am_ulb/60-JAS.usfm

215 lines
21 KiB
Plaintext
Raw Permalink Normal View History

2020-12-27 23:44:39 +00:00
\id JAS
\ide UTF-8
\h ያዕቆብ
\toc1 ያዕቆብ
\toc2 ያዕቆብ
\toc3 jas
\mt ያዕቆብ
\s5
\c 1
\cl ምዕራፍ 1
\p
\v 1 በኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር እስረኛና አገልጋይ የሆነ ያዕቆብ በክርስቶስ ኢየሱስ ለሚያምኑና በመላው ዓለም ለተበተኑት ለአሥራ ሁለቱ ነገዶች ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡
\v 2 ወንድሞቼ ሆይ፣ በልዩ ልዩ ፈተናዎች ውስጥ ማለፋችሁን እጅግ ደስ እንደሚያሰኝ ነገር ቊጠሩት፡፡
\v 3 በፈተና ውስጥ ሳላችሁ በእግዚአብሔር ስታምኑ ይበልጥ ሌሎች ፈተናዎችን በትዕግሥት ለማሳለፍ የሚረዱዋችሁ መሆኑን ትረዳላችሁ፡፡
\s5
\v 4 ክርስቶስን በሁሉም መንገድ ትከተሉ ዘንድ እስከ መጨረሻው በፈተና ጽኑ፤ ያንጊዜ መልካም ማድረግ አይከብዳችሁም፡፡
\v 5 ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡
\s5
\v 6 እግዚአብሔርን ስትለምኑ፣ የምትጠይቁትን እንደሚሰጣችሁ እመኑ፤ መልስ እንደሚሰጣችሁና ሁልጊዜም እንደሚረዳችሁ አትጠራጠሩ፤ የሚጠራጠሩ ሰዎች እግዚአብሔርን ሊከተሉት አይችሉም፤ መጠራጠር ልክ ተመልሶ እንደሚመጣ፣ ደግሞም በዚያው አቅጣጫ መጓዝን እንደማይቀጥል የባሕር ማዕበል ያለ ነገር ነው፡፡
\v 7 በእርግጥ የሚጠራጠሩ ሰዎች የሚጠይቁትን ነገር ለመፈጸም እግዚአብሔር አንድ ነገር ሊያደርግ እንደሚችል አያምኑም፡፡
\v 8 እነዚህ ሰዎች ኢየሱስን ለመከተል ወይም ላለመከተል ያልወሰኑ ናቸው፤ እነዚህም የሚናገሩትን ነገር የማያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡
\s5
\v 9 ድሀ የሆኑ አማኞች እግዚአብሔር ስላከበራቸው ደስ ሊሰኙ ይገባል፡፡
\v 10 ባለጠጋ የሆኑ አማኞችም እግዚአብሔር ትሑታን ስላደረጋቸው ደስ ሊሰኙ ይገባል፤ ልክ የበረሃ አበቦች እንደሚደርቁ ሁሉ፣ እነርሱም ሆኑ ሀብታቸው የሚያልፉ ናቸውና፡፡
\v 11 ፀሐይ በሚወጣ ጊዜ ሞቃታማ የሆነው ነፋስ ተክሎችን ያደርቃል፤ ደግሞም አበቦችን በምድር ላይ እንዲወድቁም ሆነ በውበታቸው እንዳይቀጥሉ ያደርጋቸዋል፡፡ ባለ ጠጎች ልክ እንደሚሞቱ አበቦች ሁሉ ገንዘብን እየሰበሰቡ ሳሉ ይሞታሉ፡፡
\s5
\v 12 በመከራ የሚጸኑትን ሰዎች እግዚአብሔር ያከብራቸዋል፤ ለሚወድዱት ሁሉ ተስፋ እንደ ሰጠው ለዘላለም እንዲኖሩ በማድረግ ብድራታቸውን ይከፍላቸዋል፡፡
\v 13 በኃጢአት ስንፈተን እግዚአብሔር እየፈተነን ነው ብለን ልናስብ አይገባም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ክፉን እንድንሠራ አይፈልግምና፤ ክፉን እንዲያደርግ ማንንም አይፈትንምና፡፡
\s5
\v 14 እያንዳንዱ ሰው የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲታለልና ሲሳብ ነው።
\v 15 ክፉ ምኞት ከተፀነሰ በኋላ ኀጢአት ይወለዳል፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞት ይወለዳል።
\v 16 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ አትታለሉ።
\s5
\v 17 ማንኛውም መልካምና ፍጹም ስጦታ እንደሚዘዋወር ጥላ ከማይለዋወጠው ከላይ ከሰማይ ከብርሃናት አባት ይወርዳል።
\v 18 በፍጥረታቱ መካከል እንደ በኵራት እንድንሆን እግዚአብሔር በእውነት ቃል ሕይወት ሊሰጠን ወደደ።
\s5
\v 19 የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን ዕወቁ። ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገዬ፣ ለመቆጣትም የዘገዬ ይሁን!
