932 B
932 B
መባረክ፣ ተባረክ፣ በረከት
አንድ ሰው ወይም አንድ ነገር፣ “መባረክ” በዚያ ሰው ወይም ነገር ላይ መልካምና ጠቃሚ ነገር እንዲሆን ማድረግ ማለት ነው።
- አንድን ሰው መባረክ በዚያ ሰው ላይ ጠቃሚ እና ቀና ነገር እንዲሆን ምኞትን መግለጽም ነው።
- መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈበት ዘመን ጊዜ አባት ለልጆቹ የበረከት ቃል ይናገር ነበር።
- ሰዎች እግዚአብሔርን “ሲባርኩ” ወይም እግዚአብሔር እንዲባረክ ምኞታቸውን ሲገልጹ እርሱን እያመሰገኑ ነው ማለት ነው።
- “መባረክ” የሚለው ቃል ምግብ ከመበላቱ በፊት እንዲቀደስ ወይም ስለዚያ ምግብ እግዚአብሔርን ለማመስገን ጥቅም ላይ ይውላል።