1.1 KiB
1.1 KiB
ልጆች፣ ልጅ
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ልጅ” የሚለው ቃል ሕፃንን ጨምሮ በአጠቃላይ በዕድሜ ወጣት የሆነውን ያመለክታል። “ልጆች” የብዙ ቊጥር ሲሆን፣ ጥቂት ምሳሌያዊ ጠቀሜታዎችም አሉት።
- አንዳንዴ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ደቀ መዛሙርት ወይም ተከታዮች፣ “ልጆች” በመባል ተጠርተዋል።
- የአንድን ሰው ዘሮች ለማመልከት፣ “ልጆች” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።
- “የ. . .ልጆች” የሚለው ሐረግ የአንድን ነገር ባሕርይ መያዝ ያመለክታል። የሚከተሉት ለዚህ ምሳሌ ይሆናሉ፤
- የብርሃን ልጆች
- የመታዘዝ ልጆች
- የዲያብሎስ ልጆች
ይህ አባባል መንፈሳዊ ልጆች የሆኑ ሰዎችንም ያመለክታል። ለምሳሌ፣ “የእግዚአብሔር ልጆች” ሲባል በኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር የሆኑ ሰዎችን ያመለክታል።