Tue Jun 26 2018 12:12:22 GMT+0300 (E. Africa Standard Time)

This commit is contained in:
tsDesktop 2018-06-26 12:12:22 +03:00
parent 51b8577a53
commit fca63b628b
8 changed files with 13 additions and 0 deletions

1
14/01.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\c 14 \v 1 የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በእስራኤል ላይ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ፡፡ \v 2 እርሱም በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ከኢየሩሳሌም ዮዓዳን ተብላ የምትጠራ ነበረች፡፡ \v 3 አሜስያስ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራ ሠርቶአል፤ ይሁን እንጂ እንደ ቀድሞ አያቱ እንደ ንጉሥ ዳዊት አልነበረም፤ እንደ ዳዊት በመሆን ፈንታ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ፡፡

1
14/04.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 4 ይኸውም በየኮረብታዎቹ ላይ የተሠሩትን የአሕዛብ ማምለኪያዎችን አላፈረሰም፤ ከዚህም የተነሣ ሕዝቡ በየኮረብታዎቹ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጠኑን እንደቀጠለ ነበር፡፡ \v 5 አሜስያሰ መንግሥቱን አደላድሎ እንደ ያዘ ወዲያውኑ፣ ቀደም ሲል ነግሦ የነበረውን አባቱን የገደሉትን ባለሥልጣኖች በሞት ቀጣ፤

1
14/06.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 6 ይሁን እንጂ ልጆቻቸውን አልገደለም፤ ይልቁንም በኦሪት ሕግ እግዚአብሔር ‹‹ልጆቻቸው በፈጸሙት ኃጢአት ወላጆች በሞት አይቀጡበትም፤ ወላጆችም በፈጸሙት ኃጢአት ልጆች በሞት አይቀጡበትም፤ እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈጸመው ወንጀል ብቻ በሞት ይቀጣል›› ሲል የሰጠውን ትእዛዝ ፈጽሞአል፡፡ \v 7 አሜስያስ ‹‹የጨው ሸለቆ›› እየተባለ በሚጠራው ስፍራ ዐሥር ሺህ የሚሆኑ የኤዶም ወታደሮችን ፈጀ፤ ሴላ ተብላ የምትጠራውንም ከተማ ይዞ ‹‹ዮቅትኤል›› ብሎ ጠራት፤ እስከ አሁንም በዚሁ ስም ትጠራለች፡፡

1
14/08.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 8 ከዚህ በኋላ አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዩ ልጅ ወደ ዮአስ መልእክተኞችን በመላክ ‹‹እንግዲህ ና ፊት ለፊት ጦርነት እንግጠም! ሲል ለጦርነት አነሣሣው፡፡ \v 9 ንጉሥ ዮአስ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት ‹‹አንድ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ላይ የምትገኝ ኩርንችት የሊባኖስ ዛፍ ‹ለወንድ ልጄ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሴት ልጅህን ስጠኝ› ስትል መልእክት ላከችበት፤ ነገር ግን አንድ የሊባኖስ አውሬ እግረ መንገዱን በዚያ ሲያልፍ ስለ ረገጣት ያቺ ኩርንችት ሞተች፡፡ \v 10 አሜስያስ ሆይ! እነሆ አንተ ኤዶማውያንን ድል ስላደረግህ ልብህ በትዕቢት ተሞልቶአል፤ ባገኘኸውም ድል በመደሰት ዐርፈህ በቤትህ ብትቀመጥ ይሻልሃል፤ በአንተና በሕዝብህ ላይ መከራና ውድቀት ስለ ምን ታስከትላለህ?

1
14/11.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 11 አሜስያስ ግን የዮአስን መልስ ከምንም አልቆጠረውም፤ ስለዚህም ንጉሥ ዮአስ ሠራዊቱን አስከትሎ በአሜስያስ ላይ በመዝመት በይሁዳ ምድር በምትገኘው በቤት ሳሚስ ጦርነት ገጠመው፡፡ \v 12 ይሁዳም ድል ተመታ፤ ወታደሮቹም ሁሉ ተበታትነው ወደየቤታቸው ተመለሱ፡፡

1
14/13.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 13 ዮአስም የአካዝያስን ልጅ፣ የኢዮአስን ልጅ አሜስያስን ከነሕይወቱ ማረከው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ለመድረስ ገሠገሠ፤ እዚያም እንደ ደረሰ ከኤፍሬም ቅጥር በር ‹‹የማዕዘን ቅጥር በር›› ተብሎ እስከሚጠራው በር ድረስ ጠቅላላ ርዝመቱ ሁለት መቶ ሜትር የሆነውን የቅጥር ግንብ አፈረሰ፡፡ \v 14 በዚያም ያገኘውን ወርቅና ብር ሁሉ፣ የቤተ መቅደሱን ንዋያተ ቅዱሳትና የቤተ መንግሥቱን ሀብት ሁሉ ጭኖ ወደ ሰማርያ ተመለሰ፤ በመያዣ ስም የተማረኩ ሰዎችንም ይዞ ሄደ፡፡

1
14/15.txt Normal file
View File

@ -0,0 +1 @@
\v 15 ንጉሥ ዮአስ ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ እንዲሁም በይሁዳ ንጉሥ በአሜስያስ ላይ ባደረገው ጦርነት የፈጸመው የጀግንነት ሥራ ጭምር በእስራኤል ነገሥታት መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ \v 16 ዮአስ ሞተ፤ በሰማርያ በሚገኘውም የነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ፤ በእርሱም ፈንታ ተተክቶ ዳግማዊ ኢዮርብዓም ነገሠ፡፡

View File

@ -210,6 +210,12 @@
"13-20",
"13-22",
"14-title",
"14-01",
"14-04",
"14-06",
"14-08",
"14-11",
"14-13",
"15-title",
"16-title",
"17-title",