይደለም፡፡
\s5
\v 3 መንግሥቱ በሚገባ በጸናለት ጊዜ አባቱን ንጉሡን የገደሉትን አገልጋዮቹን ገደላቸው፡፡
\v 4 በሙሴ ሕግ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት፦"አባቶች ስለ ልጆች መሞት አይገባቸውም፤ ልጆችም ስለ አባቶች መሞት አይገባቸውም፡፡ ይልቁንም ማንኛውን ሰው ለራሱ ኃጢአት መሞት ይገባዋል" በማለት እግዚአብሔር እንዳዘዘው በማድረግ የገዳዮቹን ልጆች አልገደለም፡፡
\s5
\v 5 በተጨማሪም አሜስያስ ይሁዳን በአንድነት ሰበሰበ፤ ይሁዳንና ቢንያምን ሁሉ በየአባቶቻቸው ቤቶች ከሺህ አለቆችና ከመቶ አለቆች በታች መዘገባቸው፡፡ ከሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉትን ቆጠረ፤ ወደ ጦርነት ሊሄዱ የሚችሉ፥ ጋሻና ጦርም ሊይዙ የሚችሉ ሦስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎች አገኘ፡፡
\v 6 ከእስራኤልም መቶ ሺህ ጦረኛ ሰዎች በመቶ መክሊት ብር ቀጠረ፡፡
\s5
\v 7 ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔር ሰው ወደ እርሱ መጥቶ፦"ንጉሥ ሆይ እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር፥ ከኤፍሬምም ሰዎች ከአንዳቸውም ጋር አይደለምና የእስራኤል ሠራዊት ከአንተ ጋር አይሂዱ፡፡
\v 8 ነገር ግን ብትሄድ በጦርነትም ደፋርና ብርቱ ብትሆን እግዚአብሔር በጠላት ፊት ይጥልሃል፤ ምክንያቱም የመርዳት ኃይል እና የመጣል ኃይል ያለው እግዚአብሔር ነው" አለው፡፡
\s5
\v 9 አሜስያስም ለእግዚአብሔር ሰው፦" ለእስራኤል ሠራዊት ስለሰጠሁት መቶ መክሊትስ ምን እናደርጋለን?" አለው፡፡ የእግዚአብሔር ሰውም፦ "እግዚአብሔር ከዚያ እጅግ የበለጠ ሊሰጥህ ይችላል" ብሎ መለሰለት፡፡
\v 10 በመሆኑም አሜስያስ ከኤፍሬም ወደርሱ የመጡትን ሠራዊት ለይቶአቸው እንደገና ወደ ቤት ላካቸው፡፡ ስለዚህም በይሁዳ ላይ ቁጣቸው እጅግ ነደደ፤ ወደ ቤትም በጋለ ቁጣ ተመለሱ፡፡
\s5
\v 11 አሜስያስም በርትቶ ሕዝቡን አውጥቶ ወደ ጨው ሸለቆ መራቸው፤ በዚያም አሥር ሺህ የሴይርን ሰዎች ድል ነሳቸው፡፡
\v 12 የይሁዳም ሠራዊት አሥር ሺህ ሰዎች ከነሕይወታቸው ማርከው ወሰዱ፡፡ ወደ ኮረብታው ጫፍ ላይ ወሰዱአቸውና ሁሉም እስኪንኮታኮቱ ድረስ ከዚያ ወደ ታች ወረወሩአቸው፡፡
\s5
\v 13 ነገር ግን አሜስያስ ከእርሱ ጋር ወደ ጦርነት እንዳይሄዱ ያስመለሳቸው የሠራዊት ሰዎች ከሰማርያ እስከ ቤትሖሮን በይሁዳ ከተሞች ላይ ጥቃት አደረሱ፤ ከሕዝቡም ሦስት ሺህ ሰዎች መትተው እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰዱ፡፡
\s5
\v 14 አሜስያስ የኤዶምያስን ሰዎች ገድሎ ከተመለሰ በኋላ የሴይርን ሰዎች ጣኦታት አምጥቶ የገዛ ራሱ አማልክት እንዲሆኑ አቆማቸው፡፡ በፊታቸውም ሰገደ፤ እጣንም አጠነላቸው፡፡
\v 15 ስለዚህም የእግዚአብሔር ቁጣ በአሜስያስ ላይ ነደደ፡፡ አንድ ነቢይ ልኮ፦"የገዛ ሕዝባቸውን እንኳን ከአንተ እጅ ያላዳኑትን የአሕዛብን አማልክት ለምን ፈለግሃቸው?" አለው፡፡
\s5
\v 16 ነቢዩም ከእርሱ ጋር እየተነጋገረ እያለ ንጉሡ፦"የንጉሡ አማካሪ እንድትሆን አድርገንሃል? አቁም! ለምን መገደል ይገባሃል?" አለው፡፡ ነቢዩም ንግግሩን አቁሞ፦"ይህንን ድርጊት በመፈጸምህና ምክሬን ባለመስማትህ እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንደወሰነ አውቃለሁ" አለ፡፡
\s5
\v 17 ከዚያም የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ ከአማካሪዎቹ ጋር ተማክሮ፦" ና በጦርነት ፊት ለፊት እንጋጠም" ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ኢዮአካዝ ልጅ ወደ ኢዮአስ ላከ፡፡
\s5
\v 18 የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮአስ መልዕክተኞችን ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ አሜስያስ መልሶ ላከና፦"በሊባኖስ የነበረ አንድ ኩርንችት፦ 'ልጅህን ለልጄ ሚስት አድርገህ ስጠው' ብሎ ወደ ሊባኖስ ዝግባ መልዕክት ላከ፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ መንገድ ሲያልፍ ኩርንችቱን ረገጠው፡፡
\v 19 አንተም ፦'እነሆ ኤዶምያስን መትቻለሁ' ብለህ ልብህ ከፍ ከፍ ብሏል፡፡ በድልህ ኩራ፤ ነገር ግን በቤትህ ተቀመጥ፤ አንተና ካንተ ጋር ይሁዳ ሁሉ ለምን በራስህ ላይ ችግር ፈጥረህ ትወድቃለህ?" አለው፡፡
\s5
\v 20 የይሁዳ ሰዎች ከኤዶምያስ አማልክት ምክር ከመፈለጋቸው የተነሳ የይሁዳን ሰዎች ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ዘንድ ይህ ከእግዚአብሔር ታስቦ ነበርና አሜስያስ ሊሰማ አልፈለገም፡፡
\v 21 ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮአስ ጥቃት አደረሰ፤ እርሱና የይሁዳ ንጉሥ አሜስያስ የይሁዳ በነበረችው በቤትሳሚስ ፊት ለፊት ተጋጠሙ፡፡
\v 22 ይሁዳም በእስራኤል ፊት ተመታ፤ እያንዳንዱም ሰው ወደ ቤቱ ሸሸ፡፡
\s5
\v 23 የእስራኤል ንጉሥ ኢዮአስ የይሁዳን ንጉሥ የአካዝያስን ልጅ አሜስያስን በቤትሳሚስ ማረከው፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም ይዞት መጣና ከኤፍሬም በር እስከ ማዕዘኑ በር ድረስ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አራት መቶ ክንድ ርቀት ያህል አፈረሰው፡፡
\v 24 ወርቁንና ብሩን ሁሉ፥ በእግዚአብሔርም ቤት ከዖቤድኤዶም ጋር የነበሩትን ዕቃዎች በሙሉ እንዲሁም በንጉሡ ቤት የነበሩትን ዋጋ ያላቸውን ነገሮች ከታገቱት ጋር ወስዶ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፡፡
\s5
\v 25 የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ፥ ከእስራኤል ንጉሥ ከኢዮአካዝ ልጅ ከኢዮአስ ሞት በኋላ አሥራ አምስት ዓመት ኖረ፡፡
\v 26 አሜስያስን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ የተጻፉ አይደለምን?
\s5
\v 27 አሜስያስም እግዚአብሔርን ከመከተል ከራቀበት ጊዜ አንስቶ በኢየሩሳሌም ሴራ ያሴሩበት ጀመር፡፡ ወደ ለኪሶም ሸሸ፤ ነገር ግን ከበስተኋላው ሰዎች ላኩበት፤ እነርሱም በዚያ ገደሉት፡፡
\v 28 በፈረስም ጭነው መልሰው አመጡት፤ በይሁዳም ከተማ ከአባቶቹ ጋር ቀበሩት፡፡
\s5
\c 26
\p
\v 1 የይሁዳም ሕዝብ ሁሉ አሥራ ስድስት ዓመት የነበረውን ዖዝያንን ወስደው በአባቱ በአሜስያስ ቦታ አነገሡት፡፡
\v 2 ኤላትን እንደገና የገነባትና ወደ ይሁዳ ወደቀድሞ ይዞታዋ የመለሳት እርሱ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ንጉሡ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፡፡
\v 3 ዖዝያን መንገሥ በጀመረ ጊዜ አሥራ ስድስት ዓመቱ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌምም ሃምሳ ሁለት ዓመት ነገሠ፡፡ የእናቱም ስም ይኮልያ ነበር፤ የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች፡፡
\s5
\v 4 በሁሉም ነገር የአባቱን የአሜስያስ ምሳሌነት በመከተል በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፡፡
\v 5 እግዚአብሔርን መታዘዝ ባስተማረው በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ለመፈለግ በልቡ ቆርጦ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር የተሳካለት አደረገው፡፡
\s5
\v 6 ዖዝያን ወጥቶ ከፍልስጤማውያን ጋር ተዋጋ፡፡ የጌትንና የየብናንና የአዛጦንን የከተማ ቅጥሮች አፈረሰ፤ በአዛጦን አገርና በፍልስጤማውያን መካከል ከተሞችን ገነባ፡፡
\v 7 እግዚአብሔርም በፍልስጤማውያን ላይ፥ በጉርበኣል በሚኖሩ ዓረባውያን ላይና በምዑናውያን ላይ ረዳው።
\v 8 አሞናውያንም ለዖዝያን ግብር ይከፍሉ ነበር፤ እጅግ ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ ዝናውም እስከ ግብጽ መግቢያ ድረስ ወደ ሌሎች አገሮች ተሰራጨ።
\s5
\v 9 በተጨማሪም ዖዝያን በኢየሩሳሌም በማዕዘኑ በር፥ በሸለቆው በርና በቅጥሩ መዞሪያ ላይ ረጃጅም ማማዎችን ገንብቶ መሸጋቸው።
\v 10 በቆላው እንዲሁም በደጋው እጅግ ብዙ ከብቶች ስለነበሩት በምድረ በዳው የመጠባበቂያ ማማዎችን ሠራ፤ በርካታ ጉድጓዶችንም ቆፈረ። እርሻ ይወድ ስለነበርም በኮረብታማው አገርና በፍሬያማው መስክ ውስጥ ገበሬዎችና የወይን አትክልተኞች ነበሩት።
\s5
\v 11 በተጨማሪም ዖዝያን በጸሐፊው በይዒኤልና ከንጉሡ አለቆች በአንዱ በሐናንያ ሥልጣን ስር በነበረው በመዕሤያ በሚቆጠሩበት ቁጥር መሰረት የተደራጁ በቡድን ወደ ጦርነት ይሄዱ የነበሩ የተዋጊ ሰዎች ሠራዊት ነበሩት።
\v 12 የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች የተዋጊ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።
\v 13 ከበታቻቸውም ንጉሡን ከጠላቱ ለመጠበቅ የሚረዳ በብርቱ ኃይል የሚዋጋ የሦስት መቶ ሰባት ሺህ እምስት መቶ ሰዎች ሠራዊት ነበር።
\s5
\v 14 ዖዝያንም ለሠራዊቱ ሁሉ ጋሻዎች፥ ጦሮች፥ የራስ ቁሮች፥ ጥሩሮች፥ ቀስቶችና የሚወነጭፉአቸውን ድንጋዮች አዘጋጅቶላቸው ነበር።
\v 15 በኢየሩሳሌምም ፍላጻዎችንና ትልልቅ ድንጋዮችን ለመወርወር በግንብና በመታኮሻ ቅጥር ላይ እንዲሆኑ የተካኑ ባለሙያዎች የፈለሰፏቸውን ማንቀሳቀሻ ሞተሮች ገነባ። እጅግ እስኪበረታም ድረስ እግዚአብሔር በብዙ ረድቶታልና ዝናው እስከ ሩቅ ቦታዎች ተሰራጨ።
\s5
\v 16 ነገር ግን ዖዝያን በበረታ ጊዜ እስኪበላሽ ድረስ ልቡ ታበየ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ በዕጣን መሠዊያው ላይ ዕጣን በማጠኑ አምላኩን እግዚአብሔርን በደለ።
\v 17 ካህኑም ዓዛርያስ ከእርሱም ጋር ደፋር ሰዎች የነበሩ ሰማንያ የእግዚአብሔር ካህናት ተከትለውት ገቡ።
\v 18 ንጉሡንም ዖዝያንን ተቃውመው፦"ዖዝያን ሆይ፦ ለእግዚአብሔር ዕጣን ማጠን ለእግዚአብሔር ለተቀደሱት ለካህናቱ ለአሮን ልጆች የተሰጠ እንጂ ዕጣን ማጠን ለአንተ አይደለም። ተላልፈሃልና ከቅዱሱ ቦታ ውጣ። በዚህ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ላንተ ምንም ክብር አይሆንልህም" አሉት።
\s5
\v 19 ዖዝያንም ተቆጣ። ዕጣን የሚያጥንበትን ጥና በእጁ ይዞ ነበር። በካህናቱ ላይ በተቆጣ ጊዜ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በዕጣኑ መሠዊያ አጠገብ በካህናቱ ፊት ግንባሩ ላይ ለምጽ ወጣበት።
\v 20 ዋናው ካህንና ካህናቱ ሁሉ ተመለከቱት፤ እነሆ ግንባሩ ላይ ለምጻም ሆኖ ነበር። በፍጥነትም ከዚያ ቦታ አስወጡት። በእርግጥም እግዚአብሔር በለምጽ መትቶት ስለነበር እርሱም ለመውጣት ቸኮለ።
\s5
\v 21 ንጉሡም ዖዝያን እስከሚሞትበት ቀን ድረስ ለምጻም ነበረ፤ ለምጻም በመሆኑም ከእግዚአብሔር ቤት ተገልሎ ስለነበር ከሰዎች ርቆ በተለየ ቤት ይኖር ነበር። ልጁም ኢዮአታም በንጉሡ ቤት ላይ የበላይ ሆኖ የምድሩን ሕዝብ ይገዛ ነበር።
\s5
\v 22 ዖዝያንን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች የመጀመሪያውና የመጨረሻው የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ በጻፈው ውስጥ ይገኛሉ።
\v 23 ዖዝያንም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ "ለምጻም ነው" ብለውም ከአባቶቹ ጋር በነገሥታቱ መቃብር ሥፍራ ቀበሩት።
\s5
\c 27
\p
\v 1 ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ። የእናቱም ስም ኢየሩሳ ነበር፤ እርሷም የሳዶቅ ልጅ ነበረች።
\v 2 በሁሉም ነገር የአባቱን የዖዝያንን ምሳሌ ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ። ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከመግባትም ተቆጠበ። ሕዝቡ ግን ገና በክፉ መንገድ ይሄዱ ነበር።
\s5
\v 3 የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም ኮረብታ ላይ እጅግ ብዙ የግንባታ ሥራዎችን ሠራ።
\v 4 በተጨማሪም በኮረብታማው የይሁዳ አገር ላይ ከተሞችን፥ በደኖቹ ውስጥ ደግሞ አምባዎችንና ማማዎችን ገነባ።
\s5
\v 5 ከአሞንም ሕዝብ ንጉሥ ጋር ተዋግቶ አሸነፋቸው። በዚያው ዓመት የአሞን ልጆች አንድ መቶ መክሊት ብር፥ አሥር ሺህ መስፈሪያ ስንዴ፥ አሥር ሺህ መስፈሪያ ገብስ ሰጡት። የአሞን ሕዝብ በሁለተኛውና በሦስተኛውም ዓመት ተመሳሳዩን ያህል ሰጡት።
\s5
\v 6 በመሆኑም ኢዮአታም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት በጽናት ስለተራመደ ብርቱ ሆነ።
\v 7 ኢዮአታምን በተመለከተ ሌሎቹ ነገሮች ጦርነቶቹ ሁሉና መንገዱ እነሆ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
\s5
\v 8 ኢዮአታም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ለአሥራ ስድስት ዓመታት ነገሠ።
\v 9 ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት። ልጁም አካዝ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\c 28
\p
\v 1 አካዝ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ ዓመቱ ነበረ፤ በኢየሩሳሌም አሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ። ዝርያው ዳዊት እንዳደረገው በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አላደረገም።
\v 2 ይልቁንም በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ሄደ፤ ለበኣሊምም ከብረት ቀልጠው የተሠሩ ምስሎችን ሠራ።
\s5
\v 3 በተጨማሪም በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ዕጣን ዐጠነ፤ እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ያሳደዳቸውን ሕዝቦች ክፉ ልማድ ተከትሎ ልጆቹን እንደሚቃጠል መሥዋዕት በእሳት ውስጥ አሳለፋቸው።
\v 4 በኮረብታው መስገጃዎች፥ በኮረብቶች ላይ እና በለመለመው ዛፍ ሁሉ በታች መስዋዕት ይሰዋና ዕጣን ያጥን ነበር።
\s5
\v 5 ስለዚህ የአካዝ አምላክ እግዚአብሔር ለሶርያ ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው። ሶርያውያንም ድል አደረጉት፤ የብዙ እስረኞችን ስብስብ ከእርሱ ወስደው ወደ ደማስቆ አመጡአቸው። አካዝ ለእስራኤልም ንጉሥ እጅ ተላልፎ ተሰጥቶ ነበር፤ እርሱም በታላቅ ግድያ አሸነፈው።
\v 6 የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመተዋቸው የተነሳ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ በአንድ ቀን ከይሁዳ ሁሉም ደፋር የሆኑ አንድ መቶ ሃያ ሺህ ወታደሮችን ገደለ።
\s5
\v 7 ኤፍሬማዊው ኃይለኛ ሰው ዝክሪ የንጉሡን ልጅ መዕሤያንና የቤተ መንግሥቱን ባለሥልጣን ዓዝሪቃምን ለንጉሡ በማዕረግ ሁለተኛ የነበረውን ሕልቃናን ገደለ።
\v 8 የእስራኤል ሠራዊት ከዘመዶቻቸው ሁለት መቶ ሺህ ሚስቶች፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ምርኮ አድርገው ወሰዱ። ወደ ሰማሪያም ተሸክመው ያመጡትን እጅግ ብዙ ምርኮም ወሰዱ።
\s5
\v 9 ነገር ግን አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ በዚያ ነበረ፤ ስሙም ዖዴድ ነበር። ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ሠራዊት ለመገናኘት ወጣ።" የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ስለተቆጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው። እናንተ ግን ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው።
\v 10 አሁንም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ወንዶችና ሴቶች እንደ ባሪያዎቻችሁ አድርጋችሁ ልትይዟቸው ታስባላችሁ። በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ላይ በገዛ ራሳችሁ ኃጢአት በደለኞች አይደላችሁምን?
\v 11 እንግዲያውስ አሁን ስሙኝ፤ የእግዚአብሔር የጋለ ቁጣ በእናንተ ላይ ስለሆነ ከገዛ ወንድሞቻችሁ የወሰዳችኋቸውን እስረኞች መልሳችሁ ስደዱ" አላቸው።
\s5
\v 12 ከዚያም የተወሰኑ የኤፍሬም ሰዎች መሪዎች የዮሐናን ልጅ ዓዛርያስ፥ የምሺሌሞትም ልጅ በራክያ፥ የስሎምም ልጅ ይሒዝቅያ፥ የሐድላይም ልጅ ዓሜሳይ ከጦርነቱ ተመልሰው የመጡትን ተቃወሙአቸው።
\v 13 "መተላለፋችን ታላቅ ስለሆነና በእስራኤል ላይ የጋለ ቁጣ ስላለባት በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት የሚሆንብንን ነገር ልታመጡብን፥ ኃጢአታችንንና መተላለፋችንን ልትጨምሩብን ስላሰባቸሁ እስረኞቹን እዚህ ልታመጧቸው አይገባችሁም" አሏቸው።
\s5
\v 14 የታጠቁት ሰዎችም እስረኞቹንንና ምርኮውን በመሪዎቹና በጉባኤው ሁሉ ፊት ተዉአቸው።
\v 15 በስማቸው የተመደቡትም ሰዎች ተነስተው እስረኞቹን ወስደው ከመካከላቸው እርቃናቸውን የነበሩትን ሁሉ ከተማረከው ልብስ አለበሷቸው። አጎናጸፉአቸው፤ ጫማም አደረጉላቸው። የሚበሉትን ምግብና የሚጠጡትን ሰጡአቸው። ቁስላቸውን አከሙላቸው፤ የደከሙትንም በአህዮች ላይ አስቀመጧቸው። የዘንባባ ከተማ ተብላ በምትጠራዋ ኢያሪኮ ወዳሉት ቤተሰቦቻቸው መልሰው ወሰዷቸው። ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሱ።
\s5
\v 16 በዚያን ጊዜ ንጉሥ አካዝ እንዲረዱት እንዲጠይቋቸው ወደ አሦርያ ነገሥታት መልዕክተኞችን ላከ።
\v 17 የኤዶምያስ ሰዎች አንድ ጊዜ ደግመው መጥተው ይሁዳን በማጥቃት እስረኞችን ይዘው ወስደው ነበር።
\v 18 ፍልስጤማውያንም የቆላውን ከተሞች እና የይሁዳን ደቡባዊ ክልሎች ወርረው ነበር። ቤት ሳሚስንና ኤሎንን ፥ ግዴሮትንም፥ ሦኮን ከነመንደርዎቿ፥ ተምናን ከነመንደርዎቿ እና ጊምዞን ከነመንደርዎቿ ወስደው ነበር። በእነዚያ ቦታዎችም ውስጥ ለመኖር ሄደው ነበር።
\s5
\v 19 በይሁዳ ክፉ ስላደረገና እግዚአብሔርንም እጅግ በጣም ስለበደለ ከእስራኤል ንጉሥ ከአካዝ የተነሳ እግዚአብሔር ይሁዳን ዝቅ ዝቅ አድርጎ ነበር።
\v 20 የአሦርም ንጉሥ ቴልጌልፌልሶር አካዝን በማበርታት ፈንታ መጥቶ አስጨንቆት ነበር።
\v 21 ለሦርያ ነገሥታት የከበሩትን ነገሮች ለመስጠት አካዝ የእግዚአብሔርን ቤት እና የንጉሡንና የመሪዎቹን ቤቶች ዘርፎ ነበር፤ ነገር ግን ይህ አልጠቀመውም።
\s5
\v 22 ይኸው ንጉሥ አካዝ በመከራው ጊዜ በእግዚአብሔር ላይ ይበልጥ ኃጢአት ሠራ።
\v 23 ድል ላደረጉት አማልክት ለደማስቆ አማልክት መስዋዕት አቀረበ። " የሦርያ ነገሥታት አማልክት እነርሱን ስለረዷቸው መስዋዕት ባቀርብላቸው እኔንም ይረዱኝ ይሆናል" አለ። ነገር ግን ለእርሱና ለእስራኤል ሁሉ ውድመት ሆኑ።
\s5
\v 24 አካዝም የእግዚአብሔርን ቤት እቃዎች ሁሉ በአንድ ላይ ሰብስቦ ሰባበራቸው። የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ዘጋ፤ ለራሱም በኢየሩሳሌም በየማዕዘኑ ሁሉ መሰዊያዎችን ሠራ።
\v 25 በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ለሌሎች አማልክት መሥዋዕት የሚቃጠልባቸው መስገጃዎችን ሠራ፤ በዚህ መንገድ የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔርን ለቁጣ ቀሰቀሰ።
\s5
\v 26 የአካዝ የተቀሩት ድርጊቶቹና መንገዶቹ ሁሉ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።
\v 27 አካዝም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በከተማይቱ በኢየሩሳሌምም ቀበሩት፤ ነገር ግን ወደ እስራኤል ነገሥታት መቃብር አላስገቡትም። ልጁ ሕዝቅያስ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ሕዝቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ነገሠ። የእናቱ ስም አቡ ነበር፤ የዘካርያስ ልጅ ነበረች።
\v 2 በማንኛውም ነገር የዝርያውን የዳዊትን ምሳሌ ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ።
\s5
\v 3 በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት በመጀመሪያው ወር የእግዚአብሔርን ቤት በሮች ከፈተ፤ አደሳቸውም።
\v 4 ካህናቱንና ሌዋውያኑን አምጥቶ በምሥራቅ በኩል ባለው አደባባይ ላይ በአንድነት ሰበሰባቸው።
\v 5 " እናንተ ሌዋውያን ሆይ ስሙኝ! ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሱ፤ የአባቶቻችሁን አምላክ የእግዚአብሔርንም ቤት ቀድሱ፤ ከተቀደሰው ሥፍራም ርኩሱን ነገር ሁሉ አስወግዱ" አላቸው።
\s5
\v 6 አባቶቻችን ሕጉን ስለተላለፉና በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር ስላደረጉ፥ እርሱንም ትተውታል፤ ፊታቸውንም እግዚአብሔር ከሚኖርበት ሥፍራ መልሰዋል፤ ጀርባቸውንም ሰጥተውታል።
\v 7 የበሮቹንም በረንዳዎች ዘግተዋል፤ መብራቶቹንም አጥፍተዋል። ለእስራኤል አምላክ በተቀደሰው ሥፍራ እጣን አላጠኑም ወይም የሚቃጠለውንም መስዋዕት አላቀረቡም።
\s5
\v 8 ስለዚህ የእግዚአብሔር ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ወረደ፤ በገዛ ራሳችሁ ዓይኖች ማየት እንደምትችሉት ለሽብር፥ ለድንጋጤና ለመዘበቻም ማረፊያ አደረጋቸው።
\v 9 ለዚህ ነው አባቶቻችን በሰይፍ የወደቁት፤ ለዚህም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ሚስቶቻችንም በምርኮ ውስጥ አሉ።
\s5
\v 10 አሁንም የጋለ ቁጣው ከእኛ እንዲመለስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ለማድረግ በልቤ አስቤአለሁ።
\v 11 ልጆቼ እግዚአብሔር በፊቱ ትቆሙ፥ ታመልኩትና፥ አገልጋዮቹ ልትሆኑና ዕጣንን ልታጥኑለት ስለመረጣችሁ አሁን ታካች አትሁኑ።
\s5
\v 12 ከዚያም ሌዋውያኑ የቀዓት ሰዎች የአሚሳ ልጅ መሐትና የዓዛርያስ ልጅ ኢዮኤል፥ የሜራሪ ሰዎች የአብዲ ልጅ ቂስና የይሃሌልኤል ልጅ ዓዛርያስ፥ የጌድሶን ሰዎች የዛማት ልጅ ዮአክና የዮአክ ልጅ ዔድን፥
\v 13 የኤሊጸፋንም ልጆች ሺምሪና ይዒኤል፥ የአሳፍም ልጆች ዘካርያስና መታንያ፥
\v 14 የኤማንም ልጆች ይሒኤልና ሰሜኢ፥ የኤዶታምም ልጆች ሸማያና ዑዝኤል ተነሡ።
\s5
\v 15 ወንድሞቻቸውን ሰብስበው ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀደሱ፤ የእግዚአብሔርን ቃል በመከተል ንጉሡ እንዳዘዘው የእግዚአብሔርን ቤት ለማንጻት ወደ ውስጥ ገቡ።
\v 16 ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቤት ለማንጻት ወደ ውስጠኛው ክፍል ገቡ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ያገኙትን ቆሻሻ ነገር ሁሉ ወደ ቤቱ አደባባይ አወጡት። ሌዋውያንም ወደ ቄድሮን ዥረት ተሸክመው ሊወስዱት አወጡት።
\v 17 ቤቱን ለእግዚአብሔር መቀደስን በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ጀምረው በወሩ በስምንተኛው ቀን ወደ እግዚአብሔር በረንዳ ደረሱ። የእግዚአብሔርን ቤት በስምንት ቀናት ቀደሱ። በመጀመሪያው ወር በአሥራ ስድስተኛው ቀን ጨረሱ።
\s5
\v 18 ከዚያም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ቤተ መንግሥት ውስጥ ገብተው፦" የእግዚአብሔርን ቤት፥ የሚቃጠል መስዋዕት የሚቀርብበትን መሠውያ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር እና የመገኘቱን ሕብስት ገበታ ከዕቃዎቹ ሁሉ ጋር አንጽተናል።
\v 19 በተጨማሪም ንጉሥ አካዝ ነግሦ በነበረበት ጊዜ በመተላለፍ የወረወራቸውን ዕቃዎች ሁሉ አዘጋጅተን ለእግዚአብሔር ቀድሰናል። እነሆ በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት ለፊት ይገኛሉ" አሉት።
\s5
\v 20 ከዚያም ንጉሡ ሕዝቅያስ በማለዳ ተነስቶ የከተማዋን መሪዎች ሁሉ ሰበሰበ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ወጣ።
\v 21 ለመንግሥቱ፥ ለቤተ መቅደሱና ለይሁዳ የኃጢአት መስዋዕት አድርገው ሰባት ወይፈኖች፥ ሰባት አውራ በጎችና ሰባት የበግ ጠቦቶችና ሰባት ወንድ ፍየሎች አመጡ። ካህናቱን የአሮንን ልጆች በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ እንዲያቀርቧቸው አዘዛቸው።
\s5
\v 22 በመሆኑም ወይፈኖቹን አረዷቸውና ካህናቱ ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ላይ ረጩት። አውራ በጎቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት፤ የበግ ጠቦቶቹንም አረዱ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ረጩት።
\v 23 ለኃጢአት መስዋዕት ወንድ ፍየሎቹን በንጉሡና በጉባዔው ፊት አመጧቸው፤ እጃቸውንም ጫኑባቸው።
\v 24 ካህናቱም አረዷቸው፤ ንጉሡም ለእስራኤል ሁሉ የሚቃጠል መስዋዕትና የኃጢአት መስዋዕት ሊደረግ እንደሚገባው አዝዞ ስለነበር ለእስራኤል ሁሉ ለማስተሰረይ በመሠዊያው ላይ ደማቸውን የኃጢአት መስዋዕት አደረጉት።
\s5
\v 25 ሕዝቅያስ ትዕዛዙ በነቢያቱ አማካይነት ከእግዚአብሔር ስለ ነበር በዳዊትና በንጉሡ ባለ ራዕይ በጋድ፥ በነቢዩ ናታንም ትዕዛዝ ሌዋውያኑን ከጽናጽል፥ ከበገናና ከመሰንቆ ጋር በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አደራጅቶ አስቀመጣቸው።
\v 26 ሌዋውያኑም ከዳዊት የሙዚቃ መሣሪያዎች ጋርና ካህናቱ ከመለከቶች ጋር ቆሙ።
\s5
\v 27 ሕዝቅያስም የሚቃጠለውን መሥዋዕት በመሠዊያው ላይ እንዲያቀርቡ አዘዛቸው። የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ሲጀመር የእግዚአብሔር መዝሙርም በመለከቶችና በእስራኤል ንጉሥ በዳዊት የሙዚቃ መሣሪያዎች ተጀመረ።
\v 28 ጉባዔውም ሁሉ አመለኩ፤ መዘምራኑም ዘመሩ፤ መለከቶቹም ተነፉ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ እስኪፈጸም ድረስ ይህ ሁሉ ቀጠለ።
\s5
\v 29 መስዋዕት ማቅረቡን በፈጸሙ ጊዜ ንጉሡና ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ አጎነበሱ፤ ሰገዱም።
\v 30 በተጨማሪም ንጉሡ ሕዝቅያስና መሪዎቹ ሌዋውያኑ በዳዊትና በባለራዕዩ በአሳፍ ቃል ለእግዚአብሔር ውዳሴ እንዲዘምሩ አዘዙ። በደስታም ውዳሴዎችን ዘመሩ፤ አጎነበሱ፤ ሰገዱም።
\s5
\v 31 ከዚያም ሕዝቅያስ፦"አሁን ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀድሳችኋል። ወደዚህ መጥታችሁ ለእግዚአብሔር ቤት መሥዋዕቱንና የምስጋና መሥዋዕቱን አቅርቡ" አላቸው። ጉባዔውም መሥዋዕቱንና የምስጋና መሥዋዕቱን አቀረቡ፤ ፈቃደኛ ልብ የነበራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ።
\s5
\v 32 ጉባዔው ያቀረቡት የሚቃጠል መሥዋዕት ቁጥር ሰባ ወይፈን፥ አንድ መቶ አውራ በጎችና ሁለት መቶ ወንድ ጠቦቶች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበሩ።
\v 33 ለእግዚአብሔር የተቀደሱት እንስሳት ስድስት መቶ በሬዎችና ሦስት ሺህ በጎች ነበሩ።
\s5
\v 34 ነገር ግን ካህናቱ የሚቃጠሉትን መሥዋዕት ሁሉ ለመግፈፍ እጅግ ጥቂት ነበሩ፤ በመሆኑም ወንድሞቻቸው ሌዋውያኑ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ፥ ሌዋውያኑም ከካህናቱ ይልቅ ራሳቸውን ለመቀደስ ይበልጥ ጥንቁቅ ስለ ነበሩ ካህናቱ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እስኪቀድሱ ድረስ ረዷቸው።
\s5
\v 35 በተጨማሪም እጅግ ብዙ የሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ነበሩ፤ ከሕብረት መሥዋዕት ስብ ጋር ይከናወኑም ነበር፤ ለእያንዳንዱም የሚቃጠል መሥዋዕት የመጠጥ መሥዋዕትም ነበር። በመሆኑም የእግዚአብሔር አገልግሎት በደንብ ተደራጅቶ ነበር።
\v 36 እግዚአብሔር ለሕዝቡ ካዘጋጀው ነገር የተነሳ ሥራው በፍጥነት በመከናወኑ ሕዝቅያስ ሕዝቡም ሁሉ ደስ አላቸው።
\s5
\c 30
\p
\v 1 ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የፋሲካን በዓል ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲመጡ ሕዝቅያስ ወደ እስራኤልና ይሁዳ ሁሉ መልዕክተኞችን ላከ፤ ወደ ኤፍሬምና ምናሴም ደብዳቤዎችን ጻፈ።
\v 2 ንጉሡ፥ መሪዎቹና የኢየሩሳሌሙ ጉባዔ ሁሉ በአንድነት ከተመካከሩ በኋላ ፋሲካውን በሁለተኛው ወር ለማክበር እየወሰኑ ነበር።
\v 3 ካህናቱ በበቂ ቁጥር ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ስላልቀደሱና ሕዝቡም ገና ወደ ኢየሩሳሌም በአንድነት ስላልተሰበሰበ ወዲያውኑ በዓሉን ሊያከብሩ አልቻሉም ነበር።
\s5
\v 4 ይህ እቅድ በንጉሡና በጉባዔው ሁሉ ፊት መልካም ሆኖ ታይቶ ነበር።
\v 5 በመሆኑም በመላው እስራኤል ከቤርሳቤህ እስከ ዳን የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ለማክበር ሕዝቡ እንዲመጡ አዋጅ እንዲነገር ድንጋጌ አወጡ። በእርግጥም በጽሑፍ እንደታዘዘው በብዙ ቁጥር አላከበሩትም ነበር።
\s5
\v 6 በንጉሡ ትእዛዝ መልዕክተኞች ወደ መላው ይሁዳና እስራኤል ሁሉ የንጉሡንና የመሪዎቹን ደብዳቤ ይዘው ሄዱ። "እናንተ የእስራኤል ሰዎች ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠው ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃም፥ ይስሐቅና እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።
\s5
\v 7 እንደምታዩት ለጥፋት አሳልፎ እስኪሰጣቸው ድረስ በአባቶቻቸው አምላክ በእግዚአብሔር ላይ እንደተላለፉት እንደ አባቶቻችሁ ወይም ወንድሞቻችሁ አትምሰሉ።
\v 8 አሁንም አባቶቻችሁ እንደነበሩት እናንተም አንገተ ደንዳና አትሁኑ። ይልቁንም ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡና የጋለ ቁጣው ከእናንተ እንዲመለስ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለማምለክ ለዘላለም ለእግዚአብሔር ወደ ተሰጠው ቅዱስ ሥፍራው ኑ!
\v 9 አምላካችሁ እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ስለሆነ ወደ እርሱ ብትመለሱ ፊቱን ከእናንተ ስለማይመልስ ወደ እግዚአብሔር ብትመለሱ ወንድሞቻችሁና ልጆቻችሁ እንደ እስረኛ በወሰዷቸው ሰዎች ፊት ሃዘኔታ ያገኛሉ። ወደዚህችም ምድር ይመለሳሉ።
\s5
\v 10 በመሆኑም መልዕክተኞቹ እስከ ዛብሎን ድረስ በመላው የኤፍሬምና የምናሴ ክልሎች ሁሉ ከከተማ ወደ ከተማ አለፉ፤ ሕዝቡ ግን ሳቁባቸው፤ አፌዙባቸውም።
\v 11 ነገር ግን የተወሰኑ የአሴርና የምናሴ የዛብሎንም ሰዎች ራሳቸውን አዋርደው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
\v 12 በእግዚአብሔር ቃል የንጉሡንና የመሪዎቹን ትዕዛዝ ለመፈጸም አንድ ልብ ሊሰጣቸው የእግዚአብሔር እጅ በይሁዳ ላይም መጣ።
\s5
\v 13 በሁለተኛው ወር የቂጣውን በዓል ለማክበር ብዙ ሰዎች፥ እጅግ ታላቅ ጉባዔ ለማክበር በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።
\v 14 ተነስተው በኢየሩሳሌም የነበሩትን መሠዊያዎችና ለጣዖታት የሚያጥኑበትን ማጠኛዎች ሁሉ አስወገዱ፤ ወደ ቄድሮን ወንዝም ጣሉአቸው።
\v 15 ከዚያም በሁለተኛው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካውን ጠቦቶቹን አረዱ። ካህናቱና ሌዋውያኑ አፍረው ነበርና ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጡ። ወደ እግዚአብሔርም ቤት የሚቃጠል መሥዋዕት አመጡ።
\s5
\v 16 በእግዚአብሔር ሰው በሙሴ ሕግ የተሰጠውን መመሪያ በመከተል በየሥራ ክፍላቸው በቦታቸው ቆሙ፤ ካህናቱም ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ይረጩ ነበር።
\v 17 በጉባዔው ውስጥ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ያልሰጡ እጅግ ብዙ ነበሩ፤ ስለዚህ ሌዋውያን ለእግዚአብሔር ጠቦቶቹን ለእግዚአብሔር ለመቀደስ ነጽተው ላልነበሩት ሰዎች ሁሉ የፋሲካውን ጠቦቶች የማረዱ ኃላፊነት የእነርሱ ነበር።
\s5
\v 18 እጅግ ብዙ ሰዎች ብዙዎቹም ከኤፍሬምና ከምናሴ፥ ከይሳኮርና ከዛብሎን በሕጉ መሠረት ራሳቸውን አላነጹም ነበር፤ ነገር ግን እንደ ተጻፈው ትዕዛዝ ባይሆንም የፋሲካውን ምግብ በሉ፤ ሕዝቅያስም ፦" ምንም እንኳን እንደ ቅዱሱ ሥፍራ የመንጻት መለኪያ መሠረት የነጻ ባይሆንም
\v 19 የአባቶቹን አምላክ እግዚአብሔር አምላክን ለመፈለግ በልቡ የቆረጠውን ሰው ሁሉ ቸሩ እግዚአብሔር ይቅር ይበለው" በማለት ፀልዮላቸው ነበር።
\v 20 እግዚአብሔርም ሕዝቅያስን ሰማው፤ ሕዝቡንም ፈወሰ።
\s5
\v 21 በኢየሩሳሌምም ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ሰዎች በታላቅ ደስታ የቂጣውን በዓል ለሰባት ቀናት አከበሩ። ሌዋውያኑና ካህናቱም ድምጹ በጎላ የሙዚቃ መሣሪያ ለእግዚአብሔር በመዘመር ከእለት ወደ እለት እግዚአብሔርን ያወድሱ ነበር።
\v 22 ሕዝቅያስም ለእግዚአብሔር የሚሰጠውን አገልግሎት ያስተዋሉትን ሌዋውያን ሁሉ በማበረታታት ተናገራቸው። በመሆኑም የሕብረት ሥጦታ መሥዋዕት እያቀረቡና ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር እየተናዘዙ በሰባቱ ቀናት በዓል ሁሉ ይመገቡ ነበር።
\s5
\v 23 ከዚያም መላው ጉባዔ ለሌላ ሰባት ቀናት በዓሉን ለማክበር ወሰኑ፤ እንደዚህም በደስታ አደረጉ።
\v 24 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ለጉባዔው እንደ ሥጦታ ሰጥቶ ነበር፤ መሪዎቹም ለጉባዔው አንድ ሺህ ወይፈኖችና አሥር ሺህ በጎችና ፍየሎች ሰጡ። ብዙ ቁጥር ያላቸው ካህናትም ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ሰጥተው ነበር።
\s5
\v 25 የይሁዳ ጉባዔ ሁሉ ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋር፥ ከእስራኤል በአንድነት የመጡት ሕዝብ ሁሉ፥ እንዲሁም ከእስራኤል ምድር እና በይሁዳ ይኖሩ ከነበሩት የመጡት እንግዶች ሁሉም ደስ አላቸው።
\v 26 በመሆኑም በኢየሩሳሌም ታላቅ ደስታ ነበር፤ ከእስራኤል ንጉሥ ከዳዊት ልጅ ከሰለሞን ጊዜ አንስቶ እንደዚህ ያለ ነገር በኢየሩሳሌም ምንም አልነበረም።
\v 27 ከዚያም ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ ተነስተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምጻቸውም ተሰማ፤ ፀሎታቸውም ወደ እግዚአብሔር ማደሪያ ቅዱስ ሥፍራ ወደ ሰማይ አረገ።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ሁሉም ነገር ከተጠናቀቀ በኋላ እዚያ የተገኙት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው የአምልኮ ድንጋይ ምሶሶዎችን ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹን ቆረጡ፤ በይሁዳና በብንያም ሁሉ መስገጃዎችንና መሠዊያዎችን ሰባበሩ፤ ሁሉንም እስኪያጠፉ ድረስ ይህንኑ በኤፍሬምና በምናሴም ጭምር አደረጉት። ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ገዛ ምድሩና ወደ ገዛ ከተማው ተመለሰ።
\s5
\v 2 ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን በየሥራ ክፍል በማደራጀት ለካህናቱና ለሌዋውያኑ ለእያንዳንዱ ሥራ በመስጠት በየአገልግሎታቸው መደባቸው። የሚቃጠል መሥዋዕትና የሕብረት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፥ እንዲያገለግሉ፥ እንዲያመሰግኑና በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሮች እንዲያወድሱ መደባቸው።
\v 3 በእግዚአብሔር ሕግ ተጽፎ እንደነበረውም ለሚቃጠል መሥዋዕት ማለትም ለጠዋትና ለማታ የሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለሰንበት ቀናት፥ ለመባቻዎቹና ለመደበኛ በዓላትም የሚቃጠል መሥዋዕት ከንጉሡ ከገዛ ራሱ ሃብት ድርሻውን መደበ።
\s5
\v 4 በተጨማሪም ካህናቱና ሌዋውያኑ የእግዚአብሔርን ሕግ በመታዘዝ ላይ እንዲያተኩሩ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች ለካህናቱና ሌዋውያኑ ድርሻቸውን እንዲሰጡ አዘዘ።
\v 5 ትእዛዙ እንደወጣም የእስራኤል ሕዝብ የእህሉን፥ የአዲሱን ወይን፥ የዘይቱን፥ የማሩን እንዲሁም ከእርሻው መከር ሁሉ በኩራት አትረፍርፈው ሰጡ፤ የሁሉንም ነገር አሥራትም አትረፍርፈው አመጡ።
\s5
\v 6 በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ የበሬዎቹንና በጎቹን አሥራት፥ ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር የተሰጡ ነገሮችን ጭምር አሥራት አምጥተው ከምረው አስቀመጡት።
\v 7 በሦስተኛው ወር መከመር ጀምረው በሰባተኛው ወር ጨረሱ።
\v 8 ሕዝቅያስና መሪዎቹ መጥተው ክምሮቹን ሲያዩ እግዚአብሔርንና ሕዝቡን እስራኤልን ባረኩ።
\s5
\v 9 ሕዝቅያስም ካህናቱንና ሌዋውያኑን ስለ ክምሩ ጠየቀ።
\v 10 የሳዶቅም ቤት የሆነው ሊቀ ካህን ዓዛርያስ፦" ሕዝቡ ሥጦታዎቻቸውን ወደ እግዚአብሔር ቤት ማምጣት ከጀመሩ አንስቶ በልተናል፤ ጠግበናልም፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን ስለባረከ ብዙ ተርፎአል። የተረፈውም ነገር ይህ እዚህ ያለው ታላቅ መጠን ነው" ብሎ መልስ ሰጠ።
\s5
\v 11 ከዚያም ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ መጋዘኖች እንዲዘጋጁ አዘዘ፤ እነርሱም አዘጋጇቸው።
\v 12 ሥጦታዎቹን፥ አሥራቱንና የእግዚአብሔር የሆኑትን ነገሮች በታማኝነት አመጡ። ሌዋዊው ኮናንያ የበላያቸው አስተዳዳሪ ነበር፤ ወንድሙም ሰሜኢ በደረጃ ከእርሱ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበረ። በንጉሡም በሕዝቅያስና በእግዚአብሔር ቤት ላይ ባለ ሥልጣን በነበረው በዓዛርያስ የተሾሙ፥ ከኮናንያና ከወንድሙ ከሰሜኢ እጅ በታች
\v 13 ይሒዒል፥ ዓዛዝያ፥ ናሖት፥ አሣኤል፥ ይሬሞት፥ ዮዛባት፥ ኤሊኤል፥ ሰማኪያ፥ መሐት፥ በናያስ አስተዳዳሪዎች ነበሩ።
\s5
\v 14 ሌዋዊው የይምና ልጅ የምሥራቁ በር ጠባቂ ቆሬ ለእግዚአብሔር የተቀደሱትን ሥጦታዎችና በእግዚአብሔር የበጎ ፈቃድ ሥጦታዎች ላይ የበላይ ሆኖ ለእግዚአብሔር የቀረቡ ሥጦታዎችን ለማከፋፈል አዛዥ ነበር።
\v 15 ከበታቹም በካህናቱ ከተሞች ውስጥ ዔድን፥ ሚንያሚን፥ ኢያሱ፥ ሽማያ፥ አማርያና ሴኬንያ ነበሩ። እነዚህን ሥጦታዎች ለታላላቆቹና ለታናናሾቹ ወንድሞቻቸው እንደየሥራ ክፍላቸው ለመስጠት በመታመን ሥልጣን ተሰጣቸው።
\s5
\v 16 በዕለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንደሚጠበቅባቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡ ሁሉ በቦታቸው ሆነው በየሥራ ክፍላቸው ሥራቸውን ለመሥራት በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው የነበሩ ሦስት ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ወንዶችም ሰጡ።
\s5
\v 17 በቦታቸው ሆነው በየሥራ ክፍላቸው ሥራቸውን ለመሥራት በአባቶቻቸው ቤቶች በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው የነበሩ ሌዋውያን ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆኑትም ሰጡ።
\v 18 በዘር ሐረጋቸው ተቆጥረው ለነበሩ ለሕፃናቱ፥ ለሚስቶቻቸው፥ ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቻቸው ሁሉ በመላው ሕዝብ መካከል በተቀደሰ ሁኔታ በአመኔታ ለተሰጣቸው ሥልጣን ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ስለቀደሱ ለእነርሱም ሰጡ።
\v 19 በየከተማቸው ወይም በከተሞቹ ሁሉ ባሉ መንደሮች መስኮች ላይ ለነበሩ ለአሮን ዝርያዎች በካህናቱ መካከል ለሁሉም ወንዶች በስማቸው ድርሻቸውን ለመስጠትና በሌዋውያን መካከል እንደሆኑ በትውልድ ሐረጋቸው ለተቆጠሩ ሁሉ የተመደቡላቸው ሰዎች ነበሩ።
\s5
\v 20 ሕዝቅያስም ይህንን በይሁዳ ሁሉ አደረገ። በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት መልካም፥ ትክክለኛና ታማኝ ነገርን አከናወነ።
\v 21 በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት በጀመረው በየትኛውም ሥራ በሕጉና በትዕዛዛቱ አምላኩን ለመፈለግ በሙሉ ልቡ አከናወነው፤ እርሱም ተሳካለት።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ከእነዚህ ነገሮችና ከእነዚህ የታማኝነት ድርጊቶች በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፤ ለራሱ ሊይዛቸው ያሰባቸውን የተከበቡ ከተሞች ሊያጠቃ ሰፈረ።
\s5
\v 2 ሕዝቅያስም ሰናክሬም እንደ መጣ ኢየሩሳሌምንም ሊዋጋ እንዳሰበ ባየ ጊዜ
\v 3 ከከተማው በስተውጪ የነበሩትን የምንጭ ውሃዎች ለመድፈን ከመሪዎቹና ከኃያላን ሰዎቹ ጋር ተመካከረ፤ እነርሱም እንደዚህ ለማድረግ ረዱት።
\v 4 በመሆኑም በርካታ ሰዎች በአንድነት ተሰብስበው ምንጮቹን ሁሉና በምድሪቱ መካከል አልፎ ይፈስ የነበረውን ጅረት አስቆሙ። እነርሱም " የአሦር ነገሥታት መጥተው ለምን ብዙ ውሃ ያገኛሉ?" አሉ።
\s5
\v 5 ሕዝቅያስም ተደፋፈረና የፈረሰውን ቅጥር ሁሉ ጠገነ፤ እስከ ማማዎቹ ድረስ ሠራው፤ በስተውጪ ሌላ ግንብም ሠራ። በዳዊትም ከተማ ውስጥ የነበረችውን ሚሎንም አጠነከረ፤ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን የጦር መሣርያዎችንና ጋሻዎችንም ሠራ።
\s5
\v 6 በሕዝቡ ላይም የጦር አዛዦችን አስቀመጠ። በአንድነትም በከተማይቱም በር በሰፊ ቦታ ወደራሱ ሰብስቦአቸው በማበረታታት ተናገራቸው።
\v 7 "በርቱ አይዞአችሁ። ከእርሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያለው እርሱ እግዚአብሔር የሚበልጥ ስለሆነ ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ሠራዊት የተነሳ እንዳትፈሩ ወይም እንዳትደነግጡ።
\v 8 ከእርሱ ጋር ያለው የሥጋ ክንድ ብቻ ነው፤ ከእኛ ጋር ግን ሊረዳንና ጦርነታችንን ሊዋጋልን ያለው አምላካችን እግዚአብሔር ነው" አላቸው። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ራሳቸውን አጽናኑ።
\s5
\v 9 ከዚህ በኋላ የሦርያ ንጉሥ ሰናክሬም (በዚህ ጊዜ በለኪሶ ፊት ለፊት ነበረ፤ ሠራዊቱም ሁሉ ከእርሱ ጋር ነበሩ) አገልጋዮቹን ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስና በኢየሩሳሌም ወደነበሩት ወደ ይሁዳ ሁሉ ላከ፤
\v 10 "የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የሚለው ይህንን ነው፦'በኢየሩሳሌም የተከበባችሁበትን ለመቋቋም የምትደገፉት በምን ላይ ነው?
\s5
\v 11 ሕዝቅያስ፦ 'አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ይታደገናል' ብሎ ሲነግራችሁ በረሃብና በጥማት እንድትሞቱ አሳልፎ ሊሰጣችሁ እያሳሳታችሁ አይደለምን?
\v 12 የኮረብታ መስገጃዎቹንና መሠዊያዎቹን ያስወገደና 'በአንድ መሠዊያ ላይ ታመልካላችሁ፤ በእርሱም ላይ መሥዋዕታችሁን ታቃጥላላችሁ' ብሎ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ያዘዘው ይኸው ሕዝቅያስ አይደለምን?
\s5
\v 13 እኔና አባቶቼ በሌሎች ምድሮች ሕዝቦች ሁሉ ላይ ያደረግነው ምን እንደሆነ አላወቃችሁምን? የእነዚህ ምድሮች ሕዝቦች አማልክት በየትኛውም መንገድ ምድራቸውን ከኃይሌ ሊታደጉ ችለው ነበርን?
\v 14 አባቶቼ ሙሉ በሙሉ ካጠፏቸው ከእነዚያ ሕዝቦች አማልክት ሁሉ መካከል ሕዝቡን ከእጄ መታደግ የቻለ አምላክ ነበርን? አምላካችሁስ እናንተን ከኃይሌ ሊታደጋችሁ እንዴት ይችላል?
\v 15 አሁንም ሕዝቅያስ በዚህ መንገድ አያታልልላችሁ ወይም አያሳምናችሁ። የየትኛውም ሕዝብ ወይም መንግሥት አማልክት ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ ሊታደግ ስላልቻለ አትመኑት። ይልቁንም አምላካችሁ ከእጄ እንዴት ሊያድናችሁ ይችላል?" አለ።
\s5
\v 16 የሰናክሬም አገልጋዮችም እግዚአብሔር አምላክና አገልጋዩ ሕዝቅያስ ላይ ይበልጥ የተቃውሞ ነገር ተናገሩ።
\v 17 ሰናክሬም በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ላይ ለማፌዝና እርሱንም በመቃወም ለመናገር ደብዳቤዎችንም ጻፈ። "የምድሪቱ ሕዝቦች አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ እንዳልታደጉ እንደዚሁ የሕዝቅያስም አምላክ ሕዝቡን ከእጄ አይታደግም" አለ።
\s5
\v 18 ከተማይቱን ለመያዝም በቅጥሩ ላይ የነበሩትን የኢየሩሳሌም ሰዎች ለማስፈራራትና ለማስጨነቅ በአይሁድ ቋንቋ በጎላ ድምጽ ይጮሁ ነበር።
\v 19 የሰዎች የእጅ ሥራ ብቻ በነበሩት በምድር ሌሎች ሕዝቦች አማልክት ላይ እንደተናገሩት በኢየሩሳሌም አምላክም ላይ ተናገሩ።
\s5
\v 20 ንጉሡ ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ከዚህ ጉዳይ የተነሳ ፀለዩ፤ ወደ ሰማይም ጮኹ።
\v 21 እግዚአብሔርም መልአክን ላከ፤ እርሱም ተዋጊዎቹን ሰዎች፥ አዛዦቹንና የንጉሡን ባለሥልጣናት በሰፈሩበት ቦታ ገደላቸው። በመሆኑም ሰናክሬም አፍሮ ወደ ገዛ ምድሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩ ቤት በገባ ጊዜ እዚያ ከገዛ ራሱ ልጆች አንዳንዱ በሰይፍ ገደሉት።
\s5
\v 22 በዚህ መንገድ እግዚአብሔር ሕዝቅያስንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅና ከሌሎች ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በሁሉም መንገድም መራቸው።
\v 23 በርካቶችም ለእግዚአብሔር ሥጦታዎችን፥ የከበሩ ነገሮችንም ለይሁዳ ንጉሥ ለሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጡ ነበር። እርሱም ከዚያን ጊዜ አንስቶ በሕዝቦች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።
\s5
\v 24 በዚያን ወቅት ሕዝቅያስ ለመሞት እስኪቀርብ ድረስ ታምሞ ነበር። ወደ እግዚአብሔርም ፀለየ፤ እርሱም ተናገረው፤ እንደሚፈወስም ምልክትን ሰጠው።
\v 25 ሕዝቅያስ ግን ልቡ ታብዮ ስለ ነበር እግዚአብሔር ለሰጠው እርዳታ ውለታ ቢስ ሆነ። በመሆኑም በእርሱ፥ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ቁጣ መጣባቸው።
\v 26 ቢሆንም ግን በኋላ ላይ ሕዝቅያስ ስለ ልቡ ትዕቢት እርሱና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁለቱም ራሳቸውን አዋረዱ። የእግዚአብሔርም ቁጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።
\s5
\v 27 ሕዝቅያስ እጅግ ብዙ ባለጠግነትና ብዙ ክብር ነበረው። ለራሱም ለብር፥ ለወርቅ፥ ለከበሩ ድንጋዮችና ለቅመማ ቅመሞች እንዲሁም ለጋሻዎችና ዋጋ ላላቸው ነገሮች ሁሉ መጋዘኖችን ሠራ።
\v 28 ለእህል፥ ለአዲስ ወይንና ዘይት መጋዘኖች፥ ለሁሉም ዓይነት እንስሳት ጋጣዎችም ነበሩት። በጋጣቸውም መንጋዎችም ነበሩት።
\v 29 በተጨማሪም እግዚአብሔር እጅግ ብዙ ሃብት ስለሰጠው ለራሱ ከተሞችን፥ የተትረፈረፉ የበጎችና የከብቶች መንጋዎች ንብረት አዘጋጀ።
\s5
\v 30 የግዮንን የላይኛውን ውሃ ምንጮች የደፈነና በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል በቀጥታ ቁልቁል እንዲመጡ ያደረጋቸው ይኸው ሕዝቅያስ ነው። ሕዝቅያስም በሠራው ሥራ ሁሉ ተሳካለት።
\v 31 ነገር ግን በምድሪቱ ስለተደረገው ተዓምራዊ ምልክት የሚያውቁ ሰዎችን ጥያቄ ለመጠየቅ የተላኩትን የባቢሎን መሳፍንት መልዕክተኞችን በተመለከተ ጉዳይ እግዚአብሔር ሊፈትነውና በልቡ ያለውን ለማወቅ ለራሱ ተወው።
\s5
\v 32 ሕዝቅያስን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮች የቃል ኪዳን ታማኝነት ድርጊቶቹን ጨምሮ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራዕይና በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ መጻፋቸውን መመልከት ትችላላችሁ።
\v 33 ሕዝቅያስ ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ዝርያዎች መቃብር በኮረብታው ላይ ቀበሩት። የይሁዳና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ በሞቱ ጊዜ አከበሩት። ልጁ ምናሴ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\c 33
\p
\v 1 ምናሴ መንገሥ በጀመረ ጊዜ አሥራ ሁለት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃምሳ አምስት ዓመት ነገሠ።
\v 2 እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት እንዳስወጣቸው ሕዝቦች ዓይነት አስጸያፊ ነገር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።
\v 3 አባቱም ሕዝቅያስ ያፈረሳቸውን የኮረብታውን መስገጃዎች እንደገና ገነባ፤ ለበኣልም መሠዊያዎችን ሠራ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም አቆመ፤ ለሰማይም ከዋክብት ሁሉ ሰገደ፤ አመለካቸውም።
\s5
\v 4 ምንም እንኳን እግዚአብሔር፦ "ስሜ ለዘላለም የሚኖረው በኢየሩሳሌም ነው" ብሎ ያዘዘ ቢሆንም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ለጣዖታት መሠዊያዎችን ገነባ።
\v 5 በእግዚአብሔር ቤት ሁለቱ አደባባዮች ውስጥ ለሰማይ ከዋክብት ሁሉ መሠዊያዎችን ሠራ።
\v 6 በሄኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት ውስጥ እንደሚቃጠል መሥዋዕት አቀረበ፤ ሞራ ገላጭ ሆነ፤ አስማት አደረገ፤ መተተኛም ነበረ፤ ከሙታን ጋር ከሚነጋገሩና ከመናፍስት ጋር ከሚነጋገሩ ጋር ይማከር ነበር። በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፋት በመለማመድ እግዚአብሔርን ለቁጣ አነሳሳ።
\s5
\v 7 የአሼራን የተቀረጸ ምስል ሠርቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ አኖረው፤ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን ሲናገር፦" ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ ስሜ ለዘላለም እንዲኖርበት የመረጥኩት በዚህ ቤትና በኢየሩሳሌም ነው" ብሎ የነበረው ስለዚህ ቤት ነበር።
\v 8 በሙሴ አማካይነት የሰጠኋቸው ሕግ፥ ደንቦችና ድንጋጌዎች በመከተል ያዘዝኳቸውን ሁሉ ለመጠበቅ ቢጠነቀቁ ለአባቶቻቸው ከመደብኩላቸው ምድር የእስራኤልን ሕዝብ ከዚህ በኋላ አላወጣም" ብሎ ነበር።
\v 9 ምናሴም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ነዋሪዎች እግዚአብሔር ከእስራኤል ሕዝብ ፊት ካጠፋቸው ሕዝቦች የበለጠ ክፋትን እንዲያደርጉ መራቸው።
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም ምናሴንና ሕዝቡን ተናገራቸው፤ ነገር ግን አልሰሙትም።
\v 11 በመሆኑም የአሦርን ንጉሥ ሠራዊት አዛዦች አመጣባቸው፤ ምናሴንም በእግር ብረት ያዙት፤ በሰንሰለት አሰሩት፤ ወደ ባቢሎንም ወሰዱት።
\s5
\v 12 ምናሴ በተጨነቀ ጊዜ አምላኩን እግዚአብሔርን ተማፀነ፤ በአባቶቹም አምላክ ፊት ራሱን እጅግ አዋረደ።
\v 13 ወደ እርሱም ፀለየ፤ እግዚአብሔርም ተለመነው። እግዚአብሔር ልመናውን ሰምቶ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ንግሥናው መለሰው። ምናሴም እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደሆነ አወቀ።
\s5
\v 14 ከዚህ በኋላ ምናሴ በዳዊት ከተማ በግዮን ምዕራብ በኩል በሸለቆው ውስጥ እስከ ዓሣው በር መግቢያ ድረስ የውጫዊውን ግንብ ገነባ። የኦፊልንም ኮረብታ በእርሱ ከበበው። ግንቡንም እጅግ ታላቅ ከፍታ ድረስ አነሳው። በተመሸጉት በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ደፋር አዛዦችን አኖረ።
\v 15 የባዕድ አማልክትን ጣዖቱንም ከእግዚአብሔር ቤት አስወገደ፤ በእግዚአብሔር ቤት ተራራ ላይና በኢየሩሳሌም ውስጥ የገነባቸውን መሠዊያዎች ከከተማው ውጪ ወረወራቸው።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔርም መሠዊያ አደሰ፤ የሕብረት መሥዋዕትና የምሥጋናን መሥዋዕት ሥጦታዎች አቀረበበት፤ የይሁዳ ሕዝብ የእስራኤልን አምላክ እንዲያገለግሉ አዘዘ።
\v 17 ነገር ግን ሕዝቡ እስከ አሁንም በኮረብታው መስገጃዎች ላይ ይሰዋ ነበር፤ ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር ብቻ ነበር።
\s5
\v 18 ምናሴን የሚመለከቱት ሌሎች ነገሮች ወደ አምላኩ የፀለየው ፀሎትና በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም የተናገሩት የነቢያት ቃል እነሆ በእስራኤል ነገሥታት ድርጊቶች መካከል ተጽፈዋል።
\v 19 ፀሎቱም እግዚአብሔርም እንዴት እንደተለመነው፥ ኃጢአቱና መተላለፉ ሁሉ ራሱንም ከማዋረዱ በፊት የኮረብታ መስገጃዎች የገነባባቸው፥ የማምለኪያ አጸዶችንና የተቀረጹትን ምስሎች ያቆመባቸው ቦታዎች በባለ ራዕዮቹ ታሪክ መጽሐፍ ተጽፎአል።
\v 20 ምናሴም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በገዛ ራሱ ቤት ውስጥ ቀበሩት። ልጁም አሞጽ በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\v 21 አሞጽ መንገሥ በጀመረ ጊዜ እድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሁለት ዓመት ነገሠ።
\v 22 አባቱ ምናሴ እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ። አሞጽ አባቱ ምናሴ ለሠራቸው ለተቀረጹ ምስሎች ሁሉ ሠዋ፤ አመለካቸውም።
\v 23 አባቱ ምናሴ እንዳደረገ በእግዚአብሔር ፊት ራሱን አላዋረደም። ይልቁንም ይኸው አሞጽ መተላለፉን ይበልጥ ጨመረው።
\s5
\v 24 አገልጋዮቹ በእርሱ ላይ አሲረው በገዛ ቤቱ ውስጥ ገደሉት።
\v 25 የምድሪቱ ሕዝብ ግን በንጉሡ በአሞጽ ላይ ያሴሩበትን ሰዎች ሁሉ ገደሉ፤ ልጁንም ኢዮስያስን በእርሱ ቦታ አነገሡት።
\s5
\c 34
\p
\v 1 ኢዮስያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ እድሜው ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሠላሳ አንድ ዓመት ነገሠ።
\v 2 በእግዚአብሔር ፊት ትክክለኛውን ነገር አደረገ፤ በአባቱም በዳዊት መንገድ ሄደ፤ ከእርሱም ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም።
\v 3 በነገሠም በስምንተኛው ዓመት ገና ወጣት እያለ የአባቱን የዳዊትን አምላክ መፈለግ ጀመረ። በአሥራ ሁለተኛው ዓመትም ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን ከኮረብታው መስገጃዎች፥ ከማምለኪያ ዐፀዶቹ፥ ከተቀረጹት ምስሎችና ቀልጠው ከተሠሩት ምስሎች ማጽዳት ጀመረ።
\s5
\v 4 ሕዝቡ የበኣሊምን መሠዊያዎች በእርሱ ፊት አፈረሱ፤ እርሱ ከበላያቸው የነበሩትን የዕጣን መሠዊያዎች ሰባበረ። የማምለኪያ ዐፀዶቹንም ሰባበረ፤ የተቀረጹትን ምስሎች፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች አፈር እስኪሆኑ ድረስ አደቀቃቸው። ትቢያውንም መሥዋዕት ይሰዉላቸው በነበሩ ሰዎች መቃብር ላይ በተነው።
\v 5 የካህናቶቻቸውንም አጥንቶች በመሠዊያቸው ላይ አቃጠለ። በዚህ መንገድ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አጸዳ።
\s5
\v 6 በምናሴ፥ በኤፍሬም፥ በስምዖን ከተሞችም እስከ ንፍታሌም ድረስና በዙሪያቸው ባሉት ፍርስራሾች ሁሉ ተመሳሳይ ነገር አደረገ።
\v 7 መሠዊያዎቹን አፈረሰ፤ የማምለኪያ ዐፀዶቹንና የተቀረጹትን ምስሎች አደቀቃቸው፤ በእስራኤል ምድር ሁሉ የዕጣን መሠዊያዎችን ሁሉ ቆራረጠ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ።
\s5
\v 8 ኢዮስያስ ምድሪቱንና ቤተ መቅደሱን ካጸዳ በኋላ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት የኤዜልያስን ልጅ ሳፋን፥የከተማይቱንም ገዢ መፅሤያ፥ የታሪክ ጸሐፊውንም የኢዮአካዝን ልጅ ኢዮአክን የአምላኩን የእግዚአብሔርን ቤት እንዲያድሱ ላካቸው።
\v 9 እነርሱም ወደ ሊቀ ካህኑ ወደ ኬልቅያስ ሄደው ሌዋውያኑ፥ የበሮቹ ጠባቂዎች ከምናሴና ከኤፍሬም፥ ከእስራኤል ቅሬታዎች ሁሉ፥ ከይሁዳና ከብንያም ሁሉ፥ ከኢየሩሳሌምም ነዋሪዎች የሰበሰቡትን ወደ እግዚአብሔር ቤት የመጣውን ገንዘብ አደራ ሰጡት።
\s5
\v 10 ገንዘቡን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ሥራ በበላይነት ለሚቆጣጠሩት ሰዎች ሰጧቸው። እነዚህ ሰዎች ቤተ መቅደሱን ለሚጠግኑና ለሚያድሱ ሠራተኞች ከፈሏቸው።
\v 11 የተጠረበውን ድንጋይ፥ ለማጋጠሚያ ጣውላ እንጨትና አንዳንድ የይሁዳ ነገሥታት እንዲፈርስ ለተዉት መዋቅር ወራጆች እንዲገዙ ለአናጢዎቹና ግንበኞቹ ከፈሏቸው።
\s5
\v 12 ሰዎቹም ሥራውን በታማኝነት ሠሩ። ሥራውን በበላይነት የሚቆጣጠሯቸው ሌዋውያኑ ከሜራሪ ልጆች ኢኤትና አብድዩ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ሁሉም መልካም የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾች የነበሩ ሌሎች ሌዋውያንም ሠራተኞቹን በቅርበት አቅጣጫ ይመሯቸው ነበር።
\v 13 እነዚህ ሌዋውያን የግንባታ ዕቃ የሚሸከሙትንና በሌላም መንገድ የሚሠሩትን ሌሎች ሰዎች ሁሉ ይቆጣጠሩ ነበር። ጸሐፊዎች፥ አስተዳዳሪዎችና የበር ጠባቂዎች የነበሩ ሌሎች ሌዋውያንም ነበሩ።
\s5
\v 14 ወደ እግዚአብሔር ቤት የመጣውን ገንዘብ ወደ ውጪ ሲያመጡት ካህኑ ኬልቅያስ በሙሴ በኩል የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ሕግ መጽሐፍ አገኘ።
\v 15 ኬልቂያስም ጸሐፊውን ሳፋንን፦" በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሕጉን መጽሐፍ አግኝቼአለሁ" አለው። ኬልቅያስም መጽሐፉን ወደ ሳፋን አመጣው።
\v 16 ሳፋንም መጽሐፉን ወደ ንጉሡ ወስዶ፦"አገልጋዮችህ በኃላፊነት የተሰጣቸው ማናቸውንም ነገር እያደረጉ ናቸው።
\s5
\v 17 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተገኘውን ገንዘብ ወደ ውጪ አውጥተው ለተቆጣጣሪዎቹና ለሠራተኞቹ አደራ ሰጥተዋል" በማለት ነገረው።
\v 18 ጸሐፊውም ሳፋን ለንጉሡ ፦"ካህኑ ኬልቅያስ አንድ መጽሐፍ ሰጥቶኛል" ብሎ ነገረው። ከዚያም ለንጉሡ አነበበለት።
\v 19 ንጉሡ የሕጉን ቃላት በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ።
\s5
\v 20 ንጉሡም ኬልቅያስን፥ የሳፋንንም ልጅ አኪቃምን፥ የሚክያስንም ልጅ ዓብዶንን፥ ጸሐፊውንም ሳፋንን የራሱንም አገልጋይ ዓሳያን፦
\v 21 "ሄዳችሁ ከተገኘው መጽሐፍ ቃል የተነሳ ለእኔና በእስራኤልና በይሁዳ ለተረፉት ሰዎች የእግዚአብሔርን ፈቃድ ጠይቁ። በእኛ ላይ የፈሰሰው የእግዚአብሔር ቁጣ ታላቅ ስለሆነ፥ በውስጡ የተጻፈውን ሁሉ ለመታዘዝ አባቶቻችን የዚህን መጽሐፍ ቃላት ስላልሰሙ ቁጣው ታላቅ ነው።
\s5
\v 22 በመሆኑም ኬልቅያስና ንጉሡ ያዘዛቸው ሰዎች (በኢየሩሳሌም በሁለተኛው ክፍል ትኖር ወደ ነበረችው) ወደ ልብሰ ተክህኖ ጠባቂው ወደ ሐስራ ልጅ፥ ወደ ቲቁዋ ልጅ፥ ወደ ሴሌም ሚስት ወደ ነቢይቱ ወደ ሕልዳና ሄዱ፤ እንዲህም ብለው አናገሯት።
\s5
\v 23 እርሷም፦"የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፦ወደ እኔ ለላካችሁ ሰው ንገሩት፥
\v 24 "እግዚአብሔር የሚለው ይህንን ነው፦ 'እነሆ በይሁዳ ንጉሥ ፊት ባነበቡት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን እርግማን ሁሉ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ ጥፋትን ላመጣ ነው።
\v 25 ባደረጓቸው ተግባራት ሁሉ ለቁጣ ሊያነሳሱኝ እኔን ትተው ለሌሎች አማልክት ዕጣንን ከማጠናቸው የተነሳ ስለዚህ ቁጣዬ በዚህ ሥፍራ ላይ ይነድዳል፤ ምንም ነገርም አያቆመውም' " አለቻቸው።
\s5
\v 26 ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመጠየቅ ለላካችሁ ለይሁዳ ንጉሥ የምትሉት ይህ ነው፦" የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ሰማኸው ቃል፦
\v 27 ' ልብህ ለስላሳ ስለ ነበርና በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ እንደሚመጣ የተነገረውን ቃሉን ስትሰማ በእግዚአብሔር ፊት ራስህን ስላዋረድህ፥ ራስህንም በፊቴ አዋርደህ ልብስህንም ቀድደህ በፊቴ ስላለቀስህ እኔም ሰምቼሃለሁ' እግዚአብሔር የሚናገረው ይህ ነው፤
\v 28 'እነሆ ወደ ዝርያዎችህ እሰበስብሃለሁ፤ በሰላምም ወደ መቃብርህ ትሰበሰባለህ፤ በዚህ ቦታና በነዋሪዎቹ ላይ የማመጣውን የትኛውንም ጥፋት ዓይኖችህ አያዩም'" በመሆኑም ሰዎቹ ይህንን መልዕክት ለንጉሡ መልሰው ወሰዱለት።
\s5
\v 29 ከዚያም ንጉሡ መልዕክተኞችን ልኮ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ሰበሰበ።
\v 30 ንጉሡም የይሁዳ ወንዶችና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ፥ ካህናቱም፥ ሌዋውያኑና ከትልቅ እስከ ትንሽ ሕዝቡ ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ። በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ቃል ሁሉ እየሰሙት አነበበላቸው።
\s5
\v 31 ንጉሡም በቦታው ቆሞ እግዚአብሔርን ተከትሎ ለመሄድ፥ ትዕዛዛቱን፥ የቃል ኪዳን ድንጋጌዎቹንና ደንቦቹን ለመጠበቅ፥ በሙሉ ልቡና በሙሉ ነፍሱ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተጻፉትን የቃል ኪዳኑን ቃላት ለመታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ቃል ኪዳን አደረገ።
\v 32 በኢየሩሳሌምና በብንያም የሚገኙትን ሁሉ በቃል ኪዳኑ እንዲቆሙ አደረጋቸው። የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ለአባቶቻቸው አምላክ ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን በመታዘዝ አደረጉ።
\s5
\v 33 ኢዮስያስም የእስራኤል ሕዝብ ከነበረው ምድር ላይ አስጸያፊውን ነገር ሁሉ አስወገደ። በእስራኤልም የነበሩት ሰዎች ሁሉ አምላካቸው እግዚአብሔርን እንዲያመልኩ አደረጋቸው። በእርሱ ዘመን ሁሉ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ከመከተል ዘወር አላሉም።
\s5
\c 35
\p
\v 1 ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ በመጀመሪያው ወር በአሥራ አራተኛው ቀን የፋሲካ ጠቦቶቹን አረዱ።
\v 2 ካህናቱን በየሥራ ቦታቸው አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት አበረታታቸው።
\s5
\v 3 እስራኤልንም ሁሉ ያስተምሩ ለነበሩት ለእግዚአብሔር ለተሰጡት ሌዋውያን ፦ "ቅዱሱን ታቦት የእስራኤል ንጉሥ የዳዊት ልጅ ሰለሞን በገነባው ቤት ውስጥ አስቀምጡት። ከዚህ በኋላ በትከሻችሁ እየተሸከማችሁ አታዟዙሩት፤ አሁንም አምላካችሁን እግዚአብሔርን አምልኩ፤ ሕዝቡንም እስራኤልን አገልግሉ።
\v 4 በእስራኤል ንጉሥ ዳዊት የተጻፈና በልጁም በሰለሞን ጭምር የተሰጠውን መመሪያ በመከተል በየአባቶቻችሁ ቤቶችና በየሥራ ክፍላችሁ ስም ራሳችሁን አደራጁ።
\s5
\v 5 በሕዝቡ ዝርያዎች በወንድሞቻችሁ የአባቶች ቤቶች ውስጥ በየሥራ ክፍላችሁ የኃላፊነት ቦታችሁን በመያዝና በሌዋውያን አባቶች ቤቶች ውስጥ በየሥራ ክፍላችሁ ቦታችሁን በመያዝ በተቀደሰው ሥፍራ ቁሙ።
\v 6 የፋሲካውን ጠቦቶች እረዱ፤ እናንተም ራሳችሁን ለእግዚአብሔር ስጡ። ለወንድሞቻችሁ ለእስራኤል ጠቦቶቹን ዝግጁ አድርጉላቸው፤ በሙሴ አማካይነት ለተሰጠው ለእግዚአብሔር ቃል በመታዘዝ አድርጉት።
\s5
\v 7 ኢዮስያስ ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን እዚያ ለነበሩት ሕዝብ ሁሉ ከመንጋው ሠላሳ ሺህ የበግና የፍየል ጠቦቶች ሰጠ። ሦስት ሺህ ወይፈኖችንም ሰጠ፤ እነዚህም የንጉሡ ኃብት ከነበሩት ነበሩ።
\v 8 መሪዎቹም ለህዝቡ፥ ለካህናቱና ለሌዋውያኑ የበጎ ፈቃድ ሥጦታዎችን ሰጡ። በእግዚአብሔር ቤት ባለሥልጣናት የነበሩት ኬልቅያስ፥ ዘካርያስና ይሒኤል ለፋሲካው መሥዋዕት እንዲሆን ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ትንንሽ ከብቶችና ሦስት መቶ በሬዎች ለካህናቱ ሰጡ።
\v 9 የሌዋውያኑ አለቆች ኮናንያ፥ ወንድሞቹም ሸማያና ናትናኤል፥ ሐሸቢያ፥ ይዒኤልና ዮዛባት ለፋሲካው መሥዋዕት አምስት ሺህ ትንንሽ ከብቶችና አምስት መቶ በሬዎች ለሌዋውያኑ ሰጡ።
\s5
\v 10 በመሆኑም አገልግሎቱ ዝግጁ ነበረ፤ ካህናቱም ለንጉሡ ትዕዛዝ ምላሽ በመስጠት በየሥራ ክፍላቸው ከሆኑት ከሌዋውያኑ ጋር በየቦታቸው ቆመው ነበር።
\v 11 የፋሲካ ጠቦቶቹንም አረዱ፤ ካህናቱም ከሌዋውያኑ እጅ የተቀበሉትን ደም ረጩ፤ ሌዋውያኑም የጠቦቶቹን ቆዳቸውን ገፈፉ።
\v 12 በሙሴ መጽሐፍ እንደተጻፈ ለእግዚአብሔር ለማቅረብና በሕዝቡ የአባቶች ቤቶች መሠረት በየሥራ ክፍላቸው ሊያድሏቸው የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለይተው አስቀመጡ። በወይፈኖቹም ላይ እንደዚሁ አደረጉ።
\s5
\v 13 መመሪያዎቹን በመከተል የፋሲካውን ጠቦቶች በእሳት ጠበሷቸው። የተቀደሱትን ሥጦታዎች በምንቸቶች፥ በሰታቴዎችና በመጥበሻዎች ቀቀሏቸው፤ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አዳረሷቸው።
\v 14 ከዚያም በኋላ ለራሳቸውና ለካህናቱም መሥዋዕቱን አዘጋጁ፤ የአሮን ልጆች ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስቡን በማቅረብ እስከ ምሽት ድረስ በሥራ ተጠምደው ስለነበር ሌዋውያኑ ለራሳቸውና ለአሮን ልጆች ለካህናቱ መሥዋዕቱን አዘጋጁ።
\s5
\v 15 ዳዊት፥ አሳፍ፥ ኤማንና የንጉሡ ባለ ራዕይ ኤዶታም በሰጡት መመሪያ መሠረት የአሳፍም ዝርያዎች መዘምራኑ በሥፍራቸው ቆመው ነበር። ጠባቂዎቹም በየበሮቹ ላይ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን መሥዋዕቱን ያዘጋጁላቸው ስለነበር የሥራ ቦታቸውን መልቀቅ አያስፈልጋቸውም ነበር።
\s5
\v 16 ስለዚህ ንጉሡ ኢዮስያስ ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለማቅረብ፥ በዚያን ጊዜ መላው የእግዚአብሔር አገልግሎት የፋሲካን በዓል ለማክበር ተፈፀመ።
\v 17 በዚያን ቦታ ተገኝተው የነበሩ የእስራኤል ሕዝብ በዚያን ጊዜ ፋሲካውንና ከዚያም ለሰባት ቀናት የቂጣ በዓልን አከበሩ።
\s5
\v 18 ከነቢዩ ከሳሙኤል ዘመን ጀምሮ እንደዚህ ያለ የፋሲካ በዓል በእስራኤል ተከብሮ አያውቅም፤ ከእስራኤልም ሌሎች ነገሥታት ሁሉ የትኛውም ኢዮስያስ ከካህናቱ፥ ከሌዋውያኑና ከይሁዳና እዚያ ከነበሩ ከእስራኤል ሕዝብና ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ጋር እንዳደረገው ያለ ፋሲካ አክብሮ አያውቅም።
\v 19 ይህ ፋሲካ የተከበረው ኢዮስያስ በነገሠ በአሥራ ስምንተኛው ዓመት ነበር።
\s5
\v 20 ከዚህ ሁሉ በኋላ ኢዮስያስ ቤተ መቅደሱን ካስተካከለ በኋላ የግብጽ ንጉሥ ኒካዑ በኤፍራጥስ ወንዝ ከርከሚሽን ሊዋጋ ወጣ፤ ኢዮስያስም ሊዋጋው ሄደ።
\v 21 ኒካዑ ግን ወደ እርሱ ፦" የይሁዳ ንጉሥ ሆይ ካንተ ጋር ምን አለኝ? ጦርነት የምዋጋው በሌላ ቤት ላይ ነው እንጂ በአንተ ላይ ዛሬ ለጦርነት አልመጣሁብህም። እግዚአብሔር እንድፈጥን አዝዞኛል፤ ስለዚህ ከእኔ ጋር በሆነው በእግዚአብሔር ላይ ጣልቃ አትግባ፤ አለበለዚያ ያጠፋሃል" በማለት መልዕክተኞችን ላከበት።
\s5
\v 22 ነገር ግን ኢዮስያስ ከእርሱ መመለስን እምቢ አለ። ከእርሱ ጋር ለመዋጋት ራሱን በሌላ መልክ ሸፈነ። ከእግዚአብሔር አፍ የመጣውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፤ ስለሆነም በመጊዶ ሸለቆ ውስጥ ሊዋጋ ሄደ።
\s5
\v 23 ቀስተኞችም ንጉሥ ኢዮስያስን ወጉት፤ ንጉሡም ለአገልጋዮቹ፦" ክፉኛ ቆስያለሁና ወደዚያ ውሰዱኝ" አላቸው።
\v 24 ስለዚህ አገልጋዮቹ ከሰረገላው አውርደው በሌላኛው ተጨማሪ ሰረገላ ውስጥ አስቀመጡት። ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰዱት፤ በዚያም ሞተ። በአባቶቹም መቃብር ተቀበረ። ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሁሉ ለኢዮስያስ አለቀሱለት።
\s5
\v 25 ኤርምያስም ለኢዮስያስ የሐዘን እንጉርጉሮ አወጣለት፤ እስከ ዛሬም ድረስ ውንዶችና ሴቶች መዘምራን ሁሉ ስለ ኢዮስያስ የሐዘን እንጉርጉሮ ያወጣሉ። እነዚህ መዝሙሮች በእስራኤል ልማድ ሆኑ፤ እነሆ በሐዘን እንጉርጉሮ መዝሙር ውስጥ ተጽፈዋል።
\s5
\v 26 ኢዮስያስን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮችና በእግዚአብሔር ሕግ ለተጻፈው ነገር በመታዘዝ ያደረጋቸው መልካም ድርጊቶች፥
\v 27 የእርሱ ድርጊቶች ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል።
\s5
\c 36
\p
\v 1 የምድሪቱም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወስደው በአባቱ ቦታ በኢየሩሳሌም አነገሡት።
\v 2 ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ ሦስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ።
\s5
\v 3 የግብጽ ንጉሥ ከኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አስወገደው፤ ምድሩንም አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መቶ መክሊት ወርቅ ቅጣት ጣለባት።
\v 4 የግብጽ ንጉሥ ወንድሙን ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ ንጉሥ አደረገው፤ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው። የኤልያቄምን ወንድሙን ኢዮአክስን ወሰደና ወደ ግብጽ አመጣው።
\s5
\v 5 ኢዮአቄም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ። በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ክፉውን ነገር አደረገ።
\v 6 ከዚያም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ጦርነት ከፍቶበት በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
\v 7 ናቡከደነፆር ከእግዚአብሔር ቤት ዕቃዎችም አንዳንዶቹን ወደ ባቢሎን ወሰደ፤ በባቢሎንም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ አስቀመጣቸው።
\s5
\v 8 ኢዮአቄምን በተመለከተ ሌሎቹ ጉዳዮችና ያደረጋቸው አስጸያፊ ድርጊቶች፥ በእርሱ ላይ በክፉነት የተያዙበት ድርጊቶች እነሆ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል። ልጁም ዮአኪን በእርሱ ቦታ ነገሠ።
\s5
\v 9 ዮአኪን መንገሥ በጀመረ ጊዜ ስምንት ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና አሥር ቀን ነገሠ። በእግዚአብሔር ፊት ክፉውን ነገር አደረገ።
\v 10 በፀደይ ወራት ንጉሥ ናቡከደነፆር ሰዎችን ልኮ ከእግዚአብሔር ቤት ከተወሰዱ የከበሩ ነገሮች ጋር ወደ ባቢሎን አመጣው፤ ዘመዱንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው።
\s5
\v 11 ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ሃያ አንድ ዓመቱ ነበር፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።
\v 12 በእግዚአብሔር በአምላኩ ፊት ክፉውን ነገር አደረገ። ከእግዚአብሔርም አፍ በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊት ራሱን አላዋረደም።
\s5
\v 13 ሴዴቅያስም ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር እንዲምል ባደረገው በንጉሡ በናቡከደነፆር ላይ አመፀ። ሴዴቅያስ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ላለመመለስ አንገቱን አደነደነ፤ ልቡንም አጠነከረ።
\v 14 በተጨማሪም የካህናቱ መሪዎችና ሕዝቡ የሌሎችን ሕዝቦች አስፀያፊ ነገሮች ምሳሌነት በመከተል እጅግ በጣም መተላለፍ አበዙ። እግዚአብሔር ለራሱ በኢየሩሳሌም የቀደሰውን የእግዚአብሔርን ቤት በከሉት።
\s5
\v 15 የአባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለማደሪያው ሥፍራ ከመራራቱ የተነሳ ደግሞ ደጋግሞ በመልዕክተኞቹ በኩል ቃል ይልክላቸው ነበር።
\v 16 እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪነሳ ድረስ፥ መሸሻ መንገድ እስከማይኖር ድረስ የእግዚአብሔርን መልዕክተኞች ይሳለቁባቸው፥ ቃሉንም ያቃልሉና በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
\s5
\v 17 ስለዚህም እግዚአብሔር የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም በቤተ መቅደሱ ውስጥ ወጣቶቻቸውን በሰይፍ ገደላቸው፤ ለወጣቶቻቸው ወይም ለደናግልቱ፥ ለሽማግሌዎች ወይም ለሸበቶዎች አልራራም። እግዚአብሔር ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
\s5
\v 18 የእግዚአብሔርንም ቤት እቃዎች ሁሉ ትልልቁንም ትንንሹንም የእግዚአብሔርንም ቤት ሃብትና የንጉሡንና የመሪዎቹን ሃብት እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
\v 19 የእግዚአብሔርን ቤት አቃጠሉ፤ የኢየሩሳሌምን አጥር አፈረሱ፤ ቤተ መንግሥቶቹን ሁሉ አቃጠሉ፤ በውስጧ ያሉትን ውብ ነገሮች ሁሉ አጠፉ።
\s5
\v 20 ከሰይፍም ያመለጡትን ንጉሡ ወደ ባቢሎን አጋዛቸው። የፋርስ መንግሥት አገዛዝ እስኪደርስ ድረስ ለእርሱና ለልጆቹ አገልጋዮች ሆኑ።
\v 21 ይህ የሆነው ምድሪቱ የሰንበት እረፍትዋን እስክታገኝ ድረስ በነቢዩ በኤርምያስ አፍ የተነገረውን የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈፀም ነው። በዚህ መንገድ ሰባ ዓመት በማሳለፍ ተትታ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ሰንበቷን አከበረች።
\s5
\v 22 በኤርምያስ አፍ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል እንዲፈፀም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት እግዚአብሔር የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አነሳሳ። እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ አስነገረ፤ በጽሑፍም አደረገው።
\v 23 "የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ የሚለው ይህ ነው፦ 'የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ለእርሱ ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል። በመካከላችሁ ከእርሱ ሕዝብ መካከል ማንም ቢሆን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ይሁን፤ እርሱም ወደ ምድሪቱ ይውጣ" አለ።