\v 20 ምክንያቱም የሰው ቊጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣም።
\v 21 ስለዚህ ርኵሰትንና በየቦታው ሞልቶ ያለውን ክፋት አስወግዳችሁ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁ የተተከለውን ቃል በትሕትና ተቀበሉ።
\s5
\v 22 ለቃሉ ታዘዙ እንጂ፣ ሰሚዎች ብቻ በመሆን ራሳችሁን አታታልሉ።
\v 23 ማንም ቃሉን እየሰማ ቃሉ የሚለውን ባያደርግ፣ ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ ሰው ይሆናል።
\v 24 ፊቱን አይቶ ይሄዳል፤ ምን እንደሚመስል ግን ወዲያው ይረሳዋል።
\v 25 ፍጹሙንና ነጻ የሚያወጣውን ሕግ በጥንቃቄ የሚመለከትና የሚኖርበት እንጂ፣ ሰምቶ እንደሚረሳው ያልሆነ ሰው በሚያደርገው ሁሉ የተባረከ ይሆናል።
\s5
\v 26 አንድ ሰው ሃይማኖተኛ ነኝ እያለ፣ አንደበቱን ግን ባይቆጣጠር፣ ልቡን ያስታል፤ ሃይማኖቱም ከንቱ ነው።
\v 27 በእግዚአብሔር በአባታችን ፊት ንጹሕና ርኵሰት የሌለበት ሃይማኖት ይህ ነው፤ አባት የሌላቸውንና መበለቶችን በችግራቸው መርዳት፤ በዓለም ካለ ርኵሰት ራስን መጠበቅ።
\s5
\c 2
\cl ምዕራፍ 2
\p
\v 1 ወንድሞች ሆይ፤ ለአንዳንዶች አድልዎ እያደረጋችሁ የክብር ጌታ የጌታችን አየሱስ ክርስቶስን እምነት እንከተላለን አትበሉ።
\v 2 የወርቅ ቀለበት ያደረገና የሚያማምሩ ልብሶች የለበሰ ወደ ስብሰባችሁ ሲገባና እንዲሁም አዳፋ ልብሶች የለበሰ ድኻ ቢገባ
\v 3 ትኵረታችሁ የሚያማምሩ ልብሶች የለበሰው ሰው ላይ ይሆንና፣ “እዚህ ደኅና ቦታ ላይ ተቀመጥ” ትሉታላችሁ፤ ድኻውን ግን፣ “እዚያ ቁም” ወይም “ከእግሬ በታች ተቀመጥ” ትሉታላችሁ
\v 4 ታዲያ፣ በመካከላችሁ አድልዎ ማድረጋችሁ አይደለምን፤ ደግሞስ በክፉ ዐሳብ የተያዛችሁ ፈራጆች መሆናችሁ አይደለምን?
