Mon Jun 19 2017 15:48:54 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2017-06-19 15:48:55 +03:00
parent 801e12b57f
commit 4d68c60ce8
6 changed files with 63 additions and 0 deletions

7
02/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,7 @@
\c 2 \v 1 \v 2 1. ክፉ ነገር ለማድረግ ለሚያቅዱ
መኝታቸው ላይ ሆነው ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው፡፡
ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው
ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን ሥራ ላይ ያውሉታል፡፡
2. የዕርሻ ቦታ ሲፈልጉ፣ ቀምተው ይወስዳሉ
ቤት ሲፈልጉ ነጥቀው ይወስዳሉ፡፡
የሰው መብት ረግጠው ሀብቱን ይዘርፋሉ

12
02/03.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,12 @@
\v 3 \v 4 \v 5 3. ስለዚህ ያህዌ እንዲህ ይላል
በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት አመጣለሁ
ከዚህም ልታመልጡ አትችሉም፡፡
ያ የመከራ ጊዜ ስለሚሆን
ከእንግዲህ በእብሪት አትኖሩም፡፡
4. በዚያ ቀን ጠላቶቻችሁ ይሳለቁባችኃል
በሐዘን እንጉርጉሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኃል
እኛ እስራኤላውያን ፈጽሞ ጠፍተናል
ያህዌ የሕዝቤን ንብረት ወስዶ
ርስታችንንም ለከሐሂዲዎች አከፋፈለ
5. ስለዚህ እናንተ ባለጸጐች በያህዊ ጉባኤ ውስጥ
ርስት በዕጣ የሚከፋፈሉ ልጆች አይኖሯችሁም፡፡

11
02/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,11 @@
\v 6 \v 7 \v 8 6. ‹‹ትንቢት አትናገር››
ምንም ውርደት አይደርስብንም፤ ስለ እነዚህ
ነገሮች ትንቢት አትናገር ይላሉ፡፡
7. የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ እንደህ መባል ነበረበትን?
የያህዌ ትዕግሥት አልቋልን?
እነዚህስ የእርሱ ድርጊቶች ናቸውን?
አካሄዳቸው ቀና ለሆነ ሰዎች
ቃሎቼ መልካም አያደርጉምን?
8. በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ በጠላትነት ተነሥታችኃል
ከጦርነት በኃላ ሰላም ነው ብለው ወደሚያስቡት እንደሚመለሱ ወታደሮች
ምንም ሳይጠራጠሩ የሚያልፉ ሰዎችን ልብስ ገፋችኃል፡፡

8
02/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
\v 9 \v 10 \v 11 9. የወገኔን ሴቶች ከሚወዱት ቤታቸው አባረራችሁ
በረከቴን ለዘላለም ከልጆቻቸው ወሰዳችሁ፡፡
10. በርኩሰት ምክንያት ከባድ ጥፋት ስለሚመጣ
እዚህ ቦታ መቆየት አትችሉም፤
ስለዚህ ተነሥታችሁ ሂዱ፡፡
11. አንድ ሰው በሐሰት መንፈስ ተነሣሥቶ
‹‹ስለ ወይን ጠጅና ጠንካራ መጠጥ ትንቢት እናገራለሁ›› ቢል፤
በእነዚህ ሰዎች ዘንድ እንደ ነቢይ ይቆጠራል፡፡

8
02/12.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,8 @@
\v 12 \v 13 12. ያዕቆብ ሆ በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤
የእስራኤልን ትሩፍ ጉረኖ ውስጥ እንዳለ በጐች
በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ አመጣቸዋለሁ፡፡
ከሕዝቡ ብዛት የተነሣ ታላቅ ጩኸት ይሆናል፡፡
13. መንገዳቸውን የሚከፍትላቸው መሪ ከእነርሱ ፊት ፊት ይሄዳል
እነርሱም ተግተልትለው በበሩ ይወጣሉ
ንጉሣቸው ፊት ፊታቸው ይሄዳል፤
ያህዌ መሪያቸው ይሆናል፡፡

17
03/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,17 @@
\c 3 \v 1 \v 2 \v 3 1. ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤
‹‹እናንተ የያዕቆብ መሪዎች
የእስራኤልም ቤት ገዦች አድምጡ፤
ፍትሕን ማወቅ ይገባችሁ አልነበረምን?
2. እናንተ ግን መልካሙን ጠላችሁ
ክፉን ወደዳችሁ
ቆዳቸውን ገፈፋችሁ
ሥጋቸውን ከአጥንታቸው ጋጣችሁ
የሕዝቤን ሥጋ በላችሁ
ቆዳቸውን ገፈፋችሁ
ዐጥንቶቻቸውን ሰባበራችሁ፤
በመጥበሻ እንደሚጠበስ
በድስት እንደሚቀቀል ሥጋ ቆራረጣችኃቸው፡፡
3. እናንተ መሪዎች ወደ ያህዌ ትጮኻላችሁ
እርሱ ግን አይሰማችሁም፡፡
ከክፉ ሥራችሁ የተነሣ
በዚያ ጊዜ ፊቱን ከእናንተ ይሰውራል፡፡