1.2 KiB
1.2 KiB
ኅብረት
አጠቃላይ በሆነ ደረጃ፣ “ኅብረት” ተመሳሳይ ፍላጎትና ልምምድ ያላቸው የአንድ ማኅበር አባሎች መካከል የሚደረግ የወዳጅነት ግንኙነትን ያመለክታል።
- መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ኅብረት” በክርስቶስ የሚያምኑ ሰዎች አድነትን ነው ምንጊዜም የሚያመለክተው።
- ክርስቲያናዊ ኅብረት ከክርስቶስና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ባላቸው ግንኙነት አመካይነት አማኞች እርስበርስ ያላቸውን ግንኙነት የሚገልጹበት መንገድ ነው።
- የጥንት ክርስቲያኖች ኅብረታቸውን የሚገልጹት የእግዚአብሔርን ቃል ትምህርት በመካፈል፣ በአንድነት በመጸለይ ያላቸውን ሁሉ በመካፈልና አብረው በመመገብ ነበር።
- ክርስቲያኖች በኢየሱስ፣ በሰዎችና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን መለያየት ባስወገደበት የመስቃል ላይ መሥዋዕታዊ ሞቱ በማመናቸው ከእግዚአብሔርም ጋር ኅብረት አላቸው።