\s5
\v 5 የተወደዳችሁ ወንድሞች ስሙ፤ በእምነት ባለ ጸጋ እንዲሆኑና፣ እርሱን ለሚወዱ ቃል የገባላቸውን መንግሥት እንዲወርሱ እግዚአብሔር የዚህ ዓለም ድኾችን አልመረጠምን?
\v 6 እናንተ ግን ድኾችን አዋረዳችሁ! የሚጨቁኗችሁ ባለ ጸጎች አይደሉምን? ወደ ፍርድ ቤት የሚጎትቱዋችሁስ እነርሱ አይደሉምን?
\v 7 የተጠራችሁበትን መልካም ስም የሚሳደቡ ባለ ጸጎቹ አይደሉምን?
\s5
\v 8 ይሁን እንጂ፣ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ተብሎ እንደ ተጻፈው የከበረውን ሕግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤
\v 9 ለአንዳንዶች አድልዎ ብታደርጉ ግን፣ ኃጢአት ትሠራላችሁ፤ እንደ ሕግ ተላላፊዎችም ትቆጠራላችሁ።
\s5
\v 10 ምክንያቱም ሕጉን የሚፈጽም፣ በአንዱ ግን የሚሰናከል፣ ሕጉን ሁሉ እንደ ተላለፈ ይቆጠራል!
\v 11 “አታመንዝር” ያለው እግዚአብሔር፣ “አትግደልም” ብሎአልና። ባታመነዝር ሆኖም ግድያ ብትፈጽም፣ የእግዚአብሔርን ሕግ ተላልፈሃል።
\s5
\v 12 ስለዚህ ነጻ በሚያወጣው ሕግ እንደሚፈረድባቸው ሰዎች ተናገሩ፤ ደግሞም ታዘዙ።
\v 13 ምክንያቱም ምሕረት በማያደርጉ፣ ምሕረት የሌለበት ፍርድ ይመጣባቸዋል። ምሕረት ፍርድን ያሸንፋል!
\s5
\v 14 ወንድሞቼ ሆይ፣ አንድ ሰው እምነት እንዳለው ቢናገር፣ ሥራ ግን ባይኖረው ምን ይጠቅማል? ያ እምነት ሊያድነው ይችላልን?
\v 15 አንድ ወንድም ወይም እኅት ልብስና የዕለት ምግብ ባይኖራቸው
\v 16 ከእናንተ አንዱ፣ “በሰላም ሂዱ፤ አይብረዳችሁ፤ በደንብ ጥገቡ” ቢላቸው፤ ለአካል የሚያስፈልጉ ነገሮችን ግን ባትሰጧቸው፣ ምን ይጠቅማል?
\v 17 ሥራ የሌለው እምነትም እንዲሁ በራሱ የሞተ ነው።
\s5
\v 18 ምናልባትም አንዱ፣ “አንተ እምነት አለህ እኔ ደግሞ ሥራ አለኝ” ሥራ የሌለው እምነትህን አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይል ይሆናል።
\v 19 አንድ እግዚአብሔር መኖሩን ታምናለህ፤ ትክክል ነህ። አጋንንትም ይህን ያምናሉ፤ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ።
\v 20 አንተ ሞኝ፣ እምነት ያለ ሥራ ከንቱ መሆኑን ማወቅ ትፈልጋለህ?
\s5
\v 21 አባታችን አብርሃም፣ ልጁ ይስሐቅን መሠዊያው ላይ ባቀረበ ጊዜ በሥራ ጸድቆ አልነበረምን?
\v 22 እምነት በሥራው ታየ፤ በዚያው ሥራ እምነት ዓላማውን ፈጸመ።
\v 23 “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ ጽድቅም ሆኖ ተቆጠረለት” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ተፈጸመ። ስለዚህም አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ።
\v 24 ሰው በእምነት ብቻ ሳይሆን፣ በሥራ እንደሚጸድቅ ታያለህ።
\s5
\v 25 በተመሳሳይ ሁኔታ ጋለሞታዪቱ ረዓብ መልእክተኞቹን ተቀብላ በሌላ መንገድ በሰደደቻቸው ጊዜ በሥራ አልጸደቅችምን?
