am_tw/bible/kt/clean.md

1.6 KiB

ንጽሕ፣ ማንጻት

ቃል በቃል ሲወሰድ፣ “ንጹሕ” ምንም ቆሻሻ ወይም እድፍ የሌለበት ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ “ቅዱስ” እና “ከኃጢአት የነጻ” የሚሉትን ለማመልከት በምሳሌያዊ አነጋገር ጥቅም ላይ ይውላል።

  • “ማንጻት” አንድን ነገር ንጹሕ የማድረግ ሂደት ነው። “ማጠብ” ወይም “ማጽዳት” ተብሎ መተርጎምም ይችላል።
  • በብሉይ ኪዳን ዘመን የትኛው እንስሳ በሥርዓቱ መሠረት “ንጹሕ” የትኛው፣ “ርኵስ” እንደሆነ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ነግሮአቸዋል። ለመብልም ሆነ ለመሥዋዕት የተፈቀዱት ንጹሕ የሆኑ እንስሳት ብቻ ነበሩ። በዚህ ዐውድ መሠረት፣ “ንጹሕ” የተባለው መሥዋዕት እንዲሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ እንስሳ ማለት ነው።
  • የቆዳ በሽታ ያለበት ሰው በሽታው ተላላፊ እንዳይሆን ቆዳው እስኪፈወስ ድረስ፣ እንደ ርኵስ ይቆጠር ነበር። ሰውየው እንደገና “ንጹሕ” እንዲባል ከተፈለገ ከቆዳ በሽታ ለመንጻት ሊታዘዛቸው የመገቡ መመሪያዎች ነበሩ።
  • አንዳንዴ፣ “ንጽሕ” የሚለው ቃል ግበረ ገባዊ ንጽሕናን ለማመልከት በምሳሌያዊ መልኩ ጥቅም ላይ ይውላል።