am_tw/bible/kt/holyplace.md

1.8 KiB

ቅድስት፣ ቅድስተ ቅዱሳን

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ቅድስት” እና፣ “ቅድስተ ቅዱሳን” የተሰኙ ቃሎች መገናኛው ድንኳን ወይም ቤተ መቅደሱ ውስጥ የነበሩ ሁለት ክፍሎች ያመለክታሉ። አንዳንዴ፣ “ቅድስት” ወይም፣ “ቅዱስ ቦታ” የሚለው በጠቅላላው ለእግዚአብሔር የለለየ ማንኛውንም ቦታ ያመለክታል።

  • ቅድስት” እና “ቅድስተ ቅዱሳን” በአጥር በተከለለ መገናኛ ድንኳን ወይም ቤተ መቅደስ አደባባይ የተከበበ ቦታ ነበር የሚገኙት። ቅድስተ ቅዱሳን መግቢያ ላይ በጣም ወፍራምና ከባድ መጋረጃ ነበር።
  • እስራኤላውያንን ሁሉ ከሚወክለው ከላቀ ካህኑ ጋር ለመገናኘት እግዚአብሔር ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይመጣ ነበር።
  • ቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ እንዲገባ የሚፈቀደው ለሊቀ ካህኑ ብቻ ነበር። ወፍራምና ከባድ መጋረጃ ማንም ወደዚያ እንዳይገባ ያግዳል።
  • “ቅድስት” ወይም፣ “ቅድስት ቦታ” የመጀመሪያው ክፍል ሲሆን ውስጡ ሁለት ነገሮች ነበሩ፤ የዕጣን መሠዊያና የተቀደሰው እንጀራ ያለበት መንበር።
  • “ቅድስተ ቅዱሳን” ሁለተኛው ክፍል ሲሆን በጣም ወደ ውስጥ ሲገባ የሚገኘው ነው፤ የቃል ኪዳኑ ታቦት እዚህ ውስጥ ነበር።
  • አንዳንዴ፣ “ቅድስት” ወይም፣ “ቅዱስ ቦታ” የሚለው በአጠቃላይ የቤተ መቅደሱን ሕንፃ ወይም መገናኛ ድንኳኑን ያመለክታል።