\v 26 ከመንፈስ የተለዬ አካል ሙት እንደ ሆነ ሁሉ፣ ከሥራ የተለዬ እምነትም የሞተ ነው።
\s5
\c 3
\cl ምዕራፍ 3
\p
\v 1 ወንድሞቼ፣ እኛ የባሰውን ፍርድ እንደምንቀበል በመገንዘብ፣ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አትሁኑ።
\v 2 ሁላችንም በብዙ መንገድ እንሰናከላለን። በንግግሩ የማይሰናከል እርሱ ሰውነቱን ሁሉ መቆጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።
\s5
\v 3 ፈረሶች አፍ ውስጥ ልጓም ብናደርግ ይታዘዙልናል፤ መላ አካላቸውንም መቆጣጠር እንችላለን።
\v 4 ምንም እንኳ መርከቦች ግዙፍና በኃይለኛ ነፋስ የሚነዱ ቢሆኑም፣ የመርከቡ ነጂ በትንሽ መሪ ወደሚፈልገው አቅጣጫ እንደሚመራቸው አስተውሉ።
\s5
\v 5 እንዲሁም አንደበት ትንሽ የሰውነት ክፍል ሆኖ፣ በታላላቅ ነገሮች ይኵራራል። ጫካ የቱንም ያህል ሰፊ ቢሆን፣ በትንሽ እሳት ፍንጣሪ እንደሚቃጠል ልብ አድርጉ!
\v 6 አንደበትም እንዲሁ እሳት ነው፤ ሰውነትን ሁሉ የሚያረክስና የሕይወትንም መንገድ የሚያቃጥል፣ እርሱ ራሱም በገሃነም እሳት የሚቃጠል ሰውነታችን ብልቶች መካከል ያለ ኃጢአተኛ ዓለም ነው።
\s5
\v 7 ማንኛውም እንስሳ፣ ወፎች፣ በምድር የሚሳቡና ባሕር ውስጥ ያሉ ፍጥረቶች በሰው ተገርተዋል፤
\v 8 ነገር ግን ከሰው መካከል ማንም አንደበትን መግራት አልቻለም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ዕረፍት የለሽ ክፉ ነው።
\s5
\v 9 በአንደበት ጌታና አባታችንን እንባርካለን፤ በዚያው አንደበት በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን።
\v 10 ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣል። ወንድሞቼ፣ እንዲህ መሆን የለበትም።
\s5
\v 11 ከአንድ ምንጭ ጣፋጭና መራራ ውሃ ይወጣልን?
\v 12 ወንድሞቼ፣ የበለስ ዛፍ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ያበቅላልን? እንዲሁም ከጨው ውሃ ንጹሕ ውሃ ሊገኝ አይችልም።
\s5
\v 13 ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? ያ ሰው ከጥበብ በሚገኝ ትሕትና በሥራው መልካም ሕይወትን ያሳይ።
\v 14 በልባችሁ መራራ ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ካለ ግን አትኵራሩ፤ በእውነትም ላይ አትዋሹ።
\s5
\v 15 ይህ ከላይ የሚመጣ ጥበብ አይደለም፤ ይልቁንም ምድራዊ፣ መንፈሳዊ ያልሆንና አጋንንታዊም ነው።
\v 16 ምክንያቱም ቅናትና ራስ ወዳድ ምኞት ባለበት ሁከትና ክፉ ሥራ ይኖራል።
\v 17 ከላይ የሚመጣው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላም ወዳድ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላበት፣ ለሰዎች አድልዎ የማያደርግ ቅን ነው።
\v 18 ሰላምን ለሚያደርጉ የጽድቅ ፍሬ በሰላም ይዘራል።
\s5
\c 4
\cl ምዕራፍ 4
\p
\v 1 በእናንተ መከከል ያለው ፀብና ጭቅጭቅ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ውጊያ ከገጠሙት ክፉ ምኞቶቻችሁ የመጣ አይደለምን?
