1.1 KiB
1.1 KiB
ደም
“ደም” ጉዳት ወይም ቁስል ሲኖር ከአንድ ሰው ቆዳ የሚወጣ ቀይ ፈሳሽ ነገርን ያመለክታል። ደም ለሰው አካል ሕይወት ሰጪ ምግብን ያመጣል።
- ደም የሕይወት ምሳሌ ነው፤ የደም መፍሰስ የሕይወት መጥፋት ወይም የሞት ምሳሌ ነው።
- ሰዎች ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ሲያቀርቡ እንስሳ ያርዱና ደሙን መሠዊያው ላይ ያፈስሱ ነበር። ይህም ለሰዎች ኃጢአት ክፍያ እንዲሆን የእንስሳው ሕይወት መሥዋዕት የመሆኑ ምስላ ነበር።
- በመስቀል ላይ ሞቱ የኢየሱስ ደም ሰዎችን ከኃጢአታቸው የነጻቸዋል፤ ለኃጢአታቸው ይገባቸው የነበረው ቅጣት የመከፈሉ ምሳሌ ነው።
- “ሥጋና ደም” የሰው ልጆችን የሚመለከት ፈሊጣዊ አንጋገር ነው።
- “ሥጋና ደም” በዝምድና የተሳሰሩ ሰዎችን የሚመለከት ፈሊጣዊ አነጋገር ነው።