Tue Aug 23 2016 22:18:12 GMT-0700 (Pacific Daylight Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2016-08-23 22:18:12 -07:00
parent f220ee65ff
commit 69caa2ac1e
7 changed files with 7 additions and 0 deletions

1
16/09.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 9 \v 10 9 ጳውሎስም አንድ የመቄዶንያ ሰው ቆሞ፣ “ወደ መቄዶንያ ተሻግረህ ርዳን” እያለ ሲለምነው ሌሊት በራእይ ታየው። 10 ራእዩንም ካየ በኋላ፣ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ለመሄድ ተነሣን፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ወንጌልን ለእነርሱ እንድንሰብክ እንደ ጠራን ዐሰብን።

1
16/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 \v 12 \v 13 11 ከጢሮአዳ ተነሥተንም ቀጥታ በመርከብ ወደ ሳሞትራቄ ሄድን፤ በማግስቱም ናጱሌ ደረስን፤ 12 ከዚያም የመቄዶንያ ከተማ ወደ ሆነችው ወደ ፊልጵስዩስ ሄድን፤ ከተማዋ የወረዳው ዋና ከተማና የሮም ቅኝ ግዛት ነበረች፤ በዚችም ከተማ ብዙ ቀን ተቀመጥን። 13 በሰንበት ቀንም፣ በወንዝ አጠገብ በነበረው በር በኩል ወደ ውጭ ወጣን፤ ይህም ስፍራ የጸሎት ቦታ እንደ ሆነ ዐሰብን። በዚያም ተቀምጠን ተሰብስበው ለነበሩ ሴቶች ተናገርን።

1
16/14.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 14 \v 15 14 ከትያጥሮን ከተማ የመጣችና የሐምራዊ ሐር ሻጭ የነበረች ልድያ የምትባል እግዚአብሔርን የምታመልክ አንድ ሴት ትሰማን ነበር። ጳውሎስ እየተናገረ የነበረው በሚገባ እንድታዳምጥ፣ ጌታ ልብዋን ከፈተላት። 15 ከቤተ ሰብዋ ጋር በተጠመቀች ጊዜም፣ “በጌታ ማመኔን ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ ግቡና ተቀመጡ” ብላ ለመነችን፤ አስገደደችንም።

1
16/16.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 16 \v 17 \v 18 16 አንድ ቀን ጸሎት ቦታ ስንሄድ የጥንቆላ መንፈስ ያደረባት አንዲት ወጣት አገኘን፤ በዚህ የጥንቆላ ሥራዋም ለአሳዳሪዎችዋ ከፍተኛ ገቢ ታስገኝ ነበር። ይህችው ሴት ጳውሎስንና እኛን ከኋላ እየተከተለች፣ “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፤ የመዳንን መንገድ ይነግሯችኋል” እያለች ትጮኽ ነበር። 18 ይህንም ብዙ ቀን ደጋገመች። ጳውሎስ ግን በዚህ እጅግ ተበሳጨ፤ ዘወር ብሎም መንፈሱን፣ “ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ” አለው፤ በዚያው ቅጽበትም ወጣ።

1
16/19.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 19 \v 20 \v 21 19 አሳዳሪዎችዋም ተስፋ የሚያደርጉበት የገቢያቸው ምንጭ እንደ ጠፋ ባዩ ጊዜ፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው በምድር ላይ እየጎተቱ በገበያ ስፍራ ባለሥልጣኖቹ ፊት አቀረቡአቸው። 20 ወደ ገዢዎችም አምጥተዋቸው፣ “እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ሳሉ በከተማችን ውስጥ ከፍተኛ ሁከት እየፈጠሩ ነው። 21 እኛ ሮማውያን ለመቀበል ያልተፈቀዱልንን ነገሮች ያስተምራሉ” አሉ።

1
16/22.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 22 \v 23 \v 24 22 በዚህ ጊዜ ሕዝቡ በጳውሎስና በሲላስ ላይ በአንድነት ተነሡ፤ ገዦቹም ልብሳቸውን አስወልቀው በዱላ እንዲደበድቡአቸው አዘዙ፤ 23 ብዙ ድብደባ ካካሄዱባቸው በኋላ ወደ ወህኒ ጣሉአቸው፤ የወህኒ ቤቱም ጠባቂ በጥንቃቄ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። 24 የወህኒ ቤት ጠባቂውም ይህን ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጥኛው እስር ቤት ጣላቸው፤ እግራቸውንም ከግንድ ጋር አጣብቆ አሰራቸው።

1
16/25.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 25 \v 26 25 እኩለ ሌሊት አካባቢም፣ ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ በዝማሬ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር፤ ሌሎች እስረኞችም አደመጡአቸው። 26 ድንገትም የወህኒ ቤቱ መሠረት እስከሚናጋ ድረስ ታላቅ የምድር መናወጥ ተከሠተ፤ ወዲያውም የወህኒ ቤቱ በሮች ሁሉ ተከፈቱ፤ የታሳሪዎችም ሁሉ ሰንሰለቶች ተፈቱ።