am_tw/bible/kt/foolish.md

1.2 KiB

ሞኝ፣ ሞኝነት፣ ከንቱነት

“ሞኝ” የሚባለው ብዙውን ጊዜ የተሳሳተ ምርጫ የሚያደርግ በተለይም አለመታዘዝን የሚመርጥ ሰው ነው። “ሞኝነት” ማስተዋል የሌለው ሰው ወይም ፀባይ የሚገለጥበት መንገድ ነው።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙውን ጊዜ፣ “ሞኝ” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር የማያምንና ለእርሱ የማይታዘዝ ሰውን ነው። ብዙውን ጊዜ ቃሉ ጥቅም ላይ የሚውለው በእግዚአብሔር ከሚያምንናን ለእርሱ ከሚታዘዝ ሰው አንጻር ነው።
  • መዝሙሮቹ ውስጥ ዳዊት በእግዚአብሔር የማያምንና በእግዚአብሔር ፍጥረቶች ውስጥ ያሉትን ማስረጃዎች ችላ የሚልን ሰው ሞኝ በማለት ይጠራዋል።
  • ብሉይ ኪዳን ውስጥ ያለው መጽሐፍ ምሳሌ ሞኝ ሰው ምን ማለት እንደ ሆነ ብዙ መገለጫዎች ያቀርባል።
  • “ከንቱነት” ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ በመሆኑ ማስተዋል የሌለበት ድርጊት ያመለክታል።