am_tw/bible/kt/hades.md

1.2 KiB

ሐዴስ፣ ሲኦል

ሞትንና ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበትን ቦታ ለማመልከትት “ሐዴስ” እና “ሲኦል” የተሰኙት ቃሎች ጥቅም ላይ ውለዋል። የሁለቱም ትርጕም ተመሳሳይ ነው።

  • የሙታን ስፍራን በአጠቃላይ ለማመልከት ብዙውን ጊዜ ብሉይ ኪዳን ውስጥ “ሲኦል” የተሰኘው የዕብራይስጥ ቃል ጥቅም ላይ ውሏል።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ ያመፁ ነፍሳትን ቦታ ለማመልከት “ሐዴስ” የተሰኘው ቃል ጥቅም ላይ ውሏል። እነዚህ ነፍሳት ወደ ሐዴስ እንደሚወርዱ ተነግሯል። አንዳንዴ ይህ በኢየሱስ የሚያምኑ ሰዎች ወደሚኖሩበት ወደ ሰማይ፣ “መውጣት” ጋር በንጽጽር ይቀመጣል።
  • የዮሐንስ ራእይ ውስጥ፣ “ሐዴስ” የሚለው ቃል፣ “ሞት” ከተሰኘው ቃል ጋር በአንድነት ቀርቧል። መጨረሻው ዘመን ላይ ሞትና ሐዴስ ወደ እሳቱ ባሕር ይጣላሉ፤ እርሱም ገሃነም ነው።