2027
18-JOB.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,2027 @@
\id JOB
\ide UTF-8
\h ኢዮብ
\toc1 ኢዮብ
\toc2 ኢዮብ
\toc3 job
\mt ኢዮብ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ዖጽ በሚባል ምድር ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ኢዮብም በደል የማይገኝበት፤ ትክክለኛ፤ እግዚአብሄርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው ነበረ።
\v 2 ለእርሱም ሰባት ወንዶችና ሶስት ሴቶች ልጆች ተወልደውለት ነበር።
\v 3 ሰባት ሺህ በጎች፤ ሶስት ሺህ ግመሎች፤ አምስት ሺህ ጥንድ በሬዎችና አምስት ሺህ አህዮች እንዲሁም እጅግ ብዙ ሰራተኞች ነበሩት። ይህም ሰው በምስራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ሰው ነበር።
\s5
\v 4 ወንዶች ልጆቹም በየተመደበላቸው ተራ በያንዳንዳቸው ቤት ግብዣ ያደርጉ ነበር፤ ሦስቱ እኅቶቻቸውም ከእነርሱ ጋር እንዲበሉና እንዲጠጡ ልከው ይጠሩአቸው ነበር።
\v 5 የግብዣቸውም ቀናቶች ሲያበቁ ኢዮብ፦ ያስጠራቸውና ለእግዚአብሔር መልሶ ይቀድሳቸው ነበር።ማልዶ በጠዋት ተነስቶ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ረግመው ይሆናል” ብሎ ፤ ለልጆቹ ለእያንዳንዳቸው የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል። ይህንንም ኢዮብ ሁልጊዜ ያደርግ ነበር።
\s5
\v 6 በኋላም የእግዚአብሔር ልጆች በያህዌ ፊት ራሳቸውን የሚያቀርቡበት ቀን ነበረ ፥ ሰይጣንም ደግሞ ከእነርሱ ጋር መጣ።
\v 7 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦“ ከወዴት እየመጣህ ነው? ” አለው። ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁ፥ በእርስዋም ላይ ወዲህና ወዲያ ተመላልሼ መጣሁ” አለ።
\v 8 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ”በውኑ ባሪያዬን ኢዮብንስ ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ በደል የማይገኝበት ትክክለኛ ሰው ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም“ አለው።
\s5
\v 9 ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ እንዲህ አለ፦ “ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው እንዲሁ ነውን?
\v 10 በእርሱና በቤቱ ባለውም ነገር ሁሉ ዙሪያ በየአቅጣጫው አጥር አላደረግህለትምን? የእጁን ሥራ ባርከህለታል፥ ሐብቱም በምድር ላይ በዝቶአል።
\v 11 ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሀብት ሁሉ አውድም ፤ ፊትለፊት ይክድሃል።”
\v 12 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ “እነሆ እርሱ ያለው ነገር ሁሉ በስልጣንህ ስር ነው፥ በእርሱ ላይ ግን ጉዳት እንዳታደርስ” አለው። ሰይጣንም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ።
\s5
\v 13 ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ በታላቅ ወንድማቸው ቤት በሚበሉበትና የወይን ጠጅ በሚጠጡበት ቀን እንዲህ ሆነ፤
\v 14 መልክተኛ ወደ ኢዮብ መጥቶ፦ ”በሬዎች እርሻ እያረሱ፥ በአጠገባቸውም አህዮች ተሰማርተው ነበር፤
\v 15 የሳባም ሰዎች አደጋ አድርሰው ወሰዱአቸው፥ ሰራተኞቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
\s5
\v 16 እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦“ የእግዚአብሔር እሳት ከሰማይ ወደቀ፥ በጎቹንና ጠባቂዎችን አቃጥሎ በላቸው፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
\v 17 እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦ ”ከለዳውያን በሦስት ቡድን ተከፍለው በግመሎች ላይ አደጋ ጥለው ወሰዱአቸው ፥ ሰራተኞቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
\s5
\v 18 እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ ሌላ መጥቶ፦ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት እየበሉና የወይን ጠጅ እየጠጡ ነበር፤
\v 19 ታላቅ ነፋስ ከምድረ በዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታውና በልጆቹ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም ሞቱ፤ እኔም እንድነግርህ ብቻዬን አመለጥሁ“ አለው።
\s5
\v 20 ኢዮብም ተነሣ ልብሱንም ቀደደ፥ ራሱንም ተላጨ፥ በምድርም ላይ በፊቱ ተደፍቶ እግዚአብሔርን አመለከ፤
\v 21 እንዲህም አለ፦ ”ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደዚያ እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ወሰደ፤ የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።“
\v 22 በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ኢዮብ ሐጢያት አላደረገም፥ በስንፍናም እግዚአብሔርን አልከሰሰም።
\s5
\c 2
\p
\v 1 በድጋሚ የእግዚአብሔር ልጆች በያህዌ ፊት ራሳቸውን በሚያቀርቡበት ቀን ፥ ሰይጣንም ደግሞ አብሮ መጣ።
\v 2 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦“ ከወዴት እየመጣህ ነው? ” አለው። ሰይጣንም ለእግዚአብሔር ሲመልስ፦ “ምድርን ሁሉ ዞርሁ፥ በእርስዋም ላይ ወዲህና ወዲያ ተመላልሼ መጣሁ” ብሎ አለ።
\s5
\v 3 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፦ ”በውኑ ባሪያዬን ኢዮብንስ ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ በደል የማይገኝበት ትክክለኛ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ሰው የለም። ምንም እንኳ ያለምክንያት በእርሱ ላይ በከንቱም ጥፋት እንዲመጣበት ግፊት ብታደርግብኝም ፥ እርሱ ግን እስከ አሁን በታማኝነቱ ጸንቷል“ አለው።
\s5
\v 4 ሰይጣንም መልሶ እግዚአብሔርን፦ “ቆዳ በርግጥ ስለ ቆዳ ነው፤ ሰው ያለውን ነገር ሁሉ ሕይወቱን ለማዳን ሲል ይሰጣል” አለው።
\v 5 ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንቱንና ሰውነቱ ላይ ጉዳት ብታደርስ ፊተ ለፊት ይክድሃል” አለው።
\v 6 እግዚአብሔም ሰይጣንን፦ ” ሕይወቱን ብቻ ተው፤ እነሆ፥ እርሱ በእጅህ ነው“ አለው።
\s5
\v 7 እናም ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ። ኢዮብንም ከውስጥ እግሩ እስከ ራስ ጸጉሩ ድረስ በሚያሰቃይ ቍስል መታው።
\v 8 ኢዮብም ሰውነቱን ለመፋቅ የሸክላ ስባሪ ወሰዶ በአመድ ላይ ተቀመጠ።
\s5
\v 9 በኋላም ሚስቱ ፦ ”እስከ አሁን በታማኝነት ጸንተሃል እንዴ? እግዚአብሔርን እርገምና ሙት“ አለችው።
\v 10 እርሱ ግን መልሶ ”አንቺ እንደ ሰነፍ ሴቶች ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ብቻ እንጂ ክፉን አንቀበልም ብለሽ ነው የምታስቢው? “ አላት። በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ኢዮብ በአፉ ቃል ሐጢያት አላደረገም።
\s5
\v 11 ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ከየስፍራቸው መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስ፥ ነዕማታዊው ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ከኢዮብ ጋረ ሊያለቅሱና ሊያጽናኑት በአንድነት ጊዜ አመቻችተው መጡ።
\s5
\v 12 ከሩቅ ዓይናቸውን አማትረው ሲመለከቱ በትክክል ሊለዩት አልቻሉም፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ እያንዳንዳቸውም ልብሳቸውን ቀደዱ፥ አቧራ ወደ ላይ እየበተኑ ራሳቸው ላይ ነሰነሱ።
\v 13 ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊት ከእርሱ ጋር መሬት ላይ ተቀመጡ፤ ሕመሙም እጅግ ከባድ እንደነበረ ስላዩ ከእርሱ ጋር አንድ ቃል ለመናገር የደፈረ አልነበረም።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ከዚህም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ።
\v 2 እንዲህም አለ፦
\v 3 “ያ የተወለድሁበት ቀን ፤ 'ወንድ ልጅም ተፀነሰ' የተባለበት ሌሊት ይጥፋ”
\s5
\v 4 ያ ቀን ጨለማ ይሁን እግዚአብሔርም ከላይ አያስበው ፤ የጸሀይ ብርሀንም አያግኝው።
\v 5 ጨለማና የሞት ጥላ የራሳቸው እንደሆነ ይቁጠሩ፤ ዳመናም ይኑርበት፤ ቀኑን የሚያጨልሙ ነገሮች ሁሉ በርግጥ ያስደንግጡት።
\s5
\v 6 ያንን ሌሊት ድቅድቅ ጨለማ ይያዘው፤ በዓመቱ ካሉት ቀኖች ጋር ደስ አይበለው፤ በወራት ውስጥ ገብቶ አይቈጠር።
\v 7 ያቺ ምሽት መካን ትሁን፤ ወደ እርሷም የደስታ ድምጽ አይግባበት።
\s5
\v 8 ሌዋታንን እንዴት ማንቃት እንዳለባቸው የሚያውቁ ያንን ቀን ይርገሙት።
\v 9 አጥቢያ ኮከቦች ይጨልሙ፤ ያ ቀን ብርሃንን ሲጠባበቅ አያግኝ፥ የንጋትንም ወገግታ አይመልከት፤
\v 10 ምክንያቱም የእናቴን ማኅፀን ደጅ አልዘጋምና፥ መከራንም ከዓይኔ አልሰወረምና።
\s5
\v 11 ከማኅፀን ስወጣ ስለ ምን አልሞትሁም? እናቴ ስትወልደኝስ ስለምን አልጠፋሁም?
\v 12 ጕልበቶቿ ስለ ምን ተቀበሉኝ? ጡቶቿስ እንድጠባ ስለ ምን ተቀበሉኝ?
\s5
\v 13 ይሄኔ በጸጥታ በተጋደምሁ፤
\v 14 አሁን ፈርሶ ያለውን መቃብር ለራሳቸው ከገነቡት የምድር ነገሥታትና አማካሪዎች ጋር፥ አንቀላፍቼም ባረፍሁ ነበር፤
\s5
\v 15 ወይም ባንድ ወቅት ቤታቸውን በብር ከሞሉ ወርቅም ከነበራቸው መኳንንት ጋር በተጋደምሁ ነበር፥
\v 16 ወይም ያለጊዜያቸው እንደተወለዱ፥ ብርሃንንም አይተው እንደማያውቁ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።
\s5
\v 17 በዚያ ክፉዎች ረብሻቸውን ያቆማሉ፤ የደከሙትም በዚያ ያርፋሉ።
\v 18 በዚያ እስረኞች አርፈው በአንድነት ይቀመጣሉ፤ የአስጨናቂውን ጠባቂ ድምፅ አይሰሙም።
\v 19 ታናናሽና ታላላቅ ሰዎች በዚያ አሉ፤ በዚያም ባሪያ ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።
\s5
\v 20 በመከራ ላለ ሰው ብርሃን ፤ ነፍሳቸው መራራ ለሆነችባቸውስ ህይወት፤
\v 21 የተሰወረን ሀብት ከሚፈልጉ ይልቅ ሞትን እየተመኙ ላልመጣላቸው ህይወት ለምን ተሰጠ?
\v 22 መቀበሪያቸውን ባገኙ ጊዜ እጅግ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉ ሕይወት ለምን ተሰጠ?
\s5
\v 23 መንገዱ ለጠፋበት ሰው፥ እግዚአብሔርም አጥር ላጠረበት ሰው ብርሃን ለምን ተሰጠ?
\v 24 በመመገብ ምትክ ሲቃዬ ፈጥኖ ይመጣልና፥ መቃተቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል።
\s5
\v 25 የፈራሁት ነገር መጥቶብኛልና፥ የደነገጥሁበትም ደርሶብኛል።
\v 26 በእርጋታና በጸጥታ አልተቀመጥሁም፥ አላረፍሁም ይልቅ መከራና ችግር መጣብኝ።
\s5
\c 4
\p
\v 1 ቴማናዊውም ኤልፋዝ እንዲህ ሲል መለሰ ፦
\v 2 አንድ ሰው ከአንተ ጋር ለመነጋገር ቢሞክር ታዝናለህን? ነገር ግን ከመናገር ራሱን ሊገታ የሚችል ማን ነው?
\v 3 እነሆ፥ አንተ ብዙዎችን ታስተምር ነበር፥ የደከሙትንም እጆች ታበረታ ነበር፥
\s5
\v 4 ቃልህ ሊወድቅ የተሰናከለውን ያስነሣ ነበር፥ አንተም የሚብረከረከውን ጕልበት ታጸና ነበር።
\v 5 አሁን ግን ጥፋት በአንተ ላይ መጥቶአል፥ አንተም ደከመህ፤ በርግጥ ደረሰብህ፥ አንተም ታወክህ።
\v 6 እግዚአብሔርን መፍራትህ ድፍረትን፥ ያካሄድህስ ቀናነት ተስፋን አይሰጥህምን?
\s5
\v 7 እባክህ ይህን እንድታስብ እለምንሃለሁ፥ ንጹሕ ሆኖ የጠፋ ማን አለ? ልበ ቅንስ ሆኖ የተደመሰሰ ማን ነው?
\v 8 እኔ እንዳየሁ፥ ኃጢአትን የሚያርሱ፥ ሁከትንም የሚዘሩ መልሰው ያንኑ ያጭዳሉ።
\v 9 በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፥ በቍጣውም ንዳድ ያልቃሉ።
\s5
\v 10 የአንበሳ ግሳት፥ የቁጡ አንበሳ ድምፅ፥ የደቦል አንበሳ ጥርስ ተሰባብረዋል።
\v 11 ያረጀ አንበሳ አደን አጥቶ ይሞታል፥ የአንበሳይቱም ግልገሎች የትም ይበተናሉ።
\s5
\v 12 ለእኔም ነገሩ በምሥጢር መጣልኝ፥ ጆሮዬም ስለነገሩ ሹክሹክታን ሰማች።
\v 13 ከባድ እንቅልፍ በሰው ላይ በሚሆንበት ጊዜ፥ በሃሳብ ብዛት በሌሊት ሕልም ሲመጣ፥
\s5
\v 14 ድንጋጤና መንቀጥቀጥ መጡብኝ አጥንቶቼም ሁሉ ተንቀጠቀጡ
\v 15 በፊቴም መንፈስ አለፈ የሰውነቴም ጠጕር ቆመ።
\s5
\v 16 መንፈሱም ቆመ፥ መልኩን ግን ለመለየት አልቻልሁም፥ ቅርጹ በዓይኔ ፊት ነበረ፤ ጸጥታም ሆነ እንዲህም የሚል ድምፅ ሰማሁ፤
\v 17 “በውኑ ሥጋ የለበሰ ሰው ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን?ሰውስ ከፈጣሪው ይልቅ ንጹህ ሊሆን ይችላልን?”
\s5
\v 18 እነሆ፥ እግዚአብሔር በአገልጋዮቹ ካልተማመነ፤ መላእክቱንም በስህተት ከወቀሳቸዋል፤
\v 19 ይልቁንስ በሸክላ ቤቶች ውስጥ በሚኖሩ፥ መሠረታቸውም በትቢያ ውስጥ ለሆነ፥ ከብል ቀድመው በሚጠፉት ዘንድ ይህ እንዴት እውነት ይሆን?
\s5
\v 20 በጥዋትና በማታ መካከል ይጠፋሉ፤ ማንም ሳያውቀው እስከ ወዲያኛው ይጠፋሉ።
\v 21 የድንኳናቸው ገመድ ከመካከላቸው የተነቀለ አይደለምን? ይሞታሉ፦ ያለጥበብም ይሞታሉ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 አሁን እስቲ ተጣራ፤ የሚመልስ አንድ እንኳ አለ? ከቅዱሳንስ ወደየትኛው ትዞራለህ?
\v 2 ሰነፍን ሰው ቍጣ ይገድለዋል፥ ሞኙንም ቅንዓት ያጠፋዋል።
\v 3 ቂል ሰው ሥር ሲሰድድ አየሁ፥ ነገር ግን በድንገት ቤቱን ረገምሁት።
\s5
\v 4 ልጆቹም ከደኅንነት ከለላ ውጪ ናቸው፥ በከተማም አደባባይ የተረገጡ ናቸው፥ አንድም የሚያድናቸው የለም።
\v 5 የተሰበሰበውን ሰብል በተራቡ በሌሎች ተበላ፥ ከእሾህ ውስጥ እንኳ የወጡ ሰዎች ወሰዱት፤ ያለውም ሁሉ ሀብትን በተጠሙ ሰዎች ተዋጠ።
\s5
\v 6 ችግር እንዲሁ ከአፈር አይመጣም፥ መከራም ከመሬት አይመነጭም፤
\v 7 ነገር ግን የእሳት ፍንጣሪዎች ወደ ላይ እንደሚበርሩ፥ እንዲሁ ሰው መከራን በራሱ ላይ ያመጣል።
\s5
\v 8 እኔ ግን እግዚአብሔርን ወደራሱ፥ ጉዳዬን ወደ ማቀርብለት ወደ እግዚአብሔር እመለስ ነበር።
\v 9 እርሱ ታላቅና የማይመረመሩ ዋና ነገሮችንና የማይቈጠሩ አስደናቂ ነገሮችን ያደርጋል።
\v 10 በምድር ላይ ዝናብን ይሰጣል፥ በእርሻም ላይ ውኃ ይልካል።
\s5
\v 11 የተዋረዱትን በከፍታ ሊያኖር ፥ ኀዘንተኞችንም ለደኅንነት ከፍ ለማድረግ ይህንን ያደርጋል።
\v 12 እጃቸው እቅዳቸውን እንዳይፈጽም የተንኰለኞችን ወጥመድ ከንቱ ያደርጋል።
\v 13 ጠቢባንን በተንኰላቸው ይይዛቸዋል የተንኮለኞችንም ዕቅድ ያጠፋል።
\s5
\v 14 በቀን ከጨለማ ጋር ይጋጠማሉ፥ በዕኩለቀንም በሌሊት እንዳሉ ያክል በዳበሳ ይሄዳሉ።
\v 15 ነገር ግን ድሀውን ከአፋቸው ሰይፍ፤ ችግረኛውንም ከኃያላን እጅ ያድነዋል።
\v 16 ስለዚህ ድሀው ተስፋ አለው፤ ፍትህ አልባነት ግን አፍዋን ትዘጋለች።
\s5
\v 17 እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚያርመው ሰው ምስጉን ነው፤ ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን አምላክንተግሣጽ አትናቅ።
\v 18 ምክንያቱም እርሱ ይሰብራል፥ ይጠግናል ያቈስላል በኋላም በእጆቹ ይፈውሳል።
\v 19 እርሱ ከስድስት ክፉ ነገሮች ውስጥ ያወጣሃል፥ በርግጥ በሰባተኛው ክፋት አይነካህም።
\s5
\v 20 በራብ ጊዜ ከሞት፥ በጦርነትም ከሰይፍ ስለት ያድንሃል።
\v 21 ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፤ ጥፋትም ሲመጣ አትፈራም።
\v 22 በጥፋትና በራብ ላይ ትስቃለህ፤ የምድር አውሬዎችንም አትፈራም፤
\s5
\v 23 ከምድርህ ድንጋይ ጋር ኪዳን ይኖርሃል ከምድር አራዊትም ጋር በሰላም ትሆናለህ።
\v 24 ድንኳንህም በደህንነት እንዳለ ታውቃለህ፤ በረትህን ትጐበኛለህ አንድም አይጠፋብህም።
\v 25 ዘሮችህም ታላቅ እንደሚሆኑ፥ ትውልድህም እንደ ምድር ሣር እንደሚበዙ ታውቃለህ።
\s5
\v 26 የእህሉ ነዶ ደርሶ በወቅቱ ወደ አውድማ እንደሚገባ፥ ዕድሜን ጠግበህ ወደ መቃብር ትሄዳለህ።
\v 27 እነሆ፥ ይህንን ነገር መረመርን፥ ነገሩ እውነት ነው፤ ልብ በለው፤ የራስህም እውቀት አድርገው።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህም አለ፦
\v 2 ኦ ስቃዬ ምነው በተመዘነ ኖሮ! መከራዬም ሁሉ ምነው በሚዛን ላይ በተደረገ ኖሮ!
\v 3 ከባሕር አሸዋ ይልቅ ይከብድ ነበርና ለዚህ ነው ቃሎቼ የድፍረት ቃላት የሆኑት።
\s5
\v 4 ሁሉን የሚችል አምላክ ቀስት በውስጤ ነው፥ መርዙንም ነፍሴ ትጠጣለች፤ የእግዚአብሔር ማስደንገጥ በእኔ ላይ ተሰልፎአል።
\v 5 በውኑ የሜዳ አህያ ሣር እያለው በዝለት ያናፋልን? በሬስ ገለባ እያለው በረሀብ ይጮኻልን?
\v 6 ጣዕም የሌለው ነገርስ ያለ ጨው ይበላልን? ወይስ በእንቁላል ውኃ ውስጥ ጣዕም አለን?
\s5
\v 7 ለመንካት ሰውነቴ እምቢ አላቸው፤ እንደሚያስጸይፍ ምግብ ሆኑብኝ።
\v 8 ምነው ልመናዬ በደረሰልኝ! እግዚአብሔርም መሻቴን ምነው በሰጠኝ!
\v 9 እግዚአብሔርም አንድ ጊዜ እኔን ማጥፋት ደስ ቢያሰኘው እጁንም ዘርግቶ ከዚህ ሀይወት ቢያስወግደኝ!
\s5
\v 10 ይህም መጽናናት ይሆንልኛል፤ በማይበርድ ሕመም ውስጥ ብሆንም፥ የቅዱሱን ቃል አልክድምና።
\v 11 እድጠብቅ አቅሜ ምንድን ነው? የምታገሰውስ የህይወቴ ፍጻሜ ምን ስለሆነ ነው?
\s5
\v 12 ጕልበቴ የድንጋይ ጕልበት ነውን? ወይስ ሥጋዬ የተሰራው ከናስ ነውን?
\v 13 በእኔ ውስጥ ሊረዳኝ የሚችልነገር እንደሌለ ጥበብም ከእኔ እንደ ተባረረ እውነት አይደለምን?
\s5
\v 14 ሁሉን የሚችል አምላክን መፍራት የተወ ሰው፥ በዝለት ሊወድቅ ለቀረበ ስንኳ ታማኝነት ከወዳጁ ሊሆንለት ይገባል።
\v 15 ነገር ግን ወንድሞቼ ጥቂት ቆይቶ ውሃ እንደማይኖረው r እንደ በረሃ ወንዝ የማይታመኑ ሆኑብኝ።
\v 16 ከበረዶ የተነሣ ፥በውስጡም ከተሰወረው አመዳይ፤ ወንዙ ደፍርሶ ይጠቁራል፥
\v 17 ሙቀትበመጣ ጊዜ ይደርቃሉ፤ በበጋም ወቅት ከስፍራቸው ይጠፋሉ።
\s5
\v 18 ተጔዥ ነጋዴዎች ውሃ ፍለጋ መንገዳቸውን ሲቀይሩ፤ ወደ በረሃ ገብተው ተቅበዝብዘው ይጠፋሉ።
\v 19 የቴማን ነጋዴዎች በዚያ ተመለከቱ፥ የሳባ መንገደኞችም ተስፋ አደረጉ።
\v 20 ውሃ እንደሚያገኙ ተማምነው ነበርና አፈሩ፤ ወደዚያ ደረሱ፥ ነገር ግን ተታልለው ነበር።
\s5
\v 21 አሁንም እናንተ እንዲሁ ደረቅ ሆናችሁብኝ መከራዬን አይታችሁ ለራሳችሁ ፈራችሁ።
\v 22 በውኑ እኔ፦ ”አንዳች ነገር ስጡልኝ? ፤ ከሃብታችሁ ስጦታ አቅርቡልኝ?
\v 23 ወይስ፦ ከጠላቴ እጅ አድኑኝ? ከአስጨናቂዎቼ እጅ ተቤዡኝ“ ብያችኋለሁን?
\s5
\v 24 አስተምሩኝ፥ እኔም ዝም እላለሁ፤ ምን ጋር እንደተሳሳትሁ አስረዱኝ።
\v 25 የእውነት ቃል እንዴት ያማል! ነገር ግን የእናንተ ሙግት እንዴት እኔን ይገሥጻል?
\s5
\v 26 ተስፋ እንደ ሌለው ሰው ንግግር ቃሌን እንደ ነፋስ ችላ ለማለት ታስባላችሁን?
\v 27 በርግጥ አባት አልባ በሆኑ ልጆች ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፤ ለወዳጆቻችሁም ጕድጓድ ትቈፍራላችሁ።
\s5
\v 28 አሁንም፥ እባካችሁ፥ ወደ እኔ ተመልከቱ፤ በእርግጥ በፊታችሁ አልዋሽም።
\v 29 እባካችሁ፥ ተመለሱ፤ ፍትህ አልባነት በእናንተ መካከል አይሁን፤ በርግጥ ምክንያቴ ጽድቅ ነውና መለስ በሉ።
\v 30 በውኑ በምላሴ ክፋት አለን? አፌስ ተንኰልን መለየት አይችልምን?
\s5
\c 7
\p
\v 1 ለእያንዳንዱ ሰው ህይወት በምድር ብርቱ ልፋት አይደለምን?ቀኖቹስ እንደ ተቀጣሪ ሰራተኛ ቀኖች አይደሉምን?
\v 2 የምሽት ጥላን እንደሚመኝ አገልጋይ፤ደመወዙንም በጽኑ እንደሚፈልግ ቅጥረኛ፤
\v 3 እንዲሁ የጉስቁልና ወራትና፤ መከራ የተሞሉ ለሊቶችን በጽናት እንዳልፍ ተሰጡኝ::
\s5
\v 4 በተኛሁ ጊዜ፦ መቼ እነሣለሁ? ሌሊቱስ መቼ ያልፋል እላለሁ። እስኪነጋ ድረስም ወዲያና ወዲህ እገላበጣለሁ።
\v 5 ሥጋዬ ትልና የአመድ ቅርፊት ለብሶአል፤ ደርቆ የነበረው የቆዳዬም ቁስል እንደ ገና ያመረቅዛል።
\s5
\v 6 ቀኖቼ ከሸማኔ መወርወርያ ይልቅ ፈጣን ናቸው፥ ያለ ተስፋም ያልፋሉ።
\v 7 ሕይወቴ አንድ ትንፋሽ እንደ ሆነ፤ ዓይኔም መልካም ነገርን ከእንግዲህ አንደማያይ አሳሰበኝ።
\s5
\v 8 የሚያየኝ የእግዚአብሔር ዓይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፤ ዓይኖችህ በእኔ ላይ ይሆናል፥ እኔ ግን አልገኝም።
\v 9 ደመና ተበትኖ እንደሚጠፋ፥ እንደዚሁ ወደ ሲኦል የሚወርድ ተመልሶ አይወጣም።
\v 10 ወደ ቤቱ ዳግመኛ አይመለስም፥ የነበረበት ስፍራውም ዳግመኛ አያውቀውም።
\s5
\v 11 ስለዚህም አፌን አልገድበውም፤ በመንፈሴ ስቃይ ሆኜ እናገራለሁ፤ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አቤቱታዬን አቀርባለሁ።
\v 12 ጠባቂ በላዬ ትቀጥርብኝ ዘንድ፥ እኔ ባሕር ወይስ የባህር አውሬ ነኝን?
\s5
\v 13 እኔም፦ "አልጋዬ ያጽናናኛል፥ መቀመጫዬም የኀዘን እንጕርጕሮዬን ያቀልልኛል" ባልሁ ጊዜ፥
\v 14 አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥ በራእይም ታስደነግጠኛለህ፤
\v 15 ስለዚህም እኔ አጥንቴን ከምታገስ ይልቅ መታነቅንና ሞትን እመርጣለሁ።
\s5
\v 16 ለዘላለም መኖርን እንዳልመኝ፤ ሕይወቴን ናቅኋት። ቀኖቼ ዋጋ ቢስ ናቸውና እባካችሁ ተዉኝ።
\v 17 ትኩረት ትሰጠው ዘንድ ፥ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ ሰው ምንድር ነው፥
\v 18 ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥ በየጊዜውስ ትፈትነው ዘንድ?
\s5
\v 19 የማትተወኝ እስከ መቼ ነው? ምራቄንስ እስክውጥ ድረስ የማትለቅቀኝ እስከ መቼ ነው?
\v 20 ሰውን የምትጠብቅ ሆይ፥ ኅጢያትንስ አድርጌ እንደ ሆነ ይህ ላንተ ምንድን ነው? ሸክም እ ሆንብህ ዘንድ? ስለ ምን የኢላማሀ ግብ አደረግኸኝ?
\s5
\v 21 መተላለፌን ይቅር ብለህ ስለ ምን ጉስቁልናዬን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በጥንቃቄም ትፈልገኛለህ፥ አታገኘኝም።
\s5
\c 8
\p
\v 1 ሹሐዊውም በልዳዶስ መለሰ እንዲህም አለ፦
\v 2 እስከ መቼ እነዚህን ነገሮች ትናገራለህ? የአፍህስ ቃል እስከ መቼ እንደ ብርቱ ነፋስ ይሆናል?
\v 3 በውኑ እግዚአብሔር ፍትህን ያቃውሳልን? ሁሉንም የሚችል አምላክ ጽድቅን ያጣምማልን?
\s5
\v 4 ልጆችህ በድለውት እንደ ሆነ፥ እርሱም በበደላቸው እጅ አሳልፎ እንደሰጣቸው እናውቃለን።
\v 5 ነገር ግን እግዚአብሔርን በትጋት ብትፈልገውና፥ ሁሉንም ለሚችለው አምላክ ልመናህን ብታቀርብ፥
\s5
\v 6 ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ ስለ አንተ ይቆማል፥ በርግጥ የታመነ መኖሪያ ያደርግልሃል።
\v 7 ጅማሬህ ትንሽ ቢሆንም እንኳ ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።
\s5
\v 8 ስለ ቀደመው ዘመን ትውልድ ትጠይቅ ዘንድ እለምንሃለሁ፥ አባቶቻቸውም ከመረመሩና ካገኙት ነገር ለመማር ትጋ፤
\v 9 (ዘመናችን በምድር ላይ እንደ ጥላ ስለሆነ እኛ ትናንት ተወለድን፤ ምንም አናውቅም) ፤
\v 10 እነዚህ የሚነግሩህና የሚያስተምሩህ አይደሉምን? ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?
\s5
\v 11 በውኑ ረግረግ በሌለበት ደንገል ሳር ይበቅላልን? ወይስ ቄጠማ ውኃ በሌለበት ቦታ ይለመልማልን?
\v 12 ገና ለምለም አረንጓዴ ሆኖ ሳይቈረጥ፥ ከአትክልት ሁሉ በፊት ይጠወልጋል።
\s5
\v 13 እግዚአብሔርን የሚረሱ ሁሉ የመንገዳቸው ፍጻሜ እንዲሁ ነው፤ አምላክ የሌለው ሰው ተስፋም ይጠፋል።
\v 14 መታመኛቸው እንደሚናድባቸው፥ እምነቱም የሸረሪት ድር አይነት የሆነበት።
\v 15 እዲህ አይነት ሰው ቤቱን ይደገፋል፥ነገር ግን አይቆምለትም፤ደግፎም ይይዘዋል፥ አይጸናለትም።
\s5
\v 16 ፀሐይም እንደወጣች ይለመልማል፥ ጫፉም በአትክልቱ ቦታ ጎልቶ ይወጣል።
\v 17 ሥሮቹ በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጠማሉ፤ በድንጋዮቹም መካከል መልካም ቦታን ይፈልጋሉ።
\v 18 ነገር ግን ይህ ሰው ከቦታው ቢጠፋ፦ ስፍውም "ፈጽሞ አቼህ አላውቅም" ብሎ ይክደዋል።
\s5
\v 19 እነሆ፥ የደስእንደዚህ አይነትሰው ደስታ ይህ ነው፤ ሌሎች ተክሎች ከዚያው አፈር በፋንታው ይበቅላሉ።
\v 20 እነሆ፥ እግዚአብሔር ንጹሁን ሰው አይጥለውም፥ የክፉ አድራጊውንም እጅ አያበረታም።
\s5
\v 21 አፍህን እንደ ገና ሳቅ፥ ከንፈሮችህንም በደስታ ጩኊት ይሞላል።
\v 22 የሚጠሉህ እፍረትን ይለብሳሉ፤ የአመጸኞችም ድንኳን አይገኝም።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህም አለ፦
\v 2 “ እንዲህ እንደ ሆነ በእውነት አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሰው በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል?
\v 3 ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር ቢፈልግ፥ ከሺህ ነገር አንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር በልቡ ጠቢብ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ እርሱን ተዳፍሮ በደኅና የተሳካለት ማን ነው?
\v 5 በቍጣው ተራሮችን ሲገለብጣቸው፤ ተራሮችን ሲነቅላልቸው ለማን አስቀድሞ ተናገረ።
\v 6 ምድርን ከስፍራዋ ያሚያናውጣት እርሱ፥ ምሰሶዎችዋንም ያንቀጠቅጣቸዋል።
\s5
\v 7 ይኸው እግዚአብሔር ፀሐይን እንዳትወጣ ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም ይከልላቸዋል።
\v 8 ሰማያትን በራሱ ይዘረጋል፥ የባሕሩን ማዕበል የሚገዛ በላዩም ይራመዳል።
\v 9 ድብና ኦሪዮን የሚባሉትን ኮከቦች፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ስብስቦች ሠርቶአል።
\s5
\v 10 ይኸው እግዚአብሔር የማይመረመሩ ታላላቅ ነገሮችን፥ በርግጥ የማይቈጠሩ ተአምራቶችን ያደርጋል።
\v 11 እነሆ፥ ወደ እኔ ቢመጣ አላየውም፤፤ በአጠገቤም ቢያልፍ አላውቀውም።
\v 12 እነሆ አንድን ሰው ነጥቆ ቢወስድ የሚከለክለው ማን ነው? ምን እያደረግህ ነው? የሚለውስ ማን ነው?
\s5
\v 13 እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ የረዓብ ረዳቶች ከእርሱ በታች ይሰግዳሉ።
\v 14 ይልቁንስ መልስ ልመልስለት፥ ከእርሱ ጋርስ ለክርክር ቃልን እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?
\v 15 ጻድቅ ብሆን ኖሮ እንኳ ልመልስለት አልችልም፤ የምችለው ዳኛዬን ምህረት መለመን ብቻ ነው ።
\s5
\v 16 ብጠራውና እርሱ ቢመልስልኝ ም ኖሮ፥ ድምጼን ይሰማ እንደ ነበር አላምንም ።
\v 17 በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛዋል።
\v 18 ትንፋሽ እድወስድ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም፥ ይልቅ በመራራነት አጠገበኝ።
\s5
\v 19 ስለ ኃይል ከተናገርን እንደ እርሱ ኃያል ማን ነው፤ የፍርትህ ነገር ከተነሳ፦ ”የሚጠይቀኝ ማን ነው? “ ይላል።
\v 20 ጻድቅ ብሆን እንኳ አንደበቴ ይወቅሰኛል፤ ሰበብ ባይገኝብኝ እንኳ ጥፋተኛ ያደርገኛል።
\s5
\v 21 ያለነቀፋ ብሆንም ከእንግዲህ ለራሴ ግድ የለኝም፤ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።
\v 22 ልዩነት የለውም፤ እርሱ “ጻድቁንና ሃጥኡን ባንድነት ያጠፋል" የምለው ለዚህ ነው።
\v 23 መቅሠፍ በድንገት ቢገድል፥ በንጹሐን ሰዎች ችግር ይስቃል።
\v 24 ምድር ለኃጥአን እጅ ታልፋ ተሰጥታለች፤ እግዚአብሔርም የዳኞችዋን ፊት ሸፍኖአል፤ ይህን ያረገው እርሱ ካልሆነ ታድያ ማን ነው?
\s5
\v 25 ዘመኔ ከመልክተኛ ሰው ሩጫ ይልቅ ይፈጥናል፤ ቀኖቼ፥ መልካምን ሳያዩ ይከንፋሉ።
\v 26 የደንገል ጀልባ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደሚነጥቀው ግዳይ እንደሚበርር ፈጣን ናቸው።
\s5
\v 27 “አቤቱታዬን እረሳለሁ፤ ሐዘንተኛ ፊቴን ትቼ ደስተኛ እሆናለሁ” ብዬ ብል፥
\v 28 ንጹሕ አድርገህ እንደማትቆጥረኝ ስላወቅሁ መከራዬን ሁሉ እፈራዋለሁ።
\v 29 ጥፋተኛ ሆኜ መቀጣቴ ላይቀር፤ ለምን በከንቱ እደክማለሁ?
\s5
\v 30 ራሴን በአመዳይ ውሃ ባጥብና እጆቼንም እጅግ ባነጻቸው፥
\v 31 የገዛ ልብሴ እስኪጸየፈኝ ድረስ እግዚአብሔር በአዘቅት ውስጥ ይመልሰኛል።
\s5
\v 32 መልስ እድሰጠው ፥ አብረን ወደ ፍርድ ችሎት እንዳንገባ፥ እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።
\v 33 እጁን በሁለታችንም ላይ የሚያኖር ፈራጅ፤ በመካከላችንም የሚዳኝ የለም!
\s5
\v 34 የእርሱን በትሩ ከእኔ ላይ የሚያነሳ፥ ማስደንገጡንም ከኔ የሚያርቅ ሌላ ፈራጅ የለምን?
\v 35 በሚገባ በተናገርሁ፥ ባልፈራሁም ነበር፤ ነገር ግን አሁን ነገሮች እንዲህ ባሉበት አልችልም።
\s5
\c 10
\p
\v 1 በራሴ ሕይወት ዝያለሁ፤ አቤቱታዬን ያለመቆጠብ እገልጻለሁ፤ በነፍሴም ምሬት እናገራለሁ።
\v 2 እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ ለምን እንደ ከሰስከኝ ንገረኝ እንጂ እንዲያው አትፍረድብኝ።
\v 3 የእጅህን ሥራ መናቅ፤እኔንስ ማስጨነቅ የኃጥአንን እቅድ ግን በፈገግታ ስትተወው ይህ በአንተ ዘንድ መልካም ነውን?
\s5
\v 4 በውኑ አይኖችህ የሥጋ ለባሽ ዓይኖች ናቸውን? ሰውስ እንደሚያይ ታያለህን?
\v 5 በደሌን ትከታተል ዘንድ፥ ኃጢአቴንም ትመረምር ዘንድ፥
\v 6 ቀኖችህ እንደ ሰው ቀኖች ናቸውን? ዓመታትህስ እንደ ሰው ዓመታት ናቸውን?
\v 7 በደለኛ እንዳልሆንሁ ብታውቅም እንኳ፥ ከእጅህ ሊያድነኝ የሚችል የለም።
\s5
\v 8 እጆቸህ አበጃጁኝ አሳምረህም ሠራኸኝ፤ መልሰህ ግን እያታጠፋኸኝ እኮ ነው።
\v 9 እለምንሃለሁ፤ እንደ ሸክላ አበጃጅተህ እንደ ሰራኸኝ አስብ፤ እንደገናስ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?
\s5
\v 10 እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን? እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?
\v 11 ስጋን አደረክልኝ ቁርበትንም አለበስኸኝ፥ በአጥንትና በጅማትም አቀናብረህ አጠነከርኸኝ።
\s5
\v 12 ሕይወትና የታመነ ኪዳን ሰጠኸኝ፤ እርዳታህም መንፈሴን ጠበቀ።
\v 13 ነገር ግን እነዚህንም ነገሮች በልብህ ሰወርህ፤ ይህንንም ታስብ እንደነበር አውቃለሁ።
\v 14 ኃጢአትም ባደርግ አንተ ታውቀዋለህ፤ ከአመጻዬም ነጻ አትለቀኝም።
\s5
\v 15 በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ ጻድቅ ብሆንም ራሴን ቀና አላደርግም፤ በሃፍረት ተሞልቼአለሁና፥ መከራዬንም እያየሁ ነውና።
\v 16 ራሴንም ቀና ባደርግ እንደ አንበሳ ታድነኛለህ፤ እንደገና ሃያል መሆንህን ታሳየኛለህ፤
\s5
\v 17 አዲስ ምስክሮችህን ታቆምብኛለህ ቍጣህንም በላዬ ታበዛብኛለህ፤ በአዲስ ሰራዊትም ታጠቃኛለህ።
\s5
\v 18 ታዲያ ለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ምነው ያኔ ነፍሴ በጠፋችና የሰው ዓይን ባላየኝ።
\v 19 ኖሮ እንደማያውቅ በሆንሁና፤ ከማኅፀን ቀጥታ ወደ መቃብር በወሰዱኝ።
\s5
\v 20 የቀሩኝ ቀናቶች ጥቂት አይደሉምን? ታዲያ ጥቂት እንዳርፍ ተወት አድርገኝ፤
\v 21 ወደማልመለስበት ከመሄዴ በፊት፥ ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ ምድር፥
\v 22 እንደ እኩለ ለሊት ወደ ጨለመች ምድር፥ ሥርዓትም ወደሌለበት ወደ ሞት ጥላ፥ ብርሃንዋም እንደ ጨለማ ወደ ሆነ ምድር ሳልሄድ፥ ጥቂት እጽናና ዘንድ ተወኝ።
\s5
\c 11
\p
\v 1 ነዕማታዊውም ሶፋር እንዲህ በሎ መለሰ፦
\v 2 ለዚህ ሁሉ ቃል መልስ መስጠት አይገባምን? በንግግር የተማላው ይህ ሰው እንዲያው ይታመናልን?
\v 3 ትምክህትህስ ሌሎችን ሁሉ ዝም ያሰኛቸዋልን? ትምህርታችንን ስትሳለቅበት፤ የሚያሳፍርህ ማንም የለምን?
\s5
\v 4 ለእግዚአብሔር ስትናገር “ትምህርቴ የተጣራ ነው፥በዓይንህም ፊት ነቀፋ የለብኝም” ትላለህ።
\v 5 ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!
\v 6 በማስተዋሉ ታላቅ ነውና፤ የጥበቡን ምሥጢር ምነው ገልጦ ቢያሳይህ! እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ ታውቅ ነበር።
\s5
\v 7 እግዚአብሔርን መርምረህ ልትረዳው ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን በሙላት ልታውቀው ትችላለህን?
\v 8 ነገሩ እንደ ሰማይ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?
\v 9 ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
\s5
\v 10 እርሱ በመካከልህ ቢያልፍ፥ የፈለገውን በግዞት ቢዘጋ፥ ለፍርድ የወደደውን ቢጠራ፥ የሚከለክለው ማን ነው?
\v 11 እርሱ ሃሰተኛ ሰዎችን ያውቃልና፥ አመጻንም ሲመለከት እንዳላየ ያልፋልን?
\v 12 የሜዳ አህያ ሰው በወለደ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ ሞኞች ሊረዱት አይችሉም።
\s5
\v 13 ነገር ግን ልብህን በትክክል ብታቀና፤ እጅህንም ወደ እግዚአብሔር ብትዘረጋ፥
\v 14 በደልንም ከእጅህ እጅግ ብታርቀው፤ በድንኳንህም ኃጢአት ባይኖር፤
\s5
\v 15 ያን ጊዜ በእርግጥ ያለ እፍረት ቀና ትላለህ፤ ጠንክረህም ትቆማለህ፥ አትፈራምም።
\v 16 መከራህንም ትረሳዋለህ፤ እንዳለፎ እንደሔደም ውኃ ታስበዋለህ።
\v 17 ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ይበራል፤ ጨለማም ቢኖር እንኳ እንደ ጥዋት ይሆናል።
\s5
\v 18 ተስፋ ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፤ በዙሪያህ ሁሉ ደኅንነትን ታያለህ፥ በእረፍትም ትቀመጣለህ።
\v 19 ለማረፍ ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፤ ብዙዎችም ያንተን እርዳታ ይሻሉ።
\s5
\v 20 ነገር ግን የክፉዎች ዓይን ግን ትጨልማለች፤ የሚያመልጡበትም መንገድ የላቸውም፥ ያላቸው ተስፋም የመጨረሻ ትንፋሻቸውን መስጠት ብቻ ነው።
\s5
\c 12
\p
\v 1 በመቀጠልም ኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦
\v 2 በእርግጥ እናንተ አዋቂ ሰዎች ናቸሁ፤ ጥበብ ከእናንተ ጋር ትሞታለች።
\v 3 ነገር ግን እኔ እንደ እናንተው ማስተዋል አለኝ፤ ከእናንተም የማንስ አይደለሁም፤ በእርግጥ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች የማያውቅ ማን ነው?
\s5
\v 4 እግዚአብሔርን ሲጠራ የሚመልስለት ሰው የነበርሁ እኔ አሁን ለጎረቤቶቼ መሳለቅያ ሆኛለሁ፤ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት የነበርሁ እኔ አሁን ማሾፊያ ሆኛለሁ።
\v 5 በደላው ሰው ሃሳብ ውስጥ መከራ የተናቀ ነው፤ እግሩ ለሚሸራተት ሰው ችግሩን ሊጨምርበት ያስባል።
\v 6 የዘራፊዎች ድንኳን ይበለጥጋል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ በደህና ተቀምጠዋል፤ የገዛ እጃቸውን አምላካቸው አድርገዋል።
\s5
\v 7 አሁን ግን እንስሶችን ጠይቁ፥ ያስተምሯችኋል፤ የሰማይንም ወፎች ጠይቁ፥ ይነግሯችኋል።
\v 8 ወይም ለምድር ተናገሩ፥ እርስዋም ታስተምራችኋለች፤ የባሕርም ዓሣዎች በግልጥ ይነግሯችኋል።
\s5
\v 9 ከእነዚህ ሁሉ እንስሳት የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፤ የሕያዋን ሁሉ ህይወት፤
\v 10 የሰው ልጆችንም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ እንደያዘ የማያውቅ ማን ነው?።
\s5
\v 11 ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃላትን አይለይምን?
\v 12 እድሜ በገፉት ዘንድ ጥበብ፥ በዘመን ርዝማኔም ማስተዋል ይገኛል።
\s5
\v 13 በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ምክርና ማስተዋልም በእርሱ ዘንድ ይገኛሉ።
\v 14 እነሆ፥ እርሱ ያፈርሳል፥ ተመልሶም አይሠራም፤ አንድን ሰው ቢያስር ሊፈታው የሚችል የለም።
\v 15 እነሆ፥ ውኆቹን ቢከለክል፥ እነርሱ ይደርቃሉ፤ እንደ ገናም ቢለቃቸው፥ ምድርን ያጥለቀልቃሉ።
\s5
\v 16 ብርታትና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ የሚስተውና የሚያስተው በእርሱ ስልጣን ስር ናቸው።
\v 17 መካሪዎችንም ባዶአቸውን በሃዘን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም አላዋቂ ያደርጋቸዋል።
\v 18 የነገሥታትንም የስልጣን ሰንሰለት ይፈታል፥ ወገባቸውንም በመታጠቂያ ልብስ ያስርላቸዋል።
\s5
\v 19 ይሽራል ባዶአቸውንምይሰዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል።
\v 20 የታመኑ ሰዎችንም ንግግረ ያስወግዳል፥ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል።
\v 21 በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈሳል፥ የብርቱ ሰዎችንም ቀበቶ ይፈታል።
\s5
\v 22 ከጨለማ ውስጥ ጥልቅ ነገሮችን ይገልጣል፥ ከሙታንም ሰፈር የመታየትን ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።
\v 23 ህዝቦችን ብርቱ ያደርጋል፥ ደግሞም ያጠፋቸዋል፤ ህዝቦችንም ያበዛል፥ ደግሞም ወደ ግዞት ይልካቸዋል።
\s5
\v 24 ከምድር ሕዝብ አለቆች ማስተዋልን ይወስዳል፥ መንገድም በሌለበት ምድረበዳ ያቅበዘብዛቸዋል።
\v 25 ብርሃን በሌለበት በጨለማ ይዳክራሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ።
\s5
\c 13
\p
\v 1 እነሆ፥ ይህን ሁሉ ዓይኔ አይቷል፤ ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ።
\v 2 እናንተ የምታውቁትን እኔም ደግሞ አውቀዋለሁ ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።
\s5
\v 3 ቢሆንም ግን ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር መነጋገር እመርጣለሁ፥ ከእግዚአብሔርም ጋር መዋቀስ እፈልጋለሁ።
\v 4 እናንተ ግን እውነትን በሐሰት ለባጮች ናችሁ፤ ሁላችሁ ዋጋ የሌላችሁ ሃኪሞች ናችሁ።
\v 5 ምነው ሁላችሁ ዝም ብትሉ! ይህም ጥበብ ይሆንላችሁ ነበር።
\s5
\v 6 እንግዲህ ክርክሬን ስሙ፥ የከንፈሬንም ሙግት አዳምጡ።
\v 7 ለእግዚአብሔር ጽድቅ የሌለበትን ነገር ትናገሩለታላችሁን? ለእርሱስ በማታለል ታወሩለታላችሁን?
\v 8 ቸርነትንስ ታደርጉለታላችሁን? ለእግዚአብሔርስ በሸንጎ ጠበቃ ትሆኑለታላችሁን?
\s5
\v 9 እንደ ዳኛ ወደ እናንተ ቢዞርና ቢመረምራችሁ ይህ መልካም ይመስላችኋልን? ወይስ አንዱ ሌላውን ሰው እንደሚያታልል፣ በሸንጎ ትሳለቁበታላችሁን?
\v 10 በስውር ወደ እርሱ ብታደሉ እንኳ፤ እርሱ በእርግጥ ይገስጻችኋል።
\s5
\v 11 ግርማዊነቱ አያስፈራችሁምን? ማስደንገጡስ በላያችሁ አይወድቅምን?
\v 12 አስገራሚ ንግግራችሁ ከአመድ የተሰሩ ምሳሌዎች ናቸው፤ ምላሻችሁም ከሸክላ የተሰሩ መመከቻዎች ናቸው።
\s5
\v 13 ዝም በሉ፥ እኔም እንድናገር ተዉኝ፤ የሚመጣው ነገር ይምጣብኝ።
\v 14 ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ፥ ሕይወቴንም በእጆቼ አኖራታለሁ።
\v 15 እነሆ ቢገድለኝ የሚቀርልኝ ተስፋ የለኝም፤ ቢሆንም ስለ መንገዴ በፊቱ እሟገታለሁ።
\s5
\v 16 አምላክ እንደሌለው ሰው ወደ ፊቱ አልቀረብኩምና፤ለደህንነቴ ይሆንልኛል።
\v 17 አምላኬ፡ንግግሬን በሚገባ አድምጥ፥ አስረግጬ የምለውም ለጆሮህ ይድረስ።
\s5
\v 18 እነሆ አሁን፥ ሙግቴን አሰናድቻለሁ፤ ነጻ እንደምወጣም አውቃለሁ።
\v 19 በሸንጎስ ቆሞ የሚከራከረኝ ማን ነው? ጥፋተኛ ሆኜ ከተገኘሁ፤ በዝምታ ህይወቴን ለሞት እሰጣለሁ።
\s5
\v 20 አማላኬ ሁለት ነገር ብቻ አድርግልኝ፤ እኔም ራሴን ከፊትህ አልሸሽግም፤
\v 21 ጠንካራ እጅህን ከእኔ አርቅ፤ በማስደንገጥህም አታስፈራኝ።
\v 22 ከዚያም ጥራኝ፥ እኔም እመልስልሃለሁ። ወይም እኔ ልናገር፥ አንተም መልስልኝ።
\s5
\v 23 በደሌና ኃጢአቴ ምን ያህል ሆነ? መተላለፌንና ኃጢአቴን አስታውቀኝ።
\v 24 ፊትህን ከእኔ ለምን ትሰውራለህ፥ እንደ ጠላትህስ ለምን ታደርገኛለህ?
\v 25 የረገፈን ቅጠል ታሳድደዋለህን? ወይስ የደረቀን ገለባ ትከታተለዋለህ?
\s5
\v 26 የመረረ ነገር ስለጻፍህብኝ፤ የወጣትነቴን ኃጢአት ታወርሰኛለህ።
\v 27 እግሬንም በእግር ግንድ አስገባኸው፥ መንገዶቼን ሁሉ በቅርበት አየኻቸው፤ የእግሬ መርገጫ የተራመደበትን መሬት ሁሉ መረመርህ።
\v 28 ምንምእንኳ እኔ እንደሚጣል ብስባሽ፥ ብልም እንደበላው ልብስ ብሆንም።
\s5
\c 14
\p
\v 1 ከሴት የተወለደ ሰው ጥቂት ቀናት ቢኖርም፥ በመከራ የተሞሉ ሆኑ።
\v 2 እንደ አበባ ከመሬት ይወጣል፥ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላም ይፈጥናል፥ ነገር ግን አይቆይም።
\v 3 እንደዚህ ያለውን ሰው ትመለከታለህን? ከአንተስ ጋር እኔን ወደ ፍርድ ታመጣኛለህን?
\s5
\v 4 ከርኩስ ነገር ንጹሕን ማውጣት ማን ይችላል? ማንም የለም።
\v 5 የሰው ዕድሜ የተወሰነ ነው፥ የወራቶቹም ቍጥር በአንተ እጅ ነው፥ እርሱም ሊያልፈው የማይችለውን ገደብ ቀጠርህለት።
\v 6 እንደ ተቀጣሪ ሰው የቀሩትን ቀኖች እዲደሰትባቸው፤ እዲያርፍም ከእርሱ ዘወር በል።
\s5
\v 7 ዛፍ ቢቈረጥ ደግሞ ሊያቈጠቍጥ፥ ቅርንጫፉም ማደግ እንዳያቆም ተስፋ ሊኖረው ይችላል።
\v 8 ምንምእንኳ ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅ፥ ግንዱም በመሬት ውስጥ ቢሞት፥
\v 9 የውኃ ሽታ ሲያገኝ ዳግም ያቈጠቍጣል እንደ አትክልትም ቅርንጫፍ ያወጣል።
\s5
\v 10 ሰው ግን ይሞታል፤ ይደክማል፤ በርግጥ ሰው እስትንፋሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ?
\v 11 ውኃ ከሐይቅ እንደሚያልቅ፤ ወንዙም እንደሚቀንስና እንደሚደርቅ፤
\v 12 እንዲሁ ሰዎች ይተኛሉ ዳግም አይነሱም፤ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቁም፥ ከእንቅልፉቸውም አይነሱም።
\s5
\v 13 በሲኦል ውስጥ ምነው በሰወርኸኝ ኖሮ! ቍጣህ እስኪያልፍ ድረስ በሸሸግኸኝ ኖሮ! ቀጠሮም አድርገህ ምነው ባሰብኸኝ ኖሮ!
\v 14 በውኑ ሰው ከሞተ ተመልሶ ሕያው ይሆናልን? መለወጤ እስኪመጣ ድረስ፥ የሰልፌን ዘመን ሁሉ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
\s5
\v 15 በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር፤ የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር።
\v 16 ለእርምጃዬ ጥንቃቄንና ገደብን ታደርግለታለህ፤ ኃጢአቴንም አትቆጣጠርብኝም።
\v 17 መተላልፌን በከረጢት ውስጥ ታትመዋለህ፥ ኃጢአቴንም ትሸፍንልኛለህ።
\s5
\v 18 ነገር ግን ተራራ እንኳ ይወድቃል ይጠፋልም፥ ዓለቶችም እንዲሁ ከስፍራቸው ይለቃሉ፤
\v 19 ውኆች በድንጋዮቹ ላይ ይወርዳሉ፤ ጎርፎቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፤ እንዲሁ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ።
\s5
\v 20 ሁልጊዜ ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፤ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ወደ ሞት ትሰድደዋለህ።
\v 21 ልጆቹ ወደ ክብር ቢመጡም አያውቅም፤ ቢዋረዱም ይህ ሲሆን አያይም።
\v 22 ነገር ግን የራሱ ሰውነት ሕመም ብቻ ይሰማዋል፥ ለራሱም በሃዘን ያለቅሳል።
\s5
\c 15
\p
\v 1 ቀጥሎም ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ እንዲህም አለ፦
\v 2 በውኑ ጠቢብ ሰው ከንቱ በሆነ እውቀት ይመልሳልን? ራሱንስ በምሥራቅ ነፋስ ይሞላልን?
\v 3 ትርፍ በሌለው ወሬ ወይም በማይጠቅም ንግግር ይሟገታልን?
\s5
\v 4 በእርግጥ አንተ የእግዚአብሔርን አክብሮት ታሳንሳለህ፤ ለእግዚአብሔር ያለህን መሰጠት ታስቀራለህ።
\v 5 ሃጢያትህ አፍህን ያስተምረዋል፥ የተንኰለኛ አንደበት ቢኖርህ ትመርጣለህ።
\v 6 የሚፈርድብህ የራስህ አፍ እንጂ እኔ አይደለሁም፤ በርግጥም የራስህ ከንፈሮች ይመሰክሩብሃል።
\s5
\v 7 ከተወለዱት ሁሉ አንተ የመጀመሪያ ሰው ነህን? ወይስ ከኮረብቶች በፊት አንተ ነበርህ?
\v 8 የእግዚአብሔርን ምሥጢራዊ እውቀት ሰምተሃልን? ጥበብንስ ለራስህ ብቻ ገደብሃትን?
\v 9 እኛ የማናውቀው አንተ የምታውቀው ምንድር ነው? በእኛ ዘንድ የሌለ አንተ ብቻ የተረዳኸው ምን አለ?
\s5
\v 10 ከአባትህ በዕድሜ የሚበልጡ ሽበትም ያላቸው ሽማግሌዎችም ከእኛ ጋር አሉ።
\v 11 በውኑ የእግዚአብሔር ማጽናናት፥ በየውሃነት የቀረበልህ ቃልስ ጥቂት ሆነብህን?
\s5
\v 12 የነፍስህ ስሜት ለምን ይወስድሃል? ዓይኖችህስ ለምን በቁጣ ያፈጣሉ?
\v 13 መንፈስህ በእግዚአብሔር ላይ ተነስቷል፤ እንዲህ ያለ ቃል ከአፍህ እስከ ማውጣት ደረስህ።
\v 14 ንጹሕ ሆኖ ሊገኝ ሰው ማን ነው? ጻድቅ ሊሆን ከሴት የተወለደ እርሱ ማን ነው?
\s5
\v 15 እነሆ እግዚአብሄር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ በእርግጥ ሰማያትም በእርሱ አይን ንጹሕ አይደሉም።
\v 16 ይልቁንስ ኃጢአትን እንደ ውኃ የሚጠጣ ፥ አመጸኛና የተበላሸው የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ?
\s5
\v 17 ስማኝ፥አሳይሃለሁ፤ያየሁትንም አሳውቅሃለሁ፤ በመካከላቸውም እንግዳ ያልገባባቸው ጠቢባን
\v 18 ጠቢባን ከአባቶቻቸው ተቀብለው ያስተላለፉትን ፤ የእነርሱ ቀደምት ትውልድ ያልሸሸጉትን ነገር እገልጥልሃለሁ።
\s5
\v 19 ለአባቶቻቸውም ፥ ምድሪቱ ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታ ነበረ፥ በመካከላቸው እንግዶች አልፈው አያውቁም
\v 20 ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ በሕመም ይሰቃያል፥ ግፈኛም በፊቱ ያሉት ዓመታት ለስቃይ ይሆኑበታል።
\v 21 የሽብር ድምፅ በጆሮው ውስጥ ነው፤ በብልጽግናው እያለ አጥፊው ይመጣበታል።
\s5
\v 22 ከጨለማ ተመልሶ እንደሚወጣ አያስብም፥ ሰይፍም አሸምቆ ይጠብቀዋል።
\v 23 ወዴት አለ? እያለ እንጀራ ፍለጋ ብዙ ስፍራ ይዞራል፤ የጨለማ ቀን እንደ ደረሰበትም ያውቃል።
\v 24 ጭንቀትና ስቃይ ያስፈራሩታል፤ ለጦርነት ዝግጁ እንደ ሆነ ንጉሥ ይበረቱበታል።
\s5
\v 25 ምክንያቱም እጁን በእግዚአብሔር ላይ አንስቶአል፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ ፊት በትዕቢት ሔዷልና፥
\v 26 በደንዳና አንገቱና በወፍራም ጋሻው ሆኖ፥ ይህ አመጸኛ ሰው በእግዚአብሔር ላይ ይመጣልና፥
\s5
\v 27 ይህ እውነት ነው፥ምንም እንኳ በስብ ፊቱን ቢከድንም፥ ስቡንም በወገቡ ላይ ቢያጠራቅም፥
\v 28 በፈረሱ ከተሞች ውስጥ፥ ሰውም በማይኖርበትና፥ ክምር ለመሆን በተመደቡ ቤቶች ውስጥ ይኖራልና፤
\s5
\v 29 ባለጠጋ አይሆንም፥ ሀብቱም አይጸናም፤ ጥላው እንኳ በምድር ላይ አይቆይም፤
\v 30 ከጨለማ ተለይቶ አይወጣም፤ ነበልባልም ቅርንጫፎቹን ያደርቃቸዋል፥ በእግዚአብሔር አፍ እስትንፋስም ይጠፋል።
\s5
\v 31 ዋጋው ከንቱነት እንዳይሆን፥ ራሱን እያሳተ በከንቱ ነገር አይታመን።
\v 32 ቀኑ ሳይደርስ የፍጻሜው ሰዓት ይመጣል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም።
\v 33 እንደ ወይን ያልደረሰውን ዘለላ ይጥላል፤ እንደ ወይራ ዛፍም አበባውን ያረግፋል።
\s5
\v 34 አምላክ የሌለው ህዝብ ጉባኤ ሁሉ ይመክናል፥ የሙሰኞችንም ድንኳን እሳት ትበላለች።
\v 35 ተንኰልን ይፀንሳሉ፥ በደልንም ይወልዳሉ፥ ማህጸናቸውም ማታለልን ያዘጋጃል።
\s5
\c 16
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመል እንዲህ አለ፦
\v 2 እንደዚህ ያለ ብዙ ነገር ሰምቻለሁ፤ ሁላችሁም የማትጠቅሙ አጽናኞች ናችሁ።
\v 3 ከንቱ ቃሎች መጨረሻ የላቸውምን? እንደዚህ ለመመለስ የቻላችሁት ምን ነክቷችሁ ነው?
\s5
\v 4 እናንተ በእኔ ቦታ ብትሆኑ፤ እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ እኔም ቃላቶችን ሰብስቤ እያቀናበረሁ፥ በማሾፍም በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ እችል ነበር።
\v 5 ኦ! በአፌም እንዴት አድርጌ ባበረታታኋችሁ! የከንፈሬም ማጽናናት እንዴት ሃዘናችሁን ባቀለለ ነበር!
\s5
\v 6 ብናገር ሰቆቃዬ አይቀንስም፤ ከመናገር ዝም ብል እንዴት እገዛ ላገኝ እችላለሁ።
\v 7 አሁን ግን እግዚአብሔር አድክመኸኛል፤ ቤተሰቤን ሁሉ አፈራርሰሃል።
\v 8 አድርቀኸኛል ይኸውም በላዬ ይመሰክርብኛል፤ የሰውነቴም መጨማተር ምስክር ነው፤ ክሳቴም ተነሥቶ፤በፊቴ ላይ ይመሰክራል።
\s5
\v 9 እግዚአብሔር በቍጣው ቀደደኝ፥ አሳደደኝም፤ ጥርሶቹንም አፋጨብኝ፤ ይህም ሲሆን ጠላቴ ዓይኑን አፈጠጠብኝ፤
\v 10 ሰዎችም በግርምት አፋቸውን ከፈቱ፤ እያላገጡም ጕንጬን ጠፈጠፉኝ፤ በአንድነትም በእኔ ላይ ተሰበሰቡ።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር አመጸኛ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፥ በክፉዎችም እጅ ጣለኝ።
\v 12 በሰላም ተቀምጬ ነበር፥ እርሱም ሰባበረኝ፤ በርግጥም አንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ ኢላማው አድርጎም አቆመኝ።
\s5
\v 13 ቀስተኞቹ ከበቡኝ፤ ኵላሊቶቼንም ወጋቸው፥ አላስተረፈኝምም፤ ሐሞቴንም በምድር ላይ አፈሰሰ።
\v 14 ከግድግዳዬም ጋር ደጋግሞ አጋጨኝ፤ እንደ ጦረኛ በላዬ ሮጠብኝ።
\s5
\v 15 በሰውነቴ ላይ ማቅ ሰፋሁ፥ ቀንዴንም በመሬት ላይ ጣልሁት።
\v 16 ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፤ በዓይኖቼ ቆብ ላይም የሞት ጥላ አለ፤
\v 17 ቢሆንም ግን በእጄ ዓመፅ የለም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው።
\s5
\v 18 ምድር ሆይ፥ ደሜን አትሸፍኚ፥ ለቅሶዬም ማረፊያ ቦታ አይኑረው።
\v 19 አሁንም ቢሆን፥ ምስክሬ በሰማይ አለ፥ ለእኔም የሚሟገትልኝ በአርያም ነው።
\s5
\v 20 ጓደኞቼ ተሳለቁብኝ ነገር ግን አይኖቼ በእግዚአብሔር ፊት እንባን ያፈሳሉ።
\v 21 የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ያ በሰማይ ያለው ምስክሬ በእግዚአብሔር ፊት እንዲምዋገትልኝ እጠይቃለሁ!
\v 22 ምክንያቱም ጥቂት ዓመታት ካለፉ በኋላ እኔም ወደማልመለስበት ስፍራ እሄዳለሁ።
\s5
\c 17
\p
\v 1 መንፈሴ ተጨረሰ፥ ቀኖቼም አለቁ፥ መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
\v 2 በርግጥ አላጋጮች ከእኔ ጋር አሉ፥ ዓይኔም ይህን ማላገጣቸውን ሁልጊዜ ያያል።
\v 3 አሁንም መያዣን ለራስህ ሰጥተህ ዋስ ሁነኝ፤ ከአንተ ሌላ የሚረዳኝ ማን አለ?
\s5
\v 4 እግዚአብሔር አንተ ልባቸው እንዳያስተውል አድርገሃል፤ በላዬም ከፍ እንዲሉ አታደርጋቸውም።
\v 5 ለጥቅም ብሎ ጓደኞቹን አሳልፎ የሚሰጥ ሰው፥ የልጆቹ ዓይን ይታወራል።
\s5
\v 6 ነገር ግን እርሱ ለሰዎች መተረቻ አደረገኝ፤ በፊቴም ላይ ተፉብኝ።
\v 7 ዓይኔ ከኀዘን የተነሣ ፈዘዘ፥ የሰውነቴ ክፍሎች በሙሉ እንደ ጥላ ቀጠኑ።
\v 8 ጻድቅ ሰዎችም በዚህ ነገር ይደነቃሉ፥ ንጹሑም ሰው በዐመጸኞች ላይ ይበሳጫል።
\s5
\v 9 ጻድቅ ግን መንገዱን ያጸናል፥ ንጹሕ እጆች ያሉትም ሰው ብርታትን እየጨመረ ይሄዳል።
\v 10 እናንተ ሁላችሁ ግን እስቲ ወደ እኔ ኑ፤ ከመካከላችሁ አንድም ጠቢብ አላገኝም።
\s5
\v 11 ቀኖቼ አለቁ፤ እቅዶቼ አበቃላቸው፥የልቤም ምኞት ሳይቀር ከንቱ ሆነ።
\v 12 እነዚህ አሿፊ ሰዎች ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤ ብርሃንም የሚሉተ ወደ ጨለማ የቀረበውን ነው።
\s5
\v 13 ሲኦልን እንደ ቤቴ ካየሁ፤ መቀመጫዬንም በጨለማ ከዘረጋሁ፤
\v 14 ለጉድጓድም፦ “አንተ አባቴ ነህ” ፤ ለትልም፦ “አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ” ብዬ ካልሁ።
\v 15 ታዲያ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይልኝ ማን ነው?
\v 16 ተስፋስ ወደ አፈር ስንወርድ፥ አብሮኝ ወደ ሲኦል ይወርዳልን?
\s5
\c 18
\p
\v 1 ሹሐዊው በልዳዶስ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ወሬህን የምታቆመው መቼ ነው? እስቲ አስብ፥ ከዚያም እኛ እንናገራለን።
\s5
\v 3 ለምን እንደ እንስሶች ቆጠርኸን? ለምን በአንተ ፊት እንደ ቆሻሻ ሆንን?
\v 4 አንተ በራስህ ቍጣ ተወርሰሃል፤ ምድር ለአንተ ሲባል ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ዓለቶች ከስፍራው መወገድ አለባቸው?
\s5
\v 5 በእርግጥ የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል አያበራም።
\v 6 ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ጨለማ ይሆናል፥ በላዩ ያለው መብራትም ይጠፋል።
\s5
\v 7 የብርታቱም እርምጃ ያጥራሉ፥ የራሱ እቅዶች ወደታች ይጥሉታል።
\v 8 በገዛ እግሩ ወደ ወጥመድ ይገባል፥ ወደ ጉድጓድም ውስጥ ይገባል።
\s5
\v 9 ወጥመድ ተረከዙን ይይዘዋል፥ ወስፈንጠርም በላዩላይ ይሆናል።
\v 10 በመሬትም ላይ የሸምቀቆ ገመድ፥ በመንገዱም ላይ ወጥመድ ለእርሱ ተሰውሯል።
\v 11 ድንጋጤ በሁሉ አቅጣጫ ያስፈራዋል፥ ከኋላውም ሆነው ያሳድዱታል።
\s5
\v 12 ብልጥግናው ወደ ራብ ይለወጣል፥ መቅሠፍትም ካጠገቡ ተዘጋጅቶለታል።
\v 13 የሰውነቱም ክፍሎች ፈጽመው ይጠፋሉ፤ የሞትም በኵር ልጅም አካል ክፍሎቹን ይበላል።
\s5
\v 14 ከሚታመንበት ቤት፤ ከተቀመጠበትም ድንኳን ይነቀላል፤ የድንጋጤ ንጉሥ ወደሆነው ወደ ሞት ያመጡታል።
\v 15 ዲን በመኖሪያው እንደተበተነ ይመለከታሉ፤ የራሱያልሆኑ ሰዎችም በድንኳኑ ውስጥ ይኖራሉ።
\s5
\v 16 ሥሩ ከበታቹ ይደርቃል፥ ቅርንጫፉም ከላዩ ይወድቃል።
\v 17 መታሰቢያው ከምድር ላይ ይጠፋል፥ በመንገድም ላይ ስሙ አይነሳም።
\s5
\v 18 ከብርሃን ወደ ጨለማ ይወስዱታል፥ ከዚህም ዓለም ያሳድዱታል።
\v 19 በሕዝቡ መካከል ልጅ የልጅ ልጅም አይኖረውም፤ ጥቂት የሚቆይበትም ዘመድ እንኳ አያገኝም።
\v 20 በአንድ ቀን የሆነበትን ሲያዩ የምዕራብ ሰዎች 、ይደነግጣሉ፥ በምስራቅ የሚኖሩ ሰዎችም ይፈራሉ ።
\s5
\v 21 በርግጥ የኃጥዕ ቤቶች እንዲህ ናቸው፥ እግዚአብሔርንም የማያውቁ ሰዎች ስፍራ ይህ ነው።
\s5
\c 19
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 በቃላቶቻችሁ የምታሰቃዩኝና፥ የምትሰባብሩኝ እስከ መቼ ነው?
\s5
\v 3 አሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ በጭካኔ ስትበድሉኝም አላፈራችሁም።
\v 4 በርግጥ ተሳስቼ ቢሆን እንኳ፥ ስሕተቱ የእኔ ጉዳይ ይሆናል።
\s5
\v 5 በእርግጥ ራሳችሁን በላዬ ከፍ ብታደርጉ፥ እኔንም እንደተላላፊ ለሁሉ ብታስቆጥሩኝም፥
\v 6 ግን ደግሞ እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፥ በመረቡም እንደ ያዘኝ ማወቅ ነበረባችሁ።
\s5
\v 7 ስለ መበደሌ ልናገር ብጮኽም አልሰማም፤ እርዳታ ለማግኝት ብጠራም ፍትህ የለም።
\v 8 እንዳላልፍ መንገዴን አጥሮታል፥ በመንገዴም ላይ ጨለማ አኑሮበታል።
\v 9 ክብሬን ከላዬ ገፈፈ፥ ዘውዴንም ከራሴ ላይ አነሳ።
\s5
\v 10 እስክጠፋ ድረስ፥ በየአቅጣጫው ሰበረኝ፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቀለው፤
\v 11 ቍጣውንም በላዬ አነደደው፥ ከጠላቶቹም እንደ አንዱ አድርጎ ቈጠረኝ።
\v 12 ሠራዊቱ በአንድነት መጡብኝ፥ መወጣጫም በእኔ ላይ አዘጋጁ፥ በድንኳኔም ዙሪያ ሰፈሩ።
\s5
\v 13 ወንድሞቼን ከእኔ አራቃቸው፥ የሚያውቁኝም ፈጽመው ተለዩኝ።
\v 14 ዘመዶቼ ተዉኝ፥ የቅርብ ጓደኞቼም ረሱኝ።
\s5
\v 15 አንድ ወቅት በቤቴ በእንግድነት የተቀመጡ፥ ሴቶች ሰራተኞቼም እንደ መጻተኛ ቈጠሩኝ፤ በፊታቸውም እንደ ባዕድ ሆንሁ።
\v 16 አገልጋዬን ተጣራሁ፥ በአፌም ለመንሁት ነገር ግን መልስ አልሰጠኝም።
\s5
\v 17 ትንፋሼም ለሚስቴ የሚያስጠላት ሆነ፥ ልመናዬም በገዛ ወንድሞቼና እህቶቼ ተጠላ።
\v 18 ሕፃናቶች እንኳ አንቋሸሹኝ፤ ለመናገር ብነሣም መልሰው ይናገሩኛል።
\v 19 የሚያማክሩኝ ጓደኞቼ ሁሉ ተጸየፉኝ፤ የምወድዳቸው በእኔ ላይ ተነሱ።
\s5
\v 20 አጥንቴ ከሥጋዬና ከቆዳዬ ጋር ተጣበቀ በድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
\v 21 ጓደኞቼ ሆይ፥ እዘኑልኝ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና እዘኑልኝ።
\v 22 እግዚአብሔር እንደሆናችሁ ያክል ለምን ታሳድዱኛላችሁ? ሥጋዬን ማጥፋታችሁ ስለ ምን አይበቃችሁም?
\s5
\v 23 ኦ ምነው ቃሎቼ ቢጻፍ! ምነው በመጽሐፍ ቢታተሙ!
\v 24 ምነው በብረት ብዕርና በእርሳስ ተጽፎ፥ በዓለት ላይ ለዘላለም ቢቀረጽ!
\s5
\v 25 እኔ ግን የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፥ በመጨረሻም በምድር ላይ እንዲቆም አውቃለሁ፥
\v 26 ይህ ቆዳዬ ማለትም ሰውነቴ ከጠፋ በኋላ፥ በአካሌ እግዚአብሔርን እንዳይ አውቃለሁ።
\v 27 አየዋለሁ፥ እኔ ራሴ በአጠገቤ አየዋለሁ፥ ዓይኖቼ ይመለከቱታል፥ እንግዳም አይሆንብኝም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።
\s5
\v 28 “ 'እንዴት እናሳድደዋለን! የችግሩ ሥር በእርሱ ውስጥ ነው' ብትሉ፥
\v 29 ቍጣ የሰይፍን ቅጣት ያስከትላልና፣ ሰይፍን ፍሩ፤ ፍርድ እንዳለም ታውቃላችሁ።”
\s5
\c 20
\p
\v 1 ናዕማታዊውም ሶፋር ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ከውስጤ ጭንቀት የተነሳ አሳቤ መልስ እንድሰጥ አስቸኮለኝ።
\v 3 የሚያሳፍረኝን ተግሣጽ ከአንተ ሰምቻለሁ፥ ነገር ግን ከመረዳቴ የሚያልፍ መንፈስ ይመልስልኛል።
\s5
\v 4 እግዚአብሔር ሰውን በምድር ላይ ካኖረበት፥ ከጥንት ጀምሮ እንዴት እንደ ነበር አታውቅም?
\v 5 የኃጢአተኛ መፈንጨት አጭር ፣ የአመጸኛም ደስታ ለቅጽበት መሆኑን አታውቅምን?
\s5
\v 6 ቁመቱ እስከ ሰማይ ቢደርስ፥ ራሱም እስከ ደመና ቢሆን፥
\v 7 እንዲህ ያለ ሰው እንደ ምናምን ፈጽሞይጠፋል፤ አይተውት የነበሩም፦ ወዴት ነው? ይላሉ።
\s5
\v 8 እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፤ በርግጥ እንደ ሌሊት ራእይ በርሮ ይጠፋል።
\v 9 ያየውም ዓይን ዳግመኛ አያየውም፤ የነበረበት ስፍራም እንደገና አይመለከተውም።
\s5
\v 10 ልጆቹ ድሆችን ይቅርታ ይላሉ፤ እጆቹም ሀብቱን መመለስ ይገባቸዋል።
\v 11 አጥንቶቹ በወጣትነት ጉልበት ተሞልተዋል፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በአፈር ውስጥ ይተኛል።
\s5
\v 12 ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥ ከምላሱም በታች ቢደብቀው፥
\v 13 ምንም እንኳ እዚያው ቢያቆየው ባይለቅቀውም፥ በአፉ ውስጥ ቢይዘው፥
\v 14 ምግቡ በአንጀቱ ውስጥ ወደ መራራነት ይለወጣል፤ በውስጡ እንደ እባብ መርዝ ይሆንበታል።
\s5
\v 15 የዋጠውን ሀብት መልሶ ይተፋል፤ እግዚአብሔርም ከሆዱ ያስወጣዋል።
\v 16 የእባብን መርዝ ይመጣል፤ የእፉኝትም ምላስ ይገድለዋል።
\s5
\v 17 በማርና በቅቤ ፈሳሾች፥ በወንዞችም ተደስቶ አይኖርም።
\v 18 የደከመበትንም ሳይበላው መልሶ ይሰጣል፤ ባገኝውም ሃብት ደስ አይለውም።
\v 19 ድሆችን አስጨንቆአልና፥ ትቷቸዋልም፤ ያልሠራውንም ቤት በጉልበት ነጥቋል።
\s5
\v 20 በራሱ እርካታን ስለማያውቅ፤ የሚደሰትበትን አንድ ነገር ሊያስቀምጥ አይችልም።
\v 21 ሳያጠፋ የሚያስቀረው ነገር ስለማይኖር የሚዘልቅ ብልጽግና አይኖረውም።
\v 22 በሃብት ጠግቦ እያለ ይቸገራል፤ በድህነት ያሉ እጆች ሁሉ ይነሱበታል።
\s5
\v 23 ሆዱን ሊሞላ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር ብርቱ ቍጣውን ይሰድበታል፥ እየበላም ሳለ ያዘንብበታል።
\v 24 ከብረት መሣርያ ይሸሻል፥ የናስ ቀስት ግን ይወጋዋል።
\v 25 በርግጥ ቀስቱም ከኋላ ይወጋዋል፤ የጫፉም ብልጭታ በጉበቱ በኩል ይወጣል፤ ፍርሃትም ይመጣበታል።
\s5
\v 26 ለከበረ ዕቃው ፍጹም ጥፋት ተዘጋጅቶለታል፤ ያልተራገበ እሳት ይበላዋል፤ በድንኳኑም የተረፈውን ይጨርሰዋል።
\v 27 ሰማያት ኃጢአቱን ይገልጡበታል፥ ምድርም ምስክር ሆና ትነሣበታለች።
\s5
\v 28 የቤቱም ባለጠግነት ይጠፋል፤ በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን የቤቱን ዕቃ ጎርፍ ይወስድበታል።
\v 29 ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከእግዚአብሔርም የተመደበለት ርስቱ ይህ ነው።
\s5
\c 21
\p
\v 1 ቀጥሎም ኢዮብ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ንግግሬን በጥንቃቄ ስሙ፤ የምታጽናኑኝም እንደዚህ ይሁን።
\v 3 እንድናገር ፍቀዱልኝ፤ ከተናገርሁም በኋላ ተሳለቁ።
\s5
\v 4 ቅሬታዬን የማሰማው ሰው ላይ ነውን? ትዕግስት ባጣስ፤ አይገባኝምን?
\v 5 እስቲ ተመልከቱኝና ተደነቁ፤ አፋችሁንም በእጃችሁ ያዙ።
\v 6 እኔ ስቃዬን ባሰብሁ ቍጥር እጨነቃለሁ፥ በፍርሃትምሥጋዬ ይንቀጠቀጣል።
\s5
\v 7 ለምን ኃጢአተኞች በሕይወት እስከ እርጅና ይኖራሉ? ለምን በሃይልስ ይበረታሉ?
\v 8 ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ተደላድለዋል፥ ልጆቻቸውም በአይናቸው ፊት ጸንተው ይኖራሉ።
\v 9 ቤቶቻቸው ያለስጋት ናቸው፥ የእግዚአብሔርም በትር በላያቸው የለም።
\s5
\v 10 ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩም በከንቱ አይወድቅም፤ ላማቸውም አትጨነግፍም በጊዜዋ ትወልዳለች፥ ።
\v 11 ሕፃናቶቻቸውን እንደ መንጋ ያሰማራሉ፥ ልጆቻቸውም ይቦርቃሉ።
\v 12 በከበሮና በክራር ይዘምራሉ፥ በእምቢልታም ሙዚቃ ይደሰታሉ።
\s5
\v 13 ዕድሜያቸውንም በብልጥግና ይፈጽማሉ፤ በጸጥታም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ።
\v 14 እግዚአብሔርንም፦'' ከእኛ ራቅ፤ የመንገድህን እውቀት አንፈልግም' ይሉታል።
\v 15 እናመልከው ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወደ እርሱ በመጸለይስ ምን ጥቅም ይገኛል? ይላሉ።
\s5
\v 16 እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? ከኃጥአን ምክር ጋር ምንም አይነት ህብረት የለኝም። የኃጥአን መብራት የጠፋው፥
\v 17 መቅሠፍትም በላያቸው የመጣባቸው ስንት ጊዜ ነው ፥ እግዚአብሔርም በቍጣው መከራ የከፈላቸው መቼ ነው፥
\v 18 በነፋስ ፊት እንደ ገለባ፥ በዐውሎ ነፋስም እንደ ተወሰደ ትቢያ የሆኑ ስንት ጊዜ ነው?
\s5
\v 19 እናንተ፦ 'እግዚአብሔር የበደለኛውን ቅጣት ለልጆቹ ይጠብቃል' ብላችኋል። ጥፋቱን እንዲያው ቅጣቱን ራሱ ይክፈል።
\v 20 የገዛ ዓይኖቹ ጥፋቱን ይዩ፥ ሁሉን የሚችል አምላክን ቍጣ ራሱ ይጠጣ።
\v 21 ወራቶቹስ ካለቁ በኋላ፥ ከራሱ ሌላ ስለቤተሰቦቹ ምን ገዶት?
\s5
\v 22 በከፍታ ያሉትን ለሚፈርድ ለእግዚአብሔር ማን እውቀትን ሊያስተምረው ይችላል?
\v 23 አንድ ሰው በፍጹም ሰላምና ጤና ሲቀመጥ በሙሉ ብርታቱ ሳለ ይሞታል።
\v 24 በሰውነቱ ወተት ሞልቶአል፥ የአጥንቶቹም መቅን እርጥብና በጤንነት ናቸው።
\s5
\v 25 ሌላው ሰው ደግሞ መልካምን ነገር ፈጽሞ ሳይቀምስ፤ በተመረረች ነፍስ ይሞታል።
\v 26 በአፈር ውስጥ በአንድ ላይ ይጋደማሉ፥ ሁለቱንም ትል ይጨርሳቸዋል።
\s5
\v 27 አሳባችሁን፥ያሴራችሁብኝንም ክፉ ምክር አውቄዋለሁ።
\v 28 እናንተ፦ 'የልኡሉ ቤት የት አለ? ኃጢአተኛውም ሰው ይኖርበት የነበረ ድንኳን የት ነው?'' ብላችኋል።
\s5
\v 29 መንገድ ተጓዦችን አልጠየቃችሁምን? ሊናገሩ የሚችሉትን ማስረጃ አታውቁምን?
\v 30 ኃጢአተኛው ከመቅሠፍት ቀን እንደ ተጠበቀ፥ ከቍጣው ቀን ዘወር እንደተደረገ።
\s5
\v 31 የሃጥያተኛውን መንገድ ፊት ለፊትl የሚቃወም ማን ነው? በሠራው ስራ የሚቀጣው ማን ነው?
\v 32 እርሱን ግን ወደ መቃብር ይሸከሙታል፥ ሰዎቹም መቃብሩን ይጠብቃሉ።
\v 33 የተቀበረበት አፈር እንኳ ይጣፍጥለታል፤ ሰዎች ሁሉ ይከተሉታል፥ እጅግ ብዙ ሕዝብም ከፊቱ ይሄዳል።
\s5
\v 34 መልሳችሁ ከውሸት በቀር ምንም ስለሌለበት፤ በከንቱ ነገር እንዴት ልታጽናኑኝ ትችላላችሁ?
\s5
\c 22
\p
\v 1 ቴማናዊውም ኤልፋዝ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ሰው እግዚአብሔርን መጥቀም ይችላልን? ጥበበኛ ቢሆን እንኳ ይጠቅመዋልን?
\v 3 ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን ለሚችለው አምላክ የሚጨምረው ደስታ አለን? መንገድህ ፍጹም ቀና ቢሆን የሚጠቅመው ነገር አለን?
\s5
\v 4 የሚገስጽህና ወደ ፍርድስ ስፍራ የሚያመጣ፥ እርሱን ስለፈራህ ነውን?
\v 5 በደልህ እጅግ የበዛ፣ ኃጢአትህም ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?
\s5
\v 6 ያለምክንያት ከወንድሞችህን መያዣን ወስደሃል፥ ሰዎችን ልብሳቸውን ገፈህ እርቃናቸውን አስቀረሃቸው።
\v 7 ለዛሉም ሰዎች ውኃ አልሰጠሃቸውም፥ ከራብተኛ ሰዎችም እንጀራን ከልክለሃል።
\v 8 ምድርን የገዛህ ሃያል፤ ክቡር ሰው ብትሆንም።
\s5
\v 9 መበለቶን ባዶአቸውን ሰድደሃቸዋል አባት የሌላቸው ልጆችም ክንድ ተሰብሮአል።
\v 10 ስለዚህ ወጥመድ በዙሪያህ አለ፥ ድንገተኛ ፍርሃት ያናውጥሃል።
\v 11 እንዳታይም ጨለማ ሆነብህ፥ የጎርፍ ውሃም አሰጠመህ።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር በሰማያት ከፍታ ላይ አይልምን? የዋክብትን ከፍታ ተመልከት ምን ያህል ከፍ ይላሉ!
\v 13 አንተም፦ 'እግዚአብሔር ምን ያውቃል? በድቅድቅ ጨለማ ሆኖ ሊፈርድ ይችላልን?
\v 14 እንዳያየን ጥቅጥቅ ደመና ጋርዶታል፤ በሰማይም ክበብ ላይ ይራመዳል' አልህ።
\s5
\v 15 እነዚያ ኃጢአተኞች የሄዱበትን፥ የቀድሞውን መንገድ አንተ ደግሞ ትደግመዋለህን?
\v 16 ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤ መሠረታቸውም እንደ ወንዝ ፈሳሽ ተወሰደ።
\v 17 እግዚአብሔርንም፦ “ከእኛ ዘንድ ራቅ ሁሉንም የሚችል አምላክ ምን ሊያደርግልን ይችላል? ” አሉት።
\s5
\v 18 ነገር ግን እርሱ ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞላ፤ የኃጥአን ምክር ከእኔ ይራቅ።
\v 19 ጻድቃን የነዚህን ፍጻሜ ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፤ ንጹሐንም በንቀት እዲህ በማለት ይስቁባቸዋል።
\v 20 'በእርግጥ በእኛ ላይ የተነሱ ጠፍተዋል፥ ሃብታቸውንም እሳት በልቶታል።'
\s5
\v 21 አሁን ከእግዚአብሔር ጋር ተስማማ፥ ሰላምም ይኑርህ፤ በዚያም መንገድ መልካም ነገር ያገኝሃል።
\v 22 እለምንሃለሁ፥ ከእርሱ አፉ መመሪያ ተቀበል፥ በልብህም ቃሉን አኑር፤
\s5
\v 23 ሁሉን ወደሚችል አምላክ ብትመለስ፥ እንደገና ትሰራለህ፥ ኃጢአትንም ከድንኳንህ አርቀህ ብትጥል፥
\v 24 የከበረ ሃብትህን በአፈር ውስጥ፥ የኦፊርንም ወርቅ በጅረት ድንጋይ መካከል ብትጥል፥
\v 25 ሁሉን የሚችል አምላክ የከበረ ሃብትና የተመረጠ ብር ይሆንልሃል።
\s5
\v 26 በዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።
\v 27 ወደ እርሱ ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፤ ስእለትህንም ለእርሱ ትሰጣለህ።
\v 28 በማናቸውም ነገር አዋጅ ትናገራለህ፥ እርሱም ይጸናልሃል፤ ብርሃንም በመንገድህ ላይ ይበራል።
\s5
\v 29 እግዚአብሔር ትዕቢተኛን ሰው ያዋርዳል፤ ትሑቱንም ሰው ያድነዋል።
\v 30 ንጹሕ ያልሆነውን ሰው እንኳ፤ በእጅህ ንጽሕና በኩል ይታደገዋል።
\s5
\c 23
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ዛሬም ቢሆን የኅዘን አቤቱታዬ መራራ ነው፤ መከራዬም ማቃሰት ከምችለው በላይ ይከብዳል።
\s5
\v 3 ኦ! እርሱን ወዴት እንደማገኘው ምነው ባውቅ! እርሱ ወዳለበት ስፍራ በሔድሁ!
\v 4 ጉዳዬን በፊቱ በተገቢ ሁኔታ ባቀረብሁ፥ አፌንም ለሙግት ሞልቼ አዘጋጅ ነበር።
\v 5 የሚመልስልኝን ቃሎች አውቅ ነበር፥ የሚለኝንም በተረዳሁ ነበር።
\s5
\v 6 በኃይሉ ብዛት ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? እንኳን! ያደምጠኝ ነበር።
\v 7 ጻድቅ ሰው ከእርሱ ጋር በዚያ ይዋቀሳል፤ እንደዚህም በዳኛዬ በእርሱ ለዘላለም ነጻ እወጣ ነበር።
\s5
\v 8 ነገር ግን፥ ወደ ምስራቅ ብሄድ፥ በዚያ የለም፤ ወደ ምዕራብም ብሔድ ላየው አልቻልኩም፤
\v 9 ወደሚሠራበት ወደ ሰሜን ብሄድ አላየሁትም፤ ራሱን ወደሚሰውርበት በደቡብም፥ላየው አልቻልኩም፤
\s5
\v 10 ነገር ግን የምሄድበትን መንገድ ያውቃል፤ ከፈተነኝም በኋላ እንደ ወርቅ እወጣለሁ።
\v 11 እግሮቼ እርምጃውን በጽናት ተከተሉ፤ ውልፍት ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።
\v 12 ከከንፈሩም ትእዛዝ አላፈገፈግሁም፤ የአፉን ቃል በልቤ ሰውሬአለሁ።
\s5
\v 13 እርሱ ግን በአይነቱ ብቸኛ ነው፤ እርሱንስ ማን ሊመልሰው ይችላል? እርሱ የወደደውን ነገር ያደርጋል።
\v 14 በእኔ ላይ የተወሰነብኝን ይፈጽማል፤ እንደነዚህም አይነት ብዙ አለ።
\s5
\v 15 ስለዚህ በእርሱ ፊት ደነገጥሁ፤ ስለእርሱም ባሰብሁ ጊዜ እፈራዋለሁ።
\v 16 እግዚአብሔር ልቤን አድክሞታል፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደንግጦኛል።
\v 17 እንጂ ጨለማ ወይም ድቅድቁ ጨለማ ፊቴን ከመክደኑ የተነሣ አልጠፋሁም።
\s5
\c 24
\p
\v 1 ሁሉን ከሚችል አምላክ ሃጢያተኛ የሚፈረድበት ጊዜ ለምን አልተወሰነም? ለእርሱስ ታማኝ የሆኑት የፍርዱ ቀን እንደመጣ ለምን አያዩም?
\s5
\v 2 የድንበር ምልክትን የሚያፈርሱ ኅጢያተኛ ሰዎች አሉ፤ የሌሎችን መንጋ በግፍ ወስደው የሚያሰማሩ አመጸኞች አሉ።
\v 3 የድሀ አደጎችን አህያ ቀምተው ይነዳሉ ፤ የመበለቲቱንም በሬ በመያዣ ይወስዳሉ።
\v 4 ድሆችን ከመንገዳቸው ያስወጣሉ፤ የምድርም ችግረኞች ሁሉ ከእነርሱ ይሸሸጋሉ።
\s5
\v 5 እነዚህ ችግረኞች፥ በምድረ በዳ እንዳሉ የሜዳ አህዮች ወደ ስራቸው ይወጣሉ፥ ምግብን ፍለጋ በጥንቃቄ ይሄዳሉ፤ ምንአልባት ምድረ በዳው ለልጆቻቸው መብልን ይሰጣቸዋል።
\v 6 ድሆቹም በሌሎች ሰዎች በእርሻ ውስጥ በምሽት ያጭዳሉ፤ ከበደለኞችም መከር ወይንን ይቃርማሉ።
\v 7 ራቁታቸውን ያለ ልብስ ምሽቱን ሁሉ ይተኛሉ፥ በብርድም ጊዜ መጐናጸፊያ የላቸውም።
\s5
\v 8 ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ይረጥባሉ፤ መጠለያም ስለሌላቸው ከቋጥኝ ስር ይጋደማሉ።
\v 9 ድሀ አደጉን ህጻን ከእናቱ ጡት የሚነጥሉ ኅጢያተኞች አሉ፤ በደለኞችም ልጆችን በመያዣነት ይወስዳሉ።
\v 10 ነገር ግን ድሃዎቹ ያለ ልብስ ራቁታቸውን ይሄዳሉ፤ ተርበውም ቢሆን የሌሎችን እህል ነዶ ይሸከማሉ፤
\s5
\v 11 ድሃ ሰዎች በኁጢኣን አጥር ውስጥ ዘይት ይሰራሉ፤ ወይንም ይጠምቃሉ፥ ነገር ግን እነርሱ በጥም ይሰቃያሉ።
\v 12 በከተማ ውስጥ ሰዎች ያቃስታሉ ፤ የቆሰሉም ለእርዳታ ይጮኻሉ፤ እግዚአብሔር ግን ልመናቸውን አይመለከትም።
\s5
\v 13 እነዚህ ኅጢያተኞች በብርሃን ላይ ያምጻሉ፤ መንገዱን አያውቁም፥ በጎዳናውም አይጸኑም።
\v 14 ነፍሰ ገዳዩም ማልዶ ይነሣል፤ ችግረኞችንና ድሆችን ይገድላል፤ በሌሊትም እንደ ሌባ ነው።
\s5
\v 15 የአመንዝራም ዓይን ድግዝግዝታን ይጠብቃል። "የማንም ዓይን አያየኝም" ይላል፥ ፊቱንም እንደሌላ ይለውጣል።
\v 16 አመጸኞች ቤቶችን በጨለማ ይሰረስራሉ፤ በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ ለብርሃንም ግድ የላቸውም።
\v 17 ለእነርሱ ጥዋት እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነውና፤ ከድቅድቅ ጨለማ ሽብር ጋርም ተወዳጅተዋል።
\s5
\v 18 ይሁን እንጂ በውኃ ላይ እንዳለ አረፋ በርረው ይጠፋሉ፤ የርስት እድል ፈንታቸውም የተረገመ ነው፤ በወይን ቦታቸውም ላይ ለመስራት ማንም አይሄድም።
\v 19 ድርቅና ሙቀት በረዶውን እንደሚያቀልጥ፤ እንዲሁ ሲኦል ሃጢያተኞችን ታጠፋለች።
\s5
\v 20 የተሸከመችው ማኅፀን ትረሳዋለች፤ ትልም በደስታ ይበላዋል፤ ዳግመኛም አይታሰብም፤ በዚህ ሁኔታ ዓመጸኝነት እንደ ዛፍ ይሰበራል።
\v 21 የማትወልደውን መካኒቱን ሃጥያተኛው ይጎዳታል፤ ለመበለቲቱም ምንም አይነት በጎነት አያደርግም።
\s5
\v 22 ነገር ግን እግዚአብሔር በኃይሉ ኃያላንን ጎትቶ ይጥላል፤ እርሱም ይቆማል በሕይወቱ ግን አይጠነክርም።
\v 23 እግዚአብሔር በደኅንነት እንዳሉ እንዲያስቡ ይፈቅዳል፥ በዚያም ደስ ይላቸዋል፤ ነገር ግን ዓይኖቹ በመንገዳቸው ላይ ናቸው።
\s5
\v 24 እነዚህ ሰዎች ለጥቂት ጊዜ ከፍ ከፍ ይላሉ፤ በርግጥ ግን፥ ይዋረዳሉ፤ እንደ ሌሎች ሁሉ ተሰብስበው፤ እንደ እሸት ራስ ጫፍ ይቈረጣሉ።
\v 25 እንደዚህስ ባይሆን ሐሰተኛ የሚያደርገኝ፥ ንግግሬንም ከንቱ የሚያደርግ ማን ነው?
\s5
\c 25
\p
\v 1 ሹሐዊው በልዳዶስ ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ገዢነትና መፈራት የእርሱ ናቸው፤ በሰማይ ከፍታውም ስርአትን ያደርጋል።
\v 3 በውኑ ለሠራዊቶቹ ቍጥር ፍጻሜ አላቸውን? ብርሃኑስ የማይወጣው በማን ላይ ነው?
\s5
\v 4 እንግዲህ ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ይሆናል፥ ከሴትስ የተወለደ እንዴት ንጹሕና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል?
\v 5 ጨረቃ እንኳ ለእርሱ ብሩህ አይደለም፥ ከዋክብትም በፊቱ ንጹሐን አይደሉም።
\v 6 ይልቁንስ ትል የሆነ ሰው፥ የሰው ልጅ ምንኛ ያንስ!
\s5
\c 26
\p
\v 1 ኢዮብም ሲመልስ እንዲህ አለ፦
\v 2 ኃይል የሌለውን እንዴት ረዳኸው! ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!
\v 3 ጥበብስ የሌለውን እንዴት መከርኸው! መልካም እውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
\v 4 እነዚህን ቃሎች በማን እርዳታ ተናገርህ? ስትናገርስ ከአንተ የወጣው መንፈስ የማን ይሆን?
\s5
\v 5 በልዳዶ ስ መለሰ “ሙታን ሰዎች ከውሃዎች በታች የሚኖሩ፥ጥላዎ ቻቸውም ይንቀጠቀጣሉ።
\v 6 ሲኦል በእግዚአብሔር ፊቱ ራቁትዋን ናት፥ ጥፋትም ቢሆን ራሱን መሸፈኛ የለውም።
\s5
\v 7 ሰሜንን በባዶ ሕዋ ውስጥ ዘረጋው፥ ምድርንም እንዲያው ባዶ ላይ አንጠለጠላት።
\v 8 ውሃዎችን በደመናዎች ውስጥ ያስራል፥ ደመናውም ከታች አልተቀደደችም።
\s5
\v 9 የጨረቃን ፊት ይጋርዳል፥ ደመናውንም በላይዋ ይዘረጋበታል።
\v 10 በብርሃንና በጨለማ መካከል እንዳለ መስመር፥ በውሃዎች ላይ ድንበርን አደረገ።
\s5
\v 11 የሰማይ አዕማድ ተንቀጠቀጡ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ደነገጡ።
\v 12 በኃይሉ ባሕርን ጸጥ አደረገ፥ በማስተዋሉም ረዓብን መታ።
\s5
\v 13 በእስትንፋሱ የሰማያትን ማዕበል ያነጻል፤ ሰማያትም ውበትን አገኙ፥ እጁም በራሪይቱን እባብ ወጋች።
\v 14 እነዚህም ገና የመንገዱ መጀመሪያ ብቻ ናቸው፤ ከእርሱ የሰማነው ይህ ነገር ምንኛ ጥቂት ነው! የኃይሉን ነጐድጓድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?
\s5
\c 27
\p
\v 1 ኢዮብም መናገሩን ቀጠለ እንዲህም አለ፦
\v 2 ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል አምላክን!
\v 3 ነፍሴ በእኔ ውስጥ፥ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ በአፍንጫዬ እስካለ ድረስ፥
\s5
\v 4 በርግጥ ከንፈሬ ኃጢአትን አይናገርም፥ ምላሴም ሽንገላን አያወራም።
\v 5 እናንተን ትክክል አድርጎ መቀበል ከእኔ ይራቅ፤ እስክሞት ድረስ ትክክለኛነቴን በፍጹም አልጥልም።
\s5
\v 6 ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ እርሱንም አለቅም፤ ከኖርኩባቸው ቀኖቼ ስለ አንዱም ህሊናዬ አይወቅሰኝም።
\v 7 ጠላቴ እንደ በደለኛ ሰው ይሁን፥ በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን።
\s5
\v 8 እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥ አምላክ የሌለው ሰው ተስፋው ምንድር ነው?
\v 9 መከራ በመጣበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
\v 10 ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?
\s5
\v 11 ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፤ የሁሉን ቻይ አምላክን ሃሳብ አልሸሽግም።
\v 12 እናንተ ሁላችሁ ይህንን አይታችሁ፤ ለምን ይህን ሁሉ ከንቱ ነገር ተናገራችሁ?
\s5
\v 13 ይህ እግዚአብሔር ለክፉ ሰው ያቆየው እድል ፈንታ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚቀበለው ርስት ነው፤
\v 14 ልጆቹ ቢበዙ ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ ዘሩም በቂ እንጀራን አያገኝም።
\s5
\v 15 የተረፉለትም በመቅሰፍት ምክንያት ይቀበራሉ፤ መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
\v 16 አመጸኛ ሰው ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ሸክላ ቢያከማች፥
\v 17 እርሱ ያከማቸውን ልብስ፥ ጻድቃን ይለብሱታል፤ ብሩንም ንጹሐን ሰዎች ይከፋፈሉታል።
\s5
\v 18 ቤቱን እንደ ሸረሪት ይሠራል፥ ጠባቂም እንደሚቀልሰው ጎጆ ይመስላል።
\v 19 ባለጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ነገር ግን አይዘልቅበትም፤ ዓይኑን በከፈተ ጊዜ፥ ሃብቱ ሁሉ የለም።
\s5
\v 20 ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ያገኘዋል፤ ማዕበልም በሌሊት ይወስደዋል።
\v 21 የምሥራቅ ነፋስ ይወስደዋል፥ እርሱም ይለቃል፤ ከስፍራውም ይጠርገዋል።
\s5
\v 22 ከነፋሱ ሊያመልጥ ይሞክራል፥ ነገርግን ሳያቋርጥ እየተወረወረ ይደርስበታል።
\v 23 በመሳለቅም እጁን ያጨበጭብበታል፤ በፉጨትም ከስፍራው ያስወጣዋል።
\s5
\c 28
\p
\v 1 በእርግጥ ብር የሚወጣበት፥ ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ።
\v 2 ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ መዳብም ከድንጋይ ቀልጦ ይወጣል።
\s5
\v 3 ሰው የጨለማ መጨረሻ ድረስ ይወርዳል፤ በጨለማና ባስፈሪ ስፍራ ውድ ድንጋይ ይፈላልጋል።
\v 4 ሰው ከሚኖርበት ርቆ መውረጃ ይቈፍራሉ፤ ከሁሉ እግር በተረሳ ስፍራ፥ ከሰዎችም ሩቅ ሆኖ እየተንጠላጠለ ይወዛወዛል።
\s5
\v 5 ከምድር እንጀራ ቢገኝም፤ ከታችኛው ክፍል ግን እሳት ይገላበጣል።
\v 6 ድንጋይዋ ሰንፔር የሚገኝበት ስፍራ ነው፥ አፈሯም ወርቅን ይዟል።
\s5
\v 7 ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፥ የአሞራም ዓይን አላየውም።
\v 8 ኲሩ እንስሶች ይህን መንገድ አልሄዱበትም፥ አስፈሪው አንበሳም በዚያ አላለፈም።
\s5
\v 9 ሰው ቡላድ ድንጋይ ላይ እጁን ይጭናል፥ ተራራዎችንም ከሥራቸው ይገለብጣል።
\v 10 በድንጋይ ውስጥ መንዶልዶያን ፈልፍሎ ይሰራል፤ በዚያም ዓይኑ የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያል።
\v 11 ፈሳሹም እንዳያልፉ ይገድባል፤ በዚያም የተሰወሩትን ወደ ብርሃን ያወጣቸዋል።
\s5
\v 12 ጥበብ ግን የት ትገኛለች? የማስተዋልስ ስፍራ ወዴት ነው?
\v 13 ሰው ዋጋዋን አላወቀም በሕያዋንም ምድር አትገኝም።
\v 14 ከምድር ጥልቅ ያለ ውሃ፦ "በእኔ ውስጥ የለችም' አለ፤ ባሕርም፦ "እኔ ጋር የለችም" አለ።
\s5
\v 15 ወርቅ ሊገዛት አይችልም፥ ዋጋዋም በብር አይመዘንም።
\v 16 በኦፊር ወርቅ፥ በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።
\v 17 ወርቅና ብርሌ አይተካከሉአትም፥ በነጠረ ወርቅ ጌጥም አትለወጥም።
\s5
\v 18 ዛጐልና አልማዝ ከቁጥር አይገቡም። በርግጥ የጥበብ ዋጋ ከቀይ ዕንቍ ይበልጣል።
\v 19 የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይስተካከላትም፥ በንጹህ ወርቅም አትገመትም።
\s5
\v 20 ታዲያ ጥበብ ከወዴት ትመጣለች? የማስተዋልስ ስፍራ የት ነው?
\v 21 ጥበብ ሕይወት ካላቸው ነገሮች ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፥ ከሰማይ ወፎችም ተሸሽጋለች።
\v 22 ጥፋትና ሞት፦ “ወሬዋን ብቻ በጆሮቻችን ሰምተናል” አሉ።
\s5
\v 23 እግዚአብሔር ወደ እርሷ የሚወስደውን መንገድ ያስተውላል፥ስፍራዋንም ያውቃል።
\v 24 ምክንያቱም እርሱ የምድርን ዳርቻ፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።
\v 25 እርሱ አስቀድሞ ለነፋስ ሃይል መጠንን አደረገ፥ ውኆችንም በስፍር ሰፈረ፥
\s5
\v 26 እርሱ ለዝናብ ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን አደረገ፥
\v 27 በዚያን ጊዜ ጥበብን አያት፥ ገለጣትም አጸናት፥ በርግጥም መረመራት።
\v 28 ለሰዎችም፦ እነሆ፥ “እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው” አለ።
\s5
\c 29
\p
\v 1 ኢዮብም መናገሩን ቀጠለ፥ እንዲህም አለ፦
\v 2 እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደ ነበረው ጊዜ፥ እንዳለፉት ወራት ምነው በሆንሁ!
\v 3 መብራቱ በራሴ ላይ እንደበራበት ወቅት፥ በጨለማ ውስጥ በብርሃኑ አልፌ እንደሄድሁበት ጊዜ፥
\s5
\v 4 ቀኖቼ ወደ ሙላታቸው በደረሱ ጊዜ፥ የእግዚአብሔር ወዳጅነት በድንኳኔ በነበረ ጊዜ፥
\v 5 ሁሉን የሚችል አምላክ ገና ከእኔ ጋር በነበረ ጊዜ፥ ልጆቼም በዙሪያዬ እያሉ፥
\v 6 መንገዴ በቅቤ ይታጠብ በነበረ ጊዜ፥ ድንጋዩ የዘይት ፈሳሽ ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ።
\s5
\v 7 ወደ ከተማው በር በወጣሁ ጊዜ፥ በአደባባዩ መሃል ወንበሬ ላይ በተቀመጥሁ ጊዜ፥
\v 8 ወጣቶች አይተው በአክብሮት ገለል አሉ፥ ሽማግሌዎችም ተነሥተው ቆሙ።
\s5
\v 9 በመጣሁ ጊዜ ልኡላን ከመናገር ይቆጠባሉ፥ እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር።
\v 10 የብልሆች ድምፅ ጸጥ ይል፤ ምላሳቸውም በላንቃቸው ተጣበቀች።
\s5
\v 11 በጆሮአቸው ከሰሙኝ በኋላ ይባርኩኝ ነበር፥` በአይናቸው ዓይተው ያሞግሱኝና ይመሰክሩልኝ ነበር፤
\v 12 ምክንያቱም የሚጮኸውን ችግረኛ፥ ድሀ አደጉንና ረዳት የሌላቸውን አድን ነበረና።
\v 13 ሊጠፋ የቀረበ በረከት ወደ እኔ ይመጣል፤ ባል የሞተባትንም ሴት ልብ በደስታ እንድትዘምር አደርግ ነበርና።
\s5
\v 14 ጽድቅን ለበስሁ እርስዋም ለበሰችኝ፤ ፍትሃዊነቴም እንደ መጐናጸፊያዬና ጥምጣሜ ነበረ።
\v 15 ለአይነ ስውራን ዓይናቸው፥ መራመድ ለማይችሉም ሰዎች እግር ነበርሁ።
\v 16 ለችግረኞች አባት ነበርሁ፤ የማላውቀውንም ሰው ሙግት እመረምር ነበር።
\s5
\v 17 የኃጢአተኛውን መንጋጋ ሰበርሁ፥ የያዘውንም ከጥርሱ ውስጥ አስጣልሁ።
\v 18 እንዲህም አልሁ፦ “በጎጆዬ ሆኜ እሞታለሁ፥ ቀኖቼን እንደ አሸዋ አበዛለሁ፤
\v 19 ሥሮቼ ወደ ውኃ ይሰራጫሉ፥ ጠልም ምሽቱን ሁሉ በቅርንጫፎቼ ላይ ያድራል፤
\s5
\v 20 በእኔ ዘንድ ያለው ክብር ሁልጊዜ ትኩስ ነው፥ በእጄ ያለው የብርታቴ ቀስት አዲስ ነው።
\v 21 ሰዎች እኔን ለመስማት በትዕግሥት ተጠባበቁ፥ ምክሬንም ለማዳመጥ በጸጥታ ተቀመጡ።
\v 22 ንግግሬንም ከጨረስኩ በኋላ መልሰው አልተናገሩም፤ ቃሎቼም በላያቸው እንደ ውሃ ተንጠባጠበ።
\s5
\v 23 ዝናብን እንደሚጠብቁ ሁልጊዜ ይጠብቁኛል፤ የበልግ ዝናብን እንደሚሹት፥ ከቃሎቼ ለመጠጣት አፋቸውን ከፈቱ ።
\v 24 እነርሱ ባልጠበቁተ ጊዜ ሳቅሁላቸው፤ የፊቴንም ብርሃን ቸል አላሉትም።
\s5
\v 25 መንገድን እመርጥላቸውና አለቃቸው ሆኜ እቀመጣለሁ፤ ኅዘነተኞችን በቀብር ጊዜ እንደሚያጽናና ሰው፥ በሠራዊቱም መካከል እንዳለ ንጉሥ በመካከላቸው ኖርሁ።
\s5
\c 30
\p
\v 1 አሁን ግን በዕድሜ ከእኔ የሚያንሱ፥ አባቶቻቸውን ከመንጋዬ ጠባቂ ውሾች ጎን እንዳይሰሩ ልከለክላቸው የምችል የነበሩ እነዚህ ወጣቶች፥ በእኔ ላይ ተሳለቁብኝ።
\v 2 በርግጥ የአባቶቻቸው ክንድ ጥንካሬ ምን ሊፈይድልኝ ይችል ነበር? የጉልምስናቸው ጥንካሬ ጠፍቶባቸው ነበርና።
\v 3 በድህነትና በራብ የመነመኑ ናቸው፤ በደረቅ መሬት በምድረ በዳ ጨለማና ጥፋት ይሰቃያሉ።
\s5
\v 4 ከቍጥቋጦ አጠገብ ያለውን ጨው ጨው የሚሉትን ቅጠሎች ይለቅማሉ፤ የክትክታ ሥራሥር ምግባቸው ነበር።
\v 5 ሌባን እየተከታተሉ እንደሚጮኹበት፤ ከሚጮኹባቸው ሰዎች ተለይተው ተሰደዱ።
\v 6 በወንዝ ሸለቆ በምድር ጕድጓድና በድንጋይም ዋሻ ውስጥ ይኖራሩ ነበር።
\s5
\v 7 በቍጥቋጦ መካከል እንደ አህያ ይጮኻሉ፤ ከቁጥቋጦ በታች በጋራ ተሰብስበዋል።
\v 8 በርግጥ የሰነፎችና ዋጋ የሌላቸው ሰዎች ልጆች ናቸው፤ እየተገረፉ ከምድሪቱ ተባረዋል።
\s5
\v 9 አሁን ግን ለልጆቻቸው የስላቅ ዘፈን ሆንኩላቸው፤ በርግጥም የነሱ መቀለጃ ሆኛለሁ።
\v 10 ተጸየፉኝ፥ ከእኔም ርቀው ይቆማሉ፤ ፊቴም ላይ መትፋትን አያቆሙም።
\v 11 እግዚአብሔር የቀስቴን መወጠሪያ አላልቶብኛል፥ መከራም አሳይቶኛል፤ እነርሱም በፊቴ ይሉኝታ የላቸውም።
\s5
\v 12 በቀኜ በኩል ዱርዬዎች ተነሥተዋል፥ ያሳድዱኛል፤ ለእግሬም የጥፋትን ወጥመድ ያደርጋሉ።
\v 13 መንገዴን ያበላሻሉ፤ ከልካይ እንደሌላቸው ሰዎች ጥፋትን ገፍተው ያመጡብኛል።
\s5
\v 14 በሰፊ ፍራሽ ቀዳዳ እንደሚመጣ ሰራዊት ይመጡብኛል፤ በጥፋት ላይ ተንከባልለው መጡብኝ።
\v 15 ድንጋጤ በላዬ መጥቶብኛል፥ ክብሬም በነፋስ ያሳደዱት ያክል በነነ፤ ብልጥግናዬም እንደ ደመና ተበተፈ።
\s5
\v 16 አሁንም ነፍሴ በውስጤ ፈሰሰች፤ የብዙ ቀናት መከራም ያዘኝ።
\v 17 በሌሊት አጥንቶቼ በውስጤ ተወጉ፥ የሚያሰቃየኝ ህመም ፋታ አይሰጠኝም።
\s5
\v 18 ከእግዚአብሔር ታላቅ ኃይል የተነሣ ልብሴ ተያዘ፥ እንደ ቀሚስ መቀነት ተጠቀለለብኝ።
\v 19 እርሱ ጭቃ ውስጥ ወረወረኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ።
\s5
\v 20 ወደ አንተ ጮኽሁ እግዚአብሔር፥ አንተም አልመለስህልኝም ቆምሁኝ፥ አልተመለከትኸኝም።
\v 21 ተለወጥህብኝ ፤ ጨካኝም ሆንህብኝ፤ በእጅህም ሃይል አሳደድኸኝ።
\s5
\v 22 በነፋስ አነሣኸኝ፥ በላዩም አስቀምጠኸ ወሰድኸኝም፤ በማእበልም ውስጥ አቀለጥኸኝ።
\v 23 ለሕያዋን ሁሉ ወደተወሰነው ቤት፤ ወደ ሞት እንደምትወስደኝ አውቄአለሁ።
\s5
\v 24 ነገር ግን ሰው ሲወድቅ እጁን እርዳታ ፍለጋ አይዘረጋምን? በችግር ውስጥ ያለ ማንም ለእርዳታ አይጮኽምን?
\v 25 በችግር ላለ ሰው አላለቀስሁምን? ለድሆችስ ነፍሴ አላዘነችምን?
\v 26 መልካምን በተጠባበቅሁ ጊዜ ክፉ መጣብኝ፤ ብርሃንን ስጠባበቅ፥ ጨለማ መጣ።
\s5
\v 27 ልቤ ታወከ፥ እረፍትም አላገኘም የስቃይም ቀናቶች መጡብኝ።
\v 28 ያለ ፀሐይ በጨለመ ሰማይ በትካዜ ሄድሁ፤ በጉባኤም መካከል ቆሜ ለእርዳታ እጮኻለሁ።
\v 29 ለቀበሮ ወንድም፥ ለሰጐንም ጓደኛ ሆንሁ።
\s5
\v 30 ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከላዬም ተቀርፎ ወደቀ፤ አጥንቶቼም በትኵሳት ተቃጠሉ።
\v 31 ስለዚህ በገናዬ ለኀዘን እንጉርጉሮ ፥ እምቢልታዬም ለለቅሶ ጩኸት ተቃኙ።
\s5
\c 31
\p
\v 1 ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ስለገባሁ፤ እንዴት ድንግሊቱን በምኞት እመለከታለሁ?
\v 2 ከላይ ከእግዚአብሔር የሆነው እድል ፈንታ ፥ ሁሉንም የሚችል አምላክስ ርስት ከአርያም ምንድን ነው?
\s5
\v 3 መዓት ለኃጢአተኛ፥ ጥፋትም ክፋትን ለሚያደርጉ ነው ብዬ አስብ ነበር።
\v 4 እግዚአብሔር መንገዴን አያይምን? እርምጃዬንስ ሁሉ አይቈጥርምን?
\s5
\v 5 በሐሰት ሄጄ እንደ ሆነ እግሬም ለሽንገላ ቸኵሎ እንደ ሆነ፥
\v 6 በእውነተኛ ሚዛን ልመዘን፥ እግዚአብሔርም ትክክለኛቴን ይወቅ።
\s5
\v 7 እርምጃዬ ከትክክለኛው መንገድ ፈቀቅ ብሎ፥ ልቤም የዓይኔን ምኞት ተከትሎ፥ ነውርም በእጄ ላይ ተጣብቆ እንደ ሆነ፥
\v 8 እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብላው፤ መከሩም ከእርሻዬ ላይ ይነቀል።
\s5
\v 9 ልቤ ወደ ሌላይቱ ሴት ጐምጅቶ እንደ ሆነ፥ የጎረቤቴን ሚስት ለማየት ደጃፉ አድብቼ እንደ ሆነ፥
\v 10 ሚስቴ ለሌላ ሰው እህል ታዘጋጅ፥ ሌሎችም ከእርስዋ ጋር ይተኙ።
\s5
\v 11 ይህ ክፉ ወንጀል ነውና፥ በፈራጆችም ሊቀጣ የሚገባው በደል ነውና፤
\v 12 ይህ እስከ ሲኦል ድረስ የሚበላ እሳት፥ ያመረትኩትን ሁሉ የሚያቃጥል ነውና።
\s5
\v 13 ወንድ ወይም ሴት ባሪያዎቼ ከእኔ ጋር በተምዋገቱ ጊዜ፥ ሙግታቸውን በትክክል ሳላይ ቀርቼ እንደ ሆነ፥
\v 14 እግዚአብሔር ሊከሰኝ በተነሣ ጊዜ ምን አደርጋለሁ? ሊፈርደኝም በመጣ ጊዜ እንዴት እመልስለታለሁ?
\v 15 እኔን በማኅፀን የሰራኝ እነርሱንስ የፈጠረ አይደለምን? በማኅፀንስ ውስጥ ሁላችንን የሠራን አንድ አይደለምን?
\s5
\v 16 ድሀዎችን ከፍላጎታቸው ከልክዬ፥ የመበለቲቱንም ዓይን በለቅሶ አጨልሜ እንደ ሆነ፥
\v 17 እንጀራዬን ለብቻዬ በልቼ እንደ ሆነ፥ አባት የሌላቸውንም ከእርሱ እንዳይበሉ ከልክዬ እንደ ሆነ፤
\v 18 ይልቁን እርሱ ከታናሽነቴ ጀምሬ እንደ አባቱ ሆኜ ከእኔ ጋር አሳድጌው ነበር፥ እናቱንም ከእናቴ ማኅፀን ጀምሬ መራኋት፤
\s5
\v 19 አንድ ሰው የሚለብሰው አጥቶ ሲጠፋ፥ ወይም ድሀ ያለ ልብስ ሲሆን እንዲያው አይቼ እንደ ሆነ፥
\v 20 በበጎቼም ጠጕር ያልሞቀና፥ በልቡ ያልባረከኝ እንደ ሆነ፤
\v 21 በከተማው በር ረዳት ስላለኝ፥ አባት በሌላቸው ላይ እጄን አንሥቼ እንደ ሆነ፥
\s5
\v 22 ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይውደቅ፥ ክንዴም ከመገናኛው ይሰበር።
\v 23 ከእግዚአብሔር የሆነ ቁጣ ለእኔ አስደንጋጭ ነውና ከግርማውም የተነሳ እነዚህን ነገሮች ማድረግ አልችልም።
\s5
\v 24 ወርቅን ተስፋዬ አድርጌ፥ ጥሩውንም ወርቅ ”በአንተ እታመናለሁ“ ብዬ እንደ ሆነ፤
\v 25 ሀብቴ ስለ በዛ፥ እጄም ብዙ ስላከማቸ ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፤
\s5
\v 26 ፀሐይ ሲበራ ተመልክቼ፥ ጨረቃ በድምቀት ስትሄድ አይቼ፥
\v 27 ልቤ እነርሱን ለማምለክ በስውር ተስቦ፥ አፌም እጄን ስሞ እንደ ሆነ፤
\v 28 በላይ ያለውን እግዚአብሔርን መካድ ነውና ይህም ዳኞች ሊቀጡት የሚገባ ወንጀል በሆነ ነበር።
\s5
\v 29 በሚጠላኝ በማንም መጥፋት ደስ ብሎኝ ወይም ክፉ ነገር በሆነበት ጊዜ ራሴን አስደስቼው እንደ ሆነ፤
\v 30 ለነፍሱ እርግማንን በመናገር፥ አንደበቴ ኃጢአት እንዲሰራ በርግጥ አልፈቀድኩለትም፤
\s5
\v 31 በድንኳኔ የሚኖሩ ሰዎች፦ “ከኢዪብ ማዕድ ያልጠገበ ማን ይገኛል? ” ብለው ካልተናገሩ፤
\v 32 መጻተኛው በከተማ ጎዳና እንዳያድርም፥ ሁልጊዜ ደጄን ለመንገደኛ እከፍት ነበር፤
\s5
\v 33 በደሌንም በብብቴ በመሸሸግ ኃጢአቴን እንደ ሰዉ ሁሉ ደብቄ እንደ ሆነ፤
\v 34 የሕዝብን ብዛት ከመፍራቴ የተነሳ፥ የዘመዶቼም ንቀት አስደንግጦኝ፥ ዝም ብዬ ከቤቴ ሳልወጣ ቀርቼ እንደ ሆነ፤
\s5
\v 35 ኦ የሚያዳምጠኝ አንድ ሰው ምነው በኖረኝ! ይኸው የእጄ ፊርማ ምልክት፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ! ባላጋራዬ የጻፈው የክስ ጽሑፍ ምነው በተገኘልኝ!
\v 36 በግልጽ ትከሻዬ ላይ አድርጌ እሸከመው ነበር፥ እንደ አክሊልም ራሴ ላይ አስቀምጠው ነበር።
\v 37 የእርምጃዎቼን ቍጥር በግልጽ አስታውቀው፥ እንደ ተማመነ አለቃም ፊትለፊቱ እወጣ ነበር።
\s5
\v 38 የእርሻዬ መሬት በእኔ ላይ ጮሆ እንደ ሆነ፥ ትልሞቹም አብረው አልቅሰው እንደ ሆነ፤
\v 39 የምርቱን ዋጋ ሳልከፍል በልቼ፥ የባለቤቶቹንም ነፍስ አሳዝኜ እንደ ሆነ፥
\v 40 በስንዴ ፋንታ እሾኸ፥ በገብስም ፋንታ አረም ይብቀልበት።“ የኢዮብም ንግግር ተፈጸመ።
\s5
\c 32
\p
\v 1 ኢዮብም ራሱን ጻድቅ አድርጎ ስላስቀመጠ እነዚያ ሦስቱ ሰዎች ምላሽ መስጠት አለብህ።
\v 2 ከራም ቤተሰብ የሆነ የቡዛዊው የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ እጅግ ተቆጣ፤ ከእግዚአብሔር ይልቅ ራሱን ስላጸደቀ ኢዮብን ተቈጣው።
\s5
\v 3 ደግሞም በኢዮብ ፈረዱበት እንጂ የሚገባ መልስ ስላልሰጡት በሦስቱ ጓደኞቹ ላይ ተቈጣ።
\v 4 ከእርሱ ይልቅ ሰዎቹ ሽማግሌዎች ስለነበሩ ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር ለመነጋገር ተራውን ይጠብቅ ነበር።
\v 5 ቢሆንም ግን ኤሊሁም በእነዚህ በሦስቱ ሰዎች አፍ መልስ እንደሌለ ሲያይ በጣም ተቆጣ።
\s5
\v 6 ቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ መናገር ሲጀምር እንዲህም አለ፦ እኔ በዕድሜ ወጣት ነኝ፥ እናንተም ሽማግሌዎች ናችሁ፤ ስለዚህም ሰጋሁ፤ እውቀቴን እንዳልናገር ራሴን ገታሁ።
\v 7 እንደዚህም አልሁ፦ የቀናት ርዝመት ንግግርን፥ የዓመታትም ብዛት ጥበብን ሊያስተማሩ ይገባ ነበር።
\s5
\v 8 ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፤ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጠዋል።
\v 9 ታላላቅ ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ጥበበኞች አይደሉም፣ በእድሜ የገፉ ስለሆኑ ብቻም ፍትሕን አያስተውሉም።
\v 10 ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፥ 'አድምጡኝ፤ እኔም ደግሞ የማውቀውን እነግራችኋለሁ'።
\s5
\v 11 ተመልከቱ፥ እስክትናገሩ ጠበቅኋችሁ፥ ምን መናገር እንዳለባችሁ በማሰብ ላይ እያላችሁም ክርክራችሁን አዳመጥኩኝ።
\v 12 በርግጥ ትኩረቴን ሰጠዃችሁ፥ ነገር ግን፥ ተመልከቱ፥ አንዳችሁም ኢዮብን ማስረዳት ወይም ለቃሎቹ ምላሽ መስጠት አልቻላችሁም።
\s5
\v 13 'ጥበብን አግኝተናል!' እንዳትሉ ተጠንቀቁ ኢዮብን ማሸነፍ ያለበት እግዚአብሔር ነው፤ ተራ ሰው ይህንን ለማድረግ አይችልም።
\v 14 ኢዮብ እኔን በመቃወም አልተናገረምና እኔም የእናንተን በሚመስል ቃል አልመልስለትም።
\s5
\v 15 እነዚህ ሦስት ሰዎች ዲዳ ሆነዋል፤ ከዚህ በኋላ ለኢዮብ ሊመልሱለት አይችሉም፤ ቀጥለው የሚናገሩት አንድም ቃል የላቸውም።
\v 16 እዚያ በዝምታ ስለቆሙና ከእንግዲህ ስለማይመልሱ፥ ስለማይናገሩም፥ መጠበቅ አለብኝ?
\s5
\v 17 አይሆንም፥ እኔም ደግሞ የበኩሌን እመልሳለሁ፤ እኔም ደግሞ ዕውቀቴን እነግራቸዋለሁ። ቃል
\v 18 ተሞልቻለሁና፤ በውስጤ ያለው መንፈስም ይገፋፋኛል።
\v 19 ተመልከቱ፥ ውስጤ ተከድኖ እንደሚብላላ ወይን ነው፤ ሊፈነዳ እንደተቃረበ አዲስ የወይን ጠጅ አቁማዳም ነው።
\s5
\v 20 አርፍ ዘንድ እናገራለሁ፤ አፌንም ከፍቼ መልስ እሰጣለሁ።
\v 21 አድልዎ አላደርግም፤ የትኛውንም ሰው አላቆላምጥም።
\v 22 እንዴት እንደማቆላምጥ አላውቅምና፤ እንዲህ ባደርግ ኖሮ ፈጣሪዬ ፈጥኖ ያስወግደኝ ነበር።
\s5
\c 33
\p
\v 1 አሁንም ኢዮብ ሆይ፥ ቃሎቼን እንድትሰማ፥ ንግግሬንም እንድታደምጥ እለምንሃለሁ።
\v 2 ይኸው አሁን አፌን ከፍቻለሁ፤ ምላሴም በአፌ ውስጥ ተናግሯል።
\v 3 ቃሎቼ የልቤን ቅንነት ይናገራሉ፤ ከንፈሮቼ የሚያውቁትን በታማኝነት ይናገራሉ።
\s5
\v 4 የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፤ የሁሉን ቻዩ እስትንፋስ ሕይወትን ሰጠኝ።
\v 5 ከቻልክ መልስልኝ፤ በፊቴም ቃሎችህን በቅደም ተከተል አዘጋጅና ቁም።
\s5
\v 6 ተመልከት፥ በእግዚአብሔር ፊት አንተ እንደሆንከው እንዲሁም እኔም ነኝ፤ እኔም ደግሞ ከጭቃ ተሠርቻለሁ።
\v 7 ተመልከት፥ ማስፈራራቴ አያስፈራህም፤ ተጽዕኖዬም ቢሆን አይከብድብህም።
\s5
\v 8 በእርግጥ በጆሮዬ ተናግረሃል፤ እንዲህ የሚለውንም የቃልህን ድምፅ ሰምቻለሁ፥
\v 9 ንጹሕ ነኝ መተላለፍም የለብኝም፤ አልበደልኩም፥ ኃጢአትም የለብኝም።
\s5
\v 10 ይኸው፥ እግዚአብሔር ሊያጠቃኝ አጋጣሚ ይፈልጋል፤ እንደ ጠላቱ አድርጎ ይቆጥረኛል።
\v 11 እግሮቼን በግንድ ውስጥ ያስገባቸዋል፤ መንገዶቼንም ሁሉ ይመለከታል።
\v 12 እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣልና እንደዚህ መናገርህ ትክክል አይደለም ብዬ እመልስልሃለሁ።
\s5
\v 13 ለየትኛውም ሥራው ትኩረት አይሰጠውም በማለት ከእርሱ ጋር ለምን ትታገላለህ?
\v 14 ሰው ባያስተውለውም እግዚአብሔር አንድ ጊዜ፥ አዎን፥ ሁለት ጊዜ ይናገራል።
\v 15 ሰዎች አልጋቸው ላይ ተኝተው ከባድ እንቅልፍ በሚወድቅባቸው ጊዜ በህልም፥ በሌሊት ራዕይ ይናገራቸዋል።
\s5
\v 16 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የሰዎችን ጆሮ ይከፍትና በማስጠንቀቂያው ያስፈራራቸዋል፤
\v 17 ይህንን የሚያደርገውም ሰውን ከኃጢአታዊ ዓላማው ሊመልሰውና ከትዕቢት ሊጠብቀው ነው።
\v 18 እግዚአብሔር የሰውን ሕይወት ከጉድጓድ ይጠብቃል፥ ሕይወቱንም ወደ ሞት ከመውረድ።
\s5
\v 19 ደግሞም ሰው በአልጋው ላይ በሕመም ይቀጣል፥ በአጥንቶቹም ውስጥ በማያቋርጥ ስቃይ፤
\v 20 ሕይወቱ ምግብን፥ ነፍሱም ጣፋጩን መብል እስክትጠላ ድረስ።
\s5
\v 21 ሥጋው ሊታይ እስከማይችል ድረስ ጠፍቷል፥ የማይታዩ የነበሩት አጥንቶቹም አሁን ገጠው ወጥተዋል።
\v 22 በርግጥ ነፍሱ ወደ ጉድጓድ ቀርባለች፥ ሕይወቱም ሊያጠፏት ወደሚፈልጉት።
\s5
\v 23 ነገር ግን መካከለኛ ሊሆንለት የሚችል አንድ መልአክ ቢኖር፥ የትኛውን መልካም ነገር ማድረግ እንዳለበት የሚያሳየው፥ መካከለኛ የሚሆንለት ከሺህ መላእክት አንድ ቢገኝለት፥
\v 24 መልአኩም ለእርሱ ደግ ቢሆንና እግዚአብሔርን፥ 'ቤዛ የሚሆንለት አግኝቻለሁና ይህንን ሰው ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አድነው' ቢለው
\s5
\v 25 በዚያን ጊዜ ሥጋው ከሕፃን ገላ ይልቅ ይታደሳል፤ ወደ ወጣትነት የብርታቱ ዘመንም ይመለሳል።
\v 26 እርሱ ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እግዚአብሔርም ይራራለታል፥ እርሱም የእግዚአብሔርን ፊት በደስታ ያያል። እግዚአብሔርም ለሰውየው ድልን ይሰጠዋል።
\s5
\v 27 ከዚያም ያ ሰው በሌሎች ሰዎች ፊት እንዲህ ሲል ይዘምራል፥ 'ኃጢአትን ሠርቻለሁ፥ ትክክለኛ የሆነውንም አጣምሜአለሁ፥ ይሁን እንጂ ስለኃጢአቴ አልተቀጣሁም።
\v 28 እግዚአብሔር ነፍሴን ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አዳናት፤ ሕይወቴም ብርሃን ማየቷን ትቀጥላለች''።
\s5
\v 29 ተመልከቱ፥ እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ሁሉ በሰው ሕይወት ሁለት ጊዜ፥ አዎን፥ እንዲያውም ሦስት ጊዜ ያደርጋቸዋል፤
\v 30 ይኸውም የሕይወት ብርሃን ይበራለት ዘንድ ነፍሱን ከጉድጓድ ለመመለስ ነው።
\s5
\v 31 ኢዮብ ሆይ አስተውለህ ስማኝ፤ ዝም በል፥ እኔም እናገራለሁ።
\v 32 የምትናገረው ነገር ካለህ መልስልኝ፤ ትክክለኛ መሆንህን ለማረጋገጥ እፈልጋለሁና ተናገር።
\v 33 ካልሆነ ግን ጸጥ ብለህ ስማኝ፤ እኔም ጥበብን አስተምርሃለሁ“።
\s5
\c 34
\p
\v 1 ኤሊሁም በመቀጠል እንዲህ አለ፥
\v 2 ”እናንተ ጥበበኞች፥ ቃሎቼን አድምጡ፤ እውቀት ያላችሁ እናንተ ስሙኝ።
\v 3 ምላስ ምግብን እንደሚያጣጥም ጆሮም ቃላትን ያመዛዝናል።
\s5
\v 4 ትክክለኛ የሆነውን ለራሳችን እንምረጥ፤ መልካም የሆነውንም በመካከላችን እንፈልገው።
\v 5 ኢዮብ 'እኔ ጻድቅ ነኝ እግዚአብሔር ግን መብቴን ነፍጎኛል። መብት ቢኖረኝም እንደ ሐሰተኛ ተቆጥሬአለሁ።
\v 6 ምንም እንኳን ኃጢአት ባይኖርብኝም ቁስሌ የማይፈወስ ነው' ብሏልና።
\s5
\v 7 ስድብን እንደ ውሃ የሚጠጣ፥
\v 8 ክፋትን ከሚያደርጉት ጋር እንደሚወዳጅ፥ ከአመጸኞችም ጋር እንደሚመላለስ እንደ ኢዮብ ያለ ማነው?
\v 9 እርሱ፥ 'ሰው እግዚአብሔር የሚፈልገውን በማድረግ መደሰቱ ምንም አይጠቅምም' ብሏልና።
\s5
\v 10 ስለዚህ እናንተ አዋቂዎች ስሙኝ፤ አመጻን ማድረግ ከእግዚአብሔር ይራቅ፤ ኃጢአትን ማድረግም ሁሉን ቻይ ከሆነው ይራቅ።
\v 11 ለሰው እንደ ሥራው ይከፍለዋልና፤ እያንዳንዱም በየራሱ መንገድ ወደ ብድራቱ እንዲመጣ ያደርገዋል።
\v 12 በእርግጥ እግዚአብሔር አንዳችም አመጻን አያደርግም፥ ደግሞም ሁሉን ቻዩ ከቶም ፍትሕን አያዛባም።
\s5
\v 13 በምድር ላይ እርሱን ፈራጅ ያደረገው ማነው? ዓለሙንስ በሙሉ ከእርሱ በታች ያደረገው ማነው?
\v 14 እርሱ ፍላጎቱን በራሱ ላይ ብቻ ቢያደርግና መንፈሱንና እስትንፋሱን ወደ ራሱ ቢመልስ ኖሮ
\v 15 ያን ጊዜ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በጠፋ፥ ሰውም እንደገና ወደ ዐፈር በተመለሰ ነበር።
\s5
\v 16 አሁን እንግዲህ ማስተዋል ካለህ ይህንን ስማ፤ የቃሌንም ድምፅ አድምጥ።
\v 17 ፍትሕን የሚጠላ ማስተዳደር ይችላል? ጻድቅና ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ ትኮንነዋለህ?
\s5
\v 18 እግዚአብሔር ንጉሡን፥ 'በደለኛ ነህ' ወይም ባለስልጣኖችን፥ 'አመጸኞች ናችሁ' አይልምን?
\v 19 እግዚአብሔር ለመሪዎች አያዳላም፤ ባለጸጋዎችንም ከድኾች አስበልጦ አይመለከታቸውም፤ ሁሉም የእጁ ሥራዎች ናቸውና።
\v 20 በቅጽበት ይሞታሉ፤ እኩለ ሌሊት ላይ ሰዎች ይንቀጠቀጣሉ፥ ይሞታሉም፤ ኃያላን ሰዎች ይወሰዳሉ፥ በሰው እጅ ግን አይደለም።
\s5
\v 21 የእግዚአብሔር ዐይኖች በሰው አካሄድ ላይ ናቸው፤ እርምጃዎቹንም ሁሉ ያያቸዋል።
\v 22 ክፉ አድራጊዎች የሚደበቁበት ጨለማ ወይም ድቅድቅ ጭጋግ የለም።
\v 23 እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ሰውን መመርመር አይፈልግም፥ የትኛውም ሰው በእርሱ ፊት ቆሞ መሟገት አያስፈልገውም።
\s5
\v 24 ስለ አካሄዳቸው ተጨማሪ ምርመራ እንዳያስፈልጋቸው ኃያላኑን ሰዎች ይሰባብራቸዋል፤ በስፍራቸውም ሌሎችን ይሾማል።
\v 25 እንዲህ ባለ መንገድ ሥራቸውን ያውቃል፤ እነዚህን ሰዎች በጨለማ ይጥላቸዋል፤ እነርሱም ይጠፋሉ።
\s5
\v 26 በሌሎች ፊት፥ በአደባባይ ስለ ክፉ ሥራቸው እንደ ወንጀለኛ ይገድላቸዋል፥
\v 27 እርሱን ከመከተል ተመልሰዋልና፥ ከመንገዶቹም የትኛውንም ለመቀበል ፈቃደኞች አልሆኑምና።
\v 28 እንዲህ ባለ መንገድ የድኾች ጩኸት በፊቱ እንዲወጣ አደረጉ፤ እርሱም የተጨነቁትን ሰዎች ጩኸት ሰማ።
\s5
\v 29 በዝምታ በሚቆይበት ጊዜ ማን ሊወቅሰው ይችላል? ፊቱንስ ቢሰውር ማን ሊገነዘበው ይችላል?
\v 30 አመጸኛው ሰው ገዢ እንዳይሆን፥ በሕዝቡም ላይ ወጥመድን የሚያደርግ እንዳይገኝ እርሱ በሀገሮችና በግለሰቦች ላይ ይገዛል።
\s5
\v 31 አንድ ሰው እግዚአብሔርን እንዲህ እንደሚለው ገምቱ፥ 'በርግጥ በድያለሁ፥
\v 32 ከዚህ በኋላ ግን ከቶ ኃጢአትን አላደርግም፤ ላየው የማልችለውን አስተምረኝ፤ ኃጢአትን ሠርቻለሁ፥ ከእንግዲህ ግን አላደርግም'።
\v 33 እግዚአብሔር የሚያደርገውን የምትጠላ ሰው ብትሆንም፥ እግዚአብሔር የዚያን ሰው ኃጢአት የሚቀጣ ይመስልሃል? እኔ ሳልሆን አንተው መምረጥ አለብህ። ስለዚህ ትክክል ነው ብለህ የምታውቀውን ተናገር።
\s5
\v 34 ዐዋቂዎች ሰዎችም እንዲህ ይሉኛል፥ በእርግጥ የሚሰማኝ ጥበበኛ ሰው ሁሉ የሚለው እንዲህ ነው፥
\v 35 'ኢዮብ የሚናገረው የማያውቀውን ነው፤ ቃሎቹም ጥበብ የለባቸውም'።
\s5
\v 36 እንደ አመጸኞች ሰዎች ተናግሯልና ምነው ኢዮብ ብቻውን ከጉዳዮቹ ስለ ጥቂቶቹ በዝርዝር በተመረመረ።
\v 37 በኃጢአቱ ላይ አመጽን ጨምሯልና፤ በመካከላችን እጆቹን እያጨበጨበ ተሳድቧልና፤ እግዚአብሔርን በመቃወምም ብዙ ቃል ተናግሯል።"
\s5
\c 35
\p
\v 1 ኤሊሁ እንዲህ ሲል ንግግሩን ቀጠለ፥
\v 2 “ንጹሕ ነኝ ብለህ ታስባለህ? 'ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ነኝ' ብለህስ ታስባለህ?
\v 3 ጻድቅ መሆኔ ምን ይጠቅማል? ኃጢአት አድርጌ ቢሆን ኖሮ ከዚህ የሚበልጥ ምን ያገኘኝ ነበር?' ብለሃልና።
\s5
\v 4 ለአንተና ለወዳጆችህ ምላሽ እሰጣለሁ።
\v 5 ወደ ሰማይ ቀና በሉና ተመልከቱት፤ ከእናንተ ከፍ የሚለውን ሰማይ ተመልከቱ።
\s5
\v 6 ኃጢአትን ብታደርግ እግዚአብሔርን ምን ትጎዳዋለህ? መተላለፍህ እጅግ የበዛ ቢሆን ለእርሱ ምኑ ነው?
\v 7 ጻድቅ ብትሆንስ ምን ልትሰጠው ትችላለህ? ከእጅህስ ምን ይቀበላል?
\v 8 አንተም ሰው ነህና ክፋትህ ሌላውን ይጎዳ ይሆናል፤ ጽድቅህም ሌላውን የሰው ልጅ ይጠቅመው ይሆናል።
\s5
\v 9 በብዙ በደል ምክንያት ሰዎች ይጮኻሉ፤ ከኃያላኑ እጅ የሚያድናቸውን ፍለጋ ይጣራሉ።
\v 10 ነገር ግን 'በሌሊት ዝማሬን የሚሰጥ፥
\v 11 የምድር አራዊትን ከሚያስተምርበት በበለጠ የሚያስተምረን፥ ከሰማይ አዕዋፍም ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን ፈጣሪያችን እግዚአብሔር የት አለ?' ማንም አላለም።
\s5
\v 12 በዚያን ጊዜ ይጮኻሉ፥ ነገር ግን በክፉ ሰዎች ትዕቢት ምክንያት እግዚአብሔር ምንም ምላሽ አይሰጣቸውም።
\v 13 ያለጥርጥር እግዚአብሔር የሞኞችን ጩኸት አይሰማም፤ ሁሉን ቻዩም ትኩረት አይሰጠውም።
\v 14 ጉዳይህን በፊቱ አቅርበህ እየተጠባበቅኸው እያለህ እንዳላየኸው ከተናገርክ እንዴት አድርጎ መልስ ይሰጥሃል!
\s5
\v 15 ማንንም ተቆጥቶ አይቀጣም፥ በሰዎች ትዕቢት እምብዛም ግድ አይለውም ካልክ እንዴት አድርጎ መልስ ይሰጥሃል?
\v 16 ስለዚህ ኢዮብ አፉን የሚከፍተው ስንፍናን ለመናገር ብቻ ነው፤ ዕውቀት የሌለበትን ቃል መናገርንም ያበዛል"።
\s5
\c 36
\p
\v 1 ኤሊሁ እንዲህ በማለት ንግግሩን ቀጠለ፥
\v 2 "ትንሽ ጨምሬ እንድናገር ፍቀድልኝ፥ እግዚአብሔርን በመወገን ትንሽ አክዬ የምናገረው አለኝና ጥቂት ነገሮችን አሳይሃለሁ።
\v 3 ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤ ጽድቅ የፈጣሪዬ ነው እላለሁ።
\s5
\v 4 በርግጥ ቃሎቼ ሐሰት አይደሉም፤ አንድ በዕውቀት የበሰለም ከአንተ ጋር ነው።
\v 5 ተመልከት፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፤ እርሱ በማስተዋል ብርታቱም ኃያል ነው።
\s5
\v 6 እርሱ የአመጸኞች ሰዎችን ሕይወት አይጠብቅም ነገር ግን ከዚያ ይልቅ መከራ ለሚቀበሉት ትክክል የሆነውን ነገር ያደርግላቸዋል።
\v 7 ፊቱን ከጻድቃን አይመልስም ነገር ግን ከዚያ ይልቅ እንደ ነገሥታት በዙፋኖች ላይ ያስቀምጣቸዋል፥ እነርሱም ይከብራሉ።
\s5
\v 8 ይሁንና፥ በሰንሰለት ቢገቡ፥ በመከራም ገመድ ቢታሰሩ
\v 9 ያን ጊዜ ያደረጉትን መተላለፋቸውንና በግፍ እንደተመላለሱ ይገልጥላቸዋል።
\s5
\v 10 ደግሞም እርሱ ጆሮዎቻቸውን ለትምህርቱ ይከፍታቸዋል፥ ከክፋታቸው እንዲመለሱም ያዛቸዋል።
\v 11 ቢሰሙትና ቢያመልኩት ቀኖቻቸውን በብልጽግና ዓመቶቻቸውንም በእርካታ ያሳልፋሉ።
\v 12 ይሁን እንጂ፥ ባይሰሙት በሰይፍ ይጠፋሉ፤ ዕውቀት ስለሌላቸው ይሞታሉ።
\s5
\v 13 ልባቸው ከእግዚአብሔር የራቀ እነዚያ ቁጣቸውን ያከማቻሉ፤ እግዚአብሔር በሚያስራቸው ጊዜ እንኳን ለዕርዳታ አይጮኹም።
\v 14 በወጣትነታቸው ይሞታሉ፤ ሕይወታቸውም በቤተ ጣዖት ዝሙት አዳሪዎች መካከል ይጠፋል።
\s5
\v 15 የሚሰቃዩትን ሰዎች በስቃያቸው አማካይነት ያድናቸዋል፤ በመከራቸው አማካይነትም ጆሮዎቻቸውን ይከፍታል።
\v 16 በእርግጥ እርሱ ከጭንቀት አውጥቶ የሰባ ምግብ የሞላበት ጠረጴዛ በፊትህ ወደሚቀመጥበትና ስቃይ ወደሌለበት ሰፊ ስፍራ ሊያወጣህ ይፈልጋል።
\s5
\v 17 ነገር ግን አንተ በክፉ ሰዎች ፍርድ ተሞልተሃል፤ ፍርድና ፍትሕም ይዘውሃል።
\v 18 ብልጽግና ወደ መታለል እንዲስብህ እትፍቀድለት፤ መጠኑ የበዛ ጉቦም ፍትሕን እንድታዛባ እንዲያደርግህ አትፍቀድለት።
\s5
\v 19 ብልጽግናህ ከሐዘን ሊያርቅህ ይችላል? ወይም የኃይልህ ብርታት ሁሉ ሊረዳህ ይችላል?
\v 20 ሰዎች በየስፍራቸው በሚወገዱበት ጊዜ በሌሎች ላይ ኃጢአትን ለመሥራት ጨለማን አትመኝ።
\v 21 ኃጢአትን ከማድረግ ትርቅ ዘንድ በመከራ ተፈትነሃልና ወደ ኃጢአት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።
\s5
\v 22 ተመልከት፥ እግዚአብሔር በኃይሉ ከፍ ያለ ነው፤ እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማነው?
\v 23 ስለ መንገዱ ከቶ ማን አስተምሮታል? 'በደለኛ ነህ' ሊለውስ ከቶ ማን ይችላል?
\v 24 ሰዎች የዘመሩለትን ሥራዎቹን ለማወደስ አስታውስ።
\s5
\v 25 እነዚያን ሥራዎች ሰዎች ሁሉ አይተዋል፥ ነገር ግን እነዚያን ሥራዎች የሚያዩት ከርቀት ብቻ ነው።
\v 26 ተመልከት፥ እግዚአብሔር ትልቅ ነው፤ እኛም በሚገባ አናውቀውም፤ ዘመኖቹም አይቆጠሩም።
\s5
\v 27 እርሱ እንፋሎቱ ዝናብ ሆኖ ይወርድ ዘንድ የውሃ ነጠብጣቦችን ወደ ላይ ስቦ ያከማቻል፥
\v 28 ደመናዎች ወደ ታች ያፈስሱታል፥ በሰዎች ላይም በብዙ ያንጠባጥቡታል።
\v 29 በርግጥ የደመናዎቹን መዘርጋትና ከድንኳኑ የሚወጣውን መብረቅ ሊያስተውል የሚችል አለ?
\s5
\v 30 ተመልከት፥ መብረቁን በዙሪያው ይበትናል፤ ባህሩን በጨለማ ይከድነዋል።
\v 31 በዚህ መንገድ ሰዎችን ይመግባቸዋል፥ ብዙ ምግብንም ይሰጣቸዋል።
\s5
\v 32 ዒላማቸውን እንዲመቱ እስኪያዛቸው ድረስ እጆቹን በመብረቅ ነጓድጓድ ይሸፍናቸዋል።
\v 33 ዐውሎ ነፋስ እንደሚመጣ ድምፁ ለሰዎች ይነግራቸዋል፤ መቃረቡንም እንስሶች ደግሞ ያውቃሉ።
\s5
\c 37
\p
\v 1 በርግጥ በዚህ ጉዳይ ልቤ ተናውጧል፤ ስፍራውንም ለቋል።
\v 2 ኦ እስቲ አድምጡ፤ የድምፁን ሁካታ፥ ከአፉም የሚወጣውን ድምፅ አድምጡ።
\v 3 እርሱ ድምፁን ከሰማይ በታች ወዳለ ስፍራ ሁሉ ይልካል፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም መብረቁን ይልካል።
\s5
\v 4 ከእርሱ በኋላ ድምፅ ይጮኻል፤ በግርማዊ ድምፁም ያንጎደጉዳል፤ ድምፁ በሚሰማበት ጊዜ የመብረቁን ብልጭታ አይከለክልም።
\v 5 እግዚአብሔር በድምፁ በሚያስደንቅ ሁኔታ ያንጎደጉዳል፤ ልናስተውላቸው የማንችላቸውን ታላላቅ ነገሮችንም ያደርጋል።
\v 6 በረዶውን፥ 'በምድር ላይ ውደቅ'፤ እንዲሁም ዝናቡን፥ 'ብርቱ ዝናብ ሆነህ ውረድ' ይለዋል።
\s5
\v 7 ሰዎች ሁሉ ያደረገውን ሥራውን እንዲያዩ የእያንዳንዱን ሰው እጅ ከመሥራት ይከለክላል።
\v 8 ከዚያም አራዊት ወደ መደበቂያቸው ይሄዳሉ፥ በዋሻዎቻቸውም ውስጥ ይቆያሉ።
\v 9 ዐውሎ ነፋስ ከደቡብ መኖሪያው ይመጣል፤ ቅዝቃዜም በሰሜን ከተበተነው ነፋስ።
\s5
\v 10 በእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ይገኛል፤ የውኆቹም ስፋት እንደ ብረት ይቀዘቅዛል።
\v 11 በርግጥ ጥቅጥቁን ደመና በሙቀት ይበትነዋል፤ መብረቆቹን በደመናዎች መካከል ይበትናቸዋል።
\s5
\v 12 በመላው ዓለም ላይ ፈቃዱን ያደርጉ ዘንድ በአመራሩ ደመናትን ያሽከረክራቸዋል።
\v 13 እነዚህ ሁሉ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፤ ይህንን የሚያደርገው አንዳንድ ጊዜ ለማቅናት፥ አንዳንዴም ምድሩን ለማጠጣት፥ አንዳንዴም የቃል ኪዳን ታማኝነቱን ለማሳየት ነው።
\s5
\v 14 ኢዮብ ሆይ፥ ይህንን ስማ፤ ቆም በልና የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች አስብ።
\v 15 እግዚአብሔር እንዴት ፈቃዱን በደመናት ላይ እንደሚፈጽም፥ የመብረቁንም ብልጭታ በእነርሱ ውስጥ እንዲበራ እንደሚያደርግ ታውቃለህ?
\s5
\v 16 በዕውቀቱ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራዎች፥ የደመናትንም መንሳፈፍ ታስተውላለህ?
\v 17 ከደቡብ በሚመጣው ነፋስ ምክንያት ምድር ጸጥ በምትልበት ጊዜ ልብስህ እንዴት እንደሚሞቅ ታስተውላለህ?
\s5
\v 18 ከብረት የተሠራ ጠንካራ መስታወት የሚመስለውን ሰማይ እንደ እርሱ መዘርጋት ትችላለህ?
\v 19 አዕምሮአችን ከመጨለሙ የተነሣ ክርክራችንን በሥርዓት ማቅረብ አልቻልንምና ምን እንደምንመልስለት አስተምረን።
\v 20 ላነጋግረው እንደምፈልግ ይነገረው ዘንድ ይገባል? አንድ ሰው እንዲዋጥ ይፈልጋል?
\s5
\v 21 እነሆ፥ ነፋስ በውስጡ ካለፈና ደመናውን ካጠራው በኋላ በሰማይ ላይ የሚያበራውን ፀሐይ ሰዎች ለማየት አይችሉም።
\v 22 እንደ ወርቅ የሚያብረቀርቅ ብርሃን ከሰሜን ይመጣል- በእግዚአብሔር ዘንድ አስፈሪ ግርማ አለ።
\s5
\v 23 ሁሉን ቻዩን በሚመለከት እኛ ልናገኘው አንችልም፤ እርሱ በጽድቁና በኃይሉ ታላቅ ነው። ሰዎችን አያስጨንቅም።
\v 24 ስለዚህ፥ ሰዎች ይፈሩታል። ጥበበኞች ነን ብለው የሚያስቡትን አይመለከታቸውም"።
\s5
\c 38
\p
\v 1 ያን ጊዜ እግዚአብሔር ከብርቱ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ ኢዮብን ጠራውና እንዲህ አለው፥
\v 2 "ዕውቀት በጎደለው ቃል ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማነው?
\v 3 ጥያቄዎችን እጠይቅሃለሁና አሁን እንደ ሰው ወገብህን ታጠቅ፥ አንተም ልትመልስልኝ ይገባሃል።
\s5
\v 4 የምድርን መሠረቶች ባቆምኩ ጊዜ አንተ የት ነበርክ? ከፍ ያለ ማስተዋል ካለህ ነገረኝ።
\v 5 መጠኑን የወሰነው ማነው? የምታውቅ ከሆነ ንገረኝ። በላዩ ላይስ የመለኪያ ገመድ የዘረጋ ማነው?
\s5
\v 6 መሠረቶቹስ የቆሙት በምን ላይ ነው?
\v 7 የንጋት ከዋክብት በአንድነት በዘመሩና የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ በደስታ በዘመሩ ጊዜ የማዕዘኑን ድንጋይ ያስቀመጠ ማን ነበር?
\s5
\v 8 ደመናትን ልብሱ፥ ድቅድቁንም ጨለማ መጠቅለያው ባደረግሁ ጊዜ
\v 9 ከማኅፀን የሚወጣ ይመስል ፈንድቶ በወጣ ጊዜ የባህሩን መዝጊያ የዘጋ ማነው?
\s5
\v 10 ያን ጊዜ ነበር ለባህሩ ገደብን ያደረግሁለት፥ በሮችንና መወርወሪያዎችን ባደረግሁለት ጊዜ፥
\v 11 እንዲህም ባልኩት ጊዜ፥ 'እስከዚህ ድረስ መምጣት ትችል ይሆናል፥ ከዚህ ግን አትለፍ፤ ለሞገድህ ትዕቢት ገደብ የማደርግለት እዚህጋ ነው'።
\s5
\v 12 ከተወለድክበት ጊዜ ጀምሮ ንጋት እንዲጀምር ከቶ ትዕዛዝ ሰጥተኸዋል? ወጋገኑስ በነገሮች መካከል ስፍራውን እንዲያውቅ አድርገኸዋል?
\v 13 የምድርን ማዕዘናት በመያዝ ክፉዎች ሰዎች ከእርሱ ላይ እንዲራገፉ አድርገሃል?
\s5
\v 14 ጭቃው ከማኅተም በታች እንደሚለወጥ የምድርም መልክ ተለውጧል፤ በእርሱ ላይ ያለው ነገር ሁሉ በግልጽ እንደ ቁራጭ ጨርቅ ተጠቅልሎ ቆሟል።
\v 15 ከክፉ ሰዎች 'ብርሃናቸው' ተወስዷል፤ ወደ ላይ የተነሣው ክንዳቸውም ተሰብሯል።
\s5
\v 16 ወደ ባህሩ መገኛ ሄደህ ታውቃለህ? ዝቅ ወዳለው ጥልቅ ስፍራስ ወርደህ ታውቃለህ?
\v 17 የሞት በሮች ተገልጠውልሃል? የሞት ጥላ በሮችንስ አይተኻቸዋል?
\v 18 ምድርን በስፋቱ ታውቀዋለህ? ይህንን ሁሉ የምታውቅ ከሆነ ንገረኝ።
\s5
\v 19 ብርሃን የሚያርፍበት ስፍራ መንገዱ የት ነው? የጨለማውስ ስፍራው የት ነው?
\v 20 ብርሃንና ጨለማን ወደ ሥራቸው ስፍራ ልትመራቸው ትችላለህ? ወደ መኖሪያቸው የሚመለሱበትን መንገድስ ልትፈልግላቸው ትችላለህ?
\v 21 ያን ጊዜ ተወልደህ ስለነበርና የዕድሜህም ቁጥር ታላቅ ስለሆነ ያለጥርጥር ታውቃለህ!
\s5
\v 22 ወደ በረዶው መጋዘን ገብተሃል? ወይም የአመዳዩን ማከማቻ አይተሃል?
\v 23 እነዚህን ነገሮች ለመከራ ጊዜ፥ ለጦርነትና ለውጊያ ቀናት ያስቀመጥኳቸው ናቸው።
\v 24 የመብረቅ ብልጭታ የሚሰራጭበት መንገድ የትኛው ነው? ወይም ነፋሳት ከምስራቅ በምድር ላይ የሚበተኑበት መንገድ የቱ ነው?
\s5
\v 25 ለዶፍ ዝናብ መውረጃን ያበጀለት ወይም ለመብረቅ ብልጭታ መንገድ ያዘጋጀለት ማነው?
\v 26 ሰው በሌለበት ምድር፥ ማንም በሌለበት ምድረ በዳ ላይ እንዲዘንብ ያደረገ ማነው?
\v 27 ሰው የሌለበትንና የባድማውን አካባቢ ፍላጎት የሚያረካ፥ ሣር እንዲበቅልበትስ የሚያደርግ ማነው?
\s5
\v 28 ዝናብ አባት አለው? የጤዛን ጠብታ የወለደው ማነው?
\v 29 በረዶስ የመጣው ከማን ማኅፀን ነው? የሰማዩን አመዳይ ማን ወለደው?
\v 30 ውኆች ራሳቸውን ይደብቁና እንደ ድንጋይ ይጠነክራሉ፤ የጥልቁም ገጽታ ግግር ይሆናል።
\s5
\v 31 ፕልያዲስ የተባለውን ኮከብ በሠንሰለት ልታስረው ወይም የኦሪዮንን እስራት ልትፈታ ትችላለህ?
\v 32 የከዋክብት ክምችት በተገቢው ጊዜአቸው እንዲታዩ ልትመራቸው ትችላለህ? ድብ የተባለውን ከነልጆቹ ልትመራቸው ትችላለህ?
\v 33 የሰማይን ሥርዓት ታውቃለህ? የሰማይን ሥርዓት በምድር ላይ መተግበር ትችላለህ?
\s5
\v 34 ብዙ የዝናብ ውሃ እንዲያጥለቀልቅህ ድምፅህን ወደ ደመናት ማሰማት ትችላለህ?
\v 35 'ይኸው እዚህ አለን' ብለው ይላኩህ ዘንድ የመብረቅ ብልጭታዎችን ልትልካቸው ትችላለህ?
\s5
\v 36 በደመናት ውስጥ ጥበብን ያኖረ ወይም ለእርጥበት ዕውቀትን የሰጠ ማነው?
\v 37 በጥበቡ ደመናትን ለመቁጠር የሚችል ማነው?
\v 38 ብናኙ ዐፈር ተበጥብጦ ጠንካራ ጓል በሚሆንበትና ጭቃው አፈር በአንድ ላይ በሚጣበቅበት ጊዜ የሰማይን የውሃ መያዣ አዘንብሎ ማፍሰስ የሚችል ማነው?
\s5
\v 39 በዋሻዎቻቸው በሚያደቡበትና በመኖሪያቸው ተጋድመው በሚጠባበቁበት ጊዜ
\v 40 ለአንበሳዪቱ አደን ልታድንላት ወይም ግልገሎቿን ልታጠግብላት ትችላለህ?
\s5
\v 41 ጫጩቶቻቸው ወደ እግዚአብሔር በሚጮኹበትና ምግብ በማጣት በሚንከራተቱበት ጊዜ ለቁራዎች ምግብ የሚሰጣቸው ማነው?
\s5
\c 39
\p
\v 1 የበረሃ ፍየሎች በዐለቶች መካከል የሚወልዱበትን ጊዜ ታውቃለህ? አጋዘኖችስ ግልገሎቻቸውን በሚወልዱበት ጊዜ ልታያቸው ትችላለህ?
\v 2 የእርግዝናቸውንስ ወራት ለመቁጠር ትችላለህ? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህ?
\s5
\v 3 ይንበረከኩና ግልገሎቻቸውን ይወልዳሉ፤ የምጣቸውንም ሕመም ያበቃሉ።
\v 4 ግልገሎቻቸው ይጠነክራሉ፥ በገላጣው መስክ ላይም ያድጋሉ፤ ርቀው ይሄዳሉ፥ ወደ ወለዷቸውም አይመለሱም።
\s5
\v 5 የሜዳ አህያው በነጻነት እንዲሄድ የፈቀደለት ማነው?
\v 6 አራባህን ቤቱ፥ የጨውንም ምድር መኖሪያው ያደረግሁለትን የፈጣኑንስ አህያ እስራት የፈታ ማነው?
\s5
\v 7 በከተማ ባለው ሁካታ በንቀት ይስቃል፤ የነጂውንም ጩኸት አይሰማም።
\v 8 በመሰማሪያዎቹ በተራሮች ላይ ይንከራተታል፤ በዚያም የሚመገበውን የለመለመ ሣር ሁሉ ይፈልጋል።
\s5
\v 9 ጎሽ ሊያገለግልህ ይፈቅዳል? በበረትህስ አጠገብ ለማደር ይስማማል?
\v 10 ጎሽ ትልሞችህን እንዲያርስልህ በገመድ ልትቆጣጠረው ትችላለህ? ጓሉንስ ይከሰክስልሃል?
\s5
\v 11 ጉልበቱ ብርቱ ስለሆነ ትታመነዋለህ? እርሱ እንዲያከናውንልህ ተግባርህን ትተውለታለህ?
\v 12 ምርትህን ዐውድማ ላይ እንዲያከማችልህ፥ እህልህንም ወደ ቤት እንዲያገባልህ ትተማመነዋለህ?
\s5
\v 13 የሰጎን ክንፎች በደስታ ይራገባሉ፤ ነገር ግን እነርሱ የፍቅር ክንፎችና ላባዎች ናቸው?
\v 14 እንቁላሎቿን በአፈር ውስጥ ትጥላለች፥ እንዲሞቃቸውም በትቢያ ውስጥ ትተዋቸዋለች።
\v 15 እግር እንዲረግጣቸው ወይም የዱር አውሬ እንዲጨፈልቃቸው ትረሳቸዋለች።
\s5
\v 16 የእርስዋ ያልሆኑ ይመስል በጫጩቶቿ ትጨክናለች፤ ድካሟ ሁሉ ከንቱ እንደሚሆን በማሰብ አትፈራም፤
\v 17 እግዚአብሔር ጥበብን ነፍጓታልና አንዳች ማስተዋልንም አልሰጣትም።
\v 18 በፍጥነት በምትሮጥበት ጊዜ በፈረሱና በጋላቢው ላይ በንቀት ትሥቃለች።
\s5
\v 19 ለፈረስ ኃይሉን ሰጥተኸዋል? አንገቱንስ በጋማው አልብሰኸዋል?
\v 20 እንደ አንበጣ እንዲዘል አድርገኸዋል? የማንኮራፋቱ ገናናነት አስፈሪ ነው።
\s5
\v 21 በኃይል ይጎደፍራል፥ በብርታቱም ደስ ይለዋል፤ የጦር መሳሪያዎችን ለመገናኘት ይፈጥናል።
\v 22 በፍርሃት ላይ ይሳለቃል፥ አይደነግጥምም፤ ከሰይፍም ወደ ኋላ አይመለስም።
\v 23 ከሚብለጨለጨው ፍላጻና ጦር ጋር የፍላጻዎች መያዣ ጎኑ ላይ ይንኳኳል።
\s5
\v 24 በቁጣና በጭካኔ መሬትን ይውጣል፤ የመለከት ድምፅ ሲሰማ ይቁነጠነጣል።
\v 25 የመለከት ድምፅ በሚሰማበት ጊዜ ሁሉ 'አሃ!' ይላል፤ ጦርነትን፥ የአዛዦችን የሚንጎደጎድ ጩኸትና ሁካታ ከሩቅ ያሸታል።
\s5
\v 26 ጭልፊት ርቆ የሚመጥቀው፥ ክንፎቹንም ወደ ደቡብ የሚዘረጋው ባንተ ጥበብ ነው?
\s5
\v 27 ንስር ወደ ላይ የሚበረውና ጎጆውን ከፍ ባሉ ስፍራዎች የሚሠራው ባንተ ትዕዛዝ ነው?
\v 28 በገደል ላይ ይኖራል፥ መኖሪያ ምሽጉንም በገደሉ ጫፍ ላይ ያደርጋል።
\s5
\v 29 እዚያ ላይ ሆኖ የሚነጥቀውን ይቃኛል፤ ዐይኖቹም ከርቀት ይመለከቱለታል።
\v 30 ጫጩቶቹ ደግሞ ደም ይጠጣሉ፤ በድን ባለበት እርሱም በዚያ አለ"።
\s5
\c 40
\p
\v 1 እግዚአብሔር ኢዮብን እንዲህ ሲል መናገሩን ቀጠለ፥
\v 2 "ማንም መተቸት የሚፈልግ ሁሉን ቻዩን አምላክ ማረም አለበት? ከእግዚአብሔር ጋር የሚከራከር እርሱ ምላሹን ይስጥ"።
\s5
\v 3 ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፥
\v 4 "ተመልከት፥ እኔ ከምንም የማልቆጠር ነኝ፤ እንዴትስ መልስ ልሰጥህ እችላለሁ? እጄን በአፌ ላይ እጭናለሁ።
\v 5 አንድ ጊዜ ተናገርኩ፥ መልስ መስጠትም አልችልም፤ በእርግጥ ሁለተኛ ተናግሬ ይሆናል፥ ከዚህ በኋላ ግን አልቀጥልም"።
\s5
\v 6 ከዚያም እግዚአብሔር ከኃይለኛ ዐውሎ ነፋስ ውስጥ ሆኖ ኢዮብን እንዲህ ሲል ተናገረው፥
\v 7 "እንግዲህ እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ፥ እጠይቅሃለሁና አንተም ልትመልስልኝ ይገባል።
\s5
\v 8 ፍትሐዊ ስላለመሆኔ ትናገራለህ? ራስህን ትክክለኛ አድርገህ ለመቁጠር እኔን ትኮንናለህ?
\v 9 የእግዚአብሔርን የሚያክል ክንድ አለህ? እንደ እርሱስ ድምፅህን ልታንጎደጉድ ትችላለህ?
\s5
\v 10 አሁንም ክብርንና ልዕልናን ልበስ፤ ክብርንና ግርማንም ታጠቅ።
\v 11 የቁጣህን ብዛት በዙሪያህ አፍስስ፤ ትዕቢተኛ የሆነውን ሁሉ ተመልከተውና አዋርደው።
\s5
\v 12 ትዕቢተኛ የሆነውን ሁሉ ተመልከተውና ዝቅ አድርገው፤ ክፉዎችንም ሰዎች በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው።
\v 13 አንድ ላይ ዐፈር ውስጥ ቅበራቸው፤ በተሰወረ ስፍራም ፊታቸውን ደብቀው።
\v 14 ያን ጊዜ እኔ ደግሞ የገዛ ክንድህ ሊያድንህ እንደቻለ ዐውቃለሁ።
\s5
\v 15 አሁንም አንተን እንደፈጠርኩህ የፈጠርኩትን ጉማሬ ተመልከት፤ እርሱ እንደ በሬ ሣር ይበላል።
\v 16 ተመልከት፥ ኃይሉ በወገቡ፥ ብርታቱም በሆዱ ጡንቻ ውስጥ ነው።
\s5
\v 17 ጭራውን እንደ ጥድ ያወዛውዛል፤ የወርቹ ጅማቶችም እርስ በእርሳቸው የተገጣጠሙ ናቸው።
\v 18 አጥንቶቹ እንደ ነሐስ ቱቦ ናቸው፤ እግሮቹም እንደ ብረት ዘንግ ናቸው።
\s5
\v 19 እርሱ እግዚአብሔር ከፈጠራቸው ፍጥረታት ዋነኛው ነው። እርሱን የፈጠረው እግዚአብሔር ብቻ ሊያሸንፈው ይችላል።
\v 20 ኮረብታዎች ምግቡን ያዘጋጁለታልና፤ በመስክ ላይ ያሉት አራዊትም በአቅራቢያው ይጫወታሉ።
\v 21 በረግረጉ ስፍራ ከደንገል ተክሎች ስር ይተኛል።
\s5
\v 22 በውሃ ዳር የሚበቅሉ ዛፎች በጥላዎቻቸው ይሸፍኑታል፤ የአኻያውም ዛፍ ሁሉ በዙሪያው ነው።
\v 23 ተመልከት፥ ወንዙ ቢጎርፍም እርሱ አይፈራም፤ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከ አፉ ቢሞላም እርሱ ተማምኖ ይኖራል።
\v 24 በወጥመድ ሊይዘው ወይስ አፍንጫውን በወጥመድ ሊበሳው የሚችል አለ?
\s5
\c 41
\p
\v 1 ሌዋታንን በዓሳ መንጠቆ ልትይዘው ትችላለህ? ወይስ መንጋጋዎቹን በገመድ ታስራለህ?
\v 2 በአፍንጫው ገመድ ልታስገባ ወይም አገጩን በችካል ልትበሳው ትችላለህ?
\v 3 አብዝቶስ ይለምንሃል? በለሰለሱ ቃላትስ ያናግርሃል?
\s5
\v 4 የሁልጊዜ አገልጋይህ ለመሆን እንድትወስደው ከአንተ ጋር ስምምነት ያደርጋል?
\v 5 ከወፍ ጋር እንደምትጫወት ከእርሱ ጋር ትጫወታለህ? ሴት አገልጋዮችህ እንዲጫወቱበት ታስርላቸዋለህ?
\v 6 ዓሳ አጥማጆችስ በእርሱ ላይ ይደራደራሉ? ለነጋዴዎችስ ያከፋፍሉታል?
\s5
\v 7 ቆዳውን በአንካሴ ወይም ራሱን በዓሳ መውጊያ ጦር ልትበሳው ትችላለህ? አንድ ጊዜ ብቻ
\v 8 እጅህን በላዩ ላይ አድርግ፥ ያን ጊዜ ግብግቡን አትረሳውም፥ እንዲህ ያለውን ተግባርም አትደግመውም።
\v 9 ተመልከት፥ ማንም ይህንን ለማድረግ ተስፋ ቢያደርግ ሐሰተኛ ነው፤ እርሱን በማየቱ ብቻ በድንጋጤ የማይወድቅ ማነው?
\s5
\v 10 ሌዋታንን ለመቀስቀስ የሚደፍር የለም፤ ማንስ በፊቱ ሊቆም ይችላል?
\v 11 እንድመልስለት ማንኛውንም ነገር አስቀድሞ ለእኔ የሰጠኝ ማነው? ከሰማይ በታች ያለው ሁሉ የእኔ ነው።
\v 12 ስለ ሌዋታን እግሮች፥ ስለ ብርታቱና ስለተዋበው ቅርጹ ከመናገር ዝም አልልም።
\s5
\v 13 ቆዳውን ማን ሊገፈው ይችላል? ድርብ መከላከያውንስ ማን ሊበሳው ይችላል?
\v 14 አስፈሪ ጥርሶቹ የተገጠገጡበትን የፊቱን ደጆች ማን ሊከፍት ይችላል?
\v 15 ጀርባው ተቀራርበው ከተጣበቁ ንብርብር ጋሻዎች የተሠራ ነው።
\s5
\v 16 አንደኛው ከሌላኛው ጋር እጅግ ከመቀራረቡ የተነሣ በመካከላቸው ነፋስ አያስገባም።
\v 17 እርስ በእርስ ተገናኝተዋል፥ ሊነቅሏቸው እስከማይቻልም ድረስ በአንድነት ተጣብቀዋል።
\v 18 ከእንጥሽታው የብርሃን ብልጭታ ይወጣል፤ ዓይኖቹ እንደ ንጋት ጮራ ያበራሉ።
\s5
\v 19 የሚነድ ፍም፥ የእሳትም ትንታግ ከአፉ ይወጣል።
\v 20 በእሳት ላይ ተጥዶ በኃይል እንደሚንተከተክ ድስት ከአፍንጫው ጢስ ይወጣል።
\v 21 እስትንፋሱ ከሰሉን እንዲቀጣጠል ያደርገዋል፤ ከአፉም እሳት ይወጣል።
\s5
\v 22 ብርታት በአንገቱ ውስጥ አለ፥ ሽብርም በፊት ለፊቱ ይጨፍራል።
\v 23 የሥጋው እጥፋቶች እርስ በእርሳቸው የተገጠገጡ ናቸው፤ በእርሱ ላይ ጸንተዋል፤ ሊያነቃንቋቸውም አይቻልም።
\v 24 ልቡ እንደ ድንጋይ የጠነከረ ነው፤ በእርግጥም እንደ ወፍጮ መጅ ጠንካራ ነው።
\s5
\v 25 ቀና በሚልበት ጊዜ አማልክት እንኳ ይፈራሉ፤ ከፍርሃታቸውም የተነሣ ወደኋላቸው ይመለሳሉ።
\v 26 ሰይፍ ቢቆርጠው አንዳች አይሰማውም፤ ጦር፥ ቀስት፥ ወይም የትኛውም የጦር መሣሪያ ቢነጣጠርበት አይሰጋም።
\v 27 ብረትን እንደ አገዳ፥ ናስንም እንደ ነቀዘ እንጨት ይቆጥረዋል።
\s5
\v 28 ቀስት እንዲሸሽ አያደርገውም፥ የወንጭፍ ድንጋይም ለእርሱ እንደ ገለባ ነው።
\v 29 ዱላ እንደ አገዳ ተቆጥሯል፤ በሚወረወርበት ጦር ላይም ይስቃል።
\v 30 የሆዱ ስር እንደ ገል ስብርባሪ የሾለ ነው፤ የእህል መውቂያ መሣሪያ ይመስል በጭቃው ላይ ምልክት ትቶ ያልፋል።
\s5
\v 31 በድስጥ ውስጥ ያለ ውሃ እንደሚፈላ የጥልቁን ውሃ ያናውጠዋል፤ ባህሩንም እንደ ሽቶ ቢልቃጥ ያደርገዋል።
\v 32 የሄደበት መንገድ ከበስተኋላው እንዲያበራ ያደርጋል፤ ይህንን ያየም ጥልቁን ነጭ ነው ብሎ ያስባል።
\s5
\v 33 ያለ ፍርሃት እንዲኖር የተፈጠረ በምድር ላይ እርሱን የሚያክል የለም።
\v 34 ኩሩ የሆነውን ሁሉ ያያል፤ እርሱ በትዕቢት ልጆች ሁሉ ላይ ንጉሥ ነው።"
\s5
\c 42
\p
\v 1 ኢዮብም ለእግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፥
\v 2 "ሁሉን ለማድረግ እንደምትችል፥ ዓላማህ ሊደናቀፍ እንደማይችል አውቃለሁ።
\v 3 'ያለዕውቀት ዕቅዴን የሚያጨልም ይህ ማነው?' ብለህ ጠይቀኸኛል። ስለዚህ የማላውቀውን፥ ያልተረዳሁትን፥ ለማወቅም እጅግ አስቸጋሪ የሆነውን ነገር ተናግሬአለሁ።
\s5
\v 4 አንተም፥ 'አሁንም፥ አድምጥ፥ እኔ እናገራለሁ፤ አንዳንድ ነገሮችን እጠይቅሃለሁ፥ አንተም ትነግረኛለህ' አልከኝ።
\v 5 ስለአንተ መስማትን በጆሮዬ ሰምቼ ነበር፥ አሁን ግን ዓይኖቼ አዩህ።
\v 6 ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤ በአመድና በትቢያ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ"።
\s5
\v 7 እግዚአብሔር ኢዮብን ይህን ቃል ከተናገረው በኋላ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፥ "አንተና ሁለቱ ጓደኞችህ አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ ትክክለኛውን ነገር አለተናገራችሁምና ቁጣዬ በእናንተ ላይ ነዶባችኋል።
\v 8 አሁን እንግዲህ ሰባት ወይፈኖችንና ሰባት አውራ በጎችን ለራሳችሁ ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ኢዮብ ሂዱ፤ ለራሳችሁም የሚቃጠል ምስዋዕት አድርጋችሁ አቅርቡ። እኔም እንደ ስንፍናችሁ እንዳላደርግባችሁ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን እቀበላለሁ። አገልጋዬ ኢዮብ እንዳደረገው ስለ እኔ ትክክለኛውን ነገር አልተናገራችሁምና።"
\v 9 ስለዚህ ቴማናዊው ኤልፋዝ፥ ሹሐዊው በልዳዶስና ናዕማታዊው ሶፋር እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው ሄደው አደረጉ፤ እግዚአብሔርም ኢዮብን ተቀበለው።
\s5
\v 10 ኢዮብ ስለ ጓደኞቹ በጸለየ ጊዜ እግዚአብሔር እንደገና አበለጸገው። ቀድሞ ከነበረው በላይ እግዚአብሔር ዕጥፍ አድርጎ ሰጠው።
\v 11 ከዚያም የኢዮብ ወንድሞቹና እህቶቹ ሁሉ፥ ቀድሞ ያውቁት የነበሩትም ሁሉ እርሱ ወደነበረበት መጡ፤ ከእርሱም ጋር ምግብ በሉ። እነርሱም ሐዘኑን ተጋሩት፤ እግዚአብሔር አምጥቶበት ስለነበረው መከራ ሁሉ አጽናኑት። እያንዳንዳቸውም ለኢዮብ ጥሬ ብርና የወርቅ ቀለበት ሰጡት።
\s5
\v 12 እግዚአብሔር ከመጀመሪያው ይልቅ የኢዮብን የኋለኛውን ዘመን ባረከለት፤ እርሱም ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፥ ስድስት ሺህ ግመሎች፥ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፥ አንድ ሺህም ሴት አህዮች ነበሩት።
\v 13 ደግሞም ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆች ነበሩት።
\v 14 የመጀመሪያ ሴት ልጁን ይሚማ፥ ሁለተኛዋን ቃሥያ፥ ሦስተኛዋን አማልቶያስ ቂራስ ብሎ ሰየማቸው።
\s5
\v 15 በሀገሩ ሁሉ እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች የተዋቡ ሴቶች አልተገኙም። አባታቸውም ከወንድሞቻቸው እኩል ርስትን ሰጣቸው።
\v 16 ከዚህ በኋላ ኢዮብ 140 አመት ኖረ፤ እርሱም ወንዶች ልጆችን፥ የወንዶች ልጆቹን ወንዶች ልጆች እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።
\v 17 ከዚያም ኢዮብ አርጅቶ፥ ዕድሜንም ጠግቦ ሞተ።

