am_tn/jud/01/12.md

2.5 KiB

ይሁዳ 1፡ 12-13

እነዚህ ናቸው በዚህ ሥፍራ ላይ “እነዚህ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ፈርሃ እግዚአብሐር ያሌላቸውን ሰዎችን ነው፡፡ በበገራ የደረቁ ፍሬ የማያፈሩ ዛፎች ናቸው በበጋ ወራት መጨረሻ ላይ አንዳንድ ዛፎች ፍሬ እንደማያፈሩ ሁሉ ፈርሃ እግዚአብሔር ያሌላቸው ሰዎችን ጽድቅ የሞላበት እምነት እና ሥራ የላቸውም፡፡ (ተመልከት፡ [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]]) ፍሬ ያሌላቸው፣ ሁለት ጊዜ የሞቱ ልክ ሁለት ጊዜ እንደሞተ ዘፍ ፍሬ እንደማያፈራ ሁሉ ፈርሃ እግዚአብሔር ያሌለው ሰውም በውስጡ ምንም እሴት አይኖርም እንዲሁም በውስጡ ምንም ሕይወት የለም፡፡ (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]]) ከነሥራቸው የተነቀሉ ልክ ከነሥራቸው የተነቀሉ ዛፎች ፈርሃ እግዚአብሔር ያሌላቸው ሰዎች የሕይወት ምንጭ ከሆነው ከእግዚአብሔር የተለዩ ናቸው፡፡ (ተመልከት፡ [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]]) ጨካኝ የባሕር ማዕበል፥ የባሕር ማዕበል በንፈስ እንደሚንቀሳቀስ ሁሉ ፈርሃ እግዚአብሔር ያሌላቸው ሰዎችም የእምነት መሠረት ዬለቸውም እንዲሁም በተለያየ አቅጣጫ በቀላሉ ወዛወዛሉ፡፡ (ተመልከት፡ [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]]) የገዛ ነውራቸውን አረፋ እየደፈቁ ንፋስ ማዕበሉን እየገፋ ቆሻሻ አረፋ እንደሚያስደፍቅ ሁሉ እነዚህ ሰዎችም በስህተት ትምህርታቸው እና ተግበራቸው አማካኝነት ረራሳቸውን ያዋርዳሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡ "ማዕበል አረፋ እና ቆሻሻ እንደሚያወጣ ሁሉ እነዚህ ሰዎች በእፍረታቸው ሌሎች ሰዎችን ይበክላሉ፡፡ (ተመልከት: [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]]) ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የተጠበቀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው። ለመከታተል አስቸጋሪ እንደሆኑት በሰማይ ላይ እንደሚበሩት ክዋክብት እነዚህን ሰዎች መከተል የለባችሁም፡፡ (ተመልከት፡ [[rc:///ta/man/translate/figs-metaphor]])