am_tw/bible/kt/brother.md

1.2 KiB

ወንድም

ብዙውን ጊዜ ወንድም የሚባለው ቢያንስ ከወላጆች ከአንዱ የተወለደ ወንድ ልጅ ነው።

  • በብሉይ ኪዳን ዘመን “ወንድም” የሚለው ቃል የአንድ ጎሳ፣ ነገድ አባሎችን ወይም ሰዎችን የመሳሰሉ ዘመዳሞችን የሚያመለክት አጠቃላይ መጠሪያ ነበር።
  • በአዲስ ኪዳን ዘመን ሐዋርያት ወንዶችንም ሆነ ሴቶች አማኞችን ጨምሮ ክርስቲያን ወገኖችን “ወንድም” በማለት ይጠሩ ነበር፤ በክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ እግዚአብሔር አባታቸው የሆነ የአንድ መንፈሳዊ ቤተ ሰብ አባሎች ናቸው።
  • አዲስ ኪዳን ውስጥ ሐዋርያት በተለይ ሴት ስለሆነች ክርስቲያን ሲናገሩ ወይም ወንዶችም ሆነ ሴቶች መካተታቸውን አጽንዖት ለመስጠት ጥቂት ቦታ ላይ፣ “እኅት” በሚል ቃል ተጠቅመዋል። ለምሳሌ ያዕቆብ፣ “ምግብና ልብስ የሌለው ወንድም ወይም እኅት” ሲል እየተናገረ ያለው ስለ አማኞች ሁሉ መሆኑን አጽንዖት ሰጥቷል።