am_tw/bible/kt/dayofthelord.md

9 lines
1.2 KiB
Markdown

# የጌታ ቀን፣ ይያህዌ ቀን
“የያህዌ ቀን” የተሰኘው የብሉይ ኪዳን አገላለጽ ከኀጢአታቸው የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚቀጣበትን የተለየ ቀን ወይም ቀኖች ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።
* “የጌታ ቀን” የሚለው የአዲስ ኪዳን አገላለጽ ብዙውን ጊዜ የሚያመለክተው በመጨረሻው ቀን ጌታ ኢየሱስ በሰዎች ለመፍረድ ተመልሶ የሚመጣበትን ቀን ነው።
* ይህ ወደ ፊት የሚመጣው የመጨረሻ ፍርድና ትንሣኤ አንዳንድ ጊዜ፣ “የመጨረሻው ቀን” ተብሎ ይጠራል። ይህ ጊዜ የሚጀምረው በኀጢአተኞች ለመፍረድና ለዘላለም መንግሥቱን ለመምሥረት ጌታ ኢየሱስ ሲመታ ነው።
* እነዚህ ሐረጎች ውስጥ፣ “ቀን” የሚለው ቃል አንዳንዴ ቃል በቃል “ጊዜን” ወይም ከቀን የረዘመ “ወቅትን” ሊያመለክት ይችላል።
* የቅጣቱ ቀን አንዳንዴ፣ “የእግዚአብሔር ቍጣ መፍሰስ” ተብሎ ይጠራል።