1.3 KiB
1.3 KiB
መለየት
መለየት አንድን ነገር ወይም ሰው እግዚአብሔርን እንዲያገለግል መመደብ ማለት ነው። በዚህ መልኩ የተለየ ሰው ወይም እቃ ለእግዚአብሔር እንደ ተቀደሰና እንደ ተለየ ይቆጠራል።
- የዚህ ቃል ትርጕም፣ “መቀደስ” ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ሥርዓት ባለው መልኩ አንድን ሰው ለእግዚአብሔር አገልግሎት መለየት የሚለውንም ይጨምራል።
- ለእግዚአብሔር የተለየ ነገሮች የመሥዋዕት እንስሳትን፣ የሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያንና መገናኛው ድንኳንን ወይም ቤተ መቅደሱንም ይጨምራሉ።
- ለእግዚአብሔር የተለዩ ሰዎች ካህናትን፣ የእስራኤል ሕዝብንና ያደጉ ወንድ ልጆችን ይጨምራል።
- እንደነጹና በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ ሰዎችን ወይም ነገሮችን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ዝግጁ ማድረግን ከሆነ፣ “መለየት” የሚለው ቃል አንዳንዴ፣ “ማንጻት” ከተሰኘው ጋር ተመሳሳይ ትርጕም ይኖረዋል።