am_tn/jer/26/13.md

3.0 KiB

መንገዶቻችሁ…ልምምዶቻችሁ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ከሞላ ጎደል ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "እናንተ የምታደረጎቸው ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌን ድምጽ ስሙ

ድምጽ ለሰውየው ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፤ ደግሞም ይኸው ቃል "አድምጡ" ወይም "ታዘዙ" በሚል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ያህዌን ታዘዙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በዐይኖቻችሁ መልካም እና ትክክል ሆኖ የሚገኘውን ለእኔ አድርጉ

"መልካም" እና "ትክክል" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ዐይን የሚለው ለሰው አስተሳሰብ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ "ማድረግ ይገባል የምትሉትን ትክክለኛ ለገር ለእኔ አድርጉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የንጹሃንን ደም በራሳችሁ፣ በከተማይቱ እና በነዋሪዎቿ ላይ እያመጣችሁ ነው

ደም በግፍ ለሚደርስ ሞት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን፣ በአንድ ሰው ላይ ደም ማምጣት በጥቃት ለደረሰ ሞት ተጠያቂ ማድረግ ነው፡፡ "ራሳችሁን እና ይህችን ከተማ እንዲሁም ነዋሪዎቿን በግፍ ለሚደረግ የንጹሃን ሰዎች ሞት ተጠያቂ እያደረጋችሁ ነው፡፡" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ይህች ከተማ እና ነዋሪዎቿ

እነዚህ አንድ ህዝብ የተገለጸበት ተመሳሳይ መንገድ ናቸው፡፡ ይህም ምናልባት በመጀመሪያ እንደ ቡድን ከዚያም እንደ ግለሰቦች የተነገረ ነው፡፡ ከተማይቱ የሚለው በከተማዋ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ ነው፡፡ "በከተማይቱ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ እና በዚህ የሚኖሩ እያንዳንዳቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ለጆሯችሁ

ጆሮ የሚለው ጆሮ ለሚሰማው ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ "እናንተ እንድትሰሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)