am_tw/bible/kt/covenant.md

1.5 KiB

ኪዳን

ኪዳን አንዱ ወይም ሁለቱም የሚፈጽሙት በሁለት ወገኖች መካከል የሚደረግ መደበኛ አሳሪ ስምምነት ነው።

  • ስምምነቱ በሁለት ግለ ሰቦች፣ ሕዝቦች፣ ወይም በእግዚአብሔርና በሕዝብ መካከል ሊደረግ
  • ሰዎች እርስ በርስ ኪዳን ካደረጉ አንድ ነገር ለማድረግ ቃል ይገባሉ፤ ያንንም ማድረግ አለባቸው።
  • በሰዎች መካከል ለሚደረግ ኪዳን ምሳሌ የሚሆኑን የጋብቻ ኪዳን፣ የሥራ ስምምነትና በአገሮች መካከል የሚደረጉ ውሎች ናቸው ።
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደምንመለከተው እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር በርካታ ኪዳኖች አድርጎ ነበር።
  • በአንዳንድ ኪዳኖች ውስጥ የእርሱን ድርሻ ለመፈጸም እግዚአብሔር ቃል የገባው ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ነበር። ለምሳሌ ዓለምን ሁሉ በማያዳርስ ጎርፍ ከእንግዲህ ምድርን እንደማያጠፋ እግዚአብሔር ቃል ከሰው ልጅ ጋር ኪዳን ያደረገው ሰው ማሟላት የነበረበት ምንም ቅድመ ሁኔታ ሳይኖር ነው።
  • በሌሎች ኪዳኖች የእርሱን ድርሻ እንደሚፈጽም እግዚአብሔር ቃል የገባው ሰዎች ከታዘዙትና የኪዳኑን የእነርሱን ድርሻ ከፈጸሙ ብቻ ነበር።