\v 2 የሌላችሁን ትመኛላችሁ። ትገድላላችሁ፤ ማግኘት ያልቻላችሁትን በብርቱ ታሳድዳላችሁ። ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ፤ ይሁን እንጂ፣ ከእግዚአብሔር ስለማትለምኑ አታገኙም።
\v 3 ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፤ ምክንያቱም ክፉ ምኞቶቻችሁን ለማሳካት ክፉ ነገሮችን ስለምትለምኑ ነው።
\s5
\v 4 እናንት አመንዝሮች! የዓለም ወዳጅ መሆን፣ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን እንደ ሆነ አታውቁም? ስለዚህ ማንም የዓለም ወዳጅ መሆን ቢፈልግ፣ የእግዚአብሔር ጠላት ይሆናል።
\v 5 ወይስ እግዚአብሔር እኛ ውስጥ ያኖረው መንፈስ ለእርሱ ብቻ እንድንሆን አብዝቶ ይቀናል የሚለው የመጽሐፍ ቃል በከንቱ የተነገረ ይመስላችኋል?
\s5
\v 6 እግዚአብሔር ግን አብዝቶ ጸጋውን ይሰጣል፤ መጽሐፍ፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው በዚህ ምክንያት ነው።
\v 7 ስለዚህ፣ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል።
\s5
\v 8 ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።
\v 9 እዘኑ፤ አልቅሱ፤ ጩኹ! ሳቃችሁን ወደ ሐዘን፣ ደስታችሁን ወደ ትካዜ ለውጡ።
\v 10 በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል።
\s5
\v 11 ወንድሞች ሆይ፣ እርስ በርስ አትወነጃጀሉ። ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙ ላይ የሚፈርድ ሕጉ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በእግዚአብሔርም ሕግ ላይ ይፈርዳል። ሕጉ ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ ፈራጆች እንጂ፣ ሕጉን አድራጊዎች አይደላችሁም።
\v 12 ሕጉን የሰጠና በሕጉም የሚፈርድ፣ ማዳንም መግደልም የሚቻለው አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ታዲያ፣ በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ?
\s5
\v 13 “ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ አገር እንሄዳለን፤ እዚያ አንድ ዓመት እንቆያለን፤ ነግደን እናተርፋለን” የምትሉ እናንተ ሰዎች ስሙ።
\v 14 ነገ የሚሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? ሕይወታችሁስ ምንድን ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ ጭጋግ አይደላችሁምን?
\s5
\v 15 ይልቁንም፣ “ጌታ ቢፈቅድ እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን” ማለት ይኖርባችኋል።
\v 16 አሁን ግን በዕቅዶቻችሁ ትመካላችሁ። እንዲህ ያለው ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው።
\v 17 ስለዚህ መልካም የሆነውን ማድረግ እንዳለበት እያወቀ ለማያደርግ ለዚያ ሰው ኃጢአት ይሆንበታል።
\s5
\c 5
\cl ምዕራፍ 5
\p
\v 1 እንግዲህ እናንተ ሀብታሞች ስለሚመጡባችሁ ክፉ ነገሮች አልቅሱ ዋይ ዋይም በሉ።
\v 2 ሀብታችሁ ሻግቶአል፤ ልብሳችሁንም ብል በልቶታል።