483
21-ECC.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,483 @@
\id ECC
\ide UTF-8
\h መክብብ
\toc1 መክብብ
\toc2 መክብብ
\toc3 ecc
\mt መክብብ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ይህ በኢየሩሳሌም የነገሠውና የዳዊት ልጅ የሆነው የአስተማሪው ቃል ነው።
\v 2 አስተማሪው እንዲህ ይላል፥ "እንደ እንፋሎት ትነት፥ በደመናም ውስጥ እንዳለ እስትንፋስ፥ ሁሉም ነገር ይጠፋል፥ በርካታ ጥያቄዎችን ትቶ።
\v 3 ከፀሐይ በታች በሚደክሙበት ሥራ ሁሉ የሰው ልጆች ምን ትርፍ ያገኙበት ይሆን?
\s5
\v 4 አንደኛው ትውልድ ይሄዳል፥ ሌላኛው ትውልድ ይመጣል፥ ምድር ግን ለዘላለም ትኖራለች።
\v 5 ፀሐይ ትወጣለች፥ ትጠልቃለችም፥ ዳግም ወደምትወጣበት ሥፍራ ለመመለስም ትቸኩላለች።
\v 6 ነፋስ ወደ ደቡብ ይነፍሳል፥ ወደ ሰሜንም ያከብባል፥ ሁሌም በመንገዱ ይሄዳል፥ እንደገናም ይመለሳል።
\s5
\v 7 ወንዞች ሁሉ ወደ ባህር ይፈስሳሉ፥ ባህሩ ግን መቼም ቢሆን አይሞላም። ወንዞቹ ወደሚሄዱበት ሥፍራ፥ ወደዚያው ሥፍራ እንደገና ይሄዳሉ።
\v 8 ሁሉም ነገር አድካሚ ነው፥ ሊያስረዳ የሚችልም የለም። ዓይን በሚያየው አይረካም፥ ጆሮም በሚሰማው አይሞላም።
\s5
\v 9 የሆነው ሁሉ ወደፊትም የሚሆን ነው፥ የተደረገውም ሁሉ ወደፊት የሚደረግ ነው። ከፀሐይ በታች አንድም አዲስ ነገር የለም።
\v 10 'ተመልከት፥ ይህ አዲስ ነው' ሊባልለት የሚችል አንዳች ነገር አለ? አሁን ያለው ሁሉ ለብዙ ዘመናት አስቀድሞ የነበረ ነው፥ ወደ እኛ ከመምጣቱ በፊት በዘመናት መካከል።
\v 11 በቀድሞ ዘመን የሆኑትን ነገሮች የሚያስታውስ ያለ አይመስልም። እጅግ ዘግይተው የሆኑትን ነገሮችና ወደፊት ሊሆኑ ያሉት ሁለቱም የሚታወሱ አይመስሉም።
\s5
\v 12 እኔ አስተማሪ ነኝ፥ በእስራኤልም ላይ በኢየሩሳሌም ንጉሥ ነበርኩ።
\v 13 ከሰማይ በታች የተደረገውን ነገር ሁሉ በጥበብ ለማጥናትና ለመመርመር አዕምሮዬን አሠራሁት። ይህ ምርምር እግዚአብሔር የሰው ልጆች በሥራ እንዲጠመዱ የሰጣቸው አድካሚ ተግባር ነው።
\v 14 ከሰማይ በታች የተሠሩትን ሥራዎች ሁሉ አየሁ፥ ተመልከቱ፥ ሁሉም የሚተንና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
\v 15 የተጣመመ መቃናት አይችልም! የጠፋው መቆጠር አይችልም!
\s5
\v 16 ለልቤ እንዲህ ስል ተናገርኩ፥ "ተመልከት፥ ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ጥበብን አከማችቻለሁ። አዕምሮዬ ትልቅ ጥበብንና እውቀትን አይቷል።"
\v 17 ስለዚህ ጥበብን ለማወቅ ልቤን አሠራሁት፥ ደግሞም ዕብደትንና ሞኝነትን። ይህም ደግሞ ነፋስን ለማገድ እንደ መሞከር መሆኑን አስተዋልኩኝ።
\v 18 ጥበብን በማብዛት ውስጥ ብዙ ተስፋ መቁረጥ አለ፥ እውቀትንም የሚያበዛ ሐዘንን ያበዛል።
\s5
\c 2
\p
\v 1 እኔም በልቤ፥ "ና እንግዲህ፥ በደስታ እፈትንሃለሁ። ስለዚህ እንዳሻህ ተደሰት" አልኩ። ግን ተመልከት፥ ይህም ደግሞ ልክ የአፍታ እስትንፋስ ነበር።
\v 2 ስለ ሣቅ " እርሱ ዕብደት ነው"፥ ስለ ደስታም "ምን ይጠቅማል?" አልኩ።
\s5
\v 3 በወይን ጠጅ ራሴን እንዴት እንደማስደስተው በልቤ መረመርሁ። እስካሁን ሞኝነትን ብይዛትም አዕምሮዬ በጥበብ እንዲመራ ተውኩት። ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ሊያደርጉት የሚገባቸውን መልካም ነገር ለማግኘት ፈለግሁ።
\s5
\v 4 ታላላቅ ነገሮችን አከናወንኩ። ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፥ ወይንንም ተከልሁ።
\v 5 የአትክልትና የመዝናኛ ቦታዎችን ለራሴ ሠራሁ፤ በእነርሱም ላይ ሁሉንም ዓይነት የፍሬ ዛፎች ተከልሁባቸው።
\v 6 ዛፎች የሚያድጉበትን ዱር የሚያጠጡ የውሃ ገንዳዎችን አበጀሁ።
\s5
\v 7 ወንድና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፤ በቤተ መንግሥቴ የተወለዱ ባሪያዎችም ነበሩኝ። ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነገሡት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ የከብት መንጋና የቤት እንስሶች ነበሩኝ።
\v 8 ብርና ወርቅን፥ የነገሥታቱንና የአውራጃዎቹንም ሃብት ለራሴ አከማቸሁ። ለእኔ ለራሴ ወንድና ሴት አዝማሪዎች ነበሩኝ፤ እጅግ በበዙት ሚስቶቼና ቁባቶቼም በምድር ማንኛውንም ሰው ሊያስደስተው የሚችለውን ነገር አደረግሁ።
\s5
\v 9 ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ታላቅና ባለጸጋ ሆንኩ፥ ጥበቤም ከእኔው ጋር ቆየች።
\v 10 ዓይኖቼ የፈለጉትን ማናቸውንም ነገር አልከለከልኳቸውም። በምሠራው ሁሉ ልቤ ስለ ተደሰተና ደስታ የሠራሁት ሥራ ሁሉ ብድራት ስለ ነበረ ከየትኛውም ደስታ ልቤን አልከለከልኩትም።
\s5
\v 11 ከዚያም እጆቼ ያከናወኗቸውን ተግባራት ሁሉ፥ እኔም የሠራኋቸውን ሥራዎች ተመለከትኩ፥ ነገር ግን ሁሉም እንፋሎትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነበር። በእርሱ ውስጥ ከፀሐይ በታች አንድም ትርፍ አልነበረበትም።
\v 12 ከዚያም ጥበብን፥ ደግሞም ዕብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ራሴን መለስኩ። አስቀድሞ ከተደረገው በቀር ከዚህኛው ንጉሥ በኋላ የሚመጣው ንጉሥ ምን ለማድረግ ይችላል?
\s5
\v 13 ከዚያም ልክ ብርሃን ከጨለማ እንደሚሻል ጥበብም ከሞኝነት የሚሻል መሆኑን መረዳት ጀመርሁ።
\v 14 ጥበበኛ ሰው የሚሄድበትን እንዲያውቅ ዓይኖቹን በራሱ ላይ አድርጎ ይጠቀምባቸዋል፥ ሞኙ ግን በጨለማ ይሄዳል፥ ቢሆንም ለእያንዳንዱ የተዘጋጀለት ፍጻሜ ተመሳሳይ መሆኑን አውቃለሁ።
\s5
\v 15 እኔም በልቤ፥ "በሞኙ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል። ስለዚህ በጣም ጥበበኛ ብሆን ምን ልዩነት ያመጣል?" አልኩ። "ይህም ደግሞ እንፋሎት ብቻ ነው" ብዬ በልቤ ደመደምኩኝ።
\v 16 ምክንያቱም ጠቢቡም እንደ ሞኙ ለዘላለም አይታሰብም። በሚመጣው ዘመን ሁሉም ነገር የተረሳ ይሆናል። ልክ ሞኙ እንደሚሞት ጠቢቡም ሰው ይሞታል።
\s5
\v 17 ከፀሐይ በታች የሚሠራው ሥራ ሁሉ ክፉ ስለሆነብኝ ሕይወትን ጠላሁ። ይህም የሆነው ሁሉም ነገር እንፋሎትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ስለሆነ ነው።
\v 18 ከፀሐይ በታች በሥራ የደከምኩበትን ሁሉ ጠላሁ፥ ከእኔ በኋላ ለሚመጣው ሰው ልተውለት የግድ ነውና።
\s5
\v 19 እርሱ ጥበበኛ ወይም ሞኝ ይሆን እንደሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከሰማይ በታች በጥበቤ በሠራሁት ሁሉ ላይ አዛዥ ይሆናል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
\v 20 ከዚህ የተነሣ ከፀሐይ በታች በሠራሁት ሥራ ሁሉ ላይ ልቤ ተስፋ መቁረጥ ጀመረ።
\s5
\v 21 ምክንያቱም አንዱ በጥበብ፥ በእውቀትና በብልሃት ይሠራ ይሆናል፥ ነገር ግን የነበረውን ነገር ሁሉ አንድም ላልለፋበት ሰው ይተውለታል።
\v 22 ይህም ደግሞ እንፋሎትና እጅግ የሚያሳዝን ነው። ከፀሐይ በታች ሰው ተግቶ በመሥራቱና ሥራውን ሁሉ ለማጠናቀቅ በልቡ በመሞከሩ ምን ያተርፋል?
\v 23 የየዕለት ሥራው በስቃይና በውጥረት የተሞላ ነው፥ ስለዚህ ነፍሱ በሌሊት እረፍት አታገኝም። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
\s5
\v 24 ለማንኛውም ሰው ከመብላት፥ መጠጣትና ከሥራው መልካም በሆነው ከመርካት የሚበልጥበት ምንም ነገር የለም። ይህ እውነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር እጅ እንደሆነም አየሁ።
\v 25 ከእግዚአብሔር ካልሆነ በስተቀር ማን ሊበላ ይችላል? ወይም የትኛውንም ዓይነት ደስታ ማን ሊደሰት ይችላል?
\s5
\v 26 እርሱን ደስ ለሚያሰኝ እግዚአብሔር ጥበብን፥ እውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። እንዲሁም ለኃጢአተኛው የመሰብሰብንና የማከማቸትን ሥራ ይሰጠዋል፥ እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጠው ዘንድ። ይህም ደግሞ እንፋሎትን ማብዛትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ለሁሉም ነገር የተቀጠረለት ጊዜ አለው፥ ከምድር በታች ለሚሆነውም ወቅት አለው።
\v 2 ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞት ጊዜ አለው፥ ለመትከል ጊዜ አለው፥ ለመንቀል ጊዜ አለው፥
\v 3 ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስ ጊዜ አለው፥ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመገንባት ጊዜ አለው፥
\s5
\v 4 ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሣቅ ጊዜ አለው፥ ለማዘን ጊዜ አለው፥ ለመጨፈር ጊዜ አለው፥
\v 5 ድንጋይ ለመወርወር ጊዜ አለው፥ ድንጋይ ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፥ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍ ለመራቅ ጊዜ አለው፥
\s5
\v 6 ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ፍለጋን ለማቆም ጊዜ አለው፥ ነገሮችን ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ነገሮችን ወርውሮ ለመጣል ጊዜ አለው፥
\v 7 ልብስ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋት ጊዜ አለው፥ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገር ጊዜ አለው፥
\s5
\v 8 ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላት ጊዜ አለው፥ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላም ጊዜ አለው።
\v 9 ሠራተኛው ከጥረቱ የሚያተርፈው ምንድነው?
\v 10 እግዚአብሔር እንዲፈጽሙት ለሰው ልጆች የሰጣቸውን ሥራ አይቻለሁ።
\s5
\v 11 እግዚአብሔር ሁሉን ነገር በጊዜው ተስማሚ አድርጎ ሠራው። ደግሞም በልባቸው ውስጥ ዘላለማዊነትን አስቀመጠ። ነገር ግን የሰው ልጆች ከጅማሬአቸው እስከ ፍጻሜአቸው ድረስ እግዚአብሔር የሠራውን ሥራ ሊያስተውሉት አይችሉም።
\s5
\v 12 ለሰው በሕይወት ዘመኑ ከመደሰትና መልካም ከማድረግ በቀር የሚሻል ምንም ነገር እንደሌለ አውቃለሁ።
\v 13 ደግሞም ሰው ሁሉ ሊበላና ሊጠጣ፥ ከሥራውም ሁሉ በሚመጣ መልካም እንዴት መደሰት እንዳለበት ሊያውቅ። ይህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው።
\s5
\v 14 እግዚአብሔር የሠራው ሁሉ ለዘላለም እንደሚኖር አውቃለሁ። በዚህ ላይ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይቻልም። ምክንያቱም ሰዎች በአክብሮት እንዲቀርቡት ይህንን ያደረገው እግዚአብሔር ነው።
\v 15 አሁን ያለው ሁሉ ቀደም ሲል የነበረ ነው፤ ወደ ፊት የሚኖረውም ሁሉ ቀደም ሲል የነበረ ነው። እግዚአብሔር ሰዎችን የተደበቁ ነገሮችን እንዲፈልጉ ያደርጋቸዋል።
\s5
\v 16 ከፀሐይ በታች ፍትሕ ሊኖር በሚገባበት ግፍ መኖሩን አየሁ፥ ጽድቅ ሊኖር በሚገባበትም ሥፍራ ብዙ ጊዜ የሚገኘው ግፍ ነው።
\v 17 እኔም በልቤ፥ "ስለ እያንዳንዱ ጉዳይና ስለ እያንዳንዱ ሥራ በጻድቁና በአመጸኛው ላይ በትክክለኛው ጊዜ እግዚአብሔር ይፈርዳል" አልሁ።
\s5
\v 18 እኔም በልቤ፥ "የሰው ልጆች እንደ እንስሳ መሆናቸውን ለማሳየት እግዚአብሔር ይፈትናቸዋል" አልሁ።
\s5
\v 19 በእንስሳት ላይ የሚደርሰው ያው ዕድል ፈንታ በሰው ልጆች ላይ ይደርሳልና። እንደ እንስሳቱ፥ ሰዎች ሁሉ ይሞታሉ። ያንኑ አየር ሁሉም ይተነፍሱታል፥ ስለዚህ በዚህ መንገድ ሰው ከእንስሳ ብልጫ የለውም። ሁሉም ነገር ፈጥኖ የሚጠፋ እስትንፋስ አይደለም?
\v 20 ሁሉም ወደ አንድ ሥፍራ ይሄዳሉ። ሁሉም ነገር ከአፈር ይመጣል፥ ሁሉም ነገር ደግሞ ወደ አፈር ይመለሳል።
\s5
\v 21 የሰው መንፈስ ወደ ላይ፥ የእንስሳ መንፈስም ወደ ታች ወደ ምድር ውስጥ ይሄድ እንደሆነ የሚያውቅ ማን ነው?
\v 22 ስለዚህ ማንም ሰው በሥራው ከመደሰት የሚበልጥ የተሻለ ነገር እንደሌለ እንደገና አስተዋልሁ፥ ያ ዕድል ፈንታው ነውና። ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን እንዲያይ ማን መልሶ ሊያመጣው ይችላል?
\s5
\c 4
\p
\v 1 እንደገና ከፀሐይ በታች ስለሚደረገው ግፍ ሁሉ አሰብሁ። የሚጨቆኑትን ሰዎች ዕንባ ተመልከቱ። የሚያጽናናቸውም የለም። በጨቋኞቻቸው እጅ ኃይል አለ፥ ነገር ግን የተጨቆኑት ሰዎች አጽናኝ የላቸውም።
\s5
\v 2 ስለዚህ ካሉት የሞቱት፥ እስካሁን በሕይወት ካሉት ቀደም ሲል የሞቱት ይሻላሉ አልሁ።
\v 3 ሆኖም ከሁለቱ የሚሻለው ያልኖረው፥ ከፀሐይ በታች የሚደረገውን ክፉ ድርጊት ያላየው ነው።
\s5
\v 4 ከዚያም የትኛውም ጥረትና የጥበብ ሥራ ባልንጀራውን ለቅንዓት እንደሚያነሣሣው አየሁ። ይህም ደግሞ እንፋሎትና ንፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
\s5
\v 5 ሞኝ ሰው እጁን አጣምሮ ይቀመጣል፥ አይሠራምም፥ ስለዚህ የራሱ ሥጋ ምግቡ ነው።
\v 6 ንፋስን ለማገድ በመሞከር ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ በጥሞና የተሠራ አንድ እፍኝ ይሻላል።
\s5
\v 7 ከዚያም እንደገና ስለሚበልጠው ከንቱነት፥ ከፀሐይ በታች በይበልጥ ተንኖ ስለሚጠፋው እንፋሎት አሰብሁ።
\v 8 ብቻውን የሆነ አንድ ሰው አለ። ወንድ ልጅም ሆነ አባት አንድም የለውም። ለሚሠራው ሁሉ ማለቂያ የለውም፥ ዓይኖቹም ባገኘው ብልጽግና አይረኩም። እርሱም፥ "የምለፋው ለማን ነው? ራሴንስ ከደስታ የማርቀው ለምንድነው?" ብሎ ይደነቃል። ይህ የከፋ ሁኔታ ደግሞም እንፋሎት ነው።
\s5
\v 9 ከአንድ ሰው ይልቅ ሁለቱ የተሻለ ሥራ ይሠራሉ፤ በጋራ ለሥራቸው የተሻለ ገቢ ማግኘት ይችላሉ።
\v 10 አንደኛው ቢወድቅ ሌላኛው ጓደኛውን ሊያነሣው ይችላልና። በመሆኑም በወደቀ ጊዜ የሚያነሣው ካልኖረ ብቸኛውን ሰው ሀዘን ይከተለዋል።
\v 11 ሁለቱ አብረው ቢተኙ ሊሞቃቸው ይችላል፥ ብቻውን ቢሆን ግን እንዴት ሊሞቀው ይችላል?
\s5
\v 12 አንድ ሰው ብቻውን ሊሸነፍ ይችላል፥ ሁለቱ ግን ጥቃቱን መመከት ይችላሉ። በሦስት የተገመደ ገመድ ቶሎ አይበጠስም።
\s5
\v 13 ማስጠንቀቂያዎችን እንዴት መስማት እንዳለበት ከማያውቅ ሞኝ ሽማግሌ ንጉሥ ይልቅ ድሃ፥ ነገር ግን ጥበበኛ የሆነ ወጣት ይሻላል።
\v 14 ወጣቱ ከወህኒ ወጥቶ ቢነግሥ ወይም በሀገሩ በድህነት ተወልዶ ቢያድግም ይህ አውነት ነው።
\s5
\v 15 ይሁንና ከፀሐይ በታች ሕያው የሆነና የሚንቀሳቀሰው ሁሉ ራሳቸውን ንጉሥ ሆኖ ለተነሣው ለሌላው ወጣት ሲያስገዙ አየሁ።
\v 16 አዲሱን ንጉሥ መታዘዝ ለሚፈልገው ሕዝብ ሁሉ መጨረሻ የለውም፥ በኋላ ላይ ግን ብዙዎቹ አያመሰግኑትም። በርግጥ ይህ ሁኔታ እንፋሎት፥ ንፋስንም ለማገድ መሞከር ነው።
\s5
\c 5
\p
\v 1 ወደ እግዚአብሔር ቤት በምትሄድበት ጊዜ ጠባይህን ተቆጣጠር። ለመስማት ወደዚያ ሂድ። ሞኞች ክፉ መሥራታቸውን ሳያውቁ ከሚያቀርቡት መሥዋዕት ይልቅ መስማት ይበልጣል።
\s5
\v 2 ለመናገር እጅግ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔር ፊት የትኛውንም ጉዳይ ለማቅረብ ልብህ እጅግ አይፍጠን። እግዚአብሔር በሰማይ ነው፥ አንተ ግን በምድር፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።
\v 3 የምትሠራው ከበዛና ሃሳብ ከሆነብህ፥ ክፉ ህልም ሊገጥምህ ይችላል። ቃልህ ብዙ ሲሆን ብዙ የሞኝነት ነገርም ትናገራለህ።
\s5
\v 4 ለእግዚአብሔር በምትሳልበት ጊዜ ከመፈጸም አትዘግይ፥ እግዚአብሔር በሞኞች ደስ አይለውምና።
\v 5 የተሳልከውን ፈጽመው። የተሳሉትን ካለመፈጸም ያለመሳል ይሻላል።
\s5
\v 6 አንደበትህ ሰውነትህን ለኃጢአት እንዲያነሣሣው አትፍቀድለት። ለካህኑ መልዕክተኛ፥ "ያ ስዕለት ስሕተት ነበረ" አትበል። በሐሰት በመሳል እግዚአብሔርን ለምን ታስቆጣዋለህ፥ የእጅህንስ ሥራ እንዲያጠፋ እግዚአብሔርን ለምን ታነሣሣዋለህ?
\v 7 በብዙ ሕልም ውስጥ፥ በብዙም ቃል ውስጥ እንፋሎት የሆነ ከንቱነት አለ። ስለዚህ እግዚአብሔርን ፍራ።
\s5
\v 8 በግዛትህ ውስጥ ድሃው ሲበደል፥ ፍትህንና መብቱን ሲነጠቅ በምታይበት ጊዜ፥ ማንም አላወቀም ብለህ አትደነቅ፥ ምክንያቱም ከሥራቸው ያሉትን የሚቆጣጠሩ አለቆች አሉ፥ በእነርሱም ላይ እንኳን የበላይ አለቆች አሉ።
\v 9 በአጠቃላይ የምድሪቱ ምርት ለሁሉም ነው፥ ንጉሡ ራሱም ምርቱን ከእርሻ ይወስዳል።
\s5
\v 10 ማንም ብርን የሚወድ በብር አይረካም፥ ማንም ብልጽግናን የሚወድ ሁልጊዜ ተጨማሪውን ይፈልጋል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
\v 11 ሀብት ሲበዛ በእርሱ የሚጠቀሙ ደግሞ ይበዛሉ። ባለቤቱ በዓይኖቹ ከማየቱ በስተቀር ሀብቱ ምን ይጠቅመዋል?
\s5
\v 12 ብዙም ሆነ ጥቂት ቢበላ፥ የሚሠራ ሰው እንቅልፉ ጣፋጭ ናት፥ የባለጸጋው ሀብት ግን እንቅልፉን ይነሳዋል።
\s5
\v 13 ከፀሐይ በታች ያየሁት እጅግ የከፋ ነገር አለ፡ ይኸውም በባለሌቱ የተከማቸው ሀብት መጥፊያው ሲሆን ነው።
\v 14 ባለጸጋው በክፉ አጋጣሚ ሀብቱን በሚያጣበት ጊዜ ለልጁ፥ እርሱ ላሳደገው፥ በእጁ የሚተውለት አይኖረውም።
\s5
\v 15 ሰው ከእናቱ ማኅፀን ራቁቱን እንደ ተወለደ፥ ራቁቱን ደግሞ የምድሩን ሕይወት ይሰናበታል። ከሥራው አንዱን በእጁ መውሰድ አይችልም።
\v 16 ሌላው እጅግ ክፉ ነገር፥ ሰው እንደ መጣ እንዲሁ ደግሞ መሄዱ ነው። ስለዚህ ለንፋስ በመሥራት ሰው የሚያገኘው ትርፍ ምንድነው?
\v 17 በዘመኑ ሁሉ በጨለማ ይበላል፥ በህመምና በቁጣ በብዙ ይበሳጫል።
\s5
\v 18 ተመልከቱ! እኔ እግዚአብሔር በሰጠን በምድር ሕይወታችን ከፀሐይ በታች በምንደክምበት፥ መልካምና ተስማሚ ሆኖ ያገኘሁት፥ መብላት፥ መጠጣትና ባገኘነው በሥራችን ውጤት ሁሉ መደሰትን ነው። ይህ የሰው ዕድል ፈንታው ነው።
\s5
\v 19 እግዚአብሔር ለማንኛውም ሰው ሀብትንና ባለጸግነትን፥ ድርሻውን የሚያገኝበትን ችሎታና በሥራው መደሰትን መስጠቱ ይህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ነው።
\v 20 ለመሥራት በሚያስደስተው ነገር እግዚአብሔር ባተሌ ስለሚያደርገው፥ የሕይወት ዘመኑን እምብዛም አያስባቸውም።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ለሰዎች ከባድ ነው።
\v 2 ለራሱ የሚመኘውን አንዳች ላያጣ እግዚአብሔር ሀብትን፥ ባለጠግነትንና ክብርን ይሰጠዋል፥ የሚደሰትበትን ችሎታ ግን አይሰጠውም። ይልቁንም እነዚህን ነገሮች ሌላው ሰው ይጠቀምባቸዋል። ይህ እንፋሎት፥ ክፉ ስቃይም ነው።
\s5
\v 3 ሰው አንድ መቶ ልጆች ቢወልድና ብዙ ዘመን ቢኖር፥ የዕድሜው ዘመን ቢረዝም፥፥ ልቡ ግን በመልካም ነገር ባይረካ፥ በክብርም ባይቀበር፥ ከዚህ ሰው ይልቅ ሞቶ የተወለደ ሕጻን ይሻላል አልሁ።
\v 4 እንዲህ ያለው ሕጻን እንኳን በከንቱ ይወለዳል በጨለማም ይሄዳል፥ ስሙም አይታሰብም።
\s5
\v 5 ይህ ሕጸን ፀሐይን ባያይ ወይም ምንም ባያውቅ፥ ያኛው ባይኖረውም ለዚህኛው ዕረፍት አለው።
\v 6 ሰው ሁለት ሺህ ዓመት ያህል እንኳን ቢኖር በመልካም ነገሮች ግን መደሰትን ባያውቅ፥ እንደ ሌላው ሁሉ ወደዚያው ስፍራ ይሄዳል።
\s5
\v 7 የሰው ሁሉ ሥራ አፉን ለመሙላት ነው፥ ፍላጎቱ ግን አይሞላም።
\v 8 በርግጥ ከሞኙ ይልቅ የጠቢብ ሰው ብልጫው ምንድነው? ድሃ በሌሎች ሰዎች ፊት እንዴት መመላለስ እንዳለበት ቢያውቅ ምን ብልጫ አለው?
\s5
\v 9 በምኞት ከመቅበዝበዝ በዓይን አይቶ መርካት ይሻላል፥ ይህም ደግሞ እንፋሎትና ንፋስን ለማገድ መሞከር ነው።
\v 10 ለነበረው ሁሉ ቀደም ሲል ስያሜ ተሰጥቶታል፥ ሰው ምን እንደሚመስልም አስቀድሞ ታውቋል። ስለዚህ በሁሉ ላይ ብርቱ ፈራጅ ከሆነው ጋር መከራከር አይረባም።
\s5
\v 11 የሚነገር ቃል ሲበዛ ከንቱነትም ይበዛል፥ ታዲያ ይህ ለሰው ምን ይጠቅመዋል?
\v 12 እንደ ጥላ በሚያልፍበት ከንቱና የተቆጠረ የሕይወት ዘመኑ ለሰው በሕይወቱ መልካም የሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? እርሱ ካለፈ በኋላ ከፀሐይ በታች ምን ሊሆን እንዳለ ማን ሊነግረው ይችላል?
\s5
\c 7
\p
\v 1 ከውድ ሽቶ መልካም ስም ይሻላል፥ ከልደት ቀንም የሞት ቀን ይሻላል።
\v 2 ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ሀዘን ቤት መሄድ ይሻላል፥ በሕይወቱ መጨረሻ ሰው ሁሉ ሀዘን ይገጥመዋልና፥ ስለዚህ ሕያዋን የሆኑ ሰዎች ይህንን ልብ ማለት አለባቸው።
\s5
\v 3 ከሣቅ ጥልቅ ሐዘን ይሻላል፥ ከፊት ሐዘን በኋላ የልብ ደስታ ይመጣልና።
\v 4 የጠቢብ ልቡ ሐዘን ቤት ውስጥ ነው፥ የሞኞች ልብ ግን በግብዣ ቤት ውስጥ ነው።
\s5
\v 5 የሞኞችን መዝሙር ከመስማት የጠቢብን ተግሳጽ መስማት ይሻላል።
\v 6 ከድስጥ ሥር የሚነድ እሾህ እንደሚንጣጣ የሞኞች ሣቅ ደግሞ እንደዚሁ ነው። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
\s5
\v 7 ቀማኛነት ጠቢቡን ሰው ያለጥርጥር ሞኝ ያደርገዋል፥ ጉቦም ልቡን ያበላሸዋል።
\s5
\v 8 የአንድ ነገር መጨረሻ ከጅማሬው ይሻላል፤ በመንፈሳቸው ትዕግስተኞች የሆኑ ሰዎች በመንፈሳቸው ከሚታበዩት ይሻላሉ።
\v 9 በመንፈስህ ለመቆጣት አትቸኩል፥ ቁጣ በሞኞች ልብ ያድራልና።
\s5
\v 10 "ከእነዚህ ይልቅ ያለፉት ዘመናት ለምን ተሻሉ?" አትበል፥ ይህንን የምትጠይቀው ጥበበኛ ስለሆንክ አይደለምና።
\s5
\v 11 ጥበብ ከአባቶቻችን የምንወርሳቸውን ጠቃሚ ነገሮች ያህል መልካም ነው። እርሱ ፀሐይን ለሚያዩ ለእነዚያ ትርፍ ያስገኝላቸዋል።
\v 12 ገንዘብ ጥበቃ ሊሰጥ እንደሚችል ጥበብም ጥበቃን ይሰጣል፥ የዕውቀት ብልጫው ግን ጥበብ ላገኟት ሕይወት መስጠቷ ነው።
\s5
\v 13 የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት፡ እርሱ ያጣመመውን የትኛውንም ነገር ማን ሊያቃናው ይችላል?
\s5
\v 14 ጊዜው መልካም ሲሆን በደስታ ኑርበት፥ ቀኑ ሲከፋ ግን ይህን አስብ፡ ሁለቱም አጠገብ ለአጠገብ እንዲኖሩ እግዚአብሔር ፈቅዶላቸዋል። በዚህ ምክንያት ማንም ሰው ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን የትኛውንም ነገር አያውቅም።
\s5
\v 15 ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመኔ ብዙ ነገሮችን ተመልክቻለሁ። ጻድቃን ቢሆኑም የሚጠፉ ጻድቅ ሰዎች አሉ፥ ክፋትን ቢያደርጉም ረጅም ዘመን የሚኖሩ አመጸኞችም አሉ።
\v 16 ራስህን አታጽድቅ፥ በራስህም ግምት ጠቢብ አትሁን። ለምን ራስህን ታጠፋለህ?
\s5
\v 17 እጅግ አመጸኛ ወይም ሞኝ አትሁን። ለምን ከቀንህ በፊት ትሞታለህ?
\v 18 ይህንን ጥበብ ብትይዝ መልካም ነው፥ ጽድቅንም ከማድረግ እጅህን ባትመልስ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ኃላፊነቱን ሁሉ ይወጣልና።
\s5
\v 19 በአንድ ከተማ ውስጥ ካሉ አሥር አስተዳዳሪዎች ይልቅ በጥበበኛ ሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ተጽዕኖዋ ትልቅ ነው።
\v 20 መልካምን የሚያደርግና ፈጽሞ ኃጢአትን የማይሠራ አንድም ጻድቅ በምድር ላይ የለም።
\s5
\v 21 የሚነገረውን ቃል ሁሉ አታድምጥ፥ ምናልባት አገልጋይህ ሲረግምህ ትሰማው ይሆናልና።
\v 22 በተመሳሳይ፥ ሌሎችን በልብህ ብዙ ጊዜ እንደረገምካቸው አንተ ራስህ ታውቃለህ።
\s5
\v 23 ይህንን ሁሉ በጥበብ አረጋገጥሁ። እኔም፥ "ጠቢብ እሆናለሁ" አልሁ፥ እርሱ ግን መሆን ከምችለው በላይ ነው።
\v 24 ጥበብ ሩቅና ጥልቅ ናት። ማን ሊያገኛት ይችላል?
\v 25 ለመማርና ለመፈተን፥ ጥበብንና የእውነታን ማብራሪያ ለመፈለግና ክፋት የማይረባ፥ ሞኝነትም ዕብደት መሆኑን ለመረዳት ልቤን መለስሁ።
\s5
\v 26 ልቧ በወጥመድና በመረብ የተሞላ፥ እጆቿም የእግር ብረት የሆኑ የትኛዋም ሴት ከሞት ይልቅ መራራ ናት። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ማንም ቢሆን ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛው ግን በእርሷ ይወሰዳል።
\s5
\v 27 "መርምሬ ያገኘሁትን ተመልከቱ" ይላል አስተማሪው። የእውነታን ፍቺ ለማግኘት በአንደኛው ምርምር ላይ ሌላውን እጨምር ነበር።
\v 28 እስካሁን የምፈልገው ይህንን ነው፥ ነገር ግን አላገኘሁትም። በሺህ ሰዎች መካከል አንድ ጻድቅ አገኘሁ፥ በእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ሴት አላገኘሁም።
\s5
\v 29 እግዚአብሔር ሰዎችን ቅን አድርጎ እንደ ፈጠራቸው፥ እነርሱ ግን ብዙ ችግሮችን እየፈለጉ ርቀው እንደ ሄዱ ይህንን ብቻ አገኘሁ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 ጥበበኛ የሆነ ሰው ማን ነው? በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ ሁነቶችን ትርጉም የሚያውቅ ማን ነው? በሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ፊቱን ታበራለች፥ የፊቱም ክባዴ ይለወጣል።
\s5
\v 2 እግዚአብሔር ሊጠብቀው ምሎለታልና የንጉሡን ትዕዛዝ እንድትፈጽም እመክርሃለሁ።
\v 3 ንጉሡ ደስ ያለውን ያደርጋልና ከፊቱ በችኮላ አትውጣ፥ ትክክል ላልሆነውም ነገር ድጋፍህን አትስጥ።
\v 4 የንጉሥ ቃል ይገዛል፥ ስለዚህ፥ "ምን እያደረግህ ነው?" ማን ይለዋል?
\s5
\v 5 የንጉሡን ትዕዛዝ የሚጠብቅ ጉዳትን ያርቃል። የጠቢብ ልብ የመተግበሪያ ጊዜንና ተገቢ አካሄድን ያስተውላል።
\v 6 የሰው መከራው ብዙ ነውና ለእያንዳንዱ ጉዳይ ትክክለኛ ምላሽና ምላሹን የሚሰጥበት ጊዜ አለ።
\v 7 ቀጥሎ የሚሆነውን ማንም አያውቅም። ሊመጣ ያለውን ማን ሊነግረው ይችላል?
\s5
\v 8 መተንፈስን ለማቆም በሕይወት እስትንፋስ ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም፥
\v 9 ደግሞም በሞቱ ቀን ላይ ሥልጣን ያለው ማንም የለም። በጦርነት ጊዜ ከሠራዊቱ የሚሰናበት ማንም የለም፥ አመጻም ባሪያ የሆኑለትን አይታደጋቸውም። ይህንን ሁሉ አስተዋልሁ፤ ከፀሐይ በታች ለሚሠራው ለሁሉም ዓይነት ሥራ ልቤን ሰጠሁ። አንድ ሰው በሌሎች ላይ ክፉ ለማድረግ አቅም የሚያገኝበት ጊዜ አለ።
\s5
\v 10 ስለዚህ አመጸኞች በይፋ ሲቀበሩ አየሁ። ከተቀደሰው አካባቢ ተወስደው ተቀበሩ፥ የአመጽ ሥራቸውን ይሠሩበት የነበረ ከተማ ሰዎችም አመሰገኗቸው። ይህ ደግሞ ከንቱነት ነው።
\v 11 በክፉ ወንጀል ላይ ፍርድ ፈጥኖ በማይሰጥበት ጊዜ፥ ክፋትን እንዲያደርጉ የሰው ልጆችን ልብ ያነሣሣል።
\s5
\v 12 አንድ ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፋትን ቢያደርግና ረጅም ዘመን ቢኖር እንኳን እግዚአብሔርን ለሚያከብሩት፥ አብሯቸው መሆኑን ለሚያከብሩ በጎነት እንደሚሆንላቸው አውቃለሁ።
\v 13 ለክፉ ሰው ግን በጎነት አይሆንለትም፤ ሕይወቱም አይረዝምም። እግዚአብሔርን አያከብርምና ዘመኑ ፈጥኖ እንደሚያልፍ ጥላ ነው።
\s5
\v 14 በምድር ላይ የተደረገ ሌላ ከንቱ እንፋሎት አለ። በክፉ ሰዎች ላይ የሚደርሰው በጻድቃኑም ላይ ይደርሳል፥ ለጻድቃኑ የሚደርሰውም ለክፉዎች ሰዎችም ይደርሳል። እኔም፥ ይህ ደግሞ ክፉ እንፋሎት ነው አልሁ።
\v 15 ለሰው ከፀሐይ በታች ከመብላት፥ መጠጣትና መደሰት የሚሻል ነገር ስለሌለው ደስታ ይሻላል እላለሁ። ከፀሐይ በታች እግዚአብሔር በሰጠው የሕይወት ዘመኑ ሁሉ በሚደክምበት ነገር ደስታ አብሮት ይሆናል።
\s5
\v 16 ጥበብን ለማወቅና በምድር ላይ የሚሠራውን ሥራ ለማስተዋል ልቤን በሰጠሁ ጊዜ ብዙ ጊዜ በቀንም ሆነ በሌሊት ያለ እንቅልፍ በሚሠራው ሥራ
\v 17 ከዚያም የእግዚአብሔርን ሥራ ሁሉ ተመለከትሁ ከፀሐይ በታች የሚሠራውን ሥራ ሰው ሊያስተውለው አይችልም። አንድ ሰው መልሶቹን ለማግኘት ምንም ያህል ቢጥር አያገኛቸውም። ጠቢብ ሰው እንድሚያውቅ ቢያምንም እንኳን በርግጥ አያውቅም።
\s5
\c 9
\p
\v 1 ስለ ጻድቃንና ስለ ጥበበኛ ሰዎች፥ ስለ ሥራቸውም፥ ስለ እነዚህ ሁሉ ለመገንዘብ በልቤ አሰብሁ። ሁሉም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ናቸው። አንድ ሰው ፍቅር ወይም ጥላቻ ይገጥመው እንደሆነ ማንም አያውቅም።
\s5
\v 2 ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ አለው። ጻድቃንን እና አመጸኞችን፥ መልካምና ክፉ ሰዎችን፥ ንጹሕ የሆኑትንና ያልሆኑትን፥ መሥዋዕት የሚያቀርበውንና የማያቀርበውን ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ይጠብቃቸዋል። መልካም ሰዎች እንደሚሞቱ ኃጢአተኞችም ደግሞ እንዲሁ ናቸው። የሚምለው ሰው እንደሚሞተው ሁሉ ለመማል የሚፈራው ሰውም ይሞታል።
\s5
\v 3 ከፀሐይ በታች ለተደረገው ሁሉ ክፉ ዕጣ ፈንታ አለው፥ ለሁሉም አንድ መጨረሻ። የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፥ በሕይወት እያሉም ዕብደት በልባቸው አለ። ከዚያ በኋላ ወደ ሙታን ይሄዳሉ።
\s5
\v 4 ከሞተ አንበሳ በሕይወት ያለ ውሻ እንደሚሻል በሕይወት ላለ ሰውም አሁንም ተስፋ አለው።
\v 5 ሕያዋን ሰዎች እንደሚሞቱ ያውቃሉ፥ ሙታን ግን ምንም አያውቁም። መታሰቢያቸው ተረስቷልና ምንም ብድራት አይኖራቸውም።
\s5
\v 6 ፍቅራቸው፥ ጥላቻቸውና ቅናታቸው ከብዙ ጊዜ በፊት ጠፍቷል። ከፀሐይ በታች በተደረገ በማንኛውም ነገር ዳግም ስፍራ አይኖራቸውም።
\v 7 መንገድህን ሂድ፥ ምግብህን በደስታ ተመገብ፥ በደስተኛ ልብ ወይንህን ጠጣ፥ መልካሙን ሥራህን እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።
\v 8 ልብሶችህ ሁልጊዜ ነጭ ይሁኑ፥ ራስህንም በዘይት ተቀባ።
\s5
\v 9 ከፀሐይ በታች እግዚአብሔር በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ፥ ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር በደስታ ኑር። ከፀሐይ በታች ለሆነው ሥራህ ይህ ብድራት ነው። እጅህ ለመሥራት የሚያገኘውን ሁሉ በሙሉ ኃይልህ ሥራ፥
\v 10 በምትሄድበት በመቃብር ስፍራ ሥራ ወይም ገለጻ ወይም እውቀት ወይም ጥበብ በዚያ የለምና።
\s5
\v 11 ከፀሐይ በታች አንዳንድ የሚያስደስቱ ነገሮችን አየሁ፡ ሩጫ ለፈጣኖች አይሆንም። ውጊያ ለብርቱ ሰዎች አይሆንም። እንጀራ ለጥበበኞች ሰዎች አይሆንም። ሀብት ለአስተዋይ ሰዎች አይሆንም። ሞገስ እውቀት ላላቸው ሰዎች አይሆንም። ከዚህ ይልቅ ጊዜና ዕድል በሁሉ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል።
\v 12 ዓሳ በሚሞትበት መረብ እንደሚጠመድ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚያዙ ማንም ሰው የሚሞትበትን ጊዜ አያውቅም። የሰው ልጆችም ልክ እንደ እንስሳ ድንገት በሚወድቅባቸው ክፉ ጊዜ ይታሰራሉ።
\s5
\v 13 ደግሞም ከፀሐይ በታች ያስገረመኝን ጥበብ አየሁ።
\v 14 ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚኖሩባት አንዲት ከተማ ነበረች፥ አንድ ታላቅ ንጉሥ መጣባት፥ ከበባት፥ በዙሪያዋም ታላቅ ምሽግ ገነባባት።
\v 15 በከተማው ውስጥ አንድ ድሃ ጠቢብ ሰው ተገኘ፥ በጥበቡም ከተማይቱን አዳነ። በኋላ ላይ ያንን ድሃ ሰው ማንም አላሰበውም።
\s5
\v 16 እኔም፥ "ጥበብ ከኃይል ይሻላል፥ ነገር ግን የድሃው ጥበብ ተንቋል፥ ቃሎቹም አልተሰሙም" ብዬ ደመደምኩ።
\s5
\v 17 በሞኞች መካከል ከሚጮህ ማንኛውም ገዥ ይልቅ በዝግታ የሚነገሩ የጥበበኞች ሰዎች ቃል ይደመጣል።
\v 18 ከጦር መሣሪያዎች ጥበብ ትሻላለች፥ ነገር ግን አንድ ኃጢአተኛ ብዙ መልካም ነገሮችን ሊያበላሽ ይችላል።
\s5
\c 10
\p
\v 1 የሞቱ ዝንቦች ሽቶን ያገሙታል፥ ትንሽ ሞኝነትም ጥበብና ክብርን ሊጎዳ ይችላል።
\v 2 የጠቢብ ልብ ወደ ቀኝ ያዘነብላል፥ የሞኝ ልብ ግን ወደ ግራው።
\v 3 ሞኝ መንገድ ላይ በሚሄድበት ጊዜ ማስተዋሉ ያነሰ ነው፥ ሞኝነቱን ለሁሉ ያሳውቃል።
\s5
\v 4 አለቃ በቁጣ ቢነሣብህ ሥራህን አትልቀቅ። ትዕግስት ታላቁን ቁጣ ጸጥ ማድረግ ይችላል።
\s5
\v 5 ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ አለ፥ ያም ከገዝ የሚመጣ ስህተት ነው፡
\v 6 ውጤታማ ሰዎች ዝቅተኛ የሥራ መደብ ሲሰጣቸው ሞኞች የመሪነት ሥራ ተሰጣቸው።
\v 7 ባሪያዎች በፈረስ ተቀምጠው፥ ስኬታማ ሰዎች አንደ ባሪያ በእግራቸው ሲሄዱ አየሁ።
\s5
\v 8 ጉድጓድ የሚቆፍር በዚያ ውስጥ ሊወድቅ ይችላል፥ ካብ የሚያፈርሰውንም እባብ ሊነድፈው ይችላል።
\v 9 ድንጋዮችን የሚፈነቅል በእነርሱ ሊጎዳ ይችላል፥ ግንድ የሚጠርብም አደጋ ይደርስበታል።
\s5
\v 10 የብረቱ መቁረጫ ጫፉ ቢደንዝና ሰው ባይስለው ብዙ ኃይል ሊያወጣበት የግድ ነው፥ ጥበብ ግን ውጤታማ የሚሆንበትን መንገድ ያዘጋጅለታል።
\v 11 ድግምቱ ከመደገሙ በፊት እባብ ቢነድፍ ደጋሚው ምንም አይጠቀምም።
\s5
\v 12 ከጠቢብ ሰው አፍ የሚወጣ ቃል ሞገስ አለው፥ የሞኝ ከንፈር ግን ራሱን ያጠፋዋል።
\s5
\v 13 ከሞኝ አፍ ቃል መውጣት ሲጀምር ሞኝነት አብሮ ይወጣል፥ በመጨረሻም ከአፉ ክፉ ዕብደት ይወጣል።
\v 14 ሞኝ ቃሉን ያበዛል፥ የሚመጣው ምን እንደሆነ ግን ማንም አያውቅም። ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ያውቃል?
\s5
\v 15 ወደ ከተማ የሚወስደውን መንገድ እንኳን እስከማያውቁ ድረስ ሞኞችን ሥራቸው ያደክማቸዋል።
\s5
\v 16 ንጉሣችሁ ወጣት ከሆነና መሪዎቻችሁም ግብዣቸውን በማለዳ የሚጀምሩ ከሆኑ በዚያች ምድር መከራ ይሆናል።
\v 17 ነገር ግን ንጉሣችሁ ከተከበረው ቤተሰብ የተወለደ፥ መሪዎቻችሁ ለመስከር ሳይሆን ለመበርታት በተገቢው ጊዜ ሲመገቡ ምድሪቱ ደስ ይላታል።
\s5
\v 18 በስንፍና ምክንያት ጣሪያ ይዘብጣል፥ በእጅ ሥራ መፍታትም ቤት ያንጠባጥባል።
\v 19 ሰዎች ምግብን ለሣቅ ያዘጋጃሉ፥ ወይን ሕይወትን ደስ ያሰኛል፥ ገንዘብም ፍላጎትን ሁሉ ያሟላል።
\s5
\v 20 በልብህም ቢሆን ንጉሡን አትርገመው፥ በመኝታህም ላይ ባለጸጎችን አትርገም። በሰማይ የሚበር ወፍ ቃልህን ይወስድ ይሆናልና ክንፍ ያለውም ሁሉ ጉዳዩን ሊያሰራጨው ይችላል።
\s5
\c 11
\p
\v 1 እንጀራህን በውሃ ላይ ጣል፥ ከብዙ ቀናት በኋላ መልሰህ ታገኘዋለህ።
\v 2 ከሰባት እንዲያውም ከስምንት ሰዎች ጋር ተካፈለው፥ በምድር ላይ የሚመጣውን ጥፋት አታውቅምና።
\v 3 ደመና ዝናብን ከተሞላ በምድር ላይ ይለቀዋል፥ አንድ ዛፍ ወደ ደቡብ አቅጣጫ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት በዚያው ይኖራል።
\s5
\v 4 ማንም ንፋስን የሚጠባበቅ አይተክልም፥ ደመናንም የሚጠብቅ መከሩን አይሰበስብም።
\v 5 ንፋስ ከየት አቅጣጫ እንደሚመጣ፥ እንዲሁም የሕጻኑ አጥንቶች በእናቱ ማኅፀን ውስጥ እንዴት እንደሚያድግ እንደማታውቅ ሁሉን የፈጠረውን የእግዚአብሔር አሠራር ደግሞ ለማወቅ አትችልም።
\s5
\v 6 በጠዋት ዘርህን ዝራ፤ እስከ ምሽትም ድረስ፥ የሚያስፈልገውን ያህል በእጆችህ ሥራ፤ የትኛው እንደሚበቅል፥ የጠዋቱ ወይም የምሽቱ፥ ይህ ወይም ያኛው፥ ወይም ሁለቱም መልካም ይሆኑ እንደኾነ አታውቅምና።
\v 7 በእውነት ብርሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሐይን ማየትም ለዓይን የሚያስደስት ነገር ነው።
\v 8 ሰው ረጅም ዘመን ቢኖር በእነዚያ ሁሉ ደስ ይበለው፥ ነገር ግን ብዙዎች ናቸውና ሊመጡ ያሉትን ጨለማ ቀናት ያስብ። የሚመጣውም ሁሉ እንደ እንፋሎት ጠፊ ነው።
\s5
\v 9 አንተ ወጣት፥ በወጣትነትህ ደስ ይበልህ፥ በወጣትነትህም ዘመን ልብህን ደስታ ይሙላው። የልብህን መልካም ምኞትና ዓይንህ የሚያየውን ሁሉ ተከተል። ይሁን እንጂ ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ እወቅ።
\v 10 ከልብህ ቁጣን አስወግድ፥ የትኛውንም በሰውነትህ ያለውን ሕመም ቸል በለው፥ ወጣትነትና ብርታቱ እንፋሎት ነውና።
\s5
\c 12
\p
\v 1 አስቸጋሪዎቹ ቀናት ሳይመጡ፥ "ደስ አያሰኙኝም" የምትላቸው ዓመታትም ሳይደርሱ፥
\v 2 የፀሐይ፥ የጨረቃና የከዋክብት ብርሃን ሳይጨልም፥ የጠቆረው ደመና ከዝናብ ኋላ ሳይመለስ፥ በወጣትነት ዘመንህ ፈጣሪህን አስብ።
\s5
\v 3 ያ ጊዜ የቤተ መንግሥት ጠባቂዎች የሚርበደበዱበት፥ ብርቱዎች የሚጎብጡበት፥ ጥቂቶች በመሆናቸው የሚፈጩት ሥራቸውን የሚያቆሙበት፥ በመስኮት ወደ ውጪ የሚመለከቱ አጥርተው የማያዩበት፥ ይሆናል።
\s5
\v 4 ያ ጊዜ በጎዳናው ላይ በሮች የሚዘጉበትና የወፍጮ ድምጽ የሚቆምበት፥ ከወፍ ድምጽ የተነሣ ሰዎች የሚደነግጡበትና የሚዘምሩ ልጃገረዶች ድምጻቸው ዝግ የሚልበት ይሆናል።
\s5
\v 5 ያ ጊዜ ሰዎች ከፍታዎችንና በመንገድ ላይ የሚገጥማቸውን አደጋ በማሰብ የሚፈሩበት፥ የለውዝ ዛፍ ሲያብብ፥ አንበጣዎች ተከታትለው ሲሳቡ፥ ተፈጥሯዊ ፍላጎት የሚጠፋበት ጊዜ ነው። ሰው ወደ ዘላለም ቤቱ ይሄዳል፥ አልቃሾችም በጎዳናዎቹ ላይ ይወርዳሉ።
\s5
\v 6 የብር ሰንሰለት ሳይበጠስ ወይም ጎድጓዳው የወርቅ ሳሕን ሳይሰበር ወይም እንስራው በምንጩ አጠገብ ብትንትኑ ሳይወጣ ወይም የውሃ ማውጫው ጉድጓዱ ውስጥ ሳይበጠስ፥
\v 7 አፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስና መንፈስም ወደ ሰጪው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ።
\s5
\v 8 አስተማሪው፥ "የሚተን እንፋሎት፥ ሁሉም ነገር የሚጠፋ እንፋሎት ነው" ይላል።
\v 9 አስተማሪው ጠቢብ ነበር፥ ለሕዝቡም እውቀትን አስተማረ። ብዙ ምሳሌዎችን መረመረና አጠና፥ በስርዓትም አስቀመጣቸው።
\s5
\v 10 አስተማሪው ግልጽና ቅን የእውነት ቃላትን በመጠቀም ለመጻፍ ፈለገ።
\v 11 የጠቢባን ቃል አንደ ከብት መንጃ አርጩሜ ነው። ጠልቀው እንደ ገቡ ሚስማሮች አንድ እረኛ ያስተማራቸውና አስተማሪዎች የሰበሰቧቸው ምሳሌዎችም እንዲሁ ናቸው።
\s5
\v 12 ልጄ ሆይ፥ በይበልጥ አንድ ነገር ተጠንቀቅ፡ ብዙ መጻሕፍት መጻፍ ማለቂያ የለውም። ብዙ ማጥናትም ሰውነትን ያደክማል።
\s5
\v 13 ሁሉም ነገር ከተሰማ በኋላ የጉዳዩ መጨረሻ እግዚአብሔርን እንድትፈራውና ትዕዛዙን እንድትጠብቅ ነው፥ ይህ የሰው ሙሉ ተግባሩ ነውና።
\v 14 መልካምም ይሁን ክፉ፥ የተደረገውን ሁሉ፥ ከተሰወረው ነገር ሁሉ ጋር፥ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።

