am_tw/bible/kt/faith.md

1.5 KiB

እምነት

በአጠቃላይ ደረጃ “እምነት” የሚያመለክተው በእግዚአብሔር፣ በሰው ወይም፣ በነገሮች መተማመንን፣ መደገፍን፣ ወይም፣ መመካትን ነው።

  • “ማመን” ማለት የምናምነው ሰው የሚናገረውና የሚያደርገው ሁሉ እውነትና አስተማማኝ መሆኑን በሙሉ ልብ መቀበል ማለት ነው።
  • “በኢየሱስ ማመን” ኢየሱስን በተመለከተ እግዚአብሔር የሚያስተምረውን ሁሉ ማመን ማለት ነው። በተለይም በኢየሱስና ሰዎችን ከኅጢአታቸው እንደሚያነጻቸው ከኅጢአታቸው የተነሳ ከሚጠብቃቸው ቅጣት እንደሚያድናቸው ማመን ማለት ነው።
  • አንድ ሰው በእውነት በኢየሱስ ካመነ መንፈስ ቅዱስ እርሱ ውስጥ ስለሚኖር መልካም መንፈሳዊ ፍሬ ወይም የሕይወት ለውጥ ይኖረዋል።
  • አንዳንድ፣ “እምነት” “የእምነት እውነት” በሚለው በተገለጸው መሠረት፣ በአጠቃላይ ስለ ኢየሱስ የተሰጡ ትምህርቶችን ሁሉ ያመለክታል።
  • “እምነትን መጠበቅ” ወይም፣ “እምነትን መተው” በሚለው ዐውድ ውስጥ “እውነት” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢየሱስን በተመለከተ የተሰጡ ትምህርቶችን ሁሉ ማመንን ነው።