1.3 KiB
1.3 KiB
መንፈስ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጌታ መንፈስ
እነዚህ ሦስት ቃሎች የሚያመለክቱት እርሱ ራሱ እግዚአብሔር የሆነው መንፈስ ቅዱስን ነው። እውነተኛው አንድ አምላክ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የሚባሉ አካላት አሉት።
- መንፈስ ቅዱስ አንዳንዴ፣ “መንፈስ” እና “የያህዌ መንፈስ” እና፣ “የእውነት መንፈስ” ተብሏል።
- መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር በመሆኑ ፍጹም ቅዱስ፣ እጅግ ንጹሕ፣ በባሕርዩና በሚያደርገው ነገር ሁሉ ፍጹም ጻድቅ ነው።
- ከአብና ከወልድ ጋር መንፈስ ቅዱስ ዓለምን በመፍጠር ተሳታፊ ነበር።
- እግዚአብሔር ወልድ ማለት ኢየሱስ ወደ ሰማይ ከተመለሰ በኋላ ሕዝቡን እንዲመራቸው፣ እንዲያስተምራቸው፣ እንዲያጽናናቸውና የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማድረግ እንዲያስችላቸው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ላከ።
- መንፈስ ቅዱስ ኢየሱስን መራው፤ በኢየሱስ የሚያምኑትንም ይመራቸዋል።