958 B
958 B
መርሳት፣ ተረሳ
“መርሳት” አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር ጨርሶ መተው ማለት ነው። “የተረሳ” በሌላው ወገን ጨርሶ የተተወ ግምት ውስጥ የማይገባ ሰው ነው።
- ሰዎች እግዚአብሔርን “ረሱ” ከተባለ ለእርሱ ታማኝ አይደሉም፤ ለእርሱ አይታዘዙም ማለት ነው።
- እግዚአብሔር ሰዎችን “ረሳ” ከተባለ እርሱ አይረዳቸውም፤ እንደ ገና ወደ እርሱ እንዲመለሱ የተለያየ መከራና ችግር እንዲደርስባቸው ይተዋቸዋል ማለት ነው።
- መዘንጋት ወይም የእግዚአብሔርን ትምህርት አለመከተል ማለትም ነው።
- “መርሳት” የሚለው ቃል፣ “ረስታችኋል” ወይም “ተረስታችኋል” በሚል የኀላፊ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።