\v 3 ወርቃችሁና ብራችሁ ዝጎአል፤ ዝገቱም እናንተ ላይ ይመሰክራል፤ ሥጋችሁንም እንደ እሳት ይበላዋል። ለመጨረሻው ቀን ሀብታችሁን አከማችታችኋል።
\s5
\v 4 ልብ በሉ፤ እርሻችሁን ላጨዱ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ ይጮኻል! የአጫጆቹም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ጆሮ ደርሶአል።
\v 5 በምድር ላይ በምቾትና በመንደላቀቅ ኖራችኋል። ለዕርድ ቀን ልባችሁን አወፍራችኋል።
\v 6 እናንተን ያልተቃወመውን ጻድቅ ሰው ኮንናችሁታል፤ ገድላችሁታል።
\s5
\v 7 ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፣ የመጀመሪያውና የኋለኛው ዝናብ እስኪመጣ ድረስ የምድርን ፍሬ በትዕግሥት እንደሚጠብቅ ገበሬ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ታገሡ።
\v 8 እናንተም እንዲሁ ታገሡ፤ ልባችሁን አዘጋጁ፤ ምክንያቱም የጌታ መምጫ ቅርብ ነው።
\s5
\v 9 ወንድሞች ሆይ፤ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ። ልብ በሉ፤ ፈራጁ በሩ ላይ ቆሞአል።
\v 10 በጌታ ስም የተናገሩ ነቢያትን መከራና ትዕግሥት እንደ ምሳሌ ውሰዱት።
\v 11 ልብ በሉ፤ በትዕግሥት የጸኑትን፣ “የተባረኩ” እንላቸዋለን። ስለ ኢዮብ ትዕግሥት ሰምታችኋል፤ ጌታ ለኢዮብ የነበረውንም ዓላማ ታውቃላችሁ፤ ጌታ እጅግ ሩኅሩኅና መሐሪ ነው።
\s5
\v 12 ወንድሞቼ ሆይ፣ ከሁሉም በላይ አትማሉ፤ በሰማይም ሆነ በምድር ወይም በሌላ ነገር አትማሉ። ቃላችሁ “አዎን” ካላችሁ፣ “አዎን” ይሁን፤ “አይደለም” ካላችሁም፣ “አይደለም” ይሁን።
\s5
\v 13 በእናንተ መካከል መከራ የደረሰበት አለ? እርሱ ይጸልይ። ደስ ያለው አለ? እርሱ ይዘምር።
\v 14 በእናንተ መካከል የታመመ አለ? የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት እየቀቡ ይጸልዩለት፤
\v 15 የእምነት ጸሎት የታመመውን ሰው ይፈውሳል፤ ጌታም ያስነሣዋል። ኃጢአት አድርጎ ከሆነም እግዚአብሔር ይቅር ይለዋል።
\s5
\v 16 እንዲሁ ጌታ ከበሽታ ሊፈውስና ኃጢአትን ይቅር ሊል ስለሚችል ያደረጋችሁትን ኃጢአት በተመለከተ አንዳችሁ ለሌላችሁ ተናዘዙ፡፡ ጻድቃን ሰዎች ከጸለዩና አንድ ነገር እንዲያደርግላቸው ጌታን አጥብቀው ከጠየቁት፣ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ደግሞም በእርግጠኝነት ያን ነገር ያደርገዋል፡፡
\v 17 ነቢዩ ኤልያስ እንደኛው ያለ ሰው ቢሆንም፣ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፡፡ ለሦስት ዓመት ከስድስት ወራት ጊዜ ያህልም ዝናብ አልነበረም፡፡
\v 18 ከዚያም ዝናብ እንዲዘንብ እግዚአብሔርን እየለመነ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ዝናብን ላከ፣ ተክሎችም ዐደጉና ሰብልን ሰጡ፡፡
\s5
\v 19 ወንድቼና እኅቶቼ ሆይ፥ ከእናንተ አንዱ ዕውነተኛውን የእግዚአብሔርን ቃል መልእክት መታዘዝ ቢያቆም፣ ከእናንተ አንዱ ያደርገው ዘንድ እግዚአብሔር ለዚያ ሰው የነገረውን ነገር በመንገር ሊያሳምነው ይገባል፡፡
\v 20 የሚያሳምነው ሰውም ኃጢአት እየሠራ የነበረውን ሰው ተናግሮ ስሕተት ከመሥራት እንዲመለስ ስላስቻለው፣ እግዚአብሔር ያንን ሰው ከመንፈሳዊ ሞት ያድነዋል፤ ደግሞም ብዙ የሆኑት ኃጢአቶቹን ይቅር ይልለታል፡፡