Sun Oct 14 2018 19:38:59 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2018-10-14 19:38:59 +03:00
parent 06b42df36d
commit 9949134d81
4 changed files with 11 additions and 0 deletions

4
33/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,4 @@
\c 33 \v 1 1. ያህዌ ሌላም መልእክት ሰጠኝ፤ እንዲህም አለኝ፤
\v 2 2. ‹‹የሰው ልጅ ሆይ ለአገርህ ሰዎች ለእስራኤላውያን እንዲህ በል፤ በአንድ አገር ላይ የጠላት ሰራዊትን ቢመጣ፣ ሕዝቡም በመካከሉ ጠባቂ ቢመድብ፣
\v 3 3. የጠላትን መምጣት ተመልክቶ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ መለከት ቢነፋ፣
\v 4 4. ሰው ግን ይህን የማስጠንቀቂያ ድምፅ ሰምቶ ችላ በማለት ጠላት አደጋ ጥሎበት ቢሞት ጥፋቱ የራሱ ነው፡፡

2
33/05.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 5 5. ማስጠንቀቂያውን ቢያደምጥ ኖሮ፣ ሕይወቱን ያድን ነበር፤ ያን ባለ ማድረጉ ይሞታል፤ ጥፋቱ ግን የራሱ ነው፡፡
\v 6 6. ጠባቂው ግን ጠላት እየመጣ መሆኑን ተመልክቶ ሕዝቡን ለማስጠንቀቅ መለከት ባይነፋ፣ ከሕዝቡም አንዱ በጠላት ቢገደል፣ እኔ በኃላፊነት የምጠይቀው ጠባቂውን ነው፡፡

3
33/07.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,3 @@
\v 7 7. የሰው ልጅ ሆይ፣ እነሆ እኔ አንተን የእስራኤል ሕዝብ ጠባቂ አድርጌሃለሁ፤ እኔ የምሰጥህን ማስጠንቀቂያ ሁሉ ለእነርሱ ማስተላለፍ አለብህ፡፡
\v 8 8. አንድን ዐመፀኛ፣ ‹‹በኃጢአትህ ትሞታለህ›› ብለው ቃሌን ለእርሱ መናገር አለብህ፡፡ ከኃጢአቱ እንዲመለስ ያንን ሰው ባታስጠነቅቀው፣ ያ ሰው በኃጢአቱ ይሞታል፣ እኔ ግን ለደሙ ኃላፊ አድርጌ የምጠይቀው አንተን ነው፡፡
\v 9 9. ከኃጢአቱ እንዲመለስ ብታስጠነቅቀውና እርሱ ግን ያንን ባያደርግ፣ በኃጢአቱ ይሞታል፤ አንተ ግን ሕይወትህን ታድናለህ፡፡

2
33/10.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1,2 @@
\v 10 10. ሰው ልጅ ሆይ፣ ለእስራኤላውያን እንዲህ በላቸው፤ ‹በደላችንና ኃጢአታችን ከብዶናል፤ ከዚህም የተነሣ ልንጠፋ ነው፤ ታዲያ፣ እንዴት መኖር እንችላለን? ትላላችሁ፡፡
\v 11 11. አንተም እንዲህ በላቸው፤ ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ‹እኔ ሕያው እንደ መሆኔ፣ የዐመፀኛውን ሞት አልወድም፤ ከዚያ ይልቅ ከዐመፃው ተመልሶ በሕይወት ቢኖር እወዳለሁ፡፡ ስለዚህ ንስሓ አድርጉ፡፡ ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ! እናንተ እስራኤላውያን ለምን ትሞታላችሁ?