296
22-SNG.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,296 @@
\id SNG
\ide UTF-8
\h መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን
\toc1 መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን
\toc2 መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን
\toc3 sng
\mt መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን
\s5
\c 1
\p
\v 1 ከመዝሙሮች የሚበልጥ የሰለሞን መዝሙር። ልጃገረዲቱ ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥
\v 2 ኦ በአፍህ መሳም በሳምከኝ፥ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይሻላልና።
\v 3 ሽቶህ አስደሳች መዓዛ አለው፤ ስምህ እንደሚፈስ ሽቶ ነው፥ ስለዚህ ልጃገረዶች ወደዱህ።
\v 4 ካንተ ጋር ውሰደኝ፥ አብረንም እንሮጣለን። ሴቲቱ ለራሷ ትናገራለች፥ ንጉሡ ወደ ቤቱ ውስጥ አስገባኝ። ሴቲቱ ፍቅረኛዋን እንዲህ ስትል ትናገረዋለች፥ ደስ ብሎኛል፤ ስለ አንተ ደስ ይለኛል፤ በፍቅርህ ሐሴት ላድርግ፤ እርሱ ከወይን ጠጅ ይሻላል። ሌሎቹ ሴቶች ቢያደንቁህ ተፈጥሮአዊ ነው
\s5
\v 5 አንደኛዋ ሴት ለሌላይቱ ስትናገር፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ቢሆንም ውብ ነኝ፥ እናንተ ከኢየሩሳሌም ወንዶች የተወለዳችሁ ሴቶች ልጆች፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች ጥቁር፥ እንደ ሰለሞንም መጋረጃዎች ውብ ነኝ።
\v 6 ጥቁር ስለ ሆንኩ ትኩር ብላችሁ አትመልከቱኝ፥ ምክንያቱም ፀሐይ አጥቁሮኛል። የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቆጡኝ፥ የወይን አትክልት ጠባቂም አደረጉኝ፥ የራሴን የወይን ቦታ ግን አልጠበቅሁም። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
\s5
\v 7 ንገረኝ የምወድህ፥ መንጋህን የምታሰማራው የት ነው? በቀትር ጊዜስ መንጋህን የምታሳርፈው የት ነው? ከባልንጀሮችህ መንጋ ኋላ እንደሚቅበዘበዝ ሰው ለምን እሆናለሁ? ፍቅረኛዋ ሲመልስላት፥
\s5
\v 8 ከሴቶች ሁሉ እጅግ የተዋብሽው ሆይ፥ አታውቂ እንደሆነ፥ የመንጋዬን ኮቴ ተከተይ፥ የፍየል ግልገሎችሽንም በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።
\s5
\v 9 የኔ ፍቅር፥ በፈርዖን የሰረገላ ፈረሶች መካከል ካለችው ባዝራ ጋር አመሳሰልሁሽ።
\v 10 ጉንጮችሽ በማስዋቢያ ተውበዋል፥ አንገትሽም በዕንቁ ሐብል።
\v 11 የብር ፈርጥ ያለበት የወርቅ ማጌጫ እሠራልሻለሁ። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥
\s5
\v 12 ንጉሥ ማዕዱ ላይ እያለ፥ የናርዶስ ሽቶዬ መዓዛውን ናኘው።
\v 13 ውዴ ለእኔ ልክ ሌሊቱን ሙሉ በጡቶቼ መካከል እንደሚያርፍ እንደ ተቋጠረ ከርቤ ነው።
\v 14 ውዴ ለእኔ በዓይንጋዲ የወይን ቦታ ውስጥ እንደ ሂና የአበባ ዕቅፍ ነው። ፍቅረኛዋ ሲናገራት፥
\s5
\v 15 ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ አንቺ ውብ ነሽ፤ እነሆ ያማርሽ ነሽ፤ ዓይኖችሽ እርግቦችን ይመስላሉ። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
\s5
\v 16 ውዴ ሆይ፥ እነሆ አንተ መልከ መልካም ነህ፥ ያማርክም ነህ። የለመለመው ሣር እንደ አልጋ ያገለግለናል።
\v 17 የቤታችን የማዕዘን ተሸካሚ የዝግባ እንጨት፥ የጣሪያችን ማዋቀሪያም የጥድ እንጨት ነው።
\s5
\c 2
\p
\v 1 እኔ በሜዳ የሚገኝ አበባ፥ በሸለቆም የሚገኝ አበባ ብቻ ነኝ። ሰውየው ሲናገራት፥
\v 2 ውዴ ሆይ፥ አበባ በእሾህ መካከል እንደሆነ አንቺም በሀገሬ ሴቶች ልጆች መካከል ነሽ። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥
\s5
\v 3 በዱር ዛፍ መካከል እንዳለ የእንኮይ ዛፍ የእኔም ውድ በጎልማሶች መካከል ነው። በታላቅ ደስታ ከጥላው ሥር ተቀመጥኩ፥ የፍሬውም ጣዕም ጣፋጭ ነው።
\v 4 ወደ ግብዣው አዳራሽ አመጣኝ፥ በእኔ ላይ ያለው ሰንደቁ ፍቅር ነው። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
\s5
\v 5 በዘቢብ ጥፍጥፍ ነፍስ ዝሩብኝ፥ በእንኮይ ጭማቂም አበርቱኝ፥ በፍቅር ተይዤ ደክሜአለሁና። ሴቲቱ ለራስዋ ስትናገር፥
\v 6 ግራ እጁ ከአንገቴ ሥር ነው፥ ቀኝ እጁም ያቅፈኛል። ሴቲቱ ለሌላዋ ሴት ስትናገር፥
\s5
\v 7 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች፥ በፍቅር ግንኙነታችን ወቅት እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን በሜዳ ፍየሎችና በአጋዘኖች ቃል እንድትገቡልኝ እፈልጋለሁ። ሴቲቱ ለራሷ ትናገራለች፥
\s5
\v 8 የውዴ ድምጽ ነው! ኦ፥ በተራራዎች ላይ እየዘለለ፥ በኮረብታዎች ላይ እየተስፈነጠረ ሲመጣ ይታወቀኛል።
\v 9 ውዴ የሜዳን ፍየል ወይም ግልገል አጋዘንን ይመስላል፤ እነሆ እርሱ ከቤታችን ግድግዳ በስተኋላ ቆሟል፥ በመስኮቱ በኩል አተኩሮ፥ በፍርግርጉም አጮልቆ ይመለከታል።
\s5
\v 10 ውዴ እንዲህ ሲል ተናገረኝ፥ "ውዴ ሆይ ተነሽ፤ የኔዋ ቆንጆ ከእኔ ጋር ነይ።
\v 11 ተመልከች፥ ክረምቱ አልፏል፥ ዝናቡም ቆሟል፥ ሄዷልም።
\s5
\v 12 አበቦች በምድር ላይ ታይተዋል፤ ወይን የሚገረዝበትና የወፎች ዝማሬ ጊዜ ደርሶአል፥ የእርግቦችም ድምጽ በምድራችን ተሰምቷል።
\v 13 የበለስ ዛፍ አረንጓዴ ፍሬዎቿ በስለዋል፥ ወይኖቹም አብበዋል፥ መዓዛቸውንም ሰጥተዋል። ውዴ ሆይ ተነሽ፥ የኔዋ ቆንጆ ነይ።
\s5
\v 14 በዐለት ሥንጣቂ ውስጥ፥ በድብቁ የተራራማው ቋጢኝ ስንጣቂ ውስጥ ያለሽ እርግቤ ሆይ፥ ፊትሽን ልየው። ድምጽሽን ልስማው፥ ድምጽሽ ጣፋጭ ነውና ፊትሽም ውብ ነው።" ሴቲቱ ለራሷ ስትናገር፥
\s5
\v 15 የወይናችን ቦታ አብቦአልና የወይን ቦታዎችን የሚያበላሹትን ትናንሽ ቀበሮዎች ያዙልን።
\s5
\v 16 ውዴ የእኔ ነው፥ እኔም የእርሱ ነኝ፤ እርሱ መንጋውን በአበቦቹ መካከል በደስታ ያሰማራል።
\v 17 ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ ውዴ ሆይ፥ ተመለስ፣ የንጋቱ ቀዝቃዛ ንፋስ ሳይነፍስ፥ ጥላውም ሳይሸሽ። ተመለስ፤ በጎርበጥባጣዎቹ ኮረብቶች ላይ የሜዳ ፍየልን ወይም ግልገል አጋዘንን ምሰል።
\s5
\c 3
\p
\v 1 ሌሊት በመኝታዬ የምወደውን ናፈቅሁት፤ ፈለግሁት፥ ነገር ግን ላገኘው አልቻልኩም።
\v 2 እኔም ለራሴ፥ "እነሣለሁ፥ ወደ ከተማው ውስጥ፥ ወደ ጎዳናዎቹና ወደ አደባባዮቹ እሄዳለሁ፤ ውዴንም እፈልገዋለሁ" አልኩ። ፈለግሁት፥ ላገኘው ግን አልቻልኩም።
\s5
\v 3 ጠባቂዎች በከተማው ውስጥ ለጥበቃ ሲዘዋወሩ አገኙኝ። እኔም፥ "ውዴን አይታችሁታል?" ብዬ ጠየቅኋቸው።
\v 4 ከእነርሱ ጥቂት እልፍ እንዳልኩኝ ነፍሴ የወደደችውን አገኘሁት። ያዝኩት፥ ወደ እናቴ ቤት፥ ወደ ፀነሰችኝም መኝታ ቤት እስካመጣው ድረስ አልለቀውም። ሴቲቱ ለሌላይቱ ሴት ስትናገር፥
\s5
\v 5 እናንተ የኢየሩሳሌም ሰዎች ሴቶች ልጆች፥ በፍቅር ግንኙነታችን እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን በሜዳ ፍየሎችና አጋዘኖች እንድትምሉልኝ እፈልጋለሁ። ወጣቷ ሴት ለራሷ ስትናገር፥
\s5
\v 6 ይህቺ በዕጣንና ከርቤ፥ ነጋዴዎችም በሚሸጡት ልዩ ልዩ ቅመም በተቀመመ ሽቶ ተቀብታ እንደ ጢስ ምሶሶ ከምድረ በዳ የምትወጣ ማናት?
\v 7 እነሆ እርሱ የሰለሞን ተንቀሳቃሽ አልጋ ነው፤ ስልሳ የእስራኤል ወታደሮች፥ ስልሳ ጦረኞች ከብበውታል።
\s5
\v 8 እነርሱ በሰይፍ የላቁ ናቸው፥ በጦርነትም የታወቁ። እያንዳንዱ በወገቡ ሰይፍ አለው፥ በሌሊት የሚያሸብሩትን ለመከላከል ታጥቀዋል።
\v 9 ንጉሥ ሰለሞን ከሊባኖስ በመጣ እንጨት ሰው ተቀምጦበት የሚሸከሙትን [ለአንድ ሰው መቀመጫ የሚሆን ወንበር የሚይዝ] ሳጥን ለራሱ ሠራ።
\s5
\v 10 ምሶሶዎቹን ከብር፥ ጀርባው ከወርቅ፥ መቀመጫው ከሐምራዊ ጨርቅ ተደርጎ ተሠራ። ውስጡ የተዋበው በኢየሩሳሌም ሰዎች ሴቶች ልጆች ነበር። ወጣቷ ለኢየሩሳሌም ሴቶች ስትናገር፥
\v 11 የጽዮን ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ሂዱ ውጡ፥ ንጉሥ ሰለሞንን ትኩር ብላችሁ እዩት፥ በሕይወቱ በተደሰተባት በዚያች ቀን፥ በሠርጉ ቀን እናቱ የደፋችለትን አክሊል ጭኖ።
\s5
\c 4
\p
\v 1 ኦ፥ ወዳጄ ሆይ፥ አንቺ ውብ ነሽ፥ እነሆም ቆንጆ ነሽ። በመሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እርግቦች ናቸው። ጸጉርሽ ከገለዓድ ተራራ ቁልቁል የሚወርደውን የፍየል መንጋ ይመስላል።
\s5
\v 2 ጥርስሽ በቅርቡ ተሸልቶ ከመታጠቢያው ሥፍራ የሚወጣውን የበግ መንጋ ይመስላል። እያንዳንዱ መንታ ወልዷል፥ በመካከላቸውም መካን የለም።
\s5
\v 3 ከንፈሮችሽ ቀይ የሐር ፈትል ይመስላሉ፤ አፍሽ ውብ ነው። ጉንጮችሽ በመሸፈኛሽ ውስጥ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላል።
\s5
\v 4 አንገትሽ በረድፍ በተደረደሩ ድንጋዮች ላይ የተገነባውን የዳዊትን የጥበቃ ማማ ይመስላል፥ አንድ ሺህ ጋሻ፥ የወታደሮቹ ሁሉ ጋሻ በእርሱ ላይ ተሰቅሏል።
\v 5 ሁለቱ ጡቶችሽ በአበቦች መካከል የተሰማሩ ሁለት የአጋዘን ግልገሎችን፥ መንታም የተወለዱ የሜዳ ፍየሎችን ይመስላሉ።
\s5
\v 6 ጎሕ እስኪቀድና ጥላው እስኪሸሽ ድረስ፥ ወደ ከርቤው ተራራ፥ ወደ ዕጣኑም ኮረብታ እሄዳለሁ።
\v 7 ውዴ ሆይ፥ ሁለመናሽ ውብ ነው፥ እንከንም የለብሽም።
\s5
\v 8 ሙሽራዬ ሆይ፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ። አዎን፥ ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ፥ ከአማና ጫፍ፥ ከሳኔርና ከኤርሞን ጫፍ፥ ከአንበሶች ዋሻ፥ የነብሮች ዋሻ ከሆነውም ተራራ ነይ።
\s5
\v 9 እህቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ልቤን ሰርቀሽዋል፤ በአንድ አፍታ ዕይታሽ ብቻ፥ በአንድ ሐብልሽ ብቻ ልቤን ሰርቀሽዋል።
\s5
\v 10 እህቴ ሙሽራዬ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት ያማረ ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ ምንኛ ይሻላል፥ የሽቶሽ መዓዛም ከቅመሞች ሁሉ።
\v 11 ሙሽራዬ ሆይ፥ ከንፈሮችሽ ማር ያንጠባጥባሉ፥ ማርና ወተት ምላስሽ ሥር ናቸው። የልብሶችሽ መዓዛ የሊባኖስን መዓዛ ይመስላል።
\s5
\v 12 እህቴ ሙሽራዬ የተቆለፈበት የመናፈሻ ቦታ ናት፥ የተቆለፈበት የመናፈሻ ቦታ፥ የታተመበትም ምንጭ።
\v 13 ቅርንጫፎችሽ የሮማን ዛፍ ከተመረጠ ፍሬ ጋር፥ ሂናና የናርዶስ ተክል፥
\v 14 ናርዶስና ቀጋ፥ ጠጅ ሣርና ቀረፋ ከልዩ ልዩ ቅመሞች ጋር፥ ከርቤና እሬት ምርጥ ከሆኑት ቅመሞች ሁሉ ጋር አሉባቸው።
\s5
\v 15 አንቺ የአትክልት ሥፍራ ምንጭ፥ የንጹህ ውሃ ጉድጓድ፥ ከሊባኖስ ወደ ታች የሚወርድ ምንጭ ነሽ። ወጣቷ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
\v 16 የሰሜን ንፋስ ሆይ ንቃ፤ የደቡቡም ንፋስ ና፤ ቅመሞቹ መዓዛቸውን እንዲሰጡ በአትክልት ሥፍራዬ ላይ ንፈስ። ውዴ ወደ አትክልቱ ሥፍራ ይምጣ፥ ከምርጡም ፍሬ ጥቂት ይብላ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 እህቴ፥ ሙሽራዬ፥ ወደ አትክልቴ ቦታ መጣሁ፤ ከርቤዬን ከቅመሜ ጋር ሰብስቤአለሁ። የማር እንጀራዬን ከወለላው ጋር በልቻለሁ፤ ወይኔን ከወተቴ ጋር ጠጥቻለሁ። ጓደኞች ለአፍቃሪዎች ሲናገሩ፥ ጓደኞቻችን ሆይ ብሉ፤ ጠጡ፥ በፍቅርም ስከሩ። ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥
\s5
\v 2 እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን በሕልም ነቅቷል። የውዴ ድምጽ ነው፥ በሩን ያንኳኳል፥ "እህቴ፥ ውዴ፥ እርግቤ፥ እንከን የሌለብሽ ሆይ፥ ራሴ በጤዛ ርሷል ፀጉሬም በሌሊቱ እርጥበት፥ ስለዚህ ክፈችልኝ" እያለ።
\s5
\v 3 "ልብሴን አውልቄአለሁ፤ እንደገና መልበስ አለብኝ? እግሬን ታጥቤአለሁ፤ ማቆሸሽ አለብኝ?"
\v 4 ውዴ በበሩ መካፈቻ ቀዳዳ በኩል እጁን አስገባ፥ ልቤም ስለ እርሱ ታወከ።
\s5
\v 5 ለውዴ በሩን ልከፍትለት ተነሣሁ፥ እጆቼ ከርቤን አንጠባጠቡ፥ ጣቶቼ በበሩ እጀታ ላይ በከርቤ ረጠቡ።
\s5
\v 6 ለውዴ በሩን ከፈትኩለት፥ ውዴ ግን ተመልሶ ሄዶ ነበር። ልቤ ደነገጠ፤ እኔም ተከፋሁ። ፈለግሁት፥ ነገር ግን አላገኘሁትም፤ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም።
\s5
\v 7 ጠባቂዎቹ በከተማ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ መቱኝ፥ አቆሰሉኝም፤ በቅጥሩ ላይ ያሉት ጠባቂዎችም ካባዬን ወሰዱብኝ። ወጣቷ ለከተማው ሴቶች ስትናገር፥
\s5
\v 8 እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች፥ ውዴን ካገኛችሁት ለእርሱ ካለኝ ፍቅር የተነሣ መታመሜን ልትነግሩት ቃል እንድትገቡልኝ እፈልጋለሁ። የከተማው ሴቶች ለወጣቷ ሲናገሩ፥
\s5
\v 9 አንቺ በሴቶች መካከል የተዋብሽዋ ሆይ፥ ውድሽ ከሌላው አፍቃሪ ወንድ የተሻለው እንዴት ነው? እንዲህ ያለውን መሐላ እንድናደርግ የጠየቅሽን ውድሽ ከሌላው አፍቃሪ የተሻለው ለምንድነው? ወጣቷ ለከተማው ሴቶች ስትናገር፥
\s5
\v 10 ውዴ ደስተኛና ቀይ ነው፥ ከአሥር ሺዎችም የላቀ ነው።
\v 11 ራሱ ንጹህ ወርቅ ነው፤ ፀጉሩም ዞማና እንደ ቁራ የጠቆረ ነው።
\s5
\v 12 ዓይኖቹ በጅረት አጠገብ እንዳሉ እርግቦች፥ በወተት እንደ ታጠቡ፥ በማስቀመጫቸው ያሉ ዕንቁዎችን ይመስላሉ።
\s5
\v 13 ጉንጮቹ የሽቶ መዓዛ የሚሰጡ የልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም መደብ ይመስላሉ። ከንፈሮቹ ከርቤን የሚያንጠባጥቡ አበቦች ናቸው።
\s5
\v 14 ክንዶቹ የዕንቁ ፈርጥ ባለበት ወርቅ ተሸፍኗል፤ ሆዱ በሰንፔር ያጌጠ የዝሆን ጥርስ ነው።
\s5
\v 15 እግሮቹ በንጹህ የወርቅ መሠረት ላይ የቆሙ፥ የእምነ በረድ ምሶሶዎች ናቸው፤ መልኩ እንደ ሊባኖስ፥ እንደ ተመረጠም ዝግባ ነው።
\s5
\v 16 አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፤ እርሱ ፍጹም ውብ ነው። የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ጓደኛዬም እርሱው ነው።
\s5
\c 6
\p
\v 1 በሴቶች መካከል እጅግ የተዋብሽዋ ሆይ፥ ውድሽ ወዴት ሄደ? ካንቺ ጋር እንድንፈልገው ውድሽ የሄደው በየትኛው አቅጣጫ ነው? ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥
\s5
\v 2 በአትክልቱ ሥፍራ መንጋውን ሊያሠማራ፥ አበቦችንም ሊሰበስብ፥ ውዴ ወደ አትክልቱ ሥፍራ፥ ወደ ቅመማ ቅመሞቹ መደቦች ወርዷል።
\v 3 እኔ የውዴ ነኝ፥ ውዴም የእኔ ነው፤ በአበቦቹ መካከል መንጋውን በደስታ ያሰማራል። የሴቲቱ አፍቃሪ እንዲህ ይላታል፥
\s5
\v 4 ውዴ ሆይ፥ እንደ ቴርሳ ቆንጆ ነሽ፥ እንደ ኢየሩሳሌም ውብ ነሽ፥ ሰንደቁን እንደያዘ ሠራዊት ታስፈሪያለሽ።
\s5
\v 5 አድክመውኛልና ዓይኖችሽን ከእኔ መልሺ። ፀጉርሽ ከገለዓድ ተራራ ቁልቁል የሚወርደውን የፍየል መንጋ ይመስላል።
\s5
\v 6 ጥርሶችሽ ከመታጠቢያ ሥፍራቸው የሚመጡትን የሴት በግ መንጋ ይመስላሉ። እያንዳንዱ መንታ ወልዷል፥ በመካከላቸውም መካን የለም።
\v 7 በመሸፈኛሽ ውስጥ ጉንጮችሽ ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ። የሴቲቱ አፍቃሪ ለራሱ ሲናገር፥
\s5
\v 8 ስልሳ ንግሥቶች፥ ሰማንያ ቁባቶች፥ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው ልጃገረዶች አሉ።
\v 9 እርግቤ፥ እንከን የሌለባት፥ ብቸኛዋ ናት፤ ለእናቷ ልዩ ልጅ፥ ለወለደቻት ሴትም የተመረጠች ነች። የሀገሬ ሴቶች ልጆች አይተው የተባረክሽ ነሽ አሏት፤ ንግሥቶችና ቁባቶችም ደግሞ አይተው አመሰገኗት፤ ንግሥቶቹና ቁባቶቹ እንዲህ አሏት፦
\s5
\v 10 የንጋት ብርሃን መስላ የምትወጣ፥ እንደ ጨረቃ ያማረች፥ እንደ ፀሐይ ያበራች፥ ሰንደቅ እንደ ያዘ ሠራዊት የምታስፈራ ይህቺ ማን ናት? የሴቲቱ አፍቃሪ ለራሱ ሲናገር፥
\s5
\v 11 በሸለቆው ውስጥ አዲስ የበቀለውን ለማየት፥ ወይኑ አፍርቶ እንደሆነ፥ ሮማኑም አብቦ እንደሆነ ለማየት፥ የለውዝ ተክል ወዳለበት ጥሻ ወረድሁ።
\v 12 በልዑሉ ሠረገላ እንደ ተቀመጥኩ ስለ ተሰማኝ፥ በጣም ደስ አለኝ። የሴቲቱ አፍቃሪ እንዲህ ይላል፥
\s5
\v 13 አንቺ ፍጹሟ ሴት፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፤ አተኩሬ እንዳይሽ ተመለሽ፥ እባክሽ ተመለሽ። ወጣቷ ሴት ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥ በሁለት ረድፍ ጨፋሪዎች መካከል የምጨፍር ይመስል፥ ፍጹሟን ሴት ለምን ትክ ብለህ ታየኛለህ?
\s5
\c 7
\p
\v 1 አንቺ የልዑል ልጅ! እግሮችሽ በነጠላ ጫማ ውስጥ ሲታዩ እንዴት ያምራሉ? የዳሌዎችሽ ቅርጽ በእውቅ አንጥረኛ እጅ የተሠሩ ዕንቁዎችን ይመስላሉ።
\s5
\v 2 እንብርትሽ ክብ ጽዋ ይመስላል፤ ድብልቅ ወይን በፍጹም አይጉደለው። ሆድሽ በአበቦች የተከበበ የስንዴ ክምር ይመስላል።
\s5
\v 3 ሁለቱ ጡቶችሽ መንታ የሜዳ ፍየሎችን፥ ሁለት የአጋዘን ግልገሎችን ይመስላሉ።
\v 4 አንገትሽ በዝሆን ጥርስ የተሠራ የጥበቃ ማማ ይመስላል፤ ዓይኖችሽ በባትረቢ በር አጠገብ በሐሴቦን ያሉትን ኩሬዎች ይመስላሉ። አፍንጫሽ ወደ ደማስቆ አቅጣጫ የሚመለከተውን በሊባኖስ ያለውን የመጠበቂያ ማማ ይመስላል።
\s5
\v 5 ራስሽ በአንቺ ላይ የቀርሜሎስን ተራራ ይመስላል፤ በራስሽ ላይ ያለው ጸጉር ጥቁር ሐምራዊ ነው። ንጉሡ በረጅሙ ጸጉርሽ ተይዞ ታስሮአል።
\v 6 ተወዳጇ ሆይ፥ እንዴት የምታስደስቺ፥ ውብና ያማርሽ ነሽ!
\s5
\v 7 ቁመትሽ የቴምር ዘንባባ ዛፍ ይመስላል፥ ጡቶችሽም እንደ ተከማቹ ፍሬዎች ናቸው።
\v 8 እኔም፥ "በዚያ የዘንባባ ዛፍ ላይ እወጣለሁ፤ ቅርንጫፎቹንም እይዛለሁ" ብዬ አሰብኩ። ጡቶችሽ የወይን ክምችቶች ይሁኑ፥ የአፍንጫሽ እስትንፋስ መዓዛውም እንደ እንኮይ ይሁኑ።
\s5
\v 9 አፍሽ እንደ ምርጥ የወይን ጠጅ ይሁን፥ በዝግታም በውዴ ከንፈርና ጥርስ እየፈሰሱ ይንቆርቆሩ። ወጣቷ ፍቅረኛዋን እንዲህ ትለዋለች፥
\s5
\v 10 እኔ የውዴ ነኝ፥ እርሱም ይመኘኛል።
\v 11 ውዴ ሆይ ና፥ ወደ ገጠር እንሂድ፥ በመንደሮቹም እንደር።
\s5
\v 12 ወደ ወይኑ ቦታ ለመሄድ ማልደን እንነሣ፤ ወይናቸው አፍርቶ፥ አበባቸውም ፈክቶ፥ ሮማኑም አብቦ እንደሆነ እንይ። በዚያም ፍቅሬን እሰጥሃለሁ።
\s5
\v 13 ትርንጉዎች መዓዛቸውን ሰጡ፤ በምንቆይበት ቤት ደጃፍ ሁሉም ዓይነት የተመረጡ ፍሬዎች አሉ፥ አዲስና የቆዩ፥ ውዴ ሆይ፥ ለአንተ አስቀምጫቸዋለሁ።
\s5
\c 8
\p
\v 1 ምነው የእናቴን ጡቶች እንደጠባ እንደ ወንድሜ በሆንክ። ከዚያም በውጭ ባገኘሁህ ጊዜ ሁሉ በሳምኩህና፥ ማንም ባልናቀኝ ነበር።
\s5
\v 2 በመራሁህና ወደ እናቴ ቤት ባመጣሁህ፥ አንተም ባስተማርከኝ ነበር። የምትጠጣውን ጣፋጭ ወይን ጠጅ በሰጠሁህ፥ ከሮማኖቼም ጭማቂ ጥቂቱን።
\v 3 ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥ ግራ እጁ ይዞኛል፤ ቀኝ እጁም አቅፎኛል። ሴቲቱ ለሌሎች ሴቶች ስትናገር፥
\s5
\v 4 የኢየሩሳሌም ሴቶች ልጆች ሆይ፥ በፍቅር ግንኙነታችን ጊዜ እስክንረካ ድረስ ላታቋርጡን እንድትምሉልኝ እፈልጋለሁ። የኢየሩሳሌም ሴቶች ሲናገሩ፥
\s5
\v 5 በውዷ ላይ ተደግፋ ከምድረ በዳ የምትመጣ ይህቺ ማን ናት? ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥ ከእንኮዩ ዛፍ ጥላ ሥር አነቃሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤ በዚያም አንተን ወለደችህ፤ ተገላገለችህ።
\s5
\v 6 በልብህ ላይ እንደ ማኅተም አስቀምጠኝ፥ እንደ ማኅተም በክንድህ ላይ፥ ፍቅር እንደ ሞት ብርቱ ነውና። የታማኝነቷም ጠንካራ ስሜት እንደ ሲዖል ጨካኝ ነው፤ ነበልባሏ ይነዳል፤ የምትንቦገቦግ ነበልባል ናት፥ ነበልባሏ ከሌላ ከየትኛውም እሳት ይልቅ የጋለ ነው።
\s5
\v 7 የማዕበል ውሃ ፍቅርን ለማጥፋት አይችልም፥ ጎርፍም ሊያሰጥመው አይችልም። ሰው በቤቱ ያለውን ሀብት ሁሉ ስለ ፍቅር ብሎ ቢሰጥ ስጦታው ፈጽሞ ይናቃል። የወጣቷ ወንድሞች እርስ በርሳቸው ሲነጋገሩ፥
\s5
\v 8 ታናሽ እህት አለችን፥ ጡቶቿም ገና አላደጉም። ለጋብቻ በምትሰጥበት በዚያን ቀን ለእህታችን ምን ልናደርግላት እንችላለን?
\s5
\v 9 እርሷ ቅጥር ብትሆን፥ በላይዋ ላይ የጥበቃ ማማ እንሠራባታለን። በር ብትሆን በዝግባ ሳንቃ እናስውባታለን። ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥
\s5
\v 10 እኔ ቅጥር ነኝ፥ አሁን ግን ጡቶቼ እንደ ተመሸጉ ግንቦች ናቸው፤ ስለዚህ በዓይኖቹ ፊት በሚገባ አድጌአለሁ። ወጣቷ ለራሷ ስትናገር፥
\s5
\v 11 ሰለሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፤ እርሱም የወይኑን ቦታ ለሚንከባከቡት አከራየው። እያንዳንዱ ስለ ፍሬው አንድ አንድ ሺህ ሰቅል ብር ያመጣለት ነበር።
\v 12 የእኔ የወይን ቦታ የእኔው የግሌ ነው፤ ወዳጄ ሰለሞን ሆይ፥ አንድ ሺህ ሰቅሉ ያንተ ይሆናል፥ ሁለት መቶ ሰቅሉ ፍሬውን ለሚንከባከቡት ነው። የሴቲቱ አፍቃሪ ሲናገራት፥
\s5
\v 13 በአትክልቱ ቦታ የምትኖሪ ሆይ፥ ጓደኞቼ ድምጽሽን እየሰሙት ነው፤ እኔም ከሚሰሙት አንዱ ልሁን። ሴቲቱ ለፍቅረኛዋ ስትናገር፥
\s5
\v 14 ውዴ ሆይ፥ ፍጠን፤ በቅመማ ቅመም ተራራዎች ላይ የአጋዘንን ወይም የሜዳ ፍየል ግልገልን ምሰል።

