am_tn/oba/01/12.md

1.9 KiB

አጠቃላይ መረጃ

እግዚአብሄር ለኤዶም መልዕክቱን በአብድዩ በኩል መላኩን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ

ቁጥር 12፡-14- እግዚአብሄር ለኤዶም ሕዝብ እስራኤልን ባለመንከባከባቸው ተደጋጋሚ ትእዛዝ መስጠቱን የያዘ ክፍል ነው፡፡

ደስ አይበልህ ( ደስ ይልህ ዘንድ )

እርካታ አይሰማህ

በመከራ ቀን ወንድምህን

ወንድምህ የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእስራኤልን ህዝብ ነው፡፡ ምክኒያቱም ያዕቆብና ኤሳው ወንድማማች ስለነበሩ፡፡

በመከራው ቀን

“ክፉ ነገር ባጋጠመው ጊዜ”

ቀን(ቀኑ)

ይህ ባቢሎን እስራኤልን በተደጋጋሚ ያጠቃበትና ያጠፋበት ቀንን ለማመልከት ነው

በጥፋታቸው ቀን

“ጠላቶቻቸው ባጠፏቸው ጊዜ”

በመከራቸው ቀን

በተጨነቁ ጊዜ

ጥፋት…….ውድመት……መፈራረስ

ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ቃላት ሲሆኑ አንድ ቃል ብቻ ያለው ቋንቋ በዚያው ቃል ሦስቱንም ትርጉም መጠቀም ይቻላል፡፡

በመከራቸው ላይ

መጥፎ ነገር ስለደረሰባቸው( በእነርሱ ላይ ስለደረሰ)

በሀብታቸው ላይ እጅህን አትዘርጋ

“ሀብታቸውን አትውሰድ” ወይም “ሀብታቸውን አትዝረፍ”

መንታ መንገድ

ሁለት መንገዶች የሚገናኙበት ቦታ

የሸሹትንም ለመግደል

“ለማምለጥ የሚያገለግሉትንም የእስራኤልን ህዝብ ለመግደል” ወይም ለማምለጥ የሚሞክሩትን ለመያዝ

ከእርሱ የቀሩትን አሳልፈህ አትስጥ

“በህይወት ያሉትን ይዘህ ለጠላቶቻቸው አትስጥ”