1.2 KiB
1.2 KiB
የቂሶን ወንዝ ጠራርጎ ወሰዳቸው
በከባድ ዝናብ ምክንያት ወንዙ በፍጥነት ስለሞላ ሠረገላዎቹ በጭቃ ተይዘው ስለነበር ብዙ ወታደሮች ሰመጡ። አ.ት፡ “የቂሶን ወንዝ ጎረፈና የሲሣራን ወታደሮች ጠራርጎ ወሰዳቸው”
ቂሶን
ይህንን በመሳፍንት 4፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምከው ተመልከት።
ነፍሴ ሆይ፣ በርቺ፣ ተሰለፊ
እዚህ ጋ “ነፍስ” የሰውን ሁለንተና ያመለክታል። “የእኔ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ዲቦራን ነው። አ.ት፡ “እንድበረታና እንድሰለፍ ለራሴ እነግራለሁ”
ከዚያም የሚጋልቡ የፈረሶች ኮቴ ድምፅ ተሰማ፣ የኃያላኑ ግልቢያ
ይህ የሚገልጸው ከጦርነት የሚሸሹ የብዙ ፈረሶችን ድምፅ ነው። አ.ት፡ “ከዚያም በሽሽት ላይ ያሉ የፈረሶችን ድምፅ ሰማሁ። ብርቱዎቹ የሲሣራ ፈረሶች እየሸሹ ነበር”
መጋለብ
በፍጥነት መሮጥ