434
28-HOS.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,434 @@
\id HOS
\ide UTF-8
\h ሆሴዕ
\toc1 ሆሴዕ
\toc2 ሆሴዕ
\toc3 hos
\mt ሆሴዕ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በይሁዳ ነገሥታት በዖዚያን፥ በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን፤በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን ወደ ብዔር ልጅ ወደ ሆሴዕ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
\v 2 እግዚአብሔር በሆሴዕ አማካይነት መናገር በጀመረ ጊዜ እንዲህ አለው፦« ምድሪቱ እኔን በመተው ታላቅ ምንዝርናን እያደረገች ነውና፥ሂድ፥የምንዝርናዋ ፍሬዎች የሆኑ ልጆች ያሏትን ሴተኛ አዳሪዋን ሚስትህ አድርገህ ውሰድ።»
\s5
\v 3 ስለዚህም ሆሴዕ ሄዶ የዴቤላይምን ሴት ልጅ ጎሜርን አገባ፤እርስዋም ጸነሰች፥ ወንድ ልጅም ወለደችለት።
\v 4 እግዚአብሔርም አለው፦ «ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኢይዝራኤል ስለነበረው ደም ማፍሰስ የኢዩን ቤት እቀጣለሁና፥ የቤተ እስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም አደርጋለ ሁና ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው።
\v 5 ይህም በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ የእስራኤልን ቀስት በምሰብርበት ቀን ይፈጸማል።»
\s5
\v 6 ጎሜር እንደገና ጸነሰች፥ ሴት ልጅም ወለደች። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ሆሴዕን እንዲህ አለው፦ «ቅንጣት ታህል ይቅር እላቸው ዘንድ ከእንግዲህ ወዲያ የእስራኤልን ቤት አልምርምና ስሟን ሎሩሃማ ብለህ ጥራት።
\v 7 ነገር ግን የይሁዳን ቤት እምራለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር አምላካችው በራሴ አድናቸዋለሁ እንጂ በቀስት፥ በሰይፍ፥ በጦርነት፥ በፈረሶች ወይም በፈረሰኞች አላድናቸውም።»
\s5
\v 8 ጎሜር፥ ሎሩሃማን ጡት ካስጣለቻት በኋላ ጸነሰች፥ሌላ ወንድ ልጅም ወለደች።
\v 9 በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ አለው፦« ሕዝቤ አይደላችሁምና፥ እኔም አምላካችሁ አይደለሁምና ስሙን ሎዓሚ ብለህ ጥራው ።»
\s5
\v 10 ነገር ግን የእስራኤል ቤት ቁጥር ሊለካ ወይም ሊቆጠር እንደማይችል የባሕር አሸዋ ይሆናል። «ሕዝቤ አይደላችሁም» በተባሉበት ቦታ፥«የሕያው አምላክ ሕዝብ ናችሁ» ይባላሉ።
\v 11 የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ በአንድነት ይሰበሰባሉ። የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና፥ ለራሳቸው አንድ መሪ ይሾማሉ፥ ከምድሪቱም ይውጣሉ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 ወንድሞቻችሁን «ሕዝቤ! »፥ እኅቶቻችሁንም «የተራራላችሁ» በሏቸው።
\s5
\v 2 እርሷ ሚስቴ አይደለችምና እኔም ባሏ አይደለሁምና ከእናታችሁ ጋር ተምዋግቱ፥ ተምዋገቱ። ሴተኛ አዳሪነቷን ከፊቷ፥ምንዝርናዋንም ከጡቶቿ መካከል ታስወግድ።
\v 3 አለበለዚያ እርቃንዋን እስክትቀር እገፋታልሁ፥እንደ ተወለደችበትም ቀን እርቃንዋን እገልጣለሁ። እንደ ምድረ በዳ እንደ ደረቅም ምድር አደርጋታለሁ፥ተጠምታ እንድትሞት አደርጋለሁ።
\s5
\v 4 የሴተኛ አዳሪነት ልጆች ናቸውና ለልጆቿ ቅንጣት ምሕረት የለኝም።
\v 5 ምክንያቱም እናታቸው ሴተኛ አዳሪ ናትና፥ የጸንሰቻቸውም በአሳፋሪ ተግባር ነውና። እርሷም ፦«እንጀራዬንና ውኃዬን፥ሱፌንና ሐሬን፥ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛልና ከውሽሞቼ ኋላ እሄዳለሁ» አለች።
\s5
\v 6 ስለዚህ መንገድዋን በእሾህ ለመዝጋት አጥር እሠራለሁ። መንገድዋንም እንዳታግኝ ቅጥር እገነባባታለሁ።
\v 7 ውሽሞችዋን ትከታተላቸዋለች ነገር ግን አትደርስባቸውም፤ትፈልጋቸዋለች ነገር ግን አታገኛቸውም። ከዚያም በኋላ ፦«አሁን ካለሁበት የበፊቱ ይሻላልና ወደ መጀመሪያው ባሌ እመለሳለሁ» ትላለች።
\s5
\v 8 እህሉን፥አዲሱን ወይን ጠጅና ዘይቱን የሰጠኋት፣ በአልን ያገለገሉበትን ብርና ወርቅ ያበዛሁላት እኔ እንደ ሆንኩ አላወቀችም።
\v 9 ስለዚህ እህሏን በመከር ጊዜ፥ አዲሱንም የወይን ጠጄን በወቅቱ መልሼ እወስዳለሁ። እርቃኗንም የምትሸፍንበትን ሱፌንና ሐሬን መልሼ እወስዳለሁ።
\s5
\v 10 ከዚያም ውሽሞችዋ እያዩ እርቃንዋን እስክትቀር ድረስ እገፋታለሁ፥ ከእጄም ማንም አያስጥላትም።
\v 11 ሁሉንም ክብረ በዓላቷን፦ የደስታ በዓላቷን፥የአዲስ ጨረቃ ክብረ በዓላቷን፥ ሰንበታቷንና ዓመታዊ በዓላቷን አስቀራለሁ።
\s5
\v 12 «ውሽሞቼ የሰጡኝ ክፍያዎቼ ናቸው» የምትላቸውን ወይንዋንና የበለስ ዛፎችዋን አጠፋለሁ። ጫካ አደርጋቸዋለሁ፥ የዱር አራዊትም ይበሉዋቸዋል።
\v 13 ለበአል አማልክት ዕጣን ስላጠነችባቸው፥ በቀለበቶችዋና በጌጣ ጌጦቿ ራስዋን ስላስዋበችባቸው እና እኔን ረስታ ከውሽሞቿ ኋላ ስልሄደችባችው የደስታ በዓላት እቀጣታለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
\s5
\v 14 ስለዚህ አመልሳታለሁ፥ ወደ ምድረ በዳ እወስዳታለሁ፥ በፍቅርም አነጋግራታለሁ።
\v 15 የወይን ተክሏን፥ የተስፋ በርም እንዲሆናት የአኮርን ሸለቆ መልሼ እሰጣታለሁ። በዚያም በወጣትነቷ ቀናት፥ ከግብጽ ምድር በወጣችባቸው ቀናት እንዳደረገችው ትመልስልኛለች።
\s5
\v 16 የእግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፦«በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ባሌ ብለሽ ትጠሪኛለሽ፤ ከእንግዲህ ወዲያም በአሌ ብለሽ አትጠሪኝም።
\v 17 የበአልን አማልክት ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁና ስሞቻቸው ከእንግዲህ ወዲያ አይታሰቡም።
\s5
\v 18 በዚያን ቀን ከዱር አራዊት፥ ከሰማይ አእዋፍና በምድር ከሚንቀሳቀሱት ነገሮች ጋር ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ። ቀስትን፥ ሰይፍንና ጦርነትን ክምድሪቱ አስወግዳለሁ፥ በሰላምም እንድትጋደሙ አደርጋችኋለሁ።
\s5
\v 19 ለዘላለም ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። በጽድቅ፥ በፍትሕ፥ በኪዳን ታማኝነትና በምሕረት ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ።
\v 20 በታማኝነት ባልሽ ልሆን ቃል እገባልሻለሁ። አንቺም እኔን እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።
\s5
\v 21 የእግዚአብሔር አዋጅ ይህ ነው፦ በዚያን ቀን እመልሳልሁ። «ለሰማያት እመልሳለሁ፥ እነርሱም ለምድር ይመልሳሉ።
\v 22 ምድርም ለእህሉ፥ ለአዲሱ ወይን ጠጅና ለዘይቱ ትመልሳለች፥ እነርሱም ለኢይዝራኤል ይመልሳሉ።
\s5
\v 23 ስለ ራሴ ስል በምድሪቱ ላይ እተክላታልሁ፥ ሎሩሃማንም እምራታለሁ። ሎዓሚንንም፦ አንተ ዓሚ አታህ ነህ እለዋለሁ፤ እነርሱም አንተ አምላካችን ነህ ይሉኛል።»
\s5
\c 3
\p
\v 1 እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦«እንደገና ሂድ፥ ባልዋ የሚወዳትን ነገር ግን አመንዝራ የሆነችውን ሴት ውደድ። ወድ ሌሎች አማል ክት ዘወር ቢሉና የዘቢብ እንጎቻ ቢወዱም እንኳን፥ እኔ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደምወድ ውደዳት።»
\v 2 ስለዚህ በአሥራ አምስት የብር ሳንቲሞችና በአንድ ቆሮስ ተኩል ገብስ ገዛኋት።
\v 3 እኔም፦ «ከእኔ ጋር ብዙ ቀናት ኑሪ፥ ሴተኛ አዳሪ ወይም የሌላ የማንም ሰው አትሁኚ፥እኔም እንዲዚሁ ከአንቺ ጋር እሆናለሁ» አልኳት።
\s5
\v 4 የእስራኤል ሕዝብ ያለ ንጉሥ፥ ያለ መስፍን፥ ያለ መሥዋዕት፥ ያለ ድንጋይ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድ ወይም ያለ ቤተሰብ ጣዖት ለብዙ ቀናት ይኖራሉ።
\v 5 ከዚያም በኋላ የእስራኤል ሰዎች ይመለሳሉ፥ እግዚአብሔር አምላካቸውንና ንጉሣቸውን ዳዊትንም ይፈልጋሉ። በመጨረሻዎቹም ቀናት በእግዚአብሔርና በበረከቱ ፊት እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።
\s5
\c 4
\p
\v 1 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። እውነተኛነት፥ ለኪዳን ታማኝነት፥ እግዚአብሔርን ማወቅ በምድሪቱ የለምና እግዚ አብሔር በምድሪቱ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለው።
\v 2 መርገም፥ መዋሽት፥ መግደል፥ መስረቅና ማመንዘር በዚያ አለ። ሕዝቡ ስምምነቶችን ሁሉ ያፈርሳሉ፥ ሳያቋርጡ ደም ይፋሰሳሉ።
\s5
\v 3 ስለዚህ ምድሪቱ ደረቀች፥ በእርሷ የሚኖሩ ሁሉ መነመኑ፥ የዱር አራዊትና የሰማይ አእዋፍ፥ የባሕርም ዓሦች እንኳን አለቁ።
\s5
\v 4 ነገር ግን ማንም ሙግቱን አያቅርብ፥ማንም ሌላውን ማንንም አይክሰስ። ምክንያቱም እኔ የምከስው እናንተን ካህናቱን ነውና።
\v 5 እናንተ ካህናት በቀን ትሰናከላላችሁ፥ ነቢያቶቹም ከእናንተ ጋር በሌሊት ይሰናከላሉ፥ እናታችሁንም አጠፋታለሁ።
\s5
\v 6 ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል። እናንተ ካህናት ዕውቀትን ጥላችኋልና እኔም እጥላችኋለሁ። እኔ አምላካችሁ ብሆንም ሕጌን ረስታችኋል፥ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።
\v 7 ካህናቱ በበዙ መጠን የሚሠሩብኝ ኃጢአት በዝቶአል። ክብራቸውን ወደ ውርድት እለውጠዋለሁ።
\s5
\v 8 የሕዝቤን ኃጢአት ይመገባሉ፥ ክፋታቸውም እንዲበዛ ይቋምጣሉ።
\v 9 በካህናቱ ላይ እንደሚሆን እንዲሁ በሕዝቡም ላይ ይሆናል፦ ስለ ልማዶቻቸው እቀጣቸዋለሁ፤ እንደ ሥራቸውም አከፍላቸዋለሁ።
\s5
\v 10 ከእኔ ከእግዚአብሔር ርቀው ሄደዋልና ትተውኛልምና፤ይበላሉ ግን አይጠግቡም፥ ያመነዝራሉ ግን አይበዙም።
\s5
\v 11 ሴሰኝነት፥ የወይን ጠጅና አዲስ የወይን ጠጅ ማስተዋላቸውን ወስዶታል።
\v 12 የእንጨት ጣዖቶቻችውን ያማክራሉ፥ በትሮቻቸውም ይተነብዩላቸዋል። የሴሰኝነት መንፈስ አስቶአቸዋል፥ እኔን አምላካቸውንም ትተውኛል።
\s5
\v 13 በተራሮች ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፥ ጥላው መልካም ነውና ከባሉጥ፥ ከኮምቦልና ከአሆማ ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ። ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰት ይፈጽማሉ፥ የልጆቻችሁ ሚስቶች ያመነዝራሉ።
\v 14 ሴቶች ልጆቻችሁ የዝሙት ርኩሰትን በወደዱ ጊዜ፥ ወይም የልጆቻችሁ ሚስቶች ባመነዘሩ ጊዜ አልቀጣቸውም። ምክንያቱም ወንዶቹ ራሳቸውን ለሴተኛ አዳሪዎች ሰጥተዋልና፥ እንዲሁም ከቤተ ጣዖት ሴተኛ አዳሪዎች ጋር ርኩሰትን ለመፈጸም መሥዋዕት ይሰዋሉና። ስለዚህ ይህ የማያስተውል ሕዝብ ይጠፋል።
\s5
\v 15 እስራኤል ሆይ አንቺ ብታመነዝሪም፥ ይሁዳ በደለኛ አይሁን። እናንተ ሰዎች፥ ወደ ጌልጌላ አትሂዱ፥ ወደ ቤትአዌንም አትውጡ። ሕያው እግዚአብሔርን ብላችሁም አትማሉ።
\v 16 እስራኤል እንደ እልኽኛ ጊደር በእልኽኝነት ሄዳለችና፤ እንዴት እግዚአብሔር በለመለመ መስክ እንዳ ሉ ጠቦቶች ያሰማራታል?
\s5
\v 17 ኤፍሬም ራሱን ከጣዖታት ጋር አጣምሮአል፤ብቻውን ተውት።
\v 18 አስካሪ መጠጣቸው ባላቀ ጊዜ እንኳን ማመንዘራቸውን አያቆ ሙም፤ገዢዎቿም ነውራቸውን እጅግ ይወዳሉ።
\v 19 ነፋሱ በክንፎቹ ይጠቀልላታል፥ ከመሥዋዕቶቻቸውም የተነሳ ይፍራሉ።
\s5
\c 5
\p
\v 1 በእናንተ በሁላችሁ ላይ ፍርድ እየመጣ ነውና፤ ካህናት ሆይ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት ሆይ ልብ በሉ! የንጉሡ ቤት ሆይ ስሙ! እናንተ፥ በምጽጳ ላይ ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋል።
\v 2 ዓመጸኞች በማረድ እጅግ በርትተዋል፥ ሁሉንም እገራቸዋለሁ።
\s5
\v 3 ኤፍሬምን አውቀዋለሁ፥ እስራኤልም ከእኔ አልተሰወረችም። ኤፍሬም፥ አንተ አሁን እንደ ሴተኛ አዳሪ ሆነሃል፤ እስራኤልም ረክሳልች።
\v 4 ሥራቸው ወደ እኔ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱ አይፈቅድላቸውም፥ የአመንዝራነት መንፈስ በውስጣቸው አለ፥ እኔን እግዚአብሔርን አላወቁኝም።
\s5
\v 5 የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርባታል፤ ስለዚህ እስራኤልና ኤፍሬም በበደላቸው ይሰናከላሉ፤ ይሁዳም ከእነርሱ ጋር ትሰናከላለች።
\v 6 በጎቻቸውንና ከብቶቸውን ይዘው እግዚአብሔርን ፍልጋ ይሄዳሉ፥ ነገር ግን ከእነርሱ ተለይቶ ተመልሷልና አያገኙትም።
\v 7 ዲቃሎች ልጆችን ወልደዋልና ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም። አሁንም የወር መባቻ በዓላቱ እነርሱን ከእርሻቸው ጋር ይበሉአቸዋል።
\s5
\v 8 በጊብዓ መለከትን፥በራማም እንቢልታን ንፉ። «ቢንያም ሆይ እንከተልሃለን! » እያላችሁ የጦርነት ድምጽ አሰሙ።
\v 9 በቁጣው ቀን ኤፍሬም የፈረሰ ይሆናል። በእስራኤል ነገዶች መካከል በእርግጥ ሊሆን ያለውን አውጄአለሁ።
\s5
\v 10 የይሁዳ መሪዎች የድምበር ድንጋይ እንደሚነቅሉት ናቸው። ቁጣዬን በላያቸው እንደ ውኃ አፈስሳለሁ።
\v 11 ለጣዖታት ሊሰግድ ወስኖአልና ኤፍሬም ደቀቀ፥ በፍርድ ደቀቀ።
\s5
\v 12 እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፥ለይሁዳም ቤት እንደ ነቀዝ እሆናለሁ።
\v 13 ኤፍሬም በሽታውን ባየ ጊዜ፥ ይሁዳም ቁስሉን ባየ ጊዜ፤ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፥ ይሁዳም ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኞችን ላከ። ነገር ግን እርሱ ሊያድናችሁ፥ ቁስላችሁንም ሊፈውስ አልቻለም።
\s5
\v 14 ስለዚህ በኤፍሬም ላይ እንደ አንበሳ፥ በይሁዳም ላይ እንደ አንበሳ ደቦል እሆናለሁ። እኔ፥ አዎ እኔ፥ እገነጣጥላለሁ፥ እሄዳለሁ፥ እወስዳቸዋለሁ፥ የሚያድናቸውም ማንም የለም።
\v 15 በደላቸውን እስኪያውቁና ፊቴን እስኪፈልጉ ድርስ፥ በመከራቸው አጥብቀው እስኪፈልጉኝ ድረስ፥ እሄዳለሁ፥ ወድ ስፍራዬም እመለሳለሁ።
\s5
\c 6
\p
\v 1 ኑ ወደ እግዚአብሔር እንመለስ። እርሱ ገነጣጥሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ይፈውሰናል፤ እርሱ አቁስሎናል፥ ነገር ግን እርሱ ቁስላችንን አስሮ ይጠግናል።
\v 2 ከሁለት ቀን በኋላ ያበረታናል፥ በሦሥተኛው ቀን ያሥነሣናል፥ እኛም በፊቱ እንኖራለን።
\v 3 አወጣጡ እንደ ንጋት የታመነ ነው፤ እንደ ካፊያ፥ ምድሪቱን እንደሚያጠጣ እንደ ጸደይ ዝናብ ወደ እኛ ይመጣል።
\s5
\v 4 ኤፍሬም ሆይ ምን ላድርግልህ? ይሁዳ ሆይ ምን ላድርግልህ? ታማኝነታችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በጠዋት እንደሚጠፋ ጤዛ ነው።
\v 5 ስለዚህ በነቢያቱ ቆራረጥኋቸው፥ በአፌም ቃል ገደልኋቸው። ፍርዶችህ እንደሚያንጸባርቅ ብርሃን ናቸው።
\s5
\v 6 ታማኝነትን እሻለሁና፥መሥዋዕትንም አይደለም፥ከሚቃጠሉ መሥዋዕቶች ይልቅ እኔን እግዚአብሔርን ማወቅን እሻለሁ።
\v 7 እንደ አዳም ኪዳኑን አፍርሰዋል፤ ለእኔ ያልታመኑ ነበሩ።
\s5
\v 8 ገልዓድ የክፉ አድራጊዎች ከተማ ነው፥ በደም ዱካ ተሞልቷል።
\v 9 የቀማኞች ቡድን የሚዘርፉትን አድብተው እንደሚጠባበቁ፥ ካህናቱም በሴኬም መንገድ ላይ ሰው ለመግደል በቡድን ተደራጅተዋል፤ አሳፋሪም ወንጀል ይፈጽማሉ።
\s5
\v 10 በእስራኤል ቤት የሚያሰቅቅ ነገር አይቻለሁ፤ በዚያ የኤፍሬም ምንዝርና አለ፥ እስራኤልም ተበክሏል።
\v 11 የሕዝቤን ምርኮ በምመልስበት ጊዜ፥ ይሁዳ ሆይ ለአንተም መከር ተቀጥሮልሃል።
\s5
\c 7
\p
\v 1 ማታለልን ይለማመዳሉና እስራኤልን ለመፈወስ በፈለግሁ ጊዜ ሁሉ የኤፍሬም ኃጢአት፥ የሰማሪያም ክፋት ይገለጣል፤ ሌባ ወደ ውስጥ ይገባል፥ የቀማኞች ቡድን በመንገድ ላይ አደጋ ያደርሳል።
\v 2 ክፋታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ በልባቸው አይገነዘቡም። ሥራቸው ከቦአቸዋል፥ በፊቴም ናቸው።
\s5
\v 3 በክፋታቸው ንጉሡን፥ በሐሰታቸውም አለቆቹን ደስ ያሰኛሉ።
\v 4 የተቦካው ሊጥ ኩፍ እስኪል ድረስ እሳቱን መቆስቆስ እንድሚያቆም፥ ጋጋሪ እንደሚያነድበት ምድጃ፥ ሁሉም አመንዝራ ናቸው።
\v 5 በንጉሣችን ቀን አለቆች በወይን ጠጅ ትኩሳት ታመሙ። እርሱም ለፌዘኞች እጁን ዘረጋ።
\s5
\v 6 እንደ ምድጃ በሆነ ልባቸው፥ አታላይ እቅዶቻችውን ይወጥናሉ። ቁጣቸው ሌሊቱን ሁሉ ይጤሳል፥ በማለዳም እንደሚንቀለቀል እሳት እጅጉን ይነድዳል።
\v 7 ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፥ ግዢዎቻቸውንም ይበላሉ። ነገሥታቶቻቸው ሁሉ ወደቁ፥ ከመካከላቸውም ማንም ወደ እኔ አልተጣራም።
\s5
\v 8 ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቅ፥ ኤፍሬም ያልተገለበጠ ቂጣ ነው።
\v 9 እንግዶች ጉልበቱን በሉት፥ እርሱ ግን አላወቀም። ሽበትም ወጣበት፥ እርሱ ግን አላወቀም።
\s5
\v 10 የእስራኤል ትዕቢት ይመሰክርበታል፤ ነገር ግን ወደ አምላካቸው ወደ እግዚአብሔር አልተመለሱም፥ በዚህም ሁሉ አልፈለጉትም።
\v 11 ኤፍሬም ማስተዋል እንደሌላትና ተላላ እንደ ሆነች ርግብ ነው፤ ወደ ግብጽ ይጣራል፥ ወደ አሦርም ይበራል።
\s5
\v 12 ሲሄዱ መሬቤን እዘረጋባቸዋለሁ፥ እንደ ሰማይ አዕዋፍ አወርዳቸዋለሁ። እንደ መንጋ በሚተምሙብት እቀጣቸዋለሁ።
\v 13 ወዮ ለእነርሱ! ከእኔ ርቀው ሄደዋልና። ጥፋት ይመጣባቸዋል! በእኔ ላይ አምፀዋል! ላድናቸው ወደድሁ፥ እነርሱ ግን ሐሰትን ተናገሩብኝ።
\s5
\v 14 ከልባቸው ወደ እኔ አይጮኹም፥ ነገር ግን በአልጋዎቻችው ላይ ያለቅሳሉ። እህልና አዲስ ወይን ጠጅ ለማግኘት ራሳቸውን ለይተዋል፥ ከእኔም ዘወር ብለዋል።
\v 15 እኔ ባሠለጠናቸውም፥ ክንዶቻችውንም ባበረታ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን አሴሩብኝ።
\s5
\v 16 ተመልሰዋል፥ ነገር ግን ወደ እኔ ወደ ልዑሉ አልተመለሱም። ዒላማውን እንደ ሳተ ቀስት ናቸው። ከምላሳቸው ነውረኛነት የተነሳ አለቆቻችው በሰይፍ ይወድቃሉ። ይህም በግብጽ ምድር ለመሳለቂያ ይሆንባቸዋል።
\s5
\c 8
\p
\v 1 «መለከትን በከንፈሮችህ ላይ አድርግ። በእኔ በእግዚአብሔር ቤት ላይ ንስር እየመጣ ነው። ሕዝቡ ኪዳኔን አፍርሰዋልና በሕጌም ላይ አምጸዋልና ይህ ይሆናል።
\v 2 'አምላኬ፥ በእስራኤል ያለን እኛ እናውቅሃለን' እያሉ ወደ እኔ ይጮሃሉ።
\v 3 ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ጥሎአል፥ ጠላትም ያሳድደዋል።
\s5
\v 4 ነገሥታትን አነገሡ፥ በእኔ ግን አይደለም። እኔም ሳላውቅ መሳፍንቶችን አደረጉ። በብራቸውና በወርቃቸው ለራሳቸው ጣዖታትን ሠሩ፥ ነገር ግን ለጥፋታቸው ብቻ ነበር።»
\v 5 ነቢዩ፦« ሰማርያ ሆይ ጥጃህን ወዲያ ጥሎታል» አለ። እግዚአብሔር፦« ቁጣዬ በዚህ ህዝብ ላይ ነድዶአል። ሳይነጹ እስከ መቼ ይኖራሉ? አለ።
\s5
\v 6 ይህ ጣዖት ከእስራኤል የመጣ ነው፤ ባለሙያ ሠራው፥ እርሱ አምላክ አይደለም! የሰማርያ ጥጃ ይደቅቃል።
\v 7 ሕዝቡ ነፋስን ዘርተዋል፥ ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ። ያልተሰበሰበው እህል ዛላ የለውም፤ ዱቄትም አይገኝበትም። ለማፍራት ቢደርስም እንኳን እንግዶች ይበሉታል።
\s5
\v 8 እስራኤል ተውጦአል፤ በአሕዛብም መካከል እንደማይጠቅም ነገር ወድቀዋል።
\v 9 ሁሌ ብቻውን እንደሚሆን የዱር አህያ፥ወደ አሦር ሄደዋልና። ኤፍሬም ለራሷ ወዳጆችን ገዛች።
\v 10 በአሕዛብ መካከል ወዳጆችን ቢገዙም፥ እኔ እሁን አንድ ላይ እሰበስባቸዋለሁ። ከመሳፍንቱ ንጉሥ ጭ ቆና የተነሳም ሊመነምኑ ይጅምራሉ።
\s5
\v 11 ኤፍሬም ለኃጢአት ማስተሰሪያ መሠዊያ ቢያበዛም፥በዚያ ፈንታ ግን የኃጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆኑ።
\v 12 ሕጌን አሥር ሺህ ጊዜ ያህል ፃፍሁላቸው፥ እነርሱ ግን እንግዳ እንደ ሆነ ነገር ተመለከቱት።
\s5
\v 13 መሥዋዕቴን ይሠዋሉ፤ ሥጋ ይሠዋሉ፥ ይበሉታልም፤ እኔ እግዚአብሔር ግን አልተቀበልኳቸውም። አሁን ክፋታቸውን አስባለሁ፥ ኃጢአታቸውንም እቀጣለሁ። ወደ ግብጽ ይመለሳሉ።
\v 14 እስራኤል፥ እኔን ሠሪውን ረሳ፥ አብያተ መንግሥትንም ገነባ። ይሁዳ ብዙ ከተሞችን አጸና፥ እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰድዳለሁ፤ ምሽጎቹንም ታጠፋለች።
\s5
\c 9
\p
\v 1 እስራኤል ሆይ፥ አንተ የታመንክ አይደለህምና፥ አምላክህንም ትተሃልና፤ ሌሎች ሕዝቦች ደስ እንደሚላቸው፥ ደስ አይበልህ። በአውድዎች ሁሉ ላይ ሴተኛ አዳሪ የምትጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ወድደሃል።
\v 2 ነገር ግን አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፥ አዲሱ የወይን ጠጅም ይጥላታል።
\s5
\v 3 በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይኖሩም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ ደግሞም አንድ ቀን በአሦር የረከሰ ምግብ ይበላሉ።
\v 4 ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ ቁርባን አያፈሱም፤ ደስም አያሰኙትም። መስዋዕታቸው እንደ ሐዘንተኞች ምግብ ይሆንባቸዋል፦ የሚበሉት ሁሉ ይረክሳሉ። ምግባቸው ለእነርሱ ብቻ የሚሆን ነውና ወደ እግዚአብሔር ቤት ሊመጣ አይችልም።
\s5
\v 5 በእግዚአብሔር በዓል ቀን፥ በዓመት በዓል ቀን ምን ታድርጋላችሁ?
\v 6 ተመልከቱ፥ ከጥፋት ቢያመልጡ እንኳን ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ክምችታቸውን ሳማ ይውጠዋል፥ድንኳኖቻቸውንም እሾህ ይሞላዋል።
\s5
\v 7 የቅጣት ቀን እየመጣ ነው፥የበቀል ቀን እየመጣ ነው። እስራኤል ሁሉ ይህን ይወቅ። ከክፋትህና ከጠላትነትህ የተነሳ፤ ነቢዩ ሞኝ፥ በመንፈስ የሚነዳውም ሰው እብድ ሆኖእል።
\s5
\v 8 ከአምላኬ ጋር የሆነው ነቢይ የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ ነገር ግን የወፍ ወጥመድ በመንገዱ ሁሉ ነው፥በአምላኩም ቤት ጠላትነት አለበት።
\v 9 በጊብዓ ዘመን እንደነበረው ራሳቸውን እጅግ አርክሰዋል። እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል።
\s5
\v 10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥«እስራኤልን ያገኘሁበት ጊዜ፥ በምድረ በዳ ወይን እንደማግኘት ነበረ። እንደ በለስ ዛፍ የፍሬ ጊዜ የመጀመሪያ እሸት አባቶቻችሁን አገኘሁ።ነገር ግን ወደ ብዔልፌጎር ሄዱ፥ራሳቸውንም ለዚያ አሳፋሪ ጣዖት ሰጡ።እንደወደዱት ጣዖት እነርሱም የተጠሉ ሆኑ።
\s5
\v 11 የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይሄዳል።መውለድ፥ ማርገዝና መፀነስ የለም።
\v 12 ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳን፥ አንዳቸውም እሰከማይቀሩላቸው ድረስ እወስድባቸዋለሁ። ከእነርሱ ዘወር ባልሁ ጊዜ፥ ወዮ ለእነርሱ!
\s5
\v 13 ኤፍሬም እንደ ጢሮስ በለምለም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፥ ነገር ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለሚያርዳቸው አሳልፎ ይሰጣል።
\v 14 እግዚአብሔር ሆይ ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍ ማኅፀንና ወተት የማይሰጡ ጡቶች ስጣቸው።
\s5
\v 15 በጌልጌላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሳ፥ በዚያ እነርሱን መጥላት ጀመርኩ። ከክፉ ሥራቸው የተነሣ፥ ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ አልወዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመጸኞች ናቸው።
\s5
\v 16 ኤፍሬም በበሽታ ተመታ፤ሥራቸውም ደረቀ፥ ፍሬም አይሰጡም። ልጆች ቢወልዱም እንኳን፥ የተወደዱ ልጆቻቸውን እገድላለሁ።»
\v 17 አልታዘዙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል። በሕዝቦች መካከል ተንከራታች ይሆናሉ።
\s5
\c 10
\p
\v 1 እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ ያማረ ወይን ነው። ፍሬው በበዛ መጠን፥ መሠዊያ አብዝቶ ሠራ። ምድሩ አብዝቶ ባፈራ መጠን፥የተቀደሱ አ ምዶቹን አሳመረ።
\v 2 ልባቸው አታላይ ነው፥ አሁን በደላቸውን ሊሸከሙ ይገባል። እግዚአብሔር መሠዊያዎቻቸውን ያፈርሳል፤ የተቀደሱ አምዶቻቸውን ያጠፋል።
\s5
\v 3 አሁንም እነርሱ፦ «እግዚአብሔርን ስላልፈራን፥ ንጉሥ የለንም፤ ንጉሥሥ ምን ሊያደርግልን ይችል ነበር? » ይላሉ።
\v 4 ባዶ ቃላትን ይናገራሉ፥ በሐሠት መሃላም ኪዳን ያደርጋሉ። ስለዚህ ፍትሕ፥ በእርሻ ትልም ላይ እንደሚወጣ መርዛማ አረም ይወጣል።
\s5
\v 5 የሰማሪያ ነዋሪዎች ከቤትአዌን ጥጃዎች የተነሳ ይፈራሉ። በእነርሱና በውብታቸው ደስ ይሰኙ የነበሩ እነዚያ ጣዖት አምላኪ ካህናት እንደሚያልቅሱላቸው፣ ሕዝቡም ያለቅሱላቸዋል፤ ከእንግዲህ ወዲያ በዚያ የሉምና።
\v 6 ለታላቁ ንጉሥ እጅ መንሻ ወደ አሦር ይወሰዳሉ። ኤፍሬም ይዋረዳል፥ እስራኤልም የጣዖታትን ምክር በመከተሉ ያፍራል።
\s5
\v 7 የሰማርያ ንጉሥ፥ በውኃ ላይ እንዳለ የእንጨት ፍቅፋቂ ይጠፋል።
\v 8 የእስራኤል ኃጢአት የሆኑት፥ የክፋት ቅዱስ ቦታዎች ይጠፋሉ። እሾህና አሜክላ በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ። ሕዝቡ ተራሮችን፥ «ሸፍኑን! »፥ ኮረብታዎችንም፥ «ውደቁብን! » ይላሉ።
\s5
\v 9 እስራኤል ሆይ ከጊብዓ ዘመን አንስቶ ኃጢአት ሠራችሁ፥ በዚያም ጸንታችኋል። በጊብዓ ክፉ አድራጊዎች ላይ ጦርነት በድንገት አልደረሰባቸውምን?
\s5
\v 10 በወደድሁ ጊዜ እገሥጻቸዋለሁ። ሕዝቦች በአንድነት ይሰበሰቡባቸዋል፥ ስለ ድርብ ኃጢአታቸውም ያስሯቸዋል።
\v 11 ኤፍሬም እህል ማበራየት የምትወድ የተገራ ጊደር ነች፥ ስለዚህ በሚያምር ጫንቃዋ ላይ ቀንበር አኖራለሁ። በኤፍሬም ላይ ቀንበር አኖራለሁ፥ ይሁዳ ያርሳል፥ ያዕቆብም ብቻውን መከስከሻውን ይጎትታል።
\s5
\v 12 ጽድቅን ለራሳችሁ ዝሩ፥ የኪዳኑን ታማኝንት ፍሬም እጨዱ። እስኪመጣ፥ ጽድቅንም እስኪያዝንብባችሁ ድረስ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና፤ ያልታረሰ መሬታችሁን አለስልሱ።
\v 13 ክፋትን አረሳችሁ፥ግፍንም አጨዳችሁ። በስልታችሁና በወታደሮቻችሁ ብዛት ታምናችኋልና፥ የመታለልን ፍሬ በላችሁ።
\s5
\v 14 ስለዚህ በሕዝብህ መካከል የጦርነት ሽብር ይነሣል፥ የተመሸጉ ከተሞችህም ሁሉ ይጠፋሉ። እናቶች ከልጆቻችው ጋር እንደተከሰከሱበት፥ ስልማን በሰልፍ ቀን ቤትአርብኤልን እንዳጠፋበት ጊዜ ይሆናል።
\v 15 ስለዚህ ቤቴል ሆይ፥ ከታላቅ ክፋትሽ የተነሣ በአንቺም ላይ እንዲሁ ይሆናል። ንጋት ላይ የእስራኤል ንጉሥ ፈጽሞ ይጠፋል።»
\s5
\c 11
\p
\v 1 እስራኤል ወጣት በነበረበት ጊዜ ወደድኩት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።
\v 2 አብዝቶ በተጠሩ መጠን፥ አብዝተው ራቁ። ለበአል አማልክት ሠው፥ ለጣዖታትም አጠኑ።
\s5
\v 3 ሆኖም ግን ኤፍሬምን መራመድ ያስተማርኩት እኔ ነበርኩ። ክንዶቻቸውን ይዤ ያነሳኋቸው እኔ ነበርኩ፥ እነርሱ ግን የተጠነቀቅሁላቸው እኔ እንደሆንሁ አላወቁም።
\v 4 በሰው ገመድ፥ በፍቅርም ማሰሪያ መራኋቸው። የመንጋጋዎቻቸውን ማሰሪያ እንደሚያላላ ሆንኩላቸው፥ ዝቅ ብዬም መገብኳቸው።
\s5
\v 5 ወደ ግብጽ ምድር አይመለሱምን? ወደ እኔ መመለስን እምቢ በማለታቸው አሦር አይገዛቸውምን?
\v 6 ሰይፍ በከተሞቻቸው ላይ ይወድቃል፥ የበሮቻቸውንም መቀርቀሪያ ያጠፋል፤ከገዛ ራሳቸው ዕቅድ የተነሳ ያጠፋቸዋል።
\v 7 ሕዝቤ ከእኔ ዘወር ለማለት ቆርጦአል። በከፍታ ወደ አለሁት ወደ እኔ ቢጣሩ እንኳ፥ማንም አይረዳቸውም።
\s5
\v 8 ኤፍሬም ሆይ እንዴት እተውሃለሁ? እስራኤል ሆይ እንዴት አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴት እንደ አዳማ አደርግሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዮ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተለውጦአል፤ መላው ርኅራኄዬ ተነሣሥቷል።
\v 9 ጽኑ ቁጣዬን አላመጣም፤ ኤፍሬምን ዳግመኛ አላጠፋም። እኔ አምላ ክ እንጂ ሰው አይደለሁምና፥በመካከልህ ቅዱሱ ነኝና፥በቁጣ አልመጣም።
\s5
\v 10 እነርሱም ከእኔ ከእግዚአብሔር በኋላ ይመጣሉ። እንደ እንበሳ አገሳለሁ። በእርግጥ አገሳለሁ፥ ሕዝቡም ከምዕራብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ።
\v 11 ከግብጽ እንደ ወፍ፥ ከአሦርም ምድር እንደ ርግብ እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ። በየቤቶቻቸውም አኖራቸዋለሁ።» ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው።
\s5
\v 12 «ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በማታለል ከበበኝ። ይሁዳ ግን እስካሁን ከእኔ ከአምላኩ ጋር ጸንቷል፥ ለእኔም ለቅዱሱ የታመነ ነ ው።»
\s5
\c 12
\p
\v 1 ኤፍሬም ነፋስ ይመገባል፥ የምሥራቅንም ነፋስ ይከተላል። ሐሰትንና ዓመፅን ያለማቋረጥ ያበዛል። ከአሦር ጋር ኪዳን ያደርጋሉ፥ የወይራ ዘይትም ወደ ግብጽ ይወስዳሉ።
\v 2 እግዚአብሔር ከይሁዳ ጋር ሙግት አለው፥ ያዕቆብንም ስላደረገው ይቀጣዋል፥ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።
\s5
\v 3 ያዕቆብ በማሕፀን ውስጥ የወንድሙን ተረከዝ ያዘ፥ በጎልማስነቱም ከአምላክ ጋር ታገለ።ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ።
\v 4 አልቅሶም በፊቱ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለመነው። በቤቴል ከአምላክ ተገናኘ፥ በዚያም አምላክ ከእርሱ ጋር ተነጋገረ።
\s5
\v 5 እርሱም የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው፤የሚጠራበት ስሙም «እግዚአብሔር» ነው።
\v 6 ስለዚህ ወደ አምላካችሁ ተመለሱ። ለኪዳኑ ታማኝነትን፥እንዲሁም ፍትሕን ጠብቁ፤ሁል ጊዜም አምላካችሁን ተስፋ አድርጉ።
\s5
\v 7 ነጋዴዎቹ ሐሰተኛ ሚዛኖችን በእጆቻቸው ይዘዋል፤ ማጭበርበርን ይወዳሉ።
\v 8 ኤፍሬምም፦ «በእርግጥ እጅግ ባለጠጋ ሆኜአለሁ፥ ሀብትንም አግኝቼአለሁ። በሥራዬ ሁሉ ኃጢአት የሚሆን ምንም ዓይነት በደል አያገኙብኝም» ይላል።
\s5
\v 9 ከግብጽ ምድር አንስቶ ከአናንተ ጋር የሆንኩ አምላካችሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። እንደ ዓመት በዓላት ቀናት ዳግመኛ በድንኳኖች እንድትኖሩ አደርጋችኋለሁ።
\v 10 ለነቢያቶቹም ተናገርሁ፥ ስለ እናንተም ብዙ ራዕዮችን ሰጠኋቸው። በነቢይቶቹም አማካይነት ምሳሌዎችን ሰጠኋችሁ።»
\s5
\v 11 በገለዓድ ኃጢአት ካለ፥ በእርግጥ ሕዝቡ ከንቱ ነው። በጌልጌላ ወይፈኖችን ይሰዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸው በታረሰ መሬት ላይ እንዳለ የድ ንጋይ ክምር ይሆናሉ።
\v 12 ያዕቆብ ወደ ሶሪያ ምድር ሸሸ፤ እስራኤልም ሚስት ለማግኝት አገለገለ፥ ሚስትም ለማግኘት የበጎችን መንጋ ይጠብቅ ነበረ።
\s5
\v 13 እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢይም አማካይነት ተጠነቀቀለት።
\v 14 ነገር ግን እግዚአብሔር ይቆጣ ዘነድ ኤፍሬም ክፉኛ አነሳሳው። ስለዚህ ጌታው የደሙን በደል በእርሱ ላይ ይደርጋል፥ አሳፋሪም ስለ ሆነው ሥራው የሚገባውን ይከፍለዋል።
\s5
\c 13
\p
\v 1 «ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ መንቀጥቀጥ ነበረ። በእስራኤል መካከል ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ፥ ነገር ግን በአልን በማምለኩ በደለኛ ሆነ፥ ሞተም።
\v 2 አሁንም አብዝተው ኃጢአት ሠሩ። ከብራቸው የተቀረጸ ምስል ሠሩ፥ ጣዖታት በሚቻለው መጠን በጥበብ ተሠርተዋል፥ ሁሉም የባለ ሙያ ሥራ ናቸው። ሕዝቡ ስለ እነርሱ እንዲህ ይላሉ፦ 'እነዚህ የሚሠው ሰዎች ጥጃዎችን ይስማሉ።'
\s5
\v 3 ስለዚህ እንደ ማለዳ ደመና፥በጠዋት እንደሚጠፋ ጤዛ፥ከአውድማ ላይ በነፋስ እንደሚወሰድ እብቅ፣ከጪስ ማውጫ እንደሚወጣ ጢስ ናቸ ው።
\s5
\v 4 ነገር ግን ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ አታውቅም።
\v 5 በምድረ በዳ፥ በታላቅም የድርቀት ምድር አውቅሁህ።
\v 6 መሰማሪያ ባገኘህ ጊዜ ጠገብህ፥ በጠገብህም ጊዜ ልብህ ታበየ፤ከዚህም የተነሳ ረሳኽኝ።
\s5
\v 7 እንደ አንበሳ ሆንኩባቸው፥እንደ ነብርም በመንገዳቸው አደባለሁ።
\v 8 ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ አጠቃቸዋለሁ። ደረታቸውን ቀድጄ ከፍታለሁ፥በዚያም እንደ አንበሳ እበላቸዋለሁ፥ እንደ ዱር አራዊትም እገነጣጥላቸዋለሁ።
\s5
\v 9 እስራኤል ሆይ በረዳትህ በእኔ ላይ ዓምፀሃልና ጥፋትህ እየመጣ ነው።
\v 10 በከተማዎችህ ሁሉ ያድንህ ዘንድ ንጉሥህ አሁን ወዴት ነው? ስለ እነርሱ፥ 'ንጉሥና መሳፍንቶች ስጠኝ' ብለህ የተናገርክላቸው፥ ገዢዎችህ ወዴት ናቸው?
\v 11 በቁጣዬ ንጉሥ ሰጠሁህ፥ በመዓቴም አስወገድኩት።
\s5
\v 12 የኤፍሬም ክፋት ተደብሮአል፥በደሉም ተደብሮአል።
\v 13 የምጥ ሕመም ይመጣበታል፥ እርሱ ግን ጥበብ የጎደለው ልጅ ነው፤ ምክንያቱም የሚወለድበት ጊዜ ቢደርስም ከማኅጸን አይወጣም።
\s5
\v 14 በእርግጥ ከሲዖል ኃይል አድናቸዋለሁን? በእርግጥ ከሞትስ አድናቸዋለሁን? ሞት ሆይ መቅሰፍቶችህ ወዴት አሉ? ወደዚህ አምጣቸው። ሲዖል ሆይ ማጥፋትህ ወዴት አለ? ወደዚህ አምጣው። ርህራኄ ከዓይኖቼ ተሰወረ።
\s5
\v 15 ኤፍሬም በወንድሞቹ መካከል ባለጸጋ ቢሆንም እንኳን፥ የምሥራቅ ነፋስ ይመጣል፤ የእግዚአብሔር ነፋስ ከምድረ በዳ ይነፍሳል። የኤፍሬም ምንጭ ይደርቃል፥ ጉድጓዱም ውኃ አይኖረውም። ጠላቱ የተከበሩ ዕቃዎች ሁሉ ያሉበትን ግምጃ ቤቱን ይበዘብዛል።
\s5
\v 16 በአምላኳ ላይ ዐምፃለችና ሰማሪያ በደለኛ ትሆናለች። በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ብላቴኖቻቸውም ይከሰከሳሉ፥ እርጉዝ ሴቶቻቸውም ይቀደዳሉ።
\s5
\c 14
\p
\v 1 እስራኤል ሆይ ከክፋትህ የተነሳ ወድቀሃልና ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ተመለስ።
\v 2 የኑዛዜ ቃላት ያዝና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። እንዲህም በሉት፦« የከንፈሮቻችንን ፍሬ ምስጋናችንን እንሰዋልህ ዘንድ፤ክፋታችንን አስወግድ፥በቸርነትም ተቀበለን።
\s5
\v 3 አሦር አያድነንም፤ ለጦርነትም ፈረሶችን አንጋልብም። ወይም ከእንግዲህ የእጆቻችንን ሥራዎች 'እናንተ አምላኮቻችን ናችሁ' አንላቸውም፤ አባት አልባው እንኳ በአንተ ዘንድ ርኅራኄን ያገኛልና።
\s5
\v 4 ከተውኝም በኋላ ወደ እኔ በተመለሱ ጊዜ እፈውሳቸዋለሁ፤ እንዲያው እወዳቸዋለሁ፥ ቁጣዬ ከእርሱ ተመልሶአልና።
\v 5 እኔ ለእስራኤል እንደ ጠል እሆናለሁ፤ እንደ አበባ ያብባል፥ እንደ ሊባኖስም ዝግባ ሥር ይሰዳል።
\v 6 ቅርንጫፎቹ ይዘረጋሉ፤ ውበቱ እንደ ወይራ ዛፎች፥ ሽታውም እንደ ሊባኖስ ዝግባዎች ይሆናል።
\s5
\v 7 ከጥላው በታች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ይመለሳሉ፤እንደ እህል ይለመልማሉ፥ እንደ ወይንም ያብባሉ።ዝናውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል።
\v 8 ኤፍሬም፦ 'ከእንግዲህ ከጣዖታት ጋር ምን አለኝ?' ይላል። እኔ እመልስለታለሁ፥እጠነቀቅለታለሁም። እኔ ቅጠሎቹ ሁል ጊዜ ለመለም እን ደሆኑ እንደ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህም ከእኔ ይመጣል።»
\s5
\v 9 እነዚህን ነገሮች ያስተውል ዘንድ ጠቢብ የሆነ ማን ነው? ያውቃቸው ዘንድ እነዚህን ነገሮች የሚያስተውል ማን ነው? የእግዚአብሔር መንገዶች ትክክል ናቸው፥ ጻድቃንም ይሄዱባቸዋል፥ ዓመፀኞች ግን ይሰናከሉባቸዋል።

