am_tw/bible/kt/bornagain.md

1.1 KiB

እንደ ገና መወለድ፣ ከእግዚአብሔር መወለድ፣ አዲስ ልደት

ኢየሱስ፣ “እንደ ገና መወለድ” በሚለው ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው እግዚአብሔር አንድን መንፈሳዊ ሙት የሆነ ሰው መንፈሳዊ ሕያው እንዲሆን እንደሚለውጠው ለማመልከት ነበር። “ከእግዚአብሔር መወለድ” ወይም፣ “ከመንፈስ መወለድ” የተሰኙትም ቃሎች አዲስ መንፈሳዊ ሕይወት የተሰጠውን ሰው ያመለክታሉ።

  • ሰዎች ሁሉ መንፈሳዊ ሙታን ሆነው ተወልደዋል፤ ክርስቶስ እንደ አዳኝ ሲቀበሉ ግን፣ “አዲስ ልደት” ይሰጣቸዋል።
  • አዲስ መንፈሳዊ ልደት በሚሆነበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ አዲሱ አማኝ ውስጥ ለመኖር ይመጣል፤ በሕይወቱ መልካም መንፈሳዊ ፍሬ እንዲያፈራ ኃይል ይሰጠዋል።
  • አንድ ሰው እንደ ገና እንዲወለድና የእግዚአብሔር ልጅ ማድረግ የእግዚአብሔር ሥራ ነው።