am_tw/bible/kt/conscience.md

1.2 KiB

ኅሊና

ኅሊና አንድ ሰው ኃጢአት እያደረገ መሆኑን እግዚአብሔር ለእርሱ የሚያሳውቅበት የሰውየው አስተሳሰብ አንድ ክፍል ነው።

  • ትክክል የሆነውንና ስሕተት የሆነውን ለይተው ማወቅ እንዲረዳቸው እግዚአብሔር ለሰዎች ኅሊና ሰጥቷል።
  • ለእግዚአብሔር የሚታዘዝ ሰው፣ “ንጹሕ” ወይም፣ “ያልቆሸሸ” ኅሊና አለው ይባላል።
  • አንድ ሰው፣ “ንጹሕ ኅሊና” አለው ከተባለ በውስጡ ምንም የተደበቀ ኃጢአት የለም ማለት ነው።
  • ሰዎች ኅሊናን ችላ ካሉና ኃጢአት ሲያደርጉ በደለኝነት የማይሰማቸው ከሆነ፣ ኃጢአትን በተመለከተ ኅሊናቸው ንቁ አይደለም ማለት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን በጋለ ብረት የመተኮስን ያህል፣ “የደነዘዙ” ኅሊና ይለዋል። እንዲህ ያለው ኅሊና፣ “የሞተ” ወይም፣ “የተበከለ” ሊባል ይችላል።
  • ይህን ቃል፣ “ውስጣዊ ግብረ ገብ መሪ”፣ “ግብረ ገባዊ አስተሳሰብ” ማለት ይቻላል።