158
29-JOL.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,158 @@
\id JOL
\ide UTF-8
\h ትንቢተ ኢዩኤል
\toc1 ትንቢተ ኢዩኤል
\toc2 ትንቢተ ኢዩኤል
\toc3 jol
\mt ትንቢተ ኢዩኤል
\s5
\c 1
\p
\v 1 ወደ ባቱኤል ልጅ ወደ ኢዩኤል የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።
\v 2 እናንተ ሽማግሌዎች ይህን ስሙ፤በምድሪቱም የምትኖሩ ሁላችሁ አድምጡ። ይህ፥ከዚህ በፊት በእናንተ ወይም በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ያውቃልን?
\v 3 ይህንን ለልጆቻችሁ ንገሩ፥ልጆቻችሁም ለልጆቻቸው ይንገሩ፥የእነርሱም ልጆች ለሚቀጥለው ትውልድ ይንገሩ።
\s5
\v 4 ከአንበጣ መንጋ የተረፈውን ትላልቁ አንበጣ በላው፥ከትልቁ አንበጣ የተረፈውን ፌንጣ በላው፥ ከፌንጣ የተረፈውን አባ ጨጓሬ በላው።
\s5
\v 5 እናንተ ሰካራሞች ተነሡና አልቅሱ! አዲሱ የወይን ጠጅ ከአፋችሁ ተወግዶአልና እናንተ የወይን ጠጅ ጠጪዎች ዋይ በሉ።
\v 6 ቁጥር የሌለው ሕዝብ በምድሬ ላይ መጥቶአልና። ጥርሶቹ የአንበሳ ጥርሶች ናቸው፤የሴት አንበሳም ጥርሶች አሉት።
\v 7 የወይን ቦታዬን አስደንጋጭ ስፍ ራ አደረገው፤የበለስ ዛፌን መልምሎ ባዶውን አስቀረ። ቅርፊቱን ላጠው፥ጣለውም፤ቅርንጫፎቹም ነጡ።
\s5
\v 8 ለልጅነት ባሏ ሞት ማቅ እንደ ለበሰች ድንግል አልቅሱ።
\v 9 የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከእግዚአብሔር ቤት ተወግዷል፤የእ አብሔርም አገልጋዮች ካህናቱ አለቀሱ።
\v 10 እርሻው ጠፍቷል፥ምድሪቱም አለቀሰች። እህሉ ወድሟል፥አዲሱ ወይን ደርቋል፥ዘይቱም ተበላሽቷል።
\s5
\v 11 እናንተ ገበሬዎችና የወይን አትክልተኞች ስለ ስንዴዉና ስለ ገብሱ እፈሩ። የእርሻው መከር ጠፍቷልና።
\v 12 ወይኑ ጠውልጓል፥የበለስም ዛፎች ደርቀዋል፤የሮማን፥የተምርና የእንኮይ ዛፎች፥የእርሻው ዛፎች ሁሉ ጠውልገዋል። ደስታም ከሰው ልጆች ርቋል።
\s5
\v 13 የእህሉ ቁርባንና የመጠጡ ቁርባን ከአምላካችሁ ቤት ተቋርጧልና፥እናንተ ካህናት ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ! ፥እናንተ የመሠዊያው አገልጋዮች ዋይ በሉ። እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች ኑ ሌሊቱን በሙሉ ማቅ ላይ ተኙ።
\v 14 ቅዱስ ጾም አውጁ፥የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችንና በምድሪቱ የሚኖሩትን ሁሉ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ።
\s5
\v 15 የእግዚአብሔር ቀን ደርሷልና፥ወዮ ለዚያ ቀን! ከእርሱ ጋር ጥፋት ሁሉን ከሚችል አምላክ ይመጣል።
\v 16 ምግብ ከዓይናችን ፊት፥ ደስታና ሐሴት ከአምላካችን ቤት አልተወገደምን?
\v 17 ዘሩ በምድር ውስጥ በስብሷል፤እህሉ ደርቋልና ጎተራዎቹ ባዶ ሆነዋል፥ጎታዎቹም ፈርሰዋል።
\s5
\v 18 እንስሳት ምንኛ ጮኹ! መሰማሪያ የላቸውምና የቀንድ ከብት መንጎች ተሰቃዩ። የበግ መንጎችም ተሰቃዩ።
\v 19 እሳቱ የምድረ በዳውን ማሰማሪያ በልቷልና፥ነበልባሉም የጫካውን ዛፎች ሁሉ አቃጥሎአልና፤እግዚአብሔር ሆይ ወደ አንተ እጮሃለሁ።
\v 20 ጅረቶች ሁሉ ስለደረ ቁና እሳ ት የምድረ በዳውን ማሰማሪያ ስለ በላው፥የዱር እንስሳት እንኳን ወደ አንተ አለኽልኹ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 በጽዮን መለከት ንፉ፥ በቅዱስ ተራራዬም ላይ የማስጠንቀቂያ ድምጽ አሰሙ! የእግዚአብሔር ቀን መጥቷልና፥በእርግጥም ቅርብ ነውና፤የም ድሪቱ ነዋሪዎች ሁሉ በፍርሃት ይንቀጥቀጡ።
\v 2 እርሱም የጨለማና የጭጋግ ቀን፥የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው። ንጋት በተራሮች ላይ እንደሚዘረጋ፥ታላቅና ኃያል ሠራዊት እየመጣ ነው። እርሱን የመሰለ ሠራዊት ከቶ አልነበረም፥ከብዙ ትውልድ በኋላ እንኳን ዳግመኛ አይኖርም።
\s5
\v 3 በስተፊቱ እሳት ሁሉን ነገር ይበላል፥በስተኋላውም ነበልባል ይንቦገቦጋል። በስተፊቱ ምድሪቱ የዔደን ገነትን ትመስላለች፥በስተኋላው የሚገኘ ው ግን ባዶ ምድረ በዳ ነው።በእርግጥ፥ምንም ከእርሱ አያመልጥም።
\s5
\v 4 የሠራዊቱ ገጽታ እንደ ፈረስ ነው፥እንደ ፈረሰኛም ይሮጣሉ።
\v 5 በተራሮች ራስ ላይ እንደሚሄድ የሰረገላ ድምጽ፥ገለባውን እንደሚበላ የእሳት ነበለባል ድምጽ እያሰሙ፥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ኃያል ሠራዊት ያኮበኩባሉ።
\s5
\v 6 በፊታቸው ሰዎች ይታወካሉ፥የሁሉም ፊት ይገረጣል።
\v 7 እንደ ብርቱ ተዋጊዎች ይሮጣሉ፥እንደ ወታደሮችም በቅጥሩ ላይ ይዘላሉ፤እያን ዳንዱ እርምጃውን ጠብቆ ፥ሰልፋቸውንም ሳያፈርሱ፤ ይተማሉ።
\s5
\v 8 እያንዳንዱ መንገዱን ይሄዳል፥እርስ በእርሳቸው ሳይገፋፉ ይተማሉ፤ምሽጎችን ሰብረው ያልፋሉ፥ነገር ግን ከመስመራቸው አይወጡም።
\v 9 ከተማን በድንገት ያጠቃሉ፥በቅጥር ላይ ይሮጣሉ፥ቤቶች ላይ ይወጣሉ፥እንደ ሌቦችም በመስኮቶች ያልፋሉ።
\s5
\v 10 ምድር በፊታቸው ትንቀጠቀጣለች፥ሰማያትም ይናወጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ከዋክብትም ማብራታችውን ያቆማሉ።
\v 11 ተዋጊዎቹ እጅግ ብዙ ናቸውና፥ትእዛዙን የሚፈጽሙ ኃያላን ናቸውና፤ እግዚአብሔር በሠራዊቱ ፊት ድምጽን ያሰማል። የእግዚአብሔር ቀን ታላቅና የሚያስፈራ ነውና፤ ማን ሊቆም ይችላል?
\s5
\v 12 «አሁንም እንኳን» ይላል እግዚአብሔር፥«በፍጽም ልባችሁ ወደ እኔ ተመለሱ፤ጹሙ፥አልቅሱ፥እዘኑም።»
\v 13 ልብሳችሁን ብቻ ሳይሆን ልባችሁንም ቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁም ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ። እርሱ ቸርና መሐሪ፥ለቁጣ የዘገየ፥ፍቅሩ የተትረፈረፈ ነውና፤ስቃይ ካለብት ከዚህ ቅጣት መመለስ ይፈልጋል።
\s5
\v 14 ምናልባት ይመለስና ይራራ እንደሆነ፥ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህል ቁርባንና የመጠጥ ቁርባን የሚሆን በረከት በስተኋላው ያተርፍ እ ንደሆነ ማን ያውቃል?
\s5
\v 15 በጽዮን መለከት ንፉ፥የተቀደሰ ጾም አውጁ፥ የተቀደሰም ጉባዔ ጥሩ።
\v 16 ሕዝቡን ሰብስቡ፥የተቀደሰ ጉባዔ ጥሩ። ሽማግሌዎችን፥ልጆችን፥ የሚጠቡትንም ሕጻናት ሰብስቡ። ሙሽራው ከእልፍኛቸው፥ሙሽራይቱም ከጫጉላ ቤታቸው ይውጡ።
\s5
\v 17 የእግዚአብሔር አገልጋዮች፥ ካህናቱ፥ በቤት መቅደሱ መግቢያ ደጅና በመሠዊያው መካከል ያልቅሱ። እንዲህም ይበሉ፦«እግዚአብሔር ሆይ ለሕዝብህ ራራ፥አሕዛብ ይገዙአቸው ዘንድ ርስትህን ለእፍረት አሳልፈህ አትስጥ።በአሕዛብ መካከል አምላካቸው ወዴት ነው? ስለ ምን ይበሉ።»
\s5
\v 18 እግዚአብሔርም ስለ ምድሩ ቀና፥ለሕዝቡም ራራ።
\v 19 እግዚአብሔርም ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦«እነሆ፥ እህል፥አዲስ ወይንና ዘይት እልክላችኋለሁ። እናንተም በእነርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል ለውርደት አላደርጋችሁም።
\s5
\v 20 የሰሜንን ጥቃት ፈጻሚዎች ከእናተ አርቃለሁ፥ ወደ ደረቅና ወደ ተተወ ምድር እሰድዳቸዋለሁ። የሠራዊቱ ፊተኛ ጦር ወደ ምሥራቅ ባሕር፥ የሠራዊቱ ኋለኛ ጦር ወደ ምዕራብ ባሕር ይሄዳል። ግማቱ ይውጣል፥ክርፋቱም ይነሳል፤ታላላቅ ነገሮችንም አደርጋለሁ።»
\s5
\v 21 እግዚአብሔር ታላላቅ ነገሮችን አድርጓልና፤ ምድር ሆይ አትፍሪ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሴትም አድርጊ።
\v 22 የምድር እንስሶች ሆይ፥ የምድረ በዳ ማሰማሪያዎች ለምልመዋልና፥ ዛፎች ፍሬያቸውን አፍርተዋልና፥ የበለስ ዛፎችና ወይኖች ሙሉ ፍሬያቸውን ሰጥተዋልና፤አትፍሩ።
\v 23 የበልግን ዝናብ እንደሚገባ ይሰጣአችኋልና፥እንደ ቀድሞ ዘመን የበልግ ዝናብንና የፀደይን ዝናብ ያካፋላችኋልና፤ የጽዮን ሰዎች ሆይ፥ደስ ይበላችሁ፥ በአምላካችሁም በእግዚአብሔር ሐሴት አድርጉ።
\s5
\v 24 አውድማዎቹ በስንዴ ይሞላሉ፥መጥመቂያዎችም አዲስ ወይን ጠጅና ዘይት ያፈስሳሉ።
\v 25 በመካከላችሁ የላኩት ታላቁ ሠራዊቴ፥ የአንበጣ መንጋ፥ ትልቁ አንበጣ፥ ፌንጣና አባ ጮጋሬ የበሏቸውን የምርት ዓመታት እመልስላችኋለሁ።
\s5
\v 26 ተትረፍርፎ ትበላላችሁ፥ ትጠግባላችሁም፤ በመካከላችሁም ተዓምራት ያደረገውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ እፍረትን በሕዝቤ ላይ ከቶውኑ አላመጣም።
\v 27 እኔ በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደሆንኩ፥ ሌላም እንደሌለ፥ ከእንግዲህም ወዲይ እፍረትን በሕዝቤ ላይ ከቶውን እንደማላመጣ ታውቃላችሁ።
\s5
\v 28 ከዚያም በኋላ እንደዚህ ይሆናል፡- መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈስሳለሁ፥ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ። ሽማግሌዎቻችሁ ሕልም ያልማሉ፥ጎልማሶቻችሁም ራእይ ያያሉ።
\v 29 በእነዚያ ወራት በወንዶችና ሴቶች ባሪያዎች ላይም መንፈሴን አፈሳለሁ።
\s5
\v 30 በሰማያት ድንቆችን፥በምድርም ደም፥እሳትና የጢስ ዓምድ አሳያለሁ።
\v 31 ታላቁና የሚያስፈራው የእግዚአብሔር ቀን ከመምጣቱ በፊት፥ ፀሐይ ወደ ጨለማ፥ጨረቃም ወደ ደም ትለወጣለች።
\s5
\v 32 የእግዚአብሔርን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል። እግዚአብሔር እንደ ተናገርው፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚያመልጡ ይኖራሉ፤ከትሩፋኑም መካከል እግዚአብሔር የጠራቸው ይገኛሉ።
\s5
\c 3
\p
\v 1 እነሆ፥ በዚያ ወራትና በዚያ ጊዜ፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ምርኮኞች በምመልስበት ጊዜ፥
\v 2 አሕዛብን ሁሉ እሰበስባለሁ፥ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ። በአሕዛብ መካከል ከበተኑአቸው ከሕዝቤና ከርስቴ ከእስራኤል የተነሳ፥ ምድሬን ከመከፋፈላቸው የተነሳ፤ በዚያ እፈር ድባቸዋለሁ።
\v 3 በሕዝቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ወንድ ልጅን በሴተኛ አዳሪ ለወጡ፥ ሴት ልጅንም ለወይን ጠጅ ሸጡ፥ ጠጡም።
\s5
\v 4 ጢሮስና ሲዶና የፍልስጤምም ክፍለ አገራት ሁሉ፥አሁን በእኔ ላይ መቆጣታችሁ ለምንድ ነው? ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን? ብድራትን ብትመልሱልኝ፥ወዲያው ብድራታችሁን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
\v 5 ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋል፥የከበረውንም ሀብቴን ወደ ቤተ መቅ ደሳችሁ አግዛችኋል።
\v 6 ከግዛታቸው ልታርቋቸው፥ የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን ሰዎች ለግሪኮች ሸጣችኋል።
\s5
\v 7 እነሆ እነርሱን የሸጣችሁብትን ሥፍራ እንዲለቁ አደርጋቸዋለሁ፥ ብድራታችሁንም በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
\v 8 ወንዶችና ሴቶች ልጆ ቻችሁን በይሁዳ ሰዎች እጅ እሸጣለሁ። እነርሱም በሩቅ ላለ ሕዝብ፥ለሳባ ሰዎች ይሸጡአቸዋል። እግዚአብሔር ይህን ተናግሮአልና።
\s5
\v 9 ይህን በአሕዛብ መካከል አውጁ፦ ለጦርነት ተዘጋጁ፥ኃያላን ሰዎችን አነሣሡ፥ ይቅረቡ፥ ተዋጊዎችም ሁሉ ይውጡ።
\v 10 ማረሻችሁን ሰይፍ፥ ማጭዳችሁን ጦር ለማድረግ ቀጥቅጡ፤ ደካማውም «እኔ ብርቱ ነኝ » ይበል።
\s5
\v 11 እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ፈጥናችሁ ኑ፥ በአንድነትም ተሰብሰቡ። እግዚአብሔር ሆይ ኃያላን ተዋጊዎችህን ወደዚያ አውርድ።
\s5
\v 12 በዙሪያ ባሉ አሕዛብ ሁሉ ላይ ልፈርድ በዚያ እቀመጣለሁና፤ አሕዛብ ይነሡ፥ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ ይምጡ።
\v 13 መከሩ ደርሶአልና ማጭድ ላኩ፥ የወይኑ መጭመቂያ ሞልቶ እየፈሰሰ ነውና ኑ ወይኑን ርገጡ፥ ክፋታቸው በዝቶአልና።
\s5
\v 14 የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ውስጥ ቀርቦአልና፤ ሁካታ፥ በፍርድ ሸለቆ ውስጥ ሁካታ አለ።
\v 15 ፀሐይና ጨረቃ ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይከለክላሉ።
\s5
\v 16 እግዚአብሔር ከጽዮን ይጮኻል፥ከኢየሩሳሌም ድምጹን ከፍ አድርጎ ያሰማል። ሰማይና ምድር ይናወጣሉ፥ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መጠለያ፥ ለእስራኤልም ሕዝብ መመሸጊያ ይሆናል።
\v 17 «ስለዚህ በተቀደሰ ተራራዬ በጽዮን የምኖር እግዚአብሔር አምላካችሁ እኔ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ። ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ትሆናለች፥ ዳግመኛም ሠራዊት አያልፍባትም።
\s5
\v 18 በዚያን ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ተራሮች አዲስ ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ወተት ያፈስሳሉ፥የይሁዳ ጅረቶች ሁሉ ውኃ ያጎርፋሉ፥ ከእግዚአብሔር ቤት ምንጭ ይመነጫል፥ የሰጢምንም ሸለቆ ያጠጣል።
\v 19 በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ፈጽመዋልና፥ በምድራቸው የንጽሐንን ደም አፍስሰዋልና፤ ግብጽ ባድማ፥ ኤዶምም ምድረ በዳ ትሆናለች።
\s5
\v 20 ነገር ግን ይሁዳ ለዘላለም ይኖራል፥ኢየሩሳሌምም ከትውልድ ትውልድ ትኖራለች።
\v 21 ያልተበቀልኩትን ደማቸውን እበቀላለሁ፤» እግ ዚአብሔር በጽዮን ይኖራል።

