am_tw/bible/kt/call.md

1.9 KiB

መጥራት፣ ጥሪ፣ ተጠራ፣ መጣራት

“መጥራት” እና “መጣራት” የተሰኙ ቃሎች ቅርብ ላልነበረ ሰው ጮኽ ብሎ አንዳች ነገር መናገር ማለት ነው። ሌሎች ምሳሌያዊ ትርጕሞችም አሏቸው።

  • አንድን ሰው “መጣራት” ሩቅ ላለ ሰው ጮኽ ብሎ መናገር ማለት ሲሆን፣ ርዳታ መጠየቅ፣ በተለይም የእግዚአብሔርን ርዳታ መጠየቅ ማለትም ይሆናል።
  • ብዙውን ጊዜ መጽሕፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መጥራት” ሲባል፣ “ና ማለት” ወይም፣ “እንዲመጣ ማዘዝ” ወይም፣ “እንዲመጣ መጠየቅ” ማለት ነው።
  • ሕዝቡ እንዲሆኑ ወደ እርሱ እንዲመጡ እግዚአብሔር ሰዎችን ይጣራል። ይህ ለእነርሱ፣ “ጥሪ” ነው።
  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “መጠራት” የሚለው ቃል የእርሱ ልጆች እንዲሆኑ፣ በኢየሱስ በኩል የሚገኘውን የመዳን መልእክት የሚናገሩ አገልጋዮቹ እንዲሆኑ እግዚአብሔር ሰዎችን መሾሙን ወይም መምረጡን ለማመልከትም ጥቅም ላይ ይውላል።
  • ይህ ቃል ለአንድ ሰው ስም ማውጣትን በተመለከተም ጥቅም ላይ ይውላል። “ዮሐንስ ተባለ” ሲባል፣ “ዮሐንስ ተብሎ ተጠራ” ወይም “የእርሱ ስም ዮሐንስ ሆነ” ማለት ነው።
  • “በአንድ ሰው ስም መጠራት” ማለት ለአንድ ሰው የሌላው ሰው ስም ተሰጠው ማለት ነው። እግዚአብሔር ሕዝቡን በራሱ ስም እንደ ጠራ ይናገራል።
  • “በስሜ ጠርቻችኋለሁ” የተሰኘው የተለየ ሐረግ እግዚአብሔር ሰውን በግል በስሙ ያውቀዋል በተለየ ሁኔታም መርጦታል ማለት ነው።