am_tw/bible/kt/elect.md

1.2 KiB

የተመረጠ፣ የተመረጠ ሕዝብ፣ የተመረጠው፣ ምርጦች

“የተመረጠ” ወይም፣ “ምርጦች” የሚለው ቃል በቃል፣ “የተመረጡት” ወይም፣ “የተመረጠ ሕዝብ” ማለት ሲሆን አባባሉ የእርሱ ሕዝብ እንደሆኑ እግዚአብሔር የመደባቸውን ወይም የመረጣቸውን ያመልክታል። “የተመረጡ” ወይም፣ “በእግዚአብሔር የተመረጠው፣ የተመረጠ መሲሕ የሆነው የኢየሱስ መጠሪያ ነው።

  • እግዚአብሔር እንዲቀደሱ፣ መልካም መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈሩ እግዚአብሔር ሰዎችን መረጠ። “የተመረጠ” የሚለው ቃል የሕዝቡ መሪ እንዲሆኑ እግዚአብሔር የመደባቸውን ሙሴንና ንጉሥ ዳዊትን የመሳሰሉ ሰዎች ለማመልከት ጥቅም ላይ ይውላል። እንደ እግዚአብሔር የተመረጠ ሕዝብ የእስራኤልን ሕዝብም ያመለክታል።
  • “ምርጦች” የተሰኘው ጥንታዊ ሐረግ ቃል በቃል፣ “የተመረጡት” ወይም፣ “የተመረጠ ሕዝብ” ማለት ነው።