50
31-OBA.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,50 @@
\id OBA
\ide UTF-8
\h ትንቢተ አብድዩ
\toc1 ትንቢተ አብድዩ
\toc2 ትንቢተ አብድዩ
\toc3 oba
\mt ትንቢተ አብድዩ
\s5
\c 1
\p
\v 1 የአብድዩ ራእይ። ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም እንዲህ ይላል፦ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምተናል፥ መልእክተኛውም በአሕዛብ መካከል ተልኮ፥«ተነሡ! እርሷን ለመውጋት እንነሣ» ብሎአል።
\v 2 አነሆ፥ በአሕዛብ መካከል ታናሽ አደርግሃለሁ፥እጅግ የተናቅህ ትሆናለህ።
\s5
\v 3 አንተ በዓለት ስንጣቂ ውስጥ፥በከፍታ ሥፍራ በሚገኝ ቤት የምትኖር፥ በልብህም «ማን ወደ ምድር ያወርደኛል? » የምትል ሆይ፥የልብህ ኩራት አታልሎሃል።
\v 4 እንደ ንስር እጅግ ከፍ ከፍ ብትል እንኳ፥ጎጆህም በከዋክብት መካከል ቢሆን እንኳ፥እኔ ከዚያ አወርድሃለሁ ይላል እግዚአብ ሔር።
\s5
\v 5 ሌቦች ወደ አንተ ቢመጡ፥ዘራፊዎች በሌሊት ቢመጡ (አንተ እንዴት ተቆረጥህ!) ፥የሚበቃቸውን ያህል ብቻ የሚሰርቁ አይደለምን? ወይን ለቃሚዎች ወደ አንተ ቢመጡ ቃርሚያ አያስቀሩምን?
\v 6 ዔሳው ምንኛ ተበረበረ፥የተደበቀ ሀብቱ ምንኛ ተዘረፈ?
\s5
\v 7 የተማማልሃቸው ሰዎች፥በጉዞህ ወደ ድንበር ይሰድዱሃል።ከአንተ ጋር መልካም ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች አታለሉህ፥አሸነፉህም። እንጀራህን የበሉ ከበታችህ ወጥመድ ዘረጉብህ። በእርሱም ዘንድ ማስተዋል የለም።
\v 8 በዚያ ቀን ከኤዶም ጥበበኞችን፥ ከዔሳውም ተራራ ማስተዋልን አላጠፋምን? ይላል እግዚአብሔር።
\v 9 ቴማን ሆይ፥ ሰው ሁሉ ከዔሳው ተራራ ታርዶ ይጠፋ ዘንድ፤፡ኃያላንህ ይደነግጣሉ።
\s5
\v 10 በወንድምህ በያዕቆብ ላይ ስለ ተፈጸመ ግፍ፥እፍረት ይከድንሃል፥ለዘላለምም ትጠፋለህ።
\v 11 እንግዶች ሀብቱን በዘረፉበት፥ባዕዳንም በበሮቹ በገቡበት፥በኢየሩሳሌምም ላይ ዕጣ በተጣጣሉበት ቀን፤አንተም ገለልተኛ ሆነህ በቆምህበት ቀን፥ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሆነሃል።
\s5
\v 12 ነገር ግን ወንድምህ በገጠመው ክፉ ቀን ሐሴት ማድረግ አይገባህም ነበር፥በጥፋታቸው ቀን በይሁዳ ሕዝብ ላይ መደሰት አይገ ባህም ነበር፤በጭንቀታቸው ቀን ትኩራራ ዘንድ አይገባህም ነበር።
\v 13 በጥፋታቸው ቀን በሕዝቤ በር ትገባ ዘንድ አይገባህም ነበር፥በጥፋታቸው ቀን በመ ከራቸው ሐሴት ማድረግ አይገባህም ነበር፤በጥፋታቸው ቀን ሀብታቸውን መዝረፍ አይገባህም ነበር።
\v 14 የሸሹትን ለመግደል በመስቀለኛ መንገድ ላይ ትቆም ዘንድ አይገባህም ነበር፤በጭንቀት ቀን የተረፉለትን አሳልፈህ መስጠት አይገባህም ነበር።
\s5
\v 15 የእግዚአብሔር ቀን በአሕዛብ ሁሉ ላይ ቀርቦአልና። እንዳደረግኽው እንዲሁ ይደረግብሃል፥ ሥራህ በገዛ ራስህ ላይ ይመለሳል።
\v 16 በቅዱስ ተራራዬ ላይ እንደጠጣችሁ፥ አሕዛብ ሁሉ ዘወትር ይጠጣሉ። ይጠጣሉ፥ ይጨልጡማል፤ ከዚህ በፊት እንዳልሆኑት ይሆናሉ።
\s5
\v 17 በጽዮን ተራራ ያመለጡ ይገኛሉ፥ እርሱም ቅዱስ ይሆናል፤ የያዕቆብም ቤት የገዛ ራሱን ርስት ይወርሳል።
\v 18 የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍ ቤት ነበልባል፥ የዔሳውም ቤት ገለባ ይሆናሉ፤ያቃጥሉታል፥ይበሉታልም። ከኤሳው ቤት የሚተርፍ አይኖርም፥እግዚአብሔር ተናግሮአልና።
\s5
\v 19 የኔጌብ ሰዎች የዔሳውን ተራራ ይወርሳሉ፥የቆላውም ሰዎች፦የፍልስጥኤማውያንን ምድር፥የኤፍሬምን ምድር፥ የሰማሪያንም ምድር ይወርሳሉ፤ብንያምም ገለዓድን ይወርሳል።
\s5
\v 20 የእስራኤል ሕዝብ ሠራዊት ምርኮኞች የከንዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ። በስፋራድም የሚኖሩ የእስራኤል ምርኮኞች የኔጌብን ከተሞች ይወርሳሉ።
\v 21 በዔሳው ተራራ ላይ ይፈርዱ ዘንድ ነጻ አውጪዎች ወድ ጽዮን ተራራ ይወጣሉ፤ መንግሥቱም የእግዚአብሔር ይሆናል።

107
32-JON.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,107 @@
\id JON
\ide UTF-8
\h ዮናስ
\toc1 ዮናስ
\toc2 ዮናስ
\toc3 jon
\mt ዮናስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ እንዲህ ሲል መጣ፤
\v 2 ‹‹ተነሣና ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ ክፏቷ ወደ ፊቴ ወጥቶአልና በእርሷ ላይ ስበክ፡፡››
\v 3 ዮናስ ግን ከያህዌ ፊት ኮበለለ፤ ወደ ተርሴስ ለመሄድም ተነሣ፡፡ ወደ ኢዮጴ ወረደ፡፡ ወደ ተርሴስ በምትሄድ መርከብ ተሳፈረ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ግን በባሕሩ ላይ ታላቅ ነፋስ ላከ፤ ከባድ ማዕበልም ተነሥቶ መርከቧን አናወጠ፤ ወዲያውኑ የምትሰበር መስሎ ታየ፡፡
\v 5 መርከበኞቹ በጣም ፈሩ፤ እያንዳንዱ ሰው ወደ አምላኩ ጮኸ ፡፡ የመርከቧ ክብደት እንዲቀልል በውስጧ የነበረው ሸክም ወደ ባሕሩ ተጣለ፡፡ ዮናስ ግን ወደ መርከቧ ታችኛ ክፍል ሄዶ ተኛ፤ ከባድ እንቅልፍ ላይም ነበር፡፡
\s5
\v 6 የመርከቧ አዛዥ ወደ እርሱ መጥቶ፣ ‹‹እንዴት ትተኛለህ? ተነሥና አምላክህን ጥራ! ምናልባትም አምላክህ ያስበንና ከጥፋት ያድነን ይሆናል፡፡ አለው፡፡
\v 7 እርስ በርሳቸውም፣ ይህ ክፉ ነገር የደረሰብን በማን ኃጢአት መሆኑን እንድናውቅ ኑ፣ ዕጣ እንጣጣል›› ተባባሉ፡፡ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ፡፡
\s5
\v 8 ከዚያም ዮናስን፣ ‹‹ይህ ክፉ ነገር የደረሰብን በማን ምክንያት እንደ ሆነ እባክህ ንገረን፡፡ ሥራህ ምንድነው? ከወዴትስ መጣህ? አገርህ የት ነው? ከየትኛውስ ሕዝብ ነህ? አሉት፡፡
\v 9 ዮናስም፣ ‹‹እኔ ዕብራዊ ነኝ፤ ባሕሩንና ደረቁን ምድር የፈጠረውን የሰማይን አምላክ ያህዌን አመልካለሁ›› አላቸው፡፡
\v 10 እርሱ ራሱ ነግሮአቸው ስለ ነበር ከያህዌ ፊት እየኮበለለ እንደ ነበር አወቁ፤ ስለዚህ የበለጠ ፈርተው፣ ‹‹ለመሆኑ፣ ምን እያደረግህ ነው? አሉ፡፡
\s5
\v 11 ባሕሩ ይበልጥ እየተናወጠ በመሄዱ፣ ሰዎቹ ዮናስን፣ ‹‹ባሕሩ ጸጥ እንዲልልን አንተ ላይ ምን ብናደርግ ይሻላል? አሉት፡፡
\v 12 ዮናስም፣ ‹‹አንሥታችሁ ወደ ባሕሩ ጣሉኝ፤ ያኔ ባሕሩ ጸጥ ይልላችኃል፤ ይህ ታላቅ ማዕበል የመጣባችሁ በእኔ ምክንያት እንደ ሆነ አውቃለሁ›› አላቸው፡፡
\v 13 ሰዎቹ ግን ወደ መሬት ለመመለስ የሚቻላቸውን ያህል ቀዘፉ፤ ይሁን እንጂ ባሕሩ የባሰ ይናወጥ ጀመረ፡፡
\s5
\v 14 ስለዚህም፣ ‹‹ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ሰው ነፍስ ምክንያት እንዳታጠፋን እንለምንሃለን፤ የዚህ ሰው ሞት እኛ ላይ አይሁንብን፤ ምክንያቱም አንተ ያህዌ የወደድኸውን አድርገሃል›› በማለት ወደ ያህዌ ጮኹ፡፡
\v 15 ዮናስንም አንሥተው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም መናወጡ ቆመ፡፡
\v 16 ሰዎቹም ያህዌን እጅግ ፈሩ፡፡ ለያህዌ መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለእርሱም ስእለትን ተሳሉ፡፡
\s5
\v 17 እግዚአብሔር ግን ዮናስን የሚውጥ ትልቅ ዓሣ አዘጋጀ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ዓሣው ሆድ ውስጥ ኖረ፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 ከዚያም ዮናስ ዓሣው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ ያህዌ ጸለየ፡፡
\v 2 እንዲህ አለ፤ ‹‹ተጨንቄ ሳለሁ ወደ ያህዌ ተጣራሁ፤ እርሱም መለሰልኝ፤ እርሱ እንዲረዳኝ ከጥልቁ መቃብር ጮኽኩ አንተም ጩኸቴን ሰማህ፡፡
\s5
\v 3 ጥልቅ ወደ ሆነው ወደ ባሕሩ መሠረት ጣልኸኝ፤ ፈሳሾች ዙሪያዬን ከበቡኝ፣ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላየ አለፈ፡፡
\v 4 እኔም፣ ከፊትህ ጠፋሁ፤ ሆኖም፣ እንደ ገና ወደ ቅዱስ መቅደስህ እመለከታለሁ›› አልሁ፡፡
\s5
\v 5 ሕይወቴን ለማጥፋት ውሆች ሸፈኑኝ፤ ጥልቁም በዙሪያዬ ነበረ፤ የባሕር ዐረም ራሴ ላይ ተጠመጠመ፡፡
\v 6 ወደ ተራሮች መሠረት ሰመጥሁ የምድርም በር ለዘላለም ተዘጋብኝ፤ ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ አንተ ሕይወቴን ከጥልቁ አወጣህ!
\s5
\v 7 ነፍሴ በዛለች ጊዜ ያህዌን አሰብሁት፤ ጸሎቴ ወደ አንተ ወደ ቅዱስ መቅደስህ መጣ፤፤
\v 8 ልባቸውን ከንቱ አማልከት ላይ የሚያደርጉ ለእነርሱ ያለህን ጸጋ ያጣሉ፡፡
\s5
\v 9 እኔ ግን፣ በምስጋና መዝሙር መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈጽማለሁ፡፡ ድነት ከያህዌ ዘንድ ነው፡፡
\v 10 ከዚም ያህዌ ዓሣውን አዘዘ ዮናስንም ደረቁ ምድር ላይ ተፋው፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ዮናስ መጣ፤
\v 2 ‹‹ተነሥተህ ወደ ታላቋ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔ የምነግርህንም መልእክት ስበክላት፡፡››
\v 3 ስለዚህም ዮናስ ለያህዌ ቃል በመታዘዝ ወደ ነነዌ ሄደ፡፡ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷን ዳር እስከ ዳር ለማዳረስ ሦስት ቀን ይወስድ ነበር፡፡
\s5
\v 4 ዮናስ ወደ ከተማዋ ገባ፤ ከአንድ ቀን ጉዞ በኃላ፣ ‹‹ነነዌ በአርባ ቀን ውስጥ ትገለበጣለች›› ብሎ ዐወጀ፡፡
\v 5 የነነዌም ሰዎች እግዚአብሔርን አመኑ፤ ጾምንም ዐወጁ፡፡ ከታላቁ እስከ ታናሹ ድረስ ሁሉም ማቅ ለበሱ፡፡
\s5
\v 6 ወሬውም ወደ ነነዌ ንጉሥ በደረሰ ጊዜ፣ ከዙፋኑ ወረደ፤ ልብሱን አወለቀ፣ ማቅም ለብሶ ዐመድ ላይ ተቀመጠ፡፡
\v 7 ከዚያም እንዲህ የሚል ዐዋጅ በነነዌ አስነገረ፤ ‹‹በንጉሡና በመኳንንቱ›› ሥልጣን ከነነዌ የወጣ ዐዋጅ፤ ሰውም ሆነ እንስሳ፣ የከብት መንጋም ሆነ የበግ ምጋ ምንም ነገር አይቅመስ አይብላ ውሃም አይጣጣ፡፡
\s5
\v 8 ሰውም ሆነ እንስሳ ማቅ ይልበስ፤ አጥብቆ ወደ እግዚአብሔር ይጮኽ፡፡ ሰው ሁሉ ከክፉ መንገዱ ይመለስ፤ ግፍ መሥራቱንም ይተው፡፡
\v 9 እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ራርቶ ከጽኑ ቁጣው ይመለስ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?
\s5
\v 10 እግዚአብሔርም ያደረጉትን፣ ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውንም አየ፡፡ በእነርሱ ላይ ሊያመጣ ያሰበውንም ጥፋት አላመጣም፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 ይህ ግን ዮናስን ደስ ስላላሰኘው በጣም ተቆጣ፡፡
\v 2 እንዲህ በማለትም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ‹‹ያህዌ ሆይ፣ ገና በአገሬ ሳለሁ ያልሁት ይህንኑ አልነበረምን? አንተ ቸርና ርኅሩኅ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየህ ምህረትህም የበዛ፣ ጥፋትን ከማምጣት የምትመለስ አምላክ መሆንህን ስለማውቅ ወደ ተርሴስ ለመኮብለል የሞከርኩት በዚሁ ምክንያት ነበር፡፡
\v 3 አሁንም ያህዌ ሆይ፣ ሕይወቴን እንድትወስድ እለምንሃለሁ፣ በሕይወት ከመኖር መሞት ይሻለኛል›› አለ፡፡
\s5
\v 4 ያህዌ ግን፣ ‹‹መቆጣትህ ተገቢ ነውን? አለው፡፡
\v 5 ከዚያም ዮናስ ከከተማዋ ወጥቶ በስተ ምሥራቅ በኩል ተቀመጠ፡፡ በዚያም ለራሱ ዳስ ሠርቶ በከተማዋ የሚደርሰውን ለማየት ከጥላው ሥር ተቀመጠ፡፡
\s5
\v 6 ያህዌ አምላክም አንድ ተክል አብቅሎ፣ የዮናስ ራስ ጥላ እንዲሆንና ትኩሳቱም እንዳያስጨንቀው ከበላዩ እንዲያድግ አደረገ፤ ዮናስም ስለ ተክሉ በጣም ደስ አለው፡፡
\v 7 ነገር ግን በሚቀጥለው ጠዋት ፀሐይ ስትወጣ አንድ ትል አዘጋጅቶ ያንን ተክል እንዲያጠቃ አደረገ፤ ተክሉም ጠወለገ፡፡
\s5
\v 8 ፀሐይ ስትወጣ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አመጣ፡፡ ፀሐዩ የዮናስንም ራስ አቃጠለ እርሱም ተዝለፈለፈ፡፡ ያኔ ዮናስ መሞት ፈልጐ፣ ‹‹ከመኖር መሞት ይሻለኛል›› አለ፡፡
\v 9 እግዚአብሔርም ዮናስን፣ ‹‹ስለ ተክሉ መቆጣትህ ተገቢ ነውን? አለው፡፡ ዮናስም፣ ‹‹አዎን፣ እንዲያውም እስከ ሞት ድረስ መቆጣት ይገባኛል›› አለ፡፡
\s5
\v 10 ያህዌ እንዲህ አለ፣ ‹‹አንተ እንዲበቅል ወይም እንዲያድግ ላልደከምህበት ተክል ይህን ያህል አዝነሃል፤ በአንድ ሌሊት በቀለ፤ በአንድ ሌሊትም ደረቀ፡፡
\v 11 ታዲያ፣ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺህ በላይ ሰዎችና እንስሶች ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን የለብኝምን? ፡፡››

228
33-MIC.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,228 @@
\id MIC
\ide UTF-8
\h ትንቢተ ሚክያስ
\toc1 ትንቢተ ሚክያስ
\toc2 ትንቢተ ሚክያስ
\toc3 mic
\mt ትንቢተ ሚክያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በይሁዳ ንጉሦች በአዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የያህዌ ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፡፡
\s5
\v 2 እናንት ሕዝቦች ስሙ ምድርና በውስጧ የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፡፡ ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣ ጌታ ያህዌም ይመሰክርባችኃል፡፡
\v 3 ተመልከቱ፤ ያህዌ ከመኖሪያው ስፍራ ይመጣል፤ ‹ወርዶም፣ በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል፡፡
\v 4 ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ ሸለቆዎች ይሰነጠቃሉ እሳት ፊት እንዳለም ሰም በገደል ላይ እንደሚወርድ ውሆች ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 5 ይህ ሁሉ የሚሆነው ከያዕቆብ ዐመፅ ከእስራኤልም ቤት ኃጢአት የተነሣ ነው፡፡ የያዕቆብ ዐመፅ ምክንያት ምን ነበር? ሰማርያ አይደለችምን? የይሁዳስ ኮረብታ መስገጃ ምንድው? ኢየሩሳሌም አይደለችምን?
\s5
\v 6 ስለዚህ ሰማርያን ሜዳ ላይ እንዳለ ፍርስራሽ ክምር፣ ወይን እንደሚተከልባትም ቦታ አደርጋታለሁ፡፡ የከተማዋን ፍርስራሽ ድንጋይ ወደ ሸለቆው አወርዳለሁ፤ መሠረቶችዋንም እገልጣለሁ፡፡
\v 7 ምስሎቿ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ ለእርሷ የተሰጡ ስጦታዎችም ይቃጠላሉ፡፡ ጣዎቶችዋም ሁሉ ለጥፋት ይሆናሉ፡፡ እነዚህን የሰበሰበችው ለዝሙት ሥራዋ ካገኘችው ገጸ በረከት እንደ ነበር ሁሉ አሁንም ገጸ በረከትዋ የዝሙት አዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 በዚህ ምክንያት ዋይ ዋይ እያልሁ አለቅሳለሁ፤ ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤ እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ እንደ ጉጉትም አለቅሳለሁ፡፡
\v 9 ቁስሏ የማይፈወስ ነውና ለይሁም ተርፏል፡፡ ወደ ሕዝቤ ደጅ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ደርሷል
\v 10 በጌት አታውሩ፣ ከቶም አታልቅሱ በቤትዓፍራ ትቢያ ላይ እንከባለላለሁ
\s5
\v 11 እናንት በሻፊር የምትሮሩ ዕርቃናችሁን ሆናችሁ እለፉ፡፡ በጸዓናን የሚኖሩ ከዚያ አይወጡም፡፡ ቤትዔጼል ሐዘን ላይ ስለሆነች መጠጊያ ልትሆን አትችልም፡፡
\v 12 የማሮት ነዋሪዎች መልካም ዜና ለመስማት እጅግ ጓጉተዋል፤ ምክንያቱም ከያህዌ ዘንድ ጥፋት እስከ ኢየሩሌም ደጆች መጥቷል፡፡
\s5
\v 13 እናንት በለኪሶ የምትኖሩ የሰረገሎችን ፈረሶች ለጉሙ፣ ለጽዮን ሴት ልጅ ኃጢአት መጀመሪያ እናንተ ነበራችሁ፡፡ የእስራኤልም በደል አንተ ዘንድ ተገኝቷል፡፡
\v 14 ስለዚህ እናንተ ለሞሬሴት ጌት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብም ከተሞች የእስራኤልን ንጉሦች ያታልላሉ፡፡
\s5
\v 15 እናንት በመሪሳ የምትኖሩ ወራሪ አመጣባችኃለሁ፡፡ የተከበሩ የእስራኤል መሪዎች በዓዶላም ዋሻ ይሸሸጋሉ፡፡
\v 16 ደስ ትሰኙባቸው ለነበሩ ልጆቻችሁ በማዘን ራሳችሁን ተላጩ ጡራችሁን ተቆረጡ ራሳችሁን እንደ ንስር ራስ ተመለጡት ምክንያቱም ልጆቻችሁ በምርኮ ከእናንተ ይወሰዳሉና፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 ክፉ ነገር ለማድረግ ለሚያቅዱ መኝታቸው ላይ ሆነው ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው፡፡ ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን ሥራ ላይ ያውሉታል፡፡
\v 2 የዕርሻ ቦታ ሲፈልጉ፣ ቀምተው ይወስዳሉ ቤት ሲፈልጉ ነጥቀው ይወስዳሉ፡፡ የሰው መብት ረግጠው ሀብቱን ይዘርፋሉ
\s5
\v 3 ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት አመጣለሁ ከዚህም ልታመልጡ አትችሉም፡፡ ያ የመከራ ጊዜ ስለሚሆን ከእንግዲህ በእብሪት አትኖሩም፡፡
\v 4 በዚያ ቀን ጠላቶቻችሁ ይሳለቁባችኃል በሐዘን እንጉርጉሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኃል እኛ እስራኤላውያን ፈጽሞ ጠፍተናል ያህዌ የሕዝቤን ንብረት ወስዶ ርስታችንንም ለከሐሂዲዎች አከፋፈለ
\v 5 ስለዚህ እናንተ ባለጸጐች በያህዊ ጉባኤ ውስጥ ርስት በዕጣ የሚከፋፈሉ ልጆች አይኖሯችሁም፡፡
\s5
\v 6 ‹‹ትንቢት አትናገር›› ምንም ውርደት አይደርስብንም፤ ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር ይላሉ፡፡
\v 7 የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ እንደህ መባል ነበረበትን? የያህዌ ትዕግሥት አልቋልን? እነዚህስ የእርሱ ድርጊቶች ናቸውን? አካሄዳቸው ቀና ለሆነ ሰዎች ቃሎቼ መልካም አያደርጉምን?
\v 8 በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ በጠላትነት ተነሥታችኃል ከጦርነት በኃላ ሰላም ነው ብለው ወደሚያስቡት እንደሚመለሱ ወታደሮች ምንም ሳይጠራጠሩ የሚያልፉ ሰዎችን ልብስ ገፋችኃል፡፡
\s5
\v 9 የወገኔን ሴቶች ከሚወዱት ቤታቸው አባረራችሁ በረከቴን ለዘላለም ከልጆቻቸው ወሰዳችሁ፡፡
\v 10 በርኩሰት ምክንያት ከባድ ጥፋት ስለሚመጣ እዚህ ቦታ መቆየት አትችሉም፤ ስለዚህ ተነሥታችሁ ሂዱ፡፡
\v 11 አንድ ሰው በሐሰት መንፈስ ተነሣሥቶ ‹‹ስለ ወይን ጠጅና ጠንካራ መጠጥ ትንቢት እናገራለሁ›› ቢል፤ በእነዚህ ሰዎች ዘንድ እንደ ነቢይ ይቆጠራል፡፡
\s5
\v 12 ያዕቆብ ሆ በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤ የእስራኤልን ትሩፍ ጉረኖ ውስጥ እንዳለ በጐች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ አመጣቸዋለሁ፡፡ ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታላቅ ጩኸት ይሆናል፡፡
\v 13 መንገዳቸውን የሚከፍትላቸው መሪ ከእነርሱ ፊት ፊት ይሄዳል እነርሱም ተግተልትለው በበሩ ይወጣሉ ንጉሣቸው ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤ ያህዌ መሪያቸው ይሆናል፡፡
\s5
\c 3
\p
\v 1 ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤ ‹‹እናንተ የያዕቆብ መሪዎች የእስራኤልም ቤት ገዦች አድምጡ፤ ፍትሕን ማወቅ ይገባችሁ አልነበረምን?
\v 2 እናንተ ግን መልካሙን ጠላችሁ ክፉን ወደዳችሁ ቆዳቸውን ገፈፋችሁ ሥጋቸውን ከአጥንታቸው ጋጣችሁ የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ ቆዳቸውን ገፈፋችሁ ዐጥንቶቻቸውን ሰባበራችሁ፤ በመጥበሻ እንደሚጠበስ በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቆራረጣችኃቸው፡፡
\v 3 እናንተ መሪዎች ወደ ያህዌ ትጮኻላችሁ እርሱ ግን አይሰማችሁም፡፡ ከክፉ ሥራችሁ የተነሣ በዚያ ጊዜ ፊቱን ከእናንተ ይሰውራል፡፡
\s5
\v 4 ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት ያህዌ እንዲህ ይላል፤
\s5
\v 5 ‹‹ጥቅም የሚያገኙበት ሲሆን፣ ‹‹ብልጽግና ይሆናል›› ይላሉ፤ ጥቅም በማያገኙበት ጊዜ ግን፣ ‹ጦርነት ይመጣባችኃል› እያሉ በማወጅ ሕዝቡን ያስታሉ፡፡
\v 6 ስለዚህ ራእይ የማታዩበት ሌሊት ይሆንባችኃል ሌሊት ስለሚሆንባችሁ ንግርት አታደርጉም፡፡ በነቢያት ላይ ፀሐይ ትጠልቅባቸዋለች ቀኑ እነርሱ ላይ ይጨልማል፡፡
\v 7 ባለ ራእዮች ያፍራሉ ንግርተኞችም ይዋረዳሉ ከእኔ ዘንድ መልስ የለምና ሁሉም ፊታቸውን ይሸፍናሉ፡፡
\s5
\v 8 እኔ ግን፣ ለያዕቆብ በደሉን ለእስራኤል ኃጢአቱን እንድናገር በያህዌ መንፈስ ኃይል ተሞልቻለሁ ፍትሕና ብርታትንም ተሞልቻለሁ፡፡
\s5
\v 9 እናንት የያዕቆብ ቤት መሪዎች ፍትሕ የምትጠሉ፣ ቀና የሆነውን የምታጣምሙ የእስራኤል ቤት ገዦች ይህን ስሙ፡፡
\v 10 ጽዮንን ደም በማፍሰስ ኢየሩሳሌምን በርኩሰት የምትገነቡ ስሙ
\v 11 መሪዎቻችሁ በጉቦ ይፈርዳሉ ካህናቶቻችሁ በዋጋ ያስተምራሉ ነቢያቶቻችሁ በገንዘብ ንግርት ይናገራሉ፡፡ ያም ሆኖ በያህዌ በመተማመን፣ ‹‹ያህዌ ከእኛ ጋር ስለሆነ ክፉ ነገር አይደርስብንም›› ይላሉ፡፡
\s5
\v 12 ስለዚህ በእናንተ ምክንያት ጽዮን እንደ ማሳ ትታረሳለች፤ ኢየሩሳሌም የፍርስራሽ ክምር ትሆናለች የቤተ መቅደሱ ኮረብታ ጥቅጥቅ ያለ ደን ይሆናል፡፡
\s5
\c 4
\p
\v 1 በመጨረሻው ዘመን የያህዌ ቤት ተራራ ሌሎች ተራቶች ላይ ይመሠረታል ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ይላል ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ፡፡ ብዙ ሕዝቦች መጥተው እንዲህ ይላሉ
\s5
\v 2 ‹‹ኑ ወደ ያህዌ ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንሂድ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል እኛም በመንገዱ እንሄዳለን፡፡ ሕግ ከጽዮን፣ የያህዌም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣል፡፡
\v 3 እርሱ በብዙ ሕዝብ መካከል ይፈርዳል በሩቅ ባሉ ሕዝቦችም ላይ ይበይናል፡፡ ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጉታል፡፡ መንግሥት በመንግሥት ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ከእንግዲህ የጦር ትምህርት አይማሩም፡፡
\s5
\v 4 ይልቁን፣ እያንዳንዱ ሰው ከገዛ ወይኑ ሥር ከገዛ በለሱም ሥር ይቀመጣል፡፡ የሰራዊት አምላክ ያህዌ ተናግሮአልና የሚያስፈራቸው አይኖርም፡፡
\v 5 ሕዝቦች ሁሉ በአምላኮቻቸው ስም ይሄዳሉ፡፡ እኛ ግን በአምላካችን በያህዌ ስም ለዘላለም እንሄዳለን
\s5
\v 6 በዚያ ቀን ይላል ያህዌ፣ አንካሳውን እሰበስባለሁ ስደተኞችና ሐዘንተኞች ያደረግኃቸውን እሰበስባለሁ፡፡
\v 7 አንካሳውን ወደ ተረፉት ወገኖች የተገፉትንም ወደ ብርቱ ሕዝብ እመልሳለሁ፤ እኔ ያህዌ በጽዮን ተራራ ከዘላለም እስከ ዘላለም እነግሣለሁ፡፡
\v 8 አንተ የመጠበቂያው ማማ፣ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ የቀድሞው ግዛትህ፣ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ይመለስልሃል፡፡
\s5
\v 9 አሁንስ እንደዚህ የምትጮኺው ለምንድነው? በመካከልሽ ንጉሥ የለምን? ምጥ እንደ ያዛት ሴት የምትጨነቂው መካሪሽ ስለጠፋ ነውን?
\v 10 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ምጥ እንደያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁን ከከተማ ወጥተሸ ሜዳ ላይ ስፈሪ ወደ ባቢሎንም ትሄጃለሽ፡፡ በዚያም ከጠላት እጅ ትድኛለሽ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ ይታደግሻል፡፡
\s5
\v 11 አሁን ግን፣ ብዙ ሕዝቦች አንቺ ላይ ተሰብስበዋል እነርሱም፣ ‹‹የረከሰች ትሁን፤ እኛም መፈራረስዋን እንይ›› ብለዋል፡፡
\v 12 ነቢዩ እንዲህ ይላል፤ ‹‹የያህዌን ሐሳብ አያወቁም የእርሱንም ዕቅድ አያስተውሉም፤ እርሱ ዐውድማ ላይ እንደ ነዶ ይሰበስባቸዋል፡፡››
\s5
\v 13 ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ‹‹ቀንድሽን እንደ ብረት፣ ሰኮናሽን እንደ ናስ አደርጋለሁ ብዙ ሕዝቦችን ታደቂያለሽ የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ተነሥተሸ አበራዪ፡፡ በግፍ የሰበሰቡትን ሀብት ለራሴ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ አቀርባለሁ፡፡››
\s5
\c 5
\p
\v 1 አንቺ የወታደር ከተማ ሰራዊትሽን አሰልፊ ከበባ ተደርጐብናልና የእስራኤልን ገዥ ጉንጩን በበትር ይመቱታል፡፡
\s5
\v 2 አንቺ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ ጅማሬው ከጥንት ከዘላለም ዘመናት የሆነ የእስራኤል ገዥ ከአንቺ ይወጣልኛል፡፡
\v 3 ስለዚህ ያማጠችው ልጅ እስክትወልድ ድረስ እግዚአብሔር ሕዝቡን ይተዋቸዋል የተቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ፡፡
\s5
\v 4 በያህዌ ብርታት፣ በአምላኩ በያህዌ ስም ክብር ጸንቶ ይቆማል፤ መንጋውንም ይጠብቃል፡፡ በዚያ ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ስለሚደርስ ተደላድለው ይኖራሉ፡፡
\v 5 እርሱ ሰላማችን ይሆናል፡፡ አሦራውያን ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ምሽጐቻችንም ሲገሠግሡ ሰባት እረኞችን፣ እንዲሁም ስምንት መሪዎችን እናስነሣባቸዋልን፡፡
\s5
\v 6 እነዚህ ሰዎች የአሦርን ምድር በሰይፍ፣ የናምሩዱንም ምድር እጃቸው ላይ ባለው ሰይፍ ይገዛሉ፡፡ ወደ ምድራችን ሲመጡ ወደ ድንበራችንም ሲገሠግሡ እርሱ ከአሦራውያን ይድነናል፡፡
\v 7 የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝብ መካከል ከያህዌ ዘንድ እንደሚወርድ ጠል፣ ሣር ላይ እንደሚጥል ካፊያ ሰውን እንደማይጠብቅ፣ በሰው ልጆችም እንደማይተማመን ሰው ይሆናል፡፡
\s5
\v 8 የያዕቆብ ትሩፍ በሕዝቦች መካከል፣ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይሆናል፤ በዱር አራዊት መካከል እንዳለ አንበሳ፣ በበጐች መካከል እንዳለ አንበሳ ደቦል ይሆናል፡፡ በእግሩ እየረጋገጠ ይቦጫጭቃቸዋል፤ የሚያድናቸውም አይኖርም፡፡
\v 9 እጅህ በጠላቶችህ ላይ ከፍ ከፍ በማለት ያጠፋቸዋል፡፡
\s5
\v 10 በዚያ ቀን ይላል ያህዌ ‹‹ፈረሶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ ሠረገሎቻችሁንም እደመስሳለሁ፡፡
\v 11 የምድራችሁን ከተሞች አጠፋለሁ ምሽጐቻችሁንም ሁሉ አፈርሳለሁ፡፡
\s5
\v 12 በምድራችሁ ያለውን ጥንቆላ አጠፋለሁ ከእንግዲህ አታሟርቱም፡፡
\v 13 የተቀረጹ ምስሎቻችሁንና የድንጋይ ዐምዶቻችሁን ከመካከላችሁ አጠፋለሁ፡፡ ከእንግዲህ የእጆቻችሁን ሥራ አታመልኩም፡፡
\v 14 የአሼራ ምሰሶዋችሁን ከምድራችሁ እነቅላለሁ ከተሞቻችሁንም አጠፋለሁ፡፡
\v 15 ያልታዘዙኝን ሕዝቦች በቀጣዬና በመዓቴ እበቀላሁ፡፡››
\s5
\c 6
\p
\v 1 እንግዲህ ያህዌ የሚናገረውን አድምጡ፤ ‹‹ተነሡ፤ ያላችሁንም ቅርታ በተራሮች ፊት አቅርቡ ኮረብቶችም የምትሉትን ይስሙ፡፡
\v 2 እናንተ ተራሮች እናንተ ጸንታችሁ የቆማችሁ የምድር መሠረቶች ያህዌ የሚያቀርበውን ክስ አድምጡ፤ እርሱ ከእስራኤል ጋር ይፋረዳል፡፡››
\s5
\v 3 ‹‹ሕዝቤ ሆይ፣ ምን አደረግሁህ? ያታከትሁህስ በምንድነው? እስቲ መስክርብኝ!
\v 4 እኔ ከግብፅ ምድር አወጣሁህ ከባርነት ቤትም ታደግሁህ፡፡ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ወደ አንተ ላክሁ፡፡
\v 5 ሕዝቤ ሆይ፣ የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ ያቀደብህን የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትን፣ ከሺጡም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ ስትሄድ፣ እኔ፣ ያህዌ ያደረግሁትን የጽድቅ ሥራ ታውቅ ዘንድ አስታወስ፡፡
\s5
\v 6 ለልዑል አምላክ ለመስገድ በምመጣበት ጊዜ፣ ለያህዌ ምን ይዤ ልምጣ? የሚቃጠል መሥዋዕት እንዲሆኑ የአንድ ዓመት ጥጃ ይዤ ልምጣን?
\v 7 በሺህ የሚቆጠሩ ዐውራ በጐችን ወይስ የአሥር ሺህ ወንዞች የሚያህል ዘይት ባቀርብለት ያህዌ ይደሰት ይሆን? ስለ መተላለፌ የበኩር ልጄን፣ ስለ ኃጢአቴስ የአካሌን ፍሬ ልስጥን?
\v 8 ሰው ሆይ፣ መልካሙን፣ ያህዌ ከአንተ የሚፈልገውን ነግሮሃል ፍትሕ አድርግ፤ ደግነትን ውደድ፤ ከአምላክህ ጋር በትሕትና ተመላለስ፡፡
\s5
\v 9 የያህዌ ድምፅ ከተማዋን ይጣራል አሁን እንኳ ጥበብ ስምህን ትገነዘባለች በትሩን አስታውስ፤ በቦታው ያደረገው ማን እንደ ሆነ አስታውስ፡፡
\v 10 ክፉው ቤት ውስጥ በግፍ የተገኘ ሀብት አስጸያፊ የሆነ ሐሰተኛ መስፈሪያ አለ፡፡
\s5
\v 11 ዐባይ ሚዛን የሚጠቀመውን ሰው፣ ሐሰተኛ መመዘኛ በከረጢት የቋጠረውን ሰው ንጹሕ ላድርገውን?
\v 12 ባለ ጠጐች በግፍ ተሞልተዋል በዚያ የሚኖሩ ሐሰት ተናግረዋል ምላሳቸው አታላይ ናት፡፡
\s5
\v 13 ስለዚህ በጽኑ ቁስል መታሁህ ከኃጢአትህ የተነሣም አፈረስሁህ፡፡
\v 14 ትበላለህ ግን አትጠግብም ሁሌም ባዶነት ውስጥህ ይኖራል፡፡ ታከማቻለህ ግን አይጠራቀምልህም ያጠራቀምኸውን ለሰይፍ እዳርጋለሁ፡፡
\v 15 ትዘራለህ ግን አታጭድም የወይራ ፍሬ ትጨምቃለህ፤ ግን ዘይት አትቀባም፤ ወይን ትጨምቃህ ግን ጠጅ አትጠጣም፡፡
\s5
\v 16 የዖምሪን ሥርዐት የአክዓብን ቤት ተግባርም አጥብቀህ ይዘሃል በምክራቸው መሠረት ኖረሃል፡፡ ስለዚህ አንተንና ከተማህን ለውድመት ሕዝብህንም ለመዘባበቻ አሳልፌ እሰጣለሁ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ ትሸከማለህ፡፡
\s5
\c 7
\p
\v 1 ለእኔ ወዮልኝ! የመከር ጊዜ ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ካበቃ በኃላ እርሻ ውስጥ እንደ ቀረው ፍሬ ሆኛለሁ ከዚያ የሚበላ ወይን ፍሬ አይገኝም የምጓጓለትና ቶሎ ቀድሞ የሚደርሰው በለስ አይኖርም፡፡
\v 2 ከምድሩ ታማኝ ሰዎች ጠፍተዋል በሰው ልጆች መካከልም ቅን ሰው የለም፡፡ ሁሉም ደም ለማፍሰስ ያደባል እያንዳንዱም የገዛ ወንድሙን በመረብ ያጠምዳል፡፡
\s5
\v 3 እጆቻቸው ሌሎችን ለመጉዳት ሠልጠነዋል፤ ገዦቻቸው ገንዘብ ይፈልጋሉ ፈራጁ ጉቦ ይጠብቃል፤ ኃይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ፡፡
\v 4 ከእነርሱ ይሻላል የተባለው እንደ አሜኬላ እጅግ ቀና የተባለውም እንደ ኩርንችት ነው፡፡ ነቢያቶቻችሁ አስቀድመው የተናገሩለት ቀን እናንተ የምትቀጡበት ቀን ነው፡፡ የሚሸበሩበት ቀን ደርሶአል፡፡
\s5
\v 5 ጐረቤትህን አትመን፣ ወዳጅህም ላይ አትተማመን፡፡ በዕቅፍህ ከምትተኛዋ እንኳ ለምትናገረው ተጠንቀቅ፡፡
\v 6 ወንድ ልጅ አባቱን ያዋርዳል ሴት ልጅ በእናትዋ ላይ ምራት በአማቷ ላይ ትነሣለች፡፡ የሰው ጠላቶች የገዛ ቤተ ሰቦቹ ይሆናሉ፡፡
\s5
\v 7 እኔ ግን ያህዌን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የመድኃኒቴን አምላክ እጠብቃለሁ አምላኬም ይሰማኛል፡፡
\v 8 ጠላቴ፣ ሆይ ብወድቅ እንኳ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ከወደቅሁበት እነሣለሁ በጨለማ ብቀመጥ እንኳ ያህዌ ብርሃን ይሆንልኛል፡፡
\s5
\v 9 ያህዌን ስለ በደልሁ እርሱ እስኪፈርድልኝ ድረስ ቁጣውን እታገሣለሁ፡፡ እርሱ ወደ ብርሃን ያወጣኛል በጽድቁ ሲያድነኝም አያለሁ
\s5
\v 10 ጠላቴም ታያለች፣ ‹‹አምላክህ ያህዌ የታል? ያለች ጠላቴ ታፍራለች፡፡ እኔም የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ትረገጣለች፡፡
\s5
\v 11 ቅጥሮቻችሁን የምትሠሩበት ቀን ይመጣል በዚያን ቀን ድንበራችሁ ይሰፋል!
\v 12 በዚያ ቀን ሕዝባችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል፤ ከአሦርና ከግብፅ ከተሞች ከግብፅ እስከ ታላቁ ወንዝ እስከ ኤፍራጥስ ከባሕር እስከ ባህር፣ ከተራራ እስከ ተራራ ድረስ ሕዝባችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል፡፡
\v 13 ከሚኖሩበት ሰዎች ክፋት የተነሣ ምድሪቱ ወና ትሆናለች፡፡
\s5
\v 14 በለመለመ መስክ መካከል ብቻቸውን ዱር ውስጥ ያሉትን የርስትህ መንጋ የሆኑት ሕዝብህን በበትርህ ጠብቅ፡፡ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሰንና በገለዓድ አሰማራቸው፡፡
\v 15 ከግብፅ እንደ ወጣችሁበት ዘመን ድንቆችን አሳያቸዋለሁ፡፡
\s5
\v 16 ኃይል ያላቸው ቢሆኑም አሕዛብ ይህን አይተው ያፍራሉ፤ እጃቸውን አፋቸው ላይ ያደርጋሉ ጆሮዋቸውም ይደነቁራል፡፡
\v 17 እንደ እባብ፣ ምድር ላይ እንደሚርመሰመሱም ፍጥረቶች ትቢያ ይልሳሉ፡፡ እየተንቀጠቀጡ ከዋሻዎቻቸው ይወጣሉ አምላካችን ያህዌ ሆይ በፍርሃት ወደ አንተ ይመጣሉ ከአንተ የተነሣ ይሸበራሉ፡፡
\s5
\v 18 ኃጢአትን ይቅር የሚል የርስቱንም ትሩፍ መተላለፍ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? የኪዳን ታማኝነትህን ለእኛ ማሳየት ደስ ስለሚልህ አንተ ለዘላለም አትቆጣም፡፡
\s5
\v 19 እንደ ገና ትራራልናለህ፤ ርኩሰታችንን በእግሮችህ ትረግጣለህ፡፡ ኃጢአታችንን ሁሉ ወደ ባሕሩ ጥልቅ ትጥላለህ፡፡
\v 20 በቀድሞ ዘመን ለአባቶቻችን በመሐላ እንደ ገባኸው ቃል ለያዕቆብ ታማኝነትን፣ ለአብርሃምም የኪዳን ታማኝነትን ትሰጣለህ፡፡

110
34-NAM.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,110 @@
\id NAM
\ide UTF-8
\h ትንቢተ ናሆም
\toc1 ትንቢተ ናሆም
\toc2 ትንቢተ ናሆም
\toc3 nam
\mt ትንቢተ ናሆም
\s5
\c 1
\p
\v 1 ስለ ነነዌ የተነገረ ቃል፤ የአልቆሻዊው የናሆም ራእይ መጽሐፍ ይህ ነው፡፡
\s5
\v 2 ያህዌ ቀናተኛና ተበቃይ ነው፤ ያህዌ የሚበቀል በመዓትም የተሞላ አምላክ ነው፡፡ ያህዌ ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ በጠላቶቹም ላይ ቁጣውን ይወርዳል፡፡
\v 3 ያህዌ ለቁጣ የዘገየ፣ በኃይሉም ታላቅ ነው፤ በምንም ዐይነት ጠላቶቹን ንጹሕ ናችሁ አይልም፡፡ ያህዌ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ መንገድ አለው፤ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው፡፡
\s5
\v 4 ባሕርን ይገሥጻል፤ ያደርቀዋልም፤ እርሱ ወንዞችን ሁሉ ያደርቃል፡፡ ባሳንና ቀርሜሎስ ጠውልገዋል፤ የሊባኖስ አበቦችም ረግፈዋል፡፡
\v 5 ተራሮች በእርሱ ፊት ተናወጡ፤ ኮረብቶችም ቀለጡ፤ ምድር በፊቱ፣ ዓለምና በውስጧ የሚኖሩ ሰዎችም ሁሉ ተናወጡ፡፡
\s5
\v 6 በቁጣው ፊት ማን መቆም ይችላል? ጽኑ ቁጣውንስ ማን መቋቋም ይችላል? መዓቱ እንደ እሳት ፈስሶአል፤ ዐለቶችም በፊቱ ተሰነጣጠቁ፡፡
\s5
\v 7 ያህዌ መልካም ነው፤ በመከራ ጊዜም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑበት ታማኝ ነው፡፡
\v 8 ጠላቶቹን ግን በኃይለኛ ጐርፍ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ወደ ጨለማም ያሳድዳቸዋል፡፡
\s5
\v 9 እናንተ ሰዎች ያህዌ ላይ የምታሤሩት ምንድነው? እርሱ ፈጽሞ ያጠፋዋል፤ መከራም ዳግመኛ አይነሣም፡፡
\v 10 እንደ እሾኽ ይጠላለፋሉ፤ በወይን ጠጃቸውም ይሰክራሉ፤ እሳት እንደ ገለባ ይበላቸዋል፡፡
\v 11 ነነዌ ሆይ፣ ያህዌ ላይ የሚያሤር፣ ክፉ ምክር የሚመክር ከመካከላችሁ ወጥቷል፡፡
\s5
\v 12 ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ‹‹ኅይለኞችና ቁጥራቸውም እጅግ የበዛ ቢሆን እንኳ ተቆርጠው ይጠፋሉ፤ ከእንግዲህም ሕዝባቸው አይኖም፡፡ ይሁዳ ሆይ፣ ከዚህ በፊት ባስጨንቅህም፣ ከእንግዲህ አላስጨንቅህም፡፡
\v 13 አሁንም ቀንበራቸውን ከአንተ ላይ እሰብራለሁ፤ ስንሰለትህንም በጥሼ እጥላለሁ፡፡
\s5
\v 14 ነነዌ ሆይ፣ ስለ አንቺ ያህዌ እንዲህ ብሎ አዝዞአል፤ ‹‹ስም የሚያስጠራ ትውልድ አይኖራችሁም፡፡ የተቀረጹ ምስሎችና ቀልጠው የተሠሩ ጣዖቶችን ከአማልክቶቻችሁ ቤት አጠፋለሁ፡፡ እጅግ ክፉ ነህና መቀበሪያህን እምስልሃለሁ፡፡
\s5
\v 15 የምሥራችን የሚያመጣና ሰላምን የሚያውጅ ሰው እግር በተራራው ላይ ናቸው! ይሁዳ ሆይ፣ በዓላትህን አክብር፤ ስእለትህንም ፈጽም፤ ከእንግዲህ ክፉዎች አይወርሩህም፤ እነርሱ ፈጽሞ ይጠፋሉ፡፡
\s5
\c 2
\p
\v 1 እስክትደቅቂ ድረስ የሚረግጥሽ እርሱ እየመጣ ነው፡፡ ስለዚህ ምሽጐችሽን አጠናክሪ መንገድሽን ጠብቂ፤ ወገብሽን ታጠቂ፤ ኃይልሽን ሁሉ አሰባስቢ፡፡
\v 2 አጥፊዎች ባድማ ቢያደርጓቸውም፣ የወይን ተክል ቦታቸውን ቢያጠፉባቸውም እንደ እስራኤል ክብር ሁሉ ያህዌ የያዕቆብንም ክብር ይመልሳል፡፡
\s5
\v 3 የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፣ ተዋጊዎቹም ሐምራዊ ልብስ ለብሰዋል ዝግጁ በሆኑበት ቀን የሰረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል፡፡
\v 4 ሰረገሎቹ በየመንገዱ ይከንፋሉ፤ ሰፋፊ በሆኑት መንገዶች በፍጥነት ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡ የሚንቦገቦግ ችቦ ይመስላሉ፤ እንደ መብረቅም ይወረወራሉ፡፡
\s5
\v 5 እስክትደቂ ድረስ የሚረግጥሽ እርሱ የጦር ሹማምንቱን ይጠራል እነርሱም እየተደነቃቀፉ ወደ ፊት ይመጣሉ፣ ለማጥቃት ወደ ከተማ ቅጥር ይወጣሉ፤ የሚወረወርባቸውን ፍላጻ በትልቁ ጋሻቸው ይከላከላሉ፡፡
\s5
\v 6 በወንዙ በኩል ያሉ በሮች ወለል ብለው ይከፈታሉ ቤተ መንግሥቱም ተደመሰሰ፡፡
\v 7 ንግሥቲቱ ተማርካ ዕርቃኗን ተወሰደች ሴት አገልጋዮቿ ደረታቸውን እየደቁ እንደ ርግብ ያላዝናሉ፡፡
\s5
\v 8 ነነዌ ውሃ መያዝ እንደማይችል ኩሬ ናት፤ ሕዝቧም እንደ ፈጣን ወራጅ ውሃ ፈጥኖ ይሸሻል፡፡ ሌሎች ‹‹ቁሙ ቁሙ›› ብለው ይጮኻሉ ዞር ብሎ የሚያይ ግን የለም፡፡
\v 9 የነነዌ ሀብት ስፍር ቁጥር የለውም የከበሩ ድንጋዮቿ የተትረፈረፉ ናቸው ስለዚህ ብሩን ዝረፉ፣ ወርቁንም ንጠቁ፡፡
\v 10 ነነዌ ባዶ ሆነች፣ ተራቆተች፡፡ የሰዎች ልብ ቀለጠ፤ የሰው ሁሉ ጉልበት ተብረከረከ ሁሉም ተጨንቀዋል፤ ፊታቸው ገርጥቷል፡፡
\s5
\v 11 የአንበሶች ዋሻ፣ የአንበሳ ደቦሎች የሚመገቡበት፣ ወንድ አንበሳና እንስት አንበሳ ምንም ሳይፈሩ ወዲያ ወዲህ ይሉበት የነበረ ቦታ የታል?
\v 12 አንበሳ ለግልገሎቹ የሚበቃውን ያህል ገደለ፤ ለእንስቶቹ የሚበቃውንም ያህል አድኖ ያዘ የገደለውን በዋሻው፣ የነጠቀውንም በመኖሪያ ቦታው ሞልቶአል፡፡
\s5
\v 13 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ሰረገሎችን አቃጥላለሁ፤ ደቦል አንበሶችህን ሰይፍ ይበላቸዋል፡፡ የዘረፍኸውን ከምድርህ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህ የመልእክተኞችህ ድምፅ አይሰማም፡፡››
\s5
\c 3
\p
\v 1 ደም ለሞላባት ከተማ ወዮላት! ሐሰትና የተዘረፈ ንብረት ሞልቶበታል፡፡
\v 2 አሁን ግን የአላንጋ ድምፅና የመንኰራኩር ኳኳታ ድምፅ፣ የፈጣን ፈረስ ኮቴ፣ የሰረገሎች መንጓጓት ይሰማል፡፡
\s5
\v 3 የሚያብረቀርቅ ሰይፍና የሚያንጸባርቅ ጦር የያዙ ፈረሰኞች ጥቃት ያደርሳሉ፤ የሞተው ብዙ ነው፤ ሬሳ በሬሳ ተከምሮአል እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ አጥቂዎቹ በሞቱት ሰዎች ሬሳ ይሰናከላሉ፡፡
\v 4 ይህ ሁሉ የሆነው ገደብ በሌለው የአመንዝራዋ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርሷ በዝሙቷ መንግሥታን፣ በጥንቆላዋም ሕዝቦችን ባሪያ አድርጋለች፡፡
\s5
\v 5 የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ ‹‹እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ ዕርቃንሽን ለሕዝቦች፣ ኅፍረተ ሥጋሽን ለመንግሥታት አሳያለሁ፡፡
\v 6 በጣም የሚያስጸይፍ ቆሻሻ እደፋብሻለሁ፤ እንቅሻለሁ፤ ሰው ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ፡፡
\v 7 የሚያይሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሸ፣ ‹‹ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል? የሚያጽናናትንስ ከወዴት አገኛለሁ? ይላል፡፡
\s5
\v 8 ነነዌ ሆይ፣ ለመሆኑ አንቺ ዐባይ ወንዝ አጠገብ ከተሠራችውና በውሃ ከተከበበችው፣ ወንዙ መከላከያ፣ ባሕሩ ራሱ ቅጥራ ከሆነለት ከቴብስ ትበልጫለሽን?
\v 9 ኢትዮጵያና ግብፅ ወሰን የለሽ ኃይሏ ነበሩ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ፡፡
\s5
\v 10 ያም ሆኖ፣ ቴብስ ተጋዘች፤ በምርኮም ተወሰደች ሕፃናቷ በየመንገዱ ማእዘን ላይ ተፈጠፈጡ፤ በመኳንንቷ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ፡፡
\v 11 አንቺ ደግሞ ትሰክሪያለሽ መደበቅ ትሞክሪያለሽ ከጠላቶችሽ መሸሸጊያም ትፈልጊያለሽ፡፡
\s5
\v 12 ምሽጐችሽ ሁሉ ቀድሞ እንደ ደረሰ፣ ሲነቀነቅ በላተኛው አፍ ውስጥ እንደሚወድቅ የበለስ ፍሬ ሆነዋል፡፡
\v 13 ወታደሮችሽ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል የምድርሽ በሮች ወለል ብለው ለጠላቶችሽ ተከፍተዋል፡፡ መዝጊያዎቻቸውን እሳት በልቷቸዋል፡፡
\s5
\v 14 ለከበባው ውሃ ቅጂ፣ ምሽጐችሽን አጠናክሪ፤ ጭቃ ረግጠሸ የሸክላ መሥሪያ አዘጋጂ፤ ጡብም ሥሪ፡፡
\v 15 በዚያ እሳት ይበላሻል፤ ሰይፍ ያጠፋሻል፤ አንበጣ ማንኛውንም ነገር እንደሚጠፉ ያጠፋሻል፡፡ ስለዚህ እንደ አንበጣ እርቢ እንደ ኩብኩባም ተባዢ፡፡
\s5
\v 16 ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይበልጥ አብዝተሻል፤ ይሁን እንጂ፣ ምድሪቱን እንደ አንበጣ ጋጡ፤ ከዚያም በርረው ሄዱ፡፡
\v 17 መኳንንቶችሽ የአንበጦችን ያህል ብዙ ናቸው፣ የጦር መሪዎችሽ በብርድ ቀን ቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ የኩብኩባ መንጋ ናቸው፡፡ ፀሐይ ሲወጣ ግን በርረው ይሄዳሉ፤ የት እንደሚሄዱም አይታወቅም፡፡
\s5
\v 18 የአሦር ንጉሥ ሆይ፣ እረኞችህ አንቀላፉ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፡፡ ሕዝብህ ሰብሳቢ አጥተው በየተራሮች ተበትነዋል፡፡
\v 19 ቁስልህን መፈወስ የሚችል የለም፤ ቁስልህ እጅግ ጽኑ ነው፡፡ ስለ አንተ የሚሰማ ሁሉ በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፡፡ ወሰን ከሌለው ጭካኔህ ማን ያመለጠ አለ?

