901 B
901 B
ለኪዳኑ ታማኝ፣ ለኪዳኑ እውነተኛ
ይህ አገላለጽ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለሕዝቡ የሰጠውን ተስፋ ለመፈጸም ታማኝ መሆኑን ነው።
- “ኪዳን” በተሰኘ ውል ያለው ስምምነት መሠረት እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እግዚአብሔር ተስፋ ሰጠ።
- ያህዌ፣ “ለኪዳኑ ታማኝ” ወይም፣ “ለኪዳኑ እውነተኛ” መሆኑ የሚያመለክተው እርሱ ለሕዝቡ የገባውን ቃል የሚጠብቅ መሆኑን ነው።
- የኪዳኑን ተስፋ ለመጠበቅ እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑ እርሱ ለሕዝቡ ያለው ተስፋ መገለጫ ነው።
- “እውነተኛ” የሚለው የሰጠውን ተስፋ ለመፈጸም ታማኝና መሆኑን የሚያመለክት ሌላ ቃል ነው።