Tue Aug 23 2016 22:20:12 GMT-0700 (Pacific Daylight Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2016-08-23 22:20:12 -07:00
parent 69caa2ac1e
commit e75250d3a9
5 changed files with 5 additions and 0 deletions

1
16/27.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 27 \v 28 27 የወህኒ ቤቱም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ በሮቹ እንደተከፈቱ አየ፤ እስረኞቹ ያመለጡ ስለ መሰለውም ሰይፉን መዞ ራሱን ሊገድል ቃጣ። 28 ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፣ “ራስህን አትጉዳ! እኛ ሁላችን እዚሁ አለን” ብሎ ጮኸ።

1
16/29.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 29 \v 30 \v 31 29 የወህኒ ቤት ጠባቂውም መብራት ለምኖ ሮጦ ወደ ውስጥ ገባ፤ በፍርሀት እየተንቀጠቀጠም በጳውሎስና በሲላስ ፊት ተደፋ። 30 ወደ ውጪም አስወጥቶአቸው፣ “ጌቶች፤ ለመዳን ምን ማድረግ አለብኝ?” አላቸው። 31 እነርሱም፣ “በጌታ ኢየሱስ እመን፤ አንተም ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” አሉት።

1
16/32.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 32 \v 33 \v 34 32 እነርሱም ለእርሱና አብረውት በቤት ለነበሩ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ተናገሩ። 33 የወህኒ ቤት ጠባቂውም ሌሊት፣ በዚያው ሰዓት ወስዶአቸው ቁስላቸውን አጠበላቸው። እርሱና ቤተ ሰዎቹም ሁሉ ወዲያው ተጠመቁ። 34 ጳውሎስንና ሲላስንም ወደ ቤቱ ይዞአቸው ወጣ፤ ምግብም አቀረበላቸው። በእግዚአብሔርም በማመኑ ከቤተ ሰዎቹ ጋር እጅግ ደስ አለው።

1
16/35.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 35 \v 36 35 ሲነጋም ገዦቹ፣ “እነዚያን ሰዎች ልቀቋቸው” የሚል ትእዛዝ ለጠባቆቹ ላኩ። 36 የወህኒ ቤት ጠባቂውም፣ “ገዦቹ እንድትፈቱ ትእዛዝ ለእኔ ልከዋል፤ ስለዚህ ውጡና በሰላም ሂዱ” ብሎ ለጳውሎስ ነገረው።

1
16/37.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 37 \v 38 \v 39 37 ጳውሎስ ግን እንዲህ አላቸው፤ “ሮማውያን የሆነውን እኛን ያለ ፍርድ በሕዝብ ፊት ደብድበውናል፤ ወደ ወህኒም አስገብተውናል፤ ታዲያ፣ አሁን በድብቅ ያስወጡናል? በፍጹም አይሆንም፤ እነርሱ ራሳቸው መጥተው ያስወጡን።” 38 ጠባቂዎቹም ይህንኑ አባባል ለገዦቹ ነገሯቸው። ገዦቹም ጳውሎስና ሲላስ ሮማውያን እንደ ሆኑ በሰሙ ጊዜ ፈሩ፤ 39 መጥተውም ተማጸኑአቸው። ከወህኒ ቤትም ካስወጡአቸው በኋላ ከከተማው እንዲወጡ ጳውሎስና ሲላስን ለመኑአቸው።