127
35-HAB.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,127 @@
\id HAB
\ide UTF-8
\h ዕንባቆም
\toc1 ዕንባቆም
\toc2 ዕንባቆም
\toc3 hab
\mt ዕንባቆም
\s5
\c 1
\p
\v 1 ነቢዩ ዕንባቆም የተቀበለው መልእክት፤
\v 2 ‹‹ያህዌ ሆይ፣ ለርዳታ ወደ አንተ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ ነው? ‹‹ግፍ በዛ! በማለት ወደ አንተ ጮኽሁ፤ አንተ ግን አላዳንኸኝም፡፡
\s5
\v 3 ርኩሰትና በደልን ለምን እንዳይ አደረግኸኝ? ጥፋና ዐመፅ በፊቴ ናቸው፤ ፀብና ጭቅጭቅም እየበዛ ነው!
\v 4 ስለዚህ ሕግ ላልቶአል፤ ፍትሕ ተዛብቶአል፡፡ ክፉዎች ጻድቃንን ከብበዋል ስለዚህ ፍርድ ተጣሟል፡፡›› ያህዌ እንዲህ በማለት ለዕንባቆም መለሰ
\s5
\v 5 ‹‹ቢነገራችሁ እንኳ የማታምኑትን አንድ ነገር በዘመናችሁ ስለማደርግ፣ ልብ አድርጋችሁ አሕዛብን እዩ፤ ተመልከቱ፤ እጅግም ተደነቁ፡፡
\v 6 ጨካኞቹንና ችኩሎቹን ከለዳውያንን ላስነሣ ነው፤ የራሳቸው ያልሆኑ ቤቶችን ለመውሰድ በምድሪቱ ስፋትና ርዝመት ይገሠግሣሉ፡፡
\v 7 እነርሱ አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፤ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል፡፡
\s5
\v 8 ፈረሶቻቸው ከነብር ይልቅ ፈጣኖች፣ ከማታም ተኩላ ይልቅ፣ አስፈሪዎች ናቸው፡፡ ፈረሶቻቸው በፍጥነት ይጋልባሉ፤ ነጥቆ ለመብላት እንደሚቸኩል ንስር ፈረሰኞቻቸው ከሩቅ ይመጣሉ፡፡
\v 9 ሁሉም ለዐመፅ ሥራ ይመጣሉ፤ ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ይገሠግሣል፤ ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል፡፡
\s5
\v 10 ነገሥታት ላይ ይሳለቃሉ፤ ገዥዎች ላይ ያፌዛሉ፡፡ በምሽጐች ላይ በመሳቅ ዐፈር ቆልለው ይይዟቸዋል፡፡
\v 11 ከዚያም እንደ ነፋስ አልፈው ይሄዳሉ፤ ጉልበታቸውን አምላካቸው ያደረጉ እነዚያን በደለኞች ይጠራርጋቸዋል፡፡ ዕንባቆም ለያህዌ ያቀረበው ሌላው ጥያቄ
\s5
\v 12 አንተ የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ፣ አንተ ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን? እኛ አንሞትም፡፡ እንዲፈርዱ ያህዌ ሾሟቸዋል፤ አንተ ዐለት ሆይ፣ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው፡፡
\s5
\v 13 ዐይኖችህ እጅግ የነጹ በመሆናቸው ክፉ ነገርን መመልከት አይሆንላቸውም፤ አንተም ክፉ ነገር ሲሠራ ዝም ብለህ አታይም፤ ታዲያ፣ እነዚያን ዐመፀኞች ለምን ዝም ብለህ ትመለከታለህ? ዐመፀኛው ከራሱ ይልቅ ጻድቅ የሆነውን ሰው ሲውጠውስ ለምን ዝም ትላለህ?
\v 14 ሰዎችን ባሕር ውስጥ እንዳለ ዓሣ፣ መሪ እንደሌላቸው በደረታቸው እየተሳቡ እንደሚሄዱ ፍጥረታት የምታደርጋቸው ለምንድነው?
\s5
\v 15 ዓሣ በመንጠቆ እንደሚያዝ ሁሉንም በመንጠቆ ይይዟቸዋል፤ ሰዎችን በመረቦቻቸው ይዘው ይሰበሰቧቸዋል፡፡ ደስ የሚሰኙትና ሐሤት የሚያደርጉት ከዚህ የተነሣ ነው፡፡
\v 16 የስቡ እንስሳት ድርሻዎቻቸው፣ የጣፈጠውም ሥጋ ምግባቸው ሆናልና ስለዚህ ለመረቦቻቸው ይሠዋሉ፤ ለአሸክላዎቻቸውም ያጥናሉ፡፡
\v 17 ታዲያ፣ መረቦቻቸውን ባዶ እያደረጉ፣ ያለ አንዳች ርኅራኄ ሕዝቦችን መግደል መቀጠል አለባቸውን?
\s5
\c 2
\p
\v 1 በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ፤ በመጠበቂያው ግንብ ላይ ቦታዬን እይዛለሁ፤ ምን እንደሚለኝና ለጥያቄዬ ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ፡፡
\s5
\v 2 ያህዌ እንዲህ በማለት መለሰልኝ፤ ‹‹ይህን ራእይ ጻፈው፤ በቀላሉ እንዲነበብ አድርገህም በጽላት ቅረጸው፡፡
\v 3 ራእዩ የሚናገረው ገና ወደ ፊት ስለሚሆነው ነው፡፡ በመጨረሻም ይፈጸማል እንጂ፣ በፍጹም አይዋሽም፡፡
\s5
\v 4 ተመልከት! ጠማማ ሐሳብ ያለው ሰው ታብዮአል፡፡ ጻድቁ ግን በእምነቱ ይኖራል፡፡
\v 5 ዐርፎ እንዳይቀመጥ ወይን ጠጅ ዕብሪተኛውን ወጣት አስቶታል ይልቁን ምኞቱን እንደ መቃብር አስፍቶአል እንደ ሞት በቃኝ ማለትን አያውቅም፡፡ ሕዝቦችን ሁሌ ወደ ራሱ ይሰበስባል ሰዎችንም ሁሉ ማርኮ ይወስዳል፡፡
\s5
\v 6 ታዲያ፣ በእንዲህ ዐይነቱ ሰው ላይ በማፌዝና በመዘባበት እንዲህ እያሉ ሁሉም አይሣለቁበትምን? ‹የተሰረቀውን ለራሱ ለሚያከማች፣ ራሱን በዐመፅ ባለጠጋ ለሚያደርግ ወዮለት! ይህ የሚቀጥለውስ እስከ መቼ ነው?
\v 7 በአንተ የተመረሩ ድንገት አይነሡብህምን፣ አንተን የማያስደነግጡስ አይነቁብህምን? በእጃቸውም ትወድቃለህ፡፡
\v 8 አንተ ብዙ ሕዝብ ስለ ዘረፍህ የተረፉት ሕዝቦች ይዘርፉሃል፡፡ የሰው ደም አፍስሰሃል አገሮች፣ ከተሞችና የሚኖሩባቸው ሰዎች ሁሉ ላይ ግፍ ሠርተሃል፡፡
\s5
\v 9 በማጭበርበር በተገኘ ሀብት ቤቱን ለሚገነባ ከክፉ ለማምለጥ ቤቱን በከፍታ ላይ ለሚሠራ ወዮለት!
\v 10 ብዙ ሰዎችን ለማጥፋት ደባ ፈጽመሃል በገዛ ቤትህ ላይ ውርደትን፣ በራስህም ላይ ኃጢአትን አድርገሃል፡፡
\v 11 ድንጋዮች በቅጥሩ ውስጥ ይጮኻሉ፣ ከዕንጨት የተሠሩ ተሸካሚዎችም እንዲህ በማለት ይመልሱላቸዋል፣
\s5
\v 12 ‹‹ደም በማፍሰስ ከተማን ለሚሠራ፣ በወንጀልም አገርን ለሚመሠርት ወዮለት!
\v 13 ሰዎች ለእሳት ማገዶ እንዲሆን እንዲለፉ፣ ሕዝቦችም በከንቱ እንደደከሙ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ወስኖ የለምን?
\v 14 ያም ሆኖ፣ ውሃ ባሕርን እንደሚሞላ ሁሉ ምድርም የያህዌን ክብር በማወቅ ትሞላለች፡፡
\s5
\v 15 ኅፍረተ ሥጋቸውን ለማየት ባልንጀሮቹን ለሚያጠጣ፣ እስኪሰክሩም ድረስ ወይን ለሚያቀርብላቸው ወዮለት!
\v 16 በክብር ፈንታ ውርደት ትሞላለህ፤ አሁን ተራው የአንተ ነውና ጠጣ፤ ኀፍረተ ሥጋህም ይገለጥ፤ በያህዌ ቀኝ እጅ ያለው ጽዋ በተራው ይመልስብሃል ክብርህን ውርደት ይሸፍነዋል፡፡
\s5
\v 17 ሊባኖስ ላይ ያሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤ እንስሶች ላይ የፈጸምኸው ጥፋት ያስደነግጥሃል፡፡ የሰው ደም አፍስሰሃል፤ አገሮች፣ ከተሞችና የሚኖሩባቸው ሰዎች ሁሉ ላይ ግፍ ሠርተሃል፡፡
\s5
\v 18 ታዲያ፣ የቀረጽኸው ምስል ምን ይጠቅምሃል? ምስሉን የቀረጸው፣ ከቀለጠ ብረት ጣዖት የሠራ ሰው የሐሰት መምህር ነው፤ እነዚያን የማይናገሩ አማልክት ሲሠራ በገዛ እጅ ሥራው ተማምኖአልና፡፡
\v 19 ዕንጨቱን ንቃ! ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ ተነሣ ለሚል ወዮለት ለመሆኑ፣ እነዚህ ነገሮች ማስተማር ይችላሉን? በወርቅና በብር ተለብጦአል፤ እስትንፋስ ግን የለውም፡፡
\v 20 ያህዌ ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል!
\s5
\c 3
\p
\v 1 የነቢዩ ዕንባቆም ጸሎት
\v 2 ያህዌ ሆይ፣ ስላደረግኸው ድንቅ ሥራ ሰዎች ፈራሁ፤ የቀድሞ ዘመን ሥራህን በዚህ ዘመንም አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፡፡ በቁጣህ ውስጥ እንኳ ምሕረት ርኅራኄኅን አስብ፡፡
\s5
\v 3 እግዚአብሔር ከቴማን፣ ቅዱሱንም ከፋራን ተራራ መጣ! ሴላ፡፡ ክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ ምድር በምስጋናው ተሞላች፡፡
\s5
\v 4 ኃይሉ ከተሰወረበት እጁ የወጡ ሁለት ጨረሮች እንደ መብረቅ ደምቀዋል፡፡
\v 5 መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው፡፡
\s5
\v 6 እርሱ ሲቆም ምድር ትናወጣለች፤ እርሱ ሲመለከት ሕዝቦች ይንቀጠቀጣሉ፡፡ የዘላለም ተራሮች እንኳ ተፈረካከሱ የጥንት ኮረብቶችም ዝቅ አሉ፡፡ መንገዱ ዘላለማዊ ነው፡፡
\s5
\v 7 የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣ የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ፡፡
\v 8 ያህዌ ወንዞች ላይ ተቆጥቷልን? መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን? ወይስ በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሰረገሎችህ በጋለብህ ጊዜ ባሕር ላይ ተቆጥተህ ነበርን?
\s5
\v 9 ቀስትህን ከሰገባው አወጣህ፤ ፍላጻህንም ለመወርወር አዘጋጀህ፡፡ ሴላ፡፡ ምድርን በወንዞች ከፈልህ፡፡
\v 10 ተራሮች አዩህ፤ በፍርሃትም ተጨማደዱ የውሃ ወጀብ በላያቸው አለፈ፤ ጥልቁ ባሕር ድምፁን አሰማ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ፡፡
\s5
\v 11 ከሚወረወሩ ፍላጾች ብርሃን፣ ከሚያብረቀርቀው የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣ ፀሐይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ፡፡
\v 12 በቁጣህ በምድር ላይ ተመላለስህ፤ በመዓትህ ሕዝቦችን አደቀቅህ፡፡
\s5
\v 13 ሕዝብህን ለማዳን፣ የቀባኸውንም ለመታደግ ወጣህ፡፡ ዕርቃኑን ታስቀረው ዘንድ የዐመፃን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፡፡ ሴላ፡፡
\s5
\v 14 እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትን የመጣውን፣ ምስኪኑን በስውር ለመዋጥ የመጣውን ሰራዊት አለቃ ራስ በገዛ ፍላጻው ወጋህ፡፡
\v 15 በፈረሶችህ ባሕሩ ላይ ተራመድህ፤ ታላላቅ ውሆችን ከመርህ፡፡
\s5
\v 16 እኔ ሰማሁ ውስጤም ተናወጠ፤ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፡፡ አጥንቶቼ ይበሰብሳሉ፤ እግሮቼም ከታች ይርዳሉ ወራሪዎቻችን ላይ መከራ የሚመጣበትን ቀን በትዕግሥት እጠብቃለሁ፡፡
\s5
\v 17 ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያብብ፣ ወይን ዛፍ ላይ ፍሬ ባይገኝ፣ የወይራ ዛፍ ምንም ፍሬ ባይሰጥ፣ ከእርሻዎች ሰብል ቢጠፋ፣ የበግ መንጋዎች ሁሉ ቢያልቁ፣ በረት ውስጥ ምንም ከብት ባይገኝ፣
\s5
\v 18 ይህም ሁሉ ቢሆን፣ እኔ በያህዌ ደስ ይለኛል በመድኃኒቴም አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡
\v 19 ጌታ ያህዌ ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋሊያ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎቼም ላይ ይመራኛል፡፡ - ለመዘምራን አለቃ በባለ አውታር መሣሪያዎች የተዘመረ፡፡

114
36-ZEP.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,114 @@
\id ZEP
\ide UTF-8
\h ሶፎንያስ
\toc1 ሶፎንያስ
\toc2 ሶፎንያስ
\toc3 zep
\mt ሶፎንያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ይህ በይሁዳ ንጉሥ በአሞን ልጅ በኢዮስያስ ዘመን፣ ወደ ሕዝቅያስ ልጅ፣ ወደ አማርያ ልጅ፣ ወደ ጐዶልያስ ልጅ፣ ወደ ኩሲ ልጅ፣ ወደ ሶፎንያስ የመጣ የያህዌ ቃል ነው፡፡
\v 2 ‹‹ማንኛውንም ነገር ከምድር ገጽ ፈጽሜ አጠፋለሁ! ይላል ያህዌ
\v 3 ሰውንና እንስሳን አጠፋለሁ፤ የሰማይን ወፎችና የባሕር ዓሦች አጠፋለሁ፡፡ ሰውን ከምድር ገጽ በማስወግድበት ጊዜ ክፉዎች የፍርስራሽ ክምር ይሆናሉ ይላል ያህዌ፡፡
\s5
\v 4 እጄን በይሁዳና በኢየሩሳሌም በሚኖሩ ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፡፡ የበአልን አምልኮ ርዝራዥ፣ የጣዖቶቹንና የአመንዝራ ካህናቱን ስም ከዚህ ቦታ አጠፋለሁ ስም ሁሉ ከዚህ ቦታ አጠፋለሁ፤
\v 5 በየቤቶቹ ጣራ የሰማይን ሰራዊት የሚያመልኩትን፣ በያህዌ ስም እየማሉ ደግሞም በሜልኮም የሚምሉትን ሕዝብ አጠፋለሁ፡፡
\v 6 ያህዌን ከመከተል ወደ ኃላ የሚሉትን፣ ያህዌን የማይፈልጉትንም ሆነ ከእርሱ ምሪት የማይፈልጉትን አጠፋለሁ፡፡››
\s5
\v 7 የያህዌ ቀን እየቀረበ ነውና በጌታ ያህዌ ፊት ጸጥ በሉ፤ ያህዌ መሥዋዕት አዘጋጅቷል፤ የጠራቸውንም እንግዶች ቀድሷል፡፡
\v 8 በያህዌ የመሥዋዕት ቀን መኳንንቱንና የንጉሡን ልጆች፣ እንግዳ ልብስ የሚለብሱትንም ሁሉ እቀጣለሁ፡፡
\v 9 በዚያን ቀን፣ በመድረኩ ላይ የሚዘልሉትን ሁሉ፣ የጌቶቻቸውን ቤት በዐመፅና በማጭበርበር የሚሞሉትንም ሁሉ እቀጣለሁ፡፡
\s5
\v 10 በዚያን ቀን ይላል ያህዌ፣ ከዓሣው በር ጩኸት፣ ከሁለተኛው አደባባይ ዋይታ፣ ከኮረብቶችም ታላቅ የጥፋት ድምፅ ይሰማል፡፡
\v 11 እናንት በገበያው ቦታ የምትኖሩ ዋይ በሉ፤ ነጋዴዎች ሁሉ ይደመሰሳሉ፤ በብር የሚነግዱትም ሁሉ ይጠፋሉ፡፡›
\s5
\v 12 በዚያ ዘመን፣ ኢየሩሳሌምን በመብራት እፈትሻለሁ፤ ወይን ጠጅ የሚያዘወትሩንና በልባቸው፣ ‹‹ክፉም ሆነ መልካም ያህዌ ምንም አያደርግም›› የሚሉትን ሰዎች እቀጣለሁ፡፡››
\v 13 ሀብታቸው ይዘረፋል፤ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፤ ቤት ይሠራሉ፤ ሆኖም፣ አይኖሩበትም፤ ወይን ይተክላሉ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም፡፡
\s5
\v 14 ታላቁ የያህዌ ቀን ቀርቧል፤ እጅግ እየፈጠነ ነው፤ የያህዌ ቀን ድምፅ ጦረኞች አምርረው የሚያለቅሱበት ይሆናል፤
\v 15 ያ ቀን የቁጣ፣ የመከራና የጭንቀት፣ የጥፋትና የመፍረስ፣ የጨለማና የጭጋግ፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ይሆናል፡፡
\v 16 በዚያ ቀን በተመሸጉት ከተሞችና በረጃጅም ግንቦች ላይ የጦር መለከትና የማስጠንቀቂያ ድምፅ ይሰማል፡፡
\s5
\v 17 እንደ ዕውሮች እስኪደናበሩ ድረስ በሰዎች ላይ ታላቅ ጭንቀት አመጣለሁ፤ ያህዌ ላይ ኃጢአት አድርገዋልና ደማቸው እንደ ውሃ ይፈስሳል፤ ሬሳቸውም እንደ ጉድፍ የትም ይጣላል፡፡
\v 18 ብራቸውም ሆነ ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ ያህዌ ቁጣውን በሚገልጥበት ቀን የቁጣው እሳት ምድርን ሁሉ ይበላል፤ ይህም የሆነው በምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ በድንገት ጥፋት ስለሚመጣ ነው፡፡››
\s5
\c 2
\p
\v 1 እናንት ዕፍረት የሌላችሁ ሕዝብ ሆይ፣ በአንድነት ተሰብሰቡ ተከማቹም፤
\v 2 የወሰነው ጊዜ ሳይደርስ፣ ቀኑ እንደ ገለባ ሳይጠራርጋችሁ፣ የያህዌ ቁጣ በእናንተ ላይ ሳይመጣና የያህዌ መዓት ቀን ሳይደርስባችሁ ተሰብሰቡ፡፡
\v 3 እናንተ ትእዛዙን የምትፈጽሙ በምድር ያላችሁ ትሑታን ሁሉ ያህዌን ፈልጉ፤ ጽድቅንና ትሕትናንም ፈልጉ፤ በያህዌ ቀን ምናልባት ጥበቃ ታገኙ ይሆናል፡፡
\s5
\v 4 ጋዛ ባድማ ትሆናለች፤ አስቀሎናም ትፈራርሳለች፤ አሸዶድ በቀትር ባዶ ትሆናለች፤ አቃሮንም ትነቀላለች፡፡
\v 5 እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ የከሌታውያን ሰዎች ሆይ፣ የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፣ ያህዌ እናንተ ላይ ተናግሯልና ወዮላችሁ፤ ከእናንተ ማንም እስከማይተርፍ ድረስ አጠፋችኃለሁ፡፡
\s5
\v 6 የባሕሩ ዳርቻ የእረኞች መሰማርያና የበጐች በረት ይሆናል፡፡
\v 7 የባሕሩ ዳርቻ ከይሁዳ ቤት ለተረፉት ይሆናል፤ እነርሱም በዚያ መንጐቻቸውን ያሰማሩበታል፡፡ በአስቀሎና ቤቶች ውስጥ በምሽት ይተኛሉ፤ አምላካቸው ያህዌ ይጠብቃቸዋል፤ ሀብታቸውንም ይመልሳል፡፡
\s5
\v 8 በሕዝቤ ላይ የደረሰውን የሞዓብን ሕዝብ ፌዝና የአሞናውያንን ንቀት ሰምቻለሁ፤ ሕዝቤን ሰድበዋል፤ ርስታቸውን ለመውሰድም ዝተዋል፡፡
\v 9 ስለዚህ ይላል የሰራዊት ጌታ፣ የእስራኤል አምላክ ያህዌ፣ የሞዓብ ሕዝብ እንደ ሰዶም፣ አሞናውያንም እንደ ገሞራ ዐረም እንደ ዋጠው ቦታና እንደ ጨው ጉድጓድ ለዘላለም ጠፍ እንደሚሆኑ በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ከሕዝቤ የተረፉት ይዘርፏቸዋል፤ ከወገኔ የተረፉትም ምድራቸውን ይወርሳሉ፡፡
\s5
\v 10 ከትዕቢታቸው የተነሣ፣ የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሕዝብ ላይ በማፌዛቸውና እነርሱንም በመስደባቸው የሞዓብና የአሞን ሕዝብ ላይ ይህ ይሆናል፡፡
\v 11 እርሱ የምድሪቱን አማልክት በሚያጠፋበት ጊዜ፣ ያህዌ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፡፡ በባሕሩ ጠረፍና በየምድራቸው የሚኖሩ ሁሉ በያሉበት ያመልኩታል፡፡
\s5
\v 12 እናንተ ኢትዮጵያውያንም በሰይፌ ትገደላላችሁ፣
\v 13 የእግዚአብሔር እጅ ሰሜንን ይመታል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌን ባድማ ያደርጋል፤ እንደ ምድረ በዳም ትደርቃለች፡፡
\v 14 የአራዊት መንጋዎች፣ የአሕዛብ እንስሶች ሁሉ አሦር ውስጥ ያርፋሉ፤ ወፎችና ልዩ ልዩ ዐይነት ጉጉቶች በጉልላትዋ ላይ ይሰፍራሉ፡፡ ጩኸታቸው በየመስኮቱ ያስተጋባል፤ ከዝግባ የተሠሩ ተሸካሚዎች ተገልጠዋልና ቁራዎች በየደጃፎቻቸው ይጮኻሉ፡፡
\s5
\v 15 ይህች በልቧ ‹‹እኔ ብቻ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ማንም የለም›› ያለች ያለ አንዳች ፍርሃት ተደላድላ ትኖር የነበረች ከተማ ነች፡፡ ታዲያ፣ እንዴት የዱር አራዊት የሚኖሩባት ባድማ ሆና ቀረች? በአጠገቧ የሚያልፉ ሁሉ ያፌዙባታል፤ እጃቸውንም በንቀት ያወዛውዙባታል!
\s5
\c 3
\p
\v 1 ለዐመፀኛዋ፣ ለጨቋኛና ለረከሰች ከተማ ወዮላት፡፡
\v 2 እርሷ የእግዚአብሔርን ድምፅ አልሰማችም፤ የያህዌንም ተግሣጽ አልተቀበለችም፤ በያህዌ አትታመንም፤ ወደ አምላኳም አትቀርብም፡፡
\s5
\v 3 መሪዎቿ እንደሚያገሡ አንበሶች፣ ዳኞችዋም ለነገ ሳያስተርፉ ያገኙት ሁሉ በልተው እንደሚጨርሱ እንደ ተራቡ የማታ ተኩላዎች ናቸው፡፡
\v 4 ነቢያቶችዋ ትዕቢተኞችና ተንኰለኞች ናቸው፡፡ ካህናትዋ የተቀደሰውን አርክሰዋል፤ ሕጉንም ተላልፈዋል፡፡
\s5
\v 5 ጻድቁ ያህዌ በእርሷ ውስጥ አለ፤ እርሱ ፈጽሞ አይሳሳትም፤ በየማለዳው ፍርዱን ይሰጣል፤ በየቀኑም ይህን ከማድረግ አይቆጠብም፤ ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም፡፡
\s5
\v 6 ሕዝቦችን አጥፍቻለሁ፤ ምሽጐቻቸውንም ደምስሻለሁ፡፡ ማንም እንዳያልፍባቸው መንገዶቻቸውን አፈራርሻለሁ፡፡ ከተሞቻቸው ስለ ተደመሰሱ ከእንግዲህ የሚኖርባቸው አይኖርም፡፡
\v 7 እኔም፣ ‹‹በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፣ እርምትም ተቀበዪ፤ ላደርግብሽ እንዳሰብኩት ከመኖሪያሽ አትነቀዪ አልኩ፡፡ እነርሱ ግን በሚያደርጉት ሁሉ ክፋትን እያበዙ ሄዱ፡፡
\s5
\v 8 ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ ‹‹እስከምፈርድበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፤ ምድሪቱ ሁሉ በቁጣዬ እሳት እንድትጠፋ አሕዛብን ለመሰብሰብ፣ መንግሥታትን ለማከማቸት፤ ቁጣዬንና ጽኑ መዓቴን እነርሱ ላይ ለማፍሰስ ወስኛለሁ፡፡
\s5
\v 9 በዚያ ጊዜ ሰዎች የያህዌን ስም እንዲጠሩ፣ አንድ ልብ ሆነውም እንዲያገለግሉት ንጹሑን አንደበት እሰጣቸዋለሁ፡፡›
\v 10 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ያሉት እኔን የሚያመልኩ የተበተኑ ሕዝቤ ለእኔ የሚገባውን ቁርባን ያመጡልኛል፡፡
\v 11 በዚያ ቀን በእኔ ላይ ከፈጸማችሁት በደል ሁሉ የተነሣ አታፍሩም፤ በትዕቢታቸው የሚደሰቱትን ከመካከላችሁ ስለማስወግድ ከእንግዲህ ወዲያ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ አትታበዩብኝም፡፡
\s5
\v 12 ሆኖም፣ የዋሃንንና ትሑታንን አስቀራለሁ፤ እናንተም በያህዌ ስም ትተማመናላችሁ፡፡
\v 13 የእስራኤል ትሩፋን ከእንግዲህ ፍርድ አያጐድሉም፤ ሐሰትንም አይናገሩም፤ በአንደበታቸው ሐሰት አይገኝም፡፡ ይበላሉ፤ በሰላምም ያርፋሉ፤ የሚያስፈራቸውም አይኖርም፡፡››
\s5
\v 14 የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፣ እልል በዪ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፡፡
\v 15 ያህዌ ቅጣትሽን አስወግዷል፤ ጠላቶችንም አስወጥቷል፤ የእስራኤል ንጉሥ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ ከእንግዲህ ክፉን አትፈሪም፡፡
\v 16 በዚያ ቀን ኢየሩሳሌምን እንዲህ ይሏታል፤ ጽዮን ሆይ አትፍሪ፤ እጆችሽም አይዛሉ፡፡
\s5
\v 17 አንቺን ለማዳን ብርቱ የሆነው አምላክሽ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያሳርፍሻል፡፡ በዝማሬ በአንቺ ደስ ይለዋል፡፡
\v 18 ለታወቁ ክብረ በዓላት ሐዘንን ከአንቺ አርቃለሁ፤ በመካከልሽ ሸክምና ዕፍረት ሆነውብሻል፡፡
\s5
\v 19 በዚያ ቀን የበደሉሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ያነከሱትን እታደጋለሁ፤ የተጣሉትንም እሰበስባለሁ፡፡ ዕፍረታቸውን አስወግጄ በምድር ሁሉ ላይ ለምስጋናና ለክብር አደርጋቸዋለሁ፡፡
\v 20 በዚያ ቀን እመራችኃለሁ፤ በዚያ ቀን በአንድነት እሰበስባችኃለሁ፡፡ እኔ እንደ ሰበሰብኃችሁ፣ ምርኮአችንም እንደ ሰበሰብሁ ስታዩ የምድር ሕዝቦች ሁሉ ያመሰግኗችኃል፤ ያከብራችኃል ይላል ያህዌ፡፡

81
37-HAG.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,81 @@
\id HAG
\ide UTF-8
\h ሐጌ
\toc1 ሐጌ
\toc2 ሐጌ
\toc3 hag
\mt ሐጌ
\s5
\c 1
\p
\v 1 ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት በስድስተኛው ወር መጀመሪያ ቀን በነቢዩ በሐጌ በኩል ወደ ይሁዳ ገዢ ወደ ሰላትያል ልጅ ወደ ዘሩባቤልና ወደ ሊቀ ካህኑ ኢዮሴዴቅ ልጅ ወደ ኢያሱ የያህዌ ቃል መጣ።
\v 2 የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ይህ ሕዝብ “እኛ የምንመጣበት ወይ የያህዌን ቤት የምንሠራበት ጊዜ ገና ነው” ይላል።
\s5
\v 3 የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩ መጣ፤ እንዲህም አሉ፣
\v 4 “ይህ ቤት ፈራርሶ እያለ፣ እናንተ ራሳችሁ ባማሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?
\v 5 ስለዚህ የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ እስቲ፣ የሠራችሁትን ቤት አስቡ!
\v 6 ብዙ ዘራችሁ፤ ግን ጥቂት አጭዳችሁ፤ በላችሁ ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዝ ተቀበላችሁ ግን ብዙ ቀዳዶች በሞሉበት መያዣ የማስቀመጥ ያህል ሆነባችሁ!
\s5
\v 7 የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ እስቲ የሠራችሁትን አስቡ!
\v 8 ወደ ተራራ ውጡ፤ እንጨትን አምጡና ቤቴን ሥሩ፤ ያኔ እኔ በእርሱ ደስ ይለኛል፣ እከብርበታለሁ! ይላል ያህዌ።
\v 9 ብዙ ጠበቃችሁ፤ ግን እኔ እፍ ስላልሁበት ወደ ቤት ያመጣችሁት ግን ጥቂት ነው፤ እንዲህ ያደረግሁት ለምን ይመስላችኋል? የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል! ምክንያቱም የእኔ ቤት ፈርሶ እያለ፣ ሰው ሁሉ በገዛ ራሱ ቤት እጅግ ደስ በመሰኘቱ ነው።
\s5
\v 10 ከዚህ የተነሣ ሰማያት ጠል ከለከሉ፤ ምድርም ፍሬዋን ነሣች።
\v 11 እኔ በምድሪቱና በተራሮች፤ በእህሉና በአዲሱ ወይን ጠጅ፤ በዘይቱና ምድር በምትሰጠው ሁሉ ላይ፣ በሰዎችና በእንስሳት፣ በእጆቻችሁ ሥራ ሁሉ ላይ ድርቅ አመጣለሁ!
\s5
\v 12 ከዚህ በኋላ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልና ሊቀ ካህኑ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ፣ ከምርኮ ከተረፉት ሕዝብ ሁሉ ጋር የአምላካቸው የያህዌን ድምጽ ሰሙ፤ አምላካቸው ያህዌ ልኮታልና ለነቢዩ ሐጌ ቃል ታዘዙ። ሕዝቡም ያህዌን ፈሩ።
\v 13 ከዚያም የያህዌ መልእክተኛ ሐጌ ለሕዝቡ የያህዌን መልእክት እንዲህ በማለት ተናገረ፤ “እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ! ይህ የያህዌ ቃል ነው!
\s5
\v 14 ስለዚህ ሄደው የአምላካቸውን የሠራዊት ጌታ የያህዌን ቤት እንዲሠሩ የይሁዳን ገዢ የሰላትያል ልጅ የዘሩባቤልን መንፈስና የኢዮሴዴቅ ልጅ የካህኑ ኢያሱን መንፈስ፣ እንዲሁም ከምርኮ የተረፉትን ሰዎች ሁሉ መንፈስ ያህዌ አነሣሣ።
\v 15 ይህ የሆነው በንጉሥ ዳርዮስ ሁለተኛ ዓመት በስድስተኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን ነው።
\s5
\c 2
\p
\v 1 በሰባተኛው ወር፣ ከወሩም በሃያ አንደኛው ቀን የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል መጣ እንዲህም አለ፤
\v 2 “ለይሁዳ ገዢ ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለካህኑ ኢያሱ፣ እንዲሁም ከምርኮ ለተረፉት ሰዎች ተናገሩ እንዲህም በሏቸው
\s5
\v 3 የዚህን ቤት የቀድሞ ክብር ያየ በመካከላችሁ ማን አለ? አሁንስ እንዴት ሆኖ ይታያችኋል? በዓይኖቻችሁ ፊት እንደ ተራ ነገር ቀልሎ የለምን?
\v 4 አሁንም ዘሩባቤል ሆይ፣ በርታ! ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው አንተም የኢዮሴዴቅ ልጅ ሊቀ ካህኑ ኢያሱ በርታ፤ በምድሪቱ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ በርቱ! - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና ተነሡ ሥሩ! ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው
\v 5 ከግብፅ በወጠችሁ ጊዜ በገባሁላችሁ ኪዳን፣ በመካከላችሁም ባለው መንፈሴ አትፍሩ!
\s5
\v 6 የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ በቅርብ ጊዜ ሰማያትንና ምድርን፣ ባሕርንና ደረቁን ምድር አናውጣለሁ!
\v 7 ሕዝቦችን ሁሉ አናውጣለሁ፤ ሕዝቦች የከበሩ ነገሮቻቸውን ወደ እኔ ያመጣሉ፤ ይህንንም ቤት በክብር እሞላዋለሁ! ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\s5
\v 8 ብርና ወርቁ የእኔ ነው! ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
\v 9 የወደፊቱ የዚህ ቤት ክብር ከመጀመሪያው ይበልጣል ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፤ በዚህ ቦታ ሰላም እሰጣለሁ - ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።”
\s5
\v 10 ዳርዮስ በነገሠ ሁለተኛው ዓመት፣ በዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛ ቀን የያህዌ ቃል በነቢዩ በሐጌ በኩል መጣ፤ እንዲህም አለ፣
\v 11 “የሠራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ሕጉ ምን እንደሚል ካህናቱን ጠይቁ፤
\v 12 አንድ ሰው ለያህዌ የተቀደሰውን ሥጋ በልብሱ እጥፋት ቢይዝ፣ በልብሱ እጥፋት እንጀራ ወይም ወጥ፣ የወይን ጠጅ ወይም ዘይት ወይ ሌላ ምግብ ቢነካ፣ ያ ምግብ ይቀደሳልን? ” ካህናቱም፣ “የለም፣ አይቀደስም” በማለት መለሱ።
\s5
\v 13 ሐጌም፣ “ሬሳ በመንካቱ የረከሰ ሰው ከእነዚህ አንዱን ቢነካ ይረክሳሉን? ” አለ። ካህናቱም፣ “አዎን፣ ይረክሳሉ” በማለት መለሱ።
\v 14 ስለዚህ ሐጌ መልሶ፣ “ ይህም ሕዝብ በፊቴ እንዲሁ ነው! - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው፤ የእጃቸው ሥራና ለእኔ የሚያቀርቡት ሁሉ የረከሰ ነው።
\s5
\v 15 እንግዲህ ከዘሬ ጀምራችሁ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ከመነባበሩ በፊት የነበረውን ሁኔታ ልብ በሉ፤
\v 16 ለምሆኑ ያኔ እንዴት ነበር? አንድ ሰው ሃያ መስፈሪያ እህል ጠብቆ ወደ ክምሩ ሲሄድ አሥር ብቻ አገኘ። አምሳ ማድጋ ወይን ጠጅ ለመቅዳት ወደ መጭመቂያው ሲሄድ ሃያ ብቻ አገኘ።
\v 17 እናንተንና የእጆቻችሁን ሥራ ሁሉ በዋግና በአረማሞ መታሁ፤ ያም ሆኖ ግን ወደ እኔ አልተመለሳችሁም - ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው።
\s5
\v 18 ከዚህ ቀን ጀምሮ ማለትም የያህዌ ቤተመቅደስ መሠረት ከተጣለበት ከዘጠነኛው ወር ሃያ አራተኛው ቀን ጀምሮ ወደፊት ቁጠሩ፤ ልብ አድርጋችሁ አስቡት!
\v 19 በጎተራው የቀረ ዘር ይኖራልን? የወይኑና የበለሱ፣ የሮማኑና የወይራው ዛፍ ፍሬ አላፈሩም! ከዚህ ቀን ጀምሮ እባርካችኋለሁ!”
\s5
\v 20 በዘጠነኛው ወር በወሩም ሃያ አራተኛ ቀን የያህዌ ቃል በድጋሚ ወደ ሐጌ መጣ፤ እንዲህም አለ፣
\v 21 “ለይሁዳ ገዥ ለዘሩባቤል እንዲህ በለው፤ “ሰማያትንና ምድርን አናውጣለሁ።
\v 22 የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የሕዝቦችን መንግሥት ብርታት አጠፋለሁ! ሰረገሎችንና በላያቸው ያሉትን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችና ጋላቢዎቻቸውን በገዛ ወንድሞቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።
\s5
\v 23 በዚያ ቀን - የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ እንዲህ የሚል ይሆናል- የሰላትያል ልጅ ባርያዬ ዘሩባቤል ሆይ፣ እኔ እወስድሃለሁ፤ ይህ የያህዌ ዐዋጅ ነው። እኔ መርጬሃለሁና ቀለበቴ ላይ እንደ ማህተም አደርግሃለሁ፤ ይህ የሠራዊት ጌታ የያህዌ ዐዋጅ ነው።

118
39-MAL.usfm Normal file
View File

@ -0,0 +1,118 @@
\id MAL
\ide UTF-8
\h ትንቢተ ሚልክያስ
\toc1 ትንቢተ ሚልክያስ
\toc2 ትንቢተ ሚልክያስ
\toc3 mal
\mt ትንቢተ ሚልክያስ
\s5
\c 1
\p
\v 1 በሚልክያስ በኩል ወደ እስራኤል የመጣው የያህዌ ቃል ዐዋጅ ይህ ነው።
\v 2 “እኔ ወድጃችኋለሁ” ይላል ያህዌ። እናንተ ግን፣ “እንዴት ወደድኸን? ” ብላችኋል? “ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ያዕቆብን ወደድሁ
\v 3 ዔሳውን ግን ጠላሁ። ተራራውን ባድማ አደረግሁ፤ ርስቱንም የምድረ በዳ ቀበሮዎች መኖሪያ አደረግሁ።”
\s5
\v 4 ኤዶምያስ፣ “ብንደመሰስ እንኳ፣ የፈረሰውን መልስን እንሠራዋለን” ይል ይሆናል፤ የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ “እነርሱ የሠሩ ይሆናል፤ እኔ ግን መልሼ አፈርሳለሁ።” ሌሎች ሰዎች፣ “የዐመፀኞች አገር፤ ያህዌ ለዘላለም የተቆጣው ሕዝብ” በማለት የጠሯቸዋል።
\v 5 የገዛ ዓይኖቻችሁ ይህን ያያሉ። ከእስራኤል ዳርቻዎች ወዲያ እንኳ ያህዌ ትልቅ ነው ትላላችሁ”
\s5
\v 6 ለእናንተ ስሜን ለታቃልሉ ካህናት “ልጅ አባቱን ያከብራል፤ አገልጋይም ጌታውን ያከብራል። እኔ አባት ከሆንሁ፣ ታዲያ፣ ክብሬ የታለ? ጌታስ ከሆንሁ፣ መፈራቴ የታለ? ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ። እናንተ ግን፣ “ስምህን ያቃለልነው በመንድነው? ” ብላችኋል።
\v 7 መሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ በማቅረብ ነው። እናንተ፣ “ያረከስንህ በምንድነው” ብላችኋል። የእግዚአብሔር ገበታ የተናቀ ነው በማለታችሁ ነው።
\s5
\v 8 የታወረውን እንስሳ መሥዋዕት ማቅረብ፣ በደል አይደለም? አንካሳውንና በሽተኛውን መሥዋዕት ማቅረብስ በደል አይደለም? እስቲ ያንኑ ለባለሥልጣን አቅርቡት፣ ይቀበላችኋልን? ወይስ በእናንተ ደስ ይለዋልን? ” ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ።
\v 9 አሁን ግን እንዲራራልን የእግዚአብሔርን ፊት ፈልጉ። ለመሆኑ፣ እንዲህ ዓይነቱን መሥዋዕት ይዛችሁ ስትቀርቡ እርሱ ይቀበላችኋልን? ይላል የሰራዊት ጌታ ያህዌ።
\s5
\v 10 መሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳት እንዳታነዱ፣ ምነው ከእናንተ አንዱ የቤተመቅደሱን ደጆች በዘጋ ኖሮ! በእናንተ ደስ አልሰኝም፤ ከእጃችሁም ማንኛውንም መሥዋዕት አልቀበልም ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\v 11 ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ በሕዝቦች መካከል ስሜ ታላው ይሆናል፤ በየቦታው ሁሉ በስሜ ዕጣንና ንጹሕ መሥዋዕት ይቀርባል። በሕዝቦች መካከል ስሜ ታላቅ ይሆናል” የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\v 12 እናንተ ግን “የእግዚአብሔር ማዕድ የረከሰ ነው በማለት ታረክሱታላችሁ፤ ምግቡም የተናቀ ነው” በማለት ታቃልሉታላችሁ።
\s5
\v 13 ደግሞም፣ “ይህ ድካም ነው” በማለት ፣ “በንቀት ጢቅ አላችሁበት” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። በዱር እንስሳ ተወስዶ የነበረውን ወይም አንካሳና በሽተኛውን መሥዋዕት ለማቅረብ ታመጣላችሁ። ታዲያ፣ ይህን ከእናንተ እጅ ልቀበል? ” ይላል ያህዌ።
\v 14 “መንጋው ውስጥ ያለውን ተባዕት በግ መሥዋዕት ለማቅረብ ተስሎ ሳለ ለእኔ ነውር ያለበትን እንስሳ የሚያቀርብ አታላይ ርጉም ይሁን! እኔ’ኮ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በአሕዛብ መካከል ይከበራል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\s5
\c 2
\p
\v 1 አሁንም፣ እናንተ ካህናት ይህ ትእዛዝ ለእናንተ ነው።
\v 2 “የማትሰሙና ለስሜ ክብር ለመስጠት በልባችሁም የማታኖኑት ከሆነ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፣ “መርገም እልክባችኋለሁ፤ በረከታችሁን እረግማለሁ። ትእዛዜን በልባችሁ አላኖራችሁምና በእርግጥ ረግሜአችኋለሁ።
\s5
\v 3 ዘራችሁን እገሥጻለሁ፤ የመሥዋዕታችሁንም ፋንድያ ፊታችሁ ላይ እበትናለሁ፤ እናንተም ከእርሱ ጋር ትጠፋላችሁ።
\v 4 ኪዳኔ ከሌዊ ጋር ይሆን ዘንድ ይህን ያዘዝሁ እኔ መሆኔንም ታውቃላችሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\s5
\v 5 “ከእርሱ ጋር ያደረግሁት ኪዳን የሕይወትና የሰላም ኪዳን ነበር፤ እነዚህን ለእርሱ ሰጠሁት፤ አከበርኩት፤ እርሱ አከበረኝ፤ በስሜ ፊት በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ቆመ።
\v 6 እውነተኛ ትምህርት በአንደበቱ ነበር፤ በከንፈሮቹ ምንም ሐሰት አልተገኘም። በሰላምና በጽድቅ ከእኔ ጋር ተመላለሰ፤ ብዙዎችንም ከኅጢአት መለሰ።
\v 7 የካህኑ ከንፈሮች ዕውቀትን ይጠብቃሉ፤ እርሱ የሠራዊት ጌታ የያህዌ መልዕክተኛ ስለሆነ ሰዎች ከአፉ ትምህርት መፈለግ ይኖርባቸዋል።
\s5
\v 8 እናንተ ግን ከእውነተኛው መንገድ ወጥታችኋል። ሕጉን በተመለከተም ብዙዎችን አሰናክላችኋል፤ የሌዊን ኪዳን አፍርሳችኋል።” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\v 9 “መንገዴን አልጠበቃችሁም፤ ትምሕርቱን በተመለከተ አድልዎ አድርጋችኋል፤ ስለዚህ እኔም በሰዎች ሁሉ ፊት እንድትዋረዱና እንድትናቁ አደርጋለሁ።”
\s5
\v 10 ለሁላችንም ያለን አንድ አባት አይደለምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? ታዲያ፣ እያንዳንዱ ሰው ለወንድሙ ታማኝ ባለመሆን የአባቶቻችንን ኪዳን ያረከስነው ለምንድንው?
\v 11 ይሁዳ አልታመነም። በእስራኤልና በኢየሩሳሌም አስጸያፊ ነገር ተፈጽሞአል።
\v 12 እንዲህ የሚያደርገውን ሰው፣ ሌላው ቀርቶ ለሠራዊት ጌታ ለያህዌ መሥዋዕት የሚያመጣ እንኳ ቢሆን፣ ያህዌ ከያዕቆብ ድንኳኖች ያስወግደው።
\s5
\v 13 እናንተ ይህንንም አድርጋችኋል፣ የያህዌን መሠዊያ በእንባ አጥለቅልቃችኋል፤ እርሱ ቁርባናችሁን ስለማይመለከት ወይ በደስታ ከእጃችሁ ስለማይቀበለው ትጮኻላችሁ ታለቅሳላችሁም።
\s5
\v 14 እናንተም፣ “ይህ ለምን ሆነ? ” በማለት ትጠይቃላችሁ። እንዲህ የሆነው ያህዌ በአንተና በወጣትነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለሆነ ነው፤ የቃል ኪዳን ጓደኝህና ሚስትህ ብትሆን እንኳ አንተ ለእርሷ ታማኝ አልነበርክም።
\v 15 በመንፈሱ ክፋይ እግዚአብሔር አንድ አላደረጋቸውምን? እርሱ አንድ ያደረጋችሁ ለመንድነው? ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሆን መሥዋዕት ስለፈለገ ነው። ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ከወጣትነት ሚስታችሁ ጋር ያላችሁንም ታማኝነት አታጉድሉ።
\v 16 “እኔ መፋታትን እጠላለሁ” ይላል የእስራኤል አምላክ ያህዌ፤ “ልብሱን በግፍ ሥራ የሚሸፍነውንውም ሰው እጠላለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። “ስለዚህ በመንፈሳችሁ ራሳችሁን ጠብቁ፤ ታማኝነታችሁንም አታጉድሉ።”
\s5
\v 17 በቃላችሁ ያህዌን አታክታችኋል። እናንተ ግን፣ “እርሱን ያታከትነው በምንድነው? ” ብላችኋል። “ክፉ የሚያደርግ ሁሉ በያህዌ ፊት መልካም ነው፤ እርሱም በክፉዎች ደስ ይለዋል፤ ወይም፣ “የፍትህ አምላክ ወዴት ነው? ” በመለታችሁ ነው።
\s5
\c 3
\p
\v 1 “እነሆ፣ መልእክተኝዬን እልካለሁ፤ እርሱም መንገዴን በፊቴ ያዘጋጃል። እናንተ የምትፈልጉትም ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ የመጣል። ደስ የምትሰኙበትን የቃል ኪዳኑ መልእክተፍኛ ለመጣ ነው” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\v 2 እርሱ የሚመጠበትን ቀን ማን መቋቋም ይችላል? እርሱ ሲገለጥ ማን ፊቱ መቆም ይችላል? ምክናቱም እርሱ እንደ አንጥረኛ እሳት፣ እንደ ለብስ አጠቢ ሳሙና ነው።
\v 3 ብር እንደሚያጠራና እንደ እንደሚያነጻ ሰው ይቀመጣል፤ የሌዊንም ልጆች ያጠራል እንደወርቅና እንደብር ያጠራቸዋል፤ እነርሱም የጽድቅን ቁርባን ለያህዌ ያመጣሉ።
\s5
\v 4 ያኔ የይሁዳና የኢየሩሳሌም ቁርባን እንደ ቀድሞ ዘመን፣ እንደጥንቱም ዘመን ያህዌን ደስ ያሰኘዋል።
\v 5 “በዚያ ጊዜ እኔ ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ። በመተተኞችና በአመንዝራዎች ላይ፣ በሐሰተኛ ምስክሮችና የሠራተኞቻቸውን ደመወዝ በሚከለክሉ ላይ፣ መበለቶችንና ድኻ አደጉን በሚጨቁን ላይ፣ መጻተኞችን ፍትሕ በሚነፍጉ ላይ፣ እኔንም በማያከብሩ ላይ በፍጥነት እመሰክርባቸዋለሁ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\s5
\v 6 እኔ ያህዌ አልተለወጥሁም፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች አልጠፋችሁም።
\v 7 ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከትእዛዞቼ ፈቀቅ ብላችኋል፤ እነርሱንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፤ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ። እናንተ ግን፣ “የምንመለሰው እንዴት ነው? ” ብላችኋል።
\s5
\v 8 ሰው ከእግዚአብሔር ይሰርቃልን? እናንተ ግን ከእኔ ሰርቃችኋል፤ ያም ሆኖ ግን፣ “ከአንተ የሰረቅነው እንዴት ነው? ” ብላችኋል። በዐሥራትና በበኩራት ነው።
\v 9 እናንተም ሆናችሁ መላው ሕዝብ ከእኔ ሰርቃችኋልና የተረገማችሁ ናችሁ።
\s5
\v 10 በቤቴ መብል እንዲኖር ሙሉ አስራት ወደጎተራ አስገቡ። “በቂ ቦታ እስከማይኖራችሁ ድረስ የሰማይን መስኮት ከፍቼ በረከትን ባላፈስስላችሁ በዚህ አሁን ፈትኑኝ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\v 11 የምድራችሁን ፍሬ እንዳያጠፋ እህላችሁን የሚያጠፉትን እገሥጻለሁ። እርሻ ላይ ያለው የወይን ተክላችሁም ፍሬ አልባ አይሆንም” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\v 12 የምድር ደስታ ስለምትሆኑ ሕዝቦች ሁሉ ቡሩካን ብለው ይጠሯችኋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\s5
\v 13 “እኔ ላይ የድፍረት ቃል ተናግራችኋል” ይላል ያህዌ። እናንተ ግን፣ “በአንተ ላይ የተናገርነው ምንድነው? ” ትላላችሁ።
\v 14 “እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው ብላችኋል። የእርሱን ትእዛዞች መጠበቅ፣ ወይም በሠራዊት ጌታ በያህዌ ፊት ሐዘንተኞች ሆነን መመላለሳችን ጥቅሙ ምንድነው? ” ብላችኋል።
\v 15 ስለዚህም አሁን እብሪተኞችን ቡሩካን እንላቸዋለን። ክፉ አድራጊዎችን መበልጸግ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔርን የሚፈታተኑትም ያመልጣሉ።
\s5
\v 16 ከዚያም ያህዌን የሚፈሩ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ። እግዚአብሔርም ሰማ፤ አደመጠም፤ ያህዌን ስለሚፈሩትና ስሙንም ስለሚያከብሩት ሰዎች በፊቱ መታሰቢያ እንዲሆን ተጻፈ።
\s5
\v 17 “እነርሱ የእኔ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፣ “እኔ በምሠራበት ቀን ርስቴ ይሆናሉ። ለሚያገለግለው ልጁ እንደሚራራ ሰው እኔም እራራላቸዋለሁ።
\v 18 በጻድቁና በዐመፀኛው መካከል፣ እግዚአብሔርን በሚያመልኩና እርሱን በማያመልኩ መካከል እንደገና ትለያላችሁ።
\s5
\c 4
\p
\v 1 “እብሪተኞችና ክፉ አድራጊዎች በሙሉ ገለባ የሚሆኑበት እንደምድጃ እሳት የሚነድ ቀን ይመጣል። የሚመጣው ቀን ያነዳቸዋል” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ፤ “ሥርም ሆን ቅርንጫፍ አይተውላቸውም።
\v 2 ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን ፈውስ በክንፎቹ የያዘ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላቸዋል። እናንተም ከጋጥ እንደተለቀቁ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።
\v 3 እኔ በምሠራበት ቀን ዐመፀኛውን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ጫማ በታች ዐመድ ይሆናሉ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።
\s5
\v 4 ለእስራኤል ሁሉ ሕጎችና ሥርዐቶች ይሆኑ ዘንድ ለአገልጋዬ ለሙሴ በኮሬብ የሰጠሁትን ትምህርቶች አስታውሱ።
\v 5 ታላቁና አስፈሪው የያህዌ ቀን ከመምጣቱ በፊት ነቢዩ ኤልያስን እልክላችኋለሁ።
\v 6 መጥቼ ምድርን ፈጽሜ እንዳላጠፋ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የልጆችንም ልብ ውደ አባቶች ይመልሳል።

203
manifest.yaml Normal file
View File

@ -0,0 +1,203 @@
dublin_core:
conformsto: 'rc0.2'
contributor:
- "Abera Wolde"
- "Andarge Arega"
- "Burje Duro"
- "Dagmawi Wube"
- "Daniel"
- "Ermias Gezahegn"
- "Feben Alemayehu"
- "Fikerte"
- "Kaleab Getachew"
- "LD"
- "Mesfin Tesfaye"
- "Rev. Endale Awgichew"
- "Tekalign Shiferaw Demissie"
- "Tensae Amdeyesus"
- "Tizita M"
- "Zekarias"
- "Zelalem Assefa"
creator: 'Door43 World Missions Community'
description: 'An unrestricted literal Bible'
format: 'text/usfm'
identifier: 'ulb'
issued: '2018-09-24'
language:
direction: 'ltr'
identifier: 'am'
title: 'Amharic'
modified: '2018-09-24'
publisher: 'Door43'
relation:
- 'am/tw'
- 'am/tq'
- 'am/tn'
rights: 'CC BY-SA 4.0'
source:
-
identifier: 'English ULB'
language: 'en'
version: '7'
subject: 'Bible'
title: 'Unlocked Literal Bible'
type: 'bundle'
version: '7.1'
checking:
checking_entity:
- 'Dr. Woyta Woza'
- 'Getachew Yohannes'
- 'Worku Ejere'
- 'Girma Getahun'
- 'Simon Zekewos'
checking_level: '3'
projects:
-
title: '1ኛ ሳሙኤል '
versification: ufw
identifier: '1sa'
sort: 9
path: ./09-1SA.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ሁለተኛ ዜና '
versification: ufw
identifier: '2ch'
sort: 14
path: ./14-2CH.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: '2ተኛ ነገስት '
versification: ufw
identifier: '2ki'
sort: 12
path: ./12-2KI.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: '2ኛ ሳሙኤል '
versification: ufw
identifier: '2sa'
sort: 10
path: ./10-2SA.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኦሪት ዘዳግም '
versification: ufw
identifier: 'deu'
sort: 5
path: ./05-DEU.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'መክብብ '
versification: ufw
identifier: 'ecc'
sort: 21
path: ./21-ECC.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኦሪት ዘፍጥረት '
versification: ufw
identifier: 'gen'
sort: 1
path: ./01-GEN.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ዕንባቆም '
versification: ufw
identifier: 'hab'
sort: 35
path: ./35-HAB.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ሐጌ '
versification: ufw
identifier: 'hag'
sort: 37
path: ./37-HAG.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ሆሴዕ '
versification: ufw
identifier: 'hos'
sort: 28
path: ./28-HOS.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኢዮብ '
versification: ufw
identifier: 'job'
sort: 18
path: ./18-JOB.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ትንቢተ ኢዩኤል '
versification: ufw
identifier: 'jol'
sort: 29
path: ./29-JOL.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ዮናስ '
versification: ufw
identifier: 'jon'
sort: 32
path: ./32-JON.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ኦሪት ዘሌዋውያን '
versification: ufw
identifier: 'lev'
sort: 3
path: ./03-LEV.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ትንቢተ ሚልክያስ '
versification: ufw
identifier: 'mal'
sort: 39
path: ./39-MAL.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ትንቢተ ሚክያስ '
versification: ufw
identifier: 'mic'
sort: 33
path: ./33-MIC.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ትንቢተ ናሆም '
versification: ufw
identifier: 'nam'
sort: 34
path: ./34-NAM.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ትንቢተ አብድዩ '
versification: ufw
identifier: 'oba'
sort: 31
path: ./31-OBA.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ሩት '
versification: ufw
identifier: 'rut'
sort: 8
path: ./08-RUT.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'መኃልየ መኃልይ ዘሰለሞን '
versification: ufw
identifier: 'sng'
sort: 22
path: ./22-SNG.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]
-
title: 'ሶፎንያስ '
versification: ufw
identifier: 'zep'
sort: 36
path: ./36-ZEP.usfm
categories: [ 'bible-ot' ]